Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በኖርዌይ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቸ ኮራሁ፤ ለኢትዮጵያ የጉብኝት ዘመን ደረሰ ይሆን?

$
0
0

ዳንኤል ከኖርዌይ
ይህንን ጽሁፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ april 28,2013 በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ የወያኔ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ያየሁትና የሰማሁት የኢትዮጵያውያን ጩኸት ነው። በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የወያኔ ግፍ ያንገፈገፋቸው ኢትዮጵያውያን ይጮሃሉ፥ኦሮሞው ይጮሃል፣ አማራው ይጮሃል፣ ጉራጌው ወዘተ ይጮሃል። ሴቱ ይጮሃል፣ወንዱ ይጮሃል ሙስሊሙ ይጮሃል፣ክርስቲያኑ ይጮሃል…. ኧረ የማይጮህ የለም ሁሉም ሰው ይጮሃል።

በኖርዌይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጩኸት ግን የእነርሱ ብቻ ጩኸት ሳይሆን በአለም ዙርያና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትም ኢትዮጵያውያን ጩኸት ጭምር ነው። ከወያኔና ከደጋፊዎቻቸው ዉጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጩኸት ነዉ።ግፍ በቃን፥ዘረኝነት በቃን፥አፓርታይድ በቃን፥ፉሺዝም በቃን የሚል ጩኸት፣ ከአንደበት ብቻ ሳይሆን ከልብ የሚወጣ ጩኸት።

ኢትዮጵያዊዉ በየበረሃው ይጮሃል፣በሲና በረሃ ሆዱ እየተቀደደ ሆድ ዕቃው እየወጣበት ይጮሃል፥ ወደስደት ሲነጉድ በየመንገዱ በአውሬ እየተበላ ይጮሃል፥የሚጓዝባት ጀልባ እየሰጠመች በሞት ጥላ መካከል ሆኖ ኢትዮጵያውያዊው ወገኔ ይጮሃል፣በተለያዩ ሃገራት እስር ቤቶች የታጎሩ ሴትና ወንድ ኢትዮጵያውያዊያን ይጮሃሉ።

በየአረብ አገራት ለዘመናዊ ባርነት ተሽጠው ከአሰሪዎቻቸው ግፍ የተነሳ በፈላ ዘይት እየተቃጠሉ ይጮሃሉ፣በአለንጋ እየተገረፉ ይጮሃሉ፣ ከፎቅ ላይ እየተወረወሩ ይጮሃሉ፣ የጉልበት ዋጋቸውን ተነጥቀው ይጮሃሉ፣ በወሮበሎች እየተደፈሩ ይጮሃሉ ሌሎቹም ህጋዊ ፈቃድ የላችሁም ተብለው እየተሳደዱ ይጮሃሉ፣

በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፉት ሰለባ የሆነው የአኙዋክ ወገኖቻችን ይጮሃሉ፣ አማራ ነህና በዚህ አትፈለግም ተብሎ በግፍ ከየስፍራው እየተሰደደ ያለው ወገኔ በየእስር ቤቱ የተጋዘው ኦሮሞ ወገኖቼ ይጮሃሉ፣ እውነትን በመጻፉቸውና በመናገራቸው ብቻ እስከሞት ድረስ የተፈረደባቸው ወገኖቼ ይጮሃሉ፣ በዋልድባ እየተገረፉና እየተሰደዱ ያሉ መነኮሳት ይጮሃሉ፣አብርሃና አቶ አስገደ ከትግራይ ይጮሃሉ ኧረ ዛሬማ የሚገርም ነገር ሰማሁ አባመላ የተባለ በዳያስፓራ ቀንደኛ የወያኔ ሰው ይጮሃል ሲባል።አሁንማ ማን የማይጮህ አለ? ሁሉንም የሚያስጮኸው ግን አንድ ነገር ነው፣የወያኔ ግፍ።

የኖርዌይ ኢትዮጵያዊያን ጬኸት የወያኔን ሹማምንትና ደጋፊዎች አዋርዶ እኛን ኢትዮጵያዊያንን አኩርቷል። እያሪኮን እንዳፈረሰው የእስራኤላዊያን ጩኸት ነበር።

ለእኔ ግን ለኢትዮጵያ የጉብኝት ዘመን ደረሰ ይሆን? የሚል ጥያቄ አስነሳብኝና የእስራኤላዊያን በግብፅ 400 ዓመት የባርነት ህይወት በኋላ የነፃነት ዘመን ሲደርስ የነበረው ሁኔታ ከአሁኑ የአገራችን ሁኔታ ጋር ተመሳስሎብኛልና ምስስሉን ከመፅሃፍ ቅዱስ እያጣቀስኩ ላሳይ፥

1. እግዚአብሄር ለአብርሃም የገባው የተስፉ ቃል-ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ፤ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።
ደግሞም በባርነት በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርዳለሁ፤ ከዚያም በኋላ በብዙ ከብት ይወጣሉ።(ዘፍጥረት 15፥13)

እግዚአብሄር ለኢትዮጵያ የገባው የተስፉ ቃል-ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። (መዝሙር 68፥31)

2. የእስራኤላዊያን መከራ በግብፃውያን ገዢዎቻቸው-ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች በመከራ ገዙአቸው። በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡብም በእርሻም ሥራ ሁሉ፥ በመከራም በሚያሠሩአቸው ሥራ ሁሉ፥ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር።(ዘፀአት1፥13-14)

የኢትዮጵያዊያን መከራ በወያኔ ገዢዎቻቸው-ወያኔዎችም የኢትዮጵያን ልጆች በመከራ ገዙአቸው። በጽኑ ዘረኝነት፥ በስደት፥ ከስፍራ በማፈናቀል ሁሉ፥ በእስር ሁሉ፥ ሕይወታቸውን ያስመርሩአቸው ነበር።

3. የእስራኤላዊያን ጩኸትና በእግዚአብሔር መደመጥ -ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።(ዘፀዓት 2፥23)

የኢትዮጵያዊያን ጩኸትና በእግዚአብሔር መደመጥ-ከዚያም21 አመት በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የወያኔ ንጉሥ መለስ ሞተ፤ የኢትዮጵያ ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም።

4. እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን(የእስራኤላዊያንን) ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ።(ዘፀዓት 2፥24)

ታዲያ ወገኖቸ ይህ የኢትዮጵያዊያን ጩኸት በእግዚአብሄር ዘንድ ይሰማል የሚል እምነት አለኝ።ያን ጊዜ ደግሞ እንዲህ ይሆናል፣
እግዚአብሔርም የለቅሶአችንን ድምፅ ይሰማል፥ እግዚአብሔርም ከኢትዮጵያዊያን ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ያስባል ።
የእስራኤላዊያንን ነፃነት የሰጠ እግዚአብሄር ለኢትዮጵያዊያንም ነፃነታችንን እንድንጎናፀፍ ይረዳናል። እኔ ለኢትዮጵያ የጉብኝት ዘመን እንደደረሰ አምናለሁ፥እስከዛው ጬኸታችንን እንቀጥል።

የኖርዌይ ኢትዮጵያዊያን በእናንተ ኮርቻለሁ፣በርቱ።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

↧

↧

“መሪ አጣን”እያሉ ማላዘን ይቁም –መሪነት እና የመሪነት ወለፈንዲዎች

$
0
0

“መሪ አጣን” እያሉ ማላዘን ይቁም
መሪነት እና የመሪነት ወለፈንዲዎች

ታደሰ ብሩ

መግቢያ

Leadershipማኅበራዊ ለውጥንና እድገትን የሚመለከቱ ዓላማዎች በአንድ ወይም በጥቂት ሰዎች ጥረት የሚሳኩ አይደሉም። እነዚህ ትላልቅ ዓላማዎች እንዲሳኩ የብዙ ሰዎች የተባበረ ጥረት ያስፈልጋል። በርካታ ሰዎችን ለእንዲህ ዓይነቶቹ ግዙፍ ዓላማዎች ማነሳሳትና እና ማስተባበር ነው መሪነት (Leadership) የሚባለው።
መሪነትን በአንድ ዓረፍተ ነገር እንተረጉመው ቢባል የሚከተለውን የመሰለ ዓረፍተ ነገር እናገኛለን።

መሪነት፣ ሰዎች የተለሙትን ግብ ለማሳካት የሚተባበሩዓቸውን ሌሎች በርካታ ሰዎች ቀስቅሰው አሳምነው፤ አደራጅተው፣ መንገድ እያሳዩ ለተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚያነሳሱበት እና እንቅስቃሴውንም የሚያስተባብሩበት ሂደት ነው።

በአንዳንድ ውይይቶች “መሪነት” (Leadership) ከ መሪ (Leader) ጋር ሲደባለቅ ይስተዋላል። መሪነት ከላይ እንደተገፀው ሂደት (Process) ሲሆን መሪ ግን በዚህ ሂደት ውስጥ ያለን አንድ ወይም ጥቂት ወሳኝ ሰዎችን ይመለከታል።
ዓላማን ለማሳካት፣ ገንዘብና ቁሳቁስ የመሳሰሉ ግብዓቶችንም ማቀናጀት የሚጠይቅ ቢሆንም እንኳን ስለመሪነት ስንነጋገር ዋነኛ ትኩረታችን ሰው ላይ ነው። ሰው ከማናቸውም ሌሎች ግብዓቶች (ለምሳሌ ገንዘብ፣ ቁሳቁስ፣ መረጃ፣ ንብረት) መወዳደር በማይችል መጠን ውስብስብ ነው። ሰውን መምራት ሌሎች ግብዓቶችን ከማስተዳደር የከበደ ሥራ ነው።
ኢትዮጵያዊያን በምናደርጋቸው ውይይቶች “ዋናው ችግራችን የመሪ እጦት ነው” የሚል ዓይነት ድምዳሜ መስማት የተለመደ ነው። አንዳንድ ሰዎች አገራችንን ከችግሮች ማውጣት ያልቻልነው በመሪ እጦት እንደሆነ በእርግጠኝነት ይናገራሉ።
በእነዚህ ክርክሮች ውስጥ የተወሰነ እውነት አለ ብለን ብንቀበል እንኳን “ለመሪ እጦትስ የዳረገን ምንድነው?” የሚለውን ተከታይ ጥያቄ ለማንሳት ድፍረት ሊኖረን ይገባል። መሪነትን የተሳካ የሚያደርገው መሪው ብቻ አይደለም። ተከታዮች (The Led or Followers) ለተሳካ መሪነት የሚያበረክቱት ድርሻ ከፍተኛ ነው። መሪ ከምንም ብቅ የሚል ክስተት ሳይሆን ከተመሪዎች የሚወጣ መሆኑና መሪም ተመሪም በአካባቢያው ሁኔታዎች (Conditions) ተጽዕኖ ውስጥ መሆናቸው እና በመካከላቸው ያለው የተግባቦት (Communication) ዓይነት የመሪነትን ጥራት በከፍተኛ ሁኔታ የሚወስን መሆኑ በማኅበረሰባችን ውስጥ በቂ ግንዛቤ ያገኘ አይመስልም።
ይህንን ጉልህ የግንዛቤ ክፍተት በመጠኑም ቢሆን ለመሙላት ይህ አጭር ጽሁፍ መሪነትን በአራቱ ዋና ዋና ክፍሎች (Components) ለመመርመር ይሞክራል። እነዚህ የመሪነት ክፍሎች ተከታዮች፣ መሪ፣ ተግባቦት እና ሁኔታዎች ናቸው። እግረ መንገዱንም መሪነት ምን ያህል አስቸጋሪ ሥራ እንደሆነ ለማሳየት ከታወቁ የመሪነት ወለፈንዲዎች (paradoxes) ጥቂቱን ለመመልከት ይጥራል። በመጨረሻም “ስኬታማ አመራር /Effective Leadership/ እንድናገኝ ምን እናድርግ?” ለሚለው አስጨናቂ ጥያቄ አንዳንድ የውይይት መነሻ ሃሳቦችን ይሰነዝራል።

የጽሁፉ ዋነኛ ዓላማ የውይይት መነሻ ሐሳብ ማቅረብ በመሆኑ ብዙ ሊፃፍባቸው የሚገቡ ሃሳቦችን በአጭሩ ጠቅሶ ያልፋል።

ለመሪነት አራት ወሳኝ ነገሮች

መሪነት አራት ዋና ዋና አካላት አሉት – ተከታዮች፣ መሪ፣ ተግባቦት፣እና ሁኔታ። ከአራቱ አንዱ እንኳን ቢጎድል መሪነት የለም።

ተከታዮች
ማንኛውም ሰው መሪ ከመሆኑ በፊት ተመሪ ወይም ተከታይ የመሆኑ ነገር ልጅ ሳይሆኑ ወላጅ መሆን የማይቻለውን ያህል ተፈጥሮዓዊ ህግ ነው። ይህን ሃቅ “መሪ ይወለዳል እንጂ አይሠራም (አይሰለጥንም)” የሚሉ ሰዎች እንኳን ይቀበሉታል። “ለመሪነት የተወለደው” ሰው እንኳን በልጅነቱ የወላጆቹ፣ የአሳዳጊዎቹ፣ የመምህሮቹ ተከታይ ሆኖ ማደጉ ግድ ነው።
አንዳንድ ሰዎች ለመሪነት፣ ብዙዎች ደግሞ ለተከታይነት ተፈጥረዋል የሚለው እሳቤ በተለይ በአገራችን ባይጠፋም ቀስ በቀስ እየከሰመ ያለ አስተሳሰብ ነው።
አሁን ይበልጥ ተቀባይነት እያገኘ ያለው አስተሳሰብ ተከታዮቹ ያሉት፤ ራሱን ለቡደኑ፣ ለዓላማውና ለሁኔታዎች ተስማሚ በሆኑ ባህሪያት ያነፀ፤ አና ሁኔታዎች የተመቻቹለት ማንኛውም ሰው መሪ መሆን ይችላል የሚለው እሳቤ ነው። በዚህ እሳቤ መሠረት መሪ የሚወጣው ከተከታዮች ነው። በዘመናዊ ማኅበረሰብ ውስጥ የድርጅትም ሆነ የአገር መሪዎች መሪ ከመሆናቸው በፊት በተከታይነት ልምድ ማካበት ይኖርባቸዋል። ጥሩ መሪዎች የጥሩ ተመሪዎች ውጤት ናቸው።
በዚህ እሳቤ መሠረት ጥሩ አመራር እንዲኖር ከሚያስፈልጉ ነገሮች አንዱ – ምናልባትም ዋነኛው – የጥሩ ተከታዮች መኖር ነው። ጥሩ ተከታይ በሌለበት ጥሩ መሪ ማውጣት ከባድ ነው።
ጠንካራ ተከታዮች የአመራሩ ምሰሶ ናቸው። መሪያቸው ጠንካራ ጎኖቹን ይበልጥ እንዲያጎለብት፤ ደካማ ጎኖቹን እንዲያሻሽል ማድረግ ይችላሉ። ጠንካራ ተከታዮች መሪያቸው ብቃት ከጎደለው በጊዜ በሌላ የተሻለ ሰው እንዲተካ ማድርግ ይችላሉ። ደካማ ተከታዮች ግን ጠንካራውን መሪ ያደክማሉ።
በአንድ ድርጅት ወይም ማኅበረሰብ ውስጥ የአመራር ድክመት መኖር አለመኖሩ ለማጣራት መደረግ ከሚገባቸው ጥናቶች አንዱ ተከታዮችን መመዘን ነው። ተከታዮችም ቢሆኑ “የአመራር ችግር ገጠመን”፤ “የመሪ ያለህ ” እያሉ ከማማረራቸው በፊት “እኛ እንዴት ያለን ተከታዮች ነን” ብለው ራሳቸውን ቢጠይቁ የተሻለ መፍትሔ ለማግኘት ይረዳል።
ስኬታማ አመራር ለማስፈን የሚረዱ የተከታዮች ባህሪያት ዝርዝር ረዥም ሊሆን ቢችልም ዋና ዋናዎቹ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።

• ድርጅታቸው የቆመለትን ዓላማ የሚያስቀድሙ፤ ለዓላማቸው መሳካት ዋጋ ለመክፈል የቆረጡ፤
• የጋራ ውጤት የሚገኘው በጋራ ጥረት መሆኑን የተረዱ፤ ሳየሠሩ ውጤት ከመጠበቅ አባዜ የተላቀቁ፤
• ከአድርባይነት ስሜት የተላቀቁ እና ቅነነት ያላቸው፤
• ለመመራት ዝግጁ የሆኑ፤ መብትና ግዴታዎቻቸውን የተገነዘቡ፤ ለድርጅታዊ ህጎች ተገዥ የሆኑ፤ እና
• ለመምራት ዝግጁ የሆኑ፤ በራሳቸው የሚተማመኑ፤ ኃላፊነት ለመውሰድ የተዘጋጁ።

መሪ
መሪ መሆን በተከታዮች የሚሰጥ እንጂ “እኔ መሪያችሁ ነኝ” ተብሎ የሚጫን ነገር አይደለም። ተከታዮች ናቸው “እከሌ መሪያችነን ነው፤ እከሊት መሪያችን ናት” በማለት እውቅና የሚሰጡት ወይም የሚሰጧት። መሪነት በምርጫ ውጤት የሚገኝ ነገርም አይደለም። በምርጫ ሊቀመንበር ወይም ፕሬዚዳንት መሆን ይቻላል። ሊቀመንበር ወይም ፕሬዚዳንት መሆን ግን መሪ መሆን ማለት አይደለም። መሪ መሆን የሚቻለው የተከታዮችን ልብ መማረክ ሲቻል ነው።
ጥሩ መሪ ለመሆን የሚያስፈልጉ ባህሪያት እጅግ በርካታ ሲሆኑ ርዕይ (ማለትም ግልጽ የሆነ የሩቅ ጊዜ እይታ) /Vision/፣ ጥልቅ የሆነ ስሜት /Passion/፣ የማሳመን ችሎታ፣ የማደራጀት ችሎታ፣ እና የመወሰን ችሎታ ዋነኞቹ ናቸው።
ርዕይ
መሪ ከርዕዩ ሌላ የሚሰጠው ነገር የለውም። መሪ ሰዎችን የሚያግባባው፤ ተከታዮቹን የሚያነቃቃው፣ የሚያደራጀው፣ የሚታግለው በርዕዩ ነው። “አብረን ከቆምን፤ ጠንክረን ከታገልን እዚያ መልካም ሥፍራ መድረስ እንችላለን” እያለ ምኞቱ ምኞታቸው፤ ጉጉቱ ጉጉታቸው፤ ሕልሙ ሕልማቸው እንዲሆን ማድረግ ነው የመሪ ትልቁ ሥራ። ለዚህም ነው ታላቅ መሪ ባለርዕይ /Visionary/ መሆን ይኖርበታል የሚባለው። ርዕይ የሌለው መሪ ብቁ መሪ አይደለም።
ግልጽ ላልሆነ ግብ እንኳንስ ሌሎች ሰዎችን የገዛ ራስንም ማነቃቃት ይከብዳል። ግልጽ የሆነ ርዕይ፣ ዓላማ እና ግብ መኖር የጥሩ መሪ የመጀመሪያው እና ትልቁ መለያው ነው። ጥሩ መሪ መድረሻውን የሚያውቅና ወደ መድረሻው እየተጓዘ የቀረውን ጉዞ በተመለከተ አማራጭ መንገዶችን እያሰላሰለ የሚኖር ሰው ነው።

ጥልቅ ስሜት
ጥሩ መሪ ለዓላማው፣ ለድርጅቱ፣ ለተከታዮቹ፣ እና ለድርጅቱ ደንቦችና መመሪያች ከፍተኛ ፍቅር እና አክብሮት ያለው ሰው ሊሆን ይገባል።
በሥራ አስኪያጅ (Manager) እና በመሪ (Leader) መካከል ያለው ትልቁ ልዩነት የዚህ ስሜት ጥልቀት ነው። ማኔጀሮችም ቢሆኑ ድርጅታቸውን፣ ሠራተኞቻቸውን ይወዳሉ ሕይወታቸውን ግን አይሰውላቸውም። ጥሩ መሪ ግን ለዓላማው፣ ለድርጅቱና ለተከታዮቹ ሕይወቱን ይሰጣል፤ ከእነዚህ የሚበልጥበት ነገር የለውም። ጥሩ መሪ የድርጅቱን ደንቦችና መመሪያዎች ከሚያዙት በላይ ይከውናል፤ ደንብ ከሚከለክላቸው ነገሮችም ደንቡ ከሚያዘው በላይ ራሱን ይገድባል። መሪ የመሪነት ሥራውን የሚከውነው ጥልቅ በሆነ የኃላፊነት መንፈስና ፍቅር ነው።

የማሳመን ችሎታ
መሪ ከፍተኛ የሆነ የማሳመን ችሎታ ሊኖረው ይገባል።
ሰዎችን ለማሳመን ከሁሉ አስቀድሞ ጥሩ አድማጭ መሆን ይገባል። ጥሩ መሪዎች ከፍተኛ ድርሻ ያለው የሥራ ጊዜዓቸውን ለማዳመጥ ይመድባሉ። ተከታዮች አስተያየታቸውና አቤቱታቸውን የሚያዳምጥ መሪ ይፈልጋሉ። ጥያቄዓቸው መፍትሄ ባይኖረው እንኳን በመደመጣቸው ሊረ ኩ ይችላሉ። ለዓላማቸው መሳካት፤ ለድርጅታቸው ጥንካሬ የሚያቀርቧቸው አስተያየቶች እንዲሰሙላቸው ይፈልጋሉ። የማያዳምጥ መሪ ተከታዮችን ያጣል፤ ቢናገርም የሚሰማው አይኖርም።
ጥሩ መሪ ጥሩ መረጃ አጠናቃሪ መሆን ይኖርበታል። መረጃዎችን ከተለያዩ ምንጮች መሰብሰብ እና መተንተን የመሪው የግል ኃላፊነት ነው። አጠገቡ ያሉ ሰዎች የነገሩት ሁሉ እውነት እንደሆነ ወስዶ ውሳኔ የሚሰጥ መሪ ጥሩ መሪ አይደለም።
ጥሩ መሪ ጥሩ ተናጋሪ መሆን ይጠበቅበታል። መሪ አንደበተ ርቱዕ ለመሆን መጣር አለበት። የመሪነት ሥራዎች በአብዛኛው የሚከናወኑት በሰው ከሰው ግኑኝነቶች በመሆኑ ተናግሮ ማሳመን የማይችል መሪ ጥሩ መሪ ሊባል አይችልም፡
ስለሆነም መሪ ከፍተኛ የሆነ የማሳመን ችሎታ ሊኖረው ይገባል ሲባል 1ኛ ጥሩ አድማጭ፣ 2ኛ ጥሩ መረጃ አጠናቃሪ፣ እና 3ኛ ጥሩ ተናጋሪ መሆን አለበት ማለት ነው።

የማደራጀት ችሎታ
መሪ ተከታዮችን ማወቅ እና እንደ ዝንባሌያቸውና ችሎታቸው መመደብ ይኖርበታል። መሪ ሥ.ራና ሰውን የማቀናጀት ጥበብ ሊኖረው ይገባል።
አንድ መሪ የአንድ ድርጅት የጥንካሬ መሠረቶች (1ኛ) ድርጅታዊ መዋቅር፣ (2ኛ) ድርጅታዊ ባህል እና (3ኛ) ግብዓቶች (በተለይም ሰው) መሆናቸው ያውቃል፤ እነዚህን የጥንካሬ መሠረቶችን ለማጥበቅ ይጥራል።
ብልህ መሪ ስትራቴጂያዊ ግብን ለመምታት ተስማሚ ድርጅታዊ መዋቅር መኖሩ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ያውቃል። በዚህም መሠረት ድርጅቱ ተልዕኮውን ለማሳካት በሚያመቸው መንገድ መደራጀቱ ያረጋግጣል። ድርጅታዊ መዋቅር ከእዝ ሰንሰለት ባሻገር በደንቦች፣ በመመሪያዎች፣ በኃላፊነት ዝርዝሮች መታገዝ እንዳለበት ያውቃል።
ጠንካራ መሪ፣ ዲሲፕሊን የድርጅታዊ ባህል መሠረት መሆኑ ያውቃል። ጠንካራ መሪ፣ በጠንካራ ዲሲፕሊን ያልተገነባ ድርጅት ያለመውን ማሳካት እንደሚቸግረው ይገነዘባል። ስለሆነም ጠንካራ ዲሲፕሊን የድርጅቱ ባህል እንዲኖር ይጥራል።
ጥሩ መሪ የድርጅት ትልቁ ሃብት አባላቱ መሆናቸው ስለሚረዳ የአባላት ብቃት ለማጎልበት ይጥራል፤ የአባላትን ተሳትፎ ለማጎልበት መድረኮችን ያመቻቻል።
ልዩነቶች ጠፍተው ሁሉም አንድ አይነት እንዳይሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ ልዩነቶች ሰፍተው ድርጅቱ እንዳይበጣበጥ በቅራኔዎች አፈታት ጥበብ የተካነ መሆን ይኖርበታል።

የመወሰን ችሎታ
የተዋጣለት መሪ ተገቢው ውሳኔ በተገቢው ወቅት መስጠት የሚችል መሆን ይኖርበታል። የዘገየ ውሳኔ ጥሩ እንዳልሆነ ሁሉ የተቻኮለ ውሳኔን ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጣ ሊሆን ይችላል። ውሳኔዎች በመረጃ መደገፍ ቢኖርባቸውም መረጃዎች ተሟልተው በማይገኙበት ወቅት ስሜትን ማዳመጥ (intuition) ተገቢ ሊሆን ይችላል።
የተዋጣለት መሪ ለውሳኔ አሰጣጥ የሚረዱ ቴክኒኮችን ማወቅ ይጠበቅበታል።

ስኬታማ ተግባቦት
ስኬታማ ተግባቦት /Effective Communication/ መሪዎች በተከታዮቻቸው፤ ተከታዮች በመሪያቸው እና ሁለቱም ወገኖች በድርጅታቸው ላይ እምነት እንዲጥሉ የሚረዳ ቁልፍ ነገር ነው። ስኬታማ አመራር መስጠት የሚቻለው ስኬታማ ተግባቦት ሲኖር ነው። የተግባቦቱ ዓይነትና አፈፃፀም በመሪና በተከታዮቹ መካከል ያለው ግኑኝነት እንዲጠናከር አሊያም እንዲበላሽ ያደርጋል።
ስኬታማ ተግባቦትን በተመለከተ ሁለት ነገሮች አጽንዖት ሊሰጣቸው ይገባል – የሥራ ዘገባዎች፣ እና የሰው ለሰው ግኑኝነት።

የሥራ ዘገባዎች
ስኬታማ አመራር እንዲኖር መረጃዎች ለመሪው መድረስ አለባቸው። በድርጅት ውስጥ ወቅታዊ /periodic/ እና ወቅት የማይጠብቁ ሪፓርቶች መኖር አለባቸው። የቃልም ሆነ የጽሁፍ ዘገባዎች (ሪፓርቶች) በሃቅ ላይ የተመሠረቱ መሆን አለባቸው።
እቅድና በጀት እጅግ አስፈላጊ የመረጃ ዓይነቶች ናቸው፤ ለስኬታማ አመራርም ወሳኝ ናቸው።
ጥሩ አመራር የታወቀ እዝ ሊኖረው ይገባል። በድርጅት ውስጥ የታወቀ የሥራ ድልድል ሊኖር ይገባል። በተለይ እያንዳንዱ ሰው ለማን ሪፓርት እንደሚያደርግ፤ በምን ያህል ጊዜ እና በምን ሁኔታ ሪፓርት ማድረግ እንዳለበት ሊታወቅ ይገባል።

ሰዋዊ ግኑኝቶች
ሰዋዊ ግኑኝነቶች ለመሪዎች በጣም አስፈላጊ ናቸው። ትህትና የተሞላባቸው አነጋገሮችን መልመድ ለመሪዎች በጣም ይጠቅማል።
ለምሳሌ
• መሪ ስህተት በሠራ ጊዜ “ስህተት ሠርቻለሁ፤ አጥፍቻልሁ። የምቀጣውን እቀበላለሁ” ቢል ያምርበታል።
• ተከታዮች ጥሩ በሠሩ ጊዜም “በጣም ጥሩ ሠርተሃል/ሠርተሻል” ቢል ትልቅ ማበረታቻ ነው።
• ከውሳኔ በፊትም “በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አስተያየት አለህ/አለሽ?” ብሎ መጠየቅ ከብዙ ቅስቀሳ በላይ የአባላትን ተሳትፎ የሚያበረታታ ልማድ ነው።
• “አመሰግናለሁ” ሊለመድ እና ሊዘውተር የሚገባ ቃል ነው።

ሁኔታ

በአንድ ሁኔታ ውጤታማ የነበረ የአመራር ስልት በሌላ ሁኔታም ይሠራል ማለት አይደለም። ሁኔታዎች ሲለወጡ የአመራር ስልትም መለወጥ ይኖርበታል። ሁኔታ በተመለከተ በሚከተሉት ላይ ትኩረት መሥጠት ያስፈልጋል – ጉዳዩ /Issue/ ፣ የአጣዳፊነት መጠን፣ የተከታዮች ዓይነት፣ እና ባህል።

ጉዳዩ /Issue/

የተለያዩ ጉዳዮች የተለያዩ የአመራር ዓይነቶች ይፈልጋሉ። ውትድርናና መምህርነት የተለያዩ ሥራዎች እንደመሆናቸው የሚፈልጉትም የአመራር ዓይነት ይለያያል። ወታደራዊ አመራር የተማከለ፣ ጥብቅ እና ትዕዛዝ ላይ ያተኮረ እንዲሆን ሙያው ግድ ይላል። በአንፃሩ የአካዳሚ አመራር ብዙ ነገሮችን ለመምህራኑ የግል ውሳኔ ሊተው ይችላል። እንደዚሁም፣ የፓለቲካ ድርጅት አመራር ከቢዝነስ ኮርፓሬሽን አመራር ይለያል። የሃይማኖት ተቋማት አመራር እና መንግሥታዊ አመራር የተለያዩ ናቸው።
ከላይ በምሳሌነት የተዘረዘሩት አና የሌሎች የሥራ መስኮች አመራሮች በርካታ የጋራ ባህሪያት ያላቸው መሆኑ ቢታመንም ልዩነቶቻቸውን አሳንሶ ማየት ግን ጉዳት አለው።
በተለያዩ የአመራር ጉዳዮች መሪዎች ተከታዮቻቸውን ለማነቃቃት የሚጠቀሙባቸው ስልቶችም በጣም የተለያዩ ናቸው። ወታደራዊ ሹመት ለወታደራዊ አመራር፤ የአካዳሚ እውቅና ለአካዳሚ ተቋማት፤ ቅድስና ለሃይማኖት ተቋማት፤ ትርፍና ቦነስ ለቢዝነስ ተቋማት መሪዎችና ተከታዮች ጥሩ ማነቃቂያዎች ሊሆኑ ይችላሉ።
ለነፃነት የቆሙ ድርጅቶ መሪዎችና ተከታዮች ያላቸው ማነቃቂያ የድርጅታቸው ርዕይ ነው፤ እሱ ደግሞ ሁሌ ፍንትው ብሎ ላይታይ ይችላል። ለማጠቃለል፣ ጥሩ አመራር እንዲኖር ለጉዳዩ ተስማሚ የሆነ የአመራር ስልት ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል።

የአጣዳፊነት መጠን

“ጊዜ” በአመራር ውስጥ እጅግ ወሳኝ የሆነ ነገር ነው። ጊዜ ካለ በእያንዳንዱ ነገር በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔዎች በሙሉ ድጋፍ እንዲያልፉ ማድረግ ይቻላል። ችግሩ ግን ለዚህ የሚሆን ጊዜ ሁሌ አይገኝም። ከዚህ አንፃር በተዝናና ሁኔታ እና በአጣዳፊ ሁኔታ ውስጥ ላይ የሚኖሩ አመራሮች የተለያዩ ናቸው። በተዝናና ሁኔታ ላይ አመራር አድማጭ፣ አሳታፊ፣ ምክር ጠያቂ እና ለስላሳ መሆን ይችላል። አጣዳፊ በሆነ ሁኔታ ግን እነዚህ ሁሉ የሉም። በጣም አጣዳፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መሪ ብቻውንም ቢሆን ውሳኔ መስጠት አለበት። ከጠላት ጋር በጦርነት ሁኔታ ውስጥ ያለን አመራር አሳታፊ አልሆንክም ብሎ መኮነን አመራሩን ማዳከም ነው።

የተከታዮች ዓይነት

አመራር በተከታዮች ዓይነትም ይወሰናል። ይህ ርዕሰ ጉዳይ እላይ የተነሳ በመሆኑ የተለያዩ ተከታዮች የተለያየ አመራር የሚያስፈልጋቸው መሆኑን አስታውሶ ማለፍ ይበቃል።

ማኅበራዊ ባህል

አመራር ከባህል ጋር በበርካታ ክሮች የተሳሰረ ነው። ለባህሉ ተስማሚ ያልሆነ አመራርና መሪ ተቀባይነት የለውም። ለምሳሌ የገጠር እና የከተማ አስተዳደሮች አንድ ዓይነት አይደሉም። የተለያዩ ሃይማኖቶች ባሉበት አገር ውስጥ የፓለቲካ አመራር ሃይማኖቶችንም ማቻቻል ይጠበቅበታል።

የአመራር ወለፈንዲዎች

ወለፈንዲ(paradox) ተቃርኖ ነው። አንድ ነገር እና ተቃራኒው እኩል ተቀባይንት ካላቸው ወለፈንዲ ነው። አንድ ሰው በአንድ ጊዜ አንድን ነገር አድርግም አታድርግም ከተባለ ወለፈንዲ ነው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለ ትዕዛዝ ተቀባይ ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን ይቸግረዋል፤ ማድረግ መጥፎ ነው፤ አለማድረግም መጥፎ ነው።
መሪነት በበርካታ ወለፈንዲዎች የታጀበ አስቸጋሪ ሂደት ነው። ስኬታማ መሪ ለመሆን በወለፈንዲዎች መካከል ባለ ቀጭን ክር ላይ ተዝናንቶ መቆም ያስፈልጋል። በኢትዮጵያ ሁኔታ ደግሞ በወለፈንዲዎች ከተወጠረችው ክር ሥር በርካታ ሹል ምስማሮች ተሰክተዋል። መሪዎቻችን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ያሉት።
ከዚህ በታች ጥቂት የታወቁ የመሪነት ወለፈንዲዎችን እናነሳለን። በእያንዳንዱ ላይ በርካታ ገጾች ሊፃፍ የሚችል ቢሆንም እያንዳንዱን በጥቂት ዓረፍተ ነገሮች በመግለጽ እንወሰናለን።

ለውጥ እና ሥርዓት

ጥሩ መሪ የለውጥ ሃዋሪያ ነው። ለለውጥ ያልተነሳሳ ሰው መሪ መሆን አይችልም። ለውጥ ማለት ደግሞ ነባር ህጎችንና ልማዶችን መቃወም እና በአዳዲስ ህጎችና ልማዶች እንዲተኩ መጣር ማለት ነው። ለውጥ ማፍረስን ይጠይቃል።
መሪ ህግን አክባሪ ነው፤ ባህል አክባሪ ነው። መሪ ያላከበረው ህግ አይከበረም። ልማዶችንም ማክበር ከጥሩ መሪ የሚጠበቅ ተግባር ነው። መሪ የሥርዓት ምንጭ ነው።
ለውጥንና ሥርዓትን በአንድ ጊዜ መጠበቅ በጣም አስቸጋሪ ወለፈንዲ ነው። በሁለቱ መካከል ክር መኖሩ እንኳን በአርጠኝነት መናገር አስቸጋሪ ነው። መሪዎች አንዴ ህግ ሲያፈርሱ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ደንቦችን ሲደነቡ የምናየው በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ በመኖራቸው ነው።

መምሰል እና መለየት

ጥሩ መሪ ተከታዮችን መምሰል አለበት። ተከታዮች ሲራቡ መራብ፤ ሲታረዙ መታረዝ አለበት። ተከታዮች የሚሠሩትን ሥራ እሱም መሥራት አለበት። መሪ በሁሉም ረገድ ለተከታዮቹ አርዓያ መሆን አለበት።
መሪ ከተከታዮቹ መለየት አለበት። አለበለዚያማ ምኑን መሪ ሆነው? ተከታዮቹም ቢሆኑ መሪያቸው ከእነሱ በምንም የሚለይ አለመሆኑን ሲያዩ በመሪነት መቀበል ይቸግራቸዋል። ሌላ ወለፈንዲ!
ውትድር ውስጥ መኮንኖችና ተራ ወታደሮች የሚመሳሰሉበት በርካታ ነገሮች ቢኖሩም የሚለያዩባቸው ነገሮች እንዲኖሩ የሚደረግበት (ለምሳሌ ምግቤት፣ መኝታ) አንዱ ምክንያት ከመጠን በላይ መመሳሰል አመራሩን ስለሚጎዳው ነው። ጥሩ አባት ልጁን ማቅረብ አለበት ሆኖም የልጁ ምርጥ ጓደኛ ለመሆን ቢሞክር ልጁንም ራሱን አይጠቅምም።

የሥራ ሰው እና የሐሳብ ሰው

ጥሩ መሪ ተግባር ላይ እንዲያተኩርና የሥራ ሰው (The Doer) እንዲሆን ይፈለጋል። “ወሬ በዛ! የተግባር ሰው አጣን” የሚሉ እሮሮዎች በብዛት ይሰማሉ። አዎ እውነት ነው መሪ የተግባር ሰው እንዲሆን ይፈለጋል።
በሌላ በኩል ደግሞ መሪ የሥራ ሰው ከሆነ ከተከታዮች በምን ተለየ? ጥሩ መሪ የሐሳብ ሰው (The Thinker) መሆን ይኖርበታል። የመሪ ዋነኛ ሥራ ርዕይ መንደፍ ነው፤ ማቀድ ነው። ቀጥሎም ርዕዩ ተግባራዊ የሚሆንበት አቅጣጫን ማሳየት፤ ማስተማር፤ ማሳወቅ ለሚሠሩ ሥራዎች የንድፈ ሐሳብ መሠረት መጣል ነው።
በተግባርና በንድፈሃሳብ መካከል ድልድይ ማበጀት ይቻላል። ከመሪዎች የሚፈለገው ግን ድልድይ ሳይሆን ሁለቱም በአንድነት ነው። ይቻላል ግን ከባድ ነው።

የሥልጣን ጥም እና የማገልገል ጥም

ጥሩ መሪ ኃላፊነትን ለመውሰድ የተዘጋጀ መሆን አለበት። ኃላፊነት የማይወስድ ሰው መሪ መሆን በጭራሽ አይችልም። መሪ መሆን ማለት በከፍተኛ የሥልጣን እርከን ላይ መገኘት ማለት ነው። ስለሆነም ጥሩ መሪ ሥልጣንን የመያዝ ፍላጎት ሊኖረው ይገባል። ሥልጣን መያዝ ሌላውን ሰው የማዘዝ መብት ይሰጣል።
ጥሩ መሪ የሥልጣን ሳይሆን የማገልገል ጥም ሊኖረው ይገባል። ኃላፊነቶችንም መውሰድ ሳይሆን መስጠት ነው ያለበት። ኃላፊነቶችን ጠቅልሎ የሚይዝ መሪ መጥፎ መሪ ነው። ጥሩ መሪ ኃላፊነቶችን በማከፋፈል የጋራ አመራር ያሰፍናል። ጥሩ መሪ ታዛዥ ነው። ማዘዝና መታዘዝ (የሥልጣን ጥምና የማገልገል ጥም) ተቃራኒዎች ናቸው።

ራስን በመሪነት ማቆየት እና ራስን ከመሪነት ማውጣት

ጥሩ መሪ ራሱን በነገሮች አናት ላይ ለማስቀመጥ ይጥራል። ሁሌም ራሱን ያስተምራል። መሪ በራሱ ላይ የሚያደርጋቸው “ኢንቬስትመቶች” ራሱን በመሪነት የሚያቆዩት ነገሮች ናቸው።
ጥሩ መሪ ራሱን ከመሪነት ለማውረድ መጣር ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ ከሱ የተሻሉ መሪዎች እንዲመጡ መንገድ ማመቻቸትና ማስተማር ይኖርበታል።
የገዛ ራሱን በነገሮች አናት ላይ አስቀምጦ እያለ እንዴት ከራሱ የበለጠ ሰው ማውጣት ይችላል? ወለፈንዲ!

በአንድ ጉዳይ ላይ ማትኮር እና ሁሉን ዓቀፍ እይታ

ጥሩ አመራር እና ጥሩ መሪ በአንድ አቢይ ጉዳይ ላይ ማትኮር ይኖርበታል። ያም ጉዳይ የድርጅቱ ግብና ወደዚያ ያደርሰኛል በሚለው ስትራቴጂው ላይ መሆን ይኖርበታል። በየጊዜው በሚፈጠሩ “የጎን ጉዳዮች” ትኩረቱ የሚዛባ ሰው ጥሩ መሪ መሆን አይችልም።
መሪ ሁሉን ዓቀፍ እይታ እንዲኖረው ያሻል። ጥሩ መሪ ትኩረቱ መንገዱ ላይ ቢሆንም እንደጋሪ ፈረስ ግራና ቀኙን ላለማየት ዓይኖቹን የሸፈነ መሆን የለበትም። በየጊዜው የሚፈጠሩ እድሎችን በቸልታ የሚያሳልፍ ሰው ጥሩ መሪ መሆን አይችልም።
እይታን ዓለም–ዓቀፍ፤ ተግባሮችን ግን አካባቢ–ተኮር ማድረግ እንደ መፍትሔ ይቀርባል። ይህንን በተግባር መተርጎም ግን ቀላል ነገር አይደለም።

እሳቤ እና እርግጠኝነት

መሪው ውሳኔ እንዲሰጥ የሚጠበቅበት በአብዛኛው ተጨባጭ መረጃዎች በሌሉበት ሁኔታ ነው። የመሪ ብቃቱ በእሳቤዎች (assumptions) ላይ ተመሥርቶ ትክክለኛ ውሳኔ በመስጠት ችሎታው ነው። መሪነት ሥነ-ጥበብ (art) ነው የሚባለው ለዚህ ነው።
የመሪ ስህተት ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ውሳኔዎቹ ትክክለኛ ስለመሆናቸው ማስተማመኛ ሊኖር ይገባል። ተከታዮች ለውጤት ይቸኩላሉ፤ የሚያደርጉት ትንሹም አስተዋፅዖ ወደ ትልቁ ግብ የሚያደርስ የመሆኑ ማስተማመኛ ይፈልጋሉ።
በእሳቤ ላይ ተመሥርቶ ለሚሰጥ ውሳኔ ትክክለኝነት ማስተማመኛ መስጠት እንዴት መስጠት ይቻላል? ወለፈንዲ !

በመሪነት ላይ ያሉ ወለፈንዲዎች እነዚህ ብቻ አይደሉም። ለአሁኑ ግን ይበቁናል። መሪነት ለዚያውም ስኬታማ መሪ መሆን በጣም ከባድ ነገር ነው። ለዚህም ነው በዓለም ዓቀፍ ደረጃም ቢሆን ብዙ ስኬታማ መሪዎች የሌሉት።

ስኬታማ አመራር እንዲኖረን ምን እናድርግ?

ለመሪ እጦት እኛም (ተመሪዎቹ) አስተዋጽዖ ያደረግን መሆኑ ማወቅና በራሳችን ላይ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ የመጀመሪያው አቢይ መፍትሄ ነው። እኛ ከልባችን እውቅና ካልሰጠናቸው ሰዎች የድርጅት ሊቀመንበር፣ ፕሬዚዳንት ወይም ፀሐፊ ስለሆኑ ብቻ መሪ አይሆኑም። ኃላፊነትን እየሰጠን ድጋፋችንን የምንነሳቸው ከሆነ ችግሩ ያለው እኛ ዘንድ ነው። ሁሉንም ነገር እነሱ እንዲያደርጉልን የምንፈልግ ከሆነ ጥያቄዓችን መሪ ሳይሆን ፈጣሪ ነው። መሪዎቻችን የቱንም ያህል ቢበረቱ ጥሩ መሪ እንጂ ፈጣሪ መሆን አይችሉም።
ሁለተኛ “መሪዎች ይወለዳሉ” በሚል ያረጀ ብሂል (ሳናውቀው ሊሆን ይችላል) ተታለን መሲህ የምንጠብቅ ከሆነ የመከራ ጊዜዓችንን እናራዝማለን። መሪነት ይለመዳል፣ እኛም እንልመደው። ለመሪነት ይሰለጠናል፤ እናም እንሰልጥን። መሪነትን ለመማር ፈቃደኞች እንሁን። “ባህር የሚያሻግር ሙሴ” ስለናፈቅን አይመጣም፤ “ሚኒሊክና ቴዊደሮስ ተመልሳችሁ ኑ” ብንላቸው ሊመጡልን አይችሉም፤ ቢችሉም ኖሮ ለዛሬው ሁኔታ ተስማሚ መሪዎች ሊሆኑ ይችሉ እንደነበር ማረጋገጫ መስጠት የሚችል የለም።
ለዛሬ ችግሮቻችን መፍትሔ መስጠት የሚችሉ መሪዎች መውጣት ያለባቸው ዛሬ እየኖረ ካለው ትውልድ ነው። ይህ ደግሞ ትኩረታችንን ወጣቱ ላይ እንደናደርግ ግድ ይለናል። ወጣቱ ትውልድ ብዙ ፈተናዎች ያሉበት ቢሆንም እንኳን ተስፋችን እሱ ላይ ነው። ተስፋችን እውን እንዲሆን ወጣቱን ለመርዳት ጥረት እናድርግ፤ በወጣቶች ለመመራትም ዝግጁ እንሁን።
“መሪ አጣን” እያሉ ማላዘን ይቁም። ይልቁንስ (1) አሁን የተቻላቸውን ለማድርግ እየጣሩ ላሉት መሪዎች የተመቸን ተመሪዎች እንሁን፤ ለጥሪዎቻቸው ምላሽ እንስጥ፤ እንደግፋቸው (2) ራሳችንን ለመሪነት እናዘጋጅ። መሪዎች የሚወጡት ከኛው ነው። ፍልስፍና፣ ሞዴል፣ ፎርምላ ከሌሎች አገሮች መዋስ እንችላለን። መሪዎችን መዋስ ግን አንችልም፤ ቢቻልም ኖሮ (outsource ብናደርግ) አይጠቅመንም (3) ወጣቱ ላይ እምነት ይኑረን።
የትም አገር ቢሆን ስኬታማ አመራር ማግኘት ከባድ ነው። የአገራችን የአመራር ችግር ከመጠን በላይ በማግነን መዓት የወረደብን አደርጎ ማቅረብ ጉዳት አለው። ቀላል መፍትሔ የለም ሆኖም ግን በሚገባ ካሰብንበትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ካደረግን የማንወጣው ችግር አይኖርም።
…
አስተያየት መስጠት በፈለጉ: tkersmo@gmail.com

↧

አባይ ለሕዝብ ወይስ አባይ ለኢሕአዴግ ? –ግርማ ካሳ

$
0
0

- ግርማ ካሳ
Muziky68@yahoo.com
ሚያዚያ 21  2005 ዓ.ም

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

ዶር ቴዎድሮስ አዳኖምን ጨምሮ በርካታ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣  በተለያዩ የአሜሪካና የአዉሮፓ ከተሞች በመዘዋወር፣ ለአባይ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሞክረዋል። ነገር ግን በበርካታ ከተሞች፣ ከዚህ በፊት ከነበረዉ በተለየ ሁኔታ፣ ጠንካራ ተቃዉሞ የደረሰባቸዉ ሲሆን፣ አንዳንድ ከተሞችም፣  ተቃዋሚዎች ስብሰባዉን ሙሉ ለሙሉ እስከመቆጣጠር የደረሱበት ሁኔታም እንደነበረም ታዝበናል።

በሚነሱ ተቃዉሞዎች ዙሪያ፣ በዋሺንግተን ዲስ አስተያየት የሰጡት ዶር ቴዎድሮስ  «በሃሳብ አለመስማማት በጣም ጤነኛ ነገር ነዉ። ነገር ግን እንደ ሰዉ ማመን የሚከብደኝ፣ ድህነትን ከአገራችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያደርገዉን የልማት እንቅስቃሴ በመቃወም፣ ሳይሰለቻቸው የሚጮሁትን መታዘብ ነዉ» ሲሉ በሚነሱ ተቃዉሞዎች ላይ ያላቸውን ንዴት አዘል ዘለፋ አሰምተዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ አምባሳደር ግርማ ብሩ፣  በሂዉስተን ቴክሳስ፣ ባደረጉት ንግግር፣ የአባይን ግድብ ለመገንባት ለምን እንዳስፈለገ የሚያስረዱ ነጥቦችን  ካስቀመጡ በኋላ ፣  ወደ ንግግራቸዉ መጨረሻ ላይ ድህነትን ከአገራችን ለመቅረፍ የሚረዳ ፕሮጀክትን መቃወም  ከ«ጸረ-ኢትዮጵያዊነት»  ተለይቶ እንደማይታይ በማሳሰብ ነበር፣ በተቃዋሚዎች ላይ ጠንካራ ትችት ያቀረቡት።

ለአባይ ግንባታ ያለኝን የጸና ድጋፍ፣  በተለያዩ ጊዜያት በጽሁፍ ይፋ አድርጊያለሁ። ወደፊትም ይሄንን አቋሜን ከማንጸባረቅ ወደ ኋላ አልልም። አባይን መገንባት ይቻል ዘንድ፣ ኢትዮጵያዉያንን በሙሉ ማሰባሰብ እንደሚያስፈልግ፣ ኢትዮጵያውያንን ለማሰባሰብ ደግሞ፣ በፖለቲካዉና በሰብአዊ መብት አከባበር ዙሪያ ለዉጥ መደረግ እንዳለበትም አሳስቤ ነበር። ከዚህ በፊት ኢሕአዴግ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ ለብሄራዊ እርቅ ተዘጋጅቶ ቢሆን ኖሮ፣ ዳያስፖራዉ እነ ዶር ቴዎድሮስ አዳኖምን  በተቃዉሞ ሳይሆን በአክብሮት ይቀበላቸው ነበር።

አምባሳደር ግርማ ብሩም ሆኑ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴዎድሮስ አዳኖም፣ ያጡታል ብዬ አላሳብም፤ ካጡት ግን እንዲገነዘቡ የምፈልገዉ ነጥብ አለኝ። እርሱም አባይ እንዳይገነባ የሚፈልግ ማንም ኢትዮጵያዊ እንደሌለ ነዉ። ጥያቄዉ አባይን የመገንባት አስፈላጊነት ላይ አይደለም። ኢትዮጵያዉያን «አባይ አይገንባ» የሚል መፈክር አላሰሙም።  ጥያቄዉ የፍትህ ፣ የእኩልነት፣ የዲሞክራሲና የመብት ጥያቄ ነዉ። «አባይ ይገደብ። ግን ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ» ነዉ እየተባለ ያለዉ። የሪፖርተር አባባልን ልዋስና «አባይን የመገደብ ሥራ ዴሞክራሲን ባለመገደብ ይታጀብ » የሚል ነዉ አንዱና ዋነኛዉ የኢትዮጵያዉያን  ጥያቄ።

አባይ የሚገነባዉ እኮ ሕዝብን ለመጥቀም ነዉ። አሁን እየሆነ ያለዉ ግን ኢሕአዴግ አባይን፣  ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት የሚጠቀምበት መሳሪያ እያደረገዉ፣ ለፖለቲካ ፍጆታና ጥቅም እየተጠቀመበት እንደሆነ ነዉ። አባይ ለሕዝብ መሆኑ ቀርቶ፣ ሕዝብ ለአባይ፣ አባይ ደግሞ ለኢሕአዴግ እየሆነ ነዉ። ከፈረሱ በፊት ሰረገላው እየቀደመ ነዉ። አንድ በሉ።

«አቶ መለስ ሞተዋል። የርሳቸዉን ነገር ለታሪክ እንተወዉ። ከልብ የሚወዷቸዉ ደጋፊዎቻቸውን ላለማስከፋት፣ ለእርቀ ሰላም በሩን እናመቻች» በሚል ሃሳብ ነዉ እንጂ ዝም የምንለዉ፣ ወደ ኋላ ተመልሰን ነገሮችን መምዘዝ ከፈለግን እኮ፣ ብዙ ስለ አቶ መለስ ግፍና ወንጀል መዘርዘር እንችላለን። ኢሕአዴጎች ግን ዝምታችንን እንደ ሞኝነት ቆጥረዉት ነዉ መሰለኝ፣ መለስ ዜናዊን «አምልኩት» ለማለት እየከጀላቸው ነዉ። የአባይንም ግድብ እንደመሳሪያ በመጠቀም የአቶ መለስን «ጀግንነት»፣ «ሕያውነት» በአይምሯችን ዉስጥ ሊቀርጹ ይፈልጋሉ። አባይን ብሎ የሚመጣዉ ሰው ሁሉ የአቶ መለስን ምስል ተሳልሞ እንዲመለስ ነዉ መሰለኝ፣ በዊዉስተን ቴክሳስ በተደረገው የአባይ ግድብ ስብሰባ፣  አምባሳደር ግርማ ብሩ ንግግር ያደርጉበት ከነበረዉ መድረክ በስተቀኝ፣ ትልቅ የአቶ መለስ ዜናዊ  ምስል እንደ ታቦት ተቀምጦ ያየነዉ።

እንግዲህ ሁለተኛው የሕዝብ ጥያቄ «አባይን የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ለምን ታደርጉታላችሁ ?» የሚል ነዉ። «አቦ ሰለቸን። ሱካርም ሲበዛ ይመራል!  አባይ አባይ ፣ መለስ መለስ እያላችሁ አታደንቁርን» እያለ ነዉ ሕዝቡ። ሁለት በሉ።

ኢሕአዴግ ለአቶ መለስ ዜናዊ ቀብር ስነ-ስርዓት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች አቃጥሏል። ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ አባላት አሉት። አብዛኞቹ አንድ ለአምስት በሚለዉ አሰራር፣ ሌላ ሥራ የሌላቸው፣  ሕዝብን የሚሰልሉና የሚያስጨንቁ ካድሬዎች ናቸው። በርካታ የኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዶላር እየከፈሉ ፣ ልጆቻቸዉን እጅግ በጣም ዉድ በሆኑ ዉጭ አገር ባሉ ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች ያስተምራሉ። የአዲስ ፎርቹኑ ጋዜጠኛ ታምራት ወልደ ጊዮርጊስ እንደዘገበዉ፣ ለአባይ ግድብ ከሚያስፈልገው ወጭ ሁለት እጥፍ የሚሆን፣ ወደ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የዉጭ ምንዛሪ፣ ከኢትዮጵያ በሚስጥር ተዘርፎ ወጥቷል። መቼም ወደ 99.9 በመቶ የሚሆነው ድሃዉ ሕዝባችን ዶላር በእጁ ይነካል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነዉ። በአብዛኛዉ ለአባይ ግድብ ገንዘብ የሚሰበስቡ የኢሕአዴግ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎቻቸዉ ናቸው ዶላር ወደ ዉጭ አገር የሚያሸሹት። [1]

እንግዲህ አንድ፣  እነዶር ቴዎድሮስ አዳኖም የዘነጉት ነገር ቢኖር፣ የተቃዋሚዎችና የአብዛኛዉ ሕዝብ ሌላው ጥያቄ፣ በአባይ ግድብ ላይ ሳይሆን፣ «ለአባይ ግንባታ ብላችሁ፣ ከሕዝብ የምትሰበስቡት ገንዘብ፣ ለአባይ ጥቅም ሳይሆን ወደ ባለስልጣናቱ  ካዝና አለመግባቱ ምን ማረጋገጫ አለን?» የሚል መሆኑን ነው።

እነ ዶር ቴዎድሮስ፣ በዚህ ጉዳይ ሊጠይቋቸው የሚችሉ፣  እንደ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ርዮት አለሙ፣ ዉብሸት ታዬ ያሉ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ወንጀል ከሰዋቸዋል። በሕዝቡ ፊት የኢሕአዴግ ባለስልጣናትን ቻሌንጅ ሊያደርጉ የሚሞክሩ እንደ አቶ አንድዋለም አራጌ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ በቀለ ገርባ ያሉ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን አስረዋቸዋል።  እንደ ፍትህ፣ ፍኖት ያሉ ነጻ ጋዜጦችን ዘግተዋል። ሶስት በሉ።

ዶር ቴዎድሮስ በዋሺንገትን ዲሲ የተናገሩት፣ አንድ የምጋራላቸው አባባል አለ። «የሃሰብ ልዩነቶች መኖራቸው በጣም ጤነኛ ነገር ነዉ» ባሉት እስማማለሁ። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ በሃሳብ ከሚለይዋቸዉ ጋር ለመነጋገርና ለመመካከር ፍቃደኛ የሆኑም ይመስለኛል።  የሃሳብ ልዩነቶች ሊያጣሉን፣ ሊለያዩንና ሊያቃቅሩን አይገባም። ነገር ግን፣ አንድ መረሳት የሌለበት ነጥብ ቢኖር፣  የሃሳብ ልዩነትን የማያክብረዉ፣ ቅድመ ሁኔታ እያስቀመጠ፣ አገር ቤት በሰላም ከሚታገሉ የፖለቲክ ድርጅቶች ጋር አልነጋገርም በማለት ግትር የሆነዉ፣ ለወንድማማችነትና ለብሄራዊ እርቅ በር የዘጋዉ፣  «ለምን ተቃዉሞ ተነሳብኝ ? »  ብሎ ዜጎችን የሚያስረዉና የሚያስጨንቀዉ፣ የርሳቸው ድርጅት ኢሕአዴግ መሆኑን ነዉ።

የሃስብ ልዩነቶች የሚንሸራሸሩባት፣ የመቻቻል፣ የመቀባባል ባህል የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት የሚሹ ከሆነ፣ ዶር ቴዎድሮስ በቀዳሚነት ድርጅታቸውን ይፈትሹ ዘንድ እመክራቸዋለሁ።  እርሳቸዉና ጓዶቻቸው፣  የሚነሱ ተቃዉሞዎችን ለማውገዝ ከሚቸኩሉ፣ ተቃዉሞዎች ለምን እንደሚነሱ ቆም ብለዉ ቢመረምሩ፣  እንደ  ከፍተኛ አመራር አባል ለሚነሱ ጥያቄዎች መፍትሄ ቢፈልጉ መልካም ነዉ እላለሁ።

እንደዉም እዉነት እንነጋገር ከተባለ የአባይ ጉዳይ እንደ ጉዳይ መነሳትም አልነበረበት፤  የለበትምም። አባይ የፖለቲክ ጉዳይ ሳይሆን የአገር ጉዳይ ነዉ።

ዶር ቴዎድሮስ ሃሳብ ሊገባቸው አይገባም። እርሳቸዉና ድርጅታቸው በነርሱ በኩል ማድረግ ያለባቸዉን ካደረጉ፣ እርግጠኛ ነኝ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነትና በጋራ አገሩን ለማልማት፣ አባይን ለመገንባት ይነሳል። ኢትዮጵያዉያን በአባይ ጉዳይ ቀሳቀሽና አስታዋሽ አያስፈልጋቸውም። እንኳን፣   አንዱን አባይ፣  አሥር የአባይ አይነት ግድቦች የመስራት አቅሙና ጉልብቱ አላቸው። የሚያስፈልገው ይሄንን የሕዝብ ኃይል ማዳመጥ፣ ማክበር፣ ለሚያነሳቸውም  መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ብቻ ነዉ። አለቀ። ጆሮ ያለው፣ ይስማ፣ ልብ ያለው ያስተዉል።

በተለይም የሚከተሉትን በማድረግ፣  ኢሕአዴግ ግልጽ የሆኑ የፖሊሲ አቅጣጫ ለዉጦች ከወሰደ፣  እጅግ በጣም በርካታ የአገራችን ችግሮችና እንቆቅልሾች መፍትሄ ያገኛሉ ብዬ አምናለሁ።

  1. እስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌ፣ ርዮት አለሙ፣ ዉብሸት ታዬ፣ ናትናኤል መኮንን፣ በቀለ ገርባ የመሳሰሉ የሕሊና እስረኞች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ። እነዚህን ወገኖች ሽብርተኞች ናቸው ብሎ ፈርጆ ማሰር፣   አስቂኝ ከመሆኑ ባሻገር፣  አሳፋሪና አሳሪዎቹንም ምን ያህል የጫካ አስተሳሰብ ያላቸው፣ ያነሱ መሆናቸውን የሚያሳይ ነዉ።
  1.  እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ሜዲያ፣ ፍርድ ቤቶችን የመሳሰሉ ተቋማት፣ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ማድረግ  የሚቻልበትን መንገድ ለመመካከርና፣  ስር የሰደዱ የፖለቲካ ችግሮችን ለመፍታት ይቻል ዘንድ፣ ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር/ውይይት ይጀመር። ኢትዮጵያ ቻይና አይደለችም። ተቃዋሚዎችን በመርገጥና በማፈን ብቸኛ አዉራ ገዢ ፓርቲ ሆኖ መቀጠል አይቻልም።

ይሄን አባባሌን  አንዳንድ  ኢሕአዴጎች ላይስማሙ፣ በጡንቻቸዉ ተማምነው፣ «ባለህበት ቀጥል» ሊባባሉ ይችላሉ። ነገር ግን እነርሱ ዉስጥ ያሉ፣ ብስለት ሊኖራቸው የሚችል ጥቂቶች፣  የ«ባለህበት ቀጥል» ፖለቲካ እንደማያዋጣና ኢሕአዴግ በሰብአዊ መብቶች መከበርና በዲሞራሲያዎዊ ለዉጦች ዙሪያ ትልቅ ማሻሻል ማድረግ እንደሚገባ ያጡታል ብዬ አላስብም።

  1. የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ፣  የ«ኢሕአዴግ ፕሮጀክት» ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ፕሮጀክት ይሆን ዘንድ ከኢሕአዴግ እንዲሁም ከተቃዋሚዎች የተወጣጡ ባለሞያዎች ያሉበት፣ ገለልተኛ የሆነ፣ የግልጽነትና የተጠያቂነትን አሰራር ያለው፣ ኮሚሽን እንዲመራ ይደረግ።

ያኔ፣ በአባይ ግድብ ዙሪያ በሚደረጉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ የሚነሱ ተቃዉሞች አይኖሩም። ያኔ ገንዘብ ለማሰባሰብ ብዙ ዝግጅቶችም ማድረግም አያስፈልግም። በአጭር ጊዜ ዉስጥ፣ የሚያስፈልገዉን አራት ቢሊዮን ዶላር፣ አገር ቤት ያለዉ ድሃ ሕዝባችን የአንድ ወር ደሞዝን እንዲከፍል ታንቆ ሳይገደድ፣ ዳያስፖራው ብቻ፣ በራሱ አነሳሽነት ሊሸፍነዉ ይችላል።

እንግዲህ ዶር ቴዎድሮስም ሆነ ጓዶቻቸው ልብ ይላሉ ብዬ አስባለሁ። የሚነሱ ተቃዉሞዎችን አናንቀዉ፣ ለኢትዮጵያዉያን መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ችላ ብለው የሚቀጥሉ ከሆነ ወደፊት የተወሳሰበ ሁኔታ ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ አሳስባለሁ። የሕዝብ መብት እየተረገጠ የሚደረግ የልማት እንቅስቃሴ ዘለቄታ አይኖርም። ምናልባት እድሜ ዘመኑን በጫካ ያሳለፈ ጠባብና እንጭጭ የኢሕአዴግ አመራር አባል፣ ይሄን ላይረዳ ይችላል። እንደ ዶር ቴዎድሮስ አዳኖም፣ አቶ ደምቀ መኮንን ያሉ፣  የተማሩ፣  በሳልና ትሁት ምሁራን የኢሕአዴግ አመራር አባላት ግን ይረዱኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

↧

አሥሩ ዋንጫዎች:- አሥሮቹ ጀግኖችና አሥሩ ዓመታት በኦልድትራፎርድ –ክፍል 1

$
0
0

ከይርጋ አበበ

ዓለማችን ተወዳጅ ሊግ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በየዓመቱ 20 ክለቦችን ያፋልማል። የእንግሊዟ ዋና ከተማ ለንደን በየውድድር ዘመኑ ከአምስት ያላነሱ ክለቦች ሲወክሏት ትልቋ የንግድ ከተማ የላንክሻየሯ ግዛት ማንቸስተር ደግሞ ሁለት ክለቦቿን በአምባሳደርነት መድባ ላለፉት ረጅም ዓመታት ተሳትፋለች። የዛሬ የእዚህ ገጽ ትኩረት በውጤታማው ስኮትላንዳዊ አሠልጣኝ ሰር አሌክሳደር ቻፕ ማን ፈርጉሰንና ማንቸስተር ዩናይትድ ላይ ይሆናል። የእንግሊዝ እግር ኳስ ሻምፒዮና ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከተቀየረበት 1992 ጀምሮ ላለፉት 21 ዓመታት (የዘንድሮውን ጨምሮ)የተካሄዱትን ውድድሮች ለበርካታ ጊዜያት በበላይነት የተቆጣጠረውን ክለብ የ10 ዓመታት ጉዞ ለመቃኘትም እንሞክራለን።
በ2003 የክረምት የተጫዋቾች ዝውውር ሲከፈት የዓለማችንን ከዋክብት ተጫዋቾች ካሉበት እያደነ ወደ ክለቡ የሚሰበስበው የፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ጋላክተኮስ ፍልስፍና የማንቸስተር ዩናይትድን በር ከማንኳኳት አላረፈም ነበር። መልከ መልካሙን የቅጣት ምት ስፔሻሊስት ዴቪድ ጆሴፍ ቤካምን ለመውሰድ። ሮናልዲንሆ ጎቾን ችላ ብለው እና ክሎድ ማኬሌሌን ሦስት ሜትር ርቀት ላይ ላለ ጓደኛው ኳስ በትክክል ማቀበል የማይችል ብለው የሸኙት ቱጃሩ የኮንስትራክሽን ድርጅት ባለቤት ዴቪድ ቤካምን ከአሌክስ ፈርጉሰን እጅ ለመንጠቅ ብዙም አልተቸገሩም ነበር። በቤካም ወደ ሳንቲያጎ በርናባው መኮብለል ልባቸው ያዘነውን የቲያትር ኦፍ ድሪምስ ታዳሚያንን ለማጽናናት ሲባል አንጋፋው አሠልጣኝ ዓይናቸውን ወደ ሌሎች ክለቦችና የአውሮፓ ሊጎች ላይ ማንከራተት ጀመሩ። ኤሪክ ጀምባ ጀምባን ጨምሮ ሌሎች ተጫዋቾችን ወደ ክለባቸው አመጡ። የዛሬውን ጨምሮ ለተከታታዮቹ እትሞቻችን በአሌክስ ፈርጉሰን መነጽር ታድነው ኦልድ ትራፎርድ ደርሰው ክለቡን ውጤታማ ማድረግ የቻሉትን ተጫዋች እናያለን።
ክፍል 1
man 41. ክርስቲያኖ ሮናልዶ ዶሳንቶስ ኤቬሮ
ስለ 2008ቱ የዓለም ኮከብ ምን ይባላል? በማንቸስተር ዩናይትድ ያላገኘው የግልና የቡድን ክብር የለም። በ12.24 ሚሊዮን ፓውንድ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ማንቸስተር ዩናይትድ የደረሰው ወጣት ዴቪድ ቤካም ለባሽ አልባ ያደረገውን «7 ቁጥር» ከአሌክስ ፈርጉሰን ተበረከተለት። ጆርጅ ቤስት፣ ብሪያን ሮብሰን፣ ኤሪክ ካንተናና ዴቪድ ቤካም ለብሰውት ታሪክ የሠሩበትን ቁጥር ለብሶ መጫወት ለወጣቱ ከባድ ፈተና ቢሆንም ሁሉንም ጫናዎች ተቋቁሞ ውጤታማ ግልጋሎትን ለሰር አሌክስ ፈርጉሰን ቡድን አበርክቷል። በ80 ሚሊዮን ፓውንድ ነጭ ለባሾቹን ከመቀላቀሉ በፊት በኦልድትራፎርድ 3 ተከታታይ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ አንድ ሻምፒዮንስ ሊግ፣ አንድ አንድ የዓለም ክለቦች ሻምፒዮን እና ኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎችን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን በቀዩ ማሊያ አጣጥሟል። የዓለም እና የአውሮፓ ኮከብ ተጫዋችን ሽልማት ከጆርጅ ቤስት ቀጥሎ የወሰደ ሁለተኛው የቀያይ ሰይጣኖቹ ተጫዋች ሲሆን፤ ከሉይስ ፊጎ በኋላ ፖርቹጋል ያፈራችው የዓለም ኮከብ የሆነውም በእዚሁ ግዙፍ ክለብ ውስጥ ነው። 8የሻምፒዮንስ ሊግ ጎሎችን በአንድ የውድድር ዓመት አስቆጥሮ የሻምፒዮንስ ሊግ ኮከብ ጎል አግቢነትን ክብር ጨምሮ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ጎል አግቢ ሽልማትን ለግሉ አድርጓል። ለተከታታይ አራት ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን የዓመቱ ምርጥ ሽልማቶች የተጎናፀፈው በላንክሻየሩ ክለብ ቆይታው ነው። እነዚህ እና ያልተጠቀሱት ብዙ ምክንያቶች ያለምንም ጥርጥር ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ10 ዓመቱ የማንቸስተር ዩናይትድ ምርጥ ያስብለዋል።
2. ዋይኒ ማርክ ሩኒ፡-
በኤቨርተን አካዳሚ እግር ኳስን አሀዱ ብሎ የጀመረው ታጋዩ ዋዛ ( የሩኒ ቅጽል ስም) በ2003 በየንስ ሌህማን መረብ ላይ ያሳረፉት የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጎሉ የታላላቅ ክለቦች አሠልጣኞች ዓይን እንዲያርፍበት አደረገው። የእነ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አገር ባዘጋጀችው የ2004 የአውሮፓ ዋንጫ በሦስት አናብስቶቹ ማሊያ ደምቆ የታየውን የኤቨርተን ወጣት ለማግኘት ኒውካስትል ዩናይትድን ጨምሮ ሌሎች የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ፍላጎታቸውን ቢገልጹም ስኮትላንዳዊው ውጤታማ አሠልጣኝ ሰር አሌክስ በ25.60 ሚሊዮን ፓውንድ የቀያይ ሰይጣኖቹ ንብረት አደረጉት። 8 ቁጥር ማሊያ ለብሶ የመጀመሪያ ጨዋታውን በኦልድትራፎርድ ፌነርባቸን የገጠመው ሩኒ 3 ጎሎችን ለአዲሱ ክለቡ አስቆጥሮ ጅማሬውን አሳመረ። በነገራችን ላይ ከ20 ዓመት በታች 25.6 ሚሊዮን ፓውንድ ለዝውውር ወጪ የተደረገበት የዓለማችን ተጫዋች ዋይኒ ሩኒ ብቻ ነው። በመጀመሪያ ዓመት የክለቡ ቆይታው የዓመቱ ወጣት ተጫዋች ሽልማትን ያገኘ ሲሆን፤ 12ቱ የፕሪሚየር ሊግ ጎሎቹም የክለቡ ከፍተኛ ጎል አግቢነት ክብርን አጎናጽፈውታል። ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የዘንድሮውን ጨምሮ 5 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ያነሳ ሲሆን፤ ባለግዙፍ ጆሮውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫንም ማግኘት ችሏል። በጃፓኑ የዓለም ክለቦች ሻምፒዮና ክለቡ ሻምፒዮን ሲሆን፤ ሩኒ ደግሞ በግሉ የውድድሩ ምርጥ በመሰኘት የቶዮታ ቁልፍ ተሸላሚ ሆኗል። ከሚያስቆጥራቸው ጐሎች በላይ ለጓደኞቹ አመቻችቶ የሚያቀብላቸው ኳሶች ብዛት በየውድድር ዓመቱ ለክለቡ የሚከፍለው መስዋዕትነት ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ቀጥሎ የዩናይትድ የ10 ዓመቱ ምርጥ ፈራሚ ያሰኘዋል።
3. ኤድ ዊን ቫን ደር ሳር
በአያክስ አምስተርዳም እጅግ ውጤታማ ዓመታት ማሳለፉን ተከትሎ ወደ ቱሪን ተጉዞ ውጤት አልባ ጊዜያትን በአሮጊቷ ቤት ያሳለፈው ሆላንዳዊ ግብ ጠባቂ የእግር ኳስ ህይወቱን በክራቨን ኮቴጅ ካደሰ በኋላ ነበር 2 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ተደርጎበት ኦልድትራፎርድ በር የደረሰው። 154 ጨዋታዎችን ለምዕራብ ለንደኑ ፉልሀም ያደረገው ሆላንዳዊ ሰኔ አሥር 2005 ማንቸስተር ሲደርስ ክለቡ ለ2 ተከታታይ ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በለንደን ባላንጣዎቹ ተወስዶበት ነበር።
ቀጭኑ ሆላንዳዊ ለ266 ጨዋታዎች የኦልድትራፎርዱን ክለብ የግብ መስመር በጀግንነት የጠበቀ ሲሆን፤ ማንም ግብ ጠባቂ ያልሠራውን ጀብዱ የፈጸመውም በእዚህ ክለብ ውስጥ ነው። ለ1,311 ደቂቃዎች በፕሪሚየር ሊግ መረቡን በኳስ ሳያስነካ የዘለቀው ጎልማሳ እስከአሁንም ይህ ክብረወሰን በእጁ ይገኛል። በ40 ዓመት ከ211 ቀናት ዕድሜው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ የክለቡን አንድ ቁጥር በመልበስም አንጋፋው የፍጻሜ ተፋላሚ የሚል ስም የተሰጠው ሲሆን፤ በአጠቃላይ በክለቡ አራት የፕሪሚየር ሊግ እና አንድ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨምሮ የዓለም ክለቦች ሻምፒዮና፣ የኤፍ ኤ ካፕ፣ የካርሊንግ ካፕ እና ኮምዩኒቲ ቮልድ ዋንጫዎች በሙሉ ማሳካት የቻለው በእግር ኳስ የመጨረሻዎቹ ዕድሜው ላይ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ነው። ከፒተር ሹማይክል በኋላ የጎል መስመራቸውን በብቃት የጠበቀላቸውን ሆላንዳዊ የኦልድ ትራፎርድ የታዳሚዎች የ10 ዓመቱ ምርጥ ጉዟችን ሲሉ የሚጠሩት ሲሆን፤ ሰር አሌክሰ ፈርጉሰን ደግሞ «ጀግና» ብለው የጠሩት ግብ ጠባቂ በእዚህ ምርጫ የ3ኛ ደረጃን ቦታ ሲያገኝ ቢያንሰው እንጂ አይበዛበትም።
4. ኒማኒያ ቪዲች
የ31 ዓመቱ ምሥራቅ አውሮፓዊ ከስፓርታክ ሞስኮ በ2006 ታኅሣሥ መጨረሻ የ7 ሚሊዮን ፓውንድ ቼክ የግሌዘር ቤተሰቦችን አስከፍሎ ቀይ ሰይጣን ሆነ። ከያኘ ስታም ወደ ላዚዮ ጉዞ በኋላ የኦልድ ትራፎርዱን የኋላ ክፍል በጀግንነት የመራ ሲሉ ጋዜጠኞች ያሞካሹታል። ከእንግሊዛዊው ሪዮ ፈርድናንድ ጋር የፈጠሩት የተዋጣለት ጥምረት እነ ጀራርድ ፒኬ፣ ዌስ ብራውን እና ሚኬል ሲልቨስተር የኦልድትራፎርድን የመውጫ በር እንዲመለከቱ አድርጓል። ኤድዊን መረቡን ሳያስደፍር ለ15 ጨዋታዎች ሲጓዝ ከቫንደር ሳር ፊት ለፊት እየቆመ የፕሪሚየር ሊጉን አጥቂዎች በብቃት የታገለው ይህ ሰርቪያዊ ወጣት ነው። በኒኮላስ አኔልክ ጎል የተደፈረው የቫንደር ሳር መረብ አኔልካ ይህን ዕድል ሲያገኝ ቪዳ ሜዳ ውስጥ አልነበረም። ከ260 በላይ ጨዋታዎችን በቀዩ ማሊያ ተጫውቶ 18 ኳሶችን ከተቃራኒ ቡድን መረብ ላይ ያሳረፈው ኒማኒያ ቪዲች ለሁለት ዓመታት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋችነት ዘውድ የደፋ ሲሆን፤ ለአራት ዓመታት ደግሞ የዓመቱ ምርጥ 11 ውስጥ መካተት የቻለ ተጫዋች ነው። ተደጋጋሚ ጉዳቶች የቀድሞ ምርጥ ብቃቱን ቢያሳጡትም የማንቸስተሩ አምበል ግን በደጋፊዎች ዘንድ ምርጥ ከመባል አላገደውም። «ለተከታተይ ሦስት ዓመታት በቸልሲ እና አርሴናል የበላይነት የተወሰደባቸውን የበላይነት ለማስመለስ ቀያይ ሰይጣኞቹን ወደ ሻምፒዮንነት የመራ ጀግና» ሲሉም ያሞካሹታል። በአራተኛነት ሲቀመጥ የሠራው ሥራ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ያሳያል።
5. የፓትሪስ ኢቭራ
ትውልደ ሴኔጋላዊው የፈረንሳይ የኋላ ደጀን በ5.5 ሚሊዮን ፓውንድ ከሞናኮ ወደ ማንቸስተር ዝውውር ሲያደርግ እውቅናው እምብዛም ነበር። የማንቸስተሩ ሁለተኛ አምበል ከክለብ ጓደኛው ኒማኒያ ቪዲች ጋር በአንድ ሳምንት ውስጥ ኦልድትራፎርድ የደረሰ ሲሆን፤ የአርጀንተናዊውን ጋብርኤል ሄንዝ ቦታ ሲቀበል ጊዜ አልወሰደበትም ነበር። የተጋጣሚ ቡድን የክንፍ ተጫዋቾችን ማቆም የሚፈራው አርጀንቲናዊ ላለፉት ጥቂት ዓመታት የክለቡ ድክመት እየተባለ ይተች ስለነበር የፈረንሳዊው ኦልድትራፎርድ መድረስ ቀያይ ሰይጣኞቹን እፎይ ያሰኘ ዝውውር ነበር። ታላላቁቹ ማድሪድና ሊቨርፑል ፊርማውን ለማግኘት የሞናኮን ደጅ ደጋግመው ቢጠኑም የወጣቱ ልብ ሊከፈትላቸው አልቻለም ነበር። ምክንያቱ ደግሞ የምንጊዜም ፍላጎቱ ቀይ ሰይጣን መሆን እንጂ የሌላ ክለብ ማሊያ መልበስን አስቦ አለማወቁ ነው። ኒማኒያ ቪዲች ያገኛቸውን ዋንጫዎች በሙሉ ያገኘ ሲሆን፤ በግሉም በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል። እስከአሁን ድረስም ቀያይ ሰይጣኖቹን በታማኝነትና በጀግንነት እያገለገለ ይገኛል። አምስተኛው የአሥር ዓመቱ ምርጥ የማንቸስተር ዩናይትድ ፈራሚ።
ይቀጥላል

↧

የህማማት ማሰታወሻ –‹‹ህዝቤን ልቀቅ!›› እስክንድር ነጋን ልቀቅ!… (ከተመስገን ደሳለኝ )

$
0
0
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ይህ ሳምንት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ‹‹ሰሞነ ህማማት›› ተብሎ በፀሎትና በስግደት ይከበራል፡፡ ይህ የሆነው ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ በሀሰት ተወንጅሎ ለስቅላት ተላልፎ የተሰጠበት፣ በሰው ልጅ ከሚደርስ ስቃይ፣ መከራና ግርፋት ሁሉ የከፋውን የተቀበለበት ሳምንት በመሆኑ ነው፡፡
…የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖት ጥብቅ አማኝ ነው፤ የሀይማኖቱን ትእዛዛቶች በጥብቅ ያከብራል፤ ሁሉንም አፅዋማትም ይፆማል፡፡ ዛሬ በግፍ ታስሮ በሚገኝበት የቃሊቲ ወህኒም ሆኖ እንኳ የኩዳዴን ፆም ከመፆም አልሰነፈም… (በነገራችን ላይ እስክንድር የሚገኝበት ‹‹ዞን ሶስት›› ፈርሶ እንደገና ሊሰራ ስለሆነ እስረኞቹ ወደሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ እንደሆነ ተነግሯቸዋል)
እስክንድር የተወለደው ጥቅምት 27 ነው፡፡ ይህ ዕለት ደግሞ ለእምነቱ ተከታዮች የ‹‹መድሐኒያለም ዕለት›› እየተባለ የሚከበረበት ቀን ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ምንጊዜም ጠዋት ወይም ማታ ከስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ ከፍ ብሎ በሚገኘው ‹‹ምስኪያዙና መድሐኒያለም ቤተ-ክርስቲያ››ን የፈለገ አያጣውም፡፡
…የፊታችን ሀሙስ (ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም) የእስክንድር ነጋ ይግባኝ ‹‹ለመጨረሻ ጊዜ›› ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ ዕለቱ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ‹‹ፀሎተ ሀሙስ›› ታስቦ የሚውልበት ቀን ነው (አይሁዳውያን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፈው ሰጥተው ሲያበቁ ስለሁከት፣ ስለመግደል በወሀኒ ታስሮ የነበረውን በርባንን ‹‹ፍታልን!›› ያሉበትን እና የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በትህትና ያጠበበትን ለማስታወስ ነው ቀኑ ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ተብሎ የተሰየመው)
…በድህረ ምርጫ 97 ለእስር ከተዳረጉ ጋዜጠኞች መካከል እስክንድር ነጋ አንዱ ነበር፡፡ የተፈታውም በ‹‹ይቅርታ›› ሳይሆን ፍርድ ቤቱ ‹‹ነፃ ነህ!›› ብሎ አሰናብቶት ነው፡፡  ቀኑም የ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ዕለት ነበር፡፡ …የከነገ በስቲያ ሚያዚያ 24 ግጥምጥሞሽስ ምን ያሰማን ይሆን?
የሆነ ሆኖ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃል ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት እግዚአብሄር ሙሴን እንዲህ እንዳለው ይነግረናል፡-
‹‹እኔ እግዚአብሄር ነኝ፤ ከባርነት አወጣችኋላሁ፤ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋቸኋለሁ፤ አምላክም እሆናቸኋለሁ፡፡›› (ኦሪት ዘጸአት ም.6 ቁ.6-7)
በወቅቱ ብዙ ሺህ ንፁሃን፣ ፈርኦን በተባለ ጨካኝ ንጉስ ስር ይሰቃዩ ነበር፡፡ እናም ከዕለታት አንድ ቀን  እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ፈርኦን ላከው፡፡ ሙሴም ቤተ-መንግስቱ ውስጥ ድረስ ዘልቆ በዙፋኑ ለተቀመጠው ፈርኦን እንዲህ ሲል የአምላኩን መልዕክት ነገረው፡-
‹‹እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- በፊቴ ለመዋረድ እስከመቼ እምቢ ትላለህ? ያገለግለኝ ዘንድ ህዝቤን ልቀቅ!››
…በምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያም  እስከዛሬ ድረስ ያየነው ስርዓቱና ምንደኞቹ ንፁሃንን በሀሰት ከሰው፣ በሀሰት ምስክርና በሀሰት ማስረጃ ወደ ጨለማ (ወህኒ) ሲወረውሩ ነው፡፡
በመላ ሀገሪቷ የነገሰውም የህግ የበላይነት አይደለም፤ የፈርኦን የበላይነት እንጂ፡፡ ፈርኦኖች ደግሞ ምን ጊዜም ከመከራ እንጂ ከታሪክ ተምረው አያውቁም፡፡ መልካሚቷን ምክርም ሊሰሙ አይወዱም፡፡ ስለዚህም ብቸኛው አማራጭ በአደባባይ ተሰባስበን፡-
‹‹በፊታችን ለመዋረድ እስከመቼ እምቢ ትላለችሁ? ሀገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ ወንድምና እህቶቻችንን ልቀቅ!››
‹‹እስክንድር ነጋን ልቀቅ!
በቀለ ገርባን ልቀቅ!
አንዱአለም አራጌን ልቀቅ!
ርዕዮት አለሙን ልቀቅ!
ውብሸት ታዬን ልቀቅ!
የሱፍ ጌታቸውን ልቀቅ!
አቡበክር አህመድን ልቀቅ!
ብዙ… ብዙ ሺህ ንፁሃንን ልቀቅ!››
እያሉ መጮኹ ኢያሪኮን ለማፍረስ ያልተመለሰው የጭቁኖች ጩኸት መነቃነቅ የጀመረውን ስርዓት ለመፈረካከስ ብቸኛው ምርጫችን እንደሆነ ዛሬም ደግሜ እናገራለሁ፡፡
‹‹ልቀቅ! ልቀቅ! ልቀቅ!››

↧
↧

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት የፊታችን ሐሙስ ከቦታው ይነሳል

$
0
0

ዘabune_petros-ሐበሻ በተደጋጋሚ ከቦታው ሊነሳ ነው ስትል ስትዘግበው የነበረው የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት የፊታችን ሃሙስ አሁን ከሚገኝበት ቦታ እንደሚነሳ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ማስታወቁን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ ገለጹ።

በአ.አ ከተማ እየተካሄደ ባለው የቀላል ባቡር ግንባታ ፕሮጀክት  ምንክንያት ሐውልቱ የሚያርፍበት ቦታ የሚቆፈር በመሆኑ በጊዜያዊነት ይነሳል ሲል መንግስት ቢያስታውቅም ብዙዎች ግን ተመልሶ ቦታው ላይ ለመቀመጡ ጥርጣሬ እንዳላቸው አስተያየታቸውን በተለያዩ መንገዶች እየገለጹ ይገኛሉ።  የፊታችን ሐሙስ እንደሚነሳ የሚጠበቀው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ጊቢ ውስጥ እንደሚቀመጥ ተገልጿል።

ባለሙያዎች የቀላል ባቡር ግንባታው ሐውልቱን በማይነካ መልኩ መካሄድ ይችል ነበር ሲሉ በተደጋጋሚ ቢገልጹም የመነሳቱ ነገር እርግጥ ሊሆን 48 ሰዓታት ቀርተውታል።

↧

አማራን ላሞራ-የወያኔ ሴራ!

$
0
0

ይታረድ ፍሪዳዉ ግባልኝ ከቤቴ

እነሆ የላም ልጅ ከርጎ ከወተቴ

የእግዚአብሔር እንግዳ እረፍ ከመደቡ

እግርህም ይታጠብ በወጉ በደንቡ

ያዳም ልጅ እኮ ነን የእጆቹ ሥራ

ተጫወት ወንድሜ እንግዲህ አትፍራ!

እንዲህ እንዳልነበር ባህል ልማዳችን

ዉጣልን አማራ ጥፋ ከፊታችን

ጫንልኝ ደራርበህ ዳርግልኝ ላደጋ

ጎጃምና ጎንደር ወሎም ሆነ ቡልጋ

እየገፈተርከዉ በሰደፍ ባለንጋ!

እንዳልተሰዋለት እንዳልተዋደቀ

ላገር ስልጣኔ እንዳልተጨነቀ

ለሰንደቅ ዓላማዉ ሌት ተቀን የተጋ

ኢትዮጵያን ያለ ሰዉ የለዉም ወይ ዋጋ?

ዘዉዱን ከክህነት ያስተባበራችሁ

የቅዱሳን አገር ከቶ ምን አላችሁ

በግሸኗ ማርያም በክቡር መስቀሉ

አገር እያጠፉ ወገን ሲበድሉ

ባንዳ ሲዘባነን አርበኛዉ ሲጉላላ

አይታጠንም ወይ ቅዱስ ላሊበላ?

ዓይኑ እስኪታክተዉ ጋምቤላን ሲመራ

ህንዱ ካራቱሬ ሊተክል ሊዘራ

ቻይና ኮሚኒስቱ ስንት ግፍ ሲሰራ

በገዛ አገራችን ሲኮራ ሲዳራ

ምን ዓይነት ልማት ነዉ አማራን ላሞራ

ይናገር መቅደላ ይፋረደኝ ቋራ!!

ከፋኑኤል አበበ

ኒዮርክ 


 

↧

ዶ/ር መረራ ጉዲና እና አቶ ገብሩ አስራት ለአንድነት ፓርቲን ጥያቄ ምላሽ ሰጡ

$
0
0

በአንድነት የግምገማ ሪፖርት ላይ የመድረክ

 አባል ፓርቲዎች ምላሽ

-   አንድነት በመድረክ ውስጥ ስላለው ሚና በተመለከተ ለአንድ ወር ተካሂዶአል የተባለው ጥናት የመንገድ ላይ ሥራ ነው

      ዶ/ር መረራ ጉዲና

-   የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት መድረክ እንዲገመገም ማዘዝም ሆነ በዚህ ላይ ተመስርቶ የሚሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም

    አቶ ጥላሁን እንደሻው

-   “በመድረክ ሕገ-ደንብና ፕሮግራም ላይ ለመነጋገር በመድረክ ጉባኤም ላይ ተወስኗል”

አቶ ገብሩ አስራት

 

በዘሪሁን ሙሉጌታ
Dr Merera gudinaየአንድነት ፓርቲ መድረክን የሚገመግም ሪፖርት በብሐራዊ ምክርቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተካሄደ በኋላ ሌሎች የመድረክ አባል ፓርቲ አመራሮች አስተያየት ሰጥተዋል። ምንም እንኳ የግምገማው የውሳኔ ኀሳብ በትክክል ባይረዱትም ከዚህ ቀደም በወጡ መረጃዎች በአንድነት በኩል እየተሰጠ ባለው ኀሳብ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። አመራሮቹ የሰጡት ምላሽ እንደሚከተለው ቀርቧል።
የመድረክ አባል ድርጅቶች የሆኑት የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረንስ (ኦህኮ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና በበኩላቸው አንድነት በመድረክ ውስጥ ስላለው ሚና በተመለከተ ለአንድ ወር ተካሂዷል የተባለው ጥናት ‘‘የመንገድ ላይ ስራ ነው’’ ሲሉ አጣጥለውታል። እስካሁንም በአንድነት በኩል በፅሁፍ የቀረበ ነገር እንደሌለ ገልፀዋል።
በአንድነት ፓርቲ ውስጥ መድረክን በተመለከተ ቅሬታ ያላቸው ወገኖች እንዳሉ አይካድም ያሉት ዶ/ር መረራ መገንዘብ ያለባቸው ግን ‘‘ከመድረክ ውጪ መንቀሳቀስ አይጠቅማቸውም። ሁላችንንም አይጠቅምም ተነጣጥሎ መሄድ ማንንም አይጠቅምም። ለአለፉት ሃያ አመታት ያየነው ነገር ነው። ስለዚህ ፖለቲካ ያልገባቸው ሰዎች በዛም በዚህም በሁሉም አካባቢ እንዲህ ቢሆን… እንደዚያ ቢሆን የሚሉት ነገር አይጠቅምም’’ ብለዋል።
‘‘አንዳንዶቹ በሚያውቁትም በማያውቁት ዝም ብለው እኚ… እኚ ይላሉ እንጂ ችግሩ ከብሔርና ህብረብሔር በላይ የሰፋ ነው። ህብረብሔር ነን የሚሉትም የሚባሉትን አልሆኑም። የብሔር ንቅናቄ እንፈጥራለን የሚሉትም የሚባሉትን አልሆኑም። ስለዚህ የፖለቲካ ግራ መጋባት ነው’’ ሲሉ ገልፀውታል።
ይሁን እንጂ ባለፉት አራት አመታት መድረክ በሚፈለገው ደረጃ እየተንቀሳቀሰ አለመሆኑ ግን ‘‘ሁላችንንም ያስማማናል’’ ያሉት ዶ/ር መረራ ‘‘መንግስት በፈጠረው የተበላሸ የፖለቲካ ሁኔታም ሆነ በራሳችን ችግር በምንፈልገው ደረጃ ላይ አይደለንም። ይሄ ችግር የእኛ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የሀገሪቱ ፖለቲካ ታስሮ ነው ያለው’’ ብለዋል።
መድረክ ወደ ‘‘ግንባር’’ ሲያድግ መታየት የነበረባቸው የፕሮግራም ልዩነቶች በተመለከተም ዶ/ር መረራ ሲናገሩ፤ ‘‘የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ችግር የፕሮግራም ችግር አይደለም። ከኢህአፓ እና መኢሶን ጀምሮ ያለው ችግር የፖለቲካ ፕሮግራም ችግር አይደለም። አንዳንዶች ዝም ብለው ነው የሚቃዡት፤ ለምሳሌ ኢህአፓና መኢሶን መሰረታዊ የፖለቲካ ልዩነት አልነበራቸውም። ልዩነቱ የአካሄድ ወይም የአሰራርና የስትራቴጂ ሊሆን ይችላል። አሁንም የኢህአዴግ ከሚቀልባቸው ሰዎች የሚነሳ ጥያቄ እንጂ ችግሩ የፖለቲካ ፕሮግራም አይደለም’’ ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ከአንድነት ፓርቲ እየተነሳ ያለው ጥያቄ ለወደፊቱ መድረክን ምን ያህል ሊጎዳው እንደሚችልም የተጠየቁት ዶ/ር መረራ ‘‘ማንኛውም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት ብቻውን ኢህአዴግን መግፋት አይችልም። አሁንም አስረግጬ የምናገረው ማንም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቡድን ብቻውን ይሄንን መንግስት ወደ ድርድር አምጥቼ አሸንፋለሁ ቢል ህልም ነው የሚሆነው። የሰፋ ህብረት የሰፋ ትብብር፣ የሰፋ መተማመን ያስፈልጋል። ከዚህ ውጪ የሚንቀሳቀሱ ህልመኞችና ፖለቲካም ጨርሶ ያልገባቸው ናቸው። ብዙ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው ኃይሎች በዓለም አብረው ሲሰሩ ይታያል። ለምሳሌ በጀርመን የቀኝ ኃይል ከሶሻል ዲሞክራሲ ከሚባለው የግራ ዘመም ኃይል ጋር እየሰራ ነበር። በእስራኤልም ቀኝም ግራም ሆነው መሀል ላይ ሆነው ሲሰሩ ነበር። በእኛ በኩል ዋናው ችግር አብሮ የመስራት ነው። በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ መደራደርም ይቻላል።’’ ሲሉ መልሰዋል።
Arenaየአረና ትግራይ ለሉአላዊነት (አረና) ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት በበኩላቸው የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ም/ቤት ያሳለፈው ውሳኔ ምን እንደሆነ እንደ አረናም ሆነ እንደ መድረክ የታወቀ ነገር እንደሌለ ከገለፁ በኋላ በመድረክ ህገ-ደንብና ፕሮግራም ላይ እራሱ መድረክ እንዲነጋገርበት ባለፈው የመድረክ ጉባኤ ላይ መወሰኑን አስታውሰዋል።
አንድነት እንደ አንድ የመድረክ አባል ድርጅት ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ ማንሳት እንደሚችል የገለፁት አቶ ገብሩ ሁሉም ፓርቲዎች በመድረክ ውስጥ እንዲሟሉላቸው የሚፈልጉትን ጥያቄ ማንሳት ይችላሉ ብለዋል። ይሁን እንጂ ፓርቲዎቹ የሚያሳስባቸውን ጉዳይ አነሱ ማለት በቀጥታ መድረክን ያፈርሰዋል በሚል መነሻ አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል። ነገር ግን ጥያቄዎች ካሉ ተነስተው በዛ ላይ ውይይት ማድረጉ አግባብ ነው ብለዋል።
 የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው አንድነት ፓርቲ መድረክን የመገምገም ስልጣን የለውም ብለዋል። ‘‘መድረክ እራሱን የሚገመግምበት የራሱ አሰራር አለው። የራሱ የፓርቲ አካላት አሉት። ጉባኤና ስራ አስፈፃሚ አለው። ስራ አስፈፃሚውም የራሱ የተግባር ኮሚቴዎች አሉት። ስለዚህ መድረክ በራሱ አካላት ነው መገምገም ያለበት። አባል ድርጅቶችም ቢሆኑ እዛው መድረክ ውስጥ ባላቸው ተወካዮች አማካኝነት የራሳቸውን ድርሻ ያበረክታሉ እንጂ አንድ አባል ድርጅት መድረክን የሚገመግምበት አሰራር የለም።’’ ሲሉ መልሰዋል።
አንድነት መድረክን ከመሰረቱ ፓርቲዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን የመድረክን አጠቃላይ የፖለቲካ አካሄድ የመገምገም መብት የለውም ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ጥላሁን፤ ‘‘መድረክ እራሱ ባቋቋማቸው አካላት አሰራሩን በሚገመግምበት ወቅት እራሳችንን እንገምግም ብሎ ኀሳብ ማቅረብ ይችላል። አንድነት ባቀረበው ኀሳብ ለይ ተመስርቶ የመድረክ አካላት ግምገማውን ማካሄድ ይችላሉ። ከዚህ ውጪ አንድ አባል ፓርቲ በራሱ መድረክን መገምገም አይችልም’’ ሲሉ መልሰዋል።
አቶ ጥላሁን ኀሳባቸውን ሲያጠናክሩ ‘‘የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት መድረክ እንዲገመገም ማዘዝም ሆነ በዚህ ላይ ተመስርቶ የሚሰጠው ውሳኔ ተቀባይነት የለውም። ብሔራዊ ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ደረጃ እራሱን ይገምግም። እኛ በመድረክ ጉባኤ ውስጥ ያሉትን የአንድነት ተወካዮችን ነው የምናውቀው። እነዚህ የምናውቃቸው የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች እስካሁን መድረክን እንገምግም ብለው ጥያቄ አላቀረቡም። ከዚህ ውጪ የአንድነት ብሔራዊ ምክርቤት ግምገማ ሙሉ በሙሉ ህገ-ወጥ ነው’’ ብለዋል።
የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት የመገምገም ስልጣን ያለው በመድረክ የሚሳተፉ የራሱን የአንድነት ተወካዮችን ‘‘ምንሰራችሁ?’’ ብሎ መገምገም እንጂ መድረክን እንደ አንድ አካል መገምገም አይችልም ያሉት አቶ ጥላሁን የአንድነት ግምገማ የድርጅቱ (የአንድነት) የውስጥ ትግል ነፀብራቅ ነው ብለዋል።
Medrek 2‘‘መድረክ ከተመሰረተ ጀምሮ የአንድነት አባላት መድረክ ውስጥ አብረን እንሂድ ወይስ እንተው በሚሉ ወገኖች ክርክር ነበር። የመድረክን ፕሮግራም አንቀበልም ያሉ የፓርቲው አባላት ከፓርቲው መውጣታቸውን እናውቃለን። እንቀበላለን ያሉት ደግሞ በድምፅ ብልጫ አሸንፈው አንድነት ወደ መድረክ እንዲገባ አድርገዋል። በነገራችን ላይ አንድነት ወደ መድረክ የገባው ሌሎቻችን አንድ ፎርም አቋቁመን በዛ ላይ ውይይት ካደረግን በኋላ ዘግይቶ ነው። በመድረክ ምስረታ መነሻ ላይ አንድነት አልነበረም። እንዲገባ ስንጋብዘው ‘‘እንግባ አንግባ’’ በሚል ተከራክረዋል። በድምፅ ብልጫ የተሸነፉት ወጥተው ሰማያዊ የሚባል ፓርቲ እንደመሰረቱ እናውቃለን። አሁንም እንደገና ተመልሰው መድረክ አልጠቀመንም የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይጠቅመናል መድረክ ውስጥ መቆየት ይሻለናል የሚሉም አሉ። እና በእነዚህ ሰዎች መካከል የሚደረገው ክርክር የራሱ የአንድነት የውስጥ ክርክር እንጂ እኛን የሚመለከት አይደለም። እኛ አንድነት መድረክ ውስጥ መሳተፍ ይጠቅመናል ብሎ ወስኖ ካቀረበው አካል ጋር እየሰራን ነው ያለነው። ያ አካል ደግሞ በመድረክ የተግባር ኮሚቴ ውስጥ ተመድቦ እየሰራ ሲሆን መድረክ ይገምገም የሚል ኀሳብ እስካሁን አላቀረበም’’ ሲሉ ገልፀዋል።
በመድረክ ውስጥ እንቀጥል ወይስ አንቀጥል የሚለው የአንድነት የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ እኛን አይመለከተንም የሚሉት አቶ ጥላሁን ይልቁኑ መድረክ የትግል ጉዞውን በመቀጠል በቅርቡ ይፋ ያደረገውን ማኒፌስቶ በመያዝ ሕዝብ ለማወያየት ጥረት እያደረገ መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል።n
(ምንጭ፡ ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 399 ሚያዚያ 23/2005)
↧

ኢትዮጵያ በርግጥ ዴሞክራሲ ይገባታል ወይ?

$
0
0

532059_547719218612772_154310823_n በገለታው ዘለቀ

መቼም የዶክተር ብርሃኑ ነጋን ቃለ መጠይቅ ሳዳምጥ የምማርበት ኣንዳች ነገር ኣላጣም። ይህቺን ጽህፍ ስጽፍም ለመጻፍ ብየ ሳይሆን  ከሰማሁት ላይ ቀንጠብ ኣድርጌ የተማርኩትን ለራሴው ለማጎልበት ነው። ዶክተር ብርሃኑ ከዚህ በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ኣንድ የ ፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ኢትዮጵያ ኮንስትቱየንሲ እንደሌላት ኣርጎ እንደነገራቸው ሲነግሩን ላፍታ በዚህ ኣባባል ዙሪያ ከራሴ ጋር ተወያየሁ።

 

በርግጥ በዚህ ሃሳብ ዙሪያ በተለያየ መንገድም ቢሆን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማስተናገድ የተዘጋጀች ኣገር ናት ወይ? እውነተኛው ዴሞክራሲ ቢመጣ የምንይዝበት ኣቁማዳው ኣለን ወይ? በሚል እንደ ዜጋ ኣስቤ ኣውቃለሁ። ዛሬ ደሞ የዚያ ምሁር ኣባባል ለ ውይይት የበለጠ የሚያነሳሳ ሆነና እንደ ዜጋ ታየኝ።

 

ያ ሰው እንደ ኣንድ ኢትዮጵያዊ ምሁርነቱ ያሳሰበውን ነው የተናገረው።የዚህ ሰው ስጋት የብቻው ኣይመስልም። ባንድም በሌላም በኩል ይህን ስጋት የሚጋሩ ወገኖች መኖራቸው ኣይቀርም።

 

ይህ ሰው እና ሌሎች የዚህን ሰው ኣሳብ የሚጋሩ  ዴሞክራሲን ለማስተናገድ ኢትዮጵያ ኮንስትቱየንሲው የላትም ሲሉ ምን ማለታቸው እንደሆነ ሊያብራሩ የሚገባቸው እነሱ ናቸው። ይሁን እንጂ ኮንስትቱየንሲ ሲባል መራጭ ቡድን ወይም በኣንድ የተመረጠ ወይም የተመረጡ ተወካዮች ስር የሚገኙ መራጮች እንደማለት ነው። በሌላም ኣገላለጽ የጂኦ ፖለቲካው ክፍፍል ማለትም ነው። በዚህ ጽሁፍ ኮንስትቲየንሲን በዚህ ኣጥር ክልል ውስጥ ከትተን ለመወያየት እንሞክራለን።

 

ታዲያ ይህ ቡድን ወይም ኣካል የላትም ማለት ምን ማለት ነው? መራጩ ኣካል በርግጥ ኣለ ይሁን እንጂ የላትም ሲባል ኣሁን ባለችበት ደረጃዋ ዴሞክራሲን ለማስተናገድ ኣቅም የለም ተብሎ ሊወሰድ ይችላል።

 

ርግጥ ነው ዴሞራሲ ያዢዎች (holders) ያስፈልገዋል። ግን ደሞ ዴሞክራሲን የሚይዙት ቡድኖች ብቻ ሳይሆኑ ግለሰቦችም ናቸው። ዴሞክራሲ ሁለት ያዢዎች ኣሉት ማለት ነው። ቡድኖች የቡድን ሃብት የሆኑትን ሁሉ የሚንከባከቡበት መርህ በዚህ በዴሞክራሲ የተቃኘ እንዲሆን ያስፈልጋል። ባንጻሩ ግለሰቦች ደሞ የራሳቸውን መብትና ግዴታ የሚይዙበት የሌሎችን መብትና ግዴታ የሚያከብሩበት መርህም በግለሰቦች ህይወትም ያድራል።

 

ወደ ላይኛው ሃሳብ እንውጣና እናውራ። የዚያን ምሁር ስጋትም ጥቂት እንመርምር። ኮንስትቲየንሲ የለም ሲሉ እነዚህ መራጭ ቡድኖች ያላቸውን ኣቅም ይመለከታል ብለናል። በዚህ ኣገባብ ዴሞክራሲን ለማስተናገድ ኣቅም ከሚገለጽባቸው ኣውዶች ኣንዱ ምንድን ነው?

 

ምርጫ

election

ኣንዱ የዴሞክራሲ ተከታይነት ችሎታ ተግባራዊ መለኪያው ምርጫ ነው:: ምርጫ በዴሞክራሲ ጽንሰ ሃሳብ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለው የዴሞክራሲ ተግባራዊ መገለጫው ነው። ምርጫ ደሞ ውሳኔ ነው። ለ ውሳኔ ደሞ መረጃ የማግኘትና መረጃን የመገምገምን ኣቅም ይጠይቃል። የውሳኔያችን ጥራት የሚካለውም ባገኘነው የመረጃ ጥራትና በመገምገም ችሎታችን ልክ ነው።

 

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ያላትን ተክለ ሰውነት መገምገም ይገባል። የኢትዮጵያ መራጭ ቡድኖች ይህ ኣቅም የላቸውም ወይ? ብለን መጠየቅ ኣለብን።

 

እንግዲህ ኢትዮጵያ ስንል መታየት ያለበት ነገር 80 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ በገጠር የሚኖረው ህብረተሰብ ቀድሞ ወደ ህሊናችን ይመጣል። ይህ ሰፊ ህዝብ ኣርሶ ኣደር እና ኣርብቶ ኣደር ነው።

 

ከሃይለስላሴ ጀምሮ ስልጣኔ ወደ ኢትዮጵያ በገባ ቁጥር በገጠሩና በከተማው መካከል እያደር እየሰፋ የሄደ ምጣኔ ሃብታዊና ማህበራዊ ለውጥ ግዙፍ ክፍተት እጅግ ከመለያየታቸው የተነሳ ገበሬውን ከከተሜው ለውድድር ለመቅረብ እንዳይችል ያደርገዋል። በእውቀት ሃብትም ቢሆን ዘመናዊው እውቀት ከተሞች ኣካባቢ የተጠራቀመ ሲሆን ሰማኒያ በመቶ የሚሆነው ከዘመናዊነት በጅጉ ርቆ ነው ያለው። በኢትዮጵያ ውስጥ በገጠሩና በከተማው ያለው ያልተመጣጠነ እድገት የሚገለጸው በ ኑሮ ዘያቸው ሁሉ ነው ።

 

በ ኢትዮጵያ ውስጥ ኣንድን ኣርሶ ኣደርና ኣንድን ከተሜ ስናይ ባለባበስ በኑሮ ዘየ በኣነጋገር በእውቀት ያላቸው ክፍተት በርግጥ በኣንድ ኣገር የሚኖሩ የ ኣንድ ኣገር ልጆች ኣያስመስላቸውም። ይህ ማለት ከተሜው ደልቶት ወይም በጣም የተመቸው ነው ለማለት ኣይደለም። ከ ኣርሶ ኣደሩና ከኣርብቶ ኣደሩ ጋር ያለውን ህዝብ በኢትዮጵያ ካሉ ዋና ዋና ከተሞች ህዝብ ጋር ወይም 20 በመቶ ከሚሆነው ከተሜ ጋር በኣንጻራዊ መልኩ ስናይ ለማለት ነው።

 

በርግጥ ይህ ገበሬ የራሱ የሆኑ እውቀቶች ኣሉት። በልምድ ያካበታቸው የኣስተራረስ እና የከብት ኣረባብ ዘዴዎች፣ የልምድ ያየር ጸባይ እውቀት፣ ኣጠቃላይ ኣካባቢውንና ተፈጥሮን የሚያይበት የራሱ እውቀቶች ኣሉት። በተለይ በስነ -ቃሉ የሚገልጻቸው የረቀቁ ኣሳቦች ኣንዳዴ ተምሪያለሁ የሚለውም ቶሎ ወይም በቀላሉ ላይረዳው ይችላል። ይሁን እንጂ ይህ ሰፊ ህዝብ ታድለን ዴሞክራሲ ወደ ሃገራችን ገብቶ መድብለ ፓርቲ ተመስርቶ፣ የፓርቲዎች መወዳደሪያ ሜዳ ተደልድሎ ምርጫ ቢጀመር ኣንደኛ ምርጫ ውሳኔ ሲሆን ውሳኔ ለመስጠት ደሞ መረጃ ያስፈልጋል ብለናል ይህ ሰፊ ህዝብ ደሞ ካለው የመረጃ መረብ ውሱንነትና ኣክሰስ ኣንጻር ሰፋ ያለው ህዝብ የጠራ መረጃ የሚያገኝበት ሁኔታ ኣሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ኣልተመቻቸም። የገበሬው ኣሰፋፈር ራሱ እዚያና እዚያ ከመሆኑ የተነሳ መረጃዎችን በቀላሉ ለማፍሰስ ኣይቻልም። ሁለተኛውና ትልቁ ችግር ለምርጫ የሚሆን ኣቅም ኣለን ወይ? የሚለው ጉዳይ ነው። እንግዲህ ውይይታችን በሃቀኝነትና በቅንነት ተመስርቶ መሆን ኣለበት ብለናል።

 

የዚህን ኣርብቶ ኣደርና ኣርሶ ኣደር ተክለሰውነት ስናይ በርግጥ ፓርቲዎች ኣማርጭ ፖሊሲዎቻቸውን ሲያቀርቡ የፓርቲዎቹን ኣቋም የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ፖሊሲዎቻቸውን ይረዳል ወይ? እንደው የተሸራረፈ መረጃ እንኳንም ቢሆን ቀየው ድረስ ሄዶ ቢሰማ ስንቱን ይረዳዋል? ብለን ስናስብ በርግጥ በዚህ በምርጫ በኩል ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ኣቅም ከዚህ ከሰፊው ህዝብ ኣካባቢ በኣስተማማኝ ሁኔታ ኣናገኝም። ይህ ሃብት ወይም ኣቅም የለንም። የሌለንን የለንም ነው ማለት ያለብን። ገበሬው ይህ ኣቅም የለውም ማለት የሱ ጉድለት ኣይደለም። ኣላወቀም፣ ኣልተማረም  ምን ያድረግ።ኣሁን እየተናገርኩ ያለሁት ስለምወዳት ገበሬዋ እናቴና ስለምወደው ገበሬው ኣባቴ ነው።

 

እዚህ ላይ ስለዚህ ስለ ሰፊው ህዝብ ረገጥ ኣድርገን የምናወራው በዴሞክራሲ ጊዜ በተለይ በምርጫ ጊዜ የማጆሪቲ ጉዳይ ትልቅ ቦታ ስላለው ነው። እንግዲህ ኣገራችን ኢትዮጵያ ኣዲስ ኣበባ ብቻ ኣይደለችም። በኣራቱም ማእዘናት ያለውን ሰፊውን ህዝብ የያዘውን የገጠሩን ህዝብ ተከለ ሰውነት መገምገም ዴሞክራሲ እንዴት በኢትዮጵያ ሊስተናገድ ይችላል? ለሚለው ወሳኝ ጉዳይ ለመወያየት መነሻ ይሆናል።

 

ኣገር ሲባል የሚቆመውም በማጆሪቲ ስለሆነ ማጆሪቲ ጎናችንን ማወቅ ያስፈልጋል። እውነተኛ ዴሞክራሲ ዛሬ ተጀምሮ ወደ ምርጫ ስንገባ ይህ ሰፊ ህዝብ የሚሰጠው ውሳኔ በኣገሪቱ መጻኢ እድል ላይ ምን እንድምታስ ሊኖረው ይችላል? ተብሎም ይታሰባል። ኢትዮጵያ ዛሬ ወደ እውነተኛ ምርጫ ብትገባ  ከዚህ ከሰፊው ህዝብ እድሜው ለምርጫ የደረሰውን ብናወጣ በርግጥ ሰፊው ህዝብ እውቀት በተሞላበት በመረጃ በተደገፈ ይከውናል ማለት ከ እውነት የራቀ ነው። ይህ የህብረተሰብ ክፍል በምርጫ ጊዜ የፖለቲካ ድርጅቶችን ርእዮት ገምግሞ ሳይሆን እጩዎቹን በኣካል የሚያውቃቸው ከሆነ እከሌ ጥሩ ሰው ነው ተሰሚነት ኣለው እያለ ከመምረጥ ያለፈ ሃላፊነት ሊሸከም ኣይችልም። ይህ እንግዲህ መራራም ከሆነ እውነት ነውና መቀበል ነው። የዚያ ምሁር ስጋት ኢትዮጵያ የማጆሪቲውን ኣቅም ኣገናዝቦ ያየ በመሆኑ እውነት ነው ብለን እንድንቀበል ያደረገናል።

 

ይህን መራራ እውነት ከተቀበልን በሁዋላ ኣንዳንድ ለዴሞክራሲ መልካም ቅናት ያላቸው ወገኖች ብቻ የዴሞክራሲው መሬት ይደልደል እንጂ ስለምርጫ ችሎታችን ኣንጨነቅም፣ ህዝቡ እንዳወጣለት ይምረጥ የሚል ቸርነትና ቅንነት የተሞላበት ኣሳብ ሊሰነዝሩ ይችላሉ ። ከዚህም ኣልፎ የዴሞክራሲው ወለል ከተነጠፈ በዴሞክራሲ የሚያምኑ ፓርቲዎች ከመጡ ማንም ተመረጠ ማን ይሄን ያህል ኣገር ሊጎዳ የሚችል ነገር ስለማይፈጠር ኣያሰጋም የሚል ሃሳባዊ የሆነ ኣመለካከትም ከሌላ ኮርነር ሊመጣ ይችላል።ይህ ኣባባል መልካምነትና ቅንነት ቢታይበትም ሳይንሳዊነት ስለሚጎለው ምን ያህል ሩቅ እንደሚሄድ ኣይታወቅም።

 

በሌላ በኩል ስለኮንስትቲየንሲ ስናወራ የሚመጣልን የምርጫ ኣቅማችን ብቻ ሳይሆን እነዚህ ቡድኖች ከመረጡስ በሁዋላ በዴሞክራሲ መርህ የመተዳደር ኣቅም ኣላቸው ወይ? በርግጥ ዴሞክራሲ የሚባለው ነገር ይህ ሰፊ ህዝብ ገብቶታል ወይ? ቡድኖች ወይም ክልሎች ሊባል ይችላል ዴሞክራሲን ለመተግበር ይችላሉ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችም ኣብረው ይነሳሉ። በዚህ በኩል ኢትዮጵያ በማጆሪቲው ጎኑዋ ስትታይ በርግጥ ኣቅም ሊያንሳት እንደሚችል ኣያጠያይቅም። ካላት የተማረ ሃይል እጥረት ችግር የተነሳ በመተግበሩ ጊዜ ከፍተኛ ችግሮች መታየታቸው ኣይቀርም። ይህም መራራ እውነት ቢሆንም መቀበል ነው።

 

እንግዲህ ኢትዮጵያ ያላት ገጽታ እንዲህ የሚታይ ከሆነ የሚያስፈራ ጥያቄ ይከተላል። ታዲያ ዴሞክራሲ ይቅርብን ወይ? ለዴሞክራሲ የምንበቃው በትምህርት በልጽገን ስንገኝ ብቻ ነው ወይ? የጀመርነው የዴሞክራሲ ትግላችንስ ምን ይዋጠው? ዴሞክራሲን ለመረዳት ያልቻሉ፣ ጽንሰ ሃሳቡን ለመተንተን ያልበቁ፣ ያልተማሩ ህዝቦች ባለማወቃቸው በጭቆና ስር እንዲቆዩ ሊፈረድባቸው ይገባል ወይ? ኢትዮጵያ በዚህ ተፈጥሮዋ እንዴት ነው ዴሞክራሲን ልታስተናግድ የምትችለው? የሚሉ መራራ ጥያቄዎችን እንድናነሳ ያደርገናል።

 

ኢትዮጵያ ብዙው ህዝቡዋ ኣልተማረም ወይም ኣቅም ያንሰዋል ማለት ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገር የላትም ማለት ኣይደለም። ኢትዮጵያ ከፍ ሲል እንዳልነው በከባድ ርቀት የሚሸቀዳደሙባት ኣገር ስትሆን የበራለት በቁጥሩ ኣነስተኛ ቢሆንም የተማረና ለምርጫ በሚገባ የሚበቃ ሃይል ኣላት። ይህ ሃይል በከተሞች ኣካባቢ የተከማቸ ሲሆን በገጠሩ ኣባቱና ወገኑ ዘንድ እንደ ተወካይ የሚታይ በዚህ በገጠሩ ወገኑ ላይ ከባድ ተጽእኖ ያለው ነው። ገበሬው የተማረውን ልጁን ያምናል። ሳይታደል ቀርቶ ባይማርም በትምህርት ኣጥብቆ ያምናል። በተለይ የሰሜኑ ገበሬ በስነ- ቃሉ “የተማረ ይግደለኝ” እያለ እያዜመ ለተማረ ወገኑ ያለውን እምነት ሲገልጽ ይኖራል።

 

ያልተጻፈ ስምምነት ቢሆንም ይህ ኣርሶ ኣደርና ኣርብቶ ኣደር በምርጫ ጊዜም በእጃዙር ለዚህ ለተማረው ወገኑ ውክልና የሰጠ ሁሉ ይመስላል። እዚህ ላይ ኣንድ ጊዜ የሰማሁትን ማንሳት ለሃሳቡ ማሳያ ይሆናል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ መለስ ዜናዊ ኣንድ ጊዜ በቤተ መንግስታቸው የኣዲስ ኣበባ የኒቨርሲቲ ምሁራንን ሲያነጋግሩ ኣንድ ምሁር ያሉት ኣይረሳኝም። እኚህ ምሁር ለእረፍት ጊዜ ወደ ገጠር ዘመዶቻቸው ሲሄዱ የዚያ ቀበሌ ህዝብ የሚያናግራቸው እና የሚጠይቃቸው እንደ መንግስት ተወካይ ኣድርጎ ነበር። ችግራችንን ኣሳስቡልን፣ መንገድ ስሩልን፣ ወዘተ ይጠይቁ ነበር ማለት ነው። እነዚህ ወገኖች የኣቶ እከሌ ልጅ ለትልቅ ትምህርት ኣልፎ ኣዲስ ኣበባ ነው ማለት በደመነፍሳቸው ያካባቢያቸው ተወካይ ኣይነት ነው።

 

እኒህ ሰው በሃሳብ ደረጃ የዚያ ኣካባቢ ተወካይ ናቸው ማለት ነው። እኚህ ምሁር በዚያ ኣካባቢ ህዝብ ምርጫ ላይ ከባድ ተጽእኖ ይኖራቸዋል። የሳቸው ምርጫ የዚህን ኣካባቢ ህዝብ ምርጫ በጅጉ ሊጫነው ይችላል። በምርጫ ጊዜ መተማመን የሌለው ገበሬ ከኚህ ሰው የሚያገኘው ምርጫ ለውሳኔ የማብቃት ሃይሉ ከፍተኛ ነው።

 

በቅንጅት ጊዜ ገበሬው ቅንጅትን የመረጠበት ኣንዱ ጉዳይ የልጆቹ ተጽእኖ ነበር።የኣንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳይቀሩ ከኣስተማሪዎቻቸው የሰሙትን ለወላጆቻቸው ሲነግሩ፣ ሲያስረዱ፣ያልተማረው ገበሬ በዚህ በኩል ልጆቹን ይሰማና ያምን ነበር። ዩኒቨርሲቲ ኣካባቢ ያሉ ወጣቶች በቅንጅት ልባቸው እንዳረፈ የተረዱና እነሱም በተወሰነ ደረጃ የገባቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ምርጫቸው የሆነው ቅንጅትን እንዲመርጡላቸው ቤተሰቦቻቸውን ዘመዶቻቸውን ተጭነው ነበር። ይህ ሁኔታም ቅንጅት በሰፊው ገበሬ ዘንድ ተመራጭ እንዲሆን ኣድርጎታል። ኣንዲት እድሜዋ ለምርጫ ያልደረሰ ልጅ ኣያቱዋን በስላሴ ኣስምላ እስከ ምርጫ ጣቢያ ድረስ መርታ ሄዳ ቅንጅትን እንዲመርጡላት ኣድርጋ እንደነበር ሰዎች ሲያወጉ ሰምቻለሁ።

 

እውነተኛ ምርጫ በኢትዮጵያ ቢመጣም መረጃው ከበራለት ትውልድ ሄዶ ሰፊውን ህዝብ በውዴታ እጁን ይዞ የሚያስመርጥበት ሁኔታ ነው እኛ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ በእጃችን ያለን ሃብት። ይህ ሂደት የዴሞክራሲን መስረታዊ ትምህርት ይጥሳል ኣይጥስም ኣንከራከርም። በመጀመሪያ ደረጃ ያ ብዙው ለምርጫ መረጃ የሌለው ወይም መረጃን ለመተንተን ኣቅም የሌለው ህዝብ በክፉ ተጽእኖ ሳይሆን በፈቃዱ የልጆቹን ምክር ሰምቶ መምረጡ ኢዴሞክራሲያዊ  ሂደት ግን ኣይደለም።ልጆቹ በሚገባ ቋንቋ ኣቅለው ኣስረድተውትም  ነው ብለን ለጠየቀንም እንመልሳለን።።

 

ዋናው ነገር መሆን ያለበት ኢትዮጵያ እንደ ሃገር የመምረጥ ኣቅም የላትም ተብላ ምርጫ ልትከለከል ከምርጫ ልትከላ ኣትችልም። የበራለት ትውልድ ሃይሉዋ ነውና። የዚያ ምሁር ፍርሃት ፋክቶችን ኣጥብቆ የያዘ ቢሆንም ያላየው የዴሞክራሲ ተፈጥሮም ኣለ። ዴሞክራሲ የሚወለድ፣ የሚያደግና የሚያደግ ነገር ነው። ኣሁን የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጥያቄ ዴሞክራሲ የትም ይሁን የት ተወልዶ ኣድጎ የጎለመሰውን ኣምጡልን ኣይደለም። ኣገራችን ይወለድ እና እናሳድገው ነው ጥያቄያችን። ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ኣጥብቃ እንድትፈልግ የሚያደርጋት ምክንያት ብዙህ ተፈጥሮዋን ለማስተናገድ ስለሚረዳት ብቻ ሳይሆን ለማህበራዊ ለውጥ ጎዳናዋ ኣዋጩ መስመር እሱ ሆኖ ስለሚታያትም ነው።

 

ቡድኖች ምርጫን ብቻ ሳይሆን ከምርጫም በሁዋላ ዴሞክራሲን ለመተግበር ልምምድ ውስጥ ስለሚገቡ የቡድኖች ኣቅም ማነስ ዴሞክራሲን ሊከለክላቸው ኣይችልም። መንግስት ሲባልም ፓርቲ ማለት ባለመሆኑ በመንግስት ሲስተም ውስጥ ያሉ የተማሩ ኣቅም ያላቸው ኣቅም የሌላቸውን የፖለቲካ ተወካዮች እየደገፉዋቸው ስለሚሄዱ በዴሞክራሲ የእድገት ጎዳና ላይ ይገባሉ።

 

እንግዲህ በዚህ በምርጫ በኩል በተለይ ኣሁን ኢትዮጵያ ባላት የመምረጥ ሃይል ዴሞክራሲን በእንዲህ ኣይነት ሁኔታ ኣስተናግዳ ማደግ የምትችል በመሆኑዋ መራጭ ቡድኖች ኣቅም ያንሳቸዋል ተብሎ ዴሞክራሲን ልትነፈግ ኣይገባትም።

 የፕሬስ ነጻነትን የ ማስተናገድ ኣቅም ኣለን ወይ?

Eskinder Negaበሁለተኛ ደረጃ የዴምክራት ሃገርነት ኣንዱ ተግባራዊ መገለጫ ፕሬስን መሸከም መቻል ነው። ዴሞክራሲ ምርጫ ብቻ ሳይሆን የፕሬስ ነጻነትን ማስተናገድም ኣንዱ ዋና መስፈርት ነው። በዚህ በኩል ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ኣማራጭ መረጃዎችን በመፈለግ በኩል ከባድ ጥማት እንዳለ ይታያል። ህዝቡ በተለይም ይህ የበራለት ትውልድ የምንለው ኣማራጭ መረጃዎችን በጥብቅ መፈለጉ ብቻ ሳይሆን ይዘታቸውንም የመመዘን ኣቅም ኣለው። በኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬስ ነጻነትን መሸከም ሲያቅታቸው የሚታዩት የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው። መንግስት ትልቁን ድርሻ ይውሰድ እንጂ ራሳቸው ለዴሞክራሲ ቆመናል የሚሉቱ ፓርቲዎችም ሰፊ ልብ ኣይታይባቸውም። በሁለቱም በኩል ጥብቅ ወሰን የተሰመረ ሲሆን ኣንዳንድ በመርህ ላይ ያተኮሩ ኣስተያየቶች ለሃገር የሚጠቅሙ ትችቶች ሁለቱም ወገን ሜዳ ላይ እየጣላቸው ሊቀሩ ይችላሉ።

 

ፕሬሱ ችግር ያለበት ከመንግስትና ከ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን ከራሱም በርካታ ችግሮች ኣሉበት። እውነተኛ መረጃን ማቅረብ የሃገሪቱን የዴሞክራሲ ትግል ያፋጥነዋል የሚለው እምነቱ ዝቅ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ዘለፋዎችና በመርህ ላይ ያላተኮሩ እንካ ሰላንታዎች ኣንጀቱን የሚያርሱት ይመስላል።ኣንባቢው ወይም ኣዳማጩም ለ ዴሞክራሲና ለፍትህ መቆሙን የሚያይለት በዚህ ምት (tone) ሲቀርብ ነው ብሎም ያመነ ይመስላል።

 

ታዲያ ፕሬሱ ብዙ ችግሮች ቢኖሩበትም ከፍተኛ ኣስተዋጻኦም ኣለው። ኣንዳንድ የበሰሉ ሚዲያዎች የሚያቀርቡት መረጃ ሊበረታታ ይገባዋል ይህም ዴሞክራሲ እንዲያደግ ኣስተዋ ፆ ኣለው ።

 

ዋናው ነገር ዴሞክራሲ የሚያድግ ነገር ነው ስንል ፕሬስ የሚያደግ ነው ማለታችን ነው። ፕሬስ የሚያደግ ነው ስንል ደሞ የፕሬሱ መረጃ የማቀበል ኣቅሙ ማደግ ብቻ ሳይሆን የመንግስትና የፓርቲዎች ትእግስትና ቀናነት ማደግንም ይጠይቃል።

 

 

መንግስት እንደ ዘበኛ (watchDogs) ያሉትን ጋዜጦች ወይም ሚዲያዎች እነዚህ መንግስት ጥሩ ሲሰራ ጥሩ ሰራ የማይሉ መጥፎ ሲሰራ ብቻ መጥፎውን የሚያጩሁ ናቸው እያለ ይከሳቸዋል። እነዚህ ሚዲያዎች እኮ  ጠባቂዎች (watchDogs)  ናቸው። ተፈጥሮኣቸው ይሄ ነው። በኣንድ በኩል ኢ-ፍትሃዊነት ሲፈጸም ወይም ዝርፊያ ሲፈጸም ይጮሃሉ እንጂ መንግስት ኣንድ ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ኣስፋልት ሲያነጥፍ ይህን ሰርቱዋልና ይጨብጨብለት ማለት ኣይጠበቅባቸውም።ተፈጥሮኣቸውም ኣይደለም። ይልቅ መንግስት የነሱን ጩኸት እንደ  እድል እያየው ቶሎ ጉድለቶቹን ሊሞላ ይገባው ነበር።

 

ዋች ዶግስ የማይፈሩና የማይወግኑ መሆን ኣለባቸው። ለዴሞክራሲ ትግል የቆሙትን እየታገልን ነው የሚሉትን ሁሉ ትግሉን የት ኣደረሳችሁት? ብለው ኣጥብቀው መጠየቅ ኣለባቸው። ለዴሞክራሲ ትግል የጀመሩ ቡድኖች ትግል ከጀመሩ ኣመታት ኣስቆጥረው ብዙ ፍሬ ሳይታይባቸው ሲቀር “እየተደራጀን ነው፣ ድርጅታዊ ኣቅማችንን እያጠናከርን ነው…” ሲሉ ይደመጣል። እንደው የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሆነ ኣዙሪት ውስጥ ገብቶ ነው እንጂ የኢትዮጵያን የነጻነት ትግል በሚታይ መልኩ ለመጀመር ይህን ያህል እነሱ በሚያወሩት ልክ መደራጀት ኣያስፈልገውም። ይህ መንግስት የሚወድቀው በድርጅታዊ ጥንካሬ ሳይሆን በህዝባዊ ኣመጽ ነው። ይህን ህዝባዊ ኣመጽ ለመምራት ደሞ ህዝቡን ሁሉ ኣባል ኣድርገን መዝግበን መጨረስ ኣለብን እያልን በወረቀት ስራ መድከሙ ምንም ዋጋ የለውም። እውነተኛ የሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች መመስረታቸውን ሲያበስሩና ጥቂት ሲራመዱ ኣብዛኛው ነጻነት የናፈቀው ህዝብ በሃሳብ ደጋፊና ኣባል ነው የሚሆነው። ተመዝግቦ ኣክቲቭ ፖለቲከኛ መሆን ሳይሆን ኣድርግ የሚባላውን ለማድረግ በሚቀይሱት የትግል ስልት ዋጋለመክፈል የቆረጠ ነው።

 

መቼም ያ የቅንጅት ጊዜ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ብዙ ትምህርት ጥሎ ነው ያለፈው። በዚያን ጊዜ የነበረው የቅንጅት ጥንካሬ በቅንጅት ጽ/ቤቶች ጥንካሬ ኣልነበረም። ህዝቡ ራሱ ራሱን እንደ ቅንጅት መሪም እንደ ኣባልም እያየ ነበር ሲንቀሳቀስ የነበረው። የቅንጅት ጽ/ ቤት ሳያውቅ ቅንጅትን የሚደግፉ ስብሰባዎች ሁሉ ተዘጋጅተው ተካሂደው እንደነበር ይነገራል።

 

ትንሽ የታመኑና በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ርእዩት ይዘው የተነሱ ሰዎች በትንሽ ሃይል ህዝባዊ ትግል መምራት የሚችሉበት ሁኔታ ነው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው። ኣይ የለም ሴል እየፈጠርን ብዙ ኣባል ማፍራት ኣለብን የሚል ትምህርት ጠቅላላ እውነት ብጤ ያለው ቢመስልም ተግባራዊ ኣይደለም። ኣሁን ያለው የኢትዮጵያ ትግል የፖለቲካ ሳይሆን የነጻነት ትግል በመሆኑ ህዝቡ ተፈጥሮኣዊ በሆነ መንገድ ተዘጋጅቱዋል። ይህን የተዘጋጀ ኣካል እንዲህ ኣድርግ ወደማለት ደረጃ መራመድ ነው እንጂ ድርጅታዊ መዋቅር ላይ ጊዜ ማጥፋት የ ኣርባ ቀኑን ጉዞ ኣርባ ኣመት እንዲፈጅ ነው የሚያደርገው።

 

ኢህኣዴግን የሚጥሉት በድርጅታዊ ብቃት ሳይሆን በህዝባዊ ኣመጽ ነው ስንል መደራጀት ኣያስፈልግም ወደማለት እንዳይተረጎምብን። መደራጀት ያስፈልጋል:: ግን ኣሁን በሚባለው ደረጃ ይሄን ያህል ህዝቡን ኣንድ ላምስት እያደረግን ኣደራጅተን ሳንጨርስ ይህ መንግስት ኣይወድቅም ማለት ከዚያ ከኢህኣፓ ኣካባቢ የመጣ ትምህርት ሊሆን ይችላል። ቅድም እንዳልነው ኣሁን ያለው የኢትዮጵያ የነጻነት ትግል በእንዲህ ያለ መልኩ ሳይሆን የታመኑ ድርጅቶች በሚጠቁሙት ኣቅጣጫ መሄድ የሚችል ህዝባዊ ትግል ነው ያለው። ህዝቡን በሴል እያደራጁ ቢቆዩ ማሌሊት ኣያስጠኑት፣ወይ ደሞ ስለዴሞክራሲ ወይም ስለ ነጻነት ጥቅም ኣያስተምሩትም። የነጻነት ታጋዮች እንደመሆናቸው ፖሊሲም የላቸውም። በመሆኑም ፊገር የሆኑ መሪዎቻችን የሆነ የህዝባዊ ኣመጾችን እያሳዩ ትግል ማስጀመር ነው እንጂ በሃሳብ ኣባል የሆናቸውን ሰው ሁሉ መዝግበን ካልጨረስን እያሉ ዘክዘክ ማለት የትም ኣያደርሰንም።

 

ዎች ዶግ እነዚህን የፖለቲካ መሪዎች እንዲህ መጠየቅ ማፋጠጥ ኣለበት።  የተቃዋሚ መሪዎችን ሁሉ ኣንዴ ቢጮህባቸው እንደ ወያኔ ደጋፊ ቶሎ መታየት የለበትም። እንዲህ ከሆነ መቼም ኣናድግም።

 

በኣሁኑ ሰኣት መንግስት እሱ የሚፈልጋትን ነቀፌታ ብቻ በኣንዳንድ ጋዜጦች ላይ ብቅ እያደረገ ዴሞክራት ነኝ ለማለት ሲሞክር ይታያል። ጠንከር ያሉ ሂስ የሚያቀርቡትን፣ የሚያጋልጡትን ሁሉ ኣባሮ ጨርሶ የኣለምን ሪከርድ ሰብሩዋል።

 

የተባረሩ ጋዜጠኞች ደሞ በግፍ ስለተባረሩ ከሃገር ሲወጡ የኣክቲቪስት ስራና የኣድቮኬሲ ስራ ወዲያው ተቀብሎ ስለሚውጣቸው ለዴሞክራሲ ቆመናል የሚሉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ምንም ሳንካ እንደሌላቸው እያደረጉ እያቀረቡ መንግስትን ላለማስደሰት ይሞክራሉ። ወይ በሚስጥር የፖለቲካ ድርጅት ኣባል ይሆኑና የዚያን ፓርቲ ችግሮች ለመጠቆም ሃይል ያጣሉ።  ዞሮ ዞሮ እውነተኛ መረጃ፣ ሚዛናዊ መረጃ የሚናፍቀው ህዝብ ከመንግስትም ኣያገኝም የተገፋውም ጋዜጠኛ የነጻነት ታጋይ ስለሚሆን ሚዛናዊ ዘገባ ለማግኘት ይከብዳል።

 

በኣጠቃላይ ግን ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ፕሬስን ለመሸከም ትከሻዋን ኣስፍታ፣ ተቃዋሚዎችም በኛ ላይ ሂስ የምንፈልገውና የፕሬስን ነጻነት ሙሉ በሙሉ የምናከብረው እኛ ስልጣን ስንይዝ ነው ኣይነት ሳያስቡ ፕሬስን ማሳደግ ኣለባቸው።

 

ተወልጄ ባደኩበት ኣካባቢ ባህርና ለዋና የሚሆን ውሃ የሌለበት ኣገር በመሆኑ ዋና ሳለምድ ቀረሁ። ኣሁን እዚህ ባለሁበት ኣገር ኣንድ ቀን እስቲ ዋና ልማር ብየ በስተርጅና ወደ መዋኛ ቦታ ኣመራሁ። ትጥቄን ኣታንሱ። እነዚህ ዋና የሚችሉ ሰዎች እንደሚለብሱት ሆኜ ገባሁ። ውሃው ውስጥ ስገባ የማየው ሁሉ ይዋኛል። ውሃውን ሳያስጨንቁ መሰስ እያሉ ይዋኛሉ። እኔ ትንሽ ልጅ ነው የሆንኩት። ሳንቦጫርቅ ሳንቦጫርቅ ዋልኩ። ከጎኔ ኣንዱ  “ኣይዞህ በርታ ሳያንቦጫርቅ የለመደ የለም” ኣለኝ።

 

ፕሬስ እንደዚህ ነው። በመጀመሪያዎቹ ኣካባቢ ማንቦጫረቅ ሊኖር ቢችል ኣይገርምም። ቀስ እያለ እስኪያድግ ድረስ ትእግስት ያስፈልጋል። በኣጠቃላይ ህዝባዊ ጥማት ያለው በመሆኑ ፕሬስ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊወለድና ሊያድግ የሚችል በመሆኑ ኢትዮጵያ ኣሁን ዲሞክራሲ ይቅርብሽ  ሊያስብላት ኣያስችልም።

 

ወደሁዋላ ታሪካችንን ስናይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እንዳሉት ኣዝማሪዎች ነገስታቱን በ ስነ- ጥበባቸው ይነቅፉ ነበር። መንቀፍ ብቻ ኣይደልም ይመክሩ የህዝቡንም ብሶት ጠቆም ያደርጉበት ነበር። ይህ ዳራ ያላት ኣገር ዴሞክራሲ ነጻነት በጎለበተበት ኣለም ፈጥና በዚህ የዴሞክራሲ መስመር ልታድግ በርግጥ ትችላለች።

 

መድብለ ፓርቲን የማስተናገድ ኣቅም ኣለን ወይ?

 

ይልቅ ኢትዮጵያ ሊያሳስባት የሚገባው ይሄ ነው። የሃገራችን ብዙው ህዝብ ዴሞክራሲ የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ባይረዳም ግን መብቱ እንዲከበር፣ ከዴሞክራሲ ፍሬዎች ሊመገብ መፈለጉ ምርምር የሚሻ ኣይደለም። የሰው ልጅ ሁሉ ልማትን ዴሞክራሲን ይፈልጋል። በመሆኑም የሚያሳስበው ዴሞክራሲን የሚሸከም ህዝብ ኣለን ወይ የለንም ሳይሆን መድብለ ፓርቲ ስርኣት ስንጀምር ሃላፊነት የሚወስዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጨዋታው ሜዳ ላይ በደንብ ይጫወታሉ ወይ? ይሄ ሃብት ኣለን ወይ? የሚለው ጥያቄ ነው። ።

 

የመድብለ ፓርቲ ስርኣት መቻቻልን፣ መሸነፍና ማሸነፍን የመቀበል ኣቅም ይጠይቃል።ይሄ በተግባር ታይቶ ኣስተያየት የሚሰጥበት ቢሆንም ኣሁን ያሉንን የፖለቲካ ፓርቲዎች ቁመና በሩቁ ስናይ መስተካከል ያለባቸው የኣቅም ማነስን የሚያሳዩ ብዙ ጉዳዮች ኣሉ።

 

ኢህኣዴግን ከዚህ እናውጣው። ምክንያቱም በባህላዊ ቡድን ፖለቲካ የሚያምን የመድብለ ፓርቲ ኣማኝ ስላልሆነ። በኣሁኑ ሰኣት በኢህኣዴግ  ጉያ  የሚፈለፈሉት የወንዝ ተቆርቋሪዎች ብዙ ስለሆኑ ይህ መንግስት የመድብለ ፓርቲ ኣራማጅ ሊያሰኘው ኣይችልም። የዚህ መንግስት እውነተኛ ተፈጥሮው ቡድኖች የየራሳቸውን የወንዝ ተቆርቋሪ ድርጅት እንዲያቋቁሙ ያበረታታል እንጂ በፖሊሲ ብልጫ ሃገር ለመምራት የሚፎካከሩ ድርጅቶችን ኣያፈራም። እውነተኛ ተፈጥሮው የኣንድ ፓርቲ ኣገዛዝን ማስፋፋት ነው። ኢትዮጵያ ኣንድ ብሄር ብቻ ብትሆን ኖሮ ኣንድ የፖለቲካ ድርጅት ብቻ ለማቋቋም የሚሻ ተፈጥሮ ያለው ነው የሚመስለው። ስለዚህ እሱ ከጨዋታው ይውጣና ሌሎቹ በርእዮት የሚያምኑቱን ብቻ ብናይ እነሱም የመግባባትና የመቻቻል ችግር ኣለባቸው።

 

ኢትዮጵያ ያለምንም የጎላ ርእዮት ልዩነት ብዙ የፖለቲ ፓርቲዎች ያሉዋት ኣሁንም በመመስረት ላይ ያሉባት ኣገር ናት። ይህ የሚያሳየው ተቻችሎ የመኖር ክህሎት ማነስ መሰረታዊ የሃገር ችግሮች ላይ ከማተኮር ይልቅ በየፊናው መሮጥን ያሳያል። ምንም ወይም ትንሽ ልዩነትን ይዞ ኣዳዲስ የፖለቲካ ድርጅት ማቆሙ ለምን ያስፈልጋል? በተለይ በኣሁኑ ሰኣት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን እንድትጀምር በሚፈለግበት ሰኣት ልዩነትን ኣቻችሎ መዋሃድ ስለምን ከባድ ስራ ሆነ?

 

ጋና ውስጥ ዴሞክራሲ በተሻለ መልኩ እየሄደ ወይም እየተስተናገደ ያለው ጋና ከኢትዮጵያ ብዙ የሚርቅ ነገር ስላላት ኣይደለም። የጋና ብዙሃን ዴሞክራሲን ለመረዳት ወይም ቅድም ያልነው ነገር ጋና የተዋጣለት ኮንስትቲየንሲ ስላላት ኣይደለም። ዴሞክራሲ መልካም ጅማሮን እያሳየ ያለው በ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ ብቃት ይመስላል። ተቻችሎ መኖር፣ መሸነፍንና ማሸነፍን መቀበል፣ ህግመንግስቱን ማክበር የቻሉ ይፖለቲካ መሪዎች ስለተገኙ ነው። ኢትዮጵያ ከጋና የምትማረውም ይህንን ነው።የተሻሉ የበሰሉ ታማኝ የፖለቲካ መሪዎች በሃገራችን ዴሞክራሲን ሊያስጀምሩ ሊያራምዱ ይችላሉ።

 

ዴሞክራሲን ተቋማዊ (institutionalized) ማድረግ

timthumb

ሌላው ዴሞክራሲን የማስተናገድ ኣቅም የሚገለጸው ደሞ ዴሞክራሲን ተቋማዊ (institutionalized) በማድረግ ነው። ዴሞክራሲ ሶስት የእድገት ደረጃዎች ኣሉት ኣንበል። ኣንደኛው መወለድ ሲሆን ይህም ህዝቦች ዴሞክራሲ ያስፈልገናል ሲሉ ያምኑና ዴሞክራሲን የሚያጠነክርና ሰባዊ መብትን የሚያከብር ህገ መንግስት ያረቃሉ ያውጃሉ( claim ያረጋሉ) ። ማርቀቅ ብቻ ሳይሆን መራመድም ኣለባቸውና ሲስተም ይቀርጻሉ። የተጠያቂነት፣ ግልጽነት ወዘተ. ኣሰራሮችን ይነድፋሉ። በዚህ ጊዜ ዴሞክራሲ ተወለደ ሊባል ይችላል:: ማወጅ በራሱ ዴሞክራሲ ተወለደ ሊያስብለው ኣይችልም። ያለማችን ኣንደኛ ኣምባገነን የሰሜን ኮርያው መሪ ኣገሩን ዴሞክራሲያዊ ህዝብ ሪፐብሊክ ኮርያ (Democratic People’s Republic of Korea) ብሎ ነው የሚጠራት፣ መንግስቱ ሃይለማርያምም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ…. ብሎ ነበር የሚጠራት::

 

ሁለተኛው የዴሞክራሲ የእድገት ደረጃው ተቋማዊ የመሆን ደረጃው ነው። ዴሞክራሲን በኢትዮጵያ ውስጥ ተቋማዊ ማድረግ ማለት መንግስት ከነዚህ ተቋማት ጣልቃ መግባቱን ማቆሙ ብቻ ኣይደላም። መንግስት ጣልቃ መግባቱን እንዳቆመ ዴሞክራት ኣይሆኑም። ዴሞክራት የሚያደርጋቸውን የኣሰራር ሲስተም በማዳበር ነው ወደ ዴሞክራሲ እያደጉ ዴሞክራሲ ባህላቸው እየሆነ እንዲመጡ የሚደረገው።

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ቅድም ያልነው የቡድኖች ኣቅም ማነስ በዚህ እድገት ላይ ኣሉታዊ ተጽእኖ ኣለው። ክልሎች ቀበሌዎች ካላቸው ኣቅም የተነሳ ዴሞክራሲን ሙሉ በሙሉ ላይተገብሩት በህገ መንግስቱ ላይ ያለውን በሙሉ ላይረዱት ይችላሉ። ይህ ማለት ግን መጀመር ኣይችሉም ማለት ኣይደለም። በመሆኑም በኢትዮጵያ ተቋማትን ለመገንባት ኣሁን በቂ ኣቅም የለንም እና ዴሞክራሲ ይሰንብት ማለት ኣይቻልም።መቼ ተጀምሮ እንደግ ታዲያ?

 

መንግስት ለስሙ ያልተማከለ ስልጣን (power decentralization) ዘርግቻለሁ ቢልም ግን ደሞ በውስጠ ተዋዋቂ ስልጣንን ኣምክሎ ይዞ ተቋማቱን በልጓም ጠፍሮ ይዞ ይታያል:: በተለይ እነዚህ ስድስት የዴሞክራሲ ተቋማት እንደ ፍርድ ቤት፣ ባንክ፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ወታደር፣ፖሊስና ሚዲያ መንግስት ኣሁን ኣቅም የላቸውም በሞግዚት ኣሳድጋቸዋለሁ የሚለው ኣሳቡ  ከባድ ስህተት ነው። መንግስት ይህንን ለማለት ማን ነው እሱ? ራሱ መንግስት የህብረተሰቡ ውጤት ሆኖ እነዚህ ተቋማት ያጡትን ችሎታ እሱ ከየት ኣገኘው? ሁላችን ያንድ ሃገር ልጆች ተቀራራቢ የሆነ የማሰቢያ መንገድ ያለን ካንድ ምንጭ የጠጣን ሆኖ መንግስት ልክ የተለየ ሃላፊነትና ችሎታ በድብቅ እንዳለው ኣይነት የእነዚህን ተቋማት ሃይል ገፎ መኖር ኣግባብ ኣይደለም።

 

ዴሞክራሲ የእድገቱ መጨረሻ ተቋማዊ መሆኑ ኣይደለም። ኣገራት ዴሞክራሲን በተቋሞቻቸው እያዩ ወደ ሶስተኛው እድገት ካላለፉ ወደ ሁዋላ የመመለስ እድል ይኖራቸዋል። የዴሞክራሲ ከፍተኛው እድገት ደረጃና የማይቀለበስበት ደረጃው ዴሞክራሲ ባህል ሲሆን ነው።

 

ዴሞክራሲን ባህልማድረግ

 

ዴሞክራሲ ባህል ሆነ ስንል በ መስሪያቤቶች የኣሰራሩ ዘየ በ ዴሞክራሲ መርሆዎች ላይ ተቃኝቱዋል ብቻ ሳይሆን በዜጎች የእለት ከእለት ህይወት ውስጥ መግባቢያ “ቋንቋ” ሲሆንም ነው። ዜጎች የራሳቸውን መብትና ግዴታ ሲያውቁ፣ የሌላውን የፖለቲካ ኣመለካከት፣ሃይማኖት ባህል፣የቆዳ ቀለምና ዘር፣ ታለንትና እውቀት ማክበርና ማድነቅ ሲጀምሩ ዴሞክራሲ ለማ ወይም ኣይቀለበስም ሊባል ይችላል።ዴሞክራሲን በተቋም ደረጃው ኣሳድገው ነገር ግን ባህል ያላደረጉ ህዝቦች ከፍ ሲል ያነሳነውን የግለሰብ ልዮነት(individual difference) በሚገባ የማያከብሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ቀስ እያሉ ከነዚያ ተቋማት ከሚያገኙት ኣገልግሎት እየተማሩ ባህላቸው እያደረጉት ይመጣሉ።

 

ዴሞክራሲ ኣያስፈልገንም ከኛ ባህል ጋር ኣይሄድም የራሳችን ባህል ኣለን በሱ እንተዳደራለን የሚሉ ግለሰቦች የሚኖሩ መሆኑ ቢታመንም እንደ ህዝብ ግን ዴሞክራሲን ባህሉ ለማድረግ የማይፈልግ ህዝብ ይኖራል ብሎ ማመን ይከብዳል።

 

ምእራባውያን በድሮው ጊዜ የራሳቸው ባህላዊ ኣስተዳደር ባህላዊ ኣሰራር ነበራቸው::በባህልም የበለጸጉ ናቸው።። ወደ ዴሞክራሲ ሲያድጉ ኣንዳንዶቹ ባህላዊ ኣስተዳደራቸውን ባህላዊ ይዘት ብቻ እንዲኖረው እያደረጉ ስልጣን ከእጁ ኣውጥተው ለዴሞክራሲ እየሰጡ ተቋሞቻቸውን የዴሞክራሲ ባህል ኣስይዘዋል። ዴሞክራሲ የ የዚህኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጆች ኣድገት ጥበብ (ART) ነው። በሌላ ኣገላለጽ የዚህ ዘመን ህዝቦች ባህል ነው። የድሮ ባህሎች የተፈጠሩት በእግዚኣብሄር ሳይሆን በቀደሙት ትውልዶች ሲሆን የዚህኛው ክፍለ ዘመን  ትውልድ ደሞ ንቃተ ህሊናው ራሱ የፈጠረው ባህል ነው ዴሞክራሲ ማለት።

 

በቅርቡ ተነስቶ የነበረው የ ኣረብ ስፕሪንግ ለዚህ ኣሳብ ዋቢ ነው። የኣረብ ህዝቦች ዴሞክራሲንና ሰባዊ መብት መጠማታቸውን ለኣለም ኣሳይተዋል። ትግላቸው ፍሬ እያፈራ ነው ኣይደለም ሌላ ኣነጋጋሪ ጉዳይ ቢሆንም ግን ጥማቱ መኖሩን ህዝቡ ኣሳይቱዋል። ግብጾች ዴሞክራሲን ፍለጋ ኣስገራሚ ትግል ኣድርገው ሙባረክን ጥለው ወደ ድህረ ዴሞክራሲ ለመሄድ ሽግግር ላይ ያሉ ሲመስሉ ኣሁን ያለው ርምጃቸው ግን ኣያምርም። ግልጽ ኣይደለም። ወደ ድህረ ዴሞክራሲ መስመር ለመግባት የሚያስችላቸውን ስራ በሚገባ እየሰሩ ኣይመስሉም። ኣያርግባቸውና ባለፈው ጊዜ እንደተነሳው ኣይነት ኣመጻዎች ቢነሱ ኣቅጣጫቸው ሁሉ ግልጽ ላይሆን ይችላል። በሙባረክ ጊዜ ኣላማቸው ኣንድ ነበር ያም ሙባረክን ጥሎ የዴሞክራሲ ስርኣትን መጀመር ነው። ኣሁን ዴሞክራሲያዊ  ምርጫ ኣድርገው ከመረጡ በሁዋላ በፓርቲዎቹ ኣለመናበብ ዴሞክራሲ ሲዘገይ ህዝባዊ ቁጣ ቢነሳ ኣቅጣጫው ግልጽ ስለማይሆን የከፋ ሁኔታም ሊገጥማቸው ይችላል። ዲክቴተርን መጣል ብቻውን ለዴሞክራሲ የሚያበቃ ኣለመሆኑን ከነሱ እንማራለን። ግብጾች ኣሁን ወደ ድህረ ዴሞክራሲ መሄድ ካልቻሉ ችግራቸው የኮንስትቲየንሲ ማጣት ሳይሆን የፓርቲዎች ኣቅም ማነስ ተደርጎ ሊወሰድ ይችል ይሆናል።

 

ዋናው መነሻችን ኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ባህሉዋ ለማድረግ ርምጃ ለመጀመር ምንም የሚከለክላት ነገር ኣይኖርም ለማለት ነበር ። ዴሞክራሲን ባህላቸው ያደረጉ ህዝቦች መንግስቶቻቸውን በየኣጭር ጊዜው እየቀያየሩ ሲኖሩ የሚታመኑት የፖለቲካ ፓርቲዎቻቸውን ሳይሆን የዴሞክራሲ ባህላቸውን ነው። ዘመን የማይሽረው ንጉሳቸው ይህ የዴሞክራሲ ባህላቸው ሲሆን በምርጫ ህይወታቸው ኣልፎ ኣልፎ ኣስቸጋሪ መንግስት ሊገጥማቸው ይችላል። ይሁን እንጂ የዳበረ የዴሞክራሲ ባህል ስላላቸው ኣስቸጋሪ መንግስት ቢመጣባቸውም ዴሞክራሲ ሊቀለበስ ኣይችልም።

 

ጉዞ ከመልካም ኣስተዳደር ወደ ዴሞክራሲ ቢሆንስ?

 

ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን እንዲሁ ብዙ ኣዳጊ ኣገሮች ዴሞክራሲን ለማስተናገድ ኣቅም ሊያንሳቸው ይችላል። በዚህ ጊዜ ኣንዳንድ ምሁራን ዴሞክራሲ በመልካም ኣስተዳደር ሞግዚት ስር ቆይቶ ቀስ እያለ ቢያድግ ይሻላል ኣይነት ሊያስቡ ይችላሉ።  እነዚህ ሰዎች የሚመክሩን ዝም ብላችሁ የኢኮኖሚ እድገታችሁ ላይ ኣተኩሩ፣ መንግስትም  መልካም ኣስተዳደርን   ያመጣል ኣይነት ነው። በዚህ ኣገባብ መልካም ኣስተዳደር ሲባል የዜጎች የመምረጥ መብት የሌለበት ነገር ግን የተሻለ ፍትህና ኣገልግሎት ማግኘት ነው።

 

መቼም እኛ ተራ የሆንን ሰዎች ዴሞክራሲን ከምርጫ ጀምሮ የምንፈልገው ምን ኣልባት ኣንድ ቀን እኔም ፕሬዚዳንት ልሆን እችላለሁ ብለን ቀቢጸ ተስፋ ይዞን ኣይደለም። ምርጫ የምንፈልገው የዚህ ዘመን ፍላጎታችን ዳይናሚክ በመሆኑ ዳይናሚክ ለውጦችን ለማየትና ለመለማመድ ስለምንፈልግም ነው። በየኣጭር ጊዜው መምረጣችን የሚጠቅመን ለመመረጥ የሚሹ ፓርቲዎችን ስለሚያነቃቃልን፣ የ ፈጠራ ሃሳብ ለማምጣት ሃይል ስለሚሆናቸው ነው።በዚህም ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችንን ቶሎ ቶሎ ለምፍታት፣ የተሻለ ህይወት ለመኖር ስለሚረዳን ነው። ከሁሉ በላይ ግን መልካም ኣስተዳደርን ለማስፈን ፈቃደኛ የሆነ መንግስት ምርጫን እንቢ የማለት ፍላጎቱ ዝቅተኛ ነው። በሌላ በኩል ደሞ ያለ ዴሞክራሲ መልካም ኣስተዳደር ዋስትና ኣይኖረውም። የመልካም ኣስተዳደር ዋስትናው ዴሞክራሲ ነው። በመሆኑም ማደግ ያለብን ዴሞክራሲን ጀምረን ራሱ ዴሞክራሲ እየመራን ወደ መልካም ኣስተዳደር እናድጋለን እንጂ ምርጫን ጠልቶ ወይም ስልጣን ወዶ መልካም ኣስተዳደርን ሊያመጣልን ይችላል የሚል እምነታችን በጣም ዝቅ ያለ ነው።በመሆኑም ይህ ጉዞ ዋስትና የሌለው በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ልንታለል ኣይገባንም። ዴሞክራሲን ከነሙሉ ትጥቁ ጀምረን እየተማርን እናድጋለን።

 

እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

ኣስተያየት ካለዎ እነሆ ኢሜይል ኣድራሻየ

geletawzeleke@gmail.com

↧
↧

በፌደራል መ/ቤቶች ዝርክርክነቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል (ሪፖርታዥ)

$
0
0
በፌዴራል መ/ቤቶች
 
-   ወደ 1.4 ቢሊየን ብር አልተወራረደም
-   በ30 መ/ቤቶች 353.6 ሚሊየን ብር ደንብና መመሪያን ያልተከተለ ግዥ ተፈጽሟል
-   በ9 መ/ቤቶች 3.5 ቢሊየን ብር ባልተሟላ ሰነድ ወጪ ሆኗል፣3.2 ቢሊየን ብሩ የመከላከያ ወጪ ነው
-   በ27 መ/ቤቶች ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ ብር 212.5 ሚሊየን ተጠቅመዋል
ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ

ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ

የፌዴራልና ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2004 በጀት ዓመት በፌዴራል መንግስት መ/ቤቶች የኦዲት ሥራ አከናውኗል። በትላንትናው ዕለት ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ 58 ገጽ የያዘውንና በ116 የፌዴራል መንግስት ባለበጀት መ/ቤቶችና በ283 የወረዳና ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤቶች ላይ መ/ቤታቸው ያካሄደውን የኦዲት ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አቅርበዋል። በዚህ ሪፖርት ውስጥ የተጠቀሱ ዋናዋና ግኝቶች እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርበዋል።
በፌዴራል መንግሥት የልዩ ልዩ መ/ቤቶች
የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት ወቅት የታዩ ዋና ዋና ግኝቶች
መ/ቤታችን ምክር ቤቱ ያፀደቀው በጀት የፋይናንስ አስተዳደር ሕጉ፣ ደንብና መመሪያ በሚፈቅደው መሠረት በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ በ2004 በጀት ዓመት ሂሳብ ላይ ባከናወነው ኦዲት በርካታ የሂሳብ አያያዝ ግድፈቶች እና የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶች፣ እንዲሁም አፈፃፀማቸው ከደንብና መመሪያ ውጪ የሆኑ ሁኔታዎች የተገኙ ሲሆን፤ የም/ቤቱን ትኩረት ሊያገኙ ይገባል ተብሎ የታመነባቸው አንኳር ግኝቶች ብቻ ተለይተው እንደሚከተለው ቀርበዋል።
የጥሬ ገንዘብ ጉድለት
የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ አያያዝና አጠባበቅ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በ3 መ/ቤቶች ብር 247 ሺ 210 ብር ከ19 ሳንቲም የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ተገኝቷል። በመሆኑም በጉድለት የታየው የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ እንዲተካ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ለየመ/ቤቶቹ በላክነው የስራ አመራር ሪፖርት አሳስበናል።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በሂሳብ መግለጫ ሪፖርት የተደረገውና በቆጠራ የተገኘው ጥሬ ገንዘብ መካከል ልዩነት በ2 መ/ቤቶች ቆጠራው በብር 133ሺ466 ብር ከ99 ሳንቲም በማነስ እና በ9 መ/ቤቶች በብር 3 ሚሊየን 433ሺ 156 ብር ከ03 ሳንቲም በመብለጥ የታየ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በ24 መ/ቤቶችም የተለያዩ የጥሬ ገንዘብና የባንክ ሂሳብ አያያዝ ድክመቶች እንደሚታዩ በኦዲታችን ወቅት አረጋግጠናል።
የጥሬ ገንዘብና የባንክ ሂሳቦች ላይ ተገቢ ቁጥጥር አለማድረግ ለገንዘብ ጉድለትና ምዝበራ የሚያጋልጥ በመሆኑ፤ የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ በየወቅቱ ተቆጥሮ ከመዝገብ ጋር እንዲመሳከር፣ በሂሳብ መግለጫ ሪፖርት ላይ የተመለከተው የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ በቆጠረ ከተገኘው ጋር ሊመዛዘንና ትክክለኛነቱ ሊረጋገጥ እንደሚገባ፤ በማነስና በመብለጥ የታየው ልዩነትም ተጣርቶ እንዲተካ ወይም ተገቢው ማስተካከያ እንዲደረግ እና በ24ቱ መ/ቤቶችም የታዩ የተለያዩ የጥሬ ገንዘብና ባንክ ሂሳብ አያያዝ ድክመቶች እንዲስተካከሉ አሳስበናል።
የውዝፍ ተሰባሳቢ ሂሳብ
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 190/2002 አንቀጽ 32 እስከ 35 በተደነገገው መሠረት ተሰብሳቢ ሂሳብ በወቅቱ መወራረዱ ሲጣራ በ57 መ/ቤቶች ብር 1 ቢሊየን 369 ሚሊየን 377ሺ 900ብር ከ98ሳንቲም በደንቡ መሠረት በወቅቱ ሳይወራረድ ተገኝቷል። ከዚህ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት የትምህርት ሚኒስቴር ብር 401 ሚሊየን 757ሺ 697 ብር ከ18ሳንቲም፣ የግብርና ሚኒስቴር 64 ሚሊየን 602 ሺ 005ብር ከ48 ሳንቲም፣ የግብርና ቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ 155 ሚሊየን 597 ሺ 701 ብር ከ70ሳንቲም፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 173 ሚሊየን 756 ሺ 807 ብር ከ75ሳንቲም፤ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ብር 159 ሚሊየን 455 ሺ 023 ብር ከ31ሳንቲም፤ የሀገር መከላከያ ሚ/ር ብር 86 ሚሊየን 367 ሺ 964 ብር ከ14ሳንቲም፤ በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች ኤጀንሲ ብር 83 ሚሊየን 081 ሺ 758 ብር ከ27ሳንቲም፤ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ብር 69ሚሊየን 022 ሺ 422 ብር ከ95ሳንቲም፤ የፌዴራል ፖሊስ 29 ሚሊየን 778 ሺ 302 ብር ከ26 ሳንቲም እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ብር 21 ሚሊየን 399 ሺ 805 ብር ከ70 ሳንቲም ይገኝበታል።
በተጨማሪም በተሰብሳቢ ሂሳብ አያያዝ የሚታዩ ዋና ዋና የአሰራር ችግሮች፤ ዕዳው ከማን እንደሚፈለግ ዝርዝር ማስረጃ ባለመኖሩ ከሰራተኛው የሚፈለገውን ቀሪ እዳ ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉ፤ በአንዳንድ መ/ቤቶች ገንዘቡ ወጪ ተደርጎ ለመሰጠቱ ማስረጃው ባለመቅረቡ የተሰብሳቢ ሂሳቡን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አለመቻሉ፤ የተሰብሳቢ ሂሳቡ ያልተለመደ ሚዛን /Abnormal Balance/ ማሳየቱ፤ በአንዳንድ መ/ቤቶች የተሰብሳቢ ሂሳብ ሰነዱ ለኦዲት ያልቀረበ መሆኑና ከመቼ ጀምሮ የሚፈልግ ሂሳብ እንደሆነ የሚገልጽ ማስረጃ እና ተቀጽላ ሌጀር ያልተቋቋመ በመሆኑ የሂሳቡን ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለመቻሉ ናቸው።
ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳቡ በየመ/ቤቶቹ የሥራ ማስኬጃ ላይ ተፅዕኖ በማሳደር የሥራ እንቅስቃሴ የሚያዳክምና የበጀት አጠቃቀም ላይ ተጽዕኖ ከመፍጠሩም በላይ ለምዝበራና ለብክነት በር የሚከፍት በመሆኑ መ/ቤቶቹ የፋይናንስ ደንብና መመሪያዎችን ተከትለው እንዲያወራርዱ አሳስበናል።
ethiopian-accounting2የገቢ ሂሳብ
የመንግሥት ገቢ በአግባቡ መሰብሰቡን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ ቀጥሎ የተመለከቱት ሁኔታዎች ተገኝተዋል።
በገቢ ግብር፣ ቀረጥና ታክስ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት
ሳይሰበሰብ የተገኘ የገቢ ሂሳብ
የገቢ ሰብሳቢ መ/ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በገቢ ግብር፣ ቀረጥና ታክስ እንዲሁም በሌሎች ገቢ መሰብሰብን በሚፈቅዱ አዋጆች፤ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት የመንግሥትን ገቢ የሰበሰቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በናሙና በታዩት በ4 መ/ቤቶችና በ6 የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤቶች በድምሩ ብር 29 ሚሊየን 205 ሺ 484 ብር ከ95ሳንቲም  በገቢ ግብር፣ ቀረጥና ታክስ እንዲሁም በሌሎች ገቢ መሰብሰብ በሚፈቅዱ አዋጆች መሠረት ያለተሰበሰበ የገቢ ሂሳብ መኖሩ ታውቋል።
በአዋጁ መሠረት ገቢ ካልሰበሰቡት መ/ቤቶች መካከል ምስራቅ አዲስ አበባ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ብር 25 ሚሊየን 090 ሺ 951 ብር ከ15 ሳንቲም እና ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብር 1 ሚሊየን 066 ሺ 483 ብር ከ48 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በመሆኑም መ/ቤቶች ለወደፊቱ የመንግሥት ገቢ ሕግና ደንብ በሚፈቅደው መሠረት መሰብሰብ እንዳለባቸው፣ በተለያዩ ምክንያቶች ያልተሰበሰበውም ገቢ እንዲሰበሰብ በላክነው ሪፖርት አሳስበናል።
ያልተሰበሰበ ውዝፍ የገቢ ሂሣብ
ገቢ ሰብሳቢ መ/ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በወጣው ሕግና ደንብ መሠረት የመንግሥት ገቢ በወቅቱና በአግባቡ መሰብሰባቸውን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና መ/ቤትና በስሩ ባሉ ስድስት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከውዝፍ ግብር፤ ወለድ እና ቅጣት መሰብሰብ የሚገባው ብር 853 ሚሊየን 920 ሺ 158 ብር ከ83 ሳንቲም እና በሌሎች 6 መ/ቤቶች ብር 12 ሚሊየን 250 ሺ 953 ብር ከ19 ሳንቲም በድምሩ ብር 866 ሚሊየን 171 ሺ112 ብር ከ02 ሳንቲም ያልተሰበሰበ ውዝፍ ገቢ መኖሩ ተረጋግጧል።
በመሆኑም የሚሰበሰበው ገቢ መንግስት ለሚያከናውናቸው የልማትና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መስፋፋት እንዲሁም ለሀገሪቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሳካት ወሳኝ በመሆኑ፤ ለገቢ አሰባሰቡ ትኩረት ተሰጥቶት የመንግሥት ሕግና ደንብ ተከብሮ እንዲሠራ፣ ያልተሰበሰበውም ውዝፍ ገቢ እንዲሰበሰብ በሪፖርታችን አሳስበናል።
በገቢ ሂሳብ ሪፖርት ውስጥ ያልተካተተ ገቢ
በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የመንግሥት መ/ቤቶች የተሰበሰበው ገቢ በትክክል ተመዝግቦና በሂሳብ ሪፖርታቸው ተካቶ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መቅረቡን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ በ5 መ/ቤቶች የሰበሰቡት የውስጥ ገቢ ብር 24 ሚሊየን 606 ሺ 079 ብር ከ30 ሳንቲም ባቀረቡት ዓመታዊ የገቢ ሂሳብ ሪፖርት ውስጥ ሳይካተት ተገኝቷል።
በሌላ በኩል 15 መ/ቤቶች ከልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ ምንጮች ገቢ የሚሰበስቡ ቢሆንም፤ የገቢ ሪፖርት የማያዘጋጁ በመሆኑ ሂሳቡን ኦዲት ማድረግ አልተቻለም። በተጨማሪም 5 መ/ቤቶች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ሳያስፈቅዱ የገቢ ደረሰኝ አሳትመው ገቢ እንደሚሰበስቡ ታውቋል።
ይህ አሰራር በመ/ቤቶች የሚዘጋጁት የሂሳብ መግለጫዎች ትክክለኛውን የገቢ ሂሳብ እንቅስቃሴ የማያሳይና የመንግስት አጠቃላይ ገቢና ወጪም ትክክለኛውን ገጽታ እንዳያሳይ ስለሚያደርግ መ/ቤቶች የሚሰበስቡትን ማንኛውም የመንግስት ገቢ ሕጋዊ በሆነ መንገድ በታተሙ ደረሰኞች ብቻ በመጠቀም እንዲሰበስቡና በሂሳብ መግለጫዎቻቸውም በመካተት ለገ/ኢ/ል/ሚ/ር ሪፖርት ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበናል።
የወጪ ሂሳብ
መ/ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎች መሠረት በአግባቡ መጠቀማቸውን፣ ተገቢው ማስረጃ መቅረቡንና ሂሳቡም በትክክል መመዝገቡን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ ቀጥሎ የተመለከቱት ሁኔታዎች ተገኝተዋል።
የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በውጪ ተመዝግቦ የተገኘ ሂሳብ
በወጪ ለተመዘገቡ ሂሳቦች የተሟላ ማስረጃ መቅረቡን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በ13 መ/ቤቶች የተሟላ ማስረጃ ሳይቀርብ ብር 132 ሚሊየን 364 ሺ 911 ብር ከ31 ሳንቲም በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።
ተሟልተው ካልቀረቡት ማስረጃዎች መካከል፣ የተከናወነውን ሥራ በሚያሳይ ዝርዝር ማስረጃ ሳይደገፍ በቀረበው ጥያቄ ብቻ የተፈፀመ ክፍያ፤ በባንክ በኩል ገንዘቡ ተልኮ ሥራ ላይ መዋሉን የሚገልጽ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ በወጪ የተመዘገቡ ሂሳቦች ጎላ ያሉት ናቸው።
ማንኛውም ሂሳብ በወጪ ከመመዝገቡ በፊት በፋይናንስ አስተዳደር አዋጁ፣ ደንቡና መመሪያ መሠረት ማስረጃዎች መሟላታቸው እንዲረጋገጥ፣ ያልተሟሉት ማስረጃዎች እንዲሟሉና ለወደፊቱም ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስበናል።
የወጪ ማስረጃ ያልቀረበለት ሂሳብ
በወጪ የተመዘገቡ ክፍያዎች ሕጋዊ ማስረጃ የቀረበላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በ22 መ/ቤቶች ብር 13 ሚሊየን 803 ሺ 411 ብር ከ08 ሳንቲም ማስረጃ ሳይኖረው በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።
በመሆኑም የወጪ ማስረጃ ያልቀረበለት ሂሳብ በቂ ማስረጃ እንዲቀርብለት፣ አለበለዚያ ገንዘቡ ለመንግስት ካዝና ተመላሽ እንዱደረግ፤ ለወደፊቱም ማንኛውም ወጪ ከመመዝገቡ በፊት ተገቢው ማስረጃ መቅረቡን በማረጋገጥ እንዲመዘገብ አሳስበናል።
የግዢ አዋጅ፤ ደንብና መመሪያ ሳይከተሉ የተፈፀሙ ግዢዎች
የዕቃና አገልግሎት ግዢ በመንግሥት ደንብና መመሪያ መሠረት የተፈፀመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፣ በ30 መ/ቤቶች ብር 353 ሚሊየን 568ሺ 759 ብር ከ15 ሳንቲም የመንግሥትን የግዢ አዋጅ፤ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ ግዢ ተፈጽሞ ተገኝቷል።
ከደንብና መመሪያዎች ውጭ ግዥ ከፈፀሙ መ/ቤቶች መካከል ጅማ ዩኒቨርሲቲ ብር 240 ሚሊየን 221 ሺ 573 ብር ከ63 ሳንቲም ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ብር 36 ሚሊየን 198 ሺ 641 ብር ከ27 ሳንቲም፤ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ብር 20 ሚሊየን 341 ሺ 230 ብር ከ59 ሳንቲም ፤ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ብር 14 ሚሊየን 082 ሺ 063 ብር ከ07 ሳንቲም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ብር 8 ሚሊየን 755 ሺ 250 ብር ከ38 ሳንቲም፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ብር 6 ሚሊየን 745 ሺ 462 ብር ከ35 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ካልተከተሏቸው የግዥ ደንብና መመሪያዎች ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት ሊፈፀሙ የሚገባቸው ግዥዎች ያለጨረታ ማስታወቂያ በመግዛት፣ በዋጋ ማወዳደሪያ /ፕሮፎርማ/ መፈፀም ያለበትን ግዥ ውድድር ሳይደረግ መፈፀም እና በውስን ጨረታው የግዥ ዘዴ በቂ አቅራቢዎች ሳይጋብዙ ግዥን ማከናወን የሚሉት ይገኙበታል።
የግዢ መመሪያን ሳይከተሉ ግዢ መፈፀም ለምዝበራና ለጥራት መጓደል የሚያጋልጥ በመሆኑ የመንግሥት ግዢ ደንብና መመሪያን አክብረው በማይሰሩ መ/ቤቶች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።
ደንብና መመሪያን ሳይከተሉ ያለአግባብ የተፈፀሙ ክፍያዎች
ኦዲት በተደረጉት መ/ቤቶች ደንብና መመሪያ ተጠብቆ ክፍያ መፈፀሙ ሲጣራ በ21 መ/ቤቶች ብር 137 ሚሊየን 363 ሺ 575 ብር ከ83 ሳንቲም ከደንብና መመሪያ ውጭ ተከፍሎ ተገኝቷል።
በግንባታ ቦታ ላይ ላሉ ዕቃዎች materials on site)፤ ከሚመለከተው አካል ሳይፈቀድ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በመፈፀም፤ ሰራተኞች መስክ ሳይወጡ የውሎ አበል በመክፈልና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሳይፈቅድ የኃላፊነት አበል ለዩኒቨርሲቲ የስራ አመራሮች ክፍያ በመሳሰሉት ምክንያቶች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ብር 77 ሚሊየን 611 ሺ 944 ብር ከ97 ሳንቲም፣ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ብር 34 ሚሊየን 771 ሺ 018 ብር ከ34 ሳንቲም እና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ብር 10 ሚሊየን 825 ሺ 188 ብር ከ84 ሳንቲም ወጪ ያደረጉ መሆናቸው በኦዲቱ ተረጋግጧል።
በተጨማሪም የቀድሞው የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቁጥር መ30/ጠ/ጠ13137/820 በቀን 5/13/2001 ዓ.ም በተፃፈ ሰርኩላር የትርፍ ሰዓት ክፍያ ተግባራዊ እንዳይሆን መመሪያ ያስተላለፈ ቢሆንም፤ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሳያስፈቅድ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በ2004 በጀት ዓመት ለትርፍ ሰዓት ክፍያ ፈጽሞ ተገኝቷል።
በመሆኑም ከደንብና መመሪያ ውጪ ያለአግባብ የተከፈለው ሂሳብ ተመላሽ እንዲሆንና ለወደፊቱም ደንብና መመሪያዎች ተከብረው መሰራት እንዳለበት ኦዲት ለተደረጉት መ/ቤቶች አሳስበናል።
በተሰብሳቢ ሂሳብ መመዝገብ ሲገባው በወጪ የተመዘገበ
የቅድሚያ ክፍያ ሂሳብ የተገኘባቸው መ/ቤቶች
በበጀት ዓመቱ በመንግሥት መ/ቤቶች በወጪ የተመዘገበው ሂሳብ በደንብና በመመሪያ መሠረት መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፣ በ12 መ/ቤቶች ለልዩ ልዩ ኮንትራታዊ አገልግሎቶች የተከፈለ ቅድሚያ ክፍያ ብር 546 ሚሊየን 599 ሺ 723 ብር ከ27 ሳንቲም በተሰብሳቢ ሂሳብ መመዝገብ ሲገባው በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።
ቅድሚያ ክፍያን በወጪ ከመዘገቡት መ/ቤቶች መካከል ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብር 302 ሚሊየን 924 ሺ 907 ብር ከ46 ሳንቲም ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ብር 123 ሚሊየን 905 ሺ 491 ብር ከ52 ሳንቲም፣ ትምህርት ሚኒስቴር ብር 47 ሚሊየን 988 ሺ 495 ብር ከ21 ሳንቲም እና ማዕድን ሚኒስቴር ብር 28 ሚሊየን 630 ሺ 317 ብር ከ74 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
መሆኑም የመንግሥት ሂሳብ አያያዝ በሚያዘው መሠረት አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ፤ ቅድሚያ ክፍያው ሥራው ተጠናቆ በቂ ማስረጃ እስከሚቀርብለት ድረስ በተሰብሳቢ ሂሳብ እንዲመዘገብ በሪፖርታችን አሳስበናል።
በብልጫ የተከፈለ ወጪ
በወጪ የተመዘገቡት ሂሳቦች በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ እና ደንብ መሰረት በአግባቡ የተፈፀሙ፤ እንዲሁም መ/ቤቶቹ ላገኙት አገልግሎት የተፈፀመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፤ በ7 መ/ቤቶች ለተለያዩ ግዢዎች ብር 542 ሺ 220 ብር ከ60 ሳንቲም እና ለውሎ አበልና ሌሎች ክፍያዎች በ4 መ/ቤቶች ብር 851 ሺ 589 ብር ከ66 ሳንቲም  በድምሩ ብር 1 ሚሊየን 393 ሺ 810 ብር ከ26 ሳንቲም በብልጫ ተከፍሎ ተገኝቷል።
በብልጫ የተከፈለው ሂሳብም በግዢ ሂደት ያለበቂ ምክንያት ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረቡ እያሉ ከፍተኛ ዋጋ ከቀረቡት ድርጅቶች ግዢ በመፈፀም፤ በድጋሚ ወጪ በማድረግ ወይም ከተገባው ውል ውጭ በመክፈልና ከውሎ አበል ተመንና የትርፍ ሰዓት ክፍያ በላይ በመክፈል የሚሉት ይገኙበታል።
በመሆኑም መ/ቤቶች የግዢና ፊይናንስ አስተዳደር ስርዓቱን ተከትለው መፈፀም እንደሚገባቸውና በብልጫ የተከፈለውም ገንዘብ ለመንግስት ካዝና ተመላሽ እንዲሆን አስፈላጊ እርምጃ እንዲወሰድ በሪፖርታችን አሳስበናል።
የንብረት ገቢ ደረሰኝ ያልቀረበለት
የመንግስት ገንዘብ ወጪ ሆኖ የተገዛው ንብረት ለመ/ቤቱ ገቢ ለመሆኑ የንብረት ገቢ ደረሰኝ የተቆረጠለት መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ በ6 መ/ቤቶች በብር 20 ሚሊየን 240 ሺ 407 ብር ከ36 ሳንቲም የተገዙ ዕቃዎች የንብረት ገቢ ደረሰኝ ሳይቆረጥላቸው ሂሳቡ በወጪ ተመዝግቦ ተገኝቷል።
ከዚህም ውስጥ ጂማ ዩኒቨርሲቲ ብር 18 ሚሊየን 870 ሺ 460 ብር ከ03 ሳንቲም እና መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ብር 1 ሚሊየን 325 ሺ 755 ብር ከ75 ሳንቲም ለተገዛው ዕቃና ንብረት የንብረት ገቢ ደረሰኝ ካልቆረጡት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ከውጪ ሀገር በድምሩ በአሜሪካን ዶላር 832 ሺ 255 ከ80ሳንቲም ተገዝተው የመጡ የተለያዩ ማሽነሪዎች ገቢ ያልተደረጉ መሆኑ ታውቋል።
የዚህ ዓይነት አሰራር ለንብረት ብክነት ስለሚያጋልጥ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ሁኔታ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ሊደረግና የንብረት ገቢ ደረሰኝ ያልቀረበላቸው ንብረቶች ለየመ/ቤቶቹ አገልግሎት ለመዋላቸው በማስረጃ እንዲረጋገጥ ለመ/ቤቶቹ በላክነው ሪፖርት አሳስበናል።
የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያልተቻለ ሂሳብ
በበደች ዓመቱ መ/ቤቶች የፈፀሙት ክፍያ ትክክለኛነቱን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፣ በ9 መ/ቤቶች በተለያየ ምክንያት ማስረጀ ባለመቅረቡ የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ያልተቻለ ሂሳብ ብር 3 ቢሊየን 507 ሚሊየን 062 ሺ 927 ብር ከ60 ሳንቲም ተገኝቷል።
የወጪውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ካልተቻለው ሂሳብ ውስጥ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ብር 3 ቢሊየን 169 ሚሊየን 110 ሺ 595 ብር ከ13 ሳንቲም፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ብር 187 ሚሊየን 857ሺ 058 ብር ከ5 ሳንቲም፤ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ብር 41 ሚሊየን 288 ሺ 852 ብር ከ19 ሳንቲም፤ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ብር 29 ሚሊየን 790 ሺ 947 ብር ከ40 ሳንቲም እና ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ብር 14 ሚሊየን ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
ማንኛውም የመንግስት ባለበጀት መ/ቤት የፌዴራል መንግስት የፋይናንስ አስተደደር አዋጅ ደንብና የመንግሥት የሂሳብ አያያዝ መመሪያዎችን ተከትሎ ሂሳቡን መያዝና ኦዲት ማስደረግ ስላለበት እነኚህ መ/ቤቶች ለወደፊቱ ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ የተሟላ ሰነድ በማደራጀት ሂሳባቸውን እንዲያስመረምሩ አሳስበናል።
በወጪ ሂሳብ ሪፖርት ያልተካተተ
ከውስጥ ገቢ እንዲጠቀሙ የተፈቀደላቸው መ/ቤቶች ከውስጥ ገቢያቸው ያወጡትን ወጪ በወጪ ሂሳብ ሪፖርት አካተው ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የሚያቀርቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ በ6 መ/ቤቶች የብር 159 ሚሊየን 482 ሺ 075 ብር ከ35 ሳንቲም ወጪ በወጪ ሂሳብ ሪፖርት ተካቶ በሕጉ መሠረት ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ሪፖርት ያልተደረገ መሆኑ ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ የውስጥ ገቢ ሂሳባቸውን በገቢ ሂሳብ ሪፖርት የማያካትቱ 15 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በገንዘብ መጠን ያልታወቀ ወጪ በወጪ ሂሳብ ሪፖርት የማያካትቱ በመሆኑ ሂሳቡን ኦዲት ማድረግ አልተቻለም።
ይህ አሰራር የዘመኑ የፌዴራል መንግስት ዓመታዊ ገቢና ወጪ ሂሳብ መግለጫን የሚያዛባ ከመሆኑም በላይ ሕገወጥ በመሆኑ እንዲስተካከል ባለፉት ዓመታት ሪፖርታችን ብናሳስብም ሊስተካከል አልቻለም። ስለሆነም ሊሰበሰብ የሚገባው የመንግሥት ገቢ በአግባቡ እንዲሰበሰብ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ለተከበረው ም/ቤት ሪፖርት እንዲያቀርብ ሊደረግ ይገባል።
የተከፋይ ሂሣብ
በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ
በገ/ኢ/ል/ሚ/ር መመሪያ መሠረት በበጀት ዓመቱ በተከፋይ ሂሳብ የተያዙት ሂሳቦች በተገቢው ጊዜ ውስጥ መከፈላቸውን ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ በ29 መ/ቤቶች ብር 491 ሚሊየን 128 ሺ 467 ብር ከ58 ሳንቲም በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ ተገኝቷል።
በወቅቱ ያልተከፈለ ተከፋይ ሂሳብ ከታየባቸው መ/ቤቶች ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ብር 173 ሚሊየን 824 ሺ 549 ብር ከ10 ሳንቲም፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብር 159 ሚሊየን 330 ሺ 268 ብር ከ77 ሳንቲም፤ ትምህርት ሚኒስቴር ብር 64 ሚሊየን 327 ሺ 615 ብር ከ57 ሳንቲም፤ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ብር 25 ሚሊየን 010 ሺ 347 ብር ከ 22 ሳንቲም እና የግብርናና ቴክኒክ ሙያ ማሰልጠኛ ማስተባበሪያ ብር 23 ሚሊየን 125 ሺ 504 ብር ከ24 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በሰኔ 30/2004 ከሠራዊት ደመወዝ ተመላሽ ተብሎ ሪፖርት የተደረገው ብር 163 ሚሊየን 504 ሺ 599 ብር ከ94 ሳንቲም የሠራዊቱ አባላት ደመወዝ ባለመውሰዳቸው ለረጅም ዓመታት በተከፋይ ሂሳብ የተያዘና መጠኑም እያደገ የመጣ ከመሆኑም በላይ ክፍያው ሳይፈፀም ሂሳቡ በወጪ የተመዘገበ ሲሆን፤ ቀሪው ብር 10 ሚሊየን 319 ሺ 949 ብር ከ16 ሳንቲም ለበርካታ ዓመታት በተከፋይ የተያዘና ለማን እንደሚከፈል የማይታወቅ መሆኑ ታውቋል። አሰራሩ ከመንግሥት የሂሳብ አሰራር ውጭ በመሆኑ እንደማንኛውም የፌዴራል መንግሥት መ/ቤት ያልተከፈለ ደመወዝ በቀጣዩ ወር መጀመሪያ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ፈሰስ መደረግ እንዳለበት ደመወዝ ካልተከፈላቸው አባላት ጥያቄ ሲቀርብ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እየተጠየቀ እንዲከፈልና ሌሎችም መ/ቤቶችም በወቅቱ ያልተከፈለውን ተከፋይ ሂሳብ የፋይናንስ አስተዳደር ሕጉን ተከትለው ለሚመለከተው አካል እንዲከፍሉ አሳስበናል።
በተጨማሪም በ12 መ/ቤቶች የተለያዩ የተከፋይ ሂሳብ አያያዝ ችግር ያለባቸው፤ ያለበቂ ማስረጃ በተከፋይ ሂሳብ የተመዘገቡ፤ ለማን እንደሚከፈል የሚያመለክት ዝርዝር ማስረጃ ባለመቅረቡ ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ ያልተቻለ፤ በተከፋይ ሂሳብ መግለጫ ያልተካተቱ፤ እንዲሁም ያልተለመደ የሂሳብ ሚዛን የሚያሳዩ ተከፋይ ሂሳቦች ተገኝተው አስፈላጊው ማስረጃ እንዲቀርብና ተገቢው ማስተካከያ እንዲደረግላቸው ለየመ/ቤቶቹ በላክነው ሪፖርት አሳስበናል።
የበጀት አጠቃቀም
ከተደለደለው በጀት በላይ ወጪ የሆነ ሂሳብ
መ/ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ መጠቀማቸውን ለማረጋገጥ በተደረገው ኦዲት በ27 መ/ቤቶች ለልዩ ልዩ የሂሳብ መደቦች ከተፈቀደላቸው በጀት በላይ በደንቡ መሠረት ሳያስፈቅዱ ሥራ ላይ የዋለ ብር 212 ሚሊየን 476 ሺ 799 ብር ከ01 ሳንቲም ተገኝቷል።
ከበጀት በላይ ወጪ ካደረጉ መ/ቤቶች ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ ብር 40 ሚሊየን 976 ሺ939 ብር ከ3 ሳንቲም፣ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ብር 30 ሚሊየን 910 ሺ 509 ብር ከ49 ሳንቲም፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ብር 28 ሚሊየን 217 ሺ 838ብር ከ81፣ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ብር 22 ሚሊየን 225 ሺ 409 ብር እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቆላ ዝንብ ማጥፊያ ፕሮጀክት ብር 21 ሚሊየን 636 ሺ 005 ብር ከ12 ሳንቲም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
በመሆኑም መ/ቤቶች በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና ደንብ መሠረት የተፈቀደላቸውን በጀት በተገቢው መንገድ የበጀት ዝውውር በማድረግ አስፈቅደው ሥራ ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስበናል።¾
ምንጭ የዛሬው ሰንደቅ ጋዜጣ (ሜይ 1 ቀን 2013)
↧

“ኢሕአዴግን ጥለን እኛ እዚህ የምንቧቀስ ከሆነ ኢሕአዴግ ባይወድቅ ደስ ይለኛል”–ግርማ ሰይፉ (የፓርላማው አባል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የማተሚያ ማሽን መግዢያ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ወደሚኒያፖሊስ የመጡት ብቸኛው ተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ 3 ጥያቄዎች ከሕዝብ ቀርበውላቸው ነበር።
1ኛ. 33ቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በአንድነት ቆመዋል። በተለይም ምርጫውን ቦይኮት በማድረግ። እነዚህ 33 የሚባሉት ፓርቲዎች የራሳቸው አባል አላቸው ወይንስ ፈቃድ ብቻ ስለያዙ ነው ፓርቲ የተባሉት?

2ኛ. ኢሕአዴግ እርስ በራሱ ተጠላልፎ ወደ መውደቅ ደረጃ ላይ ያለ ይመስላል። ኢሕአዴግ ድንገት ቢወድቅ ሃገር ለመምራት የሚያስችል ብቃት አላችሁ ወይ?

3ኛ. ከሰሞኑ በአማራው ሕዝብ ላይ እየደረሰው ያለውን መፈናቀል በተመለከተ አንድነት ፓርቲ መግለጫ ሲያወጣ “የአማርኛ ተናጋሪዎች” እያለ ነው የገለጸው፤ እርስዎም ዛሬ ሲናገሩ “በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ የደረሰ መፈናቀል ሲሉ” ተደምጠዋል። የ”የአማራ ሕዝብ” ለማለት የማትፈልጉት ለምንድን ነው? – ነው ወይስ አማራን በአማራነቱ ካለመቀበል ነው?

አቶ ግርማ ሰይፉ ለነዚህ ጥያቄዎች የሰጡትን አነጋጋሪ ምላሽ ዘ-ሐበሻ በምስል ቀርጻ ይዛዋለች ይመልከቱት።

↧

የፐርዝ ከተማ ኗሪዎች የዘር ማጥፋት ሰለባ ለሆነው ወገናቸው ደራሽ ለመሆን ተንቀሳቀሱ

$
0
0
↧

የጊቢ ሞት በተባለ ኦፕሬሽን በየመን ወደ 1000 የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ከአፋኞች ነጻ ወጡ

$
0
0

2221
ግሩም ተ/ሀይማኖት
(በየመን በስደት ላይ የሚገኝ የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኛ)

ለሰሞኑ የየመንን መገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበው የኢትዮጵያያኑ ላይ እየጠፈጸመ ያለው አሰቃቂ ስራ ሲሆን ከችግሩ ጀርባ ያለውን እውነታንም በይፋ እየተናገሩ ነው፡፡ እስከዛሬ የነበረ ድምጻችን፣ መፍትሄ ይፈለግ ጥያቄያችን ሰሚ አግኝቶ የየመን መንግስት በየቦታው ያሉ ታጋቾችን ሲያስለቅቅ ከችግሩ መፈጠር ጀምሮ እስከ መንግስት አካላት ድረስ መነካካት እንዳለበት አጋልጠዋል፡፡ አሁንም ከአጋቾቹ ነጻ ከወጡ በኋላ ስደተኞቹ ላይ አግባብ ያልሆነ ነገር እየተፈጸመ እንደሆነ ዘግበዋል፡፡ ስለሁኔታውና የዘገቡትን እውነት እያመሳከርኩ እንይ፡-
ባለፈው ረቡዕ ምሽት ማታ ተንቀሳቃሽ ስልኬ ደጋግሞ ‹‹ወሬ ሊያቀብልህ የመጣ ሰው አለ ክፈት..ክፈት..›› እያለ አንቃጨለ፡፡ ቁጥሩን የማወቀው ወዳጄ እና የሞያ አጋሬ ጋዜጠኛ መሀመድ ደርማን ነው፡፡ መሀመድ ደርማን ኢትዮጵያዊያኑ በህገ-ወጥ አጓጓዦች እየታገቱ የሚደርስባቸው ስቃይ የውስጥ እግር እሳት ሆኖ ያቃጥለዋል፡፡ እውነታውን ከመረጃ ጋር ካሳየሁት በኋላ በቁጭት እሳት ተርመጥምጦ ከሞት ጋር ለመታገል ቆርጦ ተነሳ፡፡ ይሄ ሰብዓዊነት የተላበሰ ሀሳቡ ነው ያገናኘን፡፡ ያግበባን፡፡ ከዚህ በፊት በሁለት ዙር የየመን መንግስት ወታደሮች ከአጋቾቹ ጋር ተዋግተው ኢትዮጵያዊያኖቹን ነጻ ሲያወጡ ቦታው ላይ በመገኘት ዘግቧል፡፡ ባለፈው ሳምንት ግን የመንግስት አካላት እጅ እንዳለበት ከዘገበ በኋላ ችግር ተፈጠረ፡፡ ደጋግሞ የሚያንጫርረው ስልኬን ከፈትኩት…
‹‹አሎ! ኬፍ አለክ ያ-አኪ ጉሮም አነ መሀመድ ደርማን…›› እንደምነህ ወንድሜ ግሩም እኔ መሀመድ ደርማን ነኝ የሚለውን ቃሉን አቀበለኝ፡፡ ‹‹አረፍት ኬፈክ ያ-ሪጃል ሰሀፊ!›› አውቄሀለሁ አንተ ወንድ(ጎበዝ) ጋዜጠኛ አልኩት
‹‹አልዬም ሾዬ መርቡሽ አሸን ከወፉኒ ሙጅሪሚን…›› ዛሬ ትንሽ ተረብሻለሁ፡፡ አሸባሪዎቹ ረበሹኝ አለኝ እና ነገ እንገናኝ የሚለውን አስከተለ፡፡ በማግስቱ በተቀጣጠርንበት ሰዓት ቤቴ መጣ፡፡ የተረበሸው ቢሯቸው ፎቅ ስር 400 ግራም የሚመዝን ቲንቲ /TNT/ ፈንጂ አጥምደውባቸው ሳይፈነዳ ለደህንነቶች ጠቁመው መክሸፉን ነገረኝ፡፡
ቀጣይ በዚህ ጉዳይ ላይ የበለጠ እንዲሰራ አደረጉት እንጂ ፈርቶ ወደኋላ እንደማይል ነገረኝ፡፡ ያበርታህ የሚለውን በሆዴ አልጎመጎምኩ፡፡ ይህን ያነሳሁት አፋኞቹ ምን ያህል የጠነከሩ ሲነኳቸው ለማጥፍት እንደሚሄዱ ላሳየት ነው፡፡ አጠቃላይ ዘገባውን ስቃኝ ደግሞ…በዚህ ወር ብቻ ባህሩን ተሻግረው የመን ከገቡ ኢትዮጵያዊያኖች መካከል በአጋቾች ከተያዙት ውስጥ ወደ 1000 የሚሆኑት ነጻ ወጡ፡፡ በሀረጥ ዙሪያ ካሉ አካባቢዎች ድንበሩን ጠባቂዎች እና የመንግስት ወታደሮች(የመከላከያን ሰራዊት) በማስተባበር አካባቢውን በመፈተሸ ከአንድ ጊቢ ብቻ 210 አስፈቱ፡፡ በ22/04/13 እሁድ ዕለት ከተያዙት ውስጥ 89 ሴቶች ሲሆኑ 10 ህጻናት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ በግርፋት፣ በድብደባ፣ በእሳት ማቃጠል፣ በመደፈር..የተጎዱ አካላቸው የደቀቀ እና የተጎሳቆሉ ናቸው፡፡
ከአፈና የተፈቱት የሰጡትን ቃል ስንመለከት……ካህሳይ ሚኬሌ እና ወንድሙ የደረሰባቸው ግፍ በጣም ሰቅጣጭ ነው፡፡ ‹‹..በጣም በጣም ነው የደበደቡን፡፡ በብረት ሁሉ ደብድበውናል፡፡ ላስቲኩን በእሳት እያቃጠሉ ሰውነታችን ላይ ያንጠባጥቡታል፡፡ ስልክ ሰተውህ ለዘመዶችህ ደውል ይሉሀል፡፡ ደውለህ የሚልክልህ ከሌለ ዘመዶችህ እንዲሰሙ ነው እላይህ ላይ የቀለጠውን ላስቲክ ጠብ እያደረጉ ስትቃጠል እና ስትጮህ ቤተሰቦችህ እንዲወሰሙ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ስቃይ መካከል ወንድሜ ህይወቱ አለፈ፡፡ገንዘብ ለማግኘት ወጥተን ወንድሜን በሞት አጥቼ ሌሎቻችንም አካላችንን ከፈልን..›› በማለት ተናግሯል፡፡ ለስምንት ወርም በእንግልት ቆይቷል፡፡
ንጉሴ በግሩፕ ሲጓዙ ከነበሩት አንዱ ነው፡፡ ‹‹.ከባህር እንደወረድኩ ተያዝኩ፡፡ ተደበደብኩም፡፡ ከሚደበድቡት መካከል ኢትዮጵያዊያንም አሉበት፡፡ ከድብደባ ብዛት ግራ እግሬ ተሰበረ፡፡ ስቃዩ ሲብስብኝ ወደ ኢትዮጵያ ደወልኩ፡፡ ግዳቸውን የሳዑዲ 1000 ሪያል ላኩልኝ፡፡ ተደብድቤ አካሌ ከጎደለ በኋላም ቢሆን ተላከልኝ አውጥተው በረሃ ላይ ጣሉኝ፡፡ ሲጥሉኝ ራሴን አላውቅም ነበር፡፡ ስነቃ ራሴን ጭው ያለ በረሀ ስጥ አገኘሁት፡፡ደግ የመናዊያን አግኝቼ 10 ኪሎ ሜትር ወስደው ተከምኩኝ፡፡ ይህን ድርጊት የሚፈጽሙት ሀይል ያላቸው እና ከመንግስት ሰው ያላቸው ናቸው፡፡….›› ንጉሴ ከኢትዮጵያ ላኩልኝ ብሏል፡፡ በደንብ ስላላብራራው እኔ ልግለጸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ወኪላቸው በፖሊስ ተይዞ ፍርድ ካገኘ በኋላ ዘዴ ቀይረዋል፡፡ ሳዑዲ አረቢያ የሚያውቁት ሰው ይፈልጉ እና እሱ በሳዑዲ ሪያል 1000 ለእነሱ ይልካል፡፡ የታጋቹ ቤተሰቦች የሳዑዲ 1000 ሪያል የሚሆነውን በኢትዮጵያ ብር ከሳዑዲ ለላከላቸው ቤተሰቦች ይሰጣሉ፡፡
አካባቢው ላይ ያለ ባለስልጣን ሲናገር ደግሞ ‹‹..ሆስፒታል ውስጥ 27 ሬሳ ፍሪጅ ውስጥ በስብሷል፡፡ የእነዚህ ሰዎች አሟሟ ት በስቃይ ለመሆኑ በሰውነታቸው ላይ ያለው ምልክት ያስረዳል፡፡ እስካሁንም ሬሳው ፍሪጅ ውስጥ ነው፡፡ መቅበር አልቻልንም፡፡ ፍርድ ቤቱ እንዲቀበሩ ቢፈርድም እስካሁን ከሶስት ወር በላይ ሆኗለወ አልተቀበረም፡፡ይህ የሆነው ግን መውበሪያ ስላጣን ነው፡፡አለም አቀፉ የስደተኞች ጽ/ቤት IOM እና UNHCR አንድ ላይ መሬት ሊገዙ ተስማሙ፡፡ እኛ ሁኔታውን ለማወቅ ከሆስፒታሉ ጋር መረጃ እንለዋወጥ ነበር፡፡ የሚገዛ መሬቱ ተገኘ አልተገኘ እንጠይቃለን፡ በኋላ መሬቱ ተገኘ ተስማሙ እና ተገዛ፡ በሳምንቱ ለመቅበር በቦታው ተገኘን፡፡ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አምጥተው ሊቀብሩ ሲሉ የአካባቢው ሰው አይቻልም እዚህ አይቀበሩም አሉ፡፡ዳግም ሆስፒታል ተወስደው እ ነው አሁንም ሬሳው….›› ብሏል ባለስልጣኑ፡፡ ጋዜጠኛው ራሱ ሲመሰክር ‹‹..ማዳ የተባለ ቦታ ብዙ የስደተኞች ሬሳ አገኘን፡፡ የብዙዎችን ሬሳ በየበረሃው አገኘን፡፡ አሰቃይተው በእሳት ካቃጠሉዋቸው በኋላ ይጥሏቸዋል፡፡
ይህን በተመለከተ አል-ተውራ ተብሎ የሚጠራው የመንግስት ጋዜጣ ደግሞ አካባቢው ላይ ያሉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው በለስልጣናት በዝምታ መለጎማቸው እና መንግስት የሰጠው ክፍተት ለዚህ አንዳደረሰ ዘግቧል፡፡ በዘገባውም ሀረጥ አል-ዘሀራ የተባለ ቦታ 48 የታፈኑ ሰዎች አሉ፡፡ በተደጋጋሚ የመንግስት ወታደሮች ሊያስለቅቋቸው ሞክረው እነዚህን አጋቾች ሊረቱ ስላልቻሉ 48 ሰዎች እስካሁን እንደያዙዋቸው ነው፡፡ የመንግስት ወታደሮች ሲናገሩ አጋቾቹ ሊያስጠጉን አልቻሉም ስለዚህ ምን ማድረግ እንዳልብን አለወቅንም ብለዋል፡፡
ይህ የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ጋዜጣ የሚባለው ቶውራ የመንግስት ቁጥጥር መላላት እንደሆነ ለችግሩ መንስኤ ገልጾዋል፡፡ ይህ ወንጀል በሚሰራበት አካባቢው ያሉት የወታደር እና ደህንነት ዝም ማለት የፈለጉት አፋኞቹ (ህገ-ወጥ አጓጓዦቹ) ከጀርባቸው ትላልቅ የመንግስት ባለስልጣናት ስላሉ መሆኑን ዘግቧል፡፡
እኔ እስካውቀው ደግሞ ይ ብቻ አይመስለኝም፡፡ አይደለምም፡፡ አካባቢው ላይ ላሉ ባለስልጣናት ብቻ ሳይሆን ድንበር ጥበቃ ላይ ያሉት ሰዎች በባህር በገባው ስደተኛ ልክ ማለት በአንድ ሰው ሂሳብ እንዳላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲያውም ከዚህ በፊት ባናገርኳቸው ሰዎች መረጃ መሰረት ጀልባው ቀድሞ ሲመጣ እንኳን ደውለው እንደሚጠሯቸው ነው፡፡ የመን ግልጽ ሙስና የሚከናወንባቸው ከሚባሉት ሀገሮች ተርታ በመሆኗ ሲታሰሩ እንኳን በገንዘብ ሀይል እንደሚወጡ የታየ እውነታ ነው፡፡ ማጣራት እስክችል ድረስ ስሙን ለመጥቀስ ባልፈልግም አንድ በዚህ ስራ የተሰማራ ኢትዮጵያዊ አግቶ ከያዛቸው 60 ኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር የየመን መንግስት በቁጥጥር ስር አዋለው፡፡ ከ80000 የሳዑዲያ ሪያል ከፍሎ ከእስር ተፈታ፡፡ ይሄ ያለውን ሙስና ለማሳየት ያሰፈርኩት ይሁን እንጂ ኤምባሲውም ሊፋረደው ሲገባ በአቅራቢያው ያሉ እዛው ብቅ ጥልቅ የሚሉ ሰዎች ሲያስፈቱት ዝም ማለቱ ምን እንደሚያሳይ መገመት አያቅትም፡፡
በኤምባሲ ዙሪያ ካነሳሁ በነካ አፌ ልጨርሰው እና ልለፍ፡፡ ሰሞኑን ቅጥ ያጣውን እና በየእስር ቤት ውስጥ ተሰግስጎ ያለውን ኢትትዮጵያዊያ ስደተኞች ወደ ሀገር ለማስገባት አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ ደፋ ቀና እያሉ መሆኑን ከቢሮው አካባቢ የገኘሁት መረጃ ያስረዳል፡፡ በየእስር ቤቱ ያሉትን ወደ 3000 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ለማሰገባት የሚደረገውን ጥረት ተቀብለው አሁን በቅርቡም 469 ስደተኞችን ወደ ሀገር ለመመለስ መመለሻ ወረቀት (ሊሴ ፓሴ) እያጋጁ መሆኑም ታውቋል፡፡ ኤምባሲው አሁን ከምን ጊዜውም በላይ ትብብር ማሳየቱ ደስ የሚል ጅምር ነው፡፡
ወደ ጋዜጣው ገባ ስገባ በየቦታው የኢትዮጵያዊያኑ ሬሳ ወድቆ እንደሚገኝ፣ እንደሚታይ እና ጸሀሪው ራሱ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ማየቱን ተናግሯል፡፡ የቀሩትን ታጋቾች ለምን እንደማያስለቅቁ ሲጠይቃቸው አለመቻላቸው እና ከመንግስት ወታደር የተሻለ ሀይል እንዳለው እንደሚናገሩ ገልጾዋል፡፡ እንዲያውም በቦታው ላይ ያሉትን ሀላፊዎች ሲያናግራቸው ከፍርሃት የተነሳ አንድም ቃል አልሰጡንም፡፡ ለነፍሳቸው ፈሩ..ብሏል፡፡ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM ጊቢ ውስጥ ሲገቡ ያዩት በጣም ሰቅጣጭ እንደነበረ የገለጸው ጋዜጠኛ ብረት አግለው ሰውነታቸውን ከጠበሷቸው አንስቶ አሰፈሪ እና ሰቅጣጭ ሁኔታ የተፈጸመባቸው ለማየት በቅተዋል፡፡ የድርጅቱ ሰራተኞች ግን በአስጸያፊ ስድብ በፖሊስ ከጊቢ እንዳስወጧቸው ዘግቧል፡፡ እንዲያውም እንዳንገባ እና ጉዱን እንዳናይ ዱላ ቀረሽ በሆነ ሁኔታ መለሱን፡፡
ይህ ሁኔታ ሲታይ እነዚህ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዱን እየደበቁ ተደፋፍኖ እንዲቀር የሚፈልጉበት ሁኔተሰ እንዳለ የዘገበ ሌላ ጋዜጠኛም አለ፡፡ እመለስበታለሁ፡፡

↧
↧

የተቃዋሚ ድርጅቶች ሰላማዊ እንቅልፍ፤ ለምን?

$
0
0

berehanu merara hailu shawel beyene petros

መልስ ለአማኑኤል ዘሰላም
መግቢያ
በኢትዮጵያ ሃገራችን የወያኔ/ኢህአዴግ ስርዓት በህዝብ ላይ እየፈፀመ የሚገኘው በደል እጅግ ከመጠን ያለፈ ደረጃ ላይ መድረሱ እሙን ነው:: በአንፃሩ ደግሞ ተቃዋሚ ድርጅቶቻችን በህዝብ ላይ እየተፈፀመ የሚገኘውን መከራ የማስቆም ብቃት ሊኖራቸው ሲገባ፤ በተቃራኒው፤ እንኳን የህዝብን መከራ ማስቆም ቀርቶ፤ ወያኔ/ኢህአዴግ በራሳቸው ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና መቋቋም አቅቷቸው በየአደባባዩ ከህዝብ ባልተለየ መልኩ ሲያማርሩ ይታያሉ:: ይህ በሃገራችን እየታየ የሚገኘው የተዛባ ታሪካዊ ክስተት አሳሳቢነትን የተገነዘቡ ኢትዮጵያን ምሁራን ፣ ፀሃፊዎችና፣ ሌሎች ግለሰቦች የበኩላቸውን መፍትሄ ሲሰነዝሩ ማየት እንግዳ አይሆንም:: እንደ አብነት ለመጥቀስ ያህል “የትግራይ ህዝብ ዝምታ ሲተረጎም” በአብርሃ ደስታ፣ “የተቃዋሚዎች ድክመትና ለስልጣኑ ያላቸው ርቀት” በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ “መሪዎች ፈራን ካሉ፤ ተመሪዎችስ ምን ይሁኑ?” በፊልጶስ፣ እንዲሁም በፕ/ር አል ማሪያም የተፃፈውን “Ethiopia’s opposition at the dawn of democracy?” ፅሁፎችን ማንሳት ይቻላል::
ሙሉውን ዘገባ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ (Read full story in PSF)

// ]]>

↧

አሥሩ ዋንጫዎች:- አሥሮቹ ጀግኖችና አሥሩ ዓመታት በኦልድትራፎርድ – ክፍል 2

$
0
0

man 2
ከይርጋ አበበ
በትናንቱ የክፍል 1 ዘገባ የእንግሊዙ ታላቅ ክለብ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ ከውጤታማው አሠልጣኝ ጋር ያጣጣማቸውን 10 ዓመታት ስንመለከት ቡድኑ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች መካከል ነጥረው የወጡትን አሥር ተጫዋቾች ለይተን እያየን አምስተኛው ውጤታማ ተጫዋች ላይ ስንደርስ ነበር ቀሪዎቹን ዛሬ ልናይ የተለያየ ነው፡፡ ዛሬ ከቆምንበት ስንቀጥል እንዲህ ሆኖ እናገኘዋለን።
6. ማይክል ካሪክ
የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ብዙም ያላጨበጨቡለትና ያልዘመሩለት የመሐል ሜዳው ሞተር እንደ ሥራው ተገቢውን ከበሬታ እንዳላገኘ ይነገርለታል። ልክ እንደቀድሞው ብራዚላዊ መድፈኛ ጂልቤርቶ ሲልቫ ሁሉ ማይክል ካሪካም ከካሜራ የተደበቁ ድንቅ ሥራዎችን በትጋት ሲከውን ነው የሚያመሸው። አየርላንዳዊው ሮይኪን ትቶት የሄደውን ቦታ ለመድፈን የሌሎች ክለቦችን በር ያንኳኩት ሰር አሌክስ ፈርጉሠን ማረፊያቸው የሰሜን ለንደኑ ቶተንሃም ሆትስፐርስ የመሐል ሜዳ አንቀሳቃሽ ማይክል ካሪክ ሆነ። 18 ነጥብ6 ሚሊዮን ፓውንድ የግሌዘር ቤተሰቦችን ያስከፈለው ወጣት የማንቸስተሩን ክለብ የመሐል ሜዳ ለማስጠበቅ ብዙም ፈተና አልገጠመውም ነበር። 16 ቁጥር ያረፈበት ቀይ ማለያ ለብሶ ሜዳ የሚገባው እንግሊዛዊ ማንቸስተር ይናይትድ ካገኛቸው ስኬቶች ጀርባ አሻራው ከፍተኛ ነበር። ለ308 ጊዜ ቀዩን ማለያ ለብሶ የተጫወተው ካሪክ 20 ግቦችን ሲያስቆጥር የጣሊያኑን ዋና ከተማ ክለብ ሮማን 7ለ1 ሲረታ ያስቆጠረው ግብ ምንጊዜም «በደጋፊዎች ልብ ውስጥ አይጠፋም» በላንክሻየሩ ክለብ ያሳየው ምርጥ አቋም ስቴቨን ጄራርድና ፍራንክ ላምፓርድ በተቆጣጠሩት የሦስት አናብስቶቹን ማሊያ 27 ጊዜ እንዲለብስ አስችሎታል።
7. ሮበን ቫንፔርሲ
አርሴናልን ለብስጭትና ለንዴት ጥሎ በ24 ሚሊዮን ፓውንድ ከለንደን ወደ ማንቸስተር የተጓዘው የ29 ዓመቱ ሆላንዳዊ ማንቸስተር ዩናይትድ የ2012/13 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ የአንበሳውን ድርሻ የተወጣው ይኸው ባለግራ እግሩ ሆላንዳዊ ነው። በመጀመሪያ ዓመት የኦልድ ትራፎርድ ቆይታው እስካሁን ድረስ ብቻ 30 ግቦችን ሲያስቆጥር ከ10 በላይ ኳሶችን ደግሞ ለጓደኞቹ አስተካክሎ በማቀበል ግብ ጨራሽ ብቻ ሳይሆን ግብ ፈጣሪነቱንም በሰር አሌክስ ፈርጉሰን ቡድን ውስጥ አሳይቷል። የእንግሊዝን ፕሪሚየር ሊግ ለ20ኛ ጊዜ ማንቸስተር ዩናይትድ ሲወስድ 20 ቁጥር ለባሹ ሆላንዳዊ የፈጸመው ተግባር በክለቡ ደጋፊዎችና የስፖርት ተንታኞች ከ10 ዓመቱ የኦልድ ትራፎርድ ምርጦች አንዱ እንደሆነ አስችሎታል።
8. ሀቪየር ሄርናንዴዝ ቺቻሪቶ
ሜክሲኳዊው ወጣት በ21 ዓመት ዕድሜው በደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ያሳየውን ብቃት ብዙዎች ድንቅ ብለውታል። ቺቻሪቶ ከዓለም ዋንጫው በፊት ግን ስኮትላንዳዊው የማንቸስተር አለቃ ልጁን በደንብ ያውቁት ነበር። ገና በሜክሲኮው ሲ. ዲ ጓዳላጅራ ክለብ ሲጫወት ቀልባቸውን የሠረቀው ትንሹ አተር ወደ ኦልድ ትራፎርድ እንዲመጣላቸው ለክለባቸው አመራር ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ በፈርጊ ላይ እምነት ያለው የክለቡ አመራር ባልተገለጸ የዝውውር ሂሳብ ወደ ክለባቸው አመጡት። የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታውን በዊብሌይ ቸልሲን 3ለ1 አሸንፈው የኮሚዩኒቲ ሸልድ ዋንጫ ሲያነሱ ተቀይሮ የገባው 14 ቁጥሩ በፒተርረቼክ መረብ ላይ ኳስ ማሳረፍ ጀመረ። የራሱን ፊት ገጭታ መረብ ላይ ባረፈች ኳስ ከግብ ጋር መተዋወቅ የጀመረ ሲሆን በመጀመሪያ ዓመት ቆይታው 13 እጅግ ወሳኝ የፕሪሚየር ሊግ ግቦችን ለቀያይ ሠይጣኖቹ ማስቆጠር ቻለ፡፡ በ26 ጨዋታዎች 13 የሊግ ግቦችን ያስቆጠረላቸውን ሜክሲኳዊ ለማድነቅ ቃላት የሚቸግራቸው ፈርጊ የ2010/11 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን እንዲሆኑ ከኮከቡ ዋይኒ ሩኒ ያልተናነሰ አስተዋጽኦ አበርክቷል። እግር ኳስ ተጫዋች ከሆነ ቤተሰብ የተገኘው ይህ ተጫዋች በሮቢን ቫንፐርሲ መፈረምና ዳኒ ዋልቤክ መጎልበት የቋሚ ተሰላፊነት ቦታውን እያጣ ቢመጣም ዕድሉን አግኝቶ በሚሰለፍባቸው ጨዋታዎች ሁሉ የቀድሞውን ምርጥ ግልጋሎት ከመስጠት አልታቀበም።
በቀጣዩ የውድድር ዓመት ኮከባቸውን ሮዳሜል ፋልኮኦን እንደሚያጡ እርግጠኛ የሆኑት አትሌቲኮ ማድሪዶች ቺቻሪቶን ከማንቸስተር ለመግዛት ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ። የፍሎሬንቲኖ ፔሬዙ ሪያል ማድሪድም ቢሆን በጎንዛሎ ሂጉየንና ካሪም ቤንዜማ ግብ የማግባት ችሎታ ባለመደሰታቸው ሜክሲኳዊውን የ24 ዓመት ወጣት ወደ ቤርናባው ለማስኮብለል የፈርጊን ፈቃድ በመጠባበቅላይ ናቸው። ማሬንጌዎቹ ቤካምንና ሮናልዶን እንደወሰዱ ሁሉ ትንሹን አተር ከኦልድ ትራፎርድ ማስኮብለል ይችሉ እንደሆነ የምናየው ይሆናል።
ቺቻሪቶ ግን በእስካሁኑ የክለቡ ቆይታው ከክለቡ ምርጦች ውስጥ ስሙን ለማስፈር ችሏል።
9. ካርሎስ አልቤርቶ ማርቲኔዝ ቴቬዝ
ከቦካ ጁኒየርስ ወደ ብራዚሉ ኮረንቲያስ ዝውውር ሲያደርግ በአሳዳጊ ክለቡ ደጋፊዎች «ገንዘብ አሳዳጅ» ተብሎ የተሰደበው «ቴብዝ» በእንግሊዝ ቆይታውም ከዚህ የተለየ አልጠበቀውም፡፡ ገና በኮረንቲያስ በነበረበት ጊዜ የቀያይ ሰይጣኖቹን ማሊያ ለብሶ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት ሲጀምር ወደ ኦልድ ትራፎርድ የሚወስደውን መንገድ ማመቻቸት ጀመረ። በአርሴናሉ አሠልጣኝ አርሰን ቬንገር በጥብቅ ሲፈለግ አሌክስ ፈርጉሰን ግን ከተጫዋቹ የኢኮኖሚ ባለመብት ኢራናዊው ኪያ ብራብችያን ላይ በሁለት ዓመት ውሰት 25 ሚሊዮን ፓውንድ ከፍለው 32 ቁጥር ማሊያን አልብሰው የክለባቸው ተጫዋች አደረጉት። ይበልጥ በታጋይነቱ እና ሜዳውን ሙሉ አካሎ መሮጡ መታወቂያዎቹ ሲሆኑ በኦልድ ትራፎርድ ቆይታው የደጋፊዎቹን ልብ ማሸፈት ችሎ ነበር። ለሁለት ዓመታት ብቻ በቀዮቹ ቤት የቆየው ደቡብ አሜሪካዊ ለ99 ጊዜ የማንቸስተርን ማሊያ ለብሶ ወደ ሜዳ ገብቷል። በ99ኙ ጨዋታዎቹ 34 ኳሶችን መረብ ውስጥ የዶለ ሲሆን በ2008ቱ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ የፈጸመው ተጋድሎ የላንክሽየሩ ክለብ ወደ ሞስኮ ያደረገውን ጉዞ የሚያሳምሩ 5 ግቦችን ለክለቡ አስቆጥሯል።
በዌስትሀም ዩናይትድ ደጋፊዎች በእጅጉ የሚፈቀረው አርጀንቲናዊ በ2008 የውድድር ዘመን ማንቸስተር ዩናይትድ አፕተን ፓርክ ላይ የምሥራቅ ለንደኑን ክለብ ሲገጥም የዌስትሀም ደጋፊዎች « አንድ ካርሎስ ቴቬዝ ብቻ ነው» እያሉ ነበር የዘመሩለት። በ2006/07 የውድድር ዘመን ከመውረድ በታደጋቸው ደቡብ አሜሪካዊ ላይ የ2008/09 የውድድር ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ከተማ ተቀናቃኙ ማንቸስተር ሲቲ ዝውውር ማድረጉ በሻፒዮናዎቹ ዩናይትድ ደጋፊዎች ጥርስ ነከሱበት። ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ታሪካዊ ተቀናቃኝ ወደ ብራዚል ዝውውር ሲያደርግ በሀገሩ ጥላቻን ማትረፍ ሳይበቃው በእንግሊዝ የፈፀመው ዝውውርም በቀድሞ ክለቡ ደጋፊዎች እና የቡድን አጋሮቹ (ጋሪ ኔቭል በጣም ይጠላው ነበር) እንደ ከሀዲ አስቆጥሮታል። ቢሆንም ግን በአልድትራፎርድ በቆየባቸው 2ዓመታት የፈጸመው ሥራ ከክለቡ ምርጥ የ10 ዓመት ግዥዎች ዝርዝር ውስጥ እንዲካተት አድርጎታል።
10. ዲሚታር ኢቫኖቭ ቤርባቶቭ
የእንግሊዝ ክለቦችን የዝውውር ሪከርድ በሰበረ ዋጋ ከፈርናንዶ ቶሬዝና ሮቢንሆ ሪከርዱ በቤርባ እጅ ነበር ከሰሜን ለንደን ወደ ላንክሻየር ሲቀላቀል ብዙ ተጠብቆ ነበር። 30 ነጥብ75 ሚሊዮን ፓውንድ ከግሌዘር ቤተሰቦች ካዝና ወደ ቶተንሃም ሆትስፐር አካውንት ያዘዋወረው የቡልጋሪያ 7 ጊዜ ኮከብ ተጫዋችና አምበል በቀዮቹ ቤት በነበረው ቆይታ 149 ጊዜ ቀዩን ማሊያ ለብሶ ሜዳ ውስጥ ታይቷል። በ149 ጨዋታዎች 54 ጊዜ ኳስና መረብን ያገናኘ ሲሆን በ2010 ኅዳር ወር ላይ በብላክበርን ሮቨርሱ ፖል ሮቢንሰን መረብ ውስጥ የጨመራቸው አምስት ግቦች ብቸኛው ተጫዋች እንዲሆን አስችለውታል። በአንድ ጨዋታ አምስት ግብ ያስቆጠረ።
እንደ ክለብ ጓደኞቹ ታጋይነት የማይታይበት መሆኑ ስሜት የሌለው እያሉ ቢተቹትም አንድ ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ ዘውድን መድፋት ችሏል። የቀድሞው ሲ.ኤስ.ኬ ሶፊያ ተጫዋች ለሀገሩ 77ጨዋታዎችን አድርጎ 48 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በአሌክስ ፈርጉሰን ቡድን ውስጥ በነበረው የሦስት ዓመታት ቆይታ እንደ እነ ቺቻሪቶ እና ቴቪዝ ባይሆንም ጥሩ ሊባል የሚችል የውድድር ጊዜያትን አሳልፏል። እነዚህ ሥራዎቹ ደግሞ እንደ ሉዊስናኒ፣ አንቶኒዮ ቫሌንሽያ፣ ሉይስ ሳሃ፣ ኦውን ሃርግሬቭስ፣ ራፋኤል ዳሲልቫ እና ደቡብ ኮሪያዊው ፓርክጄ ሱንግ የተሻለ ደረጃ ሊያሰጠው ችሏል።

↧

“የስልጣን ሽኩቻ እንጂ የሃይማኖት ችግር የለም”–አባ ገ/ሚካኤል ተሰማ (Video)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) አባ ገ/ሚካኤል ተሰማ በሚኒሶታ የቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ ናቸው። ከወራት በፊት በሚኒሶታ በዋልድባ ገዳምና በቤ/ክ አንድነት ጉዳይ ላይ በተጠራ ስብሰባ ላይ ያደረጉትን ንግግር በቪድዮ ቀርጸነው የነበረ ቢሆንም፤ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በሳናወጣው ቀርተን ነበር። ሆኖም ግን አሁንም በዋልድባ ያለው ገዳም ችግር እየተባባሰ በመምጣቱና የቤተክርስቲያን አንድነትም አደጋ ውስጥ እንዳለ በመገንዘብ ይህ ንግግራቸው ዛሬም ለዘ-ሐበሻ ተከታዮች ግንዛቤን ያስጨብጣል ብለን ስላሰብን ከወራት በኋላ አትመነዋል። ይመልከቱት።

“የስልጣን ሽኩቻ እንጂ የሃይማኖት ችግር የለም” – አባ ገ/ሚካኤል ተሰማ (Video)

↧

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ተነሳ

$
0
0
ታሪካዊው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲነሳ

ታሪካዊው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲነሳ

(ዘ-ሐበሻ፟) በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለው የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ከሚገኝበት ቦታ ዛሬ ተነሳ።  ሐውልቱ በጊዜጣዊነት ያርፍበታል ወደተባለው ብሄራዊ ሙዚየም ቢዛወርም አሁንም ሕዝቡ በሐውልቱ መመለስ ላይ ጥርጣሬ እንዳለው እየገለጸ ይገኛል።

“የመንገድ እና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች በማንኛውም ሃገር መሠራታቸው ይደገፋል። ሆኖም ግን በሚሰሩበት ጊዜ የእምነት ተቋማትንና እና ለሀገር እና ለህዝብ ትልቅ ውለታ የዋሉትን ለስማቸው መታሰቢያ የተሰየሙ ሃውልቶችን መነካት እንደሌለባቸው መታወቅ ነበረባቸው” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች “የአገራቸው በጠላት መወረር፣ የሕዝባቸው መገደልና መታሰር፣ የቤተ ክርስቲያናቸው መደፈር እስከ ሞት ያደረሳቸው እኒህ እውነተኛ ጳጳስ መታሰቢያቸውን በማንሳት በስመ የባቡር ፕሮጀክት ለዚች ሃገር የዋሉት ውለታ ፤ ለአርበኞች ያሳዩት ተጋድሎ ፤ ህዝቡ በእምነቱ አንድ በመሆን ጠላትን እንዴት መመከለት እንዳለበት ያስተላለፉት መልዕክት ከግምት ውስጥ ሳይገባ ለአንድም ቀን ከቦታው ማንሳት እምነቱንም ታሪክንም መዳፈር ነው።” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለአንድ ዓመት ያህል ከቦታው ርቆ በብሄራዊ ሙዚየም ይቀመጥና ተመልሶ የነበረበት ቦታ ይቀመጣል ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናት  ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ከተማ የተደረገ ባለው የቀላል ባቡር ግንባታ ፕሮጀክት ምክንያት  ሐውልቱ የየሚያርፍበት ቦታ የሚቆፈር በመሆኑ በጊዜያዊነት ነው የሚነሳው ቢባልም ባለሙያዎች ሐውልቱ ሳይነካ ባቡር መስመሩን መዘርጋት ይቻል ነበር ማለታቸውን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች “በአሁኑ ጊዜ የሚሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የእምነት ተቋማትንና ታሪካዊ ሃውልቶችን በጥናት ወቅት ለምን ግምት ውስጥ አስገብተው እንደማይሰሩ አይገባንም። ባልጠፋ ቦታ ዋልድባ ላይ ስኳር ልማት ማቋቋም እና ባልጠፋ መንገድ ሃውልቶችን እያነሱ መንገድ መስራት የሃገሪቱን ታሪክ ጥላሸት ከመቀባት በላይ ሃገሪቱ አለኝ የምትላቸውን ቅርሶች ከማጥፋት የማይተናነስ ስራ ነው መስሎ የሚታየው” ይላሉ።

 

አቡነ ጴጥሮስን በጥቂቱ
(አንድ አድርገን ብሎግ በአንድ ወቅት እንደጻፈው)

የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ሺ ስድስት መቶ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዕውቀት መንፈሳዊ ከእርሷ ተወልደው በእቅፏ ውስጥ ባደጉ ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት እንድትመራ ፈቃዷን ስትገልጽ ከተመረጡት አባቶች አንዱ በመሆን ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም. በእስክንድርያው መንበረ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ማዕረገ ጵጵስናን ተቀበሉ። ከዓመት በኋላም “አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዓ”ተብለው ተሾሙ።

 
abune_petros

በ1928 ዓ.ም. አረመኔው የኢጣልያ ፋሺስት በግፍ አገራችንን ለመውረር ክተት ሠራዊት ምታ ነጋሪት በማለት ውቅያኖስ አቋርጦ በመምጣት ኢትዮጵያን ሲወርና ሕዝቧን፣ ሊቃውንቷን፣ ገዳማቷንና አድባራቷን በግፍ ሲጨፈጭፍ ያዩት ብፁዕነታቸው ወራሪውን ኃይል ከኢትዮጵያውያኑ አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎት ሊዋጉት ቆረጡ። የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከአረመኔው ፋሺስት ጦር ጋር በመፋለም ላይ የነበረውን አርበኛ ለማበረታታት ወደ ማይጨው በሔዱ ጊዜ ብፁዕነታቸው ተከትለው ሔዱ። ከዚያ እንደ ተመለሱም በታላቁ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ተሰባስበው የቤተ ክርስቲያን አምላክ በኢትዮጵያውያን ላይ የመጣውን ችግር እንዲያስታግሥ በጸሎት እየተጉ ወደነበሩት አባቶችና አርበኞች በመሔድ ለአገርና ለነጻነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን በመስበክ ሁሉም እንዲጋደሉ ማሳሰብ እና ማትጋት ጀመሩ። ኋላም የገዳሙ መነኮሳትና የሰላሌ አርበኞች ይባሉ የነበሩት አርበኞች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ተሳታፊ ሆኑ። ከዚያም አርበኞቹ የቻሉትን ሁሉ አድርገው ወደ ሰላሌ ሲመለሱ ብፁዕነታቸው አዲስ አበባ ቀሩ። ብዙም ሳይቆዩ በጠላት እጅ ተያዙ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስምንት ጥይት አሁን ሃውልታቸው ከሚገኝበት ቦታ ዝቅ ብሎ ባለው ቦታ ላይ ሰማዕትነትን ተቀበሉ፡፡
↧
↧

ግልጽ ደብዳቤ ለብፁዓን ወቅዱሳን አቡነ መርቆሬዎስና አቡነ ማትያስ፤

$
0
0
abune-merekoriwos-150x150

የፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ

አቡነ ማቲያስ

አቡነ ማቲያስ

ለቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ፤ ለእግዚአብሔር፤ ለእመቤታችን፤ ለቅድስት ማርያም፤ ለሊቃነ መላእክት ለቅዱስ ሚካኤልና ለቅዱስ ገብርኤል፤ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምእመናን።

አቤቱታ፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ለተጋረጡት ከባድ ችግሮች መፍትሔ አግኙልን!

 “ዕርቅን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤ እነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።” ማቴ. ም5/9 ብፁዓን ወቅዱሳን አባቶች ሆይ! በመጀመሪያ፤ ዝቅ ብዬ እጅ በመንሳት፤ መንፈሳዊ ሰላምታዬን በከፍተኛ አክብሮትና ትሕትና አቀርባለሁ። በመቀጠልም፤ ምንም እንኳ ኢምንት፤ ተራ ምእመን ብሆንም፤ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ተጋርጠው ለሚገኙት ከባድ ችግሮች መፍትሔ ሊገኝ የሚችለው፤ በፍጡራን ደረጃ፤ ከሁሉም በላይ፤ ሁለታችሁ ብፁዓን ወቅዱሳን አባቶች፤

 ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

↧

ምርጫ የለም እንጂ ምርጫማ ቢኖር …!

$
0
0

በፍቅር ለይኩን

የዛሬው ጽሑፌን በምርጫ ዙሪያ ካጋጠመኝ ትንሽ ቆየት ካለ ገጠመኜ ልጀምር፡፡ በደቡብ አፍሪካዊቷ ቢዝነስ ከተማ ጆሐንስበርግ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ የሆኑ ካህን፣ አባትና አገልጋይ የሆኑ በ60ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙ አንድ አዛውንት አባት አሉ፡፡

election

እኚህ አዛውንት ካህን ስማቸው ፋዘር ዲሊዛ ኔልሰን ቫሊዛ ሲሆን፤ በኢትዮጵያውያን የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ምእመናን ዘንድ ደግሞ በክህነት የማእረግ ስማቸው መልአከ ሰላም ዲሊዛ ቫሊዛ በመባል ይጠራሉ፡፡ ታዲያ ፋዘር ዲሊዛ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ፣ ስለ ኢትዮጵያውያንና ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አውርተው፣ ተናግረው የሚጠግቡ ሰው ዓይነት አይደሉም፡፡

ከኬፕታውን ከትምህርት ቤት በመዘጋቱ ለእረፍት ወደ ጆሐንስበርግ መጥቼ ነበር፡፡ በጆሐንስበርግ መድኃኔ ዓለም ካቴድራል በነበረኝ የመንፈሳዊ አገልግሎት ቆይታዬም ከእኚህ አዛውንት አባት ጋር ከመንፈሳዊና ከሃይማኖታዊ ጉዳዮች ባሻገርም በበርካታ በአገራችንና በደቡብ አፍሪካ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች አብዝተን እንወያይ ነበር፡፡

ፋዘር ዲሊዛ በየትኛው አጋጣሚ ለሚያገኟቸው ኢትዮጵያውያንም ሆነ የውጭ አገር ዜጎች ሁሉ አዘወትረው የሚናገሩት አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም ለዛሬው ነፃነታችን፣ ሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ የዘረኝነት መድሎ ለሌለበት ፍትሐዊ ሥርዓት እውን መሆን እናንተ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ድርሻ አላችሁ በማለት በአድናቆትና በልዩ የደስታ መንፈስ ውስጥ ሆነው ምስክርነታቸውን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ይሰጣሉ፡፡

በአንድ ወቅት ከፋዘር ዲሊዛ ጋር ባደረግነው ውይይት እኚህ አዛውንት አባት በአገራቸው ደቡብ አፍሪካ ለሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ (Local Government Election) ከጆሐንስበርግ ከ1000 ኪ.ሜ. በላይ ወደሚርቀው የውቅያኖስ ጠረፏ የትውልድ አገራቸው ፖርት ኤልዛቤት ለመሄድ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ አንዳች ጉጉት በሚንጸባረቅበት ልዩ ስሜት ውስጥ ሆነው አጫወቱኝ፡፡

እኔም በመገረም ሆኜ እንዴ …! ፋዘር እንዴት ለአካባቢ ምርጫ ሲሉ ይህን ያህል ርቀት፣ ይህን ያህል ብዙ ብር የትራንስፖርት ወጪ አውጥተው ይሄዳሉ?! ደግሞስ እርስዎ አሁን አርጅተዋል፣ ለምን እንዲህ በመንገድ ይደክማሉ፤ ባለቤትዎና ልጆችዎ ከመረጡ በቂ አይደለም እንዴ …?! አልኳቸው፡፡

አዛውንቱ ካህን ለምርጫ ወደ ትውልድ መንደራቸው ለመሄድ ጓዛቸውን እየሸከፉ መሆናቸውን መስማቴና እርሳቸውም የጉዞአቸውን ስላረጋገጡልኝ በጣሙን ግርምትም አድናቆትም አጭሮብኝ፡፡ ፋዘር ዲሊዛ ግርምት ለተሞላበት ጥያቄዬና አስተያየቴ ሲመልሱልኝም፡-

አይ ልጄ ይህ የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብቴ በብዙ ዋጋ፣ በእልፎች ክቡር ደምና መሥዋዕትነት የተገኘ ልዩ መብት ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ከእናት ቤተ ክርስቲያናችን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር ፈጽሞ እንዳንገናኝ ዘረኛው የአፓርታይድ መንግሥት የገነባው የመለያየት ግንብ የተናደው ፓርቲዬ ኤ.ኤን.ሲ፣ በበርካታ የደቡብ አፍሪካውያን የነፃነት ፋኖዎች እና ለሰው ልጆች ነፃነትና እኩልነት ቀናኢ በሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮችና ሌሎች አጋሮቻችን ጭምር ነው፡፡

እናም ልጄ በዚህ ምርጫ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ ለመሳተፍም ሆነ ላለመሳተፍ አንተ እንደምትለው የዕድሜዬ መግፋት፣ በቦታ ርቀት፣ በገንዘብ ወጪ ፈጽሞ የሚተመን አይደለም፡፡ ይህ በምንም በማይተመን በብዙዎች የሕይወት መሥዋዕትነት የተገኘ ልዩና ክቡር መብት/መብቴ ነው፡፡ እናም መብቴን በሕይወት እሳካለሁ መጠቀም አለብኝ፡፡

አየህ አሉኝ ፋዘር ዲሊዛ ንግግራቸውን በመቀጠል በአትኩሮት እየተመለከቱኝ አየህ ልጄ የእኔ አንድ ድምፅ ለፓርቲዬ ድልም ሆነ ሽንፈት ወሳኝነት አለው፤ ስለሆነም ለዘመናት ለታገልንበትና የበርካታ አባቶቻችን ክቡር ሕይወት ተከፍሎበት አገሬ ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ለደረሰችበት ሰላም፣ ብልጽግና፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት እውን መሆን ማረጋገጫው በዚህ ያለማንም አስገዳጅነት በራሴ ፍላጎት፣ ወድጄና ፈቅጄ የምሳተፍበት ይህ ፍትሐዊ የሆነ የአካባቢ ምርጫ አንዱ ነው፡፡

እናም ልጄ ምንም ተአምር ቢፈጠር በሕይወትና በጤና እሳካለሁ ድረስ ለምርጫ ወደ ትውልድ መንደሬ ከመሄድ የሚያግደኝ ነገር አይኖርም በማለት ፈርጠም ብለው መለሱልኝ፡፡ አዛውንቱ ካህን በዚህ የዕድሜያቸው መጨረሻ እንኳን በስስት የሚያዩት የመምረጥና የመመረጥ መብታቸው ላይ ያላቸው ስሱነትና ፖለቲካዊ ንቃታቸው (Sensitivity and political consciousness) በእጅጉ አስገረመኝ፣ አስደመመኝም፡፡

በፋዘር ዲሊዛ ቫሊዛ መልስ የበዛ አድናቆትና ግርምት የተጫረብኝ ኢትዮጵያዊው እኔ ወደኋላ ዘወር ብዬ በበርካታ አፍሪካ አገሮችና በመላው ዓለም የነፃነት ሰንደቅ ተደርጋ በምትታየው ኢትዮጵያ፣ የአገሬን የምርጫ ታሪክና ዲሞክራሲዊ ግንባታ ሂደት ለመታዘብ ይህ ጥቂት የቆየ ገጠመኜ ዕድሉን ፈጠረልኝ፡፡ እናም ከዚህ ገጠመኜ በመነሳት ይህችን አጠር ያለች ትዝብት አዘል ጽሑፍ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተካሄዱት የአካባቢ፣ የቀበሌና የወረዳ ም/ቤቶች ምርጫ ዙሪያ በመመርኮዝ ጥቂት ነግሮችን ለማለት ወደድኩ፡፡

በዘመኔ የደረስኩበት፣ በሙሉ ልቤ የምመሰክርለትና በንቃትም የተከታተልኩት ምርጫ ቢኖር በአገር አቀፍ ደረጃ ተካሄደው የ1997ቱ ምርጫ ነው፡፡ ከዛን በፊት ስለ ምርጫ፣ ስለ መምረጥና ስለ መመረጥ መብት ለማወቅም ሆነ ለማገናዘብ የነበረኝ ፖለቲካዊ ንቃትና ዕድሜዬም ደረጃም ብዙም የሚፈቅድልኝ አልነበረም፡፡ እናም የትዝብቴ ዋና ትኩረት የሚሆነው ምርጫ 97ን ተመርኩዞ ከሰሞኑ በተካሄደው የአካባቢናና የወረዳ ምክር ቤት ምርጫ ላይ ነው፡፡

በዘንድሮው የአካባቢና የወረዳ ምክር ቤት ምርጫ ላይ በጥቂቱ ትዝብቴን ለማካፈል የ1997ቱን ምርጫ እንደ መነሻ ወይም መንደርደሪያ አድርጌ ለመውሰድ የተነሣሁበት የራሴ የሆነ ምክንያት ስላለኝ ነው፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የ1997ቱ ምርጫ በእኔ ብቻ ሳይሆን በብዙ ኢትዮጵውያን ልብ ውስጥ የማይረሳ ውብም አስቀያሚም የሆነ መቼም ማይረሳን ትዝታ ትቶ አልፏል፡፡

የ1997ቱ ምርጫ ምንም እንኳን ፍጻሜው ባያምርም የምርጫው ጅማሬና ሂደት መላው ኢትዮጵያውያንን ከሊቅ አስከ ደቂቅ፣ ከአፈ ነቢብ እስከ ምሁር፣ አለቃን ከምንዝር ሳይለይ ሁሉንም ኅብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ ምድሪቱን ከዳር እስከ ዳር ያነቃነቀና መላውን ዓለም ጭምር ያሰደመመ ነበር፡፡

ሚንጋ ነጋሽ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ምሁር Ethiopia’s Post Election Crisis: Institutional Failure and The Role of Mediation በሚል አርዕስት በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ከተማ በሚገኘው Witwatersrand ዩኒቨርስቲ ባቀረቡት የጥናት ወረቀታቸው፣ ምርጫ 97 በአገራችን ምርጫ ታሪክ ውስጥ ትልቅና ጉልህ የሆነ ታሪካዊ ክስተት ሆኖ ማለፉን እንዲህ በማለት ነው በጥናታዊ ጽሑፋቸው የገለጹት፡-

The 1997 elections marked an historic event in the country, as Ethiopia witnessed its first genuinely competitive campaigns period with multiple parties fielding strong candidates.

 

በወቅቱ ምርጫውን የታዘበው ካርተር ምርጫ ታዛቢ ቡድን ማእክልም ባወጣው ባለ 69 ገጽ ሪፖርቱ እንደገለጸው፣ በምርጫ 97 ወቅት ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ የነበራቸውን ሁሉን አቀፍ ሕዝባዊ ተሳትፎና ትልቅ መነቃቃት በተመለከተ ሲገልጽ፡-

The May 2005 election was started against the backdrop of tensions and unprecented level of public political consciousness. … Voters had a genuine choice in Election Day and responded with enthusiasm and high turnout. 

ከ1997ቱ ምርጫ አንፃር የዘንድሮውን ምርጫ ሂደት የታዘቡ ብዙዎች ዋ ምርጫ!፣ ዋ የምርጫ ፉክክርና ውድድር!፣ ወይ የምርጫ ነገር፣ ወይ ነዶ … በማለት ቁጭታቸውንና ብሶታቸውን የገለጹበትን አጋጣሚ ትቶ ነው ያለፈው፡፡ አንዳንዶችም በማኅበራዊ ድረ ገጾች ባሰነበቡት ምጸትን የተሞላ ሰም-ለበስ ግጥማቸው እንዲህ በማለት ነበር የዘንድሮውን የኢህአዴግን የምረጡኝ አማርጡኝ ደፋ ቀና የአካባቢና የወረዳ ምርጫ ግርግርን እንዲህ የተቀኙበት፡-

ምርጫ የለም እንጂ ምርጫ ቢኖር፣

ኑ ምረጡን የሚለን ‹‹ካድሬ›› ባላሻን ነበር፡፡

 

ከ1997 ምርጫ በኋላ የተካሄደው የ2002ቱ ምርጫ ከ1997ቱ ምርጫ በሁሉ ነገር አንሶና ኮስሶ ነበር የታየው፡፡ በእርግጥ ኢህአዴግ ከ97ቱ ምርጫ ስህተት በወሰደው ትምህርት ራሱን በሚገባ አጠናክሮ፣ ከሕዝቡ ጋር ለመገናኘት ተከታታይ የሆኑ ሰፊ ዘመቻዎችን በማድረግ በፍቅርም በጉልበትም መጪው ዘመን የእርሱና የእርሱ ብቻ እንዲሆን የተለመው እቅዱን ፈጽሟል ማለት ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ በ2002ቱ ምርጫ ላይ የነበረው ሕዝባዊው ተሳትፎው በአብዛኛው የቀዘቀዘ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከገዢው ፓርቲ የተለመደ ወከባና በትር ያላመለጡበት፣ በተሳትፎ ረገድም መሳሳት የታየበት፣ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም 99.6 በመቶ ምርጫውን ያሸነፈበትን ይህን መሬት አንቀጥቅጥ የሆነ ድሉን ለራሱና ለደጋፊዎቹ የዘከረበትና ያዘከረበት ምርጫ ሆኖ ነበር ያለፈው፡፡

በዘንድሮው 2005 የአዲስ አበባ የአካባቢ፣ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ ኢህአዴግ በየቤቱ እየዞረና ኑ እባካችሁ ምረጡ እያለ በመቀስቀስ ሕዝቡን ለምርጫ ቢወተውትም የምርጫው ድባብ ከሂደቱ እስከ ፍፃሜው ድረስ ቀዝቃዛና ደብዛዛ ነበር፡፡

አንድ በአነስተኛ የሸቀጥ ሱቅ ውስጥ የሚሰራ ወጣት ስለ መምረጡ ስጠይቀው በሰጠኝ ምላሹ በግርምታ ሆኖ ‹‹እንዴ አዲስ መንግሥት መጥቷል እንዴ!? ትላንትና ዛሬስ ያለው ኢህአዴግ አይደል እንዴ!? ታዲያ የምን ምርጫ ነው የሚሉን እነዚህ ሰዎች በማለት ያስፈገገኝንም ያሳዘነኝንም መለስ ሰጥቶኛል፡፡

ብዙዎች ደግሞ አማራጭ ሲኖር እኮ ነው ምርጫ፣ ለመሆኑ ማንን ከማን ነው የምንመርጠው፣ በእውነት ኢህአዴግ አሁንስ ‹‹ከዝንጀሮ ቆንጆ …›› እንደሚባለው ተረት አደረገው እኮ ይሄን ምርጫ የሚለውን ነገር በማለት፤ ዋ…! ምርጫስ 97 ላይ ቀረ፣ አከተመ፡፡ ሲሉ በትዝታ ሰረገላ የ97ቱን የምርጫ ውድድር ብርቱ መንፈስና ሰፊ ሆነውን ሕዝባዊ ተሳትፎ በሐዘኔታ ውስጥ ሆነው እያስታወሱ፣ ወይ ነዶ፣ ዋ ምርጫ፣ የምርጫስ ነገርስ ይቅርብን ተዉን እባካችሁ … ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በእርግጥ ከ1997 ወዲህ ለተደረጉ አገር አቀፍም ሆነ የክልል ምርጫዎች እንዲህ መቀዛቀዝና ሕዝቡ ለመምረጥም ሆነ ለመመረጥ ያለው ፍላጎትና ስሜት እየወረደና እንደ በረዶ እየቀዘቀዘ መምጣት ገዢው ፓርቲ ብቻውን ተጠያቂ አይሆንም ባይ ነኝ፡፡

በአገራችን የሚገኙ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ራእይ አልባነት፣ ቁርጠኝነት ማጣት፣ በሕዝብ ልብ ውስጥ ለመግባት የሚያስችላቸው ፕሮግራምና ፖሊሲ ለመቅረጽ መታከታቸውና ትግሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ያላቸው ዝግጁነት አናሳ መሆኑ አንዳንዶቹን ፓርቲዎችና አመራሮቻቸውን በበቃኝ ከትግሉ መድረክ እንዲያፈገፍጉ እያደረጋቸው እንዳለ እየታዘብን ነው፡፡

እንዲሁም በአገራችን የሚገኙ አብዛኛው የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም አቅቷቸው፣ እንደ እሳት ሊፈትናቸው ያለውን መከራ በሩቅ ሸሽተውትና ቀቢጸ ተስፋ ተውጠው፣ ለገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ሜዳውም፣ ፈረሱም ይኸው በማለት ለብቻው ያለአንዳች ከልካይ በአገሪቱ የፖለቲካ ሜዳ ላይ እንደ ልቡና እንዳሻው ይጋልብበት ዘንድ በከፊል ቢሆን ዕድሉን አመቻችተውለታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አለመጠናከርና በአመራሮቻቸው መካከል ያለው አምባገነንነት፣ የእርስ በርስ አለመግባባት፣ ሽኩቻ፣ መወጋገዝና መከፋፈል የራሱ ሆነ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ደግሞ ማንም የማይክደው ሐቅ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡

ከምርጫ 97 ማግስት በኋላ እርስ በርሳቸው መካሰስን፣ መወነጃጀልንና መወጋገዝን ሥራዬ ብለው የያዙት የተቀዋሚ ፓርቲ አመራሮች አንዱ የአንዱን ገበና ሳይቀር እንኳን በአደባባይ በማውጣት የገቡበት ቅሌትና የስነ ምግባር ውድቀት፣ አይወርዱ አወራረድ በብዙዎች ዘንድ ለመሆኑ እንደው የሆነስ ሆነና ኢህአዴግ ሥልጣኑን ቢያስረክባቸው ኖሮ ይህችን አገር ሊመሩ የነበሩት እነዚህ ሰዎች ነበሩ እንዴ እስኪሉ ብዙዎች በእፍረት እንዲሸማቀቁና እንዲያንሱ ያደረጉበትን በርካታ አጋጣሚዎችን ታዝበናል፡፡

በአገራችን ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና አመራሮቻቸው በሕዝብ ዘንድ አመኔታን በማጣታቸው የተነሳ አብዛኛው ሕዝብ ‹‹ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ምንትስ ይሻለናል፡፡››፤ ‹‹ትሻልን ትቼ ትብስን አመጣሁ፡፡›› እንዳይሆን በሚል ስጋት ወዶም ሆኖ ሳይወድ ኢህአዴግን የሙጥኝ እንዲል የተገደደ ነው የሚመስለው፡፡ እናም ዛሬም ድረስ ተቃዋሚ ነን በሚሉ የትላንትናዎቹ አንጋፋ ፓርቲዎች ውስጥ የተከሰተው ታላቅ የሆነ ስብራት ወይም ስንጥቃት የተጠገነ፣ ቁስሉም የተፈወሰ አይመስልም፡፡

የገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ ግትርነት፣ ለሕዝቡ ከእኔ በላይ ለአሳር የሚለው አመለካከቱ፣ በአማራጭ መንገዶችን ለማየትና ከሌሎች ጋር ለመነጋገር ያለበት ችግርና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ያሉት ኁልቆ መሣፍርት የሌላቸው ችግሮች ተደራርበው አገራችን የምታልመውን የዲሞክራሲያ ሥርዓት ግንባታን ዕድገት እያጓተተው ነው፡፡

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግና አጋሮቹ የ1997ቱ ዓይነት ሕዝብ አቀፍ የሆነ የዲሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ መንፈስና ቅናት ዳግም እንዲፈጠር ከመሥራት ይልቅ ዛሬም በለመደው ሸካራ መንገድ መጓዝን ነው የመረጠው፡፡ ኢህአዴግ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ተቀራርቦ ለመነጋገር፣ ለመወያየት የጠረቀመውን በሩን በጨዋ መንገድ ለመክፈት ዛሬም ተቸግሮ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ እናም በጠላትነት የመተያየት፣ የጥላቻና የጽንፈኝነት ክፉ መንፈስ ዛሬም ድረስ በአገራችን የፖለቲካ ሰማይ ላይ የመጠፋፋትን፣ የመበላላትን ጥቁር ደመና እንዳዘለ ነው፡፡

በዚህ ሁኔታ ደግሞ በፊታችን የሚጠበቀው አገር አቀፉ ምርጫ 2007 የተለየ አንድምታ ሊኖረው አይችልም የሚለው ተስፋ አስቆራጭ የሚመስል ድምፆች ከዚህም ከዚያም እየተሰሙ ናቸው፡፡ ያው እንደተለመደው ምርጫ ሲደርስ ከተደበቁበት ጎሬ ወጥተው አለን አለን የሚሉት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና ምርጫን ሰበብ አድርገው እንደ እንጉዳይ የሚፈሉትና እዚህም እዛም ብቅ ብቅ የሚሉት የአገራችን ፓርቲዎች እንደልማዳቸው በመጪው ምርጫ ግርግር መፍጠራቸው አይቀር ይሆናል፡፡

ግና ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውን የሚያስፈልጋቸው ፓርቲና ፖለቲከኛ የምርጫ ሰሞን አለሁ አለሁ የሚል የትርፍ ጊዜ ፓርቲና ፖለቲከኛ አይደለም፡፡ የአገሪቱን የፖለቲካ ታሪክ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቿን፣ የሕዝቦቿን ሃይማኖት፣ ታሪክ፣ ባህልና ቅርስ በሚገባና ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ በአገሪቱ ብሔራዊ እርቅ፣ መግባባትና አንድነት እንዲመጣ ጠንክሮ የሚሠራ፣ እንደ ማህተመ ጋንዲና እንደ አፍሪካዊው ኔልሰን ማንዴላ የፍቅርን፣ የወንድማማችነትንና የእርቅን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ የሚያውለበልብ፣ ቆራጥና የሕዝብ ወገንና አለኝታ የሆነ ፓርቲና ፖለቲከኛ ነው ብዙዎቻችን በእጅጉ የናፈቀን፣ የሚያስፈልገንም፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአገራችን የተከሰተው አብዮት ካመጣቸው መዘዞች አንዱ የፖለቲካ ፕሮፌሽናል ደረጃ እየወደቀ መሄድ ነው፡፡ የታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሺፈራው በቀለ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማኅበር ባዘጋጀው Vision 2020 የሥራ ባልደረባቸው የሆኑት ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ ‹‹ምን አለምን? የት ደረስን? ወዴትስ እያመራን ይሆን?›› በሚል አርዕስት ባቀረቡት የጥናት ጽሑፍ ላይ ባቀረቡት ለውይይት ማጫሪያና ማዳበሪያ የሚሆን መነሻ ሐሳብ ላይ ሲገልጹ፡-

ፖለቲካ ማለት መቀላመድ፣ ለዘመድ አዝማድ፣ ለአምቻ ለጋብቻ፣ ለዘር፣ ለወገንና ለጎሳ ‹‹ጮማ መቁረጥ ጠጅ ማንቆርቆር›› (በዚህ ዘመን እንኳን ምናልባት ውስኪ ማውረድ ቢባል ይቀላል፡፡) ማለት ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያውያን አእምሮ ውስጥ በፖለቲካና በማፈያ መካከል ልዩነቱ እየደበዘዘ ሄዷል ማለት ይቻላል፡፡ በመሠረቱ ግን ፖለቲካ በምዕራቡ ዓለም እጅግ ተከበረ ፕሮፌሽን መሆኑን በመጠቆም የታሪክ ምሁሩ በአገራችንም በጥንት ጊዜ ፖለቲካና ፖለቲከኝነት እንዲሁ እንደነበር ያስረዳሉ፡፡

ፕሮፌሰር ሺፈራው ፖለቲካና ፖለቲሺያኖች የተከበሩ፣ ጨዋ፣ የጨዋ ጨዋ ካልሆኑ፣ የሚናገሩት ከመሬት ጠብ የማይል ካልሆነ ምንም ያህል ውብ ውብ ራእዮች ስንደቀድቅ ብንውል ራእዮቻችን ዋጋ አይኖራቸውም ሲሉ ነው የሚደመድሙት፡፡

በስነ ምግባር የታነጸ፣ ጨዋ፣ ለራሱ ሳይሆን ለሕዝቡ የተሰጠ፣ ልክ እንደ እስራኤላውያኑ መሪ ሙሴ ‹‹ይህን ሕዝብ ከምታጠፋው እኔን ከሕይወት መጽሐፍ ደምስሰኝ፡፡›› የሚል በሕዝብ ፍቅር የሰከረ፣ በሳል ፖለቲከኛ/መሪ፣ ከጽንፈኝነት፣ ከጥላቻና ከጎሰኝነት የጸዳ ጠንካራ ፓርቲና ፖለቲካኞች ለማየት አልናፈቃችሁም ወገኖቼ?!

በትንሹም በትልቁም ዛቻና ማስፈራሪያ እየበረገገ፣ መከራው ሲጸናበትና ቀንበር ሲከብድበት ለሕዝብ የገባውን ቃል አጥፎ፣ ‹‹ሞቴም መቃብሬም እዚሁ ነው፡፡›› ብሎ ምሎ እንዳልተገዘተ ሁሉ ‹‹በቦሌም በባሌም›› ብሎ እግሬ አውጪኝ በማለት ወደ አውሮፓና አሜሪካ የሚሰደድ ሳይሆን፣ እዚሁ በአገሩ ከሕዝቡ ጋር ደጉንም ክፉውንም ተቀብሎ በትዕግሥት፣ በጽናት እና በሰላማዊ መንገድ የሚታገል፣ በሕዝብ ፍቅር የወደቀና የነደደ እንደ ጋንዲ፣ እንደ ማርቲን ሉተር፣ እንደ አፍሪካዊው ኔልሰን ማንዴላ ያለ የሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነ ፓርቲና ፖለቲከኛ አልናፈቃችሁም ወገኖቼ!

እንዲህ ዓይነት ከሕዝብ ለሕዝብ የሆኑ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ሲፈጠሩ ሕዝቦች ያለ ምንም ቀስቃሽና ወትዋች በነቂስ ወጥተው ያገለግለናል፣ ይጠቅመናል የሚሉትን ፓርቲም ሆነ እጩ ለመመረጥ የሌሊቱ ቁር፣ የቀኑ ፀሐይ ሳይበግራቸው መብታቸውን አውቀው ለመጠቀም ይተጋሉ፣ ይሰለፋሉ፡፡ ምርጫ 97 ደግሞ ይህን ሐቅ ለመንግሥት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ በይፋ አሳይቷል፣ አስመስክሯል፡፡

ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለመቀመጫ ወይም ለስልጣን ከመወዳደራቸው በፊት የሕዝብን ልብ አሸንፈው፣ በሕዝባቸው ልብ ዙፋን ላይ ሊቀመጡ የሚችሉበትን ፍቅርን፣ መፈራትን፣ መወደድንና መከበርን ያገኙ ዘንድ መትጋትና መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡ የዛን ጊዜ ምርጫው ምርጫ ይሆናል፤ ሕዝብም ያለ ምንም ቀስቃሽ የመምረጥ መብቱን ለመጠቀም በነቂስ ተጠራርቶ ይወጣል፡፡

ሰላም! ሻሎም!

 

↧

‹‹ጎልጎታ››፡- ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር . . . !!!

$
0
0

Gologotaበፍቅር ለይኩን፡፡

ለዚህ መጣጥፌ የመረጥኩት የእውቁ ሠዓሊና ባለ ቅኔ የገብረ ክርስቶስ ደስታን ‹‹ጎልጎታ›› በሚል ርዕስ የተጠበበትን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሥነ ስቅለት አስደናቂና ዘመን አይሽሬ (classical) ሥራውን ነው፡፡ የዚህን ገጣሚና ሰዓሊ፣ እጅግ ተወዳጅና ተደናቂው የሆነውን ‹‹የጎልጎታን›› ስነ ስቅለት፣ ፍቅርን ተጠበበትን ድንቅ ሥራውን ፅንሰትና ውልደት ታሪክ በአጭሩ ላውጋችኹ፡፡

ገጣሚና ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ ስሙ ጎልቶ ከሚጠቀሱ የስነ ጥበብ ሰዎች ዘንድ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ እውቅና ታላቅ ሰው ነው፡፡ ገ/ክርስቶስ ዘመናዊ የስዕል ሙያን በአገር ውስጥና በአውሮፓ ከተማረ በኋላ በአገሩ እምብዛም አልቆየም ነበር፡፡ በአገራችን በተከሰተው የ1966ቱ አብዮትና ከነደደው የነውጥና የለውጥ እሳት የተነሣ እንደ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ወገኖቹ የእርሱም ዕጣ ፈንታ ስደት ሆኖ ነበር፡፡
ገ/ክርስቶስ በትምህርትና በስደት ሕይወት ለረጅም ዓመታት በባሕረ ማዶ በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ አውሮፓውያኑ ወይም በአጠቃላይ ነጮች ለአፍሪካውያንና ለጥቁር ሕዝቦች ያላቸው ዘረኝነት፣ ንቀትና ጥላቻ በእጅጉ ያብሰለስለውና እረፍት ይነሳው ነበር፡፡

ከምንም በላይ ደግሞ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምድር ተምሳሌት፣ በዓለማችን ታሪክ ታይቶና፣ ተሰምቶ በማይታወቅ ጀግንነትና ወኔ ኢትዮጵያውያን፣ አባቶቹ ወራሪውን የኢጣሊያንን ቅኝ ገዢ ኃይል በዓድዋ ጦር ግንባር በአኩሪ ጀግንነት አሳፍረው የመለሱ ኃያላን መሆናቸውን አሳምሮ ለሚያውቀው ገ/ክርስቶስ ይህ የአውሮፓውኑ ትምክህትና ንቀት ከመገረምም በላይ ሆኖበት ነበር፡፡

በዚህ የአገሩ ታሪክም በእጅጉ የሚኮራውና በዓለም ታሪክ አንጸባራቂ የሆነ የጥቁር ሕዝቦችን ነፃነት ድል፣ ፋና ወጊን ታሪክ በደማቸው ከፃፉ፣ የነፃነት ምድር ከሆነችው ከኢትዮጵያ ለተሰደደው፣ ለነፃነቱና ለክብሩ ቀናዒ ለሆነው ገ/ክርስቶስ ደስታ፤ አውሮፓውያኑ በጥቁሮች ወገኖቹ ላይ ያንጸባርቁት የነበረው ንቀትና ጥላቻ ፈፅሞ ሊቀበለው የማይችልና ሊቋቋመው ያቃተው ፈታኝ ገጠመኙ ነበር፡፡

ገ/ክርስቶስ በዚህ እጅግ በከፋውና ክፉኛ ቅሬታ ስላሳደረበት የአውሮፓውያኑ ዘረኝነት፣ የስደትና የብቸኝነት ዘመኑ፣ በእናት ምድሩ ናፍቆትና ትዝታ ነጋ ጠባ እንደ ሽንብራ እየተንገረገበ በጻፈው ‹‹አገሬ›› በሚለው ግጥሙ፣ አገሩ ኢትዮጵያ የሺሕ ዘመናት የስልጣኔ፣ የታሪክና የቅርስ ባለቤት፣ እንዲሁም የጥቁሮች ሕዝቦችና የሰው ልጆች ሁሉ ነፃነትና ሰብአዊ ክብር ተምሳሌትና መገለጫ አገር መሆኗን እንዲህ በሚል ስንኝ ነበር፤ አገሩን ከነፍሱ በፈለቀች ቅኔው የገለጻት፡-
… አገሬ ዓርማ ነው የነጻነት ዋንጫ
በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ብጫ።
እሾህ ነው አገሬ፣
በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ
ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ።
… አገሬ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት
ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት።
ለምለም ነው አገሬ፣
ውበት ነው አገሬ፣
ገነት ነው አገሬ።
… ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ
እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ።
ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ
አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ።
አለብኝ ቀጠሮ
ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ …፡፡
~ገብረክርስቶስ ደስታ፡፡
በዚህ ግጥም ውስጥ ገ/ክርስቶስ ለእናት ምድሩ ያለውን ፍቅሩን፣ ሰቀቀኑን፣ ናፍቆቱንና ትዝታውን ነፍስን በሚያማልል፣ አጥንት ድረስ ዘልቆ ሊሰማ በሚችል ስዕላዊ ቋንቋ የአገር ፍቅር ህመሙን፣ ስቃዩን፣ ጩኸቱንና ሰቀቀኑን እንዲህ ባለ ሕብረ ዜማ፣ ልዩ ቋንቋ ከነፍስያው ጋር እያወጋ፣ እንዲህ ለእኛም ህመሙን፣ የአገር ፍቅር ትዝታውንና ናፍቆቱን በሚጥም ዜማና ቋንቋ አካፍሎናል፡፡

አውሮፓውያኑ ዘንድ ‹‹ጥቁር በምንም ዓይነት ከነጮች ጋር በእኩልነት እንዲመደብ የሚያስችለው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ስብእና የለውም፡፡›› በሚለው እሳቤያቸው ከአፍሪካ የጀግኖች ምድር ከሆነችው ከኢትዮጵያ ለሄደው ገ/ክርስቶስ የስነ ልቦና ቀውስ አሳድሮበት ነበር፡፡ ከዛም አልፎ ‹‹እግዚአብሔር ነጭ ወይም አውሮፓዊ›› እንደሆነ በድፍረት በሚሰብኩበት በዛ በባዕድ ምድር ያ የጥበብ ምርኮኛ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ ልቡ ተነክቶ፣ ነፍሱም ክፉኛ አዝናበት ነበር፡፡

እናም ይህ የጥቁር ምድር፣ አፈር ትሩፋት የሆነው ጥበበኛው ገ/ክርስቶስ ከእኛ በላይ ክርስቲያን ለአሣር በሚሉትና ይህን የአውሮፓውያኑን መርዘኛ፣ ዘረኛ አስተሳሰብና ምልከታ፣ ጥልቅና ምጡቅ በሆነ የጥበብ ሥራው ሊሞግታቸው፣ ሊያሳፍራቸው ከነፍሱና ከመንፈሱ ጋር ተማከረ፡፡

ከልጅነቱ ጀምሮ ከታወቁት የቅኔ መምህርና የተዋሕዶ ሊቅ ከሆኑት ከአባቱ ከአለቃ ደስታ ነገዎ ዘንድ ፊደል ቆጥሮ፣ ዳዊት ደግሞ፣ ዜማ ተምሮ፣ በዘመኑ የነበሩትን የአባቱን ዘመነኞች ሊቃውንት ቅኔና የመንፈሳዊን ዓለም ረቂቅ የሆነ ትንታኔና ትርጓሜ የሆነ ጥልቅ እውቀት ጠዋት ማታ እየሰማ ላደገው ለገ/ክርስቶስ፣ መንፈስ የሆነው እግዚአብሔር በምን መንገድ፣ በምን ጥበብ የአውሮፓዊነት ወይም የነጭነት ቆዳን ወይም መልክን እንደተጎናጸፈ ፈፅሞ ግራ ነበር ያጋባው፡፡

እናም ይህ እውቀት የሥጋ፣ ይኽ ድንቁርናም ከክፉው፣ የዚህ ጥበባቸው ምንጩም አጋንት- የሐሰት አባት ዲያቢሎስ መሆኑን ሊነግራቸው ሠዓሊው ቀለሙን በጠበጠ፣ ብሩሹን ወደረ፣ ሸራውንም ወጠረ፡፡ የአውሮፓውያኑን የዘርኝነት እኩይ አስተሳሰብ፣ ከሰው ዘር አልፎ እግዚአብሔርን ሳይቀር እንኳን ነጭና ዘረኛ ያደረጉበትን ከንቱ የሆነውን ትምክህታቸውንና ድንቁርናቸውን የእንቧይ ካብ መሆኑን በግልፅ ሊነግራቸው ቆርጦ ገ/ክርስቶስ ቀለሙን ከሸራው አዋኻደ፡፡

እናም ጥበበኛው በስዕሉ ዓለምን ያስደመመ ድንቅ የፍቅርን ቅኔን በብሩሹ ተቀኘ፡፡ ባለ ቅኔውና ሰዓሊው ገ/ክርስቶስ ይህን ‹‹ጎልጎታ›› ብሎ የሰየመውን ቆዳ አምላኪዎቹን፣ አውሮፓውያኑን ሣይቀር በእጅጉ ያስደመመውን ይህን ታላቁን የጥበብ ሥራውን በቅዱስ ቅናት፣ ከፍቅርና ከእውነት በመነጨ እውቀት ተነሳስቶ ነበር የሳለው፡፡ በዚህም ድንቅ የጥበብ ሥራው ገ/ክርስቶስ አውሮፓውያኑን ዘረኞችና ትምክህተኞች እንዲህ ሲል በጥበብ ሥራው ሞገታቸው፣ አሳፈራቸውም፡-

እናንተ እናመልከዋለን የምትሉት እግዚአብሔር ግን ነጭም ጥቁር ወይም ቢጫም አይደለም፡፡ አፍሪካዊም አውሮፓዊም ወይም አሜሪካዊ አይደለም፡፡ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ፣ የጥበብ ሁሉ መዝገብ፣ የፍቅር ምንጭ የሆነ- የፍቅር አምላክ ነው!! እናም እርሱን የዘር፣ የጎሳ፣ የነገድ፣ የቋንቋ፣ የቆዳ የቀለም ድንበር ፈፅሞ የማይለየው፣ የማይገድበው ሁለተናው ፍቅር የሆነ፣ በፍቅር የተጥለቀለቀ፣ በፍቅር ስለ ፍቅር የቆሰለ፣ በፍቅር ስለ ፍቅር በደም የተነከረ፣ ደምግባቱና ውበቱ ደም የጎረፈበት፣ በደም የተረጨ፣ በደም የታተመ፣ በደም የተጥለቀለቀ፣ ሞትን በሞት የረታ ሕያው፣ ዘላለማዊ ፍ-ቅ-ር ነው!!

ይህ ተአምረኛ የሆነው የገ/ክርስቶስ ‹‹ጎልጎታ›› የጥበብ ሥራው፡- የህማም ሰው፣ እንወደው ዘንድ ደምግባት የሌለውን፣ ውበት የራቀውን፣ የተናቀውን፣ ስለ ሰው ልጆች ሁሉ መተላለፍ ቆሰለውን፣ ስለ በደላችንም የደቀቀውን፣ ስለ እኛ ብርቱ ህመምን የታመመውን፣ በጌተ ሰማኒ የደም ላብ ያላበውን፣ ስለ ክፋታችን የተጨነቀውን፣ በቀራኒዮ አደባባይ የተቸነከረውን፣ ክርስቶስ ኢየሱስን በደም ገለጸው፡፡

የእሾኽ አክሊልን የደፋው ራሱ፣ በሚስማር የተቸነከሩት ቅዱሳን እጆቹና እግሮቹ፣ በጦር የተዋጋው ጎኑ፣ በሮማውያኑ ጅራፍ የተተለተለው ጀርባውና የቆሰለው መላው አካላቱ፣ ፍቅርንና ምሕረትን በደም ጅረት፣ ለአዳም ልጆች ሁሉ የሚያውጁ፣ ዘላለማዊ የሆኑ የፍቅር ሕያው ማህተሞች መሆናቸውን በይፋ ገለጸላቸው፡፡

እርሱ ኢየሱስ መቼም መቼም የማይደበዝዝ፣ የማይነጥፍ፣ የማይደርቅ ሕያው የፍቅር ደም ጅረት፣ የዘላለም ሕይወት ምንጭ፣ የደም መሥዋዕት፣ ረቂቅ ውበትን የተጎናጸፈ ቅዱስ መሥዋዕት መሆኑን ጠቢቡ በብሩሹ በቀይ ቀለም፣ በደም ቋንቋ ገለጸልን፣ ተቀኘልንም፡፡

የዚህ ትንግርተኛ የጥበብ ሰው የገ/ክርስቶስ ዘመን አይሽሬ ሥራው በሸራ ሰሌዳ፣ በብሩሽ ቀለም፣ በደም ቋንቋ፣ እርሱ ክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ፡- በቀራኒዮ ባፈሰሰው በክቡር ደሙ ፈሳሽነት ለሰማያዊው አባቱ ሰዎችን ሁሉ ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋም ሁሉ፣ ከወገንም ሁሉ፣ ከሕዝብም ሁሉ የዋጀ ሕያውና ዘላለማዊ ፍቅር መሆኑ ነገረን፣ አወጀልን፡፡

በእርግጥም እርሱ ሕዝብን ከአሕዛብ፣ አይሁዳውያንን ከግሪክ፣ ነጩን ከጥቁሩ፣ ኢትጵያውኑን ከአውሮፓዊው ጋር አንድ ያደረገ ፍ-ቅ-ር . . . የፍቅር አምላክ፣ ንጹሕ፣ መዓዛው የተወደደ፣ ሽታው ያማረ የፍቅር መሥዋዕት ነው!!

ስለዚህም ይህ ፍቅር አለ ጥበበኛው ገ/ክርስቶስ፣ ይህ ፍ-ቅ-ር ዘር፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ ዜግነት ሳይል ሁሉንም በእኩልነት የሚያፈቅር እንጂ እናንተ እንደምታስቡት እግዚአብሔር ነጭ፣ ፈጣሪ አውሮፓዊ ወይም አሜሪካዊ አሊያም አፍሪካዊ አይደለም …፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር፣ ፍቅርም እግዚአብሔር ነው እንጂ፡፡ ‹‹በጎልጎታ›› ድንቅ የጥበብ ሥራው ገብሬ ኢየሱስ የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ በደም የታታመ፣ በደም የተዋበ፣ ፍጹም ፍ-ቅ-ር፣ ሕያው ፍ-ቅ-ር፣ በፍቅር ስለ ፍቅር የተሠዋ የመሥዋዕት በግ ነው እንጂ፤

ሲል ገ/ክርስቶስ ይህን የእግዚአብሔር ልጅ የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን የቀራኒዮውን ፍቅሩን ‹‹ጎልጎታ›› ብሎ በሰየመው የጥበብ ሥራው በደም ቀለም፣ በደም ጎርፍ፣ በደም ብሩሽ ፅልመት በዋጠው በመሰለው ሸራው ላይ በብሩሹ ፍቅርን በደም ጎርፍ፣ ፍቅርን በደም አበላ እንዲህ ተጠበበት፣ እንዲህ ተደመመበት፣ እንዲህ ተቀኘበት፡፡

‹‹ጎልጎታ›› የገብረ ክርስቶስ ዘመን አይሽሬ (Classical) የሆነች በብዙዎች ነፍስ፣ አጥንትና ጅማት ድረስ ዘልቃ፣ የፍቅርን ብርቱ፣ ኃይልና ጽናት የምትገልጽ ሥራው እንደሆነች በርካታ አድናቂዎቹ ይመሰክራሉ፡፡ በአንድ ወቅት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢትዮጵያ ጥናት መጽሔት (Ethiopian Studies Journal) ላይ የገ/ክርስቶስ የጥበብ ልጁና የሙያው ባልደረባ የሆነው አቶ እሸቱ ጥሩነህ ስለ ገብሬ ታሪክና ስለ ‹‹ጎልጎታ›› ድንቅዬ የጥበበብ ሥራው ባቀረበው የጥናት ጽሑፉ እንዲህ ነበር ያለው፡-

… ይህ የገ/ክርስቶስ ደስታ የሥነ ሥቅለት ስዕላዊ ድርሰት የፍቅርን፣ የመሥዋዕትነትን፣ የቤዛነትን፣ የሕያውነትና የዘላለማዊነትን፣ እንዲሁም የነፃነትንና ሰላምን ምንነት ባጫሩ በሕብረ ቀለማት የቃኘበትና የተቀኘበት ነው፡፡ መስቀሉ እውነታዊ ነው፡፡ የተሰቀለው ክርስቶስ ግን ተምሳሌታዊ ነው፡፡ ሥዕሉ እስከተሠራበት እስከዚያን ጊዜ ድረስ ብዙ ሠዓሊዎች አካሉን ወይም ስጋውን አልፎም እውነታዊ ምስሉን ከነስቃዩ ይስላሉ እንጂ፣ እንደ ገብረ ክርስቶስ ክቡር ደሙን፣ ንጹሕ መሥዋዕትነቱን በቀይ ሕብረ ቀለም ብቻ ተምሳሌት አድርገውና ወሰነው የሠሩ የሉም … ፡፡

ይህን በሚመለከት ይላል አቶ እሸቱ ጥሩነህ፣ ‹‹የገብረ ክርስቶስ ደስታ፣ አጭር ትውስታና ጨረፍታዊ ዕይታ›› በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባቀረበው በዚሁ ጥናቱ፣ ይህን በሚመለከት የጀርመን አገር ጓደኛው የነበረው ዶ/ር እጓለ ገብረ ዮሐንስ እንዲህ በማለት ጽፏል ይለናል፡-

ሰዓሊ ተብሎ የጎልጎታን ተራራ ያልወጣ፣ የቀራኒዮን ትልቁን ትራጀዲ ያላየ የለም፤ ግን የገብረ ክርስቶስ ሥነ-ስቅለት ለብቻው ነው፡፡ ቀለም ተናጋሪው ነው፣ የሚታየው ንጹሕ ደም ብቻ ነው፡፡ ግራና ቀኝ የነበሩት (የተሰቀሉት) እነ ፋይታዊ ቦታ የላቸውም ተዘንግተዋል፡፡ ወይም ሠዓሊው ሊያያቸው አልፈለገም፣ ይገርማል፡፡ ጥበብ ከንጹሕነት ከጽርየት ከርቀት ብቻ እንጂ ከሌላ ጋር ግንኙነት የሌላት መሆኑን ለመረዳት ይቻላል፡፡

ዛሬም ድረስ የገ/ክርስቶስ የፍቅር፣ የናፍቆት፣ የነፍሱ ስቃይና ጣር የሆነችው ‹‹ጎልጎታ›› የፍቅር ሕያው መዝገብ፣ የጥበብ ቁንጮ ሥራ ሆና በዚህ ክብሯ፣ ማዕረጓና ሕያውነቷ ዘልቃለች፡፡ ፍቅርን በመሥዋዕትነት፣ ፍቅርን በእውነት፣ ፍቅርን በደም እየተረከች፣ በደም እየሞሸረች፣ በእሾኽ አክሊል፣ በደም እያነገሠች፣ በጦርና በችንካር በደም እያስዋበች፣ በደም እየተረከች… ፡፡

ይህ የገ/ክርስቶስ ዘመን አይሽሬ የሆነ የጥበብ ሥራው ለበርካታ ዓመታት በስደት ከቆየበት ከወደ አውሮፓ መጥቶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጀርመን መንግሥት እርዳታ በስሙ በተቋቋመው የስነ ጥበብ መዘክር ውስጥ ይገኛል፡፡ ገና ወደዚህ ቤተ መዘክሩ አዳራሽ ውስጥ ስትገቡ ዓይናችሁ ፊት ለፊት በሚታየው በዚህ ትንግርተኛ የገብሬ ጥበብ ሥራ ‹‹ጎልጎታ›› ላይ ዓይናችሁ ተተከሎ ይቀራል፡፡ በዛ ፅልመት በዋጠው በሚመስለው ሸራ ላይ በተረጨው ደም ውስጥ የሰው ልጆች ሁሉ የመውደቅና የመነሳት ታሪክ፣ ጅማሬና ፍፃሜው በደም ቋንቋ፣ በደም ቀለም፣ በደም ብሩሽ በጉልህ ደምቆ ይታያል፡፡

ያን መሳጭ፣ ያን ምሥጢረኛ፣ ያን ትንግርተኛ፣ ያን ነፍስን፣ አጥንትንና ጅማትን ዘልቆ በሚመትር ልዩ ኃይልንና ጥበብን በተቸረው ‹‹በጎልጎታ›› ድንቅ የጥበብ ሥራ ላይ መላ አካላታችን በአጠቃላይ ለቅጽበት ዓይን ሆኖ ፈዞ፣ ደንግዞና ተውጦ ይቀራል፡፡ እናም ከቤተልሔም ግርግም እስከ ጎልጎታ-ቀራኒዮ የፍቅር ኃይል፣ የፍቅር ቤዛነት፣ የፍቅር ጥበብ፣ የፍቅር ትሕትና፣ የፍቅር ትዕግሥት፣ የፍቅር ጽናት፣ የፍቅር ኤልሻዳይነት፣ ፍቅር ሕያውነት… ቃላት ሊገልጹት በማይቻላቸው በደም ቋንቋ፣ በደም ቀለም ፍቅርን ያሳያችኋል፡፡ ፍ-ቅ-ር በለሆሳስ፣ መንፈሳዊ በሆነ ሰማያዊ ቋንቋ ያናግረችኋል፣ ያወራችኋል፡፡

በዚህ በእጅጉ አስገራሚ፣ አስደናቂና አስደማሚ በሆነው የጥበብ ሥራው ገ/ክርስቶስ ፍ-ቅ-ር-ን በጥበብ ቋንቋ፣ በረቂቅ ክህሎት፣ ልዩ በሆነ ኃይል ትላንትና፣ ዛሬ፣ ነገም እስከ ዘላለምም ሲያውጅ ታዩታላችኹ፣ ትሰሙታላችኹ፣ ሊያውም በለሆሳስ በሆነ የነፍስ ጩኸት፣ የነፍስ ድምፅ፣ የነፍስ ቋንቋ!!

በገ/ክርስቶስ ‹‹ጎልጎታ›› ሥራ ላይ ይህን እውነት፣ ይህን በደም የተከፈለ፣ በደም የጸና የእግዚአብሔር ፍቅር ምሕረትን፣ ይቅርታን፣ በጎነትን፣ ቸርነትን፣ ርኅራኄን፣ ፍትሕን፣ እውነትን፣ ፍርድን፣ ጽድቅንና በረከትን የተሞላ እንደሆነ በጎልጎታ ተራራ በቀራኒዮ ላይ ተገልጦ ለሁሉ ታይቷል፡፡

 ይህ ፍቅር አሳልፎ ሊሰጠው በ30 ብር የተዋዋለውን ይሁዳን ‹‹ሰላም ለአንተ ይሁን ወዳጄ ሆይ!›› ብሎ በፍቅርና በርኅራኄ መንፈስ ተቀብሎ የሳመ ነው፣
 ይህ ፍቅር የከሐዲውን የደቀ መዝሙሩን እግር በፍቅርና በትሕትና ዝቅ ብሎ ያጠበ፣ ከከበረ ማዕዱም ያለየው ልዩ ፍ-ቅ-ር ነው፣
 ይህ ፍቅር ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ የካደውን የጴጥሮስን በዕንባ ጅረት፣ በንስሐ፣ በጸጸት ወደራሱ፣ ወደ ፍቅሩ መንግሥት የመለሰ ነው፣
 ይህ ፍቅር ለጠላቶቹ፣ ለሚሳለቁበትና ለሚወጉት ሁሉ ‹‹አባት ሆይ የሚሰሩትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው!›› ብሎ ምሕረትንና ይቅርታን የማለደ ነው፣
 ይህ ፍቅር ከእናታችንና ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሳው ሥጋ፣ በዘላለማዊ ፍቅሩና ቸርነቱ ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራን በእኛ በኃጢአተኞቹ ፈጽሞ ያላፈረብንና ያልተጸየፈን ነው፣
 ይህ ፍቅር ሰማይ፣ ሰማይ ሰማያትን በልዩ ብርሃን ያስዋበ የብርሃን ጎርፍ፣ የብርሃን ጎህ ምንጭ፣ ዘላለማዊና የማይጠፋ ፋና ነው፣
 ይህ ፍቅር በአፉ እስትንፋስ ምድርንና ሞላዋን፣ ባሕርንና ውቅያኖሶችን በውስጣቸው የሚኖሩትን ፍጥረታት ሁሉ በሕይወት ብርሃን ያስጌጠ፣ ውብ፣ ድንቅ ተዋዳጅ፣ አባትና አምላክ ነው፣
 በዚህ ፍቅር መጽሐፍ እንደሚል ሕያዋን ነን፣ ሕያው ሆነንም እንቀሳቀሳለን፣ ይህ ፍቅር ሕይወትን፣ ጸጋንና ሰላምን ሰጥቶናል፣

ይህ ፍቅር ሰላምን፣ ጽድቅን፣ ፍትህን፣ ፍርድንና ፍጹም ደስታን ለምድሪቱ ያጎናጸፈና ዘላለማዊ ሕይወትንና ነፃነትን ያቀዳጀን ነው፡፡ ለዚህም ነው በፋሲካው፣ በትንሣኤው ክብረ በዓል እኩለ ሌሊት፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶችና ሊቃውንቱ በቤተ መቅደሱ በማሕሌታቸውና በወረባቸው፡- ‹‹ወምድርኒ ትገብር ፈሲካ፣ ታሕፂባ በደም ክርስቶስ፡፡›› እያሉ ይህን ታላቅ የፍቅር ድል የምስራች ዜማ ለምድሪቱና ለፍጥረት ሁሉ በታላቅ ድምጽ ደግመው ደጋግመው በታላቅ ድምፅ የሚያሰሙት፡፡

‹‹ምድር ንጹሕ፣ ክቡር በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ታጥባና ነጽታ በሐሴትና ፍጹም በሆነ ሰማያዊ ደስታ ፋሲካን ታከብረው›› ዘንድ ልዩ በሆነ ሰማያዊ ዜማ ፍቅርን የምስራች በሚል ውብ ሰማያዊ ዜማ ሰላምንና ሕይወትን የሚያውጁት፡፡ የዚህ አምላክ ፍቅሩና ቸርነቱ በእጅጉ ያስደነቀው የቤተ ክርስቲያን አባትና ሊቅ የሆነው ዮሐንስ አፈወርቅ በቅዳሴው እንዲህ እንዳመሰጠረ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡-

‹‹ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው፣ ይህን ያህል ሰው ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር የአምላክን ልጅ ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም ድረስ አደረሰው፡፡›› በማለት የእግዚአብሔር ሰውን ፈጽሞ ስለመውደድ፣ የመሞቱ ምስጢር ከዘላለማዊውና ሕያው ከሆነ ፍቅሩ የተነሳ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለትና ትንሣኤ በዓልም ከዚሁ ጥልቅና መንፈሳዊ ከሆነ ፍቅርና ምሕረት ጋር ተያይዞ እንደሚከበር የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያስተምራሉ፡፡ አንድ ያነጋገርኳቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አባት እንደነገሩኝ የዘንድሮ ፋሲካ በዓል ለየት ያለ ነው አሉኝ፡፡ እንዴት አልኳቸውም መልሼ፣ ሲመልሱልኝም፡-

የዘንድሮውን የፋሲካ በዓል ልዩ የሚያደርገው በእግዚአብሔር የተሰጠንን ነጻነታችንና ምድራችንን በአውሮፓውያኑ ወራሪ ኃይሎች፣ በፋሽስት ኢጣሊያን ኃይል ተነጥቀን ሳለ በእግዚአብሔር ፈቃድና ኃይል፣ በአባቶቻችን ጸሎትና በዐርበኞቻችን ተጋድሎ ነጻነታችን የተመለሰበትን ቀን የምንዘክርበት ቀንም ጭምር ስለሆነ በዓሉ እጥፍ ድርብ ነው ሲሉ ነግረውኛል፡፡

በዕለተ ስቅለትም ሆነ በፋሲካ በዓላችን የምንዘክረው የታረደው የፋሲካው ቅዱስ በግ፣ የቀራኒዮው ባለውለታችን፣ የትንሣኤው ጌታ፣ ፍቅር የሆነው የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ፣ ነፍስና ሥጋችንን እንዲገዛው ስንፈቅድለት ከወዳጆቻችን ሁሉ አልፎ ለሚጠሉንና ለጠላቶቻችን ሁሉ የሚተርፈረፍ ፍቅር በውስጣችን ይበዛልናል፡፡ ሕግ ሁሉ በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ይጠቃለላሉ እንዲል ቅዱስ መጽሐፍ፡-

‹‹እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹምም አሳብህ፣ በፍጹም ኃይልህ ወደድ፡፡ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ አድርገህ ወደድ፡፡›› ፍቅሩ ለእግዚእ በመባል የሚጠራው በጌታ መስቀል ስር በዛች አስጨናቂ የጣር ሰዓት የተገኘውና በዚህም ድንግል ማርያምን የፍቅር ስጦታ ልዩና ዘላለማዊ እናት አድርጎ ለመቀበል የታደለው ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ፡- ‹‹እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል፡፡›› ይለናል፡፡ በእውነተኛ ፍቅር እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በመካከላችን ይሆናል፤ ከክርስቶስ ኢየሱስ የተሰጠችን ፊተኛይቱ ትዕዛዝም ይህች ናት፡- ‹‹እርስ በርሳችን እንዋደድ ዘንድ!!››

መልካም የስቅለትና የፋሲካ በዓል ለሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ!
ሰላም! ሻሎም!

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live