Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በሰሜን ጎንደር ቋራ ወረዳ በታጣቂ የነፃነት ኃይሎች እና በወያኔ ወታደራዊ ኃይሎች የተደረገው ፍልሚያና ትንንቅ በነፃነት ኃይሎች የበላይነት ተጠናቀቀ

$
0
0
ብርሃኑ አየለ በሰሜን ጎንደር ቋራ ወረዳ የታጠቁ የነፃነት ኃይሎች ከወያኔ ጠመንጃ አንጋች ኃይላት ጋር ቅዳሜ ከፍተኛ ጦርነት ማካሄዳቸው ታውቋል። በዚህ የጦፈ ጦርነትም የነፃነት ኃይሎች ድል የተቀዳጁ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም ተደልለውና ተታለው ወደ ጦርነት የተሰለፉ ታጣቂዎች መሳሪያቸውንና ትጥቃቸውን እየፈቱ ከነፃነት ናፋቂ ኃይሎች ጋር መሰለፋቸው ታውቋል። በርካቶች ታጣቂ ኃይሎችን ይቀላቀሉ እንጂ በውጊያው ወቅት የነፃነት […]

የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት በኮማንድ ፖስቱ ከተያዙ እስረኞች መካከል 9,800 የሚሆኑትን የፊታችን ረቡዕ እፈታለሁ አለ

$
0
0
(ዘሐበሻ) የአሜሪካ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሀላፊ ቶም ማልናዋስኪና የህዝብ ዲፕሎማሲ ምክትል ሀላፊ ብሩስ ዋርተን የተካተቱበት የልዑካን ቡድን ከጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያምደሳለኝና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ከተወያዩ ከ አንድ ቀን በሁላ የትግራዩ ነጻ ኣውጪ መንግስት በኮማንድ ፖስቱ ከታሰሩት በ አስር ሺዎች ከሚቆጠሩ ዜጎች መካከል 9,800 ተጠርጣሪዎችን እፈታለሁ አለ። ይህ የውጭ መንግስታትን ለማታለል የተዘየደ ዘዴ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች […]

ረጅም እድሜና ጤና ለግፉዓኑ ፓትሪያርክ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ

$
0
0
ከአቻምየለህ ታምሩ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪወስ በነሐሴ ወር 1983 ዓ.ም በፋሽስት ወያኔ በተጻፈ ደብዳቤ መባረራቸው ያደባባይ ሚስጢር ሁኖ ሳለ ዛሬም ድረስ ግን ሽፍቶቹ ወያኔዎች በተለመደው ቅጥፈታቸው ተመክተው ፓትሪያርካችንን «በገንዛ ፈቃዳቸው ጥለው ሸሽተዋል»፤ «ስልጣኑን ለፈለጋችሁት ስጡት ብለዋል» ተብሎ የተጻፈን የወያኔ ትዕዛዝ የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ በማቅረብ በተጨማለቁበት አሳፋሪ ተግባር ህዝበ ክርስቲያኑን ሲያታልሉ ኖረዋል። «እውነትና ጭስ መውጫ አያጣም» […]

አውሮፕላኑ ፔንሰልቫንያ ኤርፖርት በሰላም አርፏል

$
0
0
የዛሬው አነጋጋሪ ዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን ከ አዲስ አበባ ተነስቶ ዋሽንግተን ዲሲ ማረፍ ሲገባው በሰዓቱ አለማረፉን ተከትሎ አውሮፕላኑ ጠፋ ተብሎ በተለያዩ ሶሻል ሚድያዎች መነገሩ ነው። አርብ ዲሰምበር 17 ምሽት ከአዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ወደ ዋሽንግተን ተሳፋሪዎችን ጭኖ የተነሳውና ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ዋሽንግተን ዳላስ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ማረፍ ነበረበት። ይሁንና አውሮፕላን ዋሽንግተን ዲሲ […]

ሊተኮርበት የሚገባው ቁም-ነገር –ኪዳኔ ዓለማየሁ

$
0
0
  መግቢያ፤ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ አጭር ነው። በማይረባ ጉዳይ ከመወዛገብ ቁም-ነገሩ ላይ በማተኮር ዘላቂና የሚበጅ መፍትሔ እንዲገኝ ለመጠቆም ነው። መሠረታዊ ጉዳዩም የሚያጠነጥነው በኢትዮጵያዊነት ላይ በመሆኑ፤ የኔን የዜግነት ማንነት፤ ከሁሉም በላይ የሚገልጸው፤ ኢትዮጵያዊነቴ መሆኑን በቅድሚያ ለማረጋገጥ እወዳለሁ። ቢሆንም፤ በራስ ቁዋንቁዋና ባሕል የተመሠረተ ማንነት በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ስር በሰላምና በዲሞክራሲ ሥርዓት እስከ ተገለጸ ድረስ አከብራለሁ። ነገር […]

“በውሃ ቀጠነ የምናደርገው ጭቅጭቅ አሁኑኑ ሊቆም ይገባል”–ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

$
0
0
የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ ሰጡ:: ፕሮፌሰሩ ወደ አስመራ ከመመለሳቸው ጥቂት ቀናት በፊት በስዊድን ሃገር ባደረጉት ንግ ግር በቅርቡ በተመረተው ትብብር ውስጥ የ አማራ ተወካይ የለም ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። ወያኔን አስቀምጦ እርስ በእርስ እየተደረገ ባለው ሽኩቻ ዙሪያም በውሃ ቀጠነ ጭቅጭቁ አሁኑኑ ሊቆም ይገባል ብለዋል። ቪድዮውን ይመልከቱት።

“የወልቃይትና ያለውደታቸው ወደ ትግራይ የተጠቃለሉ ወረዳዎች ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው ህወሃት ከሥልጣን ሲወገድ ብቻ ነው!”–አርበኞች ግንቦት 7

$
0
0
የወልቃይትና ያለውደታቸው ወደ ትግራይ የተጠቃለሉ ወረዳዎች ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው ህወሃት ከሥልጣን ሲወገድ ብቻ ነው!!! የአርበኞች ግንቦት 7 ሳምንታዊ ርእሰ አንቀፅ ================================= አርበኞች ግንቦት7 የህወሃት አገዛዝ ካልተወገደ በቀር ላለፉት 25 አመታት በአገራችን የሰፈነው ዘረፈ ብዙ ችግሮች አይወገድም ብሎ ከሚያምንባቸው ምክንያቶች አንዱ ቋንቋንና ባህልን መስፈርት ባደረገ አከላለል ተፋቅሮና ተከባብሮ ይኖር የነበረ ህዝብ መካከል የተዘራው የመከፋፈልና የጠላትነት ስሜት […]

በኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የታመሙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል |የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ የዛሬ ዜናዎች

$
0
0
#በኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የታመሙ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል ተባለ #የታቀደውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ አስመልክቶ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሰረት የተፈጠረው የጸጥታ ሁኔታ ያሳሰባቸው መሆኑን የድርጅቱ ሊቀ መንበር ገለጹ #በአንድ ዓመት ውስጥ ከመቶ በላይ የሆኑ ኢትዮጵያን ስደተኞች በማላዊ መንግስት ተይዘው ለወያኔ ተሰጡ ###ዝርዝር ዜናዎች### #በዝዋይ እስር ቤት ታስሮ የነበረውና ላለፉት 10 ቀናት መዳረሻው ጠፍቶ የነበረው ተመስገን […]

እንዲያው ዝም እንበል? –ግጥም

$
0
0
ምርቃት እርግማን፤ ደግ ክፉ ከሆነ፤ እንዲያው ዝም እንበል፤ የሞተ ካልዳነ። እሬሳችን ቀብረን፤ ሃዘን እንቀመጥ፤ ዘመድም ተረድቶ፤ እንባውን ያሟጥጥ። ብረቱን እንጨት ነው፤ እንጨቱን ብረት፤ ብለን ላንግባባ…አጉል መሟገት። እያየ የማያይ፤ ሰምቶም የማይሰማ፤ አይን፤ ጆሮ፤ ከጠፋ በምን እንስማማ። ስራውን ለሰሪው…ላድራጊው ብንተው፤ ብድር ከነወለድ…ከፋዩ እርሱ ነው። ኢትዮጵያ ተወልደን ኢትዮጵያ ካደግን፤ የአንድ ሀገር ሕዝቦች፤ ኢትዮጵያውያን ነን። በዓለም ዙሪያ ብትሄድ፤የምትታወቀው፤ በትውልድ […]

የሞጋቾች ድራማዋ ዋና ተዋናይት መቅደስ ጸጋዬ ልትሞሸር ነው

$
0
0
የሞጋቾች ድራማዋ ዋና ተዋናይት መቅደስ ጸጋዬ ልትሞሸር ነው

መለከት ድራማ በመሪ ተዋናይዋ የተነሳ ችግር ውስጥ ሊወድቅ ነው

$
0
0
ምእራፍ ሁለት የድራማውን ክፍል ማስተላለፍ የጀመረው መለከት ድራማ በመሪ ተዋናይዋ የተነሳ ችግር ውስጥ ሊወድቅ ነው። ዝርዝሩን ያድምጡ።

“ዛሬ በ እስር ቤት ተመስገን ደሳለኝን መጠየቅ አይቻልም ተብለን ተመልሰናል”–ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ

$
0
0
የተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ በፌስቡክ ገጹ ያሰፈረውን እነሆ። ተመስገን በየቀኑ እየተፈተነ ነው። ዛሬ ታህሳስ 9/09 ዓ.ም ዝዋይ እስር ቤት ተመስገንን ለመጠየቅ ብንሄድም የእስር ቤቱ የበር ሹሞች ተመስገንን መጠየቅ አይቻልም ብለዋል። ለምንድነው የማይቻለው? ማንው የከለከለው? አለቆቻችሁን እናጋግር ብንልም አያገባቹህም አሁን ግቢውን ለቃችሁ ውጡ ተብለናል። ለ10 ቀናት ያክል ተመስገን የት እንዳለ አናውቀም በለውን በ10ኛው ቀን ለ3 ደቂቃ […]

በአትላንታ ኢትዮጵያዊቷ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው አለፈ

$
0
0
(አድማስ ራድዮ) ሰሜን አሜሪካ  በአትላንታ ከተማ ላለፉት 21 ዓመታት ነዋሪ የነበሩት ወይዘሮ ብርሃን ሃግዶ በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ። ወይዘሮ ብርሃን ህይወታቸው ያለፈው ባለፈው እሁድ ዲሴምበር 11 ቀን፣ በ እግራቸው ሲጓዙ መኪና ገጭቷቸው ነው። ወይዘሮ ብርሃን የ 48 ዓመት ሴት ሲሆኑ አንዲት የ13 ዓመት ታዳጊ ወጣት እናትም ናቸው። ታሪካቸውን የበለጠ አሳዛኝ የሚያደርገው፣ ባለቤታቸው አቶ […]

ከጎንደር በውስጥ መስመር የተላከ እጅግ አስቸኳይ መልዕክት

$
0
0
«ፋሽስት ወያኔ በአሁኑ ስዓት [እሁድ ታህሳስ 9 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከቀኑ 12፡00] ኮ/ል ደመቀ ዘዉዱን ከጎንደር አንገረብ ማረሚያ ቤት በአጋዚ ልዩ ኮማንዶ አስገድዶ በጨለማ ለመዉሰድ ግብግብ ላይ ነው። ታራሚዉ «ኡኡ!» በማለት አንደኛዉን በር ሰብሮ ወጥቷል፤ ኮሎኔሉንም ከበዉ ይዘዋል። ይህን ስራ ለመስራት ከቀናት በፊት ኮ/ሉን ከዋናዉ ታራሚ ለይተዉ ለብቻዉ አንድ ክፍል እንዲቀመጥ ትዕዛዝ ሰጥተዉ ነበር፤ ሆኖም እሱም […]

ከአማራ ሃኪሞች የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ –“ከሞትና ሥቃይ ያልታደጋት እርግዝናን አጥብቃ የገታች የአማራው እናት..”|ጥብቅ መረጃ

$
0
0
ከሞትና ሥቃይ ያልታደጋት እርግዝናን አጥብቃ የገታች የአማራው እናት፣ የኢትዮጵያ ማእከላዊ ስታትስቲካል ኤጀንሲ የ2016 DHS ቁልፍ አመልካቾች በአማራ ሐኪሞች ዕይታ፤ እድሜአቸው ከ 15- 49 ዓመት የሆኑ የአማራ ሴቶች 47 በመቶ የሚሆኑት የእርግዝና መከላከያን በመጠቀም ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በኢትዮጵያ ከፍተኛው ነው። ይህም ካጠቃላይ ካገሪቱ መጠን 9 በመቶ ከፍ ያለ ነው። የመጀመሪያ ልጇቸውን ከወለዱ የአማራ እናቶች ዉሥጥ 45 […]

ይሁኔ በላይ –“የጎጃም ኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ አምባሳደር”

$
0
0
ይሁኔ በላይ ለፈረንጆች ገና ዋዜማ የፊታችን ቅዳሜ ዲሴምበር 24 የሚያዘጋጀውን ኮንሰርት በማስመልከት ከጥቂት ዓመታት በፊት ጽፌ በዋርካ ላይ አስቀምጫት የነበረችውንና በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይም ታትማልኝ የነበረችውን ጽሁፍ እንካችሁ አልኩ:: በመጠኑም ቢሆን የአርቲስቱን ሕይወት ታስቃኛችኋለች:: ከሊሊ ሞገስ ያንን ዋሽንት አምጡት ዋ ባይ ትካዜው ቢለቀኝ መቼም ያለ ሀሳብ ዋ ባይ ምንም ዘመድ የለኝ ዋ ስንቱ ዋ ስንቱ ዋ […]

የመሳይ ከበደና የሬኔ ለፎርት ወግ

$
0
0
ታሪኩ ዉብነህ ጌታነህ ክፍል ሁለት [ ማሳሰቢያ፡ በሁለተኛው ክፍል የሚቀርበው አውሮፓዉያን እንዲት አድርገው አፍሪቃን እንደ ቅርጫ እንደተከፋፈሏት ነው፤ ይህም ያስፈለገበት ምክንያት እነዚህ ሁለት አንጋፋ ልሂቃን ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ግንዛቢ አሁን ከሚሉት ጋር ምን ያህል ግንኙነት እንዳለው ለማሳወቅ ነው፤ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ በዘውግ ፍልስፍና ላይ የተመሰረተ በርካታ ጽሑፎቹን አቅርበዋል፤ ሬኔ ለፎርት በታሪክ በፖለቲካና በአስተዳደር ላይ ያለዉን […]

“ወይ እንዳጋጣሚ!” –የጎንቻው

$
0
0
የፈሩት ይወርሳል የጠሉት ይነግሳል፤ ይኽ ንግር በኛ  አገር እየሆነ ኑሯል፤ ዘመነ ግልንቢጥ ክፍ  አዞ  ያረባል፤ ባህር  እየኖረ   ከጤዛ   ይጠጣል፤  ዙፋን ተቀራምቶ በጉልት ይቀናል፤ መቸስ ቅና ያለው ቅንቀን ይበላዋል፤ ወይ እንዳጋጣሚ! ‘ላንዱ’ ያልፍልታል፤‘ባንዱ’ ያልፍበታል። በቀል ተጸንሶ መች ቂሙ ይረክሳል፤ ያሳደጉት   ውሻ   ዙሮ   ይናከሳል፤ የዘመኑ   እረኛም  ቀበሮ   ይሆናል፤ የሰው ቆዳ ለብሶ በአገር በግ ይፈጃል፤ የመንደር ተኩላው ጋጥ […]

Hiber Radio: ሕወሃት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን አፍኖ ለመውሰድ ተደጋጋሚ የሽብር ሙከራውን ቀጥሏል –ቻይና የሕወሃት/ኢህአዲግ አገዛዝን እና የኤርትራው አቻውን ለማግባባት ፍላጎት አላት ተባለ

$
0
0
የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 9 ቀን 2009 ፕሮግራም <…ኢትዮጵያውያን ተነጣጥለን የምናደርገው ትግል ያስከተለው ተነጣጥሎ መመታት ነው።በዘርም እንደራጅ፣በሀይማኖትም ይሁን በዚያ አገር ላይ ነጻነት ለማምታት ትግሉን ብሄራዊ መልክ ካላሲያዝነው፣ትግላችን የጋራ ካልሆነ የእኛ አለመስማማት በተዘዋዋሪ የምንጠላውን ስርዓት እድሜ ማርዘም ብቻ ሳይሆን ..> ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሳዲቅ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ካደረግንለት ውይይት የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት) የዳንኤል ሺበሺ ትዝብት ከእስር ቤት ሶሪያ […]

መሬት ሳትበይኝ ልብላሽ (ከይገርማል)

$
0
0
ወያኔወች ከትግራይ ጋር የሚካለሉትን የአፋርና የአማራ ለም አካባቢወችን መቆጣጠራቸው ሳያንስ ረጅም ርቀት ተጉዘው የጋምቤላንና የቤንሻንጉልን ለም መሬት በኢንቨስትመንት ስም ሕዝቡን ሳይቀር እያፈናቀሉ እየሸጡ እንደሆነ ስሰማ በታሪክ የማውቃቸው አንድ አባት ትዝ ይሉኛል:: በርግጥ እኒህ አባት የማንንም ሳይሆን የራሳቸው የነበረውን ሰፊ መሬት ነው እየሸነሸኑ የሸጡት:: ቀኛዝማች ሰውነቴ እልምነህ ይባላሉ፥ አጭር ቀጭን ወደጥቁር ያደላ መልክ ያላቸው። ተወልደው ያደጉት […]
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live