Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ተከብሮ ያላስከበረ ሕገ-መንግስት…… ከይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ሃላፊ)

0
0

ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ የፀደቀበት ቀን ነው፡፡ይህንንም ተከትሎ በመንግስት አሳሳቢነት እልፍ ሲልም አስገዳጅነት ህዳር 29 በየዓመቱ ከተለያዩ ጎሳ የተወጣጡ ሰዎች ተሰባስበው በመንግሰት ሹማምንቶች ፊት በአደባባይ ከበሮ የሚደለቅበት ቀን ነው፡፡ይሁን እንጂ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን መልካም ፍቃድና ተሳትፎ ባልታየበት የፀደቀው ህገ መንግስት በብዙሃን ዘንድ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ የገባ ነው፡፡በዚህም መሠረት ከቃሉ አጠቃቀም ጀምሮ እስከ አከባበሩ ክብረ በዓል አብዛኛዉ ሰው እኔንም ጨምሮ ግድ አይሰጠንም፡፡
‹‹ይህ ህገ-መንግስቱን የመነዳ ተግባር ነው!!!›› ከገዢው መንግስት ተደጋግሞ የሚሰማ ለመፈረጅ ወይም ለመከሰስ የሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ ‹‹ ይህ ህገ መንግሰት ዝም ብሎ የተደረደረ ብሎኬት ነው እንዴ የሚናደው ?›› በማለት ሲተች ሰምቸዋለው፡፡በመናድ እና ደግፎ በማቆየት ላይ የተመሠረተሁን ህገ መንግስት እጅግ በጣም ብዙ ነገር ተብሎለታል፡፡

(ይድነቃቸው)

(ይድነቃቸው)


እየተንገዳገደ ያለው ህገ መንግስት ከአፀዳደቁ ጀምሮ የሚቀሩት ድንጋጌዎች መኖራቸው ለማንም ግልፅነው፡፡ ቢሆንም ፀድቆ በተግባር ላይ የሚገኘው ህገ መንግስት ዋጋ እንዳይኖረው እያደረገ ያለው የገዢው መንግስት አካሄድና ተግባር መሆኑ በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለው፡፡
1ኛ. መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለው በሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕሱ አንቀፅ 3 ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ይሁን እንጂ ገዢው መንግስት በሃይማኖት ላይ ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት እየፈፀመ ይገኛል፤ለዚህም ጥሩ ማሳያ የሚሆነው በእስልምና አይማኖታ እየተፈፀመ ያለው በደል ነው፡፡በደሉ በይፋ የወጣ ሲሆን በተለይ ለእምነታችን እንቢኝ ያሉ ለሞት፣ለእስርና ለእንግልት ተዳርገው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪ በኦርቶዶክስ እምነት ውስጥም ጣልቃ ገብነቱ እንደተጠበቀ ነው፡፡ገዳማትና አድባራት በልማት ስም ፈርሰዋል የተቀሩት ቦታቸው ተጎምዶ ተወስዶል በዚህም ምክንያት የሀይማኖት አባቶችና ጥቂት የማይባሉ የእምነቱ ተከታዮች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል፡፡
ከምንም በላይ ደግሞ በሁሉም በተለይ በኦርቶዶክስና በእስልምና የሀይማኖቱ መሪዎች (አባቶች) ሹመታቸው ከሚያመልኩት አምላክ እና ከምዕመናኖ የመነጨ ሳይሆን በመንግስት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት የተፈፀመ ነው፡፡
2ኛ. የመንግስት አሠራር ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት፡፤ በሕገ መንግስት አንቀጽ 12 ንዕሱ አንቀፅ 1 ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ቢሆንም ከታችኛው የስልጣን እርከን ከሆነው ከቀበሌ ጀምሮ እስከላይኛው የመንግስት ባለስልጣናት አማከኝነት የሚከናወኑ የመንግስት አሰራሮች ግልፅነት እጅግ በጣም ጠባብ ነው፡፡በመሆኑም ህብረተሰብ በአገሩ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን በመንገስት አሠራር ላይ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አልተደረገም፡፡
በዚህም ምክንያት የመንግስት አሠራር ለሙሱና የተጋለጠ ነው፤ሙሱና በአሁን ወቅት በአገራችን ህጋዊ እስከመሆን ደርሷል፡፡በመሆኑም ማናኛውም የመንግስት ኃላፊ ኃላፊነቱን ወይም ስልጣኑን መሠረት አድርጎ ሲበድል እንጂ ለበደሉ ተጠያቂ ሲሆን አልታየም፡፡ስለዚህም የመንግስት አሠራር በየትኛውም ደረጃ ለህዝብ ግልፅ አይደለም ይህ ደግሞ የህገመንግስቱ ድንጋጌ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
parlama
3ኛ. ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት አለው፡፡ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 14 ተፅፎ ይገኛል፡፡ነገር ግን የሰው ደህንነትን ለመጠበቅ የተቋቋመው የደህንነት መስሪያ ቤት በየደኑና በየጫካው የስንቱን ሰው ህይወት እንዳጠፋና የአካል ጉዳት እንዳደረስ የሚያውቀው ያውቀዋል፡፡ በተጨማሪ ይህ የነፃነት መብት ገዢው መንግስት በችሮታ ወይም በፍቃዱ የሰጠን እንጂ ሰው በመሆናችን ያገኘነው መብት እንዳልሆነ በሚያሳብቅ መልኩ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነፃነት መብት በገዢው መንግስት መልካም ፍቃድ ላይ የተመሠረተ እስከሚመስል ደረስ ተደርሷል፡፡
4ኛ. ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት ፣ኢሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 18 ላይ ይገኛል፤ ይህ የህገመንግስት ድንጋጌ መሸራረፍ ሳይሆን መገርሰስ የሚጀምረው በህገመንግስቱ በተቋቋመው በህግ አስፈጻሚው አካል ነው፡፡
በመሆኑም ክብርን ለማወረድና ጭካኔን ለማሳየት የሰለጠኑ አሰቃዮችና ማሰቃያ ቦታዎች መኖራቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ነገሩን ለማነፃፀር እንዲረዳ ፖለቲከኛ ወይም በህግ ጥላ ስር ያለ ሰውን ይቅርና ስታዲዮም እግር ኳስ ለመመልከት ወራፋ የሚጠብቅ በወረፋ ምክንያት ለተነሳ አለመግባባት ፖሊስ እንዴት አድርጎ እንደሚቀጠቅጥ ዱላውን የቀመሰ ያውቃል፡፡
5ኛ. በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብዓዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ መልኩ የመያዝ እና ከሰዎች ወይም ከጠያቂዎቻቸው የመገናኘት መብት አላቸው፡፡ በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 21/1እና2 ተፅፎ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ ነፃ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች አያያዛቸው ክብርን ከመንካት አልፎ በህይወታቸው ላይ አደጋ የሚያስከትል ነው፡፡በተጨማሪ ከቤተሰብ፣ከወዳጅ መጠየቅ የማይሞከር ነገር ነው፤ የመጠየቅ እድል ያላቸው እስረኞች እድላቸው በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
6ኛ. ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የአመለካከት እና ሐሳብን በነፃ የመያዝና በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ የመግለፅ ነፃነት አለው፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 29 ተፅፎ ይገኛል፡፡ በእርግጥ ይህ መብት ገደብ ሊጣልበት እንደሚችል በህገ መንግስቱ ላይ ተገልፆ የተቀመጠ ሲሆን ገደብ ግን መሠረታዊ የሆነውን መረጃን የመስጠት እና የማግኘት እንዲሁም አስተሳሰብ ላይ ወይም አመለካከት ላይ ውጤት እንደማይኖረው በህገመንግስቱ ተገልፆ ይገኛል፡፡
ይሁን እንጂ አሳብን በነፃ ማሰብና ማንሸራሸር በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አዳጋች ነው፡፡ነፃ አሳብ የሚንሸራሸርባቸው ነፃ ጋዜጦችና መፅሔቶች ምን ያህል አሉ ? እርግጥ ነው ገብያውኑ መሰረት ያደረጉ መዝናኛ ላይ ያተኮሩ መፅሔትና ጋዜጣ ለቁጥር በዝተው ይሆናል፡፡ ግን ሁሉ ነገር በአገር ነው የሚያምረው! ታዲያ ስለ አገር በነፃ አሳብ የሚንሸራሸርበት መፅሔትና ጋዜጣ ምን ያኸል ነው ? ጋዜጠኞችን በማሰቃየት፣በማሰር እና እንዲሰደዱ በማደረግ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ መጥፎ ሪከረድ አስመዝግባለች፡፡መንግስትን ተችቶ የፃፈና ፁሁፉ የወጣበት ጋዜጣ ወይም መፅሔት ጨምሮ ሁሉም ተጠራርጎ ቃሊቲ የሚገባበት ወይም አደገኛ ዛቻና መስጠንቀቂያ የሚሰጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡
7ኛ. ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ ሠላማዊ ሠልፍ እና ስብሰባ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 30/1 ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆን የቅርብ ጊዜ አይን ያወጣ የህገመንግስት ጥሰት ማቀረብ ይቻላል፡፡በሳውዑዲ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍና በደል ይቁም፣ይህንንም የፈፀሙ ለፍርድ ይቅረብ በማለት አቤቱታ ለማቅረብ የተጀመረው ሠላማዊ ሠልፍ በፖሊስ ዱላ እና እስራት ነው የተጠናቀቀው፡፡ በተጨማሪ በመንግስት እየታየ ያለው የአስተዳደር ብሉሹነት ለማመልከት እና ምላሽ ለማገኘት የተጠሩ የተለያዩ የተቃውሞ ሰልፎች እና ስብሰባዎች በመንግስት ቀጥተኛ ትእዛዝ ተከልክሏአል፡፡ሠላማዊ ሰልፍ ማድረግ እና አቤቱታ ማቅረብ መብት ነው! በማለት ክልከላውን ወደ ጎን በመተው አደባባይ ለመውጣት የሞከሩ ለእስርና ለድብደባ ተዳርገዋል፡፡በመሆኑም የተቃውሞ ሠልፍና ስብሰባ በማድረግ አቤቱታ በኢትዮጵያ ማድረግ የሞት ሽረት ትግልና ጥያቄ ከሆነ ሰንብቷል፡፡
8ኛ. የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግስት ባለስልጣን ሆነ አካል ተፅዕኖ ነጻ በመሆን በሙሉ ነፃነት ከህግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም፡፡በማለት በህገመንግስቱ አንቀፅ 79 እና በተከታዮቹ ንዑስ አንቀፅ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች የመንግስት አስፈፃሚ አካል ከሆነው ነው ሹመታቸውን የሚያገኙት፡፡በመሆኑም ከመንግስት ጋር ቀጥተኛ ግኝኙነት ያላቸው የፍርድ ውሳኔዎች ምንያኽሉ በህግ እና በህሊና ላይ የተመሠረቱ ናቸው ? በተለይ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የፍርድ ሂደታቸው ምን ይመስል ነበር ? እነዚህን እና መሰል ዳኝነቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በህገመንግስቱ የሰፈረው ነጻ ዳኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው፡፡
millitery ethiopian9ኛ. የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የጎሳዎች ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል፡፡ ተብሎ በህገመንግስቱ አንቀፅ 87/1 ተደንግጎ ይታያል፡፡ነገር ግን በየድንበር እና በተልኮ ጭዳ ከሚሆነው ውጪ አብዛኛው የሠራዊቴ አባል እና አዛዥ የአንድ ጎሳ ስብስብ ነው፡፡ ስለዚህም ሠራዊቱ የማነው የኢትዮጵያ ወይስ ወደሚል ጥያቄ እያመራ ይገኛል፡፡
10ኛ. በየደረጃው ትክክለኛ ምርጫ እንዲካሄድ ከማንኛውም ተጽእኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ይቋቋማል፡፡የሚለው በህገመንግስቱ አንቀፅ 102 ላይ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ሹመታቸው ከመንግስት መልካም ፍቃድ የመነጨ ሲሆን አሰራራቸውም ለገዥው መንግስ በእጅጉ በጣም ያደላ ነው፡፡ስለዚህም ምርጫ ቦርድ ህገመንግስቱን መሠረት አድርጎ ነጻ እና ገለልተኛ ነው ለማለት ከበድ ድፍረትን የሚጠይቅ ነው፡፡

በመሆኑም እነዚህ እና መሰል የህገመንግስቱ ድንጋጌዎች ጥሰት ወይም በእነሱ ቋንቋ የመንድ ተግባር እየተፈፀመ ያለው በህገመንግስቱ በየወንዙ ዳር የሚማማለው ገዥው መንገስት ነው፡፡ ህገመንግስት የበላይ ህግ ነው፡፡ማንኛውም ህግ፣ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣን አሰራር ከህገመንግስቱ የሚቃረነረ ከሆነ ተፈፃሚነት አይኖረውም ፡፡ የሚለው አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 የገዥው መንግስት ደራሽ ዉሃ ጠራርጎ ወስዶታል፡፡ ስለዚህም የብሔሮ፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን የሚለውን መጠሪያ ስም በመስጠት ከበሮ ተይዞ የሚደለቅለት እና የሚከበረው ህገመንገስት መልሶ ካላስከበረ ፌሽታው እና ቀረርቶው ከምን የመነጨ ነው ?


የኢትዮጵያውያን ስቃይ ከሳዑዲ ወደ ዚምባብዌ፡ በዚምባብዌ በርካታ ኢትዮጵያውያን ታሰሩ

0
0

በዚምባብዌ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን

በዚምባብዌ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን

(ዘ-ሐበሻ) በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ስቃይ ባልበረደበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያውያን አበሳና ስቃይ በየዓለማቱ እየበረታ መሄዱ እየተዘገበ ነው። ከወደ ዚምባብዌ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ይገኛሉ።

በዚህ ሳምንት ብቻ 12 ኢትዮጵያውያን ዚምባብዌ ፖሊስ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሃገሬ ገብተዋል በሚል የታሰሩ ሲሆን ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የዙምባዌ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

በርካታ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ያለው ችግርን መቋቋም ተስኗቸው በአራቱም አቅጣጫ እየተሰደዱ ሲሆን እነዚህ በዚምባብዌ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን መድረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ ያደረጉ እንደነበር ታውቋል። በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዚምባብዌ ውስጥ የሃገሪቱን ድንበር ካለ ህጋዊ ወረቀት አቋርጠዋል በሚል ክስ ተፈርዶባቸውና በክስ ሂደት ላይ ሆነ በእስር ላይ እንደሚገኙ የዚምባብዌ የዜና ምንጮች በተደጋጋሚ መዘገባቸው ይታወሳል።

እነዚህ ሰሞኑን በዚምባብዌ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን የተገኙት ወደ ደቡብ አፍሪካ አሻጋሪያቸው ሊሆን ይችላል በተባለ ዚምባብዌ ቤት ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት የሃገሪቱ ዜጎች የቤቱ ባለቤቶች በጠቅላላ ህጋዊ ያልሆኑ ስደተኞችን በመርዳት ወንጀል እንደሚጠየቁ ዘገበዋል።

በዚምባብዌ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ከሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ውስጥ በእንስሳ የሚበሉ፣ በመንገድ ላይ የሚሞቱ እንዳሉ በዚያ ቦታ ያለፉ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊነት የታላቁን የሰላም አባት የኔልሰን ማንዴላ ህይወት የታደገ ታላቅ ሚስጢር …. አነጠረ

0
0

ኢትዮጵያዊነት የታላቁን የሰላም አባት የኔልሰን ማንዴላ ህይወት የታደገ ታላቅ ሚስጢር …. አነጠረ።

ወርቁ ፈለቀ፤ ገድሉ – ተገለጠ፤ እውነት -ሳቀ፤ የሙያ ሥነ – ምግባር
ከበረ፤ በዘውዳችን በሻንበል ጉታ ዲንቃ ….
„የተከበሩ ረቂቅ ሰው ናቸው“ ይሏቸዋልም።

ታሪክ ይዋባል። ኢትዮጵያ የኔልሰን፤ ኔልሰንም የኢትዮጵያ … ፍቅር – ድህነት።

ከሥርጉተ ሥላሴ

(ስርጉት)

(ስርጉት)

ወደ አራት ወራት ሆነኝ የሲቢሊቲ ሩም ታዳሚ ከሆንኩኝ። ወረፋው አይጣል ነው። ሌሊት ላይ ተነስቼ ድንጋይ አስቀምጥና ድምጹን ቀንሼ እተኛለሁ። አሁን አሁን ሰንበት ይናፍቀኛ ጀምሯል። ያው እዬተዝናኑ ቁምነገር መልቀም መልካም ነውና ተመቸኝ። የአባ መላን ሞደሬተርነትም እወደዋለሁ። ይስቃል … ቀልድ ጣል … ጣል ያደርጋል …. ይችላልም። እርግጥ ስጀምረው ትንሽ የሚታመሱ የመንደር ጉዳዮች በተለይም እስከ አባ መላ የመጀመሪያ ቡና ድረስ ነበሩ። ከዛ በኋላ ሁሉም ነገር መልክ ይይዝና መኮምኮም ነው። … የዛሬው ሰንበት ግን ወርቅን ያነጠረ ዕንቁ ነበር …. ዋው! እግዚአብሄር የኢትዮጵያዊነትን ሚስጢር ከኔልሰን ማንዴላ የህይወት ዘመን ጋር እርስ በእርሳቸው እንደ ሊማሊሞ መንገድ አያይዞ ፍትኃት የሰጠበት ታላቅ ቀን ነበር። ሳንተኛ ተግተን ከሰራንበት ኢትዮጵያዊነትን የክብር ካባ በ21ኛው ምዕተ ዓመት የሚያጎናጽፍ ፍጹም አዲስ የወርቅ እንክብል በእጃችን ሰተት ብሎ እንሆ ገባ። ተመስገን አልኩ ማለት ነበረብኝና። እኔ እንደማስበው የኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ገና የሚፈልቅ ልዩ የሰማይ ሥነ – ጥብብ ብዬ ነበር። ዛሬም እላሁ – በድፍረትና በእርግጠኝነት።

Click here to view the embedded video.

እንደሰማን …. በተደሞና በግራሞት ሁላችንም ተደመምን … አባ መላ / አቶ ብርኃኑ ዳምጤ/ የሩሙ ባለቤት ዛሬውኑ አድራሻውን ፈልጌ ቃለ ምልልስ አድርጋለሁ በማለት በጸጸት ቃል ገባ … እየተቁነጠነጥን ሰዓቱን ጠበቀን። ሰዓቱ በጣም ራቀ … አይደረስ የለም ደረሰ …. በቀጥታ ከጀግናው ጋር ቃለ ምልልሱ ተጀመረ … በባተሌው ጠቅለል ሲል … እንዲህ ነው ….

የ78 ዓመት አዛውንት ናቸው። ምዕራብ ሽዋ አንቦ አካባቢ ነው የተወለዱት። የቄስ ትምርት ቤት ትምህርታቸውን እዛው አካባቢ አጠናቀው የአንደኛ ደራጃ ትምህርታቸውን እስከ 6ኛ ክፍል ተምረው፤ ከዚህ በኋላ ወደ ተመረጡበት ወደ ውትድርና ሙያ ተሰማሩ – በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ። ከህግ ባለቤታቸው ከወ/ሮ አስቴር ፈንታ ጋር በሥርዓተ ጋብቻ የሁለት ሴት ልጆችና የስድስት ወንድ ልጆች እንዲሁም የአራት የልጅ ልጆች አባት ባለ ጸጋ ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ ላፎቴ ካልተሳሳትኩ በ450.00 የኢትዮጵያ ብር በጡረታ ይኖራሉ። የታሪካችን አንብርት የተከበሩ ሻንበል ጉታ ልጆቻቸው የተሟላ ድጋፍና እንክብካቤ እንደሚያድረጉላቸው አባ መላ ካደረገላቸው ቃለ ምልለስ ለማወቅ ችያለሁ።

የኢትዮጵያዊነታችን ሚስጢር የሆኑት እኒህ ታላቅ ሰው እንደ ቀደምቶች ወርቆቻችን እንደ አብዲሳ አጋ፤ እንደ አብርኃም ደቦጭ፤ አንድ ሞገስ አስገዶም እንደ ዘርዓይ ደረስ ታሪክን የፈጠሩ የነፃነታችን ቀንድ ናቸው። ለእኛ ብቻ አይደለም የዓለም የነፃነት ትግል ጠባቂና አዲስ ፊኖሚና እንዲሁም አምክንዮም ናቸው ብል ማገነን ተብዬ እንደማልከሰስ ነው። ዘውዳችን የሆኑት እኒህ እንቁ የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ለተለዬ ተልዕኮ ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ በስውር፤ በረቂቅና በርቀት እንዲጠብቋቸው ከተመደቡት ወገኖቻችን አንዱ ነበሩ። የሰላም ሐዋርያውን ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ይገልፆቸዋል“ ስልጡን ….የተከበሩ ረቂቅ ሰው ናቸው። ቀልጣፋና አንባቢ፤ ሰውነታቸውን በማፍታት በተለይም በቦክስ ስፖርት ላይ የሚተኩሩና መዝናናትም የሚወዱ ነበሩ“

ብሄራዊ ኃላፊነታቸውን በጀግንነት የተወጡት እኒህ ታላቅ ሰው ሳንበል ጉታ፤ ኔልሰን ማንዴላ ለስልጠና በመጡ በወራቸው በአንድ የስልጠና ጓደኛቸው ኔልሰን ማንዴላ ህይወት በአጭሩ ለመቅጨት ከአሴረው ድርጅት ጋር አብረው እንዲሰሩ ተጠዬቁ። እዬፈሩ ፈቃዱን ተቀበሉ። ምሳ እቴጌ ሆቴል ተጋባዙ፤ ተልዕኮው ተነገራቸው፤ የ2000.00 ፓውንድ ብርና ካሜራም ተሰጣቸው። ሂደቱን በፎቶ እንዲያነሱ ተገለጸላቸው። የግድያው እቅድ መራራ ነበር። በገመድ አንቀው እንዲገድሉ ነበር የተነገራቸው። ከግድያው በኋላ ከኮልፌ የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ ጣቢያ 500 ሜትር ላይ በርቀት በመኪና እንደሚጠብቃቸውና ከዚህ በኋላ ውጭ ሀገር እንደሚኖሩ፤ ከድህነት ጋርም ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ እንደሚፈቱ ተነገራቸው። ውሉ በጳውሎስ ቤተክርስትያን ቃል እንዲታሰርም ተሰማሙ። ሁሉን ከከወኑ በኋላ ታማኙ ወታደር በቀጥታ ወደ አዛዣቸው በመሄድ ዝርዝር ሪፖርቱን ገለጹ ለጄ/ ታደሰ ብሩ። ዕለተ ሰንበት ልክ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት የነፃነትን ነፍስ የታደገ ሕይወት፤ የዘርኝነትን ቅስም የሰበረ፤ የአፍሪካ መብራታ እንዲጠፋ ነበር ብይኑተ። ለዛውም በፍጹም ሁኔታ ታምና አፍሪካ ልጇን ለላካችባት የነፃነት ዓርማ ሀገር ኢትዮጵያ መሬት ላይ። ለተልእኮው አንድ ነጭና ሌላ ጥቁር ሰው እንደነበረ ባለ ታሪኩ ይናገራሉ …. ድርድሩ ቅዳሜ ነበር።

ክቡር ሻንበል ጉታ በበነገታው ሰንበት ተራኛ ነበሩ። ቅደመ መሰናዶውን ያሟለው ወታደራዊ የደህንት ክፍል ወንጀሉን ቀድሞ ስለደረሰበት አከሸፈው። … ቅጣቱም ለስም የለሽ ተሰጠ። …. እሩቅ ቦታ ተመደበ …. ሁለቱ የውጭ ሀገር የሴራው መሪዎች በ24 ሰዓት ኢትዮጵያን እንዲለቁ ተደረገ። የኛው ክብር፤ ተክሊላችን ሻንበል ጉታም ዲንቃም ኃላፊነታቸውን በድልና በብቃት አጠናቀቁ። ታማኝታቸው ለኢትዮጵአዊነት ክብር ሸለሙ። የተሰጣቸውን የ2000.00 ፓውንድና ካሜራም አስረከቡ ለክፍሉ። ሚስጢሩ በሚስጢርነት ቀጥሎ ለሌሎች የሙያው ባልደረቦች ሹመት ሲሰጥ በሚስጢር የዛሬው ሻንበል ጉታ የ10 አለቃነት ለደበበ የ50 አለቃነት ማዕረግ ተሰጠ ይላሉ። ድንቁ …. ይህም ሚስጢር ነበር። የሚገርመው ሂደቱም ድርጊቱም ሚስጢርነቱ እጅግ ጥብቅ መሆኑ ነው።

የታወቁት የተከበሩት ኔልሰን ማንዴላ በስውርና በርቀት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ሆነ የግድያ ሙከራው ታስቦ እንደከሸፈ ሳያውቁ ነበር ያለፉት። ዛሬ …. ለነገም ሌላ ከመቃብር በላይ ሌላ አዲስ ትዕይታዊ የታሪክ ምዕራፍ ኪኖ ልበለው ገድል …. የመረጣችሁትን ብያለሁ። ያን ጊዜ በሴራው ውስጥ ስለነበረው ዛሬ 08.12.2013 አባ መላ ሲጠይቃቸውም ስሙን ለመስጠትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም። ይህ በራሱ ከወርቅ የነጠረ ወታደራዊ ሥርዓት …. ያኮራል። ግን ዛሬ …. ቅንቅን የበላው ይመስለኛል በወያኔ …

ህልም ነባራቸው የሀገራቸውን ባህላዊ ልብስና ጃኖ የተግባር አዛውንቱን፤ የጽናት አብነቱን፤ የምህረት ድርጊተኛውን አጎናጽፈው ከኔልሰን ጋር ፎቶ ለመነሳት …. ለ2 ዓመታት ቢጥሩም አልተሳካላቸውም። የመንፈስ ሚስጢራቸውን እንደ ቋጠሩ ዛሬ ሀዘናቸው መራር ቢሆንም በቀብሩ ላይ ለመገኘት ፈልገዋል። እንኒህ ታላቅ ሰው የዓለምን ተስፋ የታደጉ በመሆናቸው በርካታ ዓለም ዓቀፍ ሽልማት ማግኘት አለባቸው እላለሁ። ቢያንስ ዛሬ ለቀበር ሥርዓቱ በክበር እንዲገኙ በደስታ ምኞታቸውን ለማሳካት ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖቻችን ሥጦታቸውን በደስታ አክበረው በማሰተናገድ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ በወገኖቼ እዬተማመንኩ ቢዛ ካገኙም መሄድ በቀብር ሥርዓቱ ላይ መገኘት ስለ አለባቸው የሎቢ ተግባራትን ከመከወን በተጨማሪ ጠቅላላ ወጪያቸውን እንሸፍን ዘንድ ቆሜ እለምናችኋለሁ።

አዎን …. የመጨረሻው የተከበሩ የኔልሰን ማንዴላ ጉዞ ድንገተኛ ነበር። የምሽት እራት ግብዣ ነበር። ዝግጅቱም በክበቡ ነበር። ከሌሎች አርቲስቶች ጋር ቀደምቷ አርቲስ ሂሩት በቀለ ተገኝታለች። በመጨረሻዋ ሰዓት የፈጥኖ ደራሽ የማዕከሉ አዛዥ ጄ / ታደሰ ብሩና የሰላሙ አባት ኒልሰን ማንዴላ አብረው አሳለፉ። የነበራቸውን ልዩ አድናቆት፤ ክብርና ፍቅራቸውንም የተከበሩ ጄ/ ታደሰ ብሩ የወገባቸውን ኮልት 38 ሽጉጥ ፈተው ለኔልሰን ሸለሙ። ልጅን፤ ክብርን የመስጠት ያህል ነበር። ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ለወዳጁ ለቅዱስ ዮኋንስ ቀበቶውን እንደ ሰጠው ሁሉ። ዕንቁው አባታችን ከ ኢትዮጵያ እንደተመለሱም ነበር የካቴና ስንቅ የሆኑት።

የላቀ ሜዳሊይ፤ ዓለም አቀፍ ሽልማትና ተደማጭነትን ሊአተርፍ የሚችለው ይህን ታላቅ ተልዕኮ የእፍሪካ እናት ምድር፤ የዓለም እናት እምዬ ኢትዮጵያ ስታስተናግድ በዛን ወቅት በአጠቃላይ በካንፑ ውስጥ የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ስልጠና የሚያውቁ 5 ሰዎች ብቻ ነበሩ። ጠባቂዎቹ ከጄኒራላቸው ጋር በቀጥታ የመገናኘት መብት ነበራቸው። ተፈልፍሎ … ተዝቆ የማያልቅ ብቃትና መክሊት …. ከድንቅነሽ አንባ ….

ኮንታክት ኢሜል ለእርዳታ bdamte56@gmail.com

ኢትዮጵያዊነት የነጠረ ወርቅነት!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደትን በተመለከተ የተዘጋጀ ሁለተኛ የምክክር ጉባኤ

ባንዳ አገር ሳይመራ!! በ አንተነህ ሽፈራው

ኢትዮጵያዊነት የታላቁን የሰላም አባት የኔልሰን ማንዴላ ህይወት የታደገ ታላቅ ሚስጢር …. አነጠረ።

0
0

ወርቁ ፈለቀ፤ ገድሉ – ተገለጠ፤ እውነት -ሳቀ፤ የሙያ ሥነ – ምግባር

        ከበረ፤ በዘውዳችን በሻንበል ጉታ ዲንቃ ….

        „የተከበሩ ረቂቅ ሰው ናቸው“ ይሏቸዋልም።

ታሪክ ይዋባል። ኢትዮጵያ የኔልሰን፤ ኔልሰንም የኢትዮጵያ … ፍቅር – ድህነት።

                                            

ከሥርጉተ ሥላሴ

MwiETHወደ አራት ወራት ሆነኝ የሲቢሊቲ ሩም ታዳሚ ከሆንኩኝ። ወረፋው አይጣል ነው። ሌሊት ላይ ተነስቼ ድንጋይ አስቀምጥና ድምጹን ቀንሼ እተኛለሁ። አሁን አሁን ሰንበት ይናፍቀኛ ጀምሯል። ያው እዬተዝናኑ ቁምነገር መልቀም መልካም ነውና ተመቸኝ። የአባ መላን ሞደሬተርነትም እወደዋለሁ። ይስቃል … ቀልድ ጣል … ጣል ያደርጋል …. ይችላልም። እርግጥ ስጀምረው ትንሽ የሚታመሱ የመንደር ጉዳዮች በተለይም እስከ አባ መላ የመጀመሪያ ቡና ድረስ ነበሩ። ከዛ በኋላ ሁሉም ነገር መልክ ይይዝና መኮምኮም ነው። … የዛሬው ሰንበት ግን ወርቅን ያነጠረ ዕንቁ ነበር …. ዋው! እግዚአብሄር የኢትዮጵያዊነትን ሚስጢር ከኔልሰን ማንዴላ የህይወት ዘመን ጋር እርስ በእርሳቸው እንደ ሊማሊሞ መንገድ አያይዞ ፍትኃት የሰጠበት ታላቅ ቀን ነበር። ሳንተኛ ተግተን ከሰራንበት ኢትዮጵያዊነትን የክብር ካባ በ21ኛው ምዕተ ዓመት የሚያጎናጽፍ ፍጹም አዲስ የወርቅ እንክብል በእጃችን ሰተት ብሎ እንሆ ገባ። ተመስገን አልኩ ማለት ነበረብኝና። እኔ እንደማስበው የኢትዮጵያዊነት ሚስጢር ገና የሚፈልቅ ልዩ የሰማይ ሥነ – ጥብብ ብዬ ነበር። ዛሬም እላሁ – በድፍረትና በእርግጠኝነት።

ዕለቱ ስለ ረቂቁ ጸጋ ስለ ተከበሩት ኔልሰን ማንዴላ የክብር የሽኘታ ቀን ማወድስ ነበር። ውይይቱ ጡፏል … ዲነግዲ በሚባል አንድ ታዳሚ አንድ አውድዮ ቀረበ። ….. አውድዮው በሸገር የተጠነቀረ ነበር። እርግጥ የዲነግዲ የሰጠው ሊንክ በቃል ስለነበር ማግኘት አልቻልኩም። በፍጥነት ግን የሊበሬሽን ፍሮንት ቃሉን ቀበል አድርጎ ከብርኃን በፈጠነ ሁኔታ ለጥፎት አገኘሁት። https://www.facebook.com/pages/Ethiopian-Liberation-Front/625419210805465

እንደሰማን …. በተደሞና በግራሞት ሁላችንም ተደመምን … አባ መላ / አቶ ብርኃኑ ዳምጤ/ የሩሙ ባለቤት ዛሬውኑ አድራሻውን ፈልጌ ቃለ ምልልስ አድርጋለሁ በማለት በጸጸት ቃል ገባ … እዬተቁነጠነጥን ሰዓቱን ጠበቀን። ሰዓቱ በጣም ራቀ … አይደረስ የለም ደረሰ …. በቀጥታ ከጀግናው ጋር ቃለ ምልልሱ ተጀመረ … በባተሌው ጠቅለል ሲል … እንዲህ ነው ….

የ78 ዓመት አዛውንት ናቸው። ምዕራብ ሽዋ አንቦ አካባቢ ነው የተወለዱት። የቄስ ትምርት ቤት ትምህርታቸውን እዛው አካባቢ አጠናቀው የአንደኛ ደራጃ ትምህርታቸውን እስከ 6ኛ ክፍል ተምረው፤ ከዚህ በኋላ ወደ ተመረጡበት ወደ ውትድርና ሙያ ተሰማሩ – በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ። ከህግ ባለቤታቸው ከወ/ሮ አስቴር ፈንታ ጋር በሥርዓተ ጋብቻ የሁለት ሴት ልጆችና የስድስት ወንድ ልጆች እንዲሁም የአራት የልጅ ልጆች አባት ባለ ጸጋ ናቸው። በአዲስ አበባ ከተማ ላፎቴ ካልተሳሳትኩ  በ450.00 የኢትዮጵያ ብር በጡረታ ይኖራሉ። የታሪካችን አንብርት የተከበሩ ሻንበል ጉታ ልጆቻቸው የተሟላ ድጋፍና እንክብካቤ እንደሚያድረጉላቸው አባ መላ ካደረገላቸው ቃለ ምልለስ ለማወቅ ችያለሁ።

የኢትዮጵያዊነታችን ሚስጢር የሆኑት እኒህ ታላቅ ሰው እንደ ቀደምቶች ወርቆቻችን እንደ አብዲሳ አጋ፤ እንደ  አብርኃም ደቦጭ፤ አንድ ሞገስ አስገዶም እንደ ዘርዓይ ደረስ ታሪክን የፈጠሩ የነፃነታችን ቀንድ ናቸው። ለእኛ ብቻ አይደለም  የዓለም የነፃነት ትግል ጠባቂና አዲስ ፊኖሚና እንዲሁም አምክንዮም ናቸው ብል ማገነን ተብዬ እንደማልከሰስ ነው። ዘውዳችን የሆኑት እኒህ እንቁ የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ለተለዬ ተልዕኮ ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ጊዜ በስውር፤ በረቂቅና በርቀት እንዲጠብቋቸው ከተመደቡት ወገኖቻችን አንዱ ነበሩ። የሰላም ሐዋርያውን ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ይገልፆቸዋል“ ስልጡን ….የተከበሩ ረቂቅ ሰው ናቸው። ቀልጣፋና አንባቢ፤ ሰውነታቸውን በማፍታት በተለይም በቦክስ ስፖርት ላይ የሚተኩሩና መዝናናትም የሚወዱ ነበሩ“

ብሄራዊ ኃላፊነታቸውን በጀግንነት የተወጡት እኒህ ታላቅ ሰው ሳንበል ጉታ፤ ኔልሰን ማንዴላ ለስልጠና በመጡ በወራቸው በአንድ የስልጠና ጓደኛቸው ኔልሰን ማንዴላ ህይወት በአጭሩ ለመቅጨት ከአሴረው ድርጅት ጋር አብረው እንዲሰሩ ተጠዬቁ። እዬፈሩ ፈቃዱን ተቀበሉ። ምሳ እቴጌ ሆቴል ተጋባዙ፤ ተልዕኮው ተነገራቸው፤ የ2000.00 ፓውንድ ብርና ካሜራም ተሰጣቸው። ሂደቱን በፎቶ እንዲያነሱ ተገለጸላቸው። የግድያው እቅድ መራራ ነበር። በገመድ አንቀው እንዲገድሉ ነበር የተነገራቸው። ከግድያው በኋላ ከኮልፌ የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ማሰልጠኛ ጣቢያ 500 ሜትር ላይ በርቀት በመኪና እንደሚጠብቃቸውና ከዚህ በኋላ ውጭ ሀገር እንደሚኖሩ፤ ከድህነት ጋርም ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ  እንደሚፈቱ ተነገራቸው። ውሉ በጳውሎስ ቤተክርስትያን ቃል እንዲታሰርም ተሰማሙ። ሁሉን ከከወኑ በኋላ ታማኙ ወታደር በቀጥታ ወደ አዛዣቸው በመሄድ ዝርዝር ሪፖርቱን ገለጹ ለጄ/ ታደሰ ብሩ። ዕለተ ሰንበት ልክ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት የነፃነትን ነፍስ የታደገ ሕይወት፤ የዘርኝነትን ቅስም የሰበረ፤ የአፍሪካ መብራታ እንዲጠፋ ነበር ብይኑተ። ለዛውም በፍጹም ሁኔታ ታምና አፍሪካ ልጇን ለላካችባት የነፃነት ዓርማ ሀገር ኢትዮጵያ መሬት ላይ። ለተልእኮው አንድ ነጭና ሌላ ጥቁር ሰው እንደነበረ ባለ ታሪኩ ይናገራሉ …. ድርድሩ ቅዳሜ ነበር።

ክቡር ሻንበል ጉታ በበነገታው ሰንበት ተራኛ ነበሩ። ቅደመ መሰናዶውን ያሟለው ወታደራዊ የደህንት ክፍል ወንጀሉን ቀድሞ ስለደረሰበት አከሸፈው። … ቅጣቱም ለስም የለሽ ተሰጠ። …. እሩቅ ቦታ ተመደበ …. ሁለቱ የውጭ ሀገር የሴራው መሪዎች በ24 ሰዓት ኢትዮጵያን  እንዲለቁ ተደረገ። የኛው ክብር፤ ተክሊላችን ሻንበል ጉታም ዲንቃም ኃላፊነታቸውን በድልና በብቃት አጠናቀቁ። ታማኝታቸው ለኢትዮጵአዊነት ክብር ሸለሙ። የተሰጣቸውን የ2000.00 ፓውንድና ካሜራም አስረከቡ ለክፍሉ። ሚስጢሩ በሚስጢርነት ቀጥሎ ለሌሎች የሙያው ባልደረቦች ሹመት ሲሰጥ በሚስጢር የዛሬው ሻንበል ጉታ የ10 አለቃነት ለደበበ የ50 አለቃነት ማዕረግ ተሰጠ ይላሉ። ድንቁ ….  ይህም ሚስጢር ነበር። የሚገርመው ሂደቱም ድርጊቱም ሚስጢርነቱ እጅግ ጥብቅ መሆኑ ነው።

የታወቁት የተከበሩት  ኔልሰን ማንዴላ በስውርና በርቀት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው ሆነ የግድያ ሙከራው ታስቦ እንደከሸፈ ሳያውቁ ነበር ያለፉት። ዛሬ …. ለነገም ሌላ ከመቃብር በላይ ሌላ አዲስ ትዕይታዊ የታሪክ ምዕራፍ ኪኖ ልበለው ገድል …. የመረጣችሁትን ብያለሁ። ያን ጊዜ በሴራው ውስጥ ስለነበረው ዛሬ 08.12.2013 አባ መላ ሲጠይቃቸውም ስሙን ለመስጠትና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም። ይህ በራሱ  ከወርቅ የነጠረ ወታደራዊ ሥርዓት …. ያኮራል። ግን ዛሬ …. ቅንቅን የበላው ይመስለኛል በወያኔ …

ህልም ነባራቸው የሀገራቸውን ባህላዊ ልብስና ጃኖ የተግባር አዛውንቱን፤ የጽናት አብነቱን፤ የምህረት ድርጊተኛውን አጎናጽፈው ከኔልሰን ጋር ፎቶ ለመነሳት …. ለ2 ዓመታት ቢጥሩም አልተሳካላቸውም። የመንፈስ ሚስጢራቸውን እንደ ቋጠሩ ዛሬ ሀዘናቸው መራር ቢሆንም በቀብሩ ላይ ለመገኘት ፈልገዋል። እንኒህ ታላቅ ሰው የዓለምን ተስፋ የታደጉ በመሆናቸው በርካታ ዓለም ዓቀፍ ሽልማት ማግኘት አለባቸው እላለሁ። ቢያንስ ዛሬ ለቀበር ሥርዓቱ በክበር እንዲገኙ በደስታ ምኞታቸውን ለማሳካት ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ወገኖቻችን ሥጦታቸውን በደስታ አክበረው በማሰተናገድ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ በወገኖቼ እዬተማመንኩ ቢዛ ካገኙም መሄድ በቀብር ሥርዓቱ ላይ መገኘት ስለ አለባቸው የሎቢ ተግባራትን ከመከወን በተጨማሪ ጠቅላላ ወጪያቸውን እንሸፍን ዘንድ ቆሜ እለምናችኋለሁ።

አዎን …. የመጨረሻው የተከበሩ የኔልሰን ማንዴሌ ጉዞ ድንገተኛ ነበር። የምሽት እራት ግብዣ ነበር። ዝግጅቱም በክበቡ ነበር። ከሌሎች አርቲስቶች ጋር ቀደምቷ አርቲስ ሂሩት በቀለ ተገኝታለች። በመጨረሻዋ ሰዓት የፈጥኖ ደራሽ የማዕከሉ አዛዥ ጄ / ታደሰ ብሩና የሰላሙ አባት ኒልሰን ማንዴላ አብረው አሳለፉ። የነበራቸውን ልዩ አድናቆት፤ ክብርና ፍቅራቸውንም የተከበሩ ጄ/ ታደሰ ብሩ  የወገባቸውን ኮልት 38 ሽጉጥ ፈተው ለኔልሰን ሸለሙ። ልጅን፤ ክብርን የመስጠት ያህል ነበር። ጌታችን መዳህኒታችን እዬሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ለወዳጁ ለቅዱስ ዮኋንስ ቀበቶውን እንደ ሰጠው ሁሉ። ዕንቁው አባታችን ከ ኢትዮጵያ እንደተመለሱም ነበር የካቴና ስንቅ የሆኑት።

የላቀ ሜዳሊይ፤ ዓለም አቀፍ ሽልማትና ተደማጭነትን ሊአተርፍ የሚችለው ይህን ታላቅ ተልዕኮ የእፍሪካ እናት ምድር፤ የዓለም እናት እምዬ ኢትዮጵያ ስታስተናግድ በዛን ወቅት በአጠቃላይ በካንፑ ውስጥ የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ስልጠና የሚያውቁ 5 ሰዎች ብቻ ነበሩ። ጠባቂዎቹ ከጄኒራላቸው ጋር በቀጥታ የመገናኘት መብት ነበራቸው። ተፈልፍሎ … ተዝቆ የማያልቅ ብቃትና መክሊት …. ከድንቅነሽ አንባ ….

ኮንታክት ኢሜል ለእርዳታ bdamte56@gmail.com

ኢትዮጵያዊነት የነጠረ ወርቅነት!

ፎቶ ከኢትዮጵያ ሊበሬሽን ፍሮንት ሆም ፔጅ የተወሰደ።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Hiber Radio: “በሳውዲ አሁንም ከሰማኒያ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በየቤቱ ተደብቀው የሳውዲዎቹን ቅጣት እየጠበቁ ነው”ነብዩ ሲራክ (ቃለምልልስ)

0
0

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ህዳር 29 ቀን 2006 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

>

አቶ ኦባንግ ሜቶ ማንዴላን ስናከብር ኢትዮጵያውያን መርሳት የሌለብን ባሉዋቸው ጉዳዮች ላይ ከህብር ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተወሰደ

>

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሳውዲ አሳሳ ስለሆነው በሳውዲ ስለቀሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

ማንዴላ ልዩ ዝግጅት

የዓለም መሪዎች ስለ ማንዴላ ምን አሉ? (ልዩ ጥንቅር)

>

ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን የማንዴላ ሞት ተከትሎ ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

> ጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ የዘሐበሻን አምስተኛ ዓመት አስመልክቶ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ

ማንዴላ!(ወቅታዊ ግጥም በጸሐፊው አንደበት)

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

- በሳውዲ የቀሩ ቁጥራቸው ከ80 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አደጋ አንዣቦባቸዋል

- አገር ቤት የገቡት ንብረታቸው ቦሌ ላይ እየተዘረፈ መሆኑን ገለጹ

- በደቡብ አፍሪካ ለማንዴላ ዛሬ በአገሪቱ ብሔራዊ የጸሎት ስርዓት ተደረገ

- ዓለም ዕውቁን የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ በልዩ ልዩ ዝግጅት እያከበረ ነው

– የሱዳን ፕ/ት አልበሽር በምስጢር የኢትዮጵአና የኤርትራ መሪዎችን ለማደራደር ሽር ጉድ ማለታቸው ተገለጸ

- የኢትዮጵያ ጦር ትላንት ከአልሸባብ ጋር ሊፋለም ባኮል ግዛት መግባቱ ተዘገበ

- የሱዳን ብሔራዊ ቡድን የኢትዮጵያን ቡድን 2 ለ 0 አሸነፈ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

ግልጽ ደብዳቤ ለግንቦት ሰባት መሪዎችና አባላት –ግርማ ካሳ

0
0

Muziky68@yahoo.com

ዲሴምበር 9 ቀን 2013 ዓ.ም

 

ginbot 7በቅድሚያ ሰላምታዬ ይድረሳችሁ። ከአምስት አመታት በፊት ከአንዳንዶቻችሁ ጋር፣ በቅርበት፣ በቅንጅት ድጋፍ ማህበራት ዉስጥ አብረን ሰርተናል። አብረን ለሰላም ለዲሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት መስፈን፣ ለዜጎች ሰብዓዊ መብት መከበር፣ ለሕሊና እስረኞች መፍታት ስንጮህ፣ ስንሰራ፣ ስንደክም፣ ስንመክር ነበር። መሃከል መንገድ ላይ የፖለቲካ ስትራቴጂ ልዩነቶች ተፈጠሩ። «ሁለ ገብ» የሚል የትግል ስልት መርጣችሁ የተለየ መስመር ያዛችሁ። እኛ ደግሞ በዚያ በሰላሙ መንገድ ቀጠልን። አንዳንዴ ልዩነቶቻችን ከረዉ በድህረ ገጾች፣ ፓልቶክ ክፍሎች፣ ጋዜጣዎች ፣ ሬዲዮኖች የተካሰስንበትም ጊዜ ጥቂት አይደለም።

ወቅቱ ትብብርን ይጠይቃል። በተቃዋሚዉ ጎራ ያለው ወገን ሁሉ በአንድነት ይሰባሰብ ዘንድ፣ እናንተም የተቃዋሚዉ አንዱ አካል እንደመሆናችሁ፣ እናንተ ዘንድ ያሉ፣  መሰባሰብ እንዳይኖር  እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን፣  ትመረምሩና ታስተካክሉ ዘንድ ይሄን ጽፊያልሁ። ክስ ሳይሆን፣ መረጃ ላይ የተመረኮዘ ምክር አዘል አስተያየት በማቅረብ፣ ቻሌንጅ ላደርጋቹህ እሞክራለሁ።

 

ኤርትራና ኤርትራ የምትረዳቸው ድርጅቶች

ግንቦት ሰባት የተቋቋመው ሰኔ ወር 1999 ዓ.ም ነዉ። ከስድስት ወራት በኋላ ስድስተኛ አመቱን ያከብራል። ድርጅታችሁ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ብዙ የምናውቀዉ ነገር የለም። ነገር ግን ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዳላችሁ ግን ግልጽ አድርጋቹሃል። የኤርትራ መንግስት እናንተ ወታደሮች ስለሌላችሁ፣ ከትግራይ ብሄራዊ ዴሞክራሲ ንቅናቄ(ትብዴን) ጋር አብራችሁ እንድትሰሩ እንደጠየቃችሁና እንደተስማማችሁ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። እናንተ ፖለቲካዉን ልትይዙ፣ እነርሱ ደግሞ ሚሊታሪዉን። (ልክ ያኔ ሕወሃት ሚሊተሪዉን ይዞ፣ እነ ታምራት ላኔ ደግሞ ፖለቲካዉን እንደያዙት)

በጎንደር፣ በወሎ በሸዋ.. ፊት ፊት እየቀደሙ ፣ በፕሮፖጋንዳ ሕዝቡን እያሳምኑ፣ ትልቅና ወሳኝ የፖለቲካ ሥራ እየሰሩ፣ ሕወሃትን አዲስ አበባ ያስገቡት እነ ታምራት ላይኔ ነበሩ። ታዲያ፣ ምናልባት የኤርትራ መንግስት፣ ታሪክን ደግሞ፣  እናንተን ዳግማዊ ታምራት ላይኔዎች ሊያደርጋቹህ፣ የርሱን ፍላጎት ሊያስጠብቁ የፈጠራቸዉን ስልጣን ላይ ሊያስወጣ አስቦ እንደሆነ፣  ገምታችሁ ታውቃላችሁ ? እስቲ ጠይቁ፣ ኦነግ፣ የአርበኞች ግንባር የመሳሰሉ በርካታ ድርጅቶችን  በልጦ፣  እንዴት ትብዴን በወታደራዊ አቅሙ ጠንካራ ሊሆን ቻለ ?  ምናልባትም የ«ትግራይ ሽምቅ ተዋጊዎች» የተባሉት በርግጥ የትግራይ ሰዎች መሆናቸውን የሚያሳይስ ምን ማረጋገጫ አለ ? ከሰራኤ፣ ሐማሴን አኮሎ ጉዛይ የመጡ ኤርትራዉያን ቢሆንስ ?

ከሕወሃት በስተቀረ የኤርትራ መንግስት የረዳቸዉና የደገፋቸው ድርጅቶች፣ አንዳቸዉም ለቁም ነገር ሲደርሱ አላየንም። አልሻባብ እየተመታ ነዉ። በሶማሊያ በፑትላንድ፣ በሶማሊላንድ፣ በጁባላንድ እና ሞቃዲሾ አካባቢ ለአመታት ታይቶ ያልታወቀ መረጋጋት እየታየ ነዉ። በመሆኑም ኦብነግ መሳሪያና ስንቅ የሚያሳልፈበት ቀዳዳዎች እየተዘጉበት ነዉ። ድርጅቱ እየተከፋፈለ ፣ እየመነመነ፣ አብዛኞቹ አባላቱም ከሕወሃት/ኢሕአዴግ ጋር በመነጋገር ላይ ናቸው።

ኦነግን ከተመለከትን ደግሞ፣ በአስገራሚ ሁኔታ ፈረካክሷል።  እንደ ከማል ገልቹ፣ ሃይሉ ጎንፋ የመሳሰሉ ተወዳጅና ኢትዮጵያን ወዳድ ጀነራሎች የቁም እስረኞች ሆነዋል።  እንደ ዶር ዲማ ነግዎ፣ ሌንጮ ለታ ያሉ አንጋፋ የቀድሞ አመራር አባልትና መስራቾችም፣ የኦሮሞዎች ጥያቄ በመገንጠል ሳይሆን በዲሞክራሲ ይፈታል ብለዉ፣ እራሳቸዉን ከኤርትራ መንግስት ለይተው፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመታገል፣  የኦሮሞ ዴሞርካሲያዊ ግንባርን መስርተዋል። ብዙ አልተረጋገጠም እንጂ፣ ወደ አገር ቤት ገብተው ለመታገል ሃሳብ እንዳላቸውም የሚገልጹ ዜናዎችም የተናፈሱበት ሁኔታም አለ።

ሌላዉ በኤርትራ በኩል ይንቀሳቀሳል የሚባለው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ነዉ። ይህ ግንባር በተለያዩ ጊዜ የተለያዩ የአመራር አባላት ነበሩት። ነገር ግን ድርጅቱ ጠንከር በሚልበት ጊዜ አመራር አባላቱ እየታሰሩ ፣ ይሰወራሉ። ሻእቢያ ጠንካራ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ያለው ድርጅት እንዲወጣ በፍጹም ፍላጎት ስለሌለው ፣ የአርበኞች ግንባርም አደግ ሲል እየተኮረኮመ፣  ይኸው ከአመታት በፊት የነበረበት ደረጃ ነዉ ያለው።(እንደዉም ሳይብስ)

እንግዲህ ይሄን ሁሉ የምተነትነዉ ፣ ከኤርትራን መንግስት ጋር መስራት ታክቲክሊና ሚሊታሪሊ እንደማያዋጣ ለማሳየት ነው። በኤርትራ በኩል እንታገላለን የሚሉ አንዳቸውም፣  ይኸው ሕወሃት/ኢሕአዴግ ስልጣን ከያዘ 21 አመታት አለፉ፣ አንድ ቀበሌ ነጻ አላወጡም። ወኔዉና ጀግንነቱ ሳይኖራቸው ቀርቶ አይደለም። ነገር ግን የኤርትራ መንግስት መዳፍ ዉስጥ ስላሉ እንጂ። እናንተንም ለጊዜዉ መጠቀሚያ ያደርጓቹሃል። ትንሽ አደግ ስትሉ ግን መመታታችሁ አይቀርም። ከኦነግ፣ ከአርበኞች ግንባር ከመሳሰሉት መማር አለባችሁ። ግድ የለም ከሻእቢያ ጥገኝነት ዉጡ።

 

ኢሳያስና የኤርትራ ሕዝብ

ምን ያህል የኤርትራን ፖለቲካ እንደምትከታተሉ አላውቅም። የኤርትራን ሕዝብ ከተቀረዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለይቼ ስለማላየው የኢትዮጵያ ድህረ ገጾችን እንደማነበዉ፣ የኤርትራን ድህረ ገጾች እከታተላሁ። እናንተም እስቲ ጊዜ ወስዳችሁ ተከታተሉ። እስቲ ኤርትራዉያንን ቀረብ ብላችሁ አነጋግሩ። የሚያሳዝን፣ የሚያስለቅስ ታሪኮችን ነው የምትሰሙት።በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በሱዳን በኩል አድርገዉ፣ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሰደዱ፣ እባብ እየነደፋቸው፣ ተይዘው እየተገደሉ ሞተዋል። በሳዋና በተለያዩ ቦታዎች የኤርትራ ወጣቶች እየተቃጠሉ ነዉ። ኢሳያስ የኤርትራን ሕዝብ እያረደ ያለ እብድ ነዉ።

እናንተ፣ ቢያንስ ቢያስንስ «ለሰብዓዊነት ፣ ለፍትህ፣ ለሰላም፣ ለዲሞክራሲ የቆምን ነን» ትላላችሁ። ለዚያም ስትሉ አንዳንዶቻችሁም በቃሊቲ ትልቅ ዋጋ ከፍላቹሃል። ነገር ግን ከዚህ እብድ ጋር መስራታችሁ ምን ይባላል?  ይሄስ አያሳንሳችሁምን ? በጣም ያሳንሳቹሃል። ከዚህ እብድ ጋር ባበራችሁ ቁጥር፣ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር እየተጠላችሁ ነዉ። ኢሳያስ የጉበት በሽተኛ ነዉ ይባላል። እንቁላላችሁን ሁሉ እርሱ ቅርጫት ዉስጥ ከከተታችሁ፣ ነገ ሰዉዬው የሞተ እለት፣  ምን ልትሆኑ ነው ?

 

እርግጥ ነዉ ኢሳያስ ጥቂት አየር መቃወሚያዎችን ፣ ጥቂት ሺህ ዶላሮችን ፣ የወታደር ጫማዎችን ሊወረወርላችሁ ይችላል። ኮምፖሽታቶ ዳር፣  ከፈራረሱ ፎቆች አንዱ ዉስጥ ጽ/ቤት ሊሰጣችሁ ይችላል። ነገር ግን ሕሊናችሁን ከመሸጥ፣ በአፍሪካ ከነኢዲአሚን ጎን በሚሰለፍ ቡድን፣  ሰይጣናዊ የሰብአዊ መብት ረገጣ ሲፈጸም እያያችሁ፣   እንዳላየ ሆናችሁ ዝም ከማለት፣ ከሕዝቡ ጋር በመጣላትና ታሪካዊ ጠባሳ ከመፍጠር ፣ ከወዲሁ  ከዚህ ያበደ አገዛዝ እንድትለዩ እማጸናቹሃለሁ። ግድ የለም ከሻእቢያ ጥገኝነት ዉጡ።

 

ኤርትራና የአለም አቀፍ ማህበረሰብ

እንደምታውቁት ኢሳያስ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ የተገለለ ነዉ። ከቀይ ባህር አሳዎች ጋር በስተቀረ፣ ከኤርትራ አጎራባቾች  ሁሉ ጋር ጦርነት ገጥሟል። የኤርትራዉያን ደም ቢፈስ ምንም የማይመስለው፣ የሕዝቡን ደም በመጠጣት የሚረካ የተረገመ ሰው ነዉ።

 

በዚህም ምክንያት የተባበሩት መንግስታት የፀጥታዉ ምክር ቤት፣  በኤርትራ ላይ በርካታ ዉሳኔዎችን አላስልፏል። ከዉሳኔዎቹ መካከል ፣ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ወደ ኤርትራ እንዳይገባ፣ ኤርትራ የጎሮቤት አገሮች ላይ የምታደርሰውን «ሽብር» እንድታቆም፣ ከጎሮቤት አገሮች ጋር ያላትን ችግር በሰላም እንድትፈታ፣ በግዛቷ ያሉ ሽምቅ ተዋጊዎችን መደገፍ እንድታቆም የሚጠይቁ ዉሳኔዎች ይገኙበታል።

 

እንግዲህ ይሄ የሚያሳየው ከሻእቢያ ተወዳጅቶ የሚደረግ እንቅስቃሴ ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር የሚያጋጭ መሆኑን ነዉ። በተዘዋዋሪ መንገድ የጸጥታው ምክር ቤት ዉሳኔን እየጣሳችሁ  ነዉ። የአለም አቀፍ ማህብረሰብን ከበሬታ እያጣችሁ ነዉ። አንድ ምሳሌ ልጥቀስ። በቅርቡ ከግንቦት ሰባት አመራር አባላት ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው የተከበሩ አና ጎሜዝ አዲስ አበባ መሄዳቸዉን እና በዚያም ከነአባ ዱላ ጋር መነጋገራቸው በሰፊው ተዘግቧል። የአና ጎሜዝ ወደ አዲስ አበባ መሄድ፣ የተለያዩ ትርጓሜ ሊሰጠው ይችላል። ነገር ግን፣  ቢያንስ ቢያንስ የግንቦት ሰባት ድርጅታችሁን የዲፕሎማሲ ሽንፈትና ኪሳራ በግልጽ ያሳየ ነዉ። ግድ የለም ከሻእቢያ ጥገኝነት ዉጡ።

 

 

ማጠቃለያ

እንግዲህ የመከራከሪያ ነጥቦቼን በግልጽ አስቀምጫለሁ።  እዉነት ለመስማት ከለመፈለግ የተነሳ፣ የቀረቡ ሃሳቦች ላይ ሳይሆን፣  ሃሳብ አቅራቢዎች ላይ ማነጠጠሩን ልትመርጡ ትችላላችሁ። እንግዲህ የእናንተዉ ምርጫ ነዉ። ነገር ግን ተስፋ አደርጋለሁ፣ ቆም ብላችሁ እንደምታስቡ።

 

ይሄን መረዳት አለባችሁ፣ ነጻነታችንን ኢሳያስ አፈወርቂ አይሰጠንም።  ጠዋትና ማታ አገዛዙን ስለረገምን ለዉጥ አናመጣም። በአሁኑ ወቅት ብቸኛው አማራጭ እኛው እራሳችን የምናደርገዉ የተባበረ ሰላማዊ ትግል ነዉ።  ኢትዮጵያዉያን በአንድ ላይ ተባብረን፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ ጥቂቶች የዘረጉትን ቀንበር መስበር እንችላለን። እባካችሁ የኢትዮጵያን ሕዝብ ኃይል አሳንሳችሁ አትመልከቱ። ከሻእቢያን ጥገኝነት ዉጡ።  ወደ ቀደሞዉ ወደ «ቅንጅት» መንፈስ ተመለሱ። ያኔ በዘጠና ሰባት የጠበቅነዉን ያላገኘነው፣ በቂ ድርጅታዊ ሥራ ስላተሰራና በአመራር አባላት መካከል መከፋፈል ስለተፈጠረ፣ ሕዝቡ በአንድ ላይ በተደራጀት መልኩ፣ በሁሉም ክልሎች ማንቀሳስቀስ ስላልተቻለ እንጂ፣  የሰላማዊ ትግል ስላልሰራ ወይን የኢትዮጵያ ሕዝብ አቅም ስለደከመ አልነበረም። ካለፈዉ ትምህርት በመዉሰድ፣ ጥንቃቄ በተሞላበት፣ በክልሎች ሁሉ መረብን በመዘርጋት ፣ አቅማችንን፣ ገንዘባችንን በሙሉ አንድ ላይ በማሰባሰብ፣ የሚደረግ ሕዝባዊ ፣ ሰላማዊ የእምቢተኝነት ዘምቻ  በርግጥ ዉጤት ያመጣል።

 

ሸንጎ፣ የብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ሶሊዳሪቲ የመሳሰሉ በርካታ ደርጅቶች ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ተማምነዉ፣ አገር ቤት ለሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል አጋርነታቸውን እየገለጹ ነዉ። የእናንተ ድርጅት፣ ግንቦት ሰባት፣ ከሻእቢያ ጋር ያለዉን ግንኙነት በአስቸኳይ በጥሶ፣  ከነዚህ ድርጅትች ጋር አብሮ ለመስራት ይሞክር። እዚህ ላይ አበቃለሁ። የሚሰማ ጆሮ ካለ እንግዲህ ይሰማል።

 

 


አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸዉ ማለፉ፤ ሆድ-እቃቸዉ ተከፍቶ ኩላሊታቸዉ መሰረቁ ታወቀ

0
0


አስክሬን ምንሊክ ሆስፒታል ሄደን እንድንወስድ ስልክ ተደወለልን ለሞቱ ከደነገጥነዉ በላይ አስክሬኑን ስንመለከት ፍጹም ተረብሸናል ከአዉሬ አፍ የተረፈ አስክሬን ነበር ሚመስለዉሰዉነቱ ተቦጫጭቋል!”  ጓደኞች

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማ

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማ

ዋሽንግተን ዲሲህዳር 30/2006 (ቢቢኤን) ፦ በአዲስ አበባ ዉስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የነበሩት አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ቀደም ሲል በጥቅምት 4/2006 በአካባቢዉ ላይ ፈንድቶ ከነበረዉ ቦንብ ጋር በተያያዘ መልኩ ለምርመራ ማእከላዊ እስር ቤት መግባታቸዉ እና በማእከላዊ ቆይታቸዉ ምግብ እንዳይገባላቸዉ ቤተሰብ እንዳይጠይቃቸዉ መከልከሉም ለማወቅ ተችሏል።

እንደ አቶ ሙሐመድ ጓደኛ አገላለጽ ግለሰቡ ለተጠረጠሩበት ወንጅል የሚያበቃቸዉ ጉዳይ ባይኖርም፤ከገቡበት ማእከላዊ እስር ቤት በደረሰባቸዉ ከፍተኛ ድብደባ በህይወት መዉጣት አልቻሉም።

ለሐያ ዘጠኝ ቀናት ማእከላዊ እስር ቤት የታሰሩት አቶ ሙሐመድ ምን ያህል ድብደባ እንደደረሰባቸዉ ባይታወቅም ጭንቅላታቸዉ በጣም መጎዳቱን፣ሰዉታቸዉ እንደበለዘ፣ብዙ ሰንበሮች መታየታቸዉ፣ሆድ እቃቸዉ ተከፍቶ ኩላሊታቸዉ መሰረቁን ለአስራ ሁለትአመታት የሚያዉቋቸዉ ጓደኛቸዉ በሐዘን ይገልጻሉ።የዱር አዉሬ ቦጫጭቆ የገደለው ይመስላል በማለት ሁናቴዉን የሚገልጹት ጓደኛ ከመንግስት አካላትም ይሁን አስክሬኑ ከመጣበት የሚኒሊክ ሆስፒታል ስል አቶ ሙሐመድ አሟሟት የተሰጠ መረጃ አለመኖሩን፤ በደም በተጨማለቀ ከፈን የተከፈነ አስክሬን ብቻ  መመለሱን ገልጸዋል።

ቤተሰቡ ጉዳዩን ለሰብአዊመብት ተሟጋች ለሆኑ ድርጆቶች እንዳያመለክት ከፍተኛ ዛቻ ደርሶበታል፤በቅርበት የሚያዉቋቸዉ እንኳ በሞታቸዉ ከማዘን በስተቀር ስለ አሟሟታቸዉ ከፍርሃት የተነሳ መናገር አይችሉም በማለት የሚያስረዱት ጓደኛቸዉ ሁሉም ለሞቱ ከደነገጠዉ በላይ አስክሬኑን በማየት ተሸማቋል ይላሉ።

በጥሩ ስነምግባራቸዉ የሚታወቁት አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ሐማኖትን ተግባሪ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ከመሆን በስተቀር አገርን ወገንን ሊጎዳ በሚችል የአሸባሪ ተግባር የሚጠረጠሩ አይደልም በማለት በሐዘን የሚናገሩት ጓደኛ ሟቹ የሰባት ልጆች አባት እንደነበሩ ቤተሰቡም ለአደጋ መጋለጹንም አስረድተዋል።

በጥቅምት 4/2006 መንግስት በቂ መረጃ ለህዝብ ማቅረብ ባልቻለበት፤ የመንግስት ደህነነቶች አለም አቀፋዊ ትኩረትን ለመሳብና ፖለቲካዊ ጥቅምን ለመጎናጸፍ በቦሌ ክፍሌ ከተማ አደርሰዉታል ተብሎ በሚነገረዉ የቦንብ ፍንዳታ፤ ማመካኛን ለማግኘት የሱማሌ ብሔር ተወላጅ የሆኑትን የአቶ ሙሐመድ ህይወትን መንግስት መስዋዕት አድርጓል  በማለት አስተያያት የሚሰጡ ወገኖች አሉ።በትላንትና እለትዉ የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን በጅጅጋ ከተማ ድረስ ባሸበረቀ መልኩ አከበርኩ ለሚለዉ መንግስት፤ የአገሩን ዜጋ በብሔር ነጥሎ ማእከላዊ እስር ቤት አስገብቶ መግደሉ ለመንግስቱ አሳፋሪ ከመሆኑም ባሻገር የስርዓቱን መላሸቅ አመላካች ነዉ የሚሉም አሉ።

የአቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ታስሮ ለህልፈት መብቃት፤ የሆድ እቃቸዉ ተቀዶ የኩላሊታቸዉ መሰረቅ ከፍተኛ ምርመራ የሚያሻዉ ቢሆንም፤በሟች አስክሬን ላይ የተፈጸመው ወንጀል ስርዓቱ በህይወት ባሉ ብቻ ሳሆን በሙታንም ላይ ግፍ እንደሚፈጽም የሚያረጋግጥ ነዉ፤ በሐሰት አስሮ በመደብደብ፣በመግረፍ፣እስር ቤት ዉስጥ ከማሰቃየት አልፎ፤ ታሳሪዎች እስር ቤት ዉስጥ ሲሞቱ ሆድ እቃ ተከፍቶ የሰዉነት አካል መቸርቸር ተጀምሯልና!.. ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነዉ? የሚለዉ ጥያቄ የብዙሐኑ ነዉ።

http://goo.gl/DxqNyV

ኮ/ል መንግስቱ ስለማንዴላ ተናገሩ (አዲስ ቃለምልልስ)

በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት . (ነቢዩ ሲራክ)

0
0

ነቢዩ ሲራክ

      343ይህችን እህት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በር ተቀምጣ ካየኋት ሳምንት አልፏል። አልፎ አልፎ ላነጋግራት ብሞክርም መልስ አትሰጥም። መጀመሪያ የየኋት ቀን አካባቢ ከስራ ለተፈናቀሉ እህቶች አነሰም በዛ መጠለያ እያለ ፣ ለምን በር ላይ ትሆናለች? ብየ የጠየቅኳቸው የቆንስሉ ጸጥታ አስከባሪ ” አንተየ የዚህች እህት ጉዳይ አስቸጋሪ ነው ። ከመጠለያው ብዙ ቆይታለች ፣ አሁን በር  ላይ የሆነችው ሃገር ቤት ለመሄድ ወረቀቷ አልቆ እያለ ” ሃገር ቤት አልሄድም!” በማለቷ እነረደሆነ ተነግሮኛል ። ” በመጠለያው የነበሩት ሰነዳቸው ባሳር በመከራ አልቆ ሲሸኙ ወደ ሃገር ቤት አልሸኝም ብላ ረብሻ ከማንሳት አልፎ ከተዘጋጀው መኪና ወርዳ ይህን የምታየው ሚኒባስ መስታውት ሰብራዋለች!  ከዚያን ቀን ወዲህ አትበላም አትጠጣም ፣ እኛንም የገረመን ይሄ ነው!  ሚን ታደርጋለህ! ” ነበር ያሉኝ …

       ይህ ከተነገረኝም “ወዲህ ሃገር ቤት አልገባም!” ያለችው እህት ለቀናት  በቆንስሉ በር አልጠፋችም። ከተቀመጠችበት ወንበር ጀርባ ባለው ግድግዳ ” ህጋዊ ሰነድ የሌላችሁ እና የወጣውን የሳውዲ ህግ መስፈርት የማታሟሉ ወደ ሃገር ግቡ !” የሚለው የቆንስል ማስታወቂያ ይታያል ። ከአጠገቧ በፕላስቲክ ኪስ የታጨቀ ጓዟን አስቀምጣ ፣  በሆዷ ቁርአን ታቅፋ አንገቷን ከመድፋት ባለፈ በአካባቢው አዛን ስትሰማ የዘወትር ጸሎቷን (ሰላቷን) ወንበሯን ፈቀቅ አድርጋ እንደምትሰግድ አንድ ዘወትር እንቅስቃሴዋን የሚከታተል ወዳጀ አጫውቶኛል… እንዲህ ሆና ኮርመት ብላ ውላ ታድራለች! ቀን ጸሃይ ሲወቃት ፣ ማታ ወበቁ ይፈራረቅባታል ! ካየኋት ቀን ጀምሮ ወደ መጠለያው እንድትገባ ብዙ ሁነን ብንማጸናትም አልተሳካልንም …

       ከሃገሯ በጤና የመጣችው እህት ችግር ውጋቷን እንድንጋራ ስንጠይቃት አትመልስም  !  ወደ ሃገር ቤት እንድትገባ በጅዳ ቆንስል ልትሸኝ ቢሞከርም አልተሳካም። የ”ሃገር ቤት ግቢ!” ” አልገባም!” አለ መግባባት  ፍርሻ ከመምጣቱ በፊት አንዳንዴ ኦሮምኛና ብዙ ጊዜ ግን የተሰባበረ  አረብኛ እየቀላቀለች መናገር ይቀናት እንደነበር አንድ ” በመጠለያው እያለች አውቃታለሁ!” ያሉ ወንድም አጫውተውኛል። ያን ሰሞን ወደ መጠለያው እንድትገባ ተለምና ብትገባም በመጠለያው ውስጥ ካሉ ግፉአን ጋር ግብ ግብ ፈጥራ መውጣቷን ሰምቻለሁ  !

     ይዚህች ግፉዕ እህት ሰላም የነሳና አዕሮዋን ያወከ የውስጥ ህመም ሚስጥር አይታወቅም! ትሰማለች ፣ ለመናገር አልፈቀደችም!  ባሳለፍናቸው የበር ላይ ውሎዋ ትንፍሽ ብላ ስትናገር ቢያን እኔ እስከ ዛሬ አልሰማኋትም ! ውስጧ እንጅ ውጭ አካሏ የተጎዳ አይመስልም! ከሁሉም የሚገርመው ይህች እህት ጤናዋ ታውኮ እንኳ ሃገር ቤት ከወገኖቿ ጋር መቀናቀል ሞት መስሏታል  ! ሌላው አስገራሚ ሂደት  የዚህችን መልከ መልካም እጣ ፈንታ የምንመለከትም ህጋዊ ሰነድ የሌለን ብዙዎች የሳውዲን መንግስት የምህረት ቀቢጸ-ተስፋ ሰንቀን ጤናችን ተጠብቆ እያለ” በሰላም ሃገር ቤት ግቡ !” የሚለውን የመንግስትና የወገን ምክር መቀበል አቅቶናል !  እንዴት ነው ነገሩ …?

አንድየ ይታረቀን ከማለት ባሻገር ምን ይባላል :) ብቻ እሱ ያቅልለው እንጅ የሚሰማ የሚታየው ይከብዳል ! … ያማል … ያማል  !

ነቢዩ ሲራክ

የተከለከለ ~~ ፍቅር –ሲፈቀር –ይገርም … እኮ! ምን ልበል ታዲያ -. ከሥርጉተ ሥላሴ

0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 11.12.2013

ፍቅር የትውልድ ዋዜማ ነው።

የመንፈስ ማዕቀብ ሲነሳ የነፃነት ፈል ችግኝ ይበቅላል በዚህ ልጀምረው ….

4568ፍቅር ምንድን ነው? ማድመጥ። ፍቅር ዜማ – ጹዑም! ፍቅር የመንፈስ ጥንግ ሽብሻባ። ፍቅር የስሜት ቃናዊ መዝሙር። ፍቅር የአኃቲነት ብርቅ ወረብ። ፍቅር የመስጠት ለጋስ ፏፏቴ። ፍቅር የታሪክ ማውጫ ፍትኃ – ነገሥት። ፍቅር የውስጥነት ፍውሰት – ድህነት! ፍቅር ጣዕም ንጥር – መረቅ! ፍቅር ብጡል* ክብረት። ፍቅር ምህረት። ፍቅር ይቅርታ። ፍቅር ረቂቅ። ፍቅር ቀጥታ። ፍቅር መሆን። ፍቅር ኃብታም ነው ዲታ። ፍቅር ምህረት ነው ዘንባባ! ፍቅር ወድ ነው ስጦታ። ፍቅር ሩህሩህ ነው ርግብ። ፍቅር ፈውስ የራህብ። ፍቅር ጻድቅ የመስቀል ወተት። ፍቅር የመስዋዕትነት ጤና አዳም። ፍቅርን ሲሰጡ ሊፈቀሩ የሚችሉ ፍጡራን ፍቅርን ሲከለከሉ ደግሞ ማመጻቸው አይቀሬ ነው!  ይፈነዳል።

ዋ!

እናት ከሁሉም በላይ ትውደዳለች። እናት የመጀመሪያዋ የህይወት ትምህርት ቤት ናት። እናት መቅድመ የቤተሰብ አሰተዳዳሪ፤ የተፈጥሮ ሙሁራ ሊቀ-ሊቃውንት የርህርህና መግቢያም።  እናት ደግሞ ሴት ናት። እኔ በዓለም ደረጃ የፍቅር ምልክት ወይንም ዓርማ ሊሆን የሚጋባው ልብ ሳይሆን እናት ነው መሆን ያለበት። ስለምን? እናት ልልጇ የምትሰጠው ፍቅር የማያብል ነውና። እውነተኛ የፍቅር ተፈጥሮ የሚገኘው ከስፖርት ማልያና ከእናት ብቻ ነው። እናት የሥነ ፍጥረት ሙሉዑ አጀንዳ ናት! እናት የመንፈስ ቋንቋ ናት!  ዬዓለም ተወዳጁ ሥም እማማ!

 

እስኪ ወፍ ካወጣን አብረን … ወደ ተለምኩት ብያለሁ፤ ቀልቤን ወደ ገዛው፤ ሩኼን ወደ ዳኘው። ጉዞ በጋራ መልካም ነው። ኑሮም በወል ጣዕሜ ነው። … ሴት እህት ስትሆን ትፈቀራለች። ሴት አክት ስትሆን ትጠጋላች። ሴት ሚስት ስትሆን እንደ ነፍስ ትታያለች። ሴት ጓደኛ ስትሆን ትታመናለች። ሴት እናት ስትሆን የጸጋ ስግደት ይሰገድላታል። ሴት ይሁን ይሁን … አሜን አሜን … ስትል ….. ሰጥ ለበጥ ብላ ስትገዛና ስትረገጥ …. ስትመች ትመረቃለች ….

 

እኔ እንደማስበው በእምነቴ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት አምስቱ አዕማደ ሚስጢራት ላይ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልዑቅ ነገረ ሳይመር መቅረቱ በጣም ይጎረብጠኛል። እንደሚገባኝ ከሆነ ግን የተዋህዶ ልጆች ለቅድስት እናታችን ባለን ፍጹም ልዩ ፍቅርና ስስት ከጸጋ ስግደት ይልቅ የአምልኮ ስግደት ይገባታል ብለን እንዳንሟገት ብልሆቹ አቨው አስበውበት፤ ምንአልባትም መንፈስ ቅዱስም አቀብሏቸው ወይንም ሚስጢር ገልጦላቸው ሊሆን ይችላል። ለማንኛውም ከመንፈሳዊ ዓለም ወጥተን ወደ ገኃዱ ዓለም ስንመጣ … በፖለቲካ አስተሳሰብ ሴት ላቅ ስትል ግን „ጉልበታምንት“ ይለጠፍላታል። በጠራ ቋንቋ „ጉልበታም“ ትባላለች። ገና ሳትታወቅ እፍታ መስመር ላይ እኮ ነው …. ልደቷን ሳታከብር የምትገፋው – ገምድልንት* የተከለከለ ፍቅር ይሏችኋል ይህ ነው። ቁስለት!

 

ሴት ረድ ስትሆን ትወደዳላች። ሴት ሎሌ ስትሆን ትደነቃለች። ሴት የቤት ውስጥ ሰራተኛ ስትሆን ስንዱ ትባላለች። ሴት ጠቅልል ጠቅለል አድርጋ ስታጎርስ የራህብ ደራሽ ትባላለች። ሴት ጓዳ ጉድ … ጉድ ስትል ዓይን አብሮ ይዞራል። መንፈስም አብሮ ይንከራተታል። ልብም ዳንኪራውን ያስነካዋል ስሜትም አብሮ ይከትማል። ፍቅሬ ወ/ሮዬ ትባላለች። ዓለም የፈጠረው ቄንጠኛ የዘነጠ ሥያሜ ሁሉ ይሰጣታል። ሴት እንግዳ ስታስተናግድ ትመሰገናለች። ሴት ልጅ ስትሰጥ በዓይኔ ላይ ፍሰሺ ትባላላች። ሴት ስልጣን ልትጋራ ብቅ ስትል ግን „ኃይለኛ“ ተብላ ትኮረኮማለች ወይንም ትባረራለች። ሌላ ድልዝ ይፈልግላታል። ሌላ የሰብዕናዋ ድክምት ቁፋሮ ይጀመራል።  የተከለከለ ፍቅር … ጎባጣ

 

ሴት ገንዘብ ያዥ ስትሆን ትመረጣለች። ሴት ገንዘብ ስትሰበስብ ታማኝነቷ ይሰበክላታል። ሴት እልፍኝ ስታሰናዳ ትሞካሻለች። ሴት ስነጥፍ ወይንም ስነጠፍ እንደ ብርቅ ትታያለች። ሴት ቅራኔ ውስጥ ገብታ ስተቀረቀር ይጨበጨብላታል። ሴት መድረክ ላይ ወጥታ አቅም ባላው ብቃት በፍፁም ታማኝነትና ግልጽነት እኩል ስትመጥን አቅሟን ለአደባባይ ስታበቃ ግን በግሳፄ ትባረራለች ….. ድገም ሳትል ከቢጫው ቀዩ ካርድ ቀድሞ ያለ ማስጠንቀቂያ ከጨዋታ ውጪ ትሆናለች። ነዳላ ገጠመኝ። የአንተ ያለህ ….

 

ሴት ስትለብስ ትፈቀራለች። ሴት ስተሸቀረቀር እንጉርጉሮው ላቅ – መጠቅ ይላላታል። ሴት የተፈጥሮን ፍቅር ስትመግብ ንቢት ተብላ ትሞገሳለች – ትመገባለች – ትጎረሳለችም። ሴት ሽክ ብላ ከጎን ስትጓዝና ግብዣ ላይ እኩል ስትቀመጥ አጃችን* ይሞላል ልጎዝጎዝልሽ ነው። ሴት ገብያ ወጥታ ቀጨር መጨሬውን ስትሸማምት አበጀሽ ትባላለች። ሴት ኮስሜቲክስ ስትገዛዛ ውዳሴ ይነጠፍላታል።  ሴት ወንበርን ልትጋራ ጥንካሬዋን ስታስመከር ግን ትገፈተራለች …. ቆመጥ ይዘጋጅላታል ….. የተከለከለ ፍቅርነቀዝ!

 

ሴት ቤት ስትውል፤ እንደ እመቤት ትታያለች፤ ጨዋ የተረጋጋ መንፈስ የረበባት እዬተባለ ይሰበክላታል። – ደስታ ነዋ ስታፎከፉክ። ሴት አንገቷን ደፍታ መከራን ስትቀበል ቅኔ ይዘረፍላታል። ሴት የልጆች አሳዳጊ ብቻ ስትሆን ትበረታታለች – ትሸለማለች። ሴት በማይታዩ ሩትን /ጥቃቅን/ ተግባራት ስትሰማራ ማን እንደ አንቺ ትባላለች። ሴት አንደበቷ ታስሮ የሳሎን ጌጥ ብቻ ስትሆን ማለፊያ ይባልላታል። ሴት ግን ኃላፊነትን እኩል ለመጋራት ጠበቅ ጠንከር ብላ ብቅ ስትል ጦር ይሰበቅባታል።  ያደገ ወይንም ያልተነካ ድንግል ወጥ ሃሳብ ወይንም ግኝት ወይንም ላቅ ያለነ የቀደመ ግንዛቤ  ስታፈልቅማ እሷንማ በሽታሽቶሽ* መውቃት።የተከለከለ ፍቅር …. ምግለት!

 

ሴት ስትጋግር … ስትሰራ …. ስታጥብ … ልብስ ስትተኩስ፤ ስታረግዝ …. ስታጠባ …. ከሚፈለገው ቦታ ላይ ተገኝታለችና ይዘፈንላታል። ከዚህ አለፍ ብላ የመብትና የእኩልነት ጥያቄ ስታነሳ ግን ትወረወራለች …. እውነት ለመናገር በዘመናችን ያሉ ሴቶች እንኳን ጥቃ ሊቆምላቸው፤ እንክብካቤ ሊያገኙ ቀርቶ ገፍተው የሚወጡት በጣም ጥቂቶች ለምነው ለመታገል እንኳን ፈቃድ አያገኙም በወንድ ትምክህተኞች …. ዛሬም ከዛሬ 100 ዓመት በፊት ካላው ኮረብታ ላይ እንዳሉ አሉ እነ ተባዕት …. ከእነ- የወንድ የበላይነት ተጫኝ ስሜታቸው ጋር ተጋብተው። ስለ ሴቶች ብዕራቸው በተቆርቋሪነት የሚቃኙት ከአንድ ለእናቱ  ሙሁር ከፕ/ አለማዬሁ ገ/ማርያም በስተቀር …. ፕሮፌሰሩ ከክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ጋር በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሐሴትም አድምጠናል። ረስተውንም አያውቁም – ቅርባችን። ስለ ሴቶችን በሚያጠቃው የካንሰር በሽታ በተቆርቆሪነት የጻፉት ልብን የሚነካ ነበር። እውነት ልዩ አብነት ናቸው – ለእኔ። ድህነቴ እንጅ ለእሳቸው የምስጋና ቀን ባዘጋጅ ዕድለኛ በሆንኩ ነበር።

 

በፍጹም ሁኔታ የነፃነት ትግሉ ሆነ፤ ነገ የሚታሰበው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረቱና እርገቱ ከሴቶች ውጪ ሊታሰብም ሊሳካም እንደማይችል በጣም በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። የነፃነት ትግሉ የሴቶችን ሙሉዑ ተዋፆ በአጽህኖት፤ በተደሞና በአርምሞ ይጠይቃል። መደመጥ አለበት። አጥበቆ! አኔም የጥቃቱ ማዕደኛ በመሆኔ …. በልበ ሙለነት እጥፋለሁ … እንዲህና እንዲያ … ትርፉ ትራፊና ፍርፋሪ ካልሆነ ….

 

ይህቺ ለመላሾ እነ ተባዕት „ ቦታ አካፍለናል“ የሚሏት …. ልጥፍ ሽፋን ልግጫ ለማንም አይበጅም - ነገንም አያበጅ። የዶደመ …. መንገድ ነው። የነፃነት ትግሉ ሙሉዑነት ሊረጋገጥ የሚችለው የሴቶችን የመጠነ፤ ያስተዋለ፤ ያደመጠ፤ ያከበረ ተሳትፎ በቅንነት ተግባር ላይ ዛሬውኑ ሲያውል ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን ካላት ያልተነካ ቅምጥ ዕምቅ ኃይል በላይ የሴቶች ሃብት እስከ ዛሬ ድረስ ሥራ ላይ አልዋለም። … ነገም ከፍቶት ይታዬኛል።

 

እርግጥ ማሳሳቻ አስፓልት አለ። „የሴቶች መምሪያ ከፍተናል … ጉዳያቸውን የሚከታተል መዋቅር ዘርግተናል“ … ይህ የሴቶችን ብቃት የሚያቀጭጭ አፋኝ የማስመሰያ ጅራፍ ነው። በአንድ ወቅት ፕ/ መራራ ጉዴናን አበክሬ እጠይቃቸው ስለ ነበር ንገሩልኝ የሴቶች መምሪያ በድርጅቴ መጀመሬን አሉ። የዛሬ 14 ዓመት መሆኑ ነው። አሁንም እሳቸው ከያዟት ቁልፍ ቦታ ግን ፈቀቅ አላሉም። ጨምድደው ጉብ ብለው ይለፉንም ዘግተው አሉ እንደ አገዱ። ይህ ትልቅ ግድፈት ነው። የእኔ ሙግት የነበረው በ2ኛው  የኢተፖድህ ጉባዔ ከዬትኛውም አባል ድርጅት አንድም የአንስት ውክል አካል ልትገኝ ደረጃዋ ባለመፍቀዱ ነበር – አበክሬ እናገር የነበረው።

 

ዘግይቶ የዛሬ ዓራት ዓመት ገደማ መደረክ ሲቋቋም አዬነው በመላጣ – ጎብጦ የሴቶችን እኩልነት በባዶ ቃላት ተለብጦ። ያው ቢገላበጡም ጃኬቱም ቢቀያዬር የተባዕት ክምር። የድርጀታቸውም አቅም … የወንዶች ብቻ – ቁልቁል። ይህ ለናሙና እንጂ በሽታው ሁሉንም ያካልላል። ከእከሌ ድርጀት እከሌ ይሻላል ብዬ ውዳሴ ባቀርብ የሴትነቴ ክብር ይዘቅጣል። ሴትነቴ ካለይግባኝ ዘቅዝቆ ይሰቅለኛል። ተፈጥሮም ፊቷን ታዞርብኛለች። አምላኬም ከልቡ ያዝንብኛል። ሃቁን ለከንቱ ውዳሴ ብሸብብ።*

 

በማናቸውም ዘርፈ እኔ ነኝ ባለ ወሳኝ ኃላፊነት ሁሉ ሴቶች ጉልበታም አቅም አላቸው። ለዛ የሚመጥን ቦታቸውን አትጋፉ ነው መሰረታዊ ትግሉ። አጽህኖታዊ መጠዬቁም። እድሉን ያገኙ ሴቶች ተዝርክርኮ ሳይሆን አምሮና ሰምሮ፤ በጥራትና በጥንቃቄ እንዲሁም በስልትና በብልኃት ሁለመናው ያምርበታል። ሴቶች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት የሚተጉት …. በእናትነታቸው ፍጹም የማይታይ ሰማያዊ ጸጋ አስውበው ነው። ምቹ ሁኔታ  ካገኙ፤ በቂ እንክብካቤና ጥበቃ ለመክሊታቸው ከተደረገ …. ማን ችሏቸው። ያኮራሉ! ተወዳዳሪም የላቸውም። ሚስጢር ይመሰጠራል። ትርጉምም ይነበባል። ተፈጥሮም ይዘክራል። የሰብዕዊ መብት አከባበርም ጽኑ ባለሟል ሲገኝ በደስታ ይፍለቀለቃል። እኔ እላለሁ ሴቶች የተፈጥሮ ድንጋጌ ናቸውና።

 

አውሮፓ ያላችሁ ሁሉ እንደምትከታተሉት አውሮፓ በኢኮኖሚ ውጣ ውረድ ተሰቅዞ ሲባትልና ሲብተለተል የመፍትሄው ጭንቅላት የተገኘው አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ ማለቴ ነው ከጀርመን ነበር። የጀርመኗ መሪ ጠ/ሚ ወ/ሮ አንጅላ ሜርክል ቀጥ አድርገው በማያዝ ማገር ሆነው አውሮፓን ከውርዴት ዘመኑንም ከጥፋት ታድገውታል። ጠ/ሚር ሜርክል ፓን አውሮፓኒስት ናቸው። በተግባር የከበሩ የመጀመሪያዋ የጀርመን ተወዳጅ ሴት መሪ ናቸው። እርግጥ ከዚህ ጋር ያሉ ከፈረንሳይ ጋር የተሳሰረ ትብትብ ቢሮክራሲን  ዘልዬ …

 

ለናሙና …. የእንግሊዟ ታችር፤ ንግስት ኤልሳቢጥም፤ ተፍርተው በአጭሩ ተቀጩ እንጂ ልዕልት ዲያናም አሳይተዋል አስመስክረዋል … ያን ጉልበታም ተዝቆ የማያልቅ ብቃት …. ከብልህነት ጋር። ይህ በኒውዘላንድ፤ በአውስትራልያ፤ በፊላንድና በብራዚልም ተመሳጥሯል። ሲዊዘርላንድ በሰባት ሰዎች ትመራለች። አራቱ ሴቶች ናቸው። ያውም ቁልፍ ቁልፍ ቦታ የያዙ … በጀርመን ካለፈው ወራት ሀገራዊ ምርጫ በኋላ ያለውን ሽግሽግ አልተከታተልኩትም እንጂ ቀደም ባለው ጊዜ በርካታ ሴት ሚ/ራት ነበሩ …. የእውነት አባዛኞቹ ሴቶች በማለት ብቻ የሰከሩ አይደሉም። እናታዊ ሥነ -ምግባራቸው አይፈቅድላቸውምና! ይልቁንም በመሆን የበለጸጉ እንጂ …..

 

በዓለም በፈጠራ፤ በሳይንስና ምርምር፤ በሰብዕዊ ተግባር፤ እንዲሁም በሥነ – ጥበብ የበርካታ ምርጥ ዕንቁ ሴቶችንመዋዕለ ተጋድሎ፤ የያዘው የኖቤል ተሸላሚ ሴቶችን አስኪ ገድሉን ጎብኘት አድርጉት ….  እኔ በመንፈሴ እማማ ዊኒን፤ ሜርክልን እያጨሁ ነው። ብቁ ናቸዋ። በዬዓመቱ ከሲኤንኤን ጀግኖች ሴቶችም እኩላዊ ብቃታቸውን ለአደባባይ አብቅተዋል። እርግጥ እዬታፈኑ፤ ሳይታዩ እንዲጠፉ እዬታደመባቸው፤ እንዲከስሙ የተዘመተባቸው፤ እንዲሁም አስታዋሽና ጠበቃ ያጡት ሚሊዮኖች የነጻነት ሴት አርበኛ፤ የሥነ ተፈጥሮ ሁነኛ፤ የሥነ ጥበብ እማ ወራ … የፈጣራ ቀንዲል ዕልፍ ናቸው። የዓለም ብቁ ዜጎች ሴቶች መሆናቸው ምንም ለድርድር የሚቀርብ አይደለም። በአግባቡ ተከታታይና ባለቤት ቢኖረውማ …. በቁጥር ይበልጡም ነበር – በሁሉም ዘርፍ።

 

ለሁላችንም የሚጠቅም ስለሆነ ደግሜ በመፃፌ እንደማላሰላችሁ በማሰብ በዘመነ ክሊንተን ያን የዓለም ስሜትን የሳበ የፕ/ ቢል ክሊንተን ተብዕታዊ ቅብጠት ብልኋ ባለቤታቸው እመቤት ሄነሪ ክሊንተን የሆነውን እንዳልሆነ አድርገው ትቢያ አልበሰውታል። በወቅቱ አንድ የፕሬስ ሰው እንዲህ ሲል ጠይቋቸው ነበር … „የሚባለውን አልሰማሽንም? … አላነበብሽውንም?“ ሲል ብልኋ እመቤት ግን መንፈሱ እንዲህ ነበር „ እናቴ ከልጅነቴ ጀምሮ ያስተማረችኝ ሰው የሚለኝን ከሰማሁ የምሰራው የሰወችን እንጂ የእኔን እንዳልሆን ነግራኛለች፤ አስተምራኛለች። መርሄ ይህ ነው። እኔ የኔን ሥራ እሰራለሁ ሌሎች ደግሞ የራሳቸውን ይሰሩ“ ነበር ያሉት። ሰማዬ ሰማዬት የዘለቅ ዕጹብ መልስ ነበር። በዚህም ትዳራቸውን ከነዙፋኑ ሀገራቸውን ከነአልማዙ እስከብረዋል። አንስትን የወከለ ማለፊያ ብቃት!

 

ከዚህም በኋላ በዘመነ ፕ/ባራክ ኦባማ የውጭ ጉዳይ ሚር/ ሆነው እጅግ ውስብሰብና ፈታኝ በሆኑ መሰናክሎች ሁሉ በማለፍ የሴቶችን የመወስን አቅም በተግባር አሳብበውታል አሁንም የፕ/ ባራክ ኦባማ ባለቤት ቀዳማይ እመቤት ሚሻዬል ኦባማ ሁለገብ ንብ በመሆን ባለቤታቸውን ለሁለተኛ ጊዜ የሥልጣን ባለቤትነት አብቅተዋል … ለዚህም ደረጃ ያበቋቸው ቀዳማይ እመቤት ወ/ሮ ሚሻዬል ናቸው። ነገም ለፕሪዚዳንትንት እራሳቸውን ችለው ሊወዳደሩ ይችላሉ። ተወዳጅም ናቸው – ወ/ሮ ሚሻዬል። ወንድሞቼ ሆይ! የነፃነት ትግሉ መሪ አባ ወራዎች ሆይ! ዓይን ካላችሁ ከዚህ ሀቅ ጋር የመንፈሳችሁ ብሌን ይታረቅ ዘንድ ብዕሬ በጽሞና ያሳስባችኋል … በአክብሮት – በትሁት መንፈስ።

 

በአፍሪካ ታሪክ ጉልበታሙ የፕ/ ማንዴላ ተገዳሎ የምዕተ ዓመቱ ታላቅ መዘክር ነው። ሚሊዮን ሰማዕት ሴቶች ታድመውበታል። በፆታዊ ችግር አፓርታይድ ያሴረውን መረብ ዝለሉትና ክብርት የነፃነት ብቁ አርበኛ እማማ ዊኒ ማንዴላ ባላቤቷ እስር ቤት በነበሩበት ጊዜ የነፃነት ትግሉን በግንባር በመምራት፤ ልጆቿን በማሳደግ፤ ለትዳር አጋራ አጥር ቅጥር በመሆን የጽናት ወተት ነበረች። ይህን ከባለቤቷ ጋር ትጻጻፍ ከነበረው የነፃነት ትግሉ ዋነኛ ትምህርት ቤት ዝክረ ደብዳቤዎች ማገናዘብ ይቻላል። ህያው ምስክር ነውና። ሁሉም ፍጡር እናቱን የሚወድበት ሚስጢር በሀገር ጉዳይ ላይ ቢውለው ምንያህል ፈውስ በነበረ – ለመለውዓለም። የ ዓለም ዝበርቅ አስፈሪ ውጣ ውረድ ፍቺ ያለው ከሴቶች ነበር … ባሊህ አጣ እንጂ …

 

በእኛዋ እናት ሀገርም … በቀደመው በዘመን ንግስት ዘውዲቱ የመቻልን ተፈጥሮ፤  ከእቴጌ ምንትዋብ የተግባር ሚስትነትና አርበኝነትን፤  ከከዕቴጌ ጣይቱ ብልህነት – ፖለቲካ መሪነትና አማካሪነት – ጠበብትነትና ጀግንነትን ጠብተን አድገናል። በዘመናችንም … ሳራ ግዛውና ሺብሬ በሰማዕትንተ፤  አያልነሽ – አለምዘውድ፤  ብርቱካን ሜዲቄሳ፤ ሰርካለም ፋሲል፤  ርዕዮት ዓለሙ፤ በላይነሽን ስንቶቹን የነፃነት አርበኞች እናት ሀገራችን አፍርታለች። መሬታች መሃን አይደለም። ተሳትፎውን በጉልበት ያነጠፈው* ያንጠፈጠፈውም የወንድ በላይነት ብቻ  ነው። አሁንም  በአንድነት ወ/ት ወይንሸት የምትሰጠውን ቃለ ምልልስ አኑትና አጣጥሙት …. ያው ታች ስለሆነች ቅጥቀጣው ያልፋታል ብዬም አስባለሁ … ቀና ካላች ግን ቅንጧን ነው … በለመደ እጅ … እህህህህህ!

 

እኔ … በአጽህኖት እናገራለሁ። የፖለቲካ መሪዎቻችን የውስጥ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል። በፍጥነት። በንግግራቸው ውስጥ እንኳን ብጣቂ እርስት አልተሰጠነም። እንኳንስ በፍላጎታቸው ልብ። በራዕያቸው አንጎልም የለንም። አብሰንት ነን።  ምንአልባት ትዝ የምንላቸው የራባቸው ጊዜ ይሆናል። ለነገሩ ነጭ ሀገር ፋስት ፉድም አለ … ዘመኑ ተለውጦ እራስም ይጋገራል … ሀገር ቤትም ተለምዷል አሉ … የጓዳ ነገር። እንዲሁም በዬአጋጣሚው የሚሾሟቸው አብዛኞቹ የበታች ገዢዎቻችንም ለውጡ ገፍቶ እንዲያነጥራቸው እንሻለን። አቅም በመበተንም አንቱ ናቸውና! ይደግም። የበታቾቻቸው አቅም በመበተን አንቱ ናቸውና!

 

የበላዮች የበታቾቸውን የሚከታተሉበት መስመር ቢኖር መልካም ነው። የጉሮሮ አጥንቶች እነሱ ናቸው። የፓለቲካ አመራር ልም ነው። ጣጣውን የጨረሰ ለስምሪት የበቃ ንጥር ቅቤም፤ ለስምሪትም ስንዱ። እኔ የማዬው ዘመንተኛው ፖለቲካ ግን ሽርክትና ግርድፍ ሆኖ ነው። አብሶ አጋርን በመገፍተር እረገድ ከንፍሮ የወጣ አንድም መሪ አልገጠመኝም። ቆሞ ስለ አርበኛ አንስት የሚመሰክር ዓይናችን አላዬም …. እንደናፈቃቸው ይቅር ዓይነት ነው ነገሩ …

 

እርግጥ ነው ሥር ላይ ያለው ተግባርን የሚያደምጡት፤ ከበታቾቻቸው ለዛውም ስታስቲክሱን በሩቁ ነው። ያው ወያኔ ባላው የተዛነፈ ዳታ ይወነጀላል። የኛም እኮ ያው ነው። ከታች ወደ ላይ የሚተላለፈው ቁጥር ተብዬ። የበቃ ፍጽምና ያለው ተሳትፎ …  ለማዬት ወረድ ይበሉ። ሰፊ መድረክ ይክፈቱ። የትችት አንባ ይወጁ። እንዲያድጉ እንዲመነደጉ ከፈለጉ። … በራስ አነሳሽነት የሚደረገው የፈጠራ ተሳትፎም እምብዛም ነው። ሁልጊዜ ከላይ የተንጠለጠለ መና ይጠበቃል። የማኒፌስቶውን ጭብጥ ይዞ ጭብጥን በጭብጥ አፋጭቶና አታግሎ የነጠረውን የፓርቲያቸውን አቋም አሸናፊ ለማድረግ ፈጠራ ከአቅም ጋር ይጠይቃል። ማረር!

 

ያው ቁንጮቹ የሚሉትን በተገኘው አጋጣሚ የጎረሱትን እዬፈቱ ሲደግሙና ሲሰልሱ ዓመት ይዞ እስከ ዓመት ከዛው ለዛው ሲዳክሩ ነው የሚታዩት። ተመስገን ነው ዛሬ እድሜ ለኢሳት በተለያዬ መድረኮች መሰናዶ ከሊቃኖች አዳዲስ ነገር ስንቅ ስለሚገኝ ተሽሎ ሊሆን ይችላል። ግን የራስ ጌታ ለመሆን ማንበብ መልካም ነገር ነው። የዬትም ሀገር ነፃነት ትግሎች ለድል እርከን ያደረሱት አጋራቸውን በበሰለ ህሊና ባሊህ ብለው ነው።  … እርግጥ ላይኞቹ ሴቶች ማለት ሲጀመሩ የታችኞች ቅጂውን እንደ ገደል ማሚቶ ያስተጋቡታልና እባካችሁ ላይኖቹ ጀመሩት …. ግን በተለበጠ መልኩ ሳይሆን ቁምነገር ባለው ዕውነት – ከልብም። ዝም ብሎ ከሆነ ልጥፍ ይሆንና የተላመጠ አገዳ ይሆናል ምኖታችን።

እኛ እንላላን። እኔና ትዳሬ ብዕሬ …. ተከታታይ የሆነ አቅም ያለው የመንፈስ ጥሪት ለመገንባት ይሞክሩ ፖለቲከኞቻችን ….፤ ሙሁሮቻችን። የሴቶችንም ነገረ ሚስጢር አክለው …. የሃይማኖት አባቶቻችን ሲያሰተምሩን „ነገረ መለኮትን“ ነጥለው ሳይሆን „ከነገረ ማርያም“ ተነስተውአስቀድመው እነሱ በቅድሰት ድንግል ፍቅር ቅጥል እያሉ ነው። የእናታቸው ፍቅር ግብግብ እያደረጋቸው ነው። እኛም እንደ እነሱ ሆነን እናታችን የማናሰነካው – ተከተል አባትህን ሆኖ ነው። የድንግል ነገር የሁለመናችን ገዢ የሆነውም በዚህው ቅኝት ተቀረጽን ስለሆን። ማለት ለተዋህዶ አማንያን። አሳምረው ጠረቡን። መንፈሳችን በቅዱስ መንፈስ ገሩት ነው። ያኑርልን ሊቀ – ሊቃውንቱን። የቅድስትን የመንፈስ ድንግልና ፍቅር በማያልቅ ወተት አጥብተው አሳድገውናልና። በሥጋዊ ፍቅርም ቢሆን ፍቅር ድብን አድርጎት እያለቀሰ ከልቡ የሚያዜም ከልብ ጠብ ይላል … በስተቀር ድው የለ ትም  ….

 

ይህ ትግል የሚባለው ጀግና … አርበኛና ሰማዕት …. ድሆኖው* ጉድሎበታል፤ ጎታው* ተራቁቶበታል ታላቅ ነገር ቅናዊ ዕይታ፤ ሥልጣንን የማጋራት ግልጽነት፤ ኃላፊነትን በቅመም የመመጠን ሥልጡን ዕይታ። ትርጉም ያለው ተግባራዊ እርምጃ ከኢትዮጵያዊነት መሪዎች በአጽህኖት ይጠበቃል።  እኩላዊ መስመር ሳይፈጠር አሯል። አይታይም። የመከነ ጉድ ነው …. በዬትኛውም ሁኔታ በቦታው የሌለ ነገር ቢኖር ሴቶችን  በአክብሮት እኩል ለማሳተፍ ያለው ፈቃደኝነት ልሙጥ መሆኑ ነው ድርቅ የተጫወተበት፤ ዝናብ ሲሄድበት የከረመ አለት የመሰለ ለዛ የለሽ ጉድ። በጣም በረቂቅ ሁኔታ በሴቶች ላይ የተጣለው ማዕቀብ ዘመንና ጊዜ ይፈታዋል የሚል ግምት የለኝም። የተሳሳረ ድንቡልቡል ነገር ነው። በሩ ተቀርቀሯል። ጭላንጭል መተንፈሿ ቧንቧው የታነቀ ነው ….  ለዛውም እኮ ቆርጠው የሚወጡት ጥቂት ሆነው እነሱን እንኳን በአግባቡ ለመያዝ ምንም …. ታውቃላችሁ?! ምንም ነው 00000 በቅናሴ ያለ … ተቋም ቢኖር …. የሴቶች የእኩልነት የተሳትፎ መድረክ ድርሻ ምክነት።

 

ህይወት ካለሴቶች ኮረኮንች — አመዳም — ቡላ —- የፋደሰ —- ቀዝቃዛ — የነፈዘ —– ነው የተፈቀፈቀ። …. የትግሉም ዕጣ ፈንታው ይህ እንዲሆን ተገምድሎበታል። ይፍታህ በሉት! ነይልኝ — ነይልኝ — „የህይወቴ ህይወት“ ለዚህ ብቻ  … ። ትውልድን በአዲስ የተሳትፎ ፖለቲካዊ ባህል ለመገንባት ዳገት። ታሪካዊ ድርሻን ለመወጣት ክትከታ። የምንፈለገው ለአጃቢነት ወይንም ጥላ ለመያዝ ወይንም ለዘበኝነት ብቻ። ደንበር ሰበር ለሆነ ለሚመጥን የሥልጣን ክፍፍል ወይንም ተደማጭነት ማነቆ – እገዳ – ክልከላ … ሰባራ ጉድ፤ …. ጨምዳዳ ….. ዕጣ። የተሸበሸበ … ራዕይ። ሽራፊ …. ህልም። ያመለ … ነገ። የሻገተ … ተስፋ። ያልተጠረገው መንገድ ረቂቅ ሚስጢር ይህን ይመስላል። መፍትሄው ለዛሬ አዲስ መኃንዲሶች፤ እራሳቸውን የዘለሉ ሙሴዎች ያስፈልጉታል … ይመስለኛል።

 

እናሳርገው። ….. የምቀኝነት በሽታ ያለባቸው ድውያን በዬአጋጣሚው ያፈኑት ነገር መተንፈሻ ከሌለው አጉል ቦታ ይፈስና ብዙ መስመሮችን ይበርዛል። „ልብ ያለው ሸብ“ ብለናል … ከብሂሉ ጋር እርገት ይሁን። እኔ ምን እንደሚናፍቀኝ ታውቃላችሁ ዓይነታ የወጣለት መሪ … ደፈር ብሎ ስለ ሴቶች …. ጥብቅና አጋፋሪ የሚሆን ሊጋባ። የነፃነት እልፍኝ አስከልካይ ሀቀኛ ዓራት ዓይናማ። ሴቶች ብዙ አላቸዋ። ያጡት ያላቸውን የሚያቀኑበት ገብያ ብቻ ነው ….. ግጥም ታውቃላችሁ … ቅኔዊ። እንደ ግጥም የልብን ድርስ የሚያደርጉ ምርጥ ፉጡራን ናቸው አብዛኞቹ ሴቶች። እርዳታቸው – ፈጣን፤ ምክራቸው የልብ አድርስ፤ ጽናታቸው ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ፤ ፍቅራቸው የትውልድ ዋዜማ፤ ሥልታቸው ሥልጡን፤ ብልህነታቸው ተጨባጭን የዋጠ። ጉዟቸው ደፋር።

 

ሳልሄድበት የማልፈልገው ጥምዝ መንገድ ደግሞ ሌላው አጋር ለአጋር መገፋፋቱ ነው። ይህ ደግሞ ለአንስት የእኩልነት አንባ የከፋው ዕጣ ነውና ለአጋራችን እኛው አጋር በመሆን ጥጓ እንሁን። ብቃቷን ለመመስከር አንደበታችን እንፍታው፤ ለሴት እህታችን ብቃት ዋቢ እንሁንላት። ለሴት እህታችን ተጋድሎ ቀድመን እንገኝላት – ከጎኗ።  ለዘንካታ ትዕግስት ሞንሟና ምስጋና እንሆ!

 

ሴቶች የነፃነት ትግሉ ዓርማ ናቸው!

ሴቶች ለነጻነት ቅኔ ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

መፍቻ

 

  • አጃ የልብ መደረስ፤ ከጠበቁት በላይ መርካት።
  • ቅንጧን … ቅንድቧን …
  • ብጡል የተለዬ … የተመረጥ …
  • መገምደል … ፍትህን የጣሰ ፍርድ።
  • ያነጠፈው …. ያደረቀው … ምደረበዳ ያደረገው …. ድርቅ ያስመታው … ለዘር ያላበቃው ….
  • ሽታሽቶ  …. እያረፉ፤ በፈረቃ በድርብ …. ማድቀቅ …. ማጥቃት ….
  • መሸበብ … መሸፈን … መጋረድ … እንዳይታይ ማገድ …
  • ድሆኖ … ከጭቃ የሚሰራ መሰል ግጣም ያለው የእንጀራ መያዣ … ሌማት፤ ወይንም ጥራር እንደማለት
  • ጎታ … ከጭቃ የሚሳራ ትልቅ የ እህል መያዣ … እንደ በርሚል ….

 

 

«ድምጽ አልባው አሳዛኝ የወገኖቻችን ለቅሶ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ!»

0
0

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መዝናኛ ክበብ ሰራተኞች ሰንደቃላማችን በተሰቀለበት ግቢ ግፍ እና በደል እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ

በኢትዮጵያን ሃገሬ ከጅዳ ዋዲ

በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሁለት የጸጥታ ጥበቃዎችን ጨምሮ ከ13 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በስሩ እንደሚገኙ የሚነገርለት ይህ የመዝናኛ ማዕከል ከተቆርቆረ ሁለት አስርተ አመታትን ቢያስቆጥርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች ከትርፋማነት ይልቅ ኪሳራ፤ ከእድገት ይልቅ ውደቀትን እያቀነቀነ አሁን ላለበት ደረጃ መድረሱን የሚናገሩ እማኞች በሰራተኞቹ ላይ እየተፈጸመ ያለው በደል ከመቸውም ግዜ በላይ እየከፋ መምጣቱን ገልጸዋል።
saudi 1
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ካፍቴሪያ ማዕከል ዛሬ ላለበት አሳፋሪ ደረጃ ምክንያት መሆኑ የሚነገረው በተለያዩ ወቅቶች በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ጀርባ ታዝለው ያለችሎታቸው አመራር የሚሆኑ ግለሰቦች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች ጋር በቅርበት ተነጋግረው የካፍቴሪያውን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ከማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ እና ስርአት ውጭ በብሄር ተከፋፍለው እርስ በእርስ በመጋጨት በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ተላላኪ እና አፋሽ አጎንባሽ በመሆናቸው መሆኑንን ይጠቅሳሉ። የኮሚቲው አመራር አባላቶች ዲፕሎማቱ በሚሰጧቸው ትዕዛዝ እንደሚንቀሳቀሱ የሚናገሩ ምንጮች ከ10 አመት በላይ ያለ ደሞዝ ጭማሪ ደፋ ቀና የሚሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መብት በመደፍጠጥ ፍሬ ፈርስኪ በሆኑ ጉዳዩች ተጠምደው «ሲሻም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እንዲሉ» በተለያየ አቅጣጫ የወጪ ቀዳዳዎችን በማበጀት ወደ ማህበሩ ካዝና ዲፕሎማቱ እጃቸውን እንዲሰነዝሩ በመጋበዝ በሚፈጸም አስነዋሪ ተግባር ለኮሚኒቲው ውድቀት ግንባር ቀደም ምክንያት መሆናቸውን አክለው ይገልጻሉ። በዚህም ምክንያት የኮሚኒቲው ካፍቴሪያ በየአመቱ ኪሳራ አሳይቷል እየተባሉ አንገታቸውን እስከዛሬ አንገታቸውን ለመድፋት የተገደደዱት የኮምኒቲው ካፍቴሪያ ሰራተኞች በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የኑሮ ውድነት ተከትሎ ከዛሬ 10 አመት በፊት በተቀጠሩበት ደሞዝ የስደት አለሙን ህይወት መግፋት ተስኗቸው ለከፍተኛ ችግር በመዳረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሳውዲ አረቢያ ምድር በባዕዳን የሚፈጸምብን ግፍ እና ስቃይ ሳያንሰን ባዲራችን ከፍ ብሎ በሚውለብለበት የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ በገዛ ወገኖቻችን መገፋታችን ያሳዝናል ያሉ አንድ የካፍቴሪያው ሰራተኛ ባለተዳር እና የሶስት ልጆች አባት መሆናቸውን ገልጸው ዛሬ በየአመቱ የመኖሪያ ፈቃዳቸውን ለማሳደስ እስከ 10 ሺህ ሪያል ለማውጣት እንደሚገደዱ አውስተው ለምኖርበት መኖሪያ ቤቴ በየስድስት ወሩ ከምከፍለው የቤት ኪራይ ጋር ተዳምሮ በ 2 ሺህ ሪያል ደሞዝ አይን ካልገለጹ ልጆቼ ጋር ኑሮን ማሸነፍ ተስኖኝ አቤት ለምለው አጥቼ በነዚህ ጨካኞች የሚፈጸምብኝን በደል ሳልወድ በግድ ለመቀበል ተገድጃለሁ ብለዋል። በተጠቅሰው ካፍቴሪያ ከ 8 ሰአት በላይ ያለ ተጨማሪ ክፍያ « ኦቨር ታይም» ሃይማኖታዊ በአላትን ጨምሮ ደስታ ምን እንደሆነ ሳያውቁ ከእጅ ወደ አፍ የሆነውን ኑሮቸውን ለማሸነፍ ደፋቀና እያሉ መሆናቸውን የሚናገሩ እነዚህ ወገኖች ተጨማሪ ስራ ሰርተው እራሳቸውን መደጎም የሚችሉበት ግዜ እንደሌላቸው እና አቅማቸው እንደማይችል ጠቁመው ጉዳዩ ያችን እልባት እስኪያገኝ ለወግን ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በጸሎት ከጎናቸው ይቆም ዘንድ ተማጽነዋል።
sudi
ይህ የኮሚኒቲ ማህበር እንደ ማህበር ህጋዊ ህልውና አጊቶ ስራ ከጀመረ ሁለት አስርት አመታትን ማስቋጠሩን የሚያወጉ አንዳንድ እድሜ ጠገብ አባላቱ በተጠቀሱት አመታት የአንባሳደሩን መኖሪያ ቤት ጨምሮ በሪያድ የኢትዮጵያን ኤንባሲን በ20 ሚልዮን ሪያል ወጪ አስገንብቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስረከበ ታላቅ እና ስመጥር ማዕከል እንደ ነበር በማስታወስ ዛሬ ይህ የኮሚኒቲ ማህበር ግቢ ጥቂቶች እንዳሻቸው የሚያዙበት የአይንህ ቀለም አላማረኝም እያሉ የገዛ ወግናቸውን በቡጢ እይነረቱ ከግቢ የሚያባርሩበት ከሰሪዎቻቸው አምልጠው ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ቅጥር ግቢው በሚመጡ እህቶቻችን ላይ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጸምበት እና የወገኖቻችን ሬሳ የሚቆጠርበት የጥቂት ወሮበሎች መሸሸጊያ መሆኑ አሳዛኝ እና ሳፋሪ ነው ብለዋል። በአጠቃላይ ከቅርብ ግዜ ውዲህ ይህ በሪያድ የኢትዮጵያ የኮሚኒት መዝናኛ ማዕከል በወገኖቻችን ላይ ኢሰባአዊ ድርጊት የሚፈጸምበት መዕከል ለመሆኑ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ምንጮች የመዝናኛው መዕከል ሰራተኞች አብዛኛዎቹ የወጣትነት እድሜያቸውን እዛው የኮሚቲ ማእከል ውስጥ የጨረሱ እና በብስጨት ለስኳር በሽታ ለድም ግፊት እና መስል ተዛማጅ በሽታዎች ተዳርገው የተጎሳቆሉ በመሆናቸው ሌላ ስራ ፈልገው የማግኘት እድል እንደሌላቸው በማውሳት የሚመከተው አካል አሁን የሳውዲ አረቢያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ያወጣውን ህግ መስረት በማድረግ የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግላቸው እንደሚገባ እና የሳውዲ አረቢያ መንግስት አሁን ባወጣው ህግ መስረት የተጠቀሱትን ወገኖቻችንን ከህገወጥነት ለመታደግ የመኖሪያ ፈቃዶቻቸው በኤንባሲው ስር ሊሆን የሚቻልበትን መፍትሄ ማፈላለግ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሃላፊነት መሆኑንን ይገልጻሉ።

ይህን ተከትሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አክሳሪ ነው በሚል ለአያሌ አመታት ሲመዘበር መቆየቱን የሚናገሩ የሪያድ ነዋሪዎች በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘምድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የኮሚኒትው ሊቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አሊዬ ምንጩ የማይታወቅ 2 ሚልዮን ሪያል «25 ሚልዮን ብር » ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሶስተኛ ሃገር ሊያሻግሩ ሲሞክሩ በሳውዲ አረቢያ መንግስት ደህነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ውለው እስካሁንም እስር ቤት እንደሚገኙ ይገልጻሉ።

ሰበር ዜና: ኢትዪጲያዊ ሙስሊም የችሎት ውሎ (ቢቢኤን ልዩ ፕሮግራም)

0
0

ቢቢኤን ሰበር ዜና
ልዩ ፕሮግራም
ሁሉም ኢትዪጲያዊ ሙስሊም ሊሰማው የሚገባው የችሎት ውሎ
የኮሚቴዎቻችንን ጠበቆች ተማም አባቡልጉንና ጠበቃ  አዲስን አነጋገራናል፡፡ትግሉ በተጠናከረ መልኩ ለመቀጠል ህዝቡ የአሚሩን ትዛዝ በመጠበቅ ላይ ነው

መንግስት ከሰረየሰላም አምባሳደር በሆኑት የብርቅ ሰብእና ባሌበቶች ላይ መንግስት ፖለቲካዊ ፍረጃዉን ጭኖባቸዋል፤ ይህ ደግሞ መንግስት መክሰሩን ፍንትዉ አርጎ የሚያሳይ ነዉ።በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ዉድ ዜጎች የተወከሉትን ኢትዮጵያዉያንን ፍትህ-አልባ በሆነዉ ፍርድ-ቤት ለማሸማቀቅ መሞከሩ፤ አለም-አቀፋዊ የሆኑ የህግ መስመሮችን አልፎ ሰርዓት-አልበኝነትን ለማንገስ የሚደረግ አይን-አዉጣነት በመሆኑ በዛሬዉ ችሎት መንግስት ከስሯልና እናንተ የተስፋ ባለቤት የሆናችሁ ኢትዮጵያዉያን ድል አይቀርምና ተጽናኑ።መንግስት የኛዎቹን ማንዴላዎች መፍታት ሲገባዉ ወደ እስር ቤት ልኳቸዋል። የትላንቶቹ አፓርታይዶች ኩምሽሽ-ሽምቅቅ-ስዉር እንዳሉት የዛሬዎቹም የኢትዮጵያ አፓርታይዶች ኩምሽሽ-ሽምቅቅ-ስዉር ማለታቸዉ አይቀሬ ነዉ። ልክ እንደማንዴላ ሁሉ ኮሚቴዎቻችን ከተጎናጸፉት የሰብዓዊነት ማእረግ በላይ እፁብ-ድንቅ ምድራዊ ብሎም ሰማያዊ የሆነን የብርቅ ሰብእናን እርከንን ይሻገሩ ዘንድ የፍትህ ቀበኞች ወደ እስር ቤት መልሰዋቸዋል። ድል አይቀርምና ወደ ድል በሚያሽግረዉ ሰላማዊ ታንኳ “ድምጻችን ይሰማ!” እያልን በቃልኪዳናዊ ጥምረት እንጓዝ። ልብ ያለዉ ልብ ይበል!
BBN Your Voice

አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ ነውረኞች !

0
0

አበራ ሽፈራው
ከጀርመን

እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጥር ጥቅምት መጨረሽና  ህዳር ወር 2006 እጅግ አሳዛኝና በህይወት እስከአለን ድረስ የማንረሳው ክፉ አጋጣሚ በእህቶቻችንና በወንድሞቻችን ላይ ግድያን፣ መድፈርን፣ እስርን፣ መታረድንም፣ በመኪና እየተገጩም ጭምር መሞትንም መጀመሩን ያየንበትና የሰማንበት:: ክፉ ወር:: ብዙዎቻችን በውስጣችን ከራሳችን ጋር የተሟገትንበት፣ ምን እናድርግ? ብለን ከቅርብ ጓደኞቻችን ጋር የተነጋገርንበት:: ሌሎቻችንም ተሰባስበን በውስጣችን ያለውን ሃዘን በግልጽና በአደባባይ ዓለም ሁሉ እየሰማ የተነፈስንበት::  ሳውዲ አረቢያዎች ለዘመናት አብሮአቸው የነበረውን ጭካኔ በአይናችን የተመለከትንበት ምን አልባትም እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከዚህ በላይ ሲጨቆኑና ሲረገጡ መኖራቸውንም ለማየት የቻልንበት ጊዜ ይህ ይፋ ወጣ እንጂ::

በእርግጥም ሳውዲዎች ጨካኞች ናቸው ስራቸውም እጅግ አሳፋሪ ነው:: ጊዜ ይለወጣል ሀብትም ይጠፋል  ነገር ግን ታሪካቸው በተለይም በወንድሞቻችን ላይ የተፈጸመው ግፍ ግን ለታሪክ ሲታወስ ይኖራል :: በሳውዲዎች ድርጊት ያላዘነ ኢትዮጵያዊ የለም እኔ እስካየሁትና እስከሰማሁት ድረስ:: ታሪክ የእኛን እንግዳ ተቀባይነትን እንደመዘገበ ሁሉ የእነሱንም ውለታ መላሽነት በእኛ ዘመን ለማየት ችለናል ይህንንም ታሪክ መዝግቦታል:: በክፉ ዘመናቸው በአገራችን ተሰደው እንደ እናት ቤት ኢትዮጵያ እንዳልተቀበለቻቸው ሁሉ ዘሬ ሰርተው ሳይሆን አምላክ በተፈጥሮ በሰጣቸው ተመክተው  የጥጋብ ዱላ በወገኞቻችን ላይ አዘነቡ የብዙ የኢትዮጵያውያን እንባ በአለም ሁሉ ፈሰሰ፣ የአምላክንም እጅ ተማጸነ፣ ብዙዎች የአምላክንም ምህረት በእንባ ለመኑ በእርግጥም አምላክ ሰምቷል መልሱም አንድ ቀን ለአገሬም ይሠጣል::

ላለፉት 50 ዓመታት አረቦች ለኢትዮጵያ ያላቸውን ጥላቻ በተለያየ መልኩ ለመፈጸም ሞክረዋል ዋናው መነሻቸውም በሁሉም መልኩ ለመስፋፋት ያደረጉትን እንቅስቃሴ ሁሉ እሽ ብሎ የተቀበላቸው ያለመኖሩና በአፍሪካ ቀንድ የአረቦች አስተሳሰብ ተግባራዊ ሊሆን ያለመቻሉ ሲሆን ይሁንና ሃሳቦቻቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ግን አርፈው ተኝተዋል ማለት ግን አይደለም:: ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ኢትዮጵያን ለመበታተን የተጠቀሙት አንደኛው መንገድ የዛሬዎችን ዘረኛ የህወሓት/ ወያኔ ቡድን እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁሉ አንደኛው መሳሪያ ሆኖ ያገለገላቸው እኩይ ቡድን መሆኑ ጭምር ነው::

በእርግጥም ኢትዮጵያና ልጆቿ ለአገራችው ሳይሆን የሌሎች ህዝቦችንና አገራትን ሰላም ለማስከበር ለመስወአት የቀረቡ የህወሃት ጀነራሎች የገቢ ምንጭ ሆነዋል፣ የአረቦችን ቆሻሻ ለመጥረግና በዚህ ዘመን የሌለን ባርነት ርካሽ ጉልበታቸውን ለመሸጥ ተገደዋል ይኸም ብሶ ለአስከፊ ችግር መጋለጣቸውም ቢሆን ከኢትዮጵያው የህወሓት ሥርዓት ማንነት ጋር የተያያዙ ችግሮች ውጤቶች ናቸውና መሰደድና የህወሃት ደላሎች መጠቀሚያ መሆንና ለመከራ መዳረግም ቢሆን የሥርዓቱ መዋቅሮች ለዚህ አስከፊ ችግር መፍትሄ መፈለግ አቅቷቸው ሳይሆን እራሳቸውን እስከጠቀማቸው ድረስ በዝምታ ቆይተው ችግሩ ተባብሶ  አስከፊ ደረጃ ሲደርስ ደግሞ “ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል“ እንዲሉ አሳቢ መስለው  መነሳታቸው ደግሞ ያሳዝናል::

ለአሁኑ የአረቦችም ሆነ የሌሎች አገሮች ማጥቃት መነሻው በአገራችን ያለው የፖለቲካ ችግር ሲሆን የኢኮኖሚ ችግሩም ቢሆን የዚሁ የፖለቲካው ችግር ውጤት መሆኑ ማንም ይስማማበታል:: ለመነሻም እንዲሆነን የአገሪቷን ፖለቲካ ለ22 ዓመታት የተቆጣጠረው ህወሃት/ወያኔ  በግልጽና በአደባባይ የኢትዮጵያ ህዝብ አይኑ እያየ የአዋቀረው የንግድ ብዝበዛ፣ የአገሪቷ የንግድ እንቅስቃሴ ከፓርቲ ንግድ ወይም ከEFFORT በተጨማሪ ትልልቅ የንግድ ተቋማት በህወሃት ሰዎች መያዛቸው፣ ጠቅላላ የንግድ መድሎ መኖሩ፣ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶች በሙሉ በሚያስብል መልኩና በተጠና መልኩ በህወሃት ሰዎች መያዛቸው፣ ለንግድ ስራ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ልዩልዩ የሚንስትር መስሪያ ቤቶች በነዚሁ ሰዎች መያዛቸውና ልዩ ልዩ የአገሪቷን ንግድ በሙሉ በማክሮ ኢኮኖሚ የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ጭምር ለእነሱ የሚጥቅሟቸውን ሁኔታዎች እስከማመቻቸት ድረስ መድረሳቸውን ቀዳሚ እድሎችን የሚያገኙት እነሱ መሆናቸው ጭምር ናቸው::

ለአሁኑ ጥቃጣችን ምክንያት ከላይ የተጠቀሰው ጉዳይና ሌሎች ጉዳዮች ሲሆኑ በተጨማሪም አረቦች በተለይም ሳውዲ አረቢያ ለህወሃት ቅርበት ባለው ሼህ መሃመድ አላሙዲንና በሌሎች የንግድ ሸሪኮቻቸው አማካኝነት ባላቸው የቆየ ቅርርብ ማንነታቸውን በጥልቀት ያወቁ በመሆናቸው ወገኖቻችን ደራሽና ወገን ወይም የሚከላከልላቸው እንደሌላቸው ሰው ሆነው በአሳዛኝ መልኩ እንዲባረሩ መደረጉ ለህዝቡና ለተጎጂ ቤተሰቦች እንጅ ለህወሃት ሰዎች ቅንጣት ያህል እንደማይሰማቸው እርግጠኛ ነኝ:: ለዚህም ደግሞ የህወሃት የጭካኔ መጠንን ለመለካት የኢትዮጵያን ህዝብ ለህወሃት ያለውን አመለካከት በመለካት ማወቅ ቀላል ነው:: ይልቁንም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለህወሓት የማፍያ መዋቅር ሌላ የገቢ ምንጭ እንደፈጠረለት በቀላሉ መገመት ይቻላል:: ይህንን በቀላሉ ለመረዳት በተመላሽ ወገኞቻችን ንብረት ላይ የሚደርሰው የንብረት ንጥቂያ ብዙዎች በሳውዲ አረቢያ ከደረሰባቸው ስቃይ  ይልቅ በአገራችን በህወሃቶች የጉምሩክና በኤርፖርት አካባቢ የተደረጉት የፍተሻ ዝርፊያዎችና የንብረት ቅሚያ ቀላል ሊባሉ እንደማይችሉ እየተነገረ ይገኛል:: ይህም ችግር በአገር ውስጥ ተባብሶ ብዙዎችን ለተጨማሪ የስነልቦና ችግር ላይ መውደቅ ምክንያት እየደሆነ ይሰማል:: ታዲያ ይህንን የህወሃትን ሥርዓት ምን ልንለው እንችላለን?

ከላይ እንደገለጽኩት የህወሃት የማፍያ መዋቅር የትኛውንም አጋጣሚዎች እንደ አንድ ጥሩ አጋጣሚ የሚቆጥሩ መሆናቸውን ለማየት ከላይ ከጠቀስኩት ተግባራቸው በቀላሉ ለማየት ይቻላል:: አባይ ግድብ ብለው ይነሳሉ ከህዝቡ  ከልጆቹ ማሳደጊያ እየነጠቁ ሰብስበው ባልተጠና መልኩ የተጀመረን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በሚል የተሰበሰበውን በጀትና ገንዘብ ለህወሃት የንግድ ተቋማት ትልቅ የብዝበዛ ምንጭነት እንዲያገለግል ሲደረግ እያየን እንገኛለን፣ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ከስደት በግድ ሲመለሱ በላብና በደማቸው የሰበሰቡትንና ከሳውዲዎች እጅ አምልጦ በእጃቸው ይዘው የመጡትንም በጥሬ ገንዘብና በአይነት መበዝበዛቸው፣ በዚሁ አስከፊ ጊዜ ለእነዚህ መከረኞች መድረስ ሲቻልና የተሰደዱት ከማቋቋም ይልቅና የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆነው ሳሉ በመቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠርን ብር በብሔር ብሄረሰቦች ስም አውጥተው ሲደንሱበት ከማየት በላይና አሁንም የህወሃት የንግድ ተቋማት የኪስ ማደለቢያ ማድረጋቸውን ስናይ እጅግ የሚዘገንን ተግባር ነው ለማለት ያስችላል::

ትላንት ደርግ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1977 ዓ.ም የወሎና የትግራይ ወገኖቻችን በድርቅ ሲጠቁ የደርግ 10ኛ ዓመትና የኢሠፓን ምስረታን በከፍተኛ ወጭ አከበረ እያሉ ሲሳለቁበትና የትግላቸው መቀስቀሻ አድርገው ሲዘምሩበት እንዳልነበረ ዛሬ የትላንት ነጻ አውጭዎች ነን ባዮች የዛሬዎቹ በዝባዦች በአደባባይ ስራቸውን፣ምግባራቸውንና አላማቸውን ከመቼውም ጊዜ በላይ እንድናያቸው አድርጎናል:: ደግሞም የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቼውም ግዜ በላይ ለራሱ እያሰበ መምጣቱና እየነቃ የትኛውንም የክፋት መዋቅራቸውንም ይዘርጉ ይህንን ሁሉ በጣጥሶ እነዚህን ጎጠኞች አይናችሁ ለአፈር ያለበት ግዜ ላይ ደርሰናል:: በአገር ውስጥ መቃወም ባይችልም ዝምታን መርጠው የነበሩ ሳይቀሩ ዛሬ በአደባባይ ህወሃትን ለመጋፈጥ ቆርጠው ታይተዋል:: ትግሉንም ለመደገፍ ግልጽና ስውር ትግሉን መቀላቀል ተያይዞታል፣ ለህወሃት አስደንጋጭ በሚሆን መልኩ ትግሉን ወደከፍተኛ ምዕራፍ ለማሸጋገር ግልጽና የህቡ የትግል መስመሮችን እየተቀላቀለ ይገኛል::

ከዚህ በላይ የእህቶቻችንንና የወንድሞቻችንን ደምና እንባ ሳይደርቅ ለእነዚህ የሳውዲአረቢያ ጨካኞች የአገራችንን መሬቶችንና ሌሎች የንግድ ፍቃዶችን ለመስጠት ከ300 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን መስማማታቸውን ስመለከት ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆንንና እነሱን እስከጠቀመ ድረስ ኢትዮጵያዊነት በህወሃቶች ፊት ምንም እንዳልሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል:: እንግዲህ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባይሆንም እና በሌላ ርዕስ የምመጣበት ቢሆንም ከኢትዮጵያ ድንበርን ወደሱዳን ለማካለል መነሳታቸውንም ስመለከት በጣም የሚያሳዝን መጥፎ አጋጣሚ ላይ መኖራችንንና የማንን መሬት ለሱዳን ለመስጠት እንደፈለጉም በደንብ አልገባኝም:: ስለሆነም ህወሃቶች ምን አይነት ትምህርት እንደተማሩ ምን አልባትም ብዙዎቹ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑና በአጋጣሚዎች ኢትዮጵያ በሌሎች እኩይ ተግባርን በሰነቁ የኢትዮጵያ ጠላቶች እጅ መውደቋን ለመረዳት እንችላለን::

ዛሬ አስቸጋሪ እንዲያውም ለአገራችን ህልውና አስጊ የሆነ ጉዳይ ቢኖር ህወሃትን ለመጋፈጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ  መሆናችንን ማስብ ካልቻልን ነው :: ስለሆነም እነዚህ የታሪክ ጥቁር መዝገቦች፣የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ጠላቶች፣ የህዝብና የትውልዱ ጠንቆችንና አጋጣሚዎችን ሁሉ ለራሳቸው የብዝባዛ መሳሪያነት የሚጠቀሙትን ጠላቶቻችንን ለመጋፈጥ አሁንም ያልቆረጥን እንቁረጥ::

ይህ አስከፊ የህወሃት ሥርዓት የሚፈልገውን ሳይሆን እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ የሚመኙትን ነጻነትና ፍትህ፣ ሁሉም ብሔረሰቦችና የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ በእኩልነትና ያለመድሎ የምንኖርባት፣ ፍትህ የሰፈነባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በሁሉም ኢትዮጵያውያን ፍቃድ የምንመሰርትበት፣ የህግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከህወሃት የዘር ጭቆና መላቀቅ ያለብን ሰዓት ላይ ደርሰናል:: አጋጣሚዎችን ሁሉ እየተጠቀሙ ለብዝበዛና ለእልቂት ከሚዳርጉን ነውረኞች እራሳችንን እናድን::

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

aberashiferaw.wordpress.com

comment_stage_5

                                                              


በራሳሽን ላይ የምንሰለፍበት ቀን ናፈቀኝ? ራሳሽንን

ጠርዝ ላይ ያለ ስጋቴ –በመንትዮሽ። ከሥርጉተ ሥላሴ

0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ
12.12.2013

ስጋት እንደሚፈቀድልኝ አስልቼ ሃሳቤን ንፉግ ሳልሆን ልገልጽ ወሰንኩ። መወሰንና መቁረጥ መልካም ናቸው። ካሰቡት

የሚያድርሱ ሰጋሮችና ገሮችም።

andu-family-45

በሌላ በኩልም ከመንፈስ መታከት ይታደጋሉ – ይመስለኛል። እመቤት ነፃነትና ፊታውራሪ ሂደት እውኃ በሚያደርግ ፋስ ለማን አዘነሉት?! የፊታውራሪ ሂደት የትርታ – ትብብር አማ ስንቱን ገበርዲን ስንቱን ሙሉወርድ ዋጠው? ስንት አቅም ባከነ – ስንት ፍቅርስ አለቀሰ? ስንት አብሮነትስ ተከፋ? ሰረዘው … ሰወረው? ፊታውራሪ ሂደት ብዙም ሳንርቀው ግራው – ቀኙ – ማዕከላዊነትን አግቶ ወይንም ነካክቶ። የቅርቡን ስናስበው ሁለት ምርጫ ይዞ ቀረቦ ነበር። ዘንባባ ወይንስ ሳንጃ በማለት አሳፈን። እኔ ከአጠው ቋጥኝ አፋፍ ላይ ሆኜ ናዳውን ለእህትና ወንድሜ፤ እህትና ወንድሜም አጸፋውን በመልቀቅ ተጠን። የባሰው ግን ሺዎች አለፉ፤ በእስር ማቀቁ … ስንት የፍቅር ቤት – ትዳር ተፈታ፤ ተናደ ~~~ አብሶ ህፃናት የወላጅ ናፍቆት አሰቃያቸው፤ ፍቅርና እንክብካቤ አጥተው ቀጨጩ። ኢዲህቅ፣ አማራጭ፤ ህብረት፤ ቅንጅት ….

ቅንጀት እራሱ ኢዲአፓ፤ አላይንስ፤ ግንቦት፤ አንድነት፤ መድረክ፤ ጥምረት፤ ዝም አንልም፤ ግንቦት ዲ፤                   የጥቃቱ ሰለባዎች በፋመ በቀል እዬተቀቀጡ ያሉ- የነገ ትውልድ ተስፋዎች ትብብር …. ያንተ ያለህ …. መከታከት ምዕራፋችን

ዬት ላይ ይናጠጥ ይሆን? …

ሎቢያችን በመደማመጥ የሚሰክነውስ መቼ? መንፈሳችን ከቋሳ ጸድቶ የጸዳ ማግሥት መቼ ይሆን ልደቱ? ክብሮቼ … በመኢህድ ዙሪያ ቢሆን በሥነ ደንብ ፊርማ ግብግብ የነበረውንም ታውቁታላችሁ። አንዲት ብሄራዊት ሀገር – በህብረ ቀለም ያጌጠች፤ አንድ የነጠረ ግን በብዙ የራቀን ፍላጎት የሰነቀ የነፃነት ራዕይ፤ አንድ መነሻ – አኃቲ መዳረሻ፤ ትርጉም ሰጥና አጉራሽ ጉዞ ተከትሎ ስንጥቅ ትርትር ገጠመኝ። ያደክማል። …. እህህህ …

ባለፉት ሳምንታት አንድነት ከመኢህድ ጋር አብሮ ለመስራት አንድ እርከን ላይ መድረሱን አነበብኩ።

ተከትሎም ብቸኛው የፓርላም አባልና የነፃነት ፈላጊ ቤተሰብ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ „ኡ ኡ የመደማጥ ያለህ“ በሚል እርእስ ከዘመንተኞች ጋር አብሮ ስለመሰራት አለልስ ምኞታቸውን ከማሳሰቢያ ጋር አካፈሉን። ለማጣፈጫ አንድነት የአደራ መክሊትን ተግባር ላይ በማዋል ላይ ስለሚገኘው አቶ አንዱዓለም አራጌ የመጸሐፍ ምርቃ ላይ ሥርዓት አዘጋጅቶ አደባባይ በስሙ እንዲሰዬም ፍላጎቱን ነገረን። እንደ መዳረሻ ደግሞ ከኢሳት አንድ ሰበር ዜና አዳምጠን … ያው ዘኃ ግራው በአንድነት ዙሪያ ነው …

እኔ ልዩ ስጋት አደረብኝና … ሁኔታውን እንዲያብራሩልኝ ለተከበሩ ለአቶ ግርማ ሰይፉ ኢሜል አድራሻቸውን ከጹሑፋቸው ሥር ስላገኘሁት ቁልጭ ያለቸውን ስጋቴ ቅልብጭ ባለች አጭር ሀተታ ቋጭቼ ላኩላቸው። ቀኑ ነበር። መልሱን እዬጠበቅኩ ነው። ከትቢያም ይሁን ከጭድ ከታችኛው ክፍል የሚመጡ ቀና ዕይታዎች የነገ የተስፋችን መሪ ከሆኑት ይገኛል በማለት እዬጠበኩ ነው። መቼም ነፃነት የራበው የነፃነት ንፉግ እንደማይሆን በመስላት።

ትናንት – ደግሞ የሞቀ – የሰከነ – ጥልቅ – ተቆርቃሪነትን ያቀለመ መልእክት ከአደራ ጽኑ ጠበቂያችን ከአቶ አንዱዓለም አራጌ ዘሃበሻ ላይ አነበብኩ። ስጋቴም በዚህ ጥግ ዙሪያ ነበር። ለተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ የፃፍኩትም ይኽንኑ የሙጥኝ ያለ ነበር። ልምዱ አለና። ክብረት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እስር ቤት ላይ ሁና ነበር አንድነት በአዲስ መልክ የማጠናከሪያ ምርጫ ያደረገው። እንዲሁም መድረክ የተወለደው። ስጋቴ ቅርንጫፍ ሳይሆን ሥር ያለው ነው። ፊታውራሪ ሂደት በበለኃሰብ እጅ፤ ካቴና ላይ ሆና ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ያገለለ ድራማ ከወነ አንድ መጋረጃ። ያን ጊዜ  „ዝም አንልም“ የሚል አንጃ በአንድነት ውስጥ ተፈጠረ። ከዚህ ሁሉ በላይ ስደት ላይ የምንገኘው በክፉም በደገሙ የምንገናኝ የእትብት ልጆች የፊታውራሪ ሂደትን ሃዲድ ተከትሎ በመጣው ጦስ በኢትዮጵውያን የመወያያ የጋራ ቤታችን ስንፋጭ እስከ መለያዬት አደረሰን። ሙጃው ወያኔም አራት ኪሎ ተራራ ላይ ሆኖ ከበሮውን ደለቀ …. ሄሮድስ መለስም አፈር እንደቀራባቸው ሳይተነብዩ ፍልቅልቅ ብለው ሳቁብን – ፈነደቁ።

የተስፋችን ማህደር የነበረችው ክብረት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ለትውልዱ የመጀመሪያ ሴት በመሆን በአንድ ሀገራዊ የብሄራዊ ፓርቲ መሪ ስለነበረች የብቃቷን ጡት ወተት ለመቀለብ ቀን ስንቆጥር መክኖና ፈልሶ ቀረ። እኔ ረቂቅ ናፍቆት ነበረኝ። መድረክ ላይ በአካል ስላዬኋት እሳሳላትም ነበር። ህልሜ ግን ተኖ ቀረ። አንዲት የቆረጠች እርግጠኛ ሴት አዲስ ቡቃያ ወጣት፤ ከምንም ነገር ጋር ንክኪ የሌላት ሰንደቅን የታጠቀች ብቸኛ የነፃነት አርበኛ ያላስተናገደ የዴሞክራሲ ትግል ፍቺ የለሽ ቅልሞሽ ነበር ለእኔ። እሷ ከመፈታቷ በፊት ሁሉ ነገር ተከወነ። ስትፈታ መግቢያ ቤቷ ከውስጥ ተከርችሞ፤ አደራ ያስረከበቻቸው የአንድነት ቤተሰቦቿ ጉልቻቸውን በፋስ ፈረካክሰው፤ በጎሪጥ ዳርና ዳር ሆነው በእሳትና በቃጠሎ ታጥረው አገኘቻቸው … ምን ይሁን? መግቢያ ያጣቸው አብነት … እንደ ተዘጋባት … ጨርሱትን እኔ አቅም የለኝም። አቤቱ ድህነትህ መቼ ይሆን!

የእኔ ስጋት ምንጭ ይህ ነው። ትናት እነ – አቶ ሰዬ  ዘውድ ተድፍቶላቸው ብርቴን … ዛሬ ደግሞ እነ – አንባሳደር ስዩም አንዷለምን …. ይሆን – ይሆን? …. የፊታውራሪ ሂደት የማጥቃት ወቅቱ ተመሳሳይ ነው። ያው የምርጫ ዋዜማ። መደረክ ያን ጊዜ፤ ዛሬ መኢህድ፤ አቶ ሰዬ ትናት ዛሬ አንባሳደር ስዩም መስፍን። የሚኮረኩር ነገር አለው።  የሚመጠምጥ ነገር። ብርቴም እንደ ዛሬው እንደ አንዱዓለም ውዳሴ ይደረደርላት፤ ቅኔ ይዘርፍላት ነበር – በሁላችንም። አቡነዘሰማያት ተዘውትሮ ይደገምላትም ነበር። ስለሆነም የአደራ ዋቢው አቶ አንዱዓለም የዓመቱ ምርጥ ሰው ሆኖ መመረጡ የነገን የመታገያ ወርዱን ሊያጠበው ወይንስ ሊያሰፋው የትኛው ይሆን ቅዱ የቦዩ፤ ጥግ የሚያሳጣ ይሆንይሆን መዝሙሩ? ተንጠልጥሏል ስጋቴ …. ጭንቅን ታጥቆ – ትዝብትን ተሸክሞ – ተስፋ ማጣትን አርግዞ …. እግዚኦ ነው እግዚኦ!

በሌላ በኩል አያድርገው እንጂ አቶ አንዷለምን የሚያገል ሁኔታ ቢፈጠር እኛ እንደፈረደብን ጋ (ቡድን) ለይተን ደግሞ እንደ ትናንቱ መፋለጡን እንቀጥላለ? ይህም የመንትያው ስጋቴ ሥጋና ነፍስ ነው። የፊታውራሪን ሂደትን መርኃ ግብር ውስጥ ቼክ ማድረግ አለብን። እስከ መቼ በቆራጣና ቆልማማ አፍንጫው እዬዳነሰብን ይኑር?! ትርፍና ኪሳራውን እንመትረው። ጠቀሜታውን እንፈታትሽው። እንደ ኖርንበት ሁኔታ ይህ የታደለ የሽፍታ አስተዳደር ወያኔ በአገኘው የመተንፈሻ ጊዜ ተጠቅሞ የለበጣ ልጥፍ ድራማውን የሚከውንበት አዲስ ለም ማሳ እንዳናዘጋጅ ጠንቀቅ።

ስጋት ወጥሮኛል ~ መፈናፈኛ ነስቶ ያባትለኛል ~ ሰንጎ ይፈትለኛል። በዬጊዜው በሚከፋፈለው የኮርኒስ ግድግዳ እንኳን ሆኖ ደፋ ቀና የሚለው የነፃነት ፈላጊ ቤተኛ ዛሬም ሌላ ስንጠቃ ይጠብቀው ይሆን? ሌላ የመሬት ክፍፍል ዕጣ ፈንታ? እ! ከሁሉ የሚያሳዝኑኝ በተለይ ነጭ ሀገር ተወልደው የሚያድጉ ልጆች ደንበርና ወሰን በዬጊዜው እዬተሰራላቸው በፍልሰቱ መንደር ሰላም አጥተው ከአቻዎቻቸው ጋር አብረው እንዳያሳልፉ ተስፋቸውን ሲኦል መልቀቃችን ነው …. ተሳህለነ!

ውህደቱም ሆነ ጥምረቱ፤ አዲስ የማጠናከሪያ በሉት የማሟያ ሂደቱን እላይ ባሉት ተወስኖ ተግባራዊ ይሆናል። ታች ያለው አባል የሚሰማው አባል እንዳልሆነው ልክ እንደ እኛ በመግለጫ ነው። መግለጫውን ተከትሎ መለያዬት ሲመጣ ታች ያለው ወገን ነው በጠላትነት ተፈራርጆ ሲዋቃ ውሎ የሚያደረው።  እጅግ የማከብራችሁ መንፈሰቼ፤ የሀገሬ ልጆች ከእንግዲህስ ሞኝ አንሁን። የተስማሙት እነሱ ሲለያዩም እነሱ ብቻ ይሁኑ …። እኛ በምን እዳችን ነው በዬጊዜው እንዲህ እምንተረተረው። አለቅን – ሳሳን እኮ! ስደቱ የማይቻል ሸክም፤ በዛ ላይ ደግሞ በዬዕለቱ አጀንዳ ስንሰነጣጠቅ የምንገኘው …. ስለምን ነው? ረዳት ጠያቂ አልባ እኮ ፈለስን!

ክብሮቼ ልብ ልንለው – በማስተዋል ልንመረምረው የሚገባው ጉዳይን እንሰበው …. ከልብ ውስጣችን እባካችሁን በሞቴ እንምራው። ለምናምንበት አካል የምንችለውን እናድርግ። … ሃሳብን በሃሳብ እናታግል በመከባበር በሥልጡን ሁኔታ። ከዚህ በተረፈ እኛ ቢያንስ በስደት ተሳስብንና ተዛዝነን እንደ ተፈጥሯችን በአብሮነት እንኑር …. የሱባኤ ጊዚያችን በተመክሯችን ጥሪት እናበልጽገው። መሪዎቻችንም ቁርጣቸውን ሲያውቁ እነሱ መከባበርን አዝምረው፤ ፈርኃ ፈጣሪን ጥሪት አድርገው፤ መግባባትን አድምጥው፤ ለመቻቻል እጃቸውን ሰጥተው፤ ሁሉን ቻል በማድረግ ለኢትዮጵያዊነት ሊታገሉ ይችላሉ። አልበላም እያለ ለሚያስችግር ልጅ ብትባላ ብላ፤ ባትበላ ተዎው ሲባል፤ ራህብ ሲያኮራምቶ ለምኖ ይበላታል። እስኪ በዚህ መንገድ ደግሞ ይሞከሩ … መሪዎቻችን …

የፊታውራሪ ሂደት ከነቤተሰቡ ጥቃት ቀጥተኛ ሰለባ የሆነው የ አደራ ቤተኛ አቶ አንዱዓለም አራጌ ፤ – አምርሮ ህሊናው ያዘነው፤ ወጣት የነፃነት ደቀመዝሙር አቶ አንዱዓለም አዝመራውን ከአውድማው ማዬት ጓግቶ ግን …. ምች ሊያጠቃው ዳታ (ዝግመት)ሲፈታተነው መረረው ። መሆንን ያሰተማረን አቶ አንዷለም ይገባዋል። እውነቱንም ነው። ከትናንት ዛሬ እዬተጫነን ጉም እዬለበሰ ሲያዘግም፤ ተስፋው እዬራቀ ሲመጣ …. የፋመው ሲበርደው፤ የጋመው ሲቀዘቅዝ፤ ማግስት ከቅርበት ጋር ሲጣላ፤ ጉድጓድ ውስጥ በቋሳ የተነቀሰ በደል ተሸክሞ ፍዳ ሲከፍል፤ መተንፈሻ ቧንቧው ተጋርዶ አዬር ሲያጣ  - ሲቀረቀርበት፤ ድቅድቅ ባለ እስር ቤት – በተፈነ ጉረኖ ወይንም በረት ሁኖ ያን የመካራ ሌሊት ጋር ለሚያስልፍ የነፃነት ራህብተኛ አርበኛ ጨለማ ነው። ረግረግ ነው። ጨቀጨቅ ነው። ጥቁር ውስጥ ሆኖ ተስፋ አድርጎ እራሱን የሰጠበት ነገር ውሉ ሲላላ … ተስፋው ሲተረተር …. እሳትና ረመጥን ለመረጠ የመሆን ጀግና መርግ ነው ከባድ። ስለሆነም ከቋያው በተወሰነ ደረጃ ትንሽ ራቅ ያለው ቤተሰብ ቀለማሙን የአደራ ቡቃያ ከብክቦ ማሳደግ ግድ ይለዋል …. መልእክቱ ውስጥን ይመረምራል። መንፈሱ ውስጥን ያፋጥጣል። እያንዳንዱ ቃል ውስጥን ይፈታትሻል …. ከራስ ጋር ታርቆ „ሀ“ ብሎ „ሁ“ እንዲቀጥል መባታልን መታጠቅ … ገፋ አድርጎ መሄድን ይጠይቃል። ጫናው ከባድ ቢሆንም ….

እንደ – መሰብሰቢያ

አደራን ተቀብሎ ስለፍትህ የጸናው፤ የቀለጠበት ድርጅት ቢያንስ እውነተኛ ቦታውን እንዳይነሳው …. ስጋቴ ጠርዝ ላይ ነው ያለው … ወድቆ እንዳይፈጠፈጥ እዬሰጋሁ ነው …. እናንተስ ውዶቼ? ያቺ አጋሩም ብቻዋን በአንድ ክንድ አሳር ላይ ያለ ትዳርን ስንቅ በማቀበል፤ ሁሉን ችላ ጽናትን በመቀለብ፤ ታይተው የማይጠገቡ ጮርቃዎች የአባት ናፍቆት እዬቀጣቸው እንዲያድጉ በቀንበጥነታቸው በሄሮድስ መለስ ሰባራ ገል ሌጋሲ ተፈርዶባቸዋል። ደማሞቹ ሁለት ህጻናት ውስጣቸው ያለቅሳል – በናፍቆት ተርመጥምጧል፤ የደጁንም የቤቱንም ሙሉ ኃላፊነት …. የወሰደቸው የነፃነት ትግሉ ዓይነተኛ አካላዊ ክንፍ ባለቤቱም የሰው ህይወትን የመፈወስ የላቀ ሙያዊ ድርሻ፤ የወያኔው እውር ደህንነት አራዊቶች በዬምትንቀሳሰቀስበት ስንዝር የስለላ ጫና … ተሸክማ ያልበላቸውን ዕዳ ስትከፍል በመንፈሱ አንዱ … ያያታል። የማይገፉ ሌሊቶች ካለ መፍትሄ የተፈጥሮን ሂደት ተከትለው ይነጉዳሉ። …  ታዲያ በመራር – የብረት አጥር ኑሮው ከእንቡጦቹ ተለይቶ መኖሩ ላይበቃ የሚቀልጥለት አደራ ቡቃያው ሲጫጫ ውስጡ ተክኖ እንዳይታመም ጠርዝ ላይ ያለው ሌላው የተከደነና እምቅ ስጋቴ ነው …. ማህከነ! አብረን ቆዬን ሳትሰለቹኝ። ኑሩልኝ ታዳሚዎቼ።

 

 

እልፍነና እልፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው።

 

 

Sport: ቀነኒሳ በቀለ በኤደንበርግ አገር አቋራጭ ውድድር ላይ እንደሚሮጥ ታወቀ

0
0

ከቦጋለ አበበ

ወደር የማይገኝለት የረጅም ርቀት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በእዚህ ወር መጨረሻ በኤደንበርግ አገር አቋራጭ ውድድር እንደሚሮጥ ታውቋል፡፡ የዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማህበር ድረገፅ ሰሞኑን እንዳስነበበው ቀነኒሳ በኤደን በርግ ዘንድሮ ሲሳተፍ ለስድስተኛ ጊዜ ነው፡፡
የሠላሳ አንድ ዓመቱ የኦሊምፒክ የሦስት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ቀነኒሳ እ.አ.አ ከ2006 ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ጊዜ በኤደንበርግ አገር አቋራጭ ውድድር ቢያሸንፍም 2010 ላይ ባልተጠበቀ ሁኔታ አራተኛ ሆኖ አጠናቅቋል፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላም አሥራ አንደኛ ሆኖ ውድድሩን ማጠናቀቁም ይታወሳል፡፡
kenenisa 1
ቀነኒሳ በዘንድሮው ውድድር ግን ሁለት ጊዜ የተሸነፈበትን ታሪክ ለመቀየር መዘጋጀቱ እየተነገረ ይገኛል፡፡
ቀነኒሳ በዓለም አገር አቋራጭ ውድድር በረጅምም ሆነ በመካከለኛ ርቀት አሥራ አንድ ያህል የወርቅ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ የሚስተካከለው አትሌት የለም፡፡
በፈጣን የአጨራረስ ብቃቱ የተለየ ዝና ያለው ቀነኒሳ በቀለ እ.ኤ.አ ከ2010 ጀምሮ በጉልበቱ ላይ በአጋጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት በተለያዩ ውድድሮች ድል ሳይቀናው ቀርቷል፡፡ በተለይም በለንደን ኦሊምፒክ በአምስትና አሥር ሺ ሜትር እንዲሁም በሞስኮው የዓለም ሻምፒዮና በተመሳሳይ ርቀቶች ያመለጡት የወርቅ ሜዳሊያዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ቀነኒሳ በሞስኮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባይካፈልም ከሻምፒዮናው በኋላ በተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ወደ ድል መመለሱን አሳይቷል፡፡ አሁንም ቀነኒሳ የቀድሞ ክብሩን ለማስመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝና ለ2016 የሪዮዲጄኔሮ ኦሊምፒክ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ቀነኒሳ በመጪው ዓመት ከመም ውድድሮች ወጥቶ ወደ ማራቶን የመግባት እቅድ እንዳለው በመግለጽ አሁን ወደ ቀድሞ አቋሙ እንደተመለሰና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ለዜናው ምንጭ ከሰጠው አስተያየት ማወቅ ተችሏል፡፡
ቀነኒሳ ባለፈው ክረምት በታላቁ የሰሜን በግሬት ኖርዝ ረን ኒውካስትል ውድድር ላይ በአሥር ኪሎ ሜትር የጎዳና ተወዳድሮ ላይ ውድድር የአገሩን ጀግና አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴና የወቅቱን የአምስትና አሥር ሺ ሜትር ንጉሥ ሞሐመድ ፋራን በማሸነፍ ወደ ቀደሞ ብቃቱ እየተመለሰ እንደሚገኝ አስመስክሯል፡፡
በኤደንበርግ ለማሸነፍ እንደተዘጋጀና በራስ መተማመኑም ከፍተኛ እንደሆነ የተናገረው ቀነኒሳ፤ኤደን በርግ ላይ ከተሸነፈባቸው ውድድሮች ይልቅ ባሸነፈባቸው ውድድሮች ጥሩ ትዝታ እንዳለውና ያንን ትዝታውን አሁን መድገም እንደሚፈልግ ገልጿል፡፡ ቀነኒሳ በተለይም በ2008 በዓለም ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
በስኮትላንድ ኤደንበርግ ከተማ በየዓመቱ የሚካሄደው የአገር አቋራጭ ውድድር በዓለማችን ታዋቂ አትሌቶችን ከሚያሳትፉ ውድድሮች አንዱ ነው፡፡ ዘንድሮም ውድድሩ ከአውሮፓና አሜሪካ እንዲሁም ከአፍሪካ የተውጣጡ ጠንካራ አትሌቶችን እንደሚያሳትፍ ታውቋል፡፡

በዛሬው ችሎት በነፃ የተሰናበቱትና ተከላከሉ የተባሉት የድምጻችን ይሰማ ዋና መሪዎች ስም ዝርዝር

0
0

ዘ-ሐበሻ በዛሬ ጠዋት ሰበር ዜናዋ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ውስጥ 10 በነፃ እንዲሰናበቱ፣ 14ቱ ዋና ዋና መሪዎች እንዲከላከሉ፣ ሌሎች 4ት ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ዝቅ ተደርጎ ሰውን በማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ መወሰኑን መዘገቧ ይታወሳል። ለአንባቢዎቻችን ግልጽ እንዲሆን በማሰብ ማን እነማን ተከላከሉ እንደተባለ፣ ማን እንዲፈታ እንደተወሰነ፣ ማን ክስ ዝቅ እንዲደረግለት እንደተደረገ ስም ዝርዝራቸውን ይዘናል። በነጻ የተሰናበቱት የእስር መፍቻ እንዲጻፍላቸው እና ይከላከሉ የተባሉት ደግሞ መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን እንዲያሰሙ ከጥር 22 ጀምሮ ፍርድ ቤቱ ተከታታይ 5 ቀናት በተለዋጭ ቀጠሮ ለሕዝብ ክፍት በሚሆን ችሎት እንደሚያቀርቡ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ማንዴላ፣ ኦባማና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉዳይ – ከሳዲቅ አህመድ (ያድምጡ)
ተከላከሉ የተባሉት፦ 

1. ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
2. ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
3. ኢንጅነር በድሩ ሁሴን
4. ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
5. ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ
6. አሕመድ ሐጂ ሙስጠፋ
7. ኡስታዝ ሰኢድ አሊ
8. ጋዜጠኛ አቡበከር አለሙ
9. ሙኒር ሼኽ ሑሴን
9. ሙባረክ አደም ጌቱ
10. ሷቢር ይርጉ ማንደፍሮ
11. ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው ዘውዴ
12. ካሊድ ኢብራሂም
13. አብዱረዛቅ አክመል
14. ሙሐመድ አባተ

 የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ዝቅ ተደርጎ ሰውን በማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ የተወሰነባቸው

1. ሸኽ መከተ ሙሄ
2. ወንድም ኑሩ ቱርኪ
3. ኡስታዝ ባህሩ ዑመር
4. ወንድም ሙራድ ሽኩር

በነፃ እንዲሰናበቱ የተደረጉት፦
1. ዶ/ር ከማል ገለቱ፣
2. ሸኽ አብዱረህማን፣
3. ሸኽ ሃጂ ኢብራሂም፣
4. ሸኽ ጣሂር አብዱልቃድር፣
5. ሸኽ ሱልጣን አማን፣
6. ወንድም ሀሰን አሊ
7. ኡስታዝ ጀማል ያሲን፣
8. ወንድም አሊ መኪ፣
9. ወንድም ሀሰን አቢ እና
10. ወ/ሮ ሃቢባ መሃመድ

ጄነራል ሳሞራ የኑስ በውጭ ተቃዋሚዎች የመለስን የበላይነት መስክረዋል አሉ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ኢሕአዴግ ለይስሙላ ያከብረዋል እየተባለ በሚተቸውና ለ8ኛ ጊዜ የተከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሕገ መንግሥት ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ መንግስት ባሳተመው ‘ሕብረ ብሔር’ መጽሔት ላይ ቃለ ምልልስ የሰጡት የጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ መለስ ከሞተ በኋላ በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎች የሟቹን አቶ መለስ ዜናዊን የበላይነት መስክረዋልና እናመሰግናቸዋለን አሉ። በሰራዊቱ ውስጥ እኩልነት እንዳለ መናገራቸውም ብዙዎችን አስገርሟል።
Samora Yenus
በከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ ነው በሚል በተደጋጋሚ ተጽፎላቸው የነበሩትና አሁንም ህክምና ሁልጊዜ እንደሚከታተሉ የሚነገርላቸው ጄነራል ሳሞራ ከመንግስታዊው መጽሔት “የቀድሞው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈተ ሕይወታቸው በድንገት ከተሰማ በኋላ በውጭ የሚገኙ አንዳንድ ፀረሰላም ኃይሎች እና አንዳንድ ተቃዋሚዎች ኢትዮጵያ ለሽብርና ለሌሎች ፀረ-ሰላም ተግባር መጋለጧ አይቀርም ሠራዊቷም መዳከሙ አይቀርም በማለት ሲገልጹ ነበር። ይህ ሊሆን ያልቻለው ለምንድ ንነው ይላሉ? እነዚህ ወገኖች ይህን ተመኝተዋል ነገር ግን ያልሞከሩት ከምን አንፃር ነው?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ “ከመለስ በኋላ ሠራዊቱ ይዳከማል ብለው ማሰባቸው የመለስ አስተዋፅኦ ጠንካራ ሠራዊት እንዲኖር፣ ጠንካራ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ኃይል እንዲኖር ያስቻለ ስለመሆኑ እውቅና መስጠት ስለሆነ እናመሰግናለን።” ካሉ በኋላ ቀጥለውም “ምክንያቱም መለስ ይህቺ አገር ጠንካራ የመከላከያ ኃይል እንዲኖራት ወሳኝ ድርሻ ነበረው ብለው ስላመኑ ነው ይህንን ማንሳት የጀመሩት፡፡ ይህን ማሰብ በመጀመራቸው ደግሞ መመስገን ይኖርባቸዋል፡፡” ብለዋል።

ሳሞራ በመንግስታዊው ጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ለዚሁ ተመሳሳይ ጥያቄ በሌላ በኩል የአንድ ሰራዊት ጥንካሬ የሚለካው በሰራው አንድ ሥራ ብቻ አይደለም። ሠራዊቱ ይህቺ አገር እስካለች ድረስ አብሮ ይኖራል። ምክንያቱም ተቋሙ ቀጣይ ነው። ተቋሙ ለሁለት ነገር ብቁ መሆን አለበት። አንደኛ ለወቅታዊ ግዳጁ፣ ሁለተኛ ደግሞ ለወደፊት ለሚሰጥ ግዳጅ ብቁና ዝግጁ መሆን አለበት። የእያንዳንዱ አመራር ተልዕኮም ይሄ ነው። በተለይ የከፍተኛ አመራሩ ተልዕኮ ይህንን ማረጋገጥ ነው። ይሄን እንዴት እንፈፅመዋለን ለሚለው ደግሞ ሶስት መሰረታዊ ሥራዎችን በመሥራት ነው።
ዋናውና ወሳኙ የሰው ኃይሉን ማዕከል ያደረገ ሥራ መሥራት ነው። የሰው ኃይሉን ማብቃት። ቴክኒካዊና ሙያዊ እንዲሁም አካዳሚያዊ ብቃቱን ማሳደግ፣ ሳይንሳዊ ዕውቀቱን ማዳበር፡፡ እንግዲህ ሶስት የአቅም ግንባታ ሥራ መሥራት ዋነኛው ሆኖ የሰው ኃይል ማዕከል ያደረገ የአቅም ግንባታ ሥራ መስራት ያስፈልጋል። ሁለተኛው ሥራ በአደረጃጀቱና አሰራሩ ሕዝባዊ ባህሪውን እንደጠበቀ ከተልዕኮውና ከባህሪው የሚስማማ አደረጃጀትና አሰራር ያለው እንዲሆን ማድረግ ነው። አደረጃጀት አቅም ፈጣሪ ነው። አደረጃጀት ለዘለዓለም የሚኖር አይደለም። ከሁኔታው ጋር እየዳበረ አቅም እየፈጠረ የሚሄድ መሆን አለበት። አሰራሩም በተመሳሳይ ከሕዝባዊ ባህሪውና ከተልዕኮው የተጣጣመ አሰራር ዴሞክራሲ ያዊና ደስተኛ ሕይወቱን በአስተማማኝ የሚጠብቅ፣ የግዳጅ አስተሳሰቡንና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦችን የሚያዳብሩ አሰራሮችን ማረጋገጥ ማለት ነው። አደረጃጀቱም፣ አሰራሩም፣ የሰው ኃይሉም ሦስቱን ሥራዎች በመሥራት ነው ለተጨባጭ ግዳጅም ሆነ ለወደፊት ለሚሰጠው ግዳጅም ዝግጁ የሚሆነው፡፡
“ስለዚህ ሠራዊቱ በዚህ እየተገነባ ስለቆየ ነው ውጤትም እየተገኘ የመጣው፡፡ ካብ አይደለም ሲሠራ የነበረው። ጠንካራ የመከላከያ ተቋም፣ ጠንካራ የመከላከያ ኃይል፣ ሕዝባዊ ባህሪውን የጠበቀ የመከላከያ ኃይል ነው ሲገነባ የነበረው። እና በዚህ ምክንያት ሊፈርስ አልቻለም፡፡ አይፈርስምም ይጠነክራል።
እነዚያ ወገኖች የተመኙትን አልሞከሩትም ማለት ግን አይደለም፡፡ የብተናና የተለያዩ ሥራዎችን አልሞከሩም ማለትም አይደለም። መከላከያ ሠራዊታችንን የሚያፈርሱት ሦስት ምክንያቶች ካጋጠሙ ብቻ ነው የሚል እምነት አለን። በንግግር አይፈርስም። በሦስት ነገር ግን ሊፈርስ ይችላል። አንደኛውና ዋናው ተልዕኮው ከተቀየረ ነው፡፡ እንግዲህ አሁን ተልዕኮው ሕዝባዊ ነው። የወረራ ተልዕኮ የለውም። የሠላም ተልዕኮ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋው ከሰላም እንጂ ከጦርነት አይደለም፡፡ ስለዚህ ከዋናው ተልዕኮ አንደኛው ሠላም ማረጋገጥ ነው። ይህ ደግሞ በሕገ መንግሥቱ የተቀመጠለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ የጦርነት አደጋ ካጋጠመ በአጭር ጊዜ እና በአስተማማኝ በመጨረስ ተመልሰን ወደ ልማታችን መግባት ነው።ሌላው ተልዕኮ ደግሞ የአፍሪካ ወንድሞቻችን ከእኛ ለሚፈልጉት ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ማበርከት ነው።
የእነርሱ ሰላም የእኛም ሰላም ስለሆነ በአቅማችን በሰላም ማስከበር ሥራ መሳተፍ ነው። አራተኛው ደግሞ በአገር ውስጥ ከፀጥታ ኃይሎች አቅም በላይ የሆነ ጉዳይ ካለ መሳተፍ። በህብረተሰቡ ላይ ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ከአጋጠሙ የድርሻችንን መወጣት ነው። እነዚህ ተልዕኮዎች ሕዝባዊ ተልዕኮዎች ናቸው። ከሕገ መንግሥቱ የወጡ፣ የተቀዱ ተልዕኮዎች ናቸው።
“ሁለተኛው የሠራዊቱን ጥንካሬ ሊበረብር የሚችል ደግሞ የራሱ የሰራዊቱ የውስጥ ችግር ነው። ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ከሰፈነ ሠራዊቱን ሊያፈርሰው ይችላል። ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ከተፈጠረ በርካታ መዘዞች ይመጣሉ። ፀረ-ዴሞክራቲክ መሆን ከተጀመረ የህግ የበላይነት ይጣሳል ማለት ነው፡፡ በአንድ በኩል በህግና በአሰራር መሄድ ይቀራል። ሁለተኛ የሠራዊቱ ደስተኛና ዴሞክራሲያዊ ሕይወት ይበላሻል። ስለሆነም ጠንካራ አንድነት፣ አስተማማኝ አንድነት፣ የማይናወጥ አንድነት ያለውን ሠራዊት አንድነቱ እንዲናጋ ያደርገዋል። የጌታና የአሽከር አካሄድ ነው የሚኖረው፡፡ ይሄ ደግሞ ለአገሪቱም ለሁሉም አይጠቅምም።
“ሌላው ደግሞ ሙስና ነው። ሙስና ሠራዊቱን ሊያበላሸው ይችላል፡፡ ሙስና ፀረ ልማት ነው። ሠራዊቱን ሊበትነው እና ሕዝባዊ ባህሪውን እንዲያጠፋ ሊያደርገው ይችላል። አንድ ሠራዊት ሠራዊት ነው የሚባለው እንደ ወታደር እንደ አንድ አካል ሲያስብ እንጂ ለግሉ ሲያስብ አይደለም።
ለምሳሌ አንድ ወታደር በአንድ ሻለቃ ወይም በአንድ ቡድን ሊድን ከሆነ ሻለቃዋ መዳን አለባት፡፡ በሌላ በኩል አስሩ ከዳኑ ነው እርሱ መዳን የሚችለው። ቡድኑ ብቻውን ሊድን አይችልም። ስለዚህ ይሄ ሻለቃ አስሩን ማዳን አለበት።ወታደሩ መዳኑ የሚረጋገጠው አስሩ ከዳኑ ይሆናል። ብቻውን ሊድን ከፈለገ አይችልም። በተመሳሳይ አንድ የመቶ ካለችም ሶስት ቲም አሏት፡፡ የመቶዋ ልትድን ከሆነ ቲሟ መስዋዕትነት መክፈል አለባት፡፡ እንደዛ እያለ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ እንደ አንድ አካል የሚያስብ መሆን አለበት፡፡ ፀረ ዲሞክራሲ አካሄድ ካለ በውስጡ አንድነቱ ይላላል፤አስተሳሰቡም ይሸረሸራል ማለት ነው፡፡ ሙስናም በተመሳሳይ ለግል ማሰብን ይመጣል፤ ይህም ያፈርሰዋል። በአጠቃላይ በዚህ ነው የሚፈርሰው እንጂ በንግግርና በአሉባልታ አይደለም።” ብለዋል።

የአንድ ብሔር ተወላጆች በሰራዊቱ ውስጥ ቁልፍ ቦታ መያዛቸው፣ በትውልድ ብሔራቸው የተነሳም በሙስና ነቅዘው ሃብታም መሆናቸውን፣ መከላከያ ሰራዊቱም የሃገር ዘራፊዎች መሳሪያ መሆኑን በስፋት በሕዝብ ዘንድ የታወቀ ሆኖ ሳለ ኤታማዦር ሹሙ ይህንን ሽምጥጥ አድርገው በመካድ ለዚሁ መጽሄት “ወታደር ሲሆን ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን የመጠበቅ ተልዕኮ ነው ያለው። ሌላ ምንም ነገር የለውም። ከሌላው ዓለም የእኛ ደግሞ ትንሽ ይለያል። ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱ የሚጠበቀው በሕዝቡ፣ በሠራዊቱም በሁሉም እኩል ነው፡፡ የሁሉንም ሕዝቦች ተጠቃሚነት ስለሚያረጋግጥ በተወሰኑ ምሁራን ብቻ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ስለዚህ የሁሉንም ህዝቦች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጠውን ህገመንግስት ሁሉም ህዝብ ማወቅ አለበት፡፡ ሁሉም ህዝብ ማወቅ አለበት ብቻ ሳይሆን እንዲያምንበትም መደረግ መቻል አለበት፡፡ካመነበት በኋላ ደግሞ እንደወታደር ለመጠበቅም ለመስዋዕት ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ይገነባበታል።” ማለታቸው ትዝብት ውስጥ እንደጣላቸው ታዛቢዎች ይናገራሉ።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live