Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አዲስ አበቤነት እየተፈተነ ነው

$
0
0
ከብርሃኑ ተክለያሬድ አንዳንዶች በአዲስ አበባ ላይ ም/ከንቲባው የሰራቸውን ስህተቶችን በጠቆምን ቁጥር “ታከለ የለውጡ አካል ነው አታደናቅፉት”አይነት አስተያየቶች ይሰጡናል የለውጥ አካል ማለት በስም ሳይሆን በተግባር የሚገለፅ ሆኖ ሳለ ታከለን መቃወም ሿሚዎቹን የለውጥ አካላት መቃወም ነው ሊሉን ይፈልጋሉ (አረመኔውና አንገት ደፊው ያሬድ ዘሪሁን በለውጡ መሪዎች ፖሊስ ኮሚሽነር ተደርጎ ተሾሞ ያልነበረ ይመስል) በእርግጥም ታከለ ኡማ አዲስ አበባንና አዲስ […]

የዛሬው የኦሮሞ የፖላቲካ ፖርቲዎች ሁለት የስምምነት ጭብጦች!

$
0
0
ብርሃነ መስቀል አበበ ዛሬ በፕሬዚደንት ለማ ጥሪ እና ሰብሳቢነት የተደረገውን የኦሮሞ ተቃዋሚ የፖላቲካ ፖርቲዎች ስብሰባ ተሳትፊያለሁ። ፕሬዚደንቱ ለፖሪቲዎቹ አና ለተሰብሳቢው በሙሉ እንደ አንድ መሪ በኢትዮጵያ፣ በተለይም በኦሮሚያ ውስጥ ባለው የሰላም ሁኔታና የሰላማዊ ሽግግሩ ያሉባቸው ተግዳሮቶች ላይ በግልፅ ተናግረዋል። ተሰብሳቢዎቹም እንደዚሁ። በስብሰባው የተደረሱት የ መግባባት ጭብጦች ሁለት ናቸው። 1ኛ) ሁሉም የኦሮሞ ተቃዋሚ የፖላቲካ ፖርቲዎች የሚያደርጉት የፖላቲካ […]

ለማ መገርሳ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ዳኡድ ኢብሳ በጋራ መግለጫ ሰጡ

$
0
0
«ተጠላልፎ ከመዉደቅ ተደጋግፎ መራመድ» በሚል መሪ ቃል በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ 14 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር ተወያዩ፡፡    በአዲስ አበባ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማእከል በተከናወነው በዚሁ ውይይት ላይ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ምክትል ሊቀ መንበርና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ በተገኙበት በተደረገው በዚህ ውይይት የኦዲፒ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ […]

በጀርመን የበርሊን እና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መግለጫ አወጡ

$
0
0
“በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን እና የኢትዮጵያን ኤምባሲዎች ግንኙነት በሚመለከት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠው መግለጫ በተግባር እንዲተረጎም እንጠይቃለን አብረንም ለለውጥ እንተጋለን።” ሲሉ በጀርመን በርሊን እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  መግለጫ አወጡ:: መግለጫው እንደሚከተለው ይቀርባል:: በዋናነት የፍራንክፈርቱ ቆንስላ ጽ/ቤት እስከ ቅርብ ጊዜ ለውጡ እስከመጣበት ወቅት ድረስ ታዋቂ ተግባር ኢትዮጵያውያኖች ለዲሞክራሲ እና ለሰባዊ መብት መከበር በሚያደርጉዋቸው ሰላማዊ ሰልፎች ዝግጅቶች ስብሰባዎች […]

አንድነት ለኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ነው፤ መበታተን ጥቃት ነው!

$
0
0
——ዓለም አቀፍ የህብረት ጥሪ———   አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር) ዶር ዐብይ አህመድ ጠ/ሚንስትር ከሆኑበት ጊዜ ወዲህ የሚካሄደው ትግል፤ በአንድ በኩል መሰረታዊ ለውጥን በሚደግፉ፤ በሌላ በኩል ይህን ለውጥ በሚቃወሙ፤ ጥቅማቸው በተነካ፤ ግዙፍ ገቢና ኃብት ሰርቀው፤ ዘርፈውና ደብቀው “ሕገ መንግሥቱ ይከበር” በሚል ተንኮለኛና ከእውነቱ የራቀ ስልት በሚጠቀሙ (Restore and maintain the past at any cost)ኃይሎች መካከል ነው። ቢያንስ የየካቲት […]

ሕወሓት እነዚህን 16 የኢትዮጵያ የጦር መርከቦች የት አደረሳቸው?

$
0
0
ሕወሓት እነዚህን 16 የኢትዮጵያ የጦር መርከቦች የት አደረሳቸው?

ጋዜጠኛ አብዱረሂም እና ጋዜጠኛ ሳዲቅን ለመቀበል የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

$
0
0
ጋዜጠኛ አብዱረሂም እና ጋዜጠኛ ሳዲቅን ለመቀበል የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ብርሃኑ ጸጋዬ “መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የያዘውን ቁርጠኛ አቋም በቀጣይም በተደራጁ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ሙስናና ሌብነት ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት ወዜተ ላይ የተሳተፉ ሕገ-ወጦችን ወደ ሕግ የማቅረቡ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡” ሲሉ ዛሬ በትዊተር ገጻቸው ጽፈው አንብበናል:: ፌዴራል ፖሊስ በዚህ ሳምንት የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል 5 ባለስልጣናትን ማሰሩ ይታወሳል:: – ማረሚያ በትናንቱ የዜና እወጃችን ገዱ […]

ሁለት ከፍተኛ የደህንነት አመራሮች ታሰሩ

$
0
0
ሁለት ከፍተኛ የደህንነት አመራሮች ታሰሩ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ በቀጥታ ትዕዛዝ ሲቀበሉ የኖሩት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ መዓሾ ኪዳኔ ዓለሙ እና አቶ ሀዱሽ ካሳ ደስታ ታሰሩ:: በትናንትናው የዘ-ሐበሻ ዜና ጠቅላይ አቃቤህጉ ብርሃኑ ጸጋዬ “መንግስት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የያዘውን ቁርጠኛ አቋም በቀጣይም በተደራጁ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ሙስናና ሌብነት ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት ወዜተ ላይ […]

ዶ/ር ደብረጽዮን በመቀሌው ሰልፍ የዶ/ር አብይ አህመድን አስተዳደር ሕዝቡን ማስተዳደር ያቃተው የለውጥ ኃይል ሲሉ ኮነኑ

$
0
0
በትግራይ መዲና መቀሌ ስታዲየም በተካሄደው ህዝባዊ ሰልፍ ላይ የህወሃት ሊቀመንበርና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል; “ዘመኑ የተገላቢጦሽ ሆኖ ህዝቡን ማስተዳደር ያቃተው የለውጥ ሀይል፣ ህዝቡን በስርዓት የሚያስተዳድር ደግሞ ፀረ-ለውጥ የሚል ታርጋ ሲለጠፍበት እያየን ነው።” በማለት ተናገሩ:: መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፥ ዛሬ ህዳር 29 በእኩልነትና ፍትህ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት የሚያስችል […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት አስማኤል ኦማር ጊሌ የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክን መርቀው ከፈቱ።

$
0
0
በጨርቃ ጨርቅ፣ አልባሳት እና ግብርና ማቀነባበር ላይ ያተኮረው የኢንዱሰትሪ ፓርኩ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው። የኢንዱስትሪ ፓርኩ 61 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላርም ወጪ ተደርጎበታል። ፓርኩ የአከባቢ ብክለትን መጠበቅ በሚያስችል መልኩ የተገነባ ነው። በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የጅማ- አጋሮ – ደዴሳ ወንዝ ድልድይ የመንገድ […]

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትሰራ የነበረች አንዲት ቻይናዊት ሆስተስ በፖሊስ ከአገር ተባረረች

$
0
0
ዋንግ ዤንግዢያን የምትባለው የ28 አመት ሆስተሷ ባለፈው እሁድ ከስልጠና መባረሯን የሚገልፅ ደብዳቤ ከአየር መንገዱ የደረሳት ሲሆን ይህን ተከትሎ በንዴት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሷን ለማወቅ ችለናል፡፡ ደብዳቤው እንደደረሳት በአጠገቧ የነበረውን አውሮፕላን መስታወት ከመሰባበሯም በላይ ወደ እንግዳ መቀበያ ዴስክ በመሄድ ጠረንጴዛውን ገልብጣ ሌሎች ሰልጣኞች ላይ ጉዳት ልታደርስ ስትል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋለች ምንጮች አስረድተውናል፡፡ አየር መንገዱ ለፖሊስ እንዳስታወቀው […]

ጣሊያን ለኢትዮጵያ ለ 1 ሚሊዮን ዩሮ ሰጠች

$
0
0
በጉብኝት ላይ ያሉት የጣሊያኑ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤላ ዴልሬ አገራቸው አንድ ሚሊዮን ዩሮ መስጠቷን ተናገሩ፡፡ ይህ እርዳታ መድሃኒትን፣ የህክምና ቁሳቁስን፣ ምርጥ ዘርንና የእርሻ መሳሪያን እንደሚያካትት ገልፀዋል፡፡ በተለይም የህክምና መሳሪያውና መድሃኒቱ በቀይ መስቀል በኩል ባለፈው አመት በተቀሰቀሰው ግጭት ተፈናቅለው በመጠለያ ላሉ ወገኖች እንደሚከፋፈል አስረድተዋል፡፡

ጋዜጠኞች ሳዲቅ አህመድ እና አብዱረሂም አህመድ ወደ ሃገራቸው አቀኑ:: በነገው ዕለት አዲስ አበባ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ይጠበቃል::

$
0
0
ሳዲቅ ወደ አውሮፕላን ከመውጣቱ አስቀድሞ በላከልን አጭር መ ልዕክት “አገርን የማልማት፣ ለውጡን የማሳካትና ከግብ የማድረስ ጥሪን ተቀብለን እነሆ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዞን ጀምረናል። ከሰባት አመታት ያላሰለሰ ትግል በኋላ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ደረጃ ትደርስ ዘንድ አያሌ መስዋእትነት የከፈላቹ እንቁ ያገር ልጆችን ለማየት ወደ እናት አገር መመለስ በጣሙን ደስ ይላል። ኢትዮጵያዊነት ፈተና ነው ፈነውን ግን ያልፋል። አገራችን […]

አጫጭር የዘሃበሻ ዜናዎች

$
0
0
የአማራ ክልል ከታህሳስ 1 እስከ ታህሳስ 4 ባሉት ቀናት የጦር መሳሪያ ባለቤት ለሆኑ የክልሉ ነዋሪዎች ፍቃድ እንደሚሰጥ ታወቀ:: በክልሉ የመሳሪያ ፈቃድ መስጫው ቀን እጅግ በማጠሩ የመሳሪያ ዋጋ እንደጨመረ ሰምተናል:: – የሕወሓት ኮንደም ነው እየተባለ ሲወገዝ የከረመው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) በአሶሳ ከተማ በተከሰተው ሁከት እጃቸው አለበት ተብለው በተጠረጠሩና በተደራጀ ሌብነት ተሰማርተው ተገኝተዋል በተባሉ […]

ገነት ዘውዴ እና ሙሉ ሰለሞን እንደ አናቃቂ ተናጋሪ (Inspirational speakers) ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ ኮተቤ ሜትሮፖሊን ዩኒቨርስቲ

$
0
0
ገነት ዘውዴ እና ሙሉ ሰለሞን እንደ አናቃቂ ተናጋሪ (Inspirational speakers) ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ ኮተቤ ሜትሮፖሊን ዩኒቨርስቲ ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ ህዳር 28፣ 2011ዓ.ም. (Ensuring sustainable development through empowering women academicians) በሚል ርዕስ በግዮን ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ እንዲህ አይነት መድረኮች ወጣት ሴት ተማሪዎችን፣ መምህርትን እና ሴት ተመራማሪዎችን የሚያበረታታ ስለሆነ ጉዳዩ ወቅታዊና ተገቢ ነው፡፡ በጉባኤው […]

ለአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አጭር ማስታወሻ

$
0
0
ለአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አጭር ማስታወሻ ይነጋል በላቸው (yinegal3@gmail.com) ከኢሕዲን ወዲህ ባሉት ስሞች ብዙም ደስተኛ አለመሆኔን በዚህ አጋጣሚ ብገልጽ ደስ ይለኛል፡፡ ያ ስም ደስ ይለኝ የነበረውም ሕወሓት በሰጠው የሽፋንነት ተልእኮው ሣይሆን ስያሜው ኢትዮጵያን በመያዙ ነበር፡፡ “ኢትዮጵያ” ሲባል መቼም ስሜትን መኮርኮሩ አይቀርም፡፡ አሁን ባለው ስሙ ደግሞ በጭራሽ አልስማማም፡፡ አማራ ብሎ ዴሞክራሲያዊ ፣ ኦሮሞ ብሎ ዴሞክራሲያዊ፣ ከምባታና ሃዲያ […]

“የማይቻለውን በማብሰልሰል ሃሞታችሁን አታፍስሱ”–ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

$
0
0
“…ታጥቃችሁ በመነሳት ምርጫችሁን በ እጃችሁ ውሰዱ! ቀላሉን ሳይሆን ትክክለኛውን መንገድ ምረጡ! በምቹው ሳይሆን በጠቃውሚው ጎዳና ላይ ቀና ብላችሁ ሂዱ! የቅርቡን ብቻ ሳይሆን የሩቁንም ተመልከቱ! የማይቻለውን በማብሰልሰል ሃሞታችሁን አታፍስሱ፣ ይልቀውን የሚቻለውን ለማድረግ ክንዳችሁን ዘርጉ!” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ጅማ ላይ የተናገሩት

የአዲስ አበባ ሁሉን-አቀፍ ንቅናቄ (አሁን) ምስረታ መግለጫ

$
0
0
ቀን፡ ኅዳር 29, 2011 ይህ መግለጫ የአዲስ አበባ ሁሉን-አቀፍ ንቅናቄ (አሁን) ምስረታን ያበስራል። አሁን ‘የአዲስ አበባ ባለቤትነት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ነው’ የሚልን መሪ ሃሳብ የማእዘን ድንጋይ አድርጎ የተመሰረተ ሲሆን – የምስረታውም ዋነኛ ዓላማ ይህን እሙን ሃቅ በሃገራችን ፖለቲካዊ፥ ኢኮኖሚያዊና፥ ማህበራዊ መስተጋብር ይረጋገጥ ዘንድ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ማስተባበር ነው። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆና ከአንድ ምዕት ዓመት በላይ ያገለገለችው […]

መቆሌ ሰልፍ ትዝብት ላይ ወደቀ!!

$
0
0
እኔ በእዉነቱ ትግራይ ዩኒበርስቲያ እና ጎሎጅ ለትግራይ ብሎም ለመላዉ ኢትዮጵያ መፍትሄ ለመስጠት የለዉጥ አካል የሚሆኑ ምሁራን አሉ የሚል ግምት ነበረኝ ሚዛናዊ ትንታኔ ካሁን በፊት ባልሰማም። አሁን ንግግራቸዉን ሳዳምጥ ምሁር ተብየወች ህሊናቸዉን ሽጠዉ በተለይ የህግ ምሁራን አነጋገር ስሰማ እጅግ አዘንኩ። እን ክንፌ ዳኘዉ ለምን እጃቸዉ ታሰረ, በፍርድ ቤት ሳይወሰን በመገናኛ ብዙሃን ወንጀላቸዉ ተነገረ፤ አንድ ሰዉ በፍርድ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live