Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አማራ ያርጋል! (በላይነህ አባተ)

$
0
0
የአማራ ሰቆቃ ቁና ሞልቶ ፈሷል፣ ዛሬም ከርቸሌውን ጢም አርጎ ሞልቶታል፣ ተቤቱ ተባሮ ተመንገድ ዳር ወድቋል፣ በጨለማ ቦታ ሲገረፍ ይውላል፣ ባለ እስተንፋስ ሁሉ በቃ ሊል ይገባል! የእየሱስን እድሜ ግፍ ጽዋ ጨልጧል፣ ገደልነው ቀበርነው ብለው ፎክረዋል፣ ነገር ግን አማራ ይነሳል ያርጋል! ልክ እንደ ክርስቶስ በአንቀልባ ተሰዷል፣ ተሰፈር መንደሩ በሙርጅ ተጠርጓል፣ እንደ ማርያም ጠላት ተመንበር ተነቅሏል፣ በጦር በገጀራ […]

ኤርሚያስ ለገሰ የባላደራ ም/ቤቱን ከ ሀላፊነት ጋር ተቀላቀለ –ህብር ራዲኦ

$
0
0
አቶ ኤርሚያስ ለገስ በአዲስ አበባ ጉዳይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ባለአደራ ኮሚቴን በም/ል ሀላፊነት እንዲያገለግል ተሾመ፣ቁርጠኝነቱንም በደስታ ገለጸ። በጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ ባለ አደራ ኮሚቴ (ባልድራስ) ዛሬ በሰሜን አሜሪካ አትላንታ ከተማ በቨርጂኒያ ጎዳና በሚገኘው ቦሌ ሬስቶራንት በ ወቅታዊ ጉዳዬች ዙሪያ በተጠራው የምክክር መድረክ ላይ የምክር […]

የኦሮሞ ምሁራን መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው

$
0
0
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ምሁራን መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። የውይይት መድረኩ ምሁራኑ እንደ ክልልና እንደ ሃገር የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል በሚኖራቸው ድርሻ ላይ የሚመክር ነው። በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከ2 ሺህ በላይ ምሁራንና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። ውይይቱ አሸናፊ ሃሳብን በማመንጨት ለውጡን […]

“በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ

$
0
0
የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጠበቃ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በሂውማን ራይትስ ዋች ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግሏል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2011 እስከ 2016 የተቋሙ የአፍሪካ ክንፍ ዋና ዳይሬክተር ነበር። ኦክስፋም፣ አርቲክል 19፣ የዓለም ባንክ እና ዩኤስኤድን አማክሯል። በበርካታ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ የሠራው ዳንኤል፤ የ97ቱ ምርጫ ነጻ እንዲሆን እንዲሁም ሰብአዊ መብት እንዳይጣስ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። ከምርጫው በኋላ የተፈጠረውን ቀውስ […]

ወንጀል እና ህግ ፣ እውነት እና ውሸት በብሄረሰቦች ነፃነት ዘመን (ታሪኩ አባዳማ)

$
0
0
ታሪኩ አባዳማ ሰኔ 2011 በብሔረሰብ ተቆርቋሪ ስም የሰው ህይወት በግልፅ እና ስውር ማጥፋት ፣ ባንክ በጠራራ ፀሐይ መዝረፍ ፣ የህዝብ እና አገር ጥሪት ያለ ሰነድ ማራቆት ፣ ህዝብን ከአፅመ ርስቱ ማፈናቀል ፣ መዋሸት ፣ ስም ማጉደፍ ፣ በፈጠራ እና ግምት ላይ የተመረኮዘ ማነሳሳት ብሎም የሲቪሉን ህብረተሰብ ዕለታዊ ህይወት በመንጋ ጥቃት ማተራመስ… እነኝህ ሁሉ እንበለ ህግ […]

”እኔ ማን ነኝ ?! ”መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

$
0
0
” ፈጣሪዬ እኔ እንደነሱ ማልጓጎም አልችልምና አንተው ራሥህ አልጎምጉምልኝ።” የአንድ አርሶ አደር ፀሎት ” ያለማወቅን ማወቅ ፣ለማወቅ ብቸኛው መንገድ ነው።” የፈላስፎች ጥቅስ ሰው” እኔ ማን ነኝ?” ብሎ መጠየቅ የጀመረው መቼ ነው?የጠየቀውስ መቼ ና የት ነው?ጥያቄውን እንዲጠይቅ ያደረገው ገፊ ኃይል ምንድ ነው ?በግለሰብ ደረጃ  የሚያረካ መልሥሥ አግኝቷል ወይ??? ሰው  ጥንተ ፍጥረቱን የሚያሥረዳ መታወቂያ ለማግኘት ብዙ ርቀት […]

ለማን ብየ ላልቅስ?  አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

$
0
0
“የገደለው ባልሽ፤ የሞተው ወንድምሽ!”                         “ሃዘንሽ ቅጥ አጣ ምን ብየ ላላቅስሽ!” “እኔ ለዐማራው ሕዝብ ህይወቴን ሰጥቻለሁ” ዶር አምባቸው መኮነን የእኛ አገር ጉዳይ ቅጥ ያጣ ሆኗል። ወንድም ወንድሙን እንዲገድል ከጀርባ ሆኖ የሚቀሰቅሰው ማነው? የሚለውን ጥያቄ ለተመራማሪዎች ልተወው። የክልሉና የፌድራሉ ባለሥልጣናት ማን ገዳይ እና ማን ተገዳይ እንደሆነ ነግረውናል። ቁም ነገሩ፤ እነማን ናቸው ወይንም ከየትኛው ዘውግ ወይንም ጎጥ […]

“ቴዲ አፍሮ ከመወለዱ በፊት እናት እና አባቱን ነው የማውቀው”አለምፀሐይ ወዳጆ

$
0
0
ቴ ዲ አ ፍ ሮ በአለምፀሐይ ወዳጆ …… ከዛ በኋላ ቴዲን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት አሜሪካን ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገባ አለምፀሐይ ቤት ውሰዱኝ ይልና ለኔ ማንም ሳይነግረኝ ዲጄ መንጌ ቤትሽ እየመጣሁ ነው አለሽ አለኝ አለሁ አልኩት ሲመጡ ከቴዲ ጋር ናቸው። “ቴዲ እኔ እኮ ትንሽ ሆነህ ነው የማውቅህ መወለድህን የማወቀው ከዛ በቀር አላውቅክም” አልኩት። ቴዲ የጥበብ ሰዎችንና […]

የብ/ጄ አሳምነው ፅጌ ልጅ ዳዊት አሳምነው ከኢትዮጲስ ጋር ያደረገው ቆይታ

$
0
0
✅ኢትዮጲስ፦በመጀመሪያ ከስምህና ከእድሜህ ልጀምር… ✔️ዳዊት አሳምነው፦ስሜ ዳዊት አሳምነው ይባላል ፤እድሜዬ 15 ነው፤የተወለድኩት አዲስ አበባ ነው።በሚቀጥለው ዓመት 10ኛ ክፍል እገባለሁ። ✅ኢትዮጲስ፦ከ9 ዓመታት በፊት አባትህ ሲታሰሩ፣አንተ ትንሽ ልጅ ነበርክ።ያንን ጊዜ ምን ያህል ታስተውሰዋለህ? ✔️ዳዊትአሳምነው፦ አስታውሰዋለሁ፣ የ5 ዓመት ልጅ ነበርኩ።አንዳንድ መጥፎ ነገሮች ሲፈጠሩ፣የልጆች አእምሮ ውሰጥ ተቀርፆ ይቀራል፤አይረሳም።አስፈሪ ጊዜ ስለነበር አልረሳሁትም፤በጣም አቅልሼ ነበር።ሁሉም የደነገጠበት ሰዓት ነበር።እስር ቤት እየሄድኩኝ እጠይቀው […]

ትግራይ ክልላዊ መንግስት 16 ቢሊዮን 700ሚሊዮን ብር በጀት ጸደቅ

$
0
0
የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጉባኤ በጀትና አዋጆችን በማጽደቅ ማምሻውን ተጠናቀቀ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጉባኤ ለ2012 የስራ ዘመን 16 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ብር በጀትና የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ማምሻውን ተጠናቀቀ። በምክር ቤቱ የበጀትና ኦዲት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ንጉሰ ለገሰ እንዳስታወቁት በጀቱ የሚሸፈነው ከፌዴራል መንግስት ድጎማ ፣ከተለያዩ የውስጥ ገቢዎችና በብድር ነው። በጀቱም በዘመኑ ለመደበኛ […]

“ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ”  ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ ትናገራለች 

$
0
0
BBC : ሰኔ 15 ምን ይመስል ነበር? ጋዜጣችን የእሑድ ጋዜጣ ነው፤ ቅዳሜ ምሽት ሁልጊዜም ቢዚ ነው። ጋዜጣውን ቅዳሜ ማታ ነው .ፋሲካ ..,መጨረሻ ላይ ግን እርሳቸው ጋ ነው የደወልኩት። BBC :እርሳቸው ወዲያው አነሱት? ፋሲካ : ወዲያው። [እንዲያውም] ሁለት ጊዜ ይመስለኛል የጠራው። BBC: በዚያ ሰዓት ተጠርጣሪ እንደሆኑ ታውቂያለሽ? ፋሲካ :ምንም የማውቀው ነገር የለም BBC ምን ተባባላችሁ? ፋሲካ […]

ከጸጥታና ፍትህ የጋር ግብረ ሃይል በቅርቡ በባህርዳር እና በአዲስ አበባ በተፈጸመው የግድያ ወንጅል ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ 

$
0
0
ሰኔ 15 ቀን 2011 በባህርዳር ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ የመፍንቅለ መንግስት ለማድረግ በተፈጸመ አሰቃቂ የወንጅል ድርፈጊት ከፍተኛ የክልል እና የመከላካያ ሃላፊዎች ህይወት እንዳለፈ እንዲሁም ሌሎች የጸጥታ አካላት እንደሞቱና የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከጸጥታና ፍትህ የጋር ግብረ ሃይል መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ የተጠነሰሰው ሴራ በአማራ ክልል ህዝብ በክልሉ እና በፌደራል የፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥረት የከሸፈ ሲሆን […]

መቐለ 70 አንደርታ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ አሸናፊ ሆነ

$
0
0
የእግር ኳስ ቡድኑ የዋንጫ ባለቤት የሆነው በዛሬው ዕለት በመቐለ በተደረገ ጫወታ ድሬዳዋ ከተማን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ካሸነፈ በኋላ ነው። ውድድሩን በአሸናፊነት የማጠናቀቅ ዕድል የነበረው ፋሲል ከነማ ከስሑል ሽረ ተጫውቶ አንድ አቻ ተለያይቷል። ውጥረት ሰፍኖበት የከረመው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ዛሬ ተጠናቋል። ቪዲዮ፦ DW (ሚሊዮን ኃይለሥላሴ)

ዐብይ አንተም ስማ – እኛም ሰከን እንበል –ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

$
0
0
ሁላችንም የኢትዮጵያ ችግር እንዴት እንደሚፈታ ጭንቀት ይዞን ሀሳብ ለማመንጨት በሀገራችን ጉዳይ ተጠምደን ለሌላ ነገር ጊዜ አጥተናል።  ብርቅዬ ምሁራን የኢትዮጵያ እንቆቅልሽ እንዴት እንደሚፈታ የመፍትሄ አሳብ እንደ ዝናብ ዘወትር ያሽጎደጉዳሉ።  ያልተፃፈ የለም።  ያልተባለ የለም።  የኢትዮጵያ ልጆች ችግር ሲፈጥሩ እንዳይፈታ አርገው መቋጠር ይችላሉ።  ያንኑ ያህል ደግሞ ውሉ የጠፋበትን እንቆቅልሽ ለመፍታት ብቃትና ብልሃት ያላቸው ብዙ ልጆች ኢትዮጵያ አሏት።  በኢትዮጵያ […]

አማራ ምሁራን ሆይ! ሕዝባችሁን እየታረደ ነውና የትውልድ ግዴታችሁን ተወጡ! (በላይነህ አባተ)

$
0
0
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ለሰላሳ ዓመታት አማራ በአንድ እጁ ለማጨብጨብ ጣረ! አማራ “ኢትዮጵያ፣ አንድነት፣ ተጋብተንና ተዋልደን” እያለ ደጋግሞ በአንድ እጁ ሊያጨበጪብ ሞከረ፡፡ ዳሩ ግን አማራ ከአንድ እጅ ጭብጨባ ያተረፈው ሞትንና ስደትን ሆነ፡፡ አማራ አሁንም ባንድ እጁ እያጨበጨበ ሰላይ ሱሰኞችንና አታላይ ፓስተሮችን ስለተከተለ ሞትና ስደቱ በከፋ ሁኔታ ቀጠለ፡፡ ቲሞቲ ስናይደር የተባለ የየል ዩንቨርሲቲ ሊቅ እንደሚያስተምረው ዛሬ እሚታየው […]

ህዝብና የመከላከያ ሰራዊትን ባልተገባ መንገድ ለማጋጨት የሚሰሩ ግለሰቦችና የመገናኛ ብዙሃን ላይ ክስ ሊመሰርት ነው

$
0
0
ህዝብና የመከላከያ ሰራዊትን ባልተገባ መንገድ ለማጋጨት የሚሰሩ ግለሰቦችና የመገናኛ ብዙሀን ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የኢንዶክትሪኔሽን ዳይክቶሬት ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሃመድ ተሰማ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል ። በመግለጨቻቸውም የህግ የበላይነት የማስከበር ተግባር ከሁሉም በላይ የወቅቱ ቁልፍ የሰራዊቱ ተልዕኮ መሆኑን ተናግረዋል። በቅርቡ በባህር ዳርና በአዲስ አበባ […]

ጋዜጠኛና አክቲቪስት ኤልያስ ገብሩ ታሠረ

$
0
0
ጋዜጠኛና አክቲቪስት ኤልያስ ገብሩ ታሠረ። ፍርድ ቤት ቀርቦ ለሐምሌ 29 ተቀጥሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መከላከያ ሚኒስቴር በሚዲያዎች ላይ ክስ ልመሠርት ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ የ2012 ዓ.ም. በጀት 386.9 ቢሊዮን ብር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ጸደቀ

$
0
0
parlamaከዚህ ውስጥ ለመደበኛ ወጪ 109.5 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪ 130.7 ቢሊዮን ፣ ለክልሎች ድጋፍ 140.8 ቢሊዮን እና ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 6 ቢሊዮን ብር ተመድቧል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በአገሪቱ ምጣኔ ሐብት ላይ እየተደረጉ ስላሉ ማሻሻያዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። የገቢዎች ሚኒስቴር በአመቱ ከፍተኛ ገቢ ከአገር ውስጥ መሰብሰብ መቻሉን ጠቅሰው አድንቀዋል። ኢትዮጵያ ከነበረባት […]

ሀገር ወዳዱን አቶ ነዓምን ዘለቀን ተውት!!! –ወንድወሰን ተክሉ

$
0
0
ሰሞኑን በአቶ ነዓምን ዘለቀና ወገኖቻችን መካከል የቃላት ጦርነት የተከፈተ በሚመስል መልኩ ከየአቅጣጫው ቃላት ሲወነጫጨፍ እያየን ነው፡፡ በአቶ ነዓምን በኩል ከኢሳት ለሁለት መሰንጠቅ ማግስት ሲሰነዘሩ ባሉ ሀሳቦች ላይ ሙሉ በሙሉ እማልስማማ ሆኖ ሳለ በተለይም ሰሞኑን ከባህር ዳሩ አደጋ ጋር በተያያዘ ጉዳይ የአማራን ህዝብ ከመንግስት ጋር እንዲቆም ያቀረበውን ጥሪና ስለ አብን የገለጸውን አቋሙን ሙሉ በሙሉ ባልቀበልም አቶ […]

በመተከል ግጭት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

$
0
0
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ከሁለት ቀናት በፊት በተፈጸመ የሰዎች ግድያ የተጠረጠሩ አምስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር መሀመድ ሃምደኒል እንደገለጹት ሰኔ 30 ቀን 2011ዓ.ም በወረዳው ገነተ ማርያም ቀበሌ ተፈጥሮ በነበረ ግጭት የሰዎች ሕይወት አልፏል። በግድያው የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉን የተናገሩት ኮሚሺነሩ፥ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ሁለቱ ወንጀሉን […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live