Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አቶ አስራት ወደ ቅሊንጦ ወህኒ ቤት ተወሰዱ፤ ዳንኤል ተፈራ የፖሊስ መጥሪያ ደረሰው

$
0
0

አስራት ጣሴ

አስራት ጣሴ


በክስ ሂደት ላይ በሚገኘው የአኬልዳማ ዶክመንተሪ በድጋሚ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መታየቱን ተከትሎ በአዲስጉዳይ መጽሔት ላይ አስተያየት የጻፉትና “በፍርድ ቤት ላይ ዘለፋ አዘል ጽሑፍ ጽፈዋል” ተብለው አርብ ጥር 30፣ 2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አቶ አስራት ጣሴ ለቅጣት ውሳኔ 7 ቀናት ታስረው እንዲቆዩ የተወሰነባቸው መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ወደ ቂሊንጦ ተዘዋውረዋል ሲል አዲስ ጉዳይ መጽሔት ዘገበ።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዘጠነኛ ፍትሐብሔር ሁለተኛ የቤተሰብ ችሎት ጥር 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ወጪ ባደረገው የትዕዛዝ ደብዳቤ አቶ አስራት ጣሴ በአዲስጉዳይ ሳምንታዊ መጽሔት ቅጽ 7 ቁጥር 198 የጥር ወር 2006 ዓ.ም. ዕትም ላይ ያቀረቡትን ‹‹… አሁን ደግሞ ከሰሞኑ ‘አኬልዳማ’ ድራማ በድጋሚ በተከታታይ እየቀረበና እየታየ ነው፡፡ ይህ እየሆነ ያለው አንድነት ፓርቲ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትን በስም ማጥፋት ወንጀል በፍርድ ቤት ከሶ ገና ውጤት ባልተገኘበት ወቅት ነው፡፡ እሱም ፍትሕ ከኢሕአዴግ ፍርድ ቤቶች ይገኛል ተብሎ ሳይሆን፣ በታሪክ ምስክርነት እንዲመዘገብ ሲባል ነው፤›› የሚል ጽሑፍ ማስፈራቸውን በመግለጽ ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ በፖሊስ በኩል መጥሪያ ልኮላቸዋል።

ፍርድ ቤቱ በትዕዛዝ ደብዳቤው ላይ ያሰፈረውንና አቶ አስራት በአዲስጉዳይ መጽሔት ላይ ጽፈውታል የተባለውን ጽሑፍ ‹‹ፍርድ ቤት ፍትሕ የማይሰጥ አካል መሆኑን የሚገልጽ ዘለፋ አዘል ጽሑፍ›› ሲል ገልጾታል፡፡

የአንድነት ፓርቲ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን እና በአኬልዳማ ዶክመንተሪ አዘጋጅ ላይ ያቀረበው ክስ ሂደት በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ቢሆንም የአኬልዳማ ዶክመንተሪ ፊልምን ጣቢያው በቅርቡ በድጋሚ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት አቶ አስራት ጣሴ ከሦስት ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ሰኞ የካቲት 3፣ 2006 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ወደ ቃሊቲ ቂሊንጦ እስር ቤት መዛወራቸው ታውቋል፡፡

ፍኖተ ነፃነት በበኩሉ የፖሊስ ምንጮቹ እንዳሉት አስራት በፖሊስ ጣቢያው በቆዩባቸው ጊዜያት በእስረኛው ተገቢው አክብሮትና መልካም አቀባበል ማግኘታቸው አሳሪዎቻቸውን አላስደሰተም፡፡ አንድነት ፓርቲን ከምስረታው ጀምሮ በከፍተኛ አመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩትና በአሁኑ ወቅትም በፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤትና ስራ አስፈፃሚ የፓርቲዎችን ውህደት እንዲመሩና የአማካሪ ምክርቤት እንዲያቋቁሙ ኃላፊነት የተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ አንድነት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለፍትህ” በሚል መሪቃል የመንግስት የተለያጡ ሀላፊዎችን ለመክሰስ እንቅስቃሴ ማድረጉን ተከትሎ መንግስትም የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን ምክንያት እየፈለገ መክሰስና ማሰር መጀመሩ ገዢው ፓርቲ አለመረጋጋት ውስጥ እንደገባ የሚያመላክት ነው፡፡

አቶ አስራት በፖሊስ ሲወሰዱ የሚያሳየው ቪድዮ ይመልከቱና ዜናው ይቀጥላል

በሌላ ዜና ዳንኤል ተፈራ ቃል እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ መታዘዙን ፍኖተ ነጻነት ጨምሮ ዘገበ።

Daniel-Teferaየአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራ ማዓከላዊ ወንጀል ምርመራ በመቅረብ ቃሉን እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዟል፡፡ ፍኖተ ነፃነት ምንጮችን ዋቢ በማድረግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ በአራት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ክስ ለመመስረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መዘገቧ ይታወሳል፡፡

ይህ በ እንዲህ እንዳለ አንድነት ፓርቲ የአቶ አስራትን መታሰር ተከትሎ ባወጣው መግለጫው “የአቶ አሥራት ጣሴ እስር የኢህአዴግ የጉልበት ፖለቲካ ማሳያ ነው!” አለ። ሙሉው መግለጫ እንደወረደ፦

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ የተሠጠ መግለጫ

ፓርቲያችን አንድነት በተደጋጋሚ ከገዥው ፓርቲ ህግን ከለላ በማድረግ እና የመንግስትን ሥልጣን በመጠቀም የሚደርስበትን ከፍተኛ አፈና ተቋቁሞ የኢትዮጵያን ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን የበላይነት ለማረጋገጥ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠሉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡

በተለይም ፓርቲያችን በመላው የሀገራችን ክፍል የዘረጋውን መዋቅር በህዝባዊ አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ በማሸጋገር በአምስት ዓመት ስትራተጂክ ዕቅዱ መሰረት እያከናወነ ያለው ህዝባዊ ንቅናቄ እና በተሳካ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባዔ አካሂዶ ዴሞክራሲያዊ የአመራር ሽግግር ማድረጉ በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ያሳደረ ቢሆንም ገዥውን ፓርቲ በአንጻሩ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተው ይስተዋላል፡፡

ኢህአዴግ ቀደም ሲል የፓርቲያችንን እንቅስቃሴ በመከታተል ከከፍተኛ አመራሮች መካከል አቶ አንዱዓለም አራጌ፤ ናትናዔል መኮንን እና ሌሎች በርካታ አባላትን የተለያየ ምክንያት ፈጥሮ እየወነጀለ ለእስር መዳረጉ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህም በድንገት የተደረገ ሳይሆን የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር እና የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ በግልጽ በፓርላማ ተገኝተው ‹‹አንድነት ፓርቲ እግር ሲያወጣ እግሩን እንቆርጣለን›› ባሉት መሰረት የፈጸሙት ነበር፡፡

አሁንም የራዕያቸው አስቀጣይ ነን የሚሉ የገዥው ኃይሎች ፈለጋቸውን ተከትለው የአውራ ፓርቲ (የአንድ ፓርቲ ስርዓት) ለመገንባት አንድነትን በጉልበት ፖለቲካ ማጥፋት እንደ ብቸኛ መንገድ ወስደው እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡ በመላው የሀገራችን ክፍል በርካታ አባሎቻችን ከስራ ተፈናቅለዋል፤ በግፍ ከሀገራቸው እንዲሰደዱ ተደርገዋል፤ ታስረዋል፤ ተደብድበዋል፡፡ ይህም በየጊዜው በፓርቲያችን ልሳን በመረጃ ተደግፎ ለህዝብ ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በፓርቲያችን አመራር እና አባላት ላይ የተፈጸመውን የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት ባመላከትንበት ሪፖርትም ተካተቶ ለህዝብ ይፋ ተደርጓል፡፡

በተለይም የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት በሚል የተካሄደውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ ፓርቲያችን በተንቀሳቀሰባቸው አሥራ አንድ የሀገራችን ከተሞች ጉልህ ሚና የተጫወቱ እና በህዝብ ተቀባይነት ያላቸውን አባላት ምክንያት እየፈጠሩ እና የፍትህ ስርዓቱን የፖለቲካ መሳሪያ እያደረጉ ለእስር እና ለእንግልት መዳረጉን አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

ኢህአዴግ ገና በጊዜ የጀመረው የ2007 ዓ.ም የምርጫ ዘመቻ የተለመደውን የጉልበት ፖለቲካ የተከተለ ሲሆን በቅርቡ በምዕራብ ሸዋ ዞን ለንሴቦ ወረዳ አቶ አለማየሁ ለሬቦ የተባሉ የሲተዳማ ዞን የአንድነት ስራ አስፈጻሚ በአዲስ አበባ ተገኝተው የፓርቲ ጉባኤ ተሳትፈው ሲመለሱ በቁጥጥር ስር ውለው ለ22 ቀናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በእስር ቤት ከተሰቃዩ በኋላ መንግስትን ሰድበዋል የሚል ክስ ተመስርቶባቸው በዋስ ተለቀዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ በየካቲት 30 ቀን የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራር (የብሄራዊ ምክር ቤት አባል) የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ ፍርድ ቤትን ዘልፈዋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ሌሎች አራት ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮች ሊታሰሩ ሴራ እየተሸረበባቸው መሆኑን ምንጮች ለፓርቲያችን እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡

የፍትህ ስርዓቱን ዋነኛ የፖለቲካ መሳሪያ ያደረገው የኢህአዴግ መንግስት አቶ አስራት ጣሴን ለማሰር እንደ ምክንያት የተጠቀመው በአዲስ ጉዳይ መጽሄት 197 ቅፅ 7 ያወጡትን ጽሑፍ ሲሆን አጠቃላይ መልዕክቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ የሌለ መሆኑን፤ ህጎች አፋኝ መሆናቸውን፤ ኢ.ቲቪ የሰራቸው አኬልዳማ፤ ጀሃዳዊ ሃረካትና ሌሎች ለፖለቲካ ጥቃት ማድረሻ የተቀነባበሩ ድራማዎች ህገ ወጥ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ይህ የፍትህ ጥያቄ ደግሞ አቶ አስራት ጣሴ ገና በጠዋት ለትግል የወጡበት፤ ከመሰሎቻቸው ጋር ሆነው አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍት ፓርቲ እንዲመሰረት በርካታ መስዋዕትነት የከፈሉበት የፖለቲካ አላማቸው እና የፓርቲ አቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡

‹‹የኢህአዴግ መንግስት ከሚመራቸው ፍርድ ቤቶች ፍትህ ይገኛል ብለን ሳይሆን ለታሪክ እንዲመዘገብ ወደ ፍርድ ቤት እንሄዳለን›› ሲሉም የግል ሃሳባቸው ብቻ ሳይሆን በብዙ አንቀጽ የተጠቀሰ የፓርቲያቸው አቋም ስለመሆኑም ማሳያ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ኪሊማንጃሮ የተባለው ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በመንግስት ተቋማት ላይ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በህዝብ ከማይታመኑ ተቋማት መካከል ፍርድ ቤቶች በአንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ናቸው፡፡

ከነዚህ በህዝብ ከማይታመኑ ተቋማት ፍትህ አይገኝም ብሎ ማመን እና እምነትን መንገርም ሆነ መጻፍ ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑ እየታወቀ በአካል ባልተገኙበት ችሎት በአካል ተገኝቶ ችሎትን ያወከ ወይም የዘለፈ በሚቀጣበት ፍታብሔር አንቀጽ 480 ቀርበው እንዲያስረዱ ከተጠሩ በኋላ ለእስር ተዳርገዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተጠሩበት የፍታብሔር አንቀጽ የሚያዘው ጥፋታኛ ሆነው የተገኙ ቢሆን እንኳ በአነስተኛ የገንዘብ መቀጮ የሚቀጣ እንጂ ለእስር የሚያበቃ አልነበረም፡፡

ኢህአዴግ ይህንን እያደረገ ያለው ቀናቶች ወደ 2007 ዓ.ም ምርጫ እየገሰገሱ እና ፓርቲያችንም በህዝባዊ አቅሙ እየጎለበተ በመምጣቱ ካለቃቸው እንደተማሩት እግር ያወጣ ፓርቲያችንን እግር በመቁረጥ፤ አመራሩን ህግን ከለላ አድርገው ለእስር በመዳረግ፤ እንዳይጽፍ፤ እንዳይነገር እና በፍርሃት ቆፈን ተይዞ አንገቱን እንዲደፋ በማድረግ በምርጫ ሜዳው ከጀሌዎቻቸው ጋር ሩጠው አሸንፈናል ብሎ ለማወጅ የሚደረግ አስነዋሪ ዘመቻ ነው፡፡

ነገር ግን እንዲህ ያለው አምባገነናዊ ተግባር ትግላችንን የበለጠ አጠናክረን በመግፋት ሰላማዊ ትግሉ የሚጠይቀንን መስዋዕትነት ለመክፈል የሚያበረታን እንጂ ወደኋላ የማይመልሰን መሆኑን ዛሬም እንደ ትላንቱ ለመላው ህዝባችን እናረጋግጣለን፡፡

የፍትህ ስርዓቱም ከአንድ ፓርቲ ወገንተኝነት እንዲወጣ እና በግፍ የታሰሩ አመራሮቻችንንም በነጻ እንዲያሰናብት እንጠይቃለን !!!!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
የካቲት 1 ቀን 2006ዓ.ም


የአየር ኃይል አባሉ ም/መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ ሥርዓቱን ከድቶ አርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ

$
0
0

የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ ሥርዓቱን በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላቀሉን አርበኛ ኑርጀባ ለዘ-ሐበሻ በላከው ዜና አስታወቀ።

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት - ፎቶ ከፋይል)

(የአርበኞች ግንባር ሠራዊት – ፎቶ ከፋይል)

እንደ አርበኛ ኑርጀባ ዘገባ አምባገነኑ የወያኔ ቡድን የታጠቀ ኃይሉን መከታ በማድረግ ንጹሃን ዜጎችን ያለ አግባብ እየጨፈጨፈ የስልጣን ዕድሜውን ለማስቀጠል የሚያደረገውን እንቅስቃሴና በሰራዊቱ ውስጥ የነገሰውን የአንድ ቡድን የበላይነት በመቃወም የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረውና L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ የነበረው ም/መ/አለቃ ዳንኤል የሽዋስ አገዛዙ የሚያደርስበትን ጭቆናና እንግልት ይበቃል በማለት ወደ ኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ተቀላቅሏል።

“የደብረዘይት አየር ኃይል አባልና L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ የነበረው ም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ከእነሱም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለህ በሚል ምክንያት ተጠርጥሮ ያለምንም ወንጀል ለአምስት ወር ያህል ታስሮ እንደነበርና ከእስር እንደተለቀቀም በወያኔ የደህንነት አባሎች አማካኝነት በአይነ ቁራኛ ክትትል ይደረግበት እንደነበርም” ማስታወቁን የገለጸው የአርበኛ ኑርጀባ ዘገባ “በም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ የወያኔው የደህንነት አባሎች ጥላቻና ጥርጥር ምክንያት እንደገና ከተቃዋሚ ኃይሎች ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ደርሰንበታል በማለት ወደ እስር ቤት እንዳስገቡትና ለ23 ቀናት በደብረዘይት እስር ቤት ከቆየ በኋላ ከእስር ቤት አምልጦ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላቀሉን ገልጿል” ብሏል።

በሌላ ዜና በሁመራ አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊዎች ናችሁ በማለት ታስረው የነበሩ 10 ሰዎች ላይ ከ6 ዓመት እስከ 25 ዓመት በመፍረድ ወደ መቀሌና ሽሬ እስር ቤት እንደወሰዱዋቸው ታውቋል።

በመቀሌ እስር ቤት በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ደጋፊነትና በተለያየ የአሸባሪነት ሰበብ እየፈጠረ የሚያስረው የወያኔው አገዛዝ በመቀሌ እስር ቤት ብቻ 36,900 እስረኛ የሚገኝ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 4500 የሚሆኑት ሴቶች እንደሆኑ ታውቋል።

በዚሁ እስር ቤት ሰዎችን በሌሊት እየቀሰቀሱ በመውሰድ ደብድበው የሚመልሱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ በዚያው እንደወጡ እንደሚቀሩ ከአካባቢው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

የወያኔ ካድሬዎችም በዚሁ በመቀሌ እስር ቤት ውስጥ በሚገኙ ሴቶች ላይ የወሲብ ጥቃት እንደሚፈጽሙባቸው መታወቁን የዘገበው አርበኛ ኑርጀባ፣ በዚህም ምክንያት ሁለት ሴቶች መፀነሳቸውና አስፈላጊውን እንክብካቤ ባለማግኘታቸው ሕይወታቸው እንዳለፈ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዳንሻ አካባቢ በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ስም በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው እንግልት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የወያኔው ገዥ ቡድን በዚሁ አካባቢ እየደረሰበት ባለው ወታደራዊ ጥቃት ሳቢያ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እንደ ምሽግ የሚጠቀመው እናንተን ነው በማለት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያሰቃይ እንደነበር ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት ብዛት ያላቸው የዳንሻና የአካባቢው ነዋሪዎችን እያሰረ ሲሆን፣ የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ያስታጠቃችሁን መሣሪያ አምጡ፣ ከእነሱ ጋርም ቀጥተኛ ግኑኝነት እንዳላችሁም ደርሰንበታል በሚል ወደ እስር ቤት እያጎራቸው ይገኛል ሲል አርበኛ ኑርጀባ ለዘ-ሐበሻ የላከውን ዜና አጠናቋል።

“ጥቁሩ ሰው” –የጥቁር ሕዝብ አባት – (ከስንሻው ተገኝ)

$
0
0
minilik                                  
   አንድ ዘመን ሥርዓተ መንግስቱ በመቆየትም ሆነ አባላቱ የአሥራ ሰባተኛው ክፍለ ዘመን የተረት ዓለም ሰዎች ስለ መሰሉን- ሁሉም ነገር ስለገለማን አዲስ ሥርዓት፣ አዲስ መሪ፣ አዲስ ዘመን መናፈቅ ይዘን ነበር። ሰዓሊ ሁሉ፣ ደራሲ ሁሉ፣ ጸሐፌ -ተውኔት ሁሉ እጁን የሚያሟሸው በቴዎድሮስ ሥዕል፣ ተውኔትና ታሪክ ሆነ። ብርሃኑ ዘሪሁን- የቴዎድሮስ እንባ -(መጽሐፍ) ከዚያ በፊት ደጃዝማች ግርማቸው ተክለሐዋርያት- ቴዎድሮስ (ተውኔት) አቤ ጉበኛ – አንድ ለእናቱ (ታሪካዊ ልቦለድ) ጸጋዬ ገብረ መድኅን – ቴዎድሮስ (ተውኔት)…ሥዩም ወልዴ -ሥዕል..ታደሰ ወ.አ….ቅርጻቅርጽ እና የሥነ ጥበባት ትምህርት ቤት ሥስት አራተኛ ተማሪዎች..የቴዎድሮስ ሥዕል ግጥም -ቅኔ- ሥዕል አለፈላት።
ከአሮጌና ከገለማ ሥርዓት ነፃ የሚያወጣ አመጸኛና አመጻ የሚመራ ጀግና ስንፈልግ ባጀንና ቴዎድሮስን አገኘን። ከመቶ አመት በኋላ ነው ቴዎድሮስ የተፈለገው። በአጤው ሥርዓት በአንዳንድ ደራስያንና የዘመን ታሪክን በውዳሴና በነቀፋ በሚያቀርቡ ግለሰቦች ዘንድ እንደጭራቅ ይቆጠር የነበረው መይሳው ካሣ በለውጥ መሪነት የተፈለገበት መሪ ነበር። አብዮታዊው መሪ ጓድ መንግሥቱ እንኳ፥ “ቴዎድሮስ” (ምናልባትም ዳግማዊ ቴዎድሮስ) እኔ ነኝ። የዚህን ሕዝብ አብዮት እንድመራም ከሙታን የተጠራሁ ነኝ” እስከ ማለት ደርሰው ነበር። በቴዎድሮስ መንገድ አልተጓዘም እንጂ። በተረተኞች፣ በተረበኞችና በዋልጌዎች፣ በጐታቾችና በክፍፍል በኖሩ ዘንድ ተወዳጅ ያልሆነው ሕልመኛው ቴዎድሮስ በእርግጥ ከዘመኑ አርቆና አልቆ የሚያይ ስለሆነ ከወቅቱ ደባትርና ከመሳሰሉት ጋር ስምምነት አልነበረውም።
የአገር አመራር በተበላሸና ሕዝቡ የሚያምነው መንግስት ባጣበት፣ ብሔራዊ አንድነቱና ዳርድንበር አስከባሪ በሚሻበት ሰዓት ከመሐሉ የወጣ የጐበዝ አለቃ ሲያደንቅ ይገኛል። እንዲያ ካልሆነ ደግሞ ከአባት መሪዎቹ መካከል ያደነቀውን፣ የሚያደንቀውናና የሚያከብረውን መናፈቅ ይጀምራል። ባያውቀውም። ዛሬን ያስቡአል። አገር እንደ አቃቂ በሰቃ (ኮሎናልቤ) ከስኩት ፍርክስክሱ በወጣበት፣ ሕዝብ እንዲከፋፈልና እንዲጨራረስ ማናቸውም ዓይነት ሴራ በሚጐነጐንበትና መቀበሪያ ሳይቀር “እናገኝ ይሆን” የሚል ስጋት በተጫጫነን ሰዓት “የአንድነትን ጌታ” የአገሪቱን እውነተኛ አባት መናፈቅ ያለ ነው። እነዚህማ ሸጡን። እነዚህማ ለወጡን። መሬቱን ጋጡት። ከትውልዱ አባልነት መብታችን አንዲቱንም አላከበሩልንም። የአንድነትን አባት፣ የዘላለም ኩራታችን ምንጭ፣ ሁሉንም አበሻ በእኩልነት የመራውን ጀግና እንድንናፍቅ ጊዜው አስገድዶአል። ምኒልክን! ይኸ ደግሞ ከመካከላችን እንደ ምኒልክ ያሉ የአንድነት እምነት አራማጆች እስኪንቀሳቀሱ ድረስ ነው።
ነፃነት አንድን ሕዝብ ወደፊትና ወደላይ የሚያንደረድር (የሚወስድ) ኅይል ይሻል። ስለዚህ እውነተኛና ከዚህ በኋላ የሚመሩን (ከዘመኑ ቀድሞ እንደ ተወለደው ምኒልክ) ሰዎችም ወደፊት ብቻ ሳይሆን ወደ “ላይም” ሊመሩን የተዘጋጁ ናቸው። እነዚህ ቆነጃጅት አልተወለዱም አይባልም። እንዲያውም አይተናቸዋል። ዳስሰናቸዋል። ዓለምም አውቆአቸዋል። እኛ ግን ከጥቃት፣ ከእሥራት፣ ከእንግልት…ከመከራ አላዳናቸውም፥ እስክንድርን፣ አንዱዓለምን፣ በቀለን…ካድናቸው። ለወያኔ ወረወርናቸው ለአውሬ። አገርን የሚያድን መሪ ብቻ አይደለም። ዋናው ሕዝቡ ነው። በአድዋ ወሳኙን የመሪነት ሚና የያዘው ምኒልክ ነበር። የተዋጋው ሕዝቡ ነበር። ሕዝባችን ቅንና ጀግና መሪ፣ መሪውም ታማኝና ቆራጥ ሕዝብ ያገኘበት አንድ ወቅት ይኸ ነው።
በአንጻሩ በአመራር የጊዜ ማኅፀን ውስጥ ያሉት ወይም ቢወለዱም በአመራር ጉልምስና ዘመን ላይ የሚገኙት “መልካካም የኢትዮጵያ ልጆች” ወደ አገር አዳኝነቱ መንበር ሲመጡ የሚገጥማቸው ፈተና የትየለሌ ነው። ሁላችሁም አስቡት። የተሸጠ አገርና መሬት የማስመለስ ግዴታ ሊሸከሙ ነው። የተከፋፈለ የሕዝብ ይዞታ ሊያስተካክሉ ነው። የኢኮኖሚውን ሥርዓት መስመር ሊያስይዙት ነው። “ወደ ላይ መምራት” ባልሁት የአመራር ፈርጅ ደግሞ የሚጠብቃቸው ከዚህ ሁሉ በላይ ነው። በታላላቅ ዲታዎችና መንግሥታት ትእዛዝና መሪነት ሥር የወደቀችውን አገር ዜጐችዋ ባለሥልጣናት ይሆኑ ዘንድ መንገዱን መጥረግ አለ። የሕዝብን ነፃነት፣ መብትና ሕዝቡ በአገሪቱ ላይ ያለውን ሉዓላዊነት ማወቅና ማክበር አንዱ ነው። የሕብረተሰቡን መንፈሳዊና ባሕላዊ መብቶች ማረጋገጥና የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ፣ የጽሑፍና አሳብን በነፃ የመግለጥ ተፈጥሮአዊ መብቶቹን መንከባከብ፣ ፍትሕና ርትእ በራሳቸው ጐዳና ከመጓዝ እንዳይታወኩ ማድረግ ማለት ነው። ዝርዝሩ በዚህ ይቀጥላል። በመሰረቱ ደግሞ ታሪክ ስትቆፍሩ ብትውሉ አገር የሸጠ፥ የአገር መሬት የቸበቸበ መሪ ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። በውጭ ምስጢር ባንክ የተቀመጠውን ገንዘብ ቁልፍ መለስ ለሚስቱ ካልሰጣት እሱም በሞቱ ከስሮአል። እኛም ያንን ለማስተካከል ብዙ ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። የእሱን ወንጀል።
ጆርጅ ኦርዌል በ1984 መጽሐፉ በአምባገነኖች አገዛዝና ዘመን “እውነት ውሸት፣ ማይምነት እውቀት፣ ጥላቻ ፍቅር..ይሆናል” ይላል። ስለዚህ የወያኔን ባሕርያት የምንረዳው ዛሬ አይደለም። አብረን ኖረን የመንግስት ጠባያት ያልሆኑ- መሆንም የማይገባቸውን ስርቆትን፣ ተራ ውንብድናን፣ ቅጥፈትን፣ የጅምላ ግድያን፣ ፀረ ሃይማኖት አቋምን፣ የመብት ረገጣን…በየዓይነቱ እንደ ቡልኮ ተከናንቦ አይተነዋል። አንዳንድ ፀረ ሕዝብ ተግባራት ከየት መጡ ሳይባል እንኳ “የእሱ ሥራዎች ናቸው” ማለት ቀላል ሆኖአል። ትግርኛ ተናጋሪ ወገኖቼ ፀላዔ ሰናይ ይሉአቸዋል። አንዳችም በጐነት ያልተፈጠረባቸው ለማለት ነው። የሰሞኑን ደንባራ ፖለቲካ ለአብነት ማውሳት ለተነሳንበት ጉዳይ ብርሃን ይፈነጥቃል ባይ ነኝ።
በቅጥፈት የተካነው ሰውየ ከተለያቸው ወዲህ ወያኔዎች ያንኑ የተለመደ ውሸት ከመደጋገም በቀር ሌላ መፍጠር፣ በሌላ ስልት ማወናበድ አልሆንላቸው ብሎአል። ውሸት እንደ ቅርስ በነገሠበት አምባቸው ደግሞ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ያላትና ያፈራችው መንፈሳዊና ስጋዊ ቅርስ ሁሉ አንደኛ መጥፋት አለበት፣ ዳግመኛም- አገሪቱ ካልጠፋች..ታሪክዋ ከዛሬ ተጀመረ መባል አለበት። ታሪክ ከእነሱ አልነሳ ሲላቸው አሁንም ያለፈውን በጐ ታሪክ፣ አኩሪ ባሕልና ጀግንነት፣ የአንድነት ጥበቃ መንፈስ…እንደ ቀላል ነገር ለመግደል ወጥተዋል።
    ውሸታቸው ባያልቅም እውነት መናገር እንጀምር
ለዚህ ሥርዓት ማንኛውም ያለፈ ታሪክ፣ ታላላቅ ጀግኖች፣ ዳር ድንበር…የረከሰና የተናቀ፣ መለወጥና መደምሰስም አለበት። ሁላችሁም ለወያኔ ዓላማና ዛቻ፣ ቅጥፈትና ፀረ አንድነት እንግዳ አንዳለመሆናችሁ የሟቹንም ዛቻና አቋም ታስታውሳላችሁ። ስለ ሰንደቅ ዓላማ ምን አለ? ስለ አገሪቱ አንድነት ምን አለ? ምንስ ፈጸመ? ተከታዮቹስ ምን እያሉና ምን እያደረጉ ናቸው? በአጭሩ የሚነገረው ውሸት፣ የፈጠራ ታሪክና ከፋፋይ ፕሮፖጋንዳ አልቆ እናርፈዋለን ብለን ስናስብ ከቶውንም ወፍጮው ይበልጥ እየፈጨ ስለሆነ በውሸቱ መካከል ስለእነሱም እውነቱን መናገር መጀመር ያለብን ይመስለኛል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትሩማን “ሪፐብሊካኖች ስለእኛ ውሸት መናገርን ካላቆሙ ስለእነሱ ያለንን እውነት መናገር መጀመር ያለብን ይመስለኛል” ብለው ነበር።
ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ጥቂት ከመናገሬ በፊት ስለ መለስ ጥቂት-እጅግ ጥቂት ለማለት እወድዳለሁ። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ሲዘልፍ..ዋና ዓላማው የኢዮጵያን ስም መለወጥ ነበር። ስለዚህ ለብዙ ዓመታት ኢትዮጵያን በስም ከመጥራት ይልቅ “አገሪቱ” ነበር የሚለው። ሥልጣን ሲጥመውና አገሪቱም የማትፈርስ (በቀላሉ) ስትመስለው “ኢትዮጵያ” ማለት ይዞ ነበር።
ቀደም ሲል ጆርጅ ኦርዌልን ያነሣሁበት ምክንያት “ውሸት እውነት” የሚሆንበትን ትክክለኛ አጋጣሚ መከሰት በሚመለተው ነው። እንደሚባለው በአምባገነን መንግሥት ሥር የመጀመርያው ጥቃት የሚደርሰው “በእውነት” ላይ ነው። በሕዝባዊ እውነት ላይ! በታሪኩ ላይ ነው። በጀግኖቹ ላይ ነው። ስለዚህ በአገር የተገኘው ቀጣፊ ሁሉ ዛሬ በፕሮፓጋንዳው ሰፈር፣ በአራት ኪሎ ቤተ መንግስትና በየክልሎቹ አመራር አምባ የተሰባሰቡት የሥነ አእምሮ ጠቢባን (pathological liars) የሚሉአቸው የሚታዘንላቸው ሕመምተኞች፣ እውነትን የሚፈሩ፣ እውነት ሲነገር የሚደነግጡ፣ እውነት ሲወጣ የሚረበሹ ናቸው። ስለዚህ “አንድነት” በተፈተነበትና የአገር ሽያጭ በደራበት ሰዓት አንዱ ማወናበጃ ስልት ያው ምኒልክን በወንጀል መክሰስ ነው። “አምስት ሚሊዮን ኦሮሞ ገደለ” ነው አዲሱ አማርኛ። ለመሆኑ በምኒልክ ጊዜ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከ5 ሚሊዮን ይበልጥ ነበር? ከዚህ ውስጥ የኦሮሞው ቁጥር ስንት ነበር? ለመሆኑ ምኒልክ ማነው? ምን ሰራ? ሕዝብን ከጫጫታው (ከዘመኑ) ለማዳን መሞከር አለብን ወይስ ታሪክ ነፃ ያወጣዋል በሚል አደብ እንግዛ?
       “ ጥቁሩ ሰው” – እንደ ሰው

ታሪክ የበጐነት ምስክር – ወይም ለበጐነት የሚያደላ እማኝ ብቻ አይደለም። የአጥፊዎችን ጥፋት፣ የከሐዲዎችን አሳፋሪ ተግባር፣ የአምባገነኖችን ክፋትና ኢሰብአዊ አገዛዝ ጭምር ዘግቦ ለትውልድ ያስተላልፋል። ይሁንና ታሪክ የማያውቁ አዋቂዎች በመምሰል፣ አዳዲስ ድርሰት በመጻፍ ከሐቅ ግድግዳ ጋር የሚላተሙ፣ በባሕርያቸው ፀላዔ -ሰናይና የእውነት ጠላትነት ያላቸው ደካማ ፍጡራን መድረክ ሲደላደልላቸው የሚያዥጐደጉዱት ቅጥፈት መታለፍ እንደማይገባው እየተከሰተልን መጥቶአል። እስካሁን ግን “ለቅጥፈት ማስተባበያ” ወይም ማስተካከያ አያስፈልገውን በሚልና ውሎ አድሮ ሐቅ ይረታል በሚል እምነት ቅጥፈት ቅጥፈትን፣ ፈጠራና ድንፋታ ራሱን ሲፈጥርና እንደአሜባ ሲራባ በቸልታ ያለፍናቸው ጉዳዮች ሞልተዋል። ከሁሉም ከሁሉም አንድን ኅብረተሰብ የሚያቃጥለው የታሪኩና የጀግንነቱ መታወቂያ ሰነዶች፣ ግለሰብ ጀግኖችና ብሔራዊ መከበሪያ ሐውልቶቹና ቅሪቶቹ መደፈር ነው። በዚህ ረገድ ብዙ ተደፈርን። በዓለም አቀፍ ደረጃ የ”ታላቅ መሪነት”ን ደረጃ የተቀዳጁትን፣ ጠላት ሳይቀር የሰገደላቸውን መሪዎቻችንን ሳይቀር ዛሬ የራሳችን ልጆች በእነዚህ ላቅ ያሉ ሰዎች ላይ ሲያቅራሩ ስንሰማ እንቅልፍ መንሳቱ አልቀረም።
የወያኔ ቀዳሚ ሰልፍና ፍልስፍና ሕዝብን መከፋፈልና አገሪቱንም ማፍረስ መሆኑን ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠራጥረው ይከራከሩን የነበሩ ሰዎች ዛሬ ከግንዛቤ በመነሳትራሳቸው “አገር እየጠፋ” መሆኑን እያረዱን ነው። በወያኔዎች በኩል ደግሞ የአገሪቱንም ሲሳይ እያፈሱ መልሰው አገሪቱን ለማጥፋት ማናቸውንም ሴራ እየፈፀሙ ናቸው። የትሮትስኪ ታሪክ መዝጋቢና የሩሲያን አብዮት ክሽን አድርጐ ያቀረበው አይዛክ ዶቸር ስለ ሩሲያ አብዮት መሪዎች ሲጽፍ እነዚህ ሰዎች የማያውቁትንና ሊያውቁ ያልቻሉትንአገር ተረከቡ። ወይም በእጃቸው አስገቡ። ቀጥሎም የሚያምኑበትን አቃጠሉት። አቃጥለውም ሰገዱለት” ይለናል። አዎን ወያኔዎች ጥገትዋን አልበው እየጠጡ፣ አርደውሊበሉአትም ፈለጉ” ለማለት ይቻላል። በተአምር በእጃቸው የገባችውን አገር ማዳን የብዝበዛቸውና የዘረፋቸው ዋስትና በሆነ ነበር። ይልቁን እዚህ ከደረሱ በኋላ እንኳ የዚህንአገር አንድነት ማዳን ቢሞክሩ ቢያንስ ልጆቻቸው አገር አለን እንዲሉ ባስቻላቸው ነበር። ይልቁንም ኦሮሞዎች ነን የሚሉ በዕድሜም፣ በግንዛቤና በአእምሮ ያልበሰሉ ልጆችን በመመልመል የሚያንጫጩብን እነዚሁ አገር በእጃቸው የወደቀ ሰዎች ናቸው። ምኒልክን ለመወንጀል የክሱን ነጥብ ሁሉ ከየት አገኙት?

እውን እነዚህ ጨርቋ ሕፃናት – የጨርቋ አእምሮ ውጤት የሆነ ፕሮፓጋንዳ በጩኸትና ሰላላ መላላ በሆነ ልሳን ሲያስተጋቡ የዚህ አገር ዋልታና ወጋግራ የሆነው ኦሮሞውኅብረተሰብ ምንኛ እንደሚያፍርባቸው ትገነዘባላችሁ?

ለመሆኑ ከኢትዮጵያ ታሪክ ባለቤትነትና ክብር ሊነጥለን የሚችል ማነው? ጃዋር? አያት ቅድመ አያቶቻችን ደምናአጥንት የሰጡአት አገርኮ ናት! የወያኔ የመስዋዕት ጠቦቶች ለሆኑት እነዚህ ኅፍረተ ቢሶሽስ የኦሮሞን ውክልና ማን ሰጣቸው? ስለማያውቁት፣ ስላላወቁትና ሊያውቁትምስላልፈለጉት ሕዝብ በድፍረት መናገርን ከየት አመጡት? እነዚህ ልጆች “ወገኔ ነው” የሚሉትን ኦሮሞውን ኢትዮጵያዊ ከሌሎች (ለምሳሌም አማራው) ብሔሮች ጋርበማጋጨት ሊያመጡ የሚችሉትን ትርፍ ሊነግሩን ይችሉ ይሆን? ወይ ልክፍት!

ከሶቪየት ኀብረት ኤምፓየር መፍረስ በኋላ አንዳንድ የአሜሪካ የፖለቲካ ፈላስፎች እንደ ሶስተኛ አገር የሚታዩ የኅብረተሰብ ጽናትና ሰላም ያላቸው አገሮች በተቻለ መጠንተሸንሽነው ብዙ አገሮች እንዲወጣቸው ሰፋፊ ጽሑፎችን በገበያ አውለዋል። ከእነዚህም መካከል መለስ ዶላር ያፈስስለት የነበረው የሐርቫርዱ ሳሙኤል ሐንቲንግተን ይገኛል። ከዚያም ሌላ አንዳንድ የሲአይኤ ቅጥረኞች ጽሑፎችየጥናቱ መደብር አሉ። ዩጐዝላቪያ የዚህ ፍልስፍና “ጊኒፒግ” ናት። ከ1991 ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያየምትታመሰው በዚሁ ረቂቅ የጥፋት አውሎ ነፋስ መሆኑን አንዘንጋው። እነሆ እንደ ጃዋር ያሉ አለማወቃቸውን እንደ እውቀት፣ ጮኾ መናገርን እንደ ሐቅ፣ የፈለጉትን ጥጃየአምልኮ ጸጋ በመቁጠር አየረ አየራቱን ሲያተረማምሱት ከእንግዲህስ “ተመከር! ተሳስተሃል! በአገር፣ በሕዝብና በታሪክ ላይ ያመጽህ ባለጌ ነህ” ማለት የሚገባ ይመስለኛል።ልድገመውና “በአባቴ ሙስሊምና ኦሮሞ፣ በእናቴ ክርስቲያንና አማራ ነኝ” በማለት ጅምሩን በማይጠቅመው መደምደሚያ ያበላሸዋል። ጃዋር መሐመድ። ሙስሊም፣ ክርስቲያን፣ አማራ፣ ኦሮሞ! ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ምን ይሁን?

ጐበዝ በዚህ ዓይነቱ ጊዜ ከየጉድጓዱ ብዙ አይጦች ሊወጡ ይችላሉ። አትደነቁ። አንዳንዶቹ የመታወቅ አባዜ (የእንክብካቤ እጦት አባዜ…ዘተ) የተከሰተባቸውና “እገሌ”ለመባል የሚጣባ ሕመም ተሸካሚዎች ናቸው። አንዳንዶቹ ቀጥታ ራሳቸውን ለማያውቁት ተልእኮ በመስዋዕትነት ለመሰጠት በምንዳ የተገዙ ናቸው። ለዚህ ዓይነቱ ተልእኮየተመደበ በጀት ስላለ ሰው ከተገኘ ገዥ አለ። ሕሊና ለሌለው፣ ለሚሸጥ ወይም ለሚያከራይ ዘወትር ክፍት ቦታ አለ። እነ እንቶኔ በዚህ የሕመም ዘርፍ ላይ በመሆናቸውሊታዘንላቸው እንጂ ሊታዘንባቸው አይገባም። ቀደም ሲል የተጠቀሰውን ጉብል አንድ ጊዜ በአንድ የቨርጂኒያ አዳራሽ ትልቅ ስብሰባ ላይ አይቼዋለሁ። እዚያ ስብሰባ ላይ ወደዘጠኝ መቶ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ። ይሁንና እስኪታወቅ ሳይሆን እስክንሰለቸው ድረስ የባጡንም የቆጡንም ሲናገር ቆይቶ “እዚህ ሥፍራ ኦሮሞና ሙስሊም ለምንአልተጋበዘም?” ይላል። መቸም “ከእናንተ መካከል ኦሮሞ የሆናችሁ ተነሱ! ሙስሊም የሆናችሁ ተነሱ!” አይባልም። ይኸ ደግሞ ከቅን አእምሮ የመነጨ ነው አይባልም።የሌሎቹንም “ዋልጌ ጭንቅላት” ባለዶላሩ ዋሐቢ፣ የሽብሩ ልጆች እነ…..በማናቸውም ሂሣብ ሊገዙአቸው አይፈልጉም አይባልም። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እስከተዋጉላቸው ድረስ።

አንዳንድ የዋሐን ወገኖቼ የእነዚህን በጥላቻ የተፀነሱ፣ በጥላቻ የተወለዱና የጥላቻን መርዝ በመካከላችን የሚዘሩ ሰዎችን ተጽእኖ እስከ መፍራት ደርሰዋል። ኦሮሞውኅብረተሰብ እንዳይቀበላቸው ነው? ያፍርባቸዋል። ከአገር እድር ያስወጣቸዋል። ስለዚህ በሶሻል ኔትወርኩ ረገድ ኅላፊነት የወሰዱ ሁሉ ለኦሮሞ ወገኖቻችን የመናገር ዕድል(በሰፊው) መክፈት አለባቸው። በአንድ በኩል ደግሞ ታሪክ የሚያቆሽሹትና ወደ ኋላ እየተመለከቱ የሚናገሩት እነዚህ ወገኖች ርስበርሳችን ስለጀግንነት፣ ስለታሪክ፣ ስለታላቋኢትዮጵያ ማንነትና ምንነት….እንድንነጋገር ዕድል እያስገኙልን ይመስለኛል።

   ጥቁሩ ሰው – ለጥቁር ሕዝቦች
Adwavictoryጀርመኖች በኦቶፎን ብዝማርክ፣ ጣልያኖች በጁሴፔ ጋሪባልዲ፣ ፈረንሳዮች በናፖሊዮን ቦናፓርቲ፣ በዣንዣክ ሩሶ፣ በዣን ደ አርህ፣ አሜሪካኖች በጆርጅ ዋሽንግተን፣ አብርሃም ሊንከን…..እንግሊዞች በዊልያም ዘኮንከረር፣ በዊንስተን ቸርችል፣..ይኰሩም ይኩራሩም ይሆናል። የእነዚህን ሰዎች ጀብዱ ስንሰማ፣ በትምህርት ቤቶች ዝናቸውን ስናወሳና ስናጠናቸው ስለኖርን የራሳችን ሰዎች እስኪመስሉን ድረስ በልባችን ጽላት ላይ ታትመዋል። ሰዎቹ በየዘመናቸው ለአገሮቻቸው ባበረከቱአቸው አስተዋጽዎችና የተለዩ አገልግሎቶች የየአገራቸው “አባቶች” እስከ መባል ደርሰዋል። በፖለቲካና በወታደራዊ መስክ ብቻ ሳይሆን እነዚህ አገሮች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም አያሌ አገሮች ለአለም ጸጋ በሆኑ ልጆቻቸው አማካይነት በኪነ ጥበባት፣ በሳይንስ፣ በሥነ ጥበባትና በኬንያ (ቴክኖሎጂ) ባርከውናል። ልጆቻቸውን ተጋርተናል።
እንደገና ጀርመኖች በሒትለር፣ ጣልያኖች በሙሶሊኒ፣ ካምቦድያውያን በፓልፓት፣ ኡጋንዳውያን በኢዲአሚን፣ወዘተ እጅግ እንደሚያዝኑና እንደሚሸማቀቁ ይሰማኛል። እኛም የዚች አገር ጐስቋሎች  ኢትዮጵያውያን በሃያ አንደኛው ምዕት ዓመት መለስ የሚሉት እኩይ ነፍስ ለኢትዮጵያ የዛሬው ትውልድ በመስጠታችን ጭብጥ ልናክል ነው። ሞተ ከተባለ ወዲህ እንኳ አገር እየሰጠ፣ አረብና ሕንድ እያነገሰብን፣ ምውት መንፈሱ እንዳሸበረን ነው። ሁላችንም የዓለም ዜጎች ይቺን የጋራ መሬት እኩል እንደምንባረክባት ሁሉ ጀግንነታቸው ያሞቀን የሃያኛው ክፍለ ዘመን ግዙፋን ባለታሪኮች ነበሩ። ጀኔራል ድዋይት አይዘንሐወርን፣ ጀኔራል ጆርጅ ፓተንን፣ ፊልድ ማርሻል ሞንትጐመሪን…እንደራሳችን እንጋራለን የሚል እምነት አለኝ። “እነዚህ ሰዎች ምነው ኢትዮጵያውያን ቢሆኑ ኑሮ” ብዬ በቁጭት አልናገርም። የአንዲት ምድር (ራችን) ልጆች በመሆናቸው ብቻ እንደራሳችን ጀግኖች- የሁላችንንም እምነት በተግባር ያዋሉ፣ የሁላችንንም ጦርነቶች ተዋግተው ያሸነፉ ስለሆኑ “የሁላችንም” እናደርጋቸዋለን። እንደ ምኒልክ ያሉ – እንደ ጐበና ያሉ- እንደ አሉላ ያሉ- እንደ አበበ አረጋይና በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖች አባቶች ያሉት አገር ልጆች በመሆናችን እኛም ለዓለም ባበረከትናቸው ጀግኖቻችን ኩራት ይሰማናል። በምኒልክ የተመራው የኢትዮጵያ ሠራዊት በአንዲት ጀንበር የአንድ አውሮፓ ኅይል ካንኮታኰተ በኋላ በማግሥቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ክሪስፒ መንግሥት (በኢጣክያ ሕዝብ እንደጐርፍ መውጣት ምክንያት) ከሥልጣን ከመወገዱም በላይ በናፖሊ ከተማ የነበረውን የንጉሡን (አምቤርቶ) አልጋ ወራሽ ሕዝቡ በትከሻው ተሸክሞ “ታላቁ ምኒልክና የአድዋ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን ለዘላለም ይኑሩ ብለህ ጩኽ” በማለት ቀኑን በሙሉ በዚህ መልክ ሲያንባርቅ እንዲውል አድርገውታል። በማግሥቱ የወጡ የኢጣልያ ጋዜጦች ኢጣሊያ ራስዋ እንደተማረከች አድርገው ጽፈዋል። ምኒልክ!
አንዳንድ የጦርነት ዘገባዎችን፣ መጻሕፍትንና ታሪኮችን ለተከታተሉ ጀግኖች የሠራዊት አዛዦች ድል ካደረጉ በኋላ “ጠላት ነው” በማለት አይንቁትም። ወይም በእጄ ገብቶአል ብለው አይበቀሉትም። እንዲያውም በ”ተቃራኒ መስክ” የተሰለፈውን በክብር ያስተናግዱታል። በጦር መሪነታቸው እጅግ የተደነቁና በመሠረቱ በተቃራኒ ዐውድ ተሰልፈው ታሪክ የሰሩ ጄኔራል መኰንኖችን ላስታውስ እወዳለሁ። በአሜሪካ የሲቪል ጦርነት የኮንፌደሬሽኑ ጦር አዛዥ ሮበርት ሊ በአሜሪካ ሕዝብ ዘንድ ከሜጀር ጄኔራል ጆርጅ ማክሊላን የበለጠ ይታወቃል። በየከተማው መንገዶች ተሰይመውለታል። የጦር ምሽጐች በስሙ ተጠርተዋል። ከስለጠነው ዓለም ሌላም ማስረጃ ለማምጣት ይቻላል።
የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ከሚያውቃቸው ታላላቅ ጄኔራሎች መካከል ሒትለር በሰሜን አፍሪካ በዋና አዛዥነት ያሰለፈው ፊልድ ማርሻል አርዊን ሮሜል (የበረሃው ተኩላ) በምዕራብም ሆነ በምሥራቅ- በአክሲስ ፓወርስም ሆነ በአላይድ ፎርስስ እጅግ የተደነቀ ነው። በመሠረቱ ለጀግና ሠራዊት ባላንጣው የተከበረ ነው። በሬሳው አይጫወትም። ወይም ወያኔዎች በኢትዮጵያ ሠራዊት ሬሳና የደከመ አካል ላይ ቆመው እንደ ፈነደቁትና እንደሸለሉት ሳይሆን የሰብአዊነት ክብርና መገመቻ ጠላትን እንደአግባቡ ማድነቅ መቻልም ነው። ለተፋላሚ ክብር መስጠትና እንክብካቤ ማድረግ ነው። እነዚህ ሰነፎች ገዥዎቻችን ምንኛ ደካሞች እንደሆኑ አያችሁት?
ከአገራችንምኮ ለዚህ ክርስቲያናዊ አርአያነትና የሰለጠነ ወታደራዊ ባሕል ምሳሌ አንቸገርም። አድዋ ላይ በአንድ ጀምበር በርከት ያሉ ጄኔራል መኰንኖችን ድባቅ የመታውና ያንኑ ያህል የማረከው እምዬ ምኒልክ በእጃቸው የገቡትን ምርኮኞች ማለፊያ ምግብ እየሰሩ (ፓስታ፣ ሞኮሮኒ ወዘተ) በደንብ ከመመገብ ባሻገር ራሳቸውና ደገኛይቱ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ እንደ ሐኪም ቁስል መጥረግ፣ ፋሻ ማሠርና የመሳሰሉትን የሕክምና አገልግሎቶች ጐንበስ በማለት ፈጽመዋል። ጦርነቱ እንዳለቀ ምሽት ላይ በየድንኳኑ እየተዘዋወሩ “ገደልን ብላችሁ እንዴት እንዲህ ያለ ፍከራና ሽለላ ታደርጋላችሁ?” በማለት ኅዘናቸውን እስከ መግለጥ ደረሰዋል። (አንቶኒ ሞክለር ኅይለስላሴስ ዋር በሚለው መጽሐፉ በመጀመሪያው እትም እንደ መግቢያ አድርጐ ገልጦታል።
በሌላው ታሪካቸው እንደ ተገለጠው አጤ ምኒልክ ከንጉስ ተክለሃይማኖት (ራስ አዳል ይባሉ ከነበሩት) ጋር እምባቦ ላይ ሲዋጉ የጐጃሙ ገዥ ቆስለው ሲማረኩ ራሳቸው ከመሬት ተቀምጠው ቆስሉን በጨውና በአልኮል እየጠረጉ እንዳስታመሙአቸው ይታወቃል። በኋላ ደግሞ አጤ ዮሐንስ ያለ የሌለ ጦራቸውን አስከትተው ጐጃምን ወርረው፣ ሥፍር ቁጥር የሌለውን ሕዝብ ዓይን በጋለ ብረት አቃጥለው፣ ሠራዊታቸው ቤት እየዘረፈ፣ በወንዱ  ፊት ሚስቱን እየደፈረና ጐተራ እያራገፈ በጠቅላላው ንጉሰ ነገሥቱ እያዩ ሲያቃጥሉ አጤ ምኒልክ “እባክዎ ጃንሆይ ከንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ጋር ተጋጨሁ ብለው ሕዝብዎን አይጨርሱት” በማለት እንደተማጸኑአቸው የተጻፈ ታሪክ ሞልቶአል። እንዲያም ቢሆን የትናንት የአገሪቱን መሪዎች ለመወንጀል አልሻም።
ወደ ሃምሳ ዓመት የሚገመት ሙያዬ ከብዙ ሰዎች ጋር አገናኝቶኛል። እንደ ደጃች ኅይለ ሥላሴ ጉግሳ ካሉ ከሐዲዎች- እንደ ራስ መስፍን ካሉ አርበኞች- እንደ ጋዜጠኛ (ከንቲባ) ደስታ ምትኬ ካሉ በየአድዋው ጦርነት ላይ ከዋሉ የታሪክ ምስክሮች፣ እንደ ፊታውራሪ ተክለሃዋርያት ካሉ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ አንስቶ አገሪቱን ከፊውዳል ሥርዓት ለመጠራረግና የፖለቲካውን ሥርዓት ግልብጥብጡን ለማውጣት ከደከሙ ምሁራንና መሪዎች ጋር ትከሻ ለትከሻ ባልተሻሽም አጠገባቸው ተቀምጨ ያልነበርሁበትን ዘመን ልኖረው ሞክሬአለሁ። የሁሉም የጋራ ምስክርነት (የጀግናውም የባንዳውም) ኢትዮጵያ እንደ ምኒልክ ያለ መሪ ታድላ አታውቅም። እግዚአብሔር ይመስገን፤ ጻድቁ ዮሐንስ በጐ አእምሮ የወለደው ነው።
አዎን የዚህ መጣጥፍ አጀማመሬ አውሮፓውያንና አሜሪካውያን (ሌሎችም ሕዝቦች) የሚኮሩባቸው መሪዎችና በመሰረቱም የሚያፍሩባቸው አምባገነኖችም ሊኖሩባቸው እንደሚችል ላመለክት ሞክሬአለሁ። እንዲያውም አገር በችግር ማጥ ውስጥ ስትገባ ልባቸውን፣ ጭንቅላታቸውንና እጃቸውን አስተባብረው ሕዝብን በአንድ ጐራ አሰልፈው ከታላቅ ውጤት ላይ ያደረሱት እንዲህ ያሉ መሪዎች የየአገሮቻቸው አባቶች እስከ መባል ደርሰዋል። ጆርጅ ዋሽንግተንን አላነሣሁምን? የመቶዎች ባሪያዎች ባለቤት ቢሆን እንኳ ሁሉም አሜሪካዊ የአገሪቱ አባት ይለዋል። በዚሁ ልክ የኢትዮጵያን ታሪክ የመረመሩ የውጭ አገር የታሪክ ስዎችና ኢትዮጵያውያን ምሁራን ሁሉ አጤ ምኒልክንና አሳዳጊ አባታቸው አጤ ቴዎድሮስን የኢትዮጵያ አባቶች ይሉአቸዋል። ለከፈሉት የሞት ዋጋ፣ ለተሸከሙት የኢትዮጵያ ግዙፍ ተራራ፣…ይኸ የሚበዛባቸው ክብር አይደለም። ሁለቱ ሰዎች (ባይሆን ጣይቱን እንጨምራለን) ይህን ክብር ካልተቀዳጁ ማን ሊቀዳጅ ነው? ጣይቱን እናታችን ብንል ምንኛ ደስ ባለኝ!
ያለፈው ወር የእምዬ ምኒልክ መቶኛ ሙት ዓመት ነበር። አሸናፊዎች ሁሉንም እንደ ፈለጋቸው በሚያደርጉበት፣ በብር በወርቁ በሚያዙበት፣ ታሪክ ድርሰት ሆኖ በማረሻ በሚጻፍበት፣ የአገር ዳር ድንበር ያለ ጠባቂ በሚቀርበት፣ ጀግኖች የወደቁለት አንድነት መጫወቻ በሆነበት፣ ዜጐች እየተነቀሉ ነጩ፣ ብጫው፣ ጠይሙ…የባዕድ አገር ነጋዴ የሚምነሸነሽበት መሬት ጥንቡን በጣለበት ዘመን ላይ፣ መንግስት ሌባ፣ ሌባም መንግሥት በሆነበት ወቅት-እንደ መገኘታችን ብዙ ብዙ -የለም፤ ሁሉም በጐ አገራዊ ባሕል ትርጉም ባጣበት ሰዓት በሕዝብ ዘንድ ያለው ሐቅ ሁሉ ተጠቂ መሆኑ አንድና ሁለት የለውም። እነሆ ከሃያ ሦስት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ታሪክ ተለውጦ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ታሪክ የቆመው ሕዝብና ተቃዋሚ ኅይሎች ከሐዲ ሲባሉ…ወርቁም ሚዛኑም እንዳልነበረ ሆኖአል። ስለዚህ በምኒልክና በጣይቱ ላይ የሚወርደውን የፕሮፓጋንዳ መዓት፣ የፈጠራ ድርሰትና ልብ ወለድ ድርሳን ስታስቡት ለመሆኑ ከወያኔ አምባ የተጠበቀው ሌላ ንግርት ምን ነበር? በግልጽ የኢትዮጵያን አንድነት ተቋቁመው ከዚህ ደረጃ ያደረሱት ግለሰቦች በረከት፣ ስብሐት ነጋ፣ ዐባይ ጸሐይና ግልገል ወያኔዎችና እንደ ወያኔ የማሰብ በሽታ ከሸመቱ ግለሰቦች ምን ይጠበቅ ነበር? የኢትዮጵያን አንድነት አባቶችና ጠባቂዎች እንዲያወድሱ ነበር? ቀደም ሲል እንዳልሁት ታሪካችንን በጽሞና እንድንመረምር ዕድል የሰጡን ይመስለኛልና በበጐነት እንጠቀምበት።
ቀደም ሲል ስማቸውን ያነሣኋቸውን ጋሪባልዲንና ቢዝማርክን ለምክንያት ነበር የጠቀስሁአቸው። ጋሪባልዲ ኢጣልያንን ለማዋሐድ፣ ቢዝማርክ ተበታትና የቆየችውን ጀርመንን አሰባስቦ አንድ አገር (ኔሽን) ለማድረግ ሲወጡና ሲወርዱ የነበሩበት ሰዓት (በዘመነ ጓድነት) አንድ ነው። አፍሪካዊው መሪ (ጥቁር ሰው) ምኒልክ በተመሣሣይ ጥሪ በታሪክ መድረክ ላይ የታየውም በዚሁ የታሪክ ወቅት ነው። በዚህ ታሪካዊ ወቅት ምን ተፈጠረ? በዘመናት ውስጥ ተሸርሽራና ተበጣጥሳ የቆየችውን ኢትዮጵያ ዳር ድንበር አንድ አደረጉ። ሰበሰቡአቸው። በእነዚህ ተግባራት ብቻ ዓለም ካደነቃቸው ከነጋሪባልዲ ጋር ታሪክን ሊሻሙ የሚገባቸው ምኒልክ ዛሬ በወያኔና አንዳንድ አጫፋሪዎች ምን እየተባሉ ነው? አንዱና ጥሩ ውሸት መፍጠር ያልቻሉት ፀረ አንድነቶች የጡት ቆረጣ ወንጀል ነው። ይኸ ከየት የመጣ ነው? ለመሆኑ ወንጀሉስ የት ነው የተፈጠረው? ትክክለኛም ሆነ አልሆነ መልስ የመስጠቱን ዕዳ የሚሸከሙት ወያኔና ሁሉም ፀረ አንድነት የሚያቀነቅንበት ዜማ የሚጫወቱት ናቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ሴቶችን ጡት ስለማስቆረጥ የተፈጠረው አጉል ነጥብ ከአማራው (ማለትም ከክርስቲያን) ባሕልና እምነት ጋር ጨርሶ የሚሄድ አይደለም። በአንጻሩ ለጋብቻና ለመሳሰለው ዕድሜና እጆቹ እርፍ ለመጨበጥ የደረሰ ኦሮሞ ገበሬ ሚስት ሊያገባ የሚችለው አማራ በመስለብ መሆኑን እንኳ ለመስማት ፈልጌ አላውቅም። በእውነቱ ግን ወንጀሉ በየዘመኑ ለሚፈጠር ኦሮሞ ሁሉ እንዲቆየው አልሻም። በዚሁ ዓይነት አጤ ዮሐንስ ወሎንና ጐጃምን “ፈጅተውታል፣ አቃጥለውታል” በሚል የዛሬና የወደፊቱ ጐጃሜና ወሎየ ሁሉ ትግሬንና አጤ ዮሐንስን እንዲጠላ አላደፋፍርም። በውነቱ ደግሞ ዘወትር የምናወድሰው ታሪካችን አላስፈላጊና አሳፋሪ ጓዝም አለው። ቀደም ሲል ያነሳናቸው የኢጣልያንና የጀርመን የዛሬ ትውልዶች የየራሳቸው አንካሳ ታሪክ አላቸው። እኛ ላይ ሲደርስ ነው ከተደረገውና ከተፈጸመው ሁሉ በላይ የታሪክ ድሪቶና ቡትቶ ያየነው።
 ኢትዮጵያዊነት አረጀ?
ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና የዚችን አገር ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብታት፣ ዜግነትንና እሴትን የሚጸየፍ አንድ ምስኪን ልጅ በአልጀዚራ ሲናገር ብዙ ኢትዮጵያውያን ሰምተውታል። የጋናው ኒክሩማህ፣ የኬንያው ኬኒያታ የኮትዲቮሩ ሑፌትቧኘ፣ የማላዊው ካሙዙባንዳ…በጆርጅ ፓድሞን መሪነት..ወደ አንድ የለንደን የስብሰባ አዳራሽ (በ1953 እ.አ.አ) የገቡበት ሁኔታ ትዝ ይለኛል። አዳራሹ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆአል። እነዚህ በኋላ የአፍሪካ ታላላቅ መሪዎች የሆኑ የዚያን ዘመን የነፃነት ታጋዮች አረንጓዴ፣ ብጫና ቀይ የሆነውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለቡ ወደ አዳራሹ ሲገቡ የነበረበትን የክብር ሰልፍ ሳስብ በቦታው ለመገኘት እንደ ታደለ ሰው ዛሬ የልቤ ኩራት ወደር ያጣል! የጃንሆይ አጤ ኅይለሥላሴን ምስል በኮታቸው ክሳድ ላይ ያደረጉት እነ ንክሩማህ ሁኔታ ወለል ብሎ ይታየኛል። አዳራሹ በአእምሮዬ ይመጣል። ኢትዮጵያዊነትና “ኢትዮጵያዊ ነኝ” የዓለም ጭቁን ሕዝቦችና በተለይም የጥቁር ሕዝብ ኩራት እንደሆነ እነ ጃዋር ሰምተው ያውቃሉ? ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ “ኢትዮጵያ” ምን ትርጉም እንደምትሰጥ ለመሆኑ እነዚህ ይቺን አገር ካላፈራረስን እንሞታለን የሚሉ ሰዎች በመጠኑስ ቢሆን ያውቁ ኖሮአልን? “ኢትዮጵያዊነት” ከተራ ስያሜና ከአንድ ተራ አገር መጠሪያ በላይ መሆኑን ያውቁ ኖሮአልን?  ለእነዚህ ሕዝቦች ዞሮ መግቢያና መመኪያ …መንፈሳዊ ቤታቸውና ምስለ-ገነት የመሆንዋን ሐቅ ምን ያህል ሰምተዋል? የማርከስ ጋርቪን ፍልስፍና ያውቁታልን? ዛሬ ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር (ያህዌ ኤሎሒም) ለአዳምና ለሔዋን የፈጠረላቸው ገነት በአንደኛዋ የኢትዮጵያ ክፍል የመሆንዋ ግልጽነት አማራውን፣ ኦሮሞውን፣ ትግሬውን፣ ከምባታውን፣ ሐድያውን…ለሁሉም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት ተጨማሪ ኩራት በሆነ ነበር። (ከላይ የነካካኋቸውን ነጥቦች በይበልጥ ለማወቅ ማርከስ ገርቪንና ዱቢድ ሜሬዲትን ያነብቡአል።) በነገራችን ላይ ማርከስ ገርቪና ራስ መኮንን ይባል የነበረው ጃሜይካዊ ጓደናው በጃንሆይ ቅሬታ ያደረባቸው እነሱ ካሰናዱአቸው 3ሺ ዓለም አቀፍ ተጋዳዮች ይልቅ በእንግሊዝ ጦር በመጠቀማቸው መሆኑ ይነገራል።
jawar
በኢትዮጵያዊነት ማፈር እንደ አልጀዚራው ጉብል ባሉ የሐቅ ማይማን እየተነገረ ነው። ያ ጉብል – ጃዋር ደግሞ በሌላ ጊዜ በመቅለስለስ መልክ “ እኔ በአባቴ ኦሮሞና ሙስሊም፣ በእናቴ አማራና ክርስቲያን ነኝ።” ሲል አድምጨዋለሁ። የልጅነት ተማሪዬ ሌንጮ ለታ የደረሰበትን አጉል አጋጣሚ ያስታውሰኛል። የኦነጉ መሪ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ልብ ሲዘዋወር በነበረባቸው ወራት በጣም የተከበሩ አባቶች ወደ ነበሩበት ወደ ጅባትና ሜጫ ሄዶ ነበር። ያ አካባቢ እጅግ አስተዋይ የሆኑት ፊታውራሪ አባዶዮ ሠርገኛ ጤፍ አስመጥተው “ከዚህ መካከል ነጩንና ጥቁሩን ለይልኝ” ብለው ጥላቻንና ጠላትነትን ያወገሁበት አካባቢ ነው። ታዲያ ሌንጮ “አማሮች ያገኙን እንደእነዚህ እንስሳት ከብቶች አድርገውን ነው” ብሎ ሲጀምር “ልጆቻችንና ወንድሞቻችን..አንተ የምትላቸው አማሮች ናቸው። እኛም አማሮች፣ አማሮችም ኦሮሞዎች ናቸው።” ብለው በማስጠንቀቂያ ሸኝተውታል። የሮይተርን ቀጥታ ምስክርነት ለመጥራት እችላለሁ። ታዲያ ጃዋር እንደ ነገረን፣ ኦሮሞም ነው። አማራም ነው። ሙስሊምም ነው ክርስቲያንም ነው። ኢትዮጵያዊ ካልተባለ ምን ሊሆን ፈለገ? ቅጥ አምባሩ የጠፋበት አይደለም ትላላችሁ?
እነዚህን ሰዎች ሳስብ ኢሳይያስና መለስን አስባለሁ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሚለውን ድሪቶ የለጠፈባቸው ኢሳይያስ አፈወርቂ ነው። ወይም ኦነግን ጠፍጥፎ የሰራው እሱ ሲሆን “ኦሮሚያ” የሚለውን በታሪክም በተረትም የማይታወቅ የሕልም ዓለም ክልል ስያሜ ደግሞ በዳቦ ስምነት ያሸከማቸው አስመሮም ለገሰ የተባለው የእኛው ዩኒቨርሲቲ ውጤት ነው። በነገራችን ላይ የአስመሮም ለገሰ የገዳሥርዓት መጽሐፍ እስኪወጣ ድረስ ኦሮሚያ የሚባል ቃል አላውቅም ነበር። እንደ ነገሩ ደግሞ መጽሐፍ አገላባጭ ሰው ነኝ፥ እላለሁ።
የኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ-ይልቁንም መንግሥታዊው መድረክና አጀንዳ የፀረ አንድነቱ አቋም ማራገቢያ እንደ መሆኑ አገሪቱን ወደ ማፍረስ እየረሸጋገሩም ይመስላል። ለሱዳን፣ ለሳዑዲ፣ ለሕንድ፣ ለቻይና፣ ለፓኪስታንና ዶላር ላለው ሁሉ ተከፋፍሎ የተረፈውን ማለቴ ነው። ከዚህ መሠረትነት በመነሳት የሺህ ዘመናት ሥልጣኔ የነበረው የኦሮሚያ በአማሮች ተወርሮ “ኢትዮጵያ” የተፈጠረችው ከአንድ መቶ ዓመታት ወዲህ በዚያ መንግስት ፍራሽ ላይ ነው እየተባልን ነው። የዜጐች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች ዝምታ ለተረትና ለቧልት መፈጠር፣ ለልብ ወለድ ታሪክ መፈብረክ አስተዋጽዖ አድርጐአል። ኦሮሞው ኅብረተሰብ (በብዙዎች አካባቢዎች- ለምሳሌ በወሎ ወዘተ ጋላ ማለት ስድብ ሳይሆን የተከበረና ትርጉሙም ትልቅ ማለት ነው) የዚህ አገር ታሪክ ተጋሪ፣ ፈጣሪና በግንባር ቀደምም እንደ አገሪቱ ዳር ድንበር ተከላካይና መከታ ሆኖ የቆየ ነው። አንዲት የምኒልክ ስንኝ በማስታወሻነት ከእናንተ ጋር ባቆይስ? እነሆ!
“ጐበና ጐበና ጐበና የኔ
የጦር ንጉሥ አንተ ያገር ንጉሥ እኔ” አዳዲሱ ድርሳናቸው ከዚህ ሐቅ ጋር የሚጋጭባቸው ደራስያን “አዳዲስ ታሪክ የመጻፍን የአሸናፊዎች አንበሶችን ሚና” ይዘዋል። እኛም ማፈሪያዎች እነሱም ማፈሪያዎች ነን። ይህን እንቀበል!
   ስለ ጥቁሩ ሰው
 ወደ ሌላ ከመሻገሬ በፊት ከምኒልክ የተለያዩ ጠቅላይ ገዢዎች መካከል ዋነኞቹ (ሦስቱ) ስለ አገርና ስለ ምኒልክ የነበራቸውን ቁምነገሮች ለማንሳት እወድዳለሁ፤
“ምኒልክ ትንሽዋን ወላይታ ወስዶ ትልቂቱ ኢትዮጵያን ሰጠኝ። በእውነት ምኒልክ የእኔም የኢትዮጵያም አባት ነው። – ካዎ ጦና ጋጋ – የመላው ወላይታ ርእሰ መሳፍንት ልጅ እያሱ ቀድሞ ኩምሳ ሞረዳ ይባሉ የነበሩትን የደጃች ገብረእግዚአብሔር ሞረዳን ልጅ ለማግባት ጥያቄ ሲያቀርቡላቸው – “ ምነው! ምነው ጌታዬ! እኔና እርስዎ ኮ ወንድማማች ነን። እኔ በመንፈስ ከአጤ ምኒልክ ተወልጃለሁ (አበልጅ) ስለዚህ እርስዎና እኔ ወንድማማች ነን። የእኔን ልጅ ሊያገቡ አይችሉም። ( አንዳንድ የወለጋ አረጋውያን በዚህ ላይ ሲጨምሩ ሰምቻለሁ። ተጨማሪው ቃል “ሲሆን ባል ሲመጣለት አባት ሆነው የሚለመኑ፣ ቆመው የሚድሩ መሆን ይገባዎታል”)
የደጃዝማች አባ ጅፋር አባ ጆብር (የከፋው ገዥ) ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ዘወትር ይሹሙኝ እያለ ደጅ ይጠናቸው ነበር ይባላል። እንዲያውም አንድ ቀን እጅግ አምርሮ “ለመሆኑ እነዚህ ለሹመት ያበቁአቸው ሰዎች ከእኔ ይቀርቡዎታልን? ለእኔ አንድ የሹመት ቦታ አጥተው ነው?” ይላቸዋል።
  አባ ጅፋር በተለመደው ስል አነጋገራቸው “የሕዝብ አደራን በተመለከተ ምኒልክ እጄን ይዞ ነው የነገረኝ። ያ ባይሆን ኖሮ እኔ እዚህ አልገኝም ነበር። ምኒልክ እጁን ይዞ “ሹመት የሕዝብ ነው- ሹመት ሺህ ሞት ነው” ብሎናል። ወንድሜ! ወደ ሥልጣን የገቡት እንዴት በነፃነት እንውጣ እያሉ ይጨነቃሉ። ይህንን የማያውቁ ደግሞ እየዘለሉ መግባት ይመኛሉ። እንድታውቅልኝ የምመኘው ከዓለም መንግስታት እኩል ያደረገን ምኒልክ አደራ ከባድ መሆኑን ነው።”
በነገራችን ላይ አጤ ምኒልክ ዘወትር ምሳና ራት ሲበሉ አብረዋቸው ማዕድ የሚቀርቡ (ሁል ጊዜ) ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ፣ ደጃዝማች ወልደሚካኤል ጉዲሳ (የአጤ ኅይለሥላሴ አያት)፣ ፊታውራሪ ቱሉ፣ አፈ ንጉሥ በዳኔና ብላታ አቲከም ነበሩ።
 በአንድ ነጥብ እንለያይ። አጤ ምኒልክ በአንድነት አሰባሳቢነትና ተበታትና የቆየች አገራቸውን ወደ አንድ ኅብረት በማምጣት ረገድ የየአካባቢው መሪዎችን ትብብር በግድን በውድም ተቀዳጅተዋል። ስለዚህም በወለጋ ደጃዝማች  ገብረ እግዚአብሔር፣ በከፋ ደጃዝማች አባጅፋር፣ በወላይታ ካዎ ጦና ጋጋ አካባቢያቸውን ይዘው፣ የውስጥ አስተዳደራቸውን አደራጅተው ሕዝቡን ይመሩ ነበር። ይሁንና በአርሲ በኩል ለጊዜው ሕዝብ የሚቀበለው ጐላ ያለ ተወላጅ በመታጣቱ አጐታቸው ራስ ዳርጌ ተመደቡ። ራስ ዳርጌ ደግሞ እጅግ ሃይማኖተኛ፣ ሕዝቡን በርኅራኄ የሚመለከቱ የአባትነት ተቀባይነት የነበራቸው ስለሆኑ አንዳች ዓይነት ግፍ ለመፈጸም ባሕርያቸው የማይፈቅድላቸው ሰው ነበሩ። እንግዲህ “አጤ ምኒልክ ጡት አስቆረጡ” የሚባለው አነጋገር አርሲ ውስጥ መሆኑ ነው። ማንም እንደሚገምተው ጡት የመቁረጥ የአረመኔ ተግባር የአማራ ባሕርይም የክርስቲያን ሕዝብም ተግባር አይደለም። በአንጻሩ እነ አባ ባሕርይና ሌሎችም ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የታሪክ ጸሐፊዎችም ለአካለ መጠን የደረሰ አንድ ኦሮሞ ጐልማሳ ከማግባቱ በፊት ብልት እስከ መስለብ፣ ጡት እስከ መቁረጥ የደረሰ “ጀብድ” መቁጠር መቻል አለበት፥ ይሉናል። ይኸም የትናንት ታሪክ ነው።
ለማንኛውም ተረት እየፈጠሩ ታሪክ፣ ድርሳን እየጻፉ በሕዝብ ዴሞክራሲ ስም ወደ ኋላ እየሄዱ የአገር ጊዜና ዕድሜ ከማባከን ይልቅ ጥላቻን ቀብረን፣ ፍቅርንና አንድነትን አንግበን ሰላም የተጠማችውን አገር ወደ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ማሸጋገር አይበጅም ኖሮአል? ዓለም እየታዘበን አይደለምን? ምን ይሁን ነው የምንለው?
 በሕብረተሰብ ትክክለኛ አመራር ባሕርይ መንጸባረቅ ያለበት አንድ ክስተት “የነገው ከዛሬው” የተሻለ፣ ብሩሕ፣ አሰባሳቢ፣ እኩልነት የዳበረበት፣ ነፃነት የከበረበት መሆን አለበት። ያለፈው ጓዝና ጉዝጓዝ እንደ ጸሐይ ማብራት የሚገባውን “ነገ”ን በጨለማማ ገጽታው ሊያደበዝዘው አይገባም። ከትናንትና ከዛሬው ይልቅ “በነገው” ተስፋና አለኝታ መጣል ይገባናል። እንዲያም ቢባል ከትናንቱ ብሔራዊ ውርስና ቅርስ -ከትናንቱ የእድገትና የአንድነት መሠረት መካከል- ምኑም ማናምኑም በዛሬና በነገው ቀጣይ ታሪካችን ውስጥ ሥፍራ ሊኖረው አይገባም አይባልም። ታሪካችንም ሆነ የነገው “ጸጋችን” ምንም ዓይነት ተቀባይነት አይኖረውም አይባል። አያቱንና አባቱን የማያውቅ ትውልድ በፈንታው ለነገው ትውልድ አባትነትና አያትነት አይሰማውም። አዎን የምንኰራባቸው አባቶችና እናቶች አያቶችና ቅም አያቶች ያሉንን ያህል አሳፋሪዎች፣ ፈሪዎችና ደካሞች፣ መልቲዎችና ሰነፎች የሆኑ ዜጐችም ነበሩብን። አሉብንም።
እነዚህን ማወቁ-ታሪካችንን ጠንቅቀን መረዳቱ፣ ጀግንነትን ለማደስና ከቶውንም ያንን አዳብረን የዓለም “ጨው” እስከምንባል ድረስ ለመጓዝ ዓለማቀፋዊነት መሠረት ይሆነናል። አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን፣ ጥቁር ዓለምንም ብቻ ሳይሆን- የዓለምን ነፃነት ወዳጅና አክባሪ ሕዝቦች ሁሉ የሚያደንቁት “ምኒልክ” ከዚች አገር የጐን አጥንት የተከፈለ ነው። አንድን አገር ታላቅና ገናና፣ የተከበረችና የታፈረች የሚያደርጉአት ሕዝብዋ ሲሆኑ ለዚያ ሁሉ ታሪካዊ ሥፍራ ተቀዳጅነት የሚያስፈልጉ መሪዎች ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ በመሪነት የተነሡትን ልዩ ልዩ ነገሥታትና የዛሬዎችንም አምላክ ለቅጣት የሰጠንን ጨምሮ- ለኢትዮጵያ አንዳች ክብር ያመጣውን ዋነኛ ሰው ለማግኘት ብዙ ማሰስ አስፈላጊ አይደለም። የዶክተር ሥርግው ሀብለ ሥላሴን “አጤ ምኒልክ” ማንበብ የአሰሳው ፍጻሜ ሊሆን ይችላል። ደራሲው በዚህ መጽሐፍ ከሳባ ንግስት አንስቶ እስከ ቀዳማዊ ኅይለሥላሴ ድረስ ይዘልቃል። ለዚህ አገር ታዋቂነት- ይልቁንም ዳር ድንበርዋንና ነፃነትዋን በማስከበር ረገድ ድንቅ አስተዋጽዖ ያደረጉ፣ በመንፈሳዊና ቁሳዊ ሥልጣኔ ታስደመሙ መሪዎችን ታሪክ ለላንቲካ ያቀርባል። ከሙሉው- ከዚያ ሁሉ ጀግናም ሆነ ሰነፍ መሪ መሐል አንድ ሰው ነጥሮ ይወጣል። በፀረ አንድነት ኅይልነት ጸንቶ ያለው ወያኔ ይንጨርጨር እንጂ- ወያኔና ሻዕቢያ የፈጠሩአቸው ትንንሽ ጩዋሒዎች ይንጨርጨሩ እንጂ ሰውዬው ወጣቱ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን “ጥቁሩ ሰው” የሚለው ነው።
ይቺ አገር በነፃነት የተፀነሱ፣ በነፃነት ያደጉና ድሀም ቢሆኑ በነፃነት የሚራመዱ ዜጐች እናት ናት። ያቺ አገርና ሕዝብዋ ከምን ጊዜውም በላይ ያልተጠናቀቀ ብሔራዊ ዕዳ፣ ለትውልዶች የሚጠቅም ቅርስ ለማቆየት በጥድፊያ ላይ ያሉ ወገኖች እናት ናት። እዚህ መሬት ማሕፀን ውስጥ የተከበሩ ጀግኖች ተኝተዋል። በዚች ዛሬ የታሪክ መጫወቻ በሆነች አገር ማኅፀን ውስጥ ታላላቅ ጀብዱ ፈፅመው ያንቀላፉ፣ በልዩ ልዩ ሙያና በፍልስፍናም ጭምር ልቀው ያላቁን ታላላቅ ነፍሳት የእናት አገራቸው እቅፍ ሞቆአቸው ተኝተዋል። ዓምደ ጽዮን፣ ያሬድ፣ በካፋ፣ ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ፣ ምኒልክ፣ ሀብተ ጊዮርጊስ፣ አሉላ፣ አብዲሳ አጋ፣ በላይ ዘለቀ፣…የተኙባትና እረፍት ላይ ስላሉም መሬቲቱ በጥንቃቄ መረገጥ ያለባት ናት። እነሱን ያህል ለመሥራት ያልቻልን ሰነፎች እንደ መሆናችን ቆምብለን ራሳችንን መርገምም የሚገባን ነን። ይኽ ሁሉ የወያኔ ልዑካን ጫጫታ አያሳፍርም? ይኸ ድምፅ ከየት መጣ? ወሮበሎች አያሰኝንምን? ስድ አደግ ማለት- የእምነት ድህነት ማለት- የሕሊና ባዶነት ማለት- የአቋም ምስኪንነት ማለት ምን ማለት ነው? ይኸው በአደባባይ እየታየ ነው።
(በዚህ ጉዳይ ላይ እመለስበታለሁ) 

Health: የሳይነስ ቁስል –መንስኤው፣ የበሽታው ምልክቶችና መፍትሄው

$
0
0

ሳይነስ ቁስል ከፊት ጀርባ የሚገኙት በአየር የተሞሉት ቀዳዳዎች (sinuses) መቁሰል (inflammation) ነው፡፡ ይኽ ቁስል በአብዛኛው በራሱ ጊዜ የሚድን ሲሆን በአፍንጫ እና በአይን ዙሪያ ህመምን ያስከትላል፡፡ ከፊትህ ጀርባ በአፍንጫ ቀዳዳ ዙሪያ አራት ጥንድ የሆኑ ቀዳዳዎች(sinuse) ይገኛሉ፡፡

sinus infection
እነዚህ ቀዳዳዎች ንፍጥ (mucus) በሚያመርቱ ህዋሳት የተሸፈኑ ሲሆን ይህም ንፍጥ በትንንሽ ፀጉሮች ተገፍቶ ወደአፍንጫ ይገባል፡፡እነዚህ ቀዳዳዎች ከአፍንጫ ጋር የሚገናኙበት ትንንሽ በሮች አላቸው፡፡ እነዚህም አየር፣ ፈሳሽ እና ንፍጥ እንደፈለገው እንዲሄድ ይረዳሉ፡፡ ቀዳዳዎቹ ውስጥ የሚመረተው ንፍጥ በጤናማ ጊዜ ቀዳዳዎቹ ውስጥ አይጠራቀምም፡፡ ነገር ግን ቀዳዳዎቹ በተለያዩ ምክንያቶች ከተዘጉ አሊያም የትንንሽ ፀጉሮቹ እንቅስቃሴ ከተገታ ፈሳሹ በመጠራቀም የሳይነስ በሽታ ምልክቶች እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ጉንፋን ሲይዝህ ቀዳዳዎቹን የሚሸፈነው የላይኛው ክፍል በማበጥ ከአፍንጫ ጋር የሚያገናኛቸውን በሮች ይደፍናቸዋል፡፡ስለዚህም ቀዳዳው ውስጥ የሚመረተው ንፍጥና ፈሳሽ እዛው ውስጥ ይጠራቀማል፡፡ይኼ የተጠራቀመ ፈሳሽ ለጀርሞች ምቹ መራቢያ ቦታን ይፈጥራል፡፡ ሁለት አይነት የሳይነስ ቁስል አይነቶች ሲኖሩ እነሱንም በሚኖራቸው የጊዜ ቆይታ እንከፍላቸዋለን፡፡ ከሁለት ሳምንት በላይ የሚቆየው አይነት ሳይነስ መቁሰል በአብዛኛው በቀላል ህክምና የሚድን ሲሆን ሌላኛው አይነት ደግሞ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ እና በተለያዩ መድሃኒቶች በቀላሉ የማይድን ሲሆን አስቸጋሪ በሽታ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ከሌሎች በተለየ በዚህ በሽታ በተደጋጋሚ ይጠቃሉ፡፡ በተፈጥሮ ለብዙ ነገሮች አለርጂክ የመሆን ባህሪ ካላቸው የሳይነስ ቁስል በተደጋጋሚ ያጠቃቸዋል፡፡ እንደአስም በሽታ ሁሉ ለአበባ ብናኝ፣ ለአዋራ እና ለመሳሰሉት ነገሮች አለርጂክ መሆን በነዚህ ሰዎች ላይ የሳይነስ መቁሰልን ሲያስከትል ከሱ በተጨማሪ ደግሞ በአለርጂ ምከንያት በቀዳዳዎቹ ውስጥ የሚጠራቀመው ፈሳሽ ውስጥ ጀርሞች በመራባት በሽታውን የበለጠ ያጎሉታል፡፡ ስለዚህም በተደጋጋሚ በዚህ በሽታ ይጠቃሉ፡፡

የሳይነስ መንስኤዎች ምንድን ናቸው?

በሽታው የሚከሰተው ሳይነስ ቀዳዳዎች ሲደፈኑ አሊያም ትንንሾቹ ፀጉሮች እንቅስቃሴን የሚያግድ ነገር ሲከሰት ነው፡፡ ኢንፌክሽን ወይም ኢንፌክሽን ያልሆኑ መንስኤዎች ሲኖሩት በአብዛኛው የላይኛው የመተንፈሻ አካላት በሽታን ተከትሎ ይከሰታል፡፡

ኢንፌክሽን ካልሆኑት መንስኤዎች መካከል አለርጂ፣ የማቁሰል ብቃት ላላቸው ኬሚካሎች ተጋላጭ መሆን፣ አፍንጫ ላይ የሚበቅሉ የተለያዩ እንግዳ ነገሮች፣ ካንሰር ሊያመጡት ይችላሉ፡፡ እንደ አስም ሁሉ ለተለያዩ ነገሮች አለርጂ መሆንን ተከትሎ የሚመጣው አይነት የሳይነስ ቁስል ወቅትን ተከትሎ የመባባስ አዝማሚያ አለው፡፡ በአስም በሽታ የሚጠቁ ሰዎች ይኼኛው በሽታም ያጠቃቸዋል፡፡

በኢንፌክሽን የሚመጣው በባክቴሪያ፣ በቫይረስ አሊያም በፈንገስ ምክንያት ሊከሰት ይችላል፡፡ በቫይረስ የሚመጣው በሽታ በጣም በብዛት የሚታየው እና በራሱ የመዳን ባህሪ ያለው ነው፡፡ ከጥርስ ኢንፌክሽን ተነሰተው ወደቀዳዳዎቹ በመግባት የሳይነስ ቁስል የሚያመጡ ባክቴሪያዎች አሉ፡፡ ፈንገስ ደግሞ መጀመሪያውኑ የበሽታ የመከላከል አቅሙ በተዳከመ ሰው ላይ ለምሳሌ ለካንሰር በሽታ መድሃኒት (ኬሞቴራፒ) ላይ ያለ ሰው ላይ ይከሰታል፡፡ ይህም ከቀላል ሳይነስ ይልቅ ለህይወት የሚያሰጋ ኢንፌክሽን ያመጣል፡፡

የሳይነስ ቁስል ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የሳይነስ መቁሰል በብዛት ከላይኛው የመተንፈሻ አካላቶች በሽታ ጋር ተያይዞ ስለሚከሰት ምልክቶቹን ለብቻው ለይቶ ለማወቅ ይከብዳል፡፡ ጉንፋን የያዘው ሰው የሳይነስ ቀዳዳዎች ቁስለትም አብሮት መከሰቱ አይቀሬ ነው፡፡

የሳይነስ በሽታ አፍንጫ በፈሳሽ መታፈን፣ የፊት ህመም፣ እራስ ምታት ይኖረዋል፡፡ የሚኖረው ህመም ጎንበስ ሲባል ወይም በጀርባ ሲተኛ የመባስ ባህሪ አለው፡፡ ወፍራም፣ ቢጫ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ ካለ የባክቴሪያ መንስኤነትን ያመላክታል፣ ነገር ግን በቫይረስ በሚመጣው ጉንፋን መጀመሪያ አካባቢም የዚህ አይነት የአፍንጫ ፈሳሽ ሊያስከትል ስለሚችል ለባክቴሪያ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ሌሎች ምልክቶች ለምሳሌ ማስነጠስ፣ ሳል እና ትኩሳትን የመሳሰሉ ምልክቶችም ሊኖሩት ይችላል፡፡ የጥርስ ህመም እና የአፍ ሽታም በባክቴሪያ ከሚመጣው ሳይነስ ጋር ተያያዥነት አላቸው፡፡ አይን እንቅስቃሴን ተከትሎ የሚኖር ህመም ይኖራቸዋል፡፡ የማሽተት አቅምህም ከበፊቱ ሊቀንስ አሊያም እስከነጭራሹ ሊጠፋ ይችላል፡፡ በአለርጂ የሚመጣው በሽታ ደግሞ ወቅትን እየተከተለ ይነሳብሃል፡፡ በክረምት እና በፀደይ ከሌላው ጊዜ በተለየ ሊያስቸግርህም ይችላል፡፡

የሳይነስ በሽታ ከያዘኝ በኋላ ምን ላድርግ ?

በሽታው በብዛት በራሱ የሚድን ሲሆን የተዘጋውን ሳይነስን እና አፍንጫን የሚያገናኘውን በር መክፈት ጥሩ የህክምናው መንገድ ነው፡፡ ውሃ አሙቆ እንፋሎቱን መታጠን ውስጥ የተጠራቀመውን ንፍጥ ስለሚያቀጥን ፈሳሹን በቀላሉ ማስወጣት ትችላለህ፡፡ ንፁህ (ተፈልቶ የቀዘዘ ) ውሃ ቀጭን አፍ ባለው እቃ አድርጎ የአፍንጫን የውስጥ ክፍል ማጠብ ጥሩ መንገድም ነው፡፡ ብዙ ፈሳሽ መጠጣትም እንመከራለን፡፡ ከሳምንት ለበለጠ ጊዜ የሚቆይ ከሆነ አሊያም በጣም ሀይለኛ ህመም ካለው ወደሆስፒታል ሄዶ መታየቱ ተመራጭ ነው፡፡ በጀርሞች የሚመጣው በቀላል መድሃኒቶች ስለሚድን ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካሉብሽ ወደሆስፒታል ሄደሽ መመርመር ጠቃሚ ነው፡፡ ከሱ በተጨማሪም በአለርጂ ምክንያት የሚመጣው ቁስለት ከሆነ በሽታውን ከሚያባብስብሽ ነገር እራስሽን መጠበቅ ጠቃሚ ነው፡፡

የሳይነስ ቁስለት አንዴ ከያዘሽ በኋላ ህመሙን በተለያዩ መንገዶች መቀነስም ትችያለሽ፡፡ የሙቀት እና ቅዝቅዜ መለዋወጥ ህመሙን ስለሚያብሰው በተቻለሽ አቅም በጣም ሞቃት እና ቀዝቃዛ ቦታዎች ላይ አትሁኚ፡፡

ከጉንፋን ጋር ተያያይዞ በሳይነስ በሽታ በተደጋጋሚ የምትጠቂ ከሆነ ደግሞ በምትተኚበት ጊዜ ጭንቅላትሽን ከፍ የሚያደርግ ትራስ ማድረግ የሳይነስ በሮች እንዳይዘጉ በማድረግ ሊረዳሽ ይችላል፡፡

የህብር ሬድዮ 4ተኛ ዓመት በታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ በላስቬጋስ ይከበራል

$
0
0

የህብር ሬድዮ 4ተኛ ዓመቱን በሕዝባዊ ውይይት የተለያዩ ምሁራንን ጋብዞ በላስ ቬጋስ ከተማ ፌብሩዋሪ 26 ቀን 2014 በከተማዋ በጎልድ ኮስት ካዚኖ ያከብራል።

በዕለቱ እውቁ የኢኮኖሚስት ባለሙያ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በጥናት ላይ የተደገፈ በልማት ስም ግርዶሽ በሚል ርዕስ ገለጻ የሚያደርጉ ሲሆን ኦባማ ኬር ሬዲዮው በዚህ ዓመት በስፋት ሲዘግብባቸው ከነበሩ ጉዳዮች አንዱ በመሆኑ ሁለተኛ ዙር ምዝገባው ከሚጠናቀቅበት ማርች 31/2014 በፊት በዚህ በዓል ላይ ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን እና አቶ ተካ ከለለን ከአትላንታ ገለጻ እንዲሰጡ ጋብዟል። በዕለቱ ለውይይት የሚቀርቡትን ጉዳዮች በተመለከተ በዶ/ር አክሎግ ቢራራና በዶ/ር ኤፍሬም መኮንን በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ ጽሑፎች እና በኔቫዳ ግዛት የኦባማ ኬርን በተመለከተ የተዘጋጀውን መግለጫ ለተሳታፊዎች መዘጋጀቱን የበዓሉ አስተባባሪዎች ለዘሐበሻ ገልጸዋል።

ህብር ሬዲዮ በተለያዩ አገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ወቅታዊ መረጃዎችን ከማቅረብ አልፎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ እንግዶችን በመጋበዝ በቀጥታ በሬዲዮ፣ በኢንተርኔት እና በስልክ በተጨማሪ ሰፊ ተነባቢነት ባለው በዘሐበሻ ድህረ ገጽ አማካኝነት በየሳምንቱ ይደመጣል።

የህብር ሬዲዮ 4ተኛ ዓመትን በተመለከተ በጊዜው ተጨማሪ ዘገባ እናቀርባለን።
Hiber Radio poster

የሃገራችን ወጣት በዘመነ ወያኔ “በጨረፍታ”

$
0
0

በናትናኤል ካብቲመር (ኦስሎ ኖርዌይ) የካቲት 4 2006

ሁላችንም እንደምናውቀው ከግዜ ወደ ግዜ አሰቃቂነቱ እየጎላ የመጣው የሃገራችን ወጣት የስደት ጉዳይና ለዚህም ዋነኛ መነሾ ስለሆነው በሃገር ውስጥ የሚኖረው የኢትዮጲያ ወጣት ማህበረሰብ እጅግ የከበደ የኑሮ ሁኔታ በጨረፍታ አንዳንድ ነገር ለማለት አሰብኩ።

(ናትናኤል ካፕትይመር)

(ናትናኤል ካፕትይመር)


ለምንድነው ደሃ የሆንነው? ለምንስ ነው ደሃ ሆነን የምንቀጥለው? ለምንስ ነው ወጣቱ በሃገሩ ሰርቶ የመኖር ተስፋው መንምኖ ለህይወት አስጊ የሆነውን ስደት እየመረጠ ያለው? ተብለው ለሚነሱት ጥያቄዎች በርካታ መልሶች ሊነሱ ይችላሉ ነገር ግን ከሚነሱት መልሶች ሁላችንንም የሚያስማማውና ሚዛን የሚደፋው “የዜጎችን መብት አክብሮ የሚያስከብር እንዲሁም መሰረታዊነት ያለው የሃገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ሚዛናዊና ወጥ የሆን የኢኮኖሚ ስርዓት የሚገነባ ሁነኛ መንግስት ማጣታችን ነው” የሚለው ነው። በርካታ የሃገራችን ምሁራንም ሆነ በሞያው የበቃ ልምድ ያላቸው ግለሰቦች በሃገራቸው የኢኮኖሚ ስርዓት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ሃሳቦችን የሚያመነጩበት መድረክ እንዳይኖር የሚያደርግ ሌት ተቀን የስልጣን ዘመኑን ለማስረዘም ሲል ብቻ የኔ የሚላቸውን ግለሰቦች ከስልጣን ስልጣን እያቀያየረ የሚሾም ጎጠኛ ስርዓት እንደ እርግማን ተጭኖብናል። በዛው ፓርላማ ተብዬ እንኳን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ተቃራኒ ሃሳብ እንዳይስተናገድበት ከላይ እስከታች ለሆነው ላልሆነው እጅ ሲያወጡና ሲያጨበጭቡ በሚውሉ የህዝብ ተወካዮች ነን ባይ አስገራሚ ግለሰቦች ሞልተውታል።

Cry Ethiopia1 የወያኔ መንግስት እንደምንም ተብሎ በተገኘችው ቀዳዳ አንፃራዊ የሆን አማራጭ ሃሳብ ሲቀርብለት የሃሳብ አመንጪውን አካል ዘርና ማንነት በክፉ እየመነዘረ ሰርቶ የሚያሰራና በመጠኑም ቢሆን ሊያስተማምን የሚችል የኢኮኖሚ ስርዓት ተፈጥሮ ወጣቱ ተረጋግቶ ሃገሩ ላይ የሚኖርበትን እድል እያጨለመ የመብት ጥያቄዎችን እያፈነ ወጣቱን ለአስከፊው ስደት እየዳረገው ይገኛል።

ከዚህ ሁሉ እጅግ የሚያመው ደግሞ ለህይወት አስጊ መሆኑና ምንም አይነት የህይወት ዋስትና እንደሌለበት መዓት ግዜ የሚለፈፍለት የአረብ ሃገራት ስደት ያ ሁሉ ስቃይና ህይወትን የሚያሳጣ መከራ በተሰደዱ ዜጎች ላይ በተጨባጭ እየታየ አሁንም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሲጎርፉ ይታያል። ወጣቱም ሃገሩ ላይ ከመኖር ይልቅ ከሞት የማይሻል የስደት አማራጭ ያስደፈረው ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ህዝብን አስተዳድራለሁ ብሎ በስልጣን የተደላደለው የወያኔ መንግስት ነው።

ያደጉ ሃገሮች መንግስታት አብዛኛውን ግዜያቸውን የሚያጠፉት የሃገራቸውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት ፣ ለሰራተኛው የሚከፈለው የደሞዝ ክፍያና ዝቅተኛ የክፍያ እርከን ላለው የኑሮ ሁኔታ የሚያስኖርና በቂ ስለመሆኑ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል አስተማማኝ የሆን የጤና ሽፋን መቅረቡን ለማረጋገጥ ነው። እንደው ዘለን እነሱን እንሁን ለማለት አይቃጣኝም ነገር ግን የመፍትሄ ሁሉ መጀመሪያ ችግሩን መለየት ስለሆነ ችግሩ አገዛዙ የፈጠረብን መላ ቅጡ የጠፋ የኢኮኖሚ ስርዓት መሆኑን ለመጠቆም ነው። ከዚሁ ጋር አያይዤ አንባቢያንን አንድ ነገር እንዲያስተውሉ የምጠይቀው የሃገራችን አነስተኛው የደሞዝ መጠን ስንት መሆኑን ፣ መጠኑን የሚያውቅ ካለም ከወቅቱ የኑሮ ሁኔታጋ እንዴት እንደሚጣጣም እንዲያሰላስሉ ነው።

የህወሃት መንግስት ባለስልጣናት ግን ስር ስለሰደደው የስራ አጥነትና ተያይዞ ስለሚመጣው የህይወት መመሰቃቀል ሲጠየቁ “ወጣቱ ስራ ፈጣሪ መሆን አለበት” የሚል መሰረት አልባ ለንግግር የቀለለ ለመተግበር ግን እጅግ የከበድ ብሂል እየተቀባበሉ ያስተጋባሉ።
ከወራት በፊት አቶ ቴውድሮስ አድሃኖም በአንድ የህክምና ዶክተሮች ምረቃ በዓል ላይ ተገኝተው ለተመራቂዎቹ ሃገራቸውን በፍፁም ጥለው እንዳይሄዱ ሲደሰኩሩ ነበር። እውነታው ሁሉም ግድ ሆኖበት እንጂ ማን ሃገሩን ጥሎ መሄድ ይፈልጋል ነው። በዘመነ ወያኔ እየተንሰራፋ ያለው በትዕቢት የተሞላ የመብት ረገጣ ፣ መረን የለቀቀ የኑሮ ልዩነት ፣ ልጓም ያጣው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት እንዲሁም የስርአቱን ተጠቃሚዎችን እንጂ የማህበረሰቡን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበው የኢኮኖሚ ስርዓት የሃገራችንን ወጣቶች የወደፊት የኑሮ ተስፋና እድል ምን ያህል ጥያቄ ውስጥ እንዳስገባው ለዚህም የተቀመጠ መሬት የወረደ መፍትሄ እንደሌለ የምናውቀው ገሃድ የወጣ ሃቅ ነው።

ethiopian young የተገኘው ስራ ተሰርቶ እንኳን ኑሮን ለማሸነፍ እንደ አማራጭ የሚታየው የቁጠባ ባህልም ባልተረጋጋውና ጠንካራ መሰረት በሌለው የኢኮኖሚ ስርዓት ምክንያት በሚፈጠረው መላ በሌለው የምንዛሬና የዋጋ ከመጠን ያለፈ ግሽበት ሳቢያ ከጨዋታ ውጪ ሆኗል። ማህበረሰቡ ለአመታት ቆሎ ቆርጥሞ የቆጠበው ገንዘብ ዋጋ እያጣበት ኑሮውን ለእለት ብቻ ካረገው ሰነባብቷል። ወጣቱም ከዛችው ከአነስተኛ ደሞዙ ቆጥቦ የወደፊት ኑሮውን እንዲሁም ቤተሰብ እንዳይመሰርት ይኸው ችግር እንቅፋት ሆኖበታል።

የስርዓቱ አመራሮችና ባለስልጣናትም የደሃውን ህዝብ ገንዘብ በአግባቡ ስራ ላይ ከማዋል ይልቅ ለግል ጥቅማቸው ወደ ውጪ ሃገራት ማሸሸት ስራዬ ብለው ይዘውታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ነፍሰ ጡር ሚስቶቻቸውን ሳይቀር ምዕራባዊ ሃገራት ላይ እየወሰዱ ማስወለድ መጀመራቸው በግልፅ የሚታይ በሃገር ላይ ተስፋ የማጣት አሳፋሪ ስነ ምግባር የተለመደ ሆኗል። ሃገር እንመራለን እያሉ ነገር ግን ወጣቱ ሃገራዊ ስሜቱ እንዲዳብርና ሃገሩ ላይ ተስፋ እንዲኖረው ምሳሌ የመሆንን ሃላፊነት አሽቀንጥረው በመጣል በሃገር የመኩራትን ስሜት እንደሁዋላቀርነት ሲቆጥሩት ማየት እጅግ ያሳዝናል።
መልካም አስተዳደር ከሚፈጥራቸው መልካም እንድምታዎች አንዱ ይኸው በሃገር ላይ ተስፋ ማሳደርን ከሁሉም ሃገርን ማስቀደምን ነው። መልካም አስተዳደር ሰርቶ ያሰራል እንዲሁም የዜጋው ጉዳት ይቆረቁረዋል። ነገር ግን የሃገራችን ጉዳይ የተገላቢጦሽ ነው “መልካም አስተዳደር መስርተናል” የሚሉት ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ጭምር አካላቸው እንጂ መንፈሳቸው ሃገራቸው ላይ የለም። የወያኔ ስርዓት ለአመታት እያምታታና የተለያዩ ምክንያቶች እየደረደረ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እንዲሁም በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የሃገራችን ወጣቶች ስደትና ተያያዥ እንግልቶች የተድበሰበሰ ሰበብ ሲሰጥ ቆይቷል። አሁን ግን ወጣቱ የችግሩ ዋና መንስኤ የመንግስት ተብየው ብልሹ አስተዳደርና መሆኑን ተረድቶ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት መታገል አለበት።

አሁንም ቢሆን የወያኔ ስርዓት ካልተወገደ ህዝባችን መቸገሩን ወጣቱም ውድ ሃገሩን እየተወ መሰደዱን አያቋርጥም። የወያኔን ስርአት መወገድ ለችግራችን ሁሉ የመፍትሄ ጅማሮ ቁልፍ እርምጃ ነው።

የአ.አ ፍትህ ቢሮ የሙስሊሙን ትግል አዳክመውልኛል ያላቸውን የመንግስት ሃላፊዎችን እና የህገ ወጡ መጅሊስ አባላትን በሽልማት አንበሸበሸ

$
0
0

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዛሬ የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ (ቪድዮዎች ይዘናል)
ከአብዱ ዳውድ ኡስማን

መንግስት በኢስላም ሀይማኖት ላይ ጠልቃ እንደገባ የህወሃት መስራች አቦይ ስብሃት ለመጀመሪያ ጊዜ አምነዋል ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ አማካኝነት የተዘጋጀው ይሄው የሽልማት ስነስርዐት ዋነኛ አላማው የሙስሊሙ ትግልን ለማዳከም ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል ያላቸውን የመንግስት አካላትና የህገ ወጡ መጅሊስ አባላትን ለማነቃቃት እንደሆነ ታውቋል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀጣይ ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር ተያይዞ ለሚኖረው እንቅስቃሴ አባላቱ በሞራል እንዲሰሩ ለማድረግ ታስቦ እንደሆነ በስብሰባው የነበሩ ምንጮች ገልፀዋል ፡፡

ከትላት በስቲያ እሁድ የካቲት 2\2006 ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል በተካሄደው በዚህ የሽልማት ስነስርዐት ላይ የህወሃት አባት የሚባሉት አቦይ ስብሃትን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ፀጋዬ ሀይለማሪያም ፣ የህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዚደንት ዶክተር አህመድ አብዱረህማን ፣ የፌዴራሉ ህገ ወጥ መጅሊስ ምክትል ፕሬዚደንት ታጋይ(ሸይክ ከድር ) ፣ የአንዋር መስጂድ ኢማም ሀጂ ጡሃ ሃሩን ፣ የ10 ሩም ክፍለ ከተማ ሃላፊዎች ፣ የወረዳና የክፍለ ከተሞች መጅሊስ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ፡፡

ከሽልማቱ ቀደም ብሎ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ መስተዳድሩ የ42 መስጂዶችን ካርታ ለአዲስ አበባ ህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዚደንት ዶክተር አህመድ እንዳስረከቡ ገልፀዋል ፡፡ በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫም የመጅሊሱ አባላትም ሆኑ ሌሎች አካላት ከዚህ ቀደም ወደ 54 መስጂዶች ካርታ እንደሰጠን በዛሬው እለት ደግሞ የ42 መስጂዶችን ካርታ እንደሰጠን ለሙስሊሙ በማስተጋባት የምርጫ ስራ እንዲሰራ ጠይቀዋል ፡፡

በእለቱ የሙስሊሙን ትግልና ኢስላምን አዳክመዋል የተባሉ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ፣ እንዲሁም የህገ ወጡ መጅሊስ አባላት ከአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ተሸላሚዎቹ በየተራ ንግግር አድርገዋል ፡፡ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ በጥረታቸው እንዲገታ አድርገዋል ተብለው ሽልማቱ ከተበረከተላቸው መካከል አቦይ ስብሃት ነጋ ፣ ዶክተር አህመድ አብዱረህማን ፣ ሸህ ጡሃ ሃሩን ፣ የ10ሩም ክፍለ ከተማ ህግና ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች እና የ10ሩም ክፍለ ከተሞች የመጅሊስ ሊቀመንበሮች እንደሆነ ታውቋል ፡፡

ከሽልማቱ በኋላ ንግግር ያደረጉት አቦይ ስብሃት መንግስት በሙስሊሙ ጉዳይ ጠልቃ እንደገባ የሚያረጋግጠውን ንግግራቸውን አድርገዋል ፡፡ አቦይ ስብሃት በአዳራሹ ለተገኘው ሰው ባደረጉት ንግግር “ … ማንኛውም ነገር ከፍተኛ ጥረት ከተደረገበት ስኬት ይኖረዋል ፡፡ የሙስሊሙ ትግል ሲጀመር በጣም ተደናግሮን ነበር ፡፡ በኋላ ብዙ አስበንበት ስናበቃ ለምን መንግስትን የሚደግፍ መጅሊስ አናቋቁምም አልንና ጥረት ጀመርን ፡፡ እኔ እራሴ ሄጄ ግዴላችሁም ከየክፍለ ከተማው ሙስሊም ሆነው መንግስትን የሚደግፉ ሁለት ወይም ሶስት ሰዎችን ብቻ ፈልጉልኝ አልኩ …፡፡ የጀመርነው ከቦሌ ክፍለ ከተማ ነው ፡፡ ወደ አምስት ሰዎችን አገኘንና እነሱን አደራጀን ፡፡ በኋላ ሌሎችም ክፍለ ከተሞች የቦሌን ተሞክሮ እንዲተገብሩ አደረግን ፡፡ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ጥቂት ሙስሊሞችን አደራጁ ፡፡ ከዚህ በኋላ ነገሩ ሁሉ የተቃና ሆነ ፡፡ እኛም በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተወሰኑ ሰዎች መደራጀቱን ስናውቅ ጉዳዩን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮና ክፍለ ከተሞች እንዲረከቡንና በበላይነት እንዲቆጣጠሩት አደረግን ፡፡ እንዲህ እያለ የሄደው ጥረት አሁን አክራሪዎችን ለማቆም የሚያስችል ጉልበት እንድናገኝ ረድቶናል … ” ብለዋል ፡፡

(የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ)

(የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ)


ይህ የአቶ ስብሃት ነጋ ንግግር መንግስት በሙስሊሙ ጉዳይ ጠልቃ አልገባሁም እያለ ከሚያስተባብለው ጋር የሚጋጭ እንደሆነ ተገልፇል ፡፡ በበርካታ ጉዳዮች ንግግር ያደረጉት አቦይ ስብሃት ኢስላምን የሚያጥላላ ንግግርም አድርገዋል ፡፡ “ ቅድም የፌዴራሉ መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢው ሸህ ከድር እንዳለው የዱሮው እስልምና ሌላ ነው ፡፡ እኔ ከድርን በፊት ጀምሮ ትግራይ ውስጥ አውቀዋለሁ ፡፡ ምርጥ የህወሃት ታጋይ ነበር ፡፡ አብሮን ታግሏል ፡፡ አሁን ደግሞ ሙስሊሙን እያገለገለ ነው ፡፡ እስልምና እነዚህ የታሰሩት ሰዎች እንደሚሉት አይመስለኝም ፡፡ እስልምና እነዚህ ሰዎች እንደሚያሳዩት ዓይነት ዕምነት ከሆነ እንደ ዕምነት አያስፈልግም ፡፡ ፈፅሞ ሰዎቹ ለሀገር አይሆኑም ” ብለዋል ፡፡ በዚህ ንግግራቸው በቦታው የነበሩ ሙስሊሞችም ጭብጨባ ለግሰዋቸዋል ፡፡
የፌዴራሉ ህገ ወጥ መጅሊስ ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ሸህ ከድርም በጫካ ከነ አቦይ ስብሃት ጋር ስላሳለፉት የትግል ህይወት እና በልጅነታቸው ስለቀሩት ቁርዐን አጠር ያለ ንግግር አድርገዋል ፡፡

ሌላኛው ተሸላሚ የሆነው የአዲስ አበባ ህገ ወጡ መጅሊስ ፕሬዚደንት ዶክተር አህመድ ሲናገርም “ መስጂዶቻችንን ሁሉ ተረክበናል ፡፡ መስጂዶች የማይሆን ዳዕዋ ማድረጊና የተቃውሞ መፈንጫ እንዳይሆኑ የሁሉም መስጂዶች ኢማም እንዲቆጣጠሩ ስልጠና ሰጥተናቸዋል ፡፡ አቶ ድሪባ ኩማም ዛሬ ለ42 መስጂድ ካርታዎን እውቅና እንደሰጡልን አረጋግጠዋል ፡፡ ከዚህ በኋላ ልማታችንን ማፋጠን ነው ፡፡ በቀጣይ ከመንግስታችን ጎን ሆነን እንሰራለን ” ብለዋል ፡፡
ለአቦይ ስብሃት ነጋ እና ዶክተር አህመድ አብዱረህማን ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን የአንዋር መስጂድ ኢማም ሃጂ ጡሃ ሃሩን ላፕቶፕ ፣ የ10ሩም ክፍለ ከተማ ፍትህ ቢሮ ሃላፊዎች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው ዘመናዊ ሞባይል እንደተሸለሙ ታውቋል ፡፡ ሌሎቹም እንዲሁ በተዋረድ ሽልማቱ እንደተበረከተላቸው ምንጮች ገልፀዋል ፡፡

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ሃላፊው አቶ ፀጋዬ ሀይለማሪያም ተሸላሚዎቹ ሙሉ ለሙሉ ያልቆመውን የሙስሊሙን ትግል ለማዳፈን ጠንክረው እንዲሰሩ ፣ እንዲሁም በቀጣይ ምርጫውን አስመልክቶ ከመንግስት ጎን ሆነው እንዲሰሩ የሚያሳስብ ንግግር ካደረጉ በኋላ ተሰብሳቢዎቹ ወደተዘጋጀላቸው ምሳ እንዲሄዱ አብስረው የሽልማቱ ስነ ስርዐት እንደተጠናቀቀ ምንጮች ጨምረው ገልፀዋል ፡፡

አላህ በዳዬችን ያዋርዳቸው !!

ባለ532 ብር ደመወዝተኛው የሕወሓት ታጋይ ከ10 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት ማግበስበሱ ተሰማ

$
0
0

(ኢሳት ዜና) የደህንነት ሃላፊ ከነበሩት ከአቶ ወልደስላሴ ወልደ ሚካኤል ጋር በግብረ-አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዮች ከደሞዛቸው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ሃብት አግበሰው መገኘታቸው ታውቋል።

birr4123111በተለያዩ አለመግባባቶች የተነሳ እየተመሰረቱ ያሉ ክሶች የህወሃት ተጋዮች በህገወጥ መንገድ የሰበሰቡትን የሃብት መጠን ለማወቅ እየረዳ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን ከአቶ ወልደስላሴ ጋር በግብረ አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዩ የአቶ ወልደስላሴ ወንድም አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ የመከላከያ ሚኒስቴርን ሲለቁ በመጨረሻ ይከፈላቸው የነበረው ወርሃዊ ደሞዝ 532 ብር ብቻ እንደነበር አመልክቷል ፡፡ ይሁንና፣ ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ባደረገው ማጣራት ግለሰቡ በተለያዩ ባንኮች በስማቸው 5 ሚሊዮን ብር ከማስቀመጣቸውም በተጨማሪ፣ አዲስ አበባ ቤቴል ሆስፒታል አካባቢ በ74 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታ እያካሄዱ ፣ በአፋር ክልል ደግሞ ከ1 ሚሊዮን 400 መቶ ሽ ብር በላይ በሆነ ወጪ የእርሻ ኢንቨስትምንት እያከናወኑ መሆናቸው እንዲሁም በስማቸው 2 ሚሊዮን 700 ሺ ብር ግምት ያላቸው 2 ሎደር መኪኖች መገኘታቸውን ገልጽዋል።

የአቶ ወልደስላሴ እህት የሆኑት ወ/ሮ ትርሃስ ደግሞ የ8ኛ ክፍል ተማሪና ምንም ስራ ያልበራቸው ሲሆን፣ በወንድሞቻቸው ድጋፍ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛ አንድ ስካቫተር፣መኪና እንዲሁም በአዲስ አበባ በየካና ቦሌ ክፍለ ከተሞች፣ በለገጣፎ፣ መቀሌና አክሱም 3 ሺ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስማቸው መገኘቱ ተመልክታል ፣እንዲሁም በተለያዩ ባንኮችም 8 ሚሊዮን ብር ተቀማጭ ማድረጋቸውን አንድ ተጨማሪ ዘመናዊ መኪና በስማቸው ተመዝግቦ መገኘቱን ጸረ ሙስና ኮሚሽን በምርመራ አረጋግጧል።

ዋናው ባለስልጣን አቶ ወልደስላሴ ደግሞ ስራ ሲጀምሩ ደሞዛቸው 1600 ብር የነበረ እና በእድገት እስከ 6000 ሺ ብር ሲከፈላቸው የቆየ ቢሆንም ያካባቱት ሀብት ግን ፈጽሞ ከደሞዛቸው ጋር የማይመጣጠን ነው ተብሏል። ባለ 4 ፎቅ ህንጻ ባለቤት የሆኑት አቶ ወልደስላሴ በ1 አመት ከ2 ወራት ቤቱን አከራይተው 790 ሺ ብር ገቢ አግኝተዋል።

አቃቢ ህግ ያቀረበውን ክስ የእስረኞች ጠበቆች፣ አዲስ የተጨመረ ክስ ነው በማለት አቤቱታ አቅርበዋል።

አቶ ወልደስላሴ ከወ/ሮ አዜብ ጋር በነበራቸው መቀራረብ ከፍተኛ ሃብት ማፍራታቸውን ፤ አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በሁዋላ ግን የእርሳቸው ዋነኛ ተቀናቃኝ የሆኑት የደህንነቱ ዋና አዛዥ አቶ ጌታቸው አሰፋ ግለሰቡን በሙስና ከሰው እንዳሳሰሩዋቸው አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ገልጸው ሲዘግቡ ቆይተዋል።
ህወሃቶች እርስ በርስ በሚያደርጉት ሽኩቻ እየተካሰሱ ፍርድ ቤት መቅረባቸው የካበቱትን ሃብት ለማወቅ እየረዳ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያልተመረመረና በፍርድ ቤት ቀርቦ ያልታወቀ ከዚህም የባሰ የሙስና ታሪክ እንደሚኖር መገመት ይቻላል ሲል አስተያየቱን አስፍሯል።

ምንጭ፡ ኢሳት ቲቪ


አስገራሚው የሳውዲው “ኮራጅ ”አባት ምክር እና የኢትዮጵያ ሰርከስ መስራች በሳውዲው ስደት

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

አስገራሚው የሳውዲው “ኮራጅ ” አባት ምክር

ethiopian athelete

ነገሩ እንዲህ ነው …ከ20 ዓመት በፊት ሳውዲው ወጣት ራሱን ለሁለተኛ ደረጃ ፈተና ከማዘጋጀት ይልቅ በረቀቀ መንገድ ለፈተናው መልስ የሚሆነውን ማጭበርበሪያ የመልስ ወረቀት አዘጋጅቶ ለፈተና ይቀርባል። ፈተናውን በረቀቀ መንገድ አጭበረብሮ ሰርቶታልና ፈተናውን በተገቢ ውጤት አልፎ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ለማለፍ በቃ ! ከዚያም በታዋቂው ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ተከታትሎ ይመረቃል። ይህ ሁሉ አልፎ ስራ ይዞ እና ጎጆ ቀልሶ ለወግ ለማዕረግ በቃ ! ከጎጆም አልፎ የሰመረው ህይወቱ የልጆች አባት እስከ መሆን ታደለ !

በያዝነው ሳምንት የድሮው ተማሪና የዛሬው አባወራ ጆሮውን ያልተለመደና የማያውቀው ህመም ያሰቃየው ገባ ። ወደ ሃኪም ቤት ጎራ በማለት ምርመራ ሲያደርግ ለህምሙ ዋና ምክንያት በጀሮው ውስጥ ቁራጭ ወረቀት እንደሆነ የሚያስረዳው አስገራሚው ውጤት ተነገረው … አረጋዊው አባት በወጣትነት እድሜው ተግቶ በማጥናት ለፈተና ቀርቦ ማለፍ ሲገባው አስነዋሪ የማጭበርበር ድርጊት መፈጸሙን እያስታወሰ አልተደሰተም ፣ አዘነ እንጅ ! ዛሬ ለማጭበርበሩ የተጠቀመበትን ወረቀት በጀሮው እንዴት ሊያስገባው እንደቻለ ማመን ቢያዳግትም ከ20 አመታት በፊት ለኩረጃ እና ለማጭበርብር የተጠቀመበት ወረቀት በቀዶ ጥገና ከጀሮው እንዲወጣ መደረጉ አስገራሚውን ዜና እየተቀባበሉ እየዘገቡ ካሉት የአረብ መገናኛ ብዙሃን ለመረዳት ችያለሁ … !

ከሁሉም የሚያስገርም የሚያስደስተው በሰራው ስራ የሚያፍር እንጅ የማይኮራው አባት ልጆቹንና ወጣቶችን ሲመክር “ልጆቸ ሆይ ፈተና ለማለፍ አታጭበርብሩ! ” ማለቱ ተጠቅሷል ። የትናንቱ ተማሪ የዛሬው አባወራ ሳውዲው አባት በሰራው ስራ ተጸጽቶ ቀሪውን ለመምከር ወደ አደባባይ መውጣቱ ቢያስደስተኝ በዝንቅ መረጃየ ስር መረጃውን ላካፍላችሁ ፈቀድኩ !

ሳውዲውን አባት መልካም ምክር ካነሳሁ አይቀር ሰሞነኛ የማለዳ ወጌ እንግዳ ለማድረግ ስለፈቀድኩት አንድ ከ20 አመት በፊት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባንድ ወቅት አንቱ የተባለ ስም ስለነበረው ብርቱ ወንድም ላጫውታችሁ … አብደላ አህመድ ኦመር ይባላል ። ቀዳሚው የኢትዮጵያን ሰርከስ መስራች ነው ። በስራው ቻይናን ጨምሮ በርካታ ሃገራትን ጎብኝቷል … ብርቱ ስፖርተኛ ከመሆን ባለፈ አንድን ሙያ ልያዝ ብሎ ከተነሳ በፍጥነት ክህሎትን የማዳበር ልዩ ተፈጥሮ ያለው ወንድም እንደሆነ ሰምቻለሁ ! ዛሬ በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ነገር ቢኖር ብዙሃን ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ሰርከስ መስራች ማን እንደሆነና የት እንዳለ የሚያውቁ አይመስለኝም ! … ብርቱው የቀድሞው ስፖርተኛ እና የሰርከሱ መስራች አብደላ ግን ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ትዳር መስርቶ እና ልጆች ወላልዶ በስደት ህይዎትን በመግፋት ላይ ነው ።

አብደላን ሳላውቀው… ላውቀው!

መልከ መልካምና ደልዳላ ተክለ ቁመና ካለው ወንድም ጋር ለአመታት ልጆቸን በማስተምርበት በጅዳ የኢትዮጵያውያን አለም አቀፍ ትምህርት ቤት እንተያያለን ፣ ግን አንተዋወቅም ። በአንድ ወቅት ከአንድ ወዳጀ ጋር የትምህርት መለቀቂያ ሰአት ደርሶ ልጆቻችን ስንጠባበቅ አብደላ ሰላምታ አቅርቦልን አለፈ … አብደላን አንድ ወዳጀ ያውቀው ነበርና እንዲህ አለኝ … ” ለመሆኑ ይህን ሰው ማን እንደሆነ ታውቀዋለህ? ” ሲል ጠየቀኝ አረ አላውቀውም ስል መለስኩለት … ” አየህ ሳውዲ ያልያዘችው ፣ ያላቀፈችው ሃበሻ አይነት የለም፣ አንተ ደግሞ የሩቅ የሩቁን ፣ በበርሃ የምታገኘው ዘፋኝና ግፉዕ ተምር ለቃሚ ግመል ጠባቂ እህቶችን እንጅ እንዲህ በቅርብ ያለውን አየታይህም ” ሲል የመሰለውን አስተያየት ሲሰነዝር እንደ መቀለድ እያለ በፈገግታ ተሞልቶ ነበር እና እኔም እንደመሳቅ አልኩ ! ወዳጀ ወጉን ቀጠለ …

abdela ” አንደላን በትንሹ ከአስራ አምስት አመት በላይ አውቀዋለሁ። ስፖርተኛ ፣ አስማተኛ ፣ የስነ ጽሁፍ ክህሎትን የተካነ በሁሉም የሙያ መስክ የምታገኘው ሰው ነው። ዛሬ እንዲህ አንገቱን ደፍቶ ፣ ሰውነቱ ገዝፎ ስታየው የዋዛ አይምሰልህ (ፈገግ ብሎ) ፣ ከበርካታ አመታት በፊት ታዋቂው የአካል እንቅስቃሴ አሰልጣኝ ግርማ ቸሩ ለአመታት በአሰልጣኝነት ይሰራባቸው ከነበሩ በወቅቱ ታዋቂ ቱጃር በነበሩት የሸህ አልዙማን ስራ ተሰናብቶ ሳውዲን ሲለቅ የተተካው ፈርጣማው ጎልማሳ አብደላ ነበር ። ከዚያም የባለጸጎቹን ቤተሰቦች በአካል እንቅስቃሴ አሰልጣኝነት እና በልዩ ጥበቃ ለአመታት በመስራት ያልዞረበት ሃገር የለም ። በአዕምሮው በሳል ፣ በአካል ፈርጣማ ስፖርተኛ ነው ። አየህ ነቢዩ በሳውዲ ስደት የታቀፈው ግፉአን እህቶችና ወንድሞች ብቻ አይደሉም። እንዲህ አይነት ባለሙያም ሳውዲ ውስጥ ይኖራል። ታሪኩን ለመናገር ፈቃደኛ ከሆነ ለቀረው ትውልድ አስተማሪ ነውና አንድ ቀን አስተዋውቅህና እንዲያጫውትህ አደርጋለሁ! ” አለኝ ። … አብደላን ሊያገናኘኝ ከአንድ አመት በፊት እንዲህ ቃል የገባልኝ ቅን አሳቢ ወንድም ግን ዛሬ ከአካባቢው የለም … ኑሮው ቢከብደው ቤተሰቦቹን ይዞ እና ጥሪቱን አጠረቃቅሞ የአቅሙን ያህል ለመስራት ሃገር ቤት ገብቷል … ካንድም ሁለት ሶስት ጊዜ በፊስ ቡኩ መስመር ብንገናኝም ሃገር ገብቶ የሚይዝ የሚጨብጠው እንዳጣ መረጃ የሚያቀብለኝን ወንድም” አብደላን አገናኘኝ?” ብየ ማስቸገሩ ከብዶኝ መክረሙ እውነት ነው! መቸም ዘንድሮ መንገድና ፊስ ቡክ የማያገናኘው የለም ፣ የኢትዮጵያውን ሰርከስ መስራች በቀጭኑ የስልክ መስመር በሌላ ጉዳይ አግኝቸው ስናወጋ ማንነቱን ሲያጫውተኝ ማመን አልቻልኩም ። ፎቶዎችን ፣ ሰነዶችን በመረጃ ማስረጃነት ሲያጋራኝ ግን የማይታመነውን አጋጣሚ ለማመን ተገደድኩ ! ከወንድም አብደላ ጋር ልንገናኝ ቀጠሮ ይዘናል ። … በቀይ ባህር ዳርቻዎች ከቤተሰቦቻችን ጋር ተገናኝተን ፣ ልጆቻችን ሲጨዋወቱ ነፋሻውን የባህር አየር እየማግን የኢትዮጵያ ሰርከስ መስራቹን የአብደላን ዠንጉርጉር ህይወት እኔ እየጠየቅኩ እሱ በትዝታ እየነጎደ እስኪያወራኝ ቸኩያለሁ …
መልካም ቀን
ነቢዩ ሲራክ / የካቲት 2006 ዓም

የጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ መልዕክት ከዝዋይ ማረሚያ ቤት፡ ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ!

$
0
0

በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት

webshet taye
‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡

ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡

በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

ሁኔታው በዚህ አያበቃም፡፡ ምንም እንኳን የመጠየቂያ ሰዓቱ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆን ከቤተሰቦቻችን ጋር ገና መነጋገር ስንጀምር ‹‹በቃ… ቶሎ ጨርሱ›› የሚባልባቸው ጊዜዎች ብዙ ናቸው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የእስር ቤት ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማለትም ለሳሙና፣ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለሻይ ለቡና፣ ለውስጥ አልባሳት፣ ለውኃ ማከሚያ/ውኃ አጋር/ ወዘተ፤ ገንዘብ የሚያስፈልገን ቢሆንም እና እንደሚያስፈልጉ ቢታወቅም ጉዳዩ ለይቶለት የማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መበቀል ሆኗልና ለአንድ ወር ከአንድ መቶ ብር በላይ መጠቀም እንዳንችል የተከለከልን የመሆኑ አሳፋሪ ሐቅ ነው፡፡ ይህ እየተፈፀመ ያለው ደግሞ ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለመግለጽ በሚከብድ ሁኔታ ሰብኣዊ ክብራችንን የማዋረድ ሙከራዎች እየተፈፀሙ ነው፡፡

በአገራችን ላይ እኔ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የጨረስኩት ዝዋይ በመሆኑ ብዙ ወዳጅ ዘመዶቼ በእዚህ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ለአካባቢው ነዋሪዎች በሳምንት እንዲጠይቁን የተፈቀደላቸው አንድ ቀን /ረቡዕ/ ብቻ ሲሆን ‹‹የት ነው የምታውቁት? እንዴት አወቃችሁት? ምንድን ነው የሚያመላልሳችሁ?›› በሚሉትና በሌሎችም ጥያቄዎች ተደናግጠው መምጣቱን እርግፍ አድርገው ትተውታል፡፡

ሀገሩ ሞቃታማ ነውና በዚያ ላይ በእያንዳንዱ ቤት እስከ 150 ሰው ይታሰርበታል፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ እስረኛው የቱንም ያህል ፅዳቱን ለመጠበቅ ቢሞክርም የተባዩ መርመስመስ የእነ ትኋን እንዲህ መራባት፤ ለማሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ገላን ሲቆፍሩ ማደር ነው፡፡ ሊናገሩት ይከብዳል፣ አንባቢንም ቅር ያሰኛል፤ ግን ይህ የፊልም ትረካ ሳይሆን በእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ላይ ሆን ተብሎ እየተፈፀመ ያለ ደባ ነው፡፡ […] ግን የባሰ አታምጣ ማለት ነው!

ግን የባሰ ነገር አለ፡፡ አፈር ቅጠል የማይል ምግብ ይቀርብናል፡፡ ‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ› ከፍተኛ የውኃ እጥረት /ዝዋይ ሀይቅ አናት ላይ ተቀምጠን/ አለ፡፡ የእስር እስር እንዲሉ ጄኔራል መኮንኖቹን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አባሪዎቻቸውና ሌሎች ሌሎች የተወሰንን እስረኞች የምንገኘው በልዩ ቅጣት ጭለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ እንደምንም ለመቋቋም ጥረት ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ አዲሱ ስልት ግን መዘዙ በጣም አደገኛ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ እያንዳንዱ ሃይማኖት ያለው፣ ፈርሐ እግዚአብሔር ያለው፣ እያንዳንዱ የመሠረታዊ ሰብኣዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር የሚያሳስበው እያንዳንዱ ሰው የሆነ ሰው ሁሉ ሊያውቀው ይገባል ስንል ድምፃችንን እናሰማለን፤ በሕክምና ንፍገት ወደሞት እየተገፋን ነው፡፡

ከወር በፊት ገደማ ወጣቱ የአንድነት ፓርቲ አባል ናትናኤል መኮንን ለሕክምና በሪፈር ወደ ቃሊቲ ተልኮ የነበረ ቢሆንም፣ የዛኑ ዕለት ሕክምናውን ተነፍጎ ከሌሊቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ እስካሁን በሕመሙ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ የኢብአፓ ሊቀመንበር የነበረው ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር እንደዚሁ ለተጨማሪ ሕክምና ሪፈር ተብሎ ሲጠባበቅ ከቆየ በኋላ ዘዴው ተፈፃሚ ሆነበት እጁን አጣጥፎ ተቀምጧል፡፡ ከሕመሙ ጋር በተያያዘ በአካሉ ላይ አሳሳቢ ሁኔታ እየታየበት ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ገልጬው የነበረው የእኔ የኩላሊት ሕመም አሁን ለመቀመጥም፣ ለመንቀሳቀስ እያወከኝ የሚገኝ ሲሆን፣ እኔን ከቃሊቲ ዝዋይ ለማምጣት የተደረገው የተቀናጀ መረብ ሩብ ያህሉን ለሰብኣዊነት አውለውት ቢሆን ኖሮ እኔም ፋታ፣ እነሱም እርካታ ባገኙ ነበር፡፡ ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!

የጄኔራል መኮንኖቹ አባሪዎች የነበሩት ኮረኔል ተስፋዬ ኃይሉ እና ኢንጂነር ክፍሌ ስንሻው፣ በዶክተር መረራ በሚመራው ኦሕኮ ፓርቲ አባል የነበሩት አሕመድ ነጃሺ፣ በጭለማ ቤት የከረመው ተስፋሀን ጨመዳ፣ የቤንሻንጉሉ አዛውንት ወዘተ ተገቢውን ሕክምና በማጣት ሕይወታቸውን ያጡ የእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ እንዴት ሕክምና ይከለከላል!? ግፍና ጭቆና ተቃውመው ደማቸውን ያፈሰሱና አጥንታቸውን የከሰከሱ ታጋዮችን በሥልጣን ማግስት ከፍርድ በመለስ በየእስር ቤቱ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው በሕክምና እጦት ሲረግፉ በእርካታ ማርመምን ከየት ተማሩት!? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን ይላል!? ሰው የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከቶ ምን ይላሉ!?

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

(ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታተመው ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ የተወሰደ)

[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በዝርዝር እጃችን ገባ

$
0
0

አለምነው መኮንን: ኃላፊነት የጎደለው ኃላፊ

$
0
0

alemenew mekonn
ነጋ ዓለማየሁ
alemayehu@hotmail.com
ሰሞኑን የአማራ ክልል ባለሥልጣን ነቻው የተባሉ ሰው በአማራው ሕዝብ ላይ የጀምላ ስድብ ሲሳደቡ ተደምጠዋል። ሰውየውን ስሙንም ሰምቼው አላውቅም። እንዲህ አይነቱን ሰው አንቱ ማለትም የሚገባ አልመሰለኝም። ሀገሪቱን የሚመራው መንግሥት ከየት አምጥቶ እንዳስቀመጠው እራሱ ነው የሚያውቀው።

በሕዝብ ተመርጨ ሥልጣን ይዣለሁ የሚል መንግሥት ባለሥልጣን የመረጠውን ሕዝብ አይደለም አንድን ግለሰብም ቢሆን በመሳደብ ጸያፍ አነጋገር አይናገርም። ይህ ሰው የክልሉ መንግሥት ሁለተኛ ባለሥልጣን ነው ተብሏል። ሥልጣኑን ሕግን ለማስከበር እንደማይጠቀምበት እያረጋገጠ ነው። የፈለገውን እየተናገረ፣ መረጠኝ የሚለውን ሕዝብ እያዋረደና “ለሀጫም” በማለት እየተሳደበ በስልጣኑ ከቆየ መንግሥት የሕግ የበላይነትን እንደማያከብር ብቸኛ ማረጋገጫ ነው። ለሕግ የበላይነት ቆሜአለሁ የሚል ከሆነ ተሳዳቢው ባለሥልጣን ካለበት ሥልጣን እንዲነሳ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ለሕግም ሊያቀርበው ይገባል። ስለእኩልነት እያወሩ አንደኛውን ወገን በማቆሸሽ ያሰቡትን ማምጣት አይቻልም።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሸንጎ ‘በአማራው’ ላይ ያነጣጠረውን የዘር ጥላቻ አወግዛለው አለ

$
0
0

ጋዜጣዊ መግለጫ

የካቲት 4፣ 2006

shengo ከጅምራቸው ሕወሃትና በዙሪያው ያሰባሰባቸው ተለጣፊ የዘር ድርጅቶች ሥልጣንን ለመቆጣጠር ሆን ብለው ይዘው የተነሱትና ያካሄዱት የዘር ፖለቲካ መሠረት ያደረገው ‘የአማራውን’ ሕዝብ የሚወነጅል፣ የሚያጥላላና የሚያንቋሽሽ ብሎም ለጥፋት የሚዳርግ እንደሆነ የሚየሳዩ ከበቂ በላይ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል። ይህንንም ዓላማቸውን ለማስፈፅም ከተጠቀሙበት መንገድ ዋናው የዚህን ሕብረተሰብ መሪዎችና የቅርስ ማዕከሎች ሚናና አስተዋፅዖ የሚያንኳስሱና የሚያዋርዱ የፈጠራ ታሪኮችና ወሬዎችን መፈብረክና ማሰራጨትን ያጠቃልላል።

በቅርቡ ያለፉት መለስ ዜናዊና ጓደኞቻቸው ከሰላሳ ዓመታት በላይ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ‘የአማራውን’ ሥም አጥፍተዋል፣ ጥላሸት ቀብተዋል፣ የሚያዋርዱና የሚያጥላሉ አባባሎችን ተጠቀመዋል፤ ለተለያዩ ዘውግ ልሂቃኖችም ‘አማራዎችን’ ለዘመናት ከኖሩበት ቀዬአቸው፣ መሬታቸው፣ ንብረታቸውና ቤታቸው እንዲያፈናቅሉ የሚያነሳሱና የሚገፋፉ መልክቶችን ሲያስተጋቡ ቆይተዋል። በቀደሙት ብዙ ዓመታት የሕወሃት/ኢህአዴግ መሪዎች ‘የአማራውን’ ሕዝብ በማፈናቀልና ለይቶ በማጥቃት የተፈፀመውን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፤ ከአካባቢና ከክልል ጉዳይ ጋር ብቻ የሚያያዝ በማስመሰል ራሳቸውን ከሃላፊናትና ከተጠያቂነት ነፃ ለማውጣት ሲሞክሩ ቆይተዋል።

በቅርቡ ‘በአማራው’ ክልል ምክትል ፕሬዚደንት በአቶ አለሙ መኮንን የተሰነዘረውን ለሰሚው የሚከብድ ሕዝቡን የሚያንቋሽሽ ቅጥ ያጣ ውንጀላና ዘለፋን ሽንጎው በጥብቅ ያወግዛል።በዚህ ድርጊቱም ያሳየው ለሕዝቡ ያለው ዝቅተኛ አስተያየትና ለሰብዓዊ ክብሩም ያለው ጥላቻና ንቀት በማንኛውም መለኪያ ከወንጀለኛ ሰው የማይተናነስ እንደሆነ ነው፤ የዚህ አይነቱ ተጋባር በማንም ይቅር ሊባልም ሆነ ሊረሳ የማይችል ነው። ይህ የዝቅተኛነት ስሜት የተጸናወተው ግለሰብ ቀድሞ በሕወሃት መሪዎች በተጠነሰሰው አስቀያሚና አፀያፊ የታሪክ ተውኔት የወቅቱ ተዋናይ የመሆን ዕድልን አግኝቷል።

በእኛ ዕምነት እንደዚህ ያለ መዘላበድ ሃላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን ሁኔታዎች እንደ ዘር ማጥፋት ላሉ ያልታሰቡ እልቂቶች እንዲያመሩ አስተዋፅዖ ሊያደርግ የሚችል አደገኛ ተግባር በመሆኑ፤በሁሉም የሲቪክና የፖለቲካ ቡድኖች፤ በታወቁ ግለሰቦችና፤ በሃይማኖት መሪዎች ሊወገዝ የሚገባው ነው እንላለን።

ሸንጎው ለዚህ አሁን ለደረስንበት እጅግ አሳፋሪ ሁኔታና ጥፋት ሁሉ በዋነኛነት ተጠያቂ መሆን ያለበትና ሃላፊነቱን መውሰድ የሚገባው የሕወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነው ብሎ ያምናል። ይህ ዓይነቱ ድርጊት እንዲፈጠርና እንዲካሄድ ምክንያት የሆነው በጥቂት ዘረኝነት በተጠናወታቸው ግበሰቦችና ቡድኖች ቁጥጥር ሥር ያለው የፖለቲካ ሥርዓት ካልተወገደ በቀር ተመሳሳይ ሁኔታዎች መቀጠላቸው አያጠራጥርም።

በመጨረሻም በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማሕበራት በመሐከላቸው ያለውን አነስተኛ ልዩነቶች በማቻቻል፤ ጠንካራና ሠፊ የጋራ ትብብር በመፍጠር ኢትዮጵያውያንን እርስ በርስ በመከፋፈልና በማጋጨት ስልጣኑን በማራዘም የተካነውን አሰከፊ አምባገነን አገዛዝ፤ ለማስወገድና በምትኩም አንድነቷ በተከበረ ኢትዮጵያ ስር ሁሉንም እኩል የሚያሳትፍ ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲአዊ ሥርዓት ለመገንባት ባንድ ላይ እንዲሰሩ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም በእውነተኛ ልጆቿ ሃይል ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!

አማራውን የተሳደቡት አቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ ተደበደበ

$
0
0

alemenew mekonn
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን መኖሪያ ቤት በድንጋይ መደብደቡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች እንጠቆሙት ባሳለፍነው ሳምንት የካቲት 1 እና የካቲት 2 ቀን 2006 ዓ.ም(ቅዳሜና እሁድ) ለሊት በተደጋጋሚ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መኖሪያ ቤታቸው በድንጋይ መደብደቡን ተከትሎ ቤታቸው ቀንና ለሊት በፖሊስ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡

አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ የሚያዋርድና የሚዘልፍ ንግግር ሲያደርጉ የተቀዳ ድምፅ ለህዝብ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ በብአዴን ውስጥ የንትርክ ምክንያት መሆናቸው አይዘነጋም፡፡

በሌላ በኩልም የብአዴን ንብረት የሆነውን ዳሸን ቢራን አንጠጣም የሚለው ተቃውሞ በከፍተኛ ሁኔታ በሕዝቡ ዘንድ እየተሰራጨ የሚገኝ ሲሆን ሕዝቡም አቶ አለምነው ካልተባረሩ እየተሰደብን የነርሱን ምርት አንጠቀምም በሚለው አቋሙ እንደጸና ነው። ሕዝቡ በጠራው የቦይኮት ዳሸን ቢራ እንቅስቃሴ የተነሳ በዳሸን ቢራ ምርት ላይ ተጽእኖ እያደረበት መሆኑ የታወቀ ሲሆን አንዳንድ መጠጥ ቤቶችም የዳሸን ቢራ ጠጪዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል።
Boycott Dashen Bear

አንድነት እና መኢአድ የካቲት 16 በባህር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

$
0
0

(ከዚህ ቀደም አንድነት በባህር ዳር ያደረገው ሰልፍ - ፎቶ ፋይል)

(ከዚህ ቀደም አንድነት በባህር ዳር ያደረገው ሰልፍ – ፎቶ ፋይል)


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ብአዴንን በመቃወም በባህርዳር ከተማ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠሩ፡፡ ፓርቲዎቹ ነገ በ4 ሰዓት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት በጋራ መግለጫ እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ ለተቃውሞ ሰልፉ አስፈላጊው የማሳወቅ ተግባር መጠናቀቁ ታውቋል፡፡

አንድነትና መኢአድ እሁድ የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም የጠሩት የተቃውሞ ሰልፍ መነሻ ምክንያት እንዲያስረዱ በፍኖተ ነፃነት የተጠየቁት የአንድነት ፓርቲ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሰለሞን ስዩም “አማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብአዴን የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብን ክብር የሚያዋርድና በለሌሎች ብሔረሰቦች በክፉ እንዲታይ የሚያደርግ የጥላቻ ንግግር በማድረጋቸውና ብአዴንም እንደ ፓርቲ ማስተባበያም ሆነ የማስተካከያ እርምጃ ባለመውሰዱ የግለሰቡን አቋም እንደሚጋራ ያመለክታል” ብለዋል፡፡ የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት አቶ ተስፋዬ መላኩ በበኩላቸው “የአማራ ህዝብን እየመራሁ ነው እያለ እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ንግግር ያደረገውን ባለስልጣና የሚወክለውን ፓርቲ ለማውገዝ እንዲሁም ለህግ እንዲቀርብ ለመጠየቅ ነው ሰልፉ የተጠራው” ብለዋል፡፡

የፓርቲዎቹ የባህርዳርና አካባቢዋ መዋቅሮች የተቃውሞ ሰልፉን ለማስተባበር ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን የባህርዳር ከተማና የአካባቢዋ ህዝብ በነቂስ በመውጣት በሰልፉ ተቃውሞውን እንዲገልፅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንደዘገበው።


በሳንሆዜ ከተማ ለወራት የታቀደው የወያኔ የማጭበርበር ሴራ በሚያሳፍር መልኩ ተጠናቀቀ

$
0
0

እራሱን የአባይ ግድብ ካዉንስል ብሎ የሚጠራው የወያኔ ስርጎ ገቦች እና የባንዳወች ቡድን ለወራት ለወያኔ ቱባ ባለስልጣናት እጅ መንሻ የሚሆን ገንዘብ የማግኛ ዘዴ ላይ መዶለት እንደጀመረ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ወዲያውኑ ውጥኑን ስላወቅን በመሃከላቸው ሰርጎ በመግባት እያንዳንዶን እቅዳቸውን ስንከታተል ቆይተናል። የሴራው ዋንኛ የባንዳነት ሚና ተጫዋቾች ቀድሞውንም ለወራሪው የኢጣልያ ጦር እንቁላል አቀባይ ከነበሩ ቤተስብ የበቀሉ መሆናቸውን ስንረዳ ደግሞ ልባችን በሃዘን ደምቶል።በጣሊያን ወረራ ዘመን ድልድይና ህንጻ በመሰራቱ ወራሪው ጦር ይግዛን ያላለውን እና ነጻነቱን ያስቀዳመውን ህዝባችን ዛሬ የወያኔ ደናቁርት ካድሬዎች በህዝብ ጠኔ የትላልቅ ህንጻ ባለቤት እና የባለዘመናዊ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆናችው ያደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ፤ ላለፉት ሃያሶስት አመታት የህዝባችን ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ማምራቱ እየታወቀ ‘’ልማታዊ’’ የሚል ጭምብል ለብሰው ለማደናገር መሞከራቸውን ከጅምሩ በቁጭት ተከታትለናል።
ሴራው ወደ ተግባር የሚለወጥበት እለት እንደደረስም በከተማው የምንኖር ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖት፤ቋንቋ እና የብሄር ልዩነት ሳይከፋፍለን የእምነት እዳ የሆነውን እና በቃልኪዳን የወረስነውን ስንደቃችንን በማንገብ በቦታው ተገኝተን ካሃዲዎችን ተቃውመናል። ካአባይ በፈት ስብአዊ መብትን መገደብ ይገደብ ፤ ወያኔ ከፋፋይ ነው ፤ ወያኔ ህዝባዊ ውክልና የለውም፤ አላግባብ የታስሩ የሃይማኖት እና የፖለቲካ እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፤ ሌሎችንም መፈክሮች በማሰማት እና መዝሙሮችን በመዘመር የተነቃቃ እና የሚያስደንቅ ወኔ የተላበስ ጨዋነታችን አሳይተናል።
በሃገር ወዳዱ ተቃዋሚ ወኔ ልባቸው የራደው የወያኔ ጀሌዎች ባለ አራት ስኮድ የፖሊስ ሃይል እና ከአስር በላይ የግል ጸጥታ ስራተኞች በማስመጣት ግቢውን ለማጠር ቢሞክሩም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን የተላበሰው ተቃዋሚ ሃገር ወዳድ ለጸጥታ ሰራተኞች ህግ አክባረነቱን በማሳየት መብቱን ግን ሳይነጠቅ ድምጹን አሰምቶል። ተቃወሞውን ከሰአት በሆላ በስምንት ሰአት ግድም የጀመረው ሃገር ወዳድ እስክ ምሽቱ ሁለት ስአት በቦታው የተገኘ ሲሆን ጨለማን ተገን አድርገው ከገቡ ባንዳዎች በተጨማሪ በወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚነት የሚታወቁ ክሃዲወች ፤ ስለ ወያኔ አንጻራዊ ግልጽነት የሌላቸው ወይንም ከወያኔ ህልፈት በፊት ድርሻቸውን መውስድ የሚፈልጉ ባእዳን ተደምረው ከ40-50 ያልበለጡ ሰዎች ተገኝተውበታል።
አዳራሹ ባዶ የመኪና ማቆሚያው ባዶ ሆኖባቸው የተርበተበቱት የወያኔ ጀሌዎች ኑልን ኑልን እያሉ የተማጥኖ ስልክ ጥሪ ሰያደርጉም ተደምጠዋል። ማየት ማመን ነው እንዲሉ በቦታው የተገኙ ሃገር ዎዳዶች ለእማኝነት ያነሶቸው ፎቶግራፎች ይህን እውነታ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ። የወያኔው አይጋ ፎረም እና ትግራይ ኦን ላይን በፎቶሾፕ ኪሳራቸውን ለመደበቅ ቢሞክሩም እውነታው ፍጹም ሌላ ነው። እንደሚታወቀው በወያኔ አገዛዝ ጋዜጠኞች አሸባሪ በመባል ዘብጥያ ወርደዋል፤ የሃይማኖት አባቶች ሞት እና ሰደት እጣ ፈንታቸው ሆኖል፤ ገዳማት ተደፍረዋል፤ዜጎቸ በራሳቸው ሃገር ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሃብት እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን ተነፍገዋል፡ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ እናቶቸ እና እህቶቸ የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዲቀንስ ተደርጉዋል። እስር ቤቶች በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በተለይም በኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ተጨናንቋል፤ የኑሮ ውድነቱ እማይቀመስ ሆኖል፤ በምርጫ የተሸነፈው ወያኔ በጠራራ ጸሃይ ያልታጠቁ ህጻናትን በአደስ አበባ እና በሌሎች ክተሞች በግፍ ፈጅቷል። የእስልምና ጉዳይ አፈላላጊ ወገኖችን በአሸባሪነት ከሱዋል፤ በመሃከለኛው ምስራቅ ወጣት ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ ባርነት በመዳረግ በታሪካችን ታይቶ እማይታወቅ ውርደት እና የሰነልቦና ጠባሳ ጥሎብናል። በጋምቤላ ዜጎችን በማፈናቀል እና የውጪ ጉቦ ሰጭዎች ለም ቦታ እንዲይዙ አድርጎል፤ በኦጋዴን ግድያው አስገድዶ መድፈሩ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንደቀጠለ ነው፤ አልፎ ተርፎም የሃገራችን ድንበር ለሱዳን በእጅ መንሻነት ተሰጥቷል። ዛሬ ታድያ ምኑ ተቀየረና ነው ይህ ጎጠኛ ቡድን ጋር መተቃቀፍ ያስፈለገው?
በመጨረሻም በዚህ የባንዳወች ሴራ ኢትዮጵያውያን ግራ እንዳይጋቡ እና ሰልፋችውን ከወገኖቻቸው ጋር እነዲያደርጉ የጥሪ ወረቀቶቻችን ላወጣችሁልን ድህረገጾች እና በቦታው ተገኝታችሁ ድምጻችሁን ላሰማችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ልባዊ ምስጋናችን እየገለጽን ትግላችን ይቀጥላል ወያኔም ያለጥርጥር በህዝባዊ ትግል ይገረሰሳል እንላለን። ተቃዋሞችን ልማትን ሳይሆን በልማት ስም የሚደረገውን ሙስና እና ኢፍትሃዊ የሆነ የአስተዳደር በደል መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።
ኢትዮጵያ ለዘላላም ትኑር!!!
የሳንሆዜ ሀገር ወዳዶች ግብረሃይል::

የጤፍ ምርትን ለውጭ ገበያ ! ይቁም ሊባል የሚገባ ፤

$
0
0

አሰግድ ኣረጋ
(ኮለምበስ – ኦሃዮ)

ሰሞኑን ስለጤፍ ምርታችን የባዕዳኑ ብዙሃን መገናኛ አጀብ እያሉን ነው፤ ለዘመናት የተደበቀው የዘሩ ገመና መጋለጡን እየነገሩን ነው፤ ስለያዘው ንጥረ ነገር፣ ስለጤናማነቱ፣ በምዕራቡ ገበያ ስለመፈለጉ፣ ከሁለም በላይ ስለ ውጭ ምንዛሪ ምንጭነቱ። ምግብነቱ ተትረፍርፎ የኢትዮጵያ ህዝብ ማስቀመጫ – ቦታ ያጣ ይመስል፣ የወንዙ ልጆች ጭምር ፣ ጤፍ-የጤፍ ዘር፣ እንጀራ ፣ ብሰኩት፣ ኬክ ሆኖ ምግብ በዝቶበት ለሚቀናጣው ለውጭ ገበያ እንዲነጉድ ከምዕራባውያኑ ጋር አብረን ከበሮ እየደለቅን ነው፤ አደብ ልንገዛ ይገባል።
ባለሙያዎቹ ወቅታዊና በቂ መረጃ እሰካላስጨበጡን ድረስ፣ በዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ዕምነት፣ ምርታማነቱ ባለህበት እርገጥ የሆነውንና – በደሃው ገበሬ ማሳ ዛሬም ሆነ የዛሬ 100 ዓመት በሄክታር ከዘጠኝ ኩንታል ያልዘለለውን ፣ ተገቢ የምርምርና ጥናት እገዛ በዙሪያዉ ያላንዣበበውን ይህን ብቸኛ የኢትዮጵያ ልጅ – ጤፍ ፣ አሁን ባለበት ደረጃ ለዉጭ ገበያ በውጭ ምንዛሪ ምንጭነት በሰፊው ለማቅረብ የተያዘው እንቅስቃሴ የምርቱንም ሆነ የህብረተስቡን የኑሮ ዕውነታ ያላገናዝበ ፣ከፈረሱ ኮርቻው ዓይነት ነው። በምርቱ ህልውናና በሸማቹ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ያልተፈለገ ጦርነት ክተት የማለት ያህል ነው። በመንግስት በኩል ቆም ተብሎ እነደገና ሊፈተሽ የሚገባ አብይ ብሔራዊ ጉዳይ ነው።
ጤፋችን በመሰረቱ የማንነታችን መግለጫ፣ ረሃብን ተዋጊ – ብሄራዊ ጦራችን ነው፤ ድንበር አስከባሪያችን ነዉ። “የዕለት እንጀራችንን አታሳጣን” እያልን ለፈጣሪ ቢያንስ በቀን አንዴ፣ ከሆነልንም ሶስቴ የምንጸልይለት የጤናችን ምሰሶ ነው፤ ከሚያመጣው ዶላር ይልቅ የሚያስታግሰው የሚሊዮን ረሃብተኛ ሆድ ሚዛን የደፋ ነው፤ በየሶስትና አራት ዓመቱ አንገት አስደፊና ብሄራዊ ውርደት የሆነውን የልመና እጅ ከመዘርጋት የሚያድን ነው። ለእኛ ለዜጎቿ ምርቱ ከቡናና ከወርቃችንም በላይ ነው፤የሱስ ማርኪያ ወይም ሠርግና በዓል እየተጠበቀ ብቅ የሚል ማጌጫ አይደለም፤ ሳይተርፈን ቡናና ወርቅ ለውጭ ገበያ ብንልክ በሕብረተሰባችን ማህበራዊ ህይወት ውስጥ የሚያመጣው ቀውስ የለም፣የሚበጅ እንጂ። ሳይተርፈን የጤፍ ዘርን በጥሬውም ሆነ በእንጀራ ለውጭ ገበያ መስደድ ግን ሀገራዊ ጥቃት ነው። እኛነታችንን ሳያስከብር ከሀገር እንዳይወጣ፣ ለባዕዳን ሲሳያ እንዳይሆን በያለንበት ዘብ ልንቆምለት ያስፈልጋል፤ የመስኩ ባለሙያዎች ከምርምር ጣቢያችው ወደ ህብረተስቡ መድረክ ወጣ ብለው ስለ ጤፍ
teff3
ልዩ ባህርይ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሊነግሩንና ጥብቅና ሊቆሙ ይገባል፤ የጤፍ ምርት ያለበትን የምርታማነት ደረጃ ሊተነትኑልን ፣ ለውጭ ምንዛሪ የመዋልን ብሄራዊ ጠቀሜታና ጉዳት ግንዛቤ ሊያስጨብጡን ያሻል፤ብሄራዊ ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት ከመከላከሉ ላይ ኢትዮጵያዊ ሃይላችንን ማሳረፉ ላለውና ለመጪው ትውልድ ባለውለታ ያደርገናል።
በመሰረቱ ፣ የጤፍ ዘርን ህለውና የተፈታተነ የክተት ጥሪ ሲደረግ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ በደርግ ዘመነ መንግስት የገበሬው የጤፍ ማሳ ምርታማነታቸው ከፍ ባሉ አዝዕርቶች እንዲተካ የሚያደርግና በመንግስት የተደገፈ “ጥናት” ቀርቦ ለአፈጻጸሙ በተወሰኑ የሀገሪቱ ክልሎች ሸብ-ረብ ተብሎ ነበር። ጥናቱ ምርታማዎቹ በቆሎ፣ ስነዴና ድንች ምርታማ ያልሆነውን የጤፍ ዘር ቢተኩ፣ የሀገሪቱን ዓመታዊ የምርት እጥርት ከመሸፈን አለፈው ለመጪው አመት የሚሻገር ምርት ለማከመቸት እንደሚቻል ያስረገጠ ነበር። ተግባራዊነቱ ከአንድ ዓመት አልተሻገረም። በይዘቱ ከዛሬው ጥሪ ቢለይም በገበሬው ኑሮና በጤፍ ህልውና ላይ ጥሎት የነበረው አደጋ ተመሳሳይ ተፅእኖ ነበረው። ውሳኔውንም ሆነ አፈጻፀሙን የተቃወሙ ጥቂት ወገኖች ነበሩ፤ መድረኩም ወቅቱም ባለመፍቀዱ አልተደመጡም። ውሳኔው ከማዕከል ወጥቶ ወደ ገጠሩ – ከገበሬው ማሳ አመራ፤ ገበሬው ጤፉን ወደ ጓዳው መልሶ፣ እንደታዘዘው ማሳውን በምርታማዎቹ በቆሎና ድንች አርመሰመሰው። መሰብሰብ ከሚችለው በላይ ማረስ ልምዱም ባህሉም ያልነበረው ገበሬ አቅሙና ጎተራው የሚችለውን ያህል ሰብስቦ የቀረውን ከማሳው ላይ ተወው፤ ወድሞ ቀረ። በጎተራ ያከማቸው ስንዴም በነቀዝ ተጠቃ፤ በቆሎና ድንች የከተሜውን ገበያ ቢያጥለቀልቀውም ዋጋው በመውደቁ ገበሬውን ከኪሳራ ዳረገው፤በአርሲና ባሌ በሰፊው የታረሰው የመንግስት እርሻ ምርትም ለተመሳሳይ አደጋ ተጋለጠ፤ አቅምን ያላገናዘበ ውሳኔ፣ በበቂ ጊዜ፣ ገንዘብ ባለሙያ ያልተደገፈ ምርትና ምርታማነትን የማሳደጉ ዘመቻ አባዜ፣ ለሌላ አስከፊ ችግር ገበሬውንም፣ ሸማቹንም መንግስትንም ጭምር አጋልጦ አለፈ።
ከስህተት ያለመማር ባህል የተፀናወታቸው ገዥዎቻችን በመጪው የዕቅድ አመትም መሰረታዊ ችግሩን ባልፈታና ስሙን ብቻ በቀየረ እቅድ እንዲቀጥል ተቃጥቶ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ጥቂት ቆራጥ የሆኑ የጤፍ ምርት ተመራማሪዎች ድምጸ-አልባ የነበረውን የገበሬውን ድምጽ ከፍ አርገው በማስተጋባታቸውና በቁጥር ከሁለት ያልበለጡ የጊዜው ባለስልጣናትን ግንዛቤ ሊያገኙ በመቻላቸው፣ ከገበሬው ጉያ ተደብቆ የሰነበተው የጤፍ ዘር በግላጭ ወጥቶ ከማሳው ሊመለስ በቃ። ዛሬ ኢትዮጵያናችን እነዚያን የመሰሉ ለገንዘብና ለግል ስልጣን ያላደሩ ተመራማሪዎቿንና የመንግስት ሃላፊዎቿን በባትሪ የምትፈልግበት ወቅት ላይ ነች። አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ለማረጋገጥ መረጃ ባይኖረውም፣ በዚያን ወቅት በጤፍ ዘርና ምርታማነት ጥናትና ምርምር ዙሪያ ከተሰለፉት ሳይንቲስቶቻችን መሀከል እነ ዶ/ር ሰይፉ ከተማና ባልደረቦቻቸው ለአብነት የሚጠቀሱ የሀገሪቱ ባለውለታ ናቸው። ዶ/ር ሰይፉ የጤፍ ዘር ለዘመናት አላነዳች የቴክኖሎጂና የመንግስት ድጋፍ የመቆየት ሚስጥርን አበክሮ የሚገልጽ የምርምር ስራ (Tef ፤ Eragrostis tef , 1993) ለተነባቢነት አብቅተዋል፤ በዚያ ጥናታዊ ስራቸው ገበሬዉን ጭምር እማኝ በማድረግ እንደነገሩን፣ የጤፍ ዘር ከማንኛውም ምርት በተሻለ ድርቅንም ሆነ ከባድ ዝናብን የመቋቋም ልዩ ባህርይ የገበሬውን ቀልብ የሳበ ነው።
ጤፍ በምግብነቱ እንዲህ እንደዛሬው የሀብታሙ አልነበረም፤ ደሀው ችግር ሲጋፈጠው እየደበቀ፣ እየቆጠበ የሚበላው ሳር ነበረ። የዘሩን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ደሀውም ሀብታሙም ገበሬ በእጅጉ ከተረዱት በሗላ ከትውልድ ትውልድ እየተቀባበሉት እዚህ
ለመድረስ በቅቷል። በተዘራበት ማሳ እንደ ስንዴና በቆሎ በዝናም እጥረትም ሆነ ብዛት ወድሞ አይቀርም፤ ገበሬውን አመድ አፋሽ አያደርግም፤ የጠበቀውን ያህል ባያገኝም ለዘር ያህል አያሳጣውም። በጎተራ ሲከማች እንደተቀሩት ምርቶች በነቀዝ አይደፈርም፣ ጭዱ የእንስሳቱ ተወዳጅ ምግብ፣ የጎጆው ግድግዳ ማገር መመረጊያ ነው። በገቢ ምንጭነቱም አንጀት አራሽ ነው። የጤፍ ዘር የሸማቹም ልዩ ወዳጅ ነው፤ በረከት ያለው እህል ነው፤ ግማሽ ኩንታል ጤፍ ከወፍጮ ቤት ወስዶ ሙሉ ኩንታል ዱቄት ተሸክሞ የሚመለስበት ነው፤ ለዚህም ነው ሸማቹ የዋጋ ውድነቱን አጠብቆ የሚያማርር። በምግብነቱም ቢሆን ተወዳጅና ሁለገብ ነው፤ ችግር ከመጣ አለማባያ፣ አለዚያም በወተት ተምጎ ፣ በሚጥምጣ ተረምዶ ይበላል። ማባያዎቹ ሳይደመሩ የጤፍ ዘር በራሱ አይነታቸውና መጠናቸው የተለያዩ በርካታ ለሰውነታችን ጤና ግንባታ የሚረዱ ንጥረነገሮችን(ፕሮቲን፣ አይረን፣ ካልስየም፤ ፋይበር እና የተለያዩ ቫይታሚኖችን) አዝሎ የሚገኝ ነው። ዜናው ከምዕራቡ ዓለም የወሬ ማሰራጫ ጣቢያ ካልመጣ ጆሯችን አልሰማ ብሎ እንጂ፣ አዲስ አይደለም። የደብረዘይቱ የግብርና ምርምር ሳይንቲስቶቻችን የዛሬ 25 ዓመት አስረግጠው ነግረውን ነበር። ኢትዮጵያውያኑ ተመራማሪዎች ይህን የጤፍ ዘር ባላቸው ውስን አቅም ምርታማ ለማደረግ ጥረታቸው የመቀጠሉ ተቀዳሚ ምክንያት ለምዕራባውያን የጤፍ ብስኩትና ትኩስ እንጀራ ለመሸጥ አልነበረም፤ አይደለመም። ዋና ግባቸው በሚሊዮን የሚቆጠረው የሀገሪቱ ጤፍ አምራች ገበሬ ለዘመናት ከያዘው አድካሚ አሰራር ተላቆና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆኖ ምርቱን በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለበላተኛው እንዲያቀርብ ማስቻል ነው። በሀገር ውስጥ ምርቱን የማስተዋወቅ ስራ ሳይሆን፣ ምርቱ የያዘው ንጥረ-ነገር ምን ያህል ለጤናችን አስፈላጊ እንደሆነ አግባብ በላቸው ተቋማት በኩል ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት ነው።
በጥናታዊ ጹሁፋቸው፣ የጤፍ ተመራማሪው ዶ/ር ሰይፉ እንደሚነግሩን፣ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በጤፍ ምርቱ ላይ ያተኮረ ሳይንሳዊ ምርምር የተጀመረው እንደ አውሮጳ አቆጣጠር በ 1950 ዎቹ መጨረሻ ግድም ሲሆን፣ የመጀማሪያው ኢትዮጵያዊው የጤፍ ሳይንቲስት ዶ/ር መላክ-ሃይለ መንገሻ ይባላሉ። እኒህ ሙሁር ስለጤፍ ዘር ባህሪ ጥናትና ምርምር ከማድረግ ጀምሮ በግብርና ኮሌጆችና የእርሻ ምርምር ጣቢያዎች ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ ምርምሩ እንዲቀጥል በማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርገዋል። በመቀጠለም ሌላው ሳይንቲስት ዶ/ር ታረቀ በርሄ የተሰኙ በጤፍ ምርት ምርምር ሂደት ግኝቱ እጅግ አስቸጋሪ የሆነውንና በምርታማነቱ ልዩ ሚና የሚጫወተውን የጤፍ ባህርይ (The Pollination Habit of Tef) ግኝት በተጨባጭ በማሳየት በሙያ አጋሮቻቸው አድናቆትን ያተረፉ የመስኩ ባልደረባ ናቸው። በእነዚህ ግኝቶች ላይ በመንተራሰ ዶ/ር ሰይፉና ባልደረቦቻቸው በደብረዘይት የግብርና ምርምር ማዕከል በጀመሩት የናሙና እርሻ፣ በሄክታር 8 እና 9 ኩንታል ላይ የቆመው የጤፍ ምርት ከ 20 ኩንታል በላይ ለማምረት የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ሊያስመዘግቡ በቅተዋል። ይህ ድንቅና ተስፋ ፈንጣቂ ውጤት፣ ዛሬ ስለደረሰበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የዚህ ፁሁፍ አቅራቢ ምቹ ሁኔታ ባይኖረውም ፣ ከተጨባጩ የሀገሪቱ ሁኔታ መገንዘብ እንደሚቻለው የምርታማንቱ ማነቆ አሁንም ድረስ እነዳልተፈታ ነው፤ በአብዛኛው ገበሬ ማሳ ላይ የጤፍ ምርትና ምርታማነት ባለህበት እርገጥ ላይ ነው። በየክልሉ በደብቅና በገሀድ የረሀብ አለንጋ እየተቀጣ ያለው ህብረተሰብም በእማኝነቱ የሚያወለዳ አይደለም።
በሌላ በኩል – የተለያዩ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት – የጤፍ ምርት ከሀገር ውጭም በአሜሪካ፣በካናዳ፣ በአውሮጳ፣ በአውስትራሊያና በአፍሪካም ጭምር ለማብቀል ጥረቱ ተይዟል፤ በኢትዮጵያ አየርና አፈር የሚበቅለውን የጤፍ ዘር ሊተካ ባይችልም፣ ለጤፍ ምርታችን የሚበጁ ሁለት እገዛዎችን ለማድረግ ዕደሉ የሰፋ ነው። የመጀመሪያው፣ የጤፍን ምርታማነት ለማሳደግ ከበቃ፣ ለግብርናቸው የተጠቀሙበትን ቴክኖሎጂ በጥንቃቄ አጢኖ ለሀገራችን ጤፍ ምርታማነት በአጋዥነት ለማሰለፍ መቻሉ ነው። ሁለተኛው፣ የሀገሪቱን የምግብ ፍላጎት ሳያሟላ፣ ባልተመጣጠነ ዋጋ ከደሃው ገበሬ ተዘርፎና ከበላተኛው አፍ ተነጠቆ ወደ ውጭ በቀላሉ እየወጣ ያለውን ጤፍ ጊዚያዊ እፎይታ ለማሰጠት አቅሙ መኖሩ ነው። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የጥቂት ባለጊዜ ባለስልጣናትንና ነጋዴዎችን ኪስ ከመሙላት ባለፈ ብሔራዊ ፋይዳ እነደሌለው በይፋ የሚነገረለት ይህ የሀገሪቱ ጤፍ፣ ለውጭ ገበያ እንዳይውል ጥሪ የመደረጉ አንዱም መልዕክት የሀገር ቤቱን ጤፍ ለሃገር ፤የውጭውን ለውጭ የሚል ነው። በዋና ዋና ያሜሪካ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና ወዳጆቻቸው ከሀገር ቤት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጭምር ተጭኖ የሚመጣውን ትኩስ እንጀራና ጥሬ ጤፍ ሸማቹ እንዳይገዛ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው፤ በተሳታፊ ነጋዼዎችም ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ግፊት እያደረጉ ነው፤ ምላሹ ግን አጥጋቢ ሆኖ አይታይም። ምዕራባውያኑ ጤፍን እንደ ጣሊያኑ ፒሳ እስከሚለምዱት ድረስ እኛ በውጭው አለም ነዋሪ የሆንን ዜጎቿ የፈረጠመ ክንድ አለን፤ ከደሀው አፍ ተነጥቆ ማዕዳችንን እያጣበበ ያለውን የኢትዮጵያ እንጀራ – የጤፍ ዘር – ለማስቆም ትግሉን መቀላቀል ይጠበቅብናል፤ የይቁም ጥሪውም ቅዱስ ጥሪ በመሆኑ፤ ከጎናቸው ልንቆም ያስፈልጋል።
ጤናማውን ኦርጋኒክ ጤፍ ወደ ባዕድ ሃገር ሰደን በኬሚካል ያበደውንና ለበሽታ መራቢያነት ምቹ የሆነውን የባዕድ እህል ወደ ሀገር ከማስገባት ፣ ወይም የጤፍን ኦርጋኒካዊ ይዘት ለሚያቃውሱ ባዕዳን ነጋዴዎችና ሳይንቲስቶቻቸው አጋልጠን ከመስጠት፤ ልንድን የምንችለው፣ ዜጎቿ በአንድ ሆነን ለምርቱ ደህንነትና ምርታማነት ዘብ ስንቆም ብቻ ነው።ሀገሪቱ ወጣት የጤፍ ሳይንቲስቶች በጥራትና በብዛት እንድታፈራ ፣ የምርምርና ጥናት ዘርፉ ሀገራዊና አለም ዓቀፋዊ ትኩረት እንዲያገኝና፤ በቂ የመዋዕለ ነዋይ ፈሰስ ለዘርፉ እንዲደረግለት የሚደረጉ ተከታታይ ጥረቶች ለጤፍ ምርታችን አይነተኛ ለውጥ መምጣት መሠረት የሚጥሉ ብቻ ሳይሆኑ፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አንገቷን ቀና አድርጋ እንድትሄድ የሚያስቸላት ነው። ይህን ለመሆን ካበቃን፣ ከክረሰቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የገበሬው ችግር ደራሽና አለኝታ ሆኖ እዛሬ ድረስ እስተንፋሱ የቆየው የጤፍ ዘራችን፣ ምርታማነቱ ከፍ ብሎና ከጥቂቶች ማዕድ ወጥቶ በተመጣጣኝ ዋጋ በሚሊዮን ህዘብ ማዕድ በመደበኛም ሆነ በአማራጭ ምግብነት የምናስተናግድበት ይሆናል። ከተጠነከረም፣ ሀገሪቱ ለጤፍ ምርት በሚውል መጠነ-ሰፊ መሬት የታደለች በመሆኗ፤ ዛሬ ከኢትዮጵያ አይውጣ እያልን የምንጮህለት ጤፍ – ያኔ ለውጭ ገበያ ጭምር በመዋል- ቡናና ወርቃችን ተደምረው ከሚያገቡት የውጭ ምንዛሪ በተሻለ ገቢ አስገኚና የሀገሪቱ የልማት ገንቢ ሆኖ እንደሚቀጠል ተስፋችን በእጅጉ የፀና ነው።

የሳውዲ ጉዳይ …ሰበር የመረጃ ግብአት

$
0
0

የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ኋላፊ ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ ከኃላፊነታቸው ተነሱ !
* ትናንት ረፋዱ ላይ በገደምዳሜ “ጉልቻ ቢቀያየር …” ብለን ያንሹካሾክነው መረጃ ተረጋገጠ !
* ለጊዜው ቆንስል ጀኔራሉን ተክተው በጊዜያዊነት ቆንስል መስሪያ ቤቱን ለቀጣይ ሁለት ወራት የሚያስተዳድሩት በቆራጥ አመራራር ብቃታቸው የማይመሰገኑት ቆንስል ሸሪፍ ከይሩ ናቸውም ተብሏል ።
* ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ ትናነት ምሽት ጉዳዩን ለማሳወቅ የኢህአዴግ ድርጅት አባላት ስብሰባ ጠርተው እንደነበርና አብዛኛው አለመገኘታቸው ታውቋል። ድርጅት አባላት በተለይም ከጎናቸው የማይጠፉ የነበሩት ተጽዕኖ ፈጣሪ የህወሃት አባላት እንኳ አልተገኙም ተብሏል።
* አቶ ዘነበ ከበደ በቆንስሉ ዙሪያ የህወሃት አባላትን አምባገነንነትን በማውረድና በማቀዝቀዝ ፣ በሙስና ፣ በድለላ ፣ በማጭበርበር ስራ በቆንስሉ ዙሪያ የነበሩትን በማጥፋት እና በሌብነት አካባቢውን በማጽዳት ይታወቃሉ።
* ህግ አዋቂ ሆነው በህግ ማዕቀፍ የመጡ ዜጎች ግፍ ሲፈጸምባቸው በመከላከሉ የረባ ስራ አልሰሩም የምላች ሃላፊው ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ሶስት ከባባድ የህዝብ ማዕበል የተነሳባቸውን ፈተናዎች በጽናትና በቆራጥ አመራራቸው ድል ነስተው ማለፋቸውን አውቃለሁ። ሃላፊው በአንጻሩ በመረጃ ልውውጥ የማያምኑ ፍትሃዊ በመሆኑ ሳይሆን በግላቸው ላመኑበት ጉዳይ ግንባራቸውን የሚሰጡ ኋላፊ ነበሩ ።
* አቶ ዘነበ ከበደ በሳውዲ ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ክብር የሚሰጣቸው በአማርኛም ሲናገሩ ወጋቸውን ለማስረዳት ተረት የሚያበዙ ፣ ከዚህ በፊት ከነበሩት ኃላፊዎች እንግሊዝኛ አቀላጥፈው የሚናገሩ አንደበተ ርቱዕ ግርማ ሞገስ ያላቸው ፣ በአለባበሳቸው ጸዳ ያሉ ትክክለኛ የአንድ ሃገር ዲፕሎማት ክብርን የተጎናጸፉ ኃላፊ ነበሩ ።
* ከግማሽ ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች ባለፉት ሶስትና አራት አመታት የገቡ ሲሆነ ኮንትራት ሰራተኞች ስለመጡበት ውል አቶ ዘነበ በጀርመን ራዲዮ ውይይት ፕሮግራም ተጠይቀው በኢትዮጵያና በሳውዲ በመንግስት መካከል የሁለትዮሽ የስራተኛ ልውውጥ ስምምነት አንደሌለ በግላጭ የነገሩን ኀላፊም ናቸው ።
* አቶ ዘነበ ከበደ ከዚህ በፊት በቆንስሉ ውስጥ የነበረውን የበከተ ቢሮክራሲና ኢ ፍትሃዊ አመራር በአደባባይ የተናገሩ ደፋርም ናቸው። ነዋሪው በግዳጅ ምንም የገንዘብ መዋጮ ሲጠይቁ ያልተሰሙ ፣ ኮሚኒቲው ያልሆነ ምንገድ ሲሄድ እንደ በላይ ጠባቂነት ኢ ፍትሃዊ አካሔዱን እያዩ ሲያልፉም ታይተዋል። ለዚህ ተጠቃሹ ትምህርት ቤቱ በኮሚኒቲው ለከፋ አደጋ ሲዎድቅ የተመለከቱበት አካሔድ ሲሆን በመጨረሻው ሰአት ገብተው 120 ሽህ የሳውዲ ሪያል ከዝርፊያ አዳንኩ ብለው ቢነግሩንም ዛሬ ድረስ የ3000 ታዳጊዎችና የ200 መምህራንና ሰራተኞች ያቀፈው መመኪያችን በጅዳ የኢትዮጵያውያን አለም አቀፍ ትምህርት ቤቱን ከአደጋ አላወጡትም ። ያም ሆኖ ለትምህርት ቤቱ የተዝረከረከ አሰራር ምክንያትየየተባሉ አንዳንድ መሰረታዊ ለውጦችን ግን በቅርብ ተንቀሳቅሰው አምጥተዋል!
* አቶ ዘነበ ከበደ እንደርሳቸው ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ እንደ እርሳቸው ከስልጣን የተነሱትን አምባሳደር መርዋንን እና 12 አመት የጅዳን ቆንስል አንቀጥቅጠው የመሩት የህወሃት ከፍተኛ ሰው አምባሳደር ተክለ አብ ከበደን አስተዳደር ብልሹ አካሔድ ብቻ ሳይሆን የቆንስሉን ሰራተኞች በአደባባይ መመንቀፋቸው በኢህአዴግ የድርጅት አባላትና በሰራተኞች ዘንድ የተፈሩ ሲያደርጋቸው ለዛሬ ከስልጣናቸው መነሳትም የህወሃት አባላት ተጽዕኖ እንዳለበት ራሳቸው ህወሃቶች እየነገሩን ነው። ትናንት አንባሳደር መርዋንን ከስልጣን በማስነሳቱ ረዥም እጅ የነበራቸው ህዎሃትን ጨምሮ የተቀሩት የኢህአዲግ አባል ድርጅቶች ዛሬም በውጭ ጉዳ ከፍተኛ ሃላፊዎች ተጽዕኖ ፈጣሪነት በገሃድ ማሳያው ቀድምው የነገሩን እየደረሰ ማየት መጀመራችን ነው ! ዛሬም ማን ሊመጣ የሚችለው ሃላፊ የዲፕሎማሲያዊ እና የአስተዳደር ብቃት ሳይሆን አነጣጥሮ ተኳሽነቱና የዋለበትን የጦር አውድማ ድረስ በአድናቆት የህወሃት ካድሬዎች ይነግሩን ጀምረዋል።
መዝጊያ …
ለመዝጊያ ፣ ለመደምደሚያ ያህል ትናንት መረጃው ከምጣዱ እንደ ወጣ ስሰማ ያጫወጥኳችሁ አጭር ገደምዳሜ ወግ መዝጊያ መደምደምደሚያ ላድርግ …
ጉልቻ ቢቀያየር …
saudii
ከረፋድ እስከ ቀትር ( ትናንት ማክሰኞ መሆኑ ነው) አንዱ መረጃ ከተለያየ አቅጣጫ እዚህም እዚያም ደረሰኝ ፣ በሹክሹክታ ስሰማው የሰነበትኩትን መረጃ እውነትነት ለማረጋገጥ ቢገደኝም የጭምጭምታውን አንድምታ ለማጣራት መሞከሬ አልቀረም። ብዙ ጣርኩ ግን ከመንግስት የቀረቡት ምንጮቸ እያወቁ “አናውቁም ” ያሉኝ ! ወደው ሳይሆን የእንጀራ ነገር ሆኖባቸው እንጅ አዲስ ነገር እንዳለ በከባቢው የሚታየው ድባብ ያሳብቃል … ይህን እያሰብኩ እያለሁ አንድ የማለዳ ወግ ርዕስ ከአፊ ገባ ” ሳያልቅ የተጠናቀቀው ዘመቻና አልረጋ ያለው የጅዳ ቆንስል ወንበር … ” ብየ ጀመርኩት … መቀጠል ግን አልቻልኩም !
በሰሞነኛው በባጀንበት የሳውዲ ኢትዮጵያውያን ክራሞት ዙሪየ የወገን እንግልት የሚያማቸው ወንድም አሉኝ። እኒሁ ከወደ ጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሁሌም መረጃ የሚያጋሩኝን ወዳጀን ” ሹም ሽር ይደረጋል !” ተበሎ ሰምተው ያልተረጋገጠውን መረጃ ሲያቀብሉኝ “ስማው ብየ እንጅ ፣ እውነት እንኳ ሆኖ ወንበር ቢቀያየር ምን ዋጋ አለው ፣ ለፖለቲካቸው የሚጠቅማቸውን እንጅ ለስደተኛው የሚፈይደውን አይልኩልን ! ” ነበር ያሉኝ … … ” ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም !” እንዲሉ …
የሚፈለገው ሁሉ ይሆናል … የሚያቆመው የለም ! ለሁሉም አንድየ የሚበጀንን ይስጠን ፣ ከሁሉም በላይ ለሃገራችን ምድር አብቅቶ በሰላም በፍቅርና በህብረት የምንኖርባት ሃገር ፣ መድልኦ የማያውቅ ፣ ሃገርና ህዝቡን የሚወድና ለዜጎቹ መብት የሚቆረቆር መንግስት ይሰጠን …ትናንት የሚፈለገው ሁሉ ይሆናል… የሚያቆመው የለም ብለን ነበር የተለያየነው ! አዎ የሚፈለገው ሁኗል ፣ ይሆናል … የሚያቆመው የለም ! …
” ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይሾማል ፣ የኢህአዴግ የድርጅት አባላትና ካድሬዎች ተጽዕኖ ፈጥረው በተናጠልና ተሰብስበው ያሽሩታል ፣ እንዲህ ተጉዘን የት እንደርስ ይሆን? ” ነበር ያሉኝ አንድ አልረጋ ያለውን የጅዳ ቆንስል ሹም ሽር ያስገረማቸው እህት …
እስኪ ቸር ያሰማን
ነቢዩ ሲራክ

በፍቅር ቀንን ለገዥዎቻችን ቀይ ካርድ

$
0
0

ከጌታቸው ሽፈራው

የቫላንታይን ዳይ አብዛኛው ወጣት ቀይ ይለብሳል፡፡ በዚህ ቀን ታዲያ ለምን ይህን ቀይ ምልክት እንደ ቀይ ካርድ ተጠቅመን ምልክት አናደርገውም? በዚህ ቀን ቀዩን የታሰሩትን፣ የሚበደሉትን፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ከፍቅር የነጣጠለ ስርዓት ላይ ምልክት አድርገን አንጠቀመውም?

Valentine day1
በቅርብ አመታት ውስጥ በአገራችን ‹‹Valentine’s Day›› በተለይ በወጣቱ ዘንድ መከበር ጀምሯል፡፡ ካፌዎች፣ ሆቴሎችና ሌሎች መዝናኛዎች ቀኑን በስፋት ለገበያ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ ሆኖም አብዛኛዎቹ ወጣቶች ‹‹ፋሽኑን›› ከማሯሯጥ ያለፈ ትርጉሙን አውቀውት ነው የሚያከብሩት ለማለት ይከብዳል፡፡ የውጭ ባህል ከሆነ ባናከብረው ይመረጣል፣ ፍቅር ምን ባህልና አገር ያስፈልገዋል? ከተባለ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ብናደርገው የተሻለ ነው፡፡

ቅዱስ ቫላንታይን የታሰረበት፣ ከዛም የተገደለበት ዋነኛው ምክንያት በሮማውያን ዘመን እንዲያገቡ ያልተፈቀደላቸውን ወታደሮች አጋብቷል ተብሎ ነው፡፡ ይህ ለእኛ አገር ጠቃሚ ተምሳሌት ነው፡፡ የእምነት አባቶች ለተከታዮቻቸው ማድረግ ያለባቸውን እምነታዊ ተግባር መፈጸም ግዴታቸው ቢሆንም ከመንግስታት ጥቅም ጋር በተጋጨ ጊዜ ሲያስሩና ሲገድሉ ተስተውለዋል፡፡ ቫላንታይን የዚህ ጥቃት ሰለባ ነው፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን እሱ የሚከተለው እምነት በመንግስት ጣልቃ ገብነት ውስጥ ወድቆ ነበር፡፡ ይህ የእኛ የወቅቱ ትክክለኛ ገጠመኝ ነው፡፡

ከወራት በፊት መጅሊስ በቀበሌ ተመርጧል፡፡ በእምነታችን ጣልቃ አትግቡ ያሉት ሙስሊም ወንድሞቻችን እስር ቤት ውስጥ ታስረዋል፡፡ በእድሜ ጠገቡ የዋልድባ ገዳም የሀይማኖት አባቶች አጽም የተቀበረበት ቦታ ሳይቀር ለሸንኮራ አገዳ ማምረቻ ተከልሏል፡፡ በእምነታችን ጣልቃ አትግቡ ያሉት ሙስሊምና የማህበረ ቅዱሳን አባላት ‹‹በጽንፈኛነት›› እየተከሰሱ ነው፡፡

ቅዱስ ቫላንታይን የተከለከሉት ወታደሮቹን እንዳያጋቡ ነው፡፡ በዛን ዘመን ወታደሮቹ ትዳርን ጨምሮ በርካታ ተፈጥሯዊ መብቶቻቸውን እንዳይጠቀሙ ተከልክለው ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባለች አገር መሳሪያ ከያዙትም በላይ ለህዝብ ጥቅምና ለአገር መብት ወታደር ሆነው የሚያገልግሉት አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች ናቸው፡፡ እነሱ ወታደርም ብቻ ሳይሆኑ እንደ ቫላንታይን በየ መስካቸው ቄሶች ሆነው ከህዝብ ጎን የቀሙ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ህዝብ ዴሞክራሲያዊና ተፈጥሯዊ መብቱን በተነጠቀበት ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞቻችን፣ አክቲቪስቶቻችንና ፖለቲከኞቻችን ልክ እንደ ቅዱስ ቫላንታይን እጣቸው እስር ቤት ሆኗል፡፡ በመሆኑም ይህን የ‹‹ፍቅር ቀን›› ስናከብር በርካታ መቶ አመቶችን ወደኋላ ተጉዘን ሳይሆን አሁን ቃሊቲና ቂሊንጦ፣ ማዕከላዊ እንዲሁም በየ ቦታው ታጉረው የሚገኙትን የእኛዎቹን ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ የእምነት መሪዎች፣ ፖለቲከኞችና ህዝብ ብናስታውስ ምን አለበት?

ይህን ቀን ወደ ጾታ ፍቅር እናቅርበው ካልንም የውጭ ባህል፣ የውጭ ታሪክ፣ የቆየ አባባል ከምናስታውሰው ይልቅ ለእኛው ነባራዊ ሁኔታ ቅርብ ነው፡፡ መቼም አገር ሰላም ካልሆነች፣ ህዝብ በሰላምና በፍቅር ካልኖረ የፍቅር ጓደኛሞች፣ የባለ ትዳሮች…..ፍቅር ፍቅር ሊሆን አይችልም፡፡ በአገራችን ባለፉት አመታት ‹‹ብሄር›› የሚሉት መከፋፈያ ባልና ሚስት አፋትቷል፡፡ ወጣቶች ቢዋደዱ እንኳ ቤተሰቦች ‹‹ብሄሯ/ሩ ምንድን ነው?›› የሚል አስቀያሚ ጥያቄ ማንሳት ጀምረዋል፡፡ የጓደኛ፣ የዘመድ አዝማድ ምክርም ተመሳሳይ ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ በብልሹ ፖለቲካችን፣ በከፋፋይ ፖለቲከኞቻችንና ፓርቲዎች ምክንያት ሁለት የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎች በፍቅር የማይኖሩበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡

ይህ ብቻ ግን አይደለም፡፡ በዚህ 23 አመት ህወሓት/ኢህአዴግ አገሩን የሚጠላ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በመወለዱ የሚያፍር፣ ‹‹ጎሳ›› እንጅ ዜግነት እንደሌለው የሚያስብ ወጣት ለመፍጠር ታትሯል፡፡ ሮማውያኑ ፖለቲከኞች ወታደሮች ትዳር እንዳይዙ እንጅ ሮማን እንዳይወዱ አላደረጉምና ከእኛው ስርዓት በእጅጉ የተሻሉ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን አገራቸውን እንዳይወዱ አንዴ ‹‹ቅኝ ገዥ›› ሌላ ጊዜ በዝባዝና ጨቋኝ….ተብለው የፈጠራ ታሪክ ሲማሩ አድገዋል፡፡ እናም ይህን የፍቅረኞች ቀን ፍቅረኞች የተወለዱባትን፣ የሚኖሩባት ኢትዮጵያን እያሰብን፣ ስለ አገር ፍቅር እየተነጋገርን፣ አገራችንን እንድንጠላ የሚያደርጉትን ‹‹ቀይ ካርድ!›› እያሳየን ብንውል ትልቅ ቁም ነገር ይመስለኛል፡፡

እስኪ አሁን ደግሞ የፍቅርን ቀን ወደ ጥንዶች እናውርደው! ይህን ቀን ‹‹የፍቅር ቀን›› አድርጎ ለማክበር መጀመሪያ ሰላም መሆን ያስፈልጋል፡፡ ጓደኛዋ/ባሏ የታሰረባት፣ አገሩ ውስጥ ስቃት በዝቶበት የተሰደደበታ፣ ከዚህም አለፍ ሲል በእግፍ የሞተባት ወጣት ይህን ቀን ‹‹በፍቅር›› ቀንነት ልታከብረው አይቻላትም፡፡ በተመሳሳይ ቀኑ ሚስቱ/ጓደኛው ለታሰረችበት፣ ፤ተሰደደችበትና ለተገደለችበት ወጣትም ‹‹የፍቅር ቀን›› ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህ ወጣች የቀድሞውን ቄስ ከማስታወስ ይልቅ ስለ እውነት መስዋት የሆኑትን ጓደኞቻቸውንና ይህ መከራ የተንሰራፋባትን ኢትዮጵያን እንዲያስታውሱ ይገደዳሉ፡፡ ይህን መከራ ያደረሰውን፣ ከጓደኞቻቸው የነጠላቸውን አካል ሊያወግዙ፣ ሊቃወሙና ምልክት (ቀይ) መስጠት ሊኖርባቸው ነው፡፡

የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጓደኛና ባለቤት ባይታሰር፣ ባይሰቃይ፣ ባይሰደድና ባይሞትም ነገ እንደማይፈጠርበት እርግጠኛ ሊሆን ግን አይቻልም፡፡ ምንም ያህል በ‹‹ፍቅር ቀን›› ደስተኛ መሆን ቢቻል ነገ ወንዱ እንደ ርዕዮት ሚስቱ እንደማትታሰርበት እርግጠኛ ሊሆን አይችልም፡፡ ሴቷም ባሏ ልክ እንደ አንዱ ዓለም፣ አቡበክር፣ እስክንድር፣ በቀለ፣ ውብሸት ….ቧላ እንደማይታሰር እርግጠኛ የምትሆንበት ስርዓት የላትም፡፡ እናም በ‹‹ፍቅር ቀን›› እውነትን በመናገራቸው፣ በእምነታቸው በመጽናታቸው፣ አገራቸውን በመውደዳቸው ከባልና ሚስቶቻቸው፣ ፍቅረኞቻቸው ብቻ ሳይሆን ከልጆቻቸው ተነጥለው የዋሉትን ኢትዮጵያውያን ማስታወስ ሊኖርብን ነው፡፡ የ‹‹ፍቅር ቀን››ን ልታከብሩ ያሰባችሁ! እስኪ ፍቅረኞቻችሁንና የትዳር ጓደኞቻችሁን እነዚህ ካለ ፍትህ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን አድርጋችሁ እሰቡ?

እውነት የቀኑ ትርጉም ከገባን፣ ስለ ፍቅር ከተጨነቅን ስለ ኢትዮጵያ፣ አገሩን እንዳይወድ፣ እርስ በእርሱ እንዲናቆር ስለተደረገው ህዝብ፣ ስለ ጋዜጠኞቻችን፣ ስለ ፖለቲከኞቻችን፣ ስለ አክቲቪስቶቻችን….ስለ እኛ ስለ ኢትዮጵያውያን እያሰብን ልናከብረው ይገባል፡፡ መከራ ፈጣሪውን ስርዓት፣ ህዝብን የሚያናቁረውን ፓርቲና ፖለቲከኞች፣ አገርን የከፋፈለውን አካል፣ ፍቅረኛና ባለትዳሮችን ያለ ፍትህ የነጣጠለው ህወሓት/ኢህአዴግ ልንወቅስ ይገባል፡፡ ቀኑን የምንወክልበትን ቀን መለዮ ሁሉ የቀይ ካድር ምልክት ልናደርገው ይገባል፡፡

የዓረና ፓርቲ ወጣት አባላት በአሰብ ወደብ ዙሪያ ጥልቅ ፖለቲካዊ ውይይት አደረጉ

$
0
0

በአዲስ አበባ የሚገኙ የዓረና ፓርቲ አባል ወጣቶች የአሰብ የባህር በርን በተመለከተ በየካቲት 2/2006 ዓ.ም ፓርቲው በከፈተው አዲስ ጽ/ቤት ጥልቀት ያለው ፖለቲካዊ ውይይት አድርጓል፡፡

በእለቱ ሰፊ ትንተና ያቀረበው ደራሲ እና ፖለቲከኛ ወጣት አስራት አብረሃም ሲሆን በውይይቱ ጊዜም ወጣቶቹ የጦፈ ክርክር አካሄደዋል፡፡ ወጣት ፖለቲከኛው ስለ አሰብ ጉዳይ ሲያብራራ ንጉስ ሐይለሥላሴ በአንድ ወቅት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ወይይት ቀርበው መመለስ ያለበት የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኤርትራዊያን የዜግነት (የኢትዮጵያዊነት) ጥያቄም የአለም አቀፍ ተቋሙ በአግባቡ አጢኖ መመለስ እንዳለበት ሽንጣቸውን ገትረው በመከራከር የኢትዮጵያ አንድነት ሲያጸኑ በህወሀት የአገዛዝ ዘመን ግን የተገላቢጦሽ ድርጊት መፈጸሙ ምን ያህል ኃላፊነት በማይሰማው ግድየለሽ መንግስት እየተመራን መሆኑን ጠቅሶ፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን እያልን ያለነው «አሰብ ይገባናል» ብቻ ሳይሆን “የኛ ነው” ሲል ሀሳቡን አንጸባርቆዋል፡፡
asab port
ቀጥሎም በውይይቱ ወቅት የአልጀርሱ ስምምነት በሁለቱም መንግስታት ስላልተከበረና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እንዲሁም ሉዓላዊነት የሚጻረር ስለሆነ መከበርም እንደሌለበት በመጥቀስ ኢትዮጵያና ኤርትራ አዲስ ድርድር አድርገው የኢትዮጵያ የተፈጥሮ የባህር በር ባለቤትነትም የሚያረጋግጥና ሉዓላዊነታችን የሚያከብር ስምምነት መደረግ እንዳለበት አንስቶዋል፡፡

ኤርትራ በሪፈረንደም (ሪፈረንደም ከሆነ -ምክንያቱም “ነጻነት ወይስ ባርነት” ተብሎ ሕዝባዊ መደረጉ እጅግ አከራካሪ ሆኖ ሳለ) ከእናት አገርዋ ስትገነጠል የኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር ከየት ወዴት እንደሆነ በውል ሳይካለል የተደረገ ችኩል ፍቺ መደረጉ ይታወቃል፡፡
ወጣቶቹ በውይይታቸው ኢትዮጵያ አለአግባብ (በኢህአዲግ ችኩል ውሳኔ የተነሳ) በአመት ከ12 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለጅቡቲ ወደብ ላይ ኪራይ በመክፈል ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ከመዳረጓ ባሻገር የባህር በር አለመኖር ከብሔራዊ ጸጥታ እና ደህንነታችን በቀጥታ የተቆራኘ በመሆኑ የአጋራችን ሰላም አደጋ የተጋረጠበት መሆኑን በአጽንኦት ገልጾዋል፡፡
እናት አገር ኢትዮጵያ ልጇ ሳትክድ ከአፍንጫው አርቆ ማየት የተሳነው አምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂ፣ እናት አገሩን በመክዳት አልፎ ተርፎም የሻእቢያ ሎሌ የሆኑት የህወሀት መሪዎች «ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት ፤ አሰብም የኤርትራዊያን ነው» በማለት ኤርትራ የማታውቀውንና የማይመለከታትን የባህር በር እንድታገኝ ማድረጋቸው፣ በኢህዲግ ዘመን ከተፈጸሙ ታሪክ ይቅር የማይላቸው ከባድ ስህተቶች ቀዳሚ መሆኑ ወጣቶቹ በክርክራቸው ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም አጼ ዮሐንስ የባህር በር አስፈላጊነትን በተመለከተ “እንበለ ባህር በር መንግስት አይጸናም” በማለት ወደር የማይገኝለት የላቀ የአገር ፍቅር እንደነበራቸው፤ ጨፍጫፊው ኮሌኔል መንግስቱ ሀይለማርያምም ቢሆን በአገር አንድነት እና ሉዓላዊነት ጉዳይን በተመለከተ ድርድር እንደማያውቅ እና ጠንካራ አቋም እንደነበረው፣ በአንጻሩ ሁሌ ለኤርትራዊያን የሚያደላው መለስ ዜናዊ እና ፓርቲው «የባህር በር የኛ አይደለም። አመጣለሁ የሚል ካለም ብረት አንስተንም እንታገለዋለን» ማለቱ ከኢትዮጵያ መሪ የማይጠበቅ ንግግር መናገሩ በታሪክ ተዘግቧል፡፡

Arena-Tigray-logoዓረና ፓርቲም የአሰብ ወደብ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ የባህር በር በመሆኑ እና የአለም አቀፍ ህጎችም (International Law) ስለሚደግፋት አገራችን ህጎችን ተንተርሳ ብሔራዊ ጥቅሟን እና ሉዓላዊነቷን ማስከበር እንዳለባት የሚያምን ፓርቲ መሆኑ ይህንኑ ለማስፈጸምም በጽናት እንደሚታገል በፕሮግራሙ አስፍሮት ይገኛል፡፡
በመጨረሻም ወጣቶቹም አሰብም ሆነ ቀይባህር በጠቅላላው ከኤርትራዊያን በፊት የትግራይ ነገስታት እንደሚያውቁት እና የባህር በሩን ላለማጣት አባቶቻችን ከባድ ተጋድሎ አድርገው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ቀይ ባህርን የአረብ ባህር ለማድረግና አባይን ከምንጩ ለመቆጣጠር የነበራቸው ህልም በጽናት መክተው ያስረከቡን በመሆኑ፣ አዲሱ ትውልድ ድርብ አደራ እንደተጣለበት እና ይህንን ጥያቄ የመመለስ ታሪካዊ አደራም እንዳለበት በመጥቀስ ውይይቱ ተደምድሞዋል፡፡ ወይይቱ በተለያየ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ እንደምንቀጥልም ተረጋግጦዋል፡፡

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live