Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ ጀግኖች መስዋእትነት ከ30 አመት በኋላ ሲታሰብ- ከደረጀ ደምሴ ቡልቶ

0
0
ማስታወሻ – እንደመግቢያ የዛሬ 10 አመት 2ኛው የጀግኖች አመታዊ ክብረ በአል በዋሽንግተን ዲሲ በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ነበር፡፡ ከቀድሞ ከአየር ኃይል፣ ከሐረር እካዳሚ፣ ከምድር ጦር፣ ከአየር ወለድ፣ የባህር ሃይል የተውጣጡ አባላት የሚገኙበት ኮሜቴ ከሲቪል ደግሞ አርቲስት እክቲቪስት ታማኝ በየነና እኔ የኮሚቴ አባል ሆነን አገልግለናል፡፡የመጀመሪያው የጀግኖች ምሽት ዋና የክብር እንግዳ የአየር ሀይል አብራሪ የነበሩት ብ/ጄነራል ለገሰ ተፈራ፣ […]

ቀኛዝማች አባ ናዳ፤ (ቀኛዝማች ድልነሣሁ ጠንፉ) የኢትዮጵያ ጀግናና ዲፕሎማት –ከኪዳኔ ዓለማየሁ

0
0
መግቢያ፤ ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው የፈረስ ስማቸው “አባ ናዳ” ስለ ተሰኘው ስለ ቀኛዝማች ድልነሣሁ ጠንፉ የሕይወት ታሪክ ነው። በቤተዘመዳቸውና በሌሎችም ሰዎች ይታወቁ የነበረው እራሳቸውም በድርሳነ ሚካኤላቸው መግቢያ የተጠቀሙት በፈረስ ስማቸው ስለነበረ ከዚህ ቀጥሎ አባ ናዳ በሚለው ስያሜያቸው እጠቀማለሁ። ቀኛዝማች ድልነሣሁ ጠንፉ የአባ ናዳ ትውልድ፤ ሸዋ ውስጥ ሲጠር በሚባለው አካባቢ እንደሆነ ይነገራል። የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዝርያ ናቸው። […]

ተገዳድለህ መፍትሄ አታመጣም   (ወለላዬ ከስዊድን)

0
0
በዱላ መቀጣቀጥ ብትችልም መደባደብ፣ ማባረር፣ መግደልም መፍትሔ ሆኖ ላያኖርህ ላያቆይህ ጥፋት ነው ለጥፋት ማቆብቆብህ በጣጥሰህ ሸንሽነህ ካልከፋፈልካት ሰላም አውለህ ሰላም ካሳደርካት አገርህ እንደኹ ለሁልኽም በቂህ ናት አንባጓሮህን አሽቀንጥረህ ወርውረህ የዘር ቁርሾ ቀለምህን ከግንባርህ ፍቀህ ተመካክረህ ተግባብተህ እደር ከወንድምህ አንተስ፣ እሱስ፣ እሷስ ካለኢትዮጵያ ማን አላችሁ አንድ እኮ ናት! የጋራ መኖርያ ቤታችሁ ዛሬ ቀንቶህ የወጣልህን የነፃነት ፀሐይ […]

በሚሊኒየም አዳራሽ የአብሮነትና የምስጋና የአፍጥር ምሽት ተካሄደ

0
0
ዛሬ ምሽት በሚሊኒየም አዳራሽ የአብሮነትና የምስጋና የአፍጥር ምሽት ተካሄደ፡፡ ዋሺንግተን ዲሲ — በርካታ የሙስሊም ማኅበረሰብ አባላትና የሀይማኖት መሪዎች በታደሙበት በዚህ የአፍጥር ምሽት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ በዚህ የኢፍጣር ሥነ ስርዓት ላይ ተሳትፈዋል፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባዘጋጀው ሥነ ስርዓት ላይ የተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ስርዓቶች ቀርበዋል፡፡ በሚሊኒየም […]

#ምርጫ_ቦርድ በህግ በተሰጠው የጊዜ ሰሌዳ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ማድረግ እንጂ ምርጫ_የማራዘም ስልጣን የለውም!! –ሶልያና ሽመልስ

0
0
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መዋቅሩን ወደ ክልሎች ለማውረድ የሚያስችለውን ጥናት ማጠናቀቁን አስታወቀ። በ2012 ዓ.ም የሚካሄደውን ብሔራዊ ምርጫ ተአማኒ ለማድረግ የቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ መጽደቁ ይታወሳል። የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ለኢዜአ እንደተናገሩት በአዋጁ መሰረት የቦርዱን የውስጥ መዋቅርና አደረጃጀት በክልሎችም ለመተግበር የሚያስችል ጥናት ተጠናቋል። በህጉ መሰረት መዋቅር በመቀየር ና […]

በአዲስ አበባ ህገ ወጥ ቤት ገንብተው የሚኖሩ ዜጎች በ2 ሳምንት ውስጥ እንዲያፈርሱ የከተማ አስተዳደሩ አሳሰበ

0
0
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከክፍለ ከተማ አመራሮችና የፀጥታ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ዛሬ መክረዋል፡፡ በዚህም ህገወጥ ግንባታ የፈፀሙ አካላት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ አፍርሰው ንብረታቸውን እንዲያነሱ ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ የከተማ አስተዳደሩ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እርምጃ እንዲሚወስድ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ሂደት የመንግስት አካል ሆኖ በህገወጥ ግንባታው ሂደት የተገኘ አመራር ካለ […]

የብሔርተኞች የተቃርኖ ፖለቲካ እና ህልውናቸው!! –ራሄል አዲስ

0
0
አንድ ሀገር በመርህና በሀሳብ ልዕልና ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስርዓት ከሌላት ሁሌም የተፋርሶ የፖለቲካ መስመር ላይ (in a constant state of deconstructive political path) እንደሆነች ትቀጥላለች:: ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁሉን አቃፊነት የጎደለው ስርዓት (non-inclusive system) ተጠቂ ትሆናለች:: የፖለቲካ ስርዓቱን ፌዴራልም በለው ሌላ ስልጣን የምትይዘው ያንተን ብሔር ልዩ የስርዓቱ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስለሚሆንና ይህ ደግሞ መርህ ላይ የተመሰረተ […]

የሕብር ሬዲዮ ግንቦት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ፕሮግራም

0
0
በትግራይ ያለው እውነታ ምንድነው የሚለውን የአረና የሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ኮሚቴ ጥሪ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተደረገ ውይይት(የመጀመሪያ ክፍል አንድ ውይይት)  አቶ ጌታቸው አሰፋ ከአዲስ አበባ እስከ ደ/ሱዳን (ወቅታዊ ትንታኔ) የአንጋፋው ድምጻዊ አያሌው መስፍን የሃምሳ ዓመት ጉዞ (ክፍል ሁለት) ሌሎችም ዜናዎቻችን አቶ ጌታቸው አሰፋ ካልተያዘ በአገሪቱ ብጥብጥ ይቀጥላል ተባለ የመንግስት እና የሕክምና ባለሙያዎች ውዝግብ ከኢትዮጵያ መንግስት […]

የኢዜማ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ዝርዝር

0
0
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ-ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በስራ አስፈጻሚነት የመረጣቸውን 21 አባላት ይፋ አደረገ፡፡ አባላቱ ብቃትን፣ ትምህርትን፣ ለፓርቲው ሊሰጡ የሚችሉትን ጊዜ እና የፓርቲውን ዓላማ በትክክል መረዳታቸውን ታሳቢ በማድረግ ተመርጠዋል ብሏል፡፡ ኢዜማ በምርጫ ተወዳድረው ለማሸነፍ ያላቸው ቁርጠኝነትና ይቅር ባይነታቸው ከግምት ውስጥ መግባቱንም ነው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያስታወቀው፡፡ ስራ አስፈጻሚ አባላቱን የመምረጡ ስራ ጊዜ ተሰጥቶት ከፓርቲው መስራች ጉባዔ ጀምሮ […]

ዶክተር አምባቸው በአምቦ ስላደረጉዋት ንግግር ማብራርያ ሰጡ

0
0
ዶክተር አምባቸው በአምቦ ስላደረጉዋት ንግግር ማብራርያ ሰጡ

የወላይታው 35,000 የመከላከያ ተቀናሾችና ያልፈነዳው የግዜ ቦንብ ጉዳይ!! –ራሔል አዲስ

0
0
ትናንት በወላይታ ሶዶ ከተማ የተካሄደውና በሀገሪቱ የተለያዩ ሚዲያዎች የተዘገበው ሰላማዊ ሰልፍ ከወትሮው የተለየ ስጋት የሚያጭር አንደምታ የተስተዋለበት ነበር:: በርግጥ ሰላማዊ ሰልፉ ሌሎች አካባቢዎች ላይ እንደታየው የማንነትና የክልል ራስን በራስ የማስተዳደር ህገመንግስታዊ ጥያቄዎች: ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች: እንዲሁም በፌዴራል መንግስቱ በኩል የሚደረጉ የልማት ድጎማዎች ከበቂ በታች መሆንና በሀዋሳና ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች በብሔሩ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ብሔር […]

በባለ-አደራዉ ላይ አፈናዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል የእስር ዜና ዛሬም. –ሽዋ

0
0
የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት አባል የሆነዉ ሽመልስ ለገሰ ታሰረ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአራዳ አካባቢ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጣቢያ የባለአደራዉ አመራር ሽመልስ ለገሰ አስረውታል፡፡ ይህን ለማጣራት ወደ ቦታዉ ያቀኑት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ስንታየሁ ቸኮል በጣቢያዉ ላይ ሲደርሱ ለምን መጣችሉ እናተ ሰዎች አላሰራ አላችሁን እረፍት ነሳችሁን በማለት የገለፁ ዋና ኮማንሩ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በጣቢያው አዛዥ […]

ከብሬክሲት(Brexit) ምን እንማር –በታደሰ ብሩ

0
0
የብሪታኒያን ከአወሮፓ ኅብረት መውጣትን (Brexit) ማስፈፀም አለመቻላቸው በማመን ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሬዛ ሜይ ሥራቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስታወቁ። ዴቪድ ካሚሮንን ጨምሮ በብሬክሲት ሰበብ ስልጣን የለቀቁ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ቁጥር ወደ ሁለት ሊያድግ ነው ማለት ነው። ከሶስት ዓመታት በፊት ቀኝ ክንፍ ፓለቲከኞች “አገራችንን ከአውሮፓ ኅብረት አገዛዝ ነፃ እናወጣለን፤ የራሳችንን አገር ማንም ሳይገባብን ራሳችን በራሳችን እናስተዳድራለን፤ ከአውሮፓ ኅብረት ከወጣን ስደተኞችን […]

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢ-ዜማ/ የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጡን አስታውቋል

0
0
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢ-ዜማ/ የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጡን አስታውቋል

“አዴፓ መታረም አለበት ፤ የአማራ የፀጥታ መዋቅር ከአዴፓ ተፅዕኖ ነፃ ሁኖ እንዲዋቀር መፍቀድ አለበት ። ይህ ካልሆነ ታሪካዊ ስህተት አዴፓ ይሰራል –ጄኔራል አሳምነው ፅጌ

0
0
የምናከብራቸው ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ይህንን ብለዋል እየተባለ በሰፊው ተዘግቦ አየሁት። ምንጭ ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ብል ጄኔራሉ ባህርዳር በተደረገው ስብሰባ ላይ የተናገሩት ነገር ሌላ ነው። ጄኔራሉ እራሳቸው እኮ የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው። ፓርቲያቸው በህዝባችን የፀጥታ አጠባበቅ ጉዳዮች ላይ ዕንቅፋታ እየፈጠረ ከሆነ ጠያቂ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂም ጭምር ናቸው። -=- ለማንኛውም ከዚህ በዃላ ከጄኔራሉ ከዕራሳቸው አንደበት ካልሰማን […]

የስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ከደረሰበት የሰደድ እሳት አደጋ ለማገገም ከ10 ዓመታት በላይ ሊወስድ እንደሚችል ተገለጸ

0
0
በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን በተመራ የጥናትና ምርምር ቡድን ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ፓርኩ ከደረሰበት የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ለማገገምና ወደ ቀድሞ ይዞታው ለመመለስ ከ10 ዓመታት በላይ ሊወስድበት እንደሚችል በዳሰሳ ጥናት መረጋገጡ ተገለጸ፡፡ በተከሰተው የእሳት አደጋ በፓርኩ ውስጥ በሚገኙ ወካይ እንስሳት ማትም በዋልያ፣ ቀይ ቀበሮ እና ጭላዳ ዝንጀሮ ላይ ምንም ዓይነት የሞት አደጋ አለመከሰቱን በቅኝት […]

በሬውን ሊያልቡት ነው! –በላይነህ አባተ

0
0
ዋሽንት እየነፉ የእስስት ገሳ ለብሰው፣ ከብት እሚጠብቁ በግ እረኛ መስለው፣ ልክ እንደ ትናንቱ እንደልማዳቸው፣ ሳርን እያሳዩ በሬውን ሊያልቡት ነው፡፡   ሰማእታት ብሎ አዳም ሲጠራቸው፣ እርኩሳን የሆኑት ተጅብ ተወዳጅተው፣ ስብከት ቀጥለዋል ዛሬም ፃድቅ መስለው፡፡   በዜጋ ሰንሰለት እግሮቹን ጠፍረው፣ በአንድነት መዶሻ ፍሬውን ቀጥቅጠው፣ ብልቱን ቆራርጠው አራት ቦታ ተክለው፣ ጎልማሳውን በሬ ጾታውን ቀይረው፣ እንደ ጥገት እላም አሁንም […]

ህገ መንግስቱ እንዲቀየር ጥረት እንደሚያደርግ እና የራሱንም አማራጭ እንደሚያስቀምጥ አብን አስታወቀ

0
0
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 17/2011ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከጎንደር ከተማ ወጣቶች እና ነዋሪዎች ጋር ዛሬ ተወያይቷል። ተወያዮቹ አብን ቢያተኩርባቸው ይጠቅማሉ ያሏቸውን ሀሳቦች አንስተዋል። አብን ለአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ትንሳኤ መስራት አለበት፤ እኛ ሁልጊዜ እሳት ማጥፋት የለብንም፤ ይልቁንም ችግር ከመከሰቱ በፊት መከላከሉ ላይ መሰራት አለበት ብለዋል። ለአማራ የመኖር መብት፣ የኢኮኖሚ እና የማንነት ጥያቄዎች ትኩረት […]

‹‹የራሷ ቋንቋና ፊደል ያላት አፍሪካዊት ሃገር እያለችን ከቅኝ ገዥዎቻችን ቋንቋ ተውሰን ቻርተሩን መፈረም የለብንም፡፡›› የጊኒው ፕሬዝዳንት ሴክቱሬ

0
0
ተግባሩ በታሪክ ማህደር ውስጥ ዘመን እንዳይሽረው ሆኖ ከተፈፀመ ልክ ትናንት 56ኛ ዓመቱን ደፈነ። ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ.ም በአፍሪካ መዲናዋ አዲስ አበባ አይረሴው የአፍሪካውያን ታሪክ ተፃፈ፡፡ ከብዙ ውጣ ውረድና ድካም በኋላ ተሳክቶላቸው በነጻነት አርማቸው አዲስ አበባ የተሰባሰቡት 32ቱ ነፃ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ከግንቦት 14 እስከ 17 ቀን 1955 ዓ.ም ከመከሩ በኋላ ባለ 33 አንቀጹን የአፍሪካ […]

የአማራ ማህበር በኦሪጎን አሜሪካ ከሲያትል የአማራ ማህበር ጋር የመጀመሪያ ውይይት

0
0
የአማራ ማህበር በኦሪጎን አሜሪካ ከሲያትል የአማራ ማህበር ጋር የመጀመሪያ ውይይት
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live