Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የ37 ቢሊየን ብሩ መዳረሻና የሜቴክ የውስጥ መዝገብ

$
0
0
የሜቴክ ጉድ እንዲህ በቀላሉ ተነግሮ የሚያልቅ የሚመስለው ካለ ትክልል አይደለም:: ይልቁንስ ገና ብዙ ጉድ እየተዘረዘረ ስለሚወጣ ይልቁንስ ጆሮን ሰፋ አድርጎ መከታተሉ ነው የሚበጀው:: በዛሬው ዕለት “የ37 ቢሊየን ብሩ መዳረሻና የሜቴክ የውስጥ መዝገብ” በሚል ዋዜማ ራድዮ በድረገጹ የጻፈውን አነብላችኋለሁ – ወይ ዘንድሮ እያላችሁ ተከተሉኝ:: በነገራችሁ ላይ ይህንን ዘገባ ላቀርብላችሁ እየተዘጋጀሁበት ባለሁበት ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ […]

ጌታቸው አሰፋ ሽብርን የሚያስፋፋ? –ከኢትዮጵያ እስከ ሱማሊያ በርሃ፤ የሽብር ተመልማዮች ንሰሃ

$
0
0
አቶ ጌታቸው አሰፋ ይመራው በነበረው የቀድሞው የደህንነት መስሪያ ቤት በወጠነው ሴራ መረብ ውስጥ ገበተው ወደ ጎረቤት አገር ለሽብር ፈጠራ ስልጠና ያቀኑ ኢትዮጵያዉያን ይናገራሉ።ሶማሊያ ዉስጥ የነበረውን የሽብር ስልጠና ካምፕ የሚመራዉ ማን ነበር? ከተለያየ ቦታ ተመልምለው እንደወጡ ለቀሩ ዜጎች ተጠያቂው የቀድሞው የደህንነት መስሪያ ቤት አመራር ነውን? ኤርትራ በሽብር ተፈርጃ ማእቀብ ተጥሎባት ነበር፤ በርግጥ ኤርትራ አለችበትን? በዶ/ር አብይ […]

“ወታደራዊ ሪፎርም እና ሙስና”–ተመስገን ደሳለኝ

$
0
0
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍትህ የተሰኘችውን መጽሔቱን ማሳተም ጀምሯል:: ሁለተኛው ዕትምም ልክ እንደመጀመሪያው እትም በጠዋቱ ተሽጦ ያለቀ ሲሆን መጽሔትና ጋዜጣ አዟሪዎችም እስከ ሦስት እጥፍ በማስከፈል መጽሔቱን ሸጠውታል:: በሁለተኛው ዕትም ላይ ከታተሙት በርካታ ቁምነገሮች መካከል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የጻፈው “ወታደራዊ ሪፎርም እና ሙስና” ሲል በወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጻፈው ይገኝበታል:: በርከት ያሉ ቁምነገሮችን ስለያዘ ለዘ-ሐበሻ ወዳጆች በሚስማማ መልኩ […]

በሃገሪቱ ሰሞኑን እየተወሰደ ባለው እርምጃ የተነሳ የጸጥታ ጥበቃው መጠናከሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለጹ

$
0
0
ሰሞኑን በሃገሪቱ እየተወሰደ ባለው እርምጃ የተነሳ የጸጥታ ጥበቃው መጠናከሩን ሕዝቡን እያደረገ ላለው ትብብር ያላቸውን ምስጋና ዶ/ር አብይ አህመድ ገለጹ:: የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ እሁድ ሕዳር 8, 2011 ዓ.ም በጽሁፍ በላኩት መግለጫ “ሕዝብ ለለውጥ እንደሚደክም ሁሉ ለውጡን ለማደናቀፍ ሌት ተቀን የሚለፉ እኩያን አሉ” ብለዋል:: የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ እንደሚከተለው ይቀርባል

ጀነራሎች እና ስመጥር ባለሃብቶች እየተዝናኑ የሚደራደሩበት ጎልፍ ክለብ ጭር ማለቱ ተሰማ

$
0
0
በመከላከታ ሠራዊት ፋውንዴሽን ሥር የተቋቋመውና ጀነራሎች እና ነጋዴዎች የሙስና ድርድር ያደረጉበታል የሚባለው ጎልፍ ክለብ መዝናኛ ከወትሮው በተለየ ጭር ብሎ መሰንበቱ ተገለጸ:: ትናንት በአዲስ አበባ ታትሞ በወጣው ፍትህ ጋዜጣ ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደገለጸው በተለይ ሮብ አርብ ቅዳሜ ክራማው የሚደምቀው ይህ ክለብ የለጋስ ከበርቴዎች እና የጀነራሎች በተለይም ጀነራል ሳሞራ የኑስ; ሜጀነራል ብርሃነ ነጋሽ; ሜጀር ጀነራል መሃሪ […]

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ግርማ ዋቄ ሃላፊነታቸውን የለቀቁት በሕወሓት ሰዎች “ያልንህን ካልሠራህ”ስለተባሉ መሆኑን ገለጹ

$
0
0
የኢትዮጵያ አየር መንገደ ለሰባት ዓመት በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የመሩት አቶ ግርማ ያቀረቡት የሥራ መልቀቂያ ተቀባይነት አግኝቶ እ.ኤ.አ. በ2011 በጡረታ የተሰናበቱት በሚደርስባቸው የሕወሓት ባለስልጣንት ግፊት እንደነበር ዛሬ በአዲስ አበበባ ታትሞ ከወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ ገልጸዋል;;፡ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ከለቀቁ በኋላ የሩዋንዳ አየር መንድ የቦርድ ሊቀመንበር፣ የሩዋንዳ የትራንስፖርት ሚኒስትር የአቪዬሽን ጉዳዮች አማካሪ በመሆን ያገለገሉት […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
መነሻ እና መድረሻውን በአፍሪካ ህብረት ድንገተኛ የመሪዎች ጉባኤ ምክንያት ከመስቀል አደባባይ ወደ ስድስት ኪሎ የሰማዕታት ሀውልት በመቀየር ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የተከናወነው 18ኛው የቶታል ታላቁ ሩጫ በሰላም ተጠናቀቀ:: ውድድሩን በወንዶችም ሆነ በሴቶች ኢትዮጵያውያን ከአንድ እስከ ሦስት በመውጣት አሸንፈዋል:: በዚህ ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራውያን አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን ታዋቂው ኤርትራዊው አትሌት ዘረሰናይ ታደሰም በክብር እንግድነት ታድሟል:: በዚህ […]

ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የጸረ ሌብነቱ እርምጃ አቅጣጫውን እየሳተ ነው አሉ

$
0
0
በከፍተኛ ሌብነትና ሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ስራ መጠናከር የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ ፍላጎት ቢሆንም በሙስና እና የሰብኣዊ መብቶች ጥሰት ስም የትግራይን ህዝብ ለማንበርከክ ጥረት እያደረገ ነው ሲሉ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል አስታወቁ። ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ይህንን ያስታወቁት ዛሬ ማለዳ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በትግርኛ በሰጡት መግለጫ ነው። “መንግስት በሙስና […]

በድሬዳዋ በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ፣ ቤቶች ተቃጠሉ

$
0
0
የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ በከተማው ቅዳሜና እሁድ በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና ቤቶች መቃጠላቸውንም ይፋ አድርጓል፡፡ ይኸው የፖሊስ መግለጫ ህዳር 8ቀን 2011አ.ም ከሰአት በሃላ እና ህዳር 9ቀን እረፋድ ላይ በቀበሌ 09 ፖሊስ መሬትና መጋላ ጨብጡ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግጭት መፈጠሩን ይናገራል፡፡ ፖሊስ የግጭቱን መንስኤ እያጣራው እንደሆነ የገለፀው መግለጫው ጨምሮም ‹‹በዚህም ግጭት በህክምና ጭምር […]

የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ አዲስ ክስ ተጨመረ |ፖሊስ የሜ/ጀ ክንፈ ወንድም አቶ ኢሳያስ ዳኘው በባንክ ያላቸውን ገንዘብና ንብረታቸውን ማስረጃ አቅርቦ ዋስትና ራሳቸው ያቁሙ ሲል ጠየቀ

$
0
0
የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ዛሬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ዛሬ ቀረቡ:: ፖሊስም ከሰኔ 16ቱ የቦምብ ፍንዳታ በተጨማሪነት አዲስ ክስ ይዞ በመምጣት በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል። አቶ ተስፋዬ የደህንነት መምሪያ ሀላፊ ሆነው ሲሰሩ ሰዎችን በሽብር ተጠርጥራችኋል በሚል በስውር እስር ቤት […]

በግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚተዳደር ፈንድ ሊቋቋም ነው

$
0
0
በዛሬው እለት የግብፅ ሚዲያዎች ዋንኛ ትኩረት የኢትዮጵያና የግብፅ ጉዳይ ሆኖ ውሏል፡፡ የአገሪቱ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው የሁለቱ አገራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ላይ ትላንት እሁድ ለአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በተገናኙበት ወቅት ስለግድቡ ጉዳይ አውርተው ነበር፡፡ የግብፁ ጠ/ሚ/ር ሙስጠፋ ማድቡሊ ከዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት በግድቡ ዙሪያ ባሉ ቀሪ ጉዳዮች ላይ በሚቀጥለው ሳምንት የሁለትዮሽ ድርድሩ እንደሚቀጥል መስማማታቸውን […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
ዶ/ር አብይ አህመድ  በአዲስ አበባ የለገሀር የተቀናጀ መንደር ግንባታ ፕሮጅክትን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ያደረጉትን ንግግር ከ ቀጥሎ እናቀርባለን – ይከታተሉት:: 14 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ሊያወጣ የነበረው ግለብ ተያዘ በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ በተጭበረበረ ቼክ 14 ሚሊየን 724 ሺህ ብር ሊያወጣ ሲል ተያዙ ተዘገበ።  የተያዘው ግለሰብ አቶ ገመቹ ጫላ በሚል […]

ዶ/ር አብይ አህመድ  በአዲስ አበባ የለገሀር የተቀናጀ መንደር ግንባታ ፕሮጅክትን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ያደረጉት ንግግር

$
0
0
ዶ/ር አብይ አህመድ  በአዲስ አበባ የለገሀር የተቀናጀ መንደር ግንባታ ፕሮጅክትን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ያደረጉት ንግግር

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓል አስመልክቶ መልዕክት አስተላለፉ

$
0
0
ዶ/ር አብይ አህመድ የሀገራችን ሙስሊሞች እና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን እንደ ሁል ጊዜው በመውሊደል ነቢ በዓልም የነበሩንን የሰላም፣ የመረዳዳት፣ የመከባበር እና የመጠያየቅ ባሕል በማስቀጠል የበኩላችቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቀረቡ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የነቢዩ መሐመድ የልደት በዓል አስመልክቶ ባስተላለፉት መል ዕክት ነው:: የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል: በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ ለምትኖሩ መላው የእስልምና ተከታይ ወገኖቼ፤ እንኳን ለ1493ኛው የነቢዩ […]

አዲሱ የእስር ዘመቻ |ቆይታ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ጋር

$
0
0
አዲሱ የእስር ዘመቻ | ቆይታ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ጋር

የፌዴራሊዝሙ ትኩሳት አስከየት? |በፌዴራሊዝሙ ትኩሳት ተጨናንቆ፥ ደም ተቃባ መስቃንና ማረቆ!

$
0
0
በሳዲቅ አህመድ ዜጎች ባገሪቱ ውስጥ እንዳሻቸው ተንቀሳቅሰው የመኖርና የመስራት መብታቸው የፌዴራል ስርዓቱ የሚያከብረው ቢሆንም በብሔር ብሔረሰቦች መብት መከበር ስም የገነነው ዘረኝነት ለአገሪቷ ስጋት ሆኗል። በሶማሊ ክልል ዉስጥ ልዩ ፖሊስን አደራጅቶ የነበረው የአብዲ ኢሌ መንግስት ዜጎችን መግደሉና ማፈናቀሉ ሳያንሰው ህገወጥ በሆነ መልኩ እገነጠላለሁ ብሎ ሲያስፈራራ በነሐሴ 01/2010 አብዲ ኢሌና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ልብ ይሏል። በክልሎች […]

ኦነግ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የቀድሞ ዋና ፅህፈት ቤቱን ተረከበ

$
0
0
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር(ኦነግ) በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ የሚገኘውን የቀድሞ ዋና ፅህፈት ቤቱን በዛሬው ዕለት ተረከበ። የግንባሩ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ እንደገለፁት ኦነግ ዛሬ የተረከበው ፅህፈት ቤቱ እስከ 1985 ዓ.ም ሲጠቀምበት የነበረ መሆኑን ተናግረው ግንባሩ ከሽግግር መንግስቱ ራሱን ካገለለበት ጊዜ ጀምሮ ፅህፈት ቤቱ ከኦነግ ተቀምቶ ለተለያዩ የመንግስት ግልጋሎቶች ሲውል እንደነበር አስረድተዋል። […]

ጋናዊው የእግር ኳስ ተጨዋች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እየተፈለገ ነው

$
0
0
ኪንግ ፋይሳል የተሰኘው የጋና ክለብ አጥቂ የነበረው ሞሪሰን ኦሲይ በተቃጠለ ቪዛ አገር ውስጥ በመቆየቱና በሆቴል እዳ በኢትዮጵያ ፖሊስ እየተፈለገ ነው፡፡ ራሱ ተጨዋቹ ለጋና ጋዜጦች እንዳስታወቀው ከኢትዮጵያ ቡና ክለብ ጋር የነበረው ኮንትራት ከተቋረጠ በኋላ ላለፉት ጥቂት ወራት ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል፡፡ ሲናገርም ‹‹እኔ ወደ ኢትዮጵያ የመጣሁት ኢትዮጵያ ቡና ክለብን ለመቀላቀል ነበር፡፡ ነገር ግን እኔን ያስፈረሙኝ ሰርቢያዊው አሰልጣኝ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
በትግራይ ክልል ሽሬ የፖለቲካ ብጥብጥ መድን ውል መጀመሩ ተገለጸ:: መንግስታዊው የኢትዮጳያ መድን ድርጅት ‹‹የፖለቲካዊ ብጥብጥ መድን ውል›› ጀመረ፡፡ ድርጅቱ በአንዳንድ ቅርንጫፎቹ በለጠፈው ማስታወቂያ ላይ ይህን የፖለቲካ ብጥብጥ ውል እንደጀመረ አስረድቷል፡፡ ይህ የምትመለከቱት በሽሬ እንደስላሴ መድን ድርጅት ቅርንጫፍ የተለጠፈ የግርግዳ ማስታወቂያ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰ ብጥብጥ ንብረታቸው የተቃጠለባቸውና የወደመባቸው የፖለቲካ ብጥብጥ ውል አልተጀመረም በማለት […]

ኢትዮጵያዊያን በአዲስ አበባ እስራኤልን ለመቃወም ተሰበሰቡ

$
0
0
በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አይሁዶች በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ የእስራኤልን ውሳኔ ለመቃወም ስብሰባ አድርገዋል፡፡ የእስራኤል መንግስት ኢትዮጵያዊያን አይሁዶችን ወደእስራኤል መውሰዱን ማቆሙን ማስታወቁ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቆራርጠው እንዲቀሩ የሚያደርግ ውሳኔ መሆኑን ነው በተቃውሟቸው የገለፁት፡፡ 8 ሺህ በኢትዮጵያ የሚኖሩ አይሁዶችን እንወክላለን ያሉት እነዚህ ተቃዋሚዎች የእስራኤል መንግስት ውሳኔውን ወደገዢው ሊክዊድ ፓርቲ ወስዶ ከማስወሰኑ በፊት ቆም ብሎ እንዲያስብበት ጠይቀዋል፡፡ በአዲስ አበባና […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live