Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

እንደተፈራው በደብረማርቆስ ደመራ ላይ ሕወሓት ብጥብጥ አስነስታ ብዙ ወጣቶችን አሰረች –ስነ ሥርዓቱ ተቋረጠ –ባህርዳር ተኩስ ይሰማል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በደብረማርቆስ ከተማ በተደረገ የደመራ በዓል ላይ የሕወሓት መንግስት እንደተፈራው ብጥብጥ አስነስቶ በርካታ ወጣቶችን ማሰሩ ተሰማ::
Zehabesha-News.jpg
የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ከስፍራው እንደዘገቡት ከሆነ በደብረማርቆስ ደመራ ላይ የሕወሓት መንግስት ሆን ብሎ ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ ወጣቶችን ዳመራ በጠበጡ በሚል አስሯል:: እንዲሁም በርካታ ወጣቶች እንደተቀጠቀጡም የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል::

እንደ ምንጮቻችን ገለጻ የሕወሓት መንግስት የአማራውን ወጣት ለትግል ተነሳሽነቱን ለማኮላሸት በዚህ የደመራ ስነ ሥነስርዓት ላይ ባዘጋጃቸው ሰዎች ሆን ብሎ እንዲበጠበጥ አድርጓል:: ቀደም ብሎ ሕወሓት ይህን በማደረግ ወጣቶችን ለማሰር እንዳቀደ ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ተኩስ እየተሰማ ይገኛል:: ተኩሱ እየተሰማ ያለው በባህር ዳር ቀበሌ 13 መኮድ አካባቢ ሲሆን ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ እንደሚገኝም ታውቋል:: ዘ-ሐበሻ ተኩሱ ለምን እና እንዴት እንደተፈጠረ በማጣራት ላይ ናት::

↧

↧

ችግሩ ያለው ከመሪዎች እንጅ ከተመሪ አይደለም( አቡነ አብርሃም)

$
0
0

በልቦና ይስጠን

(ባህር-ዳር) መንግስትንና የራሱን ሚድያ ገስጹ
ህዝብ ጥያቄ መመለስ አለበት
፨፨፨ዮም ፍስሃ ኮነ በብሔረ ባህር ዳር በእንተ አቡነ አብርሃም፨፨

14502816_1836993936535481_7906889427951457037_n

ተወዳጅና መከበር ያለባቸው አቡነ አብርሃም ዛሬ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ህዝብን እልልልልል ያሰኘ ንግግር አደረጉ….እኔ ከመፍራቴ አንጻር በዓሉ ባይከበር ደስተኛ ነበርሁ ነገር ግን አባቶቼን ሳይ በየሳምንቱ ቢከበርም አይቆጨኝም።ጳጳስ አብርሃም እንዲህ አሉ፦፦
፨ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም..እልልልል…
፨የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት..ጭብጨባ ተስተጋባ
፨ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም..እልልልል.ቸብቸብ ከበሮ
፨በየ ሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለብት …እልልልልል
፨እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም..ቸብቸብቸብ..እልልልልም..ጭብጨባ..
፨ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው..እልልልል..
፨ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን??
፨የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም
፨ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልይ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ…..እልልልል…
..የሰላምና የጥበብ አባት እቡነ አብርሃም በልባችን ናቸው።
በዓሉ ጸሎትና ሀዘን የበዛበት ነበር..ሊቃውንቱ ወረብ፣የሰንበት ተማሪዎች፣የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎች መዘምራን ወቅቱን የተመለከተ መዝሙሮች ዘመሩ እንጅ ጭብጨባና እልልታ ምንም አላስተጋቡም..የበገናው እንዲህ ይላል፦
“ማዕበሉን አይቶ ልባችን አይፍራ
“ሁሉን ቻዩ አምላክ አለ ከኛ ጋራ..የሚል ነበር።
በመጨረሻም በየቤተክርስቲያኑ ይደረግ የነበረው የምህላ ጸሎት በጋራ መሀል ከተማ መስቀል አደባባይ ተስተጋባ..ይገርማችኋል ሃያል በሆነው አንደበታቸው አባ አብርሃም ጸሎቱን ….
..ምን እንላለን እውነተኛ አባት የሰጠን አምላክ ይመስገን።አባቶቻችንን ይጠብቅልን.
አባ አብርሃም ፖለቲከኛ አይደሉም የእውነት አባት እንጅ..እንወዳቸዋለን..እሱ ይጠብቅልን..አሜን

↧

አቡነ አብርሀም ታሪክ ሰሩ!

$
0
0

በአቻሜለህ ታምሩ

የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም ታሪክ ሰሩ። ከፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላዎች ፊት ለፊት እውነትን ተጋፍጠዋል። ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል። እንዲህም አሉ…

14502816_1836993936535481_7906889427951457037_n
«ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፤ በየ ሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለብት፤ እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም ፤ ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፤ ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን?፤ መንግስት የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልዩ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ» ብለዋል። ህዝብ ክርስቲያኑ አቡነ አብርሀም ይንን ንግግር ሲያደርጉ በእልልታና በጭብጨባ ድጋፉን ገልጧል።
ባህር ዳር ላይ «የተከበረው» የደመራ በዓል ጸሎትና ሀዘን ታስቦ ውሏል። የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቱ ወረብ፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎችና መዘምራን ደግሞ ወቅቱን የተመለከተ መዝሙሮችን አቅርበዋል። በገና ደርዳሪውም፦
«ማዕበሉን አይቶ ልባችን አይፍራ፣
“ሁሉን ቻዩ ጌታ አለ ከኛ ጋራ፤ ብሏል።
በመጨረሻም በየቤተክርስቲያኑ ይደረግ የነበረው የምህላና ጸሎት በጋራ መሀል ባህር ዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ተስተጋብቷል። አባታችንን አቡነ አብርሀምን፣
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቶቻችንን፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን፣ የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎችና መዘምራን ቃለ ህይወት ያሰማልን። ረጅም እድሜ ይስጥልን።
ሁሉም መርሀ ግብር ካለቀ በኋላ አቡነ አብርሐም መጀመሪያ «ሕዝቡ ወደቤቱ ሳይገባ እኔ አልንቀሳቀስም» በማለታቸው እዚያው መስቀል አደባባይ ከቀሩ በኋላ፤ በመጨረሻ ላይ የአማራ ፖሊስ ዩኒፎርም በለበሱ የትግራይ ወታደሮች ከታት በሚታየው መልኩ በፖሊስ መኪኖች ታጅበው እሳቸው ግን በእግራቸው ወደ ባዕታቸው ተመልሰዋል።

↧

(ኢሳት) በጎንደር እድገት ፈለግ ወይም አሽዋ ሜዳ ከተባለው ቦታ ቁጥራቸው ያልታወቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መጥፋታቸው ታወቀ፡፡

↧

1 የወያኔ አገዛዝና የኢትዮጵያ ወደፊት (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

$
0
0

መስፍን ወልደ ማርያም

መስከረም 2009

የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ

የወያኔን አገዛዝ ማውረድ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ሆኗል፤ ይህ የሚያከራክር አይመሰለኝም፤ ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ በጠመንጃ ጉልበትና በሲአይኤ ድጋፍ ሰንጎ የገዛ ቡድን በቃህ ቢባል አይደንቅም፤ ሌላው ጥያቄ ‹‹የወያኔን አገዛዝ ማውረድ የሚቻለው እንዴት ነው?›› የሚል ሲሆን በዚህ ላይ ስምምነት ያለ አይመስለኝም፤ መልሱ ሰላማዊ ወይም የትጥቅ ትግል የሚል ምርጫ ብቻ ሳይሆን፣ የወያኔን አገዛዝ ለማውረድ የተሰለፉትስ እነማን ናቸው? ዓላማቸውስ ከቃል ባሻገር ምንድን ነው? የሚልም ይሆናል፤ ባልተቀነባበረ መንገድ በተለያዩ ቦታዎች አሁን የሚታዩትና በያለበት ኩፍ ኩፍ የሚሉት የመንተክተክ ምልክቶች ለወደፊቱ ሥርዓት ያለውን ሰልፍ አያሳዩም፤ አዲስ ነገርና የምሬቱ መግለጫ መገዳደል መጀመሩ ነው፤ ገዳይ መለዮ ለባሹ ብቻ መሆኑ እየቀረ ነው፤ እነዚህ ምልክቶች ለውጥ ግዴታ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው፤ ችላ ሊባሉ አይገባም፤ የዛሬ ጉልበተኛነት የነገ ደካማነት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፤ አንድ አገዛዝ ከወጣቶች ጋር በጠብ እየተጋጨ ዕድሜ አይኖረውም፡፡

የወያኔ ሎሌዎች እኔ ስለትግራይ ያለኝን አመለካከት እያጠናገሩ ማውራት ከጀመሩ ዓመታት አለፉ፤ ፋይዳ የላቸውም ብዬ ንቄ ትቻቸው ቆይቻለሁ፤ አሁን ግን የወያኔ ሎሌዎች በትግራይ ሕዝብ ላይ ያደረሱትንና የቃጡበትን ከባድ አደጋ በጥልቅ ስለተገነዘብሁ፣ የምችለውን ያህል ለማስተካከል ቆርጫለሁ፡፡

ከዚህ በፊት ከክንፈ ወልደ ሚካኤል ጋር ብቻ ተነጋገሬበት ነበር፤ ዛሬ እንደክንፈ የሚያምነኝና የማምነው ወያኔ የለም፤ ችግሩም እየተባባሰ በመሄዱ ጊዜን የሚሰጥ አልመሰለኝም፤ ስለዚህ አደባባይ ላውጣውና የሌሎች ሰዎች ሀሳብ ተጨምሮበት በጊዜ መፍትሔ ብንፈልግ ተገቢ ይመስለኛል፡፡

በአጼ ዮሐንስ ዘመን የትግራዩ ራስ አሉላ መረብ-ምላሽን ይገዙ ነበር፤ ኢጣልያኖች ለመረብ-ምላሽ ኤርትራ የሚል ስም ካወጡለት እአአ ከ1900 በኋላ፡

ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣልያ በተወረረችበት ዘመናት እአአ ከ1935 አስከ1941 ኤርትራ ከትግራይ ጋር ተቀላቅሎ እንደአጼ ዮሐንስ ዘመን በአንድ ላይ ይተዳደር ነበር፤
እአአ ከ1961 እስከ1993 ኤርትራ አንድ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገር ሆኖ ነበር፤
እአአ በ1991 ሻቢያና ወያኔ በተቀናጀ ጦር የደርግን የጦር ኃይል ጥሰው ኢትዮጵያን በሙሉ ኤርትራንም ጭምር ተቆጣጠሩ፤
ኤርትራን በሚመለከት ወያኔ የመጀመሪያውን ብሔራዊ ስሕተት ፈጸመ፤ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ አገር እንዲሆን አደረገ፤
ገና አሥር ዓመታት እንኳን ሳይሞላ እአአ በ1998 ሻቢያና ወያኔ በድንበር ጦርነት ተፋልመው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አልቀዋል፤ ጦሱ አሁንም አልበረደም፤
በዚህ ጦርነት ኤርትራ ልዩና ከኢትዮጵያ ጋር የታሪክም ሆነ ሌላ ግንኙነት ካልነበራቸው አገሮች ጋር ተፈረጀ፤
የኤርትራ ሕዝብ አንኳን ለቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና ለትግራይ ሕዘብም ባዕድ እንደሆነ ታወጀ፤
የኤርትራ ሕዝብ ባዕድ ብቻ ሳይሆን ጠላትም ሆነ፤

ዛሬ ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ

ዛሬ ኢትዮጵያ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይና ኢጣልያ ዙሪያዋን ከብበው አፍነዋት እንደነበረው ዘመን አሁንም ምንም የባሕር መፈናፈኛ ሳይኖራት የተቆለፈባት አገር ሆናለች፤ ከትግራይ ጋር የኢትዮጵያ ታሪክ መካነ ልደት የሚሆነው ኤርትራ ዛሬ በባዕድነትና በጠላትነት ተፈርጇል፤ ለብዙ ሺህ ዓመታት አብሮ በመኖርና በመጋባት የተዛመደውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በፋሺስት ኢጣልያ የወረራ ዘመናት (ከ1928-1933 ዓ.ም.) እንደነበረው በጎሣና በቋንቋ ተከፋፍሎ እርስበርሱ ለመተላለቅ እየተዘጋጀ ነው፤ ኢጣልያ በአምስት ዓመት የግዛት ዘመኑ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመበታተን ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም ነበር፤ ወያኔ ያንኑ ኢትዮጵያን በጎሣና ቋንቋ የመበታተኑን ሙከራ ለአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሞከረ፡፡

እውቀትም፣ እምነትም አብሮ ሲከዳ ሰው የሚንቀሳቀሰው እንደእንስሳ በእውር-ድንብሩ ነው፤ ያለፉት አርባ ዓመትት፣ በተለይም ያለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ በእውር-ድንበር ስተመራ ቆይታለች፤ ቆይታለች ከማለት እዚህ ደርሳለች ማለቱ ሳይሻል አይቀርም፤ የቁልቁለቱ ተዳፋት እየጨመረ ሲሄድ የት እንደሚያደርሳት ገና በውል አናውቅም፤ መቼም ተለይቷት የማያውቀው የእግዚአብሔር ድጋፍ የአባቶቻችንን ወኔ በዛሬ ወጣቶች ውስጥ አስርጾ፣ በያለበት የሚታየውን የጸብ ዝንባሌ ወደፍቅርና ስምምነት ለውጦ፣ የፈይሳ ለሊሳን በጎ ማኅበረሰባዊ ግንዛቤ አስጨብጦ ተአምር እናይ ይሆናል፤ ለዚያ ብቁ ያድርገን!

የትግራይ ሕዝብ ያለበት ሁኔታ

ዛሬ የትግራይ ክልል የሚባለው ከመጀመሪያ አስከመጨረሻ ከባድ የአስተሳሰብ ስሕተት የተጠናወተው አመራር ያለው ነው፤ የሚከተሉትን የማያስፈልጉ እክሎች ለትግራይ ሕዝብ ፈጥሮአል፡–

የጎንደርንና የወሎንም፣ የአፋርንም መሬት ወደትግራይ ማካተቱ ኤርትራ ደጀን ይሆናል በሚል እሳቤ የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም፤
ከኤርትራ ጋር ግጭት፣ ከዚያም ጦርነት የተካሄደው የኢትዮጵያን ኃይል በመተማመን ነበር፤
ሁሉም እንደሚያውቀው ውጤቱ ኤርትራን ባዕድና ጠላት አድርጎ በጦርነት ማዋረድና ከአሜሪካ ጋር በመተባበር ኤርትራን ሽብርተኛ በማድረግ ማዕቀብ እንዲጣልበት አድርጎ በማደህየት የበላይነትን ለማረጋገጥ ነበር፤
የወያኔ አገዛዝ ኃላፊነት የጎደለው (ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች) በሚዘገንን ጭካኔ የታጀበ ሆኖ በሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ በመሻሻል ፋንታ እየተባባሰና እየከፋ በመሄዱ ዛሬ ሰላማዊ ዓመጽ ወደእርስበርስ ጦርነት ለመሸጋገር ተቃርቧል፤
በዚህም የተነሣ ትግራይ በሁለት ሆን ተብሎ ወያኔ ጠላት ባደረጋቸው ሕዝቦች መሀከል ተጥዶ እንደገና ዳቦ እሳት እስኪቀጣጠልበት እየጠበቀ ነው፤

ትግራይ በሰሜን በኩል ‹በባዕድ ጠላት› ታጠረ፤ ለትግራይ ሕዝብ በማናቸውም መመዘኛ የተፈጥሮ ዝምድና ያላቸው የኤርትራ ተወላጆች ባዕድና ጠላት በመደረጋቸው የኤርትራንም ሆነ የትግራይን ሕዝብ የሚጎዳ ነበረ፤ በዚህ ባበቃ!

የትግራይ ሕዝብ በችግርም ይሁን በደስታ በስተደቡብ በጎንደርና በወሎ፣ በአፋርም ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር በጣም የቀረበ ግንኑነት ነበረው፤ የወያኔ አመራር ግን ልባቸው ያረፈው በጎንደሬዎቹ፣ በወሎዬዎቹና በአፋሮቹ ላይ ሳይሆን በመሬታቸው ላይ ነበር፤ ስለዚህም ከጎንደርም፣ ከወሎም፣ ከአፋርም መሬት እየቆራረሱ ወደትግራይ ግዛት ጨመሩ፤ በዚህ የወራሪነት ተግባር ወያኔ በትግራይ በስተሰሜን የፈጠረውን ጠላት ረስቶ በስተደቡብ ደግሞ ከጎንደር፣ ከወሎና ከአፋር ጋር ለትግራይ ሌላ የጠላት ቀጣና ፈጠረ፤

እንግዲህ አሁን የትግራይ ሕዝብ የሚገኘው በሰሜን በኤርትራ ‹‹የጠላት አጥር፣›› በደቡብ ደግሞ በጎንደር፣ በወሎና በአፋር ‹‹የጠላት አጥር›› ተከቦ መውጫ በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ነው፤ ይህንን ሁኔታ የፈጠረው ወያኔ ነው፤ የትግራይን ሕዝብ መውጫ ቀዳዳ በማሳጣት በአጥሩ ውስጥ ጠርንፎ በመያዝ የማይነጥፍ የታዛዥ አገልጋዮች ምንጭ ለማድረግ ነው፤ ወያኔ የራሱን የሥልጣን ጥም ለማርካት ሲል ብቻ በኢጣልያ አገዛዝም ጊዜ ቢሆን ከኤርትራ ሕዝብ ጋር የነበረውን ዝምድና ጠብቆ የኖረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ (የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ) አጣልቶና ለያይቶ ጠላት አድርጎ ኢትዮጵያን የባሕር ወደብ የሌላት አገር አደረጋት፤ ከአንድ መቶ ዓመት በፊት የተንቤኑ ራስ አሉላ ከኢጣልያ ጋር ያለማቋረጥ እየተፋለሙ በትግራይና በኤርትራ ሕዝብ ጀግንነትና መስዋእት ተከብሮ የቆየውን ኢትዮጵያዊነት የባንዳ ልጆች ለወጡት፤ የትግራይ ሕዝብ የአባቶቹን መስዋእትነት ረስቶ የባንዳዎች ተልእኮ አስፈጻሚ ተደረገ፡፡

map-i2
ወያኔ ትግራይን ከተቆጣጠረ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የትግራይ ሕዝብ በአጠቃላይ ያገኘውን ጥቅምና የኑሮ መሻሻል — እያንዳንዱ አባወራ ራሱንና ቤተሰቡን በየዕለቱ በተሻለ ሁኔታ መመገብ፣ ማልበስ፣ የተሻለ መኖሪያ ቤት፣ የተሻለ የጤና አጠባበቅና ትምህርት … አግኝቷል ወይ? ወያኔ ያለማቋረጥ ስሐተትን መፈጸም እንጂ ስሕተትን ማረም የባሕርዩ አይደለም፤ ስለዚህም መጀመሪያ በትግራይ ዙሪያ የፈጠረውን ‹‹የጠላት አጥር›› (ካርታ አንድ) ያሻሻለ መስሎት ትልቁ ትግራይ የሚል ሌላ የበለጠ ሰሕተት ለመሥራት እየተንደረደረ ነበር (ካርታ ሁለት)፤ እንደዚህ ያሉ የእብጠት ሕመሞች ሁሉ ለሞት የሚዳርጉ መሆናቸውን የሂትለርም የዚያድ ባሬም ታሪኮች ያስተምሩናል፤ የሂትለር ጀርመን ለሁለት ተከፍሎ ከብዙ ዓመታት በኋላ ጀርመን እንደገና አንድ ሆኗል፤ የዚያድ ባሬ ሶማልያ ክፉኛ ተከፋፈሎ እስከዛሬ በትርምስ ውስጥ ይገኛል፤ የወያኔ የማሰብ ችግር መገለጫው የሚሆነው መጀመሪያውንና ትንሹን ስሕተት በሁለተኛና በባሰ ስሕተት ‹ለማረም› መሰናዳቱ ነው፤ ስለዚህም ለትግራይ ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም እንደተባለው ሆኖበታል፡፡መፍትሔው ምንድን ነው?

ችግሩን በትክክል ከተረዳነው መፍትሔው አይጠፋም፤ ችግሮቹ ሁለት ናቸው፤ ሁለት ቢመስሉም አንድ ናቸው፤ የተወሳሰቡና የተቆላለፉ ናቸው፤ ገነጣጥለን ስናያቸው አንዱ ችግር የትግራይ ነው፤ አንደኛው ደሞ የኢትዮጵያ ነው፤ ሁሌም የትግራይ ችግር የአትዮጵያ ችግር ነው፤ የኢትዮጵያ ችግር የትግራይ ችግር ነው፤ በበጎም ሆነ በክፉ ትግራይን ነክቶ ኢትዮጵያን ሳይነካ የቀረ ነገር የለም፤ አሁን በአለንበት ዘመን ትግራይን ወጥሮ ይዞ ኢትዮጵያን የጎሣዎች መንደሮች ስብስብ ያደረገ ወያኔ ነው፤ ወያኔ ትግራይን በጎሣ ተብትቦ ከኢትዮጵያ ጋር በቅራኔ ጠምዶ ትግራይን በኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያን በትግራይ ቀፍድዶ እየተቆጣጠረ ሁለቱንም አስማምቶ ሳይሆን ለያይቶ ለመግዛት እየሞከረ ነው፤ ዛሬም እንደበፊቱ ኢትዮጵያን ለውርደት ያበቃት ትግራይን ለውርደት ያበቃው ሕመም ነው፤ ትግራይ ሳይፈወስ ኢትዮጵያ ትፈወሳለች ብዬ አላስብም፤ አስቸጋሪው ጥያቄ ኢትዮጵያን በትግራይ ገመድ፣ ትግራይን በኢትዮጵያ ሰንሰለት አስሮ የያዘው ወያኔ ገመድና ሰንሰለቱን እንዲበጥስና ሁለቱም ነጻ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? ወይም ትግራይንም ሆነ ኢትዮጵያን ሳይጎዳ ገመዱንና ሰንሰለቱን መበጠስ የሚችል ሌላ ማን ነው?የሚል ነው፡፡

mapii

ብዙ ሰዎች ኢትዮጵያን የገጠማት ችግር የተወሳሰበና የተቆላለፈ መሆኑን የተረዱ አይመስለኝም፤ ይህንን ካልተረዱ ወደመፍትሔው ለመሄድ የሚቻል አይመስለኝም፤ የዋናው መፍትሔ ቁልፍ በትግራይ ተወላጆች እጅ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ተወላጆች ግምባር-ቀደም ተነሣሽነት ያልተጀመረ የኢትዮጵያ ትግል ውጤቱ እንኳን ኢትዮጵያንና ትግራይንም አያድንም፤ የቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድ ላይ ወያኔን ቢቃወም ወያኔ በቀላሉ የጎሣ ጦርነት ያደርገዋል፤ ለነገሩ አሁንም ጀምሮታል፤ ትግራይ በግንባር-ቀደምነት ከገባበት ግን ዓመጹ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሆናል፤ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ (ትግራይን ጨምሮ) ትግል መግጠም አለበት፤ ይህንን ማድረግ አይችልምና ይሸነፋል፤ ይህ አባባል በብዙ ጎሣዎች ኩራት ላይ ቀዝቃዛ ውሀ መቸለስ መስሎ ሊታይ ይችላል፤ በአንጻሩም የትግራይን ጎሠኞች ልባቸውን የሚያሳብጥ መስሎ ሊታይ ይችላል፤ ጎሣዎቻቸውን በጤናማ ኢትዮጵያ ውስጥ ማየት የማይችሉ ሰዎች በትርምስ ውስጥ ባለች ኢትዮጵያ ውስጥ የጎሣዎች ሰላም ሊኖር እንደማይችል ራሳቸውን ቢያሳምኑ ከብዙ የአስተሳሰብ ውደቀት ይድናሉ፤ አሁን ኢትዮጵያን የገጠማት ችግር ይህ ነው፤ ዋናው ጥያቄ ይህንን ችግር እንዴት ልንፈታውና የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውንም ሕዝብ ከእልቂት ማዳን እንዴት ይቻላል? የሚል ነው፡፡

ወያኔ የጀመረው ለትግራይ ሕዝብ ጠላትን የማራባት ዘመቻ የትግራይን ሕዝብ ያጠፋዋል፤ ይህንን ሳንጠራጠር ልንቀበለው ይገባናል፤ ብንደብቀው አይጠቅመንም፤ ስለዚህ የመጀመሪያው ደረጃ መፍትሔ የጠላትነት እሳት እንዳይቀጣጠልና ትግራይን እንዳይበላ መከላከል ነው፤ ይህንን የመጀመሪያ ደረጃ መፍትሔ ለመጀመር የትግራይ ሕዝብ ግምባር ቀዳሚ መሆን ያለበት ይመስለኛል፤ የገጠመውን የተቆላለፈ ችግር የትግራይ ሕዝብ በትግሬነት እፈታዋለሁ ብሎ ከተነሣ ያባብሰዋል እንጂ በጭራሽ ሊፈታው እንደማይችል መቀበል የትግሉ መነሻ ይሆናል፤ ከዚህም ጋር ወያኔ ትግራይን ድሪቶ በማድረግ ከዚያም ከዚህም መሬት እየቀነጫጨበ በማስገባት ትግራይን አሳብጦ ከጎረቤቶች ሁሉ ጋር ለማጣላት የሚያደርገውን አጉል ቂልነት መቃወም ግዴታቸው እንዲሆን በበጎ ፈቃድ ቢወስኑ ከብዙ ችግሮች የሚድኑ ያመስለኛል፤ ወደትግራይ እሳቱ ሳይቀጣጠል የትግራይ ሕዝብ ነቅቶ እሳቱን ለማዳፈን መዘጋጀት ያስፈልገዋል፤ ለዚህ ሁለት ምክንያቶች አሉ፤ አንደኛ የችግሩ ፈጣሪ የሆነው ወያኔ ቤቱና ምሽጉ ያደረገው ትግራይን ስለሆነ ለወያኔ የተቃጣው ሁሉ ትግራይ ላይ የሚያርፍ ነው፤ ስለዚህም የሚቀጣጠለው እሳት በቅድሚያ የሚበላው የትግራይን ሕዝብን መሆኑ ሁለተኛው ምክንያት ይሆናል፤ ወያኔ ሆነ ብሎ በትግሬነትና በወያኔነት መሀከል ያለውን ልዩነት አፍርሶ ትግሬንና ወያኔን አንድ አድርጎ በማቅረብ የችግሩን ፈጣሪና የችግሩን ገፈት ቀማሽ አንድ ለማድረግ እየሞከረ መሆኑ ነው፤ ይህንን ሀሳብ የትግራይን ሕዝብ ለመከፋፈል የታቀደ የፖሊቲካ ስልት አድርጎ ለመውሰድ ይቻላል፤ ግን የትግራይን ሕዝብ መከፋፈል ለኢትዮጵያ ምን የፖሊቲካ ትርፍ ያስገኛል?

ችግር ፈጣሪውን ወያኔንና የችግሩን ዋና ሰለባ የሚሆነውን የትግራይ ሕዝብ አንድ ማድረጉ የሚያስከትለውን ለትውልድ የሚተላለፍ ችግር አስቀድሞ አለማየት በጣም አደገኛ ይሆናል፤ ይህ መንገድ ለትግራይ ሕዝብ የረጅም ጊዜ ጉዳት እንደሚያመጣ መረዳት የሚያስቸግር አይመስለኝም፤ መመለስ የማይቻልበት የጥፋት መንገድ ነው፤ ኢትዮጵያ ያለትግራይ ከሲታ ሆና መኖር ትችል ይሆናል፤ ትግራይ ያለኢትዮጵያ ከሲታ ሆኖ መኖር ይችላል? ችግር የሚፈታው ችግሩን አውቀው ሲጋፈጡት ብቻ ነው፡፡

የችግሩ ሰንኮፍ

ወያኔ ያለልፋት በኢትዮጵያዊነት ሊያገኝ የሚችለውን ሁሉ በብቸኛነት ባለቤት ለመሆን ተመኘ፤

የአገሩን ሥልጣን የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
የአገሩን ሀብት (መሬትና ማዕድን፣ ገንዘብ) የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱን የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
የጦር ኃይሉንና ፌዴራል ፖሊስን የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
የአግዓዚን ጦር የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
ፍርድ ቤቶችን የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
ትግራይን የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
ወልቃይት-ጸገዴን የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
ከወሎ የቀማውን መሬት የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
ከአፋር የቀማውን መሬት የራሱ፣ የግሉ አደረገ፤
… ወዘተ.

በእርግጥ ወያኔ ይህን ሁሉ ያደረገው ብቻውን አይደለም፤ በግድም ይሁን በውድ ተባባሪ የሆኑለት ወያኔ ራሱ የፈጠራቸው ድርጅቶች ነበሩ፤ በሕግ ባይሆንም በተግባር በሕወሀት ስር የተዋቀሩትና ኢሕአዴግ በሚል መጠሪያ የተጠቃለሉት የጎሣ ቡድኖች የሚከተሉት ናቸው፤ አምስት ክልሎች (የአፋር፣ የኦጋዴን፣ የጋምቤላ የቤኒ ሻንጉል-ጉሙዝና የሀረሪ) በገዢው ቡድን አልታቀፉም፤ ማን እንዳቀፋቸው የታወቀ ነገር የለም፤

ብአዴን፣ ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፤
ኦሕዴድ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣
ደሕዴድ፣ የደቡብ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣
አሁን እንደሚታየው በአማራና በኦሮምያ ክልሎች ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ ያለመተባበር አድማ ስላነሣ በጦርና በፌዴራል ፖሊስ ኃይል ስር ወድቀው የክልሉ አስተዳደር አቅመ-ቢስ ሆኗል፤ በደቡብም ቢሆን በኮንሶ ያለው ተመሳሳይ የሕዝብ ንቅናቄ ብዙ ችግሮችን እየፈጠረ በመሆኑ ወሬው ዓለምን አዳርሷል፤ ከነዚህ ሁሉ ተለይቶ ደልቶትም ይሁን ከፍቶት ሳይታወቅ ጸጥ በማለቱ ሰላም የሰፈነበት የሚመስለው ትግራይ ነው፤ እንዲህ በመሆኑም ትግራይን በአጠቃላይ ከወያኔ ጋር የተሰለፈ አስመስሎ ያሳየዋል፤ የትግራይ ሕዝብ በሙሉ ተሰንጎ በጉልበት ተይዞ ነው እንዳይባል ብዙ ትግሬዎች በነጻነት ሀሳባቸውንና ለወያኔ አገዛዝ ያላቸውን ተቃውሞ የሚገልጹ አሉ፤ ወይም ደግሞ ብዙዎቹ በጉልበት ሳይሆን በባህላዊ ጫና (የፈረንጅ ፈላስፋዎች the tyranny of custom በሚሉት) እየተገደዱ ይሆናል፤ ለማናቸውም ትክክለኛ ምክንያቱን ባናውቅም ወያኔ አብዛኛውን የትግራይ ሕዝብ በጫማው ስር አድርጎ እንደሚቆጣጠረው የማይካድ ነው፡፡

በኦሮምያና በአማራ ክልሎች ብቻ ከስድሳ አምስት አስከሰባ ከመቶ የሚሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለበት ነው፤ ደቡብ ከአሥር ከመቶ በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚኖርበት ነው፤ እንግዲህ በሦስቱ ክልሎች ብቻ በትንሹ ሰባ አምስት ከመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይኖራል ማለት ነው፤ ይህ ሦስት ሩብ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚኖርበት መሬት የቆዳ ስፋትም በጣም ሰፊ ነው፤ እንግዲህ የትግራይ ሕዝብ ይህንን ያህሉን የኢትዮጵያ ሕዝብ አስቀይሞ ከወያኔ ጋር መሰለፉ ይጠቅመዋል ማለት በጣም ይከብዳል፤ በካርታ አንድ የሚታየውን ሁኔታ ሁሌም በዓይነ-አእምሮአችን ልናየው ይገባል፤ ለአሁኑም ይሁን ለወደፊት፣ በጦርነትም ሆነ በሰላም፣ በደሀነትም ሆነ በብልጽግና የትግራይን ሕዝብ የሚያዋጣው ከሰባ አምስት ከመቶ ከሚሆነው ከወገኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መቆም ነው፤ ለእኔ ይህ ክርክር ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም፡፡

የትግራይ ሕዝብ አስቸጋሪ ምርጫ

ምርጫ አንድ፡ የትግራይ ሕዝብ እንደጥንቱ እንደጠዋቱ ታሪኩን ይዞ በኢትዮጵያዊነቱ ይቀጥላል፤ በኢትዮጵያዊነት ታሪኩ በግምባር-ቀደም ተሰልፎ በፖሊቲካም ሆነ በመንፈሳዊ ጸጋው የኢትዮጵያዊነት ግዴታውን ይወጣል፤ ይህ ምርጫ የኢትዮጵያዊነት ግዴታ ነው፤ ይህ ምርጫ ታሪካዊ ግዴታ ነው፤ ይህ ምርጫ የዜግነት ግዴታን ከጎሣ ግዴታ ማስቀደም ነው፤ ይህ ምርጫ ከጨለማው ዘመን ወጥቶ ወደሃያ አንደኛው ምዕተ-ዓመት መሸጋገር ነው፤ ከሁሉም በላይ ይህ ምርጫ የሰፊ ሀብት ባለቤትና የመቶ ሚልዮን ዜጎች ማኅበረሰብ አባል ያደርጋል፡፡
ኢትዮጵያ የትግራይ ነች፤ ስለዚህም ትግራይ ኢትዮጵያን ነች፤ ሁለቱ አይለያዩም፤ ይህንን ወያኔም በሚገባ የተረዳው ይመስላል፤ አለዚያ ከጎንደር፣ ከላስታም፣ ከራያም፣ ከጎንደርም … የሚለቃቅመው ለምንድን ነው!

ምርጫ ሁለት፡ የትግራይ ሕዝብ የወያኔ መሣሪያ እንደሆነ ይቀጥላል፤ ይህ ሲሆን ትግራይ በመሠረቱ ከኢትዮጵያ ይገነጠላል ማለት ነው፤ በትግራይ ዙሪያ ኤርትራ በሰሜን፣ በደቡብ ደግሞ ጎንደር፣ ወሎና አፋር ይገኛሉ፤ ወያኔ ሆን ብሎ ትግራይን ከኤርትራ፣ ከጎንደር፣ ከወሎና ከአፋር ጋር አጋጭቶ ደም እንዲቃቡ አድርጓል፤ (በትግራይ ዙሪያ ያሉትን ብቻ ለማንሳት ነው እንጂ ከጂጂጋ እስከጋምቤላ፣ ከወሎ እሰከሲዳሞ ቦረና የግፍ ጠባሳዎች አሉ፤) ስለዚህም ትግራይ በወያኔ ስር ሆኖ ከአነዚህ ከከበቡትና በጠላትነት ከተፋጠጡት ሕዝቦች ጋር ዘለዓለም ሲቆራቆዝ ሊኖር ነው፤ ዙሪያውን ካሉት ሕዝቦች ሁሉ ጋር መቆራቆዝ የትግራይን ሕዝብ ያደኸያል፤ የትግራይ ሕዝብ መሸሻ ስለሌለው በአጥንቱ እየሄደ የወያኔ አገልጋይ ይሆናል፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ በምሥራቅ በአሰብ በኩል፣ በምዕራብ በጎንደር በኩል የልማትና የጋራ ደኅንነታቸውን ይመራሉ፤
የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያም ሆነ በኤርትራ በሚካሄደው ልማት ተሳታፊ አይሆንም፤ (ካርታ አንድ) የሩቅም ሆኑ የቅርብ ወዳጆች ካሉ በመሬትም ሆነ በዓየር ግንኙነት ማድረግ ከባድና አስቸጋሪ ይሆናል፤ ትግራይ በወያኔ ጫና ከኢትዮጵያ ሲለይ ኢትዮጵያ ታንሳለች፤ ትግራይ ደግሞ ይበልጥ አንሶ ኢምንት ይሆናል፤ በሌላ በኩል ሲታይ የትግራይ መለየት ኢትዮጵያዊነትን ሬሳ ሲያደርገው ትግሬነትን የሬሳ ተሸካሚ ያደርገዋል፤ ኢትዮጵያዊነት ያለነፍስ፣ ትግሬነት ያለአካል ጎረቤቶች ይሆናሉ! ነፍስና ሥጋ እየተፈላለጉ ምጽአትን ይጠብቃሉ፡፡

የወያኔ አስቸጋሪ ምርጫ

ወያኔ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች ብዙ ሀብት እንዳለው የታወቀ ነው፤ ዶላርና ወርቅ በሻንጣ ሲጓዝ ዓለም በሙሉ አይቷል፤ አንድ የእንግሊዝ አገር ዳኛ ምነው በአገራችሁ ባንክ የለም እንዴ! ብሎ ተገርሟል፤ ይህ የወያኔ ሀብት ምንጩ ሲደርቅ እየመነመነ ይደርቃል፤ በውጭ አገር ባንኮች የተቀመጠውም በግለሰቦች ስም ስለሆነ የድርጅቱ ድርሻ ትንሽ ይሆናል፤ የወያኔ አመራር ያከማቸው ገንዘብ ለልጆቻቸውና ለልጅ ልጆቻቸው በውጭ አገሮች የተመቸ ኑሮ እንዲኖሩበት የታለመ እንጂ የትግራይን ሕዝብ ለማበልጸግ አይደለም፤ አመራሩ ሁሉ ያከማቸው ገንዘብ አንድ ላይ ቢሆንም ለማያቋርጥ ጦርነት፣ ለትግራይ ልማትና ለአመራሩ ቤተሰብ መኖሪያ እየተከፋፈለ ብዙ አይቆይም፤ ከዚያ በኋላ እያፈጠጠ የሚመጣውን ችግር የትግራይ ሕዝብ ማየት ያለበት ዛሬ ነው፡፡

ወያኔ በአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ ብዙ ጥፋቶችን መፈጸሙ አይካድም፤ ምናልባት ፈረንጆች እንደሚሉት (The road to hell is paved with good intentions.) ወደገሀነመ እሳት የሚወስደው መንገድ (በአስፋልት ፋንታ) በጎ አስተያየቶች የተነጠፉበት ነው ማለት ነው፤ በሌላ አነጋገር ሰዎች ወደገሀነመ እሳት የሚገቡት ጥሩ እንሠራለን እያሉ በፈጸሙት ጥፋት ነው ማለት ነው፤ ወይም ደግሞ ወያኔ በጎረምሳነት ስሜት የአክሱም ጽዮንን ኪዳን በአጉል ማርክሳዊ ፍልስፍና በመለወጣቸው ለወያኔም፣ ለትግራይ ሕዝብም፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብም በአጠቃላይ የሚጠቅም መስሏቸው የፈጸሙት የጉርምስና ጥፋት ነው፤ ወይም ደግሞ ደርግን ለማውረድ በፈለጉ ኃይሎች እኩይ ምክር ተጠምደው ሊሆን ይችላል፤ በዚህ ሁሉ ምክንያት የወያኔን ጥፋት መከርከም ይቻል ይሆናል፤ ይህ የሚሆነው በሥልጣን ጉዳይ ብቻ ነው፡፡

ነገር ግን በወያኔ በኩል ሆነን ስናየው ከሥልጣንም ሌላ በጣም አስቸጋሪ ምርጫ ይገጥመዋል፤ ብዙዎቹ ባለሚልዮን ወይም ባለቢልዮን ዶላር ሀብታሞች ሆነዋል ይባላል፤ ይህንን ከኢትዮጵያ የተዘረፈ ሀብት መመለስ ሥልጣንን ለሕዝብ የማስረከቡን ያህል ቀላል አይመስለኝም፤ ቢሆንም በሁለት በኩል በጎ ፈቃድ ከአለ መፍትሔ የማይገኝለት ችግር አይኖርም፤ የደቡብ አፍሪካ ግፈኞች ነጮች ልክ እንደወያኔ በሥልጣንም በሀብትም ያበጡ ነበሩ፤ መፍትሔ አግኝተውለታል፤ በጎ ፈቃዱ ከአለን እኛም አያቅተንም፡፡

ፍትሐዊ የሆነ መፍትሔ ላይ ለመድረስ ለወያኔ መንፈሳዊ ወኔ ያስፈልገዋል፤ ይህ እስካሁን ያልታየባቸው ቢሆንም ከየትም ፈልገው ማግኘት አለባቸው፤ የደቡብ አፍሪካ መፍትሔ የተገኘው ብዙ ጊዜ ስሙ ከማይነሣው ከደ ክላርክ ነው፤ ያለደ ክላርክ የመንፈሳዊ ወኔ የደቡብ አፍሪካ ችግር አይፈታም ነበር፤ የደ ክላርክ ዓይነት ሰው በወያኔ ድርጅት ውስጥ መገኘቱ አጠራጣሪ ነው፤ ሆኖም የወያኔ መሪዎች የጉልበተኛነትን ጠባይ አውልቀው ጥለው ለእርቀ-ሰላም የሚያዘጋጃቸውን መንገድ ቢመርጡ ለራሳቸውም፣ ለትግራይ ሕዝብም፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብም፣ ለአፍሪካ ቀንድ ሕዝብም ትልቅ የሰላምና የልማት በርን ይከፍታሉ፤ በጉልበተኛነት ያላገኙትን ክብር በሰላም ያገኙታል፤ ኢትዮጵያ በፖሊቲካም ሆነ በመንፈሳዊ ታሪክዋ የነበራትን የሽምግልና የበላይነት የአፍሪካ ቀንድን ሕዝቦች ለመምራት ትችላለች፡፡

ወደዚህ ዓላማ ለመድረስ ወያኔ የሚከተሉትን መነሻ ሀሳቦች ተግባራዊ እንዲያደርግ ይጠበቅበታል፡—

ነጻ የተወካዮች ምክር ቤት ተቋቁሞ ሙሉ ሥልጣን ይረከባል፤
በስሩና በእሱ ተቆጣጣሪነት ከሁለት ዓመታት በላይ የማይቆይ የባለአደራ መንግሥት ያቆማል፤
የባለአደራው መንግሥት የሚቋቋምበትንና የሚሠራበትን ሕጎች ያወጣል፤
የወያኔ ባለሥልጣኖች ከሂሳብ አዋቂዎችና ከሕግ አዋቂዎች ጋር ሆነው የንብረታቸውን ጉዳይ ያጣራሉ፤ በዚህ ተግባር ላይ ከዓለም ባንክና ከተባበሩት መንግሥታት አግባብ ያላቸው ድርጅቶች፣ ከአሜሪካ፣ ከብሪታንያ፣ ከጀርመን፣ ከጃፓንና ከህንድ የተውጣጡ ባለሙያዎች እንዲማክሩ መጠየቅ ይቻላል፤
ተጣርቶ የተገኘው ሀብት (የማይንቀሳቀስ ንብረትን ጨምሮ) እንደሚከተለው ሊደለደል ይቻላል፡– ይህ መነጋገሪያ ሀሳብ ብቻ ነው፡–
ለትግራይ ልማት፤
ለሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች ልማት፤
ለትግራይ የጦር ጉዳተኞች፤ ለእያንዳንዳቸው መጠነኛ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣
ለትግራይ የሟች ቤተሰቦች፤ ለእያንዳንዳቸው መጠነኛ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣
ለሌሎች ኢት. የሟች ቤተሰቦች፤ ለእያንዳንዳቸው መጠነኛ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣
ለሌሎች ኢትዮጵያውያን የጦር ጉዳተኞች፤ ለእያንዳንዳቸው መጠነኛ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣
ለወያኔ መሪዎች፤ ለመኖሪያ የሚያስፈልጋቸውን ጡረታ መስጠት፤
የወያኔ መሪዎችና ካድሬዎች (የቅርብ አገልጋዮች) ለመጀመሪያው የክልልም ሆነ አገር-አቀፍ ምርጫ እንዳይሳተፉ በሕግ ገደብ ይጣልባቸዋል፤

መደምደሚያ

ይህ የሰላማዊ ለውጥ ወያኔን ከትግራይ ሕዝብ ጋር፣ ከቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር፣ ከዓለም ማኅበረሰብ ጋር ያስታርቀዋል፤ በተጨማሪም ሰላማዊ እርቁ የወያኔ መሪዎች በውጭ አገሮች እንደልባቸው እንዲዘዋወሩ የዜግነት መብቶቻቸው ሁሉ የሚከበሩበትን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

ዓላማችን ያለፈውን ስሕተት በማረም የሚቀጥለውን ጉዞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ አብሮ በአንድነት ለመተለምና ከሁሉም በላይ ትግራይ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ ምልክት ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ ነው፤ ደብረ ቢዘንን በማጣት ደህይተናል፤ አሁን ደግሞ አክሱም ጽዮንንና ደብረ ዳሞን በማጣት አንደኸይም፤ የያሬድን ዜማ በምን እንለውጠዋለን? ትግራይ የኢትዮጵያ መካነ ልደት ነው፤ ትግራይ የኢትዮጵያ ክብርና ሞገስ ነው፤ ስለዚህም ትግራይን በወያኔ ክህደትና ሸር አናረክሰውም፤ ወያኔን ከርክሰቱ ልንመልሰው እንሞክራለን እንጂ ወያኔ ርክሰቱን በትግራይ ላይ እንዲያጋባ ልንፈቅድለት አንችልም፡፡

በአለንበት የታሪክ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ሁለት ከባድ ምርጫዎች ገጥመውታል፤ አንዱ ምርጫ በኢትዮጵያዊነትና በትግሬነት መሀከል ነው፤ በመሠረቱ ኢትዮጵያዊነትና ትግሬነት አንድ ስለሆኑ አንዱን መርጦ ሌላውን መተው አይቻልም፤ ነገር ግን በአለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ወያኔነት ትግራይነትን ስለሸፈነው ወይም ስለበከለው፣ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያዊነትንና ትግሬነትን እያራራቃቸው ነው፤ በዚህም ምክንያት የትግራይ ኢትዮጵያዊነትን የበከለውን የወያኔነት አረመኔነት በአክሱም ጽዮን፣ በደብረ ዳሞና በሌሎችም ቅዱሳን ገዳማትና አድባራት ማጽዳት ያስፈልገዋል፤ ለትግራይ ሕዝብ ከባድ ምርጫ የሚሆነው ወያኔን አቅፎ ኢትዮጵያዊነቱን መጠበቅና ማደስ ነው፤ የትግራይ ሕዝብ ትግሬነትን ከወያኔ ነጻ ማውጣትና ኢትዮጵያዊነትን ቀዳሚ ስፍራ የማስያዝ ግዴታ አለበት፤ በሌላ አነጋገር የትግራይ ሕዝብ ወይ ወያኔን አርሞና ገርቶ ወይም ወያኔን አውግዞ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መቆም ያስፈልገዋል ማለት ነው፤ ወያኔ ጸረ-ኢትዮጵያዊነት ታሪኩንና አቅዋሙን ይዞ በትግሬነት ተሸፋፍኖ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር መቆም አይችልም፤ የትግራይ ሕዝብም ከወያኔ ጋር ቆሞና የወያኔ ምሽግ ሆኖ ወያኔ በዙሪያው ያጠረለትን የጠላትነት አጥር አልፎ ኑሮውን ለማሻሻል አይችልም፤ እንዲያውም የጦርነት ሜዳ ይሆናል፤ የወያኔ መሪዎች ዛሬም የሚያስቡት ወያኔን በሥልጣን ላይ ለማቆየት የትግራይ ሕዝብ ገና ወደፊት የሚከፍለውን መስዋእትነት ነው፤ ሥዩም መስፍን የሚከተለውን ይላል፡

ከ60 ሺ በላይ ሕይወት ከፍለን ፣ ከዚህ በላይ ሕዝብ ተጎድቶብን ነው ስልጣን ላይ የወጣነው፡፡ ዛሬ ትግራይ ላይ የሚነጣጠረው ነገር ለማንም አይተርፍም ሁላችን በዜሮ ነው የምንወጣው፡፡ ማንም አያተርፍም፡፡ ኢህአድግ መተኪያ የለውም፡፡

‹‹ሁላችንም በዜሮ እንወጣለን፤›› ፉከራ አይደለም፤ የእኩይ መንፈስ የመጠፋፋት ቃል ኪዳን ነው፤ የኢትዮጵያን መሬትና የተፈጥሮ ሀብቱን ለሌሎች ማስረከብ ማለት ነው፤ ይህንን ጤናማ አእምሮ ያስበዋል ለማለት አይቻልም፤ የወያኔ መሪዎች ዛሬም የሚያስቡት የትግራይ ሕዝብን መሣሪያቸው አድርገው ነው፤ የትግራይ ሕዝብ ነጻ ሆኖ የራሱን ውሳኔ መወሰን እንደሚችል አያስቡም፤ የትግራይ ሕዝብ መሪዎቹ በአሜሪካና በአውሮፓ ያካበቱትን ሀብትና ያጠራቀሙትን ገንዘብ የማያውቅ ይመስላቸዋል፤ በመቀሌ ለተሠሩት የባለሥልጣኖች መኖሪያ ሰፈሮች የትግራይ ሕዝብ የሰጣቸውን ስሞች — የሙስና ሰፈር፣ የአፓርቴይድ ሰፈር — አልሰሙም ይሆናል፤ ወይም ቢሰሙም አልገባቸውም ይሆናል፤ ዛሬም ሆነ ነገ የትግራይ ሕዝብ ለወያኔ መሪዎች ግዑዝ መሣሪያ ሆኖ የሚቀጥል አድርገው ይገምቱታል፡፡

ሥዩም መስፍን በሥልጣን ኮርቻው ላይ እንዲቀመጥ የተከፈለው ዋጋ ስድሳ ሺህ የትግራይ ተወላጆች ሕይወት መሆኑንና ከዚያም የበለጠ የትግራይ ሕዝብ ተጎድቶ እንደሆነ ይነግረናል፤ በዚህ አያበቃም፤ በሚቀጥለው ዙር ትግል ‹‹ሁላችንም በዜሮ ነው የምንወጣው›› ሲል ለትግራይ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በአጠቃላይ የደገሰለትን የጥፋት ማዕበል እየነገረን ነው፤ ይህ የመጀመሪያው አይደለም፤ በ1997 ምርጫ ላይም የሩዋንዳውን ‹‹ኢንተርሀምዌይ›› አንሥቶ ነበር፤ ብዙም ሳይቆይ አግዓዚ የሚባለውን የወያኔ ‹‹ኢንተርሀምዌይ››ን አሳየን፤ ዛሬም ለትግራይ ሕዝብ የተደገሰው የጥፋት ማዕበል የወያኔን መሪዎች በሩቁም እንደማይነካቸው ያውቃሉ፤ የትግራይን ሕዝብ በጥፋት ማዕበል ‹‹በዜሮ አስወጥቶ›› እሱ አሜሪካ ወይም አውሮፓ አንዱ ዘንድ ገብቶ የሙጢኝ ይላል፤ ስለዚህ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ከዚህ ከተደገሰለት የጥፋት ማዕበል ለማውጣት ወያኔን እምቢ ብሎ ኢትዮጵያዊነቱን ማጠንከሩ ይጠቅመዋል፡፡

የወያኔ መሪዎች የትግራይን ሕዝብ ይዘው የትግራይንም የኢትዮጵያንም ሕዝብ ለማጠፋፋት ታጥቀው የተነሡ ይመስላል፤ ሌላው የወያኔ መሪ ዓባይ ጸሐዬ የሚከተለውን ይነግረናል፡–

↧
↧

የአማራ ወጣቶችን የሚያስገድሉ 72 ባለሥልጣናትና ደኅንነቶች ተለይተው ታወቁ |ዝርዝራቸውን ይዘናል

$
0
0

ከሙሉቀን ተስፋው

ከሕወሓት መልዕክት እየተቀበሉ ወጣቱን በማሳፈስ እና ጊዚያዊ የፌድራል ፖሊስ እና መከላከያ ኃይል ጊዚያዊ ማዘዥያ እዝ ከመንግሥት በጀት በመመደብ፤ መኪና በማቅረብ እና በማቀናጀት በቀጥታ እየመሩት ያሉ አማራ ነን የሚሉ ባለስልጣናት ተቃወቁ፡፡ የአማራውን ተጋድሎ በሚመሩ የጎበዝ አለቆች ከተባባሪ የአማራ ተወላጅ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የፖሊስ ኃላፊዎች ጋር በመተባበር 72 ሕወሓትና የሕወሓት ቅጥረኛ ባለሥልጣናትና ደኅንነት አባላት በስም ተለይተዋል፡፡

 ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሔር

ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሔር

ጥናቱን ያካሔደው የጎበዝ አለቆች ቡድን ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሔር የተባለችውን የትግራይ ተወላጅና የክልሉ የኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊዋን በቀዳሚ ጠላትነት አስቀምጧል፡፡
ሁለተኛው አቶ ብናልፍ አንዷለም ሲሆን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና ም/ርዕስ መስተዳድር ሲሆን በየቦታው የታሰሩ እና የታጎሩ የአማራ ልጆችን ጉዳይ ይዞ በመምራት እና አስካሁን የታሰሩት ያለምንም መፍትሔ ብርሸለቆና ሰባታሚት ብሎም በየጣቢያው ለሚሰቃዩ ወገኖች ዋናውን ኃላፊነት ድርሻ ወስዷል፡፡

በተጨማሪም አቶ ደሴ አሰሜ፤ የአማራ ክልል አሰተዳደር እና ፀጥታ ጉዳየች ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ አየለ አናውጤ የክልሉ የመረጃ እና ደህንነት ጉዳይ ዋና የስራ ሂደት መሪ፣ አቶ ደሴ ደጀን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር፣ አቶ የማነ ነገሽ የአማራ ክልል አሰተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዩች ቢሮ የመረጃ እና ስምሪት ኮሚቴ አባል ናቸው፡፡

በተለይም በአሁኑ ስዓት በመላው የአማራ ክልል እየተቀጣጠለ ያለውን አመፅ እና ከግብ እንዳይደረስ ሕወሓት አዋቅሮ እያሰራቸው የሚገኙ የክልሉ 72 ባለስልጣናት እንደሚከተለው ይቀርባሉ፡፡

1. ከማነደር ኢሳያስ ገ/ ኪዳን ከብሄራዊ ደህንነት መረጃ
2. አቶ ይርሳው ታምሬ
3. አቶ ብናልፍ አንዷለም
4. አቶ አለምነው መኮንን
5. ዶ/ር ተሾመ ዋለ
6. አቶ ፍርዴ ቸሩ
7. አቶ አወቀ እንየው
8. አቶ አየልኝ ሙሉዓለም
9. አቶ አየነው በላይ
10. አቶ ደሴ አሰሜ
11. አቶ ዘመነ ፀሃይ
12. አቶ ንጉሱ ጥላሁን
13. አቶ ተስፋየ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ገበያልማት ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ፈንታ ደጀን
15. አቶ ደሳለኝ ወዳጀ
16. አቶ በላይ በጤና ቢሮ የወባ መከላከል የስራ ሂደት መሪ
17. አቶ ሃብቴ በትምህርት ቢሮ የአይሲቲ ክፍል ኃላፊ
18. አቶ ማማሩ ጽድቁ
19. ም/ኮሚሽነር ደስየ ደጀን
20. አቶ መኮንን የለውምወሰን የአብቁተ ዋና ዳይሬክተር
21. አቶ መላኩ አለበል የኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ
22. አቶ ምስራቅ የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ስራ አስኪያጅ
23. አቶ ምትኩ የጥረት ኮርፖሬት ምክትል ስራ አስፈፃሚ
24. አቶ ስዩም አዳሙ
25. አቶ ሙሉጌታ ደባሱ
26. አቶ ስዩም አድማሱ
27. አቶ ተፈራ ፈይሳ
28. አቶ ሺፈራው ግብርና ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ
29. አቶ ተስፋየ የልህቀት ማዕከል ኃላፊ
30. አቶ ቴዎድሮስ የቀድሞ ጣና ሃይቅ ትራንስፖርት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረ አሁን መቅደላ ኮንስትራክሽን
31. አቶ ዘላለም ህብስቱ
32. አቶ የማነ ነጋሽ
33. አቶ ጌትነት የገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
34. አቶ ስለሺ ተመስገን
35. አቶ ዘላለም የግብይት ልማት የስራ ሂደት መሪ
36. አቶ ዳንኤል የሆቴሎች ማህበር ፕሬዚደንት
37. አቶ ኃ/ኢየሱስ ፍላቴ
38. አቶ ብርሃኑ የባህል፣ ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ
39. አቶ ላቀ ጥላየ
40. አቶ ሙሃመድ አልማ ምክ/ስራ አስፈፃሚ
41. አቶ አለማየሁ ሞገስ
42. አቶ አጉማስ የከተሞች ልማትና ግንባታ አክስዮን ማህበር ኃላፊ
43. አቶ ደመቀ የከተሞች ልማትና ግንባታ አክስዮን ማህበር ባለሙያ
44. አቶ አሻግሬ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የህፃናት የስራ ሂደት መሪ
45. ዶ/ር ፋንታሁን መንግስቱ
46. አቶ አየለ አናውጤ
47. አቶ ሃብታሙ የርዕሰ መስተዳድሩ ፕሮቶኮል
48. ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሄር
49. ወ/ሮ አበራሽ በክልሉ ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበረች ነባር ታጋይ
50. አቶ ፈለቀ ተሰማ
51. አቶ ጌታ ኪዳነ ማርያም
52. አቶ ገሰሰው ግብርና ሜካናይዜሽን ተመራማሪ
53. አቶ ዳኜ በጤና ቢሮ የሃይጅንና ሳኒቴሽን ባለሙያ
54. አቶ ፈንታው አዋየው
55. ወ/ሮ ዝማም አሰፋ
56. ዶ/ር አምላኩ አስረስ
57. አቶ ደጀኔ ምንልኩ
58. ወ/ሮ ትልቅ ሰው ይታያል
59. አቶ ላቀ አያሌው
60. አቶ ባይህ ጥሩነህ
61. አቶ ጥላሁን የክልል ም/ቤት የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ
62. አቶ ፍስሃ ወ/ሰንበት
63. አቶ ጌታቸው በት/ት ቢሮ የፈተና ኤክስፐርት
64. ዶ/ር ይበልጣል ቢያድጌ
65. አቶ አቃኔ አድማሱ
66. አቶ የኔነህ ስመኝ
67. ኮማንደር ሰይድ የፖሊስ ኮሚሽን
68. አቶ አስናቀ በኢት. ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ኃላፊ
69. አቶ ሙሉጌታ ከግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት
70. አቶ ባየ ከልህቀት ማዕከል ኃላፊ
71. አቶ አምባው አስረስ
72. ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ
የወይዘሮ ገነት ገ/እግዚአብሔርንና የሌሎች የሕወሓት አባላት ዝርዝር መረጃዎችም አብረው ተልከዋል።

↧

የጉራጊኛ ሙዚቃ ድምጻዊው የሕወሓትን የጥበቃ መረቦች አምልጦ ከሃገር ተሰደደ

$
0
0

melaku-bireda
(ዘ-ሐበሻ) “ጉራጌ ተነሳ” የተሰኘውን ነጠላ ዜማውን ከለቀቀ በኋላ በደህንነትች ቤቱ ተበርብሮ ሲፈለግ የቆየው የጉራጊኛ ሙዚቃ አርቲስቱ መላኩ ቢረዳ የደህንነትና የጥበቃ መረቦችን አምልጦ ከሃገር መውጣቱ ተሰማ::

መላኩ ቢረዳ ይህን የትግል ዘፈን ካወጣ በኋላ ደህንነቶች ሲፈልጉት የቆዩ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ቤቱን በሌለበት በርብረውት ነበር:: አርቲስቱ ከሃገር ከወጣ በኋላ የሚከተለውን ምስል ከመል ዕክቱ ጋር አስተላልፏል::

እኔ ደርግን አላውቀውም እኔ የንጉሰ ነገስት አገዛዝም አላውቅም እኔ ያለፈውንም ናፋቂም አይደለሁም እኔ የማውቀው የኢሀዲግ ስርአትን ነው በደንብም አውቀዋለሁ እኔ ሁሉም ብሄር ኢትዮጵያዊ መሆንና ሁሉም ብሄር ሁሉም እምነት ሁሉም ሰው እኩል እንደሆነ ነው ማውቀው እኔ አንዱ ሲጎዳና ሲያዝን ሲሞትና ሲሰቃይም አይቶ እንዳላየ የሚያልፍ ህሊና የለኝም የጉራጌ ተወላጆቾች ከንግድ ቦታቸው ከኑሮአቸው ከህልውናቸው ከመርካቶ ከታይዋን ከዱባይ ተራ ከአትክልት ተራ ከጫረታ ከፎይታ ከጭድ ተራ ተፈናቅለው በየመንገዱም ሲነግዱ ህገ ወጥ ተብለው ሲያሳድዷቸው የመኪና እራት ሲሆኑ ወድቀው ሲሰበሩ በገዛ ሀገራቸው እንደ ሌባ እቃቸው ሲቀሟቸው የቤት ኪራይ የሚከፍሉት አጥተው ሀገራቸው ጠልተው በበረሀ በባህር ሲሰደዱ ሲሞቱ እንደ በግ ሲታረዱ እያየሁ ዝም የሚል ህሊና የለኝም። እኔ በኮንሶ በኦሮሞ በአማራ ባጠቃላይ በኢትዮጵያዊያን እህትና ወንድሞቼ ባሳደግኝና ባሰተማረኝ ህዝብ ላይ ጭቆናና በደል ህልውናውና ክብሩ ሲነካ ዝም የሚል አንደበት የለኝም።እኔ መተኪያ የሌላት አንዷ ኢትዮጵያ ስታዝንና ክብሯ ሲነካ በሀገሬ የሚያስጨክን አእምሮ የለኝም።እኔ ለራሴ ብቻ በልቼና ጠጥቼ ደልቶኝና ተንደላቅቄ ፈጣሪ የሰጠኝ ንፁህ ህሊናዬ ሽጨ መኖር አልፈልግም። ማነው መላኩ ለምትሉኝ እኔ ይሄው ነኝ። የጉራጌ ህዝብ ሆይ እኔም አንተው ነኝ አንተም እኔው ነህ ማንም ሰው ሰላምን ማጣት አይፈልግም ግን ሰላምና ነፃነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዋች ናቸው ያለነፃነት ሰላም ብቻውን ኦናና ባዶ ቤት ነው። አንድ ህዝብ ባገሩ መስራትና መለወጥ ካልቻለ የሚሰራበት ቦታ ከተቀማ ልጆቹን በስደት ካጣ ሰው መኖር እየፈለገ መኖር ካልቻለ አንዱ ላንዱ ማዘንና መራራት መሰብና መስተዋል ካልቻለ የነፃነት ትርጉሙ ምንድን ነው? ነ ፃ ነ ት ቃል ብቻ ሆኖ ከቀረ የአንድ ሀገርና የህዝብ ህልውና ሉአላዊነቱም ጭምር አስጊ ይሆናል እኔ ጨቅላና በዳዴ የሚሄድ አንድ ፍሬ ልጅ ነኝ ፖለቲከኛም አይደለሁም እውቀቱም የለኝም ግን ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራና መመኪያ ሀገራችን እንደሆነች በደንብ አውቃለሁ ኢትዮጵያዊ መባል ስሙ ብቻ ታላቅ ሀብትና ስጦታም መሆኑ በቂ እንደሆነ የጉራጌ ህዝብ ሆይ አንተው ያወረስከኝ አንተው ያስተማርከኝ ውርሴ ይኸው ነው ያወረስከኝን ኢትዮጵያዊነት መከባበርን መተዛዘን መግባባትን ያለበት የወረቀት ብቻ ሳይሆን የተግባር ዲሞክራሲ ነፃነትን የሁሉም ብሄር የሁሉም ህዝብ እኩልነት ሰላም ፍትሀዊ የሆነ አኗኗር የሁሉም አምነት እኩልነት መግባባትና መተሳሰብ መዋደድና መስማማት ያላት ታላቂቷን ኢትዮጵያ እኔም ለተተኪው ትውልድ የማውረስ ግዴታም አለብኝ እኔ ማነው ለሚለኝ እኔ ይኸው ነኝ።

መላኩ ቢረዳ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

↧

ጃኪ ጎሲ እየቀለድክ መሆን አለበት

$
0
0

jackyተሺቲ ደዋኖ ከአርሲ

ሰው የፈለገውን የመሆን መብት አለው:: ስር ዓቱን መደገፍም አለመደገፍም ይችላል:: አርቲስትም ቢሆን ከፈለገ ከገዳዮች ጋር ካልፈለገም ከሕዝብ ጋር መቆም ይችላል:: ግን ዘፋኝ ተነስቶ የሕዝብን አቅጣጫ ማስቀየሪያና መጠቀሚያ ሲሆን ግን ያናድዳል:: ስለዚህም የሚከተለውን ለማለት ወደድኩ::

ዛሬ በአንዳንድ የወያኔ ድረገጾች ላይ የጃኪ ጎሲ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቆ አየሁ:: ትናንት በሊቢያ ወገኖቻቸን ሲገደሉ በነጋታው ነጠላ ዜማ የለቀቀው ጃኪ ዛሬ በኦሮሚኛ አንድ ነጠላ ዜማ ለቀቀ ሲሉኝ በጣም ተደስቼ ዘፈኑን ከፍቼ ተመልከትኩት:: ጃኪ በኦሮሚኛ ዘፈን መስራቱ የሚደነቅ ቢሆንም የኦሮሞ ወጣቶች በየቀኑ እያለቁ እርሱ ግን ለምን በኦሮሚኛ የሰለቸንን ስለሴት ልጅ ፍቅር ዘፈን ሊዘፍንልኝ ቻለ? ስል ጥያቄ ውስጤ ጫረ::

ይህን ያልኩት ከጃኪ የተሻለ ሥራ ጠብቄ አይደለም:: ዘፈን ለመስረቅ አስመራ ዘፋኞች ድረስ የሚሄደው ይኸው ድምጻዊ ወደ ኦሮሚኛ ዘፈን ፊቱን ሲያዞር በኦሮሞ ልጆች ግድያ ዙሪያ ይዘፍናል ብዬ ትንሽ አስቤ ነበር:: ተስፋ የጣልኩበትም ምክንያት ባለፈው በሊቢያ ጉዳይ ተንደርድሮ ሰው እንዳይቀድመው ነጠላ ዜማ መስራቱን አይቼ ነው::

ሆኖም ግን በወያኔ ድረገጾች በኩል የተለቀቀው ይኸው የጃኪ አዲስ የኦሮሚኛ ሙዚቃ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት አቅጣጫ ለማስቀየርና አንዳንድ ሃገር ወዳድ የኦሮሚኛ; የጉራጊኛ እና የአማርኛ ሙዚቃ አርቲስቶች በሃገራቸውና በወገኖቻቸው ግድያ ዙሪያ መንግስትን ተው አትግደል ያሉባቸውን ዘፈኖች ለማዳፈን ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑ ይታመናል:: ለዚህም ነው ጃኪ በዚህ ወቅት የፍቅር ዘፈን በኦሮሚኛ መልቀቁን አይቼ እየቀለድክ መሆን አለበት ያልኩት::

ጃኪ የሊቢያ ወገኖቻችን መሞት እውነት አሳዝኖህ እንዳልዘፈንክ ዛሬ በኦሮሚኛ ዘፈንህ ላይ አሳይተኸናል:: ያኔ ያንን ነጠላ ዜማ የለቀቅከው በወገኖቻችን ሞት አንተ ዝናን ለማግኘት እንደተጠቀምክበት ነው የምቆጥረው:: ለወገንህ የምታዝን ቢሆን ኖሮ በአማራ ክልል ይህ ሁሉ ወጣት ሲሞት; በኦሮሚያ ግድያው በተጠናከረበት ወቅት እንዲህ ያለውን ልፍስፍስ ዘፈን ለቀህ የወያኔ መጠቀሚያ አትሆንም ነበር::

ጃኪ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት በትግል ላይ ነው:: አንተ ስለሴት ልጅ ውበት የምታደንቅበትን ዘፈን የሚያዳምጥበት ሳይሆን ካንተ የሚያታገል ዘፈን የሚጠብቅበት ወቅት ነው::

↧

አቡነ አብርሃም በባህርዳር ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር ድምጽ እጃችን ገባ |ይዘነዋል

$
0
0

የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሃም ታሪካዊ መል ዕክት አስተላለፉ:: አቡነ አብርሃም ዛሬ ይህን ከተናገሩ በኋላ በመኪና አልሄድም ብለው በባህር ዳር ጎዳና ላይ ከሕዝብ ጋር አብረው ወደ ማረፊያቸው ሄደዋል:: ንግግራቸውን ሼር ያድርጉት::

አቡነ አብርሃም በባህርዳር ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር ድምጽ እጃችን ገባ | ይዘነዋል

↧
↧

ዛሬ ከወደ ባህርዳር እውነት ተገለፀች |ከዘመድኩን በቀለ

$
0
0

“መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።”
የዮሐንስ ወንጌል 10፣11

“ጥልም በመስቀሉ ተገደለ”።
“ኤፌ 2፣16″።

በአባቶቻችን ዝምታ ተስፋ የቆረጥነው የእኛን አንገት ቀና ያደርጉ ፣ የህዝቡንም እንባ የጠረጉ ፣ የመረጣቸውና ለተለየ ክብርና አገልግሎትም የጠራቸውን ቅዱስ እግዚአብሔርንም ያስከበሩ ደገኛ አባት በባህርዳር ከተማ ላይ በመስቀሉ አደባባይ ዛሬ ተገልጠዋል ።

ዛሬ በባህርዳር ከተማ ላይ የቅድስት ተዋህዶ የእምዬ ኦርቶዶክስ ድምጽ ከፍ ብሎ ተሰምቷል ።
14502816_1836993936535481_7906889427951457037_n
የብዙ ሺህ ህጻናትን አንገት በመቅላት የሚታወቀውን ጨካኙን ሔሮድስን እንደገሰጸው እንደ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የለ ድምጽ በባህር ዳር ተሰምቷል ።

የአባቶቼን ርስት አልለቅም በማለቱ ምክንያት ብቻ በወይን እርሻው ውስጥ በባለ ጊዜዎቹ ንጉሥ አክአብና ንግሥት ኤልዛቤል በሰማሪያ በግፍ የተገደለውን የምስኪኑን ናቡቴ ደም ህዝቡም እግዚአብሔርም እንዲመለከቱትና ፍርዱን እንዲሰጡት በመገዘት ጭምር ስለ ምስኪኑ ናቡቴ እንደ ጮኸው እንደ ነብየ እግዚአብሔር ኤልያስ ያለ ድምጽ ዛሬ በባህርዳር ተሰምቷል ።

ኢትዮጵያ እንደ አቡነ ጴጥሮስና እንደ አቡነ ሚካኤል ያለ ጨካኞችን ፣ ገዳዮችን የሚገስጽ ፣ እንደ አቡነ ጎርጎርጎሪዮስ ቀዳማዊ አይነት ገዢዎችን የሚጋፈጥና የሚሟገት አባቶችን ነበር ያጣችው ።

ዛሬ ግን ያን የፍርሃት ሰንሰለት የሚበጣጥስ ድምጽ ከባህርዳር ተሰምቷል ። ደፋሮችን ፣ ገዳዮችን ፣ እና ጨፍጫፊዎችን ከመፍራት የተነሣ የሃይማኖት አባቶች ዝም ቢሉ እንደ ነብዩ ኢሳይያስ በእግዚአብሔር መቀጣት ይመጣል ብለው የተረዱ አባት በዚህ ዘመን ተገኝተዋል ።

ዛሬ ከወራት በፊት መንግስትን ጥያቄ ለመጠየቅ ወጥተው ብዙዎች አካላቸውን እና ህይወታቸውን ባጡበት በአዲስ አበባው የመስቀል አደባባይ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ በብዙ ሺህ ወታደሮች ታጅበው በመምጣት በዓሉን ለማክበር በብዛት በአደባባዩ ለተገኙት የፌደራል ፖሊስ አባላት የ5 ዓመቱን የመንግስት ዕቅድና የልማት ስትራቴጂ እንደ አንድ ካድሬ ሲያቀነቅኑ ቢያመሹበትም ፤ በባህርዳር ግን አዲስ ታሪክ ተመዝግቧል ።

እኚህ ሰው በቀደመ የምንኩስና ስማቸው አባ ቃለ ጽድቅ ይሰኛሉ ። በመርካቶ የሚገኘው የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ያደረጉ ፣ ኋላም ለማእረገ ጵጵስና ደርሰው አቡነ አብርሃም ተብለው ከተሾሙ በኋላ በሰሜን አሜሪካና ከዚያም ተመልሰው በምስራቅ ሐረርጌ አሁን ደግሞ የምእራብ ጎጃም ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን እያገለገሉ ያሉ አባት ናቸው ።

ዛሬ በባህር ዳር ህዝበ ክርስቲያኑ መግደል የማይሰለቻቸውና የሰው ደም በአደባባይ ሲፈስ የሚያረካቸው የአግአዚ ጦር የሰውን መሰባሰብ አይቶ ደግሞ እንደለመደው በስናይፐር ንጹሐን ዜጎችን እንዳይለቅመን በማለት ብዙዎች ከቤታቸው ቀርተዋል ። ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ግን የመጣው ይምጣ ብለው በቆራጥነት ወደ መስቀል አደባባይ ሄደው ነበር ።

በእለቱ የሚፈጸመው የጸሎትና የዝማሬ መርሀግብሮች ከተፈጸሙ በኋላ ግን ለቃለ ምዕዳኑና ለቡራኬው ወደ ዓውደ ምህረቱ የቀረቡት አባት የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ አብርሃም ነበሩ ።

ብፁዕነታቸው የክርስቶስን መስቀል በቀኝ እጃቸው ይዘው በትከሻቸው ስናይፐርና መትረየስ በያዙት ወታደሮች ፊት ቆመው እንዲህ አሉ ።

👉ሁል ጊዜ ችግር የሚፈጠር በመሪው እንጅ በተመሪው አይደለም፡፡ ሕዝብ መቼም ቢሆን ተሳስቶ አያውቅም፡፡ሕዝብ መቼም የችግር መንስዔ ሆኖ አያውቅም ። ቤተ ክርስቲያንም እንደዚያው። ሁሌም የችግር መንስኤ የሀገሪቱ መሪዎች ናቸው ። መንግስት ለህዝብ ጩኸት መልስ አይሠጥም… መንግስት አዎንታዊ መፍትሄ እስካልሠጠ ድረስ ደግሞ ህዝብ ጩኸቱን አያቆምም.።

👉 የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፡፡

👉ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፡፡

👉በስደት ያለው ወገናችን ወደ ሀገሩ መመለስ አለብት፡፡ ስደት ይብቃ

👉 ”..እናንተ ጋዜጠኞች ደግሞ ሁሌም ቃለመጠይቅ ታደርጉልናላችሁ፤ መርጣችሁ ምታስተላልፉት ግን እኛን ከህዝቡ ጋር የሚያጋጭ ነገር ነው። ህዝቡ የሃይማኖት አባት የለንም ብሎ እንዲያስብና ተስፋ እንዲቆርጥብን ከሆነ የምትፈልጉት ወደፊት እንድትቀርፁን ምንፈቅድላችሁ አይመስለኝም ። ለዛሬ ግን ችግር የለውም ነፃ ናችሁ።

👉ያለ በደላቸው የታሠሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፡፡

👉ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን?

👉 የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፡፡

👉ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ሆይ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁል ጊዜ ስለእናንተ ስለምትጸልይ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ፡፡

እውነት ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘወትር በቅዳሴዋ የሀገር ድንበር ለሚጠብቁ ወታደሮች ትጸልያለች ። የዘመናችን ወታደር ጠላት የሚመጣበትን ድንበር መጠበቁን ትቶ በከተማ የሚጸልይለትን ስንቅ የሚያቀብለውን ደሞዝም የሚከፍለውን ባዶ እጁን ያለ ወገኑን በአደባባይ የሚገድል ሆነ እንጂ ።

ይህን ሁሉ በህዝቡ ጆሮ አፍስሰው ከጨረሱም በኋላ ህዝቡ ወደ ቤቱ ሳይገባ እኔ ወደ ማረፊያዬ አልሄድም በማለት በመጨረሻ ህዝቡ ሁሉ ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ ወደ መንበረ ጵጵስናቸው ሄደዋል ።

ለማንኛውም ዛሬ ቅድስት ቤተክርስቲያን ደስ ብሎአታል ። ነገ የሚፈጠረው ባይታወቅም ለዛሬ ብፁዕነታቸው በሰላም በዓሉ ፍጻሜ እንዲያገኝ አድርገዋል ።

በነገራችን ላይ በቅርቡ ሌላም የምስራች ይኖረናል ። የግብጽ መንግስት በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ መከራ በማብዛቱ ምክንያት ሁሉን ጥለው አቡነ ሺኖዳ ወደ ገዳም እንደ ተሰደዱት ሁሉ በቅርቡም ይህን ታሪክ ለመድገምና ቀሪ ዘመናቸውንም በዚያ ለማሳለፍ የወሰኑ ሊቀ ጳጳስ መኖራቸው መረጃው ደርሶኛል ።

ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን !!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ
መስከረም 16/2009 ዓም

↧

ከታሪክ መድረክ –ለመሆኑ የብሔር ብሔረሰብ ጭቈና በኢትዮጵያ ነበር ወይ: –ከኀይሌ ላሬቦ

$
0
0

ከኀይሌ ላሬቦ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዘውገኝነትንና[1] የዓለም-አቀፍነትን ያስተዳደር ርእዮተ ዓለም የሚያራምዱ አንጃዎች ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች መታጐርያ እስር ቤት ናት እያሉ የሚሰብኩት ስብከት ተደማጭነትን ከማግኘት አልፎ፣ ብዙዎችን አገርወዳዶች ሳይቀሩ ጭምር፣ እያወነበደም እየማረከም ነው። የሰባኪዎቹ አቋም የግል ጥቅማቸውን የማራመድ ዕቅድ ካላቸው ይጠቅማቸው ይሆናል እንጂ፣ በኢትዮጵያ ታሪክና በየጊዜው በተፈጸሙት ተጨባጭ የመንግሥት ተግባራትና መመርያዎች አይደገፍም። ለዘመናት በየጊዜው የተነሡት የርስ በርስ ጦርነቶችና የሕዝብ ፍልሰቶች፣ የሃይማኖቶች መስፋፋትና እነዚህም ድርጊቶትች ያስከተሏቸው ግጭቶች፣ በተለያየ ጊዜ የማዕከላዊ መንግሥት መፍረስና መልሶ መቋቋም፣ በብዙ መልክ አገሪቷን የጐዱ ቢሆኑም፣ በሌላው አኳያ ደግሞ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማቀራረብ አልፈው አዋህደዉታል። እነዚህ ክሥተቶች ከንግድ፣ የእምነት ማዕከላትን ለመሳለም በየጊዜው ከሚደረጉት የምዕመናን ንግደቶችና ከጋብቻ ጋር ሁነው፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ በታሪክ፣ በደም፣ በቋንቋ፣ በባህል አስተሳስረው እንደሰርገኛ ጤፍ ስለደበላለቁት፣ በዘሩ ጭንጩ የሆነ ዘውግ በርግጥ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት እንደዘበት መቈጠር ይኖርበታል። እውነት ነው እያንዳንዱ ዘውግ ራሱን የሚገልጥበት የተለየ የአካባቢው ቋንቋ አለው። ቢኖረውም ግን ተናጋሪው ሕዝብ ካንድ እንጅላት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ሁሉም ለሚኖርበት መጤ፣ አለበለዚያም ከሌላ አገር ከፈለሰ መጤ ጋር  የተቀላቀለና የተዋሐደ ነው። ስለዚህም የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠቅላላ ሲታይ፣ አንዱ የሌላው የሥጋው ቊራጭ፣ የደሙ ፈሳሽ ነው ቢባል መቼም በምንም መልክ የማይካድ ሐቅ ነው።

nat-m-sa

አገሩን የገዛው እያንዳንዱ ተከታታይ ሥርወ መንግሥት የአገሪቷ የመሬት ቈዳ ይጥበብም ይስፋም ሕዝቧን በነፃነት፣ ለማንም ሳያደላ የበላይነትና የበታችነት ስሜት ሳያሳይ በእኩልነት አስተዳደሯል። ከዚያም ሕዝቡ ራሱ ከነጋሹም ክፍል ጋር ሆነ፣ እርስ በርሱ በመጋባትና በመወላለድ ተደባልቆ ተዋሀዷል። ከዚያም አልፎ፣ አንድ የኢትዮጵያውያን የጋርዮሽ ሀብት የሚያሰኝ የራሱን ቋንቋ ለመፍጠር ችሏል። ከነዚህም እሴቶች የተነሣ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከማንም የአፍሪቃ ሕዝብ በላይ የሥነ-ልቡና ኩራትና ከማንአንሼነት መንፈስ ለማዳበር በቅቷል። በዘመናዊ መልክም የተቋቋመችው ኢትዮጵያ ለሁሉም ሕዝቧ የነጻነትና የእኩልነት ማኅደር እንጂ የማንም እስርቤት አልነበረችም። ጨቋኝና ተጨቋኝ ብሔረሰብም ታይቶባት አይታወቅም ማለት ይቻላል።

ኢትዮጵያ ከሌላው የዓለም አህጉራትና ሕዝብ በተለይም ከአፍሪቃዎቹ የምትለይበት አያሌ መሠረታዊ እውነቶች አሉ። አንደኛ፣ አብዛኛው፣ (እውነቱን ለመናገር ሁሉም ማለት ይቀላል) የዛሬ የአፍሪቃ አገሮችና መንግሥታት ህልውናቸውንና ምንነታቸውን ያገኙት በውጭ አገር መጤዎች ሲሆን፣ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ መንግሥት ግን አላንዳች የውጭ እርዳታ ባገሩ ተወላጆች እጅ የተገነቡ ናቸው። የአክሱም ሐውልቶችና ቤተመንግሥቶች፣ እንዲሁም በየጊዜው የተሠሩ ሕንጻዎች፣ የአሁኗ መናገሻዋ አዲስ አበባ፣ ሌሎችም ከተሞችና የግል ሕንጻዎች የታነጹት በራሳቸው በኢትዮጵያውያን እንጂ ከውጭ መጥተው አገሪቷን በያዙ ኀይሎች አይደሉም[2]። ይኸም ማለት የውጭ አገር ሰዎች በሠራተኛነት አልተቀጠሩም አይባልም። ከመሐንዲሶች እስከተራ ሠራተኞች ባገሪቷ ውስጥ ተቀጥረው ሠርተዋል።

 

ይልቅስ ይኸ ራሱ ማለትም ምዕራባውያንንና የሌላውን አገር ዜጋ ቀጥሮ ማሠራት፣ አንድ ራሱን የቻለ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መለዮ ነው ማለት ይቻላል። ያፍሪቃ አገሮች ነጻነታቸውን እስካገኙበት ጊዜ ድረስ፣ መጤዎቹ የውጭ አገር ሰዎች [ምዕራባውያኑም ሆኑ እስያዉያኑ] ባገሩ ውስጥ ይኖሩ የነበሩት የገዢና ያስተዳዳሪ አለበለዚያም የከበርቴ ክፍል ሁነው ነበር። በነዚህ አገሮች፣ ፈረንጆችን በአዛዥነት ቦታ እንጂ፣ ባገሩ ተወላጅ ሲታዘዙ ማየት ድንቅ ግሩም ስለነበር አይታሰብም፣ አይታለምም ማለቱ ይቀላል። ያገሩ ተወላጅ የተመደበው፣ የጊዜውን አነጋገር ብንጠቀም፣ ለውሃ ቀጂነት፣ ለዕንጨት ለቃሚነትና ፈላጭነት ብቻ ነበር ማለት ይቻላል።  በኢትዮጵያ ግን ፈረንጅ በታዛዥነት እንጂ በአዛዥነት ቦታ ታይቶ አይታወቅም ቢባል ሐሰት አይደለም። ስለዚህም ባንድ የአፍሪቃ ክፍል በሆነ አገር ውስጥ ይኸ የሥልጣን ተገላቢጦሽ መፈጠሩ፣ አገሩን የጐበኙትን ፈረንጆች በጣም እንዳደናገራቸው ግልጽ ነበር።  ጆን ቦይስ የተባለ እንግሊዛዊ ከእንግሊዝ ምሥራቅ አፍሪቃ (ማለትም ከዛሬዋ ኬንያ፣ ኡጋንዳና ታንዛንያ) ወደአዲስ አበባ እንደደረሰ፣ በጣም እንግዳ የሆነብኝ ነገር ቢኖር፣ “አንድ አፍሪቃዊ [ማለትም ጥቊር] የሆነ ሰው ቤቱን እያነፀለት ያለውን ነጩን ሲያዘው” ማየቴ ነበር ይላል። ከአክሱም ሐውልት ጀምሮ አገሪቷን ሆነ፣ የአገሪቷንም ታሪክ ሠሪዎችና ገንቢዎች ኢትዮጵያኑ ራሳቸው ናቸው። ይኸ አባባል በዘመነ መሳፍንት ፈርሳ እንደገና በዘመናዊ መልክ የተገነባችውን የዛሬዪቱን ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከገናናው ከአክሱም መንግሥት እስከዘመነ መሳፍንት ድረስ የነበረውን መላውን ያገሩን ታሪክ ሁናቴ ጭምር ይመለከታል።

 

በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያ ግንባታና ታሪክ ካንድ ዘውግ ወይንም ካንድ አካባቢ በተወጣጡ ሰዎች የተካሄደ ሳይሆን ከብዙ ነገድና አካባቢ የመጣ ሕዝብ ድርጊት ነው። ታሪኩን በአክሱም መንግሥት ከጀመርን፣ አንደኛ አክሱም የኢትዮጵያ ክፍል መሆኗ በጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ልክ ሮም የተባለችው ከተማ ከኢምንትነት ተነሥታ የመላው የኢጣልያን ባሕረገብ ምድር የበላይ ሁና እንደተቈጣጠረች ሁሉ፣ አክሱምም በጊዜዋ ከከተማነት አልፋ፣ አብዛኛውን የዛሬዎቹን የኢትዮጵያን ግዛቶች እስከሱማሌ፣ ከዚያም ቀይ ባሕር አልፋ የመንንና ደቡብ ዐረብን፣ በሰሜን ደግሞ እስከግብፅ ወሰን ድረስ ትገዛ እንደነበር የአዱሊስ ዙፋን በሚል ሐውልት ላይ የተቀረፀው ጽሁፍ ይገልጥልናል[3]። ልክ ሮም የሮማዉያን መንግሥት መናገሻ ከተማ እንደነበረች ሁሉ፣ አክሱምም በስሟ የሚጠራው መንግሥት ዋናው ከተማ ስም ነበረች[4]።

 

የአክሱም ሥልጣኔና ግዛት የሚነግሩን ግልጥ ነገር ቢኖር በመንግሥታቸው ሥር የነበሩት ነዋሪዎች፣ ልክ እንደሮማው መንግሥት በቋንቋም ሆነ በሥልጣኔ ደረጃ የተለያዩ እንደነበርና፣ ንጉሥም እንደዋና ተልእኮው አድርጎ ይመለከት የነበረው በየቦታው ሰላም ማስፈን፣ ንግድ ማስፋፋት፣ ማንም በሌላው ላይ ግፍ እንዳይፈፅም ከበላይ ሁኖ መቈጣጠር ነበር። ግዛታቸው ሰፊ ከመሆኑ የተነሣ፣ አገሩን በጸጥታና በሥነሥርዐት ስላስተዳደሩ፣ ግፍና ዐመፅ ስላራቁ፣ ንግድ እንዲስፋፋ ጥርጊያውን ስላመቻቹ፣ ከያንዳንዱ ኅብረተ-ሰብ ግብር ይጠብቃሉ። ይኸ ደግሞ በየትም ያለ የዜግነት ግዳጅ ስለሆነ የአክሱሞችን መንግሥት ሆነ፣ በነሱ ምትክ የመጡትን የኋለኞቹን ሥርወመንግሥታት፣ ጨቋኞች ወይንም በዝባዦች አያሰኛቸውም። መንግሥት ነዋሪዎቹ በኢትዮጵዊነታቸው በእኩልነትና በነፃነት [ማለትም በሌላ የውስጥ ኀይል ሳይጨቈኑ በባዕድም ሳይደፈሩ) እንዲኖሩ በማድረግ የዜግነት መብታቸውን እንዳስከበረ ሁሉ፣ ለእነሱም ግብር መክፈል የመንግሥትን ሥልጣን  መቀበላቸውንና ላገሩ ሕግ የሚታዘዙ መሆናቸውን ከሚገልጡበት መሣርያዎች ዋነኛው ነው።

 

የአክሱም ሥልጣኔ በአፍሪቃ ክፍለአገር ከመላው ጥቁር ሕዝብ የሚለይበት ሌላም ነገር አለ። ሥልጣኔው ከራሱ ከአካባቢው ሕዝብ በሂደት የፈለቀና የመነጨ እንጂ ባዕዳን መጤዎች ከፈለሱበት እናት አገራቸው ይዘው የመጡት ወይንም በአክሱም ከሰፈሩ በኋላ የፈጠሩት እንዳልሆነ በእጃችን ያሉት ማስረጃዎች ይገልጡልናል። ይኸንን የሚፃረር አሳብ የሚደግፍ እስካሁን አንድም ማስረጃ የለም። በሌላው አንጻር፣ አክሱሞች ወደሌላው አገር ሂደው ሥልጣኔአቸውን እንዳስፋፉ የተውልን የሕንፃ፣ የጽሑፍ ቅርሶች ይመሰክሩልናል። ሐቁ እንደዚህ ሁኖ እያለ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ ጥናት እየተቈጣጠሩት የነበሩት (አሁንም እየተቈጣጠሩ ያሉት ማለት እንችላለን) አውሮጳያን፣ ለጥቁር ሕዝብ ከነበራቸው ንቀት የተነሣ፣ “የአክሱም ሥልጣኔ ከየመንና ከደቡብ ዐረብ ወደኢትዮጵያ ፈልሶ ባገሩ ውስጥ በየጊዜው የሰፈረው ሳባውያን በተባለ ስም የሚጠራው የሴማዊ ሕዝብ ሥልጣኔ እንጂ ካገሩ ነባር ጥቁር ሕዝብ የፈለቀ አይደለም። ይኸም አስገራሚ ሥልጣኔ ሊሞት የበቃው፣ ፈጣሪዎቹ ሴማውያን ከአገሩ ጥቁር ሕዝብ ጋር ከመደበላለቃቸውና ከመወላለዳቸው የተነሣ ነው፤ መጤዎቹ የሰውነታቸው መልክ እየጠቈረ በሄደ ቊጥር፣ አእምሯቸው እየደነዘ፣ የመፍጠር ችሎታቸውም በዚያው ልክ አብሮ ሊደበዝዝና ሊጠፋ ቻለ” ይላሉ። እነዚህ ምሁራን ነን ባዮች፣ ከዚህ ዐይነቱ የተዛባ አስተሳሰብ ተነሥተው የኢትዮጵያን ሕዝብ ሴማውያንንና አፍሪቃውያን እያሉ ለመከፋፈል በቅተዋል። ሴማዉያን ከቀይባሕር ማዶ ከዐረብ አገር የመጡና፣ የአክሱምን ሥልጣኔ የገነቡ ናቸው። ጥቁሮቹን አፍሪቃውያን ደግሞ እነሱ ባወጡት መለኪያ፣ ኩሳውያንና አባይ-ሰሐራውያን ብለው ከፋፍለው ሲያበቃ፣ እነዚህ ለአክሱማውያን ሥልጣኔ ያደረጉት አስተዋፅኦ ኢምንት ነው ይላሉ። በከፍተኛ ዕውቀት የዳበረ የዛሬ ሰው ይኸንን ሲሰማ ነጮችን አምባገነንታቸው ምን ያህል እንዳሳበዳቸው ሊገነዘብና በነገሩ ሊያፌዝበት፣ ካልሆነም ሊስቅበትም ሆነ ሊያዝንበት ይቃጣ ይሆናል። ግን ባገራችን ሌላው ቀርቶ ተምረናል የሚሉትንም እንኳን ሳይቀር አሳምኖ፣ እነርሱም በበኩላቸው ሕዝቡን እስከማወናበድና እርስበርስ እስከማፋጀት አድርሰዋል ማለቱ የለዘበ አነጋገር ይመስለኛል።

 

ሮም በ፬፻፸፮ ዓ. ም. ላይ ስትወድቅ፣ የአውሮጳውያን የሥልጣኔ መሠረት ጥላ ነበር። አክሱምም በ፱፻ ዘመን አካባቢ ላይ ፍጻሜዋን ስታይ ለኢትዮጵያዉያን ያደረገችው ልክ ይኸንኑ ስጦታ ነው። ሁኖም ሮም የግዛቷ አካል ያደረገቻትና የሥልጣኔዋ ዋና ወራሽ የሆነችው ኢጣሊያ ግን፣ ከሮም ውድቀት በኋላ የፈረሰውን አንድነቷን እስከ፲፰፻፸፪ ዓ.ም. ድረስ መልሳ ማቋቋም አልቻለችም። ኢጣሊያን ከሮም ውድቀት በኋላ የተከተላት የብዙዎች ነገዶች[5] ወረራ ሲሆን፣ ውጤቱ አገሩን መከፋፈልና የአካባቢው የኀይለኞች መንግሥታት መፈንጫ ሜዳ ሁና መቅረት ነው። በኢትዮጵያ፣ የአክሱማውያን መውደቅ ያስከተለው የድብልቅልቅና የጨለማ ዘመን የብጥብጥ፣ የሕገ-አልባነትና የሁኬት ጊዜ እንደነበር ቢነገርም፣ በሌላው በኩል ደግሞ ከፍተኛ የሕዝብ እንቅስቃሴ፣ መፈላለስና መዘዋወር የታየበት ወቅት ነበር። ሁናቴው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲደበላለቅና ርስበርሱ እንዲተሳሰር በጣም ረድቷል ቢባል ሐቅ ነው። ቀጥሎም ሥልጣኑን የተረከበው ዛጐ በመባል የሚታወቀው የአገዎች ሥርወ መንግሥትም፣ የአክሱማውያንን ሥልጣኔ እንደባዕድ ሳያይ፣ ልክ የራሱ እንደሆነ አስመስሎ ከመቀጠል አልፎ የግሉን ጨምሯል። አገዎች ግብርናን በማዳበር ረገድ፣ ለመጀመርያ ጊዜ አላምደው ወይንም ከሌላ ጋ አምጥተው ለድፍኑ ዓለም ያበረከቷቸው እንደጤፍ፣ ዘንጋዳ፣ ስንዴ፣ ገብስና ባሕርማሽላ የመሳሰሉ የእህልና የዕፀዋት ዐይነቶች በአፍሪቃ ክፍለአገር ውስጥ በመፍጠር ችሎታቸው ወደር የሌለው ሕዝብ ነው አሰኝቷቸዋል[6]። እንደላሊበላ የመሰሉ የነገሥታቱ ሕንጻም ቢሆን የድፍኑ ዓለም መደነቂያና መገረሚያ ሁኗል። በአዱሊስ ሐውልት ላይ እንደተጻፈው፣ የአገው ምድር የአክሱሙ ንጉሥ ካስገበራቸው አገሮች አንዱ ቢሆንም፣ አገዎች የተረከቡት ግዛት ከአክሱም ያነሰ ነበር። ሰለሞናዊ በተባለው ሥርወ መንግሥት እስከተተኩ ጊዜ ድረስ፣ አገሩን ያስተዳደሩት፣ እንደአክሱሞቹ ሕዝቡን በጐሣና በእምነት ሳይለዩ፣ በፍትሕና በርትዕ ነበር። ንግድ እንዲስፋፋ፣ ሰላም እንዲሰፍን፣ ሌላው ቀርቶ፣ አማኞች ንግደታቸውን አለችግር እንዲወጡ ማመቻቸት[7]ና የበላይ ሁኖ መቈጣጠር እንደዋና ተግባራቸው ያዩ እንደነበር ታሪካቸው ይመሰክራል።

 

የዛጐ መንግሥት በአገዎች እንደተቋቋመ፣ የሰለሞኖች መንግሥት የተመሠረተው ታሪክ እንደሚነግረን ከሆነ አማራ[8] ከተባለው አገር በመጣ ንጉሥ ነው[9]።  አማራ ደግሞ ያነ የሚያመለክተው የተወሰነ አካባቢ ሲሆን፣ ክልሉም በምዕራብ በአባይና በመጋቢው የበሽሎ ወንዝ፣ በሰሜን በአንጎትና ላስታ፣ በደቡብ በወንጭት ወንዝ፣ በምሥራቅ ደግሞ ወደደንከል በረሃ በሚደርሰው ሰፋፊ ገደላንገደል የተከበበውን ምድር ነው። ከዚህ የምንማረው አሁን አማራ ብለን የምንጠራቸውን እንደነጐጃም፣ በጌምድር፣ ሸዋ እንዲሁም የወሎን አንዳንድ ክፍል እንደማያካትት ነው። በዚህ ግዛት ውስጥ በሚኖሩት የአገሩ ተወላጆች [ማለትም የአማሮች] አፈታሪክ መሠረት የአማራ ሕዝብ አሁን ወዳለበት የመጣው በቀጥታ ከአክሱም ነው። የቃሉም ትርጒም “ነፃ ሕዝብ” ማለት እንደሆነ ይነገራል።  ይሁንና አፄዎቹ “ንጉሠ አምሐራ” የሚል ስያሜ ቢኖራቸውም፣ ጐንደር የኢትዮጵያ ቤተመንግሥት ቋሚ መናገሻ ከተማ ሁና እስከተቈረቈረችበት እንደአ.አ. እስከ ፲፮፻፴፪ ዓ. ም. ጊዜ ድረስ፣ ነገሥታቱ ይኖሩት የነበረው ከቦታ ወደቦታ እየተዘዋወሩ፣ አብዛኛውን ጊዜ በደቡብ ባሉት እንደነይፋት፣ ሸዋ፣ ደዋሮና ፈጠጋር በመሳሰሉት አገሮች እንጂ፣ መናገሻቸውን ክልሉን በዘረዘርነው የአማራ አገር አድርገው አያውቁም። ምናልባትም ከመጀመርያዎቹ በስተቀር፣ የአብዛኞቹ ነገሥታት አማራነትም ቢሆን እጅግ በጣም አጠያያቂ ነው ማለት ይቻላል።

 

ከዚህ በተጨማሪ፣ አማርኛ የተባለው ቋንቋው ራሱ ምንጩና መነሻው አማራ ከተባለው ግዛት ውስጥ ይሁን እንጂ፣ ያደገውና የዳበረው ግን በጠቅላላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው አስተዋፅኦ ነው። አማርኛ በመባል ከተወለደበት አገር ጋር ተቈራኝቶ ቢቀርም፣ እውነቱ ግን በየአካባቢው የሚገኙትን የተለያዩ ቋንቋዎች ቃላትንም ሆነ ሰዋስዋዊ አገባብ በመከለስና በመደቀል፣ በማዳበልና በማቀያየጥ አዋህዷቸውና አመሳስሏቸው የተውጣጣ የኢትዮጵያውያን የጋርዮሽ ቋንቋ ነው። የቋንቋ ጥናት ምሁራን አነጋገር ብንጠቀም፣ አማርኛ ጥንተ ዘሩ የሴማውያን ቋንቋዎች ከሚባሉት ክፍል ቢሆንም፣ ሐቁ ግን በኩሻውያን ቋንቋዎች ቃላትና ሰዋስዋዊ አገባብ ከሚጠበቀው በላይ ተበርዟል። ስለዚህም ከማንኛውም የኢትዮጵያውያን ቋንቋ ይበልጥ፣ የመላው ያገሪቱ ሕዝብ የትብብር ፍሬ ስለሆነ፣ እውነተኛ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት ነው ማለቱ የሚቀል ይመስለኛል። ይኸንንም በመገንዘብ ነው እንግዴህ ቋንቋው ባገሪቷ ውስጥ ያሉትን የልዩ ልዩ ብሔረ-ሰቦችን ድምፅ ለማስተናገድ ሲል ጥንት ከአባቱ ግእዝ በወረሳቸው ፊደላት ላይ አስፈላጊነቱን እያየ ሌሎች አዳዲስ ሊፈጥርና ሊጨምር የበቃው። ስለዚህም አብዛኛው የአማርኛ  ተናጋሪ የሚገኘው ከጥንት ትውልዱ ክልል ውጭ ነው። በላስታ፣ በሸዋ፣ በበጌምድር፣ በወሎና፣ በጐጃም ግዛቶች የኩሳውያንን ቋንቋዎች ተክቶ ይገኛል። ቋንቋዎቻቸው የሴማውያን ነበር በተባሉት  አርጐባና ጋፋት በመባል በሚታወቁት አገሮች ደግሞ የአፍ መክፈቻቸው ሁኖ ቀርቷል።

 

በእነዚህ አገሮች አማርኛ እናት ቋንቋቸው ቢሆንም፣ እንደአ.አ. በ፲፱፻፺ዎቹ ዓ.ም. ላይ፣ አማሮች ናችሁ የሚል ስያሜ በግድ በላያቸው ላይ እስከተለጠፈባቸው ጊዜ ድረስ፣ ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩት በሚኖሩበት የአገርና የቦታ ስሞች ጐንደሬ፣ ጐጃሜ፣ ሸዌ፣ መንዜ በመባል እንጂ አሁን በተሰጣቸው አማራ በሚል ብሔረሰብነታቸው አልነበረም። ታሪክም ራሱ የሚያመለክተው ይኸንኑ ነው። ከ፲፬ኛ ዘመነ ምሕረት ጀምሮ እስከ፲፰ኛ ዘመን  ድረስ ባሉት ጊዜ ውስጥ በተጻፉት በታሪከ ነገሥታትም ሆኑ፣ እስከ፲፱ኛ ዘመነ ምሕረት ድረስ በተደረሱት በክርስቲያኖቹና በእስላሞቹ መዛግብት ውስጥ “አማራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው አሁን ጊዜ በወሎ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የቦታ ስም ብቻ ነው። በምንም መንገድ ካንድ ከተወሰነ ብሔረሰብ ጋር የሚያይዝ ምንጭ የለም።

 

እንዲሁም ከዚሁ ጋር በማያያዝ የምጨምር ነገር ቢኖር፣ ባሁኑ አጠራር ኦሮሞ፣ ድሮ ደግሞ ጋላ በመባል የሚታወቀው ሕዝብ ሁናቴም ልክ ይኸንኑ ይመስላል። የወያኔ መንግሥት በአፄ ምኒልክ ዙፋን እንደተቀመጠ ቦረን፣ ሜጫ፣ ቱለማ፣ ኢቱና ጉጂ በመሳሰሉት ስሞች ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩትን ብሔረ-ሰቦች ፣ የፈጠራ ስም ሰጥቷቸው ኦሮሞ በሚባል በጋራ መጠርያ ስም ሥር እንዲካተቱ አስገድዷቸዋል[10]። ይኸ ጥንት ጋላ በአሁኑ መንግሥት አጠራር “ኦሮሞ” የተባለ እረኛ ሕዝብ ለከብቱ ግጦሽ ፍለጋ ሲል፣ በተለመደው አነጋገር “ኢትዮጵያን መውረር” ጀመረ ከተባለ ወደ፭፻ ዓመታት ሊያስቈጥር ነው። ወረራው የጀመረው የእስላሞች ንጉሥ ኢትዮጵያን ሊቈጣጠር ሲል፣ በክርስቲያኖቹ ንጉሠነገሥትና በአገሪቷ ላይ እንደአ.አ. በ፲፭፻፳፱ ዓ.ም. ያወጀው ጦርነት ከ፲፭ ዓመት ከፍተኛ ዕልቂት በኋላ፣ በክርስቲያኖች ድል በተደመደመው ማግሥት ነበር። ጉልበቱ በረጅም ጊዜ ጦርነት ስለተዳከመ፣ በየቦታው የነበሩት የመከላከያ ተቋማትና መዋቅርት ፈራርሰው ስለነበር፣ የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግሥት ወረራውን የመመከትና፣ ሕዝቡንም የመጠበቅ ችሎታው እምብዛም ስላልነበር፣ዘላኖቹ በየሄዱበት በአሬመናዊ ጭካኔአቸው ባደረሱት ለሰማው ሁሉ የሚዘገንን የሰው ዕልቂት፣ የንብረት ውድመት እንደፈጸሙና፣ እግራቸው የረገጠውን አካባቢ በሙሉ ወደጫካና ዱር እስከመለወጥ ደርሰው እንደነበር፣ የጊዜው ሰነዶች አበክረው የሚናገሩት ነገር ነው[11]። ያደረሱትን ጥፋት ባይናቸው ያዩት የውጭም ሆኑ ያገር ውስጥ ጸሓፊዎች፣ ‘ጋላ” ፈጸመ ከሚሉት ግፍና ጭካኔ የተነሣ ድርጊታቸውን አገሪቷን ለመቅጣት ሲባል የተላከ “የእግዚአብሔር መቅሠፍት” ነው በማለት ገልጸውታል።

 

ሁኖም ግን ኦሮሞች ወረራቸውን በጀመሩት ግማሽ ዘመን እንኳን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ሊጠብቁ ሲሉ በጦር ሜዳ ላይ እንደሌላው እንደቈየው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብርቅ ሕይወታቸውን ሲሠውና ሲሞቱ ይታያሉ[12]። ነዋሪውን ገድለው ጨርሰው፣ ወይንም ለገባርነት ዳርገው መሬቱን በጉልበት ወስደው በየሰፈሩበት አካባቢ፣ አብዛኞቹ ኦሮሞች የጥንት የእረኝነት ኑሯቸውንና የዘልማድ እምነታቸውን ትተው፣ በግብርና ሕይወት በመሰማራትና፣ የሰፈሩን እምነት በመቀበል፣ የቀረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ መስለዋል። እንደየአሰፋፈራቸው ክርስቲያን ወይንም እስላም ሁነው አብዛኞቹ እንደየእምነታቸው ስማቸውንም እስከመቀየር ደርሰዋል። በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ገብተው ልክ እንደሌላው ብሔረሰብ ተወላጆች በሥልጣን ሲሻኰቱ ማየት የተለመደ ገጽታቸው ሁኖም ይታያል። አፄ ሱስንዮስ ተቀናቃኞቹን ሁሉ አሸንፎ ለንጉሥነት የበቃው በኦሮሞች ድጋፍና የነሱን የጦር ስልት በመጠቀም እንደሆነ ታሪከ ነገሥቱ ይገልጥልናል። ሚስቱም ከርስትና ወልድሠዓላ በሚል በክርስቲያን ስም ብትጠራም፣ በትውልዷ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባል እንደነበረች ይነገራል። ይኸም ማለት ጐንደርን ከቈረቈረው ከልጇ ፋሲለደስ ጀምሮ እስከ ዘመነ-መሳፍንት ድረስ በኢትዮጵያ ዙፋን ይቀመጡ የነበሩት የሷ ልጆችና የልጅ ልጆቿ እንደነበሩ ነው የሚያሳየው። ዘመነ መሳፍንት ማለት ደግሞ የኦሮሞ ዝርያ ናቸው የተባሉት የየጁ መኳንንት ላንድ መቶ ዓመት ያህል የጐንደርን መንግሥት ሙሉ በሙሉ የተቈጣጠሩበት የኢትዮጵያ ታሪክ ዘመን ነው ማለቱ እውነትን ያንፀባርቃል ብዬ አምናለሁ። የጁዎች በክርስቲያን ቤተመንግሥት ተቀምጠው እስላሞችን ሲያገቡ ያከረስትኗቸው እንደነበረ ሁሉ፣ የወሎዎቹ ሙሐመዶች ደግሞ እስላሞች እንደመሆናቸው ከክርስቲያን ሚስቶቻቸው ይጋቡ የነበሩት እያሰለሟቸው ነበር። ሁለቱም በዝርያቸው ከኦሮሞ ብሔረሰብ እንደመሆናቸው ሁናቴው የሚያሳየው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደምና በሥጋ ብቻ ሳይሆን በእምነትና በባሕል ወወራረሱንና መዋሐዱን ነው።

 

ዘመነመሳፍንትን ያከተሙት አፄ ቴዎድሮስ ዳግማዊ የቋራ ብሔረሰብ ተወላጅ ናቸው። ቋራ የአገው እንጂ የብሔረ አማራ ዝርያ አይደለም። በሌላው በኩል ደግሞ፣ ከልክ በላይ የሚወዷት ሚስታቸው የኦሮምኛና የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብሔረሰብ ልጅ እንደነበሩ ምንም አያጠያይቅም። እንዲሁም ከአፄ ዮሐንስ ቀጥለው በኢትዮጵያ ዙፋን በየጊዜው ከነገሡት ነገሥታት በቀጥታ ኦሮሞ ያልሆነ ወይንም የኦሮሞ ደም የሌለው አንድም ገዢ አልነበረም ማለት ይቻላል። በሌላው ጐን ደግሞ ኦሮሞች በወረራቸውም ወቅት ቢሆን፣ ያካባቢውን ሕዝብ ወንድና ሴት፣ ዐዋቂና ሽማግሌ ሳይለዩ በጅምላ ሲገድሉ፣ ብዙውን ጊዜ ሕፃናቱን ማርከው ወስደው እንደሚያሳድጓቸው መታወቅ ይገባል። በዚህ መልክ ከተማረኩት ሕፃናት መካከል አፄ ሱስንዮስ አንዱ ነበሩ። እነዚህ ሕፃናት የብሔረሰቡ አባላት ሁነው ላቅመአዳም ሲደርሱ፣ ከኦሮሞው ጋር ተጋብተው ልጅ መውለዳቸው አይቀሬ ነው። ስለዚህ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ያልተዳቀለ በዘሩ ጭንጩ ኦሮሞ የሆነ ሰው፣ በኢትዮጵያ ምድር ውስጥ አለ ማለት በፍጹም ዘበት ነው። ከኔ ምርምር እንደምረዳው ከሆነ፣ የጠባብ ብሔርተኝነት አስተሳሰብ ያሰከረው ግለሰብ ወይንም ቡድን ብቻ ነው በዚህ ዐይነት ቅዠት የሚጠቃው።

 

ይኸ ሁናቴ ኦሮሞን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ የሚመለከት ነው። የዛጐን ሥርወ መንግሥት የተኩት ሰለሞናውያን ነገሥታት፣ ከቀይባሕር ማዶ ያሉትን የድሮዎቹን የአክሱማውያንን ግዛት መቈጣጠር ባይችሉም፣ እስከዘመነ-መሳፍንት ድረስ በበላይነት ይገዙት የነበረው የኢትዮጵያ የቈዳ ስፋት ከመላጐደል እንደኣ.አ. እስከ፲፱፻፹ ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ ያለውን ያጠቃልላል። የእነሱም አስተዳደር የተከተለው ልክ ቀድመው የመጧቸውን የአክሱሞቹንና የዛጐዎቹን ፈር ነበር። በእምነታቸው ክርስቲያን ቢሆኑም፣ ሕዝቡን በዘውጉና በሃይማኖቱ ምክንያት ሳይለዩ፣ በፍትሕና በርትዕ ማስተዳደር፣ ንግድ ማስፋፋት፣ ሰላምና ጸጥታ ማስፈን ዋነኛ ዓላማቸው ነበር። እንደማንኛውም የገዢ ክፍል ሥልጣናቸውን የሚቀናቀን ወይንም የሚደፍር ለነሱ ጠላት ነበር። ይኸንን ሐቅና የኢትዮጵያ ነገሥታት ምን ያህል ለማንም ሳያዳሉ ሁሉንም እምነት በደምብ ማስተናገድ ሥራቸው እንደነበር፣ ታላቁ አፄ ዐምደጽዮን [1314-1344]፣ “እኔ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር የመላው እስላም ንጉሥ ነኝ” ያሉት ንግግር መርሀቸውን ጥርት አድርጎ ይገልጻል። ይኸም ኢትዮጵያን ከአብዛኛው የክርስቲያን ዓለም በጣም ልዩ አገር ያደርጋታል። ከሳቸው በኋላ ወደመቶ ዓመት ያህል ቈይተው የነገሡት ያውሮጳ ነገሥታት መቻቻልና አብሮ መኖር የሚባለው ሐሳብ በቋንቋቸው ስላልነበር፣ እንኳን እስላም ይቅርና፣ ክርስቲያን የተባለውን ሕዝባቸውን በፀረማርያምና በካቶሊክ ጐራ ለያይተውት አላንዳች ምሕረት ሲጨፈጭፉትና ሲያስጨፋጭፉት፣ ካዘኑለት ደግሞ ከግዛታቸው ሲያባርሩት እናያለን። እውነት ነው በኢትዮጵያም ውስጥ ቢሆን ዘመናዊ አስተዳደር እስከተዘረጋ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ፣ ክርስቲያን ሁኖ የእስላምን አገር ማስተዳደር እንደማይቻል ሁሉ፣ እስላም ሁኖ የክርስቲያንን አገር ማስተዳደርም አልተለመደም። ሕዝቡም ቢሆን የሚቀበለው ሥርዐት አይደለም። የኢትዮጵያ ነገሥታት ይኸንን በመረዳት ነው እንግዴህ የመላው ኢትዮጵያ ማለትም የክርስቲያኑም፣ የእስላሙና የባህላዊ እምነቶች ተከታዩም ሕዝብ መሪዎች መሆናቸውን ለማስታወቅ ባፄነታቸው ላይ “ንጉሠ ጽዮን ወንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ[13]” የሚል መፈክር በማኅተማቸው ላይ ያኖሩት የነበረው።

 

አስተዳዳሪዎቹን በተመለክተ፣ ከሰለሞናውያን እስከ ዘመነ መሳፍንት ባሉት ዘመናት ጊዜ ውስጥ በክርስቲያኑ የኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ እከፍተኛ ሥልጣን ላይ የነበሩትን ሰዎች ብሔረሰብነት ለመመርመር ብዙ ሰነዶች የሉንም። በእጃችን ያሉን ጥቂቶቹ የሚያመለክቱት፣ ግለሰቦቹ ከሁሉም ብሔረሰቦች የተወጣጡ መሆናቸውን ብቻ ነው። በነገሥታት ደረጃ፣ ያብዛኞቹ ነገሥታት እናቶቻቸው ከሐድያና ከአካባቢዎቹ ብሔረሰቦች የተወለዱ ነበሩ። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ወደር የሌለ ሚና ተጫውተዋል ተብለው ከሚደነቁት ሴቶቹም ወንዶቹ መካከል በገናናነትና በስመጥሩነት ስሟ ዘወትር የሚነሣው ንግሥት እሌኒ[1431-1522][14] የሐድያው መሪ የሙሐመድ ወይንም የቦያሞ ልጅ ነበረች። በሥልጣን ሽኩቻ በንጉሥ ሱስንዮስ እጅ የተገደሉት አፄ ያዕቆብም ሆኑ፣ ኋላ ንጉሥነገሥትነቱን በጦር ኀይል የተጐናፀፉት አፄ ሱስንዮስ ራሳቸው ጭምር በእናቶቻቸው ከቤተእሥራኤል ናቸው። የአፄ ሱስንዮስ ታሪክ እንደሚገልጥልን ከሆነ ያነ በጣም ታላቅ ሁኖ የሚታሰበውን የጐጃምን ግዛት፣ “ጐጃም ነጋሽ” የሚለውን ከፍተኛና ክቡር የሆነውን ያገሩን የገዢ ማዕርግ ተጐናፅፎ ለብዙ ዓመታት ያስተዳደረው የጉራጌው ተወላጅ ስልቡ“ጐጃም ነጋሽ ክፍሎ” ነበር። ያፄ ሠርፀድንግልን ሁለት ልጆች አግብቶ፣ አገሩን በበላይነት ይገዛ የነበረው በጊዜው የመንግሥት ፈላጭ-ቈራጩ መኰንን፣ የወለጋው ተወላጅ ራስ ዘሥላሴ[15] ነበር። በ “ዳሞት ጸሓፊላምነት” ማዕርግ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ፣ ወሰንና ድንበር ለማስጠበቅ ሲል ብዙ ጦርነት በጀግንነት በመዋጋት፣ ንጉሠነገሥቱን እንደአ.አ. ከ፲፮፻፲፯ እስከ ፲፮፻፳፯ ዓ.ም. በታማኝነት አገልግሎ፣ በመጨረሻም የዳሞት ግዛቱን “ከጋላ ወረራ” ሊከላከል ሲል በጦር ሜዳ ላይ ሕይወቱን የሠዋው ደጃዝማች ቡኮ፣ ከመጀመርያዎቹ የኦሮሞች ታላላቅ ገዢዎች አንዱ ነበር። እንዲሁም ንጉሠነገሥቱ “እንደልቤ ታማኝ” ያሉት፣ ዋናው አማካሪያቸውና፣ ከቁመታቸው ማጠር የተነሣ በኦሮሞኛ ቃል “ጢኖ” በመባል የሚታወቁት፣ ጸሓፈ ትእዛዙ አዛዥ ተክለሥላሴ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ነበሩ። ጽሑፋቸው እንደሚያመለክተው፣ አዛዥ ጢኖ ከኦሮሞ ቋንቋና ባህል በተጨማሪ፣ አማርኛና ግእዝ አሳምረው የሚያውቁ፣ ቅኔ የሚቀኙ፣ አንደበታቸው የተባ፣ ብዕራቸው የሰላ ጸሓፊ ናቸው። እነዚህ ለእንደዚህ ዐይነት ወግና ማዕርግ ሊበቁ፣ ዕውቀትንም ሊገበዩ የቻሉት፣  “ጋላ” በኢትዮጵያ ፈጸመ የተባለው ወረራ ግማሽ ዘመን ማለት ዐምሳ ዓመት እንኳን ሳይሞላው ሲሆን፣ እስከኛ ጊዜ ድረስ ባሉት ዐራት መቶ ዓመታት ውስጥማ ምን ያኽል መቀራረብና መዋሐድ እንደተካሄደ መገናዘብ የሚያዳግት አይሆንም። እንግዴህ የአክሱማያኑን እንኳን ብንተው፣ ከሰለሞናውያን ሥርወ መንግሥት ጀምረን የኢትዮጵያን መዝገበ ታሪክ፣ በፖለቲካ ጥቅም ተገፍተን ሳይሆን ታሪክ በሚጠይቃቸው በምርምር መስፈርቶች[16] ተመሥርተን ብናሰላስል፣ በመጀመርያ ደረጃ ስለቋንቋ እንጂ ስለብሔርና ብሔረሰብ[17] ልዩነት መናገር አንችልም። ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ የቋንቋ እንጂ የዘር ልዩነት ከቶውኑ የለም ማለት የማይካድ ሐቅ ነው ማለት ይቻላል። እንግሊዝኛ የሚናገር የእንግሊዝ ዘር እንዳልሆነ ሁሉ፣ ኦሮሞኛንም የሚናገር ሁሉ የኦሮሞ ዘር አይደለም። ታሪክ የሚያስተምረን ታላቅ ነገር ቢኖር፣ ቋንቋዎች ይጠፋሉ፣ በሌሎች ቋንቋዎች ይተካሉ። የአርጐባ ተወላጆች ነን ባዮች፣ ዛሬ እንደአፍ መክፈቻቸው የሚናገሩት ቋንቋ አርጐበኛ ሳይሆን እንደየአሰፋፈራቸው አካባቢ ልዩነት፣ አማርኛ፣ አፋርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ ነው። በምዕራብ ወለጋ የሚኖሩት አንፊሎች ቋንቋቸውን ረስተው አሁን የሚናገሩት ኦሮምኛ ነው።

 

ነገሩ እንደዚህ ከሆነ ታዲያ፣ ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እኩልነትና ነፃነት ተነፍገው የሚኖሩባት እስር ቤት ናት የሚለው አስተሳሰብ ከየት መጣ ብሎ መጠየቁ ተገቢ ይመስለኛል። ባጭሩ ለመመለስ፣ አሳቡ ብቅ ያለው ኢትዮጵያ ኢጣሊያንን በአድዋ ጦርነት ድል አድርጋ ለአውሮጳውያን ከፈጠረችው ውዝግብ ጋር የተያያዘ ነው ማለት ይቻላል። ኢጣሊያም ቢሆን እንደ አ.አ. በ፲፰፻፸፪ ዓ.ም. ዓመት ላይ መልሳ አንድ አገር ስትሆን፣ እንደኢትዮጵያ በብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች የተጥለቀለቀችና የተወጠረች አገር ነበረች። ከኢትዮጵያ በተለየ መልኩ ደግሞ ቋንቋዎቹን ተናጋሪዎች ሕዝቦች ከተለያዩ አገሮች የተሰባሰቡ ጥርቅምቅም ከመሆናቸውም በላይ፣ ገዢዎቻቸውም የተለያዩና እንደየጊዜው ይለዋወጡ ስለነበር፣ ሕዝቦቹ ርስበርሰ ለመደባላለቅ፣ ከቦታ ወደቦታ ለመዘዋወር ዕድል አልገጠማቸውም። ስለዚህም አገሪቷ አንድ እስከሆነችበት ጊዜ ድረስ ለዐራት መቶ ዘመናት[18] ተለያይተው ሲኖሩ፣ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር፣ ሁላቸውም የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መሆናቸው ብቻ ነው። ኢጣሊያኖች  በኢትዮጵያ ላይ ማትኰር የመረጡት አንድነታቸውን ለማጐልበት፣ ልዩነታቸውን ለማስረሳት ሊረዳ ይችላል ብለው ከተለሙት ጥንስሶች አንዱ ስለነበር ነው። ስለዚህም፣ የሆነ ያልሆነ ምክንያት በመፍጠር፣ እጃቸውን በኢትዮጵያ ላይ ከመቅሰር መቼም ሊቈጠቡ አልቻሉም። የአድዋ ድል ጥሩ ትምህርት አስተምሯቸው ለጊዜው ተወት ቢያደርጉትም፣ ልክ አፄ ምኒልክ እንዳረፉ፣ ወደጥንት አሳባቸው ተመልሰው መጡ። የያኔ መርሃቸው “የዳር ፖሊትካ[19]” በመባል ይታወቃል። ከቅድመ አድዋው ዘዴያቸው የሚለየው፣ ይኸኛው “የሸዋና የትግራይ ፖሊትካ[20]” በመባል ሲታወቅ፣ ዐላማው የትግራይንና ባካባቢዋ ያሉትን የባላባቶችን ግዛቶች ከማእከላዊው የአዲስ አበባው መንግሥት ጋር በማጋጨት፣ ያገሪቷን አንድነት በማናጋትና የርስበርስ አለመግባባት በማጠናከር፣ አገሪቷ ተበታትና በኢጣሊያን እጅ እንድትወድቅ ማዘጋጀት ነበር[21]።

 

በኢጣሊያን ባለሥልጣኖች አገላለጽ፣ “የዳር ፖሊትካ”ም ግቡ ይኸው ነበር። ዋና ትኩረቱ ግን ባንድ በኩል የኢትዮጵያን መኳንንት በገንዘብ በመግዛት፣ ተራ ሕዝቡን በሕክምናና በትምህርት ቤቶች ስጦታና በመሳሰሉት ነገሮች ስም በማታለል፣ በሌላ በኩል ደግሞ በአዲስ አበባ ላለው መስተዳድር ወዳጅ በመምሰል፣ ማእከላዊው መንግሥት ያገሩን አንድነት ለማጠንክር የሚያደርገውን እርምጃና ጥረት በተቻለ መጠን በሙሉ ማክሸፍ ይገባል የሚል ነበር። ሁኖም እንደአ..አ. በ፲፱፻፴ ላይ የኢጣሊያን ባለሥልጣናት የጻፉት ዘገባ፣ “ኢጣሊያ እንዳቀደችው ኢትዮጵያ ደካማ ከመሆን ይልቅ”፣ አፄ ኀይለሥላሴ ከተጠበቀው በላይ አገሩን በዘመናዊ መልኩ እንዳዋሃዱትና አንድነቱን እንዳጠናከሩት፣ የኢጣሊያንም መርህ ልክ እንደቅድመ አድዋው መክኖ እንደቀረ ይናገራል[22]።

 

አፄ ኀይሌ ሥላሴ ያመጡት ለውጥ ያስተሳሰበው ኢጣሊያንን ብቻ አልነበረም። በኢትዮጵያ ውስጥ ለጥቂት ዓመታት ከሠራ በኋላ ካገር የተባረረው ሮማን ፕሮቻዝካ የተባለ የነምሳ ተወላጅ፣ ሁናቴው የሌሎችም አውሮጳውያን ዋና ሥጋት እንደነበር ይገልጣል። ፕሮቻዝካ አደጋውን ከጅምሩ ለመቅጨት ሲል፣ እንደአ.አ. በ፲፱፻፴፭ ዓ.ም. ላይ “ኢትዮጵያ የባሩድ በርሚል” የሚል መጽሐፍ አሰራጨ። በዚህ ወዲያዉኑ በብዙ ቋንቋ በተተረጐመው መጽሐፍ አባባል፣ የኢትዮጵያ ዕድገትና ልማት፣ እንዲሁም ከአውሮጳ አገሮች ተምረው የተመለሱት ወጣቶች ሥራቸውን በዚህ መልክ ከቀጠሉ፣ ያፍሪቃ ቅኝ ገዢዎች ለሆኑት አውሮጳውያን እጅግ አስጊ ሁናቴ ስለሚፈጠር፣ ኢትዮጵያ እንዲትበታተን፣ ሕዝቦቿን “በነገድ፣ በዘር፣ በቋንቋና በባህል መከፋፈልና” ሁሉም ነገዶች በአምባገነኑ አማራ እየተጨቈኑ እንዳሉ መስበክ ያስፈልጋል[23]”።  ኢጣሊያም አገሩን ወርራ እንደያዘችው፣ ሥራዬ ብላ የለፋችው፣ ኢትዮጵያ የሚል ስም ካለም ካርታ እንዲፋቅ[24]፣ ሕዝቡ በጋራ ቋንቋ አማካይነት ርስበርስ እንዳይገናኝ አማርኛን ማጥፋት፣ የአንድነት መንፈስ እንዳያዳብር አስተዳደሩን በቋንቋና በጐሣ መሠረት አወቃቅሮ መከፋፈል ላይ እንደነበር ሁላችንም የምናውቀው ነገር ስለሚመስለኝ እዚህ ላይ መተንተኑ አስፈላጊ ሁኖ ስለማይታየኝ እዘለዋለሁ። ዋናው ነገር ግን፣ እንዳለፉት ሌሎች ጥንስሶችዋ ሁሉ፣ ይኽንንም በተግባር ሊታውለው አልቻለችም። የኢትዮጵያ አርበኞች የሰነዘሩት የጥቃት ወላፈን እስከአገሯ መጥቆ ደርሶ፣ ኢጣሊያን ራሷን ባለም ጦርነት ውስጥ በመዝፈቅ ለህልውናዋ እስከማስጋት ደረሰ። ፕሮቻዝካም ኢትዮጵያን ለማጥፋት የቀየሰው ንድፍ ከኢጣልያን ሽንፈት ጋር አከተመ። ለኢትዮጵያ የቃጣው ዱላ ለራሱ አገር ለነምሳ ተረፈ[25]።

 

ይሁንና እንደአ.አ. በ፲፱፻፷ቹና ሰባዎቹ  ለመጀመርያ ጊዜ ባገር ውስጥ ከፍተኛ ትምህርት በመቅሰም ላይ የነበሩት ተማሪዎች የፕሮቻዝካን ቅያስ ከተቀበረበት አንሥተውት እንደገና ለአዲስ ሕይወት አበቁት። በጊዜው ባለም ደረጃ ደርቶ የነበሩት በወጣቶች ፊታውራሪነት የሚመሩት ፀረቅኝ ግዛትና ፀረ-ቄሳርያዊነት እንቅስቅሴዎች፣ ለኢትዮጵያም ተማሪዎች ተረፉ። እነዚህ ተማሪዎች፣ አገራቸውን ኢትዮጵያን በውጭ አገር ካዩትና በትምህርት ገበታ ከቀሰሙት ፅንሰአሳቦች ላይ በመመሥረት ሲመረምሯት፣ በምጣኔ ሀብት ዕድገት አኳያ በጉልተኛ ባላባት[26] ሥርዐት ደረጃ ያለች ኋላቀር አገር ትሁን እንጂ፣ እሷም ብሔር ብሔረሰቦችን በመጨቈን፣ ቅኝግዛትን በማስፋፋት የነጮች አውሮጳውያን አጋር ነበረች ብለው ደመደሙ። ለነዚህ ብዙውን ጊዜ ከወጣትነት ዕድሜ ጋር አብሮ በሚመጣው በኀልዮ ኑሮ በተበረዘው ጭንቅላታቸው፣ በጥራዘ-ነጠቅነት ላይ የተገነባ ማራኪው የኅብረተሰባዊነት አስተሳሰብ ሲጨመርበት የግንዛቤአቸው ሐቀኝነት እየጐላ እንደሄደ አይካድም። ጊዜው ደግሞ የቀዝቃዛ ጦርነት ወቅት ስለነበር፣ ብዙዎቹ የፖሊትካ ጥቅማቸውን የሚያራምዱ ኀይሎችና ግለሰቦቻቸው ሰለባ እንደነበሩ አይካድም[27]። ዋናው ነገር ግን የተራማጅነት ጨንበል አጥልቀው በሰላቢ ድምጻቸው፣ በኢትዮጵያም ሆነ በሌላው ለከፍተኛ ትምህርት ሲሉ በተሰማሩበት ዓለም ውስጥ ይንጫጩ የነበሩት ሁሉ፣ ባይን ዐዋጅ ተመርተው ያዩትን አሜን ብሎ ከመቀበልና በለብለብ ዕውቀታቸው ላይ ከመመሠረት ውጭ፣ ያገሩን ሁነኛ ታሪክና ባህል፣ የምጣኔውንና የማኅበራዊውን ዕድገት ደረጃና መጠን ባገናዘበ በረቀቀ ጥናትና በጠለቀ ምርምር የተመረኰዘ አልነበረም። እውነት ነው እንቅስቃሴዎቹ በርከት ላሉት መሪዎቻቸው ባገርና በዓለም ደረጃ ጐልተው እንዲታዩ፣ ዕድልና ምቹ መድረክ ሰጥቶዉአቸዋል። በጥራዘ-ነጠቅነታቸው በየቦታው እየሄዱ የነበነቡት ግራዘመም ስብከታቸው ግን፣ አገሪቷን ህልውናዋን እስከመፈታተን ድረስ ለታላቅ መከራና ሥቃይ ዳርጓታል። የጥፋት አደጋው አሁንም ቢሆን እላይዋ ላይ እያንዣበበ እንዳለ ሁላችንም ስለምናውቅ እዚህ ላይ በማተት ላሰለቻችሁ ምኞቴ አይደለም።

 

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትልቁ ችግር ኢትዮጵያ አንድ ከመሆኗ በፊት ባገሩ ውስጥ የነበረውን ያገዛዝ ሥርዐትና ሁናቴ አለማመዛዘናችውና በዙርያዋም ይካሄዱ ከነበሩት ከአውሮጳውያን ተግባራት ጋር አለማያያዛቸው ነው። ካንድነት በፊት አገሪቷን ከጫፍ እስከጫፍ ይገዙ የነበሩት፣ በተለያየ የማዕርግ ስም ይጠሩ የነበሩት የየአካባቢው ባላባቶች ነበሩ። እነዚህ አገራቸውን ወደርስበርስ ጦርነት እንደቀየሩት፣ ነዋሪዎቹን በለየለት ዐይንባወጣ ብዝበዛና ሥቃይ እያተራምሱ እንደነበርና፣ ሕዝቡ ሰላምና ዕረፍት ከማጣት አልፎ፣ የነበረው ያስተዳደር ሥርዐት ከባርነት የተለየ እንዳልነበረ ተማሪዎቹ የተረዱ አይመስልም። ሁሉንም በየዘርፉና በየቦታው መዘርዘር አስፈላጊም አይደለም። ጊዜም አይፈቅድም። ግን ለምሳሌ ያህል ብቻ ሌላውን ትቼ ሁለት አካባቢ ልጥቀስ። የጋዳን ሥርዐት አድናቂዎች፣ ሩቅም ሳይሄዱ በኦሞ ሸለቆ አካባቢ ቊብ ቊብ ያሉትን የጂማ አባጅፋርን፣ የሊሙ እናርያን፣ የጐማንና የጉማን፣ እንዲሁም የለቃ-ነቀምቴንና የለቃ-ቄለምን መንግሥታት ሊያዩ ይገባል። እነዚህ መንግሥታት አካባቢውን የያዙት፣ ነባሩን ሕዝብ በመፈንቀል፣ ወይንም በመግደልና ለባርነት በመዳረግ መሆኑ መረሳት የለበትም። አልፎ አልፎ አንዳንድ ጥሩ ገጽታ ቢኖራቸውም፣ ከመላጐደል የሚያማዝነው አስቀያሚ ጐናቸው ነበር ቢባል የሚካድ አይደለም። የደሞክራሲ ሥርዐትን ያቀፈ ነው ተብሎ የሚወራውን የጋዳ አገዛዝ አፍርሰው፣ ገዢዎቹ አምባገነኖች ሁነው በዘፈቀደ ይገዙ ነበር። ሕዝባቸውንም ሆነ፣ ከሌላ አካባቢ የሚመጣውን እንደባዕድ የሚቈጥሩትን ሌላውን መጤ መፈንገል ልማዳቸው ነበር። የእስላም ሃይማኖት በግድ ያልተቀበለ አንገቱን ለሳንጃ አሳልፈው ይሰጡ ነበር። አለበለዚያም ለስደትና ለባርነት ይዳረግ ነበር። ድንበር ለማስፋት የሚደረገው ጦርነት መቆሚያ አልነበረውም።

 

ከነዚህ ወጣ ብለን ሌሎችን ብናይ የከፋ እንጂ የተሻለ አስተዳደር አናገኝም። ዎማ ወይንም ንጉሥ በመባል የሚታወቅ የከምባታ ገዢ ለምሳሌ፣ በየጊዜው ባካባቢው ካሉት ሕዝቦችና ባላባቶች ጋር ባካሄዳቸው አስከፊ ጦርነቶች፣ መንግሥቱን እያስፋፋ በሄደ ቊጥር አምባገንነቱም በዚያው ልክ አሻቅቦ ነበር። ኦያታ በመባል ለሚታወቀው የራሱ የገዢው መደብ፣ ኮንቶማ የተባለውን ተራውን ሕዝብ እንዲበዘብዝና እንዲያዋርድ ሥልጣን በሥልጣን ላይ ካበላቸው። ለምሳሌ ያህል፣ ኦያቶች ገደብ የለሽ ሚስቶች ሊያገቡ ሲችሉ፣ ተራው ኮንቶማ ግን ካንድ ሚስት በላይ አይፈቀድለትም ነበር። ኦያታ ምርጥ ምርጥ መሬት እየነጠቀ ከተራው ኮንቶማ ወስዶ ሲያበቃ፣ ኮንቶማውን መሬት አልባ ገባር ማድረግ መብቱ ነው። ከዚያም አልፎ ኮንቶሞች አጥር ማጠር፣ በቅሎ መጋለብ አይፈቀድላቸውም፡፡ ጥሰው ከተገኙ የሚጠብቃቸው ጥቃት ቅጥ ያጣ ነበር። ንጉሡም ሲሞት ከባሮቹ ተመርጠው ቆንጆ ሴቶችና ሀብቱም አብረው ይቀበሩ እንደነበር ይነገራል።

 

አፄ ምኒልክ በጦር ኀይልም ሆነ፣ “ሕዝብ በከንቱ እንዳያልቅ፣ ሀገር እንዳይጠፋ በሰላም ግበር” የሚለውን ጥሪያቸውን ተቀብለው በፍቅር በተዋሀዱት አገሮች፣ ከእነዚህ አስከፊ ገጽታ ካላቸው ያስተዳደር ሥርዐት አብዛኛውን ሽረው፣ ሕዝቡ እፎይ እንዲል አድርገዋል። በቦታቸው የዘረጉትም አስተዳደራቸው መዋቅር ሁለት የተጠማመሩ ግቦችን ያካተተ ነበር ማለት ይቻላል። አንደኛው ሕዝብን በግድ ሳይሆን በፍቅርና በዘዴ መግዛት ሲሆን፣ ለዚህም በሕዝቡ ዘንድ እሱ የለመደውና የሚያውቀው ያገሩ ባላባት ተቀባይነት ይኖረዋል ብለው ስላመኑበት፣ የተማረከዉን ገዢ መልሰው በቦታው ይሾሙ ነበር። ካልሆነም ልጁን ወይንም ሕዝቡ ተሰብስቦ የመረጠውን ያስቀምጡ ነበር። መዋጋትንም ይመርጡት የነበረው ባላባቱ፣ በሰላም ግበር ብለው አስቀድመው ደጋግመው ለላኩት ጥሪ፣ አሻፈረኝ ሲላቸውና፣ ሌላ አማራጭ ሲያጡ ብቻ ነበር።

ሁለተኛው ዓላማ፣ ዘመኑ አውሮጳዉያን፣ ነጭ ያልሆነውን ዓለም የሚቀራመቱበት ወቅት ስለነበር፣ ቅኝ ገዢዎቹ አገሩን ለመያዝ ልባቸው እንዳይዳዳ፣ ንጉሠነገሥቱ በግዙፉ በይፋ ማስታወቅ ነበረባቸው። ለዚህም ሲባል፣ ቅኝገዢዎቹ አገሩ በአፄ ምኒልክ ሥር እንዳለና፣ ቢዳፈሩም ጦርነቱ በቀጥታ ከሳቸው ጋር መሆኑን እንዲረዱ፣ ከማዕከላዊ መንግሥት የተሾመ የታጠቀ የጥበቃ ኀይል በያገሩ ተመደበ። የውስጡ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ በባላባቱ እጅ ስለሆነ፣ ሕዝብ ተበደልሁ ካላለ በስተቀር፣ የጥበቃው ክፍል ባስተዳደሩ ጣልቃ አይገባም። ሁኖም ግን የሥልጣን አጠቃቀም ውስብስብነት ስላለው መቼም ቢሆን ችግር እንደሚኖር አይካድም፤ የሚጠበቅም ነው። ይሁንና በዚህ መልክ የተዋቀረው አስተዳደር ራሱን የቻለ እንዲሆን ሲባል፣ እያንዳንዱ ባላባት ዓመታዊ ግብር ይከፍላል። ከዚህም ግብር፣ የጥበቃው ክፍል ለራሱ የሚበቃውን ቀንሶ፣ የቀረውን ለመንግሥት ግምጃ ቤት ያስተላልፈዋል።

ሁኖም ግብሩ የተጣለበት የደቡቡ ሕዝብ ከዉህደቱ በፊት፣ ከዚህ በላይ ራሳቸውን በቻሉ በጥቃቅን የባላባቶች መንግሥታት ቢጤ ሥር ስለነበር፣ እንደሰሜኑ ሕዝብ ለማዕከላዊ መንግሥት ለብዙ ዘመናት ገብሮ አያውቅም። ስለዚህም ትውፊቱ በሌለበት አካባቢ ግብር በመጣሉ፣ እንደግፍ ተቈጥሮ በመተቸት፣ ያፄ ምኒልክን ሥራ በቅኝ-ገዢነት እስከመተርጐም አድርሷል። እንዲህ ዐይነቱ አቃቂር መሠረተ ቢስ ከመሆን አልፎ፣ በታሪክም ቢሆን በምንም መልኩ የማይደገፍ ነው። እንግሊዞች “ግብርና ሞት ሁለት አይቀሬ የመኖር ዕዳ ናቸው” እንደሚሉ ሁሉ፣ አፄ ምኒልክ በግዛታቸው ሰላም ለማስፈር፣ ጸጥታ ለማስከበር፣ የሚወጣውን ወጪ ለመሸፈን፣ እንደማንኛውም መንግሥት ግብር የማያስከፍሉበት ምክንያት የለም። እንደእንግሊዞቹ ባገራችንስ ቢሆን “ግብር ይውጣ፣ የማይቀር ዕዳ” ወይንም “ግብር፣ እስከመቃብር” ይባል የለም።  ይልቅስ ግብሩ፣ ጊዜውንና የሕዝቡን አኗኗርና ችሎታ ያገናዘበ በመሆኑ፣ ንጉሠ ነገሥቱ ምን ያኽል አስተዋይና፣ የአገራቸውንና የሕዝባቸውን የዘለቀታ ጥቅም በደምብ የተረዱ መሆናቸውን ፍርጥ አድርጎ ያመለክታል።

ግብሩ በጠቅላላ ከሕዝቡ ዐቅም ጋር የተመጣጠነ ሁኖ፣ የክልሉን አስተዳደር ወጪ ችሎ፣ ቀሪው ለመንግሥት ግምጃ-ቤት ገቢ ይደረግ ነበር። ይኸም ኢትዮጵያ ከውጭ አገር መንግሥታትና ከዓለም-አቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ ሳትበደር፣ ባላት ገቢዋ ብቻ ተቈጥባ፣ እጅግ በጣም ሰፊ አገር እንድታስተዳድርና፣ አንዳንድ የልማት ሥራዎች እንድታካሄድ አበቅቷታል። አለመበደሯ ለአብዛኞቹ የእስያና የአፍሪቃ ሀገሮች ከደረሰባቸው መጥፎ ጽዋ (በተለይም ግብፅን የገጠማት ዐይነት)፣ ማለትም አበዳሪዎቹ ኪሳራቸውን ለመሸፈን በሚል ሽፋን አገሯን በዋስትና ከመያዝ አድኗታል። አካባቢው የታወቀ የተፈጥሮ ምርት ከሌለው፣ በሰሜኑ ክፍል እንደተለመደውና ከጥንት ይሠራ እንደነበረው፣ መሬቱ ተሸንሽኖ በተወሰነ ሰው ቊጥር ይደለደልና በሰው ልክ ግብር ይጣልበታል። በተራ ቋንቋ ገባር የሚባል ቃል ከዚህ የመነጨ ነው። ትርጒሙም “ግብር የሚከፍል” ማለት ነው።

ባህሉንና አሠራሩን ባልተረዱትና፣ ከአገራቸውና ከራሳቸው ጥቅም አንጻር በሚያዩት የፈረንጅ ጸሓፊዎች ላይ በመመርኰዝና ከታሪክ ሂደት ጋር ካለማገናዘብ የተነሣ ነው እንግዴህ፣ ብዙዎች ተማርን ባዮች ኢትዮጵያውያን ለገባር መጥፎ ትርጒም ይሰጡ የነበሩት። ይባስ ብሎ፣ ከፀጥታ ጥበቃው ክፍል በማያያዝ “የነፍጠኛ ሥርዐት” ብለው የሚጠሩትም አሉ። ታሪክ ማጣመም ካልተፈለገ በስተቀር ትርጒሙ እውነቱን አያንፀባርቅም። ከጊዜው የአገሩ ምጣኔ ሀብትና ከሕዝቡ የዕድገት ደረጃ፣ እንዲሁም ከዓለም ዐቀፍ ሁናቴና ከዘመኑ መንግሥታት ኀይል አሰላለፍ አንጻር ሲታይ፣ ምንም ብንል፣ ያኔ ከገባር የተሻለ አማራጭ ከቶውኑ አልነበረም። ቢኖር ኖሮ፣ አፄ ምኒልክ በደስታ እንደሚቀበሉት በምንም አይጠረጠርም። ለዚህም ያኔ በመጠኑ በሥልጣኔ ደረጃ ከሌላው ክፍለ አገር ሻል ብላ ለሚትገኘው ለድሬዳዋ ከተማ በ፳፰ ሠኔ ፲፰፻፺፰ ዓ.ም. አስተዳደርዋ እንደሌላው አካባቢ በባላባት መሆኑ ቀርቶ በቤተ መማክርት፣ ማለትም በሥራ አስኪያጅ ቡድን እንድትተዳደር ብለው ያወጡት ሕግ እንደማስረጃ ሊጠቀስ ይችላል። እንደዚሁም የወላይታ ባላባቶች በተራው ሕዝብ ላይ በደል ቢያበዙ፣ ሽረውዋቸው ከጥብቅ ማስጠንቀቂያ ጋር በ፪ ሠኔ ፲፱፻ ዓ.ም. ያቋቊሙት የሹማምንቶች መማክርትም ሌላ ምሳሌ ነው5 ።

የገባር ሥሪት ባሕርይ በሰሜንም በደቡብም አንድ ዐይነት ሁኖ ሳለ፣ በኻያኛው ዘመን ላይ በደቡቡ ሥርዐት ሰፊ ለውጥ ታይቷል። ስለዚህም ልዩነቱ በአካባቢው የተከናውኑ የሥራዎች ውጤት እንጂ ከመንግሥት የታወጀ አዋጅ ወይንም የተወሰደ ያስተዳደር እርምጃ ያመጣው አልነበረም። የሰሜኑ ክፍል በሥልጣን ሱስኞች ባላባቶች በመበጥበጡ፣ ምንም ዐይነት የልማት ሥራ ሳይካሄድበት በቁመናው ሲቀር፣ በደቡብ የባቡር ሐዲድ መዘርጋትና የዘመናዊ እርሻ መስፋፋት ያመጡት ሀብትና ድሎት ባላባቱንም ሆነ የማእከላዊ መንግሥት ሹሞችን ስለተፈታተነ፣ ሁለቱ አንዳንዴ በመተባበር፣ አንዳንዴ ደግሞ በተናጠል ተራ ሕዝቡን እያባበሉም ሆነ እያዋከቡ፣ ወይንም ኀይል በመጠቀም መሬቱን እስከመንጠቅና ጥሎላቸው እስከሚሄድ አድርሰዉታል። ለምሳሌ አሩሲዎች ለከብታቸው ግጦሽ እስከሚያጡ ድረስ መሬታቸዉን አጥተዉት ነበር። አፄ ምኒልክና ተከታዮቻቸው ጊዜውና ዐቅማቸው በፈቀደላቸው መጠን ከሕዝቡ ጐን ተሰልፈው፣ አንዳንዴ በአዋጅ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ባለሥልጣኖቹን ሽረው ሌላ በመተካት፣ ሳይታክቱ እንደተዋጉ ሰፊ ማስረጃዎች አሉ።

 

አንድነትን ከመፍጠራቸው በፊት፣ ከላይ እንዳየነው፣ በየቦታው ይገዛ የነበረው የባላባቶች መንግሥት፣ የራሱን ሕዝብ ከታጐረበት ክልሉ ውስጥ እንዳይወጣ ሲያስገድድ፣ ከሌላው አካባቢ ወደሱ አገር የሚገባውን ደግሞ ብዙውን ጊዜ ለባርነት ስለሚፈልግ ተመልሶ ካገሩ እንዳይወጣ ይከለክል ነበር። አፄ ምኒልክ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዚህ ሁሉ የክልል መንግሥት አሰቃቂ ጭቈናና እሰር ነፃ አስወጥተው፣ በወደደበት እንደፈለገ እንዲኖር አድርገዋል። መጥፎ ልማዳቸውንም አንለቅም ላሉት እንደነጂማ አባጅፋር ዐይነቶቹ ባላባቶች ደግሞ፣ “ማንም ሰው እወደደበት ቦታ ላይ ይኖራል እንጂ … በምንም መልክ ልትይዘው አይገባም፤ ድኻው እወደደው፣ እተመቸው ቦታ ይደር[28]” ብለው የሰጡት ትእዛዝ ማንኛዉም የቅኝ ገዢ ያራምድ ከነበረው መርህ ጋር በጣም ተፃርራሪ ነበር ማለት ይቻላል።

እንግዴህ አፄዎቹ ይልቁንም አፄ ምኒልክ ያደረጉት ታላቅ ሥራ ቢኖር፣ በየቦታው በነዚህ አምባገነን ባላባቶቻቸውና፣ ንጉሥ ነን ባዮች ገዢዎቻቸው ሥር፣ እንደእስረኞች ከጠባቡ ግዛታቸው ውስጥ ታጉረው፣ በሚዘገንን ጭቈና ይማቅቁ የነበሩትን ኅብረተ-ሰቦች ነፃ አውጥተዋቸው፣ የቋንቋና የሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ፣ በኢትዮጵያዊነታቸው ባሰኛቸው ቦታ እንዲኖሩ፣ የመላዋን ኢትዮጵያን ምድር ሀብታቸው ማድረጋቸው ነው። አፄ ምኒልክ ያዋሀዷት ኢትዮጵያ “የኅብረተ-ሰቦች እስር-ቤት ናት” ማለት ታሪክን ካለማወቅ ወይንም ከማጣመም የመነጨ ሲሆን፣ እውነቱ ግን ንጉሠነገሥቱ በባላባቶች ክልል ውስጥ ታስሮ የነበረውን ሕዝብ ነፃነት አቀናጅተውለት፣ በፈለገበት ሄዶ በእኩልነት እንዲኖር፣ በወደደውም የሥራ መስክ እንዲሰማራ አድርገዋል። በዚህም ሥራቸው መደነቅና መከበር ይኖርባቸዋል። በፈጠራ ታሪክ በመመሥረት ስማቸውን ማጒደፍ ደግሞ በታሪክ ያስጠይቃል[29]።

ይሁንና በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግሥት ደረጃ አንዳንድ ያስተዳደር ጕድለቶች መኖራቸው አይካድም። ቢሆንም ግን ያንድ የተወሰነ ዘውግ ወይንም የዘውግ አባል በመሆኑ ብቻ በይፋ የተንቋሸሸ፣ የተጨቈነና ዜግነቱን የተከለከለ፣ ከሥልጣንም ከዕድገትም የታገደ፣  ግለሰብም ሆነ ብሔርና ብሔረሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የለም። ከዚያም ባሻገር  የኢትዮጵያ ሥልጣኔና መንግሥት ካንድ ብሔረሰብ ወይንም አካባቢ ጋር የተቈራኘ ሁኖም አያውቅም። ሌላው ቀርቶ በዘመነ-መሳፍንት ፈርሶ የነበረው የሕዝቡና ያገሩ አንድነት መልሶ በዘመናዊ መልኩ እንደ አንድ አገረ-ግዛት የተቋቋመው፣ በብዙ ጐን በተለያየ መልክ የተወጣጣና የተሰለፈ ብሔርንና ብሔረሰቦችን ባቀፈ ኀይል እንጂ፣ ካንድ ከተወሰነ አካባቢ ወይንም ጐሣ በመነጨ ጦር አልነበረም። አገሪቷና ሕዝቧም ይመሩ የነበሩት ለማንም ሳያዳላ ገንዘቡና ዐቅሙ በፈቀደው መጠን ሁሉንም በእኩል በሚያስተዳድር መንግሥት ስለነበር፣ አንዱን ዘውግ ከሌላው በተለየ፣ በላቀና በሞለቀቀ መልክ የሚገዛ ሕግም ልምድም ሁናቴም ባገሩ ውስጥ ከቶውኑ አልታየም።

 

ኢትዮጵያ ያቀፈችው አሁንም ቢሆን እንደጥንት የተለያየ ቋንቋ የሚናገርና ሃይማኖት የሚያመልክ የሕዝብ ሙዚዩም” ስትሆን፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በበኩሉ የዚሁ ሕዝብ ጒንጒን ነው ማለት ይቻላል። አሁን ለሀገሬ ተቈርቋሪ ነኝ ከሚል ትውልድና ግለሰብ የሚጠበቀው፣ ባለፉት ያስተዳደር ጉድለቶችና በተደረጉት አለመግባብቶች ማትኰርና መወቃቀስ ፋይዳቢስ መሆኑን ዐውቆ፣ የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት ነው። ጃገማ ኬሎ የተባሉት ሰመጥሩ ጄነራል አንዴ እንዳሉት፣ በአስተሳሰብም ሆነ በሙያ ዘርፍ ጠባብ በነበረው በጐሦችና በባላባቶች ዓለም ይኖሩ የነበሩት አባቶች፣ የጀብዱነታቸው መለኪያና ምልክት በሚጥሉት ግዳይ በሚያስቈጥሩት ሚርጋ የተመጠነ ነበር። በዛሬ ዘመን ግን የጀብዱ ሚርጋ የሚቈጠረው እያንዳንዱ ግለሰብ ለአገርና ለኅብረተ-ሰብ ዕድገትና ልማት በሚሠራው ሥራና በሚያበረክተው አስተዋፅዖ ነው። ከዚያም አልፎ በተሰማራው የሙያ ዘርፍ በሚያደርገው ፍልሰፋና ምርምር እኩዮቹን ሲያስከነዳና፣ ለዓለም ሕዝብ በጠቅላላ ጠቃሚ አገልግሎት ሲሰጥ ነው። አፄዎቹ ኢትዮጵያን አንድ አገር በማድረግ፣ ይኸንን ዓላማችን አድርገን ባገር ውስጥም ሆነ በዓለም መድረክ ላይ እንድናበረክት ዕድሉንና በሩን በሰፊው ከፍተዋል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እውድድሩ ሜዳ ውስጥ ገብቶ ድርሻውን ለገዛ አገሩም ለዓለምም መክፈል እንዲችል፣ ነገሥታቱ አመቺ ሁናቴ አደራጅተዋል። አገሩን አደላድለው ካበቁ በኋላ የዘመናዊ ሥልጣኔን መሠረት ጥለው ሜዳውን አመቻችተዋል።

 

ካርል ማርክስ እንዳለው ጐሣነት የበግ ዐይነት ስሜት ነው። በደመነፍስ ብቻ አንዱ ሌላውን ይከተላል። ሰው ግን የመራቀቅና አስፍቶ የማየት ልቡና አለው። እኔ ሁለዬ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር፣ የዘውግና የክልል መስተዳድር አራማጆች ስብከታቸውን የሚያቀነቅኑት፣ ብዙዎቹ ወደፈለጉበት ሂደው እንዳሰኛቸው በሚኖሩበትና በሚሠሩበት በምዕራብ ዓለም ተቀምጠው ነው። እንዴት ነው እንደነዚህ ዐይነቶቹ በሰብኣዊ ልቡና የማይመራውን የጐሣንና የባላባቶችን ዓለም የሚያደንቁት። ለኔ እነዚህን ሁለቱን ማድነቅም ሆነ ከሞቱበት ለማንሣት መሞከር ከታሪክ ጋር ግብግብ መያያዝ ነው።  አያዋጣም። እንዲሁም አፄዎቹን ራሳቸውን መውቀስ፣ ከሙት ጋር መሟገት ሰለሆነ ርባን የለዉም። የራስን ድርሻ መወጣትና ከአባቶችና ከፊተኛው ትውልድ የተረከቡትን አሻሽሎ ለመጪው ትውልድ ማስተላለፍ ግን በታሪክ የሚያስጠይቅ የያንዳንዱ ሰው ግዴታው ነው።

 

 

 

[1] . ዘውገኝነት ስል የጎሣ ፖሊትካን፣ በዓለም አቀፍነት ደግሞ የካርል ማርክስንና የቪላድሚር ሌኒንን ር እዮተ ዓለም የሚያተናፍሱትን ነው የማመለክተው። አብዛኞቹ ዛሬ ባገራችን ያሉት ጐሠኞችና ጐጠኞች [ወያኔዎችንና የፓለቲካ አጫፋሪያቸውን ኢሕአደግን ጭምር] የግራዘመም ፖሊትካ አራማጆች ነበሩ ማለት ይቻላል። ወደጠባብ ብሔርተኝነት የፈለሱት የግራው ርእዮተ ዓለማቸው ክሽፎባቸው ሲቀር ነው።

[2] . ይኸንን በመላዋ ጥቁር አፍሪቃ ውስጥ ከታነጹት ከተሞች ጋር ማነጻጻር ነው። ከኤርትራ ከተሞች ጀምሮ በመላዋ አፍሪቃ የተገነቡት ከተሞች በፈረንጆች እጅ ናቸው ማለት ይቻላል።

[3] . ይኸ ከአናቱ ላይ ያለው የንጉሡን ስም የሚገልጸው ወገን ከመግቢያ ተጐምዶ የጠፋበት ጽሑፍ በሦስተኛ ዘመን አካባቢ የተጻፈ ሲሆን፣ ንጉሡ በኻያ ሰባተኛ ዘመነ-መንግሥቱ ስፊ ድል የሰጡlለትን አማልክቱን ማለትም ዜውስን፣ ኤራስ [ጨረቃ]ንና፣ ጳሰይዶስን ሊያመሰግን ሲል ባቆመ ባንድ የዘውድ ቅርጽ ባለው ድንጋይ ላይ የተጻፈ ሐውልት ነው;፡ ንጉሥ አስገበርኋቸው የሚላቸው የአገሮች ዝርዝር በቅርብ ጊዜ ሊቅ ላጲሶ ድሌቦ [የድሮው ጌታሁን ድሌቦ] ለኢሳት ሬድዮ ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለምልልስ “የአክሱማያን ግዛት ከዛሬው ትግሬና ኤርትራ ክልል አያልፍም ብለው የተናገሩትን ያስተባብላል።

[4] . ያገሩ ስም አክሱም ይሁን ወይንም ሌላ ስም ይኑረው በግልጥ የሚታወቅ ነገር የለም። ግን በድሮ ዘመን ብዙውን ጊዜ አንዳንድ መንግሥታት የሚጠሩት በሚገዙት አገር ስም ሳይሆን ታዋቂነት ባላቸው መናገሻ ከተሞቻቸው እንደነበር፣ ባሁኑ ጊዜ በሱዳን ስም በሚጠራው ጥንት በግእዝ ካሱ፣ በዕብራይስጡ ኩሽ፣ በጽርዕ ደግሞ ‘ኢትዮጵያ” ከሚባለው አገር ልንገነዘብ እንችላለን። ካሱ በብዛት የሚታወቀው በየጊዜው በተከታታይ ገናናነትን ባተረፉ መናገሻ ከተሞቹ በቄርማ (2400-1570 ዓመተ ዓለም [ዓ.ዓ.)፣ በናጳታ (900-590 ዓ.ዓ.)ና በመርዌ (590 ዓ.ዓ. – 350 ዓመተ ምሕረት [ዓ.ም.] ነበር። የአክሱምም አጠራር ከዚህ ልምድ የተለየ ላይሆን ይችላል የሚለውን ግምት ከንግግሩ ውስጥ ማስገባቱ ተገቢ ይመስለኛል።

 

 

[5] . አረመኔ ጐሣዎች ወራሪዎቹ መካከል ጥቂቶቹን ብቻ ለመጥቀስ ያህል ጀርመናውያን ቭሲጎቶችና ሂሩሎች፣ ሃኖችና ኦስትሮጎቶች፣ ዐረቦች ነበሩ። ወረራዎቹ ገብ እንዳሉ ኢጣሊያ በተለያዩ የየራሳቸው ገዢ ባላቸው ግዛቶች ተከፋፍላ ሕዝቡ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር በሰፊው ለመደበላለቅና ለመወላለድ እስከ፲፰፻፸፪ ዓ. ም. ድረስ ዕድል አልገጠመውም። ስለዚህ አሁንም ቢሆን ይልቁንም የሰሜኑና የደቡቡ ሕዝብ ሃይማኖቱ አንድ ቢሆንም በቋንቋና በባህል ባስተሳሰብ በጣም ይለያል።

[6] . የዱር አህያን ያላመዱት በቅሎንም ያስገኙት አገው ናቸው ተብሎ ይታመናል።

[7] . ጊዜው በፈረንጆች ታሪክ አገላለጽ

[8] . አማራ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ስሙ የሚነሣው ድግናጃን፣ ደጋዛንና ግዳዣን በመባል በተለያየ ስም የሚታወቅ የአክሱም ንጉሥ ከመናገሻው ወደመቶ ዐምሳ ሰባኪዎች ደብተራ ብሎ ከሠየማቸው በኋላ ሕዝቡን ወደክርስትና እምነት እንዲመልሱት ወደ”አማራ” ላከ በሚል ሰነድ ነው።

[9] . አገዎቹን የተካው ሰለሞናዊ ሥርወ-መንግሥት በሥልጣን ላይ በቈየው የዘመን ርዝመት አኳያ ለጊኒስ ቡክ ቢመረጥ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ያለምንም ክብረወሰን እንደሚያሸንፍ እርግጠና ነኝ። ያገዎች መንግሥት በጦር ሜዳ ቢሸነፍም፣ ታሪክ እንደሚነግረን ሥልጣኑን ለሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት የለቀቀው በሽምግልና ተደራርድሮ ነው። ድርድሩም እንደ አ.አ. በሺ ዘጠኝ መቶ ሰባ ዐምስት ዓ. ም. የሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት እስከፈረሰ ድረስ ከመላጐደል ተከብሮ ቈይቷል።

[10] . ከደቡቡም ሕዝብ የወያኔ መንግሥት ይመሳሰላሉ ብሎ ያመናቸውን አንዳንድ ብሔረሰቦችን አጠራቅሞ “ወጋጋዳሶ” የሚል ቋንቋ ፈጥሮ የወል መታወቂያቸውና መጠሪያቸው እንዲሆን ሞክሮ ነበር። ግን ሕዝቡ በከፍተኛ ደረጃ በመቃወሙ ምርጫ አጥቶ ዕቅዱን ለሟሟላት ዐርባ ሚሊዮን ብር ቢያጠፋም ወደኋላ ማፈግፈግና መሰረዝ የግድ ሁኖበታል።

[11] ሊቅ ሙሐመድ ሐሰን በቅርቡ ባወጡት “ኦሮሞና ክርስቲያኑ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ 1300-1700.” [Mohammed Hassen, The Oromo & The Christian Kingdom of Ethiopia, 1300-1700] መጽሐፋቸው የኦሮሞ ወረራ የተፈጸመው በሰላማዊ መንገድ ነው። በግራኝ ጦርነት አገሩ ተራቁቶ ስለነበር፣ ኦሮሞች በባዶው መሬት ሰተት ብለው ገቡ ይላሉ። ይሁንና አቋማቸው በጊዜው የነበሩት የውጭም የውስጥም አገር ጸሓፊዎች ከተውት ምስክርነት ጋር በግልጽ ይጋጫል ብቻ ሳይሆን እሳቸውም በተለያዩ በሌሎች ጽሑፎቻቸው እንዳደረጉ ሁሉ አሳማኝ የሆነ ተጨባጭ ማስረጃ አያቀርቡም።

[12] . አፄ ሠርፀድንግል እንደ አ.አ. በ፲፭፻፹ ዓ.ም. ድባርዋን የያዘውን ቱርክ እስተነአካቴው ከኢትዮጵያ ምድር ሊያባርሩት ይዘው ከሄዱት ጦር መካከል “የሰውን ደም ማፍሰስ የጠማው” የጋላ ጦር ነበር። Conti Rossini, trans. Ed., The Chronicle of Emperor Sarsa Dengel [Malak Sagad], p. 129

[13] . ትርጒሙ “የጽዮን ንጉሥና የኢትዮጵያ ነጉሠ-ነገሥት” ማለት ነው። ጽዮን የክርስቲያን እምነት የሚከተለውን የኢትዮጵያን ክፍል ሲያመለክት፣ ኢትዮጵያ ደግሞ የተለያየ እምነት የያዘውን አገር በሙሉ ያካትታል።

[14] . የንግሥ ስሟ አድማስ ሞገሳ የአፄ ዘርዐ-ያዕቆብ ባለቤት ነበሩ

[15] . ጸሓፊው አባቱ ከወረብ፣ እናቱ ከጐናን ምድር ሲሆን የተወለደው በመጤንት በደርኀ ምድር ነው ይላል። አንዳንድ ጸሓፊዎች ቦታዎቹ በወለጋ ውስጥ ይገኛሉ ቢሉም የተረጋገጠ ነገር የለም።

[16] . ገብረሕይወት ባይከዳኝ የማስተዋል ጸጋ የታደላቸው ታላቅ ምሁር ናቸው። ሕይወታቸው ባጭሩ ባይቀጭ ኖሮ፣ ላገራችን ብዙ ዕውቀት ባበረከቱ ነበር። ስለታሪክ ጸሓፊነት አስፈላጊ መስፈርቶች ሲናገሩ፣ ታሪክ መጻፍ በጣም አስቸጋሪ ሙያ ነው ብለው አበክረው ካስገነዘቡ በኋላ፣ መሟላት አለባቸው የሚሉትን ሦስት የሚቀጥሉትን ነገሮች ያማጥናሉ። አንደኛ፣ ድርጊቱን ለማስተዋል አመዛዛኝ ልቡና፤ ሁለተኛ፣ ድርጊቱን ለመፍረድ የማያዳላ አእምሮ፤ ሦስተኛ፣ያመዛዘኑትንና የፈረዱትን ለማስታወቅ የጠራ የቋንቋ አገባብ ናቸው ይላሉ። የሚያሳዝነው ብዙዎቹ የኢትዮጵያ ታሪክ ምሁራን ነን ባዮች የገብረሕይወትን ምክር ለማሟላት ተቸግረዋል።

[17] . በቅርቡ ሊቀማእምራን (ዶር.) ሕዝቅኤል ኢብሳ “Ethiopia: An Oromo Dilemma. The National Question and Democratic Transition” በሚል ርእስ በድረገጾች ያሰራጩት ጽሑፍ በሰገሌ ምድር፣ ባንድ በኩል በልጅ ኢያሱና በአባታቸው ንጉሥ ሚካኤል በሌላው ደግሞ በልጅ ተፈሪና (ኋላ አፄ ኀይለሥላሴ) በደጋፊዎቻቸው መካከል የተካሄደውን የሰገሌ ጦርነት በሚገርም መንገድ በወሎ ኦሮሞችና በሸዋ አማሮች እንደሆነ አድርጎ ያቀርበዋል። በሁለቱም በኩል የሚዋጉት አብዛኞቹ ኦሮሞች ወይንም የኦሮሞ ደም ያላቸው ሲሆን፣ ምሁሩ እንዴት አድርገው እንደዚህ ለመደምደም እንደበቁ አይናገሩም። ሊቁ በጀርመን አገር በታተመው በEncyclopedia Aethiopiaca ይልቁንም በኦሮሞ ታሪክ ዐምድ [vol. 4 O-X] ላይ በተጻፈው ብዙ የተዛባ ግንዛቤና አስተያየት አስቀምጠዋል። ጽሑፎቹ የሚከተሉት እንደነጆን ማርካኪስን [John Markakis] የመሰሉ ያገሩን ባህል ቀርቶ ቋንቋውን በፍጹም የማያውቁ ግራዘመም ምሁራንን ነው። እንደዚህ ዐይነቱ የታሪክ አተረጓጐም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ምሁራን ታሪክን የፖለቲካ ደንገጡር እንዳደረጓትና ምንስ ያህል የባዕዳን ቃል አስተጋቢዎች መሆናቸውን ነው።

[18] . ልክ ለ፲፫፻፹፰ ዓ. ም. ተለያይቶ የኖረ ሕዝብ ነበር ማለት ይቻላል።

[19] በኢጣሊያንኛ  “politica periferica” ይሉታል።

[20] . በኢጣሊያንኛ “politica scioana e politica tigrina” በመባል ይታወቃል።

[21] . በአፄ ምኒልክ ብልሃትና ችሎታ “የትግሬና የሸዋ ፖሊትካ፣” ኢትዮጵያን ከመበታተን ይልቅ ኢጣሊያንን እትልቅ ሽንፈት ላይ ጣላት።

[22] . ዘገባው “ኀይሥላሴ እያካሄዳቸው ያሉት ሥራዎች እጅግ አስደናቂ ከመሆናቸው የተነሣ፣ ሁናቴው በዚህ መልኩ ከቀጠለ እስካሁን የምናውቃት ትላንት በጥንት ባህሏ ተዘፍቃ የነበረችው [ኢትዮጵያ]፣ በጣም አጭር በሆነ ጊዜ ውስጥ ወደከፍተኛ ዘመናዊ ሥልጣኔ ትደርሳለች” ብሎ ከደመደመ በኋላ፣ የዳር ፖሊትካ እንዳልሠራና በትጋት አጠናክሮ በግብር መተርጐም እንዳለበት ይናገራል።

[23] . መጽሐፉ ተሰሚነት ለማግኘት፣ “ኢትዮጵያውያን ግብረ-ገብ የሌላቸው፣ ክብረኅሊና የጐደላቸው፣ ምግባረ ብልሹና በተፈጥሯቸው ብስብስ የሆኑ ሕዝብ ናቸው። … የሚኖሩት በጉልተኛ ባላባት ሥርዐትና በባርያ ፍንገላ ነው። … አማሮች የተለያዩ ነገዶችን በብርቱ በመጨቈን ላይ ይገኛሉ፤ አገሪቷ የብዙ ሕዝቦች እስርቤት ናት” በማለት ኢጣልያኖች ይነዙ የነበሩትን ስብከት ያሰራጫል።

[24] . ሌሎቹ የኢጣሊያን ቅኝ ግዛቶች ባዲሱ መዋቅር ገብተው ከነስማቸው ሲቀጥሉ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ጠፍቶ፣ በካርታው ላይ የነበረው ስም የኢጣሊያን ምሥራቅ አፍሪቃ “Africa Orientale Italiana = አፍሪቻ ኦሪየንታሌ ኢታሊያና” ነበር።

[25] . በታሪክ እንደምናውቀው ሒትለር በአውሮጳ ወረራው ከያዛቸው አገሮች መካከል ነምሳ የመጀመርያዪቷ ነበረች።

[26] . “የጒልተኛ ባላባት” ሥርዐት ስል አውሮጳውያን ፊውዳሊዝም [feudalism] የሚሉትን ከሮማውያን ውድቀት ማግሥት ላይ የታየውን ሥርዐት ነው። የተማሪዎቹ ታላቁ ስሕተት አንደኛው የማኅበረሰብን ጥበብ [science] ልክ እንደሌላው የተፈጥሮ ጥበብ መልክ ማየታቸው ነው። ሁለተኛው ደግሞ በመምሰልና በመሆን መካከል ያለውን ልዩነት ባገባቡ አለመገንዘባቸው ነው። የኢትዮጵያ የመሬት ሥሪትና የምጣኔ ሀብት ቅርጽ ባንዳንድ ነገር ከአውሮጳውያኑ የጉልተኛ ባላባት ሥርዐት ይመሳሰላል። ግን በምንም መልኩ አንድ አይደለም። ባገራችን የባርያ ሥርዐት እንዳልነበረ ሁሉ፣ በማርክስ የተዋረድ እርከን ተከታዩ የነበረው የጉልተኛ ባላባት ሥርዐትም ከቶ አልነበረም።

[27] . የአፍሪቃን ቅኝ ገዚዎች የተካችው አሜሪቃ በቀዝቃዛ ጦርነትና በዐረብ-እስራኤል ግጭት ሰበብ ከሺ ዘጠኝ መቶ ስድሳዎቹ መጨረሻ ላይ ጀምሮ የነበራት መምርያ ከድሮው ከአውሮጳውያንን መርህ ብዙም የማይለይ እንደነበር የሚቀጥለው ክሲንጀር ለአሜሪቃ መንግሥት ያቀረበው ዘገባ የተወሰነም ቢሆን ጠቃሚ ፍንጭ ይሰጣል። “ኢትዮጵያ ሰላም ካገኘች፣ ሕዝቧ ሠራተኛና ታትሪ ሰለሆነ፣ በዓለም ብድር ዕዳም እንደሌሎቹ የሦስተኛ ዓለም አገሮች ተዘፍቃ የማታውቅና የኰራች አገር በመሆኗ አንድ ቀን አድጋ ራሷን የቻለች አገር ትሆናለች። ዕድል አግኝታ በዘመናዊ ሥልጣኔ ቢትገፋ፣ የሚትቻል አገር አይደለችም። ስለዚህ ከንጉሥ ኀይሌ ሥላሴ በኋላ ኢትዮጵያን የሚመራ መንግሥት ሰላም እንዳያገኝና፣ አገሪቷም እንደዐረብ አገሮች ተከፋፍላና ተነጣጥላ ካልተበታተነች በስተቀር፣ ለወደፊቱ በቀይ ባሕር ላይ አሜሪቃ የሚትጫወተው ሚና እንዳይመነምን እንዳያድጉ ማደናቀፍ ከሚገባቸው በቀይ ባሕር አዋሳኝ ታዳጊ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ መሆን አለባት። የቀይ ባሕር ወተት የሆነውን የዐረብን ነዳጅ በነፃ አለቀረጥ ማለብ የምንችለው፣ መንግሥታችን ኢትዮጵያን ከጎረቤቷ ከሱማሌ ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ክፍለ ሀገሮቿን ራሳቸውን በሰሜንና በደቡብ ከፋፍሎ፣ የደከመውን ወገን በመርዳት፣ ያላመፀውን ጐሣ በማነሣሣት፣ ከዳር ድንበሯ ዘላለም ሁከትና ጦርነት እንዳይለያት በማድረግ፣ ፀረ-መንግሥት ተዋጊዎችን በሲአይኤ በማደራጀት በአገሪቷ ሰላም በመንሣት ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንካራና ብርቱ ቢሆንም ቅሉ፣ በሥልጣን ፍላጎቱ ደካማ ጐን አለው። አንዱ በሌላው ላይ መንገሥ ዋና ምኞቱ ነው። በታሪካቸው ደሞክራሲያዊ መንግሥት መሥርተው አያውቁም። ከጥንት ጀምሮም ቢሆን አንዱ ንጉሥ ሌላውን በመግደል ሥልጣን መቀማትና ማመፅ ባህላቸው፣ ልማዳቸውና ታሪካቸዉም ነውና፣ እኛ ያሳደግነው ውሻም ቢሆን ሊነክሰን ቢሞክር በማስገልበጥ፣ ላንዲት ዘመን እንኳ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላም ሳይኖር፣ ሰሜናዊና ደቡባዊ፣ እንዲሁም ኤርትራ፣ ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ እየተባባሉ እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ለረጅም ጊዜ ከኖሩ፣ ቀይ ባሕር ለአሜሪቃ መንግሥት ጠቃሚ በር ሁኖ ይኖራል። ሱማሌና ኢትዮጵያ ሰላም ሁነው አንድ ቀን ከተባበሩ፣ የአሜሪቃ ታላቅነትና ብልፅግና በቀይ ባሕርና በዓለም ላይ አይኖርም። ኢትዮጵያና ሱማሌ እማዶ ካሉት የዐረብ አገሮች ጋር በቀይ ባሕር ጥቅም ላይ ተስማምተው ቢዋዋሉ፣ የአሜሪቃና የአውሮጳ ሕዝብ “ቡፋሎ” ፍለጋ ወደጫካ መሄድ ካልሆነ በስተቀር፣ ጥበባችንን እንኳን ሽጠንና ለውጠን ለመኖር እንችልም። ሊቃውንቶቻችን ወደአፍሪቃ ሲፈልሱ ከሩቁ ማየትና መገንዘብ የኛ ተራ እንደሚሆን አንርሳ።” (ይኸ አሳብ በዶክተር ሔንሪ ክሲንጀር “የቀይ ባሕር ለጦር ሰልት ያለው ጥቅም” በማለት ለመንግሥታቸው ያቀረቡት ጥናት ሲሆን የአሜሪቃ መንግሥት የፓለቲካ መርህ መሆኑን በየጊዜው የወሰዳቸው ርምጃ ይደግፈዋል።)

[28] . በቅኝ ግዛት ባሉት አገሮች ያገሩ ተወላጅ ሕዝብ ወደፈለገበት አካባቢ ሄዶ ለመኖርና ለመሥራት ከፈለገ ልዩ መታወቂያ ያስፈልገዋል።

[29] . እዚህ መነሣት የሚገባው የኦሮሞ ምሁራን ነን ባዮች ዘውገኞች በየቦታው የሚነዙት ስብከት ነው። በቅርቡ ደግሞ እንደነሊቀማእምራን ጌታሁን [ላጲሶ] ድሌቦ የመሰሉት ዐይነቶች ወደዚህ እምነት እንደገቡ ኢሳት በተባለው የብዙኃን መገናኛ በሰጡት አሳፋሪ ቃለመጠይቅ መገንዘብ ይቻላል [Getahun Lapiso Interview on ESAT Radio October 15, 2015]።

↧

አላሙዲ በ70 ዓመታቸው ሞቱ የሚለውን የሃሰት ዜና ያሰራጨው ትክክለኛው ቴሌግራፍ ድረገጽ አለመሆኑ ታወቀ

$
0
0

alamudi

(ዘ-ሐበሻ) ሼህ መሀመድ አላሙዲ በ70 ዓመታቸው በለንደን ሃገር ሕይወታቸው አለፈች ብሎ ያወራው ድረገጽ ትክክለኛው የ እንግሊዙ ቴሌግራፍ ጋዜጣ አለመሆኑ ታወቀ::

በቴሌግራፍ ድረገጽ በተመሳሳይ የተከፈተውና Te1egraph (ከTe ቀጥሎ 1 ቁጥር) የገባበት የውሸት ድረገጽ ነው:: ትክክለኛው Telegraph ድረገጽ አላሙዲ ሞተ ብሎ አለማውጣቱ የታወቀ ሲሆን ይህ ዋሾ ድረገጽ ያወጣውን መረጃ በርካታ ሰዎች በሶሻል ሚድያዎች እያሰራጩት ይገኛሉ::

እንዲህ ያሉት መረጃዎች ሆን ተብለው የሕዝብን የትግል አቅጣጫ ለማስቀየር የሚሰራጩ በመሆኑ ሕዝብ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ይመከራል::

↧

የማለዳ ወግ …የኮንትራት ሰራተኛዋ ኢትዮጵያዊት መጨረሻ   ! –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0
የማለዳ ወግ … የኮንትራት ሰራተኛዋ ኢትዮጵያዊት መጨረሻ   !
===================================
* አሰቃዩኝ “ስትል ፍልቅልቋን የ 6 ዓመት ብላቴና ለሚስን ቀጠፈቻት :(
*  ገዳይ ኢትዮጵያዊት ትናንት በሞት ተቀጣች  :(
* ዘምዘምም ለሚስም ልብ ይሰብራሉ  :( ሁሉም ልብ ይሰብራል  :(

a79  ይህን ሁለት ቀን ተረብሻለሁ ፣ ምክንያቴ ብዙ ነው ፣ ከምንም በላይ ከሪያድ የደረሰኝ መልዕክት ህመም ሆኖማል  ሰው ልምጣ ሲል እሷ ” የመጨረሻ ቀናቶቸን የወላጆቸን አይን ሀገሬን ልይ እርዱኝ  !  ወደ ሀገሬ እንድገባ እርዱኝ !” የምትለው ታማሚ የኮንትራት ሰራተኛ እህት  መልዕክት ጨካኙን ሰው ሆዴን አባባው  :(   ማምሻውን  ያነኑ ቪዲዮና ድምጽ ሳስተካክል ሌላ መረጃ እዚያው ሪያድ ደረሰኝና ቅስሜ ሰብር ብሎ አመሸ  …  ኢትዮጵያዊቷ ሌላ የቤት ሰራተኛ በሞት መቀጣቷን ሰማሁ  ! እናም ወደ መረጃው አቀናሁ … ድርጊቱ ሲፈጸምና መረጃው ሲናኝ ተከታትዬ መረጃ አቅርቤበት ነበርና ያንኑ ጊዜ እያስታዎስኩ የፍርድ ውሳኔውን ዜና ገለባብጨ አነበብኩት  !

” አተርፍ ባይ አጉዳይ  ”
===============
ከሶስት አመት በፊት ለሚስ የተባለችውን የ 6 ዓመት ታዳጊ ሳውዲ ብላቴና ” በጭካኔ አንገቷን በማረድ ገድላለች !”  የተባለችው  ኢትዮጵያዊቷ ዘምዘም አብደላ  ትናንት ሰኞ መስከረም 16 ቀን 2009 ዓም ሪያድ ላይ  በሞት ተቀጥታለች  !  … የኢትዮጵያዊቷን የቤት ሰራተኛ ዘምዘም በሞት መቀጣትን መረጃ ይዘው የወጡት የሳውዲ ጋዜጦች በዘገባቸው ዝርዝር መረጃም አካትተዋል ። የቀረበው መረጃ  እንደሚያስረዳው ዘምዘም እአአ  June 2013 ዓም ከሪያድ ሰሜናዊ ክፍል በ150 ኪሜትር ርቀት በምትገኘው  Hota Bani Tamim በተባለች ትንሽ ከተማ ከሃገር ቤት በኮንትራት መጥታ በሳውዲ አሰሩዎች ጋር ትሰራ ነበር ፤ ይሁን እንጅ ዘምዘም ከምትሰራባቸው አሰሪዎቿ ጋር ስምምነት አልነበራትም …  ባንዱ ክፉ ቀን ዘምዘም ” በደል ፈጽመውብኛል ” ብላ በአሰሪዎች የደረሰባትን በደል ለመበቀል ታዳጊዋን ብላቴና ልጃቸውን የ 6 ዓመቷን ለሚስን መግደሏን እአአ Dec. 2013 ዓም ሪያድ ላይ በዋለው ፍርድ ቤት ቀርባ የእምነት ክህደት ቃሏን መስጠቷ ተጠቁሟል። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን በማጣራት እንድትገደል በወሰነው መሰረት በኢትዮጵያዊቷ ዘምዘም ላይ የሞት ቅጣቱ ትናንት ሰኞ ሪያድ ላይ መተግበሩ ታውቋል  !

በወቅቱ የብላቴናዋ የሚስን ግድያ በመላ ሳውዲ ከፍተኛ የዜና ሽፋን ተሰጥቶት የነበረ መሆኑ ይጠቀሳል ።  ሳውዲዋ ብላቴና የለሚስና ሌላ ኢስራ የተባለች  የ 11 አመት ሶርያዊት ታዳጊ ላይ ኢትዮጵያውያን በቤት ሰራተኞች ተፈጸመ የተባለውን አሰቃቂ ወንጀል  ተከትሎ ሳውዲ  ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማስመጣት ማገዷ ቀዳሚ ምክንያት ነበር ። ይህንን ሳውዲ የምትኖሩ  የምታስታውሱት አትኖሩም አልልም  …

a78

ቀጣዩ ህምም …
============
ይህ በእንዲህ እንዳለ በተመሳሰይ ግድያ የተወነጀሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች በተለየያዩ የሳውዲ ወህኒ  ቤቶች እንደሚገኙ መረጃዎች ያስረዳሉ ። ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የኢንባሲና ቆንስል ተወካዮች ክትትትል ማድረግ ያለባቸው የዜጎች ጉዳይ በየፍርድ ቤቱ በእንጥልጥል ላይ ያለ ጉዳይ ቢሆንም የመንግስት ተወካዮች ክትትል እያደረጉ ስለመኖሩ መረጃው የለኝ ። ያም ሆኖ ጉዳያቸው በሳውዲ መንግሥት ከፍተኛ የሸሪአ ፍርድ ቤት በኩል እየተጣራ ወንጀለኛ መሆናቸው ሲረጋገጥ ሳውዲ በምትመራበት የእስልምናው የሸሪአ ህግ መሰረት ተመሳሳይ የሞት ቅጣት ውሳኔ እንደሚተላለፍባቸው ይጠበቃል  ።  ይህም ቀጣዩ ህመም ሆኖን ይዘልቃል  :(

ማነው ተጠያቂው  ?
=============
ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ዘንድሮ ” ህጋዊ አልነበረም ” በተባለው ሳውዲ ሰራተኛ ከኢትዮጵያ ማስገባት እገዳ ከመጣሏ አስቀድሞ በነበረው የስራ ስምሪት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የኮንትራት ሰራተኞች ወደ ሳውዲ መግባታቸው አይዘነጋም ። እውነት ነው ፣  በሰራተኛ ዝውውሩ የኤጀንሲ ባለቤቶች ፣ ሰራተኛ አቅራቢ ደላሎች   ፣ እዚህም ሳውዲ ሆነው ከኤጀንሲ ጋር ተሻርከው በሰራተኛ ድለላ አቅርቦቱ የተሳተፉ በርካታ ለመንግስት ቅርብ የሆኑ የምናውቃቸውና የማናውቃቸው የብዙ ደላሎች ህይዎት ተቀይሯል  ፣ በአጭር ጊዜና  በአንድት ጀንበር የናጠጡ ሃብታም ባለንብረቶች ሆነዋል !  በአንጻሩ የብዙ የድሃ ልጆች ያለ እድሜያቸው እድሜ እየቆለሉ መጥተው ያሉበት ሳይታወቅ የውሃ ሽታ ሆነዋል ፣ ጠፍተዋል  ፣ ታመው ወደ ሃገር ተለከውም ሳይላኩም የወላጅ አንጀት ታጥፏል  ፣ የወላጅ ቤት ተዘግቷል ፣ የእልፍ አዕላፍ ወላጅ እናቶች ቤት በሀዘን ተውጧል   !  በሀገር ደረጃም ስለመከበር መናቃችን ይህው ያለ ዝግጅት የተፈጸመው የስራ ስምሪት ለመሆኑ በድፍረት እነግረችኋለሁ ፣ እንግዲህ ጥቅም ፣ ጉዳት ትርፉን መዝኑት  … ? !!!

ለሀገር  ፣ ለባህሉ ፣ ለሐይማኖቱ ፣ ለቋንቋውና ለስራ ጸባዩ እንግዳ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በኮንትራት መጡ ተብሎ አመት ሳይደፍን  ራሳቸውን ሲያጠፉ ፣ አብደው ባልተለመደ መልኩ በአደባባይ ሲዘዋወሩ ተመልክተን የመንግሰት ያለህ ብንል ሰሚ አልተገኘም ። ከአማካሪ እጦትና ከጭንቀት ራሳቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው እስከ ግድያ ወንጀል የሚፈጽሙ የሉም አይባልም ። ታዝበናል ፣ እነሱም መብት አስከባሪ ተከራካሪ ባያገኙም (  ፈጸሙት የሚባለው ወንጀል ከፋ እንጅ ) ወንጀል ለመፈጸማቸው ምክንያቱ  የደረሰባቸው በደል መሆኑን መናገራቸውንም እውነት ነው  ፣ ተደጋግሞ ይጠቀሳል !

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል በስራ ብዛት ታመው ፣ ተደፈርን ፣ ተደበደብን  ፣ ግፍ ተፈጸመብን ብለው ወደ ኢንባሲና ቆንስል መስሪያ ቤቶች የሚመጡት መፍትሔና ሁነኛ ድጋፍ ባያገኙም ችግራቸውን በመናገራቸው እና ተከላትመውም ቢሆን በጉትጎታ ብዛት ወደ ሀገር መላክ መቻላቸው እድለኞች  ናቸው ማለት ይቻላል ።  ያሉበት ሳይታዎቅ ፣ ሞቱ ዳኑ የሚባል መረጃ የማናገኝላቸው ፣ አድራሻቸው የማይታወቅ  በርካታ ኢትዮጵያውያን አሁን ድረስ በየ ሳውዲው ተላልቅና ትናንሽ መንደሮች ይገኛሉ  !

በቂ ዝግጅት ሳይደረግ ” በቂ ዝግጅት ተደርጓል  !” በማለት በግፍ ዜጎችን በሌለና ባልተፈረመ የሁለት ሀገራት ስምምነት ዜጋን ለሌላ ሀገር ለስራ የማቅረቡ እርምጃ ተጠያቂው ማነው  ? ስምምነት በሌለበት ሁኔታ  በተራ “ሚሞረንደም ”  ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጋን ወደ ሳውዲ መላክ ከአንድ መንግሰት ይጠበቅ ነበርን  ?  አሁን በአረብ ሀገራት የምናየው የዜጎች እንግልት የዚህ ሁሉ በግዴለሽነት ሥራ ውጤት አይደለምን  ?  “አይደለም ?” የምትሉ ካላችሁ እማኝ ፣  ዋቢው ሞልቶ ተርፏል  ፣ ዘርዘር አድርገን በመረጃ ማስረጃ መነጋገር እንችላለን !

አሁንም አልመሸም  !
=============
አሁንም መንግሥት ባለድርሻ አካላት ሳንመክርበት ባጸደቀው  አዲስ የስራ ስምሪት ስምምነትን ዘንድሮ ከሳውዲ ጋር ለመፈራረም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ  መሆኑን አውቃለሁ  ፣ ይህንን አዲስ ስምምነት መፈራረም ጋብ አድርጉና ከዚህ ቀደም በኮንትራት ስራ  ስም የተበተበውን ዜጋ ሰብስቡት   !  አሁንም አልመሸም … በኮንትራት መጥተው ደመወዝ ሳይቀበሉ ፣ በስራ ብዛት ታፍነው መውጫ መግቢያ የጠፋቸው ፣ በስቃይ ላይ የሚገኙ ሞልተው ተርፈዋል … እነዚህን ወገኖች መታደግ ገጽታን መገንባት ነው …እነዚህን እህቶች ለችግር ጭንቀታቸው መድረስ ተበሳጭተው ወንጀል ከመፈጸም እንዲታቀቡ መርዳት ነው …  ከዚህ በተረፈ የተቸገሩትን ማዳን ከተፈለገ ይቻላል ! የታመሙ ፣  የደከሙትን ለመርዳት ልባችሁ ቀናኢ ከሆነ የተበተኑትንና በችግር ላይ ያሉትን ዜጎች ድምጽ ስምታችሁ ወደ ሀገራቸው መላክ ይቻላችኋል  ፤ ብቻ  ቅና  እዝነ ልቦና ይኑራችሁ !

ዘምዘምም ለሚስም ልብ ይሰብራሉ  :(
=========================
ካለፈው ጥፋት ካልተማርን እያለቅስን መኖራችን ግድ ነው  ፣  የዘምምዘም ጭካኔ ቢሰቀጥጥም መጨረሻዋ ያሳዝናል  :(  …  ከሀገር ቤት ስትመጣ ነፍሰ ገዳይ ሆና ለሚስን ለመግደል ደም ጠምቷት ነበርን  ?  አይደለም …  ! … ዘምዘም ለፍርድ ቤት ሰጠችው ከተባለው የእምነት ክህደት ቃሏ እንኳ ብንነሳ ዘምዘም በአሰሪዎቿ አያያዝ ተማራ ፣ ከአሰሪዎቿ ጋር ተጋጨታ ፣  ሰይጣን አሳስቷት  ” አሰቃዩኝ “ስትል አቅሏን አጥታ ለበቀል መዳረጓ እውነት ነው … እናም ዘምዘም የምትወዳትን ፍልቅልቋን የ6 ዓመት ብላቴና ለሚስን ቀጠፈቻት  :(  እሷም ሳታልም ሳታስበው ”  አተርፍ ባይ አጉዳይ ሆና  !  እንደወጣች ቀረች ፣ ትናንት የመጨረሻዋ ሆነና ገድላለችና ሰይፍ በአንገቷ ላይ አረፈና ፣  ተገላለች   :( ዘምዘምም ለሚስም ልብ ይሰብራሉ  :(  …ሁሉም ልብ ይሰብራል   :(
( ከዚህ ጋር የፍልቅል የብላቴናዋ  የለሚስንና የእኛዋን ዘምዘምን ፎቶ አያይዥዋለሁ )

እስኪ ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 17 ቀን 2009 ዓም

↧
↧

*ፋሲል ከነማ፡ እንደማንነት መገለጫ* (ዳዊት ግርማ)

$
0
0

 

(ጎንደር ፋሲል ግምብ - ፎቶ ፋይል)

(ጎንደር ፋሲል ግምብ – ፎቶ ፋይል)



ፋሲል ከነማ (አጼዎቹ) ጎንደር ፋሲለደስ ኳስ-ሜዳ ላይ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በማሸነፍ አራት ጨዋታዎች እየቀሯቸው ነበር ወደፕሪሚየር ሊግ መግባታቸውን ያረጋገጡት፡፡ ፋሲል ጅማ አባ ቡናን 3ለ1 በማሸነፍ ደግሞ የከፍተኛ ሊጉ ቁንጮ ሆነው በዋንጫ ደምድመዋል፡፡ ፋሲል ከነማ አመቱን ሙሉ በከፍተኛ ሕዝባዊ መነሳሳትና ድጋፍ ሲደገፍ እንደነበረ እናስታውሳለን፡፡ ቡድኑ ኢትዮጵያ ውስጥ በክለብ ፍቅር፣ ከሜዳ ውጭም አብሮ በመጓዝ በከፍተኛ የደጋፊ ቁጥር ከሚደገፉ እግር ኳስ ቡድኖች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የእግር ኳስ ቡድኑ በሃገር ውስጥና ውጭ የደጋፊዎች “የፌስቡክ ገጽ” ቅስቀሳ በማድረግ፣ መረጃዎችን ፈጥኖ በማድረስና የግጥሚያ ላይ ቀጥታ (ትኩስ) መረጃዎችን በየደቂቃው በማድረስ ተምሳሌትነት እንደነበረው ማንሳት ይቻላል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ ፈረንጆቹ  12ኛ ተጫዋች የሚሉት ደጋፊ ፋሲለደስ ላይ 12ኛና 13ኛ ሆኖ ተሰልፏል፡፡ የአንጋፋው ክለብ ደጋፊዎች ከተጫዋቾች ባልተናነሰ ተጫውተዋል፡፡ ቀይና ነጩን መለዮና የአንገት ፎጣ (ስካርፕ) በማድረግ ጎንደር ላይም ከጎንደር ውጭም ከቡድናቸው ጋር አብረው ተጉዘዋል፡፡ በጩኸታቸው የኢያሪኮን ግንብ እንደናጡት ቤተ አይሁድ፣ ፋሲሎችም በጩኸታቸው ተጋጣሚን በማርበድበድ፣ ተጫዋቾቹን በማነሳሳት ተአምር ሰርተዋል፡፡ ይሄ ሁነት የሚጨምር እንጂ የሚቀንስ እንደማይሆን ይጠበቃል፡፡ ከፋሲለደስ ከተማ ውጭ ያሉ ጎንደሬዎች፣ ከጎንደር ውጭም ያሉ አማራዎች ከአማራ ውጭም ያሉ ሌሎች ኳስ ወዳዶች በክለቡ ፍቅር ሲወድቁ እያየን ነውና፡፡

በመቀጠል ኳስን የማንነታቸው መገለጫ ያደረጉ ሃገራትን፣ በኳስ ቡድናቸው ማንነታቸውን ያወጁና የገለጹ ቡድኖችንና ማህበረሰቦችን፣ እና የኳስ ቡድኖችን ተያያዥ አለማቀፋዊ ታሪኮችን በማቅረብ የፋሲልን እውነታ በዚያ መለኪያነት ላቅርብ፡፡

** ኳስ እንደማንነት ማሳያ **

*ዓለም አቀፍ አውድ*

ማንነት የአንድን ተመሳሳይ ስነ ልቦናዊ ስሪት ያለው ሕዝብ ልዩ ልዩ እሴቶች ያቀፈ መገለጫ ነው፡፡ ማንነት የአንድ ማሕበረሰብ ማን እንደሆነ ማሳወቂያ፣ የእኔነቱ መገለጫ ነው፡፡ የማንነት ጽንሰሃሳብ ውስብስብና ገጸ-ብዙ ነው፡፡ ይህን ማንነት ግለሰቦች ከተለያዩ የባህል እሳቤዎች አንጻር በመቃኘት ይገልጹታል (Archetti, 1994)፡፡ እንደ Archetti  ገለጻ የእግር ኳስ ቡድኖች ማንነትን በመሳል ረገድ ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው፡፡

እግር ኳስ የማንነታቸው መለኪያ የሆኑ በርካታ ሃገራትና ማኅበረሰባት አሉ፡፡ ብራዚል ውስጥ ኳስ ሁነኛ የሃገሬው መገለጫ ነው፡፡ ኳስ ብራዚል ሃገር ከጨዋታነት የዘለለ ትርጉም አለው፤ሁሉ ነገራቸው ነው ማለት ይቀላል፡፡ የአያሌ ብራዚላውያን ህጻናት ህልም “ስመጥር ኳስ ተጫዋች መሆን” ነው፡፡ ብራዚል የእግርኳስ ቱሪዝም መዳረሻ ሃገር ናት፡፡ ውብ የባህር ዳርቻዎቿን ከውብ ቆነጃጅቷ በተጨማሪ ህጻናት አሸዋ ላይ ኳስ ሰያንቀረቅቡ ትመለከቱባቸዋላችሁ፡፡ በርካታ የዓለማችን ታላላቅ እግር ኳስ ቡድኖች መልማዮች የታዳጊዎች ፕሮጄክቶችንና የሊግ ውድድሮችን በመታደም የወደፊቱን የኳስ ንጉስ ህጻን ቀድሞ ለመቅለብ ወደብራዚል ይጎርፋሉ፡፡ የአውሮፓ ኃያላን ክለቦች የታዳጊ ማሰልጠኛዎችን ብራዚል ውስጥ ከፍተዋል፡፡ እናም ኳስ ለብራዚል ከዋነኛ የእድገት ምንጮቿ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 ዓ.ም የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመው በዓመት በአማካይ 100 ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች በሽያጭ ከብራዚል ወደተለያዩ ክለቦች ያመራሉ፡፡ ከዚያም ረብጣ ዶላር ወደእናት ሃገር ይዘንባል፡፡ ኳስ ማንነት ነው- ብራዚል፡፡ ብሔራዊ መለዮም ነው፡፡

ፍራንሲስኮ ሪቻቲ `La Roma: Soccer and Identity in Rome` በሚለው መጣጥፉ የ20ኛው ክ/ዘ የሮም ታሪክ፣ ባህልና ማንነት ከዋናው ክለቧ ከኤ.ኤስ ሮማ ጋር እንደሚቆራኝ ይናገራል፡፡ የ“ሮማ” ቡድን በሮም ነዋሪ የለት-ተለት የህይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና  ይጫወታል ይላል፡፡ 48 በመቶው የሮም ህዝብ ሮማን ይደግፋል፤ 12 በመቶው ደግሞ ሌላኛውን የሮም ከተማ ክለብ ላዚዮን ሲደግፍ ቀሪው ደግሞ ለኳስ ደንታቢስ ነው የሚለው ሪቻቲ ደንታቢሱም ቢሆን በቤተሰቡ፣ በጓደኛው አሊያም በስራባልደረባው በኩል ሮማ ሕይወቱ ውስጥ አይጠፋም ይላል፡፡ እናም ሮማ የሮም መለያ ነው፡፡

ቤል (1994)፣ እንደሚለን እግር ኳስ በተለይ ከ19ኛው ክ/ዘመን ማብቂያ ጀምሮ በብሪታንያ ቁልፍ የማንነት መገለጫ ሆኗል፡፡ ለምሳሌ የካርዲፍ ከነማ እግር ኳስ ቡድን ዋነኛ የዌልስ ብሔራዊ ማንነት መፍጠሪያ፣ ማቀጣጠያና መገንቢያ ተደርጎ ይወሰዳል- እንደ ጆንስ (2000) ጥናት፡፡ ጋሪ ሮጀርስና ጆይል ሩክውድ “Cardiff City Football Club as a Vehicle to Promote Welsh National Identity” በሚለው ጥናታቸው እንደሚያስረግጡት በብዙኃኑ የዌልስ ዜጋ ዘንድ ካርዲፍ ከነማ ማለት “ዌልሳዊነት” ማለት ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከእንግሊዛዊ ማንነት የሚለዩበት ማኅበራዊ መለዮ ነው፡፡ ደጋፊዎች ይህን አባባል ያዘወትሩታል፡- “ከነማ (ካርዲፍ) ሲጫወት ስንመለከት ስለ ዌልስ እንዘምራለን” ይቀጥላሉ፡- “ባንዲራችን እንለብሳለን፤ እንግሊዛዊ ተቀናቃኞቻችንን በየሳምንቱ እንገጥማለን፤ ዌልሳዊ መሆናችንን እናፈቅራለን፤ ለዚህ ፍቅራችን ክለባችን ድምጽ ይሆነዋል፤ እናም ዌልሳዊነታችንን እንድናንጸባርቅ ይረዳናል”፡፡ አንዳንዶች “እንግሊዝ-ጠል ብሔርተኛ ተቋም” አድርገው አሉታዊ ምስል ሊያላብሱት ይሞክራሉ፡፡ በዚህ ረገድ ባሳለፍነው የአውሮፓ ዋንጫ ዌልሳዊው ጋሬት ቤል “እንግሊዛውያንን እንጠላቸዋለን” ብሌ የተናገረውንና ባንጻሩ እንግሊዛዊው ጃክ ዊልሼል ለቤል የሰነዘረውን የጥላቻ ጥላቻ መልስ ማስታወስ ይቻላል፡፡

መቀመጫው በሃገረ ዮርዳኖስ የሆነው አል ዊህዳድ የተባለው ክለብ የፍልስጤም ብሔርተኝነት ምልክት/መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በዘመነ አፓርታይድ ጥቁር ያልተካተተበት ብሔራዊ ብድን ደ/አፍሪቃ ያበጀች ሲሆን፤ ጥቁሮቹ በበኩላቸው የነጻነት ትግሉ አካል የሆነ በተለይ ከነጻነትም በኋላ ዊሊ ማንዴላ የምትመራው የስፖርት ቡድን ነበር፡፡ ግብጽ ሃገር ውስጥ እግር ኳስና ፖለቲካ የተሳሰሩ ናቸው፡፡ ለአብነት ያህል ዝነኛው ቡድብ አል አህሊ የግብጽ ሕዝብ መለያ ሆኖ ነው የሚታየው። አል አህሊ በግብጻውያን በራሳቸው የተመሠረተው የመጀመሪያው ክለብ ሲሆን የግብጽ ብሔራዊ መለያ ነው። የየቡድኖቹ ደጋፊዎች በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን ስታዲዮሞችም ብሶትን ለመግለጽ አመቺ ቦታዎች ናቸው።

በስፔን እግር ኳስና ፖለቲካ የማይለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ ዋና ዋናዎቹ ፕሮፌሽናል ቡድኖች ከተመሰረቱበት ከ19ኛው ክ/ዘመን መገባደጃ ወዲህ፡፡ ስፔናዊው አምባገነን ፍራንሲስኮ ፍራንኮ (1936-1975 እ.ኤ.አ) በ1950ዎቹ በዓለምአቀፉ መድረክ አዎንታዊ ገጽታን ለመገንባት እግር ኳስን እንደሁነኛ መሳሪያ ተገልግሎበታል፡፡ አዲሲቷንና ማዕከላዊቷን የተረጋጋች ስፔን በዓለም ለማስተዋወቅ ትልቁን የአገሪቷን ቡድን ሪያል ማድሪድን እንደመሳርያ ተጠቀመ፡፡ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ በ1956 ሲጀመር፣ ማድሪድም ለአምስት ተከታታይ ጊዜ አሸናፊ ሆኖ በአውሮፓ ሲነግሥ፣ ጄኔራል ፍራንኮ የሎስ ብላንኮዎቹ መደበኛ ተመልካችና የቅርብ ደጋፊ በመሆን ረብጣ የፖለቲካ ትርፍ ሊሸምት ችሏል፡፡ ማድሪድም የስፔን ብሔራዊ ማንነት ማሳያና መለኪያ ሆኖ እስከ ዘመናችን ገሰገሰ፡፡ የማንነት ጥያቄን ፖለቲካ አላብሶ በእግር ኳስ ሜዳ በማንጸባረቅ ወደር እንደማይገኝለት የሚነገርለት የካታሎን ተገንጣዮች ተወካይ ባርሴሎና ከዚህ በተጻራሪ ቀጥሎ ይመጣል፡፡ የካታሎኒያ ብሔርተኝነት ማሳያው ባርሴሎና በፍራንኮ ፈላጭ ቆራጭ ዱላ ተደቁሷል፡፡ ቡድኑም የብሔርተኝነት ንቅናቄውና የጸረ-ፍራንኮ ትግል ዋነኛ ማዕከል ሆነ፡፡ በፍጹም ራሳቸውን ስፔናዊ አድርገው የማይቆጥሩት የካታሎን ተገንጣዮች ከስፔን የተለየ ማንነትን ለማራመድና ተገንጥለው ነጻ የካታሎን መንግስት ለመመስረት ያላቸውን ህልም ለማሳካት በባርሴሎና እግር ኳስ ቡድን በኩል ብዙ ተጉዘዋል፡፡ ባርሳም የዚህ ፖለቲካዊ ውዝግብ ትልቅ ባለድርሻና “ሲምቦል” ነው፡፡ በተለይ የሊጉ ጠንካራዎቹ ክለቦች የስፔን ብሔራዊ ማንነት ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደው ሪያል ማድሪድና የመገንጠል ጥያቄ አንጋቢዋ ካታሎን ግዛት ተወካዩ ባርሴሎና ቡድኖች ሲጫወቱ (ኤል-ክላሲኮ)፣ ከ“ደርቢ” ጨዋታ ተቀናቃኝነት በላይ፣ ጦር የተማዘዙ ሁለት ሉዓላዊ ባላንጣ ሃገራት የሚያደርጉት ፍልሚ እስኪመስል ድረስ ከኳስ ጨዋታነቱ ይልቅ የፖለቲካ ድባቡ ያመዝናል፡፡

በስፔን የብሔራዊ አንድነት አቀንቃኞች አማካኝነት በካታሎኗ ባርሴሎና ከተማ እንደተመሰረተ የሚነገርለት ስፓኞል እግር ኳስ ቡድንም ከስሙ ጀምሮ በስፔን ብሔርተኝነት መንፈስ የተቃኘ የባርሴሎና ቡድን የከተማ ተቀናቃኝ ነው፡፡ ይህም በስፔን ያለ የኳስና ማንነት መስተጋብር ሌላ ማሳያ ነው፡፡ ሌላው የስፔን ላሊጋ ተሳታፊ ቡድን የባስክ ተገንጣዮቹ አትሌቲኮ ቢልባኦም በባርሴሎና አንጻር የሚቀመጥ ነው፡፡ እነዚህ የሁለት ነጻነት ጠያቂ ክፍላተ ሃገራት ካታሎኒያና ባስክ ክለቦች ባርሳና ቢልባኦ በማኅበረሰባቸው ዘንድ ከእግር ኳስ ቡድንም በላይ ስዕል ነው ያላቸው፤ እንደብሔራዊ ቡድንም ይቆጥሯቸዋል፡፡ ለዛም ነው “የስፔንን እግር ኳስ ከፖለቲካዋ ነጥሎ ማየት አይቻልም” የሚለው አባባል ግዘፍ የሚነሳው፡፡

*የእኛ አገር አውድ*

ብራድሊ (1995) እንደሚለው የእግርኳስ ደጋፊዎች የቡድናቸውን ድል በመመልከት ጉልህ የሆነ ስነልቦናው ርካታ ያገኛሉ፡፡ ደጋፊነት ከስፖርታዊ አውድ ውጭም በህብረተሰቡ የለትተለት ኑሮ ውስጥ ስፍራ አለው፡፡ ይህም ማኀበራዊ ድርጊቶች፣ ሚዲያ ሽፋኖች፣ መለዮዎችን በመልበስ፣ የክለባቸውን መዝሙር በመዘመር፣ ምልክቶችን በማድረግ ታሪካቸውንና የቀንከቀን እውነታዎቻቸውን በማንጸባረቅ ይገለጻል ይለናል፡፡

ወደሃገራችን ስንመጣ ስፖርት ዘርፈ ብዙ የማንነት መወከያ ሆኖ ሲያገለግል አይተናል፡፡ ሩጫ የብሔራዊ ማንነታችን መገለጫ ሲሆን፤ የክለብ እግር ኳስ ደግሞ የተለያዩ ቡድኖችን አላማ ማራመጃነት ሲውል ነበር፡፡ በተለይ በ1960ዎቹና 70ዎቹ የነበሩ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አስመራ፣ ሻሼመኔ፣ ጎንደርና ጅማ ላይ የተቋቋሙ ህዝባዊ መሰረት ያላቸው ክለቦች የፖለቲካ ማንነት ማራመጃ ነበሩ፡፡ ገነነ መኩሪያ ኢህአፓና ስፖርት በተባለው ባለሁለት ቅጽ መጽሐፉ 60ዎቹ መጨረሻና 70ዎቹ መጀመሪያ ላይ የነበሩ የሊግ ክለቦች ዋነኛ የኢህአፓ አላማ ማቀንቀኛ እንደነበሩ ይናገራል፡፡ ህዝባዊነት ያላቸው እንደ “አንድነት”፣ “ቅዱስ ጊዮርጊስ”፣ “ቴዎድሮስ” እና “ምድር ባቡር” (ድሬዳዋ)፣ መሰል ክለቦች ኢሃፓን ደግፎ ደርግን መንቀፊያ ነበሩ፡፡ ኢህአፓም ከህቡዕነት ግዘፍ እስከመንሳት ድረስ በክለቦቹ ውስጥ እጇ ረዥም ነበር፡፡ የኢህአፓ አባላት የነበሩና ፖለቲካውን ከልባቸው የሚያንቀሳቅሱ ተጫዋቾች ነበሩባቸው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘመነ ወያኔም የደርግ ጊዜውን ያክል ጠንካራና የተደራጀ ባይሆንም አልፎ አልፎ ፖለቲካዊ ተቃውሞዎች በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በትንሹ ደግሞ በክፍለ ሃገር የኳስ ትዕይንቶች ላይ (ባለፈው ዓመት የጎንደር ፋሲለደስ ስታዲዮም የ“ወልቃይት አማራ ነው” የማንነት ጥያቄና በአጸፋው አዲግራት ላይ የፋሲል ደጋፊዎች ላይ ነውጠኛ ደጋፊዎች የወሰዱት ጠብ-አጫሪ ርምጃ እንዳብነት ሊጠቀስ ይችላል) ሲንጸባረቅ ይስተዋላል፡፡ “ሳንፈልጋቸው 20 ዓመታቸው” የሚለውን የሚስማር ተራ ህብረ ዝማሬ በዚህ ረገድ ማውሳት ይቻላል፡፡

ዐማራና ስፖርት

በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የዐማራ ህዝብ ያለ ተወካይ ለረዥም ዓመታት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ደሴ ጥቁር አባይ በአንድ ወቅት ብቅ ብሎ ጠፋ፤ ወልድያ ከነማ በ2007 ዓ.ም የውድድር ዘመን ደርሶ ተመለሰ፡፡ አምና በ2008 ዓ.ም ወደዋናው ሊግ ለመግባት በተደረገው ውድድር በከፍተኛ ሊግ ከቀጠና አንድ ፋሲል ከነማና ወልድያ ከነማ ሁለቱንም ኮታዎች በመጠቅለል አላፊ ሆነዋል፡፡ በዚህም በ2009 የውድድር ዓመት ሁለት ቡድኖች ዐማራን ይወክላሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ቡድኖች የዐማራ ብሔርተኝነት ማነቃቂ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዚህን ህዝብ ከኳስ መድረክ ለዘመናት ርቆ መቆየት ገዢው መንግስት ይህንን ህዝብ ለማጥፋት ከሚያራምደው እኩይ አጀንዳ ጋር አመሳስለዋለሁ፡፡ በ25ዓመታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዐማራዎችን የፈጀው የደደቢቱ መንግስት፣ የዚህን ህዝብ የበላይነት ከሚቀለብስባቸው መንገዶች አንዱ ስፖርት እንደሆነ ከግምት የዘለለ እውነታ ነው፡፡ እንደኦሮምያ ለሩጫ አመቺ የሆነ የአየር ንብረትና መልክዓምድራዊ አቀማመጥ ዐማራ ውስጥ አለ፤ በተለይ ሸዋና ጎጃም አካባቢ፡፡ ከነዚህ አካባቢዎች የተገኙ ጎበዝ አትሌቶችንም ታዝበናል፡፡ አገር አቀፍ ውድድሮች ላይ ውጣ ውረዶችን ተሻግረው በውድድር ሲሳተፉ ከዚያም በጎ ውጤት ሲያስመዘግቡ አይተናል፡፡ በዓለም አቀፍ መድረክ ግን አናያቸውም፡፡ ለምን? መጠርጠር ጥሩ ነው፡፡ በርግጥ ከጫካ የወጣው ገዢ ቡድን የዐማራ ህዝብ ላይ ጫካ ውስጥ ሆኖ ካረቀቀው የቂም በቀል ፖሊሲ አንጻር ስንቃኘው ጥርጣሬው ውሃ ያነሳል፡፡ ሊደረግላቸው የሚገባውን ድጋፍና ክትትል ብንተወው እንኳ በግላቸው ጥረት መሰናክሉን አልፈው እንዲወዳደሩ በሩ ቢከፈትላቸው ከነ“ገብሬ” ያነሰ “ፐርፎርም” እንደማያደርጉ አምናለሁ፡፡ ከክልሉ በጥረት የወጡ አትሌቶች ዐማራ በመሆናቸው ምን ያክል እንደሚገለሉና እንደሚገፉ ከአትሌቶቹ ጋር በቅርበት ተወያይቶ ያጫወተኝ የስፖርት ጋዜጠኛ ወዳጄ ለዚህ እማኜ ነው፡፡ እግር ኳሱም ከዚህ የተለየ ዕጣ የለውም፡፡ ስፖርት አንድን ህዝብ ለማስተዋወቅና ጥሩ ገጽታ ለማጎናጸፍ መልካሙ መንገድ መሆኑ እሙን ነው፡፡ በተለይ የሊግ ኳስ ከላይ በዓለም ዐቀፍ አውድ እንዳየነው አንድን ማህበረሰብ፣ ዘውግ፣ ተመሳሳይ ስነ ልቦናዊ ስሪት ያለው ህዝብ፣ ከተማ የመወከልና የማስተዋወቅ እድሉ ከፍተኛ ስለሆነ ሴረኛው መንግስት በዚህ በኩልም ሲደቁሰን እንደኖረ እናምናለን፡፡ እነ ይድነቃቸው ተሰማና መንግስቱ ወርቁን የመሰሉ ብርቅ የአገራችንና የአፍሪካ የእግር ኳስ ምልክቶች የወጡበት ህዝብ ለምን ያለ ተወካይ ሊቀር ቻለ? እውነቱ ከጥያቄው መልስ ውስጥ አለ፡፡ አሁን ፋሲልና ወልድያ ከዚህ ፍቱን መጠይቅ ጀርባ ያለውን ደባ እየሸረሸሩ በስፖርቱ መድረክ ገነው፣ ህዝባቸውን ከጎናቸው በማሰለፍ ብሄርተኝነትን እያቀነቀኑ፣ ፖለቲካዊና ህዝባዊ ጥያቄዎች እየተስተጋቡባቸው ይቀጥላሉ፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዋነኛ ዓላማ ፋሲል ከነማን በዚህ ነጥብ ረገድ መዳሰስ ነውና ወደዚያው ልለፍ፡፡

የፋሲል ከተማ

ምንም እንኳን በዚህ ዓመት ወደስኬት ይምጣ እንጂ ፋሲል ብዙ አስርተ አመታት ያስቆጠረ ታሪክ አለው፡፡ ጠንካራ ህዝባዊ መሰረትም አለው፡፡ በተጫዋቾች ትጋት፣ በደጋፊው ደጀንነት፣ ዓመቱን በስኬት አጠናቋል፡፡ የፋሲል የአምና ጉዞ ከስፖርትነት ባለፈ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች የተስተናገዱበት ክዋኔ ነበረው፡፡ በዓለም መድረክ ላይ እንዳየነው እግር ኳስ የተለያዩ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎች እሳቤዎችና ጥያቄዎች የሚስተናገዱበት መድረክ ነው፡፡ ፍቅርንም ጥላቻንም ማስተናገድ ይቻላል፡፡ በአንድ ወቅት የኢራን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አፍሺህን እግር ኳስ ህዝብን ለማስተሳሰር ያለውን ጉልበት ሲናገሩ “ዓለምን ወደአንድ ለማምጣት ሁለት ነገሮች ያስፈጋሉ- ፍቅርና እግር ኳስ” ብለው ነበር፡፡ ለዛም ነው በስፖርታዊ መድረኮች ህዝባዊ ጥያቄዎችን ማንሳት የተለመደ የሆነው፡፡

ዘንድሮ ፋሲል ወደፕሪሚየር ሊግ መግባቱን ተከትሎ ድጋፉ እንደሚግል ይጠበቃል፡፡ የተቀጣጠለው የዓማራ ብሔርተኝነትም ሆነ ህዝባዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በተደራጀ መልኩ ይቀርቡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ፋሲል ከክለብም በላይ ነው፡፡ ከላይ ባርሴሎና ክለብ ብቻ አይደለም እንደተባለው፤ የማንነት መጠየቂያ መድረክም እንጂ፡፡ እናም ፋሲል የዓማራነት መወከያ ነው፤ የተገፋ ህዝብ ጋሻ፤ የተንቋሸሸ ታሪክና ማንነት መመለሻና ማደሻ፡፡ ይህ ዓማራዊ ማንነትና ብሶት በደጋፊዎቹ ይዘመራል፤ ፋሲል በደጋፊ መሰረት ላይ የታነጸ ክለብ ነውና፡፡ እንደኛ ሃገሩ ቡና እና እንደአውሮፓ ታላላቅ ቡድኖች የደጋፊ ልዩነት ፈጣሪነት ፋሲል ላይ ግዘፍ ይነሳል፡፡ ህዝባዊ እምቢተኝነትና ፋሲል ከነማ ጎን ለጎን የሚሄዱ ሁነቶች ናቸው፡፡ ፋሲል የጎንደር ክለብ ነው፤ ጎንደር- የዐማራ ተጋድሎ የተጠነሰሰባትና የተቀጣጠለባት ምድር ናት! በተዋህዶ የከበረች ምድር፤ አንድም በጀግንነት አንድም በጨዋነት- በተዋህዶ መክበር የምልህ ይሄንን ነው፡፡ ጀግንነት ብትል መፈጠሪያው ጎንደር፤ እንግዲያስ ጨዋነት (ማተብ ይልሃል! ሃቀኝነት- ሰው አክባሪነት፣ እንግዳ ወዳድነት፣ አዛኝነት)፡፡ ይሄንን እንግዲህ በኳሱ መድረክ አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ ኳስ የበሬ ግንባር በምታክል ሜዳ ቅሪላ ከማንከባለል የዘለለ ነው የሚባለውም ለዛ ነው፡፡ የገሃዱ ዓለም እውነት ነው፡፡ ኳስ የዓለምን ቢዝነስ ይመራል፣ የዓለምን ፖለቲካ ይመራል፣ የዓለማችንን ሁሉ ነገር በቅጽበት መቀየር የሚችሉ አቋማሪዎችና ማፍያዎች ኳሱ ውስጥ አሉ፡፡

አሁን በዘመነ ደደቢት ዐማራነት በራሱ ፖለቲካ ሆኗል፡፡ ቀሪዋ ኢትዮጵያ በገዢዎች አምባገነናዊ ዱላ ስትመታ ዐማራ ግን ከዚህም ያልፍና በዘሩ ብቻ ደደቢት በርሃ ውስጥ በተነገፈለት የበቀል አጀንዳ ላለፉት 40 ዓመታት (በይበልጥ 25 ዓመታት) የሚገደል፣ የሚሳደድ፣ በድህነት ውስጥ ይኖር ዘንድ የተፈረደበት፣ በስነ ልቦና የሚመታ፣ ትምህርት/ጤና/መሰረተ ልማቶች የተነፈጉት፣ የሚሰደብ፣ የዘር ማጥፋት የታወጀበት ህዝብ ሆኗል፡፡ ይህም የሚሆነው ዐማራ ስለሆነ ብቻና ብቻ ነው፡፡ እናም የዐማራነት ጥያቄ የመኖር-አለመኖር ጥያቄ ነው፤ የህልውና ጥያቄ፡፡ ይህን ለመዋጋት የዐማራ ብሔርተኝነት ወሳኙ መንገድ ሲሆን ንቃተ ህሊና ደግሞ መንገዱን ይጠርጋል፡፡ ለዚህም መድረኮች ያስፈልጉናል፡፡ በማኅበራዊ ሚዲያው፣ በቡድን ውይይት፣ በመደራጀት፣ በ“አክቲቪዝም” እና ሌሎች መንገዶች ከሚደረገው የንቃተ ህሊና ማዳበሪያ መድረኮች በተጨማሪ ኳስ (ስፖርት) አንዱ ሆኖ ይቀርባል ማለት ነው፡፡ ይህን ንቃተ ህሊና የሚፈጠርበት፣ የሚሟሟቅበት፣ የሚዳብርበት መድረክ ይሆናል- ፋሲል ከነማ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በሁሉም መድረኮች ዐማራ ስም አጠራር እንዳይኖረው ላለፉት 25 ዓመታት እየተጋ ያለው ስርዓት ካቅሙ በላይ በሆነ ህዝባዊ መነሳሳትና ወኔ ፋሲል ፕሪሚየር ሊጉን መቀላቀሉ ደደቢቶቹን ውስጥ ውስጡን እርር ድብን እንዳደረጋቸው መገመት ቀላል ነው፡፡ በተለይ ፋሲልና ወልድያ የሰሜን ተወካዮችን ከስር ጥለው መምጣታቸው ንዴታቸውን ሊያንረው ይችላል፡፡ እናም እነዚህ የዐማራ ተወካዮች በመጡበት አግራቸው ተመልሰው እንዲወርዱ “ፕሮፌሽናል” ሴራ ሊያሴሩ ይችላሉ፤ ከዳኝነት እስከ ፌዴሬሽን ቢሮክራሲ፡፡ ስለሆነም ይህንን ጉዳይ ነቅቶ መከታተል ክለቦቹን ከመደገፍ ጋር ጎን ለጎን ትኩረት ሊቸረው የሚገባ አቢይ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ጽሑፍ/እይታ ፋሲል ከነማን ማዕከል አርጎ ይጻፍ እንጂ በተመሳሳይ ወልድያ ከነማንም ይወክላል፡፡ እነዚህ ሁለት ቡድኖች የዐማራ ብሔርተኝነት ማቀጣጠያ ሆነው ከዐማራነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች የሚነሰሱባቸው መድረኮች ይሆኑ ዘንድ ይጠበቃል፡፡ ፋሲልና ወልድያ ማንነታችን ያነጥሩልናል፤ ታሪካችንን መልሰው፣ ውለታችንን አወራርደው፣ ወደሰገነታችን ያወጡናል፡፡ በሰላማዊው መድረክ ዐማራ ይነግሳል፡፡ ፋሲልና ወልድያ የዐማራ ባርሴሎናዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡

ቸር ያሰማን!

ስኬት ለፋሲልና ወልድያ ከነማ!

↧

ከማዕከላዊ ኮሚቴ ውጭ ያሉ የኦህዲድ ካድሬዎች አሁኑኑ ወስዳችሁ እሰሩን እያሉ ነው ።

$
0
0

ከማዕከላዊ ኮሚቴ ውጭ ያሉ የኦህዲድ ካድሬዎች አሁኑኑ ወስዳችሁ እሰሩን እያሉ ነው ።
==========================================

Zehabesha-News.jpg
አዲሱ የኦህዲድ ሊቀመንበር ከማዕከላዊ ኮሚቴ ውጭ ያሉትን የኦህዲድ መካከለኛ እና ከፍተኛ ካድሬዎች ሰሞኑን ሰብስበው ነበር።በስብሰባው ላይ ከተነሱት ሃሳቦች መካከል
1የፌደራሉን መንግሥት ባለሥልጣናት እናንተ ከፈራችሁ እኛ እንህድ እና የህዝባችንን ብሶት እናቅርብ
2 እየተናገርን ያለነው ተቀርፆ ይሰጣቸው ።ከአ.አ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተደጋግሞ ስማቸው ለምነሳው የፌደራል ባለስልጣናት ይህንን ማልዕክታችንን ቀርፃችሁ አቅርቡልን።ይህንን መጨማለቃቸውን እንድያቆሙ ንገሩአቸው።ከፈራችሁ ደግሞ ይህንን ቭድዮ ውሰዱ እና አሳዩአቸው።
3 ኃይለማሪም ከስልጣን መልቀቅ አላበት።
4 ህዝብ ልበላን ነው።እናንተ የፌደራል ባለሥልጣናትን ትፈራላችሁ።ሥለዚህ በህዝብ ከምንበላ ውሰዱ እና እሰሩን።ከሞት የተረፍነው በጎሳችን ምክንያት ነው እንጅ በኦህዲድ ምክንያት አይደለም።ስለዚህ እናንተ ከፈራችሁ ከምንሞት እኛው ሄደን እንጋፈጥ።
5 የኦሮሞ ህዝብን ደም ኢህአዲግ በምንም መልኩ ልመልስ አይችልም ።ስለዚህ ይህንን ይተው።ይህንን ይቅርታ መጠየቅ ዋጋ የለውም።ምናልባት ከፈለገ ኢህአዲግ በሙስልሙ ህብረተሰብ ላይ ያደረሰውን በደል ይቅርታ ይጠይቅ።
ብቻ በአጠቃላይ ካድሬው (እሥከ ሚንሥትሬ ዴታ ያለበት ) እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ አሁኑን ወስዳችሁ ካላሰራችሁን እያለ ትላንት አዳማን ተሰናብቶ ወደየሃገሩ አቅንቷል።
#OromoProtests #Ethiopia

↧

ጸረ ነፍጠኛ ግንባር?! (የነስብሐት ነጋ የጥፋት ድግስ!)

$
0
0

በሙሉቀን ተሰፋው

አንድ የማከብራቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ወያኔ በአማራ ሕዝብ እምቢተኝነትና አይበገሬነት ስለተርበተበተ፣ ይህን ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለመነጠል መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው በማለት በቅርቡ የታዘቡትን አጫውተውኛል፡፡ እኚህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኅብረትና ለአገራችን አንድነት ፍጹም ቀናኢ የሆኑ የፖለቲካ ሰው እንደገለጹልኝ፣ ሰው በላው ስብሐት ነጋና ሌሎች የወያኔ መሪዎች የተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያና የኦሮሞ ፖለቲከኞችን እየቀረቡ፣ ከአማራ ውጪ ያሉት ሕዝቦች ጸረ ነፍጠኛ ግንባር ካልፈጠሩና የአማራውን እንቅስቃሴ ካልመከቱት በስተቀር የድሮው ሥርዓት ተመልሶ አስፈሪ መልክ ይዞ እየመጣ ነው በማለት እየቀሰቀሱ ነው፡፡ እነስብሐት ነጋ ጸረ ነፍጠኛ ሲሉ ጸረ አማራ ማለታቸው መሆኑን ማንም ይስተዋል ብለን አናምንም፡፡ ስለሆነም እነዚህ ነብሰ ገዳዮች ጸረ አማራ ግንባር ለመፍጠር ላይ ታች እያሉ ነው!!!

Ato_Sibhat
እንደሚታወሰው ወያኔ በምርጫ 97 አስደንጋጭ ሽንፈት በገጠመው ማግስት፣ ትምክህተኛው አንሰራርቶ ተነስቷል፤ ይህ ኃይል ሥልጣን ከያዘ አገራችን ወደትርምስ ትገባለች፤ በሕዝቦች መካከል የለየለት መተራረድ ይከሰታል ወዘተ. በማለት ከአማራ ውጪ ያሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ በተለይ ደግሞ ወያኔና የኦሮሞ ድርጅቶች ጸረ ነፍጠኛ ግንባር ሊፈጥሩ እንደሚገባ ለነዶ/ር መረራ ጉዲና ጥሪ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ መረራ በመጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት በቅርቡ የሞተው ፕሮፌሰር ዓለም ሀብቱ (የታላቋ ትግራይ ፕሮጀክት አራማጅ) እና ዘላለሙን የአማራ ሕዝብ ጠላት ሆኖ የኖረው አብዱል መሐመድ (ወርጂ) ወያኔንና እነዶ/ር መረራን ለማግባባት ሞክረው ነበር፡፡ እነመለስ በተለመደ ከሃዲነታቸው ‹‹ጸረ ነፍጠኛ ግንባር ፈጥረን፣ የተደቀነብንን ፈተና ካስወገድን በኋላ፣ እኛ ለአምስት ዓመታት ብቻ መርተን ለእናንተ እንለቅላችኋለን›› ወዘተ. የሚል ከንቱ ሙከራ ማድረጋቸውንና እነዶ/ር መረራ ይህንን የነመለስ መሰሪ አካሔድ ተረድተው ጥሪውን ውድቅ ማድረጋቸውን ሰምተናል፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡
ዋናው ነገር፣ የወያኔ መሪዎች በሥልጣን ላይ ለመቆየት የማያደርጉት ምንም ዓይነት ነገር እንደሌለ ግልጽ ነው፡፡ እነዚህ ጸረ ሕዝቦች፣ ወያኔን በሥልጣን ላይ እስካቆየ ድረስ እንኳን ከኢትዮጵያውያን ከባዕዳን ጋርም መተባበራቸው አይቀርም፡፡ ባለፉት 25 የግፍ ዓመታት በግልጽ እንደታየው፣ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲሉ ሕዝብ ይጨፈጭፋሉ፤ በገፍ እያሰሩ ዘግናኝ ቶርቸር ይፈጽማሉ፤ እጅግ ርካሽ በሆነ መልኩ ሴት ፖለቲከኞች እንዳይኖሩ፣ ተስፋ የሚጣልባቸውን ሴት ፖለቲከኞችና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች አስረው ይጫወቱባቸዋል፤ ወንዶች ብልታቸውን እየተቀጠቀጡ ከሰው ተራ እንዲወጡ ይደረጋል፤ እሳት እየጫሩ አንዱን ሕዝብ ከሌላው ጋር ያጋጩና ገላጋይና ዳኛ መስለው ይገባሉ፤ አሁን በቅርቡ በአማራ መተማ ውስጥ በግልጽ እንደታየው ጽረ ሕዝብ በሆነው የደኅንነት ተቋማቸው አቀነባባሪነት ትግሬዎችን እስከነጓዛቸው ጭነው አስወጥተውና የቀሩ አማሮችን አርደው ሲያበቁ፣ ትግሬ ተባረረ፣ በትግሬ ላይ ያነጣጠረ የዘር ጥቃት ተፈጸመ ብለው የትግራይ ሕዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ለማድረግ የፋሽስት ተግባር ይፈጽማሉ፤ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው የገበያ አዳራሾችና በሕዝብ ትራንስፖርት ላይ ቦንብ ጥለው በሌሎች ላይ ያሳብባሉ፤ ግለሰቦችን በገቡበት ሁሉ እየገቡ እየተከታተሉ ያሸማቅቃሉ፤ ያስፈራራሉ፤ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለው የሎቢ ቡድን ቀጥረው የዲፕሎማሲ ሥራ ይሠራሉ፤ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ባልደረቦች ገንዘብ ይከፍላሉ ወዘተ. ወዘተ.፡፡ እኩይ ተግባራቸው ማለቂያ የለውም፡፡ ተግባራቸው ሁሉ አገር ከሚመራ ድርጅት ሳይሆን ከማፊያዎች የሚጠበቅ የተራ ዱርዬና የማጅራት መቺ ተግባር ነው!! እንብላ ብቻ ሳይሆን ስንበላ አትዩን፣ ከዚያም አልፈው ሌላው አይብላ የሚሉ፣ ያዩትን ሁሉ በብቸኝነት ለማግበስበስ የሚጣደፉ ስግብግቦችና ጸረ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ደግነቱ ሁሉን እንብላ፣ ያየነው ሁሉ አይቅረን ሲሉ የያዙትንም የሚተፉበት ጊዜ መጥቶባቸዋል!!!
እንግዲህ፣ የአማራ ሕዝብ እየተደገሰለት ያለውን የወያኔ መሪዎች የጥፋት ድግስ ነቅቶ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ እየተሞከረ ያለው ጸረ አማራ ግንባር ምን ውጤት እንደሚያስከትል እና ሕዝባችን ከሚደገስለት የሞት ወጥመድ ራሱን ለማዳን ምን ማድረግ እንደሚገባው መወያየት ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ እኚህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ የቆዩ ምሁርና ፖለቲከኛ እንደነገሩኝ ከሆነ፣ ሁሉም ድርጅቶች ለዚህ የወያኔ የጸረ አማራ ግንባር ጥሪ ያላቸው ምላሽ አሉታዊ ነው፡፡ ዛሬ ማንም የፖለቲካ ሀ ሁ የሚያውቅ ሰውና የድርጅት መሪ ወያኔ እንዳበቃለት ይገነዘባልና የዚህ የወያኔ የጥፋት ግንባር ተባባሪ የሚሆን አካል ይገኛል ማለት ያስቸግራል፡፡ ስለሆነም ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ የተደገሰ የጥፋት ግንባር ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል የመነመነ ነው፡፡ ሆኖም ዕድሉ የመነመነ ቢሆንም ዜሮ ነው ማለት ግን አይቻልም፡፡ ሁልጊዜም ግንባር ቀደም ጠላታችን የሆነው ወያኔ የሚደግስልንን የሞት ወጥመድ ነቅተን መከታተልና ማክሸፍ ይኖርብናል፡፡ የወያኔና የእኛ ግንኙነት የአጥፊና ጠፊ ግንኙነት ነውና ወያኔ እንዲጠፋ ያለእረፍት መሥራት፣ ያለእረፍት መታገልም ግዴታችን ነው፡፡ ወያኔ እስካለ ድረስ እኛ ሰላም አናገኝም፡፡ ለእኛ፣ ሰላም ማለት ከወያኔ ነጻ መሆን ማለት ነው!!!!
ወዳጄ የነገሩኝን ነጥብ ጠቅሼ ጽሑፌን ልቋጭ፡፡ ምሁሩና ፖለቲከኛው አዛውንት፣ ‹‹በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ነፍጠኛም ትምክህተኛም ጠባብም ራሱ ወያኔ ነው፡፡ ስለሆነም የወያኔ መሪዎች የሚሉት ጸረ ነፍጠኛም በለው ጸረ ትምክህተኛ ወይም ጸረ ጠባብ ግንባር ጸረ ወያኔ ግንባር በመሆኑ፣ የዚህ ዓይነት ግንባር ከተመሠረተ ከመሥራች አባላት ውስጥ ወያኔ መኖር የለበትም፡፡ ግንባሩ ጸረ ወያኔ ነውና፡፡ ይህን ሐቅ ከያዝን በኋላ፣ ጸረ ነፍጠኛም በለው ጸረ ትምክህተኛ ወይም ጸረ ጠባብ ግንባር መመሥረት አለበት በሚለው ነጥብ ላይ መስማማት ይቻላል፤ እየተመሠረተም ነው›› በማለት አስደምመውኛል፡፡ የነስብሐት ነጋ ቀን መጨለሙን አያመለክትም ትላላችሁ? ለእኔ እንደዚያ ነው የሚታየኝ!

↧

“ሁል ጊዜ የሚሳሳቱት መሪዎች እንጂ ሕዝቡ አይደለም፤” (በቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው)

$
0
0

-ሁሉ ነገር በሚያስፈራበትና ሁሉ በፈራበት ወቅት፥በከባድ የጦር መሣሪያ በተከበበ አደባ ባይ፡- ይኸንን በሁለት ወገን የተሳለና በዚህም በዚያም የሚቆርጥ፥ሰይፍ የሆነ ኃይለ ቃል የተናገሩት፡-የም ዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፡-ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው።ከላይ እስከ ታች ድረስ ያሉ አንዳንድ በዘር የተሸነፉ፥የሃይማኖት ሳይሆን የዘር የቡድን አባቶች፡-ይህ መንግሥት ቢገድልም፥ ቢያስርም፥ቆዳ እስኪገፈፍና ጥፍር እስኪወላልቅ ድረስ ቢገር ፍም፥ሕዝቡን በዘር ቢከፋፍልም፥ ብዙዎችን በቋንቋ ምክንያት ከኖሩበት ቀዬ ቢያፈናቅልም ፥ሀብቱን፣ሥልጣኑን እና መሬቱን ጠቅልሎ ቢይዝም፥የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ቢሾምና ቢሽርም፥የጳጳሳትና የሊ ቃነ ጳጳሳት ብቻ በሆነ የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ እየተገኘ በጣልቃ ገብነት መመሪያ ቢሰጥም፥ታላቁ ገዳ ማችን ዋልድባ የስኳር ፋብሪካ ቢሆንም፥የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብት ንብረት ቢመዘበርም፥ግዴታውን እየተወጣ መብቱን ለማ ስከበር ቆርጦ የተነሣ ሕዝብ በአደባባይ ቢረሸንም፥የተቀረውም ታፍሶ ከተወሰደ በኋላ በማ ይታወቅ ስፍራ ሰቆቃ ቢፈጸምበትም፡-“ዝም በሉ፤” እያሉ በሚያስፈራሩበት ዘመን፥ይኸንን በመናገራቸው፡-“አባት ያላሳጣኸን አምላክ ተመስገን፤”የሚያሰኝ፥የጠወለገውን ተስፋም የሚያለመልም ነው። – -አባቶቻችን እኮ ያለባቸው የደኅንነት ወከባ ቀላል አይደለም፥ቤተ ክርስቲያኒቱም በሆድ አደር ካድሬዎች የተሞላች ናት።እንኳን በሀገር ቤት፥ሙሉ ነጻነት ባለበት በውጭው ዓለም እንኳ በማን እንደ ተከበብን እናውቀዋለን።ታድያ ይኸንን ቀንበር ሰብረው፥እንደ ጌታ ቃል፡- “እውነቱን እውነት፥ሐሰቱን ደግሞ ሐሰት፤” በማለታቸው፡-በሐዘን የቆሰለው ልባችን ተፈው ሷል።እኔ ትምህርታቸውን የሰማሁት በእንባ ነው፥እውነት ርቦኝ፥እውነት ጠምቶኝ ስለነበረ፥ አለቀስኩኝ።በወገኖቼ ላይ የተፈጸመውን ግፍ በመገናኛ ብዙኃን አይቼ ያለቀስኩትን ያህል አሁንም አለቀስኩኝ።ምክንያቱም፡-እነዚያ በቆመጥ ተደብድበው፥በጥይት ተመትተው የረገ ፉት ወገኖቼ፥የሚናገርላቸው አባት በማግኘታቸው፥ደስ ብሎኝ ነው።በአባቶች ዝምታ የቆሰለ ውም ሕዝብ በርሳቸው ድምፅ ተፈውሶአል፥በቅዱስ ፓት ርያርኩ፡-በግልጥ ወደ መንግስት ያደላ ንግግር አፍሮ አንገቱን ደፍቶ የነበረ ኢትዮጵያዊ ሁሉ፥በርሳቸው ጀግንነትን የተሞላ ንግግር አንገቱን ቀና
12605371_107516946297752_7964341026246359877_o
አድርጎአል።የሞቱትም ወገኖቻችን፡-በአጸደ ነፍስ ሆነው ይጽናናሉ። – -ብፁዕ አባታችን የተናገሩት፡-ስለ ሞቱት ልጆቻቸው ብቻ አይደለም፥በኃይል ታፍሰው በየማ ጎርያው ሰቆቃ ስለሚፈጸምባቸው ልጆቻቸውም ተናግረውላቸዋል።በግልጥ ቋንቋ፡-“ልጆቼን ፍቱ፤” ብለዋል።“ጥፋቱ የመንግሥት እንጂ የልጆቼ አይደለም፤”ብለው በአደባባይ ተከራክረ ዋል።ሳይፈሩ ሳያፍሩ በአፈ ሙዝ ፊት ቁመው፥በአልሞ ተኳሾች ተከብበው በሕይወት ላሉ ትም ለሞቱትም ልጆቻ ቸው ጥብቅና ቆመዋል።በዚህም የቀደሙትን አባቶቻቸውን፥በፋሽ ስት ኢጣልያ የተረሸኑትን፡-የአቡነ ጴጥሮስን እና የአቡነ ሚካኤልን አሠረ ፍኖት ተከትለዋል። እኔ አቡነ አብርሃም አልሞቱም አልልም፤እውነትን የተናገሩ ዕለት ሞተዋል፥ተሠውተዋል። ከዚያም በፊት በመንፈስ ከወገኖቻቸው ጋር ተገርፈዋል፥ቆስለዋል፥ተገ
ድለዋል።ከሁሉም በላይ ደግሞ የመነኮሱ ዕለት ፈጽመው ሞተዋል። – -በዘመናችን፡-“የቤተ ክርስቲያን ድርሻ መጸለይ ብቻ እንጂ ሌላ ነገር ውስጥ መግባት የለባ ትም፤” የሚሉ አድር ባዮች፥ከካህናትም ከጳጳሳትም አሉ።ከዚህም አልፈው አንድ ነገር በተነ ገረ ቍጥር “ፖለቲካ ነው፥በአንድ ዘር ላይ የተሰነዘረ ቃል ነው፤”እያሉ ለማሸማቀቅ ይሞክ ራሉ።ይህ ድርጊታ ቸው፡-“ሌባሸጠው እናት ልጇን አታምንም፤”የሚያሰኝ ነው።ምክን ያቱም፡-እነ ርሱ ራሳቸው በዘር ፖለቲካ ስለ ተጠመቁ እንኳን ሌላውን ጥላቸውን እንኳ የማያምኑ ሰዎች ናቸው።ለዘር የፖለቲካ ፓርቲ ወርኃዊ መዋጮ የሚያዋጡ፥በየጊዜውም ስብሰባ የሚሰበሰቡ እነርሱ ናቸው።አንድ ጊዜ ኅሊናቸውን ከመንፈሳዊነት በመውጣታቸው ይሉኝታ የሚባል ነገርም አይታይባቸውም።ዘረኝነታቸውን ስትጠሉባቸው ደግሞ “ዘራችንን ይጠላሉ ፤”ብለው ያስወሩባችኋል።በምርጫ ጊዜ ሰው ሲገደልና ሲታሰር፥መንግሥት ምርጫ ሲያጭ በረብር፥በምርጫ ይገዳደሩኛል የሚላቸውን የተቃዋሚ ተመራጮችንና ታዛቢዎችን ሲያሳ ድድ፣ሲያስርና ሲገድል፥እውነት የሚጽፉ ጋዜጠኞችን ሲያስር፥የሰው ልጅ በፖለቲካ አመለካ ከቱ ብቻ ከየመሥሪያ ቤቱ ሲባረር፡-“ለምን እንዲህ ግፍ ይፈጸማል፤” ሲባሉ ፡-“የኛን ዘር ስለ ምትጠሉ ነው፤” ብለው ሲናገሩ ፈጽሞ አያፍሩም።ምርጫውንም፡-“መቶ ፐርሰንት አሸንፈ ናል፤” ሲሉ ትንሽ እንኳ የዓይናቸውን ቅንድብ አይሰብሩም።ይህ ሁሉ መከራ ያጎበጠውም ሕዝብ፡-“መብቴ ይከበር፥ነፃነቴም ይመለስ፤” ብሎ አደባባይ ሲወጣ፥በጥይት ይቆሉታል። በዚህን ጊዜ ደግሞ፡-”መንግሥት የሚለወጠው በምርጫ ካርድእየተፈጸመ እንጂ በአመጽ አይደለም፤” ሲሉ አፋቸውን አይዛቸውም።እንዲህ የሚናገሩት ምእመናን ቢሆኑ ብዙ አይገርምም ነበር፥ የሚገርመው ካህናት መሆናቸው ነው። – -ይኸንን ሁሉ የዘረዘርኩት፥ቤተ ክርስቲያን፡-ይኸ ሁሉ ግፍ እያየች፥“ምርጫው ፍትሐዊ ነበር፥የተወሰደውም እርምጃ ሚዛናዊ ነበር፤”እያለች ትሰጠው የነበረውን ምስክር ነት ሳስታውስ፥እንደ ካህን ስለሚያመኝ ነው።ከሰሞኑ ደግሞ ታቦት አውጥታ፡-መከረኛውን ሕዝብ፡-“ዝም በሉ፥ዝም ብላችሁ ተገረፉ፥ዝም ብላችሁ ሙቱ፤” ማለቷ እጅግ ያሳዝናል። ለመሆኑ ከጀርባ ሆኖ እንዲህ የሚያስደርገው መንግሥት፡-እርሱ ራሱ በታቦት ቢለመን የሕዝቡን ጥያቄ ይመልስ ይሆን? – -ወገኖቼ ፖለቲከኞች ባንሆንም፡-የፖለቲካ ሹመኞች ሕዝቡን ሲበድሉ ይመለከተናል።ምክን ያቱም አባት ተብለን የተሾምነው፡-በዚህ ሕዝቡ ላይ ነውና።እግዚአብሔር እኮ ንጉሡን ፈርዖንን፡- “ሕዝቤን ልቀቅ፤” ብሎ ታማኝ መልእክተኛውን ሙሴን የላከበት ግፍና በደል ስለበዛ ነበር።ዘጸ፡፭፥፩።ይህም የሚያመለክተው የተሾምነው በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሆኑን ነው። – -ቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት ተቋም እንደ መሆኗ ከእርሷ የሚጠበቀው፡-“ፍርድ ተጓደለ፥ ደሀ ተበደለ፤” ማለት ነበር።ነቢዩ ኤልያስ፡-በዘመኑ የነበረውን ቤተ መንግሥት የተቃወመው ፡-“ደሀውን ናቡቴን ገድላችሁ ለምን ርስቱን ወረሳችሁ?” በሚል ነበር።“ገድለህ ወረስኸውን ? ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ የአንተን ደም ደግሞ ውሾች ይልሱታል፤”በማለት የእግዚአብሔርን መልእክት ሲያስተላልፍ፡-ንጉሡንም ንግሥቱቱንም አልፈራቸውም። እነ ዚህ ሰዎች አያሌ ነቢያትን በጭካኔ ያስገደሉ መሆናቸውን ቢያውቅም ወደ ኋላ አላፈገፈገም ። – -ዛሬም በሀገራችን እየሆነ ያለው ይኸው ነው።ድሆች በኃይል እየተፈናቀሉ፥ጉልበት ገንዘብና ሥልጣን ያላቸው እየሰፈሩ ነው።ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ሁሉ፡-“አላየሁም፥አልሰማሁም፤” ማለት አትችልም።መጽሐፍ ቅዱሱ፡-የሚለው “ጸልዩ፤” ብቻ አይደለም ፥“እንደ ነቢዩ እንደ ኤልያስም ሞትን እና ሰቆቃን ሳትፈሩ ግፍን ሁሉ ተቃወሙ፤”ይላል ።፩ኛ፡ነገ፡፳፥፲፱። ስለ ዚህ የዘመናችንን ኤልያስ አቡነ አብርሃምን መከተል ያስፈልጋል።እርሳቸው በተደገነ መትረ የስ ፊት ቁመው የነገሩን፡-“ከመሣሪያው ኃይል፥የመስቀሉ ኃይል ይበልጣል፤” ብለው ነው። ይህም፡-ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፡-“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። . . . ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ፤”በማለት ከተናገረው ጋር አንድ ነው።፩ኛ፡ቆሮ፡፩፥፲፰፣ገላ፡፮፥፲፬። – -መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስም፡-የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስ፡-የወንድሙን ሚስት በወረሰ ጊዜ፡-“የወንድምህን ሚስት ትወርስ ዘንድ አይገባህም፤”ብሎ ተቃወመው እንጂ፥ “ስለዚህ ጉዳይ ጸሎት እይዛለሁ፤” ብሎ ዝም አላለም።በዚህም ምክንያት ወደ እስር ቤት ተወርውሮአል፥ በመጨረሻም አንገቱ ተቆርጦ በሰማዕትነት አርፎአል።ማቴ፡፲፬፥፩-፲፪።ወገ ኖቼ፡-ግፍን ለመቃወም እንኳን ትልቁን ነገር ሃይማኖትን ይዘን፥ሰብአዊነት በቻ በራሱ በቂ ነበር።በሕይወት ተመሳሳይ የሆ ኑት ሁለቱ ቅዱሳን፡-ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ዮሐንስ ነገ ሥታቱን የገሰጹት ሹመት ሽልማት ፈል ገው አይደለም፥የዓለምን ሹመት የማይፈልጉ መና ኞች ናቸው።ምድራዊት ቤተ መንግሥትን የማ ይሹ፥በሰማያዊ ቤተ መንግሥት ናፍቆት የሚ ኖሩ ናቸው።ብፁዕ አቡነ አብርሃምም፡-በመስቀል አደባባይ ያንን ታሪካዊ ንግግር ያደረጉት፥ የዚህን ዓለም ክብርና ዝና ፈልገው አይደለም።የሚበልጥ ሹመት አላቸው፥አንድ ጊዜ መን ፈስ ቅዱስ ጳጳስ አድርጎ ሾሞአቸዋል።“እምነ መንግሥት የዓቢ ክህነት፤” የሚለውን አሳም ረው ያውቃሉ፥ማወቅም ብቻ ሳይሆን ያምናሉ።ምክንያቱም የሚያውቁ ነገር ግን የማያምኑ ብዙ ናቸውና።የተሾሙትም መንጋውን ለመጠበቅ እንደሆነ ያምናሉ።“ግልገሎቼን አሰማራ፤ . . . ጠቦቶቼን ጠብቅ፤ . . . በጎቼን አሰማራ፤ . . . በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳ ችሁ ተጠንቀቁ፤” ይላልና።ዮሐ፡፳፩፥፲፭፣የሐዋ፡፳፥፳፰። – -የሚገርመው ነገር፥መንግሥት፡-ከአንገት በላይም ቢሆን፥ዋናውን ችግር ደብቆ፡-“የመልካም አስተዳደር ችግር አለብኝ፥በስብሻለሁና እታደሳለሁ፤” እያለ፥ደጋፊዎቹ ግን መለኮታዊ ሊያደ ርጉት ይፈልጋሉ።ይህ አምልኮት፡-መንግሥት ለሚሉትም ሆነ ለእነርሱ የሚጠቅም አይደ ለም።የሚጠቅመው እውነት እውነቱን መነጋገር ነው።ሔዋን፡-የቃየልም የአቤልም እናት እንደ ሆነች፥ርብቃም፡-የዔሳውም የያዕቆብም እናት እንደ ሆነች፥ቤተ ክርስቲያንም የሁሉ እናት ናት።በእውነቱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፈወሱን እንጂ፥ቤተ ክርስቲያን ለአንዱ እናት ለሌላው ግን የእንጀራ እናት እየሆነች አያሌ ተከታዮቿን አቍስላ ነበር።እውነታው ግን ብፁዕ አባታችን እንደ ነገሩን፡-ትናንት የዘር አጥር ካበጀበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ጥፋቱ የመንግ ሥት ነው። እርሳቸው አታጨብጭቡልኝ ቢሉም እኔ አጨብጭቤላቸዋለሁ።

↧
↧

የፓትርያርኩ ልዩ ጸኃፊ፣ ወይንስ የህውኃት ጉዳይ አስፈጻሚ (ይገረም አለሙ)

$
0
0

ይገረም አለሙ
“በርግጠኝነት ሁልግዜም ችግር የመሪ እንጂ የህዝብ አይደለም፤” አቡነ አብርሀም
“ለጠፋው ህይወት መንግሥትን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም” አባ ሰረቀብርሀን
“በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፡፡እኩሌቶቹም ለክብር እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፡፡እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ ለክብርም የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎ ስራ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል፡፡” (ጢሞቲዎስ 2፣2፣20)
መስከረም 16 ቀን 2009 ዓም በእለተ ደመራ ምሽት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛውን ፕሮግራም እያዳመጥኩ ነው፡፡ በዜና መጽሄት ክፍለ ጊዜ የአዲስ አበባው ዘጋቢ እስክንድር ፍሬው በስብሰባ መሀል ነው ያነጋገርኩዋቸው ካላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ልዩ ጸሀፊ አባ ሰረቀ ብርሀን ወልደ ስላሴ ጋር ያደረገው አጭር ቃለ ምልልስ ቀረበ፡፡ እስክንድር በኦሮምያና በአማራ የተገደሉ ወጣቶችን ጉዳይ አንስቶ ቤተ ክህነት ምን አለች ምንስ አደረገች በማለት ላነሳቸው ጥያቄዎች በልዩ ጸሀፊው የተሰጠው ምላሽ እንደ ሰው የሚያሳዝን፣ እንደ ዜጋ የሚያበሳጭ፣ እንደ ኦርቶዶክስ አማኝ የሚያሳፍር ነበር፡፡

aba-sereke-brehan
አማርኛ ከእንግሊዘኛ እየደባለቁ የሚናገሩት አባ ሰረቀ ብርሀን አንደበታቸው ፈጽሞ የሀይማኖት አባት አይመስልም፡፡ከጠቅላይ ምኒስትሩ ጀምሮ የተለያዩ ባለሥልጣኖች ጥፋቱ የእኛ የእኛ ነው በማለት ለማታላያም ቢሆን አምነው ለዚህም ጥልቅ ተሀድሶ ያስፈልገናል በማለት እየተውተረተሩ ባለበት በዚህ ወቅት እኝህ የጳጳሳችን ልዩ ጸሀፊ ግን ከጳጳሱ ቄሱ አንዲሉ ሆነው “ለጠፋው ህይወት መንግስትን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም” በማለት በተከላካይነት ቆሙ፡፡ በዛች አጭር ቃለ ምልልስ በተናገሩት ከመንግስት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ ብሰው የተገኙት አባ ሰረቀ ብርሀን “እየወረወረ በድንጋይ የሚገልም እየተኮሰ የሚገልም..” በማለት የመንግሥትን ግድያ ልክ አንደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነሩ ዶር አዲሱ ተመጣጣኝ ሊያደርጉት ዳዳቸው፡፡ ይህን ሰምቶ የማይናደድ ሰው፣ የማያፍር የእምነቱ ተከታይ ይኖራል፡፡ ነደድሁ አፈርሁ፡፡
አባ ሰረቀ ንግግራቸውም ሆነ የቃላት አጠቃቀማቸው የሀይማኖት ሰው ሳይሆን የፖለቲካ ሰው የሚያስመስላቸው፤ ቅላጼአቸው ደግሞ የትግረኛ ነውና ግብራቸውን በማይገልጽ መጠሪያ የፓትርያርኩ ልዩ ጸሀፊ ከሚባሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የህውኃት ጉዳይ ፈጻሚ ቢባሉ የሚገልጻቸው ይመስለኛል፡፡
በሰማሁት ነድጄ በሀይማኖቴ አፍሬ እንዳይነጋ የለም ለሊቱ ነጋ፡፡ ማርፈጃው ላይ ወደ ማህበራዊ ድረ ገጽ ጎራ ስል ንዴቴን የሚያበርድ ብቻ ሳይሆን በሀሴት የሚሞላ፤ ሀፍረቴን የሚከላ ብቻ ሳይሆን በኦርቶዶክስ እምነቴ ይበልጥ እንድኮራ ያደረገኝ ንግግር አገኘሁ፡፡ ንግግሩ የተደረገው በባህር ዳር መስቀል አደባባይ የደመራ ክብረ በአል ላይ ሲሆን ተናጋሪው የአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሀም ናቸው፡፡ ያገኘሁት ንግግር ከመጀመሪያው የማይጀምር ቢሆንም ከጀመረበት አንስቶ ያለው ግን እውነተኛ የሀይማኖት አባት መሆናቸውን ያረጋገጠ ንግግር ነው፡፡ ሙሉ ንግግራቸው በጽሁፍም በድምጽም ከተቻለ በምስል ጭምር ቢገኝ ለአሁኑ አስተማሪ ለታሪክም ቅርስ ነው፡፡
ለመንግሥት ጥብቅ መልእክት፣ ለእምነቱ ልጆቻቸው አባታዊ ምክር ባስተላለፉበት ንግግራቸው “ የምናገረው ሀይማኖት ነው፤በፖለቲካ ከተረጎመው የራሱ ጉዳይ ነው” በማለት እውነቱን በድፍረት የገለጹት አቡነ አብርሀም “በርግጠኝነት ሁልግዜም ችግር የመሪ እንጂ የህዝብ አይደለም” በማለት የመንግሥት ሰዎችን መክረዋል ፣አስጠንቅቀዋል፡ጋዜጠኞችንም ወቅሰዋል፡፡ የአቡነ አብርሀምን ይህን ንግግር እያዳመጣችሁ አለያም ይህችን ከመሀል መዝዤ የጠቀስኳትን ችግር የመሪ አንጂ የህዝብ አይደለም የምትለዋን እያብላላችሁ የአባ ሰረቀ ብርሀንን “እየወረወረ በድንጋይ የሚገልም እየተኮሰ የሚገልም..” የሚለውን አገላላጽ አስቡት አነጻጻሩት፡፡ መኩሪያና ማፈሪያ በአንድ ቤት፡፡
በመግቢያ ላይ የጠቀስኩት {በትልቅም ቤት የእንጨትና የሸክላ ዕቃ ደግሞ አለ እንጂ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ አይደለም፡፡እኩሌቶቹም ለክብር እኩሌቶቹም ለውርደት ይሆናሉ፡፡እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ ለክብርም የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎ ስራ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል፡፡} (ጢሞቲዎስ 2፣2፣20) የሚለው በስማቸው ሳይሆን በግብራቸው በያዙት የሀላፊነት ቦታ ሳይሆን በፍሬቸው ለተለዩት ለእነዚህ ሁለት አባቶች ጥሩ ገላጭ ሀይለ ቃል ይመስለኛል፡፡
የሚሊዮኖች የእምነት ቤት የሆነችው ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ አንደ አቡነ አብርሀም ያሉ ወርቆችንና ብሮችን፣ አንደ እነ አባ ሰረቀ ብርሀን ያሉ የእንጨትና የሸክላ ስሪቶችን የያዘች ለመሆኗ አይደለም በምእምኑ ከእምነቱ ውጪ ላሉትም በግልጽ የሚታይና የሚታወቅ ነው፡፡
የእንጨትና የሸክላ ስሪቶቹ ያለ ቦታቸው መግባታቸው፣ ያለ ደረጃቸው መቀመጣቸው፣ ለምን እንዴት በምን ምክንያትና በማን አንደሆነ የተሰወረ ባለመሆኑ ወርቅ እንዲሆኑ ማድረግም ሆነ ከማይገባቸው ቦታ ማንሳት የማይቻል ስለሆነ የሚቻለውና መሆንም ያለበት “አንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ” የሚለውን የቅዱስ መጽኃፍ ቃል መፈጸም ነው፡፡
ከብረው ለሚያስከብሩን፣ በእውነተኛ አባትነት በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ቃልና መንገድ ለሚመሩንና ለሚያስታርቁን የአባትነት አክብሮት መስጠት፣ቃላቸውን መስማት ምክራቸውን መቀበል መሪነታቸውን መከተል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ያሉትን ደግሞ አታውቁንም አናውቃችሁም ማለት ያስፈልጋል፡፡ አቅሙ ካለና ሁኔታው ከፈቀደም ከወርቆቹና ከብሮቹ ጋር በመተባበር ቤታችንን ከሸክላና ከእንጨት ማጽዳት፡፡ ቤተ መቀደሴን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት አይደል ያለው ጌታ እየሱስ፡፡
እነዚህ አለቦታቸው ገብተው የተቀመጡ መንፈሳዊውን ሥልጣን ለአለማዊ ተግባር የሚያውሉ ከእውነተኞቹ አባቶች እየቀደሙ በተገኘው መድረክ ሁሉ እየታደሙ ምእምኑን የሚያሳቱ ናቸውና፤ በዮሐንስ መልእክት (1፣3፣17) “እንግዲህ እናንተ ወዳጆች ሆይ ይህን አስቀድማችሁ ስለምታውቁ በአመጸኞች ስህተት ተስባችሁ ከራሳችሁ ጽናት አንዳትወድቁ ተጠንቀቁ”፡ተብሎ እንደተጻፈው ሰዎቹን ለይቶ ማወቅ፣አውቆም መጠንነቅ የምእምኑ ተግባር ይሆናል፡፡
“ረጃጅም ልብስ ለብሰው መዞርን በገበያም ሰላምታን፣ በምኩራብም የከበሬታን ወንበር፣ በግብርም የከበሬታን ስፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ” ( የማርቆስ ወንጌል 12፣38/39)
ረዣም እድሜ ከጤና ጋር ለእውነተኛዎቹ የሀይማኖት አባቶች

↧

በዘ-ህወሀት የውሸት ምድር የማወንበጃ መረጃ ዘመቻ፡ ቀጣፊው በኢትዮጵያ ዉሸትን እዉነት ነው እያለ ሲሰብክ?

$
0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተጠናከረ የመጣውን የዘ-ህወሀት (ዘራፊ ህወሀት) የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ለማጋለጥ ሲባል በተከታታይ እያቀረብኩ ካለሁት ትችት ይህ ሶስተኛው ክፍል ነው፡፡ እ.ኤ.አ መስከረም 5/2016 አቅርቤው በነበረው ትችት በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የዘ-ህወሀትን የጭቆና አገዛዝ በመቃወም እየተስፋፋ እና እየተጠናከረ የመጣውን ሕዝባዊ የእምቢተኝነት አመጽ አሳንሶ እና አኮስሶ ለማቅረብ በሚል እኩይ ምግባር ዘ-ህወሀት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻውን ይጀምራል በማለት አሳስቤ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 18/2016 አቅርቤው በነበረው ሁለተኛው ትችቴ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ አስፈሪ እና የማይቀር የዘር ማጥፋት ዘመቻ እውን ይሆናል በማለት አቅርቦት የነበረውን የቅጥፈት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ መሰሪ ፕሮፓጋንዳ ሀሰት እና ተራ ቅጥፈት መሆኑን አጋልጫለሁ፡፡
በመስከረም መጀመሪያዎቹ አካባቢ አቅርቤው የነበረው የዘ-ህወሀት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ በአሁኑ ጊዜ ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ እና በተሟላ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ትችቴ ደግሞ የዘ-ህወሀት ዋና የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ/ዋና ኃላፊ (መማቆ) የሆነውን የደብረጽዮን ገብረሚካኤልን የተዛባ እና መሳቂያ የሆነ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ በማጋለጥ አቀርባለሁ፡፡ “እራሱን በራሱ ዉሸት ካሳመነ ሰው ጋር በፍጹም አትከራከር“ የሚለውን ጥንታዊ አባባል በሚገባ እገነዘባለሁ፡፡ ጭራ የቀራቸዉን ቀጣፊ ውሸታሞች በፍርድ ቤት በፍትሕ አደባባይ በመስቀለኛ ጥያቄ ማፋጠጡን የምመርጥ ቢሆንም ቅሉ ያ የፍትሕ አደባባይ የሚለው ነገር በሀገሪቱ ውስጥ ከቶውንም የሌለ እና ዳብዛው የጠፋ በመሆኑ ምክንያት በዓለም ህዝብ ህሊና ዳኝነት ክርክሬን ቀጥላለሁ።
በእኔ ዘመን ሳሙና የሆኑ አእምሮአቸው በዉሸት የተበከለ ቀጣፊዎችን አጋጥመዉኛል፡፡ እናም አንድ ቁልጭ ያለ እና በግልጽ የማስታውሰው ነገር ቢኖር እነዚህ አእምሮአቸው የታመመ ቀጣፊዎች እራሳቸዉን እንጂ ሌላ ሰው ስያታለሉ አላየሁም፡፡ ይልቁንም እነርሱ የቅጥፈት ባለሞያዎች የሆኑት እራሳቸውን በማታለል ነው፡፡ ሆኖም ግን ውሸት በሚነሳበት ጊዜ የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ (መማቆ) የሆነው ደብረጽዮን እና ሌሎች የዘ-ህወሀት ወሮበሎች የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ፍጡሮች የውሸት፣ የቅጥፈት እና የተራ አሀዛዊ ቅጥፈት ቀፍቃፊ ጌቶቸ ናቸው፡፡
መማቆ ደብረጽዮን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ለበርካታ ሳምንታት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ በመክፈት ማወናበድን በመቀጠል ረገድ 3ኛው ትልቅ ጠብመንጃ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሀትን የጭቆና አገዛዝ በመቃወም እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ በሚገኘው ሕዝባዊ አመጽ እና መገዳደር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን ከዘ-ህወሀት የአውሬዎች ዋሻ መካከል በድንገት ብቅ ብለው በመውጣት በሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት ያወጁ እና የጮኹ ተኩላዎች ናቸው፡፡
የዘ-ህወሀት የመረጃ ማወናበጃ ጨዋታ ግልጽ ይመስላል፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የቁማርና ካራምቦላ (እያጋጩ ማለት) ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡

cdo-debretsion
አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን ፍጹም በሆነ መልኩ ምክንያታዊ ያልሆነ እና እርባናቢስ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈጸማል በማለት ፍርሃት ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ “ሰማይ ይወድቃል” እያለ በሕዝብ ላይ ምዕናባዊ ፍርሀት በመልቀቅ እንደሚባለው በተመሳሳይ መልኩ አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፋት ድርጊት ይፈጸማል በማለት ሕዝቡን በማስፈራራት እና በማደናገር ላይ ይገኛሉ፡፡
እንዲያው ለመሆኑ ይህንን አዲስ ነገር አድርገው እንደበቀቀን እየደጋገሙ የሚለፈልፉት ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ምን ሲያደርጉ ነው የቆዩት? በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በጋምቤላው፣ በሶማሊው፣ በሲዳማው፣ በአፋሩ፣ በቤንሻንጉሉ፣ ወዘተ ሲፈጽሙት የቆዩትን የዘር ማጥፋት ወንጀል እስቲ ዘወር ብለው ይመልከቱት፣ ዘወር ብሎ የሚያይ አንገት ካላቸው፡፡ ምኑ ነው አሁን አዲስ የሚሆነው፡፡ ይልቁንስ አሁን የእነርሱ ማብቂያ እና መውደሚያ መሆኑን ስለተገነዘቡት ይሆናል የአቦን ቅጠል እንደቀመሰች ፍየል በመለፍለፍ ላይ የሚገኙት፡፡
ነው? ወይስ ያብየን ለምዬ?
መማቆ ደብረጽዮን የዘር ማጥፋት ወንጀል አይኖርም ይላል፡፡ በእርግጥ የራሱ ቃላት እንዲህ የሚሉ ሆነው ይገኛሉ፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት (የዘር ማጥፋት ወንጀል) ሊኖር አይችልም፡፡ በጥቂት ወንጀለኞች እና ችግር ፈጣሪዎች ሊቀሰቀሱ የሚችሉ የተነጣጠሉ ሁከቶች እና ግጭቶች (አመጾች ሳይሆኑ) ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዘህ ደግሞ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አይደሉም“ በማለት ሳያውቀው አምኗል፡፡
እንግዲህ ወገኖቼ ከነዚህ ባለመንታ ምላስ እባቦች የትኛውን እንመን? አባይ ጸሀይን፣ ስዩም መስፍንን ወይስ ደግሞ ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን?
መማቆ ደብረጽዮን በመጠኑም ቢሆን ተቀባይነት ያለው ለማስመሰል እና እራሱን ከሌሎቹ አስበልጦ እንዲታይ የማድረግ ቁመናን ለመላበስ ሙከራ አድርጓል፡፡ በስተቀኙ በኩል የዘ-ህወሀትን ባለኮከብ እርማ ሰንደቅ ዓላማ በማንጠልጠል የዘ-ህወሀት መልካም አድራጊ መስሎ መቅረብ ሞክሯል። ግን ያለው አስተሳሰብና ያደርገው ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ አርሱም ዘ-ህወሀትም ደንታ እንደሌላቸው አረጋግጧል። መማቆ ደብረጽዮን የኢትዮጵያ ህዝቦች በዓለም ላይ ታይተው የማያውቁትን ነገሮች ቀይ እና ሰማያዊ ላም እንዲሁም ቀይ ዝሆን አየን እያሉ ይናገራሉ፡፡ ዝም ብለው ይቀባጥራሉ እናም እንዲሁ በፈጠራ ወሬዎች ጭንቅላታቸውን ሞልተው ይገኛሉ ነበር ያለው፡፡
መማቆ ደብረጽዮን ሁሉም ነገር አንዳለ ሳይሆን አንደተመለከቱቱ ነው ይላል። ሲያስረዳም ፣ “አንድ ሰው የጠራውን ቀን ጨለማ ነው ደጋግሞ ካለ ሕዝቡ ያንን የጠራ ቀን ጨለማ ነው የሚል ሀሳብን ይይዛል ማለት ነው“ ነበር ያለው፡፡
ከዚህ አንጻር በዘፈቀደ አመንኩ፡፡ እጄን ሰጠሁ!
ስለጨለማ እራሱ የጨለማው ልዑል ከሆነው አስመሳይ ፍጡር በላይ ማን ሊያውቅ ይችላል?
ስለጨለማ የጨለማው ጌታ ከሆነው ከንቱ ፍጡር በላይ ማን የበለጠ ሊያውቅ ይችላል?
ስለጭለማ መማቆ ደብረጽዮንን የመሞገት ችሎታ የለኝም።
ስለጨለማ በብርሀኑ በኩል ያሉት ሰዎች ሳይሆኑ የጨለማው ጌታ የበለጠ ያውቃል።
በሚያስገርም ሁኔታ መማቆ ደብረጽዮን የእርሱን የጨለማ ተመሳስሎ የተዋሰው እንዲህ ከሚለው እና የናዚ ጀርመን የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር ከነበረው ከጆሴፍ ጎቤልስ ነው፣ “ታላቅ ውሸት ከዋሸህ እና ይህንንም ውሸት ደግመህ እና ደጋግመህ ተግባራዊ ካደረግኸው በመጨረሻ ሕዝብ እውነት ብሎ ያምናል፡፡“
ሆኖም ግን መማቆ ደብረጽዮን እንዲህ የሚሉትን የጎቤልስን አብረው የነበሩትን ቃላት ሆን ብሎ ዘሏቸዋል፡
“መንግስት ሕዝቡን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና/ወይም ወታደራዊ የሆኑ ውሸቶች ከሚፈጥሯቸው እንቅስቃሴዎች ለመከላከል ሲል ውሸቶች ለእንደዚህ ላለ ጊዜ ብቻ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ በዚህም መሰረት እውነት የሚሞተው የውሸት ጠላት በመሆኑ እና የዚህም ተቀጽላ እውነት የመንግስት ታላቁ ጠላት በመሆኑ መንግስት ሁሉንም ኃይሉን ሰላማዊ ሰዎችን ለመጨቆኛነት የሚጠቀምበት ዋናው አስፈላጊው መሳርያ ነገር ነው፡፡“
እውነት የመንግስት የመረጃ ማወናበጃ ዋና ጠላት ነው፡፡
የመማቆ ደብረጽዮን ቃለመጠይቅ፣
በቪዲዮ በተቀረጸው ቃለመጠይቅ መማቆ ደብረጽዮን በበርካታ ጉዳዮች ላይ በተደጋጋሚ ሲደነፋ ( ሲንተባተብ አላልኩም) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ስለዘ-ህወሀት እውነተኛ ምንነት መግለጽ የማይችሉ ደንቆሮዎች እና ደደቦች መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ በውሸት ላይ ያሉ ሕዝቦች በማለት እራሱን ከፍ ከፍ እያደረገ መሰረተቢስ የሆነውን የማታለል ንገግር አድርግዋል ፈጽሟል፡፡ ለመማቆ ደብረጽዮን ኢትዮጵያ ሕዝቦች በምዕናባዊ ሀሳብ እና በእውነት መካከል ያለውን ልዩነት ለይተው የማያውቁ የዋሀን ናቸው፡፡ በእርሱ ድሁር አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሚያዩት ነገር በተጨባጭ የሚያዩት እና የሚመለከቱት ነገር አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት እውነታነት የሌለው በድድብና የተሞላ ምዕናባዊ ነገር ነው፡፡ እውነታውን እንዲያውቁት እንዲመለከቱት ተደጋጋሚ የሆነ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህንን ትምህርት እንዲሰጥ እና ስራውን እንዲሰራ ለብዙሀን መገናኛ ጥሪ መቅረብ አለበት ነው ያለው መማቆው !
የመማቆ ደብረጽዮን ቃለመጠይቅ እንዲህ የሚሉ በርካታ የሆኑ የፕሮፓግንዳ እና የፖለቲካ ዓላማዎችን ለመጎናጸፍ በግልጽ የተዘየደ ዕቅድ ነው፡
1ኛ) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጣጥሎ የሚገኘው መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞ በጎንደር ላይ ተወስኖ የሚገኝ ትንሽ ነገር ነው፡፡
2ኛ) በጎንደር ውስጥ የተፈጠረው ሁከት ጥቂት የውጭ ኃይሎች እና ወንጀለኞች ስራ ነው፡፡ በጎንደር ውስጥ ወይም ደግሞ በሌላ በማናቸውም ቦታ እና አካባቢ ውስጥ ምንም ዓይነት ሕዝባዊ አመጽ የለም፡፡
3ኛ) በጎንደር የተቀሰቀሰው ሁከት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ የስራ ኃላፊዎች እና በአካባቢው አመራር ብቃትየለሽነት እና የአስተዳደር ጉድለት የተፈጠረ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ተወግደው በሌላ መተካት ይኖርባቸዋል፡፡
4ኛ) በኢትዮጵያ ሕዝቦች ፖለቲካ እና ማህበረሰብ ውስጥ የትግራይ የበላይነት የሚለው ነገር አውዳሚ የሆነ የሰዎች የተሳሳተ ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የትግራይ የበላይነት በልብወለድ ውስጥ ያለ በምዕናባዊ ሀሳብ የሚኖር እንጅ በነባራዊ እውነታ በተጨባጭ የሌለ ነገር ነው፡፡
5ኛ) የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግራይ የበላይነት የሌለ መሆኑን እንዲያውቅ ትምህርት ያልተሰጠው በመሆኑ ከግንኙነት ውድቀት የመነጨ ነው፡፡ የእራሳቸው የግንዛቤ ምዕናባዊ እሳቤ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በብርሀን እና በጨለማ መካከል ያለውን ልዩነት መናገር የማይችሉ እንደዚህ ያለ የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር ያለ መሆኑን መናገር የማይችሉ እና ትምህርት የሚያስፈልጋቸው ደንቆሮዎች ናቸው፡፡
6ኛ) ትግራውያን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የጎሳ የበላይነት እየተገበሩ ላለመሆናቸው ሊያስገነዝብ የሚያስችል የመረጃ የማወናበጃ ዘመቻ ታላቅ የብዙሀን መገናኛ ፍላጎት አለ፡፡
7ኛ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ነባራዊ እውነታ የሚያሳየው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ የጎሳ ቡድን በእራሱ ክልል (ባንቱስታን) የበላይ ነው፡፡
8ኛ) ለጎሳ ታላቅነት እና የበላይነት የጎሳ ፌዴራሊዝም የመጨረሻው ጠባቂ ኃይል ነው፡፡
9ኛ) ብቸኛው እውነታ የዘ-ህወሀት እውነታ ብቻ ሲሆን ሌላው ግን ተራ ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለኢትዮጵያ ሕዝቦች መልካም ነገር እና ጥቅም ተልዕኮው ተነግሮ ስለማያልቀው ስለዘ-ህወሀት የተሳሳተ ግንዛቤ አለው፡፡
10ኛ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዘ-ህወሀት ደም የተጠማ ወንጀለኛ የወሮበሎች ስብስብ እንደሆነ አድርገው የሚነግሯቸውን የሚዋሹ ዓይኖቻቸውን እና ጆሮዎቻቸውን ማመን የሚያቆሙ ከሆነ የዘ-ህወሀትን ደግ፣ ጓዳዊ፣ የተረጋጋ፣ ለጋሽ፣ አፍቃሪ እና ሰብአዊ ፍጡርነት ይገነዘባሉ፡፡“
በሰጠው ቃለመጠይቅ መማቆ ደብረጽዮን በቅርቡ በጎንደር የተፈጠረውን ሁከት (ሕዝባዊ አመጽ) እና ትግራውያንን ማፈናቀል እየተባለ የቀረበውን ውንጀላ ጨምሮ የትግራይ የበላይነት የሚለው መሰረተቢስ ውንጀላ እንደሆነ እና የጎሳ ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ቀውሶች ሁሉ ፈዋሽ መድኃኒት አድርጎ በርካታ ጉዳዮችን እንደሚከተለው አቅርቧል፡
መማቆ ደብረጽዮን አንደተናገረው (ከእንግሊዘኛው አንደተተረጎመ)
“በጎንደር ስለተከሰተው “ግጭት”፣ “ሁከት” ሁኔታ፣
…እንደ ቁንጮ አመራር እኔ ብቻ ስለሁኔታው አውቃለሁ፡፡ የግጭቱን ዝርዝር ሁኔታ የሚያውቁ የተለያዩ አካላት ናቸው፡፡ ያንን ሁኔታ በቅርበት አልከታተልም…በሱዳን እና ከሱዳን በተመለሱት መካከል ግጭት እንዳለ አውቃለሁ፡፡
ይህንን እንዴት መመልከት እንዳለብን፡ በተለየ መልክ እንደተገለጸው ዋናው ነገር ይህ ሁኔታ የሕዝብ ለሕዝብ ጉዳይ (ግጭት) አይደለም፡፡ ከትግራይ ጥቂት የእኛ ሰዎች እና ከሌሎች ቦታዎች በጎንደር ውስጥ በተፈጠረው አመጽ እየተሰቃዩ እና ጉዳት እየደረሰባቸው ይገኛሉ፡፡ የተቀጣጠለውን እሳት (ግጭት) ለማስፋፋት የሚፈልጉ ጥቂት ሰዎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ በጎንደር የሚኖሩ የአማራ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ሌሎችን (አማራ ያልሆኑትን) እንደሚከላከሉላቸው እና ጉዳት እንደማይደርስባቸው እንገነዘባለን፡፡ የተፈጸሙ በርካታ ድርጊቶች (ወንጀሎች) አሉ፡፡ በጣም ጥቂት የሆኑ ሰዎች በጎንደር በሚኖሩ ትግራውያን ንብረቶች ላይ ጉዳት ለማድረስ ይፈልጋሉ፡፡ ስለሆነም እነዚህ ድርጊቶች የአብዛኛው የጎንደር ሕዝብ ድርጊቶች አይደሉም፡፡ በየትኛውም ቦታ ትግራውያንን ለማጥቃት ተብሎ የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም፡፡ ሆኖም ግን በትግራውያን ላይ ወንጀሎችን ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ጥቂት ግለሰቦች በትግራውያን ላይ የወንጀል ድርጊቶችን እንደፈጸሙ እናውቃለን፡፡ ይህ ሁኔታ የጥቂቶች ድርጊት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ከእራሳቸው ዓላማ ጋር የሚደረግ እንቅስቃሴ አለ፡፡ የፌዴራል መንግስት እና የክልሉ መንግስት ይህንን ሁኔታ በቅርብ በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ግን ይህ ጥያቄ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ አይደለም፡፡ ከትንታኔው መገንዘብ እንደሚቻለው መፍትሄው በግጭቱ (መጋፈጥ) ላይ በማተኮር ብቻ ሊገኝ አይችልም፡፡ በአካባቢው አመራር፣ ለሕዝቦች መልካም አስተዳደር ማቅረብ ያልተቻለበትን፣ ለሚቀርቡት ጥያቄዎች ሁሉ በወቅቱ ምላሽ ያልተሰጠበትን፣ ችግሮች ያሉ መሆናቸውን ያለማስተዋል እና ሌሎችን እንደዚህ ያሉትን ሁኔታዎች ሰፋ ባለ መልኩ መመልከት አለብን፡፡ እናም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ፡፡ ይህ በእራሱ ችግሮችን ፈጥሯል፣ እናም በዚህ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች የምንፈታ ከሆነ ሌሎችን ችግሮችም አብረን እንፈታለን፡፡ ሌሎች አስተዳደራዊ ችግሮችን፣ የልማት ጥያቄዎችን እንፈታለን ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የፖለቲካ ጥያቄዎችን ማንሸራሸር እና መፍታት እንችላለን፡፡ እኛ እንግዲህ የምንመለከተው በዚህ ዓይነት መንገድ ነው፡፡
በጎንደር የተከሰተው ግጭት አንድ ውሱን ጉዳይ ነው፡፡ ሁሉንም አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳየን አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በተለያዩ መድረኮች ላይ እየተካሄዱ ባሉት ውይይቶች ላይ በጣም አዝነዋል፡፡ ይህ ኢህአዴግ ያመጣው ነገር አይደለም፡፡ የጎንደር እና የትግራይ ሕዝብ ለበርካታ ጊዚያት አብረው ኖረዋል፡፡ በአንድ ላይ መኖር ብቻ አይደለም ሆኖም ግን እርስ በእርስ በመጋባት እንደ አንድ ቤተሰብ ሆነዋል… ሆኖም ግን ሕዝብ ለሕዝብ ግጭት (የጎሳ ግጭት) ለመፍጠር ዓላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡ ጉዳቶች ተፈጥረዋል…እንግዲህ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እየተደረገ ያለው ውይይት ስለዚህ ጉዳይ ነው፡፡
የሕዝብ ለሕዝብ (የጎሳ) ግጭት ሊኖር አይችልም… በጎንደር ስለተፈጸመው ትንሽ ግጭት የተለየ ልዩ የሆነ መፍትሄ የለንም፡፡ በአንድ በትግራውያን ላይ ለደረሰ ጉዳት መፍትሄ የለም፡፡ ዋናው ነገር ስለሰላም እና መረጋጋት ጉዳይ ነው፡፡ ይኸ ጉዳይ በሚገባ ከተመለሰ ሌላው (የጎሳ ግጭት) ጉዳይ በእራሱ ይፈታል፡፡
በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ስለትግራይ የበላይነት ሁኔታ፣
አልጋ በአልጋ የሚሆን ነገር የለም፡፡ ውጣ ውረድ አለ፡፡ እውነታ የማይመስል አንድ ምዕናባዊ አስተሳሰብ እውነት ይሆናል፡፡ ለምሳሌም ያህል አሁን በዚህ ክፍል ውስጥ ብርሀን አለ፡፡ ነገር ግን አሁን በዚህ ክፍል ያለው ጨለማ ነው የሚባል እና የሚደገም ከሆነ ሕዝብ ጨለማ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ብርሀን መኖሩ የሚታወቅ ቢሆንም እንኳ ጨለማ ነው፡፡ ምዕናባዊው ሀሳብ ወደ ተጨባጭ እውንነት ተለወጠ ማለት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት አንድ የተረሳ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ትክክለኛው ምላሽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አልተሰጠም ማለት ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ በብዙሀን መገናኛዎች ውጤታማ የሆነ ስራ አልተሰራም ማለት ነው፡፡ ማንኛውም እውነት ሆኖ ያልተገኘ ነገር ሁሉ (ምክንያቱም ስለትግራይ የበላይነት እየተነገሩ የቆዩ ውሸቶች እስከ አሁን ድረስ ተግዳሮት ስላልገጠማቸው) አሁንም እውነት አይደለም፡፡
እውነት በእራሱ አይናገርም፡፡ እውነታውን በተለያዩ መንገዶች በብዙሀን መገናኛ እና በሌሎች መግለጽ ይቻላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስት ሜዲያ ተገቢ የሆነ ስራ መስራት አለበት፡፡ ድክመት፣ እድገት ወይም ደግሞ ወደኋላ የመንሸራተት እና ሌሎችም ጉዳዮች ካሉ የመንግስት ሜዲያ ነው እውነታውን ማቅረብ ያለበት፡፡ ሆኖም ግን ሜዲያው እውነትን ማንጸባረቅ (ማሰራጨት) አለበት፡፡
በፌዴራሊዝም መኖር ምክንያት የትግራይ የበላይነት ሊኖር አይችልም፡፡ ፌዴራሊዝም ማለት ሁሉም ሕዝቦች እኩል ናቸው ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሕዝብ እራሱን በእራሱ ያስተዳድራል፡፡ አንድ ጎሳ የበላይ ወይም የበታች የሚባል ነገር የለም፡፡ የጎሳ ቡድኖች ትልቅ ወይም ትንሽ አባላት ስለመኖር ጉዳይ አይደለም፡፡ ትግራውያን እራሳቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ ኦሮሞዎች እና የደቡብ ሕዝቦች እንዲሁም የሶማሊ ሕዝቦች እራሳቸውን በእራሳቸው ያስተዳድራሉ፡፡ ይህም ማለት የእራሳቸውን መንግስት በባለቤትነት ይይዛሉ ማለት ነው፡፡ መሰረቱ እኩልነት ነው፡፡ ይህ ማለት የእራስህን አስተዳደር አስተዳድር ማለት ነው…
በአማራ ክልል ውስጥ ትግራውያን አስተዳዳሪዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በጋምቤላ ውስጥ አስተዳዳሪው ትግራዊ ሊሆን አይችልም፡፡ እንደዚህ ያለው የጎሳ ፌዴራሊዝም አወቃቀር አንዱ ጎሳ በሌላው ላይ የበላይ እንዲሆን አያደርግም፡፡ አንድ ዓይነት የጎሳ ማንነት ያላቸው እራሳቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ ትግራውያን እዚህም እዚያም የበላይ (አለቆች) ናቸው የምትል ከሆነ መሰረትየለሽ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን በየቦታው እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ሁሉም ነገር እውነትነት የሌለው ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የትግራውያን የበላይነት እውነታነት የለውም፡፡ እንደዚህ ያለ ውንጀላ ማቅረብ መሰረተቢስ ነው፡፡ ብርሀን እየበራ እያለ ባለበት ሁኔታ ጨለማ ነው እንደማለት ያህል ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህንን በደጋገምከው ጊዜ ሌሎችም አዎ ጨለማ ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ በፌዴራሊዝም ሀገሪቱ እንዴት መተዳደር እንዳለባት ስለፌዴራሊዝም የኢትዮጵያን ሕዝቦች አላስተማርናቸውም፡፡
ያ እውነታ ለህዝቡ እንዲተላለፍ አልተደረገም፡፡ ትግራውያን በየቦታው የበላይ ናቸው ማለት እውነታ አይደለም፡፡ ያ ዜሮ ነው፡፡ ዜሮ፡፡ ከትግራይ ክልል ውጭ ትግራውያን ሰው ካለ የመዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ኢንቨስተር ሆኖ እንደማንኛውም ሰው ይኖራል፡፡ ስለሆነም ሕዝቡን ያለማስተማር የግንዛቤ ችግር አለብን፡፡ የትግራይ የበላይነት እውነት አይደለም ሆኖም ግን የእኛ ብዙሀነን መገናኛዎች ጉድለት አለባቸው፡፡ የትግራይ የበላይነት እንደሌለ ብዙሀን መገናኛዎች እውነቱን የማሰራጨት ኃላፊነት አለባቸው…
መማቆ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፡ መንታ ምላስ እና ሁለት ተጻራሪ እምነቶችን በመያዝ የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻን ማካሄድ፣
ጆርጅ ኦርዌል “ፖለቲካ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ድርሰቱ እንዲህ በማለት ጽፏል፡
በእኛ ጊዜ የፖለቲካ ንግግር እና መጻፍ በአብዛኛው መከላከል ለማይደረግላቸው መከላከያዎች ናቸው፡፡ የፖለቲካ ቋንቋ… ውሸቶችን ለመፈብረክ እና እውነት ለማስመሰል የተዘጋጀ እና የተከበሩትን ለመግደል ምንም ዓይነት ጥንካሬ በሌለበት በባዶ ነፋስ ውስጥ ጥንካሬ እንዳለ አድርጎ የማቅረብ ድርጊት ነው…“ ነበር ያለው፡፡
ከደብረጽዮን መንታ ምላስ የሚወጡ ዉሸቶችና እና ተጻራሪ እምነት የሚብሱ ብዙ የሉም፡፡
የአዞ እንባ አንቢው ደብረጽዮን በመንግስት ላይ መንግስት ላዋቀረው እና ማንኛውንም ነገር የሚቆጣጠረው የዘ-ህወሀት ፖለቲካ አጧዛዥ አድራጊ ፈጣሪ ነው፡፡ በዘ-ህወሀት አገዛዝ ውስጥ በርካታ የኃላፊነት ቦታዎችን ይዞ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኮሙኒኬሽን እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ኃላፊ (በትክክለኛ አጠራር የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ (መማቆ)/ Chief Disinformation Officer (CDO) እና ከሶስቱ የዘ-ህወሀት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አንዱ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል ይባላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የቦርድ ሊቀመንበር እና የቀድሞው የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ልማት ኤጀንሲ/Ethiopian Information and Communication Development Agency (EICTDA)፣ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የብሮድባንድ ኔትዎርክ ለመገንባት እና የአካዳሚክ እና የምርምር ኔትወርኮችን ለመደገፍ፣ የኢንፍርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኔትዎርክ እና ልማትን በማሳደግ የአካዳሚክ ተቋማትን የግል ዘርፉን ለማሻሻል ተቋቁሞ የነበረው ድርጅት ዳይሬክተር ጀኔራል ነበር ይባላል፡፡
በአዋጅ ቁጥር 691/2010 ድንጋጌ መሰረት የተቋቋመው የኮሙኒኬሽን እና የኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የEICTDA፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒከኬሽን አጀንሲ/ETA እና የዘ-ህወሀት የትራንስፖርት እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ጥምረቶች ነው፡፡
መማቆ ደብረጽዮን የዘ-ህወሀት ተቃዋሚ በሆኑት በኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ላይ ስለላ ለሚያካሂደው እና ከጣሊያን አገር የሳይበር ደህንነት ድርጅት ምርመራ ቡድን/cybersecurity firm Hacking Team የተገዛው ሶፍት ዌር በስለላ ተግባር ላይ እንዲውል እና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ዕኩይ ምግባር ዋና መሀንዲስ ሆኖ ሲያገልግል የነበረ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሬፐብሊክ ከዩኤስ አሜሪካ የቴሌፎን መስመር ጋር በማገናኘት የስለላ ተግባራትን በማካሄድ ሕግን መጣስ የሚል ውንጀላ በዩኤስ ፌዴራል ፍርድ ቤት ተመዝግቦ በፋይል ተያዘ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጉዳዩ በሕግ ማሻሻያ ሂደት ውስጥ ሲሆን በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ለዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይደርሳል፡፡
እንደ አንድ ዘገባ ከሆነ መማቆ ደብረጽዮን በጫካ ውስጥ የዘ-ህወሀት ሬዲዮ ጣቢያ የነበረውን ድምጺ ወያኔን ከመሰረቱ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው ይባላል ፡፡ ሚኒያፖሊስ አም ኤን እየተባለ ከሚጠራው የድረገጽ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪውን እ.ኤ.አ በ2011 እንዳገኘ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ “በኢትዮጵያ ድህነት ላይ የአይሲቲ ማዕከል ተጠቃሚዎችን የአይሲቲ ውጤታማነት መፈተሽ/Exploring the perception of users of community ICT centers on the effectiveness of ICT on poverty in Ethiopia“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የዶክትሬት ዲግሪው የጥናት መሟያ የመመረቂያ ጽሁፍ ምናልባትም ኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) የልማት መገልገያ መሳሪያ እንደሆነ መርምሮ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በሚያስገርም ሁኔታ በድህነት ላይ ያለውን የህልዮት ግንዛቤ በተመሳሳይ መልኩ ለፕሮፓጋንዳ እና ለመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ስራ እንደሚውል አድርጎ እምነት ያሳደረ ይመስላል፡፡
መማቆ ደብረጽዮን አሁን በህይወት እንደሌለው እንደ ወሮበላ ዘራፊው መለስ ዜናዊ (ወዘመዜ) ሁሉ የኦርዌልን ባህሪ የተላበሰ ገጽታ ያለው ሰው ነው፡፡ እንደ ወዘመዜ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ በኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ በአበዳሪዎች፣ በለጋሽ ድርጅቶች እና በዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪዎች ላይ የቁማር ጨዋታን መጫወት ይወዳል፡፡
እንደ ታላቅ ወንድሙ እንደ ወዘመዜ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ እርሱ እና የእርሱ ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች በእውነት እና በእውነታዋ ዓለም ላይ የሚኖሩ እና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ደግሞ በህልም እና በጨለማ ምዕናባዊ ዓለም እንዲሁም በሀሳብ እና በቅዠት ዓለም ውስጥ የሚኖር ነው በማለት ያምናሉ፡፡
በዘ-ህወሀት የኦርዌሊያን ፕላኔት “ጦርነት ሰላም ነው፡፡ ነጻነት ባርነት ነው፡፡ ድንቁርና ጥንካሬ ነው፡፡ አምባገነንነት ዴሞክራሲ ነው፡፡ የጎሳ ፌዴራሊዝም የጎሳ እኩልነት ነው፡፡ የጎሳ የበላይነት ሕገወጥ ሴራ ነው፡፡ የዘ-ህወሀት ባለሀብቶች አገዛዝ ማለት ሁሉም ሕዝቦች እኩል የፖለቲካ ስልጣን አላቸው ማለት ነው፡፡“
መማቆ ደብረጽዮን የኢትዮጵያን ሕዝቦች እንደሚያታልሏቸው፣ ጆሮዎቻቸው እንደሚዋሹባቸው እንዲያምኑ እና ጉድለት ያለው አእምሮ እንዳላቸው አድርገው እንዲያምኑ ይፈልጋል፡፡
ስለዘ-ህወሀት ፕላኔት መረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ከብዙ ጊዜ ጀምሬ ስጽፍ ቆይቻለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ወደ 2009 መለስ ብለን ስንቃኝ ከ3.6 ሚሊዮን የአካባቢ ምርጫዎች መቀመጫዎች ባለፈው ዓመት (2008) ከሶስት መቀመጫዎች በስተቀር ሁሉንም ማሸነፍ ፍጹም የሆነ ዴሞክራሲያዊ ነው፣ እናም ዴሞክራሲ ስለሂደት ነው፣ ስለውጤት አይደለም… ሂደቱ ንጹህ ከሆነ ስህተት ዜሮ ነው ነበር ያለው መለስ ዜናዊ ፡፡
ዛሬ መማቆ ደብረጽዮን እንዲህ ይላል፣ “የጎሳ ፌዴራሊዝም እኩልነት ነው፡፡ የዘ-ህወሀት የበላይነት ምንም ዓይደለም ግን ዱለታ ነው፡፡ ትግራውያን በየቦታው የበላይ ናቸው ማለት እውነታን የሚያመላክት አይደለም፡፡ ያ ዜሮ ነው፡፡“
የሚያስገርመው ነገር መማቆ እና ወዘመዜ ስለዜሮ አንድ ነገር አላቸው፡፡
ዘሮን በጣም ይወዱታል፡፡ በተለይም የዜሮ ድምር ምርጫ ጨዋታዎችን (ሁልጊዜ ሁሉንም ነገር እንደሚያሸንፉ እና ሌላው እያንዳንዱ ሰው ግን ሁሉንም ነገር እንደሚያጣ እና እንደሚሸነፍ) በጣም ይወዷቸዋል፡፡ ላለፉት 25 ዓመታት ከአንድ የዜሮ ድምር ጨዋታ ሌላ የዜሮ ድምር ጨዋታ እየተገለባበጡ በመጫወት ሁልጊዜ በተከታታይ ሲያሸንፉ ኖረዋል፡፡
እስቲ ጉዳዩን ግልጽ ላድርገው፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 በዘ-ህወሀት ፓርላማ መቀመጫዎችን መቶ በመቶ ያሸነፈው ማን ነው? ይኸ ነው እንግዲህ የዜሮ ድምር ጨዋታ ማለት!
ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2008 ተካሂዶ እንደነበረው የአካባቢ ምርጫዎች ወዘመዜ ኢትዮጵያውያን ስለዘ-ህወሀት የተሳሳት ግንዛቤ አላቸው እንዳለው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ ደብረጽዮን ዛሬ እንደዚሁ በማለት ላይ ይገኛል፡፡
ወዘመዜ ኢትዮጵያውያን ስለዴሞክራሲ የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው ብሏል፡፡ ስለምርጫዎች፣ የሕግ የበላይነት፣ መልካም አስተዳደር እና ስለፌዴራሊዝም የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው፡፡
መማቆ ደብረጽዮን ስለዘ-ህወሀት ዴሞክራሲ፣ ፌዴራሊዝም፣ ስለትግራይ የበላይነት፣ ስለልማት፣ ስለመልካም አስተዳደር እና ስለዴሞክራሲ የተሳሳት ግንዛቤ አላቸው ይላል፡፡
መማቆ ደብረጽዮን ኢትዮጵያውያን ከእንቀልፋቸው ተነስተው የፈላዉን ቡና ያሽትቱ ይላል፡፡
በዘ-ህወሀት ፕላኔት ውስጥ የተጻራሪ እምነቶች እና መንታ ምላሶች ውጤት፡ “ጦርነት ሰላም ነው፡፡ ነጻነት ባርነት ነው፡፡ ድንቁርና ጥንካሬ ነው፡፡ አምባገነንነት ዴሞክራሲ ነው፡፡ ድህነት ባለጸግነት ነው፡፡ ረሀብ ጥጋብ ነው፡፡ የመንግስት ስህተቶች የሰብአዊ መብቶች ናቸው፡፡ የተጭበረበሩ እና የተዘረፉ ምርጫዎች የሕዝቦች ምርጫዎች ናቸው፡፡ ሕዝቦችን ማስፈራራት ለእነርሱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ እናም የተደራረቡት የውሸቶች ቁልሎች የእውነት ማዕበሎች ናቸው፡፡“
የዘ-ህወሀት መንታ ምላስ እና ተጻራሪ እምነቶች ምርጫዎች ስለሂደት የሚዘግቡ ናቸው፡፡ የሕግ የበላይነት ማለት በዘፈቀደ የዜጎችን ህይወት የመቅጠፍ፣ የነጻነት እና ንብረት ክልከላ ሂደት ነው፡፡ አስተዳደር ስለተጠያቂነት እና ግልጸኝነት አይደለም፡፡ በላም ጡት ላይ ተጣብቆ እንደሚኖር መዥገር በስልጣን ኮርቻ ላይ ተጣብቆ መኖር ማለት ነው፡፡ ሕገ መንግስት ስለሕግ የበላይነት አይደለም፡፡ ስለሕገወጥ አገዛዝ ነው፡፡ ፌዴራሊዝም ስለግልጽ ሕገመንግስታዊ የስልጣን ክፍፍል አይደለም፡፡ ሆኖም ግን አምባገነናዊ አገዛዝን ለማጠናከር ጥልቅ የሆነ የጎሳ፣ ባህላዊ እና ክልላዊ የጎሳ ፌዴራሊዝም እየተባለ ስለሚጠራው ምዕናባዊ ሂደት ነው፡፡
መንታ ምላስ እና ተጻራሪ እምነቶች እንደ መረጃ ማወናበጃ ስልቶች፣
እ.ኤ.አ በ1984 ኦርዌል እንዲህ በማለት ጽፏል፡
ተጻራሪ እምነት ሁለት ተጻራሪ እምነቶች በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ በአንድ ጊዜ የሚያዙበት እና ሁለቱንም መቀበል ማለት ነው… በቅንነት የሚያምኑበትን ሆን ብሎ ውሸቶችን ለመናገር እና የማይመቹ የሚመስሉትን እንዲረሱ የማድረግ እና አስፈላጊ ከሆነም ብዙ ጊዜ የቆየ እና የተረሳ ቢሆንም ነባራዊውን እውነታው መካድ እና አንድ ሰው የካደውን እንዲይዝ የሚደረግበት ሁኔታ ነው- ይኸ ሁሉ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ተጻራሪ እምነቶች የሚለውን ቃል መጠቀም ቢኖርም ተጻራሪ እምነቶችን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ቃሉን ለመጠቀም አንድ ሰው ከእውነታው ጋር መጋፈጥ ይኖርበታል፡፡ አዲስ በሆኑ ተጻራሪ እምነቶች ይህንን እውቀት ለማጥፋት እና ወሰን በሌለው መልኩ ሁልጊዜ ውሸቱ ከእውነቱ በአንድ እርምጃ ወደፊት ይሄዳል፡፡
መማቆ ደብረጽዮን እና የእርሱ ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ሁሉንም ነጻ ጋዜጠኞች በማሰር እና እነርሱን ለመተቸት ድፍረቱ ያላቸውን ፕሬሶች እንዲዘጉ አድርገዋል፡፡ አሁን ደግሞ የመገናኛ ብዙሀኑ የዘ-ህወሀትን እውነተኛ አፈጻጸም ለሕዝቡ በመዘገቡ ረገድ ደካማ አፈጻጸም ነው ያስመዘገቡት በማለት ቅሬታውን በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡ ስለዘ-ህወሀት የብዙህን መገናኛ ደካማ ስራ ቅሬታ የሚያቀርብ ከሆነ የተሳሳተ የአስተሳሰብ መስመርን መከተል ማለት ነው፡፡ አሁን ማንም ኢትዮጵያዊ (ምናልባትም ከዘ-ህወሀት ታዛዥ ሎሌዎች በስተቀር) ለዘ-ህወሀት መገናኛ ብዙሀን ትኩረት አይሰጥም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዘ-ህወሀት ውሸቶች፣ ቅጥፈቶች እና ተራ አሃዛዊ አሀዛዊ ቅጥፈቶች ታመዋል፣ ደክመዋልም!
መማቆ ደብረጽዮን ምንም ዓይነት አዲስ ነገር እየተናገረ አይደለም፡፡ የእርሱ ቀደምት የሆነው አስቂኙ በረከት ስምኦን ማንም ቢሆን የዘ-ህወሀትን ቴሌቪዥን ወይም ሌሎችን መገናኛ ብዙሀን አይመለከትም በማለት በየጊዜው ቅሬታውን ያቀርብ ነበር ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከኢሳት ጋር ተጣብቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከኢሳት ሬዲዮ ጋር እራሳቸውን አዋህደዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ኢሳትን በገንዘብ እና በሌላም መደገፍ እንዲችሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
መማቆ ደብረጽዮን በጎንደር እና በሌሎች ሁከቱ በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ያለው ችግር ስር የሰደደ ሙስና፣ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ የመጠቀም እና ክልሎችን (ባንቱስታን) የሚያስተዳድሩ ባለስልጣኖች የአስተዳደር ጉድለት አለባቸው ይላል፡፡ ከዘ-ህወሀት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም፡፡
እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን እንደ እንግሊዝ የቅኝ ግዛት ጌቶች እና እንደ ደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች ዘረኛ የአፓርታይድ አገዛዝ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ዘ-ህወሀት በክልሎች (ባንቱስታንስ) ውስጣዊ ቅኝ ግዛትን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ዘ-ህወሀት ለእርሱ ታማኝ የሆኑ ብቸኛ የክልሉ ኗሪ የክልል ባለስልጣናትን ፈጥሯል፡፡ ዘ-ህወሀት የእርሱን ወኪሎች፣ አሻንጉሊት የአካባቢ መሪዎች በስልጣን ላይ ያስቀምጣል፣ እናም ምዕናባዊ የእራስ ገዝ እና የእራስ አስተዳደር መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ሆኖም ግን በክልል መንግስታት ላይ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ የክልል ባለስልጣኖች የእራሳቸውን መንግስት በነጻነት መምራት ይቅር እና ከዘ-ህወሀት ፈቃድ ውጭ ከቢሯቸው እንኳ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን መማቆ ደብረጽዮን በክልል የሚገኙትን ባለስልጣናት በማባረር ዘ-ህወሀትን ነጻ ሊያደርግ ይፈልጋል፡፡
መማቆ ደብረጽዮን ዘ-ህወሀት በጣም ወሳኝ እና አስፈላጊ በሆኑ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ተቋማት ውስጥ ዘ-ህወሀት ትንሽ ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ቁጥጥር እንደማያደርግ ይክዳል፡፡
ይህንን ጉዳይ እንዲህ በማለት በሌላ መንገድ ላስቀምጠው፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2016 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የፓርላሜንታሪ የቅርጫ ምርጫ መቶ በመቶ ያሸነፈው ማን ነበር? በኢኮኖሚው ላይ የበላይነት ያለው ማን ነው? በወታደራዊ ኃይሉ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ያለው ማን ነው? በሲቪል ሰርቪሱ ላይ ፍጹም የሆነ ቁጥጥር ያለው ማን ነው? የደህንነት አገልግሎቱን እና የፍትህ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ማን ነው? የአበዳሪ እና የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶችን እንዲሁም የዓለም አቀፍ የደህንነት አቃጣሪዎችን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ማን ነው?
ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚቀርብ ጥያቄ ቢኖር አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማቅረብ እና በማንኛውም ጊዜ ለመከራከር እርግጠኞች ነን፡፡
በመማቆ ደብረጽዮን የተደረገ አስደናቂ የእምነት ቃል፣
ለአስር ዓመታት ያህል የዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት እና የእርሱ የክልል መንግስታት ሸፍጠኞች እና ስለደቡብ አፍሪካ (ባንቱስታን) ስርዓት የጭብጥ ክርክሬን ሳደርግ እና መረጃዎችን ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡
በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት ክልል (የጎሳ ፌዴራሊዝም) ስርዓት የአፓርታይድ ባንቱስታን ወይም ደግሞ መኖሪያ ሀገር ስርዓትን በሚመለከት ከደብረጽዮን አፍ ማጠቃለያ ማስረጃ አለ፡፡
አሁን ባለፈው ሚያዝያ “ባንቱስታናይዜሽን (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችት በዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው እና እየተጠበቀ ያለው ስርዓት ከደቡብ አፍሪካ ጥቂት ነጮች ዘረኛ አገዛዝ ጋር እንደሚመሳሰል እና እ.ኤ.አ በ1994 የብዙሀኑን ጥቁር አገዛዝ ከመመስረቱ በፊት ከነበረው ጋር አንድ ዓይነት እንደሆነ ከምንም ጥርጣሬ በላይ አሳይቻለሁ፡፡
መማቆ ደብረጽዮን በቃለ ምልልሱ እንዲህ ብሎ ነበር፡
“በአማራ ክልል ትግራውያን አስተዳዳሪዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በጋምቤላ ውስጥ አስተዳዳሪው ትግራውያን ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ (የጎሳ ፌዴራሊዝም ስምምነት) ለሌሎች የበላይነት ዕድል አይሰጥም፡፡ አንድ ዓይነት ጎሳ ያላቸው እራሳቸውን በእራሳቸው ያስተዳድራሉ፡፡ ትግራውያን እዚህም እዚያም የበላይ (አለቆች) ናቸው የምትል ከሆነ መሰረተቢስ ነው“ ነበር ያለው፡፡
ይኸ ነበር እንግዲህ በአፓርታይድ ባንቱስታን ሀገር በግልጽ የተፈጸመው!
በክዋዙሉ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው ዙሉስ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በሲስኬይ እና በትራንስኬይ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የኮሳ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በቦትስዋና ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የትስዋና ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በሌቦዋ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የፔዲ እና የሰሜን ድበሌ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በቬንዳ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የቬንዳ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በጋዛንኩሉ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የሻንጋን እና የሶንጋ ሕዝቦች ብቻ ነበሩ፡፡
በክዋ ክዋ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የባሶቶስ ሕዝብ ብቻ ነው፡፡
ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ የመጨረሻውን ስልጣን የያዘው ማን ነው? የጥቂት ነጮች የአፓርታይድ አገዛዝ ነው፡፡
በደቡብ አፍሪካ ያሉ ሕዝቦች ነጻነት ምን ያህል ነጻ ነው?
እንዲያው ለነገሩ ያህል ዘ-ህወሀት ነጻ ናቸው ይላል፡፡
የኢትዮጵያ 9ኙ ባንቱስታንስ ምን ያህል ነጻ ናቸው? ዘ-ህወሀት እንዲያው ለነገሩ ያህል ነጻ ናቸው ይላል፡፡
በእውነተኛ የፌዴራሊዝም ስርዓት ዘር፣ ጎሳ፣ ጾታ፣ ኃይማኖት፣ ርዕዮተ ዓለም፣ ወዘተ የፖለቲካ መብቶችን ከመተግበር ጋር በተያያዘ መልኩ ምንም ዓይነት ጠቀሜታ የላቸውም፡፡
ለምሳሌም ያህል ሂላሪ ክሊንተን ከኒዮርክ የዩኤስ አሜሪካ የምክር ቤት አባል ከመሆኗ በፊት የሞያ ህይወቷን ያሳለፈችው በአርካንሳስ ግዛት ነበር፡፡ ሚት ሮምነይ የተወለደው በሚችጋን ሲሆን የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው በኡታህ ሆኖ የማሳቹሴትስ አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡ ባራክ ኦባማ የተወለደው በሀዋይ ሲሆን የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው ደግሞ በካሊፎርኒያ፣ በኒዮርክ እና በማሳቹሴትስ ሆኖ ከኢሊኖይስ የዩኤስ አሜሪካ የምክር ቤት አባል ለመሆን በቅቷል፡፡
የዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት የቅርብ እና ታላቅ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ አገዛዝ ተቀጽላ መሆኑን መማቆ ደብረጽዮን ማስተባበል የማይቻል ማስረጃ ያቀረበልኝ ስለሆነ አመሰግነዋለሁ፡፡
ኃይል ያለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ነው፡ የዘ-ህወሀት መገዳደር እርባናቢስ ነገር ነው፣
በዘ-ህወሀት አገዛዝ ላይ መጠነ ሰፊ እየሆነ እና እየተስፋፋ የመጣው ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና መገዳደር እልቂትን በመፈጸም፣ የተዛባ የማወናበጃ መረጃ በማቅረብ ወይም ደግሞ በሌላ በማንኛውም መንገድ የሚቆም አይደለም፡፡
በአንዲ ዊሊያም የግጥም ስንኞች ጸሀይ ሰማይን ትለቃለች ብሎ መናገር አይቻልም/ህጻንን እንዳያለቅስ መጠየቅ አይቻልም/የውቅያኖስን ማዕበል ወደ ዳርቻው እየገፋ እንዳይመጣ ለማስቆም አይቻልም/
እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሰብአዊ መብቶቻቸውን እንዳይቀዳጁ እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ የማትከፋፈል፣ ነጻነት እና ለሁሉም ፍትህ የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊ የሆነች ሀገርን እንዳይመሰርቱ ማስቆም አይቻልም፡፡
የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስቆም በፍጹም አይቻልም!!!
ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ እና ቀላል ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 ዓለም አቀፍ ንቃት የተፈጠረ መሆኑን ዥብግኒው ብርዜንስኪ እንደተናገሩት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በአሁኑ ጊዜም በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ መነቃቃት ተፈጥሯል፡፡
ብርዜንስኪ እንዲህ የሚል የመከራከሪያ ጭብጥ አቅርበዋል፡
በሰው ልጆች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉም የሰው ልጆች ሁሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው፣ የፖለቲካ ንቃታቸው ከፍ ብሏል እናም የፖለቲካ ተሳትፏቸው እየጨመረ የመጣበት ሁኔታ ተከስቷል…የዓለም አቀፉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለበርካታ ዘመናት በቅኝ ግዛት ትዝታ እና በአገዛዝ የበላይነት ተቀፍድዶ የኖረው ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ለግል ክብር መጨመር፣ ለባህል መከበር እና ለኢኮኖሚ ዕድሎች ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ በመገኘቱ ምክንያት ነው…ለክብር የሚጠየቀው ዓለም አቀፍ ጥያቄ ለዓለም አቀፉ የፖለቲካ መነቃቃት ዋና መሰረታዊ ክስተት ነው…ያ መነቃቃት ማህበራዊ መጠኑ ግዙፍ እና ስር ነቀቀል የፖለታካ ጥያቄ ነው… ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ዓለም አቀፍ የሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን ስርጭት እና እየጨመረ የመጣው የኢንተርኔት አገልግሎት የፖለቲካ ወይም የኃይማኖት ጉዳዮችን መስመር እያስያዘ ለመብቱ እና ለወደፊቱ ብሩህ ተስፋ ሲል የጋራ ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብን በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ ኃይሎች ዓለም አቀፍ ወሰንን በመሻገር በአሁኑ ጊዜ ባሉት መንግስታት እንደዚሁም ባለው ዓለም አቀፍ ተዋረድ ላይ መገዳደሮችን በመፍጠር ላይ ይገኛል…
የሶስተኛው ዓለም ወጣቶች በተለይ እረፍትየለሽ እና በቀልተኞች ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አሁን ያሉበት የሕዝብ የመጨመር አብዮትም የፖለቲካ የጊዜ ፈንጂ ቦምብ ነው…የወጣቶቹ የወደፊት አብዮተኞች የመሆንም ሁኔታ በርካታ ተማሪዎች የሶስተኛ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት በታዳጊ ሀገሮች ተከታታይ እና በምሁራን ካምፕ ውስጥም የሚገኙ በመሆናቸው የሁኔታው መከሰት ጎልቶ በመውጣት ላይ ይገኛል…
የዓለም ዋና ዋና ኃይሎች፣ አዲሶቹ እና የቀድሞዎቹ አስደናቂ ከሆነ እውነታ ጋር ተጋፍጠዋል፡ የጦር ኃይላቸው አደገኛነት ከምንጊዜውም በላይ የበለጠ ሆኖ የሚገኝ ቢሆንም የፖለቲካ መነቃቃት በተፈጠረበት ማህበረሰብ ላይ በመግባት ሁኔታውን ለመቆጣጠር መሞከር በጣም ዝቅተኛ የሆነ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አቅምን የሚገድብ ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ጉዳዩን በግልጽ ለማስቀመጥ በዱሮ ጊዜ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ በአካል ከመግደል ይልቅ አንድ ሚሊዮን ሕዝብን መቆጣጠር ይቀል ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን አንድ ሚሊዮን ሕዝብን ከመቆጣጠር ይልቅ አንድ ሚሊዮን ሕዝብን መግደል መቁጠር ከሚያስችል በላይ ቀላል ነገር ነው፡፡
ለዘ-ህወሀት የተገኙት ትምህርቶች ቀላል እና እንዲህ የሚሉ ናቸው፡
70 በመቶ ያህሉን የሕዝብ ብዛት የሚይዙት የኢትዮጵያ ወጣቶች ሕዝባዊ የእምቢተኝነት አመጹን እና አብዮቱን የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መሪዎች እና ሌሎች ቀሪዎች ሳይሆኑ ወጣቶቹ በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች የሰብአዊ ክብር እና ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡ ይኸ ነገር ምንም ዓይነት ድርድር ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች እረፍትየለሾች እና በቀልተኞች ናቸው፡፡ ምንም ዓይነት ትዕግስት የላቸውም፡፡ እንደ እቃ ሊገዙ ወይም ሊሸጡ አይችሉም፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች በዘ-ህወሀት የጭቆና አገዛዝ የሁለተኛ ዜግነት ባርነት ተጭኖባቸው የሚገኙ ስለሆነ በዚህ መቅነቢስ ዘረኛ ስርዓት ታመዋል፣ ደክመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች የዘ-ህወሀት መሪዎች ባልሰለጠነው አውሪያዊ ምዕናባቸው ከሚስሉት በእጅጉ የበለጠ ስረነቀል ለውጥን ናፋቂ እና ለተግባራዊነቱም ሌት ከቀን የሚታገሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡
ዘ-ህወሀት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ከመቆጣጠር ይልቅ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን መግደል በእጅጉ ይቀለዋል፡፡
የዘ-ህወሀት ወታደራዊ ኃይል አደጋ ጣይነት ከምንጊዜውም በላይ ከፍተኛ ነው፣ ሆኖም ግን ከኢትዮጵያ ወጣቶች ኃይል ጋር ስናነጻጽረው በአውሎ ነፋስ ዉስጥ አንዳለ የላባ ያህል ነው፡፡
እንግዲህ የዘ-ህወሀት ዕድል እንደዚህ ነው፡፡
ዘ-ህወሀት ባዶ ይሆናል እናም ወደታሪክ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ይጣላል፡፡
ዘ-ህወሀት ማወቅ ያለበት አንድ የማይሞት እና የማይበገር ሕግ አለ፡፡
ያንን ሕግ ያቀናበሩት ማህተመ ጋንዲ ሲሆኑ ሕጉ እንዲህ የሚል ነው፡
“ጨቋኞች እና ገዳዮች ለጊዜው የማይበገሩ መስለው ይታያሉ፣ ሆኖም ግን በመጨረሻ ሁልጊዜም ቢሆን ይወድቃሉ፣ አስቡት ሁልጊዜ፡፡“
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
መስከረም 17 ቀን 2009 ዓ.ም

↧

የጅምላ እስርና ግድያ እየፈጸሙ ያሉ የህወሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ

$
0
0

ኢሳት (መስከረም 17 ፥ 2009)
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ግድያና ጅምላ እስር እየፈጸሙ ያሉ ባለስልጣናት ሆነ የጸጥታ ሃይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች አንድነት ጠየቀ።
አለም አቀፍ ህብረት ለኢሳት በላከው መግለጫ ህዝብን ማገልገል የሚገባው መንግስት ዜጋውን እየጨፈጨፈ መቀጠል ስለለለበት ስልጣንን መልቀቅ ይኖርበታል ብሏል።
ከዚህ በኋላም የሚፈጸም ግድያና ጅምላ እስር በአስቸኳይ እንዲቆም አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች አንድነት በመግለጫው ጠይቋል።
ህብረቱ ለኢትዮጵያ ህዝብን የሚያገለግሉና በዕውቀት የሚሰሩ መሪዎች እንድሰጣት ሁሉ በጸሎት እንዲተጋና ህገወጥ ድርጊቶችን እንዲያወግዝ ጥሪን አቅርቧል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መዋቅርና ሃብቷ በዘር ሃረጋቸውን በፖለቲካ አቋማቸው ከገዢው ፓርቲ ጋር በወገኑ ሰዎች እየተበዘበዘ መሆኑን ህብረቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ አብራርቷል።

↧
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live