Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ወርቅና ሃቅ እያደረ ይጠራል፤ –የእነ አባይ ጸሐዬን ውሸት የሚያጋልጥ ከትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር የተላከ ጽሁፍ

$
0
0
ህወሓት በመላው ኢትዮጵያ እየተደረገበት ባለው ትግልና ጫና ተገዶ፥ እንደዚሁም በኢህአዴግ ራሱ ውስጥ ባሉት ፓርቲዎች መካከልም በተፈጠረው ፉክክርና ፍትጊያ የተነሣ ምስጢር አድርጎ ደብቆት የነበረውን ሐሰትና ማወናበድን አንድ ባንድ እያለ እያጋለጠው ይገኛል። ይህ ሁኔታ እዚህ ላይ የሚቆም ኣይደለም፣ ህዝቡ መብቱን ለማስከበር ቆርጦ ተነስተዋልና። ቀደም ብሎ የማጥራት ዘመቻ በሚል ኣስመሳይ እንቅስቃሴ፥ የማስተዳደር ድክመት እንዳለው፣ የዴሞክራሲ ሂደቱን እንዲጠብ ማድረጉን፣ […]

”ቆራጣው ዮሀንስን ”ፍለጋ [ ቬሮኒካ መላኩ]

$
0
0
እኔ ከፌስ ቡክ ከተወገድኩ በኋላ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ብዙ ነገሮች ተከስተው አለፉ። ምስኪኑ ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከስልጣኑ ተወገደ ወይም ራሱን አስወገደ ። ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ አርሲጣጢለስ፤ “የሰው ልጅ ፖለቲካዊ እንስሳ ነው” ብሎ ያኖረው ዘመን ተሻጋሪን ምልከታ እውን ይሆን ዘንድ “ፖለቲካ አልወድም ” ሲል የከረመው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስቴር በመተንበይና በጉዳዩ ላይ በመተንተን ተጠምዶ […]

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን ያዳምጥ |እኛን በማዘናጋት እየተሰሩ ያሉ ሴራዎች |ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስና ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውን ይስሟቸው

$
0
0
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን ያዳምጥ | እኛን በማዘናጋት እየተሰሩ ያሉ ሴራዎች | ዶ/ር ዲማ ነገዎ፣ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስና ዶ/ር ጌታቸው በጋሻውን ይስሟቸው

ብአዴን፤ ህወሃት፤ በረከትና ሌሎችም

$
0
0
ከሚኪ አማራ የሃይለማሪያም ስልጣን መልቀቅ የበረከትና የአባዱላ ጥምረት ግፊት መሆኑ ታዉቋል፡፡ ሀወሃት በጉዳዩ ላይ ሲያመነታ እንደነበርና እንዲሁም የእነ አባዱላን ዉሳኔ ተከትሎ የእልክ በሚመስል መልኩ ፈጥኖ ወደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሄደም ተነግሯል፡፡ በኢህአዴጉ የ 17 ቀን ስብሰባ አባዱላ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ላይ ጄኔራሎችን መቆጣጠር አልቻለም የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር፡፡ በረከትም አልቻልክም የአመራር ክፍተት ተፈጥሯል በዚህም ምክንያት ድርጅቱና […]

ዶ/ር ሐሰን ሁሴን በሚኒሶታ የተቋቋመው የኢትዮጵያውያን የዕርቅና የዲሞክራሲ መድረክ ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) ልዩነቶችን አቻችሎ አንድነትን ለማጎልበት በሚል ዋና ዓላማ በሚኒሶታ የተቋቋመው የኢትዮጵያውያን የዕርቅና የዲሞክራሲ መድረክ ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 24, 2018 በሴንት ፖል ከተማ የተሳካ ሕዝባዊ ስብሰባ አካሄደ:: ከተለያዩ ማህበረሰብ አካላትና ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች እና እንዴት ልዩነቶችን አቻችሎ ወደ አንድነት መምጣት እንደሚቻል ውይይት ተደርጓል:: በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ የተለያዩ ምሁራን እና የሃይማኖት […]

ማንም ጤነኛ የሆነ ሰው እየሰጠመ ባለ ጀልባ ላይ አይሳፈርም፤ በተለይ ለአማራና ኦሮሞ የፓርላማ አባላት |አቻምየለህ ታምሩ

$
0
0
እንደሚታወቀ በአማራና ኦሮሞ መከራ ላይ ድሎቱን ያደላደለው የፋሽስት ወያኔ አገዛዝ የትግራይ ወታደሮችን እያሰማራ አማራንና ኦሮሞን በይፋ መጨፍጨፍ ከጀመረ ሶስት አመታትን አስቆጥሯል። ሕዝባችን እስካሁን ድረስ ባካሄደው ፍትሐዊና ሰላማዊ ትግል በሺዎች የሚቆጠሩ ንጽሐን ኢትዮጵያውያንን ለትግራይ ወታደሮች ገብሯል። ባሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሐንን በግፍ የረሸነው ፋሽስት ወያኔ ተጨማሪ ሺዎችን በእሩምታ ለመጨፍጨፍና ለመረሸን የፓርላማ አባላቱ ከጎኑ እንዲሰለፉና ይፋዊ ፍቃድ […]

ጀግናው አርበኛ ጎቤ መልኬ ከተሰዋ አንድ ዓመት ሞላው

$
0
0
በአማራ ተጋድሎ ሥር የወያኔን ተገንጣይ ስርዓት ሲፋለም ቆይቶ በመጨረሻም በጠላት ተላላኪ በተኛበት እንዲገደል የተደረገው አርበኛ ጎቤ መልኬ እነሆ ከተሰዋ አንድ ዓመት ሞላው:: አርበኛ ጎቤ ቢያልፍም ብዙ ጎቤዎችን ተክቶ አልፏል:: ጎቤን ለማስታወስ ባለፈው ዓመት ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አዘጋጅቶት የነበረውን የማስታወሻ ዘገባ በድጋሚ አቅርበንላችኋል – ይመልከቱት::

ሀገር የሌለዉና ኢትዮጵያዊነቱን የተነጠቀ ህዝብ ከመሆንም የከፋዉ የጋራ መጻኢ ራዕይ የሌለዉ ህዝብ መሆን ነዉ |ሸንቁጥ አየለ

$
0
0
አንተ ኦሮሞ ነህ: አንተ ትግሬ ነህ: አንተ አማራ ነህ: አንተ ከምባታ ነህ: አንተ ሲዳማ ነህ አንተ ደግሞ ከዚህ ወይ ከዚያ ብሄር ነህ በማለት ቀዳሚ ማንነትህ ብሄርህ እንጅ ኢትዮጵያዊነትህ አይደልም ስለዚህ የምትይዘዉ መታወቂያ ኢትዮጵያዊነት የተፋቀበት : የብሄር ማንነትህ የተለጠፈበት ነዉ ሲል በዘረኝነት: በአምባገነነትና በማንነት ቀዉስ ዉስጥ የገባዉ ወያኔ አወጀ:: የብሄር ማንነት ሰጠሁህ ተብሎ በግድ የጎሳ ፖለቲካ […]

ይድረስ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት:    ድምፃችሁ ሕወሀትን ወይስ ኢትዮጵያን ለማዳን?

$
0
0
ከበድሉ በዛብህ ለዚህ ፅሁፍ  መነሻ የሆነኝ የሰሞንኛው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለምን አስፈለገ ለሚለው ጥያቄዬ አጥጋቤ ምላሽ ለማግኘት ባለመቻሌ ነው :: በመሰረቱ ሀገርን እመራለሁ ብሎ በሚልዮናች የሚቆጠሩ የአገሪቷ ሕዝቦች መፃኢ ዕድል ላይ በመወሰን ላይ የሚገኘው መንግስት ከስልጣኑ በላይ ለህዝቡ ማሰብ አለበት :: በእርግጥ መንግስት የህዝቡንም  ሰላም እና የሀገሪቱን ፀጥታ የማስከበር ግዴታ እንዳለብት አይካድም :: ሆኖም  ታድያ በአሁኑ […]

‘ሥርዓት የማፍረስ እና ሥርዓት የመገንባት ሂደት ውጣ ውረድ!’ |ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ

$
0
0
ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ (ሸክም የበዛበት ትውልድ፡ 2009 እና  የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ) ከሥልጣን ፖለቲካ ወደ ፖለቲካ ባላደገ ከተናጠል ፍላጎት በላይ የኾነ የጋራ ፍላጎት፤ ከጋራ ፍላጎት በታች የኾነ ነጠላ ፍላጎት ልዩነት በሌለው በሥልጣን ፖለቲካ አስተሳሰብና አመለካከት ቅኝ በተገዛ – በእምነቱ፣ በእውቀቱና በድርጊቱ ውስጥ አንዱና ዋነኛው ባሕሪያዊ መገለጫው አፍርሶ መገንባት – ነገሮችን ከዜሮ የመጀመር ሥነ ልቦናዊና […]

ኦህዴድ ለአባዱላ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ፤ የአባዱላና የበረከት ፍቅርና ሌሎችም

$
0
0
ከሚኪ አማራ አባዱላ ስልጣን ከለቀቀ በኋላ ምክንያቱን ሳይናገር እንደገና እንደተመለሰ እናዉቃለን፡፡ ህወሀት አባዱላን አንተ ኦህዴድ ዉስጥ ያለዉን እብደት አስተካክል እንጅ ብትፈልግ ጠቅላይ ሚኒስቴር አለያም የመከላከያ ኢታማዘዦር ትሆናለህ ተብሎ ቃል ተገብቶለት እንደተመለሰ ታዉቋል፡፡ በረከትም ቢሆን አንተ ጥለህ ወተህ ድርጅቱን ማን ሊረከብ ነዉ፡ ተመለስና ነገሮችን አስተካክል ያስቀየምንህን ነገርም እናስተካክላለን አግባብም አልነበረም ተብሎ ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት ህዋሀት ሁለቱን […]

ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት? –በታምሩ ገዳ የተዘጋጀ ዜና ትንታኔ ይመልከቱ

$
0
0
ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት? – በታምሩ ገዳ የተዘጋጀ ዜና ትንታኔ ይመልከቱ

አዋጁ!!! 

$
0
0
ከመለሰ ድርቤሳ ኦህዴድ በፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስቀረት ከፈለገ በምክር ቤቱ ካሉት ከራሱ አባላት ውጭ ውስን ድጋፍ ማግኘት ብቻው በቂ ነው፡፡ የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 93 ቁጥር 3 (ሀ) ላይ አዋጁ በ2/3ኛ ድጋፍ ድምፅ ካልጸደቀ ውድቅ እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡ ይህ ማለት ከ547 የምክር ቤቱ ኣባላት የ182ቱ መቃወም ብቻ አዋጁ እንዳይፀድቅ ማድረግ ይችላል፡፡ ኦህዴድ ለማሳለፍ ካልተባበረና ከራሱ አባላት […]

ሕወሓት የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትን ማሰር ጀመረ |ነቀምት ከተማ መረጋጋት የለም

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት ኮማንድ ፖስት በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ:: በኮማንድ ፖስቱ አማካኝነት ኦህዴድን ለመምታት ከፍተኛ ሥራ እየሰራ እንደሚገኝም ተጋልጧል:: በነቀምትና ዶምቢዶሎ ከተማ ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በነበረው ህዝባዊ አመጽ የተደናገጠው የሕወሃት መራሹ መንግስት ትናንት በኮማንድ ፖስቱ አማካኝነት ባወጣው መግለጫው ለሰራዊቱ የግደል ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል:: በዛሬው ዕለት የኦህዴድ ባለስልጣን የሆኑት የነቀምት ከተማ ከንቲባ አቶ ካባ […]

ከአድዋ ድል ማግስት፤ አጼ ምኒልክ እና ኤርትራ( ከ ሙሉጌታ ገዛኸኝ)

$
0
0
የአድዋውን ጦርነት ድባብ በርካታ የውጭ ጸሓፍት በስፍራው ተገኝተው የዘገቡት ቢሆንም ከአገሬው ዐይን እማኝ ታዳሚዎች መካከል የአጼ ምኒልክ መዋእለ ዜና አሰናጁ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሤ ወልደአረጋይ ለዛ ባለው አገላለፅ ሲፅፉት ያስደምማልI-« እንዲህም እስኪሆን ድረስ ከሌሊቱ በ 11 ሰዓት የጀመረ እስከ 4 ሰዓት ድረስ ተኩስ አላባራም፣ ድምፁም እንደ ሐምሌ ዝናብ እንደያማባራው ነበረ፤ በኖኅ ሰማዩ ተነድሎ መሬቱን አጠፋው […]

ሰሜን ኮርያ ለሶርያ የኬሚካል መሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ ተመድ አስታወቀ

$
0
0
(ቢቢኤን ዜና) የሶርያ መንግስት፣ የኬሚካል ጦር መሳሪያዎችን በድጋፍ መልክ ከሰሜን ኮርያ እያገኘ እንደሚገኝ ተመድ አስታወቀ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለጸው ከሆነ፣ የበሽር አላሳድ መንግስት በኬሚካል የሚቀመሙ የጦር መሳሪያዎችን ለማምረት የሚረዱ የተለያዩ ግብአቶችን ከሰሜን ኮርያ እየተቀበለ ይገኛል፡፡ ሰሜን ኮርያ የኬሚካል ጦር መሳሪያዎችን ለሶርያ እያቀረበች የምትገኘው በድጋፍ መልክ መሆኑን ተመድ ቢገልጽም፤ የሶርያ ሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምር ተቋም ግን […]

የፓርላማ አባላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያጸድቁት ጫና እየተደረገባቸው ይገኛል ተባለ

$
0
0
(ቢቢኤን ዜና) በገዥው ፓርቲ ፓርላማ ውስጥ አባል የሆኑ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መጽደቅ እንዳይቃወሙ ጫና እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ በመጪው አርብ የካቲት 23 ቀን 2010 አስቸኳይ ስብሰባ የተጠሩት የፓርላማው አባላት፣ በዕለቱ አዋጁ ይጽደቅ አይጽደቅ በሚለው ጉዳይ ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አባላቱ፣ በዜጎች ላይ ጦርነት የሚያውጀውን አዋጅ በመቃወም ድምጽ እንዲነፍጉት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ዘመቻ እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ […]

በነቀምት ከተማ ሰዎች እየታሰሩ እንደሚገኙ ተጠቆመ

$
0
0
(ቢቢኤን ዜና) ነቀምት ከተማ ዛሬም በውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ ታወቀ፡፡ ከተማዋ ካለፈው ሰኞ የካቲት 19 ቀን ጀምሮ ህዝባዊ ተቃውሞ ስታስተናግድ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህን ምክንያት በማድረግም አገዛዙ በንጹኃን ሰዎች ላይ ጥይት መተኮሱ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን፤ የጸጥታ አካላት በሚወስዱት የኃይል እርምጃ የተነሳ ከተማዋ በዛሬው ዕለትም በውጥረት ውስጥ ትገኛለች ብለዋል-የመረጃ ምንጮች፡፡ በከተማዋ የሰፈሩት የአጋዚ ጦር ወታደሮች፣ በየቦታው ተሰግስገው፣ የነዋሪዎችን […]

በኢትዮጵያ በድጋሚ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ

$
0
0
(ቢቢኤን ዜና) በሀገር ቤት የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠባቸው ከተሞች ቁጥር መጨመሩን ለማወቅ ተቻለ፡፡ ቢቢኤን እንዳገኘው መረጃ ከሆነ፣ ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ ተነፍጓቸው ከቆዩ ከተሞች በተጨማሪ ሌሎች ከተሞችም ከሰሞኑ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ተደርገዋል፡፡ በተለይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መውጣት ተከትሎ፣ በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ሲፈጸም የቆየው አፈና በድጋሚ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ የአዋጁ አፈጻጸም መመሪያ ተብሎ ይፋ የተደረገው ሰነድ፣ ኮማንድ ፖስቱ ባሻው […]

አድሏዊ ሐዘኔታ (Selective Sympathy) በዓለማችን ለምን ሰለጠነ? – (ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)

$
0
0
===================== +++ ለሶሪያ ሰቆቃ ዓለም የማያዝንበት ምክንያቶች፤ +++ ዓለም ለአገራችን ሰቆቃ የማያዝንባቸው ምክንያቶች ++++ «አድሏዊ ሐዘኔታ (Selective Sympathy) ምንድነው?» በሚል ርዕስ ተጽፎ የነበረና ድጋሚ የተለጠፈ የቆየ ጽሑፍ፥ ———————————————- አድሏዊ ሐዘኔታ (Selective Sympathy) ማለት ተመሳሳይ ችግር የገጠማቸው ሁለት ወገኖች ቢኖሩ፣ ለአንዱ አዝኖ ለሌላኛው አለማዘን፣ ወይም ለአንዱ የበለጠ አዝኖ ለሌላኛው የነካነካ ሐዘን፣ አላዘኑም ላለመባል፣ ዕንባ ሳይመጣ «ወይኔ […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live