Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጠቅላላ ጉባዔ የአቋም መግለጫ

$
0
0
ሰኔ 21, 2011 ዓም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከ43 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በፊንፊኔ ከተማ ዉስጥ ጠቅላላ ጉባዔዉን ኣካሄደ። የኦነግ መስራች ጉባዔ በፊንፊኔ/አድስ አበባ ከተማ ዉስጥ ከተካሄደበት ከ1976 እ.ኤ.አ. ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደዉ ይህ ታሪካዊ ጉባዔ ድርጅቱን (ኦነግን) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማስመዝገብ ያቀደ ጉባዔ ነዉ። ይህ ጉባዔ በፊንፊኔ ጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኝ የኦነግ ዋና […]

ኢትዮክራሲ፣ የኢትዮጵያ ማኅበራዊ ኃላፊነትን ያነገበ የገበያ ኢኮኖሚ (በአባተ ካሣ)

$
0
0
በአባተ ካሣ     መጋቢት 20, 2011 የዚህ ጽሁፍ ዓላማ የሀገሬ ልጆች ኢትዮጵያውያን የአባቶቻችንን የግዕዝ ፊደላትን የመፍጠር መሰል የቀደምትነት ተመክሮ እንደ አርዓያ በመከተል ሀገር-በቀል የኢትዮጵያ ርዕዮተ-ዓለም ይነድፉ ዘንድ ለማበረታታት ነው። ይህ ማዘዣ አይደለም፤ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጥቆማ እንጂ። የበለፀጉ እና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት በዓለም ላይ ይገኛሉ። አብዛኛዎቹ በአፍሪካ የሚገኙት በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ነፃነታቸውን የተቀዳጁት ገና […]

ህገ መንግስት እንዲሻሻል የሚፈልግ አካል ለሁሉም የሚሆን የማሻሻያ ሀሳብ ማቅረብ ይገባዋል –ጠ/ሚ ዶክተር አብይ

$
0
0
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ህገ መንግስት እንዲሻሻል የሚፈልግ አካል ለሁሉም ህዝብ ሊሆን የሚችል የማሻሻያ ሀሳብ ማቅረብ እንደሚገባው ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የመንግስትን የ2011 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም ህገ መንግስት እንዲሻሻል የሚፈልግ አካል ለሁሉም ህዝብ ሊሆን የሚችል […]

የዝንጀሮ ቆንጆ! (በላይነህ አባተ)

$
0
0
ጊዜው ተገልብጦ ታቹ ላይ ሆነና፣ መልከ-መልካም ጀግና ቆንጆ ሴት ተወና፣ ተዝንጀሮ መራጪ ሆነ ሰው ተላላ፡፡ ተመቀመጫው ላይ ጠባሳ ተሌለው፣ የዝንጀሮ ቆንጆ እንዴት ይመርጣል ሰው? የዝንጀሮ ታሪክ አመልም ተሌለው፣ እንዴት በግመር ፍቅር ከንፎ ይሄዳል ሰው? ተዝንጀሮ መንጋ ቆንጆ ሲፈልጉ፣ ብዙ ጂላጅሎች ወደ ገደል ገቡ፡፡ ዝንጀሮ መረጣ ሲወጡ ሲወርዱ፣ የካቡትን ሁሉ እንደ ገደል ናዱ፡፡ ያልታደለ ገላ ያልተባረከ […]

የጄ/ል ሰአረ መኮንን ጠባቂ ያልተመለሰለት ጥያቄ እና 11ኛዋ ሰዓት –ህብር ራዲኦ

$
0
0
ባለፈው ሰኔ 15 ዓም አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ከቅርብ ጎደኛቸው ከጄ/ል ገዛኢ አበራ ጋር ሳሉ በጠባቂያቸው ተገደሉ የተባለው የጄ/ል ሰአረ መኮንን የመጨረሻው ክንውናቸውን በተመለከተ ይፋ ሆነ። በአዲስ አበባ ውስጥ የሚታተመው ሳምንታዊው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ካፒታል በእሁድ እትሙ ለጄ/ሉ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች እንዳገኘሁት በማለት እንዳስነበበው ከሆነ የመከላከያ ሰራዊቱ ቁንጮ(ቺፍ ኦፍ ስታፍ ኦፍ ዘ አርሚይ) […]

 ከአማራ ህዝብ ጎን እንቆማለን! በአማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመው ወረራ ግድያና እስራትን አጥብቀን እናወጋዛለን!

$
0
0
የኢትዮጵያ ህዝብ ለለፉት 28 አመታት ያካሄደው ትግል ለነጻነቱ ለመበቱና ለህልውናው እንቅፋትና ጠንቅ የሆነውን የወያኔን የጎሳ ስርአት የማስወገድ  እንጂ የህዘባችንን ሰቆቃ የሚያራዝም፣ አንዱን አጥፊ ጎሳ በሌላ አጥፊ ጎሳ ለመተካት አልነበረም። የህዝባችን ትግል ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነትና አንድነት፣ ለፍትህና ርትእ፣ ለሰብአዊ መብት፣ ለአገራዊ ህልውና እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ለማስከበር ነበር። ይህ የነጻነት ትግል በዶ/ር አብይና ግብረ አበሮቹ በረቀቀና የህዝብን […]

“ይህ ሴራ ሆን ተብሎ የተቀነባበረው አብይ በሚመራው ፓርቲ በኢህአዴግ ነው።”–አቤል ዋበላ

$
0
0
አሁን ተሰራ የሚባለው ወንጀል የተቀነባበረ ሴራ እንጂ መፈንቅለ መንግስትም ሆነ የሽብር ስራ አይደለም። ወንጀሉን አቀነባበሩ የተባሉ ግለሰቦችም የሴራው ተጠቂ እንጂ የድርጊቱ ፈፃሚዎች አይደሉም። ይህ ሴራ ሆን ተብሎ የተቀነባበረው አብይ በሚመራው ፓርቲ በኢህአዴግ ነው። አከተመ! ~~ አላማው፦ 1. የአማራ ህዝብ አማራ ነኝ ብሎ በመደራጀቱ እየተጠናከረ መሆኑ ስላስፈራው ትግሉን ለማኮላሸትና ህዝቡ ዳግመኛ አይደለም መታገል አማራ ነኝ ብሎ […]

ከኢትዮጵያውያን ማህበረ ሰብዓዊ ድርጅቶች በወቅቱ ሁኔታ ላይ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0
ሰኔ 23,2011 ሰሞኑን በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተከሰተው አደጋ እጅግ አሳዝኖናል፣ አስደንግጦናልም። በዚህ አደጋ በርካታ ወገኖቻችን መሞታቸውና መቁሰላቸው በመንግሥትና በነጻ ሚዲያ ተገልጿል። ባህርዳር በተፈጠረው ግጭት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮነን፣ ሦስት ከፍተኛ የሥራ ባልደረቦቻቸውና የደህንነት ሀላፊው ጀኔርል አሳምነው ጽጌ መሞታቸው ተገልጿል። በአዲስ አበባው ግጭት የሞቱት ደግሞ፣ የጦር ሀይሎች ኢታማጆር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮነንና ጄኔራል […]

ትግራይን መገንጠል ያስፈልጋል? –ማሕበር ኢትዮጵያውያን ተጋሩ

$
0
0
በኣሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከኣካባቢ ኣሰተዳደር ጥያቄ ያለፈ የመገንጠል ጥያቄ ዓላማ ለመተግበር የሚታገል ቡድን የለም። ይህም የኢትዮጵያ ህዝብ የኣንድነት መንፈስ ስለሚያመለክት ተገቢ ትኩረት ሊሰጠውና ሊዳብር ይገባዋል። ከዚህ ኣንጻር ሲታይ ኢትዮጵያ በመበታተን ኣፋፍ ላይ የምትገኝ የሚያስመስል ከእውነት የራቀ ቅስቀሳ ቦታ ሊኖረው ኣይገባም። በትግራይ ውስጥም የመገንጠል ዓላማ ይዞ የሚታገል ቡድን ባይኖርም ደብረፅዮን (ዶ/ር) በትግራይ ህዝብ የመገንጠል ዝንባሌ […]

አገርህን አትልቀቅ! ሰላም ሐበሾች! ሰላም ኢትዬጲያውያን ወገኖቼ! –ዓሣዱር ከለንደን

$
0
0
ወገኖቼ፦ ይህን መልዕክት ስፅፍ ከትናንት በስቲያ ከሊቢያ ሰማይ ላይ የጦር አመፀኛው የጄነራል ካሊፋ አፍታር ተዋጊ ጄት አውሮፕላኖች ትሪፑሊ አጠገብ በቦምብ ያጋዩዋቸውን ኢትዮጲያዊያን ፣ ኤርትራውያንና ሌሎች እፍሪካዊያን ስደተኞች ልብ የሚሰብር በድን በቴሌቪዥን እየተመለከትኩኝ ነው። ለዚህም የመጀመሪያ ፅሁፌ መነሻና ምክንያቴ ይኽው የአገሬ ወጣቶችና አፍሪካዊያን ወገኖቼ አሣዛኝ አሟሟት ነው። ውድ ወገኖቼ፦ የዛሬ 30 ዓመት ገደማ ለትምህርት ወደ ውጭ […]

የአንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን) ልሳን  ኢትዮጵያችን ቅጽ 3 ቁጥር 8              

$
0
0
 ኢትዮጵያችን ቅጽ 3 ቁጥር 8                                                 ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ትግላችን ለኢትዮጵያ አንድነት ከሆነ . . . የድምጽ ቅጂውን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ (https://youtu.be/OcTmK72H68M) በቅድሚያ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በሀገራችን ኢትዮጵያ ለተሰማው የኢሕአዴግ አገዛዝ ባለሥልጣናት ግድያ የተሰማንን ሀዘን ልንገልጽ እንወዳለን። ድርጊቱና ጥፋተኛው ማነው? ሳንል በጥቅሉ የተከሰተው ድርጊት ለጆሮ አስደንጋጭ፣ ለሀገር አሳፋሪ፣ ለቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መሪር […]

ገዳይ ደስ አይበልህ፤ ሟችም ብዙ አይክፋህ –ግርማ በላይ

$
0
0
ግርማ በላይ (gb5214@gmail.com) ሰሞነኛው የሀገራችን ሁኔታ እንደብዙውን ጊዜው ሁሉ ዕንቅልፍ ይነሣል፡፡ ካለፈው ይልቅ መጪው እያስፈራን በጭንቀት ውስጥ እንገኛለን፡፡ እንደባሕር ዳሩ ዓይነት ዕብደት በአንድ ሀገር ሲደርስ ደግሞ መዘዙ ከፍተኛ ነውና ይህን ሰይጣናዊ ዕኩይ ድርጊት ያሤሩ፣ የጠነሰሱ፣ ያስተባበሩና ያስፈጸሙ ሁሉ በጊዜ ሂደት የታሪክ ቅጣታቸውን መቀበላቸው አይቀርም፡፡ ለጊዜው ግን የተወሰነ ውዥንብርንና የአቅጣጫ መደናበርን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ አያጠራጥርም፡፡ የንብ ቀፎ […]

ኢዜማ በአትላንታ ያደረገው ስብሰባ

$
0
0
ኢዜማ በአትላንታ የተደረገ ስብሰባ

ኢትዮጵያ ሁለት ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኦፕሬተሮችን በጨረታ ወደ ቴሌኮም ገበያ ልታስገባ ነው

$
0
0
የኢትዮ-ቴሌኮም እና የስኳር ፋብሪካዎች ፕራይቬታይዜሽን ሂደትን በተመለከተ የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው ላይ እንዳመለከቱትም የቴሌኮም ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የፓይቬታይዜሽን ሂደቱን በተመለከተ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ከኢትዮ ቴሌኮም በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ወደ ገበያ እንዲገቡ ያደርጋል። በተጨማሪም የኢትዮ-ቴሌኮምን አብላጫ ድርሻ እና የቦርድ አስተዳደርን መንግሥት ይዞ 49 በመቶ ድርሻውን […]

በግልፅና በቀጥታ ካልተነገርን የመከራው ፖለቲካችን ማቆሚያ አይኖረውም  –ጠገናው ጎሹ

$
0
0
June 23, 2019 ጠገናው ጎሹ ደራሲ አቤ ጎበኛ ከዛሬ አርባ አምስት ዓመት በፊት ( ሐምሌ 1966) በማህፀኗ ውስጥ ሆኖ ምስኪን እናቱን “እውነት በሌለበት ዓለም ለመኖር አልወለድም” ብሎ የሞገታትን   ህፃን  ኢይዝራኤሎስ ብሎ በምእናቡ በሰየማት ደሴት አገር እንዴወለድ አደረገው። በዚችው በውጭ ወራሪዎች ስትገዛና ስትመዘበር ቆይታ ነፃነቷን ብታገኝም ከእራሷ ብልሹ አገዛዝ ነፃ መውጣት ባልቻለችው ደሴት አገር ሳይፈልግ የተወለደው […]

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0
የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ የተጀመረውን ለውጥ ያለምንም ማወላወል እናስቀጥላለን- የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአማራ ክልል ሕዝብ በሕግ የበላይነት አጥብቆ የሚያምንና የሚታወቅበት እሴቱ ሆኖ መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ‹‹ነፃነትና ፍትሐዊነት ተጓሏል›› ብሎ ባመነባቸው ዘመናትም ይህንኑ እሴቱን ጠብቆ የታገለ ሥልጡን ሕዝብ ነዉ፡፡ አማራ ‹‹በሕግ ከተወሰደች በቅሎዬ ያለ ሕግ የተቀማች ጭብጦዬ›› በሚል ብሒል የተገነባና ‹‹በሕግ አምላክ›› ሲሉት ከምንም ዓይነት ድርጊት […]

በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ ኢትዮጵያዊያንን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ

$
0
0
በአሜሪካ የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ ኢትዮጵያዊያንን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢትዮጵያ አሜሪካዊያን የዜጎች ምክር ቤት አስታውቋል። ያነጋገርናቸው የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት አቶ አምሳሉ ፀጋዬ፤ ወንድም ወንድሙን በማጣላት፤ ብሔር ከብሔር በማጋጨት እንደ ሃገር ለመቀጠል ፈታኝ ሆኗል፤ ይህንን የሚያደርጉ ግለሰቦችን ለማስተማር ብዙ እየተሞከረ ቢሆንም ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለመጣ ምክር ቤቱ ግለሰቦቹን ወደ ህግ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ይናገራሉ። […]

በክልሎች በልዩ ሃይል ስም የተቋቋመው ከፖሊስ በላይ ነው – የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር

$
0
0
ከሰሞኑ የባለስልጣናት ግድያ ጋር ተያይዞ በየክልሉ ያሉ የ”ልዩ ኃይሎች” ጉዳይ እያጠያየቀ ነው።መንግስታዊው “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ “ክልሎች ከአስር ሺዎች እስከ መቶ ሺዎች የሚቆጠር ልዩ ሃይል እንዳላቸው የተለያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ” ብሏል። የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ተፈራ በክልላቸው “ልዩ ኃይል የሚባል መዋቅር አለመኖሩን” ለአዲስ ዘመን ተናግረዋል። በመዋቅሩ ውስጥ ያለው “መደበኛ ፖሊስ እና አድማ በታኝ” ነው ባይ […]

ሰሞኑን በተከሰቱ የባህርዳርና አዲስ አበባ ቀውሶች ተሸንፈን  አገራችንን አንድነት በሚፈትን ቀውስ ውስጥ እንዳንገባ ሰከን ባለ መንፈስ  እናት ኢትዬጵያን በጋራ እንታደግ!!

$
0
0
አበባየሁ አሉላ በባሕርዳርና አዲስ አበባ በሰሞኑ የተከሰተው ቀውስ በሁሉም አቅጣጫ የብዙ ወገኖቻችንን ሕይወት የቀጠፈ በመሆኑ በግራም ይሁን በቀኝ የዜጎቻችን ልብ የተሰበረበት ወቅት ነው! በዚህ እንቆቅልሹ ባልተፈታ ቀውስ የአማራው ክልል ወገኖቻችንም ብርቅዬ ልጆቹን ያጣበት ወቅት በመሆኑ ሐዘኑና ምሬቱ እጅግ ከፍተኛ ነው! በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አመራርና አስተዳደር ትላንት ኢትዬጵያ በሕወኃት/ኢህአደግ አመራር ውስጥ ከነበረችበት ዜጎኝ በሁሉም ማዕዘናት […]

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እስከሚያገኝ ከፕሪምየር ሊጉ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ

$
0
0
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ  ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live