Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

«ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» ምንድን ነው?

0
0

ከመ/ጥ መንገሻ መልኬ
«በሰላም ተሳስራችሁ ከመንፈስ ቅዱስ የሚገኘውን ለመጠበቅ ትጉ። በተጠራችሁ ጊዜ ለአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ። እንዲሁም አንድ ጌታ አንድ እምነት እና አንድ ጥምቀት አለ። ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ በሁሉም የሚሠራ፤ በሁሉም የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።» ኤፌ4፤3-7

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በዘመናችን የደረሰባት የመለያየት እና የመከፋፈል ዘመን፤ አንዱ ሌላውን ለማጥቃት ቀን ቆርጦ፣ቦታ መርጦ፣ ዘገር ነቅንቆ፣ ጦር ሰብቆ፣ ዝናር ታጥቆ፤ነፍጥ ቀስሮ ወረድ እንውረድ ተባብሎ በጦር መሳሪያ መዋጋት እና በሀገር፣ በሰው ኃይል፣ በማህበራዊ ግኑኝነትና ማህበራዊ ኑሮ፣በኢኮኖሚ ጥፋት ሀገሪቱን ከአንድነት ወደ መበታተን፣ ከማዕከላዊ የንጉሳዊ አስተዳደር የክፍፍሎሽ ሰለባ በማደረግ እድገትዋን እና ሥልጣኔዋን አንቆ ይዞ ለሰባ ስምንት ዓመታት ሲያንገላታት የቆየውን የዘመነ መሳፍንት ታሪካዊ የጥፋት ክስተት ወይም አገዛዝ ጋር የሚዛመድ ነው።
ቤተ ክርስቲያን የሀገራችን ኢትዩጵያን አብላጫ ቁጥር ያለውን ሕዝብ በሃይማኖት የምትመራ በመሆንዋ ሕዝቡን በቀላሉ ለመቆጣጠር ወይም ከአንድነት አስወጥቶ ከፋፍሎ ለማስተዳደር ያመች ዘንድ በተለይም ከዘውዳዊ ሥርዎ በመንግሥት ለውጥ በኃላ እራሳቸውን መንግሥት ያደረጉት ያለፉት አርባ ዓመታት የኢትዮጵያ መንግስታት፤ መንግሥት ሆነው ከዙፋናቸው በወጡ ማግስት ሕገወጥ ጥቃታቸውን እና ጣልቃ ገብነታቸውን የሚፈጽሙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ነው።
abune-merekoriwos-150x150
ቀደም ብሎም ቢሆን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሰ ነገሥት መፈንቅለ ዘውዳዊ መንግስት አደርጎ እራሱን ጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር መንግስት ብሎ የጠራው ደርግ፤ ንጉሰ ነገሥቱን በግፍ ከገደለ በኃላ ፊቱን ወደ ቤተ ክርስቲያኗ በማዞር ውስጥ ውስጡን እጅግ ተናጋሪ ደፋር የሆኑትን እነ ባህታዊ ቀለመወርቅ ካሣሁን እና ሌሎችንም ካህናት መልምሎ በለውጡ ማዕበል በማጥመቅ በቤተ ክርስቲያን ጉልላትን ዘመቻ ጀመረ፤ አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳትም የፓትርያርክነት ስልጣን ፈላጊ በመሆን በደፈጣ የለውጥ አራማጆችን ደጋፊ በመሆን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደርግ በግፍ ነዲገደሉ አስተዋጽዖ አድርገዋል።
በድጋሜ ከደርግ መንግሥት ላይ ከኤርትራው የገንጣይ ፓርቲ ጋር በመተጋገዘና በመረዳዳት ለአስራ ሰባት ዓመታት የትጥቅ ትግል ያደርገው የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር (ሕወሀት) በግንቦታ 20 ቀ 1983ዓ.ም ደርግን ተክቶ አዲስ መንግሥት ሆኖ ሥልጣኑን በተቆጣጠረበት ማግስት በኢትዮጵያ አርቶኦክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያደረገው ጣልቃገብነት በዋናነት የሚጠቀስ ቢሆንም፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት፣ በአራት ኪሎ እና በአካባቢው የሚገኙ መሀል ሰፋሪዎች ጥቂት አደባርት ካህናት ጣልቃ ገብነቱን በማጠናክር ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ችግሩን ማባባሳቸው የሚዘነጋ አይደለም።ከዚያም በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በልዩ ልዩ ምክንያት ግራ በማጋባታ እና በማዋከብ ከመንበራቸው ወርደው በግዞት እንዲቀመጡ አስገዳጂ ትዕዛዝ ደረሰባቸው፤ ከዚያም ቀጥሎ የሚጠብቃቸው የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ቴዎፍሎስ እጣ ፋንታ መሆኑን ተረድተው የሚወዷትን ሀገራቸውን ጥለው ለስደት ሕይወት ተዳረጉ።
ታሪኩን ለማሳጠር መንግሥት በተለወጠ ቁጥር በቤተ ክርስትያኗ ላይ የሚታየው ጣልቃ ገብነት ተደጋግሞ የታየ ሲሆን በዚህ ሃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት ምክንያት በቤተ ክርስቲአቲያን የአንደነት አስተዳደር ያስከተለው ችግር እጂግ በጣም መጠነ ሰፊ ነው።ከዚህም አንጻር «ፓትርያርክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይመረጥም» ከሚለው ሃይማኖታዊ ሕግጋት እና ትችት አልፎም ቤተ መግሥቱና ቤተ ክህነቱ በአንድ ክፍለ ሀገር በተለይም በአንድ የአድዋ ተወላጆች ቁጥጥር ሥር በመዋሉ መንግሥትን ይበልጥ በጠባብ ጎሰኝነት ላይ የተመሠረተ አስተዳደር እጂግ በጣም ክፍተኛ በሆነ ደረጃ እያስተቸው መጣ። የቤተ ክርስቲያኗም አስተዳደር ከመንፈሳዊነት ይልቅ ሥጋዊነትና የጎሳ ልዩነት ጎልቶ የሚታይበት ነው! የሚለው ሐሜታና ትችት የአደባባይ ምስጢር ሆነ። ይህ በዚህ ላይ እንዳለ አሁን በዋናነት የሚታየው የቤተ ክርስትያን መከፋፈል ጎልቶ ወጣ፤ ይኸውም፦

አቡነ ማቲያስ

አቡነ ማቲያስ

1ኛ. በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳሎስ/አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ፤ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ፤
2ኛ. በብጽዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ፤ ኒውዬርክ፤ አሜሪካ
3ኛ. «ገለልተኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን» በማለት እራሳቸውን የሰየሙ አዲስ ባለታሪኮች በአሜሪካ ና በአውሮፓ የሚገኙ ናቸው።
በዚህ የመከፋፈል ዘመን ከሰባት ሚሊዮን በላይ የቤተ ክርስትያኗ ተክታዮች የጠፉ ስለመሆናቸው አንዳንድ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጥናት ያደረጉ አባቶች ምስክርነታቸውን እየሰጡ ነው። ይህን ያክል ቁጥር ያለው የቤተ ክርስቲኒቱ አንጡራ ሀብቶች ሲጠፉ ተጠያቂው ማን ነው? የሚለውን ምላሽ በኃላፊነት መልስ የሰጠ የቤተ ክርስትያኗ አካል ባይኖርም፤ በዚህ ጽሑፍ አቅራቢ እምነት ለአንድ መንጋ አንድ እረኛ አለመኖሩ፤ ለአንዲት አማናዊት ቤተ ክርስቲያን አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ አለምኖሩ፣የሃይማኖቱ ባለአደራዎች ሊቃነ ጳጳሳት አባቶች የተፈጠረውን መክፋፈል ለመመለስ በቂ ጥረት አለማድረጋቸውና ከዚያም አልፎ አዲሱ የመለያየት አርበኛ «የገለልተኛው»ክፍል የውጭውን የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ደጀን አድርጎ በግለሰባዊ የጥቅም ተገዥነት የቤተ ክርስትያኗን የመከራ ዘመን እንዲራዘም አቀንቃኝ እና አራጋቢ ሆኖ በመገኘቱ ጭምር ነው።
በተለይ አሜሪካን ሀገር በኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ስም ለገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን መፈልፈል የተመቻቸች ሰገነት ሁናለች። ዛሬ በአሜሪካን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚለው ስያሜ እየተዘነጋ፤ ከሀገር ውስጥ ነው ወይስ ከወጭው ሲኖዶስ፤ ከገለልተኛ የሸዋ ፤ የጎንደር፤ የጎጃ፤ የወሎ፤ የጉራጌ፣ የኦሮሞ… ቤተ ክርስቲያን በሚል ቤተ ክርስቲያንን የመከፋፈል የዘመነ መሳፍንት አስተዳደር በቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ያነጣጠረ የጥፋት «ገለልተኛ» ዘመን እያንሰራራ መጥቷል።
ይህ አስከፊ ተግባር እና መድኅኒት የጠፋለት የጥፋት በሽታ ከአሜሪካም አልፎ ወደ አውርፓ ዘለቆ በመግባት በርዕሰ አድባራት ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን «ሲኖዶስን እንቀብላለን ፓትርያርኩን አንቀበልም» በሚለው ሰንካላ ምክንያት በር ከፋችነት የንብረት አስተዳደር በምዕምናን ብቻ በሌላ መልኩ የመንፈሳዊ አገልግሎት አስተዳደር በካህናት ብቻ ፤ የሰብካ ጉባዔ አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ እና ሥራ አስፈጻሚ ያለሆነ ተብሎ በአንዲት አጥቢያ ቤተ ክርስትያን የመክፋፈል ጥያቄ አስነስቶ ቤተ ክርስቲያንን ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ኩባንያ በማስመዝገብ፣ በመጭረሻም ሕንጻውን በግል ባለቤትነት ይገባኛል ጥያቄ የተነሳ የተፈጠረው አስቀያሚ ውዝግብ ቤተ ክርስቲያንን አስገደዶ እስከማዘጋት እና ምዕመናኑን በመከፋፈል ያደረሰው አደጋ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም።
«ነገር ግን ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልቦና በአንድ ሐሳብ የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኃለሁ።» 1ኛ ቆሮንቶስ 1፤10
ከላይ በተራ ቁጥር 1ኛ እና 2ኛ የተጠቀሱት ቤተ ክርስቲያን እና በተክታዩ ምዕመናን የተፈጠረው መከፋፈል እጅግ የሚያሳዘን ሲሆን፤ ቅዱስ ሲኖዶሳቱ በአጠራሩ ሕጋዊ ቢሆንም ባይሆንም እራሱን የቻለ ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የየራሳቸው ምክንያት ያላቸው እንደመሆኑ መጠን፤ ግራቀኙ ችግራቸውን በማወቅ በመረዳት ለእርቅ የመደራደርና የመቀራረብ ሙከራ በማድረግ ላይ ቆይተዋል። የዚህን ዝርዝር ሐተታ በሌላ ጊዜ የምንመለስበት ሲሆን ለዛሬው በተነሳሁበት «ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» ምንድን ነው? በሚለው ብቻ በማተኮሩ መልካም ነው ።
«ገለልተኛ» የሚለው የአማርኛ ቃል በእንግዚዘኛው «Independent» የሚለውን ተመጣጣኝ (አቻ) ቃል ያገኛል። ትርጉሙም ከሌላ ውጫዊ ኃይል ተጽኖ ነጻ መሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሙሉ ለሞሉም በማንም በምንም አለመታዘዝ እና አለመመራት፤ በሌሎች ላይ ጥገኛ እና ግኑኝነት ወይም ውህደት እና አንድነት አለመፍጠር፤ እራስን ችሎ በነጻነት መንቀሳቀስ የሚሉትን ትርጉሞች ይይዛል።
abunapauolos(1)ከዚህም አንጻር ኢትዮጵያ በአፍሪካ ገኖ ከነበረ የምራብ ሀግሮች (የኮሎኒአይዜሽን) የእጂ አዙር ቅኝ አገዛዝ «ገለልተኛ» «Independent» ነጻ የሆነች አንድ ሀገር ናት ሲባል፤ የተለያዩ ብሔሮች ቋንቋወች ባህሎች ሳይነጣጠሉ ሳይለያዩ በአንድነት ተቻችለው እና ግንባር ፈጥረው በወቅቱ የነብረውን የምራብ ሀገሮች የኢኮኖሚ፣ የቋንቋ፣ የአስተዳደር፣ የባህል፣የፓለቲካ እና የተገዥነት(ባርነትን)፣ማንነትን አሳልፎ መስጠት .. ከመሳሰሉት ተጽኖዎች ገለልተኛ (ነጻ) መሆንኗን በራስ መመራትን ብቃትን እና ተከላካይነትን ያመለክታል። ይህም ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ለዘመናት እንደምናውቀውና እንደተማርነው Indepandant Nation ክቀኝተገዥነት ገለልተኛ ወይም ነጻ መሆን የሚለውን የእንግሊዘኛ አቻ ቃል የሚይዝ መሆኑን ያስረዳናል ማለት ነው።
በመሆኑም «ገለልተኛ» የሚለውን ቃል ለመጠቀም ፓለቲካዊ ይዘት እና ሌሎችም በገሀዱ ዓለም በሥጋዊ ፍላጎት እና ተምኔት ዕራይና ተልዕኮ ለሚከናወኑ አንድነት እና ውህደት የሌላቸው ግለሰባዊ እና ቡደናዊ ድርጂቶች መሥሪያቤቶች
እንዲሁም የሳይንሳዊ ጠባይ ያላቸው ነገሮች እና የመሳሰሉት ሰዋዊ የምርምር ግኝቶች መገለጫ መሆኑን ይበልጥ ያስተምረናል እንጅ በክርስቲያናዊ ሕይወት እና በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ገብቶ የሚሰራ ቃል አይሆንም።
ይሁን እንጂ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት በክርስቲናዊ ሃይማኖታዊ ትውፊት እና ቤተ ክርስቲያናዊ አወቃቀር ቀኖና እና ስያሜ አንጻር «ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» የሚለው መጠሪያነት ግለሰባዊ ጠቀሜታ እና ፍላጎትን የማስከበር ዓላማ ያለው በሌላ በኩል ደግሞ ተዋህዶና እንድነት ፈጥሮ ከመኖር ይልቅ የመለያየት፣ የመበታተን የመከፋፈልና ብሎም የነበረን ማንነትን (መጠሪያን) የማጣት እና ከአንድነት ጉባኤ የመለየት የመጥፋት አመሠራረት ነው። «ሐዋርያት በሰሯት በአንዲት ቅደስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን» ከሚለው ሁሉም ካናትና እና ምዕመና በሁሉም አብያተ ከርስቲያናት በየቀኑ ከሚጸለየው የአንደነት የሃይማኖት ጽሎት እና የሊቃውንት ሃይማኖታዊ ድንጋጌ የመወጣት ነው።
ለቤተ ክርስትያናችን አንድነት የእምነታችን ሥራዓት፣ቀኖና እና ሕግጋት፣ ትውፊትና አፈጻጸም፣ አስተዳደርና የስተዳደር መዋቅር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው ነው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግኑኝነት ጥገኝነት፣ መሠረትነት፣ ተጠቃሽነት አስረጂነት የሌለው ሃይማኖታዊ ክዋኔ ሁሉ ተቀባይነት የለውም። በቤተ ክርስትያን ውስጥ የሚገኙት አገልጋዮች እና ተገልጋዮች በአንድነት ክርስቲያኖች፣ የሚደርጉት አገልግሎቶች መንፈሳዊ እና መገልገያዎች ሁሉ ንዋየ ቅሳት ተብለው የሚጠሩት በዚሁ ምክንያት ነው። ስለሆነም እነዚህ ቃላት ተደጋጋፊ ወይም ጥርስና ከንፈር ሆነው አንድ ሆነው የሚኖሩ እንጂ ምክንያት እየፈጠሩ አንዱ ከአንዱ የማይነካካ «ገለልተኛ» ተብሎ የሚጠራ አይደለም ።
መጽሐፍ ቅዱስ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ያሉት ሲሆን እነሱም የብሉ ኪዳን መጽሐፍ ነቢያት በዘመን፣ በጊዜ፣ በቦታ፣ በቀን በሳዓታት፣ አመላክተው ወደፊት የሚፈጸመውን የተናገሩትን የትንቢትና የሕግ መጻሕፍትን የሚያጠቃልል ሲሆን ሁልተኛው የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ክፍል ፈጣሪ በተነገረለት ትንቢት፣ በተቆጠረለት ዘመን፣ በታወጀለት ቦታ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ከተወለደበት ከቤተልሔም፣ በተሰደደበት ግብጽ፣ ተዘዋውሮ ባስተማረባት በከንአን/ኢስራኤል፣ በጸለየበት ገዳመ ቆረንቶስ፣ ከተሰቀለበት ቀራንዮ፣ ከተቀበረበት ጎልጎታ በአምላክነቱ ሞትን ድል አድርጎ እስከተናሳበት ድረስ ያሰተማረውን፣ ያደረገውን ገቢረ ታምራት፣የሙታን ማስነሳት እና ለእኛ የሰጠውን ተስፋ መንግስተ ሰማያት የሚያስተምረውን ነው። የሁለቱ ክፍል ጥምረት፣ አስረጂነት፣ ገላጭነትና ተወራራሽነት፣ ተግባቢነትና ተደጋጋፊነት በአንድነት መጽሐፍ ቅዱስ ተብሎ ይጠራል።በመሆኑም በውስጡ ባሉት የመጽሐፍት አንድነት መካከል «ገለልተኛ» የሚለው ስያሜ፤ አወቃቀርና አመሠራረት ቦታ የለውም።
በመጽሐፍ ቅዱስ የአንድነት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት መጽሐፍት ነጻ፣ ግኑኝነት የሌለው፣ እራሱን የቻለ፣ ለየብቻው የሆነ፣ የተከፋፈለ፣ የተለየ ግንዛቤ የሚሰጥ «ገለልተኛ» መጽሐፍ የለም፤ ይልቁንም አንዱ በአንዱ ላይ ጥገኝነት አንድነት፣ ተግባቢነትና አንድ አይነት መልዕክት የሚያስተላልፍ አንድ ቅዱስ መጽሐፍ ተብሎ የሚጠራ ዘመን የማይሽረው፣ ጥቅም የማይለያየው፣ ተነጣጥሎና ተለያይቶ የማይታይ ሁሉም በአንድነት ሕያው የአንድ የአምላክ ቃል ብለን የምንቀበለው እና የምናምነው ነው። ስለሆነም «ገለልተኛ» ብለን የምንሰይመው አንድም ነገር የለም ሊኖርም አይችልም።
«ይህንንም ያደረገው የክርስቶስ አካል የሆነችው ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ ምእመናን ለክርስቲያናዊ አገለግሎት ለማዘጋጀት ነው። እንዲሁም በእምነት የእግዚአብሔርን ልጅ በማወቅ ወድሚገኘው አንድነት ደርሰን ክርስቶስ ፍጹምና ሙሉ እንደሆነው እኛም ሙሉ ሰው እንድንሆን ነው።» ኤፌ 4፤12-13 እንግዲህ ከላይ በዝርዘር እንደተመለከትናው ከወንጌልና ከሀገራችን ታሪክ ጋር እንዳገንዘብነው በማስረጃ ይዘን እንደተከታተልነው «ገለልተኛ ቤተ ክርስትያን» የሚለው አስተሳሰብ ግለሰባዊ ጥቅም፣ ፍላጎትና እና ግብዝነት የተፈጠረ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን እንረዳለን።
«ገለልተኛ ቤተ ክርስትያን» የሚለው ከኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ አንዲት ቤተ ክርስቲያን የወጣ፣ የብልጣብልጦች የንግድ መርከብ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ የአኩራፊዎች ወይም እንቢተኞች በራሳቸው ፈቃድ የመሠረቱት መደበቂያ ዋሻ መሆኑ በሁሉም ዘንድ ይታወቃል። ይሁን እንጂ «ወልድ ሲነካ አብ ይነካል» በማለት ወንጌል የጠገቡ ምስጢር የመረምሩ አባቶቻችን እንደሚተርቱት ሁሉ ቤተ ክርስቲያኗን በሚበታትን ደካማ «የገለልተኝነት» ግለሰባዊ የመክፋፈል አስተሳሰብ ብዙዎቹ ታታላቅ የሚባሉ ዛሬ ለቤተ ክርስቲያንዋ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አባቶች ጭምር የዚህ አሳፋሪ እና የአንድነት አደራ ጠባቂነት ጉድለት ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተባባሪ እና ተሳታፊ ሆነው ቆይተዋል ፤ ለሃይማኖቱ
holyተቆርቋሪ ነን የሚሉ አንዳንድ ማህበራትም እንደዚህ ያለውን ሕገወጥ «የገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» የሚለውን የአንድነት አፍራሽ ተውሳክ ለማጋለጥ አልደፈሩም።
ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚታየው «የገለልተኝነት» ጥቃት አዲስ የሚመሠረቱትን አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ሳይሆን ከላይ እንደተ ገለጸው ወደ አውሮፓም ዘለቆ በመግባት በተለይም የዛሬ አርባ ዓመት በቅድስ ሲኖዶስ ውሳኔ እና በብጹ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ የተመሠረተችውን መንፈሳዊ መዋቅሩን ጠብቃ ስትመራና ስትገለግል የቆየችውን የርዕሰ አደባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድሥት ማርያም ነባር ቤተ ክርስቲያንን የተደራጁ ግለሰቦች የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የግል ባለቤት ለመሆን በገለልተኝነት ለማደራጀት ባስነሱት ከፍተኛ አመጽ ምክንያት መንፈሳዊ አገለግሎቱ በኃይል ተቋርጦ ምዕመናን ተከፋፍለው ከአንድ ዓመት በላይ የቆየ ውዘግብ ፈጥሮ በመጨረሻ በዚሁ ምክንያት እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በግፍ ተቋርጦ ቤተ ክርስትያኑ ከተዘጋ ስምንት ወራት ተቆጠሩ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሲመሠረተው ቢያንስ ክአራት መቶ ያላነሱ ምዕመናን የሚገለገሉበት ቤተ ክርስቲያን የሚያገለግላቸው ካህን እንደሚያስፈልጋቸው እና ለመንፈሳዊ አገልግሎቱ የሚሆነውን መባውን፣ ማስቀደሻውን እና ማወደሻውን ሁሉ እንደሚችሉ ተፈራርመው ሲያቀርቡና አስፈላጊነቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ሲታመንበት ይመሠረታል። ነገር ግን «ገለልተኛ ቤተክርስትያን» የሚለው ይህን መመዘኛ ሳያሟላ በአስተዳደር በደል ደረሰብኝ ብለው ያኮረፉ ሊቃነ ጳጳሳት፣ በግል ጥቅመኝነት ግለስባዊ ፍላጎት ያላቸው ካህናትና መነኮሳት ወዳጂነት ካላቸው ጳጳሳት በግል ጽላት እያስባረኩ እንደ ሱቅ በደረቴ በተመቻቸው አጋጣሚ «ገለልተኛ» አድርገው ይሰይሙታል። መነገጃ ታርጋው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሚል ነው። እውነታው ግን የወቅቱን ግርግር ተጠግቶ በግለሰቦች ፈቃድ ብቻ የተመሠረተ ከአንድነት ጉባዔ የተለየ አስመሳይ «ገለልተኝነት» ነው። ምክንያቱም ግለሶቹ ያለፈቀዱለት ሊቀ ጳጳስ ገብቶ ያማይባርክበት፣ ግለሰቦቹ ያልፈቀዱለት ካህን የማያገለግልበት፣ ምዕመናን ቢሆን እንደ መጻተኛ ለጎሪጥ የሚታዩበት የሚገላመጡበት እና «መጤዎች» ተብለው የሚሰደቡበት የተበሻቀጠ ግንዛቤ የጎደለው ስሪት ነው። በመሆኑም አሁን በሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው ችግር የዚህ በሽታ አዛማቾች ወይም ተላላኪወች «ገለልተኛ» እና የቤተ ክርስቲያንን ሕንጻ በግለሰብ ለመያዝ የሚደረግ እጅግ በሚቀፍ ሁኔታ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተዳደር መዋቅር ላይ የተደረገ በመለያየት የተሞላው የጥቅም ያደነዘዘው አሳዛኝ ዘመቻ ነው።
Holy Sinod Ethiopia
«ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን» ማለት በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠውን የአባቶች መለያየት ክፍተት እንዲቀጥል የተሳሳተ መገድ የሚጠርግ ነው። ቤተ ክርስቲያን ሁሉም የክርስትያኖች ማምለኪያ፣ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት መሆንዋ ቀርቶ ጊዜ የፈቀደላቸው፣ኃይለ የተሰማቸው፣ በጉልበታቸውና በገንዘባቸው የተመኩ ግለሰቦች በቡድን ተደራጅተው በቤተ ክርስትያኗ ውስጥ ግንዛቤ የጎደላቸው ግብረ በላተኞችን እና ገንዘብ አምላኪ መሰል ካህናትን በማስተባበር፤ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የወጣ፣በጠባብ ጎሰኝነትን መሠረት ያደረገ፣ በግለሰቦች የግል ባለቤትነት የተያዘ፣ አስታራቂም ታራቂም ያልሆነ፣ የቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ መንፈሳዊ መዋቅር የተለየው፣ ተቆጣጣሪና የበላይ ጠባቂ የማይታወቅበት፣ መለያየትና መበታተን የሚጠናከርበት ከሀገራችን ኢትዩጵያ እና ከኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአንድነት ታሪክ ውስጥ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ጸረ አንድነት አስተሳሰብ እኩይ ተግባር ነው።
ስለዚህ ሁሉም ኢትዩጵያዊ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተክታዩች ሁላችን «እርስ በርስሷ የተለያየች መንግሥት አትጸናም» ብሎ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እምነትን በፍቅር በሰላም ለማከናወን የሀገር አንድነትን ለማስጠበቅ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ለውጥ ለማምጣት የሚቻለው የእምነትና የታሪክ በለአደራ የሆነችውን ቅደስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን በሐዋርያት ትዕዛዝ መሠረት በአንድነት ስንጠብቅ እምነታችን የጸና መሆኑን አወቀን «ገለልተኛ» በማለት እየተቋቋሙ የቤተ ክርስቲያንን የመከራ ጊዜ የሚያረዘሙ ትርጉም የጠፋለትን የጸረ አንድነት ግለሰባዊ የጥቅመኞች ጎዞ እንዲገታ ማድረግ የአዲሱ ትውልድ ታሪካዊ ግዴታ ነው።
እንዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችን በአንድነት ይጠብቅልን!
መ/ጥ መንገሻ መልኬ
ኅዳር 2006 ዓመተ ምረት ዘመነ ማርቆስ ወንጌላዊ፤

ቢሞትም አይሞትም! (ግጥም ስለማንዴላ) –ከፋሲል ተካልኝ (አደሬ)

0
0

mandela

ቢቢሲ..አልጀዚሪያና ኤፒ የመሳሰሉ መገናኛ
ብዙኃን..በሰበር ዜናነት..የታላቁን የዓለማችን
ተምሳሌ – ተአርአያ የሆነውን የኔልሰን
ማንዴላን (የማዴባን) ዜና ዕረፍት እየዘገቡ ነው::

የዜናው እውነትነት ቢረጋገጥም..ቀደም ብዬ
በስንኞቼ..አጽንኦት ሰጥቼ እንደገለጽኩት..
የማዴባን ሕያውነት አይለውጥም::

ለማንኛውም..በሥጋዊ ዕረፍቱ የተሰማኝን ሐዘን በመግለጽ..ነፍስ ይማር እላለሁ::

የመታሰቢያ..ስንኞቹንም እነሆኝ ብያለሁ!!!

____ ቢሞትም አይሞትም ____

ከዳር እዳር ይናኝ..
ላለም ሁሉ ያስተጋባ
ስሙ የተቀደሰ ነው..
ለዘላለም ማዴባ!..ማዴባ!..

ማዴባ!..ማዴባ!..

ታቦት ተቀርጾ ለግብሩ..
ቢጠራ በቀንም ሆነ በሌት
ቢያሞጋግሱት ደጋግመው ቢቀኙለት..
ቢቆሙለት ቅኔ ማሕሌት

እማይበዛበት..
እማያንስበት..

ለሔደበት ፍኖተ-ነጻነት..
የመለኮታዊ ብርሐን ነጸብራቅ ነው!..
እሚያወጣ ተጭቆናዊ ቅሌት
ለቅኖች ሁሉ አብነት..
ለመላው ዘረ-አዳም ተምሳሌት::

ተሥጋዊ መሻቱ ‘ርቆ..ያለትዕቢት..ያለአመፃ..
በቅዱስ ውስጣዊ ሃይሉ..
የበደሉትን ይቅር ብሎ..በነጻ መንፈሱ ያነፃ

ተክፋታቸው እግረ-ሙቅ አላቆ..
በእርቀ-ሰላም በምህረትና በይቅርታ
የትም’ክታቸውን ሠንሰለት በጥሶ..
ያሰሩትን በትህትናው የፈታ
ለጨቁዋኞች ነጻ አውጪ ነው..
ለተጨቁዋኞችም እንደጌታ::

የተንኩዋሰሰው..
የዘረሰው መንፈስ..
ተዘር..ተቀለም ልቆ..በፅኑ መንፈስ ገዝፏል
ሕያው የሆነ ታሪኩን..በበጐ ምግባሩ ጽፏል

ምድረ-ደንብን ተቃርኖ..
ሕገ-ተፈጥሮን ተላልፏል
የዕድሜ ልክ ጽልመቱን እንኩዋ’..
በብሩህ ብርሐኑ ገፏል
ማዴባ ቢሞትም አይሞትም!..
ሞትን ቀድሞ አሸንፏል..
ተሚኖርበት በላይ ኖሮ..
ተሚሞትበትም ቀን አልፏል!!!

የቂም..የበቀል..የክፋት..
እሾህ እሾሁን ነቃቅሎ..
በእርቅና ሰላም ያስተቃቀፈ..
…ያበረከተ የፍቅር አበባ
ስለራሳችሁ ኑሮ ፀልዩ..
ቢሞትም እኮ አይሞትም!..
…ዘላለማዊ ነው ማዴባ::
* * *

___ፋሲል ተካልኝ አደሬ___

ኔልሰን ማንዴላ እና ኢትዮጵያ!! –በዳዊት ከበደ ወየሳ (ጋዜጠኛ)

0
0
Mandela is greeted by Ethiopian President Mengistu Haile Mariam on his arrival in Addis Ababa
የነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም ሲለዩ፤ የተለያዩ አገሮች እንደየራሳቸው ግንኙነት የራሳቸውን ታሪክ ሲያወሩ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ሃዘናቸውን ሲገልጹ ከማንዴላ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በመግለጽ ነበር። እኔ በምኖርበት አትላንታ ከተማ ዜናው ሲቀርብ፤ ኔልሰን ማንዴላ አትላንታ በመጡበት ወቅት፣ ከነአንድርው ያንግ ጋር ሆነው የማርቲን ሉተር ኪንግ ማዕከልን ስለመጎብኘታቸው ነበር – ዋናው ዜና። ሁሉም አገር ስለማንዴላ የየራሱ ትዝታ አለው። ኢትዮጵያውያንም ስለኔልሰን ማንዴላ የራሳችን ታሪክ እና ትዝታ አለን። እናም ማንዴላ የዛሬ 51 አመት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ስለነበረው ጉዳይ በማውጋት ታሪካችንን እንጀምራለን።
በዳዊት ከበደ ወየሳ

(ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ – PDF)

አለም በታላቅነቱ እኩል የሚስማማለትን ታላቅ ሰው አለም አጣች! ማንዴላን! ለማንዴላ እንዲህ ተቀኘሁ! ፍቅር አክብሮቴን መግለጹ ግን አሁንም የወገደኛል! (ነቢዩ ሲራክ)

ኑዛዜ ማንዴላ

0
0

mandela
ከገለታው ዘለቀ
geletawzeleke@gmail.com

መቼም ሰው ሥጋ ነኝና ታከተኝ
እረፍት ለጎኔ ናፈቀኝ
ሩጫዬን ግን ጨርሻለሁ
እምነቴንም ጠብቂያለሁ
እነሆ ከፊቴ ……….
ከሰማዩ ከላይ ኣባቴ
የድል ኣክሊል ተዘጋጅቶልኛል
የሰላም የፍትህና የ’ኩልነት
ደግሞ የህግ በላይነት
ዋንጫዎች ይጠብቁኛል

እስትንፋሴ ሳይለይ ግን ኣንድ ነገር ልበል……..
ኣንቺ ኣፍሪካ………
እትብቴ ስወለድ የተቀበረብሽ
ዘመኔን ሁሉ የሰጠሁሽ
እናት ዓለም ኣዳምጪኝማ
ኑዛዜ ቃሌን ጻፊልኝማ
ኣዳምጪኝማ ልንገርሽ
ምክር ተግሳጼን ልስጥሽ
ብዙህ ተፈጥሮሽን
ቀስተ ደመናነትሽን
ውበትሽ ኣርጊው ድሪሽ
ክብርና ልዕልናሽ
ኣትለይው ካንገትሽ ላይ
ዘመን ሲመጣ በዘመን ላይ
ኣንቺ ደቡባዊት ኣፍሪቃዬ
አትብቴ የተቀበረብሽ እመዬ
እንደገና ኣንድ ነገር ላስተንክርሽ
ኣዳምጪኝ እማ ሆይ እባክሽ

ያኔ በለቅሶ ዘርን ስትዘሪ
የነጻነትን፣ የፍትህን ኣባት ስትጣሪ
ጩኸትሽ ከጸባኦት ገብቶ
ቅንፈረጁን ኣምላክ ኣትግቶ
የኢያሪኮን ግንብ ኣፈረሰው
የግዞት ቤቱን ደረመሰው
የብረት በሩን ኣባተው
እግረ ሙቁንም ኣቀለጠው

ት ዝ ይለኛል……

ስወጣ እስራቴ ተፈቶልኝ
ምናቤ ተከፍቶ እንዲህ ኣሳየኝ
አነሆ ጸሃይ ህጉዋን ሰብራ
የተፈጥሮ ልማዱዋን ሽራ
በደቡብ በኩል ስትወጣ
የዘንባባ ዝንጣፊ ኣምጥታ
ኣየኋትና ደስ ኣለኝ
ተሰፋና ሃሴት ወሰደኝ
ኣይኔ በሮቶልኝ ኣሻግሬ ሳይ
ከጸሃይ መውጪያ ወዲያ ማዶ ላይ
ከኒያ ካሳለፍናቸው ክፉ ዘመናት በላይ
ክምር የመልካም ነዶ ዘመን ተቆልሎ ባይ
የኣሁኑ ዘመን ስቃይ
ሊመጣ ካለው ክብር ጋር ሲተያይ
እንደ ኢምንት ሆኖ ኣየሁትና
የዘንባባ ዝንጣፊ ኣነሳሁኝ
ሰላምና ፍትህን ኣወጅኩኝ
በቀልና ዘረኝነትን ኮነንኩኝ
የኩልነትን እጀታ ኣጥብቄ ኣጥብቄ ያዝኩኝ
ያ ነበር በውነት ያስደሰተኝ
በርጅና ዘመኔ ሁሉ እንደ ንስር የሚያድሰኝ

ኣንቺ ደቡባዊት ኣፍሪካዬ
አትብቴ የተቀበረብሽ እናትዬ
ከምድርሽ ፍሬ በልቼ
ከሖድሽ ጠበል ጠጥቼ
ኣድጊያለሁኝና
ምስጋናዬ ይሄውና
ያ የክረምቱ ጊዜ ኣልፎ
ዶፍ ዝናሙ ደመናው ሁሉ ተገፎ
እሰይ እሰይ ኣጨዳሽን ጀምረሻል
የመኸር ጊዜ መጥቶልሻል
ኣጨዳሽን እጨጂ
በርቺ ሂጂ ተራመጂ
ግን ደሞ ….
ኣንድ ነገር ኣትርሺ
ያን ያፓርታይድ ዘረኝነት እንዲያ አንደጠላሽው
ኣንገፍግፎሽ ኣንዘፍዝፎሽ ወዲያ እንዳልሺው
እንደዚያው እንደጠላሽው ኑሪ
በፍቅር ባቡር ብረሪ
አንዳትመለሽበት ኣደረሽን
ከነፍስሽ ጥይው እባክሽን
በራስሽ ላይ አንደጠላሸው
በሌላውም ላይ አታድርጊው

እነሆ አግዚኣብሄር በሰጠኝ ኣገልግሎት
የፍቅርና የሰላም ክህነት
ውጉዝ ውጉዝ ከመ ኣርዮስ
ውጉዝ ከኣፍሪካ ብያለሁ ዘረኝነትን
ኣምባገነንነትና ኢፍታዊነትን
ኣትብቀሉ በምድሪቱ
ኣትለምልሙ ኣታኩርቱ
ባለም ሁሉ በምድሪቱ
ያለም ህዝቦች ሁላችሁ
የሰው ዘር ሁሉ የሆናችሁ
ከሰላምና ከእኩልነት ገበታ ብሉና ጠጥታችሁ ርኩ
ሰላም በሰላም ላይ ፍቅር በፍቅር ላይ ተኩ

የናቴ ያባቴ ልጅ ኣፍሪካ…………

ኣሁን ስጋዬ ረፍት ብጤ ናፈቀው
መቼም ሰው ነውና ስጋ ነውና ታከተው
ሄዶ ሄዶ ከዚህ ኣይቀርምና
የተፈጥሮ ህግ ኣይሻርምና
እኔ እንግዲህ ሄጃለሁ
ፍቅር ሰላም አኩልነት ላለም ሁሉ አመኛለሁ
ኣበቃሁ ቃሌ ይሄው ነው ኑዛዜየን ኣድርሻለሁ
ሃብቴ ቅርሴ ያለኝ ይሄው
ኑዛዜየ ስጦታዬ እምነቴ ነው

ለእምነት፣ ለእውነትና ለሕሊና የሚስማማ ሥራ እንስራ

0
0

ከእውነት መስካሪ

የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ክ በዘመናት ካጋጠሟት ፈተናዎችና ችግሮች ሁሉ ምናልባትም በአይነቱ ብቻ ሳይሆን በስፋቱም ለየት ያለው ይህ አሁን በእኛ ዘመን የተከሰተው የአባቶች መከፋፈል ወይንም በፖለቲካ ጣልቃገብነት የተፈጠረው የቤተክርስቲያኗ አመራር ክፍፍል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። በአጠቃላይ በክርስትና ላይ የደረሰውን ፈተና ትተን በእኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ የደረሰውን እንኳን ብናይ በ9ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዮዲት ጉዲት፣በ15ኛው መ/ክ/ዘ በግራኝ መሐመድ፣በ18ኛው መ/ክ/ዘ በእንግሊዝ፣ በ19ኛውና በ20ኛው መ/ክ/ዘ በፋሺሰት ኢጣልያ ወረራ በቅርቡም በደርግና አሁን ደግሞ በወያኔ ኢህአዴግ መንግሥታት በቤተክርስቲያናችን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለው ጉዳት እጅግ ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን በቀደመው ዘመን የነበሩት አባቶቻችን በእምነትና በእውነት እየተመሩ ለህሊናቸው ብቻ ሳይሆን ለትውልድም የሚያኮራ ስራ ትተውልን አልፈዋል፡፡
abune_petros
በዮዲት ጉዲት 40 ዓመት የመከራ ዘመን መከራው ስለበዛባቸው 10ኛው ወይንም 20 ኛው አመት ላይ እንግዲህ በቃን እስከመቼ እንዲህ ሞተንና ተሰደን እንዘልቃለን ልጆቻችንስ እስከመቼ እንዲህ ሆነው ያድጋሉ በማለት እጃቸውን ለጨፍጫፊዋ ዮዲት አልሰጡም። 40 የመከራ አመታትን በሰማእትነት፣በስደትና በመከራ አሳልፈው ተዋሕዶ እምነታችንን እስከነምልክቷ አስተላልፈውልናል። በዘመነ ግራኝም እምዲሁ ሰማእትነትን ከፍለው ታቦታቱን በዋሻ ደብቀው ከአገር አገር ተንከራተው ኃይማኖታችንን ከነክብሯ አስተላልፈውልናል።

ፋሺት ኢጣልያንም በርካታ ገዳማትንና አድባራትን አቃጥሏል። በተለይም ታላቁን የደብረሊባኖስ ገዳም ከማቃጠሉ በተጨማሪ ቁጥራቸው ከ500 በላይ የሆኑ ገዳማዊያንን በግፍ ጨፍጭፏል። ይሁን እንጂ የቀደሙት አባቶቻችን በእምነታቸው ጽናት ለጨፍጫፊዎችና ወራሪዎች ሳይንበረከኩ ኃይማኖትን ከነምልክቱ አገርን ከነነጻነቱ አቆይተውልናል። በጣልያን የኋለኛው ወረራ ወቅት የቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ አባት የነበሩትን ፃድቁ ሰማእትና አርበኛ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስን ጣሊያን በአደባባይ ከገደለ በኋላ ለጣሊያን መንግሥት ያደሩ አንዳንድ ባንዳ ‘አባቶች’ ከጣሊያን ጎን ተሰልፈው ሕዝቡ ለጣሊያን እንዲገዛ ሲያደርጉ የነበሩ መኖራቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ በተለይም በሰማእቱ አቡነ ጵጥሮስ ወንበር አቡነ አብርሃም የተባሉ አባት ለጣሊያን አድረው በአቡነ ጵጥሮስ ቦታ ተሾመው ነበር። ጀግኖች አባቶቻችን ግን ይህን አይነቱን ክህደት አንቀበልም በማለት በዱር በገደሉ ለአገራቸውና ለኃይማኖታቸው ነጻነት ተጋድለዋል።

በተጋድሎአቸውም ተዋሕዶ እምነታችንን ከካቶሊክነት ኢትዮጵያንም ከቅኝ ግዛት ታድገዋታል። እንግዲህ እኛ አባቶቻችን የምንላቸው ሰማእታት ሆነው፣ተሰደውና በእምነታቸው ጸንተው እምነታችንን ከጠላቶቻችን ታድገው ያቆዩልንን እንጂ በክህድት፣በፍርሐት፣በወገኝተኛነት፣በዘርና በመሳሰሉት ምክንያት ከጠላት ጎን ሆነው ኃይማኖታቸውንና አገራቸውን የከዱትን አይደለም።
በዚህ በእኛም ዘመን ያለን የተዋሕዶ አማኞች አባቶቻችን የምንላቸው እነማንን ይሆን?
የኢትዮጵያ ክብር ሲዋረድና ሕዝቦቿ ሲሰደዱ ይህን ከሚያደርገው አካል ጋር የቆሙትን?
ወይንስ የአገር ዳር ድንበር መፋለስና የህዝቦቿ አንድነት መሸርሸር የለበትም ብለው ከተሰውና ከተሰደዱትን ጋር?
በቤተክርስቲያን ላይ በመጠን ሊገለጽ የሚከብድ ጥፋትን እያደረሰ ካለ ኃይል ጋር የቆሙትን? ወይንስ ይህን የቤተክርስቲያንን መጠቃት የሚቃወሙትን ነው አባቶቻችን የምንል?
ምናልባተ በዘመናችን በእውነት ስለኃይማኖትና ስለአገር ብቻ ሳይሆን የራስንም ክብርና ምኞት ለማሳካት የሚደረግ ነገር በሁሉም ዘንድ አንዳለ ቢታየን አምላካችን በእውነት እስኪገለጥልን በያለንበት እንጽና እንዳለው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከአጥፊዎችና ከጥፋቱ ተባባሪዎች ጋር ከመቆጠር ራሳችንን ልናቅብ ይገባናል። እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ መንገድ አለው፤በኃይለኛ ውኃ ውስጥ መተላለፊያ ያደርጋል እንዳለ ነብዩ ኢሳ.43፥13 ሁሉ በእግዚአብሔር ጊዜ ስለሚፈጸም፤ የቤተክርስቲያን ልዕልናና የኢትዮጵያ ትንሳዔ መምጣቱ ስለማይቀር ያለነው ትውልዶች ለእምነት፣ለእውነትና ለሕሊና የሚስማማ ሥራ ሰርተን እንድንገኝ እግዚአብሔር ይርዳን። አሜን!

ዛሬ አርብ እና የፊታችን እሁድ የተጠራ ዓለም አቀፍ የጸሎት ቀን ለሳዑዲ ሰለባዎች (Flyer)

0
0

ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በሳኡዲ አረቢያ ዛሬ አርብ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንዲሁም የፊታችን እሁድ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሳዑዲ አረቢያ ለሞቱት፣ የሰብአዊ መብታቸው ለተገፈፈና ለታሰሩት ወገኖች መታሰቢያ ዓለም አቀፍ የጸሎት ፕሮግራም ጠርቷል። ትብብሩ ለኢትዮጵያውያን የበተነው በራሪ ወረቀት (ፍላየር) የሚከተለው ነው፦
Global Alliance Prayers

አርቲስት ሻምበል በላይነህ በሳዑዲ አረቢያ ለተሰቃዩና ለሞቱ ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ አቀነቀነ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ተወዳጁ ድምፃዊ ሻምበል በላይነህ ከሰሞኑ በሳዑዲ አረቢያ ለሞቱትና ለተጎዱት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ የሚሆን አንድ ነጠላ ዜማ ለቀቀ።

ሃገራዊ ዘፈኖችን በብዛት በመዝፈን የሚታወቀው ሻምበል በላይነህ ከሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመው አሁን ያለው ስርዓትን “የምትሰራው ጥፋት ነው፤ አስተካክል” ከሚሉ ጥቂት አርቲስቶች መካከል አንዱ ሲሆን፤ ዛሬ የለቀቀው ነጠላ ዜማም እንዲሁ ለሃገሩም ሆነ ለወገኑ ያለውን ፍቅር የገለጸበት ነው። ሻምበል በተለይ ኢትዮጵያውያኑ በሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲ አለን ብለው ቢጠጉ ስለመገፋታቸው በዚህ ነጠላ ዜማው ላይ አቀንቅኗል። ዘፈኑን ተካፈሉት፦


ወያኔ የካደው = ግንቦት ሰባት የተነፈሰው = አና ጎሜዝ ያልሸሸጉት አዲስ ነፋስ (“ድርድር”)

0
0

ከምኒልክ ሳልሳዊ
ይህን ሰሞን በሃገር ውስጥ እና በውጪው ሃገር ኢትዮጵያውያን ዘንድ የመወያያ ርእስ የሆነው እና ይየወያኔ ካድሬዎችን ቀልብ የገፈፈው እና ከሰል ያለበሳቸው ወያኔ ለግንቦት ሰባት ያቀረበው የድርድር ጥያቄ ነው::በስፋት አሁንም እየተከራከሩበት ያለው ይህ ጉዳይ አገሩን በጡዘት አምሶት የሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት አንድ ተስፋ የሰጠ ሁኔታ እንደሚታይ እየተተነበየ ነው::

ወያኔ በእርግጥ በማይጥም የፖለቲካ እሰጥ አገባ የተጠመደ ቢሆንም የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ለላውን ከማዘናጋት ውጪ ምንም አይነት ፋይዳ እንዳሌለው እና ራሱን እየፈተሸ እንደሆነ ያጋለጠ ጉዳይ ነው:: የድርድር ጥያቄ አላቀረብኩም ያለው ወያኔ እንደለመደው ከኦነግ ከኦብነግ ከሻእቢያ ጋርም እየተደራደረ ጥያቄውን እራሱ እያቀረበው ሲክድ የቆየ ሲሆን በቅርቡ እንኳን በኬንያ ከኦብነግ በጀርመን ከሻእቢያ ጋይ ያደረጋቸውን ድርድሮች እየታከካቸው አልፏል::
andargachew
ወያኔ የካደው እና ግንቦት ሰባት የተነፈሰው የእንደራደር ጥያቄ የአናጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ ተከትሎ የወጣ ጉዳይ ነው:: በእርግጥ በተለያዩ ጊዜያት ለወያኔ እና ለግንቦት ሰባት የቅርብ ርቀት የሆኑ ሰዎች ይህንን ጉዳይ በግል አንስተውት የሆነ ቢሆንም ባይሆንም ግን የአና ጎሜዝ የአዲስ አበባ ምላስ ተከትሎ ግንቦት ሰባት ለህዝብ ይፋ ያደረገው ጉዳይ አሁንም ሚዛኑ ወደ ግንቦት ሰባት እንዲሆን አድርጎታል::

እንቅልፍ የነሳቸው የወያኔ ባለስልታናት የቀን ተቀን የስብሰባ መቀመጫቸው ግንቦት ሰባት ነው:; በወታደሩ በደህንነቱ እና በታማኝ ካድሬው ዙሪያ ውይይቱ ምስጢሩ ግንቦት ሰባት ነው:: እነዚህ የሚስጥር ተወያዮች እንደሚጠቁሙት ሲሰበሰቡ በውይይት ወቅት ግንቦት ሰባትን አሸባሪ ብለው አይጠሩትም:; አሸባሪ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታቸው አደባባይ ላይ መሆኑን በይፋ የተረጋገጠ መረጃ ይጠቁማል::
በቅርቡ ከአባቱ ሻእቢያ ጋር ጀርመን ላይ የተወያየው ወያኔ ግንቦት ሰባት የራስ ምታት ስለሆነበት እንዲያደራድረው አሊያም እንዲገላግለው ተማጽኖ ቢሆንስ??? ወይኔ ሻእቢያ የሚፈልጋቸውን ተቃዋሚ ኤርትራውያንን እያፈነ እንደሚሰጥ የህን ሰሞን ሃተታዎች እየጠቆሙ ነው እንዲሁም በሱዳን በኩል እያሽከረከረም እንደሚያስረክብ::ነገሩ የጨነቀው እርጉዝ ያገባል አይነት ነው ….
የአቶ ታምራት ላይኔም ወደ ፖለቲካው ለመቀላቀል ማቆብቆብ እኮ የዚሁ የድርድር አንዱ አካል ነው:; ብኣዴን ታምራት ላይኔን ይፈልገዋል:: አገሬ በፈለገችኝ ሰአት ለማገልገል ተዘጋጂቻለሁ የሚለው ታምራት ጠጋ በል እየተባል መሆኑስ የወያኔ አንድ የጭንቀት ምልክት አይደል?! … ወደ ሚዲያዎች አያሰገገ መምጣቱ ሌላ ምስጢር የለውም::
Ana Gomez
አና ጎሜዝ ከአዲስ አበባው ቆይታቸው ሁለት ንግግሮችን ከአንደበታቸው ሰምተናል:: አንዱ “ከባለስልጣናት ጋር ያደረኩት ውይይት በጎ እና ገንቢ ነው መልካም ምላሽ እንዳገኙም በእርካታ ተናግረዋል:; በመተማመን ስሜት ደሞ “አዲስ ንፋስ አለ” ሲሉ ተስፋቸውን አብርተዋል:: ይህንን የፖለቲካ ስሜታቸውን ያልተረዱ የደፈናው ጋዜጠኞች የወያኔን የሞተ እስትንፋስ ሊያበረቱ ቢሞክሩም የሚሳካ ካለመሆኑም ሌላ ወያኔም …ጌታ….ተላላኪ…;;እያለ ቢዘላብድም ታምኝነት ሊያገኝ አልቻለም:: አና ጎሜዝ ይህንን ሲናገሩ ከባለስልጣናት አንደበት የሰሙት እና የተላኩት መልእክት እንዳለ ይጠቁማል:: አና ጎሜዝ ወደ ግንቦት ሰባት ብቻ ሳይሆን ለተለያዩ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የለውጥ ጠያቂዎችም የብሄራዊ ድርድርን ጉዳይ አስረግጠው አዋይተዋል:;በእርግጥ ስለግንንቦት ሰባት ባያነሱም ይህ የእንደራደር ጥያቄ የመልስ ምቱን ወያኔ ለማወቅ ፈልጎ ያደረገው ሊሆን የሚችል የማጭበርበሪያ የፖለቲካ ስልት ቢሆንም የድርድሩ ጥያቄ ግን የአና ጎሜዝን የአዲስ አበባ ቆይታ እና የአዲስ ነፋስ ምልክታን ተከትሎ መነገሩ እውነታውን ያጎላዋል:; ይህ የሚያሳፍረው ወያኔን ቢሆንም ወያኔ ግን ምንተእፍረቱን አይኑን በጨው አጥቦ ቢክድም አሁንም ግንቦት ሰባትን እንዲያደራድሩት ከትን እንዲያደበጀርባ እየተለማመጠ እንደሚገኝ ለማስገንዘብ እወዳለሁ

በወያኔ ስርዓት ውስጥ በሙስና ያልተጨማለቀ ሰው ቢኖር እኔ ነኝ ዓሉ ወ/ሮ አዜብ

0
0

1426495_1399381543638336_1221153530_nየብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው። “የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው…ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።…….” ተከሳሾቹ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት ወንድማቸው ዘርአይ ወልደሚካኤል፣ እህታቸው ወይዘሪት ትርሃስ ወልደሚካኤልና የቅርብ ጓደኛቸው ዶሪ ከበደ ናቸው ።ተከሳሹ በ 2002 ዓ.ም ቱሪዝም ኢን ኢትዮዽያ ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙ ሲሆን ፥ ይህንን መጽሃፋቸውን በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት እንቅስቃሴም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገብረስላሴ የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ። መጽሃፉ በመስሪያቤታቸው ስም እንደተዘጋጀ በሚያስመስል ሁኔታ አቶ በየነ የሚመሯቸው የቦሌ፣ የብርሃንና ሰላምና የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች በጋራ የአቶ ወልደስላሴን 3 ሺህ መጻህፍት በ124 ሺህ ብር እንዲያሳትሙ ተደርጓል ነው የሚለው ክሱ።

ማተሚያ ቤቶቹ በርካሽ ያሳተሙት አቶ ወልደስላሴ ከነበራቸው ተሰሚነትና ስልጣን መነሻነት መሆኑንና ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ ብር ክፍያ ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍልም መደረጉንም ነው የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው። አቶ ወልደስላሴ የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝና የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ጊዜ ሃላፊነታቸውነ ተጠቅመው ፥ ሁለቱ ድርጅቶች 310 ኮፒዎችን በግድ እንዲገዙ መደረጉም ተመልክቷል። 26 የሚሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችም እያንዳንዳቸው ከ 25 እስከ 1ሺህ 500 ፥ በጥቅሉ ከ73 ሺህ የሚልቁ ኪፒዎችን ሳይወዱ በግድ እንዲገዙ መደረጉ ፣ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ተቋማቱ ለመጻህፍቱ ገንዘብ ከፍለው መጻህፍቱን አለመረከባቸውም ጭምር ነው በክስ መዝገቡ የተዘረዘረው። ተከሳሹ አቶ ወልደስላሴ ባልደረባቸወ የሆኑ አንዲት ሴት ጋር በነበራቸው መቀራረብ የመስሪያቤቱን መኪና በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እያስሞሉ ግለሰቧ እንደልባቸው በአዲስ አበበባና ከከተማ ውጪ እንዲጠቀሙበት አስደርገዋል የሚለውም ተጠቅሶባቸዋል።

ተከሳሹ ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም አቶ ሳቢር አርጋው የተሰኙ ነጋዴን ለምሰራው ቤት ሴራሚክ ስለጎደለኝ የጣሊያን ስሪት ገዝተህ ስጠኝ በማለት ፥ በስልጣናቸው አስፈራርተዋቸው የ65 ሺህ ብር ሴራሚክ ተቀብለዋል ፣ ከ 2001 እስከ 2005 ባሉት የግብር አመታት አሳትሞ ከሸጣቸው መጻህፍት ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ከ496 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት አስታውቆ አለመክፈሉም ተጠቅሷል። ተከሳሹ ባለ4 ፎቅ የግል ቤቱን ወንድሙ ለሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ ዘርአይ ወልደስላሴ ውክልና ሰጥቶና ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ አገልግሎት እንዲውል አድርጎ በ14 ወራት ውስጥ 790 ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል ፤ ከገቢው 126 ሺህ ብር የሚሆነው የመንግስት ግብርን ለግብር አስገቢው መስሪያቤት ሃሰተኛ መግለጫ በማቅረብ ሳይከፍል መቅረቱም በክሱ ተመልክቷል። ከዚሁ ቤት ኪራይ መንግስት ከተርን ኦቨር ታክስ ማግኘት የነበረበትን ከ119 ሺህ ብር በላይ ገቢ ሳያገኝ መቅረቱና ተከሳሹ በህገ ወጥ መነገድ ያገኘውን ገንዘብ ማንም እንዳያውቅበት ለማድረግ በሰኔ 28 1998 ዓ.ም ለሁለተኛው ተከሳሽ (ወንድም) ዘርአይ ወልደሚካኤል ሙሉ ውክልና መስጠቱ ተዘርዝሯል።

እንዲሁም ምንም አይነት የገንዘብ ልውውጥ ሳያደርጉ ከ3ኛዋ ተከሳሽ እህቱ ትርሃስ ጋር መጋቢት 24፣ 2005 ዓ.ም የብድር ውል ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።በተጨማሪም ተከሳሹ ከእህቱና ወንድሙ ጋር ያለአግባብ አፈሯቸው የተባሉ የገንዘብና የአይነት ሃብቶች በክስ መዝገቡ ተጠቅሰዋል። 1ኛው ተከሳሽ ወልደስላሴ ወደሚካአል ከ1983 እስከ የካቲት 2005 ዓ.ም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ ፥ ወርሀዊ ደመወዙ ከ 1,600 እስከ 6,000 ብር የነበር ሲሆን ፥ ነገር ግን ስልጣኑን እና የነበረውን ተሰሚነት በመጠቀም በፈጸመው የሙስና ወንጀል ከባለ4 ደረጃ ህንጻ ውጪ ፣ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች ተቀማጭ ማድረጉም ተመልክቷል። 2ኛ ተከሳሽ አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ከመከላከያ ሚኒስቴር በጡረታ እስከሚገለል ድረስ ወርሀዊ ደመወዙ 532 ብር የነበር ሲሆን ፥ በክስ መዝገቡ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማስቀመጡ ፣ በአዲስ አበባ ቤቴል ቁጥር 3 በተባለ አካባቢ በ74 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ መሰረት የተጀመረበት ቦታ ፣ በአፋር ክልል ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሁለት የእርሻ ኢንቨስትመንቶችና 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሎደር ማሽነሪዎችም በስሙ መኖራቸው ተመዝግቧል ።

3ኛዋ ተከሳሽ የአቶ ወልደስላሴ እህት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፥ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው።ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር ፣ አውቶሞቢል መኪና፣ በአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧል ፤ በተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።

https://ethioandinet.wordpress.com

ስለሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ፦«የዋህነት ጸባይ እንጂ እምነት አይደለም» –መጽሀፈ ምሳሌ ምዕ 3 ቁ 1

0
0

ከጦመልሳን ወንድራስ
deb
«የዋህነት ጸባይ እንጂ እምነት አይደለም»
መጽሀፈ ምሳሌ ምዕ 3 ቁ 1
«ልጄ ሆይ ሕጌን አትርሳ ልብህ ትዛንዜን ይጠብቅ»
ለእዚህ ጽሁፌ መነሻ ያደረኩት June 2, 2013 በሚኒሶታው ደብረሰላም መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ስብሰባ ላይ ያየሁትን እኔም እምነቴ የሚስማኝን ለመጽፍ ወደድኩ።
ይህ ሀሳብ የእኔ ብቻ እንደሆነ አንባቢያን እንዲረዱልን በማክበር እጠይቃለሁን።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእድሜ አንጋፋ ከሆኑ ሀይማኖቶች አንዱ ብል ማጋነን አይሆንብንም፤ ይህ ሀይማኖት ሳይከለስና ሳይበረዝ የራሱን ህግጋቶችና ደንቦች እየጠበቀ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ሲሸጋገር እነሆ ዛሬ ያለንበት ጌዜ ላይ ደርሰናል። ሂደቱም ቀላል አልነበረም። ስንት አበው አባቶች አንገታቸውን ሰተውበታል፣ ተሰደውበታል፤ ታሰረውበታል።
ላለፉት 22 አመታት ግን የምናየው የተለየ ሆኖ አግቸዋለሁን ለዚህም እንደማስረጀ ላቅርብ፦
1 የጸሎት አባቶች ከመንፈስ ስራ ይልቅ ጉቦ መዘፈቃቸው
2 ቤተክርስቲያኖቾ ለአልባሌ ንግድ መግባትና መሰማራት (ገብርኤል፤ኡራኤል፤ልደታ) ለምሳሌ መጠጥ ቤት፤ ቻት ቤት፤ ሙዚቃ ቤት ወዘተ።
3 በዋልድባ የሚኖሩ አባቶች ሲደበደቡ የሲኖዶስ አመራር አባሎች ዝም ብለው መመልከታቸው (አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ)
4 ጳጳሱ ሳይ ሞቱ ሃውልት አቁመዋል እንዲፍርስ ታዞ ድፍረቱ ያለው ነፍስ አባት ማየት ተቸግረናል
5 ጳጳሱ በአለ ሲመታቸውን በሸራተን አስረሽ ምችው ሲሉ ሌሎች ቤተክርስቲኖች የጣፍና የሻማ መግዥ አተው እናያለን
6 ጳጳሱ አቀንቃኖች አምጥትው ጉያቸው ስር እስከማስቀመጥ አዋርደዉታል
7 የስላሴ ኮሌጅ መዘጋት
8 የኦርቶዶክስ ምጽመን በጸሎት አባቶች እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ አድርግውታል
9 ከዚህ በፊት የተያዘው ሽምግልና ፈርሶ ገዥው መንግስት የራሱን ስው ሾሟል
ታዲያ በሂደት ያየናቸው ጳጳስ እንደ ብጽጹ አቡነ ተክለሀማኖትና በቅርቡ ህወታቸውን ያለፈውን ጵዉሎስን እንመልከት ማነው ለነፍሱ ያደር ማነው መንጋውን የጠበቀ ፍርዱን ለናንተ እተዋለሁኝ
ይህ በእንዲህ እንዳለ June 2, 2013 በቤተክስቲያን በተደረገዉ ጉባኤ የቤተክርስቲያኑ ቆሞስና አንዳንድ ሰንበት ተማሪዎች ተሰብስበው ይችን ቤተክርስቲያን ወደ አገር ቤት ካለው ሲኖዶስ እንቀላቀል ይሉናል እንግባ ይሉናል ፀሐይ ላይ ያሰጡት ኩታ ይመስል ይሞጉቱናል ይህ ማለት ከላይ የጠቀስዄቸውን ሁሉ አባሳ መደገፍ አይሆንም። ይቺ ቤተክርስቲያን ላለፉት 21 አመት ሕግና ደንብዋን አስጠብቃ የኖረች በአሜርካን ውስጥ ካሉት ቤተክርቲያን ለምሳሌ የምትቀርብ ብል ማጋነን አይሆንም በእዚህም ምንጊዜም እኮራለሁ።
ከሁሉም በላይ የሚገርመኝ የሰንበት ተማሪዎች ነን ባዮች ከላይ የጠቀስኩትን እውነታ እያወቁ ከቆሞሱ ጋር መወገናቸው ብዙ አይገርመኝም በየትኛውም ኦርቶዶስ ቤተክርስቲያን መዘምራን ቄሱ ፊሽካ ናቸው። ቄሱ በፈለገው ጌዜና ቦታ የሚነፋቸው ጡሩንባ ናቸው ቅዱስ ስራውን እየጣሱ ቅዱስ ማሕበር አባል ነኝ ማለት አይገባኝም ቁሞሱ ይህን ቤተክርስቲያን ወደ ሲኖዶስ ከቀላቀሉ ጳጳስ ይሆናሉ ተብለዋል ታዲያ መዘምራን ለእናንተ ምን ቃል ተገባላችሁ ንገሩን ትላንትና ቤተክርስቲያኑን ባለው ሕግና ደንብ መሰረት ስትመሩ የነበራችሁ ዛሬ ወደ እዛ እንግባ የምትሉን ቆሞሱ ቢሆን ለጳጳስነት የሚያበቃ ዕውቀት ልምድ አላቸውን እኔ እስከማቀው ድረስ በውነት፤ዛሬ፤በውነት፤ዛሬ ከማለት በስተቀር በትክክለኛው ወንጌል ሲያስተምሩ አይችሉም።
ለእዚህ ማስረጃ ሆኖ የማቀርበው ወደ ቆሮንጦስ ስዎች ምዕ 12, አንቀጽ 7-10 ምን ይላል
ቆሞሱ እግዜአብሔር በሰጣቸው ሊቅነት ቢያገለግሉ ምናለ የማታ ማታ የነፍስ አባት የሚሆኑት እርሳቸው አልነበሩምን ታዲያ የዚህን ምስኪና የዋሕነት ተጠቅመው መቼ ነው የምትቆርቡት ከማለት በስተቀር እስቲ አስራት በኩራት ስጡ አይሉም ምክኒያቱም አስራቱን ከሰጠ ቤተክርስቲን ሁሉ ለልመና አደባባይ ባልወጣች ነበር።
አሁን በቤተክርስቲናቺን ውስጥ 20% አስራቱን የሰጣል 80% አልገባውም ወይም የፀሎት አባቶች የሚነግሩት አፈታሪክ ነው የስንበት ተማሪዎች ተብየዎቹ ስንቶቻችሁ ናችሁ አስራት የምትከፍሉ ስንቶቻችሁ ናችሁ ለአዲሱ ሕንጻ መዎጮችሁን የከፈላችሁ ስም አልጠራም ሰም ማየት ይቻላል መዝገቡ ይናገራል ዳሩ አልፈርድባችሁም አንዳንዶቻችሁ ቄስ ጭን ስር ስላደጋችሁ የእግዚአብሔርን ክብር ለቄሱ ስታችሀል፤ አንዳዶቻችሁ መዋለንዋይ አማልሎችሀል ይህን እውነት ማንም ሊደፈጥጠው አይችልም። አንዳዶቻችሁ የዕውቀት ማነስ ይታይባቸዋል
ለእዚህም እንደ ምክኒያት የማቀርበው ሲኖዶስ ማለት ምን ማለት ነው(ሕግ ወይም መተዳደሪያ ደንብ)ማለት ሲሆን አስፈፃሜው አካል ደግሞ ቤተክህነት ይባላል ይህ የእኛ ቤተክርስቲያን በአንድ ኢትዮጵያ በአንድ ሲኖዶስ እናምናለን
ይህ ለእኔም ፤ለቆሞሱም፤ ለመዘምራንም፤ ለቦርዱም፤ እናም ለምመኑም ግልጽ መሆን አለበት ከዚህ ውጭ ስለ ህጉ የነገራችሁ ካለ ስህተት ነው።
ከሁሉም በላይ መናገር የምፈልፈው ማንም ሰው ኢየሱስ አላየም ሥራው፤ተአምሩ፤ ሰብስቦናል የምንጠየቀው በምግባራች ነው እንጅ በያዝነው ሀይማኖት አይደለም ይህ ቢሆንማ ኦርቶዶክስ ተለይቶ ሰማያዌ መንግስትን በወረስን ነበር ይህ አፈ ታሪክ ነው።
አንዳንድ የዋህ ምዕመን እዛ ገብተን መታገል አለብን ይላሉ።
«እግር እራስን አያክም« ትግል መሰዋትነትን ይጠይቀል የፀሎት አባቶች የያዙት ልፊያ ነዉ 22 አመት ተላፍተናል ደክሞናል፣ ለእዚህም «የዮሀንስ ወንጌል ምዕ 11 አንቀጵ 40 ማየት በቂ ነው። ወድ የቤተክርስቲያኑ አባላት ይህ የተጋረጠብን አበሳ አስወግደን ቤተክርስቲያናቺን እንጠብቅ« እምነት ሁሌም አልጋ በአልጋ ሆኖ አያቅም» ከእዚህ ትልቅ ጋሬጣ ካላስወገድን ወ ደፊት ለምናስበውና ለተለምነው የቤተክርስቲያኑ ግንባታ አንደርስም። ለእዚህም አንድ ቃል ልጥቀስና ጹሑፌን ላጠቃል።
«የያቆብ መልክት 2 ምዕ2 አንቀጵ 11 እንዲህ ይላል «ወንድሞቼ ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን ሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቀመዋል እምነቱ ሊያድነው ይችላልን»
ታዲያ ኦርቶዶክስ ነን የምንል ሁሉ ቤተክርስቲያናቺንን ማዳን ይኖርብናል ይህ ቡና ረከቦት ስር የሚወራ ወሬ አይደለም የልጆቻችሁ የወደፊት ተስፋ የሚያጠፋ ነው
ዠንጀሮ የመቀመጫዋ መላጣ አይታያትም ይህ ካልታየን በእንግሊዚ ያለውን ቤተክርስቲያን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ፣ በስላሴው ኮሌጅ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ማየት ይቻላል በዚህ ዓለም ስንኖር የምዳኘው በሕግ ነው ለነፍሳችን ግን የምንዳኘው በፈጣሪያችን ብቻ ነው።
አሁንም ቤተክርስቲናችንን ይጠብቃት መሪዎቻን ማስተዋል የስጥ ያልተከለሰና ያልተበረዘ ወንጌል ማስተማር ይጠብቅባቹኃል
እግዚአብሔር አገራችንን ይባርካት
ጦመልሳን ወንድራስ

ሚኒሶታ መድኃኔዓለም ደብረሰላማችን ፣ ትንሿ ኢትዮጵያ ምትክ አገራችን –ለሰላምና አንድነት የቆሙ ምእመናን ያስተላለፉት ጥሪ

0
0

deb
Dec.7, 2013
በሥላሴ ስም አንድ አምላክ። አሜን!
ለሰላምና አንድነት የቆሙ ምእመናን
ኢትዮጵያዊነት የሚንጸባረቅበትንና መቻቻልና አንድነት የሰፈነበትን ማኅበር ወይንም ስብስብ ሁሉ የኃይማኖት ይሁን የሌላ የማፍረስና ሰላም የመንሳት አባዜ የተጠናወተው በትልቋ ኢትዮጵያችን ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የህዝቧን ደም እየመጠጠ የሚገኘው ወያኔ ኢሕአዴግ ነው። አስቀድሞ ገና ከጫካ ወደ ከተማ ሲመጣ እንደ አብይ መፈክር ይዞ የነበረው የታላቋን አገር ታሪክ ማንኳሰስ፣ ባንዲራዋን ማዋረድና ሕዝቧን በዘር መከፋፈል ነበር። አሁንም ነው፡፡ ይህች የረዥም ዘመን ታሪክ ያላት ታላቅ አገር በዘመናት ለተቀዳጀቻቸው አኩሪ ድሎችና ገድሎች ደግሞ ሁሉም እምነት፣ ተቋማትና ብሔረሰቦች አስተዋጽኦ ነበራቸው። በተለይ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከኢትዮያ ታሪክና ሁለንተናዊ ማንነት ጋር የነበራት ትስስር የጎላ መሆኑ ለሁሉም የተገለጸ ነው። በዚህም ምክንያት ይህ መሰሪና ዘረኛ ቡድን ገና ወደ ስልጣን ሲመጣ በቅድሚያ ካደረጋቸው እኩይ ተግባራት መካከል የቤተክርስቲያኗን ቀኖና በመጣስ ሉአላዊነቷን በመግሠሥ በወቅቱ ፓትርያርክ የነበሩትን አባት እንደ ምድራዊ ባለስልጣናት ከመንበራቸው ማባረር ነበር። ይህም አስነዋሪ ተግባር የተፈጸመው የራሱን እኩይ የፖለቲካ አላማ ያለተቃውሞ ለማስፈጸምና የቤተክርስቲያኗንም ሐብትና ንብረት በቀላሉ ለመዝረፍ ያመቸው ዘንድ ነው። ይሀንንም በቅርቡ ራሱ በስልጣን ያስቀመጣቸው አባት በአደባባይ የቤተክርስቲያኗ አሰራር ምን ያሕል ብልሹ እንደሆነ ተናግረውታል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገርን የሚያጠፋና ኃይማኖትን የሚያስቀይር ወራሪ ሲመጣ በግንባር ቀደምትነት ሕዝቡን ለአሩና ለእምነቱ እንዲቆም የምትቀሰቅስ ባላደራ ነበረች። አሁን በእኛ ዘመን ግን ይህ ሁሉ ቀርቶ የራሷ ገዳማትና ቤተክርስቲያናት እንካን ሳይቀሩ ሲደፈሩ፣ሲታረሱና ሲፈርሱ ለምን ብሎ ለመጠየቅ እንኳን የማትችል ሆና ተገኘች። ያቺ ቅድስት አገርም በእነ ጻድቁ ተክለኃይማኖት፣በእነ አባ ኢየሱስ ሞዓ፣በእነ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ፣በእነ አባ ሳሙኤል ዘወገግ፣በእነ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወዘተ የተባረከችና የቀናች አገር ለአረብ፣ለቻይናና ለሕንድ ተቸበቸበች። ይህ እጅግ የሚያሳዝን ኢትዮጰያዊነት ብቻ ሳይሆን ክርስትናም ፈጽሞ የጠፋበት ዘመን በመሆኑ የሚያስደምም ነው። ይህም ሁሉ በአገር ውስጥ ሲከናወን ሕዝብ ዝም ያለው በጠብ መንዣ ተይዞ ወይንም ጊዜና ቦታ እስኪገጥምለት ነው እንል ይሆናል። በነጻነት አገር ውስጥ የምንኖር ሰዎች ግን እንዴትና በምን ሕሊና ይሆን ባርነትን መርጠን አገርና ኃይማኖትን እያጠፋ ካለ ቡድን ጋር እንቀላቀል በእርሱም እንመራ እያልን ያበድነው? ? ? ሲሆን ሲሆን በጠመንጃ አፈሙዝ የተያዘውን ወገን ከእስራቱ እንዲፈታ፣ በወያኔ አመራር ስር የወደቀችውን ቤተክርስቲያናችንን ነጻነቷን እንድታገኝ ለማድረግ መነሳት ሲገባን እንዴት ወዶ ዘማች ሆነን እንገኛለን?
ሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በዓለም ላይ ታዋቂ ከሆኑት የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያናት አንዷ በመሆኗ በውጪው ዓለም ያለውን ኢትዮጵያዊ እንደ አገር ቤቱ በመቆጣጠር የእኩይ አላማው ፈጻሚና አስፈጻሚ ለማድረግ የሚንቀሳቀሰው ወያኔ ኢሕአዴግ ኢላማ ውስጥ ከገባች ቆየት ብላለች። ሁሉም በግልጽ እንደሚያውቀው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ በወያኔ ቀጥተኛና የእጅ አዙር አመራር ሰጪነት የሚንቀሳቀስ ነው። ለዛውም መናፍቃን እና አላውያን በሆኑ ሹማምንት መሪዎች! የቤተክርስቲያናችን የሕግ ምንጭ የሆነው ፍትህ መንፈሳዊ /ፍትሐ- ነገሥት/ እንደሚደነግገው ከሆነ እንኳንስ በጵጵስና ደረጃ ያሉ ክርስቲያኖች ይቅርና አንድ ተራ ምእመን እንኳን በመናፍቃን ጉባኤ ላይ ቢገኝ የተወገዘና የተለየ ይሁን ይላል። ዛሬ ግን በተከበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ የኃይማኖቶች ጉዳይ ኃላፊ ተብለው የተሰየሙት ሰው /የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር// መናፍቅና በተለያየ ጊዜ ከጳጳሳት ጋር የሚሰበሰብ ሆኖ ስናየውና ስንሰማው ውስጣችን እጅጉን ያዝናል። ይህም ሁሉ ቀርቶ በፖለቲካው ጣልቃገብነት የተከሰተውን የጳጳሳቱን መለያየትና መወጋገዝ በአንድም ይሁን በሌላም መንገድ ፈትቶ እንደኃይማኖቷ ድንጋጌ በአንድ ዘመን አንድ ፓትርያርክ የሚለው የቤተክርስቲያን ሥርዓት ለማምጣት የተደረገው ውጣ ውረድ መምከን ስናይ በርግጥም የተመረጡትን እስኪያሰት ታአምራትን ያደርጋል የተባለው
ትንቢት እየተፈጸመ እንደሆነ እንረዳለን። የተመረጡ የተባሉ ዛሬ በአባትነት ተሹመው ብጹአን፣ንኡዳን፣ ቅዱሳን እየተባሉ የሚጠሩት ጳጳሳት ናቸውና። እንግዲህ እነኝህ አባቶች በምንኩስና ዘመናቸው አርባቸው ወጥቶ ለቤትክርስቲያንና ለክርስቶስ ወንጌል ሞተናል ብለው ቃል ከገቡ በኋላ ይህ ሁሉ ግፍ በቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጸም ግማሾቹ አባሪ ተባባሪ፣ግማሾቹ ለሕይታቸውና ለደሞዛቸው ፈርተውና ሳስተው ግማሾቹ ደግሞ አላማ አድርገውት ቅድስት አገር ኢትዮጵያንና ንጽሕት ተዋሕዶ እምነትን ሊያጠፋ ከመጣ ኃይል ጋር መሰለፋቸው በርግጥም የትውልድ እርግማን እንዳለ ያሳያል። ራሳቸው ተጣልተው ሳይታረቁ ያሉ አባቶችም እንደምን ሌላውን ሊያስታርቁ ይችላሉ? ለራሱ ሰላም የሌለው ለሌላው ሰላም ሊያስገኝ አይችልም ይለናል ፍትህ መንፈሳዊ የማቴዎስንና የሉቃስን ወንጌል ጠቅሶ። አንቀጽ 5 ቁ. 12 ማቴ.12፥ 30 ሉቃ. 11፥ 23
ስለዚህ ነብዩ በመዝሙሩ ‘ከራስ ጥቅም ይልቅ ልቤን ወደ ምስክርነትህ አዘንብል።’ መዝ.119፥2 እንዳለው በዘመናችን የተፈጠረውን የአገርም ሆነ የቤተክርስቲያን ችግር ለራሳችን ጥቅም ቆመን ሳይሆን በእውነትና በኃይማኖት ሆነን በዘመናችን እንፍታ!! ! ይህም ማለት የተፈጠረው ችግር እንዲስተካከል ይህም በቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን የቀኖና ጥሰት እንዲስተካከል ማድረግ ማለት ነው እንጂ ከተበላሸው አሰራር ወይንም ከተጣሰው ቀኖና ጋር እንተባበር ማለት አይደለም። አሁን የተበላሸው ከተስተካከለ ወደፊትም ይህ አይነት ሕግ የመጣስ ነገር ቢከሰት ተቀባይነት ስለማይኖው ትውልዱም እንደዚሁ ሕገ ወጥነትን እምቢ ማለትን ይማራል፡፡ አባቶቻችን ቅኝ ገዥዎችን እምቢ ብለው፣ ሚሲዮናዊያንን እምቢ ብለው፣ መናፍቃንን እምቢ ብለው፣ አላውያን ነገሥታትን እምቢ ብለው አገርንና ኃይማኖትን እንዳቆዩልን ዛሬም እምቢ ልንል ይገባናል።
በአሁኑ ወቅት በደብራችን በሚኖሶታ ደብረሰላም ቤተክርስቲያን ውስጥ በአንድም በሌላም መንገድ ገብተው ቤተክርስቲያናችንን አገርና ኃይማኖትን ላጠፉ ኃይል አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገውን ሽር ጉድ የሚኔሶታ ምእመናን በአንድ ድምጽ ሆነን ልካችሁን እወቁ ወያኔንም እዛው እለመድክበት ልንል ይገባናል። ቤተክርስቲያናችን ትንሿ ኢትዮጵያችን ምትክ አገራችን ናትና።
የሰላም አምላክ ሰላማችንን ይጠብቅልን! ልቦናቸውንና አዕምሯቸውን ላጡም አስተዋይ ልቦናና አዕምሮ ይስትልን።

ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎች ንብረታችንን የኢትዮጵያ ጉምሩክ እየወሰደብን ነው ሲሉ አማረሩ

0
0

ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንዳስነበበው ህገወጥ ናችሁ ተብለው ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን፤ ለበርካታ አመታት ለፍተን ያፈራነውን ንብረት ይዛችሁ መግባት አትችሉም ተብሎ ተነጥቀናል፡፡ የፍተሻ ሰራተኞች ሻንጣዎቻቸውን በመፈተሽ፣ ሞባይል ከአንድ በላይ ከያዙ ትርፉን በማስቀረት፣ አዳዲስ አልባሳት እና ኤሌክትሮኒክስ ቁሰቁሶች የተወሰኑትን ብቻ በመፍቀድ እና ያመጡትን ወርቆች ግራም በመቀነስ ንብረታቸውን እየወሰዱባቸው እንደሆነ ተመላሾቹ ገልፀዋል፡፡ መሃመድ አባመጫ የተባለ የሳኡዲ ተመላሽ፤ ከሳውዲ ስድስት ሻንጣ ይዞ መምጣቱን ገልፆ፤ ቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ ሲደርስ ግን ከሁለት ሻንጣ በላይ ይዞ መግባት እንደማይችል፣ ከአምስት ሞባይሎችም ሁለቱ ብቻ እነደተፈቀደለት ለአዲስ አድማስ ተናግሯል፡፡ የሳውዲ መንግስት ከአንድ ኪሎ በላይ ወርቅ ይዛችሁ መውጣት አትችሉም የሚል መመሪያ ማሳለፉን የጠቆመው ተመላሹ፤ ንብረቱን እዚያው ጥሎ ለመመለስ መገደዱን ገልጿል፡፡ የሳኡዲ መንግስት እንኳን ከወርቅ በስተቀር ሌላ ንብረታቸውን ሁሉ ይዘው እንዲወጡ መፍቀዱን የገለፀው መሃመድ፤ በአገራቸው ንብረታቸውን እንዳያስገቡ መከልከላቸው እንዳሳዘነው ይናገራል፡፡
neb 7
ኤሌክትሮኒክስና ለቤተሰቦቹ ያመጣውን ልብሶች ቀረጥ ከፍለህ ነው የምትወስደው በመባሉ፣ ለሁለት ቀን በስደት ተመላሾች በተዘጋጀው ድንኳን ውስጥ ያለምንም ፍራሽና ልብስ ተኝቶ ንብረቱን ቢጠብቅም ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል፡፡ “ሳዑዲም እዚህም ሀገራችን ስንደርስ እየበደሉን ያሉት ሃበሾች ናቸው” ያለው መሃመድ፤ መንግስት በሚዲያ በተሟላና በተደላደለ መንገድ እንደሚቀበለን ቢገልፅም እዚህ የጠበቀን ግን ሌላ ነው ሲል ቅሬታውን ገልፆ “ሌላው ቢቀር እስካሁን ተመላሾቹን የሚያመላልሰው እንኳን የሳዑዲ እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት አይደለም” ብሏል፡፡ ከሳኡዲ ካመጣችው ወርቅ ላይ ሃምሳ ግራሙን ብቻ እንደምትወስድ የተነገራት ተኪያ ሙሃመድን ያገኘናት በቁጭት መሬት ላይ እየተንከባለለች ነበር፡፡

ተኪያ እያለቀሰች እንደነገረችን፤ ለ14 ዓመት ሰርታ ከሶስት መቶ ሃምሳ ግራም በላይ ወርቅ እንዳጠራቀመች ገልፃ፤ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከሳውዲ እንድትወጣ ከመገደዷ በፊት ሙሉ ንብረቷን አስቀድማ ብትልክም እስካሁን እንዳልደረሰላት ትናገራለች፡፡ አሁንም፤ ከተመለሰች በኋላ የያዘቻቸውን ሻንጣዎች ለመውሰድ እንዳልቻለች የምትገልፀው ተኪያ፤ በፍተሻ ስም ሰራተኞቹ ሻንጣዋን በርብረው በማየት፣ ያመጣቻቸውን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ሶስት ሞባይሎች መውሰዳቸው ሳይንስ፣ ሶስት መቶ ግራም የሚመዝን የወርቅ ንብረቷን እንዳታስገባ መከልከሏን በጩኸት ትናገራለች፡፡ ለምን ንብረቷን እንደከለከሏት ስትጠይቅም “እናንተ ነጋዴዎች ናችሁ፤ በስደተኞች ስም ያለቀረጥ ንብረት ለማስገባት ትፈልጋላችሁ” በማለት ሰራተኞቹ እንደመለሱላት ገልፃ፤ ጉዳዩን ለአለቆቻቸው ለማመልከት ብትፈልግም የሚያናግራት ሰው አለማግኘቷን ጠቁማለች፡፡ በዚሁ ስፍራ ያገኘናቸው በርካታ ተመላሾች፤ የንብረታቸው ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ይናገራሉ። ንብረታቸውን ሳይዙ ወደቤተሰቦቻቸው ላለመቀላቀል በሚል የተሰበሰቡበት ካምፕ፣ ምንም ለማረፊያ የተመቻቸ አገልግሎት ባለመኖሩ መቸገራቸውንም ገልፀዋል፡፡ መንግስት የሚሰጣቸውን 900 ብር፣ በትራንስፖርትና በስልክ አገልግሎት እንደሚጨርሱ አክለው ተናግረዋል፡፡

tewedros adhanom with returneesበርካቶች በእቃዎቻቸው መታገድ በመበሳጨታቸው ጭቅጭቅና አላስፈላጊ ውዝግብ ውስጥ ለመግባት መገደዳቸውን ተመላሾቹ ይናገራሉ፡፡ “ስንመጣ የሚሰጠንን ሊሴ ፓሴን አይተው ማስተናገድ ሲገባቸው እነሱ ግን ንብረታችንን እየወሰዱብን ነው” በማለት የሚናገሩት ተመላሽ ዜጎቹ፤ “ምናልባትም ንብረት የላቸውም ብለው አስበውን ይሆናል፤ ነገር ግን በርካታ አመታት ስንቆይ መቼም ባዶ እጃችንን አንመጣም” በማለት በምሬት ይናገራሉ፡፡ “ዛሬ እቃችንን የከለከሉን ነገ ምን ተስፋ ይዘን ነው ተደራጅታችሁ ስራ ስሩ ለሚሉን?” የሚሉት እነዚህ ተመላሾች፤ “በመንግስት ላይ አመኔታ የጣልነው ሳውዲ ድረስ በተወካዮቹ አማካኝነት መጥቶ ባናገረን መሰረት ነበር፤ ነገር ግን የተገባልን ቃል ታጥፏል” ይላሉ፡፡ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠቱ እና ለቤተሰብ መርዶ ባለመነገሩ፣ ለሚያውቋቸው ቤተሰቦች መርዶ ለመንገር ጭንቀት ላይ መሆናቸው ሌላ ችግራቸው እንደሆነ የተናገሩት ተመላሾች፤ አሁንም ቢሆን ሳውዲ ላይ ሃበሻዎችን በመኪና እየገጩ መግደል የሳውዲ ፖሊሶች የቀን ተቀን ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ታዲያ በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ አምልጠው የሚመለሱ ዜጐችን ንብረት መቀማት ምን የሚሉት ተግባር እንደሆነ አልገባንም፤ በማለት አማርረዋል-ተመላሾቹ፡፡ ምናልባትም የፖለቲካ ማራመጃ ሊያደርጉን ነው በማለትም ስጋታቸውን አንፀባርቀዋል፡፡

ተመላሾቹ የተሟላ መጠለያ ተዘጋጅቶላችኋል በተባለበት ቦታ ሳይቀር፣ መተኛ ሥፍራ እንኳን እንዳልተዘጋጀ ሲረዱ ተስፋ መቁረጣቸውን እና ንብረታቸውን እንዳያስገቡ ሲከለከሉ፣ ተመልሰው በህገወጥ መንገድ ለመሰደድ ሙከራ መጀመራቸውን ይገልፃሉ፡፡ በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው፤ “ተመላሾቹ ስለንብረት የሚያነሱትን ጥያቄን በተመለከተ፤ እኛ ተመላሾች በሙሉ ንብረት እንደሌላቸው ነው የምናውቀው“ በማለት ተናግረዋል፡፡ አምባሳደሩ አልፎ አልፎ ባዶ እግራቸውን ከሳዑዲ የተመለሱ እንዳሉ ጠቁመው፤ በሳኡዲ መንግስት ጓዛችሁን ይዛችሁ እንዳትወጡ ተከልክላችኋል በመባላቸው፣ መጀመሪያውኑም ንብረት ይዘው ባለመምጣታቸው ነው፤ ብለዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች ከመደበኛ የአየር መንገዱ ተጓዦች እኩል እንደማይስተናገዱና ለብቻቸው ተጠብቀው እንደሚስተናገዱ ገልፀው፤ ምናልባት ከነዚህ ዜጎች ጋር ተቀላቅለው የሚመጡ ሌሎች ሰዎች ስለሚኖሩ እሱን ለማጣራት ንብረታቸው ይፈተሻል እንጂ ማንም የእነሱን ንብረት የሚወስድ እንደሌለ የተናገሩት አምባሳደሩ፤ እንኳን በሀገር ውስጥ የገባ ንብረት፣ ሳዑዲ ያለውንም የላባቸውን ውጤት ለማስመጣት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

የሟቾችን ቁጥር እና ለቤተሰቦቻቸው መርዶ አለመንገርን በተመለከተ አምባሳደሩ በሰጡት ምላሽ፣ አሁን ሙሉ በሙሉ ትኩረታችን በህይወት ያሉ፣ ንብረታቸውን ያጡ እና ጉዳት የደረሰባቸው ላይ ነው፤ ብለዋል፡፡ የሟቾቹን ቁጥር በተመለከተ ግን መንግስት ከገለፀው በኋላ፣ የተፈጠሩ ነገሮች መኖራቸውን አምነው፤ ነገር ግን ቁጥሩ ላይ ተመላሾች የሚሉትና አንዳንድ ሚዲያዎች የሚያወሩት ትክክል ሊሆን ቢችልም የተጣራ ነገር እስካላገኘን ድረስ የሞቱበትን ሁኔታ ለማወቅ ያስቸግራል፤ ብለዋል፡፡ የሳውዲ አየር መንገድ እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመመለሱ ሂደት ምንም አስተዋፅአ ለስደተኞቹ አላደረገም ለተባለው አምባሳደሩ መልስ ሲሰጡ፡- የሳውዲ አውሮፕላን የሚያመላልሰው እራሱ በማባረሩ ምክንያት ነው፤ ወጪውን የሚችለውም እራሱ ነው ብለዋል፡፡

ከሳዑዲ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዝ የነበረው አውሮፕላን በኢትዮጵያዊቷ ነብሰጡር ምጥ የተነሳ ተመልሶ አረፈ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያዊያኑን ጭኖ ከሳዑዲ አረቢያ መካ የተነሳው አውሮፕላን በውስጡ የከጫነት ኢትዮጵያያን መካከል አንዷ ነብሰጡር ምጥ ላይ በመሆኑ አውሮፕላኑ ተመልሶ የሳዑዲ አረቢያ ጠረፍ ላይ እንዲያርፍ መደረጉን አረብ ኒውስ ዘገበ።

አረብኒውስ በድረገጹ እንዳስነበበው አውሮፕላኑ ከሽሜሲ የስደተኞች መጠለያ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን ጭኖ ይጓዝ እንደነበር ገልጾ ነኢማ ከድር እስማኤል የተባለችው ይህችው ኢትዮጵያዊት በምጧ የተነሳ አውሮፕላኑ በጠረፍ ከተማ በጀዛን አውሮፕላን ጣቢያ እንዲያርፍ ከተደረገ በኋላ ወደ ሆስፒታል ተወስዳ ወንድ ልጅ በሰላም መገላገሏን ዘግቧል።

ነኢማ ለዜና ምንጮችትናንት አርብ በሰጠችው ቃል ልጇ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ገልጻለች።

የጀዛን ከተማ ሃገረ ገዢ ንጉስ መሃመድ ነስር ለኢትዮጵያዊቷ ጥሩ የህክምና እርዳታ እንድታገኝ አዘው እንደነበር የዘገበው አረብ ኒውስ በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንም ለወገናቸው ለተደረገው የህክምና እርዳታ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ብሏል።

ማንዴላ ለኢትዮጵያዊነት –ቤዛ ነበሩ! መራራ ስንብት –ከመብራታችን ጋር ….

0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ – 07.12.2013

የእኔ የዕይታዬ ጎራ ከሌሎች ወገኖች ትንሽ ለዬት የሚል ይመስለኛል። የሆነ ሆኖ ውስጤ የሚለኝን ልል ነው … እንዲህ

Nelson Mandelaበዘመነ ወያኔ የተከበሩ ማንዴላ የተስፋዬ ሀገር የሚሏትን ሀገርና ህዝብ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵውያንን ሳያዩ አረፉ። ስለ ምን? ለጥቁሮች የተፈሪነት ፍጹም ልዩ ዓርማ የሆነችውን የሀገራችን ቀደምትነት፤ ያን የአፍሪካዊ የጥቁር ገድል፤ የቅኝ ግዛትን ቀንበር በምኞት ያስቀረ የፈካ ታሪክ በዕብሪትና በበቀል የጣሰው የወያኔ ኃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አልተመቻቸውም ነበርና።

የፍቅር አባት የሆኑት የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ የወያኔ ድርጅት የወሰደውን ኢትዮጵያዊነትን  የማፍረስ ዘመቻ ጠንቅቀው ያወቁ፤ የተገነዘቡ ስለነበር እዬተቃጠሉ አምቀውና መስጥረው በማያዝ ለወያኔ ማንፌስቶ ፊት ሳይሰጡት፤ ጀርባቸውን እንደሰጡት ላይመለሱ አለፉ።

ለማዬት አብዝተው የሚናፍቋት፤ የሚጓጉላት፤ የሚሳሱላት ሀገር ኢትዮጵያ ሆና፤ ግን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድነቷን አጥታ፤ የኢትዮጵያዊነት መግለጫ እንብርት የነበሩት ተቋማት ሁሉ በጠላትንት ተፈርጀው ሲፈርሱ፤ ሲናዱ፤ ዋጋ ሲያጡ እያዩና እዬሰሙ ናፍቆታቸው ፈርሳ ከማዬት እንደናፈቀቻቸው ማሸለብ ነበር ምርጫቸውና ጸጸታቸውን ይኸው በቃል ኪዳናቸው አጸንተው ቋሚ ዓምድ አደረጉት – ልዩ  ባለውለታችን። በቀጥታም ኢትዮጵያዊነትን ለማሰንበት ሆነ ለማቆዬት ያቀረቡት ጥያቄ ነበር። ምላሹ ሬት – ኮሶ ነበረና ውስጣቸው አምርሮ እንደ አዘነ፤ እንደ ተከዘ ለኢትዮጵያዊነት ሰግደው እንደ ተርመጠመጡ መራራ ስንብት እንሆ ሆነ፤

እንደ እኔ የተከበሩት የሰላም መምህር ኔልሰን ማንዴላ በዘመናችን ከማንኛችም በላይ ለኢትዮጵያዊነት የከፈሉት መስዋዕትንት፤ ለሀገራቸው ከከፈሉት መስዋዕትንት ቢዘል አንጂ አያንስም። የአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች መሪዎችና የኢትዮጵያን ፍርሰት ምኞታቸው የነበሩ ዬአደጉ ሀገሮች መሪዎች ሁሉ አዲስ ዴሞክራሲያዊ ወጣት መሪ እያሉ ሀገር አፍራሹን ሄሮድስ መለስን ሲያንቆለባብሱ፤ ለሸሩና ለደባው ሲያሸበሸቡ፤ የምህረት ቀንዲል የሆኑት የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ግን ለኢትዮጵያ አንድነትና ልዑላዊነት በፅናት እንደቆሞ እነሆ አለፉ። ለኢትዮጵያዊነትም በ21ኛው ምዕተ – ዓመት የፓን እፍሪካኒስትንትን ልዑቅነት በተግባር አቅልመው …. ቤዛ ሆኑ። የተከበሩት የነፃነት አርበኛ ኔልሰን ማንዴላ የታሪካችን ጠበቂ፤ ሁነኛ ባለሟል፤ ትንፋሽና ማህደርም ነበሩ … አቅማቸው ኃይል ነበረው። ንጉሥ ዳዊት በምስባኩ „የቤትህ ቅናት በላኝ“ እንዳለው ሁሉ ለነፃነት ዓርማቸው – ለክብራችን፤ ለእናት ሀገራችን ለኢትዮጵያ የወጣላቸው ቀናተኛ ነበሩ ማለት እችላለሁ … ምልክታቸው ነበረችና …

እጅግ የማከብራችሁ የጹሑፌ አንባቢዎች የሀገሬ ልጆች … ውለታው … ሸቀጥ አልነበረም። ውለታው የሚሸጥ የሚለወጥ የከንቱንት ክምር አልነበርም። የእኛነታች ጠንካራ ሚስጢር በውስጣቸው በአጽህኖት የጸነሱ፤ ያረገዙ ግን ሳያገላገሉ ከነህምሙ ያሸለቡ የፍቅር አባት አካላችን ናቸው ኔልሰን ማንዴላ። በዚህ በከፋን ጠቀራማ ዘመን በህማማታችን ሳይለዩን በመንፈስ አብረውን የሆኑ፤ – ሰንደቅዓላማችን የመንፈሳቸው ማህተም ያደረጉ አርማችን ናቸው ኔልሰን።  ክቡርነታቸው … በኢትዮጵያዊነት በተፃራሪነት የቆመ ኃይል ሁሉ መስጥረው በጥርሳቸው እንደነከሱት አረፉ። የነፃነት አርበኛው … ለኢትዮጵያዊነት ተንገበገቡ። የቅኔው ልዑል ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህ በእሳት ወይ አባባ መድብሉ  „የወንድ ልጅ እንባው በሆዱ“ ነው ያለው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ….

እርግጥ ይህ ለተዋህዶ አማንያን የሚስጢረ ሥላሴ ያህል ጥልቅ ሲሆን፤ ኔልሰን በመንፈሳቸው መስጥረው በተግባር ያሳዩና ያሰመሰከሩ ድንቅ የእኛነታችንና የማንነታችን ጠበቃ አባታችን ነበሩ። የተከበሩ ክቡር ኔልሰን ማንዴላ ለእኔ  ትርጉም ነበሩ። ቅኔ ነበሩ። ውስጣቸው የምህረት ልዩ ሰፊ አንባ ነበረው፤ ለወልዮሽ የእኩልነት ማዕድ የማዬት ህልምና ዕውንነት ትግላቸው ለሰው ልጆች ሁሉ ነበር። እርግጥ ነው ይቅርታቸው ንዑድ ሆኖ፤ ግን በውስጣቸው የመሰጠሩትን የሰው ልጆች የእኩልነት፤ የነፃነት፤ የወንድማማችንት መብታዊ ጉላላት የሚያጎላ፤ እንዲያፈራ፤ እንዲለመለምልም በትህትና የሚያደርግ እንጂ የሚያከስም በፍጹም አለነበረም። ለግል ህይወታቸው ያልተጨነቁ አበው ብዙኃን፤ አበው ግፉዓን ነበሩ … ዕንባ አባሽ።

 

በድርጊት የበለጸጉት ክቡር ኔልሰን ማንዴላ ሆነው – መሆንን ለፅናት ሸለሙ። ሀገር መውደድ ምን ማለት እንደሆነ ተንትነውና በትነው እራሳቸውን አሳለፈው በመስጠት አተረፉ። ድንቁ ነገር የትርፉ ዕሴት ርትህን ወልዶ ትውልዱን ከጥፋት በማዳን አዲስ መርህና መንገድ በነፃነት ዜማ ቀይሶ እኩልነትን አበቅለ። ዘረኝነትንም ነቀለ – ከሥሩ። የክብር ምንጩ ሀገርን ከማፍቀር፤ የህይወት ዋጋ ተሽቀዳድሞ ከመክፈል የሚነሳው ከራስ ነውና እንሆ እሳቸው በተግባር ስለ አማረባቸው፤ ፍቅር ካለገደብ ስለተሸለሙ አርያንታቸው ዛሬ ዓለምን በተደሞ አስለቀሰ። የኃያሉ መንግሥት የአሜሪካ ሰንደቅዓለም ዝቅ ብሎ ለበርካታ ቀናት ተውለበለበ። ዓለም በሙሉ በአኃቲ ድምጽ ሀዘኑን ተጋራ ….። ስኬቱ ውጤትን አዝምሮ የጥቁርነትን አንገት አቀና። የኔልሰን  የአርነት እንቅስቃሴ የመከራ ዘመን ያመረተው ፍሬ፤ ብሄራዊነትን ብቻ ሳይሆን ዓለምዓቀፋዊነትን ያጸደቀ – ድንቅ ሐዋርያነት ነበር። ሁለመናው ቆሞ እንሆ ይመሰክራል። ተቋምነቱ ሳይደክመው ይሰብካል በቋሚነት – ለዘለዓለም።

 

በተከበሩ የኔልሰን ማንዴላ ዘመን ምንም የባከነ ጊዜ አልነበረም። ታሪካቸው መከራን አስመችቶ በመቀበል ትእግስትን አበራ፤ የእኩልነት የተጋድሎ ጊዜያቸው በሆደ ሰፊነት ሁሉንም የአሳር ቁልል ያስተናገደ ልዩ ትዕይንት ነበር። ስለሆነም ትርፉ መንፈስ ሆነ። በመሆኑም ጥቁርነት የቀፈፈውን … ሥር የሰደደው ዘረኝነትን አልደፈረም ቢልም አለሰለሰ፤ የከረረውን ትዕቢት አረገበ፤ የዘረንነት በሽተኞችን ፈቅፍቆ ፈወሰ – ልዩ መዳህኒት ነበርውና፤ ተጋድሎውም ትውልዱን በፍቅር አጋባ። ስለሆነም ያ ሁሉ ግፍ ተቀብሮ ብሄራዊ ክብርን ወለደ። መገለሉ ከስሞ ብሄራዊ መገለጫን አዘከረ። ስለሆነም የምልዓቱ ግራሞት ያሰበለ እንዲሆን አደረገ። ማዬት ማማን ነውና መስዋዕትነቱ ጭብጥ ሆነ። ስለሆነም የሀዘኑ ታዳሚዎች ሁሉ ከውስጣቸን አዘን። ብዙም አትኩሮትን የማይለግሱ ሀገሮች እንኳን በሚዲያ የሚሰጡት አስተያዬት ሳዳምጥ ተግባር ምን ያህል የቅዱስ መንፈስ ኃይልና መስህብም እንዳለው ተረዳሁ። ተገነዘብኩ። የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ የላቀ የተግባር ቅዱስ መንፈስ ነበሩ። ስለዚህም ኔልሰን ማንዴላ አለሞቱም አረፉ እንጂ።

 

እኔ እንደማስበው የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ቅንም ነበሩ ብዬ አስባለሁ። አምላካችን ቅኖችን ይወዳልና መስዋዕትነታቸውን በድል ቋጭቶ የዓለምን ልብ በፍቅር እንዲሰግድ እንሆ አደረገ። ደቡብ አፍሪካም ዕድለኛ ነው። ይህን መሰል እግዚአብሄርና የሰው ልጆች የሚወዱት የእርቅ ልዩ የወርቅ ድልድይ፤ የተመረቀ ሙሴ ሰጣቸው። እርግጥነው የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ከእኛዎቹ ቀደምት አርበኞቻችን ጋር የትውፊት ቅብብል አድርገዋል እላለሁ፤ ከዓፄ ቴወድሮሰ፤ ከአፄ የኋንስ ሆነ ከአፄ ሚኒሊክ እንዲሁም ከአፄ ኃይለሥላሴ፤ በተጨማሪም ከመጀመሪያው አፍሪካዊ የሽምቅ ውጊያ „ከጥቁር አንበሳ“ ጋራ የአደራ ውርስ እንደ አደረጉ ይሰማኛል። ያነሳሳቸው፤ የቀሰቀሳቸው ውስጣቸውን ለነፃነት ትግል ተክል እንዲያቆጠቁጥ፤ በጸጋ ያበረከተው ይህ አፍሪካዊ የአርበኝነት፤ የተፈሪነት፤ የመቻል ቅምጥ ጥሪትና ቅርስ ነው ብዬም አምናለሁ። የዛሬን አያድርገውና የነፃነት ትርጉም በኽረ እናት ኢትዮጵያ ክብርት ሀገራችን ነበረችና።

 

እኔ እንደሚሰማኝ የመጀመሪያ የነፃነት ፍለጋ ጽንሰት በኔልሰን ማንዴላ የወጣትነት ዘመን ህሊና የተጠነሰሰው፤ ፊደል የቆተረው ኢትዮጵያ ቅኝ ካለመሆኗ የሚነሳ ይመሰለኛል። ያ … ለእንግሊዞች፤ ለዱርቡሽቶች፤ ለፋሽስቶች ያልተነበረከከ ኢትዮጵያዊነት በመላ አካላታቸውና ደማቸው ውስጥ ቦታ ሰጥቶ ትርጉም መሆኑን ነጥሮ እነሆ ለዓለም አስነበበ …. እላለሁ እኔ ሥርጉተ ….

 

ሄሮድ መለስ ዜናዊ በማንአለብኝንት የገፉት፤ በእብሪት የጠቀጠቁት፤ በግፍ የጨፈለቁት፤ በትዕቢታቸው የደፈጠጡት፤ በበቀል የጨቀጨቁት፤ የናቁትና ያዋርዱት የኢትዮጵያዊነት ቅዱስ መንፈስ ሰንደቅነቱ ወይንም መንበርነቱ በብሄራዊነት ብቻ የተወሰነ አልነበረም።  … ለአህጉራችን ለአፍሪካ ሆነ ለዓለም ፋና ወጊና መሪ እጬጌም ነውና። ይህ ዘመን የሰጣቸው ያደጉ ሀገሮች የሚፈሩት ቢሆንም፤ አሁንም እንደ ሥርጉተ ዕይታ የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ ግን ለኢትዩጵያውያን የተለዬ ፍቅርና አክብሮት ነበራቸው እላለሁ። እርግጥ ቀደም ባላው ጊዜ ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵውያን በመኖሪያ ፈቃድ ዙሪያ የሚያነሱት ነገር ነበር። ነገር ግን ይህ በሌላ ቢሮክራሲያዊ ምክንያት የተበተበ እንጂ ኔልሰን ከልጆቻቸው ለይተው እኛን እንደማያዩን አስባለሁ። እንዲያውም አሁን ከእረፍታቸው በኋላ ደቡብ አፍሪካን ኑሯቸው ያደረጉ ወገኖቻችን ላይ ችግር ይገጥማቸው ይሆን በማለት ታላቅ ስጋት አለበኝ።

 

መቋጫ

 

ሰማዕቱ፤ መምህሩ፤ ሐዋርያውና ሰባኪው ቅዱስ ጳውሎስ …….. ወደ ቆላስያስ በላከው በአንደኛቱ መልዕክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር  ከ11 እስከ 12 „ .. ይህንን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል፡ ማለትን ተምሬያለሁና። መዋረድንም፡ አውቃለሁ፡ መብዛትንም፡ አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ፡ ነገር በነገረም፡ ሁሉ መጥገብንና መራብንም፡ መብዛትንና መጉደልን ተምሬያለሁና“ ይላል …

 

ሥልጣን ትወደዳላች፤ ክብርም ከሁሉ በላይ ትፈቀራለች ፤  የሥልጣን ዘመናቸውን ሊደግሙ ቢፈልጉ የሚያግዳቸው አልነበርም። እሳቸው ግን አላደረጉትም። ከዚህም አንጻር ኔልሰን ማዴላ ዬይበቃኛልም ልዑል ነበሩ እንደ መምህሩ ቅዱስ ጳውሎስ ….። በሌላ በኩል የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ፤ በቀልን ያሸነፉና የረቱ የአንደበተ – እግዚአብሄር ሰማዕትም ናቸው። የፈጣሪያቸውን ፈለግም የተከተሉ ማህሪ። ዓለምን የሚካልለው ዝቀሽ ተምክሮና ብቃታቸው ደግሞ ከመከራቸው ፈቅደው የተቀለቡ ስለሆኑ የነፃነት ብርቅዬ ትምህርት ቤት ነበሩ።

 

ኔልሰን በዬትኛውም አጋጣሚ በሚዲያ ሲመጡልኝ ሁሉ ፊታቸው ፈክቶ ውስጣቸውን ፈቅደው በፍቅር እንደ አስጎበኙን …. ተሰናበትን።  ገፃቸው አዘውትሮ በትጋት አስተማረን፤ በጽናት ባትለው ዘመኑን በሥልት በፍቅር ገሩት። ምህንድስናቸው  ሰባኪ … ትንግርትን መስካሪ ነበር፤ ዕውነትንም …. አፍላቂ።  የምዕተ – ዓመቱ የነፃነት ሊቅ፤ ትውልድ

ሊተካቸው የማይችሉ ዕንቋችን ነበሩ። ፅናትን በልጅነት ሸምተው ጽናትን ለሁላችን በቅንነት አቅንተው፤ ፅናትን አንግሠው ከፅናታቸው ጋር በጽናት – ድንግልና  …ትምህርት ቤት ሆነው አረፉ። በወጣትንት በዕድሜ መጥ የሆኑትን ፈተናዎች ሁሉ አንበርክከው ከወርቅ በተሰራ ብርታታቸው የነፃነት ወተት በድንበር አልቦሽ ቀለቡ።

 

የዘመናችን … የኢትዮጵያዊነት መሪዎች ትምርት ቤቱን በመሆን ካዘመሩት ማሳው ለፍሬ ይበቃል። ውዳሴ መልካም ቢሆንም፤ በመሆን ካልቀለመ … መዘክር ብቻ ሆኖ ይቀራል። …. እራሳቸውን ሳይዋሱ፤ ሳይበደሩ፤ እንደ ተፈጥሯቸው ሆነው ከተለዩን የአፍሪካ ብርኃን የኛዎቹም ዓለም ዓቀፍ ተቀባይነትን በመስዋዕትንት ይሸመቱ ዘንድ በርከክ ብዬ እለምናቸዋለሁ …. አምላካችንም ይርዳን። …. ካለጠበቂ፤  ካለአጃቢ የሚሄድ የጓደኛ መሪ …. መከፋቱ – መካፋታችን፤ ህምሙ – ህመማችን፤ ሞቱ – ሞታችን የሚሆን እረኛ አምላካችን እዬሱስ ክርስቶስ መርቆ ይሰጠን። አሜን! የናፈቀኝ እሱ ነውና ….

 

ጌጣችና ውዳችን የተከበሩ ኔልሰን ማንዴላ መከራዎትን በምድር ጨርሰውታል። ጽድቅ ለዕልፎች መቃጠል ነበርና አድርገውታል። …. መልካም የጽድቅ ጉዞና የእረፍትም  ጊዜ። ለነፃነት ቤተኞች ሁሉ መጽናነትን እመኛለሁ። ከድርጊት ለተማርነው መልካም የኔልሰን ተመክሮ ውስጣችነን ሳንሸፍን ወይንም ሳንከናንብ ገልጠን በንጽህና እንፍቀድለት – እላለሁ።

 

 

አራት ዓይናማው መንገዳችን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 


ይድረስ ለክቡር አቶ ዘውዴ ረታ እና ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት ቦታ ሁሉ ።

0
0

በ ታደለ ብጡል ክብረት (ኢ/ር)

“የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት” በሚል ርዕስ  አቶ ዘውዴ ረታ ያሳተሙትን መጽሐፍ በጥሞና አንብቤዋለሁ። መጽሐፉ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የተፈጸሙትን እውነተኛ ታሪክ በሙሉ የካተተ ነው ባልልም፤በውስጡ ያሉት በርካታ ዘገባዎች ከዚህ በፊት በሌሎች መጽሐፎች ውስጥ ተጽፈው ያልነበሩ ናቸው። በተለይም ክቡር ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስን፤ ክቡር አቶ ይልማ ደሬሳን፤ ክቡራን አቶ አክሊሉ እና አቶ መኮንን ሀብተወልድን በተመለከተ የተጻፈው፤እነዚህን የኢትዮጵያ ብርቅ ልጆች ስም ህያው የሚያደርግ ስለሆነ ለደራሲው ያለኝን አድናቆት በከፍተኛ አክብሮት እገልጻለሁ፡፡

ይሁን እንጂ “ይድረስ ለአንባቢዎቼ” በሚለው ርእስ ስር ደራሲው በአቀረቡት ዘገባ ውስጥ “ይህ ጎድሏል፤ ይህ ቀርቷል የሚባሉ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እና እንደሚኖሩ አውቃለሁ” ብለው አስተያየት እንድንሰጥ በር ከፍተዋል። እኔ ደግሞ “ጎድሏል፤ ቀርቷል” ከሚለው በተጨማሪ አቶ ዘውዴ ረታ የተሳሳቱትን ለማረም ይጠቅማቸዋል ብዬ ያሰብኩትን እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

በመጀመሪያ የማነሳው “የቫቲካን አቋም በኢትዮጵያ ጉዳይ” ብለው ስለአቀረቡት ዘገባ ነው። በዚህ ርእስ ስር፤ እሳቸው የጻፉትን እዚህ ላይ ለመድገም አልፈልግም። ዋናው ቁም ነገር፤ “የቫቲካን አቋም በኢትዮጵያ ጉዳይ” የሚል ርእስ ሰጥተው ከጻፉ ዘንዳ፤ የቫቲካንን አቋም ይገልጻሉ ብዬ ስጠብቅ፤እሳቸው ሸወድ አድርገው ወደ ፒዮስ 11ኛ አሉባልታ ገብተዋል። ለምን ይህን ለማድረግ አንደፈለጉ ስላልገባኝ፤የእኔን እይታ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

አንድ የበላይ የሆነ የሃይማኖት አባት ወይም የአገር መሪ፤ከበታቹ ያሉት ሰዎች ለሚፈጽሙት ተግባራት ሁሉ ተወዳሽም፤ተወቃሽም እደንደሚሀን እሳቸው ሳያውቁ ይቀራሉ የሚል እምነት የለኝም። ይህ ሐቅ ተቀባይነት ያለው የአስተዳደር ጽንፈ ሐሳብ በመሆኑ፤የቫቲካን ካርዲናሎች (ጳጳሶች) በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸሙት በደል ዋና ተጠያቂ፡ የቫቲካን የበላይ መሪ ፒዩስ 11ኛ ናቸው፡፡ ይህን ሐቅ አቶ ዘውዴ ረታ መካድ አልነበረባቸውም። በፒዩስ 11ኛ ስር ያሉት ካርዲናሎች የፈጸሟቸውን ተግባራት አቶ ዘውዴ እንዲያስታውሱት፤ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር አቀርባለሁ፡፡

አቶ ዘውዴ ረታ “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት” በሚል ረእስ በጻፉት መጽሐፍ ገጽ  301 ላይ “የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ኢደልፎንስ ሹስተር፤የፋሸስት መንግሥት ደጋፊነታቸውን በግልጽ አስረድተዋል” ብለዋል። በመቀጠልም “- – - – የጣሊያን መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር  የባርነትን አገዛዝ ሰንሰለት በመጣስ፤የካቶሊክን ተልዕኮ የተቀበለ ነው – - ” ብለው ከጻፉ  በኋላ፤ፒዩስ 11ኛን ለመደገፍ የተነሱበትን ዓላማ ለማሳካት ሲሉ “የሚላኖ ሊቀ ጳጳስ በተናገሩት፤ፒዩስ 11ኛ እጅግ ማዘናቸውን ገልጠዋል” በማለት ነገሩን ለማርገብ ሞክረዋል። በትልቅ ሥልጣን ላይ ያለው ካርዲናል ኢደልፎንስ ሹስተር፤የኢትዮጵያን ነፃነት የሚያሳጣ እና  ክብሯን የሚነካ ድርጊት በመፈፀሙ፤ቢያንስ አሰተዳደራዊ እርምጃ አለመውሰዳቸው ፒዩስ 11ኛ የድርጊቱ ተባባሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንጂ፤እሳቸውን ከበደሉ ነፃ የሚያደርግ አይደለም።

ከዚህ ዝቅ ብሎ የሚታየው ፎተግራፍ የሚያሳየው “የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ኢደልፎንስ”    ሕዝብ በተሰበሰበበት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በር ላይ ቆሞ፤በልበ ሙሉነት የፋሸስትን መንግሥት የሚደግፍ ንግግር ሲያደርግ ነው። በዚህ ፎተግራፍ ላይ ያሉት አብዛኛዎቹ ሰዎች ካርዲናል ሹስተር የሚናገረውን የሚያዳምጡ ቢሆኑም፡አንድ ግርምት የፈጠረበት ሰው አፉን ይዞ እናያለን።

andinet11111

ካርዲናል ሹስተር የፋሽስት ደጋፊነቱን ሲናገር

ፒዩስ 11ኛ “ፍትሐዊ ባልሆነ ጦርነት አናምንም” ከማለት ውጭ የኢትዮጵያን መብት ለማስጠበቅ ምን የተናገሩት ወይም የፈፀሙት ተግባር አለ

የጣሊያን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ በሚሳፈርበት ወቅት፤ መድፎቹንና ሌሎች አውዳሚ መሣሪያዎቹን የባረከው፣ የቫቲካን ካርዲናል ፎቶግራፍ ከዚህ በታች ያለው ነው።

andinet111111

የኒው ዮርክ ታይምስ እ.አ.አ. የካቲት 13 ቀን 1937 ባወጣው ህትመት “ዛሬ ማለዳ ላይ ጳጳሱ ለጣሊያን ንጉሥ እና ለኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፣ ለቪክቶር ኢማኑኤል፣ ብለው ቅዱስ ቡራኪያቸውን በመስጠት፣ ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ላይ ስላላት ሉዓላዊነት እውቅናቸውን ገልጸዋል” ብሏል።  የእንግሊዝኛውን ጽሁፍ ከዚህ በታች አቀርባለሁ።

(Earlier today the Pontiff had given his recognition of Italian sovereignty over Ethiopia by bestowing benediction upon Victor Emmanuel as King of Italy and Emperor of Ethiopia)

  1. የፋሽስት ኢጣሊያ ወታደሮች መረብን ተሻግረው፣ ወደ መሐል አገር ለመገስገስ ሲሰለፉ ቡራኬ ሲሰጥ በፊልም የተቀዳው በእጄ ይገኛል።
  2. እምነተ ቢስና የቀኖና አፈንጋጭ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማካሄዴ፤የካቶሊክን እምነት ለማስፋፋት በር ስለሚከፍት፤ የተቀደሰ ጦርነት ነው በማለት የቶራኖ ሊቀ ጳጳስ ተናግሯል፡፡ “The war against Ethiopia should be considered as a holy war, a crusade to open Ethiopia, a country of infidels  and Schismatics to the Expansion of the Catholic Faith.”  (By OCP on Mach 12, 2010)
  3. የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ሹስተር ከተናገሩት ቀደም ሲል ከገለጽሁት በተጨማሪ “የጣሊያን ፋሽስት ባንዲራ፤በአሁኑ ጊዜ የክርስቶስን መስቀል በኢትዮጵያ ውስጥ በድል አድራጊነት  ባሮችን ነፃ ለማውጣትና ለእኛም የሚስዮን ፕሮፓጋንዳ  መንገድ እየከፈተ ነው” ብለዋል።

The Archbishop of Milan, cardinal Schuster, went farther and did all he could to bestow upon the Abyssinian War, the nature of a Holy Crusade. “The Italian (Fascist Flag) is at the moment bringing in triumph the Cross of Christ in Ethiopia to free the road for the emancipation of the slaves, opening it at the same time to our missionary propaganda.” (By T.L. Gardini, Towards New Italy.)

ከዚያ በኋላ የሚላኖው ራሱ ሊቀጳጳሱ አንድ ታንክ ላይ ዘልሎ ወጣና ረጋ ብሎ እዚያ የተሰበሰቡትን የፋሽስት ጀሌዎች ባረከ።  የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ሳለቬሚኒ እንደገለጸው፣ ቢያንስ ሰባት ካርዲናሎች፣ 29 ሊቀ ጳጳሶች፣ 61 ጳጳሶች ወዲያውኑ ጦርነቱን ደግፈዋል።  የቫቲካን ድጋፍ በዚህ ብቻ ሳያበቃ፣ በውጭ አገርም ጦርነቱን ደግፈዋል። በየአገሩ ያሉት የካቶሊክ ጋዜጦች በሙሉ እንደ እንግሊዝ አገርና አሜሪካም ያሉት ሳይቀሩ ኢጣሊያን ደግፈዋል።

እ.አ.አ. በ1949 አቭሮ ማንሃታን በጻፈው መጽሀፍ እንደገለጸው “ፓዮስ 11ኛ ለሙሶሊኒ ትልቅ ክብር የሚሰጡ መሆናቸው ይታወቃል።  በአጠቃላይ፣ የጣሊያን ቀሳውስት በሙሉ፣ የፋሽስቶቹ ወገን መሆናቸውን በቀላሉ ለመረዳት የሚቻለው፣ የፋሽዝም መርሆ፣ ብሄርተኛነት፣ ፈላጭ ቆራጭና ሕዝባዊነትን የሚቃወም አስተዳደር መሆኑ ነው” ይላል።  በእንግሊዝኛው የተጻፈው እንዲህ ይላል።

(Pope Pius XI is credited with much admiration for Mussolini that the Italian Clergy as a whole are pro-Fascist is easy to understand, seing that Fascism is a nationalist, authoritarian, anti-Socialist Force”.) Avro Manhattan 1949.

ሀቁ ይህ ሆኖ እያለ አቶ ዘውዴ ረታ ደግሞ “- – - የዓለም የካቶሊኮች አባት (ፓዮስ 11ኛ ማለታቸው ነው) ከፋሽስቱ ዲሬክተር መሪ ተጣልተው ከባድ ችግር ላይ ከመውደቅ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ዓይነት ፍትሕን የተመረኮዘ አስተያየት ከመስጠት ታግደው መኖር የሚሻል መሆኑ ታያቸው” ሲሉ መስክረዋል።   ይሄ እንግዲህ አቶ ዘውዴ ረታ ሽንጣቸውን ገትረው የሚሟገቱላቸው የካቶሊኮች አባት፣ ፓዮስ 11ኛ፣ ለፍትሕ አለመቆማቸው በራሳቸው አንደበት ገለጹት።  ሌላው የፒዩስ 11ኛ ጥፋት፣ የራሳቸው ካርዲናሎች ከፋሽስቱ መሪ ሙሶሊኒ ጎን ቁመው ወረራውን ከፍ ብዬ በማስረጃ እንዳቀረብኩት፣ የጦር መሣሪያዎች ሲባርኩና ፋሽስቶችንም ሲያወድሱ፣ እነዚህን የቫቲካን ባለሥልጣናት ላይ የመገሰጽም ይሁን የማገድ እርምጃ አለመውሰዳቸው ነው።

 

ክቡራን አንባቢያን

ሌላም ላክልበት።  ሙሶሊኒ እና ጭፍራዎቹ ኢትዮጵያን በመውረር የፈጸሙት በደል እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ለማስታወስ ያህል፣ ጥቂቶቹን ከዚህ በታች አቀርባለሁ።

  1. የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር

2,000

  1. የተቃጠሉ ቤቶች ቁጥር

525,000

  1. በጦርነት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር

275,000

  1. በአምስት ዓመት የተገደሉ አርበኞች ቁጥር-

78,500

  1. ተማርከው የተገደሉ አርበኞች ቁጥር `

24,000

  1. በአምስት ዓመት ውስጥ የተገደሉ ሴቶችና ሕፃናት ቁጥር

17,800

  1. ታስረው የሞቱ ሰዎች ቁጥር`

35,000

  1. በስደትና በረሀብ የሞቱ ሰዎች ቁጥር

300,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ የቀንድ ከብቶች ቁጥር

5,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ በጎችና ፍየሎች ቁጥር

7,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ ፈረስና በቅሎዎች ቁጥር

1,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ ግመሎች ቁጥር `

700,000

 

ከላይ ከተዘረዘረው በተጨማሪ፤ለዚህ ሁሉ እልቂት መሪና ኃላፊ የሆነውን ጀነራል ግራዚያኒን ለመግደል ሞገስ አስገዶምና አብረሃ ደቦጭ ባደረጉት ሙከራ ሰበብ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እ.አ.አ. ከየካቲት 12 እስከ 15 1937 ድረስ ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ 30,000 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ በእነዚሁ ቀናት ውስጥ ሞገስ አስገዶምንና አብርሀም ደቦጭን ደብቀዋል በሚል ሰበብ ደብረሊባኖስ የነበሩትን ከ300 እስከ 500 የሚደርሱ መነኩሴዎችና ካሕናት ተረሽነዋል።  አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል፣ ሕዝቡ ለፋሽስት መንግሥት እንዲገዛ ስበኩ ሲባሉ አሻፈረኝ በማለታቸው በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

ይህን ሁሉ የሰው እልቂት፣ እንዲሁም የንብረት መውደም የሚያውቁት የቫቲካኑ መሪ ፓዩስ 11ኛ በዝምታ ማለፋቸው ይታወቃል።  አቶ ዘውዴ ረታ ይህን ሐቅ ወደ ጎን ትተው ፓዩስ 11ኛ የዓለም ነርሶችን ሲቀበሉ “በመንግሥታት ግንኙነት መሀከል የሚፈጠር ማናቸውም አለመግባባት – - – በሰላም መንገድ መፈታት ያለበት መሆኑን በጥብቅ ካሳሰቡ በኋላ – - -” በሚል ቃል ለማስረጃነት ለማቅረብ ሞክረዋል። ይህን መሰል አነጋገር፣ እንኳን በከፍተኛ ሥልጣን ያለ ሰው ይቅርና ማንም ተራ ሰው ሊናገረው የሚችል አባባል አለመሆኑን አቶ ዘውዴ ረታ የሚገነዘቡት ይመስለኛል።  በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር ያሉት ጳጳሶች እና ካርዲናሎች ተጠሪነታቸው ለፓዩስ 11ኛ በመሆኑ እሳቸውን ከተወቃሽነት ሊያድናቸው አይችልም።

የዓለምን ሰላም ፈላጊ የሆኑ ሁሉ፣ የፋሽስቶች መሪና ጭፍሮቹ በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ግፍ አውግዘዋል። ሐቁ ይህ ሆኖ እያለ፣ አቶ ዘውዴ ረታ የቫቲካኑን መሪ ፓዩስ 11ኛ ከደሙ ንጹህ ናቸው ብለው ለመደገፍ መነሳሳታቸው እጅግ የሚያሳዝን ጉዳይ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

የናዚ መሪ የነበረው ሂትለር፣ አይሁዳውያንን በጨፈጨፈ ጊዜ ዝምታን መርጣ የነበረችው ቫቲካን፣ ጦርነቱ ካለቀ በኋላ፣ ከአንዴም ሁለት ጊዜ፣ አይሁዳውያንን ይቅርታ ጠይቃለች። ፋሽስቶች በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸሙት ግፍ ግን ቫቲካን እስከ ዛሬ ምንም ዓይነት የመጸጸት እርምጃ አልወሰደችም።  ስለዚህ፣ ዛሬ በሥልጣን ላይ ያሉት ፓፓ ኢትዮጵያን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው የምንል ብዙ ኢትዮጵያውያን አለን።

ውድ አንባቢያን

ከዚህ ከፍ ብሎ የተጻፈው ቫቲካንን በተመለከተ ያለው ጉዳይ ብቻ ነው። “የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት” በሚለው መጽሀፍ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ግድፈቶች ልጠቁማችሁ። አቶ ዘውዴ ረታ ስለ ሙሶሊኒ አስተዳደግ፣ ጠባይ እና ተግባራት ብዙ ብለዋል።  ግን ይህ ትረካ እሳቸው ከሰጡት ርእስ አኳያ ሲታይ ምን ጠቀሜታ አለው? ይልቁንስ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ አቤት በማለት ከአገር ቢወጡም፣ ለረጅም ጊዜ እንግሊዝ አገር እንዲቆዩ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ስላደረጉት አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሼቱ ጠባይና ተግባራት ቢጽፉ ጥሩ ነበር።  ከሁሉም የሚገርመው የሲልቪያ ፓንክረስት በጥቂቱም ቢሆን መጻፋቸው ነው።

ሲልቪያ ፓንክረስት ስለ ኢትዮጵያ ልትጽፍ የቻለችው ከ1927 እስከ 1931 ዓ.ም. ድረስ በሎንዶን የኢትዮጵያ ሙሉ ባለ ሥልጣን ሚንስቴር በነበሩት አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ድጋፍና ቡራኬ መሆኑን “የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሼቱ የሕይወት ታሪክ፣ ከታደለ ብጡል ክብረት” የሚባለውን መጽሐፍ ቢያነቡ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎች ያገኙ ነበር።

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንግሊዝ አገር ሲደርሱ፤ አንድም የእንግሊዝ መንግሥት ባለሥልጣን የክብር አቀባበል አላደረገላቸውም። ከመርከብ ከወረዱ በኋላ የተቀበሏቸው የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሸቱ የግል ወዳጆች ናቸው።  ይህንን ሁኔታ የሚያሳየው ፎተግራፍ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።

andinet1111

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መርከብ ውሰጥ ገብተው የተቀበላቸው አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሸቱ መሆናቸውን የሚያሳየው ፎቶ

ከ1927 እስከ 1931 ዓ.ም. ድረስ በአወሮፓ፤ በአሜሪካ እና በሕንድ የብዙሃን መገናኛዎች፤ በጽሑፍ እና በአካል ተገኝተው፤ፋሽስት ሙሶሊኒ ኢትዮጵያን በግፍ እንደወረረ፤ ሕዝቡን እንዳሰቃየና ንብረትን እንዳወደመ በሰፊው ገልፀዋል። እንኳን እሳቸው፤ ሕፃናት ልጆቸቸው ዳዊትና ዮሐንስ ሳይቀሩ በአደባባይ ላይ ቆመው ስለ ወረራው ያላቸውን ኀዘኔታ ገልጸዋል። አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እንደ ዴል ቫዩ ያሉ ሰዎች በጦር ሜዳ ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መልምለው ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።

andinet11

የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ወዳጆች ወደቡ ድረስ ሄደው ንጉሠ ነገሥቱን ሲቀበሉ

 

andinet111

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ስለ ሥራ ጉዳይ ሲወያዩ

አቶ ዘውዴ ረታ ይህን ሁሉ ታሪክ አያውቁም ነበር ለማለት አልደፍርም። ሆን ብለው የሸሹት ጉዳይ ነውም አልልም። ግርምት እንደፈጠረብኝ ግን አልክድም

ጽሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት አንዳንድ ነገር ላክልበት፡፡

  1. በቅርቡ ከመገናኛ አውታሮች እንደ ተረዳነው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸመው ግፍ እና አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ከሰላሳ ሺህ በላይ ሰዎች ላስገደለው ለጀነራል ግራዚያኒ፣ አፊሌ በሚባል ትንሽ ከተማ ውስጥ አንድ የመታሰቢያ ሙዚየምና ሐውልት ጭምር ተሠርቷል። ሐውልቱ በተመረቀ ዕለት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካርዲናል በሥፍራው ተገኝተው ቡራኬ መስጠታቸውም ተነግሯል። ይህ ተግባር የሚጠቁመው፣ ዛሬም ቢሆን ቫቲካን ለፋሽስቶች እንጂ ለተበዳይዋ ኢትዮጵያ መብት አለመቆማቸውን ነው።  ስለዚህ የአሁኑ የሮማ ጳጳስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ ነው።
  2. ለፋሽስቱ ጨፍጫፊ ጀነራል ግራዚያኒ አፊሌ ከተማ የቆመው ሐውልት እንዲፈርስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑት ጳጳስ የጣሊያንን መንግሥት መጠየቅ አለባቸው የሚል ጥያቄ ማቅረብ ተገቢ ነው።
  3. ኢጣልያ ሊቢያ ውስጥ ለፈጸመችው ግፍ ካሳ የከፈለች መሆኗ ይታወቃል። ፋሺስት ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ውስጥ የፈጸመችው ሊቢያ ውስጥ ከፈጸመችው የማይተናነስ በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ካሳ እንድትከፍል መጠየቅም ትክክል ነው።
  4. አቶ ዘውዴ ረታ የቀዳማዊ  ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በሚለው መጽሀፍ ውስጥ ፒዩስ 11ኛን በመደገፍ ከጻፉት በተጨማሪ፣ ታኅሳሥ 7 ቀን 2005 በሪፖርተር ጋዜጣም አውጥተውታል።  ይህን ለማድረግ የተነሱበት ዓላማ ባይገባኝም አካሄዳቸው፣ በስተጀርባው አንድ ድብቅ ዓላማ ያለው አስመስሎባቸዋል።

እንደ እኔ አስተሳሰብ፣ ይህ ድርጊታቸው ትክክል እንዳልነበረ አምነው በመቀበል፣ አቋማቸውን እንዲያስተካክሉና የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ቢጠይቁ ጥሩ ነው እላለሁ።

ታደለ ብጡል ክብረት (ኢ/ር)

ሞባይል፡  00911 23 24 43

ፖ.ሣ. ቁጥር 5510

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በውሃ እጥረት እስረኞች እየተሰቃዩ መሆኑ ተገለፀ

0
0

ከምኒልክ ሳልሳዊ

kilintoበቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙ ቁጥራቸው ወደ 2500 የሚጠጉ ታሳሪዎች & የማረሚያ ቤቱን ጠባቂ ፖሊሶች በውሃ እጥረት ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡

በማረሚያ ቤቱ በተፈጠረው የውሃ እጥረት ምክንያት ለምንም አይነት አገልግሎት የሚሆን ውሃ መጥፋቱ ተሰምቷል፡፤ ይህ የውሃ እጥረት የማረሚያ ቤቱን ጠባቂ ፖሊሶችን ሳይቀር ችግር ውስጥ እንደከተታቸው እየተገለጸ ነው፡፡

ይህንን ከባድ ችግር ለመፍታት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር እስካሁን ምንም እያደረገ አለመሆኑ ተገልፆል፡፡ ውሃ ለሰው ልጅ ለመኖር ወሳኝ ግብአት እንደሆነ እየታወቀ ከ2500 በላይ ታሳሪዎች ባሉበት ማረሚያ ቤት በውሃ እጥረት ምክንያት ታሳሪዎች በውሀ እጥረት እንዲሰቃዩ ማድረግ ኢ ሰብአዊ ድርጊት መሆኑ እየተገለጸ ነው::
ማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ከ 2500 በላይ እስረኞችን ሂወት ሊታደግ እንደሚገባ መልዕክታችን ነው፡፡

በአዲስ አበባ ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ደርቷል

0
0

የትላልቅ ድርጅቶች ፀሃፊዎች፣ ሞዴሎችና ተዋናዮች አሉበት
ድንግልናን በ10ሺ ብር የሚያሻሽጡ ደላሎች ሞልተዋል
የከተማዋ ቱባ ባለሃብቶች “የአገልግሎቱ” ተጠቃሚዎች ናቸው

ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተገኘ

ethiopia wosib
ሲኤምሲ ሣሚት ማዞሪያ አካባቢ ካሉት ዘመናዊ ቪላ ቤቶች በአንደኛው 12ሺ ብር ወርሃዊ ኪራይ እየከፈለች ትኖራለች፡፡ የምታሽከረክረው ኤክስኪዩቲቭ ቶዮታ፣ በየዕለቱ የምትቀያይራቸው እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው አልባሳቶቿና በየመዝናኛ ሥፍራው የምትመዘው ረብጣ ብር የተንደላቀቀ ኑሮ እንደምትመራ ይመሰክራሉ፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናትና መዲናችን አለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በምናስተናግድበት ጊዜያት እሷን ፈልጐ ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡
ቦሌ ፍሬንድሽፕ ሕንፃ ላይ በከፈተችው ቡቲክ የምታገኘው ገቢ ይሄን ያህል ሊያዝናናት እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ ገቢ ወጪዋን አጥብቃ የማትቆጣጠርበትን ይህንኑ ቡቲኳን ታናሽ እህቷ ትውልበታለች፡፡ እሷም አልፎ አልፎ “ሥራ” በማይኖራት ጊዜ ብቅ እያለች ትጐበኘዋለች፡፡ ታናሽ እህቷ ቤተሰቡን ሁሉ ቀጥ አድርጋ የምታስተዳድረው እህቷ፤ ስለምትሰራው ምስጢራዊ ሥራ አንዳችም የምታውቀው ነገር ያለ አይመስልም፡፡ እሷ የምታውቀው ከተለያዩ የውጪ አገር ሰዎች ጋር የአየር ባየር ንግድ እንደምታጧጡፍና በየጊዜው ወደተለያዩ አገራት ለሥራ ጉዳይ እንደምትመላለስ ብቻ ነው። ሥራዋ የግል ሚስጢሯ ብቻ ሆኖ እንዲኖር የምትፈልገው ህሊና (ስሟ ለዚህ ጽሑፍ የተቀየረ) ይህንን የእህቷን እምነት አጥብቃ ትፈልገዋለች። በተለያዩ የመዝናኛ ሥፍራዎች ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር ደንበኞቿ ጋር እየከረመች በመጣች ቁጥር ለእህቷ የተለያዩ ቸኮሌቶችና ስጦታዎችን እየያዘችላት መምጣቷ የእህቷን እምነት አጠናክሮላታል፡፡
እሷ “ቢዝነስ” ብላ የገባችበት ህይወት ገቢ፣ እህቷ ቀኑን ሙሉ ተገትራ ከምትውልበት ቡቲክ ገቢ ጋር ሊወዳደር እንደማይችል ስለሚገባት “ሥራውን” አጥብቃ መያዙን ትፈልገዋለች፡፡ የንግድ ፍቃድ እድሣት፣ ቫት ምዝገባ፣ ሪሲት ማሽን፣ ቀረጥና ታክስ የሚሉ ዝባዝንኬዎች የሌሉበት፣ “ራስን እያስደሰቱ ሌሎችን በማዝናናት” በቀን የሚገኝ ረብጣ ብር ከቡቲኳ ወርሃዊ ገቢ በእጅጉ ይልቃል። ተፈጥሮ ያደላትን ውበትና ማራኪ ቁመናዋን ለገበያ እያቀረቡ በተሻለ ገንዘብ ለመሸጥና ጠቀም ያለ የኮሚሽን ገንዘብ ለመቀበል አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ደላላ ደንበኞች አሏት፡፡ ለዚህ ተግባር ብቻ የምትጠቀምበት የሞባይል ስልኳ ሲጮህ “ሥራ” እንደተገኘ እርግጠኛ ትሆናለች። ቅያሬ ልብሶችን የምትይዘበትና ሁሌም ለጉዞ ዝግጁ የምታደርገውን ቦርሣዋን አንጠልጥላ ውልቅ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ወደ ሥራ የምትንቀሳቀሰው በደላሎቹ መኪና ነው። ደላላው እሷን ካለችበት ወስዶ ወደምትፈለግበት፣ ሥራዋን ስትጨርስ ደግሞ ወደነበረችበት የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡ የኮሚሽን ክፍያው እነዚህን አገልግሎቶች ያካተተ ነው፡፡ ህሊና ይህንን ህይወት ላለፉት አራት አመታት ኖራበታለች። ከዚህ ህይወት ስለመውጣትና ቢዝነሱን ስለመተው ለአፍታም አስባ አታውቅም፡፡
ባላት ትርፍ ሰዓት ሁሉ ራሷን እጅግ አድርጋ መጠበቅ፣ ጂም መሥራት፣ ሳውና፣ ስቲምና ማሣጅ በየጊዜው መግባት ታዘወትራለች፡፡ ውበቷንና ጥሩ ቁመናዋን ጠብቃ ለማቆየት ማድረግ የሚገባትን ሁሉ ከማድረግ ወደኋላ አትልም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ለዚህ ሁሉ አዱኛ ያበቃት እሱ በመሆኑ የሚፈልገውን ሁሉ ማድረግ እንዳለበት ታምናለች፡፡ ይህ የህሊና ህይወት የብዙ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ህይወት እየሆነ ከመጣ ሰነባብቷል፡፡ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተጧጧፈ የመጣውን ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ የተቀላቀሉ የከተማችን ወጣት ሴቶች የትላልቅ ድርጅቶች ኤክስኪዩቲቭ ፀሐፊዎች፣ የሽያጭ ሰራተኞች፣ ሞዴሎች፣ የፊልም ተዋናዮች፣ የዩኒቨርስቲዎችና የኮሌጅ ተማሪዎችና ገና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያላጠናቀቁ የሀብታም ልጆች ናቸው፡፡ እነዚህን ወጣት ሴቶች ለወሲብ ሽያጭ “ሥራ” የሚያመቻቹና የማገናኘት ተግባሩን በቅልጥፍና የሚወጡ ፈረንጆች “ፒምፕ” የሚሏቸው አይነት ደላሎች በከተማችን እየተበራከቱ ነው፡፡ ደላሎቹ ራሳቸው በኔትዎርክ የተሣሰሩ፣ የራሳቸውን መኪና ይዘው የሚንቀሳቀሱ፣ በከተማው ውስጥ አሉ የተባሉ ሆቴል ቤቶችን፣ እንግዳ ማረፊያዎችን፣ መቃሚያ ቤቶችንና የመዝናኛ ሥፍራዎችን በቁጥጥራቸው ሥር ያደረጉ ናቸው፡፡

ደላሎቹ ወደ እነዚህ ሥፍራ የሚመጡ አዳዲስ እንግዶችንና ነባር ደንበኞቻቸውን ለማጥመድና እንደ እንግዳው ፍላጐት የሚጠይቀውን ለማቅረብ ሁሌም ዝግጁ ናቸው፡፡ በአንዳንድ የከተማችን ሆቴሎችና እንግዳ ማረፊያዎች ውስጥ የሚሰሩ እንግዳ ተቀባዮች፣ (receptionists) አስተናጋጆችና የትላልቅ ቪላ አከራዮች የኔትዎርኩ አባላት ናቸው፡፡ አዲስ እንግዳ የመምጣቱ ዜና እነዚህ ደላሎች ጆሮ ለመድረስ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ይበቃሉ፡፡ ከዛም ደላሎቹ ሥራቸውን ይጀምራሉ። በእንግዳው መውጫና መግቢያ ላይ መረቡ ይዘረጋል። አብዛኛውን ጊዜ የደላሎቹ መረብ አሣውን ሣያጠምድ አይመለስም። ከልጃገረድ እስከ ቤት ልጅ፣ ከቤት ልጅ እስከ የቡና ቤት ሴት ድረስ እንግዳው የጠየቀው ይቀርብለታል። በዚሁ የሴት ድለላ ተግባር ላይ የተሰማሩ ደላላዎች እንደነገሩኝ፤ በአሁኑ ወቅት በከተማችን ለገበያ የሚቀርቡ ልጃገረድ ሴቶች እየተበራከቱ ነው። ሴቶቹ በአብዛኛው ዕድሜያቸው ከ14-17 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ናቸው፡፡ አልፎ አልፎም ከክፍለ ሃገር የሚመጡ ታዳጊ ልጆች የዚህ ድርጊት ሰለባ ይሆናሉ፡፡ ወደ አረብ አገራት ለመሄድ ከተለያዩ የአገራችን ክልሎች ይመጡ የነበሩት ታዳጊ ሴቶችም የእነዚህ ደላሎች ወጥመድ ውስጥ የሚገቡበት አጋጣሚ እንዳለ ይታወቃል፡፡
ልጃገረዶቹ ድንግልናቸውን በሽርፍራፊ ገንዘብ በደላላ ሸጠው ወዳሰቡበት ባህር ማዶ ይሻገራሉ፡፡ ይህ ወደ አረብ አገር ባቀኑ በርካታ ሴት እህቶቻችን ላይ ሲፈፀም የኖረ ሃቅ እንደሆነ ደላሎቹ ያለሀፍረት ይናገራሉ፡፡ ከዚህ በተረፈ በተለያዩ ማባባያዎችና ጉትጐታዎች ከቤታቸው የሚወጡ ከየትምህርት ቤቱ የሚወሰዱ ታዳጊ ሴቶች፤ ድንግልናቸውን ከእነሱ በእድሜ እጅግ ለሚበልጣቸው (አንዳንዴም ለወጣት ሀብታም ነጋዴዎች) በ10ሺዎች በሚቆጠር ብር ይሸጣሉ፡፡ ይህ ተግባር በስፋት የሚከናወንባቸው ሆቴሎችና እንግዳ ማረፊያዎች በተለይም ከአዲስ አበባ ወጣ ባሉ ከተሞች (ዱከም፣ ደብረዘይት፣ ሞጆና ናዝሬት… በብዛት ይጠቀሳሉ) በስፋት ይገኛሉ፡፡ በዚህ “የልጃገረዶች የድንግልና ግብይት” ውስጥ በብዛት ተሣታፊ የሚሆኑት የከተማችን ቱጃር ነጋዴዎችና አልፎ አልፎ ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡
ቀይ፣ ጠይም፣ ጠቆር ያለች፣ ረዥም፣ ቀጭን፣ ቁመናዋ ያማረ… እንደ እንግዳው ስሜትና ምርጫ ተፈላጊዋን በደቂቃዎች ውስጥ መኝታ ቤት ድረስ ማምጣት ለደላሎቹ አዳጋች ሥራ አይደለም። ከውጭ አገራት ከሚመጡና ይህንን አይነት አገልግሎት በስፋት ከሚጠይቁ የውጪ ዜጐች መካከል አብዛኛዎቹ አረቦች እንደሆኑ በስራው ላይ የተሰማሩ ደላሎች ይናገራሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሱዳኖችም በብዛት እንደሚመጡ እነዚሁ ደላሎች ገልፀውልኛል። ለረዥም አመታት ውጪ ኖረው ወደ አገራቸው የተመለሱ ዳያስፖራዎች፣ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ዲፕሎማቶችና በተለያዩ ስብሰባዎችና ሥራ ሰበብ አሊያም ለጉብኝት የኢትዮጵያን ምድር የሚረግጡ የውጪ ዜጐች ሁሉ የዚህ “አገልግሎት” ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ከተማችን የምታስተናግደው አለማቀፋዊ ስብሰባ በሚኖርበት ወቅት የደላሎቹ ወይም የግብይቱ ኔትወርክ ይጨናነቃል፡፡ የአብዛኛዎቹ “አገልግሎት” ፈላጊዎች ጥያቄም “ቆንጆ የቤት ልጅ እፈልጋለሁ” የሚል ነው፡፡ ጥያቄያቸውን በአግባቡ መመለስ የቻለ ዳጐስ ካለ ክፍያ በተጨማሪ ወፈር ያለ ጉርሻ ማግኘቱም እርግጥ ነው፡፡ “አንዳንድ ጊዜ “የቤት ልጆች” ከገበያ የሚጠፉበት ወቅት አለ። እንዳልኩሽ ስብሰባዎች በሚኖርበት ወቅት ገበያው ስለሚሟሟቅ የቤት ልጆች በጊዜ ያልቃሉ፡፡ ስለዚህ ያለን አማራጭ ብዙም ያልተጐሳቆሉ ሴተኛ አዳሪዎችን እየፈለግን በቤት ልጅ ታርጋ ለገበያ ማቅረብ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ አንዳንድ ጊዜ ይባነንበታል፡፡ ሰዎቹ የቤት ልጅና ሴተኛ አዳሪን የሚለዩበት የራሳቸው መንገድ አላቸው ብሎኛል ከገበያው ደላሎች አንዱ፡፡”
በከተማችን የተለያዩ ሥፍራዎች ቦሌ፣ ወሎ ሰፈር፣ ሳር ቤት፣ ሳሚት፣ መስቀል ፍላወርና መገናኛ አካባቢዎች የሚገኙ ቪላ ቤቶች ከነሙሉ የቤት ዕቃዎቻቸው ለቀናት፣ ለሳምንታትና ለወራት ከውጪ የሚመጡ እንግዶችን ይቀበላሉ፡፡ የእነዚህ ቤቶች የጥበቃ ሠራተኞች ከደላሎቹ ጋር በኔትዎርክ የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ለሴቶቹ የሚከፈለው ዋጋ እንደ እንግዳው አይነትና እንደ ሴቷ የማስተናገድ ብቃት እንደሚለያይ ደላላው ይናገራል፡፡ ሴቷ እንግዳው በፈለገው መንገድና ሁኔታ ልታስተናግደው (ያፈነገጠ የወሲብ ጥያቄን ያካትታል) ፈቃደኛ ከሆነች ክፍያዋ ከፍ ይላል፡፡ በአብዛኛው ግን ለውጪ አገር ዜጐች የሚቀርቡ ሴቶች ለአንድ ምሽት ከ300-400 ዶላር ክፍያን ይጠይቃሉ፡፡ የቆይታ ጊዜያቸው የሚራዘምና እነሱም የሚመቻቹ ከሆነ ግን ክፍያው እንደየሁኔታው ሊለዋወጥ ይችላል። ለሁለትና ለሶስት ቀናት በነበራቸው ቆይታ እጅግ ተደስተው ከዋናው ክፍያ ጋር ተጨማሪ ቲፕ (በገንዘብም በአይነትም) ለምሳሌ ላፕቶፕ፣ ካሜራ፣ አይፎንና መሰል ውድ ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች በስጦታ ሰጥተዋቸው የሚሄዱም አሉ። ከዚህ ባስ ሲልም ወደ አገራቸው እስከ መውሰድ የሚደርሱም ይኖራሉ፡፡ በከተማዋ የሚገኙ ትላልቅ የመቃሚያ ቤቶችን እንደ እጁ መዳፍ አብጠርጥሮ እንደሚያውቃቸው የሚናገረውና በዚሁ ሴቶችን በመደለል “ቢዝነስ” ላይ የተሰማራው ሌላው የላዳ ታክሲ ሾፌሩ ታዲዮስ፤ በአሁኑ ወቅት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የምትገኝን “የቤት ልጅ” አንጠልጥሎ ለወሲብ ገበያ ማቅረብ ለእሱ እጅግ ቀላል ሥራ እንደሆነ ይናገራል፡፡

“ሴቶቹ የብር ፍቅር ሊገላቸው ነው ዝም ብለሽ እኮ አንዳንድ ትላልቅ የቁንጅና ሣሎኖች፣ ካፌዎችና መዝናኛ ሥፍራዎች ብትሄጂ ሆን ብለው ለጠለፋ የሚወጡ የቤት ልጆችን ማግኘት ትችያለሽ፡፡ በየመቃሚያ ቤቱ ለዚሁ ተግባር የሚዞሩ ሴቶች ነፍ ናቸው፡፡ እኛ ደግሞ ፈላጊና ተፈላጊን ማገናኘት ነው ሥራችን። እነሱ ሲመቻቹ እኛም ይመቸናል” ይላል ታዲዮስ። በከተማዋ ካሉ ትላልቅ ሆቴሎች በአንዱ በእንግዳ ተቀባይነት የሚሰራው ፍፁም (ስሙ የተየቀረ) በሆቴሉ ውስጥ ከሚያርፉ እንግዶች አብዛኛዎቹ የተለያዩ አገር ዜጐች እንደሆኑ በመጠቆም፤ በሥራው ወቅት የሚያጋጥመውና እጅግ ያስመረረው ጉዳይ ግን የእነዚህን እንግዶች “ሴት አስምጣልን” ጥያቄ መመለስ እንደሆነ ይናገራል። የእንግዶቹን ጥያቄ መመለስ ካቃተው እንግዶቹ በአግባቡ እንዳልተስተናገዱ ለሆቴሎቹ ኃላፊዎች ከመናገር ወደ ኋላ እንደማይሉም ይገልፃል፡፡ ይህ እንዳይሆንም በእነ ታዲዮስ ኔትወርክ መታቀፍ ግድ ሆኖበታል፡፡ እንግዶቹ በዚህ ዓይነት መንገድ በከተማችን በሚጧጧፈው ምስጢራዊ የወሲብ ገበያ ውስጥ ተዋናይ ሆነው ቆይተው ወደ አገራቸው በሚመለሱበት ወቅት ከአበሻ ውብ ቆነጃጅት ጋር የፈፀሙትን የወሲብ ገድል እንደ ፌስ ቡክ፣ ትዊተር ባሉ የማህበረሰብ ድረገፆች ላይ በማስፈር ለዓለም ያስኮመኩማሉ፡፡ ጐበዝ! ወዴት እየተጓዝን ይሆን? ምስጢሩም ቢገለጥ ዝምታውም ቢበቃ አይሻልም ትላላችሁ፡፡ ምንም ቢሆን መወያየቱ አይከፋም እላለሁ፡፡

 

comment pic

ከወያኔ ምን አተረፍን?

0
0

ከተስፋየ ታደሰ (ኖርዌ)

ኢትዮጵያ ሃገራችን 3000 ሺህ ዘመን ታሪክ ባለቤት ብትሆንም ያለመታደል ሆነና ዛሬ ድርስ ጥሩ መሪ አላገኘችም። ወያኔ የደርግን ስረዓት ጥሎ የስልጣን ኮርቻዉ ላይ ሲቀመጥ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አሜን ብሎ ተቀብሎት ነበር። አበው ሲተርቱ እዉነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንደሚሉት የወያኔ ድብቅ የፖለቲካ አጀንዳ እያደር ፍንትው ብሎ መታየት ጀመረ። ዘር ከዘር መለያየትና ማጋጨት ለከፋፍሎ መግዛት ፖሊሲው ይመች ዘንድ፣ በእምነት ላይ ጣልቃ መግባት እንዲሁም ለዘመናት በመቻቻል የሚታወቁትን ሁለቱን ታላላቅ ሃይማኖቶች ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ ጋር ማጋጨት እንዲሁም በምርጫ የህዝብ ድማፅ መስረቅ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ማፈን፣ ማሰር፣ ማሳደድ እንዲሁም መግደል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። በወያኔ ስረዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘዉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ ድህነት፣ ጉስቁልናና ስራ-አጥነት ናቸዉ።
tplf-rotten-apple-245x300
ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፍትህ በሌለበት በአጠቃላይ ፍትህ ዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር በተነፈገበት ሃገር ህዝብን ማእከል ያላደረገ ልማትና እድገት ይኖራል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን የራሱን ጉድ ለመሸፈን ሲል ኢትዮጵያ አድጋለች፣ ሁለት አሃዝ እድገት አስመዝግባለች፣ ረሃብ የለም ወዘተ….እያለ ነጋ ጠባ በአሸብራቂ ቃላት የአለም ማህበረሰብን ቀልብ በመሳብና ለማደናበር ይሞክር እንጂ በመሬት ላይ የሚታየው ሃቅ ግን በተቃራኒው ነው፡፡ በተለመደው መሰሪ ፕሮፓጋንዳው አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ ይበለን እንጂ የኑሮን ውድነት፣ መልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት በረሃብ እየተቀጣ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብን ማታለል ግን በፍጹም አይችልም፡፡ በተለይም ያልበላውን በልቷል፣ ያልሰማውን ሰምቷል ነጻ ወጥቷል የስርአቱ ልዩ ተጠቃሚ ሆኗል ወዘተ…እየተባለ ለአመታት በስሙ ሲነገድበት የኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮው በጣም ከባድ እንደሆነ ላይ የተገለጹ እውነታዎች ይመሰክራሉ።

ዛሬ በዚህ አስከፊ ስርአት ሳቢያ ከአንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመርቆ የወጣ በእዉቀቱ ሳይሆን የኢህአዴግ አባል ካልሆነ የመንግስት ስራ አያገኝም ። ገበሬው ሰፊ የእርሻ ቦታውን እየተነጠቀ ለባዕድ ኢንቨስተሮች በሊዝ እየቸበቸበ ገበሬዉን ለድህነት ለጉስቁልና እየዳረገው ይገኛል። ወያኔ የዛሬ አስራ አምስት ዓመት ገደማ በመጪዉ አስርት አመታት የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሶስት ጊዜ ይመገባል እንዲሁም የምግብ ዋስትና ይጠበቃል ብሎ ነበር ፤ ነገር ግን በየዓመቱ ከሰባት ሚሊዮን ህዝብ በላይ በረሃብ አለንጋ እየተጠበሰ ይገኛል። ሰብአዊነት ያልተላበሰ መንግስት ቢኖር እንደ ወያኔ ያለ መርዝ መንግስት ይኖራል ብሎ መናገር በጣም ያዳግታል። በአለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና መንግስታቶች ምክንያት ለተረጂዉ የመጣዉን እህል አረመኔው የወያኔ መንግስት በምስኪኑ ተረጂ ወገን ጉሮሮ ላይ ቆሞ ለስግብግብ ነጋዴዎች አየር በአየር እየቸበቸበ የግል ኪሱን እያደለበ ይገኛል።

ሀገራችን ነፃ ጋዜጠኞችን በማሰርና በማፈን ከአፍሪካ ቀዳሚ ደረጃን ከያዙ ሃገሮች ተርታ መሰለፏ ይታወቃል ። ይህ ደግሞ የመናገር የመፃፍ መብትን የሚጋፋና የሚፃረር ተግባር መሆኑ ግልፅ ነዉ፤ በሌላ አለም ባልታየ መልኩ በኤሌትሮኒክስ መገናኛዎች መረጃ ተለዋዉጣችኋል፣ መንግስት የሚተች ፅሁፍ ጽፋችኋልና ለኔ አልተመቻችሁኝም የሚል ቅኝት ያለዉ ዉንጀላ በማቀነባበር ሽብርተኛ የሚለዉን ፀያፍ ስያሜ በማሸከም ዜጎችን ለእስርና ለስደት እንዲሁም የቀረዉን ለፍረሀት የሚዳርግ ሽብርተኛ ስረአት ነዉ ተሸክመን ያለነው። በተጨማሪም በነፃነት መደራጀት እና መንግስትን መቃወም አንድም ለእስራት አልያም ለስደት እየዳረገ ይገኛል፡፡ በርካታ ጋዜጠኞች፣ ወጣት ፖለቲከኞች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ነጋዴዎች በነጻነት የመኖር፣ በነፃነት የመናገር እና የመፃፍ መብታቸው እየተገፈፈ በየእስር ቤቱ እየተሰቃዩ ይገኛለ፡፡ አሁን በሃገራችን በደልና ጭቆና በዝቷል ድህነትና ጉስቁልና ከመቸዉም በባሰ ተንሰራፍቷል እስርና ሰቆቃ ተራ ነገሮች ሆነዋል በአሸባሪዎች ስም እራሳቸዉ ቦንቦች አጥምደው ህዝቦች እየፈጁ ሰላማዊ ዜጎች በአሸባሪነት እየተፈረጁ ለስቃይ እየተዳረጉ ነዉ። ዛሬ በሃገራችን አርሶም ሆነ ነግዶ መኖር አይቻልም። መኖር የሚቻለዉ ኢሕአዴግ ልማት ነዉ የሚለዉን መዝሙር በመዘመር ብቻ ነዉ።

ባጠቃላይ ስረዓቱ ፀረ- ዲሞክራሲና ፀረ- ፍትህ አቋም የሚያራምድ ነዉ። በመሳሪያ የያዘዉን ስልጣን በዲሞክራሲና በፍትህ ለሚያምን ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንዲያስረክብ እና የነፃነት አየር እንዲተነፍስ ስለ ሀገራቸዉ በመቆርቆር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሳይሸማቀቁ ጊዜና ሰአት እንዲሁም ቦታ ሳይገድባቸዉ የመናገር፣ የመፃፍ ጥያቄ ፣የመጠየቅ መብታቸዉ ተከብሮ አለም ከደረሰበት የእድገት ደረጃ ላይ ለማድረስና ከቂም በቀል የፀዳች አገር ለመጭዉ ትዉልድ ለማቆየት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ስልጣን ላይ ያለዉን ጨቋኝና ኢ-ዲሞክራሲያዊ የሆነና አንባገነናዊ ገዥ ፓርቲ አዉርዶ በምትኩ ዲሞክራሲያዊ የሆነ እና በበለጠ መልኩ የሁላችንን ነፃነት እና እኩልነት የሚያከብር መንግስት ለመተካት በሚደረገዉ ትግል ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የአገሪቷን እድገት ጎዳና በአንድ ላይ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ጥሪዬን አቀርባለሁ። አገራችንን ከወያኔ ዘረኝነት አገዛዝ ነፃ ለማዉጣት ትግላችንን በማንኛዉም መልኩ ልናጠናክር እንደሚገባን በኢትዮጵያ ስም በድጋሚ አሳስባለሁ።

ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ኢሜል አድራሻየ፡ tesfayetadesse20@gmail.com

ይድረስ ለክቡር አቶ ዘውዴ ረታ እና ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት ቦታ ሁሉ –ከታደለ ብጡል ክብረት (ኢ/ር)

0
0

“የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት” በሚል ርዕስ  አቶ ዘውዴ ረታ ያሳተሙትን መጽሐፍ በጥሞና አንብቤዋለሁ። መጽሐፉ በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የተፈጸሙትን እውነተኛ ታሪክ በሙሉ የካተተ ነው ባልልም፤በውስጡ ያሉት በርካታ ዘገባዎች ከዚህ በፊት በሌሎች መጽሐፎች ውስጥ ተጽፈው ያልነበሩ ናቸው። በተለይም ክቡር ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስን፤ ክቡር አቶ ይልማ ደሬሳን፤ ክቡራን አቶ አክሊሉ እና አቶ መኮንን ሀብተወልድን በተመለከተ የተጻፈው፤እነዚህን የኢትዮጵያ ብርቅ ልጆች ስም ህያው የሚያደርግ ስለሆነ ለደራሲው ያለኝን አድናቆት በከፍተኛ አክብሮት እገልጻለሁ፡፡

zewede reta

ይሁን እንጂ “ይድረስ ለአንባቢዎቼ” በሚለው ርእስ ስር ደራሲው በአቀረቡት ዘገባ ውስጥ “ይህ ጎድሏል፤ ይህ ቀርቷል የሚባሉ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እና እንደሚኖሩ አውቃለሁ” ብለው አስተያየት እንድንሰጥ በር ከፍተዋል። እኔ ደግሞ “ጎድሏል፤ ቀርቷል” ከሚለው በተጨማሪ አቶ ዘውዴ ረታ የተሳሳቱትን ለማረም ይጠቅማቸዋል ብዬ ያሰብኩትን እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

 

በመጀመሪያ የማነሳው “የቫቲካን አቋም በኢትዮጵያ ጉዳይ” ብለው ስለአቀረቡት ዘገባ ነው። በዚህ ርእስ ስር፤ እሳቸው የጻፉትን እዚህ ላይ ለመድገም አልፈልግም። ዋናው ቁም ነገር፤ “የቫቲካን አቋም በኢትዮጵያ ጉዳይ” የሚል ርእስ ሰጥተው ከጻፉ ዘንዳ፤ የቫቲካንን አቋም ይገልጻሉ ብዬ ስጠብቅ፤እሳቸው ሸወድ አድርገው ወደ ፒዮስ 11ኛ አሉባልታ ገብተዋል። ለምን ይህን ለማድረግ አንደፈለጉ ስላልገባኝ፤የእኔን እይታ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

 

አንድ የበላይ የሆነ የሃይማኖት አባት ወይም የአገር መሪ፤ከበታቹ ያሉት ሰዎች ለሚፈጽሙት ተግባራት ሁሉ ተወዳሽም፤ተወቃሽም እደንደሚሀን እሳቸው ሳያውቁ ይቀራሉ የሚል እምነት የለኝም። ይህ ሐቅ ተቀባይነት ያለው የአስተዳደር ጽንፈ ሐሳብ በመሆኑ፤የቫቲካን ካርዲናሎች (ጳጳሶች) በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸሙት በደል ዋና ተጠያቂ፡ የቫቲካን የበላይ መሪ ፒዩስ 11ኛ ናቸው፡፡ ይህን ሐቅ አቶ ዘውዴ ረታ መካድ አልነበረባቸውም። በፒዩስ 11ኛ ስር ያሉት ካርዲናሎች የፈጸሟቸውን ተግባራት አቶ ዘውዴ እንዲያስታውሱት፤ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር አቀርባለሁ፡፡

 

  1. አቶ ዘውዴ ረታ “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት” በሚል ረእስ በጻፉት መጽሐፍ ገጽ  301 ላይ “የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ኢደልፎንስ ሹስተር፤የፋሸስት መንግሥት ደጋፊነታቸውን በግልጽ አስረድተዋል” ብለዋል። በመቀጠልም “- – - – የጣሊያን መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር  የባርነትን አገዛዝ ሰንሰለት በመጣስ፤የካቶሊክን ተልዕኮ የተቀበለ ነው – - ” ብለው ከጻፉ  በኋላ፤ፒዩስ 11ኛን ለመደገፍ የተነሱበትን ዓላማ ለማሳካት ሲሉ “የሚላኖ ሊቀ ጳጳስ በተናገሩት፤ፒዩስ 11ኛ እጅግ ማዘናቸውን ገልጠዋል” በማለት ነገሩን ለማርገብ ሞክረዋል። በትልቅ ሥልጣን ላይ ያለው ካርዲናል ኢደልፎንስ ሹስተር፤የኢትዮጵያን ነፃነት የሚያሳጣ እና  ክብሯን የሚነካ ድርጊት በመፈፀሙ፤ቢያንስ አሰተዳደራዊ እርምጃ አለመውሰዳቸው ፒዩስ 11ኛ የድርጊቱ ተባባሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንጂ፤እሳቸውን ከበደሉ ነፃ የሚያደርግ አይደለም።

 

ከዚህ ዝቅ ብሎ የሚታየው ፎተግራፍ የሚያሳየው “የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ካርዲናል ኢደልፎንስ”    ሕዝብ በተሰበሰበበት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በር ላይ ቆሞ፤በልበ ሙሉነት የፋሸስትን መንግሥት የሚደግፍ ንግግር ሲያደርግ ነው። በዚህ ፎተግራፍ ላይ ያሉት አብዛኛዎቹ ሰዎች ካርዲናል ሹስተር የሚናገረውን የሚያዳምጡ ቢሆኑም፡አንድ ግርምት የፈጠረበት ሰው አፉን ይዞ እናያለን።

 

ፒዩስ 11ኛ “ፍትሐዊ ባልሆነ ጦርነት አናምንም” ከማለት ውጭ የኢትዮጵያን መብት ለማስጠበቅ ምን የተናገሩት ወይም የፈፀሙት ተግባር አለ?

 

ካርዲናል ሹስተር የፋሽስት ደጋፊነቱን ሲናገር

 

  1. የጣሊያን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ በሚሳፈርበት ወቅት፤ መድፎቹንና ሌሎች አውዳሚ መሣሪያዎቹን የባረከው፣ የቫቲካን ካርዲናል ፎቶግራፍ ከዚህ በታች ያለው ነው።

 

 

 

 

  1. የኒው ዮርክ ታይምስ እ.አ.አ. የካቲት 13 ቀን 1937 ባወጣው ህትመት “ዛሬ ማለዳ ላይ ጳጳሱ ለጣሊያን ንጉሥ እና ለኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፣ ለቪክቶር ኢማኑኤል፣ ብለው ቅዱስ ቡራኪያቸውን በመስጠት፣ ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ላይ ስላላት ሉዓላዊነት እውቅናቸውን ገልጸዋል” ብሏል።  የእንግሊዝኛውን ጽሁፍ ከዚህ በታች አቀርባለሁ።

 

(Earlier today the Pontiff had given his recognition of Italian sovereignty over Ethiopia by bestowing benediction upon Victor Emmanuel as King of Italy and Emperor of Ethiopia)

 

  1. የፋሽስት ኢጣሊያ ወታደሮች መረብን ተሻግረው፣ ወደ መሐል አገር ለመገስገስ ሲሰለፉ ቡራኬ ሲሰጥ በፊልም የተቀዳው በእጄ ይገኛል።

 

  1. እምነተ ቢስና የቀኖና አፈንጋጭ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ማካሄዴ፤የካቶሊክን እምነት ለማስፋፋት በር ስለሚከፍት፤ የተቀደሰ ጦርነት ነው በማለት የቶራኖ ሊቀ ጳጳስ ተናግሯል፡፡ “The war against Ethiopia should be considered as a holy war, a crusade to open Ethiopia, a country of infidels  and Schismatics to the Expansion of the Catholic Faith.”  (By OCP on Mach 12, 2010)

 

  1. የሚላኖው ሊቀ ጳጳስ ሹስተር ከተናገሩት ቀደም ሲል ከገለጽሁት በተጨማሪ “የጣሊያን ፋሽስት ባንዲራ፤በአሁኑ ጊዜ የክርስቶስን መስቀል በኢትዮጵያ ውስጥ በድል አድራጊነት  ባሮችን ነፃ ለማውጣትና ለእኛም የሚስዮን ፕሮፓጋንዳ  መንገድ እየከፈተ ነው” ብለዋል።

 

The Archbishop of Milan, cardinal Schuster, went farther and did all he could to bestow upon the Abyssinian War, the nature of a Holy Crusade. “The Italian (Fascist Flag) is at the moment bringing in triumph the Cross of Christ in Ethiopia to free the road for the emancipation of the slaves, opening it at the same time to our missionary propaganda.” (By T.L. Gardini, Towards New Italy.)

 

ከዚያ በኋላ የሚላኖው ራሱ ሊቀጳጳሱ አንድ ታንክ ላይ ዘልሎ ወጣና ረጋ ብሎ እዚያ የተሰበሰቡትን የፋሽስት ጀሌዎች ባረከ።  የሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ሳለቬሚኒ እንደገለጸው፣ ቢያንስ ሰባት ካርዲናሎች፣ 29 ሊቀ ጳጳሶች፣ 61 ጳጳሶች ወዲያውኑ ጦርነቱን ደግፈዋል።  የቫቲካን ድጋፍ በዚህ ብቻ ሳያበቃ፣ በውጭ አገርም ጦርነቱን ደግፈዋል። በየአገሩ ያሉት የካቶሊክ ጋዜጦች በሙሉ እንደ እንግሊዝ አገርና አሜሪካም ያሉት ሳይቀሩ ኢጣሊያን ደግፈዋል።

 

  1. እ.አ.አ. በ1949 አቭሮ ማንሃታን በጻፈው መጽሀፍ እንደገለጸው “ፓዮስ 11ኛ ለሙሶሊኒ ትልቅ ክብር የሚሰጡ መሆናቸው ይታወቃል።  በአጠቃላይ፣ የጣሊያን ቀሳውስት በሙሉ፣ የፋሽስቶቹ ወገን መሆናቸውን በቀላሉ ለመረዳት የሚቻለው፣ የፋሽዝም መርሆ፣ ብሄርተኛነት፣ ፈላጭ ቆራጭና ሕዝባዊነትን የሚቃወም አስተዳደር መሆኑ ነው” ይላል።  በእንግሊዝኛው የተጻፈው እንዲህ ይላል።

 

(Pope Pius XI is credited with much admiration for Mussolini that the Italian Clergy as a whole are pro-Fascist is easy to understand, seing that Fascism is a nationalist, authoritarian, anti-Socialist Force”.) Avro Manhattan 1949.

 

ሀቁ ይህ ሆኖ እያለ አቶ ዘውዴ ረታ ደግሞ “- – - የዓለም የካቶሊኮች አባት (ፓዮስ 11ኛ ማለታቸው ነው) ከፋሽስቱ ዲሬክተር መሪ ተጣልተው ከባድ ችግር ላይ ከመውደቅ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ዓይነት ፍትሕን የተመረኮዘ አስተያየት ከመስጠት ታግደው መኖር የሚሻል መሆኑ ታያቸው” ሲሉ መስክረዋል።   ይሄ እንግዲህ አቶ ዘውዴ ረታ ሽንጣቸውን ገትረው የሚሟገቱላቸው የካቶሊኮች አባት፣ ፓዮስ 11ኛ፣ ለፍትሕ አለመቆማቸው በራሳቸው አንደበት ገለጹት።  ሌላው የፒዩስ 11ኛ ጥፋት፣ የራሳቸው ካርዲናሎች ከፋሽስቱ መሪ ሙሶሊኒ ጎን ቁመው ወረራውን ከፍ ብዬ በማስረጃ እንዳቀረብኩት፣ የጦር መሣሪያዎች ሲባርኩና ፋሽስቶችንም ሲያወድሱ፣ እነዚህን የቫቲካን ባለሥልጣናት ላይ የመገሰጽም ይሁን የማገድ እርምጃ አለመውሰዳቸው ነው።

 

ክቡራን አንባቢያን

 

ሌላም ላክልበት።  ሙሶሊኒ እና ጭፍራዎቹ ኢትዮጵያን በመውረር የፈጸሙት በደል እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ለማስታወስ ያህል፣ ጥቂቶቹን ከዚህ በታች አቀርባለሁ።

 

  1. የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር

2,000

  1. የተቃጠሉ ቤቶች ቁጥር

525,000

  1. በጦርነት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር

275,000

  1. በአምስት ዓመት የተገደሉ አርበኞች ቁጥር-

78,500

  1. ተማርከው የተገደሉ አርበኞች ቁጥር `

24,000

  1. በአምስት ዓመት ውስጥ የተገደሉ ሴቶችና ሕፃናት ቁጥር

17,800

  1. ታስረው የሞቱ ሰዎች ቁጥር`

35,000

  1. በስደትና በረሀብ የሞቱ ሰዎች ቁጥር

300,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ የቀንድ ከብቶች ቁጥር

5,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ በጎችና ፍየሎች ቁጥር

7,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ ፈረስና በቅሎዎች ቁጥር

1,000,000

  1. በጦርነቱ ዘመን ያለቁ ግመሎች ቁጥር `

700,000

 

ከላይ ከተዘረዘረው በተጨማሪ፤ለዚህ ሁሉ እልቂት መሪና ኃላፊ የሆነውን ጀነራል ግራዚያኒን ለመግደል ሞገስ አስገዶምና አብረሃ ደቦጭ ባደረጉት ሙከራ ሰበብ፤ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እ.አ.አ. ከየካቲት 12 እስከ 15 1937 ድረስ ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ 30,000 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ በእነዚሁ ቀናት ውስጥ ሞገስ አስገዶምንና አብርሀም ደቦጭን ደብቀዋል በሚል ሰበብ ደብረሊባኖስ የነበሩትን ከ300 እስከ 500 የሚደርሱ መነኩሴዎችና ካሕናት ተረሽነዋል።  አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል፣ ሕዝቡ ለፋሽስት መንግሥት እንዲገዛ ስበኩ ሲባሉ አሻፈረኝ በማለታቸው በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

 

ይህን ሁሉ የሰው እልቂት፣ እንዲሁም የንብረት መውደም የሚያውቁት የቫቲካኑ መሪ ፓዩስ 11ኛ በዝምታ ማለፋቸው ይታወቃል።  አቶ ዘውዴ ረታ ይህን ሐቅ ወደ ጎን ትተው ፓዩስ 11ኛ የዓለም ነርሶችን ሲቀበሉ “በመንግሥታት ግንኙነት መሀከል የሚፈጠር ማናቸውም አለመግባባት – - – በሰላም መንገድ መፈታት ያለበት መሆኑን በጥብቅ ካሳሰቡ በኋላ – - -” በሚል ቃል ለማስረጃነት ለማቅረብ ሞክረዋል። ይህን መሰል አነጋገር፣ እንኳን በከፍተኛ ሥልጣን ያለ ሰው ይቅርና ማንም ተራ ሰው ሊናገረው የሚችል አባባል አለመሆኑን አቶ ዘውዴ ረታ የሚገነዘቡት ይመስለኛል።  በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር ያሉት ጳጳሶች እና ካርዲናሎች ተጠሪነታቸው ለፓዩስ 11ኛ በመሆኑ እሳቸውን ከተወቃሽነት ሊያድናቸው አይችልም።

 

የዓለምን ሰላም ፈላጊ የሆኑ ሁሉ፣ የፋሽስቶች መሪና ጭፍሮቹ በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ግፍ አውግዘዋል። ሐቁ ይህ ሆኖ እያለ፣ አቶ ዘውዴ ረታ የቫቲካኑን መሪ ፓዩስ 11ኛ ከደሙ ንጹህ ናቸው ብለው ለመደገፍ መነሳሳታቸው እጅግ የሚያሳዝን ጉዳይ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።

 

የናዚ መሪ የነበረው ሂትለር፣ አይሁዳውያንን በጨፈጨፈ ጊዜ ዝምታን መርጣ የነበረችው ቫቲካን፣ ጦርነቱ ካለቀ በኋላ፣ ከአንዴም ሁለት ጊዜ፣ አይሁዳውያንን ይቅርታ ጠይቃለች። ፋሽስቶች በኢትዮጵያ ላይ ለፈጸሙት ግፍ ግን ቫቲካን እስከ ዛሬ ምንም ዓይነት የመጸጸት እርምጃ አልወሰደችም።  ስለዚህ፣ ዛሬ በሥልጣን ላይ ያሉት ፓፓ ኢትዮጵያን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው የምንል ብዙ ኢትዮጵያውያን አለን።

 

ውድ አንባቢያን

 

ከዚህ ከፍ ብሎ የተጻፈው ቫቲካንን በተመለከተ ያለው ጉዳይ ብቻ ነው። “የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት” በሚለው መጽሀፍ ውስጥ ያሉትን አንዳንድ ግድፈቶች ልጠቁማችሁ። አቶ ዘውዴ ረታ ስለ ሙሶሊኒ አስተዳደግ፣ ጠባይ እና ተግባራት ብዙ ብለዋል።  ግን ይህ ትረካ እሳቸው ከሰጡት ርእስ አኳያ ሲታይ ምን ጠቀሜታ አለው? ይልቁንስ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ አቤት በማለት ከአገር ቢወጡም፣ ለረጅም ጊዜ እንግሊዝ አገር እንዲቆዩ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ስላደረጉት አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሼቱ ጠባይና ተግባራት ቢጽፉ ጥሩ ነበር።  ከሁሉም የሚገርመው የሲልቪያ ፓንክረስት በጥቂቱም ቢሆን መጻፋቸው ነው።

 

ሲልቪያ ፓንክረስት ስለ ኢትዮጵያ ልትጽፍ የቻለችው ከ1927 እስከ 1931 ዓ.ም. ድረስ በሎንዶን የኢትዮጵያ ሙሉ ባለ ሥልጣን ሚንስቴር በነበሩት አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ድጋፍና ቡራኬ መሆኑን “የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሼቱ የሕይወት ታሪክ፣ ከታደለ ብጡል ክብረት” የሚባለውን መጽሐፍ ቢያነቡ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎች ያገኙ ነበር።

 

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እንግሊዝ አገር ሲደርሱ፤ አንድም የእንግሊዝ መንግሥት ባለሥልጣን የክብር አቀባበል አላደረገላቸውም። ከመርከብ ከወረዱ በኋላ የተቀበሏቸው የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሸቱ የግል ወዳጆች ናቸው።  ይህንን ሁኔታ የሚያሳየው ፎተግራፍ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።

 

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መርከብ ውሰጥ ገብተው የተቀበላቸው አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እሸቱ መሆናቸውን የሚያሳየው ፎቶ

 

ከ1927 እስከ 1931 ዓ.ም. ድረስ በአወሮፓ፤ በአሜሪካ እና በሕንድ የብዙሃን መገናኛዎች፤ በጽሑፍ እና በአካል ተገኝተው፤ፋሽስት ሙሶሊኒ ኢትዮጵያን በግፍ እንደወረረ፤ ሕዝቡን እንዳሰቃየና ንብረትን እንዳወደመ በሰፊው ገልፀዋል። እንኳን እሳቸው፤ ሕፃናት ልጆቸቸው ዳዊትና ዮሐንስ ሳይቀሩ በአደባባይ ላይ ቆመው ስለ ወረራው ያላቸውን ኀዘኔታ ገልጸዋል። አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ እንደ ዴል ቫዩ ያሉ ሰዎች በጦር ሜዳ ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መልምለው ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።

 

አቶ ዘውዴ ረታ ይህን ሁሉ ታሪክ አያውቁም ነበር ለማለት አልደፍርም። ሆን ብለው የሸሹት ጉዳይ ነውም አልልም። ግርምት እንደፈጠረብኝ ግን አልክድም።

 

የአዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ወዳጆች ወደቡ ድረስ ሄደው ንጉሠ ነገሥቱን ሲቀበሉ

 

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና አዛዥ ሐኪም ወርቅነህ ስለ ሥራ ጉዳይ ሲወያዩ

 

ጽሁፌን ከማጠቃለሌ በፊት አንዳንድ ነገር ላክልበት፡፡

 

  1. በቅርቡ ከመገናኛ አውታሮች እንደ ተረዳነው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጸመው ግፍ እና አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ከሰላሳ ሺህ በላይ ሰዎች ላስገደለው ለጀነራል ግራዚያኒ፣ አፊሌ በሚባል ትንሽ ከተማ ውስጥ አንድ የመታሰቢያ ሙዚየምና ሐውልት ጭምር ተሠርቷል። ሐውልቱ በተመረቀ ዕለት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካርዲናል በሥፍራው ተገኝተው ቡራኬ መስጠታቸውም ተነግሯል። ይህ ተግባር የሚጠቁመው፣ ዛሬም ቢሆን ቫቲካን ለፋሽስቶች እንጂ ለተበዳይዋ ኢትዮጵያ መብት አለመቆማቸውን ነው።  ስለዚህ የአሁኑ የሮማ ጳጳስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቁ ነው።

 

  1. ለፋሽስቱ ጨፍጫፊ ጀነራል ግራዚያኒ አፊሌ ከተማ የቆመው ሐውልት እንዲፈርስ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ የሆኑት ጳጳስ የጣሊያንን መንግሥት መጠየቅ አለባቸው የሚል ጥያቄ ማቅረብ ተገቢ ነው።

 

  1. ኢጣልያ ሊቢያ ውስጥ ለፈጸመችው ግፍ ካሳ የከፈለች መሆኗ ይታወቃል። ፋሺስት ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ውስጥ የፈጸመችው ሊቢያ ውስጥ ከፈጸመችው የማይተናነስ በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ካሳ እንድትከፍል መጠየቅም ትክክል ነው።

 

  1. አቶ ዘውዴ ረታ የቀዳማዊ  ኃይለ ሥላሴ መንግሥት በሚለው መጽሀፍ ውስጥ ፒዩስ 11ኛን በመደገፍ ከጻፉት በተጨማሪ፣ ታኅሳሥ 7 ቀን 2005 በሪፖርተር ጋዜጣም አውጥተውታል።  ይህን ለማድረግ የተነሱበት ዓላማ ባይገባኝም አካሄዳቸው፣ በስተጀርባው አንድ ድብቅ ዓላማ ያለው አስመስሎባቸዋል።

 

እንደ እኔ አስተሳሰብ፣ ይህ ድርጊታቸው ትክክል እንዳልነበረ አምነው በመቀበል፣ አቋማቸውን እንዲያስተካክሉና የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ቢጠይቁ ጥሩ ነው እላለሁ።

 

ታደለ ብጡል ክብረት (ኢ/ር)

ሞባይል፡  00911 23 24 43

ፖ.ሣ. ቁጥር 5510

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live