Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አቶ ዳውድ ኢብሳ የ ጀነራል ከማል ገልቹ ሹመት ጦርነት ውስጥ እንዳስገባቸው ገለጹ |“ሰራዊታችን ጥቃት አያደርስም እራሱን እንዲከላከል ግን ትዕዛዝ ተሰጥቶቷል”አሉ |በዶ/ር አብይና ለማ የሚመራው. ኦዴፓ ጠንከር ያለ መስጠንቀቂያ ሰጠ

$
0
0
የኦነግ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ በአዲስ አበባ መግለጫ ኦነግ ወደ ጦርነት የገባው የቀድሞው የኦነግ አመራር ጀነራል ከማል ገልቹ የኦሮሚያ ደህንነት ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው መሆኑን ተናገሩ:: በህጋዊነት በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ተስማምቶ ወደኢትዮጵያ ከገባ አራት ወራት ያስቆጠረው ላለፉት 27 አመታት ከመንግስት ጋር ጦርነት ሲያካሂድ መቆየቱን ያወሱት አቶ ዳውድ አሁን ጦርነት ለማቆም […]

ከ3 ሚሊዮን ዲያስፖራ በቀን አንድ ዶላር እንያዲዋጣ በዶ/ር አብይ ከየተጠቀው ውስጥ እስካሁን ያዋጣው 2800 ሰዎች ብቻ መሆኑ ተገለጸ

$
0
0
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በአሜሪካና አውሮፓ ተጉዘው ከኢትዮጵያውያን ጋር ባደረጉት ውይይት ዲያስፖራው በቀን $1 እንዲያዋጣ ከጠየቁ ወዲህ ከ3 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ገንዘብ ያዋጡት 2800 ብቻ እንደሆኑ አመለከቱ። እስካሁን የተገኘውም $507,094 መሆኑን ከማሰባሰቢያው ድረገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁም ተገልጿል:: ዲያስፖራው በድጋሚ አሁንም ይህንን ጥሪ ተቀብሎ በአንድ አንድ ዶላር የማዋጣቱን ተግባር እንዲቀጥል የተጠየቀ ሲሆን በአንጻሩም ዶ/ር አብይ የሾሙት ቦርድም […]

አርበኞች ግንቦት 7 በአዲስ አበባ ዋና ዋና አደባባዮች ቅስቀሳ ሲያደርግ ውሏል

$
0
0
ድርጅቱ ዛሬ በአዲስ አበባ ዋና ዋና አደባባዮች ቅስቀሳ ሲያደርግ ውሏል፡፡ ቅስቀሳውም የንቅናቄው አመራሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ውይይት የሚያደርጉበት መድረክ መዘጋጀቱን የሚገልፅ ነው፡፡ ከዚህ የመኪና ማስታወቂያ እንደሰማነው ቅዳሜ ህሳስ 13 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ሜክሲኮ በሚገኘው ኤሌክትሪክ ክበብ (መብራት ሀይል አዳራሽ) እንዲሁም እሁድ ታህሳስ 14 ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው […]

ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ዛሬ ተነጋገሩ፡

$
0
0
ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ከኢትዮጵያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ዛሬ ተነጋገሩ፡፡ ዶ/ር ወርቅነህ በፌስ ቡክ ገፃቸው ስለዚህ ጉዳይ ሲገልፁ ‹‹የኦሮሞ ጥናትን መሰረት የጣሉ ብቻ ሳይሆን በገዳ ስርዓት ለማጣቀሻ የበቁ አያሌ መፅሀፍቶችን የፃፉ እና ጥናቶችን ያደረጉ የገዳ ስርአት በዩኒስኮ እንዲመዘገብ ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ የነበራቸውን ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ዛሬ በፅ/ቤት ተቀብለን አነጋግረናቸዋል።›› ብለዋል፡፡ ዶ/ር ወርቅነህ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
– በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቀጠና 1 በሚባል አካባቢ እንጀራ ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው የሚጋግሩ ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ ተያዙ::ች በደረሰው ጥቆማ መሰረትም የወረዳው ፖሊስ በቦታው ተገኝቶ ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ አድርጓል::፡፡ ምስሉ ላይ የሚታየው በቦታው የተገኘውና ከባዕድ ጋር ተቀላቅሎ የተጋገረው እንጀራ ነው። ዘገባው የወረዳ 14 ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው:: በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት […]

ደምስ በለጠ ከአገሩ ከወጣ ከ30 አመታት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ በገባ በ21 ቀኑ በተኛበት አርፎ ተገኘ

$
0
0
የአማራ ድምፅ ራዲዮ ዋና አዘጋጅ ደምስ በለጠ ከአገሩ ከወጣ ከ30 አመታት በኋላ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ በገባ በ21 ቀኑ በተኛበት አርፎ ተገኘ:: የጋዜጠኝነት ስራውን ገና ተማሪ እያለ በሞስኮ ራዲዮ የአማርኛ ዝግጂት ክፍል የጀመረው ፤ ደምስ በለጠ ከ2016 አም ጀምሮ የአማራ ድምፅ ራዲዮ ሲያዘጋጅ ነበር። ደምስ ከረጅም ጊዜ የውጪ አገር ቆይታ በኋላ በፈረንጆቹ አቆጣጠር እሁድ ዲሴምበር 2 […]

አቶ ለማ መገርሳ ‹‹ዶክተር አብይን በጉልበት እሳት አቀጣጥለን እናስወጣዋለን የሚሉ ከመጡ እንሟሟታታለን እንጂ አይለቅም›› አሉ

$
0
0
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንቱ አቶ ለማ መገርሳ ከሰሞኑ በቤተመንግስት ከኦሮሞ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት በኦህዲድና በህወሃት መሀከል የነበረው ግጭት የቆየ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ብዙ ሰው የኢህአዲግን ሊቀመንበር ለመምረጥ የተደረገው የ17 ቀናት ፍጥጫ እንደሚመስለው ያወሱት አቶ ለማ ሲናገሩ ‹‹ጉዳዩ የተጀመረው በ17ቱ ቀናት አይደለም፣ ቆይቷል፡፡ ትግሉ ከጀመረም ሰንብቷል፡፡ ዛሬ እዚህ አንናገረውም፣ አንድ ቀን ታሪክ ያወጣዋል›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ለሰባትና ስምንት […]

በሃዋሳ አንድ ሌትር ቤንዚን 70 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተሰማ

$
0
0
– በሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ የቤንዚን እጥረት መከሰቱና አንድ ሊትር እስከ 70 ብር እየተሸጠ መሆኑ ተዘገበ፡፡ የከተማው የንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ሀላፊ አቶ ቦንቲ ቦቼ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በከተማው 15 ነዳጅ ማደያዎች ቢኖሩም በሙሉ አቅም እየሰሩ ያሉት አምስቱ ብቻ ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ እያቆራረጡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ አምስቱ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ስራ አቁመዋል፡፡ ለከተማው በቂ ነዳጅ […]

ፓርቲዎቹ ሊዋሃዱ ነው

$
0
0
ኢዴፓ፣ ሰማያዊ ፓርቲና አርበኞች ግንቦት 7 እንዲሁም የቀድሞው አንድነት አባላት ለመዋሃድና አንድ ፓርቲ ሆነው ለመስራት መስማማታቸው ተዘገበ፡፡ ዛሬ ለንባብ የበቃው አዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደዘገበው ውህደቱ እስከመጋቢት 30 ቀን 2011 አ.ም. ድረስ ይጠናቀቃል፡፡ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) ፕሬዚደንቱ ዶክተር ከበደ ጫኔ በአሁኑ ወቅት ከወረዳ ጀምሮ ያሉ የተለያዩ መዋቅሮችን ከየፓርቲዎቹ አመራሮች ጋር በመሆን እየሰሩባቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
  በኢትዮጵያና ኤርትራ መሀከል የነበረው ድንበር ክፍት ከሆና ከመስከረም ወር ወዲህ ከ27 ሺ 500 በላይ ኤርትራዊያን አገራቸውን ለቀው በመውጣት ኢትዮጵያ ውስጥ ጥገኝነት እንደጠየቁ ታወቀ፡፡ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዛሬ የአውሮፓ ህብረት ዶክመንትን በማጣቀስ እንደገለፀው 24 ሺ ኤርትራዊያን ጥገኝነት የጠየቁት በትግራይ በኩል ገብተው እንዳባጉና የተባለው ቦታ ሲሆን ቀሪዎቹ 3 ሺህ 500ዋቹ ደግሞ የገቡት በአፋር በኩል ነው፡፡ የአውሮፓ […]

ከደምስ በለጠ መስዋዕትነት አድማስ ባሻገር :- ጠላቶቻችን ጀግኖቻችንን ቀድመዉ ያዉቋቸዋል::እኛ ግን ጀግኖቻችንን የምናዉቃቸዉ መስዋዕት ሲሆኑ ነዉ::

$
0
0
—————– ሸንቁጥ አየለ —————- ደምስ በለጠ ዝም ብሎ አልሞተም:: በታላቅ ተጋድሎ ዉስጥ ሳለ ስለ ህዝቡ ተሰዋ እንጅ ! የተጀመረዉን ተጋድሎ ጀግኖችን በመመረዝ: በመግደል እና በመሰወር ማቆም አይቻልም:: ትግሉ ወደ ህዝቡ እጅ ገብቷል እና:: ትግሉን ወደ ህዝብ እጅ እና ልብ ያስገቡት ጀግኖች እነ ደምስ በለጠ ደግሞ መስዋዕትነትን ፈርተዉ ወደ ትግል ሜዳ አልወረዱም::ስለ ህዝባቸዉ መስዋዕት ሊሆኑ ወደት […]

የህወሃት ወንጀለኞችን አድኖ ለመያዝ ከአይሁዶች ምን እንማራለን?

$
0
0
የህወሃት ወንጀለኞችን አድኖ ለመያዝ ከአይሁዶች ምን እንማራለን? ክንፉ አሰፋ (የኢትዮፎረም ድረ-ገጽ አዘጋጅ እና ሶፍትዌር ኢንጂነር – አምስተርዳም) አዛውንቶቹ የህወሃት ቅሪቶች “ለመጨረሻው ፍልሚያ” ትንፋሽ ስበው፣ መሬት ልሰው ነብስ ለመዝራት ሲነሱ እና ሲወድቁ እየተመለከትን ነው። ከተከዜ በላይ እና ከተከዜ በታች ያለውን ወገን በሙሉ “ጠላት” በሚል ጸያፍ ቃል ማጀብ መጀመራቸው ግን የተስፋ መቁረጠቸው ምልክት ይመስላል። ሁሉን የክፋት መንገድ […]

የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ በሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ

$
0
0
በትናንትናው የዘ-ሐበሻ ዜና በኦሮሚያ ክልል በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እየዋሉ ስላሉ ዜጎች መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት የታሳሪዎች ቁጥር 75 መድረሱን የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። ከታሳሪዎቹ መካከልም የቀድሞው የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባና ምክትሉ እንደሚገኙበት ሰምተናል:: የኦሮሚያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አበበ ከበደ፥ዛሬ እንዳስታወቁት በሌብነት ተጠርጥረው እስካሁን በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም፦ ከኦሮሚያ ብድር እና ቁጠባ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
በሳዑዲ አረቢያ – በጂዳ፣ በጂዛን እና አከባቢዋ በተለያዩ ጉዳዮች ተከሰው በእስር ላይ የቆዩ 451 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ተመለሱ:: የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚ;ር ዕንዳስታወቀው ዜጎቹ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ምህረት እንዲያገኙ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ሥራ ተሰርቷል:: ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ባለፈው ሳምንትም ወደ 2 ሺህ 400 የሚሆኑ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ 231 ዜጎችን ደግሞ ከታንዛኒያ መመለሳቸውን ጠቅሷል:: […]

ፖሊስ የኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ብርሃንን ጉዳይ ለአቃቤ ህግ አስረከበ::

$
0
0
በሌብነት ወንጀል ተጠርትረው የታሰሩት ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ዛሬ ፍድር ቤት ቀርበው መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቆ ለአቃቤ ህግ ማስረከቡን ገለጸ:: ኮሎኔል ደሴ ዘለቀ ብርሃን የአዳማ እርሻ መሳሪያዎች ኃላፊ ሆኖ በሱማሌ ክልል ሀረዋና ኩለን በአፋር ክልል ደግሞ ሱሉታ መስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች በሚሰሩበት ወቅት ከሌሎች ግብረአበሮች ጋር በመሆን የሙስና ወንጀል ድርጊቶችን በመፈፀም በፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ […]

የዳቦ ዋጋ ሊጨምር ይችላል

$
0
0
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከዳቦ ቤቶች ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ሊሰጥ መሆኑን ካፒታል የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ዘገበ፡፡ ንግድ ቢሮው የዋጋ ግሽበትን፣ የብር ምንዛሬ መቀነስን፣ እንዲሁም የግብአቶች፣ የሰራተኛና የትራንስፖርት ዋጋ መጨመርን በተመለከተ ጥናት ማድረጉን ጋዜጣው አስረድቷል፡፡ ከዚህ ጥናት በመነሳትም ለንግድ ሚኒስቴር ፕሮፖዛል ያቀረበ ሲሆን ፕሮፖዛሉ ተቀባይነት ካገኘ የዳቦ ዋጋ ከ20 ሳንቲም እስከ 80 ሳንቲም እንደሚጨምር ገልጿል፡፡ በዚህ መሰረት […]

ለአርቲስት ይሁኔ በላይ እና መሐሪ ደገፋው ሽኝት ተደረገ

$
0
0
እየተደረገ በነበረው ትግል በሙያቸው የወገናቸውን ድምጽ በማሰማት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱት አርቲስት ይሁኔ በላይ እና መሐሪ ደገፋው ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው:: ይህን ተከትሎም ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ በወዳጅ ጓደኞቻቸው አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል:: ይሁኔ እና መሐሪ ታህሳስ 27 2011 በጎንደር በአፄ ፉሲል ስታዲየም የመጀምሪያ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ከዚያም በተለያዩ ከተሞች እየተዟዟሩ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል:: መሐሪ “እግዚአብሔር ይመስገን […]

ለኢትዮጵያ ኢንቨንስትመንት ኮሚሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ተሾመ

$
0
0
አቶ አበበ አበባየሁ ቸኮል የኢትዮጵያ ኢንቨንስትመንት ኮሚሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው መሾማቸው ተሰማ፡፡ የኮሚሽኑ ሃላፊ የነበሩት አቶ ፍፁም አረጋ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር መሆናቸውን ተከትሎ በቦታው መመደባቸው ታውቋል፡፡ የጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ቀኝ እጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አበበ ቀደም ብሎም የኢንቨስትመንት ኮሚሽኑ ምክትል በመሆን ያገለግሉ ሲሆን፤ የጠቅላይ ሚንስትሩ የሕግ ጉዳዮች አማካሪ ነበሩ። የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ አበበ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
45ኛ መደበኛ ጉባዔያቸውን ያደረጉት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳት መንግሥት ለሕዝብ ሰላም ዋስትና የመስጠት ኃላፊነት ስላለበት ይህንን ሕገመንግሥቱ ባስቀመጠው አቅጣጫ ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ ሊወጣ እንደሚገባው አሳሰቡ:: ፡ ‹‹ኢትዮጵያዊነት እንጂ ብሔርተኝነት መስበክ ለሕዝባችን አይጠቅመንምና የተሻለውን ሁሉ እንምረጥ፤›› ያሉት ጳጳሳቱ፣ ሁሉም ልብ ለልብ ተቀራርቦ ስለ አገሩ ኢትዮጵያ የሚነጋገርበትና የሚግባባበት፣ የሚረዳዳበት ብሎም ሰላምና ደስታ የሚጎናፀፍበት ዘመን እንዲመጣ ተግተን […]

አርበኛ መሳፍንት ‹‹በወልቃይት ጠገዴ ያልተነገረና የኢትዮጵያ ህዝብ በውል ያላወቀው መጠን የለሽ በደል ተፈፅሟል›› አሉ

$
0
0
አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ህወሀት በትጥቅ ትግሉ ወቅት በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ሲፈፅም የነበረውን ግፍ በመቃወም በረሃ ገብተው ህወሃትን ሲፋለሙ በትግራይ የጉድጓድ እስር ቤት ታስረው ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል፡፡ ይሁንና እስር ቤቱን ሰብረው በመውጣት እድሜያቸውን ሙሉ ሲፋለሙ የቆዩት እኚህ አርበኛ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ ሰምተው በቅርቡ ከበረሀ ወጥተዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የትግል ጓዶቻቸውን ይዘው ከመንግስት ጋር ለመነጋገር ወደጎንደርና ባህር […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live