Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ በቡራዩና አካባቢው የተፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት አስመልክቶ የተሰጠ የጋራ መግለጫ

$
0
0
ዲሞክራሲና ሽብርተኛነት የተለያዩና ተቃራኒ ናቸው   ቀን: መስከረም 13፣ 2011 ዓ.ም በአገራችን የፓለቲካ እንቅስቃሴ የዲሞክራሲውን ምህዳር ለማስፋት የሚደረገው ጥረት መልካም መሆኑ ባይካድም የህብረተሰቡን ሰላምና ህይወት የሚያናጋ መሆን የለበትም። የዲሞክራሲውን ምህዳር ለማስፋት የሚደረጉ ጥረቶችንና ተስፋ ሰጪ ጅማሮወችን ለመቀልበስ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ በተቃራኒው የቆሙ ኃይሎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ  የህብረተሰቡን ሰላማዊ ኑሮና ሕይወቱን አደጋ ውስጥ እያስገቡ ይገኛሉ።   […]

ዶ/ር አብይ አህመድ በአውሮፓ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ሊወያዩ ነው

$
0
0
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጥቅምት 21 እ.ኤ.አ አቆጣጠር ኦክቶበር 31, 2018 በአውሮጳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ሊወያዩ ነው:: ዶ/ር ዓብይ አህመድ ባለፈው ጁላይ መጨረሻ ወደ ሰሜን አሜሪካ መጥተው በዋሽንግተን ዲሲ; በካሊፎርኒያና በሚኒሶታ ከብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል:: አሁን ደግሞ በጀርመን የሚኖራቸውን ጉብኝት አስታኮ በአውሮፓ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ […]

በዘንድሮው የደመራ በዓል ላይ ፍተሻ እንደሚኖር ፖሊስ አስታወቀ

$
0
0
በአዲስ አበባ ከተማ በነገው ዕለት በሚካሄደው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ፍተሻ እንደሚኖር የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ:: ፖሊስ ይህን የማደረገው ለጥንቃቄ ስል ነው ብሏል:: “የመስቀል በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ ገብተናል:: በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ፣ የመንግስት ባለስልጣናት የውጪ ሀገር ቱሪስቶች የሚታደሙበት የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ፓሊስ ዝግጅቱን አጠናቋል:: በዓሉ በሰላም እንዲከበር ኮሚሽኑ […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሠራተኞች በዋስ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ተሰጠ:: የህዳሴ ግድብና የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ሠራተኞችን ለአድማ በማነሳሳት ተጠርጥረዋል:: የሥራ አድማ በማድረግና የኢኮኖሚ አሻጥር በመፍጠር ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት፣ በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ዘጠኝ ሠራተኞች እያንዳንዳቸው በ20 ሺሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ፣ ፍርድ ቤት ዛሬ መስከረም 15 ቀን 2011 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ:: ተጠርጣሪዎቹ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና የኢትዮጵያ […]

የአምባሰል (ጥረት)ጉድ

$
0
0
“የለውጡ ቀጣይነት ለአማራ ህዝቦች ተጠቃሚነትና ዲሞክራሲያዊ አንድነት ” በሚል መሪ ሀሳብ ብአዴን 12ኛው ድርጅታዊ ጉባኤውን መስከረም 17- ከፍቶ በመስከረም -21/2011 ዓ.ም እንደሚያጠቃልል ይጠበቃል:: 100% ማረጋገጥ ባይቻልም አቶ ደመቀ መኮንን በዶ/ር አምባቸው እንደሚተኩም እየተነገረ ነው:: በዚህ የብአዴን ታሪካዊ ስብሰባ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ዳግማዊት ሞገስም ወደ ድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴነት እንደምትገባ እየተነገረ ነው:: ከዚህ ውጭ ወሳኝ የሚሆነው […]

የነኦቦ በቀለ ገርባ መግለጫና አዲስ አበባ |ከአቻምየለህ ታምሩ

$
0
0
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደጻፍነው አዲስ አበባ ፊንፊኔ አይደለችም። ፊንፊኔ ወይንም ፍልውሃ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬም ድረስ የምትገኝ አንድ ትንሽ መንደር እንጂ በሁለንተናዊ መልኩ ሰፊና ግዙፍ ከሆነችዋ አዲስ አበባ ጋር አንድ አይደለችም። እነኦቦ በቀለ ገርባ በዛሬው መግለጫቸው አዲስ አበባን ፊንፊኔ አድርገው ለማቅረብ ቢኖክሩም ያቀረቧቸውን መንደሮች ስም ዝርዝር ለሰማ ግን እነ ኦቦ በቀለ አዲስ አበባ ማለት ፊንፊኔ […]

ዶ/ር ዓብይ አህመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት አስተላለፉ

$
0
0
ዶ/ር ዓብይ አህመድ የመስቀል በዓልን በማስመልከት ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልዕክት አስተላለፉ ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው እና በነገው ዕለት የሚከበረውን የመስቀል በዓል በማስመልከት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ አስተላለፉ::   ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች- እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! ለዘመናት ተቀብሮ የኖረው የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ከተጫነው ተራራ- ከተደበቀበት ስውር ስፍራ እና በክፋት ከተተወበት ምሽግ ጎራ ይወጣ ዘንድ በአማናዊ […]

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር በአዲስ አበባ ዙሪያ አቋማቸውን ገለጹ

$
0
0
በትናንትናው ዕለት 5 የኦሮሞ ድርጅቶች ተሰባስበው በአዲስ አበባ ላይ ስላነሱት ጥያቄ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አቶ ነአምን ዘለቀ ምላሽ ሰጡ:: “አዲስ አበባ የአዲስ አበባውያን ናት።” በሚል አቶ ነአምን ባቀረቡት ምላሽ “አዲስ አበባ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከሁለት ብሄሮች ወይንም ከዚያ በላይ የተወለዱ የአዲስ አበባ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን የአያት ቅደመ አያቶቻቸው እትብት ጭምር የተቀበረባት ዋና ከተማ ናት። አዲስ […]

ብአዴን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ሊመርጥ ነው

$
0
0
የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከሐሙስ መስከረም 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሚያካሂደው ጉባዔ፣ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለ ለውጥ በማዕከላዊ ኮሚቴው ላይ እንደሚያደርግ ተሰማ፡፡ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከመስከረም 17 እስከ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በሚካሄደው የብአዴን ጉባዔ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በአዲስና በወጣት አመራሮች ይተካሉ፡፡ በብአዴን ታሪክ ከፍተኛ ይሆናል ተብሎ […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
የዲቪ 2020 ምዝገባ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 3 ቀን 2018 እንደሚጀምርና ህዳር 6 ቀን 2018 እንደሚጠናቀቅ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ በርካቶች በየዓመቱ ይህንን ዕድል በመጠቀም ወደ አሜሪካ የሚያቀኑ ቢሆንም፣ በቅርቡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባስታወቁት መሠረት በዓመት ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሰዎች ብዛት ከ30,000 እንዳይበልጥ ውሳኔ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡ ይህ ውሳኔ የሚፈጸም ከሆነም፣ በአሜሪካ ታሪክ በዓመት ወደ አገሪቱ የሚገቡ ዝቅተኛው የስደተኞች […]

“ዶሮ ብታልም ጥሬዋን ነው”–ቬሮኒካ መላኩ

$
0
0
…… 1~ “Ulysses” በተባለው ምርጥ ልቦለድ ውስጥ ላቲቨን የሚባል ገፀ ባህሪ አለ። ይሄ ሰው ስለታሪክ የሚከተለውን ይላል << Histroy is a nightmare,which I am trying to wake> > ( ታሪክ ለመንቃት የምሞክረው ቅዤት ነው) በማለት ይገልፀዋል። ይሄ አባባል ለኦሮሞ ኤሊቶችና ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ተስማሚ አባባል ነው። ለኦሮሞ ኤሊቶች ታሪክ ቅዤት ብቻ ሳይሆን ሁሌ አልርጅክ እንደሆነባቸው ነው። […]

የነአቶ በቀለ ገርባ መግለጫ አድራሻው ለማን ነው? ከቀሲስ መልአኩ ባወቀ (ሎስ አንጀለስ)

$
0
0
እነ አቶ በቀለ ገርባ የሰጡትን መግለጫ አነበብኩ፤ የአንዳንዶችንም አስተያየት ሰማሁ። ምንም እንኳ አላማው ያነጣጠረው በኢሳትና በግንቦት ሰባት ላይ ቢሆንም እነርሱ የፈሩት፥ ግንቦት ሰባትን ወይም ኢሳትን አይደለም። የፍርሃታቸው አድራሻ ለምኒልክ ቤተ መንግሥት ለነ ዶክተር ዓቢይ ነው ። እነ አቶ በቀለ ገርባ የፈሩት ካልጠበቁት አቅጣጫ የወጣውን የኢትዮጵያዊነት እሳት ነው። ይህ አዲሱ የለውጥ አየር፥ ለብዙ ዓመታት የተለፋበትን የዘር […]

ሃገሪቱ የገባችበት አጣብቂኝ ሁኔታና ዶ/ር አብይ አህመድ |ውይይት ከአክቲቭስት ገረሱ ቱፋ እና ያሬድ ኃይለማርያም ጋር

$
0
0
ሃገሪቱ የገባችበት አጣብቂኝ ሁኔታና ዶ/ር አብይ አህመድ | ውይይት ከአክቲቭስት ገረሱ ቱፋ እና ያሬድ ኃይለማርያም ጋር

የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ እና የእኔ ዕይታ! |ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0
የኦሮሞ ድርጅቶች ነን ያሉ አምስት ድርጅቶች በኦሮሞ እሴቶችና ጥቅም ላይ በመመርኮዝ የኦሮሞን አንድነት በሚያንጸባርቅ እና እንደ በሚያደርጋቸው ፤ እንዲሁም በወቅታዊ አንገብጋቢ የፖለቲካ ጉዳዮች ናቸው ብለው ባመኗቸው ጉዳዩች ዙሪያ የጋራ ያሉትን አቋም ወስደዋል፡፡ ይህ አቋማቸው ግን በሁሉም ዘንድ በሁሉም ጉዳይ ሰምምነት ይፈጥራል ባይባልም- ጫጫታ ፈጣሪ እንደሆነ ግን የሚካድ አይደለም፡፡ በእኔ ዕይታ ይህ መግለጫ በኦሮሚያ ክልል ለሚንቀሳቀሱ […]

የመደመር ሙድ እና የጃዋር ካልኩሌተር |ክንፉ አሰፋ

$
0
0
ከኢትዮጲስ ጋዜጣ የመጀመርያ እትም ላይ የተወሰደ “ካልኩሌተሩን የሰራነው እኛ ነን!” ብሎናል ጃዋር መሓመድ፣ “ለመሆኑ አንተስ ተደምረሃል?” ተብሎ ለተወረወረበት ጥያቄ ሲመልስ። ሁለት አማራጭ ብቻ ያላት ቀላል ጥያቄ ነበረች። ጃዋር ግን ለጥያቄዋ ቀጥተኛ መልስ መስጠት አልፈለገም። “እኛ” የምትለዋን የብዝህነት ሃረግ ለግዜው ወደ ጎን እንተዋት። ግን፤ እንዲያው በደፈናው “ሁሉም ነገር በእኔ ሆነ – አንዳችም ያለእኔ የሆነ ነገር የለም!” […]

“ሀገርን ማን ይምራ?”

$
0
0
ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ የኢኮኖሚክስ መምህርና ጸሓፊ (ሸክም የበዛበት ትውልድ፡ 2009 እና የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ) በአንድ ወቅት በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሶስት ሰዎች ስለሀገራቸው ነባራዊ ኹኔታ እጅጉን ቢጨነቁና ቢጠባቸው እርስ በራስ ሲወያዩ የውይይታቸው ሂደት ሄዶ ሄዶ ጥያቄዎችን እንዲያነሡ ግድ አላቸው፡፡ “ሀገርን ማን ይምራ?”፤ “ሀገር በማን ብትመራ ውጤታማ ትኾናለች?”፤ “እንዴትስ ብትመራ ዘላቂና አስተማማኝነት ያለው ኹለንተናዊ ስኬትን […]

ኦሮማራው ‹‹እኔ›› |ከዮሐንስ መኮንን

$
0
0
(ክፍል አንድ) “””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””” ስለ ኦሮሞ ሞጋሳ (Moggaasa) የጻፍኩት አጭር ማስታወሻ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ግለታክ አካል ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቼ መልእክቱን ተጋርተውታል:: ስለ አባቴ በመተረክ የጀመርኩት ጽሑፍ የእናቴን ደግሞ እንድተርክ ገፋፍቶኛል፡፡ አሁን ደግሞ የራሴን ግለታሪክ ላካፍል ነው:: በፌስቡክ ገጽ የሚጋራ ጽሑፍ በጠባዩ አብዛኛው አንባቢ በሞባይሉ ገጽ (Screen) ስለሚያነበው ከሚገባው በላይ አጭር በመሆኑ ብዙ ጠቃሚ ታሪኮችን […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

$
0
0
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የመስቀል በዓል ስጦታ አብርክተውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ያበረከቱት የበዓል ስጦታም የሞተር ዊልቸው (በሞተር የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ወንበር) መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል። ስጦታውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ […]

በአዲስ አበባ ፖሊስ ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ከደመራዎች ላይ ሲያስነሳ እንደነበር ታወቀ

$
0
0
በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ደመራ ላይ ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ያደረጉትን ፖሊስ ሲያስነሳ ማስተዋላቸውን የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል:: ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ማንኛውም ሰው የፈለገውን ባንዲራ ይዞ የመውጣት መብት አለው ብለው በአደባባይ ቢያውጁም የአዲስ አበባ ፖሊስ በማን ትዕዛዝ ይህን እንዳደረገ አጠያያቂ እንደሆነባቸው ነዋሪዎች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል:: ፖሊሶች ባንዲራውን ማስነሳቱን ድርጊት በሁሉም የአዲስ አበባ ቦታዎች […]

በመርሐቤቴ 6 ቀበሌዎች የመሬት መንሸራተት አደጋ አጋጠመ

$
0
0
መርሐቤቴ ወረዳ በሚገኙ 6 ቀበሌዎች የመሬት መንሸራት ፣ የጎርፍና የበረዶ አደጋ በመድረሱ በሰብልና በመኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ:: የወረዳው ኮምዩሚኬሽን ጉዳዮች እንዳስታወቀው: ጉዳቱ ደረሰው በጊደብ ወረጎ፣ በአምደን ልጅ አግባ ፣ በሃሮገንዳ ፣በኮሶ ጠረህና ፣ ቆፍና ሰቧሻ እና በግሬት ቀበሌ ሲሆን በነዚህ ቀበሌዎች 281 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት የመኖሪያ ቤት እና እርሻ መሬት ጉዳት መደረሱን […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live