Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“ብአዴን ከዘበኝነት ወጥቶ ህዝብን ያገለግላል” -የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

$
0
0
ብአዴን ታሪካዊ ውሳኔ አሳልፍበታለሁ ያለውን ጉባኤ በዛሬ ዕለት በባህርዳር ከተማ ጀመረ:: በዚህ በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የአማራን ህዝብ ችግር ለመፍታት እና የአገሪቱ ለውጥ በተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ ብአዴን በተሻለ ቁመና ላይ ይገኛል አሉ:: “የጨለማው ዘመን ተዘግቶ ለህዝባችን አዲስ የተስፋ ፀዳል እንዲዲፈነጥቅ ብአዴን ከሌሎች የትግል አጋሮቹ ጋር ለውጡን በአግባቡ ለመጠቀም […]

የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው

$
0
0
ታምሩ ጽጌ/ ሪፖርተር ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ፣ የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመግደል መሆኑን በክሱ አስታውቋል፡፡ በቦምብ ጥቃቱ ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች አቶ […]

የአንድነት ፖለቲካው መልስ ሊሰጥባቸው የማይፈልግባቸው የአማራው ጥያቄ እና ወቅታዊ ጉዳይ |ከዶ/ር ሰማኽኝ ጋሹ ጋር ያደረግነው ውይይት

$
0
0
የአንድነት ፖለቲካው መልስ ሊሰጥባቸው የማይፈልግባቸው የአማራው ጥያቄ እና በወቅታዊ ጉዳይ | ከዶ/ር ሰማኽኝ ጋሹ ጋር ያደረግነው ውይይት

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
ላለፉት 8 ዓመታት በስልጣን ላይ የቆየው የቢርመጂ ቱለማ ገዳ ስልጣኑን ለሜልባቲ ገዳ አስረክቧል፡፡ የስልጣን ርክክብ ስነ ስርዐቱ ባህላዊ ክዋኔ በነገው ዕለት ይካሄዳል። 8 ዓመታት አባ ገዳ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት የክቡር ዶ/ር አባገዳ በየነ ሰንበቶ መሆናቸው ይታወሳል:: _ አስር ያህል የኤርትራ ካቢኔ ሚንስትሮች ሀገራቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈራረመቻቸውን ስምምነቶች አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተሰማ:: […]

ተሰናባችሁ አቶ ኩማ ደመቅሳ የአዲስ አባበ ማስተር ፕላን ተመልሶ ሊመጣ ይችላል ብለው እንደሚያስቡ ተናገሩ

$
0
0
በኦሮሚያ ውስጥ ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሶ የነበረው አዲስ አበባን በዙሪያዋ ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር ያስተሳስራል የተባለው ማስተር ፕላን ተራማጅና አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል ብለው እንደሚያስቡ ኦህዴድ ሊቀ መንበር እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ ለቢቢሲ ተናገሩ። ባለፈው ሳምንት ኦዴፓ (የቀድሞው ኦህዴድ) በጅማ ከተማ ድርጅታዊ ጉባኤውን ባደረገበት ወቅት ተሳታፊ የነበሩት አቶ ኩማ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት […]

ለማ መገርሳ ለኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች ማሳሰቢያ ሰጡ

$
0
0
በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የኢሬቻ በዓል የፊታችን እሁድ በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) በድምቀት ይከበራል:: በዓሉን በማስመልከት የ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በዓሉ ከምንግዜውም በላይ ባህሉን በጠበቀ መልኩ በማክበር በአለም አቀፍ ትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል {UNESCO} ቅርስነት ለማመዝገብ እየተሰራ መሆኑን ገለጹ:: ፕሬዚዳንት ለማ ለ ኢሬቻ በዓል የሚወጡ ሰዎች ፖለቲካን […]

የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው

$
0
0
በኢትዮጵያ ታትሞ የሚወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ፣ የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመግደል መሆኑን በክሱ አስታውቋል፡፡ በቦምብ ጥቃቱ […]

ዶ/ር ዓብይ አህመድ “ሰላማችንን ማስጠበቅ በእጃችን ነው”አሉ

$
0
0
በመጨረሻው ሰዓት በመጣ የጉዞ ስረዛ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 73ኛ ጉባዔ ላይ ሳይገኙ የቀሩት ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ነገ በድምቀት የሚከበረውን የ ኢሬቻ በዓልን በማስመልከት መልዕክት አስተላለፉ:: “የኦሮሞ ህዝቦች እንኳን በፍቅርና በአንድነት ለሚከበር የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን” በማለት ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መል ዕክታቸውን ያስተላለፉት ዶ.ር ዓብይ “ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አካልና የምስጋና የሰላም ቀን […]

የፌዴራል ፖሊሱ ኮሚሽነር ጀነራል ዘይኑ ጀማል ስልጣን ወንበር እየተነቃነቀ ነው

$
0
0
በዶ/ር ዓብይ አህመድ የስድስት ወር የስልጣን ዘመን ሦስተኛው የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽነር ጀነራል የሆኑት ዘይኑ ጀማል ከስልጣናቸው ሊነሱ እንደሚችሉ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለጹ:: ለረዥም ጊዜ በኬንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ በስለላና በሌሎች ሥራዎች እንደቆዩ የሚነገርላቸው አቶ ዘይኑ ከኬንያ መጥተው በዶ/ር ዓብይ አህመድ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራልነት መሾማቸው ይታወቃል:: እንደዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ስልጣናቸውን የሚያጡት በሃገሪቱ […]

በኦነግ ስም በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ጥቃት የተነሳ ከቤኒሻንጉል ከ13 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች እና አማራዎች ተፈናቀሉ

$
0
0
መንዲ ውስጥ እርቅ ላይ ቆይተው ወደ አከባቢያቸው ሲመለሱ በአራት የቤንሻንጉል ጉምዝ የካሚሼ ወረዳ ኃላፊዎች ላይ ግድያውን የፈጸሙት በኦነግ ሰራዊት ስም የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች መሆናቸውን የኦዴፓ የገጠር አደረጃጀት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታወቁ:: ይህንን ተከትሎም ወረዳዋ ወደ ቀውስ መግባቷን እና ይህንን ፈርተው ብዙ ዜጎች መፈናቀላቸውን አቶ አዲሱ አስታወቁ:: እነዚህ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ባለስልጣናትን መገደል ተከትሎ በካማሸ ዞን […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ወተር ፓርክ ሊከፈት ነው:: ይህ ወተር ፓርክ በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ሲሆን ባለቤትነቱም የኩሪፍቱ ሪሶርት እና ስፓ እንደሆነ ያገነኘው መረጃ ያመለክታል:: በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ ወተር ፓርኮች እጅግ ታዋቂና አትራፊ እንደሆኑ ይነገራል:: በተለይም ለልጆች መጫወቻና ለቫኬሽን ተመራጭ ቦታዎች ናቸው:: __ ከሁለት ቀናት በፊት ያለመከሰስ መበታቸው የተነሳው የድሬደዋ አስተዳደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ የነበሩት […]

…እያቃሰተ ነው |በመሳይ መኮንን |በጽሁፍና በቪዲዮ የቀረበ

$
0
0
የብሄር ፖለቲካ እያቃሰተ ይመስላል። ትንፋሹ ቁርጥ ..ቁርጥ ሲል ይሰማኛል:: በሞት መልዕክተኞች ተከቦ ወደመቃብሩ እያዘገመ ይታየኛል:: ከአዲስ አበባ እየተመለሱ ያሉ ሰዎች እንደሚነግሩኝ መሬት ላይ ያለው ዕውነት በዚህ መንደር ከሚናፈሰው የተለየ ነው። የብሄር ቡድኖች ጉልበታቸውን የሚያሳዩት በአብዛኛው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ለመሆኑ የተለያዩ አስረጂ ምሳሌዎችን እየጠቀሱ አጫውተውኛል። መሬት ላይ ያለው ሀቅ በእጅጉን ይለያል። መሬት ላይ የብሄር ቡድኖች ሜዳ […]

“እርካብና መንበር” –ሙሴ እና ዐብይ |ክንፉ አሰፋ |በቪድዮና በጽሁፍ የቀረበ

$
0
0
ሳይታሰብ ብልጭ ብላ እንደገና ድርግም ያለችው የለውጥ ጭላንጭል፣ በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ ተቋጥራ የነበረች የተስፋ ስንቅንም ይዛ ጭልጥ ያለች ይመስላል። አዕምሯችን ይህንን ቅጽበታዊ ለውጥ ለመቀበል ቢቸግረውም፣ በሌላኛው መነጽር ስንመለከተው ግን ይህ ሊሆን ግድ ይላል። በተዓምር የቆመች የዚህች የደም ምድር እጣ ፈንታን መጽሃፉ በአንዲት ምዕራፍ ውስጥ እንደቋጫት እንገነዘባለን። አይናችንን በደንብ ካልገለጥን ግን ነገሩን ላናየው እንችላለን። ስለዚህ መፅሐፉን […]

የአብይን ቅያስ መቀልበስ? ሳዲቅ አህመድ

$
0
0
የኢትዮጵያ ህዝብ 27 አመታት የቀፈደደውን ህወሃታዊ ክሽፈት ከጫንቃው ላይ ለማንሳት የለውጥ ሐዋሪያ ብሎ ላመናቸው አዲስ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሁለንተናውን አሳልፎ ሰጠ። በአገሪቱ ዉስጥ የመጣው ድንገተኛ ለውጥ ያልተጠበቀ ነበር።ህዝቡ ለውጡ የፈጠረበትን ሐሴት ተቆጣጥሮ ተስፋን መሰነቁን ቀጠለ። ይህንን ለዉጥ ለማሰናከል የሚጥሩ ሐይላት መታየታቸው ለዉጡ ላይ የተጋረደ መሰናክል ቢመስልም፤ በህወሃት ላይ ያመጸው ህዝብ መገለጫ የሆኑት ዶ/ር አብይ ሆኑ የኢትዮጵያ […]

አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
በሚኒሶታ ለመጀመሪያ ጊዜ 7 አብያተ ክርስቲያናት በአንድነት የመስቀል ደመራ በዓልን አከበሩ:: ውጭ ሃገር ያለው እና ሃገር ቤት የሚገኘው ሲኖዶስ አንድ ከሆነ በኋላ በሚኒሶታ 3 ቦታ ተከፍለው የቆዩት አብያተ ክርስቲያናቱ ባለፈው ሳምንት የአንድነት ጉባኤ ካደረጉ በኋላ በትናንትናው ዕለት የደመራውን በዓል በጋራ አክብረዋል:: በሚኒሶታ ሴንት ፖል በሚገኘው ትልቁ ፌለን ፓርክ በተካሄደው የደመራ በዓል ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮያውያን, […]

በቤንሻንጉልና ግሙዝ ክልል የተጠናከረ ፍተሻ እየተደረገ አለመሆኑ ተጠቆመ

$
0
0
ስጋታቸውን ለዚህ ዜና ዘጋቢ አባይ ዘውዱ ነዋሪዎች እንደገለፁት በተለይ በመተከልና በከማሸ አካባቢዎች ተገቢ የሆነ የፍተሻ ስራ እየተሰራነው ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል። በአካባቢው ያሉ ህገ ወጦች”ቀስት”የተባለ ባህላዊ ድምፅ አልባ መሳሪያን የሚያዘጋጁት ከከተማ በመኪና እየተጫነ በሚሄድ 15 ቁጥር ሚስማር መሆኑን ጠቁመዋል። በሚያዘጋጁት ድምፅ አልባ መሳሪያ”ቀስት” ተጠቅመው አገር ሰላም ብሎ በርሀ ላይ በግብርና ስራ የተጠመደውን ንፁህ ገበሬ ሳያስበው ደርሰው […]

አሁን የደረሰን ዜና

$
0
0
በመቀሌ እየተካሄደ ያለው የሕወሓት 13ኛ ጉባኤ የስብሃት ነጋ ክንፍ ነው ከተባለውን ቡድን ውስጥ አስራ ሁለቱን ከማዕከላዊ ኮሚቴው በክብር አሰናብቻለሁ አለ::  ከነዚህ መካከል ከአዜብ መስፍን ጋር አብሮ ታግዶ የቆየው የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባይ ወልዱ ይገኝበታል:: ሌሎቹም 2. ቁዱሳን ነጋ 3.ጎበዛይ ወልደኣረጋይ 4.. ኪሮስ ቢተው 5. ብሔራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ  የነበረው ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ […]

የእሬቻ በዓል በሰላም ተጠናቀቀ

$
0
0
 “ኢሬቻ ለፍቅርና ለአንድነት” በሚል መሪ ቃል  በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሰዲ በዛሬው ዕለት በድምቀት የተከበረው የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል አከባበር በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ሲዳማ ብሄር የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች፣ የጋሞ ብሔረሰብ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ የሀዲያ እና የኮንሶን ጨምሮ ሌሎች የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች ታድመዋል:: የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል አለማየሁ እጅጉ […]

ብአዴን ሕወሓት ያወጣለትን ስያሜ ቀየረ 

$
0
0
ኢህዲን የነበረውን ስሙን በሕወሓት ስም አውጪነት ወደ ብአዴን ቀይሮ የቆየው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እየተካሄደ ባለው ጉባኤው ይህን ህወሓት ያወጣለትን ስያሜ ቀየረ:: ብአዴብ በባህርዳር እያካሄደ ባለው ጉባኤ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ  (አዴፓ) በሚል የቀየረ ሲሆን  የአርማ ማሻሻያም ማድረጉን የደረሰን መረጃ ይጠቁማል:: በዚህም መሰረት አርማው መደቡ ከላይ አረንጓዴ መሃል ላይ ጎህ ሲቀድ የሚኖር ቀለም (ቢጫ) ሆኖ ከግርጌ […]

የሀዋሳው ጉባዔ |ከመሳይ መኮንን |በቪድዮና በጽሁፍ የቀረበ

$
0
0
ረቡዕ በሀዋሳ የሚጀመረው የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ጉባዔ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የመወሰን ሁነኛ ተጽዕኖ አለው። ሶስቱ አባል ድርጅቶች በተናጠል ያደረጉትን ጉባዔ አጠናቀው ለሀዋሳው የሚወክሏቸውን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን መርጠዋል። ብአዴን እየተጠበቀ ነው። ከህወሀት በቀር ሶስቱ ድርጅቶች ከስያሜ ጀምሮ የተለያዩ ለውጦችን አድርገዋል። ከብሄር ጥብቆ ተላቀው ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን ዳርዳርታውን ጀምረውታል። ህወሀት ግን እዚያው ተቸንክሮ መቅረትን መርጧል። ደደቢት ላይ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live