Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ጥንቃቄ!

0
0
ጥንቃቄ! ዶ/ር ዓብይ አህመድ ወደ ጎንደርና ባህርዳር እንደሚሄዱ መገለጹ አይዘነጋም:: ይህን ተከትሎ የሕወሓት ደህንነቶች እንደለመዱት የሕወሓትን የበላይነት በአማራውና በኦሮሞው ግጭት ላይ ለማስቀጠል በንግግሩ ወቅት የዘረኝነት ስድብ ዶ/ር ዓብይን ለማሰደብ ሰዎችን መመደባቸውን ሌሎች ደህንነቶች መረጃዎችን አሾልከውልናል:: በመሆኑም የአማራ ክልል ነዋሪዎች ከ እንደዚህ ያለው የሕወሓት ነውረኛ ተንኮል እንዳትደናገጡ እየጠየቅን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ የደህንነት ምንጮች መረጃው ለሕዝብ ይፋ […]

ምነው -ፕ/ር ጌታቸው በዚህ ሰዐት- ወደ ጎሰኝነት –ይገረም አለሙ

0
0
  የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ጋዜጠኛ አዲሱ አበበ አዲስ ተመሰረተ የተባለውን አንድ አማራ ድርጅት አስመልክቶ ከአራት ሰዎች ጋር ያደረገውን ውይይት የመጀመሪያ ክፍል አዳመጥኩት፡፡ ይሄ በአማራ ስም ድርጅት መሰረትን የሚል ነገር መች እንደሚያበቃ ከፈጣሪ በስተቀር የሚያውቅ የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ምን አልባት የድርጅት መሪ መባል የሚፈልጉት “አማሮች” በሙሉ ሲዳረሳቸው ያቆም ይሆናል፡፡ ተደራጀን ብለው የውኃ ሽታ የሆኑትም ሆኑ ከማህበራዊ […]

አባዱላ ገመዳ በወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ተተኩ

0
0
(ዘ-ሐበሻ) የኢህአዴግ ፓርላማ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ባቀረቡት መልቀቂያ መሰረት ቦታቸውን ለወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል አስረከቡ:: ከዚህ ቀደም የስልጣን መልቀቂያ አቅርበው እንደገና የሳቡት አቶ አባዱላ ገመዳ በአሁኑ ወቅት ያቀረቡት መልቀቂያ ግን በድርጅታቸው ኢህ አዴግ ተቀባይነት ማግኘቱን ዶ/ር አብይ አህመድ ለምክር ቤቱ አስታውቀዋል:: በዚህም መሰረት አባዱላ በዛሬው ዕለት የአፈ ጉባዔነቱን ቦታ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል አስረክበዋል:: ከፓርላማው […]

ዶ/ር ዓብይ አህመድ የካቢኔ ሽግሽግ አደረጉ

0
0
(ዘ-ሐበሻ) ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በፓርላማ ተገኝተው የካቢኔ ሽግሽግ ማድረጋቸው ታወቀ:: አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲጸድቅ በፓርላማው ሲያስተባብሩ የነበሩት የሶህዴፓው አህመድ ሺዴ በሚኒስትር ማእረግ የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል:: የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ሲራጅ ፌጌሳ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው ሲመደቡ እርሳቸውን አቶ ሞቱማ መቃሳ እንደተኳቸው ከዶ/ር ዓብይ ዝርዝር ለመረዳት ተችሏል:: […]

አስቸኳይ መልእክት ለአማራና ኦሮሞ ሕዝብ! –ነፃነት ዘለቀ

0
0
  ጠ/ሚ ዶክተር አቢይ አህመድ በወያኔው አከላለል ወደ አማራው ክልል ሊሄዱና የሥራና የትውውቅ ጉብኝት ሊያደርጉ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ መልካም ጉብኝት፡፡ ይህን ጉዞ በሚመለከት አንድ የማስጠንቀቂያ ጽሑፍ ከዘሀበሻ ድረገፅ ዛሬ ሌሊት አንብቤያለሁ፡፡ ጥሩ ማሰጠንቀቂያ ነው፡፡ እኔም ትንሽ ነገር መናገር ፈለግሁና መጣሁ፡፡ ወያኔዎች እንደገቡ ሰሞን አምቦ አካባቢ አንድ ስብሰባ ተጠርቶ ነበር፡፡ በዚያ ስብሰባ ላይ የኦህዴድ ይሁን የኦነግ ካድሬ […]

ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

0
0
በደርግ ዘመን በአብዛኛው ለታይታና በተግባር ለማይገለጥ ማስመሰያነትም ቢሆን “ሁሉም ነገር ለሕጻናት!” የሚል መፈክር ይሁን መመርያ በየቦታው በተለይም የሕጻናት ኮሚሽን የሚባለው መሥሪያ ቤት በነበረበት አራት ኪሎ አካባቢ ተለጥፎ ይታይ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በመፈክር ደረጃ በግልጥ ተለጥፎ አይታይ እንጂ “ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ!” እና “ሁሉም ምርጥ ምርጥ ነገር ለትግራዋይ” የሚል መፈክር በሕዝቡ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ነው፡፡ ዐይን […]

ተጨማሪ የሹመት ዜና

0
0
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ:: በዚሁ መሰረት ሹመት የተሰጣቸው የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች 1-ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር በሚኒስትር ማእረግ የዲምክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ 2-ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር 3-አቶ አባዱላ ገመዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር 4-አቶ አህመድ አብተው በሚኒስትር […]

መልካምነት እና መተጋገዝ ብቸኛ አማራጭ ሆኖብን ላደግን፣ በዚህም ለምንኮራ የሀገሬ ልጆች…

0
0
ለሚመለከተው ሁሉ ተጻፈ ዘመን ተቀይሮ አለም አንድ ሆና ጉርብትና ጠነከረ በሚባልበት በዚህ ጊዜ ላይ የምንሰማው እና የምናየው ሁሉ በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረ ከቡር የሆነው የሰው ልጅ በከባድ መከራ እና ስቃይ ውስጥ በላይ እና በታች እሳት እያለፈበት እንደሆነ ለመገንዘብ ከዛም ባለፈ ምን ተሻለን ብለን ለማሰብ አብቅቶናል፡፡ አብዛኞቻችን በየግል ማህበራዊ ገጾቻችን ግድግዳ ላይ በየሰዓቱ በሚባል ደረጃ አዳዲስ የሆኑ […]

ኮማንድ ፖስቱን ከጥቅም ውጪ ያደረገው አዲስ የካቢኔ ሹመት

0
0
(ዳዊት ከበደ ወየሳ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁ በኋላ፤ በሚቀጥለው ቀን ጠቅላይ  ሚንስትሩ ያልሰበሰበው የሚንስትሮች ምክር ቤት እንደተሰበሰበ በማድረግ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታወጀ። ከዚህ አዋጅ ጀርባ የነበሩት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ የመከላከያ ሚንስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ  እና ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ጌታቸው አምባዬ ነበሩ። አዋጁን ካወጡ በኋላ ህጋዊ እውቅና ለመስጠት በሚል፤ ጉዳዩ ወደ ምክር ቤት እንዲሄድ አደረጉት። ይኸው […]

አንዷለም አራጌ የመኪና ስጦታ ተበረከተለት

0
0
(ዘ-ሐበሻ) የሕሊና እስረኛ ሆኖ በኢህአዴግ ማሰቃያ እስር ቤቶች የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ሲሰቃይ የነበረው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራር አንዷለም አራጌ መኪና ተሸለመ:: የትግል አጋሮቹና ወዳጆቹ በማዋጣት የህሊና እስረኛ የነበረውን አንዷለምን የሸለሙት የህሊና እስረኛ የነበሩ ወገኖችን ለማሰብ በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ነው:: አንዷለም አራጌ የመኪናውን ስጦታ የተቀበለው በክብር እንግዳው ዶ/ር ኃይሉ አረአያ እጅ ነው::  

ዶ/ር ዓብይ የባለስልጣናት የውጭ ጉዞ እንዲቀንስ ያሳሰቡበት ንግግር

0
0
ዶ/ር ዓብይ የባለስልጣናት የውጭ ጉዞ እንዲቀንስ ያሳሰቡበት ንግግር

ዛሬ የተሾሙትንና ከቦታቸው ያልተነሱትን ጨምሮ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሙሉ 29 የካቢኔ አባላት ዝርዝር

0
0
1-ደመቀ መኮንን- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር 2-ወርቅነህ ገበየሁ- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 3-ሞቱማ መቃሳ- የመከላከያ ሚኒስትር 4-ታገሰ ጫፎ -የፐብሊክ ሰርቪስና እና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር 5-አብርሃም ተከስተ- የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር 6-ከበደ ጫኔ- የፌዴራል ጉዳዮች እና የአርብቶ አደር አካባቢዎችልማት ሚኒስትር 7-መላኩ አለበል- የንግድ ሚኒስትር 8-ኡባ መሀመድ- የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር 9-አምባቸው መኮንን- የኢንዱስትሪ ሚኒስትር 10-ሂሩት ወልደማሪያም- የሠራተኛና […]

እስክንድር ነጋ -ፓስፖርቱን ነጥቀው ቦሌ ላይ አገቱት

0
0
ክንፉ አሰፋ — አምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመቱን ሲያከብር ለክብር እንግድነት በሆላንድ የጠራው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሊወጣ ሲል በህወሃት ታግቷል። ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም። እስክንድር ነጋ ሃሳቡን በነጻ በመግለጹ ምክንያት የመጨረሻውን ሳንደምረው ለ8 ጊዜ ታስሯል። እ. ኤ. አ, በ 2013 በሽብርተኝነት ተከሶ […]

ጎንደር አብይን እንዴት ተቀበለችው? – (ጌታቸው ሺፈራው)

0
0
ጠዋት 1:30 አካባቢ በመኪና እየዞሩ እየለፈፉ ነው። ሕዝብ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዲቀበል። ሆኖም ሰሞኑን ለመቀበል የሚገቡት ሰዎች ተለይተው እንደታወቁ፣ ወረቀትም እንደደረሳቸው ሕዝቡ ሰምቷል። ካድሬ ነው የሚሰበሰበው ተብሏል። ስለዚህ ለመሄድ ፈቃደኛ አይደለም። ወደ ፋሲለደስ ስቴዲየም ከመግባቴ በፊት ቡና ልጠጣ ተቀምጫለሁ። ሁለት ወጣቶች ቡና እየጠጡ ያወራሉ። “በሙሉ ካድሬ ነውኮ የሚገባው” ይላል አንዱ። “እኔ ለምሳሌ ለመታዘብ ልገባ ነው፣ ለምን […]

ወልቃይት: ለዶ/ር ዓብይ አህመድ የተሰጠ መልስ –ቻላቸው አባይ እና ብርሃኑ ጥሩ ይናገራሉ

0
0
ወልቃይት: ለዶ/ር ዓብይ አህመድ የተሰጠ መልስ – ቻላቸው አባይ እና ብርሃኑ ጥሩ ይናገራሉ

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ሕዝባዊ አመጽ ተነሳ |ሕዝብ ወህኒ ቤት ሰብሮ እስረኞችን አስለቀቀ

0
0
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዛሬ በተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ሕዝብ ከፍተኛ እርምጃዎችን ወሰደ:: አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች በድሬደዋ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የሽንሌ ከተማ እስር ቤት ሰብረው በመግባት ከአንድ መቶ በላይ እስረኞችን ማስለቀቃቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል:: የሕዝቡ አመጽ መነሻ የአብዲ ኢሌ አስተዳደር በትናንትናው ዕለት በርካታ ወጣቶችን በግፍ ማሰሩን ተከትሎ ሲሆን ሕዝቡ እስር ቤት ያሉ እስረኞችን ሰብሮ ካስፈታ […]

የእስክንድር ነጋ የውጪ ሃገር ጉዞ!

0
0
( ይድነቃቸው ከበደ ) ከዛሬ 12 ዓመት በፊት በህወሃት መራሹ የኢህአዴግ “መንግስት” የደህንነት ተቋም አንድ አስገራሚ ገጠመኝ በቦሌ ሃየር መንገድ ተከስቶ ነበር ፤ ነገሩ እንዲህ ነው የደህንነት ተቋሙ ከያዘው ጥቁር መዝገብ ውስጥ “እስክንድር ነጋ” የሚል ስም ተጽፎ ይገኛል ።በወቅቱ የደህንነት መስሪያ ቤት አለኝ ባለው መረጃ “እስክንድ ነጋ” ያሳፈረው አውሮፕላን ጉዞውን ለማቅናት ማኮብኮቢያውን ለቆ ሃየር ላይ […]

ድምጻዊት ቢዮንሴ ኖውልስን የሚያወድስ ልዩ የጸሎት ፕሮግራም ሊዘጋጅ ነው ተባለ

0
0
አዘጋጁ፣ ሳንፍራንሲስኮ የሚገኘው ግሬስ ኤጲስኮፓል ካቴድራል ነው። ይኸው ካቴድራል በድረገጹ ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ “በተለይ ለጥቁር ሴቶች መብት በዘፈኖቿ ታግላለች” ላላት ለቢዮንሴ ኖውልስ የሚሆን ልዩ የጸሎት ሥነ ሥርዓት (ማስ) አዘጋጅቻለሁ፣ አድናቂዎቿ ሁሉ ተገኙልኝ ሲል ጥሪ አቅርቧል። የካቴድራሉ ዋና ፓስተር ፣ ሬቨረንድ ጁዲ ሄርመን ለክሮኒክል ጋዜጣ ሲናገሩ “ለአንዳንዶች የቢዮንሴን ስም የተጠቀምነው ሰው ለመሳብ ሊመስላቸው ይችላል፣ እኛ ግን ኢየሱስ […]

ዶ/ር አብይ የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላቱን ይቅርታ ጠይቋል

0
0
ከጌታቸው ሽፈራው ዶ/ር አብይ አቶ አታላይ ዛፌን፣ጌታቸው አደመን፣ ተሻገር ወ/ሚካኤልና ወረታው አዛናውን ጠርቶ አናግሯል። የኮሚቴ አባላቱን ከወንበር ተነስቶ ይቅርታ ጠይቋል። በውይይቱ ወቅት አቶ አታላይ ዛፌ “ወንድ ልጅ ራሱን ይዞ ያለቀሰበት ጊዜ ቢኖር እርስዎ መቀሌ ላይ በወልቃይት ጉዳይ ከተናገሩ በኋላ ነው። ወልቃይት ብዙ ስቃይ ይፈፀማል። በአማርኛችን እንኳ መዝፈን አንችልም። አስከሬን በወጉ መቅበር አንችልም። አሁንም በወልቃይት ጉዳይ […]

“…የክህደት ውጤቱ ደግሞ ሞት እንደሆነ፣ ከዶ/ር አብይ በላይ የሚያውቅ የለም።”ተማም አባቡልጉ (አንጋፋ የህግ ባለሞያ)

0
0
ሕዝቡ የፈለገው “የሕዝብ ብሶት የወለደው አብይ አህመድ ኢሕአዴግን መንግስቱን እሱ ያለውንና ይጠቀምበት የነበረውን ሁሉ ለሕዝብ ጥቅም ተቆጣጥሮታል” እንዲባል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገር ባለቤትነትን ከነገስታቱ ላይ በ1966 ዓ ም አብዮት ቢያስጥልም ደርግ ቀማው፤ ሕወሃት-ኢሕአዴግን ሆኖ (ነኝ ብሎ) ደርግን ጥሎ የሕዝብ የሆነውን ነጠቀው፡፡ ሕወሃት-ኢሕአዴግ ግንቦት 1983 ዓ.ም እንዳለው ሳይሆን ሀገሪቷንና ያላትን ሁሉ ለራሱ ወሰደ እንጂ ለሁሉም ሕዝብ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live