Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

መጋረጃው

$
0
0
ደረጀ ደስታ እያየን ነው። አይተናቸው ሰምተናቸው እማናውቃቸው ተቋማትና ግለሰቦች ብቅ ብቅ እያሉ ስለ ሥራቸው መግለጫ መስጠት ጀምረዋል። አምስቱ የፍትሕ ተቋማት የሚባሉት የፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያገናኟቸው የሥራ ዘርፎች ላይ “ውጤታማ” ሥራ እያከናወኑ መሆኑን መግለጻቸውን አንብበናል። በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሥር ከሚገኙ […]

የአሜሪካ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን ዓቢይ አህመድን፣ አሳያስ አፈወርቂንና ኢስማኢል ኦማር ጉሌህን ያነጋግራሉ

$
0
0
ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ከዛሬ አፕሪል 22 ቀን ጀምሮ እስከሚቀጥለው ሐሙስ አፕሪል 26 በኤርትራ፣ ጂቡቲና ኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ። ያማሞቶ ዛሬ የ3 ቀናት ጉብኝታቸውን በመጀመር አስመራ የገቡ ሲሆን የአሜሪካና ኤርትራ መንግስታት የጋራ ምክክር ዋናው አጀንዳቸው ሲሆን፤ በኤርትራ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትንና አስመራ ከሚገኘው […]

በቅድሚያ ራሳችንን እንለውጥ –ይገረም አለሙ

$
0
0
በኢትዮጵያችን ስለ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እየተዘመረ፣ ትግል እየተካሄደ፣ እየተሞተና እየተገደለ ከአንድ ትውልድ በላይ ዘመን ታልፏል፡ነገር ግን ለውጥ ጠያቂዎቹ/ፈላጊዎቹ  ራሳቸው ባለመለወጣቸው ሥልጣን ላይ ካሉት ገዢዎች ባልተናነሰ ራሳቸው የዴሞክራሲ አንቅፋቶች እየሆኑ ኢትዮጵያችን ለዴሞክራሲ ሾተላይ እንደሆነች አለች፡፡ዛሬ እኛ ዜጎች አይደለንም ፖለቲከኞቹ፤ እነርሱም አይደሉ ደደቢቶች ራሳቸው ባላሰቡት ሁኔታ በውስጣቸው አድገው አመች ግዜ ሲያገኙ ውስጥ ለውስጥ የደረጁትን ሀሳብና ያደራጁትን ሰው ይዘው […]

የሚኒስትሮች ሹመት አጭር ዳሰሳ (ወሰን ዘሪሁን)

$
0
0
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ጠቅላላ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶች እስከ ቅርብ 29 (አሁን የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሚኒስትር ታጥፎ 28) ናቸው። ሆኖም ዶ/ር ዓቢይ ሹመት የሰጠው ለ 16 ቱ ብቻ ነው (ከነዚህ ውስጥ 10 የሚሆኑት አዲስ ተሿሚዎች ሲሆኑ 6ቱ ሽግሽግ ያደረጉ ናቸው)። ስለዚህ ሌላ ተከታይ ሹመት ካልተሰጠ በቀር (በቅርቡ ሌላ ሹመት የሚኖር አይመስልም) 12ቱ በነበሩበት የሚቀጥሉ ይሆናል። ትናንት የተሾሙት […]

የጌዴኦ ተወላጆች የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው

$
0
0
(BBN) በምዕራብ ጉጂ ዞን በቀርጫ፣ በቡሌ ሆራ፣ በብርብርሣ ኮጆአ፣ በሻኪሶና በሐንባላ ዋማና ወረዳዎችና በቀርጫ ከተማ ያሉ የጌዴኦ ብሔር ተወላጆች ማንንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ይደርስብናል ሲሉ የድረሱልን ጥሪ አቀረቡ።ንብረታችን ይዘረፋል፣ድብደባ፣ግድያና መፈናቀል ይደርስብናል ያሉት የጌዴኦ ተወላጆች ከግማሽ ምእተ አመት በላይ ከጉጂ የኦሮሞ ተወላጆች ጋር አብረው የኖሩ አገርን ገንቢ ዜጋ መሆናቸውንም ያስረዳሉ። እነዚሁ የጌዴኦ ተወላጆች ከጉጂ የኦሮሞ ተወላጆች […]

ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹና ሶሊያና ሽመልስ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በሥልጣን ቅበላ ንግግራቸው ወቅት ያነሷቸው – SbS Amharic

$
0
0
ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹና ሶሊያና ሽመልስ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ በሥልጣን ቅበላ ንግግራቸው ወቅት ያነሷቸውን የትምህርትስ ጥራት ማሻሻል፣ የሥራ ዕድሎች ከፈታና ፖለቲካዊ ተሳትፎን ከኢትዮጵያውን ወጣቶች  የወደፊት ተስፋና ግብራዊ ዕውነታ ጋር አያይዘው ይናገራሉ። “”ኢትዮጵያ ውስጥ ለትምህርት ጥራት ዝቅተኛነት አንዱ ትልቁ ችግር ተደራሽነትን እናሰፋለን የሚል የፖሊሲ ክፍተት ነው። ትውልድን የሚጎዳ ደረጃ ላይ ደርሷል።” – ሶሊያና ሽመልስ “የገዢው ፓርቲ […]

የሕብር ራድዮ የዕለቱ ዜና –በሃብታሙ አሰፋና ታምሩ ገዳ ተዘጋጅቶ ቀርቧል

$
0
0
የሕብር ራድዮ የዕለቱ ዜና – በሃብታሙ አሰፋና ታምሩ ገዳ ተዘጋጅቶ ቀርቧል

ነፋስ ላይ የተለኮሰው ሻማ –ታምራት ደስታ

$
0
0
ነፋስ ላይ የተለኮሰው ሻማ – ታምራት ደስታ

Hiber Radio: ጋዜጠኛ እስክንድር በአዲሱን ጠ/ሚ/ር ንግግር ብቻ መዘናጋት እንደማይገባ ገለጸ ጊዜ ይሰጣቸውም አለ፣ የተመድና የአሜሪካ ባለስልጣናት አ/አ ላይ የኢህአዲግ ሹሞችን ሊያነጋግሩ ነው፣ታዋቂው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ አዲሱ ጠቅላይ ሚ/ር ለውጥ ያመጣሉ ማለቱ፣የፖለቲካ እስረኞቹ እነ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ላይ ሊበየን ነው፣በአብዲ ኢሌ ላይ የቀረበው ተቃውሞ፣የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አክቲቪስት ገዛኸኝ ነብሮ ደ/አፍሪካ መገደልና የቀሰቀሰው ቁጣ እና ሌሎችም አሉን

$
0
0
የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 14 ቀን 2010 ፕሮግራም የዶ/ር አብይ ምርጫ እና እየተደረጉ ያሉ ንግግሮችና ተስፋዎቹን በተመለከተ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር በአውሮፓ አጭር ቆይታው ወቅት ካለበት ተወያይተናል (አድምጡት) አዲሱ ጠ/ሚ/ር የኢህአዴግ ወይስ የሕዝቡን ሀሳብ ለመፈጸም ነው የወጣው? በእርግጥ ማሻሻያ ወይስ ሕዝቡ የሚጠብቀው የለውጥ እርምጃ? ከኦሮሞ የሕግ ባለሙያዎች ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ወየሳ እና ከአክቲቪስት አቻምየለህ ታምሩ ጋር […]

የጠ/ሚ አብይ ነገር…. (ክፍል አንድ) –በመስከረም አበራ

$
0
0
ንግግር አዋቂነት የስኬታማ ፖለቲከኝነት አንድ ግብዓት ነው፡፡የአቶ ሃይለማርያምን ወንበር የተኩት ጠ/ሚ አብይ ከቀዳሚያቸው በተሻለ ንግግር ይጥምላቸዋል፡፡ይሄው ጥዑም ንግግራቸው አድማጫቸው የንግግራቸውን ይዘት ወለፈንዲ ይመረምር ዘንድ ፋታ የሰጠው አይመስልም፡፡ሰውየው የፖለቲካ ፈውሳችን ሊሆኑ የሚችሉ መልካም አጋጣሚዎችን በተደጋጋሚ አርቆ የጣለብን የኢህአዴግ አባል እንደመሆናቸው መጠን የተናገሩትን በጎውን ከማዳነቅ ጎን ለጎን በመርማሪ ልቦና ማየቱ አትራፊ ያደርግ ነበር፡፡ ጠ/ሚ አብይ በበዓለ ሹመታቸው […]

እኔን እንደ ፈታችሁ እነዚህንም ፍቷቸው –ለገሠ ወ/ሃና |የ139 እስረኞች ዝርዝር በቂሊንጦ ብቻ

$
0
0
በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት አንቀጽ 25 በግልፅ እንደተደነገገው ” ሁሉም ሠዎች በህግ ፌት እኩል ናቸው በመካከላቸው ማናኛውም አይነት ልዩነት ሣይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ ይደረግላቸዋል ….. ” ይላል ህጉ የሚለው ይህ ሆኖ ሳለ በህግ የማይመራው የአገዛዙ ፈረስ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይህንን ህገመንግስታዊ ድንጋጌ በመጣስ በተመሣሣይ ወንጀል ተጠርጥረን የተከሰስን ሠዎች አንዳንዶቻችን ክሳችን ተቋርጦ ከእስር ስንፈታ ሌሎቹ በዕስር […]

በዘረኝነት=ብሔረተኝነት ልክፍት ስለተያዝን እንደወረድን አይገባንም! –ሰርፀ ደስታ

$
0
0
ሰሞኑን ፌስቡኩን ያጨናነቀው አብይ የኦሮሞ ብሔረተኝነት ኦሮሞን ከነበረበት ክብር አወረደው ብሎ ተናግሯል በሚል ብዙዎች እንዴት እንዲህ ይናገራል በሚል ሌላ ጦርነት የከፈቱ ይመስላል፡፡ እኔ ይህን ሲናገር አልሰማሁትም በምን አግባብም እንደተናገር አላውቅም፡፡ ግን ተናግሮትም ከሆን እኔን እንደሚገባኝ አንደም የተሳሳተው ነገር የለም፡፡ እውነት ነው፡፡ ችግሩ ማስተዋል አቅቶን በዘረኝነት ስለተለከፍን ብሔረተኝነትን የሚያገን ወሬ እንጂ እንደ ሰው ማሰብ አልቻልንም፡፡ አሁን […]

የአማራን መደራጀት የሚያማቸው የኢትዮጵያን ትንሣኤ የማይሹ ፀረ –ኢትዮጵያ ሃይሎች ናቸው! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

$
0
0
ሓያረ ጠንለሱ አማራና ተደራጅቶ እራሱን ከገዳዮቹ ይመክታል። አባቶቹ በደም በአጥንታቸው ያቆዩአትን ኢትዮጰያንና ኢትዮጵያዊነት ነብስ ይዘራበታል። የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስ በትህነግ-ወያኔ የተቀየሰውና በበታችነት ስሜትና በፈጠራ ትርክት ናላቸው የዞረ የጎሣ ፖለቲከኞች ድጋፍ የተቸረው “የጎሣ ፌደራሊዝም” በደደቢት በረሃ የተጠነሰሰው አማራን ቀንደኛ ጠላቱ በማድረግ ነው። በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ዜግነት፤ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ክብር አለ:: በአማራ ውስጥ ያለውን ኢትዮጵያዊነት […]

እነርሱና እኛ –የኦሮሞ ማህበረሰብን በተመለከተ –ግርማ ካሳ

$
0
0
ከጥቂት አመታት በፊት “የኦሮሞ አክራሪዎችና እኛ” በሚል አንድ ጽሁፍ አቅርቤ ነበር። በዚህ ጽሁፍ ላይ የተቀመጡ አንዳንድ ነጥቦችን ወስጄ፣ የአቶ ለማ መገርሳ ቡድን አይሎ ከመውጣቱ በፊት የነበሩ፣ የነርሱን ጠባብ ፍላጎት ለማርካት ለህወሃት የከፋፍለህ ግዛ መሳሪያና ኮርቻዎች፣ የኦነግ/ኦህዴድ ሰዎች፣ ሲያራምዱት በነበረው የኦሮሞዉን ማሀበረሰብ በፊደል፣ በስነልቦና፣ በርዮት አለም ከሌላው ማህበረሰብ የመነጠል እንቅስቃሴ፣ ከማንም በላይ የኦሮሞ ማህበረሰብን ራሱ እንደጎዳ […]

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው 100% ነጥብ ይዘው ወጥተዋል

$
0
0
በዚህ በአማራ ክልል በጎንደርና በባህርዳር በተደረጉት ስብሰባዎች ከፍተኛውን ነጥብ ያስቆጠረውና ወያኔን ወጥ በወጥ ያደረጉትና የወልቃይት ጠገዴን ጉዳይ ወደ አደባባይ እንዲመጣና መላው ኢትዮጵያዊ እንዲያውቀው የወልቃይት ጠገዴ ተወካዮችን ጠርተው ጠቅላይ ሚኒስተሩን ያገናኙት እንዲሁም በባህርዳር ህዝቡ ያለበትን ችግር አውጥቶ እንዲተነፍሱ መድረኩን ያመቻቹት የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፍተኛ በሳል የሆነ ስራ ሰርተዋል ። በተለይ በጎንደር ስታዲየም አካባቢ […]

በደጋሃቡር፣ በሽንሌና በጅጅጋ ተቃውሞው በርትቶ ቀጥሏል |ልዩ ኃይል ወደ ሕዝብ ተኮሰ |“ዳውን ዳውን አብዲ ኢሌ”

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከሽንሌ ዞን ተነስቶ ጅጅጋን አካሎ ደገሃቡር መድረሱን ከስፍራው የመጡ መረጃዎች አመለከቱ:: በፈረንጆቹ አቆጣጠር ጁን 5, 2016 በደገሃቡር ዞን በጋሻሞ ወረዳ በጀማ ዱባድ መንደር የአብዲ ኢሌ አስተዳደር በአንድ ቀን 46 ሴቶችን እና ህጻናትን እንደጨፈጨፈበት በሚነገርበት በዚህ ከተማ ውስጥ በዛሬው ዕለት ከፍተኛ ሕዝባዊ አመጽ ተነስቷል:: በሕዝባዊ ተቃውሞውም በአደባባይ የወጣው ሕዝብ […]

ኢትዮጵያዊነት ተሸንፏል? –ብርሀኑ ተክለያሬድ

$
0
0
ምስጋና በደማቸው ፍሳሽ በአጥንታቸው ክስካሽ ውዷን ሀገራችንን ላቆዩልን አበው ጀግኖች ይሁንና ከእነሱ አብራክ የተወለድን ልጆቻቸው ይቺ ውዷን ሀገር ዛሬ ከተጫነባት የአምባገነንነት የዘረኝነትና የድህነት አረንቋ ለማውጣት የአባቶቻችንን ተጋድሎ እየጠቀስን በየፊናችን መታተር ከጀመርን ሁለት አስርታትን አስቆጠርን ታዲያ የእኛ ትውልድ ተጋድሎ ስለምን ሁለት አስርታትን ወሰደ? ዛሬስ ትግሉ በጎመራበትና ህዝቡ የትግሉ ባለቤት እየሆነ በመጣበት ሁኔታ ስለምን የልዩነታችን አጀንዳ ከአንድነት […]

የጠ/ምኒስቴር አብይ ጉዞ ወዴት ያመራል ? ምንስ መስራት አለበት ? ህዝብስ ምን እያለ ነው ? |ከአስገደ ገብረስላሴ ፣ ከመቀለ

$
0
0
ደኩተር አብይ በእውነት በህዝቦች ብሶት ጥያቄ የመጣ ነውን? ወይስ በኢህአደግ ድራማ የተቀናጀ ሴራ ነው ? የዜጎች ግምገማስ ምን ይላሉ ? — የኢህአደግ ያረጀውና ያፈጀው የአቤታዊ ዲሞክራሲ አማራር ሆንብሎ በህዝብ ተጠልቶ ስለሆነ ህዝብ በኢህአደግ ስርአት የነበረውና ያለው ጥላቻ አቅጣጫውን ለመቀልበስእና የተለዬ መፎከር አስመሰሎ የተሰራ ተንኮል ይሆን ? —-የኢህአደግ ስርአት በህዝብ ላይ ያደረሰው ዘርፈ ቡዙ ጭቆና ፣ […]

Sport: ጋናዊው የ21 ዓመት አጥቂ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማውን አኖረ

$
0
0
እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር ታህሳስ 7 1996 በጋና ርዕሰ መዲና የተወለደው የ21 ዓመቱ ሪቻርድ አፒያ 1 ሜትር ከ 75 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው የቀኝ እግር አጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ፈረሰኞቹን ከመቀላቀሉ በፊት ፍሪ ኤጀንት የነበረ ቢሆንም ከዛ በፊት በሩቅ ምስራቅ እሲያ ላኦስ ፕሪሚየር ሊግ ለቻምፓሳክ ዩናይትድ እንዲሁም ለቺታ ኤፍ.ሲ ተጫውቷል። እንዲሁም ለጋና ከ20 ዓመት ብሔራዊ ቡድን ተጫውቶ […]

የሕወሓት ዶሴ ሲገለጥ |በደምስ በለጠ ባማረ መልኩ የቀረበ የቪዲዮ ዘገባ

$
0
0
የሕወሓት ዶሴ ሲገለጥ | በደምስ በለጠ ባማረ መልኩ የቀረበ የቪዲዮ ዘገባ
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live