Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አቶ አርከበ እቁባይ ለሕወሓት መልቀቂያ  አስገቡ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው

$
0
0
አቶ አርከበ እቁባይ ለሕወሓት መልቀቂያ  አስገቡ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ጋዜጠኛ እሊያስ መሰረት አስታወቀ:: ኤሊያስ በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው “”አቶ አርከበን ህወሀት ጋር ተለያይተዋል እየተባለ ነው። የዚህን መረጃ እውነትነት ሊያረጋግጡልኝ ይችላሉ?” ብዬ ለጠየቅኳቸው መልስ በኢሜይል በሰጡኝ መልስ “አመሰግናለሁ! ይህ ሀሰት ነው” ብለው መልሰውልኛል።” ብሏል:: 

ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ

$
0
0
እንግሊዝ በርኒንግሃም ውስጥ በተደረገው ሩጫ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ:: በሌላ በኩል አትሌት አልማዝ ሳሙኤል በ3,000 ሜትር ተወዳድራ በጥሩ ሰዓት አንደኛ በመውጣቷ የ2019 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ለመሆን በቃች:: – ዛሬ በመቀሌ በተደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ባህርዳር ከነማን 1ለ0 አሸንፏል::  

‹‹7 ሚሊዮን ካድሬ መጅገሮች ሳይነቀሉ የኢኮኖሚ ለውጥ አይመጣም!!!››

$
0
0
ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY ‹‹7 ሚሊዮን ካድሬ መጅገሮች ሳይነቀሉ የኢኮኖሚ ለውጥ አይመጣም!!!››            ለቪዥን ኢትዮጵያ ሀገር ወዳድ ምሁራን የተበረከተ    ሚሊዮን ዘአማኑኤል  ህብለ ሰረሰር በሌላቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኦዴፓ/ኢህአዴግ ተከቦል፣ የተጠመጠሙበት የፖለቲካ ፓርቲዎ አንዳችም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፍኖተ ካርታ ማቅረብ እስካሁን አልቻሉም፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ […]

ከኢሕአዴግ ፌዴራሊዝም ወደ መደመር ፌዴራሊዝም እንሻገር |ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

$
0
0
የኢሕአዴግ ፌዴራሊዝም በብሔር ወይም በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ነው እንዳልል ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሔሮች ሆኑ ሁሉንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ማካተት ቀርቶ ባብዛኛው እንኳን የማያሳትፍ ስለሆነ በተለምዶ የዘር (ethnic) ፌዴራሊዝም የሚባለውን አጠራር መጠቀም አልችልም። አሁን ያለው ፌዴራሊዝምን “የኢህአዴግ ፌዴራሊዝም ” ከማለት በቀር ሌላ ቃል ላገኝለት አልቻልኩም። በዚያው መልክ ወደፊት እንዲኖረን የምሞግተው ፌዴራሊዝም በዓይነቱ አዲስ መሆን ያለበት ስለሆነ “የመደመር ፌዴራሊዝም […]

ሕዝብ እንዲሰማህ ሰፊ አፍ ይኑርህ!

$
0
0
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) እንደሚታወቀው ለመስማት ተናጋሪና ሰሚ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ተመራምሮና መጻሕፍት አገላብጦ ሳይሆን ተባራሪ ዜናና አሉቧልታ በጀሮው ከጣራ እንደተቸከለ አንቴና እየቃረመ ያወቀ ለሚመስለው መንጋ ለመስማት እንደ ዲሽ የተንከረፈፈ ጆሮ ለመናገርም እንደ ሰማይ የተከፈተ አፍ ያስፈጋል፡፡ የፊደል ቆጣሪ ማይም እንደ ዝናብ አብራ በፈላባት ኢትዮጵያ ቀርቶ ፈላስፋዎችና ተመራማሪዎች በሞሉበት አሜሪካና አውሮፓም ሰፊ አፍ ዘወትር ያሸንፋል፡፡ ዓለም ከተፈጠረች […]

ቴዎድሮስ ካሳሁንየአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ትርዒት በዲቪዲ ተዘጋጅቶ የፊታችን ቅዳሜ ለሕዝብ እንደሚደርስ ታወቀ

$
0
0
ዝነኛው ድምፃዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ/ም 25 ሺህ ሕዝብ በታደመመበትና በታሪካዊው የአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ትርዒት በዲቪዲ ተዘጋጅቶ የፊታችን ቅዳሜ ለሕዝብ እንደሚደርስ ታወቀ:: ይህ ሲዲ ለገና በዓል ሊቀርብ የነበረ ቢሆንም በአርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬ ጥያቄ መሰረት መራዘሙን ዘ-ሐበሻ ቀደም ሲል መዘገቡ ይታወሳል:: ቴዲ ከ16 ዓመታት የሙያ […]

ኦዴፓ ለሕወሓት  ክስ ምላሽ ሰጠ –ፌደራል ስርዓቱ ይፈርሳል የሚባለው የኦሮሞን ሕዝብ ለማደናበርና ለማጋጨት ያለመ ነው ብሏል

$
0
0
ህወሓት የተመሰረተበትን 44ኛ ዓመት በማስመልከት ባወጣው መግለጫው በአሁኑ ሰዓት በትግላችን ያረጋገጥነውን ህገመንግስትና ፌደራላዊ ስርዓት ለማፍረስ የውስጥ የትምክህት ሀይልና ጸረ ልማታችን የሆኑ የውጭ ሀይሎች አንድ ላይ በመቀናጀት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በመሰረቱ ይህ ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ሀገራችንን ወደ ከባድ መተላለቅና መፈራረስ ሊያስገባት የሚችል አደገኛ አካሄድ መሆኑን ተረድታችሁ መላው ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ ትግል ሀገራችንና ህገ መንግስታችን […]

በሸዋ ሮቢት ከተማ ጎማ እየተቃጠለ ለሰአታት መንገድ ተዘግቶ ዋለ

$
0
0
የዛሬው መንገድ መዝጋትና ጎማ ማቃጠል ደግሞ ለየት ያለ ነበር፡፡ ከስፍራው እንደደረሰን መረጃ በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋ ሮቢት ከተማ አንዲት ሴት በጩቤ ተወግታ ስትሞት አብሯት የነበረው ህፃን ልጇ ደግሞ በመታፈን ህይወቷ አልፎ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ሰዎች በተገደሉበት ቤት ውስጥ ታፍኖ የነበረ ሌላ ህጻን ልጅ ወደ ህክምና ተወስዶ በተደረገለት እገዛ በጥሩ ጤንነት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡  ይህን ድርጊት በመፈፀመም […]

በለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሆነ አቶ ለማ መገርሳን ማነጋገር አትችሉም ተባሉ

$
0
0
  የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ሲያፈርስ ዋለ:: ትናንት ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ግለሰቦች ዛሬ ጠዋት ተሰባስበዉ ወደ ኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳን አቶ ለማ መገርሳ ቢሮ አቤቱታቸውን ለማቅረብ  ቢያመሩም እሳቸዉን ማናገር አትችሉም ተብለው ወደ ክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ  ተልከዋል:: ነገር ግን […]

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ ስምምነት ሊፈፅሙ ነው”

$
0
0
  በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ለንባብ ለሚበቃው መንግስታዊው ‹‹ኢትዮጵያን ሄራልድ›› ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ ስምምነት ሊፈፅሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህም በሁለቱ አገራት መሀከል ያለውን አዲስ ግንኑነት በህጋዊ ማእቀፍ ለማረጋገጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በአገራቱ መሀከል የሚኖረውን የንግድ ልውውጥ በተመለከተ ሰፊ ውይይት መደረጉን የጠቀሱት አምባሳደር ሬድዋን በዚህ […]

በ1997 ዓ.ም. የተደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስና የህዝብ ጭፍጨፋ በባለሙያ ተጠንቶ በመፅሀፍ መልክ እንዲቀመጥ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ

$
0
0
በ1997 ዓ.ም. የተደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስና የህዝብ ጭፍጨፋ በባለሙያ ተጠንቶ በመፅሀፍ መልክ እንዲቀመጥ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ በአዲስ አበባ ታትሞ የሚሰራጨው ሳምንታዊው በረራ ጋዜጣ በዛሬ እትሙ እንደዘገበው ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አና ጎሜዝ የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ በምርጫ 97 የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩት አና ጎሜዝ በወቅቱ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ በተመለከተ እሳቸው ዘንድም […]

የህዳሴው ግድብ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ለቻይናዊያን ተሰጠ

$
0
0
ስራው የቆመውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማስቀጠል የኢትዮጵያ መንግስት ስራውን ሙሉ በሙሉ ለቻይናዊያን መስጠቱ ታወቀ፡፡ የግድቡን ግንባታ በተመለከተ ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈፀመ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በትላንትናው እለት የተፈራረመው ስምምነት40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ሲጂጂሲ CGGC የተባለው የቻይናው ኩባንያ ግድቡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2020 ስራ እንዲጀምር የሚያስችሉ ግንባታዎችንና ሌሎች ስራዎችን እንደሚያከናውን ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ […]

በረቀቀ መንገድ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ

$
0
0
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ፡፡ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ A 77608 በሆነ «አቶዝ» የቤት መኪና በባለሙያ በመፍታት ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረየስ ጠብመንጃዎች ጥር 28 ቀን 2011 ዓ/ም […]

የአባገዳዎችን ጥሪ በመቀበል የኦነግ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገባ ነው

$
0
0
  በአባገዳዎች እና እርቅ ቴክኒክ ኮሚቴ ባደረጉለት የሰላም ጥሪ መሰረት ታጣቂ ሀይሉ ከትላንት ጀምሮ ወደ ተዘጋጀለት ካምፕ እየገባ ነው፡፡ ታጣቂ ሀይሉ በቤጊ፣ጊዳአያና፣ በቦ ገምቤል ፣ መንዲ እና ጊዳሚ ወረዳዎችም በህዝቡ እና በመንግስት አካላት አቀባበል እየተደረገለት ነው፡፡ ከምዕራብ ዞን ብቻ ከአስር ሺህ በላይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መመለሳቸውን ቀድሞ የቱለማ አባገዳ በየነ ሰንበቶ […]

እነሆ መሃከለኛው መንገድ ! አማራጭ የሽግግር ኣሳብ

$
0
0
ገለታው ዘለቀ ከተባበረችው አሜሪካ 2/19/19 መግቢያ ኢትዮጵያ ሽግግር ላይ በመሆኗ ዜጎቿ ተስፋን ሰንቀዋል:: ምንም እንኳን ስጋቶች በግራም በቀኝም የተደቀኑ ቢሆንም ነገር ግን የህዝቡ ተስፋ ሃያል ነው። በተጨባጭ እየተወሰዱ ያሉ የለውጥ ርምጃዎች ብዙዎችን አነቃቅተዋል። ታዲያ የከረምንበት ፖለቲካ ውጤትና ራቅ ካለ ዘመን ጀምሮ ሲንከባለል የመጣ ችግር አለና ይህን የማሰናከያ ድንጋይ ገለል ኣድርጎ ዴሞክራቲክ ኔሽን ለመሆን ስርዓታዊ ለውጦችን […]

በሐዋሳ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በለሊት ተጀመረ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) በሐዋሳ ከተማ የሲዳማ ክልል እንሁን ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔው ዘግይቷል በሚል የተጠእራው ሰላማዊ ሰልፍ ገና ሳይነጋ ከጠዋቱ ከ 11 ሰዓት ጀምሮ መካሄድ ጀመረ:: በዘመቻ መልክ የተጠየቀ ዘንድሯዊ ጥያቄ የለንም:: ሰማ ዕቶቻችን ምስክር ናቸው ለሕገ መንግስታዊ ጥያቄያችን ሕገመንግስታዊ መልስ እንሻለለን ሕገመንግስታዊ መብታችን ይከበር:: የሪፈረንደም ቀን ተቆርጦ ይነገረን ሕገመንግስቱ ለሰጠን መብት የግለሰቦች ይሁንታ አያስፈልግም የሲዳማ ሕዝብ መንግስትን […]

“ዜጐችን ማፈናቀል በአስቸኳይ ይቁም!!”–የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ መግለጫ

$
0
0
በኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በ01 እና 02 ቀበሌዎች፣ ጭላሎ፣ ወበሪ፣ ለገዳዲ ቄራ፣ ገዋሳ፣እና በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን “ህገወጥ ግንባታዎች ናቸው፤ ለአረንጓዴ ልማት ይፈለጋሉ” በማለት ከየካቲት 12 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ በሃይል በማፍረስ ላይ ይገኛል። የከተማዋ ከንቲባ ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለፁትም በቀጣይም ከ12 ሺህ በላይ ቤቶችን […]

የጎንደር ሕብረት ለጎንደር ተፈናቃዮች አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር መመደቡን አስታወቀ

$
0
0
  “በመሃልና በምዕራብ ጎንደር በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ሲዘገብ ሰንብቷል። ቀውሱ በመተማና አካባቢው ሲጀምር መንግሥት ፈጥኖ እርምጃ ባለመውሰዱ ልዩ ልዩ አጀንዳ ያላቸው ታጣቂ ሃይሎች ሁኔታውን በመጠቀም ቀውሱ እንዲባባስ ለማድረግ እድል አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት ከመተማ እስከ ጎንደር እና ከጎንደር እስከ ትክል ደንጋይ ከዚያም አልፎ ወደ ሁመራ በሚወስደው መንገድ ሁሉ ችግሩ እንዲባባስ ሆኗል። […]

19 ኤርትራዊያን ኬንያ ውስጥ ታሰሩ

$
0
0
  በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠሩት 19 ኤርትራዊያን በዛሬው እለት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘገቡ፡፡ እንደመረጃው ከሆነ ተጠርጣሪዎቹ በፕራዶ መኪና የኬንያን ሞያሌ ከተማ ሊያቋርጡ ሲሉ የተያዙት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ከኢትዮጵያ ተነስተው የኬንያን ድንበር ሲያቋርጡ የተያዙት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ክስ ስለቀረበባቸው ጠፍተው እየሄዱ መሆኑን ገልፀው እቅዳቸውም ዩኔንኤችሲአር ጥገኝነት መጠየቅ እንደነበር ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ […]

የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ(ጉህን) በዛሬው እለት መግለጫ አውጥቷል

$
0
0
የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ(ጉህን) በዛሬው እለት መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው  በጉራጌ ዞን የሶዶ እና የሚቄ ማዕከል የወረዳ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ያደነቀው ጉህን ‹‹የጉራጌን ህዝብ ጥያቄ በአግባቡ መመለስ የዴሞክራሲ ስርዓት ከማስፈን አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡›› ብሏል፡፡ ይሁን የመስቃን ማእከል ወረዳ ነዋሪዎችም ተመሳሳይ ጥያቄ እንዳላቸው ገልፆ ‹‹በተመሳሳይ መልኩ ሰላማዊ እና ህጋዊ በሆነ መልኩ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ተደርጎ በአፋጣኝ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live