Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የዩኒቨርስቲው ጉድ! – የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አለም እሸቱ ይናገራሉ (ልዩ ቃለ ምልልስ)

$
0
0
የዩኒቨርስቲው ጉድ! – የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር አለም እሸቱ ይናገራሉ (ልዩ ቃለ ምልልስ)

በወልዲያና በፍኖተ ስላም እስር ቤቶች ተቃጠሉ

$
0
0
በትናንትናው እለት በደብረማርቆስ ከተማ እስር ቤት መቃጠሉን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ደግሞ በወልዲያና በፍኖተ ሰላም እስርቤቶች ተቃጠሉ:: በአማራ ክልል በወልዲያና በፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤቶች በተነሳ ‹‹ግርግር›› ማረሚያ ቤቶቹ መቃጠላቸውንና ሌሎች ጉዳቶችም መድረሳቸውን፣ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታወቁ፡፡ በወልዲያ ማረሚያ ቤት ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ እሳት […]

ብአዴን አመራሮቹን ሊያባርር መሆኑ ተሰማ

$
0
0
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከታች እስከላይ ባሉ አመራሮች ግምገማዎችን የሚቀመጠው የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) አዲስ የለውጥ ንቅናቄ በመላ አገሪቱ እንዲቀጣጠል በኢሕአዴግ ውስጥ ካሉ እህት ድርጅቶችና ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና ቢጫወትም፣ በውስጡ ያሉ አንዳንድ አመራሮቹ ለውጡን ከማስቀጠል ይልቅ ዳተኝነትና መደናገር የሚታይባቸው በመሆኑ በማጥራት ለመለየት ዕቅድ መንደፉ ታወቀ፡፡ የብአዴን ክልላዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች አደራጅ ኮሚቴ […]

የትግራይ ክልል የኤርትራ ቴሌቭዥን የፊታችን ቅዳሜ በመቀሌ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲዘግብ ደብዳቤ ጻፈ

$
0
0
ከዚህ ቀደም ዶ/ር አብይ አህመድን አስተዳደር ለመቃወም በመቀሌ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቶ የነበረ ቢሆንም ሁለቱንም ጊዜ መሰረዙ ይታወሳል:: የፊታችን ቅዳሜ ደግሞ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈጸመውን ስምምነት በመደገፍ እንዲሁም ሕገመንግስቱ ይከበርና የዘር ጥቃቶች ይቁሙ የሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመቀሌ ከተማ እንደሚደረግ ትናንት በዘ-ሐበሻ ዜና ዘግበናል:: የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቅዳሜ በመቀለ ከተማ የሚደረገውን ሰልፍ የኤርትራ ቴሌቪዥን (ERiTv) […]

ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሬዎስ አዲስ አበባ ሲገቡ አቀባበል የሚያደርግ ኮሚቴ በአስቸኳይ እንዲዋቀር ቅዱስ ሲኖዶስ አዘዘ

$
0
0
  ዛሬ ወይም ነገ ይፋ የሚሆነው የኢትዮጵያ ኦርርቶዶክስ ተዋህዶ ሁለት ሲኖዶሶች አንድነትን በተመለከተ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ ነው:: ዘ-ሐበሻ ሰኞ ዕለት ከዘገበችው ጋር ተመሳሳይ የሆነ መረጃ ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ድረገጽ ይዞ ወጥቷል::  የአባቶች ዕርቀ ሰላም ሒደት፣ ፍጻሜ ባገኘበት ይህ ስምምነት፣ ኹለቱም ቅዱሳን ፓትርያርኮች፣ በአንድ የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር፣ የማዕርግ ስምና መንበር ዕውቅና አግኝተው የድርሻቸውን እየፈጸሙ የሚቀመጡበት ነው፡፡ […]

ስለ ሁለቱ ሲኖዶሶች ዘ-ሐበሻ አሁን የደረሰው መረጃ

$
0
0
ነገ በዋሽንግተን ዲሲ ዶ/ር አብይ አህመድ በሚገኙበት የሁለቱ ሲኖዶሶች አንድነትና የፓትርያሪክ አቡነ መርቆሬዎስ መመልስ ዜና ይበሰራል:: * ዛሬ ከአዲስ አበባ የመጡ ሊቃነጳጳሳት ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሬዎስ የሚገኙበት ሄደው ምሳ ይጋብበዛሉ:: * ዶ/ር አብይ አህመድ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር በአንድ አውሮፕላን መመለስ ከፈለጉ የጉዞ ሰነዶች ተዘጋጅተዋል:: አለበለዚያ ግን ከፍልሰታ ጾም ፍቺ በኋላ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ:: ሆኖም […]

የአባይ ግድብ ዋና ስራ አስኪሃጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ተገድለው መገኘታቸው ታወቀ

$
0
0
አስከሬናቸው ለምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መላኩን የፖሊስ ምንጮች ይፋ አድርገዋል። ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ሰኞ ከመላው አገሪቱ ከተውጣጡ የከፍተኛ ትምህርት መምህራንን በጽ/ቤታቸው መሰብሰቢያ ባነጋገሩበት ወቅት ግድቡ ከዚህ በሁዋላ በ10 ዓመትም እንደማያልቅና ሲወጡ የነበሩ መረጃዎች ለፖለቲካ ፍጆታ የዋሉ እንደነበሩ ማልጋለጣቸው አይዘነጋም። መንግስት የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የጣሉ መቀሌ የመሸጉትን የሕወሓት መሪዎች ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርሱ ሀላፊነቱን እንዲወጣ […]

የኢንጂነር ስመኘው በቀለ አሟሟት እያነጋገረ ነው

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) የአባይ ግድብ ስራ አስኪያጅ እና መሀንዲስ የሆኑት፣ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አብዮት አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ተገድለው መገኘታቸው ታውቋል። የኢንጅነሩ አስከሬን በምርመራ ላይ ነው። እኝህ ሰው የህወሃትን ከፍተኛ ሚስጥር ሊያወጡ ይችላሉ በሚል ምክንያት በወያኔ ባለስልጣኖች እንደተገደሉ ይገመታል። ባለፈው ሰኞ ጠ/ሚ አብይ አህመድ “የህዳሴ ግድብ አሁን ባለው አካሄድ የዛሬ አስር አመት አይጠናቀቅም” ማለታቸው ይታወሳል። የግድቡን አብዛኛውን ስራ […]

የኢትዮጲያና የኤርትራ የሰላም ስምምነት ከትላንቱ ታሪክ ጋር ስለመታረቅና በነገውን የሩቅ ጉዞ |ነዓምን ዘለቀ

$
0
0
በዚህ በዓል ላይ የተገኛችሁ ኤርትራዊያን ወንድምና እህቶቼ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶችና የውይይት ተሳታፊዎች የተከበራችሁ የክብረ በዓሉ አዘጋጆች በቅድሚያ በዚህ መድረክ ላይ እንድገኝ ስለተጋበዝኩ ከልብ አመሰግናለሁ። በዚህ ዝግጅት ላይ አርበኞች ግንቦት 7ን ወክሎ ንግግር እንዲያደርግ የተጋበዘው እንግዳ የንቅናቄው የስራ አስፈጻሚ አባልና ዋና ጸሃፊ የሆነው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ነበር። ሆኖም በመጨረሻ ሰዓት ላይ ከኤርትራ መንግስት የተደረገለትን ድንገተኛ ጥሪ […]

ከጎንደር-መተማ-ሱዳን የሚወስደው ዋና መንገድ ተዘግቶ ዋለ |በጭልጋ ቤቶች ላይ እሳት ተነሳ

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) ከጎንደር እስከ ከመተማ እስከ ሱዳን የሚወስደው መንገድ በዛሬው እለት ዝግ ሆኖ መዋሉ ተዘገበ:: የቅማንት ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ የቅማንት ማንነት ይከበር በሚል ለ3 ቀናት አድማ መጥራቱን ተከትሎ ነው ከጎንደር እስከ መተማ ከመተማ እስከ ሱዳን የሚወስደው ዋና መንገድ ተዘግቶ የዋለው:: ይህን ተከትሎም በጭልጋ ግጭት መፈጠሩን የሚገልጹ የአይን እማኞች በርካታ መኖሪያ ቤቶች ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ገልጸዋል:: […]

ሌሎች አጫጭር ወሬዎች

$
0
0
ሳውላ የደምቢ ዶሎ ከተማ ነዋሪዎች በከተማው የሚፈፀሙ ግድያዎችን በመቃወም ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ከቤት ያለመውጣት አድማ ጀመሩ። ከቤት ያለመውጣት አድማው ከደምቢ ዶሎ በተጨማሪ ጊዳሚን ጨምሮ በቄለም ወለጋ ዞን በሚገኙ ከተሞች በመካሄድ ላይ ይገኛል። ነባር የደኢህዴግ መሪዎች በጎፋ ሳውላ ከተማ ጉብኘት እያደረጉ ባለበት ሰዓት የከተማው ነዋሪዎች እነዚህ የቀን ጅቦች ከተማውን ለቀውልን ይውጡ በማለቱ በከተማዋ በሕዝቡና […]

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ይቅርታ ጠየቁ |“እርቁ የሚያስፈልገው ኦርቶዶክስ ሃገር ስለሆነች ነው”

$
0
0
የሲኖዶሱን እርቅ ውሳኔ በማስመልከት በዋሽንግተን ዲሲ ያደረጉት ንግግር “እርቁ የሚያስፈልገው ኦርቶዶክስ ሃገር ስለሆነች ነው”

ምንም ዓይነት ግድያ ምሥጢርን አይደብቅም –ምሕረት ዘገዬ

$
0
0
በዚህች አጭር መጣጥፍ ውስጥ ደግሜ ላለመመላለስ ስል ሁለት ርዕሶችን በመጠኑ እዳስሳለሁ፡፡ የመጀመሪያው ከፍ ሲል ያስቀመጥኩት የዕለቱን ሁኔታ የሚገልጽ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ስለትምህርታችን የጥራት ደረጃ የታዘብኩትና ከሥር የቀረበው ነው፡፡ ኢንጂኔር ስመኘው በቀለ በመስቀል አደባባይ መኪናው ውስጥ ሞቶ መገኘቱን በአሁኑ ሰዓት በሰበር ዜናነት እየተነገረ ነው፡፡ ስለአሟሟቱ ሁኔታ ገና የተሰማ ነገር የለም፡፡ እርግጡ ሳይታወቅ ደግሞ እገሌ ገደለው ወይ […]

ስለመቀሌዉ ሰልፍ እዉነት እንነጋገር! –በታየ ደንዳ

$
0
0
ዛሬ መቀሌ ላይ ሠላማዊ ሠልፍ ተደርጓል። አስተባባሪዉ ህወሀት እንደሆነ ይታወቃል። የሰልፉ ዓላማ ደግሞ የኢትዮ-ኤርትራን የሠላም ስምምነት መደገፍ እንደሆነ ተነግሯል። በሠልፉ ላይ የመለስ ዜናዊ እና የኢንጂነር ሰመኘዉ በቀለ ፎቶ ደምቆ ታይቷል። መለስ ለሠላም ህደቱ ትልቅ ሚና እንደነበረዉ ሲገለፅ ለክቡር እንጂነር ስመኘዉ ሀዘን ተገልፇል። ህገ-መንግስቱም ይከበር ተብሏል። ይህ ብቻዉን ስለሰልፉ አጠቃላይ እዉነታ ይነግረናል። የማስመሳያ ሰልፍ! ኢትዮጵያና ኤርትራ […]

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አውቶቡስና የቅርብ ታሪካችን ትምህርት

$
0
0
አንዱዓለም ተፈራ አርብ፣ ሐምሌ ፳ ቀን ፳ ፻ ፩ ዓመተ ምህረት ( 7/27/2018 ) ትናንት አርብ፣ ሐምሌ ፳ ቀን ፳ ፻ ፩ ዓመተ ምህረት ( 7/27/2018 ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከተቃዋሚ/ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ያደረጉትን ልውውጥ ከድረገጽ ካገኘሁት ቪዲዮ ላይ ተመለከትኩ። ዛሬም በዋሺንግተን ዲ. ሲ. ስብሰባ ያደርጋሉ። ከትናንቱ የተለየ እንደማይናገሩ እገምታለሁ። በአርቡ ስብሰባ፤ ከትንንሽ ድርጅቶች […]

“መደመሩን” ከቀኝ ጅቦች ለማዳን – ፀረ-ቅልበሳ ኃይሎችን ማደራጀት – B.K

$
0
0
1966 ዓም ተጠናክሮ የመጣው የለውጥ ማዕበል ቤተመንግስቱን ሳይቀር አንቀጠቀጠ። ንጉሡ የሕዝቡን ተቃውሞ መቋቋም አቃታቸው። በዚህን ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር አክሊሉ ሃብተወልድ ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ። ይህ ለመጀመርያ ጊዜ የተደረገ በሳል የፖለቲካ ርምጃ ነበር። ንጉሡ የሕዝቡን ንቅናቄ በጥገናዊ ለውጥ ለማስተካከል ሞክረው ልጅ እንዳልካቸው መኮንንን ጠቅላይ ሚኒስቴር አድርገው ሾሙ። ሕዝቡ አሁንም ተቃውሞውን ገፋበት። የንጉሡ አስተዳደርር ለፖለቲካ ፓርቲ እውቅና የማይሰጥ ስለነበር […]

ሳይጠየቅ የቀረ ጥያቄ ለዶ/ር አብይ –ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

$
0
0
በዋሽንግተን ዲሲ ጉብኝትዎ ብገኝም፤ ነገር ግን ዕድል አግኝቼ ልጠይቅዎት ያልቻልኩትን ጥያቄ ምናልባት ፈጣሪ ፈቅዶ ለጆሮዎ ይደርስ ይሆናል ብዬ ይህን ለመፃፍ ተነሳሳው። ጥያቄዬ የሚያጠነጥነው በአመፅ ተፀንሶ፤ በፍቅር የተወለደው ይህ የለውጥ ጅማሬ እንዴት እናስቀጥል እንችል ይሆናል ከሚል ጭንቀት ውስጥ የወጣ ነው። ሁላችንም በእርስዎ ድንቅ አመራር፥ የፍቅርና ትህትና አካሄድ ተማርከን የዛሬው ደስታችን ላይ አተኩረን በታላቅ ደስታ ላይ ነን። […]

በአማራ ክልል አዊ ዞን እና አብድራፊ የሰው ህይወት ጠፋ

$
0
0
ለገሠ ወ/ሃና በአማራ ክልል አውይ ዞን የኢንጂነር ስመኘው በቀለን የቀብር ስነስርዓት ህዝብ እየተከታተለ እያለ መብራት ይቋረጣል መብራት የተቋረጠበትን ሁኔታ እየተከታተሉ የነበሩ የአከባቢው ወጣቶች በድንገት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የሜቴክ ሰራተኞች መብራት እየቆረጡ ያገኟቸዋል በዚህ የተናደዱት ወጣቶች ሁለቱን የትግሬ ተወላጆች ወዲያውኑ በዱላና በድንጋይ ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው በስልክ ከቦታው አድርሰውኛል አንደኛው ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት በፓሊስ ተይዞ ፓሊስ ጣቢያ እንዳስገቡት […]

ትህነግ በራያ ውርደት ተከናነበች

$
0
0
(ብሩክ አበጋዝ) ትህነግ በራያ አላማጣ ጠሚ ዓብይን ተቃውማችሁ ሰልፍ ካልወጣችሁ ዘይት እና ስኳር እከለክላለሁ በማለት “ራያ ትግራይ ነው” በሉ እያለ ሰልፍ ያስወጣቸው ሰወች እኒህ ናቸው። የራያ ሕዝብ ትህነግ/ህወሓትን ስላሳፈራት ዛሬም እንደ ወትሮው ኮርቶባቸዋል። የራያ ሕዝብ የጠሚ ዓብይን የለውጥ እርምጃ ለመደገፍ ሰልፍ ሲወጣ ግን በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል፣ ቆስሏል፣ ወጣቶች ታስረው ተንገላተዋል። ትህነግ መቀለ ላይ ሰልፍ ስታደርግ […]

ትግራይን በጨረፍታ አየኋት –ይነጋል በላቸው

$
0
0
ያለፈችዋ ሌሊት እስክትነጋልኝ በጣም ቸኮልኩ፡፡ መንጋቷ አልቀረም ይሄው በሌሊቱ ቢሮየ ገብቼ ይህችን ማስታወሻ መጻፍ ጀመርኩ፤ ችኮላየም ለዚሁ ነበርና፡፡ አንዳንድ ከበድ ያሉ ሀገራዊ ጉዳዮች ሲከሰቱ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጪ ሚዲያዎች ምን እንደሚሉ ለማወቅ የዜና አውታሮችን እየለዋወጥኩ እከታተላለሁ፡፡ በዚህ የተለመደ የራሴ አካሄድ ብዙ ነገሮችን እማራለሁ፤ እታዘባለሁ፡፡ በሀገራችን እንደአማራ ቲቪ፣ ትግራይ ቲቪ፣ ኦቢኤን(ኦሮሞ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ)፣ ኢቲቪና ኢሳትን የመሳሰሉ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live