Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ የፊታችን አርብ በሼራተን አዲስ ሆቴል በይፋ ስራ ሊጀምር መሆኑ ተነገረ

$
0
0
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ የፊታችን አርብ በሼራተን አዲስ ሆቴል በይፋ ስራ ሊጀምር መሆኑ ተነገረ፡፡ ተጠሪነቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆነው ይህ የፌደራል መስሪያ ቤት በዋና ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አማካኝነት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ በመግለጫው ኤጀንሲው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ዜጎች መብትና ጥቅም የማስጠበቅ ተልዕኮ እንዳለው የጠናገሩ ወ/ሮ ሰላማዊት በየትኛውም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ልዩነት በሀገራቸው […]

ዛሬ በአርባምንጭ ከባድ የመኪና አደጋ ተከሰተ፣ አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ በፀፀት ህይወቱን አጠፋ!

$
0
0
  በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የመኪና አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በቦታው ከነበሩ አይን እማኞች በተገኘ መረጃ መሰረት አደጋው የተፈጠረው በፍጥነት ሲያሽከረክር የነበረው የሲኖ ትራክ አሽከርካሪ ባለ 3 እግር ባጃጅን ለማትረፍ የቀኝ መስመሩን ትቶ ወደ ግራ በመታጠፍ ፒካፕ መኪናን በመግጨት ከመስመር ያስወጣው ሲሆን፣ በእግረኛ መንገድ ስትጓዝ የነበረች የ13 ዓመት ሕጻንን ጨምሮ በፒካፕ መኪናው ውስጥ […]

ምስክሮችን ፎቶ በማንሳት ተጠርጥረው የታሰሩት ዋስትና ተፈቀደላቸው

$
0
0
የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ድረ ገጽ ሲለጥፉ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች የጠየቁትን የዋስትና ጥያቄ ተቀበለ። መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በምርመራ ላይ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ምስክርነት በመስጠት ፍርድ ቤት ቅድመ ምርመራ ላይ እያሉ፥ ፎቷቸውን በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በመለጠፍ መጠርጠራቸውን […]

የጄ/ል ክንፈ ወንድም የሆኑት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ለቀረበባቸው ክስ መቃወሚያቸውን አሰሙ

$
0
0
የጄ/ል ክንፈ ወንድም የሆኑት አቶ ኢሳያስ ዳኘው ለቀረበባቸው ክስ መቃወሚያቸውን አሰሙ፡፡ ተጠርጣሪው የኢትዮ ቴሌኮም ሀላፊ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ዜድቲኢ ከተሰኘው የቻይና ኩባንያ ጋር በፈፀሙት ውል መከሰሳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው በዚህ ክስ ከዜድቲኢ ጋር 44‚ 510‚ 971.00 (አርባ አራት ሚሊዩን አምስት መቶ አስር ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ) የአሜሪካን ዶላር የግዥ ውል ለጊዜው ስማቸው […]

ንግድን የማሳለጥ (Doing Business) መርሐ ግብር የአንድ ወር አፈጻጸም ግምገማ በጠ/ሚር ጽ/ቤት ሲካሄድ ውሏል

$
0
0
ንግድን የማሳለጥ (Doing Business) መርሐ ግብር የአንድ ወር አፈጻጸም ግምገማ በጠ/ሚር ጽ/ቤት ሲካሄድ ውሏል:: ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ መዋቅራዊ የሥራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ የግል ዘርፉ ንግድን ለመጀመርና ፋይናንስን በቀላሉ ለማግኘት እንዲችል ምቹ ሁኔታ የመፍጠርን አስፈላጊነት መናገራውን እንዲሁም በተለይም ጀማሪ ንግዶች ፋይናንስን በቀላሉ ለማግኘት ያሉባቸውን ማነቆዎች ከመፍታት አኳያ የብድር ሥርዓቱን በመከለስ ተንቀሳቃሽ ንብረትን በመያዣነት ለመበደር የሚያስችል አሠራር […]

Video: “ልዩ ጥቅም” ከማን? ለማን? ለምን?

$
0
0
“ልዩ ጥቅም” ከማን? ለማን? ለምን?

በፖለቲካ አውሬ የተበላችው ድሬዳዋ ጉዳይ! (በ ሙሉጌታ ገዛኸኝ)

$
0
0
ድሬዳዋ ከአመሰራረቷ ጀምሮ ነዋሪዎቿን በአንዳች ፍቅር ያቆራኘች ኮስሞፖሊታን ውብ ከተማ መሆኗን የውጭ ዜጎች ጭምር ይመሰክሩላታል፡፡ የምድር ባቡር ፀጋ የሆነችው ድሬ ለኢትዮጵውያን ከተሞች ሁለንተናዊ ዘይቤ ሆና ዘመናትን ተሻግራ የራሷን አሻራ አሳርፋለች፡፡ ወደ ድሬዳዋ ለሥራ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካቶች መጉረፋቸው አሁን ያለውን የሥነ ሕዝብ ስብጥር ፈጥሯል፡፡  የድሬ ልጆች ልዩ መገለጫቸው ጎሣና ሃይማኖት ሳይሆን ወደ ከተማቸው የመጣ ሁሉ […]

ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

$
0
0
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች በግንባር ለመስራት የሚያስችላቸውን ጥምረት ለመፍጠር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ። ሰነዱን የተፈራረሙት የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ህብረት (ኢዴህ)፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ)፣ የአፋር ህዝቦች ፍትሃዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የአፋር ህዝቦች ነፃነት ፓርቲ እና የኦሮሞ ህዝቦች ፍትሃዊ […]

ክምታደርገው ይልቅ የምትናረው ብዙ ርቀት ይጓዛል –ይኄይስ አእምሮ

$
0
0
ይኄይስ አእምሮ (yiheyisaemro@gmail.com) የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ አላስቆም አላስተኛ ብሏል፡፡ ይህችን ዐረፍ ነገር ስጽፍ ከሌሊቱ 7፡31 ይላል፡፡ ከእኩለ ሌሊት 1፡30 ገደማ አልፏል፡፡ በልጻፍ አልጻፍ ክርክር ከግማሽ ሰዓት በላይ ከራሴው ጋር ተሟግቻለሁ – “መጻፉ ብቻውን ምን ዋጋ አለው?” በሚል፡፡ ግን ይሁን ግዴለም  – ከዕንቅልፋችን ስንባንን ለ“እንዲህም ተብሎ ነበር” የታሪክ ማኅደራችን አንድ ነቁጥ ግብኣት ነው፡፡ ከትምህርቱ ዓለም ወደ […]

አባካችሁ የለውጡን ኃይል የነውጥ ኃይል ከመሆን አድኑት!(አስቴር በዳኔ)

$
0
0
የለውጡ ኃይል የነውጥ ኃይል እንዳይመስል ከባድ ጥንቃቄ የሚያስፈልግበት ሰዓት ላይ እንገኛለን፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት ሀገራችን ዙሪያዋን ተወጥራ በጭንቅ በተያዘችበት ሰዓት በፖለቲካዊ መፍትሔ ሳይሆን በተዓምራዊ ኃይል ሀገራችንን ከከበባት የስጋት ባህር ከፍሎ የሚያሻግረን ሙሴ ስንመኝ ነበር፡፡ በወቅቱ ሙሴ ይሆነናል ብለን ተስፋ የጣልንበት ሰው ወደስልጣን ወጣ፡፡ ደስ አለን “ያሰብኩት ተሳካ ያለምኩት ደረሰ” ብለን አዜምን፡፡ የለውጡ ሐዋርያት “ኢትዮጲያዊነት ሱስ […]

በአማራና በቅማንት ህዝቦች ሰላም ጉዳይ ምክክር እየተደረገ ነው

$
0
0
በአማራና በቅማንት ህዝቦች ሰላም ጉዳይ ሳንጃ ከተማ ላይ ምክክር እየተደረገ ነው። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ሳንጃ ከተማ እየተካሄደ ባለው የሰላም ውይይት ከአካባቢው ሰባት ወረዳዎች የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ከአማራ ክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው። ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን። ዘጋቢ፦ ደጀኔ በቀለ

ለቀድሞ የወላይታ ንጉሦች ካዎ ሞቶሎሚና ካዎ ጦና በሶዶ ከተማ ሀውልት ሊቆምላቸው ነው

$
0
0
የወላይታ ዞን ተጠባባቂ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የሀውልት መሰረት ድንጋዩን ሲያስቀምጡ እንደገለጹት ለትውልድ አርአያ ለሆኑ የብሔሩ መሪዎች ኃውልት ማቆም አስፈልጓል። ከሁለቱ የቀድሞ ንጎሦች በተጨማሪ ለቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለአቶ ፍሬው አልታዬ ሀውልት ይቆምላቸዋል ነው ያሉት። ኃውልቶቹ ከቱሪስት መዳረሻነት ባለፈ ታሪክን ለትውልድ ጠብቆ ለማቆየት እንደሚረዱ ተገልጿል። ምሁራንን ያሳተፈ ኮሚቴ ተዋቅሮ በተካሄደ ጥናት መሰረት ለሶስቱ የቀድሞ […]

የሚያድግ ጥጃ ከገመዱ የሚወጣ ቂጣ ከምጣዱ!! እንዲሉ

$
0
0
1/ የ1966ቱ አብዮት ግርግር ሁሉንም በየፈተቱ ከእንጉልቻው እንዲነሳ አድርጎ ግን ሲያልቅ አያምር ሆነና አንድ ትውልድ አስበልቶ በከፋ ሁኔታ ተንኮታኩቶ በመውደቅ ሕዳጣኖች (የባንዳ ትውልዶች) በለስ እንዲቀናቸው አድርጎ አለፈ።በተለይ ኢላማ የነበረው ›አማራውን‹ በሁሉም ዜጎች በኩል ፈላጭ ቆራጭ፤ጨቋኝ ፤ ትምክህተኛ ብሎ በመፈረጅ ከጫፍ እስከ ጫፍ ጠላቶቹ እንዲበዙ የውሸት ትርክት በመተረክ አማራው በጥርጣሬና ስጋት የሚታይ በበሬ ወለደ የፖለቲካ ጫጫታ […]

እስከ የካቲት 21 ድረስ ብቻ 714 ህገ ወጥ ቤቶች ፈርሰዋል ይላል የወላይታ ዞን መስተዳደር (አብነት ታምራት)

$
0
0
የወላይታ ዞን አስተዳደር ህገወጥ ቤቶችን ለማፍረስ በሚል በወሰደው እርምጃ በተፈጠረ ግጭት 4 ፖሊሶችን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ሞተዋል የሚለውን መረጃ የሀሰት ነው ሲል አስተባበለ፡፡ የዞኑ ፖሊስም ሆነ የዞኑ አስተዳደር በሰጡት መግለጫ የሞተው አንድ ግለሰብ ነው ብለዋል፡፡ ግለሰቡ የካቲት 20/2011 ዓ.ም በሶዶ ከተማ ሁምቦ ላሬና ተብሎ በሚጠራው ቀበሌ የገነባውን ህገወጥ ቤት በራሱ ፈቃድ ለማፍረስ ሲሞክር ከወጣበት ጣሪያ […]

የሕብር ሬዲዮ የካቲት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ፕሮግራም

$
0
0
የለገጣፎ የቀድሞ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ጋዜጠኛ የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት መሬቱን ሲቸበችቡ ኖረው ዛሬ ሕገ ወጥ ማለታቸው ለምንድነው ሲል ያብራራዋል ከአቶ መኮንን ተስፋዬ ጋር ያደረግነው ቃል-መጠይቅ   (ያድምጡት) አቡን በርናባስ በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ ለቤተ-ክርስቲያኑዋ ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል የሚለውን ጨምሮ ተያያዥ ጉዳዮችን አብራርተዋል  ሕዝቡ ከጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ምን ይጠብቃል? (ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም ዜናዎቻችን ለማ መገርሳ የለገጣፎ ቤት የፈረሰባቸውን ራሳቸው […]

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይና ለብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን –በሰሎሞን ዳኞ

$
0
0
የዶ/ር ዓብይ መንግሥት አልተቻለም! እንደ ራስ ዳሸን ተራራ የተቆለሉትን የአገራችንን ፈርጀ ብዙ ችግሮች ለመፍታት ቁርጠኛነቱን እያስመሰከረ ነው፡፡ የሰማነውን አጣጥመን ሳንጨርስ ሌላ አዳዲስ የምሥራቾችን በላይ በላዩ ያሰማናል፡፡ የተነገሩን ነገሮች ሁሉ ወደ ተግባር እንደሚለወጡም አንጠራጠርም፡፡ አንዳንድ ውጤቶችንም እየተመለከትን ነው፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ብሔራዊ ዕርቀ ሰላም የሚባል ኮሚሽን ስለመመሥረቱ የምሥራች ተበሰረልን፡፡ ዶ/ር ዓብይንና መንግሥታቸውን ምስር ብሉ ብለናል! ከሰላም በላይ […]

በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተመርቆ ዛሬ ሥራ ጀመረ

$
0
0
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ይገኛሉ ተብሎ ቀደም ሲል ተነግሮ የነበረ ቢሆንም በመጨሻው ሰዓት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታዋ አምባሳደር ብርቱካን አያኖና የአሜሪካ መንግግስት ባለስልጣናት በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል:: የለማ መገርሳ ንግግርን ያካተተውን ጠቅለል ያለውን ዘገባ ይመልከቱ

የኢትዮጵያ መሬት ችብቸባ፤ በታሪክ እይታአጼ ዮሐንስና አጼ ካሌብ ቢኖሩ አንዴት ያዝኑ!

$
0
0
ሕብረት ሰላሙ ከጥንቶቹ ጀግኖቻችን፤   እንደሚታውቀው፤ አጼ ዮሓንስን እጅግ በጣም ከሚያስደንቃቸውና ከሚያስከብራቸው ታሪካቸው ዋነኛው፤ ለውድ ሐገራቸው፤ ለኢትዮጵያ፤ ሉዓላዊነትና ዳር ድንበር መከበር በቆራጥነት ይከላከሉ የነበረውና ሕይወታቸውንም የሰዉለት መሆኑ ነው። የጀግናው የአጼ ዮሐንስ ራስ ተቆርጦ ሱዳን ከተወሰደ ልክ 120 ዓመት ሆኖታል። እስካሁን አልተመለሰም!   አጼ ካሌብማ ይገዙ የነበረው፤ የዛሬውን አያድርገውና፤ ኢትዮጵያ ከኃያላን መንግሥቶች አንዷ በነበረችበት ዘመን በመሆኑ፤ […]

ሽግግር ስንል ምን ማለታችን ነው? –ገለታው ዘለቀ

$
0
0
ለመሆኑ ሽግግር ስንል ምን ማለታችን ነው? ብለን ከጠየቅን የሚከተሉት አራት መሰረታዊ ነገሮች ወደ አእምሯችን ይመጣሉ አሻገሪ ኣካል ተሻጋሪ ነገሮች የሽግግር ዘዴ (methodology) የጊዜ ሰሌዳ (Time frame) እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት አራት ጉዳዮች ሽግግር የምንለውን ሃሳብ በጥራት እያገላበጥን እንድናየው ይረዱናል። በመሆኑም በነዚህ ጉዳዮች ላይ ጥቂት እንወያይ። አሻገሪ ኣካል ኢትዮጵያ ሽግግር ላይ ናት ካልን በአንደኛ ደረጃ የምንመለከተው ነገር ማን ነው ኣሻጋሪው ሃይል? ማን […]

ብሪታንያ የአጼ ቴዎድሮስን ፀጉር ለኢትዮጵያ ልትመልስ ነው

$
0
0
 የብሪታንያ ሙዚዬም የአጼ ቴዎድሮስን ፀጉር ሊመልስ ስለመሆኑ ተሰማ። ሙዜየሙ የአጼ ቴዎድሮስን ፀጉር ለመመለስ ያሰበው በኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ መሆኑን ገልጿል። ባለፈው ዓመት ታዲያ የአጼ ቴዎድሮስ ጸጉር በሙዜየሙ ውስጥ እና በኦንላይን ለዕይታ መብቃቱ ብዙዎችን ማስቆጣቱ ይታወሳል። አጼ ቴዎድሮስ ከ150 ዓመታት በፊት በአውሮፓውያኑ 1968 መቅደላ ላይ ለእንግሊዝ ወታደሮች እጅ አልሰጥም በማለት ራሳቸውን መሰዋታቸው የሚታወስ ነው። ይህንን ተከትሎ ታዲያ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live