Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

መቀሌ በእሳት ቃጠሎ አደጋ ተናጠች

0
0

አብረሃ ደስታ ከመቀሌ እንደዘገበው፦ ዛሬ ሌሊት (ማክሰኞ አጥብያ) ህዳር 23/24, 2006 ዓም በመቐለ ከተማ ሰሜን ወረዳ 06 ቀበሌ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሶ 70 የFurniture and Metal works Workshops ሙሉ በሙሉ ወድመዋል። በዎርክሾፖቹ የሚተዳደሩት ከ250-300 የሚሆኑ ሰራተኞች የነበሩ ሲሆን በጠቅላላ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድመዋል።

የመቀሌ ከተማ (ፎቶ ፋይል)

የመቀሌ ከተማ (ፎቶ ፋይል)


የአደጋው መንስኤ ባከባቢው የሚገኘው የመንግስት የመብራት ትራንስፎርመር በመቃጠሉ ነው። ትራንስፎርመሩ ከሁለት ዓመት በፊት ጀምሮ የመቃጠል ምልክቶች እንደነበሩትና ያከባቢው ኗሪዎችም በተደጋጋሚ ለመንግስት አካላት ትራንስፎርመሩ እንዲጠግኑት ጥያቄ ቢያቀርቡም መልስ ባለመግኘታቸው ችግሩ መፈጠሩ ተጠቅሷል። ስለዚህ አደጋው ያጋጠመው በመንግስት አካላት ቸልተኝነት መሆኑ ነው።

የእሳት አደጋው በቀላሉ መቆጣጠር ይቻል የነበረ ቢሆንም ሁለቱም የመቐለ ከተማ ማዛጋጃቤት የእሳት አደጋ ማጥፍያ ተሽከርካሪዎች ‘ተበላሸተው ጋራጅ ገብተዋል’ በሚል ምክንያት አደጋው የመቆጣጠሩ ጥረት አዳጋች አድርጎታል።

ማዘጋጃቤት መርዳት ባለመቻሉ ኗሪዎቹ ወደ አየርመንገድና ሲሚንቶ ፋብሪካ በመሄድ የእሳት አደጋ መከላከያ መኪኖች እንዲረዱ የጠየቁ ሲሆን የአየር መንገዱ በመጨረሻ አከባቢ ደርሷል፤ የሲሚንቶ ፋብሪካው ግን በቂ ዉኃ ሳይዝ በመምጣቱ ብዙ ንብረት ማዳን አልቻለም።

የመቐለ ማዛጋጃቤት የእሳት አደጋ ማጥፍያ ተሽከርካሪዎች ተበላሽተዋል ሲባል ገረመኝ። BTW, የተቃጠሉ ድርጅቶች ፎቶ ለማስነሳት ያደረግነው ጥረት በፖሊስ ሃይል ተከልክለናል። የመቐለው 06 ቀበሌ ‘የኢንዱስትሪ ዞን’ ነው።

በመንግስት ቸልተኝነት ምክንያት ንብረት ሲወድም ያሳዝናል።


በሚኒሶታ ቤቱ ውስጥ ተወጋግቶ የሞተው ኢትዮጵያዊ ቀብር ዛሬ ይፈጸማል፤ ባለቤቱ ታስራለች

0
0

የሃቢቢ መኖሪያ ቤት

የሃቢቢ መኖሪያ ቤት


(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው እሁድ ዴሴምበር 1 ቀን 2013 ዓ.ም በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በስለት ተወጋግቶ የሞተው ኢትዮጵያዊው ሃቢብ ገሰሰ ተሰማ የቀብር ስነ- ሥርዓት ዛሬ እንደሚፈጸም ከቤተሰቡ አካባቢ ለዘ-ሐበሻ የተላከው መረጃ አመለከተ። ፖሊስ የገዳይን ማንነት ለማረጋገጥ በምርመራ ላይ የሚገኝ መሆኑን የገለጸ ሲሆን የሟች ባለቤት በቁጥጥር ስር መዋሏም ታውቋል።

ከዲላ ከተማ የመጣውና የ48 ዓምቱ ሃቢብ ባለቤቱን እና ልጆቹን ከኢትዮጵያ በቅርብ እንዳመጣ የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ የገለጹ ሲሆን በጣም ሰላማዊ ሰው እንደነበረም ጎረቤቶቹ ለፖሊስ ተናግረዋል። በተገደለበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ከባለቤቱ፣ ከልጆቹ እና ከባለቤቱ እህት ጋር ይኖር እንደነበር የፖሊስ ሪፖርት ያመለክታል።

ከጠዋቱ 5 ሰዓት ጀምሮ ይህ ወንጀል መፈጸም ሲጀምር 911 ተደውሎ ፖሊስ የደረሰ ቢሆንም፤ ፖሊስ ሃቢብን ማን እንደገደለው ሳይገልጽ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን እንደማይፈልግ ግን አስታውቆ ነበር። ከቅርብ ቤተሰቡ በተገኘ መረጃ የሟች ባለቤት ታስራ በምርመራ ላይ እንደምትገኝ ሲሆን ፖሊስ የሃቢብን ገዳይ ተጠርጣሪ ስም በቀናት ውስጥ ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። የሃቢቢ ባለቤት ከኢትዮጵያ የመጣችው በዚህ ዓመት እንደሆነ በፖሊስ ሪፖርት ላይ ተጠቁሟል።

የሃቢብ ተሰማ አስሬን በአሁኑ ወቅት ኮለምቢያ ሃይትስ ከተማ በሚገኝ የእስላም መስጊድ (አድራሻው 4056 7th St. NE, Columbia Heights, MN 55421) የሚገኝ ሲሆን በዚሁ መስጊድ ውስጥ ዛሬ ዲሴምበር 3 ቀን 2013 በ12:30 ፒኤም ላይ የጸሎት ፕሮግራም ከተደረገለት በኋላ ቀብሩም ዛሬ በሮዝቬል የእስላም መቃብር (Roseville Islamic Cemetary) በ1:30 ፒኤም እንደሚፈጸም ለዘ-ሐበሻ ከቤተሰቡ የተላከው መረጃ አመልክቷል። የመቃብር ቦታው አድራሻም 2336 County Road B W, St. Paul, MN 55113 ነው።

ዘ-ሐበሻ በሐቢብ ግድያ ዙሪያ የደረሰችበትን መረጃና የፖሊስን ሪፖርት ተከታትላ ለአንባቢዎቿ ታደርሳለች።

የኢህአዴግ የድርድር ጥያቄና የግል እይታዬ –ከፋሲል የኔዓለም (ጋዜጠኛ)

0
0
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም

አንድ፣ ኢሳት ፣ ኢህአዴግን እና ግንቦት7ትን የተመለከተ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ አንዳንዶች ዜናውን ሲጠራጠሩት ተመልክቻለሁ፣ ያሽሟጠጡም አልታጡም። መጠራጠርም፣ ማሽሟጠጥም የሰውልጅ ባህሪ በመሆኑ አልገረመኝም። ትንሽ የገረመኝ አንዳንድ “ጋዜጠኞች” መረጃውን ካገኙ በሁዋላ በራሳቸው መንገድ አጣርተው ሀቁን ማውጣት ሲችሉ እነሱም እንደሌላው መልሱን በማንኪያ እንዲቀርብላቸው መፈለጋቸው ነው። ጋዜጠኛ “ጥቆማ” ከተሰጠው ተመራምሮ፣ የምርምር ስራውን ይጽፋል እንጅ እንደ አንባቢ መልሱ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብለት አይጠብቅም፣ ጥያቄ መጠየቅማ ማንም ይጠይቃል፣ ጋዜጠኛን ጋዜጠኛ ወይም ተመራማሪ የሚያደርገው ለጠየቀው ጥያቄ ላይ ታች ብሎ መልስ ማቅረብ ወይም በአሰባሰባቸው መረጃዎች ላይ ተንተርሶ ትንተና መስጠት ሲችል ነው ( በሁለተኛው መስፈርት መሰረት ተመስገን ደሳለኝን እና በእስር ላይ የሚገኘው ውብሸት ታየን አደንቃለሁ)።

ሁለት፣ ዜናውን እንደሰማሁ መጀመሪያ የመጣልኝ ጥያቄ “እና ምን ያስገርማል?” የሚለው እንጅ፣ “ድርድሩ የተጠየቀው መቼና በእነማን በኩል ነው?” የሚለው አልነበረም። የአለም የፖለቲካ ታሪክ በግጭትና በድርድር የተሞላ ነው። “ድርጅቶች ይጋጫሉ፣ ይደራደራሉ፣ ምን ያስገርማል?”፣ በፖለቲካ ትግል” በመቃብሬ ላይ ..” የሚባል ነገር የለም። “ለምን ሰበር ዜና ሆነ ታዲያ?’ እንዳትሉኝ፣ ሰበር ዜና ማለት አስገራሚ የሆነ ዜና ማለት አይደለም ።
TPlF
ሶስት፣ ቀጥሎ የመጣልኝ ጥያቄ “ኢህአዴግ ከግንቦት7 ጋር መደራደር ለምን ፈለገ?” የሚለው ነው። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ” የፖለቲካ ድርጅቶች የእንደራደር ጥያቄ የሚያቀርቡት መቼ ነው?” የሚለውን ማየት ነበረብኝ። የፖለቲካ ድርጅቶች በአብዛኛው ለድርድር የሚቀመጡት ህልውናቸውን ለማቆየት ወይም ተደራድሮ የሚገኝ ጥቅም ሳይደራደሩ ከሚገኝ ጥቅም ( ጉዳት) የተሻለ ሆኖ ሲያገኙት ነው። በዚህ ንድፈሀሳብ ላይ ተመስርቶ ኢህአዴግ እና ግንቦት7 አሁን ያሉበትን ቁመና መፈተሽ ይገባል። ኢህአዴግ ከመለስ በሁዋላ ኢህአዴግ አለመሆኑ ይታወቃል።ሊቀመንበሩ ድርጅቱን ይዞ ለመቀጠል ተቸግሯል፣ (ምናልባትም በቅርቡ ይፋ የሚሆኑ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከፍተኛ የገንዘብ ችግር አጋጥሞታል)፣ የ ህዝቡ ልብ እንደሸፈተ አውቋል፣ ወጣቱ ለውጥ እንደሚፈለግ ተረድቷል፣ ሰራዊቱ የሚተማመንበት ሀይል እስኪያገኝ እንጅ እንደሚከዳው ተገንዝቧል። በአጠቃላይ መጪው ጊዜ ለኢህአዴግ ብሩህ አለመሆኑን ግንባሩ ጠንቅቆ ያውቃል። በዚህ አደጋ ውስጥ ሆኖ ጊዜ ለመግዛትና ድርጅቱን ለማጠናከር የድርድር ጥያቄ ቢያቀርብ አይገርምም።

ግንቦት7 ለኢህዴግ “አጣዳፊ ጠላት” (immediate threat) ሆኗል እያልኩ አይደለም፣ ነገር ግን እምቅ ጠላት ( potential threat) መሆኑን አልጠራጠርም ። አንድ ድርጅት ለሌላው ድርጅት አጣዳፊ ጠላት የሚሆነው ፣ አሁን ባለበት ሁኔታ፣ ከተቃራኒው ድርጅት የበለጠ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ የሀይል ሚዛን ሲኖረው ነው። ግንቦት7 ኢህአዴግን ዛሬውኑ ለማስወገድ አይችልም ምክንያቱም ከኢህአዴግ የሚበልጥ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ ሀይል የለውምና ፤ ነገር ግን በጊዜ ሂደት እንደሚያስወግደው መገመት ይቻላል፣ ከመለስ በሁዋላ ያለውን ሁኔታ ብታጠኑ የኢህአዴግ የሀይል ሚዛን ወደ ታች እየወረደ፣ በአንጻራዊ መልኩ የግንቦት 7 የሃይል ሚዛን ደግሞ ወደ ላይ እየወጣ ነው፣ የ ግንቦት7 መሪዎች በዚህ አመት የሀይል ጥቃት እንደሚጀመሩ አስታውቀዋል፣ በዚህ አመት ቀርቶ በሚቀጥሉት 3 አመታት ጥቃት ከፈጸሙ እያደጉ መሆኑን የሚያሳይ ነው ( 4 ፓይለቶች መክዳታቸውንም አንዘንጋ)። የፖለቲካ ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ሁለት አይነት ሀይል አለ። አንዱ መቺው ሀይል ( hard power) ሲሆን ሌላው ደግሞ መለስተኛው ሀይል ( soft power) ነው። መቺው ሀይል የሚባለው ወታደራዊው ሀይል ነው። በዚህ በኩል ኢህአዴግ ከግንቦት7 በብዙ እጅ የሚልቅ ጉልበት አለው። ነገር ግን ግንቦት7ትም በዚያው ጎዳና እየተጓዘ መሆኑን መርሳት የለብንም።

መለስተኛ ሀይል (soft power) የሚባለው ደግሞ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎችን፣ ጥራት ያለው የሰው ሀይልን ( መሪም ተከታይም)፣ ህዝባዊ ድጋፍ ፣ የካፒታል አቅም ፣ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት የመሳሰሉትን ያካትታል። ግንቦት7 በዚህ በኩል ከፍተኛ ጉልበት መገንባቱን መመስከር ይችላል። ከኢህአዴግ ተመጣጣኝ የሆነ ካፒታል ባይኖረውም፣ ከሌሎች ድርጅቶች የተሻለ ካፒታል( ገንዘብ)እንደሚኖረው ከስራዎቹ መገመት ይቻላል ። የተማሩ ሰዎችን በመያዝ በኩልም፣ ከኢህአዴግ ቢበልጥ እንጅ አያንስም። በፕሮጋንዳውና በህዝብ ድጋፍ በኩልም እንዲሁ። እንዲያውም የግንቦት7 የፕሮፓጋንዳ ማሽኖች ከኢህአዴግ የተሻሉ ለመሆናቸው ብዙ አስረጅ አይጠይቅም፣ የግንቦት7 ራዲዮና ዌብሳይት እስከዛሬ ሳያቋርጥ እየሰራ ነው፣ ጠንካራ የፓልቶክ ደጋፊዎችም አሉት። ኢህአዴግ ራሱ የሚሰራላቸው ፕሮፓጋንዳም ቀላል አይደለም። ኢህአዴግ ቢያንስ በውጭ ያለውን ድጋፉን፣ በተለይም ለጀመራቸው የአባይ እና ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ ለመለመን ሲል ግንቦት7ን ለድርድር ቢጠይቀው አይገርምም። ኢሳት የግንቦት7 ነው ብሎ ስለሚያስብም፣ ኢሳትን እንዲያስቆምለት ልደራደርህ ቢል አሁንም አይገርምም። (በኢሳት ላይ እንኳ ቀልድ የለም፣ መደራደር ከፈለገ ከኢሳት ጋር እንጅ ከግንቦት7 ጋር ሊሆን አይችልም፣ ምክንያቱም ግንቦት7 ስለኢሳት ምንም የሚያገባው ነገር የለምና፣ ከኢሳት ጋር ድርድር ከተጀመረም ለኢሳት የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ዙሪያ እንጅ፣ ከስራው ጋር የተያያዘ እንደማይሆን መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ)
eprdf
አራት፣ ኢህአዴግ ከግንቦት7 ጋር ብቻ ነው ወይ ድርድር የመረጠው? እኔ ባለኝ መረጃ ኢህአዴግ በእነ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሀቅ በኩል ላለፉት 4 ወራት ከእነ አቶ ሌንጮ ለታ ድርጅት ጋር ሲነጋገር ነበር። ይህን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ከኦብነግ ጋርም እንዲሁ ተደጋጋሚ የድርድር ጥያቄዎች ቀርበዋል። እነዚህ ድርጅቶች በፓርላማ “አሸባሪ” የተባሉ ናቸው። እና ለግንቦት7 ጥያቄ ቢያቀርብ ምን ይደንቃል? ፖለቲካ እኮ ፊት ለፊት የምትናገርውና በውስጥ የምታደርገው የተለየ ነው። That is politics. በነገራችን ላይ ” አንደኛው የአለም ጦርነት የተጀመረው በድብቅ በሚካሄድ ፖለቲካ የተነሳ ነው” ተባለና ፖለቲካ ግልጽነት እንዲኖረው ተብሎ አዲስ አስተሳሰብ ለረጅም ጊዜ ተራመደ። ፖለቲካ ግን ዛሬም ፊትና ጀርባ እንደያዘ ቀጥሎአል።

አምስት፣ “ጥያቄው በእነማን በኩል ቀረበ?’ የሚለውንም ለራሴ አንስቻለሁ። የድርጅቱ መሪዎች መልሱን ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፣ ነገር ግን የራሴን ግምቶች አስፍሬአለሁ። አንድ፣ በቅርቡ በእነአቦይ ስብሀት የተመራ ቡድን አሜሪካ ከርሞ ሄዷል። ሁለት፣ ፕ/ር ኤፍሬም አሜሪካ ከርመዋል፣ ኦነጎችን ለማስታረቅም ላይ ታች ሲሉ ከርመዋል። ሶስት፣ በቅርቡ የአውሮፓ እና የካረቢያን አገሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፣ ብዙ ዲፐሎማቶችም አዲስ አበባ ነበሩ። አራት፣ ኖርዌይና ሆላንድ ሁሌም ተቃዋሚዎችን ለማቀራረብ ይሰራሉ። ይዋል ይደር እንጅ ትክክለኛውን መልስ እናገኛለን። መልሱ ግን ከጠቀስኳቸው ሰዎች ወይም አገሮች በአንዱ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። የእንደራደሩ ጥያቄ ለመቅረቡ ግን መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ። እስከዛው እንደ ጋዜጠኛ መላ ምት በማስቀመጥ ምርምራችን መቀጠሉ ተገቢ ነው።
ginbot 7
ስድስት፣ ግንቦት7 ለምን ይህን ድርድር ይፋ ማድረግ ፈለገ? ኢህአዴግ አስቀድሞ በኢቲቪ ” ከግንቦት7 ጋር ሲያደርግ የነበረው ድርድር ከሸፈ” ብሎ መግለጫ ቢሰጥ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቡት? የግንቦት7 ደጋፊዎች የድርጅቱን መሪዎች በጥሩ አይን የሚያዩዋቸው አይመስለኝም፤ ግንቦት7ትም ውስጥ አለመተማመን ይፈጠርና ድርጅቱን ከሁለት ሊከፍለው ይችል እንደነበር መገመት ይቻላል፣ ዲሞክራሲያዊ ነኝ የሚል ድርጅት ከአባሎቹና ከህዝቡ የሚደብቀው ነገር መኖር የለበትም። ግንቦት7 በመግለጫው “ድርድር መደረግ ካለበት ከሁሉም ድርጅቶች ጋር ነው፣ ሁሉንም ነገር ግልጽ እናደርጋለን የምንደብቀው የለንም” ብሎአል። ትክክል ነው። እውነተኛ ድርድር ሲጀመር ለጊዜው ይፋ የማይወጡ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ድርድር ተጠየቅሁ ብሎ መግለጫ መስጠቱ ግን የሚገርም አይመስለኝም። ግንቦት7 መረጃውን ከኢህአዴግ ቀድሞ ይፋ ማድረጉ ድርጅቱን ከመከፋፈል ማዳን ብቻ ሳይሆን ንቅናቄው ከኢህአዴግን አንድ እርምጃ ቀድሞ የ ሚያስብ መሆኑን ለማሳየትም ጠቅሞታል።

በአገር ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች በኢህአዴግ በኩል ያለውን መልስ ይዘውልን እንደሚቀርቡ ተስፋ እናድርግ።

“ትግራይ በመወለዴ ልዩ ነገር ይገባኛል የሚል አመለካከት የለኝም” –ዶ/ር ኃይሉ አረአያ (ቃለ-ምልልስ)

0
0

“ትግራይ በመወለዴ ልዩ ነገር ይገባኛል የሚል አመለካከት የለኝም”
“እነ አቶ ልደቱ የፖለቲካ መጠቀሚያ ነው ያደረጉን”

 

ዶ/ር ኃይሉ አርአያ

ዶ/ር ኃይሉ አርአያ በኢዴፓ በኋላም በቅንጅት አመራርነት አገልግለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የአንድነት ፓርቲ ምክር ቤት አባል ናቸው፡፡ የ”ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ከዶ/ር ኃይሉ አርአያ ጋር ሰፊ ቃለመጠይቅ አድርጓል፡፡ በሃገር ቤት የሚታተመውን ሎሚ መጽሄት በውጭ ሃገር ለማታገኙት ወገኖች ቃለምልልሱን ዘ-ሐበሻ ትካፈሉት ዘንድ አስተናግዳዋለች።

dr hailu areayaሎሚ፡- እርስዎ ያዘጋጁዋት የነበረችው “ፕሬስ ዳይጀስት” ለዲፕሎማቲኩ ማህበረሰብ ኢትዮጵያን በተመለከት መረጃ የሚሰጥ “ታብሎይድ” ነበር፡፡ የትንሿን ጋዜጣ ዝግጅት ለምን አቋረጡት?

ዶ/ር ኃይሉ፡- ጋዜጣዋ አሁንም እየተዘጋጀች ነው፡፡ እኔ ግን ያቋረጥኩት ጋዜጣዋ የምትፈልገውን ጊዜ እና ጥረት ማበርከት ባለመቻሌ ነው፡፡ በአጭሩ ብዙ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ዝግጅቱ ብዙ ጊዜ የመጠየቁን ያህል ደግሞ ብዙ ጥቅምም አያስገኝም፡፡ ከዚያም ባሻገር ስራው የሦስት ሰዎች ስራ ነበር፡፡ ግን የሦስት ሰዎችን ጥረት የሚጠይቅ ስራ አልነበረም፡፡ በዚያን ጊዜ ሌላ የምሰራው ስራ ስላልነበረ ሁላችንም ትንሽ ትንሽ እየሰራን ነበር የምናሣልፈው፡፡ የአንድ ሰው ስራ ነው፡፡ የአንድ ሰውም የሙሉ ጊዜ ስራ አልነበረም፡፡ ስለዚህ ጊዜ ከማባከን ያንን ለአንድ ሰው ትቶ ሌሎቻችን ሌላ ስራ ብንሰራ ይሻላል በሚል ነው የተውነው፡፡
ሎሚ፡- በደርግ ዘመን “የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲቲዩት” ኃላፊ እርስዎ እንደነበሩ ይታወሳል፤ ኢንስቲቲዩቱ ምን አስተዋጽኦ አበረከተ? አሁን የብሔረሰብ መብት ተከብሯል ከሚባለው ጋር ሲያነጻጽሩት “የብሔረሰብ ጥናት ኢንስቲቲዩት” ሰርቶታል የሚሉትን አብይ ጉዳይ ሊገልፁልን ይችላሉ?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በመጀመሪያ የኢንስቲቲዩቱ ኃላፊ አልነበርኩም፡፡ ኢንስቲቲዩቱ ራሱ ኃላፊ ነበረው፡፡ እንደውም ኃላፊው የሚኒስትር ማዕረግ ነበረው፡፡ በኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የብሔረሰቦች ጉዳይ መምሪያ በሚባለው ቦታ በምክትል ኃላፊነት ነበር የምሰራው፡፡ ያ መምሪያ ነው ተቋሙን ያቋቋመው፡፡ ብዙ የሚሰሩ ስራዎች ነበሩ፤ ጥናቶች ነበሩ፤ ሕገ መንግስቱን ለማዘጋጀት ብዙ ጥናቶች መደረግ ነበረባቸው፡፡ የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የነበረው የኛ መምሪያ ብዙ ስራ ሊሰራ ስለማይችል የግዴታ ራሱን ችሎ ለመንቀሣቀስ “ኢንስቲቲዩቱን” መመስረት አስፈላጊ ነበር፡፡ ስለዚህ “የብሔረሰቦች ጥናት” ኢንስቲቲዩት ተቋቋመ፡፡ ነገር ግን በመምሪያችን ስር ነበር፡፡
የእኛ መምሪያና ኢንስቲቲዩቱ አብረው ነበር የሚሰሩት፡፡ ጥናቶች ሲካሄዱ አብረን ሁላችንም እንሳተፋለን፤ አመራር የሚሰጠው ግን ከመምሪያው ነበር፡፡ በሁሉም ዘርፍ ለአምስት ዓመት ያህል ነው ኢንስቲቲዩቱ ጥናት ያካሄደው፡፡ በዛን ጊዜ የተሰሩ ስራዎች ኢህአዴግም ከመጣ በኋላ ብዙ ጠቅሞታል ብዬ ነው የምገምተው፡፡ ያኔ የህግ መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ሰው አሁን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ያሉ ይመስለኛል፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህግ አማካሪ ናቸው፡፡ ሌሎችም በሀገሪቱ አሉ የተባሉ ምሁራን ተሰባስበው ከፍተኛ ጥናት አካሂደዋል፡፡ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ጥናቶች ናቸው የተካሄዱት፡፡ ጥናቶቹ አልባከኑም ብዬ አምናለሁ፡፡ በርግጥ የተፈለገው ሕገ መንግስት በተደረጉት ጥናቶች መሠረት ተቀርጿል፡፡ መቅረፅ ብቻም አይደለም፤ ስራ ላይም ውሏል፡፡ በተለይ በብሔረሰቦች ላይ የተደረገው ጥናት በዝርዝር ነው የተካሄደው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የብሔረሰቦች መብት ምን ያህል ተከብሯል የሚለው የትኩረት መጠን ካልሆነ በስተቀር ያኔ የተደረገው የብሔረሰቦች ጥናት እና የተሰጠው የብሔረሰቦች ትኩረት በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ስለ ብሔረሰቦች መብት መከበር እንደ አዲስ የጀመረ በማስመሰል ሲናገር ስሰማ በጣም አዝናለሁ፡፡ በዛን ጊዜ የነበረውን ነገር አልተከታተለውም፤ ውጊያ ላይ ስለነበር ሊከታተልም አይችልም፡፡ ውጊያ ላይ እያለ ባይከታተልም ስልጣኑን እና ኢንስቲቲዩሹኑን ከተረከበ በኋላ በዛን ጊዜ የነበሩ ሰነዶችን መመርመር ይችል ነበር፡፡ ሰነዶቹ አሁንም ይኖራሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ኢህአዴግም ተጠቅሞባቸዋል ብዬ ነው የምገምተው፡፡
“የብሔረሰቦች መብት” ኢህአዴግ እንደ አዲስ የጀመረው ጉዳይ አይደለም፡፡ በባህላቸው፣ በቋንቋቸው…በሌላውም አቅጣጫ ኢህአዴግ እንደ አዲስ እንደጀመረ አድርጐ ነው የሚያወራው፡፡ ይህንን ትዝብት መቼም ለታሪክ እንተወዋለን፡፡ የደርግ ስርዓት ሌሎች ድክመቶች ሊኖሩበት ይችላል፡፡ የብሔረሰቦችን ጉዳይ በተመለከት ግን መሠረቱን ያስቀመጠው የደርግ ስርዓት ነው፡፡ ኢህአዴግ ምናልባት አጠናክሮታል፣ አስፋፍቶታል ማለት ይቻላል፡፡ አንደ አዲስ ጀመርኩት የሚለው ነገር ግን ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ይህ ሊስተካከል ይገባል፤ ምክንያቱም ታሪክ ራሱ ቁጭ ብሎ የሚመሰክርበት ጉዳይ ስለሆነ በዝምታ ማለፍ ነው የሚሻለው፡፡ የብሔረሰቦችን ጉዳይ በተመለከተ እንዲሁ ለይስሙላ ከሚደረግ በስተቀር ነፃ የሆነ ለውጥ ተደርጓል ብዬ አልገምትም፡፡ ምናልባት በጥቅም፣ በሀብት አከፋፈል በጀትን በተመለከተ ለብሔረሰቦች የሚመደበው ገንዘብ አሁን በከፍተኛ መጠን ጨምሯል፡፡ ሌላው የቅርፅ ጉዳይ ነው፡፡ ብሔረሰቦች የሕገ-መንግስት ባለቤት ሆነዋል፡፡ ህገመንግስትን መስርተዋል፤ ሕገ መንግስት አላቸው፤ ሰንደቅ አላማም ያውለበልባሉ…እነዚህ ከቅርፅ አኳያ ለውጦች ናቸው፡፡ እነዚህ የቅርፅ ለውጦች በተግባር ቢደገፉ ጥሩ ይሆኑ ነበር፡፡ ነገር ግን አልተደገፈም፡፡ ምክንያቱም ብሔረሰቦች አሁንም መሠረታዊ የሆኑ ችግሮች አሉባቸው፡፡ መሠረታዊ የምላቸው በኔ በኩል የህግ መከበር ነው፡፡
ህጐች ይጣሳሉ፤ መብቶች ይደፈራሉ፤ ምን ያህል ነፃነት እንዳላቸውም እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ምንም እንኳን ስርዓቱ ፌዴራል ቢሆንም ቅርፁ ፌደራላዊ ቢሆንም በተግባር ግን “አሃዳዊ” ነው፤ ምክንያቱም በደርግ ጊዜ መንግስት “አሃዳዊ” ነበር፡፡ ክልሎች የአስተዳደር መብት ነበራቸው፡፡ ያም ቢሆን በሚገባ ተግባራዊ አልሆነም፡፡ ከይዘት አኳያ በደርግ አሃዳዊ መንግስትና በኢህአዴግ ፌደራላዊ መንግስት መካከል ልዩነት አለ፡፡ “ደርግ” የነበረው የውስጥ አስተዳደር ነው፤ የኢህአዴግ ግን ፌዴራል ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ብሔረሰቦች ሕገ መንግስት አላቸው፣ የራሣቸው መንግስትና ባንዲራ….አላቸው፡፡ በዛን ጊዜ የነበረው ኢሠፓ መዋቅሩን ታች ድረስ አውርዶ ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው ኃይል እርሱ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ምንም እንኳን በቅርፅ “ፌደራላዊ” ቢባልም ሀገሪቱን ጠርንፎ በአሃዳዊ መልክ ነው የሚያስተዳድረው፡፡ በሁለቱ መካከል የይዘት ልዩነት የለም፡፡ ለውጡ ምንድነው? ብትለኝ ጥቂት ነው፡፡ እምቢልታና መለከት የሚያስነፉ አይደሉም፡፡ አሁንም ብሔረሰቦች ይጨቆናሉ፡፡
የሚጨቁኗቸው ደግሞ የራሣቸውን ቋንቋ የሚናገሩ የራሣቸው ወገኖች ናቸው፡፡ ስለዚህ አሁንም ከጭቆና እና ከችግር አልወጡም፡፡ ፌደራላዊ ስርዓት ጥሩ ሆኖ ከአሃዳዊ ሲለይ አልታየም፡፡ ሕዝቡ ቢጨቁነኝም ይጨቁነኝ፣ ቢረግጠኝም ይርገጠኝ፣ የኔን ቋንቋ እስከተናገረ ድረስ የሚል ከሆነ ሌላ ነገር ውስጥ ነው የሚገባው፡፡ ለኔ ቋንቋ አይደለም ትልቁ ነገር:: ከዛ ባለፈ ሕግ መከበር አለበት፤ ፍትህ መከበር አለበት፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት መከበር አለበት፡፡ እውነተኛ ነፃነት መኖር አለበት፡፡ አሁን የብሔረሰቦች ቀን ተብሎ “በዓል” ይከበራል፡፡ ሰባት ዓመት ሙሉ ተከብሯል መሰለኝ፡፡ ስምንተኛው በዓል በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ነው የሚከበረው፡፡ በአንድ በኩል ይህ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም በብሔረሰቦች መካከል ያለውን ስሜት በማጠናከር እና በራስ መተማመንን ለማምጣት የሚረዳ ነገር ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንዲሁ ዘፈንና ጫጫታ ሆኖ መሠረታዊ ጉዳዮች ሣይደረጉ ሲቀሩና እዛው በቦታው ሲመለስና እንደ ድሮው የሚጨቆን ከሆነ ምንድነው ትርጉሙ? የሰው ልጅ ፍላጐት ከዛ ያለፈ ነው፡፡ ይሄ ግን እየተመለሰ አይደለምና ከዳንሱና ከጭፈራው ጐን ለጐን የብሔረሰብ ነፃነት ሊከበር ይገባል፡፡ ሊሰሩ የሚችሉበት ነፃነት ይኑራቸው፡፡ ትምህርትን፣ የጤና አገልግሎትን ያየን እንደሆነ ተስፋፍቷል፡፡ “በቁጥር” ተስፋፍቷል፤ “በጥራት” ግን ገና ነው፡፡ መስፋፋቱ ጥሩ ነው፤ ግን ቁጥር ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ይሄ መንግስት አሁን እየጠቀሰልን ያለው ቁጥር ነው፡፡ ይህን ገንብቻለሁ እያለ በሁሉም ዘርፍ ይገልፃል፡፡ ያ ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በጥራት መሻሻል አለበት፡፡ ቁሣዊና ሰብአዊ ልማት አለ፡፡

መንግስት እየተገበረ ያለው ቁሣዊ ልማትን ነው፡፡ ሰብዓዊ ልማት የለም፡፡ ሰብዓዊ ልማት ያለ ነፃነት፣ ያለፍትህ፣ ያለ ዴሞክራሲ ይሄን ያህል ጠቃሚ አይደለም፡፡

ሎሚ፡- በሚያዝያ 1983 ዓ.ም. ደርግ ባቋቋመው ሸንጐ የመጨረሻ ስብሰባ ላይ አባል እንደመሆንዎ ተገኝተው ለኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም የተናገሩትን ለዚህ ትውልድ መረጃ እንዲሆን ቢያስታውሱን?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ጊዜው በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ሀገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ነበረች፡፡ ሀገሪቱን እመራለሁ፣ ግንባር ቀደም ነኝ የሚለው የፖለቲካ ድርጅት (ኢሠፓ) በየጊዜው እየተሰባሰበ የሀገሪቱን ሁኔታ እየገመገመ ሕዝቡ ምን እንደሚልና በሚለው መሠረት ምን መደረግ እንዳለባቸው ማወቅ ነበረበት፡፡ ግን ሳያደርግ ቀረ፡፡ ስብሰባዎች እንዲካሄዱ ነበር ብዙ ጊዜ የምንጐተጉተው፡፡ ከዛ ከፓርላማ ስብሰባው በፊት ኢሠፓ ተሰብስቦ የዚህችን ሀገር ሁኔታ እንዲገመግም፣ መፍትሄ እንዲፈልግና ተግባራዊ እንዲያደርግ በየጊዜው በሚደረጉ የመሠረታዊ ድርጅት ስብሰባዎች እንከራከር ነበር፡፡ ነገር ግን ምንም አይነት ውጤት አልተገኘም፡፡ ነገሮች እየተባባሱ ሄዱ፡፡
በመጨረሻ የተደረገው ተስፋ የመቁረጥ ዓይነት ሙከራ ነው፡፡ ሙከራው ቢዘገይም ከሚቀር ይሻላል፡፡ ምንም ካለማድረግ የተወሰነ ነገር ማድረግ ጥሩ ነው፡፡ ይሄ የግል ስሜቴ ነው፤ የግል ስሜቴን ለመግለፅ ነው የሞከርኩት፡፡ ግን አሁን መለስ ብዬ ያለንበትን ሁኔታ ሳይ ደግሞ ያን ያህል ጊዜ መዘግየት አልነበረብንም እላለሁ፡፡ ጊዜ መስጠት አልነበረብንም የሚል እምነት አለኝ፡፡ አሁን ደግሞ ለዚህ ስርዓት አላግባብ ተገቢ ያልሆነ ጊዜ እየሰጠን ነው፡፡ በስልጣን በቆየ ቁጥር እየበሰበሰ ነው የሚሄደው፡፡ በተፈጥሮው ስልጣን ያሞስናል፤ ያበሰብሳል፡፡ አንድ ወገን፣ አንድ ኃይል ስልጣን ላይ ከሚፈለገው በላይ በቆየ ቁጥር እየበሰበሰ ይሄዳል፡፡ ይሄ እኮ የተፈጥሮ ሂደት ነው፡፡ ሌሎች ሀገሮች የፕሬዚዳንትና የጠ/ሚኒስትር (በተለይ “የፕሬዚዳንት”ን) የስልጣን ቆይታ የቱንም ያህል ጥሩ ቢሆን ከስምንት አመት በላይ አያልፍም፡፡ ስለዚህ ሀገሪቱን ትጐዳለህና ቦታ ልቀቅ ነው የምትባለው፡፡ የኛ መንግስት እስካሁን ድረስ ብዙ ቆይቷል፡፡ 22 ዓመት ብዙ ነው፡፡ በኔ እምነት መበስበስ ከጀመረ ቆይቷል፡፡ የመበስበሱ ምክንያቶች በየጊዜው እየታዩ ናቸው፡፡ መቀጠል የለበትም ብለን መናገር አለብን እንጂ ዝም ማለት የለብንም፡፡ ከዚህ በፊት ዘግይተን ከነበረ እናዝናለን፡፡ በስንፍናችን እናዝናለን፤ እንቆጫለን፡፡ ነገር ግን ከዚያ ተምረን ያ መደገም የለበትም እንላለን፡፡ የሀገራችን ጉዳይ መፍትሄ ማግኘት አለበት፡፡ ገደብ የሌለው ስልጣን መፍትሄ ማግኘት አለበት፡፡ እነሱ ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ሕዝብ ስለፈለጋቸው አይደለም፡፡ በእንዴት ዓይነት ሁኔታ ስልጣን ላይ እንደወጡ የኢትዮጵያ ሕዝብም እነሱ ራሣቸውም ያውቁታል፡፡ አዲሱ ትውልድ በተለይ ወጣቱ ትውልድ መናገር መቻል አለበት፡፡ ለመብቱ ለነፃነቱ መቆም መቻል አለበት፡፡ አስፈላጊ ከሆነም ደግሞ መስዋዕትነት መክፈል አለበት፡፡
ሎሚ፡- በዚያ ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ ግድያ ሲፈጸም የድፍረት ንግግር ለመናገር የገፋፋዎት የተለየ ምክንያት ምን ነበር?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በወቅቱ ካለፈው ታሪኬ የተነሣ እንደ አደገኛ ሰው የታየሁ አልመሰለኝም፡፡ ፍራቻም አልነበረኝም፡፡ እንዲያውም የትግራይ ተወላጅ መሆኔን
ያስታወስኩት እኮ ዘግይቼ ነው፡፡ ጐሣ፣ ጐጥ… እየተነሣ ሲመጣ ነው ይሄ ነገር
መጉላት የጀመረው፡፡ እንጂ በፊት እኔ የዚህ ተወላጅ ነኝ፣ የዛ ተወላጅ ነኝ የሚል
ነገር አልነበረም፡፡ ስሜቱም አልነበረኝም፤ ትግራይ ነው የተወለድኩትና በተወለድኩበት አካባቢ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው ያደግኩት፡፡ በአጋጣሚ ትግራይ ማይጨው ራያ ተወለድሁ፡፡ የተወለድኩበትን አካባቢ እቀበላለሁ፡፡ ግን እዚያ ትግራይ በመወለዴ ልዩ ነገር ይገባኛል የሚል አመለካከት የለኝም፡፡ እዚያ መወለዴም ስጋት አላሳደረብኝም፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ሰው ነኝ፤ ከዛ በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ በዛ ምክንያት እንዲህ እሆን ወይ ጉዳት ይደርስብኝ ይሆን ወይ ብዬ አላስብም፡፡ እንደውም በዛን ጊዜ ኮ/ል መንግስቱ ፊት እንደዛ ስናገር ሰዎች በጣም ደንግጠው ከአካባቢው ለመራቅ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ በኋላ ደግሞ ታስታውስ እንደሆነ ኮ/ል መንግስቱ በፃፉት ጽሁፍ /እኔ እንኳን መፅሐፉን ሣይሆን በቴፕ ነው የሰማሁት/ “ዶ/ር ኃይሉ እንደዛ የተናገረው ምናልባት ዘመዶቹ አምቦ ስለደረሱ ይሆናል፤ /ሣቅ/ ነው፤ ለኔ እንዲህ ዓይነት ስሜት ነው የፈጠረብኝ” ብለው ነበር፡፡ በጣም አሣዘነኝ፤ ምናቸው ነው ለኔ ዘመድ የሚያደርጋቸው?… በጣም አዘንኩ፤ የማንነት ጉዳይ አንዳንዴ ብወድም ባልወድም ብልጭ ማለቱ አይቀርም፡፡ ትኩረት የምሰጠው ነገር ግን አይደለም፡፡ ፍርሃት አልነበረብኝም፡፡ ያኔ የትግራይ ተወላጆች ብቻ አይደለም የሚገደሉት፤ ማንም ያንን መስመር የሚቃወም ሁሉ ነበር የሚገደለው፡፡

 
ሎሚ፡- ኮ/ል መንግስቱ እንደዛ ከተናገሩ በኋላ ቤትዎ ገብተው በሰላም አደሩ?… ሌሊቱን የት አሣለፉ? የኮ/ል መንግስቱ የደህንነት ሰዎች ምላሽስ ምን ነበር?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ምንም ችግር አልደረሰብኝም፡፡ ሰዎች ወስደው የት እንዳሳደሩኝ አላስታውስም፡፡ ብቻ የሆነ ቦታ ነው የወሰዱኝ፡፡ የተለየ ነገር አልገጠመኝም፡፡ አስታውሳለሁ፤ ኮ/ል ተስፋዬ ወ/ስላሴ /የደህንነት ኃላፊው/ “ጐሽ ጥሩ ነው ያደረግከው” ብሎ መለስ ቀለስ እያለ እየፈራ እየቸረ ነው ያናገረኝ፡፡… /ረዥም ሳቅ/፡፡… በኋላ ጡረታ እንድወጣ ደብዳቤ ተፃፈ፡፡ በነገራችን ላይ ቀደም ብዬ ነበር ጡረታ እንድወጣ የጠየቅኩት፡፡ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ጥያቄዬ ተግባራዊ ሳይሆን ቆይቶ ነበር፡፡ ወዲያው የተወሰደውን እርምጃ ሰዎች ነግረውኛል፡፡ …ኮ/ል መንግስቱ በጣም ተቆጥተው ነበር፡፡ ነገር ግን ብዙዎቹ ለምነን አባብለን ነው ያስታገስናቸው ብለውኛል፡፡ አንደኛው የማውቀው ወዳጄ “እንዲያውም እግራቸው ላይም እስከመውደቅ ደርሰናል“” ሲል ነበር የነገረኝ፡፡ ይህ ምን ያህል እውነት እንደሆነ አላውቅም፡፡ መናደዳቸው አያከራክርም፤ እግዚአብሔር ይመስገን የከፋ ነገር ግን አልደረሰብኝም፡፡ በእሣቸው የደህንነት ሰዎችም የደረሰብኝ ነገር የለም፡፡
ሎሚ፡- እንግዲህ ውይይታችን ሰፊ ነውና ወደኋላም ወደፊትም እያልን ጥያቄ እናንሳ፤ ወደ ቅርብ ጊዜው እንመለስና ወደ ቅንጅት (ምርጫ 97) ግርግር እንምጣ፡፡ በወቅቱ አቶ ልደቱ የነበረው አቋም በእርግጥም የኢዴፓ ውሣኔ ነበር? በቅርቡ አቶ ልደቱ ከመፅሔታችን ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ “የስልጣን ጥያቄ ስላልነበረን የበሰሉ ሰዎች ቢመሩት ይሻላል ብለን ነው ዶ/ር ኃይሉ አርአያን እና ዶ/ር አድማሱን ከቤታቸው አምጥተን ስልጣን እንዲይዙ ያደረግነው” ብሏል፡፡ ይሄን እንዴት ይመለከቱታል?

 
ዶ/ር ኃይሉ፡- በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ መናገር አልፈልግም፡፡ ይሄ በእኔና በአንተ ቃለ መጠይቅ ላይ ብቻ ተገልፆ የሚያልቅ አይደለም፡፡ በጣም ሰፊ የሆነ ታሪክ ነው፡፡ ግን መናገር ካለብኝ አንድ ወጣት (ታምራት ታረቀኝ) የሚባል መፅሐፍ ፅፎ ነበር፡፡ ምናልባት እዚያ ላይ ያለውን ብደግመው በቂ ይሆናል፡፡ ተጠቅመውብናል ማለት እችላለሁ፡፡ በዛን ጊዜ የነበሩ የኢዴፓ አመራር /እነ አቶ
ልደቱ/ ተጠቅመውብናል፡፡ ከተጠቀሙብን በኋላ ጊዜው ሲመጣ እኛን ወደ ጐን ለማግለል ሞክረዋል፡፡ አቶ ልደቱ ብዙ ውይይት የሚከፍት ሰው ነው፡፡ መጠቀሚያ አደረገን እንጂ በምሁርነቴ ጠርቶ ይሄ ቦታ ይገባሀል ብሎ አይደለም ቦታ የሰጠኝ፡፡ በኔ ውስጥም የሚሰማኝ ይሄ ነው፡፡
ሎሚ፡- አቶ ልደቱ “ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከቅንጅት ጋር የትም አንደርስም” ብሎ
ይከራከር ነበር ሲልም ገልጿል፤ ይሄስ እውነት ነው?

ዶ/ር ኃይሉ፡- ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ በተቃራኒው ነው እሱ የገለፀው፡፡ ከቅንጅት ጋር አብሮ ስለመስራት ነበር የኔ ክርክር የነበረው፡፡ አቶ ልደቱ በወቅቱ ብዙ ነገር የተወሳሰበና የተተበተበ ነገር ነበር የሚያነሣው፡፡ እንዲያውም “ቅድመ ሁኔታዎች” በሚል ይከራከር ነበር፡፡ በኔ በኩል በቅንጅት ዙሪያ መግባባት አለብን የሚል አቋም ነው የነበረኝ፡፡ በአቶ ልደቱ የተገለፀው የተገላቢጦሽ ነው፡፡
ሎሚ፡- ኢዴፓ ያንን አጋጣሚ አክሽፏል ብለው ያምናሉ?
ዶ/ር ኃይሉ፡- አዎ! አምናለሁ! በሁለት ምክንያት፡፡ አንደኛ ከምርጫ በኋላ የቅንጅት አመራር የአራቱ ፓርቲ አመራር ከልደቱ በስተቀር ለመዋሃድ ውሣኔ ሲያሳልፍ እና መሪዎቹ ፊርማቸውን ሲያሳርፉ በስምምነቱ ላይ አቶ ልደቱ በኢዴፓ ሰነድ ላይ ማህተም ለማድረግ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማህተሙ ሳያርፍ ቀረ፡፡ ይሄ የሆነው ማህተሙን የሙጥኝ ብሎ በመያዙ ነው፡፡ ሁለተኛ ለምርጫ ቦርድ በቅንጅት የተጠየቀው የውህደት ጥያቄ ተግባራዊ እንዳይሆን የሚል ደብዳቤ በማስገባቱ ያለጥርጥር ያንን ዕድል አክሽፎታል ብዬ አምናለሁ፡፡ ይሄን ስል ግን ሌሎችም ችግሮች አልነበሩም ማለቴ አይደለም፡፡ ሌሎችም ችግሮች ነበሩ፡፡ ቀሪዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ራሣቸው አስፈላጊውን ጉባኤ አካሂደው ማሟላት ያለባቸውን ነገሮች አሟልተው አንድ መሆን ሲገባቸው ሣይችሉ ቀርተዋል፡፡ ያ ብቻም ሣይሆን ያከሸፈው ሌሎች የውስጥ ችግሮችም ነበሩ፡፡
hailuሎሚ፡- በወቅቱ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ሲመረጡ በአቶ ልደቱ ላይ ምን ዓይነት ስሜት ነበር የታየው?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ብርቱካን በተመረጠችበት ጊዜ አቶ ልደቱ መበሣጨቱ ምንም የሚያከራክርና አንድና ሁለት የሚባል ነገር አይደለም፡፡ በጣም በጣም ተበሣጭቷል፡፡ በግል የተመለከትነው ነገርም ነው፡፡
ሎሚ፡- ከእርስዎ ጋር በኢዴፓም ሆነ በቅንጅት ውስጥ ሲሰሩ የነበሩት ዶ/ር አድማሱ ገበየሁ ከፖለቲካ የራቁበት ምክንያት ምንድን ነው?
ዶ/ር ኃይሉ፡- ይህንን ጥያቄ መመለስ የሚገባው እሱ ዶ/ር አድማሱ ነው፡፡ እንደው ስገምተው ግን አንደኛ የትምህርትና የስራ ዕድልም ስላገኘ ይመስለኛል፡፡ ለባለቤቱም ጭምር ነው ይህ ዕድል የመጣው፡፡ ምክንያቱም የኛን ሃገር የመሰለ ፖለቲካ በሩቅ የሚከናወን አይደለም፡፡ ምናልባት አንድ ቀን ይመለስና የጀመረውን ትግል ይቀጥልበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ የዚህ ሀገር ተቃዋሚዎች ሁኔታ ደግሞ የሚያበረታታና ተስፋ የሚያጭርም አይደለም፡፡ ብዙ ችግሮች አሉ፡፡ አሁን አንዳንድ መሻሻሎችና መስተካከሎች የሚኖሩ ይመስላሉ፡፡ ምናልባት እነዚህ የ33ቱ ፓርቲዎች የመሰባሰብና አንድ ላይ ለመስራት የመወሰን ጉዳይ የሚያበረታታ ነው፡፡ ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራችን በፊትም ቢሆን እንኳን ሩቅ ላለና እዚህ ሀገር ውስጥ ላለም የሚያበረታታ ተስፋ የሚሰጥ አይደለምና አልፈርድበትም፡፡ እንዲህ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ወደሀገሩ ጠቅልሎ መጥቶ እገባበታለሁ ካለ መልካም ነው፡፡ ውስጡ ግን ማሰቡና መጨነቁ አይቀርም፡፡
ሎሚ፡- አቶ ልደቱ በሕይወትህ ምን የሚፀፅትህ ነገር አለ ለሚለው ጥያቄጠይቄው ነበር፡፡ ሲመልስም “በሕይወቴ ከሚፀፅተኝ ነገር አንዱ ምሁራንን ማመኔ ነው፡፡ ለምሁራን የነበረኝ ግምትና አስተሳሰብ ነው የሚጸጽተኝ” ብሏል፤ አባባሉን እንዴት አዩት?
ዶ/ር ኃይሉ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ማንን አመነና ነው፡፡ ምንስ ተጓደለበት ነው የኔ ጥያቄ፡፡ ሣልፈልግ ወደዚህ የማልወደው ነገር ውስጥ እያስገባኸኝ ነው፡፡ የሚፀፅተኝ ሊል አይገባም፤ ምንም የሚፀፅት የተፈጠረበት ነገር የለም፡፡ የእሱን ተወውና በራሴ ግን በምሁራን ዙሪያ ከተባለ “ምሁራን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሣታፊ አለመሆናቸው ነው የሚያሣዝነኝ፡፡ የማመንና ያለማመን ጉዳይ አይደለም፡፡ አምነናቸው ጉድ አደረጉን፤ አሳልፈው ሰጡን የሚል መንፈስ ያለው
ይመስላል አባባሉ፡፡ በምን ጉዳይ ምንድን ነበር የጠበቀው? ምንስ ቀረበት?

 

 

አዲሱ ነጠላ ዜማ፣ ድርድር –ከክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

0
0

andargachew
በሳውዲ የተነሳው የወገን ሰቆቃ ገና አልበረደም። ስቃዩ የበለጠ ሲከፋ እንጂ ሲቀንስ አላየንም። ለውጭ ምንዛሪ ማግኛ ሲባል ልክ እንደ ባርያ ንግድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል የተላኩት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በገዥው ፓርቲ እንደታሰበው አልሆነም። እንዲያውም ሌሎች መዘዞችን አስከትሎ መጥቷል። ዲያስፖራው እንደገና ተነሳ። ለቦንድ ግዢና ለግንቦት ሃያ በዓላት የሚሰባሰቡትም ጭምር ገዢው ፓርቲን ማውገዝ ጀመሩ። የስደተኛው ጎርፍም እንደሱናሚ ማእበል ያንን ጎራ ማጨናነቁ ግልጽ ነው። ወቅት እየጠበቀ የሚነሳው የክረምቱ ነቀርሳ አሁን በነበረከት ስምዖን ላይ ጠና ያለ ይመስላል። ይህ ህመም ማስታገሻ ያስፈልገዋል። ዘላቂ ሳይሆን ግዚያዊ ማስታገሻ። መቼም ለነቀርሳ ዘላቂ መፍትሄ የለውም። ለግዜው ግን እድሜ ማራዘሚያ … የድርድር ጥያቄ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የቀድሞ አየር ወለድ አሰልጣኝና የበረራ ደህንነት ባለሙያ የአቶ ከፍያለው ሃይሉ አጭር የህይወት ታሪክ

0
0

 

አቶ ከፍያለው ሃይሉ

አቶ ከፍያለው ሃይሉ

አቶ ከፍያለው ሃይሉ

፡ የቀድሞ አየር ወለድ አሰልጣኝና የበረራ ደህንነት ባለሙያ አጭር የህይወት ታሪክ

አቶ ከፍያለው ኃይሉ ከአባታቸው ከአቶ ኃይሉ ተሰማ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጉዳይ ዓለሙ ግንቦት 29 ቀን 1942 ዓ.ም. በጎጃም ክፍለ ሀገር በደብረ ማርቆስ ከተማ ተወለዱ፡፡

ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ በደብረ ማርቆስ ከተማ የቀድሞ ስሙ ንጉስ ተክለሀይማኖት እየተባለ በሚጠራው ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እያሉ ሀገራቸውን ለማገልገል በነበራቸው ከፍተኛ ፍላጎት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1959 ዓ.ም. የኢትዮጵያ የምድር ጦር አየር ወለድ ክፍልን ተቀላቀሉ፡፡ ከዚያም ተገቢውን ወታደራዊ ስልጠና በፍቼ ማሰልጠኛ ጣቢያ ከአጠናቀቁ በኋላ ደብረዘይት በሚገኘው የአየር ወለድ ክፍል የመጀመሪያ የዝላይ ስልጠና ትምህርት አጠናቀው በቀጣይነት የ9ኛው ኮማንዶ ኮርስ ስልጠናቸውን እና ሌሎችንም ወታደራዊ ትምህርቶች በብቃት አጠናቀቁ፡፡ ከዚያም አየር ወለድ ጦር በተሰማራባቸው የስራ መስኮች  ሁሉ ፣ አቶ ከፍያለው በብቃት ግዳጃቸውን ተወጥተዋል።

አቶ ከፍያለው በተሰለፉበት የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ባሳዩት ንቁ ተሳትፎና ወታደራዊ ብቃት ከሌሎች ዕውቅ ጓዶቻቸው ጋር ለ3ኛው የአየር ወለድ የፓራ ኮማንዶ አሰልጣኝነት ኮርስ ተመርጠው በአጥጋቢ ውጤት አጠናቀዋል፡፡ በጊዜው አብረዋቸው ከአጠናቀቁት ታዋቂና ብቁ የኮማንዶ አስተማሪዎች ውስጥ እብስቱ አያሌው፣ ድንበሩ በኩረ፣ ታዬ ቶላ፣ ተስፉ ተፈራና ፀጋዬ ሳይንቴ ይጠቀሳሉ፡፡ ዛሬ ሁሉም በተለያየ መስክ ተሰልፈው ለሀገራቸው መስዋዕትነት ከፍለዋል፡፡

አቶ ከፍያለው በደብረዘይት ከተማ የፓራ ኮማንዶ አስተማሪ በመሆን ብዙ የሀገር ገንቢ ወጣት የሰራዊት አባላትን በማፍራትና የሌሎችን ነፃ አውጭ ሰራዊት አባላት በማሰልጠን ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ቀጥሎም በዕድገት በህብረት የእውቀትና የሥራ ዘመቻ ተሰማርተው በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ወገናቸውን አገልግለዋል፡፡

ከ1970 – 1982 ዓ.ም. ድረስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ ደህንነት ስራና በአሰልጣኝነት ተመድበው  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከማድረጋቸው በላይ በተለያዩ የውጭ እና ወዳጅ አገሮች ጥያቄ የበረራ ደህንነት ትምህርት ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ከሰጡባቸው አገሮችም ውስጥ የመንና ጋና ይገኙበታል፡፡

በታሪካዊው የሕዝብ ለሕዝብ የኪነት ቡድን አባል በመሆንም አብረው ተጉዘዋል፡፡ በአጠቃላይ ለ24 ዓመታት ባገለገሉበት ከላይ በተጠቀሱት አርአያነት ባለው ተግባሮቻቸው የተለያዩ ሽልማቶችንና የምስክር ወረቀቶችን አግኝተዋል፡፡

አቶ ከፍያለው ኃይሉ ከወ/ሮ የኔነሽ ጥላሁን ጋር ህጋዊ ጋብቻ ፈጽመው 37 ዓመታት በፍቅርና በመተሳሰብ ኖረው 3 ልጆችን አፍርተው ለቁም ነገር አብቅተዋል፡፡ ወደ አሜሪካ በመምጣት ኑሮአቸውን በመጀመሪያ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከዚያም ወደ ካሊፎርኒያ ግዛት በመዛወር በሳንሆዜ ከተማ ኑሮ መስርተው እስከዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ ከሀገሩና ከወገኑ ርቆ በውጭ የሚኖር ወገናቸው በማሰባሰብ፣ በማፅናናትና በመርዳት የሚታወቁ ነበሩ፡፡

አቶ ከፍያለው ኃይሉ ፈርሀ እግዚአብሔር ያደረባቸው ለተቸገሩ ደራሽ ቅንና ሩህሩህ በሁላችንም ዘንድ ሲታወሱ የሚኖሩ ባህሪያቸው በመሆኑ በአበረከቱት ቅን አገልግሎትና በጎ ተግባር ከሀዘናችን እንጽናናለን፡፡

ለባለቤታቸው ለወ/ሮ የኔነሽ ጥላሁን ፣ ለልጆቻቸው፣ ለመላ ቤተሰባቸውና ወዳጅ ዘመድ መጽናናትን እንመኛለን ቸሩ አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን፡፡

ወጣቷ ድምፃዊት ስለሳዑዲ አረቢያ የወገኖቻችን ስቃይ “ይጣራል በርቀት”ስትል አቀነቀነች

0
0

(ዘ-ሐበሻ) “ይጣራል በርቀት የወገን ድምጽ ስሙኝ ይላል” ስትል ወጣቷ ድምፃዊት ሰላማዊት አበባየሁ በሳዑዲ አረቢያ እና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተሰቃዩና እየሞቱ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን አቀነቀነች። ልብ በሚነካ ድምጽ፣ ለኢትዮጵያውያኑ በዋሽንግተን ዲሲ የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍና አርቲስት ታማኝ በየነ በሳዑዲ አረቢያ ኢምባሲ ደጃፍ “shame on you” ሲል የተናገረውን በዘፈኗ ውስጥ ያካተተችው ይህች ወጣት ድምፃዊት ምንም እንኳ ዜማው ከጥላሁን ገሰሰ “ይህች አጋጣሚ” ዘፈን ጋር ቢመሳሰልም፤ በዚህ ‘ይጣራል በርቀት’ ዘፈን ያሳየችው ብቃት ወደ ፊት ተስፋ እንዲጣልባት አስችሏታል። ዘፈኑ የሚከተለው ነው፦

ወጣቷ ድምፃዊት ስለሳዑዲ አረቢያ የወገኖቻችን ስቃይ “ይጣራል በርቀት” ስትል አቀነቀነች

አቶ ሽመልስ “ኢሕአዴግ ለግንቦት 7 ጋር የድርድር ጥያቄ አላቀረበም”አሉ

0
0

Shimeles Kemal andargachew (ዘ-ሐበሻ) ግንቦት 7 ኢሕአዴግ የ እንደራደር ጥያቄ አቀረበልኝ ካለ በኋላ የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን የኢትዮጵያ መንግስትን ምላሽ ለመስማት ወደ አቶ ሽመልስ ከማል ደውሎ “ለኢሳት ምንም አልናገርም” ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በሃገር ቤት ለሚታተመው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ መንግስት ለግንቦት ሰባት ምንም ዓይነት የ እንደራደር ጥያቄ አለማቅረቡን ገልጸዋል።

“ኢህአዴግ ለደርድር ጥያቄ አቅርቦልኛል በሚል እያናፈሰ ያለው መሰረተ ቢስ የፈጠራ ወሬ መሆኑን አቶ ሽመልስ ከማል የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ።” በሚል ሰንደቅ ጋዜጣ ባስነበበው መረጃው “ግንቦት 7፤ ህዳር 23 ቀን 2004 ዓ.ም በኢሳት ቴሌቪዥን በኩል ባወጣው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በሁለት ወር ጊዜያት ውስጥ ለሶስት ጊዜያት ያህል የእንደራደር ጥያቄ አቅርቦልኛል ብሏል። ንቅናቄው ለእንደራደር ጥያቄው ምላሽ በሚል ባሰፈረው ሐተታ የኢህአዴግ የእስካሁኑ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ ይገዛል ካለ በኋላ ስማቸው ባልተገለጸ መልዕክተኞች በኩል ደርሶኛል ያለውን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄው በዋናነት ያየው ኢህአዴግ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ ነው በማለት ለድርድሩ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል።” ያለው ጋዜጣው
“አቶ ሽመልስ ከማል ግን በመንግስት በኩልም ሆነ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በኩል ለግንቦት 7 የቀረበ እንደራደር ጥያቄ እንደሌለ አረጋግጠው መንግስት ቢፈልግ ጌታው እያለ ከተላላኪው ጋር ምን ያደራድረዋል ሲሉ ጠይቀዋል።” ብለዋል ሲል ሰንደቅ ዘግቧል።

አቶ ሽመልስ የድርድሩን ጥያቄ “የእነዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቅጥፈት መሆኑን ጠቅሰዋል” ያለው ሰንደቅ “በዚህ መንገድ እያሞኙ ገንዘብ መሰብሰብ ለምደዋል፤ ይህም ውሽት ለዚሁ ተግባር የተፈበረከ ነው” ብለዋል ሲል ዘግቧል። አቶ ሽመልስ ኢሕአዲግ ለድርድር ጋብዘኝ ሲል ግንቦት 7 መግለጹን “ይህ ዓይነቱ አካሄድ በባዶ ሜዳ ራስን አግዝፎ ለማየት ከመመኘት የሚመነጭ ቅዥት ነው ብለውታል።” ማለታቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ ለህትመት የበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ አትቷል።


ሰማያዊ ፓርቲ የአጼ ምኒልክን 100ኛ ዓመት የእረፍት ቀን ለመዘከር በጃንሜዳ የጠራው ኤግዚቢሽን እና የፓናል ውይይት ተከለከለ

0
0

minilik
ከብርሃኑ ተ/ያሬድ
የፊታችን ታህሳስ 3 የእምዬ ምኒልክን 100ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል! በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዘሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡

በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልነሳጥችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥባቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የሚገርመዉ ደግሞ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ ነበር፡፡

እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!?

ያም ሆነ ይህ ዝግጅቱ በታቀደለት ምልኩ እንደሚፈፀም በተለመደ ቁርጠኝነት ላይ ነን! ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡
ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!

በመርካቶ ከፍተኛ ቃጠሎ ተከሰተ፤ በመቀሌም በድጋሚ በተነሳ ቃጠሎ የንግድ ቤቶች ወደሙ

0
0

merkato 1
(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ መርካቶ የተነሳው የ እሳት ቃጠሎን ይህ ዜና ለዘ-ሐበሻ እከደረሰበት ሰዓት ድረስ የከተማዋ የ እሳት አደጋ ሊቆጣጠረው አለመቻሉን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታወቁ። ዘጋቢዎቻችን እንዳሉት መሃል መርካቶ ከከምዕራብ ሆቴል ወደ በርበሬ በረንዳ በሚወስደው መንገድ ወይም በተለምዶው ቦምብ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተነሳ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ከፍተኛ ንብረት እየወደመ ነው። በዛው አካባቢ በሚገኙት ሜትሮ ሆቴል. ሐረር ዳቦ ቤት፣ ዓለም ሽንሽንና ጌጣጌጥ መሸጫ መደብሮች በዚህ ቃጠሎ የተጠቁ ሲሆን ከአንድ ሰዓት በላይ በፈጀው የእሳት ማጥፋት ሥራ ቃጠሎውን ሊቆጣጠሩት አለመቻላቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ትናንት ማክሰኞ በትራንስፎርመር መቃጠል ምክንያት 70 ዎርክሾፖች በ06 ቀበሌ (ኢንዱስትሪ ዞን) በእሳት ቃጠሎ መውደማቸውን አብረሃ ደስታ ከመቀሌ መዘገቡን ዘ-ሐበሻ ላይ አስነብበን ነበር። ዛሬም አብርሃ ከመቀሌ እንደጻፈው “ዛሬ ሮብ ሌሊት ደግሞ በዓዲ ሐቂ ገበያ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሶ ብዙ ንግድ ቤቶች ወድመዋል። በተመሳሳይ አጋጣሚ ዛሬ ሮብ ጠዋት በዓዲሹምድሑን ሰፈር በእሳት ቃጠሎ አደጋ ንብረት ወድመዋል።” ብሏል።
አብርሃ ‘መቐሌ በሁለት ቀናት ዉስጥ በሦስት አቅጣጫዎች (ሰሜን፣ ምዕራብና ደቡብ) የእሳት አደጋ ሰለባ ሆናለች። የማክሰኞው አደጋ በትራንስፎርመር መቃጠል ምክንያት ሲሆን የዛሬው የዓዲ ሐቂና የዓዲሹምድሑን ቃጠሎ መንስ ኤ ግን እስካሁን በትክክል አልታወቀም።” የደረሰበትን መረጃ በፌስቡክ ገጹ አካፍሏል።

አብርሃ የመቀሌውን ዜና ከዘገበ በኋላ በአንዳንድ ሰዎች የተሰጠውን አስተያየት ሲተች “መቐለ በ18 ሰዓታት ዉስጥ ሦስት የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች አስተናግዳለች (06፣ ዓዲሐቂና ዓዲሹምድሑን)። ህዝብ ተጨንቀዋል፣ አዝነዋል፣ ተገርመዋል። ባለስልጣናቱ ግን ምንም ዓይነት ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ እንኳን ዝግጁ አይመስሉም። ካድሬዎቹም አደጋው ከመከላከል ይልቅ ‘ንብረት ወደመ’ ስንል ‘ቃላት ተሳሳቱ’ እያሉ ያሸፉብናል። በመቐለ ከተማ በወደመው ንብረት ለማዘን ስለ እሳት አደጋው መስማት በቂ ነው። ስለ ቃላት አመራረጥ ማተኮር ግን ጥሩ አይመስለኝም። ምክንያቱም ጥረታችን ፅሑፍ መፃፍ ሳይሆን ስለ ደረሰው አደጋ መረጃ መስጠት ነው።” ብሏል።

ስለ ኮሌስትሮል: The Truth about Cholesterol

0
0

በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ታትሞ የወጣ
ኮሌስትሮል የሁሉም እንስሳት ህዋሳት አካል የሆነ የማይሟሟ ነጭ የቅባት አይነት ሲሆን በበርካታ የሰውነት ተግባራት ውስጥ ቁልፍ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ሆርሞን ዝግጅት ውስጥ አለ፤ ሰውነት ቫይታሚን ዲ መጠቀም እንዲችል በመርዳቱም ይታወቃል፡፡ የሴቶችና የወንዶችን ፆታዎች ሆርሞኖች ቴስቴስቴሮን እና ኤስትሮጅን እንዲሁም ሀይል አጠቃቀማችንን የሚያስተካክለው አድሬናል ሆርሞን ምርትም ግብአት ነው፡፡ ቅባት ነክ ምግቦችን ስንመገብ ለመፍጨት የሚያገለግለው ሀሞትም ከኮሌስትሮል ነው የሚዘጋጀው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የህዋሳቶቻችን ሽፋኖችም እንዲሁ ስሪታቸው ኮሌስትሮል ነው፡፡ ነርቭ ጫፎችን በመሸፈንም የነርቭ መልዕክቶች የተቀላጠፈ እንዲሆኑ ይረዳል፡፡

ኮሌስትሮል ራሱ የሚዘጋጀው በዋናነት በጉበት ውስጥ ሲሆን አብዛኛዎቹ የሰውነት ህዋሳቶችም ኮሌስትሮልን ይሰራሉ፡፡ በደም ውስጥ ሊፖፕሮቲንስ በተሰኙ ተሸካሚዎች ይዘዋወራል፡፡
cholestorl
የኮሌስትሮል ምንጮች

ያለው በቂ በመሆኑም ከሰውነት ውጪ የሚመጣ ኮሌስትሮል አስፈላጊ አይደለም፡፡ ከውስጥ ተጨማሪ ምግብ አያስፈልግም፡፡ ይሁንና የምንወስዳቸው ምግቦች ውስጥ ቅባት ስለሚገኝ ጤናማውን ምጣኔ በአመጋገባችን ምክንያት እናዛባዋለን፡፡ ከእነዚህ ኮሌስትሮል በብዛት ከምንወስድባቸው ምግቦች መካከል እንቁላል፣ ስጋና ሌሎች ሙሉ ቅባት ያላቸው የእንስሳት ተዋፅኦ ውጤቶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ሁሉም ከእንስሳት የሚገኙ ምግቦች ኮሌስትሮልን የሚይዙ ሲሆን ከኮሌስትሮል ነፃ የሆኑት ከእፀዋት የሚገኙ ምግቦች ብቻ ናቸው፡፡

በተለይ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከእንስሳት ተዋፅኦ የሚገኙት እንቁላል፣ ስጋ እና ቅቤ የምቾት ምግቦች ተብለው ስለሚቆጠሩ የሚበዛው ሰው ትንሽ ገንዘብ ሲያገኝ እነዚሁኑ ምግቦች ይሸምትና ይጠቀማል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከተማ አካባቢ ብዙ መቀመጥ እና ኮሌስትሮል በዝቶ የሚገኝባቸውን ፈጣን ምግችና ጥብሳ ጥብሶችን የመመገብ ልምዶች እየሰፉ በመምጣታቸውም ኮሌስትሮል ጉዳቱ በቅጡ ሳይታወቅ ለበርካቶች የጤና ጠንቅ እየሆነ መምጣቱን ባለሞያዎች ይገልፃሉ፡፡

ጥሩ ኮሌስትሮል፣ መጥፎ ኮሌስትሮል

ኮሌስትሮል በሰውነት ውስጥ የሚዘዋወርበት ዋነኛ ሁለት መልክ ያለው ሲሆን አንደኛው ‹‹ጥሩ›› ሌላኛው ‹‹መጥፎ›› ተብለው በተለምዶ ይጠራሉ፡፡ መጥፎ የሚባለው አይነት የኮሌስትሮል መልክ ዝቅተኛ ግዝፈት ያለው ኮሌስትሮል ሲሆን ከጉበት ወደ ህዋሳት የሚደርሰው ኮሌስትሮል በዚህ መልክ ይገኛል፡፡ በደም ውስጥ መጠኑ ከልክ ሲያልፍ የደም መተላለፊያ መስመሩን ሊደፍን ስለሚችል ነው መጥፎ የተባለው፡፡ የደም ቧንቧዎቹ መደፈን ደግሞ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች የሚደርሰው ደም እንዲገታ እና ለልብ እና የደም ቧንቧ በሽታዎች እንድንጋለጥ ያደርጋሉ፡፡

ጥሩው የሚባለው ከፍተኛ ግዝፈት (ዴንሲቲ) ያለው ኮሌስትሮል መልክ የደም ቧንቧዎችን ጨምሮ በህዋሳት ውስጥ የተጠራቀመውን ትርፍ ኮሌስትሮል መጥጦ ወደ ጉበት የሚያስወግድ በመሆኑ በጥሩነቱ ይነሳል፡፡ ጥሩም መጥፎም ለመባል መጠኑ ወሳኝ መሆኑን የሚናገሩት ባለሞያዎች የኮሌስትሮል ልኬትን ተለክቶ ማወቅና ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ጨምረው ይገልፃሉ፡፡

ጤናማ የኮሌስትሮል

መጠን ምን ያህል ነው?
ኮሌስትሮል ለተለያዩ የሰውነት ወሳኝ ተግባራት አስፈላጊ እንደመሆኑ በሰውነት ውስጥ እንዲገኝ ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ኮሌስትሮል ያስፈልገናል የሚለው እና መጠኑም በጤናማ ክልል ውስጥ ስለመገኘቱ እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ጤናማ የኮሌስትሮል መጠን በሐኪሞቹም ዘንድ ቁርጥ ያለ ቁጥር የሚቀመጥለት አይደለም፡፡ በአማካይ ግን በደም ውስጥ የሚገኝ የኮሌስትሮል መጠን በሊትር ከ5.5 ሚሊሞል መብለጥ እንደሌለበት ስምምነት አለ፡፡ ይህ መጠን የሚፈቀደው ግን ሙሉ ጤነኛ ለሆኑና በተለያዩ ምክንያቶች ለልብና ተያያዥ ህመሞች ተጋላጭነት ለሌላቸው ሰዎች ነው፡፡ ፆታ፣ ዕድሜ፣ በቤተሰብ ውስጥ ያለ የልብ ህመም ታሪክ፣ ሲጋራ የማጨስ ልምድ፣ ከልክ ያለፈ ክብደት እንዲሁም ከፍተኛ የደም ግፊት ወይም ስኳር ህመም በመጠኑ ላይ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት በሁለት ወይም ከዚያ በላይ ሁኔታዎች በአንድ ሰው ላይ የሚስተዋሉ ከሆነ ዝቅተኛ ግዝፈት ያለው ኮሌስትሮል (መጥፎ ኮሌስትሮል) መጠን ከ2.5 ሚሊሞል በሊትር መብለጥ አይኖርበትም፡፡

በመሆኑም የአንድ ሰው የኮሌስትሮል መጠን በተለያዩ ተጨማሪ አጋዥ ምክንያቶችም የሚወሰን በመሆኑ ለሁሉም ሰው የሚሰራ ምጣኔ ማስቀመጥ በባለሞያዎቹ አይመከርም፡፡ ይህ ግለሰብ በሐኪም ታይቶ ሊወሰን የሚገባ እንደሆነም ይጠቆማል፡፡ ነገር ግን ማንም በሊትር ከ6 ሚሊሞል በላይ ኮሌስትሮል በደሙ የሚገኝ ሰው በባለሞያ ክትትል ሊደረግለት ይገባል፡፡

የኮሌስትሮል ጠንቆች

በሰውነት ውስጥ ኮሌስትሮል በጉበት ውስጥ ስለሚመረት ተጨማሪ ኮሌስትሮል ከምግብ ማግኘት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሰውነት ለራሱ ተግባራት በቂ ኮሌስትሮል ያዘጋጃል፡፡ ይሁንና የተለያዩ የእንስሳት ተዋፅኦ ምግቦችን በምንመገብበት ወቅት የምንወስዳቸው ቅባቶች በሰውነታችን ከተመረተው ኮሌስትሮል ጋር በጉበት አማካይነት ተቀላቅለው በሊፕሮቲን መልክ ወደ ደም ዝውውር ስርዓት ይቀላቀላሉ፡፡

በደም ዝውውር ውስጥ የእነዚህ ውህዶች መጠኑን ባለፈ ሁኔታ መገኘት ቅባቶች በደም ቧንቧዎች ውስጥ እንዲጠራቀሙ ያደርጋል፡፡ ይህ የቧንቧዎች በቅባት መጠቅጠቅ ቧንቧው እንዲጠብ ቀስ እያለም ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ያስገድደዋል፡፡ የደም ፍሰቱ መገታት ለከፋ የልብ ህመም እንዲሁም በጭንቅላት የደም መቋረጥ (ስትሮክን) ይዞ ይመጣል፡፡ ስትሮክን ተከትሎ በሚገጥም የመውደቅ፣ የነርቮች መዛበት አሊያም ስራ ማቆም የበረቱ የጤና ችግሮች ይከሰታሉ፡፡

ኮሌስትሮልን መቆጣጠሪያ ስልቶች

ኮሌስትሮል የጤና እክል ከመፍጠሩ በፊት መቆጣጠር መከላከል ይቻላል፡፡ ዋነኞቹ መንገዶችም ከአመጋገብ እና የአኗኗር ስታይል ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ቅባት ያላቸውን የተጠበሱ ስጋ እና የስጋ ውጤቶችን መመገብ ይቀንሱ፡፡ የድንች ጥብስ (ቺፕስ)፣ በርገር በተለይ ቺዝ በርገር፣ ኬክ ብስኩትና አጠቃላይ ጥብሳ ጠብሶች የኮሌስትሮል ምንጭ በመሆናቸው ከእነዚህ በሚቻል መጠን መራቅ ይመከራል፡፡

ከምግብ እና መጠጦች በተጨማሪ በሰውነት ውስጥ ያለን የኮሌስትሮል ምጣኔ በመቆጣጠር በኩል የእለት ተዕለት ልምዶችና ባህሪያቶቻችንንም ወሳኝ ናቸው፡፡ አልኮል መጠጦች በተለይ ተቀላቅለው የሚጠጡ መጠጦች የደም ኮሌስትሮልን ሊጨምሩ ስለሚችሉ በቀን ከሁለት በላይ እንዲጠጡ አይመከርም፡፡ ሲጋራም ይከለከላል፡፡ ሲጋራ አደገኛ የሚባለውን ዝቅተኛ ግዝፈት ያለው ኮሌስትሮል ወደ ደም ቧንቧ እንዲገባ በማመቻቸቱ ስለሚታወቅ ሲጋራ አያጭሱ ሲሉ ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡ የአካል ብቃት እንቀስቃሴ ጥሩውን ኮሌስትሮል መጠን በሰውነት ውስጥ የጨመረም ጥቅም ስላለው በሳምንት ቢያንስ ለ3 ቀናት ለ30 ደቂቃ ፈጣን እርምጃ ቢያደርጉ እንኳ ኮሌስትሮል ምጣኔን በከፍተኛ ሁኔታ መቆጣጠር ይችላሉ፡፡ ክብደትዎ በጤናማ ክልል ውስጥ እንዲሆን ይጣሩ፣ የስኳር መጠንዎን መቆጣጠርም ይመከራል፡፡ የእንስሳት ተዋፅኦ ምግቦች ኮሌስትሮል ስላላቸው ተቆጣጠሯቸው ሲባል አይመገቡ ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ የምግብ አይነቶች ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ እንደ ካልሲየም አይነት ንጥረ ነገሮች ስለሚይዙ መጠናቸውን አያብዙ እንጂ ጨርሰው አያስወግዷቸው፡፡

በምግብ እንዲሁም በአኗኗር ስታይል ጤናማነት ኮሌስትሮልን መቆጣጠር ቢቻልም ይህ ይከብደኛል ላሉት ምዕራባውያን የኮሌስትሮል መቀነሻ መድኃኒቶች ተሰርተው ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ከፋርማሲዎች ይሸጥላቸዋል፡፡ የተሻለው ግን ባለሞያ ጋር ቀርቦ ምርመራ እና እርዳታ ማግኘት ተመራጩን መፍትሄም መከተል ተመካሪ ነው፡፡ የአመጋገብ እና አኗኗር ልምዳችን ግን በእጃችን ነውና ጥንቃቄ አይለየን፣ ጤና ሁኑ!

 

 

ልብን የሚነካዉ የኢትዮጵያዉያን ጉዞ በሳዑዲ አረቢያ

0
0

ከሳዲቅ አህመድ

በሰላም እንደገቡ በሰላም የመዉጣት ግዴታን እየተገበሩ መሆናቸዉን ይናገራሉ። በአብዛኛዉ ሰላም ወዳድ ህግ አክባሪ ቢሆንም ጥቂቶች በሚፈጽሙት ደባ ሰለባ ላለመሆን “ዉጡ እስክተባልን ድረስ እነዉጣል” ይላሉ ተጓዦቹ። የትም ቢሆን የት እምነትን ተግባሪ መሆናቸዉን እያስመሰከሩም ነበር…ለሶላት ሲጠራም አይደም አዋቂዎች፤ዉሉ ያልታወቀ ጉዞን  ህጻናት እንኳ ከሰጋጆችም ነበሩ። የስንብት ዳእዋ (ሰበካ) ተደርጎላቸዋል፤መንፈስንና አካልን ለማነቃቃት እንዳቅሚቲ ኳስን የሚጫወቱም ነበሩ። ብቻ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ቢገደዱም ፊታቸዉ ላይ የተስፋ ብርሃንን ያበሩ…ሆዳቸዉን ባር-ባር ብሎት የእንባ ዘለላን በጉንጮቻቸዉ ላይ ያፈሰሱም ነበሩ።
በደል ከበዛባት ኢትዮጵያ በደልን ሸሽተዉ በሙስሊም ወንድሞቻቸዉ ጉያ ቢሸሸጉም ተሸሽገዉ እስኪያልፍ ያለፋል ቢሉም፤ ከዚያ የጥገኝነት ጉያ ዉጡም ተባሉ። ግን በመለኮታዊ-ምሪት ‘የተበደለ ሰዉ እንባ ሊፈራ እንደሚገባ ተጠቁሟል’ ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅልታ፣ እሪታ፣ዋይታ ከሁለቱ አንባገነኖች አንዱ…ወይም ሁለቱም… የዚህን የመንፈስ-እንባ ካሳ በምድርም ካልያም በወዲያኛዉ አለም መክፈላቸዉ አይቀሬ ነዉ።
ከተመላሾቹ መካከል አንዱ አባት ያራስ-ቤት ልጁን ጸጉር እየዳበሰ እራሱን በጥልቅ ፈገግታ አንጾ ነበር! ደስ አይልምን?..ልብ ያለዉ ልብ ይበል!



 

በመርካቶ ዛሬ በተነሳው የእሳት አደጋ ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎች (Updated)

0
0

(Updated) አሁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ በመርካቶ አካባቢ በቀድሞው ቦምብ ተራ (የአሁኑ ጆንያ ተራ) የተነሳው ቃጠሎ በመጨረሻም በቁጥጥር ስር ውሏል። በአደጋው ከቀደም ብለን በሰበር ዜና 4 ሰዎች መጎዳታቸውን የዘገብን ሲሆን አሁን ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከ10 በላይ ማደጉ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአደጋው የደረሰው የንብረት ጥፋት ከፍተኛ ሲሆን እስካሁን በቁጥር የተቀመጠ መረጃ አልተገኘም። ሆኖም በርካታ ሱቆች ግን ወድመዋል።
ቀደም ሲል ከ2 ሰዓት በፊት የዘገብነው ዜና ከዚህ ሥር አለ።
merkato 1 በመርካቶ የተነሳው የእሳት አደጋ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ አልበረደም። የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ዘጋቢዎች እንዳሉት ከሆነ ከቀኑ 8 ሰዓት የተነሳው እሳት ቃጠሎ በእሳት አደጋ ብርጌድ ሊጠፋ ባይችልም 4 ሰዎች በቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸው ወደ ተክለሃይማኖት ሆስፒታል ተወስደዋል።

እሳቱ በተለምዶ ቦንብ ተራ (የአሁኑ ጆንያ ተራ) ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ ሁሉ መካለሉን፤ በአካባቢው የዘይት ሱቅ በመቃጠሉ የእሳት አደጋው መባበሱን የገለጹት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች የእሳት አደጋው ብርጌድ አደጋውን ሊቆጣጠር ያልቻለው በአካባቢው ያሉ ሱቆች በልብስ የተጨናነቁ በመሆናቸው ተብሏል። የእሳት አደጋው ኮልፌ፣ እንዲሁም አራዳ ድረስ በመሄድ የማጥፊያ ውሃዎችን እየቀዳ እንደሚገኝ የገለጹት ምንጮች ለምን መርካቶ አካባቢ ውሃ እንደማይቀዱ የተገለጸ ነገር የለም።

እስካሁን ድረስ ወደ 3 የሚጠጉ የአስፓልት መሸጋገሪያ ያላቸው መንግዶች ስር ያሉ ሱቆች መቃጠላቸውን ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአየር መንገድ እሳቱን ለማጥፋት እግዛ ተገኝቷል ብለዋል። በአካባቢው የ እሳት አደጋውን ተከትሎ ዝርፊያ ሊከሰት ይችላል በሚል ፍራቻ እንዳለ የገለጹት ዘጋቢዎቻችን ነጋዴዎች ንብረታቸውን በግልጽ መኪናዎች በመጫን ከአካባቢው እየሸሹ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል በአካባቢው ያሉ ነጋዴዎች የእሳት አደጋ አጥፊዎች በቅድሚያ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ በገንዘብ እንደሚደራደሩ ያላቸውን ብሶት ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ተናግረዋል። አንዳንድ ነጋዴዎች እሳቱ አደጋ ሆን ብሎ እንዲባባስ እና ቶሎ እንዳይጠፋ እየተደረገ ያለ ሴራ አለ ብለው የሚያምኑ ሲሆን “መንግስት ቦምብ ተራ(ጆንያ) ተራን ለማፍረስና ለባለሃብት ለመስጠት እየተጠቀመበት ያለው ሴራ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።

የዘ-ሐበሻ 5ኛ ዓመት፡ ዘ-ሐበሻን ይርዱ፤ የዘ-ሐበሻ ክንድ ይሁኑ

0
0

zehabesha 5th year
የተከበራችሁ የዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረገጽ አንባቢዎች፦

እነሆ “ዕውነት ያሸንፋል የሚለውን መርህ እንደያዘ ዘ-ሐበሻ ጋዜጣና ድረ ገጽ ዴሴምበር 28 ቀን 2013 የተመሰረተበት 5ኛ ዓመት ይሞላል። ባለፈው የኖቬምበር ወርን “የአንባቢዎች አስተያየት መቀበያ ወር” በሚል ሰይመን ከእናንተ አንባቢዎቻችን ገንቢ አስተያየቶችን አንድ ወር ሙሉ ተቀብለናል። ድረገጻችንን በየእለቱ በመጎብኘት አስተያየትም በመስጠት ለምታስተካክሉን አንባቢዎቻችን ምስጋናችንን በዚህ አጋጣሚ እየገለጽን፤ ይህን የዲሴምበር 2013 ወርን ደግሞ እስካሁን ዘ-ሐበሻን በምን መልክ እንርዳ ስትሉ ለነበራችሁ እና ለመርዳት ለምትፈልጉ “ዘ-ሐበሻን የመርጃ ወር ስንል” ሰይመነዋል። እስከ ዲሴምበር 31 ቀን 2013 ድረስም ዘ-ሐበሻን ለመርዳት ለምትፈልጉ በፔይፓል የመክፈያ ዘዴ አዘጋጅተናል።

እንደሚታወቀው ዘ-ሐበሻ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ጉዳይ ለሕዝብ መረጃ ከሚያደርሱና ከሚመረጡ የተለያዩ የዜና ምንጮች መካከል አንዷ ሆና መቀመጧ እናንተን አንባቢዎቻችንን ብቻ ሳይሆን እኛ አዘጋጆቹንም አስደስቶናል። ቀን ከሌሊት ደከመን ሰለቸን ሳንል ላለፉት 5 ዓመታት በሃገራችን ጉዳይ በቂ ነው ባይባልም ብዙ መረጃዎችን አቀብለናል የምናቀብለውም ይህን ውጤት ለመቀበልና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ አብቦ ለማየት ነው። ። ወደ ፊትም ይህ አገልግሎታችን በቪድዮና በድምጽ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ በቂ የሰው ሃይል ጨምረን አሁን ከምንሰራው የተሻለ አገልግሎት እንድንሰጥ፣ በአሁኑ ወቅት በራሳችን ሰርቨር ስለምንጠቀምና አንድ ሰርቨር ብቻ በየሰዓቱ የሚጎበኙንን ወገኖቻችንን ማስተናገድ ስለማይችል ሌላ 2ኛ ሰርቨር ለመጨመር እኛ አሁን ያለን የገንዘብ አቅም በቂ አይደለም። በፖለቲካው፣ በማህበራዊ ጉዳይ፣ በጤናው፣ በስፖርት፣ በመዝናኛ ጉዳዮች የተሻለ ሥራ ለመስራት አቅሙ አለን ብለን እናስባለን። ይህን የምናሳካው ግን አሁን የዘ-ሐበሻን 5ኛ ዓመት በማስመልከት በምታበረክቱልን የገንዘብ ድጋፍና፣ የቁሳቁስ እርዳታ ነው።

በአጭሩ ይህ መልዕክት ዘ-ሐበሻን ያግዙ ይርዱ ለማለት ነው።

ዘ-ሐበሻ በሕጋዊነት ተመዝግባ በምትገኝበት ሚኒሶታ ውስጥ በጃንዋሪ ወር ላይ የ5ኛ ዓመት እና የገቢ ማሰባሰቢያ የራት ምሽት የምታዘጋጅ ሲሆን ለዚህም ታዋቂው አክቲቪስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ ለመገኘት ቃል ስለገባልን በዚህ አጋጣሚ ልናመሰግን እንወዳለን። በሚኒሶታ የማትኖሩና በዓለም ዙሪያ የምትገኙ የዘ-ሐበሻ ደጋፊዎች ግን ዛሬ ነገ ሳትሉ የዘ-ሐበሻ ክንድ ትሆኑ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።

ዘ-ሐበሻን ለመርዳት እዚህ ጋር ይክፈሉ

እናመሰግናለን።





የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)

0
0

የሳውዲ አረቢያው ቀውስ መከሰት ለኢትዮጵያውያን/ ዲያስፖራ

ፍቅርና አንድነት ትምህርት ሰጥቶ ይሆን?

 

በፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ

teachable_moments_eth_diasp1385855011በአረብ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኞች ላይ የሚደረገው ህገወጥ የማሰቃየት እርምጃ በአስቸኳይ ይቁም! በአሁኑ ወቅት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በሪያድና በአዲስ አበባ ከተሞች ባሉ ገዥ አካሎች እየተፈጸመ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለጉዳዩ ልዩ የሆነ ትኩረት እንዲሰጡትና ለወገኖቻቸው የማያቋርጥ ድጋፍ እንዲያደርጉ ምቹ አጋጣሚን ፈጥሯል፡፡ ባለፉት በርካታ ሳምንታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየተፈጸመ ባለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት እረገጣ የቪዲዮ ምስል መታየት መጀመሩን ተከትሎከአውስትራሊያ እስከ አሜሪካ ባሉ በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ ቁጣ እና የልብ ስብራት በማስከተሉ ምክንያት በየአካባቢያቸው ባሉ የሳውዲ አረቢያ ቆንስላዎችና የዲፕሎማሲ ማዕከላት በሮች ላይ ፊት ለፊት በመሰለፍ በግንባር በመግጠም ባሳዩት ቆራጥ ኢትዮጵያዊ የተቃውሞ ወኔ የመብት ረጋጮችን የሳውዲ አረቢያ ገዥ ባለስልጣኖች በማሸማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከ6  – 7 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን/ት ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት የሳውዲ አረቢያ ገዥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየፈጸመ ያለውን ህገወጥ እርምጃና የሰብአዊ መብት እረገጣ በአስቸኳይ እንዲያቆም በመጠየቅ በሳውዲ አረቢያ ከሚገኙ ወገኖቻቸው ጋር የማያቋርጥ ትብብርና ወገናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ በአደባባይ በግልጽ አሳይተዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከአትላንታ እስከ ሲያትል ከተሞች በመሰለፍ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በአውሮፓ የተለያዩ ከተሞች በመውጣት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡ የሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች በየደረሱባቸው ቦታዎች ሁሉ ባነሮችን በመያዝ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ “ሳውዲ አረቢያ ሃፍረተኛ! ሃፍረተኛ! ሃፍረተኛ! “ሳውዲ አረቢያ ሃፍረተኛ!” በማለት ተቃዎሟቸውን አሰምተዋል፡፡

በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ እየተደረገ ያለው የሰብአዊ መብት እረገጣና ህገወጥ አያያዝ በአስተማማኝ መረጃ ላይ ተደግፎ የቀረበ በመሆኑ ሊካድ የሚችል ጉዳይ አይሆንም፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች/Human Rights Watch እ.ኤ.አ ዴሴምበር 1/2013 ባወጣው ዘገባ መሰረት “የሳውዲ አረቢያ መንግስት በግዛት ክልሉ ውስጥ በሚኖሩ የውጭ አገር ሠራተኞች ላይ የኃይል እርምጃን በመውሰድ በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞችን የአካል ጉዳት ሰለባ እንዲሆኑ አደርጓል፣አንዳንዶችንም ገድሏል፣ ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚፈልጉትን ኢትዮጵያውያን/ት ደግሞ ያለበቂ ምግብና መጠለያ አቅርቦት በጊዚያዊ የእስር ቤት ማዕከሎች አጉሮ ይገኛል“ በማለት በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ ማህበረሰብ በወገኖቹ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በመመልከት በተግባር እያሳየ ያለውን ንዴትና ቁጣ ሶስት ዋና ዋና ነገሮች በትክክል ይገልጹታል፡፡ 1ኛ) የሳውዲ አረቢያ የመንገድ ላይ ዘራፊዎች እና የፖሊስ ሌቦች እንዲሁም ህገወጦች ኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሠራተኛ ዜጎችን ከየቤታቸው በማስወጣት በየመንገዱ በመጎተት በቃላት ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ ጭካኔና አረመኔነት በተመላበት ሁኔታ ሲደበድቡ፣ ሲዘርፉና ሲያስሩ በመታየታቸው፣ 2ኛ) የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል የእራሱ ፖሊሶችና ሁከት ፈጣሪዎች በእብሪት ተነሳስተው በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ ያለምንም ማቋረጥ ጥቃት ሲሰነዝሩ እያየ ምንም ነገር ሳያደርግ በማንአለብኝነት መመልከቱ፣ 3ኛ) በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ከመሰሉ ገዥ የሳወዲ አረቢያ አካል ጋር በመሞዳሞድ የገንዘብ እርዳታ ስለሚያገኝ በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ደካማነትና የእግር ላሽነት ባህሪ በግልጽና በዓለም የአደባባይ መድረክ ላይ በማሳየት ላይ በመገኘቱ የሚሉት ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ እና በአትዮጵያ ያለው ገዥ አካል በስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል እየደረሰ ባለው የሰብአዊ መብት እረገጣና ህገወጥ አያያዝ ሁለት የማይገናኙና ተጻራሪ የሆኑ ምላሾን ሲያንጸባርቁ ይታያሉ፡፡ በአንድ በኩል በውጭ አገር ያለው የዲያስፖራ ማህበረሰብ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ስደተኛ ሠራተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ እየደረሰ ባለው መከራ እና ስቃይ ከወገኖቹ ጎን በጽናት ሲቆም በተጻራሪው ገዥው በአዲስ አበባ የሚገኘው አካል ደግሞ ጠንከር ያለ መግለጫ ከማውጣት ወደኋላ ያፈገፍጋል፣ እንደ አሉሚኒየም ብረት ወደኋላ ይለመጣል፣ የሳውዲን ገዥ አካልን ጫማ ለመላስ ወደ ተረከዙ ያጎነብሳል፣ እንዲሁም አምባገነኑን አረብ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡ በአጭሩ ሎሌነቱን በይፋ አሳይቷል!፡፡

ከወባ ትንኝ ተመራማሪነት በፍጥነት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተሸሙትና እ.ኤ.አ ከ2015 አገራዊ “ምርጫ” በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ይጠቀልላሉ ተብለው የሚጠበቁት ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣኖችን ውሳኔ እና ህገወጥ ስደተኞችን የማባረር ፖሊሲያቸውን ኢትዮጵያ እንደምታከብር በድፍረት ለብዙሃን መገናኛ ይፋ መግለጫ  ሰጥተዋል፡፡ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ በተደረገው የዜጎች ህገወጥ አያያዝ ስሜታቸው የተጎዳ መሆኑን ለሳውዲ አረቢያው አምባሳደር በቀልድ መልክ ገልጸው ይደልዎ ብለዋል፡፡ በዲፕሎማሲያዊ በእራስ መተማመን መልክ አድሃኖም “ይህ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል፡፡ እርሳቸውና ገዥው አካል ነገሮችን ሁሉ በቁጥጥራቸው ስር እንዳደረጉ በሚመስል መልኩ አድሃኖም “ዜጎቻችንን ለመቀበል ሙሉ በሙሉ ዝግጅታችንን ያጠናቀቅን መሆናችንን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ“ በማለት የምጸት ጩኸት አሰምተዋል፡፡

ማዘናቸውን የገለጹበት ሁኔታ ከልብ ያልሆነ፣ ለታይታ እና ለይስሙላ የተደረገ፣ የባለስልጣንነት ሞገስ የሌለውና እርባናየለሽ ነበር፡፡ እንዴት አንድ በከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጠ ባለስልጣን የእራሱን ዜጎች ለሚያዋርድ የሌላ አገር ፖሊሲ “ክብር” ይሰጣል? እንዴት አንድ ሰው የአንድን በባዕድ አገር የሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች አስገድዶ የሚድፍር፣ የሚገድል፣ ሰውነትን የሚበጣጥስ፣ የሚያሰቃይና ተጠርጣሪ ነው በማለት ያለፍርድ የሚገድል ኃይል በእራሱ አስተሳሰብ በመመራት “ተቀባይነት የለውም” የሚለውን ትርጉምየለሽ የዲፖሎማሲ ቃል ይመርጣል? እንዴት አንድ ሰው በትክክለኛው የዲፕሎማሲያዊ ንዴትና ቁጣ ኖሮት በህጋዊ መንገድ ጉዳዩን ለመከታተል ሳይሞክር “ስሜቴ ተጎድቷል” እንዲሁም “አዝኛለሁ” ሊል ይችላል?

ስዕል የአንድ ሺ ቃላትን ያህል የመናገር ኃይል ያለው መሆኑ ሀቅ ነው፡፡ የሳውዲ አረቢያዎች የሰብአዊ መብት እረገጣ የቪዲዮ ምስሎች የዲያስፖራውን ቁጣ የመቀስቀስ ኃይል ነበራቸው፡፡ በቀላሉ ሊታይ የማይገባው እውነታ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የተፈጸመው አሳንሶ የማየት፣ የማዋረድ፣ ማሰቃየትና ሰብአዊ መብትን መርገጥ በተመሳሳይ መልኩ በተራው ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በኢትዮጵያው ገዥ አካል ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሲፈጸም ቆይቷል፡፡ የአድሃኖም ገዥው አካል ነጻውን ፕሬስ በማሽመድመድ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የሰብአዊ መብት እረገጣ ከህዝብ ዕይታ ለመደበቅ ያደረገው ጥረት  በአብዛኛው ስኬታማ ቢሆንም ሁሉንም ደብቆ ለማስቀረት ግን አልተቻለውም፡፡

ብዙ አስደንጋጭ የፎቶግራፍ ምስሎች በማስረጃነት ቀርበዋል፣ እነዚህም የፎቶግራፍ ምስሎች የሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ከፈጸመው የሰብአዊ መብት እረገጣ የበለጠ የኢትዮጵያ ገዥ አካል በተራ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የፈጸመው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት እረገጣ ፎቶግራፍ የበለጠ አስደንጋጭ ነው፡፡ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በኢትዮጵያውያን/ት ስደተኛ ሰራተኞች ላይ በኖቬምበር 2013 የተፈጸመው የሰብአዊ መብት እረገጣ በኢትዮጵያ ገዥው አካል በተራ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ በኦክቶበር 2013፣ በኖቬምበር 2012፣ በዴሴምበር 2011፣ ወዘተ በተመሳሳይ መልኩ ተፈጽሟል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ገዥው አካል እስረኞችን ከህግ አግባብ ውጭ አስገድዶ የእምነት ቃል እንዲሰጡ ያደረገውን ሂዩማን ራይትስ ዎች በዘገባው “በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት እስረኞች በማያቋርጥ ሁኔታ በጥፊ ይጠናገራሉ፣ በእርግጫ ይደበደባሉ፣ በቦክስ ይነረታሉ፣ በዱላና በጠብመንጃ ሰደፍ ይደበደባሉ፡፡ ጥቂቶቹ በሚያሰቃይ ሁኔታ እጆቻቸውን ከኩማዎቻቸው ላይ በማንጠልጠል፣ ወይም ደግሞ እጆቻቸውን ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ አድርገው በማቆም ማሰርና  ለብዙ ጊዜ እየተደበደቡ እንዲቆዩ ማድረግ“ አካቶ አቅርቦታል፡፡

ዋናው ከክስተቱ የተማርኩበት አጋጣሚ፣ የነቃና የተበሳጨ ህዝብን መመልከት፣ እውነት ለመናገር ለእኔ አሁን ባለው የሳውዲ አረቢያ ሁኔታ ዋናው “የተማርኩበት አጋጣሚ”  ብዬ የምወስደው አብዛኛው የዲያስፖራ ማህበረሰብ በዚህች አጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰባስቦ ተቃውሞውን በመግለጽ እረገድ ውጤታማ መሆኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ በዚህ አይነት ቀልጣፋ በሆነ መልክ፣ ኃይልና አስደናቂ ፍላጎት ስልታዊ በሆነ መልክ ዓለም አቀፍ የቁጣ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አይችልም የሚለውን የቀድሞ እምነቴን እንድሰርዝ አድርጎኛል፡፡ በእርግጠኝነት ለመናገር ይህ ድርጊት ለእኔ “ይበል” የሚያሰኝ ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አይቻለሁ፣ ከተለመዱት የመብት ተሟጋቾች በስተቀር አብዛኛው ለእኔ ዝምተኛ ብቻ ሳይሆን የተኛም ጭምር መስሎ ይታየኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2013 በሚያስደንቅ ሁኔታ ግዙፉን የኢትዮጵያን ዲያስፖራ በንቃት ሲሳተፍ ተመልክቻለሁ፡፡ ወንዶች ሴቶች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች በሳውዲ አረቢያ በወንድሞቻቸውና በእህቶቻቸው ላይ የሚፈጸመውን ስቃይና የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም በመቶዎችና በሺዎች በመሆን እየወጡ ከጎናቸው ተሰልፈዋል፡፡

ይህን ግዙፍ ዲያስፖራ እንዲነቃ ያደረገው ምንድን ነው?  እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ትልቁ ስጋቴ በሳውዲ ያለው ቀውስ ካበቃ በኋላ ይህ ግዙፍ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ተመልሶ ይተኛ ይሆን የሚለው ነው፡፡

የሁላችንም ትምህርታዊ አጋጣሚዎች፣

የኢትዮጵያ ስደተኛ ሰራተኛ በሳውዲ አረቢያ ገዥ አካል በደርሰባቸው የሰብአዊ መብት እረገጣና ማሰቃየት የኢትዮጵያ ገዥው አካል ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ ልዩ የሆኑ ትምህርታዊ አጋጣሚዎችን በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ሰጥቷል የሚል እምነት አለኝ፡፡ “ትምህርታዊ አጋጣሚ” የሚለውን ሀረግ ለብዙሀን ትምህርት፣ ለህዝቦች መነሳሳትና ለግለሰቦች በንቃት መሳተፍን ሊያመጣ የሚያስችል በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ልዩ ድርጊት በማለት ተርጉሜዋለሁ፡፡ ከዚህ በመቀጠል የሚቀርቡትን ጥቂት የማስተማሪያ እና የመማሪያ ትምህርቶች የትርጉም ቅርጽ ከግንዛቤ በማስገባት ማስተላለፍ የምፈልገው ዋናው መልዕክት ቀውስ በደረሰ ጊዜ ብቻ የሚወረወር ምላሽ ነጻነትን፣ ዴሞክራሲን ለመጎናፀፍ እና በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብትን ለማስከበር ስኬታማ እና ለድል የሚያበቃ ስሌት አይደለም፡፡

በሳውዲ አረቢያ እንደደረሰው ቀውስ ሁሉ በሌሎችም ትክክል ናቸው ብለን በምናምንባቸው ጉዳዮች ሁሉ ልዩ የሆነ ዓለምአቃፋዊ ትብብር፣ ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት እና መነሳሳትን በተረጋጋ ሁኔታ ማንጸባረቅ ይጠበቅብናል፡፡ በሳወዲ አረቢያ ቀውስ ምክንያት የታየውን የመነሳሳት “አዚም” ደግመንና ደጋግመን ማሳየት ይኖርብናል፡፡ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን/ት በቋሚነት ለሰብአዊ መብት መከበር መሟገትና መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡

በኢትዮጵያውያን/ት ዲያስፖራ መነጽር መመልከት፣ ተራ ንግግር እራሳችንን ከስሜታዊነት፣ ግንፍልተኝነት እና ከቀውስ ለመውጣትና የእራሳችንን እጣ ፈንታ እራሳችን ወሳኝ እንድንሆን ሰላማዊ ሽግግር ለማድረግ “የኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” ምናባዊ ቅርጽ የሚል ላስተዋውቅ፡፡ የነቃውን ግዙፍ የዲያስፖራ ማህበረሰብ ለዘለቄታው እንደነቃ ለዘላለሙ ጠንቃቃ ተመልካች ሆኖ አንዲቀጥል ልዩ ስትራቴጂ መንደፍ ያስፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ያሉ ችግሮችና ጉዳዮች ምን ምን እንደሆኑ እናውቃለን፣ ጥቂቶች በጣም ቀላል ነገሮች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ መፍትሄ ለማግኘት የበለጠ አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ በግልጽ  በመተማመን እና በመወያየት ችግሮችን ካልፈታናቸው በስተቀር ታላቁን የነቃ የዲያስፖራ እንቅስቃሴ ወደኋላ በመመለስ እንዲተኛ ማድረግ ያስችላሉ፡፡ ከአንድ ቀውስ ወደሌላ ቀውስ መሸጋገር እኔ በበኩሌ ያመኛል፣ ይደክመኛልም፡፡

የዲያስፖራው ማህበረሰብ እርስ በእርስ እንዲዋደድ፣እንዲደራጅ፣ እንዲታደስ እና ለውጤት እንዲንቀሳቀስ ማድረግ አለብን፡፡ ከእራሳችን እና ከእያንዳንዳችን ጋር ንግግሮች ያስፈልጉናል፡፡ “በኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” እመለከታለሁ፡፡ ንግግር ለማድረግ መስታወቱን ከግድግዳው ጋር እሰቅለዋለሁ፡፡ እኔን ወደኋል ይመለከተኝ እና እንዲህ ይላል፣

ሁላችሁም ማድረግ ትጀምራላችሁ ነገር ግን አትጨርሱትም፡፡ መስታወቱ እንዲህ በማለት ያስታውሰናል፣ “በቅርቡ በህይወት የተለዩት የኢትዮጵያ ገዥ አካል መሪ እንዲህ ብለው ነበር ’የአትዮጵያ ዲያስፖራዎች ብዙ ነገሮችን ይጀምራሉ፣ የጀመሩትን ግን በፍጹም አይጨርሱትም፣ ታዲያ ስህተት ተናግረዋልን?’”

ጥያቄውን ላለመመለስ ቃላትን ለመፈለግ እሞክራለሁ፡፡ “እውነት ለመናገር ብዙ ብዙ ነገሮችን እንጀምራለን፣ ነገር ግን በጣም ጥቂቶችን ብቻ ለውጤት እናበቃለን፣ ከእኔ የግል ተሞክሮ ማስረጃ ማቅረብ እችላለሁ፣ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አጠባበቅ ትግል በንቃት ስቀላቀል ያየኋቸው፣ የሰማኋቸው፣ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የተሳተፍኩባቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ወይም የአድቮኬሲ ቡድኖች፣ ግብረ ኃይሎች፣ ኮንፈረንሶች፣ ፎረሞች፣ የምክክርና የውይይት ቡድኖች፣ ቴሌኮንፈረንሶችና የግል ስብሰባዎች፣ ወርክሾፖች፣ ስምምነቶች፣ የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና ሲምፖዜሞች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ አንዱም ፍሬ አፍርቷል ብየ ለመናገር አልደፍርም“:: ወዲያዉኑ እራሴን በፍጥነት አርማለሁ፡፡ “አንድን ነገር በግማሽ አሳክተናል፣

በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ኤችአር/HR 23ን ማን ይረሳዋል (ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እና ተጠያቂነት ድንጋጌ)፣ አዎ! ያ ታላቅ ትምህርታዊ አጋጣሚ ነበር፡፡ ያ የህግ ሰነድ በቅርቡ በህይወት ለተለዩት ጠቅላይ ሚኒስትር የእራስ ምታት፣ የልብ ስብራት፣ የሆድ ቁርጠት፣ የጀርባ ውጋት፣ የጥርስ ቁርጥማት እና የጆሮ ህመም ሆኖባቸው ነበር! ኤችአር 2003 የተለያየ አመለካከት የነበራቸውን የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ወደ አንድ እንዲመጡና ተቀራርበው ዓላማቸውን በጋራ እንዲያሳኩ ለማድረግ አስችሎ ነበር::

መስታወቱ አቁአረጠኝ፡ “እንዲህ ነው እንጂ! ሁላችሁም አንድ ሁሉን አቀፍ የሆነ ጠንካራ መሰረት ያለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የዲያስፖራ ማህበረሰብ ድርጅት ማቋቋም ትችላላችሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ለማሰቃየት፣ ከህግ  ውጭ ለሚፈጸም ግድያ፣ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር ማዋል እና እስራቶች፣ ድብደባዎች እና ለምርጫ ድምጽ ስርቆት የተለየ ትኩረት በመስጠት የማያምን ማን አለ?” ግልጽ የሆነውን መልስ ላለመስጠት ወሰንኩ፡፡ አንድ ነገር ስንጀምር ወደ ስኬታማነት ልናመጣው ይገባል ወይም ደግሞ የፈለገውን ጊዜ ቢውስድም እየሞከርነው መቀጠል ይኖርብናል፡፡

ሁልጊዜ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሁላችሁም አንድን ነገር ለመቃወም በንዴት በስሜታዊነት ትነሳላችሁ፡፡ መስታወቱ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፣ “በኢትየጵያ ያለው ታማኝነት የጎደለው ገዥው አካል አንድ ነገር ሲያደርግ ወይም ሳያደርግ ሲቀር ሁላችሁም ሁልጊዜ በንዴትና በስሜታዊነት ምላሽ ለመስጠት የምትሞክሩት ለምንድን ነው?“ በፍጥነት የሳውዲ አረቢያን ሁኔታ ሃሳብ መጣብኝ፡፡ “ስሜታዊነት መሆን ምንም ስህተት የለበትም፡፡ ሰው መሆንና ስሜታዊ አለመሆን ማለት ሮቦት መሆን ማለት ነው፡፡

ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሳውዲ አረቢያ ከሰው በወረደ መልክ ግፍ ሲፈጸምባቸው እያየን እና እየሰማን ለምንድን ነው የማንናደደውና ከቁጥጥር ውጭ የማንሆነው?“ መስታወቱ በጥንቃቄ መጠየቁን ይቀጥላል፣ “ከተነፈስክ በሁላ ንዴት ሲበርድልህ  የሚተርፍህ ምንድን ነው? ተስፋ መቁረጥ፣ በጣም ስሜታዊ መሆን፣ ማዘን? ኃይል የለሽነት፣ ተስፋቢስነት፣ ምንም ነገር ያለማድረግ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ ትችላለህን? ወይም ደግሞ እንደገና ለመደራጀትና ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ ያለ የሌለ የፈጠራ ኃይልህን ትጠቀማለህ? እራሴን በመነቅነቅ ሀሳቤን አንጸባርቃለሁ፡፡ “ምንጊዜም ቢሆን ንዴት በመጨረሻው ተፈጻሚነት እንዳይኖርና ሽባ ሆኖ ያስቀራል፡፡ በምንናደድበት ጊዜ የምናባክነው ኃይል ወደ ረዥሙና ቀጣይነት ስላለው የአድቮኬሲ እና ድርጊት በአወንታዊነት ማዋል አለብን::” ንዴታችን ለምክንያታዊነት፣ በስሌትና በጥቅል ታስቦበት ለሚሰራ ተግባር መንገድ መስጠት አለበት፡፡

ሁልጊዜ ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሁላችሁም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ቀውሶችን የመቃወም ዝንባሌ ታሳያላችሁ፣ ነገር ግን ከእነዚህ ያላነሰ ጠቀሜታ ላላቸው ሆኖም ግን ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን ችላ ትላላችሁ::  መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “ባለፈው ዓመት በርካታ አስደንጋጭ ቀውሶች በግልጽ ለመውጣታቸው ምስክር ናችሁ፡፡ በኢትዮጵያ ገዥ አካል በሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ላይ ሰብአዊ መብት መርገጥና ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲፈጸምባቸው ነበር፡፡ ጥንታዊውንና የተከበረውን የኢትዮጵያን የኃይማኖት መሬት የዋልድባን ገዳም ዓይን ባወጣ መልኩ ገዥው አካል ለውጭ የሸንኮራ አገዳ አልሚዎች ማስረከቡ ይታወሳል::  በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ከሚኖሩበት አካባቢ በኃይል በማፈናቀል የዘር ማጽዳት ዘመቻ መፈጸሙ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው::” መስታወቱ ቀጥሏል፣ “በርካታ ዝቅተኛ ገጽታ ያላቸው ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የአውዳሚነት ባህሪ ያላቸው እየተከናወኑ ያሉ ቀውሶች አሉ፣ የገዥው አካል “የሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ እድገት” ማስመዝገብ ፕሮፓጋንዳ ቢኖርም በአሁኑ ጊዜ ወደ አስር ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን/ት በረሀብና ቸነፈር የህይወት አጣብቂኝ መካከል ወድቀዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1970ዎቹና በመጀመሪያዎቹ 1980ዎቹ እንደነበሩት ዓመታት ዓይነት ረሀብ የማይታየው በዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታ ምክንያት ነው፡፡ በጎረቤት አገሮች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮያውያን/ት ቁጥር በየዓመቱ በመቶዎችና በሺዎች እየጨመር በመሄድ ላይ ይገኛል፣ በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ቀውሶች ይታያሉ፡፡ የሙስና ቀውስ እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጥራት ደካማ መሆን እና የአገልግሎቱ እጥረትም ይታያል፣ ይህም በወጣቶች ስብዕና ላይ ትልቅ የሰብአዊ መብት እረገጣ ተብሎ ሊመደብ  ይችላል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በተሳሳተ አስተዳደር እየተመሩ ነው፣ የፖለቲካ ተቋማት እየሆኑና የገዥው ፓርቲ ታማኞች የሙስና ስልጠና አካባቢዎች እየተደረጉ ነው::” በገፍ መቃወም ያለብን ትልቅ ገጽታ ያላቸውን ቀውሶች ብቻ ሳይሆን ትንሽ ገጽታ ያላቸውን ጭምርም መሆን አለበት፡፡

የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ሁላችሁም በሚባል መልኩ ሁልጊዜ ደካማ የመከላከል ጨዋታ ታደርጋላችሁ:: መስታወቱ እንዲህ ይገልጻል፣ “በዲያስፖራው ያላችሁ ሁላችሁም መንግስት የሚሰራውን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ፣ የማይሰራውን ግን በጣም ጥቂት ብቻ ትይዛላችሁ:: በቅርቡ በህይወት የተለዩት የገዥው አካል መሪ ይህንን ደካማ ጎን እንደ በሰይፍነት የመጠቀም ጉብዝና ነበራቸው::

እና እናንተ በሙሉ ለአገራችሁ እርባና ያለው ነገር ስትሰሩ አትታዩም፣ እሳቸው የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር ሲሉ አንድ አስደንጋጭ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ወይም ሲናገሩ እናንተ ለዚያ ምላሽ ለመስጠት ስትሽከረከሩ ትወጡ ትወርዱ ነበር፣ ይህንም አይተው  በዚያ ጭራቃዊ ፈገግታቸው ይመለከቱ ነበር::”

ለመስታወቱ እንዲህ በማለት ለመግለጽ እሞክራለሁ፣ “እኒያ ሰው ጨካኝ በመሆናቸው ጎበዝ ነበሩ፣ እሳቸው ዋና የነገር አጧዥ፣ የተንኮል ንድፍ አውጭ፣ ታማኝነት የሚጎድላቸው እና የብልጥነት ሴራ የሚሰሩ ነበሩ፡፡ ምርጫ አልነበረንም::” መስታወቱ ይሄን አስተያየት ችላ አለው:: “አሁንም የእርሳቸው ጋሻጃግሬዎች በእርሳቸው ፈለግ እንደዚያው እንደተለመደው የማይረባ ድርጊታቸውን እንዲቀጥሉ ትፈቅዳለህ?“ እኔ መልስ የለኝም፣ ጥያቄው እንዳልሰማ ለማስመሰል እሞክራለሁ፣ ለእራሴ ቀስ ብየ እናገራለሁ፣ “ምንም ዓይነት ቡድን ጠንካራ የመከላከያ መስመር ሳይኖረው ለድል አይበቃም“:: ጠንካራ የዲያስፖራ ቡድኖችን መፍጠርና ጠንካራ የመከላከል ጨዋዎችን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሁላችሁም ትኩረት ይጎድላችኋል፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣”ሁላችሁም ከአንድ ጉዳይ ወደ ሌላ ዝውውር ለማድረግ ትኩረትና ተስፋ ይጎድላችኋል፣ የቀውስ ሁኔታዎችን በንዴት ምላሽ ለመስጠት ስትሞክሩ ይህ ሁኔታ ደግሞ በጣም ረዥም በሆነ ምንም ነገር ያለመስራት ወሰንተኛ የሆነ ቸልተኝነት ያስከተላል::” እራሴን እጠይቃለሁ፣ “ያ የሚሆነው ለምንድን ነው?“ ድርጅትና አመራር ሳይኖር አንድ ጉዳይ ላይ ትኩረት ማድረግ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላልን? ለምንድን ነው ግልጽና ጠንካራ የአድቮኬሲና የድርጊት አጀንዳ የማይኖረን?”  ለመስታወቱ እነግረዋለሁ፣ “ትኩረት ያጥረናል ምክንያቱም ግልጽ ራዕይ የለንም፣ ራዕይ ያጥረናል ምክንያቱም ቁርጠኝነት ያጥረናል፣ ቁርጠኝነት ያጥረናል ምክንያቱም በእራሳችን  በራስ መተማመን እና በክርክር ጭብጦቻችን ላይ እምነት ያጥረናል፡፡“ እዚህ ላይ የአፍሪካን የጥንት አባባል በመዋስ፣ “ወደየት እንደምትሄድ ካላወቅህ ማንኛውም መንገድ እዚያ ያደርስሀል፡፡“

አብዛኞቻችሁ ቆሞ ተመልካች ናችሁ፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “አብዛኞቻችሁ ከጎዳና ዳር ቆሞ ማየትን ትመርጣላችሁ፣ ሌሎቹ ደግሞ ከጎን ሆነው ትችት መሰንዘርን ይመርጣሉ፡፡“ አቋረጥኩ፡፡ “ዋናው ዘዴ የተመልካቾችን ምዕናብ ለማጎልበት፣ ለእነሱ ተስፋ ለመስጠትና ለማጠናከር፣ እውቀት እና በሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ በእራስ የመተማመን ጠቀሜታ ለማጎልበት ነው፣ በዚህም መሰረት ከተመልካችነት ወደ ሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ይቀየራሉ፡፡“ መስታወቱ ስሜትን እንዲህ በማለት ያነሳሳል፣ “ሰብአዊ መብት የተመልካች እስፖርት አይደለም፣ ሰብአዊ መብት የቡድን ስራ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በሜዳው ውስጥ ነው፣ እያንዳንዱ ሰው የሚጫወተው ድርሻ ይኖረዋል እና ትልቅ ግብ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡“ ከታች ጀምረን ማነሳሳትና ማንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡

እናንተ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በሙሉ የሲቪክ ማህበረሰብ የድርጊት ዘመቻ መመስረት አለባችሁ፣ መስታወቱ እንዲህ በአንክሮ ያስጠነቅቃል፣ “እናንተ ሁላችሁም ለድል የሚያበቃችሁን መንገድ በመከተል በተለየ ሁኔታ ለመስራት፣ ቅድሚያ ዝግጅት በማድረግ ለመስራት፣ ከስሜታዊነት ነጻ ሆኖ ለመስራት መብቃት አለባችሁ፡፡“ እናንተ ሁላችሁንም ማስተማር፣ ማንቀሳቀስ፣ ማደራጀትና ማጠናከር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ ለጋራ ጥረት ማብቃት አለባችሁ፡፡ እናንተ ሁላችሁም የሰቪክ ማህበረሰቡ ጋር  በመሆን ዘመቻውን በቀልጣፋነት ማካሄድ አለባችሁ፣ ለሲቪክ ማህበረሰቡ እንቅስቃሴ ህበረተሰቡን በኮሚቴ፣ በጎ ፈቃደኞችን በመመልመል፣ ለወርክሾፖች አመራር በመስጠት፣ ከታች ጀምሮ ያለውን እያንዳንዱን ዜጋ ለማጠናከር እና በንቃት ለማሳተፍ በቴሌቪዥንና ሬዲ ፕሮግራሞች ላይ ትኩረት በመስጠት መስራት ያስፈልጋል፡፡ የሲቪክ ማህበረሰቡ ከታች ጀምሮ በሙሉ እንዲሳተፍ!

እናንተ ሁላችሁም በሌሎች ላይ ስድቦችን በመወርወር ጊዜ ማባከን፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “እናንተ ሁላችሁም ገዥውን አካል በማውገዝ እና ዘለፋዎችን በመወርወር ብዙውን ጊዚያችሁን በከንቱ ታባክናላችሁ፣ ሁላችሁም አታገኙትም፣ የዱሮ አባባል በመዋስ፣ ’ከአሳማ ጋር (ወይም ከሌባ) ከጭቃ ውስጥ ትግል አትግጠም‘ አሳማው (ወይም ሌባው) ሲደሰት አንተ ቆሻሻ ትሆናለህ::

ወሮ በላን በጭቃ ጅራፍ በዝልፍያ መስተካከል አይቻልም::” ምላሽ ለመስጠት ፈጠንኩ፡፡ “አንድ ሰው አካፋን አካፋ ማለት አለበት፡፡“ መስታወቱ እንዲህ በማለት ምክር ይለግሳል፣ “ስለዚህ አንዴ ጥራው እና ተንቀሳቀሱ፣ አስታውስ! ወደ ዴሞክራሲ ወይም ወደ ነጻነት በስድብ አትደርስም፡፡”” መስማማቴን ለመገልጽ እራሴን ነቀነቅሁ፡፡ “የእውነት ወንጭፎችን እና ቀስቶችን ታጥቀን መዋጋት አለብን፣ በእውነት ጋሻዎች መመከት አለብን፣ ከመብት እረጋጭ ኃይሎች ነጻ ሆነን በነጻነት ለመናገር፣ ለመዘመር፣ ትልቁን ጉዞ መጓዝ አለብን፡፡“ እውነትን ተናገር እንጅ የሰብአዊ መብት እረጋጭ ኃይሎችን አትሳደብ፡፡

እናንተ ሁላችሁም በክፍል ውስጥ ላለው ዝሆን ትኩረት ስጡ፣ መስታወቱ እንዲህ ይላል፣ “እነሱን ለመረዳት ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ጫማዎች ለመጓዝ ሞክር (ምክንያቱም“እነሱን ለመረዳት መሞከር ጊዜ ማጥፋት ነው) ነገር ግን የእነርሱን ፍርሃት ለመረዳት እና የድብቅ እንባ ማፍሰስ ለመገንዘብ ሞክር፣ እነሱ አደጋዎች ጭካኔ የተሞላባቸው እና ህሊና የሌላቸው ናቸው፣ ነገር ግን ፍርሃት አልባዎች አይደሉም፡፡ በፍርሃት ይኖራሉ፣ ነገር ግን መሰረተቢስ ፍርሃቶች አይደሉም፣ የእነርሱ ፍርሃት በጫካው ውስጥ በማታ አያነደደ እንደሚያበራው ነብር ሁሉ ተመሳሳይ ናቸው፡፡” ይላል ዊሊያም ብሌክ፡፡ “የቸርቺል ኬኔዲ የፍርሃት ተቃርኖ’ በሚሉት ወጥመድ ተይዘዋል፣ አምባገነኖች ደፍረው ወጥተውው በማይጋልቧቸው ነብሮች ከወዲያ ወዲህ ይላሉ፣ እና ነብሮቹ ተርበዋል”፣

ቸርችል ያስጠነቅቃሉ፡፡ ፕሬዚዳንት ጆን ኬኔዲ ለማስታወስ “በጥንት ጊዜ በሞኝነት በነብሮች ጀርባ ላይ በመቀመጥ ኃይልን ለማግኘት ይፈልጉ የነበሩ አምባገነኖች በነብሮቹ ሆድ ውስጥ ገብተዋል፣  በሌላ አባባል “በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ የሚከለክሉ እነሱ በአመጽ መወገዳቸው የማይቀር ነው፡፡“ መስታወቱ ቀጠለ፣ “አምባገነኖች እርግጠኛ እና እብሪተኛ ይመስላሉ፣ ነገር ግን ይህ ሁሉን አቀፍ የሆነ ፍርሃታቸውን ለመሸፈን ሲሉ የሚያደርጉትና ከዕለታት በአንዱ ቀን እነርሱ ከታች ለወደቁ ጭቁኖች እነርሱ በፈጠሩት ገሀነም አነርሱ ስልጣናቸውን በኃይል ተነጥቀው ወደ መቀመቅ መውረዳቸው የማይቀር ነው፡፡“ መስታወቱን እጠይቀዋለሁ፣ “አምባገነኖች ቀን በቀን ይኖራሉ ብለህ መናገር ትችላለህ? ነገ ድረስ ለመቆየት አምባገነኖች ዛሬ ሁሉን ነገር ያደርጋሉ፣ ነገ ከነገ ወዲያም እና ከዚያ ወዲያም ቀን በቀን ነው የሚኖሩት?“ መስታወቱ እንዲህ ያስተካክለዋል፣ “በፍጹም፡፡

አምባገነኖች ሰዓት በሰዓት፣ ደቂቃ በደቂቃ፣ ሰከንድ በሰከንድ በፍርሃት ተውጠው ነው የሚኖሩት፣“ የተራቡ ነብሮች? የነቁ ግዙፎች ነብሮች!  እናንተ ሁላችሁም ብቻችሁን ልትሰሩት አትችሉም፣ ከመሄድህ በፊት የመጨረሻዋን ቃል መስታወቱ እንዲህ ይናገራል፣ “እናንተ ሁላችሁም ብቻችሁን ልትሰሩት አትችሉም፣ እናንተ ሁላችሁም ጓደኞች መፈለግና ከእነርሱ ጋር ተባብራችሁ በጋራ ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡”

ማሰብ ጀመርኩ፣ “ስንቶቻችን ነን ለእኛ ምርጥ ጓደኞች ጓደኞች የሆን? ስንቶቻችን ነን የሂዩማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ዘላለማዊ መጠበቂያ አባል የሆንነው? ስንቶቻችን ነን የሲ  ፒ  ጄ የጋዜጠኞች ተከራካሪ ድርጅት መብራቱን በቃሊቲ እስር ቤት ላይ በማነጣጠር እነ አስክንድር ነጋ፣ ውብእሸት ታየ እና ሌሎች በህገወጥ መንገድ ታስረው ለሚገኙት አባል የሆንነው?

ስንቶቻችን ነን ባህላዊውን የህብረተሰብ ቡድኖች እና የኢትዮጵያን የአካባቢ ጥፋት ለመከላከል ብለው ልዩ ስራዎችን ዓለም አቀፍ ወንዞች በፍትሀዊነት እንዲያገለግሉ የሚታገሉትን ዜጎች የምናደንቅ? በዓለም አቀፍ እና በአገር ውስጥ ከሚሰሩ የመገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች ጓደኛ አለን? በድንገት በአምሮዬ ጥያቄ መጣ፡፡ ለምንድን ነው እነ ሲኤን ኤን፣ቢቢሲ፣ ኤቢሲ፣ ሲቢኤስ፣ አልጃዚራ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ኤልኤ ታይምስ፣… የእኛን ሰላማዊ ተቃውሞዎች ለህዝብ ይፋ የሚያደርጉት?“ ከእነርሱ ጋር ጓደኝነት ስላልመሰረትን ነው? ብቻችንን ልንሰራው የምንችለው ጉዳይ አይደለም፡፡ አብረን ለምንሰራው ሁሉ ሰማይ ወሰናችን ሊሆን አይችልም!

መስታወት፣ መስታወት ….

“የኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት” እውነቱን ወይም ደግሞ ውሸቱን ሊነግረን ይችላል፡፡ ምናልባት በመስታወቱ ውስጥ ማየት የምፈልገውን አይቼ ይሆናል፣ ምናልባት መስተዋቱም እኔ በመስታወቱ ላይ እንዲታይ ያስቀመጥኩትን አንጸባርቆ ይሆናል፣ ምናልባት መስታወቱ ሁሉም መልሶች ያሉት ወይም የሌሉት ይሆናል፣ ምናልባት መስተዋቱ የእኔ ህሊና ይሆናል፣ በእርግጥ በበየእለቱ  በመስታወቱ ስመለከት የምጠይቀው፣ “በግድግዳው ላይ ያለህው መስታወት የነቃው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ከዚህ በኋላ ምን ማድረግ ይኖርበታል?

ወደፊት ይቀጥላ

ለአንባቢዎች ማስታወሻ፣ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ መስታወት ንግግሮችልዩ በተከታታይነት የሚወጡ ትችቶች ናቸው፣ ወደፊት በየጊዜው

በሚስቡ ክስተቶችና ድርጊቶች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደምጽፍ እገምታለሁ፡፡ ማስተማሪያና መማሪያ በሚሆኑ ድርጊቶች ለመምህር ፈልጎ

ማውጣት መቻሉ በአጣቃላይ የሚያስደንቅ አይሆንም፡፡

12/4/2013


ከሳዑዲ አረቢያ ከተመለሱት ውስጥ 8 ሺህ የሚሆኑት ነብሰጡር ናቸው ተባለ

0
0

ኢትዮጵያን ሃገሬ ከጅዳ በዋዲ

ከሳውዲ ዓረቢያ ከተመለሱ ስደተኞች መካከል 8 ሺህ ሴቶች ነብሰ ጡሮች መሆናቸውን FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል በክር ዋቢ በማድረግ ዘገበ ።
Neb1
ከተጠቀሱት ነፍሰጡር እህቶቻችን መሃከል በሪያድ እና በጅዳ የሚገኙ የኮሚኒ ግዜያዊ መጠለያ ከገቡ በሃላ አስገድዶ መድፈር ወንጀል ሳይፈጸምባቸው እንዳልቀረ ምንጮች ገለጹ ።

እስከ ትናንት ባለው መረጃ መሰረት የወንዶች ቁጥር 58 ሺህ 529 ፣ የሴቶች ቁጥር 28 ሺህ 943 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሺ ሴቶች ነፍሰ ጡሮች መሆናቸው ታውቋል።

የህጻናት ቁጥር ደግሞ 4 ሺህ 51 መድረሱ ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት ካሳዑዲ ተመላሽ ኢትዮጵያን እንግልት እንዳይገጥማቸው ከመንገዶች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ጊዜያዊ መናኻሪያ እንደተቋቋመና ለአብነትም በትናንትናው እለት ብቻ ከ 4 ሺህ 20 በላይ ዜጎች ወደየቅያቸው እንዲመለሱ መደረጉን በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል በክር ተናግረዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል ለመታደግ ቀደም ሲል ባዲራቸው ወደ ተሰቀለችበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት እና በጅዳ ቆንስላ ግቢ ተጠልለው ከነብሩ እህቶቻችን መሃከል ከ 15 በላይ ነፍሰጡሮች መሆናቸው መዘገቡ ይታወሳል ።

neb 7እነዚህ ለስራ ወደ ሳውዲ አረቢያ አቅንተው በለስ ያልቀናቸው ወገኖች በተጠቀሱት የኮሚኒት ማዕከላት ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ እየተባለ ማታማታ ባዶ ክፍል ውስጥ ለሰአታት ቆይተው ይወጡ እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች በተጠቀሱት እህቶቻችን ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በኮሚኒቲው አላፊዎች አሊያም በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ሳይፈጸምባቸው እንዳልቀረ አክለው ይገለጻሉ። የተጠቀሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ አንዳንድ ወገኖች ጉዳዩን ለማጣራት ያደረጉት ሙከራ በሁለቱም « በጅዳ እና በሪያድ » ኮሚኒት ግቢ ውስጥ ተጠልለው የነብሩ እህቶቻችን የሪያዱን ግርግር ተከትሎ በዲፕሎማቱ ተዕዛዝ ወደ አልታወቀ እስርቤት መወስዳቸው የሚገልጹ የአይን እማኞች ነፍሰጡሮቹ እስካሁን ያሉበትን እና የተፈጸመውን ወንጀል ለማጣራት እንዳልተቻለ ይገልጻሉ።

ይህንን ጉዳይ በተመለክተ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ተጠልለው የነበሩ 12 ነፍሰጡር እህቶቻችን ስም ዘርዝር እና የኢትዮጵያ አድራሻቸው እጃችው እንደገባ የሚገልጹ እንዚህ ወገኖች ወደፊት የእህቶቻችንን ሞራል በማይነካ ሁኔታ እንደአስፈላጊነቱ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመውን አሳዛኝ እና ዘግናኝ ድርጊት ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ይሞከራል ብለዋል ።

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

የካርቱም ድራማ፡ እነ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሕዝቡን ስብሰባ ጠርተው እነርሱ ቀሩ

0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

(ከካርቱም የተላከልኝ መረጃ ነው፤ እንዳለ ለጥፌዋለሁ።)

ትላንት ማክሰኞ (ህዳር 24, 2006 ዓም) በኢትዮጵያ ስዓት አቖጣጠር ልክ ከ10:00ጀምሮ ለተለያዩ የማህበራት አመራሮችና እድሮች ዛሬ ሮብ ለሚደረግ ስብሰባ ሰዉ እንዲጠሩ መልዕኽት ተላለፈ። መልዕክቱ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለች የሚመሩትና ሌሎች ሚንስትሮች የሚገኙበት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ5:00 የሚጀመር ስብሰባስላል ከየማህብራችሁ 200 ሰዉ እንድትጋብዙ የሚል በስልክ መደወል ተጀመረ።

በተሰጠዉ መምሪያ መሰረት ሁሉም አመራሮች ወደ አባሎቻቸዉ መደወል ያዙ። በአካል ያገኙትም ለሌላዉ እንዲናገር ወሬው ድፍን ካርቱም እንዲዳረስ አደረጉ። የሚገርመዉ ከሃይለማሪያም ደሳለኝ ውጭ ሌሎች ሚኒስትሮች ከባለፈዉ ዓርብ ጀምሮ መግባት ጀምረዋል። እስከ ትላንትና ቀን ሁሉም በየመጡበት ፊና የተለያዩ ስራዎች ሲያከናዉኑ ቆይተዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደግሞ ትላንት ማክሰኞ ምሽት ላይ ካርቱም ገቡ። አይነጋ የለ ለሊቱ ነጋ። በካርቱም የሚገኙው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስትገባ የመጀመሪያዉ በር ስታልፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ/ማህበረሰብ/ ሬስቶራንት አለ ከዛ አልፎ ሌላ ሁለተኛ በር ልዩ ፍተሻ የሚደረግበት አልፎ ኤምባሲዉ ትገባለህ።
hailemariam and samora
በዚህ መስረት ስብሰባዉ ዛሬ ሮብ ይደረጋል ተብሎ የኮሚኒቲዉ ሰራተኞች ሁሉም ከጥዋቱ 2:00 ስራ ገብተዉ ግቢዉን ሲያፀዱ ዉለዉ ረፋድ ላይ በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር 6:00 ዛሬ ስራ ስለሌለ ወደ ቤታችሁ ሂዱ ተባሉ። ጊዜዉ እየገፋ ነዉ ስዓቱ እየተቃረበ ነዉ። ስብሰባዉ በማህበረሰቡ ውስጥ በሚገኙዉ መናፈሻ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር። ምክንያቱ ሁሌም የተለያዩ ፖለቲካዊ ና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚደረጉት በዚሁ አከባቢ ነበር። ዛሬ ግን ሌላ ነገር ተደረገ። ለታዳሚዉ የሚሆኑ ወንበሮች በኤምባሲው ግቢ ዉስጥ በለችሁ ትንሽ ሚዳና ዛፎች ስር ተደረደሩ። ስዓቱ ገፋ ኤምባሲዉ ውስጥ የሚገኙ ሰራተኞ ከዉትረዉ ለየት ባለ አለባበስ ግማሾች ሱፍ በከራቫታ ግማሾቹ ደግሞ ነጭ ቲሸርት በክራቫታ ለብሰዉ ውር ውር ማለት ጀመሩ። የደህንነት ሰዎች ግቢዉን ሁሉ መመርመር ጀመሩ። የተወሰኑ የፀጥታ ሰዎች ከተመደቡ በኋላ ልክ በኢትዮጵያ ስዓት አቆጣጠር 10:30 ወደ ውስጥ መግባት ተጀመረ። ህዝቡ ቀስ ያለ መምጣት ጀመረ።

ኤምባሲዉም ሆነ የኮሚኒቲ ሬስቶራንቱ በሱዳን ፖሊሶች ተከቧል። የመጀመሪያዉ በር ፍተሻ ላይ ሰዉ በማህበሩ ወይ በእድሩ እየተጠየቀ ሞቫይሉን በትልቅ ፌስታል ዉስጥ በማስቀመጥ ተፈትሾ ባዶ እጁን ወደ ግቢዉን ይገባል። ከዛም በተጨማሪ የኤምባሲዉ መግቢያ ሁለተኛ በር ጋር ድጋሜ ተፈትሾ ወደ ውስጥ ይገባል። በስተግራ ወደ ተዘጋጁት ወንበሮች ሁሉ ገብቶ ቦታ ቦታዉን መያዝ ይጀምራል። እንድህ እንዲህ እየተባለ እስከ 12:00 በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሁሉም ገብቶ ቁጭ ይላል። ሌላዉ የሚገርመዉ ትዕይንት ደግሞ የገዛ ኢምባሲያችን ህንፃ ላይ ተራ ፖሊሶች ወጥተዉ አከባቢዉን እየቃኙ ጠበቃዉን ተያይዘዉታል። በተጨማሪም በኤምባሲዉ ዙርያ በሚገኙት ህንፃዎች የተለያዩ ፖሊሶች ተመደቡ። በተለይ ከኤምባሲዉ አጠገቢ በሚገኝ ሲንድያን ሆቴል አከባቢ ትንሽ እንግዶች በመስኮት ወጣ ገባ ሲሉ በፖሊሶች አርፈዉ እንዲቀመጡ ተነገራቸዉና ተደበቁ።

ህዝቡ ተሰብስቦ ዝምታ ሰፍነዋል። መድረክ አከባቢ ለሚኒስትሮችና የተወሰኑ ዲፕሎማቶች ተብሎ 15 ቪ ኣይ ፒ ወንበሮች ተቀምጠዋል። ከነሱም አለፍ ብሎ ሶስት ጠቅላይ ሚኒስትሩና የመድረኩ መሪዎች ይቀመጡባቸዋል ተብለዉ ከነ ጠሬጲዛና ማይክሮፎን የተዘጋጁተዉ ነበሩ። ሁሉም የእንግዶችን መምጣት መጠባበቅ ጀመረ። አንዴ የኤምባሲዉ ደህንነቶች ወደዚህ ወደዚያ ይላሉ። ምንም የማያዉቁ የሱዳን ቦዲጋርዶች /አጃቢዎች/ ገብተዉ ወደዚ ወደዚያ ይላሉ። በመሃል ከተሰበሰበዉ ህዝብ 3 ኤርትራዉያን ተይዘዉ እንዲወጡ ተደረጉ። አሁን ስዓቱ ሄደ ልክ 1:30 ሆነ። እንግዶች አሁንም አልመጡም።

ሁኔታዉ ያላማራቸዉ የኤምባሲዉ ዲፕሎማቶች ግራ ተጋቡ። በዚህ መሃል የአምባሳደር አባዲ ዘሞ አማካሪ የሆኑት ወ/ሮ ፍረወይኒ እና የኤምባሲዉ ፋይናንስና አስተዳደር አቶ ቀለሙ የሃይለማርያምንና የመድረክ መሪዎች ወንበር ያዙ። ወ/*ሮ ፍረወይኒ ትንሽ ማይክሮፎኑን መታመታ በማድረግ “ሚኒስትሮቹ ወደዚህ አገር የመጡት ዋና አላማ ከሱዳን መንግስት ጋር በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ነበር የመጡት። ለዚህም ጉዳይ ዛሬ ጥዋት በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2:00 ወደ ገዳሪፍ /የሱዳን ሌላዉ ከተማ / ሄደዋል። የሄዱበት አላማ ደግሞ የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ የ200 ኪሎዋት የኤሌትሪክ ሃይል ለመዉሰድ ለማስወረቅ ነዉ። እዛ ዉለዉ ከዛ በኋላ በሱዳን ወደ ሚሰራዉ መርሃዊ በተባለዉ ቦታ ያለዉ ትልቁ ግድብ ለመጎብኘት ሄደዋል። የዛሬዉ ፕሮግራም እነሱ በፈለጉት መስረት ከህዝቡ ጋር መገናኘት እንፈልጋለን ይህንን ስዓት ያዙልን ብለዉን ነዉ ስንጠብቃቸዉ የዋልነዉ። እስከ ቅርብ ስዓት ድረስ ስንደዉልላቸዉ ነበር። እንደሚመጡ ነግረዉን ነበር። አሁን ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት ግን በኢትዮጵያ መንግስት ስም ህዝቡን ይህንን ያህል ስዓት ስላስቆየነዉ ይቅርታ ጠይቁልን ብለዋል። እኔም የመንግስት አካል ስለሆንኩኝ ይቅርታዉ እያስተላለፍኩ ነዉ” ሲሉ ተስብሳቢዉ የተወሰነ ማለትም 10% ሲያጨበጭብ 90% ማጉረምረምና በስሜት መናገር ጀመረ።

በዚህ መሃል ፍረወይኒ ንግግርዋን በመቀጠል ይቅርታ ነገ ደሞ ወደ ፈረንሳይ ይበራሉ ስለዚህ 80 ሚሊዮን ህዝብ ሃላፊነት ተሸክመዉ እየዞሩ ነው ስለዚ ምናልባት ለመናገር የምትፈልጉት ነገር ካላችሁ አንድ ሁለት ሰዉ እድል ልስጥ ትላለች።

በዚህ ግዜ የመጀመሪያ እጅ አዉጥቶ ዕድል የተሰጠዉ ሼክ ዳዉድ የአማራ ልማት ማህበር ሊቀመንበር እንዲሁም በባለፈዉ ዓመት በሱዳን የኮሚኒቲው ወክሎ ከሌላ አገራት የዲያስፖራ አካላት ጋር በመሆን የህዳሴን ግድብን ጎብኝቶ የመጣ ሰዉ ነዉ። ሼክ ዳዉድ ሲናገር ፥- እኔ በበኲሌ ይህ ይቅርታ በምንም ታአምር አልቀበለዉም ብሎ ሲናገር ህዝቡን ሁሉ አጨበጨበ ንግግሩን በመቀጠል , በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም እና ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም አለመምጣታቸዉ ለማመኑ በሚያስቸግር ሁኔታ ከብዶኛል፡ ይህ ንቀት ነዉ። የሰዉ አገር 200 ሜጋ ዋት ሃይል እሰጡ እየረዱ የኛ ችግር አልታይ ብሎዋቸዉ ነዉ ወይ በጣም በጣም ያሳዝናል። መንግስታችን የሰዉ አገር ፀጥታ እያስከበረ የኛን መብት ማስከብር አለመቻሉ ጉልበት ስላጣ አይመስለኝም በጣም በጣም አዝኛለሁኝ በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊት ለመጠየቅ ከያዝኩዋቸዉ ጥያቄዎች አንዱ በቅርቡ እምዱርማን ተብሎ በካርቱም በሚገኙዉ ሰፈር ሰሙኑን አንድ ማዚን የሚባል የሱዳን ጦር መሪ የኢትዮጵያ መንግስት ፍቃድ ሰጥቶኛል እያለ ወረቀት እያሳየ ሰዎች ከቤታቸዉ እያስወጣ ወደ እስርቤት እየወረወረ ነዉ። ይህ ለምን ይሆናል። ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጭብጨባ በዛ በመቀጠል መኪ ያተባለ የጉራጌ ልማት ማህበር ሊቀ መንበር ሲናገር ችግሩ የኛ ነዉ ሌላ ጊዜ ወደ ኢምባሲ አንመጣም ባለስልጣን ሲመጣ ግን እንዲህ ለምን እንመጣለን ለምን በማህበር አትደራጁም ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ህዝቡ ማጉረምረም እና አንዳንዶችን መሳደብ ጀመሩ። ጩሆት ሆነ በዚህ ማሃል ወ/ሮ ፍረወይኒ እንዲህ ቀጠለች “ ጠላ ቤት አይደለም ኤምባሲ ነዉ እንደፈለጋችሁት አትጭሁ ስነስርዕእት ስነስርዓት እንደማመጥ። መኪ ያለዉን ትክክል ነዉ። እስቲ እንነጋገር በእዉነት እናንተ በአገራችሁ ከፍቶዋችሁ ነዉ የመጣችሁ? ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ መጥፎ ስለሆነች ነው ወይ? በማለት ህዝቡን ለማግባባት ብትሞክርም ህዝቡ ማጉረምረሙ ቀጠለ በመጨረሻም ስብሰባዉ ያለፍሬ በይቅርታ ተበተነ። የሚገርመዉ ሰዉ ሲገባ ሞቫይል በፊስታል ነበር የተሰበሰበዉ። ከስብሰባዉ ሁሉ ሲወጣ ሌላ ግርግር ሆነ። ሁሉም እስኪወጣ ድረስ 2:30 ሆነ፡ ድራማዉ በእንዲህ ተጠቃለለ።

የመለስ ጎጂ ሃሳቦችና ድርጊቶች (የኢትዮጵያ ሲቪክ ንቅናቄ)

0
0

and ethiooia

Email: ethiocivic@gmail.com  

የመለስ ጎጂ ሃሳቦችና ድርጊቶች

ሕዳር 2006

የኢትዮጵያ አንድነትንና የመንግስት ስርዓቱን የሚመለከቱት የመለስ ሃሳቦችና ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ከባድና አሳሳቢ ትርጉም አላቸው፡፡ የአንድነቱ ጥያቄ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ሲሆን፣ ስርአቱ ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ መብቶች ላይ ማን መወሰን እንደሚችል ያመለክታል፡፡ የአገር ህልውና እና የህዝብ መብትን ያህል ትልቅ ጉዳይ ሊኖር ስለማይችል ክብደቱና አሳሳቢነቱ አያጠያይቅም፡፡

መለስ አንድነትን በሚመለከተው ሃሳቡ ትግራይን ከመገንጠል ኣላማ ጀምሮ ሳይተገብረው ቢቀርም፤ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጓል፤ ህዝብን በቋንቋ ክልሎች ከፋፍሎ በጉራ ፈርዳና ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ለተከሰቱት አማሮችን የማፈናቀል ግፍ መሰረት ጥሏል፤ የመገንጠል “ህገ መንግስታዊ” አንቀፅ አዘጋጅቷል፤ ለሱዳን መሬት አድሏል፤ ዜጎችን አፈናቅሎ ለም መሬት ለውጭ ድርጅቶች በርካሽ ለረዥም ጊዜ አከራይቷል፡፡

የመንግስት ስርዓቱ በቃላት መድብለ ፓርቲ በተግባር ያንድ ፓርቲ አፋኝ ስርዓት ነው፡ስለዚህም ስርዓቱ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ወሳኙ መለስ እንደነበረ ለ21 ዓመታት ደጋግሞ አረጋግጧል፡፡ ሰውየው በኢትዮጵያ በነበሩ መንግስታት በተለመደ መሳሪያ ማለትም የፈላጭ ቆራጭነት ስልጣንን በመጠቀም፣ በኢትዮጵያ ግን ያልተለመደና በውጭ ሃይሎችም ያልተሳካ፣ ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ ለመተግበር ሞክሯል፤ በከፊልም ተሳክቶለታል፡፡

አሁን ጥያቄው ከመለስ ህልፈተ-ህይወት በሁዋላ የኢትዮጵያ ህዝብን አፍኖ አንድነቱን የሚሸረሽረው ስርዓት ምን ይሁን? ነው፡፡ መልሱም የመለስ ስርዓት መፍረስ፣ አስተሳሰቡም መወገዝ አለበት እንደሆነ ለኢትዮጵያውን አሻሚ መሆን የለበትም፡፡

በዚህ መሰረት ካልታረሙ ለወደፊቱም ሊቀጥሉ የሚችሉ፣ ህወሓት የትጥቅ ትግል ከጀመረበት ጀምሮ እሰካሁን ያሉ በዋናነት ከመለስ የፈለቁ ጎጂ አስተሳሰቦችና አሰራሮች ባጭሩ መቃኘት ያስፈልጋል፡፡

ያልተፃፈ የጥንት ታሪክ አሁን ሲፃፍ ያልተረጋገጡ ወሬዎችና ግምቶች እንደ እውነተኛ ታሪክ የመፃፈቸው አደጋ ከፍተኛ ቢሆን የሚጠበቅ ነው፡፡ ታሪኩ ሲፈፀም የነበሩ ሰዎች በህይወት እያሉና የፅሁፍ ማስረጃዎች ሳይታጡ ያልተፈፀመ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የእውነቱ ተፃራሪ የሆነ ታሪክ ሲፃፍና ሲነገር ግን በጣም ያሰገርማል፡፡ ጠንቁም ብዙ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ውሸት የሚያሰራጩ ሰዎችን እንዴት ማመን ይቻላል? ለምንስ በዚህ መልክ ይቀጥላሉ? |ብለን መልስ-አዘል ጥያቄን በማቅረብ ጉዳዩን ላንባቢዎች ፍርድ መተው እንችል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመለስ ትእዛዝ ውሸቱን የሚያሰራጩት ሰዎች ደግሞ በበኩላቸው በውሸቱ የሚያምኑ ሰዎችን መፍጠር ችለዋል፤ ምክንያቱም በጉልበት መገናኛ ብዙሃንን ለሁለት አሰርት ዓመታት በብችኝነት በመቆጣጠር የተወሰነ ህዝብ ጀሮን አይንና አእምሮን ተቆጣጥረው ህዝቡ መስማት፣ ማየትና መግለፅ ያለበትን ሲወስኑ ቆይተዋል፡፡ ስለዚህ ውሸቱ እውነት መስሎ ህዝብን ማወናበዱ እንዳይቀጥል የሚያመዛዝን አእምሮ ያላቸው ዜጎች እውነቱን ለማወቅና ለማሳወቅ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡ ባንድ በኩል በውሸት ላይ በተመሰረተ ቅስቀሳ የተስፋፋውን ድንቁርና ማጋለጥና ማስወገድ፤ በሌላ በኩል ለዘለቄታዊ የህዝብ ደህንነት ጥፋት የሚያስከትሉትን ሃሳቦችና አሰራሮች እንደ አደገኛ ቆሻሻ ላንዴና ለሁሌ መቅበር ያስፈልጋል፡፡

መለስና ግብረ-አበሮቹ በ1968 ባወጡት የህወሓት (የዚያን ጊዜ ተሓህት) መግለጫ (ማኒፌስቶ) ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዓላማ እንደነበራቸው በይፋ ስለገለፁ፣ መለስ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ እንጂ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ራእይ ይዞ ለትግል አልተሰለፈም፡፡ ሰውየው የፈለገው ራእይ ቢኖረው ኢትዮጵያን የሚመለከት በጎ ነገር ሊሆን አይችልም፡፡ ሃቁ ይህ ነው፤ በቃ፡፡

የመለስ ፍጡራን ማኒፌስቶው መታረሙን በመጥቀስ ቁም ነገር የተናገሩ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ቁምነገሩን ጭራሽ የሳቱት ቢሆኑም፣ ማኒፌስቶው እንደታረመ የሚገልፁት ሰዎች ቢያንስ የእርማቱን አስፈላጊነት ስለሚገነዘቡ ይህንን ግንዛቤ ከሌላቸው ሰዎች ይሻላሉ፡፡ ሆኖም፡

1ኛ ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል ዓላማ ማንሳቱ ራሱ በኢትዮጵያዊነቱ በሚያምን ሰው ሊነሳ እንደማይችል ሊያስተባብሉ አይችሉም፡፡

2ኛ እርማቱ (በ1971 የህወሓት ጉባኤ) በመገንጠል ፈንታ የትግራይ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ እንዲወስን መታገል እንደ ድርጅታዊ ዓላማ ማስቀመጥ ስለነበረ ከማጭበርበር የተለየ ትርጉም የለውም፡፡ ምክንያቱም በአንድነትና በመገንጠል አማራጮች አንድ ህዝብ ድምፁን በመስጠት መወሰን የሚያስፈልገው የአንድነትና የመገንጠል ሃይሎች ሲኖሩ ነው፡፡ ደርግ ፀረ ዴሞክራሲ ቢሆንም አቋሙ ላንድነት ነበር፤ የትግራይ ህዝብም የመገንጠል ጥያቄ አላነሳም፡፡ ስለዚህ የመገንጠል ፍላጎቱ የመለስና ግብረ-አበሮቹ አቋም ነበር፡፡ መለስና ግብረ-አበሮቹ በመገንጠል ፍላጎታቸው ያልቀጠሉበት አንዱ ምክንያት በተለይ ህዝብን አፍነው ከመቆጣጠራቸው በፊት ለዓላማቸው የህዝብ ሰፊ ድጋፍና ያንዳንድ ታጋዮች ትብብር እንደማያገኙ ስለተገነዘቡ ነው፡፡ በዛም ምክንያት በድርጅታቸው ውስጥ በ68 የፃፉትን ማኒፌስቶ ለድርጅቱ አባሎች ሳያሰራጩ ቀርተዋል፡ ሁለተኛው ምክንያት የህወሓት ሰራዊት በኢትዮጵያ ደረጃ ስልጣን ለመያዝ የሚያስችል ጥንካሬ ስላካበተና እነ መለስ ራሳቸው በጠፈጠፏቸው አሻንጉሊት ድርጅቶች መሳሪያነት ኢትዮጵያውያንን እየከፋፈሉና እጨፈጨፉ መግዛትና መዝረፍ ስለቻሉ ነው፡፡ ትግራይን የመገንጠል ቅሰቃሳ ከቆመ በሁዋላም የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ በመገንጠል መብት ስም ህጋዊ ልባስ እንዲያገኝ በህገ መንግስት ተካትቷል፡፡

እውነቱ ከላይ እንደተገለፀው የማሻማ እያለ መለስ የተቆጣጠረው ህወሓት ከመጀመሪያ ጀምሮ ለኢትዮጵያ አንድነት እንደታገለ፣ ያ ቡድን ዓላማው ኢትዮጵያን ለመታደግ እንደነበረ አሁን የሚወራው የፈጠራ ታሪክ ከየት መጣ? በኢህአዴግ የረቀቀው ህገ መንግስት ኢትዮጵያን ከመገነጣጠል እንዳዳነ የሚሰራጨው ቅስቀሳ በታሪክ ውሸት፣ በአመክንዮ የተዛባ ነው፡፡ ሻዕብያ በራሱ አቅምና በመለስ ጥረት ኤርትራን መገንጠል ችሏል፤ በኢትዮጵያ የመገንጠል ጥያቄ ካነሱት በቂ ወታደራዊ አቅም ያልገነቡ ድርጅቶች ከማስገንጠል የተገቱት በኢህአዴግ ጉልበት እንጂ በህገ መንግስቱ አይደለም፡፡ ስለሆነም የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ አንድነትን የሚያጠናክር ሳይሆን በአገራችን በመታየት ላይ እንዳለው ህዝብን የሚያጋጭና የሚያፈነቅል መርዝ በመሆኑ መወገድ አለበት፡፡

መለስ በህወሓት ውስጥ በ1968 ተጠባባቂ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ከሆነ ጀምሮ እሰከ 2004 ህልፈተ ህይወቱ ድረስ ለ36 ዓመታት በሰው ህይወት ላይ ለመወሰን የሚያስችለው ስልጣን ይዞ የዜጎች ህይወት እየቀጨ ቆይቷል፡፡ የመለስን አገዛዝ መገለጫዎች በሚከተሉት አርእስት ስር ማየትና የያንዳነዱ ባህርይ፣ አቋምና ድርጊት እውነታ በማስረጃ እያረጋገጥን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ ክብሩ እንዲጠበቅ የመለስ እኩይ ስርኣት ተወግዞ ካገራችን እንዲወገድ ከፍተኛ ጥረት እንደሚያስፈልግ እናሳስባለን፡፡

የህወሓት/ኢህአዴግ ማለትም የመለስ የስልጣን መሰረት ጉልበት ነው፡፡ ውሸትና ሙስና የተንሰራፉትም ከጀርባቸው ጉልበት ስላለ እንጂ በቀላሉ ተጋልጠው ሊወገዱ ይችሉ ነበር፡፡ ስለዚህ ህወሓት/ኢህአዴግ የመለስ ፈር መከተሉን ከቀጠለ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ጉልበት ስለሚጠቀም ብዙ ዓይነት ወንጀሎች መፈፀም ይችላል፡፡ ሌሎች ፀረ ህዝብ ድርጊቶቹም ህዝብን በማሸማቀቅ ስለሚፈፅማቸው ጉልበት ሰውን እንደመጉጃና እንደማስፈራሪያ ለፖሊሲዎቹ ተፈፃሚነት የሚፈጥረው አመቺ ሁኔታ መገንዘብ ይቻላል፡፡

1.   ፈላጭ ቆራጭነት

በኢትዮጵያ ያንድ ግለ-ሰብ ፈላጭ-ቆራጭ አምባገነንነት አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ቢሆንም ከተካሄደው ረዥም ትግልና፣ ከተከፈለው እጅግ ከባድ መሰዋእት አንፃር ሲታይ ትውልዱን በበላ ትግል ፈላጭ-ቆራጭ ግለ-ሰብ መንገሱ ባንድ በኩል የሰውየው ኢሰብአዊነት አረገግጧል፡፡ የመለስ ፈላጭ ቆራጭነት በህወሓት ውስጥ ከማሌሊት ምስረታ ጋር የሚፈልጋቸውን ካድሬዎች መልምሎ፣ የማይፈልጋቸውን አባላት ካጠቃ በሁዋላ የጀመረ ነው፡፡ በሌላ በኩልም ታጥቆ ከታገለው ሃይል ጥቂቱ ባለው ሙስና ጎልቶ እንደሚታየው ለዝርፊያ የቆመ እንደሆነ፣ አብዛኛው የድርጅቱ አባል ደግሞ ታግሎ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የመገንባት ብቃት እንደሌለውና የአምባገነን መሳሪያ ሆኖ የግለ-ሰብ አምባገነንነት በመመስረቱ፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በመረገጣቸው፣ ፍትሕና የህግ የበላይነት ባለመኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ ስለዚህ የመለስ ፈላጭ ቆራጭነትና የህወሓት/ኢህአዴግ አባላት አድርባይነትና መሰሪያነት ህዝብን የሚያሸማቅቅ ገዳይና አፋኝ ስርኣት ፈጥሯል፡፡

2.   ተከታታይ የጅምላና የተናጠል ግድያዎች

ቀደም ብሎ የደርግ ግፎች የታዛቢዎችን ቀልብ በሳቡበት የትጥቅ ትግል ጊዜ ግልፅነትና ተጠያቂነት ባልነበረበት ሁኔታ የህወሓት አመራር በድርጅቱ አባላት እና በሰላማዊ ህዝቡ ላይ በምስጢር ብዙ ግድያዎች ይፈፀሙ ነበር፡፡ ብዙ የትግራይ ህዝብና የህወሓት ተራ አባሎች በዝምድና፣ በጐረቤትነትና በጓደኝነት የሚያውቃቸው የህወሓት ሰለባዎች መኖራቸውን ቢያውቁም ባገዛዙ ስለታፈኑ፣ ከስርዓቱ ጋር በጥቅም ስለተሳሰሩ፣ ወይም የህወሓት ወታደራዊ ድል እንደ ጀብድ ስለሚያዩና ጀብዱን በመጋራት ዝና የሚያገኙ ስለሚመስላቸው በህወሓት ስለተፈፀሙት ወንጀሎች በይፋ አይናገሩም፡፡

በትጥቅ ትግሉ ጊዜ በተለይ በሲቪሎች በድብቅ የተፈፀሙት ግድያዎች ተደብቀው አይቀሩም፤ በግድያው ጊዜ ህፃናት የነበሩና ባገር ቤትና በስደት ያደጉም በቤተሰብ መረጃው ስለተላለፈላቸው ያውቁታል፡፡ ስለዚህ የድብቅ ግድያዎቹ፣ በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ (1985፣ 1993፣ 1997፣ 1998) እና በሌሎች ከተሞች በይፋ እንደተፈፀሙት ጭፍጨፋዎች በታሪክ ይመዘገባሉ፡፡ ስለዚህም ግፍ ከፈፀመው ሃይል ጋር የወገኑት ዜጎች ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው፡፡

3.   የፖለቲካ ሙስና እና ጎጠኝነት

ብዙ ጊዜ ስለ ሙስና ሲወራ ከጉቦና ስልጣንን ካለአግባብ ከመጠቀምና ሃብት ከማካበት ጋር ይያያዛል፡፡ ባለስልጣኖች የሚፈፅሟቸውን የሙስና ድርጊቶች ለመፈፀም የሚያስችላቸው መሰረት ግን ስልጣኑን ለመያዝ የሚፈፅሙት በጉልበት የታጀበ ቅጥፈት ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በውሸት ምርጫ ስልጣኑን በህዝብ ፍላጎት እንዳገኘ የሚገልፀው በጉልበት የሚፈልገውን ማድረግ ስለሚችል እንጂ ማጭበርበሩ፣ ህዝብን ማስገደዱና ድምፅን መዝረፉ ህዝብ ስለማይነቃበት አይደለም፡፡ በውሸት ምርጫ ከፍተኛውን የስልጣን እርከን የመያዝ አሰራር የስርዓቱ መገለጫ እስከሆነ ድረስ ለሙስና ድርጊቶች አመቺ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ከላይ ከፈተኛውን መንግስታዊ ስልጣን በጉልበትና ቅጥፈት የሚቆጣጠሩና ስልጣኑን ለዝርፊያና ለግል ምቾት የሚጠቀሙ ሰዎች አስካሉና ለዚህ ድርጊት በውስጣቸው መተማመን እንዲኖራቸው በነገድ፣ በጎጥና በዝምድና የተሳሰሩ ሰዎች እስከገዙ ድረስ፣ ከታች የገዢዎቹን አርአያ እየተከተለ ሙሰኛ የሚሆን መብዛቱ የሚገርም አይደለም፡፡

መለስ ሙስናን በቅንነት የሚቃወም ቢሆን ኖሮ በነበረው ፍፁም ስልጣን ሊገታው እየቻለ ከሱ በፊት ከነበሩት አገዛዞች ባጠረ ጊዜ ውስጥ ለከት የሌለው ሙስና አይስፋፋም ነበር፡፡ በተፃራሪው ግን መለስ ገና ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ለተራበ ህዝብ የመጣውን እርዳታ ለምሳሌ ተጋይ የነበረውን ገብረመድህን አርአያን እህል የሚሸጥ ነጋዴ መስሎ ገንዘብ ከእርዳታ ሰጪዎች እንዲቀበል ያደርግ ነበር (Tigray, Ethiopia’s untold story, by Max Peberdy)፡፡ ትእምትን (ኢፈርት) ለመመስረት የተጠቀመበት ገንዘብ ከእርዳታ ተጭበርብሮ የተወሰደ ነው፡፡ የመለስ ሚስት የትእምት ከፍተኛ ስልጣን የያዘችው በቤተሰባዊ የሙስና አሰራር ነው፡፡ መለስ ያገዛዙ አካል ሆነው የተፈጠሩት ሙሰኞች ለስርዓቱ የቆሙ የሱ ደጋፊዎች እንደሆኑና እንደሚያስፈልጉት አያውቅም ማለት የዋህነት ነው፡፡

ሰውየው ግን ደርጊቶቹን በቃላቱ፣ ቃላቱን በድርጊቶቹ የማፍረስ አመል ነበረው፡፡ ዴሞክራሲን የማይፈልገው ወንጀሎቹ እንዳይጋለጡ ስለሚሰጋ መሆኑ እየታወቀ፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን እንዳይገነባ ሙስና እንዳደናቅፈው ለውጭ ዜጎች እንደሚከተለው ይገልፅ ነበር፡፡ ለምሳሌ አሌከስ ዴ ዋል (Alex de Waal) መለስ በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበራት ላይ በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት ለሚያወግዙት ሰዎች መልሱ ምን እንደሆነ ጠይቆት መለስ ሲመልስ „የአባታዊነትና የሙስና የበላይነት ባለበት የፖለቲካ ኢኮኖሚ (በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት እሱን) የሚያወግዙት ሰዎች ዴሞክራሲን እንዴት እንደሚገልፁትና ወደ ዴሞክራሲ የሚወስደው አዋጪ መንገድ እንዴት እንደሚፈልጉ ያውቃሉ ወይ?“ ብሎ በመጠየቅ ዴሞክራሲ እንደሌለ ከማመን አልፎ ጥያቄውን ማንሳቱን ስህተት ሊያስመስለው ይሞክራል፡፡ (Alex de Waal ፣ Dec. 06, 2012፣ ጉግል) የዜጎች መብቶችን ያፈነው ራሱ፣ ሙስና ያንሰራፋውም ራሱ መሆኑ ቢታወቅም መለስ ለኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገነባ ከመግለፅ ቦዝኖ አያቅም፡፡

4.   ህዝቡን በአንድ ሰው ሃሳብ እንዲመራ ማስገደድ

የተለያዩ ሃሳቦች ሲገለፁ እየተፋተጉ ስህተቶች ይታረማሉ፤ ከተለያዩ ሃሳቦች የተሻሉ ሃሳቦች ሊፈልቁ እና በተግባር እየተፈተኑ ሲጎለብቱ እውቀት በሂደት ያድጋል፡፡ መለስ የራሱ ሃሳብ ቢይዝና በፍላጎት ለሚቀበሉት ሃሳቡን ለማስፋፋት ቢሞክር ችግር አይሆንም ነበር፡፡ ችግሩ የፖሊቲካ ስልጣኑን፣ መገናኛ ብዙሃንን፣ የሚቆጣጠረው አስተዳደርንና ከተነገራቸው ውጪ የራሳቸውን ሃሳብ መግለፅ የማይፈቀድላቸው አሻንጉሊት ካድሬዎችን እየተጠቀመ የዜጎች ሃሳብ የሚቆጣጠርበት ስርዓት መመስረቱ ነበር፡፡

የመለስ ሃሳብ በጉልበት ከሚሰራጭ የሃይማኖት ስብከት የማይለይ፤ አማራጭ ስለሚከለክል ሚዛናዊ አስተሳሰብ ከነፃነት ጋር የሚያፍን፤ በማስረፅ (indoctrination) መልክ የሚሰራጭ፣ ካለ ደራሲው ፍላጎት አዲስ ግብአት ስለማይቀበል የማያድግና፤ የተለየ ሃሳብ የሚያቀርቡ ዜጎችን በጠላትነት በመፈረጅ በዜጎች መካከል የጠላትነት መንፈስ የሚፈጠር ቀኖና ነበር፡፡ ሰውየው ዜጎች በሱ ትእዛዝ እንዲተዳደሩ ብቻ ሳይሆን እሱ ራሱ ቢያምነበትም ባያምነበትም ላጭር ጊዜም ቢሆን ዜጎች በሱ ሃሳብ እንዲመሩ ያደርግ ነበር፡፡ በዚህ አሰራሩም ማመዛዘን የማይችሉ አምላኪዎችና አምላኪዎች በመምሰል የግል ጥቅማቸውን የሚያሳድዱ አድርባዮች ፈጥሯል፡፡ መለስ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ የማሌሊትን እምነት ያልተቀበሉ እንደ ጠላት ያሳድዳቸውና የጋንግሪን ስም አውጥተላቸው በጋንግሪን እንደተለከፈ አካል እዲቆረጡ ይቀሰቅስና በተግባር የተለየ ሃሳብን ለማጥፋት የተለየ ሃሳብ ባላቸው አባላት ላይ ግፍ ይፈፅም ነበር፡፡

መለስ ማሌሊትን በህወሓት ውስጥ ፍፁም ስልጣን ለመጠቅለል ከተጠቀመባት በሁዋላ ስለ ነጭ ካፒታሊዝም ማውራት ጀመረ፡፡ ስለዚህ ሰውየው የተወሰነ ሃሳብ ሲያሰራጭ በመርህ ደረጃ አምኖበት ሳይሆን ሃሳቡን ለስልጣን መሳሪያ ለመጠቀም ነበር፡፡ እሱ ራሱ ሃሳቡን መቀየር ስለሚችል፣ ይዞት ቆይቶ የሚጥለው ሃሳብ ትክክል እንዳልነበረ ማመኑን ያመለክታል፡፡ መሳሳቱን የሚገነዘብ ሰው ደግሞ ሌሎች ሰዎችም ትክክል ሊሆኑም ሊሳሳቱም እንደሚችሉ መገንዘብ መቻል አለበት፡፡ መለስ ሁሉንም የሱ ተከታዮች ያልሆኑትን በራሳቸው ፖለቲካዊ ሃሳብ የሚመሩትን ዜጎች በራሱ ብቻ ሳይሆን በህዝብ ጠላትነት እየፈረጀ አልፏል፡፡ ስለዚህ ማመዛዘን የሚችሉና ቅንነት ያላቸው የኢህአዴግ አባሎች ካሉ የመለስን መንገድ መከተል የለባቸውም፡፡

5.   የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መርገጥ

የኢህአዴግ ህገ መንግስት ብዙ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ቢያካትትም የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ህገ መንግስቱን ባያከብሩ አያስገርምም፡፡ ህገ መንግስቱ የተዘጋጀው በወንጀለኞች ማለትም በመለስና ግብረ-አበሮቹ ይሁንታ ስለሆነ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ ሰዎች መንግስታዊ ስልጣን ከያዙም በሁዋላ በተራ ቁጥር 1 እንደጠቀስነው ወንጀል መፈፀማቸውን ቀጥለዋል፡፡ ግፈኛ ገዳዮች “እያንዳንዱ ዜጋ በህይወት የመኖር መብት” እንዳለው ቢገልፁ ምን ትርጉም አለው?

የኢህአዴግ አባሎችና ደጋፊዎች ህገ መንግስቱን በታጋዮች ደም እንደተፃፈ ተኩራርተው ሲገልፁ ታጋዮቹ ራሳቸው የራሳቸውን መብት አስከብረው እንደማያውቁ የተገንዘቡ አይመስሉም፤ ወይም እውነቱ እንዲገለፅ አይፈልጉም፡፡ በትግሉ ጊዜ ድርጅቱን መለስና ጥቂት ግብረ-አበሮቹ ታጋዮችን ሲያስገድሉ፣ አስረው ሲያሰቃዩና ሲያባርሩ እንኳንና ተቃውሞ ማቅረብ መጠየቅም በአመራሩ የተወሰዱ እርምጃዎችን ትክክለኛነት እንደ መጠራጠር፣ በአመራሩ እምነት ማጣትና ሌሎችም እምነት እንዲያጡ በማድረግ ድርጅቱን ለማፈረስ እንደመሞከር እየተተረጐመ ያስወነጅል ነበር፡፡ ሁሉም እንደ በቀቀን የተባለውን እንዲደግም ስለሚፈለግም ዝምታም ያስጠረጥር ነበር፡፡ የድርጅቱን ማለትም የኢህአዴግን በተለይም የህወሓትን ታሪክ የማያውቁ አንባቢዎች ታሪኩን ማጥናት ሳያስፈልገቸው ከኢህአዴግ መንግስት ባህሪ የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንደሚረግጡ ያውቃሉ፤ የተለየ ሃሳብ ያላቸውና መብታቸው እንዲከበር የሚጠይቁ ሰዎች እንዴት በቅጥፈት እየተወንጀሉ እንደሚጠቁ ማንም በቅን ህሊና የሚያስተውል ኢትዮጵያዊ ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡

6.   በግድ ማደራጀትና ነፃ ድርጅቶች እንዳይኖሩ/እንዲዳከሙ ማድረግ 

የተማሩና በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች ራሳቸውን ማደራጀት ይችላሉ፤ በገጠር የሚኖረው ህዝብ ግን የመደራጀት ልምድ ስለሚያንሰው፣ እንደፈለገው በዘመናዊ መጓጓዣ መጠቀም ይሁን በስልክ መገናኘት ስለማይችል፣ ከማሃይምነት ስላልተላቀቀና፣ የኑሮረው ሁኔታ ፋታ ስለማይሰጠው ራሱን የማደራጀት አቅሙ የተወሰነ ነው፡፡

የተማሩና በከተሞች የሚኖሩ ዜጎች የገጠሩን ህዝብ እንዲደራጅ ሊያግዙት ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ኢህአዴግ የመንግስት ስልጣን፣ ጉልበት፣ አስተዳደርና የመንግስት ንብረት እየተጠቀመ ስጋት በማስፈን ህዝቡን እንደመሳሪያ ለማሽከርከርና ትእዛዙን ለማስፈፀም በመለሳዊ ነገድ-ተኮር ስልትና እስከ ቤተሰብ ድረስ ለመቆጣጠር በሚያመች መልክ በራሱ ሹመኞች ስር ያደራጃል፡፡ ይህ ኣይነት ስልት አፋኝና አማራጭን የሚነፍግ የሁሉም ጠርናፊ (totalitarian) ስርዓቶች አደረጃጀት ነው፡፡ ከኢህአዴግ ነፃ ሆነው በሙያ፣ እንደ ሲቪክ ማህበራትና እንደ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመደራጀት የሚሞክሩ ዜጎች በአገዛዙ ይዋከባሉ፤ እንቅስቃሴያቸው ይገታል፤ ፍርሃት በማስፈን አባላትና ደጋፊዎች እንዳይጠጓቸው፣ ለህይወታቸውና ነፃነታቸው ዋስትና እንዲያጡ ይደረጋሉ፤ ህይወታቸው የተቀጨም አሉ፡፡ በዚህ አሰራር አገዛዙ በቃላት ስለ መድብለ ፓርቲ እያወራ በተግባር የአንድ ፓርቲ ስርዓት አስፍኗል፡፡

7.   ህዝብን በቋንቋ መከፋፈል

የአገራችን ክፍለ ሀገሮች በቋንቋ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑና የነገድ ድርጅቶች በብዛት እንዲመሰረቱ መደረጋቸው በተወሰኑ ምሁራን መካከል የነበረውን ነገዳዊ ቅራኔ ተቋማዊ በሆነ መልክ፣ ማለትም በቋንቋ ክልሎች፣ በነገድ ድርጅቶችና ባስተዳደራዊ መዋቅር ለሁሉም ህዝብ እንዲዳረስ ተድርጓል፡፡

የብሄር ብሄረሰቦች መብት መከበር የሚደገፍ መሠረታዊ የዴሞክራሲ ጥያቄ ቢሆንም፣ የመለስ ነገድ-ተኮር ፖለቲካ ግን በዋናነት የኢትዮጵያ ህዝብን ከፋፍሎ ለመግዛት የተጠቀመበት ስልት ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት እየተሸረሸረ ይገኛል፡፡ የሱማሌ ክልል ፕረዚደንት ትግሬዎች አማሮች ወደ ስልጣን እንዲመለሱ እንደማይፈልጉ መናገሩ፣ አማሮች በአገራቸው ውስጥ ከጉራ ፈርዳና ከቤኒ ሻንወጉል-ገሙዝ በግፍ እንዲባረሩ መደረጉ፣ ባገሪቱ እስር ቤቶች የኦሮሞዎች ቁጥር መብዛቱ እና ባንዳንድ ወገኖች መለስና ተከታዮቹ ለፈፀሟቸው ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ተጠያቂና እንዲሁም በልማት ተጠቃሚ ተደርጎ መታየቱ መለስ በመሃንዲስነት የመሰረተው መርዘኛ ስርአት ውጤት ነው፡፡

8.   የተቋሞች ወገንተኝነት

መለስ ስልጣን ከመያዙ በፊት የነበሩ የተማሩና ልምድ ያካበቱ ኢትዮጵያውያን የሲቪልና የሰራዊት አባሎችን እንደ ባእድ አባርሮ ከነበቴሰባቸው ለስራ አጥነትና ለችግር እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡ ቀጥሎ ሁሉም ታጣቂ ሃይሎች፣ ህግ አውጪው፣ ያስተዳደርና የፍርድ ቤት ተቋሞች፣ የሙያና የሃይማኖት ድርጅቶች ሳይቀሩ ያንድ ፖሊቲካ ድርጅት(መለስ በህይወት እስከነበረበት ጊዜም ያንድ ግለ-ሰብ) መሳሪያ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ እነዚህ ተቋሞች ለራሳቸው ተነፃፃሪ ነፃነት እንዲኖራቸውና ህዝብን በእኩልነት እንዲያገለግሉ ያንድ ፓርቲ ስርዓቱ ፈርሶ፤ በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መገንባት አለበት፡፡

9.   መርዘኛ የጥላቻ ቅስቀሳ

በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ማንም ዜጋ ኢትዮጵያውያንን እንደ ወገኑ ማየትና ለራሱ የሚፈልገው የዜግንት ክብር ለማንም ኢትዮጵያዊም እንደሚገባ መቀበል አለበት፡፡ ፖለቲካው ነገድ-ተኮር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዋናነት በቅንጅት ላይ ተመስርቶ የነበረው የዘር ማጥፋት ክስ የጥፋት ዒላማ ተደርጎ የተገለፀው የህዝብ ወገን (የትግራይ ህዝብ) አጥፊ ተደርጎ በተወነጀለው ወገን ላይ (በዋናነት በአማራው) የጥላቻ ስሜት ለመቀስቀስ ነው፡፡

ተከሳሹ ኢንተርሃምዌን መስሎ እንዲታይ ቅስቀሳ ተደርጓል፡፡ ኢንተርሃምዌ በሩዋንዳ በ1994 እ.አ.አ. እስከ 800 000 የሚደርሱ ሰላማዊ ሰዎችን (በዋናነት ቱትሲዎችንና እንዲሁም ለዘብተኛ ሁቱዎችን) የገደለ የመንግስት አካል የሆነ የሁቱ ሚሊሽያ ነበር፡፡ በቅንጅት አባላትና ሌሎች ዜጎች ላይ የተመሰረተው የፈጠራ የዘር ማጥፋት ክስ ውድቅ ቢሆንም የቅስቀሳ መልእክቱ ተላልፏል፤ በህዝብ አለመተማመን አሰራጭቷል፡፡ ኢንተርሃምዌ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ ጥግተኛ፣ ቅንጅት ወዘተ ተመሳሳይ ትርጉም እንዲኖራቸውና በተወሰነ የህዝብ ክፍል ላይ የኢትዮጵያ አንድነትን በሚፈልጉ ዜጎች ላይ የጥላቻ መቀስቀሻና ማስፈራሪያ ተደርገዋል፡፡

10.  አስፀያፊ ባህል

አገዛዙ ህዝቡን እያሸበረ አሸማቅቆና አፍኖ ስለሚገዛ ተቃዋሚዎች፣ ጋዜጤኞችና የህዝብን መብቶች ለማስከበር የሚሞክሩ ህዝባዊ (ሲቪክ) ድርጅቶች ሊያድጉ አልቻሉም፡፡ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንደሚባለው ግን መለስ አገዛዙን አሰፀያፊ የሆነ ዜጎችን የማዋረድና የማሰቃየት አመል አስለምዶታል፡፡

መለስ ሁሉንም ስለተቆጣጠረ ተቃዋሚዎቹም በቁጥጥሩ ስር እንዳሉና ምንም እንደማያሰጉት እያወቀ የሚፈፅማቸው ድርጊቶችና የሚረጫቸው ቃላት የቆሰለ ምርኮኛን ረግጦ እንደሚደበድብ፣ በላዩ ላይ እንደሚተፋና እንደሚቅራራ ሰው ነበር፡፡ ለምሳሌ በ2002ቱ የህወሓት 37ኛ ዓመት ሲያከብር ለውሸት ምርጫም ይቀሰቅስ ስለነበረ፤ በህዝብ ድምፅ ላይ እሱ ራሱ ወሳኝ መሆኑ እያወቀ አስነዋሪ ንግግር ከማድረግ አልተቆጠበም፡፡ የድሮ ጓደኞቹን በይፋ ገለባ፣ እንጉብላይ፣ ለህዝብ ጠላቶች ሽፋን የሆኑ እያለ ሰደባቸው፡፡ ህዝባችን ጨዋነትን እንደ ትልቅ እሴት ያያል፡፡ መለስ ግን ባህላችንን የሚበክልና ለነበረው የራሱ ስልጣንም ክብር የማይሰጥ አመሉ አስፀያፊ ነበር፡፡ መለስ የተለየ ሃሳብ የገለፁ ሰዎችን አመክንዮ ባለው አቀራረብ ስህተት የሚለውን ሃሳባቸው በመግለፅ ፈንታ የሰዎቹ ጭንቅላት እንደበሰበሰ ይሰድብ ነበር፡ ሰው በፅኑ ካልታመመ ጭንቅላቱ አይበሰብስም፤ ጭንቅላቱ እስኪበሰብስ ከታመመም ተቃዋሚ አይሆንም፡፡ ስለዚህ በመለስ የሚሰደቡት ጤኔኛ ሰዎች ናቸው፡፡

አገዛዙ ራሱ ሊያስከበረው የሚገባውን ህግ በመጣስ ሊያጠቃው የሚፈልገውን ሰው (ለምሳሌ ስየን) ካሰረ በሁዋላ ያሰረውን ሰው የሚጎዳ አዲስ ህግ በማውጣት፣ ህግ ወደ ሁዋላ ተመልሶ ተፈፃሚነት እንዲኖረው ማድረጉ አሰፀያፊና ፍርደ ገምደላዊ የበቀል ድርጊት ነው፡፡ በውሸት ተከሰው ታስረው የሚሰቃዩ ዜጎችን በሽምግልና ስም እርቅ ፈላጊ መስሎ በመታየት ህዝብን ለማወናበድ የሚደረግ ቅስቀሳ፣ ነፃነታቸው የተነፈጉ እስረኞች በስነ-ልቡና በማሰቃየት ራሳቸውን እንዲወነጅሉ (ቅንጅት ወዘተ.. ብርቱካን ሚደቅሳ ለሁለተኛ ጊዜ) ማድረግ መለስ ምን ያህል የሰውን ሰብአዊ ክብር የማንቋሸሽ አመል እንደነበረው ያመለክታሉ፡፡ መለስ በአንድ በኩል ለሰብአዊና ዴሞክራሲአዊ መብቶች በሚታገሉ ዜጎች ላይ የጭካኔና አስፀያፊ ድርጊቶች ሲፈፅም በሌላ በኩል ጤንነትን ለሚጎዱና የስነ ምግባር ብልሹነት ለሚያስከትሉ የጫትና አደንዥ እፆች ሱስ መስፋፋት ሊበራል ዴሞክራሲያዊ ሆኖ አልፎአል፡፡

የውሸት ምርጫ ማካሄዱ ራሱ ብዙ አሰፀያፊ ድርጊቶችን ያጠቃልላል፤ ህዝቡንና ተቃዋሚዎችን ያሸማቅቃል፣ የምርጫ ቦርዱን፣ ዳኞቹን፣ የመንግስት ሰራተኞቹንና ካድሬዎቹን ለቅጥፈት፣ ታጣቂዎቹን ለጉልበት ተግባሮች ያሰማራል፤ ማጭበርበር፣ ጉልበት መጠቀምና፣ መዋሸት ስልጣንን ለመያዝ፣ በስልጣን ተጠቅሞም የህዝብና የእርዳታ ሃብት መዝረፍ መጥፎ አርአያ የሆኑ የአገዛኡ መገለጫዎች ሆነዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ዘርፈ-ብዙ ጎጂ ድርጊቶችና ጠባዮች ስንገልፅ ባገዛዙ የተጀመሩ ጠቃሚ ድርጊቶች የሉም ለማለት አይደለም፡፡ በተለይ የመሰረተ ልማት ጥሩ ጀማሮዎች አሉ፡፡ ያሉትም በጥራት እንዲያድጉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

ጥሩ ስራዎች እንዳሉ በመጥቀስ ጎጂዎቹን ለመደበቅ መሞከር ግን ጉዳቶቹ እንዲቀጥሉ ከማድረግ አይለይም፤ ስታሊን ከኢንዱስትሪ እድገት፣ ጋዳፊ ከውሃ አቅርቦት ጋር መንግስቱ ሃይለማርያምም ማሃይምነትን በማጥፋት ሙከራ በአዎንታዊ ሚናቸው ይጠቀሳሉ፤ በዚህ ምክንያት ግን አረሜኔያዊ ድርጊቶቻቸው እየተወገዙ እንዳይደገሙ የሚደረገው ጥረት አልተገታም፡፡ ስለዚህ ባገራችንም በዋናነት መለስ ያመጣቸው የአረሜኔው ስርአት መገለጫዎች እንዲወገዱ ጥረታችን መጧጧፍ አለበት፡፡

ከላይ እንደተገለፀው መለስ በአገርና በህዝብ ዘርፈ-ብዙ ወንጀሎች የፈፀመ፣ በወንጀሎቹ ህዝባዊ ፍርድ ሳያገኝ ያለፈ ሰው ነው፡፡ ቢሆንም እሱ ያሳደጋቸው ደጋፊዎቹና ተከታዮቹ የስልጣን እድሜቸውን ለማራዘም ታላቅ አገራዊ ራእይ የነበረው መሪ ነበር እያሉ በሚቆጣጠሩት የመገናኛ ብዙሃን ህዝብን ሲያደነቁሩ ከርመዋል፤ አሁንም ይቀጥላሉ፡፡

በተለይም መለስ „ዴሞክራሲያዊ ልማታዊ መንግስት“ እንደተመሰረተና ኢትዮጵያም በኢኪኖሚ በጣም እንዳደገች ያልተቆጠበ የውሸት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚህ የውሸት ፕሮፓጋንዳ መሠረት ደግሞ በመለስ አገዛዝ ተሰሩ የተባሉትን ወይም እሱ ያቀዳቸው ናቸው የተባሉትን የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በመጥቀስ ነው፡፡ ሃቁ ግን ከዚህ ነጭ ውሸት የተለየ ነው፡፡

በመሠረቱ ማንኛውም ስርዓት ወይም መንግስት፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነም ያልሆነም፣ የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ስራዎች መስራቱ የሚጠበቅ ነው፡፡ እጅና እግሩን አጣጥፎ የሚቀመጥ ስርኣት የለም፡፡ በተለይም ዴሞክራሲያዊ ተቀባይነት (legitimacy) የሌላቸው ስርአቶች በልማት ለውጥ አምጥተናል እያሉ አገዛዛቸውን ለማራዘም እንደሚጠቀሙ በታሪክ የታየ አሁንም በተለያዩ አገሮች የሚታይ ክስተት ነው፡፡ መለስ ባጭበረበራቸው ምርጫዎችና በፈፀማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዴሞክራሲያዊ እንዳልነበረ እንኳን የኢትዮጵያ ህዝበ ይቅርና የሚደግፉት የውጭ መንግስታትና እንዲሁም አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሚመሰክሩት ሃቅ ነው፡፡ ስለሆነም መለስ „ልማታዊ መንግስት“ የአገዛዙን እድሜ ለማራዘምና እሱና ተከታዮቹ የህዝብ ሃብትን ለመዝረፍ የተጠቀሙበት ስልት ነው፡፡

በመለስ አገዛዝ የተሰሩ የመሰረተ ልማት አውታሮች በአብዛኛው አገሪቱ ከውጭ ባገኘችው በብዙ ሚልዮን ዶላር የሚቆጠር ብድርና እርዳታ ነው፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በሚፈፅመው ሙስናና ዘረፋ አይጠየቅምና በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በአብዛኛው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ህወሓት/ኢህአዴግ ተጠቃሚ መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ ለአብነት የአባይ ወንዝ ግድብ ስሚንቶና ብረታ ብረት የሚያቀርበው የህወሓት ትእምት (EFFORT) መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

ባጠቃላይ በመለስ አምባገነናዊ አገዛዝ በዘረፋ የበለፀጉት የሱ ተከታዮችና ደጋፊዎች ሲሆኑ፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ተጠቃሚ አይደለም፡፡ የኢኮኖሚ እድገት ቢኖር አብዛኛው የከተማ ህዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በሚሄደው የኑሮ ውድነት አይሰቃይም ነበር፡፡ አርሶ አደሩም የማዳበሪያ ዕዳ መክፈል አቅቶት ሳይቸገር የምርቱ ተጠቃሚ በሆነ ነበር፡፡ በብዙ ሺ የሚቆጠር የአገሪቱ የተማረ ሃይልና ወጣት ለስደት ተጋልጦ በሳወዲ አረብያ የግፍና ውርዴት ሰለባ አይሆንም ነበር፡፡

በመጨረሻምው ኢትዮጵያውያን መለስ የፈፀማቸው ወንጀሎች አደገኛነት በመገንዘብ፣ በተለይም የቀበራቸው የአገር አንድነትን የሚሸረሽሩ ፈንጂዎችን ለማፅዳትና የአገራችን አንድነትን ለማጠናከር ከመቸውም ጊዜ በበለጠ በአንድነት መታገል ታሪካዊ ግዴታችን ነው፡፡

 

ማንዴላ፡ ጀግና አይሞትም –ከዳንኤል ክብረት (ዲ/ን)

0
0

አንዳንዱ የሞተበት ቀን የድል ቀን ተብሎ ይከበርበታል፤ ሕዝብ የመሞቻውን ቀን የሚናፍቁለት ሰውም አለ፡፡ አንዳንዱ እንኳን ተወለደ ሳይባልለት እንኳን ሞተ ይባልለታል፡፡ አንዳንዱ እንዲሞት ይጸለይለታል፤ ሌላው እድሜው እንዲያጥር ይረገማል፡፡ ከዚህ የተለየ ነው ማንዴላ፡፡
ሚሊየኖች እንዳይሞት የሚጸልዩለት፤ ሚሊየኖች እንዲኖር የሚመኙለት፤ ሚሊየኖች ከእድሜያቸው ተቀንሶ ቢሰጠው የሚፈቅዱለት፤ ሚሊየኖች እነርሱ ሞተው ሊያኖሩት የሚሹት፤ ሚሊየኖች በየቀኑ የጤናውን ሁኔታ ከራሳቸው ጤና በላይ የሚከታተሉለት ሰው ነው ማንዴላ፡፡
mandela
አፍሪካ አያሌ መሪዎችን በቅርብ ዘመናችን አስተናግዳለች፡፡ አያሌ የነጻነት ታጋዮችን አይታለች፡፡ እንደማንዴላ ታሥረው የታገሉ ነበሩ፡፡ እንደ ማንዴላ ድርጅት አቋቁመው የተዋጉ ነበሩ፤ እንደ ማንዴላ ሕዝባቸውን ለነጻነት ያበቁ ነበሩ፤ እንደ ማንዴላም ከነጻነት በኋላ የመጀመሪያው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የሆኑም ነበሩ፤ እንደ ማንዴላ ከሀገር ተሰደው የኖሩ ነበሩ፤ ታድያ ማንዴላን ምን ልዩ አደረገው?
ማንዴላ የታገለው ለፍትሐዊነት ነው፡፡ ደጋግሞ ይናገር እንደ ነበረው ‹‹እኛ የታገልነው የነጭ የበላይነትን በጥቁር የበላይነት ለመተካት አይደለም፤ የታገልነው ነጮች፣ ጥቁሮችና ሌሎች በእኩልነት የሚኖሩባትን ደቡብ አፍሪካ ለመመሥረት ነው›› ይል ነበር፡፡ በብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ከነጻነት ትግል በኋላ ጭቆና አልቀረም፡፡ ነገር ግን ነጭ ጨቋኞች በጥቁር ጨቋኞች ተተክተዋል፡፡ በነጮች ተይዞ የነበረው የገዥነት ቦታ ለሥልጣን በበቁት ታጋዮች ፓርቲዎችና ጎሳዎች ተተካ፡፡ የነጻነት ተዋጊዎች የፍትሕና እኩልነት አስፋኞች ሳይሆኑ አዳዲሶቹ ገዥ መደቦች ሆነው ብቅ አሉ፡፡ በነጮች ተይዞ የነበረውን ሀብት ነጻ አውጭ ግንባሮችና ፓርቲዎች ወረሱት፡፡ ስለዚህም ሕዝቡ በትግሉ ጨቋኞችን በሌሎች ጨቋኞች ተካቸው እንጂ ፍትሕና እኩልነትን ለማግኘት አልታደለም፡፡

ማንዴላ ይህንን ነበር የተዋጋው፡፡ እንደተመረጠ ብዙዎች የነጮች መሬት ተቀምቶ ለጥቁሮች እንዲሰጥ፣ ነጮች ከሀገሪቱ እንዲባረሩ ይፈልጉ ነበር፡፡ እርሱ ግን አላደረገም፡፡ ‹መሬቱ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ እንዲዳረስ እንጂ መሬት አልባ ነጮች የመፍጠር ዕቅድ የለንም› አለ፡፡ ጥቁሮች ይበልጥ ነጻ የሚወጡት የበለጸገች ደቡብ አፍሪካ ስትኖር እንጂ በደኸየች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ አይደለም ብሎ አመነ፡፡ ለዚህ ደግሞ የብዙ ዘመን ሀብትና ልምድ ያላቸው ነጮች ወሳኞች መሆናቸውን ተገነዘበ፡፡ ለዚህም ነበር በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ያየነው ምስቅልቅል በደቡብ አፍሪካ ያልተከሰተው፡፡
ማንዴላ የዕርቅና የፍቅር ሰው ነበር፡፡ በነጮችና በጥቁሮች መካከል ለዘመናት በአፓርታይድ የተፈጠረውን መከፋፈል፣ መጠላላትና መገፋፋት በዕርቅና በይቅር ባይነት እንጂ በመሣሪያና በበቀል ሊጠፋ እንደማይችል የተረዳ መሪ ነው፡፡ አፓርታይድ ሲገረሰስ የይቅርታ ኮሚሽን ተቋቁሞ፣ ነባር የሕዝብ ለሕዝብ ችግሮች በተቻለ መጠን በይቅርታና በዕርቅ እንዲወገዱ ሠርቷል፡፡ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ከነጻነት በፊት የነበሩ ገዥዎችና አበሮቻቸው ወደ እሥር ቤት ሲወረወሩና ወደ ውጭ ሲሰደዱ፤ በደቡብ አፍሪካ ግን የከፋ ወንጀል ካልፈጸሙና ይቅርታ ለመጠየቅም ከፈቀዱ ችግሩን በዕርቅና በይቅርታ ለመፍታት ተችሏል፡፡ በዚህም ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ብቻ ሳይሆን ሀገርን አፍርሶ ከመሥራት አባዜ ነጻ እንድትወጣ አድርጓታል፡፡

ማንዴላ ለሰዎች ልጆች ሁሉ የቆመ መሪ ነበረ፡፡ ከዊኒ ማንዴላ ጋር ያፋታቸው ዋነኛው ምክንያት ዊኒ ማንዴላ በነጻነት ትግሉ ወቅት ‹ለነጻነት ትግሉ› ሲባል ፈጽመውታል የተባለው ኢ ሰብኣዊ ድርጊት በእርቅና ይቅርታ ኮሚሽኑ መጋለጡ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ለነጻነት ትግሉ ሲባል ቢደረግም፣ ምን እንኳን ዊኒ ማንዴላ ቢሆኑም ማንዴላ ግን ሊታገሡት አልቻሉም፡፡ የነጻነት ታጋይ ድርጅቱ ኤ ኤን ሲ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ የፈጸማቸው ኢሰብአዊ ድርጊቶች ካሉ ይቅርታ የመጠየቅ ግዴታ አለበት ብለው የሚያምኑት ማንዴላ በዚህ ምክንያት ከዊኒ ጋር ተለያይተዋል፡፡ ከነጻነት በኋላ አያሌ የነጻነት ታጋይ ድርጅቶች በትጥቅ ትግላቸው ወቅት የፈጸሙት ኢሰብአዊ ድርጊት፣ ወንጀልና ግፍ ተሠውሮ እንዲቀር ሲደረግ ማንዴላ ግን ኤ ኤን ሲ ይቅርታ እንዲጠይቅ አድርገዋል፡፡
ማንዴላ ሰላማዊ መንገድን ብቻ ይመርጥ የነበረ መሪ ነበር፡፡ ኔልሰን ማንዴላ ምንም እንኳን የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረውን ኤ ኤን ሲ የመራ ቢሆንም ሰላማዊ የትግል መንገድ ከማንኛውም የትግል መንገድ ሁሉ ቅድሚያ እንዲያገኝ ሲታገል የኖረ ሰው ነው፡፡ ይህ ትግሉ ከአፓርታይድ መሪዎች ጋር ብቻ ሳይሆን በኤ ኤን ሲ ውስጥ ከነበሩ ሌሎች አመራሮች ጋርም ጭምር ነበር፡፡ የጠመንጃ ትግል ለሰላማዊ ትግል፣ ለድርድርና ለውይይት የተዘጋውን በር ማስከፈቻ እንጂ ሰላማዊ መንግሥት የመመሥረቻ መንገድ አይደለም ብሎ ያምን ነበር፡፡ በአፓርታይድ የመጨረሻዎቹ ዘመናት እነ ፒተር ቦታ ከኤ ኤን ሲ መሪዎች ጋር ለመደራደር ያቀረቡትን ጥያቄ አንዳንድ የድርጅቱ አመራሮች አልቀበል ሲሉ ‹እኔ ብቻዬንም ቢሆን እደራደራለሁ› እስከ ማለት አቋም ወስዶ ነበር፡፡ ከአፓርታይድ ጋር የሚደረገው ትግል በጠመንጃ አሸናፊነት ሳይሆን በሃሳብ አሸናፊነት መጠናቀቅ አለበት የሚል አቋም ነበረው፡፡

Mandela
በደቡብ አፍሪካ ሁሉንም ያሳተፈ የመጀመሪያ ምርጫ በተደረገ ጊዜ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ሕገ መንግሥቱን ብቻውን ለማጽደቅ የሚያስችለውን ድምጽ አላገኘም ነበር፡፡ ይሄንን አጋጣሚ ማንዴላ በደስታ ነበር የገለጠው ‹‹ሁሉንም ሕዝብ የሚመራ ሕገ መንግሥት ብቻችንን ማጽደቅ የለብንም፤ ይህ አጋጣሚ መልካም ነው፤ ከሌሎቹ ጋር ተማክረን፣ ተደራድረንና ተስማምተን እንድናጸድቅ ያደርገናል› ብሎ ነበር፡፡
ማንዴላ ሥልጣን መያዝን ብቻ ሳይሆን መልቀቅንም ያስተማረ ሰው ነው፡፡ ማንዴላ ደቡብ አፍሪካን ለአንድ ዙር ብቻ ነው የመራው፡፡ በቀጣዩ ምርጫ ብቻ ሳይሆን ለብዙ ዘመናት በሚደረጉ ምርጫዎችም የማሸነፍ ዕድል ነበረው፡፡ ነገር ግን በቃኝ አለ፡፡ እየተወደደ፤ እየተመሰገነና እየተከበረ በቃኝ አለ፡፡ በደቡብ አፍሪካውያን ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ብሎም በመላው ዓለም ‹አይከን› የመሆንን ጸጋ ተጎናጸፈ፡፡ የነጻነት፣ የጽናትና የትዕግሥት፣ የሰላምና የዕርቅ፣ የይቅር ባይነትና ከጥላቻ ውጭ የሆነ ፖለቲካ ‹አየከን› ሆነ ማንዴላ፡፡ በመላው ዓለም ሕዝብ ልብ ውስጥ ማንም ሊነቅለው የማይችል ዛፍ፣ ማንም ሊያፈርሰው የማይችል ሐውልት ሆነ ማንዴላ፡፡
ለዚህ ይመስለኛል ማንዴላን ዓለም በሙሉ የሳሳለት፤ ለጤናውም ሆነ ለእድሜው የጸለየለት፤ የተጨነቀለትና ልቡን ከልቡ ጋር ያስተባበረለት፡፡ እንደ እርሱ ዓይነት ሰዎች እንደ ሄሊኮሜት በዘመናት አንድ ጊዜ ብቅ የሚሉ ናቸው፡፡ ተወደው ሥልጣን ላይ የሚቀመጡ፣ ተወደውም ከሥልጣን የሚወርዱ፤ ተወደውም ያለ ሥልጣን የሚኖሩ፡፡ እንደ ማንዴላ ዓይነት ሰው እንኳን ሌላው የአፍሪካ ሀገር ራሱ ኤ ኤን ሲም ዳግም ሊያገኝ አልቻለም፡፡ መከፋፈል ዕጣ ፈንታ የሆነውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡
መሪነትና ባለ ሥልጣንነት ምን ያህል እንደሚለያዩ ማንዴላ አንድ ማሳያ ናቸው፡፡ ማንዴላ ባለ ሥልጣን አልነበሩም፤ መሪ እንጂ፡፡ ባለ ሥልጣን በሰው ገንዘብ ውስጥ እንጂ በሰው ልብ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ባለ ሥልጣን ይፈራል እንጂ አይከበርም፤ ባለ ሥልጣን ቢሮ አለው እንጂ ሀገር የለውም፤ ባለ ሥልጣን የሚላላኩት ሠራተኞች እንጂ የሚጸልዩለት ወገኖች የሉትም፡፡ ባለ ሥልጣን የሚያዘው ሰው እንጂ የሚያፈቅረው ሰው አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ፊርማውን የሚፈልግ እንጂ እድሜውን የሚፈልግ የለም፤ ባለ ሥልጣን ብዙ ገንዘብ እንጂ ብዙ ልቦች አያገኝም፤ ባለ ሥልጣን ከሥልጣን ወዲህ እንጂ ከሞት ወዲያ ተዝካር የለውም፡፡

ማንዴላ ከሞት በኋላም ይኖራል፡፡ በብዙ ልቦች ውስጥ ይኖራል፡፡ መቃብር እርሱን ሊያስረሳ አይቻለውም፡፡ እርሱ ከመቃብር በላይ የሆነ ተግባር አለውና፡፡ ማንዴላ የአንድ ሀገር መሆኑ ቀርቶ የዓለም ሆኗል፡፡ መሬት ላይ የሚቆም ሐውልት አያስፈልገውም፤ እርሱ በሕዝቦች ልብ ውስጥ የማይፈርስ ሐውልት በሕይወት እያለ ሠርቷልና፡፡ ብዙ ባለ ሥልጣናት በሕይወት እያሉ በሰው ልብ ውስጥ ሐውልት መሥራት ስለማይችሉ፣ ከሞቱ በኋላ የድንጋይ ሐውልት ይሠራላቸዋል፡፡ ነገር ግን ሐውልታቸው መልእክት አልባ ሐውልት ይሆናል፡፡ እንደ ማንዴላ ያሉ መሪዎች በመሬት ላይ ሐውልት ሲተከልላቸው ደረቅ ሐውልት አይሆንም፤ መልእክት ያለው ሐውልት እንጂ፡፡
ማንዴላ አይሞትም፤ ጀግና አይሞትምና፤ የማንዴላ አይረሳም፤ ሕዝብ ልብ ውስጥ የገባ ሰው አይረሳምና፤ ማንዴላ አያልፍም፣ በጎ ሥራ አያልፍምና፡፡

(ዲ/ን ዳን ኤል ክብረት ይህን ጽሁፍ የጻፈው ማንዴላ በጣም በታመሙበት ወቅት እንደነበር ለማስታወስ እንወዳለን)

አፍሪካዊው ኮከብ

0
0

mandela
ጀግናው አሸለበ፣ ደከመው ተረታ
ሞት አይቀርምና፣ የማታ የማታ፤
ምን ብርቱ ቢሆኑ፣ ሺ መካች ቢሆኑ
ሰው አያልፍ አይገደፍ፣ ተዛቹ ተቀኑ፤
አፍሪካ ሆይ መጥኔ፣ አንድ ወልደሽ ላጣሽው
ተንግዴ መሸበሽ፣ በማን ትዘከሪው? በማንስ ትጠሪው?
ማንዴላ ብረቱ፣ የሮቢን ደሴቱ
የዘረኞች ዋግምት፣ የጥቁር ኩራቱ-
ተንግዲህ የለህም፣ ታሪክ ነበርክና
ታሪክ ነህ ተንግዴ፣ ላትመጣ እንደገና፤
ዓለም አሸርግጂ፣ ቱቢት አስመቺና
ደረት እየመታሽ፣ ”ወይ ልጄን…” በዪና፤
አንበሳሽ ቀን ጣለው፣ ይውጣልሽ ሀዘንሽ
ሙሾሽን ደርድሪ፣ ማቅ ልበሽ እባክሽ
ማንዴ እኮ ነው ሃጁ፣ ሌላው እንዳይመስልሽ፤
ባፍሪካ ሰማይ ላይ፣ የበራው ኮከብ
ተወርዋሪ ነበር፣ ዐይንን የሚስብ፤
ባፍሪካ ሰማይ ላይ፣ የነጋው ጀምበር
ለወገኑ ነበር፣ ብርሃንና አድባር
ለጠላቱ ነበር፣ መራር እንደ ኮሶ
ገፍናኝ እንደንቆቆ፣ ጠላትን አድብኖ-
ጠላትን አጢሶ፤
ማንዴላ አባ ቢያ፣ ደከመኝ ባይል
በቀን ተሸንፎ፣ ኑ ሸኙኝ ባይል-
የኮከቡን ኮከብ፣ ማን እሱን ሊያህል?!
ባፍሪካ ሰማይ ላይ፣ የታየው ፀዳል
ጌጣችን ነበረ፣ ተመሃል ባይጎል፤
-በአበራ ለማ
(ኦስሎ፣ 06.12.13፣ 01፡06 ሰዓት)

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live