Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያዊው በደቡብ አፍሪካ ከነህይወቱ ተቃጠለ

$
0
0

south(አድማስ ራድዮ) Tesfu Reday lives in Johannesburg for the past 6 years. He struggled in life and was able to open a small shop.

Last Wednesday, September 14, around midnight robbers came to his shop where he also lives in a small room behind. They broke the door and went it. …… ይህ አሳዛኝ ነገር የሆነው ባለፈው ዕሮብ፣ ሴፕቴምበር 14 ነው። ተባባሪያችን ከዚያው ለአድማስ ሬዲዮ እንደዘገበው፣ በደቡብ አፍሪካ በጆሃንስበርግ ለ6 ዓመት ከዚያም ከጆበርግ 10 ማይል አካባቢ በምትርቀው ቲምቢሳ በተባለች አካባቢ ላለፉት 6 ወራት ሱቅ ከፍቶ የሚሰራ ተስፉ ረዳይ የሚባል ወጣት ነበር። በተጠቀሰው ቀን ዘራፊዎች ሌሊት ላይ ሱቁ ይመጣሉ፣ እሱም ከሱቁ ጀርባ ትንሽ ክፍል ውስጥ ነበር የሚያድረው። አስገድደው ያለውን ገንዘብ ከወሰዱ በኋላ፣ ውጭ ያቆመው መኪና ውስጥ ክትተውት ከወንበሩ ጋር በማስር መኪናው ላይ እሳት ለቀው ሄደዋል። እሱም ተቃጥሎ ህይወቱ አልፏል። የሶስት ዓመት ህጻን ልጅ አባት የሆነው ተስፉ አስከሬንም በኢትዮጵያውያን ድጋፍ ወደ አገር ቤት ተልኮ ትናንት እሁድ መቀበሩ ተነግሯል። ነፍስ ይማር።

He asked them what they want. They were looking for money, so he gave them all he has. But they didnt stop there. They took him outside where he parked his car, put him inside and tie him with the chair and then lit the car on fire.
They escaped after they did that. Our helpless brother, Tesfu Coudn’t survive the fire. His body was so damaged it took time for the police to identify him. They finally did after taking DNA sample from his son, a 3 year old boy
Once his identity is released, fellow Ethiopians were able to send his body back home and we have learnt that he got buried in Addis Abeba Sunday, Sept. 18/20016 .R.I.P
(Admas Reporter from Jo burg, SA)


የአማራ ህልውና እስኪረጋገጥ በቀጣይ የትግል ስትራቴጂዎች ዙሪያ የተሰጠ የግል አስተያየት

$
0
0

[መጠነኛ መሻሻል ተደርጎበት በድጋሜ የታተመ]

ከሙሉቀን ተስፋው

እንደሚታወቀው የአማራ ተጋድሎ ይፋዊ ጅማሮ ሁለት ወር አስቆጥሯል። ተጋድሎው ባሳለፍነው ሁለት ወር ውስጥ ልዩልዩ መርሀ ግብሮችን በማውጣት በርካታ ድሎችን አስመዝግቧል። ይህ ተጋድሎ የአማራ ህልውና እስኪረጋገጥ ድረስ እያደገ መሄድ አለበት። ይቺን ትንሽ ማስታወሻ እንድጽፍ ያደረገኝ አንዳንድ የተደበላለቁ አካሄዶችን በማየቴ ነው።
nigist-1
ወደፊት ህዝባችን እንዲወስድ የምናቅዳቸው የአማራ ተጋድሎ መርሀ ግብሮች ተጋድሎውን ወደፊት የሚያራምዱ እንጂ ተጋድሎ አሁን ከደረሰበት ደረጃ ወደኋላ የሚጎትቱ መሆን የለባቸውም። ለምሳሌ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎችና መገናኛ ብዙሀን ከዛሬ የሚጀምር የቤት ውስጥ አድማ በጎንደርና በባህር ዳር እንዲደረግ ጥሪ ሲያስተላልፉ ተመልክቻለሁ። ትግል እያደገ እንጂ ወደኋላ እየተመለሰ መሄድ የለበትም። የስራ ማቆምና ቤት ውስጥ የመዋል አድማ day one የሚደረግ ህዝባዊ ተቃውሞ ነው። ህዝባዊ ተጋድሎ incremental ካልሆነ ተንገጫግጮ ይቆማል እንጂ ወደፊት አይሄድም። ትግል ተንገጫግጮ ባለበት ከቆመ ወይንም ወደፊት መሄድ ካልቻለ በቅድሚያ የሚጎዳው ህዝቡን ሲሆን የሚጠቀመው ደግሞ ግፈኛው አገዛዝ ነው። ጎንደርና ጎጃም በአሁኑ ሰዓት እየተካሄደ ያለው የአማራ ተጋድሎ ከስራ ማቆምና ቤት ውስጥ ከመዋል አድማ ደረጃ ካደገ ረጅም ጊዜ ሆኖታል።

ዛሬ ጎንደርና ጎጃም ላይ የስራ ማቆም ወይንም ቤት ውስጥ የመዋል አድማ እንዲደረግ ህዝባችንን ብንጠይቅ ተጋድሎውን ወደ day one የሚመልስ ነው። ዛሬ ላይ ጎንደርና ጎጃም ላይ እየተካሄደ ያለው የአማራ ተጋድሎ ቀጣይ ሂደት የስራ ማቆም አድማ ወይንም ቤት ውስጥ የመዋል አድማ ሳይሆን ህዝቡ እስካሁን ባካሄዳቸው ተጋድሎዎች ጠይቋቸው አገዛዙ ያልመለሳቸውን ጥያቄዎች በራሱ ለመመለስ የራሱን አስተዳደር ወደ መመስረት ማደግ ነው። ስለዚህ በተጋድሎ ሂደት ቀዳሚውንና ተከታዩን እንለይ። አዲስ አበባ የስራ ማቆም አድማ ቢጠራ አግባብ ነው። ምክንያቱም አዲስ አበባ ገና ተጋድሎውን በይፋ አልተቀላቀለምና። ሁለት ወር በላይ ሲጋደል የከረመውን ጎንደርና ጎጃምን የስራ ማቆምና ቤት ውስጥ የመዋል አድማ እንዲያደርግ መቀስቀው በይፋ ምንም ካልተጋደለው ከአዲስ አበባ እኩል እየቆጠርነውና ወደ day one እየመለስነው ነው።

ስለዚህ የተለያየ የተጋድሎ ደረጃ ላይ ያሉ አካባቢዎች በተደጋጋሚ አንድ አይነት የተጋድሎ እርምጃ አይወስዱምና የአንዱን አካባቢ የትግል እርምጃ ሌላውም እንዲወስድ መርሀ ግብር ስናወጣ የዚያን አካባቢ ተጋድሎ ወደኋላ እንዳንመልሰው እንጠንቀቅ። ውጤታማ ትግል በተደጋጋሚ የቤት ውስጥና የስራ ማቆም አድማ እያደረገ አይቀጥልም። ማደግ አለበት። ካሁን በኋላ ጎንደርና ጎጃም ባድረግ ያለበት ሙሉ በሙሉ ከወያኔ ራሱን ነጻ አውጥቶ የራሱን አስተዳደር መመስረት ነው። በየአካባቢው ያሉ የጎበዝ አለቆችም ይህንን ያውቁ ዘንድ እናስተምር። በትግል ሒደት ቀዳሚውና ተከታዩን ካልለየን ትግሉ ውጤት አያመጣም። እንዴውም የሚጎዳው ታጋዩን ህዝብ ነው። ፖለቲካ ትግል ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ ይህንን ማወቅ አለባቸው።
በዚያ ላይ የትግል ስልቶች በህዝብ ላይ የሚያስከትሉት አደጋ መታየት አለበት። ጎንደርና ጎጃም ወያኔ ቤት ለቤት እየኖረ መጣቶችን እያሰረ ባለበት ባሁኑ ወቅት ጎንደርና ጎጃምን ቤት ዋሉ ማለት ወያኔ እንዲለቅማቸው ምቹ ሁናችሁ ጠብቁ ማለት ነው። ስለዚህ የትግል ል ስልቶች ጠላት ከሚወስዳቸው እድርምጃዎች አንጻር መቃኘት አለባቸው። ዛሬ ጎንደርና ጎጃም ላይ ወያኔ ቤት ለቤት እየዞረ አያካሄደው ካለው አፈና አንጻር ጎንደርና ጎጃምን ቤት ዋሉ ከማለት ጫካ ግቡ ማለቱ የተሻለ አማራጭ ነው። ምክንያቱም ቤት ከሚውሉ ቢያንስ ጫካ ቢገቡ ከወያኔ የቤት ለቤት አፈና ይተርፋሉ። ወያኔ ቤት ለቤት እየዞረ ወጣቶችን እያፈሰ «ቤት ዋሉ» ብሎ ጥሪ ማድረግ ወያኔ እንዲያፍሳችሁ ተመቻችታችሁ ጠብቁት ከማለት አይተናነስም። ወያኔ ቤት ለቤት እየዞረ ወጣቶችን እያፈሰ «ቤት ዋሉ» ብሎ የተቃዋሚ ካባ በመልበት ጥሪ የሚያስተላልፍ ወያኔ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ወጣቶቹ ቤት መዋላቸው ቤት ለቤት እየዞረ በቀላሉ ለማፈስ ያመቸዋልና። ስለዚህ ጎንደርና ጎጃም ህዝቡ ቀጣይ ትግሎችን እንዲያደርግ ጥሪ የምናስተላልፍ ከሆነ ህዝቡ ራሱን ነጻ አውጥቶ የራሱን አስተዳደር እንዲመሰርት ጥሪ እናቅርብ። ከዚህ በፊት ያደረጋቸውን ደግሞ ደጋግሞ እያደረገ ወደ ኋላ እየሄደ ታጋዩ ህዝብ ተጎድቶ ጠላታችን ወያኔ እንዲጠቀም አናድርግ።
ስለዚህ ተጋድሎው ታጋዩ ህዝብ ወደፊት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች በሚመለከት መርሀ ግብር ስናወጣ ሁለት ነገሮችን ከግምት ውስጥ እናስገባ። የመጀመሪያው ጉዳይ ህዝባችን ወደፊት እንዲወስድ የምንጠይቀው እርምጃ ተጋድሎውን ወደፊት የሚወስድ ነው?ወይንስ ወደኋላ የሚመልስ? የሚል ነው። ሁለተኛው ደግሞ እንዲወሰዱ የምንጠይቃቸው እርምጃዎች የትግሉን ደረጃ የሚያሳድጉ ናቸው? ወይንስ አይደሉም? የሚል ነው። ስትራቴጂካሊ እያሰብን እነዚህን ሁለቱን ከግምት ውስጥ አስገብተን እንደየአካባቢው የተጋድሎ ደረጃ መሬት ላይና ማህበራዊ ሜዲያ ላይ ካሉት የጎበዝ አለቆች ጋር ተናበን መርሀ ግብር የምናወጣ ከሆነ የምንለፍለውን መስዕዋትነት ቀንሰን ህውልናችንን ማረጋገጥ እንችላለን።
ባጭሩ በቀጣይ ተግባር ላይ የሚውሉ ማናቸውም የትግል ስትራቴጂዎች በትግሉ የሚሳተፉትን ሰዎች/ቡድኖች ጉዳት ላይ የሚጥሉና ከጀብደኝነት የጸዱ መሆን ይኖርባቸዋል። ይህ መሆኑ የሚወሰዱት ማናቸውም እርምጃዎች ቀጣይ ትግሉን የበለጠ ከማጠናክር አንጻን ፋይዳቸው የጎላ ነው። በኔ አስተያየት አገር ቤት መካሄድ ያለባቸው ቀጣይ የትግል ስትራቴጂ የሚከተለውን መልክ ቢይዙ የተሻለ ይመስለኛል።
1. የግዥ እና ሸመታ ማቆምን በተመለከተ
የግዥና ሽያጭ ተቃውሞ በተለይም በአዲስ አበባ፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ሀረር፣ ጅማ፣ ደብረ ብርሀን፣ ደሴ፣ ጊምቢ፣ ሻሸመኔ፣ ናዝሬት እና ድሬዳዋ ተግባራዊ እንዲሆን ስናስብ በዋነኛነት ቤት ተከራይተው ንግድ የሚያካሄዱ ነጋዴዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብን። አብዛኛዎቹ ነጋዴዎች ከቀበሌ፣ ከኪራይ ቤቶችና ከግል አከራይ በተከራዩት ቤት ሰለሆነ ንግድ የሚያካሂዱት በሚውስዱት የግዥና ሽያጭ ተቃውሞ ከፍተኛ ጉዳት ይደርሰባቸዋል። ነጋዴዎቹን ከጉዳት መጠበቅ ትግሉን ቀጣይት ለማረጋገጥ ወሳኝ ነገር ነው። ለምሳሌ ከዚህ በፊት በንግዱ ማህበረሰብ በተደረገው እንቢተኝነት ብዙ ነጋዴዎች ለጉዳት ተዳርገዋል። እነዚህ ነጋዴዎች ለትግሉ በተለየ መልኩ እንዲሳተፉ ማድረግ የተሻለ ትግል ይመስለኛል። ስለዚህ በተለመደ አኳኋን የሚደረገው የግዥና ሸያጭ ተቃውሞ በትኩረት ቢፈተሸ ጥሩ ይመስለኛል።
ስለሆነም፤
• ነጋዴው የንግድ ቤቱን ክፍት በማድረግ ነገር ግን በቂ አግልግሎት አለማዘጋጀት፣ ጥራት መቀነስ ወዘተ ማድረግ ቢችል አንድም በአገዛዙ ላይ ጫና ይፈጥራል፤ ሁለትም በግዥና ሽያጭ ተቃውሞ የሚደርስበትን ከፍተኛ ጉዳት መቀነስ ይችላል። ከዚህ ጎን ለጎን ነጋዴው አግልግሎት ፍለጋ የሚመጣውን ተገልጋይ መዝግቦ መረጃ እንዲሰጥ ቢያደርገው የበለጠ ጥቅም ይስጣል። ነጋዴዎች በግዥና ሽያጭ ተቃውሞ ምክንያት ጉዳት ላይ ከሚወድቁ በገንዘብ ድጋፍ ትግሉን እንዲያግዙ ማድረግ የተሻለ ይሆናል። በአዲስ አበባ ከተማ ከኪራይ ቤቶች በሁለት ሺህ ብር ተከራይተው የሚነግዱ ሰዎች የንግድ ቤታቸው ታሽጎ እንዲለቁ ቢደረጉ ሊከራዩዋቸው የሚችሏቸው ሌሎች ቤቶች በሃምሳና መቶ ሺህ ብር ሊከራዩዋቸው የሚችሉ ቤቶች ናቸው። ነገዴዎች ለዚህ ከሚዳረጉ ትግሉን በገንዘብ ቢደግፉ የተሻለ ይሆናል የሚል አስተያየት አለኝ።
• ተገልጋዮች በተለይ አግልግሎት መስጫ ቤቶች ባለመሄድ አጠቃላይ እንቅስቃሴዎችን መገደብ ትግሉን የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል የሚል እምነት አለኝ። በግድ ቢራ ጠጡ፣ ሆቴል ወይንም ሬስቶራንት ምግብ ብሉ የሚል የለም። ከውጭ የሚመገቡ ምሳ ከቤታቸው ይዘው መውጣት ይችላሉ። ምግብ የማዘጋጀቱ ጥሞና ከሌለው ደግሞ ደረቅ ነገሮችን ይዞ መንቀሳቀስ ይችላል።
2. የታክሲ አገልግሎትን በተመለከተ
የታክሲ አገልግሎት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የኤኮኖሚ ደም ስር ነው። በታክሲ አገልግሎት ሁሉም ታክሲ ሾፌሮች እና ባለንብረቶች አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ ታክሲዎቹ በተናጥል እንዲጠቁ የሚያደርግ በመሆኑ፤ ታክሲ ሾፌሮች የሚከተሉትን ቢያደርጉ ትግሉ ወደፊት ይሄዳል፤
• ታክሲ ሾፌሩ አርፍዶ ስራ መጀመር፤ ከታክሲ ሾፌሮች ቢያስን ሩብ የሚሆኑት አርፍደው ቢወጡ በትራንሰፖርት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራሉ። ታክሲ ሾፌሮች አርፍዶ መጀመር ብቻ ሳይሆን በጊዜም ሰራ ማቆም ይችላሉ። ህዝቡ በትራንሰፖርት እጦት ሲማረር መንግሰት የራሱን ትራንሰፖርት ማሰማራት እና ማቀናጀት ላይ ይወጣራል። ይህ ደግሞ በተዳከመ የመንግሰት ሰራተኛ የስራ ፍላጎት በቀላሉ አይሳካም።
• ጋራዥ መኪና አሰገብቶ ለተወሰነ ቀን ማቆም፤
• መኪናውን በጎሚስታ እና ቤንዚል ማደያ ስልፍ ላይ እንዲቆሙ፤ በተለይ ደግሞ ተሳፋሪ ጭኖ በመሰለፍ ህዝቡ እንዲማረር ማድረግ፤
• ተሳፋሪን በወቅቱ ስራ ቦታ አለማድረስ፣ ወዘተ የመሳሰሉትን በተከታታይ ማድረግ፤
እነዚህ የትግል ስልቶች ታክሲ የስራ ማቆም አድማ እንዲያደርግ ከማግባባት የተሻሉ የትግል ስትራቴጂዎች ናቸው። እነዚህ የትግል ስልቶች መንግስትን ለቁጥጥር የሚያስቸገሩ በመሆናቸው ባለንብረቶቹም ሆኑ ሾፌሮች ለእለት ጉርስ የሚሆን እያገኙ ትግሉን ለረጅም ጊዜ እንዲቀጥል ያስችላሉ። ታክሲው ስራ ቢያቆም በታክሲው አገልግሎት የሚያማርር የለም። ሆኖም ግን ታክሲ እየሰራ ሾፌሮች ከፍ ብሎ የቀረቡትን የትግል ስልቶች ቢከተሉ በተጠቃሚዎች ላይ የስራ መጓተት ሲለሚፈጥሩ የተገልጋዮች እሮሮ ይጨምርና ወደ ትግል እንዲገቡ ይገፋፋል።
3. የመንግሰት ሰራተኞች በተመለከተ
የመንግሰት ሰራተኞች በስራ ገበታቸው እንዳይገኙ ማድረግ አሁንም ለከፍተኛ ጉዳት እንደሚያጋልጣቸው የሚታወቅ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ከጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ የባንክ ሰራተኞች ላይ የደረሰው ችግር የሚረሳ አይደለም። ይህን ለመከላከል ሰራተኞች በስራቸው ላይ መገኘት ቢኖርባቸውም ተገልጋዮች ግን ወደ መንግሰት ቢሮ አለመሄድ፤ የመንግሰት ሠራተኞች ደግሞ አግልግሎት ፍለጋ የሚመጡ ተገልጋዮችን በመመዝገብ ማጋለጥ ዋና ስራቸው ማድረግ ይቻላል። ስራን በጥራት ያለማከናውን የመሳሰሉት የስራ ላይ ችግር መፍጠር የበለጠ የተሻለ ይመስለኛል።
4. የገጠር አርሶ አደሩን በተመለከተ
በገጠር ያለው አርሶ አደር በግድ ምርት እንዲያወጣ የሚያስገድደው ወይም ከብቱን ገበያ አውጣ የሚለው አሰራር ስለሌ አሁን በተጀመረው መልኩ ምርቱን ለገበያ እንዳያቀርብ ማድረግ አዋጭ ሰራ ነው። ይህን አጠናክሮ መቀጠል ያስፋልጋል።
5. ትራንስፖርት /አይሱዙ፣ ድጋፍ ሰጪ የህዝብ ትራንስፖርት እና ሌሎች የትራንሰፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መኪኖችም አደጋ በመስጋት በሚል ከስራ መቆም ይችላሉ።
6. ህክምና ተቋሞችን በተመለከተ
በህክምና ተቋም የሚሰሩ አግልግሎት ሰጪዎች ከምንጊዜውም በላይ በትጋት በስራ ላይ መገኘት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ምርጥ የሚባል አገልግሎት በመስጠት ህዝቡን ማገልገል ይኖርባቸዋል። ከተቻለ ብዙ የመንግሰት ስራተኞች እና አጠቃላይ ህዝቡ ለምርመራ እና ለህክምና ሰልፍ በመያዝ የህክምና ተቋማትን ማጣበብ፣ የሀኪም ፈቃድ በመያዝ ከስራ መቅረት ይጠበቅበታል። ለጤናቻን ጊዜ እንስጥ በማለት በጤና ጣቢያ መገኘትም ሌላ ስትራቴጂ ነው።
7. ትምህርት ቤቶች በተመለከተ
መምህራን በትምህርት ቤት ውስጥ አትገኙ መባል የለባቸው። ይልቁንም ተማሪዎች በትምህርት ገበታ እንዳይገኙ ወላጆችን ማስተባበር ይሻላል። ወላጆች ልጆችን በህመም ወይም በትራንስፖርት አመካኝተው ትምህርት ቤት አለመላክ ሊታሰቡ የሚችሉ የትግል ስልቶች ናቸው። መምህራን ከስራ ቢሰናበቱ ችግረ ላይ እንደሚወድቁ እሙን ነው፤ ተማሪዎች ግን ትምህርት ለተወሰነ ጊዜ ባይማሩ ምንም አይሆኑም። ወላጆች ነፃነት የሌለው ትምርት ምንም ዋጋ እንደሌለው ሊገነዘቡ ይገባል።
ሌሎቹም ሊታሰቡ የሚችሉ ብዙ ሰላማዊ የትግል ስልቶች ማሰብ የሚቻል ሲሆን ህዝቡ ሳይከፋፈል ከላይ የቀረቡትን የትግል ስልቶች ለረጅም ጊዜ በጋራ ማስቀጠል ከተቻለ ወያኔ ማሽመድመድ ይቻላል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በመጀመሪያው ቀን ስብሰባ ያነሷቸው ወሳኝ ጥያቄዎች መካከል ጥቂቶቹ እጃችን ገብተዋል –ያንብቧቸው

$
0
0

(መስከረም 9፣ 2009 ዓ.ም)፡- በዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ካሳ ተ/ብርሀን አጠቃላይ የውይይት መድረኩ መነሻ አሳብ ትረካ እና የእለቱ የውይይት አጀንዳ በሆነው ያለፉት 25 ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ጉዞ ዙሪያ የሚያጠነጥን ገለፃ በኃላ በምርጦቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተነሱ አስተያቶች እና የአካሄድ ጥያቄዎች:-
addis-ababa-university

1. የመጀመሪያ ተናጋሪ፡-
1.1 “የዚህ ወይይት አጀንዳ ከጠበኩት በታች ወርዶብኛል በወላይቲኛ አንድ አባባል አለ ያቺ እንትን’ኮ ወደቀች ቢሏት፤ ቀድሞም አቀማመጧ ለመውደቅ ነው አለች”፡፡
1.2 “ካሳ! አንተ ሚኒስትር ነህ በዛ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን የቦርድ ሊቀመንበር በዚህ ሁሉ ኃላፊነት ውስጥ ሆኖ PhD candidate መሆን አይቻልም ስለዚህ ስራህን ልቀቅ”
1.3 “ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ይምጣና ያወየን፣ እናንተ ውረዱና ከእኛ ጋር ተቀመጡ”
2. ሁለተኛ ተናጋሪ
2.1 “ይቺ ሀገር አንደ ሀገር አንደትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት፣ በዚህ ስብሰባ አኛ የእናንተን እንከን እናውራ እናንተ ደግሞ ዝም ብላችሁ አድምጡን”፡፡
3. ሦስተኛ ተናጋሪ
3.1 “የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ የውይይት መድረክ ብዙ ቁም ነገሮች ተነስተው ነበር ነገር ግን አንዳቸውም ሳይተገበሩ ዛሬ ደግመን ተገናኘን”
3.2 “አቶ ካሳ የመንግሰት ስልጣን ይዘህ ለግል ጥቅምህ በማዋል የዩኒቨርስቲውን ህግ ጥሰህ PhD candidate ሆነሐል”
3.3 “ውይይቱን የመምራት ሞራል የለህም”
* የአቶ ካሳ መልስ፡-
1. “እኔ ውይይቱን የመምራት ችግር የለብኝም፣ ከእኔ የምትበልጡ ትልልቅ ምሑራንና ባለዕውቀቶች እንደላችሁ እሙን ነው ነገር ግን በአጋጣሚ የቦርድ ሰብሳቢ ሆኜ እስከተቀመጥኩ ድረስ ወይይቱን የመምራት ኃላፊነት አለብኝ”
2. “ይህ የውይይት መድረክ በመላ ሀገሪቱ ባሉ የትምህርት ተቋማት የሚደረግ እና መድረኩም አንዲመራ የተያዘለት ፕሮግራም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይሆን በቦርድ ለቃነመናብርት ነው”
3. “አኔ ብማር ክፋቱ ምንድን ነው? እኔም’ኮ አንድ ዜጋ ነኝ፣ ትምሀርት የመጀመሩን እድል አግኝቼ ነበር ነገር ግን ጊዜ በማጣት ምክንያት ብቻ class attend ባለማድረጌ ለመቀጠል አልቻልኩም፣ ጊዜ ሲኖረኝ ግን ታሰተምሩኛላችው”
በመቀጠልም ከተሰብሳቢ ምሁራን አንዱ አጁን በማውጣት ማሳሰቢያ እንዳለው ተናገረ፤ አንዲናገር ዕድሉ ሲሰጠውም “በመጀመሪያ ይሄ ስብሰባ ሲጀመር በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በኮንሶ በአልሞ ተኳሾች ለተገደሉ ንፅሑን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ሊሆን ይገባ ነበር” በዚህ ጊዜ የስብሰባው አዳራሽ ለረጅም ደቂቃ ባልተቋረጠ ጭብጨባ ተስተጋባ ሲቀጥልም “ሁሌም ተደጋጋሚ አጀንዳ ነው ይዛችው የምትመጡት ካችአምና የትምሀርት ጥራት አምና እና ዘንድሮም የትምህርት ጥራት መንም አዲስ ነገር የለም፣ ለዚህ ስበሰባ የተመደበው በጀት ተቀንሶ በተለያዩ ክልሎች በተነሱ ግጭቶች የቤተሰባቸውን አባላት ላጡ ወገኖች ይሰጥ ለእኛ የሶስት ቀን ውይይት ይበቃናል”
*ቀጣይ ተናጋሪ
-› “ሰው አየሞተ እና ህዝብ ለተቃውሞ እየወጣ political crisis ውስጥ ገብተን ስለትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት መወያየት አኔን ያሳፍረኛል”
-› “ታልሞ የተመጣው ነገር ለኢቢሲ ዜና የሚሆን ነገር ለመቃረም ነው”
* ሌላ ተናጋሪ
-› “Next time I don’t want to see these board members (አቶ ካሳን ጨምሮ መድረኩን እየመሩ ያሉትን የዩኒቨርሲቲውን የቦርድ አባለት ነው)
-› “ዶ/ር አድማሱ ባለፈው ጊዜ አሜሪካን ሀገር ውስጥ በሱፐር ማርኬት ውስጥ የደረሰብዎትን አይተናል እነርሱ እዛ ወላፈኑ ገና ለገና ይደርስብናል ብለው ይህን ካደረጉ አኛስ እዚህ እንፋሎቱ ውስጥ የምንቀቀለው ምን እናድርግ?”
(ሱራፌል ሀቢብ)

ኢህአዴግ ካልታደሰ አይወድቅም

$
0
0

ከስዩም ተሾመ
አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች “ኢህአዴግ በቅርቡ ይወድቃል” ሲሉ፣ ደጋፊዎቹ ደግሞ “በቅርቡ ይታደሳል” እያሉ ይገኛል። ከመቼውም ግዜ በላይ በሀገሪቱ ፖለቲካ ለውጥ ስለማስፈለጉ ግን ሁለቱም ወገኖች አምነው የተቀበሉት ይመስላል። ይህ ለውጥ ደግሞ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ከኢህአዴግ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። የሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እንደ መንግስት በኢህአዴግ ላይ ውድቀት ወይም ተሃድሶ ሊያስከትል ይቻላል። ታዲያ እዚህ ጋር ቁልፉ ጥያቄ “ኢህአዴግ ይወድቃል ወይስ ይታደሳል?” የሚለው ነው። የጥያቄው መልስ፣ ከጭፍን ተቃውሞና ድጋፍ ባሻገር፣ በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተ ትንታኔ ይጠይቃል። በዚህ ፅሁፍ ዝርዝር ትንታኔውን ይዘን ቀርበናል።

ስዩም ተሾመ

ስዩም ተሾመ

በመሰረቱ፣ በሕዝቡ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እስካልተሰጣቸው ድረስ ግጭትና አለመረጋጋቱ እየጨመረ ይሄዳል። ለዚህም በ2008 ዓመት መጀመሪያ ላይ በተወሰኑ የአማራና ኦሮሚያ አከባቢዎች የተጀመረው የአመፅና ተቃውሞ በአመቱ መጨረሻ ላይ የት እንደደረሰ ማየቱ ብቻ በቂ ነው። የሚፈለገው ለውጥ እስካልመጣ ድረስ በቀጣይ አመትም በተመሳሳይ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች መከሰታቸው የማይቀር ነገር ነው። ሕዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ከዕለት ወደ ዕለት ከቦታና ግዜ አንፃር እየሰፋና እየጨመረ ቢሆንም፣ በመንግስትና ተቃዋሚዎች ጎራ “ኢህአዴግ ይወድቃል ወይም ይታደሳል” ከሚል ፉከራ የዘለለ በተጨባጭ የሚታይ ለውጥ የለም።

በቅድሚያ ግን “የፖለቲካ እንቅስቃሴው በዚሁ ከቀጠለ ምን አይነት ጉዳት ያስከትላል?” የሚለውን በአጭሩ ማየት ያስፈልጋል። በፖለቲካ እንቅስቃሴው ቀጥተኛ ተሳታፊ የሆኑት አካላት፡- ሕዝብ፣ መንግስትና ተቃዋሚዎች ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ሕዝቡ ብቻ ነው ወደፊት እየተራመደ ያለው። መንግስትና ተቃዋሚዎች ግን ባሉበት እየረገጡ ይገኛሉ። በእርግጥ ኢህአዴግ አሁን ባለበት ሁኔታ ከቀጠለ በትንሽ ግዜ ውስጥ ይወድቃል። ይህ ግ በዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል፣ በፖለቲካውም ትልቅ ኪሳራ ያስከትላል።

መንግስት ሕዝቡ እያነሳቸው ላሉት የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በኃይል ለማፈን የሚደረገው ጥረት ሀገሪቱን ወደለየለት ግጭትና አለመረጋጋት ያስገባታል። የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሥራና አሰራራቸውን ከማሻሻል ይልቅ ፖሊሶች፣ ወታደሮችና የደህንነት ሰራተኞች በመላክ ሕዝቡን ለሞት፣ ጉዳትና ለእስራት የሚዳርጉት ከሆነ ባለስልጣናቱ በሕዝቡ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት፣ እንደ መንግስትም ያላቸውን ተቀባይነት ከግዜ ወደ ግዜ እያጡ ይሄዳሉ። በዚህም፣ አንደኛ፡- መንግስት በሕዝቡ ዘንድ ያለውን የማስተዳደር ስልጣን ይገፈፋል፤ ሁለተኛ፡- ሕዝቡ ራሱን-በራሱ ማስተዳደር መብቱን ተጠቅሞ የጋራ ሰላምና ደህንነቱን በራሱ ለማስከበር ጥረት ያደርጋል። ይህን ተከትሎ የመንግስት ባለስልጣናትና የፀጥታ ኃይሎች በሕዝብ ላይ የሕይወትና ንብረት ጉዳት ሲያደርሱ ሕዝቡ ደግሞ በሁለቱም አካላት ላይ የአፀፋ እርምጃ መውሰድ ይጀምራል።

በመሰረቱ የሕዝብ እርምጃ በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን መግለፅ ነው። በመንግስት ኃይሎች የሚወሰደው እርምጃ በዜጎች ሕይወትና ንብረት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እየከፋ በሄደ ቁጥር ግን ተቃውሞው ባህሪውን እየቀየረ ይመጣል። በእርግጥ አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን መግለፅ ይቀጥላል። ከዚህ ጎን-ለጎን ግን መንግስትን በኃይል ለመጣል የሚታገሉ ኃይሎችን በውስጡ መደበቅ ይጀምራል። ከመንግስት ጋር የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ኃይሎች በስደት ከሚኖሩበት ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ይጀምራሉ።

የኢህአዴግ መንግስት ራሱ ለረጅም ግዜ “ሞቷል” ሲለው የነበረው የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ) እና “የኤርትራ ተላላኪ” የሚለው ግንቦት7 ባሳለፍነው የ2008 ዓመት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ግጭትና አለመረጋጋት እጃቸው አለበት ማለት ጀምሯል። ከዚህ በፊት እነዚህ ኃይሎች በመንግስት ላይ ጫና የማሳደር አቅማቸው ውስን ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያት ሕዝቡ በውስጡ ከመንግስት ኃይሎች ሊደብቃቸው ፍቃደኛ ስላልነበር ነው። ዛሬ ላይ ግን፣ በኦሮሚያና በአማራ ልጆቹ በመንግስት ኃይሎች የተገደሉበት፣ የተጎዱበትና የታሰሩበት ቤተሰብ የኦነግ ወይም የግንቦት7 ተዋጊ ከቤቱ ቢደብቅና ስንቅ ቢያቀብል ሊገርመን አይገባም።

ቁጥራቸው በጣም ጥቂት የሆኑ ግን ከሕዝቡ ውስጥ የተደበቁ የአማፂ ቡድን አባላት በመንግስት ኃላፊዎችና በፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት መፈፀም ሲጀምሩ የፖለቲካ ሁኔታው ፍፁም ይቀየራል። የመንግስት ባለስልጣናትና የፀጥታ ኃይሎች በጋራ ሕልውናቸው አደጋ ላይ ይወድቃል። ሕዝብ ጥቅጥቅ ያለ ደን ነው። በባለስልጣናትና የፀጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ፈፃሚው ማን እንደሆነ በቀላሉ መለየት አይቻልም። በዚህ መልኩ በመንግስት ኃላፊዎችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በደርግ ዘመን እንደነበረው “ነጭ-ሽብር” ያስከትላል። መንግስትና የፀጥታ ኃይሎች ራሳቸውን ለመከላከል የሚወስዱት የአፀፋ እርምጃ ደግሞ “ቀይ-ሽብር” በመባል የሚታወቀውን ጅምላ ጭፍጨፋ ያስከትላል። በደርግ ዘመን በነጭ-ሽብር ጥቃት የተገደሉት 10 የደርግ ባለስልጣናትን እና 15 የፀጥታ አስከባሪዎችን ነበሩ። ከታህሳስ እስከ መጋቢት 2008 ዓ.ም ባሉት አራት ወራት ብቻ 14 የኢህአዴግ ባለስልጣናት እና 14 የፀጥታ አስከባሪዎች መገደላቸው ወደ የት እያመራን እንደሆነ በግልፅ ይጠቁማል። ስለዚህ፣ በደርግ ዘመን የደረሰው አስከፊ ጭፍጨፋና ጦርነት በሀገራችን ተመልሶ እንዳይመጣ አስቸኳይ ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል።

ሕዝቡ እየጠየቀ ያለው ለውጥና መሻሻል እንዲመጣ “ኢህአዴግ ይውደቅ ወይስ ይታደስ?” የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል።በእርግጥ መውደቅም ሆነ መታደስ ሁለቱም ለውጥ ናቸው። ነገር ግን፣ ለውጥ (Change) ሁለት አይነት ነው፡- አፍራሽ (Destructive) ወይም ገንቢ (Constructive)። ከአፍራሽ ይልቅ ገንቢ ለውጥ ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ይሰጣል። ኢህአዴግን የጠለፈው የአመራር ወጥመድ በሚለው ፅሁፍ ላይ በዝርዝር ለመግለፅ እንደሞከርኩት፣ ኢህአዴግ ራሱን በራሱ ለማደስ የሚያስችል አቅም የለውም። ኢህአዴግና ፅንፈኞች፡ ባለበት የቆመና ባለፈው የቆዘሙ በሚለው ፅሁፍ ደግሞ ከሕዝቡ የለውጥ ፍላጎት ጋር አብሮ ለመሄድ የተሳነው ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚዎች ጭምር እንደሆኑ በዝርዝር ይገልፃል። ስለዚህ፣ በአጠቃላይ፣ ለውጥ የሚያስፈልገው ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚዎች ጭምር ናቸው።

ሁለቱም ወገኖች አስፈላጊና ተገቢ የሆነው ለውጥ ማምጣት ከተሳናቸው፤ አንደኛ፡- ከላይ በተጠቀሰው መልኩ የደርግ ዘመን ጅምላ ጭፍጨፋና በደል ሊደርስ ይችላል፣ ሁለተኛ፡- ሕዝቡ ኢህአዴግን በኃይል ገፍቶ ቢጥለው እንኳን ክፍተቱን የሚሸፍን የተደራጀ የፖለቲካ ኃይል የለም። ስለዚህ፣ እነዚህ ችግሮች በዘላቂነት እንዲወገዱ በመንግስትና ተቃዋሚዎች ዘንድ ተሃድሶ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

“አመፅ የማን ልጅ ነው፡ የልማት ወይስ አምባገነንነትን” በሚለው ፅሁፍ ላይ በዝርዝር ለማስረዳት እንደሞከርኩት፣ አሁን በሀገሪቱ የተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት ስረ መሰረቱ መንግስታዊ ሥርዓቱ ነው። ኢህአዴግ እንደ ገዢ ፓርቲ የሚመራው በልማታዊ መንግስት መርህ ነው። በመሆኑም፣ ጠዋት-ማት ስለ ልማትና የብሔሮች እኩልነት ሲያወራ ባልተጠበቀ መንገድ ሕዝቡ የዴሞክራሲ ጥያቄ ይዞ አደባባይ ወጣ።

የኢህአዴግ መንግስት ራሱን “ልማታዊ-ዴሞክራሲያዊ” እያለ ይጠራል። በእርግጥ ራሱን “ልማታዊ” ብሎ ሊጠራ ይችል ይሆናል። ነገር ግን፣ 100% ምርጫ አሸነፍኩ ብሎ ብቻውን አብኩቶ መጋገር ከጀመረ ወዲህ “ዴሞክራሲያዊ” የሚለውን እንኳን በተግባር በስም አያውቀውም። ቱባ-ቱባ ባለስልጣናቱ “ሰላማዊ ሰልፍ አልፈቀድንም” እያሉ በይፋ ሲናገሩ ሕገ-መንግስቱን እየጣሱ እንደነበረ ትዝ አላላቸውም። ሕዝብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ “የሕግ የበላይነትን ለማስከበር” በሚል ሰበብ ሕዝቡን በኃይል ማፈን ሲጀምሩ “ከሕግ ይልቅ የጉልበት የበላይነት” ነገሰ። ይህ ሲሆን ኢህአዴግ ኢህአዴግ ከልማታዊ መንግስትነት ወደ የለየለት “አምባገነንነት” ተቀየረ።

ኢህአዴግ በተሃድሶ አሁን ካለበት አምባገነንነት ወደ ቀድሞ “ልማታዊ መንግስትነቱ” መመለስ ይኖርበታል። ለዚህ ደግሞ ሕዝቡ እያደረገ ካለው ትግል በተጨማሪ ተቃዋሚዎች ወሳኝ ሚና አላቸው። የተቃዋሚዎች ተሃድሶ የራሳቸውንና የሕዝብን የፖለቲካ ጥቅም ከማረጋገጥ አልፎ ለኢህአዴግ ተሃድሶ በጣም አስፈላጊ ነው።

በ2008 አመት በተለይ የአማራና ኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብቱንና ነፃነቱን ለማስከበር ያደረገው ተጋድሎ የሚደነቅ ነው። ይህ ግን ሕዝቡ በራሱ ያደረገው የለውጥ እንቅስቃሴ እንጂ በፖለቲካ ልሂቃን የተመራ አልነበረም። እንዲህ ያለ ያልተደራጀ እንቅስቃሴ፤ አንደኛ፡- የሚፈለገውን ለውጥ የማምጣት እድሉ ጠባብ ነው፣ ሁለተኛ፡- ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት ከመንግስት ጋር ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ በማስገባት በሕይወትና ንብረት ረገድ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል። ይህን ለማስወገድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች በኢህአዴግ ቁመና ልክ የሚሆን የፖለቲካ አደረጃጀት ሊኖራቸው ይገባል።

ተቃዋሚዎች የተቀናጀ የፖለቲካ አደረጃጀት በመዘርጋት የሕዝቡን እንቅስቃሴ ማገዝ አለባቸው። ከዚህ አንፃር የዳበረ ዴሞክራሲያዊ ሥርኣት ባላቸው የምዕራብ ሀገራት ያለው አይነት ተጠባባቂ መንግስት (Shadow Government) መመስረት አንዱ ነው። በዚህ መሰረት፤ የተቃውሞ እንቅስቃሴውን ወጥና የተደራጀ ማድረግ፣ ሕዝቡ አማራጭ ፖለቲካ ኃይል እንዲኖረው ማስቻል እና እንቅስቃሴውን በማቀናጀት በአጭር ግዜ ውስጥ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት ይቻላል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ የእያንዳንዱን የመንግስት መስሪያ ቤት ተግባርና እንቅስቀሴ የሚከታተል ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ስለሚኖር፣ በዕየለቱ የሚታዩ ክፍተቶች ለሕዝብ በማጋለጥ፣ ሥራና አሰራራቸውን እንዲያሻሽሉ በማድረግ፣ የኢህአዴግ መንግስት ተሃድሶ እንዲያደርግ ያግዘዋል። በዚህ ረገድ የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄዎች ተቀብሎ በማስተጋባትና የመንግስትን ክፍተት በማጋለጥ ረገድ አቶ ጀዋር መሃመድ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ለእያንዳንዱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት እንደ ጀዋር አይነት ትንታግ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቢኖር በኢህአዴግ ለፈጥር የሚችለው ጫና በጣም ትልቅ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል።

እያንዳንዱ የፖለቲካ ኃይል መሰረታዊ ዓላማው የሕዝብን ኑሮና አኗኗር ለመቀየር የሚያስችለውን የፖለቲካ ስልጣን መያዝ ነው። ኢህአዴግ በስልጣን ላይ መቆየት ይፈለልጋል፣ ተቃዋሚዎችም መንግስት መሆን ይፈልጋሉ። በዚህ ፅሁፍ የቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ ደግሞ “ሁሉም ተቃዋሚዎች የኢህአዴግን ተሃድሶ ማገዝ አለባቸው” የሚል አድምታ አለው። ይህ ደግሞ በቅድሚያ ተቃዋሚዎች የራሳቸውን ተሃድሶ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። እውነታው ይኼ ነው – ተቃዋሚዎች ተሃድሶ ካላደረጉ ኢህአዴግ አይወድቅም፣ ሕዝብ ከፍቶ ቢጥለው እንኳን ክፍተቱን የሚሸፍን የተደራጀ የፖለቲካ ኃይል የለም።

በተለይ ከ1997ቱ ምርጫ በኋላ ኢህአዴግ “ዴሞክራሲን” ወደ ጎን ጥሎ “ልማታዊ መንግስት” በሚለው መርህ ብቻ እየተመራ እንዳለ ግልፅ ነው። በዚህ መሰረት ገዢው ፓርቲ ምንም ያህል ተሃድሶ ቢያደርግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት የሚያስቸል አቅምና አመለካከት የለውም። በዋናነት በቡድን መብት እና እኩልነት መርሆች የሚመራው የኢህአዴግ መንግስት፣ ሕዝቡ የግለሰብ መብት እና እኩልነትን መሰረት አድርጎ እያነሳበት ያለውን የዴሞክራሲ ጥያቄ መመለስ አይችልም። በመሰረቱ በግለሰብ መብቶች፡- ነፃነት፣ እኩልነትና ፍትህ ላይ የተመሰረተው የሕዝብ ጥያቄ፣ ኢህአዴግ በቡድን መብቶች፡- የብሔር፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እኩልነት፣ ሕገ-መንግስታዊ ሥርኣትና በልማት መመለስ ይሳነዋል።

የኢህአዴግ ተሃድሶ መንግስት አሁን ካለበት ፍፁም አምባገነናዊነት ወደ ቀድሞ “ልማታዊ መንግስትነት” እንዲመለስ ማስቻል ነው። ነገር ግን፣ እያንዳንዷ የልማት እንቅስቃሴ ተጨማሪ የዴሞክራሲ ጥያቄ ታስከትላለች። በዚህም፣ ኢህአዴግ ምንም ያህል ለውጥና ተሃድሶ ቢያደርግ ለዴሞክራሲ ጥያቄ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት አይችልም። ነገር ግን፣ አሁን እያደረገ እንዳለው የሕዝቡን ጥያቄ በኃይል ማፈን ሊያቆም ይችላል። ይህ ሲሆን ከወታደር ጥይትና ከፖሊስ ዱላና እስር ጋር እየተጋፋ መብቱን እየጠየቀ ያለው ሕዝብ በአጭር ግዜ ውስጥ ከስልጣን ያወርደዋል። በመሆኑም፣ የኢህአዴግ ተሃድሶ ራሱ ኢህአዴግን ነው የሚጥለው። ከሌሎች አማራጮች በተሻለ ይህ በትንሽ ዋጋና ኪሳራ ኢህአዴግን ከስልጣን ማስወገድ እና አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትም መገንባት የሚቻልበት መንገድ ነው። በአጠቃላይ፣ ኢህአዴግ ካልታደሰ አይወድቅም፤ ቢወድቅም የሚፈለገው ለውጥ አይመጣም።

መዋሽት የወያኔ ግፈኞች በተለይ የሚታወቁበት!

$
0
0

(ተንሳይት በቃና)

ወልቃይትና ጠገዴ በፍጹም የትግራይ ክልል እንዳልነበሩ የሚያሳይ ነው።ይህም “The Book of Axum.. shows a traditional schematic map of Tigray with its city Axum at its Center Surrounded by the thirteen principalprovinces: Tembein, Shire, Seray Hamasen,

Bur,Sama, Agame, Amba Senait, Geralta, Enderta, Sahart andAbergele” የሚል ነው።ማጠቃለያ የወያኔ መንግስት ግፈኝነት፣ ዘረኝነት፣ ጠባብነት፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አየፈጀ ያለበትና፣ በተመሳሳይ ከዚህ በፊት እንደለመደው የእውሸት ፕሮፓጋንዳ ወይም ቅስቀሳ የትግራይን ሕዝብ በመጠቀም በማካሄድ ያለበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። እውሸትን ዛሬም የወያኔ ባለስልጣናት እንደ እንድ የትግል ዘዴ በመጠቀም አየዋሹ በመቀስቀስ ላይ እንዳሉ ነው።ይህንን በተለይ የትግራይ ሕዝብ ሃቁን በመከታተል የወያኔ ባለስልጣናት የእውሸት ቅስቀሳ ሰላባ ላለመሆን ድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል። በአገራችን የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዜህ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ለማላቀቅና ሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚኖርባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የምትመሰረትበትን፣
እንዲሁም የመገንጠል ጥያቄ የማይነሳባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ሁለት አማራጮች ይኖራሉ። አንደኛው አማራጭ፣ በአገርና በሕዝብ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ሲባል የወያኔ መንግስት እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት በሚፈጠረው የሽግግር መንግስት ሲጠቃለልና ሲቋቋም ነው።ይህም የወያኔ መንግስት የዴሞክራሲያዊ አሰራር መርሆችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሲቀበልና አሁን እንደ መንግስት የሚቆጣጠራቸውን የመንግስት መዋቅሮችን የስልጣን አውታሮች መሉ በሙሉ ራሱን ካገለለ፣ የመጨቆኛ መሳሪያዎቹ ፈርሰው ስልጣኑን ለሚቋቋመው የሽግግር መንግስት የሚያስረክብ ሲሆን ብቻ ነው። ሁለተኛው አማራጭ፣ የወያኔ መንግስት በአንደኛው አማራጭ መሰረት ሰላማዊ ሽግግሩን የማይቀበል ከሆነ፣ የኢትዮጵያ የተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች በሙሉ የጋራ የሽግግር መንግስት ፕሮግራም በጋራ ነድፈው፣ ለነደፉትና ለተስማሙበት የሽግግር መንግስት ፕሮግራም ትግላቸውን መቀጠል ይሆናል። የመጀመሪያው ዓላማቸው የዘረኛውን የወያኔ መንግስት ከስልጣን ማስወገድና ከዚያ የጋራ የሽግግር መንግስት ለማቋቋምና ፕሮግራሙን ተግባራዊ ማድረግ ይሆናል። ተንሳይት በቃና
ሰፕቴምበር 19 ቀን 2016 ዓ.ም.

የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር ስዩም ተሾመ በወቅታዊው የመምህራን ውይይት እና የዝምታ ተቃውሞ ዙሪያ ሊደመጥ የሚገባው ቃለምልልስ ሰጥቷል |ይዘነዋል

$
0
0

“… መምህሩ ለመንግስት ደጋግሞ ተናግሯል።የሚሰማ የለም። ለማይሰማኝ አካል እንዴት ደግሜ እናገራለሁ ብሎ በዝምታ ተቃውሞውን ገልጿል። ዝምታው ውጤት ያመጣል ወይ…ሁኔታዎች ወደ ተረጋጉ የሕዝቡ ጥያቄ ተገቢ መልስ የሚያገኝበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ።ለውጥ መደረግ አለበት ይህ ካልሆነ ግን ሕዝቡ ራሱ መንግስትን ይለውጣልያ ሲሆን ግን…”   የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር ስዩም ተሾመ ከህብር ሬዲዮ በወቅታዊው የመምህራን ውይይት እና የዝምታ ተቃውሞ ላይ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በኒውዮርክ እና አካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን

$
0
0

nyc
የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በኒውዮርክ እና አካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን

“ሰው አልባ መዲና!” –የጎንቻው!

$
0
0
Woyanes shoud face justiceእነሆ ወንጀለኛው ወያኔ የሚያኖጋው የግፍና የበቀል ጅራፍ፤በወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን ግፍና በደል ስንሰማ፤ቁጭቱ፤ሃዘኑ፤ንዴቱ አንዳንዴ ውቅያኖስ አልፎም ያማል፤እንቅልፍም ይነሳል፤በእንቅልፍም፤በእውንም ያስቃዣል። እርግጥ ነው ኢትዮጵያዊያን በተለይ በውጭ ታላላቅ መዲህናዎች ጭምር ጩኸታችንን ከፍ አድርገን እያስማን እንገኛለን። አንዳንዴም የወገናችንን የግፍ መጠን በቃል መግለጽ ሲያቅተን ሹመው፤ሸልመው ወያኔን ያነገሱብንን ኃያላን መንግስታት ያበጁልንን አጥርና ድንበር አልፈን በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ቢሮ በር ደርምሰን ከገቡትም አንዱ ሆኘ ለመታዘብ በቅቻለሁ። አድራጎቱ እንደ ደንባቸው የሚያስወቅስ የሚያስከስስ መሆኑን አጥተነው አልነበረም ግን የመጣው ይምጣ ብለን ነበር፤ ምንም እንኳ በጥይት እንደማይረሽኑን ተስፋ ብናደርገም።
ታዲያ የሀገራችንን መዲና ሕዝቦች የዚህን አውሬ (ወያኔ) እራስና ሰንኮፍ አዲስ አበባ (ሸገር) በከርሷ አዛላ ዙሪያዋን ወገን በሞትና በሽረት ተጋድሎ እየዋለ ዳሩ ግጥሚያው ለግዜው (በዳዊትና ጎልያድ) ጋር የሚነፃፀር ቢመስልም በመጨረሻ ድሉ ግን የሕዝብ ነው።  ‘መናኸሪያችንን’ ግን ከ’ዝምታዋ’ ጋር መዋል ማደሯን ሳስተባቃ የወቀሳና የቅስቀሳ ብዕሬን መሰንዘር ግድ አለኝ።  [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን የመስቀልን በዓል አዲስ በገዛው ሜዳ እንደሚያከበር አስታወቀ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን አሜሪካ ካሉ ታላላቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናት መካከል አንዱ የሆነው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም የዘንድሮውን የመስቀል በዓል አዲስ በገዛው ሜዳ ላይ እንደሚያከብር አስታወቀ::

የቤተክርስቲያኑ ቦርድ ሊቀመበር አቶ መላኩ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን በሚኒያፖሊስ በገዛው መሬት ላይ ባለ3 ወይም በ5 ጉልላት ቤተክርስትያን ለመገንባት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል:: በዚህም መሰረት “የራስችን ሜዳ እያለን ፓርክ ሄደን የመስቀልን በዓል አናከብርም ያሉት: አቶ መላኩ ም ዕመናን የ እግዚአብሔርን ቤት ለመገንባት በገዙት በራሳችን መሬት ላይ የዘንድሮውን የመስቀል በዓል የፊታችን ቅዳሜ በደመቀ ሁኔታ እናከብራለን ብለዋል::

በዚሁ የመስቀል በዓልም በሃገር ቤት በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ጸሎት እንደሚደረግ አቶ መላኩ አስታውቀዋል::

ቦታውን እና ሰዓቱን የሚያሳየውን ፍላየር ይመልከቱ::
deb

በባህር ዳር ሆምላንድ ሆቴል ነጋዴዎችን ያሳተፈ ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው

$
0
0

ኢሳት (መስከረም 10 ፥ 2009)
በባህር ዳርና በጎንደር ሰኞ ዕለት የተጀመረው አድማ በቀጠለበት ወቅት በባህር ዳር ሆምላንድ ሆቴል የተጠራው ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ም/ጠ/ም/ር እና የብአዴን ሊቀመንበር ደመቀ መኮንን በመሩት በዚሁ ስብሰባ ላይ የተጠሩት ነጋዴዎችና የአካባቢው ታዋቂ ሰዎች ሃገር የመምራት ብቃት ስለሌላችሁ ስልጣን ልቀቁ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሰብሳቢዎቹን “አሁን እናንተ አማራ ናችሁ ወይ?” በማለት አስተያየት የሰጡ ተሰብሳቢ አማራ ከሆናችሁ አማራው ሲገደል ለምን አይሰማችሁም በማለት ጠይቀው እባካችሁ አቅም ላላቸው ስልጣናችሁን ልቀቁ ሲሉ የተሰብሳቢውን የጭብጨባ ድጋፍ አግኝተዋል። “መፍትሄ እንፈልግ ብላችሁ እዚህ ሰብስባችሁን ወንድሞቻችንን እየገደላችሁ ሱቆቻችንን እያሸጋችሁ እንዴት እንመናችሁ?” በሚል ለተነሳው ተቃውሞ ተሰብሳቢው ድጋፉን መስጠቱንና የኢሳት ምንጮች ከስፍራው አድርሰዋል።

ባህርዳር ከተማ ነገ እሁድ ጠዋት በሰልፈኞች ትጥለቀለቃለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው

ባህርዳር ከተማ ነገ እሁድ ጠዋት በሰልፈኞች ትጥለቀለቃለች ተብሎ እየተጠበቀ ነው


የአማራ ክልልን ወደ ሱዳን መውጫ በመንሳት፣ የራስ ዳሸንን ተራራ የትግራይ ክልል ነው በሚል በመማሪያ መጽሃፍ ላይ መታተሙን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ አቶ ደመቀ መኮንን የሰጡት ምላሽ ተሰብሳቢውን ፈገግ ያስደረገ እንደነበርም ተመልክቷል። ካርታው ሆን ተብሎ አይደለም የተሰራው በስህተት ነው ያሉት አቶ ደመቀ መኮንን፣ ካርታውን የሰራውም የትግራይ ሰው ሳይሆን፣ የጋሙ ጎፋ ሰው ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ሆኖም በተሰብሳቢው በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱም ተመልክቷል።

ሦስቱ የሕዝብ ማስጠንቀቂያዎች

$
0
0

በዲ/ን ዳንኤል ክብረት
ሕዝብ ለመሪው በሦስት ደረጃ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡ የመጀመሪያው ‹አርም› የሚል ነው፡፡ በዚህ ደረጃ ሕዝቡ ሦስት ነገሮችን አምኗል ማለት ነው፡፡ አንድም መሪው በጎ ኅሊና አለው፤ ለማረም የሚችል ዐቅም አለው፤ ችግሩ የተፈጠረው ከአሠራሩ ላይ ነው ብሏል፡፡ አንድም ደግሞ ሕዝቡ፤ መሪው እንደ ማንኛውም ፍጡር ተሳሳተ እንጂ ራሱ ስሕተት አይደለም፡፡ ስለዚህ ሊያርም ይችላል ብሎ አምኗል። በመጨረሻም ሕዝብ መሪውን ይወዳል፣ ስሕተቱን ግን ይጠላል ማለት ነው፡፡
እዚህ ላይ የደረሰ መሪ የታደለ የሚሆነው ስሕተቶቹን ነቅሶ ‹ሳይርቅ በቅርቡ፣ ሳይደርቅ በርጥቡ› ለማረም ከቻለ ነው፡፡ የሚሳሳት ፈጣሪ እንደሌለ ሁሉ የማይሳሳት መሪ የለም፡፡ መሪዎችን ታላቅና ታናሽ የሚያደርጋቸው ስሕተታቸውን ለማመንና አምነውም ለማረም ያላቸው ዐቅምና ቁርጠኛነት ነው፡፡ መሪ የሕዝቡን ጥቆማ ሰምቶ፣ የሕዝቡንም ልብ አድምጦ ችግሩን በጊዜ ካረመ ስሕተቱ ከሥራ የመጣ እንጂ ከመሪው ጠባይ የመነጨ አይደለም ብሎ ሕዝብ በመሪው እንዲተማመን ያደርገዋል፡፡ ‹ከሰው ስሕተት፣ ከብረት ዝገት አይጠፋም› ብሎ ያልፈዋል፡፡ ሕዝብ የነገረውን ስሕተት ከማረም ይልቅ ‹እኔ ደኅና ነኝ ችግሩ ከአፈጻጸሜ የመጣ ነው› እያለ ችላ ካለው ሕዝብ ወደ ሁለተኛው ደረጃ ይሻገራል፡፡ ጃን ሜዳ ሠፍሮ እያደመ ራስ ተፈሪን ወደ ዙፋን ያመጣው መሐል ሠፋሪ ጦር (ሠራዊቱ) ነበር፡፡ በኋላም አርሙ ቢላቸው አላርም ሲሉ በ1953 መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው ይኼው ሠራዊት ነው፡፡
ሁለተኛው የሕዝብ ማስጠንቀቂያ ‹ታረም› የሚል ነው፡፡ ሕዝብ መሪውን ‹ታረም› ካለ ሁለት ነገሮችን አስቧል፡፡ ‹መሪው ልክ ነበር ነገር ግን እንደ ማንኛውም ፍጡር ተሳስቷል› የሚለው ሐሳቡን ቀይሯል፡፡ ‹መሪው ስሕተቱን ሊያርም ይችላል› ከሚለው ወጥቷል፡፡ ይህንን ዕድል ላይመለስበት አልፎ መሪው ስሕተት የሚሠራ ሳይሆን ስሑት (የተሳሳተ) መሪ ነው፡፡ ስሕተቱ ከሥራ ሂደት ሳይሆን ከአመራሩ፣ ከአስተሳሰቡና ከአካሄዱ የመጣ ነው፡፡ ተግባሩ እንዲስተካከል መሪው መስተካከል አለበት ብሎ ሕዝቡ አምኗል ማለት ነው፡፡ ከኩርንችት በለስ፣ ከአጋምም ወይን ሊለቀም አይችልም፡፡ ውኃው እንዲስተካከል ምንጩ መስተካከል አለበት ብሎ ሕዝብ ማሰብ ጀምሯል፡፡ እንደዚያም ቢሆን ግን መሪው ራሱን ሊያርም የሚችል መሪ ነው ብሎ አምኗል፡፡
በዚህ እርከን ላይ የደረሰ መሪ ራሱን ፈትሾ፣ መርምሮና አንጥሮ እንደ ወይን ግንድ እየገረዘ ሸለፈቱን መጣል አለበት፡፡ ሌላውን ሰውነት ለማዳን ሲባል ሕመምተኛው የሰውነት አካል እንደሚቆረጠው ሁሉ፣ ሀገርን ለማዳን ሲባል የሚቆረጡ አሠራሮች፣ አስተሳሰቦች፣ አካሄዶች፣ መሪዎች፣ ፖሊሲዎችና መርሖች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ‹ታረም› የተባለ መሪ እነዚህን አርሞ እንደ እባብ ሳይሆን እንደ ንሥር ታድሶ ከመጣ፤ ጥፋቱ ከአፈጻጸሜ የመጣ ነው፣ ሕዝቡ ስላልገባው ነው፣ ስላልተማረ ነው፣ ስላልሠለጠነ ነው፣ እያለ የመሥዋዕት በግ ፍለጋ ካልኳተነ፤ ‹ችግሩ እኔ ነኝ፤ መፍትሔውም የእኔ መለወጥ ነው› ብሎ ካመነ፤ አምኖም ከሠራ፤ ሠርቶም ከተለወጠ፡፡ ሕዝቡ፡-

daniel
‹አሁን ወጣች ጀንበር
ተሸሽጋ ነበር› ብሎ ይቀበለዋል፡፡
ይህንን ሁሉ ትቶ መሪው በሕዝቡ ትዕግሥት ላይ ከቀለደ፤ ሕዝብም ለትዕግሥቱ ምላሹ ካለፈው የባሰ፣ ከተስፋው ያነሰ ሲሆንበት፤ ሕዝብ አመለካከቱን ይቀይራል፡፡ አርም፣ ታረም ማለት ዋጋ አልባ መሆኑን ይረዳል፡፡ ሊያርም ሊታረም የሚችል መሪና አመራር የለም ብሎ ያምናል፡፡ ችግሩ መሠረታዊ ነው ብሎ ይረዳል፡፡ በዚህ ጊዜ ሦስተኛውንና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያውን ይሰጣል፡፡ ንጉሥ ኃይለ ሥላሴን ሆ ብሎ ወደ ሥልጣን ያመጣው ወታደር፣ ስሕተቶቻቸውን ማረም ሲያቅታቸው በ1953 መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው ወታደር፤ በ1966 ደግሞ ሥልጣናቸውን አሳጣቸው፡፡ የ1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት ‹ታረም› የሚል መልእክት እንዳለው ንጉሡ ቢረዱ ኖሮ የ66ቱን ነገር ያስቀሩት ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ‹ታረም› የሚለውን አልረዳ ሲሉ ‹ተወገድ› የሚለው የመጨረሻው ማስጠንቀቂያ መጣ፡፡
ደርግም እንዲህ ነበር፡፡ በ66 አብዮቱ ሲፈነዳ፣ መሬት ላራሹ ሲታወጅ የሕዝብ ድጋፍ ነበረው፡፡ ቆይቶ ስሕተት ሲያበዛ ‹አርም› የሚለው መልእክት ከያቅጣጫው መጣ፡፡ ሰልፎች፣ ወረቀቶች፣ ተቃውሞዎች መጡ፡፡ ከማረም ይልቅ ‹መረምረም› ስለመረጠ የመጀመሪያውን ዕድል አሳለፈው፡፡ ከውስጥና ከውጭ ጠብመንጃ አንሥተው ግራ ቀኝ የወጠሩት ኃይሎች ‹ታረም› ቢሉትም መታረም ትቶ ማውደምን መረጠ፡፡ የ1981 ዓ.ም መፈንቅለ መንግሥት ‹ተወገድ› የሚለውን መለከት ነፋ፡፡ ደርግ የሚተርፍ መስሎት ለፋ፡፡ ግን ተወገድ ከተባለ በኋላ መትረፍ በተአምር ብቻ ነበርና ሊተርፍ አልቻለም፡፡
ይህ ‹ተወገድ› የሚለው ሦስተኛው ማስጠንቀቂያ የመጨረሻው የሕዝብ ጥያቄ ነው፡፡ መሪው ታምሞ አይደለም፡፡ ራሱ በሽታ ነው፡፡ ተቸግሮ አይደለም። ራሱ ችግር ነው፡፡ ደክሞ አይደለም፡፡ ራሱ ድካም ነው፡፡ ተፈትኖ አይደለም፤ ራሱ ፈተና ነው ብሎ አምኗል፡፡ ስለዚህም መፍትሔው መወገድ ብቻ ነው ብሎ ይቆርጣል፡፡ ቆርጦም ይሠራል፡፡ ሕዝብ እዚህ ደረጃ ከደረሰ በኋላ መመለስ ብዙ ጊዜ ከባድ ነው። ማረምንም መታረምንም ከሚቀበልበት እርከን አልፏልና ቀሪው ዕድል የሚሆነው በሰላም መሰናበት ነው፡፡
የአንድ መሪ ብስለት በሁለት ደረጃ ይለካል፡፡ የመጀመሪያው ሲቻል በፊተኛው፣ ሳይቻል በቀጣዩ ደረጃ ላይ መንቃት፣ ነቅቶም ተገቢውን ማድረግ። ያም ዘመን ካለፈና ጀንበር ካዘቀዘቀች ደግሞ ራሱንም ሀገሩንም ሳያጠፋ መልካም የወንድ በር ማዘጋጀት ነው፡፡
ዘቦ እዝን ሰሚዐ ለይስማዕ፡፡

ሃምሳ ሎሚ ላምሳ…

$
0
0

በፍቃዱ ዘ-ሃይሉ

ቂሊንጦ፣ ቃሊቲ፣ ሸዋሮቢት እና ዝዋይ (የፌዴራል መንግሥቱ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ) ስንት በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት የታሰሩ የኅሊና እስረኞች ያሉ ይመስላችኋል? በቂሊንጦ ብቻ ከ500 የማያንሱ እንዳሉ አውቃለሁ። እዚህ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሥማቸው ደጋግሞ የሚነሳው ስንቶቹ ናቸው?
እስር ብዙ እስረኞች አሳይቶኛል። አባል ነህ የተባለበትን ፓርቲ (አዴኃን) ሥም ለመጀመሪያ ግዜ ማዕከላዊ የሰማ ልጅ ገጥሞኛል – ተፈርዶበት ጨርሶ ወጥቷል። ‘የኦነግ አመራሮች እነማን ናቸው?’ ሲባል ‘እነ አባዱላ’ ያለ እስረኛ ገጥሞኛል። እህል ውኃ የማይለውን ‘ደያስ’ እየበላ የሚያድር፣ መቀየሪያ ልብስ የሚቸግረው የቀድሞ የጋምቤላ የክልል ፕሬዚዳንት፣ አስታዋሽ የሌላቸው የጦር ጀት አብራሪዎች፣ የፓርቲ አመራሮች… ሌሎችም ገጥመውኛል። እኔ በነበርኩበት ጊዜ የነበሩት በብዛት በሃይማኖት ነጻነት ጥያቄ የገቡ ሙስሊሞች፣ የጎንደር አማራዎች፣ የኦሮሞ ተማሪዎች፣ ከጋምቤላ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ የመጡ ወጣቶች፣ የድምሕት ትግራዋዮች፣ እንዲሁም በርካታ ኢትዮጵያውያን ሶማሊዎች ነበሩ። ብዙዎቹ አንድ የሚያደርጋቸው ብዙም (ወይም አንዳንዶቹ ጭራሽ) አስታዋሽ የሌላቸው እና ለምን እንደታሰሩ እንኳን የሚያውቅላቸው የሌላቸው መሆኑ ነው። እዚያ ውስጥ እያለሁ የእያንዳንዱን ታሪክ ላለመስማት እሸሽ ነበር። ከተፈታሁ በኋላ ደግሞ ለማውቃቸው በሙሉ መድረስ ባለመቻሌ፣ አንዳንዴ “ብታሰር ይቀለኝ ነበር?” እላለሁ። ያኔ እኔም ከነርሱ ብዙም አልለይምና ቢያንስ ቁጭቱ ይቀንሳል!

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)

(ጋዜጠኛ በፈቃዱ ኃይሉ)


መስከረም ሳይጠባ የቂሊንጦ እስረኞች በእሳት እና በጥይት ተለበለቡ። ከዚያ በኋላ ሸዋሮቢት እና ዝዋይ ሲዛወሩ ከለበሷት ልብስ በቀር ጫማ እንኳ አልነበራቸውም። ከእነዚህ ውስጥ አስታዋሽ ያላቸው ወዲያው ጫማና ልብስ ገባላቸው። የሌላቸው ግን እስካሁንም በባዶ እግራቸውን ይንከላወሳሉ። ከዚህም በባሰ በሕይወት የተረፉት እና ያልተረፉት ማንነት በቅጡ አልተለዩም፤ አስታዋሽ የላቸውማ!
‘ቂሊንጦ ካሉት ከ500ዎቹ ውስጥ ስንቱ በወንጀል የሚያስጠይቅ ጥፋት አጥፍቷል?’ ብትሉኝ መልሴ ‘ከዐሥር የማይበልጠው’ የሚል ይሆናል። ዞሮ፣ ዞሮ ለዚህ የዳረጋቸው የፖለቲካ ስርዓቱ ሲሆን፣ ሁሉም ለውጥ ያመጣል የሚሉትን መንገድ በመከተላቸው የስርዓቱ ግዳይ የሆኑ ብቻ ናቸው።
እነዚህ የኅሊና እስረኞች ሁሉም ታዋቂ አይደሉም፤ የቤተሰብ እና የወዳጅ ድጋፍ የላቸውም። ብዙዎቹ ቤተሰቦቻቸው ገጠር ያሉ ናቸው። ብዙዎቹ የሚያስተዳድሩት ቤተሰብ ሲታሰሩ የተበተነባቸው ናቸው። ይህ እና ወኅኒ ቤት ውስጥ የሚደርስባቸው የሰብኣዊ መብት ጥሰት ሳያንስ፥ በተለያዩ ችግሮች ይፈተናሉ።
1ኛ፣ የተለያዩ መሠረታዊ ቁሳቁሶች (ለምሳሌ መቀየሪያ ልብሶች፣ የሌሊት ልብስ፣ ብርድልብስ ወይም አንሶላ፣ ሲታጠቡ ማድረቂያ ፎጣ…) የላቸውም፤ እንዲሁም የጥቃቅን (ለምሳሌ የሳሙና፣ የጥርስ ብሩሽ መግዣ እና አልፎ አልፎ ቡና መጠጫ…) ወጪዎች መሸፈኛ ገንዘብ የላቸውም። ጠበቃ መቅጠር ለነዚህ እስረኞች ቅንጦት ነው። ጥቃቅን ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎች ለፖለቲካ እስረኞች አልተፈቀዱም።
2ኛ፣ የሰው ረኀብ አለባቸው። እነርሱን ለመጎብኘት ብሎ የሚሔድ ሰው ያላቸው ጥቂቶች ናቸው። ወኅኒ ቤት ውስጥ ብዙ ሰው ቢኖርም ከብቸኝነት ስሜት አያድንም።
3ኛ፣ የመረጃ ረኀብ አለባቸው። አገሪቷ ውስጥ ምን እየተካሔደ እንደሆነ እስረኞች ለመስማት የሚፈልጉት ዋና ዜና ነው። ከኢቲቪ እና እስር ቤት ግቢ ውስጥ ከሚናፈሱ መጨበጫ የሌላቸው ወሬዎች በስተቀር ታማኝ ዜና የላቸውም። ራሳቸውን ከጊዜው ዕኩል የሚያስኬዱበት መረጃ ያስፈልጋቸዋል።
እነዚህ ግን ለብዙዎቹ የሕልም እንጀራ ናቸው።
እነዚህ ለትግሉ መስዋዕት የሆኑ ሰዎችን የምንይዝበት ወይም የምንተውበት ሁኔታ፣ ለለውጥ እየታገሉ ያሉት ላይ የሚያሳድረው አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተፅዕኖ መካድ አንችልም። እኔ ምን ማድረግ እችላለሁ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። አሁን፣ እስረኞችን ለማስታወስ፣ ቢያንስ መሠረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት እየጣሩ ያሉ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። ሃምሳ ሎሚ፣ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው። ነገር ግን ሁላችንም የያቅማችንን ብንሞክርስ? ጊዜ ያለው አንድ ሰው መርጦ በቻለው ጊዜ እየሄደ ቢጎበኝስ? ገንዘብ ያለው አንድ ሰው መርጦ በየጊዜው ቢደጉምስ? ሃምሳ ሎሚው ለሃምሳ ሰው ጌጡ ማለት አይሆንም?

የወቅቱ የኢትዮጲያ የፖለቲካ ችግር መዘዝ (Root Cause) (አበራ ቱጂ)

$
0
0

መስከረም 8 ፣ 2009 ዓ.ምየወቅቱ የኢትዮጲያ የፖለቲካ ችግር መዘዝ (Root Cause) አበራ ቱጂአገራችን ኢትዮጲያ አስቸጋሪና የሚያስጨንቅ የፖለቲካና የአገር አመራር ችግር ውስጥ በገባችበት ወቅት፣ የተለያዩ የመፍትሄ ሃስቦች በፍትህ ፈላጊወችም ሆነ በገዥው ህውሃት መራሹ ኢህአድግ ይሰነዘራሉ። ብዙ ሰዎች የችግሩን መዘዝ (root cause) በተወሰኑ የመንግስትን ስልጣን፣ ደንብ ወይንም ህግ ለግል ወይም ለተውሰነ ቡድን ጥቅም ማግኛ በተጠቀሙ ግለሰቦች ወይም ቡድን የተፈጠረ ችግር አድረገው በተሳሳተ መንገድ ይመለከቱታል።የሚሰነዘሩት የመፍትሔ ሃሳቦች በእውነት ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመንቀልና ችግሩ ተመልሶ እንዳይመጣ በማድረግ በአገራችን ዘላቂ ፍትህ የሰፈነበት ስርዓት ለማምጣት ይረዳሉን ብሎ መጠየቅ ከሁሉም ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊታይ የሚገባዉ ጥያቄ ነው። ወያኔ ኢህአዲግ የችግሩን መዘዝ የተወሰኑ ባለስልጣኖች የፈጠሩትነው በማለት የተወሰኑ ባለስልጣኖችን በማተካካት የጥገና ለውጥ በማድረግ አሁንም አረመኒያዊ አገዛዙን አጠናክሮ ለመቀጠል እየተዘጋጀ ነው። ችግርን ለማስወገድ፣ የችግሩን መዘዝ (root cause) በዘዴ መመርመርና ማወቅ ያስፈልጋል። አሁን አገራችን የገባችበት ችግር መዘዝ ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ ይገባል። መዘዝ (root cause) የችግሮች መሰረት ሆኖ ችግሮች ወይንም ችግሮችን የሚያስከትሉ ሰንሰለታዊ ሁነቶችን የሚቀሰቅስና ልናስውግደው የምንችል የችግሮች ስርዎ-መንሴ ነው። መዘዝን ካስወገድነው የፈጠራቸው ችግሮችና ችግሮቹን ተከትለው የሚመጡ መጥፎ ወይም የማይፈለጉ ሁነቶች ለዘለቄታው ይጠፋሉ ወይም ተመልሰውአይመጡም። መዘዙን ሳናስወግድ፣ ሰበብ (triggering event) ወይንም ከላይ ከላይ ያሉ ችግሮች ወይንም የመዘዙ ምልክቶች ወይም መገለጫወች (manifestation) ላይ ብናተኩር፣ ችግሩ ተመልሶ መምጣቱ ወይንም ሌላ መልክ ይዞ መከሰቱ አይቀርም።በሌላ በኩል፣ ይህ አገራችን የገባችበትን ችግር፣ ኢትዮጲያ በተሻለ አቅጣጫና አስተዳደር ለመመራት የምትዘጋጅበት ጥሩ እድል ይዞልን እንደመጣ በመቁጠር፣ ይህን የቁጣና የቁጭት ሃይል ወደ አዎንታዊ ጉልበት በመቀየር፣ ከችግሩ አዙሪት መውጣት እንድንችል የአገራችንን የፖለቲካ መዘዝ በማስወገድና፣ አገራችን የህግ የበላይነት የሰፈነባትና የቂም-በቀል ፖለቲካ የማይኖርባት ሆና፣ እንድትቀጥል መስራት አለብን። አሁን ያለውን ችግር ከስፋቱና ጥልቀቱ የተነሳ በተወሰኑ ዓርፍተ ነገሮች መግለጽ ያስቸግራል። ዋናው ችግር ግን ኢትዮጲያዊያን እንደ አንድ በአገሩ በነጻነት ሰርቶ የመኖር መብት እንዳለው ሰብዓዊ ፍጡር ሳይሆን፣ የወያኔ መንግስትና የፈጠረው ስርዓት፣ ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ያለፍርድ ይገድሏቸዋል፣ሰቆቃ ይፈጽሙቧቸዋል፣ንብረታቸውን ይቀማሉ፣ እንዳይናገሩና አንዳይደራጁ ያፍኗቸዋል፣ የወያኔን ብልሹ መርህ፣ ‘ፖሊሲ’ ወይም ‘ዶክትሪን’ እንዲቀበሉ ያስገዲዷቸዋል፤ ሰወች በሰብዓዊ ሃይላቸው በነጻነት መስራትና መጣር ማደግና መጠቀም ይከለከላሉ። በአጭሩ የኢትዮጲያ ዜጎች በወያኔወችና ወያኔወች በፈጠሩት ስርዓት ተፈጥሯዊና ህጋዊ መብታቸው ተገፎ ወንጀል እየተፈጸመባቸው ነው።የዚህን የአገራችንን ዘርፈ-ብዙ ችግር መዘዙን ለማወቅ “ችግሩ ለምን ተፈጠረ ወይም ምን አመጣው’ በማለት የችግሩን ስር ወይም መዘዝ እስከምናገኝ ተከታታይ ጥያቄወችን ማንሳት ያስፈልጋል። ለምሳሌ ያህል አንድ የችግሩን ሁነት (event) እንመልከት። በሰላም የመብት ጥያቄ ያቀረቡ ሰለማዊ ሰልፈኞች ለምን በመንግስት አነጣጥሮ ተኳሾች ይገደላሉ? ለዚህ የሚጠበቀው መልስ የመንግስት ባላስልጣን የግድያ ትዕዛዝ ስለሰጠ ነው እንበል። ይህን የግድያ ትዕዛዝ የሰጠ የመንግስት ባላስልጣን ከቦታው ቢነሳ፣ ሰለማዊ ሰልፈኞችን መግደል ያቆማል ወይ? ለዚህ ምሳሌ ማየት ያለብን፣ አቶ መለስ ዜናዊ የ 1997 ምርጫ ተክትሎግድያ አዘው ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰለማዊ ሰልፈኞችን አዲስ አበባ ዉስጥ ብቻ በግፍ አስገድለዋል። እሳቸው በሞት ሲለዩ የተኳቸውና እግዚአብሄርን ይፈራሉ ይባል የነበረው የወላይታው ተወላጅ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተመሳሳይ ትዕዛዝ በመስጠት በመቶወች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን እያስገደሉ ነው።የክልል መሪወችም ሆነ የተውሰኑ የጦር ጄኔራሎች የወያኔን አጥፊ ተልዕኮ ከፈጸሙ በኋላ ተተክተው አይተናል። የህዝብ ሃብት ዘረፉ የተባሉና፣ በዘረኛ ቅስቅሳ ህዝቡን በጠላትነት ያነሳሱ የነበረው ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ተተክተው አይተናል። ሰወቹን በመቀያየር መንግስት የበለጠ ችግር ሲፈጥር እንጂ ሲያሻሽል አልታየም። የህግም ማውጣት ችግሩን አልፈታም። ለዚህ የሚጠቀሰው የጸረ-ሙስና ህግ የሚባለው ማስመሰያ ነው። የችግሩ መዘዝ የተጻፈ ህግ እጥረትም አይደለም፣ ያለው ህግ ይህን ግልጽ ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል የሚችል ነበር። ስለዚህ ተጨማሪ ህግ በማውጣት ወይንም ሰወችን በመቀየር ብቻ ችግሩን ማጥፋት ወይም ተመልሶ እንዳይከሰት ማድረግ አልተቻለም። በመሆኑም የችግሩ መዘዝ የተወሰኑ ስልጣን ላይ ያሉት ሰወች ወይንም የህግ፣የብልሹ አስተዳደር፣ የሙስና፣ የህዝብ ንብረት ምዝበራ፣የችሎታ ማነስ ወይም የአፈጻጸም ጉድለት አይደለም። እንዚህ መዘዙ ያመጣቸው የችግሩ ምልክቶች ወይም ሁነቶች ናቸው።ዛሬ የሚገድሉትና የሚያስገድሉት የወያኔ ባለስልጣኖች ከስልጣን ቢወገዱና የመሰረቱት ዘረኛ፣ አድሏዊና አፋኝ ስርዓት (system) እስካለ ድረስ ችግሩ ይቀጥላል ወይንም መልኩንና ሰወችን እየቀያየረ በድጋሜ ይመጣል። ስርዓቱ የወያኔን መሰሪና በጥላቻ ላይ የተመሰረተ ተልዕኮ ለመፈጸም ሲባል የረቀቀ መዋቅር ተዘጋጅቶለታል። ስርዓቱን እንዳይወድቅ ደግፈው የያዙ፣ የተሳሰሩና እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉ፣ ብዙ ምሶሶወች አሉት። ስርዓቱን ቀጥ አድርገው የያዙት፣ እያደሱና እየጠገኑ ያቆሙት የሚከተሉት ዋልታወች ናቸው።1. በዘርና ቋንቋ ከፋፋይ መርህ፤ የዚህ ስርዓት የመሃል ምሰሦ የሆነው አገሪቱን በዘርና ቋንቋ መከፋፈሉና የፈጠረው የዘር ጥላቻ ፖለቲካ ነው። ይህ ወያኔወች የኢትዮጲያን ታሪክ በማጥፋት ህዝቡን ለመቆጣጠር ያመጡት የጎሳ ፖለቲካ ለወያኔው ስርዓት ከሁሉም በላይ መድህኑ ሁኗል። ኢትዮጲያኖች የአገራቸውን ችግር በጋራና በሰለጠነ መንገድ ተወያይተውና ተቀራርበው እንዳይፈቱ፣በአገር አቀፍ ጉዳይ ላይ ከማትኮር ይልቅ በመንደር ድንበርና በጥላቻ ፖለቲካ እንዲጠመዱ አድርጓቸዋል።2. አፋኝ ጦርና የስለላ ድርጅት¤ ስርዓቱን የሚቃወሙትን ሁሉ ለማፈን በወያኔ ታማኞች በበላይነት የሚመራ አገርና ህዝብን ሳይሆን ወያኔወችንና ስርዓቱን የሚጠብቅ የጦርና የፖሊስ ሃይል አለ። ዜጎችን ለመቆጣጠርና የመንግስትን ተቃዋሚወች ለማጥፋት ወያኔወች ከሚመሩት የስለላ ድርጅት በተጨማሪ፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩና ቴሌኮሙኒኬሽን ይጠቀማል።3. በፖለቲካ ድርጅቱ ቁጥጥር ስር ያለ ምጣኔ ሃብትና የዕምነት ተቋማት፤ ስርዓቱን በገንዘብ ሃይል ለመደገፍና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በመስጠት ደጋፊውችን ለማብዛትና ተቃዋሚወችን ለማዳከም የኢኮኖሚ አውታር የሆኑትን ያአገሪቱን መሬት፣ ባንክ፣ የንግድ ተቋማትን እንደ አየር መንገድ፣ ኤፈርት፣ ሜቴክ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ መብራት ሃይልና የመሳሰሉትን በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል። የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በወያኔ ደጋፊወች ብቻ በመሙላት የስርዓቱን እድሜ ለማራዘምና የዜጎችን ዕለት ከዕለት ኑሮ ለመቆጣጠር ይጠቀምባቸዋል። የዕምነት ድርጅቶችን በወያኔ ታማኞች እንዲመሩ በማድረግ ህዝብ ሲበደል አንዳይነሱ አድርጓል።4. ተቃዋሚወችን የሚያጠፋ የይስሙላ የፍትህና የምርጫ ድርጅቶች፤ ካለው የአንድ-ድምፅ ፓርላማ በተጨማሪ ለይስሙላ ያሉ የፍትህ መስሪያ ቤቶች የወያኔን ስርዓት “ህጋዊ” ጠለላ ይሰጣሉ። አፋኝ ህጎችን እንደ ጸረ-ሽብርና፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ህግ በማውጣት መንግስትን የሚቃወሙትንና የመብት ጥያቄ ያነሱትን በእስር ያሰቃያል፣ ሰቆቃ ይፈጽማል። ዜጎችን የመናገር፣ የመሰብሰብ፣የመደራጀት መብታቸውን ይነፍጋል።ለይምሰል ያህል ምርጫ ያካሂዳል፣ ከወያኔ በስተቀር ተመራጭ እንዳይኖር ያደርጋል። ምርጫን ያጭበረብራል።5. አማርጭ ሃሳብ የሚዘጋና ጥላቻ የሚነዛ የመገናኛ ብዙሃን፤ በወያኔወች የሚመሩትን በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ የመገናኛ ብዙሃንን፣ በህዝቡ መሃል ጥላቻን ለመዝራት፣ ውሸትን ለማሰራጨት፣ ህዝቡን የመንግስትን አቋም ብቻ እንዲከተል ለማድረግ፣ አማራጭ ሃስቦችን ዝግ ለማድረግ ይጠቀምባቸዋል። የግል መገናኛ ብዙሃንን፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን፣ የዝቡን ችግርና በደል እንዳያሳውቁ ፣ህዝቡን እንዳያነቁ ያጠፋል። የትምህርት ተቋማትን ወጣቱን በዘር ለመከፋፈል የጥላቻ ማስተማሪያ በማድረግ የወያኔ ካድሬ መፈልፈያ አድርጓቸውል።እነዚህ እርስ በእርስ የሚደጋገፉና የተሳሰሩ ምሶሶወችና፣ምሶሶወቹ የቆሙለት መሰሪ ተልዕኮ፣ መዋቅሩና ስርዓቱን የሚመሩትና የሚያገለግሉት ሰወች፣ በአንድ ተዋህደው ነው አሁን የደረስንበትን ችግር የፈጠሩት። ለዚም ነው ችግሩ ስርዓታዊ (systemic) ነው ወይም የችግሩ መዘዝ ስርዓቱ ነው የምንለው።ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት በአገራችን ያለው አደገኛ ሁኔታ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት ማንፌስቶ እንደሚገልጸው ወያኔውች በደደቢት የጀመሩት በይበልጥ በአማራ ላይ በአላቸው ጥላቻ ላይ የተመረኮዘ በልዩተንኮል የተዘጋጀ፣ ከፋፋይ፣ አድሏዊና አፋኝ ስርዓት ነው። አሁን ያለው ችግሩ በተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ የተፈጠረ ወይም በተናጠል የሚታይ አይደለም። በአገራችን ያለው ችግር ይህ ስርዓት እስካለ ድረስ ይቀጥላል። የችግሩ መዘዝ (root cause) ይህ ወያኔ የፈጠረው ስርዓት ነው። የችግሩን ወቅታዊ ሁነቶች፣ለምሳሌ አንደ የአዲስ አበባ ድንበር መስፋፋት ወይም የወልቃይት ጉዳይ ለጊዜው መልስ በመስጠት ችግሩን ለዘለቄታው መፍታት አይቻልም። ወያኔወች ዛሬ የፖለቲካ እስረኞችን፣ ምህረት ጠየቁ እያሉ ካደነዘዙና የአዕምሮ ሰቆቃ ከፈጸሙባቸው በኋላ ቢፈቷቸውም ነገ ደግሞ ባለተራወች ይገባሉ። ዛሬ ግድያቸውን ለጊዜው ቢያቆሙ ከተውሰነ ጊዜ በኋላ ይጀምራሉ። ወያኔወች በሃያ አምስት ዓመታት አገዛዛቸው ያሳዩን ሃቅ ይህን በደል ተራ በተራ መርሃ-ግብር አውጥተዉለት በተለያየ የህብረተሰቡ ክፍል ላይ መፈጸማቸውን ነው። ከሁሉም በላይ አገር ሊመሩ የሚችሉዜጎችንና ድርጅቶችን ገና ሲያቆጠቁጡ ያጠፋሉ። ዜጎችን ሰላማዊ አማራጮች ሁሉ እንዲዘጉባቸው በማድረግ ተስፋ በማስቆረጥ ወደጦርነትና ሃይል አማራጭ ይገፋሉ። በአገሪቱ የዘር ጥላቻን ይዘራሉ። እኛ ካልገዘናችሁ ህዝቡም አገሪቱም ትጠፋለች በማለት ህዝቡን ያሸብራሉ። በመግደል፣ በመዝረፍና በማሸበር መግዛት ከአገዛዙ ስርዓት እምነትና ተልዕኮ የመጣ እንጂ የተወስኑ አምባገነኖች ፍላጎት ብቻ አይደለም። ሰወቹ ቢቀያየሩም ይህ ስር የሰደደና በተንኮል የተዘጋጀ አፋኝ ስርዓት፣ ባለው አጥፊና የማያፈናፍን የድርጅትባህል (organizational culture)፣በስፋት በተደራጀው የስለላ ድርጅትና ሌሎች ከላይ የተጠቀሱ ዋልታወቹ ጋር በመሆን፣ አዲስ የሚቀላቀሉትን ግለስቦች ባህሪ ስርዓቱ በተቃኘበት መንገድ ይለውጠዋል። አቶ ኅይለማሪያም ደሳለኝ ከአነጋገራቸው ጭምር ዳግማዊ መለስ ዜናዊ ሆኑ እንጂ ራሳቸውን አልሆኑም።ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመግደል ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት ወያኔወች የተለመደ ድራማቸውን ይዘው ለመቅረብእየተዘጋጁ ነው። የታዘዙትም የክልል ባለስልጣኖች ትዕዛዙን ተቀብለዋል። ወያኔወች “በጥልቀት እንታደሳለን” እያሉ የሚያላዝኑት፣ ችግሩን የሚያዩበት መነጸራችው ያው ሃያ አምስት ዓመታት የገዛን ወያኔየዘረጋው መሰሪ ስርዓት ነው። የሚመሩበትም ፍጹም የተማከለ፣ ሚስጥራዊና ከፋፋይ፣ የማያፈናፍን፣ በተወሰኑ የህወሃት ሰወች የሚመራ፣ ስርዓት ነው። ወያኔወች ፈታኝ ወቅት ሲያጋጥማቸው በሚስጥር በመወሰን፣ ከስራቸው ያስጠጓቸውን ተለጣፊወች ተጠያቂ ያደርጋሉ። ሰሞኑን በረከት ስምኦን ይህን ነበር ያለው። “በኢትዮጲያ ዉስጥ ፈደራል የሚባል ህዝብ የለም ክልላዊ ህዝብ ነው ያለው ኢህአዲግ ለብልሽት ብሄራዊ ካባ ልንደርብለት አይገባም የሚል በጣም ጠንካራ አቋም ነው ያለው፣ በጣም ጠንካራ፣እያንዳንዱ ክልል፣ እያንዳንዱ ብሄራዊ ድርጅት የራሱን ብልሽት ራሱ ይታገል።” ይህም ወንጀሉን የሚፈፅመዉን የፌደራል መንግስት ከደሙ ንጹህ እንደሆነ ማቅረብ፣ አፋኙን ስርዓት ለማዳንና ለማጠናከር የተወሰኑ የአማራና የኦሮሞ ተለጣፊ መሪወችን፣ ህዝባቸውን ካስጨፈጨፉ በኋላ ሊወረዉሯቸው መሆኑን ሲገልጽ ነው። የወያኔ ኢህአዲግ ሰወች ማሰብና መጓዝ የሚችሉት ይህ ስርዓት ባሰመራላቸው ቀጭን መስመር ብቻ ነው። አንዳንድ የሚባንኑ የኢህአዲግ ሰወች ቢኖሩም እንኳ፣ ከዚህ ነገሮችን የመመልከቻ ዘይቤ (paradigm) ዉጭ ሊያስቡ አይችሉም። ሌላ አዲስ ነገር እንዳያስቡ ይህ ስርዓት አፍኖ ይዟቸዋል። በወያኔ የአዕምሮ ማደንዘዣና አስገዲዶ ማሳመን (indoctrination and brainwash) ያልተረቱ አንዳንድ የስርዓቱ አባላት ቢኖሩም እንኳን ከዚህ ወጭ ማሰብ ከጀመሩ ስርዓቱ በተለያየ ዘዴ ያጠፋቸዋል። ይህ የችግሮቹ ሁሉ ዋና ምንጭ የሆነ ስርዓትና፣ የችግሩን ሁነቶች የፈጠሩት ግለስቦች፣ ችግሩን በፈጠሩበት አስተሳሰባቸው፣ አገራችንን አሁን ከገባችበት የፖለቲካ ምስቅልቅል ሊያወጧት አይችሉም። እንዲያውም የህወሃት መንግስት ተጠናክሮ ለመቀጠል ይህን አጋጣሚ እየተጠቀመበት ነው።መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በአለባት ኢትዮጲያ ይህን ለሃያ አምስት ዓመታት እየገደለ በሰቆቃ የገዛንን ስርዓት አዝለን እንድንቀጥል የሚያስገድደን ምን ሁኔታ አለ? ወያኔ ለህዝብ ባለው ንቀት፣ ይህን ሁሉ ወንጀልና ግፍ በረቀቀ ዘዴ አቀነባብሮ እየፈጸመ፣ አሁንም ለኢትዮጲያ ከኔ በላይ አሳቢ የለም ይለናል። ከዘረፉት በተረፋቸው የብድርና እርዳታ ገንዘብ መንገድ ሰርተናል ከሆነ የሚሉን፣ ጣሊያንም እየጨፈጨፈን በአምስት ዓመታት የበለጠና እስካሁን እያገለገለ ያለ መንገድ ሰርቷል። የበደለ ቢረሳ የተበደለ አይረሳም። የኢትዮጲያ ህዝብ በዚህ ስርዓትና በወያኔ የደርሰበትን ግፍ ፍጹም አይረሳም። አገር ለመገንጠልና ለማስገንጠል አቅዶ የተነሳው የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ብዙ ሺህወችን ጨፍጭፎና አስጨፍጭፎ ስልጣን ላይ ወጥቶ በኢትዮጲያ ላይ ያደረሰውን በደል በዚህ አጭር ጽሁፍ ጨርሶ መዘርዘር አይቻልም። በመሃል አዲስ አበባ የተገደሉት እነ አሰፋ ማሩ፣ የእነ ሽብሬ ህይወት በግፍ የተጨፈጨፉት የጋምቤላ፣ ኦሮምያ፣ሲዳሞ፣ ኡጋዴን፣ አዲስ አበባ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወገኖቻችን ደም አሁንም ወደሰማይ ይጣራል። በገደሉት ልጇ አስከሬን ላይ አንድትቀመጥ አስገድደው የደበደቧትን የወለጋዋ እናት ሰቆቃ እግዚአብሄር ያያል። በወያኔ እስር ቤት የሚሰቃዩ በሺወች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን፣ የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች እምባ ወደአምላካቸው ይፈሳል። ይህንና ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ በደሎችን የፈጸመብንን ስርዓት ተሸክመን የምንጓዝበት ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል? አሁን ለደረስንበት የፖለቲካ ችግርና የህዝብ እምቢተኝነት መዘዙ ይህ አፋኝና ጨፍጫፊ ስርዓት ነው። ይህ ስርዓት ለሃያ አምስት ዓመታት በኢትዮጲያ ህዝብ ላይ የፈጸመው ወንጀል ራሱን ገፍቶ ሊያጠፋው ተቃርቧል። ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጲያው በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈል በአንድ ላይ ተነስቶ ይህን ግፈኛ ስርዓት ያስውግድ። ከዛ ዉጭ በችግሩ ምልክት ወይም ግለሰቦች ላይ ያተኮረ ትግል ወያኔወች የመሰረቱትን ስርዓት ዕድሜ ያራዝማል። ወያኔና ስርዓቱ አንገፍግፎናል። ይህ መሰሪ ስርዓት ፈርሶ በህግ የበላይነት የሚመራና ለዜጎች መብት የቆመ ስርዓት መመስረት አለበት። ትግላችን የጥላቻን ፖለቲካ የሚዘጋና የችግሩ ስርዎ-መንሰኤ ላይ ያተኮረ ይሁን። የኢትዮጲያ ህዝብ የአጋዚን ‘ስናይፐር’ ሳይፈራ መስዋዕትነት እየከፈለ ያለው፣ የተውሰኑ ትንንሽ ሌቦችን ከስልጣን ለማባረር ሳይሆን፣ ሃያ አምስት ዓመታት እየጨፈጨፈ የገዛንን ስርዓት ለማስወገድ ነው። ይህን ስርዓት ለመጣልና ትግሉን ግብ ለማድረስ፣ ኢትዮጲያኖች በመተባበርና ጥቃቅን ልዩነታቸውን ወደጎን በመተው፣በችግሩ መዘዝ ላይ የተቀነባበረና ስልታዊ እርምጃወችን ሊወስዱይገባል። አንድነት ሃይል ነው

የኦህዴድ ተሃድሶ ከማሳደድ ወደ ማውረድ( በስዩም ተሾመ)

$
0
0

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ  ሁለት ከፍተኛ አመራሮቹን፤ የፓርቲው ሊቀመንበርና የክልሉ ፕረዘዳንት የነበሩትን አቶ ሙክታር ከዲር እና ምክትል ሊቀመንበር የነበረችውን ወ ሮ አስቴር ማሞ ከኃላፊነት ማውረዱ ተገልጿል። በምትኩ አቶ ለማ መገርሳን ሊቀመንበር እና ዶ ር ገበየሁ ወርቅነህን በምሊቀመንበርነት መርጧል። ኦህዴድ “ ” ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮቹን ከኃላፊነት ማውረዱ በድርጅቱ ውስጥ ተሃድሶ እየተካሄደ ስለመሆኑ ይጠቁማል ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነት ለመውረድ ለማዕከላዊ ኮሚቴ ፍቃደኝነታቸውን እንደገለፁ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከድርጅቱ ታሪክ አንፃር ሲታይ ይህ በራሱ አንድ ነገር ነው። ከዚህ ቀደም ክልሉን በፕረዜዳንትነት ያገለገሉት አቶ ሀሰን ዓሊ እና አቶ ጁነዲን ሳዶ ከሀገር ተሰድደዋል። የቀድሞዋ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የነበረችው ወ ’ ሮ አልማዝ መኮ ን ጨምሮ እንደ ዮናታን ዲቢሣና ድርባ ሀርቆ ያሉ የቀድሞ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ሀገር ጥለው ኮብልለዋል። ይህ፣ ከሌሎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለየ፣ ኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮቹን ለስደት ሲዳርግ የነበረ ድርጅት ስለመሆኑ ያሳያል።

Opdo Muktar and aster
ለስደት ከመዳረግ በተጨማሪ፣ ኦህዴድ የቀድሞ አመራሮቹን ለሞት ሲዳርግ የነበረ ድርጅት ነው። የቀድሞ የክልሉ ፕረዘዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ አሟሟት፣ ከዚያ በፊት አቶ መኮንን ፊጤ፣ ባዩ ጉሩሙ እና አልማየሁ ደሳለኝ የተባሉ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች አሟሟት የሚጠቀስ ነው። ከዚህ አንፃር፣ አቶ ሙክታር ከዲር እና ወ ሮ አስቴር ማሞ፣ እንደ ከዚህ ቀደሙ ለሞት፥ ለስደትና ለእስራት ሳይዳረጉ፣ ፍቃደኝነታቸውን ተጠይቀው ከኃላፊነት መውረዳቸው በራሱ ትልቅ ነገር ነው። ከላይ እንደተጠቀሰው፣ የድርጅቱን አመራሮች ከማሳደድ ወደ ማውረድ መምጣቱ በራሱ እንደ ለውጥ ሊጠቀስ ይችላል። ነገር ግን፣ ኢህዴድ “ ” ኢህአዴግ የሚያስፈልገው ተሃድሶ ከዚህ ፍፁም የተለየ ነው። አቶ ሰለሞን ስዩም የተባሉ ኦህዴድ “ኢህአዴግን በቅርብ የሚከታተሉ የፖለቲካ ተንታኝ ስለ ድርጅቱ ለ መፅሔት ከሰጡት አስተያየት ውስጥ የሚከተለው የድርጅቱ ተሃድሶ ከየት መጀመር እንዳለበት በግልፅ ይጠቁማል/ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ኦህዴድ ኢህአዴግ የኦሮሞን ሕዝብ መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቂ የዕውቀት፣ የታሪክና የሞራል መሰረት የለውም። በእርግጥ የሕዝቡን መብትና ነፃነት የሚነፍጉ አመራሮች ላይ የተገቢነትና አግባብነት ጥያቄ መነሳቱ አያጠራጥርም። ስለዚህ፣ ድርጅቱ የሚያስፈልገው በውስጡ ያሉትን አመራሮች መቀያየር አይደለም። በፌደራል እና በክልል ደረጃ የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ፣ ታሪክና እሴት ተገንዝበው መብቱንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል ብቃት ባላቸው፣ በመንግስታዊ ሥርዓቱ ውስጥ የሚገባውን ስልጣንና የአመራርነት ሚና መወጣት በሚችሉ የሕዝብ ልጆች መተካት ያስፈልጋል። ይህንን ኦህዴድ ኢህአዴግ በሩብ ምዕተ አመታት ግዜ ውስጥ እንኳን ማሳካት አልቻለም። ከዚያ ይልቅ፣ የኦሮሞ ሕዝብ መብትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሲሟገቱ የነበሩትን ወጣቶችና የተቃዋሚአመራሮች ለእስርና ስደት ሲዳርግ ነበር። ኦህዴድ ለኦሮሞ ሕዝብ ሊያደርግ የሚችለው ትልቅ ውለታ እነዚህ በእስር ቤት ያሉ የሕዝብ ልጆች እንዲለቀቁ፣ በስደት ያሉትም ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነው። የድርጅቱ ያሉበትን ችግሮች አውቆ ዛሬ እየወሰደ ያለውን “ የማስተካከያ እርምጃ እንዲጀምር የማንቂያ ደውል ያሰሙትን ባለውለታዎቹን ሽብር፥ ሁከትና ብጥብጥ
” አስነስታችኋል በሚል ሲወነጅል ከርሟል። አሁን ላይ ችግሮቹን እንዲረዳ ለማድረግ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች “ ” ለሞትና ጉዳት፣ ሺህዎች ደግሞ ለእስራት ተዳርገዋል። ስለዚህ፣ የፓርቲው ተሃድሶ መጀመር ያለበት እነዚህን ወጣቶችና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ከእስርና ከስደት ነፃ እንዲወጡ በማድረግ መሆን አለበት። በአጠቃላይ፣ የኦህዴድ/ ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮቹን እንደ ከዚህ ቀደም ለሞትና ስደት ከመዳረግ ይልቅ በፍቃደኝነት ከኃላፊነት ማንሳቱ መልካም ነው። ድርጅቱ የሚያስፈልገው ተሃድሶ ግን በውስጡ ያሉትን አመራሮች መቀያየር አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ የኦሮሞ ሕዝብ በራሱ ምርጫና ፍላጎት – በነፃነት እንዲቀሳቀስ መፍቀድና ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ነው። ወደፊት በሕይወትና ንብረት ላይ ጥፋት ሳይደርስ ፓርቲው ያሉበትን ችግሮች ቀድሞ እንዲያውቅ፣ ህዝቡ ብሶትና ቅሬታውን በነፃነት እንዲገልፅ መፍቀድ አለበት። በተመሳሳይ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በክልሉ ውስጥ በነፃነት እንዲቀሳቀሱ መፍቀድና አስፋላጊውን ድጋፍ ማድረግ አለበት። የተሃድሶ ስም“ ” ዴሞክራሲ ይባላል። ያኔ የኦሮሞ ሕዝብ መብቱንና ነፃነቱን ተጠቅሞ የሚያደርገውን አብረን እናያለን።

የኦህዴዱ መሪ ወርቅነህ ገበየሁ ትግሬ ነው፤ ምስጢሩ እነሆ… (ከክንፉ አሰፋ )ጋዜጠኛ

$
0
0

ከምርጫው ጥቂት አስቀድሞ የወርቅነህ ገበየሁ አያት ስም ገብረኪዳን ነበር። የቀድሞ ወዳጄ ወርቅነህ የአያቱን ስም ከገብረ- ኪዳን ወደ ኩምሳ ለመቀየር የወሰደበት ግዜ እና ምክንያቱ አላስደነቀኝም። ይህንን የዘር ፖለቲካ ጨዋታ ጠንቅቆ የሚያውቀው ዶ/ ር መረራ ጉዲናም የተቃዋሚ እጩ ተመራጭ ነበር። ጉዳዩን ጠንቅቆ ያውቀዋል። በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካ ሳይንስ ፋካልቲ ስንማር ሁለታችንንም በአንድ ክፍል አስተምሮናል። የወርቅነህ ትክክለኛ አያት ስም ያለበት ሰነድም በእጁ አለ። ግን ጉዳዩን አላጋለጠውም። ምናልባት የሙያው ስነ- ምግባር ይህንን ለማድረግ አይፈቅድ ይሆናል።

workineh-gebeyehu-e1373066643891 ወርቅነህ ገበየሁ ሻሸመኔ ነው ተወልዶ ያደገው። እዚያ መኖሩ ደግሞ ኦሮምኛን አቀላጥፎ እንዲናገር ረድቶታል። ዘር መቁጠር ጸያፍ ቢሆንም ይህ ግን ታወቅ ያለበት ጉዳይ ነውና ርቅነህ ገበየሁ ወላጆች ኦሮሞዎች አይደሉም። ከትግራዩ አቶ ገበየሁ ገብራኪዳን ይወለዳል። ወርቅነህ ገበየሁ ውሎውም ቢሆን ከጆሌ ኦሮሞ ጋር አይደለም። ከነ ጌታቸው ረዳ፣ ከትግራይ ተወላጆች ጋር በብዛት ያዘወትራል። ለዚህም ምክንያት አለው። ይህ ሰው አሁን የኦሮሞውን ድርጀት እንዲመራ መመረጡ አንደኛው ምክንያት ነው። በህወሃት የፖለቲካ ጨዋታ ምክትል ሆነው የሚቀመጡት በዘር መስፈርት ተለክተው አልያም ታማኝ አገልጋይ ሲሆኑ ብቻ ነው። ዋናውን ስራ የሚሰሩትም በምክትል ስም ያሉት ናቸው። ከስር ሆነው ዋናዎቹን እንደ ሮቦት ያንቀሳቅሷቸዋል።ጠ/ ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ምክትሉ ደብረጽዮንን ያስተውሏል! ለመሆኑ ወርቅነህ ገበየሁ ማን ነው? ለምንስ ታስሮ ተፈታ? የወንጀል እስረኛ የነበረ ይህ ሰው እንዴትስ በጥቂት ጊዜ እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ ቻለ? ከዚህ ቀደም በማስታወሻዬ ላይ ያሰፈርኩዋትን ቁም ነገር ላካፍላችሁ። መልካም ንባብ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጭር ብሏል። ኢህአዴግ ወደ አዲስ አበባ ሲጠጋ፤ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ደግሞ ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ብላቴ ማሰልጠኛ ካምፕ ገብተው የተኩስ ልምምድ በማድረግ ላይ ነበሩ። በግንቦት ወር ኢህአዴግ ከተማውን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ተማሪዎች እንደወትሮው ጥቁር ጋዋናቸውን ለብሰው፤ የአበባ እቅፍ አልተበረከተላቸውም – 1983 ዓ.ም. ። ከወራት በኋላ በዩኒቨርስቲው አካባቢ ይመላለሱ የነበሩ ተማሪዎች ተስፋ የሚያስቆርጥ ዜና ሰሙ። አዲሱ የሽግግር መንግስት እንደከዚህ ቀደሙ ተማሪዎችን በየመስሪያ ቤቱ የማይመድብ መሆኑ ተገለጸ። ከዜናው ጋር የብዙ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ተስፋ አብሮ ጨለመ። በተለይ በወቅቱ በፖለቲካ ሳይንስ ለተመረቅነው ተማሪዎች፤ ምንም ክፍት የስራ ቦታ እንደሌለ በግልፅ ተነገረን። በዚህ አይነት ያለ ስራ ብዙ ቆየን። በወቅቱ በፖለቲካ ሳይንስ ከተመረቅነው መካከል በከፍተኛ ነጥብ የተመረቀው ወርቅነህ ገበየሁ ጭምር ምንም አይነት የስራ እድል ለማግኘት አልቻለም። ህወሃት ካመጣብን የዘር ፖለቲካ በፊት በትምህርት ቤትም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ከቶውንም የትውልድ ዘራችንን ተጠያይቀን አናውቅም። ማን ምን እንደሆነ፣ ለማወቅ ፍላጎቱም አልነበረንም። የኋላ ኋላ ግን ነገሮች እየተቀየሩ መጡ። በጓደኛሞች መካከል የሚፈጠር ጥርጣሬና፣ የዘር ግንድ ማጥናቱ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ እንደተስቦ ያመጣብን በሽታ ነበር እና የቅርብ ወዳጅን ማወቁ የግድ ሆነብን። ወርቅነህ ገበየሁም የሻሸመኔ ልጅ ከመሆኑ ባሻገር፤ ከትግራይ ሰው መሆኑን ያወቅነው ከዩኒቨርስቲ ከወጣን በኋላ ነበር። በወቅቱ ነበረው የሽግግር መንግስት ባወጣው የዘር መስፈርት መሰረት፤ ወርቅነህ በትግራይነትና በደቡብ ህዝብነት መካከል የቆመ፤ ምርጥ የትግራይ ልጅ አለመሆኑ፤ በዚህም ምክንያት ሊያገኝ ይችል የነበረው ጥቅማ ጥቅም በመቅረቱ የጓደኛችን ጉዳይ ያሳዝን ነበር።
ከብዙ ጊዜ አንዴ ስንገናኝ፤ አንዳንድ ጓደኞቻችን ፀጉራቸው አድጎ፤ ንፅህናቸው ተጓድሎ፤ ከስተውና ተኮሳምነው ይታዩ ነበር። ከነዚያ ከሰውነት ውጪ ከሆኑት ተማሪዎች መካከል አንዱ ወርቅነህ ገበየሁ ይጠቀሳል።የ 1980 ዎች አጋማሽ የፕሬስ ነጻነት የታወጀበት ወቅት በመሆኑ በርካታ መጽሄቶችና ጋዜጦች በገበያ ላይ ይውሉ ነበር። ሞገድ ጋዜጣም በወቅቱ ከነበሩት ከመጀመሪያዎቹ የነጻ ፕሬስ ጋዜጦች ረድፍ ላይ ይሰለፋል። ወርቅነህ ገበየሁም በነበረው አቋም ምክንያት የሞገድ ጋዜጣ ተባባሪ አዘጋጅ ሆኖ የመስራት እድሉን አገኘ። ወርቅነህ የጋዜጣው አዘጋጅ እንደመሆኑ መጠን በእለት ተለት የጋዜጣው ህትመት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም። ሆኖም ሳምንታዊ ደሞዙን ለመቀበል ወደ ቢሮ ሲመጣ በወጡት ዜናዎችና ጽሁፎች ላይ አልፎ አልፎ እንነጋገራለን። አንዳንዴም በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ስናገኝ፤ ከማንም በፊት ከወርቅነህ ጋር በመመካከር መስራታችንን ቀጠልን። አንድ ቀን የሃሙስ እትማችንን የውስጥ ገጽ ስራዎች አጠናቀን በፊት ለፊት ሊቀርቡ የሚገቡ ዜናዎችን እየመረጥን ሳለ፤ ስልክ ተደወለ። ግርማቸው ነበር።“ ሰላም ግርማቸው? ምን ዜና አለ?”“ ብቻህን ነህ?”“ ”አዎ“ ”ጥብቅ የሆነ ሚስጥር ነው። ተጠንቀቅ።“ ” ምንም ችግር የለም፤ ንገረኝ። አልኩና እስክሪብቶና ወረቀት አዘጋጀሁ። “ ግርማቸው ጉዳዩን ሙሉ ለሙሉ በስልክ ሊነግረኝ የፈራ ይመስላል። ፈራ ተባ እያለ፤ ከውጭ አገር ወደ …”ኢትዮጵያ የገቡ የኢህአፓ አባላት ናቸው“ እና ምን ሆኑ?” “ ግርማቸው አሁንም በስጋት ስሜት፤ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። ለማንኛውም ለምንአንገናኝም?” አለኝ።“ ፖስት ራንዴቩ እንገናኝ?” “ ”ስለው ከጭንቀቱ የገላገልኩት ያህል፤ አዎ እዚያ እንገናኝ። ረቡዕ ቀን ረፋዱ ላይ ፖስት ራንዴቩ ወደ ግርማቸው ጋ ስሄድ ብቻዬን አልነበርኩም። ወርቅነህ ገበየሁ አብሮኝ ነበር። በቀጠሮው ቦታ በሰዓቱ ተገናኘን። “ ግርማቸውን ፖስት ራንዴቩ ስናገኘው ዘና ብሎ ያጫውተን ጀመር። እንግዲህ ሰዎቹ የኢህአፓ አባላት ናቸው። ጉዳያቸው በሚስጥር መያዝ አለበት። ወደ አገር ቤት የመጡት ልዩ ሚሽን ተሰጥቷቸው ” ነው። ጉዳዩን ስትገናኙ በዝርዝር ትነጋገራላችሁ። አለንና ስለሰዎቹ ማንነት አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮችን ሲገልጽልን እስክሪብቶና ወረቀት አውጥቼ መጻፍ ጀመርኩ።“ ” በምታገኛቸው ጊዜ ይህንን የሚስጥር ኮድ መናገር አለብህ አለና የድብቅ ስማቸውን ነገረኝ።“ ‘ ’ ” የድብቅ መጠሪያ ስማቸው ቤሬክ ይባላል ሲለኝ ወረቀት ላይ ይህንኑ አሰፈርኩት። ወርቅነህም እስክሪብቶውን ከኪሱ አውጣ።“በዚህ ስልክ ደውሉና የእኔን ስም ጥሩላቸው። ለጋዜጣችሁ በርካታ መረጀዎችን ሊሰጡዋችሁይችላሉ።’ አለን ግርማቸው። ስልክ ቁጥራቸውን እየነገረን ወረቀት ላይ መጻፍ ስጀምር፤ ወርቅነህም ስልክ ቁጥሩን በእጁ መዳፍ ላይሲጽፍ አይቼ ሁኔታው አስገርመኝ። ነገር ግን በይሉኝታ ዝም አልኩት። በወቅቱ በርካታ ጋዜጦች የፈሉበት ጊዜ በመሆኑ፤ ወርቅነህ ይህንን ዜና ከሞገድ ጋዜጣ ውጪለሚታተሙ ፕሬሶች አሳልፎ ሊሰጥ ነው በሚል ጥርጣሬ ብቻ ድርጊቱ አስገረመኝ። ከአንድ የትምህርት ቤት ጓደኛ፣ ከዛ በላይ ላስብ አልችልም። ልጠይቀውም አሰብኩና ጠይቆ ከመቀያየም ዝም ማለቱንመረጥኩ። በወቅቱ በውስጤ ቅሬታ አሳደረብኝ። በሚቀጥለው ቀን… ግርማቸው በሰጠኝ ስልክ በተደጋጋሚ ብደውል እነ ቤሬክን ላገኛቸው አልቻልኩም።ቀን ላይ፣ በምሽት እና በሌሊት፣ ስልኩን መቀጥቀት ያዝኩ። ስልኩ ይጠራል። የሚመልስ ግን አልነበረም።ከቀናት በኋላ ግርማቸውን ለመፈለግ ዘወትር ወደምንገናኝበት ወደ ፖስት ራንዴቩ ለብቻዬ አመራሁ።ሌሎች ጓደኞቼ እንደወትሮው ክብ ሰርተው ይጫወታሉ። ግርማቸው ግን አልነበረም። “ግርማቸውስ?” አልኳቸው ወድያው እንደተቀላቀልኩ። ሞቅ ያለ ጨዋታቸውን እንዳቋረጥኳውይሰማኛል። “ሰላምታ አይቀድምም?” አለ አንዱ፣ ከፊቴ የሚነበበውን የደንጋጤ ስሜት በማስተዋል።“ቀን ላይ ተደዋውለን ነበር። በሆነ ጉዳይ ትንሽ ተረብሿል። ለማንኛውም ዛሬ እንደምንገናኝ ነግሮኝነበር።” ሲል ሌላኛው መለሰ። ግርማቸው አረፋፍዶ ብቅ አለ። ፊቱ ላይ አንዳች የብስጭት ስሜት ይነበባል። በውስጡ የታመቀውንንዴት ያወጣው ገና ወንበሩ ላይ ሳይቀመጥ ነበር።“ሰዎቹን አሳሰራችኋቸው አይደል?” ሲል ፍጹም ሃዘን በተሞላበት አንደበት ጠየቀ፣ ወደ እኔእየተመለከተ።“ወርቅነህ!” አልኩ ሳላስበው በመጮህ። በመካከላችን ለአፍታ ጸጥታ ሰፈነ። ለተልካሻ ነገር የጠረጠርኩት ሰው ከጀርባዬ ሆኖ ከባድ ወንጀል እየሰራኖሯል! የነ ቤሬክ መሰወር በውስጤ ጥርጣሬ፣ ፍርሃት እና ቅያሜ ፈጥሮብኝ ኖሮ ወርቅነህን እርቀው ጀመር፣ ከዛስልክ ከተቀበልንበት እለት በኋላም አልተገናኘንም። ከሞገድ ጋዜጣም ቀስ በቀስ እየራቀ መጣ።አንድ ቀን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ የሃይድሮ ፖለቲክስ ምሁር የሆኑትን ዶ/ር ያቆብአርሳኖ ስለአባይ ጉዳይ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ሄጄ ወርቅነህን ከሩቅ አየሁት። ከዚያ ደግሞ ተሰወረ። ስራዬን ጨርሼም ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ለመውጣት ስሯሯጥ ከኋላዬ አንድ ሰው ያዘኝ። እኔን ያላየኝ መስሎኝ ነበር። ከእነማን ጋር እንደምንገናኝና ምን እንደምሰራ በአይነ ቁራኛው ይከታተለኝኖሯል ወርቅነህ። “ለምንድነው የምትሸሸኝ?” አለኝ፣ እንደመቆጣት እያደረገው። ትንሽ እንደመደንገጥ ብዬ ስለነበር ለሰኮንዶች ጸጥ ካልኩ በኋላ “አንተስ ለምንድ ነው የምትከታተለኝ?”አልኩት በቁጣ። “እውነቱን እንድነግርህ ነው የምትፈልገው?… ተረጋጋ እና አድምጠኝ፣ ሁሉንም ጉዳይ እነግርሃለው።”አለኝ መልሶ ረጋ ባለ አንደበት። ቁጣዬን ለማብረድ ሲል ያደረገው ይመስላል። በድንጋጤ የተነሳየምናገረውም ጠፋብኝ እና ጸጥ ብዬ ከአንደበቱ የሚወጡትን ቃለት መተባበቅ ጀመርኩ።
“በደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥሬ እየሰራሁ ነው።” ሲለኝ ያልጠበኩትን ሚስጥር ድንገትስለነገረኝ ሁኔታው አስደነገጠኝ። “በደህንነት ውስጥ በመስራቴ ደግሞ እናንተን ከስንት አደጋ ጠብቅያችኋለሁ። በአጭሩ ‘I amprotecting you’ ስለዚህ አትሽሸኝ።” አለኝ። ከእግር ጥፍሬ እስከራስ ጸጉሬ አንዳች ነገር ወረረኝ።ልቤ በፍጥነት ሲመታ፣ ደምስሮቼ ሲገታተሩ ተሰማኝ። “እና ሰዎቹን…” መናገር አልቻልኩም።“የምን ሰዎች?”“እነቤሬክን ያሳፈንካቸው?” አልኩትና መልስ ሳልጠብቅ እዛው የቆመበት ጥዬው ሄድኩ። ***

ከወራት በኋላ ወርቅነህ የደህንነት ሃላፊ ሆኖ ሻሸመኔ ስራ መጀመሩን ሰማሁ። ይህንን ዜና ሰምተን ብዙ “ ” ሳንቆይ ወርቅነህ በጦር መሳሪያ ሽያጭ ተያዘ ተብሎ ወደ እስር ቤት ተወረወረ። ከሰባት ወራት በኋላ ወርቅነህ ገበየሁ ከእስራት መፈታቱን ሰማሁ። ከእስራት ሲፈታ ግን የምናውቀው ‘ ’ የወርቅነህ ገበየሁ የዘር ሃረግ ተቀይሮ፤ የ ኦሮሞ ብሄር ተወላጅ ተብሎ፤ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) …ከፍተኛ አመራር ሆኖ፤ ሹመት አግኝቶ የኢህአዴግን ካምፕ በግላጭ ተቀላቀለ ወጣት ወርቅነህ ገበየሁ። የእድሜ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የስራ ልምድ፣ በተለይ በፖሊስ ሰራዊት ስራ የሚጠይቀው የስራው ስነ- ስርዓት እና በሙያው ስነምግባር ላልተካነ ግለሰብ ያንን ትልቅ ስፍራ እንዲመራ ነው፤ አቶ መለስ ዜናዊ ሹመት የሰጡት።አንዳንዴ ወርቅነህ ገበየሁ በቴሌቭዥን ሲቀርብ የድሮውን መልካም ሆነ ክፉ ነገር እያሰብኩ፤ “ወይ ጊዜ”ማለቴ አልቀረም። ወርቅነህ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ በባችለር ዲግሪ በጥሩ ውጤት የተመረቀ ወጣት ስለሆነ ከሌሎቹ ፊደል ካልቆጠሩ የህወሃት ባለስልጣናት የተሻለ ነው። ሆኖም “ ”በማናቸውም ጊዜ የግል ፋይላቸው ታይቶ ወደ እስር ቤት ሊወረወሩ ከሚችሉት፤ በ ቀይ መስመር ከቆሙት ባለስልጣኖች አንደኛው መሆኑ እርግጥ ነው። ግና ለጌቶቹ ታማኝ መሆኑን በዘሩ ብቻ ሳይሆን በስራውም አረጋግጦላቸዋል። ዛሬ ኦህዴድን የሚመራው የኦሮሞ ተወላጅ ሳይሆን የኦሮሞ ተናጋሪ ትግሬ እንዲሆን የተፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ትክክለኝስዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ህወሃት እምነት ስላጣ ይመስላል።


ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን ይውረድ የሽግግር መንግስት ይቋቋም (ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ)

$
0
0

ከትግራይ ተወላጆች የተሰጠ መግለጫ 8 መስከረም 2009
በአገራችን፣ ህወሓት በመጀመሪያ በትግራይ ከ40 አመት በፊት በመላ ኢትዮጵያ ደግሞ በበላይነት በሚቆጣጠረው ኢህአዴግ ከ25 አመት በፊት የጀመረው የግድያና የአፈና ስርዓት አሁንም በመቀጠል ላይ ነው፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ ተቋማዊ ባደረገው የዘውግ ፖለቲካ ምክንያት ህዝባችን ተከፋፍሎ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ውስጥ በተወሰኑ ክልሎች እንደ ባዕድ የሚታዩበት ሁኔታ ከተከሰተ ቆይቷል። ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣኑን ፍፁማዊ ለማድረግ ሃይማኖትን በመሳሪያነት ስለሚጠቀም በክርስቲያኖች ውስጥና በሙስሊሞች ውስጥም ወደ ግጭት የሚያመራ ክፍፍል ፈጥሯል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ስርዓቱን ለማቆየት የተገነባው የዘውግና የሃይማኖት ክፍፍል ስርዓቱን ለማስወገድ ወደሚጠቅም መሳሪያነት እየተቀየረ ነው፡፡
በአገራችን ያሉ ዋናዎቹ ችግሮች፡
1. ህወሓት/ኢህአዴግ ገዳይ፣አፈኝና ከፋፋይ መሆኑና ህዝባችን በህይወት የመኖር ዋስትና ማጣቱ፣ ሰብአዊና ዴሞከራሲያዊ መብቶቹ መረገጣቸውና ባገሩ ውስጥ በነፃነት መኖር አለመቻሉ ናቸው።
በኢህአዴግ ውስጥ ህወሓት፡
1.1 ጉልበት በሚጠቀሙ ተቋሞች፡ በሰራዊቱ፣ በደህንነትና በእስር ቤቶች፣
1.2 በአስተሳሰብ ላይ ጫና በሚያደርጉ ተቋሞች፡ በመገናኛ ብዙሃንና በሃይማኖታዊ አመራሮች፣
1.3 ብውጭ ጉዳይ
1.4 ከፍተኛ ያገሪቱን ሃብት በመቆጣጠርና በመዝረፍ በዘውግ ላይ የተመሰረተ ቡድናዊ የበላይነት ይዟል፡፡
እነዚህን ችግሮች ለማስወገድ ወሳኙ እርምጃ ህወሓት/ኢህአዴግ ከስልጣን አስወግዶ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ነው፡፡
ይህን ኣላማ ለማሳካት በትግሉ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከነዚህም ችግሮች ውስጥ በሚከተሉት ላይ ትኩረት ያስፈልጋል፡፡
በአገራችን ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎች፡
1. ህወሓት/ኢህአዴግ በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ሊያካሂድ ይችላል፡፡
አባይ ፀሃየና ስዩም መስፍን በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ እነሱ „የዘር“ የሚሉትና ከሆሎካውስትና ከሩዋንዳ እልቂት ጋር የሚያመሳስሉትና የእርስ በርስ ጦርነት አስከትሎ አገሪቷን የሚበታትን አደጋ እንደሚያሰጋ የሚገልፁት ማስፈራሪያ አለ፡፡
ይህ ማስፈራሪያ የእርስ በርስ ጦርነት ለመግታትና የኢትዮጵያ አንድነትን ለመጠበቅ እርምጃ የሚወስዱ አስመለስለው ተቃውሞ ያነሳባቸውን ህዝብ ለመጨፍጨፍ የሚጠቀሙበት የለመዱት ስልት ነው፡፡
አባይ ፀሃየና ስዩም መስፍን የትግራይን ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መመስረት አላማቸው እንደሆነ በማኒፌስቶ ከገለፁት ጥቂት የህወሓት መስራቾች ውስጥ ስለሆኑ ለኢትዮጵያ አንድነት ተቆርቋሪዎች መስለው የመቅረብ የሞራል ብቃት የላቸውም፡፡ እንደዚሁም ሁለቱ ሰዎች የዘውግ ልዩነት ተቋማዊ እንዲሆን ካደረጉ በሁዋላ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በዘረኝነት መፈረጃቸው ከቅንነት የመነጨ ቅስቀሳ አይደለም፡፡
ስለዚህ ሰራዊቱና የመንግስት ታጣቂው ሃይል የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች በወገኑ ላይ የጭፍጨፋ ወንጀል እንዳያስፈፅሙት መቃወም አለበት፡፡
2. ህዝብን የሚያጋጩ ስህተቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ በሚወስዳቸው የጭካኔ እርምጃዎች ምክንያት በህዝብ ውስጥ ስጋት ሰፍኗል፡፡ በዚህ የውጥረት ሁኔታ ስሜታቸውን መቆጣጠር የማይችሉና በህዝብ ውስጥ ግጭት የሚያስከተሉ እርምጃዎችን የሚወስዱ ግለሰቦችና ቡድኖች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡ በህዝብ ውስጥ ግጭት ሲከሰት ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ የስልጣን እድሜውን ለማራዘም ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ፍትህ፣ ሰላምና አንድነት የሚፈልጉ ወገኖች ለዘመናት አብሮ በኖረውና ነፃነቱን በጠበቀው ህዝብ ውስጥ ግብታዊ ግጭት እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
የስም ዝርዝር᎓
1. ህይወት ተሰማ
2. ሓረገወይኒገ/ኢየሱስ
3. ሕሉፍበርሀ
4. ሜሮን አብርሃ
5. ሲራክ ኣማረ
6. ስልጣን ኣለነ
7. በላቸውለማ
8. በየነ ገብራይ
9. ብሩክ እንግዳ
10. ተስፋዬ መሓሪ
11. ተስፋይኣፅብሃ
12. ታደሰ በርሀ
13. ታደሰ ገብረእዝጊ
14. ነጋሲ በየነ
15. ናትናኤል ኣስመላሽ
16. አሰር አሉላ
17. አባይ ኪሮስ
18. ዶክተር ኣረጋዊ በርሀ
19. ኣብራሃ በላይ
20. ኣብርሃም ኀይለ
21. ኤልያስ በየነ
22. ኪዳነ ኃይሌ
23. ኪዳነማርያም ፀጋይ
24. ካሕሳይ በርሀ
25. ዘልኣለም ንርአ
26. ዮሃንስ በርሀ
27. ዮሴፍ ብርሃነ
28. ዮናስ ሓጎስ
29. ዮናስ መብራህቱ
30. ደስታ ኣየነው
31. ገብረኪዳን ዳዊት
32. ዶክተር ግደይ ኣሰፋ
33. ጥላሁን አረፈ
34. የማነ ምትኩ
በመጨራሻም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ 16 የምንሆን የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ተመሳሳይ መግለጫ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ አሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥራችን ከእጥፍ በላይ መብዛቱ ያነሳነው ሃሳብ በብዙ ሰዎች አእምሮ እንዳለና እየተጠናከረ እንደሚሄድ ያመለክታል፡፡ ሌሎችም በዲያስፖራው የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የትግራይ ህዝብ ከጥንትም ለወደፊትም እጣ ፈንታው ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መሆኑንና ጥቅሙና ህልውናው የሚጠበቀው በፍትህ፣ በዴሞክራሲ፣ በእኩልነትና በአንድነት ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሲሆን ብቻ መሆኑን ተገንዝበው፤ የህወሓት ባለስልጣኖች በስልጣናቸው ላይ ለመቆየት የሚያደርጓቸውን መሰሪ ቅስቀሳዎች በማጋለጥና የሚፈፅሟቸውን ጭፍጨፋዎች በማውገዝ ድምፃቸውን እንዲያስሰሙና ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
በዚህ መግለጫ ይዘት ላይ የሚስማሙና አስተያየቶች ያሏቸው ሰዎች ወደሚከተለው ኣድራሻ መፃፍ ይችላሉ᎓ ethiocivic@gmail.com

ብራቮ ሸገሮች፣ ብራቮ ጋዜጠኛ ሕይወት ፍሬ ስብሐት!!

$
0
0

በፍቅር ወርቁ መንግሥት

ከሰኞ ጀምሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር የጀመረውን ውይይት በተመለከተ እየሰጣችሁን ያለው መረጃ እጅግ ሚዛናዊና የተብራራ ነው። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሚያሳዝን ሁኔታ ስብሰባው በእጅጉ የተሳካና ያለ ምንም እንከን/ተቃውሞ እየተካሄደ እንዳለ ነው የዘገቡትና እየዘገቡት ያለው …።

addis_ababa_university
ለአብነት ያህል ከሸገር ሬዲዮ ወጪ በመንግሥት ስር የሚገኙትም ሆነ የግሎቹ ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን መንግሥት ለስብሰባው አጀንዳ ይሆን ዘንድ ባሰራጨው ሰነድ ላይ ፈጽሞ ለእኛ የማይመጥንና አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትኩሳትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ በሚል- በተቃውሞ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የስብሰባው ተሳታፊ ምሁራን አዳራሹን ለቀው እንደወጡ የዘገበው የሸገር ሬዲዮ ብቻ ነው። በአጠቃላይ ከጅማሬው ቀን ጀምሮ የስብሰባውን ድባብ በሚዛናዊ መልኩ መረጃዎችን ለሕዝብ እያቀረባችሁ ነውና ሸገሮች ምስጋና እና አድናቆት ይገባችኋል። ለዚህ ለዛሬው የቁጭት ስሜት ለተቀላቀለበት አስተያየቴ ምክንያት የሆነኝ ግን፤ የዛሬውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የስብሰባ ውሎ ለመዘገብ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ዶ/ር እሸቱ ጮሌ አዳራሽ የተገኘችው ባልደረባችሁ ጋዜጠኛ ሕይወት ስለ ስብሰባው ውሎ ከተለያዩ ምሁራን ዘንድ አስተያየት ለመጠየቅ ያደረገችው ሙከራ በግቢው የጥበቃ ምናልባት የደህንነት ሃይሎች ማለት ሳይቀል አይቀርም ሀይልና ማመናጨቅ የታከለበት ሁናቴ መስተጓጎሉን ከምሽት የዜና እወጃችሁ ሰምቼያለሁ። በእውነት ያሳዝናል። በአገራችን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን፣ ሐሳብን በነፃነት የማጎልበት ረገድ ትልቅ ሚና አለው ከሚባልበት የአገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ መረጃን የሚያፍኑና ሐሳብን የመግለጽ መብትን እንደ ዝንብ ለመደፍጠጥ ተግተው የተሰማሩ የመንግሥት የደህንነት ሃይሎች እግር በእግር እየተከታተሉ ጋዜጠኞችን ለማፈን እንዲህ ዓይነት መብት የሰጣቸው መንግሥት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደታችንና አጠናክረን ለመቀጠል በሚል የይስሙላ ስብሰባ በምሁራኑ ጊዜና በአገሪቱ ሃብት ላይ እየተጫወተ እንዳለ ነው የሚሰማኝ። በእውነቱ ይሄ በጣም የሚያሳፍር፣ የሚያስቆጭ ነው። በትክክል ማለት የሚቻለው ነገር ቢኖር የሸገር ሬዲዮ አገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታና ከሰሞኑን መንግሥት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር እያካሄደ ያለውን ስብሰባ በተመለከተ ለሕዝብ እያደረሰ ባለው መረጃ መንግሥት እየተደሰተ እንዳልሆነ ይህ የዛሬው የሸገሯ ጋዜጠኛ የሕይወት ፍሬ ስብሐት አሳዛኝ ገጠመኝ – በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ የደረሰባት ወከባ፣ እንግልትና ቃለ መጠየቅ ማድረግ እንደማትችል የተላለፈላት ቀጭን የመንግሥት ካድሬ ትዕዛዝ አንድ ማሳያ ነው። መንግሥት በስብሰባው አዳራሽ ውስጥ ብቻና እኔ ከምፈቅድላቸው ሰዎች/ጋዜጠኞች ውጭ ሐሳባችሁን መግለጽ አትችሉም የሚሉ አፋኝ ሃይሎቹን/ካድሬዎቹን በግቢው ዙርያ አሰማርቶ ስለ የትኛው ዴሞክራሲ፣ ነፃነትና መብት እየተናገረ፣ እያወያየ እንዳለ ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ይህ በምሁራኑ ጊዜ፣ በሕዝብና በአገር ላይ ማላገጥ ነው። መንግሥት የሚሰማ ጆሮ ካለው ሕዝብን አፍኖ መግዛት እንደማይቻል አሁንም ማወቅ እንዳለበት ደጋግሞ ሊነገረው ይገባል። በእውነት ከሆነ በስብሰባው የመጀመሪያው ቀን አንዳንድ ምሁራን እንዳሉት ለእንዲህ ዓይነቱ የይስሙላ ውይይት የሚባክነውን ገንዘብ በድርቅ ለተጎዱ፣ በልማት ስም ለተፈናቀሉ፣ በችግር ውስጥ ለወደቁ ወገኖች ይሰጥ በማለት የሰጡት አስተያየት የሚገባና ትክክለኛ ሐሳብ ነው።

ሸገሮች በርቱልን፤ ሕዝብ ሁሌም አሸናፊ ነው!

በሁመራና በአማህጅር የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከሕወሃት ታማኞች ጋር መዋጋታቸው ታውቋል

$
0
0

በልኡል አለሜ
በሁመራና በአማህጅር እንዲሁም በአርማጭሆ የተሰማራዉ የመከላከያ ሰራዊት በጀግናዉ የአማራ ገበሬ ህዝብ ላይ አንተኩስም በማለት እርስ በእርሱ ጦር መስበቁን የዉስጥ አርበኞች አስታወቁ!
ትናንት አንድ የኦሮሞ ብሄር የመከላከያ ሰራዊት በግንባር ላይ በግዳጅ በተሰማራበት ሁኔታ እጅግ ያስቸገረ የህወሃት አመራር የሆነ መቶ አለቃን ከገደለ ወዲህ እራሱን በማጥፋቱ የተነሳ የኡማህጅር የጠረፍ ጥበቃ እና ጸረ ሽምቅ ዉጊያ ተዉጣጪ ቡድን አፈ ሙዙን በማዞር ከደጀን ጦር ጋር ተፋልሞአል።
በዚህ ድንገተኛ እልህ የተሞላበት ዉጊያ የተነሳ የህወሃት ሄሊኮፍተሮች ሳይቀሩ የተሳተፉ ሲሆን የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተደጋጋሚ ፊታቸዉን በማዞር ካደረጉት ዉጊያ ይህኛዉ ከበድ ያለ መሆኑና ከሁለቱም ወገን 102 ወታደሮች መሰዋታቸዉንና 41 መቁሰላቸዉን 1 ታንክ መቃጠሉን መረጃችን ጠቁሞአል፤
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

በአልሞ ተኳሽ እና በመሬት ስርቆት የታወቀው ህወሓት ለኢትዮጵያ አደጋ ተጠያቂነው አክሎግ ቢራራ (ዶር )

$
0
0

እኛ ጠንካራ ለመሆን የምንችለው በመተባበር ብቻ ነው፤ በተጻራሪው፤ እኛ ደካማ የምንሆነው በመከፋፈል”ነው። ጀሪ ሮሊንግ፤ የቀድሞው የጋና ፕሬዝደንት ዛሬ ግብጾች ስለ ኢትዮጵያ ያወጡትን ዘገባ ስሰማ ከዚህ በፊት ስለ ተሃድሶ ግድብ በተከታታይ ያቀረብኳቸውን ትንተናዎችና ማስጠንቀቂያዎች አስታወሰኝ። በአጭሩ ያሳሰብኩት ህወሓት/ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፋፍሎና አፍኖ ይህን ለዚህ ግድብ ዋስትና ሊሰጥ አይችልም የሚል ነው። መጀመሪያ፤ ህወሓት ለራሱ የበላይነት በማሰብ ብቻ፤ ታላቋን ትግራይን ለመፍጠር ባለው ህልም ብቻ፤ ኢትዮጵያን በፈጠራ የሕዝብ ስርጭት ከፋፈላት፤ መተከልን ወደ ቤን ሻንጉል፤ ብዙ የጎንደርና የወሎ አማራ መሬቶችን ምንም ውይይት ሳይደረግ፤ ፓርላማው ሳያውቅ ወደ ታላቋ ትግራይ ቀላቀለ። የትግራይ ወሰን በአንድ ጊዜ ሱዳንን አካለለ፤ ወደ ደቡብ ሄዶ ቤን ሻንጉል ደረሰ። ታላቁን የተሃድሶ ግድብ ለአደጋ በሚያመች ሁኔታ ወደ ወዳጁ ሰሜን ሱዳን አስጠጋው። የግድቡ የውሃ ፈሰስ ለሱዳኖች እንዲጠቅም አደረገ፤ አደጋውን ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሸከም ወሰነ። ህወሓቶች በበላይነት በቋንቋና በጎሳ ልዩነት ያዋቀሩት ስርዓት ዛሬ በግልጽ ለኢትዮጵያ ዋና የውጭ ጠላቶች መሳሪያ እየሆነ ነው። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጦርነት ቢነሳ ባድሜ እንደሆነው ሕዝብን ከዳር እስከ ዳር ለመቀስቀስ አይችልም። ህወሓት ሕዝብን እየገደለ ከህወሓቶች ጋር አብሮ የሚቆም ያለ አይመስለኝም።
Dr Aklog Birara

ሆኖም፤ የግብጾች ፕሮፓጋንዳ የሚለውን አልቀበልም። የኦሮሞ ሕዝብ ለግብጽ አጎብዳጅ አይደለም። የሚከፈለውን ዋጋ የሚያውቅ ሕዝብ ነው። የኦሮሞው፤ የአማራውና ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓትን አገዛዝ ተቃወመ እንጅ የኢትዮጵያን ነጻነት፤ ዳር ድንበር፤ አንድነትና ሉዐላዊነት አልተጻረረም። ሕዝቡ ለነጻነቱና ለአገሩ ሉዐላዊነት ከፍተኛ ቦታ ሰጥቶታል፤ እየሞተለት ነው። የህወሓቶች ክፉነት እና ጨካኝነት፤ “ ” ኢሳት እንዳቀረበው የመሬት ስርቆት ሱስ እና የአገርን ኃብት መዝረፍና ከአገር ማውጣት ዋናው ባህሪው መሆኑ በብዙ መረጃዎች ተረጋግጧል። ህወሓቶች አዲስ የመስፋፋት ካርታ ቀርጸው ወጣት ትግሬዎችን እንደሚያስተምሩ፤ የአማራውን ሕዝብ ለማድከምና ድሃ ለማድረግ የደጀን ተራራን፤ ራያና አዘቦን፤ ላሊበላን፤ የዋልድባን ገዳምና ለም መሬት፤ ወልቃይት ጠገዴና ሌሎችን ከወሰዱና ለመውሰድ ከወሰኑ አስር አመታት አልፈዋል። እስካሁን የሕዝቡን አቤቱታ የሚሰማ አልነበረም። ህወሓቶች ሰርቀውና ቀጥፈው“ ” ይቅርታ መጠየቃቸው ወደው ሳይሆን ሕዝቡ ስላስገደዳቸው ነው። ገና፤ ገና ብዙ ይቅርታ የሚጠይቁባቸው አበይት ጉዳዮች አሉ። በተለይ ግድያን በሚመለከት። ይህ ሂደት መተባበርን፤ የሕዝብ አጋር መሆንን ይጠይቃል። ያልተባበረ ሕዝብ ሁልጊዜም ተጠቂ ይሆናል። የተባበረ ግን ጊዜ ቢወስድም፤ ጥቃት ቢደርስበትም ምን ጊዜም አሸናፊ ሆኖ ይወጣል። ለዚህ ትምህርት የሚሆነኝ በጎንደር፤ በደብረ ታቦር፤ በወልቃይት ጠገዴና በሌሎች መንደሮች፤ ከተሞች፤ የገጠር ነዋሪዎችን ጨምሮ የሚደረገው አስደናቂና ብልሃት ያለው የትግል ስልት ነው። በኦሮምያም የሚደረገው ተመሳሳይ ነው። የመገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ በተዘጋበትና ሁሉም በህወሓቶችና በአካባቢ ቅጥረኞች የአይን ቁራኛ ስለላ በሚካሄድበት ሁኔታ ተራው ሕዝብ የመጣው አደጋ ይምጣ፤ ያሰሩትን ይሰሩ፤ የገደሉትን ይግደሉ፤ እስር ቤቱን፤ መኖሪያ ቤቱን፤መንደሩን፤ ገበያውን፤ ድልድዩን ወዘተ ያውድሙት፤ የአፈኑትን ያፍኑ፤ ከዚህ የባሰ ምንም ሊመጣ አይችልም እያለ ሕዝባዊ እምቢተኛነቱን ሲያስተጋባ ማየት ታሪክ ሲፈጠርና ሲሰራ እንደማየት ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የትምህርት ተቋሞች አይንቀሳቀሱም። አስተማሪዎች ሕዝብ እያለቀ ለምን በዚህ ጉዳይ አንነጋገርም እያሉ ነው። አንድ አስተማሪመሰለኝ እንዲህ ብሏል። እኔ ከአሁን በኋላ በፍርሃት ዓለም አልኖርም። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያካሂደው ትግል አስደናቂና ታሪክን ፈጣሪ ሆኗል። በራሱ ጥበብ፤ በራሱ መሪዎች፤ በራሱ መደጋገፍ። የጎንደር ሕዝብ እቀባ አድርጎ ከራሱ ምግብ ተካፍሎ የሌላቸውን ይመግባል። ይህ ነው ታሪክ ፈጣሪ! ይህ ነው ሕዝብ አፍቃሪ! ይህ ነው ከስግብግብነት ይልቅ፤ ርህራሄ፤ ሰብእነት፤ ፍቅር፤ መንፈሳዊነት የሚገዛው ሕዝብ። ለዚህ ነው ትግሉ ችግሩን ተቋቁሞ አሁንም የቀጠለው፤ ማንም አያቆመውም። በውጭ ለምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያ ከዚህ የበለጠ ቆራጥነት፤ ጀግንነት፤ ደፋርነት፤ አገር ወዳድነት ወዘተርፈ ሊመጣልን አይችልም። ሕዝቡ ፍርሃትን ሰብሮና ቀብሮ ጨካኝነትን ለመቋቋም መነሳቱን በተከታታይ አሳይቶናል። እ. አ. አ. ከ September 19, 2016, ጀምሮ የጎንደርና የጎጃም ሕዝብ ተመካክሮና ተባብሮ የኢኮኖሚ እቀባውን በቤቱ እየዋለ መቀጠሉ አስደናቂ ነው። ይህ መተባበርን፤ መቀነትን ሆነ ቀበቶን ጠበቅ ማድረግን፤ ቆራጥነትን፤ መተሳሰብን ይጠይቃል። ነጋዴው፤ የቤት ባለቤቱ፤ የመንግሥት እና የቀን ሰራተኛው፤ አስተማሪው፤ ተማሪው፤ ገበሬውና ሌላው ተባብሮ ይህን እቀባ ማድረጉ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ነጻነትና ፍትህ ለሚፈልጉ ሕዝቦች ሁሉ ከፍተኛ ትምህርት ነው እላለሁ። እኛ የማናደርገውን ተራው፤ ድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ እያደረገውነው።ለምን? ብለን ራሳችን እንጠይቅ። ህወሓቶች በበላይነት የሚያሽከረክሩት ስርዓት ከሁሉም በላይ ጨካኝ፤ ለሰው ህይወት ምንም ርህራሄ እንደሌለው በየቦታው እያየን ነው። በኮንሶ የሆነው ለህሊና የሚቀፍ ነው፤ መንግሥት የሚባል ነገር እንደሌለ ያሳያል። እ. ኣ.አ. ከ September 5-September 19, 2016 ድረስ ቢያንስ “30 ንጹህ ኢትዮጵያዊያን ተረሽነዋል፤ ከ 1,500 በላይ የሚገመቱ ቤቶች ተቃጥለዋል።” በጎንደር ከተማ እኔ በልጅነቴ የማስታውሰው በኢትዮጵያ ታሪክ ያለው ገበያ ተቃጥሏል። በትላንቱ እለት ህወሓቶች ያልተቃጠለውን ሙሉ በሙሉ ለማቃጠል የትግራይ ተወላጆችን፤ አንዲት ሴት ጨምረው ልከው ለማቃጠል ሲዘጋጁ ሕዝቡ ጠቁሞ የከተማው ፖሊሶች ያዟቸው። የተረፈውን ማቃጠል የቂም በቀል ተልእኮ ነው። ህወሓት የዚህን ያክል ጨካኝና ወራዳ መሆኑ ነው። በደብረ ታቦር፤ በጎንደር፤ በባህር ዳር፤ በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች እስር ቤቶች ተቃጥለዋል። የፖለቲካ እስረኞች ከቃጠሎው ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ የህወሓቶች አልሞ ተኳሾች ሰለባ ሆነዋል። መረጃዎች እንደሚሉት ከሆነ በቅሊንጦ ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ምክንያት የፖለቲካ እስረኞች ሆነው በዚህ እስር ቤት ህይወታቸው ያለፈው ብዙ እንደሆነ ይነገራል። ይህ የሚያሳየው ሆነ ተብሎ የአማራውን ወጣት ትውልድ ለማጥፋት የተደረገ፤ የተቀነባበረ ስራና ሴራ መሆኑን ጭምር ነው። በዐማራው ክልል በተከታታይ የሚታየው ስእል አንድና አንድ ብቻ ነው። ይኼውም፤ ህወሓቶችና የእነሱን ድርጊት ፈጻሚና አስፈጻሚ የሆኑ ግለሰቦችና ቡድኖች በወገኖቻቸው ላይ ወንጀል ለመፈጸም ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸውን ነው። ከአንድ ቤት ወደ ሌላ እየሄዱ ወጣቶች ሲያፍኑ ቆይተዋል። በባህር ዳር እና አካባቢ ብቻ “ ከ 11,000” በላይ የሚገመቱ የዐማራ ወጣቶች የት እንደተወሰዱ፤ ምን አደጋ እንደደረሰባቸው አይታወቅም። ሞቱ? አካላቸው ስንኩል/ ሽባ እንዲሆን ተደረጉ? በጫካና በሸለቆ ተወረወሩ፤ተቀበሩ? መርፌ ተወግተው ወይንም ለህይወታቸው፤ ለጭንቅላታቸው አደንዝዝ መድሃኔት ተሰጣቸው? የሚሉ አግባብ ያላቸው ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ቁም ነገሩ፤ የዐማራው ብሄር ተተኪ መሪዎች፤ ተተኪ ባለሞያዎች፤ ተተኪ ተቆርቋሪዎች እንዳይኖሩት እየተደረገ ነው።ህወሓቶች/ ኢህአዴጎች በወንጀል እንዳይከሰሱ ሁሉንም መረጃ ይደመስሳሉ፤ መገናኛ ብዙሃን እንዳይኖር ያደርጋሉ። በአካባቢው የሚኖረው የተማረ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ስብስብ ማድረግ ያለበት መረጃውን መሰብሰብና መደበቅ፤ ውጭ ለሚኖሩ ተቆርቋሪዎች ማስተላለፍ ነው። ይህን በሚመለከት በቅርቡ በሕዝብ ጥረት፤ ወጣቷ የወልቃይት ጠገዴ ዐማራ፤ ንግሥት ይርጋ የምትሰራውን ጀግንነት እና የደረሰባትን አፈናና ጭካኔ ይፋ መደረጉ በጣም ጠቃሚ መረጃ ነው። ይህች ወጣት እናትሰቃይ፤ እንዳትገደል አቤቱታ ማቅረብአለብን። የሞቱትንና እንዲሰወሩ የተደረጉትን ወጣቶች ስም ዝርዝር መሰብሰብ አስፈላጊ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ህግ አንድ መንግሥት ወይንም የዚህ መንግሥት ተጠሪ የሆነ ግለሰብ ወይንም ቡድን ግለሰቦችን አስገድዶ መሰወር ሕገ ወጥ መሆኑንና በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን አስምሮበታል (Enforced disappearances are crimes against humanity). በተመሳሳይ በቅሊንጦ ከተረሸኑት መካከል ጀግናው ሻለቃ ይላቅ አሸናፊ ይገኝበታል፤ የሌሎቹን ስም ዝርዝር መሰብሰብ ወሳኝ ነው። የዐማራው ሕዝብ እልቂት ዛሬ የተጀመረ ባይሆንም አሁን ያለው አደጋ የመኖር / አለመኖር፤ ማለትም የህልውና አደጋ መሆኑን መቀበል ግዴታችን ነው። ህወሓቶች በብዛት የሚጠቀሙበት የዐማራ ሕዝብ እልቂት ዘዴ አስገድዶ መሰወር ነው(enforced disappearances). ይህ የሆነበት ምክንያት የተሰወረ በምንም አይገኝም በሚል የተሳሳተ ስሌት ነው። “ ” ህወሓቶች፤ በተለይ የህወሓት መስራቾች፤ ዐማራውን አህያ ከማለት ደረጃ የደረሱብት የራሳችን ድክመት፤ ዝምታ ማብዛትና በጥቃቅን ነገሮች ለመተባበር አለመቻል ጭምር ነው። አሁንም፤ ብዙ የዐማራ ምሁራንና ባለሞያዎች ከዳር ቆመው ያያሉ፤ ምን እንደሚጠብቁ ምርምር ቢደረግ መልካም ነው። ለአሁኑ ግን እያንዳንዳችን ራሳችን መፈተሽ አለብን እላለሁ። የህወሓቶች ኤታ ማጆር ሹም ጀኔራል ሳሞራ ዩኑስ “ ለትግራይ ሕዝብ ንግግር ሲያቀርብ እንዲህ ብሏል። ህወሓት ማለት መስመር ነው! ህወሓት ከሌለ የትግራይ ሕዝብ የለም!” ይህ ብሂል የትግራይን ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መለየት መሆኑን ማሳሰብ ያለበት የትግራይ ምሁርና ሕዝብ ነው። በዚህ ሃተታ ለማሳሰብ የምፈልገው የዐማራው ሕዝብ ከሌለ፤ የኦሮሞው ሕዝብ ከሌለ ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ የአማራውና የኦሮሞው ሕዝብ በወንድሞቹ፤ በእህቶቹ በትግራይ ሕዝብ ላይ አልተነሳም፤ አይነሳም፤ መነሳትም የለበትም። የሰላማዊ ሕዝብ እምቢተኛነት ኢላማ የህወሓት ጭካኔና አፋኝነት እንጅ የትግራይ ሕዝብ አለመሆኑን አምናለሁ። ቢቻል ኖሮ፤ ህወሓቶች የጣናን ኃይቅ፤ የአባይን ወንዝ ወደ ትግራይ እንደሚወስዱ መረጃዎች ብዙ ናቸው። አንድ የውጭ አገር ቱሪስት ጎንደር ከተማ ሆቴል አርፎ ምን ልታይ መጣህ? ተብሎ ሲጠየቅ ቤተ “ ” ክርስቲያኖችን፤ የፋሲልን ግንብና በትግራይ ክልል የሚገኘውን የዳሸን ተራራ ብሎ ይመልሳል። ይህ የጎንደር አንጡራ ኃብት የሆነ ተራራ ወደ ትግራይ መጠቃለሉን የማያውቅ ወጣት ገርሞት ተራራው እኮ “ ” በጎንደር እንጅ በትግራይ አይደለም ሲል እኔ የተነገረኝ ትግራይ ውስጥ መሆኑን ነው ሲል ተናግሯል።“ ” ተራራውም ይሰረቃል የሚለው ብሂል የመጣው ከዚህ ነው። የላሊበላ ገዳማት ተነጥቀው ወደ ትግራይ ተላልፈዋል፤ ነገ የፋሲለደስ ግንብ፤ በደብረ ታቦት የኢየሱስ ተራራና ቤተክርስትያን ትግሬ ነው ቢባል ምን ያስደንቃል። ወይ ጉድ! እንዴት ጎንደሬውን፤ እንዴት አማራውን ቢንቁት ነው ተራራ የሚነጥቁት የሚሉ ብዙ “ ” ናቸው። የራስ ዳሸን ትግራይነት የችግሩን ክብደት ያጠናክረዋል። የሰው ዜግነት መከበር ከተፈጥሮ ኃብት ባለቤትነት ተለይቶ ሊታይ አይችልም። ይህ በምንም አይነት ማባበል ሊፈታ አይችልም። በባህር ዳር ከተማ እነ በረከት ሰምኦን፤ አዲሱ ለገሰና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮነን ሕዝቡን ለማባበል ያደረጉት ሙከራ በጎንደር ከተደረገው የተለየ አይደለም። ህወሓቶችና ታዛዦቻቸው ወጣቱን “ እየገደሉ ግድያው እንዲቆም የራሳቸውን የበላይ አዛዥ ህወሓትንና በዐማራው ሕዝብ ላይ ማንኛውንም ” “ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል ብሎ ትእዛዝ የሰጠውን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ይህ ትእዛዝ ” በአስቸኳይ ይነሳ በማለት ፋንታ ተጠቂውን የዐማራ ሕዝብ ማነጋገራቸው ለዐማራው ሕዝብ ያላቸውን ንቀት ያሳያል። በአምባ ጊዎርጊስ የተረሸኑት ወጣቶች ብቻ ከፍተኛ ዋጋ እንዳላቸው ምንም አልተረዱትምÉÉ በእነሱ ግምት የትግሬዎች ኃብት መቃጠል ከህይወት በላይ ሆኗል ማለት ነው። አስደናቂው ቁም ነገር ግን ይህ አይደለም። ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክፍለ ሃገር ድረስ የብአዴን አባላት፤ ዝቅተኛና መካከለኛ ኃላፊዎች“ወንበራችሁን ”አንፈልግም፤ ተረከቡን ማለታቸው ነው። ብአዴኖች፤ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ በታሪክ ተጠያቂ እንዳይሆኑ ከፈለጉ የሕዝቡን ትግል ሙሉ በሙሉ መደገፍ ግዴታቸው ነው። ወገኖቻቸው እንዲገደሉ አጋር መሆን ከወንጀለኛነት አያድናቸውም፤ ተባባሪ ናቸውና። የዩንቨርስቲ አስተማሪዎች የተለመደውን የህሓት ግምገማ እንዲያዳምጡ ተጠርተው ምንም ድምጽ አንሰጥም ብለዋል። አንድ ተማሪ “ እንዲህ ብሏል። እኔ ፈርቸ ፈርቸ ፍርሃቴ ለቆያኛል፤ ለምን አሁን ስላለው እልቂት፤ ስላለው ሁኔታአንወያይም?” የሚል ጥያቄ አቅርቧል፤ ሁሉም የሚፈልገው ጥያቄ። በተደጋጋሚ እንዳሳሰብኩት የዐማራው ወጣት ትውልድ እየታፈነ፤ እየተገደለ፤ እየቆሰለ፤ እየተራበ ነው። አስተማሪው፤ ተማሪው፤ ሰራተኛው በአንድ ላይ፤ ለአንድ ዐላማ መነሳትና መታገል አለበት። በሕዝቡ ዐመጽ ያልተሰበሰበው ህሊናውን መጠየቅ አለበት። ሆዱ ከጎንደሬው ሆድ፤ ከኦሮሞው ሆድ፤ ከኮንሶው ሆድ የተለየ አይደለም። ለአንድ ህይወት ከመሳሳት ለፍትህ፤ ለነጻነት፤ ለእኩልነት፤ ለዲሞክራሲ ራስን መስ ዋእት ለማድረግ መነሳት ይመረጣል። ታሪክ ስሩ። ምክንያቱም፤ ተራው የጎንደር፤ የባህር ዳር፤ “ የደብረ ታቦር፤ የኮንሶ፤ የአዋሳ ወዘተርፈ ሕዝብ ከአሁን በኋላ በህወሓት/ ” ኢህአዴግ አንገዛም እያለ ነው። ታሪክ እንስራ፤ ሕዝቡን እንደግፍ። ተቃውሞን በዝምታ፤ ተቃውሞን በእገባ፤ ወዘተ ሲያሳዩ ችግሩ ስር የሰደደ እና ህወሓት/ “ ኢህአዴግ ሊፈታው ከማይችልበት ደራጃ መድረሱን ያሳያል። ግምገማ የሚባለው ዘዴ እኔን” እመኑኝ ከማለቱ ሌላ የሕዝቡን መሰረታዊ ችግር አይፈታም። የዝግ ችሎት አድርጎ ራሱን መገምገም ያለበት አፋኙ አገዛዝ ነው። ይህን አያደርግም።ለመደምደም፤ በዐማራው ሕዝብ ላይ የብሄር ማጽዳትና እልቂት የሚካሄድ መሆኑን የሚያሳይ በውጭ አገር ባለሞያ ዶኪመንተሪ ቀርቧል፤ ወደፊትም እንደሚቀርብ ይገመታል። በጉዳዩ ክብደትና ስፋት መሰረት በሙሉቀን ተስፋ መጽሃፍ ተጽፎ በአዲስ አበባ እንዳይበተን ተከልክሏል። የተከለከለበት ምክንያት ሕዝቡ ሃቁን እንዳያውቀው ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ይህን እልቂት አያውቅም የሚል ግምት የለኝም፤ “ ” ያውቃል። ይህን ጭካኔ እያወቀ ለህወሓቶች ደህንነትና ሰራዊት የግድያ ፈቃድ መስጠቱ ስርዓቱ በጠቅላላ ለሰው ህይወት ደንታ እንደሌለው በተደጋጋሚ ያሳያል። የህወሓት የስለላና የመከላከያ ኃይል 30 ሚሊየን “ ” የዐማራ ሕዝብ ለመቆጣጠር እንችላለን፤ እንኳን ለዚህ ሕዝብ ለአፍሪካም የሚመጥን ኃይል አለን ብለው ፎክረዋል። ጥናቶች የሚያሳዩት ማንም ኃላፊነት የሚሰማው አመራር በራሱ ሕዝብ ላይ ጦርነት እንደማያውጅ ነው፤ ከወሰደ ህይወቱ አጭር እንደሚሆን ነው። ነገ ከትግራይ ውጭ የሕዝቡ እምቢተኛነት አገር አቀፍ ቢሆን ሕዝቡን በጀትና በሄሊኮፕተር፤ በታንክና በሌላ መሳሪያ ሊጨፈጭፉት ነው? ምን ይደረግ ?“ ” አንድነት ኃይል ነው ብለን እንነሳ!“ ” አንድ ሰው ሲገደል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን መገደል ነው እያልን እናስተጋባ !“ ” አዲስ ዓመት ምንም አዲስ አይደለም ለማለት እንድፈር“ ተራው ገዳይና ተራው ሟች ወንድማማቾች ናቸው ! ተጠያቂው ህወሓት ነው ! ለማለት እንድፈር ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን መብትና እኩልነት አብረን እንስራ!

23/45….የምድር ሲኦል!

$
0
0

“የአማራ ክልል ልጆች የሚሰቃዩበት ልዩ ቦታ…2345-ሃያሶስትአርባምስት!” ታውቋል። 2345 ቁጥር አይደለም። በዚህ ልዩ የኮድ ስም የሚታወቀው ቦታ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፓዊ ከተማ መንደር 7 የሚባለዉ አካባቢ ከመድረሳችን በፊት በስተቀኝ በመታጠፍ ወደ ዉስጥ 25 ኪሎ ሜትር አካባቢ ገባ ብሎ ገደል ዉስጥ የሚገኝና በሀገራችን ከሚገኙት ማሰቃያ ቦታዎች መካከል የመጨረሻ አስከፊው ቦታ ነው።
ይህ የመጨረሻ አረመኒያዊ ተግባራት የሚፈፀሙበት ቦታ ዙሪያ ገባዉን ግራርን በመሰሉ ዛፎች ጥቅጥቅ ደን የታጠረ፤ የደገላ ሳር በሚባሉት ረጃጅም የበረሃ ሳሮች የተከበበ በዉስጡ ለሰው ልጅ አደገኛ የሆኑ አዉሬዎች የሞሉበት፤ በአለም ላይ እጅግ መርዛማ የሆኑ እባብና ጊንጦች የሞሉበት፤ እንስሳትን ሳይቀር በጥቂት ደቂቃዎች የሚውጡ ዘንዶዎች የተከማቹበት፤ ከአካባቢው ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ እዚህ ጉድጓድ ማሰቃያ ቦታ ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ሰዉ የቆዳ ቀለሙ በራሱ ተጠብሶ ወደ ካርቦናማነት እንደሚለወጥና የአካባቢው ሰዉ እራሱ አካባቢው ላይ ከአደገኛነቱ ባሻገር ለሚስጥራዊነቱ ሲባል ወደዛ አካባቢ እንዲቀርብ የማይፈለግበት ከአለም የተገለለ እጅግ አሰቃቂ የበረሃ ጉድጓድ ማሰቃያ ቦታ ነዉ።
ከዚህ የምድር ሲኦል ለማምለጥ የሚሞክር ግለሰብ ካለም የምን ሰለባ ሊሆን እንደሚችልና ምን እንሚያጋጥመው መገመት አይከብድም። እዛ አካባቢ በሕይወት አጋጣሚ ደርሶ የመጣ ግለሰብ እንዳስረዳኝ ከሆነ እዛ የበረሃ ሲኦል ዉስጥ የገባ ሰው የት እንዳለ በምንም መንገድ የሚያውቅበት ሁኔታ የለም ብሎኛል። ይህ አካባቢም ከሃገራችን ማህበረሰብ የተሰወረና በሃገራችን ዉስጥ ከሚገኙ እንደ ብርሸለቆ፤ ሽዋሮቢት፤ ዴዴሳ አይነት ታዋቂ ማሰቃያ ቦታዎች ስም ዝርዝር ዉጭ የሚገኝ በስዉር ለሺዎች ኢትዮጽያዊያን በማሰቃያነት በወያኔ አማካኝነት ለአመታት አገልግሎት ላይ እየዋለ የሚገኝ ሚስጥራዊ ቦታ ነው። እንግዲህ በዚህ ቦታ ነው ከ2ሺ ያላነሱ የባህር ዳርና የጎንደር ወጣቶች ስቃይ ላይ ናቸዉ የተባለው።
2345….የምድር ሲኦል! በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል!

አበራ አየለ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live