Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

አምቦ ትናንትና ዛሬ!

$
0
0
ከአንተነህ መርዕድ (ሚያዝያ 2018) አምቦ ስሟ ሲጠራ የብዙዎቻችን ልብ በሃሴት እንደሚሞላ ሁሉ ወያኔዎችና አሽቃባጮቻቸው አጥንታቸው ድረስ የሚዘልቅ ብርድ እንደሚሰማቸው ግልፅ ነው። ያች ምድር የብዙ ጀግኖች መፈጠርያ ናት። ጣልያንን ብርክ ያስያዙ ጀግኖቿን ታሪክ ሲያስታውሳቸው ቢኖርም ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው የአባቶቻቸውን ጋሻ አንስተው የሃገር ጠላት የሆነን ስርዓት በመፋለም ለሌላውም አንቂና አበረታች ሆነው እነሆ እነሱም ታሪክ ሠሩ። አምቦዎች ወያኔን […]

ዶ/ር መረራ ከዶ/ር ዓብይ ጋር ስለነበረው ራት ተናገሩ

$
0
0
ዶ/ር መረራ ከዶ/ር ዓብይ ጋር ስለነበረው ራት ተናገሩ

የምንመኘውን እናገኝ ይሆን?- ባይሳ ዋቅ-ወያ

$
0
0
የዶ/ር ዓቢይን መሾም አስመልክቶ ብዙዎቻችን የተሰማንን ስሜት ከያቅጣጫው አሰምተን ነበር፣ ዛሬም እያሰማን ነው። የሚሰነዘሩትን አስተያየቶችና የድጋፍ ወይም የተቃውሞ ድምጾችን በሚከተሉት አራት ክፍሎች መድቤያቸዋለሁ። የመጀመርያው ቡድን የዶ/ር ዓቢይን መመረጥ ለኢትዮጵያ ትልቅ እፎይታ ነው፣ ሰላምና መረጋጋትን ብሎም ዲሞክራሲና እኩልነትን ያሰፍንልናል፣ እግዜር እንደ ሙሴ ከምድረ በዳ አውጥቶ ወደ ተስፋዋ ምድር ሊመራን በትሩ ተሰጥቷቸዋል በማለት መቶ በመቶ እምነታቸውን የጣሉባቸው ነው። ሁለተኛው ቡድን ደግሞ […]

ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተጻፈ የግል ደብዳቤ (ትርጉም ከንግሊዘኛ)

$
0
0
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ  እ.ኤ.አ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዲስ አበባ   ኢትዮጵያ   “እንደማንኛውም ተራ ደቡብ አፍሪካዊ ዜጋ ዕለት በዕለትየምናከናውናቸው ተግባራት የሰው ልጆች በፍትህ ላይያላቸውን እምነት እና በእራስ የመተማመን መንፈስበማጠናከር ለሁሉም ሕዝብ የተመቸ እና አንጸባራቂ ህይወትለማስገኘት እንዲቻል ይህች ቆንጆ የሆነች ሀገር በፍጹምበፍጹም እንደገና አንዱ በሌላው የማትጨቆን እና የዓለም ሁሉውራጅ እንዳትሆን ጠንክረን መስራት አለብን፡፡” ፕሬዚዳንትኔልሰን ማንዴላ እ.ኤ.አ በ1994 ካደረጉት የመክፈቻ ንግግር የተወሰደ ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾምዎ ልባዊ የሆነ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክቴን ይቀበሉኝ፡፡ የኢትዮጵያ አዲስ ትውልድ አባል በኢትዮጵያ በጣም ከፍተኛውን የስልጣን እርካብ ተቆናጥጦ በማየቴ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ በጋናዊው የኢኮኖሚ ጠበብት እና ጓደኛዬ በሆነው […]

የዋልድባ አባቶች ከእስር ቤት ተለቀቁ

$
0
0
(zehabesha) ዋልድባ መነኮሳት አባ ገ/የእሱስ ኪ/ማርያም እና አባ ገ/ስላሴ ወ/ሃይማኖትን ዛሬ አርብ ሚያዚያ 5ቀን 2010 ከእስር ተፈተዋል፡፡ የኤች አር 128 የሕግ ረቂቅ ማክሰኞ በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መፅደቅን ተከትሎ ክሳቸውን ካቁዋረጡላቸው የ114 የፓለቲካ እስረኞች መካከል የዋልድባ መነኮሳት ይገኙበታል መባሉ ይታወሳል። ባለፈው ሳምንት የዋልድባ አባቶች ተፈተዋል ተብሎ የተወራ ሲሆን የትንሳኤ ዕለት ሊጠይቁዋቸው ለሔዱ ወጣቶች አለመፈታታቸውን መግለፃቸውን […]

ለክቡር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ አገራችን መድበለ ፓርቲ ስርዓት ለመገንባት ከገዢው ፓርቲ/መንግስት ምን እንደሚጠበቅ ለመጠቆም የቀረበ የመነሻ ሃሣብ

$
0
0
ከግርማ ሠይፉ ማሩ girmaseifu@gmail.com girmaseifu.blogspot.com ከብር ጠቅላይ ሚኒሰትር ይህን ከባድ ሃላፊነተት በተረከቡ ዕለት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረጉት  አነቃቂ ንግግር “የሃሣብ ልዩነት መርገምት አይደለም፣ ይልቁንም በረከት ነው፡፡” ባሉት መነሻ፣ ከኢህአዴግ ጋር የሃሣብ ልዩነት ያለን ዜጎች በተናጥል ይሁን በተደራጀ መልክ ሃሣባችንን ለሕዝብ ማቅረብ እንደሚገባን መረዳቶን ተገንዝቢያለሁ፡፡ ከዚህ አንፃር ክቡር ጠቅላይ ሚንሰትር መወሰድ አለባቸው፤ ይገባልም ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች በግሌ […]

የሕብር ዜና ትንታኔ በታምሩ ገዳ ተዘጋጅቶ ቀርቧል –ይመልከቱት

$
0
0
የሕብር ዜና ትንታኔ በታምሩ ገዳ ተዘጋጅቶ ቀርቧል – ይመልከቱት

የቶሎሣ ኢብሳ እናት ዘርሽ ይባረክ! –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አንዳንዴ መመሰጋገን መጥፎ አይደለም፡፡ እንደባህል ሆኖብን ይመስለኛል በሀገራችን ሰውን ማመስገን ብዙም አልተለመደም፡፡ በፈረንጆች ዘንድ ግን ሰውን ማወደስ በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መልካም ነገር ነው፡፡ ሰለጠነ በሚባለው ዓለም “አመሰግናለሁ፤ ይቅርታ(in both senses of ‘sorry’ and ‘excuse me’)፤ እሽ፤ እግዜር ይስጥልኝ…” በጣም የተለመዱ ናቸው፡፡ ጥፋትን ለማረም ራሱ የሚጀምሩት በአወንታዊ አቀራረብ እንጂ እንደኛ ሰውን በመነጀስና […]

ቤት የለሾች ተቀምጠው ዛሬም ባለቤቶች ሊሰበሰቡ ነውን? – (ቃል ኪዳን ኃይሉ)

$
0
0
. አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ ስራቸውን የጀመሩት ህዝቡን በማነጋገር ነው፡፡ ህዝብ ማነጋጋር ደስ የሚል ነገር ነው፡፡ ይበልጥም ደግሞ የመሪዎች ቀርቦ ማወያየት የናፈቀን እኛ፤ እንደውም በስንት ደጅ ጥናት ቢያወያዩንም እነኳ በተለመደና በቆረፈደ እነሱ በማይተውት እኛም በሚሰለቸን አሸባሪ፣ ጠባብ፣ ትምክህተኛ….. በሚሉ አሰልቺ ቃላት የታጨቁ ነገሮች በተሞሉ ንግግር ስናደምጥ ለከርምን፤ እንኳን ቀርበው ርቀው ለማይይናፍቁን መሪ ለነበረን፤ […]

ከመጥረቢያ ብረት የተሰራ ጦር ወደ አቡጀዲ ቢወረውሩት ወደ ጉቶ ይሄዳል –ይገረም አለሙ

$
0
0
በርዕስነት የተጠቀምኩበት አባባል በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍል በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚነገር ነው፡፡ ከ አስራ አምስት አመት በፊት ነው ማሻ የሚኖር ወዳጄ የነገረኝ፡፡በአካባቢው ቋንቋ ሲነገር ለጆሮ ይጥማል፡፡ የጦር ጉዞ አንደወርዋሪው ፍላጎት በመሆኑ  ምሳሌው የሚመለከተው እኛን የሰው ልጆች ነው፡፡ ወረድ ብለን አንመለከተዋለን ፡፡ ሰሞነኛ አጀንዳ የሆኑት የለማ ቡድን የሚባሉት እዚህ ደረጃ ለመድረስ ብዙ ዳገት መውጣታቸውን ቁልቁለት መውረዳቸውን ከእኛ […]

ጎብላንድ ፣ አጭበርባሪው ጦጣ –አገሬ አዲስ

$
0
0
ሚያዝያ 6 ቀን 2010ዓም (14-04-2018) ከአርባ አምስት ዓመት በፊት ተዋቂው ጋዘጠኛ፣ ታሪክና ትችት አቅራቢው አቶ ጳውሎስ ኞኞ በአንድ ወቅት ላይ ባስነበቡን ጽሁፋቸው የጎብላንድን ወይም የአጭበራባሪውን ጦጣ ታሪክ  አቅርበውልን ነበር።ታሪኩ ሲጨመቅ በጥቂቱ ይህን ይመስላል። ከጅንጀሮዎች ጋር ሲሆን ጅንጀሮ፣ ከሰዎችም ጋር ሲሆን እንደሰው ለመሆን የሚቃጣው፣በደረሰበት ሁሉ የሄደበትን የመምሰልና እንደ እስስት የመቀያዬር ችሎታ የነበረው ጎብላንድ የተባለ ጦጣ ነበር።በዚህም […]

ጀኔራል ሳሞራ ተነስተው ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ኤታማዦር ሹም እንዲሆኑ ታጭተዋል

$
0
0
ለጻድቃን ይተርፋል (ደረጀ ደስታ) ሌተና ጄኔራል ጻድቃን በቅርቡ ለሪፖርተ ሲናገሩ እሚከተለውን ብለዋል። የተሾሙትን ምክትል ጠቅላይ ኤታ ማጆር ሹሞች ሁሉንም አውቃቸዋለሁ፡፡ ከተሾሙት መካከል ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ነው ለውድድር የማቀርበው፡፡ ጄኔራል ሰዓረን ከትጥቅ ትግል ጀምሮ ነው የማውቀው፡፡ ረዥም ልምድ ያለውና በብቃቱም በስትራቴጂካዊ አመራሩም የሚታወቅ ነው፡፡ ጄኔራል ብርሃኑ ጁላንም በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት አውቀዋለሁ፡፡ ክፍለ […]

ከ18 አመታት በኋላ… እናቴን አየኋት! |ዳዊት ከበደ ወየሳ

$
0
0
አዲስ አበባ ውስጥ ሊኖር ይችላል ተብሎ በማይገመት፤ ከአንድ ትልቅ ቪላ ስር በተሰራ የምድር እስር ቤት ውስጥ ለአንድ ሳምንት ያህል ቆየሁ። ማንኛውም ሰው ወደዚህ እስር ቤት ውስጥ ሲገባ እንጂ፤ በሰላም ሲወጣ አይታይም። የህወሃት ደህንነት እስር ቤት ነው። እስረኛ ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ፤ አስፈላጊውን መረጃ እንዲሰጥ ይደረግና በለሊት ተወስዶ ይገደላል። እኔ ከዚህ እስር ቤት ልወጣ የቻልኩት፤ “በደህንነቶች ታፍኜ […]

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ ዳግም ኦባማ ወይንስ ዳግም ፑቲን?

$
0
0
ከበየነ ከበደ የራሽያ ፕሬዚደንት በመሆን ከ 2000 ዓም እስከ 2008 ዓም ያገለገሉት እንደገና በ2012 ዓም ለተመሳሳይ ሥልጣን የበቁት ቭላድሚር ፑቲን ቀድሞ ሌኒንግራድ ኋላ ፒትስበርግ እምትባለዋ ከተማ7 Oktober 1952 ዓም ነው የተወለዱት። በ1999 ዓም ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ያባረሩት ቦሪስ የልሲን (Boris Yelsin) የኬጂቢ (KGB) አገልጋይ በመሆን ሲሰሩ የቆዩትን ፑቲንን ወደ ስልጣኑ በማምጣት ወንበሩን በፈቃዳቸው ለቀቁላቸው። ፑቲን በ […]

አቢይ ህዉሀትን በማወደሱ ለተከፋችሁ ደጋፊዎች የቀረበ ጥያቄ:- አቢይ ህዉሃትን ከማወደስ ዉጭ ምን ምርጫ አለዉ? 

$
0
0
ሸንቁጥ አየለ ——————- በራሱ በህዉሀት/ኢህአዴግ በጎ ፈቃድ የተሰዬመዉን እና የህዉሃት/ኢህአዴግ መሪ የሆነዉን አቢይን አንድ ሰሞን አቢዮት ሊያመጣ ነዉ: ወያኔን ሊያፈርስ ነዉ ብላችሁ ያልተመጠነ ድጋፋችሁን ለአቢይ ስትቸሩ የሰነበታችሁ ሰዎች አሁን በፍጥነት በአቢይ ላይ ተቀይማችሁ ባይ ተገረምሁ እና ጥያቄ ልጠይቃችሁ ፈለግሁ:: ጥያቄዬ ቀላል ነዉ:: 1. አቢይ ህዉሃትን ከማወደስ እና የህዉሃትን ተጋድሎ ከማወደስ ዉጭ ምን አማራጭ አለዉ? መለስን […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ እያደረጉት ያለው ጉዞ ቅድምያ የሚሰጠው የነበረ ትክክለኛ ጉዞ ነው (የጉዳያችን ማስታወሻ)

$
0
0
  ጉዳያችን / Gudayachn ሚያዝያ 6/2010 ዓም (አፕሪል 14/2018)ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ ቅድምያ ወደ ሱማሌ፣በመቀጠል ወደ አምቦ፣መቀሌ እና በመጪው ጊዜ ደግሞ ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር መሄዳቸው ትክክል ነው? አይደለም ? ቅድምያ ወደ ካብኔ ምስረታ መሄድ የለባቸውም ነበር? የሚሉ አስተያየቶች እዚህም እዝያም ይሰማሉ።ይህ ግን ከትክክለኛ የስልት እሳቤ አንፃር መመልከት ያልቻሉ ሰዎች አተያይ ነው።ስለሆነም  ቅድምያ ለጉዞ መስጠታቸው […]

የፖለቲካ እስረኛው ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ለጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ደብዳቤ ጻፉ

$
0
0
የፖለቲካ እስረኛ የሆኑት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ደብዳቤ መስደዳቸው ታወቀ፡፡ የልብ ስፔሻሊስት የሆኑት ሐኪሙ ፍቅሩ፤ ለረዥም ዓመታት ከኖሩበት ስዊድን ሀገር፣ ‹‹ወገኔን በሙያዬ አገለግላለሁ›› ብለው መምጣታቸውን ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኋላ ‹‹ታክስ ያልተከፈለበት ዕቃ ከውጭ አስገብተዋል›› በሚል ክስ በቀድሞው የገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በእነ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ከታሰሩ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ […]

የቀድሞው ደህንነቱ ሹም ስለዶ/ር ዓብይ አህመድ አንዳንድ መረጃዎችን አጋለጡ

$
0
0
የቀድሞው ደህንነቱ ሹም ስለዶ/ር ዓብይ አህመድ አንዳንድ መረጃዎችን አጋለጡ

የዐብይ ትዝብት በዐብይ ጾም –ከእውነቱ ፈረደ

$
0
0
  ይህ የትዝብት ጽሁፍ በጥያቄና መልስ ላይ የተመሰረተ ነው። ጠያቂው እውነቱ ፈረደ ሲሆን ተጠያቂው አዲሱ የአሕአዴግ ጠ/ሚኒስትር ሆነው የተመረጡት ዶር አብይ አህመድ እና ተፎካካሪ ነን ባዮች ናቸው። ጥያቄ? ሊቀመንበርና ጠ/ሚንስትር ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት፤ግን የማን ሊቀመንበርና በማን የተመረጡ ጠ/ሚንስቴር ነኝ ብለው ያምናሉ? መልስ ! ዶር ዐብይ፤ እኔ ኢሕአዴግ የመረጠኝ ፣የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ነኝ።ጠቅላይ ሚኒስትርነቴም በኢሕአዴግ […]

ቴዲ አፍሮ እንደዳይመንድ ያንጸባረቀበት ታሪካዊው የአትላንታ ኮንሰርት |ልዩ ዘገባ

$
0
0
እኔ ከሚኒያፖሊስ ዘላለም ከቺካጎ በቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ላይ ለመገኘት አርብ ኤፕሪል 13, 2018 አመሻሽ ላይ አትላንታ ጆርጂያ ገባን:: ቴዲ አፍሮ በተለያዩ ጊዜያትና ምክንያቶች ፓስፖርቱን ሳይቀር ከአውሮፕላን ማረፊያ እየተቀማ ከሃገር እንዳይወጣ በመደረጉና ኢትዮጵያ የሚለው ተወዳጅ አልበሙን ከለቀቀ በኋላ የመጀመሪያው የውጭ ሃገር ኮንሰርት በመሆኑ ይህን ኮንሰርት መታደም ለኛ ልዩ ስለነበር 1,127.3 ማይል አቆራርጠን አትላንታ ደርሰናል:: ከሚኒያፖሊስ አትላንታ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live