Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የዘር ፖለቲካ –መስከረም አበራ

$
0
0
ፍርድ ቤት እስከ ፖሊስ፣ ልዩ ሃይል ወዘተ የተባሉ ህግ አስከባሪ አካላት በዘር ተመልምለው እስከተመደቡ ድረስ ከእነሱ ዘር ያልሆነ ሰው በሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው፡፡እነዚህ የዘር ህግ አስከባሪዎች ሌላውን ሰው ከዘራቸው እኩል አይተው ከለላ ይሆናሉ ማለትም የሞኝነት ምልክት ነው፡፡በመተከል እየሆነ ያለው እጅግ አሳዛኝ ሁነት የዚህ አካሄድ ውጤት ነው፡፡መተከል በተነሳው ግጭት አስራ ሰባት ሰው መሞቱን እና ሃያ […]

ጂጂን ፍቱልን! የገብረክርስቶስ ደስታ ይበቃናል፤ (መስቀሉ አየለ)

$
0
0
የሰው መዓዛ ከሩቅ በሚጣራባት ብቸና የበቀለች ጂጂ ሰውነት ትርጉም ባጣበት፣ ግለኝነት በገነነበትና አፍቅሮ ንዋይ ግን ቤተመንግስቱን በገነባበት በኒውዮርክ ከተማ ውስጥ ባይተዋር ሆና መኖሯ ስለምንድን ነው? ድሮ ድሮ ያኔ አሜሪካ የማርስን ያህል እሩቅ በነበረችበት በስልሳዎቹ ዓም ነፍሱን ለኪነጥበብ የሰጠውና በብሩሹም በደማሙ ብእሩም የነፍሱን እውነት አውጥቶ የማሳየት አቅም የነበረው የኢትዮጵያው ልዩ አፈር ረቂቁ ገብረክርስቶስ ደስታን ያጣነው በዚሁ […]

አብርሃ ደስታ እና ዓምዶም እንዲታሰሩ ተወስነዋል!. –ናትናኤል አስመላሽ

$
0
0
ህወሓት የመጨረሻ እድልዋን ለመሞከር ማሰር ትቀጥላለች፣ እስሩ ከመፈፀሙ በፊት ህወሓት እነ ኪዳነ ከዓረና እንዲወጡ በሰጠችው መመርያ ዓረና ከለቀቁ እንሆን ሁለት ቀናቶች ተቆጥረዋል። የትግራይ ህዝብ ከዚህ ቦሃላ ለህወሓት ፊት እንደማይሰጥ የገባቸው ህወሓቶች ሁሉም አምባገነን እንደሚያደርገው፣ በህዝቡ ላይ ፍራቻ ለመፍጠር መጀመርያ አብርሃ ደስታ እና ዓምዶም ለማሰር ወስናለች። ሚኪ ተስፋየ ትናንትና ማታ በፖሊስ ታስረዋል። አመት ብአል ጠብቀው በቅዳሜ […]

ሕዝባዊ ንቅናቄው መቀጠል አለበት –አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0
ለውጥ ስለተመኘነው ብቻ ዱብ የሚል ክስተት አይደለም። ለረጅም ጊዜ የሕዝብን ልብ ሲያቆስል የኖረ መንግሥት፤ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰው የበደል ክምችት ከቋቱ ሞልቶ ሲፈስ፤ ሕዝቡ ሆ! ብሎ ይነሳል። ያን ማዕበል የሚያግደው ወታደራዊ ኃይል የለም። በርግጥ በሞት ቋፍ ላይ ያለ ባለሥልጣን፤ ሥልጣኑን ላለመልቀቅ፤ ብዙ ይገድላል፣ ብዙ ያስራል፣ ብዙ ያሰድዳል። የብዙ ሰዎችን ንብረት ያጠፋል። የሀገርን ሀብት ያጋፍፍና ወደ ራሱ […]

በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው

$
0
0
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ በዚህ የውይይት መድረክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ተገኝተዋል፡፡ በዚህ ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንደተናገሩት ለችግሮች የሚመጥን የህግ […]

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኦሮሚያ ከልል ተፈናቃዮች ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

$
0
0
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኦሮሚያ ከልል ተፈናቃዮች ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ። ባንኩ በዛሬው እለት ለተፈናቃዮች ማቋቋሚያ የሚውል የ33 ሚሊዮን 612 ሺህ ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የገንዘብ ድጋፉን የክልሉ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አበዲሳ ተረክበዋል።

“እንዴት ይረሳል…ተረሳሽ ወይ?” –ሰሎሞን ዳኞ

$
0
0
ሰሎሞን ዳኞ – ዘብሔረ ዓባይ (sent to Reporter on Friday, April 19, 2019)   ከአንድ ዓመት በፊት አገራችን የነበረችበትን ቀውስ አልፋ እዚህ መድረሷን ሳስብ ታምር መስሎ ይታየኛል፡፡ በአስከፊ ማዕበል ውስጥ እንደምትናወጥ መርከብ የማያባራ ሕዝባዊ አመጽ ወዲያና ወዲህ ያላጋት ነበር፡፡ በሰላም ወጥቶ መግባት ብርቅ ሆኖ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ስንቱ በሽብርተኛ ስም እየታፈሰ እስር ቤት […]

በወቅታዊ የትግል ሁኔታዎች ላይ የሲዳማ ኤጄቶ ያወጣው የአቋም መግለጫ

$
0
0
በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የሲዳማ ኤጄቶ በሀዋሳ ከተማ ባህል ማዕከል አዳራሽ በአጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በተለይም በሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ፣ በፀጥታ ጉዳዮች ላይ እና በቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን ከዚህ በታች የተገለፀውን የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። ~~~~ “ለሲዳማ የክልልነት ጥያቄ የሚታገል የመጨረሻው ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ህጋዊና ሰላማዊ ትግል እያደረገ የሚገኘው […]

የልብ እምባ –ሳዲቅ አህመድ

$
0
0
ጎርፍ ነው፣ሐያል ነው ያ…የልብ እምባ ጨቋኝን ጠራርጎ ኪሳራ የሚያስገባ አይኖች የማያዝሉት ተሳማይ አራጊ ከምድር ላይ ዘንቦ ግፈኛን አናጊ። የልብ እምባ ምስጢር ቁጥር አበዛዙ በቃ ይፍሰስ ተውት ተወደ ጽድቅ ወንዙ ለተበዳይ ክብሩ ለበዳይ መዘዙ ሐዘን ሲርድ ሐሴት ነው ምድቡ ድል እኮ ቅርብ ነው ልቦች ሲያነቡ። እምባው በአምባው ላይ ከመንታ አይን ርቆ ላይዘንብ በምድሪቱ ከመፍለቂያ ደርቆ በልቦች […]

ሙስሊሙ ህብረተሰብ የአስተምህሮው ማእከል የሆነውን ሰላም ለማምጣት ዛሬ የተጀመረው ጉባኤ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

$
0
0
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 23 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ሙስሊሙ ህብረተሰብ አጥብቆ የሚፈልገውንና የአስተምህሮው ማእከል የሆነውን ሰላም ለማምጣት እየተካሄደ የሚገኘው ጉባኤ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ። በሸራተን አዲስ “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ እና የአንድነት ሀገር አቀፍ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህ የኡለማዎች ጉባኤ ላይ በመገኘትም ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ […]

በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ

$
0
0
በአማራ ክልል ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ፣ መርዓዊና ሌሎችም ከተሞች ዛሬ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። ከሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ እንዳላማው ክንዴ ለቢቢሲ እንደገለፁት ሰልፈኞቹ ካነሷቸው ጥያቄዎች ውስጥ አዴፓ ስሙን ከመለወጥ ውጭ ክልላዊም ሆነ ተቋማዊ ለውጥ አላመጣም፤ የህዝቡን ጥያቄ በተገቢው መንገድ አልመለሰም፣ እንዲሁም የክልሉ #ፕሬዚደንት ስልጣናቸውን ይልቀቁ የሚሉ ይገኝበታል። https://bbc.in/2GKgpE0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት ላደረጉት አስተዋፅኦ የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት

$
0
0
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት ላደረጉት አስተዋፅኦ የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት 2019 አሸናፊ ሆኑ። የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት ለሃያ በላይ አለም አቀፍ ታዋቂ ግለሰቦች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1991 ጀምሮ ሲሰጥ ቆይቷል። ይህ ሽልማት “ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በመፍታት፣ የውይይትን እና ድርድርን ሚና በማጉላትና በመቻቻል፣ በእኩልነትና በመግባባት ሰላም እንዲሰፍን አስተዋፅኦ ላደረጉ […]

አቶ  ገዱ አንዳርጋቸው ከእንግሊዙ አቻቸው ጋር ተወያዩ!!

$
0
0
አቶ ገዱ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በለውጥና በዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት ላይ የምትገኝ መሆኑን አብራርተዋል። በዚህ ረገድ እንግሊዝ እያደረገች ያለውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍም አመስግነዋል። አቶ ገዱ ከኤርትራ ጋር ስለተደረስው የሰላም ስምምነትም የገለፁ ሲሆን በደቡብ ሱዳን እና በሶማሊያ ሰላም እንዲሰፍን በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኗንም ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የእንግሊዝ ባለሀብቶች በአገራችን እያደረጉ ያለውን የኢቨስትመንት እንቅስቃሴ አድንቀዋል። እንግሊዝ በአገራችን በንግድ እና […]

አዲስ የሚቋቋመው ዜግነትን መሰረት ያደርገው ፓርቲ መሪዎቹን በቀጣዩ ሳምንት ያሳውቃል

$
0
0
አርበኞች ግንቦት 7፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢዴፓ እና የአንድነት ፓርቲ መስራቾችን ጨምሮ 7 ፓርቲዎች ራሳቸውን በማክሰም ወደ አዲሱ ፓርቲ ምስረታ የሚያደርጉት ጉዞ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መገኘቱ ታወቀ። የአዲሱ ፓርቲ መስራቾች ለአባላት እና ለደጋፊዎቻቸው ትናንት አዲስ አበባ ፍሬንድ ሺፕ ሆቴል ባደርጉት የዕራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ እንደተገለጸው አዲሱ ፓርቲ ከሳምንት በኋላ በይፋ ይመሰረታል። በፓርቲው መስራች ጉባኤ እና የአመራር […]

የጋዜጣዊ መግለጫው ዝርዝር –ኤልያስ መሰረት

$
0
0
የአማራ ክልል ቃል- አቀባይ አቶ አሰማኸኝ አስረስ በቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጃዊ ወረዳ ላይ ደረሰ ስለተባለው ግጭት እና ሞትን አስመልክቶ ዛሬ ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተወሰደ: – ሚያዝያ 17 ግጭቱ ከጀመረ በሁዋላ እና በቀጠሉት ቀናት በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በዚህ ቀን በሁለት ግለሰቦች መሀል በተፈጠረ አለመግባባት የአንድ ጉሙዝ ህይወት አልፏል። ከዛ ቀጥሎ በብቀላ መልክ […]

ትግራይ :- ባለቤት ያጣች የአፈና የእስርና የጨለማ ደሴት ሆናለች (በላይ)

$
0
0
ይድረስ ለኢትዮ  ያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዶክተር ዓቢይ አህመድ አዲስ አበባ ጉዳዩ:- በዲያስፓራ የዓረና መድረክ ድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር አባላት በትግራይ ክልል በወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ስላለው አፈናና ሰብኣዊ መብት ረገጣን በማውገዝ ያወጡት የጋራ መግለጫና ውሳኔን ይመለከታል :: ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆይ !! እኛ በውጭ ዓለም በሰሜን አሜሪካና በሌሎች ክፍላተ ዓለም በተለያዩ […]

የጠቅላይ ሚንስትሩ “የሰላም” ሽልማት እና የምዕራባውያን ሴራ –በተመስገን አስጨነቅ ዘለቀ

$
0
0
ምዕራባውያን ተንኮል ብቻ ሳይሆን ቀልድም በድንብ ይችሉበታል። ሰሞኑን የነገሩን ቀልድ ደግሞ ለሚያውቃቸው ፈገግ ሲያሰኝ ለማያውቃቸው እና ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ለተረዳ ደግሞ ቀንድ ያቆማል ። ጠቅላዩ “የዩኒስኮ የሰላም አዋርድ” ተሸላሚ ሆኑ ይላል። ሀገር በአራቱም አቅጣጫ እንደበሬ ቆዳ ተወጥራ በየቀኑ የምንሰማው ግድያ እና እልቂት ለምዕራባውያን እንደ ሰላም ተቆጥሮ ሽልማት ያሰጣል። እነሱ ምን አሻቸው እጃቸውን የሚያስገባላቸው እና ገብተው […]

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አስከሬን አዲስ አበባ ገባ 

$
0
0
የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አስከሬን በዛሬው ዕለት ንጋት ላይ ከጀርመን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ገብቷል። አስከሬኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት የአቀባበል ስነስርዓት ተደርጓል። አስከሬኑ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ሃያት ሆስፒታል ተወስዷል፡፡ አስከሬኑ እሁድ ከጠዋቱ 1 […]

የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የመጨረሻ የስንብት እና የቀብር ስነ ስርዓት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

$
0
0
የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ድንገተኛ ሞት ተከትሎ ብሄራዊ የቀብር አስፈፃሚ ግብረሃይል ተቋቁሞ የተለያየ ስራ በመሰራት ላይ ይገኛል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት የቀብር ስነስርዓት የመንግስት ከፍተኛ ባላስልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር እሁድ ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ በ9:00 ስዓት ይፈፀማል። እስከ ግብዓተ መሬቱ ድረስ የሚከተሉት ስነስርዓቶች ይከናወናሉ። […]

የአንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን) –ልሳን ኢትዮጵያችን ቅጽ 3 ቁጥር 6

$
0
0
ኢትዮጵያችን ቅጽ 3 ቁጥር 6                                                  ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በምርጫ ስም ኢትዮጵያችን “አትከፋፈልም” የድምጽ ቅጂውን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ https://www.youtube.com/watch?v=8tJQcZdGiLY የኢትዮጵያ ሕዝብ በመረጠው መንግሥት ይተዳደር ዘንድ የነበረው ጥረት እንደ አንድ ተውኔት ሲያስገርም፣ ሲያስደንቅ፣ ሲያስቅ፣ ሲያበግን፣ ተስፋ ሲያስቆርጥ አልፎ ተርፎም ሲያሳስር፣ ሲያስደበድብ፣ አካል ሲያቆስል፣ ሕይወት ሲቀጥፍ አይተናል ታዝበናል። ምርጫ ከአካባቢ፣ ከቀበሌ፣ ከወረዳ እየጀመረ ከፍ ብሎ አውራጃ፣ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live