Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያ ስለምታቋቁመው የባህር ሃይል ማብራሪያ ተሰጠ |ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ቤተመንግስት የሄዱት ወታደሮች ጉዳይም ተናገሩ

$
0
0
የመከላከያ ሰራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ባህር ሃይል ልታቋቁም መሆኑን አስታወቁ፡፡ ጄኔራሉ ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስረዱት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቀደም ሲል ባህር ሀይል የነበረው እንደሆነ ጠቁመው የባህር በር የለንም በሚል አስተሳሰብ እንደፈረሰ አስረድተዋል፡፡ አሁን ግን ዘመናዊና ጠንካራ ጦር ሃይል ለመገንባት እቅድ ስለተያዘ […]

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አዲስ ፕሬዚደንት ሾመ

$
0
0
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው ክልሉን ለ13 ዓመታት ያገለገሉት አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ያቀረቡት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሏል፡፡ በምትካቸውም አቶ አርዲን በድሪን የክልሉ ፕሬዚደንት አድርጎ ሾሟል፡፡ አቶ ኦርዲን በድሪ ለፕሬዚደንትነት የተጠቆሙት በሐረሪ ብሔራዊ ሊግ/ሐብሊ/ ሲሆን በምክር ቤቱ 29 ድጋፍና አምስት ተቃውሞ አግኝተው በአብላጫ ድምጽ ፕሬዚደደንትነታቸውን አጽድቋል። አቶ ኦርዲን በድሪ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በፔዳጎጂ ሳይንስ ፣ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
ከጦሩ አመራሮች ጋር ሲወያዩ ያረፈዱት ጠቅላይ ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ  ያደረጉትን ውይይት ካጠናቀቁ በኋላ ጎንደር ገቡ::   በአካባቢው ስላለው የሰላም ሁኔታ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከነዋሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሏል::  ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ ጎንደር ከተማ ሲደርሱም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል አደርገውላቸዋል። ዶር አብይ ወደጎንደር ያቀኑትም በነገው እለት ወደአማራ ክልል የሚመጡትን ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂን ለመቀበል ነው፡፡ የኤርትራው ፕሬዚዳንት […]

የቁጥር ዕውቀቴ ካናካቴው ከዳኝ! –ይሄይስ አእምሮ

$
0
0
ይሄይስ አእምሮ (ከአዲስ አበባ፣ ፊንፊኔ፣ ሸገርና በረራ) ስለምንም ነገር መጻፍ አልፈለግሁም ነበር፡፡  “ተጻፈ፣ ተጻፈ ግን እንዳልተጻፈ ሆነ” በማለት ወዳማርኛ ሲመለስ “ጮህን፣ ጮህን እንዳልጮህንም ሆን” ወይም በመገኛ ቋንቋው “ነባይነ፣ ነባይነ ከእምዘባይነ ኮነ” ተብሎ የተነገረውን ነባር ብሂል ልኮርጅና መጻፍ ብቻውን ትርፉ ድካም ብቻ መሆኑን በእግረ መንገድ ልጠቁም፡፡ የዚህች ሀገር ነገር እየፈጩ ጥሬ ወይንም አድሮ ቃሪያ እየሆነ መሄዱ […]

የጀነራሎቹ እስር –መሳይ መኮንን

$
0
0
የኢሳትና የሪፖርተር ዜናዎች አንዳች ነገር አመልካች ናቸው። በኢሳት የትላንት መረጃ መሰረት ከ160 በላይ ጄነራሎችና የጦር አዛዦች በጠ/ሚር አብይ ትዕዛዝ ከሰራዊቱ እንዲሰናበቱ ተደርገዋል። አብዛኞቹ የህወሀት ጄነራሎች ናቸው። ዛሬ ደግሞ ሪፖርተር ጋዜጣ ከ40 በላይ የሜቴክና የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሚያትት ዜና ይዞ ወጥቷል። የጠ/ሚር አብይ ጥርስ እየተሳለ ነው። አድፍጦ መገዝገዝ ጀምሯል። የህወሀትን የጥፋት እጆች ከየክልሉ በመቁረጥ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጦ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ ጥቅምት 27, 2011 በኦቢኤን ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ኦነግን እና መንግስትን ለማስታረቅ የሄዱ ሽማግሌዎች ተደብድበው የሄዱበት ጉዳይም ሳይሳካ መመለሳቸውን በመናገራቸው; የተሳሳተ መረጃ ለህዝብ አስተላልፈዋል ሲል ኦነግ ቅሬታ አቀረበ። በመንግስትና በኦነግ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ወደ ምዕ/ኦሮሚያ የተንቀሳቀሱ የሀገር ሽማግሌዎች ተዘርፈው ተደብድበውና ጉዳያቸው ተሰናክሎ ተመልሰዋል […]

መምህር ግርማ ወንድሙ በነጻ ተለቀቁ

$
0
0
ዛሬ ለንባብ የበቃው ኢትዮጲስ ጋዜጣ መምህር ግርማ በነፃ መለቀቃቸውን ዘገበ። እንደጋዜጣው መምህር ግርማ ወንድሙ ነፃ የወጡት ከተከሠሡበት የወንጀል ክስ ነው። ለሶስት አመታት ከገንዘብ ማጭበርበር ጋር የተያያዘውን ጨምሮ ስምንት የተለያዩ ክሶች ቀርበውባቸው ፍርድ ቤት ሲመላለሡ ነበር ያለው ጋዜጣው ጥቅምት 28 ቀን 2011 ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ነፃ እንደተባሉ ገልፆዋል። በክሡ ምክንያት ከአገር […]

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሃገራቸው በሰላም ተመለሱ

$
0
0
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ወደ ሃገራቸው በሰላም ተመለሱ:: የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን በትናንትናው ዕለት ከጎንደር የጀመሩት መሪዎቹ በባህር ዳር ከጠሚር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በመሆን በሶስትዮሽ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ ውለው ሀገራቱ የደረሱትን የሶስትዮሽ ስምምነት አፈፃፀም ላይ ተነጋግረዋል:: መሪዎቹ ከውይይታቸው በኋላ በሰጡት መግለጫ የኢኮኖሚ ትብብርና ቀጠናዊ ሰላምን የማስጠበቅ እቅድ በሚገባ እየተተገበረ […]

በሌብነትና በሌሎች ወንጀሎች የሚፈለጉ የጦር መኮንኖች ታፈሱ |ልዩ ግብረ ኃይል ወደ መቀሌ አቀና

$
0
0
በሌብነት እና በሌሎች ወንጀሎች የሚፈለጉ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አመራሮች በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ነው:: መቀሌ ላይ የተደበቁትን ለመያዝ አንድ ልዩ ኃይል ወደዚያው ማቅናቱ ተሰማ:: ከአርባ በላይ የሚሆኑ የጀነራልነት የኮለኔልነትና ሌሎችም ማዕረግ ያላቸው ከአርባ በላይ የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በትናንትናው ዕለት ለስብስባ ተጠርተው በዚያው ታፍሰው እንደታሰሩ መረጃዎች ወጥተዋል: በመከላከያው አመራር ውስጥ የነበረውን የአንድ ብሄር የበላይነት […]

በወቅታዊ የራያ ሁኔታ በሰሜን አሜሪካና ካናዳ አካባቢ በሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች የተሰጠ  የአቋም መግለጫ!

$
0
0
እኛ በሰሜን አሜሪካና ካናዳ አካባቢ የምንኖር የራያ ተወላጆች ከሐምሌ ወር ጀምሮ በአላማጣ፤ዋጃ- ጥሙጋ እንዲሁም በአጠቃላይ በራያ ማህበረሰብ ላይ የትግራይ ልዩ ሀይል ባደረሰው ሞት፤ የአካል ጉዳት እንዲሁም መፈናቅል የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን።የፈሰሰው የወገኖቻችን ደም የኛም ደም ነው፤ የነሱ ህመም የኛም ህመም ነው።ምንም እንኳ ማህበረሰቡ ጥያቄውን ያነሳው ሰላማዊ እና ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት ቢኖንም በወገኖቻችን ላይ በትግራይ ልዩ […]

የሐረርጌ መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ለእሁድ (November 11, 2018) ሰዓት 3:30 PM

$
0
0
የሐረርጌ መረዳጃ ማህበር ስብሰባ ለእሁድ (November 11, 2018) ሰዓት 3:30 PM

ለአቶ ባይሳ ዋቅወያ –ከተፈራ ድንበሩ

$
0
0
ለአቶ ባይሳ ዋቅወያ፣ እንደምን ሰነበቱ? ከአዲስ አበቤዎች ጋር በተያያዘ የጻፉትን ጦማር  በተመለከተ አጭር አስተያየት ልሰጥዎት እሻለሁ፡፡ ቡራዩ ላይ የተፈጸመው ኢሰብአዊ ዘረፋ፣ የሰው ሕይወት  ጉዳትና መፈናቀል ብዙዎችን ያሳሰበ መሆኑን በመጥቀስ “ፈተና ላይ ለወደቀው ኢትዮጵያዊነት አዲስ አበቤዎች የመታደግ ሚና እንዳላቸውና ሌሎች ደግሞ ወራሪዎችና ባዕዶች እንደሆኑ ያመለክታል…” ብለው ገልጸዋል፡፡ አክለውም “የቡራዩ ጉዳይ  በብዙ ሚሊዮን የሚደርስ መፈናቀል ከደረሰበት የኦሮሞ ተፈናቃዮች እኩል ወይም ይበልጥ…እንዴት ትኩረት አገኘ” ብለው ተደንብቀዋል፡፡ አዲስ አበባ ርዕሰ ከተማ መሆኑን […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረማርቆስ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተደረገ:: ሰልፈኞቹ መንግስት ለወልቃይትና ራያ የማንነት ጥያቄዎች ምላስ እንዲሰጥ የሚጠይቁ መፈክሮችን ከማሰማታቸውም በተጨማሪ ደጋ ለተጋረጠባቸው ለጣናና ለላሊበላ ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል:: በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በአፋር ክልል የሚደረገውን የሰብ አዊ መብት ጥሰት ያወገዙ ሲሆን የአፋር ደም ደሜ ነው የሚል መፈክር ይዘውም ነበር:: በተመሳሳይም በፍኖተ ሰላም ሰላማዊ ሰልፍ […]

ፕሮፌሰር መረራ ‹‹የጠመንጃ ፖለቲካ ማብቃት አለበት›› አሉ

$
0
0
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የጠመንጃ ፖለቲካ መብቃት እንዳለበት አሳሰቡ፡፡ ፕሮፌሰሩ ሲናገሩ ‹‹ይህ የጠመንጃ ፖለቲካ መብቃት አለበት፡፡ ደርግ 17 አመት በጠመንጃ ገዛ፣ የአንድ ትውልድ ልጆችን ገድሎ መጨረሻ ራሱም ተዋረደ፡፡ ኢህአዲግም በ27 አመታት ያንኑ ሞከረ፡፡ ህዝብን ዘላለም በጠመንጃ መግዛት አትችልም፡፡ ህዝብን የምትመራበት የተሸለ ልማትንና ብልፅግናን የምታመጣበት የተሻለ ህዝባዊ አስተዳደር የምታሰፍንበት መንገዶች አሉ፡፡ ውድድሩ ካለ እዚህ ላይ መወዳደር ነው፡፤ […]

ለ18 አመታት ያህል በትግራይ ክልል ታስሮ የቆየው ካሳሁን ሲሳይ ‹‹በትግራይ የሚታሰር አማራ የከፋ ግፍ ይፈፀምበታል›› አለ

$
0
0
በጎንደር ወልቃይት ተወለልዶ ያደገው ሲሳይ በአዲስ አበባ ከሚታተመው ጊዮን ከተባለው መፅሄት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የታሰረው መስከረም 11 ቀን 1986 እንደነበር አስረድቷል፡፡ መጀመሪያ በትግራይ ሽሬ ከተማ ከጓደኛው ጋር መታሰሩን የገለፀው ሲሳይ ጓደኛው ከአምስት አመት እስር በኋላ እዛው እስር ቤት መሞቱን ገልፆዋል፡፡ ስለጓደኛው አሟሟት ተጠይቆም፡- ‹‹ታሞ ቢሞትም ለህመሙ መንስኤ የሆነ መድሃኒት ሰጥተው የገደሉት ግን ወያኔዎች ናቸው፡፡ በመድሃኒት […]

የቀድሞው የፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ታሠሩ |ቀድሞው የማእከላዊ ምርመራ ምክትል አዛዥ እየታደኑ ነው

$
0
0
ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከዘይኑ ጀማል ቀደም ብሎ ለቀናት ፌዴራል ፖሊስ አዛዥ ሆነው ተሹመው የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ታሰሩ:: ትንናት የታሰሩት የጦር መኮንኖች ቁጥር ወደ 50 ያደገ ሲሆን ከሃገር ያመለጡ እንዳሉም ተዘግቧል:: ካፒታል የ እንግሊዘኛው ጋዜጣ ምንጮቼ ነገሩኝ ሲል እንደዘገበው አቶ ያሬድ ዘሪሁን ታስረው እየተመረመሩ ይገኛሉ:: አቶ ያሬድ ከተሾሙ በኋላ ወዲያውኑ ከኃላፊነታቸው […]

ጎንደር ሕብረት የቀረበበት ቅሬታ እና የአዲሱ ሊቀመንበር ምላሽ

$
0
0
– በታጋዮችና በሌሎችም ስም የተሰበሰበው ገንዘብ የት ገባ? – ጎንደር ህብረት እና አ. ግንቦት ምን እና ምን ናቸው? – የቅማንት ኮሚቴን ይረዳ ነበር? – የልማት ወይስ የፖለቲካ ድርጅት? – ጎንደር ሕብረት እና የአማራውን እንቅስቃሴ ሌሎችንም አዲሱ ሊቀመንበር ተጠይቀዋል ፤ ይመልሳሉ ጎንደር ሕብረት የቀረበበት ቅሬታ እና የአዲሱ ሊቀመንበር ምላሽ

የታሰሩት ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የደህንነቶች ቁጥር 126 ደረሰ |ጌታቸው አሰፋ የ እስር ማዘዣ ወጦበታል

$
0
0
ባለፉት ሦስት ቀናት ከየአቅጣጫው ታፍሰው ሰለታሰሩት ባለስልጣናት ቁጥር 126 አካባቢ መድረሱ ተገለጸ:: በታሰሩት እና እየተፈለጉ ባሉት የጦር መኮንኖች እና ባለስልጣኖች ዙሪያ በዛሬው ዕለት በቢሯቸው መግለጫ የሰጡት የፌዴታል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ እንደገለጹት እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት በጥቅሉ 126 አካባቢ ናቸው፡፡ ከእነዚህም 63 በሽብር ድርጊት፣ 27 በሙስና፣ 36 ደግሞ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ናቸው። ከነርሱ […]

ሀይሌ ገብረስላሴ ስልጣን ለቀቀ

$
0
0
በተለያየ ጊዜ ተቃውሞው የበረታበት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ስልጣን መልቀቁን አስታወቀ፡፡ ዛሬ በቢሮው መግለጫ የሰጠው ሀይሌ ላለፉት ሁለት አመታት አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑን ሲመራ እንደቆየ ገልፆ፣ በእነዚህ አመታት ውስጥ የተለያዩ ከበድ ያሉ ችግሮችን ከስራ አስፈፃሚው ጋር በመሆን ሲፈታ እንደቆየ አስረድቷል፡፡ ‹‹በተለያዩ ወቅቶች የፌዴሬሽናችንን የአሰራር ችግሮችን አንዳንድ ግለሰቦች ትልልቅ ተቋማትን መከታ አድርገው የፌዴሬሽኑንና የአለም አቀፍ አትሌቲክስ መርሆዎችን ለማስቀልበስ ጥረት […]

ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ የህግ የበላይነት ከሌለ ሁሉም እያዘዘ የሚኖርበት ስርአት ይፈጠራል አሉ

$
0
0
የቀድሞዋ የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኛ፣ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ አመራርና የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ መስራችና መሪ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ለንባብ ከበቃው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ሰፋ ያለ ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡ በዚህ ቃለምልልስ ከሌሎቹ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ዘግየት ብለው ለምን እንደመጡ ሲጠየቁ፡- ‹‹እኔ የዚህ አገር ለውጦች መታየት ከጀመሩ ወዲህ ሁልጊዜ ወደዚህ መምጣት እፈልግ ነበር›› ካሉ በኋላ ያለባቸው […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live