ለተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች በቅድሚያ የከበረ ሠላምታዬን እያቀረብኩኝ ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያዊነትን በማፈንና ብሄራዊ ስሜትን በማደብዘዝ አገራችንን ለአደጋ ከዳረገው ስርአት ለመላቀቅና በምትኩ አንድነትን ፥ መተባበርን እና ፍትህን ለማስፈን ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ለማዳን በተለያየ አቅጣጫ ብዙ እንቅስቃሴዎች በሚካሄድበት በአሁኑ ወቅት፦ በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ኢትዮጵያዊነትን እና ይቅር መባባልን ይዘው ብቅ ላሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድና ባልደረቦቻቸው […]
ቴዲ አፍሮ ለዶ/ር ዓብይ አህመድ የላከው መልዕክት
↧
↧
ከብሔራዊ ባንክ ገዢነት የተነሱት አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የጠ/ሚ.ሩ የፋይናንስ አማካሪ ሆነው ተሾሙ
(ዘ-ሐበሻ) የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋይናንስ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ተገለጸ:: የብሔራዊ ባንክ ገዢ በነበሩበት ወቅት በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዲያገግም ለማድረግ የገንዘብ አቅርቦትን በተመለከተ የተዛባ ሪፖርት እንዲወጣ ምክንያት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ተክለወልድ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አልቻሉም በሚል እርሳቸውና ምክትላቸው የተሰናበቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መንበረ ስልጣኑን እንደተቆጣጠሩ […]
↧
መቶ አለቃ አይዳ ኤሌሮ በዘር ከተዋቀረው ሰራዊት ልትኮበልል ነበር በሚል ክስ እስር ተፈረደባት
(ዘ-ሐበሻ) መቶ አለቃ አይዳ አሌሮ ትባላለች፡፡ በአየር ወለድ አሰልጣኝነት ስታገለግል ነበር፡፡ በፖሊሶች ታፍና ከተወሰደች በኋላ ለተወሰኑ ቀናት አይታወቅም ነበር:: ከዚያም በቅድሚያ ታፍና የተወሰደችው 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደነበር ታወቀ:: ቀጥሎም ወደ ታጠቅ ወታደራዊ ካምፕ አዘዋወሯት:: በሽተኛ እናቷን እያስታመመች የምትጦረው መቶ አለቃ አይዳ; በመከላከያ ውስጥ የተሰገሰጉ ክፉ አዛዦች የብዙ ሺህ ወጣቶችን ህይወት ማበላሸታቸው እንዳንገሸገሻት ያወቁት ወታደሮች አፍነው […]
↧
ቴዲ አፍሮ ዶ/ር ዓብይ አህመድን እንደሚደግፍ አስታወቀ
(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች ላለፉት 2 ወራት በላይ እያቀረበ የሚገኘው ድምጻዊው ቴድሮስ ካሳሁን በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳይ ዶ/ር ዓብይ አህመድ እያደረጉ ያለውን አድንቆ እርሳቸውን ለመደገፍ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እደመራለሁ ብሏል:: ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር የተሰኘ ኮንሰርቶቹን እያቀረበ የሚገኘው ቴዲ በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መል ዕክቱ “ለተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች በቅድሚያ የከበረ ሠላምታዬን እያቀረብኩኝ ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያዊነትን በማፈንና […]
↧
ቴዲ አፍሮ –ከዶ/ር አብይ ጎን ለመቆም ጊዜው አሁን ነው |ክንፉ አሰፋ
“ኢትዮጵያዊነትን እና ይቅር መባባልን ይዘው ብቅ ላሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድና ባልደረቦቻቸው አጭር በሚባል የስልጣን ቆይታቸው ለወሰዶቸው በጎ እርምጃዎች እና ላሳዩን ኢትዮጵያዊ አለኝታነት አጋርነትን ማሳየት እና ከጎናቸው መቆም ጊዜው የሚጠይቀው አስፈላጊ ተግባር መሆኑን ስገልፅ በሚደረጉት የድጋፍ እንቅስቃሴዎች ላይ በሥራ አጋጣሚ በቦታው ባልገኝም በመንፈስ አብሬያችሁ መሆኔን ሳረጋግጥ በታላቅ ኢትዮጵያዊ ስሜት ነው።” ብሎናል ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ! […]
↧
↧
ዶ/ር ዓብይ አህመድ በአዋሳና በወላይታ ሶዶ ከሕዝብ ጋር ተወያዩ |የወላይታ ሕዝብ ሽፈራው ሽጉጤ ከመድረክ ይውረድ ሲል ተቃወመ
ከአስር ሰዎች በላይ ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነውን የአዋሳ, የወላይታ ሶዶ እና የወልቂጤ ግጭቶችን ለመፍታት ወደ ስፍራው ለውይይት ያመሩት ዶ/ር ዓብይ አህመድ ዛሬ ጠዋት በአዋሳ ከሕዝብ ጋር የተወያዩ ሲሆን ከሰዓት በኋላ ደግሞ በወላይታ ሶዶ ሕዝባዊ ውይይት እያደረጉ መሆናቸውን የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል:: ዶ/ር ዓብይ በፍቼ ጫምባላላ በዓል ላይ ግጭት እንዲፈጠር ያደረጉ ለህግ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል:: በአዋሳው ስብሰባ ላይ […]
↧
የጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ የሰራዊቱ የመዋቅር ማሻሻያ በእርግጥ ተግባራዊ ይሆናል? ኮ/ል ደረሰ ተክሌ ይናገራሉ
የጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ የሰራዊቱ የመዋቅር ማሻሻያ በእርግጥ ተግባራዊ ይሆናል? ኮ/ል ደረሰ ተክሌ ይናገራሉ
↧
ወፌ ላላ –ጌታቸው ኃይሌ
ወፌ ላላ 1 አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴራችን በእኛ አገር ብርቅ የሆኑ ነገሮችን እንደሌላው አገር ተራ ነገሮች እያደረገ፥ አንዱን አጣጥመን ሳንጨርስ ሌሎቹን ሲያከታትል ሰነበተ። ይኸን ካላደረገ እያሉ የሚያደርገውን ሁሉ እንደ ትንሽ ነገር የሚያጣጥሉ፥ አድርጎት ሊያዩ ቢቸግራቸው ሊያደርግ የማይችለውን እየፈለጉ መጠየቅ ጀመሩ። አሁን ደግሞ፥ “እንዲህ ያሉ ታላላቅ ጉዳዮች በአንድ ሰው የሚወሰኑ አይደሉም” የሚሉ ተነሡ። “ለውጡ የምንፈልገውን አቅጣጫ ይዞ […]
↧
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የግሌ አቋም |ለገሰ ወልደሃና
በመጀመሪያ ለጠቅላያችን ከሁሉም አቅጣጫ ድጋፍ እየጎረፈላቸው በመሆኑና እሳቸውም ለለውጥ ቆርጠው እንደተነሱ በስራቸው እያስመሰከሩ ነውና ከፍ ያለ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ እንዲያውም ከድጋፍ ይልቅ የሰላ ትችትና አቅጣጫ አመላካች ምክር እጥረት እንዳያጋጥማቸው በመፍራት አቋሜን እንደሚከተለው እገልጻለሁ፡፡ 1. ዶ/ር አብይ ይዘውት የመጡት የለውጥ መንፈስ ህዝቡ መልካም ተስፋ እንድሰንቅ አድርጎታል፡፡ በየማጎሪያ ቤቱ ሲሰቃዩ የነበሩ ወገኖቻችን መፈታትም ምን ያህል ዋጋ እንዳለው የሚያዉቁት […]
↧
↧
በዘመናት መካከል ቁመናል (የሰማያዊ ፓርቲና የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባላት በአንድነት)
የአንዱዓለም አራጌ ንግግር አጠር ያለውን ንግግሬን ከመጀመሬ በፊት ጥቂት ነገሮችን ለማለት ይፈቀድልኝ፡- ድንገት ካወቃችሁኝ በብዙዎቻችሁ ዘንድ ከፖለቲከኛነቴ ይልቅ በእስረኛነቴ ይመስለኛል፡፡ በፖለቲካ እስረኛነቴ፡፡ አሁን ከፖለቲካ እስረኛነት ወደ ፖለቲከኛነት ለመሸጋገር የስነ – ልቦና ዝግጅት በማድረግ ላይ እገኛለሁ፡፡ የእስረኛነት ስሜት እንደልብስ በቀላሉ አውልቆ የሚጥሉት አይደለም፡፡ ለተወሰነ ጊዜም አብሮኝ ይቆያል፡፡የህይወቴ አካልም ሆኖ ይዘልቃል፡፡ ብዙዎቻችሁ ስለ እኔና ስለሌሎች እስረኞች እንደ […]
↧
ማስታዋሻ ቁጥር 10፡ አብይ አህመድ፣ የኢትዮጵያ “ሕይወት አድን”ጠቅላይ ሚኒስትር
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በዚህ ማስታዋሻ ውስጥ ሁለት ትችቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው እና “አጭሩ“ (ቢያንስ እንዲህ እያልኩ የምጠራው አስተያየት ከዚህ በታች ) የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ክልል ውስጥ በመስጠት ላይ ስላለው አመራር የቀረበ ትችት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያውያንን ከበርካታ ሀገሮች ከእስራት እና ከእስር ቤቶች በማውጣት እያደረጉት ስላለው ህይወት አድን ልዩ ስራ አድናቆቴን […]
↧
ሰበር ዜና –ኢሳያስ አፈወርቂ ልዑካናቸውን ወደ አዲስ አበባ ሊልኩ ነው
(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት አቅራቢነት የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እቀበላለሁ ካለ በኋላ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ምላሽ ሳይሰጡ ቆይተዋል:: በዛሬው ዕለት ግን በጃፓን የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር እስጢፋኖስ አፈወርቂ ዝምታውን ሰብረውታል:: አምባሳደር እስጢፋኖስ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያ ጋር ገንቢ ውይይት ለመጀመር አንድ የልዑካን ቡድን አባላትን ወደ አዲስ አበባ ሰሞኑን ይልካሉ:: ዶክተር […]
↧
ዶ/ር ዐብይን ከስልጣን ለማስወገድ አሲረዋል የተባሉት ካሳ ተክለብርሃን፣ ተቀዳ አለሙ እና አስቴር ማሞ ሊጠሩ ነው
ከብሔራዊ ጥቅም በተቃርኖ ቆመዋል የተባሉ፤ ሶስት አምባሳደሮች ሊጠሩ ነው Source: ሰንደቅ ጋዜጣ የሰኔ 13, 2010 ዕትም ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱ ተከትለው ወደ ስልጣን በመጡት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደር ላይ አሲረዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት አምባሳደሮች ሊጠሩ መሆኑን ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ በሴራ የተጠረጠሩት አምባሳደር ዶክተር ተቀዳ አለሙ በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ፣ በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ አስቴር ማሞ እና በአሜሪካ […]
↧
↧
በቅርቡ ከእስር የተለቀቁት መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እና አበበ ካሴ በጎጃም ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ከእስር የተለቀቁት መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እና አበበ ካሴ በመርጦለማርያም እና ግንደወይን ከተሞች ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተመስገን ወንድይፍራው ዘግቧል:: “መርጦለማርያምና ግንደወይን ላይ ትናንት አማራነት ሲቀነቀን ነው የዋለው።” የሚለው የተመስገን ዘገባ እንደሚከተለው ይቀርባል:: ታሪካዊቷ መርጦለማርያም በአማራነታቸው ብቻ ተነግሮ የማያልቅ የግፍ አይነት የተፈፀመባቸውን ጀግኖች የክብር አቀባበል አድርጋለች። ማስረሻ በወኔ እንዲህ አለ፥ “የአማራ ህዝብ ለ27 […]
↧
በኬንያ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ሲሰልሉ የከረሙት ደህንነት የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ተሾሙ
(ሪፖርተር) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አዲስ ካቢኔ ሲያዋቅሩ፣ የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አድርገው ሾመዋቸው የነበሩት ኃላፊ ተነስተው ሌላ ኃላፊ መሾሙ ተጠቆመ፡፡ በቅርቡ ተሹመው የነበሩትና ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሌላ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል የተተኩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ናቸው፡፡ አቶ ያሬድን በመተካት የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው የተሾሙት ደግሞ አቶ ዘይኑ ጀማል መሆናቸውን የሪፖርተር ምንጮች […]
↧
በደቡብ ክልል ሰሞኑን ግጭት በተነሳባቸው ከተሞች ያሉ ባለስልጣናት በራሳቸው ፈቃድ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ዶ/ር ዓብይ አህመድ አሳሰቡ
(ዘ-ሐበሻ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በደቡብ ክልል ግጭት የተከሰተባቸው አካባቢዎች የሥራ ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው እንዲለቁ ማሳሰቢያ ሰጡ:: ዶክተሩ ይህንን ያሉት፣ በቅርቡ ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ በሐዋሳ፣ በወላይታ ሶዶና በወልቂጤ ከተሞች ከኅብረተሰቡ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሲዳማ፣ የወላይታ፣ የጉራጌና የቀቤና የዞንና የወረዳ አስተዳደር ኃላፊዎች ሥራቸውን በአስቸኳይ እንዲለቁ ያሳሰቡት አመራሮቹ ይህን ተቀበለው ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል:: […]
↧
ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ለመኖር መፈለጉ አዲስ ነገር አይደለም አሉ
(ዘ-ሐበሻ) በሕወሓት አቅራቢነት የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እቀበላለሁ ካለ በኋላ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ምላሽ ሳይሰጡ ቢቆዩም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያ ጋር ገንቢ ውይይት ለመጀመር አንድ የልዑካን ቡድን አባላትን ወደ አዲስ አበባ ሰሞኑን እንደሚልኩ መግለጻቸውን ዘ-ሐበሻ በሰበር ዜና ከሰዓታት በፊት መዘገቧ አይዘነጋም:: በኤርትራ የሰማ ዕታት ቀን በዓል ሲከበር ለኤርትራ ህዝብ ንግግር ያደረጉት አቶ […]
↧
↧
የሳዲቅ አህመድ ዜና ትንታኔ: ኢትዮጵያ vs ኤርትራ |ከጀርባው ያሉ ምስጢሮች ይተነተናሉ
ኤርትራ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋጋር የልኡካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ ነው የአገራቱ ዉጥረትና አዲሱ መልከዓምድራዊ የፖለቲካ አሰላለፍ የባህረሰላጤው አገራት ወደ አፍሪካ ቀንድ መዘንበል ለምን ይሆን? የጠ/ሚ አብይ አህመድ የሳኡዲና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ጉብኝት ኢድን በአራት ኪሎው ቤተ-መንግስት ሉኡሉ ለምን አከበሩ የቀድሞው ጠ/ሚ ሐይለማሪያም በሳኡዲና ኤምሬት ዝተው ነበር የአረብ አገራት ረብጣ ዶላርና ኢትዮጵያ የሚያሻት ጥንቃቄ **** […]
↧
ኮለኔል ጎሹ ወልዴ ዝምታቸውን ሰበሩ –በድምጽ መል ዕክት አስተላልፈዋል
የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የትምህርት ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ሳይቀጭ ዳር እንዲደርስ፤ ኢትዮጵያውያን ሙሉ ልባዊ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ያቀርባሉ። የግል ድጋፋቸውንም ይቸራሉ። “ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያውያን አስተሳሰብና ስነ ልቦና ላይ እየቀሰቀሱ ያለው የለውጥ፣የዲሞክራሲና የነፃነት ጥማት፤ በኢትዮጵያ አኩሪ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ታይቶ የማይታወቅ ክስተት ነው ለማለት ይቻላል። ዛሬ […]
↧
አርበኞች ግንቦት 7 ልዩ መግለጫ አወጣ: “የሰለጠነ ፓለቲካ” የምንመርጠው፣ የምናውቀውና የምንመኘው የትግል ስልት ነው!
የአርበኞች ግንቦት 7 ልዩ መግለጫ ሰኔ 11 ቀን 2010 ዓም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡትን የሥራ ዘገባ እና ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች የሰጡትን ምላሽ በአንክሮ ተከታትለናል። ዶክተር አብይ በዚሁ ማብራሪያቸው የኢህአዴግ መንግሥት የፀጥታና የደህንነት ኃይሎች የአሸባሪነት ተግባራትን የሚፈጽሙ እንደሆኑ በይፋ ከመናገራቸውም ባሻገር፤ ፓርቲና መንግሥት ተቀላቅለው ነፃ ተቋማት እንዳይኖሩ መደረጉን […]
↧
More Pages to Explore .....