Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በአስቸኳይ አዋጅ ስም የተያዙ ሰዎች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም

$
0
0

BBN News |  ከመስከረም 28 ቀን 2009 ጀምሮ መተግበር የጀመረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ፣ በአፈሳም ሆነ በሌላ መልክ የተያዙ ዜጎች ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ ተገለጸ፡፡ መንግስትም ቢሆን የተያዙ ሰዎችን ሁኔታ እናገራለሁ ከማለት ውጪ እስካሁን ድረስ ይፋ ያደረገው መረጃ አለመኖሩ ታውቋል፡፡ አንድ ወሩን ሊደፍን የአንድ ቀን ዕድሜ የቀረው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ለበርካታ ሰዎች መታሰር፣ መገደል እና አካል መጉደል ምክንያት መሆኑ ይታወቃል፡፡

Demonstrators chant slogans while flashing the Oromo protest gesture during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people, in Bishoftu town, Oromia region, Ethiopia
አዋጁን በበላይነት እንደሚያስፈጽም የተነገረለትን ኮማንድ ፖስት በዋና ጸሐፊነት ይመሩታል የተባሉት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ በተደጋጋሚ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የታሰሩ ሰዎችን ኣያያዝ በይፋ ለመናገር አልደፈሩም፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ አባላት ናቸው ከተባሉ ሰዎች ጋር ስለተያዙ ሰዎች አያያዝ ተመካክረዋል ቢባልም፣ በውይይታቸው ወቅት ስለ ታሰሩ ሰዎች ወቅታዊ ሁኔታ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡


አዋጁ መተግበር ከጀመረ አንስቶ ባሉት ቀናቶች ውስጥ በተለይም ከኦሮሚያ እና ከአማራ ክልሎች በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአፈሳ መልክ መያዛቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡ ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች ጭምር ያወገዙትን አዋጅ የሚያስፈጽሙ በተለይ አጋዚ ወታደሮች በርካታ ዜጎችን ሲገድሉ፣ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹኃን ሰዎችንም ማሰራቸው ይታወቃል፡፡ ሴቶችን መድፈርም የኮማንድ ፖስቱ አንዱ አካል ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሰዎች፣ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈጸሙባቸው የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡


በብሄር የተዋቀረ ፓለቲካ አደረጃጀት የኢትዮጵያን የፓለቲካ ችግር ሊፈታ አይችልም –ከደመቀ ገሰሰ (PhD)

$
0
0

ethnic-federalismየብሄር ፓለቲካ ማለት በአንድ ብሄር ወይም ዘውግ ለምሳሌ አማራ፣ኦሮሞ፣ትግሬ፣ጉራጌ፣ሶማሌ፣ወዘተ በሚሉ ብሄርን መሰረት ያደረገ የፓለቲካ አደረጃጀት ማለት ነው። ይህ የፓለቲካ አደረጃጀት በኢትዮጵያ ታሪክ በተግባር ላይ የዋለው የትግራዮ ነፃ አውጪ ድርጅት ህወዓት በ1983 አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ኢህዴግ በሚባል ብሄር ተኮር የፓለቲካ ፓርቲወች ጥምረት በመመስረት ነው። ምንም እንኳ ከ80 በላይ የሚሆኑ ብሄሮች ያሉበት አገር ቢሆንም የስልጣን በትሩን በበላይ በሚያዝዘው የትግራዮ ህወዓት የብሄር ፓለቲካ ፓርቲ በሚመቸው መልኩ ያለምንም የህዝብ ተሳትፎ ከ54 በላይ ብሄሮች የሚኖሩበት ደቡብ ኢትዮጵያን “ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች” በሚል ስብስብ ውስጥ በመክተት የሶማሌ፣የሃረር፣የትግራይ፣የአማራ፣-የጋምቤላ፣የቤንሻንጉል ጉምዕዝ፣የአማራ እና የኦሮሞ የብሄር ፓለቲካ ብቻ ሳይሆን እኒህ የብሄር ፓለቲካ ፓርቲወች የሚያስተዳድሩት ጂኦግራፊያዊ ክልልም በመወሰን የተከናወ ነው።

እንግዲህ የብሄር ፓለቲካ ቋቅ እስኪለን 25 ዓመታት ተግተነው የመጣ ለውጥ ምንድን ነው? ይህን ጥያቄ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እራሱን ይጠይቅ።

ይህ የብሄር ፓለቲካ ገና ከጅምሩ በብጥብጥ እና በዘር ፉጅት ነው ሃሁ ያልነው። የእኛ ክልል በሚሉት ውስጥ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ አማራወችን በመጨፉጨፉ እና በማባረር ተጀመረ። ይህ እስካሁን እልባት ያላገኘ ችግር ሆኖ ቀጥሏል። ከጉራፈርዳ፣ከአፋር፣ሶማሌ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ በቅርቡ ደግሞ በጌዲዬ ዞን የሆነውን አይተናል።

እንግዲህ በብሄር የተደራጀ የፓለቲካ ፓርቲ በመሰረቱ የሚያደላው ለሚወክለው ብሄር ነው። ይህ በግልፅ የታየ ጉዳይ ነው። ምንም እንኳ በርካታ ሚሊዮን አማራወች እና ሌሎች ብሄሮች ኦሮሚያ ውስጥ ቢኖሩም የኢህዴግ ብሄር ፓለቲካ ግን እንኳን የፓለቲካ ተሳትፎ እድል ሊሰጣቸው ይቅርና በኦሮሚያ ሲቭል መስሪያ ቤቶች በቅድሚያ ስራ ለማግኘት ኦሮሞ ልትሆን ግድ ይላል። በሌሎችም ክልሎች ተመሳሳይ ችግር ነው። የክልሉ ትምህርት በኦሮምኛ ይሰጥ ብሎ ሲል በርካታ የሌሎች ብሄሮች ልጆቻቸው በቋንቋቸው እንዳይማሩ ተፈረደባቸው። ይህ ምን አይነት ፉትሃዊነት እንደሆነ አስረዱኝ?

ወያኔን የሚኮንኑ የብሄር ፓለቲካ ፓርቲወች ወያኔን የሚከሱበት ትልቁ ክስ የብሄር ፓለቲካው የይምሰል ነው በማለት ነው። ይህም ማለት ኦሮሞ ክልል ለኦሮሚያ፣ሶማሌ ለሶማሌወች ፣ወዘተ መሆን አለበት ነው የሚሉት። ህወዓት በሞግዚትነት የሚመራን ነገር ይቅር ነው የሚሉት። ነገር ግን እነዚህ በብሄር የተደራጁ ተቀዋሚ የፓለቲካ ፓርቲወች ወያኔ ቢወርድ እነርሱ የእኛ ብለው በሚጠሩት ክልል ውስጥ አገሬ ብለው ለሚኖሩት ሌሎች ወገኖች መፉትሄ የሚሰጥ አማራጭ ሲያቀርቡ አይታይም። የሚሉት ሙሉ በሙሉ ትግራይ ክልል ለትግሬ፣ ኦሮሞ ክልል ለኦሮሞ፣ሶማሌ ክልል ለሶማሌ ወዘተ ነው።

ሌላው ትልቅ ችግር ይህ የብሄር ፓለቲካ ከ13% በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ድብልቅ ህዝብ የሚወክለው ፓርቲ አይኖርም ማለት ነው።

ኢትዮጵያ ምድሬ፣ አገሬ፣ አፈሬ ናት ብሎ እትብቱ የተቀበረበት መሬት የአንተ አይደለም እየተባለ በብሄር ፓለቲካ ስም የሚደርስበትን እያየን ነው።

ኢትዮጵያ እንደ አገር ስትመሰረት ተለያይተው ይኖሩ የነበሩ አገሮች በፌደሬሽን አልያም በሃይል አንድ ላይ ተጨፉልቀው አይደለም። የአውሮፓ ቅኝ ገዥወች ወደ አፉሪካ ከመምጣታቸው በፊት ኢትዮጵያ ጥንት የነበረች ታሪካዊ አገር ነች። ይህ ማለት የትኛውም የኢትዮጵያ መሬት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ቅድመ-አያቶች ደም እና አጥነት ተጠብቆ የኖረ አገር ነው። መቼም ፈጣሪይ ከላይ ይህ ላንተ፣ያኛው ለዚያ ብሎ ከልሎ የሰጠን የግዛት መሬት የለም። ሁሉም አገሮች እንደ አገር ሲመሰረቱ እንደሆነው ቅድመ-አያቶቻችን ከደርቡሾች፣’ከጣሊያን ጋር፣ከእንግሊዝ ፣ከኦቶማን ቱርኮች እና ከሌሎች ጋር እየተፋለሙ ያቆዮልን በጋራ ደም እና አጥንት የተከበረ የጋራ አገር ነች ኢትዮጵያ።

ጣሊያን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ በሽንፈት የወጣበትን የአድዋን ቂም ለመበቀል በሁለተኛው አለም ጦርነት ዋዜማ ወቅት ኢትዮጵያን ዳግም ወሮ ለአምስት አመት ሲቆይ ይቺን ተከብራ የኖረችውን አገር ከፉፈሎ ለመግዛት እና ለማዳከም ዛሬ ላይ ወያኔ የተጠቀመበትን የብሄር ካርታ በመስራት አንዱ በአንዱ ላይ እንዲነሳ ተንኮል በመሸረብ ትልቅ የክፋት ስራ ሲሰሩ ቆይተው በእንግሊዝ እርዳታ ኢትዮጵያን የመውረር ህልማቸው እውን ሳይሆን ቀረ።

ወያኔ በ1983 ዓም ወደ ስልጣን ማማ ሲመጣ ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያን ለማፉረስ የሰራውን የብሄር ካርታ አቧራ አራግፈው እየው ዛሬ ለደረስንበት ውድቀት ዳረጉን።

ወገኖቼ

ይህ የብሄር ፓለቲካ በኢትዮጵያ ውስጥ ከእልቂት እና እርስ በእርስ ግጭት ውጭ ምንም መፉትሄ እንደማይኖረው አንድ አንድ ነገሮችን እያነሳን እንነጋገር።

የብሄር ጂኦግራፊያዊ አከላለል በብዙ መልኩ መዘዙ የከፋ ነው። ለምሳሌ ወያኔ በስራው የአማራ ክልል ውስጥ ብናይ በአማራ ክልል ውስጥ ከአማራ ብሄር ውጭ የሆኑ ቅማንት፣ኦሮሞ፣ትግሬ፣አገው፣ወዘተ ብሄሮች ይኖራሉ። ደቡብ ክልል ብቻ ከ54 በላይ ብሆሮች አሉ። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በርካታ ሌሎች ብሄሮች አሉ። በሌሎችም ክልሎች ተመሳሳይ እውነታ ነው ያለው።

እንግዲህ እስካሁን ባየነው የብሄር ፓለቲካ በየክልሉ ላሉት ሌሎች ብሄሮች እኩል መብት የሚሰጥ ፉትህዓዊ የሆነ አሰራር የለም ወይም ደግሞ እኒህ ብሄሮች የራሳችን ክልል ይኑረን ጥያቄወች ተደፉጥጠው እንጂ ጥቄቃወችን ያነሳሉ።

ሌላው እያንዳንዱ የብሄር ክልል የእራስን እድል በራስ የመወሰን መብቱ ይጠበቅልን ካለ የክልሉ አከላለል በራሱ ፉትሃዊ አይደለም። ቀድሜ ያነሳውትን ታሪክ እዚህ ላይ ለማስታወስ ኢትዮጵያ የዛሬዋን ጂኦግራፊያዊ ቅርፅ እንድትይዝ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከቅድመ አያቶቻቸው ጀምሮ እስካሁኗ እለት በእኩል ደም እና አጥንት የተጠበቀ ነው። ይህ ከሆነ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሚደረገው የክልል አከላለል እኩል ባለቤትነት ሊኖራቸው ግድ ይላል። ለምሳሌ የዛሬው ደቡብ ህዝብ ወይም ኦሮሚያ ክልሎች ከጥንት ጀምሮ የሰሜኑም ፣ምስራቁም ፣መካከለኛው ኢትዮጵዊ አብሮ ዋጋ ከፉሎ እንደ አገር ባይቆይ ኖሮ ይህ አካባቢ ወይ ኬንያ አልያም ሱዳን በሆኑ ነበር። ስለዚህ የአፋር ህዝብ ወይም የትግራይ ህዝብ አሁን ባለበት ትንሽ እና ደረቃማ ቦታ ብቻ ይወሰን ካልን ፉትሃዊነቱ ምን ላይ ነው?

ለዚህ ነው የብሄር ፓለቲካ በፉፁም ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋት የማያመጣው። ይህ የብሄር ፓለቲካ መቼውንም ቢሆን ችግራችንን ይበልጥ ውስብስብ እያደረገው ከመሄድ ውጭ መፉትሄ ሊሆን አይችልም።

ስለዚህ ብቸኛው መፉትሄ በብሄር ሳይሆን በዜግነት ብቻ ላይ ትኩረት ያደረገ የፓለቲካ አደረጃጀት ነው። የግለሰብ መብት ላይ ትኩረት ያደረገ የዴሞክራሲ ስርዓት ብቻ ነው የተረጋጋች አገር የሚመሰርተው። ይህን የሳተ የስሜት ፓለቲካ ለጊዜው ይምሰለን እንጂ መዘዙ እጅግ ከባድ ነው።

ማስተዋልን አብዝቶ ይስጠን
አሜን!

ሰይፉ ፋንታሁን “አርቲስት ይርዳው ጤናውን ያፈቀረች ልጅ በሳዑዲ አረቢያ የመርሳት ችግር ያዛት”ሲል ይናገራል

$
0
0


ሰይፉ ፋንታሁን “አርቲስት ይርዳው ጤናውን ያፈቀረች ልጅ በሳዑዲ አረቢያ የመርሳት ችግር ያዛት” ሲል ይናገራል
ሰይፉ ፋንታሁን “አርቲስት ይርዳው ጤናውን ያፈቀረች ልጅ በሳዑዲ አረቢያ የመርሳት ችግር ያዛት” ሲል ይናገራል

መታየት ያለበት ልዩ ዝግጅት ከቢቢኤን |ዶ/ር ሽፈራው ለምን ለትምህርት ሚ/ርነት ተመረጠ –ምስጢራዊ ዘገባ

$
0
0


መታየት ያለበት ልዩ ዝግጅት ከቢቢኤን | ዶ/ር ሽፈራው ለምን ለትምህርት ሚ/ርነት ተመረጠ – ምስጢራዊ ዘገባ
መታየት ያለበት ልዩ ዝግጅት ከቢቢኤን | ዶ/ር ሽፈራው ለምን ለትምህርት ሚ/ርነት ተመረጠ – ምስጢራዊ ዘገባ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችን የሚያስደስት ታላቅ ዜና –በሰሜን አሜሪካ ትልቁ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በሚኒሶታ ሊገነባ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን አሜሪካ ትልቁ ሊሆን እንደሚችል የሚነገርለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሚኒሶታ ሊገነባ ነው:: በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ::

በሚኒሶታ የሚገኘው ደብረሰላም መድሃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን የሚያሰራው ትልቁ ቤተክርስቲያን በሚኒያፖሊስ ከተማ ውስጥ ሲሆን የህንጻው ዲዛይንም የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ቅርጽና ታሪክ የተከተለ እንደሚሆን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቁሟል::

ባለ 3 ወይም ባለ 5 ጉልላት ቤተክርስቲያን እንደሚገነባ የቤተከርስቲያኑ የቦርድ ሊቀመንበር ዛሬ ከመሰረት ድንጋዩ ማቆም በኋላ በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል:: በሚኒሶታ ለሚሰራው የሰሜን አሜሪካ ትልቁ ቤተክርስቲያን የመሬት ግዢው ተጠናቆ በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋዩን ያስቀመጡት ብጹዕ አብነ ዳንኤል ናቸው:: አቡነ ዳንኤል አሁን ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን እስከ አዲስ የተገዛው መሬት የሰረገላ ጉዞ ካደረጉ በኋላ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል:: ቭድዮ ይዘናል – ታሪካዊ በመሆኑ ይመልከቱትና ያስቀምጡት::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞችን የሚያስደስት ታላቅ ዜና – በሰሜን አሜሪካ ትልቁ ቤተክርስቲያን በሚኒሶታ ሊገነባ ነው

በሲያትሉ የአማራ ተጋድሎ ኮንፍረስ ምን እየተነገረ ነው? |ቪድዮ ይዘናል

$
0
0


በሲያትሉ የአማራ ተጋድሎ ኮንፍረስ ምን እየተነገረ ነው? | ቪድዮ ይዘናል

ለማህበረ ቅዱሳን ህብረት –በላይ አበራ

$
0
0

ቀን፡ 22/01/09 ዓ.ም
ለማህበረ ቅዱሳን ህብረት
አዲስ አበባና ሐዋሣ፤
ጉዳዩ፦ ሀሳብን ስለማጋራት ይሆናል፡፡

mk-logo11በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዶ አምላክ ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት እናንተ ወንድሞቸቼና እህቶቼ እያደረጋችሁ ያላችሁት ከፍተኛ ትግል ቅድስት ቤተክርስትያንን ከሌሎች ዘመን አመጣሽ ሃይማኖቶች ወረራ ለመጠበቅ በታላቁ እግዚአብሔር ከፍተኛ ዋጋ ያሰጣችኋል፡፡ እኔም ወንድማችሁ ክርስቲያን እንደመሆኔ መጠን ይህንን ትግል ለመቀላቀል ያስችለኝ ዘንድ ጥቂት ሃሳቦቼን ከናንተ ጋራ ለመጋራት ስል ከታች በዘረዘርኩት መሠረት ለመጥቀስ እሞክራለሁ፡፡

1. የቤተክርስቲያን በዓላት ዝግጅቶች ላይ አልኮል( ጠጅ ፣ አረቄ ፣ ቢራና ውስኪ) ፈፅሞ እንዶይኖር በተለያዩ መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች ማስደረግ ቢቻል፤ ብዙዎች አልኮልን ከዚህ ይለምዳሉ፡፡
2. ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሰሜኑ ህዝብ ሀይማኖት ነው ተብሎ የመታመን ነገር ስላለ ከሌሎች ክልሎች ካሉ ምዕመናን ዲያቆናትን ቄሶችንና ሰባኪዎችን በመመልመል ማብቃት ቢቻል፤
3. የምዕመናን ክትትል ኮሚቴ በማቋቋም የምዕመናን የዕምነት ሁኔታ ክትትል በማድረግ በዕምነቱ ለሰነፈና አላስፈላጊ ሱሶች ዉስጥ ለገባ ምዕመን አስፈላጊዉን እርዳታ ማድረግ ቢቻል፡፡
4. የቤተክርስቲያን አባቶች መደበኛ የምዕመናን የቤት ለቤት ፀበል የመርጨትና የምክር አገልጎሎት የመስጠት ፕሮግራም እንዲያከናውኑ ማስቻል፡፡ ምዕመናኑ ለቤተክርስቲያን አባቶች የታከሲ ወጪ እንዲከፍሉ ማመቻቸት፤
5. የምዕመናን ልጆች ተመዝግበው ከህፃንነታቸው ጀምሮ የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲከታተሉ ማስቻል፡፡ በዕውቀት የዳበር ትውልድ በመፍጠር ወደፊት ለሚከሰቱ የሃይማኖት ወረራዎች ከወዲሁ ለመዘጋጀት እንዲያስችል ማድረግ፤
6. የክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር የሚያንስባቸው አከባቢዎች ለዩ ትኩረት በመስጠት በየቋንቋቸው ማስተማርና መፅሐፍ ቅዱስን በመተርጎም በሰፊው ማዳረስ ቢቻል፡፡ ደቡብና አንዳንድ የኦሮሚያ አከባቢዎች፤
7. ልዩ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ አባላትን በመለየት በልዩ መልኩ ማስተማር ቢቻል፡፡ የፋብሪካ ሰራትኞች ፣ ዲያስፖራዎች ፣ ተማሪዎች ፣ ምሁሮችና ህፃናት ልዩ ትኩረት ቢያገኙ፡፡
8. የዘመኑ ማህበራዊ ጉዳዮችን ከመፅሐፍ ቅዱስን አኳያ ማብራራት ቢቻል፡፡ ሱሰኝነት ፣ ፍቺ ፣ ከጋብቻ በፊት ወሲብ ፣ አግባብ ያልሆነ ወሲብ ሥርዓት ፣ ሀሜት ፣ ዉሸት ፣ ሙስና ፣ የአለባበስ ሁኔታ ፣ ፊልሞች ፣ ሙዚቃ ፣ የመገናኛ ብዙሀንና የምሽት ከለቦች ቢዳሰሱ፤
9. ለዘብተኛ ምዕመናን ከወጣቱና ከተማ ነዋሪ ከሆነው ክፍል እየተበራከተ ስለሆነ ልዩ ትኩረት ቢሰጠው፡፡ ለዘብተኞች ከእውቀት ማነስና ከግድየለሽነት የተነሳ ሀይማኖት ወደ መቀየር ፣ ሱሰኝነት ፣ ለአጥፊ ዘመን አመጣሽ ድርጊቶች አና ለተበላሸ የግል ህይወት የተጋለጡ በመሆናቸው ትኩረት ቢሰጣቸው፤
10. ንቁ ምዕመናን ለዘብተኞችን ማበረታታት እንዲችሉ ማስደረግ፡፡ ለምን አትፆምም? ለምን አታስቀድስም? ለምን አታነግስም? ለምን መዝሙርና ስብከት አታዳምጥም? ለምን ቤተክርስቲያን አብረን አንሄድም? የሚሉ ግሰፃዎች ጠቃሚ ስለሆኑ ቢደረጉ ይጠቅማሉ፡፡
11. የቤተክርስቲያን አስራት ማጠራቀሚያ ሣጥኖች በተለያዩ ሆቴሎችና ቦታዎች የሚገኙት በሐጥያት ከሚሰበሰብ ገንዘብ የተገኘ ስለሆነ ከቅድስት ቤ/ን መተዳደርያ ደንብ አንፃር ተገቢ ባለመሆኑ ህብረቱ ከየትኛውም ቦታ የሚሰበሰቡ አስራቶች ዝሙት ፣ ሥካርና ወንጀል መሠረት ባላደረገ መሰረት መሆኑን እስካልተረጋገጠ ድረስ ገቢ እንዳይሆን ማድረግና ሣጥኖችን ከነዚህ ቦታ ማንሳት፡፡
12. ምዕመናን ኦርቶዶክሳዊ ባህርያት እንዲላበሱ ማስቻል.. አንድ ኦርቶዶክስ የማይቅም ፣ የማያጬስ የማይጠጣ/የማይሰክር ፣ የማይዘሙት እና ከመደበኛው ህዝብ የተለየና የተስተካከለ ባህርያት መሆን አለበት፡፡ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ባህርያት መወገድ አለባቸው፡፡
13. ጠጣ አትስከር ከሚለው ከአስርቱ ትዕዛዛት አንዱ ጋር በተያያዘ ክርስቲያን አልኮል ጠጣ ወይም አልኮል መጠጣት አለብህ/አለብሽ ተብሎ ልክ አንደ ትዕዛዝ የተላለፈ በሚመስል መልኩ ምዕመናኑ ኦርቶዶክሳዊ መገለጫ በማድረግ እየተጠቀሙ ይገኛል፡፡ አንድ ክርስቲያን ፈፅሞ መጠጣት አልፈልግም ማለት ይችላል ወይም ከጠጣ መጥኖ መጠጣት አለበት፡፡ እህልነት ያላቸው መጠጦችና ሆን ተብለው የሰው ልጅን አዕምሮ በስካር በመቆጣጠር ላልተፈለገ ሐጥያት የሚዳርጉ በፋብሪካ የተሰሩ መጠጦች ላይ ውይይት ቢደረግ፡፡
14. ጠንካራ የምዕመናን ማህበራትን ከሚሰሩት ሥራና አኗኗር አኳያ እውቅና በመስጠት ማቋቋም፡፡ የመንግስት ሠራተኞች ተዋህዶ ማህበር ፣ የተማሪዎች ተዋህዶ ማህበር ፣ የፋብሪካ ሠራተኞች ተዋህዶ ማህበር ፣ የዲያስፖራዎች ተዋህዶ ማህበር ፣ የደላላዎች ተዋህዶ ማህበር ፣ የሾፌሮች ተዋህዶ ማህበር ፣ የእስፖርተኞች ተዋህዶ ማህበር ፣ የነጋዴዎች ተዋህዶ ማህበር ፣ የአርቲስቶች ተዋህዶ ማህበር ፣ የግል ድርጅት ሠራተኞች ተዋህዶ ማህበር፡፡
15. የዘመኑ ትውልድ አለማዊ ትምህርት ላይ ብቻ በማተኮሩ የተነሳ ወደፊት የዲያቆናት ፣ ቄሶች እና ሰባኪዎች ቁጥር ማሻቀብ ስለሚገጥም ከወዲሁ መፍትሄ ቢመቻች፡፡ ደምወዝ ጭማሪ ማድረግና ሌላ ስራ እየሰሩ በትርፍ ሰዓታቸው ቤ/ንን የሚያገለግሉ ምዕመናንን መፍጠር፡፡
16. የመረጃ ማዕከል ጽ/ቤት በማቋቋም የተጠናከረ የምዕመናን ምዝገባ ሥርዓት መዘርጋት(Orthodox Statistics)፡፡ ሥም ፣ ዕድሜ ፣ ጾታ ፣ የጋብቻ ሁኔታ ፣ ሥራ ፣ የዕምነት ሁኔታ (ንቁ/ለዘብተኛ) ፣ አድራሻ ፣ የትምህርት ደረጃ ፣ የልጆች ቁጥር ፣ ክርስትና የተቀበሉበት ጊዜ ፣ የማህበራት ተሳትፎ ፣ የሱስ ሁኔታ…………………………..፡፡
17. Orthodox ID: ለምዕመናን እንዲዘጋጅ በማድረግ የምዕመናን የተዋህዶ መለያ መታወቂያ ካርድ ማዘጋጀት…………ምዕመናኑ በ10 ብር መታወቂያ ካርዱን እንዲገዙ ማስደረግ፡፡
18. Orthodox Financing: ከብሄራዊ ባንክ ጋር በመነጋገር ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ማስጀመር ……ገንዘብን ከስራ አንጂ ገንዘብን ከገንዘብ በወለድ መልክ ማግኘት በመፅሐፍ ቅዱስ የተከለከለ በመሆኑ ነው፡፡
19. International Orthodox Alliance (IOA) በማቋቋም ከተመሳሳይ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያናት ጋር ጥንቃቄ የተሞላበት በልዩነት የአጋርነት ድርጅት በመፍጠር የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ባለው አንጋፋነት ለሌሎች ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት ድጋፍ በማድረግ ተቀራርቦ መስረት…..አዲስ አበባን የአሊያንሱ መቀመጫ ማድረግ፡፡
20. International Preachers፡ ብዙ ቋንቋ የሚናገሩና ጠንካራ እውቀትና ፀጋ ያላቸው አለማቀፍ ሰባኪዎችን በመፍጠር በአለማቀፍ ደረጃ የሀይማኖት ማስፋፊያ ስራ መስራት…..የስበከት አገልግሎት በአብዛኛው ኢትዮጲያዊያን ላይ መሰረት ያደረገ በመሆኑ ነው፡፡
21. አንዳንድ የቤተክርስቲያን አባቶች | ቄሶችና ዲያቆናት የኑሮ ውድነት በማሳበብና አለማዊ ዲሎትን በማሰብ በንግድና በተለያዩ ተጨማሪ ስራዎች ላይ ተሠማርው ስለሚገኙ ለኑሮ በቂ የደምወዝ ጭማሪ ማድረግና ጥብቅ የሆነ የስነ ምግባር ደንብ (Ethical Code for Servicemen) በማውጣት ለዚህና ለሌሎች እንደ ስካርና ዝሙት ላሉ የባህሪ መሰል ግድፈቶች ማስተራረሚያ ማድረግ፡፡
22. እድሳትና ጥገና የሚያስፈልጋቸው ቤተ-ክርስቲያናትና ገዳማት በተለይ በሀገራችን ሩቅ አካባቢዎች የሚገኙ እርዳትና ጥገና ሳያገኙ በችግር ውስጥ ስላሉ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ተለይተው በአፋጣኝ እድሳት ቢደረግ፡፡
23. በምዕመናን የክትትል ኮሚቴ አማካኝነት አንዳንድ ምዕመናን በአጥፊና አሰናካይ የስራ ዘርፎች ለምሳሌ የምሽት ክበብ | አደንዣዥ ዕፅ | ዝሙት | ሰው ማዘዋወርና ለመሳሰሉት ተሠማርተው ስለሚገኙ ኮሚቴው አነዚህን ምዕመናን በማማከር ሌላ ተቀያሪ ሥራ እንዲሠሩ ወይም ሌላ መፍትሔ ተፈልጎ ምዕመናኑ ኦርቶዶክሳዊ ባህሪያት እንዲላበሱ ማስደረግ፡፡
24. የኦርቶዶክስ ተራድዖ ድርጅት (Orthodox Charity Org.) በማቋቋም በኢኮኖሚና በማህበራዊ ጉዳዮች ችግርተኛ ለሆኑ የገንዘብና ነፃ የማህበራዊ አገልግሎት ዕርዳታ እንዲያገኙ በማስቻል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት የመልካም ተምሳሌትነትን ማጠናከር … በዚህ ተራድዖ ድርጅት ስር አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ በገንዘብ ሀብታም የሆኑ ምዕመናን ችግርተኛችን በምግብ | በገንዘብ | በህክምና ወጪ | በአልባሳትና በሌሎች አገልግሎቶች እንዲረዱ ማስቻል፡፡
25. የኦርቶዶክስ አስተዳደር ጽ/ቤት | ማህበረ ቅዱሳን | ሐገረ ስብከትና የመሳሰሉት በተዋህዶ ስር የሚገኙ ጽ/ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በቋሚ ቅጥር ሠራተኞች እንዲሠሩ ቢደረግ የተሻለ ነው ምክንያቱም አሁን አየሠሩ ያሉት በአብዛኛው በመንግስት ወይም በግል ሥራ ላይ ተሠማርተው ስለሚገኙ በብዛት የጊዜ መጣበብ ይገጥማቸዋል፡፡
26. የኦርቶዶክስ ምርምር ማዕከል በማቋቋም የክርስትና አስተምሮትን በተጠናከረ መልኩ ማስተማር…..በየጊዜው የሚከሰቱ ችግሮችን በማጥናት መንፈሳዊ መፍትሄ አንዲፈጠር ማስደረግ፡፡
27. በአብዛኛው የጋብቻ ስነ ሥርዓተች በቤተ-ክርስቲያን አባቶች ቅደሳ አስጀማሪነት ተጀምሮ ወደ አለማዊ ገፅታ እየተቀየረ ስለሆነ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ጠንካራ አቋም በመያዝ ምዕመናኑ መንፈሳዊና አለማዊ ጋብቻን ለይቶ እንዲያከብር ማስደረግ ቢቻል……….ሀይማኖት የባህልን ተፅዕኖ ተቋቁሞ በከፍታ ደረጃ ላይ መቀመጥ ስላለበት ነው፡፡
28. ሥርዓተ ለቅሶ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ተከትሎ ባህላዊ ደንብ በምዕመናን ስለያዘ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ጠንካራ አቋም በመውሰድ ከምዕመናን ጋር በሰፊው የምክክር ጉባኤ በማድረግ ሀይማኖታዊ ስርዓቱን ብቻ ተከትሎ እንዲተገበር ቢደረግ…አንድ ምዕምን በአምላክ ተፈጥሮ በአምላክ ስለሚወሰድ የምዕመናን ከመጠን ያለፈ የሐዘን ስርዓት አምላክን ማማረርና መፈታተን ስለሆነ ነው፡፡
“ከእግዚአብሔር ሠላምታ ጋር”
ከወንድማችሁ በላይ አበራ

ጄኔራሉና ያልከፈልነው ዕዳ

$
0
0

ምስክር

በዚህ የመጽሔት ስራ ውስጥ ትልቁን ሚና ከሚጫወት ወዳጄ የተደወለልኝን ስልክ ከአነሳሁ በኋላ ሌላ በዚሁ ስራ ላይ የበኩሉን ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ ወዳጃችን ተቀላቀለን ። ትልቁ እንግዳ የመጡት መጨረሻ ላይ ነው ።

gen-ashefafi-gebre-tsadik

ስናስባቸው ከርመን ነበር ። ስላለፈው ደግም ሆነ ክፉ ቀን ፣ ስለዛሬው ጥረታችንና ሰለወደፊት ተሰፋችን የሚሉትን ከአንደበታቸው ለማዳመጥ ጓግተናል ። ትሁትና ቅን ሰላምታ ተለዋውጠን ወደጉዳያችን ገባን ።

ብርጋዴር ጄኔራል አሸናፊ ገብረጻዲቅ ይባላሉ ። ዛሬ አሜሪካ ውስጥ በስደት ሲኖሩ አስራ ሁለት ዓመታትን አስቆጥረዋል ። በክፉ ቀን ኢትዮጵያን ከታደጓት የቀድሞው አየር ኃይል አባላት መሃከል አንዱና ግንባር ቀደሙም ናቸው ። በእኛ ዘመን ሃገሪቷ በይፋ ከመሰከረችላቸው ጥቂት ጀግኖች መሃከል በሕይወት ሰንብተዋል ። የላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይ ተሸላሚው ጄኔራል ስለነገም ብሩህ አመለካከት አላቸው ። ወደፊት ለማየትም ወስነዋል ።

ጥያቄያችንን አሃዱ ብለን የጀመርነው አሁን በመቋቋም ላይ ስለአለው የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዓለም አቀፍ ሕብረት ነበር ። ምን ሃሳብ አለዎት አልናቸው ። መልሳቸው ወደፊት ለማየት ዝግጁ ከሆነ ሰው የሚጠበቅ ነበር ። እንዲህ አሉን ። “ይህ ትልቅ ዓላማ ነው ። ጅምሩን ወድጄዋለሁ ። እሰከአሁን በተሰራው ላይ አንድ እርከን የሚጨምር ነውና መበረታታ አለበት” … ፤ አሉና በሳል አመለካከታቸውን ጫን በማድረግ አከሉበት ።

በጄኔራሉ አነጋገር ትልቅ ዓላማ ስኬታማ የሚሆነው በጎ (positive) አመለካከት ቅድሚያ ሲሰጠው ብቻ ነው ። ይህንን ከጅምሩ አይተዋል ። ጎጂ ሃሳቦች ትርፍ አያስገኙም ባይ ናቸው ። እናም ይህ ማሕበር ጠቃሚና ገንቢ ሰራዎችን እንዲሰራ ይጠብቃሉ። በእሳቸው አመለካከት ብዙ ስራዎች

ከፊታችን ተደቅነዋል ። በዓለም ዙሪያ የተበተነው ፣ ዛሬ ዲያስፖራ ተብሎ ስም ከወጣለት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን መካከል የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ቁጥር ጥቂት አይደለም ። ይህንን ኃይል ማሰባሰብ ፣ ታሪኩን ፣ ሙያውንና ልምዱንም ዘግቦ ለትወልድ ማሰተላለፍ በራሱ ትልቅ ስራ ነው ይላሉ።

ጄኔራል አሸናፊ መሰረታቸው ሲዳሞ ነው ። ክበረመንግስት ከተማ ውስጥ በ1937 ተወልደው እዚያው አድገው ፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ከአጠናቀቁ በኋላ ነው በ1954 ተግባረ ዕድ ትምህርት ቤት ሰርቬይንግ (ቅየሳ) ለማጥናት አዲስ አበባ የመጡት ። አየር ኃይልም የመለመላቸው እዚያው ተገባረ ዕድ የሶስተኛ ዓመት ተማሪ እያሉ በ1957 ዓም ላይ ነበር ።

ምልመላው የሚጠይቀውን መመዘኛ ሁሉ አሟልተው በዚያው ዓመተ ምህርት የበረራ ኮርሳቸውን ደብረ ዘይት ሐረር ሜዳ ወዲያው ቀጠሉ። ዩኒት P-16 ፣ ሃያ አንድ የበረራ ተማሪዎችን ሳፋየር አውሮፕላን ላይ አሰልጥኖ ከአስመረቃቸው ሰድስት ዕጩ መኮንኖች መሃከል ጄኔራል አሸናፊ አንዱ ነበሩ ። ከዚያ በኋላ T-28 ዲ ታክቲካል ተዋጊ አውሮፕላን ላይ ስልጠናቸውን ቀጥለዋል ። OCS – 6 ገብተው በም/መቶ አለቃነት ማዕረግ ከተመረቁ በኋላ በበረራ አስተማሪነት ከ1961 እስከ 1963 ድሬደዋ ተመድበው አገልግለዋል ። ከዚያም ወደ አስመራ ቀጥሎ ደግሞ ወደ ደብረ ዘይት ተዛውረው F- 5 ላይ ተመድበው ከሰሩ በኋላ በ1967 F- 5E ላይ ለመሰልጠን ወደ አሜሪካ ተልከዋል ።

ከዚያ በኋላ ነው ኢትዮጲያን ከጠላት ለመታደግ ግንባር ላይ የተሰለፉት ። ሶማሊያ ለረዥም ዘመናት ስትዘጋጅበት የቆየችውን ጦርነት ቀድመው ከተጋፈጡት መሃከል ጄኔራል አሸናፊ አንዱ ናቸው ። አሁንም ድረስ እንደሚያስታውሱት ኢትዮጲያ ለዚህ ጦርነት ዝግጁ አልነበረችም ። በተለይም በምድር ጦሩ በኩል ዝግጅቱ አልነበረም። አየር ኃይላችን በመሳሪያ ኃይል አነስተኛ ይሁን እንጂ ያሉትን አውሮፕላኖች በሚገባ ሊጠቀሙ የሚችሉ ጥቂት ምርጥ በራሪዎች ነበሩት ። ጄኔራል አሸናፊን ጨምሮ።

ጄኔራል አሸናፊ ቀድም ሲል የአየር ለአየር ውጊያ በግሩም ሁኔታ የተለማመዱ ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባር ላይ ያዋሉት የሶማልያ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ላይ ነበር ። በዚህ አሃዱ ባሉበት የጦር ሜዳ ውሎአቸውም ግዳይ ጥለዋል ። አድብቶ ከኋላ ሲከተላቸው የነበረውን የሶማልያ ሚግ አውሮፕላንን ፈጣንና ድንገተኛ የአቅጣጫ ለውጥ አድርገው በታጠቁት ሚሳይል ደረቱን ለሁለት በመግመስ አየር ላይ ብትንትኑን አውጥተውታል።

በዚያን ዘመን ለረዣዥም ሰዓታት ፣ ሌትና ቀን ሰማይ ላይ ነጭ ላብ ፈሷል ። ሕይወትም ተገብሯል ። ለግዳጅ ሸኝተን መልሰን ያልተቀበልናቸው ጀግኖች ዛሬም ባለውለታዎቻችን ናቸው ። ይሄ ሁሉ ለነጻነትና ለሉአላዊነት የተከፈለ ክቡር መስዋዕትነት ነበር ። ከዚያ ሁሉ መዓት ተርፈው ገና ብዙ ሊያገለግሉን ፈቃደኛ የነበሩ ወደር የማይገኝላቸው የአገሪቷ ሃብቶች መንግስት ስለተለወጠ ብቻ እንደ ተራ ወንጀለኛ አለም በቃኝ መውረዳቸው ታሪክ ይቅር የማይለው ክህደት ነው ። እንዲህ አይነቱ ክፉ ዕጣ ከደረሰባቸው የአየር ጀግኖች መሃከል ጄኔራል አሸናፊ ገ/ፃድቅ አንዱ ናቸው ። ህውሃት ደብረ ዘይትን የተቆጣጠረ ዕለት ሻቢያዎች ነበሩ ጀነራል አሸናፊ መኖሪያ ቤት ድረስ በመምጣት በቁጥጥር ስር ያዋሏቸው ። ቆይተውም ለህውሃቶች አስረከቧቸው ።  ህውሃት ከተረከባቸው በኋላ ታድያ ድፍን አስር ዓመት እስር ቤት ውስጥ ማቀዋል ። ገና ባልቀዘቀዘ የተዋጊነት ስሜት ፣ ባልተኮላሸ ወኔ ላይ የነበሩ ጀግና የአየር ሰው ለእስር ተዳረጉ ። አስር ዓመት ሙሉ ከአንዱ እስር ቤት ወደሌላው እያዟዟሩ አንገላተዋቸዋል ። ይሄ ከዕድሜዬ ላይ በግፍ የተነጠቀ ዘመን ነው ይላሉ ጀነራሉ ። ሆን ተብሎ አስር ዓመት ታሽጎ እንዲዝግ የተበየነበት ዕውቀትና ልምድ ብዙ ወጪ የወጣበት የሃገር ሃብት ነበር።

ኢሕዲግ አዲስ አበባ እሰከገባበት ቀን ድረስ ጠቅላይ መመሪያ ውስጥ የስራ ገበታቸው ላይ የነበሩት ጄኔራል አሸናፊ የዘመቻ አዛዥነት ግዳጃቸውን እየተወጡ ነበር ። እንዲያው ስለ አጠቃላይ ሁኔታው ምን ይሰማዎታል ? አልንና ጠየቅናቸው ። መቼም የመንግስት ስልጣንን በጠመንጃ የጨበጠ ኃይል መረጋጋት እስኪፈጠር ድረስ የተሸነፈውን ሰራዊት ለሶስት ወር ያህል አግልሎ ቢያቆይ የአባት ነው ብለው ለጥያቄያችን መልስ በመስጠት ጀመሩ። በማስከተልም አስር ዓመት አስሮ ማንገላታት ግን ግለሰቡን ብቻ ሳይሆን ሃገሪቱንም መጉዳት ነው ይላሉ ። ለምን እንዲህ ማድረግ እንደተፈለገ  እሰከ አሁን ድረስ መልስ ያላገኙለት ጥያቄ እንደ ሆነ አለ ።

gen-ashefafi-gebre-tsadik1

እስኪ አስቡት ኢትዮጲያ ለዓመታት ሰማይ ላይ በመዋል ከጠላት የታደጓትን ጀግኖች ሐውልት ልታቆምላቸው ሲገባ ጭራሽ አስራ አንገላታቻቸው ፣ ሞት ፈረደችባችው  ቢባል እንዴት ይታመናል ?  እንደኔ ሃገሬ ያልከፈለችው ዕዳ አለባት ።

ጄኔራል አሸናፊ በቅንነት ከልብ ያገለገሉበትን መስሪያ ቤት የራሳቸውን ያህል ይወዱታል ። ኢትዮጲያ ልጆቼ የምትላቸውን ሁሉ ከአሉበት አሰባስባ የምታሰለጥንበት ፣ አብሮ መኖርንና መከባበርን በተግባር የምታስተምርበትን የያኔውን አየር ኃይል በእጅጉ ያስታውሳሉ ። የድርጅቱን ጥንካሬም ከዛሬው ጋር ሲለኩት በእጅጉ ይቆጫሉ ። እሳቸው የሚያውቁት አየር ኃይል አባላቱን በቅብብሎች ነበር የሚያሰለጥነው ። ዕውቀትና ልምድ ከአባት ወደ ልጅ እነደሚተላለፍ አይነት ። ለዚህም ነበር ከጊዜው ቴክኒዎሎጂ ጋር የሚሄዱ ብቁ ሰዎችን ማፍራት የተቻለው ። ይሄ ዛሬ አለ ብለው አያምኑም ።

ወደፊት እንዴት መኖር አለበን ? ብለን ለጠየቅናቸው ጥያቄ የሰጡን መልስ ለብዙዎቻችን ፣ መጽሐፉን ከድነን ማስቀመጥ ለከጀለን ሰዎች ትልቅ ትምህርት ሊሆን ይችላል ። መግቢያችን ላይ እነደጠቀስንላችሁ ሁሉ ጄኔራሉ የሚያዩት ሩቅና ወደፊት ነው ። መጀመሪያ እንደ እምነታችሁ ኑሩ አሉ ። እኔ ክርስቲያን ነኝና እንደክርስቲያን መኖር አለብኝም አሉ ። ይህም ደግና መልካም የሆነውን ብቻ መስራት ማለት ነው ። ከዚያ ተስፋ አለመቁረጥ ነው አሉን ። ብዙ ታለንት (ተሰጥዖ) አለ ፤ ባክኖ እንዳይቀር መታገል አለብን ። ይህንን ታለንት ጥቅም ላይ ለማዋል መዝግበን ለልጆቻችን ማስተላለፍ አለብን ባይ ናቸው ። እኛም ብንሆን አርቀን ማሰብ አለብን ። ዕድሉ ሲፈጠር ሃገራችን ገብተን ብዙ ለመስራት እራሳችንን ማዘጋጀት አለብን ነው ያሉት ጄኔራሉ።

ጄኔራል አሸናፊ ምንም እንኳን አሁን ለጊዜው ተለይተዋቸው ባሕር ማዶ ቢኖሩም ባለትዳር ፣ የአንድ ልጅ አባትና የሁለት የልጅ ልጆች አያት ናቸው ። ያላቸውን ጥቂት የዕረፍት ጊዜ ሰውተው ታሪካቸውንና ሃሳባቸውን ስላካፈሉን መስጋናችን እጅግ የላቀ ነው ። ይህ ጽሑፍ ከሰፊው ታሪካቸው ላይ በማንኪያ የተጨለፈ መሆኑን ግን አትዘንጉ። ባለታሪኩ ልከውልን ዘግይቶ እጃችን የገባው መረጃ የሚናገረው ይህንን ነው። ወደፊት በሰፊው እንመለስበታለን።


“የጎሣ ፖለቲካ ማለት የጥላቻ ፖለቲካ ነው፤ ከጎሣ ፖለቲካ መውጣት አለብን” –ኦባንግ ሜትሆ

$
0
0

አቶ ኦባንግ ሜትሆ፤ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር፤ ስለ ኒውዝላንድና የአውስትራሊያ የጉዞ ዓላማቸው፣ እንዲሁም የወቅቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ አስመልክተው ይናገራሉ። SBS Amharic Radio:

“የጎሣ ፖለቲካ ማለት የጥላቻ ፖለቲካ ነው፤ ከጎሣ ፖለቲካ መውጣት አለብን” – ኦባንግ ሜትሆ

በሰሜን ጎንደር ደባርቅ የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት የጅምላ እስር እያካሄደ ነው |ሕዝብ ቁጣው ገንፍሎ ያሰራችሁትን ፍቱ እያለ ነው

$
0
0
ደባርቅ ከተማ በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች እንዲህ ተከባለች

ደባርቅ ከተማ በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች እንዲህ ተከባለች

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች በሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የጅምላ እስር እያደረጉ መሆኑ ተዘገበ:: አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሐንስ እንደዘገበው በደባርቅ በርካታ ወጣቶች ከቤታቸው እየተወሰዱ ሲሆን በትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ታፍነው የተወሰዱ ወጣቶችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል::

1. አግንቸ ማውሻ
2. ሐብታሙ መኮነን
3. መልስ ጌታቸው
4. ይርጋ መኩርያው
5. ለምለም አዲሱ
6. ሰለሞን ክንዴ
7. ቀናው መዝን

ወጣቶቹን ለትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት አብረው እያሳፈኑና የባንዳ ሥራ እየሰሩ የሚገኙት የከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ ኃላፎውፕች አቶ አዳነ ዳኘውና ሻምበል አምባቸው ሲሆኑ በሕዝቡ ጥርስ እንደተነከሰባቸውም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል::

እንደ አክቲቭስት ሙሉነህ ገለጻ የደባርቅ መውጫ መግቢያ በወታደር ታጥሯል እስር ቤቶች በህዝብ እየተጨናነቁ ነው። ሕዝቡ በጣም ቁጣው ገንፍሎ የታሰሩትን ፍቱ በማለት ላይ ይገኛል። ያ ካልሆነ የአፀፋ እርምጃዎች ለመውሰድ እንገደዳለን እያለ ነው። እስር የህዝብን ትግል ያባብሰዋል እንጅ ማስቆም አይችልም።

የዶ/ር ቴድሮስ ነገር ………….|በጌታቸው ማሩ እና ሳጅን ዮሮሱን 

Next: Hiber Radio: በታች አርማጭሆ በሳንጃ በአውቶብስ ይጓዙ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች በፈጠሩት ትንኮሳ በተወሰደ የአጸፋ እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው፣የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት እንዲከበር እና የኢንተርኔት መረቡ እንዲከፈት ጠየቀ፣በመተማ የአገዛዙ ኮማንድ ፖስት ታጣቂዎች በአንድ ቡናቤት ላይ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ወጣቶችን ገደሉ፣የአማራ እና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ጥንቃቄ ካልወሰዱ ትግሉ እንደሚጎዳ የሕወሃት አገዛዝን አዲስ ሴራ አንድ የውጭ የስለላ ድርጅት አጋለጠ፣ በጎንደር ዲሽ በቤታቸውና በድርጅታቸው የተገኘ መታሰር ጀመሩና ሌሎችም
$
0
0

በቅርብ ጊዜ ቀነኒሳ በቀለ በፈይሳ ለሊሳ ላይ በሰጠው አስተያየት ፣ ከሃሳቡ ጀምሮ እስከ ተናገረበት ቋንቋው ድረስ ብዙ ታምቶበታል፡፡ ብዙም ተብሎበታል፡፡ ቢሆንም ግን ‹‹ሰው በሃሳቡ ነው መመዘን ያለበት›› የሚል ጥብቅ አቋም አለን፡፡

adhanom

አንድ ሰው እንደልቡ በማይናገረው ቋንቋ ከሰው ፊት ቀርቦ በድፍረት ለመናገር ከሞከረ ግለሰቡ የማሰብ (ያላዋቂነት) ችግር እንዳለበት እሙን ነው፡፡ ስለዚህ ለዚህ አይነት ድፍረቱ ሊተች ወይም ሊታማ ግድ ነው፡፡ በመቀጠልም የአፍ መፍቻ ቋንቋውን ተጠቅሞ ማስተላለፍ የፈለገውን ሃሳብም በልኩና በትክክል ማስተላለፍ ሳይችል ከቀረም ለሚፈጠረው ችግር አሁንም ተጠያቂና ተተቺ  የሚሆነውም ራሱ ግለሰቡ ነው፡፡ ሲሰልስ  ደግሞ በውል ያልተረዳውን ፅንሰ ሀሳብ በትክክል በማይችለው ቋንቋ ለማስተላለፍ መሞከር ‹‹ተያይዞ ገደል!›› ዓይነት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ያ ማለት ራሱ ብቻ ሳይሆን በዙሪያው ያሉትንም ገደል ይከታል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነት ደፋር ሰው መተቸት ግድ ነው፡፡

ለዚህ ጹሁፍ መነሻ የሆነው በደጋፊዎቹ  ዘንድ እንደ እንቁ የሚታየው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በየዓለም የጤና ድርጅት ሀላፊነት ውድድር ላይ ያደረገው ንግግር ሲሆን፣ የዶ/ሩ የመድረክ ቆይታ የሦስተኛውን ሁኔታ ወይም  ‹‹የቋንቋ እና የሀሳብ እጥረት አብረው ተያይዘው መፈጥፈጥ››  የተንጸባረቁበት  ሆኖ  አልፏል፡፡ በዚህ የስራ ውድድር ወቅት ለመታዘብ እንደቻልነው ፓኪስታናዊቷ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር በቋንቋ አጠቃቀሟ ብቻ ሳይሆን በሚገርም የስራ እቅድ እና ለተጠየቁት ጥያቄዎች በልበ ሙሉነት መልስ በመስጠቷ የአድማጮችዋን ቀልብ ለመግዛት ችላለች፡፡ በዚህ አጋጣሚ እንደ ትንቢት እንኳን ከተያዘ እኝሁ እንስት አሸናፊ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት አለን፡፡

በአንድ ወቅት በትግሪኛ ለሚዘጋጅ የሃገር ውስጥ መጽሔት ጆቤ በመባል በቅጥል ስሙ የሚጠራው ጀኔራል አበበ ሲናገር ‹‹ዋናው ችግራችን (ኢህኣዴጎች ማለቱ ነው) አላዋቂነትና እብሪነት (Ignorance and arrogance) ነው›› ብሎ ነበር፡፡ ይህንን አባባል ዶ/ር ቴዎድሮስ በግልጽ በዚህ ውድድር ላይ አንጸባርቆታል፡፡ በእንደዚህ አይነት አለማቀፋዊ ውድድር ላይ በወረደ የምሁር ስብዕና መቅረቡ በራሱ ‹‹እብሪተኛነቱን›› ሲያሳይ፣ በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጠው መልስና ያሳይ የነበረው ግራ መጋባት እንዲሁም ለድርጅቱ ያቀረበው ፕሮፖዛል ‹‹አላዋቂነቱን›› አጋልጦበታል፡፡ እስቲ ከቋንቋ እጥረቱ ባሻገር ዶ/ሩን በትንሹ እንየው/ እንገምግመው፡፡

  1. ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም የጤና ድርጅት ዓመታዊ በጀቱን ለማሟላት በምን መልኩ የገንዘብ አሰባሰብ ማድረግ እንዳለበት ሲያስረዳ የድርጅቱን መሰረታዊ የገንዘብ አሰባሰብ አሰራር እንደማያውቅ በግልፅ አሳይቷል፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት ዓመታዊ ባጀቱን የሚያገኘው ከሀብታም ሀገሮች፣ ከመድሃኒት አምራቾች እና ከለጋሽ ድርጅቶች በሚደረግለት የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡ ነገር ግን የኛው ጉድ ዶ/ር ቴዎድሮስ የአክስዮን ድርሻን እንደምሳሌ በማንሳት ከ51 እጁ በላይ አባል ሀገራቱ በማዋጣት ድርጅቱን እና ስራውን በባለቤትነት መምራት አለባቸው የሚል ፕሮፖዛል አቅርቧል፡፡ ይህ ሃሳቡም ሁለት ነገሮችን እንዳልተረዳ አሳይቷል፡፡ አንደኛ ድርጅቱ ለዘመናት የሚሰራበትን አሰራር ወደ ኋላ እና ሊሆን ወደ ማይችል የበጀት ወጭ ስልት ለመጎተት መፈለጉን  ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ  ሃያላን ሀገሮች እና እንደ ቢልጌት ያሉ ለጋሾች በድርጅቱ ላይ ያላቸውን  ከመጋረጃ በስተጀርባ ፍላጎት የማያውቅ መሆኑን አሳይቷል፡፡ እንደሚታወቀው ታላላቅ ለጋሾች በዚህ አይነት ወሳኝ ምርጫ ላይ ይቅርና በሌሎች ባደጉትም ሆነ ባላደጉት አገሮች  ምርጫ ላይ እንኳን ፍላጎታቸውን ለማሳካት ረጅም እጃቸውን በመዘርጋት በምርጫዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ዶ/ር ቴዎድሮስ ይህንን የተገነዘበ አይመስልም፡፡ ነጮቹ እንደሚሉት pay to play ጨዋታንም ፈፅሞ አልተረዳውም፡፡ የለጋሽ አካላትን ፍላጎትና የሚኖራቸውን ተጽዕኖ፣ እንዲሁም ለድርጅቱ እርዳታ በማድረግ ፍላጎታቸውን  በቀጥታ ማስፈፀም እንደሚፈልጉም አልተረዳም ፡፡ ዶ/ሩ ጎበዝ (አዋቂ) ቢሆን  ኖሮ የልቡን በልቡ አድርጎ በዚህ ጉዳይ ላይ ፖለቲካዊ እና ዲመፕሎማቲካዊ አቋሞችን ማንፀባረቅ ነበረበት፡፡ በመሆኑም የርሱ የበጀት ፕሮፖዛል በለጋሾቹ ፍላጎት ላይ ደንቃራ ሆኖ እንደመቆም ስለሚቆጠር ተፈላጊነት የለውም፡፡ ባጠቃላይ በድርጅቱ የገንዘብ አሰባሰብ ዙሪያ የነበረው መረዳት የድርጅቱን አሰራር አላዋቂነቱን አስመስክሯል፡፡
  2. የዶ/ሩ ሌላው ችግር ዓለም አቀፋዊ የህብረተሰብ ዓቀፍ የጤና አጠባበቅን በሚገርም ሁኔታ አለማወቁ ነው፡፡ ከወባ ውጪ ሌላ ነገር የሌለ ይመስል በወባ ጀምሮ ወባ ላይ ተንቀጥቅጦ ጨርሶታል፡፡ ብዙ የተባለለትን የሰሜን እና የደቡብ ሀገሮች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ሁኔታን አያውቀውም ብቻ ሳይሆን እንደዚህ ሰሜን እና ደቡብ ተብለን ስለመከፋፈላችንም ሰምቶ የሚያውቅ አይመስልም፡፡ ስለዚህ በሁለቱ ማህበራዊ ክፍሎች የተለያዩ ችግሮች መኖራቸውን  እና ለተለያዩ ችግሮች ደግሞ የተለያየ ስትራቴጅ አስፈላጊ እንደሆነ ማወቅን ይጠይቃል፡፡ በደመነፍስ ማንም እንደሚረዳው ተላላፊ በሽታዎች እና የማይተላለፉ ገዳይ በሽታዎች የትኛውን የዓለማችን ክፍል እንደሚያጠቁ ጠንቅቆ ማወቅ አለበት ብቻ ሳይሆን ተገቢ መፍትሄ ማዘጋጀት ጭምር ነበረበት፡፡ በዚህም ረገድ የመጣባት አገራችን ኢትዮጵያ በበሽታ ከሚሞቱባት ሰዎች መካከል ከ40% በላይ የሚሆኑት የሚሞቱት እሱ መቶ ጊዜ በተናገረው ወባ ብቻ ሳይሆን በዘመን አመጣሾች ማይተላለፉ በሽታዎች ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ጠንቅቆ ማወቅ ተላላፊ እና የማይተላለፉ በሽታዎች እኩል ትኩረት እና የፖሊሲ አቅጣጫ ያስፈለጋቸዋል ለማለት ነው፡፡ በዚህም ዙሪያ እብሪቱንና አላዋቂነቱን ባደባባይ አሳይቷል፡፡
  3. ዶ/ሩ የብዙ ሀገሮች መሪዎችን እንደሚያውቅ፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶችን መምራቱን እና ሌሎችን ጉዳዮች እንዲሁ በደመ-ነፍስ ሲያዎራ ነበር፡፡ ከየሀገራቱ ለተጠየቀው ጉዳይ ለምሳሌ ላቲኖች ቴድሮስ ሊሉ ብለው ፔድሮ ይሉኛል እያለ ለቦታው እና ለወቅቱ የማይመጥን ቀልድ መሳይ ዘረኛ ንግግር በማድረግ ከጥያቄው ለመሸሽ ሲሞክር ታይቷል፡፡ ሰውየው አይደለም  የ180 ሀገራትን ሁኔታ የሚያውቅ፣ የኢትዮጵያን ችግር እንኳን በቅጡ እንደማያውቅ ያሳየ ሲሆን  ከወባ በሽታ የዘለለ ሌላ ጉዳይ ማንሳት አልቻለም፡፡
  4. ሌሎችም

ከላይ የተጠቀሱት ሃሳቦች ዶ/ር ቴዎድሮስ ለምርጫው የማይመጥን እንደሆነ ማሳያ ቢሆንም ኣላዋቂነቱን ተረድተው ለጋሾችና አንዳንድ ቡድኖች እንደፈለግነው እናዘዋለን  ወይም እናሽከረክረዋለን ብለው ሊያስመርጡት ይችላሉ የሚል ስጋት በአንዳንዶች ላይ አለ፡፡ ይህም ቢሆን ከሰውዬው የቋንቋ ችግር ባሻገር ተናግሮ የማሳመን ችሎታው እዚህ ግባ የሚባል ስላልሆነ ተስፋው የሞተ ነው፡፡ ከእሱ ይልቅ ሌሎች ተወዳዳሪዎች በልምድም ሆነ በሙያ የዚህ ዓይነት የማሳመን ስራ በየሀገራቱ ይሰሩ ስለነበር ከእሱ ልቀው ሊመረጡ ይችላሉ፡፡

ሰውየው ሊመረጥበት የሚችለው አንድ እና አንድ ምክንያት ብቻ ነው፡፡ ይህም የዓለም የጤና ድርጅት እስካሁን በአፍሪካውያን ተመርቶ አለማወቁ እና አሁን የአፍሪካውያን ወቅት ነው የሚለው ሀሳብ ሚዛን ከደፋ ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሰውዬው ፐርፎርማንስ የወረደ ስለሆነ  ድምፅ የሚሰጠው አይኖርም፡፡

Hiber Radio: በታች አርማጭሆ በሳንጃ በአውቶብስ ይጓዙ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች በፈጠሩት ትንኮሳ በተወሰደ የአጸፋ እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው፣የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት እንዲከበር እና የኢንተርኔት መረቡ እንዲከፈት ጠየቀ፣በመተማ የአገዛዙ ኮማንድ ፖስት ታጣቂዎች በአንድ ቡናቤት ላይ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ወጣቶችን ገደሉ፣የአማራ እና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ጥንቃቄ ካልወሰዱ ትግሉ እንደሚጎዳ የሕወሃት አገዛዝን አዲስ ሴራ አንድ የውጭ የስለላ ድርጅት አጋለጠ፣ በጎንደር ዲሽ በቤታቸውና በድርጅታቸው የተገኘ መታሰር ጀመሩና ሌሎችም

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 27 ቀን 2009 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ስለ ቀድሞ ወዳጁ ዛሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ገ/ኪዳን የትግራይ ተወላጅነትና ስለ አዲሱ ካቢኔ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ(ክፍል አንድ ያድምጡት)

ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ የወቅቱ የአፍሪካ የደህነትና የሲኩሪቲ ጥናት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር በአራት ድርጅቶች ስምምነት ይፋ ስለሆነው የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ እና ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድን ያዳምጡት)
habtamu-assefa-hiber
አቶ ኤልሻዳይ ተስፋዬ በሲያትል የአማራ ሕዝብ አንድነት ግብረ ሀይል አስተባባሪዎች አንዱ በከተማዋ ስለተካሄደው የአማራ ሕብረት እና ህልውና ላይ ስለተደረገው የጋራ ስብሰባ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

ከመጨረሻው ምእራፍ የደረሰው የአሜሪካው የፕ/ታዊ ምርጫ አስገራሚ እና አስደንጋጭ ክንውኖቹና የአለም መራጮች ስለ ዕጩዎቹ የሰጡት ምላሽ(ልዩ ዳስሳ)

ከፕ/ር አለምአንተ ገ/ስላሴ የጎንደር ህብረት የቦርድ አባል ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ ክፍል ሁለት

ዜናዎቻችን

በጎንደር ዲሽ በቤታቸውና በድርጅታቸው የተገኘ መታሰር ጀመሩ

በመተማ የአገዛዙ ኮማንድ ፖስት ታጣቂዎች በአንድ ቡናቤት ላይ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ወጣቶችን ገደሉ

በታች አርማጭሆ በሳንጃ በአውቶብስ ይጓዙ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች በፈጠሩት ትንኮሳ በተወሰደ የአጸፋ እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው

የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በሁሉም ወገኖች እንዲደገፍና እንዲጠናከር ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ጥሪ አቀረቡ

በአዲስ አበባ የዶላር ዋጋ በጥቁር ገበያ ጨመረ በስርዓቱ ላይ ጫናው ቀጥሏል

የአፍሪካ ህብረት የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት የዜጎቹን የሰብዓዊ መብትን እንዲያከብር እና የኢንተርኔት መረቡን እንዲከፍት ጠየቀ

ኢህአዲግ ኮምፒውተራቸውን አሜሪካ ውስጥ የበረበርው ግለስብ ይግባኝ ጠየቁ

በአዲስ አበባ የሚገኙ የ ደቡብ ሱዳን ተማሪዎች በኢህአዲግ ደህንነቶች ተደብድብድበው ታስሩ

አቶ ሐ/ማሪያም ደሳለ ኝ የውጪ አገር ኢምባሴዎችን ለመጠበቅ ቅድመ ሁኔታ እስቀመጡ

አቶ ሐይለማሪያም ደሳለኝ አዋቀርኩት ያሉት የካቤኔዎች ስብስብ በህዋት ባለስልጣናት መንደር ታላቅ መደናገጥ መፍጠሩ ተነገረ

የሕወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝን ለማንበርከክ የአማራ እና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ጥንቃቄ ካልወሰዱ ትግሉ እንደሚጎዳ የስርዓቱን ሴራ የውጭ የደህነት መረጃ አጋለጠ

በኢትዮጵያ የተከስተው ያለመርጋጋት በርካታ ቱሪስቶችን እያሽሻቸው መሆኑ ታወቀ

አዲስ አበባ ሰሞኑን ለጉብኝት የመጡት እንግሊዛዊ ዜጋ ደብዛቸው ጠፋ

አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ በሙስና የተዘቀጠው የኢ/አ/ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመረጠ

ሌሎችም

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

የአትላንታ ቅድስት ማርያም የቤተክርስቲያን ችግር መነሻና መድረሻ

Previous: Hiber Radio: በታች አርማጭሆ በሳንጃ በአውቶብስ ይጓዙ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች በፈጠሩት ትንኮሳ በተወሰደ የአጸፋ እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው፣የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት እንዲከበር እና የኢንተርኔት መረቡ እንዲከፈት ጠየቀ፣በመተማ የአገዛዙ ኮማንድ ፖስት ታጣቂዎች በአንድ ቡናቤት ላይ በከፈቱት ተኩስ ሁለት ወጣቶችን ገደሉ፣የአማራ እና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ጥንቃቄ ካልወሰዱ ትግሉ እንደሚጎዳ የሕወሃት አገዛዝን አዲስ ሴራ አንድ የውጭ የስለላ ድርጅት አጋለጠ፣ በጎንደር ዲሽ በቤታቸውና በድርጅታቸው የተገኘ መታሰር ጀመሩና ሌሎችም
$
0
0

የሰዐሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን፣የቦርድ አባላት እና የአባቶች መከፋፈል የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህም መከፋፈል በዓለማዊ ሕግ እንዲወሰን ፍርድ ቤት በመቅረቡ በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን እጅጉን አሳዝኗል። ሃዘኑ እጥፍ ድርብ ያረገው ዛሬ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ ወጣቶችን በጅምላ ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ በመጨፍጨፍ፣ በማሰርና በመግደል ላይ ባለበት ወቅት መሆኑ ነው። የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ አባተ ዘውዴ እና ጓደኞቹ እነ አቶ አየለ ገብሩ በሊቀ ጳጳሳት እና በሽማግሌዎች ፤ በሞቱ ከአባቱ ጋር እና ከራሱ ጋር ባስተረቀን አምላክ ስምእንዲሁም በአግአዚ ጦር አልሞ ተኳሾች የልጆቻቸው ግንባር እየተመታ የተገደሉባቸው ስለሚያለቅሱት እናቶች ስትሉ ፣ ስለ ቅድስቲቷ አገራችን የኢትዮጵያ አምላክ ብላችሁ እባካችሁ ለሰላም እጃችሁን ዘርጉ ሲባሉ ልባቸው እንደ ፈርዖን ደንድኖ እንቢ ሲሉ ማየት ልብን የሚያሳምም ክስተት ነው። ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥምና አሁንም በግራም ሆነ በቀኝ የተሰለፉት ምእመናን እና አባቶች በእግዚአብሔር ቸርነት ችግሩን በሰላም ይፈታሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ምእመናን በሳምንት ከአርባ እስከ ስልሳ ሰዓት እግራቸው እየነደደ ቆመው ሰርተው እንዲሁም በጸሃይ እና በብርድ እየተቃጠሉ ታክሲ እየነዱ ካገኙት ገንዘብ ለእግዚአብሔር ቤት ያቀረቡትን መባ ለፈረንጅ ጠበቃ ሲሳይ ማድረግ የማንም ሰው ህሊና ስለማይፈቅድ በሽምግልና እንደሚያልቅ ሙሉ ተስፋ አለኝ።አንደ ቤተክርስቲያን አባልነቴ እንደዚሁም ከዚህ በፊት እንደ አስተዳደር ቦርድ አባልነቴ የቤተክርስቲያናችን ችግር መነሻ ብዬ የተገነዘብኩትን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

congregation_four
የዚች ቤተክርስቲያን አባል ከሆኑኩ ከ18 ዓመት በላይ አስቆጥሬአለሁ። ያኔ የነበርነው በትንሿ ቤተክርስቲያን ሲሆን አሁን የማውቃቸው ምእመናን በሙሉ ያወኳቸው እዛ ነበር። አሁን በተነሳው ውዝግብም የቦርድ አመራር የነበሩት ያኔም የቦርድ አመራር ነበሩ። ያንጊዜም ተፈጥሮ ለነበረው ያለመግባባት የተወሰደው መፍትሔ አሳዛኝ ነበሩ። የቦርድ አባላት የነበሩ ጥለው ሄደዋል፤መዘምራን ተባረዋል። አሁንስ የተፈጠረው አለመግባባት እንዴት ተጀመረ?
ጊዜው ብጹዕ አቡነ ያዕቆብ የኤጲስ ቆፖስ ሹመት ያገኙበት ነበር። በወቅቱ አቡነ ያዕቆብ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ነበሩ።እነ አቶ አባተ ያቀዱትን ድብቅ አላማ ወደ ግብዓት ለማድረስ ይችሉ ዘንድ አቡነ ያዕቆብ የጵጵስናውን ማዕረግ በተቀበሉ ማግስት የአስተዳዳሪነቱን ስራ እንዲያስረክቡ ውትወታ ጀመሩ። ብጹዕነታቸውም ጥያቄውን ተቀበሉት። ለአቶ አባተና ጓደኞቹ እንዲሁም ከውጭ ሆነው ከአቶ አባተ ጋር በመተባበር ቤተክርስቲያኗን ከሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ አውጥቶ በመጀመሪያ ወደ ገለልተኛ ቀጥሎም ወደ ሀገር ቤቱ በወያኔ የሚዘወረው ሲኖዶስ ለማስገባት ጥሩ አጋጣሚ ፈጠረ።በመቀጠልም በህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ላይ የጥላቻ ዘመቻ ከፈቱ።ያንኑ ሰሞን ከአንድ ቦርድ አባል ኢሜይል ተላከልኝ እና ሳየው ጽሁፉ ከወያኔ ደጋፊ ከሆነ ድረ ገጽ ላይ የተገኘ ሲሆን መልእክቱ በስደት ላይ የሚገኘው ሲኖዶስ ውስጥ የሚገኙት ሊቀ ጳጳሳት ሁሉ ጎንደሬ መሆናቸውን ገልጾ ይህንን ሲኖዶስ መዋጋት እንዳለብን አስረግጦ የሚናገር ነበር።
አቡነ ያዕቆብን ከቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪነት ከማስወገዳቸው በፊት ለአላማቸው የሚረዳ ቄስ ማፈላለግ ጀመሩ። ይህ መደበኛውን የአስተዳደር ቦርድ ያልተከተለ እንዲሁም የቦርድ አባላት ያልተሳተፉበት ካህን ፍለጋ ሂደት በአቶ አባተና በአቶ ቴዎድሮስ ነበረ የተከናወነው። ሆኖም ቤተክርስቲያናችን በአገልጋይነት የምታስመጣቸው ካህናት የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟሏት አለባቸው።
1፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና ስርዓት መሰረት ስልጣነ ክህነቱን ያገኘ።
2፦ ስለ መልካም ስነ ምግባሩ የተመሰከረለት ፤በቂ የቤተክርስቲያን ትምህርት እና ችሎታ እንዳለው የተረጋገጠ።
2፦ቤተክርስቲያናችን የምትቀበለውን ሲኖዶስ የሚቀበልና የሚያከብር።


የችግሩ ዋና መንስኤ
ከላይ እንደተገለጸው ካህን የማፈላለጉ ጉዳይ ሂደት አልቆ መጋቤ ብሉይ አባ ኃ/ሚካኤል የሚባሉ ካህን መመረጣቸውን በዚያን ጊዜ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ለነበርነው ተነገረን። የቤተክርስቲያን ትምህርት ችሎታቸው ተገልጾልን ምርጫው እንድናጸድቅ ተጠየቅን። በወቅቱ መተማመን ስለነበረ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ተንኮል ያስባል ብለን ስሳሳሰብን አፀደቅነው። ሆኖም አቶ አባተ እና ጓደኞቹ አባ ኃ/ሚካኤል ሲያስመጡ የሚከተሉትን ጉዳዮች ለማስፈጸም ተስማምተው መሆኑን ቆይተን ተረዳን። እኝህ አባት የውጭውን ሲኖዶስ እና በውስጡ ያሉትን አባቶች በአባትነት ስለማይቀበሉ አቡነ ያዕቆብን በተለይ መምህር ልዑለ ቃልን ለማባረር በሚደረገው ጥረት አንዲያግዙ እና በስደት የሚገኘውን ቅዱስ ሲኖዶስ በተሃድሶነት በመፈረጅ ቤተክርስቲያናችን ከሲኖዶስ እንድታፈነግጥ ነው።
ሁላችንም እንደምንገነዘነበው በስራችን ገበታ ላይ አንድ አዲስ ሰራተኛ በአንድ ኩባንያ ውስጥ ሲቀጠር የሚከተሉትን መስረርቶች ሲያሟላ ነው። በመጀመሪያ የኩባንያውን ህገ ደንብ ተቀብሎ እና አስተዳደሩን ሲያከብር ቀጥሎም ከማንኛውም ወንጀል ነጻ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።በአንጻሩ አባ ኃ/ሚካኤል ህገ ደንባችን አይቀበሉም እንዲሁም በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተዋረድ ሊቀ ጳጳስ የበላይ መሆኑም አያምኑም። በተደጋጋሚ የቦርድ ስብሰባ ላይ ተጠሪነቴ ለቦርድ ሊቀመንበር ሲሉ ሰምተናቸዋል። በተጨማሪም ወደ እኛ ከመምጣታቸው በፊት ያገለግሉበት ከነበረው ዱባይ ቤተክርስቲያን በስነ ምግባር ጉድለት ማለትም በዝሙት ቅሌት ተከሰው እንደነበር ይነገራል። ማስረጃ አለን የሚሉት አባላት ለኔ በግል አሳይተውኛል። አንድ የቦርድ ሊቀ መንበር እንዲህ ዓይነት ችግር ያለበትን ካህን አስመጥቶ በፍጥነት አስተዳዳሪ እንዲሾሙ ማድረግ ፤ ለቤተክርስቲያን አስቦ ነው ወይስ ሌላ ድብቅ አጀንዳ?
ከላይ ከዘረዘርኳቸው መረጃዎች ተነስቼ ለአንባብያን ማስጨበጥ የምፈልገው እውነታ፤ የዚች ቤተክርስቲያን ችግር የጀመረው አባ ኃ/ሚሳኤል የቤተክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ከሆኑ በኃላ ነው። ግን በጥፋተኝነት የምፈርጀው አባ ኃ/ሚካኤልን ሳይሆን የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ አባተን ነው። አባ ኃ/ሚካኤል ይዘው የመጡት የሚያምኑበትን ዓላማ ነው። ሄደውም የተቀላቀሉት የሚያምኑበትን ዓላማ የሚያራምድ የቤተክርስቲያን ነው።
ቤተክርስቲያናችን አሁን ለደረሰችበት ሁካታ እና ብጥብጥ ሃላፊነቱን የሚወስዱት አቶ አባተ እና ጓደኞቹ ናቸው። ምክንያቱም የኚህን ካህን አቋም እያወቁ ከቤተክርስቲያኒቱ ሰላም ይልቅ የግል ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም እኚህን አባት በማስመጣታቸው ነው። አባ ኃ/ሚካኤል የዜማ ትምህርት የተማሩ እና ነገር አሳክተው መናገር የሚችሉ ጮሌ መነኩሴ ናቸው።አብዛኛው የቤተክርስቲያናት አባላት ህገ ደንቡ በሚያዘው መሰረት በስደት የሚገኘው ሲኖዶስ ተቀብሎ የሚኖር ህዝብ ነው። ታዲያ ህጋዊውን ሲኖዶስ የማይቀበል ካህን አምጥቶ የክርስቶስን መንጋ ማበጣበጥ ብሎም መከፋፈል ክርስቲያናዊነት ነው? አቶ አባተን እና ጓደኞቹን እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው!
አባ ኃ/ሚካኤል በአስተዳዳሪነታቸው ዘመን አውደ ምህረት ላይ የሚያቀርቡት መልእክታት አሽሙርን እና ዘለፋን እንዲሁም ከፋፋይና አወዛጋቢ በመሆኑ ምእመናንን ከፋፍሏል ። ስለዚህም ምእምናን፣ መዘምራን እና የቦርድ አባላት ተከፋፈሉ። ክፍፍሉ ከቤተክርስቲያን አልፎ በማኃበራዊ ህይወት ውስጥ ለቤተክርስቲያናችን እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የጽዋ ማኀበራት እና ቤተሰብ ጋር ደርሶ በመከፋፈላቸው ዛሬ ቤተክርስቲያናችን ወደ ዓለማዊ ፍርድ ቤት እነ አቶ አባተ ወስደዋቷል። በመጨረሻም አባ ኃ/ሚካኤል ከአቡነ ያዕቆብ ጋር በእምነት የተለያየን አብረን መስራት አልችልም ብለው በመሰናበት የሃገር ቤቱን ሲኖዶስ ተቀላቅለዋል።
የተከበራችሁ አንባብያን በአሁኑ ሰዓት እዚህ የሌሉትን አባ ኃ/ሚካኤል ማንሳት ፈልጌ ሳይሆን አቶ አባተ እና ጓደኞቹ እሳቸውን ተጠቅመው ቤተክርስቲያኗን እንደበጠበጡ የምስክርነት ቃሌን ለመስጠት ነው።
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችን እና ሀገራችንን ከጥፋት ይጥብቅልን
የቀድሞ የአስተዳደር ቦርድ አባል

የአማራ ማህበረሰብ መሐበር በደቡብ አፍሪካ ተመሰረተ!!

$
0
0

በልሁል አለም
ጀግኖች አባቶቻችን በደማቸዉ የዋጇትን ኢትዮጵያ ሐገራችንን በክብር ለዘላለም ለማቆየት የአማራዉ መሐበረሰብ መሐበር በደቡብ አፍሪካ ተመስርቷል።
የአማራ መሐበረሰብ ማህበር የተሳኩ ዉይይቶችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በነዚሁ ወይቶች ላይ በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት ከህወሃት ወያኔያዊያን ባንዳዎች የጠራና የጸዳ አመራሮችን በማዋሃድ መሐበረሰቡን በትጋት የሚያገለግሉ የህዝብ ልጆችን በማቀራረብና ኢትዮጵያዊነትን በማስቀደም ” ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር” የሚል መሪ ሐሳብ በመያዝ በክብር በመደራጀት ላይ የሚገኘዉ የአማራ መሐብረሰብ መሐበር ሐገር የማዳንን እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ወገኖችን በማደራጀት ለወገኖቹ ጥቅምና ሰባዊ ክብር በብርቱ እንደሚታገልና በህወሃት ወያኔ የተነጠቅነዉን ህዝባዊ ማንነት ለማስመለስ እንደሚተጋ ተረጋግጧል።
በሲያትል የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት ስኬታምና የተዋጣለት ዉይይት በማድረግ ኢትዮጵያዊነትን ኩራት ያደረጉ ጽንሰ ሐሳቦች ጎልተዉ ወጥተዋል።
በተያያዘ ዜና በመላዉ አለም አማርድ በሚል መጠሪያ የተመሰርተ የጉራጌ ህዝቦች መሐበር በነገዉ እለት በደቡብ አፍሪካ ታላቅ ዉይይት መጥራቱን በኢትዮጵያዊነቱ ከማይደራደረዉ የጉራጌ ህዝብ ምንጭ ለማግኘት ያቻልን ሲሆን ህዝቦች በአንድነት በመደራጀት ሐገራቸዉን የማዳን እርብርቡ በየሐገሩ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ኬርቲና የጉራጌ ህዝቦች የሬዲዮ ጣቢያ የሙከራ ፕሮግራሞችን በማድረግ ላይ ይገኛል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%8c%8d

%e1%88%8d%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%8a%ad%e1%88%8d%e1%8a%ad

ወያኔ ሸሪክ የሆነው የአላሙዲ ድርጅት ሚድሮክ ኢትዮጵያ አሁንም በይቅርታ ታለፈ –ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባህላዊ አባቶችን ዘለፈ

$
0
0

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ የዛሬ ዜናዎች
ፍካሬ ዜና ጥቅምት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. . (November 07, 2016 Weekly NEWS SUMMARY)
alamudi
#ርዕሰ ዜና #የትምህርት መጻሕፍት ዋጋ መጨመር ተማሪዎችንና ወላጆችን እያማረረ ነው #የወያኔ ሸሪክ የሆነው የአላሙዲ ድርጅት ሚድሮክ ኢትዮጵያ አሁንም በይቅርታ ታለፈ #የወያኔ ባለሥልጣናት አሜሪካንንና አንዳንድ የምዕራብ አገሮችን አስጠነቀቁ #አገር ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በማቆማቸው በርካታ ድርጅቶች እየተጎዱ ነው ተባለ #ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባህላዊ አባቶችን ዘለፈ #የውጭ ምንዛሬ ዋጋ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው #ቻይና በኢትዮጵያ ውስጥ ያላት ሚና አነጋጋሪ እየሆነ ነው #እስራኤል ለደቡብ ሱዳን መንግሥት የመሳሪያ እርዳታ እያደረገች ነው ተባለ

#የትምህርት መጻሕፍት ዋጋ መጨመር ተማሪዎችንና ወላጆችን እያማረረ ነው
 ወያኔ በትምህርት መጽሀፍት ላይ የጣለው ዋጋ ወላጆችና ተማሪዎችን ማማረሩ ታወቀ፡፡ ወያኔ በየአመቱ የትምህርት መጸሀፍትን የመሸጫ ዋጋ እየጨመረ፣ ዘንድሮ ከወላጆች አቅም በላይ እንደሆነ በርካታ ወላጆች በማማረር ያስረዳሉ። የአንድ የትምህርት መጸሀፍ ዋጋ ከ120 ብር በላይ በመሆኑ ከዘጠና ከመቶ በላይ ለሚሆነው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ እየገፋ ላለው ሕዝብ በእጅጉ ውድ መሆኑን ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ ለዚህ ዋጋ መጨመር እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚቀርበው መጸሀፍቱ የሚታተሙት በህንድ አገር መሆኑን ብዙዎች ሰንካላና አሳፋሪ ሰበብ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ የትምህርት መጸሀፍት ህንድ አገር የሚታተሙበት ለሌላ ሳይሆን ለስርቆት እንዲያመች መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ወያኔ ሀገሪቱን በህትመት እጅግ ኋላ ቀር ከሚባሉ ሀገራት ተርታ እንዳሰለፋት የሚታወቅ ነው፡፡ በተባበሩት መንግስታት የትምህርትና የሳይንስ ተቋም በየትኛውም ሀገር በአጠቃላይ ለትምህርት ማበልጸጊያ የሚውሉ ከቀረጥ ነጻ መሆን እንዳባቸው የደነገገው በወያኔ እየተሻረ መሆኑን የትምህርት ባለሙያዎች በምሬት ይገልጻሉ፡፡
#የወያኔ ሸሪክ የሆነው የአላሙዲ ድርጅት ሚድሮክ ኢትዮጵያ፣ አሁንም በይቅርታ ታለፈ
 የአላሙዲን የንግድ ድርጅት የሆነው ሚድሮክ የተሰኘው ግዙፍ ኩባንያ ሀገርን እየዘረፈና ሕዝብን እየመዘበረ መሆኑ ብዙዎችን እያስቆጣ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ አላሙዲንና ድርጅቶቹ ከህግና ከደንብ በላይ በመሆናቸው ዛሬ በኢትዮጵያ ሁለት ዓይነት የአምባ-ገነን ስርአት መስፈኑን ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ ይህ ሚድሮክ የተሰኘው ድርጅት ከሚዝቀው የወርቅ ማዕድን ለብሔራዊ ባንክ ማስገባት የሚገባውን አያስገባም፣ ከዛሬ አስራ ስምንት አመታት በፊት ለሸራተን ሆቴል ግንባታ ከንግድ ባንክ የተበደረውን እየከፈለ አይደለም፣ ገበሬዎችን በማፈናቀል መሬት በወረራ እየያዘ ነው፣ በበርካታ ከተሞች መሬት እየወሰደ አጥሮ ያስቀምጣል፣ በሠራተኞች ላይ በማን አለብኝነት ግፍ ይፈጽማል፡፡ ይህ ድርጅት በአዲስ አበባ ከአስራ አምስት አመታት በላይ ካለምንም ግንባታ አጥሮ ያስቀመጣቸው በርካታ ቦታዎች እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ሌሎች ግንባታ ያልጀመሩ መሬታቸውን ሲነጠቁ ይህ ድርጅት በየጊዜው በይቅርታ እንደሚታለፍ ይነገራል፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንትም ለአምስተኛ ጊዜ በይቅርታ መታለፉ ብዙዎች በቁጭት ጡንቻ ያለውን ቡድን ማን ይናገረዋል በማለት በሀገር ላይ እየተደረገ ያለውን ቁማር ሲኮንኑ ይደመጣል፡፡
#የወያኔ ባለስልጣኖች አሜሪካንና አንዳንድ የምዕራብ አገሮችን አስጠነቀቁ
 ወያኔ አሜሪካንና አንዳንድ የአውሮፓ አገራትን ማስጠንቀቁ ብዙዎችን እያነጋገረ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ አንዳንዶች እቃ፣ አንዳንዶች ምስለ-ወያኔ፣ አንዳንዶች ርኆቦት፣ አንዳንዶች ተላላኪ የሚሉት ኃይለማርያም በአሜሪካ፣ በስዊድንና በእግሊዝ የወያኔ ኤምባሲዎች ቅጥር ግቢ ገብተው ወያኔን ያወገዙ ኢትዮጵያውያንን ለመክሰስ የፈረንጅ ጠበቆችን እንደሚገዙ መዛቱ አይጥ ለሞቷ ሄዳ ታሸታለች የድመት አፍንጫ እንደሚባለው እንደሆነ ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ለወያኔ ኤምባሲዎች ጥበቃ የማያደርጉ ከሆነ ወያኔም በእነዚህ ሀገራት ላይ አርምጃ እንደሚወስድ በደፈናው ዛቻ መሰንዘሩ ከአፍንጫ አርቆ የማሰብ ባህርይ እንደሌለው የሚያሳይ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ የፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚያስረዱት ይህ ጉዳይ የአሜሪካንና የአውሮፓ ሀገራትን አቋም ለማስቀየር በሚል ወያኔ ሶማሌ ውስጥ ያስገባቸውን ወታደሮች ሙልጭ አድርጎ እንደሚያወጣ መዛቱ በቀጥታ ለአሜሪካና ለሌሎች ሀገራት ተገቢ የሆነ ጥበቃ ላለማድረግ መዛቱ ሌላ ሳይሆን ወያኔ ከተነሳ ሽብር ይሰፍናል የሚልን ቅብዠራ ለመንዛት እንደሆነ ነው፡፡ ወያኔ ጥበቃ የሚያደርግላቸው ለአሜሪካ፣ ለእንግሊዝ፣ ለጀርመን፣ ለፈረንሳይ፣ ለግብፅ ምናልባትም ለሌሎች ጥቂት ሀገራት ብቻ እንጂ የየሀገራቱን ኤምባሲዎች ሁሉ አይጠብቅም፡፡ በኤምባሲዎቹ ላይ ወያኔ የሰነዘረው ዛቻ ወደ ፊት ሕዝባዊ አመጹ እየጋመና እየጎመራ ሲሄድ ወያኔ በሽምቅ በተወሰኑ ኤምባሲዎች ላይ የሽብር ጥቃት በመፈጸም በተቃዋሚ ኃይሎች ላይ ለማላከክና የምዕራቡን ዓለም ድጋፍ ለመሸመት በእንዲህ ያለው አረመኔ ድርጊት መሰማራቱ ሊጠረጠር እንደሚገባው በርካቶች አበክረው
ያስረዳሉ፡፡

#አገር ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በማቆማቸው በርካታ ድርጅቶች እየተጎዱ ነው ተባለ

 የሀገር ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት በማቆማቸው የተለያዩ ድርጅቶች ፈተና ላይ መውደቃቸውን በመጥቀስ ምሬታቸውን እየገለጹ መሆናቸው ታወቀ፡፡ ወያኔ የህዝብ አመጽን በአዋጅ ለማፈንና ለመግታት በሚል በአጉራ ዘለልነት ያወጣው የአፈና አዋጅ አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ እያሰኘ መሆኑ ታወቀ፡፡ ማንኛውም የውጪ ሀገር ዜጋ ከአርባ ኪሎ ሜትር በላይ ለመጓዝ ማሳወቅና መመዝገብ ገዴታ በመሆኑ እንዲሁም ይህ በእራሱ ወያኔ ገመዱ ጫፍ ላይ መድረሱንና ነገ ውድቀቱ እንደማይቀር ጠቋሚ በመሆኑ ማንኛውም ሀገር ጎብኚ ቀጥ እንዳለ መረዳት ተችሏል፡፡ አስቀድመው ከአስጎብኚ ድርጅቶች ጋር ተዋውለው የነበሩና ሆቴሎች ተይዞላቸው የነበሩ በወያኔ አፋኝ ህግ ሳቢያ መሰረዛቸውና አስጎብኚ ድርጅቶችንና ሆቴሎችን ለኪሳራ መዳረጋቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከሆቴሎችና አስጎብኚ ድርጅቶች ጎን ለጎን መኪና አከራዮች፣ የባህል እቃ ነጋዴዎች፣ ሌሎች ከሀገር ጎብኚዎች ጋር የእለት ተእለት ገቢያቸው የተሳሰሩ ለአደገና ኪሳራ እንደተጋለጡ ያስረዳሉ፡፡ ሆቴሎች የተገነቡት በብድር ሲሆን ብድራቸውን ለመክፈል ደግሞ ተስፋ የተጣለበት ከሀገር ጎብኚዎች የሚገኘው ገቢ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ ጋ በተያያዘም የተንቀሳቃሽ ስልክ የኢንተርኔት አገልግሎትና የሶሻል ሚዲያዎች መታገድ የሀገር ጎብኚዎችን እንደሚያሳቅቅ የሚታወቅ እንደሆነ በአስጎብኚነት ሥራ ላይ የተሰማሩ ያስረዳሉ፡፡

#ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባህላዊ አባቶችን ዘለፈ
 ወያኔ የሕዝብ ተጠሪዎችና ባህላዊ አባቶች ላይ ዘለፋ መሰንዘሩ ሕዝብን ጥርስ ማስነከሱን መገንዘብ ተችሏል፡፡ የወያኔ ተላላኪ የሆነው ኃይለማርም የባህላዊ መሪዎችንና ሽማግሌዎችን መዝለፉ ብዙዎችን ማሳዘኑ ታወቀ፡፡ የህላዊ አባቶች በተለያዩ ሕብረተሰቦች ያላቸውን ተቀባይነት ለመቦርቦር በስርዐት መመረጥ እንደሚገባቸውና ይህንን የሚጋፋ እርምጃ እንደሚወስዱ መናገሩ ብዙዎችን አስቆጥቷል፡፡ በተለይ የኮንሶ ሕዝብ ባህላዊ ወኪሎችንና የኦሮሞ አባ ገዳዎችን ክብርና ባህላዊ ተቀባይነትን የደፈረ ስድብ መሰንዘሩ ብዙዎችን እያነጋገረ መሆኑ ታውቋል፡፡

#የውጭ ምንዛሬ ዋጋ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው
 የውጪ ምንዛሪ እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ እየጨመረ መቀጠሉ እያነጋገረ መሆኑ ታወቀ፡፡ በዚህ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የውጪ ምንዛሪ ከሁለት ብር በላይ ጭማሪ ማሳየቱ ተውቋል፡፡ የወያኔው ብሔራዊ ባንክ ማንኛውም ባንክ የውጪ ምንዛሪ ማግኘት ለሚፈልግ አገልግሎት መስጠት እንዳለበት በቅርቡ ያስተላለፈው መመሪያ ውስጠ ወይራነት እንዳለው የኤኮኖሚ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡ የወያኔ ሹሞች ካደረባቻው ስጋት የተነሳ በእጃቸው ላይ ያለውን ብር ወደ ውጪ ገንዘብ በዘመቻ እየለወጡ መሆናቸውን ለጥቁር ገበያ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ለባንኮቹ የተላለፈው መመሪያ ወያኔዎችን ለመጥቀም የታሰበ መሆኑንም የባንክ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ሳምንት ባለው በጥቁር ገበያ የውጪ ምንዛሪ አንድ የአሜሪካን ዶላር 26.50፣ አንድ ዩሮ 28.60፣ አንድ የእንግሊዝ ፓውንድ 33.40 መሆኑን ማወቅ ተችሏል፡፡

#ቻይና በኢትዮጵያ ውስጥ ያላት ሚና አነጋጋሪ እየሆነ ነው
 ወያኔ ቀጥተኛ የውጪ መዋእለ ንዋይ በመሳብ ስም ኢትዮጵያን ለቻይና ቅኝ ግዛትነት መስጠቱ አሳሳቢ መሆኑ ብዙዎችን እያነጋገረ መሆኑ ታወቀ፡፡ ቻይና በመንገድ ሥራ፣ በባቡር ሀዲድ ዝርጋታና ባቡር ከእነፉርጎዎች በማቅረብ፣ የስልክ አገልግሎት መስመር ዝርጋታ፣ አሁን በቅርቡ በንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ፤ …ወዘተ በቀጥታ ብድር በማስገኘት የግንባታ ሥራ ላይ የቻይና ኩባንያዎች በብዛት እየተሰማሩ በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የቻይናዎች ቁጥር መቶ ሺዎች ውስጥ መግባቱ፣ ቻይና ሀገራችንን እየወረረች ለመሆኑ እንደማያጠራጥር ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ ወያኔ በተደጋጋሚ ከቻይና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንደሚኖር ቢለፈልፍም ቅንጣት ታህል እንደሌለ ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ወጣት ቻይናውያን አብዛኛዎቹ እዚህ ግባ የሚባል የሥራ ልምድ እንደሌላቸውና ኢትዮጵያና የአፍሪካ ሀገራት የመለማመጃ አምባዎቻቸው እንደሆኑ ነው የሚታወቀው፡፡ ይህ የቻይናዎች ቁጥር ካለ ስሌት እየጨመረ መሄድ የኢትዮጵያ ወጣቶችን ሥራ የማግኘት እድል የሚጋፋ ከመሆኑም በላይ የእህልና የአትክልት ዋጋ እጥረትንና የዋጋ መናርን እያስከተለ መሆኑን ብዙዎች በቁጭት ያስረዳሉ፡፡ ቻይናዎች ሠራተኞችን ሲበድሉና ሲደበድቡ እርምጃ የሚወሰደው በምስኪኑ ተበዳይና ተደብዳቢ ላይ መሆኑ ቻይና በወያኔ አስተናጋጅነት ኢትዮጵያን ቅኝ እየገዛቻት ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በተረፈም ወያኔ ከሰሜን ኮርያ በሚስጥር ከሚገዛው የጦር መሳሪያ በተጨማሪ ከቻይና በብድር መግዛት መጀመሩ ሲታወቅ በቅርቡም የአየር ኃይል ጄቶችን በብድር ለመግዛት ድርድር መጀመሩን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ወያኔዎችን ለመተካት በሚል በመመሪያ የወያኔ ሹመኞች ልጆቻቸው ቻይና የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪዎቻቸውን እንዲያጠኑ ተደርጓል፡፡ ከእነዚህ ተማሪዎች ውስጥ የትግራይ ሹሞች ልጆች በርካታ እንደሆኑ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ለመጪዎቹ አመታት በእነዚህ ወጣት ትግሬዎች የትግራይን ፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ በቻይና አጋርነት ለማስቀጠል ከሚል ቅዠት የተቀዳ መሆኑን መገንዘብ ችለናል፡፡

#እስራኤል ለደቡብ ሱዳን መንግስት የመሳሪያ እርዳታ እያደረገች ነው ተባለ
 የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የፖለቲካ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ መሄዱ ሲታወቅ ባዕዳን ደቡብ ሱዳንን ወደ ባሰ የእርስ በርስ ጦርነት እያስገቧት መሆኑ ታውቋል። ከዚህ በተያያዘ ዜና እስራኤል ለሳልቫ ኪር ጦር መሳሪያ መላክ መጀመሯ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። እስራኤል በደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ስታድርግ የቆየችው የሱዳንን አክራሪ መንግስት
ለማጥቃት ነው የተባለ እንደነበር ሲታወስ በአሁኑ የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ከሳልቫ ኪር ጎን መሰለፏ ግን አጠያያቂ መሆኑ አልቀረም ።


ትንቅንቁ ሊለይለት ሰዓታት ቀሩት

$
0
0

የአሜሪካው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የመጨረሻው ምዕራፍ የጦፈ ቅስቀሳ እና አስደንጋጭ ክንውኖቹና የዓለም መራጮች ስለ ዕጩዎቹ የሰጡት ምላሽ(ልዩ ዳሰሳ) በታምሩ ገዳ

ስኬት የሚገኘው ራዕይ ፣ ዕሴትና ተግባር ሲዋሃዱ ብቻ ነው –ማርእሸት መሸሻ 

$
0
0

ማስገንዘቢያ፡

visionየዚህ ፅሑፍ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለይም የሰባ ዓመታት የፖለቲካ ጉዞ የዘውዳዊውን፤ የወታደራዊውንና የዘረኛውን ወያኔ ሥርዓቶች ሲቃወሙ በባጁት ወገኖቼ መሃከል ውይይትን ለመቀስቀስ ነው። ይህን ጽሁፍ በእንግሊዝኛ ቋንቋ  “a way forward to a post-woyane demoratic and Just Ethiopiaበሚል ርዕስ አዘጋጅቼ ለንባብ አብቅቼዋለሁ። የቀየርኩት ነገር ቢኖር ርዕሱን ብቻ ነው። የእንግሊዝኛውን ጽሁፍ ለማንበብ :      http://www.ethiomedia.com/1016notes/a_way_forward.pdf

ይጫኑ።  ፅሑፉን በታችኛው የላቲኑ ፊደል ‘a’ የጀመርኩት ሆን ብዬና ለአንባቢዎቼ በዚያ ፅሑፌ ያስቀመጥኩት ትንተና ከገባንበት ቅርቃር መውጫ መንገድ የእኔ ብቻ አይደለምና ሌሎች ሊቀርቡ ከሚችሉ አማራጮች እንደ ኣንድ ኣማራጭ እዩልኝ ለማለት ነው። የነቃሁ የበቃሁና የመጠቅሁ ነኝና “የእኔን መንገድ ካልተቀበላችሁ” ለማለት ሳይሆን እንዲያውም በተፃራሪው ያለኝ ዕውቀትና ልምድ በሳይንስና ቴክኖሎጂው መስክ ነውና የፖለቲካ ሳይንቲስት፤ የሥነ-አዕምሮ ጠቢብ ወይም የፍልስፍና አዋቂ አለመሆኔ በግምት ተይዞልኝ፤ እንደማንኛውም አገሩንና ወገኑን እንደሚወድ ዜጋ በጉዳዩ ያገባኛልና ባለኝ አቅም የድርሻዬን ላበረክት ለማለት ነው።

 

የምፅፈው ባለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት በፀረ-ወያኔው ንቅናቄ ካዳበርኩት ልምድ ላይ በመመርኮዝ ነው። በዚህ ልምዴም ከተቃራኒው ወገን የኣሰራርና የኣላማ ጉድለትን አያለሁ። በዚያ ላይ ደግሞ ዴሞክራሲና ፍትህ የሰፈነባት አገርን በመመስረት ራዕይ ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች – ሕፃናትና አረጋውያንን ጨምሮ – ከፍተኛ የሆነ መስዋዕት እየከፈሉ ነውና ስለታዘብኳቸው ጉድለቶች መናገር አለብኝ – እየተከፈለ ያለው መስዋዕትም መና ሆኖ እንዳይቀር መናገር አለብኝ!  በተጨማሪም ይህ ለዘመናት በተቃዋሚነት ሥነልቦና ብቻ የተተበተበ የሚመስለው ትግላችን ተቀይሮ ውጤት-ተኮር በሆነ ሥነልቦና ተተክቶ ይጓዝ ዘንድ ለማሳሰብም መፃፍ አለብኝ።

 

እንደገና መስቀለኛ መንገድ ላይ ደርሰናል

መቼም ቢሆን የኋሊት ማሳያ መስተዋትን ብቻ ተጠቅሞ መንዳት ከግጭት ላይ ማድረሱ አይቀሬ ነገር ነው ይባላል። ያ እንዳይሆን ሹፌሩ በሁሉም የማሽከርከር ወቅት ቀልቡን ሁሉ አሰባስቦ የሚጓዝበትን መንገድ ብቻ ሳይሆን አካባቢውን በሰፊ ዕይታና ቅኝት ውስጥ አስገብቶ  ወጣ ገባውንና ጠመዝማዛውን ሁሉ እያማተረ ሲያሽከረክር ነው የወደ መድረሻው ጉዞ ቀና የሚሆነው። ማንኛውም እይታና ራዕይ ምን ያህል የተወሳሰበ እንኳ ቢሆን – “ግብ” ብለን የተቀበልናቸው እምነቶቻችን ላይ ያደርሰን ዘንድ በጥንቃቄ የተሰላ ውጤት-ተኮር ተግባር ማካሄድን ይጠይቃል።

 

የወያኔን አገዛዝ ስቃወም ይኸው ሃያ ዓመታት ሆነኝ።  የምወዳትን ሀገሬን ኢትዮጵያን ከለቀቅሁበት ጊዜ ጀምሮ የምወደውን አፈሯን ተመልሼ ሳልረግጥ አብዛኛውን የጉልምስና ሕይወት ያሳለፍኩት አውስትራሊያ ውስጥ ነው። በዚህም ምክንያት እንደ ቅንጅትና ህብረት ያሉ ፖለቲካዊ ቅርርቦችን ሳስተውልና ስከታተል  ቆይቻለሁ። የትብብር ምሥረታዎቹም ሆነ የፍርሻዎቹ አካል የነበርኩበት ጊዜ ግን አልነበረም። ዛሬም የወያኔን በጭቆናና በአፈና ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ሽረው ዴሞክራሲና ፍትህ የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ እየታገሉ ያሉ ፖለቲካዊና ማኅበረሰባዊ/ሲቪክ ስብስቦች አባል በመሆን የበኩሌን ላበረክት የንቅናቄው አካል ነኝ።

 

በወቅቱ ባለው አለመርካት ጥሩ ነው፤ በዚያም ምክንያት መብከንከን ካለ ደግሞ የተሻለ፤

ብሎም አለመረጋጋት ከተከሰተ ደስ የሚል፤ ከዚያ ሃሳቦች ይመንጩ፤ ከባድ ሃሳቦችከባድ ሥራዎችም ይፍለቁ፤

በዚህ ሁሉ ውስጥ ራሱን አሳንሶ የሚመለከት ራሱን ከፍ ያድርግ ሒዉበርት ሐምፍሬ

 

ሕዝባችን በጨካኝ ዘረኛ አገዛዝ ሥር ከወደቀ ሩብ ምዕተ አመት ተገባደደ። ለማምጣት ያለምነውን ስኬት ሲታይ ግን የዛሬ ሃያ ዓመት ከነበርንበት ምንም ያህል ፈቀቅ እንኳ አላልንም። ለመሆኑ ግባችን (ያጭሩ ሆነ የረጅሙ) ያልነው ላይ የነጠረ ዕይታ አለን?  ግባችን ብለን ወደአቀድናቸው ዐቢይ ጉዳዮች ሊያድርሱን በሚችሉ ተከታታይ ራዕዮቻችን፤ ልንከውን በምንፈልጋቸው ተግባሮችና ልናበረክት በምንችላቸው ድርሻዎች ላይ የጠራ ግንዛቤ አለን? በነዚህ ከልባችንና ከአዕምሮአችን መንጭተው  ከወያኔ በኋላ የምንመኛትን ኢትዮጵያ ዕውን ለማድረግ መከናወን ስላለባቸው ጉዳዮች የዳበረ ግልፅነት አለን? ራዕዮቻችንን የምናስተነትነው ፍፁም በሆነ ግልፅነት ላይ ተመስርተን ነው? ያንንስ ራዕይ በጸና ዕምነት ላይ አስደግፈን እናጸናዋለን? እያደረግን ያለው ሁሉ በጠንካራ የተልዕኮና የስኬታማነት መንፈስ ላይ በፅኑ የተመሰረተ ነው? እነኝህ ሁሉ በጭንቅላቴ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄወች ናቸው።

 

ዛሬም ገና በተቃውሞው ምዕራፍ ውስጥ ነው ያለነው። ታዲያ ያለማቋረጥ እያዥጎደጎደን ያለነው መፈክርና እያከናወንን ያለው ከባድ ሥራ ሁሉ ህዝባችንን ወደተስፋይቱ ምድር ወደነፃነት እኩልነትና ፍትህ ሊያደርስ የሚያስችለውን ግልፅነትንና ጥራትን የተጎናፀፈ ነው? ከወያኔ ወዲያ ለምንፈጥራት ኢትዮጵያ ያሉን ራዕዮች ለመሆኑ ምንድን ናቸው? አልፈው አልፈው ብልጭ ድርግም ከሚሉ ቀውጢ ጊዜ ከሚወልዳቸውና በጥቂት ድርጅቶች መሃል ከመነጩ በትብብር የመስራትና የመግባባት መግለጫዎች ባሻገር እስካሁንም የጠራ የጉዞአችን አመላካች ካርታ ያለን አይደለንም።  ይህ አጭር ፅሁፍ በርከት ያሉ ጥያቄዎችን በማንሣት ራዕያችን፣ እሴቶቻችንና ተግባራችን  ምን ምን መሆን አለባቸው ከሚሉ ነጥቦች ላይ በመንተራስ አማራጭ ምላሾችን ለማበርከት ይሞክራል። ኣቢይ ኣላማው ግን የወደፊቷ ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ዜጎች ሁሉ ያሉብንን ድርጅታዊና ግለሰባዊ ድክመቶች አንጥሮ ለማሳየትና እንድንወያይበት ለማበረታታት፤ እንዲሁም ሕብረተሰባችን ተሳስሮ የኖረበትን ማሕበረሰባዊ ድርና ማግ በማይሽር ሁኔታ ለመበጣጠስ ከዲያብሎስ ጋር እንኳን ሊዶልት የማይመለስን ወያኔን እኩይ ኣላማ ለማክሸፈና፤ ኣዲሲቷን ኢትዮጵያን ለመገንባት የተጠየቀውን መስዋዕትነት ሁሉ ያለስስት ከፍሎ ሊያስወግድ የተዘጋጀ በሃገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ኗሪ ኢተዮጵያዊ ትግል የራዕይ፣ የዕሴትና የተግባር ጉድለቶች ያለምንም ፍርሃትና በግልጽነት መጠቆም ኣለባቸው ከሚል ዕምነት የመነጨ ነው።

 

ራዕይ በረጅሙ ታይቶ ታልሞና ታቅዶ ስኬታማ ለሆነ የረጅም ጊዜ ለውጥ የተቀረፀ የተልዕኮ መርሐግብር ስልትና ግብን ስሜት በሚያቃጥል ጽኑዕ ኣላማ ወዳድነት ያካተተ ነው። በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ የፖለቲካና ማህበረሰባዊ/ሲቪክ ድርጅት ወይም ስብስብ ነን የሚሉ በሙሉ ወያኔ የሚባል የጋራ ጠላት እንዳላቸው ከመግለፅ በተጨማሪ ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ የሆነ ሥርዓትን መፍጠርንና መገንባትን የሚያስችል የሚል አንድ ወጥ የግብይት ቋንቋ አላቸው ለማለት እቸገራለሁ። ከላይ ከላይ ሲታይ ሁሉም መልካም ይመስላል እንጅ። ሁሉም ዲሞክራሲ ኣስተዳደርን ይፈልጋል። ዕኩልነትና ፍትህንም እንደዚሁ። ታዲያ በዚህ ራዕይ ዙሪያ በጋራ መሰለፍ እንዴት ኣልቻልንም? የፊደል ጋጋታ ድርጅት ስሞቻችንን ከማብዛት ይልቅ።

 

ፍትሓዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትም በህግ የበላይነት ላይ የተመሰረተና ሁሉንም ዜጋ ነፃና እኩል በሆነ መንገድ የሚያስተናግድና ለፀረ-ወያኔው ትግል የጋራ መግባቢያ ቢሆንም በራሱ ብሔራዊ/ሀገራዊ ራዕይ ሊሆንም፣ ሊያሳይም አልቻለም። ምክንያቱም ይህ ዓይነቱ ራዕይ ገና የጉዳይ ባለቤት ነንና ያገባናል በሚሉት ፖለቲካዊና ማህበረሰባዊ ድርጅቶች ገና አልተቀረፀምና ነው።  ይህ ደግሞ ገና ተገንጥለው የራሳቸው ሥርዓተ-መንግሥት የመፍጠር ምኞታቸው ያልሰከነውን እንኳን ግምት ውስጥ ሳናስገባ የፀረ-ወያኔው ትግል አካል ነን ከሚሉትና በውጭ አገራት እየተደረጉ ካሉ የኦሮሞ የዑጋዴን የሲዳማ ወዘተ ማህበረሰብ አባላት በየጊዜው በሚያደርጓቸው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ የሚንፀባረቅ ሀቅ ነው። የባንዴራ ትርጉም መጥፋቱ፤ ህጋዊ እውቅና የሌለውና ያገባኛል የሚል ሁሉ ያልተወያየበት፣ ውሳኔም ያልተደረሰበት ኣዕምሯዊ ሃገር ስም ወዘተ ……የመሳሰሉት ራዕየ ቢስነትን ወይም ብዥታን የሚያሳዩ ክስተቶች በሰፊው ሰፍነዋል።

 

ችግራችን የወያኔ መወገድ ብቻ አይደለም። የወያኔን ኣምባ ገነናዊ ስርዓት ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ገጽ መክሰምና መጥፋትማ ልክ የፀሐይን ከበስተምሥራቅ የመውጣቷን ያህል (ያ ደግሞ በቅርቡ እንደሚሆን ተስፋዬ ነው!) እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል።  ራዕያችን፣ እሴቶቻችንና ተግባራችን ግን ከወያኔ ባሻገርና ወዲያውኑ የምንፈጥራትን ሀገር – “ኢትዮጵያችንን” –  በግልፅ ተንትኖ ማስቀመጥ መቻል አለበት።

 

እያንዳንዳችን ምንም የፖለቲካ ኣመለካከቶቻችን ተጻራሪ ቢሆኑ እንኳን እነዚያኑ እምነቶች በግልፅና በመልክ መልኩ አስቀምጠንና ከወዲሁ አርቀን ማቅረብ መቻል አለብን። የፖለቲካ ኣመለካከቶቻችን ድርጅታዊ ፍላጎቶቻችንና ኣላማወቻችንን በተደበቀ ካዝና ውስጥ ታሽገው ለአባላት ብቻ እየተመጠኑ የሚገለፁና ከህዝብ ዕይታ ተሰውረው በሚስጥር የሚያዙ መሆን የለባቸውም። ግልፅነትና ቅንነት ብቻ ነው መንገዳችን አባጣ ጎባጣ እንዳይሆን የሚያደርገው። ስለሆነም “ለመሆኑ ዕምነቶቻችን ምን ምን ናቸው?” የሚለው ጥያቄ መነሳት ያለበት ነው። ለምሳሌ ያህል – ኣለም ኣቀፍ ዳር ድንበሯ የታወቀ፣ የታፈረና የተከበረ፤ ሁሉም ዜጋ የታወቀ ክልሏን እያንዳንዷን ካሬ ሴንቲ ሜትር በደሙ ጠብታ ሊከላከል ቁርጠኛ የሚሆንላትን ኢትዮጵያ መፍጠር እንችላለን? ወይንስ የግልም ሆነ የጋራ የረዥም ጊዜ ትግላችን ወራሪው ጣሊያን ያለመውንና ኣገር ኣጥፊው ወያኔ የተገበረውን   የዘር ማንዘሬ አፅመ-ርስት የሚለውን የክልል ፍልስፍና ለማስረገጥ ብቻ ነው?

 

የመንግሥት ግንዛቤያችንስ ምንድነው? አሀዳዊ የተማከለ መንግሥት? ወይስ ፌደራላዊ? አሀዳዊና የተማከለ ማለት ሥልጣኑን አማክሎ የያዘው ኅይል ለየክፍለ ሀገራቱ ተሿሚዎቹ በሚያወጣቸው ህጎችና በሚደነግጋቸው አዋጆች እየቆነጠረ ውስን ሥልጣን የሚቸርበት የሥነ-መንግሥት ዓይነት ነው። በንጉሳዊውና በደርግ ዘመን የነበሩት አስራ አራት ክ/ሀገራት የእንደራሴ ሥልጣን ሹም ሽር የአሀዳዊና የተማከለ መንግሥት ምሳሌ ነው። ሌላም ምሳሌ ካስፈለገ የታላቋ ብሪታኒያ የተባበሩ መንግስት United Kingdom ሥርዓተ መንግስትና ሥልጣንን በፈለገው መጠን ቀነጣጥቦ የሚቸራቸው ሰሜን አየርላንድ፤ ስኮትላንድና ዌልስ ተጠቃሽ ናቸው።

 

በአንፃሩ ደግሞ ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያውያን ፖለቲካ ኣቀንቃኞች በግርድፍ የሚገለጸው ፊዴራላዊ መንግሥት እንኳን ተግባራዊ በሆነባቸው እንደ ጀርመን፣ ቤልጂየም፣ ካናዳ፣ ኣውስትራሊያ ወዘተ ባሉ በቅልቅል ባህል፣ ፍልስፍናና ፖለቲካ በተመሰረቱ ሃገራት ምን ያህል ችግር ፈጣሪ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። እኛስ በእያንዳንዱ ክ/ሀገር እኩል ሥልጣን ያለበት ፌዴራሊያዊ የመንግሥት ሥርዓት (Symmetric Federal System) ነው የምንሻው? ወይንስ በሥልጣን ክፍፍሉ ጊዜ አንዳንድ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለባቸው (የህዝብ ብዛት፤ የተፈጥሮ ሀብት ክምችት፤ ምርታማነት ሌላም ሌላም) ጉዳዮች ግምት ውስጥ አስገብቶ ሥልጣንን እንደየአበርክቶው የሚያደላድል (Asymmetric Federal System) ፌዴራሊዝምን?

 

ሁለተኛው ጠቃሚ መነጋገሪያችን መሆን ያለበት ዕሴቶቻችን (የምናምናቸውና የምንታመንባቸው የህይወት መመሪያወቻችን)  (Values) ጉዳይ ነው።  እነዚህ ዕምነቶች የምንከተለውን የተግባር ክንዋኔና (Action) ውጤት ማስተንተኛ መሳሪያና የዕምነቶቻችን ዝንባሌዎቻችንና ባህሪዮቻችን ቅኝት ማስተካከያም ናቸው። ዕምነት የሞራል (ቅንነት፤ መከባበር፤ ፍትሃዊነት ወዘተ) የፍልስፍና ግንዛቤ (ኃይማኖት፤ ርዕዮተዓለም፤ ፖለቲካ) እንዲሁም ማህበረሰባዊ (የጋራ ብሩህ ተስፋ፤ የጋራ ዕድገት ምኞት፤ አብሮና ተባብሮ መኖር፤ የጋራ ክብርና ሞገስ፤ ከራስ-በላይ-ንፋስ-አለማለትን ወዘተ) የሚያካትት ሲሆን ቅዱስ ነው። “ነፃና ፍትሃዊ የሆነና ግልፅ ምርጫ፤ ኢትዮጵያዊነት፤ የዜጎች እኩልነት ወዘተ” የመሳሰሉት ዕሴቶች የጋራና የተቃውሞ ቋንቋችን ከሆኑ ውለው አድረዋል። ተግባራችንስ በነዚህ ቅዱስ ዕሴቶች የተደገፈ ነው ወይ?

 

ተስፋ ያለው ወገን ሕልሙ ዕውን ይሆንለት ዘንድ ይመኛል፤

                 ተስፋ ያጣው ግን ቅዠቱ ዕውን እንዲሆን ይጠብቃል…. ምንጩ ያልታወቀ

 

ፈታኝ በሆነ ወቅት የምንሰራው አምነንና የኛ ብለን አንግበን ያቆየናቸው ዕምነቶች ነፀብራቅ ነው።  ስለሆነም ለወደቁ ጀግኖቻችን እናነባለን። አንዳርጋቸውን፤ እስክንድርን፤ አንዱዓለምን ስናስብ እናለቅሳለን። በኃዘን የተጎሳቀለች እናትን ስንመለከት ልባችን ይደማል። እምቢ ባይ አትሌት በዓለም ፊት የሕዝብን የተቃውሞ ምልክት ሲያሳይ “እሰይ! እንኳን የኛ ሆነ” ብለን ኩራት ይሰማናል። በኣንጻሩ ደግሞ በመሃላችን የቅቤ-ገበያ-ውሎ ዓይነት ቋንቋን ተጠቅመን ክቡሩን የሰው ልጅ ለማዋረድ፤ ዝቅ አድርገን ለመመልከትና (በነጠላም ሆነ በቡድን) ለማቅለል የምንሞክር ሞልተናል። ዮዲት ወ/ሩፋኤል የተባለችና የአሪዞና ነዋሪ የሆነች ሴት በፌስ ቡክ ላንጎደጎደችው ስድብ የሰተጣት ምላሽ በትግሬና አማራ/ኦሮሞ ዜጎቻችን መሀከል የዘር ፍጅት ጦርነትን ሊጭር የተቃረበ ይመስል ነበር። በርግጥ የዮዲት አባባል የትግራይን ህዝብ ሊወክል ይቅርና እዚህ ግባ የሚባል ግምት ሊሰጠው ባልተገባ ነበር። ለኦሮሞና ለኣማራ ጥብቅና የቆሙትም ከትግሬ የተለየ ብልሃት ወይም ጀግንነት፣ ድድብና ወይም ዕውቀት እንደሌላቸው ማወቅ የተሳናቼው መስሎ ነበር።  በእንዲህ ያለው ፈታኝ ወቅት በግለሰብ ድርጊት ወይም ርምጃ ተጎትተን ከወደቅንና በሁሉም ማህበራዊና ባህላዊ መስክ መከባበራችን በአንዴ ጥሎን ከነጎደ ታዲያ የቱ ጋ ነው ፍትህ እኩልነትና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያን የመፈለግ አመክንዮአችን?

 

ኣስተሳሰባችን ሁሉንም ፖለቲካዊና ማህበረሰባዊ ስብስቦችን አካታችና ቀና ኣመለካክትና ፉክክርን healthy competition የሚያበረታታ መሆን አለብን።  ኢትዮጵያችን የበርካታዎች እናት፤ የብዙ ብሔር/ብሔረሰቦች አገር፤ የተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከቶች ክምችት ናትና ምንም ወይም ማንም ህብረ ብሄራዊም ሆነ ብሔር/ብሔረሰባዊ ድርጅት በኃይል ሊገዛት የሚገባት አይደለችም – በፍፁም! ሌላው መረዳት ያለብን የማንም ብሔር/ብሔረሰብ ከፖለቲካው ምህዳር መገለል ሰላምንና መረጋጋትን ሳይሆን ቅሬታንና መተረማመስን የሚያስከትል መሆኑን ነው።

 

ስለዚህም ነው ሁሉም የፈረስ-ግብይት በግልፅና ባልተሸፋፈነ መንገድ ተካሂዶ የነገይቱ ኢትዮጵያ የምትገነባበት የመሰረት-ድንጋይ የሚተከልበት ሰነድ በሌጣ ወረቀት ላይ ሁሉም ያገባናል የሚል ወገን በተገኘበት መቀረፅ አለበት የምለው። ይህን ስል የቀደመ ማህበራዊና ባህላዊ የፖለቲካ ታሪካችን በፍፁም መረሳት የለበትም ማለቴ አይደላም። ያንን አለመርሳታችን ነው እንዲያውም የግድ በአስቸኳይ ማደራጀት የሚያስፈገልንን የሐቅና ዕርቅ ሒደት ሥራችን የሚያቀልልን እላለሁ።

 

ያ ኢትዮጵያና ህዝቧን ለመግዛት ተብሎ በወያኔ የተቀረፀና የተደነገገ ሕገመንግሥት ዕርባና ቢስና መና ነውና ወዳቂ ነው። ስለሆነም የነገዋን ኢትዮጵያ የምንገነባበትን፤ ፖለቲካዊና ማህበራዊ/ሲቪክ አደረጃጀትን የምንከባከብበትን፤ ግለሰባዊ ነፃነትን የማይገስሰውን፤ የሕግ የበላይነትን የሚያረጋገጠውን የመሰረት ሰነድ ለመቅረፅ የመንቀሳቀሻ ጊዜው አሁን መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ አለብን።  ያን ስናደርግ ነው ያለፈውን ምዕተ ዓመት በሙሉ ስንመለከት ከነበርነው የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ታሪክ ቅርቃር ልንወጣ የምንችለው።

 

ይህ የመሰረት ሰነድ የእያንዳንዱን ዜጋ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተሳትፎ ያለምንም ገደብ፤ አድልዎ፤ ማግለል፤ ወይም ማስፈራራት ማስገደድና ማጉላላት ማስከበር መቻል አለበት።  ሁላችንም የሕይወትን ክብርነት መቀበልና በማንም ላይ ቢሆን የሚደርስን የአካልና የአዕምሮ ሥቃይን ማስቀረት እንዲሁም በጎሣ፤ በኃይማኖት፤ በፆታም ሆነ በዕድሜ ማግለልን ማስወገድ  ዕምነታችን ሊሆን ይገባል። የምንፅፈውም ሰነዳችን ይህን ሁሉ በማያሻማ ቋንቋ መመዝገብ አለበት።  ከሁሉም በላይ የሰዎችን የመንቀሳቀስና  የመደራጀት መብትን፤ በንግግር፣ በፅሑፍና ኪነጥበብ በነፃነት መብት መግለጽ መቻልንና የነፃ አስተሳሰብ መጎልበትንና  የእምነት ነፃነትን ማክበር አለብን። ፖለቲካዊ ነፃነት፤ በሕግ ፊት በእኩልነት መታየት፤ የተከሳሽን የመከራከር መብትና ማንም ተከሳሽ በሕግ ፊት በማስረጃ እስኪረጋገጠበት ድረስ ጥፋተኛ ተደርጎ ያለመወስድ መብቱና ጥፋተኛ ሆኖ ካለተገኘም ካሣ የመጠየቅና የማግኘት መብት፤ የዜጎች ኑዛዜ  የማድረግ መብት፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፊርማ የማሰባሰብ መብት ወዘተ፤ በአጠቃላይ በዓለም ዐቀፉ ህብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነትን አግኝተው የተደነገጉ መብቶች ሁሉ የሚከበሩበት እንዲሆን መትጋት አለብን።

 

በተጨማሪም ራዕዬና ግቤ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባትና ማዳበር ነው ያለ ድርጅት ሁሉ ያንኑ ራዕይና ግብ ከአሁኑ በውስጠ-ድርጅት አሰራሩና አካሄዱ ሁሉ ሳይቀር መተግበር አለበት። በድርጅት ውስጥ የአመራር ክፍተት ሲፈጠር ዴሞክራሲያዊ ከሆነ ሁኔታ ውጭ የኣመራር ለውጥ የሚደረግ ከሆነ ይህን መሰል ድርጅት በምንም ዓይነት ሁኔታ ለማንም አድማጭ ስለዴሞክራሲ መስበክ የለበትም። የምንለውና የምንፈልገው ይሳካልን ዘንድ የምንሰብከውን መተግበር የግድ ይለናል።  ፍትህን የምንሻ ሁሉ ፍትሓዊ መሆን ይኖርብናል። እኩልነትን የሚያነበንብ ሁሉ ሰብዓዊነታችን ብቻ ዕኩል እንደሚያደርገን  መሆኑን መቀበልና ለዚያም መቆምና መሟገት አለበት።  እኛ መሆን የምንፈልገውን ለመሆን መብት የምንጠይቅ ከሆነ የሌሎችንም ለመሆን የሚወዱትን የመሆን ነፃነት ማክበር ይጠበቅብናል።

 

ተግባራችን ዕምነታችንና ራዕያችን ያንጸባርቃል?

እኔ ማንም በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለና ለነፃነት ተፋላሚ የሆነ ሁሉ የተሳተፈበት ድርጅት ግልፅና ተጠያቂ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲኖርበትና እንዲሰማው እንዲሁም የድርጅቱ ባለቤት አመራር ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ አባል መሆኑን አበክሮ እንዲገነዘብ ብሎም የጎለበተ የድርጅት ውስጥ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፤ ግልፅ የሆነ ህግና ደንብ የተነደፈበትና በተለይም አመራር የተደነገጉ ህጎችን ቀስ በቀስ ሲሽር በተገኘበት ተጠያቂ የመሆን ፖለቲካዊ ባህል እንዲሰፍን ማንሳትና ማሳሰብ እወዳለሁ።  መሪወቻችን ወንበር ላይ የሚኮፈሱ ሳይሆን ከአባላት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት proactive relationship ያላቸው፤ ኣባላትን  እንደ ሃሳብ ማፍለቂያ think tank የሚጠቀሙ፤ የብዙሃን ኣባላትን ሃሳብና ውሳኔ የሚያከብሩና የሚያስተገብሩ መሆን ኣለባቸው። ጤናማ ኣዕምሮና ሰውነት ሊኖራቸውም ግድ ነው። ካልሆነ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር፣ ብሩህ ሃሳብ የማፍለቅ፣ ረዥም ሰዓት የመስራት ችሎታቸው ውስን ይሆናል። የጤና ችግር ካለባቸው ልምድና ዕውቀታቸውን በማካፈል እንደኣቅማቸው ድርጅታቸውን መርዳት ይችላሉ። እስከ ዕለተሞት ስልጣን የሚባል ባህል ግን ማስቀረት መቻል ኣለብን።

 

አባላት የድርጅታቸው የተልዕኮ ምሕንድስና ላይ መሳተፍ፤ ራዕያቸው ጥሩ ድምዳሜ ላይ ይደርስ ዘንድ መትጋት፤ አስተዳደራዊ ብቃቱን ማዘመንና ለመጪው ጊዜ ፈተና ማብቃት ይጠበቅባቸዋል። በድርጅት ውስጥ ግማሽ ሰው-ግማሽ አምላክ (ትናንሽ ታቦቶችን) መቅረፅን ማቆም አለብን።  ተገቢውን መከባበር ሳይለየን ታማኝነታችን ለራዕዮቻችንና ለአመንባቸው አቋሞች መሆን ነው ያለበት። ይህ ፅሁፍ በሁሉም የትግሉ ተሳታፊዎች (መቼም አንዱ ያለ ሌላው አይኖሩምና በአመራር ደረጃ ባሉትም ሆነ የታች አባላት) ዘንድ ውይይት ያስነሳል የሚል ተስፋና እምነት አለኝ። ይህንንም ስል በየድርጅቱ ውስጥ ያሉ የአመራር አባላትና ሊተኳቸው በሚመኙ አባላት ራዕይና አቋም ላይና የመመሪያ ሰነዶቻቸው ላይ በቂ ዕውቀት ይኖረን ዘንድ እወዳለሁ።

 

ዜጎችም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲወች የሚያቀርቡልንን የድጋፍ ጥያቄም ብዙ ጥያቄወችን መጠየቅ ኣለባቸው። ለመሆኑ  ፖለቲካዊና ማህበረሰባዊ ድርጅትና ስብስቦች ስንት አባላት አሏቸው? ካሏቸውስ ምን ያህል? ለመሆኑ ፅ/ቤቶቻቸው የት ነው የሚገኙት? ስላላቸው ካፒታልና ስለምንጩም መጠየቅ መቻል አለብን።  እያንዳንዱ ድርጅት የቆመለትን ዓላማ የጉዞ ስትራቴጂውን፤ ድህረ-ወያኔ ኣዲሲቷ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ያለውን ፖሊሲና ነገ ማንነቱን የምንሰፍርበትን የድርጊት መመሪያ መግለጫውን ማየትና ማወቅ አለብን። የመመሪያው፤ የዕምነት፤ የራዕዩና ንድፈ ሃሣባዊ መሰረትና ምንጭ ከየት እንደሆነ ማወቅ አለብን።

 

ራዕያችን ዕሴቶቻችንና ተግባራችን ይገጣጠሙ። ቆም ዕያልን ያሳለፍነውን ጊዜ እንፈትሽ። ውጤት ያላመጣልንን ስልት ችክ ብለን ኣንያዘው። ለመለወጥም ኣንፍራ። ኣስተሳሰባችን ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር እንዲጓዝ እናድርግ። በዚህ መንገድ በጊዜ የቤት ሥራችንን በአግባቡ ሳንሰራ ቀርተን ዘለዓለም ተቃዋሚዎች ሆነን እንዳንቀር። ንጉሳዊ ስርዓቱን የተቃወሙት ራዕያቸው ስኬታማ ኣልሆነም። ደርግንም የተቃወሙት እንደዚያው። ኣሁን ያለን “ዕኩልነትና ፍትህ የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ” ራዕያችንስ ተሳክቶ እናየው ይሆን?

 

የዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሕልማችን ይጠንክር!

ነፃነት እኩልነትና ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

 

ጥቅምት ፪፭ ቀን ፪፻፱ / 4 November 2016

mareshetmeshesha@gmail.com

የአዛውንቶቹ እጅ በኢህአዴግ ውስጥ –መሃዲ ሀርፓስ

$
0
0

TPLFበኢህአዴግ ስም በዋናነት በአራት የብሄር ድርጅቶች ስም የተዋቀረው ገዢውና ጠቅላዩ ፓርቲ፣ ከሚታየው ይልቅ የማይታየው እጅ፣ ከተመደበው ሰው ይልቅ የተደበቀው፣ ከሚሰራው ይልቅ የሚዶልተው፣ከወጣቱ ይልቅ ሽማግሌው፣…  እንደሚዘውረው የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰነበተ፡፡   ቀጥቅጦ የሚገዛን ገዢው ስርዓት ትንሽ ወለም ባለው፣ ወይም ወለም ያለው በመሰለ ቁጥር ቀድሞ በማነከስ የሚታወቁት አዛውንቶቹ ናቸው፡፡ ከአዛውንቶቹም ሶስቱን በጭራሽ የሚቀድማቸው ያለ አይመስልም፡፡ ወዲ ጸሀዬ (አባይ ፀሀዬ)፣ በረከት ሰምኦን እና አዲሱ ለገሰ ከስርዓቱ ጋር ያላቸው ጋብቻ አንድም ሶስትም ነው፡፡

ዘወትር በሰመመን ውስጥ ያለው ኢህአዴግ፣ ብንን ብሎ በበረገገ ቁጥር ሶስቱም አዛውንቶች ከኛ ውጪ ይህንን ስርዓት የሚታደገው የለም በሚል፣ ከፊትለፊት በመሰለፍ ከፖለቲካው የሚገኘውን ትርፍ ለመጋራት በሚያደርጉት ጥረት አንድ ናቸው፡፡ በማነኛውም ጊዜ ፖለቲካዊ ዱለታ ካለም እኚህ በምንም የማይገጥሙ ሰዎች አንድ ናቸው፡፡ ጠላትን ለማሸነፍ ብቻ በሚል በሚፈጥሩት ግንባርም አንድ ናቸው፡፡ በተቀናቃኞቻቸው ላይ የበላይነትን ለመውሰድና አልንበረከክ ያለውን ለማንበርከክ በሚፈልጉበት ጊዜ አንድ መስሎ ለመታየት መሞከራቸውም ሌላው አንድ የሚያደርጋቸው ነጥብ ነው፡፡

በተግባር መሬት ላይ ያለውን እውነታ ወርደን ለመፈተሸ ብንሞክር ግን፣ ሶስቱም ከሶስት የተለያየ ዓለም የመጡ ግራዎች ናቸው፡፡ ምናልባት ብናበላልጣቸው የተሻለ አዛውንትና የበለጠ ሎሌ፣ ተገዳዳሪ አሽከር እና አሽከር ቀጣሪ በሚል ልንመድባቸው እንችላለን፡፡ እነኚህ ሶስት ሰዎች በደህናው ጊዜ በየራሳቸው የሀሜት ጥጋጥግ ውስጥ ተወትፈው በመዶለታቸውም ሶስት የተለያዩና የማይተማመኑ አውሬዎች ናቸው፡፡

በረከትና አባይ የምናምንና ምን ምርምር ማዕከል በሚል በሰየሙት የመዶለቻ ጠጅ ቤታቸው አማካኝነት መጠነኛ መፍጨርጨር እያደረጉ የህወሀትን የበላይነት ለማስጠበቅ ሲጥሩ፣ የ67 ዓመቱ አዛውንት አቶ አዲሱ ግን ምንም ጠብ በሚል ስራ ውስጥ ተሳትፎ የሌላቸውና እራሳቸውን ለተሻለ ሎሌነት አቀባብለው ያስቀመጡ ተራ ሰው ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ አንድን ተራ የብአዴን አባል ብቻ መጠየቅ በቂ ነው፡፡ የአቶ አዲሱ ዋነኛ የጸቡና የወቀሳው መነሻም እጅ አትነሱኝም፣ አትጠይቁኝም፣ አትደውሉልኝም፣ አታከብሩኝም፣ ዉለታዬን አትቆጥሩም፣ ወዘተ ከሚል ከፍ አይልም፡፡

እነዚህ አዛውንቶች በኢህአዴግ የመተካካት ፖሊሲ ከየድርጅታቸው ቢሰናበቱም አርፈው አልተቀመጡም፡፡ በየጊዜው በቀደመው ካባቸው እየተሸፋፈኑና እያስፈራሩ እዛም እዚም ብቅ ጥልቅ እያሉ አሉ፡፡ ያሻቸውን ባለስልጣን በግል እየጠሩና እያስጎነበሱም ፓርቲውን ወደ ሻይ ቤትነት ዝቅ አድርገውታል፡፡ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ የተለያየ ሰበብ በመደርደር መተካካቱን ሊሽሩት ሞክረዋል፡፡

ሰሞኑን ኢህአዴግ ከምንጊዜውም በላይ ጭንቅ ጥብብ ባላት ጊዜ እንኳን ተሀድሶ በሚል ሰበብ ከፊት ፈጥኖ ለመሰለፍ የሞከሩት እኚሁ ትንፋሽ አልባ አዛውንቶች ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ይዘውት የመጡት ትንፋሽ ግን አይደለም ከመረረው ህዝብ ጋር፣ ካማረሩት ካድሬ ጋር   አንኳን ተሰልፈው ለማሸነፍ የሚያስችላቸው አልነበረም፡፡

ተሀድሶ በሚል ጨርቅ ተጀቡና ብቅ ያለችው የአዛውንቶቹ ጉዞ የተጀመረው እንደለመዱት የፌዴራል መንግስቱን ቱባ ባለስልጣናት በተናጠል በመጥራት ለማስጎንበስ በመሞከርና ቀጠን ያለ ትዕዛዝ በማስተላለፍ ነበር፡፡ ይህ አካሄድ አላዋጥ ያላቸው አዛውንቶች በመጨረሻ ትንፋሻቸውን ሰብስበው ያደረጉት አንድ ነገር ነበር፡፡ ይህም ወደየክልላቸው በመሄድ መልሰው በክልል ላይ ያለውን ስልጣን በመቆጣጠር እራሳቸውን አዳኝ አድርጎ ብቅ ማለት፡፡ ይህም እንዳልተሳካ ሰሞኑን በየደረጃው ይፋ ከሆኑት የካቢኔ አወቃቀሮች በይፋ መረዳት ይቻላል፡፡

እነዚህ የሀገሪቱ ነቀርሳ የሆኑትና የመጨረሻውን ትንፋሻቸው የተጠቀሙት አዛውንቶች ከአሁን በኋላ በዛው ይቅሩ አለያም ከሞት የተረፋቸውን ትንፋሽ አሰባስበው ብቅ ይበሉ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም፣ ለጊዜው ግን የቀየሱት ሴራ በእድሚያቸው ልክ የጃጀ በመሆኑ ከመንገድ ላይ ወድቆ ቀርቷል፡፡

 

ምክረ ይገርማል (ከይገርማል)

$
0
0
comment symbol icon

comment symbol icon

አማራው በዘሩ ሲደራጅ እሳትን በእሳት ማጥፋት አይቻልም: በዘር መደራጀት በወያኔ የዘር ፖለቲካ መጠለፍ ነው: ያሉ በርካታ ሰዎች ነበሩ:: ነገር ግን እሾህን በሾህ ነው ያሉ ወጣቶች አዲስ የትግል ምእራፍ ከፍተው የትግሉን ደረጃ ከፍ ማድረጋቸው ይታወቃል::

ይሁን እንጅ ከሰሞኑ የጎጃም ማህበር: የጎንደር ማህበር ምናምን የሚባሉ ድርጅቶች ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል:: ፕሮፌሰር አለም አንተ ገብረሥላሴ የሚባሉ ሰው በአካባቢ የመደራጀትን አስፈላጊነት  ሲናገሩ ሰምቸ በጣም አዘንሁ;; ለነገሩ ገብረ: ወልደ የሚል ተቀጽላ ያለበት ስም አይመቸኝም:: ሰውየው የጎንደርን ህብረት ለመጠበቅ በሚል የአማራውን አንድነት የሚሸረሽር ስራ እየሰሩ ነው:: ወልቃይት አማራ ነው ብለው ደም የከፈሉትን የጎጃም ልጆች ደመከልብ የሚያደርግ ነው:: ቅማንትን አተርፋለሁ ብሎ የጎጃምን: የወሎንና የሸዋን አማራ የሚያርቅ ነው:: አማራው ከስህተቱ ተምሮ በአንድነት መቆም ሲጀምር እንዲህ አይነት ከፋፋይ ርምጃ መውሰዱ ከወያኔ ተግባር የሚለይ አይደለም::

የጎሣን ፖለቲካ አንደኛ ምርጫው ያደረገ አማራ የለም:: አማራው በአማራነቱ እንዲደራጅ ያስገደደው እንዲጠፋ  ስለተፈረደበት ብቻ ነው:: በዘሩ እንዲደራጅ ያስፈለገበት ምክንያት ዘር ተኮር ጥፋት እየተፈጸመበት ስለሆነ እንጅ ዘረኛ ስለሆነ አይደለም;; እንደሚታወቀው የአማራው ጠላት ብዙ ነው:: በአንድነት ካልቆመ በስተቀር ህልውናውን ማስጠበቅ ይከብዳል:: በአማራው ላይ የሚፈጸመውን መከራ በጋራ እሳቤ ማስወገድ ስላልተቻለ ነው በአማራነት መደራጀት ያስፈለገው:: የአማራው ጉዳት አማራውን ብቻ ስለጐዳ ነው::  በአንድነት ስም ብዙ ተደክሞ ስላላስሄደ ነው::

አሁን እየታየ ያለው የጎንደር ህብረት የሚለው ነገር የበለጠ ጎጅ ነው:: የወልቃይት ጉዳይ የጎንደር ችግር ነው ብሎ ሌላው አማራ ቸል እንዲል የሚያደርግ ነው:: ለመሆኑ ጎንደር በጎንደር ማህበር: ጎጃም በጎጃም ማህበር: ሸዋም ወሎም በየራሳቸው ማህበር ከተደራጁ ከአማራ ክልል ውጪ በሌሎች ክልሎች የሚኖረው አማራ እጣ ፈንታ ምንድን ነው የሚሆነው? አዲስአበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚኖሩት አማሮች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጥቃት መከላከል የሚቻለው በጎንደር: በጎጃም: በወሎና በሸዋ ማህበራት በመደራጀት ሳይሆን በአማራነት በመሰባሰብ ነው:: በጥቅሉ የማህበራቱ መመስረት እየተፋፋመ ያለውን የአማራ እንቅስቃሴ የሚያበርድ ነው::

“በጎጃም ውስጥ የሚኖረው አማራ ብቻ አይደለም:: በጎንደርም: በወሎም: በሸዋም ውስጥ የሚኖረው ሕዝብ የአማራ ሕዝብ ብቻ አይደለም” የሚሉን ምን ለማለት ነው? ማንም ቢሆን በአማራ ክልል የሚኖረው ሕዝብ አማራ ብቻ ነው ያለ የለም:: አማራ የሚለው የአንድ ሕዝብ ጥቅል መጠሪያ ብቻ ሳይሆን የክልል መጠሪያ ስም መሆኑም መዘንጋት የለበትም:: አማራ እንዲህ አደረገ ስንል እንደ ደቡብና ሌሎች ክልሎች ሁሉ የአማራው ክልልም ያደረገውን ለመግለጽ እንጅ ስለአማራው ሕዝብ ነጥሎ ለመናገር አይደለም:: ለዚያም እኮ ነው የጎጃም አማራ ትግል የጎጃም የአማራ ሕዝብ ትግል ብቻ ያልሆነው! የአዊ ዞን በአማራ ክልል የሚኖር ሕዝብ ነው:: በክልሉ በሚደረጉ እንቅስቃሴወች ሁሉ ግምባር ቀደም ተሰላፊ ሆኖ የሚደማና የሚቆስለው የክልሉ ጉዳይ የራሱም ጉዳይ ስለሆነ ነው:: የጎጃም አገው ከአማራው ተነጥሎ የሚታይ አይደለም;; የጎጃም አማራም እንዲሁ ራሱን ከአዊ ሕዝብ ነጥሎ አያይም:: ለዚያም ነው በኮሶበር: በዳንግላ: በቻግኒ ያሉ የአዊ ልጆች መሰዋእትነት የከፈሉት::

የቅማንት ሰዎችም ቢሆኑ ከአማራው የተለዩ አይደሉም:: አንዳንድ የወያኔን ተልእኮ የተሸከሙ ወይም ያልገባቸው ካልሆኑ በስተቀር ብዙሀኑ ህዝብ ራሱን ከአማራው ነጥሎ አያይም:: በማይሆን ስሌት ትልቅ ኪሳራ የሚያስከትል ስራ መስራት ተገቢ አይደለም::

በሌላ በኩል የአማራውን መደራጀት እንደስጋት የሚያዩ ግለሰቦች/ቡድኖች መኖራቸውን እየሰማን ነው:: እንደ እኔ ከሆነ ይህ ስጋት ተገቢ ያልሆነ ስጋት ነው:: አማራው እኮ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓል ተብሎ የሚወቀስ እንጅ በአፍራሽነት የሚከሰስ አይደለም:: የአማራው በአማራነቱ መደራጀት በምንም ስሌት ኢትዮጵያዊነትን የሚያደበዝዝ አይሆንም::

ነገር ግን ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንዳልሁት የኢትዮጵያ ጉዳይ የአማራው ጉዳይ ብቻ ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም:: ስለኢትዮጵያ ማሰብ ያለባቸው ሁሉም ጤነኛ ዐዕምሮ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን መሆን አለባቸው:: ኢትዮጵያ አንድ ስትሆን ነው ሁላችንም በአንድነት በሰላም መኖር የምንችለው:: መለያየት ከመጣ የእኛ ነው የምንለው ሁሉ የእኛ ላይሆን ይችላል:: ከኦሮሚያ የሚባረር ሁለት ሚሊዮን አማራ ካለ አማራው ራሱን ሲችል ክልሌ ነው ከሚለው የአማራ ክልል የሚፈናቀለውን ኦሮሞ ቁጥሩን መገመት ሊከብድ ይችላል:: ከክልላችን የምናባርረውን የእኛ አይደለም የምንለውን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ክልሎች የሚፈናቀለውን የእኛ ነው የምንለውን ሕዝብም ማሰብ ያስፈልጋል:: የመሬት ይገባኛል ጥያቄና መፈናቀሉ ሊፈጥር የሚችለው ማህበራዊ: ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካው ቀውስም ሊስተዋል ይገባል:: እንዲያው ከመሬት እየተነሱ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ግዴለሽነትን እንጅ አስተዋይነትን አያመለክትም:: የተሻለ ስርአት መስርቶ በፍቅርና በሰላም አብሮ መኖር እየተቻለ መለያየትን መምረጥ የጤና አይደለም:: መለያየት ከምንገምተው በላይ ጥፋት ይዞ ነው የሚመጣው:: የኢትዮጵያ ጉዳይ እንደኤርትራና ሌሎች ሀገሮች ቀለል ብሎ የሚታይ አይደለም:: ኤርትራ ብትገነጠል ለ60 አመታት ያህል ከኢትዮጵያ ተነጥላ ስትኖር የነበራትን ክልል ይዛ ነው:: በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የመገንጠል ጥያቄን የሚያራግቡ ቡድኖች መገንጠል የሚፈልጉት የትኛውን ታሪካዊ ድንበር መሰረት አድርገው ነው:: በኦነግና በወያኔ የተመሰረተው ክልል እንደሆነ የሌላውን ይሁንታ ያገኘ አይደለም:: ለዚያም ነው ሳንለያይ እንኳ የመሬት ይገባኛል ጥያቄወች እዚያም እዚያም ብልጭ ድርግም እያሉ ያሉት::

ስለዚህ እኛ ያልነው ካልሆነ ኢትዮጵያ ትፈራርሳለች ብሎ ዱቲ ማለት ከየዋህነት ያለፈ ጅልነት ነው:: አንዳንድ ተማሩ የሚባሉ የሚገርሙ ሰዎች ሳይቀሩ በትንሽ በትልቁ ብድግ እያሉ መለያየትን እንደማስፈራሪያ ሲጠቀሙ መስማት ተለምዷል:: ይህ ስህተት ነው:: ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን እያላችሁ አታስፈራሩን:: የኢትዮጵያ ጉዳይ ሊያሳስብ የሚገባው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ነው:: ችግሩ እንደሰደድ እሳት ሁላችንንም ሳይመርጥ የሚበላን መሆኑ ቢታወቅ የጅል ቀልድ ባልተቀለደ::

አሁን የሚያስፈልገው በየቦታው ስለመለያየት የሚሰብኩትን ሰዎች/ቡድኖች ትቶ ስለአንድነት ከሚከራከሩት ወገኖች ጋር ስትራቴጅካዊ ግንኙነት መፍጠር ብቻ ነው:: የተሻለ አማራጭ ነው ብለን የምናምነው ልጇን ገድለው በልጇ ሬሳ ላይ እንድትቀመጥ እየተደረገ ያለበትን የአሁኑን ግፍ ወደጐን ብለው ከ130 አመት በፊት ተፈጽሟል ለሚባለው ልብ-ወለድ ታሪክ  ከሚጮሁት ሰዎች/ቡድኖች ጋር ዝምድና ለመፍጠር ላይ ታች ከማለት ወጥተን በኢትዮጵያዊነታቸው የማይደራደሩትን ወገኖች ማስተባበርን ነው:: የወያኔ ሻእቢያ መጫወቻ አሻንጉሊቶች ሆነው ያም ያም እየተነሳ የሚነግራቸውን ታሪካዊ መሰረት የሌለው ተረት እንደ እውነት ተቀብለው: ሕዝባችን አሁን እየኖረበት ያለውን አሰቃቂ ህይወት ረስተው የዱሮ ተረት ማነብነብ የሚወዱትን ሰዎች: ክፉውን ከደጉ ያልለዩ ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት ናቸው ብሎ ንቆ መተው ነው::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ ምሥከር ሆነች

$
0
0

ከአሰፋ ምንተስኖት (ለንደን)
በስመ አብ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ፤ አሀዱ አምላክ አሜን።
ዕለቱ ጥቅምት 27 2009 ዓ/ም (06/11/2016) ዕለተ ሰንበት የመድኃኒዓለም ክብረ በዓል ነበር። በቤተ ክርስቲያን ሕዝቡ ጢም ብሎ ሞልቶ እጅግ ደማቅ የቅዳሴ አገልግሎት ከተካሄደ በኋላ ዘማርያን አውደ ምሕረቱ ላይ ወጥተው ያሰሙት የመጀመሪያው መዝሙር ስለሃገራችን ኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ ስለሚደርሰው ሰቆቃ ወደ እግዚአብሔር ተማጽኖን የሚያሰማ ነበር።Reese Adbarat
በሚዘመርበት ወቅት በስክሪን ላይ በኢትዮጵያ ሀገራችን ውስጥ ልጃቸውን፤ አባት እናታቸውን፤ ወንድም እህታቸውን እና ዘመድ ወዳጃቸው በአረመኔ ዘረኞች (ሕ.ወ.ሓ.ት.) ጥይት የተነጠቁ ሴትና ወንዶች ለቅሶና እግዞታ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል (Video clip) ይታይ ነበር። መዝሙሩ ሆነ ምስሉ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያን እያስታወሰ በሕዝቧ እየደረሰ ያለውን መከራና ሰቆቃ እያሰቡ ቁጭት ሃዘንና ትካዜ ውስጥ ገብተው በእንባ እንዲታጠቡ የሚያደርግ ነበር።

e2e518b5
በሃገራችን ኢትዮጵያ ዘረኛው የትግራይ ነጻ አውጪ (ሕ.ወ.ሓ.ት.) በሕዝባችን ላይ የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ (Genocide) በደልና ግፍ፤ ከፈጣሪ የተደበቀ አይደለምና ቸሩ መድሐኒዓለም ይህንን አይቶ ሕዝባችንን እና ሃገራችንን እንዲታደግልን ከመቸውም የበለጠ ጸሎትና ተማጽኖ የምናቀርብበት ወቅት ነው።
መገንዘብ ያለብን አቢይ ጉዳይ
በአሁኑ ወቅት የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም የቤተ ክርስቲያን አባላት ይህን በሃገራቸውና በሕዝባቸው ላይ ስለሚደርስ ሰቆቃ፤ በደል፤ ግድያና የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደ ክርስቲያንና እንደ ኢትዮጵያዊ ቁጭታቸውን ሃዘናቸውንና ተማጽኖአቸውን ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ ሆነው በመዝሙርና በፀሎት ለእግዚአብሔር በነጻነት መግለጽ የቻሉት የቤተ ክርስቲያናቸውን አስተዳደር አዲስ አበባ ከሚገኘውና በትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን (ሕ.ወ.ሓ.ት.) ከተሞላው መንበረ ፓትሪያርክ ቤተ ክህነትና ሲኖዶስ ተጽዕኖ ነጻ ማድረግ የቻሉት ወገኖች እንጂ በተጽዕኖ ሥር የሚገኙት ወገኖች ቢሆኑ ይህንን ማድረግ አይችሉም ነበር። ይህ ደግሞ በዓይን የታየና በጆሮ የተሰማ ሃቅ ነው።
ይህ ብቻም አይደለም፤ ያለፈውን የጳጉሜ ወር ወያኔ ከሚቆጣጠረው ሃገረ ስብከትና ሲኖዶስ ራሳቸውን ነጻ ያደረጉ ቤተ ክርስቲያናችንን እናድን ማሀበር አባላት በኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ ለሚገደሉት ወገኖቻቸው የሻማ ማብራትና የጸሎት ሥነስርዓት ለ5 ተከታታይ ቀን በማካሄድ ሲያስቡ ከርመዋል። በየዕለተ ሰንበቱ ደግሞ ያለማንም ተጽዕኖ ሳያቋርጡ በሃገራቸውና በሕዝባቸው ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እያስታወሱ ወደ ፈጣሪአቸው ጸሎትና ተማጽኖ እያቀረቡ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ግን በለንደን ከተማ የሚገኙት የሥላሴና የገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት በትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት (ሕ.ወ.ሓ.ት.) ተጽዕኖ ስር የሚገኙ በመሆናቸው ምክንያት ከምእመኑ መካከል ለወገኑ የሚቆረቆር ቢኖርም እንኳ ልክ ኢትዮጵያ እንደሚገኙ ሁሉ በተጽዕኖ ስር መብታቸው ተገፎ ስለሚገኙ ስለሚደርሰው ግፍ ሰቆቃና የዘር ማጥፋት መጸለይም ሆነ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ሊያደረጉ አልቻሉም።
እንደውም ከወር በፊት እዚሁ ለንደን በሚገኘው በገብርኤል ቤተ ክርስትያን አንዳንድ ካህናትና ምእመናን ከቅዳሴ በኋላ ለሚገደሉት ኢትዮጵያኖች ጸሎት ለማድረግ ሲሞክሩ በUK የሕ.ወ.ሓ.ት. ተወካይ የሆነው ቄስ ገብረ ጊዮርጊስ ድምጹ የተባለው እኔ ሞቼ ነው የምታደርጉት በማለት ሊያስቆማቸው ችሏል።
ይህ ዘረኛ የትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን (ሕ.ወ.ሓ.ት.) ተወካይ ቄስ ገብረ ጊዮርጊስ ይህን ዓይነት ነገር ሲፈጽም የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም በ1997 ዓ/ም (2005) ወያኔ ከ200 በላይ ወገኖቻችንን በጥይት ከገደለ በኋላ የለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት ለሞቱት ወገኖቻቸው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጸሎት ለማድረግ ሲዘጋጁ ጸሎት አይደረግም ብሎ የተቃወመና ጸሎቱም ሲካሄድ ቤተ ክርስቲያን ረግጦ በመውጣት ከዛ በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ሳይመለስ ሌላ ቤተ ክርስቲያን የከፈተ ነው።
አሁን ግን የዋህ ክርስቲያኖች ይህንን ሁሉ ባለማወቅና ባለማገናዘብ ወይም በስንፍና እሱ ለዘረኝነቱ ዓላማ እከፈተው ቤተ ክርስቲያን ድረስ እየሄዱ የሱን የዘረኝነት ዓላማ ሲያጠናክሩለት ቆይተው እሱ በሚያዝበት ቤተ ክርስቲያን ለወገኖቻችን ጸሎት ይደረጋል ብለው አስበው መሞከራቸው በእጅጉ የሚያስገመው የእነሱ ቂልነት ካልሆነ በስተቀር እሱ ከአቋሙና ከዓላመው የተለወጠው ነገር የለም።
በዚህ መልክ ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንም ሆነች በአጠቃላይ በውጪ ሃግራት የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች የሆን ሁሉ እስከ አሁን ያልገባን ካለን አሁን ዓይናችንን በመግለጽ የሚከተሉትን ነጥቦች በሚገባ ማጤን ይገባናል።
1ኛ፡ ኢትዮጵያ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፤ በውጪ ሃገራት የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በበላይነት የሚቆጣጠረው መንበረ ጵጵስናም ሆነ ቤተ ክህነት በሙሉ በዘረኛው የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት (ሕ.ወ.ሓ.ት.) ካድሬዎች አመራር ሥር መዋሉ ተረጋግጧል።
2ኛ፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ በኦሮሞና በአማራ ክልል የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት በሕዝብ ላይ ቀጥተኛ ጦርነት በማወጅ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አማራና ኦሮሞችን፤ እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያኖችን በጥይት እየጨፈጨፈ እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠረውን ክቡሩን የሰው ልጅ በኢትዮጵያ ውስጥ ደሙ ደመ ከልብ ሆኖ በየመንገዱና በየጢሻው እየተጣለ ከፊሉም የአውሬ እራት እየሆነ ይገኛል።
3ኛ፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፉ ሞልቶ ተርፎ እናት በአስገደጅነት እልጇ እሬሳ ላይ እንድትቀመጥ ተደርጎ የምትደበደብበት ጊዜ ሆኗል።
4ኛ፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ሕ. ወ.ሓ.ት.ን ተቃውመዋል ወይም ወደፊት ሊቃወሙ ይችላሉ የተባሉ ከ100 ሺህ የማያን ባብዛኛው የአማራና የኦሮሞ ወጣቶች ፀጉራቸው እየተላጨ እንደ ጀርመኑ ናዚ የግድያ ማጎሪያ (Concentration Comp) ውስጥ ታስረው ሥጋን በልቶ በአጥንት የሚያስቀርና ሰውነትንና አዕምሮን የሚያደክም መድሃኒት በግዴታ እየተሰጣቸው ግፍና መከራ በዝቶባቸው ተመልሰው ሰው እንዳይሆኑና ኢትዮጵያም ተተኪ ትውዷን እንድታጣ እየተደረገ ይገኛል።
ይህ ሁሉ ግፍ በደልና ሰቆቃ በሃገርና በሕዝብ ላይ በሚደርስበት ወቅት አዲስ አበባ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትሪያርኩም ሆኑ ቤተ ክህነት አረመኔውን አገዛዝና የሚደርሰውን የሰው ልጆች ጭፍጨፋና ሰቆቃ ደግፈው የሚጨፈጨፈውንና የሰቆቃ ሰለባ የሆነውን ሕዝብ መልሰው ለመገሰጽ ሞከሩ እንጂ እንደ ቤተ ክርስቲያን አባት አረመኔያዊ ተግባር በመፈጸም ላይ ስላለው አገዛዝ ያሉት አንዳችም ነገር ባለመኖሩ ቤተ ክርስቲያኗ በአጠቃላይ በዘረኛው አገዛዝ ቁጥጥር ሥር መዋሏን መቶ በመቶ የሚያረጋግጥ ሃቅ ሆኗል።
ይህ ትላንትም የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ግን ከፍቶና ከርፍቶ የወጣ ሃቅ በመሆኑ በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንም አባላትና ወዳጆች ሁሉ ሊገነዘቡት የሚገባው በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የተፈጠረው ችግር የተለያየ ሽፋን እየተሰጠው ሰዎች በሃሰት እየተወናበዱ ዘመድ ጓደኛ ትዳር ሳይቀር መፍረስ ደረጃ ላይ የተደረሰበት በአሁኑ ወቅት ለመደባበቅና ለማወናበድ በማያመች ሁኔታ ነገሮች ሁሉ ግልጽ ሆነው ቁልጭ ብለው በመታየታቸው ካሉት ሁለት አማራጮች አንዱን መርጦ መከተል ግድ ይለናል።
ይህ መጥፎና የከፋ ጊዜ እስከሚያልፍ ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 25 ዓመታት እንደነበረችው ሁሉ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ያለ ሕ.ወ.ሓ.ት. አገዛዝ ተጽዕኖ መብትን አስከብሮ ቤተ ክርስቲያንን በነፃነት መምራትና ማስተዳደር?
በሕ.ወ.ሓ.ት. አገዛዝ ከድሬዎች ተጽዕኖ ስር እንደዋሉት አብያተ ክርስቲያናት በነጻነት የማምለክንም ሆነ ቤተ ክርስቲያንን በነፃነት የማስተዳደር መብትን አሳልፎ ሰጥቶ በተገዢነት መኖር።
ሁሉም ማስታወስ ያለበት ጉዳይ ትላንት አባ ግርማም ሆኑ ቄስ አባተ፤ ቄስ ዳዊትና ተከታዮቻቸው በተራ የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ላይ የተነሳን የሃሳብ ልዩነት ሰበብ አድርገው ጳጳሳትን ከኢትዮጵያ በማስመጣት በደንቡ ላይ ለክርክር ያልቀረበውን በሃገረ ሰብከትና በሲኖዶስ ሥር መሆን አለብን በሚል ሽፋን የቤተ ክርስቲያኗና የአባላቶቿ ነፃነት ተገፎ በነፍሰ ገዳዩ የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ካድሬዎች ተጽዕኖ ስር ለማዋል ሲጥሩ ጉዳዩን በትክክል የተረዱት የቤተ ክርስቲያኑ አባላት እንቢ አሻፈረኝ ብለው ለነጻነታቸው በጥንካሬ ቆሙ፤ ዛሬም ድረስ በአቋማቸው ጸንተው በነፍሰ ገዳዮች ተጽዕኖ ስር ላለመውደቅ ትግላቸውን ቀጥለው ይገኛሉ። የሆነው ይኸው ብቻ ሲሆን ከዚህ ውጪ ይነገር የነበረው ሁሉ ግን በሃሰት ላይ የተመሠረተ ሰዎችን ከሰዎች መከፋፈያና ማታለያ ውሸት መሆኑ ይኸው አሁን ይፋ ወጥቷል።
እሺ ትላንትስ ተታለልን ተሞኘን ይባል ዛሬም ይህ ሁሉ ነገር ግልጽ ሆኖ እያለ አሁንም ድረስ የሰው መከፋፈል ጥላቻና መቃቃር እንዳይረግብ የሚደረገው፤ የሰዎችን ቅርስ ጨራሽ የሆነው የፍርድ ቤት ክርክርም እንደቀጠለ የሚገኘው አሁንም እንደ ትላንቱ እነዚህ ተረስቲ ነን ባይ ሰዎች መብትና ነጻነታችንን አዲስ አበባ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ሲኖዶስ አሳልፈን ካልሰጠን አይሆንም በማለታቸውና ቤተ ክርስቲያኗ የምትተዳደረው ሲኖዶሱ ሹሞ በሚልከው አለቃ ብቻ ነው በሚለው ግትር አቋማቸው በመጽናታቸው መሆኑን ሁሉም ወገን ሊያውቀው ይገባል።
ይህንን ቤተ ክርስቲያን ለወያኔ ካድሬዎች አሳልፎ የመስጠት ዓላማ ተፈጻሚ ለማድረግ በአሁኑ ወቅት ምን እየተደረገ ነው?
የዚህ ሁሉ ችግር ግንባር ቀደም መንስዔና ተዋናኝ የሆኑት አባ ግርማ ከበደ ወደ ኢትዮጵያ ሄደው በገጠር ቤተ ክርስቲያን ተመደቡ በሚል ሽፋን በክርስቲያኖች መካከል መከፋፈልን በማምጣት ያሳዩትን ችሎታና ድፍረት በማየት ይህ ማህበረ ሰብን የመከፋፈል የድፍረት ተግባራቸው በእውቀት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን በወያኔ የደህንነት ሰራተኞች አማካኝነት ልዩ የደህንነት ስልጠና ሲሰጣቸው ከቆዩ በኋላ ያለው ችግር ቀጥሎ መከፋፈሉ ወያኔን ሊጠቅም በሚችል መንገድ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ በድፍረት እንዲሰሩ መመሪያ ተቀብለው በአሁኑ ወቅት ወደ ለንደን እንደተመለሱ በውስጥ መረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል።
በUK የሕ.ወ.ሓ.ት. ተወካይ የሆነው ካህን ቄስ ገብረ ጊዮርጊስ ድምጹና በአቡነ ገብረኤል አማካኝነት የለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ተብሎ የሃሰት ሹመት የተሾመው የአማርኛ ቋንቋ እንኳ የማይችለው የካረቢያኑ ተወላጅ ቄስ Edward ሁለቱም በአንድነት ባለፈው ወር ወደ ኢትዮጵያ ተጠርተው በመሄድ በሕ.ወ.ሓ.ት. ካድሬዎች የተሞላው መንበረ ፖትሪያርክ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ቀርበው የለንደኑ አብያተ ክርስቲያናት የወያኔን አገዛዝ ዓላማ የሚደግፍ እንጂ በሚነቅፍና በሚያጋልጥ ተግባር ላይ አንዳችም ድምጽ እንዳያሰሙ ከኤምባሲውና ከወያኔ አባላት ጋር በቅርብ ሆነው እንዲሰሩና ከዛ መሥመር እወጣለሁ የሚለውን እንዲከላከሉ መመሪያና ትዕዛዝ ተቀብለው ባለፈው ሳምንት ተመልሰው ለንደን መግባታቸው ተደርሶበታል።
እዚህ ላይ ሁሉም ሰው መረዳት ያለበት በተጀመረው የቤተ ክርስቲያኗ የፍርድ ቤት ክርክር እነዚሁ ሁለት ካህናት እነ አባ ግርማን በመደገፍ ዋንኛ መስካሪ ሆነው Witness statement ያቀረቡ ሰዎች ሲሆኑ በተዘዋዋሪ የቤተ ክርስትያኑን አባላት በፍርድ ቤት እየሞገተ ያለው የሕ.ወ.ሓ.ት. ኤምባሲና አባላት እንደሆኑ መገንዘብ ተገቢ ይሆናል።
ይሄ ሁሉ እየታየ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፤ ግማሹም በየዋህነትና በችላ ባይነት ወዳጅና ባላጋራውንም ሆነ ክፉና በጎውን መለየት የተሳነው ሁሉ ከዚህ በኋላ ጊዜ ሳያጠፋ ሚናውን ሊለይ ይገባዋል።
ምርጫውም እንደሚከተለው ነው።
በነፃነት ሃገር ሆኖ ያለማንም የነፍሰ ገዳዮች ቀጥታም ሆነ ተዘዋዋሪ ተጽዕኖ ሃይማኖትንና ቤተ ክርስቲያንን በነጻነት ማራመድ መቻልና ከገዳዮችና ከዘር አጥፊዎች ጋር ሳይተባበሩ መብትን አስከብሮ በነፃነት መኖር፤
በነፃነት ሃገር ሆኖ የክርስትናንም ሆነ የቤተ ክርስቲያንን መብት ለወያኔ አገዛዝ የቀጥታና ተዘዋዋሪ ተጽዕኖ ስር መውደቅ ተቀብሎ የገዳዮችና የዘር ፖለቲካ አስፋፊዎች ተባባሪ ሆኖ መኖር!!
ወዳጅና ባላጋራችንንም ሆነ ክፉና በጎውን ለይተን እነውቅ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር! አሜን!

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live