Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የዶ/ር አብይ አህመድ ቀጣይ እርምጃ ምን መሆን አለበት? (ሥዩም ወርቅነህ)

$
0
0
ዶ/ር አብይ አህመድ ኢህአዴግ የግንባሩ ሊቀመንበር ሆኖ መምረጡን ተከትሎ ብዙ ሰዎች ጮቤ ሲረግጡ ለመገንዘብ ችያለሁ። ለኢትዮጵያ ለውጥ ያመጣል ብላችሁ ተደስታችሁ ከሆነ ሃሳባችሁ እንዲሰምር ምኞቴ ነው። እኔ ግን ዶ/ር አብይ የመጡበት ወቅት ሳየው ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ ስለገባ የማዕበሉ ማብረጃ ሊያደርጋቸው በመሳብ የሾማቸው ይመስለኛል። የኢህአዴግ መዋቅርና የፓርቲው አሰራር በቡድን በመሆኑ ዶ/ር አብይ የለውጥ ፈር ቀዳጅ ለመሆን ቢፈልጉም […]

አራተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር

$
0
0
ሁንዴሳ አብዱል ህወሓት/ኢህአዲግ ሥልጣን ከያዘ አራተኛውን ጠ/ሚ/ር በትናንትናው ዕለት እንደመረጠ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሰበር ዜና ብሎ በጥንቃቄ የተዘጋጀውን መልዕክት ባልተለመደ ሁኔታ ሶስት ጊዜ ደጋግሞ አንብቦልናል። በደንብ እንዲገባን ታስቦ ሳይሆን አይቀርም። እርግጥ ፓርቲው ሊቀ መንበሩን ቢሆንም የመረጠው የፓርላማ ሥርዓትን በሚከተሉ ሀገሮች እንደሚደረገው የገዢው ፓርቲ ሊቀ መንበር የሀገሪቱ መሪ ይሆናል። ሥርዓቱ የተሟላ እንዲሆን በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት […]

የድርሰቱ ሴራ ሲተነተን :- አቢይን በመምረጥ ህዉሃት ለሶስተኛ ጊዜ ጊዜአዊ ባለ ድል ሆናለች:: እንዴት? ሸንቁጥ አየለ

$
0
0
ህዉሃት በ1983/84 ዓም ኦነግን ይዛ ቀሪዉን የኢትዮጵያ ህዝብ አግልላ ምናምንቴ ህገ መንግስት እና ኢትዮጵያዉያንን የሚያባላ ክልል ያጸደቀች ጊዜ ብዙ ኢትዮጵያዉያንን እና አለም አቀፍ ማህበረሰብን ማታለል ችላ ነበር:: በድጋሚም በ1997 ዓም ምርጫ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ለዉጥ ፈልጎ ቅንጅትን ሲመርጥ ሶስት ጣምራ ስትራቴጂዎችን ተጠቅማ ህዝባዊዉን ሀይል ከጫዋታ ዉጭ እንዲሆን አድርጋዉ ነበር::ይሄዉም የቀኝ ክንፍ አክራሪ ሀይሎች መጡብህ የሚል ማስደንበሪያ: […]

አዲሱ የኢህአዴግ ሊ/መንበር የኢትዮጵያን ህዝብ ጥያቄ በተግባር መመለስ አለበት! አርበኞች ግንቦት 7

$
0
0
የዶ/ር አብይ መመረጥ ኢህአዴግ ውስጥ ያሉት እስካሁን የህወሀት ሎሌ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ድርጅቶችና በህወሓት ውስጥም ያሉ አንዳንድ ለውጥ ፈላጊዎች በጋራ አሸንፈው ከሆነና እነ ዶ/ር አብይ በተለይ በኦህዴድ ምክር ቤት ስብሰባ መግለጫ ላይ ያወጡትን ለውጥ ፈላጊ አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ ወስነው ከሆነ እሰየው ነው። የኢህአዴግ ዉሳኔ በአገራችን በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል፥ ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና […]

የዶ/ር አብይ ሹመትና የሙሴ በትር

$
0
0
ከያሬድ ኃይለማርያም፤ መጋቢት 28፣ 2018 እ.አ.አ ዶ/ር አብይ አህመድ ቀጣዩ ጠ/ሚ ሆነው የመመረጣቸው ነገር በብዙዎች ዘንድ ቀድሞ የተገመተም ቢሆንም በሰበር ዜና መልክ ስሰማ ደስታና ስጋት የተቀላቀለበት ስሜት ተሰምቶኛል። ደስታዮ ከሁለት ምክንያቶች የመነጨ ነው። የመጀመሪያው የህውሃት ግትርነትና ማናለብኝ ባይነት በሕዝብ ትግል፤ በተለይም ቄሮዎች ባደረጉት ትንቅንቅ እና በከፈሉት ከፍ ያለ መስዋዕትነት ሲሰበር ማየቴ ነው። ይህ ድል ላለፉት […]

የለዉጡ ማዕበል የመጨረሻዉ ምዕራፍ ደረሰ – ዳንኤል ጎበዜ

$
0
0
ዓለም ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ትኩረት ሠጠ የለዉጡ ማዕበል የመጨረሻዉ ምዕራፍ ደረሰ አገራችን ኢትዮጵያ በትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ቁጥጥር ስር ከወደቀችበት ጀምሮ በዉስጥም በዉጭም በዜጎች ላይ የአፈና ዘመቻ ለ27 ዓመታት ያህል ተካሂዷል፤ የአገሪቱን አንጡራ ሃብት እያጋበሱ የአካባቢ መሪወችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በገንዘብ እዬደለሉ ኢትዮጵያዊያንን አጥቅተዋል/ ለሞት ዳርገዋል፤ ጩኸታቸዉ በየዲፕሎማሲዉ ማህረሰብ እንዳይሰማ በአጎራባች አገር ተሰደዉ እንኳ እንዳይቀመጡ ነብሰ […]

‎የህወሃት የበላይነት እንኩትኩቱ የወጣበት የምርጫ ውጤት ምስጢር

$
0
0
(ወንድወሰን ተክሉ) *** ህወሃት በራሷ የቆረጣ ስልት ፈረንጆቹ Bit by their own game እንዳሉት ክፉኛ ተቆራርጣ ተመትታለች፡፡ የአቶ ለማ መገርሳና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቀደም ሲል የተመሰረተ ህብረትና አንድነት ህወሃትን በታሪካ ለመጀመሪያ ግዜ ተንበርካኪና ተሸናፊ በማድረጉ ታላቁ ድል ዛሬ ነው ስል ልናገር የቻልኩት፡፡ በህወሃታዊያን የሆርን አፌሩ ዳንኤል የአይጋ ፎረሙ እና መሰሎቹ ሲቀደዱብን ፤ አቶ ደመቀ ተመርጧል፤ […]

አብይ ጉዳይ! ይፈቱ! ይፈቱ! ይፈቱ!

$
0
0
ጌታቸው ሽፈራው ጋዜጠኛ እስክንድርን ጨምሮ መጋቢት 17/2010 ዓም 30 ሰላማዊ ሰዎች ታስረዋል። እነ እስክንድር አዲስ አበባ ላይ ለእስረኞች ምስጋና የተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ነው የታሰሩት። ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ አራት ቀን ሞላቸው፣ ባለፉት ሁለት ቀናት የእስር ቆይታቸው የተሻለ ነበር። ዛሬ ደግሞ አስከፊ ወደሆነው የእስር ክፍል መልሰዋቸዋል። “የኮማንድ ፖስቱን ውሳኔ እየጠበቅን ነው” እየተባለ እነሱ በአስከፊ እስር ላይ ናቸው። […]

የጠ/ሚ አቢይ ምርጫ አንድምታ (Implications) –ከያሬድ ጥበቡ

$
0
0
ከእፎይታ ምሽትና መኝታ በኋላ ስለአቢይና የመመረጡ ትርጉም ብዙ አውጠነጠንኩ ። በአቢይ ምርጫ አንዱ ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ የተነሳው ቀንበር፣ ኦሮሞ በመሆናችን፣ ሙስሊም በመሆናችን እኩል አንታይም የሚለው ትርክት ነው ። ይህ ትርክት እውነትም ሆነ ምናባዊ፣ ዛሬ በአቢይ ምርጫ የተነሳ መፍትሄ አግኝቷል። ይህ ትልቅ ክንዋኔ ነው። ዴሞክራሲያዊ የሚባሉ ብዙ የምእራብ ሃገሮች እንኳ ሊያደርጉት የማይችሉትን ነው ኢትዮጵያችን ባለፉት ስድት […]

ለ ዶ/ር አብይ አህመድ አቅ ማሳያ ወሳኝ ማስታወሻ! ከሙሉቀን ገበየው

$
0
0
የገዢው ፓርቲ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መጋቢት 18 ፣ 2010 በመምረጦው እንኳን ደስ አለዎት። በአሰራር ደንባችሁ መሰረት በቅርብ ቀን ደግሞ የኢትዮጲያ መንግስት ጠቅላይ ሚኒስቴር ይሆናሉ። እርሶዎ ስልጣን ላይ የመጡበት ግዜ በአገራችን ታሪክ እጅግ ወሳኝ ሰአት ላይ ነው። ኢትዮጲያ መስቀለኛ መንገድ ላይ ናት። እጅግ ፈታኝና የተወሳሰበ ስራ ይጠብቆታል። በልጅንትዎ ገና 15 ወይም 16 አመት ወጣት ሁነው በ […]

ዶ/ር አብይ አህመድ እና የኢትዮጵያ ህልውና! |ዳዊት ከበደ ወየሳ

$
0
0
በአጼ ምኒልክ ዘመን ነው። የራስ ደረሶ ጦር አባይን ተሻግሮ፤ የራስ ጎበና ጦር ደግሞ ጊቤን አልፎ መሃል መንገድ ላይ ይጋጭ ጀመር። የግጭቱ ምክንያት… አንደኛው ጦር ሌላውን፤ “ድንበር አልፈህ የኦሮሞን ህዝብ የሚያስቀይም ስራ ሰርተሃል።” የሚል ነው። ሁለቱም እርስ በርሳቸው መወቃቀሳቸው ሳያንስ፤ ጉዳዩ ወደሁለቱም አለቆች ዘንድ ደረሰና፤ የጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት እና የሸዋ ንጉሥ የነበሩት ንጉሥ ምኒልክ ተቀያየሙ። ከዚያም […]

ማደንዘዣ ወይንስ ዕድሜ መግዣ?

$
0
0
መጋቢት 18 ቀን 2010ዓም (28-03-2018) በበሽታ ዕድሜ ልኩን የሚሰቃይ ሰው እድልና አቅሙ ፈቅዶለት ለሕክምና ቢሄድ፤የመረመረው ሃኪም ለበሽታው የሚሆን ትክክለኛ መድሃኒት ሳይሰጠው ማስታገሻ ወይም ማደንዘዣ ወይም የተሳሳተ መድሃኒት ቢሰጠው ከሚያሰቃዬው በሽታ ወይንም ህመም ተገላገለ ወይም ተፈወሰ ማለት አይደለም።ማደንዘዣውም ለተራዘመ ጊዜ ሳይሆን ለአጭር ጊዜ የበሽተኛውን ጩኸትና ስቃይ ለማለሳለስ የሚረዳ በመሆኑ የማደንዘዣው አቅም እየቀነሰ ሲሄድ የሚያሰቃዬው በሽታ ተመልሶ […]

ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰረቱ ሞክረዋል በሚል በሃሰተኛ ወንጀል የተከሰሱትና በእነ አቡበክር አብደላ መዝገብ የተካተቱት ግለሰቦች ከ 4 እሰከ5 አመት በሚደርስ የእስር ጊዜ ተቀጡ

$
0
0
(ቢቢኤን) በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች “ሃይማኖታዊ ዓላማን ለማራመድ በመንግስት መመራት የለብንም፣ ለመንግስት ግብር ሊከፈል አይገባም እና እስላማዊ መንግስት መመስረት አለብን” በማለት ተንቀሳቅሰዋል በሚል ሃሰተኛ ክስ በፌደራሉ አቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸውና በእነ አቡበክር አብደላ መዝገብ የተካተቱ ግለሰቦች የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ታወቀ። ኢስላማዊ መንግስት ሊመሰረቱ ሞክረዋል በሚል የተከሰሱት በእነ አቡበክር አብደላ መዝገብ የተካተቱ ግለሰቦች ዛሬ መጋቢት 19/2010 ከቂሊንጦ […]

ኢትዮጵያዊው አባት በአሜሪካ በግፍ በጥይት ተገደለ

$
0
0
ነገሩ የሆነው ዳላስ ቴክሳስ ነው። የ72 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ አቶ አዳነ የምሩ፣ በዳላስ ቴክሳስ ፣ ቬንቴጅ ፖይንት ድራይቭ ላይ በሚገኝ ሆሊዴይ ኢን በጸጥታ አስጠባቂነት (ሴኩሪቲ) ይሰሩ ነበር። ፖሊስ እንደሚለው ዛሬ ዕሮብ (ማርች 28) ንጋት ላይ ራንዳል ቴሪል የተባለ አፍሪካ አሜሪካዊ በሆቴሉ አካባቢ፣ ያለ ሥራ ሲመላለስ ያገኙትና ፣ ከአካባቢው እንዲርቅ ይነግሩታል። በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ለከተማው ቴሌቪዥን እንደተናገሩት፣ […]

የትግራይ ወያኔ በሰሜን ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ ከተማ ትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ተማሪዎችን በእሳት አቃጠለ

$
0
0
መጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:45 ሲሆን በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ ከተማ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በክፍል በተቀመጡቀት በእሳት አቃጥለውታል ፡፡ ይህን ቃጠሎ የፈፀሙት የህወሓት አባላት ሲሆኑ እነዚህ ይህን እኩይ እና አስነዋሪ ዘግናኝ ስራ የፈፀሙት የህወሓት ደህንነቶች ሲዝቱ እንደነበር እና በአካባቢው ለሚገኙ የብአዴን ሰዎች ቢነገራቸውም ችላ በማለታቸው ይህ ድርጊት ሊፈፀም […]

ከሆነማ መልካም? –ከገዙ በቀለ (ዶ/ር)

$
0
0
ነገሩ አንዳንዴ ቢሆንም፣ ከሐዘን ወደ ደስታ የሚወስድ ነገር መቼም አይታጣም። በዚህ አኳያ ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ምድር ላይ ካላው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሲተያይ ደስታዬን ከፍ አድርጎታል። ቀጥሎም ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ የሚለው ግምቴም ትልቅ ነው። ገና ምኑ ታይቶ ሊባል ይቻላል፤ ተገቢ ነው።አላያማ ያመኑት… የተባለው ብሂል መከተሉ ነው። የታሰበው  ካልሆነ የተለመደውን ብዕሬን ማሾሌ አይቀሬ […]

“እስከቤተሰቦቼ ድረስ ያስፈራሩኝ ነበር”–ሃይለማርያም ደሳለኝ

$
0
0
ከውስጥ አዋቂ የመጣ መረጃ እንደወረደ: አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተጠቃሎ ወደ ድምፅ አሰጣጥ ከመኬዱ በፊት የምናገረው ነገር አለኝ በማለት የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል። “እኔን ሊተካ የሚሄደው ሰው እንደእኔ እንዳይሆን እውነቱን እናገራለሁ። ሊያሰሩኝ አልቻሉም፣ ያስፈራሩኛል። እስከቤተሰቦቼ ድረስ ያስፈራሩኝ ነበር ፣ እኔ ምንም ልሰራ ያልቻልኩት ለዛ ነው ” ብለዋል ። ከህወሃት ከተገኙ የምክር ቤት ተወካዮች […]

ዛሬ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ተፈታታኝና ወጣሪ ሁኔታ ኢ.ሕ.አ.ፓን መተንኮስ ለምን አስፈለገ? (ፍየል ወዲህ፣ ቅዝምዝም ወዲያ!)

$
0
0
ታምሩ ባልቻ   ኢትዮጵያ ሕዝብ ልጆቹ እየተፈጁበትም አዳዲስ ትውልድ መተካቱን አያቆምም። ዛሬ በሀገራችን ዉስጥ እያደገ፣ እያወቀና እየጎመራም በመምጣት ላይ ያለው ኢትዮጵያዊ ትውልድ ስለ ቀዳሚው ትውልድ፣ መጥፎውንም ሆነ ጥሩውን ታሪኩን ማወቁ የማይቀር ነው። ኢ.ሕ.አ.ፓን ጭምር ስላካተተው ትውልድ፣ በተለይም የትውልዱ ፈርጦች ከነበሩት፣ ከኢ.ሕ.አ.ፓ አባላት የሀገራዊ ለውጥና ዕድገት ራዕይ፣ እምነትና ገድሎች ትክክለኛውን ነገር አዲሱ ትውልድ ማወቅ ይገባዋል:: ኢትዮጵያችን […]

ተስፋና ስጋት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሹመት |ከሳዲቅ አህመድ

$
0
0
 “ከቃለ-መሓላ በሗላ ተራምደው ወደ አራት ኪሎ የሚገቡበት ቀይ ምንጣፍ በመላው አገሪቱ የፈሰሰው የሰማእታት ደም መሆኑ መዘንጋት የለበትም!”    ከሳዲቅ አህመድ ልክ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ሲሞቱ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የነበረው ተስፋ አሁን ናኝቷል። ጠቅላዩ ቢሞቱም ተጠቅላዩ ሐይለማሪያም መጡና ሐይል-አልባ መሆናቸውን አሳዩ። የመለስ ሞት በዙፋኑ ላይ ያፈናጠጣቸው ሐይለማሪያም ደሳለኝ ፈልገውትም ይሁን በህወሃት አለቆቻቸው ታዘው እነደሆነ ዉሉ ባለየ […]

ተስፋና ስጋት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሹመት –ከሳዲቅ አህመድ

$
0
0
 “ከቃለ-መሓላ በሗላ ተራምደው ወደ አራት ኪሎ የሚገቡበት ቀይ ምንጣፍ በመላው አገሪቱ የፈሰሰው የሰማእታት ደም መሆኑ መዘንጋት የለበትም!”    ከሳዲቅ አህመድ ልክ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ሲሞቱ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የነበረው ተስፋ አሁን ናኝቷል። ጠቅላዩ ቢሞቱም ተጠቅላዩ ሐይለማሪያም መጡና ሐይል-አልባ መሆናቸውን አሳዩ። የመለስ ሞት በዙፋኑ ላይ ያፈናጠጣቸው ሐይለማሪያም ደሳለኝ ፈልገውትም ይሁን በህወሃት አለቆቻቸው ታዘው እነደሆነ ዉሉ ባለየ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>
<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596344.js" async> </script>