Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በዶክተር አብይ ደብዳቤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተባረሩት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት ተመደቡ

$
0
0
የሕወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ ከፓርላማ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትርነት መባረራቸው ይታወቃል፡፡ ይሁንና አሁን በኢሕአዴግ ጽሕፈት ቤት በአማካሪነት እንደተመደቡ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡  የሕወሓትና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር በመሆን እስከ ቅርብ […]

ደብረጺዮን ተስፋ ቆረጠ? –በጎረቤቶቻችንም በፌደራል መንግስቱም እምነት የለንም አለ

$
0
0
የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዴብረጺዮን ገብረእሚካኤል በጎረቤቶቻችን ላይም ሆነ በ ፌዴራል መንግስቱ እምነት የለንም ሲል ተናገረ:: በሕወሓት ተከፋይ ካድሬዎች በኩል እንዲለቀቅ በተደረገው ቭዲዮ ደብረጽዮውን በጠለምት ከተማ በትግርኛ ባደረገው ንግግር መሳሪያዎቻችን እያጸዳን ነው ማለቱ ተሰምቷል::

ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ከእስር እንዲፈቱ ወሰነ

$
0
0
ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው ከእስር እንዲፈቱ ወሰነ

በሰሞኑ በቅማንትና በአማራ ማህበረ ሰቦች መካከል ስለተፈጠረው ግጭት ከጎንደር ህብረት የተሰጠ መግለጫ

$
0
0
gyisma83@gmail.com ለኢትዮጵያ አንድነት www.gonderhibret.org 4126 Deerwood Trail, Eagan MN 55122 Tel 651 808 3300 ጥር 9 2019 ዓ. ም. በሰሞኑ በመሃከልና በምእራብ ጎንደር የደረሰው የብዙ ዜጋዎች መሞት፣ መፈናቀልና የንብረት መውደም በጣም አሳዝኖናል፤ ልባችንንም ሰብሮታል። በቋንቋ፣ በባህል፣ በሃይማኖት አንድ የሆኑ፣ ተጋብተውና ተጎራብተው አንድ ስነልቦና አንግበው በክፉም ሆን በደጉ ጊዜ ሳይለያዩ የኖሩ ወንድማማች ማህበረ ሰቦችን ሲዳሙ እያየን […]

“ጎንደር የራሱን ክልል መመስረት አለበት”–የጎንደር ሕብረት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን

$
0
0
“ጎንደር የራሱን ክልል መመስረት አለበት” – የጎንደር ሕብረት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን

ጥብቅ መረጃ –አላሙዲ አዲስ አበባ እንደደረሰ መታሰር ያለበት ለምንድን ነው?

$
0
0
ጥብቅ መረጃ – አላሙዲ አዲስ አበባ እንደደረሰ መታሰር ያለበት ለምንድን ነው?

የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሚያከናውኑ ሰዎች ቆጠራ ከመጀመራቸው በፊት ሊምሉ ነው

$
0
0
መንግስት አሁን ቆጠራውን ከሚያደርግ ሃገር በማረጋጋት ሥራ ላይ ቢጠመድ ይሻለዋል – የቆጠራውን ውጤት ተከትሎ ሊከሰት ለሚችል ግጭት አልተዘጋጀም እየተባለ አስተያየት በሚሰጥበት በዚህ ሰዓት  ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራው ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ወደ ሥራው ከመግባታቸው በፊት ቃለ መሃላ እንደሚፈፅሙ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡ ቆጠራውን በተመለከተ በቂ ዝግጅት […]

በነአብዲ ኢሌ የክስ መዝገብ ላይ የምስክሮች ማንነት ለተከሳሶች እንዳይገለጽ ተፈቀደ

$
0
0
ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ቀርበው የቀረበብኝ ክስ ድራማና ውሸት ነው ያሉት አብዲ ኢሌ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረብይ:: በዛሬው የችሎት ውሎ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በሶማሌ ክልል የቀድሞ ርእሰ መስተዳድር  አብዲ መሀመድ የክስ መዝገብ ላይ የምስክሮች ማንነት ለተከሳሶች እንዳይገለጽ ያቀረበውን አቤቱታ ተቀበለ። ክስ ከተመሰረተባቸው 47 ግለሰቦች ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የተነበበላቸው አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር፣ […]

የትግራይ ልዩ ሃይል መካከል 29 የልዩ ሃይል አባላት ለመጥፋት በዝግጅት ላይ እያሉ ተይዘው በወታደራዊ እስር ቤት ገቡ

$
0
0
በራያ ወረዳዎች እና አካባቢው ከተሰማሩት በሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ልዩ ሃይል መካከል 29 የልዩ ሃይል አባላት; ለመጥፋት በዝግጅት ላይ እያሉ ተይዘው በወታደራዊ እስር ቤት መግባታቸውን የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር አቶ ደጀኔ አሰፋ ገለጸ::  እንደ አቶ ደጀኔ ገለጻ  እነዚህ ሊያመልጡ ሲሉ የተያዙት የልዩ ኃይል ወታደሮች ሕወሓት በራያ ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወም ከህዝቡ ጋር መጣላት […]

ጌትሽ ማሞ በሚኒሶታ አስገራሚ ብቃቱን መድረክ ላይ ያሳየበት ሙዚቃ –‘የጠላሽ ይጠላ”

$
0
0
ጌትሽ ማሞ በሚኒሶታ አስገራሚ ብቃቱን መድረክ ላይ ያሳየበት ሙዚቃ – ‘የጠላሽ ይጠላ”

ሁለት የራያ ተወላጅ ዲፕሎማቶች ሕወሓትን ለቀቁ

$
0
0
ሁለት የራያ ተወላጅ ዲፕሎማቶች ሕወሓትን ለቀቁ:: ሌሎችም እየተከተሉ ነው:: በራያ ሕዝብ ላይ ሕወሓት እየፈጸመ ያለውን ግፍ በማውገዝ፣ የራያ ማንነት እንዲከበር ሕዝቡ እየጠየቀ ያለው ጥያቄ እንዲመለስ የሚደግፉ፣ በፓርቲው ውስጥ የራያ ተወላጆች መገፋትና አለመታመንን የተቃወሙ ሁለት የራያ ተወላጅ ዲፕሎማቶች ሕወሓትን መልቀቃቸው ታወቀ:: በሳዑዲ አረቢያ በዲፕሎማትነት እያገለገለ የሚገኘው ሚስባህ ማህመድ እና በካይሮ በዲፕሎማትነት እያገለገለ የሚገኘው አሊ መሀመድ ሕወሓትን […]

አቶ ኤርሚያስ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የላኩት ደብዳቤ

$
0
0
የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም/ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት/ አ/አ ከ20 አመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ አገር ቤት ተመልሼ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ስስራ እንደመቆየቴ፣ የስራዬ ባህሪ ከባንኮች ጋር ያገናኘኝ ነበርና አዘውትሬ ወደተለያዩ የአገሪቱ ባንኮች እሄድ ነበር፡፡ ሁሉም ባንኮች ግን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የማይጠቀምና የደንበኞችን ፍላጐት በተቀላጠፈ መልኩ የማያረካ ኋላቀር የባንክ አሰራር ይዘው ነበር የማገኛቸው፡፡ በ2001 ዓ/ም […]

ኤርሚያስ አመልጋ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በላኩት ደብዳቤ ዘመን ባንክን ቦይኮት አድርጉ ብለዋል (በቪዲዮ የቀረበ)

$
0
0
የአክሰስ ሪል እስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ አሜልጋ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የበላይ አመራሮች ጋር በጥቅም በመተሳሰር የቀድሞውን ኢምፔሪያል ሆቴል ያለምንም የጨረታ ሂደት በ75 ሚሊየን ብር ውል ስምምነት በማሰር ሽያጭ እንዲፈፀም በማድረእግ የድርጅቱ ወቅታዊ ዋጋ 51 ሚሊየን ብር መሆኑ እየታወቀ በተጋነነ ዋጋ እንዲሸጥ በማድረግ በመንግስት ሀብት ላይ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል […]

“ከኢትዮጵያዊነት አንሸሽም” –ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ –ክፍል ፩ | SBS Amharic

$
0
0
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር፤ ስለ ንቅናቄው ዓላማና ግቦች፣ የማንነት ፖለቲካና የወቅታዊውን የኢትዮጵያ ጉዳዮች አንስተው ይናገራሉ። – SBS Amharic

አርበኞች ግንቦት 7 በደብረማርቆስ ሕዝባዊ ስብሰባ አደረገ

$
0
0
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ መሪዎች ዛሬ በደብረማርቆስ ከተማ ከሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ጋር ተወያዩ። የድርጅቱ አመራሮች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል:: አርበኞች ግንቦት 7 የዜግነት ፖለቲካ ብቸኛው ብሎም ሀገራችን ከገባችበት የዘርና የመከፋፈል አደጋ የምንወጣበት ስልት ነው ብሎ እንደሚያምን አመራሮቹ በስብሰባው ላይ ተናግረዋል:: –

ልእልት ሳራ ግዛው በ90 አመታቸው አረፉ

$
0
0
የግርማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ልጅ የልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ ባለቤት የሆኑት ልዕልት ሳራ ግዛው በ90 አመታቸው ማረፋቸው ተሰማ፡፡ ልእልቲቷ የንጉሡን አመራር የሚቃወሙ የኢትዮጵያ ወጣት ተማሪዎች ንቅናቄ አመራር ከነበሩት አንዱ የነበረውና አፍንጮ በር አካባቢ የተገደለው የጥላሁን ግዛው ታላቅ እህት ናቸው፡፡   በ1920 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት እኚህ ልዕልት እቴጌ መነን ካለፉ በኋላ በእሳቸው ምትክ የንጉሱ ልዩ […]

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት አንድ አስገራሚ የሰርግ ስነስርአት ተከናውኗል

$
0
0
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት አንድ አስገራሚ የሰርግ ስነስርአት ተከናውኗል፡፡ ሙሽራው አንተነህ አፖሎ የሚባል ሲሆን ለ14 አመታት በእስር ቤቱ የቆየ ታራሚ ነው፡፡ ሙሽሪት መስከረም ደገፉ ከዛሬው ባለቤቷ ጋር የተዋወቀችው እዚያው እስር ቤት የዛሬ ስምንት አመት ሰው ልትጠይቅ በሄደችበት ወቅት ነበር፡፡ ስምንት አመት ሙሉ በአይን ፍቅር የቆየው ግንኙነት ዛሬ ለየት ባለ ሰርግ ወደትዳር አምርቷል፡፡ በሰርጉ ስነስርአት […]

በጎንደር ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ |መከላከያ ገባ 

$
0
0
በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የተከሰተውን ግጭት ለማርገብ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ጥያቄ ማቅረቡ ታወቀ፡፡ በዚህ መሰረት የመከላከያ ሠራዊቱ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር ከዛሬ ጀምሮ ተሰማርቷል፡፡ በፀጥታ ኃይሉ አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ በአካባቢው የተከለከለከሉ ተግባራትም ዛሬ ይፋ ተደርገዋል፡፡ በዚህም መሠረት ከጎንደር-መተማ መስመር ከመንገድ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም፤ በሁመራ […]

ዶ/ር አብይ አህመድ እና ለማ መገርሳ ም ዕራብ ወለጋ ተገኙ

$
0
0
ኦሮሚያን እያስተዳደረ የሚገኘው ኦዴፓ ሊቀመበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲሁም የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ  ከምዕራብ ወለጋ ከማኅበረሰብ አባላት ጋር ተወያዩ። አብዛኛው የም ዕራብ ወለጋ አካባቢ በኦነግ ቁጥጥር ሥር ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል:: ሁለቱ መሪዎች በምዕራብ ወለጋ የቄለም ወለጋ ዞን አዋሳኝ ከሆነችው ቤጊ ወረዳ የማህበረሰብ አባላት ጋር በዛሬው ዕለት ሲወያዩ የአካባቢው […]

ሕወሓት የተመሰረተበትን 41ኛ ዓመት በዓል ለማክበር የወጡ የመቀሌ የሕወሓት ካድሬዎች “ጌታቸው አሰፋ ውስጤ ነው”የሚል መፈክር ይዘው በአደባባይ ወጥተዋል

$
0
0
ሕወሓት የተመሰረተበትን 41ኛ ዓመት በዓል ለማክበር የወጡ የመቀሌ የሕወሓት ካድሬዎች “ጌታቸው አሰፋ ውስጤ ነው” የሚል መፈክር ይዘው በአደባባይ ወጥተዋል:: የትግራይ ሕዝብ አንገቱን የሚደፋው ለጸሎት ብቻ ነው እና ሌሎችንም መፈክሮች የያዙት እነዚሁ የሕወሓት ካድሬዎች አበል ከ75 ብር እስከ 125 ብር እንደተከፈላቸው ታውቋል::
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live