Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

0
0
የሳዑዲ ንጉስ የሆኑት ንጉስ ሳልማን: የሳዑዲ አልጋ ወራሽ ሙሃመድ ቢን ሳልማን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬስ በተገኙበት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለደረሱት አስደናቂ የሰላም ስምምነት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአገሪቱን ታላቅ ሜዳልያ በዛሬው ዕለት በጂዳ ከተማ መሸለማቸውን አቶ ፍጹም አረጋ አስታወቀዋል:: ካሁን ቀደም እ.ኤ.አ. ጁላይ 24: 2018 ላይ በተመሳሳይ […]

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በቡራዩና አካባቢው ለንጹሀን ሞትና ጉዳት እንዲሁም ለንብረት ውድመት ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን ከ70 በላይ የተደራጁ ዘራፊዎችን ማሰሩን አስታወቀ

0
0
በቡራዩና አካባቢው ለንጹሀን ሞትና ጉዳት እንዲሁም ለንብረት ውድመት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ከ70 በላይ የተደራጁ ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ:: በቡራዩ አሸዋ ሜዳ፣ አንፎ ከታና የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት 2 ቀናት ለንጹሀን ሞትና ጉዳት እንዲሁም ለንብረት ውድመት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ከ70 በላይ የተደራጁ ዘራፊዎች በቁጥጥር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ እጅጉ ተናግረዋል:: እስካሁን ከአርባ እስከ […]

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ መንግስት የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ ጠየቀ

0
0
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ ባወጣው መግለጫ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ሊያስጠብቅ ይገባል አለ::  “ከቅዳሜ መስከረም 05 ቀን 2011 ዓም ምሽት ጀምሮ በቡራዩ፣ በአሸዋ ሜዳ፣ በቡራዩ እና ገፈርሳ አካባቢ በቡድን የተደራጁ አካላት የመኖሪያ ቤቶች ሠብረው በመግባት በንፁሃን ዜጎች ላይ ንብረት ከማውደም እና አካላዊ ጥቃት ክማድረሳቸውም በላይ ሴቶችና ህጻናት መደፈራቸውን እንዲሁም በአሰቃቂ ሁኔታ እየታረዱ መገደላቸውን ምንጮች ገልፀዋል፡፡” ያለው […]

በቡራዩና አካባቢዋ ያለው አለመረጋጋት እንደቀጠለ ነው

0
0
በቡራዩና አካባቢው ባሉ ከተሞች በደረሰ ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸዉ ታወቀ፡፡ ከሐሙስ መስከረም 3 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በተፈጸመዉ ጥቃት በዋናነት የጋሞ ፣ የወላይታ፣ የጉራጌና የስልጤ ብሔር ተወላጆች ጥቃት እንደደረሰባቸዉ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ተጎጂዋች ገልጸዋል፡፡ ጥቃቱም በዋናነት በቡድን ይንቀሳቀሱ በነበሩ ወጣቶች መፈፀሙን ተጎጂዋች ለሪፖርተር ተናግረዎል፡፡ በጥቃቱም እስካሁን […]

አዲስ አበባ አምርር!? –ቃል ኪዳን ኃይሉ

0
0
ይኽውልህ የአዲስ አበባ ልጅ መምረር፤መክረር አያውቅም፡፡ ይገባኛል አምርሮ አይጨክንም፡፡ ግን አትሳሳት ጸጋዬ አራርሳ ከአሜሪካ፤ ጃዋር ከአዲስ አበባ እያመረሩብህ ነው፡፡ ጃዋር አዲስ አበባ ሆኖ ሊለው የማይችለውን ፀጋዬ አራርሳ አሜሪካ እንደልቡ ይለዋል፡፡ አትሸወድ ሁሉም አምርረውብሀል፡፡ . አይተሀል ሰፈርህን ልጠብቅ ብለህ የቆምክ ቀን ፌደራል ፖሊሱ ወደ አንተ አስለቃሽ ጭሱን ሲለቅ እንደነበር፤ ነጥሎ የአዲስ አበባን ልጅ ሲያስር እንደነበር፤ ሌሎች […]

ፀጥታ አስከባሪው እንደዚህ እየተባበረ ለምን ሰው እንደሞተ አልገባኝም!?

0
0
አንዋር አንዋር እንደጻፈው ማታ ሰልፍ እና የታክሲ አድማ እየተባለ ፌስቡክ ላይ ሲሰራጭ፣ ሰልፉን መገደብ ባይቻልም የታክሲው አድማ ግን መደረግ እንደሌለበት ፅፌ ነበር፣ ሆኖም ሰው ስሜቱ ስለተነካ የሚመራውም ስለሌለ በስሜቱ ተነሳስቶ ሰልፍ እንደሚወጣ ጠብቄ ነበር፣ ጠዋት ከቤቴ ስወጣ ሰልፍ ይጀመራል ብዪ ግን አልገመትኩም ነበር፣ ሆኖም ገና አንዋር መስጂድ ስደርስ ጎርፍ የሆነ ህዝብ መፈክር እያሰማ ከወደ አውቶብስ […]

Hiber Radio:የተቃውሞ ሰልፉና ግድያው፣ዶ/ር አብይን ከስልጣን ለማውረድ ያሰቡ መኖራቸው፣በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈናቀሉ ወገኖች መበራከት አለማቀፋዊ ስጋት መፍጠሩ፣በኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ስምምነት ያልታየ ጉዳይ፣አርበኞች ግንቦት 7 አማራውን ለይቶ አትደራጅ ማለት አግባብ አለመሆኑ ተገለጸ፣ የቡራዩው ጎሳ ተኮር ግጭት በአለማቀፍ ሚዲያወች እይታ እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

0
0
የሕብር ረዲዮ መስከረም 7 ቀን 2011 ፕሮግራም የአንድነት ፖልቲካው መልስ ሊሰጥባቸው የማይፈልግባቸው የአማራው ጥያቀ እና በወቅታዊ ጉዳይ ከዶ/ር ሰማኽኝ ጋሹ ጋር ያደረግነው ውይይት (ቃለ መጠይቁን ያድምጡት) የኦነግ ወታደሮችና ስብሃት ቁርኝት እና በውቀታዊ ጉዳይ ከአመራሮቹ አንዱ ከሆኑት አሚን ጁዲ ጋር ተወያይተናል በሆስፒታል አልጋቸው ላይ በመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ ከወገኖቻቸው ጋር የተደመሩት ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት ሲዘከሩ(ልዩ ዘገባ ) ሌሎችም […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

0
0
ታዋቂው ድምጻዊ ድምጻዊ አስጌ ዴንዳሾ በሃገሪቱ የተለያዩ ከተሞች እየተፈጸመ ያለው ጥቃት እና ሞት ተሰምቶት በኢንስታግራም ገጹ ላይ ያሰፈረው መልዕክት የብዙዎችን ልብ ሰብሯል:: ድምጻዊው “‘ወንድ ልጅ አያለቅስም..’ .. ቢሆንም ተረቱ…. እኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አልቅሼ እርሜን አውጥቼልሻለሁ እናት ሀገር ።…. ወገኔን ለእኔ ያርገው” ሲል ከፎቶዎች ጋር በማህበራዊ ገጾች የለቀቀው መልዕክቱ ብዙዎችን እንዳስለቀሰ ከፎቶዎች ስር ከተሰጡ አስተያየቶች […]

የሰንቀሌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ሰልጣኞች የሆኑ ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በአንድ ጊዜ የጤና እክል ገጠማቸው

0
0
BBC Amharic – የሰንቀሌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል ሰልጣኞች የሆኑ ወደ 3 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የጤና እክል እንደገጠማቸው ተገለጸ። ሰልጣኞቹ ከትላንት ምሽት ጀምሮ በአቅራቢያቸው ወደሚገኙ የህክምና መስጫዎች አቅንተዋል። ህክምና ከተሰጠባቸው ሆስፒታሎች አንዱ የሆነው የአምቦ ሪፈራል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ጎንፋ ሞቲ ለቢቢሲ እንደገለጹት፤ ሰልጣኞቹ የገጠማቸው የጤና እክል መነሻው የምግብ መመረዝ አልያም የተበላሸ ምግብ መብላት ሊሆን ይችላል። […]

በአዲስ አበባ ዛሬ 5 ሰዎች በመከላከያ ሰራዊቱ ተገደሉ

0
0
በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች እየተፈጸመ ያለውን ብሔር ተኮር ግድያ ዝርፊያና ጥቃት በመቃወም ዛሬ ሰኞ መስከረም 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ሠልፍ ከወጡ ሰዎች መካከል አምስት ሰዎች መሞታቸውንና ሌሎችም መቁሰላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ለመንግሥት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ አስታወቁ:: ከአንድ ሳምንት በፊት ጀምሮ ዘ-ሐበሻ የደህንነት ምንጮችን በመጥቀስ ከዶ/ር ዓብይ አህመድ ስልጣንን ሕዝብን በማበጣበጥ ለመቀማት […]

የትግራይ ክልል መንግስት ለዶ/ር አብይ የፌዴራል አስተዳደር ማሳሰቢያ ላከ

0
0
ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ —————————————————– ካለፉት ሶስት ዓመታት ጀምሮ በተለያዩ የሃገራችን ኣከባቢዎች በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሳቢያ የዜጎች ሰላምና ደህንነት ኣደጋ ውስጥ እንደገባና በርከት ባሉ ኣከባቢዎች ሰዎች ለስራ በወጡበት በሰላም መመለስ እያቃጣቸው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ዜጎች በተለያዩ የኣገራቸው ኣከባቢዎች በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ የመኖር፣ሃብት የማፍራትና የማካበት ሕገ መንግስታዊ መብታቸውና ነፃነታቸው ከመገደቡ ባሻገር በኣገሪትዋ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ እድገት […]

ዶ/ር አብይ ከማቀፍ ወደ መገፋተር ይሻገሩ?

0
0
የዶ/ር አብይን መንግስት ለማዳከምና ለስላሳ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ የሚደረገው ሴራ እስከየት? ከህግ በላይ የሆኑ ሰዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ አሉን? በርግጥ የዶ/ር አብይ መንግስትና ሌላ ምስጥራዊ መንግስት ኢትዮጵያ ዉስጥ አለን? ዶ/ር አብይ የጦር ሐይሉን ሙሉ ለሙሉ የማዘዝ ብቃት አላቸውን? ካላቸው ለምን እንደ አብዲ ኢሊ ሁከት ፈጣሪ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር ማዋል አይጀምሩም? ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋና ሳዲቅ አህመድ ይወያያሉ!

“ህወሓት ሽብር ስፖንሰር ያደርጋል!!! የአህያ ባል፣ ከጅብ አያስጥልም!!!”

0
0
ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY ‹‹ ህወሓት ሽብር ስፖንሰር ያደርጋል!!! የአህያ ባል፣ ከጅብ አያስጥልም!!! ›› ‹‹ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር›› ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም 1-የትግራይ ክልል፣ 2- የአማራ ክልል፣ 3-የኦሮሚያ ክልል፣ 4- ደቡብ ክልል፣ የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግሥት የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ኃይል ማለትም የአየር ኃይል ተዋጊ ጀቶችን በውቅሮ ተራሮችን ቦርቡሮ አኑሮቸዋል፣ የሃገሪቱ ታንኮች ወርሶል እንዲሁም የጦር ግምጃ ቤቱ የጦር መሣሪያ […]

ዓረና ትግራይ መንግስት ወንጀለኞችን ለህግ እንዲያቀርብ ጠየቀ

0
0
ከዓረና ትግራይ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ ! ****** በዚህ ሳምንት በኣዲስ ኣበባና ዙርያዋ እያጋጠመ ያለው ግጭትና ግጭቱ ተከትሎ በደረሰው ግድያ ዓረና የተሰማው ሓዘን እየገለፀ ድርጊቱም በፅኑ ያወግዘዋል። የኦነግ ኣመራሮች ለመቀበል ዝግጅት ሲደረግ በኣርማና ባንዴራ የሚል ኣሳማኝ ያልሆነ ምክንያት የተጀመረው ግጭት ተስፋፍቶ ለበርካታ ዜጎቻችን ሂወት መጥፋት፣ ኣካል መጉደል፣ ንብረት መውደምና ከቤት ንብረታቸው መፈናቀል ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። የሃገራችን […]

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በጠራው ስብሰባ ላይ ያደረገው ንግግር ሙሉ ቃል

0
0
………………………… “አማራ በብሔር መደራጀት ችግር የወለደው ቢሆንም አማራ በብሔረ መደራጀት መብታችን ነው፡፡ የማንንም ፍቃድ አያስፈልገንም፡፡ ሀቁ ይህ እንደሆነ የአማራ ህዝባችን ከስሜት ነፃ በሆነ አስተምህሮ በመስጠት ህዝቡን ጠንካራ አቋም እንዲይዝ በማድረግ ራሱን ከማንኛውም የዘር ጥቃት እንዲከላከል ማድረግ” ~ህወሓት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ብሔርተኝነት አለመመለሱ ከጊዜ በኋላ ውጤቱ ቀሪው ኃይል በታሪክ ሊነግረን ይሆናል፡፡ ህወሓት የአማራ ህዝብ ጥያቄ ላለመመለስ […]

የኢትዮጵያ ደህንነት ምክር ቤት አክቲቪስቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እጃሁን ሰብስቡ ሲል አስጠነቀቀ

0
0
ከብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ ብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤት በ08/01/2011 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በአገራችን እየተስተዋሉ ያሉ ህገ-ወጥና የስርዓት አልበኝነት እንቅስቃሴዎችን ገምግሞ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል። ባለፉት አምስት ወራት የዴሞክራሲ ምህዳርን ለማስፋት በርካታ ስራዎች ተከናውነው ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል። በዚህም መላው ህዝባችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በአገሩ ተስፋ እንዲሰንቅና በሃገሩ መጻዒ እድል ላይ የራሱን አስተዋፅኦ ለማበርከት እንዲነሳሳ […]

ዶ/ር ዓብይ በሃገሪቱ ግጭት እያስነሱ ላሉት ኃይሎች “የወንድሞቻችሁን ደም በማፍሰስ ተሳክቶላችኋል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ግን አይሳካላችሁም”አሉ

0
0
(ዘ-ሐበሻ) ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ቡራዩና አካባቢው የተፈናቀሉትን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የሚገኙበት ሥፍራ ሄደው ጎበኙ:: ሃዘናቸውን ለመግለጽ ጥቁር በጥቁር ለብሰው ጥቁር መነጽር አድርገው የተፈናቀሉትን ወገኖች ያጽናኑት ዶ/ር አብይ ይህ ሁሉ ማፈናቀልና ግድያ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች እንዲፈጸም የሚያደርጉት ሃገሪቱን ወደ ኋላ እንድትመለስ በሚፈልጉ ኃይሎች ነው ብለዋል:: “በታላቅ ትዕግስት ይህን አስቸጋሪ እንድናልፍ ከመንግስት […]

ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች በባህርዳር ከተማ ቤተክርስቲያን ደጃፍ በልዩ ሃይል ተደበደቡ

0
0
(ዘ-ሐበሻ) በሱማሌ ክልል የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስ ተከትሎ የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች፣ መንግስት እርዳታ እያደረገልን አይደለም በማለት ዛሬ በባህርዳር ጥያቄያቸውን በሰልፍ ለማቅረብ በሞከሩበት ወቅት በፀጥታ ሀይሎች ተደብድበው እንዲበተኑ ተደረጉ:: በላይነህ አለምነህ እንደዘገበው የአማራ ክልል ልዩ ሀይል (አድማ በታኝ) በዋና አዛዝ ኮማንደር መለስ ካሴ ትዕዛዝ ወጣቶችን በአደባባይ እየደበደበ ነው። ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት በባህርዳር ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ውስጥና […]

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች

0
0
በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የተፈጠረውን ግድያና ዝርፊያ ለማውገዝ ትናንት በአርባ ምንጭ የተደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ሰው ሕይወት ማለፉንና በ13 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የጋሞ ጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቁ። አስተዳዳሪው አቶ ኢሳያስ እድሪስ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ሰላማዊ ሰልፉን ለመበጥበጥ በሞከሩና በወታደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት በ13 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል:: —- በጋሞ የታየው ጨዋነት […]

በሐሰት ፕሮፓጋንዳ ማንንም አታታልሉም! –ከሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ እጃችሁን አንሡ!

0
0
ከይስሃቅ እሸቱ . የሕዝበ ሙስሊሙን ስም ባገኙት አጋጣሚ ለማጥፋት የሚፈልጉ አካላት በሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ላይ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ መንዛት ጀምረዋል። የዛሬው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሰለባ ደግሞ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የታሪክ ምሑሩ Ahmedin Jebel ሆኗል። አሕመዲንን አገር የማፍረስ ተልእኮ እንዳለው እና የኦነግ አባልም እንደሆነ አድርገው ከዐውድ ውጭ የወጡ ፎቶዎችን እያስደገፉ ማሳየታቸውን ቀጥለዋል። እውነታውን ለሕዝብ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live