Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አንድ አገር ታሪክ የሚሰራበት መድረክ እንጂ የጦርነት መድረክ አይደለም |ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

$
0
0
2018 መግቢያ ያለፉትን አርባ ዓመታት በአገራችን ምድር በፖለቲካ ስም የተፈጸመውን ግፍና አገርን የማፈራረስ ድርጊት ስንመለከት በአብዛኛው የፖለቲካ ተዋናይ ነኝ ባይ መንፈስ ውስጥ የተቀረጸው አርቆ-አስተዋይነት ሳይሆን ስሜታዊ አስተሳሰብ እንደሆነ መገንዘቡ ከባድ አይሆንም። በተለይም የግዴታ ስልጣን ላይ መውጣት አለብን ብለው በደመ-ፍላት ይታገሉ የነበሩና አሁንም የሚታገሉ ኃይሎች የተወሰነውን የህብረተሰብ ክፍል፣ በተለይም ወጣቱን በመፈክር ጋጋታና በጥላቻ መንፈስ በመመረዝ በቀላሉ […]

ዶ/ር አብይ አህመድ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጡ

$
0
0
የቀድሞው ኦህዴድ የአሁኑ ኦዴፓ የፖሊት ቢሮ አባልና የኢህአዲድ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው ተሾሙ፡፡ በመሆኑም ለስድስት ወራት ያህል የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከፍተኛ አማካሪ ሆነው የሰሩትን አቶ ፍፁም አረጋን ተክተዋቸዋል፡፡ ለተለያዩ ሚዲያዎች የመረጃ ምንጭ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ፍፁም ቀድሞ ወደነበሩበት የፌዴራል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቢሯቸው ተመልሰዋል፡፡ አቶ […]

በነብይ እዩ ጩፋ መድረክ ላይ የታየውና አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው የመከላከያ ሰራዊት አባል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡

$
0
0
በነብይ እዩ ጩፋ መድረክ ላይ የታየውና አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተው የመከላከያ ሰራዊት አባል በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡፡ ሸገር ታይምስ መፅሄት በድረ ገፁ ዛሬ እንዳቀረበው መረጃ የመከላከያ ሰራዊት አልባሳትን ባልተገባ መንገድ በተጠቀሙት ላይም ምርመራ ተጀምሯል፡፡ ከነብይ እዩ ጩፋ ጋ በተገናኘ የሰራዊቱን አልባሳት እና መለዮ በመጠቀም ያልተገባ ተግባር ፈፅመዋል በተባሉ በሰራዊቱ ውስጥ ባሉ እና በተሰናበቱ የቀድሞ አባላት ላይ […]

ወሳኙ የአሜሪካ ምርጫ –“አሜሪካ መንታ መንገድ ላይ ናት”ኦባማ |“ሕዝቦች ሆይ! ጨዋታ አይደለም የያዝነዉ”ትራምፕ

$
0
0
«የግማሽ ዘመን ምርጫ» በሥልጣን ላይ ላለዉ ፕሬዝደንት እና ፓርቲ እንደ ሕዝበ-ዉሳኔ የሚቆጠር ነዉ።ከ1932 (እ.ጎ.አ) ወዲሕ በተደረጉ ምርጫዎች በስልጣን ላይ ያለዉ ፕሬዝደንት የሚወክለዉ ፓርቲ በምክር ቤቶች አብላጫ መቀመጫ ያገኘዉ አምስቴ ብቻ ነዉ።የነገዉ ስድስተኛ ይሆን ይሆን? ነጋሽ መሐመድ ከጀርመን ድምጽ ራድዮ ያሰናዳውን ዘገባ ይመልከቱ

ሸገር ደርሶ መልስ ፫

$
0
0
ክንፉ አሰፋ ታማኝ በየነ ይዟት የመጣትን ላፕቶፕ እንደያዘ ወደ አሜሪካ ተመልሷል። ያልተቋጨ የትግል ምዕራፍ ቢኖር እንጂ፤ እሱም እንደ አጅሬ ኖት-ቡኩን ለቲም ለማ ያስረክብ ነበር እያሉ ያራዳ ልጆች ሲቀልዱ ሰማሁ። ትልቁ ችግር መፍትሄ ያገኘ ቢመስልም፤ በትናንሾች የሚፈጠሩ ጥቃቅን ችግሮች ገና አልተፈቱም። እርግጥም ትንሽ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ከባድ ችግርን መፍታት ቀላል ነው። እነኚህ ትናንሽ ቀውሶች ተጭነው የመጡት […]

ጥብቅ መረጃ –የቀድሞው ሜቴክ አውሮፕላን ገዝቶ ነበር፣ አሁን የት እንዳለ አልታወቀም

$
0
0
ጥብቅ መረጃ – የቀድሞው ሜቴክ አውሮፕላን ገዝቶ ነበር፣ አሁን የት እንዳለ አልታወቀም

ሕወሓት የቅማንትን ካባ ለብሶ በመተማ ጥቃት አደረሰ

$
0
0
ሕወሓት ታላቋን ትግራይ ለመመስረት የቅማንትን ሕዝብ ከአማራ በመነጠል ትግራይን ከቤኒሻንጉል በማገናኘት አባይን ለትግራይ እንደ ኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭነት መሬቱን ደግሞ ለልማት መጠቀም ይፈልጋል ሲሉ የቀድሞው የየጎንደር ሕብረት ሊቀምንበር አቶ አበባ ንጋቱ ሚኒስታ ውስጥ በተደረገ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ በጥናት የተደገፈ መረጃ አቅርበው ነበር:: ሕወሓት የቅማንት ማንነት በሚል በውጭ ሃገር የሚገኙ የቅማንት ተወላጆችን በገንዘብ በመግዛት እንዲሁም የዳኡድ ኢብሳ […]

ፓርላማው አዲስ ታሪክ ሰራ

$
0
0
በዛሬው እለት በተደረገው የፓርላማው ውሎ እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍተኛ ክርክርና ሙግት ተደርጎበታል፡፡ ሙሉ በሙሉ ኢህአዴግ በተቆጣጠረው ፓርላማ የተፈጠረው ጉዳይ በርካቶችን ያስገረመ ሆኗል፡፡ የተወካዮች ምክር ቤቱ በዛሬ ጥቅምት 27 ቀን 2011 አ.ም ስብሰባው በምክር ቤቱ የነበሩት 20 ቋሚ ኮሚቴዎች ወደ 10 ዝቅ እንዲሉ በቀረበለት ሃሳብ ላይ ወደሁለት ሰአት ያህል ከፍተኛ ሙግት አድርጎ ሃሳቡን ተቀብሏል፡፡ ቢሆንም […]

በጎንደር እጃቸው የያዙት ቦምብ ይሰራል አይሰራም በሚል ሲከራከሩ ፈንድቶ አራት ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ

$
0
0
በሰሜን ጎንደር ደባርቅ ወረዳ አደባባይ ፅዮን ቀበሌ ኤፍ ዋን የተባለ ቦንብ በግለሰብ ቤት ሲነካኩ በመፈንዳቱ 4 ሰዎች የሞት አደጋ 2 ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የደባርቅ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ገለፀ፡፡ በአደጋው የእግርና የእጅ ጉዳት የደረሰባቸው አቶ አወቀ ሲሳይ ለደባርቅ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንደገለጹት አደጋው ከደረሰበት ቤት ድግስ ለመብላት እንደተሰባሰቡና በጨዋታ መሃል የቤቱ ባለቤት […]

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደሮችን ሾመ

$
0
0
የለውጥ እርምጃ እየሰራሁ ነው ያለው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው እለት ለአምስት አምባሳደሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡ ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፣ አምባሳደር ማህሌት ኃይሉ፣ አምባሳደር ዶ/ር ቦጋለ ቶሎሳ፣ አምባሳደር ነጋ ፀጋዬ እና አምባሳደር ደዋኖ ከድር መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ገልጻል፡፡ በሹመቱ መሰረትም፡- አምባሳደር ወይንሽት ታደሰ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ጉዳዮች ቋሚ ተጠሪ አምባሰዳር ማህሌት […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የአለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ አደገኛው ቢጫ ወባ 10 ሰው መግደሉን ገለፀ የአለም ጤና ድርጅት ትላንት ሰኞ ባወጣው መግለጫው ቢጫ ወባ በደቡብ ምእራባዊ ኢትዮጵያ ክልል 10 ሰው መግደሉን አስታወቀ፡፡ በመግለጫው 35 ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸው እንደተጠረጠረ ገልፆ ሁኔታውን ለመቆጣጠር ከ1 ሚሊዮን በላይ መከላከያ ክትባት እንደሚያስፈልግ አስረድቷል፡፡ ይህ የወባ ወረርሽኝ የተቀሰቀሰው በወላይታ ዞን ነው ተብሏል፡፡ እንደድርጅቱ መግለጫ […]

ህዝብንና አገርን በሚያተራምሱት ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ፈጣን ፍርድን ይሻል!!! (ከተማ ዋቅጅራ)

$
0
0
መንግስት በህዝብና አገርን ለከፋ ትርምስና እልቂት የዳረጉትንና እየዳረጉ ያሉትን በአፋጣኝ ከያሉበት ሰብስቦ ህግ ፊት አቅርቦ ህጋዊ እርምጃ በአፋጣኝ ካልወሰደ ገዳዮችና ዘራፊዎቹ በሚፈጽሙት አደገኛ ነገር  በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰላም ሁኔታ ወደከፋ ደረጃ መድረሱ የማይቀር ነው። ሌላው ደግሞ የከፋ ነገር የሚከሰተው የኢትዮጵያ ህዝብ ያመነውን መንግስት በቸልተኝነቱና ወንጀለኞችን እንደፈለጉ ሲንቀሳቀሱ እና አገርንና ህዝብን ሲያተራምሱ ዝም ማለቱ መንግስት መፍቴ […]

ለክቡር የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶር አብይ አህመድ – የኢትዮጵያ ክፍላተሃገር ህብረት በአውሮፓ

$
0
0
ከስምንት ወራት ወዲህ የጠ/ሚኒስትርነቱን ቦታ ከያዙ ጀምሮ የወሰዷቸውን ቀና  እርምጃዎች በአድናቆት እንከታተላለን፣እንደግፋለንም።ባለፉት መሪዎች ያልተለመደ እንደዚህ ሕዝብ መካከል ተገኝቶ፣ከሕዝብ ጋር ለመወያዬት የሚያደርጉት  ቀና ፍላጎት በመሪና በተመሪ መካከል የነበረውን የእሩቅ ግንኙነት እንደሰበረው ማስረጃ ነው።በመቀራረብና በግልጽነት የአገርን ጉዳይ አንስቶ መወያዬቱ ለይስሙላና ለዝና ሳይሆን የሚቀርቡት አስተያዬቶች ቦታና ትርጉም ይኖራቸዋል ብለን እናምናለን። ኢትዮጵያ አገራችን ለአያሌ ዘመናት ስርዓት መሥርታ ስትተዳደር የቆዬች […]

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አርብ አማራ ክልል ናቸው

$
0
0
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዓርብ ጎንደር ከተማ የሚገቡ ሲሆን፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ያደርጉላቸዋል። በቆይታቸውም በጎንደር እና አካባቢው የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችን እና የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ፥ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ሞገስ ተናግረዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሃገር ደረጃ የተጀመረውን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ታምኖበታል። በጎንደር ከተማ በርካታ ኤርትራውያን […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ዕሁድ ህዳር 2/2011 ዓ.ም. ሰላማዊ ሰልፍ ሊያካሂዱ ነው፡፡ ላቀረቡት ጥያቄም ከተማ አሥተዳደሩ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ በጣና ሀይቅ እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ የተጋረጠውን አደጋ አስመልክቶ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ከሰላማዊ ሰልፉ ዓላማዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ የማንነት ጥያቄዎች በህጋዊ መንገድ እንዲፈቱም መልዕክቶች እንደሚተላለፉ ይጠበቃል፡፡ – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና […]

አብን ቢሮ የተጠለሉት የወልቃይት ተፈናቃዮች በፖሊስ ተከበናል ሲሉ ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቀረቡ፣ ፖሊስ በበኩሉ ‹‹የከበባኳቸው ለደህንነታቸው ነው›› አለ

$
0
0
ከወልቃይት ተፈናቅለው ለፌዴራል መንግት ባለስልጣናት አቤቱታ ለማቅረብ አዲስ አበባ የሚገኙት ግለሰቦች በፖሊስ ተከበናል አሉ፡፡ ዛሬ ለንባብ የበቃው ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው እነዚህ ‹‹የአማራ የማንነት ጥያቄ አንስታችኋል›› ተብለው ከቀዬአቸው ተባረው አዲስ አበባ ከተማ የመጡት 180 ሰዎች መንቀሳቀስ እንዳይችሉ በፖሊስ መታገታቸውን ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ አቤቱታቸው ከትውልድ ቄዬአቸው በመባረራቸው ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ የፌዴራል መንግሥት ዕርዳታና ዕገዛ እንዲደረግላቸው ለማመልከት፣ […]

የአማራ እና የትግራይ ክልል በመግለጫ በመጎሻሸም ቀጥለዋል

$
0
0
የደብረጽዮን ገብረሚካኤል የትግራይ ክልል አስተዳደር ትናንት “የተለያዩ ኣጀንዳዎች በመቅረፅ በትግራይ ህዝብ ሰላምና ድህንነት በማወክ ዙርያ የሚደረግ ዘመቻ ኣሁንም ሳያቋርጥ እንዲቀጥል እየተደረገ ነው፡፡ በትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ እጅን ከማስገባት በተጨማሪ ከትግራይ ጋር የሚያስተሳስሩ መንገዶች በመዝጋት እና የትግራይን መሬት በሃይል ለመውረር መፈለግ የመሳሰሉ ያረጁና ሃሏ ቀር ኣስተሳሰቦችና ክፉ ተግባራትም እየታዩ ናቸው፡፡” በሚል በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራ ክልል […]

በከንባታ ጠንባሮ ዞን ተቃውሞ ያነሱ ወገኖች ወደ አዲስ አበባ እና አርባ ምንጭ የሚወስደውን መንገድ ዘጉ

$
0
0
በደቡብ ክልል፤ ከከምባታ ጠምባሮ ዞን ወደ አዲስ አበባ የሚያቀናው መንገድ ዛሬ ዝግ ሆኖ ዋለ:: የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች ሕዝቦች ክልል መንግሥት ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ ላይ በሐዋሳ ያከናወነው 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የወረዳ ጥያቄ ተነስቶ፤ ለተወሰኑ ቦታዎች ሲፈቀድ ለ እኛ አልተፈቀደም በሚል ነዋሪዎቹ ተቃውሟቸውን እንደጀመሩ የአካባቢው የዜና ምንጮች ይገልጻሉ:: በከባታ ጠንባሮ ዞን ባሉት 7 ከተሞች […]

ዶ/ር አብይ ከከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ተወያዩ

$
0
0
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ከክፍለ ጦር አዛዦች በላይ ካሉ ወታደራዊ አመራሮች ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። በዚሁ ውይይት ወቅት መከላከያ ሰራዊትን በሁሉም መስክ ብቁ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት በከፍተኛ ግለት እንደሚቀጥል አስታውቀው ይህም ከለውጡ ጊዜ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው ዘርፉን ዘመናዊ፣ ብቁ እና ውጤታማ ለማድረግ የሚከናወን ጥረት አካል መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በቅርቡ በተወሰኑ ወታደሮች የተከሰተው ከወታደራዊ […]

ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ያቀኑት የሃገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ

$
0
0
(BBC) በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የጸጥታ መደፍረስ በሽምግልና ለመፍታት ወደ ስፍራው አቅንተው የነበሩ የሃገር ሽማግሌዎች ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ቢቢሲ ዘገበ:: ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ካቀኑት የሃገር ሽማግሌዎች መካከል አንዱ የሆኑት ኢንጂነር መስፍን አበበ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ነጋዴዎች፣ አባ ገዳዎች እና የሃይማኖት አባቶች ከልዑኩ ቡድን አባላት መካከል ይገኙበታል። “አስቀድመን ከነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢ ዶሎ ከተሞች ነዋሪዎች ጋር ውይይት […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live