Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአብርሃ ደስታ የሰሞኑ ምርጥ ዘገባዎች

$
0
0

የህወሓት የኮብልስቶን ፖለቲካ (መቐለ)
========================

አብርሃ ደስታየመቐለ ወጣቶች (የዩኒቨርስቲ ምሩቃን) ተደራጅተው በኮብልስቶን ስራ ለመሳተፍ ቢወስኑም የህወሓት መንግስት ሊያስሰራቸው እንዳልቻለ ገለፁ። ወጣቶቹ በኮብልስቶን ስራ ተሰማርተው ስራ ለመፍጠርና ህይወታቸው ለመቀየር በተገባላቸው ቃል መሰረት ቢደራጁም መንግስት ግን በዝቅተኛ ዋጋ (ትርፍ የሚገኝበት ሳይሆን ለኪሳራ በሚዳርግ) እንዲሰሩ እያስገደዳቸው ይገኛል።

የኮብልስቶን ገንዘብ በእርዳታ ከዎርልድ ባንክ የሚገኝ ሲሆን የህወሓት ባለስልጣናት የኮብልስቶኑ ፕሮጀክት ተከናውኖ ለሚመለከተው አካል እንደለመዱት የዉሸት ሪፖርት ማቅረብ ይፈልጋሉ። ይህ እንዳለ ሁኖ ከዓለም ባንክ ከተገኘው ገንዘብ ከወጣቶቹ ተቀንሶ ለሐላፊዎቹ የሚተርፍበት ሁኔታም ያመቻቻሉ።

አሁን ግን አንድ ችግር ተፈጠረ። ወጣቶቹ በስራቸው ትርፍ ማግኘት ይፈልጋሉ። ወጣቶቹ ትርፍ ካገኙ ለባለስልጣናቱ የሚተርፍ ገንዘብ (የሚመዘበር ገንዘብ) አይኖርም። ባለስልጣናቱም የኮብልስቶን ገንዘቡ መመዝበር ይፈልጋሉ። የኮብልስቶን ገንዘቡ ከተመዘበረ ግን ለወጣቶቹ የሚሰጥ ገንዘብ ያንሳል። ካነሰ ደግሞ ወጣቶቹ ይከስራሉ። ወጣቶቹ ደግሞ ኪሳራውን አልፈለጉትም። እናም አሁን ከባድ ዉጥረት ነግሷል።

ባለስልጣናቱ የኮብልስቶን ተጫራቾች በትንሽ ዋጋ እንዲሰሩ ያስገድዳሉ፤ ምክንያቱም የኮብልስቶን ስራ መቋረጥ የለበትም። ምክንያቱም የዓለም ባንክ ገንዘቡ ስለሰጣቸው ስራው ተሰርቷል ብለው ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ገንዘብ ደግሞ ማትረፍ ይፈልጋሉ። ወጣቶቹም መክሰር አይፈልጉም። እናም ወጣቶቹ ፍቃደኞች አይደሉም። ባለስልጣናቱ ደግሞ ወጣቶቹን ባለስልጣናቱ በፈለጉት የዋጋ መጠን እንዲሰሩ ያስገድዷቸዋል።

ከዚህ አልፎ የህወሓት ባለስልጣናት የኮብልስቶን ገንዘብ ከዓለም ባንክ የተገኘው በህወሓት ትብብር ስለሆነ በኮብልስቶን ስራ የሚሰማራ ማንኛውም ወጣት የህወሓት አባል መሆን እንዳለበት ትእዛዝ አስተላልፈዋል። የህወሓት አባል መሆን ብቻ በራሱ በቂ እንዳልሆነና በኮብልስቶን ስራ ለመሰማራት ባለስልጣናቱ ባዘዙት የዋጋ መጠን መስራት እንዳለበትም አክለዋል። በተጨማሪም ወጣቶቹ የሚያገኙትን ገንዘብ በደደቢት ማይክሮፋይናንስ (የህወሓት ነው) ማስቀመጥ እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል።

ወጣቶቹን እንዲሰሩ ማስገደድ ምን አመጣው? የሚያዋጣቸው ቢዝነስ ከሆነኮ በፍቃዳቸው ይሰራሉ? በዓለም ባንክ ገንዘብስ ለምን የፓርቲ አባል እንዲሆኑ ይገደዳሉ? የዓለም ባንክ ገንዘብ የሰጠው ለህወሓት አባላት ብቻ ነው እንዴ? ወጣቶቹ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ሲቀሩስ ለምን ማስፈራርያና ማስጠንቀቅያ ይሰጣቸዋል? ሐሳባቸው የመግለፅ መብት የላቸውም እንዴ?

እስከመቼ ነው በህወሓት የባርነት ቀንበር ስራ የምንኖረው? የህወሓት የአገዛዝ ስትራተጂ ከ”ከፋፍለህ ግዛ” ወደ “አስርበህ ግዛ” የተሸጋገረበት አጋጣሚ ነው ያለው። ህዝብ በሆዱ ተይዟል። ከተቃወመ የሚበላና የሚሰራ ያሳጡታል። በህወሓት አገዛዝ የወደቅንበት ምክንያት ድሆች ስለሆንን ነው። ህይወታችን በህወሓቶች (የመንግስት) እርዳታ ስለተጠለጠለ ነው። መቃወምን የሚያስፈራን ሆዳችን አቅፈን ስለምንኖር ነው።

ግን እስከመቼ? ከተባበርን ህወሓትን ከስልጣን ማውረድ እንችላለን። ከስልጣን ካወረድነው ደግሞ ነፃነታችን እናገኛለን። ነፃነታችን ካስመለስን የስራ ዕድል ይከፈትልናል። የስራ ዕድል ከተከፈተልን በልተን በሀገራችን በነፃነት መኖር እንችላለን።
__________________________________________________________________________________________

የመንግስት ጣልቃ ገብነት በሀይማኖት: የስብሃት ነጋ ምስክርነት
==========================

Sebhat Negaበሀይማኖት ጣልቃ ገብነት ጉዳይ በኢትዮጵያ ሙስሊም ማሕበረሰብና በኢህአዴግ መንግስት መካከል አለመግባባት መስፈኑ ይታወቃል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መንግስት በሀይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱ እንዲያቆም ሲጠይቁ መንግስትም የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ማሳሰሩ ይታወሳል። (ኮሚቴዎችን በማሳሰር የህዝብን ጥያቄዎች ማዳፈን ይቻል እንደሆነ እንጂ መመለስ ግን አይቻልም)።

መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ የሚገባው በተለያዩ መንገዶች ሊሆን ይችላል። አንዱና ዋነኛው ግን የሀይማኖት መሪዎችን በመደለል የፖለቲካ መሳርያ እንዲሆኑ ማድረግና የፖለቲካ ካድሬዎች የሀይማኖት መሪዎች አድርጎ መሾም ነው።

የፖለቲካ ሹመት (ካድሬነትና አገልጋይነት) ሌላ የሀይማኖት መሪነት ሌላ። ፖለቲካና መንፈሳዊ ህይወት የተለያዩ ናቸው። የፖለቲካ ሹመት ከሆነ በገዢው ፓርቲ ሊመረጥ ይችላል። የሀይማኖት መሪ ግን በምእመናን ነው መመረጥ ያለበት። ስራውም ፖለቲካ ሳይሆን ሀይማኖታዊ ነው የሚሆነው። ሀይማኖታዊ መሪው በፖለቲካ ተፅዕኖ ስር መውደቅ የለበትም።

የኢህአዴግ መሪዎች ሁሉንም የሀይማኖት ተቋማትን ለመቆጣጠር የራሳቸው የፓርቲ አባላት የሀይማኖት መሪዎች አድርገው ይሾማሉ። ጓደኛዬ ናስሩዲን በፌስቡክ ገፁ እንዳስቀመጠው ከሆነ አቶ ስብሃት ነጋ እንዲህ ተናግረዋል:

“ቅድም የፌደራሉ መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢው ሸህ ከድር እንዳለው የዱሮው እስልምና ሌላ ነው፡፡ እኔ ከድርን በፊት ጀምሮ ትግራይ ውስጥ አውቀዋለሁ፡፡ ምርጥ የሕወሓት ታጋይ ነበር፡፡ አብሮን ታግሏል፡፡ አሁን ደግሞ ሙስሊሙን እያገለገለ ነው፡፡ እስልምና እነዚህ የታሠሩት ሰዎች እንደሚሉት አይመስለኝም፡፡ እስልምና እነዚህ ሰዎች እንደሚያሳዩት ዓይነት እምነት ከሆነ እንደ እምነት አያስፈልግም፡፡ ፈፅሞ ሰዎቹ ለሀገር አይሆኑም፡፡”

ሼህ ከድር የሙስሊሞች ሀይማኖታዊ ተቋም የመጅሊስ ምክትል ሰብሳቢ ነው (ወይም ነበር)። ግን ሼህ ከድር የህወሓት ታጋይ ነበር። የህወሓት አባል ነው። ስለዚህ ሼህ ከድር የፖለቲካ መሪ እንጂ የሀይማኖት መሪ አይደለም። መጅሊስ የፖለቲካ ተቋም አይደለም። የፖለቲካ ሰው አይደለም የሚፈልገው። መጅሊስ የሀይማኖት ተቋም ነው። የሀይማኖት መሪ ይፈልጋል። እንደምናየው ግን የመጅሊስ አመራር አባላት የሀይማኖት መሪዎች ሳይሆኑ ፖለቲከኞች (እንዲሁም የጉሪላ ታጋዮች) ናቸው። እንዴት ይሆናል? ይሄ ተግባር ጥያቄ አያስነሳም? በዚህ መሰረት የሙስሊሞች ጥያቄ ትክክል ነው ማለት ነው።

ሙስሊሞቹ እንደ ምእመናን የሀይማኖት መሪ አያስፈልጋቸውም? “በሀይማኖታችን የፖለቲካ ካድሬዎች አያስፈልጉንም። የሀይማኖቱ እውቀት ያላቸውና በምእመናኑ እውቅና ያላቸው ሀይማኖተኞች እንዲመሩን እንፈልጋለን!” ብለው ቢጠይቁ አግባብነት የለውም? ከመቼ ጀምሮ ነው በማርክሲስታዊ አስተሳሰብ ያደገ የህወሓት ታጋይ ሀይማኖት ኖሮት የመጅሊስ ምክትል ሰብሳቢ የሚሆነው? ወይስ ሙስሊሞችን ለመቆጣጠር ነው የተፈለገው? ደግሞ የሀይማኖቱ ተከታዮች ሳይደግፉት?! የሀይማኖት መሪ’ኮ የምእመናኑ ድጋፍና እውቅና ያስፈልገዋል።

ሙስሊሞች ስለሀይማኖታቸው ሲጠይቂ ሌላ ስም ከመስጠት መጀመርያ መንግስት ከሀይማኖቱ እጁ ያንሳ። ካድሬዎቹን የሀይማኖት መሪዎች እያደረገ አይሹሙብን! ካድሬ በትምህርትቤት ይሾማል፣ በቤተክርስትያን ይሾማል፣ በመጅሊስ ይሾማል!??? ኧረ ተዉ ኢህአዴጎች! ፖለቲካና ሀይማኖት እንለይ!

ሁሉም ሃይማኖቶች ከፖለቲካ ነፃ የሆኑ የሀይማኖት መሪዎች ያስፈልጉዋቸዋል። የሀይማኖት ጉዳይ የመንግስት ጉዳይ ሳይሆን የምእመናኑ ጉዳይ ነውና።

ሙስሊሞች (ና ክርስትያኖች) ሆይ! መንግስት በሀይማኖታቹ ጣልቃ እንዲገባ የማትፈልጉ ከሆነ የመንግስትን በሀይማኖት ጣልቃ የመግባት ተግባሩ አጥብቃቹ ተቃወሙት። እየተቃወማችሁት ነው። ግን መፍትሔ የለም፣ ሰሚ የለም። ለጥያቅያቹ መልስ ከመስጠት ይልቅ መንግስት እያሰራቹ፣ እያሰቃያቹ ይገኛል። የመንግስት መፍትሔ ኮሚቴዎችን ማሳሰር ከሆነ በኢህአዴግ እምነት ሊኖራቹ አይገባም። እናም ኢህአዴግ መፍትሔ ሊያመጣላቹ እንደማይችል አረጋግጠዋል። ስለዚህ ምን ይደረግ? የሀይማኖት ጥያቄው ታፍኖ ይቅር?

የሀይማኖት ጥያቄማ መፍትሔ ይሻል። ምክንያቱም የሀይማኖት ጥያቄው ትክክለኛና አስፈላጊ ነው። ጥያቄው ሁላችን የምንደግፈው ነው። ጥያቄው ትክክል ከሆነ መልስ ያስፈልገዋል። መልስ የሚሰጥ አካል (መንግስት) ከሌለስ? መንግስት መልስ ሊሰጥ እንደማይችል ካረጋገጠልን ለህዝብ የሚቆረቆር፣ የህዝብን ጥያቄዎች መመለስ የሚችል፣ የሀይማኖት ችግሮች የሚፈታ፣ የሀይማኖት ነፃነት የሚፈቅድ፣ ሰብአዊ መብት የሚያከብር ዴሞክራሲያዊ መንግስት ያስፈልገናል ማለት ነው። ስለዚህ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ለመመስረት ጥረት እናድርግ። የምርጫ ድምፃችን የህዝብን ጥያቄዎች ሊመልሱ ለሚችሉ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲዎች እንስጥ። የህዝብን ጥያቄ መመለስ የሚያስፈራው ኢህአዴግ ከስልጣን (በዴሞክራሲያዊ መንገድ ወይ ምርጫ) እናውረደው። ሌላ ፓርቲን በመምረጥ ኢህአዴግን አውርደን ጥያቄያችንን የሚመልስልን ሌላ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ስልጣን እንዲይዝ እናድርግ። ከዛ የሀይማኖት ይሁን የሌላ ነፃነታችን ይከበርልናል። ካልተከበረ ትግላችን ይቀጥል።
__________________________________________________________________________________________

ኢትዮጵያዊው ዓረናና ኤርትራዊው ህወሓት!
=======================

Arena-Tigray-logoዓረናዎች “ህወሓት ኤርትራን ያስቀድማል። በመሆኑም ህወሓት የሻዕቢያ ተላላኪ ነው” ስንል ህወሓቶች ደግሞ “ዓረና ከትግራይን ህዝብ ጠላቶች ከሆኑ እንደነ አንድነት ፓርቲ ጋ ለመዋህድ ጥረት እያደረገ ነው” ይላሉ።

እርግጥ ነው፤ ዓረና ኢትዮጵያዊ ነው። ከኢትይጵያውያን ድርጅቶች ጋርም አብሮ ይሰራል። ከአንድነት፣ ደቡብ ሕብረት፣ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ እና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ፓርቲዎች ጋር ለመዋሃድና አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነው።

ዓረና እንደ ህወሓት ኤርትራዊ አይደለም። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ለመጉዳት ከሻዕብያ ጋር በማበር አይሰራም። ኢትዮጵያውያንን በጠላትነት እየፈረጀ የሻዕብያ አገልጋይ አይሆንም። ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን እንጂ ኤርትራውያን አይደለንም። ኤርትራውያንን ለመጥቀም ኢትዮጵያውያንን አንበድልም። ስለዚህ ከሻዕብያ በላይ አንድነት ፓርቲን እናስቀድማለን። ምክንያቱም አንድነት ፓርቲ ኢትዮጵያዊ ነው። ኢትዮጵያም የሁላችን የጋራ ነች። ምናልባት ከሻዕብያ ጋር አብረን የምንሰራው የኢትዮጵያና የኤርትራ የጋራ ጥቅም የሚከበርበት መድረክ ሲፈጠር ብቻ ነው።

ዓረናና ህወሓት አልተሳሳቱም። ዓረና ከኢትዮጵያውያን ጋር ይሰራል። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ነው። ህወሓት የሻዕብያ ተላላኪ ነው። ምክንያቱም ህወሓት ኤርትራዊ ነው። ህወሓት ኤርትራዊ መሆኑ ችግር የለውም። ችግር የሆነው ህወሓት ኤርትራዊ ሁኖ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ለኤርትራ አሳልፎ እየሰጠ ግን የኢትዮጵያ መንግስትነት መቆጣጠሩ ነው። ለኤርትራውያን እየሰራ ኢትዮጵያውያንን እወክላለሁ ማለቱ ነው ችግሩ። ህወሓት ለኤርትራ መቆም የሚያስደስተው ከሆነ ኤርትራን ያስተዳድር፤ የኤርትራን ህዝብ ይወክል። ኢትዮጵያን እያስተዳደረ፣ የኢትዮጵያ ህዝብን እወክላለሁ እያለ ለኤርትራ ጥቅም መስራቱ፣ ኤርትራውያንን መወከሉ ግን ወንጀል ነው። ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስትነት ከተቆጣጠረ ለኢትዮጵያውያን ጥቅም መስራት ነበረበት።

ህወሓት የኢትዮጵያ ስልጣን ይዞ ኤርትራን ለማስገንጠል ይሰራል፣ ዓሰብን ለኤርትራ ይሰጣል፣ ዓሰብ የኛ መሆኑ ስንከራከር ህወሓት ከኤርትራውያን በላይ ዓሰብ የኤርትራ መሆኑ ይሟገታል። ለኤርትራውያን መቆም ካለበት ለምን ወደሚወክለው ኤርትራ አይሄድም?

ዓረና ከኢትዮጵያውያን ድርጅቶች መዋሃዱን ይቀጥላል። ህወሓትም ለኤርትራውያን ማገልገሉ ይቀጥል። በዚሁ መሰረት “ዓረና ከአንድነት ፓርቲ ጋር እየተወሃደ ነው” ብላች ሁ ክሰሱን። ለኛ ችግር አይሆንም፤ ምክንያቱም በኢትዮጵያውነታችን አምነን በኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን አማራጭ የፖለቲካ አቅጣጫ የሚያቀርብ ጠንካራ ሀገራዊ ፓርቲ የመመስረት ዕቅድ አለን። ህወሓትም ሻዕብያን ማገልገሉ ይቀጥል ምክንያቱም ህወሓት የኤርትራ ተወካይ (በኢትዮጵያ) መሆኑ እናውቃለን።

ህወሓት ግን ዓረና ከአንድነት ጋር የመዋህዱ ዜና ሲሰማ እንዲህ ከተደናገጠ ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጭምር ስንዋሃድስ ምን ሊሆን ነው? ዓረና ከአንድነት ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ብዙ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋርም ይወሃዳል። ጠንካራ ሀገራዊ ፓርቲ መመስረት እንፈልጋለንና።

ህወሓት ኤርትራን ሲያስበልጥ ዓረና ግን ኢትዮጵያንን ያስቀድማል።
__________________________________________________________________________

“የካቲት 11″ን እናክብረው?!
=============

የየካቲት 11 ዓላማ ዴሞክራሲ፣ ነፃነት፣ ሰላምና ልማት ነበር። ህዝቦች ታገሉ፤ መስዋእት ከፈሉ፤ ለነፃነት ሲሉ። ግንቦት 20 ሆነና ስልጣን ተያዘ። መስዋእት የተከፈለበት ዓላማ ፍሬ አፍርቶ ከሆነ ለማረጋገጥ በህይወት የተረፉ ታጋዮች ጠየቁ። ታጋዮቹ በጠላትነት ተፈርጀው በ1985 ዓም ተባረሩ፣ ታሰሩ፣ ተገደሉ። የወላጆቻችን መስዋእትነት ፍሬ ለመቅመስ ሞከርን። በድንጋይ ተወገርን። ወላጆቻችን መስዋእት የከፈሉ ለኛ ነፃነት ነበር።

ነፃነት የመቃወም፣ የመደገፍ ወይም ከሁለቱም ዉጭ መሰለፍን ያጠቃልላል። ወላጆቻችን የተሰዉለት የነፃነት ዓላማ አለን ብለን የፈለግነውም ሐሳብ ለህዝብ ማቅረብ መረጥን። ስለተቃወምን ታፈንን። እናም የየካቲት 11 መነሻ ዓፈና ነበር፤ መድረሻውም ዓፈና ሆነ። ፀረ ዓፈና መታገል እንዳለብን ገባን። የወላጆቻችን ዓለማ ነፃነት ነበር። የኛ ዓላማም ነፃነት ነው። ስለዚህ የኛና የወላጆቻችን ዓላማ አንድ ነው፤ ነፃነት። ያሁኗ ህወሓት ዓላማ ግን ዓፈና ሆኗል።

ያሁኗ ህወሓት በተግባር እያፈነች በሚድያ ግን “የካቲት 11″ን ማክበሯ አይቀርም። “ለካቲት ብርሃን ዉፁዓት እያ!” እያለችም እንደተለመደው ማደንቆሯ አይቀርም። የየካቲት 11 ዓላማ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የሰማእታት ልጆችን በድንጋይ መውገር ነበር ማለት ነው? ነፃነት ማለት ጭቆና ማለት ነው?

በተግባር ስንቃወም ታፈንን። ስንቃወም ከታፈንን መቃወማችን ትክክል ነው ማለት ነው። ምክንያቱም እኛ ወጣቶች የመቃወም መብት አለን። “ስንቃወም ለምን እንታፈናለን?” ብለን መቃወም እንችላለን። የህወሓት የዓፈና ተግባር የኛን የመቃወም አስፈላጊነት የሚያረጋግጥ ነው።

ስለዚህ የወላጆቻችን የትግል ዓላማ ተጠልፎ ለስልጣን ማራዘምያ ሆኗል። ስልጣንም ልማት ለማፋጠንና ነፃነትን ለማረጋገጥ ከማዋል ይልቅ ዜጎችን ለማፈን እየዋለ ነው። ስለዚህ የወላጆቻችን መስዋእት ግቡ አልመታም።

በኔ አመለካከት ህወሓት በሁለት ይከፈላል፤ ስልጣን ፈላጊ መሪዎቹና ነፃነት ፈላጊ ታጋዮቹ። ስልጣን ፈላጊ የህወሓት መሪዎች ስልጣን ጨብጠው ህዝብ እየጨቆኑ ይገኛሉ። ነፃነት ፈላጊ ታጋዮቹ ደግሞ ለነፃነት ሲሉ መስዋእት ከፍለው ለራሳቸውም ነፃነት ተነፍገው እየተጨቆኑ ይገኛሉ። ጭቆናን መቃወም ሲጀምሩ ደግሞ በድንጋይ ይወገራሉ (አስገደ ገብረስላሴ በዓዲግራት)። ስለዚህ የህወሓት የነፃነት ታጋዮች ተጨቁነው ይኖራሉ። የህወሓት መሪዎች ደግሞ ታጋዮቹን በማባረር፣ የራሳቸውን ቤተሰብ ይዘው የሀገር ሃብት እየበዘበዙ ህዝቦችን በማሸበር ይገዛሉ።

ስለዚህ የህወሓት ታጋዮች የነፃነት ዓላማ ተኮላሽተዋል። የወላጆቻችን የነፃነት ተልእኮም ተጠልፏል። የወላጆቻችን ዓላማ አሁን ለምናየው ዓፈና የታለመ ነበር ካላችሁኝ አላምናችሁም። ካመንካችሁ ግን ዓላማው ስህተት ነበር እላችኋለሁ። ምክንያቱም የመስዋእትነት ዓላማ ነፃነት ነው። የወላጆቻችን ዓላማም ነፃነት ነበር። ስለዚህ ነፃነታችንን በተግባር መከወን አለብን። ነፃነታችንን ከተነፈግን ግን ነፃነታችንን ለማስመለስ መታገል ይኖርብናል።

ነፃነት የሌለው ህይወት አንፈልግም። እየኖርን አንሞትም።


አንድነት እና መኢአድ በባህርዳር የካቲት 16 ለሚያደርጉት የተቃውሞ ሰልፍ ለከንቲባው ጽ/ቤት ያስገቡት ደብዳቤ

$
0
0

አንድነት እና መኢአድ በባህርዳር ከተማ የካቲት 16 ቀን 2014 ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋሉ። ለከተማው አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ያሳወቁበት ደብዳቤ የሚከተለው ነው።
bahar dar

ጥንቃቄ የሚያሻው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የትግል ጉዞ (ገዛኽኝ አበበ ከኖርዌይ)

$
0
0

miyazia 30
አሁን አሁን በፊስቡክ፣ በየሚዲያው እና በየማህበራዊ ድህረ ገጹ እንደምናየው እና እንደምንሰማው ወያኔ ወይም የወያኔን የልብ አጀንዳ ለማስፈጸም ጎንበስ ቀና እያሉ ያሉ ቅጥረኞች ድርጅቶች ነን ባዮች የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማደናገር በየሚዲያው መንቀሳቀስ ጀምረዋል :: እነዚህ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በአንድ ጎኑ ወያኔን የሚቃወሙ እየመሰሉ በሌላ በኩል ደግሞ የወያኔን መንግስት ለመፋለም ቋርጠው የተነሱትን ጠንካራ እና እራሳቸውን በማደራጀት ላይ የሚገኙትን ፣ ለወያኔ መንግስት አስፈሪ እና ስጋት በመሆን ላይ ያሉትን እራሱም ስጋት ይሆኑብኛል ብሎ የሚፈራቸውን የፖለቲካ ድርጅቶችን ወይም የፖለቲካ ሰዎችን በማሳደድ እና በመቃወም የሚሰሩትን ስራ እና ትግላቸውን በማጣጣል ፣በማንቋሸሽ የበሬ ወለደ ያህል የሃሰት ቅስቀሳቸውን ሲደሰኩሩ መስማት የተለመደ ነገር ሆኖል:: በእነዚህ የፖለቲካ ድርጅቶች ላይም ሆነ የፖለቲካ ሰዎች ላይ በየሚዲያው የሚደረገው የሀሰት የወሬ ዘመቻ (propaganda) ሕዝብን ግራ ለማጋባት እና የወያኔን የስልጣን እድሜ ለማራዘም የወያኔ መንግስት በስፋት በየ አቅጣጫው ያሰማራቸው ለወያኔ እየሰሩ ያሉ አስመሳዬች የወያኔ ምልምሎች ሲሆኑ ስራቸውም የተቀዋሚዎችን የፖለቲካ ትግል መሰለል እና ማዳከም ሲሆን ይህም የሚያሳየው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭም እየተደረገ ያለው ፖለቲካዊ የትግል ጉዞ የወያኔን ባለስልጣኖች ምን ያህል እረፍት እንደነሳቸው እና እንቅልፍ እንዳሳጣቸው ነው : :

ከዛሬ ዘጠኝ ዓመት በፊት ማለትም በ1997 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ የነበረውን የፖለቲካ መነቃቃት ሁላችንም የምናስታውሰው ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ አይምሮ ሊጠፋ የማይችል አጋጣሚ እንደነበር እና ኢትዮጵያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የወያኔን የኢሕአዴግን መንግስት የስልጣን እድሜ ሊያሳጥር የሚችል ጥሩ አጋጣሚ ተፈጥሮላት እንደነበር ሁሉም ሰው የሚስማማበት ሀቅ ሲሆን በጊዜው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ መንግስት ላይ የነበራቸውን የመረረ ጥላቻ በአደባባይ በመውጣት ለአለም ሕዝብ ያሳዩበት ወቅት ነበር ::በጊዜውም ሕዝቡም በወያኔ መንግስት ላይ ያለውን የመረረ ጥላቻ በግልጽ በማሳየቱ ወጣት ወገኖቻችን በአንባባ ገነኑ የወያኔ መንግስት እንደ ሌባ እና እንደወንበዴ ተቆጥረው በግፍ የተጨፈጨፉበት እና የተገደሉበትን ጊዜ ማንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊራሳው የማይችል እውነታ ነው :: በዛን ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ በመፈለግ እና በወያኔ የዘረኝነት አገዛዝ በመማረር ታሪክን ሊሰራ ቆርጦ መነሳቶን በተግባር አስመስክሮል:: ለዚህም ማስታወሻ ይሆነን ዘንድ በሚያዚያ 30/1997 በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የወያኔን አንገት ባስደፋ እና ቅስም በሰበረ መንገድ ከ2.5 ሚሊዮን የሚበለጥ ሕዝብ ማንም ሳያስገድደው አደባባይ በመውጣት ያሳየው ትዕይንት ማረጋገጫ ነው: ::

በወቅቱ በነበረው የሕዝቡ አንድነትእና ህብረት ፣ ሕዝቡ ለለውጥ በነበረው ጉጉት ያደርግ የነበረው እንቅስቃሴ ለወያኔ መንግስታት አስደንጋጭ ከመሆኑ የተነሳ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፍርሀት ደንብረው በደብረ ዘይት በሚገኘው አየር ሀይል ተሸሸገው ህዝቡ መብራት ጠፍቶበት፣ ደግሞም ዝናብ ዘንቦ ወደ ቤቱ ከተመለሰ በኋላ ወደ መንበራቸው መመለሳቸውን በጊዜው የነበሩ የአይን አማኞች ተናግረዋል:: : ከዛም በመቀጠል ግንቦት 7 19 97 የነበረው ክስተት በየሰው ፊት ላይ ይነበበ የነበረውን ተስፋ ለመግለጽ ያስቸግር ነበር :: ወጣቶች በሙሉ ሀይላቸው ፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የገቡበት፣ ሁሉም ሰው ፍርሃት እና የፍርሃት ምንጭ የሆነውን የወያኔን አገዛዝ ደህና ሰንብት ያለ ይመስል ነበር በወቅቱ ይሆን እንጂ ምን ያደርጋል በጊዜው ተፈጥሮ የነበረውን የፖለቲካ መነቃቃት በአንዳንድ የበግ ለመድ በለበሱ አስመሳይ ፖለቲከኞች እንደነ አቶ ልደቱ አያሌው በመሳሰሉ ሰዎች በጊዜው የነበረው የፓለቲካ መነቃቃት (revival ) መኮላሸቱ እና እንደ ጉም በኖ መጥፋቱ እስከ ዛሬም ድረስ አብዛኛውን ለውጥ እና ነጻነት ናፋቂ ሀገር ወዳት ኢትዮጵያ ዜጎችን የሚያስቆጭ እና የሚያንገበግብ ሲሆን ወያኔን ለማንበረከክ እና ከስልጣን ለማስወገድ የነበረው ወርቃማ ዕድል መበላሸቱ አብዛኛውን የኢትዮጵያን ሕዝብ አስቋጥቷል ተስፋም አስቋርጦል:: በጊዜውም በነበረው ክስተት የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብም ልብ ተሰብሮል:: እስከዛሬም ድረስ አንዳንድ ሰዎች በኢትዮጵያ የሚደረገውን ማንኛውንም ፖለቲካዊ ትግል በጓሬጥ እና በጥርጣሬ ዳር ላይ ቆመው እየተመለከቱት ይገኛል ::

የ19 97 ምርጫን ተከትሎ የተፈጠረውን የፖለቲካ መነቃቃት መኮላሸቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ባለፉት ጊዚያቶች የነበሩት የፖለቲካም ሠዎች ሆኑ የፓለቲካ ድርጅቶች ባረጀ እና በገረጀፈ ጭፍን የፖለቲካ አመራር እና የትም በማያደርስ አመለካከት የወያኔን የስልጣን እድሜ እያራዘሙት ይገኛሉ:: እንደእኔ አመለካከት የወያኔ ኢሕአዲግ የስልጣን እድሜ እስከዛሬ ሊረዘም የቻለበት ዋንኛው ምክንያት በራሱ በኢሕአዲግ ጥንካሬ ሳይሆን በተቃዋሚዎች በደከመ እና በተልፈሰፈሰ አመራር ነው:: በኢትዮጵያ ውስጥ ያለፉትን 22 አመታቶች ብዙ የተቃዋሚ ፓርቲ ተብለው ስም የተሰጣቸው ስብስቦች ቢፈጠሩም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ አንዳችም የፈየዱት ነገር ሳይኖር ብዙ ጊዚያቶች አልፈዋል:: አሁን አሁን ግን እንደምናየው እንደነ አንድነት፣ አራናት ትግራይ እና ሰማያዊ ፓርቲ ያሉ በወጣቶች የተገነቡ የፓለቲካ ፓርቲ ድርጅቶች መፈጠራቸው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተስፋ ቆርጦ የነበረው ሕዝብ ላይ እስትንፋስ እየዘሩበት ይገኛሉ:: ከምርጫ 97 በኋላ በነበሩት አመታቶች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ልቡ ተሰብሮ እና ተስፋ ቆርጦ የተኛውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እየቀሰቀሱት ቢሆንም ራዕያቸውን ወደ ፊት ለማስጓዝ ብዙ የቤት ስራ ከፊታቸው የሚጠበቅባቸው ይመስለኛል:: በራቸውንም ነቅተው ከጠላት ወያኔ በመጠበቅ በጥንቃቄ መጓዝ ይገባቸዋል:: ምክንያቱም እስከዛሬ ወያኔ እንደ እስስት እየተለዋወጠ እና እንደ እባብ እየተሽለኳለኳ ስንቶቹን የፖለቲካ ፖርቲ ድርጅቶችን እንደሽመደመዳቸው አይተናልና ::

በምርጫ 97 ጊዜ የነበረውን ቅንጅት ማንም ሰው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደዛ ፍርክስክሱ ይወጣል ብሎ የጠበቀም የገመተም አልነበረም ነገር ግን ባልተጠበቀ ሁኔታ ባልተገመተ ሰአት ብትንትኑ ሊወጣ የቻለበት ምክንያት ጥንቃቄ በጓደለው አካሄድ እና በተዝረከረከ አሰራር የተነሳ ለጠላታቸው የወያኔ መንግስት መጠቀሚያ መሆናቸው ነበር :: ወያኔም እንደ እባብ ተሹለክልኮ በመካከላቸው ለመግባት እና ለመበታትን ጊዜም አልወሰደበትም ነበር : :: በወቅቱም የቅንጅት መፈራረስ ወያኔ እና የወያኔ ካድሬዎች ጮቤ ያስረገጠ ክስተት የነበር ሲሆን ወያኔ እንዳለመው እና እንዳሰበው ለተወሰነም ጊዚያቱችም ቢሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዳፍኖ የጠነከረ የፖለቲካ ድርጅት በሌለበት በማን አለብኝነት ለአጭር ጊዜም ቢሆን ተረጋግቶ እንዲቀመጥ አስችሎታል:: ይሁን እንጂ አሁን ላይ ግን ነገሮች ሁሉ እየተቀየሩ እና እየተለወጡ በውስጥም በውጭም ያለው የፖለቲካው ትግል እሳት እየነደደ እና እየተፋፋመ ሲሆን በቅርብ እንኮን እንደምንመለከተው የህወሃት ወያኔ መንግስት የሚመካበት የትግራይ ህዝብ ሳይቀር የህውሃት መንግስት ለትግራይ ሕዝብ እንደማይመጥን ለወያኔ መንግስት በግልጽ በአደባባይ እየነገሩት ይገኛሉ::በወያኔ መንግስት የስልጣን አገዛዝ መገዛት ያልሰለቸው እና ያልመረረው ብሔር እና የሀገሬቱ ዜጋ የለም :: ለሆዳቸው እና ለጥቅማቸው ህሊናቸውን ሽጠው ከሚኖሩት ከራሱ ከወያኔ ካድሬዎች በስተቀር በመሆኑም እየተፋፋመ ያለው የፓለቲካው ትግል መነቃቃት መላውን ሀገር ወዳድ የኢትዮጵያ ዜጎችን ከዳር እስከዳር ማዳረሱ እና ማነቃነቁ የማይቀር ሀቅ ነው :: ስለዚህ የፖለቲካውን እሳት እያጋጋሉ እና እያፋፋሙ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆነ የፖለቲካ መሪዎች ባለፈው ከነበረው ስህተት በመማር በራቸውን ከጠላት ወያኔ ተጠንቅቆ በመጠበቅ ትግሉን ማስቀጠል እና ማፋፋም ይጠብቅባቸዋል :: ወጣቱ ለለውጥ ልቡ ተነሳስቷል የወያኔ ኢህአዲግም የስልጣን ዘመን የጭቆና አገዛዝ የሚከስምበት ጊዜ እሩቅ አይሁንም ::

ኢትዮጵያ በቆራጥ ታጋይ ልጆቿ ከወያኔያዊ አገዛዝ ነጻ ትወጣለች::

gezapower@gmail.com

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

“[ከፖለቲካው ውጭ ሃገር ቤት መመለስ የሚያስደስተኝ] ከብርድ መላቀቁ ነው”–ሌንጮ ለታ ለቪኦኤ

$
0
0

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰኞ ዕለት ለጋዜጠኞች ቃለምልልስ ከሰጡ በኋላ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ለቪኦኤው ሄኖክ ሰማዝጌር ቃለምልልስ ሰጥተዋል። በተለይ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሌንጮ ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ወረቀት አስገብተዋል በሚል በተናገሩት ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። “”በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል ያስገባነው ደብዳቤ የለም” ሲሉ ጠ/ሚ/ሩ በአደባባይ የተናገሩትን አስተባብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በቃለምልልሳቸው መጨረሻ “[ከፖለቲካው ውጭ] ሃገር ቤት መመለስ የሚናፍቀኝ ከብርድ መላቀቁ ነው” ሲሉ መልሰዋል። በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ ነው ወይ ወደ ኢትዮጵያ የምትገቡት? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም ሌንጮ ምላሽ ሰጥተዋል። “ደርግ ከወደቀ በኋላ አንድ ቀንም ጠመንጃ የያዝኩበት ቀን የለም፤ አዝዤም አላውቅም” በሚል የተናገሩበት ቃለምልልሱ የሚከተለው ነው፦

lencho leta

ነይ ነይ (ለዘፈን የሚሆን ግጥም) – (ከፍቅሬ ቶሎሳ፣ ዶ/ር)

ዶ/ር መረራ ጉዲና የሕይወቱ ምስቅልቅሎች –የእብደትና ቅሌት ቅልቅል – (ዶ/ር አማረ ተግባሩ ከላይቤሪያ)

$
0
0

Dr merera gudina Book
ከዚህ በታች ላቀረብኩት ፅሑፍ የመረጥኩት ርዕስ ዶ/ር መረራ ጉዲና “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ትግል ምስቅልቅል ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ” (2006 2ተኛ ዕትም) በሚል ርዕስ ያቀረበውን መፅሐፍ ከዳር እስከዳር በማሰስ ላይ የተመሰረተ አይደለም። ይህ ርዕስ የሚመለከተው ደራሲው በመፅሐፉ ገፆች በመደዳውና አልፎ አልፎም እየተመለሰ ስሜን በማንሳት የዛሬ ሰላሳ አምስት ዓመት ገደማ በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ይመራ የነበረው መንግሥት በጅባትና ሜጫ አውራጃ ጥቁር እንጭኒ በሚባል አካባቢ በመላው ኢትዮጵያ ሶሺያሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) አባላት ላይ ከፈፀመው አረመኔያዊ ግድያ ጋር ከማነካካት ያለፈ የ”ክህደት” (የመረራን ቃል ለመጠቀም) ወንጀል ፈፅመሃል በሚል እጅግ ምሬትና ብሶት ባልተለየው አንደበት በመረጃ ያልተደገፈና ሊደገፍም የማይችል በርካታ ክሶች በመቃወም መልስ ለመስጠት ነው። ስለዚህም በዚህ ግለሰብ የቀረበውን በጎ ትውስታዎችም ሆነ የሕይወት ምስቅልቅሎቹን በሰፊው ለመገምገምና አስተያዬት ለመስጠት አልተነሳሁም። ከኔ ይልቅ ይህ መዘክር ምን ያህል ብስለትና ተመክሮን የተላበሰና በአንደበቱም ሆነ ባቀራረቡ አንባቢን ለመማረክ የቻለ ሥራ ለመሆኑ ለመናገር ብቃቱ ያላቸው ይመለሱበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ባለፉት 30 እና 40 ዓመታት በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ላይ በየትኛውም ርዕዮተ ዓለማዊና ድርጅታዊ አካባቢ ለነበሩ፣ላለፏና አሁንም በመሰላቸውና ባመኑበት ተሳትፎ ላላቸው ሁሉ ከበሬታን ያዋደደ ሙገሳም ሆነ ነቀፌታ በማቅረብ ምን ያህል እንደተዋጣለት የሚፅፉና የሚያወያዩ ወገኖች ብቅ ብቅ ማለታቸውን ያየሁ በመሆኑ እኔን በሚመለከተው ጉዳይ ላይ ብቻ በማተኮር ምላሽ አቀርባለሁ።

ከሁሉ አስቀድሞ የዛሬ ሰላሳ አምስት ዓመታት ገደማ በጅባትና ሜጫ፣ በጫንጮ፣ በሲዳሞም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች በድርጅቱ አባላት ላይ የደረሰውን እልቂትና ጭፍጨፋ ሳናነሳውና “እከሌ መረጃ ሰጥቶ ነው እከሌ ደግሞ ተዝረክርኮና ተባብሮ ወይም ጠቁሞና ክህደት ፈጽሞ ነው” በሚል የርስ በርስ መካሰስ ውስጥ ሳንገባና ወደዚያ እጅግ መሪርና አሳዛኝ ታሪክ ሳንመለስ አፈር እንደለበሰ መካነ መቃብር ሳንነካካው እንዳለና እንደተከበረ ብንተወው የተሻለ ነበር እስከማለት እደፍራለሁ። ምን እንደተከሰተና ምን በመሳሰሉ በርካታ ምክንያቶች ያንን የመሰለ እልቂት ሊደርስ እንደቻለ ለመናገር ድፍረቱ እንኳ ቢኖረን የዚያኑ ያህል ደግሞ በተለይ በጊዜው የግለሰቦችን ሚና በሚመለከት በትክክልና እርግጠኛ ሆነን ልንናገርባቸው የማንችልባቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን በመገንዘብና ቋሚ ምስክር ሊሆኑ የሚችሉትም ሰዎች ከሞት ተነስተው ሊመሰክሩ እንደማይችሉ በማወቅ ይህንን ታሪክ በተመለክተ ጥንቃቄና ሃላፊነት የተሞላው አቀራረብ መምረጥ በተገባ ነበር። ከሁሉም በላይ የምንቀሰቅሰው የኛን ስሜት ብቻ አለመሆኑን በማሰብና ሌሎችንም ብዙ ሰዎች መልሰን ወደዚህ ጉዳይ ውስጥ በማስገባት እንደገና ደግመን ልናሳዝናቸው እንደምንችል በማስተዋል ያንን አስከፊ ታሪክ በዚህ መልክ ባንነካካ የተሻለ ነበር። ወደዚህ ዘመን እንመለስ ያልንም እንደሆነ ዓላማችን ርስ በርስ የመካሰስን ባህል ከሰላሳና አርባ ዓመታትም በኋላ መልሶ ነፍስ እንዳይዘራ ተጠንቅቀንና በአሳማኝ መረጃ ተደግፈን ከሁሉም በላይ ላለውና ለመጭው ትውልድ ምን ሊያስተምር እንደሚችል አስበን ይመስለኛል። በታሪካዊው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ ’ረዳት ፕሮፌሰር’ ደረጃ የሚታወቅ ምሁር ይህንን የመሰለ ከበሬታ ያለው ማዕረግ ላይ የደረሰው መረጃዎችን በሚገባ በማጥናትና በርካታ አመሳካሪ ሊሆኑ የሚችሉ ተጨማሪ መረጃዎችን በማከል ወደ እውነት የቀረበ ሥራ ለማቅረብ ያለውን ችሎታ አስመስከሮ እንጂ ባቋራጭ ሊሆን እንደማይችል የታወቀ ነው። ራሱ የተሳተፈበትም ታሪክ ቢሆን ስሜቱን ዋጥ በማድረግ፤ ትዝታውን በጥናት አጠናክሮ ለመጨረሻው አንባቢ (audience) ለማቅረብ ሲወስን ላለውና ለመጭው ትውልድ ምን ሊያስተምር እንደሚችል የሚመዘንበትና ምርምር ለሚጠይቀው ኤትካል መርህ ላሳየው ተገዥነት የሚመሰከርለት እንጂ የሚመሰከርበት እንዳይሆን ተጠንቅቆ ይመስለኛል። እኔ በተማርኩበትና ለ13 ዓመታት ባስተማርኩበት አገር ባለ ዩኒቨርስቲ በተራ ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እንኳን የግለሰብን ስምና ታሪክ ያለበቂ መረጃ ያዋረዱ የዩኒቨርስቲ መምሀራንና ፕሮፌሰር ድረሰ የደርሱ ሰዎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው ከሳሽ ሳይቀርብባቸው ዩኒቨርስቲው ራሱ በራሱ የኤቲክ ኮሚቴ እንዲከሰሱ በማድረግ ዲስፕሊነሪ ቅጣት ብቻ ሳይሆን መምሀራኑን ከሚወክለው የሙያ ማህበር ለተውሰኑ ዓመታት እንዲታገዱ ያደረገበት ሁኔታ እንዳለ መረራ እንዲያውቀው እፈልጋለሁ። በዚህ መለኪያ የሄድኩ እንደሆነ መረራ ጉዲና ከመንደር ትምህርት ቤት መምህር ያነሰ ሰው ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የታዩኝና ያሳዘኑኝ የሱ ተማሪዎች ናቸው። እኔም አልገፋሁበትም እንጂ ለነገሩ ያህል የፖላቲካል ሳይንስ ተማሪ ነበርኩ። መረራ ምን እንደተማረና እንዳነበበ ተማሪዎቹንም ምን እንደሚያስተምር ግራ የሚያጋባ ሆኖብኛል። የዚህ ሰው አመለካከትና ግንዛቤ ከዛሬ ሰላሳና ዓርባ ዓመታት ንቅንቅ አለማለቱ ከመጽሐፉ የተሻለ አስረጅ አይገኝም።

merara gudina በቅደሚያ መረራ ጉዲና የሚባል የመኢሶን ካድሬ በጅባትና ሜጫ አውራጃ አምቦ ከተማ መኖሩን እንጂ ምን ዕልቅና በድርጅቱ ውስጥ ይኑረው አይኑረው የማውቀው ነገር የለም። ይህንን ሰው ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ አይቼው አላውቅም ። ስለዚህ ሰው ከርቀት የነበረኝ እውቀት ከሌሎቹ ወጣት የመኢሶን ካድሬዎች ታናሽ ወንደሜን ጨምሮ የተለየ አልነበረም። እሱ እንደሚለው ሳይሆን ለዚህ ሰው በስሙ መልዕክት ልኬበትም ለስብሰባ ጠርቼው አላውቅም። የድርጅቱ የግንኙነት መዋቅር በፈረሰና ባካባቢው የድርጅቱ ተጠሪ የነበሩትና እኛን ወደ ጅባትና ሜጫ የወጣነውን ከድርጅቱ አመራር አካል ጋር አገናኝ የነበሩትና ከመረራ ይልቅ ላመራሩ አባላት ቅርበት የነበራቸው አስፋው ሽፈራውና ሃምሳ ዓለቃ ማህተሙ በኩረ ነበሩ። አስፋው ከተያዘና ያምሳ አለቃ ማህተሙም ጉዳይ አጠራጣሪ ከመሆን አልፎ አቋሙን ቀይሮ ወደ አብዮታዊ ሰደድ ገብቷል የሚል ዜና ከመድረሱ በፊትም ሆነ ክደረሰም በኋላ እኔን ወደ ጥቁር እንጭኒ ከሄደው በዶ/ር ተረፈ ወ/ጻዲቅ ከሚመራው ቡድን ጋር ባንድ በኩልና አዲስ አበባ አካባቢ ህቡዕ ከነበረው ተተኪ የደርጅቱ አመራር አካል ጋር ታገናኝና መልዕክት ታደርስ ትመለስ የነበረችው መክሊት ግርማ የምትባል መረራ በመፅሐፉ ውስጥ ሰለጥንካሪዬዋና መስዋዕትነቷ የሚያወሳትሳት ወጣት ነበረች። እዚያው አሞግሶ እሟሟቷን በሚመለከት ከሁላችንም ቀድሞ ብሎ ከተያዘው አስፋው ሽፈራውና ሃምሳ ዓለቃ ማህተሙ ጋር በማነካካት በ”ይመስለኛል” ያቀረበውን ከእውነት የራቀ ጉዳይ ሌሎች ሰዎች እንዲመለሱበት በመተው ከድርጅቱ የተመደበችልኝም ተገናኝ እሷዋ ብቻ እንደነበርችና ለዚህ ሰው በስሙ መልዕክት ልኬበትም ለስብሰባ ጠርቼውም እንደማላውቅ ላሰምርበት እወዳለሁ። ስለዚህ ሰው የነበረኝ እውቀት ከሌሎቹ ወጣት የመኢሶን ካድሬዎች ታናሽ ወንደሜን ጨምሮ የተለየ አልነበረም። በዚህ መሃል የመኢሶን ድርጅታዊ መዋቅር ሲፍረከረክ መረራ ተወካይ ወይም ተጠሪ ሆኖ ተመድቦ ሊሆን ይችላል። ባነጋገሩም መሰረታዊ ነገሮች ላይ እየታከከ የሚያውቀውንና የሰማውን ከማያውቀውና ካልሰማው ጉዳይ ጋር በማገናኘት “ቀድመው ሊጎዱኝ” ይችላሉ ብሎ በጠረጠርን ሰዎች ላይ እብደትና ቅሌት ባቀላቀለ Paranoia መክሰሱ የራሱን የሕይወት ምስቅልቅልና እስከዛሬ ሊያገግምለት ያልቻለውን የሕሊና ሥቃይ በማተራመስ ያባብስበት እንደሆን እንጂ እውነትን አይናገርም።

በመጽሐፉ ገጽ 84 እኔና ታናሽ ወንድሜ እሱን “ሊጎዳ የሚችል ሪፖርት” ለመጻፍና እኔ ላዘጋጀሁለትም “የረቀቀ ወጥመድ አስፈጻሚ ነበር” በሚለው ወንድሜ ለመጠቀም እንደማልመለስ ያትታል። ለመሆኑ ይህንን ለማድረግ የምነሳበት ምክንያት ምንድነው? መረጃውስ ምንድን ነው? መረራን ሊጎዳ ወይም ሊያጠፋው የሚችል ሪፖርት በወንድሜ መረጃ ሰብሳቢነት ለመኢሶን የበላይ አካልም ሆነ ወደ ውጭ ጉዳዩ ለማይመለከተው ወገን ለመጻፍም ለማውራትም የሞክርኩበት ጊዜ የለም። የሰማሁት ነገር አልነበረም ለማለት ሳይሆን በእርግጠኛነት የማውቀው ጉዳይ ባለመኖሩና ከሁሉም በላይ ላለውም ሆነ ለመጭው ትውልድ የሚሰጠው ትምህርት እንደሌለ ስለማምን ነበር።
በዚሁ ገጽ መረራ ከአብዮታዊ ሰደድ አዲሱ ተወካይ በሚል ካነሳው ሰው ጋር መቻቻሉን ይናገራል። የሚታወቀው የአብዮታዊ ሰደድ ተወካይ ሆነው መኢሶንን ለመተካት በየክፍለ ሃገሩ፤ አውራጃና ወረዳ የተላኩ ካድሬዎች በመኢሶንነት የሚጠረጥሩትን ሁሉ ከማሳደድና ቢቻላቸው ከማጥፋት ካልተቻላቸው ደግሞ ከማሰር ያለተመለሱብት ጊዜ ነበር። ጥቁር እንጭኒ ለግድያ ከተሰማራው ቡድን ጋር አብሮ አንደነበር ሲነገር የሰማነውንና ያንን ያህል አመኔታ የተጣለበትና ከበደ ድሪባም የከርስትና አባቱ መሆኑን የነገረን ሰው ምን እንደገፋፋው ከሞት አስነስተን ልንጠይቀው የማንችለወን ሃምሳ ዓለቃ ማህተሙ በኩረንም በሚመለከት ስለዚህ ሰው የሰማው “እውነትም ይሁን ሃሰት … እኔ እንድሞት ቢንቀሳቀስ ኖሮ ከሞት የምተርፍ አይመስለኝም” ነበር “ የሚል ነው። እንዲያውም በመፅሐፉ ላይ ባንድም ሥፍራ ሃምሳ ዓለቃ ማህተሙን ከግድያው ጋር ሳያነካካ በተጠያቂነት ሳያመለክት አልፎታል። ከዛሬ 10 እና 15 ዓመታት ገደማ መረራ ጉዲናን ጅባትና ሜጫ ለደረሰው ዕልቂት ተጠያቂ በማድረግ ተነስተውበት የነበሩትንና ሃምሳ ዓለቃ ማህተሙ በኩረም “የእናቱ እህት” ነው በሚል ሲከሱት የነበሩትን ወደ ኦነግ የተጠጉ ወገኖችንም በዚህ “ታሪካዊ ትዝታው” አብክሮ ሳይወቅሳቸው ማለፉ አስገርሞኛል። ይህ መብቱ ነው። ምንም ቅሬታ የለኝም።

በዚሁ ገፅ 84 እና 85 እኔ ከዘረጋሁለት “የረቀቀ ወጥመድ ሕይውቱ የተረፈበትን አጋጣሚ” እና ብዙም ሳይቆይ ስለዘረጋሁት “የተንኮል ድር” ይህንኑ የዘረጋሁትን “የከህደት መስመር የሚያንቀሳቅሰለት ሲራክ ተግባሩ የተባለ ታናሽ ወንድም” እንደነበረኝ ያትታል። እኔ የሕዝብ ደርጀት ጽ/ቤት ተቀጣሪም ሆነ በመኢሶን ውስጥ ካድሬ የመሾም የመሻር ሥልጣን አልነበረኝም። ይህንንም በመረጃ ያልተደገፈ ክስ ከየት እንዳመጣው መልስ መስጠት ይኖርበታል።

በዚሁ ገጽ 85 ስለመቀደም ያወራል፡ የተቀደመውስ ምን ለማድረግ ነበር? መልሱን ፍለጋ ሩቅ መሄድ አያስፈልግም። በዚሁ ገጽ 85 መጨረሻ ገደማ “ከመግደል ውጭ አማራጭ አልነበረም” የሚለውን ስመለከት የተቀደመበትን ምክንያት ማሰላሰል አላስፈለገኝም። ይህም የሰው ሕይወት ከማጥፋት የማይመለስ ፍላጎት (INTENT) እንደነበረው ያጠናክራል።

በዚሁ ገፅ 84-85 ዝቅ ብሎም ስሜን በማንሳት “አማረ ብዙም ሳይቆይ የተንኮል ድሩን መዘርጋት ይጀምራል …” ይልና በመቀጠል “በእውነቱ ከኔ የተሻለ አማረን የሚያውቀው ኢዮብ ታደሰ መጠርጠሩ መረጃ ቢኖርኝም … “ (ስርዝ የተጨመረ ገፅ 85) በሚል ይቀጥላል።

እነኚህ ከላይ ስማቸውን የሚጠቅሳቸው ሰዎች አንዳቸውም በሕይወት የሉም። በስም እየጠራ እከሌ ይህንን ማለቱን፤እከሌ ደግሞ ያንን “ማለቱን አስታውሳለሁ” ይላል። እዚያው በዚያው ደግሞ “በቦታው ያልነበረ” እና “በሕይወት ለወሬ ነጋሪነት የተረፈው እሱ ብቻ መሆኑን በመጥቀስ “የቡድኑን ጭቅጭቅ በለማ ፊዳ በኩል ሲከታተል” እንደነበር ይናገራል። ለማ ፊዳን ከሞት አስነስቶ መጠየቅ አይቻልም። “በለማ ፊዳ በኩል ስከታተል ነበር” ብሎ ነገር እንዴት ሊሆን ይችላል? እውነትስ ቢሆን በስለላ ሥራ እንዲሰማራ ያዘዘው ማነው? በበኩሌ ይህ አዲስ ነገር ነው። በመኢሶን ታሪክ አንዱ ሌላውን የመሰለል ሥራ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም። በድርጅቱ አባላት መካከል የ “አግድሞሽ” (horizontal) ግንኙነት ተገቢ እንዳልነበር በመጽሐፉ ውስጥ የሚናገረው ይህ ሰው ለሱ ይህንን የአግድሞሽ ግንኙነት የፈቀደለት ማነው?

ወደ ገጽ 86 እና 87 ስንሄድ አቅጣጫ ለማሳስት ወንድሜን መሳሪያ በማድረግ አንድ በዚያን ጊዜ ስለቻይና አብዮትና ረጅም ጉዞ ከጻፍኩት ጋር አያይዞ እውነት ያልሆነ ነገር ያነሳል። እኔ የነበርኩት ወለንኮሚ ሲሆን እነዶ//ር ተረፈ ያረፉበትን የነመረራ ጉዲናን ዘመዶች ቤት ይቅርና ጥቁር እንጭኒን ደርሼበት አላውቅም። ሲራክም ከመረራ፤ ሃምሳ ዓለቃ ማህተሙና መክሊት በስተቀር እነዶ/ር ተረፈ በየትኛው ሥፍራና መረራ እንደሚለው በየትኛው የነ ”መረራ አጎት ቤት” ቤት እንዳረፉ እንደማያውቅ ለመረራ ጉዲና ከተቀባይ ደረሰኝ ጋር ከላከለትና ለማንም ባላሰራጨው የሚስጥር ደብዳቤ ይነበባል። የዚህ ደብድዳቤ ኮፒም በጄ ይገኛል።

ወደ ገጽ 88 እና 89 ደግሞ መናገሻ አካባቢ የኔ ወንድምና በሌላ በኩል መረራ “ወንድሜና ረዳቱ” በሚላቸው መካከል በሌላ በኩል ተፈጠረ የሚለውን የጥቆማ፤ የደብደባና የግድያ ታሪክ የምሰማውና የማነበው ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ነው። ይህንን የመሰለ ከባድ ጉዳይ ቀርቶ በየቦታው በመኢሶን ደጋፊና ተባባሪ በነበሩ ሰዎች ላይ ይደርሱ የነበሩትን ጉዳዮች ደርግ ጽ/ቤትም፤ ፖሊስ ጣቢያም ወህኒ ቤትም ሆነ ለእኛ አራተኛ ክፍለ ጦር ለነበርነውም በሆነ መንገድ ይደርስ ነበር። በመናገሻ አካባቢ በሌላ አጋጣሚ በእርግጠኛነት የደረሰ ነገር አልነበረም ለማለት አልችልም። መረጃ የለኝም።

የዛሬ 30 ዓመት እ.አ.እ 1983 በጅባትና ሜጫ የነበረውን ሁኔታ በተመለከተ ለድርጅቱ አመራር አካል አንድ እጅግ ዝርዝር ሰነድ አቅርቤ ነበር። በዚህ ሰነድ ታናሽ ወንደሜን ሲራክ ተግባሩን ለመገናኘት የወሰንኩበትን ምክንያት ያስረዳል። እሱም የኔን መልዕክት ይዞ ወደአዲስ አበባ ለመግባት ሲሞክር ገፈርሣን አለፍ ብሎ “ኢያሱ ጠበል” በመባል በሚታወቀው አካባቢ በተዘጋጀው Road Block ሲደረስ ቀድመው እዚያ ሲጠብቁት በነበሩት የደርግ ምርመራ አባላት መያዙን፤ በዚህም ጊዜ ብቻውን እንጂ ማንም እሱን ተከትሎ የሄደ፤ የተያዘ፤ የተደበብደበና እዚያው “እሱን ገድለናል” የተባለና እንደገና ደግሞ ሞትን አሸንፎ “ራሱን ስቶ” እንደነበረ መረራ የሚነግረንና “ወደአምቦ ተወስዶ የተገደለ” የሚለውን ወንድሙን የሚመለከት ታሪክ የማነበውም የምሰማውም በዚህ መጽሐፍ ነው። መረራ ወንድም ይኑረው አይኑረው የምውቀው ነገር የለም። የትም ቦታ ይሙት በመስዋዕትነቱ ሊከበር ይገባል። በተረፈ የወንድሙ ረዳት የሆነ የሆነ ሰው የነመረራን አጎት ቤት አውቆ መምራቱን ከሞት አስነስቶ መጠየቅ አይቻልም። ሲራክ እንደሚለውና ለመረራ በጻፈው ደብዳቤ ያረጋገጠው መረራ ጉዲና የኮማንዶው ቡድን ተባባሪ እንደነበርና አምቦ ከተማ ሲደርሱ ከተደባለቀው ሃምሳ ዓለቃ ማህተሙ ጋር ሆነው ያጎቱን ቤት መርቶ ማሳየቱን፤ ሲራክም እዚያው ግድያው የተፈጸመበት ሥፍራ እንደነበረ ይመሰክራል። ክርክር መግጠም የነበረበት ከኔ ወንድም ጋር ነበር።

ስለእኔ መኢሶንን መክዳት በማያውቀው ጉዳይ ከመዘባረቅ በስተቀር መረጃ አላቀረበም። እውነተኛው ታሪክ ግን እኔ ከእሰር ተፈትቼ ወደ ስዊድን አገር ከገባሁ በኋላ በውጭ ካለው የመኢሶን ድርጅቱ አመራር አካል ጋር በመደባልቅ የድርጅቱ የውጭ ልሣን በነበረችው “አዲሲቱ ኢትዮጵያ” ጋዜጣና የደርጅቱንም ታሪክ ለመፃፍ በተደረገው ሙከራ ተሳትፌአለሁ። በዚህ ሳልቆጠብ ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ሥልጣን እስከያዘበት ዘመን ድረስና ከዚያም በኋላ በድርጅት ከታቀፈ የፖለቲካ ተሳትፎ ራሴን እስካገለልኩበት ድረስ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሠርቼ ያፈራሁትንም ቅርስ ጭምር ለድርጅቱ ሥራ አበርክቻለሁ። ተጨባጭ መረጃዎቸን በሰፊው ማቅረብ ካስፈለገ የነበረንን ግንኙነት የሚመሰክሩ የጽሑፍ መረጃዎችን የማቅረብ ችግር የለብኝም። ለአብነት ያህል ወደ ስዊድን አገር በገባሁበት ዘመን የስደተኝነት ማመልከቻዬን በመደገፍ በድርጅቱ የተጻፈልኝልን ደብዳቤ እዚህ ላይ አባሪ አድርጌአልሁ።

መላ ኢትዮጵያ ሶሽያሊስት ንቅናቄ – መኢሶን
All Ethiopian Socialist Movement (ME’ISONE)
05/08/82
To: The Office of the UNHCR
Stockholm, Sweden
Dear Sir,
It has come to our knowledge that MR. AMARE TEGBARU, born in Addis Ababa, Ethiopia on the 10th of October 1952 has filed an application in order to obtain the status of Political Refugee in the Kingdom of Sweden.

MR. AMARE TEGBARU is a long time militant who has suffered persecution, imprisonment and torture both in the hands of the former regime of Emperor Haile Selassie and the present military government.
A member of the “University Students’ Union of Addis Ababa” from 1969 to 1972, Mr. Tegbaru served as the Secretary General of this militant organization for the year 1971/ 1972. During this period, he was condemned to serve a six months’ prison term and was severely tortured during his detention.

In 1972, Mr. Tegbaru left Ethiopia for France where he joined the local branch of the Ethiopian Students’ Union in Europe. During the 1974/ 1975 he served as the President of the Union and the next year became an advisor of its Executive Committee.

He became a member of ME’ISONE, The All Ethiopian Socialist Movement in 1976 and returned to Ethiopia to become the editor of the organization’s paper, “ADDIA FANA”. When the organization broke with the military regime in August 1977, Mr. Tegbaru was one of those ordered to go underground. A few months later, he was arrested by the government’s security forces and detained at the Headquarters of the 4th Army Division in Addis Ababa.

During his second stay in prison which lasted for over Four (4) years, Mr. Tegbaru was subject to inhuman torture and mistreatment which damaged his health seriously.

We believe that Mr. Tegbaru’s request for Political Asylum in Sweden is justified and hope that his application would be considered favorably by your office.

Yours Sincerely,

DR. NEGEDE GOBEZIE
For the Foreign Mission
ME’ISONE

የኔን መያዝ በተመለከተ በኢማሌድህ ዘመን ከማንም በላይ ውስጠ አዋቂና የማሌሪድ መሪ የነበረው ተስፋዬ መኮንን “ይድረስ ለባለታሪኩ” በሚል በጻፈው መጽሐፍ ታናሽ ወንድሜ “በዚያን ጊዜ 17 ዓመት ዕድሜ ያለው … ወጣቱ ልጅ በመሆኑ ያንዣበበውን አደጋ ሲያይ የወንድሙን መሞት ሊቀበል ይቸገራል። ቀደም ሲል ሀገሩ ሁላ እንደሰማው የእነዶ/ር ከበደን መሞት ሰምቶታል፡ የእነ ሃይሌ ፊዳም መያዝ አስደንግጦታል፡ ስለዚህም ወንድሙንና ራሱን ማዳን ፈለገ ማለት ነው” (ገፅ 255 -256)) በሚል የጻፈውና ሲራክ በቤተሰብ አካባቢ ከዚያም ከ20 ዓመታት በኋላ ባካል ስንገናኝ ከነገረኝና ለመረራ ጎዳና በሚስጥር ከላከለትና ለማንም ባላሰራጨው ደብዳቤ ከገለፀው ጋር አንድ ነው። መረራ ይህንን እውነት ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን በሱ ቤት ቀድሞ መጉዳቱ ነው።

በገፅ 85 መረራ ሥልጣኔ (civility) ባልጎበኘው ቋንቋው ያነሳው “እግር ማከክ” እና የጤንነት ጉዳይ እሱም ራሱ ሳያውቀው አይቀርም ብዬ የምገምተው ጉዳይ አልተነሳም ለማለት አይደለም። ከሃዘኔታ፤ ቁጭትና እንክብካቤ በስተቀር ምንም ነገር ያላየሁባቸውን ሰዎች በዚህ መልክ “እንልቀቀው” ወይም እሱ በገፅ 85 መጨረሻ ገደማ እንዳመለከተው “ከመግደል ውጭ አማራጭ አልነበረም” ወደሚለው ሃሳብ የሚዘቅጡ ሰዎች አድርጎ ማቅረቡ እነኚህን ሰዎች በራሱ ደረጃ እጅግ ዝቅ አድርጎ መገመቱና ከራሱ ተመክሮና ሞራል ጋር አዳምሮ ማቅረቡ እጅግ የሚያሳዝን ነው። እንደ መረራ ጉዲና ዝቅ ባለ የካድሬ ደረጃ ምን ይደረግ እንደነበር አላውቅም። እሱን የመሳሰሉ በድርጅት ለመገዛት የሚያስቸግሩ፣ ከዕብድ የማይሻሉ ሰዎች በድርጅቱ አልነበሩም ማለት አልችልም። ድርጅቱ ከተመሰረተበት እ.አ.አ 1968 ጀምሮ የድርጅቱ መሥራች አባላት ከነበሩ ጋርና ከዚያም በ1974 የኢትዮጵያ አብዮት ከፈነዳ በኋላ በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ወስጥ በነበሩ ሰዎች መካከል ልዩነቶች ተፈጥረው እስከመለያየት የተደረሰበትና አንዳንዶችም ድርጅቱን ጥለው የወጡበት ታሪክ ነበር። ከነኚያ ድርጅቱን ጥለው ከወጡ ሰዎች ጋር በግለሰብ ደረጃ የወዳጅነት ግንኙንት ቀጠለ እንጂ አንዱ ሌላውን demonize የማድረግና አንዱ ባንዱ ላይ እየተነሳ የመወነጃጀልና ስም የማጥፋት ዘመቻ ያካሄደ አልነበርም። ስለ”ዕልቅና” ከመናገር በፊት በቅድሚያ የድርጅቱን ታሪክ ማጥናት

የዛሬ 30 ዓመት ገደማ ለድርጅቱ የውጭ አመራርና ወደ አገር ቤትም ተልኮ ከተመረመረ በኋላ በዚያን ጊዜና በዚያ ሥፍራ በትክክል ምን እንደተፈፀመ የማይታወቁ ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው አማረን ባንድም ጉዳይ የሚያስጠይቅ ምንም መረጃ የለም በሚል ከድርጅቱ አመራር ጋር ተደባልቄ አብሬ ለመስራት ካበቃኝ ጽሑፍ ውስጥ በዚያን ጊዜ በመካከላቸን ተነስቶ የነበረውን ችግር እንዴት እንደፈታነው የሚመለከት ለአብነት ሲታወስ የሚኖር ታሪክ እንደሚከተለው አነሳለሁ።

እኛን ከበላይ አካል ጋር ባገናኝነት ከተመደቡልን ሰዎች መካከል አንደኛው ወደኛ በመጣ ጊዜ በመጠጥ ኃይል መድከሙ ብቻ ሳይሆን ለመናገርም ለመንቀሳቀስም ተቸገሮ ባየንበት ሰዓት ይህንን ሰው “አንልቀቀው”፣ “እንሰረው” ወዘተ አላልንም። ለደህንነታቸን አስደንጋጭ እንደነበር ጠፍቶን አልነበረም። የተጠቀምንበት ዘዴ ይህ ሰው ከተሰጠው ሃላፊነት የተገፈፈና የተዋረደ ሳይመስለውና የኛንም ደህንነት compromise በማያደርግ መንገድ፤ ትዕግሥት በተመላው ብልሃት ይህ ሰው ተመልሶ ወደኛ እንዳይመጣ ተደርጓል። ሌላም የነሃይሌ ፊዳን መያዝና የነከበደ መንገሻን መገደል፣ የነዶ/ር ካሣሁን ብርሃኑንና ሃይሉ ገርባባን፣በኢሊባቦርም የነዶ/ር ከድር መሐመድንና አዲሱ በየነን መያዝ ስንሰማ አስደንጋጭ ከመሆኑ የተንሳ በመካከላችን ከነበሩት ኦሮሞዎች አንዱ ከንግዲህ የሚያዋጣው መኢሶንን በመሰለ በመደብ ጥቅም ላይ በቆመ ድርጅት ሥር መታገል አይደለም። የሚያዋጣው በየብሔር ድርጅቶችና ነፃ አውጭ ግንባሮች ውስጥ ገብቶና ተመልምሎ ትግሉን መቀጠል ነው በሚል በመኢሶን ውስጥ ያሉትም ኦሮሞዎች ከነወራቃና ኦነግ ጋር በመደባለቅ ትግሉን መጀመርና በቅድሚያ የየራሳቸውን ብሔር ብሔረሰቦች ነፃ ማውጣት አለባቸው እስከማለት ደርሶ ነበር። ይኸው ሰው በተለይም መኢሶንን በመሰለ በነፍጠኛ ድርጅት ስም በሚከሰስ ድርጅት ውስጥ መቆየት በብሔረሰቦቻችን ዘንድ ተቀባይነት እንዳናግኝ ችግር ይፈጥርብናል በሚል በቶሎ ከመኢሶን ተሰናብቶ ከመሄድ የማይመለስ ጥያቄ እስከማንሳት ደርሶ ነበር። ይህንን ጉዳይ ካነሳው ጋር የረጋ ውይይት ከማድረግና ሃሳቡን በማክበር ሁኔታውና ጊዜው በሚፈቅድ ጊዜ ይህንን ውሳኔ ለመውሰድ የሚከለክለው እንደሌለ ተነግሮት፤ በነበርንበት ሁኔታ ግን ደርግ ማንኛቸንንም የሚምርበት ሁኔታ ስለሌለ ሌላው ቢቀር ለጊዜው በትግል ሕብረት ደርጃ አብረን ልንቀጥል እንችላለን በሚል መስማማት ላይ ደርሰን ነበር። ይህንን ጉዳይ ያነሳውን ሰው “የክህደት ድሩን መዘርጋት መጀመሩ ነው”፣ “አንልቀቀቀው”፤ እንሰርው ወይም ደግሞ መረራ እንዳመለከተው ለክሃዲ አማራጩ በሕይወቱ ላይ እርምጃ መውሰድ ነው የሚል ነገር ያነሳ አንድም ሰው አልነበረም። ይህንን ያነሳውም ቢሆን ከቅንነትና ከመደናገጥ መሆኑን በመረዳት ለማረጋጋት የተደረገው ሙከራ ፍሬ ሰጥቶ በሌላ ጊዜ ሃሳቡን ቀይሮ መኢሶን የነፍጠኛ ድርጅት እንዳልሆነና ያውም ያለበቂ ድርጅታዊ ዝግጅት ከደርግ ጋር ለመቆራረጥ መምረጡ ለሥልጣን የቋመጠ አድርባይ ድርጅት በሚል ሲከሰስበት ለኖረው ጉዳይ ቆራጥ ምላሽ ነው እያለ እስከመከራክር ደርሶ ነበር። በመጨረሻውም በጥቁር እንጭኒ ተሰውቷል። ይህንንና ሌላም እጅግ ዝርዝር ትዝታዎቼን ለማቅረብ ዕድሉና ዕድሜው በሰጠኝ ጊዜ ላሉትም ለሞቱትም አክብሮት ባለው መንገድ ይፋ ለማድረግ እሞክራለሁ። ይህ የሚይሳየው መአኢሶን የተለየ የአመራር ባህል እንደነበረው ሲሆን፣ ርስ በርስ በመጫረስ የትም ሳይደርሱ ከጠፉትም ሆነ የትግል ጓደኞቻቸውን እየጨረሱ የተመኙትንም የፖለቲካ ሥልጣን ሳይጨብጡ ርስ በርሳቸው በመባላት ከጠፉና ለጓደኞቻቸው ሕይወት መጥፋት ከተጠያቂነት ከማይድኑ ወገኖች ከመደመር አድኗል።

መረራ በመፅሐፉ እንደሚገልፀው ይህንን ያህል ድርጅታዊ አመኔታ የተጣለበት ሰው እንደነበርና እኔን የመሳሰሉ ከሃዲዎች ባይገጥሙት ኖሮ እሱን የመሰለ ‘አብዮታዊ ጀግና’ ሌላው ቢቀር የድርጅቱ በዚያ አካባቢ የተሻለ እንቅስቃሴ እንኳን ማድረግ ቢሳነው ያባላቱን ሕይወት ለማዳን ብቃትና ችሎታ እንደነበረው ይናገራል። እስከዚህ ድረስ በዕድሜም ሆነ ተመክሮ ከሁላችንም ወጣት የነበረ ሰው በሥነ ልቦናዊ ቀውስ ካልተነካ በስተቀር ወይም Narcissism ካልሆነ በስተቀር እንዲህ በድፍረት ስለራሱ ለመናገርና ለመጻፍ መድፈሩ የሚገርም ነው። ወይ “ዝም በል የሚለው ሰው” የለም። ወይም ደግሞ ሰውዬው በተፈጥሮው “ደብረ በጥብጥ ነው” ከማለት በስተቀር ሌላ ቋንቋ አላገኝለትም። አንድ ልብ ያላለው ጉዳይ ቢኖር ግን የሚከተለው ነው፡

ከፍ ብዬ እንደገለፅኩት የዛሬ 30 ዓመት ገደማ እኔ የማውቀውንና የማስታውሰውን በዝርዝር እንዳቀርብ በድርጅቱ የበላይ አካል ተጠይቄ ባቀረብኩት ሰነድ ይህንኑ ወደጅባትና ሜጫ ለወጣው ቡድን ደህንነት የሚበጅ ስፍራ በግንባር ቀድምትነት አዘጋጀሁ የሚለው ይህ ሰው በ“ንቃት” ደረጃውና “ዕልቅናው” እየተኩራራ የሚገልጸው ሥፍራ ምን እንደሚመስል የገለፅኩበትን እያሳጠርኩ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

ከጉደር ወጣ ብለው ወደሚገኙ መንደሮች የሄድነው በሁለት ቡድን ተከፍለን ነበር። ለጥቂተ ቀናት ቀድመውን አንድ የገበሬ ማህበር የአብዮት ጠበቃ አባል ቤት የደረሱት የነኢዮብ ቡድን ነበር። ይህም ሰው ዱጋሣ ይባላል። ስለ መኢሶን የሚያውቀው ነገር አልነበረም። የተቀበለንም ጉድታ የሚባል ጉደር አፋፉ ላይ የሚኖር “የ42 ቀበሌ ሊቀ መንበር” አደራ ስላለው ነበር። ዱጋሣ አንድ ጥይት ብቻ ባላት ምንሽር ጠመንጃ መታጠቁን ታጥቋል። እንደአጋጣሚ ጠመንጃው የጎረሰውን አንድ ጥይት ነክሶ ከተቀመጠ መሰንበቱንና ተወርዋሪውም እንደተከፈተ ዝገት እንደበላው ባይናቸን አይተናል። እኔና ዶ/ር ተረፈ ያለንበት ቡድን አቶ ዱጋሣ ቤት ደርሰን ከተደባለቀን በኋላ ከነኢዮብ ጋር አብረን የቆየነው ላንዲት ቀን ብቻ ነበር። በሚቀጥለው ቀን እኛ እዚያው ስንቀር የእነኢዮብ ቡድን ራቅ ብሎ ወድሚገኝ የገበሬ ማህበር አባል ቤት ተዛውረዋል። ይህም ቤት የአቶ ቃበታ ቤት ሲሆን እሱም የገበሬ ማህበር የአብዮት ጥበቃ አባል ነው። ቃበታም እንደ ዱጋሣ መታጠቁን ይታጠቅ እንጂ ትጥቃቸው ለየቅል ነው። እንደጠመንጃ የተሰራውን የቃበታን የዱላ ትጥቅ ባይናቸን አይተናል። ወደእኛ በመጣ ጊዜ አንግቷት ነበር። በሌላም ጊዜ ወደኛ በመጣ ቁጥር የሚያነገትውም ይህንኑ በጠመንጃ ቅርፅ የተሰራውን የዱላ ትጥቅ ነበር። ድጋሣም ሆነ ቃበታ ዕቃ ባደራ እንዲያስቀምጡ ተጠይቀው እንዳስቀመጡ ያህል እንጂ ምንም አይነት አብዮታዊ ንቃትም ሆነ ድርጀታዊ ዕውቀት አልነበራቸውም። ይህ አንዳለ ሆኖ ለሁለት ተከፍለን ገሚሳቸን ከነዱጋሣ ቤት ገሚሳችን ደግሞ ወደቃበታ ቤት ለመሄድ የተወሰነው ሁላችንም ባንድ ቤት ወስጥ መሸሽጉ ከደህንነት አንፃር ተገቢ እንደማይሆንና አንድ ድንገተኛ አደጋ እንኳ ቢያጋጥም አንዱ ወገን በድጋፍ ሰጭነት ወይም ደግሞ አቅጣጫ ቀይሮ ወደሌላ አካባቢ ለመሸሽ ይረዳል በሚል ነበር፡ ከዚህም በላይ አንድ ደሃ የገበሬ ማህበር አባል፥ ከአሮጊት እናቱ፥ ሚስቱ፥ ልጆቹና ሁለት እህቶቹ ጋር የሚኖር ሰው ያንን ያህል ብዛት ያለንን እንግዶች ለማሳረፍ የሚያስችል ቦታ ስላልነበረውና በተለይም ገባ ወጣ ባልንም ቁጥር ያካባቢውን ዓይን ልንስብ እንችላለን በሚል ለሁለት መከፈል ነበረብን። በዚህ መሰረት እኔ፤ ተረፈ፤ አጥናፍ፤ ከበደ ድሪባና ለማ ፊዳ አንድ ቤት ስንቀር ኢዮብ፤ መርዕድ፥ ሽመልስ ኦላናና ስሙን በትክክል የማላስታውሰው የሸዋ ሕዝብ ድርጅት ካድሬና ከበደ ድሪባን በከፊል ሾፌርነት የሚረዳው ምናልባት ስሙ ታደሰ ሳይሆን አይቀርም ብዬ የምገምተው ሰው ከእኛ ራቅ ብሎ በሚገኝ የገበሬ ቤት ነበሩ። መሸትና ላይን ያዝ ሲያደርግ አንዳንድ ጊዜ ተረፈና ከበደ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከበደ ብቻውን እነኢዮብ ወዳሉበት በመሄድ ሲገናኙ አብዛኛውን ጊዜ ግንኙነቱ በወረቀትና በመልዕክተኛ ስለነበር የሚላላክልንም መጠጊያ የሰጠን ገበሬ ዱጋሣ ወይም እህቱ ሶርሴ ነበረች። በዚያች አብረን በዋልንባት ቀን የተነጋገርነው ተረፈ ባንሳው ጉዳይ ላይ ነበር። እሱም ለጠመንጃ ትግል ወደገጠር የወጡ አብዮታውያን ምን ያህል ጊዜ በትግሉ እንደሚቆዩ አወቁም አላወቁም ከመሃላቸው በየቀኑ የሚሆኑትን ጉዳዮች በዲያሪ መልክ የሚይዝ ክሮኒክለር ነበራቸው። አባቶቻችን ሳይቀሩ ወድ ማይጨው ሲዘምቱ አንድ ቀለም የለየ ሰው አብሮ ይዘምትና እሱም በየዕለቱ የሆነውንና የደረሰውን በጽሑፍ እንዲያስቀር ያደርጉ ነበርና አሁንም አንድ ሰው ከመሃላቸን ይህንን ማስታወሻ በዲያሪ መልክ የሚይዝ ያስፈልገናል የሚል ሃሳብ አቅርቦ በዚህ ተነጋግረናል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሳይሆን እንግሊዝ አገርም አብረን ላጭር ጊዜ አብረን የነበርነው ኢዮብ ታደሰና ከበድ ድሪባ እኔን ኖሚኔት ሲያደርጉ ሌሎችም ይህንኑ ሲስማሙ ተረፈም ቀድሞ በልቡ ይዞ የነበረ የኔን ስም ለመስጠት እንደነበር ገልጾ ያ ስብሰባ በዚያው ተደመደመ። አንድም ጊዜ ሁላቸንም ባንድ ጊዜ ባንድ ቦታ ተገናኝተንና ተቀምጠን የተወያየንበት ጊዜም አልነበረም። ከጥንቃቄም አንጻር ተገቢ አልነበረም። በህይወት የሌሉ ሰዎቸ ለማንኛችንም ምስክር አይሆኑም። ከሳሽ መረራ ጉዲና ነውና መረጃ የማቅረብ ዕዳው ከኔ ይልቅ የሚወድቀው እሱ ላይ ነው።

መረራ ጉዲና ለአማረ ተግባሩ ስፍራ አዘጋጀንለት ወዳለው ወለንኮሚው ታሪክ ስመለስ ደግሞ በየተራ እየተቀባበሉ የደበቁኝ ሃይሉ ጉርሙ የሚባል ቀድሞ አየር ወለድ፤ በወለንኮሚ የንግድ መደብር የነበረውና የኤፒድ ሠራተኛ የነበረቸው እልፍነሽ ደበሌ ነበሩ። መጀመሪያ እንዲቀበለኝ የተጠየቀው ገረመው የሚባል “በድርጅት ተይዟል” የተባለ ሰው ሲሆን እሱ ግን ሊቀበለኝ እንደማይችልና በሥራ ምክንያት ተዛውሮ ወደ መርሐ ቤቴ ለመሄድ ጓዙን በማንሳት መሆኑን ይገልፃል። ወደ ሃይሉ ጉርሙ መደብር ስንሄድ ደግሞ እሱም ሚስት ለማግባት አዲስ አበባ ስለምሄድ ጥቂት ቀናት ጊዜ እንዲሰጡትና እስከዚያ እንደሚዘጋጅ ይነግራቸዋል። እልፍነሽ ዘንድ ስንሄድ ፈቃደኛ ሆና ልትቀበለኝ ቻለች። እልፍነሽና ሃይሉም ቢሆኑ ደጋፊ እንጂ የድርጀቱ አባላት አልነበሩም። እየተቀባበሉ ባስቀመጡኝ ጊዜ ሁሉ ቀን ቀን ቤቱ እየተዘጋብኝ መብራት ሳላበራ መፀዳዳትም ቢያስፈልገኝ እዚያው የምፀዳዳበት ተዘጋጅቶልኝ አሳልፍ ነበር። መብራት የማብራት እድል የነበረኝ ማታ ሃይሉ መደብሩን ሲዘጋ ወይም ደግሞ እልፍነሽ ከሥራ ስትመለስና ሲመሻስ ብቻ ነበር። ይህ ሰው ድርጀታዊ ንቃቱና ብቃቱ በዚያን ጊዜ ይሻል ነበር በሚል ስለራሱ የሚናገር ሰው ያን ጊዜም ሆነ ዛሬ ስለ ድርጅት ጥንካሬና ብቃት ያለው ዕውቀት ጉደር ከደበቁን ገበሬዎች ንቃትና ብቃት ምን ያህል እንደሚሻል አንባቢ እንዲታዘበው እተውዋለሁ።አዘጋጀሁ የሚለው ሥርቻ በመፅሐፉ ውስጥ በልጅነቱ ላምና ጥጃ ከሚጠብቅበት የዘመዶቹ ማሳ ታጭዶ የተወቃ በቆሎና ማሽላ ያስቀምጥ እንደሆን እንጂ ድርጅታቂ ንቃትና ብቃት አለኝ ብሎ የሚኩራራ ሰው ደፍሮ አዘጋጀሁ በሚል በኩራት የሚናገረው ሥፍራ አልነበረም።

መረራ ጥቁር እንጭኒ የደረስውን ዕልቂት እንደሰማ በአምቦ ገጠር ሲባዝን ቆይቶ በመጨረሻ እጅ እንደሰጠና ለምን መስጠት እንደወሰነ ያትታል። የኔ ወንድም ደብዳቤ ደግሞ እሱ ከ2ተኛ ፖሊስ ጣቢያ መረራ ደግሞ “ምርጫ ተሰጥቶኝ” (ለማንም ያልተሰጠ ምርጫ ለሱ ብቻ እንዴት እንደተሰጠው ምክንያቱን የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው) በሚል ከተናገረው 6ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደውና በወታደር ማመላለሻ መኪና (MACK) ተጭነው ከተባለው የኮማንዶ ቡድን ጋር አምቦ ከተማ እንደተወስዱና እዚያም ሲደርሱ ሃምሳ ዓለቃው ተደባልቋቸው ወደ ጥቁር እንጭኒ እንደተወሰዱ ነው። የኔ ወንድም እንደሚለው መረራና ሃምሳ ዓለቃው አምቦ ከተማ ሲገናኙ እሱ በማያውቀው ኦሮምኛ ቋንቋ እያወሩ እነዶ/ር ተረፈንና ቡድኑን ወዳስቀመጡበት ዘመዶቻቸው ቤት መርተው ማሳየታቸውን ይናገራል። እሱም ራሱ (ሲራክ ተግባሩ) ጭምር በዚያን ሰዓት እዚያው ጥቁር እንጭኒ ተወስዶ እንደነበር በማብራራት ግድያው እንዴት እንደተፈፀመ ሲናገር በዚያን ሰዓት መረራ የወንድሜ ረዳት በሚል ያቀረበው ሰው መኖሩን አይናገርም። የሲራክ ትወስታ እነርሱም ተደምረው ለመረሽን ከተደባለቁ በኋላ የግድያው ተሳታፊ በነበረው የወዛደር ሊግና የአብዮታዊ ሰደድ አባሎች ባንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ ከደርግ ምርመራ ከፍል በተላከው በአንድ መኮንንና የበታች ሹም የሚመራው የኮማንዶ ቡድን መካከል በተነሳው አለመግባባት በመጨረሻዋ ደቂቃ “እኒኚህንም ልጆች ጨምራችሁ ግደሉ አልተባልንም” በሚል ያንደኛው ወገን እሪታ መትረፋቸውንና ጭፍጨፋውን ከፈፀመው ቡድን ጋር እሱም፤መረራ ጉዲናም፤ ሃምሳ ዓለቃውም ተመልሰው ከሃምሳ ዓለቃው በስተቀር እነርሱ በእስር እንዲቆዩ መደረጋቸውን ነው። ሲራክ ተግባሩም ለመረራ ጉዲና በፈረንጅ አቆጣጠር በ2010 የላክውና መልስ ሳያገኝ የቀረው በዲችልና ኢሜል የተላከው ደብዳቤ ይህንን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ለምን ለመረራ ጉዲና ለመፃፍ የተገደደበትንም ምክንያት አብሮ ያነሳል።

“ለማስመሰል ደርግ ጽ/ቤት እንደ እስረኛ” እንደወሰዱኝ የሚናገረውም አንባቢ የሚታዘበውና የሚያሳዝን ነው። መረራ በመጽሐፉ ውስጥ እንደጠቀሰው ‘ምርጫ’ ተሰጥቶት ወደስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ፤ ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ተወስድኩ ሲል ነግሮናል። ለእኔም ሆነ ለሌላ የመኢሶን አባላት ምርጫ ሳይሰጥ እኔ ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከዚያም ወደ 4ኛ ክፍለ ጦር ተወስኛለሁ። እኔም ሆንኩ መረራ ለረጅም ዓመታት የቆየንባቸው እሥር ቤቶች “ለማስመሰል” ሰው የሚታሰርባቸው ቦታዎች አይደሉም። በአንፃራዊ ደረጃ ያወዳደርን እንደሆነ 4ኛ ክፍለ ጦር ያለስንቅ፡ ነፃ ህክምናና እንደልብ ነፋስ ለመቀበልና ለመንቀሳቅስም ሆነ ዘመድ ለጥየቃ ብቅ በማይልበት ማጎሪያ በጥብቅ መታሰርና በወህኒ ቤት ተበላም አልተበላም መንግሥት ስንቅ በሚያቀርበብትና የዘመድ ጥየቃ በማይከለክበት፣ አልፎ ተርፎም ለመንቀሳቀስና ከሌላው እሥራኛ ለመገናኝት ይህን ያህልም ገደብ በሌለበት ቦታ መታሰር መካከል የትኛው እንደሚሻል መረራ ጠፍቶት ነው ለማለት ይቸግረኛል። ከሌላው የመንግሥት ቀለብ ከነበረው እሥረኛ የሚተርፈው ትርፍራፊ በሙሬ ከየሳህኑና ከየወለሉ ላይ እየተሰበሰበ፣ በባሬላ ከተጫነ በኋላና ጠባቂዎቻችን ፈቅደው ወደእኛ እስኪመጣ ድረስ የዝንብ መንጋ ሲተራመስበት ቆይቶ የሚደርስልንን፣ ዘመዶቻችን የሚያቀርቡትን እንደማጣፈጫ አያይዘን ለመብላት ስንጣደፍ ከምግቡ ማነስ የተንሳ ገና እጃችንን ለሁለተኛ ጊዜ ሳንሰድ ቦዶ ከመሆኑ የተነሳ ረሃብ ማለት ምን እንደሆነ ልንገነዝበ በቻለንበት ቦታ መታሰር ምን ማለት እንደነበር ሳስበው ያሳለፍነው መከራን ችግር እስካሁን ዓይኔ ላይ ድቅን ይላል። ይህ ብቻ አይደለም ዝንብ ሲተራመስበት ውሎ የሚመጣልን ትርፍራፊ ያስከትል የነበረውን የሆድ ሕመምና ተቅማጥ ተቆጥረን ከተዘጋብን በኋለ ለመጽዳዳት ስለማይፈቀድለን ቀን በበላንበት ለመጸዳዳት የመንግደድበትን እሥር ቤት ማንም “ለማሰመሰል” ለዘመናት የሚቆይበት እንዳለነበር ሕሊና ላለው ሰው የሚጠፋ አልነበረም። በ4ኛ ክፍለ ጦር እጅግ ዝቅተኛ የሆነው የሰው ልጅ መብት በተገፈፈብት ቦታ የነበሩ ሁሉ ሊታዘቡት እንደሚችሉት በመኢሶን ድርጅት ውስጥ “ዕልቅና” ነበረኝ ከሚል ሰው ይቅርና ከውጭ ወሬውን የሰማ ሰው የማንኛችንንም በየትኛወም ቦታ መታሰር “ለማሰመስል” በሚል የሚፈርጅ ሰው ቢኖር መረራ ጉዲና ብቻ ይመስለኛል። ግራ የሚገባኝ ይህ ሰው ምን እንደተማረና ከሃምሳ ዓመት በላይ በሆነው ዕደሜው ምን ተመክሮ እንዳካበተ ነው። ባጭሩ ይህ ሰው እንዳለ ዜሮ ነው ማለት እችላለሁ።

መረራ ጉዲና በመፅሐፉ ገፅ 89 እና 92-93 ጥቁር እንጭኒ ከወደቁት ጓዶቼ ጋር ባንድ ጉድጓድ ሳልገባ በመቅረቴ የገባውን መቆጨትና ባሰበውም ቁጥር በሞት ከተለዩት ዘመዶቹም ሆነ ለተሰዉት ጓዶች ካለቀሰው የበለጠ የኔን ነገር ሲነሳ ከመዘግነን አልፎ ዕንባው እንደሚፈስ የገለፀውን ስመለከት ከዚህም የተሻለ የሰውዬውን ትምህርት፤የዕድሜ ተመክሮም ሆነ ሥልጣኔ (civility) ያልሞረደውን የጭካኔ (sadistic) አመለካከት የሚያስረዳ ዓረፍተ ነገር አላገኘሁም።

በገፅ 124 – 125 ደግሞ እኔ “የዘመኑ ቀንደኛ ነፍጠኛ የነበረው የደጃዝማች ፀሐዩ ዕንቆ ሥላሴ የእህት ልጅ” መሆኔን በማንሳትና ዝቅ ብሎም በባሌ ተነስቶ ለነበረውና በዋቆ ጉቱ ይመራ ለነበረው የኦሮሞ ገበሬዎች እንቅስቃሴ መደምሰስ ምክንያት አድርጎ ከሚያቀርበው ከሌላው የእናቴ አጎት ጋር በማገናኘት እኔም “ያቀነባበርኩት ክህደት” ከነፍጠኛ” ዘመዶቼ ተነጥሎ እንደማይታይ አድርጎና አያይዞ ማቅረቡ ከአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊም ሆነ በሶሺያልስት ንቅናቄ ስም በሚጠራ ድርጅት ላንድ ሳምንት ያህል እንኳን በአባልነት ከታቀፈ ሰው የማይጠበቅ ወራዳ አነጋገር መሆኑን አንባቢ እንዲታዘበው እተወዋለሁ። ይህንን የመሰለ ወደ ዘርና ብሔር የሚዘቅጥ የማነካካት ቋንቋ ወደኦነግ ከተጠጉ አክራሪ ኦሮሞ ብሄርተኞቸ ሰሰማው የነበረ ፀረ አማራ አነጋገር ከዚህ ሰው መስማቴ አስገርሞኛል። መረራ በኦሮሞ ገበሬ ቤተስቦቹና ዘመዶቹ የሚኮራውን ያህል እኔም ከላይ በጠቀሳቸው አጎቶቼ ብዙ የምኮራበት ቅርስ ያለኝና በዚህም የማላፍር ሰው መሆኔን እንዲረዳው እፈልጋለሁ። ማንኛችንም መርጠን ከዚህ ብሄር ወይም ከዚያ ዘር አልተወለድንም። ልንከሰስበትም ሆነ ልንመጻደቅበትም አይገባም።

መረራ ጉዲና በተለይ የደጃዝማች ፀሐዩን ስም በዚያው በጅባትና ሜጫ ግንደበረትና ጥቁር እንጭኒ ይፈፀም ከነበረ አንድ ታሪካዊ ጉዳይ ጋር በማያያዝ ስማቸውን በክፉ እንደሚያነሳ ከታናሽ ወንድሜ በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ። ነገር ግን ይህ ተራ ጉዳይ በመሆኑና መረጃም ስለሌለኝ ምክንያቱ ለዚህ ነው ብዬ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መረራን ለመክሰስ መሞከር እሱን ራሱን መሆን ነው። እርግጥ ደጃዝማች ፀሐዩ የጅባትና ሜጫ አውራጃ ገዥና ከዚያም የሸዋ ክፍለ ሃገር ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ ሆነው በቀዳምዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ባገለገሉበት ዘመን በዚህ በጅባትና ሜጫ አውራጃ በግንደበረትና ጥቁር እንጭኒ አካባቢ በባሪያ ሽንገላ የተሰማሩ የኦሮሞ ባላባቶችንና ከመካከለኛ እስክ ሃብታም ገበሬ ድረስ የሚደርስ መተዳዳሪያ የነበራችወን በዚሁ በባሪያ ንግድ ተሰማርተው የነበሩትን በማሰስና በባርነት የፈነገሏቸውን በነፃ እንዲለቁ ከማስገደድና በዚህ ንግድ አካብተውት የነበርውንም ሃብትና ንብረት በመውረስ፣ ገሚሶቹንም ወህኒ ቤት በማውረድ የባሪያ ንግድ እንዲወገድ አድርገዋል። ይህ ብቻ አይደለም። ከሕዝብ ንብረት በመንጠቅ አላግባብ የበለጸጉ አማሮችን ንብረት ጭምር በመውረስ ንብረታቸው ለተነጠቀው ኦሮሞ ገበሬ በመመለስ ለሕግና ፍትህ የቆሙ ሰው እንደነበሩ ዶ/ር ሥዩም ሐረጎት ከጻፉት መጽሐፍ አንብቦ መረዳት ይቻላል። ይህ ብቻ አይደለም። በዚያን ዘመን ከአውጫጭኝ ለማምለጥ የሞከሩ ባሪያ ሸንጋዮች ከሥርቻ ጥለውት የሄዱትን ከመረራ ብሔር/ብሔርሰብ የሚወለድ ሕፃን ወንድ ልጅ ደጃዝማች ፀሐዩ እንደልጃቸው ወስደው በማሳደግ አርበኞች ት/ቤት በማስገባት፣ ከዚያም ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጭ አገር በመላክ በስማቸው የሚጠራ፣ አገራችን ካፈራቻቸው አጅግ ታዋቂ የቀዶ ጥገና ሐኪም ለማፍራት የቻሉ ሰው መሆናቸውን ልነግርህ እወዳለሁ። መረራን ከመሰለ አሳዛኝ ፍጡር “ቀንደኛ ነፍጠኛ” በሚል የማዋረድና አክብሮት የመንሳት አነጋገር በሱ ዙሪያ ያሉትን ያስደስት ይሆናል። ብስለት ያላቸው ወገኖች ግን መረራ ለኦሮሞ ሕዝብ ምን ተጨባጭ ቁም ነገር እንደሰራና ምን ያህልስ ከበሬታ ያለው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ እንደሆነ ይጠፋቸዋል ብዬ አላሳብም።

የኔን አጎትች በሚመለከት አገራችን በኢጣልያ ፋሽስት በተወረርችበት ዘመን በዱር በገደሉ በመንከራትተት የሰሩትን ጀብዱና የፈጸሙትን ያርበኘነት ታሪክ መረራ ቢቀር ለብዙ ውድና እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች የሚያኮራ ቅርስ መሆኑን ላስገነዝበው እወዳለሁ። እንዲሁ በመደዳው (simplistic በሆነ መንገድ) “ነፍጠኛ” በሚል ለማዋረድ የሚሞከር ትምሀርት ቤት ያልገባና ታሪክን፣ በመወለድ ማነንትን፣ በአዲስና ዘመናዊ የፖለቲካ ባህል አእምሮውን ማነፅ ያልተሳካለትና በዘር ላይ የተመሰረተ ጥላቻወን መደበቅ ያልቻለ ከንቱ ሰው ብቻ ነው።

መረራ ጉዲና የባሌው የነዋቆ ጉቱ ትግል ከራሱ ብሔር/ብሔረሰብ ከመጡ ኢትዮጵያዊ ፀረ ፋሽስት አርበኛና ጄነራል እንዳከተመ እዚያው አዲሰ አበባ ዪኒቨርስቲ ካሉት የታሪክ ምሁራን ጠይቆ መረዳት አለመቻሉን ሰመለከት ይህ ሰው በዚያ ዩኒቨርስቲ በጉርብትና ካልሆነ በስተቀር በማስተማርና ምርምር ሥራ ላይ መሰማራቱ የሚያጠራጥር ሆኖ አግቼዋለሁ።

ይህ ሰው ስለራሱ ያለው ግምትና የሚሰጠው ምስክርነት ከየትኛወም ኢትዮጵያዊ አንደበት ተሰምቶ የማይታወቅ ነው። ይህ የበሽታ ካልሆነ በስተቀር ከጤነኛ ሰው የሚጠበቅ አይደለም። የምደመድመው ግን እንደሱ የሚያስጨንቅ የሕሊና ሥቃይና በቅሌት የሚጠረጠር የሕይወት ታሪክ እንደሌለኝ እንዲገንዝብ በመንገር ነው። በራሴ ላይ እምነትና የመንፈስ ጥንካሬ ያለኝ፣ እንደ መረራ በጠባቡ ሳይሆን፣ ካንድ አገር ግዛት ክልልና ብሔራዊ ጥቅም ባሻገር ዓለም ዓቀፋዊነትንና (Internationalism) እና ሰብዓዊነትን (Humanism) የሕይወት ተመክሮዬ በማድረግ ባለም ዙሪያ ያሉትን የሰው ልጆች በተማርኩትና በልምድ ባካበትኩት ቅርስ በማገልገል ላይ እገኛለሁ። ስለዚህም እንደ መረራ ጉዲና ወደዚያ የዛሬ 35 ዓመት ታሪክ ከመመለስና ጊዜ ከማጥፋት ይልቅ ትምህርታዊና ላለውም ሆነ ለመጭው ትውልድ የሚጠቅም በመቻቻልና መከባበር ላይ ለቆመ፣ ዘላቂና ሰላማዊ የፖለቲካና የልማት አማራጭ ሃሳቦች ላይ ማተኮር እንደሚገባ በማሳሰብ ጽሑፌን እደመድማለሁ።

“ሕዝቡን ሳያደራጁ፣ ታግለው ሳያታግሉ መግለጫ ብቻ የሚያወጡ ነጻ አውጪዎችን ከመተቸት መቆጠብ የለብንም”–አበበ ገላው

$
0
0

abebe gelaw
ታዋቂው ጋዜጠኛ አበበ ገላው በፌስቡክ ገጹ “ተቃዋሚዎች አይተቹም ያለው ማነው?” በሚል ባስተላለፈው አጭር መልዕክት ተቃዋሚዎች ሲሳሳቱና ሲዳከሙ በመተቸት “በወያኔያዊ ቋንቋ ሂሳቸውን” እንዲውጡ ማድረግ ያስፈልጋል አለ::

“በኢትይዮጵያ ፍትህ፣ እኩልነት፣ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ ምናምን የማምጣት አላማ አለን ብለው አውጀው እያንቀላፉ ምንም ሳይሰሩ፣ ህዝቡን ሳያደራጁ፣ ታግለው ሳያታግሉ መግለጫ ብቻ የሚያወጡ ነጻ አውጪዎችን ከመተቸት መቆጠብ የለበንም።” ያለው አበበ ለዚህም ምክንኒያት ሲያቀርብ “ለነጻነት የሚታገሉ የወያኔ ተቃዋሚዎች መከፋፈልና መዳከም የጎዳው የኢትዮጵያን ህዝብ የጠቀመው ደግሞ አረመኔውን የወያኔ ስርአት ስለሆነ ነው።” ይላል። አበበ በመጨረሻም መል ዕክቱን ሲያስተላልፍ “ይህን የነቀዘና የበሰበሰ አንባገነናዊ ስርአት ገርስሶ ለመጣል በቅንጅትና በህብረት መታገል ወሳኝ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።”

New Picture (4)

የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች በዚህ ዙሪያ ምን ትላላችሁ?
እንደጋዜጠኛ ሁሉን ነገር ለሕዝብ ማድረስ ግዴታ መሆኑ ቢታመንም፤

* እውን ተቃዋሚዎችን በአደባባይ መተቸት፣ ሲያጠፉ ማጋለጥ ትግሉን ይጎዳዋል?
* ተቃዋሚዎችን መተቸት ወያኔን ማስደሰት ነው ወይ?

አስተያየታችሁን እንጠብቃለን፦

የጀርመን ድምጽ ራድዮ ጋዜጠኛው ከአንድነት ጽ/ቤት ሲወጣ በመኪና ተገጨ

$
0
0

Fnote Breaking News(ፍኖተ ነፃነት) ጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ዮሃንስ ገ/እግዚያብሄር ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በመኪና እንደገጩትና “ገና እንገድልሃለን” የሚል ዛቻ እንደሰነዘሩበት ለፍኖተ ነፃነት ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛው ከአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ጋር በፓርቲው ጽ/ቤት ቃለምልልስ አድርጎ ወደ መገናኛ አካባቢ ሲደርስ ኮድ 1 የታርጋ ቁጥር18345 የሆነ ሚኒባስ ታክሲ ሆነ ብሎ አደጋ አድርሶበታል፡፡ “ገጭታቸሁኝ ወዴት ትሄዳለትሁ” በማለት ሲጠይቃቸውም “ገና እንገድልሃለን” ብለውት እንደሄዱ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡

ጋዜጠኛው ላይ የመኪና አደጋ ያደረሰው ታክሲ ውስጥ ሹፌሩና አንድ ግለሰብ ብቻ እንደነበሩም ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛ ዮሃንስ ገ/እግዚያብሄር በአሁኑ ሰአት ጉዳዩን ለፖሊስ በማስመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡


የአውሮፕላን ጠለፋውና የኢህአዴግ ማአከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ (አጭር ወግ)

$
0
0

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠለፈ፤ ጠላፊው ምክትል አብራሪው ነው ተባለ
ከወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

የኢህአዴግ አመራሮች ለአስቸኳይ ጉዳይ ቤተመንግስት ተጠርተዋል:: ሊቀመንበሩን የስብሰባውን አጀንዳ መናገር ጀመሩ::

እንደምታውቁት መጪው 2007 የምርጫ ጊዜ ነው:: እና ጠላቶቻችን ከአሁኑ ምርጫው ; ፓርቲው እና አገሪትዋ ላይ አደጋ ለማድረስ እየሞከሩ ነው:: ለዛ ምሳሌ የሚሆነው እና ዛሬ የተሰበብንበት ምክንያት ትላንት የተጨናገፈው የአውሮፕላን ጠለፋ ነው:: ፓርቲያችን እንደ ትላንት አይነቱ ጸረ-ልማት የሆነ ተመሳሳይ ተግባር እንዳይፈጸም ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት:: ለዚህም አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ይጠበቅብናል::
በእዚህ አጀንዳ ላይ ያላችሁን አስተያየት ስጡና እንወያይበት::

አንዱ አመራር እጁን አወጣ:: እንዲናገርም ተፈቀደለት::

>
እሱ ተናግሮ እንዳበቃ ሌላኛው እጁን አወጣ::

>

ሌላኛው ቀጠለ

>
ሌላኛው አከለ

>

ሌላኛው የህወሃት አመራር እንዲህ አለ

> አለ

በስብሰባው መጨረሻ ፓርቲው ጠለፋውን የሚያወግዝ ጽሁፍ አውጥቶ እና ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ ላይ በመወሰን አምራሩ ተበተነ::
በነጋታውም በከተማው የታክሲ እና አውቶቡስ ተሳፋሪ መጫኛ እና ማውረጃ ቦታዎች ላይ የፌዴራል ፖሊሶች ተመድበው ተሳፋሪው ጥብቅ ፍተሻ እየተደረገበት መሳፈር እና መውረድ ጀመረ::

ረዳት ፓይለቱ ለኢትዮጵያ ተላልፎ የማይሰጥባቸው 6 ምክንያቶች

$
0
0

ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

hailemariam abera tegegn ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን ተላልፎ ይሰጣል የሚል እምነት የለኝም።

አንደኛ፣ ኢትዮጵያ የሞት ቅጣትን ተግባራዊ የምታደርግ አገር ናት።

ሁለተኛ፣ ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት ጥሰት በአለም የምትታወቅ ናት።

ሶስተኛ፣ ኢትዮጵያና ስዊዘርላንድ ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ( extradition treaty) የላቸውም::

አራተኛ፣አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዝም ብለው አይቀመጡም።

አምስተኛ፣ እንደሚባለው ጭንቀት ኖሮበት ድርጊቱን ከፈጸመም የበለጠ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይመለስ ያደርገዋል። ምክንያቱም በስደተኝነት ህግ የአእምሮ ጭንቀት ያለባቸው ሰዎች ጥገኝነት ለማግኘት ከፍተኛ እድል አላቸውና።

ስድስት፣ የአእምሮ ጭንቀቱ መንስኤ የቅርብና ከአጎቱ ሞት ጋር በተያያዘ ከሆነ ደግሞ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጉዳዩን ይበልጥ ያከብድለታል ምክንያቱም የአጎቱ ሞት መንስኤ እስካሁን እንቆቅልሽ እንደሆነ አለና። እህቱ የጻፈችውም ደብዳቤ የሃይለመድህንን ችግር ይበልጥ የሚያሳይ ነው ። “ጠላቶች እንዳሉ እንደሚያምን ፣ ስልኩን እንደጠለፉት እንደሚያስብ፤ በላፕቶፑ ካሜራ ሳይቀር ያዩኛል ብሎ ስለሚሰጋ ካሜራውን ሳይሸፍን እንደማይከፍት እንዲሁም፤ ወጥቶ እስኪገባ ቤቱን ሲበረብሩ የቆዩ ስለሚመስለው ካሜራ ጠምዶ መሄድ ” መጀመሩን መግለጿ፣ የሃይለመድህ መሰረታዊ ችግር የደህንነት ዋስትና ማጣት መሆኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የደህንነት እጦት (insecurity) የሚያሳይ ነው። በቤተሰቡ በተለይም በአባቱ ላይ ተከፍቶ የነበረው የማጥፋት ዘመቻም ለጭንቀቱ መንስኤ ሊሆን ይችላል።

የሃይለመድህን ድርጊት ባለሁለት ሰይፍ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት በሁለቱም ሰይፍ መቆረጡ አይቀርም። ፓይለቱን የአእምሮ በሽተኛ አድርጎ ቢያቀርበው፣ ለአየር መንገዱ ትልቅ ኪሳራ ነው። መንገደኞች ከእንግዲህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመጓዝ ድፍረቱ አይኖራቸውም፣ ለዚህም ይመስለኛል አቶ ሬድዋን ፓይለቱ ሙሉ ጤነኛ ነው ሲሉ መግለጫ የሰጡት። ወጣቱ ለስደት መጠየቂያ በማሰብ የወሰደው እርምጃ ነው ቢሉም፣ ” በደህና የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሰው እንዴት ስደትን ሊመርጥ ቻለ?”፣ ከስደት የከፋ ችግር ቢያጋጥመው ነው ተብሎ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ መነሳቱ አይቀሬ ነው። መንግስት ግራ ሲጋባ ይታየኛል
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠለፈ፤ ጠላፊው ምክትል አብራሪው ነው ተባለ

(የአውሮፕላኑ ጉዳይ) ምንድን ነው ኩራት?

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ዘጠና ደቂቃ በኢንተቤ በሚል እርስ በታዋቂው ጸሐፊ ማሞ ውድነህ የተተረጎመ አንድ የእውነት መጸሐፍ በልጅነቴ ማንበቤን አስታውሳለሁ። ግን በጣም በተደራጀና በርካታ ጉዳዮችም በቅንብር የተከወነበት ነበር። ዛሬ ደግሞ በአንድ ዕጣ ነፍስ ቀንበጥ እጅግ የተጠና የታቀደ የቀደመ ሥልጡን ተግባር ተከወነ። ትውልዱና ታሪኩ በአዲስ መልክ አዲስ ምዕራፍ ከፈቱ። ለእኔ ኩራት ማለት የወገንን ጥቃት በረቀቀ ግን በታቀደ በተረጋጋ መንፈስ የሚከወን ተግባርን ነው።
እርግጥ ሌትና ቀን ወያኔና አጃቢዎቹ ተደናብረዋል። የኢትዮጵያ አዬር መንገድ ክብር፤ ዝናና ታሪክ ጎደፈ ሲሉም ይደማጣሉ። ኩራትና ዘረፋ ቀረ አይነት። መጀመሪያ ነገር አይደለም የኢትዮጵያ አዬር መንገድ ኢትዮጵያ ከነሙሉ አካሏ አለችን? የትናንት የኩራት የነፃነት አንባ አይደለም ለእኛ ለጥቁር ህዝብ አርማ የነበረችው ሀገራችን ከነሙሉ ወርድና ቁመናዋ አሉን? ለእኔ የለችም ነው የምለው። ….. ይህቺ ናት እኮ ኢትዮጵያ ስንት ጊዜ ቀዶ ጥገና ያደረጋላት ወያኔ …. ያፈረሳት፤ እንደ ሰንጋ ለባዕዳን ያቀራመታት። ባህሏም፤ ታሪኳም፤ ጥሪቷም፤ ቅርሷም፤ የዕምነት ሥርዓተ ህግጋቷም፤ ህይወቷም ጠረናቸው የተበከለ ሆነው ከእኛነታችን ውስጥ እንዲፋቁ መርዝ የነሰነሰባት። ባዕዳን ሲገቡ ከነሁለመናቸው ነው። ለጆሮ ከሚዘገንኑ ልማዳቸው ጋር …. በቻይና ሃብታሞቹ ምን እንደሚበሉ ታውቃላችሁ? በልጅነታችሁ ሲተረትላችሁ የነበረውን የጭራቅ ታሪክ እሰቡት …. ይቀፋል ….
New Picture (5)
በወያኔ – ትራፊ በሰልፍ የሚጠበቅባት፤ ሚሊዮን የነገ ፍሬዎች ነገ ሳይመጣ ተስፋቸው ደርቆ እራብ እዬቆላቸው የሚያልቁባት። ሊለምኑ ያፈሩ ሚሊዮኖች እንደ ተዘጋባቸው የሚያልፉባት። ህጻናት እንደ አወጡ ለንግድ ጨረታ የወጡባት፤ ሴት ታዳጊ ወጣት ደመ ከልብ ሆነው አረብ ሀገር ተደፍረውና ተዋርደው የሚቀቀሉባት፤ ሀገር ውስጥ ያለው ወጣት በቤንዚን አርከፍክፎ እራሱን የሚያቃጥልባት፤ ታንቆ ወንዝ ገብቶ የሚሞትባት፤ በዘሩ በሃይማኖቶ እዬተለቀሙ ዕልፎች ከሥራ ገበታቸው የሚባረሩባት የዕንባ ባዕት … ለእለት ጉሮሮ፤ ለመጠለያና ለከፈን ያልተበቃባት።
አዬሩ የስጋት ዓውድ ያፈናት፤ ስደት ከሃይማኖት አባቶች ጀምሮ በፆም በጸሎት የሚናፈቅባት፤ ሰው በነፃ ቤቱ በሰላይ ታፍኖ የሚኖሩባት የረመጥ ሀገር እኮ ናት ኢትዮጵያ ዛሬ። መሬቷ ለነገ ሳይታሰብ ተሸጦ በኬሚካል የሚቃጠልባት ኖሪዎቿ እዬተፈናቀሉ ባለቤት አልባ የትም የሚበተኑባት፤ ህጻናት ወላጅ አልባ የሚቀሩባት እኮ ናት ዛሬ እናት ሀገር። የሰው ልጅ በአስተሳቡ የሰበውን ያለመውን እንዳይናገር ጉሮሮውን የተዘጋበት መንፈሱ የተቆለፈባት ወጥቶ ለመግባት ማስተማመኛ የሌለበት፤ የክትና የዘወትር የሚለይባት፤ ለዘመንተኞች ገነት ለብዙኃኑ ሲኦል የሆነች ሀገር እኮ ናት።
በደም በአጥንት በክብር የተከበረች ሀገር ለውጪ ኃይል ለገጸ በረከት የተሸለመች ሀገር ሆና … እንዴት ኩራት ይታሰባል?
hailemariam abera tegegn
ይህ ያንገፈገፈው የመረረው የዘገነነው ወጣት እንሆ ቆረጠ ወሰነ አደረገውም። ገድል ነው። ብቻውን ከሀገርም ሲዊዘርላንድ መረጠ – ረቂቅ። በተረጋጋ መንፈስ ሳይታወክ ፍላጎቱን በጥቂት ቃላት ብቻ ልብን እንደ ቅል አንጠልጥሎ ገለጸ። ምንም ዓይነት አይደለም የድርጊት የቃል እንኳን ግድፈት ሳይኖርበት። ምንም አይነት የቅድመ ሁኔታ ድርድር ሳይጠይቅ፤ እጅግ በቀደመ ጨዋነት ለሚሊዮኖች እራሱን ሰጠ። በቃ! ፍቅር ይሏችኋል ይህ ነው! ኩራትም ይሏችኋል ይህ ነው! ጀግንነትም ይሏችኋል ይህ ነው! የእናት ሀገር ጥሪ ከሰማያተ ሰማያት ፈቅዶ ተቀበለ። የተሳካ በፍጹም ሁኔታ የተሳካ ድርጊትም እንሆ ከወነ። በድርብ አንጎል። ሌላው ወያኔ ሊደበቅበት የሚገባው ጉዳይ ለኣለም ድንቅ ትምህርት ቤት የሆነው አዬር መንገዳችን የትውስት ዋና አብራሪ ሲኖረው ይህ ነው ታላቁ ውርዴት ለወያኔ … ይህን የመሰለ ጭንቅላት ያለው ወጣት ረዳት፤ ጣሊያናዊ አብራሪ ዋና …. ዓለም ከሃቅ ጋር እስኪ ይፋጠጥ ….

ትውልዱ ይህን ይመስላል ወያኔ ቢማርበት። 40 ዓመት የደከመበት መና ከንቱ መቅረቱን። ዛሬም እናት ጀግና ትወልዳለች። ዛሬም ኢትዮጵያዊነት ግብግብ ቅጥል ርምጥምጥ የሚያደረገው አርበኛ እንዲህ በልበ ሙሉነት ሙያ በልብን ከውኖ ገዢ መሬቱን ካለምንም ብክነት የሚቆጣጠር ቀንዲል ትወልዳለች አምላኳ አልረሳትም እና።
ዓለም ፊቱን አዞረ፤ ሰንደቃቸውን እንደ ለሰበሱ በትቢተኛው ሳውዲ አደባባይ ወገኖቻችን ደማቸው ሲንዶለዶል ሚዲያው ሁሉ ዘጋን፤ እኮ ታምረኛውን አምላክ አዘጋጅቶ ኖሮ ዛሬ አንደበታቸውን አስከፈተ። ጀግናው አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ተገኘ በክፉ ቀኗ ለእናት ሀገሩ የተገኘ የቁርጥ ቀን ልጅ። ሥሙ እራሱ ሥም ነው።
እኛ ስለ እስራቱ፣ ስለነገ ህይወቱ ተጨንቀን ይሆናል። እሱ ግን ሁሉንም ዓይነት መስዋዕትነት ለመቀበል አውቆ የቆረጠ የወሰነ ምርጥ ዘር ነው። ቀደምቶቹ – አብርኃም ደቦጭ፤ ሞገስ አስገዶም፤ አብዲሳ አጋ፤ ኃይለማርያም ማሞ፤ በላይ ዘላቀ፤ ዘርአይ ደረስ – ተፈጠሩ። ዳግም ተነሱ። የትንሳኤ መግቢያ ዋዜማ …..
በተጓዦች ዘንድ አንድም የመንፈስ ቅንጣት ጭንቀት ሳይፈጠረ፤ በረቀቀ ጥበብ በአውሮፕላኑ ድንበር ወስጥ ሳይሆን ከዛ ውጪ በሆነ ሁኔታ በመስኮት የላቀ ትዕይንት …. ፈጸመ። በሰለጠነው አለም ቢሆን ስንት ኪኖ ያሰራ ይሆን ይህ ታዕምር? …. ይህን የዘመናችን አዲስ ትውልድ እኮ ለመተርጎም የሰማይ ጸጋ ይጠይቃል አባቶቼ ያመሳጥሩት እኔስ አቅም የለኝም።
አጓጒ ሂደቱ ልብን እንደ አንጠለጠለ ይቀጥላል። የተረጋጋችውም ሲዊዝም ሰከን ብላ ለየት ባሉ ህጎቿና ተፍጥሯዋ ትንሽ በትንሽ እያቃመሰች የኢትዮጵያን መከራ ፈተና ስቃይና ዕንባ በዓለም አደባባይ ታስፈትሻለች ….
በጀግናው ፊት ለፊት በጎኑ በስተኋላው ያለው ነፃነት የናፈቃት እናት ሀገሩና የፈጠረው አምላኩ ደግሞ ከመቼውም በላይ ጥበቃቸው አይለዩትም። ሲፈጠር የተቀባበትን ጸጋ ነው የፈጸመው አትርፏል። ትርፉ 150% ነው። እነሱ ዋስ ጠበቃ ይሆኑታል። በእኛ በኩል ደግሞ ለዚህ ለላቀ መስዋዕትነቱ እኛ ነፍስ ያለው ጠበቃ አቁመን መሟገት። የጠነከረ ተከታታይነት ያለው የሎቢ ተግባር መሰራት። ለምናውቃቸው ሁሉ የኢትዮጵያን መከራና ሰቀቀን እስካሁን ድረስ በኣለም ዐቀፍ ሰብዕዊ መብት ድርጅቶች የተዘገቡትን ሪፖርቶችን ሊንኮችን እያሰባሰብን መላክ። ከጎኖ መቆም ያስፈልጋል። አብሶ በእንግሊዘኛ ቋንቋ አጫጭር ጹሑፎች በምልሰት በደሎች እዬተቃኙ ማቅረብለወቅቱ ተስማሚዎች ይመስሉኛል።
ዜግነት እንዲህ ሲያምርበት፤ እንዲህ በድርጊት በጥበብ ልቆ ባለማዕረግ ሲሆን ከማዬት በላይ ምን ሐሴት አለ?! የጉዞ አቅጣጫ ካለምንም የሰው ህይወት ጥፋትና ንብረት እንዲሁም ወድምት መሆኑስ አይገርምም! በሌላ በኩል ብልሹውን የወያኔን ሴራ ከመሰረቱ ተተራመሰ። የዘመኑ ምርጥ ወጣት ታላቅ ተጋድሎ …. ሳይ በህይወት መኖሬን ዛሬ ወደድኩት። ለእኔስ ኩራቴ ወጣት ኃይለመድህን አበራ ተገኘ። የኢትዮጵያዊነት ሚስጢሩም ተዚህ ላይ ተገኘ። እግዚአብሄር ይስጥልን የ እኛ ብቁ የተስፋ ቡቃያ! እናመሰግንኃለን፤ እናከብርህምአለን። እንወድህምአለን። ታሪክ-በትውልድ፤ ትውፊት -በድርጊት፤ አደራ – በጀግነነት በልበ ሙሉነት ተፈጸመ። ተመስገን!

ኢትዮጵያን በልጆቿ መስዋዕትነት ከዘላለማዊ ክብሯ ጋር አምላካችን ያኑርልን። አሜን።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ትግሉን ይቀላቀሉ ፣ ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊ ይሁኑ !

$
0
0

የካቲት 16 በሚደረገዉ የባህር ዳር ሰልፍ፣ መኢአድ እና አንድነት በጋራ የጠሩት ነዉ። ድርጅቶች እንዲህ ሲተባበሩ ያስደስታል። የተናጥል የብቻ ጉዞ የትም አይደርስምና።
abugida
ይህ ሰልፍ ምንም እንኳን የብሃአዴን አንድ አመራር አባል ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ቢሆንም፣ ጉዳዩ ከአንድ ግለሰብ ያለፈ መሆኑን መረዳት አለብን። ባለስልጣኑ ጸያፍና ነውረኛ አስተያየት ሰጡ የሚል ክስ ሲቀርበባቸው ፣ ገዚው ፓርቲ ፣ ግድ የለም፣ አሁኑኑ አይቅጣቸው፣ ቢያንስ ቢያንስ ግን «ጉዳዩን እመረምራለሁ። የተባለዉ እዉነት ከሆነ አስፈላጋዉን እርማት እሰጣለሁ» ማለት ሲገባው፣ ነገሩን አድበስብሶ ማለፉ፣ ገዢው ፓርቲ ምን ያህል ሕዝብ በፓርቲ ደረጃ እንደሚንቅ፣ ከሕዝብ ክብር ይልቅ የካድሬዎቹ ደህንነት የሚያሳስበው እንደሆነ ያመላከተ ነዉ።

በመሆኑም የሚሊየነም ድምጽ ፌስቡክን፣ የምንከታተል ሁላችንም፣ በኤሜል ፣ በትዊተር ፣ በእጃችን ያሉ መንገዶችን ሁሉ በመጠቀም ቅስቀሳዉን እንቀላቀል። ከአንድ፣ መቶ፣ ከመቶ፣ ሺህ፣ ከሺህ ሚሊዮኖች ይበልጣሉና።

በባህር ዳር ፣ ዘመድ፣ ወዳጅ፣ ጓደኛ ያለን፣ ደዉለን ወደ ሰልፉ እንዲወጡ እናበረታታ። ለሰልፉ የሚያስፈልጉ ብዙ ወጪዎች አሉ። በገንዘባችን ድጋፍ እናድርግ። ጋዜጠኞች፣ የድህረ ገጽ ሃላፊዎች፣ የተለያዩ ሜዲያዎው፣ ሰልፉን ለሕዝባችን በማስተዋወቁ ረገድ ድጋፋቸዉን ያበርክቱ። ጸሃፊያን ብእራቸውን እንዲያነሱ፣ ስለሰላም፣ ስለዴሞርካሲ፣ ስለመበት፣ ለሕግ የበላይነት እንዲጽፉ እናበረታታለን።

የቻልን በአካል ሰልፉን እንቀላቀል። ያልቻልን በመንፈስ የትግሉ አጋር እንሁን። የሁላችን የሆነቸዋን አንዲ አገር በጋራ እናድናት::

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ

$
0
0

ኢትዮጵያ ሃገሬ ከጅዳ በዋዲ

ከተመሰረተ 20 አመታትን እንዳስቆጠረ የሚነገርለት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የተፈጠረው ቃርኔ መልኩን ለውጦ መቀጠሉን የሚናገሩት ምንጮች በቀደሞው የኮሚኒትው ሊቀመንበር እና በመሃበሩ ስራ አመራር መሃከል በተነሳው አለመግባባት የፌታችን አርብ ፊብርዋሪ 21 / 2014 ምሸት ስራ አመራሩ በጠራው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አሰቃቂ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል።

በቅርቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የጠራውን የአባላት ሰብሰባ ተከትሎ የአንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቀርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ደጋፊዎቻቸውን ወደ አዳራሹ በማስገባት ከማህበሩ ሊቀመንበርነቴ የተነሳሁት ያለአጋባብ ነው በሚል በኮሚኒቲው ሊቀመንበር ላይ ቡጢ በመሰንዘራቸው ተከትሎ በተቀሰቀሰው መለስተኛ ግጨት ስበባው ሳይጀመር መበተኑ ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሺክ ሙስጠፋ ሁሴን የፊታችን አርብ ፌብርዋሪ 21-2014 የኮሚኒቲው ስራ አመራር በጠራው ጠቅላላ የአባላት ጉባኤ ላይ ሁከት ለመፍጠር በብሄር ላይ የተመሰረተ ቀስቀሳዎችን በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች ከሪያድ አረጋግጠዋል።

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ፊብርዋሪ 14-2014 ምሸት አያሌ ደጋፊዎቻቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ በሚገኝ አንድ ቢሮ ውስጥ በማን አለብኝነት ሰብሰብው ሲመክሩ መታየታቸውን የሚገልጹት ምንጮች ሼኩ ለግብረ አበሮቻቸው “አማራ ስልጣናችን ስለነጠቀን ማንነታችንን ለማስከበር እና ስልጣናችንን ለማስመለስ እኛ ኦሮምዎች እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ አይገባንም” ብለው በመናገር የጥቂት መስል ደጋፊዎቻቸውን በተሳሳተ መንገድ ቀልብ በመሳብ የኮሚኒቲውን አባላት በዘር በሃይማኖት ከፋፍሎ ለማጋጨት አቅማቸው የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አጋልጠዋል። የሼክ ሙስጠፋን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም ብሄርተኝነትን በስፋት በማራገብ ላይ የተሰማሩት ቅጥረኞች በህገ ወጥ የሃዋላ ንግድ ላይ የተሰማሩ እና ቀደም ሲል በእህቶቻችን ህይወት ዶላር ሲሰብሰቡ የከረሙ የሰራተኛ እና አሰሪ አገናኝ ኤንጀንሲ ባለቤቶች እና ደላላዎቻቸው መሆናቸውን የሚናገሩ ወገኖች ግለሰቦቹ የትኛውንም በሄር አሊያም የሃይማኖት ተቋም እንደማይወክሉ ገለጸው ህብረትሰቡ ከእንደነዚህ አይነት ሴጣናዊ መርህ ካነገቡ መሰሪዎች እራሱን በመከላከል በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈል እንደወትሮው ሁሉ በአንድነት የኮሚኒቲውን ንብረት ነቅቶ መጠበቅ እንደሚገባው መክረዋል።

የቀድሞው የኮሚኒቲ ለቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን በስማቸው በከፈቱት ሁለት ሰራተኛ እና አስሪ አገናኝ እጄንሲ ያስመጦቸው እህቶቻችን በህክምና እጦት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን የሚያስታውሱ ታዛቢዎች ሼኩ በሳውዲ አረቢያ የደህነት ሃይሎች ለእስር በመዳረጋቸውን ተከትሎ በኮሚኒቲው መተዳዳሪያ ህገ ደንብ መስረት የሊቀምንበሩን ቦታ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት ምክትል ሊቀምንበሩ አቶ ቃሲም ያሲን ተረክበው መሸፈናቸው ሊያስመስግናቸው እንጂ ቡጢ ሊያሰነዘርባቸው እንደማይገባ የሚናገሩ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ሼኩ ከወህኒ ከወጡ በሃላ ጤንነት እደማይሰማቸው በመጥቀስ የኮሚኒቲ ሊቀምንበርነቴን ለምን በአማራ ብሄር ተነጠኩ በሚል ዘረኝነት የተጠቀሱትን ደጋፊዎቻቸውን በመስብሰብ በአባላቱ መሃከል የብሄር እና የሃይማኖት ግጭትን ለመጫር እያሰሙ ያለው ጩሀት አብነት መሆኑንን ይገልጻሉ ።

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር በስሩ ከሁለት ሺህ በላይ ህጻናትን ተቀብሎ የሚያስተናገድ አንድ አለም አቀፍ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባለቤት እንደነበር የሚገልጹ አንጋፋ የማህበሩ አባላት ት/ቤቱን ከኮሚቲው በመነጠል ኤንባሲው በራሱ ስልጣን ባስቀመጣቸው የቦርድ አባላት ት/ቤቱን እንዳሻው እይዘወረ ላለፉት 4 አመታት ገቢ እና ወጪው ሳይለይ እስካሁንም የጥቂቶች ኪስ ማደለቢያ ሆኖ መቀረቱን ይናገራሉ። ዛሬ በኮሚኒቲው ስራ አመራር እና በሼክ ሙስጠፋ ደጋፊዎች መሃከል የተነሳው የስልጣን ሹክቻ ከጥቅም ጋር የተቆራኘ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች በአሁኑ ግዜ ብቸኛ የማህበሩ ንበት የሆነው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል ከት/ቤቱ ባላነሰ ሁኔታ ዘረፋ እየተፈጸመበት መሆኑን ይገልጻሉ፡፤

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ከ 8 መቶ የሚበልጡ አባላት እንዳሉት የሚናገሩ እነዚህ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ማህበሩ የፊታችን አርብ ፌብርዋሪ 21 2014 ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ መወሰኑን በመግለጽ በወቅቱ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ኤንባሲው እና የሚመለከታቸው አካላቶች የዜጎቻችን ህይወት ለመታደግ ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባቸው አክለው ጠቁመዋል።

ማሳሰቢያ ከዚህ በታች የተመለክተው የቪድዮ ሰዕላዊ መግለጫ ቀደም ብሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ውስጥ ጥቂቶች ብዙሃኑን በዘር በሃይማኖት ሲከፋፍሉት የሚያሳይ ነው።

ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ፤ ለተፈጥሮ ሃብት የጠየቀው ዓለም ዓቀፋዊ እውቅና ውድቅ ሆነ

$
0
0

አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለጋራ ንቅናቄ ለዘ-ሐበሻ የላከው መረጃ

ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር።

EITI
EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ መሆኑን የሚያምን ሲሆን ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት – ማዕድን፣ ዘይት፣ ብረታብረትና ጋዝ – ከመሬት በሚወጣበት ጊዜ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚኖረውን ያህል ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለባቸው አገራት ድርጊቱ ለሙስና እና ግጭት በር እንደሚከፍት ይናገራል፡፡ በመሆኑንም ድርጅቱ አገራት ለሚያቀርቡት የዕውቅና ጥያቄ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ልማትና እድገት በሚል ሰበብ የሕዝብ ሃብት የሆነውን የተፈጥሮ ሃብት በማውጣት የህዝባቸውን መብት ለሚረግጡ አገራት የሚያቀርቡትን የዕውቅና ማመልከቻ ውድቅ ያደርጋል፡፡

የጎልጉል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጭ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ እውነት ነው። ምንጩ እንዳሉት ኢህአዴግ በውሳኔው በመበሳጨት ይግባኝ ለመጠየቅ በዝግጅት ላይ ነው። ድርጅቱ (EITI) አንድ አገር ለሚያቀርበው የእውቅና ማመልከቻ በመስፈርቱ መሰረት ግምገማ ካካሄደ በኋላ እውቅና እንዲሰጥ ሲያምን በራሱ ድረገጽ ላይ የዚያን አገር ስም በመመዝገብ ተጠቃሹ አገር ከተፈጥሮ ሃብት ጋር በተያያዙ ኢንቨስትመንቶች የሚገኘው ትርፍ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ያደርጋል የሚል እውቅና በመስጠት ምስክርነቱን ያሰፍራል፡፡

ኢህአዴግ የመጀመሪያው የማመልከቻ ጥያቄ ያቀረበው በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ2009 አካባቢ ነበር፡፡ ከEITI አምስት መስፈርቶች መካከል አንዱ፤ ማመልከቻ የሚያቀርቡ አገራት ከመያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ጋር ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ በመያዶች ላይ አፋኝ ሕግ አውጥቶ የነበረ በመሆኑ እውቅና ሰጪው ድርጅት – EITI – የኢህአዴግን ማመልከቻ ውድቅ አድርጎታል፡፡ የEITI ቦርድ ይህን ዓይነት ውሳኔ ሲያስተላልፍ ያሰፈረው ነገር ኢትዮጵያ በእጩ አባልነት ለመመዝገብ በመጀመሪያ በመያዶች ላይ ያወጣችውን ሕግ ማስወገድ አለባት የሚል እንደነበር የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት በድረገጹ ላይ አስቀምጦታል፡፡ በወቅቱ የተሰጠው ይህ ብያኔ በEITI እውቅና አሰጣጥ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ እንደሆነ ተጠቁሞም ነበር፡፡
የEITI ዕውቅናን ለማግኘት ቋምጦ የነበረው ኢህአዴግ በድርጅቱ ውሳኔ ባለመደሰት ጥቂት ዓመታትን ቆጥሮ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ በአቶ ሃይለማርያም በመመራት በድጋሚ ዕውቅና የማግኘት ዘመቻውን ማጠናከር ጀመረ፤ በይፋም እንቅስቃሴውን ቀጠለ፡፡ የማዕድን ሚ/ር መ/ቤትም ዕውቅና ማግኘቱ በጣም የሚያስፈልግ እንደሆነ በይፋ በመናገር ዘመቻውን አጧጡፎ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ለዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አሠራር በዓለምአቀፉ ድርጅት ላይ ተግባራዊ በማድረግ ኢህአዴግ Ethiopia Revenue Transparency Initiative (ERTI) የሚባል “ተለጣፊ” ተቋም በመመሥረት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደቆየ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ለEITI በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጾዋል፡፡

ጉዳዩን በቅርብ ይከታተሉ የነበሩ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ኢህአዴግ በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር 2013 ዓ.ም በድጋሚ ማመልከቻ የማቅረብ ዓላማ እንዳለው ለዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አሳወቁ፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ ማሻሻያ እያደረጉ ነኝ የሚል ማስመሰያ ለማቅረብ የሞከረ ቢሆንም የመያዶችና የጸረ አሻባሪነት አፋኝ ሕጎቹ በተጨማሪ በቴሌኮሙኒኬሽን በኩል በስልክና ኢንተርኔት የሚያደርውን ህዝብን የመሰለል ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት እንደሆነ በመጥቀስ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ክፍሎች EITI ዕውቅና እንዳይሰጥ መወትወታቸውን ተያያዙ፡፡

እነዚሁ ወገኖች በተደጋጋሚ ያደረጉት “የወረቀትና የፔቲሽን ትግል” እየተባለ የሚቃለለው ትግል ውጤት በማምጣት ኢህአዴግ በደጋሚ ያስገባው የአባልነት ማመልከቻ ሰሞኑን ውድቅ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ EITI ማመልከቻ በሚመዝንበት በሁሉም መስፈርቶች ኢህአዴግ ወድቋል፡፡
አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኢህአዴግ “ልማታዊ” የሚላቸው ኢንቨስተሮች ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሃብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አገር ለመምረጥ የመጀመሪያው መለያቸው የEITI ድረገጽ የአባል አገራት ዝርዝር እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ።

ኢህአዴግም አስፈላጊውን የምዝገባና የማመልከቻ መስፈርት በማሟላት የተቋሙን እውቅና የጠየቀው በድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመመዝገብ ነበር። የሁለት ጊዜ ሙከራው መክሸፉ ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ህግ መታፈኑ የሚያመላክት እንደሆነ የሚጠቅሱ ክፍሎች፤ ከኢህአዴግ ከፍተኛ ፍላጎት አኳያና ሰሞኑን በተለያየ አቅጣጫ እየተወጠረ ከመምጣቱ አንጻር ሁኔታው አጣዳፊና ፋታ የማይሰጥ በሽታ ምልክት እንደሆነ በምጸት ይናገራሉ፡፡

ስለEITI ውሳኔ ባጭሩ እንዲያብራሩልን የጠየቅናቸው ባለሙያ እንዳሉት “አንድ ዩኒቨርሲቲ ህንጻ በማስገንባቱና አስተማሪዎችን በመቅጠሩ ብቻ ዩኒቨርስቲ ተብሎ ሊጠራ አይችልም። ዩኒቨርስቲው ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ መስፈርት መሰረት ተገምግሞ እውቅና የሚሰጠው መስፈርቶቹን በሙሉ አሟልቶ ስለመገኘቱ ምርመራ ተደርጎበት ፈተናውን ሲያልፍ ብቻ ነው። በዚሁ መሰረት አልፎ እውቅና ያላገኘ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገብቶ መማር የተሳትፎ ያህል ነው። መስፈርቱን አሟልተው እውቅና ካገኙት ጋር መወዳደር ስለማይችል ተመራጭ አይሆንም። በተመሳሳይ Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የተባለው ድርጅትም ከየአገራቱ እውቅና እንዲሰጥ የሚቀርብለትን ጥያቄ /ማመልከቻ/ የሚመዝንበት መስፈርቶች አሉት። ኢህአዴግ የተፈተነው በዚሁ አቅልጦና አንጥሮ በሚያወጣው መመዘኛ ነው ብለዋል፡፡”

ስለጉዳዩ የተጠየቀው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የህዝብ ግንኙነት ግብረ ኃይል ጉዳዩን በጥልቀት የሚያውቀውና ገና ከጅምሩ ሲከታተል የቆየው መሆኑን በመግለጽ በበርካታ ፈርጆች ከሚያካሂደው ትግል አንጻር በዕቅድ ሲያከናውነው የቆየ መሆኑን አመልክቷል። የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለጎልጉል እንዳለው ከሆነ “የEITI ውሳኔ ኢትዮጵያን እንደ አገር የሚጎዳ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ውሳኔው ኢህአዴግ በራሱ ግትረኝነትና እብሪት ያመጣው ጣጣ በመሆኑ የራሱን ተግባር ተከትሎ የተወሰነው ውሳኔ በአገሪቱ ላይ በማንኛውም መልኩ ለሚያደርሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግና ህወሃት ናቸው” ብሏል። በማያያዝም የጋራ ንቅናቄው ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ በማውጣት አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው ወገኖች እንደሚበትንና ተቋሙ በውሳኔው እንዲጸና የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ለተሰማሩ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ የድህነት አዙሪት መንስኤና መፍትሄዎች “በጥቂቱ”

$
0
0

(ክፍል አንድ)

ናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ ኖርዌይ)

(ናትናኤል ካፕትይመር)

(ናትናኤል ካፕትይመር)

አርእስቴን በጥቂቱ ያልኩበት ምክንያት የተነሳሁበት ርእስ ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ ስለማውቅ ነገር ግን ልንወያይበት እንደሚገባ በመረዳቴ ለውይይት መክፈቻ ይሆን ዘንድ እንጂ እኔ ባለኝ እውቀት ብቻ ሙሉ በሙሉ ልተነትነው እንደማልችል በማመኔ ነው። ይህም ቢሆን እንደዜግነቴ ሃገሬን ለዘመናት ለተቆራኛት የድህነት ችግር መንስኤና መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ዋና ዋና ነጥቦች በመጠኑ ለመተንተን ለመሞከር ነው።

በአንድ ሃገር ወይም አካባቢ የሚኖር ማህበረሰብ ለግላዊም ሆነ ማህበራዊ ፍላጎቶቹ በበቂ ሁኔታ መሟላት አጣጥሞና አስማምቶ በእኩልነት ሊያኖረው የሚችል ህግና ስርዓት በብዙሃኑ ፍላጎትና ስምምነት ላይ ተመስርቶ መቀረፅ አለበት። የሰውን ልጅ ከእንሰሳት የሚለየውና የተሻለ ያደረገውም አንዱ ሌላውን በእኩልነት ማየቱ እንዲሁም ሰው በጉልበቱ የበላይ መሆን የማይችልበት ሁናቴ መፈጠሩ ነው። ነገር ግን አንድ ጉልበተኛ ሌላውን አቅመ ደካማ በጉልበትና በማስፈራራት ፍላጎቱን ከተጫነው ከሰውነት ደረጃ ወርዶ በሰውና በእንስሳ መሃከል ሆነ ማለት ነው። ለዚህም ነው የሰብዓዊ መብት መነሻ ሃሳቡ ሰውን ሁሉ እኩል አድርጎ የማየት ላይ የተመሰረተው።

እንግዲህ ከላይ እንደጠቀስኩት ለአንድ ሃገር ወይም ማህበረሰብ የኑሮ ግብዓቶች መሟላት ማህበረሰቡን አንድ የሚያደርገው በብዙሃኑ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ህግና ስርዓት መኖሩ ነው። የእያንዳንዱ ግለሰብ ለተቀረፀው ህግና ስርዓት በመገዛት የሚያደርገው የግል አስተዋፅኦ የማህበረሰቡን አባላት ፍላጎት ከማሟላቱም ባሻገር በመተባበር ክድህነት ወደተሻለ የኑሮ ደረጃ ያሸጋግራል። ይህም ስኬት የሚገኘው ማህበረሰባዊ ወይም ሃገራዊ ህጉ በእኩልነት ላይ ሲመሰረት ነው። ጤናማ የሆነ እኩልነት መኖር በዜጎች መካከል የምርት ፣ የሞያና የክህሎት ፍሰት ፈጥሮ የዛን ሃገር ወይም ማህበረሰብ መሰረታዊ ፍላጎቶች ብቻ ሳይሆን የኑሮ እርካታን የሚፈጥሩ ተጨማሪ ፍላጎቶችንም ወደ ማሟላት ሊሻገር ይችላል።

ነገር ግን ልክ እንደ አሁኑ የአትዮጲያ መንግስት የወጡትና የሚወጡት ህጎች አቀራረፃቸው እንዲሁም አተረጓጎማቸው ለተወሰነ የማህበረሰብ አካል በአድሎአዊነት ከተንጋደዱ በዜጎች ወይም በጠቅላላ ማህበረሰቡ መካከል ፍትሃዊ የሆነ እኩልነት ከማስፈን ይልቅ የእርስ በእርስ ቂምና ግጭት በመፍጠር ሃገርን ከድህነት ለማውጣት ወሳኝ ግብዓት የሆነውን “በጋራ የማደግና የመግባባት እሴት” ያመነምናል። የዚህ የህግ አተረጓጎም መጣመም ጥቂቶችን ብቻ ጠቅሞ ብዙሃኑን ስለሚጎዳ የሃገር ሁለንተናዊ ብልፅግና ገላጭ የሆነው የወል እድገት ይቀጭጭና የድህነት አዙሪት ይፈጠራል።

አሁንም ሃገራችንን የተቆራኛት ይኸ ችግር ነው። ከዚህ አስከፊ ችግር ለመውጣት ወሳኝ ግብዓቶች ናቸው ብዬ ያሰብኳቸውን ዋና ዋና የ ሃገራዊ መዋቅር መሰረቶች በተናጠል እንደሚከተለው ለማስቀመጥ ልሞክር።

ማህበረሰባዊ  አንድነት

ማህበረሰባዊ አንድነት በአንድ ሃገር የሚኖሩ ዜጎችን በመግባባትና በመዋደድ እርስ በእርስ  የሚያስተሳስር እንደ ሀግ የተፃፈም ሆነ ያልተፃፈ ነገር ግን በዜጎች መካከል የመንፈስ አንድነት የሚፈጥር ጠንካራ የሆነ የሃገራዊ መዋቅር እሴት ነው።ማህበራዊ አንድነት በሃገራችን ከቅርብ ግዜ ወዲህ እየተገፋ ከሄደበት አዲስ የአመለካከት ጠርዝ ማለትም “ማህበረሰባዊ አንድነት የሚኖረው ተመሳሳይ ብሄር ፣ ዘር ወይም ሃይማኖት ላላቸው ሰዎች ነው” የሚባለው ውስን እይታ እንደ ኢትዮጲያ ያሉ የበርካታ ብሄርና ብሄረሰቦች ያሏት ሃገር ሁለንተናዊ ብልፅግና የማይበጅ በዜጎች መካከልም ተከባብሮና ተዋዶ አብሮ ሰርቶ የማደግን ትልም የሚንድ ፣ ምርታማነትን አቀጭጮ ሃገራችንን ጥልቅ የድህነት አዙሪት ውስጥ የሚጨምር ክፉ የአመለካክት ደዌ ነው።

ማህበረሰባዊ አንድነት ለብሄራዊ አንድነት የጀርባ አጥንት ነው።  ቢሆንም የአንድን ሃገር አንድነት በማጠንከርም ሆነ በማበላሸት በኩል የዛ ሃገር መንግስታዊ አወቃቀር ወሳኝ ግብዓት መሆኑ መዘንጋት የለበትም። ነፃ በሆነ የብዙሃን ህዝብ ምርጫ ስልጣን የጨበጠ መንግስት የሃገር አንድነት ስጋት እምብዛም አይኖርበት ይሆናል ነገር ግን በመፈንቅለ መንግስት ወይም በጦርነት ስልጣን ላይ የወጣ መንግስት አገራዊ አንድነትን በዘላቂነት ከማረጋግጥ አንፃር የከበደ ችግር ሊያጋጥመው ይችላል።

576647_490486777735898_594658576_nይህንን የከበደ ችግር በሁለት አቅጣጫ ላስቀምጠው።

የመንግስት ስልጣኑን በጉልበት የያዘው ቡድን የተመሰረተው በርእዮተ አለም መመሳሰልና መግባባት ከሆነ ስልጣኑን ለማደላደል የተቀረውን ህዝብ በርእዮተ አለም በመከፋፈል የራሱን የተመረጠና ለዛች ሃገር ሁነኛ መሆኑን ለማሳየት ይጥራል ከቻለም በህዝቡ ውስጥ በማስረፅ ተከታዮችን ለማፍራት ይጥራል ወይም ከባሰበት በአምባገነናዊነቱ ይቀጥላል።

በሌላ መልኩ ደግሞ የመንግስት ስልጣኑን በጉልበት የያዘው ቡድን የተመሰረተው በዘር ላይ ከሆነ ስልጣኑን ለማደላደል የተቀረውን ህዝብ በዘር ላይ በተመሰረት የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ይከፋፍላል። ይህኛው ከላይ ከጠከስኩት እጅግ የከፋ ሃገርን ሊከፋፍል የሚችል እንዲሁም የሃገራዊና ማህበራዊ አንድነት ፀር የሆነ አደገኛ አካሄድ ነው። ለምሳሌም በኢትዮጲያ የሰፈነው ዘር ላየ የተመሰረተው የፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀት ከተወሰነ ግዜ ወዲህ እየፈጠረ ያለው እንድምታ በሃገራችን እንጭጭ የፖለቲካ ባህል ከጅምሩ የጥላቻ ስሜት ከመፍጠሩም ባሻገር የሃገራችንን የወደፊት የፖለቲካ ባህል ወደ አሳሳቢ ደረጃ ምን ያህል እንደገፋው ልብ ይሏል።

በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ አንዱ ካንዱ የመማር እና በመከባበር ላይ የተመሰረተ የሃሳብ መለዋወጥ ሊኖር ግድ ነው። ይህም ደግሞ በዛ ማህበረሰብ ውስጥ እኔ አቅልሃለው እንዲሁም እኔ የምለውን በግድ ተቀበሉኝ የሚል የተፅእኖ ስሜት ሳይኖር ማንኛቸውም ውሳኔዎች የአብዛኛውን የማህበሩን አባላት ፍላጎት በሚዛናዊነት ሊያሟላ በሚችል መልኩ የውሳኔ ሃሳብ አመንጭዎችን እይታ (perspective) በአክብሮት ማስተናገድ አለበት። ነገር ግን የአንድ ግለሰብ ወይም ቡድን የበላይነት ከሰፈነ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ከዚሁ ቡድን ወይም ግለሰብ ጥቅምና ፍላጎት አንፃር ብቻ ይሆኑና የጋራ ብልፅግና በእጅጉ ይጎዳል።

በዚህ ዘመን የአለማችን ህዝቦች በልዩነት ተዋዶ አብሮ የመኖር መንፈስ ጠንካራ ደረጃ ላይ ያደረሱት ሲሆን እንዲሁም በርካታ ፍፁሞ የተለያየ ባህል ፣ ቋንቋና እሴቶች ያሏቸው ሃገራት በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ህብረቶችን እየፈጠሩ ሃገራቸውንና ህዝባቸውን ተጠቃሚ እያደረጉ ይገኛሉ። በሚያሳዝን መልኩ ደግሞ እንደ ኢትዮጲያ ያሉ አምባገነናዊ ስርዓት የተጫናቸው ሃገራት ለስልጣን ቆይታ አንድነትን ከማጠናከር ይልቅ ህዝባቸውን በጎሳ እየለያዩ የስልጣን እድሜያቸውን ለማራዘም ሲጥሩ እየተስተዋሉ ነው።

በጠነከረ ማህበረሰባዊ አንድነት ላይ ተመስርቶ ስለሚገኝ አመርቂ የሃገር እድገት አንድ ጥሩ ምሳሌ ላቅርብ በ1940ዎቹ የሁለተኛው የአለም ጦርነት በእጅጉ የጎዳትና በርካታ ወጣቶቿ በጦርነት ያለቁባት ጃፓን ማህበረሰብ በቁርጠኛነትና  በፅኑ ሃገር ወዳድነት ላይ የተመሰረተ ሁሉን አቀፍ ሃገራዊ እቅድ ከጦርነቱ ማብቂያ ማቅስት ለማውጣት ተስማሙ። በ 1950 ያስቀመጡት እቅድ እስከ 10 አመት ግዜ ውስጥ በጨርቃ ጨርቅ ምርት ከአለም አንደኛ መሆን ነበር ሆነላቸው። እንደገና በ1960 ከአለም በብረታ ብረት ምርት አንደኛ ለመሆን አቀዱ በ 1970 ተሳካላቸው። እንደገና በ1970 ከአለም በመኪና ምርት አንደኛ ለመሆን አቀዱ ተሳካለቸው። እንደገና በ1980 በኤሌክትሮኒክስ ምርት አንደኛ ለምሆን አቀዱ ተሳካላቸው። ለነዚህ ሁሉ ተከታታይ አመታት በቁርጠኝነት ለፍተው ሃገራቸውን አሳደጉ። አሁን ጃፓን ምን አይነት የእድገት ደረጃ ላይ እንዳለች ሁላችንም እናውቃለን። በአንድ ወቅት የኢትዮጲያ ኢኮኖሚ ከጃፓን ኢኮኖሚ እኩል ነበር ሲባል ሰምቻለሁ ምንም እንኳን ይህ ነው የሚባል መረጃ ባይኖረኝም ሆኖም ከሆነ እኛ መላ ቅጥ በሌለው የፖለቲካና የርስ በርስ ጦርነት ስንታመስ እነሱ ግን ማህበረሰባዊ አንድነት ላይ በተመሰረት የሃገር እድገት ውጥን የት እንደደረሱ አሁን ያሉበትን ደረጃ አይቶ መረዳት ይቻላል።

የሃገር እድገት ያለውን ማህበረሰባዊ ጥቅም የገባቸው እንደ ጃፓን ያሉ ሃገራት እንደዚህ ሲያድጉ በአንፃሩ ደግሞ  እንደ ኢትዮጲኣያ ያሉ የተወሰነ ቡድን ፍላጎት ማሟላት ላይ የተመሰረተ አምባገነናዊ ስርዓት ያላቸው ሃገራት በአስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰነዘሩ አንፃራዊ አማራጭ ሃሳቦችን አለመቀበል ብቻ ሳይሆን የአንፃራዊ ሃሳብ አመንጪውን ቡድን ፣ ማህበር ወይም ግለሰብ ሰብአዊ መብትን በእጅጉ በሚጥስ መልኩ ማሰር ፣ ማንገላታት እንዲሁም ከሃገር ማባረርና ህይወትን እስከመንጠቅ ይደርሳሉ።

የዚህም የጉልበት ሚዛን ባለው ግለሰብ ወይም ቡድን በሌላው አማራጭ ሃሳብ አመንጪ ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ ይዞት በተነሳው ሃሳብ ሳቢይ ጉዳት ሲደርስበት የሚመለከቱ የተቀሩት የማህበረሰብ አባላት ለጋራ እድገት የሚበጅ አመለካከት ቢኖራቸውም አንኳን ለሚደርስባቸው ነገር እርግጠኛ ስለማይሆኑ ያላቸውን አመለካከት በግልፅ ከማውጣት ይቆጠባሉ ለሃገር ከማሰብ ይልቅ ለግላቸው ወይም ለቡድናቸው ብቻ ማሰብ ይጀምራሉ። ለሃገር ቢያውሉት ከፍተኛ ጥቅም ሊያስገኝ የሚችለውን እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ወይ ለባዕድ ሃገር ያውሉታል ወይም ደግሞ ጥቅም ላይ ሳይውል ባክኖ ይቀራል።

በዚህም ሳቢያ አቅም ያለው የማህበረሰብ አካል ሌላውን ሊጠቅም የሚችልበትን እንዲሁም ሃገር ከዜጎቿ ልትጠቀመው የሚገባትን በእጅጉ ያስቀራል፡ ይህ ደግሞ ማህበረሰባዊ የሆነ የወል እድገትን ፣ ማህበረሰባዊ መተሳሰብና አንድነተን እንዲሁም ለሃገርና ለህዝብ የመቆርቆር ስሜትን ቀስ በቀስ ሸርሽሮ ሊያጠፋውና ሃገርና ህዝብን መጠኑ የሰፋ የድህነት አዙሪት ከመክተት ባለፈ የሀገርን ጨርሶ የመበታተን አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

ሰብዓዊ መብትና እኩልነት

Police-Addisከላይ በዝርዝር ያስቀመጥኩት የማህበረሰባዊ አንድነት ሙሉ በሙሉ በእኩልነት ላይ ተመስርቶ ባይሆንም እንኳን በ አንፃራዊ መልኩ የኑሮ ህበረት ያላቸው ሃገራት ቀጣይ አጀንዳቸው የሚሆነው ለሁለንተናዊ ማህበረሰባዊ እድገት ወሳኝ የሆነው በእኩልነት ላይ የተመሰረት የዜጎች ሰብዓዊ መብት ማረጋገጥ ነው። እንደው ለፅሁፌ ዝርዝር አቀራረብ እንዲሚቸኝ ብዬ ነው እንጂ ሰብዓዊ መብት መከበርና እኩልነት የህብረተሰባዊ አንድነት ቁልፍ አካል መሆኑን ልብ ይሏል። ምንም እንኳን እውነተኛ ዲሞክራሲ እጅግ ፍፁም የሆነና የጠለቀ መሆኑ እንዲሁም ትርጉሙና ፍፁም የሆነ ተግባራዊነቱ አሁን ባሉት የአለማችን መንግስታት “በዚህ ሃገር እንዳለው” ለማለት ሙሉ ለሙሉ የሚያስደፍር ባይሆንም በንፅፅር ከመጥፎ እስከ እጅግ በጣም የተሻለ እያልን መመዘን እንችላለን። ምንም እንኳን በዲሞክራሲ ተግባራዊነት ዙሪያ የጠለቀ ትንተና ባላቀርብም የተውሰኑ ግብዓቶቹን ለተነሳሁበት ወሳኝ የዲሞክራሲ አካል ለሆነው የዜጎች ሰብዓዊ መብትና እኩልነት ስል በመጠኑ ነካካዋለሁ።

ባለፈው ምዕተ አመት ማለትም ከ1900 እስከ 2000 ባሉት መቶ አመታት በጉልበትና ዕብሪት ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስልጣን ወይም ርእዮተ አለም  የበላይነት ማግኘት ሳቢያ ወደ መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ህይወት እንደጠፋ የታሪክ መዛግብቶች ያስረዳሉ። የዚሁ ሁሉ መነሻ አንዱ ካንዱ በግድና በጉልበት የበለጠ ለመሆንና አንዱ ቡድን የሚከተለውን የፖለቲካ ርዕዮተ አለም በግድ በሌሎች ሃገራት ወይም ማህበረሰቦች ላይ ለማስረፅ በመነሳቱ ነው። አሁን በርካታ የአውሮፓ ሃገራት ያንን ሁሉ አልፈው የሚስማማቸውንና የሚያስማማቸውን የሃገር አስተዳደር ርዕዮተ አለም እንዲሁም የዜጎች ሰብዓዊ መብት የተረጋገጠበት እጅግ በጣም የተሻለ የሚባል የዲሞክራሲ ስርዓት ፈጥረዋል። ዜጎቻቸውም የዚሁ መልካም ስርዓት ፍሬ የሆነውን ከድህነት ነፃ የሆነ የኑሮ ደረጃ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር ደረጃ ተጎናፅፈዋል።

እነዚህ ሰብዓዊ መብት በበቂ ሁኔታ የተረጋገጠባቸው ሃገራት ብዙ ነገር ካጠፋባቸው በውሃላ በብዙ ጥረት ያረሙትን ስህተት እንደ ኢትዮጲያ ያሉ በጉልበተኞች የሚተዳደሩ ሃገራት በፓርላማ ደረጃ እየተስማሙ ስህተቱን ሲደግሙት ይታያል። የተለመደው ብሂላችን “ብልህ ከስህተቱ ይማራል” ቢሆንም የተሻለ ብልህ ደግሞ ከሌሎች ስህተት መማር ይገባዋል እላለሁ። በኢትዮጲያ የሰብዓዊ መብትን ያዘቀጡትና የዜጎችን እኩልነት ጥያቄ ውስጥ የከተቱት ከብሄራዊ ጥቅም አንፃር የሚነሱ ጠቃሚ ሃሳቦችን ከቡድናቸው ወይም ከጎሳ ጥቅም አንፃር የሚመነዝሩ የሃገር አመራሮች ስልጣኑን መቆጣጠራቸውና የሃሳቡን አመንጪዎችንና የደጋፊዎችን ፍላጎት ማፈናቸውና መጫናቸው እንዲሁም ለተለያየ እስርና እንግልቶች መዳረጋቸው ነው።

የሰብዓዊ መብቱ የተጣሰና እኩልነቱ ያልተከበረለት ማህበረሰብ ሃገርን ከድህነት ለማውጣትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው የጋራ ጥረት ከመሳተፍ ይቆጠባል እንዲሁም የችግሩ ተጠቂ ያልሆነ የማህበረሰብ አካልም ቢሆን የሰውን ልጅ መሰረታዊ መብት ከሚጥስ መንግስት ጋር ለመተባበር አይነሳሳም። ዜጎችም የሃገር ልማት ላይ ከመሳተፍ ይልቅ መብታቸውን ለማስከበር ትግል ይጀምራሉ። መብት የማስከበር ትግሉ ዘርፍ እየበዛ ሲሄድ ተነጋግሮ መግባባት ጭራሽ ይጠፋና ዲሞክራሲያዊ የሆነ አሳታፊ የወል እድገት ህልም ሆኖ ይቀራል። ይህ ደግሞ ሃገርን ማለቂያ የሌለው የድህነት አዙሪት ውስጥ ይከታል።

የሚቀጥለውን በክፍል ሁለት ይመልከቱ  . . . . .

የኢትዮጲያ የድህነት አዙሪት መንስኤና መፍትሄዎች “በጥቂቱ” (ክፍል ሁለት)

በክፍል አንድ ፅሁፌ ሃገርንም ሆነ ዜጎችን ከድህነት አዙሪት ለማውጣት አስፈላጊ ስለሆኑት ስለ ማህበራዊ አንድነት እንዲሁም ስለ ሰብዓዊ መብትና እኩልነት አንዳንድ ነገር ብያለሁ የቀሩትን ዋና ዋና ነጥቦች ደግሞ እነሆ።

የዜጎች ነፃነት

የዜጎች ነፃነት ዘርፈ ብዙ መገለጫ አለው። የዜጎች ነፃነት ለሃገር ሁለንተናዊ እድገት ሌላው ወሳኝ ግብአት ነው። በጥቅሉ የዜጎች ነፃነት ጥሩ የሆነ ደረጃ ላይ ደረሰ የሚባለው በፖለቲካዊም ሆነ በማህበራዊ ዘርፍ አንፃራዊ የሆነ ነፃነት ሲሰፍን ነው። በነዚህ ሁለት ዘርፎች ነፃነት አለው የመባል ደረጃ የደረሰ ማህበረሰብ ከሌሎች በእጅጉ የተሻለ ምርታማነትን የማሳደግም ሆነ ከድህነት የመላቀቅ እድል አለው። ለመተንተን እንዲመች ፖለቲካዊና ማህበራዊ ነፃነትን ለየብቻ ላስቀምጣቸው።

ሀ.ፖለቲካዊነፃነት

sa12ዜጎች በሃገራቸው ፖለቲካ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን የሚንቀሳቀሱበት ፣ ለሃገራቸው ይጠቅማል ብለው ያመኑበትን ሃሳብ በተለያዩ መድረኮች ወይም ሚዲያዎች የሚገልፁበትን አሰራር እንደመንግስት የተቀመጠው ቡድን ወይም አካል የመቅረፅ ሃላፊነት አለበት። የዚህ አይነት አሰራር አለመኖርና የዜጎች የፖለቲካ ነፃነት ታፍኖ እንደወንጀል መቆጠር ለሃገር እድገትና ምርታማነት የመረባረብና የመጨነቅ ባህልን ከዜጎች አመለካከት ያጠፋና ከፍተኛ የሆነ የፍርሃት ስሜት በጠቅላላ ማህበረሰብ ላይ እንዲሰፍን ያደርጋል።

ከዚህ መሰል የአፈና ስርዓት ከሚፈጥረው ፍርሃት በመጠኑም ቢሆን የተላቀቁ የማህበረሰብ አባላት ለሃገር ምርታማነትና እድገት ቢውል ይህ ነው የማይባል ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚኖርውን አቅማቸውን ፣ እውቀታቸውን አንዲሁም ግዜና ገንዘባቸውን ባስ ሲልም ህይወታቸውን ለዜጎች የፖለቲካ ነፃነት መከበር ይሰዋሉ። በተቃውሞ ሰልፎችና የፖለቲካ ክርክሮች የበርካታ ዜጎች ውድ ግዜ ይባክናል። እንደ ኢትዮጲያ መንግስት ያሉ አምባገነኖችም የመብት ጥያቄዎችንና አማራጭ ሃሳቦችን የሚያመነጩ አካላት ማስራቸውን ፣ ማዋከባቸውን ባስ ሲልም እንደህዝብ ጠላት መቁጠራቸውን ይቀጥላሉ። እዚህ ደረጃ ላይ ነው እንግዲህ የፖለቲካ ነፃነት መጥፎ ደረጃ ላይ ደረሰ የሚባለው።

የዜጎች የፖለቲካ ነፃነት አለመከበር የአንድን ሃገር የፖለቲካ ምህዳር ያጠባል እንዲሁም ከፖለቲካ በተያያዘ የፍርሃት መንፈስ ያነግሳል። ይህ ደግሞ ሰፋ ካለ የፖለቲካ ምህዳር ከሚሳተፉ አቅም ያላቸው ዜጎች የሚመነጩ ሁነኛ የሃገር እድገት አምጪና ምርታማነትን አሳዳጊ እይታዎች ከናካቴው እንዲጠፉ ያደርጋል። ሃገርም በተወሰኑ ግለሰቦች ወይም ቡድን አመለካከትና ፍላጎት ብቻ መመራት ትጀምራለች። ከዚህ መሰል ሃገራዊ አመራር ዜጎችን ከድህነት አዙሪት መላቀቅ መጠበቅ በአንድ እጅ እያጨበጨቡ ድምፅ መጠበቅ ማለት ነው።

ለ.ማህበረሰባዊነፃነት

በአንድ ሃገር ወይም አካባቢ ተሰብስበው የሚኖሩ ማህበረሰቦች በሃገር ወይም መንግስት ደረጃ ከተደነገገው ህግ ባሻገር ሲወርድ ሲዋረድ የኖረ ያልተፃፈ ህግ አላቸው። ማህበረሰባዊ ነፃነት በጥቅሉ የዛ ማህበረሰብ አባላት ውስጥ አንዱ ያንዱን አመለካከት፣ ግላዊ ማንነት እንዲሁም እምነት የሚያከብርበት የተፃፈም ሆነ ያልተፃፈ የነፃነት መርህ ነው። ይህ የማህበረሰብ ነፃነት ለፖለቲካ ነፃነት እንደ አይነተኛ ግብዓትም ያገለግላል። ዜጎች የተለያዩ ፖለቲካዊም ሆነ ማህበራዊ አጀንዳዎችን እያነሱ በተዘጋጁም ሆነ ባልተዘጋጁ የማህበራዊ የውይይት መድረኮች ተቃራኒ ሃሳቦችን በመከባበር ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ሃሳቦችን የሚያንሸራሽሩበትና የሚከራከሩበት ፍላጎታቸውን በነፃነት ሌላውን ባለመጫን ወይም መብቱን ባለመጋፋት የሚገላለፁበትን ባህል ካጎለበቱ ፡ ይህም ባህል ሃገራዊ መልክ ከያዘና ወደ መንግስት ደረጃ ካደገ በውይይትና በበሳል ክርክር የተፈተነ ሃሳብ ነጥሮ ይወጣና ሃገርን የማሳደግ ህልም እውን ይሆናል።

ይህ ተቃራኒ ሃሳብን የማዳመጥና የማንሸራሸር ባህል ከማህበረሰብ ወደ መንግስት ደረጃ የማደግ ወይም ከመንግስት ወደ ማህበረሰብ የመስረፅ እድል አለው። ከማህበረሰብ ወደመንግስት የሚያድገው የዛ ማህበረሰብ አባላት ሁለንተናዊ ማህበረሰባዊ እድገት ለማምጣት በሚል ተነሳስተው በነፃነት የራሳቸውን መንግስታዊ አካል ሲያዋቅሩ ወይም በቀላል ቋንቋ መንግስታቸውን ሲመርጡ ነው። በዚህ መልኩ ለስልጣን የበቃ መንግስት የመረጠውን ህዝብ ለማገልገል ስለተነሳ የህዝቡን ነፃነት አያፍንም ባህሉን እንደጠበቀ ይቀጥላል። ነገር ግን እንደ ሃገራችን ኢትዮጲያ አይነት በህዝብ የተመረጠ መንግስት ማለት ምን አይነት እንደሆነ በታሪካቸው አጋጥሟቸው የማያቁ ሃገራት መንግስት ላይ የማህበረሰባዊ ነፃነት ባህልን ማሳደር እጅግ ከባድ ይሆንባቸዋል።

በጦርነት ወይም በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጣ መንግስት አብዛኛውን ግዜ በማንነትም ሆነ በሃሳብ ልዩነት ላይ የተመሰረቱ ነፃ የሆኑ ማህበራዊም ሆነ ፖለቲካዊ ውይይቶች ባህልን አሳድጎ ወደ ህዝብ ሲያሰርፅ አይታይም። የሃገራችን መንግስት የሚያደርጋቸው የሃሳብ ነፃነትን የማፈን ሂደትና እንዲሁም አማራጭ ሃሳብ አመንጪና የመብት መከበር ጠያቂ አካላት ላይ የሚያደርገው ኢሰብአዊ ተፅዕኖ በተጠቂዎች ላይ ከሚፈጥረው የአካልና የስሜት ጉዳት ባሻገር እጅግ አሳሳቢ የሆነው በተለያየ የማንነት ወይም የርዕዮተ አለም ልዩነት የሚፈጠሩ ማህበራት አባላትና ደጋፊዎች  መካከል አንዱ አንዱን እንደጠላት የማየት እንድምታን ባስ ሲል ደግሞ የርስ በርስ ግጭትን መፍጠሩም ነው። ይህ ደግሞ በዜጎች መከባበርና መዋደድ ላይ የተመሰረተ መተባበር ብቻ ሊገኝ የሚችለውን የምርታማነት መጨመርና እድገትን እንዲሁም ከድህነት አዙሪት የመውጣት ጥረትን በከፍተኛ መልኩ ያቀጭጨዋል።

ዘላቂነት ያለው የፖለቲካ ስርዓት

ሁነኛ የፖለቲካ ስርዓት ማለት በጥቅሉ አንድን ሃገር ወይም ማህበረሰብ የአገዛዝና አስተዳደራዊ መዋቅር በአለማቀፍ ደረጃ ከተቀመጡት ስርዓቶች ጋር በማዛመድ ለዛ ሃገርና ማህበረሰብ እንዲመች ተደርጎ የተቀረፀ ማለት ነው። በፖለቲካ ስርዓት ዜጎች መንግስት እንዲሆን በመረጡት ወይም መንግስት ሆኖ በተቀመጠው አካል ጤናማና ሚዛናዊ  የሆነ የህግና ስርዓት ፣ የኢኮኖሚ ስርዓት ፣ የባህላዊና ማህበረሰባዊ ስርዓት የማዋቀርና የማስተዳደር ሃላፊነት ሲሰጡት ያም መንግስት ዘላቂነት ያላቸው ህግጋትና ፖሊሲዎችን ለመረጠው የፖለቲካ መንገድና ለማህበረሰቡ እሴቶች በሚስማማ መልኩ ቀርፆ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ የአገዛዝ ስርዓት ሲመሰርትና ይህንንም ለማስከበር በአግባቡ ሃላፊነቱን ሲወጣ ማለት ነው።

በአለማችን በርካታ ሃገራት ለዜጎቻቸውና ለነባራዊ ሁኔታቸው በሚመች መልኩ የፖለቲካና የአገዛዝ ስርዓት ገንብተዋል ለአብነት ለመጥቀስ ያህልም የአሜሪካ መንግስት የሚከተለው የፖለቲካ ስርዓት ከሁለት ምዕተ አመት በላይ መሰረታዊ መርሁን ሳይለቅ ሊቀጥል ችሏል። ከዚህም ወጥነት ካለው የፖለቲካ ስርዓቱ የመነጩት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ስርዓቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እየጠነከሩ አሁን ላሉበት ደረጃ ደርሰዋል። በአንፃሩ እንደ ኢትዮጲያ ያሉ ያላደጉ ሃገራት ለአለማደጋቸው እንደምክንያት ከሚጠቀሱት ውስጥ ዋነኛው የሆነው በየግዜው የሚቀያየር ስርዓት መኖሩ እንዲሁም ጭራሽ ይህ ነው የሚባል ስርዓት አለመኖሩ ነው። በኢትዮጲያ የሚመጣው መንግስት ሁሉ የራሱን ስርዓት እንደ አዲስ መጀመሩ ከፖለቲካው ስርዓት  ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን የኢኮኖሚና ማህበረሰባዊ ስርዓቶች እንደገና ፈርሰው እየተሰሩ የተወሰኑትም “የቀደመው መንግስት አሻራ አለባቸው” በሚል ምክንያት እየፈረሱ አጠቃላይ የሃገር እድገትን ባለበት እንዲሄድ አርጎታል።

የአሁኑ የኢትዮጲያ መንግስት ስልጣኑን በእርስ በርስ ጦርነት አግኝቶ ያዋቀረው የአገዛዝ ስርዓት ስልጣኑን ያገኘው በህዝብ ምርጫ ስላልሆነ ስርዓቱ ለተወሰኑ የማህበረሰቡ አካላት ብቻ ሲያደላ ቆይቷል። በዚህም ሳቢያ መጠነ ሰፊ የሆን የፍትህ መጓደል ይስተዋላል። ከማህበረሰብ ውይይትና ይሁንታ ውጪ ስልጣኑን ለማደላደል የሚያወጣቸው የተለያዩ ህግጋት በህዝብ ዘንድ በግድ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ሲያደርግ የለየለት አምባገነን ሆኗል።

እንደ ኢትዮጲያ መንግስት አይነት አምባገነናዊ ባህሪይ ያላቸው መንግስታት በተለየ መልኩ አማራጭ የፖለቲካ ስርዓት ወይም በተመሳሳይ ስርዓት የተለዩ ዝርዝር ፖሊሲዎችን ይዘው ለተነሱ የፖለቲካ ማህበራት በግልፅ ውይይትና ክርክር ማንኛቸው ለህዝብ እንደሚሻሉ ከማሳየት ይልቅ አማራጭ ሃሳብ አመንጪዎችን ይዘው የተነሱትን አላማ ለህዝብ እንዳያስተዋውቁ በማፈን ፣ በማዋከብ ፣ በማሰርና ውድ ህይወትን እስከመንጠቅ ይደርሳሉ።

የኢትዮጲያ መንግስት የራሱን ፖሊስዎችና መርሆች በግልም ሆነ በህዝብ ሚዲያ እንደልቡ እያስነገረ ነገር ግን አማራጭ የፖለቲካ ማህበራትን መሰብሰብ እስከመከልከልና ብሎም እንደ ህዝብና ሃገር ጠላይ ይፈርጃል። ይህ መረን የወጣ አምባገነናዊ ስርዓት ዜጎች ሃገራዊ እድገት ላይ ሊኖራቸው የሚገባውን ተሳትፎ አሳንሶ በገዛ ሃገራቸው ባይተዋር የሚያደርግ እንዲሁም ሃገርን ከድህነት የማውጣት ጥረት እጅግ ጠቃሚ ተሳትፎ እንዳያረጉ የሚያስቀር ለተወሰኑ ቡድንና ግለሰቦች የስልጣን ጥምና ጥቅም ሲባል ሃገርን የድህነት አዙሪት ውስጥ የመዝፈቅ ሃላፊነት የጎደለው ስርዓት ነው።

አስተማማኝ የኢኮኖሚ መዋቅር

የኢኮኖሚ መዋቅር ወይም ስርዓት ማለት በጥቅሉ በአንድ ሃገር ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ያለ ምርትና አገልግሎትን የማምረትና የማሰራጨት እንዲሁም የተለያዩ ግብዓቶችን በተገቢው መልኩ የማዳረስ ስርዓት ማለት ነው። በዚህ ስርዓት ውስጥ የማህበረሰቡን የተለያዩ ምርትና አገልግሎቶች አቅራቢ ተቋማት ፣ ማህበራትና ድርጅቶች እንዲሁም ተጠቃሚዎች መካክል ጤናማ የሆን ፍሰት እንዲኖር የሚያደርግ ስርዓት ማለት ነው። ይህም ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተስተካከለና ጤናማ እንዲሆን መንግስት የተለያዩ ህግጋቶችንና ድንጋጌዎችን በማውጣት ከአለማቀፍ ኢኮኖሚ ስርዓቶች ጋር የማጣጣም ሃላፊነት አለበት።

ጤናማ የኢኮኖሚ ስርዓት መኖር የአንድን ማህበረሰብ ወይም ሃገር የኑሮ ደረጃ በማሳደግ በኩል ቀጥተኛ አስተዋፆ አለው። ኢኮኖሚያዊ መዋቅሩ በተገቢው መልኩ እንዲቀጥል ሰላማዊና በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሃገራዊ አንድነት መኖር ወሳኝ ሚና አለው። አንድ መንግስትም የሃገርን ኢኮኖሚ በተገቢ መልኩ እየመራ ነው የሚባለው አጠቃላይ ፍሰቱን ለሁሉም ዜጋ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ሲያስተዳድር ፣ ሲዳኝ እንዲሁም ሲያበረታታ ነው።

ፍሰቱ ሚዛናዊ አደለም የሚባለው ለተወሰኑ የንግድ ተቋማት መንግስታዊ የሆነ አድልዎ በማድረግ የተቀሩትን  የመጫን ሂደት ሲኖር እንዲሁም ኢኮኖሚውን የማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጣቸው መንግስታዊ ተቋማት በገለልተኝነት በማስተዳደር ፈንታ በአድሎአዊነት ጣልቃ ሲገቡና በጥቅማ ጥቅም ሲያዙ ነው። ይህ ሚዛናዊነቱን የማሳት ተግባር ለተወሰኑ ግለሰቦች ጥቅም ሲባል በሃገር ኢኮኖሚ እድገት ላይ ከፍተኛና ቀጥተኛ ሚና የሚኖራቸውን ድርጅቶችን ለክስረትና ለመዘጋት ይዳርጋል ፣ ሃገርና ህዝብ ከንግድ ፍሰቱ የሚያገኙትን ጥቅማ ጥቅሞች ያሳጣል ፣ ወደ ንግድ ስራዎችና መሰል እንቅስቃሴ ለመግባት ያቀዱ ሃገራዊም ሆነ አለማቀፋዊ ድርጅቶችን ፍላጎት ይገታል ፣ የስራ አጡን ቁጥር ይጨምራል እንዲሁም በርካታ መሰል ችግሮችን በመፍጠር ሃገር ወይም ማህበረሰብ ከድህነት አዙሪት ለመውጣት የሚያረገውን ጥረት ያቀጭጨዋል።

ለምሳሌ በሃገራችን ኤፈርት የተባለው የንግድ ተቋም በመንግስት በሚደረግለት ግልፅና ቀጥተኛ ድጋፍ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚንቀሳቀስ ፣ ከዛ ሁሉ የኢትዮጲያ ብሄርና ክልል አንድ ክልልና ብሄርን ለማልማት በሚል የተዋቀረ ድርጅት አለ። የዚህ ድርጅት በተለያዩ ውድድር በሚያሻቸው የንግድ ዘርፎች ተሰማርቶ ነገር ግን በመንግስት ድጋፍ በሞኖፖል መንቀሳቀሱ ሌሎች ቀድመው የነበሩ እንዲሁም አዲስ የሚፈጠሩ የንግድ ተቋማትን ምን ያህል እንደጎዳ በዘርፉ ባለሞያዎች ብዙ ተብሏል። መሆን የነበረበት ግን የኢትዮጲያ መንግስት እከተለዋለው ያለውን የኢኮኖሚ ስርዓት በአግባቡ ቢያስተዳድር ፣ ጤናማ የውድድር መንፈስ ቢፈጥር እንዲሁም የሁሉንም ሃገራዊ ድርጅቶች ምርቶች ከአድልዎ ውጪ በሆነ መልኩ አለማቀፍ ገበያ ውስጥ እንዲታወቁ በቅንነት ቢጥር ሃገራችን በቅርቡ ከድህነት አዙሪት ትወጣ ነበር።

እንግዲህ ከተነሳሁበት ሃሳብ ስፋትና ጥልቀት አንፃር በእኔ አቅም ይህችን ብያለው። አንባቢዎች የማይስማሙባቸው ወይም የቀረ የሚሉት ብዙ ሊኖር ይችላል ነገር ግን እኔ ሃገር የምትገነባው በጎ መሰረት ያለው ግልፅ ውይይት ሲኖር ነው ብዬ ስለማምን እንደ አንድ ተቆርቋሪ ዜጋ ይህችን አዋጥቻለሁ።

ሃገራችን ከአምባገነናዊ ስርዓት የምትላቀቅበትን ህዝቦቿም ከድህነት አረንቋ የሚወጡበትን ቀን ቅርብ ያርግልን !!

 


“ከሃገሬ የወጣሁበት ቀን በረዘመ ቁጥር፣ ሀገሬ ላይ በጣም ክህደት የፈፀምኩ ያህል ይሰማኛል” –ታማኝ በየነ (ቃለ ምልልስ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር)

$
0
0

tamagne beyene
የዚህ ዕትም እንግዳችን ታዋቂው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነው። ረዥም ጊዜያት በኪነ-ጥበብ ሙያ ላይ የቆየው ታማኝ፣ የደርግ መውደቅን ተከትሎ ኢሕአዴግ የአራት ኪሎውን ቤተ-መንግስት ከተቆጣጠረበት ዕለት (ግንቦት 20/1983 ዓ.ም) ጀምሮ በድፍረት የስርዓቱን አምባገነንነት፣ ፋፋይነት፣ በብሔራዊ ጥቅም ላይዝ ያለውን ቸልተኝነት… ጠቅሶ ተችቷል። ይህንንም ተከትሎ በደረሰበት ከባድ ጫና፣ እስርና ግርፋት ሀገሩን ለቆ ለመውጣት ተገድዷል። በስደት በሚኖርባት አሜሪካም ያለውን የተከፋፈለ የተቃውሞ ፖለቲካ አስተባብሮ ከመምራቱም በላይ በየጊዜው የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁና መሰል ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ የሚዘጋጁ የተቃውሞ ሰልፎችን አስተባብሮ መርቷል። በዚህም በመላው ዓለም በሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከበሬታን አትርፏል። አክትቪስት ታማኝ በየነ፣ ከተመስገን ደሳለኝ ጋር ያደረገው ቃለ-መጠይቅ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

Read Full Story in PDF/ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በሃገሪቱ የተነሰራፋው ዘረኝነት፣ የደህንነት ሥጋትና አድልዎ አውሮፕላን እንዲጠለፍ አድርጓል

$
0
0

ከምኒልክ ሳልሳዊ

በሃገሪቱ የተንሰራፋውን የደህንነት ስጋት በመልካም አስተዳደር እና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አድልዎ ተከትሎ የተደረገው የአይሮፕላን ጠለፋ ህዝቦች በገዛ አገራቸው በደህንነት ላይ ምን ያህል ስጋት እንዳጠላበት እና በመኖር ህልውናቸው ላይ ኢትዮጵያውያን የስርአቱ ፖሊሲዎች እያሸማቀቋቸው እንደሚገኙ አለም ካለፈው ጊዘ በተሻለ እውነታውን ፍንትው አድርጎ እየመሰከረ ነው።

hailemariam abera tegegnየሕወሓት መራሹ ጁንታ ወደ ስልጣን በጠበንጃ ሃይል ከመጣ ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የተደነገጉ የሰብኣዊ መብት ህጎችን ካለምንም ማርቅርቅ እና ድካም ከሌሎች በመገልበጥ በወረቀት ላይ ከማስፈሩም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአለም ላይ የሰው አገር ህግን እና አለማቀፍ ድንጋጌን ከሃገራችን ሁኔታ ጋር ሳይገናዘቡ በስፋት በደመነፍስ ለፍጆታ የተጻፈበት ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን በየትኛውም አለም ሃገራት ያልተከሰተ የአለም አቀፍ ህጎችን ግልባጭ በከፊል በህገመንግስት እንዲሁም የገዢ ፓርቲን የፖለቲካ ፕሮግራም በከፊል ደባልቆ በጋር እንደ አውራ ህግ የወጣባት ሃገር ብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት::ኢትዮጵያ በታሪኳ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የመብቶች ሕጋዊነት በተጨበጨበለት ሁኔታ እና ይህ በማይባል ደረጃ የተደነገጉባት አገር ነች፡፡ እንግዲህ ይህ ሆኖ እያለ ነው በአገሪቱ የመብቶች ጥሰት ጉዳይ ከአገሪቱ ብሔራዊ አነታራኪ ፖለቲካዊ አጀንዳነት አልፎ ዓለም አቀፍ አጀንዳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::

የቀድሞ መንግስትን ሽንፈት ተከትሎ በኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች የፍፃሜ ምዕራፍ ይሆናል ተብሎ ተስፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ጭራሽ ብሶበት ቁጭ አለ፡፡ የሕወሓት ወንበሩን መቆጣጠር ተንተርሶ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተለይም ሒዩማን ራይት ዎችና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የወያኔን ጁንታ በሰብዓዊ መብት ጥሰት በማብጠልጠል ነበር የተቀበሉት፡፡ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት የሰብኣዊ መብት ጥያቄዎች አቤቱታ ማሰማታቸውን አላቆሙም፡፡ ጋዜጠኞችን የሃሳብ ነጻነት ከሚገድብ ጥቃት በመከላከል ላይ የተሰማሩ የመብት አስከባሪ ድርጅቶችም ወያኔ በሚፈጥረው ከባድ የሰብኣዊ መብት ጥሰት በየጊዜው መክሰስ ሥራቸው ሆኗል::የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት በየጊዜው በሚያወጣው ዓመታዊ መግለጫው ወያኔን በሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፖለቲካ መብቶችን ማፈን ይከሰዋል፡፡ ባሁን ወቅትየእነኚህን አካላት መግለጫዎች የታወቁ ዓለም አቀፍ መገናኛ ድርጅቶች በመቀባበል ኢትዮጵያ የዜጎቿን መብቶች በመጣስና በማፈን ወደር የሌላት አገር እንደሆነች ዓለም እንዲረዳው እያደረጉ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠለፈ፤ ጠላፊው ምክትል አብራሪው ነው ተባለ
ኢትዮጵያ በአስከፊ ድርቅና ረሃብ ለመታወቅ እንደበቃችው ሁሉ ወያኔ የዜጎችን መብቶች በመጣስና በማፈን እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጽመው ወንጀል በዓለም ላይ ታዋቂነትን እያተረፈ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም;ወያኔ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን መብቶች ለመጣስ ስለሚጠቀምባቸው ዘደዎች የሚቀርቡ ማስረጃዎች እና ማብራሪዎች እጅግ ዘግናኝ ናቸው፡፡የወያኔ መሪዎች የፖለቲካ ተቀናቃኖችን ለማዳከም ሲሉ ንፁኃንን ወንጀለኛ የሚያደርግ ዘዴዎችን ሥራ ላይ እንደሚያውሉ በተለያዩ ይፋዊ ሪፖርቶች ላይ ሁሉ ከነማስረጃው እየተነገረ ይገኛል::

የህ የሰብኣዊ መብጥ ጥሰት እየተባባሰ የሚሄድበት ምክንያት ወይኔ በአብዛኛው ካድሬዎች ዘንድ በስፋት ሰርጾ እንዲገባ ያደረገው የተቃዋሚዎች ጥላቻ እና እንዲሁም የተቃዋሚው ቡድን የትግል አቅጣጫው በተመሳሳይ መልኩ በጥላቻ ላይ የተመረኮዘ መሆኑ ነው::ተቃዋሚዎች የታጠቁ ሃይላት ባለመሆናቸው የመርሃቸው እንቅስቃሴ የተገደበ እና ለፖለቲካ እና ለሚዲያ ፍጆታ የዋለ ተዳፍኖ የሚገኝ ሲሆን የወያኔው ግን በታጠቁ የጸጥታ ሃይሎች እና በፖለቲካ ማጭበርበሮች ላይ ስለተመረኮዘ ካድሬዎቹ በተሰጣቸው የጥላቻ ተግዳሮት እና ወያኔያዊ ስልቶች የፈጠሩትን ጥቅማጥቅሞች ጠብቀው ለማቆየት ሲባል ጥላቻ በፈጠረው ፍርሃት ብቻ የሃገሪቱን ህጎች ዜጎች ለመጥለፍ እያዋሉት ነው::

ይህ ፍርሃት እና ጥላቻ በወያኔ ከትልቅ እስከ ትንሽ ካድሬዎች አናት ውስጥ ስር ለስር በመስደድ የፈጠረው ነገር ቢኖር ማንኛውም ዜጋ ተቃውሞ ካሰማ በወንጀለኛነት በመፈረጅ በማሳደድ በማጥፋት እረፍት ለማግኘት እና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲራወጡ የህዝብን የበላይነት አፈር ከተውታል::ማእከላዊ የወያኔ ጁንታ በዲሞክራሲ ባለመወቀጣቸው የህጎችን የበላይነት ማረጋገጥ ካለመቻሉም በተጨማሪ በህዝብ እና በዲሞክራሲ ላይ በደሎችን የሚያደርሱ ባለስልጣናት የሚጠየቁት በሃገሪቱ የበላይ ህጎች ሳይሆን በወያኔያዊ የፓርቲ መመሪያዎች በመሆኑ በጥቅም መተሳሰር በፈጠርው ዝግ መንገድ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች እየተብራከቱም ከመሆኑ አልፎ የእለት ተእለት ተግባራት አካል ሆነዋል:: የአይሮፕላን ጠለፋዉም ከላይ ከገለጽኩት ጉዳዮች ጋር ቁርኝት ያለውና በሃገሪቱ እየተተገበረ ያለውን የቡድን አምባገነንነት በማጋለጥ ረገድ ትልቁን ሚና ተጫውቷል።

የአውሮፕላኑ ጉዳይ፡ የረዳት አብራሪው ውሳኔ በውጭ ሚዲያዎች ዓይን

$
0
0

ethio airlines
በፀጋው መላኩ

በበረራ ቁጥር ET702 የተመዘገበውና ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 767 አውሮፕላን በረዳት አብራሪው ተጠልፎ የጉዞ መስመሩን በመቀየር ጄኔቭ ኤርፖርት ካረፈ በኋላ በጉዳዩ ዙሪያ በርካታ ዘገባዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ። በዚህ ዙሪያ በየድረገፆቻቸው ሰፋ ያለ ዘገባዎችን ካሰራጩት ታዋቂ መገናኛ ብዙኀን መካከል አልጀዚራ፣ ቢቢሲ፣ ሲ ኤን ኤን፣ ፎክስ ኒውስ፣ ዘጋርዲያን፣ ሲ ቢ ኤስ፣ ዋሽንግተን ፖስትና አሶሼትድ ፕሬስ ይገኙበታል። የብዙዎቹ መገናኛ ብዙኀን ሽፋን በእለቱ ድርጊት ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ከዚያ ባለፈ መልኩ “ረዳት አብራሪው ለምን ድርጊቱን ፈፀመ” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ሞክረዋል።

በዚህ ዙሪያ ዴቪድ ብለየር በተባለ ፀሐፊው “ረዳት ፓይለቱ ለምን ይሄንን ድርጊት ፈፀመ” ለሚለው ምላሽን ለመስጠት ሞክሯል። ዴቪድ ብለየር በዴይሊ ቴሌግራፍ የአፍሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ ዘጋቢ ሆኖ አገልግሏል። ከዚያ በኋላ ቴሌግራፍን በመተው በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን በተንታኝነት ያገለገለ ሲሆን እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ ወደ ቴሌግራፍ ተመልሶ የተለያዩ ዘገባዎች ከማቅረብ ባለፈ ልዩ ልዩ ሙያዊ ትንታኔዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ዴቪድ ብለየር በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተካሄደውን ጠለፋ አስመልክቶ “ጠለፋው ለምን ተከናወ” በሚለው ጉዳይ ላይ የራሱን ትንታኔ ለመስጠት ሞክሯል። እንደ ባለሙያው ገለፃ የፓይለቱ የጠለፋና የጥገኝነት ጥያቄ በኢትዮጵያ የተስፋፋው የዜጎች ሀገር ጥሎ መሰደድ አንድ ማሳያ ነው። ባለሙያው በዜጎች ሀገር ጥሎ መሄድ ሁለት ምክንያቶችን ያስቀመጠ ሲሆን፤ እነዚህንም ጭቆና እና ድህነት በማለት አስቀምጧቸዋል። “ሀገሪቱ የአንድ ፓርቲ ሀገርና በጥቂት ሰዎች የምትመራ ናት” ያለው ይሄው ተንታኝ ዜጎች ከሚደርስባቸው ጭቆና በተጨማሪ የነፍስ ወከፍ ገቢያቸውም በዓለም ድሀ ከተባሉት ሀገራት ውስጥ የሚመደብ በመሆኑ ዜጎች ሀገር ጥለው የሚሄዱ መሆኑን ገልጿል።

ባለሙያው በዚህ ትንታኔው የአለም ባንክን መረጃ ዋቢ በማድረግ በሰጠው ትንታኔ 620 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ውጪ የሚኖሩ መሆኑን ገልፆ ከእነዚህም ውስጥ 10 በመቶው የሚሆኑት የዩኒቨርስቲ ዲግሪ የያዙ መሆናቸውን አመልክቷል። ፀሀፊው ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከገበያ ባላንጣዎቹ የገልፍ ሀገራት በኩል እየገጠመው ያለውን የባለሙያ ማስኮብለልንም በምክንያትነት ያነሳል። ከሶስት ዓመታት በፊት 60 የአየር መንገዱ ቴክኒሻኖች በገልፍ ሀገራት አየር መንገዶች በተሻለ ክፍያ ስራ ያገኛሉ። ይህንንም ተከትሎ ባለሙያዎቹ አየር መንገዱን ለቀው ለመሄድ ስማቸውን ለኢሜግሬሽንና የዜጎች ጉዳይ ቢያስተላልፉም ሀገር ጥለው መሄድ እንደማይችሉ ተገልፆላቸው የሥራ እድሉን መከለከላቸውን በመግለፅ ይህንንም መሰል ችግር ለጠለፋው በምክንያትነት ያስቀምጣል። ምንም እንኳን የሚያስከፍለው ዋጋ ከባድ ቢሆንም ይህ ረዳት ፓይለት ከሀገሪቱ ወጥቶ ሊሰራ የሚችልበት ህጋዊ አካሄድ ስለሌለ ያለው ነባራዊ ሁኔታ ይህን እርምጃ እንዲወስድ ሊገፋፋው እንደሚችል በመግለፅ ፀሐፊው ሙያዊ አስተያየቱን በዴይሌ ቴሌግራፍ ላይ አስነብቧል።

በዚሁ ዙሪያ በትላንትናው እለት ማብራሪያ የሰጡት የኩሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ ፓይለቱ የትም ሀገር ሄዶ መቀጠር የሚችልና የቪዛ ችግር የሌለበት ነው በማለት ድርጊቱን ኮንነዋል። ፎክስ ኒውስ በበኩሉ ኢትዮጵያ መንግስት የሂውማን ራይትስ ዎችን ሰብዓዊ መብት ረገጣ ሪፖርትን በማጣቀስ በሀገሪቱ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ፣ የመሰብሰብና በማህበር መደራጀት አለመቻልን በመግለፅና ጉዳዩን ከዚህ ጋር አያይዞ ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ አባላትም የጥቃት ኢላማ በማድረጉ መንግስት በተደጋጋሚ ክስ የሚሰማበት መሆኑንም ዘገባው አመልክቷል።
ከዚህ ውጪ ያሉት ዘገባዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ ጊዜያት በተደጋጋሚ የጠለፋ አደጋዎች እየገጠሙት መሆኑን ገልጸዋል። እ.ኤ.አ በ2002 በሀገር ውስጥ የአየር መንገዱ በረራ ሁለት ጠላፊዎችን ቢላዋ፣ ተቀጣጣይ ፈንጂ በመያዝ አውሮፕላኑን ለመጥለፍ ሙከራ ቢያደርጉም በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል። ዘገባው ከዚህም በተጨማሪ እ.ኤ.አ. በ1996 ተጠልፎ በኮሞሮስ ደሴት በህንድ ወቅያኖስ የተከሰከሰውን አውሮፕላን ታሪክም ያስታውሳል።

የረዳት ፓይለቱን ቀጣይ እጣፈንታ በተመለከተ በርከት ያሉት ዘገባዎች ጉዳዩ ወደ ክስ የሚያመራ መሆኑን በመግለጽ ጥገኝነት በመሰጠቱ በኩልም ቢሆን ከበርካታ የአውሮፓ ሀገራት በበለጠ ሁኔታ የሲውዘርላንድ ህግ ጥብቅ መሆኑን ያትታሉ። የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ ተላልፎ እንዲሰጠው የሚፈልግ መሆኑን በአቶ ሬድዋን በኩል ተገልጿል። እንደ ፎክስ ኒውስ ዘገባ ከሆነ በጣሊያንም ሆነ በሲዊዘርላንድ ሕግ መሰረት አንድ ግለሰብ በሌላ ሀገር በሞት የሚያስቀጣው ወንጀል ከፈፀመ ለዚያ ሀገር ተላልፎ አይሰጥም።

ይህ ጽሁፍ ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሚ በተሰራጨው ሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ነበር።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ከዚህ ቀደም የተደረጉ 8 የአውሮፕላን ጠለፋዎች (ለጠቅላላ እውቀት)

$
0
0

ethio airlines

1

እ.ኤ.አ ህዳር 1991 ዓ.ም ሁለት የሌላ ሃገር ግለሰቦች እና አንድ ኢትዮጵያዊት ሴት ተመሳስሎ የተሰራ እና የማይሰራ መሳሪያ በመጠቀም 88 ሰዎችን አሳፍሮ በሀገር ውስጥ በረራ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጀት በመጥለፍ ጅቡቲ ላይ ካሳረፉት በኋላ ሁሉንም ተሳፋሪዎች ለቀዋቸዋል።
2
እ.ኤ.አ ነሐሴ 1992 ዓ.ም አራት ኢትዮጵያውያን በሃገር ውስጥ በረራ ላይ የነበረን አውሮፕላን ከጠለፉ በኋላ ጅቡቲ ላይ በማረፍ ያገቷቸውን መንገደኞች የለቀቁ ሲሆን በመቀጠል ወደ ጣሊያን በመብረር ጥገኝነት ጠይቀዋል።

3

የካቲት 1993 ዓ.ም አንድ ኢትዮጵያዊ አብራሪው ላይ መሳሪያ በመደቀን ከፍራንክፈርት ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረውን የሉፍታንዛ ንብረት የሆነውን አውሮፕላን በመጥለፍ አሜሪካ ጆን ኤፍ ኬኔዲ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲያርፍ አድርጓል።

4

እ.ኤ.አ በህዳር 1995 ዓ.ም አንድ ኢትዮጵያዊ ከአውስትራሊያ በመጠረዙ ምክንያት የኦሎምፒክ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ጀት የምግብ ቢላዋ በመጠቀም በመጥለፍ ወደ ሀገሩ እንዳይላክ የጠየቀ ቢሆንም በመንገደኞች ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

5

እ.ኤ.አ መጋቢት 1995 ዓ.ም አምስት የታጠቁ ሰዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ጀት ሊነር አውሮፕላን በመጥለፍ እና ሱዳን ላይ በማሳረፍ ወደ ግሪክ ከዛም ወደ ስዊድን እንዲበር ከሞከሩ በኋላ የሱዳን መንግስት ጠላፊዎቹ በስዊድን ጥገኝነት እንዲያገኙ እንደሚረዳቸው ቃል በገባላቸው መሰረት አውሮፕላኑ በ24 ሰዓታት ውስጥ ሊለቀቅ ችሏል።

6

እ.ኤ.አ ህዳር 1996 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ወደ አይቮሪኮስት በኬንያ በኩል ይበር የነበረውን አውሮፕላን አብራሪዎቹን በማሰገደድ ወደ አውስትራሊያ እንዲሄድ በማስገደዳቸው እና የአውሮፕላኑ ነዳጅ በማለቁ በኮሞሮስ ደሴት ላይ የመከስከስ አደጋ ገጥሞት እውቁ የኬንያ ፎቶ ጋዜጠኛ መሐመድ አሚንን ጨምሮ ለ175 ሰዎች ህልፈት ምክንያት ሆኗል።

7

እ.ኤ.አ ሚያዝያ 2001 ዓ.ም አምስት የጦር አውሮፕላን ሰልጣኞች የሚሰለጥኑበትን የጦር አውሮፕላን ከባሕር ዳር ከተማ በመጥለፍ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ለመሄድ ቢያስቡም አውሮፕላኑ የነበረው ነዳጅ አነስተኛ በመሆኑ ሱዳን ላይ ለማረፍ ተገዷል።

8

እ.ኤ.አ ሰኔ 2002 ዓ.ም ስለታማ እና ተቀጣጣይ ነገር የያዙ ሁለት መንገደኞች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ በረራን ለመጥለፍ ቢሞክሩም በበረራ ደህንነት ሰራተኞች በተተኮሰባቸው ጥይት በመሞታቸው የጠለፋው ሙከራ አልተሳካም።

ቴዲ አፍሮ በሱዳን ለመሐመድ ወርዲ በተዘጋጀ የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ በአረቢኛ አቀነቀነ

$
0
0

teddy afro sudan(ዘ-ሐበሻ) “የፍቅር ጉዞ” በሚል በሙዚቃዎቹ ፍቅርን ይሰብካል በሚል የሚወደሰው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሱዳን ካርቱም የፊታችን አርብ ፌብሩዋሪ 21 እና እሁድ ፌብሩዋሪ 23 ሁለት ታላላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን እንደሚያቀርብ ከዚህ ቀደም መዘገባችን አይዘነጋም። ቴዲ ለዚህ ኮንሰርት ሱዳን ከገባ በኋላ በካርቱም ለዝነኛው የሱዳን ድምጻዊ መሐመድ ወርዲ በተዘጋጀው የመታሰቢያ በዓል ላይ “ሰበርታ” የተባለውን ተወዳጅ የሱዳን የአረቢኛ ዘፈን በድንቅ ሁኔታ ተጫውቶታል።

ባለቤቱ አምለሰት ሙጬን ከፊት ለፊት አስቀምጦ ለሱዳናውያኑ ያቀነቀነው ቴዲ ከፍተኛ አድናቆትን አግኝቷል። የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች በሱዳን በጣም የሚወደዱ ከመሆናቸውም በላይ በተለይ ከ8 ዓመት በፊት ሱዳን የነበረው የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ ሱዳኖች ለቴዎድሮስ ካሳሁን እና ለሃይማኖት ግርማ ልዩ ፍቅር እንደነበራቸው በአይኑ ማየቱን ያስታውሳል። ድምፃዊት ሃይማኖት ግርማ “ዞል ቲቪ” በሚባል የቴሌቭዥን ጣቢያ የፕሮግራም አቅራቢ ሆና እንደነበርም ያስታውሳል።

በካርቱም ቴዲ የፊታችን አርብ እና እሁድ ሥራዎቹን የሚያቀርብ ሲሆን፤ በመሀመድ ወርዲ መታሰቢያ ላይ የተጫወተውን ሰበርታ ሙዚቃ እንጋብዛችሁ፦

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live