Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ከስልጣን መውረድ እንዳለበት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የተካሄደው የምሁራን ጉባዔ ጠየቀ

$
0
0

a12

ኢሳት (ጥቅምት 14 ፥ 2009)

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ በመቀበል ከስልጣን መውረድ እንዳለበትና በሃገሪቱ የሽግግር ስርዓትና የህገ-መንግስት ረቂቅ እንደሚያስፈልግ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የተካሄደው የምሁራን ጉባዔ አስገነዘበ።

a11የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው የጉባዔውን መጠናቀቅ አስመልክተው ለኢሳት እንደገለጹት “ህወሃት የሚመራው መንግስት ህዝብን እየገደለና ሰብዓዊ መብት እየረገጠ በመሆኑ ስልጣኑን ሊለቅ ይገባል።
በቪዥን ኢትዮጵያና በኢሳት ትብብር በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜና እሁድ የተዘጋጀው ኮንፈረንስ ሲጠናቀቅ እንደተገለጸው አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ የሽግግርና አዲስ ህገመንግስት ያስፈልጋል።
በኮንፈረንሱ ማጠቃለያ ላይ በኢትዮጵያ አዲስ ስርዓት ለማበጀት የሽግግር ካውንስል ማቋቋም እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

የቪዥን ኢትዮጵያ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር አሸናፊ ጎሳዬ ለኢሳት እንደገለጹት፣ የሰላም ሚና ያለውና ሃገሪቱን ወደ ሽግግር ሂደት የሚወስደው ካውንስል የተለያዩ አካላት እንዲወስኑበት ማድረግ ያስፈልጋል።
አሁን ያለው ገዢ ፓርት ህወሃት/ኢህአዴግ ግድያውን እንዲያቆምና ለሰላም በሩን በመክፈት ለድርድር ፈቃደኛ እንዲሆን ጥሪ መተላለፍን ገልጸዋል።

ዶ/ር አሸናፊ እንዳሉት በኢትዮጵያ በተካሄደው ግድያና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እጃቸው ያለበት ባለስልጣናት ማንኛውም የገዢው ፓርቲ አባላት በህግ መጠየቅ ይኖርባቸዋል።

በቪዥን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ስብሰባ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በፌስቡክና በኢሳት ድረገጽ ቀጥታ ስርጭት መከታተላቸው ታውቋል። የአጠቃላይ የስብሰባውን መግለጫና የተደረሰበትን ድምዳሜ ቪዥን ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጿል።


በተለይ ለኦሮሞ ልሂቃን የተላከ ማስታወሻ (ከነፃነት ዘለቀ)

$
0
0

ከነፃነት ዘለቀ (nzeleke35@gmail.com)

መድሓኒት ከምን እንደሚሠራ አለማወቃችን በጄ እንጂ ብዙ ፈዋሽ መድሓኒቶች የሚቀመሙት ከመርዝና ብዙም ከማንወዳቸው ነገሮች ነው፡፡ ግን መዳን ስላለብን ሃኪምና ዐዋቂ እንድንወስዳቸው የሚመክሩንን የሚቀቡም ሆኑ የሚዋጡ መድሓኒቶች አለማመንታት እንወስዳቸዋለን፡፡ በቤታችንስ ስንቶቻችን ነን የገዛ ሽንታችንን የምንጠጣ? አዎ፣ መድሓኒት ነው ከተባለ የጅብ ጉበትም ይበላል፤ የአህያ ወተትም ይጠጣል፡፡ ዋናው ከሚያሰቃየን ደዌ መፈወሱ ነው፡፡ “ምንም ቢያስቀዝን ጮማ” ብሎ ነገር በጭንቅ ወቅት አይሠራም፡፡ አሁን ያለንበት ሀገራዊ ድባብም እንዲሁ በጣም አስጨናቂና አሳሳቢ ነው፡፡
ልዩነትን ስናሽኳልለው “ልዩነት ጌጥ ነው” እንላለን፡፡ ግን ልዩነት የብልቃጥ መርዝ ነው፡፡ የብልቃጥ መርዝ ደግሞ እንደያዥው ነው፡፡ ከተፈለገ በመርዝነቱ ሰውን መጨረስ ራስንም ማጥፋት ይቻላል፡፡ ካስፈለገም ወደመድሓኒትነት ለውጦ ትክክለኛ መጠኑንና የአቀማመም ቀመሩን በጠበቀ ሁኔታ ወደ ፈዋሽ መድሓኒትነት መለወጥ ይቻላል፡፡ ምርጫው ሁለት ነው፡፡ አንድም ልዩነትን በጌጥነት ለመጠቀም ቀመሩን ማወቅና ውበትን መላበስ አንድም በመርዝነት መጠቀምና መተላለቅ፡፡

አስተሳሰብ ወደፊት እየመጠቀ እንጂ ወደኋላ እየተጎተተ ሊሄድ አይገባም፡፡”በምኒልክ የደነቆረ ዕድሜ ልኩን በምኒልክ ይምላል” እንዲሉ ሆኖብን እንጂ የሀገራችን ልሂቃንና ተማርን የምንል ወገኖች ሁሉ አስተሳሰባችን ዘመንንና ወቅትን የዋጀ ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ቢያንስ ቢያንስ ከነሲንጋፖርና ከነማሌዥያ ተርታ በተሰለፈች ነበር፡፡ ነገር ግን በማይማዊ እልህ እግር ከወርች ታስረን ያልተገባ ፉክክርና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተን እኛንም ሕዝባችንንም አገራችንንም የኋሊት ሽምጥ ስናስጋልብ እንገኛለን፡፡ ዛሬ አደጉ በሚባሉ ሀገሮች ውስጥ የሰው መሠረታዊ ፍላጎቶች ተሟልተው አንድም የሚራብና የሚጠማ የሚታረዝም ሆነ ካለመጠለያ የሚኖር ዜጋ የለም፡፡ ካላፈርክ በነፃ ብፌ በሚበላባቸው ምግብ ቤቶች፣ በነፃ በሚታደርባቸው አዳራሾችና በነፃ በሚለበስባቸው ቤተ-አልባሳት በመሄድ ራስህን አንደላቅቀህ ማኖር ትችላለህ፡፡ ድህነት ሲባል በእኛና በነሱ መሥፈርት የተለያዬ ነው፡፡ ይህን ግን መንግሥታችንን ጨምሮ ብዙዎቻችን አናውቅም፡፡ እኛና ሀገራችን ሊናገሩት የሚዘገንን የድህነት አረንቋ ውስጥ ልንገኝ የቻልነው እንግዲህ በቅድሚያ የአስተሳሰብ ድሆች በመሆናችንና ያንንም ተከትሎ በየጊዜው በሚከሰት የርስ በርስ ግጭት በምናጠፋው የሰው ሕይወትና የሀገር ሀብት ውድመት ሳቢያ ቁልቁል ስለምንጓዝ ነው፡፡
አሁንስ? እያሳለፍነው የምንገኘው መከራና ስቃይ አስተምሮናል? በውጪ ሀገራት በስደትም ይሁን በትምህርት ምክንያት ስንሄድ ከምናየው የሕዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማኅበረሰብኣዊ ሕይወት ምን ትምህርት ቀሰምን? እነዚህ ሕዝቦች ርሀብንና የርስ በርስ ቅራኔን እንዴት ፈትተው አሁን ወደሚገኙበት የዕድገት ደረጃ ደረሱ? ለመሆኑ በነሱ ሀገር አሁን በቀን ስንት ጥይት ይጮሃል? ስንትስ ሰው በገዛ መንግሥታቸው ጥይት እንደቅጠል ይረግፋል? እንደሰው ከማያያቸው ባዕድ-መሰል መንግሥት ከተላቀቁ ስንት ዘመን አለፋቸው? የልዩነታችን መሠረትና መንስኤው ምን ይሆን?
ባላምባራስ ጓንጉል ድፋባቸውና ቀኛዝማች አዝብጤ መሸሻ የዛሬ መቶ ዓመት አንዳች ጥፋት አጥፍተው ሊሆን ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሤ ጠንክር ጉዲሣና የደርጉ ሊቀ መንበር ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ፈይሣ ያዘዟቸው ወታደሮች ደግሞ እነስንሻው መኳንንትን፣ እነለጥይበሉ ማንደፍሮህን፣ እነአበጋዝ ይማምን፣ እነሐጎስ ገመቹን፣ እነሸንቁጥ ለሊሣን… ገድለዋል፡፡ መበደልና መበዳደል ማኅበራዊ ክስተት እንጂ ለአንድ ዘውግና ለአንድ ሀገር ብቻ የሚተው ብርቅዬ ነገር አይደለም፡፡ ባለፉ ዘመናት ማን ማንን በጣም በደለ በሚል አላስፈላጊ እንካስላንትያ ውስጥ መግባት ካላስፈለገ በስተቀር ሁሉም ተበዳድሏል፤ ሁሉም ተሰዳድቧል፤ ሁሉም ይቅር ለእግዜር ተባብሏል፡፡ በጊዜ ሂደት ሁሉም ተቀያይጧል፤ ሁሉም አንድ፣ አንዱም ሁሉም ሆኗል፡፡ ያለፈን ታሪክ እያሞሰኩ ባለፈ ሕይወት አሁን መኖር ምን ዓይነት ውድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ከእኛ በላይ የሚያውቅ ከቶ ሊኖር አይችልም፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ዘመን የለዬለትን መገደልንና መሞትን ለ‹ዕድለኛ› ሟች እንደመልካም አጋጣሚ እንቁጠረውና በርሀብና በዕርዛት በቁም መሞትን የመሰለ በዓለማችን ፊት የሚያሰቅቅ ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ለዚህ የበቃነው ደግሞ የቤት ውስጥ ቀጋው ወያኔ ሳይረሳ በተባባሪነት በቆሙ በውጪ ሀገራት በተለመደው አገላለጽ በርገር እየቆረጡ በሞቀ ቤታቸው ውስጥ በሰላም በሚኖሩ ወገኖቻችን ነው፡፡
ይህ አካሄዳችን መለወጥ አለበት፡፡ መለወጥ ያለበትም አሁን ነው፡፡ መድሓኒት መዋጥ አለብን፡፡ መድሓኒት ሲዋጥ መረረኝ ጣፈጠኝ የለም፡፡ መድሓኒት በተፈጥሮ መራራ መሆኑን እናውቃለን – ጣፋጭ እንኳን ቢሆን በሥነ ልቦናችን መራራ እንደሆነ ስለምናስብ ጥፍጥናው በምሬት ይተካና እየጎመዘዘን እንውጠዋለን፡፡ ስለዚህ ስለኛ ብቻ ብለን ሳይሆን ስለልጆቻችንና ስለመጪው ትውልድ ብለን ቢመረንም በፈዋሽነቱ ወደር የማይገኝለትን ፍቱን መድሓኒት መርጠን አሁኑኑ እንዋጥ፡፡ ጊዜ የለም!
“እግዜር ሲቆጣ ሽመል አይቆርጥም፤
ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም፡፡” እንዲሉ ሆኖብን እስካሁን ድረስ ጥቃቅን ነገሮችን በምክንያትነት እየደረደርን ላለመግባባት ስንግባባ ቆይተናል፡፡ ይህ ሂደት ግን እኛን አልጠቀመንም ብቻ ሣይሆን ሕዝባችንን ከመኖር ወዳለመኖር እየለወጠው ነው – እስካሁን ኖረ ከተባለ ሊያውም፡፡…
ልክ እንደዐማራው ሁሉ ኦሮሞም በጣም ሰፊና ታላቅ ሕዝብ ነው፡፡ ሰፊነትና ታላቅነት የሚገለጽባቸው ባሕርያት አሉ፡፡ ከነዚህም ጥቂቶቹ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸው የሚሸፍኑት የቦታ ስፋት፣ በሕዝብ ቁጥር ያላቸው አብላጫነት፣ በብሔራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው የተማረ የሰው ኃይል ብዛት፣ ጎላ ብለው የሚታዩት ባህላዊና ሥነ ልሣናዊ የዘዬ ልዩነቶች ወዘተ. ለሰፊነታቸው በዋቢነት ሊጠቀሱ ሲችሉ ለታላቅታቸው ደግሞ ኢዮባዊ ትግስታቸው፣ ተቻችሎ የመኖር ችሎታና ብቃታቸው፣ በተራ ወፍ ዘራሽ ስብከት ያለመወሰድ ዝንባሌያቸው፤ በቋንቋ፣በባህል፣ በሃይማኖት፣ በጋብቻና በመሳሰሉት ማኅበራዊ ክሮች በፍቅርና በውዴታ መተሳሰራቸው ወዘተ. ከብዙው በጥቂቱ ሊወሱ የሚችሉ ናቸው፡፡
ኦሮሞ ያልገባበት የኢትዮጵያ ግዛት የለም – አለ ከተባለም ጥቂት የኤርትራና የትግራይ ሥፍራዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ሲወራ እሰማለሁ፡፡ የኦሮሞ ዘር ያልገባበት ኢትዮጵያዊ የዘር ሐረግ በፍጹም የለም፡፡ እያንዳንዳችን ከአባታችን ተነስተን ወደኋላ ብንቆጥር አብዛኞቻችን የኦሮሞ ስም ለማግኘት እስከ ሰባት ትውልድም መሄድ ላያስፈልገን ይችላል – የዐማራ ወይ የሌላ ስም ለኦሮሞ እንደሚሰጥ ግን ልብ አድርጉ! እናም በለየለት ሁኔታ “ገመቹ” ወይም “ረጋሣ” ዓይነት ስም በትውልድ ሐረጋችሁ ፈልጉ ማለቴ እንጂ በሌሎች ስሞችማ ኦሮሞ በሽበሽ ነው – ጋዲሣ የሚባል አማራም ስለማውቅ ይህ አሰያየም ለሁሉም የሚሠራ እንጂ ለኦሮሞው ብቻ እንዳልሆነ ይያዝልኝ (በብዙ ምዕተ ዓመታት የረጂም ጊዜ ተራክቦ ኦሮሞው በአማራው ውስጥ፣ አማራውም በኦሮሞው ውስጥ ቀልጠዋል)፡፡ “ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ይገነጠላል” ለሚለው የመነቸከ ቀልድ ኦሮሞዎችን ራሳቸውን ጨምሮ ብዙ ዜጎች “ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ ሊገነጠል ይችላል ወይ?” የሚል ትክክለኛ መልስ የሚሰጡበት አንደኛው ምክንያት ይሄው የኦሮሞዎች ሁሉንም የመሆን ተፈጥሯዊ ጠባይ ነው፡፡ በአዲሱ የወያኔ ዘፈን ካልጨፈርን በስተቀር የኢትዮጵያ ትልቁ መለያም የሕዝቧ የደም ትስስር ነው – ለዚህም እኮ ነው እንደወያኔና ደቀ መዛሙርቱ ሤረኛ አጠራር “የኢትዮጵያ ሕዝቦች” ሣይሆን “የኢትዮጵያ ሕዝብ” ሲባል ከውስጠ-ውሳጤያችን ጀምሮ አንዳንዶቻችንን ደስ የሚለን!
ኦሮሞ እንደትግሬ ወይም እንደጽዮናውያን በጣም የተቀራረበ ጎሣዊ አስተሳሰብና ዘውጋዊ ትስስር የለውም ፤ ዐማራም እንዲሁ ነው ወይም ቢያንስ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ እንዲሁ ነበር፡፡ ብዙኃት ተጋሩን ወደዚህ እጅግ አስቀያሚ የጎሠኝነት ስሜት ለማድረስ ሕወሓት የወሰዳቸውን እርምጃዎችና በዚያም ሳቢያ ያደረሰውን ዕልቂት፣ በተጋሩና በተለይም በዐማሮች መካከል የነዛውን የጥላቻ መርዝና የዘመናት ፕሮፓጋንዳ ስናስብ ጥፋትን ዘርቶ ዕልቂትና ውድመትን ለማዝመር ከባድ አለመሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ግን በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እነዚህን ሁለት ሕዝቦች – ኦሮሞንና አማራን – እየገፉ ወደ ደምና አጥንት ጅረት ሊከቷቸው ሌት ተቀን በመትጋት ላይ የሚገኙ ይመስላል – እንደኔ ደግሞ ጨለማው ሊነጋ የተቃረበ ይመስለኛልና ከዚህ በኋላ ይህ እንደውሻ አጥንትና ዘር እያነፈነፉ መጠራራትና ለጥፋት መሰማራት ሊያከትም ጫፍ ላይ ደርሷል እላለሁ፡፡ እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባን ጉዳይ ግን አንድን ማኅበረሰብ ጊዜ ይፍጅ እንጂ ሸረኞችና ተንኮለኞች በቀደዱት የጥፋት ቦይ መክተት የሚቻል መሆኑን ነው፡፡
ውድ ወገኖቼ! አሁን ጊዜ የለንም፤ ዐማራና ኦሮሞ ወደ ዐማራነትና ኦሮሞነት ለይቶላቸው ከመዝቀጣቸው በፊት እንድረስላቸው፡፡ ልድገመው – ኦሮሞና ዐማራ ወደ ኦሮሞነትና ወደ ዐማራነት በአራዶቹ አገላለጽ ከመሸብለላቸው በፊት ቀድመን ካልደረስንላቸው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከታሪክ መዝገብም ተፍቃ ትጠፋለች፤ ይህ ሰይጣናዊ ትንቢቴ እውን እንደማይሆን በአንድዬ ብተማመንም “ጠርጥር ገንፎም አለው ስንጥር” ይባላልና የሆነው ይሁን በሚል እጃችንን አጣጥፈን መቀመጡ ከእስካሁኑ የከፋ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ትላልቅ ምሠሦዎች ሦስት ናቸው፤ አንደኛው ሳይወድ በግዱ አዝምሟል – የጊዜ ጉዳይ ነው እንዳዘመመም አይቀርም፤ ሁለቱ ግን እስካሁን ደህና ነበሩ – በብዙ የንፋስ ንፅውፅውታ እየተመቱም ቢሆን በጽናት እንደቆሙ እስከቅርብ ዓመታት ዘልቀው ነበር፤ ከአሁን በኋላ ግን አስጊ ነው፤ የጽናታቸውም ምክንያት ሳይደግስ አይጣላምና (a blessing in disguise) በአካባቢና በሕዝብ ብዛት የበላይ እንደመሆናቸው ሁሉንም ወደ አንድ ለማሰባሰብና በአንድ ጠባብ ሥነ ልቦናዊ ቦይ እንዲፈሱ ለማደረግ ባለመቻሉ ነው – እነዚህን ዘውጎች በትናንሽ ነገዶች ሣይቀር ለመበጣጠቅ ሳይሞከር ቀርቶ ሣይሆን ለመሠሪዎች ተንኮል ምቹ አልነበሩም፡፡ ቀስ በቀስና በጊዜ ሂደት ግን የማይቻል ነገር የለምና እነዚህ ሕዝቦች ወደተዘጋጀላቸው የጥበት መንገድ ሊገቡ ይችላሉ፤ አዝማሚያዎችም በግልጽ እየታዩ ነው፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮጵያ አምላክ በቅርብ ጣልቃ የሚገባው፡፡ ደስ ይበለን – ጣልቃ ይገባል!…(እውነቴን ነው የምላችሁ ማን እንዲህ በል እንደሚለኝ አላውቅም፤ግን እውነቱ ይሄውና ይው ነው – በቅርብም ኢትዮጵያን የሚያድን ተዓምር እናያለን፡፡ ታሪክም ለዚህ ምሥክሬ ው፡፡)
ኦሮሞ ሰፊ ነው፡፡ የሸዋ ኦሮሞ አለ፡፡ የወለጋ ኦሮሞ አለ፡፡ የአርሲ ኦሮሞ አለ፡፡ የባሌ ኦሮሞ አለ፡፡ የወሎ ኦሮሞ አለ፡፡ ባጭሩ የሌለ ኦሮሞ የለም፡፡ “ኦሮሞ ታዲያ ከየት ነው የሚገነጠለው?” ብለን ስንጠይቅ ችግሩ ከሕዝብ ሣይሆን ከሌላ ሆኖ እናገኘዋን፡፡ ያ “ሌላ” ነገር ደግሞ በዋናነትም ባይሆን በመለስተኛ አጫፋሪነትና በዕቅድ አስፈጻሚነት ልሂቅ ተብዬውን ሀገር አጥፊና ሀገር አልሚ ይይዛል፡፡ የተማረ ሰው ለልማት ቅርብ የመሆኑን ያህል ለጥፋትም በጣም የቀረበ ስለመሆኑ በተለይ ያሳለፍናቸው 42 የመከራና የስቃይ ዓመታት በግልጽ ይናገራሉ፡፡ ልሂቅ ሀገር አጥፊና አልሚ አልሁኝ? ራሳችንን እንመርምር፡፡
ኦሮሞን እገነጥላለሁ ብሎ የተነሣ ወገን ካለ ዕብድ ነው፡፡ እርግጥ ነው አማራጭ ሚዲያ ባለመኖሩ ምክንያት በተወሰኑ በሞኖፖል በተያዙ የሚዲያ አውታሮች የተወሰነ ግርግርና ጊዜያዊ የልብ መሸፈት መፍጠር ይቻላል፡፡ እውነቱ ሲገለጥ ግን ሁሉም አቅል ይገዛል፡፡ እስከዚያውና እንደ እውነቱም ከሆነ ግና “mob” የምንለው ነገር በጣም መጥፎ ነው፡፡ ክርስቶስን ያሰቀለው ሞብ ነው፡፡ ብሩተስን ያሰቀለው ሞብ ነው፡፡ በሞብ ምክንያት ብዙ ሀገሮች ፈርሰዋል፤ ተፈጥረዋልም፡፡ በሞብ ምክንያት እጅግ ብዙ ንጹሓን የዓለም ዜጎች ለሰይጣን ጭዳነት ተዳርገዋል፤ አሁንም ድረስ፡፡ በሞባዊ እንቅስቀሴ ወቅት ምክንያትና ሎጂክ እሥር ቤት ይገባሉ፤ ይገረፋሉ፤ በጭካኔም ይታረዳሉ፡፡ ስለሆነም “ሞብ አያስፈራም፤ ሞብ አገር አይበትንም፤ ሞብ አገር አያስገነጥልም ….” አልልም፡፡ ብዙ መጥፎ ውሳኔዎችና መጥፎ ድርጊቶች በሞብ ጊዜ – በስሜት ግልቢያ ወቅት – ይከናወናሉ፡፡ በነዚህን መሰል መጥፎ ድርጊቶች ወቅት የሚከሰቱ የክፋትና የውድመት ተግባራት ለከፍተኛ ጸጸት የሚዳርጉና ብዙዎቹም የማይቀለበስ አሉታዊ ጠባሳ የሚያኖሩ ናቸው፡፡ በተለይ ወጣቱ – የነብር ጣቱ – ትኩስ ኃይል እንደመሆኑ አዲስ ነገርን የማየት ጉጉት አለው፡፡ መሠሪዎች ይህን ኃይል ተጠቅመው ታሪክን ቢያንሻፍፉና ቢያጣምሙ በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ – ይህን እስኪበቃን አይተናል፤ እያየንም ነውና ለኛ አዲስ አይደለም፡፡ ስለሆነም ምራቅ የዋጡ የማኅበረሰቦቻችን አባላት ብዙ ይጠበቅባቸዋል – ከየጎሣው ያሉ አባቶችና እናቶች ዝም አይበሉ፡፡
ኢትዮጵያዊነትን በተመለከተ በኦሮሞ ሕዝብ ውስጥ የተለያዩ አስተሳሰቦች እንዳሉ ማንም ይገነዘባል፡፡ ጥቂት የማይባሉ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት አቋም ያላቸው የኦሮሞ ልሂቃን መኖራቸውም የማይታወቅ አይመስለኝም፡፡ ጥሪየ እነዚህ ወንድሞቼና እህቶቼ እንዲሁም ልጆቼ ወደኅናሊቸው እንዲመለሱና የጋራ ሀገር እንዲኖረን በጋራ ትግል እንዲሠለፉ ነው፡፡ ከስሜት የወጣ የሰከነ ትግል እስካልተደረገ ድረስ የጠላት መሣሪያ እንደሆኑ ዕለተ ምፅዓትን እየተሰቃዩ መጠበቅ ነው – ተነጣጥሎ ደግሞ ነፃነት ዕርም ናት፤ አትገኝም፡፡ ከእልህ ወጥተን ወደ አመክንዮ እንግባ፡፡ ሥልጣን እንደሆነች ወንበሯ አንዲት ናት፡፡ ያቺን ወንበር ደግሞ ማንም ይያዛት ግን አንዲት እንደሆነች ዓለም ታልፋለች እንጂ እንኳንስ ሺህና ሚሊዮን ሁለትም አትሆንም፡፡ ለሚራኮትባት ሁሉ ብትሆን ደስታውን ባልቻለችው – ስገምት፡፡ ግን ካንድ በላይ ቢቀመጡባት ትሰባበራለችና አትችልም፡፡ ታዲያ ለዚህች አንዲት ምሥኪን ወንበር ይህን ያህል ሕዝብ በውጪና በሀገር ውስጥ በጎሣና በዘር፣ በሃይማኖትና በወንዝ ልጅነት ጎራ ለይቶ አበሳውን ማየቱ ለጤና ነው ትላላችሁ? አቅል እንግዛ እንጂ! “ሀበሻ ዱሮውንም…” ከሚል ትችት መውጣት አለብን – ሀበሻነትና ሀበሻዊ ማንነት በራሱ አጠያያቂ ቢሆንም፡፡
ትናንት በኦኤምኤን – በዐዋጅ ብከለከልም በድብቅ – አንድ ልዩ ዝግጅት ተከታትያለሁ – ባማርኛ፡፡ በዚህ ዝግጅት አወያዩ ደጀኔ ጉተማ ለጠየቀው አንድ ጥያቄ ጃዋር መሀመድ የሰጠው መልስ እንዲህ ነበር – “የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ከሩዋንዳ ጋር የሚመሳሰል አይመስለኝም፡፡ እንደኔ የዚህች አገር መፃዒ ዕጣ-ፋንታ ከዩጎዝላቪያና ከሶቭየት ኅብረት ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡” የመልሱ ጥቅል ይዘት እንዲህ ነበር፡፡
በጣም ገረመኝ፡፡ ከዚህ አባባል ብዙ ነገር መገንዘብ ይቻላል – “የዘፈን ዳር ዳሩ እስክስታ ነው”፤ ጃዋር ምን ማለት እንደፈለገ ብቻ ሣይሆን ምን እንዲሆንለት እንደሚፈልግ ሣይቀር ወደየትም የጥንቆላ ቤት መሄድ ሳያስፈልገን በቀላሉ መረዳት አይከብድም – ከዚያ ይሰውር እንጂ፡፡ በነገራችን ላይ ከሁለትና ከዚያ በላይ ዘውጎች የምትወለዱ ወገኖቻችን ልዩነቶቻችንን ለማጦዝና የሆነ ዓላማ ለማሣካት ከምትሞክሩ ይልቅ የሁለት ቤት አባልነታችሁን የማይገሠስ ወርቃማ ዕድል በመጠቀም ሕዝቦችን ለማስማማትና ለማዋሃድ ብትጥሩ በታሪክም በትውልድም ትከበራላችሁ፡፡ ሰዎች ክፉ ከሆኑ ፣ በሀብትና በሥልጣን ሱስ ከተለከፉ፣ በእርኩስ መንፈስ ከተነዱና ጤናማ ኅሊናቸውን በሆነ ኃይል ከተነጠቁ … ልዩነትን ለክፉ ዓላማ መጠቀም ይችላሉ – እንደ አብነት ጎጃሜዎቹን መለስ ዜናዊንና ገብሩ አሥራትን(የአሁን እሱነቱን አይደለም!)፣ ኦሮሞውን አዲሳለም ባሌማንና ወሎየውን ሼህ አላሙዲንን መጥቀሱ በቂ ነው፡፡ ልዩነትን በተለይም በራስ ውስጥ የሚገኝን የሁለትነት ልዩነት በጎ ላልሆነ ዓላማ መጠቀም ከኩነኔዎችና ከክፋቶች ሁሉ የበለጠ መጥፎ ተግባር ነው፡፡ በኔ ውስጥ ያለውን አንዱን ማንነት በኔ ውስጥ በሚገኝ ሌላ ማንነት ብደበድበው፣ ደብዳቢውም ተደብዳበውም እኔ ራሴው ነኝና በየትኛውም መለኪያ ልክ አልሆንም ብቻ ሣይሆን ትልቁን የወንጀል ፍርድ ያስበይንብኛል – ራስን መግደል ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ነውና! እነጀዋርም የዚህ ሾተላይ ሰለባዎች ናቸው፡፡ ሙሉ በሙሉ “እኔ ‹ንጹሕ‹ አማራ ነኝ” የሚልና ሙሉ በሙሉ “እኔ ‹ንጹሕ› ኦሮሞ ነኝ” የሚል ሰው (ደግነቱ በየዋህነት እንዲህ የሚል ቢኖርም ከእውነት ግን ሊኖር አይችልም እንጂ) ይህን ዓይነት ስህተት ቢሠራ ንስሃ አለው – አለማወቁና አለኝ የሚለው “ንጹሕ” የኦሮሞ ወይም የአማራ ደም መጠነኛ አዘኔታና አመክሮ ሊያስገኝለት ይችል ይሆናል፤ እነጀዋር ግን ሕዝብን አንድ ለማድረግ ማድረግ ከሚጠበቅባቸው መልካም እንቅስቃሴ ውጪ ለመለያየትና ክፍፍል ለመፍጠር ጥረት ቢያደርጉ አይደለም እግዚአብሔር ሰይጣን ራሱ ይታዘባቸዋል – መሬቱ የተደላደለላቸው ኅብረትንና ስምምነትን ለመፍጠር ብቻ ነውና ሁለቱንም ሆነህ ወደ አንዱ ብታዳላ ማዳላትህን ማንኛውም ወገን በፀጋ ሊቀበለው አይገባም – ነግ በኔም እኮ አለ! ለምሣሌ እኔ የጉራጌ ደም እያለብኝ በጉራጌ ላይ ከዘመትኩ ጤናየ ተቃውሷል ማለት ነውና የሀኪም ክትትል በእጅጉ ያስፈልገኛል፡፡ ምን ማለት እንደፈልግሁ በተለይ የሁለት ዘውጎች ውጤት የሆናችሁ ዜጎች በደንብ የገባችሁ ይመስለኛል፡፡
ለማንኛውም የዚህ ንግግር አንድምታ (implication) ኦሮምያ የሚባል በታሪክ የሚታወቅ አንድ ሀገር ኖሮ፣ አማሪያ የሚባል ራሱን የቻለ ግዛት ኖሮ፣ ከፊቾ የሚባል፣ ሃዲያ የሚባል፣ ጠምባሮ የሚባል፣ ጌዲዮ የሚባል፣ ከምባታ የሚባል፣አፋር የሚባል…. ራሳቸውን የቻሉና በተባበሩት መንግሥታት መዝገብ ውስጥ እንደነፃ ሀገር ተመዝግበው የሚኖሩ “የምሥራቅ አፍሪቃ ሀገራት” ኖረው በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በሕወሓት የአፓርታይድ አገዛዝ ሥር ያሉትን “ነጻና ፌዴራል መንግሥታት” በቅጡ የማያስማማ ሁኔታ ከተፈጠረ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሩዋንዳ ዓይነት የዘር ፍጅት ሣይሆን እንደቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረትና ዩጎዝላቪያ “ኢምፓየሪቱ” ትበታተናለች የሚል አስተያየትና ቅድመ ትንበያ ነው ጆሃር የሰጠው – “ህልም እልም” ብያለሁ ጆሃር፡፡ ይቺ የፈረደባት ኢምፓየር ደግሞ ስንቶች የኦሮሞ ነገሥታትና መሣፍንት ወያኔ ወደ ሥልጣን እስከመጣበት እስከ 1983ዓ.ም ድረስ ሲገዟትና ሲነዷት እንደነበሩ መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ ዕንቆቅልሽ ምን አውቅልህ፡፡ (ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ ምነው ሰሞኑን ፀጥ አልክ? ኧረ ብቅ በል!)
እንደኔ እንደኔ ኢትዮጵያ መጥፎ ዕድል ከገጠማት የምታመራው ወደ ራሺያና ወደ ዩጎዝላቪያ ሣይሆን ወደ ሶማሊያና ሦርያ እንዲሁም ወያኔዎች በጭካኔያቸው ቀጥለው የትግራይን ሕዝብ መከታና ደጀን በማድረግ ሌሎችን መጨፍጨፋቸውን አባብሰው ከገፉበት ጉዟችን በቀጥታ የሚያመራው ወደ ሩዋንዳ ነው – ማንም ሲያምረው ይቅር እንጂ ኢትዮጵያ ወደ ራሺያ ሊያስኬዳት የሚያስችል ታሪካዊ መደላድልም ሆነ ማኅበረሰብኣዊ ዝግጅት የላትም፤ እውነትና ትንቢት ይለያያሉ ወንድሞቼ፡፡ ይህን መጠራጠር ቂልነት ነው፡፡ በመሠረቱ እኔ የፖለቲካ ሣይንስ ተማሪ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን “የኢትዮጵያ ሁኔታ እየከፋ ከመጣ የምንሄደው ወደ ዩጎዝላቪያ ነው ወይንስ ወደ ሩዋንዳ?” ተብዬ ብጠየቅ መልሱ እጅግ በጣም ቀላልና እርሱም ወደ ሩዋንዳ መሆኑን ማስረዳት አይቸግረኝም፡፡ ይልቁንስ “አይመጣምን ትተሸ ይመጣልን ባሰብሽ” ነውና ነገሩ ጤነኛ ነኝ የሚል ዜጋ ሁሉ ይህን ነገር አሁኑኑ ይጨነቅበት፡፡
ብዙ ስናገር መዋል እንደሌለብኝ አውቃለሁ፡ አንዳንድ የኦሮሞ ልሂቃን ከገባችሁበት ወረተኛና ከፋፋይ የባዕዳን አስተሳሰብ ባፋጣኝ ውጡ፡፡ ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ከሞላ ጎደል በእኩል ደረጃ ተረግጠው የሚኖሩባት የምስኪኖች ሀገር ናት፡፡ መበታተን የሚባል ቃል ያለው በልሂቃን ምናብ ውስጥ እንጂ በእውን ምድር ላይ የለም፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ታች ወርዶ ማየትና ኑሮውን እየኖሩ የሚፈልገውንና የማይፈልገውን ማጥናት ይገባል፡፡ የሚሻው አምባነኖችን በአምባገነኖች መተካት ወይም እንደዶሮ ተገነጣጥሎ ለየብቻው መኖርን ሳይሆን እፎይ ብሎ በአንድነትና በነፃነት የሚኖርባትንና ሰብኣዊ መብቶች የሚከበሩባትን የጋራ ሀገር መፍጠር ነው፡፡ በጥቃቅን ታሪካዊ ቁርሾ ምክንያት ትልቅ ሀገር አትፈርስም፡፡ ብትፈርስ ደግሞ ማንም ከማንም በልጦ የማይጠቀምባት ወይም የማይጎዳባት የጃርት መፈንጫ ትሆናለች እንጂ በላም አለኝ በሰማይ በሚገነቡ ትናንሽ መንግሥታት ውስጥ ማንም አፄ በጉልበቱ ከኮልኮሌዎቹ ጋር የሚዘባነንባቸው ብጭቅጫቂ ሀገራት አይመሠረቱም፡፡ ይህ አስተሳሰብ ህልም ነው፡፡
ባንዴራን በሚመለከት ሕዝብን ባናወናብድ መልካም ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንደነበረችና እንደነገሩም ቢሆን አሁንም እንዳለች የማንቀበል ከሆነ እንደእስካሁኑ ሁሉ ስምምነቶችና ድርድሮች ሳይጀመሩ እያለቁ ዕዳችን ይቀጥላል፡፡ ይህም ሁኔታ ለጋራ ጠላቶቻችን ምቾትንና እፎይታን እየፈጠረ የግፍ አገዛዙ – እንደሰውኛ አስተያየትና ግምት – ማብቂያ የሌለው ይሆናል፡፡ አዲስ ነገር እየፈጠርን ሕዝብን በተለይም ወጣቱን ውዥንብር ውስጥ አንክተት፡፡ ችግራችን የእራፊ ጨርቆች ቁጥር ማነስ ወይም መብዛት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን ለዘመናት የገዙ የኦሮሞ ነገሥታት ያውለበልቡት የነበሩት የትኛውን ባንዴራ እንደነበረ ታሪክና የታሪክ ሰዎች ቀርተው መሬቱም ያውቃል፡፡ ከዚህ ከኢትዮጵያዊነት አኩሪ ነጥብ አንጻር ራስ አሊ ሚራህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ አባት ነበሩ – “የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን የአፋር ሰው ግመሎቻችንም ያውቃሉ” ብለው የተናገሩት ዘመናትን ተሻጋሪ በሳል ንግግር አሁንም ትኩስ እንደሆነ አለ፡፡ ከርሳቸው እንማርና ከታሪክ ተወቃሽነት እንዳን፡፡ የወረት ፍቅር ወረት ነውና ያልፋል፡፡ ስካርም ምን ጊዜም ስካር ነውና በስካር ወቅት የምናደርጋቸው አንዳንድ አልባሌ ነገሮች ለትዝብት እንዳይዳርጉን መጠንቀቅ አለብን፡፡ ወረትም ስካርም ቢያልፉም ጠባሳ ትተው እንጂ እንዲሁ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከብዥታ እንውጣና ወደ እውነቱ እንቅረብ፡፡ እውነት እንደፀሐይ ጨረር በቀጥታ ሲያዩት ቢያጥበረብርም አማራጭ የለንምና ትውልዳችንን ማዳን ከፈለግን ከልቦለድ ዓለም ባፋጣኝ እንውጣ፡፡ ወያኔ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን በቀላሉ እየጨፈለቀ ለጊዜውም ቢሆን ትንሽ ፋታ ያገኘ የመሰለው በኦሮሞና በአማራ ልሂቃን ዕርዳታ ነው – በተለይም በኦሮሞዎቹ፡፡ ችግሩን ቀን ይፈታዋል፡፡ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን እነሱ ምቹ ቦታ ተቀምጠው ሕዝብን የሚከፋፍሉና ልብ ለልብ እንዳይገናኝ ለማድረግ ልዩነትን የሚዘሩ ክፉ ሰዎች አሉ፡፡ ከናዝሬት አዲስ አበባ በደቂቃዎች ውስጥ በኅብረት ጉዞ መድረስ እየተቻለ በኬኒያና በደቡብ ሱዳን ዞረው በሊማሊሞና በግራካሱ በኩል ወደ ፊንፊኔ ለመግባት የሚቋምጡ ኃይሎች እንዳሉ በበኩሌ አውቃለሁ፡፡ ማንም ግን ብቻውን ተጉዞ አራት ኪሎ ይቅርና ቃሊቲም ይሁን ሰንዳፋ አይደርስም፡፡ የዐዋቂ አጥፊ አንሁን፡፡
ቋንቋና ባህልን በተመለከተ ማንኛውም ዜጋ የራሴ ነው የሚለውን ቋንቋና ባህል ማሳደግና ለትውልድ ማስተላለፍ መብቱ ብቻ ሣይሆን ግዴታውም ነው፡፡ ስለሆነም የዚህን ሰፊ ሕዝብ ቋንቋና ባህል ማክበርና ጥቅም ላይ ማዋል የኦሮሞ ብቻ ሣይሆን የሌሎቻችንም ሁሉ የውዴታ ግዴታ ነው፤ የኦሮሞው ብቻም ሣይሆን – የጋራችን ሀብታችንን አማርኛን ሳንዘነጋ – የሁሉም ዘውግና ነገድ ቋንቋ ማደግና መበልጸግ አለበት፡፡ ይህ ሲባል ደግሞ በተለይ ቋንቋ የመግባቢያ መሣሪያ እንጂ አለልክ የሚኮፈሱበት ወይም ሌሎችን ለመናቅና ለማናናቅ የሚጠቀሙበት የግል ዕቃ እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው – አንተ ቶሎሣ ባጋጣሚ ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋህ ሆነ፤ ማነህ አንተ ወንድሜ አቻምየለህ ደግሞ ዐማርኛ ሊሆንብህ ተገደድህ ልበል፡፡ እናሳ? ወደንና ፈቅደን ባልሆንነው ነገር ዝንታለሙን የቋንቋ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቀን መኖር አለብን? እንደግ እንጂ! ሰው የሆነ ፍጡር ሁሉ ኦሮምኛን/አማርኛን መናገር ባይችል እንኳን የኦሮሞነትን/የአማራነትን ማንነት መላበስ ይከብደው እንደሆነ እንጂ የኦሮምኛን/የአማርኛን የባለቤትነት ይዞታ የመጋራት ያልተሸራረፈ መብት አለው – ሁሉም ቋንቋ የሁሉም ነው – ቋንቋ የሰው ነው፤ ባለቤት አልባ የሆኑ ነገሮች ውስጥ ቋንቋ የመጀመሪያው ነው – ባለማወቅና በሞኝነት ግን ሰዎች በቋንቋ ምክንያት ብዙ ሲነታረኩ ይስተዋላል፡፡ ለምሣሌ እንግሊዝኛ አሁን ባለቤት የለውም፡፡ አማርኛም በኢትዮጵያ የዚያኑ ያህል ነው፡፡ በሂደት ደግሞ ሁሉም ቋንቋዎች ወደዚህ ደረጃ ሊደርሱ ይገባል ወይም መድረስ አለባቸው፤ ይህ የኔ ምኞት ነው – ምናልባትም በተግባር ሳይታይ ዓለማችን ቅርጽዋን የምትቀይርበት ከንቱ ምኞት፡፡ ለማንኛውም አንዱ የሌላውን ልሣን ሲያውቅና ሁሉም የሁሉንም ቋንቋ ተናጋሪ ሲሆን ማንም እየተነሣ “የኛ ቋንቋ የናንተ ቋንቋ” የማለት ሥልጣን የለውም፡፡ የኔ ያንተ፣ ያንተም የኔ ይሆኑና አንደኛው የግጭት መንስኤ ይወገዳል፡፡ መሆን ያለበት እንደዚያ ነው፡፡
በቋንቋ አርበኝነት የሀገርም ሆነ የግለሰብ ዕድገት አይመጣም፡፡ የሥነ ልሣንን ህገ ተፈጥሮ እንወቅ፡፡ በሥነ ልሣን ልደትና ሞት የሚጠቀሱ መሠረታዊ አላባውያን አሉ – በጉልበትና በዐዋጅ፣ በዕብሪትና በጥላቻ ግን አንድ ቋንቋ አያድግም፤ አይጠፋምም፡፡ ስለዚህ ትልቁ መፍትሔ ወደ ኅሊና መመለስ ነውና ከጥላቻ መንፈስ መውጣትም ነውና በፍቅር ማዕበል ውስጥ እየዋኙ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ዜጋን በዜግነቱ ብቻ መቀበልና ተፈቃቅዶ አብሮ መኖርም ነው በነዚህ ነጥቦች ዙሪያ እናተኩር፡፡ ኦሮሞና አማራ ትግሬና ጊሚራ የመጣው የዛሬ ስንት ዓመት ገደማ ነው፤ ሰው ግን ሲፈጠር አንድ ብቻ ነበር – ከዚያ ሔዋን ተጨመረችና ሁለት ሆኑ፤ ቀስ ብሎ ደግሞ እኛ ተጨመርንና ሰባት ቢሊዮንን አለፍን፤ ሰው በዛ ነገር በዛ፡፡ እናም ግዴላችም “ፍቅር ካለ ዘጠኝ ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል” ይባላልና ፍቅር ይኑረን፡፡ ፍቅር ካለን የሚጎድለን ነገር አይኖርም፡፡ ፍቅር ከሌለን ግን አለን የምንለው ብዙ ነገር ሁሉ የኛ አይደለም – በዪና ቀማኛ ይታዘዝበታልና፡፡ መደማመጥንና መግባባትን ያድለን፤ ሰላም፡፡

ኢትዮጵያዊው የቀድሞ ሚስቱን ገድሎ እጁን ለፖሊስ ሰጠ።

$
0
0

14681585_1140461742734757_1673739465202327646_n

ከዳላስ ቴክሳስ አካባቢ እንደሰማነው፣ ይህ የሆነው ትናንት ሰኞ ኦክቶበር 24 ነው።

ሃናን ሰይድ እና ስሙ ያልተጠቀሰው የቀድሞ ባለቤቷ ፣ ሁለት ልጆች ቢኖሯቸውም የተፋቱት ከዓመት በፊት ነበር። ቢሆንም በተለያየ ጊዜ ይከታተላት ነበር ይላሉ ታዛቢዎች። እናም ባልታወቀ አጋጣሚ ትናንት ሰኞ አግኝቷት በጥይት ሊገድላት ችሏል።

በኋላም ለፖሊስ ደውሎ እጁን ሰጥቷል። የ2 ዓመት እና የ 4 ዓመት ዕድሜ እንዳላቸው የተነገረው ልጆቻቸውም በዘመዶች ጥበቃ ሥር ይገኛሉ።

ከሶስት ሳምንት በፊት እዚያው ቴክሳስ ዓሊ ኢድሪስ የተባለ ኢትዮጵያዊ ሚስቱን እና አንድ ልጁን ገድሎ የራሱንም ህይወት ማጥፋቱን መዘገባችን ይታወሳል። በሶስት ሳምንት ውስጥ በቴክሳስ እንዲህ ዓይነት ነገር መከሰቱ ያሳስባል።

የሃናን ሰይድ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ እዚያው ዳላስ ቴክሳስ ይፈጸማል።

(pic. credit yoni Djutopia)

Source :-Admas News

በደቡብ ክልል በዘረኛ ጥቃት ሰለባ ሆነው የተፈናቀሉትን ወገኖች ለመርዳት እንቅስቃሴ ተጀመረ

$
0
0

ህብር ሬዲዮ (ላስ ቬጋስ ) | በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን በዲላ፣በይርጋጨፌ፣ወናጎ፣ጨለለቅቱና ፍስሃ ገነትን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን በገዛ አገራቸው የአካባቢው ባለስልታናት ጭምር በተሳተፉበት ጥቃት ለጊዜው ቁጥራቸው በአነስተና ግምት ከመቶ በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ በርካታ መኖሮያ ቤቶች፣የተለያዩ አገልግሎት መስቻ የንግድ ተቋማት በእሳት ወድመዋል በጥቃቱ ሳቢያ ከአካባቢአቸው ተፈናቀሉትን ለመርዳት በመላው ኣለም የሚገኙ የአካባቢው ወጣቶች አስተባባሪነት የዕርዳታ ማሰባሰብ በጎ ፈንድ አማካይነት ተጀምሯል ሲሉ የኮሚቴው ተወካይ ለህብር ሬዲዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገልጹ።

south-ethiopia

አቶ መድሃኒት ሳሙኤል የዕርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት አንዱ በሰጡት በዚሁ ቃለ መጠይቅ በአካባቢው ከደረሰበት ጥቃት በተጨማሪ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ በየቤተስኪያኑና መስጊድ ሜዳ ላይ የወደቁ ወገኖቻችነን ወገን ለጊዜውም ቢሆን መርዳት ይገባላል ሲሉ ተቅሰዋል።በአካባቢው በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ስጋት እንዳለ ጠቁመው በፌዴራል ቁጥጥር ስር ሰሆን የተወሰደው ጥቃት ፌዴራል ሲወጣ ይቀጥላል የሚል ዛቻ በጥቃት አድራሾቹ እየተገለጸ ነው ብለዋል።

በጌዲኦ ዞን በአካባቢው ለረጅም ዘመን የኖሩ ብቻ ሳይሆን ሌላው ቀርቶ እዛው ተወልደው አድገው ቤት ንብረት ያፈሩ ሳይቀር ካድሬዎች፣የአካባቢው ታጣቂዎችና ፖሊሶች ጭምር ቀጥተኛና ስውር ድጋፍ በመስጠት ባቀጣጠሉት በዚህ ግጭት ኢትዮጵያውያንን አማራ፣ጉራጌ፣ኦሮሞ፣ትግሬ እና ሌላም በማለት በመጤነት በመፈረጅ በተወሰደው በዚህ ጥቃት ሃያ አምስት ሺህ በላይ መፈናቀሉ፣የደረሰው የሰው ሕይወት ጥፋት ተጣርቶ አለመታወቁና መረጃው ዛሬም በመታፈኑ የደረሱትን ችግሮች ደረጃ በአግባቡ ማሳት አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል።

በአካባቢው የአሁኑ የከፋ ይሁን እንጂ ተመሳሳይ ጥቃት ሲፈጸም ይሄ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ያሉት አቶ መድሃኒት ጉዳዩ ዘላቂ መፍትሄ የማይበጅለት ከሆነ ዛሬም ጥቃቱን አድራሾች በጥላቻ ቅስቀሳ መጠመዳቸውንና በዛቻ ላይ እንዳሉ ጠቁመዋል።

የኮሚቴው አባል ለህብር ሬዲዮ በሰጡት በዚህ ቃለ መጠይቅ የተቃተሉ ቤቶችን ችግሮች ተከሰቱባቸውን አካባቢዎች ሌላው ቀርቶ ፖሊስ አባላት የሚቃተሉ ቤቶችን አስቀድመው እየለዩ ተቃዋሚዎች እንዲያቃጥሉ በር ላይ ቅጠል ያስቀምቱ እንደነበር ገልጸዋል።

ለተፈናቀሉና ችግር ላይ ለወደቁት ቢያንስ ለምግብና ለመድሃኒት የበኩላችንን አስተዋጽዎ እናድርግ በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በጎ ፈንድ ለመርዳት ከዜናው ግርጌ የምታገኙትን ሊንክ በመጫን ድጋፍ ማድረግ ይቻላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአካባቢው በምርቻ 97 ቅንጅትን ማሸነፍ ተከትሎ ሕወሃት ሆን ብሎ የየአካባቢውን የአስተዳደር መዋቅር በመጠቀም በጥላቻ ቅስቀሳ መጤ ያሏቸውን ኢትዮጵአውአን ቅንጅትን መርጠዋል በሚል ከፍተኛ ጫና፣እስራትና ድብደባ ይፈጽም እንደነበር ይታወሳል።

በቅርቡ የዚህ ሁሉ ጥቃት መነሻ ተደርጎ በምክንያት የሚቀርበው የጌዲዮ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት አስቀድሞ በካድሬዎች በጉልበት የተወሰደውን ቦታ ለባለንብረቶቹ ለጉራጌ ማህበር ይገባል ብሎ መወሰኑን ተከትሎ የፍርዱን ውሳኔ ወደ ጎን በማድረግ ሌላው ቀርቶ ዳኞቹ ራሳቸው አካባቢው ተወላጆች መሆናቸው እየታወቀ በካድሬዎች ጭምር መጤ በገዛ አገራችን አንሸነፍም በማለት በወሰዱት ዘረና ቅስቃሳ በተመሳሳይ ወቅት በየአካባቢዎቹ ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱ ጥቃቱ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሳይሆን እንዳልቀረ ግምታቸውን የሚሰጡ ወገኞች አሉ።

በዲላ፣በወናጎ፣በይርጋጨፌ፣በፍስሃ ገነት፣በቸለለቅቱነ ጥቃቱ በተፈጸመባቸው ሌሎቹም ቦታዎች የተፈናቀሉትን ለመደገፍ ለማገዝ ጥረት የጀመረው ኮሚቴ በጎ ፈንድ የከፈተውን አካውንት ሊንክን በመጫን ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡ ሊንኩ፡የሚከተለው ነው

https://www.gofundme.com/reach-out-to-victims-in-gedeo-zone-2ut6ssn8

“የእሬቻውን ዘር ማጥፋት እያዩ በዚህ ጊዜ ሕዝብ ካልተባበረ አንድ ካልሆነ ምንድን ነው የምንጠብቀው?”–የኦቦ ነጌሳ ኦዶ ዱቤ ታሪካዊ ንግግር በሚኒሶታ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በጽናት የውይይት መድረክ አማካኝነት ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወለዱ የፖለቲካ አክቲቭስቶችን እና መሪዎችን በአንድ መድረክ በማገናኘት እንዲመክሩ አድርጎ ነበር:: ትናንት የአማራ ተጋድሎ አክቲቭስት ቤተልሄም ዓለምሰገድ በዚሁ የሚኒሶታው ታሪካዊ መድረክ ላይ ያደረገችውን ንግግር ዘ-ሐበሻ ማቅረቧ ይታወሳል:: ለዛሬው ደግሞ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ኮሚቴ መሪ የሆነውን ኦቦ ነጌሳ ኦዶ ዱቤ ያደረገውን ታሪካዊ ንግግር ይዘን ቀርበናል:: “የእሬቻውን ዘር ማጥፋት እያዩ በዚህ ጊዜ ሕዝብ ካልተባበረ አንድ ካልሆነ ምንድን ነው የምንጠብቀው?” የሚሉት ኦቦ ነጌሳን ንግግር ቢያደምጡት አይቆጩበትም::

ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወዴት?

$
0
0

አገም ጠቀም ሲል ላለፉት አምስት አመታት ሲካሄድ የነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞና ትግል ፣ ብዙ መስዋአትነት አስከፍሎ፣ አንዳንድ የማይናቁ ድሎችን አስገኝቶ፣ ገዢውን ፓርቲ አስደንግጦና፣ በያዘው መንገድ ከቀጠለም ሕልውናው ጥያቄ ውስጥ አንደሚገባ ግልፅ በማድረጉ አስቸኩዋይ ጊዜያዊ ዓዋጅ አንዲያውጅ አስገድዶ አዚህ ደርሰናል። ከአንግዲህ ትግሉ ምን አይነት አቅጣጫ ሊይዝ ይችላል ፣ ምንስ አይነት አቅጣጫ ይዞ ቢሄድ ለሕዝባዊ ትግሉ ስኬትና ብዙዎቻችን ለምንመኘው የሕግ የበላይነት የሰፈነባትና የዜጎች ሁለንተናዊ መብቶች የሚከበሩባት ኢትዮጵያ አውን መሆን ሊያበረክት ይችላል የሚለውን ለማየት ትንሽ ወደሁዋላ ማየት የግድ ይላል።

Police fire tear gas to disperse protesters during Irreecha, the thanks giving festival of the Oromo people in Bishoftu town of Oromia region, Ethiopia

በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የተደረገው ትግል

ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የተለያዩ ተቃውሞዎች አንደነበሩ ባይካድም በ1997ቱ አገር አቀፋዊ ምርጫ የኢህአዴግን የምርጫ ኮሮጆ ግልበጣና ስርቆት አስመልክቶ ከነበረው ተቃውሞ ቀጥሎ በስፋትና በቀጣይነት የተካሄደው ያለፈው አምስት ዓመት ሕዝባዊ ትግል ፣ አንደኛው ከአንደኛው ልምድ በመማር ሚሊዮኖችን ያሳተፈ፣ የህዝብን የትግል ወኔ ያነሳሳ ልምድን ያጋራና ያዳበረ ፣ሕዝባዊ አጋርነትን የፈጠረ ፣ ሕዝባዊ አምቢተኝነትን በጠነከረ መልኩ በማካሄድ በገዥው ክፍል ውስጥ ጥርጣሬንና ክፍፍልን ከመፍጠርም በላይ አስገድዶ የመንግስት ውሳኔዎችን ያስለወጠ ሂደት ነበር።

ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ውስጥ ካላደረገ አንቅልፍ የሚነሳው ኢህአዴግ አዲስአበባ በሚገኘው የአወሊያ ትምህርት ቤት ዉስጣዊ አስተዳደራዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሿሚና ሻሪ ካልሆንኩ በሚል የወሰደውን አርምጃ ተማሪዎቹ በመቃወማቸው፣ ተቃውሟቸውም በቤተሰቦቻቸውና ጉዳዩን በሰሙ ሰፈርተኞች ድጋፍ በማግኘቱ ሁኔታው አስደንብሮት፣ ይቺ ባቄላ የሚል አሳቤ ውስጥ ገባ ።ይሄም በመሆኑ ፣መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለበትም የሚለውን የሕገመንግስት አንቀጽ የተጻረረና ባፍጢሙ የደፋ፣ አህባሽ የተባለውን አስላማዊ አስተምህሮ፣ ማጥመቅ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ካልጫንኩ ብሎ በመውተርተሩና የመጅሊሱን ምርጫ አስመልክቶ የወሰደው አቋም፣ አብዛኛውን ህዝበ ሙስሊም ያስቆጣ ሀገር አቀፍ አንቅስቃሴ ለመፈጠር ምክንያት ሆነ። መጀመሪያ የተነሳውን ተቃውሞ በተገቢው መንገድ ማስተናገድ ባለመቻሉና ነገሮችን በማባባሱ ለተቃውሞው አዲስ ጉልበት በመስጠት ድርጅታዊ ቅርጽ ይዞ “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን ” ወለደ ።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት፣ የወከላቸውን ህዝበ ሙስሊም ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ረጅምና አልህ አስጨራሽ ውይይቶች ከመንግስት አካላት ጋር በማድረግ ቢቀጥሉም፣ ጥያቄዎችን በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ችግሮቹን በማባባሱ ተቃውሞው አየከረረ ሲመጣና ሀገራዊ መልክ መያዝ በመጀመሩ መንግስት የሀሰት ወንጀል ፈብርኮ የኮሚቴው አባላትን ለአስር ዳረጋቸው ።

ይሄ ምናልባት በመንግስት በኩል ተቃውሞውን ያበርደዋል በሚል አሳቤ የተወሰደ አርምጃ ህዝበ ሙስሊሙን የበለጠ አስቆጥቶ ፣ በአንድ ወገን የታሰሩት ወኪሎቻቸው አንዲፈቱ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ጥያቄያቸው በአግባቡ አንዲመለስ መጠነ ሰፊ አገራዊ አንቅስቃሴ ተቀጣጠለ ። ይሄ ባለ በዙ ፈርጅ ሰላማዊ አንቅስቃሴ በየጊዜው ስልቱን አየቀያየረ አዳዲስ የሰላማዊ ትግል አካሄዶችን በመጠቀም፣የመንግስትን አፈና ተቋቁሞ ቀጣይነት አሳየ። የህዝባዊ ትግሉ እየጎለበተ መሄድና ከአጠቃላይ ህብረተሰቡ ድጋፍ ማግኘት (ለምሳሌ ሰምያዊ ፓርቲ ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ)ያስበረገገው ኢሕአዴግ፣ ከዚህ ቀደም በነበሩት ያገዛዝ ስርዓት ያልታየ ቤ ተ መስጊድን ደፍሮ ሰዎችን መደብደብ፣ማሰርና መግደል በአንዋር መስጊድ ጀምሮ በልዩ ልዩ የሀገራችን ከተሞችና ትናንሽ ቀበሌዎች ማካሄዱን ተያያዘው ።

ይህ አፈናና ግድያ ግን ትግሉን ለጊዜው ትንሽ ያለዘበ ቢመስልም ‘ድምጻችን ይሰማ ‘ በሚል የተደራጀው አካል የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ጥያቄ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንዲሁም ለፍትህ ተቆርቋሪዎች በሰፊው በማስተዋወቅ የኢህአዴግን አስከፊ በደል ለማሳወቅና ትግሉም ቀጣይነት አንዲያገኝ አድርጉአል ። ከዚህ ባለፈም በልዩ ልዩ ስልት የተካሄዱት ትግሎች፣ በኋላ የተቀጣጠሉት ሕዝባዊ ትግሎች ጥቅም ላይ ያዋሏቸውና ውጤታማ የሆኑ የትግል ተሞክሮዎች በርካታ ናቸው። በፈይሳ ሌሊሳ አማካኝነት አለም አቀፍ አውቅና ያገኘው ሁለት አጅን አቆላልፎ ወደላይ በማሳየት ተቃውሞን መግለጽ ጅማሮውን ያገኘው በዚሁ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በየመስጊዱ ይካሄድ በነበረው የተቃውሞ አንቅስቃሴ ወቅት ነበር።

በኦሮሚያ የተካሄደውና በመካሄድ ላይ ያለው ትግል

የአዲስ አበባ የተቀናጀ “ማስተር ፕላን” ተብሎ የሚታወቀው በፌደራል መንግስት ተቀርጾ ፣እንደተለመደው ለይስሙላ እንኳን ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ያካባቢ ከተሞች ተጠሪዎችና የህብረተሰብ ክፍል ጋር ምንም አይነት ውይይት ሳይካሄድ የወጣው ሰነድ የዛሬ ሁለት አመት የመጀመሪያ ተቃውሞ የገጠመው አምቦ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኙ ተማሪዎች ነበር። ይህን ከተማሪዎች የተሰነዘረ ተቃውሞ፣ በእንዴት ተደፈርኩኝ በሚል፣ መንግስት ርህራሄ በጎደለው መንገድ የወሰደው የቅጣት እርምጃ በአንዳንዶች ግምት ወደ ሰባ የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈና መቶዎችን ያቆሰለ፣ ከዚህ ያለፈ ቁጥር ሰዎችን ወደ እስር የሰደደ በመሆን ተጠናቅቆ ነበር።

መንግስት በወሰደው አረመኔያዊ እርምጃ “ማስተር ፕላኑን “ አስመልክቶ የነበረው ተቃውሞ ለጊዜው ረገብ ያለ የነበረ ቢመስልም፣ ከአመት በኋላ ጊንጪ ከተማ የሚገኝ ትምህርት ቤት ቦታን፣ ለአልሚ ለመስጠት በሚል በተንቀሳቀሱ የመንግስት ህይሎች ላይ ተማሪዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ያስነሱት ተቃውሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት ወደ አብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ተዛመተ። ይሄ ባብዛኛው በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆችን ማእከል አድርጎ መቀጣጠል የጀመረው ተቃውሞ፣ የሁለተኛ ደረጃና ከዛም በታች ያሉ ተማሪዎችን ማካተት ሲጀምርና በተለይም የተማሪዎቹን ቤተሰቦችና የየአካባቢውን አርሶ አደር ወደ ተቃውሞው ጎራ መሳብና ጥንካሬ መያዝ፣የኢህአዴግን መንግስት ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከተተው።

የተቃውሞው ስፋትና ጥልቀት ያስደነገጠው መንግስት ፣ ተቃውሞውን ይገታልኛል ብሎ ያሰብውና ተግባራዊ ያደረገው የህዝብን ድምፅ ማዳመጥ ሳይሆን፣ የተለመደውን የሀይል እርምጃ በጅምላ ተቃውሞ ታይቷል በተባሉት ስፍራዎች ላይ በማካሄድ ነበር። ይሄ የጅምላ የሀይል እርምጃ ወንድ ከሴት፣ ልጅ ከአዋቂ፣ ሽማግሌና አሮጊት ሳይለይ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈ በርካቶችን ደግሞ የአካል ጉዳተኛ ያደረገ ነበር። መንግስት የወሰደው አስከፊ እርምጃ ግን፣ መንግስት ያሰበውን ውጤት ሳይሆን በተቃራኒው የህዝብ ቁጣ የበለጠ ገንፍሎ እንዲወጣ በማድረግ፣ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ተቃውሞ በየከተሞችና እንዲሁም በአብዛኛው የኦሮሚያ ገጠር ቀበሌውች ተስፋፋ።

የተቃውሞው ጥልቀት፣ ስፋትና፣ ቀጣይነት ያሳሰበው ኢህአዴግ አድርጎት የማያውቀውን “እኛ ድሮም ያለ ህዝብ ይሁንታ ምንም ነገር አድርገን አናውቅም”በሚል ቅጥፈት “ማስተር ፕላኑ” መታጠፉንና ከእንግዲህም ማናቸውም ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ህዝብን አወያይቶና አሳምኖ ተግባራዊ እንደሚሆን በይፋ አወጀ። በኢህአዴግ ታሪክ የማይታወቀውን በጠቅላይ ምኒስትሩ በኩል የህዝቡን ጥያቄዎች ትክክለኛነት ከመቀበልም በላይ ለሰዎች ህይወት መጥፋት ይቅርታን ጠየቀ። (በጎን እነ አባይ ፀሀዬ ልክ እናስገባዋለን -የኦሮሞን ማስተር ፕላን ላይ ያለ እምቢተኝነትን መሆኑ ነው-ብለው ሲደነፉ ሾልኮ በወጣ የድምፅ ቅጂ የተገኘ ቢሆንም የትግሉ ግለት፣ ይሄንንም እንኳን በአደባባይ ወጥተው እንዲክዱ አስገድዷቸዋል)
ችግሩ ግን ኢህአዴግ ዘገምተኛ በሆነ መንገድ ተጉዞ ውሳኔውችን ወደ መቀልበስና ይቅርታ ወደ መጠየቅ በገባበት ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደው ትግል በታላቅ ፍጥነት በመጓዝ አንዳንድ ውሳኔውችን ከማስለወጥ ባሻገር ፣ ለረጅም ጊዜ ህብረተሰቡን አፍኖ መሬቱን በልማት ስም ዘርፎ አናቱ ላይ የተፈናጠጠውን የኢህአዴግ ስርዓት ከነአካቴው መለወጥ አለበት ወደሚል ድምዳሜ ተሻግሮ ተግባራዊ ትግል የሚያካሂድበት ወቅት ነበር።

በ አማራው ክልል የተነሳው ትግል

በኦሮሚያ የሚካሄደው ትግል ፋታ አልሰጥ ብሎ በቀጠለበት ወቅት ለኢህአዴግ እንደ ዱብ እዳ የመጣበት በጎንደር የተቀሰቀሰው ትግል ነው። መነሻው የወልቃይት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀን ለማፈን በፌዴራል ፖሊሶች የተሞከረውን ከማክሸፍ ጋር የተያያዘ ነው።

የህወሃት ቱባ ባለስልጣናትና ደጋፊዎች የወልቃይት ጥያቄ ትናንት የተነሳ ለማስመሰል ቢሞክሩም ጥያቄው ህወሃት አዲስ አበባ ላይ ስልጣን ይዞ፣ ሀገሪቱን በቋንቋ ፌዴራሊዝም እናዋቅራለን በሚል ማካለል ሲጀመር የአካባቢው ሰዎች በተቃውሞ ድምፃቸውን እንዳሰሙ የትናንት ትዝታ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጅ የሆኑ ህለት አዛውንት ለወቅቱ የሽግግር ፕሬዘዳንት ለመለስ ዜናዊ እርምጃው ወንድማማች ህዝብ ለዘመናት የሚያጣላና ደም የሚያፋስስ ሊሆን ስለሚችል እንዲታጠፍ የማሳሰቢያና የምልጃ ደብዳቤ ፅፈው እንደነበር ይታወቃል።

በጸረ-ደርግ የትግል ወቅት ለአጠቃላይ ስትራቴጂ ጠቀሜታ ይሰጠኛል በሚል የተቆናጠጠውን ወላቃይት ላለመልቀቅ ወስኖ የነበረው ህወሃት፣ የኛን ይዞታ ሊቃወሙ ይችላሉ የሚሉአቸውን ከቀዬው በጦርነቱ ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ገብተው የነበሩ ወልቂቴዎች ወደ ቀድሞ ይዞታቸው እንድይመለሱ ትልቅ ዘመቻ በማካሄድ እንዳከላከሉ ገህድ የሆነ ሀቅ ነው። ከዚህም በላይ አዲስ አበባ በገቡበት አመት ከህወሃት በቅነሳ የተሽኙ ሰላሳ ሺ ወታደሮች ከነመቋቋሚያ ገንዘብ ሰፈራ እንዲያካሂዱ የተወሰነውም ወልቃይት ውስጥ ነበር። ሀገሬውም በክፉ አይን ሳያይ እንደወንድሞቹ አስተናግዶ የነበረ ቢሆንም የባለቤትነት ጉዳይ በተነሳ ጊዜ ግን እጅግ በጣም አዝኖ እንደነበር የሚካድ አይደለም። ለዚህ ነው አሁን አንዳንድ የህወሃት ጮሌዎች ምናለ ችግር ካለና የይገባኛል ጉዳይ ከተነሳ በህዝበ ውሳኔ ማለቅ ይችላል የሚለው ስላቃቸው አሳዛኝ የሚሆነው። ይሄ የሚይስታወሰኝ የእስራኤል ሰፋሪዎች በግዥም ሆነ በማፈናቀል የፍልስጤሞችን ስፍራ ወስደው ሲያበቁ፣ በመሬት ላይ ያለው ነባራዊ እውነታ ፍልስጤሞች የኛ መሬት ነው የሚለውን አያንፀባርቅምና ጥያቄያቸው ውድቅ መሆን አለበት የሚል የጉልበተኛ ክርክር የሚያሰሙትን ነው።

የወልቃይት ጉዳይ ጫሪ ምክንያት በመሆን፣ እንቅስቃሴው ቢነሳም፣ ለሃያ አምስት ዓመት በብአዴን አጋፋሪነት ህወሃት በአማራው ክልል የሚያካሂደው በደልና፣ በተለያዩ ጊዜያትና በበርካታ ስፍራዎች፣ ከበደኖ እስከ አርባጉጉና ጉራ ፈርዳ በአማራው ህዝብ ላይ የሚደርሰው ሞት እንግልትና ግፍ ሞልቶ በመፍሰሱ የተፈጠረ ተቃውሞ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ህወሃት ከተቋቋመበት ጅምሮ የአማራውን ህዝብ እንደዋና ጠላት አድርጎ ሲቀሰቅስበት እንደነበረና ስልጣንም ከያዘ በኋላ እስካሁንም ድረስ ትምክህተኛ የሚል ተለዋጭ ስም በህዝቡ ላይ ለጥፎ መከራውን የሚያበላው በመሆኑ፣ አዲሱ ትውልድ በአዲስ ብሄርተኝነትና በቆራጥ ተነሳሽነት በቃኝ ብሎ የተነሳበት አጋጣሚ ነው።

በኢሬቻ በዓል 2009 የብዙ መቶ ዜጎች ሀይወት መቀጠፍና የህዝብ ቁጣ

ዘንድሮ ቢሾፍቱ ላይ ይካሄድ በነበረው የኢሬቻ በዓል ማሳረጊያ ቀን በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በተሰበሰበበት ዙሪያው በውሃና በገደል ፣ቀሪው መውጫና መግቢያ ደግሞ በታጠቁ ወታደሮች የታጠረ መስክ ላይ ወጣቶችሰላማዊ ተቃውሞ በማሰማታቸው፣ በእንዴት ተደፈርን በሚል በስፍራው በነበሩ አለቆች ትዕዛዝ የኢህአዴግ ወታደሮች፣ በአጠቃላይ የተሰበሰበው ህዝብ ላይ አስለቃሽ ጢስና የጎማ ጥይት (ባለቀለህ ጥይት ነው የሚልም ዘገባ አለ)በብዛት አፈንድቶ ሽብር በመፍጠር የተሰበሰበው ህዝብ ነፍሱን ለማትረፍና ከስፍራው ለማምለጥ ሲል በብዙ መቶ ለሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።
የሀያ አምስት አመታት ግፍ ሳያንስ ባለፈው አመት በኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ልዩ ልዩ ቀበሌዎችና የገጠር ከተሞች ከአምስት መቶ በላይ ንፁሃንን ህይወት ማጥፋት አልበቃ ብሎ፣ በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል ላይ በማንአለብኝነት ኢህአዴግ በወሰደው እርምጃ በህዝብ ላይ በደረሰው አሰቃቂና መጠነ ሰፊ ሞት በቁጣ የገነፈለው ህዝብ፣ ለቀናት የዘለቀ ከመንገድ መዝጋት እስከ ንብረት ማቃጠልና የመሳሪያ ፍልሚያ ያካተተ ተቃውሞውን በመንግስት ላይ አደረገ።
ኢህአዴግ ይሄ ህዝባዊ ቁጣ ያስነሳውን ተቃውሞ በመደበኛ የፖሊስ ሃይል መቋቋም ስለማልችል ሁኔታው አስገድዶኝ ለስድስት ወር የሚቆይ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጄአለሁ ማለቱን በጠቅላይ ምኒስትሩ አማካይነት፣ ተግባራዊ በሆነ ማግስት ለህዝብ አሳውቋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ የህዝቡ ቁጣና የደረሰውም ጉዳት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በምንም መለኪያ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያሳውጅ ህኔታ እንዳልነበር በርግጠኝነት እየታወቀ፣ መንግስት ለምን ይሄን እርምጃ ወሰደ የሚል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን።
በአገራችን ባለፉት አመታት በተለይም ደግሞ ባለፉት አስራ አንድ ወራት በኦሮሚያና በአማራው ክልል እንዲሁም በኮንሶና ሌሎች ስፍራዎች በመካሄድ ላይ ያሉት ትግሎች የስልጣን መሰረቱን እንዳናጉበት የተረዳው ኢህአዴግን በበላይነት የሚመራው የህወሃት ቡድን፣ ትግሉን ቢቻል ለመግታት ካልተቻለም ለማዳከም የወሰዳቸው ማስፈራሪያ እስር፣ ድብደባና ግድያን ያካተቱ ዘርፈ ብዙ እርምጃዎች የታሰበውን ግብ ሊመቱ አልቻሉም።
ከላይ እንደጠቀስኩት በጎንደር የተነሳው ተቃውሞ ለህወሃት ዱብዕዳ የሆነበት በኦሮሚያ ያለው ተቃውሞ ሳይረግብ በመቀስቀሱ ብቻ ሳይሆን፣ ለሃያ አምስት ዓመታት ሲስራበት የነበረው ሁለቱን አንጋፋና የሀገሪቱን ሁለት ሶስተኛ የሚወክል ህዝብ እርስ በርስ የማናከስ ፕሮጀክት “ በኦሮሚያ የሚደረገው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም”“ በኦሮሚያ የሚፈሰው የኦሮሞ ደም ደማችን ነው”… በሚሉ መፈክሮች እንደ ነጎድጓድና መብረቅ በመላው ሀገር መሰማቱ ነው።ጎንደር ላይ በተካሄደው መሬት አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ የተስተጋቡት መፈክሮች ለሁለቱ ታላቅ ህዝብ የትግል አጋርነት መልካም ጅማሮነትን ባበሰረበት ቅጽበት፣ የህወሃት መራሹን መቃብር ቁፋሮ መጀመርን ያበሰረ ነበር። የዚህ የትግል አጋርነት ጅማሮ ለስልጣናቸው የሚያመጣውን ዘለቄታዊ ችግር ወዲይውኑ የተገነዘቡት የህወሃት ቁንጮዎቹ ሳይውሉ ሳያድሩ ዋልጌ የ”ኮምዩኒኬሽን” ሚንስትራቸውን አሰማርተው ፣ በየቴሌቪዥንና ራዲዮ ጣቢያ እየተወዛወዘ የአጋርነት ጅማሮውን ለማጠልሸትና ተጨማሪ መርዝ ለመርጨት ሲውተረተር ከርሟል።
ዘመቻው በዚህ ብቻ ሳይገታ፣ የጥፋት መልክተኛ የሆኑቱን አባይ ፀሃዬና ስዩም መስፍንን በቴሌቪዥን አቅርቦ፣ የኛን የበላይነት ተቀብላ የማትኖርን ኢትዮጵያ፣ የጦርነት አውድማ አድርገን ህዝቡን እርስ በርሱ በማናከስ እንደ ሀገር የማትኖርበትን ሁኔታ እንፈጥራለን የሚል እንድምታ ያለው አሰልቺና ባዶ ማስፈራራት ለማካሄድ ሞክረው ነበር። ይሄ እናባላችኋለን የሚል ሰይጣናዊ የማስፈራሪያ ፕሮፓጋንዳ ህዝብን ከማስበርገግ ይልቅ በበለጠ እልህ ትግሉን እንዲያቀጣጥል ተጨማሪ ነዳጅ ሆነ፣
የዛሬ አስራ አምስት አመት ከላይ እስከታች መበስበሱን ያወጀ ድርጅት እስካሁን ድረስ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጦ ለመቆየቱ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም፣ ላለፉት አስራአንድ ወራት የተካሄዱት ህዝባዊ ትግሎች ግልፅ እንዳደረጉት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከእንግዲህ ፣በራሱ አንደበት በሙስና የተጨማለቀ፣ ራሱ ያፀደቀውን ህገ መንግስት በየጊዜው የሚደፈጥጥና በውስጡ የማፊያ ቡድኖችን አቅፎ የሚጓዝን የገዢ ስብስብ የመሸከም ትከሻ የለውም።
ይሄን የተገነዘበው የህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያወጀው፣ በኢትዮጵያ የተቀጣጠለው ህዝባዊው ተቃዎሞ በያዘው ፍጥነትና ስፋት እየቀጠለ ከሄደ መፍረከረከ የጀመረው ድርጅቱ አጠቃላይ ውድቀት ሊደርስበት ይችላል ብሎ በመፍራት ድርጅቱን ለማዳንና በአገሪቷ ላይ ያለውን የበላይነት ለማስቀጠል የወሰደው እርምጃ ነው ለማለት ይቻላል።

ምን ይደረግ?
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መከታ በማድረግ ከአሁኑ በርካታ ሺህ ዜጎችን በእስር እንዳጎረና አንጻራዊ ሰላምም እያሰፈነ እንደሆነ የሚፎክረው የህወሃት መንግስት፣ በዚህ መጠነ ሰፊ እስር ፣ግድያና አጠቃላይ የሆነ መንግስታዊ ሽብር፣ጊዜያዊ እፎይታ ያገኝ እንደሆን እንጂ፣ የህዝቡ አልገዛም ባይነትና ትግሉ አሁን በደረሰበት ደረጃ ለረጅም ጊዜ ግፊቱን ተቋቁሞ በስልጣን ይቆያል ለማለት አዳጋች ነው።
እርግጥ ነው ግፍና ጭቆና አንገፍግፎት ያለ ተቀናጀና፣ በትግል ሂደት የዳበረ ልምድ ያለው ድርጅት አመራር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ወጥቶ በቃኝ! በማለቱ ብቻ ፍትህና ርትዕ የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይቻላል ማለት እጅግ አስቸጋሪ ነው።

ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ኢህአዴግ በየጊዜው የሚያካሂድባቸው አፈናና፣ አላፈናፍን ባይነት ከራሳቸው ከድርጅቶቹ ድክመት ጋር ተዳምሮ፣ ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ያሉትም ሆነ ውጭ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ህዝብን መርቶ ለድል ማብቃት ይቅርና አመርቂ በሆነ መንገድ ለማታገልም በቂ አቅም የላቸውም። የተጠራቀመው የህዝብ ብሶት በእንዲህ ያለ ስፋት ተቀጣጥሎ አገር አቀፍ መልክ ሲይዝና መንግስትን ሲያርበደብድ፣ ሱሬውን ሳይታጠቅ የተያዘ መንግስት ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚዎችም ጭምር ናቸው።

በዚህ በተዳከመ ሁኔታ ቢሆንም ፣ባሁኑ ወቅት የድርጅቶች ዋና ሃላፊነት አባሎቻቸው በሙሉ ልብ በህዝባዊው ትግል እንዲሳተፉ ማድረግ፣ በተሳትፎአቸውም አዳዲስ የትግል አጋሮችን ማፍራት፣ ትግሉ አሰባሳቢ የሆኑ እገራዊ አጀንዳዎችን እንዲይዝ ያለሰለሰ ጥረት ማድረግ፣ ያላቸውንም ሃይል በበለጠ ማሰባሰብ፣ መቀናጀት ከሚችሉት ጋር መቀናጀትና ድርጅታዊ ጥንካሬአቸውን ማጎልበት መሆን ይኖርበታል።

አታግሎና ሁነኛ አመራር በመስጠት ህዝባዊ ትግሉን ስኬታማ ሊያደርግ የሚችል ድርጅት ባይኖርም፣የህዝብ ምሬት አሁን በደረሰበት ደረጃ፣ ምንም እስሩና ግድያው ቢበረታ እንቢተኝነቱ የሚቀጥል በመሆኑ አገሪቷን ወደ ጦር ቀጠናነት ሊለውጥ፣ የሀገሪቱንም ህልውና ሊፈታተን የሚችል አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠር እነደሚችል ግልጽ እየሆነ ሄዷል።

የህወሃት ቁንጮዎች አገሪቷ ላይ ያላቸውን ሁለንተናዊ የበላይነት ለማስቀጠል በሚል ያወጁት ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው በአገሪቱ የመከላከያና የደህንነት እንዲሁም የልዩ ልዩ የፖሊስ ሃይል እንደሆነ ይታወቃል። እነዚህ ተቋማት ሃገራዊ ተቋማት እንደመሆናቸውና አገሪቱም አሁን በምትተዳደርበት ህገ መንግስት ሃላፊነታቸው በዋናነት የሀገሪቷን ህልውና ማስጠበቅና ህገ መንግስቱን ማስከበር እንጂ ስልጣን ላይ ያለውን ፣ ህዝብ በቃኝ መረረኝ ብሎ፣ እንዲወርድ የሚጠይቀውን ቡድን ህይወት ማራዘም እንዳልሆነ ይታወቃል።

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ አሁን በያዘው ጎዳና ከቀጠለና የሀገሪቷ መከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ ሃይሎች የሃገሪቱን ህልውና የማስጠበቅ መሰረታዊ ተግባር ወደ ጎን ትተው፣ የአንድ ጠባብ ቡድንን ዓላማና ፍላጎት ተግባራዊ የማድረግ እንቅስቃሴያቸውን ከቀጠሉና የተደገሰውን የጥፋት ድግስ በህዝቡ ላይ ካደረሱ፣ የሰራዊቱን መፍረክረክ ብቻ ሳይሆን፣ አገራችንን በፍጥነት ወደ መበታተን እንደሚይስኬዷትና ፣በዚህም ታሪክ በፍጹም ይቅር የማይለው ሀገራዊ ክህደት እንደሚፈጽሙ ሊያምኑ ይገባል።
በአሁኑ ወቅት ታሪክ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ታላቅ ፈተና ከፊቱ ደቅኗል። የኢህአዴግ ቁንጮ ሰዎች የፖለቲካ ስልጣኑን በመቆጣጠር ዛሬ እነሱ፣ የስልጣን ማማውን ሙሉ ለሙሉ ካልተቆጣጠሩ፣ የህዝብ ብሶትና በደል፣ ብሎም የሀገር መበታተን ደንታ የማይሰጣቸው መሆናቸውን በግልጽ እያሳዩ ያሉበት ወቅት ነው። በመሆኑም፣ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ልትወጣው ወደ ማትችለው አዘቅት ሊከቱ የሚፈልጉ እኒህ እኩይ አካላት መሳሪያ መሆንን አሁኑኑ ገትታችሁ፣ የሀገርን ህልውናና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታችሁን የመወጣት ታሪካዊ ሃላፊነት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

ኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበውን አደጋና የገባንበትን አሳሳቢ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የመከላከያ ሰራዊቱና የፀጥታ ሃይሎች ብቸኛ አማራጭ የሚሆነው፣ መቶ በመቶ ምርጫውን አሸንፈን የህዝብ ይሁንታ አግኝተን ነው መንግስት የመሰረትነው ነው የሚለው የፖለቲካ ስልጣኑን የተቆጣጠረው ቡድን በፍፁም ተአማኒነት የሌለው መሆኑን፣ ህዝብ ወክለን ነው ፓርላም የተቀመጥነው የሚሉትም አንዳችም ውክልና እንደሌላቸው ያለፉት አስራ አንድ ወራት የህዝብ እንቢተኝነት በማያወላዳ መንገድ በማረጋገጡ፣ ቡድኑ ፓርላማውን አሁኑኑ በትኖ አዲስ ሀገራዊ ምርጫ እንዲያደርግ ጠንከር ያለ ጫና ማድረግ ነው የሚል እምነት አለኝ።

በመንግስት አካባቢ የተሰባሰበው ይሄ አጥፊ ቡድን ጫናውን አልቀበልም ብሎ እንቢተኝነትን የሚመርጥ ከሆነ ፣ ለሀገር ህልውናና ለህዝብ ደህንነት ሲባል ቡድኑን ሙሉ ለሙሉ ከስልጣን አግዶ ብሄራዊ መግባባትና ድርድር የሚካሄድበት የጊዜ ገድብ አበጅቶ ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ሁኔታውን እስከ ማመቻቸት የሚሄድ እርምጃ ሊወስድ እነድሚችልም የመከላከያ ሰራዊቱና የፀጥታ ሃይሉ ማሳወቅ ይኖርበታል። ይሄንን በማድረግም የተቋቋመበትን መሰረታዊ ዓላማ ማለትም የሀገርን ህልውናና ህዝብን ከክፉ መጠበቅን ተግባራዊ ያደርጋል ።

ፓርላማው ይበተን! ሃገራዊ ምርጫ አሁኑኑ ይካሄድ! የህዝብ እንቢተኝነት ወቅታዊ ያደረጓቸው ጥያቄዎች ናቸው።

የብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች ዋና ዋና ስህተቶች

$
0
0

ከደረሰ ለማ

1. ሌሎች ሰዎች/ድርጅቶች እንዴት መደራጀት እንዳለባቸው ምን አላማ ማራመድ እንዳለባቸው የሚፈልጉትን ለማግኘት በምን አይነት የትግል ስልት መታገል እንዳለባቸው ገደብ ሲጥሉና እነርሱ በፈለጉት መንገድ ብቻ እንዲመሩ መፈለጋቸው አንዱና ዋነኛው ችግር ወይንም ስህተት ነው። ምክንያቱም አንዱ ፈቃጅና ከልካይ ሌላው ደግሞ ተቀባይ ሊሆን አይችልምና ነው። ሁሉም ድርጅት ወይንም ሰው እኩል መብት ያለውና የፈለገውን የማሰብ እና በፈለገው መንገድ አላማውን ማስፈጸም መብትና ምርጫ ስላለው።
minnesota
2. ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የአማራጭ ሃሳብ ወይንም ጥናት አቅራቢዎች እነርሱ ያሰቡትን ያቀዱትን እና የፈለጉትን ነገር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ወይንም እነርሱ የተገኙበት ብሔር ወይንም ጎሳ የፈለገው እንደሆነ አድርገው መናገር መግለጫ መስጠት መወሰን እና ሕግ/ቻርተር ማውጣት ሌላው ፈጽሞ የተሳሳተ አሰራር ነው።
ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ አስተሳሰብ እና አካሄድ አሁን ያሉትን ብዙዎቹን ድርጅቶች ከነገሥታቱ ሥርአት ከደርግ እና ከወያኔ አካሄድና ድርጊት ምንም የሚለያቸው አይደለም።
ኢትዮጵያ ውስጥ ትክክለኛ ፍትሐዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ተፈጥሮ ህዝቡ በነጻና ትክክለኛ የምርጫ ሂደት የፈለጋቸውን ድርጅቶች እና ግለሰቦች ካልመረጠ በስተቀር ማንም በየትኛውም ህዝብ ስም መናገር ሕግ ማውጣት እና መወሰን አይችልም።

ስለሆነም ሕዝብ በነጻነት የፈለገውን መምረጥ እስኪችል ድረስ ማንኛውም ድርጅት ሊያደርግ የሚገባው ከሁሉ በፊት በሃገሪቱ ላይ ፍትሐዊ ሥርዐት ለመፍጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ብቻ ማተኮር ያንን እውን ለማድረግ በጋራና በትብብር መስራት ብቻ ነው። ለሃገርም ሆነ ሊወክለው ለፈለገው ህዝብ ይበጃል የሚለውን የራሱን የሃሳብ አማራጭ ወይንም እቅድ ደግሞ ፍትሐዊው ሥርዐት ከተመሠረተ በኋላ ለህዝብ ማቅረብ ነው። ያኔ ሕዝቡ የፈለገውን ይመርጣል።

ስለሆነም ማንም ሳይወክላቸው በየትኛውም ሕዝብ ስም ሊሆን የሚገባው ይህ ነው ያ ነው ይሚሉ ሁሉ ተሳስተዋል ሊታረሙ ይገባል።
አለበለዚያ ነገሩ ሁሉ ወያኔ የሚፈልገውን ሕዝብ ላይ ጭኖ ያንን እርሱ የፈለገውን አስተሳሰብ እቅድና አካሄድ የተቃወመን ሁሉ እንደሚገድለው እንደሚያስረው እና እንደሚያሳድደው ያለ ወንጀል መፈጸም ይሆናል መጨረሻው።

3. ምንም እንኳን የተለያዩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ያበረከቱት አስተዋጾ ባይናቅም ወደፊትም የሚኖራቸው ድርሻ ቀላል ባይሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረውና የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ወሳኙ ክፍል ህዝቡ እንደሆነ አለመረዳት ይህን የህዝቡን ተጋድሎና ወሳኝነት እነርሱ እንዳደረጉት ወይንም በእነርሱ አመራር ሰጪነት እንደተደረገና ወደፊትም እነርሱ ከሌሉበት ትግሉ እንደማይሳካ መቁጠር ሌላው ከእውነታው የራቀ ነገር ነው።

4. ብዙዎቹ ድርጅቶች እነርሱ ተቀራርበው ቢሰሩ ሊያመጡት ከሚችሉት ውጤት ይልቅ በኢትዮጵያ ላይ/ውስጥ ላለው ችግር የችግሩ ጠንሳሽ ለሆኑት እና እንዳላየ እንደማያውቅ ለሆኑት የውጪ መንግሥታት በከንቱ መጮህ አቤቱታ ማቅረብ ሌላው የብዙ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ችግር ነው።

ከዚህ ይልቅ እርስ በእርስ ተቀራርበው ልዩነቶቻቸውን በልዩነት ይዘው በሚያስሟሟቸው ነገሮች ላይ ግን በጋራ ቢሰሩ የተሻለ ውጤት ያገኛሉ ባይ ነኝ። ማን እንዳገር ልጅ የሚለው ቢሂል በከንቱ አልተነገረምና። እስኪ ከዚህ በኋላ በዚህኛው መንገድ እንሞክረው። ውጤቱ ያማረ እንደሚሆን ይታመናል።

“የኛ አንድ መሆን ለወያኔ መንግስት ቅዠቱ ሲሆን ለሕዝባችን የዘወትር ሕልሙ ነው”–ሁድ አብዱላሂ |የኡጋዴን ኮምዩኒቲ ም/ል ሊቀመንበር በሚኒሶታ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ በተካሄደው ሁሉን ኢትዮጵያዊ ባካተተው የጽናት ውይይት መድረክ ዝግጅት ላይ ከቀረቡት ንግግሮች መካከል የአማራ ተጋድሎ አክቲቭስት ቤተልሄም ዓለምሰገድ እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዓለም አቀፍ የድጋፍ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑትን የኦቦ ነጌሳ ኦዶን ንግግር አቅርበን ነበር:: አሁን ደግሞ የኦጋዴን ኮምዩኒቲ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሁድ አብዱላሂ ያደረጉትን ንግግር ዘ-ሐበሻ ይዛላችኋለች:: አቶ ሁድ “የኛ አንድ መሆን ለወያኔ መንግስት ቅዠቱ ሲሆን ለሕዝባችን የዘወትር ሕልሙ ነው” ብለዋል:: ያድምጡት::


“የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈሪ አይደለም”–ኦቦ ነጌሶ ዋቀዮ በሚኒሶታ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ከትብብር ለአንድነት እና ዴሞክራሲ የተወከሉት አቶ ነጌሶ ዋቀዮ በሚኒሶታ በተደረገው ሕዝባዊ ውይይት ላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዙሪያ ጠለቅ ያለ ጽሁፍ አቅርበዋል:: “የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈሪ አይደለም” ያሉት ኦቦ ነጌሶ በብሄር በተደራጁ ድርጅቶች እና በወቅታዊው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ያደረጉትን ንግግር ያድምጡት::

ሰበር ዜና-የህወሃት ሰራዊት ባለ ቀይ መስመር የአርማጭሆ ወረዳዎችን ተቀማ!

$
0
0

በልኡል አለም

በጎንደር ሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ በሱዳን ጠረፍ አዋሳኝ በደቡብ ተከዜ አቅጣጫ ሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ የላይኛዉ አርማጭሆን ጨምሮ ተሰማርቶ የነበረዉ የህወሃት ጦር በደረሰበት ተደጋጋሚ ጥቃት ምክንያት የጥቃት ወረዳዎቹን ባጠቃላይ እየተነጠቀ ይገኛል ።
ጀግናዉን የአማራ ገበሬን ትጥቅ ለማስፈታት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ያደረገዉ ህወሃት በ14/02/2009 ማምሻዉን የተጠናከረ ሐይሉን ቢያሰማራም በለሱ አልቀናዉም! ወደፊት ለማጥቃት የማይመቸዉ የአማራዉ የነጻነት ምድር አርማጭሆ! ጀግናዉ ህዝብ ከነጻነት ሀይሎች ጋር በመተባበር ዙሪያ ገጠም እሳት በህወሃት ሰራዊት ላይ አርከፍክፏል
ሄሊኮፍተሮች ቢያንባርቁ! ዝቅ ብለዉ ለመብረር እንዳይችሉ የነጻነት ሐይሎች ዙ23 እና ሞርተሮች ከተራራዎች ስርቻ እየተስፈነጠሩ የህወሃትን አየር ሐይል መድረሻ ያሳጡት ሲሆን። የጦር መሳሪያ ድምጽ የሰሙ የአካባቢዉ ገበሬዎች ከየአቅጣጫዉ በማጥቃታቸዉ ምክንያት ወደ ሗላ ማፈግፈግ ያልቻለዉን የወያኔ ሐይል አኮላሽተዉታል።
ከፍተኛ መሰዋትነውት በመክፈል ትጥቅ በማቀበልና በመተባበር ድል የቀናቸዉ የነጻነት ሐይሎች ቆላ ድባትን ጨምሮ ዙሪያ ቁልፍ የጥቃት ወረዳዎችን በቁጥጥራቸዉ ስር ማድረጋቸዉን የህወሃት ወታደራዊ አስተዳደር መርዶዉን ዛሬ የተረዳ ሲሆን መልሶ ጥቃት ለመፈጸም የ 25ተኛ እና ሌሎች ተጨማሪ ክፍለ ጦሮች ተዉጣጪ ወታደሮችን እንዲያሰማሩ መመሪያ ወጥቷል።
ህወሃት ወያኔ በአካባቢዉ ላይ በቀሰቀሰዉ ጦርነት የቆሰሉ ወታደሮችን በሄሊኮፍተር በማመላለስ ከመጠመዱ ባሻገር ቁጥራቸዉ 200 የሚጠጉ የጦር አባላቱ የነጻነቱን ትግል ከነሙሉ ትጥቃቸዉ ተቀላቅለዋል።
እጁን ለነጻነት ሐይሎች በፍቃዱ የሰጠ በቅጽል ወዲ ሳንጃ የተባለ አንድ የ24ተኛ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራር እንድተናገረዉ
” የምንዋጋዉ አርሶ ካበላን ካሳደገንና ካጎለበተን አባት ገበሬ ጋር ነዉ ጸጉሩ ሸበት ያለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ በብርቱ አይኖቹ አሻግሮ የሚመለከት አዛዉንት አባት ላይ ከመተኮስ እጅ መስጠቱና ወደ ህወሃት መዞሩ አዋጪ ሆኖ አግኝቼዋለዉ ” በማለት የገበሬዉን ብቃት አረጋግጧል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
Zehabesha-News.jpg

ለኢትዮጵያ የመከላከያና ፓሊስ ሠራዊት አባላት የተደረገ ጥሪ

$
0
0

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፤ የፌደራልና የክልል ፓሊስ አባላት፤ የአጋዚ ልዩ ኮማንዶ ጦር አባላትና ሌሎች የሥርዓቱ ታጣቂዎች። አገራችን በለውጥ ሂደት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ለእናንተ ቀጥታ መልዕክት ማስተላለፍ የሚገባ ሆኖ ስላገኘሁት ይህንን አጭር መልዕክቴን በጥሞና እንድታዳምጡኝ፤ የሰማችሁ ላልሰሙት እንድታደርሱልኝ እጠይቃለሁ።

Birhanu Nega
የአገር መከላከያ ሠራዊት አባል መሆን ከፍተኛ ክብር ያለው ሙያ እንደነበር የምታውቁት ነው። ለሀገር ዘብ መቆም መልካም ዜጎች ሁሉ የሚመኙት ተግባር ነው። አንድ ሰው ቃለ መሀላ ፈጽሞ የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም ከለበሰ በኋላ ተራ ዜጋ አይደለም። አገሪቷ በዜጎቿ ማየት የምትፈልጋቸውን መልካም እሴቶችን ሁሉ በወታደሮቿ ማየት ትሻለች፤ ለሕዝብ ተቆርቋሪነት፣ ሀገር ወዳድነት፣ ፍትሀዊነት፣ ጀግንነት፣ ታማኝነት በወታደሮቿ ማየት ትሻለች። ለዚህም ነው በብዙ አገሮች ውስጥ ያሉ ሕፃናት “ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?” ሲባሉ ከሚሰጧቸው መልሶች ግንባር ቀደሙ “ወታደር” የሚሆነው። በሀገራችንም ዘመናዊ ጦር ከመደራጀቱ በፊት አያት ቅድም አያቶቻችን ራሳቸውን በወታደርነት አሰልጥነው፤ ወራሪ ሲመጣ በየጎበዝ አለቆቻቸው እየተቧደኑ ዘመናዊ ጦሮችን ሳይቀር ተዋግተው በማሸነፍ የአገራችንን ሉዓላዊነት አቆይተውልናል። ዘመናዊ ጦር ከተደራጀ ወዲህም እስከ ህወሓት አገዛዝ የነበሩ አስተዳደሮች ብዙ እንከኖች ቢኖርባቸውም እንኳን የመከላከያ ሠራዊትን የአገር መከላከያ ሠራዊት አድርገውት ቆይተዋል። የሠራዊቱን ክብርና ሞገስ ለመጠበቅም የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል። ይህ ጥረት ግን በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ሙሉ በሙሉ ተቀልብሷል።
የፓሊስ ሠራዊት ሥራ ለሕዝብ የዕለት ተዕለት ኑሮ ዋስትና መስጠት ነው። ዜጎች በሰላም ከቤታቸው ወጥተው በሰላም የመመለሳቸው ዋስትና ከወገናቸው ከፓሊስ ሊያገኙ ይሻሉ። ሕዝባዊ ፓሊስ የወሮበሎች፣ የሌቦችና የማጅራት መቺዎች ጠር፤ የድሆችና ደካሞች አጋር ነው። ሕዝባዊ ፓሊስ የፍትህ ጠበቃ ነው። እንዲህ ዓይነቱን ፓሊስ በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ማየት አልቻልንም።
የህወሓት አገዛዝ የተከበሩትን የውትድርናና የፓሊስ ሙያዎችን አዋርዶ ለሀገርና ሕዝብ ደህንነት ሳይሆን ለአንድ ቡድን ሥልጣን መከበር የቆሙ ኃይሎች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። አሁን ያለው የኢትዮጵያ መከላከያና የፓሊስ ሠራዊትን ስናስብ በአዕምሮዓችን የሚመጡት የሚከተሉት ሀቆች ናቸው።
1. የጦር ሠራዊቱ፣ብቃትና ዕውቀት እንዲሁም የሀገር ፍቅር ባላቸው ጄኔራሎችና የጦር መኮንኖች የሚመራ ሳይሆን በተቃራኒው ምንም ዓይነት ወታደራዊ ትምህርት በሌላቸው ከሽምቅ ውጊያ ቡድን አዛዥነት ወደ ዘመናዊና መደበኛ ጦር አዛዥነት በድንገት ያደጉ፤ ራሳቸውን ከዘመናዊ ሠራዊት አደረጃጀትና አመራር ጋር ያላዋሃዱ፤ ከሀገር ጥቅም ይልቅ የራሳቸው የግል ጥቅም የሚበልጥባቸው፤ የማይጠረቁ ስግብግቦች፤ ታማኝነታቸው ለሀገር ሳይሆን አባል ለሆኑባቸው ፓርቲዎች የሆኑ ግለሰቦች ናቸው።
2. ዛሬ ያለው የኢትዮጵያ ሠራዊት በወያኔ የስለላ መረብ ተተብትቦ ወይም በእነርሱ ቋንቋ “ተጠርንፎ” በግድ የተያዘ እንደቁም እስረኛ ሊቆጠር የሚችል በከፍተኛ ምሬትና በደል ውስጥ የሚገኝ ሠራዊትመሆኑን እናውቃለን። የሠራዊቱን ክብር በሚነካ፤ ስብዕናን በሚያዋርዱ ዘለፋዎችና በግምገማ ናላው እንዲዞር፣ሞራሉ እንዲላሽቅ የተደረገ ሠራዊት ነው።የህወሓት ጄኔራሎችና ካድሬዎች የሚያወርዱበት ዘለፋና ስድብ የዕለት ተዕለት ቀለቡ የሆነ፤ ሞራሉም የላሸቀ ሠራዊት ነው።
3. አንድ ተራ የህወሓት ካድሬ ወይንም የበታች ሹም የዘረኛው ሥርዓት በሚሰጠው ልዩ ግምትና ስልጣን ከሌሎች ብሔሮችና ብሔረሰቦች የመጡ በማዕረግም በዕውቀትም የበላይ የሆኑንትን ሻለቆችና ኮሎኔሎችን የሚያንጓጥጡበት፣ የሚያዋርዱበትና የሚያሸማቅቁበት፤ አመራሩ በወታደራዊ እዝና ወታደራዊ ስነምግባር መሠረት የሚመራ ሳይሆን በብሄር የበላይነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ዲሲፕሊንና ውህደት የሌለው ሠራዊት ነው። በብሔር የተከፋፈለ በመሆኑ በውስጡ ያለው ጓዳዊ ስሜት በእጅጉ የላላ ሠራዊት ነው።
4. የፍትህ ጥያቄ የሚያነሱ የሠራዊቱ አባላት ለህወሓት ካድሬዎች ስላልጣማቸው ብቻ ያለ ወታደራዊ ህግና አግባብ በአንድ የህወሓት ካድሬ ትዕዛዝ ብቻ ደብዛቸው ሊጠፋ እንደሚችል ስለሚያውቁ በከፍተኛ የፍርሃት እና በራሳቸው ላይ እምነት እንዲያጡ የተደረጉ ናቸው።
5. ይህ ሠራዊት ለወያኔ ጠባብ አጀንዳ በየግንባሩ ዘመቻ እንዲሄድ ሲገደድና ሲማገድ የህወሓት ካድሬዎችና ጄኔራሎች የሕይወትና የደም ግብር እንዳይከፍሉ ከአደጋ እንዲጠበቁ የሚደረግበት ዘዴና ስልት የተቀየሰበት የዘረኝነትና የአድሎ ሥርዓት ውስጥ የተጣደ ሠራዊት ነው።
6. ሠራዊቱ ሲቆስል፣ ደሙን ሲያፈስ፣ ፈንጂ ሲረግጥ፣ ሕይወቱን ሲገብር የህወሃት ቅምጥል ጄኔራሎችና መኮንኖች ቅጥ ባጣ አስረሽ ምችው በየከተማው እንደሚባልጉ የሚያውቅ ሠራዊት ነው።
7. ጫማና የደንብ ልብስ ከዚያም አልፎ የሚበላዉን ምግብ ከሚከፈለዉ ትንሽዋ ደሞዙ ላይ እየተቆረጠበት እናት አባቱን ለመጦር እና ልጆችን ለማሳደግ ፈተና ውስጥ የሚገባ፤ ለበርካታ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተዳረገ ሠራዊት ሆኖ ሳለ በአንፃሩ የህወሓት ጄኔራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች በኮንትሮባንድ ንግድና በዘረፋ ሲከብሩ፤ ንግዳቸውን በግላጭ ሲያጧጥፉ፤ ባለብዙ ህንፃዎች ባለቤቶች በመሆን በዘመድ አዝማዶቻቸዉ ስም ጭምር ሀብት ሲያካብቱ፤ የህዝቡን መሬት ያላግባብ ሲቀሙና ሲቀራመቱ፤ በሰላም አስከባሪ ኃይል ስም በተባበሩት መንግስታት በየሀገሩ እየተመደቡ በወር እስከ 25,000 የአሜሪካ ዶላር ተከፋይ ሆነው ሲቀማጠሉ በሚገባ እያስተዋለ የሚገኝ ሠራዊት ነው።
8. በተጨማሪም እንደው ድንገት ለምርጦቹ የሚደርሰው የሰላም ማስከበር ተሳትፎ ግዳጅ ሲሄድ ሊያግኝ ከሚገባው የኪስ ገንዘብ ላይ አብዛኛውን ለራሳቸዉ ጥቅም በማዋል እና ሀገሪቷ ከዚህ ከሰላም ማስከበር ልታገኝ የሚገባትን ጥቅማ ጥቅም በራሳቸዉ በህዉሃት ጄኔራሎችና አመራሮች የግል ኪስ በማስገባት ራሳቸውንና ዘመድአዝማዶቻቸዉን እያበለጸጉበት ይገኛሉ።
9. ሠራዊቱ ከትንሿ ደመወዙ ለመለስፋ ዉንዴሽን፣ ለአባይ ግድብ ግንባታ፣ ለተለያዩየ ተሃድሶ መዋጭዎች፣ ለአመት በአል ድግሶች መዋጮ እንዲፈል የሚገደድ ምስኪን ነው። አላዋጣም፤ ገንዘብ የለኝም ብሎ ቢል ጸረ ሰላም ወይንም ሌላ ስም ተሰጥቶት ለተለያዩ አይነት ቅጣቶች ይዳረጋል። ሕገ መንግሥቱ በግልጽ ቢከለክልም እንኳን በሰራዊቱ ውስጥ የድብቅ የሕወሀት አደረጃጀት ፈጥሮ በሰራዊቱ ውስጥ የልጅና የእንጀራ ልጅ ስሜት ፈጥሮ የሚከፋፍል እኩይ ኃይል ነው ይህን ሰራዊት የተቆጣጠረው።
በፌዴራል ፖሊስና በአጋዚ ልዩ ኮማንዶ ውስጥ ነግሶ የሚታየው ሁኔታ ከላይ ከዘረዘርናቸው የተለየ አይደለም። ሠራዊቱ የአዛዦቹ አገልጋይ በመሆን የበይ ተመልካች የሆነበት መዋቅር ነው። ሞት፣ የአካል መጉደልና ድህነት ለሠራዊቱ አባላት፤በአንፃሩ ምቾችና ድሎት ግን ለአዛዦቹ እንዲሆን ታቅዶ የተደራጀ ሠራዊት ነው።
ኢትዮጵያ በየዘመኑ እያደገና እየዘመነ የመጣ ሞያን፣ ችሎታንና ወታደራዊ ሳይንስን አዳብሎ የታጠቀና ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የተዉጣጣ ዘመናዊ የአገር መከላከያ ተቋም የነበራት አገር ነበረች። ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ ይህንን ዘመናዊ የአገርና የወገን መከታ የሆነዉን ሠራዊት አፍርሰዉና ለእናት አገሩ የተዋደቀዉን ሠራዊት ለማኝ አድርገዉት ነዉ በህወሓት የበላይነት የሚመራ አዲስ የመከላከያ ሠራዊት የገነቡት። ይህ ህወሓት የገነባዉ ሠራዊት በአደረጃጀቱም ሆነ በቀን ከቀን ስራዉ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅምና ፍላጎት ጋር በምንም መልኩ የተገናኘ አይደለም። ይህንን መከላከያ ሠራዊት የፈጠረዉ ህወሓት፣ የሚመራዉና የሚቆጣጠረዉ ህወሓት፤ ሠራዊቱ በሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ሁሉ ዋነኛዉ ተጠቃሚም የህወሓት/ኢህአዴግ ጥቂት ዘራፊ መሪዎች ብቻ ነዉ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሆይ!
ህወሓት/ኢህአዴግ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ የደገሰዉ የጥፋት ተልዕኮ ካልተሳካ አንተን እንደለመደዉ ሜዳ ላይ በትኖና ባንተ ትከሻ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የዘረፈዉን የአገር ሀብትና ንብረት ይዞ አገር ለቅቆ እንደሚጠፋ ምንም ጥርጥር የለዉም። ለዚህ የሽሽት ጉዞዉ ደግሞ ለረጂም ግዜ ተዘጋጅቷል። በቢልዮኖ ዶላሮች የሚቆጠር ሀብት በውጭ ሀገሮች አስቀምጧል። በዚህ ሠራዊት ዉስጥ የአገሩን ዳር ድንበር የጠበቀ እየመሰለዉ የህወሓት መሳሪያ ሆኖ የራሱን ወገኖች ከሚገድለዉ ኢትዮጵያዊ ዉስጥ ከአስር ዘጠኙ የህወሓት/ኢህአዴግን መወገድ የሚናፍቅ ዜጋ ነዉ። ችግሩ ይህ ሠራዊት ልክ እንደ ሲቪል ወግኖቹ በዘርና በቋንቋ ተለያይቶ የተደራጀ በመሆኑ እርስ በርስ ተገናኝቶ መነጋገርና መወያየት አለመቻሉ ነው።
ይህ ሙሉ በሙሉ በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘዉ ሠራዊት ባለፉት ሀያ አምስት ዓመታት የወሰዳቸዉን ፀረ ሕዝብና ፀረ አገር እርምጃዎች አንድ በአንድ ስንመለከት ይህ ተቋም በሚወስዳቸዉ እርምጃዎች የሚጎዳዉ የሠራዊቱ ጡንቻ የሚያርፍበትን የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱ አባላት እራሳቸዉም የራሳቸዉ እርምጃ ሰለባዎች ናቸዉ። ታድያ ለምንድነዉ ይህ ሠራዊት ከ25 አመት በላይ እሱን እራሱን፣እናቱን፣አባቱን፣ እህቱንና ወንድሙን የሚጎዳ እርምጃ የሚወስደዉ? የአገርን ዳር ድንበር ከባዕዳን ወራሪዎች ለመከላከል የተደራጀና የታጠቀ መከላከያ ሠራዊት ለአዛዦቹ መታዘዝ እንዳለበት ከማንም የተሰወረ አይደለም። ሆኖም አንድ የአገሬን አንድነትና የወገኖቼን ደህንነት እጠብቃለሁ ብሎ ቃለ መሃላ የፈጸመ የመከላከያ ሠራዊት አባል ደህንነቱን መጠበቅ የሚገባዉን ሕዝብ በነጋና በጠባ ግደል ተብሎ ትዕዛዝ ሲሰጠዉ ትዕዛዙን ከመፈጸሙ በፊት ማንን ነዉ የምገድለዉ ለምንስ ነዉ የምገድለዉ ብሎ እራሱን መጠየቅ አለበት።
ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘመናዊ የባርነት አዋጅ ታዉጆበታል። ህወሓት ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ የሚሯሯጠዉ አንተን ከሕዝብ አብራክ የወጣኸዉን የሕዝብ ልጅ በመጠቀም ነዉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ ሀይል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነትና እኩልነት ይዋጋል እንጂ እሱንና ወገኖቹን የህወሓት ባሪያ የሚያደርግን አዋጅ አያስፈጽምም። ይህ አገርንና ሕዝብን ለመጠበቅ ህገ መንግስታዊ አደራ የተሸከመ ሠራዊት የታጠቀዉን መሳሪያ ማዞር ያለበት በወንድሞቹና በእህቶቹ ላይ ሳይሆን ሠራዊቱንና ኢትዮጵያን በትኖ ለመጥፋት ዝግጅት እያደረገ ባለዉ በጠላቱ በህወሓት ጥቂት ዘራፊ የሲቪልና ወታደራዊ መሪዎች ላይ ነዉ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ሆይ!
የኛ ፍላጎት ፍትህ፣ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፉኑባት ኢትዮጵያ እዉን ሆና ማየት ነዉ። እርግጠኞች ነን የእናንተም ፍላጎት ከዚህ የተለየ አይደለም። እነዚህን እኛም አናንተም የምንፈልጋቸዉን እሴቶች ቀምቶን ሁለታችንንም እንደ ባሪያ ረግጦ የሚገዛን ዘረኛዉ የህወሓት/ኢህአዴግ ሥርዓት ነዉ። እናንተና እኛ ይህንን አንድ ላይ የሚረግጠንን ሥርዓት ጎን ለጎን ቆመን በጋራ መታገል ነዉ ያለብን እንጂ እርስ በርስ መተላለቅ የለብንም። ደግሞም ሁለት ፍትህ፣ነፃነትና እኩልነት የናፈቃቸዉ ወንድማማቾች ነፃነታቸውን ቀምቶ የሚረግጣቸዉን ኃይል አንድ ላይ ሆነዉ ይፋለሙታል እንጂ እርስ በርስ አይተላለቁም። በዚህ የነጻነት ትግል ላይ የምንሳተፍ ወገኖችህ ወንድሞቻችንን በመግደል አናንተም እኛን ወንድሞቻችሁን በመግደል የሚገኝ ነገር ቢኖር ባርነትና የአገር አንድነት መፍረስ ብቻ ነዉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አገሩንና ወገኖቹን የሚጠብቅ ኃይል ነዉ እንጂ ጠላቶቹ ግደል የሚል ትዕዛዝ በሰጡት ቁጥር በገዛ ወገኖቹ ላይ የሚተኩስ ኃይል አይደለም።
አንተ የኢትዮጵያ መለዮ ለባሽ ሆይ!
ዛሬ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በኮንሶ፣ በቤኒሻንጉልና ኦጋዴን ዉስጥ እህቶችህ “ወንድም ጋሼ” ድረስልን ብለዉ እየተጣሩ ነዉ፤ ወንድሞችህ “ጋሽዬ” አድነን እያሉህ ነዉ፤ አባትህና እናትህ “ልጄ አንተ እያለህ እንዴት እንዲህ ይደረጋል?” ብለዉ እየጮሁ ነዉ። መቼ ነዉ የምትደርስላቸዉ? መቼ ነዉ ከእስርና ከጥይት የምታድናቸዉ? መቼ ነዉ ተስፋ የምትሆናቸዉ?
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ፓሊስ አባላት ሆይ!
የህወሓት አገዛዝ ልትጠብቀው ከሚገባህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ደም እያቃባህ ነው፤ የውጭ ወራሪን ሳይሆን ፍትህ የናፈቀውን የገዛ ራስህን ወገን እንድትወጋ እያደረጉህ ነው፤ አገርህ ለጥቂቶች ብቻ የምትታለብ ጥገት ሆና ለማቆየት አንተን በመሣሪያነት እየተጠቀሙብህ ነው። የነፃነት ኃይሎች ትግል የገጠሙት ከህወሓት ዘራፊ ወታደራዊና ሲቪል መሪዎች ጋር እንጂ ከአንተ ጋር አይደለም። እነሱ ሁኔታው አላምር ሲል መሸሻ አዘጋጅተዋል፤ እድሜ ልካቸውን በልተው የማይጨርሱት ሀብት በውጭ አገራት አከማችተዋል። ያ ቀን ከመምጣቱ በፊት ግን አንተ የገዛ ወገንህን ገድለህ እንድትጨርስ፤ አሊያም በገዛ ወገንህ ተገድለህ እንድትጠፋ ይሻሉ። እንደምታውቀው በገባንበት ትግል አንተ ብቻ ተኳሽ፤ አንተ ብቻ ገዳይ አይደለህም። የነፃነት ኃይሎች ሊገላቸው የመጣን ኃይል ከመግደል አይመለሱም። በአሁን ሰዓት እንኳን ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሠራዊቱ አባላት በነፃነት ኃይሎች ተጋድሎ መውደቃቸውን ታውቃለህ። ይህ መሆኑ ያሳዝነናል፤ ልትገድለን ስትመጣ ግን ባዶ እጃችንን አንጠብቅህም። እርስ በርስ የሚያጋድለን የህወሓት አገዛዝ ማብቃት አለበት። አንተ የዚህን እኩይ ስርዓት ትዕዛዝ አልቀበልም፤ ከድንበር መጠበቅ ውጭ የሀገሬን ህዝብ አልገልም ያልክ ቀን፤ ይህ ጦርነት ይቆማል። እንደልባቸው የሚያዙት ጦር እንደሌለ ሲያውቁ የሀገሪቱን የፖለቲካ ችግር በጉልበት ሳይሆን በፖለቲካዊ መንገድ ለመፍታት ይገደዳሉ። ለነጻነትና ለእኩልነት እየተዋደቁ ያሉት ወገኖችህ ልክ እንዳንተ ይህ በአንድ ሀገር ህዝቦች መሀከል የሚደረግ ጦርነት እንዲቆም ይፈልጋሉ። በረሀ የገቡት ገበሬ ዘመዶችህ በሰላም አርሰው ልጆቻቸውን አሳድገው ጥሩ ዜጋ ማድረግ ይፈልጋሉ። መገደል፤ መታሰርና መሰቃየት ሰልችቶት በረሃ የገባው ወጣት ሀገሩ ሰላም ሆና፤ የነጻነት አየር እየተነፈሰ ትምህርቱን በነጻ አዕምሮ ተምሮ ለሀገሩ በጉልበቱና በእውቀቱ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚፈልግ እንጂ የጦርነት አባዜ ኖሮበት አይደለም በረሃ የወረደው። ስለዚህ ይህን ጦርነት ማስቆም የምትችለው አንተ ነህ። ይህን የምታደርገው ደግሞ እንዳንተ ሰላምና ነጻነት የሚፈልገውን ወገንህን በመግደል ሳይሆን አንተንም መላው ህዝቡንም አዋርደው መግዛት የሚፈልጉትን ጥቂት ዘራፊዎች እምቢ ማለት ስትችል ነው።
ከዛሬ ጀምሮ የተገኘውን ሁሉ አጋጣሚ ተጠቅመህ ሥርዓቱን በመክዳት የነፃነት ኃይሎችን ተቀላቀል። የሕዝብ ወገኖችን እንድትወጋ ስትታዘዝ እንድትወጋቸው ከተላክባቸው የነጻነትና የእኩልነት ታጋዮች ጋር ተቀላቀል። በአገኘኅው አጋጣሚ ሁሉ በግልም በቡድን መሣሪያህን ወደ ጥጋበኛ ህወሓት አዛዦችህ አዙር።
በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ከነፃነት ኃይሎች ጋር የሚቀላቀሉ የሠራዊቱ አባላት የክብር አቀባበል ይደረጋል። ሠራዊቱን የሚቀበሉ የሚያስተናግዱ፣ የሚያቋቁሙ ቡድኖችን በየቦታው አደራጅተናል። ሕዝብ በህወሓት አገዛዝ ላይ እንጂ በአንተ በሠራዊቱ አባል ላይ የያዘው ቂም የለም። እንዲያውም አንተ ራስህ ትግሉን እንድትቀላቀል ይፈልጋል። በሕዝብና በአገር ላይ በደል ሲፈጽም የኖረው የህወሓት አገዛዝ ፍፃሜ ለማፍጠን በሚደረገው ትግል የአንተ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
በኢትዮጵያችን ውስጥ እንዲኖር የምንፈልገው ሠራዊት ታማኝነቱ ለፓርቲ ሳይሆን ለሀገር የሆነ፤ ድንበሯን ከጠላት የሚከላከል፤ በሀገር ፍቅር ስሜት የነደደ፤ ሕዝብ የሚወደውና የሚያከብረው ሠራዊት ነው። ይህ ሠራዊት የሚገነባው በአንተው ነው። የህወሓት ወንበዴዎች ከዚህ በፊት እንዳደረጉት ሠራዊቱን የመበተን ዓላማም ሆነ ፍላጎት ያላቸው የነፃነት ኃይሎች የሉም። እነኝህ ብልሹ መሪዎቹ ተወግደውለት መዋቅሩ እንደተጠበቀ፤ ሹመትና የደሞዝ ጭማሪ በችሎታና ባደረገው አስተዋጽኦ ብቻ እንጂ ለአንድ ድርጅት ባለው ድጋፍ ወይም በዘውግ ማንነቱ ያልሆነ፤ ሙያውና ተጋድሎው ሀገሩን ከጠላት መጠበቅና የህዝቡን ደህንነት ማረጋገጥ የሆነ፤ በተልዕኮ ላይ ቢሰዋ ህዝቡ እንደጀግና የሚቀብረው፤ አካለ ስንኩል ቢሆን ህዝቡ በአክብሮት እስከ እድሜ ልኩ የሚጦረው፤ መለዮ ለብሶ በህዝቡ ውስጥ ሲገኝ ወጣቱ እንደሱ ለመሆን የሚመኘው አኩሪ የኢትዮጵያ ሠራዊት ሆኖ እንዲቀጥል ነው ፍላጎታችን። ይህ ምኞት እንዲሳካ ግን ዛሬ የምትፈጽፈው ተግባር ወሳኝ ነው።
ውድ የአገሬ መለዮ ለባሾች፤
ለዴሞክራሲ ሲሉ እየታገሉ በሞቱትና አሁንም በሚታገሉት የሕዝብ ኃይሎች ስም የማቀርብላችሁን ጥሪ አድምጡኝ። ነፃ ሊያወጣችሁ እየታገለ ባለ ሕዝብ ላይ ፈጽሞ አትተኩሱ። ሕዝብ ላይ መተኮስ ማለት፤ የነፃነት ታጋዮች ላይ መተኮስ ማለት፤ በገዛ ራሳችሁ ላይ መተኮስ ማለት እንደሆነ እወቁ። ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው እንዴት በገዛ ራሱ ጭንቅላት ላይ ይተኩሳል? የእስከዛሬው በቅቶን ከእንግዲህ መንገዳችሁን አስተካክሉ። ከቻላችሁ ይህን የባርነት አዋጅ ለማስፈጸም ስንል ከሕዝብ ጋር አንዋጋም ብላችሁ በኅብረት ቆማችሁ ይህንን ጦርነት አስቁማችሁ ሀገሪቱን ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር ለመውሰድ ታገሉ። ይህን ካልቻላችሁ የሕዝብን ትግል ተቀላቀሉ። በግልም ይሁን በቡድን መሠሪ የህወሓት ጄኔራሎችና አለቆቻችሁን በማስወገድ የጀግንነት ታሪክ ሥሩ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና ፓሊስ አባላት ሆይ!
የኛ ፍላጎት ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈነባት ኢትዮጵያ እዉን ሆና ማየት ነዉ። የእናንተም ፍላጎት ከዚህ የተለየ አይደለም።ከሕዝብ ጎን ቁሙ፤ ሕዝብ በጎናችሁ ይቆማል:
ኢትዮጵያ አገራችን በክብር ለዘላለም ትኑር።

የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የታወጀ የዘመናዊ ባርነት አዋጅ ና በሕዝባዊ ትግሉ የሚወሰዱ እርምጃዎችና ዋና ዋና ዒላማዎች

$
0
0

መግቢያ
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ፤
በሀገራችን ኢትዮጵያ የተከሰተው ስር የሰደደ የፖለቲካ ቀውስ በሰለጠነ የውይይትና የድርድር መንገድ እንዲፈታ ለሀገር ደህንነት ከሚያስቡ የአገር ሽማግሌዎችም ሆነ ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ወዳጆቹ ጭምር የቀረበለትንና የሚቀርብለትን ጥሪ አሌ ብሎ፤ ይህ እኩይ የጥቂት ሽፍቶች ሥርዓት ለ25 ዓመታት ሲያካሄድ የቆየውን የሕዝብና የሀገር ሀብት ዝርፊያ ከማቆም ይልቅ “ሀገሪቷን መዝረፍ ካልቻልኩ አቃጥያት እጠፋለሁ” ብሎ የመጨረሻው የሆነውን የጥፋት መንገድ ከሰሞኑ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” በሚል ስያሜ ባወጀው “የባርነት አዋጅ” ለሁሉም ግልጽ አድርጓል። ይህንን የወያኔ የዘራፊዎች ቡድን ለረጅም ጊዜ በቅርብ ስንከታተልና በተግባርም ስንፈትነው ለቆየነው የነፃነት ኃይሎች ይህ እርምጃው ስንጠብቀውና ስንዘጋጅበት የነበረ ስለሆነ በእውነቱ በፍጹም አልገረመንም። ትንሽም ቢሆን ያስገረመን ይህንን የመጨረሻ ጥይቱን እንደዚህ በቶሎ መጠቀሙ ነው። የመጨረሻ ጥይቱ ነው የምንለው ከዚህ በኋላ ሊጠቀምበት የሚችለው ምንም ሌላ መሳሪያ እንደሌለው ስለምናውቅ ነው።
በእርግጥ በዚህ አዋጅ ውስጥ አገዛዙ ሊወስዳቸው ያሰባቸው እርምጃዎች አብዛኛዎቹ ከዚህ በፊትም እራሳቸው ካወጧቸው ህጎችና ህገመንግስቱም ውጪ ያለምንም ከልካይ ሲተገብሯቸው የነበሩ እርምጃዎች ናቸው። የመንግሥትን ስልጣን ከተቆጣጠሩ ጀምሮ በስልጣናቸው በመጣ ጉዳይ አንድም ጊዜ ህጋቸውን አክብረው አያውቁም። ያለህግ ሲያስሩ፤ ያለህግ ሲገድሉ፤ ያለህግ የመገናኛ ብዙሀንን ሲዘጉና ሲያፍኑ፤ ከህግ ውጪ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን ሲያፈርሱና ያላፈረሱትን ደግሞ እራሳቸው የመረጡላቸውን መሪዎች ሲያስቀምጡ ነው እስካሁን የዘለቁት። ከዚህ አንጻር ይህ አዋጅ ቀድሞውንም ኢህጋዊ የሆነ ስራቸውን ይበልጥ ኢህጋዊ በሆነና አይን ባወጣ መንገድ፤ ለፈረንጆች ማባበያ ያጠለቁትን የህጋዊነት ጭምብል አውልቀው እርቃናቸውን ከመታየታቸው ባሻገር ብዙ አዲስ ነገር የለውም። ይህን አዋጅ ከዚህ በፊት ሲያደርጉት ከነበረው በተለየ እንድንመለከተው የሚያደርገን ከአዋጁ እናገኝበታለን ብለው የሚያስቡትና ዘላቂነት ይኖረዋል ብለው የገመቱት በሕዝባችን ላይ ሊያሳርፉት የፈለጉት፤ ዘላቂነት ያለው የተገዢነት ስነ ልቦና ውስጥ ሕዝቡ እንዲገባ የሚያደርጉት ሙከራ ላይ ነው።
በተግባር ይህ አዋጅ ተግባራዊ እየሆነ ባለበት ሁኔታ ምንም አይነት የፖለቲካ መፍትሄ ሊኖርም ሊሞከርም የማይችል እንደሆነና ግልጽ አድርጓል። የህወሓት አገዛዝ ከጉልበት ውጭ ምንም ሌላ መንገድ የማያውቅ አጥፊ ኃይል እንደሆነ ለወዳጅም ለጠላትም ያሳወቀበት አዋጅ ነው። ይህን አዋጅ ሲያውጁ ሰው ሆኖ መኖርን የናፈቀውና ካሁን በኋላ ያለነፃነት በፍጹም አልኖርም ብሎ ፍርሀትን በሚገርም ጀግንነት አሸንፎ ውድ ሕይወቱን እየከፈለና እየታገለ ያለውን፤ ከሞላ ጎደል መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ እንደገና በፍርሀት ቆፈን ውስጥ መልሼ ከትቼ ከቀድሞውም የባሰ ባርነት ውስጥ ዘፍቄ እገዛዋለሁ ብሎ አምኖ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ካሁን በኋላ ባርነትን የሚሸከምበት ምንም ጫንቃ የለውም። በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ሕዝብ በፍጹም በፍጹም ተመልሶ የባርነት ሕይወት ውስጥ ሊኖር አይፈቅድም። ስለዚህ ከዚህ በኋላ የፍትህና የነፃነት ኃይሎች ዋና ተግባር ያላቸውን አቅም ሁሉ አስተባብረውና ነፃነት የራበውንና የጠማውን ሕዝባቸውን ከጎናቸው አሰልፈው፤ ጊዜውና ሁኔታው የሚፈቅደውን ተለዋዋጭና ተለማጭ የትግል ስልት እየተጠቀሙ ይህ አዋጅ በፍጹም ተግባራዊ እንዳይሆንና እንዳይሳካ ማድረግ ነው። ይህን የባርነት አዋጅ ለማስፈጸም በመሪነትና በዋና አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች፤ ይህ የባርነት አዋጅ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲተገበርና እንዲሳካ ለማድረግ የሚሞክሩ ወይንም ከዚህ ዘራፊ ሥርዓት ጋር በጥቅም ተሳስረው ከዚህ የባርነት አዋጅ ጋር የሚተባበሩ ማናቸውም ኃይሎች ሁሉ ከአሁን ጀምሮ የሕዝባዊ ትግሉ ቀንደኛ ዒላማዎች መሆናቸውን ግልጽ አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል። በዚህ ሕዝባዊ ትግል ላይ የሚሳተፉ የሕዝብ ወገኖችም ሆነ ይህንን ዘራፊ ሥርዓት የሚያግዙ ኃይሎች በደንብ እንዲረዱት የሚያስፈልገው ይህን አዋጅ አከሸፍነው ማለት የወያኔ ሥርዓት አከተመለት ማለት እንደሆነ ነው። ይህ አዋጅ ተሳካ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላልተወሰነ ጊዜ በባርነት መቀመቅ ውስጥ ሊኖር ተፈረደበት ማለት ነው። ለዚህ ነው አሁን የገባንበት ትግል የመጨረሻው የሞት ሽረት ትግል ነው የምንለው።
ለመሆኑ ይህ አዋጅ የሚደነግገው ምንድን ነው? ለምንድን ነው በፍጹም እንዲሳካ የማንፈቅድለት “የዘመናዊ ባርነት አዋጅ” ነው የምንለው?
“ባርነት” የሰውን ልጅ ሰው የሚያደርገውን መሠረታዊ ነጻነቱን ገፍፎ፤ ፈንጋዩ ከሚሰጠው ፈቃድ ውጭ በራሱ ምንም የሚወስነው ነገር እንዳይኖር ከልክሎ፤ ያለውን የጉልበትም ሆነ የማሰብ አቅሙን ሁሉ በባርነት ለሚያሳድረው ባለቤቱ ሀብት መፍጠርና አገልግሎት መስጠት ላይ ብቻ እንዲያውል የሚያደርግ ሥርዓት ነው። ባርያ የኔ የሚለው ንብረት የለውም፤ በገዛ ራሱ ሰውነትና አዕምሮ ላይ ሥልጣን የለውም። የሰው ልጅ እንዲህ ዓይነቱን ማንነቱን የሚነጥቅ በደል እሺ ብሎ በፈቃደኝነት አይቀበልም። ስለዚህ ይህን እንዲቀበል በጉልበት ማስገደድን ይጠይቃል። ይህን ለማድረግ ደግሞ ባርያ ፈንጋዮች የመጀመሪያ ሥራቸው ባርያ የሚያደርጉትን ሰው ከሰውነቱ የሚመነጨውን የነፃነትና ሰው የመሆን ፍላጎት በጉልበትና በሰቆቃ መንጠቅ ነው። አንዴ ይህን የውስጥ ማንነቱን ከነጠቁትና ባርያውን ወደ እንሰሳነት ከቀየሩት በኋላ እንደፈለጉት ለማድረግ በቀጣይነት ጉልበት መጠቀምም አያስፈልጋቸውም። በሕይወት የሚያቆየውን የሚበላውን መጥነው እየሰጡ እስከሚሞት ድረስ ጉልበቱን እየበዘበዙ ለራሳቸው ሀብት ማጋበስ ነው። ይህን በቀጣይነት ለማድረግ ባርያው ለራሱ ጥቅም እንዳያስብ መሆን አለበት። የሚያስበውን የሚነግሩት እነሱ፤ የሚሰማውን ወሬና ከማን ጋር መነጋገር እንዳለበት የሚወስኑለት እነሱ፤ የሚንቀሳቀስበትን ቦታ የሚወስኑለት እነሱ፤ መቼ መተኛትና መነሳት እንዳለበት የሚፈቅዱለት እነሱ፤ ምን ሥራ መሥራት እንዳለበት የሚፈቅዱት እነሱ፤ በሕይወት መኖርና አለመኖሩን የሚፈቅዱለት እነሱ፤ ባጠቃላይ ሕይወቱ በነሱ ፈቃድ ላይ የተመሰረተች እንጂ ከዚያ ውጭ ሕይወት እንደሌለው እንዲቀበል ማድረግ አለባቸው። ይህን ለማድረግ ከሚጠቀሙት ጉልበት በተጨማሪም ሰውየው ይህ ኑሮው በግድ የተጫነበት ሳይሆን በተፈጥሮ የተለገሰው እጣ ፈንታው እንደሆነ እንዲያምን ይጥራሉ። ይህን የሚያደርጉት ሰዎች በቁጥር ትንሽ ስለሆኑ በባርነት የሚኖሩት ሰዎች ተባብረው ከገቡበት የባርነት ቀንበር ራሳቸውን እንዳያላቅቁ ይህ የማይቻል እንዲሆን በባርያዎቹም መሀከል ልዩነት መፍጠርና አንዱ ባርያ ሌላውን የሚጠብቅበት መንገድ ማመቻቸትም አንዱ የመግዥያ መሣሪያቸው ነው። የተወሰኑትን ጥቂት ባርያዎች በአንጻራዊነት ቀለል ያለ የቤት ውስጥ ሥራ እያሠሩና ከሌሎች ባርያዎች በተለየ ከጌቶቻቸው የተረፈ ፍርፋሪ ምግብ እያበሉ እራሳቸውን እንደባርያ እንዳያዩና ሌላውን የመስክ ሥራ እየሠራ የሚፈጋውን ባርያ እየናቁና እንዳያምጽ የመቆጣጠር ሥራ ያሠሯቸዋል። ለሌላውም ባርያ “የጥሩ ባርያነት” አርአያ አድርገው ያቀርቧቸዋል። የሰው ልጅ እዚያ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ያገራችን ሰዎች አገሩን ላጣ ሰው እንሚተርቱት “ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ” የሆነ እንሰሳ ይሆናል ማለት ነው።
የወያኔ ጥቂት ዘራፊ መሪዎች ይህን አዋጅ ሲያውጁና በተግባር እናሳካዋለን ብለው ሲገምቱ በትግሉ ነጻነቱን እያወጀ ያለውን የኢትዮጵያን ሕዝብ እዚያ ባርነት ደረጃ ላይ እናደርሰዋለን ብለው ገምተው ነው። በዚህ አዋጅ ላይ እነሱ ከፈቀዱለት ሰው ውጭ ያለ ኢትዮጵያዊ ምን መናገር እንደሚችል፤ ምን ማሰብ እንደሚችል፤ ከማን ጋር እንደሚያወራ፤ ምን ዜና እንደሚሰማ፤ ምን ማንበብ እንዳለበት፤ የት የት ቦታ መንቀሳቀስ እንደሚችል፤ ምን ሥራ እንደሚሠራ፤ በስንት ሰዓት ከቤቱ ወጥቶ በስንት ሰዓት እቤቱ መግባት እንደሚችል፤ የራሱን ንብረት እንዴትና መቼ ማንቀሳቀስ እንደሚችልና ይህንን እነሱ ከፈቀዱለት ውጭ በራሱ ፍላጎትና ተነሳሽነት ምንም ዓይነት ነገር ቢያደርግ ሕይወቱን እስከመንጠቅ ድረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስዱበት በዚህ የዘመናዊ ባርነት አዋጃቸው አውጀዋል። በቃሊቲ፣ ቂሊንጦ፣ ዝዋይና ቁጥራቸው ተዘርዝሮ በማያልቅ የማጎርያና የማሰቃያ እስር ቤት ያሰሯቸውን ዜጎች ከንጋት 11 ሰዓት እስከ ቀን 11 ሰዓት ድረስ ውጭ ወጥተው ጸሀይ እንዲሞቁና እግራቸውን እንዲያፍታቱ ከመፍቀድ በቀር ቀሪውን ሰዓት በተቆለፈ ቤት ውስጥ እንዲቀመጡ እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህ አዋጅም በሀገሪቱ ድንበር 50 ኪሎ ሜትር ሬድየስ እና ከዋና ዋና መንገዶች በግራና በቀኝ 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ (ይህ ባገሪቱ ያሉትን ሁሉንም ከተሞችና ትናንሽ መንደሮች ከሞላ ጎደል ያካልላል) ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ እራሱን በገዛ ቤቱ ውስጥ እንዲያስር የወሰነ እጅግ የሚገርምና በዛሬ ዘመን ሊታሰብ የማይችል የጅምላ እስር አዋጅ ነው። ይህ አዋጅ ከተሳካለት ማንም ኢትዮጵያዊ፤ ከነሱና ከቡችሎቻቸው በቀር፤ እራሱን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስፈልገውን ማናቸውንም ዓይነት መሣሪያ እንዳይይዝ የሚከለክልና ያለውንም የሚቀማ ስለዚህም ለዘላለሙ በፍርሀትና በድንጋጤ እንዲኖር፤ በራስ የመተማመን ስሜቱን እንዲሰልብ ያለመ አዋጅ ነው። ይህ አዋጅ ከተሳካ እነሱ የኢትዮጵያውያንን ጉልበት እንደፈለጉ እየመዘበሩ የሚደልቡበት፤ ሌላው ኢትዮጵያዊ በገዛ ሀገሩ የበይ ተመልካች ብቻ ሳይሆን ጉልበቱንና የሀገሩን ሀብት ለነሱ እየገበረ የሚኖርበትን የዘመናዊ ባርነት ሥርዓት እንዲቀበል የሚያደርግ ነው። በዚህ ስድስት ወራት ውስጥ ይህንን ፍላጎታቸውን በኃይል ካሳኩ ከዚያ በኋላ አዋጁን ቢያነሱት እንኳን፤ ማሰሩንና መግደሉን ቢያቆሙት እንኳን፤ ይህ ቅስሙ የተሰበረ ሕዝብ ሰጥ ለጥ ብሎ ይገዛልናል ብለው አምነው የሚወስዱት እርምጃ መሆኑን ላንድ አፍታ እንኳም መዘንጋት የለበትም።
ለመሆኑ እንዲህ አይነት እርምጃ በዛሬው ዓለምና በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሊሠራ ይችላል ብለው እንዴት ገመቱ?
አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የደረሰበትን የነፃነት ፍላጎት ደረጃና ባጠቃላይ የዓለማችንን ሁኔታ በክፍት ልቦና ለሚመለከት ሰው በሀገራችን ያለውንና እነሱ ራሳቸው የፈጠሩትን የፖለቲካ ቀውስ በዚህ ዓይነት አዋጅ እንፈታዋለን ብለው ማሰባቸው በራሱ በነሱ በሞራ በተሸፈነ ትንሽ ጭንቅላት ውስጥ የሚርመሰመስ የራሳቸው የተለየ የቅዠት ዓለም ውስጥ የሚኖሩ፤ ይህ የቅዠት ዓለማቸው ግን ከእውነተኛው ዓለም እውነታ ጋር ሲጋጭባቸው የሚሠሩትን እስከማያውቁ ድረስ የሚምታታባቸው እብዶች መሆናቸውን ነው የሚገልፀው። በመጀመሪያ፣ በዚህ አዋጅ አማካይነት እየታገሉት ያሉት ከማን ጋር እንደሆነ በፍጹም አላወቁም። በነሱ የቅዠት ዓለም፤ ትግላቸው ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሳይሆን እነሱ “ጥቂት” ከሚሏቸው የነሱን “የልማትና የሕዳሴ ጉዞ” ከሚቃወሙ ወይንም ካልተዋጠላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ነው። ከእነኝህ ጥቂት ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ለሚደረግ ትግል ግን ለምን በመላው ሕዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ እንዳስፈለጋቸው መቼም በትክክል በሚሰራ አዕምሮ ታስቦ የሚደረግ አይደለም። ከመላው ሕዝብ ጋር በሚደረግ ትግል ደግሞ እነኝህን እርምጃዎች በመውሰድ እናሸንፋለን ወይንም ያለሕዝብ ትብብር እነኝህን እርምጃዎች ተግባራዊ እናደርጋለን ብለው እንዴት ሊያምኑ እንደሚችሉ በሙሉ አዕምሮው ለሚያስብ ሰው ለመገመት አስቸጋሪ ነው። ሕዝቡ ቤቱ ውስጥ ያለው ቴሌቪዥን ላይ ምን እንደሚሰማ ለመቆጣጠር ቀደም ብሎ በሕዝቡ ትግል የፈረሰው “የአንድ ለአምስት” ጥርነፋ አሁንም ይሠራል ስለዚህም ልጅ አባትና እናቱን፤ ወላጆች ደግሞ ልጆቻቸውን ይሰልሉልኛል ብለው በቅዠት ዓለማቸው ካላመኑ በስተቀር ዛሬ እውነታው በምድር ላይ የለም። ለመሆኑ፣ በሀገሩ ውስጥ ያለውን የሳተላይት መቀበያ ሳህን ሁሉ ከየቤቱ ጣርያ ላይ ለማውረድ የሚያስችል የሰው ኃይል አለን ብለው እንዴት ሊያምኑ ቻሉ? በየመንግሥት መሥሪያቤት ያለውና በግል ድርጅቶች ውስጥ የሚሠራውን ሠራተኛ ሁሉ “በሥራ መለገም ወንጀል ነው” ብለው ሲደነግጉ ይህንን እንዴት እናስፈጽማለን ብለው ገምተው ነው? ዳሽን ቢራና ፔፕሲ አልጠጣም፤ የህወሓት ንብረት በሆነው ሰላም አውቶብስ አልሄድም፤ ገንዘቤን በህወሓትና እሱን በሚያገለግሉ ባንኮች ውስጥ አላስቀምጥም፤ የመሶቦ ሲሚንቶን አልገዛም ብቻ ሳይሆን በባርነት ታስሬ የምኖርበትን ቤት ከናካቴው አልሰራም ብሎ ያመረረን ሕዝብ እንዴት አድርጎ ነው ፔፕሲንና ዳሽን ቢራን ሊግተው ያሰበው? እንደው እዚህ ግባ የማይባል ደሞዝ ከፍለው መሣሪያ ያስታጠቁት የወታደርና የፖሊስ ኃይል ለዚህች ደሞዙ ብሎ ራሱንና ወገኖቹን ለዘላለማዊ ባርነት ለመዳረግ የሚተጋ ግዑዝ ኃይል ነው ብሎ ቢያስብ እንኳን፤ ይህ ቢበዛ ከ200ና 300ሺ በላይ የማይደርስ ኃይል የሀገሪቱን ድንበር የመጠበቅ ሥራውን ሁሉ ትቶና ከድንበር ላይ ነቅሎ ለዚህ አዋጅ ማስፈጸሚያ ሥራ ቢያውለው እንኳን፤ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የተነሳንና እንዳስፈላጊነቱ በመሣሪያ ኃይል እራሱን ለመከላከል ያደራጀን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብ እንዴት አድርጎ ያሸንፋል ብሎ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው ሊያምን ይችላል? ከዛሬ በኋላ እንኳንስ ሠራዊቱን በፍላጎት ለመልቀቅ እረፍት እንኳን መውስድ አትችልም ተብሎ በኃይል ተሰንጎ እንዲዋጋ የታወጀበት ሠራዊት ከሕዝቡ ጋር ጦርነት መግጠሙን ሲያውቅ አይደለም ከልቡ ሊዋጋና ሊያሸንፍ ከሕዝቡ ጋር ወግኖ መልሶ አዛዦቹንና ከሕዝብ ጋር የሚያዋጉትን የሀገርና የሕዝብ ጠላቶች ሊወጋ እንደሚዘጋጅ፤ ይህን እንኳን ማድረግ ቢያቅተው ከነመሣሪያው ጠፍቶ ሊሰወር እንደሚችል በትዕቢት የተወጠረና ማሰብ ያቆመ ጭንቅላት ካልሆነ በስተቀር በትክክል ለሚያስብ ሰው እንዴት ይሳነዋል? በመቶ ሺ እስኴር ኪሎ ሜትሮች በሚቆጠር አካባቢ የሚንቀሳቀስን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝብን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ስንት ሚሊዮን ተባባሪዎቹን ተማምኖ ነው ሊቆጣጠረው የሚችለው? በሌላ አነጋገር የማሰብ ኃይላቸው ፍጹም ተመናምኖ ያለቀው የአገዛዙ መሪዎች እንኳን ይህንን አዋጅ ያለሕዝብ ትብብር እጃቸው ላይ ባለው ኃይል እናሳካዋለን ብለው ያምናሉ ለማለት በጣም አስቸጋሪ ነው። ሕዝቡ ደግሞ በዛሬ ዘመን በራሱ ላይ ባርነትን ለመጫን ይተባበራል ብሎ መገመት በፍጹም የሚቻል አይደለም። ይልቁንም ወያኔዎች የተማመኑበት የሚመስለው በተለመደ ባዶ ድንፋታቸው ሕዝቡን አስፈራርተው፤ ወይንም የተወሰኑ ሰዎችን ገድለውና አስረው በዚህ እርምጃቸው ሕዝቡ ከተሸማቀቀ በኋላ ለነጻነቱ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ያቆማል ብለው ነው እየቆመሩ ያሉት። የዚህ ክፉ ቁማር ውጤት ግን እነሱ የጠበቁት ሳይሆን እስካሁን ዘርፈው ያካበቱትን ንብረት ሳይበሉ ተሰባብረው የሚወድቁበትን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም በዚህ ዘረኛና ዘራፊ ሥርዓት መቃብር ላይ እውነተኛ ነጻነቱን የሚቀዳጅበት የመጨረሻው ሂደት እንደሚሆን አያጠራጥርም።
ይህ ግን ስለተመኘነው የሚመጣ ሳይሆን በሥራችንና በትግላችን እውን የምናደርገው ድላችን ነው የሚሆነው!
በሕዝባዊ ትግሉ የሚወሰዱ እርምጃዎችና ዋና ዋና ዒላማዎች
ቀደም ብዬ እንዳልኩት የወያኔ መሪዎች ይህን በፍጹም ሊሳካ የማይችል እርምጃ መውሰዳቸው ሳይሆን የሚገርመው ይህንን የመጨረሻ የተስፋ መቁረጥ እርምጃቸውን እንዲህ በቶሎ መውሰዳቸው ነው የሚገርመው። እንዲህ ዓይነት ፍጹም በቅጡ ያላሰቡበት እርምጃ ውስጥ የከተታቸው ደግሞ በዚህ ባጭር ጊዜ ሕዝባዊ ትግሉ የወሰዳቸው እርምጃዎች ከሚጠበቀው በላይና ባልተጠበቀ ፍጥነት ውጤታማ በመሆናቸው ነው። ባንድ በኩል በሀገር ውስጥ የሚደረገው የሕዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ ባጭር ጊዜ ትግል የበሰሉ ወጣት አመራሮችን አፍርቶ በየጊዜው የሚቀያየሩና በምድር ላይ የሚፈጠሩ ሁኔታዎችን ከግምት እያስገባ የሚሄድ ተለዋዋጭ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ሕዝቡን በሰፊው ያሳተፈ ቀጣይነት ያለው ትግል ማካሄድ በመቻላቸው ነው። ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለው ትልቁ ነገር ይህ ህዝባዊ እምቢተኛነት እንቅስቃሴ በአንድ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በፍጹም ባልተጠበቀና የወያኔን ዘረኛ መሪዎች ባስደነገጠ መልኩ በደል ባስተሳሰረው የአንድነት መንፈስ መካሄዱ ነው። የወያኔን ዘረኛ መሪዎች ብርክ ያስያዛቸው ጎንደር ላይ የአማራ ሕዝብ ተገልብጦ ወጥቶ ወያኔን ወጊድልኝ ከማለቱ ባሻገር የበቀለ ገርባን ምስል ይዞ “የኦሮሞ ደም ደማችን ነው” የሚል መፈክር እያሰማ መውጣቱና ከኦሮሞ ሕዝብ ትግል ጋር አጋርነቱን ማሳየቱ ነው። በኢሬቻ በዓል ላይ የኦሮሞ ወጣቶች “የአማራ በደል የኛም በደል” ነው ብለው በጎንደርና በጎጃም ለሚደረገው ትግል ወገንተኛነታቸውን ማሳየታቸው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በሁሉም ክልሎች ሕዝቡ ለሚያደርገው ሰላማዊና የሰለጠነ ትግል የወያኔ መሪዎች መልስ ጥይት መሆኑን በዓይኑ እየተመለከተ ሲሄድና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የትግል ጓዶቹን እየቀበረ ሲሄድ፤ አረመኔን በሰለጠነ ትግል ብቻ ማስቆም እንደማይችል አውቆ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ትግሉን በሕዝባዊ አመጽ ለመደገፍ እየወሰደ ያለው ዝግጅትና መለስተኛ እርምጃዎች ናቸው።
ዛሬ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ለመሞት ብቻ ሳይሆን ለመግደልም የቆረጡ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አርበኞች በረሀ የወጡበት ጊዜ ነው። ዛሬ የአርበኛ ታጋይ አበራ ጎባውን ዓይነት ጀግና ተዋጊዎችና አዋጊዎች ብዙ የአጋዚ ጦር ደምስሰው የሚሰዉ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆች ይህን ሥርዓት ከስሩ ለመመንገል የተዘጋጁበት ጊዜ ነው። እንዲህ ዓይነቶች ጀግኖች በኦሮሚያ የተለያዩ ቦታዎች፣ በአርባ ምንጭ፣ በቴፒ፣ በኮንሶ፣በጋምቤላ፣ በአፋር የጀንግንነት ተግባራትን ፈጽመው አሳይተውናል። ዛሬ የህወሓት አገዛዝ የሚመራው ጦር እየከዳ እንዲህ ዓይነት ጀግኖችን የሚቀላቀልበት ወቅት ነው። ዛሬ የብዙ ጊዜ እንቅስቃሴያችን ፍሬውን ለማፍራት የተዘጋጀበት፤ ትግሉን ከዳር ለማድረስ ሁኔታዎች የተመቻቹበት ጊዜ ነው። የወያኔ መሪዎች ይህንን ጠንቅቀው አውቀዋል። ለዚህ ነው ይህንን የመጨረሻ የተስፋ መቁረጥ እርምጃዎችን እየወሰዱ ያሉት።
ይህ በጥሩና በአመርቂ ሁኔታ እየተካሄደ ያለ ትግል ግን እመጨረሻው ምዕራፉ ላይ ሳይደርስ በፍጹም መቆም የለበትም። “የነብርን ጅራት አይይዙም፤ ከያዙም አይለቁ” የሚለውን የአበው ብሂል እዚህ ላይ ይሠራል። ሕዝባዊ ትግሉን እዚህ ካደረስነው በኋላ ከዳር ሳናደርሰው መመለስ ከቶ አይቻለንም። ማድረግ ያሉብን ነገሮች ደግሞ ግልጽ ናቸው። አሁን በመላ አገራችን የተቀጣጠለው ሕዝባዊ ትግል እስካሁን ከነበረው በላይ አጠናክሮ መቀጠልና አዲስ ለተፈጠረው ሁኔታ የሚመጥኑ አዳዲስ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል። የትግል ዒላማዎቻችንን ከዚህ በፊት ከነበሩት በተጨማሪ ይህንን የባርነት አዋጅ ለመተግበር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ላይ ሁሉ ማነጣጠር ይኖርበታል። ከዚህ አንፃር ይህንን የባርነት አዋጅ ለማክሸፍና ትግላችንን ከዳር ለማድረስ የሚከተሉትን ተጨባጭ እርምጃዎች በቀጣይነት እንወስዳለን፤
1. ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ነፃነትን የሚሻ ሁሉ ከሚመስለው ጋር ይደራጅ ስንል ቆይተናል፤ አሁን ከመደራጀትም አልፎ ራሱን ለመከላከል ከዚያም አልፎ ለሚደርስበት ጥቃት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመስጠት ይዘጋጅ። ከእንግዲህ ባይሆን ገድሎ መሞት እንጂ “በሰላምተኝነት” መሞት የለም። ራስንና ሕዝብን ከህወሓት ሽብር ለመከላከል በየቦታው የተደራጁ ቡድኖች አሉን፤ ተጨማሪ ቡድኖች እናደራጃለን፤ በተቻለን ሁሉ እንደግፋለን። ነፃነት የጠማው ኢትዮጵያዊ ሁሉ እነዚህ ቡድኖች ይደግፍ፣ ይቀላቀል። በቡድን ብቻ ሳይሆን በግልም ጭምር ለህወሓት አመፃ የአመፃ ምላሽ ይስጥ።
2. ይህ የባርነት አዋጅና የአዋጁ ባለቤት ህወሓት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ መንገዶች “መሠረተ – ልማቶች” ሳይሆኑ መሠረተ – ጥፋቶች ናቸው፤ አውራ ጎዳናዎች አስጠቂዎቻችን ናቸው። በእነዚህ መንገዶች እየተጓጓዘ ነው የአጋዚ ጦር ወገኖቻችንን እየፈጀ ያለው። ስለሆነም መንገዶችንና መዝጋት ብቻ ሳይሆን ማፍረስም ተቀባይነት ያለው ሥራ ነው፤ ከነፃነታችን የሚበልጥ አንዳችን ቁሳዊ ሀብት የለም። ለግንባታው ከነፃነት በኋላ እንደርስበታለን። የሕዝብ ጠላት የሆነ መንግሥት ንብረት ሁሉ የጠላት ንብረት ስለሆነ እናወድመዋለን፤ “የመንግሥት ንብረት የሕዝብ ንብረት ነው” እያሉ የሚያሞኙንን አንሰማም።
3. የታወቁ የሥርዓቱ ቀንደኛ አራማጆች ብቻ ሳይሆኑ ይህንን የባርነት አዋጅ ለማስፈፀም የሚራራጡ ግለሰቦች፣ ቡድኖችና ተቋማት ሁሉ ጠላቶቻችን ናቸው። እነዚህ ሁሉ የትግላችን ዒላማዎች ናቸው። በየሠፈሩ አዋጁን የሚያስፈጽሙ ስማቸው ተለይቶ ይፋ ይደረጋል፤ የፃነት ኃይሎች በእነዚህ ኃይሎች ላይ እርምጃ ይወስዳሉ።
4. የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት – በተለይም የአጋዚ ጦር አባላት – ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለእናንተ ገደብ የለሽ ሥልጣን የሰጠ በመሆኑ የምትጠቀሙ አይምሰላችሁ። እናንተ ዜጎችን በመግደላችሁ፣ በማሰራችሁና በማሰቃየታችሁ የሚጠቀሙት አለቆቻችሁ ጄኔራሎች እና የህወሓት/ኢህአዴግ ሹማምንት ናቸው። አዋጁ ከሌላው ሕዝብ ያላነሰ እናንተንም ባርያ የሚያደርግ ነው፤ የዓመት እረፍት እንኳን መውሰድ እንኳን መውሰድ እንዳትችሉ የተገደባችሁ መሆኑን እወቁ። በአዋጁ ተፈፃሚነት ለእናንተ የሚተርፋችሁ የእድሜ ልክ ፀፀትና ከሕዝብ ጋር የምትገቡት ቁርሾ ነው። የእናቶችና የሕፃናት ዋይታና ለቅሶ ይሰማችሁ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ እናንተን ተጠቅሞ የኢትዮጵያም ሕዝብ በባርነት እየገዛ መሆኑ ይታያችሁ። ከኢህአዴድ መወገድ በኋላ የሚመጣው ሥርዓት እናንተን የሚጠቅም እንጂ የሚጎዳ አለመሆኑን አውቃችው ከአገዛዙ ጋር ያላችሁን ግኑኝነት በጥሱ። ዛሬውኑ ወስኑ ! በወገኖቻችሁ ላይ ላለመተኮስ ለራሳችሁቃል ግቡ !!! የመሣሪያዎቻችሁን አፈሙዝ በሙስና ወደደለቡት አለቆቻችሁ አዙሩ፤ አልያም ሥርዓቱን ከድታችሁ የነፃነት ኃይሎችን ተቀላቀሉ። ሥርዓቱን ለሚከዱ የሠራዊቱ አባላት የክብር አቀባበል እናደርጋለን፤ በየቦታውም ይህን የሚያስተባብሩ አካላትን አደራጅተናል። ይህን ዕድል ከመጠቀም ይልቅ ሥርዓቱን ለማቆየት የወሰናችሁ የሠራዊቱ አባላት የምትዋጉት የጠላት ጦርን ሳይሆን የራሳችሁን ሕዝብ መሆኑን መሆናችሁን እወቁ። በምንም ዓይነት ሕዝብን ማሸነፍ አትችሉም።
5. የጦርና ፓሊስ ሠራዊት አባላት ቤተሰቦችና መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሠራዊቱ ላይ ጫና ያሳድር። ሠራዊቱ ከኢትዮጵያ አብራክ የወጣ ነውና የኢትዮጵያ ሕዝብን ይሰማል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለህወሓት ሹማምንት ድሎት ሲባል በገዛ ልጆቹ መገደልና መረገጥ የለበትም። ሠራዊቱ የህወሓት/ኢህአዴግ ሠራዊት መሆኑ እንዲያበቃ ሁለገብ ጥረት እናደርጋለን።
6. በአገዛዙ የስለላ መዋቅሮች የምትሠሩ ወገኖቻችን ኃላፊነት አለባችሁ። ማንን እየተከላከላችሁ፤ ማንን እያጠቃችሁ እንደሆነ አስተውሉ። ለራሳችሁ ደህንነት እና ለህሊናችሁ የሚበጃችሁ ከሕዝብ ጎን መቆም ነውና ዛሬውኑ ወስኑ፤ እናንተም ወደ ሕዝብ ትግል ስትመጡ ለመቀበል ዝግዱ ነን፤ ይህን እድል አታስመልጡ። በተመሳሳይም የኢህአዴግ አባላት ጎራችሁን ለዩ። አምርሮ ለዘመተብን ጠላት የመረረ ምላሽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል።
7. ህወሓት/ኢህአዴግ ከመነሻው ጀምሮ በአርሶ አደሩ እየነገደ ያለ እኩይ ኃይል ነው። ዛሬ የመንግሥትን ሥልጣን የያዙት ኃይሎች አርሶ አደሩ እየተራበና እየታረዘ ጠግቦ የሚያድር አስመስሎ ለዓለም የሚናገሩ ውሸታሞች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ መሬትን እየቀሙ ለራሳቸውና ለወዳጆቻቸው የሚያድሉ በልተው፣ ገፈው፣ በዝብዘው የማይጠግቡ ሆዳሞች ናቸው። ከእንግዲህ የኢትዮጵያ አርሶ አደር በባርነት ለሚገዛው አገዛዝ ግብር፣ መዋጮ፣ የምርጥ ዘርም ሆነ የማዳበሪያ እዳ አይከፍልም፤ ካድሬዎች ለሚጠሩት ስብሰባ አይወጣም፤ ራሱ በመረጣቸው የአገር አስተዳዳሪዎች እንጂ በሥርዓቱ ካድሬዎች አይተዳደርም፤ ለዳኝነት ወደ አገዛዙ ፍርድ ቤት አይሄድም።
8. በማናቸውም የመንግሥት ሥራ ላይ የተሠማራ የመንግሥት ሠራተኛ ሥራውን በአግባቡ ሠራ ማለት ይህንን የባርነት አዋጅ አስፈፃሚ ሆነ ማለት እንደሆነ ይወቅ። እያንዳንዱ ነፃነቱን የሚወድ የመንግሥት ተቀጣሪ የዕለት ተዕለት ሥራውን ሲፈጽም የሥራው ውጤት ህወሓት/ኢህአዴግን የሚያዳክም እንጂ የሚያጠናክር እንዳልሆነ እርግጠኛ ይሁን። ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አሻጥር በሁሉም ቦታዎችና በሁሉም የሥራ ዓይነቶች ተግባራዊ ይሆናሉ። በባርያ ፈንጋይ ላይ አሻጥር መፈፀም በምድር የሚያስመሰግን በሰማይም የሚያፀድቅ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ያውቃል፤ በጣሊያን ፋሽስት የወረራ ዘመን የመንግሥት ሠራተኞች የነበሩ የውስጥ አበርኞች አብነቶቻችን ናቸው። ሕዝባዊ አሻጥር የኢትዮጵያ በህወሓት አገዛዝ ሥር ያለ መንግሥት ሠራተኛ የሥራ ባህል ይሆናል።
9. ኢትዮጵያዊያ በአገራችን በነፃነት መኖር የምንችለው ይህን የባርነት አዋጅ በማክሸፍ የህወሓት/አገዛዝን አስወግደን የሕዝብ ይሁንታ ያለው መንግሥት ስንመሠርት ብቻ እንደሆነ እያንዳንዱ ወጣት ይወቅ። ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ሕዝባዊ አመጽና ሕዝባዊ አሻጥር የወጣቱ ትውልድ ባህል ይሆናሉ። ከእንግዲህ የወጣቱ ሙሉ አካላዊና አዕምሮዓዊ ጉልበት ይህንን አዋጅ በማክሸፍ ሥራ ላይ ይውላል። በየቦታውና ጊዜው ተስማሚ የሆነ የትግል ስልት በመቀየስ የዚህን አስከፊ ሥርዓት ፍፃሜ ለማፍጠን የተለያዩ አደረጃጀቾችን በሥራ ላይ አውለናል። ወጣቶች የራሳቸው ፈጠራና አካባቢያዊ ግብዓቶችን በመጠቀም የህወሓት አገዛዝን በኃይል ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን፤ እናበረታታለን።
10. በየአካባቢው አካባቢያዊ ጥያቄዎች ሊኖሩን ይችላሉ፤ አካባቢያዊ ጥያቄዎችን ለትግል ማንሳት የሚበረታታ ነው፤ ያም ሆኖ ግን ትግላችን የሚደጋገፍና ወደ ጋራ ድል የሚያመራ እንዲሆን የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን። በተለያዩ ማኅበረሰቦችና በተለያዩ እምነት ተከተያዮች መካከል የተፈጠረውን መግባባትና መተጋገዝ ለማዳበር ጠንክረን እንሠራለን። አገራዊ ኅብረት ለመፍጠር ቀንና ሌሊት እንተጋለን።
11. በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም ሙሉ ጉልበታቸውና ኃይላቸውን የህወሓት አገዛዝን ማዳከም ብቻ ሳይሆን ማጥፋት ላይ እንዲያተኩሩ እንሠራለን። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የባርነት አዋጅ ታውጆበታልና በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም ምላሽ የመረረ ይሆናል።

birhanu nega
በመጨረሻም ማሳሰብ የምሻው ነጥብ አለ። ይህ የህወሓት ዘራፊ ቡድን በአንድ በኩልና በዋናነት ይህንን የባርነት አዋጁን በጉልበት ለማስፈጸም ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሰላም የሚፈልግ ለማስመሰል እሱ ከመረጣቸውና ባፈና መዋቅሩ ውስጥ ከቦ እያስፈራራ ካስቀመጣቸውና በተግባር ሽባ ካደረጋቸው የፖለቲካ ሰዎች ጋር እደራደራለሁ የሚል የተለመደ ማደናገሪያውን ለማስኬድ እየሞከረ እንደሆነ እያየን ነው። ይህ አካሄድ አውቀው ሊታለሉ የሚፈልጉ ፈረንጆችን ያታልልበት እንደሆነ እንጂ በሀገሪቱ ያለውን የፖለቲካ ቀውስ በፍጹም ሊፈታ እንደማይችል የታወቀ ነው። የፖለቲካ ኃይሎች በነፃነት መንቀሳቀስና እንወክለዋለን ከሚሉት ሕዝብ ጋር በነፃነት መምከር ሳይችሉ ትርጉም ያለው ወደ ዘላቂ ሰላም የሚወስድ ድርድር ማድረግ ከቶውኑም አይችሉም። ሽጉጥ በግንባር ደግኖ “ከነብስህ ወይንም ከገንዘብህ” ብሎ ምርጫ ለሚሰጥህ ማጅራት መቺ ሕይወትን ለማትረፍ “ገንዘቤን ውሰድ” ቢባል በማጅራት መቺውና በሰባው መካከል “የሰጥቶ መቀበል ድርድር ተደረገ” እንደማይባል ሁሉ በግንባራቸው ላይ ሽጉጥ ደግኖ፤ ወይንም በእስር ቤት ከከተተ በኋላ የሚደረግ ድርድር በምንም አይነት በነፃነትና በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ድርድር ተደርጎ አይወሰድም፤ ተቀባይነትም የለውም። ስለዚህ ይህ አዋጅ በተግባር ላይ እስካለ ድረስ የሀገር ውስጥ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በማስፈራራት እየሰበሰቡ ወያኔን ብቻ አሸናፊ የሚያደርግ የድርድር ሙከራ ከእስረኞች ጋር የሚደረግ ድርድር ስለሆነ ምንም ተቀባይነት የለውም። የሕዝባዊ ትግሉም በእንዲህ አይነት የማደናገሪያ ሂደት ከጀመረው የነፃነት ትግል ላንዲት ጋት እንኳን እንደማይዘናጋ እንዲታወቅ ያስፈልጋል።
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ!!!!
በዚህ የመጨረሻ የፍልሚያ ወቅት ጥቂቶቻችን ልናልፍ እንችላለን። ለነፃነታችን ስንል ሕይወታችንን ብንሰጥ ፈጣሪያችን በአምሳሉ ሲፈጥረን የሰጠንን የሰውነት ማንነት እውን ለማድረግ በምናደርገው ትግል ነውና የምናልፈው፤ የፈጣሪያችንን ፈቃድ ለማስፈጸም የገበርነው ሕይወታችን ነውና በደስታ የምንጠጣው ጽዋችን ነው። ይልቅስ ፈጣሪያችን ለምንግዜውም ይቅር የማይለን ከሌላው እንሰሳ ለይቶ የሰጠንን ይህን በነፃነት የታጀበ የሰው ልጅነት፤ እንደ እንሰሳ ለሚበላና ለሚጠጣ ቁሳዊ ጥቅም ሸጠን፤ ሰው መሆንን በእንሰሳዊ የባርነት ሕይወት ቀይረን እኛ ባርነትን ተቀብለን ከራሳችን አልፎ ባርነትን ለልጆቻችን ያስተላለፍን እንደሆነ ነው። የዛሬ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የባርነትን ኑሮ ከኛ እንዳያልፍና ወደ ልጆቻችን እንዳይጋባ ማስቆም ታሪክ የጣለብንና በእርግጠኛነት የምንፈጽመው ተግባራችን እንደሆነ ከቶውንም አልጠራጠርም።
ጥቅምት 7 ቀን 2009 ዓ.ም.
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ
አንድነት ኃይል ነው !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚፈልግን ሁሉ መራራ ዉጊያ እንደምንዋጋዉ ብቻ ሳይሆን እንደምንደመሠዉም በደንብ ይወቅ (ሸንቁጥ አየለ)

$
0
0

አበሻን የማያዉቁት አክራሪ እስላማዉያን በጀዋር እየተመሩ ኢትዮጵያን ፍርስርሷን ነዉ እምናወጣት::ሌሎቻችሁም ተባበሩን ሲሉ ፎክሩብን::ከኢትዮጵያ ተገንጥለንም አይበቃንም::ኢትዮጵያን ግንጥልጥል : ፍርስርስ እናደርጋታለን ብለዉ ተቀናጡብን::

የአናሳ ስነልቦና አንጠልጥለዉ ብዙሃን ህዝብ እንወክላለን ለማለት የማያፍሩት ጀዋራዉያን መቼም ኢትዮጵያ ባለቤት የላትም እና ሌሎቻችሁ ኢትዮጵያዉያንም ኢትዮጵያን በመበታተን ተባበሩን ሲሉ ለንዶን ላይ ተሰብስበዉ በኢትዮጵያ መበተን ተሳለቁ::
ባለጌ ካልነገሩት አይገባዉ:: እነዚህ በአናሳነት ስነልቦና የተወጠሩ: የአረብ አክራሪ አማካሪ እና የአረብ ገንዘብ እጀርባቸዉ ላይ አዝለዉ የሚዞሩ ጀዋራዉያን ቢመቻቸዉ መላዉ የኢትዮጵያን ክርስቲያን እንደ ግራኝ ማህመድ ስሩን ሊነቅሉት እንደሚንቀሳቀሱ የታወቀ ነዉ::

ጥቂት የበሰለ ፖለቲካ ያደርጋሉ ብለን 10 % (አስር ፐርሰንት ጓጉተን ነበር)::ግን አንድ ፐርሰንት እንኳን ፖለቲካ እንደማያዉቁ እና ለድርድር እንደማይበቁ አስመስክረዋል::

እንግዲህ እዚያዉ ጦር ሜዳ እነገናኛለን::ኢትዮጵያ በእናንተ አይነት ምናምንቴ እና በአናሳ ስነልቦና በተወጠሩ ፈሪዎች እንደማትፈርስ ጦር ሜዳ ስንገናኝ ብዙ የምትናዘዙት ነገር ይኖራችኋል::

ኢትዮጵያ ዛሬም ባለቤት አላት:: በቃላት ሳይሆን በመረጣችሁት ጦር ሜዳ ላይ እንገናኝ::

ኢትዮጵያዉን ለማይቀረዉ ጦርነት መዘጋጀትን አትርሱ::እነጀዋር ከወያኔ እኩል መደምሰስ ይኖርባቸዋል:: ያዉም ከመላዉ ኢትዮጵያ ርዝራዣቸዉ እንዳይገኝ ተደርጎ:: ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚፈልግን ሁሉ መራራ ዉጊያ እንደምንዋጋዉ ብቻ ሳይሆን እንደምንደመሠዉም በደንብ ይወቅ::

ማጠቃለያ:-
—————
ጀዋር የሚወክለዉ የአክራሪ እስላሞችን (ISS) አጀንዳ ነዉ::የኦሮሞን ህዝብ ፈጽሞ አይወክልም::ጀዋር ዋና ግቡ በጽንፈኛዉ አይ ኤስ ኤስ (ISS) አንቀልባ የታዘለ አክራሪነትን አንግቦ ይዞ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ኢትዮጵያን ማፈራረስ እና ክርስቲያኖችን ሁሉ መጨረስ ነዉ::ልክ ኢራቅ: ሶሪያ እና ሌሎችም አረብ አገሮች ዉስጥ አክራሪ እስላሞች መልካሞቹን ሙስሊሞች እንደሚጨርሷቸዉ ሁሉ ጀዋርም የኢትዮጵያ መልካም ሙስሊሞች ከእርሱ አላማ ጋር ካልተባበሩ የማጥፋት ስራ ይሰራል::

ስለዚህ ጀዋር የኦሮሞን ህዝብ የሚወክል የሚመስላችሁ ኢትዮጵያዉያን እዉነቱን ተረድታችሁ ጀዋርን በአለም አቀፍ ሚዲያ ሁሉ ማጋለጥ አለባችሁ:: ጀዋር አላማዉ አክራሪ እስልምና (ISS) ነዉ::ጀዋር በጀርባዉ ያዘለዉ ተልዕኮ አክራሪ እስላም (ISS) ብቻ ነዉ:: ሌላዉን ነገር እሚናገረዉ ደጋፊ ለማግኘት ነዉ::

ኢትዮጵያን የምትወዱ የኦሮሞ ልጆችም ጀዋር ያነገበዉን የአክራሪ እስልምና ተልዕኮ ተረድታችሁ ጀዋርን ከኦሮሞ ህዝብ ቆርጣችሁ ጣሉት:: የኢትዮጵያ ህዝብ በአጠቃላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ህልዉናን ለማስከበር ለረዥሙ እና ለመራራዉ ጦርነት የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ ያስፈልግሃል::

የተዋህዶ ቤተክርስቲያን: የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን እንዲሁም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከእንቅልፋችሁ ንቁ::አክራሪዎች ኢትዮጵያን ካጠፏት ብኋላ ነጠላ ለብሳችሁ ወይም ጃንጥላ ይዛችሁ አክራሪዎችን ብትማልዷቸዉ አይምሯችሁም::ህዝባችሁን አንገቱን ብቻ ሳይሆን የሚቆርጡት ሬሳዉንም በሳት ነዉ የሚያቅጥሉት:: አክራሪ እስላሞች (ISS) እንኳን ክርስቲያኖችን ቀርቶ መልካም ሙስሊሞችን በሶሪያ: በኢራቅ: በግብጽ: በመላዉ አረብ ያለርህራሄ ሲያርዱ እያዬን ነዉ::

እንግዴህ ጦርነቱን ማን ይመራዋል ብላችሁ አትጨነቁ:: ብቻ የስነልቦና ዝግጅት አድርጉ::ይሄ በአረብ ረብጣ ገንዘብ ያበጠ አክራሪ ጀዋር ኢትዮጵያን ለማጥፋት በጌቶቹ የአረብ አክራሪዎች ስም ምሎ መገዘቱን እንዳትረሱ::

ተሰብሳቢውን በእምባ ያራጨው የታማኝ በየነ ንግግር በሚኒሶታ –“ቢያንስ ለቅሷችንን እንኳ በጋራ እናልቅስ”

$
0
0

ተሰብሳቢውን በእምባ ያራጨው የታማኝ በየነ ንግግር በሚኒሶታ – “ቢያንስ ለቅሷችንን እንኳ በጋራ እናልቅስ”(ዘ-ሐበሻ) ጽናት የውውይት መድረክ በሚኒሶታ ባዘጋጀው ሁሉን ያካተተ የውይይት መድረክ ላይ ተወዳጁ አክቲቭስትና አርቲስት ታማኝ በየነ ተገኝቶ ተሰብሳቢውን እምባ ያራጨ ንግግር አድርጓል:: በዚህ ዝግጅት ላይ ከጋምቤላ; ከኦጋዴን; ከኦሮሞና ከአማራ የተወከሉ ተናጋሪዎች የነበሩ ሲሆን በሕዝባችን ዘንድ ያለውን አንድነት ለማጠናከር ወይም በአንድ ላይ ለመጓዝ ሁኔታዎችን ያመቻቹ ንግሮች ተደርገዋል:: ታማኝ በየነ “ቢያንስ ለቅሷችንን እንኳ በጋራ እናልቅስ” ሲል ስለአንድነትና መተባበር አስፈላጊነት ያደረገውን ንግግር ቢያድምጡት ይጠቀማሉ:: ሌሎች እንዲመለከቱትም ያካፍሉት::

ድል ለኮማንድ ፖስት!

$
0
0

ዳኒሄል ሽበሺ

ኀወሓት-ኢህአዴግ የኢት/ያን ሕዝብ ዒላማ ባደረገ መልኩ የሞባይል ኢንተርኔት አቋርጧል፡፡ በዚህም ምክንያት ያጣው የገንዘብ ገቢ ብቻ አይደለም፡፡ ክብራቸውን፣ ሞራላቸውን፣ ሰላማቸውን፣ ዲፕሎማሲያቸውን፣ የሕዝብና የዓለም አቀፉን ማኀ/ሰብ ይሁንታን፣ ተሰሚነታቸውንና ሌሎችንም ፈርጀ ብዙ መንፈሳዊና ቁሳዊ ጥቅሞቻቸውን አተዋል ፡፡ ጨቅ ያለ የገንዘብ አፈሣቸውን ብቻ ነጥለን ብናይ እንኳ ከወትሮው የተለየ የሀገር ኢኮኖሚ ተጎዳ ባልልም ግን የባለሥልጣናቱ የአገር ውስጥ ገቢና በውጭ ሀገር ባንኮች የሚከማቸው ገንዘብ መጠን እንደጎደለባቸው በርግጠኛነት መናገር ይቻላል፡፡
[ባጠቃላይ ካተረፉት ይልቅ የከሰሩት ያመዝናል ብለን መደምደም ይሻላል፡፡]
በቅርቡ በአንድ ባለሙያ ተጠንቶ በተለያዩ መገነኛ ዘዴዎች እንደተሰራጨው ከሆነ፤ ቴሌ ከሚትባል የወተት ላም የሚታለበው ወተት ከላምቷ ጊት እየደረቀ ነው ፡፡ ይህንን አስመለክተው በአንድ ወቅት የተናገሩት ክቡር ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ በጥሩ አገላለጽ “የሚትታለብ ላም” ብለውታል፡፡ ይህ የኢህአዴግ ቴሌ-ላም አገ/ት ወይም #Services የሚትሰጠው ለማኀበራዊ ሚዲያዎችም ጭምር ሲሆን፤ ለአብነትም facebook viber whatsapp imo twiter ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡ በእነዚህና ሌሎች መሰል አገ/ት በሚሰጡባቸው ማኀ/ዊ ሚዲያዎች አማካኝነት የስልክ፣ የጹሁፍ፣ የኦዲዮ፣ የቪዲዮ ወዘተ አገለግሎቶችን እንጠቀምበታለን ፡፡ በዚህ አገ/ት በሀገር ውስጥና ውጭ ሀገር ካለው ወዳጅ ዘመድ ከሚደረገው ግንኙነት … ከተጠቃሚዩ ብዛት አንፃር ምን ያህል እንዳጡ መገመት ይቻላል፡፡ ወረቀት እየተፋቀ ቁጥር በሚሞላው ሒሳብ አማካኝነት በሚሰራው ሞባይል ዳታ በኩል የሚታፈሰውን ገቢ አጥተዋል ማለት ነው፡፡

stateofeme-1
በአንፃሩ ከሥርዓቱ አራማጆች/ተጠቃሚዎች ጉዳት አኳያ የተገልጋዩ ጉዳት ዝቅተኛ ቢመስለንም ግን የዋዛ አይደለም፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው አጢኚው ገለፃ ከሆነ ባለፉት ጥቂት ቀናት ማለትም ከጥቅምት 5ቀን፡ 2009 ዓም ወዲህ ብቻ (በ10ቀናት) ከ#9 ሚሊዮን ዶላር ወይም #ከ190 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳጡት ይፋ የሆነውን ማስታወስ በቂያችን ነው፡፡ ሌሎቹም ለምሳሌ በንግዱ፣ በቱሪዝም፣ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ መስክ የተሰማሩም ቱጃሮቻችም እሪሪ እያሉ ነው፡፡ ሌሎቹም በማይክሮና በማክሮ ምጣኔ ሀብት ዘርፍ የተሰማሩም ዛሬ ላይ ደም-እምባ እያለቀሱ መሆናቸውን እየሰማን ነው፡፡
አዋጁ ባይታወጅ ኖሮስ ከዚህ የከፋ ጉዳት ይደርስ ነበር ወይ? ይህ የኔ ጥያቄ ነው፡፡
በሌላ በኩል ከአንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ለቀውሱ እንደመፍትሄ የተቀመጠው የሚል ነው፡፡ ይህንንም ባሳለፍነው ሳምንት የመቀሌው የቪኦኤው ዘጋቢ በዘገባው እስደምጠውናል ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የኢፌዴሪ ዋና ዐ/ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ በበኩሉ “በእርቀ ሰላም ሰልጣን ለመያዝ የተደረገው ጥረት ከሽፏል” በማለት የአስገዳጅ አዋጆችንና የክላሽ መንገድ ብቸኛ የመፍትሄ አማራጮች መሆናቸውን አብስረዋል፡፡ በዚህ መንገድ ካልሆነ በስተቀር ምንም እርቅ ሰላም ንግግር ገለመለ እንደማያስፈልግ እንቅጩን ነግረውናል፡፡
በጤናማ አዕምሮ ለሚያስብ ሁሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሳይታወጅ ቀውሱን መቆጣጠር የሚቻልባቸው አማራጮችም እንዳሉ እንረዳለን፡፡ ነገር ግን በዚህ አዋጅ ሽፋን፤ ከፍ ስል የጠሉትን ከምድር ገጽ ለማጥፋት፤ ዝቅ ሲል ዳግም ቀና እንዳይሉ አከርካሪያቸውን ለመምታት አዋጁ ሠፊ ዕድል ሊሰጥ ይችላል ብለው ማርቀቃቸውን መገንዘብ የሚቻል ይመስለኛል ፡፡ በውጤቱም በብዙ የሚቆጠሩ የዲፕሎማሲያዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኪሣራቸው በአዋጁ ካተረፉት እንደሚልቅ መገመት ይቻላል ፡፡ ሰብሰብ አድርገን ስናይ አምባገነንነት ኪሣራው ብዙ ነው፡፡ መከራው ብዙ ነው፡፡ ጨቋኝ ሲትሆን ቂምና ቁርሾ ጥልቅ ነው፡፡ ኪሣራው መዓት ነው፡፡ ለዛሬም ሆነ ለመጪዩ ጊዜ/ትውልድ የሚሻገር መዘዝ ሰፊ ነው ፡፡ ባጠቃላይ ሰዎቹ በጎናቸው የሚቆም ሕዝብ አጥተዋል፡፡ ኢንቬስትሜንታቸውን አጥተዋል፡፡ ገቢያቸውን አጥተዋል፡፡ ሞራላቸውንና ክብራቸውን አጥተዋል፡፡ የመንግሥትነት ፀጋን #Grace ተገፏል፡፡ በሥጋትና በፍርሃት ቆፈን ሰምጠዋል፡፡ ድሮ፣ድሮ ኀወሓት አፈር ልሶ መነሣትን ያውቅበታል ይባል ነበር፡፡ ዛሬ ግን ወደማይወጡበት መቅመቅ ውስጥ ራሳቸውን ከተዋል፡፡ ከዚህ በኀላ እንደልማዳቸው እየረበሹ ካልሆነ በስተቀር እምነትና ተስፋ ተጥሎባቸው መኖር ታሪክ ሆኖባቸዋል፡፡
ሰሞኑን በገዥውና በእነርሱ በተመረጡ ሰዎቻቸው መካከል (ቅዳሜ ጥቅምት 5ቀን፡ 2009 ዓም) አንድ ቀን የፈጀ የወይይት መድረክ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አዘጋጅነት “የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ከየት ወዴት? ፈተናዎችና መልካም ዕድሎች” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ውይይት ላይ የተገኙት #አቶ በረከት ስምዖን የገለጹትን ሳይ ከምር አስደንቆኛል ፡፡ ነገሩ ለእኛ (ለሕዝቡ) ወይም ለእነርሱ ገና እንዳልገባን እንረዳለን፡፡ ሕዝቡማ ስለገባው መንገዱን ቀጥለውበታል፡፡ ስለዚህ ከሰዎቹ ዐእምሮ ዛሬም ጫካው እንዳልወጣላቸው ነው መረዳት የሚቻለው ፡፡ በኤርትራዊነት የሚታሙት አቶ በረከት ስምዖን፦ ስለ ምርጫ 2002 እና 2007 የአሸናፊነታቸውን ምስጢር በድፍረት ሲያበስሩልን … “ባለፉት በሁለት ምርጫዎች ተቀዋሚዎች ማሸነፍ ያልቻሉት ወይም ኢህአዴግ ፓራላማውን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረበት ምክንያት “ ብለው ካሣቁን በኀላ ቀጠሉና <...>” በማለት የመጡበት መንገዳቸውን አጽንተዋል፡፡ ስለዚህ እንቅጩን ነግረውናል ማለት ነው፡፡ አገላለፃቸው ለፓርቲያቸው ያላቸውን ታማኝነታቸውን ማረጋገጥ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ምንም አታመጡም፤ አርፋችሁ ቁጭ በሉ… መልዕክታቸውንም ማስተላለፍ ነበር ፡፡ አምባገነኖች ሀገር መምራት ሥልታቸው ጡንቻ ስለሆነ፤ ሌሎች መንገዶችን ይዘጉታል፡፡ ኢንተርኔት፣ ሚዲያ፣ ሲቪክ ማኀ/ብን፣ የመደራጀት ነፃነቶችን ወዘተ ይዘጉታል፡፡ ከዕውቄታቸው/ከአቅማቸው ሆነባቸው ሆነባቸው እንጂ እስትፋስህን፣ ፀሐይዋንና ጨረቃዋንም ወዘተ መቆጣጠር ፍላጎታቸው ነው፡፡
ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ አንድ ጥያቄ ልሰንዝርና ወደ ማጠቃለያው ላምራበት፡፡ የኢት/ያ ሕዝብ ይህን ያህል ከወደዳቸው፤ ተመርጠናል ባሉት በ4እናበ5 ወራት፣ በአንዳንድ አከባቢዎች 1ና2 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የኦሮሚያ፣ አማራና በደቡብ ሀገራችን ክልሎች የሞት ያህል የከበደ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንደት ሊገጥማቸው ቻለ? የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስኪታወጅ ያስገደደ አንቀጠቅጥ ተቀውሞ በሀገራችን ለምን ተከሰተ? ሕዝቡ ፀረ ሰላም ስለሆነ? ወይስ አሸባሪ?
ላጠቃልል፦ የሰው ልጅ ወፍ መሆን አይችልም፤ ወፎችም ሰው መሆን በፈጹም አይችሉም፡፡ የተፈጥሮ/የፈጣሪ ህግ ስለሆነ፡፡ ይህ ማለት አምባገነኖችም ዴሞክራቲክ ሊሆኑ አይችሉም!! ማለት ነው፡፡ የትም ሀገር የሚኖሩ አምገነኖች ሁሌም ተመሳሳይ ባሕርይ አላቸው፡፡ የሚነግሩን እንዲሁ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁሌም ቢሆንም የመታረም ብዙ ዕድልና ሰፊ ጊዜ አላቸው ግን አይጠቀሙም፡፡ እንግዲህ! ምንም ምርጫ የለንምና ድል ለኮማንድ ፖስቱ! ብንልስ? ቸር ያሰማን፡፡


በተስፋ መቁረጥ ኦነግ ሲጋለጥ

$
0
0

ከሃምሳ ዓመት በላይ ኢትዮጵያን ለመሰባበር ታጥቆ የተነሳው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ነኝ የሚለው አሸባሪና ቅጥረኛ ቡድን ፣ ሲዳክርበት ከነበረው አሮንቃ ውስጥ ሆኖ አሁን ተስፋ በቆረጠ መልኩ አቋሙን በይፋ ቁልጭ አድርጎ በአደባባይ አውጥቷል።ይህ ቀደም ሲል በሶማሊያና በአረቦች እርዳታ ኢትዮጵያን ለመሰባበር ጫካ ገብቶ ሳይሳካለት ቀርቶ በየአገሩ ተበታትኖ የነበረ ቡድን ፣ከዛሬ ሃያ አምስት ዓመት በፊት በወያኔ ጥላ ስር ተሰብስቦ የወደቀ ዓላማውን ከቤተመንግሥት ተግባራዊ ለማድረግ ሲል ኢትዮጵያን ለማፈራረስ በሚያስችለው ቻርተር አውጭነት ተሳትፎ እንደነበረና በሽግግርም ስም የሥልጣኑ ተቋዳሽ እንደነበረ የሚታወቅ ነው።“ሌባ ሲሰርቅ ይስማማል ሲካፈል ይጣላል” እንደሚባለው ከሽግግሩ በዃላ በቅርምቱ ድርሻ ላይ በተነሳ አለመግባባት ከወያኔ ጋር ተጣልቶ አገር ጥሎ ወደመጣበት የውጭ አገር ጓዳ እንደገባ የሚታወቅ ነው። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በወያኔና በሻብያ መካከል በተፈጠረው የጥቅም ግጭት አሥመራ ከተማ ቢሮ ከፍቶ የመንቀሳቀስ ዕድል አግኝቶ የተበታተነ ሃይሉን ለማሰባሰብና የዘረኛ መርዙን መርጨት ከጀመረ ውሎ አድሯል።ይህን የመሰለውን አገር አጥፊና የውጭ ቅጥረኛ ቡድን የሚረዱት የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም የማይሹ ታሪካዊ ጠላቶቿና በወረራና በዘረፋ የተካኑት የውጭ አገሮች ጭምር ናቸው። በጣም የሚያሳዝነው በኢትዮጵያ መሬት ተወልዶ፣አድጎና ተምሮ ለቁም ነገር የበቃውም ዜጋ ለዚህ አደገኛ ቡድን ጆሮውን መስጠቱና ለራሱም የሚተርፈውን የጥፋት ነጋሪት አዋጅ በትእግስት ማዳመጡ ነው።በሌላም በኩል አንዳንድ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንታገላለን የሚሉ ቡድኖች ለምሳሌም እንደግንቦት ሰባት አይነቶቹ ከዚሁ ዘረኛ የኦነግ ቡድን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ “የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው”፣ወይም ወያኔን ለመጣል ከጸሃይ በታች ካለ ጋር እንስማማለን በሚል ጮርቃ ስልት ከኦነግና ከመሳሰሉት ጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ተሰልፈው ማየቱ ብዙዎችን ያሳሰበ ቢሆንም አሁን የቆሙበትን ዓላማ ከጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል።ከአሁን በዃላ እያምታቱ የሚጓዙበት ሰዓት አይደለም፣ከወሳኝ ሰዓት ላይ ደርሰናል። ጠላታችንን አውቀናል ፣በአገር ቤት ወያኔና ደጋፊዎቹ፣በውጭ ደግሞ ኦነግና የኦነግ ደጋፊዎች ናቸው። በአገር ቤት በተቀጣጠለው ሕዝባዊ ትግል የኦሮሞና የአማራው ማህበረሰብ ለጋራ መብቱ ተቀራርቦ ሲታገል ያስበረገጋቸው የኦነግ መሪዎች ሕዝቡ ለምን ተቀራረበ፣ ኢትዮጵያን የመበታተን ተልእኮአችንን አከሸፈብን በሚል ቁጭት ሰሞኑን በእንግሊዝ አገር ዋና ከተማ ለንደን ውስጥ ተሰብስበው በተናገሩት ይፋ አድርገውታል።ያም አላማቸው ኢትዮጵያን መበታተን እንደሆነ ደጋግመው ሳያፍሩና ሳይፈሩ አረጋግጠዋል።የጥላቻ ዶር.የሆነውና የሱም አውታንቲ የሆነው ጁዋር ሙሃመድ የተባለው ተላላኪ የተናገሩትን በብዙሃን የዜና ማሰራጫዎች ያልሰማ ቢኖር ጥቂቱ ነውመሰማትም ያለበት ነው።ወያኔ ሳይቀር በአገር ቤት ሕዝቡን በሸምቀቆው ውስጥ ለማስገባትና ከተሳተፈበት ትግል እንዲርቅ ለማድረግ ቅስቀሳ አካሂዶበታል። እኔ ከሄድኩ የሚጠብቃችሁ ይህ ነው ብሎም ለማስደንበር ተጠቅሞበታል።በሌላ መልኩ ሲያዩት የኦነግን ስብሰባ ወያኔ ስፖንሰር ያደረገው ይመስላል።ታዲያ ኦነግን የትግል አጋሬ ነው የሚለው ግንቦት ሰባት ምን ዋጠው? አሁንም ተቃቅፎ ይሄዳል?በኦነግም ሆነ በሌሎቹ የነጻ አውጭ ነን ብለው ከጎኑ በተሰለፉት ቡድኖች ላይ ያለውን አቋሙን ግልጽ ማድረግ ይጠበቅበታል።ያንን ካላደረገ በገንዘብና በሃሳብ የሚረዳው ኢትዮጵያዊ ጉዳዩን በጥሞና መመርመርና አቋም መውሰድ ይገባዋል። በኦሮሞ ማህበረሰብ ስም የሚነግዱ ብዙ ድርጅቶች እንዳሉ አይካድም፤ በሌላውም ማህበረሰብ ስም እንዲሁ።ዓላማቸው አንድ ሲሆን የሚለያቸው ዓላማቸውን ለመተግበር የሚሄዱበት ስልት ነው።ይህ ያልገባው የዋህ ኢትዮጵያዊ በፊለፊት የገባውን ሌባ ወያኔን እየተቃወመ በጓዳ በር ልግባ የሚለውን ሌባ እንደቤተሰብ አይቶ አጅቦ መሄድ አይኖርበትም።ሌባ ሌባ ነው ብሎ ለንብረቱ ዘብ መቆም ይኖርበታል። በዚህም ሆነ በዚያ ኢትዮጵያን እንደ አንድ አገር፣ኢትዮጵያውያንን እንደ አንድ ሕዝብ የማያይ ቡድንም ሆነ ግለሰብ መልካም አቋም አለው ብሎ መገመትና ፣በዚያ ላይ ያለ ልዩነትን የዲሞክራሲና የእኩልነት መብት አድርጎ መቀበል ጅልነት ነው። ሰው በአገሩና በማንነቱ ላይ አይደራደርም።ይህ አገር የማዳን ትግልና አላፊነት የአንድ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ከጠባብነትና ከትንሽነት ይልቅ ትልቅነትን፣ከክልል እስረኝነት፣ይልቅ የሰፊ አገር ባለቤትነትን የሚሻ፣እንደአውሬ ሳይሆን እንደጤነኛ ሰው የሚያስብ ሁሉ የሚሳተፍበት ትግል መሆን ይኖርበታል። ከሃገር ወጥቶ መንደር ውስጥ መሰግሰግ የድህነትና የአውሬ ኑሮ ናፋቂ መሆን ነው።

አገር ሲባል መግለጫው ሰንደቅ ዓላማው ነው።ማንኛውም አገር የሚኖረው ሰንደቅ ዓላማ አንድ ብቻ ነው።ሌላ ባንዲራ ማውለብለብ ማለት የተለየሁ ነኝ ማለት ነው።የተለየሁ አገር ዜጋ ነኝ ብሎ የተሰለፈን ቡድን ማጀብ እራሱ የተለየህ ነህ ብሎ ማጽደቅና መቀበል ማለት ነው።ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው ካልን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ልንነፍገው አይገባም።የነውጠኞቹን ባንዲራ ተሸክሞ የሚነጉደውን የዋህ ከጥፋት ጎዳና እንዲወጣ መምከር እንጂ፣ በርታ እያሉ ከጎኑ ሊሰለፉለት አይገባም። የተለያዩ ቋንቋዎች ባህሎችና፣እምነቶች መኖር የሌላ አገር ዜጋ አያደርግም።እንደ ኢትዮጵያ ባለብዙ ቋንቋና ባህል እንዲሁም ሃይማኖት ባለቤት የሆኑ አገሮች ብዙ ናቸው።እነዚያ ግን በዛው ተዋረድ ተለያይተው እርስ በርስ ሲጋጩ አይታይም።በልዩነት አንድነትን፣በመከባበር መተባበርን መርጠው የእድገትና የሥልጣኔ ባለቤቶች ለመሆን በቅተዋል። የኦነግንና የመሰሎቹን፣ የዘር ትግል የሚያራምዱትን ቡድኖች እራሱ የራሳቸው ቋንቋ ተናጋሪ የሆነው በስሙ የሚነግዱበት ማህበረሰብ ሊታገላቸው ይገባል።አይሳካላቸውም እንጂ ቢሳካላቸው መልሰው የሚቀጠቅጡት መሆኑን ካሁኑ መገንዘብ አለበት።ብዙ የኦሮሞ ተወላጅ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምንና ለኢትዮጵያ አገሩም የደም ዋጋ የከፈለ ለመክፈልም ዝግጁ የሆነ ነው።በስሙ ስልጣን ይዘው መቀመቅ ሊከቱት የተነሱትን በየአገሩ ተበትነው በስሙ የሚነግዱትን ተዋርደው ሊያዋርዱት የሚቅበዘበዙትን ቅጥረኞች ወግዱ ሊላቸው ይገባል።በሰሞኑ የለንደኑ ስብሰባ የኦነግን ዓላማ የተገነዘቡት የኦሮሞ ልጆች በቁጣ ተነስተው ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው።ኢትዮጵያዊነታቸውን አስመስክረዋል።ሌላውም እንዲሁ የዝምታንና የፍርሃትን አጥር አፍርሶ ኢትዮጵያዊነኝ ፣አትወክሉኝም ብሎ ሊያሳፍራቸው ይገባል። አሁን ጊዜው የመኖር ወይም ያለመኖር ነው።በኦነግና በመሰሎቹ ፣በወያኔና ባጃቢዎቹ የዘረኞች ካምፕ ውስጥ የሚከናወነው ደባ በተባበረ የኢትዮጵውያውያን ክንድ መሰበር አለበት።እነሱን ማሶገድ ማለት ኢትዮጵያን ከመበታተን፣ እራስን ከእልቂትና ከሽብር ማዳን፣ሁሉንም የሚያገለግልና የሚያረካ ስርዓት ማስፈን ማለት ነው።መቀራረብና መነጋገር የሚቻለው አንድ አይነት ዓላማና ፍላጎት ካለው ጋር እንጂ ልዩ ነኝ ከሚልና ሊያጠፋ ከመጣ ጠላት ጋር አይደለም።ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ድርጅትም ሆነ ስብስብ ከኦነግና ከመሳሰሉት ጋር መደራደሩን ማቆም አለበት።ግንኙነቱ በግልጽ ያጥፊና የጠፊ እየሆነ መጥቷል።ለይቷል! እራስንና አገርን ከአደጋ ለማዳን ከሚሹት ጋር ውይይት ማድረግ እንጂ በስም ከሚለዩ ከጥፋት ሃይሎች ጋር መደራደር አይገባም።ትልቅ ስህተት ነው።ምርጫው ከጅንጀሮ ቆንጆ ነው።ትግሉ የወያኔን ስርዓት በኦነግ ወይም በተመሳሳይ ስርዓት ለመተካት አይደለም።መሆንም የለበትም።የዘረኞችን ስርዓትና ዓላማ የሚደመስስ ፣ዳግም አምባገነኖች የሚፈልቁበትን ምንጭ የሚያደርቅ መሆን አለበት። መጃጃል ይብቃ! የአንድነት ሃይሉ በዚህ ወሳኝ ወቅት መሰባሰብ አለበት!
ኢትዮጵያ በነጻነት ለዘላለም ትኑር!! ፣
አገሬ አዲስ

የትግራይ መንግስት የሰሜን ምዕራብ ወታደራዊ ሹም ሌተና ኮለኔል ሰብስቤ ጓዴ በባህርዳር ተገደለ

$
0
0


የትግራዩ መንግስት የሰሜን ምዕራብ ወታደራዊ ሹም ሌተና ኮለኔል ሰብስቤ ጓዴ ከሚጠጣበት መጠጥ ቤት ስልክ ሊያወራ ሲወጣ ታርዶ መገደሉን የአማራ ድምጽ ራድዮ ዘገበ:: ዝርዝሩን ያድምጡት::
የትግራይ መንግስት የሰሜን ምዕራብ ወታደራዊ ሹም ሌተና ኮለኔል ሰብስቤ ጓዴ በባህርዳር ተገደለ

በኢትዮጵያ በተከሰተው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሳብያ እርሻቸው ከጥቃት የተረፈው ሆላንዳዊው ባለሀብት ስለ ተሞክራቸው ይናገራሉ (ልዩ ጥንቅር) በታምሩ ገዳ

$
0
0


በኢትዮጵያ በተከሰተው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሳብያ እርሻቸው ከጥቃት የተረፈው ሆላንዳዊው ባለሀብት ስለ ተሞክራቸው ይናገራሉ (ልዩ ጥንቅር) በታምሩ ገዳ
በኢትዮጵያ በተከሰተው ሕዝባዊ ተቃውሞ ሳብያ እርሻቸው ከጥቃት የተረፈው ሆላንዳዊው ባለ ሀብትስለ ተሞክራቸው ይናገራሉ (ልዩ ጥንቅር) በታምሩ ገዳ

ሁለት የኤርትራ ጀት አብራሪዎች ከነጀታቸው መቀሌ ገቡ |መንግስት ጥገኝነት ጠየቁ አለ

$
0
0
ይህ የኤርትራ ተዋጊ ጀት ቆየት ብሎ የተነሳና ከኤርትራ ድረገጽ የተገኘ ነው:: ለዜናው ከፋይል ተጠቀምንበት እንጂ መቀሌ የገባው ጀት ይሄኛው ላይሆን ይችላል::

ይህ የኤርትራ ተዋጊ ጀት ቆየት ብሎ የተነሳና ከኤርትራ ድረገጽ የተገኘ ነው:: ለዜናው ከፋይል ተጠቀምንበት እንጂ መቀሌ የገባው ጀት ይሄኛው ላይሆን ይችላል::

(ዘ-ሐበሻ) ሁለት የኤርትራ የጀት አብራሪዎች ከነጀታቸው ትናንት መቀሌ መግባታቸውን እና ጥገኝነት መጠየቃቸውን የትግራዩ መንግስት የሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ዘገቡ::
እንደዜናው ከሆነ መብራህቱ ተስፋማርያምና ኣፈወርቂ ፍሰሃየ የተባሉ አብራሪዎች ጀታቸውን በመያዝ መቀሌ ኤርፖርት ከገቡ በኋላ ጥገኝነት ጠይቀዋል::
ዲሴምበር 2014 ልምምድ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ ሄሊኮፕተር በዋና አብራሪው አስገዳጅነት ኤርትራ ማረፉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የኤርትራ ወታደሮች ጀት ይዘው መቀሌ ገብተዋል:: በተለያዩ ጊዜያትም የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ኤርትራ እየገቡ ጥገኝነት መጠየቃቸው አይዘነጋም::

ፉክክር፣ ብሔረተኛነትና ትብብር በለውጡ ዋዜማ (ዩሱፍ ያሲን)

$
0
0

Yesuf Yasin AG7
1. ኢትዮጵያ በለውጥ ዋዜማ
በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ቀጣይነት ሊኖረው የሚችል ሁኔታ አይደለም (Unsustainable) ሲባል ሰንበትበት ብሏል። አንድ ሓሙስ ቀረው እየተባለ መነገር የጀመረው ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው። የሥርዓቱ እድሜ ካንድ ሓሙስ ይልቅ ከላይ ወደ ዜሮ በሚደረግ የኋሊት መቁጠር የሚዳዳቸው ታዛቢዎቹም አሉ። በፈረንጅኛው Count Down የሚሉት ስሌት መሆኑ ነው። እንደ ተለመደው ኢትዮጵያ ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ ቆማለች፣ በመንታ መንገድ ላይ ናት መባሉ እንደገና እየተዘወተረ መጥቷል። ሁሉም ግን ኢትዮጵያ ወዴት? የሚለውን ጥያቄ እያስጨነቀው ነው። ኢትዮጵያ አሁንም ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ መቆሟ አያነጋግርም። ወያኔ/ኢሕአዴግ አንድ ሓሙስ ቀርቷታል ትንበያ ላይ ሁላችን ባንስማማም በለውጥ ዋዜማ ላይ ናት መባሉ ያስኬዳል። “በለውጥ ማዕበል ዋዜማ ላይ መገኘቷ ሁሉን ቢያስማማም የጉዞዋ አቅጣጫ ወዴት እንደሆነ ግን አነጋጋሪ ይሆናል። አገራችን በዲሞክራሲ ለውጥ አቅጣጫ ትከንፋለች ወይስ ፍርስርሷ ወጥቶ ትበታተናለች? ምኞትና ሟርት፣ ተስፋና ስጋት የሚደበላለቅ ቢሆንም መፃኢ እጣ ፋንታዋ ብዙዎችን ስጋት ላይ ጥሏል። የተወሰኑ ዜጎቿን ያስቆዝማል፤ ያሳስባልም።”ይህንን የከተብኩት የዛሬ ሦስት ዓመት ገደማ ነው”1 ። ኢትዮጵያ በመንታ መንገድ ላይ ናት መባሉም ትክክል የሚሆነው በሀገሪቷ የሰፈነው ሊቀጥል የሚችል ሁኔታ አይደለም ከሚለው መሠረታዊ ግንዛቤ ነው። ፈረንጆቹ Unsustainable የሚሉት ዓይነት መሆኑ ነው። ወያኔ/ኢሕዴአግ አደርገዋለሁ ያለው ጥልቅ ተሓድሶ ለጊዜው ወደ ጎን አቆይተን በጥልቅ የለውጥ ማዕበል ዋዜማ ላይ ናት መባሉ ያስኬዳል። ልክ እንደ 1974(1966) ። ልክ እንደ 1991 (1983)።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ | PDF

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live