Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“እኔ መገንጠል አልደግፍም፡፡ ይሄ ለሁሉም ችግሮች መፍትሄ አይሆንም”–አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

$
0
0
እውቁ የፖለቲካ ሰው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ስለ መገንጠል ጥያቄ ምላሽ ሰጡ:: መገንጠልን እንደማይደግፉ ይፋ አድርገዋል:: ቡልቻ እንዲህ አሉ “እንደኔ አሁን የመገንጠል ጥያቄ አያስፈልግም። እኔ መገንጠል አልደግፍም፡፡ ይሄ ለሁሉም ችግሮች መፍትሄ አይሆንም፡፡ ግን ፌዴሬሽን ሲባል ትክክለኛ ፌደሬሽን መሆን አለበት፡፡ ፌዴሬሽን አካላዊ ህመም የለውም፡፡ ቁንጥጫው አይሰማም – እንደመገንጠል፡፡ […]

 በጆርጂያ ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በግድያ ወንጀል ተጠርጥረው ተያዙ

$
0
0
(አድማስ ራድዮ) እዚህ ጆርጂያ ፣ ክላርክስተን በሚባለው ትንሽ ከተማ ውስጥ ነው ድርጊቱ ተፈጸመ የተባለው። የክላርክስተን ከተማ ፖሊስ እንደሚለው ክብሮም ገብሬ እና ቢኒያም መለሰ የተባሉ የ 18 ዓመት ወጣቶች ፣ አንድ ሃሰን አብዱላህ የተባለ የ 20 ዓመት ሱዳናዊ ወጣትን በጥይት ገድለዋል ተብሎ ነው የታሰሩት። ግድያው ተፈጸመ የተባለው የታንክስ ጊቪንግ ቀን ሲሆን፣ ፖሊስ ማጣራት አድርጎ ከጥቂት ቀናት […]

የ2017 የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫልን ለማዘጋጀት ዳላስ እና ሲያትል እየተፎካከሩ ነው

$
0
0
(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በጉጉት የሚጠብቁት ዓመታዊው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ዘንድሮም ከጁላይ 2, 2017 እስከ ጁላይ 8, 2016 የሚካሄድ ሲሆን የሚዘጋጅበት ከተማም ከዳላስ እና ከሲያትል አንዳቸው እንደሚሆን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል:: የዘ-ሐበሻ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) ምንጮች እንዳስታወቁት የዘንድሮውን ቶርናመንት ለማስተናገድ የተለያዩ ከተሞች ጥያቄ አቅርበው የነበረ ሲሆን በመጨረሻ ላይ የቀሩት ግን ሲያትል እና ዳላስ […]

ሞረሽ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ያወጣውን መግለጫ በ7 ነገሮች ታዘብኩት

$
0
0
አይቸው መንግስቴ (ጎንደሬው ነኝ) #የግል ምልከታ አይ እነ ሞረሽ ና …!!! የጨቅሎች ጨዋታ!! ከነ ሞረሽ መግለጫ እንደተረዳሁት ከሆነ ገና አልበሰሉም ። 1# ሲጀመር ፅሁፉ በስሜት የተነዳና በሆይሆይታ ያበጠ ከፌስ ቡክ ያየነውን በማሰባሰብ በድርጅት ስም የወጣ የአሉቧልታ ና የጨቅሎች ጨዋታ ነው። 2#ሞረሽ በፌስ ቡክ በተገነባ የአሉቧልታና የሆታ ሰራዊት መሪ ነኝ በሚል ልቡ አብጦ ታላቁን ድርጅት አርበኞች […]

ጎንደር ላይ ወያኔ በጭንቅ ውስጥ ነው |ወያኔ የራሱን ባለስልጣናት እያሰረ ትርምስ ውስጥ ነው

$
0
0
በመላ አማራ አካባቢ ህዝባዊ አብዮቱ እየተቀጣጠለ ነው! ታህሳስ 25 ቀን 2009 በሰሜን ጎንደር የቆላማው ወገራ ገበሬዎች ለወያኔ ሰራዊት የምግብ አቅርቦት አናደርግም በማለት ስላመፁ እንኳን ሰው የቆላው አየር ንብረቱ ጭምር የተዋጋው የወያኔ ሰራዊት ከሶስት ቀን በፊት ቦታዉን ለቆ መውጣቱ ታውቋል። ነገር ግን ዱር ቤቴ ያለውን ታጋይ ህዝብ ለማዘናጋትም ሊሆን ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግ ከጎበዝ አለቆች ማሳሰቢያ ተላልፏል። […]

መጠላለፍ ለሕወሓት ህልውና ትልቅ ግባት ነው።

$
0
0
#መደማመጥና_ቀናነት ቡድን ለሀያ አምስት አመት ተንሰራፍቶ ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ የሚገኘው ትግራይን ለመገንጠል አላማ አድርጎ የተነሳ ግን የሚታገለው በማጣቱ የሀገሪቱ መራሒ መንግስት በመሆን በሀገሪቱን ዜጎች የፈለገውን በማሰር፣ ኣሰቃቂ ድብደባ በመፈጸም እና በመግደል እስከወዲያኛው ትውልድ ድረስ ተከፍሎ የማያልቅ ብድር በሀገሪቱ ስም በመበደር የሕወሓት ባለስልጣናት በየግል ካዝናቸው በስበብ አስባቡ ዘርፈው አከማችተውታል። ግፍ የመረረው ህዝባችን በእልህ እና በቁጭት መሳሪያ […]

ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት አንገብጋቢ ሁኔታ ሚዛናዊና አስተዋይ አንድነትን አርቆ የሚያይ ሃይል ያስፈልጋታል።

$
0
0
#መደማመጥና_ቀናነት ቡድን   #መደማመጥና_ቀናነት ቡድን — እኛ በተሻለ ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያን በነፃ ሀሳብን ማንሸራሸር ለድምፅ አልባ ወገኖቻችን ድምፅ መሆን እንችላለን ።የተሻለ ዕድሉ አለን።በውጭው ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲን በተግባር ምን እንደሚመስል ከሀገር ቤቱ ወገን በበለጠ እናውቃለን የሕግ የበላይነት ምን እንደሆን እናውቃለን።ያወጣው ሕግ በማያከብረው የሕወሓት መንግሥት ሥር ሆነው ስለሕገ መንግሥት ትርጉም አልባነት በተግባር እያዩና ለዚያም ሰለባ ሆነው […]

በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ቀሪ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ቀጠሮ ተሰጠ |የታህሳስ 20 የፍርድ ቤት ውሎ

$
0
0
ታህሳስ 20 በዋለው ችሎት 2ት ምስክሮች ተሰምተዋል:: አቃቢ ህግ በ6ኛ (ገላና ነገራ) እና 11ኛ(በየነ ሩዳ) ተከሳሽ ላይ የሚመሰክሩ ምስክሮች እንደቀረቡ ለችሎት አሳውቆ የሚመሰክሩበትን ጭብጥ አሲዟል፡፡ 11 ተከሳሽ በሆነው በየነ ሩዳ ላይ ለመመስከር የቀረቡት አቶ ዳውድ አበጋዝ ሲሆኑ በ20/05/2008ዓም በፌደራል ወንጀል ምርመራ ማእከል ተገኝተው ከተከሳሽ ኢሜል፣ ፌስቡክ እና ሞባይል ላይ መረጃዎች ሲወጡ የታዘቡትን እንደሚመሰክሩለት አቃቢ ህግ […]

Wazema Radio:- አዲስ አበባ በስኳርና በዘይት ሰልፎች ተጨንቃለች –

$
0
0
ከሰሞኑ አዲስ የፉርኖ ዱቄት እጥረት ተከስቷል፡፡ ባለሱቆች ስኳር የሚሸጡለትን ዜጋ ሙሉ አድራሻ እንዲይዙ ተነግሯቸዋል የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት የሌላቸው ዜጎች ስኳር መግዛት አይችሉም ዋዜማ ራዲዮ- ከአውድ ዓመት መቃረብ ጋር ተያይዞ ለስኳርና ዘይት ግዢ በየወረዳው የሚገኙ የሸማች ማኅበራት ሱቆች ታይቶ የማይታወቅ ረዣዥም ሰልፎችን እያስተናገዱ ይገኛሉ፡፡ በአንዳንዶቹ የኅብረት ሱቆች ወረፋ ከሌሊት ጀምሮ መያዝ እየተለመደ መጥቷል፡፡ በጎላ ሚካኤል […]

አገሪቷ ወደ ብተና ማምራቷ አይቀርም – አቶ ስብሃት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ

$
0
0
የኢህአዴግ ጉባኤ አሰራሩ መፈተሽ እንዳለበት አቶ ስብሃት ነጋ አመለከቱ ኢህአዴግ ሙሰኞችን ካልከሰሰ አገሪቷ ወደ ብተና ማምራቷ አይቀርም ብለዋል የኢህአዴግ ጉባኤ አሰራሩ የብሄራዊ ድርጅቶችን ወቅታዊና ትክክለኛ አቋም የሚያሳይ ነው ብለው እንደማያምኑና መፈተሽ እንዳለበት አንጋፋው የኢህአዴግ ታጋይ/የህወሓት መስራች/ አቶ ስብሃት ነጋ ተናገሩ፡፡ ኢህአዴግ ባመነው ልክ ሙሰኞችን ካልከሰሰ አገሪቷ ወደ ብተና ማምራቷ አይቀርም ብለዋል፡፡ አቶ ስብሃት ለአዲስ ዘመን […]

አማራ ተባብሮ መዳን ወይንስ ተለያይቶ መጥፋት።

$
0
0
ከማተቤ መለሰ ተሰማ እንደማነኛውም የሰውልጅ አማራውም የህግ የበላይነትን፣ እኩልነትና ነጻነትን፣ የሰባዊ መብት መከበርን፣ እድገትንና ብልጽግናን ወ.ዘ.ተ. አጥብቆ ይናፍቃል። እነዚህን ሰው ለመሆን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ለመቀዳጀትም ዋጋ ሲከፍል አመታትን አስቆጥሯል። እስካሁን ግን ልፋቱ ሁሉ አልተሳካም ብቻ ሳይሆን ከጊዜ ወደጊዜ እየከፋና እየመረረ፣እንቅስቃሴው ሽባ ውጤቱ ፍሬ አልባ። እየሆነና ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለቱ በሌላው ወገኑ እንደጠላት እየታየ በመገደል ላይ ነው። […]

ጋሽ ደቤ ! –ይድነቃቸው ከበደ

$
0
0
ተዋናይ ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆነ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራ እና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል ። በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል ፣ በአትላንታ ጆርጂያ በበረከተው የሙያው ሥራ ኖቬምበር 24 ቀን በስሙ ተሰይሞለታል። (ጋሽ ደቤ) በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት ካሉት አርቲስቶች ግንባር ቀደሙና አንጋፋው ነው። ጋሽ ደቤ ከሰራቸው ስራዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ፤ ያላቻ […]

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ዋስትና ተከለከለ

$
0
0
ከሽብርተኝነት ክስ ነጻ ተብሎ በመደበኛ የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ እንዲከላከል ብይን የተሰጠው የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የዋስትና ጥያቄው ውድቅ ተደርጎበታል፡፡ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 13/2009 ዓ.ም ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ከቀረበበት የሽብር ክስ ነጻ በማለት ክሱ ወደ መደበኛ የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ተቀይሮ አንቀጽ 257 (ሀ) ላይ የተመለከተውን እንዲከላከል […]

እንኳን ለገና አደረሰን |አሰፋ ጫቦ 

$
0
0
Dallas Texas USA የፈረንጅ ገና ዋዜማ ለት በሆንኩት ልጀምር።ሁለት ወዳጆቼ፤አንደኛው ከዚሁ ከቨርጂኒያ ፤ሌላው ከሳሳከችዋን፤ካናዳ ደውሎ ስለበእሉ ትንሽ ተነጋገርን። እነሱም የሚሰማቸውን እኔም የሚሰማን ያዝ ለቀቅ አደርገነው። “ዞር ዞሮ ከቤት!” እንዲሉ ያው ሁሌም  ሚዛኑ የኢትዮጵያ አመትበአላት ናቸው። “ባሻ አሸብር ባሜሪካ “መሆንናችን መስለኝ። ከካናዳ የደውለው የቁጫ ልጅ ነው። ቆጫ ጋሞ ውስጥ አንድ ወረዳ ነው። እኔ እስከማውቀው ዝነኛነቱ በቅቤ […]

በሰውነታችን የኮሌስትሮል መብዛት እንዴት እናውቃለን?

$
0
0
ኮሌስትሮል በሰውነታችን ውስጥ ስላለው ጥቅምና ጉዳት ከመነጋገራችን አስቀድሞ ስለምንነቱ የተወሰነ ነገር እናንሳ፡፡ ኮሌስትሮል ቅባታማ ተፈጥሮ ያለው፣ ከሰው ልጆች በተጨማሪ በሁሉም እንስሳት ሰውነት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ነው፡፡ ይህ ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ላሉት የተለያዩ ሴሎችና ሆርሞኖች የተፈጥሮ አካላቸው ነው፡፡ ኮሌስትሮል በተፈጥሮ ቅባታማ ስለሆነ ከደም ጋር በቀላሉ ተዋህዶ መዘዋወር አይችልም፡፡ ስለዚህ በደማችን ውስጥ ያሉትን የተለያዩ ኮሌስትሮል […]

ዛሬ ኢትዮጵያ የምትሄድበትን መንገድ እያየን የነገ መውጫውን ካሁኑ መተለም የግድ ይላል |ክፍል 2 እና የመጨረሻው

$
0
0
የአርባ ሶስት አመታቱ የፖለቲካ አለመረጋጋት ከእዚህ ፅሁፍ በፊት በተመሳሳይ ርእስ በክፍል አንድ ላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የኢትዮጵያ መጪ የፖለቲካ ሂደት ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ እና ለእዚህም ሃሳብ ማምጣት እንደሚገባ ለመግለፅ ተሞክሯል።እንደ ኢትዮጵያ ባለ ከአርባ አመታት በላይ ባልተረጋጋ፣በአምባገነን እና የጎጥ ፖለቲካ ሲታመስ ለኖረ ሀገር እና ሕዝብ መጪ ጉዳይ ላይ የመስራት አስፈላጊነት ላይ መነጋገር እና ኃላፊነቱ የማን እንደሆነ ማውሳት ከጊዜው የቸኮለ ሃሳብ […]

ህዝብ እንደ ህዝብ የመለኪያ ሚዛኑን መጠበቅ አለበት –    ነጋ አባተ (ከዋሽንግተን ዲሲ)

$
0
0
ክፍል አንድ ስመ ገናናው ናፖሊዎን አንድ ወቅት ወታደሮቹን መጎብኘት ፈለገና ዝግጅቱ እንዲከናወን ለበታች  ሹማምንቱ ትዕዛዝ ያስተላልፋል ። የሚጎበኝበት ስዓት ከመድረሱ በፊት ወታደሮቹ በታዘዙት መሰረት ሰልፋቸውን ይዘው ይጠባበቃሉ፤ ናፖሊዎን  በቦታው እንደደረሰ አንድ እንግዳ ነገር ትኩረቱን ይሰበዋል ያ ትኩረቱን የሳበው ጉዳይ ከሰልፈኛው መካከል አንዱ ወታደር ከመሰመር አፈንግጦ ወጥቶ መቆሙ ነው። ናፖሊዎን በቀጥታ ወደዚሁ ሰው ይሄድና  “ስምህ ማን […]

ሃይማኖታዊ መንግሥት ለማቋቋም ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 20 ተከሳሾች የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው

$
0
0
ከሁለት ዓመት በፊት ‹‹ሃይማኖታዊ መንግሥት ማቋቋም›› የሚል ፖለቲካዊ ግብ በማስቀመጥ ሲንቀሳቀሱ ተገኝተዋል ተብለው ክስ ተመሥርቶባቸው ሲከራከሩ የከረሙት የቢላል ሬዲዮ ዋና አዘጋጅን ጨምሮ 20 ተከሳሾች፣ ማክሰኞ ታኅሳስ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. የቅጣት ውሳኔ ተላለፈባቸው፡፡ በወቅቱ በሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የነበሩትን እነ አቡበከር አህመድንና እነ ኤልያስ ከድር የተባሉ ተከሳሾችን ከእስር ለማስፈታት […]

መሬት የማስተዳደር ኃላፊነቱን ያጣው ኤጀንሲ ትኩረቱን ባለሀብቶችን መደገፍ ላይ አደረገ

$
0
0
– ለባለሀብቶች የተላለፈ መሬት ሙሉ በሙሉ ባለመልማቱ 11.3 ቢሊዮን ብር ታጣ ከክልሎች በውክልና የወሰደውን የእርሻ ኢንቨስትመንት መሬት መልሶ ለክልሎች እንዲያስረክብ የታዘዘው የኢትዮጵያ የግብርና ኢንቨስትመንት መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ትኩረቱን ለባለሀብቶች ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት ላይ አድርጓል፡፡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 283/2005 የተቋቋመው የኢትዮጵያ የግብርና ኢንቨስትመንት መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ በውክልና የወሰደውን መሬት ለክልሎች እንዲመልስ ታዟል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር […]

የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት 40 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ድርድር መጀመሩ ተሰማ

$
0
0
– የመርከብ አገልግሎት ዋነኛውን ድርሻ ይይዛል ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውስጥ በግዙፍነታቸው ከሚጠቀሱ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ፣ 40 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ለመሸጥ ድርድር እየተካሄደ ነው፡፡ አራት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን በመዋሀድ እንደ አዲስ የተቋቋመውን ኢንተርፕራይዝ 40 በመቶ የሚሆነውን የባለቤትነት ድርሻ በመሸጥ ማኔጅመንቱን በጋራ ለማስተዳደር ከመንግሥት እየተደራደረ ያለው፣ አንድ የቻይና ኩባንያ መሆኑን […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live