Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአማራው ክልል ባለስልጣን አማራውን ከተሳደቡ በኋላ “ባለስልጣኑ ካልተባረረ ዳሽን ቢራን አንጠጣም”የሚል ቦይኮት ተጠራ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአማራ ሕዝብ ተቋቁሞ ሆኖም ግን የጥቂት ብአዴን ባለስልጣናት ከርስ መሙያ ሆኗል የሚባለው ዳሸን ቢራ ላይ ኢትዮጵያውያን የመጠጣት ማእቀብ (ቦይኮት) እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ። ጥሪው የቀረበው ሰሞኑን በተለያዩ የሶሻል ሚድያዎች የክልሉ ባለስልጣን የሆኑት አቶ አለምነህ መኮንን እመራዋለሁ የሚሉትን የአማራ ሕዝብ ለመጻፍ በሚከብዱ ጸያፍ ቃላት ሲሳደቡ የሚያስደምጥ ድምጽ ከተለቀቀ በኋላ በተቆጡ ኢትዮጵያውያን ነው።

የቦይኮት ጥሪው በፌስቡክ እና ትዊተርን በመሳሰሉ ታላላቅ የሶሻል ሚዲያዎች እየተሰራጨ ሲሆን በተለይም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በተለይም በአማራ ክልል የዳሽን ቢራን አንጠጣም የሚለው አድማ በሰፊው እንደተሰማ ነው። የቦይኮቱ እንስቃሴ መሪዎች በሶሻል ሚድያ እንደገለጹት ብአዴን የተባለው በአማራው ሕዝብ ስም የተቋቋመው የሕወሓት ተላላኪ ድርጅት እንደ አቶ አለምነህ መኮንን ያሉ ሰዎችን በስሩ ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ይህ ዳሸን ቢራን ያለመጠጣት አድማ ይቀጥላል።

አቶ አለምነህ መኮንን ሕዝብን በመናቅ አንድን የተከበረ ሕዝብ በአጸያፊ ቃላት ሲናገሩ ማድመጥ በጣም የሚሰቀጥጥ መሆኑን የሚገልጹት እነዚሁ የቦይኮት ዳሸን ቢራ አስተባባሪዎች ሰውዬው ከስልጣናቸው ወርደው ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

በሶሻል ሚድያዎች የተበተነውና ብዙዎች በየገጻቸው ላይ እያባዙት የሚገኘው የቦይኮት ዳሸን ቢራ መልዕክት የሚከተለው ነው፦
Boycott Dashen Bear


የማለዳ ወግ …ትምህርት ቤታችን እና ኮሚኒቲውን የከበበው አደጋ … !

$
0
0

የመምህራን ማስጠንቀቂያ …
ሰሞነኛው የጅዳዎች ጉዳይ የመኖሪያ ፈቃድን በማስተካከል ዙሪያ ቢሆንም ከ 3000 (ከሶስት ሽህ) በላይ ታዳጊዎችን የሚያስተናግደው የጅዳው አለም አቀፍ ት/ቤት አሁንም አደጋ ላይ መሆኑን እየሰማን ዝም ብለናል! ከሳምንታት በፊት መምህራን አመጽ አድርገው ነበር ። ከቀናት በፊትም 25 መምህራን ስብሰባ ተቀምጠው ፣ በአንድ አቋም ጸንተው ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። ላለፉት 8 ወራት ጉዳያቸው በትምህርት ቤቱ ባለቤት በኮሚኒቲው ጉዳያቸው ቢያዝም እስካሁን ከወሬ ያላለፈ አርምጃ አለማየታቸውን ገልጸዋል። 25 ቱ መምህራን ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ፣ ለኮሚኒቲውና ለጅዳ ቆንስልና ለወላጅ መምህራን ህብረት ባስገቡት ደብዳቤ እስከ ቀጣዩ ሳምንት የሁለተኛው የትምህት አጋማሽ መጀመሪያ የመኖሪያና የስራ ፈቃዳቸው ተስተካክሎ ካልተሰጣቸው በማስተርማር መደበኛ ስራቸው እንደማይገኙ በላኩት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ማስጠንቀቃቸውን በእጀ የገባው ሰነድ ያመላክታል !

nebiyu
የወላጅ መምህራን ህብረት ስብሰባ ጥሪ …
“ወላጅና መምህራን ህብረት ” በሚል ካች አምና በመንግስት ትዕዛዝ የወላጅ ኮሚቴን የተካው ኮሚቴ በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ለመምከር ለነገ ሃሙስ ስብሰባ ጠርቷል። ኮሚቴው የሳውዲን የምህረት አዋጅ ማለቅ ተከትሎ የጅዳ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ለሳምንት ሲዘጋ የሚወክለውን ወላጅም ሆነ መምህራኑን ብሎ ድምጹን አላሰማም ። ትምህርት ቤቱ ካንድም ሁለት ሶስቴ በመምህራን ስራ ማቆም አድማ ሲናጥ ፣ ከፍተኛ የማህበረሰቡ መዋዕለ ንዋይ ከመጋረጃ ጀርባ ለሚደረጉ የመምህራን እና ሰራተኛ ዝውውር መባከኑ ሲሰማ የዝሆን ጀሮ ስጠኝ ማለቱ አይደንቅ ይሆናል ። የመንግስት ሃላፊዎች ትኩረትና ጥበቃ የማይደረግለትን የትምህርት ማዕከል ህልውና ለማስጠበቅ ስብሰባ መጥራትና ወላጁን ባለማማከሩ ተወቃሽ ከመሆን ግን አላመለጠም። ለሚታየው እንግዳ ፣ ለሚሰማው ባዳ መሆናቸው ያስከፋው ወላጅ ከትናንትም ዛሬ ተስፋ ቆርጧል።
ዛሬ የወላጅ መምህራን ህብረት ተብየውን ምን እንዳሰናከለው ፣ ምን እንዳሽመደመደው መስማት ባያጓጓም የወደፊት የወላጁን ፣ የመምህራንንና የታዳጊዎችን ትምህርት ቤት አደጋ ላይ መውደቅ እያየ ስለያዘው አቋም መስማት ጓጉተናል። ማስታወቂያ ባወጣ በሳምንቱ ፣ ስብሰባውን ሊያደርግ ቀናት ሲቀሩት ደግሞ ዛሬ ምሽት የህብረቱ አመራሮች በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተዋል ። አሁንም ኮሚቴው በዚህ ስብሰባ ምን በል ሊባልም ሆነ ከወላጅ መምህራን ጋር በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዳይነካ የሚፈለገውን ቦታና እንዳይታለፍ የሚፈለገው የቀይ መስመር ገደብ ምን ሊሆን እንደሚችል አንገምትም ። ብቻ ሁነኛ ባለቤት አጥቶ አንደ ስደተኛው ተገፊ ወገን ለሚከላተመው የ3000 ታዳጊዎች ትምህርት ቤት መጻኢ ህይዎት ወላጁ በስብሰባው በመሳተፍ መምከር ይኖርበታል ።
በመግስት ሊደራጅ ያታቀደው ኮሚኒቲ …
nebiyu2
ዛሬ ያለው ኮሚኒቲ በአዲስ የመተኪያው የምርጫ ጊዜ በቆንስል መስሪያ ቤቱ ትዕዛዝ ተላልፏል ። የሚተካው ኮሚቴ ደግሞ የሚደራጀው በመንግስት እንደሆነ እየተነገረን ነው ። የምርጫው መዘግየትም ዋናው ምክንያት ይህ እውነት መሆኑ ቆንስል መስሪያ ቤቱ ከመካከለኛው ምስራቅ አገኘሁ ያለውን ሞዴል የኮሚኒቲ ህግና ደንብ ረቂቅ ጊዜውን ለጨረሰው ኮሚኒቲ ይፋ አድርጎታል። ቅንነት በሌለበት መንደር በወረቀት ላይ በሰፈረ ህግና መመሪያ ለወጥ ያማጣ ይመስል የማይገባ ስራ መሰራት ተጀመሯል። የሚጠፋውን ጊዜና የሚባክነውን የማህበረሰብ ንብረት ብክነት ነዋሪው ህብረት ፈጥሮና ማህበሩን ከፖለቲካና ከድርጅት አደረጃጀት ጣለቃ ገብ ሂደት በማስቆም ነጻ ካላወጣው አደጋው የከፋ እንደሚሆን ጥርጣሬው ያየለብኝ ለእኔ ብቻ ቢሆን መልካም ነበር ። ግነወ አይደለም ። ብዙ ነዋሪ አዲሱን አካሄድ አልወደውም ።
nebiyu3
ኮሚኒቲውን በአንድ ባንዴራ ስር ከማደራጀት ተወጥቶ በብሔር ብሔረሰብ ስብጥርና የፖለቲካ ድርጅት ሰወች በኮሚኒቲው በማሰግሰግ የሰራነው ስራ እንዳላዋጣን እናስተውለው። ወላጁም ሆነ አብዛኛው የጅዳና አካባቢው ነዋሪ ለአመታት የራቀው ኮሚኒቲ የጥቂቶች መፈንጫ ከሆነ ወዲህ የሆነውን ቆም ብለን እናስብ ! እናም ቢያንስ በልጆቻችን ትምህርት ቤትን ህልውና ለማስጠበቅ ኮሚኒቲውን ሊውጠው ከተዘጋጀ ክፉ አውሬ አፍ ለማዳን እንረባረብ ! በኮሚኒቲውና በትምህርት ቤቱ ዙሪያ በሚደረጉ ስብሰባዎች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የልጆቻችን ትምህርት ቤት ለመታደግና ለህልናው ወሳኝ የሆነውን ኮሚኒቲ ከወደቀበት አዘቅት አውጥተን ለብሩህ ተስፋ ሂደቱ እንታደገው ፣ እናጎልብተው ! ወላጅና መምህራን ህብረት በጠሩት ስብሰባ ተሳታፊ እንሁን ፣ በነጻነት ሃሳባችን እናንሸራሽር ! የልጆቻችን ትምህር ቤተችን ከአደጋ እንታደገው ! ይህ ማንም የማይገሰው መብታችን ነውና!
ጀሮ ያለው ይስማ !
ነቢዩ ሲራክ

“እግዚአብሔርና ፋሺሽቶቹ”

$
0
0

ቫቲካን ከሙሶሊኒ ጋር ስለ ነበራት ሕብረት
ስለ ዴሽነር መጽሐፍ፤ በኪዳኔ ዓለማየሁ
God and the Fascists _Critique by Kidane Alemayehu_
ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው ዋናው ምንጩ በሆነው፤ እ.አ.አ በ2013 (2006 ዓ/ም) ታትሞ ለንባብ በደረሰው፤ ካርልሔንዝ
ዴሽነር (Karlheinz Deschner) “እግዚአብሔርና ፋሺሽቶቹ – የቫቲካን ሕብረት ከሙሶሊኒ፤ ፍራንኮ፤ ሒትለርና ከፓቬሊች
ጋር” “God and The Fascists – The Vatican Alliance with Mussolini, Franco, Hitler, and Pavelic” በተሰኘው
መጽሐፍ በተካተተው ማስረጃ ላይ ነው። የጽሑፌ ዓላማም በፋሺሽቶች ኢትዮጵያ ላይ ስለ ተፈጸመው እጅግ መራር የጦር
ወንጀል፤ የቫቲካንና የሙሶሊኒ ግንኙነት ምን ይመስል እንደ ነበር ደራሲው ተመራምሮ ያቀረበው ማስረጃ በኢትዮጵያውያን
ዘንድ ሰፊ ግንዛቤ እንዲያገኝ ለማድረግ ነው። ስለዚህ፤ ደራሲው ቫቲካን ከሒትለር፤ ከፍራንኮና ከፓቬሊች ጋር ስለ ነበራት
ግንኙነት ያቀረበውን ማስረጃ በዚህ ጽሑፌ አላካተትኩትም።
god
እንደሚታወቀው፤ በሙሶሊኒ ትመራ የነበረችው ፋሺሽት ኢጣልያ፤ በቫቲካን ያልተቆጠበ ድጋፍ፤ ኢትዮጵያ ላይ
በፈጸመችው የጦር ወንጀል አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከመጨፍጨፋቸው በላይ 2 000 ቤተ ክርስቲያኖችና 525 000
ቤቶች ወድመዋል። ሌላም እጅግ አስከፊ ግፍ ተፈጽሟል።
በዓለም-አቀፍ ሕግ በተከለከለ የመርዝ ጋዝ ጭምር በመጠቀም ፋሺሽቶች በፈጸሙት የጦር ወንጀል፤ ቫቲካን ስለ ነበራት
ሚና በተለይም መሪዋ ስለ ነበሩት ፖፕ ፓየስ 11ኛና ፋሺሽቱ ሙሶሊኒ ሕብረት በብዙ ማስረጃ ተረጋግጧል። በበኩሌ ከዚህ
ቀደም ባቀረብኳቸው መጣጥፎች፤ እነአልቤርቶ ስባኪ (Alberto Sbacchi, “Ethiopia Under Mussolini”) አቭሮ
ማንሐታን (Avro Manhattan: “The Vatican in World Politics”), ሥዩም ገብረእግዚአብሔር (“The Symphony of
My Life”) ወዘተ. መጽሐፎች እንዲሁም ታዋቂ በሆኑ ጋዜጦች (New York Times) እና (Manchester Guardian)
የቀረቡትን አስተማማኝ ማስረጃዎች አካፍያለሁ። በተገኙት ማስረጃዎች ሁሉ ፖፕ ፓየስ 11ኛ ከሙሶሊኒ ጋር በነበራቸው
ፖለቲካዊ ቅርበትና የመጠቃቀም ሥልት፤ “ላተራን” (Lateran) የተሰኘ ውል ተፈራርመው ሲደጋገፉ እንደ ነበር፤ ፖፑ
ራሳቸው የኢጣልያን ንጉሥ፤ ኡምቤርቶን “የኢጣልያ ንጉሥና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት” ብለው የባረኳቸው መሆኑን፤
የቫቲካን መሪዎችና ካሕናት የፋሺሽቱን ጦር መባረካቸውን በተጨባጭ ማስረጃ ፍንትው ብሎ ቀርቧል።
ፖፕ ፓየስ 11ኛና ሙሶሊኒ እጅና ጓንት ሆነው እንዲተባበሩ ያመቻቸላቸው ዋናው መሠረታዊ ምክንያት ሁለቱም መሪዎች
ለዲሞክራሲ፤ ለሕብረተ-ሰብዓዊነትና ለኮሙኒዝም ይጋሩት የነበረው ጥላቻ ነበር። በአበው አነጋገር፤ “የጠላቴ ጠላት፤ ወዳጄ
ነው” በሚለው ሰንካላ መርሆ ይመሩ ነበር ማለት ነው።
የ”እግዚአብሔርና የፋሺሽቶቹ” ደራሲ፤ ካርልሄንዝ ዴሽነርስ ምን ብሏል?
1ኛ/ እ.አ.አ ከ1922 በፊት፤ ቫቲካንና የኢጣልያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተጻራሪዎች ነበሩ። ቫቲካን ባንድ በኩል ስትሆን
በሌላ በኩል፤ የሶሺያሊስትና የኮሚዩኒስት ፓርቲዎች ሐገሪቱን ለመቆጣጠር ይፎካከሩ ነበር። በተለይ ሙሶሊኒን
በተመለከተ፤ በጊዜው እሱ በእግዚአብሔር የማያምን፤ እንዲያውም ስለ ክርስቶስ ተገቢ ያልሆኑ ቃላት በጽሑፍ ያቀርብ
እንደ ነበረና ይህንን ሁኔታ የተገነዘቡ ሌሎች ጸሐፊዎች በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንና በፋሺሽቶቹ መሀል ምሕረት የሌለው
ግጭት ሊከሰት እንደሚችል ይተነብዩ ነበር። (ገጽ 28-29)
“Mussolini was certainly an atheist. His first essay, published in 1904 and titled “There is No
God.” was about the nonexistence of God…..” (p 28) (ትርጉም፤ ሙሶሊኒ በእርግጥ በእግዚአብሔር
የማያምን ሰው ነበር። (እ.አ.አ.) በ1904 ያሳተመው “እግዚአብሔር የለም” የተሰኘው የመጀመሪያ ጽሑፉ ስለ
አምላክ አለመኖር ነበር።)(ገጽ 28)
2ኛ/ እ.አ.አ በ1921 ግን ሊከሰት የሚችለው ግጭት ቀርቶ ፋሺሽቶቹ ባወጡት መግለጫ፤
“…the Fascist leader announced “that the only universal idea that exists in Rome today is
the one that emanates from the Vatican.” (p. 29) (ትርጉም፤ የፋሺሽቱ መሪ (ሙሶሊኒ)፤
“ባሁኑ ጊዜ በሮም የሚገኘው ዓለም-አቀፋዊ አስተሳሰብ ከቫቲካን የሚመነጨው ነው።” በማለት
አስታውቋል። (ገጽ 29)
ስለዚህ፤ አኪሌ ራቲ (Achille Ratti) በመባል ይታወቁ የነበሩት የካቶሊክ ካርዲናል እ.አ.አ የካቲት 5 ቀን 1922
(February 5, 1922) ፖፕ ፓየስ 11ኛ (Pope Pius XI) ተሰኝተው እንደ ተመረጡ ሙሶሊኒ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር
በእለቱ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ የቫቲካን አደባባይ በመሔድ የተሰማውን ጥልቅ ስሜት አንጸባርቆ ነበር። ከጥቂት ጊዜ
በኋላም ሙሶሊኒ በጻፈው ደብዳቤ ለፖፕ ፓየስ የነበረውን አድናቆት እንዲሁም በፖፑና በኢጣልያ መሀል
የነበረው ግንኙነት እንደሚሻሻል አስተያየቱን ገልጾ ነበር። (ገጽ 29፤ ምንጭ (Neisser Zeitung, March 12, 1929)
የሙሶሊኒ ድርጊት ግን ሃይማኖተኛ ወይም ካቶሊካዊ በመሆኑ አልነበረም። እንዲያውም፤ ሃይማኖት ንጉሦችና
ጨቋኞች ለሥልጣናቸው የሚጠቀሙበት መሣሪያ መሆኑን ያምን ነበር።
“But on the other hand, Mussolini knew that religion, as he had himself stated in his
first atheist piece of writing, is “a trick of kings and oppressors to keep their subjects
and slaves under control” (p. 30) (ትርጉም፤ በሌላ በኩል፤ በሙሶሊኒ እውቀት፤
በመጀመሪያው የኢአማኝ ጽሑፉ፤ “ሃይማኖት ንጉሦችና ጨቋኞች ሕዝቦቻቸውንና
ባሪያዎቻቸውን በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ የሚጠቀሙበት ማታለያ” መሆኑን አትቶ ነበር።)(ገጽ 30)
3ኛ/ ካርዲናል አኪሌ ራቲ፤ ለፖፕነት ከመመረጣቸው በፊት እ.አ.አ. በ1921 ስለ ሙሶሊኒ የነበራቸውን ከፍ ያለ
አድናቆት እንደሚከተለው ገልጸው ነበር፤
“ Mussolini is making quick progress and will crush everything that gets in his way with
elemental force. Mussolini is a wonderful man. Did you hear? A wonderful man!…..
The future belongs to him.” (p 30)(ትርጉም፤ ሙሶሊኒ በፍጥነት እየገሰገሰ ነው፤ የሚጋረጥበትንም ማንኛውንም ነገር በኃይል ያወድመዋል።
ሙሶሊኒ ግሩም ሰው ነው። ሰማችሁኝ? ግሩም ሰው!…..መጪው ዘመን የሱ ነው።” (ገጽ 30) (ምንጭ፤ Paris,
The Vatican, 69)
4ኛ/ አኪሌ ራቲ፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ በመባል ከተመረጡ በኋላ ከፈጸሟቸው ለሙሶሊኒ እጅግ ጠቃሚ ተግባሮች
አንደኛው እ.አ.አ. ጥር 20 ቀን 1923 (January 20, 1923) የቫቲካን ዋና ደጋፊ የነበረውን “ፓርቲቶ ፖፑላሬ” (Partito
Populare) የተሰኘውን የካቶሊክ ፓርቲ ማውደም ነበር። የዚህም ዋናው ምክንያት ለቫቲካን የፋሺሽቱ ፓርቲ የተሻለ ጥቅም
የሚያስገኝ መሆኑን በማመን ነበር።
5ኛ/ ሙሶሊኒ ለቫቲካን ያበረከተው የመጀመሪያው አገልግሎት 1.5 ቢሊዮን ሊሬ በማበርከት ነበር፤
“The first service the ex-socialist rendered to the Holy See was a financial one. He saved the
“Banco di Roma” to which the curia and many of its prelates had entrusted large amounts of
money, from bankruptcy by stepping in with approximately 1.5 billion lire at the expense of the
Italian state.” (p31-32) (ትርጉም፤ የቀድሞው ሶሺያሊስት (ሙሶሊኒ) ለቫቲካን ያበረከተው የመጀመሪያው
አገልግሎት የገንዘብ እርዳታ ነበር። በኢጣልያ መንግሥት ወጪ፤ 1.5 ቢሊዮን ሊሬ በማበርከት ቫቲካንና
መንፈሳዊ መሪዎቿ ብዙ ገንዘብ ያስቀምጡ የነበረበትን “ባንኮ ዲ ሮማ”ን ከክስረት አዳነው። (ገጽ 31-32፤ ምንጭ፤
Manhattan, 112)
በሙሶሊኒና በፖፕ ፓየስ 11ኛ መሀል የነበረው ግንኙነትና ሕብረት እጅግ የተጠናከረ ስለ ነበረ፤ ፋሺሽቶች
ተቃዋሚ ካቶሊኮችን ሲያሰቃዩና ሲገድሉ ፖፑ ምንም ተቃውሞ አላሰሙም ነበር። እንዲያውም፤ የካቶሊክ ካሕናት በሙሉ
ከካቶሊክ ፓርቲ ራሳቸውን እንዲያገልሉ በማዘዝ ለፋሺሽት ፓርቲ ከፍተኛ እንቅፋት የነበረውን ሁኔታ አስወገዱለት። ከዚህ
በተጨማሪ፤ ከዚህ በታች ያለውን መግለጫ ለዓለም አስታወቁ፤
“Mussolini has been sent to us by Providence.” (p. 33) (ትርጉም፤ ሙሶሊኒ በፀጋ (በአምላክ) የተላከልን
ነው።) (ገጽ 33፤ ምንጭ፤ Manhattan, 115)
6ኛ/ ሌላው ሙሶሊኒና ፖፕ ፓየስ 11ኛ የተጠቃቀሙበት እጅግ ከፍተኛ ጉዳይ፤ “ላተራን” (Lateran) የተሰኘውን
ውል በመዋዋል ነበር። በዚህ ውል መሠረት፤ ቫቲካን መንግሥታዊ ልዑላዊነት እንዲኖራት ከመደረጉ በላይ የኢጣልያዊ
ብሔራዊ ሃይማኖት ካቶሊካዊነት እንዲሆን ተደረገ። ቫቲካንም የፋሺሽቶቹ ዋና ደጋፊ፤ አጋር ሆነች፤
“The church rejoiced. On February 13, 1929, the pope once again praised Mussolini as the man
“who was sent to us by Providence” and shortly after ordered the clergy to say prayer “for the
King and the Duce” (“Pro Rege et Duce”) at the end of daily mass.” (p. 36) (ትርጉም፤ ቤተ
ክርስቲያኗ (ቫቲካን) ፈነደቀች። እ.አ.አ. የካቲት 13 ቀን 1929 ፖፑ (ፖፕ ፓየስ 11ኛ) ሙሶሊኒን አመሥግነው
“በፀጋ የተላከ ሰው” መሆኑን እንደ ገና ገልጸው፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ካሕናቱ ለንጉሡና ለዱቼ (ለሙሶሊኒ) በየእለቱ
ሥርዓት እንዲጸልዩ አዘዙ።) (ገጽ 36፤ ምንጭ፤ Tondi, Die geheime Machr [The Secret Power], 34,
and Die Jesuiten [The Jesuits], 73, Manhattan, 118)
7ኛ/ የሙሶሊኒና የፖፕ ፓየስ 11ኛ ጠንካራ ሕብረት የተንጸባረቀበት ከባድ ክስተት በኢትዮጵያ ላይ የተፈጸመው
የጦር ወንጀል ነበር። በቫቲካን በኩል፤ እነካርዲናል ኢልዲፎንሶ ሹስተር (ሚላን) (Cardinal Ildefonso Schuster of
Milan) ኢትዮጵያን የካቶሊክ ሃይማኖት ተከታይ ለማድረግና የኢጣልያን ግዛት ለማስፋፋት ወረራውን በይፋ ሲደግፉ
በፋሺሽቶቹ በኩል ደግሞ ቁጥሩ እየጨመረ ለሔደው ለኢጣልያ ሕዝብ የቅኝ ግዛት ማስፈለጉን እንደ በቂ ምክንያት
በማቅረብ ጦርነቱ እንዲከናወን ገፉበት። ፖፕ ፓየስ 11ኛ የፋሺሽቱን ወረራ በሚቀጥለው ቋንቋ ደገፉት፤
“On August 27 (1935), when the Italian war preparations were running at full speed, the
Pope announced-interwoven in many calls for reason and peace-that a defensive war (!) for
the purposes of the expansion (!) of a growing population could be just and right.”
(ትርጉም፤ እ.አ.አ. ነሐሴ 27 (1935) የኢጣልያ የጦርነት ዝግጅት እየተጧጧፈ ሳለ፤ ፖፑ (ፖፕ ፓየስ 11ኛ)-
ከተገቢነትና ከሰላም ጥያቄዎች ጋር እያወሳሰቡ፤ ታዳጊ ለሆነው የሕዝብ ብዛት ግዛትን ለማስፋፋት (!) የመከላከያ
ጦርነት (!) ማከናወን ተገቢና ትክክል መሆኑን ገለጹ።” (ገጽ 43፤ ምንጭ፤ Manhattan, 121 ff. The speech is
Printed in Reichspost, Vienna, August 30, 1935)
ፖፕ ፓየስ 11ኛ የፋሺሽቱን የኢትዮጵያ ወረራ የደገፉት ከላይ በተጠቀሰው መግለጫ ብቻ አልነበረም። ብዙ ሌሎች
ተጨባጭ እርምጃዎች ወስደው ነበር። ከነዚህ ውስጥ፤ (ገጽ 41-49)
(ሀ) ጳጳሶቹ የወርቅ መስቀሎቻቸውንና የአንገት ሰንሰሎቻቸውን እንዲያስረክቡ አዘዙ። በተጨማሪም፤ ጳጳሶቹና
ካሕኖቹም የካቶሊክ ምእመናን ወርቆቻቸውንና ጌጦቻቸውን ለፋሺሽቱ መንግሥት ጦርነት እንዲያበረክቱ
አደረጉ።
“According to Professor Salvemini from Harvard University, at least seven Italian
cardinals, twenty-nine archbishops, and sixty-one bishops supported the Fascist
raid (on Ethiopia) immediately,….) (p. 46) (ትርጉም፤ የሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር
ሳልቬሚኒ (እንዳቀረቡት) ቢያንስ 7 (የካቶሊክ) ካርዲናሎች፣ 29 ሊቀ-ጳጳሶች እና 61 ጳጳሶች ወረራውን
(በኢትዮጵያ ላይ) ወዲያውኑ ደገፉ።” (ገጽ 46፤ ምንጭ Manhattan, 123)
(ለ) ጀርመን ሐገር የነበረው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ንብረት ለሙሶሊኒ እንዲዛወርና ለጦርነቱ የሚያስፈልገው
እንዲገዛበት አደረጉ፤
(ሐ) ሌሎች ሐገሮች የሚገኙ ካቶሊኮች የኢጣልያን ወረራ እንዲደግፉ አደረጉ፤
(መ) የካቶሊክ ካሕናትና ሰባኪዎች ለኢጣልያ ጦር ድል እንዲጸልዩ ተደረገ፤
(ሠ) የፋሺሽት ወታደሮች፤ መድፍና የመርዝ ጋዝ በተጋዘበት መርከብ የቅድስት ማርያም ምስሎችም አብረው
እንዲጓዙ ተደረገ፤
“…..Abyssinians, who had neither gas masks nor shelters, unsuspectingly fell victim to the
dangers of Catholic culture. After the so-called Battle of Amba Aradam, an Italian
captain counted more than sixteen thousand butchered “enemies” (Ethiopians). They lay
there, dead or half-dead, where the skin-burning, lung-tearing gas that was sprayed
from the air had reached them, and they were all eliminated in the most hygienic
possible way – that is, by flamethrowers. (p. 49) (ትርጉም፤ ጭንብልና መጠለያ
የሌላቸው ያልጠረጠሩ ሐበሾች (ኢትዮጵያውያን) የካቶሊክ ባህል ሰለባ ሆኑ። አምባ አራዶም
ከተሰኘው ጦርነት በኋላ አንድ የኢጣልያ ካፕቴን በቆጠረው መሠረት ከ16 000 “ጠላቶች”
(ኢትዮጵያውያን) በላይ ከአየር በተነሰነሰባቸው የመርዝ ጋዝ ቆዳቸው ተቃጥሎ፤ ሳምባቸው ተበጣጥሶ
የሞቱ ወይም በመሞት ላይ የሚገኙ ነበሩ። ሁሉም በተወረወረባቸው የእሳት ቃጠሎ በቅልጥፍና
ተወገዱ። (ገጽ 49፤ ምንጭ፤ Borgese, 400)
(ረ) የፋሺሽቱ ጦር ኢትዮጵያን 90% ሲቆጣጠር፤ ፖፕ ፓየስ 11ኛ የደስታ መግለጫ አሰምተው ነበር፤
“And the Pope also shared in the “triumphant joy of the truly great and good people
about the peace, which,” he said on May 12, 1936, “as one may hope and agree, will be
an effective contribution, a prelude to true peace in Europe and the whole world”. (p 49)
(ትርጉም፤ እ.አ.አ. ግንቦት 12 ቀን 1936 ፖፑ (ፖፕ ፓየስ 11ኛ) የደስታ ተካፋይነታቸውን ሲገልጹ፤
“ለአውሮፓና ለመላው ዓለም እውነተኛ ሰላም አስተዋጽኦ የሚኖረው ለታላቅና ግሩም ሕዝብ (የኢጣልያ)
ታላቅ ድል መሆኑ እንደሚታወቅ ተስፋ ይደረጋል።” (ገጽ 49፤ ምንጭ፤ Manhattan, German edition,
116)
8ኛ/ ፖፕ ፓየስ 11ኛን የበታቾቻቸው ከሆኑት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተግባሮች ነጻ ለማድረግ
የሚደረገው ሙከራ ሁሉ መሠረተ ቢስ ነው።
“….But all attempts to exculpate the pope are in vain because his own words are a testament
to the contrary. Quite apart from the fact that the bishops can do only what he wants. Or
should they collect gold, bless weapons, and give martial speeches to Italy, of all places, if
the pope has banned it? If he really desires peace? (p. 44) (ትርጉም፤ የራሳቸው ቃላት
ተቃራኒውን ስለሚያረጋግጡ፤ ፖፑን ከኃላፊነት ለማዳን የሚደረገው ሙከራ ዋጋ ቢስ ነው። ተጨባጩ ጉዳይ
ጳጳሶቹ ሊያከናውኑ የሚችሉት ፖፑ የፈቀዱትን ብቻ ነው። ፖፑ ከልክለው ቢሆን ኖሮ (ጳጳሶቹ) ወርቅ
መሰብሰቡን፤ የጦር መሣሪያ መባረኩንና ቀስቃሽ የሚሊታሪ ንግግሮችን፤ ሌላ ሐገር ሳይሆን በኢጣልያ ማከናወን
ይችሉ ነበር?(ፖፑ) ሰላም ቢፈልጉ ኖሮ? (ገጽ፤ 44)
መደምደሚያ፤
በኢትዮጵያ ላይ ለተፈጸመው አሰቃቂ ግፍና የጦር ወንጀል፤ በሙሶሊኒና በፖፕ ፓየስ 11ኛ መሀል ስለ ነበረው የጠበቀ
ግንኙነትና ሕብረት፤ ብዙ አስተማማኝ ማስረጃ በማቅረብ ግንዛቤያችንን ስላጠናከረልን፤ ደራሲውን ዴሽነርን
አመሠግናለሁ። ስለዚህ ጉዳይ፤ ተቃራኒውን በመጻፍ የማያስፈልግ ውዥንብር የፈጠሩ ጸሐፊዎችም፤ በተለይ
ኢትዮጵያውያን፤ ተገቢውን እርምት በማከናወን ለውድ ሐገራችን ለኢትዮጵያ የሚገባትን ፍትሕና ክብር ለማስገኘት
እንዲተባበሩ በዚህ አጋጣሚ አደራ እላለሁ።
በተጨማሪም፤ ዓለም-አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ – የኢትዮጵያ ጉዳይ (Global Alliance for Justice – The Ethiopian
Cause) የተሰኘው ድርጅት በኢትዮጵያ ለደረሰው የፋሺሽት ግፍ ተገቢው ፍትሕ እንዲገኝ ለሚከተሉት ዓላማዎች እየጣረ
ነው፤
(ሀ) ቫቲካን የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንድትጠይቅ፤
(ለ) የኢጣልያ መንግሥት ተገቢውን ካሣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲከፍል፤
(ሐ) ቫቲካንና የኢጣልያ መንግሥት ከኢትዮጵያ የተዘረፉትን ንብረቶች እንዲመልሱ፤
(መ) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፤የፋሺሽቱን ጦር ወንጀል በመዝገቡ እንዲያውል፤ እና
(ሠ) በቅርቡ፤ የቫቲካን ተወካይ በተገኙበት፤ አፊሌ (ኢጣልያ) ለፋሺሽቱ ወንጀለኛ የተመረቀው ኃውልት
እንዲወገድ።
ባሁኑ ጊዜ፤ ከላይ የተጠቀሰው ድርጅትና ደጋፊዎቹ በመተባበር፤ የዚህ ዓመት የካቲት 12 የሰማእታት ቀን በዓለም ዙሪያ በ30
ከተሞች እንዲከበር ጥረት እየተደረገ ነው።
ለበለጠ ዝርዝር የድርጅቱን ድረገጽ፤ www.globalallianceforethiopia.org መመልከት ይቻላል። በዚያውም፤ ኢጣልያኖች
ጭምር የፈረሙት አንድ ዓለም-አቀፍ አቤቱታ ስለሚገኝ አንባቢዎች በፊርማችሁ ድጋፋችሁን እንድትገልጹ በትሕትና
ተጋብዛችኋል።
ለኢትዮጵያ ክብርና ፍትሕ እንታገል!

ወያኔ: የነፃው ፕሬስ ፀር!

$
0
0

በቅዱስ ዩሃንስ

ነፃ- ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው።
freedom
ነፃ ፕሬስ የሀሳብ ነፃነት መብት አልፋና ኦሜጋው ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የነፃ ፕሬስ መኖር የሚያረጋግጠው ጋዜጠኞች ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት የሚያስቡትን፡ የሚሰማቸውን፡ የሚሰሙትን እንዲሁም ምርምር አድርገው የደረሱበትን ዜናዎች በነፃ ለመፃፍና ለማሰራጨት ብሎም ሕዝብ እንዲወያይበት ለማድረግ ያላቸው ያልተገደበ መብት ነው። ይህም ጤናማ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን ለእድገቶቹም ጉልህ ድርሻ አለው። ነፃ ፕሬስ የኃሳብ ነፃነት ተግባራዊ ለመሆኑ ዋስትናም መፈተኛም ነው። ኃሳብን ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት በነፃ ለመግለፅ መቻልና መለዋወጥ እንደ ምግብና መጠጥ፤ ሁሉ ሰብአዊ ክቡርነትን የተላበሰ ሕይወት ለመጎናፀፍም አስፈላጊም ናቸው። ሃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት መኖርና ዋስታናው ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሕግ መረጋገጥ ማለት ዘላቂነት ላለው ዴሞክራሲያዊ እድገት ለማገኘትም ዋና መሰረት ነው።

የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት የነፃ ፕሬስ አስፈላጊነት ትልቅ ቦታ እንዳለው ከልብ ይታመናል፡፡ ያለነፃ ፕሬስ ዴሞክራሲ አለ ብሎ መናገር ማወናበድ እንጅ እውነት ሊሆንም አይችልም፡፡ የነፃ ፕሬስ መኖር በራሱ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መኖር መገለጫ ነውና፡፡ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ሲኖርም ነፃ ፕሬስ ይኖራል፡፡ ወደ እኛ ሃገር ስመለስ ግን ነገሮች ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ወያኔ መንግስት ሆኖ ላለፉት 23 ዓመታት ሃገሪቱን ሲያስተዳድር ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን በወረቀትና በቃል እንጂ ከዚያ በዘለለ በተግባር ሲፈፅም አላሳየንም፡፡ ለመተግበር የሞከራቸውንም እንደ ቀንዳውጣ ቀንድ መልሶ ሸሽጎታል፡፡ ስለዚህ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት የማያምን አምባገነን ስርአት ስለሆነ ለነፃው ፕሬስ ፀር በመሆን ተገቢውን ጥበቃና እንክብካቤ በመስጠት ፋንታ አጥፊና ደምጣጭ ሆኖ እየሰራ ይገኛል።

ዛሬ በዘመነ ወያኔ በኢትዮጵያችን ነፃ ፕሬስ በአሳሪና አስፈሪ የፕሬስ አዋጅ ተጠፍሯል። ጋዜጠኞች ሰበብ አስባብ እየተፈለገ በየፍርድ ቤቱ እየተጎተቱ ነው። ወደ እስርቤት እየተጣሉ፤ እየተሰደዱም ነው። የጋዜጣ፣ የመጽሔት፣ የመጻሕፍት ማሳተሚያ ዋጋ ሰማይ ጠቅሷል። በሀገሪቱ ሕገመንግሥት ቀርቷል የተባለ ቅድመ ምርመራ (ሳንሱር) በብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ጓሮ በኩል በእጅ ኣዙር ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጔል። ሌሎች በከተማው ያሉ ማተሚያ ቤቶችም ሳንጃ የተከለ ጠመንጃ ወድሮ የሚያስፈራራ ኃይል ያለባቸው ይመስል “የተቃዋሚ ጋዜጣን አናትምም” ብለዋል። በቅርቡ በሰማያዊ ፖርቲ ‘‘ነገረ ኢትዮጵያ’’ ጋዜጣ ላይ የተሰተዋለው ችግር ይሄው ነው። ጋዜጣዋ ተዘጋጅታ ለማተምያ ቤት ብትበቃም ስርአቱ በፈጠረው የማደናቀፍ ተንኮል ለህትመት ሳትበቃ በመቅረቷ በፓርቲው ቀና ትብብር በድህረ ገፃቸው እንድናገኛት ተገደናል። ማተሚያ ቤቶች ሠርቶ የማትረፍና ሀብት የመፍጠር ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን እንዲሁም ሕዝብን የማገልገል ግዴታቸውን በፍርሀት ጨርቅ ገንዘው በየማተሚያ ቤታቸው ጓሮ ቀብረውታል። የሕዝብ ንብረት የሆኑ፣ በሕዝብ ሀብት የሚተዳደሩ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሃያ አራት ሰዓት በወያኔ በሞኖፖል ተይዘዋል፡ የገዥው ልሳን ብቻ መሆናቸውንም አስመስክረዋል። ሌሎችም የተለያየ ስም እየተሰጣቸው በአየር ላይ አለን የሚሉ ጣቢያዎች ልሳናቸው የበዛ ቢመስልም ከሞላ ጎደል ቋንቋቸው አንድ ነው። ያ ቋንቋ ግን የእውነተኛ ነፃ ፕሬስ ቋንቋ አይደለም። በዚህ ዓይነት የፕሬስ ሁኔታ በሀገራችን ዴሞክራሲ ሊኖር አይችልም።

ይህ ነፃ ፕሬስን ማቀጨጭ ብሎም ለመቃብር ማብቃት ደግም በአለም ላይ በስፋት እንደታየው የአምባገነን መንግስታት መለዬ ካባ ነው። አምባገነኖች የሚገዙትን ህዝብ ለመቆጣጠር ከሚወስዷቸው እርምጃዎች ቀዳሚው ፕሬስን መቆጣጠር ነው። በጉልበት የሚገዙት ህዝብ እነሱ ከሚሉት ውጭ እንዳይሰማ ለማድረግ ወደ ህዝብ ጆሮ የሚደርሱትን ነገሮች ሁሉ የመቆጣጠር ተግባር ይፈጽማሉ። ከዚህም በተጨማሪ ውሸትን ደጋግሞ በማውራት እውነት ለማስመሰል ይተጋሉ። ይህ የአምባገነን ሥርዓቶች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው። ስለዚህ ወያኔም ነፃ ፕሬስን የሚፈራበት ትልቁ ምክንያት በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት አምባገነንነቱንና የጥፋት ተልዕኮ ሚናውን አጋልጠው በሕዝብ እንዲተፋ ማድረጋቸውን በሚገባ ስለሚያውቅ ነው። ይህም ብቻ አይደለም። ነፃ ፕሬሶች ወያኔን ከሥልጣን ለማስወገድ በሚደረገው ሕዝባዊ ትግል የሚያበረክቱት አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑን በማወቁ ጭምር ነው።

ወያኔ ለሙያቸው ክብር ያላቸው ጋዜጠኞችን በክሶች ብዛት፤ በእስርና እንግልት እንዲሁም ከአቅማቸው በላይ በሆነ የገንዘብ ቅጣት እንዲሸማቀቁ በማድረግ እውነት ዘጋቢ ስታጣ የኢትዮጵያ የመረጃ አየር በውሸት የተሞላ እንዲሆን አድርጎታል። ወያኔ በፈለገው መልክ ሊተረጉመው በሚችለው አንቀጽ ጋዜጠኞችን እያስፈራራና እያዋከበ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነፃነት መብትን ይኸው እስካሁን ድረስ እንዳፈነ ይገኛል። ወያኔ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ለታሰሩ፥ ለተገደሉ፥ ለስደት ለተዳረጉ በርካታ ጋዜጠኞች ዋና ተጠያቂ ነው። የእስራት ፍርድ ተፈርዶባቸው በመማቀቅ ላይ የሚገኙ አሁንም በርካታ ናቸው። የተወሰኑትም ደግሞ ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርገዋል። በአገር ውስጥ የሚገኙ የመረጃ መረቦችን በማናለብኝነት ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር፤ ከውጭ አገራት የሚተላለፉ የሬድዮና የቴሌቪዥን ሞገዶችን በይፋ በማፈን ኢትዮጵያ አገራችን በመረጃ ከዓለም የተነጠለች ደሴት ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፤ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሃብትንም ለዚህ እኩይ ስራው ያባክናል። ነፃ- ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው።

በመጨረሻም ወያኔ የነፃ ፕሬስ ጠላትነቱን ያረጋገጠው ሥልጣን እንደጨበጠ በመሆኑ ላለፉት 23 አመታት አንድን አፋኝ ሕግ በሌላ አፋኝ ህግ እየተካና እያጠናከረ የነፃ ፕሬስ ፀር መሆኑን ያስመሰከረ በኢትዮጵያ ላይ የመጣ መቅሰፍት ነው። ስለዚህ ለእውነት የቆመ ነፃ ሚዲያ መወለድና ማበብ በአገራችን እንዲኖር ለምንሻው ዲሞክራሲ የመሰረት ድንጋይ መሆኑን በማመን፤ ለእውነት የቆሙ ነፃ ፕሬሶች እንዲፈጠሩ መታገል የሁላችንንም ርብርብ የሚጠይቅ ሃላፊነት መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። ራሷ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ያለ ነፃ ፕሬስ ማሰብ አይቻልምና:: መረጃ የተጠማው የኢትዮጵያ ህዝብም ነፃ የሚዲያ ተቋማት እንዲፈጠሩና እንዲጠናከሩ እንቅፋት የሆነውን የአንባገነኑን የወያኔ አገዛዝ ከጫንቃው ለማውረድ በጋራ መታገል ይኖርበታል። በተጨማሪም ነፃ ፕሬስ ለሃገራችን ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በመረዳትና፤ መብትም በትግል እንደሚገኝ በማመን የፕሬስን ነፃነትን ለማምጣት በአንድነት በመነሳት እንቅፋት የሆነውን አገዛዝ በቃህ ልንለው ይገባል።

በመረጃ የዳበረ ህዝብ አንባገነኖችን ቀባሪ ነው!

ለአስተያየትዎ፡ kiduszethiopia@gmail.com አድራሻየ ነው።

በፊላደልፊያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ለተመለሱ መርጃ $23,000 ሰጡ

$
0
0

ከግራ ወደ ቀኝ ሻፊ አደም፣ ግርማዬ ጅሩ፣ በለው አሰፋ፣  ነጋሽ ገብረህይወት . ማርያ ሞሬኖ (ከIOM),  ሃብታሙ ጌታሁን፣ ጌታቸው ወርቅዬ እና አዲሱ ሃብቴ

ከግራ ወደ ቀኝ ሻፊ አደም፣ ግርማዬ ጅሩ፣ በለው አሰፋ፣ ነጋሽ ገብረህይወት . ማርያ ሞሬኖ (ከIOM), ሃብታም ጌታሁን፣ ጌታቸው ወርቅዬ እና አዲሱ ሃብቴ


(ዘ-ሐበሻ) በሳዑዲ አረቢያ ስቃይ ደርሶባቸው ወደ ሃገራቸው ለተመለሱ መርጃ ይሆን ዘንድ ሰሜን አሜሪካ ፊላደልፊያ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአንድ ላይ ያሰባሰቡትን 23ሺህ ዶላር ለIOM አስረከቡ።

ኢትዮጵያውያን ወደ ፊላደልፊያ ስቴት ሄደው መስፈር የጀመሩት ከ1960 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን፤ ስቴቷም በርካታ አፍሪካውያን ይኖሩበታል። በአሁኑ ወቅት በም ዕራብ የፊላደልፊያ ግዛት 10 ኢትዮጵያያን ሬስቶራንቶች፣ ባር እና ሌሎች ቢዝነሶች የሚገኙ ሲሆን የራሳቸው የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲም አላቸው።

በምዕራብ የፊላደልፊያ ግዛት የሚገኙት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላይ ፌብሩዋሪ 2 ቀን 2014 ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የሰጡት 23 ሺህ ዶላር በቀጥታ ሃገር ቤት ለተመለሱና በችግር ላይ ላሉ የሳዑዲ ተመላሾች መርጃ ይውላል ተብሏል።

እንደ ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ዳታ ከሆነ ከ150 ሺህ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ የተመለሱ ሲሆን፤ ለተመላሾቹ ህክምና፣ የስነልቦና እርዳታ፣ ምግብ፣ የመጓጓዣና ለሌሎች ወጪዎች IOMና ሌሎች ድርጅቶች ሲሸፍኑ ቆይቷል።

በፊላደልፊያ የሚገኙት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ለወገን ደራሹ ወገን ነው በሚል መርህ ያዋጡት ገንዘብ ችግሩን በሙሉ የሚቀርፈው ነው ብለው ባያስቡም፤ ለችግሩ ማቃለያ መርጃ ይሆናል በሚል ወደፊትም እንዲህ ባለው ወገናዊ ትብብር ላይ እንደሚሳተፉ ቃል ገብተዋል። የዚህ ዝግጅት አስተባባሪ አቶ አዲሱ ሃብቴ እንደገለጹት ለዓለም አቀፉን የሥደተኞች ድርጅት ገንዘቡን የምናስረክበው ተመላሾቹን ለመርዳት ሲሆን፤ የተዋጣውን 23ሺህ ዶላር በቼክ አስረክበናል ብለዋል።

The photo above is from the check presentation event on Sunday, Feb. 2, courtesy of Addisu Habte.

The photo above is from the check presentation event on Sunday, Feb. 2, courtesy of Addisu Habte.

አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ተነሱ

$
0
0

sewenet Bishaw
(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ያበቁት፣ ለዓለም ዋንጫ ተሳትፎም ጥሩ ውጤት በምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ያስመዘገቡት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ከአሰልጣኝነታቸው ተነሱ።

ከቀናት በፊት በቻን የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደካማ ውጤት መመዝገቡን ተከትሎ በተሰጡ አስተያየቶች የተበሳጩት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው “በፌስቡክ የሚሰጡ አስተያየቶች ቡድኔን ጎድተውታል” ማለታቸው አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በአሰልጣኝ ሰውነት መባረር ዙሪያ ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ተጨማሪ ዝርዝር ዘገባ ወደ በኋላ ይጠብቁ

ግጥም፡ ጤናችን ይጠበቅ በሁላችን

$
0
0

poem(ተፈራ ድንበሩ)

የወጣችሁትን ተራሮች ጥላችሁ
የሮጣችሁትን ሜዳዎች ትታችሁ
አፈር ሳር ቅጠሉ እየናፈቃችሁ
በምኞት በተስፋ ቀን እንዲያልፍላችሁ
በረሀ አቋርጣችሁ የተሰደዳችሁ
ከዘመድ አዝማዱ በመለየታችሁ
ባይተዋርነቱ ናፍቆት ሳያንሳችሁ
በሰው አገር ደግሞ ኑሮ እንዳይከፋችሁ
ያገር ቤቱን እድፍ ከልብ አጥባችሁ
ንጹሕን ልበሱ እናንተም ታጥባችሁ
ተባይ ተከትሎ ጤና እንዳይነሣችሁ።
ዘመንና ትውልድ የማያስተምረው
ተመክሮም ተምሮም እጁን የማያጥበው
ከእድፍ እንዳይጠራ አዚሙ የያዘው
አውቆ የለገመ ይነግሣል መከራው።
ከእግዜር በተሰጠ የማሰብ ፀጋው
ራሱ ንጹሕ ሆኖ ሰው መርዳት ሲገባው
በሽታ ያረባል ወይ በገዛ ሆዱ ሰው?
ነግቶ እሰከሚጠባ አፈር ለሚሆነው
ለቁርሱ ለጉርሱ የሚያደላ ሰው
ከመንደር ቡችዬ በምን ተሻለው?
የወደቀ ሥጋ አፈር ያነሣል
እንዳገኙም መብላት አይቀርም ይጎዳል
ሰው ለነገ ጤናው ቢያስብ ይሻለዋል።
አንጀራ ከመሶብ በእጅ መቁረስን ረስቶ
እንዴት ሰው ይበላል ከመሬት አንሥቶ?
አይሰቀጥጥም ወይ አያሳፍረን?
አይጠዘጥዝም ወይ እንዴት አያመን?
እንዴት ይሸከማል መዥገር ገላችን?
እንዴት በራስ ተባይ ይበከል ባህላችን?

በሃያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን
በእንዝህላልነት ኮሶ ተጣብቶን
የሚያሽር መድሐኒት መምረጥ አቃተን።
በአንድ አምላክ ሥር ሆነን በሰብአዊነት
እንድንፈቃቀር ተሰጥቶን እርስት
ታሪካችን ሆኖ የሰው ልጅ ሥርየት
ደም መጣጭ የሆነ የጉያ ጠላት
ምነው ማምለካችን ጥቃቅን ጣኦት?
በሽታ ካልጠፋ ከየመንደራችን
ሰላም የት ይገኛል በመካከላችን።?
በሽታ ከረባ ምን ሰላም ያገኛል?
ባገር ላይ ተስቦ ለጥፋት ይነግሣል፤
እየተላለፈ ሁሉንም ይፈጃል።
በወረርሽኝ ገብቶ እየተስፋፋብን
ያገር ቤት በሽታ ደግሞ ተከትሎን
ባለንበት ሁሉ እንዳያጠቃን
ገና ያልታመምነው ተራ እስከሚደርሰን
መጠበቅ ሳንሻ ዳግመኛ ሰንፈን
የዘር ነው ተብሎም ሳይተረትብን
እንደሌላው ዓለም እኛም አስተውለን
ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገንም ተንብየን
ጤናማ ሆድና ሳንባ ልብ ይዘን
ዞሮ መግቢያችን ቤት እንዲፀዳልን
እንከላከለው እናጥፋው ተባብረን፤
እኛ ለኛው እንሁን ተፈጠሮ እንደሰጠን፤
ሰላምና ጤና እንዲሰፍንልን።

“መልካም አስጀምሮ እንዲያስጨርሰን”
“አልፋና ኦሜጋን ተስፋ አድርገን”

ጦሰኛው የዐይን ኩልና መሬት ቅርምት በኢትዮጵያ

$
0
0

ይሄይስ አእምሮ

እንደመነሻ – በዚህች ቅጽበት በኢቲቪ እየተላለፈ የሚገኘውን አንድ የእንግሊዝኛ ፕሮግራም ብትመለከቱ አዲስ አበባን የምታውቋት በጣም ልትገረሙ ትችላላችሁ፡፡ ወጣቷ ሴት ጋዜጠኛ ለፈረንጆችና አዲስ አበባን ከእግር እስከራሷ ለማያውቋት ቄንጠኛ የኢትዮጵያ ወይም የሌላው ዓለም ዜጎች ስለዚህችው ገሃነም ከተማ ቆንጆ ምስል ለመፍጠር እየቃተተች ስሰማት ሚስቴ እስክትታዘበኝ ድረስ ከንፈሬን ጠመም በማድረግ አሽሟጠጥኳት፤ ሳላውቅ በስሜት ነውና ጋዜጠኚት ይቅርታሽን እባክሽ፡፡ ሚስቴን ግን ታዘብኳት – “ሞጥሟጣ” ብላ አትሰድበኝ መሰላችሁ፤ ሆ! ለካንስ “ሰው የሚሰደበው በሚያውቀው ነው” መባሉ አለነገር አይደለምና – ዳሩ መጽሐፉስ ቀድሞውን “ኢይከብር ነቢይ በብሔሩ” ብሎት የለም? በጥቂት የሌሊት የመንገድና የዳንስ ቤት መብራቶችና በጥቂት ዘመነኛ ዳንኪራ ረጋጮች፣ በጥቂት ተምነሽናሾችና በጥቂት ገንዘብ መንዛሪዎች የሚሊዮኖች እሥር ቤት የሆነችው አዲስ አበባ እንደለማችና እንዳለፈላት የሚቆጠር ከሆነ የኢቲቪ ድካም በርግጥም ዋጋ አገኘ ማለት ነው፡፡ እውነቱ ግን ይህች ጋዜጠኛ እንደምትለው አይደለም፤ በራሱ ርዕስ ስመለስበት እዳስሰዋለሁ፡፡ ግን ግን ስድስት ሚሊዮን አካባቢ ነዋሪ በሚገኝባት አዲሰ አበባ በጥቂቱ አሥር ሺህ ሰዎች ቢቀማጠሉባትና የሰማይን ጣሪያ በኋላ እግሯ ረግጣ እንዳራቀችው በቅሎ አለልክ ጠግበው ሌት ተቀን እየፈነጠዙ ያሻቸውን ቢያደርጉ አዲስ አበባና አዲስ አበቤዎች አልፎላቸዋል ማለት እንዳልሆነ ኢቲቪዎችም ሆኑ የወያኔው መንግሥት ሊሸፋፍኑት እንደማይችሉ ልናስታውሳቸው ይገባል፡፡ ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ ነው ነገሩ፤ አዲስ አበባ እነሱ እንደሚያሳዩዋት አይደለችም፡፡ አሁን ወደተነሳሁበት ላምራ፡፡
552741_10151371281167365_1241834616_n
“ይበጃል ብለው የተቀቡት ኩል ዐይን አጠፋ፡፡” የምንለው ግሩም ሥነ ቃል አለን፡፡ ጦሰኛ የዐይን ኩል ነው፤ ለጌጥ ብለው ቢቀቡት ዐይንን ከነጭርሱ ደርግሞት ዐረፈው፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በሕይወት ዘመኔ እስካሁን ከታዘብኳቸውና አሁንም ድረስ ከምታዘባቸው በርካታ መንግሥታዊ ዐዋጆችና ደንቦች መካከል ብዙዎቹ ከመንግሥቶቻችን የሚፈልቁ ሣይሆኑ ከውጭ የተኮረጁ ናቸው – እንደዬመንግሥቶቻችን የርዕዮተ ዓለም ቅኝት ከምሥራቁ ወይም ከምዕራቡ፡፡ የሚኮረጅ ነገር ደግሞ አዋጭነቱና ተግባራዊነቱ አጠያያቂ ነው፡፡ የጦጢት ምሳሌ ቀላል አስረጂ ነው፡፡

ተማሪው ዛፍ ሥር ሆኖ ሲያጠና ቆይቶ ምሳውን በልቶ እስኪመለስ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በሚያጠናበት ዛፍ ላይ ሆና የተማሪውን ድርጊት ትከታተል የነበረችዋ ጦጣ ትወርድና ደብተሩን ልክ እሱ ሲያደርግ እንደነበረው አደርጋለሁ ብላ በእስክርቢቶ ትሞነጫጭርበታለች፡፡ ሲመለስ ተበለሻሽቶ ያገኘዋል፡፡ በዚህ ነገር ሁሌ ይበሳጫል፡፡ አንድ ቀን ግን ቢላዎ አምጥቶ በደንደሱ በኩል አንገቱን ይገዘግዝና ደብተሮቹ ላይ በማስቀመጥ ለምሳው ወደቤቱ ይሄዳል፡፡ ሲመለስ ኮራጇ ጦጢት ራሷን በራሷ ገዝግዛ ገድላ አስከሬኗን ተዘርግቶ ያገኘዋል፤ እሱም እሷም ተገላገሉ፡፡ ከዚያን በኋላ የሚያናድደው ጦጣ አልነበረም፡፡ በዱሮው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መጻሕፍት በአንደኛው የሚገኝ ጥሩ አስተምህሮ ያለው ታሪክ ነው – አስተዋይ ካለ፡፡

ብዙ የአፍሪካ በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥታት ኩረጃ ይወዳሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት ከራሳቸው ማመንጨት የማይችሉ ቀፎ ራሶች ስለሆኑ ሊሆን ይችላል፡፡ በቂ የመንግሥት አመራር ዕውቀትና ችሎታ ስለሌላቸውም ሊሆን ይችላል፡፡ ከየዘርፉ ዕውቀትና ችሎታ ያላቸውን ምሁራን ስለማያስጠጉና ከደደቡ ጭንቅላታቸው አሟጠው ሊያወጡት የሚችሉት የሕዝብ አስተዳደር ጥበብ ስለሌላቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ ዋናው ጉዳይ ግን ከሕዝባቸው ሥነ ልቦናዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ሕይወት ጋር ፍጹም ሊስማሙ የማይችሉ ኩረጃዎችን ከሌሎች ሀገራት በተለይም አደጉ ከሚባሉና በስንትና ስንት ተሞክሮ ከተፈተኑ መንግሥታት እንዳለ እየገለበጡ በሀገርና በሕዝብ መቀለድን እንደዋና መዝናኛቸው ያደረጉት ይመስላሉ፤ አለማወቃቸውን ሊያውቁም ፈቃደኞች አይደሉም፡፡ ሶሻሊዝም ግልብጥ ነው፤ የሠፈራ ፕሮግራም ግልብጥ ነው፤ ሕገ መንግሥት ግልብጥ ነው፤ የትምህርት ሥርዓቱና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፓኬጁ ግልብጥ ነው፤ የአስተዳደር መዋቅሩ ግልብጥ ነው፤ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች አወቃቀር ግልብጥ ነው፤ ከሞላ ጎደል ሁሉም ግልብጥ(ቅጂ) ነው፡፡ ያልተገለበጠ ነገር የለም፡፡ እኛም ተገልብጠናል፤ ኢትዮጵያዊነታችን ቀርቶ ሌላ ሌላ ነገር ሆነናል ወይም እየሆንን ነው፡፡ ግልብጥነት ከዚህ በላይ የለም፡፡ ብዙዎቹ ሲገለበጡ ግን ስማቸውና ቅርጻቸው እንጂ ከአንጀት ለሀገር ዕድገትና ልማት ታስቦ አይደለም፡፡ በዚያ ላይ የመንግሥቶቻችን ውሸት አይነሣ፤ ለውሸትና ስለውሸት የቆረቡ ናቸው፡፡ ከነሱ አንደበት እውነት እንደናፈቀን እንኖራለን፡፡ መንግሥት በተለዋወጠ ቁጥር የሚተኩት መሪዎችና ጭፍሮቻቸው በውሸትና ዕብለት የተጠመቁ ናቸው – ሸምጣጮች፡፡

አንዲትም ትንኝ አልገደልኩ፡፡
አንድም አማራ ከሚኖርበት አካባቢ አልተፈናቀለም፡፡
አንድም ሰው ከቀዬው አልተፈናቀለም፡፡
አንድም ኢትዮጵያዊ (በሳዑዲና በዐረቡ ዓለም) አልተንገላታም፡፡
አንድም ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ ምክንያት አልታሠረም፡፡
አንድም ዜጋ በተቃውሞ ሠልፉ ምክንያት አልተገደለም ወይም ማረሚያ ቤት አልገባም፡፡
አንድም ዜጋ ከእርሻውና ከመኖሪያ ቦታው (ቦታው ለኢንቬስተሮች በሊዝ በመሸጡ ምክንያት) አልተፈናቀለም፡፡
አንድም ሰው አልተራበም፡፡
አንድም ነጋዴ በግብር ብዛት አልተማረረም፡፡
አንድም የመንግሥት ሠራተኛ በኑሮው አልተሰቃየም፡፡
አንድም ገበሬ ኢሕኣዴግን እጠላለሁ አላለም፡፡
ወዘተረፈ………………………………………………………………….

ኦ! ኦ! ኦ! ኦ! በጣም፣ በጣም፣ እጅግ በጣም ዕድለኞች ነን፡፡ ብዙ “አንድም”-ኦችን መጥቀስ ይቻላል – የመንግሥት ሰዎቻችን የኛን የሞልቃቃ ዜጎቻቸውን የተደላደለ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ኑሮ ለሚዲያ ፍጆታና ለዓለም አቀፉ ማኅበረስብ ለማስረዳት በሚያደርጉት የዘወትር ጥረት የሚናገሩትን ለማስታወስ ነው እነዚህን ጥቂት ምሳሌዎች ያነሳሁት እንጂ ሁሉም ነጭ ውሸቶች ቢጠቀሱ ሰማይ ብራና ውቅያኖሶች ቀለም ሆነው ቢጻፍ የውሸት ስንክሳራቸው ተጽፎ አያልቅም፡፡ (ማሳሰቢያ፡ ይህን ጦማር የምጽፈው በታሪክ መዝገብ ቤት የሚቀመጥልኝ በዚህ ጉዳይ ዙሪያም የጮኽሁት አንዳች ነገር እንዲኖረኝ በመሻት እንጂ ወያኔ ሰምቶኝ፣ ከሚያደርገው ነገር ይታቀባል ከሚል ሞኝነት እንዳልሆነ አስፈላጊ ባይሆንም እዚህ ላይ መጠቆም እፈልጋለሁ፤ የተረገመ ቡድን ጊዜውን ጨርሶ በታሪክ ወጀብ እስኪጠራረግ ድረስ የዜጎችን ብሶትና የታላላቆችን ምክር የሚሰማበት ጆሮም ሆነ ትግስት እንደሌለው የታወቀ ነው፡፡ ወያኔዎች በተለይ የሚቃወማቸው የሚመስላቸውን ወገን ‹ጭራ ለማስበቀል› የሚወዳደራቸው የለም፡፡ ጠላቶቻቸውን በማናደድ በምድር አንደኞች ናቸው ቢባል አልተጋነነም – የሰማዩን አላውቅም፤ ያው የነሱው ጌታ ሊቀ መላኩ ሣጥጥናኤል ሊሆን እንደሚችል ከመጠርጠር በስተቀር፡፡)
የወያኔን ምግባር የምታስታውስ የአንዲት ሴት ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ሴትዮዋ ባሏ ከሚለው በሁሉም ነገር ተቃራኒ ናት፡፡ “እንብላ” ሲላት “እንፍሳ” የምትል በባሕርይዋ ፍጹም ጋግርታም የሆነች የትዳር ላይ ወያኔ ናት – ስለድንበር ዘለሉ ግልጽነቴ ይቅርታ፡፡ እኛ የወያኔን ጠባይ ማወቅ አቅቶን በትንሹ 23 ዓመታትን በ“እንካስላንትያ በብጣሽ” “ምናለ በድሪቶ” ዓይነት መደናቆር ስንጃጃልና ወርቃማ ጊዜያችንን በከንቱ ስናባክን ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ እንደዘለቅነው የዚች ሴትዮ ባልም አንዳች መፍትሔ በመፈለግ ወርቃማ ሊያደርገው ይችል የነበረውን የትዳር ሕይወቱን በከንቱ በማባከን ሲደናቆር ባጅቶ በመጨረሻው ያቺ ሴት ጎርፍ ወስዷት ትሞታለች፡፡ መንደርተኛው ተጠራርቶ የዚያችን ሴት ሬሣ ፍለጋ ወደ ወንዝ ይወርዳል፡፡ ባል “ወንድሞቼና እህቶቼ አንደዜ ስሙኝማ!” ይልና እንዲህ ይላቸዋል፡፡ “ሚስቴ ለኔም ሆነ ለቤተሰባችን ቀና ሆና አታውቅም፤ ነፍሷን ይማረውና ምነዜም ተቃራኒ ነበረች፡፡ ስለዚህ ለጎርፉም ስለማትታዘዘው እንዲህ ሽቅብ ወደላይ እንጂ ወደታች አትሄድለትምና ወደታች ትተን እንዲህ ተወደላይ በኩል እንፈልጋት” በማለት ጎርፉ በሚሄድበት አቅጣጫ ሣይሆን በሚመጣበት አቅጣጫ በኩል እንዲፈልጓት ሃሳብ አቀረበና በጎርፍ ሰውን የመውሰድ ዓለም ውስጥ አዲስ ታሪክ አስመዘገበ፡፡ ወያኔም ሆን ብሎና እንደሥልት የሚከተለው ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን የሚበጅ ሃሳብ ከቀረበ ሁልጊዜም – ከጥቂት በጣት የሚቆጠሩ አብነቶች በስተቀር – ተቃራኒውን መንገድ ነው የሚከተለው፡፡ ያንንም የሚያደርገው ለኢትዮጵያ የሚበጀውን አጥቶት ሣይሆን ሀገራዊ ስሜት የሌለው በመሆኑና እንደስትራቴጂ የሚከተለው የአገዛዝ ዘይቤ ከቀድሞዎቹ ገዢዎች በተለዬ ፍጹም ፀረ-ኢትዮጵያ በመሆኑ ብቻ ነው፡፡ የሚገርመው ታዲያ የሱ የለዬለት ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ሣይሆን የኛ በወሬና በጩኸት ዕድሜያችንን ለመፍጀት የመሃላ ያህል ቆርጠን መነሣታችን ነው፡፡ የበሬው ምናምን ይወድቅልኛል ብላ ስትከተለው እንደዋለችው ቀበሮ እኛም ወያኔ ሰው ይሆናል ብለን አገዛዙን እንዲያሻሽል ብዙ ብንጮኽም እስካሁን ምንም አልለወጥነውም፤ ወደፊትም ለመቼውም ቢሆን ከዚህ ፀረ-ኢትዮጵያዊ ተፈጥሮው ልንለውጠው አንችልም፡፡ ይልቁንስ እየሣቀብንና የለመደውን የግመሎቹንና የውሾቹን ተረት እየተረተብን ሲዖላዊውን የናቡከደነፆርንና የፈርዖንን አገዛዝ እንዳነገሠብን ይኖራል፡፡ ማርሽ መለወጥ ያለብን እኛው ነን፡፡ ወያኔ ወሬን በማሳመርና በጥናት ጽሑፎች ጋጋታ ወይም በእርግማንና በተቃውሞ ሠልፎች ብዛት ወይም በጋዜጣዊ መግለጫና ኆልቁ መሣፍርት በሌላቸው ፓርቲዎች ምሥረታ ወይም በጎጥና በዘውግ በሚደራጁ ንቅናቄዎችና ግምባሮች ቱማታ … ከሥልጣኑ ሊወገድና እውነተኛ ዲሞክራሲ ሊመጣ አይችልም – በነዚህ ነገሮች ወያኔ ቢወገድ ኖሮ እስካሁን ከምድረ ገጽ ጠፍቶ ነበር፡፡ ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን ጊዜ እጅግ ቢያልፍም አሁንም ቢሆን ችግሮች እየከፉ እንጂ እየተሻሻሉ ባለመሄዳቸው የምናደርገውን የተናጠል እርምጃ ገታ አድርገን ወይም ከተኛንበት ጥልቅ እንቅልፍ ነቅተን በጋራ አንድ ነገር ማድረግ ይገባናል፡፡ ፈረንጆቹ “Better late than never.” እንደሚሉት እየሞተ ላለ ሕዝብ በማንኛውም ሰዓት የሚደርስለት ረድኤት ትልቅ ፀጋና በረከት ነውና ሀገራችንን ከገባችበት አዘቅት ለማውጣት እንተባበር፡፡ መፍትሔው እሱና እሱ ብቻ ነውና፡፡

መሬት ቅርምት ስለሚባለው የወያኔ አንዱ ፋሽን ትንሽ እንነጋገር፡፡ በመሠረቱ ቀደም ሲል እንዳልኩት ወያኔ በተፈጥሮው ዐይንና ጆሮ ስለሌለው እንጂ በዚህ ጉዳይም ያልተባለ የለም፡፡ ፈረንጁም ሀበሻውም ብዙ ተናግሮበታል፤ ብዙም ጽፎበታል፡፡ ሁኔታው እየተባባሰ ከመሄድ በስተቀር የተለወጠ ነገር የለም፡፡ ለአሁኑ ሰሞኑን ከወጡ ዜናና ሀተታዎች መካከል ከሁለት ምንጮች ያገኘኋቸውን ሁለት ዜናዎችን ተመርኩዤ ጥቂት ላውራና እፎይታ ላግኝ – የከበደኝ ጭንቅላቴም ቀለል ይልልኛል፡፡ እነዚህ ምንጮቼ ሪፖርተርና ኢትዮሚዲያ ናቸው፤ በቅርቡ በዚህ ጉዳይ ላይ ያሉት ነገር አለ፡፡
ሪፖርተር “መንግሥት ‹የውጭ ባለሀብቶች የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን አይመለከትም› አለ” በሚል ርዕስ ባወጣው ዜና የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ሰሞኑን ለፓርላማ ተብዬው የደናቁርት እንቅልፋሞች ስብስብ የተናገሩትን የስድስት ወር ዘገባ በመጥቀስ ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገርም እዬዬው የሚሉት እንግዲያውስ የጂቡቲና የሣዑዲ ዐረቢያ የእርሻ መሬቶች ለኢንቬስተሮች ስለተሸጡ ይሆናል፡፡ በአምስቱም በሮች ከአዲስ አበባ ስንወጣ የሚታዬው ለሕዝቡ ከጥፋት በስተቀር ተጨባጭ ዕድገትና ልማት የማያመጣ የአበባ እርሻና የኢንዱስትሪና የሆቴል መናፈሻ ከየት የመጣ መሬት ነው? ጭቁኑ ገበሬ በመናኛ ሣንቲም የካሣ ክፍያ እትብቱ ከተቀበረበት የአያት ቅድመ አያቶቹ ሥፍራ እየተነቀለ አይደለምን ለሀብታም የተሰጠውና እየተሰጠም ያለው? በየክልሉ ለህንድና ለቻይና ኩባንያዎች በነጻ ሊባል በሚችል እጅግ አነስተኛ ዋጋ የተቸበቸበውና እየተቸበቸበ ያለውስ መሬት ገበሬዎች እየተፈናቀሉ አይደለምን? ታዲያ የሚኒስትሮቹና የምክትል ሚኒስትሮቹ ውሸት ይህን ፀሐይ የሞቀው እውነት በምን አቅሙ ነው ሊሸፍነው የሚችለው?

“መሬት የሚሸጠውና የሚለወጠው በኢሕአዴግ ከርሰ መቃብር ላይ ነው” ሲሉ የነበሩትና የገበሬው መጨቆንና መራብ መጠማት የትግላቸው መነሻ እንደሆነ አዘውትረው ይሰብኩ የነበሩት የሕወሓት ታጋዮች ዛሬ ምን ነካቸውና ተገልብጠው በዚህ የዋህ ባላገር ላይ ሊዘምቱበት ቃጡ? ቤት ያፈራውን በፈቃዱ ወድዶ እየሰጠ ወይም እንደዬሁኔታዎች አስገዳጅነት በወያኔው ጉጅሌ በጉልበት እየተነጠቀ ካባና ቀሚስ ሆኖ እንዳይበርደውና እንዳይርበው ሸፋፍኖ ቤተ መንግሥት እንዲገቡ የረዳቸውን ገበሬ ጨረቃ ላይ ያስቀሩት ለምንድነው? የሚታየው ኢፍትሃዊ የመሬት ክፍፍልና የእራሽ መሬት እየጠበበ መሄድ ያመጣው ችግር አነሰና ያቺ ያለቺው መሬት በምን ምክንያት ነው ለባዕድ እየተሸጠች ምርቱም የሀገሪቱ አንጡራ ሀብትም ለውጪ ባዕዳን የሚሰጠው? እኛ የሥጋና የሌሎች እህልና ጥራጥሬዎች ዕጥረትና የዋጋ ንረት ሊገድለን ተቃርቦ የኛ ምርቶች በዐረቡ ዓለም እንዲትረፈረፉና ለውጭ ምንዛሬ ሲባል በርካሽ ዋጋ እንዲሸጡ የሚደረገው ለምንድን ነው? መንግሥት የሚባለው ይሄ የወያኔ የጅቦች መንጋ በምኑ እያሰበ ይሆን እንዲህ ያለ የዓለም መንግሥታትን የሚያስደምም የመንግሥት አስተዳደር በኢትዮጵያ ውስጥ የተከለው? ከግዛቱ አንዳች አንዳች እሚያካክለውን መሬት እየገነደሰ ለጎረቤት ሀገራት ማደል፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ከጭቁን ገበሬዎች እየቀማ ለውጭ ባለሀብቶች ለዚያውም ተጨማሪ ብድር ሳይቀር እየፈቀደና እየሰጠ ማከፋፈል፣ በነዳጅ ቁፋሮ ሰበብ በሺዎች በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ ጦርነት ማወጅና እንደዐይጥ መጨፍጨፍ… ምን የሚሉት የሕዝብ አስተዳደር ሣይንስ ነው? ከየትስ ተማሩት ይባላል?

በሪፖርተር ዜና ላይ እንደተመለከተው የ“ፌዴራል ኢትዮጵያ” መንግሥት (ፐ! አይ ቋንቋ! ‹ፌዴራል› ሲባል ተሰምቶ እነዚህ የማያፍሩ ጉዶች ይህን ክቡር ቃል አምጥተው አለቦታው ደነቀሩት፤ ለነገሩማ ሰላም፣ ዴሞክራሲና ነጻነት ይሉስ የለምን? ብቻ ይህም ከመጥፎ ኩረጃዎች አንዱ ነው [It is a mockery or parody of the real democracy which is said to be practiced in the so called civilized world.]

የግብርና ሚኒስቴር፣ “የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቬስትመንት ላይ ለመሰማራት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው እያለሙ እንጂ፣ መሬት ለመቀራመት ብለው ወደ ኢትዮጵያ አልገቡም” ሲል ማስታወቁ በእግረ መንገድ ይህን የተናገረው ሰውዬኣቸው የሃሳብ መንጠፍ ብቻ ሣይሆን የቋንቋ ችግርም እንዳለበት ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ከማን ወሰዱ የሚለው በተለይ ለእኛ ግልጽ ስለሆነ እሱን እንተወውና ከማንም ይሁን ከማን መሬቱን መውሰዳቸው በራሱ መቀራመት አይደለም ወይ? ይህን የተናገረው ሰው እስኪ ደግሞ ያጢነው፡፡ ሰፋፊ የእርሻ መሬት ከጁፒተርና ከማርስ ወርዶ የኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ተንሳፍፎ – የገበሬዎችን መሬት ሳይነካ – ለምድረ ዐረብና ህንድ ተቃረጠ እንበል? የኛ ገበሬዎች ከመሬታቸው መፈናቀላቸውንና በፖሊስና በመከላከያ ኃይል ብዙ ሥነ ልቦናዊና ማኅበራዊ ትስስር ካላቸው የመኖሪያና የእርሻ ቦታቸው እንዲወገዱ መደረጉን በአንደኛው አንጎላችን ይዘን በሌላኛው አንጎላችን ደግሞ የኢትዮጵያን የመሬት ወቅታዊ ሥሪት ስናስብ ከሕዝብ ብዛት የተነሣ ለአንድ ገበሬ የሚሰጠው የእርሻ መሬት ስፋት ስንት ነው ብለን እንጠይቅ፡፡ የአብዛኛው ገበሬ የእርሻ መሬት ከኩርማን ያነሰና እንኳንስ ለሽያጭ ሊተርፍ ራስን ለመቀለብ የማያስችል አነስተኛ ምርት የሚመረትበት ነው፡፡ ታዲያ የውጪዎቹ ባለሀብቶች ከየት የመጣ “ሰፋፊ መሬት” ነው የሚሰጣቸው? በምንም መንገድ ያግኙት ይህ ክስተት “የመሬት ቅርምት” ካልተባለ የትኛው ነው ሊባል የሚችል? ግብርና ሚኒስትሮች – እባካችሁን የቋንቋ ትምህርት ቤት ግቡ! አለበለዚያ “የሚሉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” እየተባላችሁ የዝንታለም መዘባበቻ እንደሆናችሁ ትቀራላችሁ፡፡ ከደደቢት በረሃ ይዛችሁት የመጣችሁት ዘረኛና ግፈኛ አገዛዝን እንጂ የእርሻ መሬትን እንዳልሆነ ልትረዱ ይገባል – ተጋደልቲ አኽዋትና!! የሌላችሁን ነገር ደግሞ አትሰጡም ወይም አትሸጡም፡፡ እየቸበቸባችሁት ያላችሁት ገበሬውን በማፈናቀልና ዜጎችን ለሀገር ውስጥና ለውጪ ስደት በመዳረግ የምታግበሰብሱትን የሕዝብ መሬት ነው፡፡ ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል፤ ወያኔም ቀን ወጥቶለት ከጉድጓድ ወጣና መንግሥትም ሆነና የንጹሓን ዜጎችን መሬትና ሀብት ንብረት በጠራራ ፀሐይ እየዘረፈ፣ ባለመብት ጭቁኖችንም እየገደለ መሬታችንን ለባዕዳን ይሸልማል፡፡

አቶ ተፈራ ደርበው የተባለ አጋሰስ ሆዳም (ሆዳም አጋሰስ? እኔም እንደነሱው አማርኛው ጠፋኝ ልጄ!) ደግሞ እንዲህ ይላል፤ “መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም”፡፡ ይሄም ሰውዬኣቸው የቋንቋ ትምህርት ቤት ይግባና በእግረ መንገድም የሎጂክ ትምህርት በዚያው ያጥና፡፡ በል የተባለውን እንደበቀቀን ቃል በቃል እየደገመ ኅሊና ካለው ከኅሊናው ጋር እየተጋጨ የሰው መሣቂያና መሣለቂያ ከመሆን የሚድንበትን ብልሃት ይፈልግ፡፡ ዕድሜ ለቴክሎጂ ሕዝቡም ሆነ መላው ዓለም በኢትዮጵያ እየሆነ ያለውን አንድ በአንድ ያውቃሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈሳች በሴከንድ ውስጥ ዋሽንግቶንና ኒዮርክ ላይ ትሸታለችና ወያኔዎች እንደልማድና እንደተፈጥሮ ጠባያቸው ልፉ ብሏቸው እንጂ ማንንም ሊያታልሉ አይችሉም፡፡ ዋሹም አልዋሹም ለቅጣት መጥተዋልና እንደዮዲት ጉዲት፣ እንደግራኝ አህመድና እንደመንግሥቱ ኃይለ ማርያም የመጡበትን ኃጢኣተኛና ተንኮለኛን የመቅጣት ተልእኮ ሣይጨርሱ ንቅንቅ አይሉም፤ ነገር ግን “እስከወዲያኛው ማንም ሊያነቃንቃቸው አይቻለውም፣ ዘላለማዊያን ናቸው፤” ማለት እንዳልሆነ እነሱም ሆኑ ማንኛውም ወገን ሊገነዘብ ይገባል – የቀን ጉዳይ እንጂ ድቡሽት ላይ ቤቱን የሠራው ወያኔ ይቅርና ስንትና ስንት ለሰማይ ለምድር የከበዱ ታላላቅና ኃያላን መንግሥታት ጊዜያቸው ሲደርስ አይሆኑ ሆነው ተፍረክርከዋል፤ እንደሮምና እንደባቢሎን ወድቀዋል፡፡ የላይኛውም በሉት የታችኛው ትዕዛዙን እስኪሰጥ ነው የሚዘባነኑት – ቀናቸው ነውና፡፡ (ይህችን ሃሳቤን እንኳን ብዙ ሰው እንደሚቃወመኝ አውቃለሁ – የራሴ ብቻ ናትና እለፉኝ! መተላለፍ ተገቢ ነው፡፡) በእግረ መንገድ ግን ወደፍቅርና መተሳሰብ መንገድ እንግባ እያልኩ እንደሆነ ከሾርኒ ባለፈ አፍ አውጥቼ ማሳሰብ እፈልጋለሁ፤ ቀኑ የጨለመብን ፍቅር ስለጎደለንና አንዳችን ለአንዳችን የማንተዛዘን ድንጋይ ልቦች ስለሆንን ነው – ሁላችንም ባንሆን “ጥቂቶቻችን”፡፡ አቤት ፍርሀቴ! አንዳንድ ደመ ፍሉ ሰው ቱግ እንዳይልብኝ እኮ ተጨንቄ ነው፡፡

በነገራችን ላይ የመሬት ቅርምቱ የገበሬውን የእርሻና የመኖሪያ ቦታዎች በመቀማትና ከንብረቱም ከኑሮውም ሳይሆን ሜዳ ላይ ከነቤተሰቦቹ በትኖ በማስቀረት ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በከተሞችም በተለይም በአዲስ አበባና አካባቢዋ እጅግ ብዙ የሚዘገንን የመሬት ዘረፋ እየተካሄደ ነው፡፡ በከተማ ልማት ስም መንግሥት ተብዬው ወያኔ የአንድን አካባቢ ነዋሪ ተገቢውን ካሣ ሳይከፍል ያስነሳል፤ በደህናው ቀን በሚሊዮን ሊሸጥ ይችል የነበረውን የግል ይዞታ የመንግሥት ፍርደ ገምድል መሃንዲሶች አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ ይገምቱና ዜጋውን ባዶ እጁን ያስቀሩታል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖርክ በአሁኑ ወቅት አለኝ የምትለው ነገር የለም፡፡ የአምሳና ዐርባ ዓመት ይዞታ ያለውን ሰው አንድ ወያኔ በጨበጣ ይመጣና ያፈናቅለዋል፡፡ ይህ ወያኔ፣ ከሆነ ቦታ ማዘዣ ሊይዝ ይችላል ወይም በፌዴራል ሊያስገድድም ይችላል፡፡ “ሁሉ በጁ ሁሉ በደጁ” በመሆኑ የፈለገውን ለማድረግ፣ ቀልቡ ያረፈበትን መሬት ከዕድለቢስ ምሥኪን ኢትዮጵያዊ ወገኑ ለመቀማት ብዙም አይቸገርም፡፡ ለድሃ መጣሁ የሚለው ወያኔ በሰውነቱ ውስጥ በተካሄደበት ኬሚካላዊ ለውጥ በ23 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የለዬለት ፀረ-ድሃ ሆነና የማይፈጽመው ግፍና በደል የማናየውም የድሆች ብሶት የለም፡፡ ዱሮ በትግሉ ዘመን በዐይኔ ሂዱብኝ እንዳላለ፣ ዛሬ ወያኔ ስኳር ሲቀምስ ድሃ አልይ አለና ከጥቂቶች ጋር በሂልተንና ሼራተን አሼሼ ገዳሜውን ከአዳዲስ ባልንጀራዎቹ ከነአላሙዲንና አብነት ጋር ማጧጧፉን ቀጠለ፡፡ አዲስ አበባ በአሁኑ ወቅት የሚሊዮኖች ሲዖል የጥቂቶች ግን ገነት ሆና ሌላው ቀርቶ ከሰባትና ስምንት ዓመታት በፊት ደህና ነዋሪ የነበሩ ዜጎች ዛሬ በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ደረጃቸው ወርዶ የለዬላቸው ለማኞች ሆነዋል፡፡ የወያኔ መቶ ብር ምንዛሬ የደርግን አምስት ብርና የኃይለሥላሴን ሃምሳ ሣንቲም (ኧረ እንዲያውም ከዚያም በጣም ያንሳል) በሆነበት ሁኔታ የሦስትና አራት ሺህ የተጣራ ደሞዝ ተከፋዮች ይህ ገቢያቸው ከቤት ኪራይና ከጓያ ሽሮ እንዲሁም ከትራንስፖርት አላለፈም፤ እናም ይህ የወያኔዎች መሠረታዊው ድል በመሆኑ ሊኮሩበትና ሊኮፈሱበት ይገባል፡፡ ጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከልቡ የሚወዳቸውና ጠብ እርግፍ የሚልላቸውም ለዚህ ድል ስላበቁት ነው፡፡ አዲስ አበቤ ስለሳቀና ‹እኝ› እያለ ጥርሱን ስላገጠጠ ብቻ እየኖረ ያለ ሕዝብ ከመሰለን ስህተት ነው፤ ብዙዎቻችን እያኗኗርን እንጂ እየኖርን አይደለንም፤ አሸር በአሸር በልቶ እንደከብት መኖርን መኖር ካላችሁትም በዚህ ደረጃ የምንኖር በብዛት አለን፤ የለየላቸው ያጡ የነጡ ደግሞ በሥውር የርሀብ ጦርነት አንጀታቸው እርስ በርሱ እየተፋተገ የመሞቻቸውን ጊዜ የሚጠብቁ በየጎዳናውና በየቤቱ ሞልተዋል፡፡ አንዳንድ ጣዕረ ሞቶች ደግሞ በተፈጥሯቸው አስቸጋሪ ከመሆናቸው የተነሣ የሟቹን የመሞቻ ቅጽበት ለመተንበይ ያስቸግራሉ፡፡ ለዚህም ነው -ለምሳሌ- ለ23 ዓመታት ያጣጣረን አንድ ሰው በየትኛዋ ደቂቃ እስትንፋሱ ልትወጣ እንደምትችል መገመት የሚያቅተን፤ ነግር ግን ይህ ሰው አልሞተም ብሎ መዋሸት አይቻልም፡፡ ሞቱን ሞቷል፤ ችግሩ ዕድሩ አልለፈፈም፤ ለቀስተኛውም አላወቀለትም፡፡ አይደለም እንዴ ጓዶች? “ያልተነካ ግልግል ያውቃል” ነውና ደልቶት ለሚኖር ሰው ይህ የምለው ነገር ላቲን ሊሆንበት ይችላል፤ ግን ሰው ነውና የሰውን ችግር በመረዳት ቢያንስ በልቡ ቢያዝንና ለፈጣሪው ቢጸልይ የእውነትንና የአምላክን መንገድ በመከተሉ ይጠቀምበታል እንጂ አይጎዳም፡፡ በዚያ ላይ ነገን ማወቅ አይቻልም፡፡ ሦርያን ማየት ነው – ችግሮች በገንዘብ ዕጦት ብቻ አይወሰኑም፡፤ ገንዘብ ሞልቶህ ሰላም የምታጣበት ጊዜም አለ፡፡ የት ሆነህ ትበላዋህ? ከኢትዮጵያ ውጪ እንዲያውም ከገንዘብ ችግር ይልቅ የሰላም ዕጦት ችግር ነው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን መቆሚያ መቀመጫ እያሳጣቸው የሚገኘው፡፡ እኛ ሀገር ግን አንጻራዊ ሰላም ቢኖርም ብዙዎቻችንን ድህነቱ እያንገፈገፈን ስለሚገኝ በመኖርና ባለመኖር መካከል እየተንጠራወዝን ኤሎሄ እያልን ነው፡፡ ስለዚህ አንዱ ለአንዱ፣ ያለው ለሌለው፣ ጤናማው ለታማሚው፣ ያልተጨነቀው ለተጨነቀው … ማዘን ይገባዋል! (Empathy/sympathy is a vital virtue in the education of morality.)
ወደኢትዮሚዲያ እንለፍና ከሚለው ነገር ድረ ገጹን ያልገበኘንና ያን ዜና ያላየን እንቋደስ፡፡

“Land for Sale” በሚል ርዕስ ሥር ባስነበበን በእንግሊዝኛ የተዘጋጀ ዜና ብዙ ቁም ነገሮች ተጠቅሰዋል፡፡ በምንጭነት የጠቀሰው አልጀዚራ በ“People and Power” ፕሮግራሙ ለሥርጭት ያበቃውን ሀገራችንን የሚመለከት ዝግጅት ነው፡፡ ከጊዜ ዕጥረት አኳያ ዋና ዋና ነጥቦችን ብቻ መርጬ ባጭሩ እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡

ይህ የዜና ዘገባ የሚነሣው ኢትዮጵያ አስደማሚ የኢኮኖሚ ዕድገት እያመጣች ያለች ሀገር መሆንዋን በመጥቀስ ነው፡፡ ወደዚያ ከገባን መውጫ የለንምና ዕድገታችን ተከድኖ ይብሰል፤ ወደ አንገብጋቢ የመሬት ሽያጭ ማለፉ ይሻላል፡፡

“… ነገር ግን” ይላል ይህ ዜና – ስለኢትዮጵያ አወንታዊ ነገሮችን ከጠቀሰ በኋላ –

ነገር ግን አሉታዊ ዜናዎችም ከዚህ መልካም [የሚመስል] ወሬ ጋር ተጫፍረው ማለፊያውን ዜና ሊያደበዝዙት ሲሞክሩ መታዘባችን አልቀረም፡፡ 87 ሚሊዮን ከሚሆነው የሀገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ መካከል 90 በመቶ የሚሆነው የትምህርት ዕድልን ካለማግኘት ጀምሮ እስከ (የ)ጤና አገልግሎት ሽፋን በበቂ አለመዳረስና በመሳሰሉት በርካታና የተለያዩ ችግሮች እየተሰቃዬ ነው፤ [የአላሙዲንን ሀብት ለአጣሙዲኖች በምናብ የሚያከፋፍለው] የሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢ በዓመት ከ1500 ዶላር በታች ነው፡፡ ከ30 ሚሊዮን የሚበልጠው ሕዝብም ሥር በሰደደ ጠኔና ርሀብ እየማቀቀ ነው፡፡(ትንሽ ከፍ ሲል ስለአዲስ አበባ ርሀብ የተናገርኩትን እዚህ ላይ ያስታውሷል)፡፡ ከኢኮኖሚው ዕድገት አንጻር እየታዩ ያሉት በጎ ጅምሮች ተስፋ ሰጪነታቸው እንዳለ ሆኖ በቢዝነስና በህጎች ላይ ማሻሻያ ቢደረግ፣ የመንግሥት አግልግሎት ሰጪ ተቋማት በዘርፉ በሠለጠነና በቂ ዕውቀት በቀሰመ የተማረ የሰው ኃይል እየተመሩ የተቀላጠፈና ከሙስና የጸዳ ዘመናዊ አሠራር ቢከተሉ ሀገሪቱ የበለጠ ዕድገት ልታስመዘግብ በቻለች ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ከመቶው እኩሌታውን ያህል የሚሸፍነው የግብርናው መስክ እየተነዳ ያለው ከቁጥጥር በወጣ የመሬት ቅርምት ነው፡፡ ይህን የመሬት ቅርምት የሚያካሂዱት ደግሞ መንግሥት የፈቀደላቸውና ሽያጩን ራሱ መንግሥት የሚፈጽምላቸው የዓለም አቀፍ ኩባንያዎችና የግል ኢንቬስተሮች ናቸው፡፡ የሚገዙበት ዋጋ ደግሞ በሊዝ ጨረታ (ሆኖ እጅግ አነስተኛ ገንዘብ) ነው፤ በዚህ ዓይነት የመሬት ሽያጭ በብዙ ሚሊዮን ጋሻ የሚገመት ለም የእርሻ መሬት ለውጪ ባለሀብቶች ይሸጣል፡፡ [የገበሬው መሬት በዚህ መልክ ተቸብችቦ ሊያልቅ የቀረው ጊዜ አንድ ሐሙስ ብቻ ነው፡፡ ህልምና ትርጉም እንደፈቺው ነው - ደግሞ፡፡]

ይህ የመሬት ሽያጭ በመንግሥት ዐይን እንደ ጥሩ ነገር ይታያል፡፡ በሚገኘው ገቢ የገጠሩን ሕዝብ ለማሻሻል የሚረዱ ትምህርትና ጤናን የመሳሰሉ መሠረታዊ የልማት አውታሮችን ለመዘርጋት፣ ሥራ አጥነትን ለመቀነስና አዲስ ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር ለማስገባት እንደሚውል የግብርና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ይገልጻል፡፡ …

ነገር ግን ኦክስፋም፣ ዓለም አቀፉ የሰብኣዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅትና የኦክላንድ ኢንስቲትዩትን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይህን የመንግሥት የመሬት ሽያጭ ድርጊትና የኩባንያዎቹን የመሬት ቅርምት ለሀገሪቱ አደጋ እንደሚያስከትል እያስጠነቀቁ ናቸው፤ መንግሥት ግን ማንኛቸውንም ሊሰማቸው ፈቃደኛ አይደለም፡፡ እነዚህ ድርጅቶች እንደሚሉት የመንግሥት ድርጊት የዓለም አቀፉን የሰብኣዊ መብቶች ድንጋጌ ይጥሳል፡፡ ምክንያታቸውን ሲገልጹ መንግሥት በሚሊዮኖች ሄክታርና ጋሻ የሚገመት ለም መሬት ለገዢዎች ለማዘጋጀት ከየትም አያመጣውም፡፡ ሊያደርግ የሚችለው በዝቅተኛ የካሣ ክፍያ ከገበሬው እየቀማ መሬት መሸጥና ዜጎቹን በኃይል እያፈናቀለ የትሚናቸውን ማባረር ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከራሱ ዜጎች ይልቅ ለውጭ ሀገር ቅድሚያ መስጠቱን ያመለክታል፡፡ በዚህ ኢሰብኣዊ ድርጊት የሚፈናቀሉት በመቶ ሺዎችና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገበሬዎች ሰብኣዊ መብታቸው ይገፈፋል፤ ባህላቸውና የአኗኗር ዘይቤያቸው ለአደጋ ስለሚጋለጥ በሥነ ልቦናዊ ችግር ሊጠቁ ይችላሉ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ለርሀብና ለበሽታ ስለሚጋለጡ ሁልጊዜም ዕርዳታ ጠባቂዎች ሆነው የሰው እጅ እያዩ ለመኖር ይገደዳሉ፡፡

ደሳለኝ ራህመቶ የሚባሉ የሥነ ሕዝብ ዕውቀት ባለቤት እንደሚሉት ተፈናቃይ ገበሬዎች በፍንቀላው ከሚያገኙት ጥቅም ይልቅ የሚደርስባቸው ጉዳት የከፋ ነው፡፡ እንደሳቸው አባባል ገበሬዎቹ መሬታቸው ይወሰድባቸዋል፤ ዘላኖቹ ኢንቬስተሮች መሬቱን ለእርሻ ወይም እነሱ ለሚፈልጉት ነገር ሲያዘጋጁ ሥፍራውን ስለሚመነጥሩትና ደኑን ስለሚያጠፉት የአካባቢያቸው የተፈጥሮ ሀብት ይወድምባቸዋል (ቢመለሱ እንኳን አያገኙትም)፤ የተፈጥሮ ሚዛንም ይዛባል፤ መንግሥት እንደሚለው እነዚህ ኩባንያዎች ለአካባቢው መሠረታዊ ልማት ጥቅሞችን ያበረክታሉ፤ እነዚህ ጥቅሞች ግን በሰዎቹ ቸርነትና በጎ ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር የኮንትራት ስምምነቱ ላይ አልተገለጹም፡፡ እነዚህ ኢንቬስተር ተብዬዎች ደግሞ የራሳቸውን ፍላጎት ከማሳካት ውጪ ለአካባቢው ልማትና ለገበሬዎች ደንታ ያላቸው አይመስሉም፡፡ በገዙት እርሻ ላይ እነሱ የሚፈልጉትን የእህል ዓይነት እንጂ የአካባቢው ሕዝብ ወይም ሀገሪቷ የምትፈልገውን ምርት ላይሆን ይችላል የሚያመርቱት፡፡ ገበያቸውን የሚመርጡትም እነሱ ናቸው – ‹ይህን እዚያ ወይም ያንን እዚህ ሽጡ፤ እንዲህ ያለ ሰብልም አምርቱ› ብሎ የሚያስገድዳቸው አንድም የህግ አንቀጽ ወይም የስምምነት ሰነድ የለም፡፡ ስለዚህ ምንም ዓይነት ምርት አምርተው የትም ሊሸጡት ይችላሉ፡፡ እንዲያውም ለሀገር ውስጥ ገበያ ሣይሆን ለውጪ ገበያ ነው የአብዛኛው ምርታቸው ዒላማ(ታርጌት)፡፡ ለምሳሌ ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከገበሬዎች ተነጥቆ የተሰጠው አንድ የሣዑዲ ኩባንያ በመሬቱ ላይ ሩዝ አብቅሎ ምርቱን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ነው እሚልከው፤ ሩዝ ደግሞ ከዚያ አካባቢ ሕዝብ የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ የለምና ለከብት ካልሆነ ለራሱ አይመገበውም፡፡ ስለዚህ እነዚህ ኩባያዎችና ባለቤቶቻቸው በዘርም በሃይማኖትም ላልተወለዱትና ላልተዛመዱት ሕዝብ እንዲጨነቁ አይጠበቅም፡፡ ገበሬው የገዛ መንግሥቱ ያላሰበለት ደግሞ ባዕዳኑ እንዲጨነቁለትና እንዲቆረቆሩለት አይጠበቅም፡፡ (“ኩባያዎች” አልኩ እንዴ? ኩባንያ በሉት እባካችሁ)

መንግሥት ከሚያራምዳቸው ፕሮግራሞቹ አንዱ የመንደር ምሥረታ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እንደደርግ ዘመን የመንደር ምሥረታና የሠፈራ ፕሮግራም ሁሉ ጥናት ያልተደረገበትና ምንም ዝግጅት የሌለው በመሆኑ ከልማቱ ጥፋቱ ያመዝናል፡፡ ከትውልደ ትውልድ ጀምረው የኖሩበትን ቀዬ በአንድ አዳር ልቀቁና ውጡ ሲባሉ ዙሪያው ገደል ይሆንባቸዋል፡፡ መንግሥት ሠራሽ ወደሆነ አዲስ መንደርም ሄደው መልመድም ሆነ ሕይወትን እንደገና “ሀ” ብለው መጀመር ይቸግራቸዋል፡፡ ሰማይ ምድሩ ነው የሚደፋባቸው፡፡

እንደዚህ ያለ አሰቃቂ መንግሥት ወለድ መፈናቀል ከደረሰባቸው ወገኖች መካከል ጋምቤላ ውስጥ የአኙዋክና የኑዌር ጎሣዎች አባላት የሆኑ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን ይገኙበታል፡፡ አቶ ሙት የሚባል አንድ አኙዋክ ተፈናቃይ፣ “የመንግሥታችን ተቃዋሚዎች ‹መሬት ቅርምት› በሚሉት ፈሊጥ አንድም ዜጋ አልተፈናቀለም፤ በማንም ያልተያዘ መሬት ነው ለኢንቬስተር በሊዝ የሸጥነው” የሚሉንን የወያኔ ባለሥልጣናት ለማሳጣት በሚመስል አኳኋን እንዲህ ይላል፤ በጥሞና አድምጡት፡፡

“ኢንቬስተሮቹ እንደመጡ ጓዛችሁን ሸክፉ ተባልን፡፡ እምቢ ብንላቸው ንብረታችንን፣ ከብቶቻችንን፣እህላችንንና ቤቶቻችንን ሁሉንም ድምጥማጡን እንደሚያጠፉት እናውቃለን፤ [መግደልና ማሳደድ ለነሱ ብርቃቸው አይደለም፤ በኛ በአኙዋኮች ላይ ደግሞ የለመዱት ተግባር ነው]፡፡ ማካካሻ ስጡን ብለን ብንጮኸም ሰሚ የለንም፡፡ ምክንያቱም ቦታው የኢንቬስተሮቹ እንጂ የናንተ አይደለም ብሎ መንግሥት ቁርጡን ነግሮናል፡፡ ይህ ቦታ ደግሞ አያት ቅድመ አያቶቻችን የኖሩበትና ለየትውልዶቻቸው ሲተላለፍ የኖረ ነው፡፡ በመንግሥት አቋም በጣም ፈራን፡፡ ተበሳጭተህ መሬቴን ተቀማሁ ብትል እሥር ቤት ትጣላለህ፡፡ ለምን ታሰርኩ ብለህ ብትጠይቅ ይባስ ብለው ይገድሉሃል፡፡ [ጠያቂ የላቸውም፡፡ ሕግም የላቸውም፡፡] መሬቱን ተቀምተናል፤ ከአሁን በኋላ የኛ አይደለም፡፡ እኛንም በፈለጉ ጊዜ ሊገድሉን የሚችሉ [የውሻን ያህል እንኳን ክብር የሌለን] ነን፡፡”

ኢትዮጵያውያንም ሌሎች ጉዳዩ ያሳሰባቸው የዓለም ዜጎችም በዚህ ጉዳይ ቢጮሁ ቢጮሁ የወያኔው መንግሥት እንደልማዱ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ፀጥ ረጭ ብሏል፡፡ እንዲያውም ችግሩን አባብሶ ቀጥሎበታል፡፡ በኦክላንድ ኢንስቲትዩት የጥናት ዘገባ መሠረት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2008 ጀምሮ ባሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ እንኳን፣ የወያኔው መንግሥት ለውጪ ባለሀብቶችና ኩባንያዎች በመጣያ ዋጋ የሸጠው የገበሬዎች መሬት አንድ ላይ ቢደመር የፈረንሣይን ሀገር አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ያክላል፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ደግሞ የዚህችኑ የፈረንሣይን የቆዳ ስፋት ከሁለት ዕጥፍ በላይ የሚሆን የእርሻ መሬት ከዚሁ ከፈረደበት ገበሬ እየተነጠቀ ሊሸጥ እንደሆነ እነዚሁ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

ስለዚህ መሬቱም እኛ ኢትዮጵያውያንም እንዳወጣን በወያኔ ተቸብችበን እስክናልቅ በጉጉት መጠበቅና የመጨረሻውን ለማየት እንድንበቃ ዕድሜን ከፈጣሪ መለመን ነው የሚኖርብን፡፡ የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን፡፡ አሜን፡፡ (ካህኑ እግዚኦ ሲሉ አሁን ከጎረቤት ቤ/ክርስቲያን ይሰማኛል፤ ቅዳሴ እየጨረሱ ነው ማለት ነው፡፡ እኛም በያለንበት እስኪ እግዚኦ እንበል፡፡ እግዚኦታ መጥፎ አይደለም፡፡ ሙስሊሙም፣ አይሁዱም፣ ክርስቲያኑም፣ ሁሉም እንደየእምነቱ ይጸልይ፤ እነዚህ ሰዎች በቀጥታ የተላኩት ከጥልሚያኮሱ ዓለም (from the underworld/netherworld) በመሆኑ እነሱን ለማስወገድ እንደግንቦት ሰባት እምነትና ውሳኔ እውነትም በተገኘው ዘዴ ሁሉ – ጸሎትንም ጨምሮ ማለቴ እንደሆነ ይሰመርልኝ – አስተሳሰባዊ ዘርማንዘራቸው ለትውልድ ብክለት ሳይተርፍ ወደመጡበት መመለስ ነው፡፡ ወደዚምባብዌ … ማነው ወደ ደደቢት ማለቴ አይደለም፡፡ ከዚያስ ሊመለሱብን ይችላሉ፡፡ ማስወገድ ከምድረ ገጽ ነው፡፡ ማስወገድ ደግሞ ሥጋን አይደለም – መጥፎ አስተሳሰብን እንጂ፡፡ መጥፎ አስተሳሰብን ለማስወገድ መታጠቅ ከሚገባን የመሣሪያ ዓይነቶች አንዱና ዋናው ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ እነዚህን ሰዎች ፍቅርን ጨምሮ በሁሉም መሣሪያ እንረባረብባቸውና የሀገራችን የጋራ ባለቤቶች እንሁን፡፡ ለሀገርና ለራስ ኅልውና ሲባል በፍቅርም በሠይፍም መዋጋትን እነቅዱስ ዳዊትና ልጁ ሶሎሞን፣ እነሙሤም በተግባር አሳይተውናል፡፡ አሁንም በድጋሚ የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን፡፡ “ቧይ! ተቓጺልና!” አለ ገብረ መድኅን – አረርን’ይ፡፡


ደመቀ መኮንን: ልምድ ያለው ውሸታም

$
0
0

(ከሁኔ አቢሲኒያዊ) *

v ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 3481 መምህራን ከስራቸው ለቀዋል
v አዲስ አበባ ውሰጥ በበርካት ት/ቤቶች በአንድ ክፍል ውስጥ ከ90 በላይ ተማሪ ይማራል
v ልጁን በመንግስት ት/ቤት የሚያስተምር አንድም ባለስልጣን የለም
v በስኳር ቴክኖሎጂ የተማረ የሰው ኃይል የለም ብለዋል አቦይ ስብሀት
v ለየወረዳው ካድሬዎች እስከ 2500 የሚደርስ የደመወዝ ጭማሪ ተደርጓል
v በስብሰባ ምክንያት ቅዳሜ ማስተማር ያስቀጣል

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ትምህርት አስተሳሰብን ብሎም ኑሮን ይቀይራል ብለው በማመን ልጆቻቸውን ወደ አሰኳላ በመላክ የማስተማር ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው ለዚህም እንደምክንያት የሚያቀርቡት ልጆችን ማስተማር የነገ ህወታቸውን ማስተካከል ነው ብለው ስለሚያምኑ እና ትክክልም ስለነበሩ ነው ነገር ግን ባለፉት 23 ዓመታት የህወሀት ኢህአዴግ ዘመን ከጊዜው እና ካለው የህዝብ ቁጥር አንፃር የተማረ የሰው ኃይል ቁጥር ከፍ ያለ ቢሆንም ብዙሀኑ ህዝብ ግን ትምህርትን የሚማረው ነገ ተምሮ ምንም ተስፋ እንደሌለው ተረድቶ ነው፡፡
ከሰሞኑ ሀገራችን ኢትዮጵያ ትምህርት ለሁሉም በማዳረስ አቻ እንዳልተገኘላት የህወሀት ታማኝ አገልጋይ የሆነው ደመቀ መኮንን በቴሌቪዥን መስኮታችን ብቅ ብሎ ነግሮናል ወይም ዋሽቶናል፡፡
bereket alamudi demeke
የዚህ ፅሁፍ ፀሀፊ ሀሳብ ኢትዮጵያ እውን ቁጥሩን አሳክታለች አላሳካችም ሳይሆን ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ የትምህርት አሰጣጥን ማሳየት ነው፡፡

በአንድ ወቅት ሁሉንም አውቃለው የሚለው ስብሀት ነጋ በስኳር ቴክኖሎጂ ሀገሪቷ ውስጥ ምንም የተማረ የሰው ኃይል እንደሌለ ሰንደቅ ለተበላው ጋዜጣ ተናግሮ ነበር ነገር ግን ይህ የህዝቡ በስኳር ቴክኖሎጂ ተምሮ ያለመመረቅ ፍላጎት ሳይሆን የመንግስት የተሳሳተ የትምህርት ፖሊሲ በዘልማድ እና ገበያውን እንዲሁም ሀገራችን የሚያስፈልጋትን የተማረ የሰው ኃይል አይነት ካለማወቅ የሚመጣ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዐት በርካታ ወጣት ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ኬሚስትሪ እና ፊዚክስ ተምረው እቤት ተቀምጠዋል ድህነታቸው ለህወሀት አሽከር ያደረጋቸው ወንድሞቻችን ደግሞ ኮብልስቶን እየሰሩ ይገኛሉ እነዚህ ወጣቶች ቀድሞውኑ የተሻለ የትምህርት ስርዓት እና ፖሊሲ ቢኖር ኖሮ አቦይ ስብሀት እንደሚሉን ምንም የተማረ የሰው ኃይል በሌለበት የስኳር ቴክኖሎጂ ተምረው እራሳቸውንም ሀገራቸውንም በቀየሩ ኖሮ፡፡

ደመቀ መኮንን እንደዛ ያለማፈር አፉን ሞልቶ የተናገረለት የሀገራችን የትምህርት ስርዐትን ለመታዘብ አዲስ አበባ የሚገኝ አንድ የመንግስት ትምህርት ቤት ጎራ ማለት አልያም መምህራኑን ማነጋገር በቂ ነው፡፡

በትምህርት የተሻለ ደረጃ ደርሳለች በምትባለው አዲስ አበባ በርካታ ት/ቤቶች ውስጥ በአንድ ክፍል እስከ 90 የሚደርስ ተማሪ ይማራል ይኸውም ተማሪው በትክክሉ ትምህርት አንዳያገኝ ብሎም መምህሩ እውቀቱን በአግባቡ እንዳያደርስ የሚያደርግ ነው ይህንንም ችግር ስለሚያውቁ ነው ሁሉም ባለስልጣኖች ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ሀገራት ብሎም ከፍተኛ ክፍያ በሚያስከፍሉ ት/ቤቶች የሚያስተምሩት ነገር ግን ልጆቻቸው እንኳን እንዲማሩ የማይፈቅዱበትን የመንግስት ት/ቤቶች ሀገሪቷ እንደተቀየረች ማሳያ አድርገው ያቀርቡልናል፡፡

መንግስት ማለትም ህወሀት ከትምህርት ይልቅ የፖለቲካው ነገር ያንገበግበዋል ፡፡ በቅርቡ ለሁሉም የህወሀት ኢህአዲግ ተቀጣሪ የየወረዳው የፖቲካ ሹመኞች በሀገሪቱ ታይቶም ተሰምቶም የማያውቅ እስከ 2500 ብር የሚደርስ የደመወዝ ጭማሪ አድርጓል ከዚህ ቀደም በኑሮ ውድነቱ ተሰቃየን ሲሉ ከፍተኛ ዛቻ እና ከስራ ማባረር ለፈፀመባው መምህራን እና የመንግስት ሰራተኞች ትኩረት አለመስጠቱ ብሎም ደመወዛቸውን ለመጨመር አለማሰቡ ህወሀት ኢህአዴግ ከዜጎች በላይ ካድሬዎች የሚል ፅንሰ ሀሳብ ውስጥ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡

ት/ቤቶች በአሁኑ ሰዐት እንደበፊቱ ቅዳሜ እና እሁድ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጫ ከመሆን ይልቅ የካድሬ መሰብሰቢያ ማዕከል ወደመሆን ተሸጋግረዋል ቅዳሜ ቀን ተማሪዎቹን የማጠናከሪያ ትምህርት የሚጠራ ማንኛውም መምህር ስብሰባ እንዳወከ ተቆጥሮ በት/ቤቱ ኃላፊዎች ከፍተኛ ሆነ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይደርሰዋል ይህንንም ተከትሎ በርካታ መምህራን መምህርነት ሙያን እንደስራ መፈለጊያ ይጠቀሙበታል፡፡ በቅርቡ ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ለከተማው የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲላሞ ኦቶሬ የቀረበው ማስረጃ እንደሚያሳየው ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 3481 መምህራን ስራቸውን ለቀዋል፡፡

እንግዲህ ይህንን ነው ባለልምዱ ውሸታም ደመቀ መኮንን ለውጥ ብሎ የሚነግረን፡፡

(የዚህ ጽሁፍ ጸሀፊ በ2004 ዓ.ም የመምህራን ደመወዝ ጭማሪን አስመልከቶ በተነሳው ተቃውሞ መምህራኑን አነሳስተሀል ተብሎ ከመምህርነት ሙያው የተባረረ ነው)

ኢትዮጵያን ከቅርጫ ለማትረፍ –ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም

የአሁኑ አስገራሚ ጊዜ ሸክስፒር፣ ጁሊየስ ቄሳር በሚለው ፅሁፉ ላይ ለተናገረው አነጋገር ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል፣ “ሰዎች የሰሩት ተንኮል ከመቃበራቸው በላይ ሀያው ሆኖ ይኖራል” ብሎ ነበር ሸክስፒር፡፡ በአሁኑ ጊዜ አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ከሰሩት ተንኮሎችና ጭራቃዊነት የሞላው አስቀያሚ ተግባር ውርስ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠን እንገኛለን፡፡ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የግዛት አካል ተቆርሶ እንደገና ለሽያጭ ለሱዳን ቀርቧል፡፡ ይህንንም ጭራቃዊነት ተንኮል የቀበሮ ባህታውያኑ “የድንበር ማካለል“ ብለው ይጠሩታል፡፡ እኔ ደግሞ ድንበር መቁረስ፣ መቆራረስ፣ መሽረፍ እና መሸራረፍ ብዬ እጠራዋለሁ፡፡ ባጭሩ ኢትዮጵያን ለቅርጫ ማቅረብ እለዋለሁ… ደግሞ ለሰላሳ ቁርጥራጭ የመዳብ ዲናሮች!
meles cartoon
እ.ኤ.አ በ2008 “የኢትዮጵያ ጋሻ“ ተብሎ በሚጠራው የሰሜን አሜሪካ የሲቪል ማህበረሰብ ስብስብ ጉባኤ ላይ በመገኘት የእናት አገር ኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጠበቅ በሚል ርዕስ ስሜትን የሚቀሰቅስ ንግግር አድርጌ ነበር፡፡

በዛሬዋ ዕለት እዚህ የተሰባሰብንበት ዋናው ምክንያት አቶ መለስ ዜናዊ እናት አገራችንን መቅን አሳጥተው ለመበታተን እንዲመቻቸው በበረሃ ሳሉ ነድፈው ያመጡትን ጭራቃዊ ዕቅድ እና ዕኩይ ምግባር ለማውገዝ እና ለማስቆም ነው፡፡ አቶ መለስ የአሰብን ወደብ አሳልፈው በሰጡበት ወቅት ዝምታን በመምረጣችን ወደብ አልባ የመሆንን ዋጋ ከፍለናል፡፡ እ.ኤ.አ በ1998 ባድመ ተወረረች፣ እናም የ80,000 ኢትዮጵያውያን ህይወትን የበላ መስዋዕትነት ተከፍሎ ጠላቶቻችን ከግዛታችን እንዲወጡ ተደረገ፡፡ ሆኖም ግን አቶ መለስ በብርሃን ፍጥነት ተገልብጠው የኢትዮጵያን አንጸባራቂ የጦር ሜዳ ድል ቀልብሰው የዲፕሎማሲያዊ ሽንፈትን በመጋት በእርቅ ሰበብ ስም ባድመን ለወራሪው ኃይል አሳልፈው ለመስጠት ስምምነት አደረጉ… (ዛሬ) በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ወገኖቻችን በግልጽ እንደነገሩን የአያት ቅድመአያቶቻቸውን መሬት እና መኖሪያ ቤታቸውን ሳይቀር አቶ መለስ ለሱዳኑ አምባገነን [በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በወንጀል ለሚፈለጉት እና ከፍትህ ለማምለጥ እራሳቸውን በመደበቅ ተወሽቀው ላሉት] መሪ ኦማር አልባሽር አሳልፈው ለመስጠት በሚስጥር ስምምነት ፈጽመዋል…

ያንን ንግግር ካደረግሁ ከስድስት ዓመታት በኋላ እንኳን በሚያሳዝን ሁኔታ እናት አገራችንን ለመበታተን አቶ መለስ ከበረሃ ውስጥ ነድፈው ያመጡትን ጭራቃዊ ዕቅድ እኩይ ምግባር ለመቀልበስ ባለመቻላችን አዝናለሁ፡፡ አቶ መለስ አሁን በህይወት የሉም፣ ሆኖም ግን እኛን እንዲያጠፋ ጥለውት ከሄዱት ተንኮላቸው ስራቸው ጋር ፊት ለፊት ተጋትረናል፡፡ “መልካም ሰዎች ዝም ስላሉና ምንም ባላማድረ ጋቸው ይሆን ተንኮል የሚበረታው” የሚለው አባባል እውነታነት አለውን? በመጨረሻም ተንኮልና ጭራቃዊነት ድል ተጎናጽፏልን?

ኢትዮጵያ በአቶ መለስ ዜናዊ ቅርጫ መግባት

እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2013 የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ዓሊ ካርቲ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ገዥ አካላቶች “ፋሻጋ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የነበረውን የድንበር አለመግባባት እና በሌሎች አካቢዎችም ያሉትን የድንበር ማካለል ስራዎችንም በሰላማዊ መንገድ ለማጠናቀቅ ስምምነት አድርገናል“ በማለት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ ስለሁለቱ አገር መሪዎች አስመልክቶ ካርቲ እንዲህ ብለዋል፣ “የመጨረሻውን የማካለል ስራ ለመተግበር ታሪካዊ ስምምነት አድርገናል፡፡“ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያሉትን “የድንበር ውዝግቦች” በማስመልከት ለሚቀርቡ አስተያየቶች ሁሉ ምንም ዓይነት ሀሳብ እንደማይቀበል ጠቅሶ ሲናገር፣ “በጠረፉ በተወሰኑ የወሰን ድንበር ነጥብ ቦታዎች ላይ“ በጣም ቀላል የሆኑ አለመግባባቶች ከመኖር በስተቀር ሌላ ቸግር እንደሌለ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሳምንታት የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት መምሪያ እንደ ዔሌ አንገቱን ብቅ ጥልቅ እያደረገ በድብቅነት እና ማደናገር በተላበሰ ስልት/strategy “የድንበር ማካለሉን ጉዳይ“ እና “መጠነሰፊ ጠቀሜታ“ አላቸው እያለ ከበሮ የሚደልቅላቸውን “የደህንነት ትብብር ስምምነት፣ የኢኮኖሚ፣ የግብርና፣ የትምህርት እና የባህል“ “የስትራቴጅክ ስምምነት ማዕቀፍ“ በማለት በሚጠራቸው ጉዳዮች ላይ እምነት እንዲያድርብን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን በመሰለቅ ጊዜውን በከንቱ አሳልፏል፡፡

እ.ኤ.አ በ2001 “ለድንበር ውዝግቡ” ይሰጡ የነበሩት ምክንያቶች አሁን እየተሰጡ ካሉት ምክንያቶች ፍጹም የተለዩ ነበሩ፡፡ በዚያን ጊዜ የሱዳን ገዥ አካል እንደገለጸው የድንበር ማካለሉ ስራ አስፈላጊነቱ “የአልቃዳሪፍን ግዛት በሰሜን ኢትዮጵያ ከሚገኘው የትግራይ ግዛት ጋር ‘ለማልማት እና ለማቆራኘት‘ የሚል ነበር… ሁለቱ አካባቢዎች በጣም ለም የነበሩ ሲሆኑ፣ ከዚህም በላይ አልቃዳሪፍ ለሱዳን የዳቦ ቅርጫት ተደርጎ የሚቆጠር ነበር… ከአልቃዳሪፍ እስከ መቀሌ ያለው የመኪና መንገድ…እየተጠገነ እና ደረጃው ከፍ እየተደረገ ነው… የትግራይ ግዛት ከዚህ በመነሳት በዚህ በኩል ወደ ቀይ ባህር የሚያሸጋግረው ዕድል ስለሚያገኝ እና አልቃዳሪፍ ደግሞ ከፖርት ሱዳን ጋር የሚያገናኘው ስለሆነ ተቃሚ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ፖርት ሱዳን ለመቀሌ በኤርትራ ግዛት ከሚገኘው የአሰብ ወደብ እና በሶማሌ ግዛት ከሚገኘው የበርበራ ወደብ የበለጠ ቅርብ ትሆናለች…“ የሚል ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 አቶ መለስ ዜናዊ ከሱዳን ጋር የተደረገውን “ስምምነት” አስመልክቶ በውሸት ባህር ውስጥ እየተንቦጫረቁ የጭቃ ጅራፋቸውን ማጮህ ጀመሩ፡፡ በዚያው ዓመት በግንቦት ወር ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ሙልጭ አድርጎ በመካድ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድም ጋት የሚሆን የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተደረገ ሰምምነት የለም የሚል መግለጫ ሰጠ፡፡ ያ መግለጫ በውጭ የሚገኙትን “የዜና አውታሮች” እና “ኃላፊነት የማይሰማቸው” በበሬ ወለደ የፈጠራ ወሬ የተሰማሩ ሽብር እና ፍርሀትን በህብረተሰቡ ዘንድ የሚነዙ አሸባሪዎች ናቸው በማለት ከሷቸው ነበር፡፡ የሱዳን ባለስልጣኖች ግን ያንን መግለጫ በሚጻረር መልኩ “ከኢትዮጵያ መሬት እንዳገኙ“ በይፋ በአደባባይ ተናግረዋል፡፡ በግንቦት አጋማሽ አቶ መለስ እና አጫፋሪዎቻቸው የመሬት ማደሉን ሚስጥር ደብቀው ማቆየት ባለመቻላቸው ወደ ቀድሞው ታሪካቸው ለመመለስ ተገደዋል፡፡ በድንበር ማካለሉ ወቅት አንዳንድ የቅድመ ስራ እንቅስቃሴዎች ብቻ እንደተከናወኑ፣ እናም የተጠናቀቀ ነገር የለም በማለት በግልጽ ተናግረዋል፡፡ በቀናት ጊዜ ውስጥ አቶ መለስ እና አጫፋሪዎቻቸው ሌላ አዲስ ቅጥፈትን ፈብርከው ብቅ አሉ፡፡ የሆነው “ቀደም ሲል በንጉሱ እና በደርግ ዘመን ከሱዳን ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን ተግባራዊ አደረግን” ብለው ጭራ ቀረሽ ዉሸት ፈጠሩ፡፡

metama gonder
የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ጉዳዩን በግልጽ ሲያቀርበው እና በተጨባጭ በድንበሩ ባሉ አካባቢዎች ላይ ምን እየተደረገ እንዳለ ይፋ ሲያደርግ እስከ አፍ ጢሙ ተቀብትቶ/ሞልቶ የነበረው የውሸት ጎተራ መፈረካከስ ጀመረ፡፡ በአቶ መለስ ለሱዳን መሬት ዕደላ ፖሊሲ ምክንያት የተጎዱ ዜጎቻችን ለአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት እና ለሌሎች ዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛ ተቋማት ቃለመጠይቅ መስጠት ጀመሩ፡፡ በመሬት ዕደላው ምክንያት ቀጥተኛ ተጎጅ የሆኑ ወገኖቻችን አያት ቅደመ አያቶቻቸው ጠብቀው ያቆዩት መሬት በሱዳን ኃይሎች እየተወረረ ይዞታቸው ሲወሰድባቸው እና ከቀያቸው እና እትብቶቻቸው ከተቀበሩባቸው ቦታዎች ሲባረሩ የነበረውን ሁኔታ በመረረ አኳኋን የተሰማቸውን ቅሬታ በሰፊው ማሰማት ጀመሩ፡፡ የእርሻ መሳሪያዎቻቸው እና የመገልገያ ቁሳቁሶች በሱዳን ወራሪ ኃይሎች መወረሱን ገለፁ:: እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያን በሱዳን እስር ቤቶችም ታስረው እንዲማቅቁ አስታወቁ፡፡ በዚያን ጊዜ አቶ መለስ ምንም ምርጫ አልነበራቸውም፣ በግዴታ ሳይወዱ መሬት ለመስጠት ከሱዳን ጋር መፈራረማቸውን ለማመን ተገደዋል፡፡

እ.ኤ.አ በሜይ 2008 አቶ መለስ ከኦማር አልባሽር ጋር ያደረጉትን ስምምነት እንዲህ በማለት ይፋ አድርገዋል፣ “እኛ ኢትዮጵያውያን እና የሱዳን መንግስት የድንበር ማካለሉ ስራ በሚሰራበት ወቅት ከሁሉቱም ወገን አንድም ዜጋ እንዳይፈናቀል ለማድረግ ስምምነት ተፈራርመናል… በ1996 የወሰድነውን መሬት መልሰን ለሱዳን ሰጥተናል፣ ይህ መሬት ከ1996 ዓ.ም በፊት የሱዳን ገበሬዎች ይዞታ ነበር፡፡ አንዳንድ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት እንደሚያናፍሱት ሳይሆን በድንበሩ ዙሪያ አካባቢ አንድም የተፈናቀለ ዜጋ የለም፡፡”

እ.ኤ.አ በ2008 በዊክሊስ (የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ አመራር ሚስጥር ሰነድ) ሌላ ወሳኝ የሆኑ መረጃዎች ይፋ ተደርገዋል፡፡ “የቀድሞው የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከለዊ ኮሚቴ አባል እና የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዬ አብርሃ እንዲህ በማለት ተናግረዋል፣ ‘አቶ መለስ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ተፈጥሮ የነበረውን የድንበር ውዝግብ ውጥረት ለማርገብ ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት “ለአማራ ክልል ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል ግዙፍ መሬት“ አቶ መለስ ለሱዳን ሰጥተዋል፡፡ እናም የአቶ መለስ አገዛዝ “በድብቅ ይዞ ለማቆየት ሞክሯል” አሉ አቶ ስዬ አብርሃ::
ቀደም ሲል አቶ መለስ፣ አሁን ደግሞ የዕኩይ ምግባር ውርስ አጫፋሪዎቻቸው ያንን ስምምነት “በድብቅ ይዘው ለማቆየት” በመውተርተር እና በመዳከር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን እ.ኤ.አ በ2008 አቶ መለስ ከኦማር አልባሽር ጋር ባደረጉት ስምምነት ላይ የሰጡት መግለጫ አንዳንድ ጠቃሚ ምልክቶችን ይሰጣል፡፡ እራሳቸው አቶ መለስ ባመኑት እ.ኤ.አ በግንቦት 2008 በእርሳቸው እና በኦማር አልባሽር መካከል በተደረገው “የመሬት መስጠት ስምምነት” ዝርዝር የስምምነቱን ሁኔታ የሚያመላክት መሆኑ የሚያጣያይቅ አይደለም፡፡ “የስምምነቱን” ሁኔታ ስናጠናው አቶ መለስ በስምምነት መዝገቡ ላይ በርካታ ጠቃሚ ማስረጃዎችን አስቀምጠዋል፡፡ “ስምምነቱ” 1ኛ) መሬቱ በሚሰጥባቸው አካባቢዎች ሰዎችን ሊያፈናቅል የሚችል ጥያቄ መነሳት እንደሌለበት 2ኛ) ከድንበር ማካለሉ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ ከማካለል ስራው ጋር ተያይዞ ጉዳት የሚደርስባቸውን ሰዎች ጥቅሞች የማስጠበቅ ሁኔታ መኖር እንዳለበት 3ኛ) በኢትጵያውያን ገበሬዎች በህገወጥነት መልክ ተይዞ የነበረ የተባለውን መሬት ለሱዳን ገበሬዎች የባለቤትነት መብትን ማስጠበቅ 4ኛ) በ1996 ዓ.ም በህገወጥ መልክ በኢትዮጵያውያን ተይዞ የነበረውን መሬት ለሱዳናውያን መመለስ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በአቶ መለስ ፈቃድ እና አዛዥነት በእራሳቸው እና በኦማር አልባሽር የተፈረመው መሬት የመስጠት ስምምነት “የ1902 የግዌን መስመር/Gwen Line of 1902” (የ1902 የአንግሊዝ-ኢትዮጵያ ስምምነት) እየተባለ የሚጠራው “በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር” መስመር ማስያዝ ከሚለው ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው መገንዘብ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ እንደዚሁም እ.ኤ.አ ከ1974 በፊት በንጉሱ ዘመን እና በደርግ ዘመን ከ1995 እስከ 1991 ድረስ የተረቀቁ እና የተፈረሙ የድንበር መካለል ወይም ደግሞ መፍትሄ መስጠት ስምምነቶች ካሉ ከዚህ ስምምነት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም፡፡ እ.ኤ.አ ከ1996 መጀመሪያ አካባቢ ጀምሮ አቶ መለስ በእራሳቸው ፈቃድ ከድንበር እና ተመሳሳይ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መልኩ ያደረጉት “ስምምነት” በአቶ መለስ ግላዊ አተያይ የሱዳን መሬት በኢትዮጵያውያን በኃይል የተቀማ ነው በማለት በግላቸው ያደረጉት ህገወጥ እርምጃ እንጅ ሌላ ምንም ዓይነት ማስረጃ የሌለው እርባናቢሰ ስብከት መሆኑ በውል ሊጤን ይገባል፡፡

የኢትዮጵያን “ግዙፍ መሬቶች” በድብቅ እና ለህዝብ ይፋ ሳያደርጉ በሚስጥር ለሱዳን የሚሰጡበት “ስምምነት”ምክንያቱምንድን ነው”?

አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም በአጠቃላይ “በድንበር ስምምነቱ” ዙሪያ እያቀረቡት የነበረው እና ያለው የውሸት ፍብረካ ድሪቶ ሪፖርት እውነታውን ለመደበቅ ከሚሽመደመደው ድሁር አስተሳሰባቸው ያለፈ ፋይዳ አይኖረዎም፡፡ እውነተኛው የድንበር መስጠት ስምምነት እ.ኤ.አ በ2008 ተጠናቁአል፡፡ በምንም ዓይነት መልኩ ቢሆን አቶ መለስ “ግዙፍ የሆነ መሬት ከአማራ ክልል” ቆርሰው ፈርመው፣ አትመው እና አሽገው ለሱዳን መስጠታቸውና በድብቅ “በድብቅ ተይዞ እንዲቆይ” መጣራቸው የሚያጠያየቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 የኢትዮጵያ የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የአቶ መለስን የበከተ ውሸት እንደተለመደው “በሀሰት መጋረጃ ደብቀው” ለዘላለም ለማቆየት በማሰብ ሌላ ዘርዘር ያለ ፖለቲካዊ ድራማ ለመተወን በመውተርተር ላይ ይገኛሉ፡፡

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ጌቶቻቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ሊያታልሉ፣ ሊያጭበረብሩ እና በውሸት ሊደልሉ የሚችሉ ይመስላቸዋል፡፡ እነዚህ የዕኩይ ምግባር ባለቤቶች መሬትን ያህል ነገር በድብቅ ሸፍኖ የመስጠት ጨዋታቸውን ኢትዮጵያውያን የማያውቁ እና የማይገነዘቡ ሞኞች አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ እነርሱ ይህን የሞኝነት ጨዋታቸውን እንደፈለጉ መጫወት ይችላሉ፣ ሆኖም ግን አቶ ኃይለማርያም አንድ ጥያቄ እንዲመልሱልኝ እፈልጋለሁ፣ ይኸውም “ ‘ከአማራ ክልል ግዙፍ መሬቶችን ቆርሰው የሰጡት’ “ድብቅ የሚስጥር ስምምነቶችን የት እንዳስቀመጧቸው ሊያሳዩኝ ይችላሉን? አቶ መለስ እ.ኤ.አ በ2008 እና አሁን ደግሞ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የዕኩይ ምግባር አጋሮችዎ የድብቅ ስምምነቶችን ከህዝብ ፊት ደብቃችሁ ከፊታችሁ ላይ የውሸት መጋረጃ በማድረግ ለመዝለቅ የምትፈልጉት ለምንድን ነው?” ከአገር መሬት ቆርሳችሁ ለባዕድ አገር ስትሰጡ በአገሪቱ ህገመንግስት ስልጣን ለተሰጠው ፓርላማ (ለተወካዮች ምክር ቤት) ተብዬው ለይስሙላ እንኳን ቢሆን መቅረብ የለበትምን“? ህገመንግስቱ የሚለው ሌላ የስርዓቱ ቁንጮዎች የሚያደርጉት ሌላ! አራምባ እና ቆቦ!

ከላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች መልሱ ቀላል ነው፣ እ.ኤ.አ 2008 አቶ መለስ የተናገሩለት “የሚስጥር ስምምነት“ እና አሁን ደግሞ አቶ ኃይለማርያም እያነበነቡት እንዳለው አይደለም እውነታው፡፡ ህዝብ ግብር እየከፈለ በሚያስተዳድራቸው መገናኛ ብዙሀን ብቅ እያሉ በእብሪት የሚያሰራጩት ነጭ ውሸት ነው፡፡ በእርግጥ አቶ መለስ ይዋሻሉ ማለት “መለስ ወይስ መቀልበስ” መጠሪያ ስማቸው ነው፡፡ ሁሉም አፍጥጠዉ ይዋሻሉ፡፡ አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም ከኦማር አልባሽር ጋር በስምምነቶች ላይ ያስቀመጧቸው ቃላት፣ ሀረጎች እና ዓረፍተ ነገሮች ወደ እውነት ተግባርነት የሚሸጋገሩ ከሆነ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አደጋዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? በእውነት እነዚህ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ የግዛት አንድነት በመዳፈር መሬቱን እየቆረሱ ለመስጠት ተፅፈው ተፈረመው የተደበቁ ስምምነቶች የአቶ መለስን እና የአቶ ኃይለማርያምን ቀጣፊነት የሚያስረዱ መረጃዎች ሊሆኑ አይችሉምን?
ድብቅነት በኢትዮጵያ በመግዛት ላይ ላለው ገዥው አካል ዋና መለያ ባህሪው ነው፡፡ ነገሮችን ደብቆ በመያዝ እያንዳንዱን በማሞኘት ላይ ይገኛሉ፡፡ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ጊዜ እና በአሁኑ ጊዜ ያሉት ሎሌዎቻቸው ደግሞ የቅብብሎሽ ዱላውን ከጌታቸው ራዕይ በመቀበል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያሳዩ ያሉት ንቀት የህዝቡን ምንነት ሳይገመግሙ እና ሳይረዱ በራቁት ገላው ላይ ሱፍ እየጎተቱ መሆኑን በውል ሊያጤኑት ይገባል፡፡ አቶ መለስ እና ጋሻጃግሬዎቻቸው አሰብን እና ባድመን በቤሣ ቁርጥራጮች ካስረከቡ በኋላ ዝምታ ብቻ መልስ ስላገኙ ከዚያ ነገር አንድ ቁም ነገር ተምረዋል፡፡ ይኸውም ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያን ግዛት የእነርሱ የግል እንደፈለጉ የሚለውጧት፣ የሚሸጧት የህግ ተጠያቂነት የሌለበት የግል ንብረታቸው መሆኗን አረጋገጡ፡፡

በመለስ/ኃይለማርያም ከምዕራብ ኢትዮጵያ የግዛት አንድነት መሬት በመቁረስ ለሱዳን ለመስጠት የሚደረግ ማንኛውም “ስምምነት” ህገመንግስታዊ አይደለም፡፡

እ.ኤ.አ. ወደ 2008 መለስ ብለን ስናይ አቶ መለስ የኢትዮጵያን መሬት ቆርሰው ለሱዳን ወይም ደግሞ ለማንም ቢሆን ለመስጠት ህጋዊ ስልጣን የላቸውም ብዬ ተከራክሬ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን አቶ ኃይለማርያም የኢትዮጵያን መሬት ቆርሰው ለሱዳን የመስጠት ህጋዊ መብትም ሆነ ስልጣን የላቸውም፡፡ ይህንን ካልኩ ዘንድ አቶ መለስ “ከአማራ ክልል ግዙፍ የሆነ መሬት” ቆርሰው ለሱዳን ለመስጠት “ስምምነት” እንደተፈራረሙ አጠያያቂ ነገር አይደለም፡፡ አቶ ኃይለማርያም እና ጌቶቻቸው ይህን ህገወጥ የመሬት ዕደላ ዕኩይ ተግባራቸውን “የስልታዊ/ስትራቴጂክ ስምምነት ማዕቀፍ” በማለት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመክፈት ጣፋጭ በማስመሰል በማር የተለወሰ መርዛቸውን ሊግቱን ይፈልጋሉ፡፡ እውነታው ግን በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ገዥ አካል ምንም ዓይነት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳንም ሆነ ለማንም ሌላ አገር አሳልፎ የመስጠት ህገመንግስታዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ መብትም ስልጣንም የለዉም፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ሊታይ የሚችለው ይህ የተካሄደው የድብቅ ስምምነት የኢትዮጵያን ህገመንግስት አንቀጽ 12 የሚጻረር ስለሆነ የህገመንግስት ጥያቄን ያስነሳል፡፡ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ጊዜ እና እርሳቸውን ተክተው በመስራት ላይ ያሉት የአሁኖቹ ገዥዎቻችን ከኢትዮጵያ ህዝብ እና ከተወካዮች ምክር ቤት በሸፍጥ ደብቀው ከኦማር አልባሽር ጋር ያደረጉትን የሚስጥር “ስምምነት” እየተባለ የሚጠራውን ተግባራዊ ለማድረግ ይፍጨረጨራሉ፡፡ በኢትዮጵያ ህግመንግስት አንቀጽ 12 ስር (“የመንግስት የስራ ድርሻ እና ተጠያቂነት“) እንዲህ ይላል፣ “መንግስት ተጣያቂነት እና ለህዝብ ግልጽነት ባለበት ሁኔታ ስራውን ይሰራል… ማንም የህዝብ ባለስልጣን ወይም ተመራጭ በህግ የተሰጠውን ስልጣን በህግ አግባብ ካልተጠቀመ ተጠያቂ ይሆናል፡፡” አቶ መለስ እና ተኪዎቻቸው “የህዝብ ባለስልጣን” እንደመሆናቸው መጠን ግልጽነት እና ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ ስራቸውን ለማከናወን ህገመንግስታዊ ግዴታ አለባቸው፡፡ ለህዝብ ሳይቀርብ እና የስምምነቱ ሁኔታም በዝርዝር ምን እንደሆነ ሳይታወቅ እንዲሁም ህጋዊ ስልጣን የተሰጠው የተወካዮች ምክር ቤት ሳያጸድቀው የአገርን የግዛት አንድነት በመጣስ መሬት ቆርሶ ለሌላ አገር ለመስጠት በእራስ ፈቃድ የሚደረግ የሚስጥር ስምምነት የህገመንግስቱን አንቀጽ 12 ይጻረራል፣ ሙሉ በሙሉም ህገመንግስቱን ይደፈጥጣል፡፡

እዚህ ላይ በአቶ መለስ እና በተኳቸው የዕኩይ ምግባር ተባባሪዎቻቸው ሸፍጥ በተሞላበት ሁኔታ በስውር መሬት ለሱዳን ለመስጠት እየተደረገ ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ መልኩ ቁልፍ የሆኑ የህግ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ እነዚህም፣ 1ኛ) አቶ መለስም ሆኑ አቶ ኃይለማርያም በኢትዮጵያ ስም ሆነው ቀያጅ የሆኑ “ስምምነቶችን” ወይም “ውሎችን” በግል ለመፈረም ህገመንግስታዊ ስልጣን አላቸውን? 2ኛ) በአቶ መለስም ሆነ በአቶ ኃይለማርያም ፊርማ የሚደረጉ “ስምምነቶች” ከኢትዮጵያ ህገመንግስት አኳያ ህጋዊ ጠቀሜታ ሊኖራቸው ይችላልን? 3ኛ) በአቶ መለስ እና በአቶ ኃይለማርያም የሚደረግ/ጉ ስምምነት/ቶች በቀጣይነት በኢትዮጵያ ስልጣንን በሚይዙ መንግስታት ተግባራዊ መሆን የሚችል/ሉ መሆን እና አለመሆኑ/ናቸው ከዓለም አቀፍ ህግ አንጻር እንዴት ሊታይ ይችላል? 4ኛ) በአቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም በተፈረመ ስምምነት የተሰጠ የትኛውም በሱዳን የተያዘ የኢትዮጵያ ግዛት በዓለም አቀፋዊ ህግ መሰረት በሌላ አገር እንደተያዘ ሊታይ የሚችል ነው ወይስ አይደለም? 5ኛ) የኢትዮጵያ ህገመንግስት በግልጽ እንዳስቀመጠው “የፌዴራል መንግስቱ ስልጣን እና ኃላፊነቶች” መካከል “የውጭ ፖሊሲ ማውጣት እና መተግበር፣ ዓለም አቀፍ ውሎችን መዋዋል እና ማጽደቅ“ “የፌዴራል መንግስቱ” አጠቃላይ የውጭ ግንኙነቶች እና ስልጣኖች በስራ አስፈጻሚ ማኔጅመንት ተፈርመው የውጭ ግንኙነት መስኮች እና “የዓለም ዓቀፋዊ ስምምነቶች“ በፓርላማው ይጸድቃሉ/አይጸድቁም፡፡ አንቀጽ 55 (12) በግልጽ እንዳስቀመጠው ዓለም ቀፍ ስምምነቶችን በሚመለከት በስራ አስፈጻሚው ተፈርሞ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በፓርላማው ታይቶ ይጸድቃል፣ የተወካዮች ምክር ቤት ከተሰጡት ዋና ዋና ኃላፊነቶች አንዱ ስራ አስፈጻሚው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ህጎችን ፈርሞ ሲያቀርብለት ፓርላማው መርምሮ ያጸድቃል፡፡”

የአቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም በራሳቸው ፈቃድ መሬት ለመስጠት የሚያደርጓቸው “ስምምነቶች” የህገመንግስቱን አንቀጽ 55 (12) የሚደፈጥጥ ነው፡፡ አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም ከሌላ መንግስታት ጋርም ስምምነቶችን ለመደራደር እና ለመፈረምም ይችላሉ፡፡ በህገ መንግስቱ የተሰጣቸው ስልጣን ለመደራደር፣ ለማርቀቅ እና ዓለም አቀፋዊ ስምምነቶችን በመፈረም ላይ ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ ሆኖም ግን አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም ከሌላ መንግስታት ጋር የሚያደርጓቸው “ስምምነቶች” ፊርማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአንቀጽ 55 (12) በግልጽ እንደተቀመጠው ሁሉ ካልጸደቀ በስተቀር የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል አያወጣም፡፡

አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም ሁለቱም መሬት ለመስጠት ከሱዳን ጋር ያደረጓቸውን ስምምነቶች ፓርላማው እንዲያጸድቃቸው ለማቅረብ ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡ እንዲሁም በጨዋነት መንፈስ ቢያንስ ፓርላማው እንዲወያይበት እንኳ ስምምነቶች ለመስጠት ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡ ስምምነቶችን ፓርላማው እንዲያጸድቃቸው ለማቅረብ አለመቻል ህገመንግስታዊ የስራ ኃላፊነት ድርሻን እና መርሆዎችን የጣሰ ከመሆኑም በላይ ፓርላማው ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ለማጽደቅ ባለው ስልጣን ላይ እየተደረገ ያለ ጣልቃገብነትን የሚያመላክት ነው፡፡

አንቀጽ 86 “የውጭ ግንኙነት መርሆዎችን“፣ የ“ፌዴራል መንግስትን“ (የጠቅላይ ሚኒስትሩን፣ የተወካዮች ምክር ቤትን) ኢትዮዮጵያ ከሌሎች አገሮች ጋር እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ያላትን ግንኙነት ይገልጻል፡፡ አንቀጽ 86 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 3 የፌዴራል መንግስቱ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ “በእኩልነት እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ፣ ዓለም አቀፍ ህጎች እንዲከበሩ የማድረግ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም ማስጠበቅ“ እና ዓለም አቀፍ ህጎች እና ስምምነቶች እንዲከበሩ፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ከህዝብ ፍላጎት በተጻራሪ የሚቆሙትን እንደማይቀበል በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም ከሱዳን ጋር የተፈረመውን ስምምነት ሚስጥር አድርገው የያዙበት ዋናው ምክንያት እነዚህ ስምምነቶች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በግልጽ በአገጠጠ እና በአፈጠጠ መልኩ የሚጥሱ መሆናቸውን ስለሚያውቁ ዕኩይ ምግባሮቻቸውን ለመደበቅ ያሰቡት የሸፍጥ ስራ ነው፡፡ እነዚህ የሸፍጥ ሰዎች “ስምምነቶችን” ሚስጥር ማድረግ ይፈልጋሉ ምክንያቱም የኢትዮጵያን ጥቅም አሽቀንጥረው የጣሉ በመሆኑ እውነታው በተጫባጭ ጎልቶ እንደሚታይ እና ከኢትዮጵያ ጥቅም በተቃራኒ የቆሙ ከሀዲዎች መሆናቸውን ያውቃሉ እና ነው፡፡ ስምምነቱን ሚስጥር አድርጎ መያዝ ከላይ ከተጠቀሱት የተለዬ ሌላ ምክንያት በፍጹም ሊኖር አይችልም፡፡ በሌላ በኩል ሚስጥር አድርገው የያዟቸውን ስምምነቶች ግልጽ ያድርጉ እና እኔ እነዚህ ስምምነቶች የተደረጉት እኩልነትን ባዛነፈ መልኩ ነው፣ ኢትዮጵያን ብቸኛ ተጎጅ ያደረገ ነው እያልኩ የምሟገተውን በመርታት ማስተባበል ይችላሉ፡፡
አንቀጽ 9 (“የህጎች ሁሉ የበላይ“) ይህንን አስመልክቶ ህገመንግስቱ የአገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ መሆኑን በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ሁሉም ህጎች፣ ወጎች፣ ልማዶች እና በመንግስት አካላት የሚደረጉ ውሳኔዎች ወይም የህዝብ ባለስልጣኖች ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ተጻራሪ ሆነው ከተገኙ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡ ሁሉም ዜጎች፣ የመንግስት አካላት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሌሎች ማህበራት እና ባለስልጣኖቻቸው ህገመንግስቱን ማክበር ማስከበር እና በህጎቹም መገዛት… ማንኛውም ስልጣንን ለመያዝ የሚፈልግ አካል ሁሉ በህገመንግስቱ ከተደነገገው ውጭ ስልጣንን ለመያዝ ማሰብ የተከለከለ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል፡፡”

በአቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም የሚደረግ ማናቸውም “ስምምነት” “ውል” “የጋራ ስምምነት” “ድርድር” አንቀጽ 55 (12)፣ አንቀጽ 86 (2) (3) ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ህገመንግስት ተፈጻሚነት የማይኖረው ህግ ወደፊት ስልጣን የሚይዙ ህጋዊነትን የተላበሱ ተከታታይ የኢትዮጵያ መንግስታት ሊቀበሉት የማይችል ዓለም አቀፍ ህግ በኢትዮጵያ ተፈጻሚነት ሊኖረው ይችላልን?

አንቀጽ 9 (4) የኢትዮጵያ ህገመንግስት እንዲህ ይላል፣ “በተወካዮች ምክር ቤት የጸደቁ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች“ የአገሪቱ የህጎች ሁሉ የበላይ ናቸው፡፡” ሌሎችስ በኢትዮጰያ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያልጸደቁ ዓለም አቀፍ ህጎች ምን ሊባሉ ነው? ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ማንም ቢሆን የህገመንግስት ልሂቅ መሆንን አይጠይቅም፣ ዓለም አቀፍ ህጎች በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እስካልጸደቁ ድረስ የተጻፉበትን ወረቀት ያህል ዋጋ አያወጡም፡፡ ማንም ህጋዊነትን ተላብሶ ስልጣን የሚይዝ ቀጣይ የኢትዮጵያ መንግስት ተፈጸሚነት በማይኖራቸው ህጎች ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን የመፈጸም ግዴታ የለበትም፡፡ ኢትዮጵያ እንደዚህ ያሉትን ስምምነቶች የማውገዝ እና ሱዳኖች ከህግ አግባብ ውጭ በተጽዕኖ ከያዟቸው ይዞታዎች ለኢትዮጵያ አስረክበው በዓለም የህግ አግባብ መሰረት ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ ይደረጋል፡፡

የዓለም አቀፋዊው ህግ ስምምነቶች በመንግስታት መካከል መተግበር እንዳለባቸው ግዴታ የሚጥል እንደመሆኑ መጠን (ስምምነቶች መጠበቅ አለባቸው በሚለው መርሆ መሰረት) እንደዚሁም የተወሰኑ የህግ ማዕቀፎች መንግስት ሊያወግዛቸው እና ከመተግበርም ሊቆጠብ የሚችልባቸው (ሊያቋርጣቸው) ወይም ደግሞ በመጀመሪያ ስምምነቶቹ በሚፈረሙበት ጊዜ ስህተት ተሰርቷል ብሎ ካመነ እና ካረጋገጠ ስምምነቶችን ሊሰርዛቸው ወይም ከስምምነቶች እራሱን ሊያገል እንደሚችል ዕድል ይሰጣል፡፡

የቬና ስምምነት በህግ ውል ላይ ውዝግብ በሚነሳበት ጊዜ ውሳኔ ሊያሳልፍ እንደሚችል ብዙ ስምምነቶች የህግ መሰረት የሌላቸው ብሎ ውድቅ ሊያደርግ እንደሚችል በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ አንቀጽ 46 (1)፣ (2) (“ተፈጻሚነት የማይኖራቸው ውሎች“) ተፈጻሚነት የማይኖራቸውን ስምምነቶች ከአንድ አገር “የውስጥ ህጎች” አንጻር ተፈጻሚነት ሊኖራቸው እንደማይችል ከግንዛቤ በማስገባት እንዲህ ይላል፣መንግስት ለአንድ ስምምነት ተገዥ ሊሆን የሚችለው በሀገሩ ያለውን ህግ የሚጥስ እስካልሆነ ድረስ እና ያደረገው ስምምነትም በአገሪቱ ካለው የህግ ማዕቀፍ ጋር የማይቃረን እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው፡፡በተግባር እና በልማድ መተግበር ካለበት ሁኔታ ውጭ በሆነ መልኩ አንድ መንግስት በእራሱ ህግ አውጥቶ ስምምነት ቢገባ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይችልም፡፡

አንቀጽ 49 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፣ “አንድ መንግስት ከሌላ እምነት ከማይጣልበት መንግስት ጋር ስምምነት ቢዋዋል ይህ ውል ተፈጻሚነት አይኖረውም“ አንቀጽ 50 እንዲህ ይላል፣ “መንግስት ከሌላ መንግስት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የማይገባ ጥቅም በመስጠት ውል የተዋዋለ ከሆነ ያ ውል በአገሪቱ ህግ ተፈጻሚነት አይኖረውም“ መንግስቱን ወይም ደግሞ የመንግስቱን ተወካይ በማስገደድ የተደረገ ስምምነት ካለ ይህ የግዳጅ ስምምነት ስምምነቱን ለማፍረስ መሰረት ይሆናል፡፡

ሊካድ የማይችለው ነገር እነዚህ ተአማኒነት የሌላቸው ስምምነቶች በአቶ መለስ እና በአቶ ኃይለማርያም በሁለቱም ባለስልጣኖች የተፈረሙ ቢሆንም ከላይ በግልጽ ለማመልከት እንደተሞከረው ከኢትዮጵያ ህገመንግስት አንጻር ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡ ሌሎች ሊነሱ የሚችሉ ጥያቄዎች ቢኖሩ የሚከተሉት ናቸው፣ 1ኛ) አንቀጽ 55 (12) ከሚፈልገው የህግ ማዕቀፍ አንጻር ከሱዳን ገዥ አካል ጋር ገና ስምምነቶቹ ሲፈረሙ ግልጽ በሆነ መልክ ጉዳዩ ለሚመለከተው ፓርላማ ቀርቦ እንዲጸድቅ የተደረገ መሆን አለመሆኑ፣ 2ኛ) ስምምነቱ በሚከናወንበት ወቅት “ሙስና” እና “የማጭበርበር ወንጀል” የነበረ ወይም ያልነበረ መሆኑ፣ 3ኛ) ስምምነቱ በሚካሄድበት ጊዜ “አስገዳጅነት” ያላቸው ወይም ለማስገደድ የሚያበቁ ድርጊቶች የነበሩ ወይም ያልነበሩ መሆናቸው፣ በኢትዮጵያ ወገን በኩል ህጉን መርምሮ የማጽደቅ ሂደት ያልተከናወነ ስለነበር ኦማር አልባሽርን በሚጠቅም መልኩ የተፈጸመ እንዲሁም ስምምነቱ ለኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ እና እንዲጸድቅ ያልተደረገ ስለሆነ የተፈጻሚነት ዕድል እንደማይኖረው የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ በቬና ስምምነት መሰረት ሱዳን ለኢትዮጵያ መንግስት ስምምነቱን የማጽደቅ ዕድል መስጠት እንዳለባት የህግ ግዴታ አለባት፡፡ እራሷን ከጉዳዩ ጋር በማስተሳሰር በተለመደው ልምድ እና እምነት መሰረት ሱዳን ስምምነቱን ለማጸደቅ ስራዎችን ልትሰራ ይገባል፡፡ በአጠቃላይ ከስምምነቱ ጋር በተያያዘ መልኩ ሚስጥር ሆኖ መያዙ እና በስምምነቱ ዙሪያም ምንም ዓይነት ፍንጭ እንዳይኖር ድብቅ ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት አንጻር ወደፊት ስምምነቱን በጥልቀት እና በዝርዝር በመመርመር የሚገኘው የመረጃ ውጤት ሙስና፣ የማጭበርበር ወንጀል እና የግዳጅ ውል ሆኖ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን የመስጠት ስምምነቶችን ተፈጻሚነት የመሆን ዕድል የሚጻረሩ ሌሎች ህገመንግሰታዊጉዳዮች

አቶ መለስ እና አቶ ኃይለማርያም ግዙፍ የሆነ መሬት “ከአማራ የግዛት ክልል” በመቁረስ ለሱዳን በማስረከባቸው የአማራን ህዝብ የጋራ መብቶች ደፍጥጠዋል፡፡ “ስምምነቶቹ” አንቀጽ 39ን (የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት) እንዲሰጥ ስምምነት በተደረገበት መሬት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በግዳጅ ከሉዓላዊ ግዛታቸው በመነጠል ከፍላጎታቸው ውጭ ወደ ሱዳን አሳልፎ የሚሰጥ ስለሆነ ህጉ ተፈጻሚነት እንዳይኖረው ይጻረራል፡፡ አቶ መለስም ሆኑ አቶ ኃይለማርያም መሬት የማስመለስ፣ ብልህነት በጎደለው መልኩ በግዛት ላይ እና በግዛቱ በሚኖሩ ህዝቦች ላይ ድርድር የማድረግ ወይም ደግሞ በእራሳቸው ውሳኔ “የብሄሮችን እና የህዝቦችን” በመሬታቸው ላይ ያላቸውን መብት በመንጠቅ ሳይጠየቁና ምክር እንዲያደርጉ ዕድል ሳያገኙ በሌላ አባባል ሪፈረንደም ሳይሰጥ የመሬት ግዛታቸውን በድብቅ በተሸፈነ ሴራ በመንጠቅ ለሌላ አገር አሳልፎ የመስጠትም ሆነ ስምምነት የማድረግ ህገመንግስታዊ ስልጣን የላቸውም፡፡ በዓለም አቀፋዊ ህግ መሰረት መንግስት የአንድን አገር ሉዓላዊ ግዛት ለሌላ ባዕድ አገር አሳልፎ ከመስጠቱ በፊት ሊሰጥ በታሰበው መሬት ላይ ወይም በዚያ ግዛት ላይ የሚኖሩ ህዝቦችን የማማከር ግዴታ አለበት፡፡ ማማከር ሲባልም የህግ ሂደቱን ለመጠበቅ እንጅ መንግስት ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ መልኩ እጁን ዘው አድርጎ በማስገባት ምንም ዓይነት ውሳኔ መስጠት እንደማይችል ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ይህም ሆኖ “በአማራ ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የመሬት ግዛት” ለሱዳን መንግስት አሳልፎ ለመስጠት ስምምነት ከመፈራረማቸው በፊት በአቶ መለስም ሆነ በአቶ ኃይለማርያም በኩል ህዝቡን ለማማከር የተሞከረ ነገር የለም፡፡

ከዚህም በላይ የኢትዮጵያ ህግመንግስት አንቀጽ 2 የሚከተለውን መብት ያጎናጽፋል፣ “በዓለም አቀፍ ህግ ስምምነት እና ኢትዮጵያም ተቀብላ ባጸደቀቸው ህግ መሰረት የኢትዮጵያ ሉዓላዊ የግዛት አንድነት በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ አባል ክልላዊ መንግስታት ፌዴሬሽን ድንበሮችን አካትቶ የያዘ ነው፡፡“ ይኸ ህገመንግስታዊ ቋንቋ የአገር ውስጥ እና የውጭ የወሰን ድንበሮቻቸው ሲካለሉ እና ሲዘጋጁ “የክልል አባል መንግስታት” የሚኖራቸውን ቀጥተኛ ሚና መስተጋብር በግልጽ ያሳያል፡፡ የህገመንግስቱ አንቀጽ 2 የኢትዮጵያ የፌዴራላዊ መንግስት አካል መሬቱን ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት ከመፈረሙ በፊት “በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት” የወሰን ክልል ውስጥ የሚኖረው ህዝብ ሪፍረንደም/referendum (ጠቅላላ የህዝብ ድምጽ) ማድረግ እንዳለበት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡
ከሱዳን ጋር የተደረገው ህገወጥ ስምምነት ተፈጸሚነት ስለማይኖረው ብዙም አያሳስብም

በአቶ መለስ፣ አቶ ኃይለማርያም እና ጓዶቻቸው የተደረገው ህገወጥ ስምምነት ተፈጻሚነት የማይኖረው ቢሆንም በመጠኑም ቢሆን አሳስቦኛል፣ ሆኖም ግን በግልጽ እና ጥልቀት ባለው መንገድ ሳገናዝበው ብዙ የሚያሳስበኝ አይሆንም፡፡ “ስምምነት” እየተባለ ስለሚጠራው ጉዳይ ብዙ የሚታወቁ ድብቆች አሉ፡፡ ስምምነቶቹን ካባ ደርበው ትልቅ ነገርን እንደፈረሙ እናውቃለን፡፡ ሆኖም ግን ምን እንደደበቁ በእርግጠኝነት ለመናገር አይቻልም፡፡ ስምምነቶቹን ከህግ አግባብ ውጭ በሙስና እንዳደረጉ እናውቃለን፣ ሆኖም ግን የሙስናውን ስፋት እና ጥልቀት እስከምን ድረስ እንደሆነ በግልጽ አይታወቅም፡፡ ስምምነቶቹ ሲፈጸሙ ማታለል እንዳለባቸው እናውቃለን፣ ሆንም ግን የማታለሉ ደረጃ እስከምን ደረጃ እንደሆነ አናውቅም፡፡ ስምምነቶቹ ሲፈጸሙ ማጭበርበር እንዳለባቸው እናውቃለን፣ ሆኖም ግን የማጭበርበሩ ስፋት እና ጥልቀት ደረጃ እስከምን ድረስ እንደሆነ አናውቅም፡፡ የስምምነት ሰነዶች ሲፈረሙ ሁሉንም ዓይነት ያካተቱ ማጭበርበሮች እንዳሉ እናውቃለን፣ ሆኖም ግን የማታለል፣ የማጭበርበር እና የመሰሪነት ዓይነቶችን አናውቅም፡፡ በድብቅ የተፈረሙት ስምምነቶች እና አሁንም ሚስጥር ሆነው የተያዙት ድሁር እና ኮሳሳ ስምምነቶች ወደፊት በጊዜ ሂደት እርቃናቸውን ወጥተው ሚስጥሩ ግልጽ የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ”እውነት ለዘላለም ተቀብራ እንደማትኖር ሁሉ ተንኮልም በዙፋን ላይ ለዘላለም ተቀምጣ አትኖርም”፡፡

የኢትዮጵያ የግዛት ሉዓላዊነት አንድነት በምንም ዓይነት መልኩ ለድርድር አይቀርብም፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ፣ አቶ ኃይለማርያም ዳሳለኝ…ሌላም ማንም… ቢሆን በኢንቨስትመንት የማስመሰያ ጨዋታ የኢትየጵያን ለም መሬቶች በቅርጫ ለሱዳን፣ ለሳውዲ ወይም ለህንድ “ባለሀብቶች” ሊሰጥ አይችልም፡፡ እውነታው ግን ጀሴ ጀምስ እና ወሮበላ ጓዶቹ (በአሜሪካ የታውቁ ዘራፊዎች) የዘረፏቸውን ባንኮች ለሌላ የመስጠት መብት እንዳላቸው አድርገው እንዳሰቡት ሁሉ የኢትዮጵያ ቁንጮ አምባገነን መሪዎች ደግሞ የኢትዮጵያን ለም መሬት የመስጠት መብት እንዳላቸው ቆጥረውታል፡፡
ጥንታዊ የሆነች ኢትዮጵያ የምትባል አገር አለች፣ የእኛ እናት ሀገር፡፡ ኢትዮጵያ በክልል መከፋፈል የለባትም፣ “በጎሳ ፌዴራሊዝም” መበጣጠስ የለባትም፣ ወይም ደግሞ በድንበር መካለል ሰበብ “ስምምነት” መሰረት ግዛቷ መሸጥ የለበትም፡፡ ወደ የግዛት ሉዓላዊነት አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያ ስንመጣ ኦሮሞ ኢትዮጵያ የለችም፣ አማራ ኢትዮጵያ የለችም፣ ትግሬ ኢትዮጵያ የለችም፣ ጉራጌ ኢትዮጵያ የለችም… ወይም ደግሞ ጋምቤላ ኢትዮጵያ የለችም፡፡ በቀላሉ አነጋገር የኢትዮጵያ ህዘቦች ኢትዮጵያ ናት ያለችው፡፡ በሉዓላዊነት የግዛት አንድነት ዙሪያ በመሰባሰብ ኢትዮጵያ የማትከፈል እና የማትከፋፈል መሆኗን በማመን መተባበር አለብን፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ጠንቃቃ ሆነን መገኘት አለብን፣ እናም ከመቃብር አፋፍ ላይ ሆነው ለማትረፍ የሚፈልጉ ተንኮለኛ ጭራቆችን እራሳቸው በመቃብር ውስጥ እንዲቀሩ እናድርግ፡፡ አምላክ ሁላችንንም አንድ አድርጎ እንደፈጠረን ሁሉ በፍቅር እና በመከባበር በአንድነት በመኖር ለአምባገነንነት፣ ለጨፍጫፊነት፣ ለመለያየት ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ ዛሬም አንዲት ኢትዮጵያ! ነገም አንዲት ኢትዮጵያ! ለዘላለምም አንዲት ኢትዮጵያ!
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!
ጥር 27 ቀን 2006 ዓ.ም

አማራውን በተሳደቡት አቶ አለምነው መኮንን ላይ በባህር ዳር ሰልፍ ሊደረግ ነው፤ በአድዋና አዲስ አበባ የአድዋ ድል በዓል ዝግጅቶች ይኖራሉ

$
0
0

– አማኑኤል ዘሰላም

የአንድነት ፓርቲ፣ በሶስት ከተሞች ታላላቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች፣ ለማድረግ መወሰኑን ከሚሊየነሞች ድምጽ ለነጻነት ፌስቡ ገጽ አነበብኩ። እንቅስቃሴዎቹ የሚደረጉባቸው ከተሞች፣ አድዋ፣ አዲስ አበባ እና ባህር ዳር ናቸው። በአድዋ እና በአዲስ አበባ ከሌሎች ደርጅቶ ጋር በጋራ በመሆን (መኢአድ፣ አረና፣ ትብርር፣ መድረክ..) ፣ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ሕዝቡ ሁሉ ኩራት የሆነውን የአድዋ ድል በማሰብ ትልቅ አከባባር ለማድረግ ነው የታቀደው። በአድዋና በአዲስ አበባ ባሉ ብዙ ህዝብ ሊይዙ በሚችሉ አደባባዮች አከባበሩ ሊደረግ እንደሚችል ግምት ቢኖርም ፣ የአንድነት ፓርቲ የአከባበሩ ይዘት፣ ሰዓትና ቦታን ገና ይፋ አላደረገም።
alemenew mekonn
በባህር ዳር የሚደረገዉ ግን ከአድዋና ከአዲስ አበባዉ የተለየ ነዉ የሚሆነው። በቅርቡ የአማራ ክልል ም/ ፕሬዚዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው፣ በክልሉ የሚኖረው ሕዝብ ላይ የሰነዘሩት ጸያፍና ከአንድ መሪ የማይጠበቅ አባባሎችን በመቃወም የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ነዉ። ጉዳዩ አንድ ሰው የተናገሩት ቢሆንም፣ ኢሕአዴግ እንደዚህ አይነት ሕዝብን የናቀና ያዋረደ አስተያየት የሰጡ ባለስልጣን ከሃላፊነታቸው ወዲያዉኑ እንዲነሱ አለማድረጉ፣ በሕግም አለመጠየቁ፣ ችግሩ ከግለሰብ አልፎ ድርጅታዊ መሆኑንም የሚያመላክትበትም ሁኔታም አለ።

«የአማራው ህዝብ ሰንፋጭ የሆነ ትምክተኝነት የተጠናወተው በመሆኑ በቤንሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች ለመሰደዱ ምክንያት ሆኖታል»፣ «አማራዉ በባዶ እግሩ እየሄደ የሚናገረው ንግግር ግን መርዝ ነው»፣ «የአማራዉ ሕዝብ የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት» …. የመሳሰሉ አስተያየቶችን ነበር ባለስልጣኑ የሰነዘሩት።

ሰልፍ መጥራት በራሱ ለዉጥ አያመጣም። በባህር ዳር፣ አድዋ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ የሚደረጉ ሰልፎችና ዝግጅቶች በማይሻማ መልኩ ፖለቲካዉን እንዲያናጉት፣ የማያሻማና የሚያስተጋባ መልእክት እንዲያስተላለፉ ከተፈለገ፣ ሕዝብ በነቂስ መዉጣት አለበት። ለዚህም ትልቅ ድርጅታዊና የቅስቀሳ ሥራ መስራቱ የግድ ነዉ። በየወረዳው፣ በየመንደሩ ፣ ቅስቀሳዎች መደረግ አለባችው። በራሪ ወረቀቶች፣ ፓምፍሌቶች በስፋት መዘጋጀትና መበተን ይኖርባቸዋል።

አንድ ነገር አንርሳ። እኛ ኢትዮጵያዉያን ካልደገፍናቸው፣ ከጎናቸው ካልቆምን ፓርቲዎቹ ብቻቸውን በራሳቸው ምንም ሊያመጡ አይችሉም። ገዢው ፓርቲ የሚተማመነው በያዘው ጠመንጃ፣ ባሰማራቸው ሰላዮቹና ካድሬዎችቹ ነዉ። አንድነቶች ግን የሚተማመኑት በሕዝብ ጉልበት ብቻ ነው። እያንዳንዳችን የድርሻችንን ከተወጣን፣ በአዲስ አበባ፣ በአድዋና ባህር ዳር የምንኖር የሚደረጉ ሰልፎችን እና ዝግጅቶችን ከተቀላቀልን፣ ነጋሪና ቀሳቅሽ ሳንፈልግ፣ በኛዉ አነሳሽነት ቅስቀሳ ካደረግን፣ ተዓምር የማንሰራበት ምንም ምክንያት የለም።

በሰልፉ ለመገኘት የማንችል ደግሞ፣ በተለይም በዉጭ አገር ያለን፣ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ከማሳወቁ በተጨማሪ፣ በገንዘባችን ትልቅ ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅብናል።

(ሰበር ዜና) በሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ዙሪያ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጠ

$
0
0

(Updated) (ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የሚገኘው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ውስጥ የተፈጠረውን የሃሳብ ልዩነትና የህግ ተጥሷል ጥያቄ በተመለከተ በገለልተኛነት እንዲቆይ ከሚፈልገው ወገን በተወከሉት ወገኖች የቀረበውን አቤቱታ እና በተከላካይ ደብረሰላም ቦርድ መካከል ያለውን ጉዳይ (Temporary Restraining Order Hearing) የተመለከተው የሚኒሶታው ፍርድ ቤት ዛሬ ፌብሩዋሪ 5 ቀን 2014 ዓ.ም አባላት ተሰብስቦ የቤተክርስቲያኒቱን ቀጣይ ሁኔታ እንዲወስን ያ ካልሆነ ለማርች 10 ቀን 2014 ክሱ መታየት እንዲቀጥል ውሳኔ አስተላለፈ።
debereselam Minnesota
በፍርድ ቤቱ ከታደሙ እማኞች ባገኘነው መረጃ መሠረት የሚኒሶታ ስቴት የሄኒፐንካውንቲ ፍርድ ቤት (state of Minnesota, county of Hennepin district court fourth judicial district) በሁለቱም ወገኖች በጠበቆች አማካኝነት የቀረበውን አቤቱታ ከተመለከተ በኋላ የቤተክርስቲያኑን ቀጣይ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ምዕመናኑ እንዲወስን፤ ያካልሆነ ግን ለማርች 10 ቀን 2014 ቀጣይ ቀጥሮ እንዲሆን አዟል። በዚህም መሠረት እሁድ ፌብሩዋሪ 23 ቀን 2014 በደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ አባላት ተሰብስበው የቤተክርስቲያኒቱን አጠቃላይ ሁኔታ ለመወሰን ቀጠሮ ተይዟል።

“ቤተክርስቲያኑ ወደ ሃገር ቤት ሲኖዶስ እንዲቀላቀል የሚፈልገው” ወገን በጠበቃው አማካኝነት የቀድሞውን ሊቀመንበርን በሚመለከት ቀድሞ ያሰባሰበውን ፒትሽን በጠበቃው አማካኝነት ያቀረበ ሲሆን በጠብቃቸው አማካኝነት “ማን ነው ቤ/ኑን የሚመራው?” በሚል ያቀረቡትን ጥያቄ ዳኛዋ ምንም ምላሽ እንዳልሰጡበት ከታዛቢዎች ያግኘነው መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል “በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ያለው ሲኖዶስ መካከል እርቀሰላም እስኪወርድ ድረስ በገለልተኛነት መቆየት አለብን” የሚለው ወገን ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራልን በሚል ያሰባሰበውን የምዕመናን ፒትሽን በጠበቃው አማካኝነት ለፍርድ ቤት ማቅረቡ ታውቋል።

አሁን በደረሰን መረጃ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የማይወሰን ከሆነ ፍርድ ቤቱ በማርች 10 ቀን 2014 ዓ.ም ጉዳዩ ይታያል።

ከአዘጋጁ፦ ዘ-ሐበሻ ከሁሉም ወገን ያለውን መረጃ ለማቅረብ እየጣረች ቢሆንም ዲያቆን ኤፍሬም መገንታ ወደ ዘ-ሐበሻ ዝግጅት ክፍል በመደወል ለማስፈራራት ሞክሯል። በፌስቡክ ገጻችን ላይ በመምጣትም ዘ-ሐበሻ የምትጽፈው ሚዛናዊ አይደለም፤ የውሸት ዘገባ ነውና ይቁም ሲል ጠይቋል። ይኸው የርሱም አስተያየት፦

New Picture

(ተጨማሪ መረጃዎች ከደረሱን አሁንም ዜናውን በአዳዲስ መረጃዎች እናድሰዋለን።)

በሳንሆዜ፤ ከተማ እና አጎራባች ከተሞች፤ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ በህብረት የወያኔን ሴራ እናምክን!!

$
0
0

በሳንሆዜ፤ ከተማ እና አጎራባች ከተሞች፤ ለምትኖሩ
ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤
በህብረት የወያኔን ሴራ እናምክን!!

UDJ - Ethiopia ሐገራችን ኢትዮጵያ የአንጸባራቂ ታሪክ ባለቤት፤ ለአፍሪካና እንዲሁም በአለም ዙሪያ ለሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች በሙሉ እንደ አጥቢያ ኮከብ የምትታይ መሆኑዋ በወዳጅም በጠላትም የተመሰከረ ሃቅ ነው። ታሪካዊ ጠላቶች፤ የሀገራችንን ሉአላዊነት፤ የህዝባችንን በራስ መተማመን፤ ሀገር ወዳድነት፤ የራሱ የሆነ ባህል፤ ወግ እና እምነት ጠብቆ መቆየት እንቅልፍ
ነስቷቸው፤ ሲቻላቸው ከመሃከላችን፤ ለጠላት ያደሩ ከሃዲ ባንዳዎችን በመመልመል፤ ሳይቻል ደግሞ በቀጥታ በመዝመት እኛነታችንን ለማክሰም፤ የነበራቸው ህልም፤ በጀግኖች አባቶቻችን እና ጀግኖች እናቶቻችን ቆራጥ ተጋድሎ የወራሪው ሃይል ህልም መክኖ ቀርቶዋል።

እንዳለመታደል ታዲያ በህዝባችን ጫንቃ ላይ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት የስልጣን መንበር ላይ የተፈናጠጠው ጎጠኛውና አምባገነኑ የወያኔው ቡድን ከህዝባችን ፍላጎት በተቃራኒው በመቆም፤ የታሪካዊ ጠላቶቻችን ባለሙዋልና ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን፤ የሺ አመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችውን ሃገራችንን፤ ህዝቦችዋን እና በውስጡዋ ያዘለችውን
አኩሪ ባህል፤ በመናቅ፤ በመካድ፤ ብሎም በዘርና በጎሳ በመከፋፈል፤ በጎጥና በቁዋንቁዋ በመነጣጠል፤ በመንደር እና በወንዝ በመለያየት፤ የሃይማኖት ልዩነትን ወዳልተፈለገ ጥግ በመግፋት፤ የጋራ የሆኑ ታሪካዊ እሴቶቻችንን፤ እንደ ህዝብ የሚያስተሳስር ሰንደቅ አላማችንን ሳይቀር በመለወጥ፤ ህልውናችንን ከመፈታተን አልፎ፤ ወደ ማጥፋት ግስጋሴ ላይ እንደሆነ የታወቀ ነው። በዚህ ጠባብና ጎጠኛ ቡድን የአገዛዝ ዘመን፤ ታሪካዊ ሃገራችን ወደብ አልባ፤ ትውልድ አልባ፤ እምነት አልባ፤ ጀግና አልባ፤ ብሎም በአጎራባች ሃገሮች ቸርነት ላይ ተስፋዋን የጣለች፤ መጻግኡ ሆናላች ብንል የተጋነነ አይደለም። ጀግኖች ኣባቶቻችን ኣጥንታቸውን ከስክሰው፤ ከባሩድ እና ከጥይት ጋር ተጠራምሰው፤ በመርዝ ጭስ ተጨርሰው፤ እነሱ አልፈው ያቆዩትን ሰነደቅ አላማ፤ ይሄ ዘረኛ ቡድን በበርሃ ስኩዋርና በሶ ሲሸከምበት፤ ከተማ ከገባ በሁዋላም ጨርቅ ነው እያለ ሲራቀቅ እና ሲመጻደቅ የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

united we stand በወያኔ አገዛዝ ጋዜጠኞች አሸባረ በመባል ዘብጥያ ወርደዋል፤ የሃይማኖት አባቶች ሞት እና ሰደት እጣ ፈንታቸው ሆኖል፤ ገዳማት ተደፍረዋል፤ዜጎቸ በራሳቸው ሃገር ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ሃብት እና ንብረት የማፍራት መብታቸውን ተነፍገዋል፡ አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ እናቶቸ እና እህቶቸ የሚያመክን መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዲቀንስ ተደርጉዋል። እስር ቤቶች በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት በተለይም በኦሮመኛ ተናጋረ ወገኖቻችን ተጨናንቋል፤ የኑሮ ውድነቱ እማይቀመስ ሆኖል፤ በምርጫ የተሸነፋው ወያኔ በጠራራ ጸሃይ ያልታጠቁ ህጻናትን በአደስ አበባ እና በሌሎች ክተሞች በግፍ ፈጅቷል። የእስልምና ጉዳይ አፈላላጊ ወገኖችን በአሸባረነት ከሱዋል፤ በመሃከለኛው ምስራቅ ወጣት ሴት እህቶቻችን ለዘመናዊ ባርነት በመዳረግ በታረካችን ታይቶ እማይታውቅ ውርደት እና የሰነልቦና ጠባሳ ጥሎብናል። በጋምቤላ ዜጎችን በማፈናቀል እና የውጪ ጉቦ ሰጭዎች ለም ቦታ እንዲየዙ አድረጎል፤ በኦጋዴን ግድያው አስገድዶ መድፈሩ እና የሰብአዊ መብት ጥሰቱ እንደቀጠለ ነው፤ አልፎ ተርፎም የሃገራችን ድንበር ለሱዳን በእጅ መንሻነት ተስጥቷል።

በጣሊያን ወረራ ዘመን ድልድይና ህንጻ በመሰራቱ ወራረው ጦር ይግዛን ያላለውን እና ነጻነቱን ያስቀዳመውን ህዝባችን ዛሬ የወያኔ ደናቁርት ካድሬዎች በህዝብ ጠኔ የትላልቅ ህንጻ ባለቤት እና ባለዘመናዊ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆናችው ያደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ፤ ላለፉት ሃያሶስት ያገዛዝ አመታት የህዝባችን ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ማምራቱ እየታዎቀ ’ልማታዊ’’ የሚል ጭምብል ለብሰው ለማደናገር መሞከር ከጀመሩ ሰንበትበት ብሎል በየሄዱበት ቢከሽፍም። ዛሬ ታድያ በዚህ ብምንኖርበት በሳን ሆዜ ከተማ ውህዳን የወያኔ ጀሌዎች የወያኔን ጭምብል ለብሰው “ልማታዊ” የልመና አኩፋዳቸውን አዘጋጅተው ለፌብሯዋሪ 8፣ በ770 ሞንታጊዩ ኤክስፕሬስ ዌይ ሳን ሆዜ ካሊፎርኒያ (770 Montague Expressway San Jose CA 95134) በህዝባችን እንባ ሊሳከሩ እና በሃዘኑ ሊሳለቁበት ተዘጋጅተዋል።

እኒኚህ ከሃዲዎች የወያኔን ሹማምንትም ጋብዘዋል። ከሃዲዎችን ማጋለጥ እና ቅስማቸውን መስበር ኢትዮጲያዊ ግዴታችን በመሆኑ ሁላችንም ኢትዮጲያውያን አንድ ላይ በመሆን በሌሎች ከተሞች እንደተደረገው ሳን ሆዜ ለባንዳዎች አይሆንም ልንላቸው ይገባል። እላይ በተጠቀሰው አድራሻ ክ3፡00PM በመገናኘት ድምጹን ማሰማት ላልቻለው ህዝባችን ድምጽ እንሆነው ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።

ከአባይ በፊት ሰብዓዊ መብትን መገደብ ይገደብ !!!!
ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ይፈቱ!!!!
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር!!!
የሳንሆዜ ሀገር ወዳዶች ግብረሃይል።

ስልክ ጠላፊው ሰላይ “ጋዜጠኛ”

$
0
0

በማህሌት ነጋ (ሲያትል)

ከሁሉ የእኔን ቀልብ የሳበው የቀጂው ማንነት ነበር። ለማጣራት ያደረኩት ጥረት ብዙም ግዜ አልፈጀብኝም። አበበ ገላው በዚሁ “ሊክድ” በተባለው ቅጂ “እኔ ከሞትኩም እንደ ሃየሎም መጠጥ ቤት በከንቱ መሞት አልፈልግም። መሞት የምፈልገው ለአላማ ነው ይላል።” በዚህ ግዜ አንድ ሳቅ ይሰማል። የኢያጎ ሳቅ። ዳዊት ከበደ ስለመሆኑ ብዙም አልተጠራጠርኩም።

dawit kebede cellphone

ሰሞኑን አንድ ሚስኪን ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ከአንድ የከሰረ ፖለቲካኛ ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርግ በቪዲዮ ለቆ ስለነበር ለሶስት ደቂቃ ያህል ተምልክቼ ጭንቅላቴን በሃዘን እየነቀነኩ ዘጋሁት። እኔን ጨምሮ በርካቶች ድረ ገጾችን የምናስሰው መረጃ ፍለጋ እንጂ የከሰሩ ግለሰቦችን ደረቅ ወግ ለማዳመጥ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው። በአንድ ወቅት ያዙን ልቀቁን ይሉ የነበሩት ሁለት ግለሰቦች የዛሬን አያድርገውና ኢትዮጵያዊያን እንደ ማንዴላ የነጻነት ታጋዮች አድርገው ያከብሯቸው ስለነበር ድምጻቸው የጎላ በራስ መተማመናቸው ከውስጣቸው ሞልቶ በአፋቸው ይገነፍል ነበር። ዛሬ ግን ድምጽ አጥሯቸው ቀልብ እርቋቸው ሲንሾካሾኩ ያየ ሁሉ እንደ እኔ ከንፈር መጦ የሁለቱን ምስኪኖች ወግ በግዜ ዘግቶ ወደ ስራው እንደሚመለስ ብዙም አያጠራጥርም።

“ምስኪኖች እነማን ናቸው?” እንደማትሉኝ እርግጠኛ ነኝ:: የአውራምባው ዳዊት ከበደና የኢዴአፓው ልደቱ አያሌው ጉዳይ መቼም አንገት ያስደፋል። ሁለቱም ጠላታቸው ወያኔ እንዳልሆነ እነርሱ እንደሌሎች “ጽንፈኛ” እንዳልሆኑ ሌሎችን ከሰው እራሰቸውን ከፍ ለማድረግ ሲጥሩ ላስተዋለ ጠበል የሚወስዳቸው ያጡ በሽተኞች መሆናቸውን ድርጊታቸው ይመሰክራል። ዲያስፖራውና የግል ጋዜጦች በተለይ የጋራ ጠላቶቻቸው ይመስላሉ። እንደው ለመንደርደሪያ እንጂ የዚህ ጹሁፍ አላማ የሁለቱ ምስኪኖች ወግ ስላልሆነ ወደ ቁም ነገሩ ልመለስ::

ሾተላዩ ሰላይ ዳዊትን ለመጀምሪያ ግዜ በአካል ያገኘሁት ወደ ሲያትል የዛሬ ሶስት አመት በመጣ ግዜ ነበር። አስተባባሪዎች መርጠን፣ ገንዘብ አዋጥተን፣ ድግስ ደግሰን፣ ሽልማት አዘጋጅተን ነበር የጀግና አቀባበል ያደረግንለት። ወቅቱ የብርድ እና የበረዶ ግዜ ስለነበር እኔም እንደሌሎች ይህንን “ጀግና ጋዜጠኛ” ለመቀበል ብዙ መስዋእትነት ነበር የከፈልኩት። በተለይ የኢትዮሜድያው አብርሃ በላይና ሼክስፒር ፈይሳ እንግዳውን ተቀብለው ቤታቸው ከማሳደር አልፈው ለዝግጅቱ ስኬት ያበርከቱት አስተዋስኦ ቀላል አልነበረም። ሰላዩ ጋዜጠኛ ግን አብርሃ በላይን አራክሶ፣ ሼክስፒር ፈይሳን ደግሞ ስምህን አጠፋለሁ ብሎ በማስፈራራት ከንቱነቱን ብቻ ሳይሆን የኢያጎ ባህሪውን ፍንትው አድርጎ አጋልጧል።

ይሁንና ኢያጎን (ዳዊትን) በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ አትመኑት ማለታቸው አልቀረም። እውነት ለመናገር ዳዊት እነ ውብሸት ታዬ እና ርእዮት አለሙን በማሳሰሩ ድርጊት እጁ አለበት የሚል ሹክሹታ ከወደ አገር ቤት ሲናፈስ ማናችንም የዚህ ጎጠኛ “ጋዜጠኛ” ወዳጆች በቁም ነገር አልወሰድነውም። መቼም ሰው በምልካም ስራው ሲታወቅና ሲወደስ ምቀኛ እንደማይጠፋ ለማንም ግልጽ ነው። ስለዚህም ነበር ዳዊትን አትመኑት የሚለውን የአገርቤት መልእክት ማንም ትኩረት ያልሰጠው። አሁንም ስለዚያ ድርጊቱ ተጨባጭ መረጃ ስለሌለኝ ድርጊቱን ፈጽሟል አልፈጸም ለማለት ባልችልም ከጀርባ የመውጋት ጋህሪውን ለማስተዋል በመቻሌ አያደርግም ብዬ መከራከር አልችልም።

ዳዊት ተራ የሆኑ ጉዳዮችን ሁሉ የመቅዳት ባህሪ አለው። ሰው ሲጎርስ፣ ሲጠጣ፣ ሲናገር፣ ሲቀልድ (ከተቻለውም ሽንት ቤት ሲጸዳዳ) ቪዲዮና ፎቶ ማንሳት ድምጽ መቅዳት ይወዳል። በስውር የሚቀዳበት ሪኮርደርም ይዞ እንደሚዞር ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። ብዙ ሰው ግን የዳዊትን ድርጊት ከጋዜጠኝነት ስራው ጋር ስለሚያያይዘው ተንኮሉን አይጠረጥርም። ነገሩ ያልጠረጠረ ተመነጠረ መሆኑን ነው።

አሁን እንደምንሰማው ነዋሪነቱ በአሪዞና ፊኒክስ የሆነው የዳዊት ከበደ ታላቅ ወንድም ብስራት ከበደ የሚታወቀው በተመሳሳይ የመቅዳት ባህሪው ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት ብስራት ምንም ጭንብል ሳያጠልቅ አይኑን በጨው አጥቦ ስለሚንቀሳቀስ የህወሃት ታማኝ ካድሬና ሰላይ መሆኑ በስፋት ይነገራል። እርሱም እንደ ወንድሙ የትርፍ ግዜ ስራው ስለሆነ እንኳን ፖለቲከኞችን እና ታጋዮችን በስካይፕም ይሁን በስልክ የሚያናግራቸው ሴቶች ምስልና ድምጽ ሳይቀር እንደሚቀዳ በጉራ ይናገራል፣ ለቅርብ ጓደኞቾም ያሳያል። እዚህ ላይ ግለሰቡን እምታውቁ ሴቶች ጠንቀቅ በሉ ማለት ሳያስፈልግ አይቀርም።

የኢያጎ ጩቤ ወደ ዲሲ ደዋውዬ እንዳጣራሁት ዳዊት ወያኔ አባረረኝ ብሎ ወደ አሜሪካ ፈርጥጦ ሲመጣ የኢሳት ሰዎችም የተቀበሉት በመልካም አይን ነበር። በተለይ ከሲሳይ አጌና፣ ከመሳይ መኮንን እንዲሁም አበበ ገላው ጋር መልካም ወዳጅነት ለማፍራት፣ አብሮ ለመጠጣትና ለመብላት ግዜ አልወሰደበትም። ለጋዜጠኝነት ስነምግባር እጨነቃለሁ የሚለው ይሄው ግለሰብ ወያኔ ጠለፍኩ ያለውን የዶ/ር ብርሃኑን የስካይፕ ውይይት በድህረ ገጹ ላይ በማውጣት የራሱ አጸያፊ ድርጊት መነጋገሪያ ሆኖ እንደ ነበር ይታውሳል። ዳዊት ከበደ በኢሳት፣ ግንቦት ሰባትን እና ዶ/ር ብርሃኑ ላይ በተከታታይ የሰራውን አሳፋሪ ግን ደግሞ የከሸፈ ፕሮፓጋንዳ ሁሉም ስለሚያውቀቅ መድገም አያስፈልግም። ከሁሉ የገረመኝ ሰሞኑን ዳዊት ኢያጓዊ የስለላ ስራውን ለማራቀቅ መሞከሩ ነው። ሞኝ እራሱን ያታልላል ነው ነገሩ።

ልክ እንደ ኢያጎ ዳዊትም ጩቤን በጀርባው ደብቆ ያመኑትን እና ያቀረቡት ሁሉ ላይ ከማሴር ቦዝኖ እንደማያውቅ ሙሉ በሙሉ ግልጽ ሆኗል። በቅርቡ ለመረዳት እንደቻልኩት በርግጥም የዛሬው ኢያጎ ዳዊት ከበደ መስዋእትነት ከፍሏል፣ መልካምነቱንም በስራው አስመስክሯል በማለት እንደ ትግል አጋር ያዩት ከነበሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን አንዱ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ይገኝበታል። ለዚህም ምክንያት አንዱ ኢያጎ ከእስር ወጥቶ በሲፒጄ ሳይቀር ለፕሬስ ነጻነት ላበረከተው አስተዋጽኦ በታላላቅ የአለማችን ጋዜጠኞች ፊት በኒውዮርክ ቀርቦ ሽልማት ሁሉ መውሰዱ ነው። ይቺም ስኬት ለዳዊት ጥሩ ጭንብል ሆና ቆይታለች።

በወቅቱም ወያኔ ይገለኛል ያስረኛል እንጂ አገር ለቅቄ አልሰደድም ብሎ በየመድረኩ ሲደነፋ በእውነትም የጎልያድ ጠላት ቅዱስ ዳዊትን ነበር የመሰለን። ያሁሉ ተረት ሆኖ ወያኔ ሊያስረኝ ነው ብሎ አገር ጥሎ ሲፈረጥጥ አሜሪካ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ክብርና ፍቅር አልነፈጉትም ነበር። የእኛው ኢያጎ ግን ያን ሁሉ ክብር ትቶ በእኩይ ተግባሩ የነጻንት ትግሉን የሚጎዳና የህወሃት አንባገነኖችን በሚጠቅም እኩይ ተግባራት ላይ ለመሰማራት ግዜ አልፈጀበትም።

በቅርቡ ወያኔዎች ክፉውን ጎልያድ መለስ ዜናዊን በአለም መሪዎች ፊት አዋርዶና አስደንግጦ የመጨረሻና ወሳኝ ስንብት ላደረገለት ጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላውን ለማስጠላት እንዲሁም ኢትዮጵያዊውን ለመከፋፈል በህገወጥ መንገድ የተቀዳ የግል የስልክ ንግግር አዛብተው፣ ቆርጠውና ቀጥለው በኢንተርኔት ላይ ለቀቁ። ይሄም የተለቀቀው በዳዊት ድርገጽ ሳይሆን በቀንዲል የወያኔ የፈስቡክ አቀንቃኝ ዳንኤል በርሄ አማካኝነት በሆድ አደሩ ሹምባሽ ከበደ ካሳ አቀናባሪነት ነው። ደግነቱ የተባለው ሁሉ ምንም ሚስጥር የሌለው ስለነበር እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው እነርሱንው መሳለቂያ አድርጓቸዋል።

ከሁሉ የእኔን ቀልብ የሳበው የቀጂው ማንነት ነበር። ለማጣራት ያደረኩት ጥረት ብዙም ግዜ አልፈጀብኝም። አበበ ገላው በዚሁ “ሊክድ” በተባለው ቅጂ “እኔ ከሞትኩም እንደ ሃየሎም መጠጥ ቤት በከንቱ መሞት አልፈልግም። መሞት የምፈልገው ለአላማ ነው ይላል።” በዚህ ግዜ አንድ ሳቅ ይሰማል። የኢያጎ ሳቅ። ዳዊት ከበደ ስለመሆኑ ብዙም አልተጠራጠርኩም። ሳቁ በጣም የተለየች ውስጧ ሸፍጥና ተንኮል ያዘለች ነች። ዳዊትን ለሚያውቁት ወዳጆቼ አስተያየት ሳልሰጥ ይቺን አምልጣ ስትቆረጥ የወጣች ወሳኝ መረጃ አድምጣችሁ የማን ሳቅ እንደሆነ ንገሩኝ ብዬ በኢሜይል አያይዤ ላኩላቸው። አራቱም መልሳቸው አንድ ነው፣ የኛው ኢያጎ ዳዊት ከበደ።

ዳዊት በጣም አሳዘነኝ። ብዙ ተስፋ የጣልንበት “ጋዜጠኛና የነጻነት ታጋይ” እንዴት ከክብር ወንበሩ ወርዶ ቆሻሻ ትቦ ውስጥ ይወድቃል? ለነገሩ ከልብ ያልሆነ ነገር ሁሉ እራሱን መግለጡ አይቀርምና ዳዊትም ከልቡ ኢያጎ እንጂ ሌላ አልነበረም። በጣም ተምታቶበታል። እኛ ግን የበለጠ ነቃን። እነዳዊት ከበደ ግን ግራ እንደተጋቡ እንደሰካራም በየትቦው ውስጥ እየወደቁ ይገኛሉ። ተመስገን ደሳለኝ ከጥቂት ወራት በፊት “የፖለቲካ ስር ቁማርተኞች” በሚል የጻፈው አንጀት አርስ ጹሁፍ ትዝ አለኝ። ተመስጌን የጠየቀው መሰረታዊ ጥያቄ በእኔም አእምሮ ውስጥ ያቃጭላል። ለመሆኑ ወደ አገር ቤት ከአሜሪካ ልክ እንደ አመጣጡ ፈርጥጦ ያስመለሰው ጉዳይ የፕሬስ ነጻነት መሻሻሉና “የጽንፈኞችን” ፖለቲካ በመጸየፉ ነው ወይንስ ደግሞ ኢሳትን የማፍረስ እና በጸረ-ወያኔ ትግሉ ግንባር ቀደም ሚና ይሚጫወቱ ኢትዮጵያዊያንን ለማምታታትና ለመሰለል ስላላመቸው? መልሱ ግልጽ ነው።

ወያኔዊ ኢያጎነት በቀላሉ እንደማይለቅ ከዳዊት መማር ይቻላል። ዲሲ አካባቢ በቅርብ የታዘቡት እንደነገሩኝ ዳዊት ሁለት ነገሮች አብዝቶ ይወዳል፣ መጠጥና ሴት ማባረር። ከአገር ቤት ፈርጥጦ ዲያስፖራ የተቀላቀለው ዳዊት ሲነቃበትና ይሄ የሱስ ጥማት ሲያስቸገረው ፈርጥጦ እነአቦይ ስብሃት እና ሽመልስ ከማል ጋር ብርጭቆ ማጋጨት መጀመሩን ሰማን። ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ግር ይላሉ አሉ ፈረንጆች። አበው ሲተርቱ ግም ለግም አብረህ አዝግም እንዳሉት መሆኑ ነው። መልካም እድል፣ መልካም ቅምቀማ ብለናል ከወደ ሲያትል!!

Sport: የዛሬ ምሽቱ የገንዘቤ ዲባባ እና የአበባ አረጋዊ ፍጥጫ በስቶክሆልም

$
0
0

ከቦጋለ አበበ
genzebe d
ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው የወቅቱ የመካከለኛ ርቀት ኮከብ አትሌቶች መካከል ገንዘቤ ዲባባና አበባ አረጋዊ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። አበባ አረጋዊ ካለፈው የለንደን ኦሊምፒክ በኋላ ዜግነቷን ቀይራ ለስዊድን መሮጥ ብትጀምርም የኢትዮጵያ ፍሬ መሆኗ አይካድም።

ሁለቱ አትሌቶች በአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ለአገራቸው በአንድ ላይ በመሮጥ የተለያዩ ድሎችን ቢያስመዘግቡም አሁን ግን የሚሮጡት የተለያየ ሰንደቅ ዓላማ ለማውለብለብ ነው። ቀድሞ የነበራቸው አንድነትና ትብብርም አሁን ላይ አይሰራም።

አበባ ባለፈው የውድድር ዓመት በርቀቱ ጎልታ የወጣችበትን ድል አስመዝግባለች። በተለይም የዳይመንድ ሊግ ውድድሮችን ጠራርጋ ከማሸነፏ በላይ የሞስኮው የዓለም ሻምፒዮና ላይ የርቀቱ ሻምፒዮን መሆኗ ከገንዘቤ በበለጠ ትኩረት እንዲሰጣት አድርጓል።

ገንዘቤ ደግሞ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ገና ከመጀመሪያው ያማረ ሆኖላታል። ይህም ባለፈው ቅዳሜ በቤት ውስጥ ሻምፒዮና የዓለምን ክብረወሰን በማሻሻል ማሸነፏ እንደ ምክንያት የሚወሰድ ነው።

አበባ የወቅቱ የአንድ ሺ አምስት መቶ ሜትር ሻምፒዮን ነች። ገንዘቤ ደግሞ የርቀቱ የቤት ውስጥ ባለ ክብረወሰን መሆኗን ከቀናት በፊት አሳይታለች። እነዚህ ሁለት እንቁዎች በአንድ የውድድር መድረክ ተፎካክረው የትኛዋ ምርጥ አትሌት እንደሆነች ለማየት የስፖርት ቤተሰቡ ጉጉት ነው። የሁለቱ አትሌቶች ፍልሚያም ጊዜ ሳይፈጅ ዛሬ ምሽት የምናይበት አጋጣሚ ተፈጥሯል።

አበባ በዛሬው ምሽት ውድድሯ የቀድሞ የአገሯን ልጅና የውድድር ባልደረባዋን ገንዘቤን በስዊድን ስቶክሆልም ታስተናግዳለች። የቤት ውስጥ የዓለምን ክብረወሰን 3፡55፡17 በሆነ ሰዓት የጨበጠችው ገንዘቤም ያለፈው ዓመት መጥፎ ትዝታዋን ለመካስ የዓለም ሻምፒዮን ጓደኛዋን ትገጥማለች።
aregawi abeba
የሁለቱ አትሌቶች ፍጥጫ በዛሬው ምሽት የሚከናወኑ ሌሎች ውድድሮችን አደብዝዘዋል ማለት ይቻላል። ምናልባትም እነዚህ አትሌቶች ከአስራ ስድስት ዓመት ወዲህ በርቀቱ ያልተመዘገበ ፈጣን ሰዓት ሊያስመዘግቡ እንደሚችሉ የስፖርቱ ተንታኞች እየተነበዩ ይገኛሉ።

አበባ በደጋፊዎቿና በአገሯ ላይ እንደመሮጧ መጠን የአሸናፊነት ግምት ቢሰጣትም ገንዘቤ ባለፈው ቅዳሜ የዓለም ክብረወሰን ያሻሻለ ብቃት ማሳየቷን ተከትሎ የዛሬ ምሽቱን ውድድር ማን እንደሚያሸንፍ መገመት አዳጋች ሆኗል።

ለዘገባው የመረጃ ምንጭ የሆነን የዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማህበራት ፌዴሬሽን ድረ -ገፅ ውድድሩን አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አበባ አረጋዊን አግኝቶ የተለመደውን «ምን አስበሻል?» የሚል ጥያቄ አንስቶላታል።
«ባለፈው የውድድር ዓመት ጥሩ ጊዜ አሳልፌያለሁ፤ አሁንም ጥሩ ልምምድ አድርጌያለሁ፤ የቀድሞው ብቃቴ አብሮኝ ነው፤ ከቻልኩኝ የዓለምን ክብረወሰን ለማሻሻል ሮጣለሁ» በማለት አበባ አረጋዊ መልሳለች።

አበባ የገንዘቤ ወቅታዊ ብቃት እቅዷን ሊያፋልስባት ይችል እንደሆን ተጠይቃም «ገንዘቤ ጥሩ ልምምድ አድርጋለች፤ በመልካም አቋም ላይም ትገኛለች፤ እኔም እንደዚያው፤ ስለዚህ አሸንፋታለሁ» በማለት አስተያየቷን ሰጥታለች።

አበባ አረጋዊ ባለፈው ዓመት በስቶክሆልም በሦስት ሺ ሜትር የዓለምን ክብረወሰን ለማስመዝገብ ሦስት ሰከንድ ያህል ተጠግታ ሳይሳካላት ቀርቷል። ይህ የሦስት ሺ ሜትር ክብረወሰን በመሰረት ደፋር የተያዘ መሆኑ ይታወሳል።


በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ የቴሌኮንፍረንስ ጥሪ ለመላው ኢትዮጵያውያን

$
0
0

ሸንጎ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይትና ገለጻ ለማድረግ የፊታችን እሁድ ፌብሩዋሪ 9 ቀን 2014 ቴሌኮንፈርንስ ጠርቶ ማንኛውም ስለድንበሩ ያገባኛል የሚል ኢትዮጵያዊ እንዲገኝ ጥሪውን አቅርቧል። የጥሪው ወረቀት የሚከተለው ነው፦
shengo forum

የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር «ኦሮሞዉን» ጎድቷል

$
0
0

- አማኑኤል ዘሰላም

የኢትዮጵያ ፈዴራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 46 «ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ የማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነዉ» ይላል። አንቀጽ 47 ደግሞ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሩፑብሊክ አባላት የሆኑቱን ክልሎች ይዘረዝራቸዋል። እነርሱም የትግራይ፣ የአፋር ፣ የአማራ፣ የሱማሌ፣ የቤኔሻንጉል/ጉሙዝ፣ የደቡብ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ፣ የጋምቤላ ሕዝቦች እና የሃረሪ ሕዝብ ክልሎች ናቸው።

የዚህን የፌደራል ክልልን በተመለከተ በክልሎች እየታዩ ያሉትን አንዳንድ ሁኔታዎች ለማሳየት እንሞክራለን። ከትልቁ ክልል ኦሮሚያ እንጀምር።

ኦሮሚያ ክልል ዉስጥ ሃያ ዞኖች አሉ። ሶስቱ «ልዩ ዞኖች» ይባላሉ። ናዝሬት/አዳማን ያካተተ፣ የአዳም ልዩ ዞን፣ ጂማን ያካተተው፣ የጂማ ልዩ ዞን እና የቡራዮ ልዩ ዞን ናቸው። በነዚህ ዞኖች የመጀመሪያ ቋንቋቸው አፋን ኦሮሞ የሆኑቱ ቁጥራቸው ከ45 በመቶ በታች ነዉ። በአዳማ 26%፣ በጂማ 39% እና በቡራዮ 44% ናቸው።
Oromia
በአሥራ ሶስቱ ሌሎች የኦሮሚያ ዞኖች አፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ቋንቋቸው የሆኑ ከ90 % በታች ናቸው። እነዚህም ምስራቅ ሸዋ ( 69%)፣ ጉጂ (77%) ፣ አርሲ ( 81%)፣ ሰሜን ሸዋ ( 82%)፣ ደቡብ ምስራቅ ሸዋ (84%)፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ (85%) ፣ ምእራብ አርሲ (87%)፣ ምስራቅ ወለጋ (88%) ፣ ምእራብ ሃረርጌ (89 %)፣ ኢሊባቡር (90%) ፣ ጂማ – የጅማ ከተማ አካባቢ ( 90%)፣ ባሌ (90%)፣ ቦረና (90%) ናቸው። እንግዲህ ከሃያ የኦሮሚያ ዞኖች፣ በአሥራ ስድስቱ፣ ምን ያህል አፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን በስፋት እንዳሉ እያየን ነዉ። በአራት የኦሮሚያ ዞኖች፣ በአፋን ኦሮሞ አፋቸዉን የፈቱ፣ ከዘጣና ሶስት በመቶ በላይ ናቸው። እነርሱም ምእራብ ወለጋ (97%) ፣ ምእራብ ሸዋ (93%)፣ ምስራቅ ሃረርጌ፣ (94%)፣ ቀለም ወለጋ ( 94%) ናቸው።

አሁን በሥራ ላይ እየተተገበረ ያለው የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ 33 «በክልሉ ዉስጥ ነዋሪ የሆኑና የክልሉን የሥራ ቋንቋ የሚያውቅ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በማንኛዉም የክልሉ መንግስታዊ ወይም ሕዝባዊ ሥራ ተመርጦ ወይም ተቀጥሮ የመስራት መብት አለዉ።» ይላል። አንቀጽ 5 ደግሞ « ኦሮምኛ የክልሉ መንግስት የሥራ ቋንቋ ይሆናል። የሚጻፈዉም በላቲን ፊደል ነው» ይላል።

74% የአዳማ፣ 61% የጂማ ከተማ ፣ 56% የቡራዩ ዞን፣ 31% የምስራቅ ሸዋ ዞን፣ 23% የጉጂ ዞን ፣ 25% የሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን፣ 23% የምእራብ አርሲ ዞን … ነዋሪዎች የመጀመሪያ ቋንቋቸው አፋን ኦሮሞ ባላመሆኑ፣ አፋን ኦሮሞ ካልተማሩ በቀር፣ የመመረጥ፣ በኦሮሚያ ክልል የመስራት መብት የላቸውም። ይህም አማርኛና ሌሎች ቋንቋዎች የሚናገሩ፣ በኦሮምያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንን እንደ ሁለተኛና ሶስተኛ ዜጋ እንዲቆጠሩ የሚያደርግ ነዉ። በብሄረሰብ መብት ስም የግልሰበ መብት እየተረገጠ ነዉ።

«ኦሮሚያ ፈርስት» የሚል እንቅስቃሴን የሚመራው ጃዋር ሞሃመድ፣ አንድ ወቅት «Ethiopians Out from Oromia» የሚል መፈክር ያሰማበትን ቪዲዮ ተመልክቻለሁ። ጃዋር በአጭሩ አነጋገር፣ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ እንደሆነችና ሌሎች «ኦሮሞ» ያልሆኑ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ እንግዶች፣ ኦሮሞዎች ሲፈቅዱላቸው ብቻ ሊኖሩ የሚችሉ እንደሆኑ ነው የነገረን። ይህ የጃዋር አባባል፣ ብዙዎችን እንዳስገረመ ተመልክቻለሁ። ነገር ግን አንድ የዘነጋነው ነገር ቢኖር፣ ይህ የጃዋር አባባል ፣ ጃዋር የፈጠረዉ ሳይሆን በኦሮሚያ በአሁኑ ሕግ መንግስት፣ በሰነድ የተቀመጠ እንደሆነ ነዉ።ይህ አይነቱን ዘረኛ የጃዋር አባባል፣ የኦሮሚያ ክልል «ሕግ» ይደግፈዋል።

የኦሮሚያ ክልል ሕገ መንግስት አንቀጽ ስምንትን ይመልከቱ። «የኦሮሞ ሕዝብ የክልሉ የበላይ ስልጣን ባለቤት ሲሆን ..» ሲል የኦሮሚያ ባለቤት «ኦሮሞው» ብቻ እንደሆነ ነው የተቀመጠው።

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ፖሊሲን ካየን ደግሞ፣ አዲስ አበባ አካባቢ ያሉ እንደ አዳማ/ናዝሬት ያሉ ቦታዎች ሕዝቡ ተቃዉሞ ስላስነሳ፣ በዚያ ተማሪዎች አማርኛም ከአፋን አፋን ኦሮሞ ጎን ለጎን እንዲማሩ ከመደረጉ በስተቀር፣ በኦሮሚያ የሚኖሩ ተማሪዎች አማርኛ እንዲማሩ አይደረግም። አማርኛ ማንበብና መጻፍ አይችሉም።

አንድ የግል ባለሃብት ከአዲስ አበባ ሄዶ አንድ ኩባንያ በአንድ የኦሮሚያ ከተማ ይመሰርታል። ሰራተኞች ቀጥሮ ያሰራል። ሰራተኞቹ ስራቸዉን በተመለከተ፣ ሪፖርት ማቅርብ ሲጠበቅባቸው ሪፖርት ሳያቀርቡ ይቀራሉ። አለቃቸው ያስጠራቸዉና ይጠይቃቸዋል። ሪፖርታቸውን በቃል ያቀርቡለታል። «እሺ በፋይል እንዲቀመጥ በጽሁፍ አምጡልኝ» ሲላቸው፣ ማንገራገር ጀመሩ። «ጌታዬ እኛ አማርኛ መጻፍ አንችልም። በቁቤ እንጻፈዉና ከፈለጉ ያስተርጉሙት፤ ወይም እኛ አስተርጉመን እንመጣለን» ይሉታል። ሰዎዬዉ ባንድ በኩል በጣም ተናደደ፣ በሌላ በኩል አዘነ። ቢዝነስ ነዉና፣ ለስራው ብቃት ከሌላቸው ሰራተኞቹ መባረር አለባቸው።

አማርኛን የመጥላት የኦህደድ እና ኦነግ ፖለቲካ ፣ ዜጎች አፋን ኦሮሞን ያዉም በቁቤ ብቻ እንዲማሩ በማድረግ፣ ትልቅ የኢኮኖሚ ጉዳት በ«ኦሮሞዎች» በትግራይ ከአንደኛ ክፍል ጀመሮ ከትግሪኛ ጎን አማርኛ እንዲማሩ ይደረጋል።

የኦሕደድ ባለስልጣናት እነ አባ ዱላ ገመዳ፣ ኩማ ደመቅሳ የመሳሰሉት ልጆቻቸዉን የሚያስተምሩት በአዲስ አበባ ሃሪፍ ተምህርት ቤቶች ነዉ። ሃብታም የሆኑና አቅሙ ያላቸው ልጆቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እየላኩ ያስተምራሉ። ለምን ቁቤ ብቻ ተምረው ልጆቻቸው የትም እንደማይደርሱ ስለሚያወቁ።

የግል ኢንቨስተሮች የሥራ ቋንቋቸው በኦሮሚያም ሳይቀር በብዛት አማርኛ ነዉ። በናዝሬት፣ በጂማ በመሳሰሉት ቦታዎች ሂዱ፣ የንግድ ተቋማት፣ የግል መስሪያቤቶች .. የሚጠቀሙት አማርኛን ነዉ። ከክልል መንግስት ጋር አንዳንድ ደብዳቤዎች መላላክ ካስፈለገ ፣ የክልሉን የአፋን ኦሮሞ ብቻ ፖሊስ ሕግን ለማክበር ፣ ተርጓሚ ይቀጥራሉ።

በኢትዮጵያ ካሉ 9 ክልሎች በአራቱ (አማራዉ፣ ደቡብ፣ ጋምቤላና ቤኔሻንጉል ጉሙዝ) ክልሎች፣ እንዲሁም በአገሪቷ መዲና አዲስ አበባ፣ በድሬደዋ የሥራ ቋንቋ አማርኛ ነው። የፌደራልም ቋንቋ አማርኛ ነዉ።

በመሆኑም ኦሮሚያ ያለው የቁቤ ትዉልድ፣ በፌደራል መንግስት ዉስጥ ተቀጥሮ የመስራት አቅሙ ዜሮ ነዉ። እንደ ባህር ዳር፣ አዋሳ፣ ድሬደዋ፣ አዲስ አበባ በመሳሰሉ ታላላቅ ከተሞች ለመኖርና ለመስራት፣ ለመቀጠር በጣም ይቸገራል። በአጭሩ በኢኮኖሚ እንያድጉና እንዳይሻሻሉ ትልቅ ማነቆ ነው እየሆነባቸው ያለዉ ይህ የኦሮሚያ ክልል አሰራር። በሌሎቹ ክልል ካሉ ጋር ሲወዳደሩ ወደኋላ ቀርተዋል። ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የኦነግ መሪዎች ልጆቻቸው በበርሊን ሚኒሴቶች …በመሳሰሉ ቦታዎች ናቸዉ። አማርኛም ባያወቁ፣ እንግሊዘኛ እስካወቁ ድረስ ችግር አያጋጥማቸዉም። የኦህደድ መሪዎች ልጆቻቸውን ሃሪፍ ትምህርት ቤቶች ነዉ በአዲስ አበባ የሚያተምሩት። ድሃዉና ምስኪኑ የኦርሚያ ተማሪ ግን፣ አጥር ታጥሮበት፣ በአጉል የኦሮሞ ብሄረተኘንት ስም እንዲተበተብ ተደርጎ ጉዳት እየደረሰብት ነዉ።

ይህ በኦሮሚያ የሚኖረው ወገናችን በኢኮኖሚ፣ በትምህርት ፖሊሲ ረገድ እየደረሰበት ካለው ግፍ በተጨማሪም፣ ኦነግ እየተባሉ በሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እየታሰሩና እየተሰቃዩ ናቸው። ሕወሃት/ኢሃዴግ በአንድ በኩል እነሌንጮን ቀንደኛ ኦነጎችን እያባበለ፣ በሌላ በኩል የነሌኝቾ ደጋፊ ናችሁ እያሉ ሰላማዊ ዜጎችን ያስራል።

ታዲያ መፍትሄዊ ምንድን ነዉ ? አራት መፍትሄዎች አሉ፡

1. ኢትዮጵያዉያን አፋቸዉን በየትኛው ቋንቋ ነዉ የፈቱት የሚለዉን ጥያቄ ብንጠይቅ ፣ በአንደኝነት የሚቀመጠዉ ኦሮምኛ ነዉ። በበርካታ ዞኖች ከዘጠና በመቶ በላይ ኦሮምኛ የሚነገርባቸው ቦታዎች አሉ። 33.8 % የሚሆነው ሕዝባችን አንደኛ ቋንቋዉ አፋን ኦሮሞ ነዉ። 29.36% የሚሆነው ህዝብ አማርኛ አንደኛ ቋንቋዉ ነዉ። ሁለቱ ቋንቋዎች እንደ አንደኛ ቋንቋ የሚናገሩ 63.2% ይደርሳሉ። በመሆኑም ኦሮሞኛ ከአማርኛ ጎን የፌደራል ቋንቋ ቢሆን ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል።

2. በሁሉም ክልሎችና ወረዳዎች፣ በአካባቢዉ ከሚነገረው ቋንቋ ጎን ለጎን፣ ተማሪዎች አማርኛ እንዲማሩ መደረግ አለበት። አማርኛ እንደ አንደኛ ቋንቋ 29.3% የሚሆነው ሕዝብ ይናገረዋል። እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ደግሞ፣ ከ30፣ 40 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሊናገረው ይችላል ብዬ አስባለሁ።በመሆኑም አማርኛ ማወቅ ጥቅም አለው። ቋንቋ በአጠቃላይ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። አማርኛን መማር ኦሮሞኛን አይጎዳም። የኦሮሞ መሪ ነን የሚሉ ፖለቲከኞች፣ ለራሳቸው ልጆች እንዳሰቡት፣ ለተቀረዉም የኦሮሞ ልጅ ሊያስቡ ይገባል ባይ ነኝ።

3. የኦሮሚያ ክልል መንግስት አማርኛን ከኦሮሞኛ ጎን የሥራ ቋንቋ ማድረግ አለበት። ኦሮሞኛ የማይናገር በክልሉ አስተዳደር ዉስጥ የመስራት መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። በኦሮሚያ 95% ነዋሪዉ ኦሮሞኛ የሚናገር ቢሆን፣ እሺ አንድ ነገር ነዉ። ግን ከ 15% በመቶ በላይ ሕዝብ አንደኛ ቋንቋም ኦሮሞኛ ባልሆነበት፣ «አፋን ኦሮሞ ብቻ ወይንም ሞት» ማለት ትልቅ ስህተት ነዉ። በክልሉ ዋና ከተማ አዳማ/ናዝሬት እንኳን ፣ አንድ አራተኛ ሕዝብ ብቻ ነው ኦሮሞኛ የሚናገረው።

4. ናዝሬት/አዳም እና ጂማ የመሳሰሉ እንደ አዲስ አበባና ድሬደዋ፣ ለጊዜዉ ቻርተር ከተማ ቢሆኑ መልካም ነዉ። (ለዘለኬታዉ፣ ለሁሉም በሚበጅ፣ የተለያዩ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባና በተጠና መልኩ ፣ፌደራል አወቃቀሩ እንደገና በአዲስ የሚዋቀርበትን ሁኔታ በመፈለግ ለብዙ ችግሮች መፍቴሄ ማግኘት ይቻላል)

ከላይ የዘረዘርኳቸዉ አሃዞች በኦፊሴል ከተመዘገበዉ የኢትይጵፕያ ሕዝብ ቆጠራ ሪፖርት ነዉ። በሚቀጥለው ጊዜ የቤኔሻንጉል ጉምዝ እና ሃረሪ ክልሎችን እንመለከታለን።

ገንዘቤ ዲባባ በ3000 ሺህ ሜትር ስቶክሆልም ላይ ዛሬ ያሸነፈችበት ቪድዮ

[የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ] የፍርድ ቤቱ ውሎ ይህን ይመስል ነበር –ከቤዛ ለኩሉ ሰንበት ት/ቤት ሕዝብ ግንኙነት

$
0
0

debereselam Minnesota
ከሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ የቤዛ ኩሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ለሕዝብ ያወጣው መረጃ ለዘ-ሐበሻ ደርሷል። የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሕዝብ ግንኙነት ያሰራጨው ዜና እንደወረደ ይኸው፦

የቤተክርስቲያን ውሎ በጲላጦስ አደባባይ

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን

ዛሬ ቤተክርስቲያናችን በጲላጦስ አደባባይ ላይ እንደምትቆም ስላወቃቸሁ ግማሾቻችሁ በአካል በመገኘት፤ አብዛኞቻችሁ ድግሞ ካላችሁበት ቦታ “እለት እለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሃሳብ ነው” እንዳለ ቅዱሱ ሐዋርያ (ቆሮ ፲፩፡፳፰) ( በፀሎትና እንባ ቀኑን ለቤተክርስቲያን ድል የሆን ዘንድ ፀልያችኋል አልቅሳችኋል።

የእግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን ውሳኔው ይህን ይመስል ነበር……
፬ቱ የቦርድ አባላት (አቶ ጥበቡ፤ ቀስስ አዲስ፤ ወ/ሮ ደብረ ወርቅና አቶ አዳም) የቤተክርስቲያን አስተዳደሩን የከሰሱት በነዚህ ነጥቦች ዙሪያ ነበር…
1- – የሕዝቡን ውሳኔ አንቀበልም አሉ
2-ያለ ሊቀ መንበርና ም/ሊመንበር ፍቃድ ያደረጉት የ January 23, 2014 ስብሰባ ሕጋዊ አይደለም
3- አቶ ጥበቡን ከሊቀመንበርነት አወረዱ
እነሱ ዳኛዋ እንድትወስን የፈለጉት….
1- በ ጃንወሪ 23 የተጠራው የቦርድ ስብሰባ ኢ-ሕጋዊ አይደለም ዳኛዋ እንድትል
2- ምንም አይነት ስብሰባ እስከ ፌብ 23 ቦርዱ እንዳያደርግ፡ ለጊዜው እንዲታገድ (Temporary injunction)
3- ፍራቻቸው– ብር ያዘዋውርሉ፡

ይህንን ሁሉ ክስ ዳኛዋ ከአዳመጠች በኋላ ያቀረቡትን ሁሉ ክስ ውድቅ አድርጋለች። ስለዚህ በ ጃንዋሪ 23 የተደረገውን የቦርድ ስበሰባ ሕጋዊነቱን ዳኛዋ አስድቃለች። ነገር ግን እንደ መተዳደሪያ ደንቡ መሠረት (by law) ጠቅላላ ጉባዔ ሲጠራ የአቶ ጥበቡን ከሥልጣን መውረድና የአቶ ይመርን ሊቀመንበርነት ጠቅላላ ጉባዔው ያፀድቃል። እሰከዛ ድረስ አቶ ይመር ሕጋዊው ሊቀመንበር ናቸው። አቶ ጥበቡ በቦርድ ስብሰባ መሳተፍ አይችሉም። ባንኩኑም ቦርዱ unfreeze አድርጎ መደበኛ አገልግሎቱን ይቀጥላል።
-የ፬ቱ ካሳሾች ጠበቃ፤ ቀሲስ አዲስ ወደፊት የሚጠራውን ስብሰባ እንዲመራ ጥያቄ (recommendation) አቅርበዋል። ቦርዱም ለስብሰባ ሲቀመጥ ይወያይበታል።
የፌብ 23 ጠቅላላ ጉባዔ ይኑር አይኑር ወይንም ወደፊት ይራዘም የሚወስኑት ቦርዱ ነው እንጂ አቶ ጥበቡ በቦርድ ስብሰባ ምንም ተሳትፎ ከአሁን በኋላ አይኖራቸውም።
- March 10 2014 የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተይዟል

እንግዲህ ቅድስት ቤተክርስቲያን በራሷ ልጆች ተጎትታ በዛሬው አማኑኤል ቀን (ጥር 28. 2006 ዓ/ም) የፍርድ ቤት ውሎዋ በአጭሩ ይህን ይመስል ነበር።
በእግዚአብሔርም ክብርም ተስፋ እንመካለን። የህም ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን በመከራችን ደግሞ እንመካለን በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። (ሮሜ ፭፡፪-፭)

ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥
2ቆላስይስ 3፡23

ብሄሬ ኢትዮጵያዊነት ነዉ

$
0
0

- ግርማ ካሳ

ከበደ ካሳ የሚባሉ አፍቃሪ ኢሕአዴግ ግለሰብ “አንዳንድ ሰዎች «ብሄር ..?» ተብለው ሲጠየቁ «ኢትዮጵያዊ!!!…» እያሉ የሚመልሱት፣ የራሳቸዉን ማንነት የኢትዮጵያ ማንነት አድርገው ያስቀመጡና በራሳቸው ማንነት የሌሎቹን ለመጨፍለቅ የሚያልሙ – የቅዠት ታንኳ ቀዛፊዎች ናቸው…. ተዛብታችሁ ሌላንም ለማዛባት ለምትፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት እንጂ ብሄር አይደልም። ኢትዮጵያ ሃገር እንጂ የአንድ ሕብረተሰብ ክፍል መለያ አይደለም።” የሚል አባባል ፌስቡክ ላይ ለጥፈው አነበብኩ።
በአንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስቱ እንዲህ ይላል ፡
UDJ - Ethiopia
“በዚህ ሕገ መንግስት ዉስጥ «ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝብ» ማለት ከዚህ ቀጥሎ የተገለጸዉን ባህርይ የሚያሳይ ማህበረሰብ ነዉ። ሰፋ ያላ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምዶች ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ሕልዉና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የስነ-ልቦና አንድነት ያላቸውና በአብዛኛዉ በተያያዘ መልክአ ምድር የሚኖሩ ናቸው»

እንግዲህ እዚህ ላይ እናስተዉል። ለብሄር የተሰጠው ትርጉምና ለብሄረሰብ የተሰጠው ትርጉም አንድ አይነት ነዉ። በአጭሩ ብሄር ማለት ብሄረሰብ ማለት ነዉ በሕገ መንግስቱ መሰረት።

ብሄር በእንግሊዘኛ ኔሽንስ ማለት ነዉ። «ዩናይትድ ኔሽንስ» ስንል የተባበሩት መንግስታት (የተባባሩት አገሮች ማለታችን ነዉ) ። እንደሚገባኝ ኢትዮጵያ እንጂ፣ ኦሮሞ፣ ወይንም፣ ትግሬ ወይንም ወላይታ የተባበሩት መንግስታት አባል አይደሉም።
«ብሄር» የሚለዉን ቃል የመጀመሪያ አመጣጥ ስንመለከት ፣ ከግእዝ የተወሰደ እንደሆነ እንረዳለን። ትርጉሙም በግእዝ አገር ማለት ነዉ።

ስለዚህ ኢሕአዴግን እና ኦነግ በሕገ መንግስቱ ብሄር የሚለዉን ቃል ያኔ የወሸቁት፣ ኢትዮጵያን እንደ አንዲት አገር ሳይሆን የተለያዩ የአገሮች ስብሰብ እንደሆነች ለማሳየት፣ በፈለጉ ጊዜ ደግሞ ከኢትዮጵያ ለመለየት አማራጭ እንዲኖራቸው ከመፈለግ የተነሳ ነዉ።
ፕሮፌሰር ተኮላ ሃጎስ ደግሞ ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ የሚለውን ለምን ሕገ መንግስቱ ዉስጥ እንደገባም ሲጽፉ የሚከተለዉን ነበር ያሉት፡

“The phrase “the nations, nationalities and peoples” thus found in the Ethiopian Constitution is a legacy from the writings of immature and juvenile diatribe of badly educated and socially disfranchised and radicalized students of Haile Selassie I University of the 1970s. It is the ersatz voice of Meles Zenawi forcing himself through the 1995 Constitution on the People of Ethiopia his narrow and ignoramus ideas on the history of Ethiopia and the process of nation building”

ስለዚህ «ብሄርህ ምንድን ነዉ ?» ተብሎ አንድ ሰው ሲጠየቅ «ኢትዮጵያዊነት» ብሎ ከመለሰ፣ በትክክለኛዉ የግእዝ አተርጓጎም እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ ብሄር የሚለው ቃል ያለው አጠቃቀም አንጻር፣ ትክክለኛ መልስ ነዉ።
«ብሄረሰብህስ ምንድን ነዉ ? » የሚል ጥያቄ ቢነሳስ ?

አንድ መርሳት የሌለብን ነገር አለ። አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ የተደባለቀ ነዉ። ሰሜን ጎንደና ሰሜን ወሎ ከሄዳችሁ ትግሪኛ ተናጋሪዉና አማርኛ ተናጋሪዉ ተደበላልቋል። ኦሮሚያ ዉስጥ በሸዋ፣ በሰሜን እና በምስራቅ ወለጋ..፣ አማራዉ ክልል ደግሞ በወሎ ፣ ኦሮሞኛ ተናጋሪው ከአማርኛ ተናጋሪው ተደባልቋል። በምስራቅ ሃረርጌና በባሌ ደግሞ ሶማሌዉና ኦሮሞዉ የተደባለቀበትም ሁኔታ አለ። በደቡብ ክልል ከሄድን፣ ወላይታዉ ከሲዳማው፣ ከንባታዉ ከሃዲያዉ …ሁሉም ተበራርዟል። ስለዚህ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን የብዙ ብሄረሰቦች ድብልቅ ናቸው። በመሆኑም «ብሄረሰብህ ምንድን ነዉ?» ተብለው ሲጠየቁ እዚም እዚያም በመሆናቸው፣ ለመመለስ ይቸግራቸዋል። ስለዚህ በአጭሩ በብሄረሰባቸው ወይንም ዘራቸው ሳይሆን በኢትዮጵያዊነታቸው መለየትን ይመርጣሉ። ከነዚህ ሰዎች መካከል አንዱ እኔ ነኝ።
አቶ ከበደ፣ ኢትዮጵያዊያን፣ ብሄራችን ኢትዮጵያዊነት ነው ማለታቸው፣ የሌሎችን ማንነት ለመጨፍለቅ እንደመሞከር አድርገውም ወስደዉታል። አንድ ሰው «ኦሮሞ ነኝ፣ ትግሬ ነኝ ወዘተረፈ » የማለት መብቱ ከተከበረለት፣ ሌላው «አይ እኔ በዘሬ መለየት አልፈልግም፣ በኢትዮጵያዊነቴ ነዉ መለየት የምፈልገው » ካለ የርሱስ መብት ለምን አይከበርለትም ? ኦሮሞ፣ ወይም ትግሬ ፣ ወይም አማራ ያለመባል መብቱ መጠበቅ የለበትምን?

በኢሕአዴግ መንግስት፣ ይሄ መሰረታዊ መብት እየተጠበቀ አይደለም። እያንዳንዱ ዜጋ፣ እነርሱ ብሄር ብሄረሰብ የሚሉት አንዱ የዘር ሳጥን ዉስጥ መግባት አለበት። ያ ካልሆነ መታወቂያ እንኳ ማግኘት አይቻልም።

እንግዲህ ይሄንን ነዉ የምንቃወመው። «ለአገራችን የሚያዋጣዉ ዘር ላይ ማተኮር ሳይሆን፣ሥራ ላይ ማተኮር ነዉ። መመዘን ያለብን በዘራችን ሳይሆን በስራችን መሆን አለበት» እያልን ነዉ።
አፋን ኦሮሞ፣ ትግሪኛ፣ ጉራጌኛ፣ ሃምባሻ፣ ቆጮ ….በተለያዩ የአገራችን ግዛቶች ያሉ የተለያዩ ባህሎች፣ ቋንቋዎችን ፣ ምግቦች …ሁሉም «ኢትዮጵያዊነት» ናቸው። ሁሉም የኢትዮጵያ መገለጫዎች ናቸው። ኢትዮጵያ አንድ ወጥ አይደለችም። የተለያዩ ባህሎችን ፣ ቋንቋዎች፣ በአጭሩ የተለያዩ ብሄረሰቦች ያሉባት አገር ናት። ቢራቢሮዎችና አበባዎች የተለያዩ ቀለማቶቻቸው ዉበታቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ዉበቷ ብሄረሰቦቿ ናቸው።

ግርማ ጌታቸዉ ካሳ
ዘብሄረ ኢትዮጵያ ( የዶር ፍቅሬ ቶሎሳን አባባል ልዋስና)

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live