Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ፍትህን እና እዉነትን በእግራችሁ ለመርገጥ አትንጠራወዙ ! (ከመኢአድ የተሰጠ መግለጫ)

0
0

aeupየመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አንድ ብቻ ነዉ::እሱዉም በአቶ ማሙሸት አማረ ነዉ የሚመራዉ:: በ2006 ዓም በተደረገዉ ጠቅላላ ጉባኤ ከ483 ጠቅላላ ጉባኤ ተሰብሳቢዎች ዉስጥ በ477 ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች የተመረጠዉ የአቶ ማሙሸት አመራር ነዉ::ሆኖም ወያኔ በምርጫ ቦታ እንኳን ተገኝቶ የማያዉቀዉን ተላላኪዎቿን አቶ አበባዉን እና ዶ/ር በዛብህን መርጣ የመኢአድን ቢሮዉን አስረክባቸዋለች::ከዚያ ጊዜ ጀምሮ መኢአድ በአቶ ማሙሸት እየተመራ ፍትህን እና እዉነትን የማስከበር ተጋድሎ ላይ ነዉ:: የመኢአድ ቢሮ ሲጀምር የመኢአድ የትግል ሜዳ አይደለም እና ቢሮዉን ነቅለዉ መዉሰድ ሲፈልጉ ማቃጠል ይችላሉ::መኢአድ የሚታገለዉ የወያኔን ኢፍትሃዊ ህግ እና ኢ ፍትሃዊ የህግ አፈጻጸምን ነዉና ወያኔ በህገ ወጥ መንገድ ህግ ነዉ እያለች ወያኔ እያነሳች የምትጭንብንን ነገር ሁሉ አንቀበልም:: ስለሆነም መኢአድ የሚከተሉትን እርምጃዎች በመዉስድ የወያኔን ኢፍትሃዊ እና ኢ-ዲሞክራሲያዊ አካሄድ አምርሮ ይቃወማል:-

-የወያኔን ምርጫ ቦርድ በወያኔ ፍርድቤት ከሶ መፈናፈኛ ቢያሳጣዉም የወያኔ ካንካሮ ፍርድቤት እንደተለመደዉ ፍትህን ሽሮታል::ቢሆንም መኢአድ ትግሉን ቀጥሏል:: እናም መኢአድ ተቃዉሞዉን እና ለፍትህ ብሎም ለእዉነት የሚያደርገዉ ተጋድሎ ቀጥሎ የወያኔን ፍርድ ቤት ዉሳኔ እንደማይቀበለዉ መግለጫ ሰጥቷል::
-መኢአድ የተመሰረተዉ በወያኔ ፈቃድ ስላልሆነ መኢአድ ህልዉናዉን ይዞ እንደሚቀጥል እና የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ እስከሚወጣ እንደሚታገል ግልጽ አድርጓል
-መኢአድ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገዉን የዲሞክራሲ ተጋድሎ እያበረታታ እና እየደገፍ በተግባር ከህዝብ ጋር የቆመ እና በህዝብ ዉስጥ የሚመላለስ ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል

ለዚህ ዉሳኔዉም መኢአድ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለበት ነዉ:: በርካታ አመራሮቹ ታስረዋል: በቅሊንጦ ተቃጥለዋል: ተደብድበዋል: አሁን ድረስ የመኢአድ አባላት በመላ ሀገሪቱ ቤታቸዉ በከፍተኛ ከበባ ዉስጥ ነዉ:: በኢትዮጵያ እስር በቶች ዉስጥ ካሉ የማንኛዉም ፓርቲ ታሳሪዎች ቁጥር በላይ የሚበዛዉ የመኢአድ ታሳሪ ነዉ:: ወያኔም ሀገሪቱ ኮሽ ባለች ቁጥር : ምርጫ በመጣ ቁጥር: ህዝባዊ አመጽ በተቀሰቀሰ ቁጥር የሚበረግገዉ እና ለማሰር ሽህ እና ሽህ ሰራዊቱን እና ፖሊስ ሀይሉን የሚያሰማራዉ በመኢአድ አመራሮች እና አባላት ላይ ነዉ:: ወያኔ እዉነት አለዉ::ማን ጀግና እንደሆነ እና ማን ሞት ፊት በጀግንነት እንደሚቆም ጠንቅቆ ያዉቃል::ማን ለፍትህ ለመሞት እንደወሰነ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት እየዘመረ በታላቅ ተድጋድሎ እንደሚሞት ጠንቅቆ ያዉቃል::

እናም መኢአድ ለእዉነት እና ለፍትህ እስከ መጨረሻዉ የሚሞት ድርጅት መሆኑን ሁሉም ይወቅ:: አንዳንድ በነፈሰበት የሚነፍሱ ሰዎች እንደሚሉት ወያኔ ተቀበል የሚለዉን ሁሉ የሚቀበል ድርጅት አይደለም:: መኢአድ በደም እና በአላማ ተላቁጦ የተፈጠረ ድርጅት ነዉ:: መኢአድ በወጀብ እና በመከራ መሃከል ማለፍ የለመደ: በደም ታሪክ ከሚጽፉ አባቶች አብራክ በተወለዱ ልጆች በጥልቅ መሰረት ላይ የቆመ ድርጅት ነዉ::

ጠላትም ወዳጅም ይሄንኑ ይወቅ ! የፍትህ ህሊና የሌላችሁ : የባንዳ ልጆች እና በጥላቻ የተሞላችሁ አንዳንድ ወገኖች በመኢአድ መንገድ ላይ መቆማችሁን አቁሙ:: ፍትህን እና እዉነትን በእግራችሁ ለመርገጥ አትንጠራወዙ !
መኢአድ አሸናፊ ድርጅት ነዉ !
አንዲት ኢትዮጵያ ! አንድ ህዝብ ! አንድ ሀገር !

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት

የመኢአድ የህዝብ ግንኙነት ም/ ኃላፊ
ለገሰ ወ/ሃና


የኮንሶ ቀውስ: “ጥያቄያችን በኦሮሚያ ክልል እስከመጠቃለል ይዘልቃል” አቶ ገመቹ ገንፌ የኮንሶ ኮሚቴ አባል “ጥያቄው የህዝብ ሳይሆን የጥቂቶች ነው” –የክልሉ መንግስት

0
0

konso

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ታትሞ የወጣው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገባ

አለማየሁ አንበሴ

ከኮንሶ የዞንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት የበርካቶች ህይወት ጠፍቶና በሺህ የሚቆጠሩ ቤቶች ተቃጥለው ዜጎች የተፈናቀሉሲሆን የኮንሶ ህዝብ ኮሚቴ፤ ጥያቄያችን ወደ ኦሮሚያ ክልል እስከመጠቃለል ይዘልቃል ብለዋል፡፡

በአካባቢው እስከ ትናንት ድረስ ግጭቶች መቀጠላቸውንና የታጠቁ የመንግስት ኃይሎች የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ እንደነበር የኮንሶ ኮሚቴ አባል አቶ ገመቹ ገንፌ ለአዲስ አድማስ የገለፁ ሲሆን በሰሞኑ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና አስክሬናቸው እስከ ትናንት ድረስ ለቤተሰብ እንዳልተሰጠ ተገናግረዋል።

የደቡብ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ አይረዲን በበኩላቸው፤ ግጭቱን ያስነሱትና በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉት የኮሚቴው አባላት ናቸው ይላሉ፡፡
“የፀጥታ ኃይሉ ጥፋቱ ከደረሰ በኋላ ነው ህዝቡን ለመታደግ ወደ አካባቢው የገባው፤ በአሁን ወቅት ግን በኮንሶ ምንም ግጭት የለም፤ ሰላማዊ ነው”፤ ብለዋል ኃላፊዋ፡፡

የኮሚቴው አባል አቶ ገመቹ፤ ጥያቄያችን በፌደሬሽን ምክር ቤት ተቀባይነት ካላገኘ በሪፈረንደም ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመጠቃለል ጥያቄ እናቀርባለን ያሉ ሲሆን ወ/ሮ ሂክማን በበኩላቸው የዞንነት ጥያቄው ተቀባይነት እንደሌለው ምላሽ ተሰጥቶቷል፤ ከህዝቡ ጋር በተደረጉ ውይይቶች አሁን ባለው የወረዳ አወቃቀር ለመቀጠል ህዝቡ ፍላጎት እንዳለው ታውቋል ብለዋል፡፡
የፌደሬሽን ም/ቤት፤ የቀረበው ጥያቄ የአስተዳደር ጉዳይ ስለሆነ ሊመለከተው እንደማይችል ጠቁሞ፤ ም/ቤቱ የሚመለከተው የማንነት ጥያቄን እንደሆነ አመልክቷል፡፡ የኮንሶ ጥያቄ የማንነት አለመሆኑን በመግለፅ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል መንግስትና የኮንሶ ኮሚቴ አባላት በበርካታ ጉዳዮች ላይ እየተወዛገቡ ይገኛሉ፡፡

ዓለም አቀፍ ደረጃ October 3, 2016 በጀርመን ኢምባሲ ደጃፍና እዚያው ጀርመን በርሊን October 2, 2016 ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

0
0

google

ዓለም አቀፍ ደረጃ October 3 2016 በጀርመን ኢምባሲ ደጃፍና እዚያው ጀርመን በርሊን October 2 2016 ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጀርመን የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ።
October 2 2016 በርሊን
የጀርመን መራህት መንግስት አንጀላ መርክል ወደ ኢትዮጵያ ለስራ ጉብኝት ጉዞ አጋጣሚ በማስመልከት
እሁድ ጠዋት 10:00 October 2 . 2016
አድራሻ Willy-Brandt-Str. 1 · 10557 Berlin
የጀርመን መራህት መንግስት አንጀላ መርክል ጽ፨ቤት ፊትለፊት ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን
በኢትዮጵያ በንጹሃን ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየትካሄደ ያለው አፈና እና ጭፍጨፋ ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የለጋሽ አገር መሪ ጉዞ የመጀመሪያ ነው። ለታፈኑት ለሚታፈኑት ለተገደሉት ለሚገደሉት ለታሰሩት ለሚታሰሩት ለተፈናቀሉት ለሚፈናቀሉት ለተጨፈጨፉት ለሚጨፈጨፉት ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ኑ በበርሊን ድምጻችንን እናሰማ።
የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።

በዚህ አጋጣሚ በአለም ያሉ ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰኞ በኦክቶበር ሦስት Monday October 3. 2016 ጀርመን የተዋሃደችበት የጀርመን መንግስት በጀርመን የምስራቁን ከዲክታተር ወደ ነጻነት ዲሞክራሲ በሚያከብርበት ቀን በኢትዮጵያ የጀርመን መንግስት እየደገፈው ያለውን የሰብአዊ መብት ረጋጭ ስርዓት በአለም ለማጋለጥ የፈሰሰውን እና የሚፈሰውን የንጹሃን ኢትዮጵያውያን ደም በማስታወስ በአለም ላይ በጀርመን ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ እንድትጠሩ እንድታደርጉ ዘንድ በማክበር እንጠይቃለን። በኢትዮጵያ በንጹሃን ሰላማዊ ዜጎች ላይ እየትካሄደ ያለው አፈና እና ጭፍጨፋ ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የለጋሽ አገር መሪ ጉዞ የመጀመሪያ ነው።

ለመረጃ ያህል

የጀርመን መንግስት እና ህዝብ እ.ኤ.አ ኦክቶበር ሦስት የምስራቁም ጀርመን ክፍል ከዲክታተር ተላቆ የህግ የባላይነት ዲሞክራሲ እንዲሁም ሰብአዊ መብቶች በማረጋገጥ ጀርመን የተዋሃደችበት ቀን ሆኖ በዲክታተር የተሰቃዩት እሚታወሱበት ዲክታተር የሚወገዝበት ቀን ነው።

በተለይ የጀርመኑ ፕሬዚደንት ዮአሂም ጋውክ እንዲሁም መራህት መንግስት አንጀላ መርክል ሁለቱ ጀርመኖች እስከ ተዋሃዱበት ድረስ በዲክታተር አገዛዝ ስር በምስራቅ ጀርመን ዜጋ እና ነዋሪ ነበሩ ሁለቱም ነጻነት ያገኙት ሁለቱ ጀርመኞች ከተቀላቀሉ በሁዋላ ነው ሁለቱም በዲክታተር ስርታአት የማይቻለውን በዴሞክራሲ ሁለቱም የተዋሃደው ጀርመን የአገር መሪ ለመሆን በቅተዋል። ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።

ፕሬዚደንት ዮአሂም ጋውክ በ እ.ኤ.አ March 17 – 20፣ 2013 የኢትዮጵያ ጉዞዋቸው ከፖለቲከኞች እና የታወቁ ሰዎች ተገናኝተው ይህ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ የድሮ አገሬን ምስራቅ ጀርመንን ያስታውሰኛል ብለው ነበር። በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን ጥያቄ በእዚሁ በጀርመን ኤምባሲ በተካሄደው (ሪሴፕሽን) አቀባበል ላይ ተጋብዘው የነበሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን በወቅቱ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ ጀርመን በጹሁፍ የገለጡት ነው ። ዶር ነጋሶ ጊዳዳ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ለሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ የፖለቲካ ክፍል የጹሁፍን ኮፒ ልከውለታል ደርሶታል። ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።

ጂ.አይ.ዜድ ወይም በቀድሞ ስሙ ጂ ቲ ዜድ በተባለው የጀርመን የርዳታ ሚኒስትር ስር የሚተዳደር ድርጅትም ባለፈው አመት 2015 የኢትዮጵያ ታላቁ ሩጫ ላይ ሦስት ሺ ወጣቶች የጀርመንን ሰንደቅአላማ ቀለም በማስለበስ የጀርመንን ውህደት ምስራቅ ጀርመን ከዲክታተር ሥርዐት ተላቅቃ ወደ ሰብሳአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት እንዲሁም የህግ የበላይነት ከተረጋገጠበት ምዕራብ ጀርመን ጋር የ ሃያ አምስተኛ አመት መዋሃድ በአዲስ አበባ አስከብሯል። ስለዚህ የሚያወግዙትን ዲክታተር ለምን በኢትዮጵያ እንደሚደግፉ ልንጠይቅ እና ልናጋልጥ ይገባል።

ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ
ጀርመን

በመንግስት ትዕዛዝ እንጂ በፌስቡክ መረጃ የሞተ ሰው የለም |ከስዩም ተሾመ

0
0

hailemariam

አንድ መሪ

ስዩም ተሾመ

ስዩም ተሾመ

በየትኛውም መድረክ ቢሆን የሚናገረው ነገር ሀገርና ሕዝብን ወክሎ እንደመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል። ከዚህ ቀደም፣ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ በሀገሪቱ የተከሰተውን ግጭትና አለመረጋጋት አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” የሚለውን ዓ.ነገር በመናገር ብቻ እንዴት በህዝብ ላይ ጦርነት እንደ አወጁ ተመልክተናል። አሁንም ጠ/ሚኒስትሩ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ሌላ ታሪካዊ ስህተት ፈፅመዋል። በዚህ ፅሁፍ ይህን ንግግር መሰረት በማድረግ በውስጡ የሚንፀባረቀውን የተዛባ አመለካከት እና በዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ዘንድ የሚሰጠውን ትርጉምና ፋይዳ በዝርዝር እንመለከታለን።

“Social media offered a platform to enhance popular participation, but misinformation could go viral and mislead, especially the youth. It had empowered extremists to exploit genuine concerns and spread messages of hate.” H.E. Mr Hailemariam Dessalegn, General assembly of the United Nations, General Debate of the 71st Session.

በእርግጥ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እኔ በምኖርበትና ሌሎች አመፅና ተቃውሞ በተቀሰቀሰባቸው አከባቢዎች ማህበራዊ ሚዲያዎች በመንግስት ተዘግተዋል። ከጠ/ሚኒስትሩ ንግግር መገንዘብ እንደሚቻለው፣ አሁን መንግስት በውጪ የሚኖሩና በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት በፖለቲካው ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ኢትዮጲያኖችን ለመቆጣጠር ፍላጎት እያሳየ ነው።

በቅድሚያ በጠ/ሚኒስትሩ ንግግር ውስጥ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ጋር በተያያዘ ያለውን የተዛባ አመለካከት በግልፅ የሚጠቁሙ ሁለት ቃላቶች አሉ። እነሱም፡- “misinformation” እና “mislead” የሚሉት ናቸው። በዚህ መሰረት፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁት “የተሳሳቱ መረጃዎች” እና “ወጣቶችን ለስህተት የሚዳርጉ” ናቸው።

ስለዚህ፣ እንደ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም አነጋገር መንግስት፤ አንደኛ፡- “በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ላይ ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባል”፤ ሁለተኛ፡- “በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ በሚለቁ ሰዎች ላይ ክትትል ሊያደርግ ይገባል”። ይህ አቋም “የፍፁማዊነት/አለመሳሳት” (infallibility) አመለካከት ውጤት ነው።

የአምባገነንነት ስረ-መሰረቱ ራስን ፍፁም ትክክል (infallible) አድርጎ ማየት ነው። “በሁሉም ነገር ላይ ‘እኛ እናቅላችኋለን’ ማለታቸውና ስለ ሕዝቡ ግን ምንም አለማወቃቸው” የአምባገነኖች መለያ ባህሪ ነው። በተመሣሣይ፣ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር የራሳቸውንና የመንግስታቸውን አምባገነንነት ከማንፀባረቅ የዘለለ ትርጉምና ፋይዳ የለውም።የኢህአዴግ መንግስት በማህበራዊ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎችን “ትክክለኝነት” እና “አግባብነት” ለመከታተልና ለመቆጣጠር ያለውን ፍላጎት በግልፅ አንፀባርቀዋል።

በመቀጠል የጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ንግግር ከመረጃና ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ መብት አንፃር ያለበትን መሰረታዊ ችግር የ“John Stuart Mill” – “On Liberty” መፅሃፍን ዋቢ በማድረግ በዝርዝር እንመለከታለን። ይህ እንግሊዛዊ ፈላስፋ ከሰው ልጅ ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ጋር በተያያዘ የሚከተሉትን መሰረታዊ መርሆች ያስቀምጣል፤ አንደኛ፡-“የተሳሳተ መረጃን መከልከል በራሱ ስህተት ነው”፣ ሁለተኛ፡- “ሰው በተሳሳተ መረጃ አይመራም።” የጠ/ሚኒስትሩን ንግግር መርሆች አንፃር እንመልከት፡-

1ኛ፡- የተሳሳተ መረጃን መከልከል በራሱ ስህተት ነው
አንድ ሰው በራሱ “ትክክል ነው” ብሎ ያመነበትን ሃሳብ በነፃነት እንዳይገልፅ መከልከል ፍፁም ስህተት ነው። ከሁሉም ሰዎች በተቃራኒ አንድ ሰው ብቻውን የተለየ ወይም የተሳሳተ አቋም የሚያራምድ ከሆነና ሃሳቡን እንዳይገልፅ የሚከለከል ከሆነ፣ ከግለሰቡ በላይ ተጎጂው አመለካከቱን እንዳገልፅ የከለከለው አካል ነው። ነገር ግን፣ “John Stuart Mill”፣ አንድ ግለሰብ ሃሳቡን የመግለፅ ነፃነቱን ሲገፈፍ በከለከሉት ሰዎች ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ እንደሚከተለው ይገልፀዋል፡-

“If all mankind minus one were of one opinion, and only one person were of the contrary opinion, mankind would be no more justified in silencing that one person, than he, if he had the power, would be justified in silencing mankind. …the peculiar evil of silencing the expression of an opinion is, that it is robbing the human race; those who dissent from the opinion, still more than those who hold it. If the opinion is right, they are deprived of the opportunity of exchanging error for truth: if wrong, they lose, what is almost as great a benefit, the clearer perception and livelier impression of truth, produced by its collision with error.” John Stuart Mill, On Liberty, Page 13.

ለምሳሌ ከዚህ ቀድም ለጠ/ሚ ኃ/ማሪያም “ሁሉንም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” በማለት በሰጡት መግለጫ ላይ ተመስርቼ “በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል” ብዬ ግልፅ ደብዳቤ ፅፌያለሁ። ፅሁፉ በማህበራዊ ድረገፆች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። እኔ ያስቀመትኩት የመከራከሪያ ሃሳብ “ስህተት” ከሆነ ጠ/ሚኒስትሩ “የሕግ የበላይነትን ለማስከበር” የወሰዱትን እርምጃ “ትክክለኝነት” ያረጋግጣል። የእኔ ሃሳብ “ትክክል” ከሆነ ጠ/ሚኒስትሩ “ለሁሉንም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ” የሰጡት ትዕዛዝ “ተጠያቂነትና ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ተግባራዊ እንዳይደረግ” ለቅድመ ጥንቃቄ ያግዛል።

የእኔ ፅሁፍ ትክክልም ሆነ ስህተት ጠቀሜታው ለጠ/ሚኒስትሩ ነው። ነገር ግን፣ ፅሁፉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች እንዳይወጣ ከተከለከለ ግን የውሳኔው ትክክለኝነት ወይም ስህተትነት የሚታወቀው በጠ/ሚኒስትሩ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ የፍፁማዊነት ወይም አለመሳሳት (infallibility) አመለካከት ነው።

2ኛ፡- ሰው በተሳሳተ መረጃ አይመራም
ከላይ በአንደኛ ላይ የተጠቀሰው “በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁት የተሳሳቱ መረጃዎች (misinformation) ናቸው” የሚል ነበር። በጠ/ሚ ንግግር ውስጥ ታሳቢ የተደረገው ሁለተኛው ችግር “በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ የተሳሳቱ መረጃዎች ወጣቶችን ወደ ተሳሳቱ ተግባራት (ድርጊቶች) ይመራሉ (mislead)” የሚለው ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው ስለ መረጃዎቹ “ትክክለኝነት” (truth) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለ መረጃዎቹ ጠቀሜታ (utility) ነው። ነገር ግን፣ እንደ “John Stuart Mill” አገላለፅ፣ በመረጃ መመራት በራሱ አመለካከት ስለሆነ በተሳሳተ መረጃ መመራት የመረጃውን ትክክለኝነት ከማረጋገጥ ጋር ተነጥሎ ሊታይ አይችልም ይለናል፡-

“…there can be nothing wrong, it is thought, in restraining bad men, and prohibiting what only such men would wish to practice. This mode of thinking makes the justification of restraints on discussion not a question of the truth of doctrines, but of their usefulness; …[But] the usefulness of an opinion is itself matter of opinion: as disputable, as open to discussion, and requiring discussion as much as the opinion itself. …
The truth of an opinion is part of its utility. …Those who are on the side of received opinions never fail to take all possible advantage of this plea; you do not find them handling the question of utility as if it could be completely abstracted from that of truth: on the contrary, it is, above all, because their doctrine is “the truth,” that the knowledge or the belief of it is held to be so indispensable.” John Stuart Mill, On Liberty, Page 18.

ከላይ እንደተጠቀሰው፣ ወጣቶች የመረጃውን ትክክለኝነት ሳያረጋግጡ የተሰጣቸውን የተሳሳተ መረጃ ዝም ብለው ተቀብለው ተግባራዊ አያደርጉም። በማህበራዊ ሚዲያ በተለቀቀ መረጃ መመራት የመረጃውን ትክክለኝነት ከማረጋገጥ የተቆራኘ ነው። ለምሳሌ፣ የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች፣ የሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር እና የክልሉ ፕረዘዳንት በኢብኮ ያስተላለፉትን መረጃ በመተው፣ ከአሜሪካ አቶ ጀዋር መሃመድ በፌስቡክ ያስተላለፈውን መረጃ ተግባራዊ የሚያደርጉት፣ ካለው ነባራዊ እውነታ አንፃር የአቶ ጀዋር መረጃ ከጠ/ሚኒስትሩ ሆነ ከፕረዘዳንቱ በተሻለ ትክክለኛ እና ጠቃሚ ስለሆነ ነው። በአጠቃላይ፣ ወጣቶች ከኢብኮ (EBC) ይልቅ “OMN” እና “ESAT”ን፣ ከ“FANA” ይልቅ “VOA”ን፣ ከመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ይልቅ የጀዋር መሃመድ የፌስቡክ ገፅን እንደ ዋና የመረጃ ምንጭ የመጠቀማቸው ሚስጥር የመረጃው ትክክለኝነት ነው።

ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በንግግራቸው፤ “አክራሪ ኃይሎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ መረጃ በማቅረብ ተገቢ ጥያቄ ያነሱ ወጣቶችን ለራሳቸው አጀንዳ ማስፈፀሚያ ይጠቀሙባቸዋል” በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል። ነገር ግን፣ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨውን መረጃ ተቀብለው ተግባራዊ የሚያደርጉት የአክራሪ ኃይሎች መጠቀሚያ ሆነው ሳይሆን መረጃው ትክክል እና መልዕክቱም አግባብ ስለሆነ ነው። አሁንም፣ የጠ/ሚኒስትሩ ንግግር፣ “መንግስት ለወጣቶች ትክክል የሆነውን መረጃ እና ተግባር ከራሳቸው ከወጣቶቹ በላይ ያውቃል” በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው። ይኼ ሁለተኛው የፍፁማዊነት ወይም አለመሳሳት (infallibility) አመለካከት ማሳያ ነው።

3ኛ፡- የመንግስት ትዕዛዝ እንጂ የፌስቡክ መረጃ ሰው አይገድልም
በ“John Stuart Mill” ትንታኔ መሰረት ከላይ 1ኛ እና 2ኛ ላይ በዝርዝር ለማሳየት እንደተሞከረው፣ ወጣቶች በፌስቡክ የቀረበላቸውን የሰለማዊ ሰልፍ ጥሪ ተቀብለው ወደ አደባባይ የሚወጡት ከመረጃው ትክክለኝነት በተጨማሪ በመረጃው አግባብነትና ጠቃሚነት ላይ ሙሉ እምነት ስላላቸው ነው። ምክንያቱም፣ እንያንዳንዱ ወጣት ተግባራዊ የሚያደርገውን መረጃ ትክክለኝነት የሚመዝንበት የራሱ ምክንያታዊ አስተሳሰብ (rational thinking)፣ ተግባሩን የሚመራበት የሞራል እሴት (Moral value) አለው።

ጠ/ሚኒስትሩ “በማህበራዊ ሚዲያ አማካኝነት በሚቀርቡ የተሳሳቱ መረጃዎች ወጣቶች የአክራሪ ኃይሎች መጠቀሚያ ይሆናሉ” የሚለው ስጋት እውን ሊሆን የሚችለው ወጣቶቹ ምክንያታዊ አስተሳሰባቸውን እና የሞራል ስብዕናቸውን ሲያጡ ብቻ ነው። ሰው የቀረበለትን መረጃ ትክክለኝነት እና ስህተትነት ሳያጣራ፣ ከሞራል እሳቤ ውጪ የሆኑ ተግባራትን የሚፈፅመው በመንግስት ትዕዛዝ እንጂ በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቀቁ መረጃዎች አይደለም።

ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚ ኃ/ማሪያም፡ “በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል” በሚለው ፅሁፍ በዝርዝር እንደገለፅኩት፣ የጠ/ሚኒስትሩ ስጋት እውን ሊሆን የሚችለው የሚከተሉት ሦስት መስፈርቶች ሲሟሉ ነው፤ አንደኛ፡- በዕዝ ሰንሰለት (Chain of commands) የታሰሩ ከሆነ፣ ሁለተኛ፡- በተግባራቸው ላይ የማዘዝ ስልጣን (Commanding Power) ከሌላቸው፣ እና ሦስተኛ፡- ስለሚፈፅሙት ተግባር ተገቢነት የማሰብ ግዴታ (Justifications) ከሌለባቸው ነው።

እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉት ደግሞ የመንግስት ወታደሮች፣ ፖለሶች ወይም የደህንነት ሰራተኞች ብቻ ናቸው። የጦር ኃይሎች አዛዥ እና ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች ተግባርና እንቅስቃሴ የሚቆጣጠሩት ደግሞ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ናቸው። በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጥፋት እየደረሰ ያለው በባለስልጣናት ትዕዛዝ እንጂ በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚለቀቁ መረጃዎች አይደለም። በአጠቃላይ፣ የመንግስት ትዕዛዝ እንጂ የፌስቡክ መረጃ ሰው አይገድልም።

ማጠቃለያ
ከስህተቶች ሁሉ ትልቁ ስህተት፣ የዜጎችን አመለካከት “ስህተት” ነው ብሎ ማሰብ ነው። የአምባገነንነት የመጨረሻ ደረጃ ደግሞ፣ የሕዝብ አመፅና ተቃውሞ በመንግስት ስህተት ሳይሆን በፀረ-ሰላም ኃይሎች አነሳሽነት እንደተፈጠረ ማሰብ ነው። ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ፣ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት ላይ፣ የራሳቸውንና የሚመሩት መንግስት የተዛባ አቋምና አመለካከት በይፋ ገልፀዋል። በዚህም፣ የኢህአዴግ መንግስት የተለየ አመለካከት ያላቸውን ወገኖች ከሀገሪቱ በማጥፋቱ የራሱን አቋም ትክክለኝነት እንኳን መለየት እንደተሳነው በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ አረጋግጠዋል። በዚህ መሰረት ጠ/ሚኒስትሩ ለዓለም አቀፍ ማህብረሰብ የመንግስታቸውን “አምባገነንነት” መስክረዋል።

ሕዝብ በመንግስት ላይ አመፅና ተቃውሞ የወጣበት ዋና ምክንያት ኢህአዴግ ከእሱ የተለየ አቋምና አመለካከት ያላቸውን አካላት በሙሉ ከሀገር ውስጥ ጠራርጎ በማጥፋቱ እንደሆነ ግልፅ ነው። የኢህአዴግ መንግስት ከእሱ የተለየ አቋምና አመለካካት አላቸው ያላቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣…ወዘተ ከሀገር ጠራርጎ በማባረሩ፣ ይኼው ዛሬ ላይ የሕዝቡን ጥያቄና የለውጥ ፍላጎት መስማትና ማየት ተስኖታል። ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ፊት፣ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የቀጥታ ስርጭት ላይ ይህን የመንግስታቸውን አባዜ በግልፅ አንፀባርቀዋል። የጠ/ሚኒስትሩ ንግግር በዓለም አቀፉ ማህብረሰብ ዘንድ የሚሰጠው ትርጉምና አንድምታ እንደሚከተለው ሊገለፅ ይችላል፡-

“በኢትዮጲያ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን፣ ነፃ-ፕሬስ፣ የሲቭልና ሙያ ማህበራትን፣ እንዲሁም ለሀገርና ሕዝብ የሚቆረቆሩ ታዋቂ ግለሰቦችና ምሁራንን ከሀገሪቱ ጠራርጌ አጥፍቼ ሳበቃ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሕዝቡን ችግርና ጥያቄ እያጋለጡ አስቸገሩኝ። በሀገር ውስጥ እነዚህን ሚዲያዎች በመዝጋት መቆጣጠር ስችል፣ በውጪ ሀገር ያሉ ትውልደ ኢትዮጲያኖች አስቸገሩኝ። ስለዚህ፣ እባካችሁ እነዚህን ሰዎች አሳልፋችሁ ስጡኝና ማዕከላዊ እስር ቤት አስገብቼ ወፌ-ላላ ልግረፋቸው?”

በቅርቡ ከእስር የተፈታቸው ሀያተል ኩብራ ነስረዲን በእስር ቤት ስለደረሰባት ሁሉ ትናገራለች | BBN TV

0
0

በቅርቡ ከሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ አባላት ጋር ከ እስር የተፈታችው ሀያተል ኩብራ ነስረዲን የቢቢኤን እንግዳ ሆና ቀርባለች:: የቢቢኤኑ ጋዜጠኛ አብዱረኢም አህመድ ሃያትን ስለ እስር ቤት ቆይታዋና በሌሎችም ጉዳዮች አነጋግሯታል – ይመልከቱት::

በቅርቡ ከእስር የተፈታቸው ሀያተል ኩብራ ነስረዲን በእስር ቤት ስለደረሰባት ሁሉ ትናገራለች  | BBN TV

ብአዲንና ኦሕዲድ በወያኔ የሚጋለቡ ሰጋር በቅሎዎች ናቸው |መሰረት ቀለመወርቅ

0
0

cartoonወቅቱ የአማራውና የኦሮሞው ሕዝብ ህልውናው አደጋ ላይ የወደቀበት በወያኔ አልሞ ተኳሽ ትግሬዎች ግድያ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ የምንገኝበት ዘመነ-ጥፋትና ዘመነ-ምፅት ላይ ነን። ይኸው ነፍሰ ገዳይ ቡድን ሕዝብ እንደ ሕዝብነቱ በአገሩ ተከብሮ እንዳይኖር ለረጅም ዘመናት ከደደቢት እስከ ቤተመንግስት ያሴረው ተንኮል ተዘርዝሮ አያልቅም። ወያኔ የአማራውንና የኦሮሞውን ማሕበረሰብ አጥፍቶ ለመጥፋት ወስኖ ሰላማዊ ነዋሪውን ሕዝባችን በሚኖርበት ትውልድ ቦታው ነፍሰ-በላው አጋዚ የተባለውን የትግሬ ሚሊሻ በማሰማራት ወረራ ፈፅሞ ወታደራዊ ቀጠና አድርጎታል።

አሁን የሚያደርገውን ሰይጣናዊ ድርጊት በመፈፀም ሕዝቡን ለማጥፋትና ለማፅዳት የደፈረው ለዘመቻው መሳካት ከአገር ውስጥም ሆነ ከአለም አቀፍ አጋሮቹ ጋር የጋራ ግንባር ፈጥሮ ነው። አገሩንና ሕዝቡን አጥፍቶ ሐብትና ንብረቱን ዘርፎ የጥቂት ምርጥ ትግሬዎች መንደላቀቂያና በቅጥረኝነት ላሰለፉት ቅኝ ገዠዎች እጅ መንሻ ለማድረግ ከተጠቀመባቸው ሴራዎች ውስጥ አንዱ ከተጎጅው አማራና ኦሮሞ ማህበረሰብ መካከል መልምሎና አሰልጥኖ እንደፈለገ የሚጋልባቸው ሰጋር በቅሎዎችን ለመፍጠር መቻሉ ነው። ከነዚህ ሰጋር በቅሎዎቹ ውስጥ ዋንኛዎቹ የመንግስትነት ስልጣን ቀርቶ የሚገዙት ሕዝብና መሬት የሌላቸው ብአዲንና ኦሕዲድ የተባሉት አሻንጉሊቶቹ ይገኙበታል። ነፍሰ-በላው ወያኔ ለሚጋልባቸው ሰጋር በቅሎዎቹ የስራ አፈፃፀም ያመች ዘንድ የረጅም ጊዜና የአጭር ጊዜ የካድሬ ስልጠናዎችን በመስጠት ያሰልፋቸዋል።

ከካድሬው ስልጠና በፊት ምልመለው ቀዳሚ በመሆኑ ጥብቅ ጥንቃቄ ተደርጎበት የካድሬ ምልመላው ይከናዎናል። በምልመላው ወቅት ከሚጠቀምባቸው መመዘኛዎች ውስጥ፦

1 ኛ. አማራውና ኦሮሞው በተፈጠሩበት አካባቢ አብሮ የኖረ በአባቱ ወይም በእናቱ የትግሬ ዘር ያለው እንዲሆን ይፈለጋል። 2 ኛ. አማራ ወይም ኦሮሞ ሆኖ አስተሳሰቡ ካለበት ማህበረሰብ እጅግ የወረደ ደካማና በቀላሉ የሰጡትን የሚቀበል በሆዱ ብቻ

የሚገዛ መሆን ይሮርበታል።

3 ኛ. በሚኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ቁርሾ ኖሮት የተፈጠረበትን ማህበረሰብ አማራውን ወይም ኦሮሞውን የሚጠላ መሆኑ ይፈለጋል።

4 ኛ. እምነትን ምክንያት በማድረግ በእምነት ተቋማት ውስጥ ገብቶ የካድሬነት ስራ መስራት የሚችል መሆኑ ይረጋገጣል።

September 25, 2016

ከምልመላው መጠናቀቅ በኋላ ስልጠና በመሆኑ ሁሉም ካድሬ የብአዲንና የኦሕዲድ የፖለቲካ ድርጅቶች አባል ተብለው ይሰየማሉ። ነገር ግን ብአዲንም ሆነ ኦህዲድ የነሱ የሆነና ለተፈጠሩበት ማህበረሰብ በሚጠቅም መልኩ የተቀረፀ የፖለቲካ አጀንዳ የላቸውም። እንዲያውም የተጠቀሱት ድርጅቶች መስራቾች ናቸው የተባሉት ሳይቀር የወያኔው የምልመላ መመዘኛዎች እንደተጠበቀ ሆኖ ተመልምለው የመሰረቱት ጀማሪዎች የግለሰብ ነፃነት ያልነበራቸው ወታደራዊ ምርኮኞች እንደሆኑና የአማራ ወይም የኦሮሞ ተወላጆች እንዳልሆኑ ይታወቃል።

ይሁንና አዲስ ተመልማዮችና የድል አጥቢያ አርበኞቹም ቢሆኑ በወያኔ ዘንድ የግል ነፃነት የሚባል ነገር በፊታቸውም እንዲዞር አይፈቀድም። ስለዚህ ስልጠናውን የሚሰጡት ወያኔወች ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ታሪክ አቋም ያለቸው፤ በመሰሪ ተንኮል የተካኑ በተለይም በአማራው ላይ ከፍተኛ ጥላቻና የጠላትነተ ስሜት ያዳበሩ አስተማሪ ሆነው ይመደባሉ። በዚህ አይነት ሁኔታ የተመለመሉት ሰልጣኞችና አሰልጣኞች ከፍተኛ የህዝብ ሐብት ፈሶበት የካድሬነት ትምህርቱ ይሰጣል። ለስልጠናው በተዘጋጀው ማስተማሪያ ጥራዝ መግቢያ ላይ ስለወያኔ አመሰራረትና ወታደራዊ ደርግን ስላንበረከከበት ሐያል ገድል ይነገራል። በመቀጠልም ማንኛውም ሰልጣኝ የራሱን ማንነት ትቶ የትግሬነትን የበላይነት ከፈጣሪ የወረደ እስኪመስል ድረስ እንዲቀበል ይደረጋል። በዚህ ትምህርት ትግሬዎቹ የሚያዙትን ብቻ እንዲያስፈፅም እራሱን ለባርነት ያዘጋጃል። ሐሳቡን እስካመነና ተቀብሎ እስከቀጠለ ድረስ ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞች እንደሚያገኝ ቃል ይገባለታል። ከዚህ በተፃራሪ ህዝቡንና የህዝቡን ተቆርቋሪዎች ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ የድሮው ሰርዓት ናፋቂ፣ ጠባብ፣ አሸባሪ የሚባሉትን ወያኔ የፈጠራቸውን ፍረጃዎች እስኪበቃው ድረስ ይጋታል። ወልዶ ያሳደገውን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎቱን ማክበር ይቅርና በክህደት ተወዳዳሪ የማይገኝለት የወያኔ ተላላኪና የሚጋለብ ሰጋር በቅሎ ሆኖ ይገራል።

ከስልጠናው ማግስት ችሎታውም ሆነ ክህሎቱ በማይፈቅደው የስራ መሰክ ይመደባል። ከዚያች እለት ጀምሮ ለወያኔ ታማኝነት ጅራቱን የሚቆላ ተጋላቢ ሰጋር በቅሎ ይሆናል። ከቶውንም አንዳንዶቹ በታማኝነቱ ዙሪያ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ውድደር በመግባት ወገንን አስገድሎና አሳስሮ የበለጠ የገንዘብ ዳረጎት፣ ሹመትና ሽልማት ለማግኘት የሚያደርጉትን ፉክክር ለተመለከተ ሰው በጣሊያን ወረራ ወቅት ሕሊናቸውን ሽጠው ህዝባቸውን አስጨፍጭፈው በእንቁላል ሻጭነት ካስመዘገቡት የባንዳነት ታሪክ ቢበልጥ እንጅ የሚያንስ አይደለም።

ውድ አንባቢያን ለፅሁፌ መነሻ ነጥብ የሆነኝ በሰሞኑ በሕዝባች ላይ የሚደርሰው ፍጅት ነው። በጎጃምና በጎንደር የአማራ ሕዝብ ላይ ዛሬ ወያኔ የሚፈፅመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በማከናወን ላይ የሚገኘው ብአዲን የተባለውን ሰጋር በቅሎ እየጋለበ በመንገድ መሪነት፣ በጀሮጠቢነት፣ በጠቋሚነት እየተጠቀመ ነው። ዛሬ በጎጃም ውስጥ ደብረማርቆስ ባህርዳንና በጎንደር ልዩ ልዩ ከተሞች ውስጥ እድሜቸው ከ 14 -17 የሚሆኑትን ታዳጊ ለጋ ወጣቶች በብአዲን መንገድ መሪነትና ጠቋሚነት የትግራይ ነፍሰባለ አጋዚ ሚሊሻ እየገደለ፣ እየደበደበ፣ ወደ ጅምላ ግዞት ማጠራቀሚያ በማስገባት ሰቆቃና ስውር ግድያ እየፈፀመ ነው። ወላጆች በየጎዳናውና በቤታቸው በራፍ ተኮልኩለው የደም እንባ በማንባት ላይ ናቸው። እንደሚታወቀው በአማራው ባህል እንዲህ አይነቱ የወገንን ደም እየሸጡና እየለወጡ መብላት ብዙ ያልተለመዳ ቢሆንም በኛ ዘመን ግን የትግሬዎችን የባንዳነት ታሪክ እንዳለ በመቀበል ብአዲን የተባለው አውሬ አገርና ትውልድ እያጠፋ ነው። ብአዲን ለ 25 ዓመታት በአማራው ሕዝብ ላይ የደረሰውን ግፍ የፈፀመና ያስፈፀመ ካሀዲ ብድን መሆኑ ሳያንስው አሁንም ወያኔ አማራውን ጨርሶ ለማጥፋት በጀመረው ወታደራዊ ወረራ ዘመቻ ውስጥ በተላላኪነቱ ቀጥሎበታል። ሕዝባችን በማስገደል፤ በማዘረፍና ሐብትና ንብረቱን በማቃጠል እንዲወድም በማድረግ ላይ ይገኛል። ስለዚህ በዚህ ከሐዲ ቡድን ላይ አንድ መላ ሊፈጠርለትና ከጠላታችን ወያኔ ባላነሰ መንገድ ሕዝባችን ማንኛውንም እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ተገቢ ነው ብየ አምናለሁ።

ስለዚህ ብዕረኛውም ጦረኛውም ብአዲን ብሎ እራሱን በሚጠራው ቅጥረኛ ቡድን ላይ ክንዱን ማሳረፍ አለበት። “ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው አስቀድሞ ማጥፋት አሾክሿኪውን ነው” በማለት አባቶቻችን በምሳሌ ገልፀውታል። የአማራው ወጣት ክንዱን በወያኔው ሰጋር በቅሎ ብአዲን ላይ ማንሳት የወቅቱ የትግላችን ዘርፍ ነው። ይህንን ባናደርግ በለጋ እድሜቸው በጨካኙ አጋዚ የተጨፈጨፉት ልጆቻችንና ወንድሞቻችን ደም ይፋረደናል። በየመንገዱ፣ በየታዛው፣ በየጫካውና በየገደሉ የደም እንባ እያነቡ የሚንከራተቱት አባቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን እንባ ይፋረደናል። በአጠቃላይ ስናየው በጨካኝ አጋዚ ትግሬዎች የሚፈሰው የአማራ ደም ከአፋፍ ላይ ሆኖ ይጣራል። ከዚህ በኋላ ጠላታችን ወዳጅ ላይሆነን መለማመጡ ማብቃትና መዘጋት ያለበት ምዕራፍ ነው። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በመላው አማራ ሕዝብ ክልልና መኖረያ መንደር በወረራ ገብቶ ሕዝባችንን ጨርሶ በማጥፋት ላይ የሚገኘው ጨካኙና ሰው በላው አጋዚ ግድያውን አቁሞ በአስቸኳይ ለቆ መውጣት እንዳለበት ተገንዝበን ትግሉን በቆራጥነት መቀጠል ግዴታችን ነው ። ሕዝባዊ ተጋድሎውም ቀጥሎ ሕዝቡ የኔ ብሎ ሊቀበለው የሚገባ ህገ- መንግስታዊ ለውጥና ስርአት በመፍጠር ሕልወናውንና መብቱን በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ አለበት።

ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት አማራ ነው!!! ድል ለተገፋው ሕዝባችን !!!

8 አውቶቡስ ሙሉ እስረኛ ከሸዋሮቢት መትረየስ በጫኑ መኪኖች ታጅበው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ

0
0


(ዘ-ሐበሻ) ከሸዋሮቢት እስር ቤት በ8 አውቶቡሶች የተጫኑ እስረኞች በምሽት እየተጓጓዙ መሆኑ ተሰማ:: የአካባቢው ነዋሪዎች በቭዲዮ አስደግፈው ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ መሰረት ማንነታቸው ያልታወቀና 8 አውቶቡስ ውስጥ የታጨቁ እስረኞች በምሽት ከተኙበት ተቀስቅሰው እየተወሰዱ ነው::

እስረኞቹን የጫኑት አውቶቡሶች መትረየስና ከባድ መሳሪያዎችን ከወታደሮች ጋር በጫኑ መኪኖች ታጅበው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል::

ከ4 ሳምንት በፊት በቅሊንጦ እስር ቤት በቃጠሎና በጥይት ከ49 በላይ እስረኞች ሕይወት መጥፋቱ አይዘነጋም::
8 አውቶቡስ ሙሉ እስረኛ ከሸዋሮቢት መትረየስ በጫኑ መኪኖች ታጅበው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ

“12 ሰዓት ላይ ማታ ፖሊስ ጠራኝ…”–ስማችንን ለደህንነታች ስንል አንናገርም

0
0

በቶማስ ሰብሰቤ

 በአዲስ አበባ ፍተሻው ዛሬም እደቀጠለ ነው አለም ባንክ የነበረው ፈተሻ ፈረንሳይ ለጋሲዎን ደርሷል። ፈረሳይ ለጋሲዎን አካባቢ መንገድ ዝግ ነው መኪናም ሆነ ሰው ማለፍ አይችልም።

በአዲስ አበባ ፍተሻው ዛሬም እደቀጠለ ነው አለም ባንክ የነበረው ፈተሻ ፈረንሳይ ለጋሲዎን ደርሷል። ፈረሳይ ለጋሲዎን አካባቢ መንገድ ዝግ ነው መኪናም ሆነ ሰው ማለፍ አይችልም።

ሰማችንን ለደህንነታች ሰንል አንናገርም። ትላንት ከጓደኛዮ ጋር ሆንን የዘወትር ውሎችንን አያሳለፍን ነበር። አዲስ አበባ ሰታዲየም ዙሪያ ካሉ ሆቴሎች አንዱ ውስጥ ቁጭ ብለን የሳምንቱ ውሎችንን እየተጫወት ነው።ሳቅ እና ጫወታ ፣ ስለ ስራ ፣ሰለ ቤተሰብ ብቻ ብዙ ነገር እተጫወት እያሳለፍን ነበር። በጫወችን መሃል ላይ ያላሰብነው እንግዳ አናገረን። ሰላምታ ከሰጠን በሃላ መታወቂያውን አሳየን ። ለእኛም እድል ሳይሰጠን እንደሚፈልገን ነገረን። ከአንድ ወደ ሁለት ሆኑ ፤ወደ ያዙት ነጭ ቲካፕ መኪና ወሰዱን። ሰለማንነታቸው ነገሩን ። መኪና ውስጥ አሰገቡን ሞባይሎቻችንን ወሰዱት። እኔ ምን እየበረበሩ እንደሆን ሰላልገባኝ ምን አጠፋን ፣ምንድ ነው እያረጋቹ ያላችሁት አላካቸው። «እኛ ከምንፈለገው ነገር ነፃ ከሆናቹ አሁን እንለቃችዋለን አይዦቹ አለኝ»ከሁለቱ አንዱ።
ሚሴጅ ይበረብራሉ ፣የፌስ ቡክ ፓስወርድ አሰከፈቱን። ፎቶዎች ተመለከቱ። የሚስቴን የሀፍረት ፎቶ እንካን አልቀራቸውም። ብቻ ፍተሻው ከጨረሱ በሃላ ጓደኛ በጥፊ መታው።ፌ ስ ብኩን ከፍቶ የሆነ ምስል ካሳየው በሃላ ማለት ነው።በቃ ይዘው ወደ ስድተኛ ሄዱ።አ ነስተኛ ክፍል አስቀመጡን።እኛ ስንገባ ብዙ ወጣቶች አሉ በክፍል ውስጥ።አብዛኛው የሞባይል ብርበራ የተካሄደበት ነው።በታክሲ ውስጥ ፣ሰራ ቦታ ሰውጣ ፣ሰፈር ቁጭ ብለን ፣ካፌ ውስጥ እያለን ነው ብርበራ የተካሄደባቸውነው የሚሉ ናቸው ብዙዎቹ ።ሁሉም አሁን እዚህ ከገባ በሃላ ጫወታው ገብቶናል።ፖለቲካ እና ማህበራዊ ሚዲያ የሚል ሽብር ነው።በጣም ገርሞናል።እኔ አልፈራውም።ለምን ፖለቲካ ላይ ምንም ነገር የለኝም።ፌሰቡክ ሆነ ሚሴጄ ከፖለቲካ ነፃ ነው።እንደሚለቁኝ ተሰፋ አደረኩ።ግን መቼ አላውቀውም።

12 ሰዓት ላይ ማታ ፖሊስ ጠራኝ። ወደ መርማሪውም ከያዙን ሰዎች የተሻለ የከተማ አማርኛ የሚናገር ነው።ሰላምታ ከሰጠኝ በሃላ።ሰልኬ ላይ በዚህ ሰልክ የተለያዮ የሽብር ምልዕክት ትለዋወጥ ነበር አለኝ።ደነገጥኩ።እኔ ከፖለቲካ ነፃ ነኝ አልኩት።ሰልኬን አሳየኝ ይህ የማን ሰልክ ነው አለኝ።የእኔ አልኩት።ይህ ሚሴጅስ ብሌ ሲያዳየኝ ደነገጥኩ።ወደያው የማን ሰልክ እንደ ሆነ ሳየው በጣም የምወደው ወዳጄ ሰም ነው።ደነገጥኩ።መቼ።እንዴት ተረበሽኩ።13 ሚሴጆች አሳየኝ።ፍርሃቴ በዛ።ሚሴጆቹ መልዕክታቸው የእኔ ሳይሆን የአልቃይዳ ነው የሚመስለው።በቃ አበቃልኝ አልኩኝ።

አትደንግጥ አለኝ መርማሪው እየሳቀ።መፍትሄው በእጃችን ነው።እኔው ነኝ አንተን እስር ቤትም ወይም ወደ ቤት የምልክህ እናም ሁለት አመራጭ አለ ነገረኝ።የጓደኛህን ሁለት ስልክ ጨምሮ ካንተ ጋር ፤ለአንዱ ሰልክ ሶስት ሺ ብር ክፈለኝ ወይም እስር ቤት ትከርማለህ አለኝ።ደነገጥኩ።አመራጩን ተጠቀምኩ ።እኔን ለቆኝ 9000 ብር አመጣው ጓደኛ ተፈታን።ሰልኬን ሲሰጠኝ የእኔ አንደኛው ሰልክ ታብሌት ሰለሆነ።ሚሴጁን አጥፍቶ ሲሰጠኝ ሪሳይክል ውስጥ ገብቼ አገኘው።የወዳጄ ስም የተፃፈው እና የፖለቲካ ሚሴጅ የተላክበት የተባልኩት ሰልክ የማለቃው አዲስ ቁጥር ነው።ግን መፈታታችን ቢያስደሰተኝም።ለሰው በብዙ ሺዎቹ ብር ለሌለው ፣ዘመድ ለሌለው ለንፁሃን ወገኖቻችን አዘንኩኝ።ለቶማስም የላክንለት ሌላው ይጠንቀቅ ብለን ነው።

ኢህአዴህ እንዲ ነው።እንደ አልቃይዳ ያሉ አሸባሪ ድርጅቶች ሆነ አንደ ኢህአዴግ ያሉ አምባገነን መንግስታት ዓላማቸው የፍርሃትና ስጋት ድባብ በመፍጠር የራሳቸው የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ አጀንዳ፣ እንዲሁም የራሳቸውን አመለካከት ማስረፅ ነው።

«በኢትዮጲያ የፀረ-ሽብር ሕግ መሰረት ማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ “በአሸባሪነት” ሊያስከስስ ይችላል። ለምሳሌ፤ “‘የፀረ-ሽብር ሕጉ ይሻሻል!’ የሚል መፈክር ይዛችሁ ውጡ” ማለት – “አመፅና ሁከትን በማነሳሳት – ‘inciting violence and protest’” በሚል ያስከስሳል፤ በሰላማዊ ሰልፍ መንገድ ከተዘጋ – “የሕዝብ አገልግሎትን በማቋረጥ – “disruption of public services’” በሚል አንቀፅ፤ ሰልፈኞቹን “አይዟችሁ በርቱ” ብሎ የተናገረ – “ለአሸባሪዎች የሞራል ድጋፍ በመስጠት – ‘providing moral support or …advice’”፤ “ኦነግ በሰላማዊ መንገድ’ ለመታገል ቆርጧል” ማለት – “አሸባሪነትን በማበረታታት – ‘encouragement of terrorism’” በሚለው አንቀፅ ያስከስሳል። አሁን ባለው ሁኔታ፣ ጠዋት አሸባሪነትን ለመቃወም አደባባይ የወጣ ከሰዓት “በሽብር ወንጀል ተከሶ” ራሱን ማዕከላዊ እስር ቤት ሊያገኘው ይችላል» የሚለው በእንደ ወቅት በዞን ዘጠኝ የፃፈውን መልዕክት ያሰታውሰኛል።


የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች በነቀምቴ ሰላማዊውን ወጣት በጥይት በሳስተው ገደሉት

0
0

ethiopia

(ዘ-ሐበሻ) ተሐድሶ ላይ ነኝ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በኦሮሚያ ሁለት አሻንጉሊት መሪዎችን ካስቀመጠ በኋላም በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርገውን ግድያ አጠናክሮ ቀጥሏል::

መንግስትን በሰላማዊ መንገድ መቃወም ምላሹ ሞት በሆነባት ኢትዮጵያ ዛሬም በነቀምት አስደንጋጭ ኹነት ተከስቶባታል:: እንደመረጃዎች ከሆነ ይህ በፎቶ ግራፉ ላይ በትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች በጥይት ተበሳስቶ የተገደለው ወጣት የተገደለው በነቀምት ነው:: ኢፋ አዲሱ የተባለው ይኸው ወጣት ሰላማዊ ሰው ቢሆንም የሕወሓት ወታደሮች ግን ስሙን ከተቃውሞ ጋር በማያያዝ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ገድለውታል::

ይህን ተከትሎ በነቀምት ከፍተኛ ውጥረት አለ:: ጉዳዩን ተከታትለን ለመዘገብ እንሞክራለን::

screen-shot-2016-09-25-at-12-57-08-pm

ትናንት በጎንደር በትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በጥይት ተደብድቦ የቆሰለው የአማራ ወጣት ደም በሆስፒታሉ የለም ተብሎ ሕይወቱ አለፈ

0
0

ከሙሉቀን ተስፋው

ቀናት በሄዱ ቁጥር ወያኔ በሕዝባችን ላይ የሚያደርሰው ጥፋት እየጨመረ ነው ፤ ይህ ወንድማችን አላምረው የኋላ ይባላል፤ ትናንት ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት አቅራቢያ በአጋዚ ወታደሮች በጥይት አንገቱ ላይ በጠሱት፤ ወደ ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ባሕር ዳር ተወሰደ ፤ 3 የፈጀ ቀዶ ጥገና ቢደረግለትም ደም በሆስፒታሉ በአለመገኘቱ ሕይወቱ መትረፍ አልቻለም። ለምን ለልጁ ደም አልተሰጠም? ጊዜ ይመልሰዋል!!

የዐማራ ወጣቶች ሆይ፤ ከከተማ በመውጣት ራሳችሁን ትከላከሉ ዘንድ መልካም ነው፤ እመኑኝ የትግሬ ወያኔ ለመጨረሻ ጊዜ በዐማራ ተጋድሎ ይደመሰሳል!!

north-gonder

የጎንደርና ባህርዳር የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ የመስቀል በዓል በባህርዳር፣ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በፍኖተሠላም፣ በደብረታቦርና በደሴ ከተሞች በአደባባይ እንደማይከበር አስታወቀ

0
0
መስቀል በጎንደር ሲከበር (ፎቶ የቆየ ከፋይል)

መስቀል በጎንደር ሲከበር (ፎቶ የቆየ ከፋይል)

ከጎንደርና ባህር ዳር የህዝባዊ እምቢተኝነት የተሠጠ መግለጫ!

እንደሚታወቀው አምባገነኑን ዘረኛ የህወሀት ገዥ ቡድን ከአገራችን ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማሥወገድ ህዝባዊ ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠሉ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የፊታችን ማክሠኞ የሚከበረውን የመስቀል በአል ዘረኛው የህወሀት ቡድን የተለያዪ አገራትን ጋዜጠኞች ወደ አማራ ክልል በማስገባ ከተወሠኑ የአሸባሪ ቡድኖች አቀንቃኝ በስተቀር ህዝብ ከመንግሥት ጎን ነው በማለት ዶኪመንታሪ ፊልሞችን ለመሥራት የተዘጋጀ ሥለሆነ በተለይ በክልላችን ዋና ዋና ከተሞች ማለትም በባህር ዳር፥ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በፍኖተ ሠላም፣ በደብረ ታቦርና በደሴ ከተሞች የመስቀል በዓል በአደባባይ ስለማይከበር ህዝቡ ዝግጅት በማድረግ በየቤተክርስቲያኑ እንዲዬደርግ የትግል ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ በሠሜንጎንደርና ደ/ጎንደር ጳጳስ አቡነ ኤልሳ መሪነት የተደረገውን የስብሰባ ቃለ ጉባኤ አያይዘን ልከናል፡፡

 

በጐንደር የመስቀል በዓልን አከባበር በተመለከተ የተነሳው ውዝግብና የመጨረሻ ውሳኔው ዘሀባሻ የተባለው የዜና ማሰራጫ አውታር በጐንደር ያሉ የውስጥ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው የ2009 ዓ.ም. የመስቀል በዓልን አከባበር በተመለከተ በዛሬው ዕለት መስከረም 13 ቀን 2009 ዓ.ም ረፋድ ላይ የሰሜን እና ደቡብ ጐንደር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ፣ በጐንደር ከተማ ያሉትን የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች እና አገልጋዮች ያካተተ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ጠርተው ነበር። በስብሰባው ላይም በዚህ ዓመት የመስቀል በዓል በጐንደር ከተማ በአደባባይ እንደማይከበር ተሰብሳቢዎች ወስነው ተለያይተዋል።

 

ዝርዝሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል። ስብሰባውን የጠሩት የዞኑ ቤተክነት ስራ አስኪያጅ አቶ ከለመወርቅ አሻግሬ ሲሆኑ ስብሰባው እንዲጠራ ያዘዙት ደግሞ የሰሜን ጎንደር ዞን እና የደቡብ ጎንደር ጳጳስ የሆኑት አቡነ ኤልሳ ናቸው ፡፡

በስብሰባው መድረክ ላይ የተቀመጡት አቡነ ኤልሳ ፣ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ቀለም ወርቅ አሻግሬ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ፀሀፊው አቶ ቀለም ወርቅ አለሙ ናቸው ፡፡ በስብሰባው የተገኙት:- – የሁሉም አድባራት አስተዳዳሪዎች – የሁሉም አድባራት ወንጌል ሰባኪያን – የሁሉም አድባራት መርጌታዎችና – የከተማዋ ታዋቂ ግለሰቦች ናቸው በአጠቃላይ የስብሰባው አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በሙሉ የሞላ ሲሆን የስብሰባው አጀንዳ ፡- የመስቀል በዓልን አከባበር በተመለከተ መከበር አለበት ወይስ የለበትም? እንዴትስ እናድርግ በሚል ነው? ሁሉም ተሰባሳቢዎች በከፍተኛ ደረጃ ሀሳብ ለመስጠት እጃቸውን ያወጡ ሲሆን አንድ ተሰብሳቢ ይህን የተሰበሰብንበትን አዳራሽ ፣ ቤተክርስቲያናትን ሌሎችንም ህንጻዎች የሚሰሩ ወጣቶች በበዓላት ወቅት ምንጣፉን እያነጠፉ በራሳቸው ወጭ ሰረገላ አሰርተው በአሉን በአል የሚያደርጉትን ወጣቶች እየታሰሩ ፣ እየተገደሉ ፣ አየታፈኑ ፣ የት እነዳሉ እነኳን በማናውቅበት ሁኔታ በዓል እናክብር ብላችሁ መጥራታችሁ ያሳዝናልም ያሳፍራልም ብለው ሲናገሩ ተሰብሳቢው በሙሉ በጭብጨባ የተቀበላቸው ሲሆን ስለዚህ በምንም ተአምር ሊከበር አይገባም ብለው ሲጨርሱ ፡፡ ሌላኛው ተናጋሪ ተጨማሪ ሀሳብ የሰጡ ሲሆን ለተነሱት ነጥቦች ሊቀሊቃውንት እዝራ ሃዲስ ተነስተው ቀደም ሲል መከበር አለበት ብየ ተናግሬ ነበር አሁን ደግሞ ስብሰባውን የጠራነው መስከረም 7 ቀን ሶስት የመከላከያ ጄኔራሎች ፣ ብፁአባታችንን አቡነ ኤልሳን እንዲሁም ስራ አስኪያጁን አቶ ቀለምወርቅ አሻግሬንና ሌሎችንም ጠርተው በምንም አይነት ይህን የመስቀል በዓል ሊከበር ይገባል በዓሉን አናከብርም የምትሉ ከሆነ እርምጃ እንወስዳለን በማለት የዛቻ እና ማስፈራሪያ ንግግሮች ሲያደርጉ ዋሉ:: መጀመሪያ ላይ አታክብሩ ሲሉ የነበሩት እነዚሁ ጀነራሎች ሃሳባቸውን ቀይረው አሁን ደግሞ አክብሩ ማለታቸው ከጀርባው ሴራ አለው:: እንደዚህ ዜና ዘጋቢ ገለጻ “በአሉን እናከብራለን ነገር ግን ይህን በዓል በዋናነት የሚከበረው የሚያደምቀው ወጣቱ ነው በመሆኑም ወጣቱን ፍቱልን መከላከያም ከከተማው ይውጣልን እና እናከብራለን አልናቸው:: እነሱም ከተወሰኑ ሰዎች ጋር በስልክ ተዎያይተው ከዚያም ሰዎችን አንፈታም እነዚህ የታሰሩት በህግ ይጠየቃሉ በማለት መልስ ሰጡን” እኛም ሲጨንቀን እናንተን ሰብስበን ምን እናድርግ ብለን ነው የጠራናችሁ አሉ? ስራ አስኪያጁም አቡነ ኤልሳ ሊቀሊቃውንት እዝራ ያሉት ትክክል ነው ለዚህ ነው የጠራናችሁ አሉ:: ከዚያም ከተሰብሰሰቢዎች አንዱ ጄኔራሎቹ እናንተን ጠርተው ከማናገር እኛን ለምን ጠርተው አያናግሩም:: ስለእኛ የመስቀል በአል እነሱ ምን አገባቸው? የሚል ንግግር ሲመጣ ሁሉም በጭብጨባ ተቀብለውታል:: ከዚያም ሊቀሊቃውንት እዝራ ተሰብሳቢው ሁሉ ያለው ትክክል ነው:: እኔም መንግስት የሚሰማ መስሎኝ የታሰሩትን የሚፈታ መስሎኝ ነው በአሉን እናክብር ያልኩት አሁን ግን ሳየው ጎንደር የምትተዳደረው በወታደር ነው:: ሁኔታው የሚያሳዝንና ፀሎት የሚያስፈልገው ነው ብለው ይህ የመስቀል በአል በአደባባይ ሊከበር አይገባም ሲሉ በሙሉ ተሰብሳቢው ከወንበር በመነሳት በጭብጨባ ደግፏቸዋል:: ከዚያም ሰብሳቢዎቹ ሌላ የተለየ ሃሳብ ካለ እናክብር የሚል ካለ ብለው ጠየቁ ምንም እናክብር የሚል ሰው ጠፋ:: ከዚህ በኋላ እንዴት እናክበረው ታዲያ የሚል ሀሳብ ከሰብሳቢዎቹ ተነሳ:: ተሰብሳቢዎቹም ሁላችንም በየደብራችን / በየቤተክርስቲያናችን/ እናክብር በማለት በጭብጨባ በሙሉ ድምፅ መስከረም 17 ቀን መስቀል በዓል በአደባባይ እንደማይከበር ተወስኗል፡፡ የመንግስት አካላት ግን በግልፅ ቤተክነት ጦርነት አውጃለች ማለት ነው ብለው ተናግረዋል ፡፡

ከኢህአዴግ የባሰ ፀረ-ልማት አለ እንዴ? |ከስዩም ተሾመ

0
0

eprdf

ለዘመናት ዩራኒዩም (uranium) ከብር ማዕድን የሚገኝ አላስፈላጊ ተረፈ ምርት ተደርጎ ይወሰድ ነበር። የዩራኒዩም የቀድሞ መጠሪያው “pitchblende” ሲሆን ቃሉ “pechblende” ከሚለው የጀርመንኛ ቃል የመጣ ነው። በጀርመንኛ “pech”ማለት ደግሞ አላስፈላጊ የሆነ ውዳቂ ነገር (failure, nuisance) እንደማለት ነው። በዚህ መልኩ አላስፈላጊ ተረፈ-ምርት ተብሎ ሲጣል የነበረ ማዕድን በ1930ዎቹ ከፍተኛ የኃይል ምንጭ ለመሆን በቃ። ለረጅም ዘመናት እንደ ተራ ውዳቂ ሲቆጠር የነበረ ማዕድን እንዴት በአንድ ግዜ ወደ ከፍተኛ የኃይል ምንጭነት ተቀየረ?

ስዩም ተሾመ

ስዩም ተሾመ

ይህን ውዳቂ ተረፈ-ምርት ወደ ከፍተኛ የኃይል ምንጭነት ለመቀየር ከዩራኒየም የበለጠ ሌላ ከፍተኛ የኃይል ምጭ ያስፈልጋል። እሱም የሰው ልጅ አዕምሮ ነው። የሰው ልጅ ዕውቀት ከውሃ፣ ንፋስ፣ ዩራኒየም ወይም ሌሎች የኃይል ምንጮች የበለጠ ኃይል ያመነጫል። ለዚህም ደግሞ እነዚህ የኃይል ምንጮች በራሳቸው የሰው ልጅ አዕምሮ ውጤት መሆናቸው በራሱ ራሱን የቻለ ማስረጃ ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ “Human Capital and Sustainability” በሚል ርዕስ የቀረበ አንድ ጥናታዊ ፅሁፍ የልማትና እድገት ስረ-መሰረቱ የዜጎች አዕምሮና ዕውቀት እንደሆነ እንዲህ ይገልፀዋል፡-

“Other species do survive on the basis of natural resources, but no other species consciously applies its mental capacities to identify and utilize different forms of capital for its development. Materials exist in nature, but anything becomes a resource only when its potential value is recognized by the human mind. Human mental activity creates resources by discovering new productive relationships between existing elements.” Human Capital and Sustainability, Sustainability Journal, Volume 3 Issue 1.

በእርግጠኝነት በዕለት-ከዕለት ኑሯችን ልክ እንደ ዩራኒየም አላስፈላጊ ብለን የምንጥላቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እነዚህን ነገሮች ወደ ጠቃሚ የምርት ግብዓትነት ተቀይረው የሃብት ምንጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ይህን ለማድረግ ግን ከተለመደው ወጣ ያለ አስተሳሰብ ያላቸው፣ አስተዋይና አዲስ ነገር የመፍጠር ብቃት ያላቸው ወጣቶች ያስፈልጉናል። እንደ ሀገር ነገሮችን ከተለየ አቅጣጫ ማየት የሚችሉ፣ ደፋርና ችግሮች ባልተለመደ መልኩ የመፍታት ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶች ያስፈልጉናል።

በመሰረቱ፣ እንዲህ ያለ ስብዕና ያላቸው ወጣቶች ለማፍራት ከቤተሰብ እስከ ማህብረሰብ፣ ከትምህርት ቤት እስከ መንግስታዊ ሥርዓት ድረስ ስር-ነቀል የሆነ ለውጥ ያስፈልጋል። ለምሳሌ፣ በቤተሰብ ደረጃ ልጆች ለሚያነሷቸው ወጣ ያሉ ጥያቄዎች በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምላሽ የመስጠት ባህል የለንም፤ ሕብረተሰቡ ከተለመደው ወጣ ያለ ባህሪን እንደ “ብልግና” የመውሰድ አባዜ ተፀናውቶታል፣ በትምህርት ቤት መምህራን ከሚያውቁት ውጪ መጠየቅ እንደ ጥፋት ይቆጠራል። መንግስት ደግሞ የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት እንደመሆኑ ከሁሉም የባሰ ነው።

የኢህአዴግ መንግስት ከእሱ የተለየ ሃሳብና ተግባር በመጣ ቁጥር እሱን ለማጥፋት ከመጣጣር ውጪ ልዩነትን ተቀብሎ የማስተናገድ ባህል በጭራሽ አልፈጠረበትም። በተለይ የመንግስትን ሥራና አሰራር ዝርክርክነት የሚያጋልጥ ከሆነ ደግሞ ባለ-በሌለ አቅሙ ሃሳቡና ተግባሩን ለማስቆም ይጣጣራል። ከዚህ አንፃር የኮሚውተር ነክ ወንጀል ረቂቅ አዋጅን መጥቀስ ይቻላል። ከ#Oromoprotest ጋር ተያይዞ በጥቂት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ድህረ ገፆች የተፈጠረው ችግር እንደ መነሻ ሊጠቀስ ይችል ይሆናል። ነገር ግን፣ የሕጉ መሰረታዊ ዓላማ እንደ ፌስቡክ ባሉ ማህበራዊ ድረገፆች ላይ ያለውን ፈጣን የመረጃ ፍሰት እና በፖለቲካው ዘርፍ ያለውን ተፅዕኖ መግታት ነው።

ለምሳሌ፣ ከ2008 ሚያዝያ ወር ጀምሮ እኔ በምኖርባት የወሊሶ ከተማ በሞባይል ኢንተርኔት እንደ ፌስቡክ ያሉ ማህበራዊ ድረገፆችን እንዳንጠቀም ተደርጓል። ይህ በሆነበት ቅፅበት ከዚህ በፊት ስለመኖራቸው እንኳን የማናውቃቸው ሶፍትዌሮች መጡ። ይኼው በየቀኑ በጦማር ገፄ እና ፌስቡክ ላይ የማወጣቸው ፅሁፎች በእነዚህ ሶፍትዌሮች ድጋፍ ነው። መንግስት የማህበራዊ ድረገፆችን እንዳንጠቀም የጣለው እገዳ ተግባራዊ ከሆነ አምስት ወራት አልፈውታል።

በመሰረቱ፣ መንግስት የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂዎችን ሆነ ሌሎች መሰረተ-ልማቶችን እንዴትና ለምን ዓላማ መጠቀም እንዳለብን የመቆጣጠር ሆነ የመከታተል መብትና ስልጣን የለውም። በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም መሰረተ-ልማቶች ከሕዝብ በተሰበሰበ ግብር (ታክስ) የተገነቡ መሆናቸው ሊሰመርበት ይገባል። የኢህአዴግ መንግስት ከሕዝብ በሰበሰበው ብር (ያውም ግማሹን በሙስናና ለአስተዳደር በሚል ከዘረፈ በኋላ) በሚገነባው መሰረተ-ልማት ላይ ከተወካይነት የዘለለ ባለቤትነት ሊኖረው አይችልም። መንግስት ማንኛውንም ዓይነት መሰረተ-ልማት ከገነባ በኋላ ለባለቤቱ፥ ለህዝቡ አስረክቦ ከመሄድ ባለፈ እንዴትና ለምን ዓላማ መጠቀም እንዳለበት የመወሰን ስልጣን ሊኖረው አይችልም።

የኢህአዴግ መንግስት ሀገሪቷን በዓለም ዝቅተኛ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቦት እንድታገኝ አድርጎ፣ በዓለም ከፍተኛ የሆነ ታሪፍ ያስከፍለናል። በዚህ ላይ ሕዝቡ የተለየ ሃሳብና አመለካከት በአንፀባረቀ ቁጥር የኢንተርኔትና ስክል አገልግሎቶችን ያቋርጣል። ሰሞኑን ደግሞ የእኛ ሳያንስ አሜሪካን ድረስ ሄዶ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንድቆጣጠር ይፈቀድልኝ ብሎ ጠይቋል። መንግስት እጅግ ኋላቀር የቴሌኮምዩኒኬሽን አግልግሎት መስጠቱ ሳያንስን በነጋ-በጠባ አገልግሎቱን የሚያቋርጥብን ለምንድነው?

የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ለወጣቱ ትውልድ የማህበራዊ፥ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ግንኙነት መሳሪያ ነው፤ የመረጃ፣ ክህሎትና ዕውቀት ምንጭ ነው፤ ሰፋ ያለ ግንዛቤና ከተለመደው ወጣ ያለ አመለካከት የሚያዳብርበት ነው። ከዓለም ማህብረሰብ ጋር የምንቀላቀልበት፣ ከሁሉም ጋር እኩል የምባውቅበትና የምንወዳደርበት ነው። በአጠቃላይ፣ ይህ ዘርፍ ወጣቶች የተለየ አመለካከትና ሰፊ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ የሚያግዝ፣ ደፋርና ችግሮች ባልተለመደ መልኩ የመፍታት ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶች ለማፍራት የሚያስችል ነው።

ታዲያ የኢህአዴግ መንግስት ይሄን ዘርፍ ብቻ ለይቶ እድገቱን ከማቀጨጩ አልፎ፣ የተለየ ሃሳብና አመለካከት በሰማ ቁጥር አገልግሎቱን የሚያቋርጠው ለምንድነው? ከራሱ የተለየ አቋምና አመለካከት ያላቸው ወጣቶችን ስለሚፈራ፣ ሃሳብና አስተያየታቸውንም ስለሚፀየፍ ነው። ታዲያ ከኢህአዴግ የባሰ ፀረ-ልማት ኃይል ከቶ ከወደየት ይገኛል?

በአዲስ አበባ ዛሬ የተጀመረው ፍተሻ እስከ ማክሰኞ ይቀጥላል ተባለ |ሕዝብ እየተሸበረ ነው

0
0
 በአዲስ አበባ ፍተሻው ዛሬም እደቀጠለ ነው አለም ባንክ የነበረው ፈተሻ ፈረንሳይ ለጋሲዎን ደርሷል። ፈረሳይ ለጋሲዎን አካባቢ መንገድ ዝግ ነው መኪናም ሆነ ሰው ማለፍ አይችልም።

በአዲስ አበባ ፍተሻው ዛሬም እደቀጠለ ነው አለም ባንክ የነበረው ፈተሻ ፈረንሳይ ለጋሲዎን ደርሷል። ፈረሳይ ለጋሲዎን አካባቢ መንገድ ዝግ ነው መኪናም ሆነ ሰው ማለፍ አይችልም።

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በአዲስ አበባ አደባባዮች ማምሻውን ፍተሻ ተጀመረ:: ፍተሻው እስከማክሰኞ ምሽት ድረስ እንደሚቀጥል የፖሊስ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል::

እንደ ፖሊስ ምንጮች ገለጻ ከሆነ ሕወሓት የሚመራው መንግስት የጸጥታ ስጋት አለብኝ በሚል በአዲስ አበባ ዛሬ ማምሻውን ፍተሻ የጀመረ ሲሆን ፖሊሶችም በቀን 12 ሰዓታት እየሰሩ ነው::

በምሽት ከ4 እስከ 5 ሰዓት የሚቆይ ፍተሻ አድርጉ ተብለው ትዕዛዝ የወረደላቸው ፖሊሶች በተመረጡ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የጀመሩትን ፍተሻ እስከ ማክሰኞች ምሽት ድረስ ይቀጥላሉ ተብሏል::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአዲስ አበባ የሚከበረውን የመስቀል በዓል ተከትሎ የሆነ ነገር ሊፈጠር ይችላል በሚል ለፖሊሶች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ያስታወቁት የፖሊስ ምንጮች በየሰፈሩ በሚደረጉ የደመራ ቦታዎችንም በአይነቁራኛ እንዲከታተሉ መታዘዙን አስታውቀዋል::

ዛሬ ማምሻውን የተጀመረውን ፍተሻ ተከትሎ ሕዝብ እየተሸበረ መሆኑም ታውቋል:: አንዳንድ ፖሊሶች በተለይ ሕዝቡን እያመናጨቁ እንደሚፈትሹ የደረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል::

 የዲምክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ እና የኢትዮጵያ የጋራ መድረክ የተሰጠ የአቋም መግለጫ!!

0
0

nowayቀን 25 september 2016

አገራችን ኢትዮጵያ በጎጠኛና ዘረኛ ቡድን መዳፍ ስር ወድቃ  ህዝቦቿ ከመቼውም እጅግ የከፋ የመከራና ስቃይ  ፅዋ  እየጠጡ ተዋርደውና ተንቀው በመኖር እነሆ 25 የግፍ አመታት ተቆጠሩ፤ ዘረኛውና አምባገነኑ ቡድን ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውንና ማህበራዊ እሴቶችን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ በማንአለብኝነት፣ ቅጥ በአጣ ትምክህትና አረመኔያዊነት በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ላይ ሂትለራዊና ፋሽስታዊ ተግባሩን እየፈጸመ ይገኛል።  

ይህ አይነት ዘረኛ ቡድን በማነኛውም መለኪያ እንዲሁም ታሪካዊ ዳራ ኢትዮጵያን ያክል ታላቅ ታሪክ ያላት ሀገር ለማስተዳደርም ሆነ ለመምራት ፈጽሞ  ብቃትና ሞራል እንደሌለው ከፈጸማቸውና ከሚፈጽማቸው እኩይ ተግባር በተጨባጭ ለማየት ችለናል፤ በድርጊቱም እጅግ አዝነናል፣ ተቆጭተናል፣ የበለጠ እልህ ውስጥም ገብተናል። ይህም የወያኔ አረመኔያዊነት በቅርቡ በአገራችን ተቀጣጥሎ በመካሄድ  ላይ የሚገኘው ህዝባዊ እምቢተኝነት ደረጃ  ላይ እንዲደርስ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል። 

እንደ  አገዛዙ ሥርዓት የፖለቲካ ዓለማና ግብ ኢትዮጵያዊያን በዘርና በሃይማኖት ተከፋፍለው እርስ በእርስ እየተጋጩና እየተናቆሩ ለአገዛዙ የሥልጣን ማራዘሚያ  የሚጠቀምበት ከንቱ ስልት ተዳክሞ የአንድነት ኃይሉ ተጠናክሮ  በጋራ የኢትዮጵያ ታላቅ ጠላት በሆነው በወያኔ ሥርዓት ላይ በቁርጠኝነት እንዲነሳ  ጊዜ የማይሰጠቅ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህን የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ከመጨረሻው ግብ ለማድረስ የተያዘው የነጻነት ትግል ለውጤት እንዲበቃ  ምን መደረግ አለበት የሚለውን ዋና ሃሳብ በመያዝ ሁሉም ለኢትዮጵያ  ፍትህና ዲሞክራሲ መስፈን፣ ዲሞክራሲያዊና  ሰባዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ የሚሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ህዝባዊ ተቋማትና የእያንዳንዳችን እንደግለሰብ ልናበረክት የሚገባን አስተዋጾ ላይ ለመምከር ይህ ዛሬ የተጠራው ህዝባዊ ውይይት  እጅግ  ጠቃሚ ወቅታዊ ጉዳዮችና የመፍትሄ ሃሳቦች የተነሱበት፣ ከፍተኛ የትግል መነቃቃትና አብሮነት የተንጸባረቀበት ነበረ። 

የተጀመረው  ህዝባዊ እምቢተኝነት ከጫፍ ደርሶ  አረመኔያዊ አገዛዝ ከህዝባችን ጫንቃ አውርደን ለአንዴና ለመጨረሻ  ጊዜ ለመቅበር ሁለገብ እንቅስቃሴ  አስፈላጊ እንደሆነ በመድረኩ ከቀረቡ የውይይት ርዕሶች፣ ነጥቦችና  በተሳታፊዎች ከተሰጡ አስተያየቶችና የሃሳብ ልውውጦች  የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ተችሏል። በተጋባዥ እንግዶች በዶ/ ሙሉዓለም አዳም፣ በዶ/ ተክሉ አባተ እና ወጣት ኤልሳቤጥ ግርማ የቀረቡ የመወያያ ነጥቦችም  በሚገባ ወቅቱን ያገናዘቡና የታለመላቸውን ግብ ማሳካት እንደሚችሉ ከውይይቱ በአጽንኦት ተረድተናል።

 

እያ ዛሬ በዚህ አዳራሽ ለውይይት የተገኘን ኢትዮጵያውያን አገራችን ከገባችበት አስቸጋሪ አጣብቂኝ ውስጥ በማውጣትእውነተኛ ሰላም፣ ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የበኩላችንን ጥረት ማድረግ እንደሚገባን በውይይቱ የተሰጡትን የመፍትሄ ሃሳቦች፣ አቅጣጫዎችና የትግል ስልቶች በሚገባ ተረድተን ለአፈጻጸማቸው አውንታዊ ምላሽ ለመስጠትና በትግሉ ጎራ ሙሉ በሙሉ ለመሳተፍ በአንድ ድምጽ ተስማምተን ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች በጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተናል። 

  1. በአገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ  አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ወቅት በንጹሃን ዜጎች ላይ በአረመኔው የወያኔ አግዓዚ ጦርና ልዩ ኃይል የተወሰደውንና እየተወሰደ ያለውን እጅግ ዘግናኝ አረመኔያዊ ግድያዎችን አምርረን እናወግዛለን፤ ገዳዮችንም በህግ እንፋረዳቸዋለን፤ ሰማዕታትንም በታሪክ ለዘላለም እንዘክራቸዋለን!
  2. የጥፋት መልዕክተኛ ዘረኛ የፋሽስት ስርዓትንና ተባባሪዎቹን ለማሶገድ የሚደረጉ ማናቸውንም አይነት የትግል ስልቶችንና ህዝባዊ እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ በአንድነት እንደግፋለን!እንሳተፋለን!
  3. ዘረኛውና አንባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በዓለም አቀፍ መድረክ ያለውን የድፕሎማሲ ቁመና በማጋለጥ ድጋፋ የሚያደርጉ አጋሮቻቸውንም ከሚሰጡት እርዳታ እጃቸውን እንዲሰበስቡ አጠክረን እንመክራለን! እንዲሁም በውጭ በሚገኙ ማነኛውም የወያኔ ተቋማትና መጠቀሚያ ድርጅቶች ላይ አስፈላጊውን ህጋዊና ሞራላዊ እርምጃ በመውሰድ እና ማዕቀብ በማድረግ እንዲዳከሙ እናደርጋለን!
  4. በኢትዮጵያ የተረጋገጠ ሰላም፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ለማስፈን የቆሙ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ህዝባዊ ተቋማት የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት መምራት፣ ማስተባበርና በቀጥተኛ ተሳትፎ ተገቢውን ሚና እንዲጫዎቱ እንጠይቃለን። 
  5. በአገራችን በሚካሄደው የለውጥ ትግል ሂደት መሪ ተዋናኝ በመሆን ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት ላይ ያለውና በትግሉም ከፍተኛ መስዋዕትነትን እየከፈለ በሚገኘው ከወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ እንሰጣለን! በማነኛውም ጊዜ ከጎናቸው እንቆማለን!
  6. በኢትዮጵያ መፃኢ እጣ ፈንታ ለመወሰን በጋራና በተናጠል ለሚታገሉ አካላት መካከል ያለውን መለስተኛ የአመለካከት ልዩነት በማጥበብና በመቻቻል ተከባብረው  በጋራ ጠላታችን ላይ ያነጣጠረ ትግል እንዲያካሂዱ ጥሪ እናደርጋለን!
  7. ዘረኛውና አንባገነኑ የወያኔ ስርዓት ከአሁን በኋላ በብሄር ብሄረሰቦች መካከል ጥርጣሬና ያለመተማመን ስሜት በመፍጠር የአገዛዝ እድሜውን ለማራዘም የሚጠቀምበት ኋላቀር አካሄድ ከዚህ በኋላ እንዳይቀጥልና ትግሉ ኢትዮጵያዊነትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን በጋራ እንታገላለን! 

ድል ለሰፊው ኢትዮጵያዊ ህዝብ፤ ውድቀትና ሞት ለወያኔ ዘረኛ ቡድን!  መስከረም 14 , 2009 ዓም ኖርዌይ ኦስሎ

አርቲስት ዝናብዙ ጸጋዬ በአማራነቱ ከሚደርስበት ጋር በተያያዘ እንደተሰደደና የፖሊስ መጥሪያ እንደመጣ ተናገረ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ሳምንት ጥሩ ኑሮውን እና ሃገሩን ጥሎ መሰደዱ የተዘገበው አርቲስት ዝናብዙ ጸጋዬ በተደጋጋሚ ከሚደርስበት በደል እና አሁን ደግሞ በአማራነቱ ከሚደርስበት ነገሮች ጋር ተያያዞ ሃገሩን ለመልቀቅ መገደዱን ለአሜሪካን ድምጽ ራድዮ ተናገረ:: አርቲስቱ እርሱ ከሃገር ከወጣ በኋላም የፖሊስ መጥሪያ ቤቱ እንደመጣ ገልጿል:: የመጀመሪያውን ክፍል ቃለምልልስ ያድምጡት::


የከፍተኛ ዋጋ ግዥ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ያደርጋል?

0
0

 

ፔፔ ጋርዲዮላ ከወዲሁ የሚፈልጋቸውን ተጨዋቾች በማግኘት ላይ ነው፡፡ በአሁኑ የዝውውር መስኮት 5ኛው የማንቸስተር ሲቲ አዲስ ፈራሚ ሆኖ ኢትሃድ ደረሰው ብራዚላዊው የክንፍ ተጨዋች ጋብርኤል ጆንስ የተገባበት 27 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ የክለቡ የዘንድሮው ፕራሲዝን ዝውውር መስኮት የተጨዋቾች ግዥ ዋጋ ወጪን 100 ሚሊየን ፓውንድ በላይ ያደረሰው ሆኗል፡፡

pogba

ማንቸስተር ዩናይትድም የጁቬንቱሱን አማካይ ፖል ፓግባን በሚጠበቀው መልኩ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ሂሳብ የክለቡ የዘንድሮው ፕራሲዝን ዝውውር መስኮት የተጨዋቾች ግዥ ዋ ወጪን 100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ያደረሰው ሆኗል፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድም የጁቬንቱሱን አማካይ ፖል ፓግባን በሚጠበቀው መልኩ ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ሂሳብ በማውጣት ለማስፈረም ከቻለ የማንቸስተር ሲቲ አርአያነትን የሚከተል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በቅርብ ዓመታት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በአንድ የፕሪ ሲን ዝውውር መስኮት ከ100 ሚሊዮን በላይ ሂሳብ አውጥቶ ለሻምፒዮንነቱ ክብር ለመብቃት የቻለ ክለብ አልታየም፡፡

ለሁለቱ የማንቸስተር ከተማ ክለቦች ደጋፊዎች ሌላው ትልቅ ፀፀት የሚሆነው የዛሬ ዓመት ሁለቱም ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ለአዳዲስ ተጨዋቾች ግዢ እያንዳንዳቸው ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ አውጥተው የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብርን በመቀዳጀት ያለፈው ሲዝንን ያጠናቀቀው ሌይስተር ሲቲ መሆኑ ነው፡፡

ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ግን በ4ኛ እና በ5ኛ ስፍራ ላይ ተቀምጠው ማጠናቀቃቸው ይታወቃል፡፡ ማንቸስተር ሲቲ ልክ የዛሬ ዓመት በቺሊያዊው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ ስር ኬቪን ደብሩያንን እና ራሂም ስተርሊንግን የመሳሰሉ ተጨዋቾችን ጨምሮ በአጠቃላይ ለአዳዲስ ፈራሚዎች እስከ 150 ሚሊየን ፓውንድ የሚደርስ ሂሳብ ማውጣቱ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብርን ለመቀዳጀት ያለውን አላማ ለማሳካት ሳይረዳው መቅረቱ ይታወቃል፡፡

የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ የነበሩት ሉዊ ቫንሃልም ከ150 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ በማውጣት እስከ ስድስት የሚደርሱ ተጨዋቾችን ገዝተው ክለቡን የ2016/17 ሲዝን የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎን በሚያገኝበት ስፍራ ላይ በማስገባት ለማስጨረስ ባለመቻላቸው የኦልድ ትራፎርድ ስራን ለማጣት መገደዳቸው ይታወቃል፡፡

ማንቸስተር ዩናይትድ ያለፉት ሁለት ሲዝኖችን በፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ለማጠናቀቅ የተሳነው በሁለት ተከታታይ የፕሪ ሲዝን የዝውውር መስኮቶች በእያንዳንዳቸው ላይ ከ100 ሚሊዮን በላይ ዋጋ በማውጣት አዳዲስ ተጨዋቾችን አስፈርሞ እውነተኛ የሆነ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክርን ሲያደርግ አልታየም፡፡

ማንቸስተር ሲቲም በፕራሲዝን ዝውውር መስኮት ሪከርድ የሰበረ የተጨዋች ግዥን ሲያወጣ የዘንድሮው ለጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡ በ2009 እና በ2010 ፕራሲዝኖች በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ከፍተኛ የተጨዋች ግዥ ዋጋን አውጥቶ ሁለቱንም ሲዝኖች ያጠናቀቀው ግን የሻምፒዮንነቱ ክብር በሌሎች ክለቦች እጅ ሲገባ ለማየት ተገድዷል፡፡ ሊቨርፑል፣ ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ቼልሲም ከዚህ በፊት በአንድ የፕራሲዝን የዝውውር መስኮት እያንዳንዳቸው ከ100 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ የተጨዋች ግዥሂሳብን አውጥተው ክለባቸውን ለፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ለማብቃት ተስኗቸው ያጠናቀቋቸው ሲዝኖች አሏቸው፡፡

በተለይም ቼልሲ በጁላይ 2003 በራሽያዊው ቢለየነር ሮማን ኢብራሂሞቪች እጅ መግባቱን ተከትሎ የ2003/04 ሲዝንን የጀመረው ለአዳዲስ ተጨዋቾች ግዢ በአጠቃላይ 110 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ በማውጣት መላው ዓለምን በማስገረም ነበር፤ ሆኖም ግን ያንን የውድድር ዘመን ያጠናቀቀው አርሰናል ለሙሉ ሲዝን በአንድም የፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ ሳይሸነፍ ለሻምፒዮንነት ክብሩ ለመብቃት አስገራሚ ገድልን ሲፈፅም በማየት ነው፡፡

ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም ስፖርትስ ሜይል ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በፕሪሲዝን ዝውውር መስኮት ሪከርድን የሰበረ የተጨዋች ግዢ በጀትን ያወጡት ክለቦች በሲዝኑ ዘመቻቸው ያጋጠማቸው እጣ ፈንታን ከዚህ በታች ባለው መልኩ ዳስሶታል፡፡

ማንቸስተር ሲቲ (2015)

አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ በማንቸስተር ሲቲ ስራ ባሳለፉት የመጨረሻው ፕራ ሲዝናቸው ኪቪን ደብሩይን እና ራሂም ሰተርሊንግ ብቻ በድምሩ ከ100 ሚልየን ፓውንድ በማውጣት ገዝተዋቸዋል፡፡ በሁለቱ ተጨዋቾች የማንቸስተር ሲቲ የተጨዋቾች ግዢ ሪከርድን ከአንዴም ሁለቴ ለመስበር ተገድደዋል፡፡ ሆኖም ግን የ2015/16 ሲዝን የፕሪሚየር ሊግ ዘመቻቸውን የጨረሱት በኃላፊነት ዘመናቸው ዝቅተኛውን ስፍራ ማለትም 4ኛ ደረጃን በማግኘት በመሆኑ ከስራቸው ተነስተዋል፡፡

የሲቲ 2015 ፕራሲዝን ፈራሚዎች

ከቪን ደብሩያን፡- 52 ሚሊየን ፓውንድ

ራም ሰርተርሊንግ፡- 40 ሚሊየን ፓውንድ

ኒኮላ ኦታሚንዲ፡- 32 ሚሊየን ፓውንድ

ፋቢያን ዴልፕ፡- 8 ሚሊየን ፓውንድ

ፓትሪክ ሮበርትስ፡- 48 ሚሊየን ፓውንድ

ዴኔስ ዩናል፡- 2 ሚሊየን ፓውንድ

በአጠቃላዩ ያወጣው፡- 151 ሚሊየን ፓውንድ

በሻምፒዮንነት ያጠናቀቀው፡- ሌይስተር ሲቲ

ማንቸስተር ዩናይትድ 2014

ሉዊ ቫንሃል የሆላንድ ብሔራዊ ቡድንን በ2014 የዓለም ዋንጫ በአሰልጣንነት መርተው 3ኛ ደረጃን እንዲያገኝ ከረዱት በኋላ የማንቸስተር ዩናይትድ ስራን የያዙት ክለቡ ከፍተኛ የተጨዋች ግዢ በጀትን መድቦላቸው ነበር፡፡ በ2014 ፕሪ ሲዝንም በአጠቃላይ ስድስት አዳዲስ ተጨዋቾችን በድምሩ 156 ሚሊየን ፓውንድን በማውጣት ገዝተዋቸዋል፡፡ አዲስ ካስፈረሟቸው ተጨዋቾች ውስጥ አርጀንቲናዊው ኢንተርናሽናል አንሄል ዲ ማሪያን በ60 ሚሊየን ፓውንድ ሂሳብ በመግዛት በብሪቲሽ ፉትቦል አቻ ያልተገኘለት በታሪክ ከፍተኛ የግዢ ዋጋን ያወጡበት ይገኝበታል፡፡ ሆኖም ግን ክለቡ ከመደበው ከፍተኛ የተጨዋች ግዢ በጀት በአግባቡ ተጠቃሚ ለመሆን ተስኗቸው ማንቸስተር ዩናይትድን በፕሪሚየር ሊግ ዘመቻው በ4ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ የተገደበ አጨራረስ እንዲኖው አስገድደውታል፡፡
spendros

የዩናይትድ 2014 የፕራሲዝን ፈራሚዎች

አንሄል  ዲ ማሪያ፡- 60 ሚሊየን ፓውንድ

ሉክ ሻው፡- 31.5 ሚሊየን ፓውንድ

አንደር ሄራራ፡- 20 ሚሊየን ፓውንድ

ማርክስ ሮሆ፡- 16 ሚሊየን ፓውንድ

ዳሊ ብሊንድ፡- 14 ሚሊየን ፓውንድ

ቫራያ ሚሊንኮቪች፡- ባልተገለፀ ዋጋ

ራዳሜል ፋልካኦ፡- 6 ሚሊየን ፓውንድ (በውሰት)

በአጠቃላይ ያወጣው፡– 155 ሚሊየን ፓውንድ

በሻምፒዮንነት ያጠናቀቀው፡ ቼልሲ

ሊቨርፑል 2014

የቀድሞው የክለቡ አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ ሊቨርፑልን በ2013-17 ሲዝን ለፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ለመብቃት አቅርበውት በ2ኛ ደረጃ እንዲጨርስ በማስቻላቸው በመነቃቃት የክለቡ ቦርድ ሪከርድን የሰበረ 116 ሚሊየን ፓውንድ የተጨዋች ግዢ በጀትን መድቦላቸዋል፤ ሆኖም ግን በ2014-15 ሲዝን ክለቡን ያስጨረሱት በ5ኛ ደረጃ ላይ በማስቀመጥ ነው፡፡

የሊቨርፑል 2014 ፕራሲዝን ፈራሚዎች

አዳም ላላና፡- 23 ሚሊየን ፓውንድ

ማሪዮ ባሎቲሊ፡- 16 ሚሊየን ፓውንድ

ላዛር ማርኮቪች፡- 20 ሚሊየን ፓውንድ

አልቤርቶ ሞሬና፡- 12 ሚሊየን ፓውንድ

ኢምሬ ቻን፡- 9.8 ሚሊየን ፓውንድ

ሪኪ ላምበርት፡- 4 ሚሊየን ፓውንድ

ዴጃን ሎቨረን፡- 20 ሚሊየን ፓውንድ

ዳርክ ኦሪጊ፡- 10 ሚሊየን ፓውንድ

በአጠቃላይ ያወጣው፡- 111.8 ሚሊየን

በሻምፒዮንነት ያጠናቀቀው፡- ቼልሲ

በከፍተኛ ምስጢር የተያዘው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳብያ በአ.አ. ከፍተኛ የሰራዊት ክምችት ይታያል

0
0

26 ሴፕቴምበር 2016 (EMF) በከፍተኛ ምስጢር የተያዘው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ ሳብያ በአዲስ አበባ በተለይ ደግሞ በአራት ኪሎ አካባቢ ከትላንት ምሽት ጅምሮ ከፍተኛ የሰራዊት ክምችት ይታያል።

feteshaከትላንት ማምሻ የጀመረው ፍተሻ አሁንም እንደቀተለ ሲሆን የአጋዚ ሰራዊት አላፊ አግዳሚውን በማሸበር እና በመፈተሽ ላይ እንደሚገኝ የአይን ምስክሮች ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። የአይን ምስክሮች እንደሚሉት መሃል አዲስ አበባ- የገዢው ፓርቲ መቀመጫ ኣራት ኪሎ አካባቢ ውጥረቱ የከፋ ይመስላል። በአካባቢው ይሰማ የነበረው የተኩስ ልውውጥ በዚያው በቤተ-መንግስት እንደሆነም ይነገራል። የከባድ መሳርያው ጩኸት እንደተሰማ በከፊል አዲስ አበባ መብራት እንዲጠፋ ተደርጎ እነደነበርም ከስፍራው ያነጋገርናቸው እማኞች ገልጸዋል።

አለም አቀፍ እና የግል መገናኛ ብዙሃን በተከለከሉበት በአሁኑ ሰዓት በጨለማ እየተደረገ ያለውን ሁሉ ለማጣራት ቢቸግረም – አንደኛ በኢሃዲግ ድጅቶች መካከል ሁለተኛ ደግሞ በሕወሃት ከፍተኛ አመራር እና መካከለኛ ካድሬዎች መሃል የከረረ አለመግባባት እንዳለ እየተሰማ ነው። የዚህ የጥቅም እና የሃሳብ ልዩነት እየሰፋ መጥቶ ወደ ከፍተኛ ፍልሚያ ሊያመራ እንደሚችል የሚገምቱም ጥቂቶች አይደሉም።

በሃገሪቱ ያሉ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እስካሁን ድረስ እንዳይከፈቱ ትእዛዝ ተሰጥቷል። የትምህርት ቤቶችን የልብ ትርታ ለማዳመጥ በመምህራን የተጀመረው ስብሰባ ውጤት ገዥው ፓርቲ እንደጠበቀው አልሆነም። የመምህራኑ ቁጣ እንዲህ ከበረታ የተማሪዎቹ የከፋ እንደሚሆን በመገንዘባቸው ትምህርት በቶችን የመክፈቱ አደጋ ስጋት ውስጥ ከትቷቸዋል።

በፊታችን የሚከበሩ ሁለት በዓላት (የመስቀል እና የእሬቻ በዓላት) አከባበርም ገዥውን ፓርቲ አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።

አገዛዙ በአካባቢ እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ላይም እምነት በማጣቱ የአጋዚ ሰራዊቱ እና ታማኝ ደህንነት አባላት ብቻ ናቸው ፍተሻውን እና ግድያውን እያካሄዱ ያሉት።

በኤርትራ ጠረፍ (ባድመ) ላይ ተሰማርቶ የነበረው የህወሃት ሃይል አካባቢውን ለቅቆ ወደ አዲስ አበባ እና ጎንደር እንዲዘምት ተደርጓል።

የሕዝብን ውጫዊ አካል ሊፈትሹ ይችላሉ – የሸፈተ ልቡን ግን ለመፈተሽ አይቻላቸውም። ወከባው ችግሩን ያባብሰዋል እንጂ አይፈታውም።

Hiber Radio: በኢትዮጵያ ለውጡ ተግባራዊ ሲሆን አገሩን የሚጠብቀው ሰራዊቱ አይበተንም ተባለ ፣በመተማ የሕወሓት አገዛዝ ደህንነቶች ጥቃት ይደርስባቸዋል በሚል በሀሰት ከአካባቢው ያስወጧቸው የትግራይ ተወላጆች እየተመለሱ ነው ፣ኦነግ ጎረቤት ኬኒያ እና የሕወሓት ኢሕአዲግ መንግስት በጣምራ ሊወጉኝ መሆኑን መረጃ ደረሰኝ አለ፣የሕወሃት አገዛዝ የደህነት መ/ቤት ስጋት ላይ በመውደቁ የኦህዴድና የብአዴን አመራሮችን በመሰለል ላይ መጠመዱ ተገለጸ

0
0

የህብር ሬዲዮ መስከረም 15 ቀን 2009 ፕሮግራም
habtamu-150x150.jpg

ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ባለፈው ቅዳሜ በሆላንድ ዘ-ሔግ ላይ በኢትዮጵያ ጉዳይ የተደረገውን ውይይት መሰረት በማድረግ ከአክቲቪስት ገረሱ ቱፋና አክቲቪስት መስፍን አማን ጋር ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

አክቲቪስት ገረሱ ቱፋ የሔጉን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ስብሰባ አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ(ቀሪውን ያዳምጡት)

አክቲቪስት መስፍን አማን በጋራ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ(ቀሪውን ያዳምጡት)

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ እያደረገ ስላለው ዲፕሎማሲያዊ ትግል ተጠይቀው ከሰጡት ተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

ሰሞነኛው የአቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ በአትሊት ፈይሳ ሌሊሳ እና በኦነግ ላይ የከፈቱት የቃላት ጦርነት እና ምላሹ ሲዳሰስ(ልዪ ዘገባ)

አቶ ያሬድ ሀይለማሪያም ከቤልጂየም የሰብኣዊ መብት ተሟጋቹ ስብስብ ለኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ዳይሬክተር (ሁለተኛ ክፍል) ሌሎችም…

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ ለውጡ ተግባራዊ ሲሆን አገሩን የሚጠብቀው ሰራዊት አይበተንም ተባለ

በመተማ የሕወሓት አገዛዝ ደህንቶች በተቀነባበረ ሁኔታ ጥቃት ይደርስባቸዋል በሚል በሀሰት ከአካባቢው ያስወጣቸው የትግራይ ተወላጆች እየተመለሱ ነው

ኦነግ ጎረቤት ኬኒያ እና የሕወሓት ኢሕአዲግ መንግስት በጣምራ ሊወጉኝ መሆኑን መረጃ ደረሰኝ አለ

የሕወሃት የደህነት መ/ቤት ስጋት ላይ በመውደቁ የኦህዴድና የብአዴን አመራሮችን በመሰለል ላይ መጠመዱ ተገለጸ

ስርዓቱ ጊዜው ያለፈበት በመሆኑ ሊለወት ይገባል ተባለ

እስራኤል አ/አ ውስጥ በእስራት ላይ የሚገኝ ዜጋዎን ለመታድግ ከፍተኛ ባለስልጣናን ላከች

ታሳሪው ዜጋዎ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ደርሶብኛል ይላሉ

በጎንደርና በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች የመስቀል በዓል በአደባባይ እንዳይከበር ሕዝቡ ወሰነ

ስጋት የገባው የሕወሃት አገዛዝ በአዲስ አበባ በምሽት የተጠናከረ ፍተሻ ጀመረ

ፕ/ት ባራክ ኦባማ ከወ/ሮ ሂላሪ ጋር የኤሎክትሮኒክስ መልእክት/ኢሚል/ ላይ የሀሰት ስም ይጠቀሙ ነበር ተባለ

ዶናልድ ትራምፕ በነገው በምረጡኝ ዘመቻችው ላይ የፕ/ት ክሊንትን የቀድሞ ቅምጥን ይዘው ሊቀርቡ ነው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነጻነት እና ለእኩልነቱ ከፍተኛ መስዋትነት ብፕመክፈል ላይ መሆኑ ተገለጸ

ቀነኒሳ በጀርመን ማራቶን አሸነፈ የአትሌት ፈይሳን ተቃውሞ በተዘዋዋሪ ለማጣጣል በመሞከሩ ተቃውሞ እየበረታበት ነው

ሌሎችም


Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች በምዕራብ ወለጋ ወደ መስቀል በዓል እየሄደ ያለን ወጣት ገደሉ

0
0

selamawi
(ዘ-ሐበሻ) የመስቀልን በዓል ለማክበር እየሄደ የነበረ ሰላማዊ ወጣት በአጋዚ ወታደሮች ጥይት ራት መሆኑ ተሰማ::
ትናንት በነቀምቴ የኦሮሞ ወጣት የሆነውን በጥይት በሳስተው የገደሉት የአጋዚ ወታደሮች ዛሬ ደግሞ በ ም ዕራብ ወለጋ መንዲ ከተማ ይህን በፎቶ ግራፉ ላይ የምታዩትን ወጣት ገድለውታል::
በመንዲ የተገደለው ይኸው ወጣት ስሙ ልደታ አማና ሰንበታ እንደሚሰኝ የተገለጸ ሲሆን አጋዚዎች ይህን የመስቀልን በዓል ሊያከብር የሄደውን ሰላማዊ ወጣት የገደሉት ብጥብጥ ልታስነሳ ነበር በሚል ባልተረጋገጠ ጥርጣሬ እንደሆነ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል::

መሪዎቻችን ስልጣን ሙጭጭ የሚሉባቸው ሦስት ምክንያቶች –ከስዩም ተሾመ

0
0

Hailemariam

የእኛ ሀገር ባለስልጣናት ከስልጣን መውረድ በጣም ያስፈራቸዋል። ይህ ከሚኒስትር እስከ ቀበሌ ሊቀመንበር ባሉት የስልጣን እርከኖች የሚስተዋል ችግር ነው። በራስ ፍቃድ ስልጣን መልቀቅ ቀርቶ፣ “በስራው ላይ ከፍተኛ የአቅም ማነስ ችግር አለበት” የተባለ ባለስልጣን እንኳን ከስልጣኑ ወርዶ-አይወርድም።

ስዩም ተሾመ

ስዩም ተሾመ

አንዳንድ ምሳሌዎችን ለመጥቀስ ያህል፤ ከሚኒስትርነት ወረደ የተባለ ባለስልጣን በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ይሆናል፣ ከክልል ወይም ከዩኒቨርሲቲ ፕረዘዳንትነት የወረደ ቀጣይ ሥራው በአንዱ ሀገር የኢትዮጲያ አምባሳደር መሆን ነው፣ የክልል ሴክተር መስሪያ ቤትን መምራት የተሳነው ካቢኔ ወደ ሌላ ሴክተር መስሪያ ቤት ይዛወራል፣ በአንዱ ዞን፥ ወረዳ፥ ከተማ ወይም ቀበሌ በሙስና የተጠረጠረ ወይም የመልካም አስተዳደር ችግር የፈጠረ ካድሬ ወደ ሌላ ዞን፥ ወረዳ፥ ከተማ ወይም ቀበሌ ይዛወራል። ከገዢው ፓርቲ ጋር ፀብ ያላቸው ከሆኑ ግን ያው መጨረሻቸው ወይ እስር ቤት ወይም ስደት መሆኑ እርግጥ ነው።

በተለይ ደግሞ የኢህአዴግ ባለስልጣናነት እንኳን በራሳቸው ፍቃድ በግድ ተገፍተውም ከስልጣን አይወርዱም። “ከስልጣን መውረድ እንዲህ የሚያስፈራቸው ለምንድነው?” የሚለው ጥያቄ ዘወትር በውስጤ ይመላለስ ነበር። በመጨረሻም ስልጣን ላይ እንዲህ ሙጭጭ የሚሉባቸውን ሦስት መሰረታዊ ምክንያቶችን መለየት ቻልኩ። እነሱም፡- ተፈላጊነት፣ ተጠቃሚነት እና የአመራር ወጥመድ ናቸው። እስኪ እያንዳንዳቸውን በዝርዝር እንመልከት፡-

1ኛ፡- ተፈላጊነት

የተፈላጊነት ችግር በዋናነት ባለስልጣናቱ ለራሳቸው ከሚሰጡት ግምት ጋር የተያያዘ ነው። አንድ ሰው በየትኛውም የኃላፊነት ደረጃ፤ በዝቅተኛ የኃላፊነት እርከን፣ ያለ ምንም ስልጣን (በተራ ሰራተኝነት) ወይም ስራውን ለቅቆ በራሱ የተሻለ ነገር መስራት እንደሚችል የሚያስብ ከሆነ ከስልጣን መውረዱ የተለየ ስሜት አይፈጥርበትም። በመሆኑም፣ በሌሎች ሰዎች፤ በቤተሰቦቹ፣ በባልደረቦቹና ተገልጋዮቹ ዘንድ ያለው ክብርና ተፈላጊነት የሚቀንስ መስሎ አይሰማውም። ስለዚህ፣ ከስልጣን መውረድን የተሻለ ነገር ለመስራት እንደ ምቹ አጋጣሚ ይወስደዋል። እንዲህ ያለ ስብዕና ያለው ግለሰብ እንኳን ከስልጣን ውረድ ተብሎ ይቅርና፣ ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በአለቆቹ ተቀባይነት ስላላገኘ ብቻ ከስልጣን ሊወርድ ይችላል።

ነገር ግን፣ አብዛኞቹ የሀገራችን ባለስልጣናት ከስልጣን ቢወርዱ በቤተሰቦቻቸው፣ ባልደረቦቻቸው እና በአጠቃላይ በማህብረሰቡ ዘንድ ያላቸው ክብርና ተፈላጊነት የሚቀንስ መስሎ ይሰማቸዋል። በመሆኑም፣ ከስልጣን መውረድን ልክ እንደ ሞት ይፈሩታል። በተለይ የፖለቲካ ተሿሚዎች ስልጣንን ለሕዝብ ጥቅምና አገልግሎት ከማዋል ይልቅ እንደ ክብርና ዝና ስለሚቆጥሩት፣ ከስልጣን ውረዱ ሲባሉ ክብርና ሞገሳቸው ተገፎ “እርቃናችሁን ቁሙ” የተባሉ ይመስል ይሰቀጥጣቸዋል። ስለዚህ አንዴ ስልጣን ላይ ከወጡ በኋላ እዚያ ሙጭጭ….

2ኛ፡- ተጠቃሚነት

ይህ በዋናነት ከስልጣን ከሚገኙ ጥቅማ-ጥቅሞች ጋር የተያያዘ ነው። አንድ ባለስልጣን ከደሞወዝ በተጨማሪ የወንበር፣ የነዳጅ፣ የሞባይል፣…ወዘተ አበሎች ያገኛል። እንደው በጥቅሉ ለመናገር ያህል፣ ለአንድ ቀን ሥራ የወጣ ኃላፊ ከሦስት ቀን በታች ውሎ-አበል አይታሰብለትም፡፡ በአበል መልክ ከሚያገኘው ያልተገባ ጥቅም በተጨማሪ፣ ሙስና እና ሌሎች ያልተገቡ ጥቅማ-ጥቅሞች እንዳሉ ግልፅ ነው።

አብዛኞቹ የሀገራችን ባለስልጣናት የእነዚህ ጥቅሞች “ሱሰኛ” ናቸው። ለምሳሌ፣ አብዛኞቹ ባለስልጣናት በዚህ መልኩ በሚያገኙት ጥቅም የልጆቻቸውን የትምህርት ቤት ክፍያ እየከፈሉ ወይም ትልቅ መኖሪያ ቤት እየገነቡ ሊሆን ይችላል። ታዲያ እነዚህን ከስልጣን ውረዱ ሲባሉ በቅድሚያ ወደ አዕምሯቸው የሚመጣው የልጆቻቸው የትምህርት ክፍያ ወይም በጡረታ እንድሜያቸው እንኳን የማይጨርሱት ቤት ነው። ስለዚህ፣ እዚያው ሙጭጭ….

3ኛ፡- የአመራር ወጥመድ (Leadership Trap)

የዚህን ፅንሰ-ሃሳብ “ኢህአዴግን የጠለፈው የአመራር ወጥመድ” በሚለው ፅኁፍ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቼበታለሁ። አጠቃላይ ሃሳቡን ለመዳሰስ ያህል፣ ችግሩ “ለምን ወደ አመራርነት መጣሁ?” ከሚለው እሳቤ ጋራ የተያያዘ ነው። ብዙውን ግዜ የሀገራችን ባለስልጣናት “ለምን ወደ ስልጣን እንደመጡ” ሲጠየቁ “ሕዝብን ለማገልገል” እንጂ “ባለስልጣን መሆን ስለፈለኩ” አይሉም። ነገር ግን፣ የመጀመሪያው እሳቤ ያላቸው ባለስልጣናት “በአመራር ወጥመድ” የመጠለፍ ዕድላቸው የሰፋ ነው።

“ባለስልጣን መሆን ስለፈለኩ” የሚል እሳቤ ያላቸው ባለስልጣናት በሥራቸው ውስጣዊ እርካታ (Internal Satisfaction) ስለሚያገኙ፣ የተሳሳተ ውሳኔ ከወሰኑ ወይም ዝቅተኛ የሆነ አፈፃፀም ካስመዘገቡ በሥራቸው ደስተኛ አይሆኑም። ስለዚህ፣ የበለጠ ስራቸውን በመስራት፣ በዚህም ደንበኞችን/ሕዝብን በማገልገል እርካታ ያገኛሉ።

“ሕዝብን ለማገልገል” ከራሳቸው ይልቅ ሌሎች ሰዎችን በማስደሰት (External Gratification) የሚያተኩሩ ናቸው። እነዚህ ባለስልጣናት ደስታቸውን በራሳቸው ሳይሆን ከሌሎች ሰዎች እርካታ የሚያገኙ ናቸው። ነገር ግን፣ ዘወትር ለትችትና ነቀፌታ ስለሚጋለጡ በሥራቸው ደስተኛ አይሆኑም። ስለዚህ፣ በቀጣይ ስህተት-አልባ ሥራ ለመስራት (perfectionism) ጥረት ያደርጋሉ። ይህ ደግሞ ጭራሽ ድክመቶቻቸውን ተለይተው እንዳይታወቁ ይጋርዳቸዋል። እንደዚህ ያሉ አመራሮች “የአመራር ወጥመድ” (Leadership Trap) ውስጥ የወደቁ ናቸው።

በአመራር ወጥመድ ውስጥ የወደቁ ባለስልጣናት መሰረታዊ ችግር ከማህብረሰቡ የሚሰጣቸውን ትችትና አስተያየት ለመቀበል ዝግጁ አለመሆን ነው። በመሆኑም፣ እንደ አምላክ ፍፁም መሆን ይቃጣቸዋል። በዚህ ምክንያት፣ በስህተት ላይ ስህተት እየሰሩ፤ “ተሳስታችኋል” ሲባሉ አይሰሙም፣ “ተሳስተናል” ብለው አያምኑም። በየግዜው ይሳሳታሉ፣ ሲነግሯቸው ስለማይሰሙ ስህተታቸውን መልሰው ይሳሳታሉ። በቃ…”ውረዱ” ቢባሉ እንኳን መስሚያቸው ጥጥ ነው። እዚያው ሙጭጭ….

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live