Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የመቀሌው ትዕይንት –ከመሳይ መኮንን

$
0
0
የመቀሌው ትዕይንት መቀሌ ዛሬ የሰሜን ኮርያዋን ፒዮንጊያንግን መስላ ውላለች። እንደዚያ የመሰለኝ የህወሀት ዓርማ ከሰሜን ኮርያው ጋር ተቀራራቢነት ስላለው ብቻ ይሆን? የሟቹ መለስ ዜናዊና የደብረጺዮን ፎቶግራፎች በቲሸርት ላይ ታትመው መቀሌን ያጥለቀለቁበት ሁኔታም የሰሜን ኮርያው ሟቸ መሪ ኪም ጆንግ ኢልና አሁን በስልጣን ላይ ያለው ልጃቸው ኪም ጆንግ ኡን ፎቶግራፋቸውን ሰሜን ኮርያውያን እንደማህተብ አንገታቸው ላይ ሳይቀር እንዲያንጠለጥሉ የተደረጉበትን […]

በጎንደር በተጠራ የሰላም ኮንፍረንስ ላይ የአማራ ወጣቶች ጀነራል አሳምነው ጽጌ እንዲያስታጥቋቸው ጠየቁ |ጀነራሉ ለTplf አገልጋይ የሆነን በየትኛውም ደረጃ ላይ የሚገኝ ኮሚቴን እጁን እንቆርጠዋለን አሉ

$
0
0
በጭልጋ አካባቢ አሁንም ግጭቱ ባልበረደበት ሰዓት ዛሬ በጎንደር እና በአካባቢዋ ተከስቶ የነበረውን ችግር ወደሌላ አካባቢ እንዳይዛመት ለማድረግ እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በጎንደር ከተማ የሰላም ኮንፈርንስ ተካሄደ:: በሰላም ኮንፈርንሱ የአማራ ክልል የሰላም ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴል ጀኔራል አሳምነው ጽጌን ጨምሮ ከሁለቱ ወገኖች የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የገኙ […]

አቶ ያሬድ ዘሪሁንና አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ያፈሩት ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ለፍርድ ቤት በዝርዝር ቀረበ

$
0
0
በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ዘሪሁን ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ማፍራታቸውን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤት ገለፀ፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው አቶ ያሬድ በስማቸው የተመዘገቡ ቤቶችና ድርጅቶች እንዳላቸውና ለሚስታቸው አባት ውክልና ሰጥተው እያሰሩ መሆኑን ፖሊስ ተናግሯል፡፡ እንዲሁም በሚስታቸው እናት ስም የተመዘገበ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ማከራየት ንግድና በሚስታቸው ወ/ሮ አዳነች ተሰማ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ የአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ወረዳዎች የፓርቲ መዋቅር ጊዜያዊ አደራጆች ዛሬ እሁድ ህዳር 30 ቀን 2011ዓ.ም. የመጀመሪያ ስብሰባውን የድርጅቱ አመራሮች በተገኙበት በራስ ሆቴል አካሄደ:: በስብሰባው ላይ ከአዲስ አበባ ሁሉም የምርጫ ወረዳዎች የተወጣጡ 120 ጊዜያዊ አደራጆች የተገኙ ሲሆን የንቅናቄው ሊቀ መንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የንቅናቄው ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ […]

«የቅማንቶች ጥያቄ» ነበር. . . |አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0
«የቅማንት ኮሚቴ» ነን የሚሉ የወያኔን ባለ አምባሻ ባንዲራ እያውለበለቡ በፋሽስት ወያኔ ዘመን ሕግና ስርዓት እንዳለ አድርገው በመቁጠር «በሕገመንግሥቱ መሰረት» እያሉ «ራስ በራስ የማስተዳደር ጥያቄ» ያሉትን የሕወሓት አጀንዳ ይዘው አብረዋቸው ከኖሩት፤ አባትና ልጅ፤ እናትና ልጅ እንዲሁም ቤተሰብ ከሆኑት ከአማራ ወገናቸው ጋር ግጭት ውስጥ ሲገቡ ስመለከት ግርም ይለኛል። ያለፉት ሀያ ሰባት የፋሽስት ወያኔ የአፓርታይድ አገዛዝ ዓመታት በባህላቸን […]

ለአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አጭር ማስታወሻ

$
0
0
ይነጋል በላቸው (yinegal3@gmail.com) ከኢሕዲን ወዲህ ባሉት ስሞች ብዙም ደስተኛ አለመሆኔን በዚህ አጋጣሚ ብገልጽ ደስ ይለኛል፡፡ ያ ስም ደስ ይለኝ የነበረውም ሕወሓት በሰጠው የሽፋንነት ተልእኮው ሣይሆን ስያሜው ኢትዮጵያን በመያዙ ነበር፡፡ “ኢትዮጵያ” ሲባል መቼም ስሜትን መኮርኮሩ አይቀርም፡፡ አሁን ባለው ስሙ ደግሞ በጭራሽ አልስማማም፡፡ አማራ ብሎ ዴሞክራሲያዊ ፣ ኦሮሞ ብሎ ዴሞክራሲያዊ፣ ከምባታና ሃዲያ ብሎ ዴሞክራሲያዊ…. የሚታሰብ አይመስለኝም፡፡ ስሙ […]

ፍርድ ቤቱ በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የቀረበውን የሽብር ክስ ውድቅ አደረገው

$
0
0
የኦነግን አቀባበል ምክንያት በማድረግ በቡራዩና አካባቢው ተከስቶ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የቀረበውን የሽብር ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አደረገው፡፡ በመሆኑም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የግድያ ወንጀል ክስ ሊመሰረት ነው። በከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎች በዛሬው እለት 17 ያህል ተጠርጣሪዎች የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የቀረበባቸው ክስ የሽብር ወንጀልን አያሟላም በማለት በግድያ ወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው ውሳኔ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
-• ከምርጫ 97 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም የሚታወቁት የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባሏ አና ጎሜዝ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አጭር የጽሁፍ መል ዕክት በትዊተር ገጻቸው አስተላለፉ:: ወ/ሮ አና ጎሜዝ የጠ/ሚር አብይ አህመድ ከቀድሞው የእንግሊዝ ጠ/ሚር ቶኒ ብሌር ጋር የጀመሩትን ግንኙነት ጥሩ ስላልሆነ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል ብለዋል:: “ቶኒ ብሌር ውሸታም እንዲሁም የጨቋኙ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ደጋፊ ነው” […]

Hiber Radio: ብ/ል ጄኔራል አሳምነው የሕወሓት ተላላኪዎችን አስጠነቀቁ |እነ ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ጨምሮ በከፍተኛ ዝርፊያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ የሕወሓት ጄኔራሎች ይጠየቁ ተባለ

$
0
0
የሕብር ሬዲዮ ሕዳር 30 ቀን 2011 ፕሮግራም የሕወሓት ጦርነት አማራ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አለመሆኑን ከፍተኛ የሰራዊቱ መኮንን የነበሩ ገለጹ (ቀሪውን ያድምጡት) የተጀመረው ሌቦችና ከፍተኛ የሰበዓዊ መብት የጣሱትን ለፍርድ ማቅረብ ከቆመ ዲሞክራሲ ስርዓት አይታሰብም ይላሉ እንዴት?(ያድምጡት) ለጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ ህዝባዊ ጥሪ ጆሮ ዳባ ልብስ ያለው ታዋቂ አትሌት መከራዎቹ ሲዳሰሱ (ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም ዜናዎቻችን ብ/ል ጄኔራል አሳምነው […]

ሕወሓት የትግራይን ሕዝብ እንዲጫወትበት አንፍቀድ!!

$
0
0
ከዘምዘም ከሁለት አስርት አመታት በፊት በዝሆኖቹ ጠብ እና በጥቂት አጋፋሪዎች ኢትዮጲያ እና ኤርትራ የሚያቋስል ጠብ ተጨጭረው ብዙዎች ሲረግፉ እንደ ህዝብ የምንወዳቸውን አጥተን፣ እንደ ሀገር በኢኮኖሚ ትስስር ተጎድተን፣ እንደ አህጉር ደግሞ የምስራቅ አፍሪካ(በተለይ ደግሞ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ) የጦርነት መጠቋቆሚያ ሆነን ታሪካችን ተጽፏል። የኢትዮጲያ እና የኤርትራ እንካሰላምቲያ ሲጀመር አካባቢ እንደዋዛ የዝሆኖች ጠብ ነው በራሱ ጊዜ ይበርዳል ተብሎ […]

በትግራይ በሶማሊላንድ በኩል የነዳጅ ኮንትሮባንድ ንግድ ተጧጡፏል |የመሐል ሃገር በነዳጅ እጦት እየተንገላታ ነው

$
0
0
በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች በተከተሰተው የነዳጅ እጥረት የንግድ እንቅስቃሴውን እያዳከመው መሆኑ ተገለጸ:: በነዳጅ አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት በየጊዜው የነዳጅ እጥረቱ እየጨመረ መምጣቱን የነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች ቢገልጹም መንግስት ግን ነዳጅ በህገወጥ መንገድ ከአገር እንዲወጣ እየተደረገ በመሆኑ ለእጥረቱ መንስኤ መሆኑን ገልጿል:: መንግስት በአሁኑ ወቅት በቂ የሆነ ነዳጅ ወደ አገር ውስጥ በማስገባትና ለኩባንያዎቹ በፍትሃዊነት እንዲዳረስ እያደረገ መሆኑን የማዕድን፣ ነዳጅና […]

በሶማሊያው ፕሬዝዳንት ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ ሆነ

$
0
0
በሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ላይ በሃገሪቱ ፓርላማ አባላት ላይ ከስልጣናቸው እሰከመባረር የሚያደርሰው በቂ የፓርላማው አባላትን ድጋፍ ባለማግኘቱ ውድቅ ተደረገ። እሁድ ዕለት በሃገሪቱ ሕግ አውጪ ምክር ቤት አባላት በፕሬዝዳንቱ ላይ የቀረበው እንዲከሰሱ የሚጠይቀው የውሳኔ ሃሳብ አስፈላጊ ቁጥር ባላቸው የምክር ቤቱ አባላት ድጋፍ ማግኘት አልቻለም። ከሶማሊያ ፓርላማ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው መጀመሪያ ላይ በፕሬዝዳንቱ ላይ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
  የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መዳረሻ በመሆኗ ምክንያት የአፍሪካ መዲና በመባል የምትታወቀውን አዲስ አበባ፣ በእጅጉ ያዘምናል የተባለ ፕሮጀክት ቀረፃ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡ ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ‹‹እጅግ አስደናቂ›› በመባል የተወደሰ ፕሮጀክት፣ በተለይ ለቱሪስቶችና ለነዋሪዎች ምቹ የሆነች አዲስ አበባን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ከሚሆኑት መካከል የሽቦ […]

ጀዋር መሐመድ ስለመቀሌው ሰልፍ የሰጠው ያልተጠበቀ ምላሽ

$
0
0
ጀዋር መሐመድ ስለመቀሌው ሰልፍ የሰጠው ያልተጠበቀ ምላሽ

Video: የዶ/ር አብይ አህመድ ቆፍጠን ያለ የዛሬ መልዕክት –“ግፍ ሠርቶ መደበቅ ሰርቆ መንደላቀቅ አይቻልም”

$
0
0
የዶ/ር አብይ አህመድ ቆፍጠን ያለ የዛሬ መልዕክት – “ግፍ ሠርቶ መደበቅ ሰርቆ መንደላቀቅ አይቻልም”

የአፋር ክልልን እንደ አዲስ ማደራጀት፥

$
0
0
ከአካደር ኢብራሂም የአፋር ክልልን ከምስረታው ጀምሮ የሚያስተዳደረው የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ‘’አብደፓ’’ ከብዙ ሽኩቻና ትግል በኃላ 7ተኛ መደበኛ ጉባኤዉን ነባር የተባሉ አመራሮቹን በማሰናበት አጠናቋል። ላለፉት 27 አመታት ህዝብን ያሰቃዩ በ1983 ዓ.ም በህወሀት ጫካ ውስጥ የተደራጁ ነባር የፓርቲው መሪዎች ከፍተኛ የሆነ የመሪዎች ውድቀት እንዳለባቸው ቀደም ስል በአዲስ አበባ ላይ እርስ በእርስ ከተገማገሙ በኃላ ተነግሮ ነበረ። ከጉባኤ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የአቶ ዮሐንስ ተፈራ ልጅ አፋር ክልል ተገኘ። ትናንት በተመለከትነው ዶክመንተሪ ፊልም ከተጠቂዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ተፈራ ልጃቸው አቤል የት እንዳለ እንደማያውቁ በሀዘንና በምሬት እምባ እየተናነቃቸው ስለ ልጃቸው መጥፋት በተሰበረ ልብ ነግረውን ነበር። የጠፋው አቤል ዮሐንስ፣ የተሳቢ ሾፌር ሲሆን ትናንት ማታ እንደ ማንኛውም ሰው በአጋጣሚ አፋር ክልል አፍዴራ ላይ ዶክመንተሪ ፊልሙን ያያል። የሚያየውን ማመን […]

በአዲሱ የመከላከያ ሰራዊት መዋቅር ከአሁን ቀደም 6 የነበረው የእዝ ብዛት ወደ 4 እንዲቀነስ ተደረገ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) ዶ/ር አብይ አህመድ በመከላከያ ውስጥ የጀመሩትን የማሻሻል ያሉትን እርምጃ ቀጥለዋል:: ዛሬ በተደረገው የመከላከያ ሰራዊት መዋቅር ማሻሻያ ከአሁን ቀደም 6 የነበረው የእዝ ብዛት ወደ 4 እንዲቀነስ ተደረገ:: በዚህ መሰረት 4ቱ እዞች የምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ደቡብና ሰሜን መሆናቸውን የልዩ ዘመቻ አዛዥ ሌቴናል ጄኔራል ሞላ ኃይለማርያም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል:: ሌቴናል ጄኔራል ሞላ ኃይለማርያም በመግለጫቸው የባህር ሀይልን […]

ተመድ ለኢትዮጵያ ተረጂዎች 1.2 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል አለ

$
0
0
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ዛሬ ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ በመጪው የፈረንጆች አመት 2019 ወደ8 ሚሊዮን ያህል ዜጎች በተረጂነት እንደሚቀጥሉ አስታውቆ ለዚህ ስራውም 1.2 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገለፀ፡፡ የ2019 እ.ኤ.አ. እቅዱን በተመለከተ በድርጅቱ የአስቸኳይ እርዳታ አስተባባሪ ማርክ ሎውኮክ ሲናገሩ ‹‹ከየመን የበለጠ ከፍተኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሶሪያ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያና ደቡብ ሱዳን ናቸው›› ብለዋል፡፡ […]

–የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ሀሙስ ሶማሊያ ገቡ፡፡

$
0
0
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር ይህንን አገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ከፈጠረች ወዲህ የታየ አዲስ ክስተት መሆኑን አስረድቷል፡፡ ፕሬዚደንት ኢሳያስ ዛሬ ጠዋት ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ ከደረሱ በኋላ በቀጥታ ወደሶማሊያው ፕሬዚደንት ፅህፈት ቤት ማምራታቸውን የጠቆመው ሮይተርስ በከተማው ጥብቅ የፀጥታ ቁጥጥር እንደነበር ገልጿል፡፡ የፕሬዚደንቱ አማካሪ አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው ‹‹ይህ የፕሬዚደንት ኢሳያስ ጉብኝት የኤርትራ፣ ኢትዮጵያና ሶማሊያ መሪዎች የፈጠሩት የሶስትዮሽ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live