Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

መሬታቸው ለህንድ ሻይ ልማት ኩባንያ መሰጠቱን የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን ከመንግስት ዱላ ገጠማቸው

$
0
0

ሰንደቅ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው፦

በጋምቤላ እና በሸካ አዋሳኝ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ህዝቦች መካከል 100 ሺ የሚሆኑ የሸካ ተወላጆች 3012 የሚደርስ ሄክታር መሬት ከአካባቢያችን ጥብቅ ደን ተወስዶ ቨርዳንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ለተሰኘ የህንድ ኩባንያ መሰጠቱን በመቃወማችን ጉዳት እየደረሰብን ነው ሲሉ የብሔሩ ተወላጆች ምሬታቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለጹ። በክልሉ እንደተካተቱት ሌሎች አምስት ብሔሮች ስድስተኛ ሆነን አልተመዘገብንም፤ ልጆቻችን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር አልቻልንም፤ በክልሉ ተገቢ የሆነ የመሰረተ ልማት ግንባታ ተጠቃሚ አልሆነም፤ ለዚህም አካባቢው የሚካሄደውን ኢንቨስትመንት ተቃዋሚ እንደሆነ ተደርጎ መታሰቡ አግባብ አለመሆኑን የሸካ ህዝቦች ተወካይ በመሆን አቤቱታቸውን ለማሰማት የመጡት አቶ ታምሩ አምበሉ አስረድተዋል።
tea
በጋምቤላ ክልል የመጀንግ ዞን አመራር የሆኑት አቶ ይማም ቃሪስ በበኩላቸው ይህንን አቤቱታ የሚያሰሙት ጥቂት ግለሰቦች የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት ያላቸውና ተጨፈጨፈ የሚሉትም ጥብቅ ደን ሳይሆን ቁጥቋጦ ነው ብለዋል። አክለውም እንደጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ደንብና አሰራር መሰረት የህንዱ ኩባንያ መሬቱን እንዲያለማ መፍቀዳችን ትክክል ነው ይላሉ።

የሸካ ህዝቦች ለዘመናት ጠብቀው ባቆዩት ጥብቅ ደን ውስጥ ማር በማምረት እንደሚተዳደሩ ያስረዱት አቤቱታ አቅራቢዎቹ የአካባቢውን ህዝብ ባላማከለ መልኩ ጥብቅ ደኑን እንዲጨፈጨፍ ማድረግ ከውስጡ የሚመነጩትን ወንዞች መጉዳት ነው ሲሉ ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል ይላሉ። ይህንንም አስመልክተው በ1999 ዓ.ም የብሔር ብሔረሰቦች መብት ተጠቃሚዎች አይደለንም በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የ1200 ሰዎችን ፊርማ አሰባስበው የመብት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር በማስታወስ፤ የመብት ጥያቄያቸው ሳይመለስ እስከ 2002 ዓ.ም መጠበቃቸውንና አልፎም የህዝቡን ዋና መተዳደሪያ የሆነውን ጥብቅ ደን ለማጥፋት ምክንያት ሆኖብናል ይላሉ።

በተለይም የህንዱ ቨርደንት ሃርቨስት አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መዠንገር ዞን ጎደሬ ወረዳ የጎማሬ ቀበሌ አስተዳደር በሸካ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን 3012 ሄክታር ጥብቅ ደን ለሻይ ልማት መፈቀዱ አግባብ አይደለም ሲሉ በተለያዩ መንገዶች አቤቱታቸውን አሰምተዋል። “እኛ ምንም አይነት ኢንቨስትመንትን የመቃወም ኀሳብ እንደሌለን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን” የሚሉት የህዝቡ ተወካዮችና አቤቱታ አቅራቢዎች፤ ይህ ቦታ አማራጭ ቢፈለግለት ይሻላል። ደን ከጠፋ ዘራችን የአኗኗር ባህላችን ሁሉ ይጠፋል የሚል እንደሆነም ተናግረዋል። ያም ሆኖ ለኩባንያው ግንባታ ሲባል በ67 ሄክታር ላይ የሚገኝ ደን ተጨፍጭፎ 1640 በላይ ጣውላዎች ወጥተው ተገኝተዋል ሲሉ አስረድተዋል።

ይህን ጉዳይ አስመልክቶ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በወቅቱ ለአካባቢ ጥበቃ ኃላፊ በፃፉት ደብዳቤ፤ በጋምቤላ አካባቢ ያለውን የተፈጥሮ ደን ያለበት ሰፊ መሬት ደኑ በጣም ጥቅጥቅ ያለና ለአየር ጥበቃ ሊቆይ የሚገባው ሆኖ ሳለ ለሻይ ልማት ኢንቨስትመንት ተሰጥቶ ሊመነጠር ስለመሆኑ የአካባቢው ህዝብ ይህን ችግር ለማሳወቅ ሰዎች ወክሎ መላኩን በመግለፅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል።

በበርካታ ባለሙያዎች ጥናት ተደርጎለት የአካባቢው የደን ሀብት እንዲጠበቅ ቢወሰንም አሁንም ድረስ የተሰራ ስራ አለመኖሩንና የአካባቢው ህዝብም ስጋት ላይ መሆኑን በመጥቀስ ህዝብና መንግስት ጉዳያችን ተረድቶ ጥብቁን ደን ከጥፋት ይከላከለው ዘንድ ድምጻችንን እናሰማለን ብለዋል፤ አቤቱታ አቅራቢዎቹ።
የመጀንግ ዞን አመራር በሰጡት ምላሽ ቦታው ጥናት ተደርጎበት ለልማት የተመራ መሆኑን በመግለፅ፤ ኩባንያው የሻይ ልማት ስራውን ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እየሰራ እንደሚገኝና ነገር ግን ጥቂት የግል ፍላጎት ያላቸው ግሰቦች እንቅፋት የሚሆን እንቅስቃሴ አድርገዋል ሲሉ ይወቅሳሉ።


ቴዲ አፍሮ የቅኔ ዕንቡጥ –ለእናቱ ልዩ ዓርማ ነው!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 16.01.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

“የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል እግዚአብሄር፤ ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ (ምሳሌ ምዕራፍ 16 ቁጥር 9 )

የሀገሬን ክብር አዝልቀህ – ልታደምቅ
ታጥቀህ ተነስተኃል – አንተ የቅኝት ብርቅ፤
ራዕይ — አብነት።
እማን ከፍ አድርገህ ልታሸልማተኝ ጌጥ
ዕውቅናዋ ፈክቶ ዓለምን ልትመስጥ።
ተግተህ ትሠራለህ – አንተ የቅኔ ዕንቡጥ፤
የነፃነት ቃና – የትውልዳችን – ፈርጥ!

ባልባለቀው መንፈሴ – ቴዴ አፍሮ የተስፋዬ ፀሐይ ነው። ማህተም አለበት!
teddy afro
ዋና በር … ከሳቢያ ጥረት ምክንያታዊ፤ ከሳቢያ ተኮር ድካምም ምክንያታዊ ተግባራት የድል ዋዜማ ናቸው። ምክንያቱም የችግሩን ምንጭ ከሥሩ የሚያደርቀው በምክንያታዊና መሬት በረገጠ ተግባር ብቻ ጨለማው ነግቶ፤ የምሥራች ለነፃነት የመሸለም ስበታቸው ሆነ አስገዳጅነታቸው ጉልበታም ናቸው። የሚያስቀሩት ፍርፋሪ ስለማይኖርም ዘላቂ ድህነት ያስገኛሉ። የመፍትሄ መንገድ ጠራጊ የችግሩን ሳቢያ ማወቁ ሳይሆን ይልቁንም ምክንያቱን በሚገባ በልቶ ያማያዳግም መለስ ከመስጠቱ ላይ ነው። ምክንያት ተኮር የምርምር ተግባር በሸታውን ያገኛል። ህመሙን ከሥሩም ይነቅላል። ሳቢያ ተኮር እርጃዎች አቅመቢስ በመሆናቸው፤ ዋስትና የማይሰጡ ማስታገሻ ናቸው፤ አዘናጊ ልፈስፍስ ዝልቦ መንገዶች ናቸው!

ምልሰት፣ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2008፤ በኢትዮ – አፍሪካዊው የቅኔው ልዑል በብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ሥም በሰዬምኩት ማህበራዊ ድህረ ገጽ፤ እንዲሁም በጸጋዬ ድምጽ ራድዮ ፕሮግራሜ ቃሊቲ ውስጥ ለነበረው ታናሼ „ሥምን መላዕክ ያወጣዋል“ በሚል አንድ መጣጥፍ መጻፌን ብቻ ሳይሆን በድምፄም ማቅረቤን አስታውሳለሁ። ልቤ ውስጥ የገባ የቅኔ ቀንበጥ ነበርና ቴዲ አፍሮ። ስለ ወጣቱ ከያኒ – ገጣሚ – ዜመኛ – ድምጽ ቃና፤ እንዲሁም የአቀራረብ ብቃት- በዛ ጹሑፌ ላይ ሥራዎቹ ተተርጓሚነታቸው (interpretable) እንዲሁም ተዋራራሽነታቸውን በስፋት ነበር የገለጽኩት።

የድርሻዬን ይባልለት – ስለ ይፈልቃል ገና!

ዛሬም ደግሞ ትንሽዬ የግል ዕይታዬን ለማለት ትክሻዬን ለሚወርደው ዱላ አስመችቼ ለመቀበል ቆረጥኩና እንዲህ ልል ነው። በዚህ ፈታኛ ወቅት መቆስቋሻ የሚያስፈልግበት ሳይሆን ገብቶ መርመጥመጥም ይጥማል። ፈተና ተፈልጎ የማይገኝ ከተገኘ ግን አንጥሮ የሚያሳምር ሜሮን ነው። አባቶቻችን ፈተናቸው ሲዘገይ ወይንም ፈተና ቸልም ብሎ ሲረሳቸው ሁለት ሶስት ሱባኤ ይይዛሉ። እኔው የእነሱ ህይውት ኑሮኝ በመንፈሳዊ ዘርፍ ብጣቂ ዘር ባይኖረኝም። በገኃዱ ዓለም ግን እኔም ፈተና ሥልጡን አድርጎ ቀርፆኛል። ተላምጄዋለሁ። ከጋሼ ጸጋዬ ፍቅር መንጭቶ በውሰድኩት የድህረ ገጽ ስያሜ ብርትዬም ታስራ በነበረችበት ውቅት ተግቼ በብዕር ብቻ ሳይሆን በተገኘው አጋጣሜ ሁሉ መፋለሜ፤ እኔን ቢደቁሰኝም፤ ክሱ ሀገር ምድሩን ቢያዳርስም እኔኑ ቢያደቃኝም፤ የወረደው ማዕት …. ግን ኃይልና ብርታት ሰጥቶት ከዛ በኋላ የተከደኑ ብዙ ሲሳዮችን እንድከውን አምላኬ ረዳኝ። ቀን ሲወጣ ታላቋ ኢትዮጵያ ትንቆጠቆጥበታለች። አዎን! እኔ በምኖርበት ሀገር ኢትዮጵያ የምትባል ታላቅ ሀገር ጸጋዬ የሚባል የኢትዮ አፍሪካዊ ፈላስፋ ዕውቅናቸው ሙሉዑ እንዲሆን ሆኗል። የኦነግን ተልዕኮ ለማሳካት ሆነ በቅዱስ ወንጌል ሰባኪ ተብዬ ክስ ተመስርቶብኝ ነበር። ለዛውም ለአንስት ባልተሰጠኝ ጸጋ ብከሰስም አሸነፍኩ። ተመስገን። እድሜ ለሚሹንግ ዩንቨርስቲ ታላቅ ሚዛናዊ ኢትዮጵያዊ ሙሑር። ብዕራቸው ከእሥር አስለቀቀን በጋራ ….. ሰላምም አሰፉን። ምስክርነታቸው አንጀት አርስ ነበርና። አለን ሚዲያዎቼ እና እኔ እንደ አመረብን። ፈቃዱን ለሰጠኝ ለራዲዮ ፕሮግራሙ ቲም የተሰጠው አጥጋቢ ጥሁፍም በእጄ ላይ ይገኛል።

እግዚአብሄር ይመስገን የ21ኛው ምዕተ ዓመት ታላቅ ሥራ የሆነውን የደራሲ አቶ ምስብእክ ወርቁን „ዴርቶ ጋዳን“ ረቂቅ ወጥ ሥራ ጭብጥ ሳስብ፤ የቴዲን በጋሼ ጸጋዬ ዙሪያ የሰራቸውን ድንቅ ጽጌረዳዊ ተግባር በመንፈሴ ደም ሳዘዋውር፤ የመንፈስ ቋሚ ትውፊታችን በዕድሜ ተከታዮቼ እንዲህ ፋፍቶ ሳልሞት ቆሜ በህይወት በማዬቴ እግዜአብሄር ይመስገን። አሜን! የኔ ታናሾችን እግዚአብሄር ያኑልርኝ። ደሜ ቋንቋ ቢኖረው የሚናገረው ቋንቋ ጸጋዬ በሆነ ነበር – ተግባባን?! እኔ ጋሼ ጸጋዬን እማውቀው ኢትዮጵያዊ ሆኖ እናቱን – ሰንደቁ ሲያደርግ ነው። ክብራችንም ነው። ጉልህ የቋንቋ ሊቅም።

አሁን ወደ ተነሳሁበት ወጣቱ የተወቀሰበትን „ጥቁሩን ሰው“ ለእኔ የሰጠኝን ንጹህ ትርጉም ለሌሎች ወገኖቼ ለምን አልሰጣቸውም ብዬ አላዝንም። ውበት እንደ አካባቢው ስለሚተረጎም። እኔ በሚታዬኝ፣ ለእኔ በሚሰማኝ ውስጥ እነሱ ላይኖሩ ይቻላሉ – ለእኔ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ሥጦታ ነው። ለትውልዱ በጣምራ ገለጻ አንገት ነው። ባለዜማዎችን ለዘመኑ ሊመራ የሚችል ምልክትም ነው። ይህ ወጣት የከወናቸውን ተግባራት በማስተዋል ሆነን ስናነባቸው አሱም ሆኑ ሥራዎቹም አርማችን ናቸው። ባለመታደል ሆኖ እንጂ። ከዚህ ሌላ እኔ የወጣቶች አደራጅ ስለነበርኩኝ ስሜታቸው በጣም ቅርቤ ነው። „የልጅ ነገር አንዱ ፍሬ አንዱ ጥሬ ሆኖ“ ነው እንጂ በዚህ ዙሪያ መሬት ዬያዘ ሰፊ ጥናት ከወጣቶቹ ጋር ሰርተን ነበር። ከእጄ ቢኖር እንዴት ወርቅ በነበረ። በሌላ በኩልም ወጣትነት ሁላችን ያለፍንበትም ነው።
ለማንኛውም ወጣት አትሁን ማለትም የፈጣሪን ታላቅ ተፈጥሮዊ ዶግማ ሆነ ሥልጣን መጋፋት ይመስለኛል። በዚህ አፍላ ዘመን ስንት ቦታ ይደረሳል። ወጣትነት ሳተናነት ነው ….. በእኔ ስሜት ማዕቀፍ ውስጥ ያለው የነፃነት ትርጉም፤ የማንነቴ ጣዝማ በመሆኑ የውስጤ ፍጹም ገዢ ነው። ነፃነት ማንነት ላለው እኔነቴ አንጎሉም ነውና። ማናቸውም የገኃዱ ዓለምን የኑሮ ስንክሳሮች የማያቸው ሆነ የምመዝናቸው እኔን ከሰጠኝ ብሄራዊ ነፃነት በታች እንጂ በላይ ከቶም ሊሆን አይችልምና። ከዚህ አንጻር ቴዲ አፍሮ ለትውልዱ ጥበብ ነው። አጀንዳዎቹ ኢትዮጵያና ነፃነቷ ስለሆነ – የሥርጉተም።

ስለሆነም „የጥቁሩ ሰው“ ፊልም በሙዚቃ የተቀነባበረ ብቻ ሳይሆን እኔ ሳዬው፤ እውነትም ለመናገር፤ ፊልሙ በዛ ዘመን የተሰራ ነው የመሰለኝ። ማለት ትዕይንቱ ጦርነቱ እዬተካሄደ የተቀረጸ ዓይነት ነው። ጭብጡና የጭብጡ ማዕከላዊ ተልኮዎ በሥርዓተ ተክሊል በፍጹም ሁኔታ በተፈጥሯዊ አኃታዊነት የተጋቡ ናቸው። በጣም የተዋጣለት ታላቅ ተግባር ሆኖ ነው ያዬሁት። ከዚህ ባለፈ ድሉ ሙሴውን – የህዝብ ስለመሆኑም አባወራ ጀግኖቻችን በነቂስ አውጥቶ ነው የተቃኘው ስለሆነ ይህ ወጣት በቀደመው፤ በዛሬው ወይንስ በሚመጣው በዬትኛው ዘመን የተፈጠረ ነው በማለት በልቤ ውስጥ ባለችው ሙዳይ ወስጥ እጅግ መስጥሬ አስቀመጥኩት። መብቴ ነው። እኔ እንደዚህ ላሉ ወጣት ጀግኖቼ አብዝቼ እሳሳላቸዋለሁ፤ ሰብስቤ በማህጸኔ ውስጥ ባስቀምጣቸውም እወዳለሁ፤ ዓለም ቀናተኛ ስለሆነች እንዳትነጠቀኝ ስለምሰጋ

teddy afroየወጣቱን ንጥር ተግባር ብቁ ከሚያደርጉት መሰረታዊ ነገሮች ግጥሞቹ ጥልቅ መሆናቸው ነው። ትናንትን ከዛሬ፤ ዛሬን ከነገ በነብይነት ማያያዣ ፈጥሮ ያወራርሳቸዋል። ጥበብ ማለት ይህ ነው። ግጥምጥሞሽ ያልሆነ። እርግጥ ነው በግልብ ካዬናቸው ጊዜያዊ ደስታ ወይንም የማንደግፈው ከሆነም ጠብ አጫሪነ ስሜትን ቀስቅሶ ሊያበሳጨን ይችላል። አብሶ ከመልዕክቱና ሰብሉ ሊያለማ ከፈለገው ማዕከላዊ ማሳ ካልተነሳን እንደ መደዴ የቃላት ድርደር አድርገን ልንመከተው እንችላለን። የመልዕክቱ ውስጥ ንዑድ መንፈስ ነፃነት ነፃነት ነፃነት፤ ተፈሪነት ተፈሪነት፤ ገናናነት ገናናነት፤ ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያዊነት – አፍሪካዊነት ነው – የዓለም አብነት ኢትዮጵያ! ይህ ነው ውስጣችነን የወያኔ ሸፍጥ ካላሸፈተው …..
እያንዳንዱን ስንኝ በተን አድርገን በቁሙ ሳናነብ ውስጡን በቅንነትና በአዎንታዊነት ስንፈትሸው ቃሎችን ከስንኙ ሐረግ ነጥለን በመልካቸው ስናይ ደግሞ ቀለማችን አጉልቶ፤ እኛነታችን አብርቶ፤ ፍቅርን እንደ ታቦት ከብክቦ፤ ሩቅ ተጉዞ ሰላምን በናፍቆት ይጠራና ውስጣችን አስተቃቅፎ፤ ነገን በተስፋ ቀይሶ ይመከረናል፤ ያስተምረናል። ይፈትሸናል። ፍላጎታችን ኮትኩቶ የአቅጣጫውን ቅዬሳ ናሙና ከመንፈሳችን ሰርበዬር ውስጥ በሳቢነት ይቀርጸዋል። …..

እንዲሁም „ጥቁሩ ሰው“ በሀገራችን የነበረውን፤ አሁን ያለውን የሥነ ጥብብ እድገት ሥልጣኔም ቁልጭ አድርጎ ያሳዬናል። „ይህ የትውልድ ክፍተት አለበት፤ ወጥ ሥራዎች ተራቆቱ፤ የቀደሙት የሙዚቃ ስንኞች ቃናቸው ከዕውነተኛው ወይንም ከጋህዱ ዓለም ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ነበሩ። መሬት ያያዙ ነበሩ፤ ስለሆነም ወስጥን የመግዛት አቅም – ኃይልና – ስበት ነበራቸው። የዛሬዎቹ ግን ቤታቸው እንኳን አይመታም፤ ሥር አልሰደዱም“ … ወዘተ
… ለሚሉት ዕውነት ለመናገር የአርቲስት ቴዲ አፍሮ የመንፈስ ምርት ጥያቄያቸውን ሁሉ በአግባቡ የመለሰ ይመስለኛል። ደግሜም እላለሁ … እኔ አሁን ለተፈጠሩት ወጣቶች እጅግ ታላቅ አክብሮትና አድናቆት አለኝ። በስለው ነው የተወለዱት ማለት እችላለሁ። መድረክ ሲያገኙ የማዬው ብቃት ከቶውንም ሊለካ የማይችል የመንፈስ ሐሴት ይሰጠኛል። ለዛውም በዚህ ሙጃ ሥርዓት፤ በዘመነ ወያኔ ተወልደውና አድገው … ሞት ያልተዋጀበት አንድም የኢትዮጵያዊነት የመንፈስ ተቋም በሌለበት …. ይህን ጥሰው የወጡ የዘመኑ ጥቁር አንበሶች ናቸው – ለእኔ።

ንጽጽር፤
የብዙ ታዋቂ ዓለምዓቀፍ ባንዶችን ኮነሰርትን አብዝቼ እከታተላለሁ። የወጣቱ የፈጠራ ብቃት እኔ ነኝ ካለ ባንድ ጋር ሊመጥን የሚችል በቂ አቅም እንዳለው ነው ያዬሁበት። የቴዴ ሥራዎች መነሻ እሩቅ አይደለሙ። ከእናቱ ጓዳ፤ ከተጨባጩ ጭብጥ ስለሆነ፤ ስሜትን የመሳብ ችሎታው ብቻ ሳይሆን ስሜትን ተቆጣጥሮ የማቆዬት ጉልበቱም አንቱ ነው። ሁሉን ነገር፣ ሁሉን አካባቢ በቅኑና በትሁት መንፈስ ይዳስሳል። አንዱ የግጥም ዜማ በራሱ አንድ መጸሐፍ ይወጣዋል። ይህ ለኢትዮጵያ የሥነ – ግጥም ሆነ ሙዚቃ ነገ አዲስ አቅጣጫ ነው። ለማግሥትም ብቁ እርሾ!

ሌላው ቅኝቱ ራሱ መሰራቱ፤ ፍሬዘሩ ከውስጡ መፍለቁ፤ ከዚህም በላፈ የስንኙን ፍሰት ሳይጎዳ እንደ ራሱ ውስጠት አድርጎ፤ ጤናቸውን ጠብቆ፣ ሴላቸው ሆነ ደም ሥራቸው ሳይጎዳ፤ ኦርጋናቸው ሳይነደል እንደ ተፍጥሯቸው ስለሚቀርበው ይህ ደግሞ የወጣቱ ልዩ መለያ ጸጋው ነው። /ጀርመኖች አውስጌቦልሼ ታለንት/ ከሰው ዘር የተለዬ መክሊት እንደ ማለት። በዬሙያው እንዲህ ያሉ ሁለት አንጎል ያላቸው ይፈጠራሉና። በዚህ ዘመን ኢትዮጵያዊነት በጠላትነት ተፈርጆ፤ በፖሊሲ ደረጃ ወያኔ ተግቶ እዬሰራ፤ በዘመኑ ተፍጠሮ ግን፤ የወያኔን ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ ፖሊሲ የቀደመ፤ የበለጠ ሥራ ነው። አንድ የፖለቲካ ድርጅት ረጅም ዓመት ከደከመበት የቴዲ ስንኞች የበለጠ ያፈሩና አርበኞች ናቸው። ለኢትዮጵያዊነትም ዘብ አደርም ናቸው። ሥነ ጥበብ ወተቱ የአድማጭ የሰላ እርምት ነውና ወጣቱ እርማቶችን በጸጋ ተቀብሎ ማስተናገድ ከቻለ አንድ ትውልድ የመፍጠር አቅሙ አንቱ እንደሚሆንም አልጠራጠርም።

የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ያን የመሰሉ ሥራዎቹን፤ ትውልድ የማይተካው ያ …. ዕንቁው ጋሼ ወጋዬሁ እሸቱ ነበር የሚተውንለት – የሚያነብለት። መዳህኒተዓለም አባታችን ንጉሥ ዳዊትን „እንደ ልቤ“ አለው ለጋሼ ጸጋዬም እንደ ልቤ ነበረው ጋሼ ወጋዬሁ። ዕድለኛ ነበር። እንደ ውስጡ ሆኖ፣ ከውስጡ የተቀመጠ ለእሱ ጸጋ ብሎ አምላኩ የመረቀለት ጋሼ ወጋዬሁ ነበር። ትውናው እንደ እራሱ ውስጥ አድርጎም ያቀርብለት ነበር። የጋሼ ጸጋዬ ስሜቱ መንትዮሽ በአህትዮሽ እንደ ነበር ይሰማኛል። መቼም እንዲህ ዓይነት አጋጣሚ በሺ ዘመናት አንድ ጊዜ ወይንም ሁለት ጊዜ ነው የሚከሰተው። ከዚህ አንፃር ውስጡን ከእነተፈጥሮው ማቅረብ መቻሉ ለቴዴ ዕድለኛነቱን ድርብ ያደርገዋል። በስሜቱ የፍልጎት ልብ ውስጥ እሱ እራሱ በመንፈስም በአካልም አለና። ተቀድቶ የማያልቀው ውበቱም ይህ ነው። ወጣቱ ከያኒ የጻፈውን እራሱ ያቀርበዋል …. እራሱ አቀናብሮ እራሱ ያስጌጠዋል። አደራጅቶ፤ ውስጡን የሚገልጽለት ሌላ ሰው ቢያስፈልገው ኖሮ ከባድ ነበር። ግን እድሉና ምርቃቱ ወፍ አወጣቸው። ስለሆነም ተ — ጠ – በ – በ – በ – ት።

የሰማይ የላቀ ስጦታ!

እኔ የእግር ኳስ ፍቅረኛ ነኝ። እጅግ በጣም እግር ኳስን እወዳለሁ። አሁን ዬይድነቃቸው ልጆች ለእፍሪካ ዋንጫ በ2013 እ.ኤአ. ሲታደሙ ሰፊ የሆነ አትኩሮት ነበረኝ። ኢሮ ስፖርት ሀገራችን እንዴት ከፍ እዬደረገ ሲገልጸው እንደ ነበረ ማመን እስኪያቅት ድረስ እጅግ እጅግ ድንቅ ነበር። ያን ጊዜ አጋጣሚው ረድቶ ሀገሬ ኢትዮጵያ ከፍ አለች። ታሪኳ፤ የህዝቧ ባህል፤ ወግ ልምዷ፤ የነፃነት ገድሏ ሁሉ ተዘከረ። ኢትዮጵያን የኢሮ ስፖርት ፕሮግራም አቅራቢዎች ሆኑ አዘጋጆች ውስጣችን አሳምረው ነበር ኪናዊ አድርጎ ያነበቡን – ቀለማም አድርገው ነበር የኳሉን። ለእኔ ፈውስ ነበር። ዳንኩኝ!
መቼም ትውልዱ አዲሱ ማለቴ ነው በብዙ ፈታና ውስጥ ሆኖ፤ ግን ድንቅ ነገር ያሳዬናልና ከዓለም ዋንጫ ዝርዝር ውስጥ ዬኛዎቹ ሲገቡ ደስታዬ ወደር አልበረው። ታዲያ የመጨረሻ ማጣሪያው ከናይጀሪያ ጋር ሲሆን ግን አልተመቸኝም ነበር። አሳምሬ ናይጀሪያዎችን አውቃቸዋለሁና። የሆነ ሆኖ የኔዎቹ ማጣሪያ ሳያልፉ ሲቀሩ ዕንባ አውጥቼ ነበር ያለቀስኩት። የእውነት። እናት ሀገሬ፣ የመንፈስ ተክሊሌ፤ እምዬ ኢትዮጵያ – እንጀራዬ የመላ ዓለምን የእግር ኳስ ጨዋታን አለመገኘቷ አስከፋኝ። ልክ እንደ መጻፍ፤ መጸሐፍ ማንበብ ድንቡልቡሏንም ስለምወድ ብራዚል ላይ እመቤት ኢትዮጵያ ስትደምቅ ናፈቆኝ ግን ሳይሆን ሲቀር በጣም ተጎዳሁ። የኢትዮጵያ ጎል ጠበቂ ገና አልተወለደምና።

እግዚአብሄር ይመስገን … ሁልጊዜም የማምናበት ነገር፤ ኢትዮጵያ አምላክ አላትና ዕንቡጡ ቅኔ አህጉርን ወክሎ በ2014 የዓለም ዋንጫ ብራዚል ላይ መገኘት በራሱ ክብር ነው። የሰማይ የላቀ ሥጦታ ነው። ልዩ ምርቃት ነው። የሥነ ጥበብ ቤተኛ ታዳሚዎች ሁሉ ልንደሰትብት የሚገባው መሪ ድል ነው። ቅኔኛው ቴዲ አፍሮ እንደ አባቶቹ እንደነ የቅኔው ልዑል ብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህን መንገድ ተከትሎ፤ የአፍሪካ ነገር መስመሩ ነበርና፤ ፈልጎ የተነሳለት ድንቅ ራዕይ ከሀገሩ አልፎ አህጉሩንም ሊወክል ነው። እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነው እንሆ አደረገለትም። ጉዞው አቅጣጫው እጅግ አጓጊ ነው።

ፅኑ ዕይታ!

እናት ሀገር ኢትዮጵያ ስትከብር፣ ስትደምቅ፤ ከፍ ስትል፣ ዜግነት ሲያበራ፣ እንደ ትናንቱ ኢትዮጵያ አፍሪካን በሥነ ጥበብ ጎራ ዳግም ልትመራ ስትመረጥ፤ ለመልካም ነገር ስትታጭ፤ ልዩ ፍጹም ልዩ ትርጉም ነው – ዕጹብ ድንቅ። ፍካታዊ ገጸ በረከት ነው። አበባዊ ረድኤት ነው። ለዚህ ተግባር ስኬታማነት እንደ ሰው የተገባን እናድርግ እንጂ፤ ትዕዛዙ ከመዳህኒተዓለም አባቴ ስለሆነ ሳንኩን ሁሉ አሸንፎ ሚሊዮን ፈን ያፈራል። አብሶ ጀርመኖች የሥነ – ጥበብ አክባሪና አፍቃሪ በመሆናቸው ለሽልማት ያጩታል። ጠብቁ። ቴዲን የቆዬ ሰው ይዬው። አፍሪካዊ ቪቫ ይሆናል። ዕውቅናውን አሳምረው ይሰጡታል። ሰፊ የሆነ በር ተክፍቶለታል። በሰውኛ ሥልጣን በሩን መዝጋት አይቻልም። „ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል“ ይላል ጎንደሬ ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነውና!
ጀርመን በሥነ ጥበብ ጉዳይ 13ኛው ፕላኔት ነው – ለእኔ። ፍጹም የተለዩ ናቸው። በደንበር – በክልልል – በቀለም በምንም ነገር አይደለም የጥበብን ልዩ ጸጋ የሚለኩት፤ በመንፈስ ቅዱስ ንዑድ ስሜት እንጂ። የሰማይ ጸጋን ለመተርጎም ሆነ ለማመሳጠር ተስጥቷቸዋል። ይህ ቀን እኔ ስመኘው ነበር። አንድ ዝግጅት ለጀርመን ህዝብ ቢኖረው በማለት። የለመኑትን የማይነሳ አምላክ ከጀርመን አልፎ ዓለም ሊታደምበት እንሆ ፈጣሪ አምላክ ወሰነ። ተመስገን!
እኔ በግሌ በፈጣሪዬ ስለማምን፤ ደግሞም የሥነ ጥብብ ሰውነት ሥጦታው የሰማይ ስለሆነ ጥበቃው ሰማያዊ ነው። በድንግልና ውስጡን ሆኖ ስለሚጫወተው ሥነ ጥበብን ያምርበታልና ሰጪው አጥር ቅጥር ይሆንለታል።

አዎን! ቀኑ እስኪደርስ ድረስ በጥንቃቄ፣ በፆም በጸሎት፣ ከብዙ ነገር ታቅቦ፣ ለዚህ ማዕረግ ካበቃው ከአምላኩ ጋር ቴዴ መሆን እንዳለበት እንደ ታላቅ እህታዊ አስተያየቴን አካፍለዋለሁ፤ ህይወቱ ያላችሁ ደግሞ እንደ ዕምነታችሁ በጸሎት ትደግፉት፣ ትረዱት ዘንድ በትሁት መንፈስ እጠይቃችኋለሁ። ከፀሎት በላይ ጠበቂ የለምና። ከጸሎት በላይ ዘበኛ የለምና። ምክንያቱም ያቺ መከራዋና ፍዳዋ የጠናባት ልዕልት ኢትዮጵያ፣ ልጆቿን አብልታ ማሳደር ያቃታት እናት ሀገር፤ ሚሊዮን የነገ ፍሬዎች ጉርሻ አጥተው በጠኔ የሚረግፉባት አምላኳ አረሳትምና እንሆ ከፍ ሊያደርጋት ማቀዱ ዬምልዓት ዕንባ ካሳ ነው። ለአምላካችንም ለቅዱስ እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገውን ምስጋናችን ሳናቋርጥ እንግለጽለት። በዚህ ዘመን አንድ ታዊቂ፤ ተደማጭ ለዛውም ወጣት ማፍራት ነገን ያበራልና።
የአይቮሪው ዓለምዓቀፍ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫወች ዝሆኑ ድሮግባን፤ የዩክራይን ሁለት ወንድማማቹች የጀርመን ዓለም ዓቀፍ ቦክሰኞች ወስጥ ታናሹ ለዩክሬን ፍትኃዊ አስተዳደር ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሲገኝ የዓለም ሚዲያ እንዴት ያረብርባል መሰላችሁ፤ የኛ ግን ትዕቢተኛው የሳውዲ መንግሥት የታላቅ ሀገርን ክብር ጠቅጥቆ ልጇቿን እንደ እንሰሳ አስፓልት ላይ እንደዛ ሲያርድ አንድ ለዕንባችን ዕውቅና የሚያሰጥ ታዋቂ፤ ተደማጭ፤ ዓለም ጆሮውን የሰጠው ዋቢ አልነበረንም። ነገ ግን ይኖረናል ….. ለዚህ ፈታናውን ተጋርቶ መረባረብ የግንባር ተልዕኳችን ነው። ጦርነቱ ተክፍቷል በድል ማጠናቀቅ አለብን! ማቄን ጨርቄን የለም! ለተደራጀ መሬት ለያዘ ተግባር እያንዳንዳችን በግል ሁላችንም በጋራ እንትጋ! ኢትዮጵያ ናት ፊት ለፊት ቁማ እሳት ውስጥ እዬተርመጠመጠች ያለችው። በኪነጥበቡ ይህ ዕውቅና ሲመጣ ደግሞ ግንባር መሆን!

በተረፈ ትምክህት ጎርፍ ነው፤ አድማም ጤዛ ነው። በሥነ ጥበብ ላይ ተደራጅቶ ጦርነት መክፈትም ወስጥን መፋቅ ነው። ፍቅር ግን የጸደቀ ፍሬ ነው። ኢትዮጵያዊነት የሚያሳፍር ሳይሆን የሚያኮራ፣ ተለምኖም የማይገኝ ምርጥ ዘርነት ነው። ውስጣችን የነጠረ ወርቅ ነው። ድህነታችን፣ የህዝብ መበደል፣ መንገላታት ደግሞ የሥርዓታት እንጂ እናት አንዱን ልጅ የክት ሌላውን የዘወትር፤ አንዱን አብልታ ሌላውን አስርባ በፍጹም አታውቅም። የወተት ጡት ጋቶቻ ለሁላችንም እኩል ማጥባትን አዘውትረው ይሻሉ …. ህግጋቶቿ ናቸውና። እቅፏም ለሁላችን ሳይዛነፍ በእኩልንት ነው። ማዕዷም እኩል ለሁላችንም ነው። ስለሆነም በእናት ሀገራችን ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሁሉ መቆስቆሻ ሳንፈልግ ሁላችንም እኩል መማገድ በእጅጉ ያስፈለገናል። ፈተና መጥቷል – ማለፍን ይጠይቃል_! እናት ኢትዮጵያ የበደለችው አንድም ሰው የለም!

ክወና! …

ኢትዮጵያን የፈጠራት አምላኳ ምንጊዜም ስለማይረሳት እሷን ለማጠቃት የተነሱት ሁሉ የዶግ አመድ ይሆናሉ። በእኛ እድሜ እንኳን ሱማሌ፤ ኤርትራ፤ ግብጽ፤ አሁን ደግሞ ሱዳን ይታመሳሉ። አምላኳ ቀናተኛ ነውና። በ2012 እ.ኣ.አ. የአሳ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ እጬጌውን ከመንበራቸው፤ የጎጥ አፄውንም ደግሞ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ለኑዛዜ ሳያበቃ ነበር ያነሳቸው። ይህ ምርታማ መሬት፤ ለምለም አካባቢ፤ ሃብታምነት የሚባለውም ቢሆን አባታችን ከተከፋ ትል ከሰማይ ሊያዘንብበት ይችላል። እናስተዋል! —- ጉዳቱ ደግሞ የጋራ ነው እንደ ሰው ለምናስበው – ለእኛ።
እንኳንስ በተፈጥሮ ኤኪኖሚዋ ጥገኛ ለሆነ፤ ያልጠመጣጠነ ኤኮኖሚዊ ዕድገት ለሚገርፋት ኢትዮጵያ ቀርቶ የሰማይን ቁጣ እንጃፓን፣ ሱናሜም ማስቆም አልቻሉም። ይልቅ እንደ ሰው አስበን በዛ ቦታ ማን ይኖራል? ህፃናትን፣ አቅመ -ደካሞችን፤ ህሙማን፤ ነፍሰጡር ሴቶችን፤ እንሳሰት ሳይቀሩ ሊታስብላቸው ይገባል። ቀይ ቀበሮ እኔን ይገልጸኛል። ሶፍ ኡመር ዋሻ እኔን ያብራራኛል። ልዩ የሚባሉ አብዛኞቹ ሌላ ዓለም የማይገኙ አዕዋፋት ኢትዮጵያ ብቻ ነው የሚገኙት፤ ሁሉንም የሰማዩ ቁጣ ውስጣችን አብሮ እንዳያጭደው አደብ ገዝተን ወደ ፈጣሪያችን እንመለስ!
… ለሰው አይደለም። ወደ ፈጣሪያችን ቀልባችን መልሰን እራሳችን አዋርደን፤ ይቅርታ አምላካችን እንጠይቅ …. ኢትዮጵያ ሶስት አፄዎቿ ዓለም በቃኝ ብለው ገዳምን የመረጡ ንዑዳን የፈጠረች ቅድስት ሀገር ናት። ዘጠኙ ቅዱሳን ከተፈጠሩባት ሀገር አስበልጠው የመረጧት ሀገር ናት። ነብዩም ለጆቻቸው የተመኩባት ተምሳሌት ሀገር ናት።

የማከብራችሁ ወገኖቼ …. እጅግም የምናፍቃችሁ ደሞቼ … መንጠራራት መልካም ባይሆንም፤ ሰው ባላው ነገር ወይንም በቀጣይ ፍላጎቶቹ ዙሪያ አብዝቶ ሊንጠራራ ወይንም ሊመካ ይችላል። በተማመነበት ጉዳይ። በክርስቶ ወይንም በአላህ ሥልጣን መንጣራራት ግን ዕጣው ትውልድን ያሳርራል – ያርሳልም። ቅጣቱን የሚያቆም ምድራዊ ኃይልም አይኖርም፤ አባ ጳውሎስን አተረፈ ተዋህዶ? ወይንስ ቲፒ.ኤል.ኤፍ ሄሮድስ መለስን ታደገ? ገዳማት ታረሱ …. ቁጣውም ነደደ!
ፍቅር ተንበርክኮ እንሆ ይለምናል። አሁንም ህዝባችን በፍቅር ይጋባል፣ ይዋለዳል፣ አብልጅነት ይናሳል፣ ይጎራበታል፣ ጡት ይጣባል፤ ጓደኝነት ይገጥማል፣ ማህበሩን ዝክሩን አብሮ ይጠጣል፤ ሀዘን ተፍሰኃውን ፈቅዶና ደስ ብሎት ይጋራል፤ ይረዳዳል፤ ይህን የደም ግንኙት መበጠስ አይቻልም … ሰውኛ አይደለምና ….. በቁጭት ምክንያት ምላሽ ለመስጠት ፍላታችን ለማስታጋስ ስንል በምንሰነዝራቸው ቃሎች ከእልህና ከግብታዊነት ጸድተን እንስከን። ማስተማር የሚቻለው የሚወረወረውን ናዳ መልሶ በመልቀቅ ሳይሆን፤ ጨዋነታችን በለገሰን አርምሞ፤ በተደሞ፤ በትግሥትና በሆደ ሰፊነት ወያኔ ያዘጋጀውን ሴራ ማክሸፍ ስንችል ብቻ ይሆናል ብጡልነት። የዚህ ሁሉ ትርምስ ተዋናዩ ወያኔ ነው። ይህ አውሬ ያዘጋጀው መርዝ ወገኖቻችን አልተረዱትም። ዕውነተኛውን ነገር ወስጣችን ፈቅዶ ይቀበል ዘንድ እግዚአብሄር ይርዳን። ትጉኃን ቀጥሉ የሃቅ ምስክር መረጃዎችን በሚዛን ቀልቡን። አትናቁ ወይንም አቅልላችሁ አትዩትት። የተደራጀ ፈተና ነው። ፈተናው የሚረታው ደግሞ በበለጠ በተደራጀ ሥልጡንና ብልህ ተግባር ብቻ ነው።
ቀኑ እዬናፈቀኝ – የሰንደቄ ዜማ …
ህብር ስንኞችህ ማንነት ሊያለማ።
አፍሪካዊነቴ ሊደምቅም – ሊያበራ
በፈጠራ ዓውራ! ….
ዛሬ ለትናንቱ፤ ትናንትም ለነገ – አድዮ አጎመራ፤
ሉሲ ከፍ ትላላች በመንፈስ – በማማ
በፍውሰትህ – ጣዝማ …..።
እናት ታጌጣለች ….. በሞገስህ ግርማ፤
ታሪክ ይዘከራል – በወጣቱ ዓርማ!
ዓለም ይታደማል በመረዋ እማማ!
ህበረ – ቀለማቱ፤ — የቁንጅና ዋና!
አማንህ – ሊያዘመር ….
እሙ – ልትቀምር
የታጠቀ ዕውነት ብቃት ሊመሰክር፤
ያ …. የደግ ታሪክ ገር፤ መቅድምን ሊመራ
የዘማናት ሂደት …. ትውፊት ሊያነባብር
ዋዜማን – ሊያዘመር …. ብቃት አጎመራ!

ማሰሰቢያ።
• ግጥሞቹ 13.01.2014 00.17 (እ.ኤ.አ) ተጻፉ።
• ጎልተው የተጻፉት ፊደላት ጠብቀው እንዲነበቡ የሻትኳቸው ናቸው።
• የግጥሞቹ – ዕርእሶቹ ጎልተው የተጻፉት የተሰመረባቸው ቃሎች ናቸው። ነፃነት ታወጀላቸው ከፈለጉት ቦታ ላይ ሆኑ፤
• ፎቶው ከቴዲ አፍሮ የግል ድህረ ገጹ የተወሰደ ነው።
መፍቻ።
ዋና ሁለቱንም ትርጉም ይዞ ነው የታደመው። ለሁለተኛው ግጥሜ እርእስም ነው።
• ላልቶ ሲነበብ አብይ፣ ኣናት፣ አለቃ፣ መሪ፤ አስተዳደሪ፤ ሰብሳቢ፤ አዛዥ፤ ሙሴ፣ እረኛ፣ ተጠሪ፣ እርእሰ ጉዳይ እንደ ማለት … ሁሎችም እንደ አረፍተ- ነገሩ ፍሰት ይተረጉሙታል። ለእኔ ግጥም ሙሴ የሚለው ግጥሙ ነው።
• ሁለተኛው ጠብቆ ሲነበብ ደግሞ የአሳን ተፈጥሮዊ የኑሮ ልማድን የሚከተል ይሆናል። … የሰው ልጅ በእህልና በመጠጥ ብቻ አይኖርም። ህሊናው መስኖ ይፈልጋል። መስኖው ደግሞ ሥነ ጥበብ ነው። ሥነ ጥበብ ጥሩ ዋናተኛ ነው። ዋናው በውጭ ሳይሆን ውስጥን የሚቀድስ የሚፈውስ፤ የሚጠግን፤ የሚያጽናና፤ የሚያጸና፤ የውበት ውበት፤ የጌጥ ጌጥ ነው። ልዩነት በአንድነት አንድነት በልዩነት አኃቲነት በመፈቃቀድ የሚያበቅል – የሚያጸድቅም ነው … በዚህ ሂደት ህልም ህልም ነው ነገሩ የሚመስለው የዓለም ብቸኛ ፍቅረኛ በሆነው የእግር ኳስ ትንሳኤ የኢትዮጵያ ሥነ – ጥበብ በበትሩ አሳላፊ በውስጥነት ሊዋኝ ነው …. ያ … የዓለም ሚዲያ ሰልፉ፤ ያ … የዓለም ዕውቅ ሰዎች ታዳሚነት ውስተት እኛነት መስፍን ሆኖ ሊሰነቅ፤ እሰቡት ….. ውህድነት። በአንድ ለጋ ሊጋባ …. ይህ የምልዓት መንፈስ በሐሤት ኢትዮጵያን በዕዝነ – ህሊናን ሲዳስሳት … የቅዝፈቱን ቅኔ ዘጉባኤን የዳጎሰ ድምር ነው ዋና ያልኩት ….
• ጣዝማ …. ከተለመደው ውጪ የሚገኝ የተፈጥሮ የማይረጋ ማር። ለጤና እጅግ መዳህኒት የሆነ። አብዛኛውን ጊዜ የሚገኘው በቆላማ የሀገራችን ቦታዎች ነው። ቀለሙም ትንሽ ደመቅ ያለ ነው።
• አድዮ ማንም ሀገር ብሄራዊ አበባ የለውም። ኢትዮጵያ ግን አላት። መንገድ ጠራጊዋ የተስፋ አበባ አድዮ የአዲስ ዓመት ዋዜማ! የሰንደቅዓላማችን ማዕከላዊ ቀለም ከዚህ ተፈጥሮ ጋር የተሳሰረ ይመስለኛል – በኪዳን። በ5ኛው መጸሐፌ ላይ „በፊደል“ የልጆች የግጥም መድብል የተሰራበት ነው፤ እንደዚህ ለዬት ያሉ ተፈጥሯችነን ከፊደል ላይ ዘርዘር አድርጌ ጽፌዋለሁ። በነገራችን ላይ የፊደል የፊት ሽፋን ከዓለም የሚለዬን፤ እንደ ውስጣችን የተፈጠረው ድንቁ የፊደል ገበታችን ሲሆን ከሌሎቹ መጸሐፍቶቼ በበለጠ በነጮች ተወዳጅም የሆነው እሱ ነው። ይወዱታል … በጣም። ቋንቋው አማርኛ ግን ተማረኩለት … ሌላ ቀን በዚህ ዙሪያ እመጣላሁ … አሁን ደግሞ የአፈሙዙ አቅጣጫ በእሱ ዙሪያ ስለሆነ ….
መንፈሶቼ – ታዳሚዎቼ! የፍቅር ማዕድ በመከባባር አብሮ አቆዬን ፤ለተሰጠኝ በቂ ጊዜ ምስጋናዬን በቅኑ ውስጠት – እንሆ!
ፈጣሪ አምላካችን የተበተነን ልቦናን ስበስቦ፤ እናታችን ከፍ ትል ዘንድ የጀመረውን ይጨርስ።
ልብ ይስጠን – ለሁላችን! የምንችለበትም ጽናትም! አሜን

ጨረስኩ — ንጹህ አዬርም አገኘሁ – ዱላውን የምችልበት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የአንድነት ተልእኮና የፋሲል የኔአለም ጫፍ የቆመ እይታ

$
0
0

ዳንኤል ተፈራ

Daniel-Tefera አንድነት ፓርቲ በተሳካ ሁኔታ ጠቅላላ ጉባኤውን ፈጽሞ በበርካታ ወጣቶች የተገነባውን ካቢኔ ይፋ ካደረገ በኋላ ጥቂት ሳምንታት አለፉ፡፡ በነዚህ ጥቂት ሳምንታትም ትግሉን በማያዳግም ሁኔታ የህዝብ አድርጎ የሚፈለገውን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን ለማድረግ ቀን ከሌሊት መስራት ይገባል የሚል እቅድ አንግቦ ደፋ ቀና በማለት ላይ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለን ግን የግል አስተያየት በማለት የኢሳቱ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም “የአንድነት ፓርቲ የመጭው ጊዜ ፈተና›› በሚል የፃፈውን ያልታሰበበት ጽሁፍ አነበብኩ፡፡

በቅድሚያ ጽሁፉን አንብቤ ሳበቃ ለምን መልስ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ እንዳገኘሁት መግለጽ ይገባኛል፡፡ ፋሲል ማስተላለፍ የፈለገው ‹‹አንድ ጫፍ ብቻ›› የረገጠ መልእክት የተዛነፉ ሃሳቦች የተላለፈበት፣ ከግለሰብ ጥላቻ በመነሳት ፓርቲውን ፈተና ውስጥ ያለ በማስመሰልና ዋጋ እየከፈሉ ያሉትን ውድ አባሎቻችንን በግብአትነት በመጠቀም ክፍፍል ለመፍጠር የፈለገ በመሆኑ ነው፡፡ ወይም ፀሀፊው ‹‹ሁለት የከረሩ ጫፎች ብቻ ያስፈልጋሉ›› ከሚል አይነት አመለካከት ላይ ቆሞ ከመፃፍ የመነጨ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያቴ በአምባገነኑ ስርዓት ተጠፍንገው ከተያዙ የብሮድካስት ሚዲያዎች ውጭ አማራጭ አልባ ለሆነው ህዝብ በአማራጭነት ለቀረበው ኢሳት ካለኝ አክብሮት ነው፡፡ ምክንያቱም ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም የኢሳት ባልደረባ እና ኃላፊነት ያለበት ሰው በመሆኑ፡፡

ፋሲል በጠቅላላ ጉባኤው በከፍተኛ ድምጽ የአንድነት ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው የተመረጡት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ቃለ-ምልልስ ካደረጉት ውስጥ ‹‹ከኢህአዴግ ጋር ገንቢ ግንኙነት (Contractive engagement) እንዲኖረን እንፈልጋለን. . .›› የሚለው ለሱ ሃሳብ የሚመቸውን ቆንጥሮ በማውጣት ከልደቱ አያሌው ‹‹ሦስተኛ መንገድ›› ካለው ወይም ‹‹ መሀል ላይ መቆም›› ብሎ ከተረጎመው ሃሳብ ጋር ለማያያዝ ሞክሯል፡፡ ስህተቱ እዚህ ላይ ይጀምራል፡፡ አንድነት ሊበራል አስተሳሰብ የሚያራምድ በመሆኑ የግለሰቦች መብት በቅድሚያ መረጋገጥ አለበት ብሎ ያምናል፤ በስትራቴጂው እንዳስቀመጠውም የኢህአዴግ አይነት ብሔር (የቡድን) መብትን ማክረር ወይም የዚህ ተቃራኒ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ላይ ብቻ ቆሞ ሌሎችን አለማዳመጥ ዴሞክራሲያዊ አይደለም ይላል፡፡ ሁሉም ባልተሸራረፈ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ያለምንም ጣልቃ ገብነት የመደራጀት መብታቸው መከበር አለት፡፡ ስለዚህ ጥያቄው ጫፍ የመቆም ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመፍጠር ነው፡፡
UDJ
ስለዚህ አንድነት እንደ ሊበራል ፓርቲ ከገዢው ፓርቲ ጋር መደራደር ይገባል፡፡ መደራደር፣ ሰጥቶ መቀበል እንደነውር መታየት የለበትም ብሎ አስቀምጧል፡፡ ኢ/ር ግዛቸውም በቃለ ምልልሱ ያስቀመጡት ይህንን ነው፡፡ መደራደር የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዱ ሥራ ነው፡፡ መደራደር ዘመናዊ አስተሳሰብም ነው፡፡ አሁንም እየታገልን ያለው ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ እንፍታ፣ ሆደ ሰፊ እንሁን፣ ጠርዝ ከያዘና ከፍረጃ ፖለቲካ እንላቀቅ በማለት ነው፡፡ አቶ ፋሲል ‹‹መሀል ላይ መቆም›› ያለው እንደዚህ አይነቱን ሃሳብ ነው፡፡ እንጅ ራሱ ፀሀፊው አንድነትም ሆነ አመራሩ ተንበርክኮ እንዳልሆነ፣ እንደ አንድነት ዋጋ የከፈለና እየከፈለ ያለ ፓርቲ እንደሌለ የሚያውቅ ይመስለኛል፡፡

ጠርዝ ላይ የቆመ ሃሳብ አለማራመድ ወላዋይ አያሰኝም፡፡ አንድነት መሀል መንገድ የሚለው የብሔረሰብ አክራሪነትም ሆነ የህብረ ብሔር አክራሪነት አይጠይቅምም ከሚል ነው፡፡ ሁለቱን የሚያቀራርብ የመሀል መንገድ መኖር አለበት እንደማለት፡፡ እንደዚህ ማሰብም ጤናማ ነው፡፡ መብትም ነው፡፡ ሁላችንም ሃሳብ የምናቀርበው ለሀገር ይጠቅማል የምንለውን ነው፡፡ አሸናፊው ሃሳብም በህዝብ ዘንድ ቅቡል ይሆናል፡፡

ጋዜጠኛ ፋሲል ግን ለኢ/ር ግዛቸው ካለው የግል ጥላቻ ይመስለኛል ጥቂት ነገር ቆንጥሮ ‹‹ፍርሃት ነው›› ለማለት ይሞክራል፡፡ በውጭ ሀገር እየኖሩ መታገል፣ ትግሉን መደገፍ እንደሚችል አምናለሁ፡፡ ለፋሲል ግን አንድ ጥያቄ መጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡ የሚፈራ ሰው መቀመጫው የት ነው? እንደሚመስለኝ ወይ የኢኮኖሚ ጥያቄ ካልሆነ በስተቀር ፀሀፊው ከሀገር የወጣው ሀገሩን ስለሚጠላ ሳይሆን ሥርዓቱን ስለፈራ ነው፡፡ ሥርዓቱን ፈርቶ በተሰደደ ሰውና ከሥርዓቱ ጋር ፊት ለፊት ግብግብ እየፈጠረ ያለ ሰው መካከል ትልቅ የሞራል ልዩነት አለ፡፡ ስለዚህ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ፍርሃትን የተረጎመበት መንገድ ድንጋዩ ተመልሶ ወደ እርሱ እንዲያርፍ የሚያደርግ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ከሀገር ወጥቶ ትግሉን መደገፍ ትክክል ቢሆንም ፖለቲካውን ለመምራት መሞከርም ሌላ ትልቅ ስህተት ይሆናል፡፡ እንዲህ ሲባል እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት የአቅማችንን እያደረግን ያለን ሰዎች መተቸት የለብንም ብዬ አላምንም፡፡ በመሳደበና በመተቸት መካከል ግን ትልቅ ልዩነት እንዳለ ሊሰመርበት ይገባል፡፡
ሌላው ማንሳት የምፈልገው ጋዜጠኛ ፋሲል የአንዱዓለምንና ናትናኤልን ስም በመጥቀስ ጫፍ ላይ የቆመ ሃሳብ የሚያራምዱ አድርጎ መግለፁም ስህተት ነው፡፡ አንዱዓለምም ሆነ ናትናኤል ፋሲል የጠቀሰውን አይነት ሃሳብ የሚያራምዱ አይደሉም፡፡ ሆነውም አያውቁም፡፡ በተለይም የአንዱዓለምን ሃሳብ ለመረዳት መጽሀፉን ማንበብ ተገቢ ነው፡፡ ወጣቱ ፖለቲከኛ በሆደ ሠፊነት ‹‹ ኧረ የመቻቻል ያለህ፣ ኧረ የድርድር ያለህ፣ ኧረ የመደማመጥ ያለህ . . .›› በማለት አንድ ጫፍ ላይ ቆሞ ማክረር እንደማይጠቅም ገልጿል፡፡ ለአዲሱ አመራርም እውቅናና ድጋፍ ሰጥቷል፣ ደስተኛም ነው፡፡ ይሄን የምለው አንዱዓለም ለገና በዓል በአካል አግኝቼ ሃሳቡን ለረዥም የማዳመጥ እድል ስለገጠመኝ ነው፡፡

በመጨረሻ ግን ስለ ኢሳት ማንሳት እፈልጋለሁ፡፡ ኢሳት ለኢትዮጵያውያን በአማራጭነት ብቅ ያለ ትልቅ ሚዲያ ነው፡፡ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ያለውን አበርክትቷል ማድነቅ እፈልጋለሁ፡፡ እኔም በተለያየ ጊዜ በዚሁ ሚዲያ ላይ የተለያዩ ሃሳቦችን ሰጥቼ አውቃለሁ፤ ወደ ፊትም እድሉን ባገኘሁ ቁጥር እሰጣለሁ፡፡ የተለያዩ አማራጭ ሃሳቦችን በተደራጀ ነፃ ሚዲያ ማግኘት የተራበው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳያዝን የኢሳት ጋዜጠኞችን የኢዲቶሪያል ቦርድ አባላት በእጅጉ ሊየስቡበት ይገባል፡፡ ማንኛውም ሚዲያ ከአድሎ አሠራር ነፃ መሆን አለበት፡፡ በዚህ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ጋዜጠኞቹ ግን የግል አመለካከታቸውንና እምነታቸውን በማስቀደም አንድን ድርጅት ለማጥቃት የሚሄዱበትን መንገድ መፈተሽ ጠቃሚ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ፋሲል በአንድነትና አመራሩ ላይ የሰነዘረው የተዛባ አስተሳሰብ “በግል አስተያየት ስም” የቀረበ ቢሆንም ግለሰብ አንድ ትልቅ ፓርቲ ላይ ሲጽፍ መውሰድ የሚገባውን ጥንቃቄ አላደረገም፡፡ ስለዚህ ብዙ ተሳሳተ፡፡ ለማንኛውም ሁሌም ከጥላቻ የሚነሳ ሃሳብ ለህዝብም አይጠቅምም በማለት ላጠቃልል፡፡

በትግራይ ክልል የአፅቢ ወንበርታ የተነሳው ህዝባዊ ዓመፅ ቆመ፤ መንግስት ካሳ ሊከፍል ነው

$
0
0

ህዝብ ተበትኗል፣ መንግስት ካሳ ይከፍላል፣ የታሰሩ አይፈቱም

አብርሃ ደስታ

አብርሃ ደስታ

የአፅቢ ወንበርታ ወረዳ (ጣብያ ሩባፈለግ፣ ቁሸት ሕኖይቶ) ህዝብ የከፈተው ዓመፅ ዛሬ (ዓርብ 09/05/06 ዓም ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ከአስር ደቂቃ (12:10) ላይ ቆሟል። ህዝብ ወደየቤቱ ተመልሷል። የፀጥታ ሃይሎች ግን ከአከባቢው አልራቁም።

አስተዳዳሪዎች ህዝቡን በፌደራል ፖሊስ አስከብበው ሲያስፈራሩት የዋሉ ሲሆን የህዝቡን ጥያቄ (ካሳ የመክፈሉ ጉዳይ) ለመመለስ ተስማምተዋል። ስለዚህ ህዝቡ በጠየቀው መሰረት መንግስት ተገቢውን ካሳ ይከፍላል። የታሰሩት የአከባቢው ኗሪዎች ግን አይፈቱም። ህዝቡ “የታሰሩትን ይፈቱልን” ብሎ ሲጠይቅ “እርምጃ እንወስድባችኋለን፣ ማንም መጥቶ አያድናችሁም” የሚል ማስፈራርያ ደርሷቸዋል። ስለዚህ መንግስት ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት የታሰሩትን ዜጎች ለመልቀቅ ዝግጁ አይደለም።

የመንግስት አካላት ህዝቡን ካሳ ለመክፈል ሲስማሙ የህዝቡን ጥያቄ ትክክለኛነት ተቀብለውና አምነው እንደሆነ አቅርበዋል። ጥያቄው ያነሱት ዜጎች ከእስር ለመፍታት ግን ፍቃደኛ አይደሉም። በትግራይ ዜጎች መብታቸው ሲጠይቁ ለእስር ይዳረጋሉ። የአፅቢ ወንበርታ ጠያቂዎች ምሳሌ ናቸው። ታሳሪዎች የዛሬን ጨምሮ ስምንት ናቸው።

ጥያቄ የጠየቀ ዜጋ ለምን ይታሰራል? ጥያቄ የመጠየቅ መብት የለውም? መንግስት የህዝብን ጥያቄ በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ለምን ወደ ሃይል እርምጃ ይሄዳል? አምባገነኖች በራስ የመተማመን ባህሪ ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።

“ብጥብጥና ሁከት” የህወሃት የተለመደ አባባል: “መንግስት ሆይ ህዝቦችህ ይወዱሃል የምንልህ እኛ ነን እንጂ እነሱስ ሞትህን ይመኛሉ”

$
0
0

ናትናኤል ካብቲመር ኦስሎ ኖርዌይ 5 ጥር 2006

መቼም በኢትዮጲያ ብጥብጥና ሁከት የሚባለውን አባባል የማያቅ አለ ለማለት ያሰቸግራል። ምክንያቱም የመብትና የፍትህ ጥያቄ በተነሳ ቁጥር የህወሃት መንግስት “ ብጥብጥና ሁከት ሊያሰነሱ ሲሉ” ማለቱ የተለመደ ነው። ምንም አይነት መብትን የተመለክቱ ጥያቄዎች በድርጅት ወይም በግለሰብ በተነሱ ቁጥር “ብጥብጥና ሁከት” ሊያስነሱ ሲሉ ይባልና እስር ቤት ይወረወራሉ። እዚህጋ በርካታ ጥያቄዎችን የሚያስነሳ ነገር ይታያል። በኢትዮጲያ መብት ማለት ምንድነው? አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን የመብት ጥያቄዎቹን ለመንግስት እንዴት ነው ማቅረብ ያለበት? ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ግን አንድ መራራ እውነት አለ እሱም መብት ማለት በኢትዮጲያ መንግስት መጥኖና ለክቶ ለራሱ በሚስማማ መልኩ ለማህበረሰቡ መብቶች ብሎ የተዋቸው ናቸው። መብት ሲባል በወያኔ ካድሬ አመለካከት ያው ሁሌ ንፅፅሩ ከዛ ከፈረደበት ደርግ ነው “በደርግ ጊዜ ሰአት እላፊ ነበር አሁን ግን የለም” ፣ “በደርግ ጊዜ ብሄራዊ ውትድርና ነበር አሁን ግን የለም” ስለዚህ ወያኔ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ነው እንባላለን።
semayawi
ብጥብጥና ሁከት ምን ማለት እንደሆነ ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን ነገር ግን በአሁኑ ሰኣት በየእስር ቤቱ እየማቀቁ የሚገኙት ወጣቶች የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ነው እንጂ በጥብጠው እንዳልሆን ለማንም ግልፅ ነው። ደሞ ሌሎች አባባሎች አሉ “የተወሰኑ” ፣ “አንዳንድ” የሚባሉ ለምሳሌ ባለፈው ምስኪኖቹ የኢትዮጲያ መምህራን ደሞዝን አስመልክቶ ላነሱት ጨዋነት የተሞላው የመብት ጥያቄ ሟቹ አቶ መለስ “አንዳንድ ብቃት ያነሳቸው መምህራን ብጥብጥና ሁከት ሊያስነሱ ሲሉ” ብለው በአነስተኛ ገቢ በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩትን ምስኪን የኢትዮጲያ መምህራን በሃዘን አንገታቸውን አስደፏቸው። እብሪት ከተሞላው ስድብና ማስፈራሪያ ውጪ ላነሱት ጥያቄ በአግባቡ እንኳን ማብራሪያ አልተሰጣቸውም።

የኢትዮጲያ ሙስሊም ማህበረሰብም ከህፃን እስከ ሽማግሌ እምነታቸውን አስመልክቶ ላነሱት ጨዋ የመብት ጥያቄ “አንዳንድ ብጥብጥና ሁከት ፈጣሪዎች” እየተባለ ይዘገባል። ባለፈው የብራዚል ማህበረሰብ ላነሳው የመብት ጥያቄ ፕሬዝዳንቷ ዲልማ ሩሴፍ የተናገሩት ንግግር እጅግ ያስቀናል “መብታችሁን ለማስከበር በመነሳታቹ ኮራሁባቹ” ነበር ያሏቸው። አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው በወያኔ አገዛዝ ይህንን በፍፁም አንሰማም። ለምን? የኢትዮጲያ ህዝብ በጥባጭ ስለሆነ? ወይም መንግስትን አጉል ጥያቄ ስለሚጠይቅ? አይደለም። ህወሃት ራሱ የሰራውና እየሰራ ያለው ኢሰባዊ የሆን ግፍና የመብት ረገጣ ስለሚያስበረግገው ሰው ሲሰብሰብ አይወድም። እጅግ በሚያስገርም መልኩ በቅርቡ የሳውዲ መንግስት በኢትዮጲያዊያን ላይ ያደረሰውን አስከፊ ግፍና የመብት ረገጣ ለመቃወም የወጣውን ህዝብ እንኳን “ብጥብጥና ሁከት” ሊያስነሱ ተብሎ እየተደበደቡ ተበተኑ። ኧረ ሌላም ብዙ አይተናል።
ነፃና ዲሞክራሲያዊ መንግስትማ የህዝቡን የመብት ጥያቄ እንዴት እንደሚመልስ እናያለን። እንደውም የኢትዮጲያ ህዝብ ሲበዛ የዋህ ነው ባለፈው ውጥንቅጡ በወጣውና መላቅጡ በጠፋው የኢትዮጲያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ የተነሳ ተሰደው በሳውዲ ሲሰቃዩ ቆይተው ወደሃገራቸው ከተመለሱት ስደተኞችጋ አንድ ሁለት ፎቶ ስለተነሱ ብቻ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን የሚያደንቁም ተነስተው ነበር። ምን ስላደረጉ? ምንም። እንደው ህዝባችን ትንሽ ሲያረጉለት ወዲያው ለምስጋና አንገቱን ስለሚያጎነብስ ነው እንጂ። ይህን የመሰለ የዋህ ምስኪን ህዝብ በዘርፈብዙ ችግር ሲሰቃይ ማየት እጅግ ያበሳጫል።
ለምሳሌ የመብት ጥያቄ ማንሳት “ብጥብጥ” መባሉ ቀርቶ ለማንኛውም ኢትዮጲያዊ ተፈቀደ እንበልና ምስኪኑ የኢትዮጲያ ህዝብም “ኧረ ተው ከዚህ ሀገር ንቀለኝ” እያለ አማልክትን ከማስቸገር መብቱን ለማስከበር ቢነሳ ምን ያህሉ የሃገራችን ህዝብ የመብት ጥያቄ እንደሚያነሳ ሁላችንም መገመት አያቅተንም።
Muslim Etiopia 1
አንዳንዴ ሳስበው መንግስት ዝም ሲባል የተወደደ ይመስለዋል መሰለኝ ምናልባትም አንዳንድ አገልግሎት ሰጪ ቦታ የሚሰሩ ካድሬዎች የህዝቡን ሮሮ ትተው “ህዝቡ ለመንግስት ፍቅር አለው” ብለው ሪፖርት ስለሚያቀርቡ ይሆናል። እውነታው ቢገለፅ ግን ሪፖርታቸው የሚሆነው “መንግስት ሆይ ህዝቦችህ ይወዱሃል የምንልህ እኛ ነን እንጂ እነሱስ ሞትህን ይመኛሉ” ነበር።

ታስታውሱ እንደሆን አቶ መለስ “ይህ ማዕበል” ብለው አለወትሮአቸው ድምፃቸውን ሞቅ አርገው የተናገሩት መንግስታቸው የተወደደ መስሏቸው ነበር ወዲያው በነጋታው መልሱን አገኙት እንጂ። ግን እንዴት እንደዛ አሰቡ? በትክክል ቁጥሩን የማያውቁትን ህዝብ ፣ መንግስት በስርአቱ መዝግቦ ያልያዘውን ህዝብ ፣ በኑሮ ውድነት ፣ በነፃነት እጦት እያሰቃዩት ያለውን ህዝብ እንዴት ይወደኛል ብለው አሰቡ። ያስገርማል።

ወደዋናው ሃሳቤ ስመለስ ማንኛውም የሰው ልጅ መብቱን መጠየቅ ማስከበር አለበት ማንኛውም ኢትዮጲያዊም እንድዚሁ። ይህን ስል ግን የግድ መስቀል አደባባይ መሰብሰብ ላይቻል ይችላል ቢሆን ጥሩ ነበር ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጲያዊ በሚኖርበት ፣ በሚሰራበት ፣ በሚማርበት ፣ አገልግሎት በሚያገኝበት ቦታ መብቱን ማስከበር አለበት። ባገኘው አጋጣሚ እምቢ ማለት አለበት።

የማለዳ ወግ ..ኢትዮጵያን ለማየት ፣ ጥምቀትን በጎንደር ማክበር!… (ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ)

$
0
0

የከተራው በአል

ከተራ ምንድን ነው? ከሚለው ትርጓሜ እንነሳ … በየዓመቱ የጥምቀት በዓል በድመቀት ይከበራል፡፡ ከበዓሉ በፊት የከተራ በዓል የሚከበርበትን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ገለጻ ከተራ ከበበ ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡ የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥል ይውላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ፣ ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡

ከተራ በዓል በየዓመቱ በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ይውላል ። የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ ምእመናን ሲወርድ ሲዋረድ ይዘው በመጡት ሃይማኔታዊና ባህላዊ እሴት መሰረት በጥምቀትን በዓል ዋዜማ ወንዝ ምንጭ ውሃው ይገደባል ፣ ይከተራል። ውኃው የሚከተረው በማግሥቱ ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው። ይህ በጥምቀት ዋዜማ የሚደረገው ውኃውን መከተርና መገደብ ስርአትም ” ከተራ ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

405383_3133893752237_1633541756_n

543833_10200420756947440_784368804_a

images-171

images-226

የከተራው በዓል ሲከበር

ታቦተ ሕጉን ተሸክመው ዮርዳኖስን እንደ ተሻገሩት ካህናተ ኦሪት፤ ካህናቱ የማይለወጠውን ታቦተ ሕጉን በራሳቸው ተሸክመው የብሉዩን ሥርዓት ከሐዲስ ኪዳን ጋር አንድ አድርገው የሐዲስ ኪዳን መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስን እያሰቡ፤ ካህናተ ሐዲስም ወደ ከተራ (ዮርዳኖስ) ይጓዛሉ፡፡ ሊቃውንቱም እንዲሁ ለበዓሉ የሚስማማውን ቃለ እግዚአብሔር እያደረሱ እንደሚያድሩ የሃይማኖት ልሂቃን አባቶች ያስረዳሉ።

ከተራ ዕለት ጥር 10 ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የሄደበትን ለማዘከር ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን “ኃዳፌ ነፍስ ለጻድቃን” የሚለውን ዋዜማ ይቆማሉ፡፡ የዋዜማው ቀለም ከቀኑ በአራት ሰዓት በመላው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ይጀመራል ። ከዚያም የዋዜማው ሥርዐት ቅዱስ ተብሎ እስከ ሰላም ያለው ቀለም ይደርሳል፡፡ በዕለቱም ቅዳሴ ይቀደሳል፡፡ ታቦተ ሕጉን የሚያነሡት ሰሞነኛ ካህን ከምግበ ሥጋ ተከልክለው ለዕለቱ የሚገባውን ጸሎት ያደርሳሉ፡፡በከተራው ዕለት ድንኳን ተተክሎ፣ ዳሱ ተጥሎና ውኃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ታቦተ ሕጉ የሚንቀሳቀስበት ሰዓት ሲደርስ የየቤተ መቅደሱ ታቦታት በወርቅና በብር መጎናጸፊያ እየተሸፈኑ በተለያየ ኅብር በተሸለሙ የክህነት አልባሳት በደመቁ ካህናትና የመጾር መስቀል በያዙ ዲያቆናት ከብረው፣ ከቤተ መቅደስ ወደ አብሕርት /ምጥማቃት/ ለመሄድ ሲነሡ መላው አብያተ ክርስቲያናት የደወል ድምፅ ያሰማሉ፡፡ ምእመናን ከልጅ እስከ ዐዋቂ በዐጸደ ቤተ ክርስቲንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው ህዝበ ክርስትያኑ ያጅቧቸዋል። በአማሩ አልባሳት ተውበውም መንገዶች በእልልታ በሆታና በጭፈራ በማድመቅ ታቦቶችን በክብር ወደ ተዘጋጀው የበዓሉ ቦታ አጅበው ይደርሳሉ!

በዓለ ጥምቀት እና ኢትዮጵያ

ታላቁ የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሲነሳ ኢትዮጵያውያን ሩቅ ዘመንን ተሻግረን ቅዱሳን ሰማዕት አባቶችን ሊቃውንት አባቶችን አስተምሮት እናዘክራለን። በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡ በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና ክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል፡፡ የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ፡፡

ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ(1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡ ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት በዐዋጅ አስነግረው ነበር፡፡ ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከአወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ። …

ኢትዮጵያ ዜና ጥምቀተ ክርስቶስን ከሰማችበት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በተለይም ከአጤ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (6ኛው መ/ክ/ዘ) ወዲህ የጥምቀትን በዓል ዛሬ በሚታየው አኳኋን ስታከበር እንደ ቆየች ይታመናል፡፡ በክብረ በዓሉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱት ታቦታት በካህናቱ ሃሌታ፣ በምእመናኑ እልልታ እና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ በተቋቋሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዝሙሮች ታጅበው በተመሳሳይ አኳኋን እንደሚመለሱ ይታወቃል፡፡
ኢትዮጵያን ለማየት ፣ ጥምቀት በጎንደር ማክበር …
timket_in_gondar

በአርባ አራቱ ታቦት መናህሪያ በጎንደር ከልጅነት እስከ እውቀት የማውቀው ታላቅ ህዝባዊ በአል ቢኖር የጥምቀት በአል ነው . . . የጎንደር አባቶችና እናቶች ባማረ የባህል ልብሶቻቸው ተውበው ደምቀው ጎንደርና ጥምቀትን ያደምቋታል። ጥምቀት ገና ከጥንት ከጠዋቱ የውጭ ሃገር ጎብኝዎችን ቀልብ ከሚስቡት በአላት ቀዳሚ መሆኑንም አውቃለሁ ። አባቶች ጥንግ ድርብ እና አልፎ አልፎም ቀደምቱን ያማራ በርኖስ የባህል ልብሳቸውን ለብሰው ጥምቀትን ደምቀው ሲያደምቁት ፣ የቀረው ነዋሪም “ለጥምቀት ያልሆነ ልብስ ይበጣጠስ” ሆነና አቅሙ የፈቀደ አዲስ ልብስ አስገቶ ይለብሳል። ያጡ የነጡት ደግሞ ያላቸውን መላብስ አጣጥበውና በወግ በወጉ ጠቅመው በአደባባይ የሚታዩት በጥምቀት ነው፡፡ በጥምቀት የጎንደር ስመ ጥሩ የአርባ አራቱ ታቦት ፣ ሊቃውንት፤ ስመጥር የደብር አለቆችና ካህናት በሚያምረው ልብሰ ተክህኖ አምረውና ደምቀው ይታያሉ . . . በነጭ የባህል ልብሳቸው ላይ ጣል ከሚያደርጉት ጥቁር ካባቸውንና በራሳቸው ጥምጣም የሚታወቁት በጎንደር የቅኔ ፤ የመወድስና የአቋቋም ዝማሬ ሊቃውንት ባማረው አንደበታቸው የውዳሴ መዝሙር ጣዕመ ዜማ፣ ወርብና ሽብሸባውን በአደባባይ የሚያሰሙበት ልዩ አጋጣሚ ቢኖር ይህ የጥምቀት በአል ነው . . . ዘመን በዘመን ሲተካ ጥምቀት በጎንደር እንዲህ እያደመቀ እዚህ ደርሰናል . . . !
ዛሬም ጎንደር በጥምቀት በቱሪስት መናህሪያ ሆና ዘመንን የኢትዮጵያ መገለጫ ሆና አይን እንደሳበች ትገኛለች ! ከዛሬ አራት ከፍለ ዘመን (400 አመት ) በፊት የተሰሩት የጎንደር ቤተ መንግስቶች አስገራሚ ጥበብ ዛሬ ድረስ ውበትና ግርማ ሞገስ ይታይባቸዋል፡፡ የዚያን ዘመን ሰማይ ጠቀስ ቤተ መንግስቶችን አስገንብተው የጎንደርን ከተማ በመቆርቆራቸው የሚታወቁት አጼ ፋሲል ሱስንዮስ ጥምቀት መዋኛ ገንዳንም ከቀሃ ወንዝ ዳረወቻ ገንብተዋል። አጼ ፋሲለደስ ሃገሬው በአሉን የሚያከብርበትን የመዋኛ ቅጽግ ግቢ ከልለው ያሰሩ ብልህ መሪ ነበሩ ! ይህም የያኔው ብልህ መሪ ለጥምቀት የሰጠውን ልዩ ክብር አመልካች ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም ፡፡ አጼ ፋሲል በቀሃ ወንዝ ዳርቻ ያሰሩት የመዋኛ ገንዳ ዛሬ ድረስ ለጎንደር ጥምቀት መድመቅ ፈርጥ ሆኖ ዘመን ሲነጉድ የዚያ ዘመን የስልጣኔ አሻራችን ያስቃኘናል፡፡ ከመዋመኛው አንድ ጫፍ ታቦተ ጽላቱ በክብር የሚያርፍበት መቅደስ አሰርተዋል፡፡ በዚያ የጸሎት ቤት ስርአተ ቅዳሴ ፤ ማህሌት ሽብሸባው ጥምቀት በመጣ በሄደ ቁጥር ይከወንበታል፡፡ ግራማ የተላበሰውን ይህን መዋኛ ሶስት ፎቅ ህንጻ በአስገራሚ ጥበብን ይታይበታል።
ጥምቀት በጥንታዊዋ መዲና በጎንደር ሲከበር የጥበብና የስልጣኔ አሻራ ሲከበር ለበአል አክባሪዎቹ ብዙ መልዕክትን ማጫሩ አይቀርም ! የአጼ ፋሲል የቀደመ ስልጣኔ ቅሪት ውብ ህንጻዎች የጥንቱን ማንነታችን እያወሱ ካወቅንበት ከዛሬ የኢሊ ጉዞዋችን እንድንነቃም እያደመቀ እያዋዛ ያዘክሩናል …
ጥምቀትን ታኮ የተመረቀው የመይሳው ካሳ ሃውልት ፣ የማይረሳኝ የመኪና አደጋ … ትዝታ

ዛሬ ዛሬ የጥምቀት በአል በአብዛኛው በወጣቱ ሙሉ ተነሳሽነት በልዩ ስሜትና ዝግጂት በልዩ ስሜት እንደሚከበር በስልክ ያጫወተችኝ እድሜዋ ከ80 የዘለለው የእድሜ ባለጸጋ እማሆይ እናቴ ነበረች ። ዛሬን አያድርገውና ድሮ በልጅነት ካህን አባቴንና እናቴን ተከትየ በፋሲል ውቅር ከተማ በጎንደር በአሉ አከባበር ደምቄ አድጌበታለሁና የጥምቀትና ጎንደር ትዝታ አብረውኝ ይኖራሉ …፡፡

ከሁለት አመት በፊት ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር ባደግኩበት ቀየ ተገኝቸ ነበር ። በከተራው በአል በጥምቀት ዋዜማም በጉጉት ይጠበቅ የነበረው የአጼ ቴዎድሮስ ሃውልት ምረቃ ላይ ተገኝቸም ኢትዮጵያን በጎንደር አይቻታለሁ ፡፡ በተወለዱ ባደጉበት ምድር ለአንድ ክፍለ ዘመን ጥርኝ አፈር ለመታሰቢያቸው የተነፈጋቸው የኢትዮጵያ አንድነት ተምሳሌት የአጼ ቴዎድሮስ ሃውልት በጎንደር ከተማ እምብርት በፒያሳ መሃል አደባባይ ተሰርቶ የምረቃውን ስነ ስርአት ሲካሔድም ተመልክቻለሁ ። ካች አምና በተከበረው ጥምቀት በጎንደር ደመና አሳዛኝ ትዕይንት ሲስተናገድም እማኝ ነበርኩ !
394801_3133895432279_2125852827_n
የአባይ በርሃው የመኪና አደጋ : (

የጎንደር ጥምቀት ክብረ በአል ጋር የቴዎድሮስ ሃውልት ምረቃ ሊከበር በዝግጅት ላይ እያለ ከወደ አባይ በርሃ የተሰማው መርዶ የከፋ ነበር። መርዶው በመይሳው ካሳ ሃውልት ምረቃና በጥምቀቱ የደመቀ ዋዜማ ስሜታቸው በደስታ ላይ የነበርነውን በአል አክባሪ ሁሉ ቅስም የሰበረ ነበር። በአሉን ለማክበር አስበው ወደ ጎንደር ሲገሰግሱ በአባይ በርሃ በተከሰተው የመኪና አደጋ ህይዎታቸው ያጡበት ወገኖች ቁጥርም ከፍ ያለ ነበር ። በርሃው ወገኖቹን በልቶታልና ጎንደሬውን አንገቱን በሃዘን ደፍቶ ማቅ ያለበሰው ቀን ቢኖር ይህ ቀን ነበር :( ደስታቸውን ለመግለጽ ሳግ እየተናነቃቸው ለቴዎድሮስና ለሚናፍቋት አንድነቷ የተጠበቀች ኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅር በመግለጽ ላይ የነበረው ኢትዮየጵያዊ ከትንሽ እስከ ትልቅ በርሃው በበላቸው ወገኖቹ በሃዘን ቅስሙ መሰበሩና ስሜቱ መጎዳቱን በእያንዳንዱን ፊት ይነበብ እንደነበር አይረሳኝም …
በአባይ በርሃ ገደል ገብቶ ሰው የጨረሰው አውቶቡስ እኔ ልጆቸና እህቴ በአንድ ሆነን በተሳፈርንበት አውቶቡስ እኩል ከአዲስ አበባ ነበር የተነሳው። ከአዲስ አበባ እስከ አባይ በርሃ ድረስ ከበስተኋላችን ይጓዝ ነበር ። በአባይ በርሃ ደልደል ባለ መንገድ ዳር በአንድነት ለደቂቃዎች እረፍት አድርገንም ነበር ። እኛ ቀድመን አቀበቱን ወጠን ደጅን እንደደረስን የማይታመነውን አደጋ መርዶ ሰማን… ይከተለን የነበረው አውቶቡስ ከሃምሳ በላይ አብዛኛው እንደኛ ጥምቀትን በጎንደር ሊያከብር የተሳፈረው ወገን ገደል ገብቶ ሰው አንዳለቀ በቀትሩ የራዲዮ ዜና እወጃ ሰማን! ያ ቀን. ለእኔ የሚረሳ እና የሚዘነጋ አይደለም ! በአባይ አፋፍ አንድ ጫፍ እረፍት ባደረግንባት ደቂቃ ሰላምታ የተለዋወጥኳቸውን ወገኖች በሰአታት ልዩነት የማለቃቸውን አሰቃቂ ዜና የሰማሁባት እለት ሆዴን ያላወሰኝና ያስደነገጠኝ ስሜት ትዝታው አሁን ድረስ ያውከኛል …ነፍሳቸውን ይማር !
ኢትዮጵያ የምትከብርበት የጎንደር ጥምቀት …

ከአካባቢ የወረዳ የዞንና የገጠር ከተሞች የመጣው ኮበሌ ባለጀንፎ ሽመል ከዘራውን ወልውሎ ለሆታና ጭፈራው ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል፡፡ ከሁሉም ቀልብን የሚስቡት የከተማ ጎረምሶች በህብረት ተሰባስበው በዘመነኛና በባህላዊው ዘፈን ጥምቀቱን ሲያደምቁት ፣ ወጣት አርሶ አደሮች በበኩላችው የሚያምር አረንጓዴና ሰማያዊ በቁልፍ የተንቆጠቆጠ ቂምጣና ጨሸሞዞቻቸው በተጨማሪ የሚያምር ገናባሌ አድርገው በአልባሳት ደምቀዋል፡፡ ኮበሌዎች ጠባብቡን ቁምጣ ፣ ሸሚዝና ገንባሌ ለብሰውና ከጎፈሬያቸው ላይ ሚዷቸውን ሻጥ በማድረግ በአሉን ለማድመቅ የበኩላቸው በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡ አልፎ አልፎም ቢሆን ኮረዳ ሴቶች ጭምር በቅባት የጠገበ ጸጉራቸውን ቁንዳላ ተሰርተው አረንጓዴ ቀሚስ አሰፍተውና በነጩ ቁልፍ አሽቆጥቁጠው ከመቸውም ጊዜ በላይ ለጎንደር ጥምቀት ህብረ ባህላዊ ድምቀትን ሰጥተው አድማቂዎች ናቸው። ወጣቶች ፣ ሃገር ቤት ከመጣው ቢጤያቸው ጋር ሲላቸው ሰይ ሰይ ተብሎ የሚታወቀውን ባህላዊ የዱላ ጫወታ እየተጫወቱ ባአሉን ያደምቁታል። እንዲያው በአጠቃላይ ከህጻናት ጀምሮ ኮበሌው፣ ኮረዳው ፣ እና እድሜ ጠገብ አባቶችና እናቶች የጎንደር ጥምቀትን በአል ልዩ ውበት ናቸው . . .
አንተ የት መጣህ አይባልም …ማን የማንን ይጫወት አይባልም! ኦሮሞው ፤ከንባታው ፤ ጉራጌው፤ ሃረሪው ፤ትግሬው ፤ አማራው ፤ ሱማሌው ይዘፈናል ፣ የደለቃል ፣ ጃሎ ይባላል! ኢትዮጵያዊ በጎንደር የጥምቀት በአል አንድ ሆኖ ባንድ ክብረ በአሉን ይታደማል ! አገር ጎብኝው ፈርንጅና ጥቁሩ ከሃገረ አሜሪካ ፤ ከአውሮፓን ከሩቅ ምስራቅና ከአውስትራልያና ከተለያዩ አለማት የመጡት ሀገር ጎብኝዎች በካሜራቸው እያጠመዱ ጥምቀትን በጎንደር ሲያከብሩ የኢትዮጵያን በጎንደር እያዩ ነው! የእረፍት ጊዜያችውን በዓለ ጥምቀትን ተጠግተው ጎንደርን ሲጎበኙ በጨዋታው ደምቀው ተውበው፣ የዚያን ዘመን የእነ አጼ ፋሲልን ቤተ መንግስቶች ፣ የቅድመ አያቶቻችን ድንቅና ውብ ባህልና ያለፈ መልካም ስራ እየተደነቁ የሚያልፉበት ትዕይንት በመሆኑ ኢትዮጵያን ለማየት ጎንደርን በጥምቀት ማየት ያሰኝዎታል! በሀገሬው ሆታ ጭፈራ ተደምመው የደስታ የፌስታ ቀንወትን እያሳመሩ ኢትዮጵያን በጎንደር እያዩ ጥምቀትን ያከብራሉ ! . . . የካች አምናው ትዝታ ራሴን ቢያነሆልለው በከተራው በአል በትዝታ ተጉዠ በማለዳ ወጋዎጌ ይህችን ያህል ላስቃኛችሁ ወደድኩ . . .

መልካም የከተራና የጥምቀት በአል !
ነቢዩ ሲራክ

የግርጌ ማስታዎሻ : ስለከተራና ጥምቀት ብዙን መረጃ ያገኘሁት ከሐመር መጽሔት ሲሆን ለወዳጆች እንዲስማማ አድርጌ ማቅረቤን ሳልጠቁም አላልፍም።

ምርጫ እና የስርዓት ለውጥ

$
0
0

ሙሉጌታ አሻግሬ
mulugetaashagre@yahoo.com

አገራት ዘመናዊ የተባለውን የመንግስት አስተዳደር መተግበር ከጀመሩበት ግዜ አንስቶ እስከዚህኛው ዘመን ድረስ የተለያዩ የመንግስት አወቃቀርና ርዕዮተ ዓለም ተስተናግደዋል። ሰዎች መለኮታዊ እምነታቸውን ወደጎን አድርገው ከማኦ እስከ ማርክስ ከሌኒን እስከ ካስትሮ ‘ማርክሲዝም ያነበቡና የተገበሩ ብፁዓን ናቸው’ ብለው የችግርን ጥግ እስኪገነዘቡ ድረስ ነጉደዋል። ዓለማችን በሶሻሊዝም ስትናጥ፤ ኮምኒዝምም የዓለማችንን ህዝቦች ሁሉ እኩል አደርጋለሁ ብሎ በተነሳ ሰባ ምናምን ዕድሜው ተንኮታኩቷል። ምዕራባውያን ምስራቆችን በኢኮኖሚ ብልጫ ማርከዋቸዋል። የምስራቅ አውሮፓ አገራት ከምዕራብያውያኑ በኢኮኖሚ አቅማቸው እጅግ ዘቅጠው ተገኝተዋል።
election
ይሁን እንጂ አሁንም የዚህ ርዕዮተዓለም አራማጆች በአንድ ወይም በሌላ መልኩ እዚህም እዚያም ይታያሉ። የቻይናው ዘመናዊ ‘ልማታዊ መንግስት’ አወቃቀር ለዚህ አባባል አንዱ ማሳያ ነው። አሁን በአገራችን ያለው መንግስት ትላልቆቹ ‘ተሰሚ’ ባለስልጣናት የማሌሊት ደቀመዛሙርት ነበሩ። አሁንም በውስጣቸ እንደዛው ሊሆኑ ይችላሉ…ማን ያውቃል። ለዚህም ይሆናል ኢትዮጵያ የቻይናን ጠረን እየያዘች የመጣችው። የቻይና አካሄድ የአፍሪካ አምባገነን ባለስልጣናትን በወንበራቸው ለማቆየት ፍቱን መንገድ ነው። “ከዳቦ በኋላ ዲሞክራሲ”። አጭር እና ግልጽ አምባገነናዊ አካሄድ። ስለዚህ የመጨረሻው ሰው ዳቦ እስኪያገኝ ድረስ ዴሞክራሲ አላስፈላጊ ትሆናለች። ይህች አካሄድ በአገራችን መንግስት ይፋ ዕውቅና የተሰጣት ግዜ… አዲዮስ መድብለ ፓርቲ ስርዓት በኢትዮጵያ።

በሌላ በኩል ‘ ዲሞክራሲ ዘመናዊነት ነው’ ብለው የተነሱት ምዕራባውያን፤ ሃሳብን የመግለፅና የመንግስትን በህዝቦች በጎ ፍቃድ የመመረጥ ሁኔታን ጠቅልለው ለህዝባቸው በመስጠት ህዝቡ የዚህ ዕድል (መብት) ተጠቃሚ እንዲሆን አድርገውታል። ይሁን እንጂ እንደ ኮሚኒስቶቹ የጎላ የኢኮኖሚ ችግር ባይታይም በዲሞክራቶች በኩልም የኢኮኖሚው ሁኔታ ኮለል ብሎ እየፈሰሰ ነበር ለማለት ያስቸግራል። ዓለማችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተዘፈቀችበት የኢኮኖሚ መውሸልሸል ምክንያትም ሃብት በተወሰኑ ቡድኖች እጅ እየተጠቀለለች መግባቷና የመንግስታት (የመስተዳድሩ) ኢኮኖሚውን የመቆጣጠር አቅም መልፈስፈስ ውጤት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ። ይህ አስተያየት ትክክል ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም ስርዓቱ ሃብትን ማዕከል በማድረግ ስለተገነባ ኢኮኖሚው ጡንቻ አውጥቶ የመንግስታትን የመወሰን አቅም ሲፈታተነው ታይቷል።

ከዚህ በተቃራኒ ጠንካራ ኢኮኖሚ በራሱ አገራትን እንደ አገር ሊያቆም እንደሚችል በተለያዩ አገራት በተከሰቱ ሁኔታዎች ታዝበናል። ከጥቂት ዓመታት በፊት ቤልጄየም ያለመንግስት ከአንድ ዓመት በላይ ቆይታለች። በዚህ ግዜ ውስጥ ሁሉ ይህ ነው የሚባል ችግር ሳይከሰት ዜጎች በነባር ህጎች ሲተዳደሩና ባለሃብቱም የታክስ ግዴታውን ሲወጣ ተስተውሏል። አንዳንድ ግለሰቦች የዚህ ውጤት ምክንያት የህግ የበላይነት በአገሩ በመስፈኑ ነው ብለው ቢከራከሩም የኢኮኖሚው ጥንካሬ በራሱ ትልቁ የወሳኝነት ድርሻ ነበረው። በእርግጥ የተዘረጋው አስተዳደራዊ ስርዓት(System) ጉልህ ድርሻ ነበረው። በኔዘርላንድም የተከሰተው ተመሳሳይ ሁኔታ ነበር። የመንግስት ካቢኔ አባላት ተኮራርፈው ምክር ቤታቸውን ከአንዴም ሁለቴ ዘግተው ፓርላማውን የልጆች እቃ እቃ ጨዋታ ባስመሰሉበት ግዜ ሁሉ የአገሩ ዜጎች ይህ ትርምስ እና ጫጫታ ትዝ ሳይላቸው የዕለት ተዕለት ድርጊታቸውን ሲያከናውኑ ታይተዋል። ዲሞክራሲና ኢኮኖሚ ከተባበሩ አይቀር እንዲህ ነው።

ስለዚህ በአግባቡ የተገራ ኢኮኖሚ የዜጎችን ሰላምና አኗኗር ለማቃናት ብቻ ሳይሆን ለአገር ህልውናም የራሱ አስተዋፅኦ አለው ማለት ነው።

ወደ አገራችን ይህን ሁኔታ ስንወስደው ያለመታደል ሁኖ ኢትዮጵያ ባዶ እጇን እያጨበጨበች ትገኛለች። ኢኮኖሚው የለ፣ ዲሞክራሲው የለ።

ኢትዮጵያችን ከተገነባችበት የነፃነትና የተጋድሎ ታሪክ ባሻገር ነፃነታችን ዳቦ እንዲሆንና አገራችን ዘመናዊ የመንግስት አወቃቀር እንዲኖራት ሁሉም ቅን አሳቢ ዜጋ ይመኛል። ዘመናዊነት ዘመናዊ ቁሶችን መጠቀምና ዘመን አመጣሽ ሁኔታዎችን መከተል ብቻ አይደለም። ዘመናዊነት ማለት መግባባት፤ ዘመናዊነት ማለት መቻቻል፤ ዘመናዊነት ማለት እርስ በእርስ መቀባበል፤ ዘመናዊነት ማለት ሃሳብን የመግለጽ ሁኔታ መመቻቸት፤ ዘመናዊነት ማለት የሕግ የበላይነት፤ ዘመናዊነት ማለት ህዝቦች በመረጡትና በፈቀዱት አካል መወከልና አገር እንድተዳደር ማድረግ ነው። በዚህ ዓለምአቀፋዊ የኢኮኖሚና ማህበረሰባዊ ትስስር (Globalization) ስርዓት ውስጥ ለመኖር የሌሎችን በጎ ልምድ መውሰዱ ብልህነት ነው። ካልሆነ ግን ያለንበትን ደረጃ አሻሽለን ቁልቁል እናድጋለን። ስለዚህ በአንጻራዊ ሁኔታም ቢሆን የተሻሉ የሚባሉትን አገራት የኢኮኖሚና መንግስት አስተዳደር ስርዓት ከኢትዮጵያ ባህልና አኗኗር ጋር አስታርቆ መተግበሩ እጅግ አስፈላጊ ነው።

አገራችን ንጉሣዊ ስርዓትን በሰፊው አስተናግዳለች። ከዚያም ሶሻሊዝምን ብሎም ያለፈው ስርዓት ዕድሜ ጥንፋፊ ላይ ቅይጥ ኢኮኖሚ ጭልጭል ብላ አልፋለች። በዚህኛውም መንግስት ‘ዲሞክራሲያዊ’ (እንዳትታዘቡኝ) ስርዓት እየተከተለች ነው።

በጄ!!! ዲሞክራሲውን ተቀብለን ስርዓቱን ለመገንባት ሰማይ እየቧጠጥን ይኼው ሃያ ሦስት ዓመት እንደምንም አለፈ። በ1997 አገር ጉድ ብሎ ፤ ህዝብ ተጨንቆ፤ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ ልትወለድ የምጥ ሂደት ውስጥ ገባን። ዲሞክራሲ ለጥቂት እውን ሳትሆን ጨነገፈች። ‘ዲሞክራቶቹ’ መግደል ጀመሩ። ዲሞክራሲ ናፋቂዎች ታሰሩ፤ ተገደሉ። ሌሎች የሚዜ አገልግሎት ለመስጠት ፓርላማ ገቡ። ለአምስት ዓመት በዘለቀው የመሣቂያ መሣለቂያ ድራማ እንደ ችሎታቸው ተውነው፤ ህዝቡ ዲሞክራሲ ይዘውልን ይመጣሉ ብሎ ደጅ ደጁን እያየ ሲጠብቅ ከፓርላማ ተሰናበቱ። አራት ነጥብ።
ቀጠለች አብዮታዊ ዴሞክራሲ። ምረጡ አስመርጡ ። ሃሳባችሁን ስጡ ተናገሩ ተባለ። እጅግ የተሳካ ምርጫ ተደርጎ ታሪካዊዋ አብዮታዊ ዲሞክራሲ 99.96% የፓርላማ ወንበር አግኝታ ኑሮ ቀጠለ።

አሁንም በቅርቡ ምርጫ አለ። ህዝቡ ጥያቄ አለው፤ ነፃነትና ፍትህ። ልማትና ዕድገት። እኩልነትና ሰላም። ይኽን ጥያቄ እንመልሳለን ያሉት ሰላማዊ የትግል ስልት የሚከተሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ጓዛቸውን እየሸከፉ ነው። በምርጫ ሊወዳደሩ። መንግስትም የ ’ ይቻላል’ አረንጓዴ መብራት አሳይቷቸዋል። ለእነዚህ ድርጅቶች ጥያቄው የሚጀምረው እዚህ ላይ ነው።

የመጀመርያው ጥያቄ፣ የመጪው ምርጫ ዓላማ ምንድን ነው?

ህዝቡ የአጃቢነት ስራ የሚሰሩ ግለሰቦችን በፓርላማ ማየት አይፈልግም። ፓርላማ ገብቶ የአምስት ዓመት የስራ ኮንትራት የሚፈልግ የሰላማዊ ትግል አራማጅ አባል ካለ፤ በህዝቡ ስም ከመነገድ በየትኛውም የመንግስት ይሁን ሌላ ድርጅት መቀጠር ቢሞክር መልካም ነው። ለፓርላማ የሚደረገው ሩጫ ውጤት ለህዝቡ የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ ማምጣት አለበት። ካለፉት የፓርላማ ኳኳታዎች እንደታዘብነው፤ ድምፀ ተዓቅቦ በማድረግ ይሁን ድጋፍ ባለመስጠት አንዲት ነገር ስትለወጥ አሊያም ስትስተካከል አላየንም። ለውጥ ለማምጣት ደግሞ ፓርላማ ገብቶ በቃላት ጉሽሚያ የነፃ ትግል ማድረግ የትም እንደማያደርስ በደማቁ አይተነዋል።

የመንግስትን ኪሳራነትና ድክመት ዲያስፖራው ሳይቀባባና ሳይፈራ እንደ ጉድ ያጎነዋል። “የተከበሩ” “ክቡርነትዎ” ምናምን ሳይል አካፋን አካፋ ይለዋል። ጉድለትን መናገር ለውጥ የሚያመጣ ቢሆን፤ የህዝቡን ጥያቄ እያሽጎደጎደ በየዕለቱ በሚጮኽው ዲያስፖራ ብቻ ኢትዮጵያ ውስጥ ከዛሬ ስንት ዓመት በፊት ዲሞክራሲ በነገሰች። የመንግስት ተቃዋሚ ነን የሚሉት ፓርላማ ቁጭ ብለው የሚያሽሞነሙኑትን ጥያቄ ገዥው መንግስት እጅግ ቀድሞ ከዲያስፖራው እርቃኑን ይነገረዋል። ስለዚህ ይህ ችግር “በክቡርነትዎ ታጅቦ ሲቀርብ የፓርላማው ስራ እንደተለመደው የፕሮቶኮል አገልግሎት ይሆናል ማለት ነው። የፓርላማ መግባት ዋነኛ ግብ በስማ በለው “የተከበሩ” ለማለት ሳይሆን የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ብቻ ነው። የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ ደግሞ በተግባር መሆን አለበት። ዳቦ እና ነፃነት ከቃላትነት ወርደው የሚዳሰሱ መሆን አለባቸው። የመንግስትን አሰራር አቃቂር በማውጣትና በቃላት መጎንተል ዳቦ አልሆነም። የህሊና እስረኞችንም ነፃ አላወጣም። በዚህ ሂደት ውስጥ አንድም ግዜ ቢሆን ገዥው መንግስት ለማከናወን ያቀደው ተግባር ተከልሶ አሊያም ተሰርዞ አያውቅም።

ስለዚህ። ስለዚህ ህዝቡ ለውጥ ይፈልጋል። ይህ ለውጥ የሚመጣው ደግሞ በ50+ የፓርላማ ጨዋታ ብቻ ነው። ይህን በኢትዮጵያ ፓርላማ ስንተረጉመው በፓርላማው ካሉት 547 መቀመጫዎች ቢያንስ 274 መቀመጫዎች (ሁሉም ተመራጮች አምስቱን ዓመት በሰላም ካጠናቀቁ) ያስፈልጋል። በመሆኑም የሰላማዊ ትግል አቀንቃኞች ይህን ያህል መቀመጫ ማግኘት ግድ ይሆንባቸዋል። የወንበሯ ቁጥር ከዚህ ዝቅ ካለች የተለመደው አጃቢነት በመሳቂያ መሣለቂያነት ይቀጥላል። ስለዚህ አጃቢነት መብቃት አለበት።
ሁለተኛው ጥያቄ፣ የሰላማዊ ትግል ሰልፈኞች ድል ለማድረግ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?

የፓርቲዎቻችንና ድርጅቶች ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ናት። ሁሉም ሰላማውያን የሰፈሩት ከከተሜው ጋር ነው። አገሪቱ ደግሞ 85% ህዝብ አለኝ የምትለው ከከተማው ውጭ ነው። ስለዚህ የፓርላማው ወንበር ያለው ከተማ ላይ አይደለም። ወንበር ከድሃው ገበሬ ጋር ነው ያለችው። ከህዝቡ የወንበር አደራ ለመቀበል መታመን ያስፈልጋል። ህዝባችንስ ደግሞ ለማያውቀው ሰው እንዴት ወንበሩን በአደራ ይሰጣል ? ለዚያውም ለአምስት ዓመት። ስለዚህ እንሂድ ፤ እንውረድ። የደፈረሰውን ጠጥተን፤ ጢስ አይናችንን እየወጋን የድሃውን ወገን ክፉ እና ደግ እንካፈል። የሃዘን እንጉርጉሮውን ቅኔ እንፍታ።
የእኛ ነጭ ሸሚዝ በከረቫት መታነቁ በጠኔ ለሚመታው፤ በበሽታ ለሚማቅቀው፤ ለታረዘው ላልተማረው ወገን ምኑም አይደለም። ምናልባት የበላይነታችንን ለማሳየት ካልተጠቀምንበት በስተቀር። ነገርግን አገሪቷን እንደ አገር ለማቆም ደም እና ላቡን ለማፍሰስ የማይሰለቸው ወገን የእኛ ነጭ መልበስና ማማር መሠረት ነው። አገር ስትወረር ደሙን የሚያፈስ ድሃው ገበሬ ነው። ሃገርህ አይደለም ተብሎ የሚፈናቀለው ይሄው ወገን ነው። ረሃብና ድርቅ ሲመታው የሚረግፈው ይሄው ድሃ ዜጋ ነው። እኛ ነጭ ከሻኛ እያማረጥን እንድንበላ አፈር ምሶ አፈር ሆኖ የሚለፋው ይህ ድሃ ገበሬ ነው። ስለዚህ እሱን ሳንይዝ ሰላማዊ ታጋዮች ሆነን ከተማ ውስጥ ተሞሽረን በአምስት ዓመት ውስጥ ሁለት ቀን ሄደን ምረጠን ስንለው ይታዘበናል። መቼም ቋንቋውን ስለምንናገር፤ ብንወዛም መልኩን ስለምንመስል የአንድ አገር ህዝብ እንደሆንን ከመገመት ውጭ ችግሬን ይገነዘባሉ ፤ መፍትሄ ያመጣሉ ብሎ አያምንም። ህዝባችን እንዲያውቀን አብዛኛው ኑሯችን ከእሱው ጋር ይሁን።

ፓርቲዎችና ድርጅቶች በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት እንዳላቸው ይናገራሉ። የእነዚህ ጽህፈት ቤቶች ስራ ምን እንደሆነና ምን እንደሰሩ የሚያሳይ ሪፖርት ለህዝብ የቀረበበት ግዜ የለም። አንዳንዶቹ በራቸው በወር አንዴ ይከፈት ይሆናል። የበዙት ደግሞ የሸረሪት ትዕይንት ማሳያ ሆነው ይከርማሉ። የተወሰኑት ደግሞ የፊት በሩ ተቆልፎ በስተጀርባው የግለሰብ መኖሪያም እንደሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ምን እየሰራን ነው የህዝቡን ጥያቄ እንመልሳለን የምንለው? በቃ ከታገልን የእውነት እናድርገው። ከተማ ላይ ተከማችተን በፓርላማ ናፍቆት ከምንቆዝም ፤ ህዝቡን ተጠግተን ኑሮውን እንኑር።

ስለዚህ የፓርላማ ወንበር የምታልሙ ድርጅቶች ተባብራችሁም፤ ተዛዝላችሁም ቢያንስ 274 ወንበር ማምጣት አለባችሁ። ሰሞኑን እንደተሰማው ከሆነ አዳዲስ ድርጅቶች ልምድ ለማግኘት እንዲችሉ ፓርላማ ቢገቡ የተሻለ ነው የሚል አንዲት ቀልድ ተለቃለች። የምን ልምድ እንደሆነ ግልፅ አይደለም። የፓርላማ ወንበር ምን ያህል እንደሚመች? አፈጉባዔው ስንት ግዜ እንደሚያስፈራራና መነጋገሪያውን ስንት ግዜ እንደሚያጠፋብን? ወይስ የፓርላማው በር ላይ ጫማ እና ቀበቶ እያወለቁ የሚደረገው ቅጥ አንባሩ የጠፋውን ፍተሻ መለማመድ?
የኢትዮጵያ ህዝብ ሲጀመር ሰው ነው። ከዚያም የአገሩ ዜጋ። መለማመጃ አይደለም። ስለዚህ ለፓርላማ እንሮጣለን የምትሉ ወገኖች የተለመደውን የሚዜ አገልግሎት ላለመስጠት እርግጠኞች መሆን ያስፈልጋችኋል። ከዚህ በዘለለ ፓርላማ በመግባት በገዥው ስርዓት የሚዘጋጀውን ድራማ በአጃቢ ተወናይነት በመተወን የምታተርፉት መሳቂያና መሳለቂያ መሆን ብቻ ሳይሆን የህዝቡንም ችግር ለአምስት ዓመት ማራዘም ነው። በጥልቀት አስቡበት።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ክህደት ከአናት ሲጀምር:- በቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ

$
0
0

እውነት ቤት ሥትሰራ …
ውሸት ላግዝ ካለች
ሚስማር ካቀበለች
ጭቃ ካራገጠች
ቤቱም አልተሰራ … እውነትም አልኖረች ።
… እንደዚያ ነው በባቢሎን ዘመን ።

የአንዱ ቋንቋ ከአንደኛው ይዘበራረቃል ….. መግባባትና መረዳዳት ብርቅ ይሆናል ። በጠራ አማርኛ የተጣፈውን በጉግማንጉግኛ በመተርጐም ከውስጡ የሚፈልጉትን ብቻ አለፍ አለፍ እያሉ ያነቡታል ። እናም የራሳቸውን ትርጉም ይሰጡታል ። ፍየል ወድያ ….. ቅዝምዝምም ወዲህ ይሆናል ።
ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት መካከል ጥቂት አዛውንቶች ታሪክን ደልዘው በወያኒኛ አዲስ ታሪክ ስለ አየር ኃይሉ እንዲፅፉ በህውሃት እየተጠየቁ ነው ። እነዚህ ባለ ብዙ አኩሪ ታሪክ ባለቤት አዛውንቶች መንታ መንገድ ላይ ቆመዋል ። በዓለም ዙርያ ተበትነው ያሉት የቀድሞው አየር ኃይል አባላት ሃሳባቸውን እንዲደግፉና የእርዳታ እጃቸውንም እንዲዘረጉ ለማግባባት እየሞከሩ ነው ። እኛም የቀድሞው የአየር ኃይል አባላት እንዲህ አልን ……….
ethiopian airforce
“ የአየር ኃይልን ታሪክ ለትውልድ ለማስቀረት የምታደርጉት ጥረት በጐና የሚደገፍ ምግባር ነው በርቱ ፤ ነገር ግን የገዢው ፓርቲ ሞግዚትነት አያስፈልጋችሁም ። በተጨማሪም በተፅዕኖ ስር ሆናችሁ ሚዛናዊነት የሚጐድለውና የተደለዘ ታሪክ ለትውልድ እንዳታቆዩ ሥጋት ቢጤ አለችን ።
(ያም ቢሆን መፅሃፉን ካነበብን በኋላ የምንታዘበው ይሆናል … አያጣላም ።) የአየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽንን እናቋቁማለን የምትሉትን በተመለከተ ግን ወራጅ አለ ። እጅግ ከስጋት በላይ የሆኑ ጥያቄዎች አሉን ። “ የቀድሞው አየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽን ” እያላችሁን ከሆነ ግን እንግባባለን ።
የሚለውን ጥቅል ሃሳብ በመልዕክታችን ብንሰድላቸው በጉግማንጉግኛ በመተርጐም እኛ ፖለቲካ አንነካካም …. ፖለቲካንና ኰረንቲን በሩቁ ነው ብለናል ይሉናል ከአዲስ አባ ደብዳቤ እየፃፉ ። እነሱ ለካ የአሁኑን የህውሃትን መንደርተኛ አየር ኃይል ነው ቬተራን እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት ። በህውሃት ሰማይ ስር ጉድ ሳይሰማ አያድርም አይደል !

እኛ ድፍን የአየር ኃይል ተቋም ላይ ስለተፈፀመ ክህደት ስናወራ …. እነሱ አንድ ግለሰብ አገርንና ህዝብን ለከዳ ስርዓት ስለሚመሰርተው ዕድርና የተዝካር ግርግር ሊያስረዱን ይሞክራሉ ። እኛ እኰ የቆማችሁበት አፈር ሥር ነፍሱ ያልወጣች የምታጣጥር የገዛ ጓደኛችሁ ነፍስ አለች ነው የምንላቸው ።
መጀመሪያ ባለንጀራችሁን ነፃ አውጡት ፤ እናንተም በጐን በሾርኔ ሳይሆን በአደባባይ በህግ ነፃ ውጡ ምክንያቱም እንደ ዶሮዋ ገመዳችሁ ረዘመላችሁ እንጂ ፈፅሞ አልተለቀቃችሁም እያልን ነው ።

ህውሃት እንደሆነ በሰው ተጠቅሞና አዋርዶ እንደሚያባርር የአደባባይ ሚስጢር ነው ። ደግሞም ይህ ይጠፋችኋል ብለን አንሞግትም ፤ ….. የመሰንበት ጉጉት ህሊናን ፈፅሞ ካልተቆጣጠረ በቀር ። አየር ኃይል ለአገር አንድነት የተፋለመ ጀግና እንጂ ጨፍጫፊ ያለመሆኑን በአደባባይ ስትመሰክሩና በህግ
ስታስነግሩ ….. የአየር ኃይል ተቋም እንደ ተቋም ነፃ ሲወጣ …. እርቅ ሲወርድ ፣ አገርን ከጠላት በመከላከላቸው ብቻ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኞች በአደባባይ ነፃ ሲወጡ …. ያን ጊዜ ሁላችንም በአንድነት ነፃ እንወጣለን ። ያለበለዚያ ግን ትውልድም አገርም ላይ ይቅር የማይባል ክህደት ትፈፅማላችሁ እያልን ነው ያለነው ፤ በጠራ አገርኛ ቋንቋ ።

የቬተራን አሶሴሽንን በመወከል ያገባኛል ብለው ከአዲስ አበባ መልዕክት የሰደዱልን ሰው በፍፁም ሃሳባችንና ሥጋታችንን በትክክል የተገነዘቡ አይመስሉም ወይንም ዛሬ ኢትዮጵያ በምትባለው አገር ውስጥ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የሚከታተሉም መሆናቸውን እንድንጠራጠር እያደረገን ነው ። ድንገት ዘንድሮ ጆሮዋቸውም ዓይናቸውም የተከፈተላቸው ይመስል በቃል ያጠኑትንና ስለ አየር ኃይሉ የሚገምቱትን በጐ ፍላጐት ለመተግበር የተነሱ ይመስላል ።

የህውሃት አስተዳደር አዛውንት የአየር ኃይሉን አባላት በማምሻ እድሜያቸው ታሪክን ደልዘው የእራሱን የተንጋደደና የተንሸዋረረ ታሪክ እንዲፅፉለት እየተጠቀመባቸውና ከጠራ ታሪካቸው አንስቶ ከራሱ ቆሻሻና ስውር ፍላጐት ሥር እያንደባልላቸው ያለ ይመስላል ። አየር ኃይሉ በአዋጅ ሙሉ ለሙሉ ከስራ ውጪ በተደረገበት ዘመን ላይ ፤ ጨፍጫፊ ተብሎም ቅፅል ስም ወጥቶለት ወደ ከርቸሌ መጋዙንና በመንደርተኛ ፓይለቶች እየተተካ መሆነኑን ትንፍሽ እንዳይሉ በዚሁ በምሽት እድሜያቸው እየተደለሉ ናቸው ። እንዲያውም ሙዝየም እስከ መክፈት የዘለቀ ህልምም እንዳላቸው እየጠቀሱ ነው ። አገር ቢኖረንማ ኖሮ ለትውልድ የሚቀር ፣ ታሪክን የሚዘክር ሙዝየም ማቆም እንዴት የተባረከ ህልም ነበር ? ነገር ግን አገርም ዜግነትም በተዋረዱበትና እድሜያቸውን ሙሉ ለአገር አገልግሎት ያበረከቱ አንጋፎች እንደ አሮጌ ቁና በውርደት እንዲኖሩ በአደባባይና በአዋጅ ባይበየን ኖሮ ፣ ትውልድም በበጐ መሰረት ላይ ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ …. ሁሉም አላማ በጐና ለአገርም ሆነ ለትውልድ የሚጠቅሙ ይሆኑ ነበር ።

እንግዲያውስ እነዚህ በህውሃት እየተደለሉ ያሉት የአየር ኃይሉ ነባር አዛውንቶች እርማቸውን ያውጡ ። ህውሃት አገሪቷን ከተቆጣጠረ ወዲህ ያለውን አየር ኃይል ተብዬ እንጂ የቀድሞውን ታሪክ ምናምኒት አሻራ እንኳ አያገኙም ። አጠቃላይ ሰፈሩና ቢሮዎቹም ጭምር በአይጥ መንጋ እንደተመታ ባድማ ዶክመንቶች ተፈርፍረው ድምጥማጣቸው መጥፋቱን አይጠራጠሩ ። የአየር ኃይሉን የታሪክ አሻራ ሊያስረዱ የሚችሉ የተለያዩ አውሮፕላኖችን ማናምኒት ሳያስቀር አቧራቸውን እያራገፈ የህውሃቱ አበበ ተ/ኃይማኖት (ጆቤ) እዚህ ግባ በማይባል ዋጋ መቸብቸቡን እንዴት ሳይነግራቸው እንደቀረ ይገርመናል ? ይህ ቀበኛ ሽፍታ ለጌጥና ለታሪክ በአየር ኃይሉ ጠ/መምሪያ ፊት ለፊት እንኳ ተቀምጣ የነበረችውን ገብሬ ቦላሌን ሳይቀር አንጠፍጥፎ መሸጡን ለምን ደበቃቸው ? ታሪክ በመስራት አገራችንን ያስከበረችውን ኤፍ-5 አውሮፕላንንስ አንዲት ሳያስቀር መቸብቸቡንስ ?

በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር የሚመራውን የአሁኑን ሥርዓት አያውቁትም እንበል ወይስ የክፋትና የብቀላ ምግባሩን ሁሉ ትተው በጐ ተክለ ሰውነት ሊገነቡለት እየሞከሩ ይሆን ? ታዲያ ይህንን እየሰሩ እንዴት ፖለቲካ አንነካካም ይሉናል ? በእነርሱው አመራር ስር የተገነባው የአየር ኃይል ሰራዊት እኰ በጅምላ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ ተብሎ እድሜውን ሙሉ ከአቀናው መስሪያ ቤት በውርደት ተባሮ ቤተሰቡ ተበትኖ በረሃብና በችጋር እንዲያልቅ ተፈርዶበታል ! እውነተኛዎቹ የአየር ኃይሉ አርበኞች ድፍን 22 ዓመታት ሙሉ ተሸማቀውና አንገታቸውን ደፍተው መሃል ደ/ዘ ውስጥ (በቀለ ሞላ ሆቴል ፊት ለፊት) በጠጠርና በቆርኪ ዳማና ቼዝ ሲጫወቱ የአዛውንቶቻችን መንግስት የት ነበር ? ለዚህ ሁሉ ግፍና በደል ተጠያቂው ማነው ? እነዚህንና ሌሎች በደሎችን እንዴት ነው የሚያስታርቁት ? በምንስ መመዘኛ ቀበኛ ሽፍታ የመሰረት ድንጋይ እንዲያነጥፍላቸው ያደርጋሉ …. ! ከረገጡት ምድር ስር
የባልንጀሮቻቸው የምትቃትት ነፍስ ምን ትላቸው ይሆን ? ፖለቲካ … ፖለቲካ …. ለምን እንደሚሉን አልገባንም ። ፖለቲካ ምንድነው ?

ለዘመነኖቹ የመንግስት ባለስልጣናት ማደር ? ለስብሰባ ሲጠሩ ፈጥኖ ሸገር ላይ መከሰት ? ወይስ ሲመሩት የነበረውን ሰራዊት አስማርኰና ክዶ ለትግራዩ የነፃነት (ተገንጣይ) ግንባር በፈቃደኝነት መገበር ? እኛ ፖለቲከኞች እያሉን የሚያበሻቅጡን ከአገር በግፍ ተገፍታሪ ስደተኞች በሰላም ተከባብረንና ተዛዝነን ድፍን 20 ዓመታትን እንዳሳለፍን በአለፈው የበጋ ወቅት በዋሽንግተን ከተማ ተገኝተው መታዘባቸውን እናውቃለን ። አየር ኃይል ማለት ለኛ መታወቂያችን ፣ ማንነታችንና ዜግነታችንም ጭምር ነው ። በህብረት ተደጋግፈን እንኖራለን ፤ የተቸገረን እንረዳለን ፣ የታመመን እናስታምማለን … እንጠይቃለን ፣ እስከወዲያኛው የሚሰናበተንንም በኃዘን እንሸኛለን ።

ጀግኖቻችንን ከተጣሉበት እያስታወስንና እያነሳን እናከብራቹኋለን እንላለን ። በየዓመቱም የአየር ኃይል ቀን በማለት በህብረት ዩኒፎርማችንን ለብሰን ባንዲራችንን ከፍ አድርገን እያውለበለብን ኢትዮጵያ ሃገሬን እንዘምራለን ….. ። ይህንን ባንዲራና ዝማሬ የአሁኑ መንግስት አይወደውም ። በዘር ከፋፍሎ እኛ እና እነርሱ ፣ የቀድሞውና የአሁኑ ፣ ጨፍጫፊና ዲሞክራቲክ በማለት እየለያየ አጥፍቶናል ። አሁን ደግሞ እዚሁ ያለንበት አገር ድረስ ክንዱን እያረዘመ መካከላችን ሊገባ እየተቅበዘበዘ እንደሆነ ይገባናል ። እባካችሁን አዛውንቶቻችን ለዚህ መንደርተኛ ስርዓት ክርንና ጅማት እየሆናችሁ ህውሃት ጣቱን እቤታችን ድረስ እንዲያረዝም እየረዳችሁ መካከላችን እንዲገባ አታድርጉ ፤ በማህበራችንም በኩል አትምጡ ።

በግል እኰ መፅሃፍ አይደለም ኤግዚቢሽንም መክፈት ትችላላችሁ ። አሁን እየመጣችሁበት ያለው መንገድ ግን የሁሉንም ምክር ፣ የብዙሃንን ይሁኝታ ይጠይቃል ። እናንተ ደግሞ እዚያው አገር ቤት ያሉትን እውነተኞቹን አርበኞች አንድ በአንድ ሲያልቁ ጠብቃችሁ ፣ በህይወት የተረፉትንም ንቃችሁና ገፍትራችሁ ቀበኛ የሃገር ጠላት የሆኑትን ቱባ የህውሃት ባለስልጣናትን በጀርባችሁ አዝለችሁ አትላንቲክን በማቆራረጥ ልታነታርኩን ትሞክራላችሁ። ለምን ድምፃችሁን አጥፍታችሁ ታሪክ መፃፍም ሆነ ዕድር ማቋቋም አልመረጣችሁም ? በማህበራችን በኩል ለመምጣት ለምን መረጣችሁ …. ? በብዙሃን ስደተኛና በውርደት ተባራሪ ስም በየሸራተኑ ከበሮ መደለቁንስ ምን አመጣው ?

እንግዲያውስ ለሁለተኛ ጊዜ ምክር እንለግስ ……….
ሰው ባለቀ እድሜው ላይ ለኑዛዜ ይመቻቻል ….. እውነትን ተናግሬ ካልሞትኩ ብሎ ከህሊናው ጋር ትንቅንቅና እልክ ይጋባል ….. እውነቱን አፍርጦ በመሸበት ያድራል … እንጂ ለዳግም ምርኰ እራሱን አሳልፎ አይሰጥም ። በዚህ እድሜ እኰ ግጥም ብሎ ከሞላ የውስኪ ባንኰኒ ላይ የምንጭ ውሃ ካልሆነ ንክች አላደርግም .. ፣ ከተትረፈረፈ ጮማና ቁርጥ መሃል ቲማቲምና ቅጠላ ቅጠል ካልሆነ ምናምኒት አልቀምስም እየተባለ የሚኖርበት እድሜ ነው ፣ ብዙ የሚያጓጓ ህይወት የለም ። ታዲያ ምንድነው በዚህ በኪኒኒ ተደግፎ በሚኬድበት የምሽት እድሜ ላይ ሆኖ ውሃና ዘይትን ለመቀላቀል መሞከር ? በዚህ ምግባር ትውልድ አይደለም ከአብራክህ የወጣ ልጅ ይጠየፍሃል ።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
ታዛቢዎች በህብረት !
ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በያሉበት ።

PDF created with pdfFactory trial version www.pdffactory.com


ከ18 በላይ የሙስሊም ተቋማት “ዘወትር ከመፍትሄ አፈላላጊው ኮሚቴ ጎን ነን፤ ትግላችንም ተጠናክሮ ይቀጥላል”አሉ

$
0
0

muslim dim
(ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ከ18 በላይ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የቋማት በ እስር ላይ ከሚገኙት መፍትሄ አፈላላጊው ኮሚቴ ጎን እንቆማለን፤ ትግላችንም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታወቁ።

“በመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴአችን በቅርቡ የተሰጠው መግለጫ ለትግሉ መነቃቃትን የፈጠረና አባላቱም ከረዥም ጊዜ እስራትና ሰቆቃ በኋላ ለተነሱለት ዓላማ በጽናት ለመቆማቸው አድናቆታችን የላቀ ነው፡፡ የህዝብ ልጅነታቸውንና የእምነት ነጻነት አውነተኛ ጠበቆች መሆናቸውን በተግባር አስተምረውናል፡፡” ያሉት ተቋማቱ “ይህም ለትግሉ ቀጣይነት በአንድነት ለመሥራት ቃላችንን የምናድስበት አጋጣሚ የፈጠረልን ሲሆን የፍርድ ቤቱን ውሳኔና ባጠቃላይ መንግስት በተያያዘው ሙስሊሙን የማዋከብ፣ የማሸበር እንዲሁም ንብረቶችን የመቀማት ህገወጥ ድርጊት በሚመለከት የሚከተለውን ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፤” ብለዋል።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በሃይማኖት ጭቆና ስም የሚረጩ አደገኛ መርዞች –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

$
0
0

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

(የግል አስተያየት)

አራተኛውን የኢቲቪ “ጥናታዊ ፊልም” አየሁት፤ ዝቅ ሲል ለምርጫ ቅስቀሳ፣ ከፍ ሲል ደግሞ ከፋፍሎ ለመግዛት ተብሎ የተዘጋጀ ይመስለኛል። ፊልሙ ኢህአዴግንና የቀድሞ ስርዓቶችን ያነጻጽራል፤ ማንም ነፍስ ያለው ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ጭቆና አልነበረም ብሎ አይክድም፤ ልዩነቱ የሚጀመረው “ጨቋኙ ማን ነው? ተጨቋኙስ?” የሚለውን ለመመለስ ሲሞከር ነው። በእኔ እይታ ጨቋኞቹ የኦርቶዶክስ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ መንግስታት ብቻ እንደነበሩ ተደርጎ የሚቀርበው አስተያየት ስህተት ነው፣ ተጨቋኞቹ ከኦርቶዶክስ ውጭ ያሉ ሃይማኖቶች ብቻ እንደነበሩ ተደርጎ የሚቀርበውም አስተያየት በታሪክ ያልተደገፈ፣ የስህተት ትምህርት ነው ። ታሪካችን እንደሚነግረን ከ66ቱ አብዮት በፊት፣ ሁሉም ስልጣን የያዙ ሃይሎች ስልጣናቸውን ለማቆየት ወይም ግዛታቸውን ለማደራጀት እነሱ የሚደግፉትን ሃይማኖት በሌላው ላይ ለመጫን ሙከራ አድርገዋል። የአጼ ሃይለስላሴ መንግስት የመጀመሪያውን የጽሁፍ ህገመንግስት ስላረቀቀና በህገመንግስቱ ላይ “ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት” የመንግስት ሃይማኖት መሆኑን በይፋ ስላወጀ ዛሬ እንደ ትልቅ ግኝት ተጋኖ ይቀርባል እንጅ፣ ከዚያ በፊት የነበሩት ገዢዎች ኦርቶዶክስን ብቻ ሳይሆን፣ካቶሊክንና እስልምናን የመንግስት ሃይማኖት ለማድረግ ሞክረዋል። ክርስትናን በይፋ ከተቀበለው ከመጀመሪያው ንጉስ ኢዛና ጀምሮ እስከ አክሱም ስርወ-መንግስት ውድቀት ድረስ ኦሮቶዶክስ ሃይማኖት የመንግስት ድጋፍ ነበራት፤ ዮዲት መጣችና ስርዓቱን ለማፍረስ ሞከረች። ቀደም ብሎ ክርስትናን የማያውቁት አገዎች፣ ክርስትናን ከአክሱሞች ስለተቀበሉ፣ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ያለምንም ችግር የመንግስት ሃይማኖት ሆኖ ቀጠለ። ይኩኖ አምላክ ከዛግዌዎች ስልጣኑን ከቀማበት እስከ ግራኝ አህመድ ዘመቻ ድረስ ኦሮቶዶክስ አሁንም የመንግስት ሃይማኖት ሆና ቆይታለች። ይሁን እንጅ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑት ነገስታት ከኦሮቶዶክስ ውጭ ያሉ ሃይማኖቶችን ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ሆነው፣ የአስተምህሮ ልዩነት የነበራቸውን ሳይቀር፣ ሃይማኖታቸውን በነጻነት እንዳያስፋፉ ያግዱ ነበር። የደቂቀ እስጢፋኖሳውያን ታሪክ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነው። ደቂቀ እስጢፋኖሳውያን እስከመጨረሻው ኦርቶዶክሶች ነበሩ፣ከሙስሊሙ ወይም ከቤተ-እስራኤላውያን ባላነሰ መልኩ ወከባ ደርሶባቸዋል።
muslim and christian
ግራኝ አህመድ ዘመቻውን ወደ ሰሜን ባስፋፋበት ወቅት ደግሞ ቀድም ብሎ ክርስቲያን የነበሩት ዜጎች እስልምናን በግድ እንዲቀበሉ ተደርጓል። ግራኝ ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ ቆይቲ ቢሆን ኖሮ እስልምና የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እድሉ ሰፊ ነበር። ግራኝ በስልጣን ላይ በነበረባቸው አመታት እስልምና ዋና የአገሪቱ ሃይማኖት ነበር። ግራኝን ለመውጋት የመጣው የፖርቱጋል ጦር በበኩሉ አንዱ አላማው የካቶሊክ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ማስፋፋት ነበር። ገልውዲዎስ ፈቃደኛ ቢሆን ኖሮ ካቶሊክ የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እድሉ ሰፊ ነበር፤ አጼ ሱስንዮስ ሲነግሱ ግን ካቶሊክ የመንግስት ሃይማኖት ሆነ ። ኦርቶዶክስ የሆኑትም ያልሆኑትም እኩል ሃይማኖታቸውን እንዲለውጡ ተገደዱ። ካቶሊክ ለአጭር ጊዜም ቢሆን የመንግስት ሃይማኖት ሆነ፣ በዚህም የተነሳ ብዙ ደም ፈሰሰ። አጼ ፋሲል ሲነግሱ ደግሞ ኦርቶዶክስ ተመልሳ ከበሬታ አገኘት- “አጼ ፋሲል ነገሱ፣ ሃይማኖትን መለሱ” ተባሉ። ይሁን እንጅ በእርሳቸውም ጊዜ “ሁለት ልደት ፣ ሶስት ልደት፣ ቅባት ፣ ተዋህዶ” በሚሉ የአስተምህሮ ልዩነቶች ኦርቶዶክስ ትናወጥ ጀመር። ከዚያ በሁዋላ በመጡ መንግስታት ቅባቶች ሲያሸንፉ ተዋህዶዎች ተሳደዱ፣ ተዋህዶዎች ሲያሸንፉ ደግሞ ቅባቶች ተሳደዱ። በዘመነ መሳፍንት ጊዜ ደግሞ ለ90 ዓመታት ገደማ ማእከላዊ መንግስት የሚባልም ነገር ስላልነበር፣ የመንግስት ሃይማኖት የሚባል ነገር አልነበረም፣ መንግስት ነበር ከተባለም የይስሙላ ነበር። ከዚያ በሁዋላ የመጡት አጼ ቴዎድሮስ በኦርቶዶክስ ውስጥ የአስተዳደር“ ተሃድሶ” ለማካሄድ ሞከሩ። አብዛኞቹ አማካሪዎቻቸው ፣ ፈረንጆቹ ማለቴ ነው፣ ፕሮቴስታንቶች ነበሩ። ንጉሱ የኦርቶዶክስ ተከታይ ቢሆኑም ሃይማኖቱን ለማስፋፋት ወይም ሌላው ሰው ሃይማኖቱን እንዲቀይር ሲያስገድዱ አልታየም፤ ከኦርቶዶክስ ጋር የነበራቸው ግንኙነት መበላሸት ለውድቀታቸው አንዱ ምክንያት ሆኗል፣ ታሪክ አስተማሪዎቻችን እንደነገሩን ንጉሱ የፕሮቴስታንቱ ትምህርት እየጣማቸው ሄዶ ነበር። ከዚያ በሁዋላ የመጡት አጼ ዮሃንስ አራተኛ ደግሞ አጥባቂ ኦርቶዶክሳዊ ነበሩ። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በይፋ የመንግስት ሃይማኖት እንዲሆን ቦሩ ሜዳ ላይ ደንግገዋል። ሙስሊሙ ሃይማኖቱን እንዲቀይር አስገድደዋል፤ ከተዋህዶ ውጭ ያሉት፣ በተለይ ቅባቶች በጎጃም ( ምስራቅ ጎጃም) አካባቢ ተጠልለው እንዲቀሩ አድርገዋል። ለእርሳቸው ሃይማኖት ትልቅ ቦታ ነበረው።

እርሳቸውን የተኩዋቸው አጼ ሚኒሊክ ኦርቶዶክስ ቢሆኑም፣ ቀደም ብሎ ሃይማኖት የነበራቸው ሰዎች ፣ በተለይ ሙስሊሞች፣ ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ሲያስገድዱ እምብዛም አይታይም፤ ሃይማኖት የላቸውም ተብለው የሚታሰቡት ወይም ከኦርቶዶክስና እስልምና ውጭ ያሉት ግን ኦርቶዶክስን እንዲቀበሉ ተጽእኖ ይደረግባቸው ነበር። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ግን የመንግስታቸው ሃይማኖት ነበር፡፡ ከእርሳቸው በሁዋላ የመጡት ልጅ እያሱ፣ኦርቶዶክስን የሚወዱ ሰው አልነበሩም፣ ከስልጣን የወረዱትም የመንግስትን ሃይማኖት እስልምና ለማድረግ አስበዋል በሚል ተዶልቶባቸው ነው፤ በእርሳቸው ዘመን፣ ጊዜው አጭር ቢሆንም ከኦርቶዶክሶች ይልቅ ሙስሊሞች የተሻለ ተቀባይነት ነበራቸው፤ በእርግጥ አባታቸውም ቀደም ብሎ ሙስሊም የነበሩ ናቸው። ልጅ እያሱ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ ቆይተው ቢሆን ኖሮ፣ እስልምና የመንግስት ሃይማኖት እንኳን ባይሆን፣ እንደ ኦርቶዶክስ እኩል የመንግስት ሃይማኖት የመሆን እደል ይኖረው ነበር ብየ አስባለሁ።

አጼ ሃይለስላሴ ከእያሱ ውድቀት ተምረው ኦርቶዶክስ ተዋህዶን መንግስታዊ ሃይማኖት ሆኗል ብለው በህገመንግስት ደነገጉ፤ እርሳቸውን ዘመናዊውን ትምህርት ያስተሟሩዋቸው ሰው ካቶሊክ ነበሩ። አጼ ሃለስላሴ “ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት፣ የመንግስት ሃይማኖት ነው” ቢሉም፣ ሙስሊም በሙሉ በአንድ ጊዜ ኦርቶዶክስ እንዲሆን አላዘዙም፣ በሙስሊሙ፣ በካቶሊኩና በሌላው ሃይማኖት ተከታይ ላይ አስተዳደራዊ ተጽኖዎች አልነበሩም፣ የመንግስት አድልዎ አልነበረም ማለት ግን አይደለም ። ኮሎኔል መንግስቱ ሃየለ-ማርያም መጡና “እግዚአብሄር የሚባል የለም” ብለው ሙስሊሙንም ክርስቲያኑንም ኩምሽሽ አደረጉት፤ ሙስሊሙ የአሁኑ ይባስ አለ፣ ክርስቲያኑም፣ እግዞዎ አለ። ሙስሊሞች “አላህ በኖረና በተጨቆንን ፣ ኦርቶዶክሶች ደግሞ “እግዚአብሄር በኖረና መንግስታዊ ሃይማኖት መሆኑ በቀረብን” ሳይሉ የቀሩ አይመስለኛም ። መንግስቱ በሁሉም ሃይማኖት ላይ ሳያዳላ ነው የተነሳው፤ ያም ሆኖ ግን ጓድ መንግስቱ ሰዎች በአንድ ጀንበር ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ አላስገደዱም፤ የሚከተለውን ያውቁ ነበርና። ፕሮቴስታንትን በተመለከተም ኮሎኔል መንግስቱ፣ ፕሮቴስታንት ስለሆነ ብቻ፣ የተለየ አሉታዊ ተጽእኖ አላደረጉበትም፤ እርሳቸው ፕሮቴስታንት እንዲስፋፋ ያልፈቀዱት ሌላ ራስ ምታት ላለመጨመር ነው፣ ራሳቸውን ለማዞር ኦርቶዶክስና እስልምና በቂዎች ነበሩ። መንግስቱ ኮሚኒዝምን ትተው የምእራባውያንን ዲሞክራሲ ቢከተሉ ኖሮ፣ ፕሮቴስታንት ሃይማኖት እንደልቡ እንዲንቀሳቀስ ይፈቀድለት ነበር።

በኢህአዴግ ጊዜ ደግሞ ፣ ሙሉ መብትን የማይጠይቁ ሃይማኖቶች እስካልተነሱ ድረስ፣ ማንም የፈለገውን ሃይማኖት መከተል ይችላል። ሙሉ መብትን የሚጠይቁ ሃይማኖቶች ከመጡ ግን በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው መቀመቅ ይወርዳሉ።

እንግዲህ ሳጠቃልለው፣ ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እና ሃይማኖቱን ይከተሉ የነበሩ ነገስታትን ብቻ ጨቋኝ አድርጎ ማቅርብ ስህተት ነው። የኦርቶዶክስም ሆነ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ገዢዎች፣ ሃይማኖታቸውን በሃይል ለማስፋፋት ጥረት አድርገዋል፤ ገዢዎቹ እነሱ ከሚከተሉት ሀይማኖት ውጭ ያሉትን ዜጎች ብቻ ሳይሆን በአንድ ሃይማኖት ስር እንኳ ሆነው የተለየ አስተምህሮ ይከተሉ የነበሩትን ሳይቀር አሳደዋል። ኦርቶዶክስን ጨቋኝ ፤ ሙስሊሙንም ተጨቋኝ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው ሙከራ እጅግ አደገኛ ነው። ገዢው ፓርቲ ራሱን ለአንዱ የመስቀል ጦረኛ፣ ለሌላው ጂሃዲስት እያደረገ ለማቅረብ የሚያደርገው ሙከራ ከራሱ አልፎ ለአገር እንዳይተርፍ ፣ከአሁኑ እረፍ ሊባል ይገባዋል።

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ ገብተዋል ሲል ዘገበ

$
0
0

አቶ ሌንጮ ለታ “”ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን” አሉ
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ የሚታተመው አዲስ አድማስ ጋዜጣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ ከ3 ቀናት በፊት ገብተዋል ሲል ዘገበ። ዘ-ሐበሻ በዚህ ጉዳይ ላይ ለማጣራት ወደ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሕዝብ ግንኙነት አቶ ሌንጮ ባቲ በተደጋጋሚ ደውላ መረጃውን ለማረጋገጥ ባትችልም፤ ጋዜጣው ሌንጮ አዲስ አበባ ናቸው ሲል ዘግቧል። ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት “እነ ሌንጮ ለታ ኢትዮጵያ ሊገቡ ነው” የሚል እና “አቶ ሌንጮ ለታ “ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን” አሉ” የሚሉ ሁለት ዘገባዎችን ማስነበቧ ይታወሳል።

ከቀናት በፊት የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ መሳይ ዓለማየሁ ለኦቦ ሌንጮ በስልካቸው ደውሎ በጉዳዩ ላይ ሊያነጋግራቸው ፈልጎ ነገ ደውልልኝ የሚል ምላሽ ከሰጡ በኋላ በነጋታው ሲደወልላቸው ስልካቸውን ሳያነሱ እንደቀሩ የሚታወስ ሲሆን የኦቦ ሌንጮን ድርጅት እና ኢሕአዴግን እያደራደሩ ነበር የተባሉት ኤፍሬም ይስሃቅም እንዲሁ ድርድሩ ገና ያላለቀ በመሆኑ የምናገረው የለኝም ብለው ነበር። ዛሬ አዲስ አድማስ ሌንጮ አዲስ አበባ ገብተዋል ብሎ መዘገቡ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

የአዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደወረደ ዘገባ የሚከተለው ነው፡-

በኢትዮጵያ መንግስት “ሽብርተኛ ተብሎ የተሰየመው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር /ኦነግ/ ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ፣ አዲስ ያቋቋሙትን ፓርቲ ይዘው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል አዲስ አበባ መግባታቸውን ምንጮች ገለፁ፡፡ ኢህአዴግ የደርግ ስርዓትን አስወግዶ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ለፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ ተጠቁመው አልፈልግም ማለታቸው የሚነገርላቸው አቶ ሌንጮ፤ ወደ ሰላማዊ ትግል መግባታቸውን በተመለከተ ብዙዎች አምነው እንዳልተቀበሏቸው የገለፁ ሲሆን ከሶስት ቀናት በፊት አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል፡፡ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ኢትዮጵያ መግባታቸውን አስመልክቶ የቀድሞ ድርጅታቸው ኦነግ ስላለው አቋም ከውጭ ሚዲያዎች የተጠየቁት አቶ ሌንጮ፤ “እሱን ኦነግ ነው የሚያውቀው” ሲሉ መልሰዋል፡፡ የአቶ ሌንጮ ለታን ወደ ሀገር ቤት መመለስ አስመልክቶ አስተያየት የተጠየቁት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ቀደም ሲል ኦነግ በሁለት አመለካከቶች መሃል ሲዋልል የነበረ ፓርቲ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ አንደኛው፤ ኦሮሚያ ሙሉ ለሙሉ መገንጠል አለባት የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ትገንጠልም አትንገንጠልም በሚለው አመለካከት መሃል የሚዋልል ነበር ይላሉ፡፡

አሁን የእነ አቶ ሌንጮ ወደ ሠላማዊ ትግል መመለስ፣ በኢትዮጵያ አንድነት እምነት የነበረው አካል ተለይቶ መውጣቱን ያመለክታል ብለዋል፡፡ ይህም በበጐ የሚታይ ነው ያሉት ዶ/ር ነጋሶ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኦሮሞ ህዝብ ትግል መልካም መንገድ እንደሚከፍትም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ቀደም ሲል በኦነግ የፖለቲካ ትግል ውስጥ ማለፋቸውን “ዳንዲ፣ የነጋሶ መንገድ” በሚለው መጽሃፋቸው ጠቁመዋታል፡፡ ከኦነግ ዋና ዋና መሪዎች አንዱ የነበሩት ሌንጮ ለታ “ወደ ሰላማዊ ትግል ተመልሻለሁ” ማለታቸውን መንግስት ያውቀው እንደሆነ የተጠየቁት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል፤ በበኩላቸው፤ በግለሰብ ደረጃ የተሟላ መረጃ እንደሌላቸው ጠቁመው፣ አንድ ሽብርተኛ ተብሎ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰየመ ድርጅት ወደ ሰላማዊ ትግል መመለሱ የሚረጋገጥለትና ስያሜው የሚነሳለት ግን በራሱ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነው ብለዋል፡፡ አቶ ሌንጮ ለታን በአካል አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

ከቀናት በፊት ኦቦ ሌንጮ ለጀርመን ድምጽ ራድዮ የሚከተለውን ብለው ነበር፦

ሌንጮ ባቲ “ኦቦ ሌንጮ ፊንፊኔ አልገቡም፤ ኖርዌይ ነው ያሉት፤ በቅርቡ በግልጽ እንገባለን”ሲሉ የአዲስ አድማስን ዘገባ አስተባበሉ

$
0
0

lencho bati
(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሌንጮ ባቲ ከዘ-ሐበሻ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ የድርጅታቸው መሪ አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዛሬ እንደጻፈው ኢትዮጵያ አልገቡም፤ ኖርዌይ ነው ያሉት አሉ። ዛሬ ኦቦ ሌንጮ ባቲን ኖርዌይ ደውዬ በስልክ አዋርቻቸዋለሁ ያሉት አቶ ሌንጮ ኢትዮጵያ የምንገባው በድብቅ ሳይሆን በግልጽ ነው ብለዋል። ድርጅታችን ሃገር ቤት ገብቶ መታገልን የወሰነው አሁን አይደለም ያሉት አቶ ሌንጮ ባቲ በቅርቡ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ፤ የአዲስ አድማስ ወሬ መሠረተ ቢስ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

ከዘ-ሐበሻ ጋር ያደረጉትን አጭር ቃለ ምልልስ ለማድመጥ ይኸው ሊንኩ

የአዲስ አድማስ ዘገባን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ዴሞክራሲ ከማን ይጠበቃል??

$
0
0

ከነብዩ አለማየሁ /ኦስሎ ኖርዌይ
ዴሞክራሲን ለማምጣት እርስ በእርስ መደማመጥና ሃሳብን በነፃ ማንሸራሸርን ይጠይቃል ይሄ ዋና መሰረታዊ ነገር ንው።
እስቲ የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ እንዳስ በኢትዮዽያ የህውሀት መንግሥት አመጣጡ እንደኔ ዓመለካከት ጥቂት የትግራይ ገበሬ ልጆች በኤርትራ የሻብያ እንቅስቃሴ በማየት ለምን እኛስ ሀገራችንን ትግራይን ነፃ አናወጣም ብለው ነፍጥ ይዘው ጫካ ገቡ በጊዜው የደርግ መንግስት በብዙ ሀገር ወዳድ ኢትዮዽያዊያን የተቀጣጠለውን ዘውዳዊውን ስርኣት አስወግዶ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲውተረተር የእንዚህ ጥቂት የዘረኝነት ዐባዜ የተፀናወታቸው ጥቂቶች ኣላማቸውን ለማሳካት ኣመቺ ጊዜ ተፈጠረላቸው በተጨማሪም በወቅቱ ሿብያ በኤርትራ በኩል ያድርገው የነበረው ጦርነት የደርግን አትኩሮት በተሻለ መልኩ መሳቡ ተመቻቸው በሶማልያ በኩል የሚካሄድውም ጦርንት ሌላው ምቹ ኣጋጣሚን ፈጥሮላቸው ነበር።
tplf
እነዚህም የትግራይ ልጆች በዙ ተባዙ በትግራይም ጫካዎች ውስጥ ተሰባሰቡ ነገር ግን በህልምም ይሁን በውን በኢትዮዽያ ዴሞክራሲን ለማስፈን የህግ የበላይነትን ለማስከበር ኣላማ አልነበራቸውም በጭራሽ ኣላማቸው ኣንድ ና ኣንድ ነበር የትግራይ ህዝብ ነፃ ኣውቺ ነበሩ ከእነርሱ ዴሞክራሲን መጠበቅ የማይታስ ነው።

የእውነቱ ሌላው እይታ በትግራይ ጫካ የበዙት የቀድሞው ታጋዮች የደርግ መዳከም ምቹ አጋጣሚ ፈጠረላቸው ተከዜን ተሻገሩ ያኔ ኢትዮጵያን መቆጣጠር እንደሚችሉ ሁኛ ሰው ከወደ UN ሹክ ኣላቸው ያኔማ ለኣማራው ፥ ለኦሮሞው ፥ ለቤሄሩ ሁሉ ተወካይ ፈላልገው ካገኙ ቡሃላ ሰተት ብለም ገቡ ።

በስልጣን ለመቆየት አንዱን ብሄር ከሌላው ማጋጨቱን ተያያዙት ከዚያም እነርሱ የተዋደቁለትን ዐላማ ማራመድ ጀመሩ የሃገሪቱን ዋና ዋና ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታነት በማዘዋወር ሰበብ ወሰዱ ትልቅ የቢዝነስ ኢምፓየር አቋቋሙ ለኢትዮዽያ ህዝብም የይስሙላ ህገ መንግስት ጣል ተደረገለት እንርሱ ቀጠሉ መሠሎቻቸውን አምጥተው በመሀበር ቤት ስም ና በኮንዶሚኒየም ስም ከተሙ።
hailemariam and samora
ኢትዮጵያ ያሉ ጥቂት ጋዜጦችና ፓርቲዎች ዴሞክራሲን እንፈልጋለ ሲሉ እሺ ይታሰብበታል በማልት ስራቸውን ቀጠሉ የሃገሪቱዋን መሬት ለበዓድ ሸጡ ተከታዮቻቸውን በሃገር ውስጥና በውጪ ልከው አስተማሩ ኣላማቸውን የሚያሰናክልና ከእንርሱ ሃሳብ ውጪ የሆነውን ሁሉ ኣሰሩ ዓልያም ከሀገር አስወጥተው ለስደት ዳረጉት ዋናውን ዓላማቸውን ኣልሳቱም የራሳቸውን ሰዎች ኑሮ ማሻሻልና በኢትዮዽያ የበላይ ሆኖ መታየት። እኛም ኧረ ዴሞክራሲ ኧረ ነፃነት ኣልን ወይ ዴሞክራሲ ዓንዳንዶቹ እንዳውም ዴሞክራሲ ከፈለጋችሁ ጫካ ግቡ ማለት ጀመሩ በዚ መሃል ባዘጋጁት ምርጫ በተገኘች ትንሽ ክፍተት ያኔ የኢትዮዽያ ህዝብ እንድሚጠላቸው ግልብጥ ብሎ ውጥቶ ኣሳያቸው ከዚያም ገድለውም ኣስረውም ገርፈውም ቢሆን ካረጋጉ ቡሃላ በውንም ይሁን በህልም ይህ ኣይነቱ ስተት ዳግመኛ እንደማይደገም ቃል ገብተው እስከ መጨረሻው ጭላንጭሉን አዳፈኑት።

ሀይልማርያም ጠቅላይሚንስትር ሆነ ያኔ ከጀርባ ሆነው ኢኮኖሚውን ፥ መከላከያውን ፥ ደህንነቱንና ውጪጉዳዪን ህውሀቶች በመቆጣጠር እኛ ዴሞክራሲያዊነን በህጉ መሰረት የስልጣን ርክክብ ዓደረግን ኣሉን ታድያ እውነት ከነኚህ የምንሻውን ዴሞክራሲ የሠፈንባት እኩልነትና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ኢትዮዽያን ከህወሓት መጠበቅ የዋሀneት ነው ። ካለን ተሞክሮ እናም እንደኔ ሃሳብ ስልኛ ነፃነት ከኛ ሌላ ሊጮህልን የሚችል የለምና ልዩነታችንን አቻችለን ሁላችንም በትግላችን እንፅና።

ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ የኅዝብን/የምዕመናንን ውሳኔ በሙሉ ማስፈጸም ነው!!!

$
0
0

ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የአስተዳደር ቦርድ ኃላፊነትና የሥራ ድርሻ የኅዝብን/የምዕመናንን ውሳኔ በሙሉ ማስፈጸም ነው!!!

01/19/2014

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ፤ አሜን።

በምእመናን ተመርጠው ቃል የገቡ አንዳንድ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ባለፈው ዲሴምበር 15 ቀን 2013 ዓ.ም የቤተከርስቲያናችን ጠቅላላ ጉባዔ ቤተከርስቲያናችን በአባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየትና መወጋገዝ እስኪያበቃና አንድ እስኪሆኑ ድረስ ለ20 ዓመታት ስትመራበት የነበረው የገለልተኝነት አስተዳደር እንዲቀጥል በማለት በከፍተኛ አብላጫ ድምጽ የወሰነውን ውሳኔ አንቀበለውም አናስፈጽምም በማለት ላይ ይገኛሉ። ይህም የተመረጡበትን አላማ አለማወቅና ኅዝብንም የመናቅ አካሔድ ነው። በምእመናን የተመረጡት የራሳቸውን ፍላጎትና አላማ ለማስፈጸም ሳይሆን የህዝቡን ውሳኔና ድምጽ በሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ ነው።
deb
የቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5 ክፍል 3 ‘ሀ’ በግልጽ እንደሚደነግገው ‘‘ የቦርዱ አጠቃላይ ኃላፊነት ጠቅላላ ጉባኤው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በሙሉ በሥራ ላይ ማዋል ይሆናል’’ ይላል። በተጨማሪም በአንቀጽ 4 ‘ሸ’ ላይ ‘‘ በጠቅላላ ጉባዔ የሚወሰኑ ውሳኔዎች በሙሉ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተግባራዊ ይሆናሉ’’ ካለ በኋላ የቦርዱን ሊቀመንበር የሥራ ኃላፊነትና ተግባር በዘረዘረበት አንቀጽ 6 ክፍል 3 ‘ሀ’ ላይም ‘ሊቀመንበሩ የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔዎችን በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል።’ በማልት በማያሻማ ሁኔታ በኅዝብ ድምጽ የተመረጡ የቦርድ አባላትን ኃላፊነትና ተልዕኮ ደንግጎ ይገኛል።

ቤተክርስቲያናችን ደብረሰላም መድኃኔዓለም የምትተዳደረው በሕግና በሥርዐት ነው። በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 1 ክፍል 3 ውስጥ እንደሰፈረው አስተዳደርን በተመለከተ ቤተክርስቲያኗ የምትመራው በሚኔሶታ የቤተክርስቲያናት ማቋቋሚያ ሕግ መሠረት ነው። ግልጋሎትም የምትሰጠው በአሜሪካ የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት ከታክስ ነጻ የሚያደርገውን መመሪያ 501c(3)ን ተከትላ ሲሆን ከእነኝህ ሕግጋት መውጣት ወይንም ባልተጻፈና ስቴቱም ሆነ ፌደራል መንግሥቱ በማያውቁት ሕግና አሠራር መመራይ ቅጣቱ ከባድ ነው። ከዚህ አኳያ የቤተክርስቲያናችን የኅዝብ ተመራጭ የቦርድ አባላትም ሆኑ ካህናት እንዲሁም ምእመናን ባጠቃላይ ቤተክርስቲያናችን የምተደዳደርበትን የውስጥ ደንብና ሕግጋት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሕጎችን ማወቅና ከእነርሱም ጋር የማይጋጭ አካሔድን መከተል ይጠበቅባቸዋል። ይህን ባለማወቅ ከሕግና ሥርዓት ውጪ በሆነ አካሔ በሚደረግ እንቅስቃሴ ምክንያት በግል ሕይወትና ታሪክ እንዲሁም የሕብረትሰባችንን መልካም ስም በማጉደፍ የሚደርሰው ጉዳት ቀላል ሊሆን እንደማይችል ከወዲሁ አበክሮ ሊታሰብበት ይገባል። ሕግን አለማወቅ ከቅጣት አያድንምና!

በምንኖርበት አገር ሰው ሁሉ በማናቸውም ሁኔታ ድምጹን የመስጠትና ያለምስጠት፣ የመደገፍና ያለመደገፍ መብት ያለው ሲሆን፤ ትክክል አይደለም ብሎ ያመነበትን ጉዳይ ደግሞ ሕግን ብቻ ተከትሎ አቤቱታውን ማቅረብና በፍርድቤትም ሆነ በሚመለከትው አካል ብይን የማግኘት መብት አለው። ከዚህ ተጻራሪ በሆነ ሕገ-ወጥ አካሔድ በመሔድ ግን ማናቸውንም ፍላጎት ወይንም አላማን ማስፈጸም ግን በፍጹም አይቻልም። ምክንያቱም በተለምዶ እንደሚባለውና በርግጥም እንደምናየው THIS IS AMERICA! ስለሆነ ነው።

ምናልባት ከውጪ ሆነው ግፋ በለው እያሉ የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለማናጋት እየሰሩ ያሉ የወያኔ ፖለቲካ ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ሆድ አደር ጋሻ ጃግሬዎች በተለያዩ አካባቢዎች እንዳደረጉት ቤተክርስቲያናችንን የማዘጋትና አገልግሎቷን የማቋረጥ አላማ የሚሳካላቸው መስሏቸው ከሆነ ፈጽሞ ተሳስተዋል።

ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም እውነተኛው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነትና ሥርዓት ብቻ የሚፈጸምባት ቦታ እንጂ የዘረኝነት አቀንቃኞች መፈንጫ ከቶውንም አትሆንም!

በኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፖለቲካ ጣልቃገብነት(በወያኔ ቀጥተኛ ጣልቃገብነት) በአባቶች መካከል የተፈጠረውን መለያየት በምንም መሸፋፈንና መቀባባት አይቻልም። ይህ መከፋፈል የመጣው በኃይማኖት ላይ የተለያየ አቋም ስላለ አይደልም። የቤተክርስቲያንን መዋቅራዊ አሰራር ባለማወቅ የተከሰተም አይደለም። ወይንም የአባቶች ጳጳሳትን ክብርና ድርሻ ካለማወቅ የመጣ አይደለም። በውጪ አገርም አገር ቤት የሌለው ነፃነት ስለተገኘ አይደለም። የቤተክርስቲያን ቀኖናና ነፃነት በፖለቲከኞች መጣሱን፣ የአገር ሉአላዊነት መገሠሡንና የኅዝብ መብት መገፈፉን ተከትሎ እንጂ! ስለሆነም በማጭበርበርና ሕገወጥ አካሔድ በመከተል የሚመጣ ለውጥ ስለሌለ አርፎ መቀመጥ ይበጃል እንላለን።

እጅጉን ከሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ለዚሁ የጥፋት ተልእኮ ወያኔ ያሰማራቸው የቤተክርስቲያንን እና የህዝብን ገንዘብ ዘርፈው ሳለ በወንጄል የሚፈለጉ ሰው ስለመልካሚቷ ቤተክርስቲያናችን የሐሰትና የጥላቻ ስብከታቸውን ማሰማታቸው ነው። አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዲሉ በዘረፉት የኅዝብ ገንዘብ ምክንያት በወንጀል ስለሚፈለጉ ወደ አገር ቤት ለመሔድና በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንኳን ለመገኘት የማይችሉ ሰው በዓለም ላይ የተናኘ ኦርቶዶክሳዊ አገልግሎት እየሰጠች ያለችን ቤተክርስቲያን መሳደባቸው ከማሳዘንም አልፎ ያስገርማል። ይቅርታ አባ ዘካርያስ ሚኔሶታ የሚዘረፍ ቤተክርስቲያንም ሆነ ገንዘቡንና ንብረቱን አሳልፎ የሚሰጥ ምእመንም የለም!!!

እኚህ ሰው ላለፉት 5 ዓመታት በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አልተገኙም። እንደቤተክርስቲያ ሕግ ግን ከሁለት ጊዜ በላይ መቅረት አይቻልም። እርሱም በፈቃድና በበቂ ምክንያት ብቻ ነው። የቀድሞው አባ ጳውሎስ ከወንጀል ክስ ለማሸሽ ሲሉ በቅጡ መናገር እንኳን የማይችሉትን ሰው በአሜሪካ መድበው በውጪው ዓለም ብዙ መስራት የሚጠበቅባትን ቤተክርስቲያን እያዘቀጧት ይገኛሉ። ገንዘብና ንብረታቸውንም አናዘርፍም ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይዘልፋሉ። ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ሞተናል ካሉ በኋላ ለአለማዊ ፖለቲከኞች ተገዝተው ቅድስቲቱን አገርና ንጽሕት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ከሚያጥፋ ኃይል ጋር ሆነው ፍርድን ለራሳቸው ያከማቻሉ። እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው።

በመጨረሻም የሚኔሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ምእመናን ዛሬም እንደትናንቱ ቤተክርስቲያናችንን ከውስጥና ከውጪ አፍራሽ ቡድኖችና ግለሰቦች ነቅተን እንጠብቅ።
ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምእመናን።

በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!

$
0
0

By BERHANE ASSEBE

Dccc
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።
በአሁኑ ስዓት ኢህአዴግ/ህወሃት ለግልና ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል የኢትዮጵያን አንድነት በማደብዘዝ እንሆ በእኛ ዘመን ለዘመናትተደፍሮ የማያውቀውን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የኢትዮጵያ የሉአላዊነት ባለቤት የሆኑት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሳይወያዩበትና ሳያፀድቁት በጓሮ በር የኢትዮጵያን መሬት ለባዕድ ሃገር/ሱዳን ቆርሶ ለመስጠት ሽርጉዱን ተያይዞታል። ከአመታት በፊት በምዕራቡ የሃገራችን ክፍል /ድንበር በኩል/ በመሸራረፍ ለም የሰሊጥ ምርት የሚሰጥ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ዝም በማለታችን እንሆ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጋፋ ፣ የኢትዮጵያን ቅርጽ የሚያጠፋ ረጅም ርዝመት ያለው ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ሰማን ።

ዛሬ ላይ ሆነን ይህንን መሰሪ ተግባር አንድነታችንን አጠናክረን መግታት ካልቻልን ነገ ደግሞ በሌላኛው የኢትዮጵያ ጫፍ በኩል የኢትዮጵያ መሬትተቆርሶ ለሌሎች አጎራባች ሀገራት ላይሰጥ ምን ዋስትና አለን ?
አያቶቻችንና አባቶቻችን ደማቸውን ገብረው ፣አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡንን የሀገር ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የእኛ የአሁኑ ትውልድ የታሪክ ግዴታ ነው። ይህን የታሪክ ግዴታችንን ሳንወጣ/ችል በማለት/ በመሰሪው የህወሃት/ ኢህአዴግ አመራር የሃገራችን ሉአላዊነት እየተሸራረፈ ለባዕድ ሀገራት ሲሰጥ በምን አገባኝ ስሜትዝም ብለን ብንመለከት በ– ዚ–ያ ዘመን ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ የውጭ ጠላትጋር የሀገሬን ሉአላዊነት አላስደፍርም በማለት በዱላ፣ በጦርና ጋሻ፣ ዘመናዊ ባልሆነ የጦር መሳሪያ ፣በባዶ እግራቸው በመዝመት ደማቸውን አፍስሰው ፣ አጥንታቸውን ከስክሰው የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ሳያስደፍሩ ያስረከቡን የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይወጋናል።

«የኢትዮጵያ ድንበሮች በኢትዮጵያውያን ደም የራሱ፣ በኢትዮጵያውያን አጥንት የተገነቡ ሲሆኑ ድንበሮቻችንን ለማስከበር ከሁልቆ መሣፍርት፣ ተራ ዜጐች አንስቶ እስከ አንድ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት አጼ ዮሐንስ አንገታቸው ሰጥተዋል፡፡ በዶጋሊ፣ በጉራዓ፣ በጉንዲት፣ በመተማ፣ በአድዋ፣ በወልወል በቅርብ ጊዜያት ደግሞ በሶማሊያና በኤርትራ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም የሌላውን ግዛት በመቋመጥ ሳይሆን ድንበሬን አላስነካም በሚል ነበር፡፡ እንደዛሬው መኪና ወይንም ባቡር ባልኖረበት የቀደምት ኢትዮጵያውያን ከመሃል አገር ተነስተው በእግር ለወራት በረሃውን አቋርጠው፣ ተራራውን ወጥተው፣ ንዳዱን ተቋቁመው፣ ወባውን ደፍረው ከሙስታሂል እስከ ጋምቤላ፣ ከራስ ካሣር እስከ ሞያሌ ዘልቀው ድንበሩን ሰፍረው ኢትዮጵያን ለዚህ ትውልድ አስረክበው ሄዱ፡፡ ይህ ተረካቢ ትውልድ የተረከበውን መሬት ሳይቀነስ ለቀጣዩ ትውልድ ያስተላልፋል ይሆን—-«ከያዕቆብ ኃይለማሪያም/20 July 2008/።
ይህ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን አደራ ጠብቆ የሀገሩን ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ በማስከበር ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት የለበትም ። ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ውጭ በሚስጥር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተደረገውን የውል ስምምነት የፖለቲካ ልዩነት፣ ብሄር፣ ሃይማኖት፣አመለካከት ሳይለያየን የፖለቲካፓርቲዎች ፣ ድርጅቶች፣ ሲቪክስማህበራትና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በጋራ ተንቀሳቅሰን አሁኑኑ ማስቆም ካልቻልን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከማስደፈርም አልፎ እስከ ወዳኛው ትውልድ ድረስ ብጥብጥና ትርምስን የሚያወርስ ስውር ደባ ነው።
በመሆኑም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት በመጋፋት ለም መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት አገር ወዳድ የሆንን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በጋራ በመንቀሳቀስ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም! በሚል መርህ ተግባብተን ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም ግዜ ሳንወስድ በያለንበት ፈጥነን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል።
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ ሀገር አሳልፎ የመስጠት ታሪክ አልወረስንም!


የውስጤ ብቁ ዳኛ!

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

አምቄ ብይዘውም ጠብታወቼ ዘመን አመጣሹን ብራና አራሱት
አይቀርም ደግሞ ደረሰ …. ጥር 21 የሚሉት ….
ለብር አንባር – የካቴና እራት የዶለተ – ጨጎጎት ….
የዓይናማዋ የመከራ ቀን አከባበር የልደት።
reeyot alemu
ወጣትነት ውበት የሚሆነው ቀድሞ ማለም፤ ቀድሞ መሆን ሲቻል ብቻ ነው። ወርቅ በእሳት እንደሚነጥረው እንሆ በዬጊዜያቱ የነፃነት ደቀ መዝሙራት የሆኑት የኢትዮጵያ ወጣቶች ማገዶ ሆነው ይነዳሉ፤ ይፈልቃሉ ወጣትነታቸውን በመሰዋት — በሐዋርያነት። እነሱ አራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡበት ሚስጢር ኢትዮጵያዊነት ነው – ትኩስ ሁልጊዜም ቋያ ነው። የእናቱ ነገር አይሆንለትም። ገላጫቸው ብሄራዊነት ነው፤ ማንነት ላላው ጌጣማ ዜግነት የሚከፈል ታላቅ ዋጋ፤ አብይ ጉዳይ፤ እራስን ፈቅዶ ለበለኃሰብ የሰጠ የፍጽምና ገድል። ወጣቶቹ የሚከፍሉት ምክንያታዊ ግብር የአደራ ዕዳ ነው። ወጣት የሀገሩን ክብር ረዘም አድርጎ የሚያይ ድንቅ የማህበረስ አካል ነው። እግዚአብሄር ይስጥልን የእኛ መብራቶች። ለሰማዕታትም በአርያመ – ገነት ያኑርልን አባታችን ክርስቶስ። አሜን!

ጥር ጣና ዘገሊላ – የእናት ክብር ብቸኛው ጊዜው ሳይደርስ ታዕምር የተገለጸበት ሚስጢራዊ ወርኽ ነው። ወጣትና የእኩልነት መምህር፤ ዓላማውን ያወቀች፤ መንገዷን ጠንቅቃ የተረዳች፤ የምልዕትን አንጡራ የህልውና ፍላጎትን አስመችታ በልቧ ጽላት በቋሚነት ያነጸች የጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ልደት እ.ኤአ. ጥር 21.20014 በነፃነት ፈላጊ ቤተሰቦች በውስጥነት ደምቆ ይከበራል። በቃሊቲ እስር ቤት በአጋዚ የጭካኔ መጋዘን ግን ይከበራል ከምል ይልቅ በቋሳ ይቀጠቀጣል፤ በግፍ ይቀጣል፤ በበቀል ይጨቀጨቃል ብል ይሻላል። አህህህ …

ክብርት እህታችን … በወፈ በላ ታጥራ፤ በጉልበተኞች ታፍና፤ እዬተገላመጠች፤ በክፉ ዓይን እዬተገፈተረች የሚከበር ጥቁር ዕለት። አስኪ ይሁን ትኑርልን። … ትሰንብትልን። እርግጥ ነው ይህ ጥንካሬ የሴቶችን የብቃት ልኬታ ሙሉ አቅም በእጅጉ ያጎላዋል – ነገ ደግሞ ካልዘለልነው።
በ2005 ዓ.ም የዘሃበሻ ማህበራዊ ድህረ ገጽ ድንቅ ሰው ተብላ በህዝብ ድምጽ የደመቀቸው፤ በተመሳሳይ ዓመት ማለት በ2013 እ.ኤአ. ዬዓለምዓቀፍ ሽልማት ያገኘችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የ2006 ዓዲስ ዓመትን በወያኔ ቀደመት አቀንቃኝ በኮ/ሌ ኃይማኖት የሚደርስባትን ዙሪያ ገብ ፈተና አሻም ብላ፤ በራህብ አድማ ነበር የተቀበለችው። ከወላጅ እናቷ በስተቀር ከዕምነት አባቷ ጀምሮ የቤተሰብ ጥዬቃ ማዕቀብም ተጥሎባት እንደ ነበር ይታወሳል።
የእኩልነት ህሊናችን! ለወያኔ ቀለጦና ተውሳክ ፍላጎት እስር ቤት ሆና የምትጋተራዋ ቀንበጥ፤ በራስ የመተማመን ስሜቷ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ነው፤ ድፍረቷም ሙሴ ነው፤ ስለሆነም ወጣቷ ጋዜጠኛ ነገሮችን ከተለያዬ አቅጣጫ ተመልክታ የምትሰጠው አፋጣኝ ውሰኔና የምተወስደው ቁርጠኛ እርምጃ ለተለዬ ተልዕኮ ፈጣሪ አምላካችን መምረጡን ያመላክታል። ከልብ ካስተዋልነው። የምትመክታቸውን የፈተና ትብትቦች ሁሉ በዘርፍ በዘርፍ ለይተን ስንመረምራቸው አባታችን መዳህኒተአለም ለዚህ ታላቅ ኃላፊነት እንደመረጣትም ይተረጉምልናል። የህሊናዋን መስኮት ቧ አድርጎ ከፍቶ የብርሃኑ ተጠቃሚ እንድንሆንም ፈቅዶልናል። አዬን ሰማን … በታናሻችን …. ድንቅ ነገር። ከድንቅ ፍሬ ሲገኝ ዘሩን ማብቀል ደግሞ የእኛ ተግባር ይመስለኛል።
አህትዓለም! እንኳንም አደረሰሽ የእኔ የነፃነት አረበኛ! አንበሲት! ግንባር ቀደምት ቅንነት – የውስጤ ብቁ ቀጥተኛ ዳኛ! እንኳንም በመከራ ተከበሽ ይህን ቀን ለማዬት አበቃሽ – አንቺ ቀለሜ! እመቤቴ ….. ዘመኑን በመከራ፣ እኩልነትሽን በአሳር በከዘነው፤ የአፍላ ዕድሜሽን የወጣትነትሽ ውበት ፈተና በስፋት በሚናኝበት፤ አፍ ባላው መቃብር ሆነሽ፤ በሰንሰለት ታስረሽ እኩልነትሽን በነጠረ አስተምህሮ በኪዳን አከበርሽው። እግዚአብሄር ይስጥልን አንቺ የጽናት ልዩ አድማጭ።

እንቺ …. ትርጉም
የማንነት ንቁ ዓለም!
መሆንን በመቻል ይሁንተኛነት፤
ቀደምሽለት ….
አንችኑ እራስሺን ማግደሽ …. በሐሤት – በቀሉን – አዋዋጥሽበት፤
አዳራን – ልታበሪ
ዘመንን – ልትገሪ
ነገን ልታስተምሪ! ውብ ድሪ …. የእናት ጠበቃ – የነፃነት ቃና ዘማሪ!

አንቺ ፋና! … ፈተናው በጸጋ ተቀብልሽ፤ መንፈስሽን በቋሚ ብርታት ገርተሽ፤ ወጣትነትሽን ለእኛ ሸልመሽ። አንቺ በጨለማ አሳርሽን – ፍዳ – መከራሽን – ታያለሽ። በጽኑ በሽታ እዬተሰቃዬሽም እንሆ ለእኛ አንችን – ውስጥሽን በልግሥና ታድያለሽ። አንቺ የዕልፍ ትውልዳዊ ድርሻ ቀዳሚ …. ችግርን በፈቃድሽ ተቀብለሽ የምትቀልጪ የአንስት አብነት፤ የወጣትነት ልዩ ጉልላት፤ ማን እንደ አንቺ? …. – ሁሉንም ታግሰሽ ተሸከምሽ።

ውዴ! ታመሽ ባጠገብሽ ማንም ሳይኖር፣ አረመኔው ወያኔ እያለሽ ሞት የፈረደብሽ የዛሬም፤ የነገም የነፃነት ወጋገን…. አይዞሽ! … እናትዬ አምላካችን ፈተና ከሰጣቸው ጋር ነውና ብርታቱ ተስፋሽ፤ ቅዱስ መንፈሱ ደግሞ ጠባቂሽ ይሆናል። ቀን ደግሞ ለቀን ይሰጥና ቋሰኞችን እዬደነ ይቀጣል። ይህን ያደርጋል የፈጠረሽ አምላክ። ለቅኖች ቅርብ ነውና የመሃፀን ምር ሀዘንም ፈሶ አይቀርም … እንዲህ እንደ ዋዛ ወጣትነትሽን ለነፃነት አርበኝነት ወደሽ ማስበለታሽ ከንቱ አይሆንም። አንድ ቀን አዎን አንድ ቀን … ምላሹ ጣፋጭ ይሆናል። የመከራሽ ዋጋ ታሪክን ይፈጥራል – ይሰራልም። ታሪክ ያደምጣል – ትውፊት በአስር እጣቱ ፈርሞ ይቀበላል። የሴቶች የወጣቶች ዝክረ ገድል የህዝብ አንጡራ ሃብት ይሆናል።

ውስጥሽ ፍሬ – ዘር
ትንፋሽሽ – የነፃነት ሃር፤
ርዕዮት የነገ መንበር!
አንቺ የእኛ ….
አንቺ ብርቱ የአርነት ጽኑ ዘበኛ፤
የፍቅር ማዕድ ሁነኛ!

ይህቺ ፍቅር! ትንሽ ብልህ ብላቴና! በዚህ ዕድሜ፤ ከእሳት ከውሃ በሚባልበት ወቅት ላይ ወጣትነቷ የሚያዛትን ሥነ – ሕግጋት ተላልፋ በቃኝን በድርጊት ቀድማ፤ በአርያነት እንሆ ትመራናለች የመሆን እሸት። ወጣትነቷን ይፈሩታል፤ ሴትነቷንም እንዲሁ። ለዚህም ነው የእግር ብረት ቤተኛ እንድትሆን የተፈረደባት። በፈንጅ ወረዳ ተከባ ስለ እውነት መሰከረች፤ ስለሃቅ ሰበከች፤ ስለ ነፃነት አወጀች፤ ረመጡን ፈቅዳ በመቀበል ስለ ነገ ብሩህ ቀን ተግባርን ቀለበች፤ ስለ አዲስ የፍትህ ሥርዓት ነገረች – „ጠንክራቸሁ ታገሉ“ ብላም ጥብቅ መልዕክት ላካች – ጋዜጠኛና …. መምህርት ርዕዮት ዓለሙ።
እኛስ ወገኖቼ … ካለንበት ወይንስ ብጣቂ ፈቀቅ አልን ይሆን? እንፈታተሽ – ከህሊናችን ጋር …. ለፊርማ አንኳን ተለምነን ነው። የእኛ ተግባር የሎቢ ሆኖ፤ አትራፊነቱም የወርቅ ክምችት ሆኖ ግን አንተጋም። ነጮቹ አይደለም የብዙኃን ሰብሰብ ያለ ድምጽ ቀርቶ ለአንድ ሰው ብጣቂ አረፍተ ነገር እንኳን ክብር አላቸው። እባካችሁ እንበርታ፤ ቋሚ ተግባራትንም ተከታታይነት ባለው ሁኔታ እንፈጽም። አንድ ሰሞን ሞቅ ሌላ ጊዜ ቀዝቀዝ አናድርገው፤ የወያኔ የካቴና ኑሮ እዬባሰ፤ እዬከፋ ከመሄድ እኮ ለዘብ አላለም ….

መንፈስሽ ሲያማትር
ነፃነት ሊመትር …..
ሆንሽለተኝ ማገር።

የእኔ ውስጥ!…. የእኔ እናት አንቺ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን አሥራት ….
ለህግ የበላይነት፤ ለሰብዕዊ መብት መከበር፤ ለተስተካከለ ሚዛናዊ አስተዳደር፤ እኩልነትን ለሁላችን ልትመግብ የምትችል እናት ኢትዮጵያን ለማግኘት፤ ከቶም በማይቻልበት ሁኔታ፤ ፊት ለፊት ተጋፍጠሽ የምትከፍይው መስዋዕትነት ለትውልዱ ታላቅ ክበረ ወሰን ነው። ዓለምንም አስተምሯል። እስር ቤት እንኳን፤ በዛች በተጣበቀች የድቅድቅ ዛኒጋባ እንኳን፤ ይህም ተቀንቶበት አዬሩ እንዲታውክ በውስጥም በውጭም ሙጃው ወያኔ የሚያደርስብሽ ተጽዕኖ የበቀል አምላክ ቸል ሳይለው በእጥፍ ድርብ ዋጋቸውን እንደሚሰጣቸው በፈጣሪዬ እተመመናሉሁ! ዕንባ ፈሶ አይቀርም፤ ዋጋ ያስከፍላል በእጥፍ ድርብ።

ጌጤ! … አንቺ የነገን ቀና መንገድ አላሚ — የዕውነት ፍሬ እግዚአብሄር አምላክ መከራውን ሁሉ የምትታገሺበት ጉልበትና አቅም ይሰጥሽ ዘንድ አዘውትሬ ለአምላኬ፤ ለፈጣሪያ ሳልቦዝን አቀርባለሁ። ድንግልም አትተውሽም እናት ትደባብስሽአለች። አቅሜ ይህ ብቻ ነውና። አሁንም አይዞሽ! በርችልን የእኛ የነፃነት ራህብተኛ፤ የርትህ ናፋቂ፤ የእኩልነት አስተማሪ – የሰማይ ሲሳይ!
ክውና
አንቺ የእኔ ለጋ፤ እጅግ የምሳሳልሽ ታናሼ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ … እንዲህ የተግባር ጋት ሙሉዑ ሆኖ መስካሪ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ክብር ነው። በዚህ ዘመን ኢትዮጵያን ከገደለ፤ ዳር ደንበሯን ካስደፈረ፤ ትውልዱን ከተበቀለ፤ ታሪክን ከደለዘ፤ ነገን ሳይመጣ አስቀድሞ ለማሰረር ታጥቆ ከተነሳ፤ እልፎችን በማንአለብኝነት ከቀጠቀጠ አረም ድርጅት ከወያኔ – ፓሊሲ ጋር – ግብረ አበር ሳትሆኝ፤ ነገር ግን የነፃነት መዝሙር፤ የአርነት ዜማ መሆንሽ ኩራት ነሽና ጽናቱን ፈጣሪ አምላካችን ጨምሮ በገፍ ይሥጥልኝ። አሜን! የተመረጥሽው ለዚህ ነው። ይህ ጸጋሽ ነው። አምላክሽ የመረቀልሽ – ሻማነት! እኛም ታድለናል ለሞት የቆረጣች ታናሽ እህት ስለ አገኘን። ከሁሉም ነገር መማርን ከፈቀድንለት መማር እንችላላን። ባለውለታችን ነሽ። የሀገራችን ሆኖ የመገኘት ሰንደቅዓለማም።
በተጨማሪም ድንቁ ነገር የቤተሰቦችሽ ብርቱነት ናሙናነት ነው። የነፃነት ትርጉም የገባቸው ወላጅ አባትሽም በጣም ብዙ ርቀው አሰተማሩን። አጋጣሚው በብዕር ካገናኘን ዘንዳ ዝቅ ብዬ ምስጋናዬን አቀርብላቸዋለሁ። አምላካችን እኛን የፈጠረበት ምክንያት እንድናመሰግነው ነውና አንቺን ለሰጡን እንዲሁም በቅርብ ሆነው ሁሉንም ፈተና ለሚጋሩት ለተከበሩት መላ ቤተሰቦችሽም እግዚአብሄር ይስጥልን እላለሁ። ለወላጅ በዚህ ቀንበጥ ዕድሜ ከሙሽርነት – እስር ቤት ፍሬን ማዬት ከባድ ነው – እጅግ። እነሱም አብረው እዬደቀቁ ነውና ብርታቱን ይስጥልኝ አምላኬ። አሜን!

የማከብራችሁ ታዳሚዎቼ ቀለማሙ የብዕር ቆይታ ከአድማስ ባሻገር አብሮ በፍቅር አቆዬን። ፈቅዳችሁ ለሰጣችሁኝ ቅኑ ጊዜ ዘንካታውን ኢትዮጵያዊ ምስጋና በአክብሮት እንሆ – የኔዎቹ! እናንተን ያኑርልኝ።

ሴቶች የድርጊት ጀግኖች ናቸው!
ሴቶች የመሆን መቻል ጉልህ ምልክት ናቸው!

ማሳሰቢያ …
* እናንተ ድንቅ የሀገሬ ልጆች በዘመን አመጣሹ ፌስ ቡክና ሌሎችም አካውንት ያላችሁ የእንኳን አደረሸሽ ሻማ ትለዋወጡ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። ከዋዜማው ጀምራችሁ …. በእጃችን ባለ፤ ማድረግ በምንችለው አጋርነታችን አዳንቆታችን ምስጋናችን እንገልጽላት ዘንድ አሳስባለሁ። አብሶ ሴቶች ቅን ወንድሞቻችንም በዬቤታችን ሻማ እናበራለት ዘንድም እጠዬቃለሁ በጥር 21. 20014 … እንዳትረሱ አደራ! ፍቅራችሁን በፊርማችሁም ግለጹ …. አመሰግናችኋለሁ።
Facebook – just click here to share the petition on Facebook.
Here’s the link:

http://www.change.org/petitions/free-reeyot-alemu-imprisoned-award-winning-ethiopian-journalist-with-breast-tumour?share_id=tzbOCsHCEK&utm_campaign=signature_receipt&utm_medium=email&utm_source=share_petition

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

“ወደው አይስቁ”ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ። “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። … የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”
በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል። የሚናገሩትን አያውቁትም። የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ። እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።
ተናጋሪው የእለቱ የክብር እንግዳ መሆኑ ነው። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት እንዳደረገም አስቀድሞ ገለጻ ተደርጓል። ሰዎቹ የወንዶች ብልት መቆረጥን የፈጠራ ታሪክ ያነሱት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጡትን በአደባባይ ያቆሙ እብዶች፣ የወንድ ብልትን አያቆሙም ማለት አንችልም። “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” ይላል የሃገሬ ሰው። ስለ አኖሌ የፈጠራ ውጤት በያዝነው አዲስ አመት አውርተን ሳንጨርስ፤ ይኸው የባሰ ነገር እየመጣ ነው። ምኒሊክ የወንድ ብልትምም ቆርጠዋል ነው እያሉን ያሉት – ጨዋታቸውን ሲያራዝሙት። አጼ ሚኒሊክ ለካ የጉጂ ኦሮሞ ኖረዋል። ትንሽ ቆይተው ጉጂዎች የወንድ ብልት መቁረጥ የተማሩት ከምኒሊክ ነው ይሉናል። እዚህ ላይ ሰዎቹ እየቀለዱ ብቻ አይደለም። እየቀለዱብንም ነው። ወዳጆቼ ግን አሁንም ሙድ ይዘዋል።…
በነዚህ ቀልደኞች ዘና እንል ይሆናል። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ። የሴት ልጅ ጡት በአደባባይ ሃውልት የተሰራለት በእኛ ምድር ላይ ብቻ ነው። ይኸውም በእኛ ዘመን። ሴት ልጅ በሃገራችን ትከበራለች። የውስጥ አካልዋ እንዲህ በአደባባይ ላይ ሲውል ክብርዋን ይቀንሰዋል። የሴትን ልጅ ጡት በአደባባይ ላይ አውለው፤ ህጻናትና አዋቂው እንዲመለከተው ማድረግ በባህላችንም እጅግ ነውር ነገር ነው።
“ምሁሩ” የታሪክ ተንታኝ ንግግሩን በዚህ አላበቃም። ማብራራቱን እንደቀጠለ ነው። “…ይህንን ታሪክ ለማወቅ የታሪክ መጽሃፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። በኢንሳይክሎፔዲያ ላይም ግዜያችሁን አታባክኑ። በቀላሉ ጉግል አደርጉና ታገኙታላችሁ… ” አለ። ጉግል ስናደርግ ይህንኑ መረጃ በራሱ ድረ-ገጽ ላይ ልናገኘው እንችል ይሆናል።
አጼ ምኒሊክ አምስት ሚሊዮን ጡት ቆርጠዋል ሲሉን ግን፤ ስሌቱ ላይ የቤት ስራቸውን በደንብ የሰሩት አይመስልም። በአጼ ምኒሊክ ዘመን አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ቁጥሩ ስምንት ሚሊዮን ነበር። የአምስቱ ሚሊየን ህዝብ ጡት ከተቆረጠ፣ በዘመኑ ወንዶቹም ጡት እንደነበራቸው ያመላክታል። ግን ያንን ሁሉ ጡት እንዴት ሊቆርጡት እንደቻሉ ተናጋሪው አላብራሩም። ስልጣኔን ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት አጼ ምኒሊክ በመጀመሪያ ያደረጉት የጡት መቁረጫ ማሽን ማስገባት መሆኑን ከጉግል ላይ በቅርቡ ሊገኝ ይችላል።
ጉግል፣ ጉግል፣ጉግል፣ጉግል፣…… እያለ መነጋገርያውን ለቆ ወረደ – የምኒሊክን አዲስ ታሪክ የሚያስተምረው።
“ሉሲ ኦሮሞ ናት። ጎንደርም ከኦሮሞ ላይ የተቀማች ሃገር እንደሆነች ጥናት አድርገን ጨርሰናል።… ይህንንም በቅርቡ ይፋ በሚሆነው ጥናት ታገኙታላችሁ… ።” የሚል ሌላ ተናጋሪ መድረኩን ይዞ ሲናገር ከማርስ የመጣ ፍጡር ነበር የመሰለን።
ጨርቁን ጥሎ እርቃኑን መንገድ ለመንገድ የሚሄድ፤ ወይንም ደግሞ እጅና እግሩ በሰንሰለት የታሰሩ ሰው ስናይ፤ በተለምዶ ይህ ሰው አብዷል እንላለን – ውጭውን ብቻ አይተን። ጥሩ ልብስ ለብሰው በስነልቦና እና በአእምሮ መታወክ የሚሰቃዩ እጅግ ብዙ እብዶች እንዳሉ ብዙውን ግዜ እንዘነጋለን። እንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች በቀን ቅዠት የሚሰቃዩ፣ የስነምግባርና የሞራል እስረኞች በመሆናቸው አእምሯቸው ይታወካል። በእውናቸው ይሁን በህልማቸው የአጼ ምኒሊክ ጣእረ ሞት እየመጣ እንቅልፍ እንደነሳቸው ግልጽ ነው።
ፓልቶክን ከሰባት አመታት በኋላ መስማቴ ነው። ይህን ትልቅ መድረክ፣ አንዳንዶች ታሪክ ሰርተውበታል። ሌሎች ታሪክ ሲያወሩበት ሰንብተዋል። እነሆ ዛሬ ደግሞ ታሪክ የሚያጎድፉ ጉዶች ይዘውታል። ከሰባት አመታት በኋላ የኛ ፓልቶክ ሽቅብ ሳይሆን ቁልቁል አድጎ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱ ቢገርመኝም፤ በአንጻሩ ግን እንደ አዝናኝም እየሆነ መምጣቱን አልጠላሁትም።
እንደሰማነው የፓልቶክ ርእሱ ላለፉት ሶስት ሳምንታት አልተቀየረም። የዛሬውም መነጋገርያ ርእስ ዳግማዊ ምኒሊክ ናቸው። እኚህ መሪ ካለፉ እነሆ መቶ አመት ሆናቸው። “የሞኝ ለቅሶ፣ መልሶ መላልሶ!” እንዲሉ አንዳንዶቹ ቀኑን ሙሉ ስለ አጼ ምኒሊክ አውርተው ሌሊቱንም ይመለሱበታል። ዛሬ ግን ወሬውም፣ ስድቡም ያለቀባቸው ይመስላል። ዛሬ ስለጀኖሳይድ እያወሩ አይደለም። ይልቁንም ጀኖሳይድ እያወሩ ነበር። ወንጀሉን ራሳቸው በቃል እየፈጸሙት…።
ሌላኛው ተናጋሪ ተራውን ጠብቆ መነጋገርያውን ያዘ። የተለመደውን የአጼ ምኒሊክን አጽም ከመቃብር እየጠራ ካወገዘ በኋላ፤ እንዲህ ሲል ተናገረ። “…አበበ ቢቂላን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ አድርገው ታላቅ በደል ፈጽመውበታል።”
መቼም ወደው አይስቁ። እንዲህ አይነቶቹ ሰዎች እንኳ አይፈረድባቸውም። ገና ሃገር ሲለቅቁ የለቀቁ ስለሆኑ ለክርክርም አይመቹም። “አበበ ቢቂላ በሮም እና በቶክዮ ላይ የሮጠው በአጼ ምኒሊክ ዘመን ነው።” ብሎ ከሚከራከር ሰው ጋር ሙግት መግጠም እብደት ይሆናል።
“የቁቤ ትውልድ ነን።” የሚል ሌላ ታናጋሪ ደግሞ መጣ። ይሄኛው ደግሞ የቆሪጥ መንፈስ የሰፈረበት ሳይሆን አይቀርም። የሚያወራው ሁሉ ስለ መቁረጥ ብቻ ነው። ሚኒሊክ ጡት፣ እጅ፣ ቆለጥ፣ እግር፣ ጥፍር… ቆርጠዋል አለን። እንደታናጋሪው ከሆነ እኚህ መሪ ያልቆረጡት ብልት የለም። ሃገር ማስተዳደሩን ትተው አስራ ሁለቱንም የሰውነት አካል ሲበልቱ ኖሯል!
አርፍደው የሚገቡት ተሳዳቢዎች ከአፋቸው የሚወጣውን ጸያፍ ስድብ ለመድገም ይዘገንናል። በ”ምሁሮቻቸው” ገለጻ መሃል እንደ አዝማች ጣልቃ እየገቡ በአማራው ህዝብ ላይ ይወርዱበታል። በዚህ ሁሉ መሃል ትንሽ የገረመኝ አንድ ክስተት ነበር። የክፍሉ መሪ በስድድቡ መሃል ገብቶ በኦሮምኛ እንዲህ ሲል ተናገረ።
“ጀሪን ወል አኛተኑ። ማይኪ ኢቲ ኬኒ። ኑ ሂንደጌኛ”።
ወደ አማርኛው በግርድፉ ሲመለስ፣ “ማይኩን ስጣቸው። እነሱ እርስበርስ ይባሉ። እኛ እንሰማለን።” እንደማለት ነው። ዋናው ጨዋታ እዚህ ላይ ኖሯል። ምክንያቱም ይህንን ውግዘት እና ውርጅብኝ ሜንጫዎቹ ያለምክንያት በዚህ ሰዓት አላነሱትም። ነብሳቸውን ይማርና አፄ ምኒሊክ ካረፉ 100 አመት አለፈ። የሙት አመታቸው መከበር ከጀመረ ደግሞ 70 አመት ሆነው። ይህንን ወቅት ጠብቆ በአማራ እና በክርስትና እምነት ላይ ለመዝመት የሚደረገው ሙከራ፣ ግብታዊ ሳይሆን በጥናት የተደረገ ስለመሆኑ ያመላክተናል። ግርግር በመፍጠር እና ዜጎችን እርስበርስ በማባላት፣ ትንሽ የፖለቲካዊ ትርፍ ለማግኘት የሚፈጸም የፖለቲካ ዝሙት መሆኑ ነው።
ልብ በሉ! የዚህ የሜንጫ ዘመቻ መሪዎች ኦሮሞዎች አይደሉም። አብዛኞቹ በግማሽ ከሌላ ዘር የሚወለዱ ናቸው። በእምነታቸውም ሆነ በዘራቸው የተቀላቀሉ ሰዎች ብዙውን ግዜ የማንነት ቀውስ ውስጥ ይገባሉ።
ስድስት ሚሊየን አይሁዶችን የፈጀው አዶልፍ ሂትለር ግማሽ አይሁድ እንደነበር አንዘንጋ።

“የአፄ ምኒልክ ወታደሮች በአያቴ ላይ ብዙ በደል አድርሰዋል” –ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (ቃለምልልስ)

$
0
0

“በኢህአዴግ በኩል የአፄ ምኒልክ ሐውልት ይፍረስ የሚል እንቅስቃሴ አልነበረም”
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (ቃለምልልስ)

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለ3 አመት የመሩትን አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ለኢ/ር ግዛቸው አስረክበዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በፓርቲ ፖለቲካ እንደማይታቀፉ ከተናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር በፓርቲ ቆይታቸው፤ በቀጣይ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው፣ በአፄ ምኒልክ፣ በደቡብ ሱዳን በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ ዙሪያ ከ“ሎሚ” መፅሔት ም/አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

negaso gidada
ሎሚ፡- ያለፉት 3 ዓመታት የአንድነት ፓርቲ ቆይታዎ ምን ይመስላል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ከጤንነትም ከቴክኒክ ሁኔታ (ለምሳሌ መኪና የለኝም)፤ ከዚህ ከዚህ አኳያ የመንቀሳቀስ ብቃቴ የተገደበ ነበር፡፡ ይሔ መገደቡ ደግሞ ለፓርቲው አይጠቅምም፡፡ ብዙ መሠራት ያለበትን ነገር ያለመስራት ሁኔታ አለ፡፡ በሌላ በኩል እኔ ስመረጥ በስራው ላይ እኔ የፈተንኳቸውን ሰዎች አይደለም በካቢኔው ውስጥ ያስገባሁት፡፡ በተለያዩ ሠዎች ሃሣብና አስተያየት ይሄ ይሻልሃል በሚል ነው የመረጥኳቸው፡፡ ካቢኔውን የሚያቋቁመው ሊቀመንበሩ ነው፡፡ በዛ መሠረት ነው ያቋቋምኩት፡፡ ወደ ስራ ከገባን በኋላ ስትፈትናቸው፣ ስታያቸው አንዳንድ ወደ ፅንፍ የሚሄዱ አብረን መስራት ያልቻልናቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ በተግባርም ላይ ሌሎችም ድክመቶች ነበሩ፡፡ ይህ ሁኔታ ሙሉ ጊዜያቸውን ያለመስጠት ፍላጐት ሣይሆን ስራ ስላለባቸው ነው፡፡ የራሳቸውን ስራ እየሠሩ ኑሯቸውን እየኖሩ በትርፍ ጊዜያቸው መጥተው ነው የድርጅቱን ስራ የሚሠሩት፡፡ ማስገደድ አትችልም፤ ስለዚህ ማስገደድ በማትችልበት ሁኔታ ብዙ ለመስራት ያስቸግራል፡፡ ይህ ደግሞ በስራ አስፈፃሚው ላይ ድክመት እንዲታይ አድርጓል፡፡
ሌላው ደግሞ የግል አመራርና የጋራ አመራር የሚባል ነገር አለ፡፡ እኛ በጋራ አመራር ላይ ነው የተመሰረትነው፡፡ በአንድ በኩል ለሊቀመንበሩ ስልጣን ይሰጣል፤ በሌላ በኩል የጋራ አመራር በሚባልበት ጊዜ ስራ አስፈፃሚው መግባባት አለበት፡፡ በአቋምም የጋራ አመራር ስለሆነ አመራር ሲሰጥ የአቋም መለያየት ሊኖር ይችላል፡፡ በዚህ መካከል አብሮ በትክክል ያለመስራት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡ እነዚህ፣ እነዚህ ችግሮች ቢኖሩም በሌላ በኩል ጥሩ ነው፡፡ ድርጅቱ ሣይከፋፈል መቆየቱ እንደገና ደግሞ ሁሉንም ያሰብናቸውን ነገሮች ባናከናውንም፤ አንዳንድ ስራዎች ተሠርተዋል፡፡ በህዝብ ግንኙነት በኩል ውይይቶች መካሄድ፣ እንደገና የሚሊየኖች ድምፅ ለነፃነት የሚለውን ሠላማዊ ሠልፍ ማከናወንን የመሳሰሉ፣ በተጨማሪም ምንም እንኳን ችግር ቢኖርበትም በ34 አካባቢዎች በቅርንጫፍ ቢሯችን መስራት የምንችለውን ሰርተናል፡፡ እነዚህ እነዚህ ጥሩ ነበሩ፡፡ በግለሰብ ደረጃ ከሁሉም አባላት ጋር ከስራ አስፈፃሚ፣ ከብሄራዊ ምክር ቤት ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበረኝ፡፡ ያለፉት ሶስት አመታትም ይሄን ይመስላል፡፡

ሎሚ፡- ጊዜዎት ደርሶ ከፓርቲው ሊቀመንበርነት ለቀዋል፤ ከፖለቲካው ለመራቅ መወሰንዎም እየተነገረ ነው፤ ይሄ ነገር ምን ያህል እውነት ነው? እንዴት እዚህ ውሳኔ ላይ ደረሱ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- አንደኛው እውነት በፓርቲ አመራር ውስጥ አልገባሁም፤ ይሔ ተርሜ (የሊቀመንበርነት ጊዜዬ) ስላለቀ የወሰንኩት አይደለም፡፡ ብዙ ሠዎች ለምን አትቀጥልበትም ብለው ጠይቀውኛል፡፡ ብቀጥል ደስ ይላቸው ነበር፡፡ ከአራት ወር በፊት ተግባራዊ ያደረግነው አካሄድ አለ፡፡ ለሊቀመንበርነት፣ ለብሄራዊ ምክር ቤት ለመወዳደር የሚፈልጉ ሠዎች ማመልከቻ አቅርቡ ተብሎ መስፈርቶች ተዘጋጅተው በዛ መሠረት ማመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ እኔ ግን ለሊቀመንበርነትም ሆነ ለብሄራዊ ምክር ቤት ማመልከቻ ለማቅረብ አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም በአመራር ቦታ ላይ ለመስራትም ሆነ ለመቀጠል ስላልፈለኩ ነው፡፡ ሁለተኛው አንተ እንዳልከው ከፖለቲካ መራቅ ሣይሆን የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆኜ ለዛ ወገንተኛ ሆኜ በዛ ፕሮግራም፣ በዛ ህገ ደንብ ተገዝቼ እቀጥላለሁ እንጂ የአመራር ፖለቲካ እንቅስቃሴ አቆምኩ ማለት ነው እንጂ ፖለቲካውን ከነጭራሹ ለቀኩ ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ሠዎች የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ካልሆንክ፣ ፖለቲካ ውስጥ የለህም ብለው ያስባሉ፡፡ ሠው እስከሆንክ ድረስ ፖለቲካ ነው የምትሠራው፡፡ ዝም ማለትም ፖለቲካ ነው፤ ገለልተኛ መሆንም ፖለቲካ ነው፡፡ እኔ የፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ አልገባም ማለቴ ነው እንጂ ከፖለቲካ እርቃለሁ ማለት አይደለም፡፡ ከፖለቲካ የማልርቅበት ምክንያት ደግሞ የተለያዩ መንገዶች አሉ፡፡ አሁን ካንተ ጋር ስነጋገር መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡ የፖለቲካ አስተያየት ነው የምሠጠው፡፡ ገለፃ ማድረግ አለ፤ አርቲክሎች መፃፍ አለ፤ መፅሐፍ ማሣተም አለ፤ ምክር የመስጠት ሁኔታ አለ፡፡ ከዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ ወጣሁ ማለት አይደለም፡፡

ሎሚ፡- ከሠሞኑ አፄ ምኒልክን የተመለከቱ ፅሁፎች በተለያየ መገናኛ ብዙኃን እየተንፀባረቁ ነው፤ የገዢው ፓርቲ ብሎገሮች ይህንን በማስተጋባት ላይ ይገኛሉ፤ መነሻው ምንድነው ይላሉ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የአፄ ምኒልክ 100ኛ የሙት አመታቸው ሲከበር እርሳቸውን ደግፈው የሠሯቸውን ጥሩ ጥሩ ነገሮች የሚያጎሉ ጽሑፎችን ነው ያነበብኩት እንጂ በተቃራኒው መጥፎ ስራቸውን በሚመለከት የተፃፈ ነገር አልተመለከትኩም፡፡

ሎሚ፡- አይ እኔ የጠየቅኩት በብሎገሮች ላይ የወጡትን ነው፤..
ዶ/ር ነጋሶ፡- እኔ ብሎገሮችን አላነበብኩም፡፡ ሆኖም ግን የማያቸው ሚዲያዎች የእርሳቸውን ጥሩ ጥሩ ጐን ብቻ አጉልተው የፃፉ ናቸው፡፡ የፖለቲካ አቋማቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሌላ አቋም ያላቸው ደግሞ የተደረጉ ጥፋቶች አሉ፡፡ የተሠሩ ስህተቶች አሉ፡፡ እነርሱ ጐልተው አልታዩም፤ የአንድ ወገን አስተያየት ብቻ ነው ያየሁት፡፡ ሁለቱንም ሚዛናዊ ያደረገና ያመጣጠነ መጥፎ ተሰርቶ ከሆነ መጥፎ፣ ጥሩውም በጥሩ ታይቶ መሠራት ያለበት ይመስለኛል፡፡

ሎሚ፡- ገዢው ፓርቲ ስልጣን ላይ በወጣ ሠሞን የተጀመረው “የምኒልክ ኃውልት ይፍረስ” ተቃውሞ አሁንም የቀጠለ ይመስላል፤ ገዢው ፓርቲ አፄ ምኒልክን በተመለከተ ያለውን አቋም እንዴት ይገልፁታል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ያን ጊዜም ሆነ አሁንም በኢህአዴግ በኩል የምኒልክ ኃውልት ይፍረስ የሚል እንቅስቃሴ አልነበረም፡፡ አሁንም ያለ አይመስለኝም፤ ከየት እንዳመጣችሁ አላውቅም፡፡ ይሄንን ነው የማስታውሰው፡፡
ሎሚ፡- በዛን ሠሞን በገዢው ፓርቲ አማካይነት ሠልፍ የወጣ አልነበረም ነው የሚሉት?

ዶ/ር ነጋሶ፡- ኦህዴድ ለምሣሌ አንስቶ ነበር፡፡
ሎሚ፡- እርስዎ ኦህዴድ ነበሩ፤ ተሰልፈው ወጥተዋል?

ዶ/ር ነጋሶ፡- አዎ! ወጥቻለሁ፡፡
ሎሚ፡- ኦህዴድ የኢህአዴግ አጋር ድርጅት ነው፤ የኦህዴድ አቋም በኢህአዴግ ሊንፀባረቅ አይችልም ብለው ያምናሉ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ቢንፀባረቅ ኖሮ ያን ጊዜ ይነሣ ነበራ፡፡ እነ አቶ ተፈራ ዋልዋ ከንቲባ ነበሩ፤ የዛን ጊዜ ኦህዴድ ጫና ቢፈጥር በእርሳቸው ላይ ይንፀባረቅ ነበር፤ በኢህአዴግም ላይ ይንፀባረቅ ነበር፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢሆን ኢህአዴግ የመንግስቱ ኃ/ማርያምን ኃውልት አንስቷል፤ የሌኒንን አንስቷል፡፡ እንጂ የምኒልክን ለማንሣት የተደረገ እንቅስቃሴ የለም፡፡ ኦህዴድ ደግሞ ተፅዕኖ ቢያሳድር ኖሮ እናይ ነበር፤ አላደረገውም፡፡

ሎሚ፡- እርሶ በግል አፄ ምኒልክን እንዴት ይገልፁቸዋል? ንጉስ ነገስቱ በሃገር ውስጥ ፈፅመውታል የሚባለው መጥፎና መልካም ጐናቸውን ቢጠቅሱልን? የአሁኑዋን ኢትዮጵያ በመፍጠሩ ረገድ የነበራቸውን ሚና እንዴት ይገልፁታል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ቀደም ብዬ ገልጬዋለሁ፤ በግል ከነጋሶ ታሪክ ነው የምነሣው፡፡ የአፄ ምኒልክ ወታደሮች መጥተው አያቴን በሠንሠለት አስረው እህል አስፈጭተዋቸዋል፡፡ እንዳያመልጡ ተብሎ ይህ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ሌላ ለ6 ሠዓት ያህል ረጅም መንገድ እህል አሸክመው ወስደዋቸዋል፡፡ እና ይህንን ለመርሳት አልችልም፡፡ የተገደሉ ሠዎች አሉ፤ በባርነት የተሸጡ ሠዎች አሉ፡፡ አስገድዶ የማስገበር ሁኔታም ነበር፡፡ የሆነውንና የተፈፀመውን ጥፋት መርሣት አይቻልም፡፡ ይሔ እንዳለ ሆኖ የተሰሩ ስራዎች አሉ፡፡ ሚዛኑ ይሄ ይደፋል፡፡ “ይደፋል” የሚባል ነገር ውስጥ ሳንገባ፡፡ ለምሣሌ ዘመናዊ ነገሮችን ወደ ሃገሪቱ የማስገባት ሁኔታዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን በነዚህ ላይ ብቻ አተኩሮ ሌላውን መርሳት አንችልም፡፡ ያኔ ያጡትን የራስን መብት በራስ የመወሰን መብት ያጡ ህዝብች አሁንም መብታቸው አልተከበረም፡፡ እስካሁን ድረስ የራስን ጉዳይ በራስ የመወሰን ሁኔታ አልተፈጠረም፡፡ በዚህ ምክንያት አገርን አንድ አደረጉ፣ የኢትዮጵያን ነፃነት አስጠበቁ፤ ምናምን የሚል ነገር አለ፡፡ ግን ደግሞ መጥፎውንም መርሣት የለብንም፡፡

ሎሚ፡- ምኒልክ በኦሮሞ ተወላጅ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ጉዳት አድርሰዋል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- እኔ አላልኩም፤ ለምን እንደዚህ እንደሚባልም፣ ለምን እንደዚህ ብለህ እንደምትጠይቀኝም አላውቅም፡፡ በአንድ በኩል የደቡብ አካባቢን ካየህ ከኡጋዴን እስከ ቤንሻንጉል ድረስ፤ ከቦረና እስከ ሠሜን ሸዋ ድረስ በምኒልክ ተበድሏል፡፡ ስለዚህ ይሄ ጉዳይ በኦሮሞ ብሔር ላይ ብቻ የደረሰ በደል አይደለም፡፡
ሎሚ፡- የአፄ ምኒልክም ሆነ የቀረው የኢትዮጵያ ታሪክ ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል አለመሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህንን ልዩነት በመዘላለፍ ከመግለፅ ይልቅ በሰለጠነ አካሄድ እና በሰከነ ሁኔታ ለመነጋገር ምን መደረግ ይኖርበታል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ምኑ ነው ስልጡኑ? እውነት መናገሩ ነው ስልጡን አለመሆኑ? መጥፎም የሚናገር አለ፤ ጥሩም የሚናገር አለ፡፡ ስልጡን የሚሆነው መደማመጡ ነው፡፡ ማንም ሠው የፈለገውን ይናገር፤ የፈለገው ደግሞ ይስማ፡፡ ሁሉም ሠምቶ በጠላትነት ባይተያይ ጥሩ ነው፤ እርሱ ነው ዋናው ቁም ነገሩ፡፡

ሎሚ፡- የሕወሓት ነባር ታጋይ የሆኑት አቶ ብስራት አማረ “ፍኖተ ገድል” በተሰኘው መፅሃፋቸው “የምኒልክ የስልጣን ጥማት ለትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ የነበረውን ከባድ ጥላቻ ኢትዮጵያን ወደ ቀውስ እንዳመራ ይታመናል” ይላል፤ እርሶ ይሄን እንዴት ያዩታል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- አላነበብኩትም፤ አንደኛ እርሱ የግሉ አቋም ነው፡፡ የእኔ አቋም ግን ቀድሞ የገልፅኳቸው ናቸው፡፡

ሎሚ፡- ሠማያዊ ፓርቲ በአፄ ምኒልክ 100ኛ አመት የሙት ዝክር ዝግጅት ወቅት የክብር እንግዳ የነበሩት ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም “አፄ ምኒልክ ከአሁን በኋላ ታላቁ አፄ ምኒልክ” ተብለው እንዲጠሩ ሃሣብ አቅርበዋል፤ ይሄን እንዴት አዩት?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የራሳቸው አመለካከት ነው፤ ሌላው ደግሞ እንደዛ ላይል ይችላል፤ በአንድነት የሻማ ምሽት ላይ የቀበና አደባባይ የአንዱዓለም አደባባይ እንዲሆን ሲሉ ሠምቻቸዋለሁ፤ ይሄ የራሳቸው አመለካከት ነው፡፡

ሎሚ፡- ገዢው ፓርቲ ያለበትን የችግር አቅጣጫ ለማስቀየር ይህን ጉዳይ ተጠቅሞበታል የሚሉ አስተያየቶች አሉ፤
ዶ/ር ነጋሶ፡- በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የተከታተልኩት ወይም ትኩረት የሰጠሁት ነገር የለም፤ ኢህአዴግ አደረገ ወይም አላደረገም ለማለት መከታተል አለብኝ፡፡

ሎሚ፡- ባለፈው የመፅሔታችን ዕትም አቶ በቀለ ድሪባ ካባ የተባሉ የቀድሞ የፓርላማ አባል “የምኒልክን ስህተቶች” ከዘረዘሩ በኋላ እንደ ራስ ጐበና ደጩ የመሠሉ የምኒልክ ባለሟሎች “የምንሸማቀቅበት ታሪክ አጉዳፊ ግለሰብ ናቸው” ብለዋል፡፡ ይህን መሠሉ አቋም ምን ያህል የኦሮሞ ተወላጆችን አቋም ይወክላል ማለት ይቻላል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ይሔንን ቅድም ካልኳቸው ጉዳዮች ጋር ልታስታርቅ ወይም ልዩነታችንን ልታስተውል ትችላለህ፡፡ ሁሉም ኦሮሞ እንደ እኔ ያስባል ወይስ እንደሳቸው የሚለውን ለመደምደም አስቸጋሪ ነው፡፡

ሎሚ፡- ቴዲ አፍሮ ከሠሞኑ ለአፄ ሚኒልክ አድናቆቱን ገልጽዋል፤ ለኮንሠርቱ ስፖንሰር የሆነውን በደሌ ቢራ ላለመጠጣት አድማ እንዲደረግ ጥያቄ ቀርቧል፤ የደቹ ሄኒከን በትዊተርና ፌስቡክ ከ18ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች “ምኒልክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችን” የጨፈጨፉ ኢትዮጵያዊ ሂትለር ናቸው” የሚል የተቃውሞ መልዕክት እንደደረሰው ገልጿል፡፡ አፄ ምኒልክን ኢትዮጵያዊ ሂትለር የሚለው ቃል ይመጥናቸዋል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በዛን ጊዜ በነበረው ሁኔታ ምክንያት አፄ ምኒልክ ላይ ስሞታ የሚያነሱ ሠዎች አሉ፡፡ የሚደግፏቸውም አሉ፤ የሁሉም መብት ነው፤ ከሂትለር ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው? በምን ዓይነት መንገድ? በኢኮኖሚው ነው? የዛኔ የኢኮኖሚ ኢንዳስትሪ አልነበረም፤ ፋሽስት ነበር፤ ፋሺዝም ደግሞ የሚመጣው ከኢንዱስትሪው ጋር በተያያዘ ነበር፡፡ አፄ ምኒሊክ ፊውዳል ነበሩ፤ ታዲያ እንዴት አድርገህ ነው ከናዚ መሪ ጋር የምታመሳስላቸው?

ሎሚ፡- ምኒልክን የሚመለከቷቸው እንደ “ተበዳይ ተበዳይ ባይ ነኝ ሰው” ነው? ወይስ እንደ ሆደ ሰፊ ፖለቲከኛ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ኦሮሞ ስለሆንኩ ነው እንደዚህ የምጠየቀው? ትኩረት ያልሠጠሁትን ጉዳይ ለምን ትኩረት እንድሰጠው ይደረጋል?

ሎሚ፡- ለወደፊቷ የጋራ ቤታችን ኢትዮጵያ ጉዳዮችን ለማስታረቅና ለመቀየር ምን ማድረግ ይኖርብናል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- አሁን ካነሣሃቸው አንደኛውን እና የፈለከውን ልታሳካ ትችላለህ፤ እኔም የፈለኩትን ሃሣብ ላነሣና ልከተል እችላለሁ፡፡ እኔ መብትህን እንደማከብርልህ አንተም መብቴን ታከብርልኛለህ፡፡ ሰብዓዊ መብትን፣ የዲሞክራሲያዊ መብቶችን ማክበር እንደገና የህዝቦች የራሳቸውን መብት በራሳቸው እንዲወስኑ መፍቀድ ሲቻል ነው ኢትዮጵያ በሰላም ልትኖር የምትችለው፡፡

ሎሚ፡- አንድነት በወጣት ፖለቲከኞች ያምናል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- አዎ!
ሎሚ፡- በወጣት የሚያምን ከሆነ የአመራር ቦታዎችን ለወጣቶች ለምን ለመስጠት አልፈለገም? ወይም ሙከራውን አላሣየም?
ዶ/ር ነጋሶ፡- እንዴት?
ሎሚ፡- ጥሩ ጥያቄ ነው፤ በወጣት የሚያምን ከሆነ የኢ/ር ግዛቸው ወደ አመራር መምጣት እንዴት ተፈጠረ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- የእኛ አሠራር ይሔ ወጣት ነውና ይህንን ቦታ ይያዝ፤ ይሄ ይሻላልና ይሄ ዞር ይበል አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ሠዎቹ ታውቀው “እችላለሁ እመራለሁ” ብለው ማመልከቻ ካቀረቡ በኋላ በማመልከቻው መሠረት መስፈርት ተቀምጦ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሠዎች፣ ለምርጫ ይቀርባሉ፡፡ በዚህ መሠረት ነው የተመራው፡፡ ለምሣሌ የብሔራዊ ም/ቤት ምርጫ በቀደም ተካሂዶ ነበር፡፡ 65 ሠዎች ናቸው ተለዋጭና ሙሉ አባል የሆኑት፡፡ ከ50 አመት በታች የሆኑ ሠዎች ምን ያህል ናቸው ብለህ ትገምታለህ?
ሎሚ፡- አላውቅም፤ ይቅርታ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ከ65 ተለዋጭና ሙሉ አባላት 47ቱ ከ50 አመት በታች ናቸው፡፡ የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ባለበት መልኩ እንዴት ወጣቶች አልተካተቱም ይባላል? ሁለተኛ በፕሬዚዳንቶች ምርጫ ወጣቶችን ጨምሮ ኢ/ር ግዛቸውን ነው የመረጡት፡፡ ለምን ግዛቸውን መረጡ ነው? (ሣቅ…) ከ50 አመት በታች የሆኑት ተክሌና ግርማ ተወዳድረው ነበር፡፡ ቤቱ አልመረጣቸውም፡፡ እናስ ይሄ ቤቱ ወጣቶችን አይፈልግም ለማለት ነው? በነገራችን ላይ ሁለቱም ከ50 በታች ናቸው፡፡ እንደገና ደግሞ አሁን የተመረጡት ኢ/ር ግዛቸው ከተመረጥኩኝ 65 ፐርሰንቱን የስራ አስፈፃሚ ወጣቶች አደርጋለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡ ወጣት ሊቀመንበር ተወዳድሮ ስላልተመረጠ ድርጅቱ ወጣቱን አይፈልግም ብሎ ማሠብ ትክክለኛ ያልሆነ ግንዛቤ ነው፡፡ ፓርቲው ወጣቶችን ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በፊትም ነበሩ፤ ነጋሶ ወደ 70 አመት ተጠግቶ በሊቀመንበርነት ስላገለገለ ይሄ ወጣቶችን አይፈልግም ማለት ትክክል አይመስለኝም፡፡
ሎሚ፡- ፓርቲው ቀጣዩን የ2007 ዓ.ም ምርጫን እንዴት ያየዋል? ሠልፎች፣ ስብሰባዎች እክል ይገጥማቸዋል ተብሎ ይገመታል፤ ከዚህ አንፃር ምርጫውን እንዴት ያስቡታል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ከፓርቲው አመራር ለቅቂያለሁ፤ ሊቀመንበሩ አዲስ ናቸው፤ ስራ አስፈፃሚው የሚወስነውንና ያላቸውን አቋም አናውቅም፡፡
ሎሚ፡- የአቶ ስዬ አብርሃ ጉዳይ ግልፅ አይደለም፤ ፓርቲውን ለቀዋል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- እስካሁን በፅሁፍ ያስታወቁት ነገር የለም፡፡
ሎሚ፡- በዚህ ዓይነት ርቀትና ምንም እንቅስቃሴ በማያደርጉበት ሁኔታ ከፓርቲው ጋር መስራት ይቻላል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በግል የማውቀው የሚሠሩበት ስራ የፖለቲካ አባል እንዲሆኑ የሚፈቅድላቸው አይደለም፡፡ በምን መልኩ ፓርቲውን ይረዳሉ? ምን ዓይነት ግንኙነት አላቸው? የሚለውን ውስጥ ገብቼ ለመግለፅ አልችልም፡፡ ዋናው ነገር ግን በፅሁፍ እኔ ከፓርቲው ለቀቅቄያለሁ ብለው የፃፉት ነገር የለም፡፡
ሎሚ፡- ደቡብ ሱዳን ከአንድ አመት በኋላ ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ሁከት ገብታለች፡፡ የደቡብ ሱዳንን ጉዳይ እንዴት ተመለከቱት? የሃገሪቱ ጉዳይስ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው ጫና ምንድነው? ምንስ መደረግ ይኖርበታል ብለው ያምናሉ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ደቡብ ሱዳንና ጐረቤት ሃገሮች ውስጥ እንዲህ ያለ ችግር በሚነሣበት ጊዜ ችግሮቹ የሚዛመቱት ወደ ጐረቤት ሀገሮች ነው፡፡ የስደተኞች ጉዳይ አለ፡፡ ያም ብቻ አይደለም፤ ኑዌር ለምሣሌ ደቡብ ሱዳንም አለ፤ ኢትዮጵያም አለ፡፡
ችግር በሚነሣበት ጊዜ ሸሽተው ወደዚህ ሊመጡ የሚችሉ ሊኖሩ ይችላል፡፡ ስደተኝነት ብቻ ሣይሆን ያም ምን ዓይነት ችግር ሊያስነሣ እንደሚችል አናውቅም፡፡ በአካባቢያችን ሠላምና ፀጥታ ከሌለ እኛም ሠላምና ፀጥታ ማግኘት አንችልም ማለት ነው፡፡ የደቡብ ሱዳን ሁኔታ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ከሦስት ሣምንት በላይ ሆኖታል፡፡ እንደማይቀጥል ተስፋ አለኝ፤ ከስምምነት ላይም እንደሚደርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ሎሚ፡- የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ አሁንም እንደቀጠለ ነው፤ ለውጦች የሉም፤ 15 አመት ተቆጥረዋል፤ መጨረሻው ምን ይሆን?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በሪፖርቴ ላይ የገለፅኩት ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይ በጦርነትና በሠላም መሃል ነው ያለው፡፡ ወደ ጦርነት ተገብቶ አንዱ ወገን አሸንፎ ተሸናፊው ተቀብሎት እርቅ ወርዶ አግባብ ያለው የመንግስታት ግንኙነት ተፈጥሮ አልተስካከለም፡፡ በዚህ መቀጠሉ ጥሩ አይደለም፤ ምን ሊሆን እንደሚችል እንዲህ ነው ብዬ ለመናገር ያስቸግረኛል፡፡
ሎሚ፡- በኢትዮጵያ ላይ በኢኮኖሚ ዙሪያ የሚፈጥረው ተፅዕኖ የለም?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በፍጥጫ ላይ የመቆየቱ ጉዳይ ሣይሆን ወደብ የለንም፤ በአሰብ ምክንያት ብዙ ገንዘብ እናወጣለን፡፡ ይሔ ብዙ የኢኮኖሚ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ ይሔ ነገር አንድ እልባት ቢያገኝ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
ሎሚ፡- ከአቶ መለስ ሞት በኋላ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካና አካባቢው ያላትን የበላይነት አጥታለች የሚሉ ወገኖች አሉ፤ ከኢትዮጵያ ይልቅ የዩጋንዳ ተፅዕኖ ፈጣሪነት መስፋቱ ይነገራል፤ ይሄን እንዴት ታዘቡት?
ዶ/ር ነጋሶ፡- በእውነት አልገባኝም፤ በምንድነው ተፅዕኖ የፈጠረው?
ሎሚ፡- ጥሩ ምሣሌ የሚሆነው የደቡብ ሱዳን ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ወገኖች በስልጣን ላይ ያለው እና ለጉዳዩ ቅርብ የሆነው ፓርቲ በደቡብ ሱዳን ጉዳይ ዙሪያ ማድረግ የሚገባውን ያህል አላደረገም ይላሉ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ምን ማድረግ ነበረባት ኢትዮጵያ?
ሎሚ፡- ዩጋንዳ የበላይ ሆኖ ለአንድ ወገን በማገዝ የወሠዳቸው እርምጃዎች ነበሩ፤
ዶ/ር ነጋሶ፡- ይሄ ነገር የውስጥ ጉዳይ ነው፤ ከዚህ በፊት በሶማሊያ ጣልቃ በመግባታችን ብዙ ችግር ተፈጥሯል፤ አሁንም እየተፈጠረ ነው፤ ለወደፊትም ብዙ ችግር ያስከትላል፤ እንደዛ ለምን አልገባችም ነው ኢትዮጵያ?
ሎሚ፡- እንደዛ አይደለም ዶክተር፤ ለምሣሌ ዩጋንዳ ጣልቃ የገባችባቸው ሱዳን ላይ ሊሆኑ የማይገባቸው ነገሮች መደረጉ ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ያሉ ኑዌሮች አሉ፤ ዩጋንዳ ለሳልቫኪር በመደገፍ የአየር ጥቃት ማድረሱ ይነገራል፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች ለምን ሆኑ ብላ ማጣራት አልነበረባትም ወይ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- እያደረገች አይደል አሁን?
ሎሚ፡- በተወሰነ መልኩ የማርፈድ ሁኔታዎች አለባት፤
ዶ/ር ነጋሶ፡- እንዴት ማርፈድ?
ሎሚ፡- ለምሣሌ ኬኒያ ላይ የተደረገው ድርድር የኢጋድ ሣይሆን የዩጋንዳ ሃሣብ የተተገበረበት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ?
ዶ/ር ነጋሶ፡- እኔ አላውቅም፤ ይሄ በኢጋድ ተዘጋጅቶ ነው የተከናወነው፡፡ ስህተት ተሰርቷል ወይስ አልተሠራም? ጥናት ያስፈልገዋል፡፡ ኢትዮጵያ ኢጋድን ወክላ ነው እየሠራች ያለችው ነው የሚባለው? እንደዛ ከሆነ አላውቅም፡፡
ሎሚ፡- የሃገሪቱን ሁኔታ እንዴት ይገልፁታል?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ኢኮኖሚካሊ ሙስና ሠፍኗል፤ መንግስት ራሱ የመንግስት ሌቦች የበዛበት ነው ብሎ ተናግሯል፡፡ በሌላ በኩል ድህነት አለ፤ እየሠፋ ነው፡፡ በፖለቲካው መታፈን አለ፤ ነፃነት የለም፤ ከድህነቷ በመነሣት ደግሞ የማህበራዊ ችግሮች አሉ፡፡
ሎሚ፡- ለነዚህ ሁሉ ጉዳዮች መፍትሄ ሊሆን የሚችለው ምንድነው?
ዶ/ር ነጋሶ፡- ኢህአዴግ ራሱ በሩን ክፍት ማድረግ አለበት፤ የዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር አለባቸው፡፡
ሎሚ፡- ዶክተር በጣም አመሰግናለሁ፡፡
ዶ/ር ነጋሶ፡- እኔም በጣም አመሰግናለሁ፡፡

Hiber Radio: “እነ ሌንጮ ሰልፋቸውን እስከምናውቅ አቋም አልያዝንም”ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ አቶ ቡልቻም ስለ ሌንጮ ይናገራሉ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ጥር 11 ቀን 2006 ፕሮግራም
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ

>ዶር መራራ ጉዲና የአቶ ሌንጮን አገር እገባለሁ በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቀወ የመለሱት ቃለ መጠይቁን አዳምጡት

ሌንጮ ለታ በህወሃት ወዳጅነት የሚታወቁ በአቋማቸው አወዛጋቢ ናቸው። መለስ ከሌንጮ ጋር ስለነበራቸው ወደጅነት በሚስጥር ለአሜሪካዋ ዲፕሎማት የተናገሩት ምን ነበር? (ይህንና ሌሎች ጉዳዮችን ትንታኔ ከዊክሊክስ ፋይል ቅኝት)…

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ስለሌንጮ ለህብር የተናገሩትን ይዘናል

ስለማርቲን ሉተር ኪንግ ልዩ ዘገባ

አጠር ያለ ቃለ መጠይቅ ከዶር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

- የኦሮሞ ወጣቶች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግድያ እንዲቆም ጥሪ ቀረበ

- ዶ/ር መራራ በእነ ሌንጮ ለታ ጉዳይ ሰልፋቸው እስኪታወቅ በአሁኑ ወቅት አቋም አለማያዛቸውን ገለፁ

- ኢትዮጵያዊቷ በኩዌት የወለደችውን ገድላለች ተብላ ታሰረች

- ዶ/ር ነጋሶ የፓርቲ ፖለቲካ እንጂ ፖለቲካ በቃኝ አላልኩም ሲሉ ገለጹ

- ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ አለምግባታቸውን የድርጅታቸው ቃል አቀባይ ገለጹ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

“ኢትዮጵያ እየተበታተነች፤ እየጠፋች ስትሄድ ሳይ መተኛት አልቻልኩም”–አርቲስት ሻምበል በላይነህ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ከአውስትራሊያ ከሚሰራጨው ኤስቢኤስ ራድዮ ጋር ቃል የተመላለሰው ዝነኛው አርቲስት ሻምበል በላይነህ “ኢትዮጵያ ታላቅ ሃገር ናት። ይህች ሃገር እየተበታተነች እየጠፋች ስትሄድ መተኛት አልቻልኩም” አለ። ሻምበል ይህን ያለው ከጋዜጠኛው “እንዴት ዘፈኖችህ በሃገር ጉዳይ እንዲያተኩሩ መረጥክ?” በሚል ላቀረበለት ጥያቄ ነው። ሙሉ ቃለ ምልልሱን እነሆ፦

“ኢትዮጵያ እየተበታተነች፤ እየጠፋች ስትሄድ መተኛት አልቻልኩም” – አርቲስት ሻምበል በላይነህ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live