Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የመተማው “የዘር-ፍጅት” ትርክት በደህንነት ተቋሙ የተቀናበረ ነበር (ዋዜማ ራዲዮ)

$
0
0

ዋዜማ ራዲዮ- በቅርቡ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ መተማ- ዮሀንስ አካባቢ በትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ላይ ተፈፀመ የተባለው ዘርን ያማከለ ጥቃት ሆነ ተብሎ በፀጥታ ሰራተኞች የተቀነባበረ እንደነበረ ጉዳዩን በቅርብ የመረመሩ የዲፕሎማቲክ ምንጮች መሰከሩ።

አጋጣሚውን የትግራይ ክልል መንግስት አልያም የሀገሪቱ የደህንነት ባለስልጣናት “የዘር-ፍጅት አደጋ” እንደተከሰተ አድርገው በማቅረብ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ሀዘኔታና ድጋፍ ለማግኘት ሙከራ ማድረጋቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች ተገኝተዋል።

የዋዜማ ሁነኛ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ባደረሱን መረጃ- ድርጊቱ በተፈፀመበት ወቅት በስፍራው የነበሩ የረድኤት ስራተኞች ፣ ከድርጊቱ በኋላ ወደ ስፍራው ያመሩ ሁለት አጣሪ ቡድኖችና የአማራ ክልል መንግስት ባልስልጣናት የደረሱበት መደምደሚያ፣ የመንግስት የደህንነት ሰራተኞች በበላይ አለቆቻቸው ትዕዛዝ መሰረት የትግራይ ተወላጆች ሸሽተው ወደ ሱዳን እንዲገቡ አድርገዋል።

ሽሽቱ ከመጀመሩ በፊት በአካባቢው ውጥረት እንደነበረ ግን ደግሞ የትግራይ ተወላጆች ላይ በተለይ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ኋላ ግን በርካታ ትግርኛ ተናጋሪዎች ሽሽት መጀመራቸው ድንጋጤን ፈጥሮ እንደነበር ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ የሆነ ዲፕሎማት በፃፉት የውስጥ ስነድ ላይ ገልፀዋል።

ይህን ጉዳይ ማጣራት ያሰፈለገው የተባለው እውነት ከሆነ ችግሩን ለመቀልበስ በማለም እንደነበር ሰነዱ በመግቢያው ያትታል።

የትግርኛ ተወላጆቹ ሽሽት ከመጀመራቸው በፊት ፀጉረ – ልውጥ የፀጥታ ሰራተኞች ወደስፍራው መድረሳቸውንና የአካባቢው (የአማራ ክልል ባለስልጣናት) ስዎች በመኪና ተጭነው እስኪወጡ የሚያውቁት ነገር እንዳልነበር ምስክርነት ሰጥተዋል። የትግርኛ ተናጋሪዎቹ ከአካባቢው ሲወጡና ጉዞ ሲጀምሩ በደህንነት ሰራተኞቹ ፊልም መቀረፃቸውን መመልከታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ቢያንስ ሶስት መኖሪያ ቤቶች ላይ ነዋሪዎቹ ከወጡ በኋላ ባልታወቁ ሰዎች ጥቃት መፈፀሙን የሚያሳይ መረጃ አለ።

በወቅቱ በስፍራው የነበሩ ሶስት የረድዔት ሰራተኞች በአጋጣሚ ሰዎች የተሰባሰቡበት አካባቢ በመገኘታቸው ለአራት ሰዓታት በአነስተኛ ምግብ ቤትውስጥ ታግተው እንደነበርና ስልኮቻቸውና ካሜራቸው ላይ የነበሩ ምስሎች መበርበራቸውን ተናግረዋል።

ይህን ጉዳይ ለማጣራት ወደ ስፍራው የተላኩ ሁለት የተለያዩ መረጃ አሰባሳቢዎች ያገኙት መረጃ የትግርኛ ተናጋሪዎቹ ሽሽት በተደራጀ መልክ መካሄዱን የሚያሳዩ መረጃዎች መኖራቸውን ሪፖርት አድርገዋል።

“አካባቢው ለድንበር ቅርብ በመሆኑ ከፍተኛ ወታደራዊና የደህንነት ሰራተኞች የሚንቀሳቀሱበት ሆኖ ሳለ ለምን ሌሎች የደህንነት ሰራተኞች ከመቀሌ ወይም ከአዲስ አበባ ወደ ስፍራው እንደተላኩ ግልፅ አይደለም” ይላሉ መረጃ አሰባሳቢዎቹ።

“በትግርኛ ተናጋሪዎች ላይ ስጋትና ፍራቻ መኖሩን መካድ አይቻልም ይሁንና ኢትዮጵያውያን በአመዛኙ ለማህበራዊ ትስስር በሚሰጡት ልዩ ዋጋ ይህ አብሮነት እንዲናጋ የሚፈቅዱ አይደሉም፣ በመተማ የነበረው ሁኔታም በዚህ መነፅር መታየት ይኖርበታል” ይላሉ ዲፕሎማቱ በሰነዱ ላይ ባሰፈሩት አስተያየት።

“እስካሁን ባለን መረጃ ጥቃት የተፈፀመባቸው የትግርኛ ተናጋሪዎች በቁጥር እጅግ ኢምንት ናቸው። በአብዛኛው ገና ለገና ጥቃት ይፈፀምብኛ በሚል ስጋት ከባህር ዳር ጎንደርና የኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች መኖሪያቸውን ለቀው ወደ አዲስ አበባና ወደ ትግራይ ያመሩ መኖራቸውንእናውቃለን” ይላል ሪፖርቱ ።

“ይህን ስጋት የደህንነት ተቋሙ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ሊጠቀምበት መሞከሩን በቂ ፍንጮች አሉ” ይላል ሰነዱ። “ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታና የትግራይ ተወላጆችን ከጎኑ ለማሰለፍ ፍላጎት እንዳለው ማሳያ ነው”

“ለሌሎች ኢትዮጵያውያንም ሀገሪቱ በዘር ፍጅት አደጋ አፋፍ ላይ እንዳለች አስመስሎ በማሳየት በሀገሪቱ ያለው ተቃውሞ ‘አደጋ ያመጣል’ የሚል ስጋት የማጫር ዕቅድም ሊኖረው ይችላል። ይህን ዋናው የደህንነት መስሪያ ቤት ወይም የትግራይ ክልል በተናጠል/ በጋራ ያደረገው መሆኑን መረጋገጥ አልቻልንም”

የትግራይ ክልል አልያም የማዕከላዊ መንግስት የዘር ፍጅት አደጋ ማንዣበቡን በመተማው አጋጣሚ በማሳየት ራሱን አረጋጊና የሰላም ዋስትና የማድረግ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ያለ ኢህአዴግ አመራር ሀገሪቱ ወደ እልቂት እንደምትገባ ለማመላከት ዓላማ ሊያውለው መሞከሩን ዲፕሎማቱ በሰጡት አስተያየት አስፍረዋል።

በጎንደር ተቃውሞ ተባብሶ በነበረበት ሀምሌ 2008 የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን (ኢሳትና) በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል (VOA ላይ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ አድርገውብኛል ሲል ለአሜሪካ መንግስት ክስ አቅርቦ ነበር። ክሱ ተቀባይነት አላገኘም።

የኢትዮጵያ ደህንነት መስሪያ ቤት ራሱ ፈንጂ በማፈንዳት ተቃዋሚ የፖለቲካ ሀይሎችንና ኤርትራን ይወነጅል እንደነበረ ከዚህ ቀደም ይፋ የሆነ የአሜሪካምስጢራዊ የዲፕሎማቲክ ሰነድ መግለፁ ይታወሳል።


ለድርብ አድርባዮች: ለሙክታር ከዲርና አስቴር ማሞ ዝክር (ታደሰ ብሩ)

$
0
0

አንድ ሰው ወይም ቡድን መልካም ነገር እንደሆነ እያወቀ የግል ዝናውን፣ ሀብቱን ወይም ምቾቱን ለመጨመር ሲል ማድረግ የነበረበትን ሳያደርግ ሲቀር እና/ወይም መልካም ነገር እንዳልሆነ እያወቀ የግል ዝናውን፣ ሀብቱን ወይም ምቾቹ ለመጨመር ሲል ማድረግ ያልነበረበትን ሲያደርግ አድርባይ ይባላል። አድርባይ ሰው ችሎታዎቹንና እውቀቱን ብቻ ሳይሆን የገዛ ራሱንም ጭምር ከፍ ያለ ዋጋ ላቀረበት ገዢ ይሸጣል። አድርባይ ጥሩ ፓለቲከኛም ሆነ ጥሩ ነጋዴ አይወጣውም።
በኔ እምነት የህወሓት አገዛዝ በኢትዮጵያ ውስጥ ካስፋፋቸው ማኅበራዊ በሽታዎች ትልቁ አድርባይነት ነው። ህወሓት ራሱ አድርባይ ድርጅት ነው፤ የአጭር ጊዜ ጥቅሙን ለማብዛት (ለምሳሌ፣ በስልጣን ላይ ለመቆየት) እድል እጁ ውስጥ ያስገባችለትን መሣሪያ ሁሉ የሚጠቀም፤ አንዳችም የስነምግባር ልጓም የሌለው ድርጅት ነው። በዚህ አድርባይ ድርጅታዊ ባህሪው ምክንያት ነው ህወሓት ሌሎች ድርጅቶችን አሰናክሎ ብቻውን በትግራይ ገኖ የወጣው፤ በአሸዋ የተሞሉ ጆንያዎችን ከላይ ስንዴ በትኖባቸው ስንዴ በማስመሰል ለዕርዳታ ድርጅቶች የሸጠው፤ የትግራይን ሕዝብ ለማነሳሳት ሲል በደርግ ያስጨፈጨው፤ አንዴ የቻይናው ማኦ፣ ሌላ ጊዜ የአልባኒያው ኤንቨር ሆዣ፣ ቆይቶ የእንግሊዙ አዳም ስሚዝ ለመምሰል የሞከረው። በዚሁ የአድርባይነት ባህርዩ ምክንያት ነው ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ራሱ ቦንብ አፈንድቶ ተቃዋሚዎችን የሚከሰው፤ በድምፃቸው ምረጡኝ ብሎ ደስ ያለው ቁጥር ለራሱ የሚሞላው፤ ሆነ ብሎ አንዱን የማኅበረሰብ ክፍል ከሌላው ጋር የሚያጣላው …. ስለህወሓት አድርባይ ተግባራት ዘርዝሮ መጨረስ ስለማይቻል በነጠብጣቦች ልለፈው። የህወሓት ሹማምንት ከድርጅታቸው የወረሱት ስር የሰደደ አድርባይነት ስላለባቸው ነው ሥልጣን፣ ሀብትና ውሸት በቃኝ የማይሉት።
አድርባይ መሆን ራሱ የሚያሳፍር ሆኖ እያለ ለአድርባይ ማደር ደግሞ ድርብ እፍረት ነው። ለአድርባይ ማደር ድርብ አድርባይነት ነው። የብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ እና “አጋር” እየተባለ የሚንቆላጰፁት የአብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊ እና ኢሶዴፓ አባላት ለአድርባር ህወሓት ያደሩ ድርብ አድርባዮች መሆናቸው በእጅጉ ሊያሳፍራቸው ይገባል።

Tadesse Biru
ድርብ አድርባዮች በአድርባይነታቸው የመጠቀሚያ ጊዜዓቸው አጭር እንደሆነ እንዴት እንደማይረዱት ይገርመኛል። ለሥራው ያስመረጣቸው የራሳቸው አድርባይነት ቢሆንም አሠሪያቸውም አድርባይ በመሆኑ የተሻለ ጥቅም ካገኘ እንደሚሸጣቸው እንዴት ማወቅ ይሳናቸዋል?
ከህወሓት በላይ ህወሓት ለመሆን ይጥር የነበረው ዳባ ደበሌ ዛሬ የት ይሆን ያለው? ለአንድ ቀን አብሬው ምሳ የመብላት እድል አጋጥሞኝ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‘እጃችን በሥራ ተጠምዶ እያለ ስልጤ ኪሳችን ገባ’ ብሏልና ስልጤ ተስፋ የሌለው ሕዝብ ነው” ብሎ ብዙ ሰው በተሰበሰበት የተናገረው የመለስ ዜናዊ አምላኪው ጁነዲን ሳዶ ዛሬ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? የጣና በለስ ፕሮጀክትን ለቤንሻንጉል ጉሙዝ አገልግሎት እንደገና እንዲያስጀምር የጥናት ሀሳብ ሲቀርብለት “ከህወሓት አታጣሉኝ” ያለው ያረጋል አይሸሹም ዛሬ የት ነው ያለው? ዘላለም ጀማነህና ለገሠ ቢራቱ የት ነው ያሉት? የአርከበ እቁባይ የግል ሎሌ የነበረው የእዣው ፊታውራሪ ፀረ-ቅንጅት መኩሪያ ኃይሌ አሁን እንግሊዝ ውስጥ ምን ይሠራል? …. አንድ ቀን በምሬት ራሱን ያጠፋል ብዬ እየጠበቅሁት ያለው የራሱን የቀድሞ የግል ወዳጆችን ማሰቃየት የሚያስደስተው ሳዲስት ሺመልስ ከማል ምነው ድምጹ ጠፋ? …. ተመሳሳይ ጥያቄዎቼ ብዙ ናቸው።
ዛሬ ደግሞ ሁለት ተጨመሩልኝ። ልባቸው በህወሓት ፍቅር የነደዱ ሁለት “ምስኪኖች” — ሙክታር ከዲርና አስቴር ማሞን — ፍቅር አላስጨርስ አላቸውና በአደባባይ አጋልጦ ጣላቸው። ህወሓት አዟቸው ለሠሩት ክፋት በራሳቸው ነፃ ህሊና የሠሩት ተደርጎ ቀረበባቸው። ከእንዲህ አምባሳደርነትም “ቢሾሙ” ካሳ አይሆንም። አድርባይ ድርጅት ጥቅም እንጂ ፍቅር አያውቅም። ሙክታርና አስቴር አድርባዮች ነበሩ፤ እነሱ ራሳቸው አድርባዮች ሆነው እያለ ለአድርባይ ድርጅት ማደራቸው ድርብ ጥፋት ሆነ። የዛሬው የቅጣቱ መጀመሪያ ነው። ፀፀቱም፣ ቅጣቱም ገና መጀመሩ ነው።
ወገኖቼ!!!!
ለአድርባይ ማደርን ያህል አሳፋሪ ነገር የለም። ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ፣ አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊ እና ኢሶዴፓ ውስጥ ያላቸው ህሊና ያላችሁ ወገኖች ወደ ህሊናችሁ ተመለሱ። አለበዚያ የእድሜ ልክ ፀፀት ይከተላችኋል። ክፋቱ ፀፀቱ እናንተ ስታልፉ አያልፍም፤ ልጆቻችሁ እና የልጅ ልጆቻችሁ በእናንተ ያፍራሉ። ይህን ስታስቡት አይሰቀጥጣችሁም?

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ጥሪ በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እንመካከር !

$
0
0

decison

በኖርዌይ ለምትኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ በሙሉ !
የዲሞክራሲዊለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ/DCESON/ እና የኢትዮጵያን የጋራመድረክ ኖርዌይ /COMMON FORUM/ በጋራ በመሆን በሰሞኑ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በጋራ በኖርዌይ ከሚኖሩ ትውልደኢትዮጵያ ጋር ለመወያየት ! ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ አዘጋጅተዋል
======================
ኢትዮጵያዊን እንደ ወያኔ ዘመን የተዋረዱበት የተናቁበትና የተበደሉበት ጊዜ የለም። በአሁኑ ወቅት አገሪቱ ና ህዝቧ ከፊታቸው የተጋረጠውችግር የመሰረታዊ የዲሞክራሲ ና የሰብኣዊ መብቶች አለመከበር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሕልውና ጥያቄ ና ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠልናያለመቀጠል ጉዳይ ሆኖዋል።በመሆኑም
የዲሞክራሲዊለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ/DCESON/ እና የኢትዮጵያን የጋራመድረክ ኖርዌይ /COMMON FORUM/ በሰሞኑ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በጋራ በኖርዌይ ከሚኖሩ ትውልደኢትዮጵያ ጋር ለመወያየት ! ታላቅ ህዝባዊ ስብስባ አዘጋጅተዋል እርስዎም በዚህ ፕሮግራም ላይ በመገኘት እንዲሁም ሌሎችንም በመጋበዝ ታሪካዊና ወቅታዊ አገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንንእናቀርባለን።
ቀን መስከረም 24፣2016 ከቀኑ 1 pm ጀምሮ

“ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ” ሲባል አፌን ኩበት…ኩበት ይለኛል (ስዩም ተሾመ )

$
0
0

እኔ የምለው… ከእናንተ ውስጥ የኢትዮጲያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) (EBC) የሚመለከት አለ? ካላችሁ የከበረ ሰላምታዬን አድርሱልኝ። እሱን መመልከት ካቆምኩ ሦስት አመት ይሆኛል። ይህን ያህል ከኢብኮ ጋር ያቆራረጡኝ “ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ” በሚሉት ቃላት ናቸው። ላለፉት አስር አመታት እንደነዚህ ቃላት ለዛና ትርጉም ያጣብኝ ቃል የለም። በዜና እወጃ፣ በባለስልጣናት መግለጫ ወይም በተመልካቾች አስተያየት መስጫ፤ “ሰላም፥ ልማት፥ ዴሞክራሲ” የሚሉትን ቃላት ስሰማ ጆሮዬን ይኮረኩረኛል። ምንም ድምፅ ሳላሰማ በውስጤ ስደጋግማቸውማ ቃላቱ “ኩበት…ኩበት” የሚል ቃና ያላቸው።

ስዩም ተሾመ

ስዩም ተሾመ


ታዲያ ዘንድሮ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የተዘጋጀው የስልጠና ሰነድ የመጀመሪያው ርዕስ ምን ቢል ጥሩ ነው፡-“የሩብ ምዕተ ዓመታት የልማት፥ ሰላምና ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ጉዞ፣….” ከዚያ በኋላ፣ በጨፈገገ ስሜት ውስጥ ሆኜ “ለምንድነው እነዚህ ቃላት ለዛ ቢስና ትርጉም አልባ የሆኑት?” ብዬ ራሴን ጠየቅኩ። ምላሹ ግን ለእኔ ለራሴ በጣም አስገርሞኛል። በእርግጥ ቃላቱ ምንም ጥፋት የለባቸውም። እንኳን ቃላቱ፣ ኢብኮ ራሱ ምንም ጥፋት የለበትም። “ሰላም፥ ልማት፥ ዴሞክራሲ” የሚሉት ቃላት ለዛና ትርጉም ያሳጣቸው የኢህአዴግ መንግስት ነው።

በመሰረቱ፣ ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ የመንግስት መሰረታዊ ዓላማዊች ናቸው። የኢህአዴግ መንግስት ላለፉት 25 ዓመታት ከዚህ አንፃር ያስመዘገበው ስኬት ዝቅተኛ መሆኑ ችግር አልነበረውም፡፡ ምክንያቱም፣ የኢህአዴግ ችግር ለፖለቲካ ፍጆታ ያለ ቅጥ ከማጋነን ያለፈ ነው። እንደ መንግስት ሆነ እንደ ፓርቲ የኢህአዴግ መሰረታዊ ችግር “ነፃነት” ነው። በራሱም ውስጥ ሆነ በሌሎች ዘንድ ነፃነት የሚባል ነገር በፍፁም ማየት አይፈልግም። ነገር ግን፣ ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ ደግሞ እንደ ማንኛውም መንግስት የኢህአዴግም መሰረታዊ ዓላማዎች ናቸው።

የሀገር ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ ስኬት መለኪያ መስፈረት ነፃነት ነው። እያንዳንዱ መሰረታዊ ዓላማ በነፃነት ፅንሰ-ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ነው። ኢህአዴግ እንደ መንግስት እነዚህን መሰረታዊ ዓላማዎች የማሳካት ግዴታና ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን፣ በእያንዳንዱ ዘርፍ ያስመዘገበውን ስኬት ግን ከዜጎች ነፃነት አንፃር የመለካት ባህሪ የለውም።

ከዚያ ይልቅ፣ ፓርቲው ያስመዘገባቸውን አንኳር ለውጦች በቁጥር ነው የሚለካቸው። ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲን በቁጥር መለካት ደግሞ ክብደትን በሜትር እንደመለካት ነው። በመሆኑም፣ የኢህአዴግ መንግስት “ሰላም፥ ልማትና ዴሞክራሲ” ብሎ የሚያቀርባቸው ዘገባዎች፣ ሃሳቦችና አስተያየቶች በሙሉ ለዛ ቢስ እና ትርጉም አልባ ይሆናሉ። እስኪ እያንዳንዱ ቃል ከነፃነት ጋር ያለውን ቁርኝነትና ኢህአዴግ ያለበትን መሰረታዊ ችግር በአጨሩ እንመልከት፡-

1ኛ፡- ሰላም

አስተማማኝ ሰላም የሚረጋገጠው ዜጎች በነፃነት ወደ ፈለጉት ቦታ በፈለጉት ግዜ መንቀሳቀስ፣ ለደህንነታቸው ሳይሰጉ በሰላም ወጥተው በሰላም መግባት ሲችሉ ነው። የፀረ-ሰላም ኃይሎች ዓላማ ደግሞ በሕይወትና ንብረት ላይ ድንገተኛ ጉዳት በማድረስ ይህን የዜጎችን በሰላም የመንቀሳቀስ ነፃነት ወደ ፍርሃት መቀየር ነው። ስለዚህ፣ “ሰላም” ማለት በፈለጉት ግዜና ቦታ ያለ ስጋት መንቀሳቀስ መቻል ነው። “ነፃነት” ደግሞ ያለ ማንም አስገዳጅነት በራስ ምርጫና ፍላጎት መንቀሳቀስ መቻል ነው። ስለዚህ፣ ሰላም ማለት ነፃነት ነው።

የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር በሚል በመንግስት የሚወሰድ ማንኛውም ዓይነት እርምጃ የሰላማዊ ዜጎችን ሰላምና ነፃነት መገደብ የለበትም። ሰላም ማለት በራስ ምርጫና ፍላጎት መሰረት በፈለጉት ቦታና ግዜ የፈለጉትን ነገር ማድረግ መቻል እንጂ በኢህአዴግ መንግስት ምርጫና ፍቃድ መሰረት መንቀሳቀስ አይደለም። የኢህአዴግ መንግስት ግን ነፃነቴን ገድቦ ስለ ነፃነት መስበክ ይቃጣዋል፤ ሰላሜን አሳጥቶኝ ስለ ሰላም አስፈላጊነት ያወራል። በዚህ ምክንያት፣ “ሰላም” የሚለው ቃል ለዛና ትርጉሙን አጥቷል። ሌላው ቀርቶ፣ ኢህአዴግ ስለ ሰላም ሲያወራ እኔን ሰላም ይነሳኛል።

2ኛ፡- ልማት

“ልማት” ማለት በአጭሩ “ሰላም፣ ጤና፣ ትምህርትና መሰረተ-ልማት” ማለት ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ ዘላቂ ልማት ሊኖር የሚችለው እነዚህ ለአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል በእኩልነት ተደራሽ ሲሆኑና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ ነው። በኢህአዴግ መንግስት የልማት መርህ መሰረት ግን፣ ማህብረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ግለሰቦች ጥቅማቸውን ማጣት አለባቸው። ነገር ግን፣ የልማቱ ጥቅምም ሆነ ጉዳቱ ለአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል እኩል መዳረስ ነበረበት።

በኢህአዴግ የልማት መርህ መሰረት፣ ሀብታም ለሚያቋቁመው የአበባ ፋብሪካ ደሃ ገበሬ ከእርሻ መሬቱ ይፈናቀላል፣ ሀብታም ለሚገነባው ፎቅ የደሃ መኖሪያ ቤት ይፈርሳል። ይህ ለአንዱ ልማት ሌላው ግን ጥፋት ነው። በመሰረታዊ የነፃነት መርህ መሰረት ደግሞ የእኔ መብት የሌላን ሰው ነፃነት መገደብ የለበትም። የባለሃብት ፋብሪካ የማቋቋም መብት አርሶ-አደሩን የእርሻ መሬት ማሳጣት የለበትም። ሀብታም የሚገነባው ቤት በደሃ መኖሪያ ቤት ፍርስራሽ ላይ መሆን የለበትም። የአንዱ ዜጋ በነፃነት የመስራት መብት የሌላውን ዜጋ በነፃነት የመኖርና የመስራት መብት ማሳጣት የለበትም።

በዚህ መሰረት፣ የልማታዊ ስራ አግባብነትና የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚለካው ከዜጎች ነፃነት አንፃር ነው። የኢህአዴግ መንግስት ከልማቱ እኩል ተጠቃሚ ሳልሆን ስለ ልማት ይደሰኩራል። እኔ በነፃነት የመስራትና የመኖር መብቴን ተነፍጌ ሌሎች ሀብትና ንብረት ሲያፈሩ እያየሁ ስለ ልማት ሲያወራ ከመስማት የበለጠ ምን ጸያፍ ነገር አለ?

3ኛ፡- ዴሞክራሲ

ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሕግ የበላይነት ላይ የተመሰረተና የዜጎች እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚረጋገጥበት ስርዓት ነው። በዚህም፣ የዜጎች አስተማማኝ ሰላምና ደህንነት፣ እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ይረጋገጣል። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን፣ ኢትዮጲያ ውስጥ ማንኛውም ግለሰብ፥ ቡድን፥ ማህበር፥ ድርጅት፥…ወዘተ፣ ከኢህአዴግ መንግስት ምርጫና ፍቃድ ውጪ እስከሆነ ድረስ “ከፀረ-ሰላም ኃይሎች” ጎራ ሊመደብ ይችላል። ሌላው ቀርቶ፣ ስለ ሰላም መናገርና መፃፍ በራሱ “ፀረ-ሰላም” ሊያስብል ይችላል።

በኢህአዴግ አመለካከት መሠረት “ለሰላማዊ ሰልፍ” እና “ለትጥቅ ትግል” ጥሪ ያቀረቡ ወገኖች ሁለቱም “ፀረ-ሰላም” ሃሎች ናቸው። “የአማፂ ቡደን አባል” እና “ስለ አማፂ ቡዱኑ የፃፈ ጋዜጠኛ” እኩል በፀረ-ሽብር ሕጉ ተከሰው ራሳቸውን ማዕከላዊ እስር ቤት ሊያገኙ ይችላሉ።

የኢህአዴግ መንግስት በሚያከናውነው ማንኛውም የልማት ሥራ ላይ የእኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ የሚያነሱ ግነሰቦች፥ ቡድኖች፥ ማህበራት፥ ድርጅቶች፥ …ወዘተ በሙሉ “ፀረ-ልማት፣ የኒዮ-ሊብራል ተላላኪዎች፣ የኪራይ ሰብሳቢዎች፣…” በሚል የውግዘት መዓት ሊወርድባቸው ይችላል። እንደ ዜጋ ከልማቱ እኩል ተጠቃሚ አለመሆኔ ሳያንስ “ፀረ-ልማት” የሚል ተቀፅላ ስም ይሰጠኛል።

በአጠቃላይ፣ ኢህአዴግ ከእሱ አቋምና አመለካከት ውጪ ያሉትን በሙሉ “ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ኃይሎች ተላላኪዎች፣ ኪራይ ሰብሳቢዎች፣…” እያለ ስም ያወጣል። ሰላሜን ያሳጣኝ ሳያንስ “ፀረ-ሰላም” ይለኛል። ከሀገሪቱ ልማት እኩል ተጠቃሚ አለመሆኔ ሳያንሰኝ “ፀረ-ልማት” ብሎ በቁስሌ ላይ እንጨት ይሰዳል። ይህን ባለበት አንደበቱ ደግሞ ተመልሶ ስለ ሀገሪቱ “ሰላምና ልማት” ሊሰብከኝ ይሞክራል።

በሰላም ስም ሰላሜን አሳጥቶኝ፣ ከልማት ተጠቃሚ እንዳልሆን ከሌሎች ለይቶ በድሎኝ፣ በደልና ቅሬታዬን ብናገር የሀገሪቱን ሰላም እና ልማት ለማደናቀፍ በሚል አስሮ ያሰቃየኛል። ይህን እያደረገ ስለ ዴሞክራሲ ሊያወራኝ ይፈልጋል። ነፃነቴን አሳጥቶኝ ስለ ነፃነት ሊሰብከኝ ይሞክራል። በዚህ ምክንያት ይኼው በዜና፣ በመግለጫ ወይም በአስተያየት፣…ብቻ በማንኛውም አጋጣሚ ኢህአዴግ ስለ ሰላም፥ ልማት ወይም ዴሞክራሲ ሲናገር በሰማሁ ቁጥር ጆሮዬን ይኮረኩረኛል፣ አፌን “ኩበት…ኩበት” ይለኛል!

ኢትዮጵያ ሽምግልና ለምኔ?ዶ/ ር ዘላለም እሸቴ

$
0
0

ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ችግሮች ለመውጣት ሽምግልናን እንደ መፍትሄ አድርጋ መውሰድ ትችላለች ወይ? እስቲ ይህንን ሀሳብ በተመለከተ ጉዳዩን ከሁሉም አቅጣጫ ረጋ ብለን እንመልከት። ከኢአዴግ አንዳንዶች አንድ ምርጫ ብቻ እንዳለ ሊያስቀምጡ የፈለጉ ይመስላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሆን ፀጥ ለጥ አሰኝቶ መግዛት አሊያም በሃይልም ቢሆን መግዛት እንችላለን ብለው የሚያምኑ እስኪመስል ድረስ ሃይልንም ሲጠቀሙ ይታያል። በተቃዋሚ ጎራ ያሉ አንዳንዶች ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ምርጫ ብቻ እንዳለ አድርገው ያስቀምጣሉ። ያም የሚያስከትለውን ዋጋ ከፍሎና በአመፅ አብዮት አካሄዶ መንግስትን መገልበጥ ነው እንጂ መነጋገር የትም አያደርስም ብለው ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ። እና ምን ይሻላል? ተያይዞ ገደል መግባት ወይስ አውጥቶ አውርዶ፥ ከሁለቱም ተቃራኒ አስተሳስብ ይልቅ ሌላኛ ሶስተኛ አስተሳሰብ አለ ብለን መንግስትንና የተቃዋሚ አካላትንመሞገት? የኢትዮጵያ ሕዝብ በመቻቻልና በመተሳስብ አብሮ የኖረ ሕዝብ ነው። ያልታደለው እኩልነትን አንግሶ በፍቅር የሚያያይዘውና አንድ የሚያደርገው አስተዳደር እስካሁን አለመገኘቱ ነው። ፈሪሃ ፈጣሪን የተላበሰው ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእውነት ላይ የተመሰረተ ጥል ሆነ ጥላቻ አንዱ በሌላው ላይ የለውም። መሪዎች እንደ ሕዝቡ ቅን ሆነው እኩልነትና ፍቅርን ቢዘሩ የሚታጨደው የፍቅር አዝመራ የሚያስጎመጅ በሆነ ነበር።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ህብረ ብሔር በሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በመሪዎች የስህተት አካሄድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። ስለሆነም መንግስት በተቀዳሚነት ለዚህ ስጋት ሃላፊነትን ራሱ መውሰድ ይገባዋል። ራሱንም ተጠያቂ ካደረገ በውኋ ላ፥ ወደዚያ ጥፋት ከሚመራው የሃይል እርምጃ ታቅቦ ኢትዮጵያን ለማዳን ውይይትና መግባባትን እንደ ብቸኛ አማራጭ በመውሰድ አማራጭ ሃይሎችን ለሰላሙ ጉዞ መጋበዝ ይኖርበታል። አብዮት ላለፉት አራት አስርተ አመታት ያተረፈልንን እያየነው ነው። ችግርን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ለዛሬና ለወደፊቱ ፍቱን መድሃኒት ነው። አብዮት የዛሬን ችግር ፈቶ ሲያበቃ የነገውን ችግር ይወልዳል። መንግስት ጊዜ ሊገዛ ፈልጎ የውሸት ሽምግልና ቢመርጥ ያንን ውድቅ ማድረግ ያባት ነው። አለበለዚያ ግን በጭፍን ሽምግልና ዋጋ የለውም ማለት ከማስተዋል ሃላፊነት መጉደል ይሆንብናል። ሽምግልና ይሰራል አይሰራም ሳይሆን ጥያቄው፥ የትኛው ሽምግልና ይሰራል ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ሁለት አይነት የሽምግልና አካሄድ ሊኖር ይችላል። አንድም አድሏዊ የሆነ ከሃይለኛው ጋር የወገነ የይስሙላ ሽምግልና ሲሆን ሌላኛው ደግሞ፥ አድሏዊ ያልሆነ ከማንም ያልወገነና እውነተኛ ሽምግልና ነው። በርግጥ የይስሙላ ሽምግልና ምንም ፋይዳ ላይሰጥ ይችላል። ነገር ግን ለእውነተኛው ሽምግልና እድል ተሰጥቶት ኢትዮጵያ ካለችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ ድልድይ ቢሰራ ሀገራችን ዘላቂ ሰላም ይሰፍንባታል። የዚህ እውነተኛ ሽምግልና ግብና ዓላማ የሚያዛልቀው ሶስተኛው (ሌላኛው) መንገድ፥ በውይይትና በመግባባት አገሪቱን በሰላማዊ መንገድ ወደ ዘላቂ ዲሞክራሲ ፍትህ እኩልነትና ዕድገት የሚያመራውን ሂደት ለመፍጠር ሁኔታዎችን የሚያመቻች ነው። ዞሮ ዞሮ ይህን ዓላማና ግብ ሁላችንም የምንፈልገው ነው። እግዚብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

31 ሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን |ከታደሰ ብሩ

$
0
0

File Photo

File Photo


በ2009 የትምህርት ዓመት በመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ የሕዝባዊ አሻጥር ዓይነቶች
1. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ስለሰብዓዊ መብቶች ሉዓላዊነት እና ስለ ሰለሰው ልጆች ክብር አስተምሩ፤ በተግባርም አሳዩ። የትምህርቱ መርሀግብር (curriculum) አይፈቅድልኝም የሚለውን ሰበብ አስወግዱ። ራሱ “ትውልድን ገዳይ“ የሆነው ካርኩለም ላይ ነው አሻጥር መሥራት ያለባችሁ።
2. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ተማሪዎች እውነትን ራሳቸው እንዲሹ፣ ብዙ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ እንዲመራመሩ፣ እንዲሞግቱ አበረቷቷቸው። የትምህርት ቤቱ ህግ ባይፈቅድም ተማሪዎች የተሰማቸውን በነፃነት እንዲናገሩ፣ እንዲጽፉ፣ እንዲዘምሩ ፍቀዱላቸው።
3. ተማሪዎች “እኔ ማነኝ?” “ማንን መምሰል እፈልጋለሁ?” “ምን ማድረግ እችላለሁ?” ብለው እንዲጠይቁና ራሳቸው ፈልገው እንዲያገኙ፤ እያንዳንዳቸው Potentially ዓለምን መቀየር የሚችሉ ሰዎች መሆናቸውን እንዲረዱ አበረቷቷቸው።
4. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ተማሪዎች ከግላቸው አልፈው ስለማኅበረሰብ እንዲያስቡ “ይህች አገር የማናት?” “ማን ጠግቦ፤ ማነው የሚራብባት?” “ማን ዘፍኖ ማነው የሚያለቅስባት?” “መጪው 20, 30, 50 ምን ሆኖ ማየት እንፈልጋለን?” “የምንፈልገው እንዲመጣ አሁን ምን ማድረግ እንችላለን?” ብለው እንዲጠይቁ አበረቷቷቸው።
5. በትምህርት ወቅት የምትሰጧቸው ምሳሌዎች ሁሉ አገራዊና ወቅታዊ ይሁኑ። ለምሳሌ በሂሳብ ክፍለ ጊዜ የ EBC “ልማታዊ ዜና” ውሸትነት በቀላል ሂሳብ ማረጋገጥ በመልመጃነት ይቅረብ (ለዚህ የሚሆን ማስረጃ በገፍ ነው ያለው)።
6. ምሳሌዎቻችሁና ቀልዶቻችሁ የህወሓት አገዛዝ ብልሹነት ቢቻል በቀጥታ ካልሆነም በተዘዋዋሪ የሚገልጹ እንዲሆኑ አድርጉ።
7. በፓሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በወታደር፣ በደህነት (ጆሮ ጠቢዎች)፣ በምርጫ ቦርድ፣ በእምባጠባቂ፣ በ EBC፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን፣ በ EFFORT … ወዘተ ቀልዱ። በእነዚህ ተቋማት ላይ እንዲቀለድ አበረታቱ።
8. በዘር፣ በፆታ፣ በሀይማኖት መተራረብና መከፋፈል ጊዜ ያለፈበት አስተሳሰብ እንደሆነ አስተምሩ። ጊዜው ባለፈበት አስተሳሰብ የሚመሩት የኢህአዴግ ካድሬዎች መሆናቸው አስረዱ።
9. ኢህአዴግን ከወቅቱ ጋር መቀየር ባለመቻሉ ከጠፋው ዳይኖሰር ጋር አመሳስሉት፤ በ 2009 የትምህርት ዘመን ዳይኖሰሩ ይጠፋል ብላችሁ አስተምሩ።
10. የትምህርት ቤቱ አፋኝ ደንቦችን በእናንተ ክፍል ውስጥ ተግባራዊ አይሁኑ። በአገሪቱ ያሉ አፋኝ ህጎችም በእናንተ ክፍል ውስጥ ይጣሱ።
11. ለአካዳሚ ነፃነት፣ ለተሻሻለ የትምህርት ሥርዓት፣ ለመምህራን መብት፤ ለተሻለ ክፍያና የደረጃ እድገት እድሎች ታገሉ። በወያኔ የተጠለፈውን የመምህራን ማኅበርን አውግዙ፤ የራሳችሁን ነፃ ክበባት ፍጠሩ።
12. ከለውጥ ፈላጊ ተማሪዎች ጋር አብሩ፤ በሃሳብ፣ በቁሳቁስ፣ በተግባር እርዷቸው። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ፀረ ህወሓት/ኢህአዴግ ምስጢራዊ ድርጅት አቋቁሙ።
13. ተማሪዎች የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የነፃነት፤ የማኅበራዊ ወይም የፓለቲካ ጥያቄዎች ሲያነሱ ከጎናቸው ቁሙ።
14. የኅበረተሰቡን የነፃነት፣ የፍትና የእኩልነት ጥያቄዎች በመደገፍ ታገሉ፤ ለትግሉ የሙያ ድጋፍ ስጡ።
15. የአቃጣሪ ተማሪዎችና የካድሬ መምህራንን የሞባይልና የቤት ስልኮችን ለምስጥራዊ ድርጅታችሁ ስጡ።
16. በማኅበራዊ ሚዲያዎች (ፌስቡክ፣ ቱተር፣ ኢንስታግራም፣ ዩቱብ) የአቃጣሪ ተማሪዎች፣ የካድሬ አስተማሪዎችና ሠራተኞች ስብዕና የሚያንቋንሽሹ ጽሁፎችንና ምስሎችን አሰራጩ።
17. የነፃነት ታጋዮችን የሚያሲዙ ካድሬ መምህራንና ተማሪዎችን ተግባር ከትምህርት ቤታቸው አልፎ የሰፈራቸው ሰዎች እንዲያውቁ አድርጉ። እንዴት ክፉ ሰዎች እንደሆኑ ወንድሞቻቸው፣ እህቶቻቸው፣ ልጆቻቸው፣ ሚስቶቻቸው፣ ዘመዶቻቸውና ጎረቤቶቻቸው እንዲያውቁ አድርጉ።
18. የተለያዩ የተቃውሞ መግለጫ መንገዶችን በማስተዋወቅና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ግምባር ቀንበር ሁኑ።
19. “ቀበሌና ፓሊስ ትምህርት ቤታችንን አይርገጥ” በሉ።
20. የትምህርት ቤቱን የተለያዩ ክበባት ተማሪዎችን ለትግል ማዘጋጃነት አውሉ። ሚኒ ሚዲያ፣ ድራማ፣ ስነጽሁፍ፣ ቅርፃ ቅርጽ፣ ስፓርት፣ ሙዚቃ፣ … የሂሳብና የፊዚክስ ክበባት ሁሉ ሳይቀሩ ተቃውሞ ማሳያዎችና አሻጥር መሥሪዎች ይሁኑ።
21. ተማሪዎች በግጥም፣ በልበወለድ ታሪኮች፣ በድራማዎች፣ በዘፈኖች፣ በስዕሎች … የተቃዉሞ መልክቶቻችሁን እንዲያስተላልፉ አስተባብሩ፤ እናንተም ተሳተፉ።
22. የስፓርት ሜዳዎች የትግል ሜዳዎች ይሁኑ። የስፓርት ሜዳ መዝሙሮች ፀረ-ህወሓት/ኢህአዴግ የትግል መዝሙሮች ይሁኑ። የስፓርት ክበባት የአሻጥር ጥናትና ሙከራ ማዕከላት ይደረጉ።
23. የነፃነት ታጋዮች የሚያትሟቸው ወረቀቾችን በትምህርት ቤት ውስጥ አሰራጩ።
24. የነፃነት ታጋዮችን ስም አወድሱ። በእስር ላይ የሚገኙ፤ በትግል ላይ የሚገኙ ብሄራዊ ጀግኖችን አወድሱ። በአንፃሩ፣ የኢህአዲግ ሹማምንትን አራክሱ።
25. በተገኘ አጋጣሚ ሁሉ ወረቀት፣ ኮምፒውተር፣ ማባዣ እና የመሳለሉትን ውሰዱና የነፃነት ትግል መልዕክት ማባዣ አድርጓቸው።
26. የኢሳትና የ OMN ቴሌቪዥኖች ዜናዎችንና ፕሮግራሞችን ተከታተሉ፤ በየትምህርታችሁ መሀል የኢሳትና OMN ዜናዎች በማንሳት የሰማችሁ ላልሰሙት አዳርሱ።
27. ስለ እውነትና ውሸት ስትናገሩ ምሳሌዎቻችሁ EBC እና ኢሳት ይሁኑ። ውሸት እና EBC አቻ ቃላት ይሁኑ። የውሸት ማምረቻዎች በተማሪዎች ተለይተው እንዲታወቁ አድርጉ: የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፣ የጠቅላይ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት፣ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶች፣ EBC፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን፣ የክልል መንግሥታት ቢሮዎች …
28. ፓሊሶች ሰው ሲደበድቡ፣ ሲያንገላቱ፣ የድሆች ቤቶች ሲፈርሱ፣ ፍትህ ሲጓደል አይታችሁ ዝም አትበሉ፤ ተማሪዎቻችሁን አስተባብራችሁ ጩኹ።
29. ማኅበረሰቡ በሚያደርገው ተቃውሞ – ሰልፍ፣ የቤት ውስጥ መቀመጥ፣ የግዢ ማዕቀብ … ወዘተ. – በንቃት ተሳተፉ።
30. ተቃውሞዎች ሲበስሉ ከምን በላይ ነፃነት ነውና ትምህርት በማቆም አምባገነኑን ሥርዓት ለማንበርከበብና የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ለማምጣት ግንባር ቀደም ሁኑ።
31. 2009 የትምህርት ዓመት የውጤታማ ፀረ-ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል ዓመት እንዲሁን ትጉ።

በምዕራብ አርሲ ሻላ እና አጄ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ጫካዎች ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ነው |የአጋዚዎች አለቃ ተገደለ

$
0
0
ይህን ኦፕሬሽን የመራው የአጋዚ ሰራዊት አዛዥ መኮንን የተባለ ወታደር አጄ አካባቢ የሚገኘው ጫካ ውስጥ ተገድሏል

ይህን ኦፕሬሽን የመራው የአጋዚ ሰራዊት አዛዥ መኮንን የተባለ ወታደር አጄ አካባቢ የሚገኘው ጫካ ውስጥ ተገድሏል

(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ሕዝብን ትጥቅ ለማስፈታት ተንቀሳቅሶ ሽንፈትን የተከናነበው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት አጋዚ ጦር ወደ ም ዕራብ አርሲ በተመሳሳይ ተንቀሳቅሶ በሕዝብ ድባቅ እየተመታ መሆኑን እና በአሁኑ ወቅትም በም ዕራብ አርሲ ሁለት ጫካዎች ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ::

ከአካባቢው የመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ለምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ እና ለአጄ ከተማ ቅርብ በሆኑት ጣጤሳ እና አርጆ ጫካ ውስጥ ይህ ዜና እየተጠናቀረበት ባለበት ወቅት ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው::

የሕወሓት መንግስት ሕዝቡን ትጥቅ አስፈታሁ ብሎ ወደ ሰላማዊ ገበሬዎች ጠመንጃ የታጠቁ የአጋዚ ሰራዊቶችን መላኩን ያስታወቁት የዜና ምንጮቹ እነዚህ ወታደሮች እንደሚመጡ አስቀድሞ መረጃው የደረሰው ሰላማዊው የአካባቢው ገበሬ አድፍጦ በመጠበቅና ራሱን በመከላከል እርምጃ ወስዷል:: በዚህም መሰረት ይህን ኦፕሬሽን የመራው የአጋዚ ሰራዊት አዛዥ መኮንን የተባለ ወታደር አጄ አካባቢ የሚገኘው ጫካ ውስጥ ተገድሏል:: ፎቶም ተነስቶ ሕዝብ እንዲያውቀው ተደርጓል:: ከመኮንን ጋር አብሮ ሌሎች አራት የአጋዚ ወታደሮች ሲገደሉ ከሕዝቡም 3 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል::

የሕወሃት መንግስት በደረሰበት ምት ጦሩን ከነዚህ ጫካዎች አሽሽቶ ተጭማሪ ሃይል በሻሸመኔ በኩል አምጥቶ በአሁኑ ወቅት ከሕዝቡ ጋር እየተታኮሰ መሆኑን ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመልከታል::

ይህን ጉዳይ ዘ-ሐበሻ እየተከታተለች ለመዘገብ ትሞክራለች::

“ሶማሌ አጋር ነው የሚባለው፤ አጋር ማለት ተመልካች ማለት ነው። ድምፅ የለንም።” –ዶ/ር ኡስማኢል ቋዳህና ዓሊ ሁሴን |ሊደመጥ የሚገባ

$
0
0

ዶ/ር ኡስማኢል ቋዳህ፤ የኢትዮጵያ ሶማሌ ዲሞክራሲያዊ ሸንጎ ሊቀመንበርና አቶ ዓሊ ሁሴን፤የኢትዮጵያ ሶማሌ ዲሞክራሲያዊ ሸንጎ ሥራ አስፈጻሚ አባል፤ ስለ ሸንጎው ሚናና ወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ይናገራሉ።
“ሶማሌ አጋር ነው የሚባለው፤ አጋር ማለት ተመልካች ማለት ነው። ድምፅ የለንም።” – ዶ/ር ኡስማኢል ቋዳህና ዓሊ ሁሴን


ዶክተር መረራ ጉዲና ስለወርቅነህ ገበየሁ በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል

ከስልጣንዎ ሲባረሩ እውነቱን ይነግሩናል (ከይገርማል)

$
0
0

በወያኔው የዘረኛ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ይዘው በህዝብ እምባና ደም ሲቀልዱ የነበሩ በተለያየ ምክንያት የተባረሩ ሰዎች በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ሊያዩ የቻሉት ከስልጣን ከተባረሩ በኋላ ነው:: ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ህዝባዊነታቸውን ሊያሰሙ ሀሳቡ እንኳ ያልነበራቸው የቀድሞ ባለስልጣናት ከስልጣን ከተባረሩ በኋላ አይናቸው ተገልጦ “ሕዝብ ተበደለ” እያሉ መንግስትን ሲነቅፉ እየሰማን ነው:: አንዳንዶቹ ደግሞ ከስልጣን ከተባረሩም በኋላ ጥቅማቸው ተከብሮላቸው ተንደላቀው እየኖሩ ለወያኔ መንግስት በስልት የመከላከል ስራ እየሰሩ ነው:: ወያኔ መራሹ አገዛዝ የሲቭል መንግሥት እንደሆነ የሚናገሩ እንደነ ጀኔራል አበበ ተ/ሀይማኖት ያሉ ሆን ብለው የሚያሳስቱ ሰዎች መንግስት አንዳንድ መሻሻሎችን አድርጎ እንከን የሌለው የሚሉትን ህገ-መንግሥት ለማስፈጸም እንዲንቀሳቀስ እየመከሩ ነው:: የመንግስት ባለስልጣኖች ሀገሪቱን ለመምራት ድክመት እያሳዩ መሆናቸውን በመግለጽ ጀኔራል ሳሞራ የኑስ ያደረጉትን ንግግር መሰረት አድርገው ጀነራል አበበ ሲያብራሩ የተፈጠረውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ወታደራዊ ሀይሉ መፈንቅለ መንስት አድርጎ ስልጣን እንዳይዝ የኢትዮጵያ ህዝብ በንቃት እንዲጠብቅ መክረዋል:: እያሉን ያሉት አሁን ያለው የሲቭል አስተዳደር መፈንቅለ መንግስት ተደርጎበት ስልጣን ወደወታደሩ እንዳይገባ ህዝብ ጥበቃ ያድርግ ነው:: ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ህዝብምን ቢሆን አሁን ያለው መንግሥት የወታደር መንግሥት መሆኑን የረሳው ይመስላል:: በ 1966 ዓ.ም ከጦር ሀይሎች: ከፖሊስና ከማረሚያ ቤቶች ተውጣጥቶ ሀገሪቱን በበላይነት የመራው ደርግ ከአመታት በኋላ የወታደራዊ መለዮውን አውልቆ የህዝብ አስተዳደር መስርቻለሁ ብሎ ማወጁ ይታወሳል:: ደርግ የወታደራዊ ልብሱን ሲቀይር ወታደራዊ ባህሪውን ግን ሊቀይር የሚቻለው አልነበረም:: ከሲቭል ማህበረሰቡ የተወሰኑ ሰዎችን መራርጦ ካስጠጋ በኋላ እየተገዛን ያለነው በወታደራዊ ኃይል ነው ሲሉ የሚሞግቱትን ሰዎች እንዲያው ክፋታችሁ ሆኖእንጅ እውነት አሁን ደርግ አለ? ሲል ነበር ምላሽ የሰጠው:: የአሁኑ ወያኔም ቢሆን የደርግን ፈለግ ተከትሎ ራሱን ከወታደር ወደ ሲቭል ቀይሮ ሕዝባዊ መንግሥት መስርቻለሁ እያለን ነው:: እንደእኔ እምነት ከሆነ ወታደር ማለት በውትድርና ሙያ ሰልጥኖ በየትኛውም ጎራ የሚሰለፍ ተዋጊ ሀይልነው:: በዚህ አረዳድ ስንሄድ ወያኔወችም ሆኑ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በውትድርና ሰልጥነው በሙያው ተጠምቀው ተዋግተው አሸንፈው ወደስልጣን የመጡ መሆናቸውን እንገነዘባለን:: ደርግ እንዳደረገው ሁሉ ወያኔም ከራሳቸው አልፈው ስለህዝብና ስለሀገር ማሰብ የተሳናቸውን ሰዎች በመብራት እየፈለገ በየብሄረሰብ ጉረኖ እንዲሰበሰቡ አድርጎ ሲያበቃ ከላይ ተቀምጦ እንደፈለገው እያሽከረከረ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ስርአት ተዘርግቷል ሲል ይቀልዳል:: እውነታው ግን ሀገሪቱ እየተመራች ያለችው በዘረኛ የወያኔ ወታደሮች ሲሆን ሌሎቹ ከወያኔ ጉያ የተወሸቁቱ በራሳቸው አስበውና አቅደው መስራት የማይችሉ የትእዛዝ ተቀባይናእንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ የማፈን ድርሻ ያላቸው ናቸው::
ለምሳሌ ያህል ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያምን ብናነሳ ከእምነትም ሆነ ከህግ ያፈነገጠ ስራ የሚሰሩት የታዘዙትን ብቻ የሚፈጽሙ በመሆናቸው ነው:: የመብት ጥያቄ ያነሱትን ኢትዮጵያውያን በሀይል እንዲያፍን ለፖሊስና ለመከላከያ ሀይል ትእዛዝ ሲያስተላልፉ የመናገርና የመቃወም መብት መኖሩን ረስተውት አይደለም:: በሰሞኑ የተመድ ስብሰባ ላይ ተገኝተው: የህዝብ ተቆርቋሪ እንደሆኑ የሚገልጹ ጽንፍ የረገጡ ቡድኖች በማህበራዊ ሜዲያ ሁከትን እየቀሰቀሱእንደሆነ ተናግረዋል። የህዝብ ጩኸት ተዳፍኖ ወያኔወች የፈለጋቸውን እያደረጉ ይቀጥሉ የሚል እንደምታ ያለው ይህ ንግግራቸው ምን አይነት ሰው እንደሆኑ የሚያሳይ ነው:: ወያኔወች በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ጭፍጨፋና ዘረፋ በአለም አደባባይ ለመናገር ድፍረቱ የሌላቸው እኒህ ሰውየ በሚደርስበት ዘርፈ ብዙ ግፍ እየጮኸ ያለውን ህዝብና ተቆርቋሪወቹን ለማፈን የሚያደርጉት ድርጊት ሀገሬንና ህዝቤን እወዳለሁ ከሚል ጤነኛ ሰው የሚጠበቅ አይደለም:: በወያኔ ግፍ እየተፈጸመብኝ ነው የሚለው ህዝብ ለምን ድምጹን አጥፍቶ መከራውን አልተቀበለም: የሕዝብን ጩኸት እያስተጋቡ ያሉት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና አለም አቀፍ ድርጅቶችም ለምን አይተው እንዳላዩ ሰምተው እንዳልሰሙ አልሆኑም በሚል መልኩ ሲወቅሱ ሰምተናል:: ድመት ወተት ሰርቃ ስትጠጣ አይኗን የምትጨፍነው እንዳትታይ ነው እንደሚባለው ሁሉ የወያኔው መልእክተኛ ኃ/ማሪያምም ጌቶቻቸውና ድርጅታቸው የሚፈጽሙትን በደልና ዘረፋ የአለም መንግስታት የማያውቁት መስሏቸው የህዝብ አመጽ የሚቀሰቅሱትና ዘረኝነትን የሚሰብኩት የሀገሮችን ሰላምና እድገት የማይፈልጉ ሀይሎች እንደሆኑ አርገው በማቅረብ ለጌቶቻቸው ሲከላከሉ ለወያኔ ያላቸውን ታማኝነት አስጠብቀው ጥቅማቸውን ለማስከበር አይናቸውን ጨፍነው ሲዋሹ ሰምተናል:: እውነት ህዝብ ማንም እንደፈለገ የሚነዳው በሆነ ባልሆነው ቅስቀሳ ለአመጽ የሚነሳ ነው? ቢያንስ አለ ብለው ያመኑትበመንግስት ባለስልጣናት የሚፈጸም የተቀናጀ ሙስና ሕዝብን ሊያሳምጽ አይችልም? ሌላው ቢቀር ጣራ የነካው የኑሮ ውድነት መንግስት ከስልጣን እንዲለቅ የሚያስጠይቅ ምክንያት አይሆንም? ቀደም ሲል የኢህአዴግ ባለስልጣን የነበሩ ሰዎች አልፎ አልፎ ብቅ እያሉ መንግስትን እየነቀፉ ሲናገሩ እየሰማን ነው:: እንደ ገብሩ አስራት: ታምራት ላይኔና ጁኔዲን ሳዶ ያሉት የቀድሞ ባለስልጣኖች ከኢህአዴግ ተወንጅለው ከተባረሩ በኋላ መንግስት እየተከተለ ያለው አካሄድ የተበላሸ ነው ብለው አውግዘው ለህዝብ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ እንዲሰጥ እየጠየቁ የመፍትሀ አቅጣጫ እየጠቆሙ ነው:: እኒህ ሰዎች ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ የተሰጣቸውን ተልእኮ ከመፈጸም ውጪ ሳት ብሏቸው ህዝብ እየተበደለ ነው ብለው መንግስትን ሲሞግቱ የተደመጡበት ጊዜ አልነበረም:: ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያምም እውነቱን እንዲናገሩ ከኢህአዴግ እስኪባረሩ መጠበቅ ይኖርብናል:: ሟቹ ጠ/ሚኒስትር እንዳሉት የኢህአዴግ ስልጣን ልክ እንደዛፍ ላይ እንቅልፍ ነው:: ከአንቀላፉ የጨበጡትን ይለቁና መውደቅ ይከተላል:: ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማሪያም ላያዘልቁት የወያኔ ባለስልጣናትን በሙስና ሲከሱ ከዛፍ ላይ ተኝተው የጨበጡትን ግንድ መልቀቅ መሆኑን የተረዱት አይመስልም::አንድ ቀን ስምና መልክ ተሰጥቶወት ይወረወሩና ከበታችወ ተኮልኩለው የርስዎን ስልጣን ከሚቋምጡት ሰዎች አንዱ በወንበሩ ተተክቶ እርስዎ ይሉ የነበሩትን ሲል: ሲያደርጉ የነበሩትን ሲያደርግ ያኔ በሀገር ውስጥም ይሁን በስደት ላይ ሆነው መንግስትን እያወገዙ ከወያኔ ጋር የቆዩባቸውን ጊዚያት እየረገሙ እውነቱን ይነግሩናል::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

ነጻነት ምድን ነው ? የነጻነት ዋጋው ስንት ነው? – ልዑለቃል አካሉ ዓለሙ (መጋቤ ሐዲስ)

$
0
0

ለሰው ልጅ ከነጻነት የበለጠ ትልቅ ነገር ስለሌለው የተፈጥሮ ሀብቱም ስለ ሆነ በቀላሉ ነጻነቱን አሳልፎ አይሰጥም ፤ ነጻነት በተፈጥሮ የተሰጠው የሰው ሕይወት እና የማንነት ክብር ስለ ሆነ ሰው ነጻነቱን ከሚያጣ የሕይወት ዋጋ መክፈልን ይመርጣል ፤ Patrick Henry “give me liberty or give me death” ix ያለው ለዚህ ነበር። በሕወሀት እጅ የወደቀው የኢትዮጵያ መንግሥትም ነጻነት እንፈልጋለን ያሉትን ዜጎቹን በመግደል ፥ በማፈን ፥ ቶርች በማድረግ ፥ ሞትን እንጂ ነጻነትን አልሰጣችሁም ሲላቸው የምንሰማው ፥ የምናየው ለዚህ ነው ። ነጻነት የሰብአዊ ማንነት መሠረት ሲሆን ፣ የነጻነት መወሰድ ደግሞ ሰብአዊ ክብርን ማጣት ስለ ሆነ ሰው ሁኖ በነጻነቱ ላይ የሚደራደር የለም።

hqdefault-2
(ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር )
ነጻነት ፣ እኩልነት ፣ አንድነት ፣ ጠባብነት ፣ ትምክህተኛነት ፣ ኢትዮጵያዊነት የተሰኙት ቃላት በዚህ ወቅት ከምንም በላይ የሚነሡ የወቅቱ አሳብ ገላጭ ቁልፍ ቃልት ሁነው ታይተውኛል ። ለመሆኑ እነዚህን ቃላት የሚጠቀሙ ሰዎች ሁሉ እነዚህን ቃላት በእውነተኛ ትርጕማቸው ተረድተው ፣ በተገቢው ቦታ ቃላቱ የሚወክሉትን መሠረተ ሐሳብ ለመግለጽ ነውን የሚጠቀሙባቸው ? ወይስ ሲባል ሰምተው ነው የሚያስተጋቡአቸው ? እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ ። ይልቁንም Sep 20/16 የተላለፈው የESAT ራድዮ ሳዳምጥ ልብ የሚነካ ፣ ነጻነት የሌላቸውን ወገኖቼን ጩኸት የሚያስተጋባ ፣ በእንባ የታጀበ ፣ ልብ የሚሰብር ቃለ መጠየቅ ሰማሁ ። ይህ ሰው በሕወሀት ወታደሮች ታፍኖ ከብዙ ልጆች ጋር 9-10 ሰዓታት በመኪና ተጓጉዞ ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ ለቍጥር የሚያታክቱ ወጣቶች በሞትና በሕይወት መካካል ወዳሉበት የሥቃይ ቦታ መወሰዱን ይናገራል ። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ያለፍትሕ የታሰሩት ወንድሞቻችን ድንጋይ ሲፈልጡ ውለው የሚመገቡት እንደ ሌላቸው ፣ ብዙዎቹ በድብደባ ብዛት ራሳቸውን የሳቱ እንደ ሆኑ ይመሰክራል ። ቢሞቱ እንኳ ቀባሪ እንደ ሌላቸው ከሲቃ ጋራ ይናገራል። እርሱንም አንድ የሚያውቀው ወታደር በሌሊት አሾልኮ በመኪና ሸኝቶ እንዲያመልጥ እንደ ረዳው ሲናገር አደመጥኩ ፤ የሚናገርበት ድምጽ ነጻነት የሌለው ዜጋ ፣ የተጠቃ ትውልድ ድምጽ ምን እንደሚመስል በግልጽ ያሳያል ። ከአሁን አሁን ገድለው ቱቦ ውስጥ ሊጥሉት እንደሚችሉ እንደሚያስብ ይናገራል ፤ ምሥጢር አወጣህ ተብሎ የሚመጣበትን መከራ ቢያውቅም ስለ ወንድሞቹ መናገርን መምረጡን ይገልጻል ።
ስለታሰሩት ወጣቶች ሥቃይ ሲናገር – በወታደር ተከበው ፣ ራሳቸውን ተላጭተው ፣ ሙሉ ቀን ድንጋይ ሲፈልጡ ይውላሉ፣ ልጆቹ ያሉት ቤንሻንጉል ጉምዝ ጫካ ውስጥ ነው ፣ ውጡና ሂዱ እንኳ ቢሉአቸው ወጥተው መሄድ ከማይችሉበት ጫካ ውስጥ ነው የተጣሉት ፤ በሽታና ረኃብ እየፈጃቸው ነው ። ብዙዎቹ በድብደባ አእምሮቸውን ስተዋል ፣ አይሰሙም አይለሙም ፤ ቢሞቱም ቀባሪ የላቸውም ፤ ጉንዳን ነው የሚበላቸው ፤ ልጆቹ ከጎንደር ፥ ከባሕርዳር ፥ ከጭልጋ የመጡ ናቸው ፤ እነዚህ ወጣቶች በረኃብ ሊሞቱ ይችላሉ ፣ ምን ብየ ለማን እንደማወራ ፣ ምን ብየ እንደምናገር አላውቅም ። ሁኔታው ከባድ ነው» እያለ ስሰማው ለሰው ልጅ ነጻነቱን ከሚነጥቀው የበለጠ ባላጋራ እንደሌለው ተሰማኝ ። አንባቢዎች ይህን ነጻነት ያጣች ነፍስ ልቅሶና ጩኸት መስማት ትችላላችሁ? ። i

ብዙ አዘንኩ ወደ እግዚአብሔርም ስለ ተጠቁት ጸለይኩ ፤ ይህ ሁኔታ ብዙ እንዳስብ ምክንያት ሆነኝ ። እንዲህ እያልኩ ፦ ለመሆኑ ነጻነት ምንድ ነው ? የነጻነትስ ዋጋው ስንት ነው ? እኩልነትስ ማለት ምን ማለት ነው ? አንድነት ማለት ምን ማለት ነው ? አንድነትስ የሚጠቅመው ማንን ነው ? በሀገር አንድነትና ሉዓላዊነት የሚያምኑ ዜጎችስ ስለ አንድነት መክፈል ያለባቸው ዋጋ ምን ያህል ነው ? ጠባብነት ምንድን ነው ? ጠባብስ ማን ነው ? ትምክህት ማለት ምን ማለት ነው ? ትምክተኛስ ማነው ? ኢትዮጵያዊነት የሠለጠነበት ሕሊና ባለቤት መሆን ትምክት ነውን ? ከሆነስ ጉዳት አለውን ? የሚሉትን ጥያቄዎች አእምሮየ ሲያወጣ ሲያወርድ ከቆየ በኋላ አሳቤን ለአንብያን ለማካፈል ስወስን መጀመሪያ ስለ ነጻነት ልጽፍ ወሰንኩ ፤ ዛሬ ነጻነት ምንድን ነው ? ነጻነትስ የሚያስከፍለው ዋጋ ስንት ነው ? የሚሉትን ነጥቦች በአጭሩ እናያለን ።
ነጻነት ምድን ነው?
1) ነጻነት ማለት ለማንኛውም ሰው በተፈጥሮ የተሰጠውን ሕይወት ያለግዳጅ የመኖር ፣ በተፈጥሮ በተሰጠው አእምሮ የማሰብ ፣ ያሰበውን የመናገር ፣ የመጻፍ ፣ ላመነበት ነገር የመሰብሰብ ፣ በነጻነት የማምለክ ፣ ይጠቅመኛል ያለውን የማድረግ ፣ አይጠቅመኝም ያለውን የመተው መብት ነው ። ለመንግሥት ይህንን የዜጎችን ነጻነት ማክበር የመጀመሪያ ተግባር መሆን ነበረበት ። ሰውን ፈጥሮ የሚገዛ አምላክ ይህንን የሰውን የነጻነት መብት ተጋፍቶ አያውቅም ። በአደጉት አገሮች የነጻነት መብት ትርጉም ሰፍቶ የሰው ልጅ የዕለት ምግብ ፣ መጠለያና ልብስ እንዲሁም ሕክምና የማግኘት መብት አለው ።
በሀገራችን ነጻነት የለም ስንል ከላይ የተዘረዘሩት የሰው ልጅ የተፈጥሮ መብቶች በመሣሪያ ኃይል በሚገዛው የሕወሓት መንግሥት ከሕዝቡ ላይ ተወስደዋል ማለታችን ነው ። ሕዝብን እና ሕወሓትን ሆድና ጀርባ ያደረጋቸው ፥ ይህ የተፈጥሮ የነጻነት ሕግ በጉልበት ስለ ተደመሰሰ ነው ። ነጻነት ቅንጦት አይደለም ፣ ነጻነት ህልውና ነው ። ነጻነት ሰው መሆን ሲሆን ፥ነጻነትን መግፈፍ ሰውን ከሰውነት ውጭ ማድረግ ነው ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምን እንደሚያስብ መንግሥት የማወቅ ችሎታ ስለሌለው እንጂ ቢችል ኑሮ ሕዝቡን በሰልፍ አቁሞ ለምን እንዲህ ታስባላችሁ እያለ በጥይት ከመደብደብ ወደ ኋላ የሚል አይመስለኝም ።
ይህም የሚታወቀው ያሰቡትን ደፍረው የተናገሩ የጎንደር ፥ የጎጃም ፥ የኦሮሞ ወጣቶችን በጥይት እይመታ የጣላቸው ፣ በዱላ ሰባብሮ ፥ ጠጉራቸው ላጭቶ ፥ ድንጋይ እያስፈለጠ በረኃብ እየቀጣ ፣ በርሃ ጥሏቸዋል ። የወልቃይትን

የጠገዴን አማሮች የሀውና ያለማቋረጥ ለ25 ዓመታት ይጨፈጭፉቸዋል፤ ንብረታቸውንና ቤታቸው ያቃጥልባቸዋል ፣ ያመለጡትን ያሳድዳል ፣ የያዛቸውን ሌትና ቀን ያሰቃያቸዋል ። ነጻነት ማጣት በተግባር ይህን ሲመስል ፣ የሰው ልጅ ለነጻነት ያለውን ፍላጎት ብርታት የሚያሳየን ይህን ሁሉ ተቋቁሞ ከታጠቁ እና ከሠለጠኑ የሕወሀት ወታደሮች ጋር ገበሬው ሕዝባቸን በሚከፍለው የሕይወት ዋጋ በገሀድ ይታያል ።
2) ነጻነት የሚለውን ቃል የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ምን ብሎ እንደ ፈታው ለማየት ስመለከት ነጻነትን በመተርጎም ፈንታ «ባርነት» የሚለውን ይመልከቱ ብሎ አልፎት አየሁ ። ii በዚህ ጊዜ የነጻነት ትርጉም የበለጠ ተገለጠ ፤ ነጻነት የባርነት ተቃራኒ ነው ፤ ባርነት በራስ ሕይወት አለማዘዝ ፥ በራስ ፈቃድ አለመኖር ፥ የሌላ መጠቀሚያ እቃ መሆን ነው ። ነጸነት ደግሞ ከዚህ ሁሉ ነጻ ሁኖ መኖር ነው ። ሕዝባችን ነጻነት ከሌለው እንደ ክላሽ እንደ መትረጌስ ማንም የሚያጮኸው ፣ እንደ መኪና ማንም የሚዘውረውና ወደ ፈቀደው የሚያሽከረክረው ይሆናል ። በእኔ ግንዛቤ ሕወሀት ከሕዝቡ ጋር የተጣላው ይህን በማድረጉ ነው እንጂ ከትግራይ በመፍለቁ አይደለም ። የትግራይንም ሕዝብ በክፉ እያስነሡት ያሉ የሕወሀትን ክፉ ተግባርና የሕወሐትን አገር ገዳይ መመሪያ እየተቀበሉ የሕዝብን ንብረት የሚያቃጥሉ ፣ ሕዝብን በሀገሩ ላይ አላኖር ያሉ የትግሬን ሕዝብ የማይወክሉ ትግሬዎች ናቸው ። በዚህ ወቅት የኢትዮጵያን ሕዝብ ደስታና ኀዘን አብረው ለዘመናት ሲካፈሉ የኖሩ ንጹሐን ትግሬዎች ይህንን በአገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጸም በደል ዝም ብለው ማየታቸው ገዳዩን ሥርዓት እንደ ተባበሩ ያሳይባቸዋል የሚሉ በዝተዋል ። «በጎን ነገር አውቆ ለማይሠራው በደል ይሆንበታል» እንደ ሚለው የመጽሐፍ ቃል መሆኑ ነው። iii
3) አንድ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ስለ ነጻነት እንዲህ ይላል «ለሰው ልጅ ነፍስ ፣ ሳትገደድ ፥ ሳይፈረድባት ፥ የወደደችውን ታደርግ ዘንድ ነጻነት ተሰጣት (በተፈጥሮ ማለት ነው) መልካምነቷም ሆነ ክፉነቷ በራሷ ፈቃድ የተከናወነ ይሆን ዘንድ» ይላል ። iv «Freedom is the power or right to act, speak, or think as one wants without hindrance or restraint, and the absence of a despotic government» v የሚለው የእንግሊዝኛ ፍች በግእዝ “ወገብረ ላቲ ሥልጣነ በውስቴታ ትግበር በከመ ኃርየት ፣ እንዘ አልቦ ዘይኬንና ፥ ወዘይሄይላ ፥ ከመ ይኩን ሠናያቲሃ ወእከያቲሃ በሥምረተ ሕሊናሃ በአምሳለ መላእክት” ። (መቅድመ ወንጌል) ከሚለው የግእዝ ጥቅስ (ከላይ በአማርኛ የተረጎመው ማለት ነው) ጋር ምንም አይነት የሐሳብ ልዩነት የለውም ። vi ይህን የነጻነት መርህ መጋፋት ከሰውም ከእግዚአብሔርም ጋራ ያጣላል ። አሁን በአገራችን እየሆነ ያለውም ያ ነው ። ነጻነትን ለሰው ልጅ መንግሥትም ሆነ የሃይማኖት ተቋማት አልሰጡትም ። ሰው የተፈጠረው በነጻነት፣ ለነጸነት፣ ነጻ

ሁኖ ነው የተፈጠረው ። ሰው ከሰው ጋር በስምነት ሁሉን ነገር ማድረግ ይችል፤ የሰውን ነጻ ፈቃድ በመጠቀም ሰውን የገዥ መዶቦችም ሆኑ የእውቀት ሰዎች ፣ የወደዱትን እንዲወድ ፥ የጠሉትን እንዲጠላ ሊያደርጉት ይችላሉ ፤ ያ ማለት ግን ነጻነቱን አጣ ማለት አይደለም ። ነጻ ፈቃዱንና ነጻ አስተሳሰቡን በአስተሳሰብ ፣ በትምህርት ማርከው ፣ ግለሰቡ አምኖበት እስካደረገው ድረስ በፈቃዱ አደረገው ሊባል ይችላል ። ነገር ግን ሳይፈልግ ፥ ሳይፈቅድ ፥ ሳያምንበት ፥ እያስፈራሩ ፣ ቅድመ ሁኔታ እያስቀመጡ ፣ ይህን ካላደርክህ እንዲህ ትሆናለህ ፣ ይህን ካደረግህም እንዲህ ትደረጋለህ እያሉ ፣ ያለፈቃዱ አስገድደው ከያዙት ግን ነጻነነቱን አጣ ማለት ነው ። እግዚአብሔር እንኳ የፈጠረውን ሰው በፈቃዱ እንዲያመልከው እንጂ ተገዶ እንዲያመልከው አላደረገም ። ያ ቢሆን ኑሮ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የሆነውን ነገር ባላደረጉም ነበር ። vii ሰው ሁልጊዜ በጎውን ከክፉው ነገር ለይቶ እዲመርጥ ይመክራል እንጂ በግዳጅ የሚጠቅመውንም ሆነ የሚጎዳውን ነገር እንዳያደርግ መገደድ የለበትም ። የሰውልጅ ለደረገው በጎ ነገር «መልካም አደረግህ » ለሰራው ክፉ ነገር ደግሞ «እንዴት ይህን ታደርጋለህ» የሚል የህሊና ሕግ ተሰጥቶታልና።viii
የነጻነትስ ዋጋው ስንት ነው?
ለሰው ልጅ ከነጻነት የበለጠ ትልቅ ነገር ስለሌለው የተፈጥሮ ሀብቱም ስለ ሆነ በቀላሉ ነጻነቱን አሳልፎ አይሰጥም ፤ ነጻነት በተፈጥሮ የተሰጠው የሰው ሕይወት እና የማንነት ክብር ስለ ሆነ ሰው ነጻነቱን ከሚያጣ የሕይወት ዋጋ መክፈልን ይመርጣል ፤ Patrick Henry “give me liberty or give me death” ix ያለው ለዚህ ነበር። በሕወሀት እጅ የወደቀው የኢትዮጵያ መንግሥትም ነጻነት እንፈልጋለን ያሉትን ዜጎቹን በመግደል ፥ በማፈን ፥ ቶርች በማድረግ ፥ ሞትን እንጂ ነጻነትን አልሰጣችሁም ሲላቸው የምንሰማው ፥ የምናየው ለዚህ ነው ። ነጻነት የሰብአዊ ማንነት መሠረት ሲሆን ፣ የነጻነት መወሰድ ደግሞ ሰብአዊ ክብርን ማጣት ስለ ሆነ ሰው ሁኖ በነጻነቱ ላይ የሚደራደር የለም ።
በመሆኑም ስለ ነጻነት በምንነጋገርበት በዚህ ጊዜ – ለምን የነጻነት ጥያቄ ጠየቃችሁ ብሎ አፋኙ የሕወሓት ሥርዓት የጎንደርን የገበያ ማዕከላት በካድሬዎቹ በኩል በእሳት እያቃጠለ ፣ ኮንሶዎቹን በምድራቸው ላይ እየገደለ ፤ ኦሮሞዎችን አፍኖ እየገረፈ ፣ የወልቃይትን ባላባቶች ዝክረ ስም ለማጥፋት እየሰራ ፣ ምድራቸው የእኔ ነው ብሎ በመቀማት ይህ ነው የማይባል ጥቃት እየፈጸመ ፣ በሽዎች የሚቈጠሩ አገር ተረካቢ ወጣቶችን እየገደለ ፣ በእስር ቤት

እያሰቃየ ባለበት ወቅትነው ። ስለ ነጻነት ዋጋ የምንነጋገረው ፥ ስለ ነጻነት በምጽፍበት በዚህ ሰዓት በጎንደር ከተማ የቅዳሜን ገባያ ያቃጠሉት ትግርኛ ተናጋሪ ሰዎች የቀሩትን የከታማይቱን ተቅዋማት ለማቃጠል ጥረት ሲያደርጉ በሕዝብ ተይዘው ዛሬ መስከረም 11 ቀንም 2009 ዓ/ም በመገናኛ ብዙኃን ይነገር ነበር x። ነጻነቴ መብቴ ይከበር ያለ ሕዝብ ከተማው በገዡ ፓርቲ ድጋፍ በተሰጣቸው ትግሬዎች ለ50 ለ60 ዓመታት የደከመበት ሀብቱ ንብረቱ እየተቃጠለ ነው ። ሕዝብ ነጻነትን ሀብት ለማድረግ እየተዋደቀ ነው ። ልጆቹ ለእስራትና ለሞት ፣ ሀብቱና ንብረቱ ለእሳት እየተሰጠ ዛሬም ሕዝባችን አስገድደህ ልትገዛኝ አትችልም በማለት ከገዳዩ ሥርዓት ጋር ለነጻነቱ እየተዋደቀ ነው ።ከዚህ አንጻር የነጻነት ዋጋ እጂግ የከበረ ነው ።
በጎንደር እና በጎጃም – ሕዝብ ዕለት ዕለት እየታፈነ ነው ። በጎንደር በአምባ ጊዮርጊስ በእብናት በበለሳ ብዙዎች ነጻነታቸውን ለመንጠቅ ከሚታገላቸው ገዳይ ኃይል ጋር እየተዋደቁ ነው ። ከዚህ አንጻር ስናየው የነጻነት ዋጋ እጅግ ውድ ነው ። ነጻነት የሕይወት መሠረት ስለ ሆነ የነጻነት ዋጋ ደም ነው ። ነጻት የሕይወት ትርጉም ስለ ሆነ ነጻነት የሚጠበቀው የሕይወት ዋጋ እየተከፈለ ነው ። ክርስቶስ የሰው ልጆችን መንፈሳዊ ነጻነት ያስገኘውም ሕይወቱን ስለ ተጠቁት አሳልፎ እከመስጠት ደርሶ የነጻነት ባላጋራ የሆነውን ስውር ኃይል ድል በመንሣት ነበር ። ስለዚህ የነጻነት ዋጋ የከበረ ዋጋ ነው ።
የጎጥ ፖለቲከኞች ያንሸዋረሩት የነጻነት ትርጉም ፦
የነጻነትን ትጉም የሚያንሸዋርሩ አንዳንድ ጠባብ የፖለቲካ አቀንቃኞች እንደሚሉት ነጻነት ማለት አንድ ክፍለ ሀገርን ወይም ክልልን ከእናት ሀገር መገንጠል ማለት አይደለም ። ከእናት ሀገር መገንጠል ነጻነትንና ብልጽግናን የሚያመጣ ቢሆን ኑሮ ዛሬ ኤርትራ ባለፈላት ነበር ። ነጻነት ማለት አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ለይቶ ወደ ሥልጣን ማውጣት ሌላውን ማግለል አይደለም ። ያ ቢሆን ኑሮ ሕወሀት የሰላም እንቅልፍ በተኛ ነበር ።በአንድ ቋንቋ መናገር የነጻነት ምንጭ አይደለም ። ያ ቢሆን ሕወሀት የትግራይን ሕዝብ እየገደለ ፣ ብአዴን የአማራ ወጣቶችን እያፈነ ፣ ኦሕዴድ የኦሮሞ ወጣቶችን እያሰቃየ ፣ አይስስ በቋንቋው የሚናገሩትን እስላሞችና ክርስቲያኖችን እያረደ ባልተገኘም ነበር ። ነገር ግን ነጻነት ማለት እያንዳንዱ ሰው በተፈጥሮ የተሰጠው መብቱና ነጻነቱ ተጠብቆለት ፣ ሰው በሰውነቱ ብቻ ተከብሮ ከሌላው ጋር በፍቅርና በአንድነት ለመኖር ሲችል ነው ። ነጻነትን የሚገፍ መንግሥት ብቻ አይደለም ፣ አባወራ የሚስቱን የልጆቹን ነጻነት ይገፋል ፣ ሴት ልጅም የባሏን እና የልጆቿን መብት ታስነጥቃለች ፤ ነጻነት በሥጋና

በደም በተሳሰሩ ኅብረተ ሰቦች መካካልም ይደመሰሳል ። አንድ ሕዝብ ነጻነት አለው ወይም ነጻ ሕዝብ ነው የሚባለው የሁሉም ዜጎች ግላዊ ነጻነት ተከብሮ ፣ በነጻነት በእኩልነት በአንድነት በነጻነት የሚኖርባት ነጻ ሀገር ስትኖረው ነው ።
ማጠቃለያ
የዜጎችን ነጻነት አለማክበር ማለት?
 የሰውን ሰውነት አለመቀበል ማለት ነው ፤
 ሰውን ከእንስሳትና ከግዑዛን ጋራ ማስተካከል ነው ፣
 የራስን ክብር (የነጻነት ተጋፊውን ክብርም) ማሳነስ የተፈጥሮን ሕግ መሻር ነው ።
 እናንተ ለእኛ መጠቀሚያ እንጂ የተፈጠራችሁት አንዳችን ለአንዳችን በረከት ሁነን አልተፈጠርንም ፣ እኔ የማስፈልጋችሁን ያክል እናንተ አታስፈልጉኝም ብሎ ማሰብ ነው ፣
 እኔ ላንተ አውቅልሃለሁ ፣ ራስህ ስለ ራስህ እንድታውቅ ሁነህ አልተፈጠርክም ብሎ የሰውን ተፈጥሮ ከመስደብ ይቆጠራል ።
 ዜጎችን መናቅ ማዋረድ የተገኙበትን ኅብረ ተሰብ ክብር ዝቅ ማድረግ፣ የሀገርን ክብርና ታሪክም ማዋረድ ነው ።
በአንጻሩ አንድ ዜጋ ነጻነቱ ሲከበር፦
1. ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ይሆናል ፤ ምክንያቱም ነጻነቱን የሚጠቀም ሰው በነጻነት በወሰነው ውሳኔ ምክንያት ስለሚደርስበት ጥፋት እራሱን ያስተካክላል እንጂ በሌላው ላይ እጁን አያነሣም ። በነጻነት ወዶ ፈቅዶ ለሠራው ነገር ሌላውን እንዲከስ ሕሊናው አይፈቅድለትም ።
2. ልበ ሙሉ ነው ፥ ለእድገትና ለሥልጣኔ ይራመዳል ፤ 3. ሌላውን አይከስም ፣ በአንጻሩ ስለ ሌሎች ያስባል ፤
7
4. ነጻነት የሌለው ሕዝብ ግን ስለ ሌሎች ለማሰብ አይችልም ። አገራችን ኢትዮጵያ ለሌሎች ነጻነት ምሳሌ ሁና የኖረቸው ከቀኝ ገዝዎች ነጻ ሀገር ነጻ መንግሥት ነጻ ሕዝብ ስለ ነበራት ነው ።
ስለዚህ የነጻነት ዋጋ ውድ መሆኑን በማወቅ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት በመሰለፍ ፍትሕ ርትዕ የሰፈነባት ፥ የግለሰቦች መብትና ነጻነት የሚከበርባት ፥ አንድነቷ የተጠበቀ አገር እንድትሆን መሥራት ይጠበቅበታል ።
ይቆየን ።
ልዑለቃል አካሉ ዓለሙ (መጋቤ ሐዲስ) mhleulekal@gmail.com

አቶ ኤልያስ ሽኩር (እነሞርና ኤነር) ማን ነው?

$
0
0

በሥዩም ወርቅነህ

elias-shkur
2002 ዓ/ም – የጉራጌ ዞን ሲቨል ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ
2003 ዓ/ም – የድርጅት ኃላፊ
2004 ዓ/ም – 2007 ዓ/ም የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ
2008 ዓ/ም – እስካሁን የደቡብ ክልል ደኢህዴን የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
ይህ ግለሰብ በስልጣን በቆየባቸውና አሁንም በጉራጌ ዞን የፈፀማቸው ወንጀሎች ብዙ ቢሆንም ለአብነት ያህል ጥቂቶቹን ልዘርዝር፦
1. በወልቂጤ ኬላ ለዞኑ ከሚገባው ገቢ ለሙስና በዘረጋው መረብ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፈ፣
2. የወልቂጤ ማካለል ስራ ዳር እንዳይደር ቀቤና ከሌላው የጉራጌ ማህበረሰን ሲያጋጭ የኖረ። አሁን ክልል ከሄደም በኋላ ይህ መሰሪ የወያኔ የተልኮ ስራው ገፍቶበታል፣
3. ለሙስና እንዲያመቸው ከወልቂጤ ከንቲባ ጀምሮ ሌሎችም የዞኑ አመራሮች የአካባቢው ተወላጆችን የሰገሰገ፣
4. የወልቂጤ ኮንዶሚንየም ቤቶች ሲሰሩ ኮንትራት ከተሰጣቸው ማህበራት ጀምሮ ከሌሎችም ሙስና በመቀበል የራሱ ጥቅም በማከበት ጥራት የሌላቸው ፎቆች እንዲሰሩ ያደረገ።
5. ህገ-ወጥ ቤቶችን ሲሸጥ የራሱን ኃብት ሲያካብት የኖረ፣
6. በአሁን ወቅት ከተጠያቂነት ለማምለጥ በጉራጌ ህዝብ በተለይ በወጣቱ እይቀለደ ያለ፣
7…..
ሌሎችም
አቶ ኤልያስ ሽኩር በጉራጌ ማህበረሰብ ይህን ሁሉ በደል ቢፈፅምም ህዝብን በማጋጨትና በሙስና የተሳሰረው የወያኔ ስርዓት በህግ ተጠያቂ ማድረግ ሲገባው እድገት ሰጥቶት ወደ ክልል ኃላፊነት አሳድጎታል።
አቶ ኤልያስ በወያኔ ብብት እስከመቼም ተሸሽጎ ስለማይኖር ይህን ስርዓት ስናስወግድ ለፍርድ እናቀርበዋለን። ስርዓቱም ይወገዳል፤ በጉራጌ ህዝብ ወንጀል የፈፀመው አቶ ኤልያስ ሽኩርም ለፍርድ ይቀርባል።
ትግሉ ይቀጥላል!

በባህር ዳር ከተማ ድባንቄ መድሃኒ አለም በመባል በሚታወቀው የቀብር ቦታ ሌሊት ሌሊት ያልታወቁ ሰዎች እንደሚቀበሩ የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ተናገሩ፡፡

$
0
0

መስከረም ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃይማኖቱ አባቶች እንደሚሉት በየቀኑ ከሶስት እስከ አምስት የሚደርሱ አስክሬኖችን የመንግስት ወታደሮች ማንም በማያይበት ሰዓት አምጥተው የቀብራሉ፡፡
አባቶቹ በሌሊት ማህሌት ለማድረስ በሚንቀሳቀሱበት ሰዓት ከባህር ዳሩ መኮድ የጦር ካምፕ አካባቢ በሚመጡ ፒክ አፕ መኪናዎች ተጭነው የሚመጡ አስክሬኖች እንደሚቀበሩ የሚገልጹት ምንጮች፣ ባህርዳርን ጨምሮ ከተለያዩ የአማራ ከተሞች በሰላማዊ ሰልፍ ተሳትፋችኋል በሚል የሚታፈሱት ወጣቶች አስከሬን ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ተናግረዋል፡፡
ወጣቶቹ በተለይ ቤንሻንጉል ጉሙዝ በሚገኝ ጫካ ውስጥና በብር ሸለቆ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ተሰቃይተው ሲደክሙ ባህር ዳር ወደ ሚገኘው የመኮድ ወታደራዊ ሆስፒታል አምጥተው ህክምና እንደሚያደርጉላቸውና ከአቅምበላይ የተደበደቡት ህይወታቸው በሚያልፍበት ጊዜ በባህር ዳር መድሃኔያለም ቤተ ክርስቲያን በድብቅ እንደሚቀበሩ ጉዳዩን በቅርብ የሚያዉቁ ሰዎች ይናገራሉ።
bahir_dar_city_03

ሞጣ ቀራንዮ የመስቀል እለት ቀጠሮ ይዟል። የጎበዝ አለቆች ይህንን መልዕክት ልከዋል።

የሕዝባዊ አሻጥር ሥራዎች: ለመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን

$
0
0

በታደሰ ብሩ

Tadesse Biru
በ2009 የትምህርት ዓመት በመለስተኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ የሕዝባዊ አሻጥር ዓይነቶች
1. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ስለሰብዓዊ መብቶች ሉዓላዊነት እና ስለ ሰለሰው ልጆች ክብር አስተምሩ፤ በተግባርም አሳዩ። የትምህርቱ መርሀግብር (curriculum) አይፈቅድልኝም የሚለውን ሰበብ አስወግዱ። ራሱ “ትውልድን ገዳይ“ የሆነው ካርኩለም ላይ ነው አሻጥር መሥራት ያለባችሁ።
2. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ተማሪዎች እውነትን ራሳቸው እንዲሹ፣ ብዙ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣ እንዲመራመሩ፣ እንዲሞግቱ አበረቷቷቸው። የትምህርት ቤቱ ህግ ባይፈቅድም ተማሪዎች የተሰማቸውን በነፃነት እንዲናገሩ፣ እንዲጽፉ፣ እንዲዘምሩ ፍቀዱላቸው።
3. ተማሪዎች “እኔ ማነኝ?” “ማንን መምሰል እፈልጋለሁ?” “ምን ማድረግ እችላለሁ?” ብለው እንዲጠይቁና ራሳቸው ፈልገው እንዲያገኙ፤ እያንዳንዳቸው Potentially ዓለምን መቀየር የሚችሉ ሰዎች መሆናቸውን እንዲረዱ አበረቷቷቸው።
4. የምታስተምሩት የትምህርት ዓይነት ምንም ይሁን ምን ተማሪዎች ከግላቸው አልፈው ስለማኅበረሰብ እንዲያስቡ “ይህች አገር የማናት?” “ማን ጠግቦ፤ ማነው የሚራብባት?” “ማን ዘፍኖ ማነው የሚያለቅስባት?” “መጪው 20, 30, 50 ምን ሆኖ ማየት እንፈልጋለን?” “የምንፈልገው እንዲመጣ አሁን ምን ማድረግ እንችላለን?” ብለው እንዲጠይቁ አበረቷቷቸው።
5. በትምህርት ወቅት የምትሰጧቸው ምሳሌዎች ሁሉ አገራዊና ወቅታዊ ይሁኑ። ለምሳሌ በሂሳብ ክፍለ ጊዜ የ EBC “ልማታዊ ዜና” ውሸትነት በቀላል ሂሳብ ማረጋገጥ በመልመጃነት ይቅረብ (ለዚህ የሚሆን ማስረጃ በገፍ ነው ያለው)።
6. ምሳሌዎቻችሁና ቀልዶቻችሁ የህወሓት አገዛዝ ብልሹነት ቢቻል በቀጥታ ካልሆነም በተዘዋዋሪ የሚገልጹ እንዲሆኑ አድርጉ።
7. በፓሊስ፣ በፍርድ ቤት፣ በወታደር፣ በደህነት (ጆሮ ጠቢዎች)፣ በምርጫ ቦርድ፣ በእምባጠባቂ፣ በ EBC፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን፣ በ EFFORT … ወዘተ ቀልዱ። በእነዚህ ተቋማት ላይ እንዲቀለድ አበረታቱ።
8. በዘር፣ በፆታ፣ በሀይማኖት መተራረብና መከፋፈል ጊዜ ያለፈበት አስተሳሰብ እንደሆነ አስተምሩ። ጊዜው ባለፈበት አስተሳሰብ የሚመሩት የኢህአዴግ ካድሬዎች መሆናቸው አስረዱ።
9. ኢህአዴግን ከወቅቱ ጋር መቀየር ባለመቻሉ ከጠፋው ዳይኖሰር ጋር አመሳስሉት፤ በ 2009 የትምህርት ዘመን ዳይኖሰሩ ይጠፋል ብላችሁ አስተምሩ።
10. የትምህርት ቤቱ አፋኝ ደንቦችን በእናንተ ክፍል ውስጥ ተግባራዊ አይሁኑ። በአገሪቱ ያሉ አፋኝ ህጎችም በእናንተ ክፍል ውስጥ ይጣሱ።
11. ለአካዳሚ ነፃነት፣ ለተሻሻለ የትምህርት ሥርዓት፣ ለመምህራን መብት፤ ለተሻለ ክፍያና የደረጃ እድገት እድሎች ታገሉ። በወያኔ የተጠለፈውን የመምህራን ማኅበርን አውግዙ፤ የራሳችሁን ነፃ ክበባት ፍጠሩ።
12. ከለውጥ ፈላጊ ተማሪዎች ጋር አብሩ፤ በሃሳብ፣ በቁሳቁስ፣ በተግባር እርዷቸው። በትምህርት ቤቱ ውስጥ ፀረ ህወሓት/ኢህአዴግ ምስጢራዊ ድርጅት አቋቁሙ።
13. ተማሪዎች የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የነፃነት፤ የማኅበራዊ ወይም የፓለቲካ ጥያቄዎች ሲያነሱ ከጎናቸው ቁሙ።
14. የኅበረተሰቡን የነፃነት፣ የፍትና የእኩልነት ጥያቄዎች በመደገፍ ታገሉ፤ ለትግሉ የሙያ ድጋፍ ስጡ።
15. የአቃጣሪ ተማሪዎችና የካድሬ መምህራንን የሞባይልና የቤት ስልኮችን ለምስጥራዊ ድርጅታችሁ ስጡ።
16. በማኅበራዊ ሚዲያዎች (ፌስቡክ፣ ቱተር፣ ኢንስታግራም፣ ዩቱብ) የአቃጣሪ ተማሪዎች፣ የካድሬ አስተማሪዎችና ሠራተኞች ስብዕና የሚያንቋንሽሹ ጽሁፎችንና ምስሎችን አሰራጩ።
17. የነፃነት ታጋዮችን የሚያሲዙ ካድሬ መምህራንና ተማሪዎችን ተግባር ከትምህርት ቤታቸው አልፎ የሰፈራቸው ሰዎች እንዲያውቁ አድርጉ። እንዴት ክፉ ሰዎች እንደሆኑ ወንድሞቻቸው፣ እህቶቻቸው፣ ልጆቻቸው፣ ሚስቶቻቸው፣ ዘመዶቻቸውና ጎረቤቶቻቸው እንዲያውቁ አድርጉ።
18. የተለያዩ የተቃውሞ መግለጫ መንገዶችን በማስተዋወቅና ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ግምባር ቀንበር ሁኑ።
19. “ቀበሌና ፓሊስ ትምህርት ቤታችንን አይርገጥ” በሉ።
20. የትምህርት ቤቱን የተለያዩ ክበባት ተማሪዎችን ለትግል ማዘጋጃነት አውሉ። ሚኒ ሚዲያ፣ ድራማ፣ ስነጽሁፍ፣ ቅርፃ ቅርጽ፣ ስፓርት፣ ሙዚቃ፣ … የሂሳብና የፊዚክስ ክበባት ሁሉ ሳይቀሩ ተቃውሞ ማሳያዎችና አሻጥር መሥሪዎች ይሁኑ።
21. ተማሪዎች በግጥም፣ በልበወለድ ታሪኮች፣ በድራማዎች፣ በዘፈኖች፣ በስዕሎች … የተቃዉሞ መልክቶቻችሁን እንዲያስተላልፉ አስተባብሩ፤ እናንተም ተሳተፉ።
22. የስፓርት ሜዳዎች የትግል ሜዳዎች ይሁኑ። የስፓርት ሜዳ መዝሙሮች ፀረ-ህወሓት/ኢህአዴግ የትግል መዝሙሮች ይሁኑ። የስፓርት ክበባት የአሻጥር ጥናትና ሙከራ ማዕከላት ይደረጉ።
23. የነፃነት ታጋዮች የሚያትሟቸው ወረቀቾችን በትምህርት ቤት ውስጥ አሰራጩ።
24. የነፃነት ታጋዮችን ስም አወድሱ። በእስር ላይ የሚገኙ፤ በትግል ላይ የሚገኙ ብሄራዊ ጀግኖችን አወድሱ። በአንፃሩ፣ የኢህአዲግ ሹማምንትን አራክሱ።
25. በተገኘ አጋጣሚ ሁሉ ወረቀት፣ ኮምፒውተር፣ ማባዣ እና የመሳለሉትን ውሰዱና የነፃነት ትግል መልዕክት ማባዣ አድርጓቸው።
26. የኢሳትና የ OMN ቴሌቪዥኖች ዜናዎችንና ፕሮግራሞችን ተከታተሉ፤ በየትምህርታችሁ መሀል የኢሳትና OMN ዜናዎች በማንሳት የሰማችሁ ላልሰሙት አዳርሱ።
27. ስለ እውነትና ውሸት ስትናገሩ ምሳሌዎቻችሁ EBC እና ኢሳት ይሁኑ። ውሸት እና EBC አቻ ቃላት ይሁኑ። የውሸት ማምረቻዎች በተማሪዎች ተለይተው እንዲታወቁ አድርጉ: የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት፣ የጠቅላይ ስታትስቲክስ ጽ/ቤት፣ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቶች፣ EBC፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን፣ የክልል መንግሥታት ቢሮዎች …
28. ፓሊሶች ሰው ሲደበድቡ፣ ሲያንገላቱ፣ የድሆች ቤቶች ሲፈርሱ፣ ፍትህ ሲጓደል አይታችሁ ዝም አትበሉ፤ ተማሪዎቻችሁን አስተባብራችሁ ጩኹ።
29. ማኅበረሰቡ በሚያደርገው ተቃውሞ – ሰልፍ፣ የቤት ውስጥ መቀመጥ፣ የግዢ ማዕቀብ … ወዘተ. – በንቃት ተሳተፉ።
30. ተቃውሞዎች ሲበስሉ ከምን በላይ ነፃነት ነውና ትምህርት በማቆም አምባገነኑን ሥርዓት ለማንበርከበብና የፓለቲካ ሥርዓት ለውጥ ለማምጣት ግንባር ቀደም ሁኑ።
31. 2009 የትምህርት ዓመት የውጤታማ ፀረ-ህወሓት/ኢህአዴግ ትግል ዓመት እንዲሁን ትጉ።


መረጃና ጥቅሙ…–አቻምየለህ

$
0
0

[መጠነኛ ማስተካከያ ተደርጎበት በድጋሜ የታተመ]

social-mediaየወያኔ ድርጅታዊና ስርዓታዊ ሞዴል ቁሳቁሳዊ ግብዓቶችን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ጉልበት ማግኘት ላይ የተመሠረተ ነው። ይህ ሞዴል እስከ ዛሬ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በነበሩት ስልጣኔዎች ሁሉ የሰራሞዴል ነው። የሞዴሉ ጽንስ ሀሳብ እንደሚከተለው ነው። ቁሳቁሱን የተቆጣጠረ አካል ሁኔታዎች ወዴት እንደሚያመሩ መቆጣጠር ይችላል የሚል መነሻን ያደርጋል። የቁጥጥሩ ስርዓት የሚከናወነው ደግሞ የመረጃ ስርጭትን በመቆጣጠር ሲሆን ይህንን ለማድረግ በቁጥጥር ስር ያለውን አካላዊ መሳሪያ ሁሉ ይጠቀማል። ይህ የተለመደ ሁኔታ ነው።

ዛሬ ላይ ግን መሳሪያ ብቻ ይረዳል ማለት ዘመኑን የዋጀ አስተሳሰብ አይደለም። ምንም እንኳን ይቺን የአሁኗን ቅጽበት የሚቆጣጠረው ብረቱን የያዘው አካል ቢሆንም የምትቀጥለውን ደቂቃ ወይም ሰዓት ዕጣ ፈንታ የሚወስነው ግን መረጃውን የሚቆጣጠረው አካል ነው።

እስከ አለፉት ሁለትና ሶስት አስርት ዓመታት ድረስ መሳሪያውን የያዘው የሚተላለፈውን መረጃ ይወስን ነበር። ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል። ዛሬ መረጃን መቆጣጠር ማለት ተደማጭነት መኖር ማለት ነው። መረጃ ካለህ ሰው ሊሰማህ ይፈልጋል። መረጃ ከሌለህ የለህም። መረጃ ከሌለህ ማንም ሊሰማህ አይፈልግህም። ማንም ሊሰማህ ካልፈለገ ምንም መስራት አትችልም። ይህ ማለት እንግዲህ የአድማጭ መልካም ፈቃድ የሚገኘው በመረጃ ነው ማለት ነው። አንድ ሰው ሌላውን ለማዳመጥ መልካም ፈቃድ ከሌለው በመሳሪያ አስገድደህ ሙሉ ቀን ስብሰባ ላይ ብታውለው፤ ሙሉ ቀን በሬዲዮና በቴሎቭዥን ብትለፈልፍ ምንም የምታመጣው ለውጥ የለም። በርግጥ ሰውን ያለፍላጎቱ አግተህ ፖለቲካ በመጥመቅ ጊዜያዊ ግንዛቤ መፍጠር ይቻል ይሆናል። ይህ በሚሊዮን ብር የተገነባው ግንዛቤ ግን በአንድ የፌስቡክ መልዕክት ሊፈርስ ይቻላል።

ይህ እንዲሆን ትክክለኛ መረጃ ያስፈልጋል። ትክክለኛ መረጃ መሰብሰብ ከሁሉ አስቀድሞ ለራስ አስፈላጊ ነው። እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ ራሱን ነጻ ለማውጣት የሚያስችል ፍላጎትና አቅም አለው። ሆኖም የያንዳንዱ ሰው ፍላጎትና አቅም ብቻውን ነጻነት አያመጣም። ፍላጎትና አቅም በመረጃ ታጅለው ጣምራ መሆን አለባቸው።

መረጃ ሲጠራቀምና ጣምራ ሲሆን አቅምና ፍላጎትን አቀጣጥሎ ወደተፈለገበት የሚያደርስ ነዳጅ ነው። ትክክለኛ መረጃ ወደነጻነት ሲያደርስ የተሳሳተ መረጃ ነጻነትን ያስነጥቃል። አንድ ሃላፊነት የሚሰማው ሰው ለቤተሰቡ፣ ለጎረቤቱ፣ ለማኅበረሰቡ፣ ለሃገሩ ሊያደርግ የሚችለው አነስተኛው ነገር፣ ያለውን ትክክለኛ መረጃ ለሁሉም ማካፈል ወይንም ለሁሉ ወደሚደርስበት የመረጃ ቋት መላክ ነው። በየትኛውም መንገድ መረጃ ያገኘ ሰው ለነጻነቱ የሚችለውን እንዲያደርግ የሰው ተፈጥሮ ያስገድደዋል። ባጭሩ በባርነት እየኖርን ያለነው ሁላችንም ተባብረን የጋራ የመረጃ ቋት ባለመፍጠራችን ወይንም ያወቅነውን ትክክለኛ ነገር ለሁሉም ባለማሳወቃችን ነው።

ያየውንና የሚያውቀውን ትክክለኛ መረጃ የሚደብቅ ሰው ሃላፊነት የማይሰማው ሰው ነው። እውነቱን የሚደብቅ ሰው ለሰው ጥሩ የሚያስብ ሰው አይደለም። አውቆም ሆነ ሳያውቅ የውሽት መረጃ የሚያጋራ ሰው ደግሞ የሰውን ጥፋት የሚሻ ተልኮለኛ ሰው ነው። የግራ ፖለቲካ ወደ አገራችን ከገባ ወዲህ እኛ አገር አንዱ ትልቁ ችግር የተንኮለኛና ሴረኛ ሰዎች መብዛት ነው። ያ ደዌ ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ የዛሬው ትውልድ በሽታም ሆኗል። ካለፉት አርባ አመታት ወዲህ ባዳበርነው የፖለቲካ ባህል መረጃን መደበቅ ወይም ስህተት የሆነን መረጃ ማስተላለፍ እንደባህል ሆኗል። ለዚያም ነው የግራ ፖለቲካ ባህል ወደ አገራችን ከገባ ጀምሮ አለመተማመን ባህላችን የሆነው። ይሄ የፖለቲካ ባህል እውነት ቢነገርም በጥርጣሬ ለማየት እንድንገደድ አድርጎናል። በዚህም የተነሳ ዛሬ ችግራን ብዙ ሆኗል።

በሶማሌና በአፋር ባህል ውስጥ ግን የሚደነቅ የመረጃ ልውውጥ ባህል አለ። ለሶማሌና ለአፋር መረጃ የነፍስ ያህል ነው። እንደሚታወቀው የዘላን ህይወት ዛሬ እዚህ ነገ እዚያ ነው። ዘላን ከአንዱ ቦታ ተነስቶ ወደሌላው ቤተሰቡን፣ ከብቱንና ባጠቃላይ በዚህች አለም ላይ ያለውን ሁሉ ይዞ በረሃውን አቋርጦ ሲሄድ ስለሚያጋጥመው ነገር ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። በመዳረሻ ቦታው ውሃው ደርቆ ከሆነ ሁለት ቀን ተጉዞ እዚያ ሲደርስ ጉድ ሊሆን ይችላል። ቤተሰቡ ሊያልቅበት ይችላል። በዚያ መንገድ ላይ ሽፍቶች ወይም ተቀናቃኝ ጎሳዎች ካሉ ካላወቀው ከነቤተሰቡ ያልቃል። ስለዚህ ምንም ሌላ የመገናኛ መሳሪያ በሌለበት አንድ አፋር ወይም ሶማሌ በአካባቢው ስላለው ሁኔታ በየቀኑ በትክክል ማወቅ አለበት። የተሳሳተ መረጃ ካለው አለቀለት። የዚህ ችግር መፍትሄ በነዚህ ጎሳዎች ባሕል ውስጥ አለ። ይኸውም መረጃን በትክክል ለጎሳቸው አባል ለሆነ ሰው በትክክል ማስተላለፍ ነው።

ሁለት አፋሮች መንገድ ላይ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ሲሄዱ ከተገናኙ ይቆሙና፣ ዱላቸውን መሬት ላይ ተክለው ተደግፈው መረጃ ይለዋወጣሉ። የመረጃ ልውውጡ ስርዓት አለው። አንዱ ሲናገር ሌላኛው እህ! እህ! እህ! እህ! እያለ ከማዳምጥ በስተቀር አያቋርጠውም። መንገድ ላይ ያለውን አደጋ፣ የማን ቤተሰብ የት ጋ እንዳለ፣ የትኛው የውሃ ምንጭ እንደደረቀ፣ ሌላም ሌላም ነገር ይነግረዋል። ተራው ሲደርስ ያኛውም እንደዚያው ያደርጋል። ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ከሰጠ በሰውዬውና ቤተሰቡ ህይወት ላይ ፈረደ ማለት ነው። ስለዚህ በዛ እልም ያለ በረሃ ውስጥ እያንዳንዱ አፋር የሚሆነውን፣ የሚያጋጥመውን፣ የቱ ጋ ምን እንዳለ በደምብ ያውቃል ማለት ነው።

ይህንን ፈረንጆቹ situational awareness ይሉታል። አሁን አሁን ግን ከባድ የነበረውን የአፋሮና የሶማሌዎች ህይወት ሞባይል ስልክ የበለጠ አቃሎታል።
ትግራይ በነበርሁ ጊዜ «ዞን ሁለት» በሚባለው የአፋሮች አካባቢ ለመስክ ጥናት ሄጀ አርባ ግመል የሚጎትት የአብር አባወራ አርባውን ግመል ሰትሮ በሞባይል ስልኩ ሌላ ቦታ ላለው የጎሳው አባል መረጃ ሲያቀብልና situational awareness ሲሰጥ በአይኔ አይቻለሁ። ይህንን ለመገንዘብ የቻልሁት አፋርኛ የሚችለው ትግሬው ሾፌራችን አርባውን ግመል ሰትሮ ለረጅም ጊዜ በሞባይሉ ያወራ የነበረው አፋር ምን እያወራ እንደሆነ ጠይቄው ሌላ ቦታ ላለው የጎሳው አባል መረጃ እየሰጠ እንደሆነ ተርግሞ ነግሮኝ ነው። ሾፌራችን አጠገባችን የቆመው አፋር ወዲያ ማዶ ላለው የጎሳው አባል… በዚያ አትሂድ፣ በዚህ አቋርጥ፣ እዚያ ብትሄድ ይህ ይገጥምሀል፣ በዚህ ብትሄድ ይህንን ታገኛለህ፣ ወዘተ እንደሚለው ተርጉሞልኛል።

እስካሁን ወያኔ በህዝባችን ላይ ተነግሮ የማያልቅ ሰቆቃ ሲታደርስ ለምንድነው የረባ ራስን ነጻ የማውጣት የተባበረ እንቅስቃሴ ያልተደረገው ለሚለው መልሱ እዛ ጋ ያለ ይመስለኛል። ዘላኖቹ አፋሮችና ሶማሎዎች እንዳላቸው አይነት ትክክለኛ የሆነ የዳበረ የጋራ የሁኔታዎች ምልከታ (situational awareness) የለንም። ካለንም የተሳሳተ፣ የተዛባ ነው። ከፍ ብዬ እንዳልሁት እውነት ቢሆንም አናምነውም፤ እንጠራጠራለን። የምንጠራጠረውን ከማረጋገጥ ይልቅ ይዘነው እንቀራለን። የማረጋገጥ ፍላጎቱ ካለ ግን ለማንጠር [refine ለማድረግ] ቀላል ነው። ቀላሉ ዘዴ ማመሳከር ነው፤ ከሌላው ጋር መለዋወጥ ነው። ሁሉም ሰው «ይህ በዛ ያ አነሰ» ሳይል ያለውን መረጃ ጠረጴዛው ላይ [ፌስቡኩ ላይ ማለቴ ነው] [ስጋት ያለበት ካለ ደግሞ በውስጥ መገናኛ መስመር ለሚያምነው ሰው ሊልክ ይችላል] ከዘረገፈው የዚህ ሁሉ ሰው አይን እውነቱን ከውሸቱ ለይቶ ያወጣል። ማመሳከር ማለት ያ ነው። አፋር ውስጥ የሰውን ስም ማጥፋት ከባድ ነው። ሲስተሙ እያመሳከረ እውነቱን ያወጣዋል። ለነፍስህ ስትል ሁሉንም ስለምታዳምጥ እውነቱ ወዲያው ይወጣል። ውሸታሙ ወዲያው ይጋለጣል። ውሸቱ ሲጋለጥ ህይወት ሊጠፋውም ይችላል።

በኛ አካባቢ እንደ አፋርና ሶማሌዎች እውነቱን እያመሳከረ የሚያወጣ ሲስተም ስለሌለ ሰው ጥይት መተኮስ አያስፈልገንም። አንዱን የማንፈልገውን ሰው ልናጠፋው ከፈክለግን ያልሆነ ወሬ አንስተን «ቱስ» ብንል የፈለገ ትልቅ ሰው፤ ደግ ፍጡር ቢሆን ደብዛውን ልናጠፋው እንችላለህ። ይህም የሚሆነው ውሸት ብናወራ ስለሚወራው ነገር ስለማናመሳክር ነው። እውነት በቀላል ይገኝ ይመስል ውሸት በቶሎ እንቀበልና ስለእውነት የሚገባውን ክብደት አንሰጥም።

ያለንበትን ጊዜ መጠቀም ከቻልን ይህንን ሁሉ ችግር ማስወገድ የምንችልበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። የዘመኑ ቴክኖሎጂው ነገሮችን አቅሏቸዋል። ከኛ የሚጠበቀው ያለውን ሁሉ መረጃ በትክክል ማቅረብ ነው። ቴክኖሎጂውና የሰው ልጅ የእውቀት ደረጃ አንድን መረጃ እውነት እንኳ ባይሆን በቀላሉ ያጣራዋል። ቴክኖሎጂው የቀረበለትን መረጃ በተቻለ መጠን ማዛመድ፣ ማጣራት፣ ማመሳከር ይችላል።

ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂና እውቀት ከሌለን ግን የአፋሮችንና የሶማሌዎችን የመረጃ ልውውጥ ዘዴ ብንከተል ብዙውን ችግራችንን ማቃለል እንችላለን። ስለዚህ እንደ አፋሮች የሰማኸውን ነገር ሁሉ ሰማሁ ብለህ አቅርብ፤ ያየከውንም አጋራ። የሰማኸውን አየሁ ካልህ፤ ያላየኸውን አይቻለሁ ካልክ መረጃውን በከልከው ማለው ነው። የተበከለ መረጃ ሰው ርግጠኛ ሳይሆን እንዲፈርድ ያደርገዋል።

በሰለጠኑት ፈረጅኖች ዘንድ ዛሬ የአንድን መረጃ ትክክል መሆን አለመሆን በሂሳብ ቀመር የሚፈትን ነጻ የኮምፒዩትር ፕሮግራም አለ። ይህ ምናልባትም ላይመስል ይችላል። በርግጥ ይህ ፕሮግራም የሁሉን ተሳትፎ ይጠይቃል። ፕሮግራሙ swiftriver ይባላል። እውነቱን ከውሸቱ አበጥሮ ያወጣል።

ፕሮግራሙ ስለራሱ እንዲህ ይላል… «SwiftRiver is a platform that helps people make sense of large amounts of information in a short amount of time. It’s also a mission to democratize access to the tools used to make sense of data – to discover information that is authentic.»

አንድ አይነት ራዕይ ያለን ሰዎች የራሳችን swiftriver መፍጠር እንችላለን። ታዲያ የኛው swiftriver የኮምፒዩተር ፕሮግራም አይደለም፤ መረጃ የምንልክለት የኛ የሆነ ሁነኛ ሰው እንጂ። ይህ የኛ swiftriver የመረጃ ማእከል ይሆንና አጠቃላይ የመረጃ ፍሰቱን ይቆጣጠራል። ይህ ማለት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከት የመረጃ ፍሰቱን የሚቆጣጠረው ይህን አካል ካወቅን ወይንም ያን አካል እኛ ከፈጠርነው ወደፊት በማን ራዕይ እንደምንመራ ማወቅ እንችላለን ማለት ነው።

ስለዚህ በተለይ አገር ቤት ያላችሁ የመረጃ ትንሽ የለውምና በእጃችሁ ያለውን ስልክ ሳይቀር በመጠቀም መረጃ ሰብስቡ። የሰበሰባችሁትን መረጃ ደግሞ የኛ swiftriver ነው ብላችሁ ለምታስቡት ሰው ላኩ። ይህ ሰው የላካችሁትን መረጃ አደራጅቶ ፤ ትርጉም ሰጥቶ፤ሁኔታ አበጅቶ፤ መልክ አስቀምጦና ተንትኖ የዳበረ የጋራ የሁኔታዎች ምልከታ ይፈጠራል። ይህ የነጻነታችን ሞተር ነዳጅ ነው። ያየነውን፤ ያወቅነውን ወደ አንድ swiftriver የሆነ ሰው በመላክ ያለብንን ሃላፊነት በመወጣታችን ነጻ እንወጣለን።

ሁላችንም በኃላፊነት ስሜት ያለንን፣ ያየነውን፤ ያወቅነውን ሁሉ ወደ መረጃ ቋታችን ማለትም ወደኛው swiftriver መላክ ከቻልን በቀላሉ መጻኢ እድላችንን መቅረጽ እንችላለን፤ መረጃ ፍሰቱን የሚቆጣጠረው አካል የወደፊቱን ሁሉ ይቆጣጠራልና!

አክባሪያችሁ!

አቻምየለህ ነኝ!

“የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ያዘነው ዘፋኞቹ ዘፈን ስላልዘፈኑ እንጂ 60 ሰዎች በእስር ቤት በመቃጠላቸው አይደለም”–ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ መላኩ ባወቀ |ሊታይ የሚገባው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ መላኩ ባወቀ በካሊፎርኒያ ቹላ ቭስታ በሚገኘው የደብረ ሳህል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በተደረገ ታላቅ ሃይማኖታዊ ጉባኤ ላይ በወቅታዊው የሃገራችን ሁኔታ ዙሪያ ታላቅ መልዕክት ማስተላለፋቸው ተሰማ:: “ይቅርታ” በሚል ርዕስ ትምህርታቸውን የሰጡት ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ መላኩ ባወቀ የተለያዩ ወቅታዊው የሃገራችን ትኩሳት ዙሪያ ያስተማሩ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ተቃጥለው ስለሞቱት 60 ስለሚደርሱት እስረኞች ጉዳይና ስለመንግስት ምላሽ ለም ዕመናኑ በትምህርታቸው አስረድተዋል:: እሙ የጌታ ልጅ ይህን ቭድዮ አግኝተናል ይመልከቱት::

BBN Radio: ህወሃት ጎንደርን መሳሪያ ለማስፈታት ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ ነው * የደንቢዶሎን ግድያ ለመካድ ሞከረ |የመምህራን እምቢተኝነትና ተቃውሞ እንደቀጠለ ነዉ

$
0
0

BBN Radio: በምዕራብ አርሲ ትጥቅ ለማስፈታት የሞከሩ አጋዚዎች ተገደሉ – ህወሃት ኢህአዴግ የግዳጅ ሰልፍ ለማድረግ እያስገደደ መሆኑ ታወቀ * ጠ/ሚ ሐይለ ማርያም ስለ ኢንተርኔት የተናገሩት አነጋጋሪ ሆነ * የመምህራን እምቢተኝነትና ተቃውሞ እንደቀጠለ ነዉ * ህወሃት ጎንደርን መሳሪያ ለማስፈታት ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ ነው * የደንቢዶሎን ግድያ ህወሃት ለመካድ ሞከረ

“ከትግራይ አብራክ የወጡና ይህን ስርዓት የሚቃወሙትን በቆራጥ ወኔ ነው የምናደንቀው”–ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በድህሚት 2ኛ ጉባዔ ላይ ያደረጉት ንግግር

$
0
0

እሁድ መስከረም 8፤ 2009 ዓ፡ም

– ታጋይ መኮንን ተስፋዬ፤ የዴምህት ተመራጭ ሊቀመንበር
– በተለያየ ደረጃ የምትገኙ የድርጅቱ ያመራር አባላት
– ሰፊው የዴምህት ታጋዮች
– ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች
– ክቡራትና ክቡራን

በመጀመሪያ ለትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ወይንም ካሁን በኋላ በትግርኛው ስሙ ለምጠራው ዴሞክራሲያዊ ምንቅስቃስ ህዝብ ትግራይ (ዴምህት) ታጋዮች፤ አመራሮችና ደጋፊዎች ድርጅታዊ ጉባኤያችሁን ስኬታማ በሆነ መንገድ በማጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። የእናንተ ስኬትና ደስታ የእኛም ስኬትና ደስታ ነውና ደስታችሁን ስንጋራ ደስ ይለናል። ይህ ጉባኤ ድርጅቱን ከድቶ፤ ምንም የማያውቁ ታጋዮችን አስከትሎና ለአደጋ አጋልጦ ከህወሀት/ኢህአዴግ ጋር የተቀላቀለው የቀድሞው የዴምህት ሊቀመንበር ሞላ አስገዶም (የአዲስ አበባ ወጣቶች ሞላ አስከዶም ነው አሉ የሚሉት) በከዳ በአመቱ፤ የሱ መክዳት በድርጅቱ ውስጥ ይዟቸው የመጣውን ብዙ ራስን የመመዘንና የማወቅ ጥያቄዎች በእርጋታና በሰከነ መንገድ፤ ከበቂ በላይ ግዜ ሰጥቶ መርምሮና መልሶ፤ ከዚህ በፊት ከነበረበትም የበለጠ የጠራ መስመርና የተጠናከረ ድርጅት ይዞ፤ የተነሳበትን የትግል አላማ ከዳር ለማድረስ ቆርጦ፤ የተነሳ ድርጅት ሆኖ በመውጣቱ ደስታችሁ የላቀ መሆኑ ይሰማኛል። ይህ ሂደት በራሱ ትልቅ ድል ነውና እንደገና እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ።
Birhanu Nega

እኔ ዴምህት ስለሚባል ድርጅት በመጀመሪያ የሰማሁት ከምርጫ 97 በኋላ ቃሊቲ እስር ቤት ሆነን በአንድ ወቅት በጊዜው የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበረው ታጋይ ፍሰሀ ኃይለ ማርያም ከዴምህት ሬድዮ ጋር ያደረገውን ሰፊ ቃለምልልስ ከሰማሁ በኋላ ነበር። መቼም እስር ቤት ውስጥ በተለይ በ11 ሰዓት አንዴ በር ከተዘጋብን በኋላ ከእስር ቤት ውጭ ስላለው ሁኔታ በዋናነት እንከታተል የነበረው የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች ከተለያየ ቦታ የሚያስተላልፉትን የሬድዮ ፕሮግራም በመስማት ነበር። የፍሰሀ ቃለ መጠይቅ እንደማስታውሰው ከሆነ በ3 ክፍል ተቆራርጦ ነበር የቀረበው። ሶስቱንም በጥሞና ነበር የተከታተልኩት። በጊዜው እኛ በሰላማዊ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት ያደረግነው እንቅስቃሴ በወያኔ ጉልበት ከተጨናገፈና እኛም ፍጹም አይን ባወጣ ውሸት “በዘር ማጥፋት ወንጀል” ተከሰን ወህኒ ከወረድን በኋላ “ያለው አማራጭ ምንድን ነው?” ብዬ እራሴን የምጠይቅበት ጊዜ ነበር። ምናልባት እኛም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት የጀመርነው ሰላማዊ ትግል በህወኃት/ኢህአዴግ ግፊት ወደ ትጥቅ አመጽ መሸጋገሩ ላይቀር ነው የሚል ግምት ነበረኝ። ስለዚህም በትጥቅ ትግል ከተሰማሩ ታጋዮች አቅጣጫ የሚሰጡትን መግለጫዎች ዝም ብሎ እንደ ተራ አድማጭ ሳይሆን
“በእርግጥ ይህ አካሄድ ያዋጣል ወይ? ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ይወስደናል ወይ? በመሳሪያ ታግዞ ስልጣን የያዘ ኃይል ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ አምባገነናዊ የመሆን እድሉ የሰፋ አይደለም ወይ? (ከህወኃት/ኢህአዴግ ታሪክ እንደምናየው) በብሄር ላይ አተኩረውና መሳሪያ ይዘው የሚታገሉ ኃይሎች እንታገልለታለን ከሚሉት ብሄረሰብ ውጭ ለሁሉም የምትሆን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ከልባቸው ለመገንባት ይፈቅዳሉ ወይ? ህብረ ብሄር የሆኑና አገራዊ አጀንዳዎች ያነገቡ የትጥቅ ትግል የሚያካሄዱ የተለያዩ ድርጅቶች ትግሉ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ሲደርስ እርስ በርሳቸው ከመጋጨት
የሚከለክላችው ምንድነው? የሚሉና ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎች ለመመለስ እንደሚፈልግ ዜጋ ነበር በጥሞና የምከታተለው። በዚያ ቃለ መጠይቅ ውስጥ ታጋይ ፍሰሀ ከተናገራቸው ነገሮች እስካሁን ትዝ የሚሉኝና ዴምህትን በቅርብ እንድከታተል ያደረጉኝ (የቀጥታ ጥቅስ ሳይሆን እኔ እንደገባኝና በጥቅሉ) የሚከተሉት ሁለት አቋሞች ነበሩ::

ሀ)ዴምህት እንደ ድርጅትና፤ (በተለይ ስሙን ብቻ ለተመለከተ) በትግራይ ብሄረሰብ ስም የሚንቀሳቀስ ቢመስልም ድርጅቱ ግን ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ነው። ህወሀት የትግራይን ህዝብ በተለይ ጠርንፎ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ለማጋጨት ስለሚፈልግ እኛ የትግራይ ልጆች የትግራይን ህዝብ ከህወሀት የተለየ ኢትዮጵያዊ አቅጣጫ እንዲይዝ ለማድረግ ለጊዜው በስሙ መንቀሳቀስ ከስልት አኳያ ይጠቅማል ብለን እንጂ በድርጅታችን ውስጥ ትግራዋይ ያልሆኑ የሌሎች ብሄረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ ስለዚህ በስም እንጂ በተግባር ኢትዮጵያዊ ድርጅት ነን::

ለ) መሰረታዊ ትግላችን ህወሀት/ኢህአዴግን ጥለን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ እኛ ብቻችንን የምናደርገው ሳይሆን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ጋር በጋራ የምንሰራው ስራ ነው፤ ስለዚህም ሰፋ ያለ የድርጅቶች ህብረት እንዲፈጠር ማገዝና መስራት ቀዳሚ ስራችን አድርገን የምንወስደው ነው፤ የሚሉት አቋሞች ነበሩ።

ከእስር ቤት ወጥቼና የትግል ስልት መቀየር አስፈላጊ መሆኑን አምኜ ከጓዶቼ ጋር ሆኜ ግንቦት 7ን ከመሰረትን በኋላና የትግል እስትራቴጂያችን “ሁለንተናዊ ትግል” ነው ብለን ካወጅን በኋላ ከዚህ ሁለንተናዊ ትግል ውስጥ አንዱ የሆነውን በመሳሪያ የታገዘ ትግል እንዴት ነው የምናስኬደው በሚለው ጉዳይ ላይ ከሁለት አመታት በላይ ስንመክርበት ቆይተን ጓዳችን አንዳርጋቸው ይህን ስራ እንዲሰራ ወክለነው ወደዚህ ወደኤርትራ መምጣት ከጀመረ ጀምሮ ነበር ስለዴምህት በቅርብ ማወቅ የጀመርነው። ከሞላ ጎደል አንዳርጋቸው ስለ ዴምህት የነገረን ከላይ ፍሰሀ በቃለመጠይቁ ያነሳቸው አቋሞች አሁንም የድርጅቱ አቋሞች መሆናቸውን ነበር። በዚህ በመበረታታትም ይመስለኛል አንዳርጋቸው ከዴምህት አመራርና ታጋዮች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንደመሰረተ የምናውቀው። አርበኞች ግንቦት 7 በውህደት ከተመሰረተ በኋላና እኔም እዚህ ከመጣሁ በኋላ ይህን የቅርብ ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል ነበር ስንሞክር የነበረው የሞላ መክዳት እስከሚፈጠር ድረስ። ሞላም ከከዳ በኋላ እኛ በጊዜው ምክትል ሊቀመንበር ከነበረው ከመኮንን ጋር በግል ብዙ ጊዜ እየተገናኘን ለረጅም ሰዓታት ከመወያየታችንም በላይ ባንድ ወቅት ከሙሉ አመራሩ ጋር ረጅም ጊዜ የወሰደ ስብሰባ አድርገን ባጠቃላይ ስለትግሉና ስለሁለቱ ድርጅቶች ግንኙነት በሰፊው ተወያይተናል። በኛ በኩል ከነኝህ ውይይቶች በመነሳት ዴምህት በሞላ ምክንያት የተፈጠሩትን ችግሮች ቀርፎ ጠንክሮ እንደሚወጣ ምንም አልተጠራጠርንም። ምንም እንኳን ሂደቱ ከጠበቅነው በላይ ጊዜ ቢወስድም በሂደቱም ሆነ በውጤቱ (እስካሁን ከሰማናቸው የጉባኤው ውሳኔዎች) ደስተኞች መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እወዳለሁ።

ምንም እንኳን ይህ የጉባኤያችሁ የመዝጊያ ፕሮግራም የደስታ ፕሮግራም ቢሆንም አሁን በሀገራችን እየተካሄደ ያለውና በጣም በፍጥነት እየተቀያየረ ያለው ሁኔታ ሁላችንንም ከዚህ በፊት ስንጓዝ ከነበረበት አካሄድ በተለየና በጣም ባስቸኳይነት ስሜት እንድንሰራ የሚገፋፋ ሁኔታ ስለተፈጠረ፤ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ በሀገሪቱ ስላለው ሁኔታና ይህም በትግላችን ላይ ባጠቃላይ፤ በተለይ ደግሞ በዴምህት ላይ ይዞ የመጣው የተለየ ሀላፊነት ላይ አንድ ሁለት ነጥቦች ለማንሳት ይፈቀድልኝ።

ሀገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ ምን ይመስላል? ከኛ ምን ይጠብቃል?

ሁላችንም እንደምናውቀው በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን በህዝባዊ እምቢተኛነት እየተናወጠች ነው። ከዘጠኝ ወራት በፊት ጀምሮ በኦሮምያ ክልል የተጀመረውና በፍጹም ሊበርድ ያልቻለው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተተው የህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ የብዙ ህዝብ ህይወት ቀጥፎም እንደቀጠለ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ አድማሱን ወደ አማራ ክልል አስፍቶ በተለይ ጎጃምና ጎንደር ሰፊ ህዝባዊ አመጽ የሚደረግበት ቀጠና አድርጎታል። በነኝህ ሁለት ዞኖች በኅወሀት/ኢህአዴግ እየተፈጸመ ያለው ወደር የማይገኝለት አፈናና ግድያ ትግሉን ሊያስቆመው አልቻለም። ከሰሞኑ ደግሞ ተዳፍኖ የቀረ ይመስል የነበረው የኮንሶ እንቅስቃሴ አገርሽቶ ብዙ ሰላማዊ ሰዎችን እየገበረ ይገኛል። ይህ ሁኔታ ክረምቱ ከወጣና ትምህርት ቤቶች ከተከፈቱ በኋላ ከኦሮምያና ከአማራ ክልሎች በተጨማሪ በሌሎችም የደቡብ ክልል ወረዳዎችና እንደ ጋምቤላና አፋር ባሉ ክልሎች ይሰራጫል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በሀገራችን ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ መጠነ ሰፊ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ብዙ ትርጉም ያለውና እኛንም እንደ ታጋይ ድርጅቶችና የህዝቡን ትግል እንደሚደግፉ ኃይሎች እስካሁን ስንሄድበት የነበረውን አካሄድ በደንብ መርምረን ለጊዜው የሚመጥን አካሄድ እንድንቀርጽ ያስገድደናል። ከዚህ አንጻር ይህ አዲስ ኩነት በህዝቡ የትግል ስሜት ላይ፤ ህወኃት/ኢህአዴግ ለዚህ የህዝብ ትግል በሚሰጠው መልስ ላይና፤ እኛ እንደታጋይ ድርጅቶች ሁለቱንም ከግምት ወስደን በምንሰጠው መልስ ላይ ያላቸውን አንድምታዎች በአጭሩ ላቅርባቸው።

በመጀመሪያ የሀገሪቱን ፖለቲካ በቅርብ እንከታተላለን የሚሉትን ሳይቀር ጉድ ያስኘው፤ ህወኃት/ኢህአዴግ በልማት ፕሮፓጋንዳ፤ በአፈናና በትር፤ ቅስሙን ሰብሬ የፍርሀት ቆፈን ውስጥ አስገብቼዋለሁ፤ ህዝቡ ከኛ ሌላ አማራጭ ፖለቲካ ሊያይ እንኳን የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ለዚህም ማሳያው በ2007ቱን የይስሙላ ምርጫ 100% ማሸነፌ ነው፤ ይህንንም ኦባማ ሳይቀር የአለም ታላላቅ ሀገሮች መስክረውልኛል ብሎ በትእቢት በተወጠረበት ወቅት ነው ህዝቡ ምንም አይነት ፍርሀት የማያሸንፈውና ከሚፈልገው ነጻነት የሚያስቆመው ምንም ምድራዊ ኃይል እንደሌለ ደረቱን ለጥይት ሰጥቶ የሞቱ ጓደኞቹንና ልጆቹን እየቀበረ ትግሉን የቀጠለው። ይህ ለገዢው ኃይልና ለተባባሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ህወኃት/ኢህአዴግን በተለያየ መንገድ ለሚቃወሙ ተቃዋሚ ድርጅቶችም ግልጽ ያደረገው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለነጻነት መኖር እንደሰለቸው፤ ለነጻነቱ ህይወቱን ለመስጠት ዝግጁ እንደሆነ፤ በዚህ ትግሉ ህወሃት/ኢህአዴግን ገርስሶ መጣሉ የማይቀር ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ ራሱ በመረጣቸው መሪዎች መተዳደር የሚፈልግ፤ ሰው ሆኖ ሰብአዊ መብቱ ተከብሮ፤ ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ጋር በእኩልነት መኖር እንጂ ካሁን በኋላ በምንም አይነት የጉልበት አገዛዝ እንደማይተዳደር ያወጀበት ነው ብለን ልንወስድ እንችላለን። ይበልጥ የሚገርመው ደግሞ በዚህ የትግል ሂደት እንደተፈራውና ህወኃት/ኢህአዴግ አጠንክሮ ሲሰራበት የቆየው የብሄር ክፍፍል ሀገሪቷን ወደ ቀውስ ሳይሆን፤ የተለያዩ ብሄረሰቦች አንዳቸው ለሌላው በደል የሚያስቡበትና ነጻነታቸውን በግል ሳይሆን በጋራ ትግል እንደሆነ የሚያገኙት በማመን ትግላቸውን በጋራ የነጻነትና ያንድነት መንፈስ ማስተሳሰራቸው ነው። ምንም እንኳን የዚህ ትግል የመጨረሻው ውጤት ምንነት ገና ያልተጻፈ ቢሆንም፤ ይህ ለሀገሪቱ የወደፊት እጣ ፈንታ እጅግ አወንታዊ የሆነ ክስተት ነው።

ሁለተኛውና ይህን ሁኔታ በአጽንኦት እንድንመለከተው የሚያስገድደንና እኛም የምንሄድበትን አካሄድ በጥሞና እንድንመረምር የሚያደርገን ከዚህ ጋር የተያያዘው ክስተት ህወኃት/ኢህአዴግ ለዚህ የህዝብ ትግል እየሰጠ ያለው መልስና እንዴት ሊሄድበት እንዳሰበ የሚያመለክቱት አደገኛ አዝማሚያዎች ናቸው። ምንም እንኳን የህዝቡ ትግል ባብዛኛው ሰላማዊ የነበረ ቢሆንምና የህዝቡ ጥያቄም በድርድርና በሰላማዊ መንገድ ሊፈታ እንደሚችልና እንዲፈታ ከተለያየ አቅጣጫ ጥያቄዎች ቢቀርቡም፤ (ለምሳሌ እንደነ ጀነራል ጻድቃንና አበበ ጆቤ ያሉ ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎችም በጽሁፍ ያቀረቡት ቢሆንም) መንግስት የመረጠውና የሚያውቅበት ብቸኛ አካሄድ ባንድ በኩል ፍጹም ያረጀና ካሁን በኋላ ምንም ሰሚ የሌለውን ፍጹም የተምታታ የሽንገላ አካሄድ፤ (ዋና መስመራችን ትክክል ነው ግን ትንሽ የአሰራር ስህተቶች ሰርተናል እሱን ደግሞ እናርማለን…ወዘተ) በይበልጥ ግን ችግሩን ይበልጥ በማጦዝ በመሳሪያ ኃይልና በጉልበት ለመጨፍለቅ፤ አልፎም ችግሩን የዴሞክራሲና የነጻነት ፍለጋ ትግል አድርጎ ሳይሆን በጣም በሚገርምና ለወደፊቷ ኢትዮጵያ እጅግ አደገኛ በሆነ መንገድ ትግሉ የኦሮሞና በተለይ የአማራ ህዝብ በትግራይ ህዝብ ላይ የተነሳና በትግራይ ህዝብ ላይ “የዘር ማጥፋት” ለማካሄድ የሚደረግ እንቅስቃሴ አድርጎ ሰፊ ፕሮፓጋንዳ መክፈቱ ነው። ይህ ህወኃት “ስልጣኔ ሊነካ ነው” ብሎ ሲያስብ የትግራይን ህዝብ ከጎኑ በማስፈራራት ለማሰለፍ የሚያደርገው የተለመደ መሰሪ አካሄዱ እንደሆነ እኛ በምርጫ 97 ወቅት በተቃዋሚው ጎራ ተሰልፈን ፖለቲካው ውስጥ የነበርን ሰዎች ያየነው፤ እኩይና ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚፈልግ ለሀገሪቱ ምንም በጎ የማይመኝ የውጭ ኃይል የሚያደርገው እንጂ፤ ከዚህ ህዝብ ጋር ወደፊት አብሬ እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ሀገራዊ ኃይል ሊያስበው እንኳን የማይገባ እጅግ አደገኛ አካሄድ ነው።

በምርጫ 97 ወቅት የህወኃት የደህንነት ክፍል ሌሊት ሌሊት ጸረ ትግራይ የሆኑ ፓንፍሌቶች በተቃዋሚው ስም እያወጣ ይበትን እንደነበር እናውቃለን። “እቃ ወደ ቀበሌ ትግሬ ወደ መቀሌ” የሚል ያነጋገር ፈሊጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመው የህወሀት ባለስልጣን የነበረ ሰው በቪኦኤ ቀርቦ ነው ግን ይህንን ማን እንዳለው ሳይናገር “ተቃዋሚዎች እንዲህ ይላሉ” ብሎ የነዛው እሱ ነው። እራሳቸው ያሰራጩትን ከፋፋይ የጸረ ትግራይ ፓንፍሌቶች “ሚዲያ ላይ ወጥተን በጋራ እናውግዝ” ስንላቸው ስራቸውን ስለሚያውቁት እምቢ ይሉ የነበሩት እነሱ ነበሩ። ኢንተርሀምዌ የሚባል አስከፊውን የሩዋንዳን ጭፍጨፋ የሚያስታውስ ቃል በኢትዮጵያ ያስተዋወቀው በአሳፋሪ ሁኔታ በምርጫ መሸነፉ ያስደነገጠው፤ ክፋት እንጂ ለሀገሪቱ ምንም ጥሩ ራዕይ ያልነበረው፤ የህወሀት መሪ የነበረው መለስ ነበር። ይህንን መለስ ከቤተመንግስት ሆኖ የተፋውን መርዝ ነበር ስዩም መስፍን እንደ በቀቀን በምርጫ ክርክሩ ወቅት ሊያስተጋባ የሞከረውና የከሸፈበት። ይህ ያንጊዜ የትግራይ ሰዎችን ለማሰባሰብና ተቃዋሚውን ለማስጠላት፤ ይበልጥ ደግሞ ፈረንጆቹን ለማጭበርበርና የምንወስደውን የኃይል እርምጃ ዝም ብለው እንዲመለከቱት ጠቅሞናል ያሉትን አደገኛና ፍጹም ሀላፊነት የማይሰማው “ከኔ በላይ ሰርዶ አይብቀል” የሚለውን አህያማ ፍልስፍና የሚያስታውስ አካሄድ ነው አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ስልጣናቸው በህዝብ ትግል መነቃነቅ ሲጀምር እንደገና ይዘው ብቅ ያሉት። መቼም ከሰሞኑ እነ አባይ ጸሀዬና ስዩም መስፍን የመሳሰሉ የህወኃት ቱባ ባለስልጣናት የሚናገሩትን እጅግ አሳፋሪና የሚያቅለሸልሽ፤ ፍጹም ሀላፊነት የማይሰማው ንግግር “እንዴ እነዚህ ሰዎች እኛ ከስልጣን ከምንወርድ ሀገሪቱ ትጥፋ ብለው የሚያምኑ ሰይጣኖች ናቸው እንዴ?” ብሎ ያልታዘበና ያላዘነ የኢትዮጵያ ወዳጅ ያለ አይመስለኝም። ይህ ግን እንደገና “እንዲሰራላቸው” በፍጹም መፍቀድ የለብንም።

ይህ አዲሱ “የዘር ማጥፋት” ሟርት በምርጫ 97 ጊዜ ከነበረው ጋር የሚያመሳስለው ሁለቱም የተፈበረኩት የህወኃት መሪዎች በአራት ኪሎ ላይ በጉልበት ያገኙት ስልጣን ሲነቃነቅ ያንን ለመከላከልና የትግራይን ህዝብ አስፈራርተው ከጎናቸው ለማሰለፍ ያደረጉት እኩይ ስራ መሆኑ ነው። በሁለቱም ጊዜ በትግራይ ህዝብ ላይ እንደ ህዝብ የተቃጣ፤ አይደለም የተቀነባበረና ተግባራዊ የሆነ፤ የታሰበ እንኳን ጥቃት አልነበረም። የለም። በምርጫ 97 ጊዜ ለዚህ የዘር ማጥፋት ሙከራ በማስረጃነት የቀረበውን የአቶ ኑር ሁሴንን ምስክርነት ፍርድ ቤት ሆኖ ለሰማ እነኝህ ሰዎች የሚሰሩትን ያውቃሉ? በእርግጥ ህዝቡን ለማባላት ይፈልጋሉ? ይህን በዘር ላይ የተመሰረተ የጥላቻ እሳትስ አንዴ ከለኮሱት በኋላ እነሱን ሳይበላ ያልፋል ብለው የሚያስቡ ደንቆሮዎች ናቸው? ብሎ ነው የሚገረመውና ለሀገሪቱም የሚፈራላት። የአሁኑን የህወሀት ሟርት ለማስረዳት የሚቀርበው ማስረጃ ተብዬው ደግሞ ባንዳንድ ትግሉ በሚካሄድባቸው የአማራና የኦሮምያ ክልሎች አንዳንድ የትግራይ ብሄረሰብ አባላት የሆኑ ግለሰቦች ንብረት ላይ የሀይል እርምጃ ተወስዷል የሚል ነው። የሰላም ባስ መቃጠልም እንደ ማስረጃነት ይቀርባል።

በመጀመሪያ አንድ ነገር ያለምንም ማሽሞንሞንና ምክንያታዊ ለማድረግ ሳይሞከር ግልጽ መሆን ያለበት ነገር አለ። በማንም ኢትዮጵያዊ ላይ በብሄር ማንነቱ ምክንያት ብቻ የሚደርስ ምንም አይነት የኃይል እርምጃ ብቻ ሳይሆን ምንም አይነት ትንሽም እንኳን የመብት መጣስ ሁላችንም አጥብቀን ከልባችን ልናወግዘው የሚገባን ጉዳይ ነው። ይህንን የምናደርገው ደግሞ ለግዜያዊ የፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን እንደሰው ልጆችና እንደ ኢትዮጵያውያን በማንም ሰው ላይ የሚደርስ ኢፍትሀዊ በደል ውስጣችንን ስለሚያመን ሊሆን ይገባል። በተለይ በዚህ የትግል ወቅት በፍጹም ልንረሳው የማይገባው ዋና ነገር ይህ ትግል ከምንም በላይ ለፍትህ የሚደረግ ትግል መሆኑን ነው። ህወሀት/ኢህአዴግን የምንታገለው መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ (የትግራይን ህዝብ ጨምሮ) ፍትህ ስለከለከለ ነው። ፍትህን አውቀው እየረገጡ ለፍትህ የሚደረግ ትግል ፍጹም አላማውን የሳተ የእውር ድንብር ትግል፤ ሲያልፍም ጥላቻን ብቻ ሰንቆ ለጉልበትነት የሚጠቀም ፍጹም አጥፊ ጸረ_ኢትዮጵያ ጉዞ ነው የሚሆነው። ከዚህ ለፍትህ ካለን ፍጹም የማያወላዳ አቋም ነው በኦሮሞ ወገኖቻችንም ሆነ በአማራ፤ በጋምቤላ ሆነ በኮንሶ፤ በቤንሻንጉል ሆነ በአፋር፤ በትግራይ ሆነ በጉራጌ፤ በክርስቲያኖች ሆነ በሙስሊሞች፤ በቡድኖች ላይ ሆነ በግለሰቦች፤ ላይ የሚደርሱ በደሎች ግፎችና የአድሎና የዘረፋ ስራዎችን ሁሉ የምናወግዘው። በጋራ ታግለን እጅ ለእጅ ተያይዘን ለሁላችንም የምትሆን፤ ሁላችንንም እንደ ኢትዮጵያውያን በእኩልነት የምታይና የምታስተናግድ ሀገር እንገንባ የምንለው። ለዚህ ነው ከህወሀት/ኢህአዴግ ጋር የሞት የሽረት ትግል ውስጥ የገባነው።

ይህንን ለፍትህ የሚደረግ የህዝብ ትግል የሰዎችን እንሰሳዊ የሆነ የራስ የመከላከል ስሜት አነሳስተውና በዚህም ጊዜያዊ ድጋፍ ባንዳንድ ወገኖች ዘንድ እናገኛለን፤ ይህንንም ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጉልበትነት እንጠቀምበታለን ብለው የሚያስቡ አክራሪና አጥፊ ኃይሎች ትግሉን ወደ ጥላቻ ትግል ለማስቀየስ የሚሞክሩ ሊኖሩ እንደሚችሉ እናውቃለን። እንደነዚህ አይነት ጥቂት ኃይሎች በህዝቡ ትግል ውስጥ ተመሽገው የሚወስዷቸው እርምጃዎችንና የሚያካሂዷቸውን የጥላቻ መርዛማ ፕሮፓጋንዳ ህወኃት/ኢህአዴግን ስለተቃወሙ ብቻ ዝም ብለን “የህዝቡ ትግል አካላት ናቸው” ብለን የምናልፋቸው ሊሆኑ በፍጹም አይገባም። እንዲህ አይነት እኩይ ኃይሎችን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን አስቀያሚ ገጽታቸውን በሚያሳዩበት ጊዜ ሁሉ እነሱን ማጋለጥና ከህዝቡ ፍትሀዊ ትግል ማግለል ለእውነትና ለፍትህ፤ ኢትዮጵያችንን ከተጋረጠባት አደጋ ለመታደግ፤ ብሎም ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንታገላለን የምንል ኃይሎች ሁሉ ያለማሰለስ ልንሰራው የሚገባን ስራችን ነው።

ይህ ግልጽ ከሆነ በኋላ ግን የህወኃት እልቂት ጋባዥ መሪዎች የሚያቀርቡት ክስ በእርግጥ እውነትነት ያለው ነው? የሚለውን ከስሜት ነጻ ሆኖ ማየትና መሞገት፤ ስለዚህም የህወሀት የአጥፍቶ መጥፋት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንዳንሆን (በተለይ ታፍኖና ሌላ ሀሳብ እንዳይሰማ የተከለከለው የትግራይ ህዝብ) መከላከል ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር በመጀመሪያ መታየት ያለበት በየት ቦታ ነው “የትግራይን ህዝብ የማጥፋት” እንቅስቃሴ አይደለም፤ ሙከራውስ የተደረገው? የሚለውን ማየት ተገቢ ነው። በቅርቡ በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው ቃለምልልስ የሰጡት ሁለቱ ቆራጥ የትግራይ ልጆች (እነወዲ ሻምበል) በቃለምልልሱ ላይ እንደተናገሩት ይህ የአሁኑ የህዝብ እንቅስቃሴ እየተደረገ ያለው በዋናነት በኦሮሞና በአማራ ክልል እንጂ በጣም ብዙሀኑ የትግራይ ህዝብ በሚኖርበት የትግራይ ክልል አይደለም። በወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ዙሪያ እንኳን እስካሁን እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ብናይ፤ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ጥያቄ እኛ በታሪካችንም ሆነ በባህላችን አማሮች ነን፤ ይህ ያማራ ማንነታችን ይታወቅልን የሚል ጥያቄ ያነገበ እንጂ ለረጅም ጊዜ አብሮን ሲኖር የነበረውና የተዋለድነው የትግራይ ብሄረሰብ ህዝብ አይደለም ይጥፋልን፤ ካካባቢያችን ይውጣልን የሚል ጥያቄ እንኳን የለውም። ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚታገሉ ሁሉም ኃይሎች (ምናልባት እዚህ ግቡ ሊባሉ የማይችሉ በጣም ጥቂት ጥግ የያዙ አክራሪዎች ካልሆኑ በስተቀር) እስከሚሰለች ድረስ ሁሌም የሚሉት ህወኃት የትግራይን ህዝብ አይወክልም፤ የትግራይ ህዝብ እንደሌላው ብሄረሰብ ሁሉ ታፍኖ የተያዘ ህዝብ ነው፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ይናፍቃል፤ ስለዚህም እንደህዝብ የለውጡ አካል ነው፤ በትግራይ ክልል እንደሌሎች ክልሎች ጎልቶ የሚታይ (እንደነ አረና ያሉ ድርጅቶች የሚያደርጉት ትግል እንደተጠበቀ ሆኖ) የህዝብ ጸረ_ህወኃት እንቅስቃሴ የማይታየው በትግራይ ያለውን መጠነ ሰፊ አፈና የሚያመለክት እንጂ የትግራይ ህዝብ ከሌላው ህዝብ የተሻለ ደልቶት ወይንም የመብት መከበር ስላገኘ አይደለም ነው የሚሉት። በሌላ አነጋገር የዴሞክራሲ ትግሉ ኃይሎች በጣም አብዛኛው አቋም፤ እንደነሳሞራ ያሉ የህወሀት አላዋቂና ዘራፊ መሪዎች የሚሉትን “ህወሀት ማለት የትግራይ ህዝብ ማለት ነው፤ ህወሀት ከጠፋች የትግራይ ህዝብ ይጠፋል…ወዘተ” የሚል ቀጣፊና ጸረ_የትግራይ ህዝብ ንግግር ፍጹም በመጻረር፤ ህወሀት ከትግራይ ህዝብ አብራክ የወጣ ጭንጋፍ የዘራፊዎች ቡድን እንጂ በፍጹም የትግራይን ህዝብ የማይወክል ሀይል እንደሆነ ነው።

በየትኛውም ክልል በሚደረገው ህዝባዊ ትግል ህወሀት/ኢህአዴግን ባጠቃላይ፤ ህወሀት በመንግሥት ስርዓቱ ላይ ባለው ትልቅ ሚና ደግሞ በተለይ፤ ይወገዝና ከጫንቃችን ይውረድልን የሚል ካልሆነ በቀር የትግራይን ህዝብ ያጠቃለለ አንድ መፈክር እንኳን ታይቶ አይታወቅም። የሰላም ባስ ሲቃጠል ድርጊቱ ያነጣጠረው በህወሀት የማፍያ የዝርፊያ ቡድን ላይ እንጂ በፍጹም በትግራይ ህዝብ ላይ አይደለም፤ ልክ በባህርዳር የዳሽን ቢራ ማከፋፈያ ሲቃጠል ያነጣጠረው የብአዴን ዘራፊዎች ላይ እንጂ እሱ እወክለዋለሁ የሚለውን የአማራውን ህዝብ እንዳልሆነ ሁሉ። ከእንደዚህ አይነት እርምጃዎች ባሻገር በዚህ በአሁኑ የትግል ሂደት “የዘር ማጥፋት እርምጃ” ማስረጃ ተብሎ የሚቀርበው በተወሰኑ የትግራይ ባለሀብት ግለሰብ ንብረቶች ላይ በተለይ በጎንደር ተወሰዱ የተባሉ እርምጃዎች ናቸው። ምንም እንኳን በጎንደር በነበረው እንቅስቃሴ ላይ የተሳተፉ ወገኖች በሰጧቸው ቃለመጠይቆች እንደሚሉት ተጠቁ የሚባሉት ንብረቶች የትግራይ ባለሀብቶች ስለሆኑ ሳይሆን እነኝህ ሰዎች በቀጥታ የህወሀት ወኪሎች የሆኑና ባካባቢው ከህወሀት የስለላ አካሎች ጋር በቅርብ የሚሰሩ ሰዎች ስለሆኑ ነው፤ እንጂማ የትግራይ ባለሀብቶችን ትግራዋይ ስለሆኑ ብቻ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ ታስቦ ቢሆን፤ ከነኝህ ንብረቶችም ለማውደም እጅግ ይቀሉ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ባለሀብቶች ንብረቶች በጎንደር ዙሪያ ሞልተው አልነበር ወይ? ባካባቢያችን አብረው ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ በአንድ ሲቪል ሰው እንኳን የደረሰ ጉዳት አለ ወይ? የሚለው መከራከሪያ ምክንያታዊ ቢሆንም፤ ቢያንስ እንደ ህወሀት ላሉ (ሌሎችም አክራሪ ቡድኖች) እኩይ ሀይሎች መጠቀሚያ እንዳይሆን እንዲህ አይነቱ እርምጃ ከትግሉ አንጻር ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን በፍጹም መወሰድ የሌለበት ነውና መታረም ያለበት መሆኑን መቀበል ይገባል። ያም ሆኖ ግን እነኝህ እርምጃዎች በምን ሂሳብ ነው የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴ የሚሆኑት? ልክ በጊዜው የህወሀት ታጣቂ በነበሩት በአቶ ኑር ሁሴን ላይ የድብደባ እርምጃ የወሰዱ ወጣቶች (በፍርድ ቤት በቀረበው ማስረጃ ዱላው መሳሪያ ለመቀማት ይሁን ለምን ባይታወቅም እሳቸውን ከዱላው ያስጣሏቸው ያካባቢው ወጣቶች የቅንጅት ደጋፊዎች ተብለው በዘር ማጥፋት የተከሰሱት ናቸው) ለዝርፊያ ብለው ይሁን በወጣትነት እድሜ በስሜት ተገፋፍተው እንዲህ አይነት እርምጃ ቢወስዱ እንዴት ነው ይህ የዘር ማጥፋት ስራ የሚሆነው? ጥቂት በትዕቢት የተወጠሩ የትግራይ ወጣቶች ቡና ቤት ውስጥ እየጠጡ ባካባቢያቸው ያሉትን ሌሎች ደንበኞች አላስቆም አላስቀምጥ ቢሉና በዚህ ድርጊት ከተበሳጩት ሌሎች ደንበኞች ጋር (ባጋጣሚ ትግራዋይ ያልሆኑ) ድብድብ ቢገጥሙ እንዴት ነው ይህ ግጭት ጥቂት የጠገቡ ወጣቶች የተነኮሱት ግጭት መሆኑ ቀርቶ የዘር ግጭት የሚሆነው?

ያንድ ሀገር ሰው፤ ያውም ህዝብን ለማስተዳደር በጉልበት እንኳን ቢሆን ስልጣን ላይ ያለ ኃይል፤ አይደለም ያልሆነ የውሸት ድራማ ፈጥሮ የሌለ የህዝብ ለህዝብ ጸብ ሊጭር፤ ህዝብን ከህዝብ ሊያባላ የሚችል ነገር እንኳን ቢፈጠር ክስተቱን የግለሰብ ጠቦች አድርጎ አለስልሶ ለማለፍ መሞከርና ባይሆን ክስተቱን የፈጸሙት ሰዎች ላይ ጠንካራ እርምጃ ወስዶ እንዲህ አይነት ክስተት ዳግም እንዳይፈጠር መከላከል ነው እንጂ የሚጠበቅበት እንዴት እንዲህ አይነቶችን ግጭቶች የዘር ግጭት እንዲሆኑ ለማባባስ ተግቶ ይሰራል? (ድሮ ትዝ ይለኛል ለጥምቀት በዓል ጊዜ በጭፈራ ወቅት የተለያዩ የብሄረሰብ ጭፈራዎች ሲደረጉ የጭፈራው ስሜት የሚፈጥራቸው የብሄረሰብ ግጭቶች ይከሰቱ ነበር። እነኝህ ግን ከጭፈራው ጋር የተገናኙ የወጣቶች የደም ትኩሳት የፈጠራቸው ክስተቶች ሆነው እዚያው ባካባቢው ፖሊስ ያልቃሉ። ለሚዲያ ፍጆታ እንኳን አይቀርቡም ነበር እንኳን እንደ ዘላቂ የብሄሮች የመጠፋፋት ጠላትነት ሆነው በመንግሥት መገናኛ ብዙሀንና በመንግስት ባለስልጣናት ለሚዲያ ፍጆታ ሊውሉ)። ይህን አይነቱን በፍጹም ሀላፊነት የጎደለው አካሄድ ነው እንግዲህ የህወሀት ጀሌዎች ከሰሞኑ ስራችን ብለው የተያያዙት።

ይህንን የሰሞኑን ሟርት ግን በምርጫ 97 ጊዜ ከተጠቀሙበት ሁኔታ የሚለያቸው ሁለት ወሳኝ ነገሮች አሉ። በምርጫ 97 ጊዜ ይህ ፕሮፓጋንዳቸው ያነጣጠረው ቅንጅት የሚባል በምርጫ ያሸነፋቸው አንድ የፖለቲካ ድርጅት ላይ ነበር። ብዙው የግጭቱ ክስተትም የነበረው በትላልቅ ከተሞችና ከህወሀት/ኢህአዴግ የአፈና ኃይሎች ውጭ ምንም ባልታጠቁ ሰዎች ላይ ነበር። ያሁኑን አካሄዳቸውን ግን ፍጹም አደገኛ የሚያደርገው አንድም ትግሉ በራሱ በህዝቡ የሚመራና በነኝህ ክልሎች ውስጥ ያሉትን በጣም አብዛኛውን ህዝብ ያሳተፈ መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ የህወሀትን የፕሮፓጋንዳና የማጥፋት ዘመቻ ባንድ ድርጅት ላይ ሳይሆን በየክልሎቹ ባለው ህዝብ ላይ ያነጣጠረ እንዲሆን ያደርገዋል። ሁለተኛው ይህ የህዝብ እንቅስቃሴ የሚካሄደው በከተሞችም በገጠሮችም ስለሆነና በተለይ በገጠር ያለው ህዝብ (በተለይ በሰሜኑ ያገራችን ክፍል) በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የታጠቀ ስለሆነ እንደ 97ቱ ዝም ብሎ የሚገደል ሳይሆን በጎንደር እንዳየነው እራሱን በመሳሪያ ኃይልም ቢሆን ለመከላከል የተዘጋጀ ህዝብ መሆኑ ነው። ይህ አዲስ ሁኔታ የህወሀትን አጥፊ ፕሮፓጋንዳ ሰፊ ውጤት የሌለውና እንደ ምርጫ 97ቱ ጊዜ ለህወሀት የፖለቲካ ጥቅም በማስገኘት (የትግራይን ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ) ብቻ ይደመደማል ማለት በእሳት ላይ የሚጫወት ህጻን ልጅ የሚያደርገው አይነት የጨቅላነት አለማወቅ ነው። ወይም ደግሞ የህወሀት አይነት ስልጣኑን ቢያጣ ከሚያጣው ዝርፊያ በቀር ለሀገርና ለህዝብ ምንም ደንታ የሌለው የማፍያ ቡድን የሚሰራው፤ ለማጥፋት ያለውን ኃይል ውጤቱ ምንም ይሁን ምን እስከመጨረሻው ለመጠቀም ቅንጣት ታክል ሀፍረት የሌለው በአደገኛ ተስፋ መቁረጥና በህዝብና በሀገር ላይ የሚደረግ ግዴለሽ የቁማር ጫወታ ነው። ለዚህ ነው ይህንን ያሁኑን የጥፋት መንገዳቸውን በምንም አይነት መንገድ ባስቸኳይ ማስቆም የሚኖርብን።

እንዴት ነው ይህንን የህወሀት ቁማር ሃገራችንን ሳያጠፋት የምናስቆመው? ዴምህትም ሆነ የህወሀትን ምንነት የተረዱ የትግራይ ድርጅቶችስ ምን ይጠበቅባቸዋል?

ይህንን የህወሀት አጥፊ መንገድ እንዴት ነው የምንከላከለው የሚለው ለአንድ ወገን የሚቀርብ ጥያቄ ሳይሆን ሁላችንንም እንቅልፍ ሊነሳ የሚገባና በከንፈር መምጠጥ ሳይሆን በተግባር ልንቋቋመው የሚገባን የጊዜው ችግር ነው። በመጀመሪያ ለወያኔዎች ግልጽ ሊሆን የሚገባው አሁን ህዝቡ የገባበት ትግል በምንም አይነት የጥፋት ሟርት ተታሎ የሚተወው ሳይሆን እስከ ነጻነት ድረስ የሚገፋበት መሆኑን ነው። ይህ የማስፈራራት ጫወታ የተበላ እቁብ ነውና በዚህ የሚቆም ትግል የለም። ይህ ግልጽ ከሆነ በኋላ ግን ለፍትህ፤ ሀገርን ለማዳንና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚታገሉ ኃይሎች በሙሉ የፍትህ ትግሉ ያልሆነ አቅጣጫ እንዳይይዝ በሚያደርጓቸው የፕሮፓጋንዳ ስራዎችም ሆነ በተግባራዊ ትግሉ ወቅት ማድረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄ ከላይ በትንሹ ጠቅሼዋለሁ። ዛሬ ይህን ንግግር የማደርገው ባብዛኛው የትግራይ ታጋዮች በሚገኙበት ስብሰባ እንደመሆኑና፤ ይህ ህወሀት ከስልጣኔ ይታደገኛል ብሎ እንዲፈጠር የሚፈልገው ግጭት ከሌሎቻችንም በላይ በስሜት አጣብቂኝ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ብዬ ከማስባቸው የትግል ጓዶቻችን ጋር ስለሆነ (ከዚህ በፊት ካደረግናቸው ውይይቶች ይህንን የስሜት ጭንቀት ስለታዘብኩ) ሃሳቤን በተለይ የትግራይ ወገኖቻችንን በተመለከተና በተለይም ዴምህት ላይ ያለውን ሀላፊነት አጽንኦት ለመስጠት በዚያ ላይ ብቻ አተኩሬ፤ ከዚህም በላይ ሳላሰላቻችሁ እንዲሁም የረዘመው ንግግሬን በቶሎ ልቋጭ።

በዘር ማንነታቸው የትግራይ ብሄረሰብ አባላት ሆነው ህወሀትን የሚቃወሙና በተቻላቸው መጠንና በተለያየ የትግል ዘዴ፤ አንዳንዴ በግለሰብ ደረጃ በሌላ ጊዜ ደግሞ በተደራጀ መልክ፤ ሲመቻቸውና ሁኔታው ሲፈቅድላቸው እራሳቸውን በትግራይ ብሄረሰብ ዙሪያ ባጠነጠኑ ድርጅቶች ሌላ ጊዜ ደግሞ በህብረ ብሄራዊ ድርጅት ውስጥ በመሆን ሥርዓቱን የታገሉ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ህወሀት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እንደነበሩና አሁንም እንዳሉ ይታወቃል። ቀድሞ ህወሀት ውስጥ ሲታገሉ የነበሩና እንዲያውም ባመራር ደረጃ ሲሰሩ የነበሩ እንደነ አረጋዊ በርሄ፤ ግደይ ዘራጽዮን፤ ገብረመድህን አርአያ፤ ተስፋዬ ቼንቶ…ወዘተ ያሉ አሁን ድረስ ህወሀትን የሚታገሉ ታጋዮች እንዳሉ ይታወቃል። እንደዚህ በሚዲያ ከሚታወቁት ውጭ በጣም ብዙም ባይባሉ ሌሎችም የቀድሞ የህወሀት ታጋዮች አሁን ግን በውጭ ሀገር ከዴሞክራሲ ትግሉ ጋር አብረው ያሉ እንዳሉ እናውቃለን። ህወሀት ከተመሰረተ ጀምሮ ያቀነቅን የነበረው ብሄር ተኮር ትግል ስለማይጥማቸው ህብረ ብሄራዊ ትግል ውስጥ (በተለይ በኢህአፓና ኢህአሰ ውስጥ) ገብተው ከከፍተኛ ያመራር ቦታዎች ጀምሮ እስከ ተራ አባልና ታጋይ ድረስ ሲታገሉ የወደቁ ብዙ የትግራይ ጓዶቻችን እንደነበሩ በጊዜው የነበርነው እናውቃለን፤ ስለ ብዛቱ ባላውቅም አሁንም እንኳን በኢህአፓ ውስጥ ያሉ የትግራይ ልጆች እንዳሉ አውቃለሁ። ህወሀት/ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላም ቁጥራቸው እየቀነሰ ቢሄድም በህብረ ብሄራዊ ድርጅት ውስጥ ሆነን ነው ለዴሞክራሲ የምንታገለው ብለው እንደነ ዶ/ር ሃይሉ አርአያ፤ ሸዋዬ ኪሮስ፣ አስራት አብርሃ ያሉ የህወሀት ዘረኝ ቅስቀሳ ሳይበግራቸው ቀድሞ ቅንጅት በኋላም አንድነት ጋር ሆነው ለአላማቸው ጸንተው የቆሙ ምርጥ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ልጆች አሉ። ከኔ በስተቀር ሌላ ትግራዋይ ድርጅት ሊኖር አይችልም ብሎ ህወሀት ፍጹም ጠርንፎ በያዘው በትግራይ ክልል እንኳን “ጸረ_ትግራዋይ” ፤ “የትምክህተኞች መሳሪያ” እየተባሉ፤ ከማህበረሰቡ እንዲነጠሉ እየተደረጉ ጥርሳቸውን ነክሰው ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እንታገላለን ብለው ህይወት እየገበሩም በአረና ስር ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ትግራውያን አሉ። በድርጅት ባይታቀፉም እንኳን ይህንን የህወሀት መሰሪ አካሄድ ቀደም ብለው ተገንዝበው ከቅድም ጀምረው ህወሀትን ሲያጋልጡና ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ሽንጣቸውን ገትረው እስከአሁን የሚከራከሩ እንደነ ዶ/ር ግደይ አይነት እውቅ ምሁራንም አሉ። የህወሀት ሁሉን ጠርንፎ የመያዝ አባዜ በተለይ ትግራዋይ የሆኑ ተቃዋሚዎቹን ከሌሎቹም በላይ እንደሚጠላ፤ በዘር ሀረጋቸው “ትምክህተኛ” ሊላቸው የማይችል ከትግራይ አብራክ የወጡ ልጆቹን ዘረኛ አካሄዱን ስለሚያጋልጡበት ከፍተኛ ማህበራዊና ቤተሰባዊ መገለል እንደሚያደርስባቸው ይታወቃል። ለዚህም ነው በዚህ ከባድ ፈተና ላይም ሆነው ለአላማ ሲሉ ህወሀትን የሚቃወሙ የትግራይ ወገኖችን፤ ህወሀት በትግራይ ህዝብ ስም በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ካለው መከራ አንጻር በቁጥር በቂ ናቸው ማለት እንኳን ባይቻል፤ የነኝህን ቆራጥ ወገኖች ወኔ የምናደንቀው። የህወሀትን ሰይጣናዊ ተግባር ለማርከስ ግን ከነኝህ ወገኖቻችን ከዚህም በላይ ብንጠብቅ ተገቢ ነው። በተለይም ደግሞ ብዙሀኑ የትግራይ ምሁራን ይህ ድርጅት የሚያደርሰውን አደጋ እያዩ ህወሀትን ባይደግፉም እንኳን ዝም ብለው ከዳር ቆመው ማየታቸው ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። የሚሰራው ወንጀል በስማቸው ስለሆነ ቢያንስ በስማችን እንደዚህ አትነግድ፤ እናንተ በስልጣን ማማ ላይ ሆናችሁ ስለዘረፋችሁ ሁሉም ትግራይን የሚወክል ጥቅም አስመስላችሁ ማህበረሰባችንን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር አታጣሉት ብለው ደፍረው መናገራቸው ከሞራል ሀላፊነት አንጻር አስፈላጊ ነው ብቻ ሳይሆን ህወሀትን ለማረቅም ያለው አቅም በቀላሉ የሚታይ አይሆንም።

በእርግጥም በቅርብ ጊዜ ይህ የህወሀት አደገኛ አካሄድ እያሳሰባቸው ድምጻቸውን የሚያሰሙ ትግራውያን እየተበራከቱ መጥተዋል። ለምሳሌ በውጭ የሚገኙ 16 ታዋቂ የትግራይ ምሁራን ያወጡት መግለጫ፤ ወይም እንደ ሲራክ አማረ (ወዲ ሻምበል) ና ጥላሁን ወልደስላሴ አይነቱ በግልጽ በኢሳት ላይ ወጥተው እንዳደረጉት ይህንን የህወሀት አካሄድ የሚያወግዙ ንግግሮች በማድረግ ህወሀት የትግራይን ህዝብ ለዚህ እኩይ ተግባሩ ለማሰለፍ የሚያደርገውን ሙከራ ለማክሸፍ የሚያደርጉት ሙከራ አበረታች ነው። ይህ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለሙሉ ተስፋ ነኝ። ይህ ግን በፍጹም በቂ አይደለም። ከትግራይ ምሁራን ወገኖቻችንና ለኢትዮጵያ በጎ ከሚመኙ ትግራዋይ ወገኖቻችን ከዚህም በላይ ብንጠብቅ ተገቢ ነው። በነጻነትና በእኩልነት ታጋዮች በኩል ደግሞ እንዲህ አይነት ወገኖቻችንን ማበረታታት፤ መቅረብና አብረውን እንዲሰሩ ማድረግ፤ በረጅም ጊዜ የህወሀት ፕሮፓጋንዳ ምክንያት፤ ወይንም ደግሞ ባንዳንድ አክራሪ ኃይሎች አካባቢ በሚሰሙት የጥላቻ ወሬ ተወናብደው በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ ይዘውት ያሉት ጥርጣሬ ካለ ጥርጣሬውን ለመግፈፍ ቀርቦ መወያየትና የትግሉን እውነተኛ ኢላማ ማስረዳት ይጠበቅብናል። የህወኃትን የጥላቻ መርዝ ለማርከስ እጅግ ያስፈልጉናልና! ተግባር ከብዙ ቃላት በላይ ይናገራልና በዚያው ልክ ደግሞ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚደረገው ህዝባዊ ትግልና አመጽ ከህወኃት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ንጹሀንና ሰላማዊ የትግራይ ወገኖቻችንን እንዳይነካ መጠንቀቅና በስህተት እንኳን እንዲህ አይነት ክስተት ከተፈጸመ አጥብቆ በማውገዝ ትግሉ ሁሉንም የሀገሪቱን ህዝቦች (በህወሀት መዳፍ ስር እየማቀቀ ያለውን የትግራይ ህዝብን ጨምሮ) ነጻ ለማውጣት የሚደረግ ትግል መሆኑን ያለማሰለስ ለህዝቡ ማስረዳት ነው በትግሉ ደጋፊዎችና መሪዎች በመደጋገም እንዲሰራ የሚጠበቀው።

ዴምህት አሁን በሀገሪቱ በተፈጠረው ውጥረት ላይ ሊጫወት የሚችለው ልዩ ታሪካዊና ገንቢ ሚና

ስለሌሎች የትግራይ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሚና ባጭሩ ይህን ያክል ካልኩ ዴምህትን በተመለከተ አንድ ሁለት ነገሮች ብዬ ላብቃ። ዴምህት ህወሀትን ከሚቃወሙት ከሌሎቹም የትግራይ ድርጅቶች በላይ ያለበት ሁኔታ በህወሀቶች ዘንድ የማይወደድ መሆኑ ይታወቃል። የህወሀትን መስመር ከስሩ የሚቃወም ድርጅት ብቻ ሳይሆን፤ ከሌሎችም በተለየ ይህ መሰሪ ስርዓት በአመጽ ካልሆነ እንደማይንበረከክ አምኖ የትጥቅ ትግል የጀመረ ድርጅት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ይህን ትግሉን ለማድረግ ህወሀቶች “የትግራይ ዋና ጠላት” ብለው ከሚፈርጁት የኤርትራ መንግሥት እርዳታ ይቀበላል መባሉ በራሱ ለህወሀት ድርብ ጠላት ያደርገዋል። ከዚያም በላይ ግን በኤርትራ በመታገዙ ምክንያት ብቻ የህወሀት ተቃዋሚ በሆኑት የትግራይ ተወላጆችም እንኳን በጥርጣሬ አይን ነው የሚታየው። ይህ ለዴምህት አካሄድ እንደ ተግዳሮት የሚታይ ቢሆንም፤ ዴምህት ያለበት ሁኔታ ደግሞ የወያኔን መሰሪና መርዛማ አካሄድ ለማርከስ የሚያስችል የተለየ ቦታ ላይ ያስቀምጠዋል። ያለ ምንም ማጋነን ህወሀትን የሚቃወሙ፤ ብዙ ጠንካራ ታጋይ የትግራይ ልጆች ባንድ ላይ የተሰባሰቡበትና የህወሀትን መሰሪ አካሄድ በኃይል ለመቋቋምም የሚያስችል አቅምና ፍላጎት ያለው ብቸኛ ድርጅት ዴምህት ነው ማለት ይቻላል። ስለዚህም በነጻነት ትግሉ ሂደት ከፍተኛ ሚና መጫወት የሚችል ድርጅት ነው። ያለበት ቦታ ደግሞ ልክ እንደሱ ለነጻነት የሚታገሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ያሉበት አካባቢ ስለሆነ በስማ በለው ሳይሆን ከነኝህ ድርጅቶች ጋር በቅርበት በመገናኘት ስለጋራ ትግሉ መምከር፤ መወያየት፤ አልፎም በጋራ አብሮ ለመታገል የሚያስችለው ሁኔታ ላይ ይገኛል። አብዛኛው የትግራይ ህዝብ በህወኃት አፈና ተለጉሞ በዴሞክራሲ ትግሉ ላይ እንደሌሎች ክልሎች በጣም በግልጽ የሚታይ አጋርነት ማሳየት ለጊዜው ባልቻለበት በአሁኑ ሁኔታና፤ ህወኃቶች ሆን ብለው ህዝቡን ከህዝብ ጋር ለማጋጨት ፕሮፓጋንዳ በሚያናፍሱበት በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ፤ እንዲሁም በአጋዚ ጦር በየቀኑ የሚያልቀው የአማራና የኦሮሞ ህዝብ የህወሀት/ኢህአዴግን ጦር በአብዛኛው የሚመሩትን የህወኃት መኮንኖች እያየ ልቡ ሲያዝንና ስሜቱ ሲጨነቅ፤ እንዲህ ያለ ትልቅ የትግራውያን ድርጅት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆኖ ለነጻነትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሲዋደቅ ሲያይ፤ በትግሉ ውስጥ ለሚሳተፈው ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰጠው የአጋርነትና የአለኝታነት ስሜት ከትግሉ ወቅትም ባለፈ ለምትፈጠረዋ የጋራ ሀገር ትልቅ አንድምታ ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። አፉ በህወሀት ጥርነፋና አፈና ለተዘጋው የትግራይ ህዝብም፤ ከሚወደው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በዘላቂ ክር ከሚያስተሳስረው ባህሉና ታሪኩ ባልተናነሰ ላለፉት 25 አመታት ከአብራኩ የወጡት መሰሪ ልጆቹ በሚወዳት ሀገሩ ላይ ያዘነቡበትን መከራ እያየ የሚያዘነውን ያክል ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆነው ሀገራቸውን ለመታደግ በሚወድቁት ልጆቹ ክፉኛ እንደሚኮራ ጥርጥር የለኝም። ከዚህ አንጻር ዴምህት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆኖ ለነጻነት፤ ለእኩልነትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያደርገው ትግል ለትግራይም ህዝብ ትልቅ ቤዛ እንደሚሆን ነው የሚሰማኝ።

በመጨረሻ ማለት የምፈልገው እኛ እንደ አርበኞች ግንቦት 7 ዴምህት ይህን ውስጣዊ መርሁ አድርጎ ለሚያደርገው ትግል በምንችለው አቅም ሁሉ ለመርዳት ከጎኑ መሆናችንንና፤ ዝግጁ ነኝ በሚልበት ጊዜም ከዚህ በፊት ጀምረን የነበርነውንና በሞላ መክዳት ምክንያት ተግባራዊነቱ የተስተጓጎለውን ትብብር እንደገና ለማስነሳትም ሆነ በሌላ በማንኛውም መልኩ ተባብረን፤ ሀገራችንን ከገጠማት አደጋ ለማውጣት ባስቸኳይነት ስሜት ለመታገል ያለንን ፍላጎት በዚህ አጋጣሚ እንደገና መግለጽ እፈልጋለሁ። እንዲህ አይነት ትብብር ሲፈጠር ደግሞ ጊዜያዊ ለሆነና ያጭር ጊዜ የሀይል ሚዛንን ባሰላ ስሌት፤ ወይንም ደግሞ ዝም ብሎ ህወሀት/ኢህአዴግን ለማስወገድ ብቻ ባለመ የስልት አሰላለፍ ሳይሆን፤ በጥርጣሬ አይን እየተያየንና እንደማይተማመን ባልንጀራ አንዳችን ያንዳችንን የውስጥ ግፊት በመጠየቅ ሳይሆን፤ ያችን ሁላችንም እንድትፈጠር የምንፈልጋትን ለሁላችንም እኩል የሆነች እውነተኛ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ማቆምን ግቡ ያደረገና በዚህ ጠንካራ አለት ላይ የቆመ የውስጥ መተማመን ያለበት ስትራቴጂካዊ ትብብር ማድረግን ኢላማው ያደረገ ትብብር እንዲሆን ያለንን ተስፋ በአጽንኦት እገልጻለሁ።
የወያኔን መሰሪ አካሄድ በጋራ እንመክት!
አንድነት ኃይል ነው

የታሪክ ሂደት ርቃናችንን እንዳያስቀረን፣ –ይገረም አለሙ

$
0
0

shimeles-book-satenaw-newsገና እንደባተ ተዋቂ ኢትዮጵያውያንን በተከታታይ ነጥቆ ሀዘን ያስቀመጠን የተሰናበተው  የግፍ ዓመት ሊባል የሚችለው 2008 ዓም   የሞት መርዶ፣  የእስር እንግልትና ስቃይ ዜና ሳይለየው ከል እንዳለበሰን ነው ወደ 2009 ዓም ያሸጋገረን፡፡ ፈጣሪ በቃችሁ ካላለን በስተቀር የ2009 ዓ.ም አጀማመርም አስፈሪ ነው፡፡

በ2008 መባቻ በሞት ከተለዩን ሰዎች አንዱ ዶ/ር ሽመልስ  ተክለጻድቅ  በዚህ ሳምንት ሙት አመታቸው ሲታሰብ በተለያየ ግዜ ከአስነበቡን ጽሁፎች መካከል ግዜ የማይሽራቸው ተሰባስበው  “የመብትና የነጻነት ጥያቄ በኢትዮጵያ  በሚል ርእስ የታተመ  መጽሀፍ ተመርቋል፡፡   በ1990ዎቹ መጀመሪያ ግድም የጻፉትና በመጽሀፉ የተካተተው  አንድ  ጽሁፍ ውስጥ ዛሬ የተጻፈ የሚመስል የእኛን ሁኔታ የሚገልጽ እንዲህ የሚል የጸሀፊው ስጋት  ይገኛል፡፡

“የትውልድን ርቀት በፍጡራዊ አስገዳጅነት ገጽታው ብናየው የሰላሳ ዓመት ገደማ ልዩነት ባላቸው አያት፣ እናት/አባት፣ልጅ በሚል ሶስት የዕድሜ ክልል ተለይቶ ይገኛል፡ ይኸን የዕድሜና የኑሮአቸውን ሁኔታ ተንተርሶ ለነዋሪዎቹ የተለያየ ትኩረትና ግንዛቤ ቢሰጣቸው አያስገርምም፡፡ እንዲያውም የሚገርመው ልዩነት ባይኖር ነው፡ የጉዳዩን ቁም ነገር አቀለልከው ባትሉኝ አያት ያለፈውን ፣እናት/አባት የጊዜውን ፣ልጅ ደግሞ የወደፊቱን የበለጠ ያስቡታል፣ ትኩረት ይሰጡታል  ቢባል ግንዛቤው እምብዛም ከሀቁ አይርቅም፡፡

በትውልድ ልዩነትና መራራቅ ላይ በሚከሰት የኢኮኖሚ አቅም፣ በቤተሰብና ማሕበራዊ ኑሮ ላይ የተመሰረተ የተለያየ ደረጃ ላይ በመገኘት መንስዔነት በፖለቲካ ግንዛቤና አመለካከት ፣የምርጫ ዝንባሌ ዜጎች እንደሚለያዩ እነዚህ ጉዳዮች በመረጃ የተደገፈ ጥናትና ታሪክ ያላቸው አገሮች ተሞክሮ በግልጽ ያሳያል፡፡

የሦስቱን ትውልድ ያቀፈ ቤተሰብ በጸጋ የሚኖረው የሦስቱንም ፍላጎት፣ትኩረትና አመለካከት አዛምዶ ሲያቅፍ ነው፡፡ እንዲሁም አንደማንኛውም ግለሰብና ቤተሰብ ፣ሕብረተሰብም ያለፈውን ከጊዜው ጋር አገናዝቦ የወደፊቱን አልሞና ተልሞ መኖር ካልቻለ ብዙ ችግር እንደሚገጥመው እሙን ነው፡፡

እኛም ዛሬ በሀገራችን መካሪ አያት እንደሌለው አልባሌ ልቅ ሰው ፣ካለፈው ትውልድና ታሪክ ጋር ክህደት ላይ በተመሰረተ ጥል ስንናቆር፣ልጅ እንደሌለውና እኔ ከሞትኩ.. እንዳለችው  አህያ ሊገጥመን የሚችል የወደፊት የከፋ ችግር ከመከላከል ወይም ቢያንስ ተዘጋጅቶ ከመጠበቅ ይልቅ ጊዜው የሚያቀርብልንን ያላመረትነውን ስንቃርም በሱም ስንብለጨለጭ የታሪክ ሂደት ርቃናችንን እንዳያስቀረን ያሰጋል፡፡ ” ይህ 15 ዓመት ገደማ ያለፈው ጽሁፍ የያዘው መልእክት ዛሬም ወቅታዊ ነው፡፡ ምን አልባት ነገ ከነገ ወዲያም እንዲሁ፡፡

ህዝቡ የወያኔን አገዛዝ የተሸከመበት ጫንቃው ተልጦ፣ ከአገዛዝ ይገላግሉኛል ብሎ ተሰፋ ባሳደረባቸው ተቀዋሚ ፖለቲከኞች  ተስፋ ቆርጦ ራሱን በራሱ አደራጅቶ ነጻነት ወይንም ሞት ብሎ በጀመረው ትግል መስዋእትነት እየከፈለ ባለበት፣ ይህን የህዝብ ተቃውሞ በሀይል ለመጨፍለቅ አቶ ሀይለማሪም ደሳለኝ ሰራዊቱን ማዘዛቸውን በእብሪት በገለጹበትና ትእዛዙ ተግባራዊ ሆኖ ዜጎች በየቀኑ በገፍ እየተገደሉ ባሉበት ወቅት ከወያኔ በተቃራኒ ያለን ዜጎች  በትናንት መነታረኩን ትተን ፤የየግል ጉዳያችንን ቁረሾአችንና ድብቅ አጀንዳችንን ወደ ጎን ብለን  ስለ ነገ ተጨንቀን በአንድ ለመነሳት አልቻልንም፡፡

ግድያ እስርና ስቃይ ለአንድ ዓመት ያህል የእለት ተእለት ዜና ሆኖ ሕዝቡ በዚህ ሳይረታ ደረቱን ለወያኔ ገዳዩች አረር ሰጥቶ ሞትን ንቆ፣ ነጻነቱን ሽቶ መስዋእትነት ሲከፍል፣ከሀገሩ እርቆ በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በየሚኖርበት ሀገር በአንድነት  ተነስቶ ብርድና ሀሩር ዝናብና ጸሀይ ሳይል ተቃውሞውን ሲያሰማ፣ የፖለቲካ ድርጅት ነን ባዮች ከየጓዳቸው ሆነው መግለጫ ከማወጣት ሊያልፉ አልቻሉም፡፡ ዶ/ር ሽመልስ ከ15 ዓመት በፊት “ካለፈው ትውልድና ታሪክ ጋር ክህደት ላይ በተመሰረተ ጥል ስንናቆር” በማለት የገለጹት ልዩነት በህዝቡ አንድነት  በተወሰነ ደረጃ ቢረግብም በፖለቲከኞቹና ምሁራኖቹ ዘንድ ግን ዛሬም እንዳለ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ  በአደረጃጀት የተለያዩት ቀርቶ የአንድ ብሄር ስም ይዘው የተደራጁት እንኳን ወደ አንድነት መምጣቱ ቀርቶ በጋራ ለመታገል አልሆነላቸውም፡፡

ወያኔ ያለርህራሄ  እየገደለ እያሰረና እያሰቃየ ሥልጣኑን ለማቆየት በሚያደርገው ጥረት እስካሁን ከሆነው የወደፊቱ ሊከፋ እንደሚችል በጉልህ እየታየ ባለበት በዚህ ወቅት በተቃውሞው ጎራ ወቅቱን የሚመጥን ተግባር እየታየ አይደለም፡፡ ወያኔ እያደረሰ ያለውን አደጋ በመከላከልና ትግሉን  በማጠናከር ለድል የሚበቃበትን ስራ መስራትና ከድል በኋላ በኢትዮጵያ እውን ሊሆን ስለሚገባው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ቅድመ ዝግጅት ማድረግ  ከተቃውሞው ሰፈር የሚጠበቅ ወቅታዊ ተግባር ቢሆንም ዛሬም ከአንድ ሰሞን ጩኸትና መግለጫ ያለፈ ተግባር ማየት አልተቻለም፡፡ ይህም  “ልጅ እንደሌለውና እኔ ከሞትኩ.. እንዳለችው  አህያ ሊገጥመን የሚችል የወደፊት የከፋ ችግር ከመከላከል ወይም ቢያንስ ተዘጋጅቶ ከመጠበቅ ይልቅ ጊዜው የሚያቀርብልንን ያላመረትነውን ስንቃርም በሱም ስንብለጨለጭ የታሪክ ሂደት ርቃናችንን እንዳያስቀረን ያሰጋል፡፡” በማለት ዶ/ር ሽመልስ ከ15 ዓመት በፊት ከገለጹት ስጋት ዛሬም ያልተላቀቅን መሆናችንን ነው የሚያሳየው፡፡ ከዚህ ለመውጣት ስንት ዓመት ይሆን የሚያስፈልገን?   የስንት ሰው ህይወትስ ነው  መጥፋት ያለበት?  የወያኔ አረመኔያዊ ተግባርስ ከምን ደረጃ መድረስ አለበት? እያዳንዱ ፓለቲከኛስ ምን ሲያገኝ ወይንም እንደሚያገኝ ርግጠኛ ሲሆን ይሁን የሚተባበረው?

ትናንትን ስናስብ በቀዳሚነት  ሊያሳስበን የሚገባው ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለቀው ትግል ለመስዋዕትነት እንጂ ለድል ያልበቃው ለምንድን ነው? ዓላማውን ትግራይን ነጻ ማውጣት አደርጎ የተነሳው ኃይል እንዴት ኢትዮጵያ ቤተ መንግሥት ሊደርስ ቻለ ?ስሙን እንኳን ሳይቀይር ነጻ አውጪ እንደተባለ በአምባገነንነት ሀያ አምስት አመት ለመግዛት የመቻሉ ምስጢርስ ምንድን ነው? ወዘተ የሚለው ሆኖ ሳለ እኛ የምናስበው የታሪካችን መጥፎ ገጽታዎችን መመዘዝና ማጉላትን ነው፡፡ ወያኔዎች  ግን ስለትናንት የሚያስቡት ከመቶ አመት በፊት ርቀው በመሄድ  በዮሀንስ እጅ የነበረ የትግሬ ሥልጣን በማን እንዴት ለምንና በምን ሁኔታ እንደተነጠቀ፣ እንዴት እንዳስመለሱትና ያ ስለማይደገምበት ነው፡፡

በተቃውሞው ጎራ ስለ ነገ መታሰብ የነበረበት ወያኔ ስልጣኑን ለማቆየት የሚፈጽመውን  አደጋ ስለመከላከል፤  እኔ ካልኖርኩ በማለት ስልጣኑን ቢያጣ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያቀደው ሴራ  ተግባራዊ እንዳይሆን ስለ ማድረግ፣ አደጋን በቀነሰ ሁኔታ ወያኔን ማስወገድ ስለሚቻልበትና ኢትዮጵያን ለአስተማማኝ የዴሞክራሲ ሥርዓት የሚያበቃት መሰረት ስለ መጣል መሆን ሲገባው ከግል ጥቅምና የሥልጣን ጥም ያለፈ ማሰብ አልተቻለም፡፡ በመሆኑም  በዶ/ር ሽመልስ ጽሁፍ እንደተገለጸው ያላመረትነውን እየቃረምን፣ ባልሰራነው እየፎከርን ቃልና ተግባራችን እየተቃረነብን ዛሬን ብቻ መኖር ነው የተያያዝነው፡፡

ወያኔዎች ግን ስለ ነገ የሚያስቡት “በመራራ ትግል” ከእጃቸው ያስገቡት ሥልጣን ዝንተ አለም ስለሚቆይበት ካልሆነም ወደ መነሻቸው ተመልሰው ትግራይን ስለሚገዙበት ነው ፡፡ እንዲህ በማሰባቸውና በመስራታቸውም ነው  ሀያ አምስት አመት ተደላድለው ለመግዛት የበቁት፡፡ ወያኔዎች እንዲህ በማሰብና በመስራት ብቻ አይወሰኑም፡፡  በአጼ ዮሀንስ የሆነው በእኛም ሊደገም ነው ብለው በሰጉ ሰአት በጡረታ የተገለሉት፤በመተካካት ስም ከፊት ለፊት ገለል የተደረጉት ተወንጅለው የተባረሩት ሳይቀሩ ታውሞውን ለማብረድና የተነቃነቀውን የድርጅታቸውን ወንበር ለማጥበቅ በሚችሉት ይንፈራገጣሉ፡፡

ስለትናንት አስቦ መነሳት ስለ ነገም ተጨንቆ መስራት የማይታይባቸው   የተቃውሞው ጎራ አብዛኛዎቹ ፖለቲከኞች ግን የዘመመው እንዳይቃና  የተነቃነቀው እንዳይረጋ ተባብረው ከመስራት ቤተ መንግስቱን አሸጋግረው እያዩና እየተመኙ በሚፈጥሩት ሴራን ፉክክር ለወያኔ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት በመሆን ብዙ አጋጣሚዎችን አምክነዋል፡፡ ከትናንት ተምረው ይህን ህዝባዊ አምቢተኝነት  ወደ ድል የማሸጋገር ዝግጁነት አይደለም ፍላጎት አይታይባቸውም፡፡ እንደውም በተቃራኒው   ህዝቡ ወያኔ አጥብቆ የሚጠላውንና ለአመታትም በብርቱ የሰራበትን ኢትዮጵያዊነትን የማጥፋት ሴራ በጣጥሶ  የአንድነት ዜማ እያሰማ በመስዋእትነቱ ያቀለመውንና  በቁርጠኝነት የተያያዘውን ትግል  ወደ ብሄር/ጎሳ ደረጃ በማውረድ ለወያኔ ማገገሚያ እንዲመች ለማድረግ ሲጮሁ መስማት ሲደክሙ ማየት በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ ወያኔ የህዝቡ አንድነት አበሳጭቶት እሳትና ጭድ በማለት ዛሬም ለማለያየት ቀን ተለሊት ሲደክም በተቃራኒው ተቀዋሚዎች ህዝቡ ከእነርሱ ቀድሞ ሴራውን አክሽፎ በአንድነት በመነሳቱ ተደስተው ቀጣዩን የወያኔ ሴራና ስራ ለማክሸፍና የህዝቡን አንድነት ለማጽናትና ለማጥበቅ መስራት ሲገባቸው ዛሬም በትናንት ዜማ ሲያቀነቅኑ መስማት በጣሙን ያማል፡፡ ነገር ግን ህዝቡ ቀድሟቸዋልና በእነርሱ ማዘን ካልሆነ በስተቀር ተስፋ አያስቆርጥም፡፡

የበሽታችን ክፋቱ፣ ከራስ በላይ ለማሰብ ያለመቻላችን ግዝፈቱ ተባብረን አንባገነን ስርዓትን ለማስወገድ አላስችል ብሎን ሀያ አምስት አመት በጥቂቶች ያውም ራሳቸውን ነጻ አውጪ በሚሉ ሀይሎች ተገዛን፡፡ በዚህ መቆጨት ከድርጊቱም መማርና መለወጥ ሲገባን ህዝቡ ከመመረር አልፎ ተማሮ ህይወቱን እየገበረ ለነጸነቱ ሲታገል እንኳን ከአመታት በፊት ከቆምንበት መነቃነቅ የያዘነውን አቋም መለወጥ ተስኖን ህዝባዊውን ትግል መምራት ቢቀር ተከታይ መሆን አልቻልንም፡፡ በዚሁ ከተቀጠለ የህዝባዊው ተቃውሞ ውጤት ሁሉንም የሚጠራርግ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡

በህዝባዊው ማዕበል አብሮ መጠረጉም ሆነ  በዚህ ወሳኝ ወቅት ተገቢውን ተግባር ሳይፈጽሙ በተአምር ከማእበሉ መትረፍ መቻል ከታረክና ከትውልድ ተጠያቂነት አያድኑም፡፡ የታሪክ ሂደት አርቃናችንን እንዳያስቀረን የሚለው የዶ/ር ሽመልስ ግዜ ያላደበዘዘው ስጋትም ይሄ ይመስለኛል፡፡

 

 

 

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live