Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ የዋይ ፋይ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው

0
0
ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች ላይ የዋይ ፋይ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ በሁለቱ ኩባንያዎች መሀከል ስምምነቱ የተፈፀመ ሲሆን የዋይፋይ አገልግሎቱ ሲጀምር በአለም አቀፍና በአገር ውስጥ በረራዎች የሚሰጥ ይሆናል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም አለም አቀፍ ንግድ ኦፊሰሩ አቶ ሰይድ አራጋው ለካፒታል ጋዜጣ ሲናገሩ ‹‹ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ስምምነት ከፈፀምን በኋላ ለአገልግሎቱ ሳተላይት የሚያቀርብልን አለም አቀፍ ኩባንያ እያነጋገርን […]

የህወሃት መኳንንት ነገር….  

0
0
መስከረም አበራ በሃያ ሰባት አመታት የህወሃት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ ስርዓት የኖረው የሃገራችን ህዝብ በትግሉ የህወሃትን የበላይነት ከኢትዮጵያም ከኢህአዴግም ትከሻ ማሽቀንጠርን ችሏል፡፡ስልጣን ሲጥመው የቀረበት ህወሃት ታዲያ እሱ የማይዘውራት ኢትዮጵያ በሰላም ውላ ማደሯን የሚወድ አይመስልም፡፡ በስልጣን ዘመኑ “እኔ ከሌለሁ ሃገር ይፈርሳል” እያለ ሲያስፈራራ ስለኖረ እሱ በሌለበት ሃገር ሰላም ውላ ማደር እንደማትችል ማስመስከር ይፈልጋል፡፡ህዝብ ለውጡን ለመደገፍ ነቅሎ በወጣበት የድጋፍ ሰልፍ […]

ከተራ በዓል በድምቀት በመላው ኢትዮጵያ ተከበረ

0
0
ጎንደር !     የዐፄ ፋሲል መዋኛ ገንዳ (ታደሰ ጥበቡ)   “ጎንደር”ማለት “ጉንደ ሀገር”ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም “የሃገር ግንድ፣የሀገር መሰረት፣ርዕሰ ሃገር ወይም የሀገር ራስ ማለት ነው።   ይኸውም ኖህ ከጥፋት ውሐ በኋላ የተቀመጠበት በእንተላ፣በአይዋርካ፣በሽሌ፣በአይከል፣በኩል አድርጎ ጎንደር ላይ ብዙ ዘመን ፈጣሪውን እያመሰገነ እየቀደሰ የኖረባትና የተቀበረባት ቦታ በመሇኗ የሃገር መጀመሪያ ዋና ግንድ ተባለች።   እንዲያውም […]

በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የቅማንት ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ

0
0
አገራችን ኢትዮጵያ ለሃያ ሰባት ዓመታት ከተጓዘችበት የውድቀት፣ የሰቆቃ፣ የዘረፋና የጥፋት ጎዳና ወጥታ የተስፋ፣ የስላምና የዴሞክራሲያዊ መንገድ ጀምራለች። ይሁን እንጂ ህወሐት ሲመራው የነበረው መንግስት የሕዝቡን የቆዩ የአንድነት እሴቶችን አደጋ ላይ ጥሎ ሕዝቧን በዘር፣ በቋንቋ፣ በሐይማኖት፣ በጎሳና በነገድ በመከፋፈል የጥላቻ ግንብ በማቆምና የቆየውን የአንድነት ትስስር በመናድ በሐገሪቱና በሕዝቧ ሕልውና ላይ ከፍተኛ አደጋ እንዲፈጠር አድርጓል። የዚህ የህወሐት እኩይ […]

የአሜሪካ እርዳታ በግማሽ ሊቀንስ ነው

0
0
የአሜሪካ እርዳታ በግማሽ ሊቀንስ ነው

የአንጋፋው የኦሮሞ አርቲስቶች ባንድ አርፈን ቀሎ አባላት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

0
0
የአንጋፋው የኦሮሞ አርቲስቶች ባንድ አርፈን ቀሎ አባላት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት የባንዱ አባላት 17 ሲሆኑ፥ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና በአድናቂዎቻቸው አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የባንዱ አባላት ከአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ጀምሮ ህዝቡ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ መነቃቃት እንዲፈጥር የበኩላቸውን ሲያበረክቱ መቆየታቸው ተዘግቧል;; ዛሬ  ኢትዮጵያ የገቡት የባንዱ አባላት በአርቲስት አሊ […]

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱ..

0
0
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ሂደቱ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ መቋረጡንና ላለፉት ዘጠኝ ቀናትም በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ተማሪዎች ወደክፍል አለመግባታቸውን ዩኒቨርሲቲው ገለጸ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት በሁለት ቀናት ውስጥ በሚደርሰው ውሳኔ መሰረትም ችግሩን ለይቶ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድና ተማሪዎችም ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የሚደረግበት ሂደት እንደሚፈጠርም አስታውቋል፡፡ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት የተቋረጠው በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው ሦስት ልጆች ባልታወቀ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፎ […]

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ምዕመናን ዘንድ በድምቀት ተከበረ

0
0
የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ምዕመናን ዘንድ በድምቀት ተከበረ:: በተለይም በዓሉ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ  መርቆሬዎስ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያና ፓትሪያሪክ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምዕመናንና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት እንዲሁም በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ዘንድም በድምቀት ተከብሮ ዋለ::   በጃንሜዳ በተከናወነ […]

የጥምቀትን ከተራ በዓል ለማክበር የወጣው የወልቃይት ሕዝብ በትግራይ ክልል ፖሊሶች አስገዳጅነት አማርኛ ዘፈኖችን እንዳይዘፍኑ …

0
0
በትናንትናው ዕለት የጥምቀትን ከተራ በዓል ለማክበር የወጣው የወልቃይት ሕዝብ በትግራይ ክልል ፖሊሶች አስገዳጅነት አማርኛ ዘፈኖችን እንዳይዘፍኑ በመከልከል በዓሉን ወደ ውጥረት ውስጥ ሊከተው ቢሞክርም  ሕዝቡ እንደውም በአማርኛ ቋንቋ ወልቃይት አማራ ነው በሚል እየዘመረ መዋሉን ሰምተናል:: 

ሕወሓት እንዴት አደብ ይግዛ?

0
0
መረጃ – ሕወሓት እንዴት አደብ ይግዛ?  

የአዴፓ እና ህወሃት”እርቅ”ይሰምራል?  

0
0
ከመስከረም አበራ ህወሃት አንጉቶ የጋገረው ኢህዴን ፈጣሪው ህወሃት ሁን ያውን ሁሉ እየሆነ ሰላሳ አምስት የታዛዥነት ዘመናትን አሳልፏል፡፡ ኢህዴን መነሻው የወቅቱን የሃገራችንን ፖለቲካ ቀልብ ስቦ ከነበረው ኢህኣፓ ነው፡፡ኢህአፓ ደግሞ ህወሃቶች ማኒፌስቶ እንኳን ሳይፅፉ ታጋይ ነን የሚሉ ልሙጥ ፖለቲካኞች መሆናቸውን እየጠቀሰ ከመናቅ አልፎ ሲዘባበትባቸው የነበረው ፓርቲ ነው፡፡ነገሮች ተገለባብጠው የተናቀው ህወሃት በሃገራችን ፖለቲካ ላይ ጌታ መሆኑን አስረግጦ ጭራሽ  […]

ድሬዳዋ ዛሬ በጎማ ጭስ ስትታጠን ዋለች

0
0
በዛሬው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት ጀምሮ በድሬደዋ ከፍተኛ ተቃውሞ ተደርጓል፡፡ ከንቲባው ያነጋግሩን ያሉ ወጣቶች መንገድ ዘግተው ጎማ በማቃጠል ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ የዋሉ ሲሆን በፖሊስ ላይም ድንጋይ ወርውረዋል፡፡ ተቃውሞው ከፍተኛ ደረጃ ሲደርስ መከላከያ ገብቶ የማረጋጋት ስራ መስራቱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል፡፡ የተቃውሞው መነሻ በጥምቀት በአል አከባበር ወቅት የተፈጠረው ረብሻ ነው፡፡ የድሬዳዋ ፖሊስ ትላንት ባወጣው መግለጫ በጥምቀት በአል […]

መንግስትና ኦነግ ተኩስ ለማቆም ተስማሙ

0
0
የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት በዛሬው እለት በአምቦ ከተማ ባዘጋጀው የእርቅ ስነ ስርአት ላይ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና ኦነግ ከዛሬ ጀምሮ የተኩስ ማቆም ውሳኔ አሳልፈዋል። ከዚህ በተጨማሪም የኦነግ ሰራዊት በጥቂት ቀናት ውስጥ ካለበት ጫካ ወጥቶ ወደ ካምፕ እንዲገባም ውሳኔ አሳልፈዋል። ሁለቱ አካላት ከስምምነት የደረሱባቸውን ዝርዝር የውሳኔ ነጥቦችንም ይፋ አድርገዋል፡፡ የስምምነቱን ዝርዝር ነጥቦች አቶ ጃዋር መሀመድ […]

አዴፓ ከዳተኝነት፣ ከለዘብተኝነትና  ከይሉኝታ ፖለቲካ ወጥቼ በቁርጠኝነት የህዝባችንን ጥቅም ለማረጋገጥ እየተንቀሳቀስኩ መሆኑ ይታወቅልኝ አለ

0
0
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፖርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከጥር 13-15/2011 ዓ.ም ድረስ  ያደረገውን መደበኛ ስብሰባ ካጠናቀቀ በኋላ ባወጣው መግለጫው  ድርጅታችን ከዳተኝነትና ለዘብተኝነት እንዲሁም ከይሉኝታ ፖለቲካ ወጥቼ በቁርጠኝነት የህዝባችንን ጥቅም ለማረጋገጥ እየተንቀስቀስኩ መሆኑን ተገንዘቡልኝ አለ::   “ለዚህ ተልዕኮ መሳካት ወሳኙ ቀዳሚ ጉዳይ በክልላችን ህግ የማስከበርና ሰላም የማረጋገጥ ተልዕኳችን በተሣካ ሁኔታ መፈፀም የሚገባን መሆኑን ማዕከላዊ ኮሚቴው ትኩረት ሰጥቶ ገምግሟል፡፡ ይህ […]

በቾክ እጥረት ትምህርት ቤቶች ስራ እያቆሙ ነው ተባለ

0
0
በአማራ ክልል ማእከላዊ ጎንደር አለፋ ወረዳ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በቾክ እጥረት ስራ እያቆሙ መሆኑን ትላንት ለንባብ የበቃው በረራ ጋዜጣ ዘገበ፡፡ እንደጋዜጣው ዘገባ በወረዳው ጫራ ሰቀላ ቀበሌ የሚገኝ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጀት ስላልተለቀቀ ከጥር 15 ቀን 2011 ጀምሮ ስራ ማቆሙን የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር አቶ ጌታቸው ማንደፍሮ በፊርማቸው በወጣ ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡ ‹‹የትምህርት ቤቱ በጀት በመታገዱ […]

በባሌ ሀገረ ስብከት ሮቤ ከተማና አካባቢው የተቃጠለው ቤተክርስቲያን ጉዳይ…

0
0
በባሌ ሀገረ ስብከት ሮቤ ከተማና አካባቢው ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መቃጠሉ ይታወቃል፡፡ የተቃጠለውን መልሶ ለመገንባት ዛሬ በተደረገ ገንዘብ ማሰባሰብ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማግኘት ተችሏል፡፡ እሳቱን ለማጥፋት የተረባረቡት የእስልምና እምነት ተከታዮች በገንዘብ ማሰባሰቡም ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን የመንግስት ባለስልጣናትም በቦታው በመገኘት ህዝበ ክርስቲያኑን አፅናንተዋል፡፡ […]

የወልቃት ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ ሕዝባዊ ስብሰባ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጠርቷል

0
0
ጥር 19 ቀን 2011 ዓ/ም የወልቃት ጠገዴ አስመላሽ ኮሚቴ ሕዝባዊ ስብሰባ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ጠርቷል። በውይይቱ ኮሚቴው የሄደባቸውን ርቀቶችና ያጋጠሙትን ፈተናዎች ያቀርባል። ምሁራን ስለወልቃይት ከጥንት እስከ ዛሬ ያለውን እውነታ ያስረዳሉ ተብሏል። ስብሰባውን ለማካሄድ እንዲቻልም የባለሃብቶችን ድጋፍ ኮሚቴው ጠይቋል፡፡ በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፊርማ የተፃፈው ድጋፍ መጠየቂያ ጥሪ የሚከተለው ነው፡፡ ኮሚቴው ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የህዝብ መድረኮችን በመክፈት […]

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ለኢትዮጵያ የ130 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ሰጠ

0
0
የጠ/ሚር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በብራስልስ የሚያደርጉትን ስብሰባ በመቀጥል ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ጆን-ክላውድ የንከር ጋር ተገናኝተው ተወያዩ:: ሁለቱ ወገኖች ሶስት የፋይናንስ ስምምነቶች ሲፈረምም ተገኝተዋል:: እነዚህም የ 130 ሚሊዮን ዮሮ ስምምነቶች ዘላቂ ሀይል ማመንጨት: አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክና ስራ ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ ይውላል:: ሌላ በኩል ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት […]

በትግራይ ክልል ከ20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የአስተዳደር አደረጃጀት መዋቅር ለመቀየር የሚያስችል ሪፎርም እየተካሄደ መሆኑን ዶ/ር ደብረጺዮን ገለጹ

0
0
በትግራይ ክልል ከ20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የአስተዳደር አደረጃጀት መዋቅር ለመቀየር የሚያስችል ሪፎርም እየተካሄደ መሆኑን ዶ/ር ደብረጺዮን ገለጹ:: የትግራይ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 14 ተኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በመቐለ ሲጀመር ዶክተር ደብረጽዮን  ገብረሚካኤል የክልሉን መንግስት የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።  ዶክተር ደብረጽዮን ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው  ባቀረቡት ሪፖርት የክልሉ ተወላጆች ከተለያዩ አካባቢዎች የመፈናቀል ሁኔታ […]

ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ…

0
0
ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ ተገልብጦ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል። የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎቹ ትናንት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት በባህርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ መካከል ከተደረገው ጨዋታ በኃላ ወደ ጎንደር እየተመለሱ ጣራ ገዳም በሚባል አካባቢ ሲደርሱ ነው የመኪና አደጋው ያጋጠማቸው። በአደጋውም የሁለት ደጋፊዎች […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live