Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ወግ –ከበእውቀቱ ስዩም

0
0

abune_petros ማለዳ መነሣት አልወድም፡፡ ዛሬ ግን አቡነ ጴጥሮስ ከመታሰቢያቸው ዙፋን ሲወርዱ ለመታዘብ በማለዳው ካልጋየ ጨክኘ ወረድሁ፡፡ ለአቡነ ጴጥሮስ ፍቅር ስል የማለዳ እንቅልፌን ብሰዋ አይቆጨኝም፡፡ በቅርቡ በሚከፈተው ጦማሬ ላይ ስለ ጀግናው ጴጥሮስ በሰፊው የመጻፍ ሐሳብ አለኝ፡፡
በቦታው ስደርስ፣የጴጥሮስ ሀውልት በጣውላ ተገንዞ ቆሟል፡፡ድብርት ተጫጫነኝ፡፡ምናልባት አያቶቼ አቡኑ ሲረሸኑ በተመለከቱበት ሰአት የተሰማቸው ስሜት እንዲህ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የራስ ቁር የደፉ የቀን ሠራተኞች በአቡኑ ትክሻ ላይ እንደ ወፍ ሰፍረዋል፡፡ ወደ መርካቶ በሚሄዱ ተሳፋሪዎች የተሞሉ ሚኒባሶች አደባባዩን ታክከው ሽው ይላሉ፡፡ ተሳፋሪዎቹ፣ በመስታውት አሻ…ግረው የሚመለከቱት ትእይንት ብዙ የመሰጣቸው አይመሰልም፡፡
በፋሲካ አስፈሪ የዶሮ ዋጋ ለተጠመደ አእምሮ ታሪክ ምኑ ነው??
ከተመልካቹ በላይ የፖሊሱ ቁጥር የሚበልጥ መሰለኝ፡፡አንድ ፒካፕ መኪና ስትበር መጣችና ቁና ሙሉ ፌደራል ፖሊስ አራገፈች፡፡ሰብሰብ ብለን በቆምንበት አንዱ ፖሊስ ጠጋ አለና‹‹ እናንተን አይመለከታችሁም ከዚህ ሂዱ›› አለ፡፡ካጠገቤ የቆመ ጎበዝ ‹‹ማየት መብታችን ነው›› ብሎ መልሶ ጮከበት፡፡አሀ! የጴጥሮስ መንፈስ አልከሰመም ማለት ነው፡፡ፖሊሱ ምንም ሳይመልስ ከሬድዮ መገናኛው ጋር እየተመካከረ ካካባቢው ራቀ፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ጋዜጠኛ ጓደኞቼ ካሜራቸውን ታጥቀው ደረሱና ተቀላቀሉኝ፡፡ ሀውልቱን ማስቀረት ስላልቻሉ ምስሉን ቀርጸው ለማስቀረት ተሯሯጡ፡፡
ድንገት ቀና ብየ ሳይ ከሀውልቱ ፊትለፊት ጅማ በር የሚባል ፣ጣልያን የሠራው አሮጌ ሕንጻ ይታየኛል፡፡ባቡሩ የአቡነ ጴጥሮስን መታሰቢያ ደቅድቆ ሲያልፍ፣ጣልያን ሠራሹን ግንብ ንክች አያደርገውም፡፡ጉደኛ ባቡር!!!
በጣውላ የተገነዘውን የአቡኑን ሀውልት ለመሸከም አንድ አዳፋ ረጅም ተጎታች መኪና ብቅ አለ፡፡ዳይኖሰር የመሰለ ክሬን ሀውልቱን ነቅሎ ሲያንጠለጥለው፣ሀውልቱ የነበረበት ቦታ ጥርስ የወለቀበት አፍ መሠለ፡፡ቀሪውን የማየት ፍላጎት ስላልነበረኝ ከጓደኛየ ጋር ወደ ፒያሳ አቀናሁ፡፡ብዙ ነገር እዬተለወጠ መሆኑን አየሁ፡፡የጥንቱ መሀሙድ መዚቃ ቤት ወደ ቡቲክ መቀየሩን አስተዋልሁ፡፡ የጥንቱ አያሌው ሙዚቃ ቤት ፍራፍሬ መሸጫ ሱቅ ሆኗል፡፡ከጥቂት ወራት በፊት ብርቱካኔ የሚለው ሙዚቃ ይንቆረቆርበት የነበረው ቦታ ፣አሁን ብርቱካን በኪሎ ይሸጥበታል፡፡
አዲስአበባ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ያለጥርጥር፣ባቡር ይኖራታል፡፡ቀለበት መንገዶች ይኖሯታል፡፡ አሪፍ ህንጻዎች ይኖሯታል፡፡ነገር ግን፣ ትናንት የሚባለው ነገር አይኖራትም፡፡ A city without past ላዲስ አበባ የተገባ ቅጽል ነው፡፡
ወደ ሰፈሬ የሚሄድ ታክሲ ስፈናጠጥ፣ የሚከተሉት የጸጋየ ገብረመድህን ግጥሞች ሽው አሉብኝ፡፡
….መጭው ደመና ጥቁረቱ፣
ጮቁ፣ ማጡ፣ የክረምቱ፣ አቤት ዝቅጠቱ ማስፈራቱ
የኛስ ትውልድ አከተመ፣ አገራችንን አምክነን
የነገስ ዘር ምን ይበለን፣ስንተወው ሲኦል አውርሰን
(ከበ እውቀቱ የቀደሙ ሥራዎች መካከል ካላያችሁት እዩለት ዘንድ እነሆ፡)


እሪ በል ሚኒሶታ! –ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክን ወያኔ ጉያ ሊወስዱልህ ጁን 2 ቀጠሮ ያዙልህ

0
0
አባ ሃለሚካኤል (የደብረሰላም መድሃኔዓለም አስተዳዳሪ)

አባ ሃለሚካኤል
(የደብረሰላም መድሃኔዓለም አስተዳዳሪ)

ሊቀትጉሃን ጌታሁን (ከአስተዳዳሪው የተሻለ ሃሳብ የማቀርበው እኔ ነኝ የሚል መከራከሪያ ቢያቀርቡም ከቦርድ ስብሰባ የታገዱ)

ሊቀትጉሃን ጌታሁን
(ከአስተዳዳሪው የተሻለ ሃሳብ የማቀርበው እኔ ነኝ የሚል መከራከሪያ ቢያቀርቡም ከቦርድ ስብሰባ የታገዱ)

"አቶ መለስ ንሰሃ ገብተው ነው የሞቱት" በሚል በድፍረት ያስተማሩት ቀሲስ አሃዱ

“አቶ መለስ ንሰሃ ገብተው ነው የሞቱት” በሚል በድፍረት ያስተማሩት ቀሲስ አሃዱ

ቀሲስ ስንታየሁ

ቀሲስ ስንታየሁ

 

(ከደብረሰላም ቦርድ አባላት አንዱ ህዝብ እንዲያውቀው የተላከ መልዕክት)

በገለልተኛነት ለረዥም ዓመታት ከቆዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ.ክ አንዱ ነው። ይህ ቤ/ክ በተለይ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን በሥሩ የያዘ መሆኑን ትናንት በደብረሰላም አገልግለው ዛሬ በወያኔው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር “ዋልድባን ጆሮ ዳባ ልበስ” በሚል ለሕሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው እየሰሩ ባሉት አቡነ ዳንኤል አማካኝነት የኢትዮጵያ መንግስት ጠንቅቆ ያውቀዋል። ታዲያ ይህን የምርጥ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ቤተክርስቲያንን በእጁ በማስገባት እነዚህን ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ለመበታተን የወያኔ መንግስት በአንዳንድ ገጣሚያን ነን ባይ የቤተክርስቲያኑ አስተናጋጆች በአራቱ ካህናት አማካኝነት እጁን በማስገባት ይህችን ውድ ቤ/ክ ለመበታተን ለጁን 2 ቀን 2013 ቀጠሮ ይዟል።

የቤተክርስቲያንን ሥራ በአግባቡ ሳይወጡ በታክሲ ሾፌርነት ሥራ ላይ የተሰማሩት 3ቱ ካህናት በየቤቱ እየዞሩ አንዴ “ደመወዝ ካልተጨመረን ይህን ደብረሰላምን እንበትናለን” እያሉ ሲፎክሩ፤ በሌላ በኩል የዋልድባን ገዳም መፍረስ በመቃወም ኑ ሰልፍ ውጡ ሲባሉ “ሃገር ቤት መግባት እንፈልጋለን እና አንቃወምም፤ ሃገር ቤት የገዛነው ቤት እንዲወሰድብን ስለማንፈልግ አንገኝም” በሚል፤ ሲቀጥሉም “ደብረሰላምን በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር ስናስገባ የትም አንሄድም” በሚል ምዕምናኑን እያስፈራሩ ካሉት ከነዚህ ካህናት መካከል አንዱ ቀሲስ አሃዱ ከአንድ አባት በማይጠበቅ ሁኔታ በውሽት አቶ መለስ ዜናዊ ንሠሃ ገብተው ነው የሞቱት በሚል በደብሩ በመስበክ ከየትኛው ወገን እንደቆሙ ራሳቸውን አጋልጠዋል። ከትናንት በስቲያ እሁድም በሚኒሶታው የኢትዮጵያ ድምጽ ራድዮ በርከት ያሉ የሚኒሶታ ም ዕምናን “የሚኒሶታውን ደብረሰላም መድሃኔዓለም ወደ ወያኔ መዳፍ ከመውደቁ እናድን” የሚል አይነት አስተያየት በቀጥታ ስርጭት አስተያየት መስጠቱ ድንገት በውስጣቸው ያለውን የፈነቀለባቸው ቀሲስ ስንታየሁም ወደ ራድዮ ጣቢያው በመደውል የወያኔ መንግስት በሃገር ቤት የከለከለውን ሃሰብን በነፃነት የመግለጽ መብት እዚህ ሰሜን አሜሪካ ውስጥ መረጋገጡ ጠፍቷቸው ይሆን አይሆን በማይታወቅ መልኩ በስሜታዊነት “እናንተ ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ ለማወያየት ስልጣን የላችሁም” በማለት የሃገር ቤት ወያኔዎች ለ20 ዓመታት ሲነግሩን የነበረውን በመድገም የት እንዳሉ አሳይተውናል።

በሁለት መንታ መንገድ ላይ የሚገኘው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ

በሁለት መንታ መንገድ ላይ የሚገኘው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ

ሌላው እዚህ አሜሪካ በኢንጂነርነት ሙያ ተመርቆ ሥራ በማጣቱና ሃገር ቤት በመግባት በዚያ ሥራ ለመሰማራት የቋመጠውና ቃልም የተገባለት ግለሰብ በየለቅሶ ቤቱ ም ዕምናኑን ከሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ጋር እንዲቀላቀል ሲሰብክና ምርጫ ሲያለማምድ በብዙሃኑ ትችት ቢደርስበትም ማን እንደሆነና ምን እንደሚፈልግ ከወዲሁ ታውቆበታል።
ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል መነገሪያ እንጂ የግጥም ማንበቢያ እንዳልሆነች እየታወቀ በቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መልዓከ ሰላም አባ ሃይለሚካኤል “ይህ ሰው ግጥም እንዳያነብ ክልክዬ አልነበር እንዴ” ተብሎ በምዕመናን ፊት እስከ መታገድ ደርሶ አሁንም በድፍረት ግጥም እያነበበ በበርካታ ም እመናን የተተፋው ግለሰብ ሃገር ቤት ሄዶ መጽሐፍ ለማሳተም ሲኖዶሱን ሲጠይቅ “አንተ ገለልተኛውን ቤ/ክ እያገለገልክ ነውና በቤ/ክ ስር ያንተን መጽሐፍ አናትምም፤ በነፃ እንዲታተምልህ ከፈለህ አጀንዳችንን አሳካ” ተብሎ የተላከው እናንተ የምታውቁት ግለሰብም ደብረሰላምን ወደ ወያኔ መንደር ለመውሰድ ቀን ከለሊት እየሰራ ነው።

እንደቦርድ አባልነቴ ከቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ ጥበቡ የተሰጠውን “እኛ የቦርድ አባላት ከየትኛውም ወገን ሳንወግን የሕዝቡን ድምጽ መስማት አለብን” በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አከብራለሁ። የተከበረችውን ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክንን ወደ ሃገ ቤቱ ሲኖዶስ ለመውሰድ ሲሯሯጡ የነበሩ የቦርድ አባላትን ዝም አስብሏል። ሆኖም ግን ግጥም አንባቢውና ኢንጂነሩ አንዳንድ ተከታዮቻቸውን በመያዝ (73 ይሆናሉ) ጁን 2 ቀን 2013 ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲወሰድ ለማስወሰን ስብሰባ ጠርጠዋል። የሚገርመው እነዚህ 73 የሚሆኑት አባላትን ስም ዝርዝራቸውን ለህንጻ ማሰሪያ ከተሰበሰበው ገንዘብ ሰጪዎች ዝርዝር ላይ ሳየው የአንዳቸውም ስም የለም። አላማቸው ደብረሰላም ትልቅ ካቴድራል እንዲገነባ ሳይሆን እንዳለ ሆኖ ለወያኔ አሳልፎ መስጠት ነው። ልብ በሉ እነዚህ ከሃገር ቤቱ ሲኖዶስና ከመንግስት ጥቅማጥቅም እናገኛለን ብለው እየሰሩ የሚገኙ ግለሰቦች በጁን 2ቱ ስብሰባ ለምርጫ ለማቅረብ የፈለጉት ደብረሰላም በኢትዮጵያው ሲኖዶስ ይመራ ወይስ በገለልተኛነት ይቆይ? በሚለው እንጂ እንደ 3ኛ አማራጭ በስደተኛው ሲኖዶስ ስር ይጠቃለል የሚል ነገር አልቀረቡም፤ ይህ ምርጫ ቢቀርብ የሚወሰነውን ያውቃሉና ። ምናልባት ይህን የኔን ግልጽ መል ዕክት ካነበቡ በኋላ ብዙዎች ሶስተኛውን አማራጭ ይዘው እንደሚነሱ እተማመናለሁ።

በሌላ በኩል ለደብረ ሰላም አዲስ ሕንጻ ለማሰራት በትጋት እየሰራ የሚገኘው ቡድን ይህ የምርጫ ጊዜ ይራዘም እያለ እየተከራከረ ነው። የዚህ ቡድን ፍራቻ ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ይኬድ ከተባለ ገንዘብ የሚሰጥ አይኖርም። የሕንጻው ሕልምም ያከትማል። ጁን 2 ደብረሰላምን የወያኔ ቅጥረኞቹ ግሩፖች ከወሰዱት ደብረሰላም በ እርግጠኝነት ለ2 ይከፈላል። ከወዲሁም የወረቀት ብተናው፤ በኢሜይል የሚደረገው ቅስቀሳ ተጠናቅሮ ቀጥሏል።

በነገራችን ላይ “በደንቡ መሰረት በቦርድ ስብሰባ ላይ ከካህናቱ አንድ ሰው ነው መወከል ያለበት ቢባልም 2 ካህን ሲወከል ቆይቷል። አሁን ግን ይህ ቀርቶ በአስተዳዳሪው ብቻ ካህናቱ እንዲወከሉ በመደረጉ የተከፉትና እኔ ከአስተዳዳሪው መልዓከ ሰላም አባ ሃይለሚካኤል የተሻለ ሃሳብ የማቀርብ ሰው ነኝ። እኔ ከቦርድ ስብሰባው መታገድ የለብኝም በማለት ሲከራከሩ የነበሩት መልዓከ ሃይል ቀሲስ ጌታሁን መኮንን (መሪጌታ)” በቦርድ ስብሰባ ላይ እንዳይገኙ ታግደዋል። ይህ ለምዕመናኑ ትልቅ ዜና ነው።

የኒሶታ ምዕምናን ሆይ ደብረሰላም መድሃኔዓለምን በወያኔ ልትቀማ ጁን 2 ቀጥሮ ተይዞልሃል። ንቃ!

ለግንዛቤ ለቦርዱ ተልከው ከነበሩ ደብዳቤዎች መካከል የሚከተለውን ላካፍላችሁ፦

ሰላመ እግዜብሔር ለመድሃኔ ዓለም ቦርድ አባላት ይድረስ

ተጠሪ፡ አቶ ጥበቡ ታምራት

የካቲት 10 2005 ዓ.ም. የግል ስሜ ተጥቅሶ ለነ አቶ ታየ ረታ በማለት የጻፋችሁልኝ ደብዳቤ ደርሶኝ ተመልክቼዋለሁ። እናንተንም እግዜር ያክብርልኝ።

ሁለትም ሦስትም ሆነን በቃል ማስረዳቱ ለሌሎቹ ፈራሚዎች ተወካይ አያደርገንም። እያንዳንዱ ፈራሚ በግሉ አምኖበት ያደረገው ነውና። ሆኖም ከጠየቃችሁኝ ዋና ዋና ነጥቦቼን እንደሚከተለው እገልጣለሁ።

——————————————————————————————————

የካቲት 12 2005 ዓ. ም

ይድረስ ለደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ያስተዳደር ቦርድ አባላት

ሚኔያፖሊስ፡ ሚኔሶታ 55406

ተጠቃሽ፡ አቶ ጥበቡ ታምራት ሊቀ መንበር

የካቲት 5, 2005 ከአስተዳደር ቦርዱ ለነአቶ ታየ ረታ ተብሎ የተጻፈ ደብዳቤ ደርሶኝ ተመልክቼዋለሁ። ጉዳዩም በደብራችን ስላለው የአስተዳደር ይዘትና ስነ-ሥርዓት ጉድለት 73 ተቃዋሚ ተብዬዎች በኢሜይል ሳይሆን ፈርመን በወረቀት ጽፈን ላቀረብነው መልስ ሲሆን ለኔ ብቻ መጻፉ ስህተት ነው እላለሁ። ማንም ማንን ስለማይወክልና አንድ ግለ ሰብ ተጠሪ ስለሌለ፤ ሁላችንም መጠራት አለብን።የውስጠ ደንቡን ለመከተል በመጀመራችሁ እሰይ በርቱልን እላለሁ።

ለማናቸውም በደብዳቤው የላካችሁልኝ አስተሳሰብም ሆነ የሂሳብ ስሌት በጣም የተሳሳተ መሆኑ እንዲታወቅ አሳስባለሁ። ከ73 ፈራሚ

ላይ 24 ሲቀነስ 49 እንጂ 45 አይሆንም። 24ቱ ለአባልነት አልበቁም ከተባለ 525 አባላት የሉንም ማለት ነው። 24ቱ እነማን እንደሆኑ

ዝርዝሩን ለማስተካከል ስማቸው ቢገለጽልን እናመሰግናለን።

ለተጻፈልኝ ደብዳቤ ከዚህ በታች ባሰፈርኳቸው ዘጠኝ ነጥቦች መልስ እሰጣለሁ። የውስጥ ደንቡን በማገናዘብ ተመልከቱልኝ።

1. በተጠቀሰው የመተዳደሪያ የውስ ደንብ ክፍል 3 (ለ) ሃያው ፐርሴንት ባያሟላም በጉዳዩ አሳሳቢነት ምክንያት በክፍል ሦስት (ሀ) ጠቅላላ ስብሰባ መጥራት ይቻላል። እኔ ራሴን ብቻ ስለምወክል ደብዳቤው ለያንዳንዱ ፈራሚ መላክ ይኖርበታል።

2. በውስጠ ደንቡ መሰረት ሲገመገም የአባሎች ቁጥር 525 ይደርሳል ብትሉም ከግማሽ የማይበልጥ ነው እላለሁ።

3. በደምቡ መሰረት በቦርዱ ስብሰባ ላይ ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ ተሣታፊዎች የቤተ ክርስቲያን ከፋይ አባል የሆኑና በሕዝብ የተመረጡ መሆን ሲገባቸው አስመስለው በሕገ-ወጥነት የሚሳተፉት ባስቸኳይ ሊወገዱ ይገባል።

4. ካሁን ቀደም በኦዲተር ተጠንተው ጠቅላላ ጉባኤው ያጸደቃቸው ያሠራር ደንቦች በሥራ ላይ እንዲውሉ ለማስገንዘብ፤

5. ማናቸውም ቤተ ክርስትያኑን ለማገልገል የሚቋቋም ኮሚቴ አባላቱ በጠቅላላው ጉባኤ እንዲጸድቅና ምእመናን ባሉበት ቃለ ምህላ እንዲቀበሉ ማስፈለጉ ለማንም ግልጽ ስለሆነ፤ ይኸው እንዲፈፀም።

6. እኛ የደብረ ሰላም መ/ዓ ምዕመናን ገለልተኝነትን ባፀደቅንበት ጊዜ በኢትዮጵያ የነበረው ያቡነ ጳውሎስ አመራር ብልሹና ዘረኛ በመሆኑ ነበር። ከዚያም አመራረጡ ሥርዓት ሲይዝ ወደእናት ቤተ ክርስቲያን እንደምንመለስ ታውቆ ነው። ተዋህዶነታችንን ለመለወጥ ያሰብንበት ጊዜ የለም። አንዳንድ ሰዎች በጎን መጠቀሚያ ለማድረግ ቢሞክሩም ቤቱ አልተቀበለውም። የፓትርያርክ ምርጫ ገና ቁርጡ ሳይለይለት ‘ሳይከካ ተቦካ’ እንዲሉ፤ በአዲስ አበባ ጉዳዩ ሳይስተካከልና ጠቅላላው ጉባኤአችን ሳይፈቅድ ‘አንድነት’ እያሉ የሚሯሯጡት ለምን እንደሆነ አልተረዳነውም። በዴሞክራሲ አገር እየኖርን የመደብ አምባገነንነት ከየት መጣ? የሕዝብን መብት መድፈር ወይም የተሳሳተ መልዕክት መስጠት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላልና። የምንተዳደረው በሚኔሶታ ሕግ መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል።

7. አሁንም በድጋሜ የማስገነዝበው የጻፋችሁልኝን በመጥቀስ “ለካህናት የተደረጉት የደመወዝ ጭማሪዎች፤ የካህናት አቀጣጠር፤የቤት አበል ክፍያዎች” በብልሹ አመራር፤ ስድብና ዛቻ ተጨምሮ ባለ ጉዳዮቹ አፍጥጠው ባስገደዱበት ግምት ባጣ አሠራር የሆነው መታረም አለበት።

8. ሥጋ ወደሙ ሲፈተት ስለ ክፉ ነገር፤ ስለጥፋት፤ መዓትና ቅጣት ዐውደ ምሕረት ቆመው ክፉ ከሚለፍፉ መንፈሳዊ ትምህርት ላይ ቢያተኩሩ በበጀን !!! በተመሳሳይ የእግዚአብሔርን ስም አንስተው በቀደሱበት አንደበታቸው፤ ዐውደ ምሕረት ላይ ቆመው ከቅዳሴ በኋላ የሚያሰሙት አሽሙር ሽሙጥና ስድብ አባሎችን እያራቀብን ሆኗልና ጥንቃቄ!! ጥንቃቄ!!

የሁነታው አሳሳቢነት ሁዳዴ ገብቷል ሳይባል ጠቅላላ ጉባኤ የሚያስጠራ ነውና አደራ ጭምር እጠይቃለሁ።

9. ቅጥር ካህናት ግዳጃቸውን ለማሟላት ቅዳሜ በየሣምንቱ ፕሮግራም ይዘው የቤተ/ክ ሕፃናትና ወጣት ልጆችን እንዲያስተምሩ ግዴታ ማስገባት ያሻል።

የዚህ ደብዳቤ አዘጋጅና አቅራቢ፡ ታዬ ረታ

ለማውቃቸው አባሎችም በግልባጭ አስታውቃለሁ።

ከአዘጋጁ፡ በደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ የሚደርሱን አስተያየቶች በርካታ ናቸው። አሁንም የሁሉንም አስተያየት ተቀብለን ለሕዝብ ማድረሳችንን እንቀጥላለን።

“አንተ የኔ ጀግና ነህ፡፡ ብትሞትም በእውነትህ ኮርተህ ሙት!” ሰርካለም ፋሲል

0
0
Eskinder Nega

እስክንድር ነጋ

ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገብረ ኪዳን እንደሚከተለዉ የዛሬዉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዉሎና አሳዛኝ ክስተት እንደሚከተለዉ አስቀምጦታል፡

የእነአንዱአለም እና እስክንድር ነጋ ነገር

በጠቅላይፍ/ቤት
ወሰንሰገድገብረኪዳን

“ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላ፣ ታሳዝነኛለች” – አዝማሪ

ሌሊት ሌሊት እንደ “ዳዊት ደጋሚ” ስለማመሽ ጠዋት ጠዋት ተጋድሜ ማርፈድ ልማዴ ነበር፡፡ ዛሬ ዕለተ ሐሙስ ሚያዝያ  26 ቀን 2005 ዓም፣  ካለወትሮዬ በጠዋት ከዕንቅልፌ ተነሳሁ፡፡ እናም ወደ ጠቅላይ ፍ/ ቤት አመራሁ። ዕለቱን እያሰ ብኩ፡፡

የዛሬው ሐሙስ በክርስትና አማኞች ዘንድ በተለየ መልኩ የሚታሰብ ቀን ነው፡፡ ክርስቶስ ትህትናን በተግባር ያስተማረበት ቀን ነው፡፡የሐዋርያዎቹን እግር ዝቅ ብሎ ያጠበበት ቀን፡፡ በልማድም ቢሆን ሐሙስ የቀን ቅዱስ ነው ይባላል፡፡ ስለዚህም ከእነ አንዱአለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የይግባኝ ማመልከቻ “የተቀደሰ”  ዜና እሰማለሁ የሚል ሃሳብ ተሞልቼ ነበር  6 ኪሎ ወደሚገኘው ጠ/ፍ ቤት በእግሬ ያቀናሁት፡፡

በእግሬ ያመራሁት ተከሳሾቹ ከማረሚያ ቤት የሚመጡት አርፍደው ነዉ በሚል እሳቤ ነበር፡፡ ነገር ግን ከጠዋቱ  3  ሰዓት ላይ እስረኞቹ ችሎት ገብተው ተቀምጠዉ ነበር፡፡ ወዲያው ከእስረኞቹ ውጪ ችሎቱን ለመከታተል የመጡ ሁሉ ከክፍሉ እንዲወጡ ተደረገ፡፡ ችሎቱ ውስጥ አንዱአለም አራጌ እና እስክንድር ነጋ እንዲሁም በሌላ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች 3  እስረኞች ከአጃቢዎች ቀሩ፡፡ በእነ አንዱአለም መዝገብ ተከሰው ይግባኝ የጠየቁት ሌሎች እስረኞች በስፍራው አልታዩም፡፡ እኛ ኮሪደር ላይ ተሰባስበን ለምን ሌሎቹ እስረኞች እንዳልመጡ እየተወያየን ደቂቃዎች በደቂቃዎች ላይ ነጎዱ፡፡

“ ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላ፣ ታሳዝነኛለች ”

3 ሰዓት ከ50  ደቂያ ሲል ናትናኤለ መኮንን እና ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)  አንድ አንድ እጃቸውን በካቴና ታስረው ከውጪ ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ ኮሪደር ላይ ችምችም ብሎ በሚጠብቃቸው ሰው መሃል እያለፉ አንዱ በግራ እንዱ በቀኝ እጁ እየጨበጡኝ አልፈው ወደ ችሎት ገቡ፡- በፖሊስ ታጃበው፡፡ 3  ሰዓት ከ55  ደቂቃ፤ ዳኞች ወደ ችሎት ገብተው ቦታቸውን ያዙ፡፡ ወዲያው ታዳሚ እንዲገባ ፈቀዱ፡፡ ጥቂት ለችሎቱ በር በቅርበት የቆሙ ታዳሚዎች ገቡ፡፡ የደሃ ሳሎን የምታክለው(ደሃ ሳሎን አለው እንዴ?)

ችሎቷ ወዲያው ጢም አለች፡፡ 4 ሰዓት የግራ ዳኛው አንድ እስረኛ ጠሩ፡፡ እናም ውሳኔያቸውን በቃል ቅልብጭ አርገው ተናገሩ – በነፃ፡፡ በሌላ ክስ የታሰረውን ሁለተኛ ተከሳሽ ጠሩ – በነፃ፡፡ እኔ ከጠቀመጥኩበት ወንበር ጀርባ ያሉ ሁለት ሴቶች ወደመሬት ተደፍተው በደስታ አለቀሱ፡፡ መደሰት እንጂ ማዘን አይገባም ብለን ገፋፍተን “አስወጣናቸው፡፡”  የቀጣዩን የእነ እስክንድርን መዝገብ ውሳኔ ለመስማት እየቋመጥን፡፡

“ሀገሬን ሀገሬን -የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላ፣ ታሳዝነኛለች”

የመጀመሪያዎቹ መዝገቦች ፍርድ ሲነበብ እኔ በዚያች ጠባብ አዳራሽ ውስጥ ተደራርቦ የተቀመጠውን ሰው ሆን ብዬ ቆጠርኩ፡፡ የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ቦታ አጥታ ከእኔ ጋር አንድ ወንበር ተዳብላ ተቀምጣለች፡፡ ሌሎችም ሰዎች እንደዛው፡፡ ብቻ በዚያች ጠባብ ችሎት ውስጥ ከተሳሾች፣ ከጠበቆች፣ ከእስረኞችና ከችሎት አስከባሪዎች ውጭ 48 ሰው ታፍጓል፡፡ ሌላው ሰው በቦታ ጥበት ኮሪደር ላይ ተኮልኩሏል፡፡ የመሃል ዳኛው ከፊት ለፊታቸው ተደጉሶ የተቀመጠውን ፋይል እየነካኩ በለሠለሰ አንደበት

“እንግዲህ እናንተ ፍ/ቤቱን … ውሳኔ መቀበል አለባችሁ አሉ፡፡

በአንድ ወንበር ላይ ተፋፍገን የተቀመጥነው እኔና ሰርካለም እርስ በርስ ተያየን፡፡ ዳኛው ቀጠሉ“በዚህ መዝገብ የቀረበው ክስ በባህሪው ከሌሎች መዝገቦች የሚለይና ውስብስብነት ያለው ነው፡፡ አዋጅ ቁጥር 652/2001 በመሆኑ፣ ሕጉ የተቃኘበትን መርህ መቃኘትን” እንደሚጠይቅ አብራሩ፡፡

በዚህ መሰረት በአምስት የይግባኝ ፋይሎች የቀረቡትን አቤቱታዎች ተያያዥነት ያላቸው በመሆናቸው ፍ/ቤቱ በአንድ ላይ በጥልቀት መርምሮ ዉሳኔ መስጠቱንና ገለፁ፡፡ በቅድሚያ የአቃቤ ሕግን ክስ፣ ቀጥሎም የይግባኝ ባዮችን አቤቱታ፣ ከዚያም በከሳሽና በተከሳሽ ወገኖች የቀረቡትን ምስክሮችና ማስረጃዎችን ይዘት በመመርመር ፍ/ቤቱ የሰጠውን ትንታኔና ውሳኔ በንባብ እንደሚያሙ አሳውቁ፡፡

“ ሀገሬን ሀገሬን- የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላኝ፣ ታሳዝነኛለች”

ከእኔ በስተቀኝ የተቀመቡት ዕድሜአቸው ወደ ሰባዎቹ የሚጠጋ ጎስቋላ እናት ዳኛው የሚያነቡትን ነገር በቅጡ የተረዱት አይመስሉም፡፡ አንዴ ወደ እኛ፣ አንዴ ወደተከሳሶቹ እየተንጠራራሩ ያያሉ፡፡ እንደዘበት ሸብ ያደረጉት ሻሻቸውን አልሮ የወጣውን ሽበታቸው እየደባበሱ ቁና ቁና ይተነፍሳሉ፡፡ ገፅታቸው ላይ አንዳች ድካምና የሕመም ስሜት የሚነበብባቸው እኚህ እናት ምቾት አልተሰማቸውም፡፡ ዳኛው ንባባቸውን ከጀመሩ ድፍን አንድ ሰዓት አልፏል፡፡ ድንገት ወደቀኝ ዞር ስል ሴትዮዋ የሆነ ስሜት ስልም ሲያደርጋቸው አየሁ፡፡

ሰርካለምን በክርኔ ጎሽመ አድርጌ ወደሴትየዋ ጠቆምኳት፡፡ እጆቺን በእኔ ላይ አሸጋግራ “አይዞዎት”  እያለች ጎናቸውን ጨመቅ ጨምቅ፣ አሸት አሸት አደረገቻቸው፡፡ ወዲያው የእፎይታ ትንፋሽ በረዥሙ ተንፍሰው “ነቃ”  አሉ፡፡ የክንፈሚካኤል እናት መሆናቸውን ነገረችኝ እየደባበሰቻቸው፡፡ የእስረኛ ቤተሰቦች ከመላመድ ብዛት እርስ በርስ የሚበረታታበት ሕክምና መሆኑ ነው፡- አልኩ ለራሴ፡፡

“ ሀገሬን ሀገሬን- የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላኝ፣ ታሳዝነኛለች”

ዳኛው ንባባቸውን አላቋረጡም፡፡“ አንዱአለም አራጌን በሚመለከት፡- ሕገመንግስታዊ መብትን ሽፋን አድርጎ በመጠቀም፣ ከግቦት 7 ጋር ለሽብር ተግባር በመመሳጠር፣ ወጣቶችን ለሽብር ተግባር በማደራጀት፣ ለሽብር በመምራት… ወዘተ ናትናኤል መኮንን፡-እንዲሁ ወጣቶችን ወኪል አስተባባሪ በመሆን…. ክንፈሚካኤል ደበበ በህኑዕ የግንቦት 7  አባለ በመሆን፣ በማሴር…. እስክንድር ነጋ በሕገመንግስቱ ለዜጎች የተሰጠውን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ሽፋን በማድረግ የግንቦት ሰባትን ዓለማ ለማስፈፀም፣ በስብሰባና በፅሁፍ ሕዝብን ለአመፅ በመቀስቀስ፣ ለኢሳት መረጃ በማቀበል፣ ከጋዜጠኛ ፋሲል የኔ አለም ጋር በመመሳጠር..ወዘተ”  መከሰሳቸውን መረጃና ምስክር የቀረበባቸው መሆኑን አተቱ፡፡

ሁሉም ተከሳሾች በተራ ቁጥር 1  በቀረበባቸው ክስ የሥር ፍ/ቤት ያሳለፈውን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚነቀፍ ሆኖ እንዳላገኘው ገለፁ፡፡ ሁለተኛው ክስ በአንደኛው ክስ ስር የሚጠቃለል በመሆኑ መሻሩንም አክለው አሳወቁ፡፡ በአጠቃላይ ሁሉም ተከሳሾች በ1ኛ እና በእራተኛ ክስ ጥፋተኛ ተብለው የተወሰነባቸው ውሳኔ የሕግ ስህተት እንደሌለበት አሳወቁ፡፡ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው የተገኙበት አንቀፅ 17  እና 18  ዓመት እስራት በአጠቃላይ ድምር ወደ 34  ዓመት እስራት የሚደነግጉ ቢሆንም፣ በሃገሪቱ ከ25  ዓመት በላይ እስር ስለማይፈቀድ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዲፀና መወሰኑን ገለፁ፡፡ይሁን እንጂ የሥር ፍ/ቤት ክንፈሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)  ፍ/ቤት በመድፈር በተጨማሪነት የተላለፈበት የ5 ዓመት እስር እንዲሻር ሲሉ ትዕዛዝ ሰጡ፡፡

“ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላኝ፣ ታሳዝነኛለች ”

የፍርዱ ውሳኔ ምንም ለውጥ እንዳላመጣ ቀድማ የተረዳችው ሰርካለም ፋሲል “እስክንድር ወንጀለኛ ነው ከተባለ፣ ወንጀሉ ሃገሩን መውደዱ ነው” ብለህ ፅፍ አለችኝ -በንዴት። “ግንቦት 7  የእስክንድርን እጅ የመጠምዘዝ ኃይል የለውም”  አለችኝ በቁጭት፡፡

ችሎቱ ውሳኔውን አሳውቆ ዳኞች እንደተነሱ፣ ተከሳሾች ከፍርድ ሳጥን እየወረዱ ባለ እስክንድር እልሀ በተናነነቀው ስሜት ጮክ “አትጠራጠሩ እውነት ተደብቃ አትቀርም”  አለ፡፡ ናትናኤል “የተከራከርነው ፍትህ እናገኛለን ብለን አይደለም፤ ፍትህ ወዳድ ስለሆንን ነው” አለ፡፡ አበበ ቀስቶ “ ለማንኛውም እዚህ መጥታችሁ በእናንተ ኮርተናል”  ሲል በችሎት የሰገኘውን ሰው አመሰገነ፡፡ “አንተ የኔ ጀግና ነህ፡፡ ብትሞትም ሙት፣ በእውነትህ ኮርተህ ሙት!”  አለች ሰርካለም እንባ እየተናነቃት፡፡ ወዲያው ፖሊሶች ታዳሚውን እየገፋፉ ከችሉት አስወጡ፡፡ በሌላኛው በር አንዱአለምና እስክንድርን አንድ ላይ፣ ክንፈሚካኤል እና ናትናኤልን በአንድ ላይ በካቴና አስረው፡- ወደ ቃሊቲ፡፡“

“አንተ የኔ ጀግና ነህ፡፡ ብትሞትም ሙት፣ በእውነትህ ኮርተህ ሙት!”  አለች ሰርካለም እንባ እየተናነቃት። ወዲያው ፖሊሶች ታዳሚውን እየገፋፉ ከችሉት አስወጡ፡፡ በሌላኛው በር አንዱአለምና እስክንድርን አንድ ላይ፣ ክንፈሚካኤል እና ናትናኤልን በአንድ ላይ በካቴና አስረው፡- ወደ ቃሊቲ፡፡

አይዞዎት እማማ፤ ወደፊት የሚመጣው አይታወቅም አልኳቸው ” የክንፈሚካኤልን እናት፡፡ በእኔ ቤት ማፅናናቴ ነው፡፡“ አዎ የሚመጣው አይታወቅም፣ ይኼስ ይመጣል ብሎ ማን አሰበ፡፡ እናንተ ወጣቶች ራሳችሁ አይ ዞአችሁ፡፡ ታሰሩ፡፡ አይዞአችሁ፡፡ ግን አትሙቱ”  አሉኝ የክንፈ እናት፡፡“

አይዞአችሁ ታሰሩ!  ግን አትሙቱብን!”  የእኚያን እናት አባባል እያላመጥኩ ከዳኝ፡፡ እንባዬ መጣ፡፡ ዓዓይኔን እንዳያዩ ፊቴን አዞርኩ፡፡

“ ሀገሬን ሀገሬን – የምትል ወፍ አለች
እኔን እኔን መስላኝ፣ ታሳዝነኛለች ”

አበቃ፡፡

 

በቬጋስ ላለፉት ሁለት ወራት በሥራ ማቆም አድማ ላይ የነበሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች በድል ወደ ሥራ ተመለሱ

0
0


የሀበሻውን ህ/ሰብ ላደረገላቸው እገዛ አመስግነዋል
የፍሪያስ አሽከርካሪዎች ተቃውሞ ቀጥሏል

በቬጋስ ለሁለት ወራት በዘለቀ የስራ ማቆም አድማ ላይ የቆዩት የየሎ ቼከር ስታር የታክሲ አሽከርካሪዎች በዩኒየኑ አማካኝነት ሲያደርጉት የነበረውን የኮንትራት ድርድር የኩባንያውን ማሻሻያ ተቀብለው ወደ ስራ ለመመለስ ዛሬ በቬጋስ የኩባንያው ቅጥር ግቢ ዛሬ ሐሙስ ሜይ 2/2013 ባደረጉት ስምነት ወደ ስራ ለመመለስ ወሰኑ።የአሽከርካሪው ተወካዮች 75 በመቶ ድል አግኝተናል ሲሉ ገልጸዋል።
vegas ethiopian and erirtian taxi drivers
አቶ ሽመልስ ደረሱና አቶ ቢኒያም ሰመረአብ የአሽከርካሪዎቹ የስራ ማቆም አድማ አስተባባሪዎች ሁለቱ በጋራ ለህብር ሬዲዮ ዘጋቢ በሰጡት መግለጫ በስራ ማቆም አድማው ሲጠይቋቸው ከነበሩ በርካታ ጥያቄዎች መካከል የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም የተወሰነ ሳንቲም ጭማሪ፣የፔሮል አከፋፈል ግልጽ እንዲሆን መደረግ፣ በአድማው ላይ የነበሩ አራት ዓመት ድረስ ሲገቡ የስራ ዋስትና እንዲከበርላቸው መደረጉ፣ የዓመት ፈቃድም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንደተጠበቁ መሆን በዋና ዋናነት ይጠቀሳሉ።
> ያሉን እነዚህ የተቃውሞ አስተባባሪዎች በከተማዋ የሚኖሩ የቢዝነስ ተቋማት፣የተለያየ ሙያ ያላቸው ግለሰቦችና ተቃውሞው በቀጥታ የማይመለከታቸው በስራ ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች ህብር ሬዲዮም ላደረገው ሙያዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
> ያሉት ሁለቱ የተቃውሞ አስተባባሪዎች ለነሱ ስራ ቢጀምሩም > በእረፍታቸው ከመቆም ጀምሮ ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ የቀረውም ህ/ሰብ የጀመረውን ድጋፍ እንዲቀጥልላቸው ጠይቀዋል።
> ያሉት አቶ ሽመልስ ደረሱ በስራ ላይ ሆነውም የፍሪያስ አሽከርካሪዎች ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ማንኛውንም እንቅስቃሴ በዕውቀትም ስራ የጀመሩት ሁሉ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በዛሬው የኮንትራት ስምምነት መሰረት የየሎ ቼከር ስታር የኩባንያው 1800 ታክሲ አሽከርካሪዎች ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በአዲሱ የኮንትራት ስምምነት መሰረት ይሰራሉ።በቬጋስ ካሉት የታክሲ ኩባንያዎች ዛሬ ከስራ ማቆም አድመኞቹ ጋር የተስማማው ሁለተኛው ሲሆን አሁን በተቃውሞ ላይ የቀሩት አሽከርካሪዎች የሚሰሩበት ፍሪያስ ኩባንያ አንደኛው ትልቁ ሲሆን ሁለት ሺህ አሽከርካሪዎች ሲኖሩት ከነዚህ ውስጥ 72 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ቢሆኑም ከዚህ ቀደም ሲያነሱት ለነበረው የጋራ መብታችንን የሚያስከብር ኮንትራት ይኑር ጥያቄ የስራ ማቆም አድማ ሲያደርጉ ተከፋፍለው መቆማቸው ለእርስ በእርስ የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። ችግሩ ወደ ከፋ ማህበራዊ ቀውስ ከመሄዱ በፊት በአንድ ላይ እንዲቆሙ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲደረግ ቆይቷል።
ዮናስ ተሰማ የፍሪያስ የስራ ማቆም አድማ አስተባባሪ ለህብር ሬዲዮ በሰጠው መግለጫ በየሎ ቼከር ስታር አሽከርራሪዎች ድል አግኝተው መግባት መደሰቱን ገልጿል። የፍሪያስ አሽከርካሪዎችም በአንድ ላይ ቆመው ውጤት እንዲያመጡ ማመን እና ለመብታቸው የጀመሩትን ትግል በውጤት እንደሚያጠናቅቁ ያለውን ተስፋ ገልጾ ዛሬም በታቃውሞ ላይ ያሉ ባልደረቦቹን እንበርታ በአንድ ላይ እንቁም ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
በቬጋስ የታክሲ አሽከርካሪዎች ታሪክ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ይህ ተቃውሞ አሁን የተጀመረው የመብት ጥያቄ ውጤት ካስገኘ በሁዋላ እያንዳንዱ አሽከርካሪ የራሱን ሜዳሊያ ለማግኘት በጋራ ቆሞ የሚታገልበትን ስልት ወደፊት እንደሚነድፉ አስተባባሪዎች ጠቅሰዋል።

ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በርዕዮት ጉዳይ ያልተጠየቀውን መለሰ

0
0

ከዳዊት ሰለሞን

Dawit

ዳዊት ሰለሞን

ባሳለፍነው እሁድ ለንባብ የበቃው የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ በደብዳቤዎች አምዱ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተላከ ያለውን ደብዳቤ አስነብቧል፡፡ከተቋሙ ተላከ የተባለው ደብዳቤ ማህተም፣የአስተዳደሩን ፊርማና ወጪ የተደረገበትን ቀን ያላካተተ ቢሆንም ጋዜጣው ሪፖርተር ታማኝ በመሆኑ ከማረሚያ ቤቱ የተላከ ነው ለማለት በግሌ ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ፡፡በሪፖርተር ታማኝ ምንጭነት ዙሪያ ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች ደብዳቤውን ሰንደቅና አዲስ ዘመን ገጽ 3 ላይ የሚጽፉ ያዘጋጁት ይሆናል በማለት መጠርጠር መብታችሁ ይመስለኛል፡፡ወደ ደብዳቤው ዝርዝር ስንገባ ያልታረሙ ሰዎች እነርዕዮትን እናርማለን ብለው በአስተዳደርነት መቀመጣቸውን ወለል ብለውላችሁ ትመለከታላችሁ ፡፡ታገሱኝማ

አስተዳደሩ ደብዳቤውን የላከው አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት(ሲፒጄ)በማረሚያ ቤቱ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን በማስመልከት መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ የድርጅቱን ክስ ለማስተባበል ነው፡፡ሲፒጄ በመግለጫው ርዕዮት በርቀት ሁለተኛ ድግሪዋን ለማግኘት ከተመዘገበች በኋላ በማረሚያ ቤቱ እንዳትማር መከልከሏንና  ደረጃውን የጠበቀ የህክምና ክትትል እንደማይደረግላት ማተቱ አይዘነጋም፡፡ለወቀሳው ምላሹን በሪፖርተር የሰጠው ማረሚያ ቤቱ

1)‹‹ርዕዮት ለብቻዋ በዝግ ቤት ታስራለች የተባለው ውሸት ነው፡፡እንዲህ በማለት መናገርም አብረዋት የታሰሩና በአንድ ክፍል ውስጥ የሚገኙ እስረኞችን ሰው አይደሉም በማለት እንደመናገር ይቆጠራል፡፡››ብሏል፡፡አስቂኙ ነገር ሲፒጄ በመግለጫው ርዕዮት ለብቻዋ በዝግ ቤት ታስራለች አለማለቱ ነው፡ከዚህ ይልቅ ሲፒጄ ያለው ‹‹ርዕዮት በቀጣይ ለብቻዋ ልትታሰር ትችላለች›› ነው፡፡ያልተጻፈ መግለጫ በማንበብ መልስ መስጠት ምን ሊሰኝ እንደሚችል ለማንም ግልጽ አይመስለኝም፡፡

2)‹‹ርዕዮት የርቀት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ትገኛለች፡፡ይህንንም ከቅድስት ማርያም ዮኒቨርስቲ ኮሌጅ በመጠየቅ ማረጋገጥ ይቻላል››ተብሏል፡፡ወዳጆቼ ተቋም ሲዋሽ ምን ይባላል? ጋዜጠኛዋ ቤተሰብ፣ወዳጅ፣አድናቂና በየሳምንቱ እየሄደ የሚጎበኛት ቁጥሩ ቀላል የማይሰኝ አጋር አላት፡፡ማረሚያ ቤቱ ቢያንስ እነዚህ ምን ይሉኛል አይልም? እንዴት ነው እነዚህ ሰዎች የታረሙ ሰዎችን ሊያፈሩ የሚችሉት?እውነቱ ግን እነርሱ እንደሚሉት አይደለም፡፡ለርዕዮት ከህንዱ ዮኒቨርስቲ የመጡ የመማሪያ መጻህፍት ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዲገቡ ያልተፈቀደላቸው በመሆኑ የሚገኙት የጋዜጠኛዋ ወኪል ጋር ነው፡፡(እናንተም ተመልክታችሁ ትፈርዱ ዘንድ መፃህፍቱን ፎቶግራፍ አንስቻለሁ)

3) ርዕዮት የዲሲፕሊን ችግር አለባት ያለው የማረሚያ ቤቱ ደብዳቤ በስነ ምግባር ጉድለት መከሰሷን በመጥቀስ እንደ አስፈላጊነቱ በቀጣይ በቀረበባት ክስ ቅጣት ሊጣልባት እንደሚችል አስፈራርቷል፡፡ ርዕዮትን የከሰሳትና የሚመሰክርባት ማን ነው?ዳኞቹስ እነማን ናቸው ? (መቼስ በሪፖርተር ላይ የወጣውን ደብዳቤ የጻፉ ከሆኑ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት አያስቸግርም)ጋዜጠኛዋ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ለቀረበባት ክስ ጠበቆቿን በማማከር ምላሽ መስጠት ትችላለች?ምስክሮችን የማቅረብ መብትስ አላት?ደብዳቤው ስለ እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚለው አንዳች ነገር የለውም፡፡

ባሳለፍነው እሁድ ለንባብ የበቃው የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ በደብዳቤዎች አምዱ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ተላከ ያለውን ደብዳቤ አስነብቧል፡፡ከተቋሙ ተላከ የተባለው ደብዳቤ ማህተም፣የአስተዳደሩን ፊርማና ወጪ የተደረገበትን ቀን ያላካተተ ቢሆንም ጋዜጣው ሪፖርተር ታማኝ በመሆኑ ከማረሚያ ቤቱ የተላከ ነው ለማለት በግሌ ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ፡፡በሪፖርተር ታማኝ ምንጭነት ዙሪያ ጥያቄ ያላችሁ ሰዎች ደብዳቤውን ሰንደቅና አዲስ ዘመን ገጽ 3 ላይ የሚጽፉ ያዘጋጁት ይሆናል በማለት መጠርጠር መብታችሁ ይመስለኛል፡፡ወደ ደብዳቤው ዝርዝር ስንገባ ያልታረሙ ሰዎች እነርዕዮትን እናርማለን ብለው በአስተዳደርነት መቀመጣቸውን ወለል ብለውላችሁ ትመለከታላችሁ ፡፡ታገሱኝማ

አስተዳደሩ ደብዳቤውን የላከው አለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት(ሲፒጄ)በማረሚያ ቤቱ የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን በማስመልከት መግለጫ ማውጣቱን ተከትሎ የድርጅቱን ክስ ለማስተባበል ነው፡፡ሲፒጄ በመግለጫው ርዕዮት በርቀት ሁለተኛ ድግሪዋን ለማግኘት ከተመዘገበች በኋላ በማረሚያ ቤቱ እንዳትማር መከልከሏንና  ደረጃውን የጠበቀ የህክምና ክትትል እንደማይደረግላት ማተቱ አይዘነጋም፡፡ለወቀሳው ምላሹን በሪፖርተር የሰጠው ማረሚያ ቤቱ

1)‹‹ርዕዮት ለብቻዋ በዝግ ቤት ታስራለች የተባለው ውሸት ነው፡፡እንዲህ በማለት መናገርም አብረዋት የታሰሩና በአንድ ክፍል ውስጥ የሚገኙ እስረኞችን ሰው አይደሉም በማለት እንደመናገር ይቆጠራል፡፡››ብሏል፡፡አስቂኙ ነገር ሲፒጄ በመግለጫው ርዕዮት ለብቻዋ በዝግ ቤት ታስራለች አለማለቱ ነው፡ከዚህ ይልቅ ሲፒጄ ያለው ‹‹ርዕዮት በቀጣይ ለብቻዋ ልትታሰር ትችላለች›› ነው፡፡ያልተጻፈ መግለጫ በማንበብ መልስ መስጠት ምን ሊሰኝ እንደሚችል ለማንም ግልጽ አይመስለኝም፡፡

2)‹‹ርዕዮት የርቀት ትምህርቱን በመከታተል ላይ ትገኛለች፡፡ይህንንም ከቅድስት ማርያም ዮኒቨርስቲ ኮሌጅ በመጠየቅ ማረጋገጥ ይቻላል››ተብሏል፡፡ወዳጆቼ ተቋም ሲዋሽ ምን ይባላል? ጋዜጠኛዋ ቤተሰብ፣ወዳጅ፣አድናቂና በየሳምንቱ እየሄደ የሚጎበኛት ቁጥሩ ቀላል የማይሰኝ አጋር አላት፡፡ማረሚያ ቤቱ ቢያንስ እነዚህ ምን ይሉኛል አይልም? እንዴት ነው እነዚህ ሰዎች የታረሙ ሰዎችን ሊያፈሩ የሚችሉት?እውነቱ ግን እነርሱ እንደሚሉት አይደለም፡፡ለርዕዮት ከህንዱ ዮኒቨርስቲ የመጡ የመማሪያ መጻህፍት ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዲገቡ ያልተፈቀደላቸው በመሆኑ የሚገኙት የጋዜጠኛዋ ወኪል ጋር ነው፡፡(እናንተም ተመልክታችሁ ትፈርዱ ዘንድ መፃህፍቱን ፎቶግራፍ አንስቻለሁ)

3) ርዕዮት የዲሲፕሊን ችግር አለባት ያለው የማረሚያ ቤቱ ደብዳቤ በስነ ምግባር ጉድለት መከሰሷን በመጥቀስ እንደ አስፈላጊነቱ በቀጣይ በቀረበባት ክስ ቅጣት ሊጣልባት እንደሚችል አስፈራርቷል፡፡ ርዕዮትን የከሰሳትና የሚመሰክርባት ማን ነው?ዳኞቹስ እነማን ናቸው ? (መቼስ በሪፖርተር ላይ የወጣውን ደብዳቤ የጻፉ ከሆኑ መጨረሻው ምን እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት አያስቸግርም)ጋዜጠኛዋ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ለቀረበባት ክስ ጠበቆቿን በማማከር ምላሽ መስጠት ትችላለች?ምስክሮችን የማቅረብ መብትስ አላት?ደብዳቤው ስለ እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚለው አንዳች ነገር የለውም፡፡

ጽናት –ሁሉም ሊያየው የሚገባ ፊልም (Video)

የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ

0
0

ከነመራ ዲንሳ

ነመራ ዲንሳ

ነመራ ዲንሳ


ከ፩፯ አመት የደርግ የጭቆና አገዛዝ ማብቂያና ስርአቱ ካበቃበት ከ፩፱፰፫ ወርሐዊ ግንቦት ጀምሮ ለ፪፪ አመታት የስርአቱን ለዉጥ ተከትሎ ስልጣንላይ በሀይል ተቆናጦ ያለዉ የህወሐት መንግስት አምባገነንነቱ ወደ አፓርታይድ ስርአት ተቀይሮዋል።
ለዚህም ማሳያዉ ላለፋት ፪፩ አመታት በሙዋቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መሪነት በሐገሪቱዋ ዉስጥ እጅግ ኢሰብአዊ ድርጊት ዘርንና ክልልን መሰረታዊ ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም እየተፈፀመ ነዉ።
ለመጥቀስ ያክል ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ የህወሐት ባላስልጣናት ትእዛዝ መለስን ጨምሮ በጋምቤላ፣በኦሮሞ፣በአማራ፣በኦጋዴን እና በደቡብ ህዝቦች ላይ አስከፊ የእስራት የግርፋት እና የጅምላ ግድያ ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም ድረስ የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ ዜጎችን በሀገሪቱዋ በየትኛዉም አካባቢ የመኖር የሀገሪቱዋ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ የዘር ማፅዳት ወንጀል በህወሐት አምባገነን መሪዎች እየተፈፀመ ነዉ።
በ፩፱፰፫፣፰፬ ጋምቤላ፣ከ፩፱፰፬ እስከ ፩፱፰፮ በኦሮምያ ጅማ፣ሰጠማ፣ሲጊሞ እና ጌራ የሚባሉ አካቢዎች፣ከ፩፱፰፬ እስከ ፩፱፰፰ በአማራ ተወላጆች ላይ በበደኖ፣ወተር፣በአርሲ ባሌ፣በሐረር ጉርሱም አካባቢ፣ከ፩፱፱፱ እስከ ፪፲፻ በደግሐቡር፣በቀብሪደሐር እና በኦጋዴን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በመከላከያ ሠራዊት በጦር ሄሊኮፕተር በመታገዝ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል።ከወራትም በፊት በደቡብ ኦሞ እና በጋምቤላ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል። ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀምና አሁንም እየተፈፀመ ባለበት ወቅት በሀገሪቱ ፍርድ ቤት ማንም ተከሶ ለፍርድ የቀረበ የለም ነር ግን ይሄን ሁሉ በደል እና ግፍ የተቃወሙና የፃፋ ንፁሀን ያገሪቱ ዜጎች ለአፈና፣ለስደትና ለእስር ተዳርገዋል።
bekele gerbaበስደት ያሉትን ባልዘረዝርም ሀገር ዉስጥ ሆነው በሀገሪቷ ህገመንግስት ተጠቅመው ስርዐቱን ስለተቃወሙና ስለፃፋ ከእድሜ ልክ እስከ ረጅም አመት እስራት ተፈርዶባቸዉ በእስር ላይ ያሉና እስርቤትም ሆነው ይግባኝ በማለትም ሆነ ባለማለት በሀገሪቷ የመጨረሻዉ ጠቅላይ ህወሐት ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን ያበሰሩንን ጀግኖች ጠቅሳለሁ፣
ሌልሴ ወዳጆ፣ርዮት አለሙ፣እስክንድር ነጋ፣በቀለ ገርባ፣አንዱአለም አራጌ፣ዉብእሼት ታዬ፣የድምፃችን ይሰማ ኮሚቴዎች>>>ወዘተ ኮራንባችሁ ያላችሁበት ህይወት የኛ ሆኖ ቢያቃጥለንም።
በአንዱአለም እና እስክንድር ነጋ ላይ የይግባኝሽ ፍርድ ቤት ያፀናዉ ፍርድ ከመለስ ሞት በውሓላም ህወሐት ፍትህን የገደለ የአፓርታይድ ስርዐት መሆኑን አሳውቆናል።
ስለሆነም ከሰሜን ኮርያ በላይ የከፋው የህወህት ስርዐት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እየተደገሰለት ባለዉ የዉሸት ፖለቲካ ክስ እሱንም በይግባኝ ፍርድ ቤት ጭምር ከምናምን እድሜ እስር ጋር ቂሊንጦ ወይም ዝዋይ እስርቤት ማየታችን አይቀርም።
እናም የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገሪቷ ፍትህ መቀበሩን አረጋግጦልናል።
ውድ አንባቢዎቼ ነገር ግን እኔም ተመስገን ደሳለኝ ነኝ እናንተስ?
ሀገራችንን እና ህዝቧን ከአፓርታይድ ስርዐት ዛሬዉኑ እንታደግ!!!
ህዝብ ያሸንፋል።

ግርማዊነታቸው የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ሲያቆሙ የተናገሩት


ኮትዲቯር ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ሻምፒዮን ሆነች

0
0

cot d'vowa
በፊፋ የእግር ኳስ ደረጃ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ኮትዲቯር የአፍሪካ ከአስራ ሰባት ዓመት በታች ሻምፒዮን መሆኗን አረጋገጠች።
በሞሮኮ ማራኬች ከተማ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን የአፍሪካ ከአስራ ሰባት ዓመት በታች ዋንጫ ኮትዲቯር በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳችው ናይጄሪያን በመርታት ነው።
የዋንጫ ተፋላሚ የነበሩት ናይጄሪያውያን በፍፃሜው ጨዋታ መደበኛ ሰዓቱን አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ቢያጠናቅቁም በመለያ ምት አምስት ለ አራት ከመሸነፍ አልዳኑም።
ናይጄሪያ በፍፃሜው ጨዋታ ገና በ ስምንተኛ ደቂቃ መሪ ለመሆን የሚያስችላትን ግብ በ አይዙ ኦሚንጐ አማካኝነት ብታስቆጥርም የፊት መስመር ተጫዋቹ ቢል ዴዲአ ከአስራ ስምንተኛ ደቂቃ በኋላ ለኮትዲቯር የአቻነቷን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
በጨዋታው አስራ ስድስተኛ ደቂቃ ላይ ኦሚጐ የተባለውን ተጫዋች በቀይ ካርድ ያጣችው ናይጄሪያ አብዛኛውን የጨዋታ ጊዜ በአቻ ውጤት ብታጠናቅቅም በመለያ ምት ያባከነችው አንድ ኳስ ዋንጫውን እንዳታገኝ አድርጓታል።
ኮትዲቯር ና ናይጄሪያ በምድብ ጨዋታ ተገናኝተው ኮትዲቯር አንድ ለ ዜሮ በሆነ ውጤት ማሸነፏ ይታመናል።
የደረጃ ጨዋታቸውን ያካሄዱት ቱኒዚያና አስተናጋጇ ሞሮኮ ሙሉውን የጨዋታ ጊዜ አንድ ለአንድ በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተው በመለያ ምት ቱኒዚያ አስራ አንድ ለ አስር አሸንፋለች። በዚህም መሠረት ቱኒዚያ ሦስተኛ ሞሮኮ አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።
በዚህ ሻምፒዮና ከአንድ እስከ አራት ባለው ደረጃ ውስጥ ያጠናቀቁት አራት አገሮች በመጪው ዓመት በሚካሄደው የዓለም ከአስራ ሰባት ዓመት በታች ዋንጫ ተሳታፊ ይሆናሉ።
በመጪው ዓመት የሚካሄደውን የዓለም ከአስራ ሰባት ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እንደምታዘጋጅ ይታወቃል።

አንድነት “የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ የኢህአዴግ የዕድሜ ማራዘሚያና መጠቀሚያ ከመሆን በዘለለ ፋይዳ አለው ብለን አናምንም”አለ

0
0

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ “የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ የኢህአዴግ የዕድሜ ማራዘሚያና መጠቀሚያ ከመሆን በዘለለ ፋይዳ አለው ብለን አናምንም” ሲል ትናንት በነአንዷአለም አራጌ ላይ የወሰነውን የፍርድ ውሳኔ አጥብቆ አወገዘ። ፓርቲው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “አሁንም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በአፋጣኝ እንዲፈቱ እንጠይቃለን!!!” ብሏል። ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል።

UDJ Images አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በሰላማዊና ህጋዊ የትግል መንገድ ለውጥ ማምጣት ይቻላላል፤ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንፈጥራለን፤ ስልጣንም በግለሰቦች ወይም በቡድኖች ይሁንታ የሚገኝ ሳይሆን በህዝቡ በልካም ፈቃድ ይሆናል የሚል ጠንካራ እምነት በመያዝ ከአምባገነኑ ስርዓት ጋር እየታገለ የሚገኝ ነው፡፡

ይሄ ጠንካራ የትግል መነሳሳታችን እና ያለን የህዝብ ድጋፍ ጠንካራ ተቃዋሚ በዓይኑ ማየት የማይፈልገው ገዥ ፓርቲ ጥርስ ውስጥ የከተተን በምስረታችን ማግስት ጀምሮ ነው፡፡ በርካታ አባሎቻችንንና አመራሮቻችንን ተልካሻ ምክንያት እየተለጠፈባቸው ታስረዋል፣ ተሳድደዋል፣ ተደብደበዋል፡፡

በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ ጠንካራ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችና ተቃውሞዎች ሁሉ የሚሰጣቸው ስም ሽብርተኝነት የሚል ነው፡፡ የስርዓቱ የስልጣን ማቆያ፣ የሀቀኛ ተቀናቃኞችና ስርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞች ማሸማቀቂያ ብሎም ማስወገጃ መሳሪያ ሽብርተኝነት ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

ፓርቲያችን አንድነትም ጠኋትና ማታ እየተጠቀሰ ዜጎች እንዲሸማቀቁ የሚደረግበትና የፖለቲካ አመራሮች የሚታሰሩበት የፀረ-ሽብርተኝነት ህግ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ ሰኔ 18 ቀን 2001 ዓ.ም የፀረ ሽብር ህጉ ገና ረቂቅ አዋጅ እንደነበረ ለማፈን እየተሰናዳ መሆኑን በመጥቀስ ‹‹የፀረ-ሽብርተኝነት ረቂቅ አዋጅ በዜጎች ላይ ሽብር ፈጣሪ ነው›› በሚል ርዕስ ባወጣነው መግለጫችን ረቂቅ አዋጁ እንዳይፀድቅ የሚሰማ ባይኖርም አበክረን ጩኸታችንን አሰምተን ነበር፡፡

ወዲያው ህግ ሆኖ እንደወጣም የፀረ ሽብርተኝነት ትግልን ሽፋን በማደረግ የገዥው ፓርቲ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የማፈን ድብቅ ፍላጎት ተግባራዊ መሆን ጀመረ፡፡ የመጀመሪያው ሰለባ አንድነት ፓርቲ ነው ብንል ማጋነን አይደለም፡፡ አንዱአለም አራጌንና ናትናኤል መኮነንን የመሰሉ ከፍተኛ የፓርቲ አመራሮችንና ሌሎችን የፓርቲያችን አባሎች በእስር አጥተናል፡፡ እነዚህ በማናለብኝነት የሚፈፀሙ የገዥው ፓርቲ ሸፍጦች ትግላችንን የበለጠ የሚያጠናክሩና አፈናውን ለመስበር ጉልበት የሚሆኑን ናቸው እንጂ አንገታችንን አያስደፉንም፡፡ የፍትህ ተቋማት ላይ እምነት መጥፋቱ፣ ከላይ እስከታች ያለው የአፈና ቋንቋ ተመሳሳይ መሆኑና የገዥው ፓርቲ እጅ መርዘም ትግሉን ማፋፋምና አጠናክሮ መቀጠል ዋና መፍትሄ እንደሆነ የሚጠቁመን ነው፡፡

Andualem-Aragie ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም ይግባኝ ሰሚ ችሎት በነ አንዷለም አራጌ ፍርድ ላይ በአንድ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል የአንዱን ጥቂት ዓመታት ከመቀነስ ባለፈ የስረኛውን ፍ/ቤት ውሳኔ ትክክል ነው ብሏል፡፡ ይሄ ፍርድ የሚያስታውሰን የኪሊማንጃሮ ኢንተርናሽናል ኮርፖሬሽን ሊሚትድ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ከፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር ይፋ ያደረገውን ጥናት ነው፡፡ በ27 የመንግስት ተቋማት ላይ በተደረገ ጥናት ‹‹በከፍተኛ ደረጃ የህዝብ አመኔታ ያጡ ተቋማት›› በሚል ርዕስ ስር በመጀመሪያ ደረጃ የተቀመጡት ፍ/ቤቶች ናቸው፡፡ ይሄ የሚያሳየው ፍ/ቤቶች የገዥው ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚዎች እንጅ ገለልተኛ ተቋማት አለመሆናቸውን ነው፡፡

ከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ወጣቱን ፖለቲከኛና ከፍተኛ አመራር አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን ሽብርተኞች እንደሆኑና በሰላማዊ ትግል ሽፋን ሽብርተኝነትን እንሚያራምዱ ተደርጎ የቀረበው ሀተታ የፓርቲያችንን ጠንካራ መዋቅር ያላገናዘበ፣ የፓርቲያችንን መልካም ስም የሚያጎድፍ ነው፡፡ እነ አንዷለምም ሰላማዊ ታጋዮች እንጅ ሽብርተኞች አይደሉም፡፡ ሽብርተኝነት በኮሃራም ናይጀሪያ፣ በፓኪስታንና አፍጋኒስታን በየዕለቱ የምንሰማው እንጅ የኢትዮጵያ ችግር አይደለም፡፡

በአጠቃላይም የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ የኢህአዴግ የዕድሜ ማራዘሚያና መጠቀሚያ ከመሆን በዘለለ ፋይዳ አለው ብለን አናምንም፡፡ የአመራሮቻችንንና አባሎቻችንን መታሰር አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ አሁንም ደግመን ደጋግመን የምንለው በሽብርተኝነት ስም ዜጎችን ማሰር ይቁም፤ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ሽብርተኝነት አይደለም፤ የፖለቲካና የህሊና እስረኞ በአስቸኳይ ይፈቱ፡፡

ትግላችን እስከለውጥ ድረስ ይቀጥላል!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት)

ሚያዝያ 25 ቀን 2005 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የአቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation)! ክፍል ሁለት –ከግርማ ሞገስ

0
0

ግርማ ሞገስ (girma.moges@yahoo.com)
አርብ ሚያዚያ 25 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት (Friday, May 03, 2013)

Meles Foundationመንግስት በመፈንቀል ስልጣን የጨበጠው የትናንቱ አምባገነን መንግስቱ ኃይለማሪያም የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ አብዮቱን እንድጠብቅ አደራ ሰጥቶኛል ብሎን ነበር። ስልጣን አልለቅም ማለቱ ነበር። የአምባገነኑ መለስ አደራ መፈክሮች ቢለዋወጡም “የልማት ጠባቂ ነኝ” እያለ መሞቱ ይታወሳል። ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉት የአቶ መለስ ፍጡራን አምባገነኖች ደግሞ “የአቶ መለስ ራዕይ ሞግዚት” ነን ይላሉ። ሌላ ሃያ አመቶች ሊገዙን። የትናት በስቲያው አብዮት ጠባቂ፣ የትናንቱ ልማት ጠባቂ፣ የዛሬዎቹ ደግሞ ራዕይ ጠባቂ። የአምባገኖች መተካካት በኢትዮጵያ የሚያከትመው የኢትዮጵያ ህዝብ አፉን እና እጁን አንድ አድርጎ አደባባይ በመውጣት የስልጣን ባለቤት እኔ ነኝ ሲላቸው ብቻ ነው። በሰላማዊ ትግል የመንግስት ስልጣን ባለቤት ሲሆን ብቻ ነው።ለማንበብ እዚህ ይጫኑ   - የአቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም – ክፍል ሁለት

ስቅለትና ትንሣዔ ወያኔና ኢትዮጵያ (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

0
0

tinsae

ለክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቼ እንኳን ለብርሀነ ትንሣዔው አደረሳችሁ። የስግደትን ክቡርነት፣ የይቅር በለን የንስሀ ጸሎትን ታላቅነት በማክበር ለአመት ከዘለቀው የድምጻችን ይሰማ ትግል ጋብ ብላችሁ ለጸሎታችን ይሰማ ክብር ለሰጣችሁ እግዚአብሄር ያክብራችሁ። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊነት ታላቅ መሆኑን ስላስተማራችሁ የተመሰገናችሁ ሁኑ። በፍቅር እንደምንከብር በነጻነትም እንደምናድግ ከዚህ በላይ ትምህርትስ እንደምን ይገኛል? መሪውን የሚያስተምር፣ ከመሪዎቹ ቀድሞ ከፊት የሚገኝ ሕዝብስ እንደ ኢትዮጵያውያን ያለ ወዴት አለ?

አይሁዶች የአብራካቸው ክፋይ ኢየሱስን የማርያምን ልጅ ለመስቀል አላመነቱም። ፍርድ ሰጪው ከደሙ ንጹህ ነኝ ብሎ እጆቹን ታጠበ። እየወገሩ የሰቀሉት ግን ሀሴትን አገኙ። ሟቹ ከመስቀሉ ላይ ሆኖ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው እያለ ወደ አባቱ ጮኸ። እየጮኸም ምህረትን እየለመነም ህይወትን ለመሰናበት ከመስቀሉ ላይ ተቸንክሮ የፀሀይን ብርታት የሰውን ጭካኔ እየተመለከተ አዘነ። ዛሬ ላይ ቆመን ስንመለከት ግን እግዜር ካልጠፋ ነገር ለሰው ልጅ ምህረት ማድረግ ነበረበት ወይ? ያሰኛል። በዚህች ምድር ውስጥ እግዜር ከፈጠረው መካከል እንደሰው ልጅ ክፉ እንደሰው ልጅ አጥፊ ነበርና ነው ወይ የሚምረን? ማለት ፌዘኛነት አይደለም። በዚህች ምድር ላይ የራሱን ዘር ለማጥፋት ሌት ተቀን የሚያደባና የመሳርያ አይነት የሚፈብርክ ቢኖር ‘ሆሞ ሳፒየንስ’ ነኝ ብሎ ራሱን የጠራው የሰው ዘር ብቻ ነው። ወይም ከአዳምና ከሄዋን መጣን ብሎ የሚያምነውና እግዜር በአምሳሉ ሰራኝ የሚለው ፍጡር ብቻ ነው። እናም በሰንበት ቀን በመስራቱ፣ የታወረን ብርሀኑን ስለሰጠው ኢየሱስን የራሱ ወገኖች በጎልጎታ ላይ ቸነከሩት።

ይኸው ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያ ወደ መሰቀያዋ እየተገረፈች እየተነዳች ነው። ቀሚስዋ ብጥስጥሱ ወጥቷል። ያጠቡና ያሳደጉ ጡቶችዋ በመንጠቆ እየተጎተቱ ነው። ፀጉርዋ ተገምዶ ቁልቁል ወርዷል፣ አይኖችዋ ጎድጉደዋል። በጭኖችዋ ላይ ደም እየተንዠረገገ ይወርዳል። እናም ወደሞትዋ እየተነዳች ነው። አሞራዎች ጣዕረ ሞትን አጅበው የሚመጡ ይመስል ሰማዩን ክብ ሰርተው ይከንፉበታል። ጅቦቹም እንዲሁ ዙርያውን አስፍስፈዋል። ከጉልበተኞች የተረፈውን ለመቀራመት ተኩላና ቀበሮ ቦታ ቦታ ይዘዋል። የትግሬ ጎጠኞች እንደ እሾህ አክሊል አናትዋ ላይ ሆነው ይጠቀጥቋታል። ጀሌዎቻቸውን እያዘዙ ጎንዋን፣ እግርዋን፣ ሽንጥዋን መላ አካልዋን በጦር ይሸቀሽቃሉ። ዘርፈው የያዙትን ወርቅ በከረጢት ጀርባቸው ላይ አንጠልጥለው፣ ሚስቶቻቸውም ቁልል ሹሩባቸው ላይ ወርቁን ገምደው ከበሮ እየደለቁ ትሰቀል! ትሰቀል! እያሉ ይጮሃሉ። እኒህ ገራፊዎች በእቅፍዋ የነበሩ ልጆችዋ ጡትዋን ጠግበው እሸትዋን በልተው ሀ..ሁን ቆጥረው ያደጉቱ ግን ክህደት፣ እብሪትና ጎጠኛነት እንደ አደንዛዥ እፅ ያሰከሩዋቸው፣ ያንቀዠቀዣቸው ክፉ ፍሬዎችዋ ናቸው። ኢትዮጵያ ሆኖ የማይታወቅ ክህደት፣ ተደርጎ የማያውቅ በደልን የምትሸከመው ልጆቼ ባለቻቸው የሰው አሜኬላዎች መሆኑ ይሆንዋል እጆችዋን ወደ ፈጣሪዋ እንድትዘረጋ የሚያደርጋት። የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው የምትል ይመስላል። አዎ የሚሰሩትን ቢያውቁ አጥፍተው ለመጥፋት ባልተጣደፉ ነበር። እንኳን ኢትዮጵያ እኛም ትቢያዎቹ የሚሰሩትን አያውቁምና በአዋቂዎች ይተኩ የምንለው ለዚሁ ነው።

ትንሣዔ መኖሩን ቢያውቁ ሰቃዮች ለመግደል ባልቸኮሉ ነበር። ትንሣዔ መኖሩን ቢያውቁ ራስህን አድን እያሉ በኢየሱስ ላይ አያሾፉም ነበር። ኢትዮጵያም ከወደቀችበት ቀና እንደምትል፣ ኢትዮጵያም ጎጠኞችና ሆዳሞችን አሽቀንጥራ ጥላ ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና እናም ትንሳዔዋ እውን እንደሚሆን ቢያውቁ እፍኝ የማይሞላ ወርቅ አያሳሳቸውም ነበር። እነርሱ የታሪክ ቅጽበቶች፣ እየጠፉ ያሉ ሻማዎች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ በህይወት እያሉ፣ ብርሀናቸው ሳይጠፋ ንስሀ በገቡ፣ ምህረትን በጠየቁ ነበር። ግን ለዚህ አልታደሉምና ስቀላት ስቀላት እያሉ እየጮሁ ነው። ኢትዮጵያ እጆችዋ ግራና ቀኝ ተለጥጠው የማኅጸንዋ ፍሬዎች ሲያጠፏት እየተመለከተች ነው። የእናት ነገር ሆኖባት አሁንም የሚሰሩትን አያውቁምና… ትላለች።

የኢትዮጵያ ቆነጃጅት፣ እሸትና እምቡጦቹ የነገዎቹ እናቶች፣ የነገዎቹ ሚስቶች አገር አጥተው፣ ጠባቂና ተንከባካቢ ጠፍቶ፣ በባርያ ፈንጋይ የትግሬ ገዢዎች ይሁንታ በትግሬ ነጋዴዎችና ደላላዎቻቸው ለገበያ ቀርበው እየተቸበቸቡ ነው። የማንም ዝተታም አረብ፣ ጋጠወጡና ባለጌው በኒህ ሕጻናቶችና ወጣቶች ላይ ቅንዝረኛ ገላውን ያሳርፋል። ያቆሽሻቸዋል ያረክሳቸዋልም። በወር አንድ መቶ ዶላር ለማግኘት አንድ መቶ ጊዜ ይዋረዳሉ፣ አንድ መቶ ጊዜ ይገረፋሉ። እንዲያም ሆኖ የለፉበትን እንኳን ሳያገኙ አብደው ይመለሳሉ ወይም ራሳቸውን ያጠፋሉ። ባይሞቱም ሞተናል ተዋርደናል ረክሰናል ብለው የሚያምኑ ይሆናሉ። አዎን ኢትዮጵያ በልጆችዋ ክፋት ወደ ሞት እየተነዳች ነው። የትግሬ ጎጠኞች ቅንጣት ታክል አያመነቱም። ጥላቻና ንቀታቸው ጥግ ደርሷል። አረቦች ወይም ሌሎች ወጣቶችን የሚመለከቱት በግ ተራ እንደወረደ ሸማች ነው። ኩላሊት አላቸው፣ ልብ አላቸው፣ አይናቸው ያምራል ምርጥ መለዋወጫዎች እያሉ ያዩዋቸዋል። የሰው ቅርጫ ሊያደርጉዋቸው አሰፍስፈው ይጠብቃሉ። የአማራ፣ የኦሮሞና የሌላው የጠላት ልጆች ናቸውና ጎጠኞች እብሪትና አሸናፊነት በተሞላው ፌዝ ገንዘባቸውን እየቆጠሩ ወላጅ እናታቸውን መስቀል ላይ ቸንክረው ትሰቀል! ትሰቀል! ይላሉ።

የኢትዮጵያ ህጻናት ወላጅ አልባና ችግረኛ ወላጆች ያሉዋቸውም ጭምር እየተለቀሙ በግላጭ እየተሸጡ ነው። ገበያውን ያደሩትና በንግዱ የከበሩት ባለ ንግድ ፈቃዶቹ፣ ሻጮቹና አሻሻጮቹ ወይም ጎጠኞቹ አለዚያም ከነርሱ የተጠጉቱ ሆዳሞች ናቸው። ምንኛ ጭካኔ ምንኛ ክፋትስ ነው ይህንን የሚያስፈጽም ብሎ ለማሰብ ይከብዳል። ከተሸጡት ህጻናት ውስጥ ራሳቸውን የገደሉ፣ አእምሮአቸው የታወከና ሌላም በደል የደረሰባቸውን ቤቱ ይቁጠረው። የህጻናት ፖርኖግራፊና፣ የዝሙት ባርያ የሆኑ ውብ ወጣት ሴቶች ብዛትን ኢትዮጵያ በቅርቡ ሬከርድ ትበጥስ ይሆናል። እነዚህ ለባርነት የተጣሉ ህጻናት እንባ እንደ ጅረት ይፈሳል። በዚያ ጨቅላ እድሜ አምሳያቸው የሌሉበት የራሳቸው የቆዳ ቀለም ግራ የሚገባቸው እርዳታ ፍለጋ የሚቁለጨለጩ አይኖች የሚፈልጉት ሀብታም እናትና ብዙ አሻንጉሊት ሳይሆን ወላጅ እናትና አባታቸውን ወንድም እህቶቻቸውን ነው። ይህንን ፍቅር የሚነፍጉና ህፃናትን እንደ ድንች ደርድረው የሚሸጡ ነጋዴዎች ተዘቅዝቀው ቢሰቀሉና ከስራቸው እሳት ቢነድም እንኳ የሚበቃቸውን ያህል ቅጣት የሚያገኙ አይመስለኝም። ያደኸያቸው ስርዐት መጠየቁ ቀርቶ የግፍ ግፍ በፎጣ ተጠቅልለው እንደ ቅርጻ ቅርጽ የውሸት ስም፣ የውሸት ታሪክ ተሰርቶላቸው ይሸጣሉ። ህፃናቱ በመላው ዓለም ተበትነው የሚደርስላቸው ወገን አጥተው ከንቱ ጩኸት ያሰማሉ። የጣር ጩኸታቸውን የደስታ ዘፈን አድርገው የሚጨፍሩት ጨካኞች አገራቸውን እናታቸውንን ከተራራው አውጥተው ሥጋዋን ሊቃረጡ ትሰቀል ትሰቀል ይላሉ ከበሮ እየመቱ። ትሰቀል! ትሰቀል!

ጠላት ሲመጣ ጓዜን ጨርቄን የማይለውና በባዶ እግሩ ጦሩን እየሰበቀ ዳር ከዳር ይዘምት የነበረው ገበሬ። ዳገት እየቧጠጠ ግን በኢትዮጵያዊ ኩራቱና በእምነቱ ጸንቶ የኖረን የህብረተሰብ ክፍል አማራ ነህና አገርህ አይደለም ተብሎ አገር ባቀና ደሙን ባፈሰሰ፣ በረሀብ በተቆላ፣ የውሸት የገዢ ስም ለጥፈው፣ ኢትዮጵያዊነቱን ተጠይፈው፣ ለነጻነት ቀናዒ መሆኑን አውግዘው እያሳደዱ ባለሀገሩን አገር አልባ ያደርጉታል። በትግራይ ጎጠኞች አስጨፍጫፊነት ቀሳውስቱን ከደብር፣ ገበሬውን ከኖረበት መንደር፣ እያፈናቃሉ ለሀገሩና ለባንዲራው ክብር በመሞቱ ይጨፈጭፉታል። ያቺን አገር ያቺን እናት የሆነችንን አገር ከጠላት መንጋጋ ያወጡት ለጠላት እየተሰጡ የሚጠሉዋትን ኢትዮጵያ ደግሞ ጎጠኞቹ ትሰቀል! ትሰቀል እያሉ ይጮሃሉ።

የሚያድኗት ልጆች ካሉ፣ ጣርዋና ጩኸትዋን ሰምተው ከህልፈትዋ በፊት የሚደርሱላት ጀግኖች ካሉ፣ ከራሳቸው ቅንጣቢ የእድሜ ዘመንና የስልጣን ጥም በላይ በሞታቸው ህይወትን፣ የሚሰጡ ልጆች ካሉ ለኢትዮጵያም ትንሳዔ ይኖራታል። የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል እምነት ካለ ይላል መጽሀፉ…. ያለ ጥርጥር ከዚያም የገዘፈ እምነት አለን የተጋረጠውን ክፋት የሚገፋ ።

የሀገራችን ኢትዮጵያ ትንሣዔም ቅርብ እንዲሆን ፈጣሪ ይርዳን።

biyadegelgne@hotmail.com

ይግባኝ ለመድሃኒያለም ፍትሕ ስለተነፈጉት ስለእነ እስክንድር ነጋ –ከኃይለገብርኤል አያሌው

0
0

ከኃይለገብርኤል አያሌው

Eskinder Nega

ፎቶ ሰኔ 25 1995 ዓ/ም ፒያሳ ካፌ የተነሳንው

የፍትህ ምንጭ የህግ ባለቤት በመንግስቱ አድሎ የሌለበት እንደ ክፋታችን ሳይሆን እንደቸርነቱ ጠብቆ የሚያኖረን እውነተኛ ዳኛ የሆነው አምላካችን መድሃኒታችን እየሱስክርስቶስ እውነትና መንገድ ዳኛና ፈራጅ እርሱ በመሆኑ ቀን ያነሳቸው ነፍጥና ጎመድ ለታጠቁት በሃይልና ጉልበታቸው የፍትህን ምንጭ አድርቀው ግፍ ለሚፈጽሙ ደሃ ለሚበድሉትና ህግ ለሚያጣምሙት አህዛብ ፈርዖኖችን ድል የሚያደርግ ሃያሉ አምላክ ይግባኝ የምንለው ከምክርና ተግሳጽ በላይ መከራ ሊመክራቸው ያልቻሉ የታዘዘው መቅሰፍት ጥጋብና ትዕቢቱ ለከት አጥቶ የነበረው ለምህረትና ይቅርታ ልቡ ታውሮ ሕሊናው በጥላቻ ጠቁሮ ይመራ ዘንድ በታሪክ አጋጣሚ ያገኘውን የመሪነት ጸጋ አድፋፍቶ ከክፋት መንገድ ሊመለስ ያልቻለውን መለስ ዜናዊን አምላክ በኪነጥበቡ በአጭር ሲቀጨው የደሃ እንባ የግፉአን በደል ሰማይ መድረሱን ተገንዝበው ለመቻቻል ለእርቅና ሰላም በራቸውን መክፈት የነበረባቸው የዚሁ አረመኔ አልጋ ወራሾች በበጎነት ፋንታ ያንንኑ ዴያቢሎሳዊ መንገዳቸውን አባብሰው መቀጠላቸውን ዳግም አረጋግጠውልናል።

ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ለትንሣኤ በዓል ቃለ-ምእዳን አስተላለፉ

0
0

abune-merekoriwos-150x150

አባ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ-ኢትዮጵያ የትንሣኤን በዓል በማስመልከት ያስተላለፉትን ቃለ ምእዳን ለዘ-ሐበሻ ልከዋል።

ለ ምዕዳኑን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ Read full story in PDF

// ]]>

ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ

0
0
  obang                                  “በአስመሳይ ስደተኞች ላይ በቂ መረጃ አለ”
 
“ክፉን በክፉ መመከት ባያስደስትም ወቅቱ ያስገድደናል” ሲሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል ተናገሩ። አገዛዙን ሸሽተው በተለያዩ አገራት ከለላ አግኝተው በስደት የሚኖሩም ሆኑ ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ አስጠንቅቀዋል።
 
የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህግ አውጪዎች፣ የጀርመን የኢሚግሬሽን ሃላፊዎችና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች፣ ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ጉዳይ ሃላፊዎችና ተዛማጅ ሃላፊነት ካላቸው የህግ ክፍሎች፣ በካናዳ በተለያዩ ደረጃ ካሉ ባለስልጣናትና ወትዋቾች (አክቲቪስቶች)፣ በስዊድን አንዲሁም በእንግሊዝ በተመሳሳይ ግንኙነት ፈጥረው እየሰሩ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አገራቱ የስደት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ለስደት ዳረገን ከሚሉት መንግሥት ጋር በቅርብ እየሰሩ ስላሉ አስመሳይ ስደተኞች አስገራሚ መረጃዎች መሰብሰባቸውን አውቃለሁ” ብለዋል።
 
አቶ መለስ በሞቱ በወር ጊዜ ውስጥ ብቻ በካናዳ ቫንኮቨር 27 አንድ አይነት ቋንቋ ብቻ የሚናገሩ ወጣቶች ጥገኛነት መጠየቃቸውን ጉዳዩን በጥብቅ እየመረመሩት ካሉ ክፍሎች ማረጋገጣቸውንና የምርመራውን ውጤት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ “ወጣቶቹ ካናዳ የገቡት ለእያንዳንዳቸው 75 ሺህ ዶላር በማውጣት ነው። ይህን ገንዘብ ማን ሰጣቸው? እንዴት አገኙት? እንዴት ከአንድ አካባቢ (ክልል) ብቻ ሊሆኑ ቻሉ? የሚሉት ጉዳዮች ምርመራውን በያዙት ወገኖች ላይ ግራሞት የፈጠረ ትልቅ ጉዳይ ነው” በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከገንዘብ ማሸሽ ጋር በማያያዝ አመላክተዋል። ለምሳሌ አንድ ጉዳይ አነሱ እንጂ በመላው ካናዳ በተመሳሳይ የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ተናግረዋል።
 
የካናዳው አንድ ማሳያ ሲሆን በአሜሪካ ግዙፍ ቪላዎችን እየገዙ ያሉት ክፍሎች ጉዳይ ከገንዘብ ማሸሽ ጋር ተያይዞ እየተመረመረ እንደሆነ አቶ ኦባንግ አስረድተዋል። ጥገኝነት ካገኙ በኋላ “ሊገለን ሲል አመለጥነው” ያሉትን ኢህአዴግን የሚደግፉ ክፍሎች ላይም ለሚመለከታቸው ባለስልጣናትና ተቋማት ከሚቀርበው መረጃ በተጨማሪ ከፍትህ ወዳድ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ድርጅታቸው በጥምረት እየሰራ መሆኑን አቶ ኦባንግ አልሸሸጉም፡፡
 
በጀርመን ኑረንበርግ በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ ባለስልጣናት በተመሳሳይ የምርመራ ስራ እያከናወኑ እንደሆነ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ በግል በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል። የጥገኝነት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ዲያስፖራውን በመከታተልና አገር ቤት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንዲዳረጉ የሚያደርጉትን ክፍሎች ማንነት ነቅሰው እንደሚያውቋቸው ባለሥልጣናቱ በግንኙነታቸው ወቅት እንዳረጋገጡላቸው አመልክተዋል።
 
“ኢህአዴግ ለጊዜው የጠመንጃ ሃይል አለው። የገንዘብ አቅም አለው። ወዳጆችም አሉት። እኛ ደግሞ በየአቅጣጫው ፍትህ ወዳድ አጋሮች አሉን። ከነሱ ጋር እየሰራን ነው” በማለት አስረግጠው የተናገሩት ኦባንግ በማንኛውም መስፈርት ስደት ላይ ያሉ ወገኖችን መከታተልና መሰለል ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
 
“አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ኖርዌይ፣ እንግሊዝ፣ ስዊድንና ጀርመን አገር ባለስልጣናቱ ከበቂ በላይ መረጃ አግኝተዋል። እኛም እየሰራንበት ያለ ተከታታይ ስራ አለ። በየአቅጣጫው የሚደረገው ትግል በቅርቡ ፍሬው መታየት ይጀምራል” የሚሉት ኦባንግ ርምጃው መወሰድ ሲጀምር ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ዓመት እስር እንደሚያስከትል፣ ከዚያም የከፋ አደጋ እንዳለው ጠቁመዋል።
 
በትምህርትና በተለያዩ ስልጠናዎች ወደ ተለያዩ ዓለማት የሚሰማሩ የአገዛዙ አገልጋዮችም ቢሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው የሚያሳስቡት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር “አገዛዙ መድቧቸው በየኤምባሲው ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ የስለላ ሰዎች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት ምስላቸውንና ማንነታቸውን ባደባባይ አይገልጹም። በኤምባሲዎች ድረ ገጽ ላይ እንኳ ስለማንነታቸው በቂ መረጃ ለመስጠት ድፍረት የላቸውም። የስርዓቱ ባህሪና የወንጀለኛነቱ መጠን ራሳቸውን እንዲገልጹ አይፈቅድላቸውም” በማለት በተራ መደለያና ጥቅማ ጥቅም ደረታቸውን እየሰጡ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን በመመርመርና የሚያስከብራቸውን ተግባር እንዲፈጽሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።
 
“ምክር በመለገስ ሰፊ ጊዜ የወሰድነው ክፉን በክፉ የመመለስ እምነት፣ ክፉ እንድናደርግ የሚገፋን  ድርጅታዊ አቋም ስለሌለንና የሚጠሉንን ጭምር ነጻ የሚያወጣ ግዙፍ ራዕይ ስላለን ነው” የሚል ጥልቅ አስተያየት የሰነዘሩት አቶ ኦባንግ፣ በአገራቸው መኖር ያልቻሉ ወገኖች ተሰደውም ሰላም ሲያጡ መመልከት ግን የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን አመልክተዋል። ከዚህም በተጨማሪ እሳቸው በግል፣ ድርጅታቸው በመርህ የሚታገሉለት የሰዎች መብት መከበር ብሩህ አጀንዳ በዝምታ እንዲቀመጡ እንደማይፈቅድላቸው ተናግረዋል።
 
ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር በተገናኙባቸው ወቅቶች ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በግልጽ እንደነገሯቸው ያመለከቱት ኦባንግ ሜቶ፣ አሁን ስሙንና ዝርዝር ጉዳዩን ለመናገር ፈቃደኛ ካልሆኑት ክፍል ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑንን ጠቁመዋል። አኢጋን ያቋቋመው የግልጽነትና የተጠያቂነት ግብረ ሃይል አንዱና ትልቁ ስራው እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን መርምሮና አጣርቶ ለሚመለከታቸው በማቅረብ ፍትህን መጠየቅ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ዝርዝሩን መናገር ቢከብድም ብዙ ስራ እየሰራንበት ያለው የስደተኞች ጉዳይ የሌሎችንም ተሳትፎና ትብብር ይጠይቃል” ብለዋል።
 
“በስሜት መታገል አያዋጣም” የሚል የትግል ማስተካከያ ሃሳብ ፈንጠቅ ያደረጉት አቶ ኦባንግ የስደት ማመልከቻቸው ተቀባይነት አግኝቶ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ አገር ቤት በመመላለስ፣ ህግ በመተላለፍ ለአገዛዙ የሚሰሩ በሙሉ “ብልጥና አዋቂ ነን፣ ባለጊዜዎች ነን” በሚል አስተሳሰብ የሚንቀሰቀሱ አንደማያዋጣቸው ሲያሳስቡ “ለእንደዚህ አይነቶች ሁሉም ዓይነት መንገድ አይሰራላቸውም። ግለሰቦችንና ባለስልጣናትን ሳይሆን አሰራርን በማጭበርበር ይጠየቃሉ። አገራቱ እንደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ስራ ላይ የሚውል ህግ አላቸውና ይተገብሩባቸዋል። አሰራራቸው ሲጭበረበር ዝም የማይሉት ለማንም ሲሉ ሳይሆን ለራሳቸው ሲሉ ነው። አሰራር / ሲስተም/ ሲበረዝ የሚያስከትለውን አደጋ ስለሚረዱ የሚታገሱ ካልሆነ በቀር በዝምታ አያልፉም። በኖርዌይም ሊሆን የታሰበው ይህ ነው። 
 
አሁንም ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እቸገራለሁ” በማለት ነው። አቶ መለስ ህይወታቸው ባለፈ ወቅት በስደት ካምፕ የሚኖሩ ጭምር ለቅሶ መቀመጣቸው በኖርዌይ ሚዲያዎች አስገራሚ ተብሎ መዘገቡ፣ በህዝቡና በፖለቲከኞች ዘንድ መነጋገሪያ አጀንዳ እንደነበር አይዘነጋም።
 
በርካታ አሳዛኝና ህሊናን የሚፈታተኑ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ያወሱት ኦባንግ ሜቶ፣ ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም በመቸብቸብ፣ ሴት እህቶቻችንን አረብ አገራት ያለ ዋስትና በመላክ ከፍተኛ ገበያ እየሰሩ ያሉት የህወሃት ሰዎች እንደሆኑ በበርካታ ማስረጃዎች መረጋገጡን ያስታውሳሉ። አያይዘውም አገራቸውን ለቀው ለስደት የሚወጡትን ወደ ኬኒያ፣ ታንዛኒያና ደቡብ አፍሪካ ብሎም በጅቡቲና በሶማሌ በኩል ገንዘብ እያስከፈሉ የሚያሻግሩት አሁንም እነሱ ናቸው ሲሉ አስቀድመው ስለ ጠየቁት ትብብር ማሳሰቢያቸውን ያጠናክራሉ።
 
“በማስተዋል እንስራ” የሚሉት ኦባንግ በየአቅጣጫው መረጃ ላይ የተኙና፣ በምን አገባኝ ስሜት ዝምታን የመረጡ ወገኖች ያላቸውን መረጃ በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ከተለያዩ አካላት ጋር እየሰራ ያለውን ስራ እንዲያግዙ አሳስበዋል። ይህንን ማድረግ አቶ ኦባንግንና እርሳቸው የሚመሩትን ድርጅት መርዳት ሳይሆን ራስንና አገርን መርዳት እንደሆነም አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
 
ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ ሕግ ባለሙያዎች ማኅበር (ABA) እየተባለ በሚጠራውና 400 ሺህ በላይ አባላት ባሉት የህግ ባለሙያዎች ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ወቅት አቶ ኦባንግ ሜቶ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ድጋፍ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ ጠቅሰዋል፡፡ 
 
በርካታ የህግ ባለሙያዎች በተገኙበት ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ኢህአዴግ ህግን ከለላ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል፣ ለእንደዚህ ዓይነት ተግባሩ ማስፈጸሚያም የጸረ ሽብርተኝነትን፣ የመያዶችን፣ ወዘተ ህጎች በማውጣት ዜጎችን ለእስር፣ ለስደት፣ ለስቃይ መዳረጉን፣ የፍትህ አካላቱን ህግን በሚያከብሩና ፍትህ በሚያስፈጽሙ ሳይሆን ራሱ በመሠረተው ተቋም እያመረተ ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረገ መሆኑን፣ ከዚህ አልፎ ደግሞ በስደተኛነት ስም ደጋፊዎቹን ወደ ውጪ በመላክ በሃሰት የኢህአዴግ ሰለባ በማስመሰል በየምዕራቡ ዓለም የመኖሪያ ፈቃድ እንዲያገኙ በማስደረግ መልሶ ስደተኛውን እዲሰልሉና ለሥርዓቱ እንዲሰሩ እያደረገ መሆኑን፣ ወዘተ በስፋት አብራርተዋል፡፡ 
 
የባለሙያዎቹ ማኅበር ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚያየውና ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል በመጠቀም ከአኢጋን ጋር እንደሚሰራ ከሌሎች ማኀበራት ጋር በመሆንም በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተሰገሰጉትን አስመሳይ ስደተኞች ወደ ፍትህ የማምጣቱ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ለአቶ ኦባንግና ለድርጅታቸው አረጋግጠዋል፡፡
 
http://www.goolgule.com/false-refugees/

ፍራንክ ላምፓርድ –የቸልሲው በራሪ ኮከብ

0
0

frank-lampard 1121

ከይርጋ አበበ

የምሥራቅ ለንደኑ ዌስትሃም ዩናይትድ የክለቡ ታላቅ ውጤት የተመዘገበው በ1997/98 የውድድር ዘመን ሲሆን ውጤቱም 5ተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀበት ነው። የምእራብ ለንደኑ ቼልሲ ደግሞ ከ50 ዓመት በኋላ ከእንግሊዙ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ጋር የተገናኘው በ 2004/05 የውድድር አመት ነበር።በታላቁ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ያስመዘገበው የመጀመሪያ ታላቁ ውጤቱ የሩብ ፍፃሜ ተፋላሚነት ቦታ ነበር በኋላ ዋንጫውን በአሊያንዝ አሬና ማንሳት ቢችልም።

የሮማን አብራሞቪች ቡድን በሀገር ውስጥ እና በአውሮፓ መድረክ ላለፉት አስር አመታት ጡንቻውን ማሳየት ሲጀምርም ሆነ ዌስትሃም ዩናይትድ የአውሮፓ ማህበረሰብን ኮታ ሲያሳካ በሁለቱም ክለቦች የአንበሳውን ድርሻ መወጣት የቻለው ፍራንክ ጀምስ ላምፓርድ ነበር። አባቱ በተጫወቱበት ዌስትሃም ዩናይትድ ውስጥ በአጎቱ ሃሪ ሬድናፕ ስር እየሰለጠነ ያደገው ፍራነክ ጀምስ ላምፓርድ በ2001 የውድድር ዘመን መባቻ ላይ ከምስራቅ ለንደን ወደ ምእራብ ለንደን በ11 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ ዝውውር በመፈጸም ሰማያዊ ለባሽ ሆነ።

ስምንት ቁጥር ለባሹ እንግሊዛዊ በኦክቶበር 1995 የውድድር ዘመን ወደ ዌልሱ ክለብ ሰዋንሲ ሲቲ በወሳሱል ተዘዋውሮ ጨዋታዎችን ብቻ በሊበርቲ ስታዲየም ተጫውቶ አንድ ግብ አስቆጥሮ ወደ አሳዳጊ ክለቡ ተመለሰ። ሁለት መቶ አንድ ጎሎችን ለሰማያዊ ለባሾቹ በማስቆጠር የምንግዜም የክለቡ ባለብዙ ጎል የመሀል ሜዳ ተጫዋች የሚል ክብርን የተጎናፀፈ ሲሆን አንድ መቶ ስልሳ አራት ጨዋታዎችን ለፕሪሚየር ሊጉ በተከታታይ በመሰለፍም ባለክብረ ወሰን ነው።

ላምፓርድ በቼልሲ

2001-2004

የመጀመሪያ የቼልሲ ጨዋታውን ያደረገው ኦገስት 19/2001 ከሰሜን ምስራቁ የእንግሊዝ ክለብ ኒውካስትል ዩናይትድ ጋር ነበር። በአለን ሺረር ፊት አውራሪነት የሚመራውን ክለብ ገጥሞ አንድ እኩል በመለያየት የስታንፎርድ ብሪጅ ቆይታውን ፋይል ከፈተ። በእዚህ የውድድር ዘመን በሰላሳ ስምንቱም የቼልሲ ጨዋታዎች ሰልፎ ስምንት ግቦችን ለሰማያዊዎቹ አስቆጠረ። የውድድር ዓመቱን በጥሩ እረፍት ጨርሶ ወደ ሜዳ የተመለሰው የቻርልተን አትሌቲክን መረብ በመድፈር ነው።

የቼልሲን 2002/03 የውድድር ዘመን የመክፈቻ ግብ በእዚህ ሁኔታ አስቆጠረ። በአመቱ መጨረሻ ሩሲያዊው ቢሊየነር ረብጣ ዶላሮችን ይዘው ስታንፎርድ ብሪጅ ሲደርሱ በአንፃሩ የክለቡ የምንግዜም ምርጥ ተጫዋች ጣሊያናዊው ጂያንፍራንኮ ዞላ ከክለቡ ጋር ያለውን ጋብቻ ቀደደው።

ጣሊያናዊው የሮቴሽን ሲስተም ተከታይ አሰልጣኝ ክላውዲዎ ራኒዮሪ ደግሞ ዳሚን ዳፍ ሴቫስቲያን ቬሮን ክሎድ ማኬሌሌ ሄርናን ክርስፖን እና የመሳሰሉትን ከዋክብት ወደ ክለባቸው አስመጥቶ የውድድር ዘመናቸውን ሲጀምሩ እንግሊዛዊው አይደክሜ ፍራንክ ላምፓርድ የወሩ ምርጥ ተብሎ በመስከረምና በጥቅምት ወር ተመረጠ።

«የማይበገሩት» የሚል ስም የተሰጣቸውን የቬንገርን ልጆች ተከትለው ሁለተኛ የወጡት ምዕራብ ለንደናውያኑ ኮከባቸው ፍራንክ የዓመቱ ምርጥ ሁለተኛነት ክብርን ከአርሰናሉ ህያው ቴሪ ዳንኤል ሆነሪ ቀጥሎ ተቀበለ። አስራ አራት ግቦችን ደግሞ ለራኒየሪ ቡድን በማስቆጠር የክለቡ ባለውለታ ሆኖ ዓመቱን አጠናቀቀ።

2004 እስከ 2005

ትእግስት አልባው ሩሲያዊው ከበርቴ አሰልጣኞችን መቀያየር የጀመሩበት ዓመት 2004 የክረምት ወቅት። ወጤት አልባውን ጣሊያናዊ ራኒየሪ በማሰናበት በምትካቸው የቼልሲ ደጋፊዎችንና ተጫዋቾችን ፍቅር ዉጤጣማውን ፖርቹጋላዊ ጆዜ ሞሪኒዮን አመጡ። በፖርቹጋሉ ኃያል ክለብ ፖርቶ ያሳኩትን ውጤት ተከትሎ ስታን ፎርድ ብሪጅ የደረሱት ታክቲካሉ ጆዜ ለፍራንክ ላንፓርድ ምቹ ሆነውለት ነበር የቀረቡት።

በዚህም ልጁ 38ቱንም የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ለ3ኛ ተከታታይ ዓመት በመሰለፍ ዓመቱን ፈፀመ። በውድድር ዓመቱ 19 ጐሎችን ሲያስቆጥር 16 ኳሶችን ደግሞ ጣጣቸውን ጨርሰው ለጓደኞቹ አመቻችቶ አቀበለ። ቼልሲ ከግማሽ ክፍለ ዘመን እልህ አስጨራሽ ትዕግስት በኋላ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ ከወራት ቀደም ብሎ ደግሞ በካርዲፍ ሚሊኒየም ስታዲየም የራፋዬል ቤኔቴዝን ሊቨርፑልን በማሸነፍ የካርሊን ካፕ ዋንጫን አነሳ።

ለዚህ ሁሉ ውጤት መገኘት የቀድሞ የዌስት ሃም ዩናይትድ ተጫዋች ሚና ከሁሉ የላቀ ነበር። በጠንካራ ምቶቹ በሚያስቆጥራቸው ጐሎች ይበልጥ የሚታወቀው ላምፓርድ ሪ2004/05 የውድድር ዘመን ከዓለም ምርጥ አማካኞች ሊያሰልፈው የሚችለውን ብቃት ማሳየት ጀመረ፡፡

በተለይም በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በስታንፎርድ ብሪጅ የፍራንክ ራይካርድን ባርሴሎና አራት ለ ሁለት ሲያሸንፋ ሁለት ጐሎችን በማስቆጠር የነሮናልዲንሆ ጐቾን ቡድን ከሩብ ፍፃሜ ውጪ አደረጉት። በሩብ ፍፃሜ ደግሞ የጀርመኑ ኃያል ቡድን ባየር ሙኒክን ነበር የተገናኙት፡፡

በሚሼል ባላክ የሚመራው ሙኒክ ከሩብ ፍፃሜ በፊት በጥሎ ማለፋ የቬንገርን ቡድን በደርሶ መልስ ሦስት ለ ሁለት አሸንፈው ስለነበር ቼልሲንም በቀላሉ አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ይቀላቀላል የሚል የቅድመ ግምት አሸናፊነት አግኝቶ ነበር።

በሙኒክ ተጀምሮ ለንደን ላይ በተጠናቀቀው የሁለቱ ክለቦች የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ 11 ጐሎች የተቆጠሩ ሲሆን፤የጆዜ ሞሪኒሆ ልጆች ስድስቱን በማስቆጠር የበላይ ሆነው ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ። የምስራቅ ለንደኑ ልጅ በሁለቱ ጨዋታዎች በኦሊቨር ካን መረብ ላይ ሦስት ጊዜ ጐል ያስቆጠረ ሲሆን በተለይም አንዷ ጐሉ እጅግ ማራኪ ነበረች።

በፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ለጓደኛው ኳስ ማቀበል አይችልም ተብሎ የተገፋው ክሎድ ማኬሌሌ ያሻገረለትን ኳስ በደረቱ አብርዶ እና ተገልብጦ ሲመታት የመጨረሻ ማረፊያዋ ኦሊቨር ካን ጀርባ ከተወጠረው መረብ ውስጥ ነበር። ከዚች ጐል መቆጠር ሁለት ወራት በኋላ ቦልተን ወንደረስን ሁለት ለባዶ አሸንፎ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሲያነሱ ሁለቱም ጐሎች በነ ጄይ ጄይ ኦካቻ ቡድን ላይ ያስቆጠረው ይኸው እንግሊዛዊ ነበር። የ2004/05 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክብርን ተቀዳጅቶ ዓመቱን ዘጋ።

2005-06

ባለፈው የውድድር ዘመን የዓለም ምርጥ 11 ውስጥ ስሙን ያስመዘገበበትን ምርጥ አቋም አሳይቶ የውድድር ዓመቱን የዘጋ ሲሆን፤በዚህ የውድድር ዓመት ደግሞ 16 የፕሪሚየር ሊግ ጐሎችን አስቆጥሮ የውድድር ዘመኑን ጨረሰ፡፡ የዓለም እና የአውሮፓ ምርጥ ተጫዋችነት ክብርን በባርሴሎናው ብራዚላዊ ጥበበኛ ሮናልዲኒሆ ጐቾ ተበልጦ የብር ዋንጫ አሸናፊ ሆነ።

በዴቪድ ጀምስ 159 ጊዜ በተከታታይ የመሰለፍ ሪከርድን በካሻሻለ በኋላ ታህሣስ 28 2005 ፍፃሜው ሆነ። ከማንቸስተር ሲቲ ጋር በነበረበት ጨዋታ በህመም ምክንያት ባለመሰለፍ። በዚህ የውድድር ዓመት የመጀመሪያዎቹ ወራት ብቻ 12 ጊዜ የተቃራኒ ቡድኖችን መረብ ደጋግሞ ጐበኘ። ብላክበርን ሮቨርስ እና ቼልሲ ያደረጉትን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ባለሜዳው አራት ለ ሁለት ሲያሸንፍ ሁለት ጐሎች አስቆጥሮ የወጣላቸውን የመሀል ሜዳ ሞተር ጆዚ ሞሪኒሆ እንዲህ ሲሉ ነበር የገለፁት።

ብላክ በርን ሮቨርስን አራት ለባዶ አሸንፈው ሲወጡ ሁለት ግቦችን ያስቆጠረውን ፍራንክ ላምፓርድ ማወደሻ ቃላት ከጆዜ ሞሪንሆ አንደበት የወጣውን ቃል ልናነብ ስንዘጋጅ የቦታ ጥበት ለነገ ብሎን ነበር የተለያየነው ። ጆዜ «የዓለማችን እጅግ ምርጡ አማካይ» ሲሉ ነበር የተናገሩት።
2006-07
የቼልሲ ደጋፊዎች ሚስተር ቼልሲ የሚሉት ግዙፉ እንግሊዛዊ ተከላካይ በደረሰበት ከባድ ጉዳት ከሜዳ መራቁን ተከትሎ የቀድሞው የዌስትሃም ዩናይትድ አማካይ የስታንፎርድ ብሪጁን ክለብ ለረጅም ወራት በአምበልነት መምራት የጀመረበት ዓመት ነበር ። በስምንት ተከታታይ ጨዋታዎች ለሰባት ጊዜያት ኳስ እና መረብን በማገናኘት የቼልሲን ጉዞ አሳመረለት። በቼልሲ ክለብ ታሪክ ከመሃል ሜዳ እየተነሳ ብዙ ግቦችን ለሰማያዊዎቹ በዴቪድ ሞይሱ ኤቮርትን ላይ በማስቆጠር ባለ ታሪክ የነበረውን የዴኒስ ዋይዝን ሪከርድ የሰበረውም ከላይ በተጠቀሰው የውድድር ዘመን ነበር ። የ2007 የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ቼልሲ ከማንችስተር ዩናይትድ ላይ ሲነጥቅ በፍጻሜው አይቮሪያዊው ዲዲዬር ድሮግባ ያስቆጠራትን ግብ ላምፓርድ ነበር ጣጣዋን ጨርሶ ያቀበለው። በግሉም በሁሉም የኤፍኤ ካፕ ጨዋታዎች 6 ጊዜ በተጋጣሚ መረብ ላይ አግብቶ የውድድሩ ኮኮብ ግብ አግቢ ሆኗል። ክለቡ ማንቸስተር ዩናይትድን በማሸነፍ የዓለማችንን አዛውንት ውድድር ዋንጫ ሲያነሳ የፈጠረበት ደስታ ጫማውን በስታንፎርድ ብሪጅ ለመስቀል ፍላጎት እንዳለው ተናገረ።
2007-08
ከ1996/97 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቂት ግጥሚያዎች ወደ ሜዳ የገባበት የውድድር ዘመን ነው። 40 ጨዋታዎችን ብቻ ለሰማያዊዎቹ ሲጫወት 24ቱ ብቻ በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያደረጋቸው ናቸው። ምንም እንኳ ከሌሎች ዓመታት ያነሱ ጨዋታዎችን ይጫወት እንጂ በዚህ ዓመት በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች የፈጸማቸው ተግባራት እጅግ ከፍተኛ ነበሩ። ክለቡ በኤፍኤ ካፕ ሁደርስ ፊልድ ታውንን ሦስት ለምንም አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያልፍ ስምንት ቁጥር ለባሹ 100ኛ ግቡን ማስቆጠር ቻለ። 100ኛ ግቡን ሲያስቆጥር ለብሶት የተጫወተውን ማሊያ እና ከማሊያው በታች በጽሑፍ የተሞላውን ቲ-ሸርት ወደ ደጋፊዎቹ ወረወረ።  የቲ-ሸርቱ ጽሑፍ መልዕክትም «አንድ መቶ ግቦች፤ ሁሉም ለናንተ ናቸው፤ አመሰግናለሁ» የሚል ነበር ። እግረ መንገዱንም በየጨዋታው ስሙን እያነሱ የሚዘምሩለትን ደጋፊዎቹን ማመስገኑ ነው። የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ተፋላሚ እንዲሆን የአንበሳውን ድርሻ የተወጣ ሲሆን ፣በተለይም በ2005 መረብ ያልነካች የሉይስ ጋርሺያ ግብ የፈጠረችባቸውን ጸጸት ያስረሳች ግብ በሊቨርፑል መረብ ላይ ማሳረፉ በክለብ አጋሮቹ እና በደጋፊዎቹ ጀግና አሰኝቶታል ።
በቀዝቃዛማዋ ሩሲያ ቼልሲና እስራኤላዊው አሰልጣኝ አብርሃም ግራንት አሳዛኝ ሽንፈትን ሲጎነጩ ፍራንክ ላምፓርድ ግን የመድረኩ ምርጥ አማካይነት ክብርን ለማንም ሳያስረክብ ምርጥነቱን ዳግም ለዓለም አስመሰከረ። በሩሲያዋ ሉዚንክ ስታዲየም ከስድሳ ሰባት ሺ ተመልካቾች በላይ  በተከታተሉት የፍፃሜ ጨዋታ አምበሉ ጆን ቴሪ እና አጥቂው ኒኮላስ አኔልካ የመለያ ፍጹም ቅጣት ምት አምክነው ዋንጫው በአሳዛኝ ሁኔታ ከጃቸው ሲወጣ የጨዋታውን የመጀመሪያ ግብ ማስቆጠር የቻለው እንግሊዛዊው ላምፓርድ ነበር።
2008-09
ኦገስት 13/2008 ከሰማያዊዎቹ ጋር ያለውን ቃል ኪዳን ያጠናከረበትን ፊርማ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት አራዘመ ። ይህም ሰላሳ ዘጠኝ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ፓውንድ በደመወዝ መልክ እንዲከፈለው የሚያደርግ የውል ስምምነት ነበር። ይህ ደመወዙ በወቅቱ የፕሪሚዬር ሊጉ ከፍተኛ ተከፋይ አድርጎት ነበር። የምሥራቅ እንግሊዙን ሰንደርላንድን አምስት ለምንም ሲያሸንፉ ፍራንክ ያስቆጠራት ግብ 100ኛ የፕሪሚዬር ሊግ ግቡ ሆነች። በሃል ሲቲ መረብ ላይ ከሃያ ያርድ ርቀት መትቶ ያስቆጠራት ግቡ ደግሞ  ለሰማያዊ ለባሾቹ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 150 ያሳደገች ግብ ነበረች። በጊዜው የቼልሲ አሰልጣኝ የነበሩት የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሉይስ ፍሊፕ ስኮላሪ ስለ ላምፓርድ ግብ ሲናገሩ በሕይወቴ ካየኋቸው እጅግ በጣም ምርጥ ግቦች አንዷ ነበር ያሉት።  የዓለም ኮኮብ መሆን የሚገባው ተጫዋች ያስቆጠራት ምርጥ ግብም በማለት ነው የተናገሩት። ሃያ ግቦችን አስቆጥሮና በሚሊ ሜትር የተለኩ 19 ኳሶችን ደግሞ ለጓደኞቹ በማቀበል የምንጊዜውም ከፍተኛ ግብ ፈጣሪ ያስባለውን ብቃት ለክለቡ ማበርከት ቻለ።
ስኮትላንዳዊው የማንቸስተር ዩናይትድ ውጤታማ አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስለ ላምፓርድ ችሎታ እማኝነታቸውን ሲሰጡ ኳሶችን ሳያዛንፍ የሚያቀብል በአማካይ ከሃያ በላይ ግቦችን በያመቱ የሚያመርት ሜዳውን ከጫፍ እስከ ጫፍ አካሎ የሚሮጥ ከሁሉ በላይ ደግሞ ይህንን ሁሉ ሲፈፅም ቀሽም ሸርተቴዎችን በመውረድ የተጋጣሚ ቡድን ተጫዋቾችን ሳይጎዳ መሆኑ ነው በማለት የተናገሩት ንግግራቸው ብዙዎችን ያስማማ ነበር ። በኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ በኤቨርተን መረብ ውስጥ የጨመራት ግብ የዓመቱ ሃያኛ ግቡ ናት። ግቧን እንዳስቆጠረ ወደ ማዕዘን መምቻው በመሄድ ባንዲራውን ደጋግሞ በመምታት ደስታውን ሲገልጽ ታይቷል። ይህንን ያደረገው ደግሞ ከ30 ዓመት በፊት በ1979 የውድድር ዓመት አባቱ ፍራንክ ላምፓርድ ሲኒዬር በተመሳሳይ መድረክ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ኤቨርተን ላይ ግብ አስቆጥረው ያደረጉትን ነበር የደገመው። ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመት የቼልሲ ኮኮብ በመሆንም በክለቡ ደጋፊዎች ዲዲዬር ድሮግባ እና አምበሉ ጆን ቴሪን አስከትሎ ተመረጠ።
2009-10
በግዝፉ ዌምብሌይ ስታዲየም የፕሪሚዬር ሊጉን ሻምፒዮን ማንቸስተር ዩናይትድን በመለያ ምት አራት ለአንድ በማሸነፍ የኮምዩኒቲ ሼልድ ዋንጫን በማንሳት የውድድር ዓመቱን የከፈተው ቼልሲ በኤድዊን ቫን ደር ሳር መረብ ውስጥ ካስቆጠራቸው ፍፁም ቅጣት ምቶች አንዱን ከፍራክ ላምፓርድ ነበር ያገኘው። በታህሳስ ወር የዓለም እግር ኳስ የበላይ ተቆጣጣሪ ፊፋ የዓመቱ ምርጥ አስራ አንድ ውስጥ ካካተታቸው አስራ አንድ የዓለማችን ከዋክብት አንዱ የቼልሲው ምክትል አምበል ነበር። ላምፓርድ ይህንን ክብር ሲያገኝ ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ ለስድስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። እንዲሁም ለአምስት ተከታታይ ዓመታት 20 ግቦችን ለሮማን አብራሞቪቹ ክለብ ያስቆጠረውም በዚሁ የውድድር ዘመን መሆኑ ተጫዋቹ ብቃቱ ሳይወርድ ለ10 ዓመታት ክለቡን አገልግሎት የሰጠበት ዓመት ነበር። የካርሎ አንቼሎቲ ቡድን ማንቸስተር ዩናይትድን በአንድ ነጥብ በልጦ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ እና አፍሪካዊው ዲዲዬር ድሮግባ 29 የፕሪሚዬር ሊግ ግቦችን በማስቆጠር ኮኮብ ግብ አግቢነቱን ከዋይኒ ሩኒ በሁለት በልጦ ሲቀዳጅ በፕሪሚዬር ሊጉ 37ኛው ሳምንት አንፊልድ ላይ ያስቆጠራት ግብ የላምፓርድን ወሳኝነት ያሳየች ነበረች። በዓመቱ መገባደጃ እንግሊዛዊው ኮኮብ 22 የፕሪሚዬር ሊግ ግቦችን በስሙ በማስመዝገብ ብቸኛው ተጫዋች እንዲሆን አስችሎታል።

የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አንዷለም አራጌን እንዳይጠይቁ በልዩ ሀይል ተባረሩ

0
0

 

photo0977_001

የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ወጣቱን ፖለቲከኛና የፓርቲው አመራር አንዷለም አራጌን እንዲሁም ሌሎችን የፖለቲካና የህሊና እስረኞች  ለመጠየቅ ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ቃሊቲ ቢሄዱም ለመጠየቅ እንዳይችሉ መደረጋቸውንና እስካፍንጫቸው በታጠቁ ልዩ ሃይሎች በግድ ከአካባቢው እንዲርቁ መደረጋቸውን የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አስታወቀ፡፡

እንደፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ገለፃ ከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ወጣቱን ፖለቲከኛና ከፍተኛ አመራር አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን ሽብርተኞች እንደሆኑና በሰላማዊ ትግል ሽፋን ሽብርተኝነትን እንደሚያራምዱ ተደርጎ የቀረበው ሀተታና ውሳኔ እጅግ ያሳዘናቸው በርካታ አመራሮችና አባላቱ በከፍተኛ መነሳሳትና ቁጭት ከ 20 በላይ የሚሆኑ የፓርቲው ሰዎች ከ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ቢገኙም የተሰጣቸው ምላሽ አንዷለምን ምግብ ከሚያመላልሱለት ጥቂት ቤተሰቦቹ ውጭ ማንም መግባት እንደማይችል ተገልፆላቸው በታጠቁ ሃይሎች ከአካባቢው እንዲርቁ ተደርገዋል ብሏል፡፡

በዕለቱ ቃሊቲ እስርቤት ለመጠየቅ ከተገኙት መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም፣ አቶ አክሉ ግርግሬ፣ አቶ ሙላት ጣሰው፣ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ትዕግስቱ አወሉ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራና ሌሎችም የፓርቲው አመራሮችና አባላት እንደተገኙ የህዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የማረሚያ ቤቱ የወቅቱ ተረኞች የስም ዝርዝራቸውን መታወቂያቸውን እያዩ ከተመዘገቡ በኋላ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ ገልጠው ወደ ዋናው የአስተዳደሩ የመግቢያ በር በመግባት ሃላፊዎችን እንዲያነጋግሩ ነግረዋቸው ወደዚያው በማምራት ቢጠይቁም እንዲጠብቁ ከነገሯቸው በኋላ የተሰጣቸው ምላሽ መጠየቅ አትችሉም የሚል ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተለይ አንዷለም አራጌን ከጥቂት ቤተሰቦቹ በስተቀር ማንም እንዳይጠይቀው የተደረገ ሲሆን በተደጋጋሚ ቢያመለክትም ምንም ምላሽ ማግኘት አለመቻሉ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በፊት ግን የበዓል ቀናት ብቻ የፓርቲው አመራሮችና የስራ ባልደረቦቹ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በጅምላ እንዲጠይቁት ቢደረግም በዘንድሮው የትንሳዔ በዓል ግን የገጠማቸው በልዩ የታጠቁ ሃይሎች መባረር ሆኗል፡፡ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ አካባቢውን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ወረውታል፡፡ ለመጠየቅ የመጡት መጠየቅ መብታቸው እንደሆነ ለማስረዳት ቢሞክሩም እነዚህ ሃይሎች መሳሪያቸውን በተጠንቀቅ በመያዝ ፀብ ለማስነሳት ሙከራ አድርገዋል በማለት የህዝብ ግንኙነት ክፍል ገልፆልናል፡፡

http://www.fnotenetsanet.com/?p=4273

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ዋንጫ ውጭ ሆነ

0
0

St George(ኢትዮፉትቦል እንደዘገበው) በአፍሪካ ክለቦች በሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ ከግብፁ ዛማዜክ ጋር ዛሬ አዲስ አበባ ላይ የመልስ ጨዋታውን ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-2 በመለያቱ ከሻምፒዮናው ውጪ ሆነ፡፡ ዛማሌክ ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ የቻለው ከሃገሩ ውጪ ቡዙ ባገባ በሚለው ህግ ነው፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ካይሮ ላይ ከ15 ቀን በፊት አንድ ለአንድ ነበር የተለያት ፡፡በዛሬው ጨዋታ ዛማሌኮች ጨዋታው በተጀመረ በመጀመሪያው ደቂቃ ላይ ነበር የመሪነቱን ግብ በአብዱላሂ ሴሲ ግብ ማስቆጠር የቻሉት፡፡ከግቧ መቆጠር በኋላ ጫኛ ፈጥረው የተጫወቱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በ14ኛው ደቂቃ አቻ የምታደርጋቸውን ጎል በሽመልስ በቀለ ማስቆጠር ችለዋል፡፡ከግቧ መቆጠር በኋላ በተደጋጋሚ የግብ እድል የፈጠሩት ጊዮርጊሶች የመጀመሪየው ግማሽ የጨዋታ ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩ ሁለተኛውን ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡
በአንድ የግብ ልዩነት እየመሩ የሁለተኛውን ግማሽ የጀመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በመጀመሪያው ግማሽ የነበራቸውን በማጥቃት ላይ ያዘነበለውን አጨዋወት በመቀየር በመከላከልላይ ያዘነበለ አጨዋወት ተከትለዋል፡፡የጌዮርጊስ አጨዋወት መከላከል መሆኑን የተረዱት  ዛማሌኮች ጫና ፈጠረው በመጫወት በ69ኛው ደቂቀቃ አደገኛ የግብ ሙከራ ማደረግ ችለው ነበር፡፡ጊዮርጊሶች የያዙትን ውጠት አስጠብቆ ለመውጣት መከላከሉን በመምረጣቸው ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሶስት ደቂቃዎች ሲቀሩ በተቆጠረባቸው ግብ ከአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ውጪ ለመሆን ተገደዋል፡፡አቡዱለሂ ሴሲ ከክንፍ የተሻገሩለትን ኳሶች በጭንቅላቱ ገጭቶ ከመረብ በማገኛኘት ለዛማሌክ ጣፋጭ ድል አሰገኝቷል፡፡ በደርሶ መለስ ጨዋታዎቹ ዛማዜክ ጊዮርጊስ ላይ ያስቆጠራቸውን ሶስቱንም ጎሎች ከመረብ ያገናኘው ቡኪናፋሶዊው አብዱላሂ ሴሲ ነው ፡፡
የግብፁ ዛማሌክ ጠንካራ ከሚባሉት የሰሜን አፍሪካ ክለቦች እንዱ ነው፤ክለቡ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና የአምስት ጊዜ አሸናፊ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫውን ያነሳው በ2002 ነበር፡፡ዛማሌክ በታሪኩ ከኢትዮጵ ክለቦች ለመጀመሪያ ጊዜ የገጠመው መቻል ሲሆን በ1997ዓ.ም ቅዱስ ጊዮርጊስን፤በ2000ዓ.ም ከኢትዮጵ ቡና ጋር ተገናኝቷል፡፡

 

ሁለቱን በጣምራ/በአንድነት ማስኬድ አይቻልም?

0
0

በይበልጣል ጋሹ

በሁሉም ማለት ይቻላል የሃይማኖት አስተምሮ ሥጋዊና መንፈሳዊ ሥራዎችን ሁለቱን በጣምራ ማስኬድ እንደሚቻል በሚያስተምሩት የአስተምሮ ዘይቢያቸው ይሰብካሉ። በተለይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንደ ቀደምትነቷ ለዚህ በር ከፋችም አይነተኛ ምሳሌም ናት። “ሥጋ ካለነፍስ፡ ነፍስ ካለ ሥጋ አትቆምም”፤ ሁለቱ ተያያዥና ተደጋጋፊ ናቸው፤ አንዱ ካለአንዱ መቆምና ሥራቸውን ማከናወን እንደማይችሉ አስፍታና አሙልታ ታስተምራላች።

ምንም እንኳ መንፈሳዊነቱ ጥያቄ ውስጥ ቢገባም ብዙ አገሮች ይህንን መርህ ተከትለው ተግባራዊ ሲያደርጉ ይታያሉ፤ለስኬትም በቅተዋል። ይህንንም አብነት አድርገው የበለጸጉ አገሮችም ሆነ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ተያያዥ ነገሮችን ዛሬም በጣምራ/በአንድነት ለማስኬድ ሲሞክሩ ይታያሉ። በሙከራቸውም እድገትን፣ ብልጽግናን፣ ሰባዊ ርኅራሄንና እኩልነትን በመጠኑም ቢሆን ህዝባቸው ተጠቃሚ እንዲሆን አድርገዋል።

ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስንመለከት ግን ሌሎች በርካታ ነገሮችን ትተን እጅግ ለሰው ልጅ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን እንኳ በአንድነት ለማስኬድ አልተቻለም፤ ለማድረግም ሙካራ ሲደረግ ጎልቶ አይታይም። ለዚህ ችግር ሁላችንም በትንሹም ቢሆን ከተጠያቂነት ባናመልጥም በዋናነት ግን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግሥት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል።UDJ Unite

 

የአገራችን መንግሥት ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ነኝ ብሎ ከነገረን አመታትን አስቆጥሯል። በእውነት ሁኖ ከተገኘና ለመሆን ጥረት የሚያደርግ ከሆነ በእርግጥም መልካምና የሚደገፍ ሃሳብ ነው። በእርግጥ አቶ መለስ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ልማትና ዲሞክራሲ ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረው ነበር። ፓርቲያቸውም የእርሳቸውን ቃል ተግባራዊ ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰራ እንደሆነ ምስክር መሆን ይቻላል። በልማት ስም ነጻነት ሲገፈፍ፣ በልማት ስም የእምነት ተቋማት ሲፈርሱ፣ በልማት ስም ታሪካዊ ቦታዎች ታሪካቸው ሲጠፋ፣ በልማት ስም ሰዎች ከቦታቸው ከንብረታቸ  ሲፈናቀሉ እያየን እየተመለከትን ነው። እኔ የዝወትር ጥያቄዬ ግን  ሁለቱን በጣምራ ማስኬድ አይቻልም? የሚለው ነው። ዶ/ር ዘላለም ተክሉ፡ አቶ መለስ”ዲሞ ክራሲና ልማት ምንም ግንኙነት የላቸውም” ብለው በተናገሩት ላይ ትችታቸውን በጥናታዊ ጽሁፍ እንዲ አቅርበዋል።

የዲሞክራሲ ጥንታዊ ትርጉም “ የህዝብ ሃይል” ወይም “ የህዝብ አስተዳደር” ሲሆን መሰረቱም ሁለት የግሪክ ቃላቶች ዴሞስ(demos)  “ህዝብ” እና ክራቶስ (kratos) “ሃይል” ውህደት ነው:: የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በነበሩት አብረሃም ሊንከን አተረጓጐምም መሰረት ደግሞ ዲሞክራሲ ማለት በህዝብ የተመረጠና ለህዝብ የቆመ የህዝብ መንግስት ማለት ነው:: በዚህ ዓይነት ስርዓት ውስጥ የተመረጡ መሪዎች ቀጥተኛ ተጠሪነታቸው (accountability) ለህዝቡ ሲሆን የሚሰጡት አገልግሎትም በህዝቡ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ብቻ እንደሆነ ይገለጻል:: ዘመናዊው የዲሞክራሲ ምንነት በቀደምቶቹ ትርጉሞች ላይ የዳበረ ሲሆን የሰው ልጅ መሰረታዊና ፖለቲካዊ መብቶች የማክበር፣ በህዝቦች መካከል የሰፈነ እኩልነት፣ ነጻና ፍትሃዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት ያለው፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ የሚፈቅድ፣ እንዲሁም ከማንኛውም ተጽዕኖ ነጻ የሆነ የፍትህ ሥርዓትንና ነጻ ፕሬስ ያካተተ ተቋምም እንደሆነ ይታወቃል::

 

የኢኮኖሚ ልማትም በጣም የሰፋ፣ ከጊዜ ጊዜ ተለዋዋጭና አከረካሪ ትርጓሜ የያዘ ንድፈ ሃሳብ ነው:: ልማት ቀደም ባሉ ጊዜያት ሲተረጎም የሰው ልጅ ያለውን የጉልበት፣ የካፒታልና የዕውቀት አቅም አሻሽሎ ምርታማነትን በማሳደግ በሚያገኘው የተሻለ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከድህነት የተላቀቀና የተመቻቸ ኑሮ መኖር መቻል ነበር:: የኖቤል ተሸላሚው ኢኮኖሚስት አማርቲያ ሴን እንደሚያስረዳው ደግሞ በ1980ዎቹና 90ዎቹ በኋላ የልማት ትርጉም እየሰፋ መጥቶ ከኢኮኖሚ ጠቀሜታ በተጨማሪ የሰብዓዊና የፖለቲካ ነጻነት መብቶችን፣ ስፋት ያላቸው ማህበራዊ ዕድሎችን፣ የአመራር ግልጽነትና የደህንነት ዋስትና እንዲያካትት ተደርጎ እንዲሰራበት ተደርጓል:: የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ደግሞ የልማት ትርጓሜ ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ የሰፋ የህብረተሰብ ተሳትፎና የመሪዎች ግልጽነት (transparency) መያዝ እንዳለበት አበክረው ያሳስባሉ:: ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት ተቀባይነት ያገኘውና በብዙ ሃገራት፣ ዓለም አቀፍ የልማትና የፋይናንስ ተቋማት እየተሰራበት ያለው ደግሞ የሌላውን የኖቤል ተሸላሚ ኢኮኖሚስት ጆሴፍ ስቲግሊትዝ ትንታኔን መሰረት በማድረግ የጎለበተው አስተሳሰብ ሲሆን በዚህ ትርጓሜ መሰረት ልማት ማለት ከኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር የሰው ልጅ ከማህይምነት የሚላቀቅበት፣ ለረጅም ዕድሜ ሊኖር የሚችልበትና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚጎናጸፍበት ደረጃ እንደሆነ ታምኖበታል::

 

ስለዚህ የሃገራችን መንግሥትም በስም ከመነገድና ህብረተሰቡን ግራ ከማጋባት ይልቅ እነዚህ ሁለቱን በጥምረት ማስኬድ ይችል ነበር። እርግጥ ነው በአንድ ጊዜ ተግባራዊ ማድረግ ከማሰብ በላይ እጅግ አዳጋች ነው፤ ሆኖም ግን በሂደት መድረስ የማንችልበት ምንም ምክንያት የለም። ምክንያቱም ይህን በጥምረት ከሚያስኬዱ ሃገራት በአቅምም በሰው ኃይልም የተሻልን እንጂ ያነስን አይደለንምና።

ዲሞክራሲንና ልማትን፤ ነጻነትንና ልማትን፣ እኩልነትንና ልማትን፣ ሰላም ፍቅርንና ልማትን፣ የህብረተሰቡን ፍላጎትና ልማትን፣ የእምነት ተቋማት ሳያፈርሱ ልማትን በጣምራ ማስኬድ አይቻልም? መልሱ ይቻላል ነው። ብዙዎች እንደሚስማሙት ነጻነት ካለ ልማት አለ፣እድገት አለ፣ ብልጽግና አለ፣ መከባበርና ግልጽ ውይይት በህብረተሰቡ ዘንድ ይኖራል። ስለዚህ ከሁሉም በፊት ለነጻነትና ለዲሞክራሲ ቅድሚያ በመስጠት ሁለቱን በጣምራ ብናስኬዳቸው መልካም ይሆናል የሚል ሃሳብ አለኝ።

የእያንዳንዳችን ድርሻ፦ በጉልበታችን፣በገንዘባችን፣በሃሳባችን/በእውቀታችን እና በአገኘነው አጋጣሚ ተጠቅመን ከዘረኝነት ርቀን መንግሥት መልካም ነገሮችን በጥምረት እንዲያስኬድ ድጋፍና አቅጣጫ ማሳየቱ የውዴታ ግዴታችን መሆኑን አውቀን ብንሰራ ለውጥ ልናመጣ እንችላለን።

 

መልካም የትንሣኤ በዓል!

የዘወትር ምኞቴ የነጻነት ትንሣኤ ለኢትዮጵያ……………..

ወገኔ ይጮሃል !

0
0

Zekariasዘካሪያስ አሳዬ

ኢትዮጵያዊዉ በየበረሃው ይጮሃል፣በሲና በረሃ ሆዱ እየተቀደደ ሆድ ዕቃው እየወጣበት ይጮሃል፥ ወደስደት ሲነጉድ በየመንገዱ በአውሬ እየተበላ ይጮሃል፥የሚጓዝባት ጀልባ እየሰጠመች በሞት ጥላ መካከል ሆኖ ኢትዮጵያውያዊው ወገኔ ይጮሃል፣በተለያዩ ሃገራት እስር ቤቶች የታጎሩ ሴትና ወንድ ኢትዮጵያውያዊያን ይጮሃሉ።የወያኔ ግፍ ያንገፈገፋቸው ኢትዮጵያውያን ይጮሃሉ፥ኦሮሞው ይጮሃል፣ አማራው ይጮሃል፣ ጉራጌው፣ከመሀል እስከ ጥግ  ኢትዮጵያዊው ወገኔ  ይጮሃል። ሴቱ ይጮሃል፣ወንዱ ይጮሃል ሙስሊሙ ይጮሃል፣ክርስቲያኑ ይጮሃል…. ኧረ የማይጮህ የለም ሁሉም ሰው ይጮሃል።

በየአረብ አገራት ለዘመናዊ ባርነት ተሽጠው ከአሰሪዎቻቸው ግፍ የተነሳ በፈላ ዘይት እየተቃጠሉ ይጮሃሉ፣በአለንጋ እየተገረፉ ይጮሃሉ፣ ከፎቅ ላይ እየተወረወሩ ይጮሃሉ፣ የጉልበት ዋጋቸውን ተነጥቀው ይጮሃሉ፣ በወሮበሎች እየተደፈሩ ይጮሃሉ ሌሎቹም ህጋዊ ፈቃድ የላችሁም ተብለው እየተሳደዱ ይጮሃሉ፣

በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፉት ሰለባ የሆነው የአኙዋክ ወገኖቻችን ይጮሃሉ፣ አማራ ነህና በዚህ አትፈለግም ተብሎ በግፍ ከየስፍራው እየተሰደደ ያለው ወገኔ በየእስር ቤቱ የተጋዘው ኦሮሞ ወገኖቼ ይጮሃሉ፣ እውነትን በመጻፉቸውና በመናገራቸው ብቻ እስከሞት ድረስ የተፈረደባቸው ወገኖቼ ይጮሃሉ፣ በዋልድባ እየተገረፉና እየተሰደዱ ያሉ መነኮሳት ይጮሃሉ፣አብርሃና አቶ አስገደ ከትግራይ ይጮሃሉ ኧረ ዛሬማ የሚገርም ነገር ሰማሁ አባመላ የተባለ በዳያስፓራ ቀንደኛ የወያኔ ሰው ይጮሃል ሲባል።አሁንማ ማን የማይጮህ አለ? ሁሉንም የሚያስጮኸው ግን አንድ ነገር ነው፣የወያኔ ግፍ።

ክርስትያኑ

ይጮሃል

ሙስሊሙም

ይጮሃል

የመንግስትሰራተኛ

ይጮሃል

የግልተቀጣሪ

ይጮሃል

ቀጣሪው

ይጮሃል

ስራ እጡ

ይጮሃል

ነጋዴው

ይጮሃል

ሸማቹ

ይጮሃል

ሰራዊቱ

ይጮሃል

ጋዜጠኛው

ይጮሃል

እምነት የሌለው

ይጮሃል

የጠገበው

ይጮሃል

የራበው

ይጮሃል

ይጮሃል

ይጮሃል

ፖለቲከኛው

ይጮሃል

ፍትህ ያጣው

ይጮሃል

እስረኛው

ይጮሃል

ታሪክ

ይጮሃል

ሰሚአልባ

ይጮሃል

ጩኸት

ይጮሃል

እሪ

በከንቱ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ኢትዮጵ ውስጥ የሕግ የበላይነት አለ ብለው ያስባሉ??????

የኢትዮጵያዊያን መከራ በወያኔ ገዢዎቻቸው-ወያኔዎችም የኢትዮጵያን ልጆች በመከራ ገዙአቸው። በጽኑ ዘረኝነት፥ በስደት፥ ከስፍራ በማፈናቀል ሁሉ፥ በእስር  ቤት ሁሉ ያሉ ይጮሃል፥የእስራኤላዊያንን ነፃነት የሰጠ እግዚአብሄር ለኢትዮጵያዊያንም ነፃነታችንን እንድንጎናፀፍ ይረዳናል። እኔ ለኢትዮጵያ የጉብኝት ዘመን እንደደረሰ አምናለሁ፥እስከዛው በአንድነታችን ፀንተን ጬኸታችንን ወደ ነፃነት እንቀይረዋለን።

ስቃይ

ይበቃል!

እስራት

ይበቃል!

ስልጣን

ይበቃል!

ስደት

ይበቃል!

የጎሳ ግጭት

ይበቃል!

የህዝብን ድምፅ መስረቅ

ይበቃል!

ማፈናቀል

ይበቃል!

ማስፈራራት

ይበቃል!

ህዝብን መናቅ

ይበቃል!

ዛቻ

ይበቃል!

አገርን መከፋፈል

ይበቃል!

ድብደባና አፈና

ይበቃል!

የወያኔ ስልጣን

ይበቃል!

 

 

 

 

 

 

                            ወያኔን ይበቃል ልንለው ግድ ይላል !!!

ጽናት – ሁሉም ሊያየው የሚገባ ፊልም (Video)

ከወያኔ/ሕወሃት ደርዝ የሳቱ ቃሎች ይልቅ ሀገራችን ብዙ አንገብጋቢና ያገጠጡ ችግሮች አሏት። ሕዝባችን ነጻ አልወጣም በጎጠኝነት የአገዛዝ ቀንበር ስር ይማቅቃል። በየዓመቱ ባስር ሽዎች የሚቆጠሩ ዘለው ያልተገቡ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሕወሃት የተምታታ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ምክንያት ተስፋ አጥተው በስደት ዓለም እየተንከራተቱ ይገኛሉ። በሕወሃት ውስጠ ተንኮል የተነሳም የሀገር ውስጥ ስደተኛው የትየለሌ ሆኗል። ወደድንም ጠላንም ዛሬ በዓለም ፊት ከውርደት በታች ተዋርደን የዓለም መሳቂያዎች ሆነናል። ሕወሃት ግን በኛ ኪሳራ የንግድ ኢምፓሩን በአፍሪካና በዓለም ደረጃ እያስፋፋ ቀጥሏል። ይህ የሀገራችን ቀውጢ ወቅት እኛን ካላስነሳን፤ ይህ የሕዝባችን ችግር እኛን ካላነቃን፤ ምን በጽናት ሊያቆመንና ሊያስተባብረን ይችላል? ይጠቅማል ባልነው መንገድና ወቅት ሁሉ የሕወሃትን ጎጠኛ አገዛዝ የሚያዳክም  የሀገራችንን ሰላምና ጸጥታ የሚያስጠብቅና የሕዝባችንን ጥንካሬና ስነ ልቦና የሚያጠናክሩ እርምጃዎችን እንውሰድ። የኢትዮጵያዊነታችን ክብርና ኩራቱ ሀገራችን ከሕዝባችን ጋር በሰላም ተጠብቃ አስከኖረች ድረስ ብቻ ነውና።

እውነታው ግን የአባይን መገደብ የሚቃወም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የለም ። ነገር ግን አባይ የሚገደበው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲጠቀም ከሆነ ፤ ህዝብ ይከበር ነው የምንለው ። ከአባይ በፊት፦

ዘረኝነት ይገደብ !

ህዝብን ማፈናቀል ይቁም !

ሰብአዊነት ይቅደም !

በሃገራችን የአፓርታይድ ስርዐት ይወገድ !

የሃይማኖት ነጻነት ይከበር !

አባይን ለርካሽ ፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ ይቁም !

በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ !

የሙስሊም ድምጽ ይሰማ !

ታሪካዊ ገዳማችን ዋልድባ ይከበር !

በህዝብ የተመረተ መንግስት ይምራን !

የህዝብ ድምጽ ይሰማ !

ነብሰ ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡ !

እና ሌሎችን ተያያዥነት ያላቸውን መሰረታዊ ጥያቄዎችን ነው የተጠየቀው ።

ከቀረን ነገር በላይ ያጣነው ነገር ይበልጣል !

Amhara Women Cryበተለያ ሀገር የምትገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥ ለሚፈጸመው የሰብአዊና የዴሞክራሲ ጥሰቶች ከሌላው ጊዜ በተለየ እና እጅግ በጣም በሚማርክ ፍጹም ጨዋነት በታየበት በስልጣን ላይ ያለው የወያኔን መንግስት እግር በእግር እየተከታተላችሁ የምታሰሙት ተቃውሞ በሀገር ውስጥ ላለን ለሀገዛዙ ቀጥተኛ ተጋላጭ ለሆነው ተስፋ እና ጉልበት እንደሚሆነን ምስክርነቴን ለመስጠት እወዳለው፤ለዚህም ተግባራችሁ ምስጋና ይገባችኃል፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ በሀገር ውስጥ የምንኖር ተገፍተናል፣ ተበድለናል፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን ተነጥቀናል የምንል ከቀረን ነገር በላይ ያጣነው ነገር ይበልጣል እና የሚቀርብን ነገር የለም፡፡ በመሆኑም ከገባንበት የፍርዓት ቆፈን ማንም ሳይሆን የራሳችን ችግር አፈትልኮ ሊያወጣን ይገባል አለበለዚያ ስቃዩ የእድሜ ልካችን ይሆናል እናም በቤታችን ፣በሰፈራችን ፣በመስሪያቤታችን ፣በመንቀሳቀስበት ስፍራ ሁሉ ስለ ነፃነት እንዘምር እንጩኹ !!!

 

ወያኔዎች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የማፈራረሱና ትውልድን የማጥፋቱ እኩይ ምግባር ሙሉ በሙሉ አለመሳካቱን ከቀንደኛ መሪያቸው ሞት በኋላ እንኳ’ ለራሳቸው ሲሉ ካለፈው ለመማርም ሆነ ለመጸጸት አለማሰባቸው ፕሮፌሰር እንደሚሉት ”ያሳዝናል” ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን፤ ሀገራችን ለማጥፋትና ለማውደም፤ አስፈላጊ ከሆነም ህዝብን ከመጨረስ በምንም አይነት መንገድ ወደ ኋላ እንደማይሉ ነው ደጋግመው እየነገሩንና እያሰረዱን ያሉት። ይሁን እንጅ ትላንት ዛሬ አይደልም፤ ዛሬም ነገ አይደለም።
…….ይዘገያል እንጅ ታሪክ ውል አይስትም በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም።……

ከእንግዲ የዉሸት ፋብሪካ የሆነው ኢቲቪ ነጠላ ዜማውን  ሲለቅ መስማቱ ፋይዳ የለውም።

እንደተለመደው “ጸረ ሰላም እና ጸረ ልማት ሃይሎች ” እያለ በቱልቱላ ጋዜጠኞቹ የህዝብን ጆሮ ሲያደማ እንሰማም ።  በአንድነታችን ፀንተን ጬኸታችንን ወደ ነፃነት እንቀይረዋለን።

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

ከዘካሪያስ አሳዬ( edenasaye@yahoo.com)

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live