Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ በነበረ ሚኒባስ ላይ  የፈንጂ አደጋ ደረሰ

0
0
 የኦሮሚያ ክልል የገጠር ፖለቲካ የኦዴፓ ዘርፍ አላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ እንዳስታወቁት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተሸከርካሪ ላይ በደረሰ የፈንጂ አደጋ የአስር ሰዎች ህይወት አልፏል:: የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ሃሩንም እንዳረጋገጡ አደጋው የደረሰው ዛሬ ጥዋት 18 ሰዎችን አሳፍሮ ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ቤጊ መገንጠያ በተባት […]

28 ትልልቅ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ከሰሞኑ የሌብነት ታሳሪዎች ጋር ግንኙነት ይኖራቸዋል በሚል ተጠርጥረው ታገዱ

0
0
በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የሚመራው የሪል ስቴቶች ጉዳይ አጣሪ ኮሚቴ በህገወጥነት በተጠረጠሩት ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰዱ ተሰማ፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው በከተማው የታወቁና ትላልቅ የሚባሉ 28 የሪል ስቴት ኮባንያዎች ከታህሳስ 8 ጀምሮ ማንኛውንም አገልግሎት እንዳያገኙ ታግደዋል፡፡  እንደጋዜጣው የታገዱት የሪል ስቴት ኩባንያዎች ኖህ ሪል ስቴት፣ ሰንሻይን፣ አያት፣ ሳትኮን ኮንስትራክሽን፣ ሴንቸሪ 21 ኮንስትራክሽን፣ ሙለር ሪል […]

ኮለኔል ካሳ ሮባ ታሰሩ

0
0
በሜቴክ የንብረት ማሰባሰብና መልሶ መጠቀም ሃላፊ ሆነው ይሰሩ የነበሩት ኮሎኔል ካሳ ሮባ ከትናንት በስቲያ በቁጥጥር ስር  መዋላቸው ተሰማ:: በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀረቡ። ኮ ሌነሉ ተቋሙ በተጠቀሰው የሃላፊነት ቦታ ይሰሩ በነበረበት ወቅት የብረት ቁርጥራጭ ወይም ስክራፕ የመሰብሰብና የማጓጓዝ ፈቃድ ለድርጅቱ ተሰጥቶ ሳለ ማህበራትን በማቋቋምና ከግለሰቦች ጋር በመመሳጠር በርካታ ሃብት ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ እና መንግስትን በርካታ […]

ፈገግታ ነው የሚቀድመኝ ( በእውቀቱ ስዩም)

0
0
የድሜ ነፋስ በገላየ : ተረማምዶ ኮበለለ ልቤን ክንዴን እያዛለ ያቀፍኩትን እየቀማ : የያዝኩትን እያስጣለ:: እድል በኔ ጨከነ ስል-በምረት እጅ ደባበሰኝ አንቺ ነጥቆ ከቅፌ ላይ-በትውስታ ደሞ ካሰኝ:: አሰታወሰኝ አስታወሰኝ:: ወድያው ታይቶ :ጠፊ ኩርፍያሽ ገራም ሳቅሽ : ልዝብ ልፍያሽ ያለም ዘፋኝ የማያውቀው የግልሽ ዳንስ ውዝዋዜ ትውስ ትውስ ባለኝ ጊዜ ከግር ጥፍሬ እስከ ጠጉሬ ደስታ ነው የሚያቀልመኝ ያንቺ […]

ግርምሽ ሲታወሱ ( በእውቀቱ ስዩም)

0
0
ግርማ ወልደጊዮርጊስ ፕሬዚዳንት ሁኑው የተመረጡ እለት ብዙ ሰዎች ተገርመዋል :: ከእስክንድር ነጋ ጋዜጦች አንዱ ዜናውን የዘገበችው ” ወያኔ አበደች ” በሚል ርእስ እንደነበር ትዝ ይለኛል:: አንድ አሙስ የቀረው ሽማግሌ እንዴት ለዚህ ሚና ይታጫል በሚል እብሪት የተቹ አልጠፉም :: ብዙዎቻችን “ሽማግሌ ከወጣት ቀድሞ ይሞታል ” የሚል ጅልነት ሰለባ ነን:: አፈሩን የስፖንጅ ፍራሽ ያድርግለትና አቶ አሰፋ ጫቦ […]

በአዲስ አበባ ከአፍንጮ በር እስከ ፒያሳ አካባቢ በወንዝ ዳርቻ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መኖሪያ ቤታቸው በቅርቡ ሊፈርስ ነው፡፡ 

0
0
የዘሃበሻ ምንጮች እንደተናገሩት የአዲስ አበባ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ከወርቅ ቤቶቹ ጀርባ ያሉ መኖሪያ መንደሮች ለሚገኙ ነዋሪዎች ቤቶቹ እንደሚፈርሱ የሚገልፅ ደብዳቤዎች መስጠት ጀምሯል። ለነዋሪዎቹ በተሰጠው ወረቀት የቤቶቹ ሕጋዊ ነዋሪነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ይዘው እንዲቀርቡ ተነግሮዋቸዋል።   እነዚህ ሰፈሮች ከወርቅ ቤቶቹ ጀርባ እስከ ሰራተኛ ሰፈር እንደሚፈርሱ የተነገራቸው ከአመታት በፊት የነበረ ሲሆን ዝም ተብሎ ቆይቶ አሁን ግን […]

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትላንት ታህሳስ 9 ባደረገው ስብሰባ የአቶ ገብረእግዚአብሄር አርአያን ሹመት አልቀበልም አለ

0
0
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባልተለመደ ሁኔታ ጥርስ ያወጣው ፓርላማው ምንም እንኳ መቶ ፐርሰንት በኢህአዲግ ቁጥጥር ስር ቢሆንም የቀረበለትን ሁሉ ሳያላምጥ መቀበል ትቷል፡፡ ትላንትም ለፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባልነት ከቀረቡለት ዕጩዎች መካከል፣ በምክር ቤቱ የመንግሥት ተጠሪ ሚኒስትር የሆኑትን የአቶ ገብረ እግዚአብሔር አርዓያን የሹመት ጥያቄ ሳይቀበል መቅረቱ ታውቋል፡፡ ሪፖርተር ዛሬ እንደዘገበው በዕለቱ ምክር ቤቱን በመወከል የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ […]

ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ትግሉ ሀገር በማቆየትና በማፍረስ መካከል ያለ ትግል መሆኑን ገለፁ |የባህርዳር ከንቲቫ ‹የግንቦት 20› ክፍለ ከተማንም ሆነ ‹የግንቦት 20› አየር ማረፊያ ስያሜ መለወጥ ይቻላል› አሉ

0
0
የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ጽጌ በባሕር ዳር ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች፣ ሃይማኖት አባቶች እና ከባሕር ዳር ከተማ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር ምክክር ማድረጋቸውን ሰምተናል፡፡ ዛሬ በተደረገው በዚሁ ምክክር ጄ/ል አሳምነው ሲናገሩ ‹‹በመደራጀት ችግር ለመፍጠር እየተሰራ ያለበት ጊዜ ላይ ነን፡፡ ቅማንት እና አማራን የሚያጋጭ ፖለቲካዊም ሆነ ታሪካዊ ጉዳይ የለም፡፡ ይህንን ለመቀልበስም በሰላም […]

ኣጫጭር ዜናዎች

0
0
በርካታ ትችቶች የሚሰነዘርበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የማዕከላዊ ባንክነቱን ሚና በአግባቡ እንዲጫወት፣ ከማንኛውም የመንግሥት ተፅዕኖ ነፃ ሆኖ እንደ አዲስ እንዲዋቀር የተለያዩ ባለሙያዎች ሐሳብ ቀረቡ፡፡ ማክሰኞ ታኅሳስ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተከፈተው ሦስተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፖለቲካ ሹመኞች ሲመራ በመቆየቱና የመንግሥት ፖሊሲ […]

ኦነግ በኦሮሚያ ነጻ መሬት እንዳለው ይፋ አደረገ

0
0
ኦነግ በኦሮሚያ ነጻ መሬት እንዳለው ይፋ አደረገ

መለስ ዜናዊ በየቀኑ እየሞተ ነው |አቻምየለህ ታምሩ

0
0
የመለስ ዜናዊ አሻራ በያለበት እየታደነ እየተደመሰሰ ይገኛል። በጅግጅጋ ከተማ በስሙ ይጠራ የነበረው «መታሰቢያ ሆስፒታል» ስሙ ተለውጧል። በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች እየተደረገ ያለው ይህ የመለስ ዜናዊን አሻራ የመደምደስ ዘመቻ ሕዝብ ባሄደው ትግል ራሱን ነጻ ማውጣት ሲችል እውነት እየተናገረ መሆኑን የሚያሳይ ነው። እውነቱም መለስ ዜናዊ የገዳይና ዘራፊ ወያኔዎች አለቃ እንጂ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስት እንዳልነበር የሚያሳይ ነው። አማራ ክልል […]

አብዲ ኢሌ ለ14 ቀን ተቀጠሩ

0
0
የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድና ሌሎች ባለስልጠናት ላይ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ችሎት 14 ቀን ቀጠሮ ሰጠ፡፡   በዛሬው ውሎ መርማሪ ፖሊስ ከሀምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2011 ዓ.ም በጂግጂጋ ከተማና ሌሎች አካባቢዎች በተከሰተው ሁከት 742 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ከክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባሰባሰበው መረጃ ማረጋገጡን ለችሎቱ አስረድቷል። በምርመራ […]

በአማራ ክልል ተማሪዎች ለኩረጃ እያሉ ስማቸውን እየቀየሩ ስለሆነ ዘንድሮ ስም እንዳይቀይሩ እገዳ ተጣለ

0
0
 በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዓለምእሸት ምህረቴ እንደተናገሩት አንዳንድ ተፈታኞች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን ከጎበዝ ተማሪዎች የስም ፊደል ጋር እያመሳሳሉ በፍርድ ቤት እየቀየሩ እንደሆነ ጠቅሰው ይህን በተመለከተ ትምህርት ቢሮው ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ደብዳቤ መፃፉንም አውስተዋል።   ባለፈው አመትም 1 ሺህ 550 ተማሪዎች ለኩረጃ ሲሉ ስማቸውን መለወጣቸውን አስረድተዋል፡፡ በተያዘው የትምህርት ዘመንም ተመሳሳይ […]

እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊውን ፓይለት አስመረቀች

0
0
እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊውን ፓይለት አስመረቀችሲል የአገሪቱ ጦር ሀይል ሬዲዩ አስታወቀ፡፡ ኦፕሬሽን ሰለሞንና ኦፕሬሽን ሙሴ በሚል ወደ140 ሺህ ያህል ቤተ እስራኤላዊያን ከኢትዮጵያ ወደእስራኤል ተሻግረው መኖር ከጀመሩ በርካታ አመታት ቢያስቆጥሩም የዘር መድልኦ ሲፈፀምባቸው ቆይቷል፡፡ በተለይም በወታደራዊ መስኮች ከተሰማሩ ከፍተኛ ጫናና አድልኦ እንደተፈፀመባቸው ሲናገሩ ነበር፡፡ ይህንን ከባድ ፈተናና ጫና አብርሃም ይስሀቅ የተባለው ቤተ እስራኤላዊ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣጥሶ […]

33ንየሕወሓት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ አቀረቡ |ጌታቸው ረዳ ወደ ፓርላማው ሲገቡ አልፈተሽም ብለው አመጹ

0
0
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ አስፈጻሚው መንግሥት የቀረበለትን የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን፣ ዛሬ ሐሙስ ታኅሳስ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በተለየ ሁኔታ የጋለ ክርክር አካሂዶ በአብላጫ ድምፅ አፀደቀ። 33 የሕወሓት የፓርላማ ተወካዮች ከፍተኛ ተቃውሞ አንስተዋል:: በምክር ቤቱ መቀመጫ ያላቸው የሕወሓት አባላት ረቂቅ አዋጁ ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጋጭ በመሆኑ መፅደቅ የለበትም በማለት ከፍተኛ […]

የዝቅጠታችን ጥልቀት

0
0
ስንታየሁ ደምሴ መቼም እንደ ሀገርና እንደ ማህበረሰብ ዛሬ ያለንበትን የዝቅጠት ፈርጅና ጥልቀት ለመግለጽ ይቸግራል፡፡ በነዚህ አመታት አይናችን እያየ ነገሮች ለማስተካከል በሚቸግሩበት ሁኔታ ሲለዋወጡ አይተናል፡፡ ዛሬ ላይ ምንም ያህል ተስፋ ብንሰንቅ ያለንበትን ዘረፈ ብዙ ችግር ቀርፈን መጨረሳችንና ከገባንበት ጥልቀት ተጎትተን መውጣት መቻላችንን ሳስብ ጭንቅ ይለኛል፡፡ አንዳንድ ወቅት በተለየ የምሰማቸው ዜናዋች ተስፋ ያስቆርጡኛል፡፡ አስራ ሶስት የህዳሴ ግድብን […]

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ‹‹ማንንም የፀጥታ አካል አልገደልኩም፣ ራሴን ነው የተከላከልኩት›› አሉ

0
0
ሀምሌ 5 ቀን 2008 እቤታቸው ድረስ ከመጡ የህወሃት ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ያደረጉትና በዚህም ታስረው የተፈቱት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በወቅቱ የተፈጠረውን ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ አስረዱ፡፡  በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው አማካኝነት በአዲስ አበባ መታተም የጀመረው በረራ ጋዜጣ ቃለምልልሳቸውን ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡ በዚህ ቃለምልልስ ስለ ሀምሌ አምስቱ ጥቃት ኮሎኔሉ ሲያስረዱ ማንንም የፀጥታ ሀይል እንዳልገደሉና ራሳቸውን እንደተከላከሉ ገልፀዋል፡፡ በእለቱ […]

አጫጭር ዜናዎች

0
0
በ2008 ዓ.ም በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ነፍጥ አንግበው ወደ በርሃ ከወረዱ አርሶ አደሮች መካከል 250 የሚሆኑት ከመንግስት ጋር ስምምነት ላይ በመድረሳቸው ወደ ቀያቸው ተመለሱ። ታጣቂዎቹ ወደ ህብረተሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት ስልጠና ይሰጣቸዋል ተብሏል። ከሳምንታት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎች ታጣቂዎች መመለሳቸው ይታወሳል። – በምዕራብ ወለጋ ነጆ ከተማ አቅራቢያ በአንድ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የቦንብ ጥቃት የአምስት […]

በቤኒሻንጉል ጉሙዝና አካባቢው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ፣ |ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል

0
0
በቤኒሻንጉልና በኦሮሚያ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች ባለፉት ሦስት ወራት በተከሰተ የጸጥታ ችግር ከ100 በላይ ሰዎች ሲሞቱ፣ በ10 ሺህ የሚቀጠሩ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ ይህ ችግር ከእለት ወደእለት እየተባባሰ ከመምጣቱም በላይ በትላንትናው እለት በህዝብ ትራንስፖርት ሚኒባስ ላይ ቦምብ ፈንድቶ በርካታ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ዘግበናል፡፡ በዛሬው እለት ችግሩን ለመቅረፍ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ አካባቢውን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስተዳደር እንደተጀመረ ሰምተናል፡፡ ኮማንድ […]

”ትራንዚት” ድራማ አጭር ቅኝት |ክንፉ አሰፋ (አምስተርዳም)

0
0
“ስለ ህይወት መጻፍ ከመጀመርህ በፊት ህይወትን መኖር ይገባሃል።” ይላል ስመ ጥሩ አሜሪካዊ ጋዜጠኛ፣ እርነስት ሄሚንግዊይ። በመኖር እና በመስማት መካከል ትልቅ ጅረት አለ ሊለን ፈልጎ ነው። የህይወትን ክፉም ሆነ ደግ ገጽ ሊለይ የሚችለው፤ ያለፈባት ብቻ ነው። መራራም ትሁን ጣፋጭ፤ የስደትን ጣዕም ጠንቅቆ የሚያውቃት የቀመሳት ብቻ ነው። የ ”ትራንዚት” ድራማ ደራሲ እና አዘጋጅ ቢንያም ወርቁ ስደትን ኖሮባት […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live