Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

በአማራ ክልል የሞት ቅጣት የተወሰነባቸው የ20 ሰዎች ስም ዝርዝር ለፌደራል አቃቢ ህግ ተላከ

$
0
0

ከአያሌው መንበር

(ዘ-ሐበሻ) በአማራ ክልል የሞት ቅጣት የተወሰነባቸው ሰዎች ዝርዝር እንዲላክለት ፌደራል አቃቢ ህግ በጠየቀው መሰረት የ እስረኞች ስም ዝርዝር መላኩ ተሰማ::

አፈትልኮ የወጣው ደብዳቤ እንደሚያሳየው ለምን ጉዳይ እንደሆነ ባይታወቅም በተለያየ ወቅትና በተለያየ ክስ የሞት ቅጣት ውሳኔ የተወሰነባቸው ዝርዝር ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ተልኳል። የ20 የሚሆኑ ሞት ፍርድ ውሳኔ የተጣለባቸው የነዚህ ወገኖች ስም ዝርዝር ለምን እንደተፈለገ የታወቀ ነገር የለም::
amhara1

amhara2

amhara3


ከቀልድ ቁምነገር እንማር እንጅ ቁምነገር የሌለው ቀልድ አንቀልድ (ከይገርማል)

$
0
0

ethnic-federalismበሕጻንነቴ ትዝ ከሚሉኝ ነገሮች ዋናው እንደእናት ተንከባክባ አዝላ: በዳውጃ ላይ አስቀምጣ እየጎተተች አጫውታ:  ሽንትና ካካየን ሳትጸየፍ አጸዳድታ: አስቸጋሪ ባህሪየን ችላ በተረት አዋዝታ: ጸጉሬን እያሻሸች የምታስተኛኝ የአክስቴ ሁኔታ ነው:: ከድሀ ቤተሰብ የተወለድኩ ብሆንም አስተዳደጌ ግን የቀበጥ ነበር: በትንሽ በትልቁ የማኰርፍ: ውሀ ቀጠነ ብየ የምናደድ: አፌን ከፍቼ ማልቀስ ከጀመርኩ ደግሞ መመለሻ ያልነበረኝ:: እናትና አባቴ እኔን ለአክስቴ እርግፍ አድርገው ትተው ካለሀሳብ በዋናው ቤት አለማቸውን ይቀጩ ስለነበር ገመና ከታቼ: ሞግዚቴ: ጓደኛየ: እናቴ: አክስቴ ነበረች:: ካልሁት ለምን ጎድሎ ብየ ወይም በሆነ ሰንካላ ምክንያት ማልቀስ ከጀመርኩ እንደሀምሌ ዝናብ እኝ-ኝ-ኝ እንዳልሁ መዋሌ ነው:: አባትና እናቴ የእኔን ልቅሶ በሰሙ ቁጥር “ይህን ልጅ ካለልክ አቅብጣው!” እያሉ አክስቴን ከመወንጀል: እኔን ባገኙት ነገር ከመጨርገድ: በቁንጥጫ ከመመዝለግ ውጪ እንደወላጅ አንስተው ታቅፈው እምባየን እየጠረጉ ያባበሉበት ጊዜ ትዝ አይለኝም:: ታዲያ ይህን መያዣ መጨበጫ የሌለውን ባህሪየን እና የወላጆቼን ምላሽ የምታውቀው አክስቴ: ለማልቀስ አፌ ከመከፈቱ በፊት የምፈልገውን አሟልታ: ኮራኩራ አሳስቃ: ከምታውቃቸው ተረቶች አንዱን: ፈጥራም ቢሆን እየነገረች ማረሳሳት የዕለት ከዕለት ተግባሯ ነበር:: አክስቴ ከነገረችኝ ተረቶችና ቀልዶች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር:: “ሰማይና መሬት የወለልና የጣሪያ ያህል መቀራረብ ነበራቸው:: በቅሎ ናት በርግጫ ብላ ወዲያ አሽቀንጥራ የጣለችው:: ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አምላክ ከሰው ርቆ መኖር ጀመረ:: በቅሎም በሰራችው ሥራ ተረገመች”

ተረቱን ስትነግረኝ በቅሎዋ በኋላ እግሮቿ ሰማዩን እንዴት አድርጋ እንደመታችው በእንቅስቃሴ ጭምር እያሳየችኝ ስለሆነ እግሯን ባፈራገጠች ቁጥር ሽንቴ ፊር ፊር እስኪል ድረስ በሳቅ እንከተከት ነበር:: እማማ:- ሳላውቅ በስህተት አውቄም በድፍረት ላስቀየምሁሽ ሁሉ ይቅርታ እንደምታደርጊልኝ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ የለኝም:: ብድሬን ለመክፈል አቅሜም ጥረቴም እዚህ ግባ የሚባል ስላልነበረ የዕውነት የፍቅር አምላክ በበኩሉ ይቅር ይበለኝ: ለእኔ የዋልሽውን ውለታ እርሱ ይክፈልልኝ:: ነፍስሽን በገነት ያኑርልኝ:: አሜን!

የአክስቴ ጨዋታ ሲተነተን እንዲህ የሚል ይወጣዋል:: ‘ዱሮ ዱሮ ሰማይ ለመሬት በጣም ቅርብ ነበር:: ታዲያ ያኔ በሰማይ የሚኖረው አባታችን የልብ ትርታችንን ሳይቀር ማዳመጥ ይችል ስለነበር የሰው ልጆች ብሶት ይሰማ: ችግራቸው በቀላሉ ይቀረፍ ነበር:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ከእለታት በአንዲት ቀን በቅሎ ሆዬ ጥጋብ ንፍት አድርጓት የምትሆነውን ያሳጣታል:: ወዲህና ወዲያ የምትፈነጭበት ቦታውም ይጠባታል:: በዚህም ምክንያት አገጯን ወደመሬት ተክላ: የኋላ እግሮቿን እንደጉድ አንስታ: ሽቅብ ተስፈንጥራ: ባለ በሌለ ኃይሏ ሰማዩን ስትደልቀው ሰማዩ እያጉረመረመ የትየለሌ ሄዶ ተሰቀለ:: ከዚያ ወዲህ “ከዐይን የራቀ ከልብ ይርቃል” እንዲሉ ፈጣሪ በአካል ብቻ ሳይሆ በመንፈስም ራቀን:: የገጻችንን መዳመን የስሜታችንን መጎፍነን አስተውሎ: ጸሎታችንን ሰምቶ: የምንጠይቀውን ያሟላልን: የሚበጀውን ያደርግልን የነበረው አባት ዛሬ ላይ ብንጮህ ብናለቅስ አልሰማ ብሎናል:: የሰውን ልጅ ከፈጣሪ ያራራቀችው በቅሎ “ወልደሽ አትሳሚ!” ተብላ ብትረገም ይኸው የመወለድ እንጅ የመውለድ ጸጋን ተገፋ “ብዙ ተባዙ!” የሚለው የፈጣሪ ቃል ዘሏታል::’

በአንድ ወቅት ከአንድ አርብቶአደር ጋር ስናወራ ከሆነ ሰው ጋር በመጣላቱ የተጣላውን ሰውየ ልጅ ገድሎ ታስሮ እንደቆየ ነገረኝ:: ‘እንዴ! ልጁ ምን አድርጎህ ነው የገደልኸው? ሲሆን ሲሆን የበደለህን ሰው በህግ መጠየቅ በተገባ ነበር: ካልሆነ ደግሞ መቅጣት የሚኖርብህ ምንም ያላጠፋውን ልጁን ሳይሆን አጥፍቷል ያልኸውን አባቱን መሆን ነበረበት’ ስለው አርብቶአደሩ ወንድሜ እየሳቀ “አባቱ ውሻ ነበር:: የውሻ ልጅ ውሻ ነው” በማለት የወሰደው ርምጃ ትክክለኛ መሆኑን ሊያሳምነኝ ሞከረ:: እስካሁን ባለው እውነታ የውሻ ልጅ ውሻ መሆኑን የሚክድ አይኖርም:: የፈረስ ልጅ ፈረስ ስለመሆኑ ምን ያህል እርግጠኛ መሆን ይቻላል? ያም ሆነ ይህ በቅሎ የሰራችው ሥራ የሚያቀባብር አይደለም:: ግን ማንን ልኰንን? በቅሎዋን ወይስ አህያና ፈረስን አዳቅለው በቅሎን ያመጡብን ናቸው የሚባሉትን አገወች?

ጀብሀን: ሻዕቢያን: ኦነግን: ወያኔን: ኦብነግን: ሶማሌ አቦን:  – – -ማን ፈጠራቸው? ማንን ከማን አዳቅሎ? እኒህ ዲቃላወች ምን ጉዳት አደረሱ?

ግብጽ ጀብሀን ፈጠረ: ሻእቢያን ጀብሀን ወለደ: ሻእቢያ በበኩሉ የፈጠራቸው- – – እያልን እንቀጥል ወይስ የልብ-ወለድ ታሪክና የስልጣን ጥም ተዋህደው እኒህን ጉዶች ፈጠሩ እንበል? የሆነው ሆኖ አንዳንዶች “በለጋነታችሁ ይቅጫችሁ: ለቁምነገር አትብቁ!” ተብለው ተረግመው መንቦራቸት ሳይጀምሩ ሳያምርባቸው: ከተቀመጡበት መሬት ላይ ሳይነሱ አርፈው ተቀብረዋል:: አንዳንዶቹ ደግሞ “ህልማችሁ እንደጉም ይትነን: እንደባዘናችሁ ኑሩ!” ተብለው ይኸው የማይደርስ ህልም: የማይጨበጥ ተስፋ ይዘው ቀጥለዋል:: እምባና ደም እያፈሰሱ: ጤና አጥተው: ጤና ነስተው: እየኖሩ ያሉም አሉ:: በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው የሞቱት ቡድኖች የማይሞት መጥፎ አሻራወቻቸውን ጥለው እንዳለፉ ሁሉ በህይወት አሉ የሚባሉትም እንዲሁ አሳፋሪ ታሪካቸውን ጥለው እንደሚያልፉ ነው:: ይህ የሚሆነው ከታወቀበት ብቻ ነው::

የጎሣ ድርጅቶችን አባብሎ ኢትዮጵያዊ መስመር እንዲከተሉ ለማድረግ ብዙ ተሞክሯል: ብዙ ተደክሟል:: ግን ያው “ውሀ ቢወቅጡት—” ሆኖ የተለወጠ ነገር የለም:: ሰማዩን አይተው የዝናቡን አቅጣጫ መረዳት የሚችሉ እነሱ በዝናብ ከመበስበስ ይድናሉ:: “እወቅ ያለው በአርባ ቀኑ ያውቃል: አትወቅ ያለው ግን በአርባ አመቱም አያውቅ” የሚለው አባባል ዝም ብሎ የተባለ አይደለም:: እናሳ! ሕዝቡን አስተምሩና አደራጁ እንጅ እኒህን ቡድኖች አትለማመጡ የሚሉትን ሁሉ እንደ ጸረ-አንድነት አድርጎ መመልከቱ ዛሬም አይበቃም! ካለፈው ስህተት መማር የማይችል ሰው ለወደፊቱ በጐ ነገር መስራት የሚሳነው ብቻ ሳይሆን የዐዕምሮ ጤንነቱም የሚያጠራጥር ነው:: አሁን ያለው የኃይል አሰላለፍ በዋናነት በሁለት የሚመደብ ነው: ጎሣዊና ሕብረ-ብሔራዊ:: የአንድነት ኃይል (ሕብረ-ብሔራዊ) ነን የምትሉ ሁሉ በአንድነት እንዳትቆሙ የሚያደርጋችሁ መሰረታዊ ልዩነት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም:: የአረብ ገንዘብ የሚፈስላቸውን ጎጠኛ ድርጅቶች ለማባበል ከሄዳችሁበት ርቀት ግማሽ ያህሉን እንኳ ተጉዛችሁ ችግሩንም ሆነ ደስታውን ተካፍሎ የሚኖረውን ሕዝብ ለማቀፍ ብትሰሩ እዳው ገብስ ይሆናል::

ሰሞኑን የኦሮሞ ድርጅቶች ለንደን ላይ ተሰብስበው ከተነጋገሩት ውስጥ ተቀንጭቦ የሰማነው ኦሮሚያ የምትመሰረተው በኢትዮጵያ ከርሰ-መቃብር ላይ እንደሆነ ነው:: የኦሮሞ ድርጅቶች የሚሰሩት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እንጅ ለመደገፍ እንዳልሆነ ነው:: ከዚህ በላይ ምን ብለው ይንገሩን? እህሳ! እኒህን የዘረኝነት ቫይረስ ተሸካሚ ቡድኖችን መለማመጥ እንቀጥላለን ወይስ በኢትዮጵያዊነታቸው የማይደራደሩትን ወገኖቻችንን ይዘን ወደሕዝብ እንዘልቃለን?

አክስቴ ከነገረችኝ ተረቶች መሀል ትዝ የሚለኝ ሌላው የአንድ ባልና ሚስት ልብ-ወለድ ታሪክ ነው:: በአንድ ወቅት በአንድ አካባቢ የሚኖሩ ድሀ ባልና ሚስት ነበሩ:: ባልና ሚስቱ ጠንክረው በመስራት ኑሯቸውን ለማሻሻል ከመጣር ይልቅ እጃቸውን እና እግራቸውን አጣጥፈው ቁጭ ብለው በማይጨበጥ ምኞት የጎደለውን ሊሞሉ: የዘመመውን አቃንተው ህይወታቸውን ሊያደላድሉ የሚደክሙ የህልም እንጀራ ጋጋሪወች ነበሩ:: አንድ ቀን ባልና ሚስቱ እንደተለመደው ቁጭ ብለው ሲጫወቱ ሚስት “ሞሰብ ሰፍቼ: ሞሰቡን ለንጉሥ አበርክቼ: ንጉሡ በሚሰጡኝ ሽልማት ላም ገዝቼ: ላሟ ስትወልድልኝ ጥጃዋን ከመደብ ላይ አስራታለሁ” ብላ ምኞቷን ትናገራለች:: ይኸኔ ባል በንዴት ቱግ ይልና “ጥጃይቱን ከመደብ ላይ አታስሪያትም!” በማለት ይናገራል:: ሚስትም የዋዛ ስላልነበረች ከባልዮው በላይ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ “ምን የቆረጠው ነው ጥጃየን መደብ ላይ እንዳላስራት የሚከለክለኝ?” በማለት ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለች:: “አታስሪያትም ብያለሁ አታስሪያትም” ባል ከሚስት በላይ ጮሆ ያስጠነቅቃል:: ሚስት የምትረታ አልነበረችም: ባልዮውም ነገሩን ችላ ብሎ የሚያልፍ አልሆነም:: ‘አታስሪያትም! – አስራታለሁ’ የሚለው ጭቅጭቅ እየተካረረ ሄዶ በመጨረሻ ወደድብድብ ያድጋል:: ባል ሆየ በያዘው ከንተሮ ሚስቱን ኩኳን ሲላት እንደ እስክስታ ወራጅ እየተውረገረገች ወደ ታች ወርዳ ከመሬት ላይ ትዘረራለች:: ባል በበኩሉ ሚዛኑን መጠበቅ አቅቶት ከድንጋይ ላይ ወድቆ ሳይነሳ በዚያው ይቀራል:: በሌለ ነገር: ባጉል ተስፋ ባልና ሚስቱ ሕይወታቸውን አጡ::

በባዶ ስልጣን የሚራኮቱ የፖለቲካ ድርጅቶችን ባሰብሁ ቁጥር የባልና ሚስቱ ታሪክ ትዝ ይለኝና ፈገግ ያሰኘኛል:: ኢትዮጵያ በጎጠኞች እየተደገሰላት ያለውን ጥፋት እያዩና እየሰሙ ያሉት የአንድነት ተሟጋች ነን የሚሉት ድርጅቶች ከስህተታቸው ተምረው የግል ፍላጎታቸውን ወደጐን በማድረግ በአንድነት ለመቆም ፍላጎት ባለማሳየታቸው እንወዳታለን የሚሏትን ሀገር ዕጣ ፈንታ ለጐጠኞች አሳልፈው በመስጠት የእርስ በርስ የመጠፋፋት ስራ እየሰሩ ነው::

የሀገራችን ተረትና ምሳሌወች ከአዝናኝነት በላይ አስተማሪነታቸው አሌ የሚባል አይደለም:: ተረትና ምሳሌወች ሰዎችን እያዝናኑ ትምህርት ለማስጨበጥ ተመራጭ መንገዶች ናቸው:: ክርስቶስ እራሱ ሰዎችን ሰብስቦ ሲያስተምር ምሳሌወችን መጠቀም ያዘወትር እንደነበር ነው ከመጽሀፍ ቅዱስ የምንረዳው:: ከቀልዳ-ቀልዶችና ከተረትና ምሳሌወች ቁምነገር የሚቀስሙ ሰዎች ባይበዙም አይጠፉም:: በቁምነገር መሀል የጅል ቀልድ የሚቀልዱ ግን ሞልተዋል:: ደግሜ እለዋለሁ:: ልብ ያለው ሰው የሚነገሩትን ቀልዳ-ቀልዶችን: ታሪክና ምሳሌወችን ስቆ የሚያልፋቸው ሳይሆን ትምህርት የሚቀስምባቸው ናቸው:: አንዳንዶቹ ግን ከተረትና ምሳሌም ሆነ ከሚታየውና ከሚደረገው ተጨባጭ ክስተት ሊማሩ የማይችሉ የልማድ ደንበኞች ናቸው:: ሕዝብ በጎጠኞች ግራና ቀኝ ተወጥሮ ተይዟል:: የአንድነት ኃይሎች ነን የሚሉት ቡድኖች ግን በአንድነት መቆም ተስኗቸው የሀገር ጠላቶችን ከጎን አስቀምጠው በእርስ በርስ የቀዝቃዛ ጦርነት ተጠምደዋል:: ይህ ሊታረም ይገባል:: በጊዜ ያልተሰራ ስራ ለዐይን ሲይዝ (በአመሻሽ) ልስራህ ቢሉት ስለሚያስቸግር አሁኑኑ ተሰባስበን ደርሰናል እንበል::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ

የዐማራ የጎበዝ አለቆች ሕብረት ተጋድሎ ወደ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊያድግ ነው፤

$
0
0

በሙሉቀን ተሰፋው

በተለያዩ አካባቢዎች ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች የወያኔ መንግሥት በዐማራው ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ በመቀጠሉ በተበታተነ መልኩ በየአካባቢው ሲደረግ የነበረው ሕዝባዊ ተጋድሎ ድርጅታዊ መዋቅር የያዘ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊሆን ነው ብለዋል፡፡ የጎበዝ አለቆቹ ሕብረት የመሠረቱት የሕዝባዊ ንቅናቄ ትግል በቅርብ ይፋ እንደሚደረግም አክለው ገልጸዋል፡፡

amhara
‹‹ወሳኙ›› በመባል የሚታወቀው የጎበዝ አለቃ ‹‹ሕይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ከሆኑ ወጣቶች ጋር በአንድ ላይ መክረንበታል፡፡ በማንነታችን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመመከት የእኛን መስዋእትነት ይጠይቃል፤ በተለያዩ አካባቢዎች ካሉ የጎበዝ አለቆች ጥምረት ጋር መክረንበታል›› ሲል ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. አረጋግጦልናል፡፡ ወሳኙ ያለበትን ቦታ ዕቅድም በድፍረት የተናገረ ቢሆንም ለጥንቃቄ ሲባል ቦታዎቹን ይፋ አለማድረግ መርጠናል፡፡ ‹‹ፈላሻው›› በመባል የሚታወቀው ሌላው የጎበዝ አለቃ ደግሞ ‹‹ወያኔ በዐማራው ላይ እያደረሰው ያለው ጥፋት ምንም ዓይነት መሻሻል አላሳየም፤ የማንነት ጥያቄ ያቀረቡ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ ኮሚቴዎችን ጥያቄያቸውን ከመፍታት ይልቅ እያሳደደ ማሳር ሥራየ ብሎ ይዞታል፡፡ የዐማራ ወጣት ለበለጠው ተጋድሎ መዘጋጀት አለበት፡፡ ሁሉም የዐማራ ወጣት እንደ አንድ መነሳት አለበት፡፡ ወጣቱ ዛሬ ወይም ነገ ለሚደረግ ጥሪ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ አለበት፡፡ ከሕዝባችን ላይ የተጣለውን ጭቆና ለመገርሰስ የእኛ መስዋትነት የግድ ብሏል›› ሲል አብራርቷል፡፡
የጎበዝ አለቆቹ በሰሜን ጎንደር የኮማድ ፖስት የሚባለው የወያኔ አገዛዝ የገበሬውን ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ መፍጠሩንና በርካታ ወጣቶችን ማሰሩን አውስተዋል፡፡ በምስራቅ ጎጃም በጎንቻ ሲሦእነሴ ጉንደወይን ከተማ የሁለት ወያኔዎች ንብረት የሆነ ዓለም ሆቴል የተባለን ለማቃጠል አስባችኋል በሚል ሳጅን ምናሉ የተባለ ቅጥረኛ የዐማራ ወጣችን ዛሬ ማሰሩን የጎበዝ አለቆቹ ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ሳጅን ምናሉ እና ተመሳሳይ ወንጅል እየፈጸሙ ያሉ ቅጥረኞች ከዐማራ ሕዝብ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ የአበባ እርሻ ባለንብረቶች ዐማራ የሆኑ የድርጅቱን ሠራቶች የሁለት ወር ደመወዝ ካለመክፈላቸውም በተጨማሪ ሠራተኞችን ያለ አግባብ ማንገላታታቸው በኋላ የእጃቸውን እንደሚያገኙም አሰጠንቅቀዋል፡፡ የአበባ እርሻ ጥበቃ ሠራተኞች በገበሬዎች ላይ ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳይወስዱ አሳስበዋል፡፡

ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም! |ከፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

$
0
0

mesfin

ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች! ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ” ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል! የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም!

የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ ግለሰቦችም መንግሥቶችም ሞልተዋል፤ ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ የሚመኙ ጭንጋፍ ልጆችም አሏት፤ ማኅጸንዋ እየደማ እየረገማቸው ሰላምና እንቅልፍ አጥተው አብጠው ይፈነዳሉ፤ የኢትዮጵያን መፈራረስ የሚመኙ መንግሥቶች ሁሉ ከዚህ በፊት ቀድመው ፈራርሰዋል፤ ወደፊትም ይፈራርሳሉ።

የአገራቸው ፍቅር፣ የእርስበርሳቸው ዝምድና፣ የተራራውና የሸለቆው፣ የሜዳውና የገደሉ፣ የበረሀውና የለምለሙ፣ የዝናቡና የወንዙ፣ የዓየሩና የነፋሱ፣ የበዓላቱና የድግሱ፣ ያለውን አብሮ መቋደሱ፣ ተዝካሩ፣ ሙታዓመቱ ለሞቱ፣ መላእክቱ፣ ቅዱሳቱ፣ ሰማዕታቱ፣ እየተሸከሙ ያደረሱት ጸሎቱ፣ ለምዕተ-ዓመታት የተከማቸው እምነቱ፣ ሃይማኖቱ፣ በዚህ ሁሉ የተገነባው ኅብረቱ እንዴት ይፈርሳል! ማን ችሎ ያፈርሰዋል! አፍራሾች ቀድመው ይፈርሳሉ!

አንዳንዶች ቢጨነግፉም፣ አንዳንዶች ቢክዱም፣ አንዳንዶች ሆዳም ቢሆኑም፣ አንዳንዶች ቢወላውሉም፣ ኢትዮጵያ ልጆች አሏት፣ አሁንም የሚሞቱላት፣ ያልበሏት፣ የሚሳሱላት፤ ያልሸሿት፤ አፈሯን የሙጢኝ ብለው አፈርሽ እንሁን የሚሏት፣ ደሀነትም ሆነ ጭቆና ካንቺ አይለዩንም የሚሏት፤ ኢትዮጵያ ዛሬም ልጆች አሏት ስትፈርስ ቆመው የማያዩ፣ ሲያማት ነፍሳቸውን ዘልቆ የሚያማቸው፣ ሳልፈርስ አትፈርስም ነው ቃል ኪዳናቸው!

ቱርክና ግብጽ መጥተው ሄደዋል፤ ፖርቱጋል መጥቶ ሄዷል፤ እንግሊዝ መጥቶ ሄዷል፤ ኢጣልያ መጥቶ ሄዷል፤ ጠላቶች እየመጡ በመጡበት ተሸኝተዋል፤ ወዳጆች በጨዋነት ተስተናግደው ተዋኅደዋል፤ ቤተ ሙሴ፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ቤተ እስልምና ኢትዮጵያዊ ሆነዋል፤ ዛሬ እንግዳ አይደሉም፤ ዛሬ ባዕድ አይደሉም፤ ኢትዮጵያ በፍቅር ለመጣ ፍቅር ነች፤ ምቹ ነች፤ በጠብ ለመጣ እሾህ ነች፤ ትዋጋለች።

ኢትዮጵያ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ለአንቺ የተናገረው ይመስለኛል፤ ‹‹ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፤ አብሪ፤ እነሆ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤ አሕዛብም ወደብርሃንሽ፣ ነገሥታትም ወደመውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ። ዓይኖችሽን አንስተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደአንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል፤ በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደአንቺ ስለሚመለስ፣ የአሕዛብም ብልጥግና ወደአንቺ ስለሚመጣ አይተሽ ደስ ይልሻል፤ ልብሽም ይደነቃል፤ ይሰፋማል፤ የግመሎች ብዛት የምድያምና የጌፌር ግመሎች ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፤ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ፤ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ፤ የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደአንቺ ይሰበሰባሉ፣ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፤ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።›› (60፡1-7)

ኢትዮጵያ ትወድቅ ይሆናል፤ ግን ያለጥርጥር ትነሣለች፤ በፊትም ወድቃ ተነሥታለችና፤ ኢትዮጵያ ትሰነጠቅ ይሆናል፤ ግን ያለጥርጥር ትገጥማለች፤ በፊትም ተሰንጥቃ ገጥማለችና፤ ለኢትዮጵያ በጎ የማይመኙላት የአየሉ ቢመስሉም የንስሐ ጊዜ ስትሰጣቸው ነው፤ ኢትዮጵያ ዕብሪተኞችንም ትሕትና ታስተምራቸዋለች፤ ዕብሪተኞች ከነዕብሪታቸው በራሳቸው እሳት ቀልጠው እስቲያልቁ ኢትዮጵያ ትእግስትዋ አያልቅም፤ ኢትዮጵያ ትእግስት ነችና።

በበጎ መንፈስ እስከተመራን ድረስ፣ ፍርሃትንና አለመተማመንን፣ ጥላቻን፣ ጠብንና ድብድብን፣ ሊዘሩብን ከሚፈልጉ ርኩሳን መናፍስት ከራቅን ኢትዮጵያችን አትፈርስም፣ የደፈረሰውም ቶሎ ይጠራል።

ኦሮሞ ዴ. ግንባር፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ የአፋር ህዝብ ፓርቲና የሲዳማ ህዝብ ዴ. ንቅናቄ የትግራይ ነጻ አውጪን መንግስት ለማፋለም የፊታችን እሁድ የጋራ ንቅናቄያቸውን ይፋ ሊያደርጉ ነው

$
0
0

ethiopian-people-unity

(ዘ-ሐበሻ) በሌንጮ ለታ እና በምክትላቸው ዲማ ነገዎ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር፣ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው አርበኞች ግንቦት 7፣ በዶ/ር ኮንቴ ሙሳ የሚመራው የአፋር ህዝብ ፓርቲና አቶ በቀለ ዋዩ የሚመራው የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ የትግራይ ነጻ አውጪውን መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገንድሰው ለመጣል የሚያስችል የጋራ ንቅናቄ እንደመሰረቱና ይህንንም የፊታችን እሁድ ኦክቶበር 30, 2016 ይፋ እንደሚያደርጉ ለዘ-ሐበሻ የተላከው መረጃ አመለከተ::

በውስጣቸው አንጋፋ ታጋዮችን የያዙት እነዚሁ አራት ድርጅቶች የኢትዮጵያን ህዝብ “ተባባብሩ ወይም ተሰባበሩ” የሚለውን ጥሪ ተቀብለው የፊታችን እሁድ ይፋ የሚያደርጉት የጋራ ንቅናቄ ስም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ እንደሚሰኝ የደረሰን መረጃ ጠቁሟል::

የፊታችን እሁድ ኦክቶበር 30/2016 የአራቱ ድርጅቶች መሪዎች በዋሽንግተን ዲሲ የፊርማ ስነ-ስርአት እንደሚደረግ የታወቀ ሲሆን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአስመራ ተነስተው አሜሪካ መግባታቸውን እንዲሁም አቶ ሌንጮ ለታ፣ ዲማ ነገዎ፣ ዶ/ር ኩንቴ ሙሳ አሜሪካ መግባታቸው ለዘ-ሐበሻ መረጃ ደርሷታል::

የፊታችን እሁድ በሚደረገው የፊርማ ስርነ ስርዓት ላይም ሕዝባዊ ስብሰባ እንደሚኖር ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

የመን ሁቴ አማጽያን ወደ መካ የላኩት ሚሳኤል ከሸፈ |ሚሳዬሉ ከመካ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት በመቃዎሚያ ከሽፏል

$
0
0

yemen-hute

* ሚሳዬሉ ከመካ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት በመቃዎሚያ ከሽፏል
* ከኢራንና ሊባኖስ በየመኑ ፕሬዘደንት ተወግዘዋል
* የሳውዲ መከላከያ ተመሳሳይ ጥቃቶችን ለመከላከል ተዘጋጅቷል

የመን ሁቴ አማጽያን ከየመን የሁቲ አማጽያን ይዞታ ከሳአዳ Saada ወደ ቅዱስ መካ የላኩት ምድር ለምድር ተወንጫፊ እስከድ ሚሳኤል መክሸፉን የአረብ ህብረት ጦሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል ። ከየመን በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ቅዱስ ከተማዋ መካ ያነጣጠረው የሚሳዬል ጥቃት ከመካ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ሲደርስ መክሸፉ ተነግሯል። ይህው ትናንት ከቀትር በኋላ በግምት 9 p.m በሳውዲ መከላከያ ሰራዊት የምድር ጦር መቃዎሚያ የከሸፈው ጥቃት ጉዳት አለማድረሱን ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው የሳውዲ ፕሬስ ኤጀንሲ መግለጫ ያስረዳል ።

ካሳለፍነው አመት ጀምሮ በየመን የሚገኙትን አማጽያን ለማንበርከክ ሳውዲና ሳውዲ መራሽ አረብ ሀገራት የአየር ላይ ጥቃታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸው ይታወቃል ። ይሁን እንጅ የህብረት ጥቃቱ አብዛኛው የመንን ተቆጣጥረው ያሉትን የሁቲ አማጽያን እና የቀድሞው መሪ የአሊ አብደላህ ሳላህን ደጋፊዎች መቆጣጠር አልቻላቸውም ። ሳውዲ መራሹ ጦር በአማጽያኑ ላይ ከበድ ያለ ኪሳራና ጥቃት ቢያደርስም አማጽያኑ ድንበር አሻግረው የሚልኳቸውን ሚሳኤሎች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አለመቻላቸው ይነገራል ።

ከድንበር ከተማዎች አልፈው ከመካ የቅርብ ርቀት በምትገኘው የጣይፍ ከተማ የቅርብ ርቀት ሚሳዬል ባስወነጨፉ በሳምንታት እድሜ ዛሬ መካን ኢላማን ማድረጋች የሰማነው መረጃ አነጋጋሪ መሆኑ አልቀረም ። አማጽያኑ ከቅዱስ ከተማዋ መካ የ65 ኪሎ ሜትር ርቀት ሚሳዬል መተኮሳውና መክሸፉ በሚነገርበት በዚህ ሰዓት በሳውዲና በህብረት ጦሩ በኩል የሚሰጠው ምላሽ የከበደ እንደሚሆን ይገመታል። የሳውዲ መከላከያ ሰራዊት ተመሳሳይ የሚሳኤል ጥቃትን ከመመከት የሚያስችሉ እጅግ ዘመናዊ የሚሳኤል መከላለከያ Patriot missiles በተለያዩ ቦታዎች በመትከል ተመሳሳይ ጥቃቶችን ለመከላከል መዘጋጀቱም ታውቋል ።

ይህ በእንዲህ አንዳለ የሁቲ አማጽያን በሳውዲ ድንበር ከተማ በጀዛን በሰነዘሩት ተመሳሳይ ጥቃት የመኖሪያ ቤቶች ጥቃት የደረሰባቸው ቢሆንም በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱ የሳውዲ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 15 ቀን 2009 ዓም

“የኦሮሞና ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ካልተባበረ ነጻ መውጣት አይችልም”–የኦሮሞ አክቲቭስት ግርማ ሃሰን በሚኒሶታ (ቪድዮ)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ በጽናት የውውይት መድረክ አማካኝነት ማህበረሰብን ለማቀራረብ በተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ ከተገኙት መካከል የተወሰኑ ተናጋሪዎችን ቪድዮዎችን ስናቀርብ ሰንብተናል:: በተራ ሁሉንም ለማቅረብ እንሞክራለን:: ለዛሬው ደግሞ የኦሮሞ ካልቸራል ኢንስቲትዩት መሪ የሆኑት አክቲቭስት ግርማ ሃሰን ያደረገውን ንግግር ይዘናል – ቢያደምጡት ይጠቀማሉ::

በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ ኢትዮጵያውያኑን ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት የሶማሊያ ተወላጆች እየተፈለጉ ነው

$
0
0
 እነዚህ በፎቶዉ ላይ የምትመለከቷቸዉ ሶማሌያዉያኖች ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ግለሰቦች ሲሆኑ ግለሰቦቹን ለፖሊስ በመጠቆም ወንጀልን እንድንከላከል ጥሪ ተደርጓል።

እነዚህ በፎቶዉ ላይ የምትመለከቷቸዉ ሶማሌያዉያኖች ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ግለሰቦች ሲሆኑ ግለሰቦቹን ለፖሊስ በመጠቆም ወንጀልን እንድንከላከል ጥሪ ተደርጓል።

(በልኡል አለሜ )

የላንግላታ ፖሊስ ስቴሽን ወይም ላንግላታ እየተባለ የሚጠራዉን አካባቢ የሚቆጣጠረዉ ፖሊስ ስቴሽን ኮምንደር እንደገለጸዉ በጆሐንስበርግ ሜይፌር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ የሚኖሩ ሶማሌዎች እና ኢትዮጵያዊያን የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች በፈጠሩት አለመግባባት የአካባቢዉ ሰላም ከመቃወሱ በላይ ግጭቱ ለ7 ሰዎች የሞት ምክንያት ሲሆን ለሁለት ግለሰቦች የመቁሰልና ለ5 ሰዎች የእስር እንዲሁም ለበርካቶች የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ችግር ፈጥሯል።

በሶማሌ የአዉያ ብሔር ግለሰቦች እና በኢትዮጵያዊያኖች መካከል የተፈጠረዉ ግጭት ከተከሰተ ወዲህ የኦሮሞ ህብረተሰብ ለተገደሉ ሁለት የሶማሌ ልጆች 800.000 ሺ ራንድ ካሳ ከከፈሉ በሗላ አለመግባባቱ ይበርዳል ተብሎ ቢገመትም በትናንትናዉ እለት ሁለት ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸዉ አህመድ ጀማል እና ሐፊዝ የተባሉ የኦሮሞ ወጣቶች ከረፋዱ ላይ በባለ 38 ሚሊ ሜትር ማካሮዝ ሽግጥ በሶማሌ ወጣቶች ከተገደሉ ወዲህ ችግሩ እንደና ያገረሸ ሲሆን ከግድያዉ በሗላ የበቀል እርምጃ ለመፈጸም የተንቀሳቀሱ 3 የኦሮሞ ወታቶች ከነታጠቁት መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዉለዋል::

ፖሊስ ፈይሰል የተባለ ግለሰብን ጨምሮ ሁለት ኢትዮጵያዊያንን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ከመግለጹ በላይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት አላቸዉ የተባሉ ሌሎች ግለሰቦችን ለመያዝ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታዉቋል

አንድ በሜፌር አካባቢ የሚኖር ግለሰብ እንደገለጸልን ከሆነ ” ሶማለዎቹ ሆን ብለዉ ከሗልህ ይመጡና በኦሮምኛ ሰላምታ ይሰጡሃል በኦሮምኛ መልስ ስትመልስ በጥይት ጀርባህን ብለው ይሄዳሉ በንግድ ቤታችን ዉስጥ በመሳሪያ የታገዘ ዘረፋ ይፈጽሙብናል መኖሪያ ቤታችን ይከበባል መንገድ ላይ ስትሄድ አስነዋሪ ስድብና ዛቻ ይደርስብናል ” ሲል ተናግሯል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያናገርናቸዉ የፖሊስ ኮማንደር እንደገለጹት በማንኛዉም መልኩ አደጋ ይፈጥራሉ ወይም አደጋ ፈጥረዉ የተሰወሩ ግለሰቦችን የተመለከተ ማንኛዉም ግለሰብ በነዚህ ስልኮች መረጃ እንዲሰጥ ኤጻጽቤኣል Langlaagte – 011 473 6200 Johannesburg Central – 011 497 7000 እነዚህ በፎቶዉ ላይ የምትመለከቷቸዉ ሶማሌያዉያኖች ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ግለሰቦች ሲሆኑ ግለሰቦቹን ለፖሊስ በመጠቆም ወንጀልን እንድንከላከል ጥሪ ተደርጓል።


በደቡብ አፍሪካ ህወሃት በድጋሚ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን ደግፉልኝ ስብሰባ ጠራ!

$
0
0

Zehabesha-News.jpg

( በልኡል አለም )

በቅርቡ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ የደነገገዉ ህወሃት በመላዉ አለም በሚገኙ ተቃዋሚዎች ላይ ተጽእኖ ለማሳደር በኢንባሲዎች አማካኝነት የስብሰባና የተቃዉሞ ሰልፍ በደጋፊዎቹ አማካኝነት ሊያደርግ እንደነበር መጠቆማችን የቅርብ ግዜ ትዉስታ ነዉ።

በመሆኑም ህወሃት የመጀመሪያዉን ስብሰባ በደቡብ አፍሪካ ፍሪ እስተት ሊያደርግ ዝግጅቱን ጨርሶ በነበረት ወቅት መረጃዉ ቀድሞ በመዉጣቱ ምክንያት ዉድ የኢትዮጵያ ልጆች በግንባር ስፍራዉ ድረስ በመሄድ በዚህ እኩይ ተግባር ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን በማነጋገር ከዚህ አስነዋሪ ተግባር እራሳቸዉን እንዲያገሉ በማድረጋቸዉ የወያኔ ተንኮላዊ ሴራ ከሽፏል።

ነገር ግን በቃኝ የማይለዉና ሽንፈቱን የምይቀበልዉ የህዝብ ተላት የሆነዉ የጎጥ ቡድን አሁንም በድጋሚ በ30/10/2016 ፕሪቶሪያ እስኩማን እስትሬት በሚገኘዉ ኢንባሲዉ ዉስጥ በዚሁ በመከረኛዉ እና በከሸፈዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ምክንያት እንነጋገር እያለ እትዮጵያዊያንን እያስጨነቀ እንደሚገኝ ከስፍራዉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ተወካዩ የህወሃት ኢንባሲ በሊስቱ ዉስጥ የመዘገባቸዉን ወገኖቻችንን በተለይም የስርአቱ ደጋፊዎች እና ሐገር ቤት ሀብት ንብረት ያፈሩ እንዲሁም ከኢናባሲዉ ጋር በተገናኘ መልኩ አንዳንድ ቁልፍ የቤተሰብና የግል ጉዳይ ያላቸዉ ግለሰቦች ጋር እየደወለ በስብሰባዉ ላይ ካልተገኛችሁ

” በስቸክዋይ ግዜ አዋጁ አፈጻጸም ላይ ትብብር አለማድረጋችሁንና ከህዝብ ጋር አለመቆማችሁን በመገንዘብ ሚናችሁን ለሚመለከተዉ አካል ኢናስተላልፋለን ”

በማለት እያስፈራራ እንደሚገኝ ከኢንባሲዉ ዉስጥ እና በደቡብ አፍሪካ መሐበረሰብ ዉስጥ ከሚኖሩ ወገኖቻችን የደረሰን መረጃ ጠቁሟል።

ዉድና የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ይህ የህዝብ ጠላት የሆነዉ ስርአት በሀገር ቤት በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ የፈጸመዉንና እየፈጸመ የሚገኙዉን አፈና ደግፉልኝ እንዲሁም ከሀገራቸዉ ተሰደዉ ስለ ነጻነታቸዉ እና ስለመብታቸዉ የሚጮሁትን ስደተኞች ተቃወሙልኝ በማለት የጠራዉ ስብሰባ ላይ ባገኘት ብቻ ሳይሆን ስብሰባዉን በመቃወም የበኩላችሁን አስተዋጾ ኢንድትወጡ እናሳስባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

ኢትዮጵያዊነትን ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ተውላቸው!!

$
0
0

(አብዱልጀሊል አሊ ካሣ)
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊነትን በወግ የወረስን አይደለንም! ኢትዮጵያዊነትን በእቶን ፈተና ውሥጥ ተፈትነን ያረጋገጥን እንጂ! ኢትዮጵያዊነት ደምና አጥንታችን ነው፡፡ ለኢትዮጵያም ደም ግባቷ ነን! የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊነት “በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሙስሊሞች!” መግፍኤ ያልገፈፈው ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡መገለል ያላገለለው….መደቆስ ያልደቆሰው…. መገፋት ያልገፋው!…. መፋቅ ያልፋቀው!….መናቅ ያልናቀው!…..ኢትዮጵያዊነት!!! የእኛ ኢትዮጵያዊነት የገራፊው ወገን አይነት አይደለምና! ገራፊው ጅራፉን በተቀማ ጊዜ ኢትዮጵያ ጅራፉን እየመሰለችው በህልሙ ጅራፉን ይመስል ገርፎ ሲጮህ የሚያደር ወገን ነውና በእውኑ የጅራፉን እና የኢትዮጵያን አንድነት ሲያኖጋ የሚውለው ነው፡፡ የእኛ ኢትዮጵያዊነት ግን የጅራፍ ጩኸት ያጸናው፣ የግርፋቱ መከራ ኢትዮጵያዊነትን ሰንበርና ጎዳንዲሳ አድርጎ ከልባችን አትሞ ያስቀረው ነው፡፡

mus

“ኦሮሞን የሚያክልን ታላቅና ግዙፍ ብሄር በጎሳ ፖለቲካ መፈረጅ ትልቅ ሃጥያት ነው”ተ/ፕ/ር ሃሰን ሁሴን (የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር አመራር)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጽናት የኢትዮጵያ የውይይት መድረክ አማካኝነት በሚኒሶታ በተደረገው ሁሉን ማህበረሰብ ክፍል ያካተተው ውይይት ላይ በግል የተገኙት ታዋቂው ጸሐፊና ሌንጮ ለታ የሚመሩት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር አመራር ተባባሪ ፕሮፌሰር ሃሰን ሁሴን ባደረጉት ንግግር “በኦሮሞ ዘንድ ጎሳ ማለት ከቤተሰብ ቀጥሎ ያለ ከጥቂት መንደርተኞች የማያልፍ የጠበቀ የስጋ ወይም የባህል ትስስር ያለዉ የኣናሳ ቡድን ስያሜ ነው። ኦሮሞን የሚያክልን ታላቅና ግዙፍ ቢሄር በጎሳ ፖለቲካ መፈረጅ ትልቅ ሃጥያት ተደርጎ የሚወሰደውም ከዚህ ኣንፃር እንደሆነ ማሰብ ይበጃል።” ብለዋል:: ሙሉ ንግግራቸውን ዘ-ሐበሻ በቭዲዮ ይዛዋለች – ያድምጡት::

ዲማ ነገዎ እና ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በወደፊቷ ኢትዮጵያ ዙሪያ ተናገሩ |ሊያዩት የሚገባ

ግልፅ ደብዳቤ ለአቶ ጀዋር መሐመድ |ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

$
0
0

jawar

በኢትዮሚዲያ ላይ በለንደን ላይ ያደረጉትን ንግግር ከዚህ በታች የተቀነጨበውን አየውና ይህንን ልፅፍ ተነሳሳሁ።

“የኦሮሞ ወጣቶችን ወክዬ ለውጭው ማህረሰብ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ። ካሁን በዋላ በኢትዮጵያ ቢሆን ቢሆን ታግለን መብታችንን አስመልሰን ከሌሎች ጋር አብረን እንኖራለን። ካልሆነ ግን ያችን ሀገር በታትነን ጥለናት እንሄዳለን እንጂ እንደ ትላንቱ የማይረቡት እላያችን ላይ ተጭነው እንዲያስተዳድሩን አንፈቅድም።”
– ጀዋር መሐመድ፥ ከለንደን ንግግር ከኢትዮሚዲያ የተወሰደ።

በመጀመሪያ አሳቤን ይረዱልኝ። በክርክር ለማሸነፍ አሳቡም ምኞቱም የለኝም። እርስዎንም እንደ ጠላት ለመቁጠርና ለመፈረጅ በልቤ ውስጥ ያለው ፍቅር አይፈቅድልኝም። ነገሬ ከአስተሳሰብዎ ጋር ነው። ለማሳመን ብዙ ትንታኔ አልገባም። ቃሌን አጭር በማድረግ ከቃሌ ጀርባ ያለውን ቅን መንፈስ እንዲረዱ ተስፋ ማድረግን እመርጣለሁ። እርስዎ እስላም እኔ ክርስቲያን፥ እርስዎ ኦሮሞ እኔ አማራ መሆናችን ለመግባባት እንቅፋት ይሆናል ብዬ አላስብም። ለእኔ እርስዎ የሀገር ልጅ ነዎት። ሃይማኖት የግል ሀገር የጋራ ነው የሚለውን አባባል ልቀያይረውና፥ በጥንድ እውነት መግለፅ ይፈቀድልኝ፤ ሃይማኖት የግል ፈጣሪ የጋራ ነው። ዘራችን የግል ኢትዮጵያ የጋራ ናት። ስለዚህም የጋራ በሆነ ነገር ላይ ሁለታችንም አንድ ነን። በዚህ መንፈስ እንዲያደምጡኝ አደራ እላለው።

በመጀመሪያ ራሴን ላስተዋውቅና፥ እኔ ያለፈውን የታሪክ ቁርሾ በይቅርታ ዘግተን፥ የወደፊቱን ታሪካችንን በፍትህ መስርተን፥ ነፃ የሚያወጣንን እውነት ተነጋግረን፥ አዲሲቷን ኢትዮጵያ እንገንባ ብዬ የምሞግት ነኝ። ይህንን ካልኩ አሁን ወደ ዝርዝር ሀሳቤ ልግባ።

የጎንደር ሕዝብ ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ወንድምነት በአደባባይ አጋርነቱንና ፍቅሩን ሲያስተጋባ፥ የፍቅር ቋንቋ መናገሩን ያሳይ ነበር። ያንንም የፍቅር ጥሪ ወንድሙ የኦሮሞ ሕዝብ ተረድቶ፥ ምላሹን ፍቅሩንና አጋርነቱን በአደባባይ ሲያሳይ ፍቅርን መናገሩ እንደሆነ ይገልጥ ነበር። ይህንን የሕዝብ ፍቅር ቋንቋ ለምድራችን ፈውስ ተስፋ ጭላንጭል ያመጣል ተብሎ ሲጠበቅ፥ በዚህ ወሳኝ ወቅት በለንደን ያቀረቡት ንግግርዎ ተስፋውን በዜሮ እንዳባዙት ይቆጠራል። ይህንን ግልፅ ደብዳቤ ለመፃፍ የፈለኩት እንኪያ ሰላምታ ከእርስዎ ጋር ለመግጠም ሳይሆን፥ ለሚያየንና ለሚሰማን ሁሉ መግባባትን ፍንጥቅ ማድረግ ይቻል ይሆናል የሚል ተስፋ ፍቅር በልቤ ውስጥ ስለጫረብኝ ነው። ለዚህም የምተማመነው በሀገር ልጅነታችን ላይ ያለኝ አመኔታ ነው።

ኢትዮጵያ የአንድነቷ መሰረት የሕዝቧ ማንነት ነው። የኢትዮጵያ አንድነት በመንግስት ስራ ወይንም መንግስት በሚያወጣው አዋጅ ቁጥጥር ስርም አይደለም። ነገሩን ካስተዋልነው በሊሂቃን አስተሳሰብና ፍልስፍና ስርም አይደለም። በእኔና በእርስዎ እጅም አይደለም። የታሪክ ጉዳይ ሆኖ የኢትዮጵያ አንድነት ጅማሬው ላይ የመንግስታት እጅ ቢኖርበትም፥ ሕዝቡን የሚያስተሳስረው ፍቅር ግን ሰው ሰራሽ አርተፊሻል ሳይሆን “ተፈጥሯዊነት”(organic) ነው። ይህን ሕዝቡ በታሪክ አጋጣሚና በፈጣሪ አሳብ አብሮ ለዘመናት በመኖር ያመጣው እውነታ ነው።

ኦሮሞ ፍታዊ ሆኖ የሚኖርበት ለመድረስ በመንገዱ ላይ የቆመው ኢትዮጵያ ሳትሆን እንደ እርስዎ ያለው አስተሳሰብ ነው ብዬ እገምታለሁ። ለኔ ኢትዮጵያ ከኦሮሞ ተነጥሎ በኦሮሞ የድል መንገድ ላይ የቆመ ደንቃራ አድርጌ አልወስድም። ለምን ቢባል መላውን ኢትዮጵያ በጂኦግራፊ፥ በቤተሰብነት፥ በአብሮ ነዋሪነት፥ በደግነቱ አያይዞ፥ ተጋብቶ ተደባልቆና ተዋልዶ እዚህ ያደረሰው በተቀዳሚነት የኦሮሞ ሕዝብ ነው። ፍትህና ዲሞክራሲ ያለባት መድረሻ እንድትሆን የሚፈልጉት ኢትዮጵያ ከሆነ መነሻዎን ኢትዮጵያ ማድረግ ያለብዎት ይመስለኛል። ያልተነሱበትን ነገር መድረሻ ላይ አገኘዋለው ማለት ዘበት ነው።

ለእኔ ኦሮሞ የኢትዮጵያን የወደፊት ብሩሕ ተስፋ ለመቅረፅ የመሪነቱን ሚና ይጫወታል። ለዚያም በሀገር ቤት ያለው የኦሮሞ ሕዝብ የመሪነቱን ሃላፊነት በብቃት እየተወጣው ነው። እርስዎስ አጥር ሆኖ ከሌላው ሕዝብ የሚከልልዎትን የውልጃ ማንነት ሳይለቁ(ወደው አይደለም ኦሮሞ ሆነው የተወለዱት)፥ በምርጫዎ ከሁሉ ሕዝብ ጋር በእኩልነት የሚያያይዝዎትን ኢትዮጵያዊነትን መርጠው በጋርዮሽ ቢሞግቱ ምን ይመስልዎታል? አንደኛ ኦሮሞ መሆንዎን መምረጥዎ ባልከፋ፥ መልካም ነውና። ለነገሩ ሁሉም በግሉ በመጀመሪያ የተለያየ ዘር ግኝት ነው። ታዲያ የሚያስተሳስረን ጉራጌው ጉራጌ ኢትዮጵያዊትን አንግቦ፥ ጋምቤላው ጋምቤላ ኢትዮጵያዊነትን ወዶ፥ ትግሬው ትግሬ ኢትዮጵያዊነትን መርጦ፥ አማራው አማራ ኢትዮጵያዊነትን ተቀብሎ ወዘተረፈ በጋሪዮሽ መያያዛችን ነው። ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ መሆንና ለኦሮሞ እኩልነት ማቀንቀን የሚቃረኑ አይደሉም፥ እንደውም የሚደጋገፉ እንጂ። ዋነኛው ጉዳይ ከኖርንም አብረን፥ ተበታትነን ከጠፋንም አብረን እንደሆነ በማወቅ የመቆራኘታችንን ሚስጢር ጥልቀቱን ማስተዋሉ ላይ ነው።

ኢትዮጵያን በታትኖ ኦሮሞን መገንባት የሚለው አሳብ የማይሆን ነገር ነው። በኢትዮጵያ መቃብር ላይ የሚገነባ የኦሮሞ በረከት በዚያች ምድር ይኖራል ብሎ ማሰብ ከንቱ አስተሳሰብ ነው ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም የኢትዮጵያ መቃብር ካለ፥ ከኢትዮጵያ መቃብር ስር የኦሮሞ መቃብር አለ። ለምን ቢባል ከማንም ይልቅ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ የሚያሰኛትና እንደ ደም ስር ሁሉንም የሚያያይዘው ኦሮሞ ከሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመዋለድና በመደባለቅ ስርና መሰረት ስለሆነ ነው።

ነገር በምሳሌ እንዲሉ ሁላችንም ያለነው ውቂያኖስ ላይ የሚንሳፈፍ ኢትዮጵያ በሚባል ትልቅ መርከብ ላይ ነው። እርስዎ የሚሉት ቢሆን ቢሆን ተባብረን መርከቡን በእኩልነት እየኖርንበት እንሂድ፥ ካልሆነ መርከቡን በታትነን በኦሮሞ ጀልባ እንኖራለን ነው። ያስተውሉ፥ 1ኛ/ ሌላው ይበታተን የሚሉት ትልቁን 80 በላይ ብሔረሰብ የሚይዘውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ነው። 2ኛ/ ኦሮሞ እንደ ጀልባ በኢትዮጵያ መርከብ ላይ የተቀመጠ ማንነት ያለው አይደለም። ኦሮሞ የመርከቡ አካልና መካከለኛ ክፍል ነው። ይህ መሬት ላይ ያለ በሕዝቡ አብሮነት ለዘመናት የተገለጠ ሐቅ ነው። 3ኛ/ መርከቡ ከተበታተነ፥ የመርከቡ መካከለኛም አብሮ ሰምጦ ይቀራል። ከዚህ ውጭ ያለ አስተሳሰብ ሕልውና በሕልም ደረጃ ያለ ነው። 4ኛ/ የመርከቡን መሪ ማን ይያዝ የሚለው ጉዳይ የእኛ ምርጫ አይደለም። የእኛ ትግል መሪዉን ለመያዝ ሳይሆን፥ መሪዉን የሚይዘውን አካል ሕዝብ እንዲመርጥ እውነተኛ ዲሞክራሲ እንዲኖር ነው። እውነተኛ ዲሞክራሲ ባለበት ብዙ የሕዝብ ቁጥር ያለው ኦሮሞ ከሁሉ ይበልጥ ይመቸዋል። ታዲያ የነገሬ ፍፃሜ ይህ ነው፥ ከ 50 ዓመታት በላይ ከቆየው የኦሮሞ ትግል ልምድ ከቀሰሙ በዋላ የደረሱበት ይህ አስተሳሰብዎ፥ ሁሉም የሚፈልገውን ይህንን ዲሞክራሲ እውን ለማድረግ የሚያስችል መላ በውኑ ነውን?

ለማንኛውም ለሁላችንም ልቦና ይስጠን።
አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ!

ሌንጮ ለታ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳና በቀለ ዋዩ በዋሽንግተን ዲሲ የፊታችን እሁድ ንቅናቄውን የሚያበስሩበት አዳራሽ ታወቀ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሌንጮ ለታ እና ምክትላቸው ዲማ ነገዎ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳና አቶ በቀለ ዋዩ የሚመሯቸው ድርጅቶች በጋራ የመሰረቱትን ንቅናቄ ነገ እሁድ ይፋ የሚያደርጉ ሲሆን ይህን ይፋ የሚያደርጉበት ሕዝባዊ ስብሰባ የሚደረግበት ቦታ ታወቀ:: ሁሉም ሕዝብ እንዲገኝ ተጋብዟል:: አድራሻውን ከሚከተለው በራሪ ወረቀት (ፍላየር) ያገኛሉ::
poster-1-1

የለውጥ ሃይሎች ግልጽና……. ክፍል ሁለት –ኤርሚያስ ለገሰ

$
0
0

ጆቤ እንኳን ደህና አልመጣችሁ!!

ለህዝብ ውይይት መድረክ የተዘጋጀ (ሂውስተን/ቴክሳስ)

                                       

   ኤርሚያስ ለገሰ

       የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ራዲዮ(ኢሳት)

    ጥቅምት/2016

                                

                  ማስታወሻ        

ይህ ጽሁፍ ከራሴ ውጭ የምሰራበትን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬዲዮ (ኢሳት)ን ጨምሮ የማንንም አቋም አያንፀባርቅም::

 

 

መግቢያ

ermias copy“የለውጥ ሃይሎች ግልፅና ደፋር ውይይት ለመፍትሔና የጋራ ድል” በሚል አቢይ ርዕስ ተከታታይ መጣጥፍ እየቀረበ ነው። ከዚህ ቀደም “በክፍል አንድ” በተሰራጨው ጽሁፍ ሁለት ቁምነገሮችን ለመዳሰስ ተሞክሯል። የመጀመሪያው፦ ግልጽና ደፋር ውይይት የምናደርግባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ለመዘርዘር ተሞክሯል። ዛሬ አገራችን ያለችበት ሁኔታ የሚያሳስበው ዜጋ ባለመኖሩና አገር አደጋ ላይ በወደቀችበት ሁኔታ በመተማመን ላይ የተመሰረተና የጋራ ድል (win- win) በሚያረጋግጥ መልኩ ምክክር መካሄድ እንዳለበት የተገለጠበት ነው። መጣጥፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የስርአት ለውጥ መምጣት አለበት በማለት የሚንቀሳቀሱት ሁሉም የለውጥ ሃይሎች የዛሬና የነገን ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ በሚወስኑ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ምን እንደሚያስቡ ለህዝቡ ማቅረብ እንዳለባቸው የሚጠይቅ ነው።

ሁለተኛው፦ በተከታታይ ለሚቀርቡት ጽሁፎች መነሻ ከተደረጉ አምስት ታሳቢዎች ውስጥ ሦስተኛው ታሳቢ (“የአዲስ አበባ ነዋሪ የስርአት ለውጥ ይፈልጋል። ህዝባዊ ማዕበሉን ለማቀጣጠል ዝግጁነቱ ከፍተኛ ነው”) የሚለው ሃሳብ የተስተናገደበት ነው። ለማስታወስ ያህል “በክፍል አንድ” በቀረበው ጽሁፍ የቀረቡት አምስት ታሳቢዎች የሚከተለውን ይላሉ

 

ታሳቢ አንድ፦ የህዉሃት አገዛዝ ይወድቃል። የሚወድቀው ግን በከባድ መስዋዕትነት ነው። ከተከፈለው ያልተከፈለው መስዋዕትነት ይበልጣል።

ታሳቢ ሁለት፦ የኢትዮጵያ አንድነት እንደተጠበቀ ይቆያል። የለውጥ ሃይሉ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ አይደራደርም።

ታሳቢ ሦስት፦ የአዲስ አበባ ነዋሪ የስርአት ለውጥ ይፈልጋል። ህዝባዊ ማዕበሉን ለማቀጣጠል ዝግጅነቱ ከፍተኛ ነው።

ታሳቢ አራት፦የለውጥ ሃይሉ ከህወሃት የቀድሞ የጦር ጄነራሎችም ሆነ አመራሮች ብዙ መጠበቅ የለበትም።

ታሳቢ አምስት፦ ከአጭር ጊዜ አኳያ የተገኘው ድል በብስለትና በፅናት ካልተያዘ ሊዳፈን ይችላል።

 

 

በመሆኑም በዚህ ጽሁፍ ላይ ለዋናው ሰነድ መነሻ ከሆኑት ውስጥ በ”ታሳቢ አራትነት” የለውጥ ሃይሉ ከህወሃት የቀድሞ የጦር ጄነራሎችም ሆነ አመራሮች ብዙ መጠበቅ የለበትም”) የሚለው ይቀርባል። በመጣጥፍ ሆድ እቃ ውስጥ የትግራይ ኤሊቶች በተለይም የቀድሞ የህዉሃት የጦር መኮንኖች መደ መድረኩ አሁን ለምን እንደመጡ፤ ይዘው የመጡት እጀንዳ ምን እንደሆነ፤ ወደፊት መምጣታቸው የሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት ለውይይት መነሻ በሚሆን መልኩ የቀረበበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ህሃትን ከመገርሰስ አኳያ ዋነኛ የትግል ማዕከሎችና ፓሎች (ምሰሶዎች) የትኛዎቹ እንደሆነ ለማሳየት ይሞክራል።

(“ክፍል አንድ” አግኝታችሁ ማንበብ ያልቻላችሁ ሰዎች በሳተናው፣ ኢትዮ-ሚዲያ ፎረም፣ ዘሃበሻ፣ ህብር-ሬዲዮ ድረ-ገጾች ላይ ማግኘት ይቻላል።)

 

 

(ታሳቢ አራት)

 የለውጥ ሃይሉ ከህወሃት የቀድሞ የጦር ጄነራሎችም ሆነ አመራሮች ብዙ መጠበቅ የለበትም።

 

 

ላለፉት ሩብ ክፍለ ዘመናት ህዉሃት በብሔር ብሔረሰቦች ዲሞክራሲያዊ መብቶች እየማለና እየተገዘተ ህዝቡን ለማታለል ብሎም ለመለያየት ቢሞክርም ያሰበውን አላማ ሊያሳካ አልቻለም። ለሁሉም ግልጽ እንደሆነው በአገራችን የሰላም እጦት ከጫፍ እስከ ጫፍ እየታየ ነው። የስርአት ለውጥና የነፃነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ የትግል ስልቶች ተቀርፀው ወደ ትግባር ተቀይረዋል። እየተደረጉ ያሉት ትግሎች አስተሳስረን ስንመረምር አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ወደ መቃብር የወረደበት ሆኖ እናገኘዋለን። ከዚህ በኋላ ህዉሃት መንግስታዊ የበላይነትን ባገኘበት ሁኔታ የምርጫ ፖለቲካ አጀንዳው ተዘግቷል። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እንዳሉት በምርጫ ፖለቲካ መቃብር ላይ ጥቁር አበባ ተቀምጦበታል። መቃብር ፈንቅሎ ትንሳኤ ይፈፀም ይሆን ለወደፊት የምናየው ይሆናል። ተስፋ አለኝ።

 

ከዚህ ጋ ተያይዞ ህዉሃት መራሹ ድርጅት በየጊዜው የሚሰጠው ድርጅታዊ መግለጫና እሱን ተከትሎ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተስፋ የሚያስቆርጠው የአገሬው ህዝብና የአለም መንግስታትን ብቻ አይደለም። የስርአቱ መስራችና ባለቤት የነበሩ እንዲሁም በተለያየ ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ ስልጣን ላይ የነበሩትን ጭምር ነው። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሚዲያዎችን ያጨናነቁት ጄኔራል አበበ እና ጄኔራል ፃድቃን በስርአቱ ምላሽ ላይ ምን ያህል ተስፋ እንደ ቆረጡ መገመት ይቻላል። “የስርአት ችግር ስላለ፣ ኢህአዴግ የተቀባይነት ችግር ስላጋጠመው የስርአት ለውጥ መምጣት አለብት!” ብሎ የተናገረው አንደበታቸውና የከተበው ብዕራቸው ዞር ብለው ሲመለከቱ ማፈራቸው የሚቀር አይደለም። እነ ፃድቃን “ሀገሪቷ የመበታተን አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል” ቢሉም የቀድሞ የትግል ጓዶቻቸውና የስልጣኑ ባለቤቶች “ህገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርአት በጽኑ መሰረት ላይ ተገንብቷል” የሚል ዲስኩር ያሰማሉ።

 

እነ ጆቤ “ህዝቡ በተስፋ እጦት ውስጥ ገብቷል” ብለው ሲፅፉ በተቃራኒው እነ አባይ ፀሀዬ “የአገራችን ህዝቦች በኢትዮጵያ የፈነጠቀውን የልማትና የዲሞክራሲ ጮራ ተማምነው በለመለመ ተስፋ ወደፊት ይመለከታሉ” የሚል ዘመን ተሻጋሪ ማብራሪያ ይሰጣሉ።  እነ ፃድቃን በቀኝ ሆነው የመቶ ፐርሰንት ምርጫ በህዝብ ማላገጥ ነው” በማለት ብዕራቸውን ሲያነሱ በግራ የተሰለፉት እነ በረከት “ኢህአዴግ ስራ በምርጫ ካርድ የተሰጠውን ሃላፊነት አደራ ለመወጣት ቆርጦ ተነስቷል” ይሉናሉ። አራንባና ቆቦ!!

 

እዚህ ላይ በሁለቱ የቀድሞ የጦር አዛዦችና የህዉሃት መራሹ መንግስት ሃይሎች መካከል በሁሉም ጉዳይ ተቃርኖ ውስጥ እንደገቡ የሚያስብ ካለ በደንብ ተሸውዷል። ሁለቱም ሃይሎች የህዉሃትን ብሎም የትግራይ ህዝብ ጥቅም ይነካል ብለው በገመቱት ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው። ከዚህ አንፃር በቅድሚያ ሊነሳ የሚችለው በቀድሞ በትግራይ አስተዳደር ስር ያልነበሩና ዛሬ የተካለሉት ወልቃይትን የመሳሰሉ ቦታዎች ናቸው። የጦር አዛዦቹም ሆነ የህዉሃት ታጋይ ባለስልጣናት መጀመሪያ ሰሞን የወልቃይትና ተመሳሳይ ቦታዎች ፈጽሞ አንዳይነሱ፤ የሚዲያ ትኩረት እንዳያገኙ አድርገው ነበር። በጽሑፎቻቸውም ሆነ በመግለጫዎቻቸው በየትኛውም ቦታ ከመግለጥ ተቆጥበው ነበር። የቅማንትን ጉዳይ አጉልቶ የገለጠው “ጆቤ” ወልቃይት ላይ ሲደርስ የብዕሩ ቀለም በሚያስፎግር ሁኔታ አልቆበት ነበር። በኦሮሚያ ጥያቄዎች ላይ በምናቡ ከፈጠራቸው የኦሮሞ ልጆች ጋር ማውራቱን ሊነግረን የፈለገው ጄነራል አበበ ጠገዴና ጠለምት ፀለምት(ጨለማ) ሆነውበት ግድግዳ ተስታኮና ተንፏቆ ሲያልፋቸው ተመልክተናል።

 

ሁኔታዎች እየገፋ ሲመጡና የትግሉ ማዕከሉ “ወልቃይት” መሆኑ ሲረጋገጥ እየተንፏቀቁም ቢሆን የወልቃይትን አጀንዳ ማንሳት ጀመሩ። ለምን ከዚህ በፊት ልታነሡት አልሞከራችሁም ሲባሉ “ይሔ ትልቅ ጉዳይ አይደለም። መደረግም አልነበረበትም” የሚል ምላሽ ሰጡ። ቁምነገሩ እዚህ ጋር ነው። ለእነ ጄነራል ፃድቃን የቅማንት ጉዳይ ትልቅ እንደሆነ አድርገው ሊያገኑት ሲሞክሩ የማያቋርጥ የህዝብ ደም እየፈሰሰበት ያለውን ወልቃይት ንቀው እንደተውት ሊያሳዩ ሞከሩ። እነዚህ ሰዎች ይህን ምላሽ ሲሠጡ ወልቃይት “የትግል ማዕከል” እና “የኢፍትሃዊነት ማሳያ” መሆኑን ጠፍቷቸው አይደለም። ልክ አቶ መለስ በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት ካድሬዎች “ለምን ባድመን ለመሰለ ቁራሽ መሬት የ10ሺዎች ደም ይፈሳል?” ብለን ሥንጠይቀው እጁን እየጠበጠበ “ባድመ የትግላችን ማዕከል የሆነችው የኢፍትሐዊነት ማሳያ ስለሆነች ነው” በማለት የንዴት ምላሽ ሰጥቷል። በመሆኑም ባድመ የኤርትራ መንግስት በሃይል ስለወሰዳት መጀመሪያ ወደቀድሞው ቦታዋ ትመለስና ህጋዊ ውሳኔ ይሰጥባት እንደተባለ ሁሉ የወልቃይትም ተመሳሳይ ነው። ወልቃይት “ኢፍትሃዊነት ማሳያ” ስለሆነች መጀመሪያ ወደቀድሞው ታሪካዊ ባለቤቷ ትመለስና ሌሎች የህዝብ ጥያቄዎች ቂም በቀል በማይፈጥሩና የጋራ ድል (Win_Win) በሚያረጋግጡ መልኩ ይፈቱ ማለት የአባት ነው። ይገባልም። ይህ ካልሆነ ግን ምንአልባት ከባድመው ባልተናነሰ በ100ሺዎች የሚጠጋ ህይወት የሚወድቅበትና ደም መቃባቱ የሚያባራ ሊሆን ይችላል።

 

በመቶ ሺዎች ሊገደሉ ይችላሉ የሚለውም ተራ ማስፈራራት አይደለም። ህዉሃት በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ የቋጠረው የቂም ቋጠሮ ከዚህ በላይ ሊገድል እንደሚችል ፍንጭ የሚሰጥ ነው። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር አሰፋ አቢዩ ከሳምንታት በፊት በሰጠው መግለጫ “99 ፐርሰንት ንፁህ ናቸው። እርምጃ የምንወስደው በተቀሩት ላይ ነው” በማለት ይፋ አድርጓል። አሁን ባለው የአማራ ክልል ንቅናቄ ከ5 ሚሊዮን የአማራ ተወላጆች በቀጥተኛ እየተሳተፉ እንደሆነ ዝቅተኛ ግምት ቢወሰድ እንኳን በኮሚሽነር አሰፋ ስሌት መሠረት ከ50 ሺህ በላይ ሠዎች እርምጃ ይወሰድባቸዋል። ህዝባዊ ማዕበሉ እየሰፋ ሲሄድ በአስቸኳይ የስርአት ለውጥ ካልመጣ እርምጃ የሚወሰድበት የአማራ ተወላጅ ሁለትና ሶስት እጥፍ ይሆናል። ስለዚህም፣ ለህዉሃት “የትግል ማዕከል” (centrifugal force) የሆኑትን ቦታዎች አሳልፎ መስጠት መቃብሩን በጥልቀት የመቆፈር ያህል ስለሚመለከተው በጅምላ ከመግደል የሚመለስ አይሆንም።

 

በእኔ እምነት ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ማዕበል ከህዉሃት ህልውና አንጻር በርካታ ዋልታዎች (Multi- Polar) ያሉት ቢሆንም፣ የዋልታዎቹ ምሰሶ ወልቃይት (Wolqayit Factor) ተደርጎ የሚወሰድ ነው። የኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ኮንሶ የተነሱት እምቢተኝነቶች ትላልቅ ዋልታዎች ቢሆኑም ህዉሃት ልቦና ገዝቶ በህይወት መቆየት ከፈለገ ወደ ምሶሶነት ሳያድጉ በተራዘመ ሂደት ሊያዳፍናቸው ይችላል። ለምሳሌ ህዉሃት ኤርትራ ላይ የሚያስበው (Eritrian-Factor፡ ኤርትራ በጦርነት ማሸነፍና አስመራ ላይ አሻንጉሊት መንግስት መመስረት) ከተሳካና ህዉሃት ኢትዮጵያን መምራት ከተነሳው የኦሮሚያን ጥያቄ እስከ ጫፍ በመውሰድ ምላሽ ሊሰጥበት ይችላል። ይህም በኦሮሞ ጉዳይ የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና አክቲቪስቶችን የመከፋፈል እድሉ ሰፊ መሆኑ አይቀርም። ህዉሃት እስከ ጫፍ የሚወስደውን ፍላጎት ለመቀበል አዳዲስ ሃይሎች (Emerging Powers) የሚፈልቁበት ሁኔታ ይፈጠራል። በመሆኑም ህዉሃት በሚቀደው ሀገር የማፍረስ ቦይ የሚፈሱ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሰዎች ይኖራሉ። ከሰሞኑ የድል አጥቢያ አርበኛ ሆነው ብቅ ብቅ ማለታቸው አይቀርም። በጅምር ላይ ያለውን የትብብር መንፈስም ውሃ ሊቸልሱበት ይሞክራሉ።

 

ወደተነሳንበት ስንመለስ ሁለቱ የህዉሃት የቀድሞ ጦር አዛዦች በተለይም ሌ/ጄነራል ፃድቃን ወልቃይትና ሌሎች “የኢፍትሐዊነት ማሳያ” ቦታዎችና “የትግል ማዕከሎች” በተመለከተ ያስቀመጡት ምላሽ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን የበለጠ ነዳጅ የሚጨምር ነው። ጄነራል ፃድቃን መጀመሪያ አካባቢ ባቀረባቸው ጽሁፎች በብልጣብልጥነት ሊያልፈው ቢፈልግም ቦታዎች ይበልጥ “የትግሉ ማዕከሎች” መሆናቸውን በህዝባዊ ማዕበሉ ሲመለከት ከድርቅና በተሻገረ አይን አውጣነት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ እርስ በራስ የተምታታ ምላሽ ሰጠ። ይህ የጦር መኮንኑ ምላሽ የአማራ ህዝብ ትግልና መነቃቃት ከደረሰበት ደረጃ ጋር ፍፁም የማይመጥን ነው። የአሁኑ የአማራ ትግል የደረሰበት ደረጃ ፍልሚያው ተጧጡፎ አድማሱን በመስፋት ቅኝቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሯል። ከአስር አመት በፊት ሃሰን ዑመር አብደላ በመጣጥፋቸው እንደገለጡት ቅኝትና ምቱ ከተቀየረ እስክታውም መቀየር አለበት። በመሃመድ አህመድ የትዝታ ቅኝትና ምት ጥላሁን ገሠሠን “አንቺን ነው! ሰማሽ ወይ” የሚለው አይደነስም። በ “እምበር ተጋዳላይ” አጨፋፈር ስልት የይሁኔ “ሰከን በል” አይጨፈርም። እንደዚህ ከሆነ በአራዳ ቋንቋ ሽወዳ ይሆናል። አሁን ትግሉ በደረሰበት ደረጃ ደግሞ ውሽልሽል ምክንያት ሸውዶ ማለፍ የሚችልበት ወቅት ላይ አይደለንም። አለበለዚያም እውነት መድፈር ካልተቻለና የሚያስፈራ ከሆነ (ኮንስቲትወንሲያቸውን እንደሚያጡ ይገባኛል) ምላሽ አለመስጠት ይቻል ነበር። ፃድቃን ሊጠቀምበት የፈለገው “የሽወዳ ፖለቲካ” ህዝባዊ እምቢተኝነቱን አቀጣጥሎ መስዋዕትነቱን ከመጨመሩ ባሻገር በሌሎች ያቀረባቸው የመፍትሄ ሃሳቦችም ላይ በጥርጣሬ እንዲታይ ያደረገ ነው።

 

ለማንኛውም ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳይ “የትግሉ ማዕከል” በሆነው ወልቃይት ዙሪያ ለአዲስ አድማሱ ጋዜጣ የሰጠውን መግለጫ በመመልከት ፍርዱን እንስጥ። አዲስ አድማስ ጋዜጣ “በሰሜን ጎንደር አካባቢ ያለው ተቃውሞ በተለይ ከ “ወልቃይት አማራነት” ጋር የተያያዘ ነው። የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጉዳይ በምን አግባብ ነው መፈታት ያለበት?” ለሚለው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል።

 

“እኔ የወልቃይት ጉዳይ ለአንዳንድ ፖለቲካዊ አላማዎች ሽፋን ነው ብዬ ነው የማምነው። እንዴት ነው የሚፈታው ላልከው እኔ የሚታየኝ ህገ- መንግስቱን መሠረት አድርጎ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ይሔ ትልቅ ጉዳይ መደረግ አልነበረበትም። ህዉሃትና ብአኤን ተመካክረው መፍታት የሚችሉበት ደረጃ ላይ መድረስ ነበረባቸው።…. በህጋዊ መንገድ ስንሄድም ህገ-መንግስቱን መሰረት አድርጎ መፍታት ያስፈልጋል ነገር ግን ክልሎች በሚወሰኑበት ወቅት ከፍተኛ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ ነበርኩ። በወቅቱ ቋንቋና የህዝብ አሰፋፈርን መሰረት አድርገን እንወሰን በሚል ነው የወሰነው። በዚህ መሰረት ደግሞ የተወሰነው ተወስኗል።”

 

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቀጥሎ የጠየቀው “በወቅቱ ወልቃይት እንዴት ነው ወደ ትግራይ የተላከው?” በማለት ነበር። ሌ/ጄነራሉ እንዲህ በማለት አስገራሚ፣ አሳዛኝና እርስ በራሱ የሚደባደብ ምላሽ ሰጠ።

 

“አሁን እየጠየከኝ ያለኸው መረጃ ነው። ይሄን መረጃ አሁን አላስታውሰውም። እንደዚህ  ሆኖ ነበር ብዬ ለማለት አልችልም። የተጠቀምንበት አቅጣጫ ግን የፌደራሊዝሙን መነሻ ነው። የህዝቦች ቋንቋና ባህልን መነሻ አድርገን ነው የከለከልነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ እዚያ አካባቢ ያለው አብዛኛው ህዝብ ትግርኛ ተናጋሪ ነው። ባህሉ የትግራይ ነው። በትግራይ ውስጥ ሊካተት የሚችል ህዝብ ነው። የሆነውም በዚህ አግባብ ነው።”

 

በመሆኑም እነዚህ የህዉሃት ጦር ጄነራሎች “ህዉሃት አደጋ ላይ መውደቁን ሲያዩ ሊታደጉት መጡ” የሚለውን አባባል ለጊዜው እንተወውና የጎደላቸውን ነገር በጨዋ ቋንቋ እንንገራቸው። በእኔ በኩል  የጦር ጀነራሎቹ ወደፊት መምጣት ቢያንስ በአራት መሰረታዊ ጉዳዮች እደግፈዋለው።

አንደኛው ያልተገለጠ ማንኛውም አስተሳሰብ ስለማይታወቅ መገለጥ አለበት የሚል የፀና እምነት አለኝ። የሉቃስ ወንጌል (መዕራፍ 6 ቁጥር 45) በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራል።….. ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝገብ ክፉ ውን ያወጣል። መልካም ሰውም ከመልካም መዝገብ መልካም ያወጣል” አንዲል አንደበታቸውና ብዕራቸው የተፋው ቁምነገር ከየትኛው ልብ እንደመነጨ ማወቅ የሚጠቅም እንጂ ጉዳት የሚያደርስ አይደለም።

 

ሁለተኛው ምክንያት እነዚህ የህዉሃት የጦር ጄኔራሎች የቀድሞ ድርጅታቸው ምን ያህል ኋላቀር፣ ለለውጥ ዝግጁ ያልሆነ ግትረኛ፣ ፈሪ ድንጉጥ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ። እንደጠበኩት በጥቂት ቀናት ውስጥ በህዉሃት ስፖንሰርነት የሚንቀሳቀሱት የውጭ ድረ-ገጾቻቸው ዘመቻቸውን በተጠናከረ መንገድ ከፈቱ። የአየር ሃይል አዛዥ የነበረውን አበበ ተ/ሃይማኖት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የአውሮፕላን ግዥ ላይ ፈፀመ ያሉትን ሌብነት እየጠቀሱ  ወረዱበት። “የፈፀምከውን ሌብነት ዝም ስንልህ የረሳነው መሰለህ እንዴ?” በሚል ማስፈራራቱን ቀጠሉ። ጄኔራል ፃድቃንን ደግሞ “የስልጣን ፍላጎት የቀፈቀፈው ሃሳብ” በማለት አብጠለጠሉት። ይባስ ብለው በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስም ባወጡት ድርጅታዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም የህይወት መለኩ (መንፈሳዊንንም ይጨምራል) ከፍተኛ ለውጥ እንዳመጣ፣ ህገ-መንግስታዊ ስርአቱ ጠንካራ መሠረት ላይ እንደተጣለ፣ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ (100%) አሽንፈው የመንግስት ስልጣን እንደተቆጣጠሩ፣ ባለሁለት አሀዝ ተከታታይ እድገት አምጥተናል….ወዘተ የሚሉ አስደንጋጭ ቃላትን በመጠቀም የጦር መኮንኖችን ቆሌ ገፈፋ።

ሦስተኛው ምክንያት የህዉሃት የጦር ጄነራሎች የሚያቀነቅኑት ሃሳብ ምን ያህል የአገራችንን ችግሮች በጥልቀት ይዳሳሳል፤ ምን ያህል ተቀባይነት ይኖረዋል፤ ከመንግስትና የለውጥ ሃይሎች ፍላጎት አንፃር የተቃኘ ነወይ፤ የደበቋቸውና ለህዝብ ይፋ ቢደረግ ራሳቸውንም ሆነ የቀድሞ ድርጅታቸውን ተጠያቂ የሚያደርግ ነገር ይገልጡ ይሆን ወይ?….. ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ በሚል ነው። በግሌ የጠበኳትን አግኝቻለሁ። መኮንኖች የስርአቱ ችግር አለ መፍትሄው ስርአታዊ (systemic) መሆን አለበት ብለዋል። እርግጥ መፍትሄው አሁን ባለው የህዉሃት/ኢህአዴግ ህገ-መንግስት ማዕቀፍ ስር መሆን እንዳለበት ያስገነዝባሉ። አሁን ባለው ህገ- መንግስት እንዴት አድርጎ ስርአታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚቻል እንቆቅልሽ ቢሆንም  እንደ ሃሳብ መነሳቱ የሚያበረታታ ነው። በተለይ ህዉሃት አሁን ከዚያው አቋም ሲነፃፀር ምን ያህል የሰማይና ምድር ልዩነት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ሰሞኑን አቶ በረከት የኤፈርት ኩባንያ ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና በጠራው ኮንፈረንስ ላይ አይኑን በጨው አጥቦ “18 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መክረው የተጻፈ ህገ-መንግስት፣ በአለም ላይ ካሉ ጥቂት ምርጥ ህገ- መንግስቶች አንዱ የሆነ” በማለት ዲስኩር ሲያሰማ እንደነበር ለሁሉም ግልጽ ነው። ህገ-መንግስታዊ ፍርድቤት የሌለው፤ ፍርዱን የሚሰጡት እነ አባዱላ፣ ሙክታር አህመድ፣ አባይ ወልዱ፣ ገዱ አንዳርጋቸው…… ወዘተ የሆኑበት ህገ-መንግስት ምርጥነትን ለመናገር በበረከት የአስተሳሰብ ደረጃ ዝቅ ማለት ይጠይቃል።

አራተኛው ምክንያት፡ የህዉሃት የጦር መኮንኖች በአንዳንድ የለውጥ ሃይሎችና በአለም አቀፍ ተቋማትና ሀገሮች ያለው ግንዛቤ በጣም አደገኛ መሆኑ ላይ ነው፡፤ እነዚህ ግለሰቦችና ተቋማት የጦር መኮንኖች የውስጥ አዋቂ አድርገው ስለሚቆጥሩ እንደ ዋነኛ የመፍትሄ አካል አድርገው የሚወስዱበት ሁኔታ በተደጋጋሚ ይታያል። ይህ አረዳድ በጣም አደገኛ ከመሆኑም ባሻገር የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ወደኋላ የሚመልስበት እድል ሰፊ ነው። የም ዕራብ ሐገሮች በተለይም ሰሜን አሜሪካ (ለምሳሌ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት) በተለያዩ ጊዜያቶች ህዉሃት አደጋ ውስጥ ሲወድቅ እነዚህን የጦር መኮንኖች እንደ አማራጭ የሚያማትሩበት ሁኔታ መኖሩ የሚታወቅ ነው። በምርጫ 97 ማግስት (አቶ በረከት ስምኦን ያጫወተኝ ስለሆነ በከፊል እመኑኝ) የቅንጅት አመራሮች ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ጋር በሚወያዩ ሰዓት ጄኔራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ እንዲያካትቱ ጠይቀዋቸው እንደነበረ በንዴት ውስጥ ሆኖ አውግቶኛል። ይሄ የበረከት አገላለጥ እውነት ይሁን ውሸት ታሪክ የሚገልጠው ቢሆንም ዊክሊክስን ያገላበጠና የአሜሪካ ኤምባሲ ከቀድሞ የህዉሃት አመራሮች ጋር ያደረጉትን ሚስጥራዊ ውይይት ለተመለከተ አሜሪካኖቹ የሚይዙት የተሳሳተ አመለካከት እንደሚኖር መገመት ይቻላል።

 

አንዳንድ የለውጥ ሃይሎች ነን የሚሉና አለም አቀፍ ተቋማትና ሀገራት የጦር መኮንኖቹን እንደዋና መፍትሄ የሚወስዱ ከሆነ በጣም አደገኛ ሁኔታ የሚፈጥርበት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ የመጀመሪያው የህዉሃት የጦር መኮንኖች ህዉሃት የኢህአዴግ የፖለቲካ አስኳል መሆኑን ሌሎች የኢትዮጵያ ማህበረሰቦችና የውጭ ሃይሎች እንዲያውቁ አይፈልጉም። ጄኔራሎቹ በጠመንጃ፣ በደህንነት፣ በኢኮኖሚና ፖለቲካ የበላይነት የአገሩ ባለቤት የሆነውን የትግራይ ነፃ አውጪ (ህዉሃት) ወደ ጎን ትተው የህይወት እስትንፋስ የሌለውን ኢህአዴግ እንደ መፍትሄ አመንጪና ተጠያቂ አድርገው ያቀርባሉ። ለስሙ ቦታውን የያዙትንና አንዳችም ስልጣን የሌላቸውን ከህዉሃት ውጪ ያሉ ባለስልጣናትን ከፍ ከፍ በማድረግ የተለየ ምስል ለመፍጠር ጥረት ያደርጋሉ። በተለይም የአየር ሃይል አዛዥ የነበረው ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት በሙት መንፈስ የሚመራውን ሃይለማርያም ደሳለኝ ብዕሩን ባነሳ ቁጥር ሲያንቆለጳጵስና ሲያሞካሽ ማየት የተለመደ ሆኗል። “ይድረስ ለክቡር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝየጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ” የሚል ርዕስ በመጠቀም “ለሰራዊቱ ግንባታ የተዘጋጀው መጽሀፍ አግዱልኝ!” በማለት ተማፅኖ ሲያቀርብ ይስተዋላል። ጀቤ ይሄን የሚያደርገው የሃይለማሪያምን “የህዉሃት ትሮይ ፈረስነት” አጥቶት አይደለም። ኢህአዴግ የሚባለው አደረጃጀት ለህዉሃት ጭምብልነት የተፈጠረ መሆኑን ዛሬም የሚመራበት መርሆ በጫካ የተቀረፀና ከዘመኑ ጋር የማይሄድ፤ ሸረሪት የሚሯሯጥበትና ያደረበት መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉ።

 

ከጄኔራል ፃድቃን አስተያየት ሳልወጣ አድናቆቴን መግለጽ የምፈልግበት አንድ አረፍተ ነገር አለ። ጄኔራሉ በሌሎች የህዉሃት ታጋዮች ባልተለመደ መልኩ አሁን ያለውን ሁኔታ ሲገመግሙ “የትግራይ ህዝብ በተለይም በከተሞች አካባቢ በሌሎች ማህበረሰቦች የመገለል ሁኔታ አጋጥሞታል። መተማመኛውንም የስልጣን የበላይነት አስጠብቆ ማቆየትና በመከላከያና ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ተከልሎ መኖር” እንደሆነ ገልጧል። ይሄንን ግምገማ ሙሉ በሙሉ የምቀበለው ነው። ለረጅም ጊዜያቶች ይሄ ችግር እየመጣ እንደሆነ ደጋግመን ስንለፈልፍ በህዉሃት ጎራ ያሉ ሰዎች “ዘረኞች” የሚል ታፔላ ተለጥፎልን ነበር። ዛሬ የጦር መኮንኑ በግላጭ ሲያወጣው በህዉሃት መንደር የተፈጠረ ብዙም መንጫጫት አይታይም። ታዲያ! ጄኔራል ፃድቃን በዚህ ጉዳይ ላይ ይሄን ያህል ርቀት መጓዝ ከቻለ ከጥያቄው ጋር አብረው ለሚነሱት ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ ቢሰጥበት እኛንም ከስድብና ውርጅብኝ ያድነናል። ጥያቄው የትግራይ ህዝብ በተለይ በከተሞች ውስጥ በሌላው ማህበረሰብ እየተገለለ መሄዱ እውነት ሆኖ ሲያበቃ፤ የመገለሉ መንስ ኤና መሰረታዊ ምክንያት ምንድነው? መገለሉስ ከመቼ ጀምሮ የተፈጠረ ነው? ተጠያቂው ማነው?…. ወዘተ የሚሉ ናቸው። ይህንን ቁልፍ ጉዳይ መመለስ ከተቻለ ወደ ቁልፍ መፍትሄው የምንሄድበት መንገድ አልጋ በአልግስ ይሆናል።

 

ከዚህኛው ክፍል ከመውጣቴ በፊት ሁለቱን የህዉሃት የጦር ጄኔራሎችም ሆነ እነሱን ተከትለው ሃሳባቸውን በሰፊው ተቀብለው ያራመዱ የአገር ውስጥ ሚዲያዎች የቀጣይ እጣፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን የራስ ግምት አስቀምጬ መሄድ እፈልጋለሁ። ከልምድ ማየት እንደሚቻለው ህዉሃት በአንድ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ አቋም ወስዶ መግለጫ እስኪያወጣ ድረስ የቀድሞ አባላቱንም ሆነ በግል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሚንቀሳቀሱ (ሸገር 02) ድርጅቶች ትንሽ ለቀቅ ያለ ሃሳብ የሚያራምዱበት በር ገርበብ ይደረግላቸዋል። የዛን ሰሞን አፋችንን ይዘን በመገረም “በሸገር ካፌ” ላይ ወይዘሮ መዓዛ ብሩና ጓድ አብዱ የጄኔራል ፃድቃንን “የስርአት ለውጥ” አስተሳሰብ ተገቢ እንደሆነ በአድናቆት ሲነግሩን ነበር። እርግጥ የደርግ ዘመን ጥያቄና መልስ ላይ “አብዮታዊ” ማብራሪያ ሲሰጥ የምናውቀው ጓድ አብዱ በእያንዳንዱ ንግግሩ ሟቹ መለስ ዜናዊን ሲያንቆለጳጵስ መደመጥ ብዙዎችን አስገርሟል። በጣት ቆጠራ አልፈው ካልሆነ በስተቀር ጓድ አብዱ ከሰባት ጊዜ በላይ ባደርገው የሟች ጥሪ በስላሴ 24 ሰዓት ቁጭ ብለው መቃብር የሚጠብቁ የህዉሃት ዋርድያዎችን ሳያስበረግግ አይቀርም።

 

ወደ ገደለው ጉዳያችን ስንመለስ የህዉሃት የቀድሞ ጄኔራሎችም ሆነ እንደ ሸገር ያሉት የሚዲያ ተቋማት ህዉሃት/ኢህአዴግ መግለጫ ካወጣ በኋላ ቀስ በቀስ ወደ ኋላ መንሸራተታቸው የግድ ይሆናል። ያለ አንዳች ጥርጥር ጄኔራሎቹ ወደ አፎታቸው ይገባሉ። ሸገርና ተመሳሳይ ሚዲያዎች ደግሞ ወደ ሰገባቸው። ይህን ማድረግ ካልቻሉ “የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም” የሚለው ብሂል ወደተግባር ተገልብጦ ለመመልከት ሩቅ አይሆንም። ለነገሩ ጆቤና ጓድ አብዶ በአክሮባት የሚታሙ ስላልሆነ ካናዳው ለማምለጥ እንደ አቦሸማኔ መሮጣቸው ሳይታለም የተፈታ ነው።

 

የትግራይ ኤሊቶች፣ የህዉሃት የቀድሞ የጦር ጄኔራሎችም ሆነ የቀድሞ ታጋይ ባላስልጣናት ከህዉሃት በፍጥነት ተፋተው ለአዲስ የስርአት ለውጥ ዝግጁ የማይሆኑባቸው ሌሎች ተጨማሪ መሰረታዊ ምክንያቶች አሏቸው። ከዚህ ውስጥ የቅድሚያ መስመር የምትይዘው ኤርትራ ናት (Eriteria-Factor)። ህዉሃት ከኢርትራ ጋር የገባበት ጦርነት ፍፃሜ የረጅም ጊዜ የመጠባበቂያ ህልሙን ያጨለመ ነው። ለሁሉም ግልጽ እንደሆነው ከጦርነቱ በፊት ከኤርትራ መንግስት ጋር ለአመታት የተካሄደው ድርድርም ሆነ የጦርነት ውሳኔ የተወሰነው በህውሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው። ወደ ጦርነት ከተገባም በኋላ የመሪነቱን ሚና የጨበጡት ህዉሃቶች ናቸው። በጦርነቱ ምክንያት የአገሪቱ ካዝና በተራገፈና ሙጥጥ ባለ ሰዓት መንግስት ከሶስት ቢሊዮን ብር ያላነሰ የተበደረው ከህዉሃት የኢኮኖሚ ኢምፓወ ከሆነው ኤፈርት (ትእምት) ነበር። ለጦርነቱ የሚሆነውን የጦር መሳሪያ (ታንክ፣ ሮኬት፣ ሚሳየል፣ የውጊያ አውሮፕላኖች……) በየአህጉራቱ የተሽከረከሩ የሚገዙት የህዉሃት አመራሮችና የጦር አዛዦች ናቸው።

 

(በነገራችን ላይ በአውሮፕላን ግዢ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ከነበራቸው የጦር አዛዦች ግንባር ቀደሙን የሚይዘው የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበረው ሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ነው። አበበ የክፍፍሉ መጀመሪያ ወቅት እንቡር እንቡር ቢልም የአንጃዎቹ መጨረሻ ኩምሽሽ አድርጎታል። “አይተነው ጊዜ ወደሚያደላው” አይነት ባህሪ ያለው አበበ ገልብጦ የመለስን ቡድን ይቅርታ ቢጠይቅም የመለስን የቃሪያ ጥፊ ከማግኘት አልታቀበም። ከአዛዥነቱ በንፋስ ፍጥነት ተባረረ። ከዛ በኋላ ጆቦ በሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከኪሱ በማውጣት አሜሪካን ሀገር ተማረ። በትምህርቱም “የአሰብ ኢትዮጵያዊነት” ተገለጠለት። መገለጡ ቀልብ ይስባልና በኢትዮጵያ አየር ሃይል ላይ በተነው። ጆቤ! ዛሬ በወር 150ሺህ ብር የሚከራይ ቪላ አለው። ያውም በአዱገነት እምብርት! ለ100 አመት ይዞ ቢቆይና ከደሞዙ ሰባራ ሳንቲም ባያወጣ አሁን ያለውን ሀብት ሩብ አይኖረውም። እርግጥ ከርቀት እንደሰማነው ባለቤቱ ብቸኛዋ ሴት ጄኔራል ሆናለች።)

 

እዚህ ላይ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ውጤት ለህዉሃት የበላይነት መምጣትና የትግራይ ተጠቃሚነት ዋስትና የፈጠረው አደጋ ለህዉሃት መሰንጠቅ መሰረታዊ ምክንያት ቢሆንም ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች አሉት። እነዚህ አደጋዎች ከህዉሃት አፈጣጠር፣ የዘረጋው ስርአት ባህሪና ውስጠ- ድርጅት ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው። ህውሃት የበላይነቱን ያረጋገጠባት ኢትዮጵያ ካልቀጠለችና የአገር መበተን ካጋጠመ “የትግራይ ሪፐብሊክ” ነፃ ሀገር ፈጥሮ መኖር እንደ መጨረሻ ግብ ያስቀመጠ ቢሆንም ከኤርትራ ጋር የገባበት ቁርሾና ደም መፋሰስ ይህን ፍላጎቱን ከሞላ ጎደል ዝግ አድርጎታል። Eriteria-Factor የተባለው አንዱ ገፅታ ይሄ ነው። የጎንደር፣ አፋር፣ ወሎ ህዝብ ከታች ኤርትራ ከላይ ሆነው ትግራይን ሳንድዊች የሚያደርጉበት ሁኔታ ስለሚፈጠር ከዚህ በኋላ “የትግራይ ሪፐብሊክ” ከህልም የዘለለ አይሆንም። ትግራይን ገንጥለን በሰላም እንኖራለን የሚባል ህልም ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣……ወዘተ ወደ ትግራይ የተከለሉ ሰአትና የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በተነሳ ሰአት ወደ መቃብር ወርዷል።

የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት አጨራረስ በአንድ በኩል ነፃ ሀገር ለመመስረት ህልም የነበረችውን የህዉሃት አመራሮች ወሽመጥ የቆረጠ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊነቱን አጥብቆ ለሚፈልገው የትግራይ ህዝብ ትልቅ ብስራት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው። በአጭሩ ኢትዮጵያን ወዳድ ለሆነው የትግራይ ህዝብ የጦርነቱ አጨራረስ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ የሚፈጠር ጥሩ አጋጣሚ ነው። Blessing in disguise!!

 

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አጨራረስ ህዉሃትን ለሁለት ሰንጥቋል የሚባልበት መሰረታዊ ምክንያት ይሄ ነው። የስዬ አብርሃ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብትና ደም መከታ አድርጎ ኤርትራ በመደምሰስ አሻንጉሊት መንግስት ለመመስረት ሲያስብ ሌሎች አላማዎችን ለማሳካትም ጭምር ነበር። ህዳጣኑ ህዉሃት ከትግራይ ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ መግዛት ካቃተውና ህዝባዊ ማዕበሉ ካናወጠው ያለ ኤርትራ ስጋት “ነፃ የትግራይ ሪፐብሊክ” መመስረት ይችላል። የስዬ ቡድን ኤርትራ ላይ ለራሱ ተጠሪ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት መመስረት አለመቻሉ በክፉ ጊዜ መጠጊያ የምትሆነውን “ሪፐብሊክ ትግራይ” የመመስረት ራዕይ ተጨናገፈበት። በተለይ በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቹን በመገብሩ ቁጭት ላይ የወደቀ መሆኑና ከዚህ በኋላ ጋሻነቱ ባከተመበት ሁኔታ ከኤርትራ ጋር ጦርነት መግጠም ማለት የህዉሃት ፍፃሜ መሆኑ አይቀርም። በሌላ በኩል ጓድ መለስ በስልጣን ለመቆየት ካለው ጥማት በመነሳት ጦርነቱ ሊገፋበት አለመቻሉ እዛው ሳለ የትግራይን ነፃ መንግስት ህልም ባጭሩ የቀጨ ሆኗል። ይህ በመሆኑ ምክንያት በህዉሃት/ኤህአዴግ ህገ-መንግስት ውስጥ የሰፈረው አንቀጽ 39 ከህዉሃትና ትግራይ ህዝብ አኳያ ከወረቀት አንበሳነት የዘለለ አይሆንም። የህዉሃት አፈጣጠር መነሻ የሆነው “የትግራይ ነፃ ሪፐብሊክ” መመስረት እውን ሊሆን የሚችለው ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ሲሟሉ ብቻ ነው። አንደኛው ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት….. የመሳሰሉ መሬቶችን ለባለቤታቸው ሲመልሱ ይሆናል። ሁለተኛው ኤርትራ ላይ (Eriteria-Factor) ዳግም ጦርነት በመክፈትና ኤርትራን ወደ ዳግም ሱማሊያ መውሰድ፤ ከተቻለም ለህዉሃት ተጠሪ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት በመመስረት በተራዘመ ጊዜ በኮንፌደሬሽን መዋሃድ። የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሌሎች ቀድሞ በትግራይ ክልል ያልነበሩ ቦታዎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው ይመለሳል የሚለው ጥያቄ “በህዉሃት መቃብር” ላይ ብቻ የሚፈፀም ነው። ለዚህም ነው ከየትኛውም የኢትዮጵያ ቦታዎች በበለጠ ሁኔታ እነዚህ አካባቢዎች “የትግሉ  ማዕከል” ናቸው የተባለበት ምክንያት። ኤርትራን በጦር ገጥሞ ለህዉሃት ተገዢ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት በአስመራ እናቋቁማለን የሚለውም ፍላጎት ያስቀና የደቀቀ ተደርጎ ባይወሰድም ወደ ዜሮ የቀረበ እድል (Probability) ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው።

 

እርግጥ ሌሎች ህዉሃትን ለሁለት የሰነጠቁ እንጭፍጫፊ ምክንያቶች እዚህ ላይ ሊጨመሩ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩ እሙን ነው። የህዉሃት የፍጥረቱ የመጨረሻ ግብ ከመኮላሸቱ ጎ ለጎን የዘረጋው ስርአት ባህሪና የውስጠ- ድርጅቱ ሁኔታ ለመሰነጣጠቁ ምክንያት ነው። ህውሃት የዘረጋው ስርአት የፓርቲውን የበላይነትና የትግራይን የተለየ ተጠቃሚነት ዝርፊያ (ሙስና) አንዱ መለያ ባህሪው ነው። መንግስት እንደመሆኑ መጠን ወረራና ዝርፊያው “መንግስታዊ” መሆኑ አይቀርም። “መንግስታዊ ሌብነት”…. “መንግስታዊ ዝርፊያ”…. “መንግስታዊ ሙስና”…. “መንግስታዊ ውንብድና!”…. በመሆኑም የህዉሃት አንዱ መሰረታዊ መለያ ባህሪ በአዋጅ፣ በህግ፣ በመመሪያ የሚፈፅም የቡድን ዝርፊያ (“መንግስታዊ ሙስና”) ነው። ህዉሃት ገና ከጠዋቱ ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ የመንግስትና ድርጅታዊ የስልጣን ቦታዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለው በዚህ ምክንያት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ውጭ ጉዳይ፣ መከላከያ፣ ደህንነት፣ ፖሊስ፣ ሚዲያ፣ የድርጅት ቢሮ፣ የክልሎች ሞግዚት በመሆን አይናቸውን በጨው ያጠቡት ለዚህ ነው።

ይህም ሆኖ የህዉሃት ስርአት በትግራይ ህዝብና ልሂቃን ዘንድ ያለው አረዳድ ከሌላው አካባቢ ጋር ተመሳሳይ አይደለም። አሁን ባለው ነባራዊ እውነታ ከትግራይ ህዝብ የወጡት ህዉሓቶች በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በሆኑበት፤ ገዳዩ አሳሪው ገራፊውና መርማሪው እነሱ በሆኑበት፤ የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም በገነቡበት፤ በትግራይ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅና ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እልፍ አእላፍ ፋብሪካና የኢኮኖሚ አውታሮች በተገነቡበት፤ በጠብታ ኢኮኖሚ መልኩ በትግራይ ክልል የተገነቡት፤ መሰረተ ልማቶችና ማህበራዊ ፍትህ ማምጫ ተቋማት….. ወዘተ በፍጥነት ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ሊቀላቀላቸው አይችልም። ራሳችንን ማምሸት ካልፈለግን በስተቀር የትግራይ ህዝብ በህዉሃት አገዛዝና አፈና ተማሮ ሊሆን ይችላል እንጂ “አዲስ ስርአት” ለመቀበል ዝግጁነቱ አይታይም። የህዉሃት አገዛዝ በፓርቲ መዋቅሩ አማካኝነት የሚፈጥረው ጭቆና፣ የዘመድ አዝማድ አድሎአዊ አሰራር፣ ኋላቀርነት፣ “አህያ ቢራገጥ” የሚመስል አይነት ቂም በቀል፣… አሰልቺ ስብሰባዎች እና መዋጮ….. ወዘተ የትግራይን ህዝብ ሊያስመረምረው ይዝል ይሆናል እንጂ ለስር-ነቀል ለውጥ የተዘጋጀ አይደለም። ግፋ ቢል ከአጭር ጊዜ አኳያ “ላም እሳት ወለደች” ከሚለው ብሂል የሚርቅ አይደለም። ይህ የብዙሃኑ የትግራይ ተወላጅ ፍላጎት አድርገን ልንወስደው የምንችል ነው።

 

 


ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በጅምላ ማሰር፣ መሰወር፣ በግፍ መግደል፣ ማሰቃየት ለዚች አገር መፍትሄ አይሆንም!

$
0
0

elias-daniel

ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን በጅምላ ማሰር፣ መሰወር፣ በግፍ መግደል፣ ማሰቃየት ለዚች አገር መፍትሄ አይሆንም!

በኢትዮጵያውያን ላይም የጦርነት አዋጅ ማወጅ ምንም ጠብ የሚል ፋይዳ አያስገኝም!

ጭቆናን፣ አፈናን፣ ግፍን፣ የዘር ማፅዳት እርምጃን እንቃወማለን – ሁሌም!

የሙታን ድምፅ ይጣራል? –ዴሬ አይሣ፤ አርባ ምንጭ ፤ኢትዮጵያ

$
0
0

 

59cbcc0b93dc457ea0f6f5000f4fef1d_18የመቶ አለቃ ጳዉሎስ ቦጋለ “የሕዝብ ምጥ” በሚል ካናዳ ሆነ የጻፈውን  Ethiomedia ላይ አነበበኩ። ጽሁፉ ረዥም ነው። መዝጊያው ላይ “የዘበዘብኩት” ይላል። እውነትነው! ስለምንና ስለማን  እንደጻፈ እንኳን እኔ ራሱም የተረዳው አይመስለኝም።ጳዎሎስ ቦጋለ መዘብዘቡ ሳይሆን ደፍሮ መጻፉ ገረመኝ! ተርቱ “ ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ!” ነበር። የዛሬ ጅብ የሚያውቁት አገርም ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ማለት ቻለ። በዛሬ መገናኛ ካናዳ ከኢትዮጵያ የአንድ ቀን መንገድ ነው። በማህበራዊ ገጽ (Social Media,Internet) የደቂቃ መንገድ ነው። ስለዚህ ጳዉሎስ ቦጋለ የሚኖርበት ካናዳ  “የማያውቁት አገር” አይደለም።

የጳውሎስ ቦጋለ “ደፍሮ መጽፉ ገርመኝ!” ያልኩት ሌላ ተረት አስታወሰኝ። “የአቦን ስለት የበላ ያስለፈልፈዋል!” ሲባል “የት አለ እኔ የለፈለፍኩት!”አለ የሚባለውን። ድፍረቱ ገረመኝ ያልኩትን በሁለት ማስረጃ ለማስረዳት እሞክራለሁ። አንደኛው ከራሱ ከጳውሎስ አንደበት የስማሁትና ሁለተኛው በዚሁ በEthio Media  ላይ የያዛሬ ሁለት አመት ገደማ (February 18, 2015 ) ሽመልስ አበበ የጻፈውን በከፊል እዚህ በመለጠፍ ነው።

                                                  *

1.በዘመን ደርግ ፤በ1960ዎቹ ውስጥ ጳውሎስ ቦጋለ የጋሞ ጎፋ ክፍለ ሐገር ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ነበር።። ሰው- በላው የደርግ አባል ሻለቃ ለአሊ ሙሳ አርባ ምንጭ መጣ።  በመቶ አለቃ ጳዎሎስ አዘጋጅነት የ11 የጎፋና የገለብና ሐመር ባኮ አውርጃ ነፍጠኞች ስም  በወቅቱ “አብዮታዊ እርምጃ!” ለሚባለው  ለአሊ ሙሳ ቀርበለት። ዋና አስተዳዳሪው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ድርጅት አባል የሆነው መኮንን ገላን ነበር። ጳውሎስ  አቀረበ ያልኩት መኮንን ክፍለ ሐገሩንና ማን ምን እንደሆነ አያውቅምና  ተባባሪ እንጅ ጠንሳሽ ሊሆን አይችልም በሚል ነው። ከነዚህ 11 ስዎች ውስጥ አንዱ ዳኛቸው ከጥቂት አመታት በፊት በወ ቅቱ ለነበረው  የንጉሱ ፓርላማ ከጳውሎስ ጋር የተወዳደር ሰው ነበር። የግል ቂም በቀል ነበራቸው ይባላል።

በቀረበው መሠረት ሻለቃ አሊ ሙሳ “አብዮታዊ ውሳኔ!” አሳለፈ። “አብዮታዊ እርምጃ!” ማለት ይረሸኑ ማለት ነዉ።ብዙ ባለስልጣናት የነበርቡት ስብሰባ ስለነበር ውስኔው ወዲያውን አርባ ምንጭ ናኜ። ትልቅ ድንጋጤና መሸበረም ፈጠረ። “ማነው ተረኛው?” የሚለው በሁሉም ዘንድ ጭንቀትን ፈጠረ። ከተሰበሰቡት ባለስልጣናት አንዱ “እኔ እዚህ ውስጥ የለሁበትም!” ብሎ ስብሰባውን ረገጦ እንደወጣም ተወራ። ሒሊናውን እንጅ 11ዱን ሰዎች አላዳነም።የግለስቡን ስም እዚህ ማንሳት ለጊዜው አስፈላጊ አልመስለኝም።

11 “አብዮታዊ እርምጃ!” የተወሰነባቸው ሰዎች ሰዎች ጎፋ አውራጃ ዋና ከተማ የላ-ሳውላ በእስራት ላይ ነበሩ። በነጋታው ማታ ተረሸኑ። መረሽናቸው ሳይሆን ግድያው እንዴትና ማን አንደፈጸመው መስማቱ የበለጠ የሚዘገንን ነበር። 11ንም ግድያውን( መረሸኑን) የፈጸመው የመቶ አለቃ ጳውሎስ ቦጋለ ነበር። ይህንን የሰማሁት ከራሱ ከጳውሎስ አንደበት ነበር።

“አብዮታዊዊ  ውሳኔ!” በአሊ ሙሳ በተሰጠ ማግስት የመቶ አለቃ ጳውሎስ ቦጋለ በአውሮፕላን ወደየላ-ሳውላ በረረ ።ይህን የሚነግረን ጳውሎስ ነበር። ድርጊቱ ከተፈጸመ በኋላ በሁለተናኛው ቀን አርባ ምንጭ በቀለ ሞላ ሆቴል ጀርባ ፤ወደሐይቆቹና የእግዜር ድልድይ ፊቱን ያዞረው  ጉብታ ላይ ከጓደኞቼ ጋር ቢራ ስንጠጣ የመቶ አለቃ ጳውሎስ መቶ ተቀላቅለን። ወሬውን ማን እንዳነሳው በደንብ አላስታውስም ። ጳውሎስ ሳውላ ግድያው እንዴት እንደተፈጸመ ያወጋን ጀመርን። ያምስታውሰው  “ ሳውላ  ቀን ደርስኩ.. ከማውቃቸው ሰዎች ጋር ሆነን ስንቀመቀም ሞቅ ብሎኝ አመሸን። ከምሸቱ  ሁለት ሰአት ገደማ ወደወህኒ ቤት ሔድን። እስረኞቹ የፍጥኝ ታስረው መጡ። ግርግዳ አስደግፏቸው አለኩ። ከዚያ ኡዚያን አውጥቼ ተራ በትራ አርከፍኩባቸው። ግማሹን በደርቱ፤ሌላው ጭንቅላቱን ፤..የልፍለፋሉ ..ይናዘዛሉ ..ልጆቼን ሳላስድግ … ሳልናዘዘ.. ቤተሰቤን ሳልስናበት ። የደሙ ፍንጣሪ ልብሴን አበላሸው …”  የጦር ሜዳ ፊልም የሚያወራ ነበር የሚመስለው። ዜማ አይኑረው እንጅ ፉከራና ቀረርቶ ይመስል ነበር። የዚያን ቀን የደነገጥኩትን ያክል  ከዚያ በፊትም ከዚያ ወዲህም ደንግጨ አላውቅም።

                                                  *

  1. አሁን ደግሞ ሽመልስ አበበ በ Ethiomedia ላይ February 18, 2015 ከጻፈው ከዚህ ጋር ተዛማጅነት አለው ብዬ ያሰብኩትን ከዚህ በታች አቀርባለህ

“…..እ. ኢ. አ. በ1969 ዓ. ም. በአንድ ወቅት የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍሎች ዴስኮች ላይ ለእያንዳንዱ ተማሪ ተብሎ በእጅ የተጻፉ የኢሕአፓ ወረቀቶች ተበትነዉ ነበር። ክፍል ስገባ ወረቀቱን አነበብኩ። ወረቀቱ የተሞላዉ በኢህአፓ መፈክሮች ነዉ። እያንዳንዱም ተማሪ አንብቦት ዝም ብሏል። ትምህርትም ተጀምሮ ሳለ የአርባ ምንጭ ወረዳ ፖሊስ ጣቢአ አዛዥ የነበረ ሻምበል ተስፋዬ የሚባል ከጠቋሚ ተማሪዎች ጋር በመሆን በየክፍሉ እየዞረ ማን ነዉ ወረቀት የበተነዉ እያለ ይጮህ ነበር።እኔ የነበርኩበት ክፍልም መጥቶ ጮኸብን። ብዙ ተማሪዎች ክፍል ለቅቀዉ ሲወጡ እኛም ወጣን። ብዙ ጠቋሚ ተማሪዎች በቦክስ ተመቱ። ቁጥሩ አንድ መቶ የሚሆን ማስ የሚባል (ፈረንሳይ የተሰራ አስር ጥይት ጎራሽ) ግማሽ አዉቶማቲክ ጠብመንጃ የታጠቀ የፈጥኖ ደራሽ ሀይል ትምህርት ቤቱን ከበበ። በዚህን ጊዜ ነበር አቶ አሰፋ ጫቦ ወደ ትምህርት ቤታችን የመጡት።

አቶ አሰፋ በጉርድ ላንድሮቨር ሲመጡ ተማሪዎች አሰገቧቸዉ ብለዉ ሲጮሁ ዋና መግቢያዉን በር ይጠብቁ የነበሩት ተማሪዎች አስገቧቸዉ። ከዚያም ሰንደቅ አላማ የሚከበርበት ቦታ መኪናዉን አቁመዉ ከመኪና ሲወጡ ተማሪዎች ከበቧቸዉ። ከዚያም ተማሪዎች ጪኸታቸዉን ማሰማት ጀመሩ። አቶ አሰፋ የላንድሮቨሩ ሞተር ኮፈን ላይ ቆመዉ ሳለ የድምጽ ማጉያ ተሰጥቶአቸዉ ከተማሪዎች ጥያቄ መቀበል ጀመሩ። ከዚያም መልስ መስጠት ጀመሩ። ተማሪዎች በጥሞና አዳመጧቸዉ። እርሳቸዉም “…ይህቺ የዴሞ ቅስቀሳ ነች። ትምህርታችሁን ብትከታተሉ ይበልጥ ትጠቀማላችሁ…” ብለዉ ተናገሩ። ሌሎች መልሶችም ባያረኩን እንኳ እሳቸዉ ምልስ ሊሰጡ እንደማይችሉ ተማሪዎች የተረዱትም ይመስለኛል። በቦክስ የተመቱና የደሙ ተማሪዎች በአምቡላንስ ወደ ሆሲፒታል ተላኩ። ጥቃቱን የፈጸሙ ተማሪዎች ከተጠያቂነት እንደማይድኑ አቶ አሰፋ ማሳሰቢያ ሰጡ። ይህ እየሆነ ሳለ የመቶ አለቃ ጳዉሎስ ቦጋለ መጥቶ አቶ አሰፋ እንዲናገር እድል ሲሰጠዉ ድምጽ ማጉያዉን ተቀበሎ መደንፋት ጀመረ። “…የአድሀሪያን ልጆች የሬሳ ሳጥን በሚያክል አገልግል ፍትፍትና ጭኮ እየተላከላቸዉ ተንደላቅቀዉ እየተማሩ የጭቁን ልጆች እንዳይማሩ ለማድረግ የተጠነሰሰ ሴራ ነዉ…” እያለ ደነፋ። ብዙ ዛቻዎችንም ዛተ። ከዚያም አቶ አሰፋ ከመቶ አለቃ ጳዉሎስ ጋር ለጥቂት ደቂቃዎች ተነጋገረ። የመቶ አለቃ ጳዉሎስ እየተቆጨ ሲናገር እንደነበር ታዘብኩ። ኮሎኔል ተስፋዬ የሚባል የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉን መርቶ የመጣዉ ወደነርሱ ጠጋ ብሎ የነገሩትን ሰምቶ ሄደ። ከዚያም አቶ አሰፋ ለዚያኑ ቀን ትምህርት እንደሌለና ወደ ቤታችን እንድንሄድ ነገሩን። እኛም ወደ ቤት ስንሄድ የታዘብኩት ነገር ቢኖር የመቶ አለቃ ጳዉሎስ ቦጋለ ከአቶ አሰፋ ጋር ሲጨቃጨቅ እንደነበር ነዉ። በወቅቱ ከጓደኞቼ ጋር ስንነጋገር የደረስንበት መደምደሚያ ቢኖር የመቶ አለቃ ጳዉሎስ እርምጃ ለመዉሰድ ፈልጎ በአቶ አሰፋ እምቢተኝነትና ተጽእኖ ደም ላይፈስ እንዳልቻለ ነዉ። በወቅቱ ቁጥሩ አንድ መቶ የሚሆነዉ የፈጥኖ ደራሽ ሀይል የግድያ ትእዛዝ ቢሰጠዉ ኖሮ ምን ያህል ተማሪ እንደሚሞት መገመት አያዳግትም. በተማሪዎችም ዘንድ አቶ አሰፋ ክብር ሊያገኙም ችለዋል ይህችን ዉለታ ለተማሪዎች ስለዋሉ።

ከአቶ አሰፋ ጋር በርእዮተ አለም አመለካከት ብለያይም አንኳ በእርሳቸዉ ብርታት ከሞት ልድን ችያለሁ። በወቅቱ ከከበቡን ፈጥኖ ደራሾች ቢያንስ ወደ አስር የሚሆኑትን አዉቃቸዋለሁ። ተማሪዎች የነበሩ ናቸዉ። በሌላ ወቅት አግኝቼ ስጠይቃቸዉ በአቶ አሰፋ እምቢተኝነት የመቶ አለቃ ጳዉሎስ ቦጋለ ትእዛዝ ለመስጠት እንዳልፈለገ አዛዣቸዉ የነበረዉ ኮሎኔል ተስፋዬ እንደነገራቸዉ አጫወቱኝ። ትእዛዝ ቢሰጣቸዉ ኖሮ እኔንም ሊገድሉ እንደሚችሉ ነገሩኝ። እኔም የህችን የአቶ አሰፋን ዉለታ ሁል ጊዜ እንዳስታዉስ አደረገኝ። አቶ አሰፋን ወድጄ አላዉቅም። ግን ይህ ዉለታቸዉ እንዳከብራቸዉ አድሮጎኛል።

ብዙ ሰዎችን አስገድለዋል የሚል ክስና ስሞታ በተደረጉት ትችቶች ዉስጥ ተካትተዋል። አርባ ምንጭ ዉስጥ የተደረጉት ግርፊያዎች ናቸዉ የኢሕአፓን አባላትና ደጋፊዎች ለማጋለጥ ተብሎ። ፋሺስቱ አሊ ሙሳ በገዛ እጁ የገደላቸዉ አተ ተፈሪ (የእኔ ዘመድ የሆነችዉ አየለች ማመጫ ባለቤት)፣ ክፈተዉ (የአጎቴ ባለቤት ወንድም)፣ እና ኑሩ (አቶ አሰፋ ሲታሰሩ በእርሳቸዉ ምትክ የተመደበዉ) ሲሆኑ አርባ ምንጭ ዉስጥ ምንም የፖለቲካ ግድያ አልተካሄደም። አንድም የኢሕአፓ አባል አልተገደለም። ግርፋት ግን ተካሂዷል። በጎፋ አዉራጃ ዋና ከተማ ሳዉላ ከተማ የመቶ አለቃ ጳዉሎስ ቦጋለ ፊዉዳሎች ናቸዉ ብሎ የረሸናቸዉ ጥቂት ግለሰቦች ናቸዉ። የገለብና ሀመር ባኮ አዉራጃ ዋና ከተማ ዉስጥ አንድ የጊዶሌ ተወላጅ የሆነ ካድሬ አንድ ነጋዴ ገድሏል። እ. ኢ. አ. በነሐሴ ወር 1976 ዓ. ም. (August 1984 G. C.) ለትምህርት ኢትዮጵያን ለቅቄ እስከምወጣ ድረስ እዚያዉ ጋሞ ጎፋ የኖርኩ ስለሆነ ሁኔታዎችን ጠንቅቄ አዉቃለሁ። በአቶ አሰፋ ላይ የተደረገዉ አሳዛኝ ትችት ከእዉነት የራቀ መሆኑ በጣም አሳዘነኝ። ጸሀፊዎቹና ተቺዎቹ ከተባራሪ ወሬ የቀሰሙትን ነገር እንደ እዉነታ አድርገዉ ማቅረባቸዉ ዋጋ ቢስነቱን ከማጋለጥ በስተቀር የሚያመጣዉ ነገር ያለ አይመስለኝም። አቶ አሰፋ ቢጠየቁም እንኳ በኢሕአፓነት ተጠርጥረዉና ታስረዉ ለተገረፉት እንጂ በአስገዳይነት አይደለም። ብዙ ተማሪዎች በኢሕአፓነት ተጠርጥረዉ በተለያዩ ቦታዎች ታስረዉና ተገርፈዉ ወደ ሰላማዊ ኑሮና ትምህርት እንዲመለሱ ተደርጓል። ግድያ እንዳይካሄድ ካድሬዎች እንኳ አቶ አሰፋን ያሙ የነበረ ለመሆኑ ሲነገር ሰምቻለሁ። አቶ አሰፋ ኢሕአፓዎች እንዳይገደሉ አድርገዋል። ጋሞ ጎፋ ዉስጥ ባጠቃላይ እስራትና ግርፊያ ተካሄደ እንጂ የፖለቲካ ግድያ አልተካሄደም። ይህ ደግሞ በአዲሰ አበባና ሌሎች ከተሞች አንዳንድ የቀበሌ ሊቀመናብርት በቀይ ሽብር ወቅት ወጣቶች እንዳይገደሉባቸዉ ያስሯቸዉና ይገርፏቸዉ ከነበረዉ በምንም ተአምር አይለይም።

ኢሕአፓዎች ያደረጉትስ የከተማ ቃፊር የግድያ ዘመቻ እና በመካከላቸዉ በነበረዉ የፖለቲካ መከፋፈል እርስ በእርስ የተጋደሉት፤ እንዲሁም ወጣቱን ያስጨረሱት ተረሳና የአቶ አሰፋ ድርጊት ጎልቶ ታይቶ ነዉ ወይ እንዲህ አይነቱ ትችት የተደረገዉ? ትችት በትክክል መረጃ ተይዞ ሲቀርብ ያምራል። ያለበለዚያ ቂም መወጣጫ ወይም ለፖለቲካ ፍጆታ ይዉላል። ደርግም፣ ኢሕአፓም፣ መኢሶንም፣ ወያኔም ሆን ማንም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ከተጠያቂነት አይድንም።

ኢትዮጵያ ለሁላችንም እኩል እናት አገር ነች። ማንም ከማንም አይበልጥም። የበደሏት፣ የገደሏትና የሞቱላትም እንዲሁ አሉ። እያንዳንዱ ትዉልድ የራሱ የሆነ ባህርይ እንዳለዉ ሁሉ ለቀጣዩ ትዉልድ የሚያስተላልፈዉ ትምህርት ገንቢ ሀሳብና ራእይ ያለዉ ቢሆን ይመረጣል። ካልሆነም ደግሞ የታሪክ ተወቃሽ ሆኖ ይቀራል። አገር በቂም በቀል የሚመራ መሆን የለበትም። ታሪክም ቢሆን የሚጻፈዉ በቂም በቀል አይደለም። ወቀሳ፣ ትችትና ሂስ ገንቢ የሚሆኑት አግባብ ባለዉ ሁኔታ ሲፈጸሙ ነዉ። ታሪክም እንዳይወቅሰን ደግሞ ብናስብበት የበለጠ ጠቃሚነት አለዉ ብዬ አምናለሁ።

ሺመልስ አበበ shimelisabebe@gmail.com

*

ይህ በሆነ በሶስተኛው ወር ይሁን ጳውሎስ ቦጋለ ከምክትል አስተዳዳሪነቱ ተነሳ። ድርጊቱ ተደርሶበት በቁጥጥር ስር ውሏል የሚል ወሬ ናኝቶ ነበር። በቁጥጥር ስር ሳይሆን ንግድ ሚኒስቴር መዝገብ ቤት መደቡት። ከዚያም ዛሬ ነገ ቁጥጥር ስር ይውላል የሚል ወሬ ነበር። ጳውሎስም አመኖበት  በቁሙ የሚቃዥ ሁኖ ነበር ተብሎ ሲወራ እስማለሁ። ከዚያ ለማምለጥ አንድ የሚያውቀውን ሰው ተማጽኖ ለፖለቲካ ትምህርት ኩባ ተላከ። ለዚያ ለመሔድ የነበረው ቀዳዳ በወቅቱ ከነበሩት የፖለቲካ ድርጅቶች የአንዱ አባል መሆን ነበር። ኩባ  አንድ አመት ተኩል ቆይቶ ወደኢትዮጵያ ሲመለስ የሰደድ አባል ሁኖ ተመለሰ።  ይህ ደግሞ አዲስ አበባ እንደገባ  ሌላ ችግር ፈጠረበት። የሁለት ድርጅት አባል ሆኖ መገኘት በወቅቱ ሲበዛ ለሞት ሲያንስ ለእስራት የሚያበቃ ነበር። ሰደደ የነመንግስቱ ኃይለ ማርያም ፓርቲ መሆኑ ነው። በፖሊስነቱ የሚያውቀው፤የሰደድ አመራር አባል የነበረው  ሻለቃ ጌታቸው አግዴ ከዚህ ማጥ ውስጥ አስወጣው ሲባል ሰመቻለሁ።

ይህ ነው የሚባል  ስራም  ሳያገኝ ወያኔ ገባ። ወያኔ እንደገባ ሊጠጋቸው መንገድ በመፈላለግ ላይ እንዳለ ይህንን ኢሰብዐዊ ድርጊቱን ደርሱበትና በቁጥጥር ስር ሊያውሉት ሲፈልጉ በጅቡቲ በኩል ሾልኮ ካናዳ ገባ ተባለ። የሰማሁት ይህንን ያክል ነው እንጅ በተለየ ያጣራሁት አልነበረም። አሁን ካናዳ ሁኖ ለኢትዮጵያ ሕዝብ  ተቆርቋሪ ሁኖ “የሕዝብ ድምጽ” ብሎ  ጻፈ።እኒዚያ የረፈራፋቸው  ሰዎች የህዝብ አካል አልነበሩም? አርባ  ምንጭ ሁለተኛና ደርጃ ሊያስፈጃቸው የነበሩት   ተማሪዎች ሕዝብ ቁጥር ውስጥ አይገቡም? የሕዝብ ትርጉም ትላንት፤ተትላንት ወዲያ፤ ዛሬ፤ ነገ፤ ኢትዮጵያ ይሁን ካናዳ እንደ አመችነቱ የሚለዋወጥ ተለዋዋጭ ትርጉም አለው?  ፀፀት የሚሉት፤መሰቅጠጥ የሚሉት አንዳንዱ ቤት፤ጳውሎስ ቦጋለ ቤት  ሞቶ ቀበረ?አንድ ልዩነቱ ቢኖር፣ጳውሎስ ቦጋለ ሲያመልጥ  ሻለቃ አሊ ሙሳ ግን “የቁርጡ ቀን ሲመጣ” የገዛ ሹጉጡን ጠጥቶ ሞተ ! ይገርመኛል!

የመቶ አለቃ ጳውሎስ ቦጋለ “የሕዝብ ምጥ” በሚለው ጽሁፉ መግቢያ አካባቢ “አስጨናቂው ምጥ አገርንና ሕዝብን ከገጠማቸው አስከፊ አስተዳደር ለመገላገል ..”ይላል። ወደማጠቃለያው ላይ ደግሞ “እንግዲህ ለብዙ አመታት አምቄው የኖረውን እንዳለ ዘረገፍኩት” ይላል ። ጳውሎስ ንዳለ ዘርገፍኩት ማለቱን እንኳን እኔ ራሱም የሚያምነው አልመስለኝም።ጎፋ የላ-ሳውላ በኡዚ ያጨዳቸው 11 ሰዎች ጉዳይ አላነሳም። ይህ በአደባባይ፤ሳውላ ወህኒ ቤት፤ አገር ሲያየው የፈጸመው ነበር። ጳውሎስ ቢረሳው፤ቢዘነጋው፤ ወይም ሊረሳው ሊዘነጋው ቢፈልግም እኒያ  አይን ምስክር የነበሩ ሊረሱትና ሊዘነጉት የሚችሉት አይመስለኝም። እነዚህ 11 ስዎች እንደማንኛችንም ባል፤አባት፤ ወንድም፤ አጎት፤አክስት፣ጎሮቤት፣ዘመድ-አዝማድ አገር የሚያውቃቸው ዘመድ አዝማድ ፣ከሁሉም በላይ ልጆች ያላቸው ነበሩና ትላንትም፤ዛሬም ነገም ሊረሱ የሚችሉ አይመስለኝም።

የጳውሎስ ቦጋለ “የሕዝም ምጥ” ጽሁፍ መደመደሚያው “በቅርቡ የምለው አለኝ!” ይላል። ይህንን ወድጀዋለሁ! በቅርቡ ይህንን አስቃቂ ግፍ ታሪክ ይነገራናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። እኔም ሆንኩ ሌላው ከጳውሎስ ቦጋለ መስማት የምንፈልገው አንዳች ነገር ቢኖር የዚህን የየላ-ሳውላ ወህኒወኔ ቤት ግድያ ታሪክ ብቻ ነው።

ወይም አማራጭም አለ።ካናዳ የወንጀለኛና ፤የነፍሰ ገዳይ መሽሸጊያ፤መታጎሪያ ፤መሸፈቻ ጫካ አይደለችም። የአለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ ስምምነት(International Court of Criminal Justice,ICC )December 18,1998 በ  ፈርማ ተቀብላ  አጽድቃለች። በዚሁ መሠረት በየአገሩ የተሽሸጉ የሰው ዘር አጥፊዎች እየተፈረደባቸው ወህኒ ወረደዋል።  ለሰው  ዘር መዳን የሚሟገቱ ድርጀቶችና ግለሰቦች ተባብረው ማስረጃውን ለካናዳ መንግስት የማቅረብ ጉዳይ እንጅ ጳውሎስ ቦጋለን  ፍትሕ አደባባይ ማድረስ ዛሬ በጣም  ውስብስብ አይመስለኝም።

ጳውሎስ ቦጋለ “በቅርቡ የምለው አለኝ!” የሚለውን ለዚያ ፍርድ ቤት ይንገርና ከዚያ ብንስማው እምርጣለሁ!

 

 

በግፍ የተገደሉት ወንድሞቻችን በደቡብ አፍሪካ ሙሃመድ ጀማልና ሃፊዝ

$
0
0

አብዱረሂም አህመድ
south-afri

south

ክስተቱ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመጻፍ የተወሰኑ ቃላትን ከመጻፍ ውጭ አልቻልኩም ነበር፡፡ ዛሬም ሀዘኑ ክስተቱ እንደ አዲስ ይሰማኛል ፤ያንገበግበኛል ፡፡ የወገኖቼ በግፍ መገደል ያባንነኛል ፡፡
ነገሩ የሆነው እንደዚህ ነው፡፡ ከትላንት ወዲያ ሀሙስ የጅማው ሙሃመድ ጀማል እንደ ወትሮው በደቡብ አፍሪካ ሜይፌር የሚገኘውን ሱቁን ከፍቶ ይሸጣል፡፡ ከሰው ጋር ተግባቢ እና ሰላምተኛ የሆነው ሙሃመድ ጀማል አላፊ አግዳሚውን ሰላም እያለ በሱቁ ውስጥ መሸጥ መለወጡን ቀጥሏል፡፡ በመካከል አንድ ሃሺሽ ተጠቃሚ ቀዥቃዣ ሶማሌ ወደ ሙሃመድ ጀማል ሱቅ ገባ፡፡ ከዚህ ቀዥቃዣ ሶማሌ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ይህ ሰይጣን የጋለበው ሶማሌ እየፎከረ በመውጣት ሽጉጥ ይዞ በመምጣት መጀመሪያ ተኩሶ ይመለሳል፡፡ በሁለተኛው ዙር መጥቶ ሚስኩኑን ሙሃመድ ጀማል በግፍ ተኩሶ ገደለው፡፡

የልጆች አባት የሆነው ሙሃመድ ጀማል ባላሰበው አጋጣሚ ለራሱ ብሎ ባሰበለት ሶማሌ በግፍ በጠራራ ጸሃይ ተገደለ፡፡ ክስተቱ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ሃፊዝ የሙሃመድ ጀማልን ገዳይ እጁን አንቆ ያዘው፡፡ የሚያሳዝነው የያዘው ሽጉጥ ያልያዘበትን እጁን ነበር፡፡ ይህ ነፍሰ ገዳይ የሆነ ሶማሌ ሃፊዝንም ተኩሶ ገደለው ከዚያ በሁላ አመለጠ፡፡ ክስተቱ አሳዛኝ ነበር፡፡ የሚገርመው ፖሊሶቹ ገዳዩን አሳደው ከመያዝ ይልቅ በሄሌኮፍተር ጭምር በአካባቢው ላይ በመሰማራት የሟች ወገኖቹን የኦሮሞ ወገኖችን ቤቶችና መኪና በመፈተሸ መሳሪያ ነበር የቀሙት፡፡መሳሪይ የተገኘባቸውን ነበር ያሰሩት
ሙሃመድ ጀማልና ሃፊዝ በግፍ ተገደሉ፡፡ ክስተቱ እጅግ መሪር ሁኗል፡፡ መላው በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዪጲያዊያን በሀዘን ድባብ ተውጠዋል፡፡ የሙሃመድ ጀማልና የሀፊዝ በግፍ መሞት አንገብግቧቸዋል፡፡ በሀገራቸው የወገኖቻቸው በግፍ በመንግስት መገደል አልበቃ ብሎ በክልፍልፍ በዚህ መልኩ የወገኖቻቸው ማለፍ በርግጥም እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡

ሁለቱ ሟቾች በትላንትናው እለት ተቀበረዋል፡፡ አካላቸው ከአፈር በታች ይውረድንጅ ሃዘናቸው ግን በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ አሻራውን ጥሎ አልፍዋል፡፡
የሶላት ሰአት ሲደርስ ሱቁን ዘግቶ የሚሄደውን፤አላፊ አግዳሚውን ሰላም የሚለውን ሚስኪኑን የአባጅፋር አገር ልጁ ሙሃመድ ጀማልን በህይዎት አለማየት በርግጥም እጅግ ያማል፡፡ ከገዳዩ ጋር ተናንቆ በግፍ የተሳዋውን ሃፊዝን ማሰብ በርግጥም አሳዛኝ ነው፡፡ አላህ የፈቀደው ሆነ፡፡

አላህ ሁለቱንም የጀነት እንዲያደርጋቸው ዱአችን ነው፡፡ ቤተሰቦቻቸውን ወዳጅ ዘመዶቻቸውን አላህ ሶብሩን ይስጣቸው

በአማራው ተጋድሎ የተነሳ ዳሸን ቢራ ኪሳራ ውስጥ እየወደቀ ነው |“ዳሸን ቢራ የጠጣ የወገኑን ደም የጠጣ ነው”

$
0
0

dashen
(ዘ-ሐበሻ) የአማራው ሕዝብ ከትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ጋር እያደረገ ባለው የነጻነት ትግል አንደኛው አካል ዳሸን ቢራን ማዳከም እንደሆነ በተደጋጋሚ ከአማራው ተጋድሎ አስተባባሪዎች ሲገልጹ ነበር:: የአማራው ተጋድሎ በተፋፋመባቸው ጎንደር እና ጎጃም የዳሽን ቢራን የጫኑ መኪኖች ጥቃት ሲደርሰባቸው ቆይቷል:: በተለይም ዳሸን ቢራ በአማራ የልማት ድርጅት ስም የተቋቋመ የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ንብረት በመሆኑ ይኸው ጨካኝ መንግስት አማሮችን ሲገድል የዳሸን ቢራ ንብረቶችን ሁሉ ተጠቅሟል::

በአሁኑ ወቅት በመላው አማራ ክልል ዳሸን ቢራን የጠጣ የወገኑን ደም የጠጣ ነው በሚል በተደረገ ቅስቀሳ ሕዝብ ቢራውን መጠጣት አቁሟል:: ሰዎች ሲጠጡ ከተገኙም “የወንድምህን ደም ጠጣ” እየተባሉ እንደሚረገሙ የሚደርሰን መረጃ ያመለክታል::

ከአማራ ክልል አሞራው ምንአለ ባሻ በለቀቁት መረጃም ይህንኑ አረጋግጠዋል:: መረጃቸው እንደወረደ ይኸው:-
የልጆቻችን ደም አንጠጣም ያለው የአማራ ህዝብ ከዳሸን ጋር እጅግ ተለያይቷል።በተለይም የባህርዳሩ ብቸኛ አከፋፋይ #ኮበል ኢንዱስትሪ ጥበቃዎች ባህር ዳር ላይ ወጣቶችን ከአጋዚ ጋር በመተባበር በጥይት ካረገፏቸው በኋላ ዳሸን በሁሉም የአማራ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ከህዝብ ተለይቷል።

ጎንደር እንፍራንዝ አካባቢ የተወሰደው እርምጃ ለዚህ ማሳያ ነው።ይህ ያስጨነቀው የጥረት ኮርፖሬት በግዳጅ እንዲሸጡ እና እንዲገዙ በሚል #የባህርዳር ግሮሰሪ ባለቦቶችን #በአቫንቲሊሰበስብ መሆኑን መረጃው ደርሶናል።የዳሽን ቢራ ስራአስኪያጅ በጠራውና ታደሰ ጥንቅሹ ይመራዋል በተባለው ስብሰባ ውይይቱ ምን ላይ ይደረሳል የሚለው መልስ እጅግ በጣም ቀላል ነው። #የልጆቻችን ደም አንጠጣም የሚለው የአማራ ህዝብ በሁሉም አካባቢ ቀጥሏል።

የደህንነት ሹሙ የሕወሓትን ጉድ ማፍረጥረጣቸውን ቀጥለዋል –“አብዛኛው ስልክ ጠላፊዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው –አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ፕ/ትም ስልክ ጠለፋ ተምሯል”|ያድምጡት

$
0
0

የደህንነት ሹሙ የሕወሓትን ጉድ ማፍረጥረጣቸውን ቀጥለዋል – “አብዛኛው ስልክ ጠላፊዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው – አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ፕ/ትም ስልክ ጠለፋ ተምሯል” | ያድምጡት
(ዘ-ሐበሻ) ቢቢኤን ቴሌቭዥን ከቀድሞ ከፍተኛ የደህንነት አባል አቶ አያሌው ጋር ባደረገው ቃለምልልስ በርካታ ምስጢሮችን እያወጡ ነው:: ቃለምልልሱን ያድምጡት::

የደህንነት ሹሙ የሕወሓትን ጉድ ማፍረጥረጣቸውን ቀጥለዋል – “አብዛኛው ስልክ ጠላፊዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው – አዲሱ የኦሮሚያ ክልል ፕ/ትም ስልክ ጠለፋ ተምሯል” | ያድምጡት

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>
<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596344.js" async> </script>