Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ኤርሚያስ ለገሰ አዲሱን የመለስ ልቃቂት መጽሐፉን እንዲህ ያስተዋውቃል

0
0


ኤርሚያስ ለገሰ አዲሱን የመለስ ልቃቂት መጽሐፉን እንዲህ ያስተዋውቃል
ኤርሚያስ ለገሰ አዲሱን የመለስ ልቃቂት መጽሐፉን እንዲህ ያስተዋውቃል


Breaking: በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) የሚገኘውና ለውጭ ሀገራት የስጋ ውጤቶችን በማቅረብ ላይ ያለው ግዙፍ የቄራ ድርጅት በእሳት ወደመ

0
0


Breaking: በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) የሚገኘውና ለውጭ ሀገራት የስጋ ውጤቶችን በማቅረብ ላይ ያለው ግዙፍ የቄራ ድርጅት በእሳት ወደመ

ህውሓት/ኢህዴግ በቆፈረው ጉድጎድ ለመግባት አፋፍ ላይ ነው -ከለለው ዑርጋ

0
0

TPLF

በመላው የሀገራችን ክፍል በተለይም በኦሮምያ እና በአማራ ክልል በተቀሰቀስው የመብት እና የማንነት ጥያቄ ዙርያ የሀገራቸው ጉዳይ ስለሚመለከታቸው ፍፁም ሰላማዊ እና በሰለጠነ በሆነ መልኩ ከሕፃን እስከ አዋቂላለፉት ወራቶች ኢትዮጵያዊያን ልዪነታችውን ወደ ጐን ትተው በአንድ ላይ አንባገነን ሥርዓትን እና የአንድ ብሔር የበላይነት አክትሞ ሁሉም ብሔር፣ብሔረሰቦች በእኩልነት የሚኖሩባት ሥርዓት ለመገንባት በሰላማዊመንገድ ጥያቄቸውን በማቅረብ ላይ የገኛሉ ነገር ግን የቀረበውን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ሀይል ግጭት ሆን ብሎ ወያኔ ስለቀየረው ዜጎች ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው ለህዝባቸው መሰዋት በማቅረብ የፍርሃትቆፈን ሳይሽብባቸው በመታገል ላይ አሉ። የነዚህ ግጭቶች ፣አለመግባባቶች ለሕይወት እና ንብረት ውድመት ዋንኛ መንሴ ሆኖ የሚጠቀሰው በማንአለብኝነት ገደብ የለሽ መንግስታዊ ግፍና በደል እየፈፀመ ያለውሀገሪቶን በመምራት ላይ የሚገኝው ህውሓት/ኢህዴግነው።

ከዚህ በተጨማሪ በሀገራችን እየተካሄደ ካለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ባሻገር የብሔርና የዘር ጉዳይ ርዕሠ ጉዳይነቱ ተጠናክሯል፡፡ሰሞኑን የመንግሥት ባለስልጣናትና ካድሬዎቹ “የዘረኝነት ጉዳይ በእጅጉ አሳስቦናል”ሲሉም እየተደመጡ ነው፡፡የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚከታተሉ ብዙዎች ግን ለጉዳዩ ዋነኛ ተጠያቂ የሚያደርጉት ራሱን ኢሕዴግን ሲኾን የሰሞኑንም የኢሕአዴግን ጩኸት እንደ አስገራሚ ትእይንት የሚያዩት ብዙዎችናቸው። አሁን አሁን ከሌሎች ወገኖችም የሚሰነዘሩት የዘርናየጥላቻ ፖለቲካ ምንጩ ኢሕዴግ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በላይሲዘራው የኖረው የፖለቲካ ዘር ፍሬ እንጂ ሌላ ነገር መስሎ የማይታያቸው በቁጥርቀላል የሚባሉ አይደሉም፡፡ የብሔር/ብሔረሰብን መብት በማስከበር ሽፋን የዘር ጥላቻእንዲቀሰቀስ፣ ክፍፍል እንዲካረር፣ አለመተማመን እንዲሠፍን ገዢው ፓርቲ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በላይ እንቅልፉን አጥቶመሥራቱን የሚገልጹ ወገኖች ኢሕአዴግ ደርሶ ዘረኝነት አውጋዥ መሆኑ አይዋጥላቸውም፡፡

እንዲያውምበሥልጣን ዘመኑ ሁኔታውን በመጥፎ ጎኑ ሲያቀጣጥል የቆየው ገዢው ፓርቲ ባሻው ወቅት ሁሉ ይሕን መሰሉንክስ ሌሎች ላይ ሲለጥፍ መታየቱም የተለመደ ባህርይው ሆኖም ይወሰዳል፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት በብሔሮች መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር ቅስቀሳ ከማድረግ አንስቶ የአረካን፣ የበደኖንና የአርባጉጉን በመሰሉእልቂቶች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደነበረም የሚያሳጡት ምስክሮችም ይቀርቡበታል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት “ላስከብር ተነስቻለሁ” በማለቱ ረገድ ኢሕአዴግ የመጀመሪያው የአገሪቱ መንግሥት አይደለም፡፡እንዲያውም የፌደራሊዝም አወቃቀር ‘እርሾውን’ ከቀድሞው መንግሥት የብሔረሰቦች ጥናት ኢኒስቲቲዩት እንደወሰደው ነው የሚነገረው። “የብሔረሰብ መብት ማስከበርን ከኔ በላይ ላሳር” የሚለው የኢትዮጵያሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢሕአዴግ) በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሐት) ቁጥጥር ስር መቀፍደዱ የፕሮፓጋንዳውን ያህል የሌሎች ብሔረሰቦችን መብት ጉዳይ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለማንሳትእንዳላስቻለውም ይገመታል፡፡“…በነጻ ፍላጎትና በሕግ የበላይነት አንድ የፖለቲካ ማሕበረሰብ በጋራ የመገንባት” ሐሳብ እንደያዘ የሚነገርለትን ሕገ መንግስት ይዞም ከሩብ ክፍለ ዘመን በኋላ እንኳ ወሳኝ የሆኑ የሥልጣንቦታዎችን ለሌሎች ለማካፈል ያለው ፍላጎት አነስተኛ መሆኑም አገዛዙን የሚያሳማው ጉዳይ ነው። “መጪው የጋራ ዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅምንበማሳደግ ላይ ነው” የሚለውን በሠነድ እንዲሰፍር ቢያደርግም የጋራ ጥቅምን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ለማድመጥ ዝግጁ አይመስልም፡፡“…ጥቅማችን፣ መብታችንና ነጻነታችንን በጋራ እና በተደጋጋፊነት ለማሳደግአንድ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ መገንባት አስፈላጊ ነው” የሚለውም እዚያው ሕገ መንግሥቱ የታተመበት ወረቀትላይ ብቻ እንዲወሰን አድርጎታል፡፡ እነዚህኑ መብቶች በመጠየቃቸው ምክንያትም ዜጎች ይታሠራሉ፤ይገደላሉ፤ ለእንግልትና ለስደት ይዳረጋሉ፡፡ ኢሕአዴግ ልዩነትን በማስፋት፣ ጥርጣሬና ፍርሃትን በማንገሥ መንገዱ ዘልቆበታል፤ የገዢው ፓርቲማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰሞኑ ለአራት ቀናት በዝግ ያካሄደውን ስብሰባሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫም ዘረኝነት የአገሪቱ ሥጋት ነው ብሏል፡፡ ተቃዋሚዎች ግን ዘረኝነትን በማቀጣጠል፣ አየሩ በጥርጣሬና ፍርሃት እንዲሞላ፣ አንድነት እንዲናጋ በማድረጉ ረገድ የኢሕአዴግን ያሕል የደከመምየተሳካለትም የለም ነው የሚሉት፡፡

ኢሕአዴግ በሥልጣን ዘመኑ ይህን በተመለከተ የሚነቀፍበት ብዙ ምሳሌዎችም እዚህ ላይ ይጠቀሳሉ፡፡ ብዙዎች ከማይዘነጉት የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑነው ከሚለውአባባል ባሻገር በኢሕዴግ ዘመን ከጋራ እሴቶች ይልቅ ልዩነት ላይ ትኩረት እንዲደረግ የተሰሩ ብዙ ስራዎች መኖራቸው ተደጋግሞ ይጠቀሳል። ዩኒቨርሲቲዎችና ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የአገዛዙ ልዩነት መፍጠሪያ ዋናማዕከላት ተደርገዋል፤ ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ሃገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዳያተኩሩ ገደብ ይደረግባቸዋል፡፡ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ስለ ሃገራዊ ትስስርና አንድነት ትንፍሽ አይሉም፡፡ በብሔራዊና አብይበዓላት አከባበር እንኳ የክልል ቴሌቪዥኖችና ሬዲዮ ጣቢያዎች ከክልላቸው አርቀው እንዳይመለከቱ ተደርገዋል፡፡ በብሔር ብሔረሰቦች በዓል ሳይቀር ደም አፋሳሽ ግጭቶች መቀጣጠላቸውም ተስተውሏል፡፡ ኢሕአዴግበመታወቂያ ካርድ ላይ ብሔር እንዲሠፍር ያደረገበት አካሄድ አደጋ ይደቅናል ያሉ ብዙዎች ነበሩ።

አደጋው አሁን በመጠኑ ብልጭ እያለ ነው፡፡ በሩዋንዳ እልቂት ወቅት በመታወቂያ ላይ ብሔር እንዲሠፍር መደረጉአንዱ የችግሩ ማቀጣጠያ እንደነበር የሚያወሱ ብዙዎች በኢትዮጵያም ይህንኑ ብሔርን በመታወቂያ የመጻፍ አስገዳጅነት በስጋት ያዩታል፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ ለተቃውሞ ሠልፍ የወጡ የኦሮሞ ተወላጆችበመታወቂያ ካርዳቸው ላይ በሠፈረ የብሔር ማንነት እየተነጠሉ ለጥቃት እንደተዳረጉም ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ከሠሞኑ በአዲስ አበባየሚገኙ ሆቴሎችና ፔኒሲዮኖች በተላለፈላቸው ትዕዛዝ ከአማራ ክልል የሚመጡ አዳዲስእንግዶችን ጠቁሙ የተባሉትም ከመታወቂያ ካርድ በሚገኝ መረጃ ነው፡፡ ዘረኝነትን እያወገዝኩ ነው የሚለው ኢሕአዴግ በተግባር ተቃራኒውን ሲፈጽምም ይስተዋላል፡፡

በጎንደር አካባቢ ተቃውሞ በጀመረ ሰሞንመንግሥት በጸጥታ ክፍሉ አማካይነት ባወጣው መግለጫ… በአንድ ብሔር ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ እንደነበር ነው የገለጸው። የአማራ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ በበኩላቸው በተካሄደ ማጣራት በዘር ላይየተነጣጠረ ጥቃት እንዳልነበር ጠቆሙ፡፡ እንዲህ ያለው አደገኛ ጉዳይ በመንግሥት ሲገለጽ አደጋና ሥጋቱ ከፍ ያለ ይሆናል፡፡ እዚያው ጎንደር አካባቢ ከሕዝቡ ጋር በነበረው ግጭት ላይ ሕይወታቸው ያለፈውን የጸጥታሰዎችስማቸውን መግለጽ በቂ ሆኖ ሳለ…

ፈርዖን ሆይ! ልብ ግዛ |ከቀሲስ ዲበኩሉ በላይ

0
0

ስለ ሀገሬ ኢትዮጵያ፣

14316701_10154433670574373_6431339515156611656_nስለ ሕዝቤና ወገኔ የደም ማዕበልና የእንባ ጎርፍ ሳስብና ስመለከት ምን እንደምል ግራ ገብቶኝ በዝምታ ተውጬ ትንሽ ቆየሁ። ከልቤ የመረረ ኃዘን የተናሣ ፊቴ ጠቁሯል ውስጤም እየደማ ነው።ወደ ውስጥ የፈሰሰው ደም በውጭ ከሚፈሰው በላይ ጉዳት አለው። ይህ የልብ መድማት የእኔ ብቻ አይደለም።የአብዛኛው ኢትዮጵያዊም እንጂ።በአደባባይ ደማቸው ፈስሶ ከሚታዩትና ከሞቱት በላይ በቤታቸው ውስጥና በልባቸው ጫካ ውስጥ አጥንታቸው ችቦ፣ደማቸው ነዳጅ ጋዝ ሆኖ በሚንቀለቀል እሳት ውስጥ በዝምታ የሚሞቱት ይበልጣሉ።ስለዚህ በውስጤ የሚፈሰውን ደም ዛሬ በትንሹ ወደውጭ ለማስተንፈስ ወደድሁ።በተለይ ስለ ሃይማኖት መሪዎችና አባቶች ሳስብ ወደ አገልግሎት የተጠራሁበትን ቀን አጥብቄ እረግመዋለሁ።በሕዝብ የደምና የእንባ ባሕር ላይ የሚዋኙትን ግፈኞችና አረመኔዎች መገሰጽና ማውገዙ ቢቀር ቢያንስ በተኩላ መንጋ ውስጥ ያሰማሯቸውን በጎች ወደ እውነተኛው እረኛና ነፍሱን ስለበጎቹ ወዳኖረው፣ ወደሰጠው ብቸኛው ጌታ እንዲጮሁ ክርስቶስን ወክለው በበላይነትበሚመሯትና በሚያስተዳድሯት በቤተ ክርስቲያኗ ስም ጥሪ ቢያቀርቡ ምን አለበት?

ይህ ጥያቄዬ ሃይማኖታዊ ግዳጃቸውን ከሚወጡት የእግዚአብሔር ምርጦች አንዳንድ አባቾችና አገልጋዮች በስተቀር ላሉት ነው።ለእነዚህ ክብር ይገባቸዋል።ባሉበት ኃላፊነት ሀገራችንንና ሕዝባችንን በጸሎት የሚያስቡትን እግዚአብሔር በሰማያዊ መንግሥቱ ያስብልን።

ፈርዖን ይሞታል።ያውም ሬሳው ላይገኝ ተሰጥሞ።
ፈርዖን መሞቱ ላይቀር ስለ ሚያልፈው ስልጣን ብሎ ስልጣን ተረካቢውን የበኩር ልጁን አስገደለው።የእሱን ብቻ ሳይሆን የግብፃውያን የበኩር ልጆች ሁሉ አስገደለ።
ፈርኦን ሆይ! ልብ ግዛ።
ማለፍህና መሞትህ ላይቀር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ በምታደርሰው ግፍና ጭቆና ለአንተና ለነገሥህበት ሕዝብ ሕይወት የሆነውን የሀገርህን የወንዝ ውሃ ወደ ደም አትቀይረው።ውሃው ሕይወትህ ነውና የምትጠጣው አጥተህ እንዳትሞት።
ፈርዖን ሆይ! ልብ ግዛ።
ማለፍህና መሞትህ ላይቀር የእግዚአብሔር እጆች ባበጃጁትና በፈጠሩት ክቡር የሰው ልጅ ላይ በሬዎችህ የማይሸከሙትን ከባድ ቀንበር አትጫን።ይህ ሕዝብ የሰባት ዓመት ርሃብህን ያስወገደ፣አሁንም ድረስ ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ጉልበቱን እየገበረልህ ያለ፣ስልጣንህ፣ደሞዝህ፣ክብርህ…ሁለመናህ ነው።
ፈርዖን ሆይ!የውርደትህን ዘመን አስብ።
ይህ ሕዝብ ትሁት ነው።የስምህ መጠሪያ የሆኑትን እነዚያ ታላላቅ ፒራሚዶች በልጆቹ ደም የገነባልህ ይህ ትሁትና ትእግስተኛ ሕዝብ ነው።
ራሔል ኢትዮጵያ ስለ ልጆችሽ ደም ጩኺ።ዝም አትበይ ጩኺ።ስለ ልጆችሽ ማልቀስ ተፈቅዶልሻል አሰምተሽ ጩኺ።
ፈርዖን ሆይ!ልብህን አታደንድን።
ይህ ሕዝብ አንተ እንዳትራብ የእርሻ ማሳዎችህን በስንዴ ሞልቷል።ሰብሉ ሳይታጨድ አንበጣና ኩብኩባ ወጥቶ ሳያጠፋብህ ምርቱን ከገለባው የሚለይልህን ይህንን ትሑትና ባሪያ ሕዝብ ልቀቅ አዝመራውን ይሰብስብ።

ፈርዖን ሆይ!ልብ ግዛ።
አንተ ደምቀህና አምሮብህ በአደባባይ እንድትታይ ቁምጣህን አውልቆ፣ንጹህ ልብስ ያለበሰህን፣የክብር ዘውድ የጫነልህንና ካባ የደረበልህን ትሑት ሕዝብ አስብ።እርቃንህን የሸፈነልህ ይህ ሕዝብ ከሌለ ቅማል ይበላሃል።

ፈርዖን ሆይ!እግዚአብሔር ይበቀልሃል።

ስለ ሕዝቡ መከራና ስቃይ አንተን ግፈኛውን የሚበቅል እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል!”ወእትቤቀል ደመ ንጹሐ” የንጹሑ የአቤልን፣የንጹሑ የበራክዩን ልጅ የካህኑ የዘካርያስን፣የንጹሓን የሕጻናቱን፣ስለ ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን፣ስለ ሀገር… የታረዱትን የሰማእታትን ደም እበቀላለሁ ።ደማቸውንም ከአንተና እኔን ትተው አንተን ከሚያገለግሉ የጥፋት የሃይማኖት አባቶች ዘንድ እፈልጋለሁ።
ሀገሪ መሪ የምትመስሉ የጥፋት መሪዎች ፈርዖንና ሠራዊቱ፣ ሃይማኖታዊ በሚመስል ተዓምራት ሕዝብን የምታደናግሩ የፈርዖን ጠንቋዮች ኢያኔስና ኢያንበሬስ መሬት ተከፍታ ሳውጣችሁ፣ በሞት ባሕር ሰጥማችሁ ከሞታችሁ በፊት ንስሓ ግቡ፤ንስሓ ያልገባ መሪ የእግዚአብሔር ሕዝብ መምራት አይችልምና የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለቀቁ።
ንስሓ ግቡ።እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው ይቅር ይላችኋል።
አሜን ሁላችንንም ይቅር ይበለን።

የዘመናት ባለቤት እግዚአብሔር መጭውን ዘመን ከፈርዖን አገዛዝ ነጻ የምንወጣበትና ወደ ርስታችን ኢትዮጵያ በድል ዝማሬ የምንገባበት ይሁንልን።አሜን።
ቀሲስ ዲበኩሉ በላይ
መስከረም 1-2009 ዓ.ም

ብሔራዊ ትያትር ለበዓል ዋዜማ ባዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት የተገኘው 19 ሰው ብቻ ነው

0
0
ፎቶ ከፋይል

ፎቶ ከፋይል

(ዘ-ሐበሻ) የጥቁር ሳምንትን በማስመልከት በርካታ አርቲስቶች ኮንሰርታቸውን ቢሰርዙም በመንግስት የሚተዳደረው ብሔራዊ ትያትር እንዲሰርዝ ተጠይቆ እምቢ ብሎ የዋዜማውን ኮንሰርት ቢያካሂድም 19 ሰው ብቻ እንደተገኘ ዘ-ሐበሻ ያነጋገረችው አንድ የትያትር ቤቱ ባለሙያ ገልጿል::

የትያትር ቤቱ አርቲስቶች መስራት ባይፈልጉም በግድ ተገደው እንዲዘፍኑ መደረጉን የገለጸው ይኸው አርቲስት ሕዝብ እንዲህ ያለውን በኮንሰርቱ ላይ ባለመገኘ ምላሽ በመስጠቱ አራቲስቶቹም ደስተኛ ናቸው ብሎናል::

ለበዓሉ ዋዜማ ከተዘጋጁት ፕሮግራሞች 50% የማይሞላው ዝግጅት ለተመልካች መቅረቡን ያስታወቀው ይኸው ባለሙያ የትይትር ቤቱ አስተዳደሮች ቀድመን ብንሰርዝ ይሻል ነበር የሚል ቁጭት ውስጥ እንደወደቁ ይኸው ምንጫችን ገልጾልናል:: እንደ ባለሙያው ገለጻ የተገኙትም 19 ሰዎች የትይትር ቤቱ አስተዳደር ቤተሰቦች ሳይሆኑ አይቀሩም::

ብሔራዊ ትያትር ሰው እየሞተ ለጠራው ኮንሰርት የበተነው የጥሪ ካርድ እንዲህ ነበር ሕዝብ ቀዳዶ ሲጥለው የነበረው

ብሔራዊ ትያትር ሰው እየሞተ ለጠራው ኮንሰርት የበተነው የጥሪ ካርድ እንዲህ ነበር ሕዝብ ቀዳዶ ሲጥለው የነበረው

ባህር ዳር እሁድንና ዘመን መለወጫን በለቅሶ እያከበረች ነው

0
0

bahirdar

አያለው መንበር ክ ባህር ዳር

ባህር ዳር እሁድንና ዘመን መለወጫን በለቅሶ እያከበረች ነው።

(#ማንደፍሮ_አስረስ ለ35 ቀናት የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም ሊተርፍ አልቻለም)

 ባህር ዳር የአማራ ተጋድሎ በፍፁም ሰላም ተጀምሮ እስካሁንም ጭፍጨፋ የቀጠለባት ከተማ ናት።
ለቁጥር አዳጋች ወጣቶችና ህፃናት ተሰውተዋል።

ዛሬም በአጋዚ ቆስለው በሞትና ህይወት መካከል ካሉት ውስጥ አንዱ የቀበሌ አራት እንቁጣጣሽ ሆቴል ፊት ለፊት ወጣቱ #ማንዴ_ህይወቱ አልፏል። ቀብሩም በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ደምቆ አሁን።ከደቂቃዎች በፊት መድሃኒያለም ቤተ ክርስትያን ተፈፅሟል።

ማንዴ በአጋዚ ጥይት ሆዱን የተመታው አባይ ማዶ (August 1) ነው።

ይህ ዕለት ማንዴና መሰሎቹን ያስነጠቀን ክፉ ቀን ነው።ሰዎች ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲገልፁ መስዋት ሆነዋል።

ማንዴና መሰል የአማራ አብራኮች የዘላለም የትግል ምሰሶ ተክለው አልፈዋል።እኛ የምንሞተው የተሰው ጓደኞቻችን አላማ ዳር ሳናደርስ ስንቀር ነው።

 

ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ –“እውነትንና ፍትህን በመያዝ ትግላችንን እንቀጥል!”

0
0

muslim
እሁድ መስከረም 1/2009 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፣ በጣም አዛኝ በሆነው!

ውድ የአገራችን ህዝቦች ሆይ!
አገራችን ኢትዮጵያ ያሳለፈችው የረጅምና የአጭር ጊዜ ታሪክ አካል የሆነው የህዝብ ስልጣን ባለቤትነት አለመከበር፣ የእኩልነትና የእኩል ተጠቃሚነት መርህ አለመተግበርና በአጠቃላይ ዜጎችን ሁሉ ሊያሳተፍ የሚችል ዱሞክራሲያዊ ስርዓት እጦት አሁን ላለንበት እጅግ አሳሳቢ ወቅታዊ ሁኔታ እንዳበቃን ለማንም ግልፅ ነው፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ | PDF

Press Release by the Ethiopian Muslims’ Arbitration Committee

0
0

muslim

Sunday September 11/2016 Addis Ababa/Ethiopia

In the Name of Allah, Most Beneficient, Most Merciful

Dear Ethiopians!

It is clear that our present distressful state owes itself to our long culture of lack of public empowerment, lack of equality & the exercise of equal opportunities and the absence of a participative democratic system. Accordingly, people have gone out to the streets to protest against the government and are paying a lot of sacrifice. Tension has prevailed nationwide.

The protests are results of a prolonged public grievance and they are hardly unanticipated immediate turn of events. The government’s long standing culture of total disregard to public opinion and grievance has expressed itself through the labeling of even peaceful human rights movements as acts of terrorism. The manner in which the government handled the case of the peaceful resistance movement of Ethiopian Muslims is a major witness to this fact. The unjust conviction and sentencing of the committee members and their associates also proves the fact that the law is being used for political ends to suppress dissent. Thus, owing to the suppression of public demands, the prevalence of injustice and the widespread grievance, the people have gone out to the streets to protest against the government.

We believe it is the duty of all citizens, local and abroad, to handle this matter with the utmost caution. The demands of the public should be met so that the hatred and vengeance ridden politics can come to an end and leave its place to a trouble-free environment where rights and liberties are respected, citizens live in harmony and respect, equality and the exercise of equal opportunities are guaranteed, and the rule of law is upheld.

The government needs to understand that the suppression of public demands through the use of force will not work. There is no worldly power that can stop the people, the real source of all political power, from achieving its needs. Carrying out military action against the people is no more a solution. Nor is the public ready to accept false appeasements and hollow attempts as real solutions to its demands. On the contrary, the government should break free from party-centered selfishness and not lose sight of the bigger picture; the well being of the nation. It should strive to fix its reputation in time before it goes down through the pages of history with a guilty conviction. All members of the bureaucracy should play their historic roles to do good to the nation and not strangle it.

Religious leaders and the elderly figures in the country also have the cultural and religious duty to stand with the people and be truthful. They should advice and counsel the government so it listens to the public. They should also work to strengthen public ties. Quite unfortunately, the leaders of the illegal Mejlis (Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council) have been engaged in encouraging the government to take forceful measure against the people. It should be well noted that these individuals and their opinions are not representative of the Muslim community in Ethiopia.

You have been rallying for the last 5 years peacefully to fight against government interference in religious affairs and to protect your religious rights. It is our sincere wish that the Almighty rewards your actions.

Dear Ethiopians!

Freedom and rights are indeed treasures the public holds dear. Anyone deprived of such treasures should take it upon himself to struggle hard for his equality and the exercise of equal opportunities in the country. We, as human beings, are obliged to seek out our freedom that is also our birth right. Thus, we would like to remind all Ethiopians, both local and abroad, to go hand in hand and attend to their duties in the struggle to secure justice, freedom and equality in the country. As Muslims our Prophet Mohammed (peace be upon Him) taught us and set for us practical examples to stand in unity for the struggle of justice and fairness.

Fellow Countrymen!

We believe all academicians and activists, both local and abroad, should work day and night to bring about all-encompassing and participative solutions that can pull the country out of the pit of crisis it is diving in. The political elite should also address the issue of public harmony and societal unity in addition to promoting a polity of mercy and forgiveness. We believe it is possible to bring about an end to our hateful and marginal culture of politics once and for all.

Fellow Countrymen!

We should take extra care to avoid all kinds of hate speech and propaganda that generically labels, characterizes and condemns one specific ethnicity or society for such propaganda endangers our welfare as a nation. All stakeholders should stand guard and play their respective parts to block the way for any destructive and anti-public behavior.

We have no doubts whatsoever that all Ethiopians, famous for their strong brotherly relationship that has endured through the ages despite ethnic and religious differences, will be able to reform the nation into becoming a country of prosperity and freedom. We also would like to express our admiration to all Ethiopians who, in the midst of the recent countrywide protests, stood hand in hand in proving “what concerns one concerns all” in the country despite differences in race and religion. Accordingly, we express our deep sadness in all the sacrifice the people paid in Oromia, Amhara and other regions (both in death and disability). We offer our condolences to their families and friends and all Ethiopians in general.

We ask everyone to be steadfast in prayer so that justice, peace, equality and prosperity can prevail in our motherland.

Dear Lord, we beseech you to make our beloved motherland a country full of freedom, justice, equality and peace. Make Ethiopia stand recognized in the midst of all countries as a sanctuary of material and moral success. Amen!

———————————————————— Copies to:- all media outlets local and abroad

 


በደቡብ አፍሪክ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት ጥቁር ለብሰው ጧፍ በማብራት በሕወሓት መንግስት የተገደሉ ወገኖቻቸውን አሰቡ

0
0

new-year south-africa south-africa2

(ዘ-ሐበሻ) በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት ጥቁር በጥቁር በመልበስ ወገኖቻቸውን በጧፍ ማብራት ሲያስቡ መዋላቸውን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የተላኩ መረጃዎች አመለከቱ::

እንደ ዘጋቢዎቻቸን ገለጻ ከሆነ በአምባገነኑ የሕወሓት መንግስት የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ለመርዳት ቃል የገቡት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ጸሎትም አድርገውላቸዋል::

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግድያ ለማስቆም የግድ ሕወሓት የሚመራው መንግስት መውደቅ እንዳለበት ያሰመሩበት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ሕዝብ እያደረገ ያለውን ትግል በሚችሉት አቅም ሁሉ እንደሚደግፉ ቃል ገብተዋል::

የዳዊት ነጋ (ወዛመይ) የስዊዘርላንድ ኮንሰርት በአዳራሹ ውስጥ በተነሳ ጭስ ፖሊስ ኮንሰርቱን ሰረዘው | 50 ሰው ኮንሰርቱ ላይ ታድሞ ነበር

0
0
wezamey
የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል ሳይውል ሳያድር ይጥልላታል ጠላቷን ከባንዲራዋ ስር በስዊዘርላንዷ ቢል-ቢዬን ከተማ የትግርኛ ሙዚቃ ተጫዋቹ ዳዊት ነጋ (ወዛመይ) የአዲስ አመት የሙዚቃ ዝግጅት እንዲሰርዝ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም አሻፈረኝ በማለት ቅዳሜ ማታ ዝግጅቱን ለማቅረብ ወደተዘጋጀለት አዳራሽ ቢያመራም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በዕለቱ ለመታደም ባለመፈለጋቸው በምሽቱ ከ 50 ሰው ያነሰ ብቻ በመገኘቱ በአስመጭዎቹና በዘፋኙ መካከል ቀሪዬን ገንዘብ ክፈሉኝ አንከፍልም ግብግብ የተፈጠረ ቢሆንም ጥቂት ሳይቆይ ከየት እንደተነሳ ባልታወቀ መልኩ ጭስ አዳራሹ ውስጥ በመታየቱ የከተማው ፖሊስ የሙዚቃውን ዝግጅት ለመሰረዝ ተገዷል። ይህንንም ተከትሎ ዘፋኙ የፊታችን ቅዳሜ ሴፕቴምበር 16 ቀን በሌላዋ የስዊዝ ከተማ ሊያቀርበው የነበረውን የሙዚቃ ዝግጅት መሰረዛቸውን የዙሪክ አዘጋጆች ማምሻውን በማኅበራዊ ኔትዎርኮች እየገለፁ ይገኛሉ። አሁንም እንላለን: ሙዚቀኞችና የሙዚቃ አዘጋጆች ከሕዝብ ጋር ቁሙ! ለሚያልፍ ቀን ከሕዝብ ጋር እልህ አትግቡ! ሕዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው! የኢትዮጵያ አምላክ አያንቀላፋም!

ታሪካዊ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ |በመላው ሰሜን አሜሪካ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን

0
0

2
ታሪካዊ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በዋሽንግተን ዲሲ| በመላው ሰሜን አሜሪካ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን

ህውሓት/ኢህዴግ በቆፈረው ጉድጎድ ለመግባት አፋፍ ላይ ነው

0
0

በመላው የሀገራችን ክፍል በተለይም በኦሮምያ እና በአማራ ክልል በተቀሰቀስው የመብት እና የማንነት ጥያቄ ዙርያ የሀገራቸው ጉዳይ ስለሚመለከታቸው ፍፁም ሰላማዊ እና በሰለጠነ በሆነ መልኩ ከሕፃን እስከአዋቂ ላለፉት ወራቶች ኢትዮጵያዊያን ልዪነታችውን ወደ ጐን ትተው በአንድ ላይ አንባገነን ሥርዓትን እና የአንድ ብሔር የበላይነት አክትሞ ሁሉም ብሔር፣ብሔረሰቦች በእኩልነት የሚኖሩባት ሥርዓት ለመገንባትበሰላማዊ መንገድ ጥያቄቸውን በማቅረብ ላይ የገኛሉ ነገር ግን የቀረበውን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ሀይል ግጭት ሆን ብሎ ወያኔ ስለቀየረው ዜጎች ግንባራቸውን ለጥይት ሰጥተው ለህዝባቸው መሰዋት በማቅረብየፍርሃት ቆፈን ሳይሽብባቸው በመታገል ላይ አሉ። የነዚህ ግጭቶች ፣አለመግባባቶች ለሕይወት እና ንብረት ውድመት ዋንኛ መንሴ ሆኖ የሚጠቀሰው በማንአለብኝነት ገደብ የለሽ መንግስታዊ ግፍና በደል እየፈፀመያለው ሀገሪቶን በመምራት ላይ የሚገኝው ህውሓት/ኢህዴግነው።

Oromo amhara unity

ከዚህ በተጨማሪ በሀገራችን እየተካሄደ ካለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ባሻገር የብሔርና የዘር ጉዳይ ርዕሠ ጉዳይነቱ ተጠናክሯል፡፡ሰሞኑን የመንግሥት ባለስልጣናትና ካድሬዎቹ “የዘረኝነት ጉዳይ በእጅጉ አሳስቦናል”ሲሉም እየተደመጡ ነው፡፡የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚከታተሉ ብዙዎች ግን ለጉዳዩ ዋነኛ ተጠያቂ የሚያደርጉት ራሱን ኢሕዴግን ሲኾን የሰሞኑንም የኢሕአዴግን ጩኸት እንደ አስገራሚ ትእይንት የሚያዩትብዙዎች ናቸው። አሁን አሁን ከሌሎች ወገኖችም የሚሰነዘሩት የዘርናየጥላቻ ፖለቲካ ምንጩ ኢሕዴግ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በላይሲዘራው የኖረው የፖለቲካ ዘር ፍሬ እንጂ ሌላ ነገር መስሎ የማይታያቸውበቁጥር ቀላል የሚባሉ አይደሉም፡፡ የብሔር/ብሔረሰብን መብት በማስከበር ሽፋን የዘር ጥላቻእንዲቀሰቀስ፣ ክፍፍል እንዲካረር፣ አለመተማመን እንዲሠፍን ገዢው ፓርቲ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታትበላይ እንቅልፉን አጥቶ መሥራቱን የሚገልጹ ወገኖች ኢሕአዴግ ደርሶ ዘረኝነት አውጋዥ መሆኑ አይዋጥላቸውም፡፡ እንዲያውምበሥልጣን ዘመኑ ሁኔታውን በመጥፎ ጎኑ ሲያቀጣጥል የቆየው ገዢው ፓርቲ ባሻውወቅት ሁሉ ይሕን መሰሉን ክስ ሌሎች ላይ ሲለጥፍ መታየቱም የተለመደ ባህርይው ሆኖም ይወሰዳል፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት በብሔሮች መካከል አለመተማመን እንዲፈጠር ቅስቀሳ ከማድረግ አንስቶ የአረካን፣ የበደኖንና የአርባጉጉን በመሰሉ እልቂቶች ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንደነበረም የሚያሳጡት ምስክሮችም ይቀርቡበታል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት “ላስከብርተነስቻለሁ” በማለቱ ረገድ ኢሕአዴግ የመጀመሪያው የአገሪቱ መንግሥት አይደለም፡፡ እንዲያውም የፌደራሊዝም አወቃቀር ‘እርሾውን’ ከቀድሞው መንግሥት የብሔረሰቦች ጥናት ኢኒስቲቲዩት እንደወሰደው ነውየሚነገረው።

“የብሔረሰብ መብት ማስከበርን ከኔ በላይ ላሳር” የሚለው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢሕአዴግ) በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሐት) ቁጥጥር ስር መቀፍደዱ የፕሮፓጋንዳውን ያህል የሌሎች ብሔረሰቦችን መብት ጉዳይ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለማንሳት እንዳላስቻለውም ይገመታል፡፡“…በነጻ ፍላጎትና በሕግ የበላይነት አንድ የፖለቲካ ማሕበረሰብ በጋራ የመገንባት” ሐሳብእንደያዘ የሚነገርለትን ሕገ መንግስት ይዞም ከሩብ ክፍለ ዘመን በኋላ እንኳ ወሳኝ የሆኑ የሥልጣን ቦታዎችን ለሌሎች ለማካፈል ያለው ፍላጎት አነስተኛ መሆኑም አገዛዙን የሚያሳማው ጉዳይ ነው። “መጪው የጋራዕድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅምን በማሳደግ ላይ ነው” የሚለውን በሠነድ እንዲሰፍር ቢያደርግም የጋራ ጥቅምን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን ለማድመጥዝግጁ አይመስልም፡፡“…ጥቅማችን፣ መብታችንና ነጻነታችንን በጋራ እና በተደጋጋፊነት ለማሳደግ አንድ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ መገንባት አስፈላጊ ነው” የሚለውም እዚያው ሕገ መንግሥቱ የታተመበት ወረቀትላይብቻ እንዲወሰን አድርጎታል፡፡ እነዚህኑ መብቶች በመጠየቃቸው ምክንያትም ዜጎች ይታሠራሉ፤ ይገደላሉ፤ ለእንግልትና ለስደት ይዳረጋሉ፡፡ ኢሕአዴግ ልዩነትን በማስፋት፣ ጥርጣሬና ፍርሃትን በማንገሥ መንገዱዘልቆበታል፤ የገዢው ፓርቲማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰሞኑ ለአራት ቀናት በዝግ ያካሄደውን ስብሰባ ሲያጠናቅቅ ባወጣው መግለጫም ዘረኝነት የአገሪቱ ሥጋት ነው ብሏል፡፡ ተቃዋሚዎች ግን ዘረኝነትን በማቀጣጠል፣ አየሩበጥርጣሬና ፍርሃት እንዲሞላ፣ አንድነት እንዲናጋ በማድረጉ ረገድ የኢሕአዴግን ያሕል የደከመም የተሳካለትም የለም ነው የሚሉት፡፡ኢሕአዴግ በሥልጣን ዘመኑ ይህን በተመለከተ የሚነቀፍበት ብዙ ምሳሌዎችምእዚህ ላይ ይጠቀሳሉ፡፡ ብዙዎች ከማይዘነጉት የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑነው ከሚለው አባባል ባሻገር በኢሕዴግ ዘመን ከጋራ እሴቶች ይልቅ ልዩነት ላይ ትኩረት እንዲደረግ የተሰሩ ብዙ ስራዎችመኖራቸው ተደጋግሞ ይጠቀሳል። ዩኒቨርሲቲዎችና ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት የአገዛዙ ልዩነት መፍጠሪያ ዋና ማዕከላት ተደርገዋል፤ ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ሃገራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንዳያተኩሩ ገደብ ይደረግባቸዋል፡፡ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ስለ ሃገራዊ ትስስርና አንድነት ትንፍሽ አይሉም፡፡ በ

ብሔራዊናአብይ በዓላት አከባበር እንኳ የክልል ቴሌቪዥኖችና ሬዲዮ ጣቢያዎች ከክልላቸው አርቀው እንዳይመለከቱ ተደርገዋል፡፡ በብሔር ብሔረሰቦች በዓል ሳይቀር ደም አፋሳሽ ግጭቶች መቀጣጠላቸውም ተስተውሏል፡፡ኢሕአዴግ በመታወቂያ ካርድ ላይ ብሔር እንዲሠፍር ያደረገበት አካሄድ አደጋ ይደቅናል ያሉ ብዙዎች ነበሩ። አደጋው አሁን በመጠኑ ብልጭ እያለ ነው፡፡ በሩዋንዳ እልቂት ወቅት በመታወቂያ ላይ ብሔርእንዲሠፍር መደረጉ አንዱ የችግሩ ማቀጣጠያ እንደነበር የሚያወሱ ብዙዎች በኢትዮጵያም ይህንኑ ብሔርን በመታወቂያ የመጻፍ አስገዳጅነት በስጋት ያዩታል፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ ለተቃውሞ ሠልፍ የወጡየኦሮሞ ተወላጆች በመታወቂያ ካርዳቸው ላይ በሠፈረ የብሔር ማንነት እየተነጠሉ ለጥቃት እንደተዳረጉም ሲነገር ሰንብቷል፡፡ ከሠሞኑ በአዲስ አበባየሚገኙ ሆቴሎችና ፔኒሲዮኖች በተላለፈላቸው ትዕዛዝ ከአማራክልል የሚመጡ አዳዲስ እንግዶችን ጠቁሙ የተባሉትም ከመታወቂያ ካርድ በሚገኝ መረጃ ነው፡፡ ዘረኝነትን እያወገዝኩ ነው የሚለው ኢሕአዴግ በተግባር ተቃራኒውን ሲፈጽምም ይስተዋላል፡፡ በጎንደር አካባቢተቃውሞ በጀመረ ሰሞን መንግሥት በጸጥታ ክፍሉ አማካይነት ባወጣው መግለጫ… በአንድ ብሔር ላይ ጥቃት ተሰንዝሮ እንደነበር ነው የገለጸው። የአማራ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ በበኩላቸውበተካሄደ ማጣራት በዘር ላይ የተነጣጠረ ጥቃት እንዳልነበር ጠቆሙ፡፡ እንዲህ ያለው አደገኛ ጉዳይ በመንግሥት ሲገለጽ አደጋና ሥጋቱ ከፍ ያለ ይሆናል፡፡ እዚያው ጎንደር አካባቢ ከሕዝቡ ጋር በነበረው ግጭት ላይሕይወታቸው ያለፈውን የጸጥታ ሰዎችስማቸውን መግለጽ በቂ ሆኖ ሳለ… ብሔረሰባቸው ጭምር ተዘርዝሮ እንዲጠቀስ የተደረገበት አካሄድም “…የተገደሉት የእከሌ ብሔር ተወላጆች ናቸው” የሚል አቀጣጣይአጀንዳ እንዲኖር ተፈልጎ ሳይሆን እንዳልቀረ የሚገምቱ አልጠፉም፡፡

የኢሕአዴግ ካድሬ መሆናቸው የሚታወቁ ሰዎች ከሰሞኑ በማሕበራዊ ሚዲያዎች “የኦሮሞ ተቃውሞ ትክክለኛ ነው፤ የአማራ ተቃውሞ ሕገ ወጥነው” በሚል መልዕክት መጠመዳቸውም ክፍፍል የመፍጠሩ ሌላ አካሄድ እንደሆነ የሚጠረጥሩም አሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ዘር ላይ ያነጣጠረ አሉታዊ ቅስቀሳ እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጹ ጥቂቶችአይደሉም፡፡ ሆኖም ግን በተቃዋሚዎች ስም በማሕበራዊ ድረ ገጾች ይሕ ዓይነቱ የዘር ጥላቻ ቅስቀሳ እየተሠነዘረ የሚገኘው ከአገዛዙ ካድሬዎች ሠፈር መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

አሁን የኦሮሞ ሕዝብም ይሁን የሌሎች የመላው ሀገሪቶ ብሔር /ብሔረሰቦች መሰረታዊ እና ዋናኝ ጥያቄ የመብትና ዲሞክራሲ ስለሆነ ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ ና ከአንባገነን ነፃ የመሆን የነፃነት ጥያቄ ነው።

ድል ለጭቁኑ ሕዝብ!!

ከከልለው ኡርጋ

kiyu297@gmail.com

በአምባሳደር ግርማ ብሩና ቤታቸው ባለች ሴት ተደብድበናል ያሉ በዋሽንግተን ዲሲ ክስ ሊመሰርቱ መሆኑን አስታወቁ

0
0

girma biruu

የኦሮሞ ወጣቶች ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ ዛሬ አምባሳደር ግርማ ብሩን ቤታቸው ድረስ ለማነጋገር ሄደው ነበር:: አብረው ከሄዱት ወጣቶች መካከል ኪያ እና ኤደን የተባሉት ወጣቶች ለጀዋር መሐመድ በላኩት መረጃ እንደገለጹት “አቶ ግርማ ብሩ መኖሪያ ቤት ጥበቃዎች ካስገቧቸው በኋላ እነዚህ ሴቶች አቶ ግርማ ብሩን እንዴት ራስህን ኦሮሞነኝ ብለህ ትቆጥራለህ? ለምን ኃላፊነት አይሰማህም? ብለው ይጠይቁታል::

አምባሳደሩም ወጣቱን ኪያን እንደተማቱና ከአምባሳደሩ ጋር አብራ የነበረች ሴትም ኤደን የተባለችውን ወጣት እንደተማቱ ለጀዋር መሐመድ በላኩት መረጃ አስታውቀዋል:: በግርማ ብሩ እንደተመታ የሚገልጸው ኪያ አንገቱና ጆሮው ላይ ጉዳት እንደደረሰበት ገልጿል::

ወጣቶቹ ለህዝብ ይፋ አድርግልን ብለው በላኩት መረጃ ላይ ለጊዜው በወቅቱ የደረሰባቸውን ድብደባ ለሕዝብ ይፋ እንዳማያደርጉና ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ይዘው ሄደው ክስ እንደሚመሰርቱ ለጀዋር በላኩት መረጃ አመልክተዋል::

አምባሳደር ግርማ ብሩ በደረሰባቸው ውንጀላ ላይ ያላቸውን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም::

screen-shot-2016-09-11-at-7-57-48-pm

ያቺ “ባነር”….. ! –በመስከረም አበራ

0
0

(በመስከረም አበራ; e-mail meskiduye99@gmail.com)

Ethiopian-Flag1.jpgየኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ መባቻ ከዘመነ መሳፍንት ማክተም ጋር የሚቆራኝ ነው፡፡የሃገራችንን የቀደመ ግርማ አኮስሶ፣ የጦር አለቆች የረብሻ ምድር አድሮጓት የኖረው፣ በታሪክ ዘመነ መሳፍንት ተብሎ የሚታወቀው ወቅት የቆየበት ጊዜ ዘለግ ያለ በመሆኑ ተክሎት ያለፈው ችግር ስርም ጠለቀ ያለ ነበር፡፡በተለይ ከዘመነ መሳፍንት በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ ነገስታት በታላቅ ሃገር ላይ ታላቅ መሪ የመሆን አልፎም ቀይባህርን ተሻግሮ የማስገበር የታላቅነት ምኞት በትንንሽ መንደሮች ትንሽ አለቃ ለመሆን ወደ መቃተት የንዑስነት ምኞት አንሶ ነበር፡፡ ይህ የንዑስነት ዘመን መንደርተኛነት በሃገራዊነት ላይ የገነነበት፣ መነጣጠል አብሮነትን የረታበት፣የኢትዮጵያዊነት ስሜት የሰለለበት  ዘመን ነበር፡፡ ይህ የድቀት ዘመን ያከተመው ከወደ ጎንደር በተነሳ የቀደመ ታላቅነትን የመናፈቅ ሃሳብ ነበር፡፡ስር የሰደደው የዘመነ መሳፍንት ዘመን የንዑስነት ምኞት እና የመከፋፈል አባዜ በቋራው ካሣ ታላቅነት የመናፈቅ ከፍ ያለ እሳቦት ፍፃሜውን አገኘ፡፡የካሣን ውድ ህይወት ቢነጥቅም በዘመነ መሳፍንት የመንደርተኝነት ዝንባሌ  እልም ስልም ሲል የባጀው የኢትዮጵያዊነት ስሜት ወደ ህዝብ ልቦና ተመለሰ፡፡

ሆኖም ከዘመነ መሳፍነት ማክተም ብዙ ዘመን በኋላ ኢትዮጵያዊነት ሌላ ፈተና ገጠመው፡፡በተለይ ከኢህአዴግ ወደ ወንበር መምጣት በኋላ ኢትየጵያዊነትን የማቀንቀን ፖለቲካዊ አቋም፣ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ቱርፋቶች መስበክ፣ ስለኢትዮጵያዊ ወንድማማች/እህትማማችነት ማውራት  እንደ መርገም ጨርቅ ያለ ነገር ሆኖ ኖረ፡፡የመርገም ጨርቁ ስም ደግሞ “ትምክህተኛ አማራነት” ነው፡፡የኢትዮጵያ አንድነት የሚጠቅመው ለአማራው ብቻ ባለመሆኑ ኢህአዴግ አማራ ከሚላቸው ሰዎች ሌላም  በሁሉም የሃገራችን ጥግ ለኢትዮጵያዊነት የሚቃትቱ ኢትዮጵያዊያን በብዛት አሉ፡፡ኢህአዴግ ለእነዚህም ስም አለው – “የአማራ ተላላኪዎች” ሲል አንድ ሰው ስለ ሃገሩ ህልውና እና የሃገር ባለቤትነት ጥቅም በራሱ ጭንቅላት አስቦ ይረዳ ዘንድ የማይቻል አስመስሎት ቁጭ ይላል፡፡ እውነታው ኢትዮጵያዊነት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ልቦና ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያለው ነው፡፡ አከራካሪው ነገር ኢትዮጵያ እንዴት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሆነች እናት ትሁን በሚለው ታሪክ ከማቃለል  ይልቅ እያከማቸው በመጣው የቤት ስራ ላይ ይመስለኛል፡፡ከእውነት ጋር ብዙ የማይስማማው ኢህአዴግ ታዲያ ይህን የታሪክ ክፍተት ለተፈጠረበት ኢትዮጵያዊነትን የማደብዘዝ እኩይ አላማ በደንብ ተጠቀመበት፡፡ አገዛዙ በቆይታው ስኬታማ የሆነበት ዋናው ጉዳይ ይህን አኩይ አላማ ከግብ ለማድረስ የሮጠው ሩጫ ይመስለኛል፡፡

ህወሃት አስራ ሰባት አመት ጭንጫ ገደሉን ረግጨ ቧጥጬ የታገልኩት ለብሄር ብሄረሰቦች መብት ስል ነው ባይ ነው፡፡ይህን ያስመሰክር የነበረው ደግሞ የአማራ ህዝብን ቅስም የሚሰብሩ ንግግሮች፣ ድርጊቶች በማድረግ ነው፡፡ ህወሃት ወደ ስልጣን ከመምጣቱ በፊትም ሆነ ከመጣ በኋላ የፖለቲካ ግንዛቤው ጥግ የአማራን ህዝብ ማጥላላት፣ ያልሆነ ስም መለጠፍ፣ማሰር፣ ማፈናቀል፣መግደል፣ ሰድቦ ለተሳዳቢ መስጠት ይመስለው ነበር፡፡ ለሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች መብት መቆሙን የሚያስመሰክረውም የጠየቁትን፣ራሱም በህገመንግስቱ የፃፈውን እስከ መገንጠል የዘለቀውን መብት በመተግበር ሳይሆን የአማራን ህዝብ በአደባባይ በማበሻቀጥ፣ ‘የድሮ በዳያቸውን’ (አማራን መሆኑ ነው) የማጥፋቱን ታዳጊነት ገድል በመተረክ ነው፡፡ የድሮው ይቅርና በቅርቡ የአቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ወደ ስልጣን መምጣት አስመልክቶ አዛውንትነታቸውን የሚመጥን የንግግር ጭዋነት የሚያጥራቸው አዛውንቱ ስብሃት ነጋ ‘ሰውየውን መሾማችን  አማራን እና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይን ከስልጣን አጥረገጥ የማጥፋታችን ምልክት ነው’ ሲሉ ጫካ የለከፋቸው የጥላቻ ክፉ ደዌ እያደር የሚብስ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ይህን ክፉ ጥላቻ ያረገዙት ህወሃትዎች የህዝብ መገናኛ ብዙሃንን ለብቻቸው አንቀው መያዛቸው፣በመገናኛ ብዙሃን ይህንኑ የጥላቻ ስብከት ለማጧጧፍ እፍረትም ሆነ ሃላፊነት የማይሞክራቸው መሆኑ ደግሞ የነገሩን ውጤት በተለይ በአማራው ህዝብ ላይ ክፉ አድርጎት ኖሯል፡፡ ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ከኢህአዴግ በኋላ ያለችውን ኢትዮጵያ እጣፋንታ አጨልመው የሚያቀርቡትም ከዚህ እውነታ ጋር በተያያዘ ነው፡፡የሰራውን የሚያውቀው ኢህአዴግ ደግሞ በዚህ ሃላፊነት በጎደለው ስራው ሊያፍር ሲገባው ይኩራራል፣ ‘ከሌለሁ ወዮላት ለኢትዮጵያ’ ሲል ያስፈራራል፡፡በሃገሪቱ ሌላ ፍጥረት ያልተፈጠረ ይመስል የእልቂቱ ተዋናዮች፣የሃገሪቱ እጣፋንታ ወሳኞች የአማራ አና የኦሮሞ ህዝብ እንደሚሆኑ ይተነብያል፡፡የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ለመገዳደል ብቻ የሚፈላለጉ ታሪካዊ ባላንጣዎች አድርጎ ውሸትን እጅግ ደጋግሞ እውነት ሊያስመስል ምንም አልቀረውም ነበር፡፡

ከንቱው ልፋት

የስሌት አውዳችን ጎሳን ማዕከል ያደረገ ከሆነ ህወሃት ወጣሁበት የሚለው የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያ ንዑስ ቁጥር ካላቸው ጎሳዎች ወገን ነው፡፡ እንደ እውነቱ ቢሆን የጎሳ ፖለቲካ መሲህ ነኝ የሚለው ህወሃት  የሰፈሩን ልጆች ጠርቶ የወረረውን የፖለቲካ ስልጣን ለተላላቆቹ ኦሮሞ እና አማራ ጎሳዎች መልቀቅ ነበረበት፡፡ ይህን እንደማያደርግ ልቦናው የሚያውቀው ንዑሱ ህወሃት ታዲያ እንደ አማራጭ ያየው  ስልጣኑ ለሚገባቸው ጎሳዎች እርስበርስ የመናቆር፣አይን እና ናጫ የመሆን የቤት ስራ መስጠት ነው፡፡ ለኦሮሞዎች የተበዳይነት ሙዚቃ ከፍቶ ሲያስቆዝም ለአማራው እንደጉተና የከበደ የበዳይነት ሸክም ጫነው፡፡ አማራው በተነፈሰ ቁጥር በእብሪተኛነት፣በጭካኔ፣በትምክህተኛነት እየፈረጀ ሁለተኛ ወደ ስልጣን ዝር ማለት የሌለበት እኩይ አድርጎ ያቀርባል፡፡

በትዝታ እንዲቆዝም የተደረገው ኦሮሞ ታዲያ አሁን ሊቀመጥበት የሚችለውን የፖለቲካ ስልጣን ወንበር ጥያቄ ረስቶ ቀና ብለው “አቤት” የማይሉትን አፄ ምኒልክን በመርገም፣በመውቀስ እንዲጠመድ ተደርጓል፡፡አፄ ምኒልክም መላውን አማራ ወክለው የሞቱ ይመስል ለእርሳቸው በተነሳው የጭቃ ጅራፍ አማራ የተባለው ሁሉ ይገረፍ ያዘ፣ ለምኒልክ የተከፈተ የበደል ሙዚቃ ለአማራ ሁሉ የሚበቃ የጥላቻ ስንቅ አስቋጥሮ በጎሪጥ ሲያስተያይ፣ አፍንጫ ሲመታ አይን እንዳያለቅስ እንባ አድርቆ ኖሯል፡፡ አማራውም በፊናው በዋናነት በኦሮሚያ፣ በደቡብ እና በሌሎች ክልሎችም ለፍቶ ያፈራውን ንብረት ለቆ እንዲወጣ ሲደረግ ይህን ያደረገው ማን እንደሆነ ስለሚያውቅ በተዋለደው እና አብሮ በኖረው ህዝብ ላይ አፉን አላላቀቀም፡፡አማራነቱ ብቻ በደል ሆኖ ተቆጥሮ የሚገረፍበትን በትር ብርታት ስላወቀ አድርጎት የማያውቀውን አንገቱን መድፋት ተማረ፣ቅዝምዝምን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ ተሽሎት ወገኖቹ ሲታሰሩ፣ሲገደሉ፣ ከምድር ዳርቻ ሲሳደዱ አዝኖ እንዳላዘነ ሆኖ አለፈው፡፡ሽሽት የማያውቀው ህዝብ ሽሽት ለመደ፡፡ይሄኔ ነው እነ ስብሃት ነጋ፣ሳሞራ የኑስ እና መለስ ዜናዊን የመሰሉ የጥላቻ ሰባኪዎች ‘አማራን እንዳይነሳ አድርገን ቀበርነው’ ያሉት፡፡

ሰፊውን የአማራ ህዝብ ብቻቸውን ገድሎ ለመቅበር የንዑስነት አቅማቸው እንደማይፈቅድ የተረዱት ህወሃቶች ባለግርማውን የኦሮሞ ህዝብ መጠለያ ማድረግን መረጡ፡፡ ‘ከየት አመጣችሁት?’ ተብለው የሚጠየቁበት መድረክ የለምና የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ አለም ከተፈጠረ ጀምሮ በኖረ የመረረ፣ የከረረ ጠላትነት እንዳላቸው ብቻቸውን በያዙት መገናኛ ብዙሃን ሲያላዝኑ ኖሩ፡፡ በሃሰት የተለወሰ የፈጠራ እና የጥላቻ  መርዛቸውን መድሃኒት አስመስለው የሚያቀርቡበትን ስብከት ስለሚያረክስባቸው በሳይንሳዊ መረጃ ላይ የቆሙ የታሪክ ድርሳናትን አጣጣሉ፡፡እውነትን ለመፈለግ በየዋሻው የተሻጡ ‘ኦርጅናል’ የታሪክ መዛግብትን የሚያስሱ ኢትዮጵያ-በቀል የታሪክ  ተመራማሪዎችን ፈተናቸውን አብዝተው ከሃገር አሰደዱ፡፡ ሰሞኑን በፕ/ሮ ፍቅሬ ቶሎሳ አዲስ መፅሃፍ ሽያጭ ላይ የተዘመተው ዘመቻ ለዚህ አንድ ማሳያ ነው፡፡

 

የጎንደሩ ጥሎሽ …

ህወሃት ሁለቱን ህዝቦች እርቅ ሊጎበኘው በማይችል የጠላትነት አዘቅት ውስጥ ለመክተት የተጠቀመው መንገድ መገናኛ ብዙሃን፣የራሳቸውን ሃላፊነት አልቦ አንደበት እና ከሁለቱም ብሄር የወጡ ግዙ ባለስልጣን እና ካድሬዎችን ብቻ አይደለም፡፡ የነመለስ ዜናዊ የጥፋት መንገድ እጅግ ረቂቅ ነውና የተስፋየ ገብረአብን ውብ ብዕርም ለዚሁ እንቅልፋቸውን ለሚነሳቸው የሁለቱ ህዝቦች አብሮነት ማፍረሻ በደንብ አድርገው ተጠቅመውበታል፡፡ ተስፋየም ሃፍረት እና ይሉኝታ ባለፈበት ያለፈ ሰው ስላልሆነ  ‘ነቅተንብሃል’ እየተባለም በልጅነቱ እንደማተብ የታሰረለትን የጥላቻ ክታብ ሊያወልቅ አልቻለም፤ ከቀድሞ አልባሽ አጉራሾቹ ጋር ከተጣላ በኋላም የጥላቻ ብዕሩ መርዝ መትፋቱን አላቆመም፡፡ ህወሃት ይህን ሁሉ ከንቱ ድካም ሲደክም የኖረው በአሽዋ ላይ የቆመ ቤት ለመስራት ነበርና የአንድ ቀን የህዝብ ድምፅ የሃያ አምስት አመት ድካሙን ገደል ከተተው፡፡ ከወደ ጎንደር በፍቅር ብዕር፣ በመተሳሰብ ሸማ ላይ የተከተበች አንድ ባነር ታሪክ ለወጠች፡፡ “በጎዳና ላይ የሚፈሰው የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን ደም የእኛም ደም ነው” የምትል የአቶ በቀለ ገርባን ምስል የያዘችው ባነር ስንቱ ፊደል ጠገብ አጥብቆ የፈተለውን የጥላቻ ገመድ በጣጠሰች፤በምትኩ ሁለቱን ታላላቅ ህዝቦች በፍቅር እንባ አራጨች፤ ያች ባነር!!! መብቱን ከማስከበር ጎን ለጎን የጠፋ ወንድማማች/እህትማማችነትን ፍለጋ የወጣው የጎንደር ህዝብ በፍቅር ፊት መቆም የማይችለውን የህወሃት በአሸዋ ላይ የተገነባ የጥላቻ ቤት በፍቅር አውሎ ንፋስ ከስሩ ነቀነቀው፡፡የጥላቻ መንገድ አይቀናም፡፡ የሴራ ወንበር አይፀናምና ይህ የሚጠበቅ ነው፡፡የጥላቻ ሰባኪዎች ግን ይህን ይረዱ ዘንድ ብቁ አይደሉም፡፡ በወርቅ የማይገዛውን  የወንድማማችነት ፍቅር “ያልተቀደሰ ጋብቻ” ሲሉ ያልተቀደሰ ጭንቅላታቸው ያቀበላቸውን ዘባረቁ፤ ፍርሃት ያራደው ከንፈራቸው ላይ የሞላውን ስድብ ሁሉ በሰፊው ህዝብ ላይ አወረዱ፡፡

ኢህአዴጎች ጥሩ የተናገሩ እየመሰላቸው ከአንደበታቸው የሚወረውሯቸው ቃላት እና ሃረጋት በመንግስት መንበር ላይ መሰየማቸውን አይመጥኑም፡፡ ሌሎቹ ቀርተው የአንደበታቸው ርቱዕነት ወፍ ያረግፋል ይባሉ የነበሩት የአቶ መለስ አንደበት እንኳን በግሌ ጨዋነት የጎደለው፣ማናለብኝነት ያሸነፈው፣ አንዳንዴም ግልብ  እንደነበረ ይሰማኝ ነበር፡፡በተከበረው ፓርላማ ፊት ‘ጣትህን እቆርጣለሁ፣ ምላስ እዘለዝላለሁ’ ይሉ ነበር፡፡ የሁለት አካላትን ሰላማዊ ግንኙነትም ከዕቁባታዊ ግንኙነት ጋር እየመሰሉ ማስረዳቱ ይቀናቸው ነበር፡፡ በ1997ዓም አላሰናዝር ብለው የነበሩትን አናጎሜዝን በተመለከተ ለአዲስ ዘመን እና ዘኢትዮጵያን ሄራልድ ጋዜጦች ኤዲተር በፃፉት ማስታዎሻ “what love has to do with this” የሚለውን የታዋቂዋን ዘፋኝ የቲና ተርነርን ሙዚቃ ግጥም መንግስትነትን በማይመጥን አላስፈላጊ ሁኔታ አስገብተው ነበር፡፡

አሁን የመንግስት አንደበት ተደርገው የተሰየሙት አቶ ጌታቸው ረዳ መሆናቸው ደግሞ በኢህአዴግ መንደር ለአንደበት ጨዋነት ብዙ ቦታ እንደሌለ አሳባቂ ነው፡፡ ብሶት በጠበንጃ ፊት እንደቆመ እንኳን አስረስቶ የሚያጮኽውን የኦሮሞ ህዝብ ከጅኒ ጋር እያነፃፀሩ ሲያስረዱ ለአቶ ጌታቸው በአማርኛ መራቀቅ፤ በሃሳብ መምጠቃቸው ሊሆን ይችላል፡፡ለሰሚ ግን ትርጉሙ ሌላ ነው፡፡ አንድ ሰው በቤቱ የቀረ በማይመስል ሁኔታ ነቅሎ የወጣውን የአማራ ህዝብ ትቂት የሽፍታ ጠበቆች ሲሉ ዘለፉ፡፡ ሁለቱ ህዝቦች ከተገደሉ ልጆቻቸው እኩል የተሰደቡት ስድብ አስቆጥቷቸዋል፡፡ በዚህ የማያበቁት አቶ ጌታቸው ‘ሁለት ባላንጣዎች ያተቀደሰ ጋብቻ መስርተዋል’ ሲሉ አከሉ፡፡ እውነት ለመናገር ነገሩ በጋብቻ ሁኔታ ባይገለጽ ደግ ነበር:: ሆኖም ሰው በልቡ የሞላውን  በአንደበቱ ይናገራልና አቶ ጌታቸው በልባቸው የሞላውን ገለፁ፡፡ነገሩ የሚገባቸው በጋብቻ ሁኔታ መገለፅ ካለበት የኦሮሞ እና የአማራ ታላላቅ ህዝቦች ቅዱስ ጋብቻ ጎንደር ላይ በቀረበችው የፍቅር ጥሎሽ (ያቺ ባነር)ተጀምሮ ኦሮሚያ ላይ “አማራ የኛ” በሚል ሙዚቃ ታጅቦ ተፈፅሟል፡፡ይህ ቢመርም ሊቀበሉት የሚያስፈልግ ሃቅ ነው! በምድር ላይ የሚያስተዳድረው ህዝብ መተሳሰብ የሚያናድደው፣ክፉ የሚያናግረው መንግስት ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡፡ “የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ይህን አይነት መፈክር ይዘው መውጣታቸው የእኛን ስራ ለ,ያለመስራት ያመላክታል”  አሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለፋና ሬዲዮ፡፡ ፋይሉ በድህረገፆች ስላለ ዝርዝሩን አንባቢዎቼ ቢያዳምጡ ሙሉ ስዕሉን ለማግኘት ይችላሉ፡፡ይህ ከአእምሮ በላይ ነው!

ቅዱሱ ጋብቻ!   

የኢህአዴግን እግር ተከትሎ በሃገራችን የተንሰራፋው እትብት እየተማዘዙ የጎሪጥ የመተያየት አባዜ አሁንም የሃገራችን ፖለቲካ ዋና ነቀርሳ ነው፡፡ ችግሩ የሚመነጨውም ሆነ የሚበረታው ተማርኩ በሚለው የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ መማሩ ስነልቦናውን ከታሪክ ጋር እያዋቃ ጥላቻን ብቻ እንዲሰብክ ያደረገው የትየለሌ ነው፡፡እንደ ደህና ነገር ስንት ገፅ መፅሃፍ አሳትሞ በየገፁ ጥላቻን ሳይረሳ የሚሰብክ ምሁር በበዛበት ሃገር፤ኢህአዴግም ይህን በደንብ ሲያሳልጥ ሃያ አምስት አመት ከንቱ ሲደክም ቢኖርም ሰሚው ሰፊ ህዝብ ጥላቻን የሚሰማበት የጆሮ መስኮቱን ዘግቶ ኖሯል፡፡ የጎንደር ህዝብ የጀመረውን የፍቅር ምልክት የኦሮሚያ ህዝብ ወዲያው ማስተጋባቱ ድሮም ኢህአዴግ በሚያራግበውን እና ፅንፈኛ የጎሳ ልሂቃን በሚያንፀባርቁት ደረጃ ህዝቦች በጠላትነት እንደማይፈላለጉ ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ሳይውልሳያድር እናንተም የእኛ ናችሁ ሲል መልስ የሰጠው በፍቅር መበለጥን ስላልፈለገ ነው፡፡በፍቅር ላለመበላለጥ መሽቀዳደም ደግሞ የመልካም ልቦና ዝንባሌ ነው፡፡ይህ ብው በሚያደርግ ንዴት ውስጥ የሚከተው ደግሞ ራሱን መመርመር ግድ ይለዋል!

ጎንደር እና አዳማ አፋፍ ላይ ሆነው “ደምህ ደሜ፣አጥንትህ አጥንቴ” ሲባባሉ ሌሎች ከተሞችም ይህን ሲከተሉ የኮምፒውተር “በተን” በነኩ ቁጥር ህዝብን የመሩ የሚመስላቸው የጥላቻ ሰባኪዎች የወንጀለኝነት ስሜት እንደሚሰማቸው ጥርጥር የለኝም፡፡ ወትሮም ገታራነት የማይጫናቸው የኦሮሞ ምሁራን ይህ የህዝብ መተሳሰብ የኖሩበትን የፖለቲካ አቅጣጫ እንዳስቀየራቸው በአንደበታቸው ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ሁሉም የሚሉት ‘ህዝብ መራን፤ህዝብ በለጠን፤ ህዝብ ቀደመን’ ነው ! የትምህርት ደረጃን ቆጥሮ ብዙሃኑን ህዝብ ሳይንቁ፣ እኔ አውቅልሃለሁ ሳይሉ፣ይልቅ መበለጥን  አውቆ አካሄድን ማስተካልም የምሁራኑን ትህትና ያመለክታልና በተለይ የኦሮሞ ምሁራን ለዚህ ትህትናቸው  ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ያመኑት ፈረስ …..

ከህወሃት የወቅቱ ዘዋሪዎች አንዱ አይተ ኣባይ ፀሃይየ የፓርቲያቸውን አርባኛ አመት ድል ባለ ድግስ ሲያከብሩ ‘እነ ኢህአፓ ሲንኮታኮቱ እኛ ድል የተቀዳጀነው ህዝብን ለማታገል ቀለል ያለውን የጎሳ ፖለቲካ የሙጥኝ ስላልን ነው’ አይነት ንግግር ሲናገሩ ተገርሜ ነበር ያዳመጥኳቸው፡፡ህዝብን የማታገያ ዘይቤ የሚመረጠው ስለቀለለ ነው ወይስ የህዝብ እውነተኛ ጥያቄ ስለሆነ? ቀላል የተባለው የጎሳ ፖለቲካ ከምክንያት ይልቅ ስሜትን ስለሚፈልግ ብልጣብልጦቹ የህወሃት መኳንንት በጎሳህ ምክንያት የፈረደበት አማራ ቆረጠህ ፈለጠህ እያሉ  የብረት ተሸካሚ፣ ወላፈን እሳት ላይ ተማጋጅ ነፍስ ለማግኘት  ስለማያስቸግር ነው፡፡ስልጣን ላይ ከተሳፈረ በኋላም ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ ከላይ ለመጥቀስ በተሞከረው መልክ በሃገሪቱ የሚገኙ ወንድማማች ህዝቦችን  ከአንድነታቸው  ይልቅ ልነት ላይ እንዲያተኩሩ ማድረጉን በቀላሉ ስልጣን ላይ ተወዝቶ የመኖሪያ ሁነኛ ዘዴ አድርጎት እንደነበር ነገራ ነገሩ ያስታውቃል፡፡ በዚሁ በጎሳ እና በጥላቻ ፖለቲካ ተፀንሶ፣አድጎ ዙፋን ላይ የተሰየመው ህወሃት/ኢህአዴግ የሚወደውን ዙፋኑን እየነቀነቀው ያለው ከጎሳ ፖለቲካ ጋር በተዛመደ የመረረ ጥያቄ መሆኑ ትልቅ የፖለቲካ አያዎ ነው!

በወልቃይት ዐማሮች ላይ በአዲስ ዓመት ምሽት ተኩስ ሲዘንብባቸው አምሽቷል

0
0

ከሙሉቀን ተስፋው

ትናንት መስከረም 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት በወልቃይት አዲ ረመጥ ከተማ አዲስ ዓመቱን የተወሰዉ ወገኖቻቸውን በማሰብ በቤታቸው ሲያከብሩ ውለዋል፡፡ ምሽት 3፡00 ሲሆን የትግራይ ልዩ ኃይል ፖሊስ የዐማራ ተወላጅ በሆኑ ቤተሰቦች ቤት ላይ ጥይት መተኮስ ጀመረ፡፡ የወልቃይት ወጣቶች ምንድን ነው በማለት ከቤታቸው ወጡ፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት እኩለ ሌሊት ድረስ በዐማሮች ላይ ተኩስ የተከፈተ ሲሆን ወጣቶች የአጸፋ መልስ አልሰጡም፡፡
Wolqite News
ከአዲ ረመጥ ከተማ እኩለ ሌሊት ላይ መረጃውን የሰጡን ሰዎች በምን ምክንያት ይህ ተኩስ ሊፈጠር እንደቻለ ላነሳንላቸው ጥያቄ ‹‹ዛሬ የአዲስ ዓመት በመሆኑ ብዙ የወልቃይት ልጆች ይመጣሉ በሚል አስቀድሞ ዝግጅት ነበር፤ ወደ ምሽት አካባቢ መረጃው ደርሶናል፡፡ ምንም ዝግጅት ባላደረግንበት ወጣቶች የአጸፋ መልስ ሰጥተው ቢሆን ኖሮ በመከላከያ ሰራዊትና በፖሊስ በተቀነባበረ ኦፕሬሽን ዐማሮችን በጅምላ ለመጨረስ የታቀደ ነው፡፡ ሆኖም አላስፈላጊ መስእዋትነት ላለመክፈል ወጣቶቻችን እንዲሸሹ አድርገናል፡፡ አሁን የሞተ ሰው ስለመኖር አለመኖሩ የምነግርህ ነገር የለም›› ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አቶ ዘነበ ፋንታና አቶ ተስፋየ የተባሉ ዐማሮች እከለ ሌሊት ታፍነው ተወስደዋል፡፡

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ‹‹አዲስ ዓመት በሰላም የሚያከብረው ትግሬ ብቻ ሆኖ እስከመቼ እንደሚቀጥል የምናየው ይሆናል›› ሲሉ ቁጭታቸውን ገልጸዋል፡፡


የሽግግር መንግስት እና የእርቅ ኮምሽን ጉዳዮች! –ግርማ ሞገስ

0
0

ክፍል አንድ/ ከሶስት

መስከረም 01/2009 ዓ.ም.

ግርማ ሞገስ

 

Girma-Moges.jpg

ግርማ ሞገስ

የህውሃትን ወንድም ከወንድም የማጋደል ዘመን ማሳጠር ይቻላል። ህውሃት ያሉት ጭንቅላቶች ከአንድ ሚሊዮን አይበልጡም። የቀረነው ግን ከሰማኒያ ሚሊዮን በላይ ጭንቅላቶች፣ አይኖች፣ እግሮች፣ እጆች አሉን። ትብብራችንን ከነፈግናቸው የህውሃት መሪዎችን በዚህ አመት በቅርቡ የኛን አይነት ሌሎች ተራ ዜጎች ማድረግ እንችላለን። ሁሉን-አቀፍ የሽግግር መንግስት እና የእርቅ ኮምሽን በቅርብ እውን ማድረግ እንችላለን! አፋችንን እና እግራችንን አንድ ካደረግን ይቻላል! በዚህ በክፍል አንድ “ዛሬ ትግላችን ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ” በአጭር ብንቃኝም የሚያመለክተውም የፈለግነውን ማድረግ እንደምንችል ነው።

 

አፋችንን እና እግራችንን አንድ ካደረግን በአረመኔነቱ እና በድርቅና ፖለቲካው በታሪካችን ተወዳዳሪ በማይገኝለት የአምባገነኑ ህውሃት/ኢህአዴግ ዘመነ-መንግስት ስር ሳይቀር ሰላማዊ ትግላች ማደግ እንደሚችል አይተናል። ድምጽ የማስከበር አቅም መገንባት ቢሳናቸውም ሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ እንዲታወቅ በማድረግ “የመንግስት ስልጣን ከጠብ መንጃ አፈሙዝ ሳይሆን ከምርጫ ሳጥን መገኘት አለበት በሚል በየምርጫው ወቅት አባሎቻቸው ሲዋከቡባቸው፣ ሲታሰሩባቸው፣ እና ሲገደሉባቸው ተሰፋ ሳይቆርጡ እና ለግል ህይወታቸው ሳይፈሩ ከትግላቸው ፎቀቅ ያላሉትን” ሃቀኛ የምርጫ ፓርቲዎች አንረሳም። ለጥቆ “ድምጻችን ይሰማ” በሚል መታገያ መርህ የኢትዮጵያ ሙስሊም እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን የተጠየቁትን መስዋዕት በመክፈል ያደረጉት እንከን የለሽ ሰላማዊ ትግልም ለትግላችን  እድገት አስተዋጽኦ ማድረጉን አንዘነጋም።

 

በ2007 ዓ.ም. ምርጫ ግን በአይና አውጣ አሰልቺ ፖለቲካው አቻ የሌለው ህውሃት/ኢህአዴግ የኢትዮጵያ የገዢነት ህጋዊነቱን በ100% ማሸነፉን አሳወቀን። አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ አወጣ እንደሚባለው ሁሉ ከዚያ ወዲህ ግን ለህውሃት/ኢህአዴግ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስልጣን ትግል ሁኔታ እንደቀድሞው ሊቀጥል አልቻለም። በተለይ የኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ወጣቶች የርህራሄ-አልባዎቹን የህውሃት ቅጥረኞች ጥይት በግንባራቸው፣ በደረታቸው አና በቀረ አካላቸው እየተቀበሉ ደማቸውን በመርጨት ሰላማዊ ትግሉን ወደ ሰላማዊ ህዝባዊ እምቢተኛነት ደረጃ ከፍ በማድረግ ለሰላማዊ ትግሉ ቀጣይነት ዋስትና ሰጡት። ህዝባቸው ለሞታቸው አዘነ። ለጀግንነታቸው ግን  ክብሩን ለገሰ። የተፈጸመው አስከፊ ግድያ በተቀረው ክልል የሚገኘውን ወጣት አእምሮ እና ልቦና ቀሰቀሰ። በዲፕሎማሲውም መስክ የውጭውን አለም አይንና ህሊና በአጭር ጊዜ ውስጥ ማረከ።

 

በተለይ በተሰናባቹ 2008 ዓ.ም. የወጣቱ ህዝባዊ እንቢተኛነ ትግል ስብዕና የሌለውን  ህውሃት/ኢህአዴግ በብዙ ፖለቲካዊ፣ ህጋዊ እና ማህበራዊ ግንባሮች ድል ነሳው። በሌላ ወገን ደግሞ የትግል ግንባሮቹን ቁጥር ጨመረ። የኦሮሞ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ደም መፍሰስ የኛም ደም መፍሰስ ነው በሚል ህውሃት የጀመረውን ግድያ እንዲያቆም በሰላማዊ ሰልፎች አደባባይ ተቃወመ የክልለ-አማራ ወጣት። ይህን አዲስ መነሳሳት በክልለ-አማራ የሚገኙ የክርስትና እና የሙስሊም እምነት መሪዎች በጎንደር አደባባይ በይፋ ባረኩት።  የክልለ-አማራ ወጣት ህዝባዊ እምቢተኛነቱን ተቀላቀለ። ደሙን ከወንድሞቹ እና ከእህቶቹ ክልለ-ኦሮሞ ወጣቶች ጎን በመርጨት ሰላማዊ ትግሉ ከፍተኛ ደረጃ አደረሱት። በአሁኑ ሰዓት በሁለቱ ክልሎች የሚካሄዱት ህዝባዊ እምቢተኛነት ትግሎች እርስ በእርስቻው በመመጋገብ እና እርስ በእርሳቸው በመጠነካከር በታሪካችን አይተን በማናውቀው ደረጃ ብልጣ ብልጡን የህውሃት/ኢህአዴግ አምባገነን መንግስት በብድር ሰዓቶች እንዲኖር አስገድደውታል። የሁለቱ ክልሎች ትግሎች በአለም አቀፍ ከሚኖሩት ዘመዶቻቸው ከሚያገኙት የትግል እገዛ ጋር ተዳምረው የህውሃት/ኢህአዴግ አረመኔ አምባገነን መንግስት ቀብሩን ከቅርበት እንዲያስተውል አድርገውታል።

 

የህዝባዊ እምቢተኛነቱ ሰላማዊ ትግል ካስገኛቸው ድሎች ውስጥ የሚከቱልትን መጥቀስ ይቻላል።

(1) ትግላችን ዛሬ ህውሃት/ኢህአዴግን ነባር ትረካዎቹን ካስጨረሰበት እና አዲስ የፖለቲካ ትረካ መፍጠር ካልቻለበት ደረጃ አድርሶታል። ህገ-መንግስት አክባሪነት፣ የብሔር ብሄሮች እኩልነት፣ የልማት መንግስት፣ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ አውራ ፓርቲ፣ የሚሉትን የትናንት የጠዋት ማታ ማጭበርበሪያ ትረካዎቹን የዛሬው ህውሃት መልሶ መተረክ ከሚያፍርበት ደረጃ አድርሶታል ትግላችን። መንግስትን ከሌባ ሙስኞች ማጽዳት የሚል አዲስ ትረካ ቢጀምርም እሱም አልሰራ ሲለው ጥሎታል። በቅርቡ ደግሞ  እንዴት የአማራ ትምክህተኞች እና ኦሮሞ ጠባቦች ተባበሩ በማለት ማላዘን ጀምሮ እሱንም ትቶ ዛሬ ስለ ሩዋንዳ በማንሳት ወደቀድሞው የመከፋፈል እና የማስፈራራት የተንኮል ፖለቲካ ትውስታው የተመለሰ ቢመስልም ሃቁ ግን ዛሬ ህውሃት የምድርም ሆነ የሰማይ ኮምፓሱ ጠፍቶበት ቦዞበት ሲባዝን እያስተዋልን ነው። የህገ መንግስቱ ጠበቃ እና ጠባቂ ህውሃት/ኢህአዴግ መሆኑ ቀርቶ OromoProtest (#ኦሮሞተቃውሞ)  እና #AmharaResistance (#አማራእምቢተኛነት) ከሆኑ ውለን አድረናል። ህውሃት/ኢህአዴግ ከዚህ በኋላ በውጭም ሆነ በአገር በውስጥ ሰሚ የለውም።

(2) በክልለ-ኦሮሚያ እና በክልለ- አማራ ህዝቡ ለህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት የገዢነት መብቱን በመግፈፍ በየቦታው የራሱን አስተዳደር መስርቶ እራሱን በራሱ ማስተዳደር ከጀመረ ውሎ አድሯል። በዚህም የህውሃትን/ኢህአዴግ መንግስት 100% ምርጫ አሸናፊነት ለአገር ውስጥ እና ለዓለም ህዝብ መሳቂያ እና መሳለቂያ አደረገ ህዝቡ። ይህን በመከተል በውጭ የሚገኙ ወጣቶችም በእየእምባሲው እየገቡ የህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት የተከለውን የህልውናው መግለጫ ባንዲራ አወረዱ። ይህ ለህውሃት መንግስት ህጋዊነት የመንፈጊያ መግለጫ እርምጃ የሽግግር መንግስት ጉብኤ እስኪጠራ ድረስ በሰፊው ይቀጥላል፡፡

(3) በአገር ቤት የመለስ ዜናዊን ፎቶዎች የተሸከሙ ቢል ቦርዶች በእሳት ጋዩ። የመታሰቢያ ፓርኮች ወደሙ። “ከኢህአዴግ ጋር መጨው ዘመን ብሩህ ነው” የሚሉት የህውሃት ፌዞችን የተሸከሙ ቢል ቦርዶችም በሁለቱ ክልሎች ተቃጠሉ። ይህን የህዝባዊ እምቢተኛነት እርምጃ በመደገፍ በውጭ የሚገኘው ወጣት ደግሞ በየኢምባሲው ቢሮ የተሰቀሉትን የመለስ ዜናዊ ፎቶዎች ማውረድ እና መቅደድ ጀመረ። ቆሻሻ ጨመራቸው። ይህ ለህውሃት መንግስት ህጋዊነት የመንፈጊያ መግለጫ እርምጃ የሽግግር መንግስት ጉብኤ እስኪጠራ ድረስ በሰፊው ይቀጥላል፡፡

(4) ህዝቡ ከህውሃት/ኢህአዴግ ባንኮች ገንዘቡን በማውጣት፣ ግብር ባለመክፈል፣ ስራ ያለመግባት አድማዎች በመፈጸም፣ የህውሃትን የኢኮኖሚ እና የፖለኪ ኃይል አቅም ምንጮች ከምንጫቸው የማድረቅ ዘመቻ ጀመረ።

(5) በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ አርቲስቶቻችም የአዲሱን አመት ዋዜማ የሃዘን ቀን በማድረግ ከህዝባቸው ጎን መቆማቸውን ገለጹ።

(6) በአገር ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኘው ሰላማዊ ህዝባዊው አመጽ በኢትዮጵያ አማራጭ የፖለቲካ ኃይል እየሆነ መምጣቱን ምዕራቡ ማስተዋልም ማመንም የጀመረ ይመስላል።  አሚሪካ፣ እንግሊዝ፣ አውሮፓ ህብረት እና የመሳሰሉት አድርባዮቹ ምዕራባውያን መንግስቶች ላለፉት 25 አመቶች በህዝቡ ላይ ሲፈጽም የነበረውን መብት ረገጣ እያዩ እንዳላዩ ሆነው ለብልጣ ብልጥ ፖለቲካው አወቀው በመታለል በቀይ ባህር አካባቢ እና በጸረ-ሽብር ጉዳይ የሚሰጣቸውን ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ጥቅም በማስቀደማቸው ሲተባበሩት መክረማቸውን እናውቃለን። ዛሬ ግን የምዕራብ አለም በይፋም በስውርም ከህውሃት እየራቁ እና በምትኩ ወደ ህዝብ መቅረብ መጀመራቸውን የሚያመላክቱ አንዳንድ ምልክቶች መታየት ጀምረዋል።

 

ስለዚህ በአገር ውስጥ በክልለ-ኦሮሚያ እና በክልለ-አማራ ወጣቱ ደሙን በጀግንነት እየዘራ በሚያካሂደው ሰላማዊ ህዝባዊ እምቢተኛነት የነጻነት ትግል ላይ በውጭ የሚገኙት ዘመዶቹ በሚለጉስት የትግል ትብብር ታግዞ የአረመኔውን ህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት የህጋዊነት፣ የገዥነት መብት፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አስተዳዳሪነት ስልጣን፣ የንግድ ተቆጣጣሪነት፣ ከግብር ሰብሳቢነት የሚያፈሱለት የፖለቲካ አቅም ምንጮች መድረቅ ጀምረዋል። በእነዚህ ምንጮች ላይ የበቀሉት የህውሃት/ ኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካ ድጋፍ ምሶሶዎችም መናድ ጀምሯል።

 

እነዚህ ድሎች በሙሉ መባከን የለባቸውም። የተገኙ ድሎች ሳይባክኑ የወደፊቱንም ድል አድራጊነት ፍሬ ለቃሚ ህዝቡ መሆን ይችል ዘንድ ብቸኛው ዋስትናችን ትግሉ የባለህበት እርገጥ ባህሪ እንዳይጠናወት ማድረግ ነው። ትግሉ የቀጣይነት እና የእድገት ባህሪ ካጣ አምባገነኖች የማንሰራራት እድል ሊያገኙ ይችላሉ። የህውሃት/ኢህአዴግ አምባገነን መንግስት የመንሰራራት እድል እንዳያገኝ ለማድረግ መፍትሄው ትግላችንን ወደሚቀጥለው ደረጃ ከፍ ማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ የሽግግር መንግስት እና የእርቅ ኮሚሽን እውን መሆን ከመቻላቸው በፊት እስከዚህ ድረስ በሚያስገርም ብልህነት፣ ጽናት፣ ብስለት  ትግሉን መርተው እዚህ ደረጃ ያደረሱት #OromoProtest (#ኦሮሞተቃውሞ)  እና #AmharaResistance (#አማራእምቢተኛነት) በሚል መጠሪያ የሚታወቁት ወጣቶች አንድ ቀላል የማስተባበር ተጨማሪ ስራ በመስራት ትግሉን ማጠናከር ያለባቸው ይመስለኛል። እሱም በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚካሄደውን ባለ ብዙ መስከ ትግል በሁሉም መስክ ባይሆንም በተወሰኑ መስኮች ማስተሳሰር እና ማስተዳደር ይኖርባቸዋል። ይኽን ጉዳይ እንደተለመደው በፌስቡኮቻቸው ሊያከናውኑት ይችላሉ። በውጭ ያሉት የ#OromoProtest (#ኦሮሞተቃውሞ) እና #AmharaResistance ወጣት መሪዎች የጎንዮሽ ውይይት ማድረግ ካስፈለጋቸውም የሎጂስትኩ ጉዳይ ለእነሱ መተው የግድ ነው። የኛ ሚና ማገዝ እንጂ ማዘዝ መሆን የለበትም። ለትግሉ ደህንነትም ይጠቅማል። ማድረግም ይቻላል።

 

ባጭሩ ይህን ከፍተኛ የትግል ደረጃ ተፈጻሚ ለማድረግ እስከዚህ ድረስ ትግሉን በዋንኛነት በመምራት ላይ የሚገኙት የ#OromoProtest (#ኦሮሞተቃውሞ) እና የ#AmharaResistance ወጣቶች ጣልቃ-ገብ ድርጅት (ጣልቃ-ገብ ድርጅት/Parallel Organization) ያስፈልጋቸዋል። የዚህ ጣልቃ-ገብ ድርጅት ዋንኛ ግብ ኢትዮጵያን በማስተዳደር ስም የህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት በአለም አቀፍ እና በአገር ውስጥ መስኮች እንደቀድሞው በነጻ የሚጋልበው ሜዳ እንዳይኖረው ጣልቃ መግባት እና ጨርቁን ጥሎ እስኪሄድ መከራ ማሳየት ይሆናል።

 

የጣልቃ-ገብ ድረጅት የማስተባበር እና የማስተዳደር ተግባሮች ከፍ ብለው ከ(1) እስከ (6) በተዘረዘሩት እምቢተኛነት ተግባረት ላይ የሚከተሉትን ዘጠኝ ተግባሮች ሊያካትት ይቻላል፥

(1) በአሁኑ ጊዜ በአገር ውስጥ ከ80% በላይ የሚገመተው የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፉን እና ታማኝነቱን የሚለግሰው ለህውሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ሳይሆን ለ#OromoProtest (#ኦሮሞተቃውሞ)፣ ለ#AmharaResistance (#አማራእምቢተኛነት) እና ለሌሎች ተቃዋሚዎች በመሆኑ የገዢነት መብቱን እና ህጋዊነቱን ማጣቱን የምዕራቡ አለም መንግስታት እንዲያውቁ እና በተግባርም እንዲያዩ ለማድረግ በጽናት እና በብልሃት መስራት።

(2) ከ80% በላይ የሆነው ህዝብ የህውሃት/ኢህአዴግን የገዢነት ህጋዊነት መብት በመንፈጉ በውጭ ጉዳይ ሚ/ር አድሃኖም የሚመሩት ኢምባሲዎች ትብብራቸውን ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ወደ ህዝባቸው እንዲያሸጋገሩ ማበረታት።

(3) ከ80% በላይ የሆነው ህዝብ የህውሃት/ኢህአዴግን የገዢነት ህጋዊነት መብት በመንፈጉ በተባበሩት መንግስታት ውስጥ የአድሃኖም ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ የመወከል ህጋዊነት እንደሌለው በቀረው አለም ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ።

(4) ከ80% በላይ የሆነው ህዝብ የህውሃት/ኢህአዴግን የገዢነት ህጋዊነት መብት በመንፈጉ የውጭ ጉዳይ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም ከውጭ ገንዘብ እና መሳሪያ ማሰባሰብ እንዳይችል ጣልቃ መግባት።

(5) ከ80% በላይ የሆነው ህዝብ የህውሃት/ኢህአዴግን የገዢነት ህጋዊነት መብት በመንፈጉ በአገር ውስጥ ግብር የማሰባሰብ ህጋዊነት እንደሌለው ለህዝብ ማስገንዘብ እና ህዝብ ለመንግስት ግብር እንዳይከፍል በህዝብ እና በመንግስት መካከል ጣልቃ መግባት።

(6) ህዝቡ የጀመረውን ከህውሃት ባንኮች ገንዘቡን እንዲያወጣ እና በመረጣቸው ባንኮች እንዲያስገባ ማድረጉን እንዲቀጥል ማበረታታት።

(7) የህውሃትን የሃሰት ገንዘብ መቀፍቀፍ እና በገበያ ውስጥ የማሰራጨት ተግባር የመከታተል እና የማጋለጥ ስራዎች ማከናወን።

(8) መንገዶችን በመዝጋት ከድንበር የባህር በሮች ነዳጅ ወደኢትዮጵያ የሚገባባቸውን መንገዶች ለይቶ በማወቅ ህውሃት እንደልብ ነዳጅ እንዳይገባለት ማድረግ። በአገር ውስጥም መንገዶችን የመዝጋትን ዘመቻ ከፍተኛ ደረጃ በማድረስ የህውሃት ገዳዮች (አጋዚ ጦር) እንደልብ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ማድረግ።

(9) በዚህ ረገድ ተጨማሪ አስፈላጊ ስራዎች በማጥናት እና በመተለም (በመቀየስ) በህውሃት/ኢህአዴግ እለት ከለት ተግባር ውስጥ ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያን በፈለገው መጠን በነፃ ማስተዳደር አዳጋች እንዲሆንበት እና ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ። ከዚህ በኋላ ስልጣን ላይ መቀጠል ለህውሃት መሪዎች ከመከራ ውጭ ምንም የሚያስገኝላቸው ጥቅም እንደሌለው በአይናቸው እንዲያዩ እና እንዲያምን ማድረግ፡፡ ለዘብ ያሉት ጥለው እንዲሄዱ ማበረታታት።

 

ልብ በሉ። በኢትዮጵያ እና በውጭው አለም ከሰማኒያ ሚሊዮን በላይ ጭንቅላቶች፣ አይኖች፣ እግሮች፣ እጆች፣ ያሉት ህውሃት ሳይሆን እኛ በመሆናችን ከፍ ብለው የተዘረዘሩትን ቀርቶ ከዚያ ይበልጥ የጣልቃ መግባት ትግባሮች መጸም እንችላለን። አፍና እግራችንን አንድ ካደረግን ይቻላል።

 

ለኢትዮጵያ መለዮ ለባሽ ደግሞ “ሰከን በል” የሚለውን የይሁኔ በላይ መልዕት እና ሌሎች ተመሳሳይ ትምህርት አዘል ምክሮች በማዘጋጀትም ጭምር ማሰራጨት። ወታደሩን ሰላማዊ እንዲሆን በማስተማር ለመግራት መሞከር ጠቃሚ ነው። ሁሉም ሳይሆን ብዙው መለዮ ለባሽ ሌላ ስራ ማግኘት ቢችል ኖሮ ግድያን እንደ መደበኛ ስራው አድርጎ እንደማይመርጥ ግልጽ ነው። አብዛኛው ወጣት ይህን ስራ የሚመርጠው በኢትዮጵያ አይነት ኢኮኖሚ ትልቁ ስራ ቀጣሪ የህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት በመሆኑ ነው። አማራጭ በማጣቱ እራሱን እና ልጆቹን ለማስተማር ወይንም ወላጆቹን ለመርዳት ሲል ነው። ኢትዮጵያም ብትሆን አሁን መለዮ ለባሹ ያለውን ሙያ እና ስልጠናም ለወደፊት ትሸዋለች። ወደፊት የዴሞክራሲ ስልጠና ይሰጠዋል። ከወዲሁ ሰላማዊ ለማድረግ መሞከር ብልህ እርምጃ ነው፡፡ የይሁኔ በላይ አገር ወዳድ ሰላማዊ እንጉርጉሮ ግጥም ውስጥ በተለይ ለወታደሩ የሚሰጠውን ምክር በጥቂቱ ላካፍላችሁ፥

……. ሰከን ማለት ፣ ነው ጨዋነት፣

ሰከን ማለት ፣ ነው ጀግንነት፣

ወታደሩ ሰከን በል፣

አፈ ሙዙህን ሰከን አድርገው፣

ቃታህን እንዳትስበው፣

ባዶ እጁን የሚጮኸው፣ ሰላማዊ ወንድምህ ነው፣

……. እያለ ቁም ነገር የሞላው ወርቅ ምክሩን ለአዲሱ አመት ስጦታ ለግሶናል። በግሌ ይሁኔ በላይን አመሰግናለሁ።  ሙሉውን ለመስማት አድራሻው፡ https://www.youtube.com/watch?v=TE2Zfo51K0c

 

እንግዲህ በዚህ በክፍል አንድ ስለ ጣልቃ-ገብ ድርጅት ምንነት፣ ግብ እና ተግባሮች በአጭሩ ካየን በኋላ የሽግግር መንግስት ምስረታ ጉባኤ እንዴት ይጠራ? ማን ይጥራው? የሽግግር መንግስት መጥራቱን ጉዳይ እንደተለመደው ለአድርባዮቹ እና ዝግመተኞቹ ምዕራቦች ብቻ እንተወው ወይ? የእነሱን በጎ አድራጊነት እስክናገኝ እነሱኑ መቀላወጥ እና ደጃቸውን መጥናት እንቀጥል ወይ? ወይንስ የ#OromoProtest (#ኦሮሞተቃውሞ)፣ #AmharaResistance (#አማራእምቢተኛነት) ቀስ በቀስ ወደፊት ከሌሎች ተቃዋሚዎች ጋር አብሮ በመስራት ይኽን ስራ መስራት የሚችል አዲስ አቅም መፍጠር እንችላለን? በዚህ አይነት የተጠናከረው ጣልቃ-ገብ ድርጅት በምዕራቡ አለም የቀድሞውን የተባበሩት መንግስታት መሪ እንደነ ኮፌ አነን የመሳሰሉትን ታዋቂ ግለሰቦች በማግባባት መወዳጀት እና የጉዳችን አጋሮች ማድረግ እንችላለንን?  ከዚያም ለምዕራቡ ዓለም ህውሃት ሳይሆን አዲሱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይል ህዝባዊ እምቢተኛነቱን የሚያስተዳድረው ወጣት እና የቀረው ተቃዋሚ መሆኑን በተጨባጭ በማሳመን የምዕራቡን መንግስት መሪዎች ወደ ሽግግር መንግስት ጉባኤ ጠሪነት ማነሳሳት (መጫን) እንችላለንን? ከሽግግር መንግስት ጎን የእርቅንስ ኮሚሽን እንዴት መመስረት እና ማንቀሳቀስ ይቻላል ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ መስጠት የዚህ ጽሑፍ ክፍለት ሁለት አና ክፍል ሶስት ግቦች ናቸው። የህግ ተመራማሪው ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ለሰላማዊ ትግል ከሚያደርገው ድንቅ ምሁራዊ አስተዋጽኦ በተጨማሪ እርቅን በሚመለከት  ብዙ ዘመናዊ እውቀትን፣ ምርምርን እና የሌሎች አገሮችን ልምዶች መሰረት ያደረጉ ጠቃሚ ጽሑፎች፣ ጥያቄ እና መልሶች፣ ንግግሮች አድርጓል። በተለይ እነዚህ ሰነዶች በምናውቀው ቋንቋ በመሆናቸው ወደፊት በኢትዮጵያ ለማናልመው እርቅ ለወጣቶቻችን ማሰልጠኛ እና ለአገር ሽማግሌዎቻችንን መዘጋጃ ጠቃሚ ሰነዶች ናቸው። ከወዲሁ ቢሰበሰቡ ጥሩ መሆናቸውን እግረ መንገዴን ለሳስባችሁ እወዳለሁ።

 

መልካም ንባብ።

ከሰላምታ ጋር

ግርማ ሞገስ።

በደም እየተጠመቁ አዲስ ዓመት አይጠባም! –በላይነህ አባተ

0
0

በላይነህ አባተ (abatebeai@yahoo.com)

14316857_1695388227454511_625065289199732991_nበአዲስ ዓመት ልጃገረዶች በአደይ አበባ፣ በጠልስም፣ በመስቀል፣ በድሪ፣ በአንባርና በአልቦ ተውበው አበባየሁ ሆይን ይዘምሩ ነበር፡፡ እነዚህ ልጃገረዶች ዛሬ ክር አስረው፣ ፊታቸውን ልጠውና ራሳቸውን ተላጭተው ለታረዱት ወንድሞቻቸውና አባቶቻቸው ሚሾ ያወርዳሉ፡፡ ጎረምሶች በአዲስ ዓመት ችቧቸውን አብርተው “በቆላ በደጋ ያላችሁ እንዴት ከረማችሁ?” እያሉ ሆያ-ሆየን ይጨፍሩ ነበር፡፡ ዛሬ እነዚህ ጎረምሶች መብት ስለጠየቁና የቅድመ አያቶቻቸውን ሰንደቅ ስለሰቀሉ እንደ በግ ታርደው ያሞራ ሲሳይ ሆነዋል፤ ካሞራ ሲሳይነት የተረፉትም ከርቸሌ ተጠብሰዋል፡፡ እናቶችና አባቶች በጳጉሜ ውኃ ተጠምቀውና ልባሳቸውን አጥበው አዲስ ዓመትን ይቀበሉ ነበር፡፡ የዛሬ እናቶችና አባቶች የታረዱና የተቃጠሉ ልጆቻቸውን በላስቲክ እንደ አዲስ ዓመት ስጦታ ተቀብለዋል፡፡

የታረዱና የተቃጠሉት ልጆቿ ደም ኢትዮጵያን ከፋሽሽት ዘመን የባሰ ጃኖ አልብሷታል፡፡ ከተከዜ እስከ ዓባይ፤ ከዓባይ እስከ አዋሽ፤ ከአዋሽ እስከ ሸበሌ፣ ከሸበሌ እስከ ገናሌ፣ ከገናሌ እስከ ባሮ ያሉ ወንዞቿ ደም ጎርሰዋል፡፡ ከወልቃይት እስከ ጎንደር፤ ከጎንደር እስከ ደብረታቦር፣ ከደብረታቦር እስከ ባህርዳር፣ ከባህርዳር እስከ ደብረ ማርቆስ፤ ከደብረማርቆስ እስከ አምቦ፣ ከአምቦ እስከ ደንቢ ዶሎ፤ ከደንቢ ዶሎ እስከ ወሊሶ፤ ከወሊሶ እስከ ቂሊንጦ፤ ከቂሊንጦ እስከ ዶዶላ፣ ከዶዶላ እስከ ያቤሎ ያሉ ኩሬዎች ደም ቋጥረዋል፡፡ ደም ያልነካው ውኃ እንኳን ለመጠመቂያ ለጸበልም ጠፍቷል፡፡ ይህንን ደም የጎረሰ ውኃ የማትያስ ሲኖድ የልማት ውኃ እያለ ወደ ሕዝብ ይረጨዋል፡፡ በኢትዮጵያ እሚወርደው የግፍ ዶፍ በጥፋት ውኃ፣ በሰዶምና ገሞራ ከጎረፈው የግፍ ዶፍም ከፍቷል፡፡

ከጥፋት ውኃንና ከሰዶም ገሞራ በኋላ ክርስቶስ ለፍትህ በመስቀል ተሰቅሏል፡፡ ክርስቶስ ለፍትህ የተሰቀለበትን መስቀል “አባ” ማትያስና ጳጳጳሳቱ ሳህን ሰርተው ፍትፍት ይዝቁበታል፤ ቪላ ገንብተው ይዘንጡበታል፤ ሉመዚን ቀጥቅጠው ይንፈላሰሱበታል፡፡ ፍትፍት ዘክዛኪውና በሉመዚን ተንፈላሳሹ አባ ማትያስና ተቋዳሽ ጳጳሳቱ “እስተንፋስ ያለው ሁሉ ይተንፍስና አትግደል” የሚሉትን ቃላት ሽረው “አትተንፍስ፤ አለዚያ ትሞታለህ” እያሉ ሟቹን ሲያስጠነቅቁ ይታያል፡፡ እነዚህ ፍትፍት ዘክዛኪዎች በሐዘን የተጎዳውን ሲያጽናኑና የታሰረውን ሲጠይቁ ሳይሆን በነፍሰ-ገዳይ ሰይጣኖች “ለሽምግልና” ታዝዘው ከነካባቸው ሲግበሰበሱ ይታያል፡፡ በሰማእታት አስከሬን ከበሮ እየመቱ እሚጨፍሩትን ሲያሳልሙ ይስተዋላል፡፡ አናባቢ ሆይ! ቤተመንግስትን ሰይጣን ቤተክርስትያንን ይሁዳዎች ነጥቀዋታል፡፡ በዚህም ምክንያት የግፉ ዶፍ አላባራ ብሏል፡፡ የማያባራው የግፍ ዶፍም እንኳን ወተትን ውኃ በማስሸፈት ይገኛል፡፡

ወተት ቀርቶ ውኃ በሚሸፍትበት ወቅት “እንኳን አደረሰህ” የሚባልለት አዲስ ዓመት አይኖርም፡፡ የገዳይ ደጋፊዎች በሲዳሞና በወለጋ ወርቅ ተሽቆጥቁጠው ከበሯቸውን እየወቀሩና እየዘለሉ በሰማእታት አስከሬን ስለጨፈሩ ሰዶምና ገሞራ እንጅ አዲስ ዓመት መጣ አይባልም፡፡ እነ ተከዜ፣ እነ አንገርብ፣ እነ ዓባይ፣ እነ ጨሞጋ፣ እነ አዋሽ፣ እነ ደዴሳ፣ እነ ባሮና ገናሌ ደማቸው ሳይጠራ አዲስ ዓመት አይነጋም፡፡ እነ ራስ ዳሽን፣ እነ ቋራ፣ እነ በላያ፣ እነ አመዳሚት፣ እነ ዝቋላ፣ እነ ጭላሎ የጎረምሶችን ሆያ-ሆየና የልጃገርዶችን አበባየ-ሆይ ሳያስተጋቡ አዲስ ዓመት አይጠባም፡፡ የሊማሊሞ ዳገት፣ የጣራ ገዳም ጋራ፣ የጮጨ ግርግዳ፣ የየረር ተራራ፣ የዓባይ በረሃ፣ የዋልድባ ገዳም፣ የዘጌ አድባራት፤ የሰብስቤ ዋሻ፣ የጋንቤላ ጫካ የሰማእታትን ጩኸት እያስተጋቡ አዲስ ዓመት አይከበርም፡፡ የማእከላዊ፣ የቃሊቲ፣ የቂሊንጦ፣ የዝዋይ፣ የሰንዳፋ፣ የብርሸለቆ፣ የአንገርብና የአሶሳ እስር ቤቶች የጦቢያን ልጆች ስቃይና ጣረ ሞት እየተመለከቱ አዲስ ዓመት አይከበርም፡፡

የዲያብሎስ ብሮድካሽን ኮርፖሬሽን(EBC=DBC) የሰማእታት ዓይን ሳይፈርስ አስረሽ ምቺው ስለጨፈረ አዲስ ዓመት ገብቷል አይባልም፡፡ “አባ” ማትያስ የምድርን ችሎት አምልጦ ከእግዜር ችሎት እንደቀረበው ወንድሙ “አባ” ገብረመድህን የደም ውኃን የልማት ጸበል እያለ ስለረጨ አዲስ ዓመት ተከበረ አይባልም፡፡ የለም! የለም! አዲስ ዓመት የለም፡፡ በፍልሰታና በጳጉሜ በደም እየተጠመቁ አዲስ ዓመት አይጠባም፡፡

 

መስከረም አንድ ሁለት ሺ ዘጠኝ ዓ.ም.

 

 

“ደስታ ነገ ጠዋት አሸብርቆ ይመጣል!”፡ ለ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት መልዕክቴ

0
0

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

ያለ መራራ ትግል ምንም ዓይነት ዕድገት ሊኖር አ ይችልም!

እ.ኤ.አ መስከረም 11/2016 የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት የ2009 ዓ.ም የመጀመሪያ ዕለት ነው (እንደ ኢትዮጵያውያን ዘመን አቆጣጠር መስከረም 1 ቀን)፡፡

“2009 መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልዎ“ የሚሉትን ቃላት መናገር ለእኔ በጣም የሚያም እና የሚቆጠቁጥ ነገር ነው፡፡

ወገኖቻችን በየቦታው በገዛ ሀገራቸው መብታቸው ተገፍፎ እንደ ፋሲካ ዶሮ እየታረዱ እና በየእስር ቤቶች እንደ ደመራ በእሳት እንዲቃጠሉ የሚደረጉበት አስከፊ ሁኔታ ላይ ያለንበት ጊዜ ስለሆነ እንደዚህ ያሉትን ቃላት ደፍረን እንዴት “መልካም አዲስ ዓመት” ልንል ይቻለናል?!

no-struggle-5-628x417
ወገኖቻችን እንደዚህ ባለ አስከፊ ሁኔታ በጅምላ እያለቁ ባለበት ሁኔታ ከኢትዮጵያውያን ባህል እና ልማድ ባፈነገጠ መልኩ በተጠሩባቸው መድረኮች ሁሉ በመገኘት መልካም አዲስ ዓመት በማለት ሲዘፍኑ የነበሩ አርቲስት ተብዬ አዝማሪዎች ዘፋኝ የዘፈነ ሳይሆን አለሌ አህያ እንዳክላላ ያህል ነው የምንቆጥራቸው፡፡

እናት በልጇ ሬሳ ላይ እንድትቀመጥ የምትገደድበት ድርጊት እየተፈጸመ ባለባት ሀገር ውስጥ ምን ዓይነት ደስታ ሆኖ ነው አዲስ ዓመት እያሉ በማለዘን ላይ የሚገኙት?! አሳፋሪ እና የወረደ ነገር ነው፡፡ ባለቁት ሰማዕታት ነብሶች ለህሊና መንበር ለፍርድ ይቀርባሉ፡፡

የተጠናቀቀው እና አሮጌው የ2008 የበጀት ዓመት የኢትዮጵያን ሕዝብ እጅግ ያሳዘነ እና ማቅ ያለበሰ አስከፊ ዓመት ነበር፡፡

የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ከሩብ ክፍለ ዘመን በፊት ስልጣንን በሕዝብ ድምጽ ሳይሆን በጠብመንጃ ኃይል ከተቆጣጠረበት እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ በዜጎች ላይ ሲፈጽመው የቆየውን የሞት እልቂት አባዜ እ.ኢ.አ በ2008 ዓ.ም የበለጠ መጠኑን እና ስፋቱን አጠናክሮ ቀጥሎበት ይገኛል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች (ሂራዎ) የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እ.ኤ.አ ሰኔ 2016 እንዲህ የሚል ዘገባ ይፋ አድርጓል፣ “በኢትዮጵያ የደህንነት ኃይሎች እ.ኤ.አ ከህዳር 2015 ጀምሮ በሀገሪቱ ትልቅ በሆነው በኦሮሚያ ክልል በአብዛኛው በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በመግለጽ ላይ በነበሩት ዜጎች ላይ ከመጠን ያለፈ ኃይል መጠቀምን እና ጥልቅ ጥላቻን አሳይተዋል“ ብሏል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች (ሂራዎ) ዘገባ ከሆነ የዘ-ህወሀት የደህንነት ኃይሎች፡

“ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ለመግለጽ በተሰባሰቡ ሰዎች ላይ የእሩምታ ተኩስ በመክፈት ዜጎችን ገድለዋል፣ አሰቃይተዋል፣ እንዲሁም በእስር ዘብጥያ እንዲወርዱ አድርገዋል፡፡ ቀደም ሲል በመጀመሪያ የሰላማዊ ተቃውሞውን ያቀጣጠሉት በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በመሆናቸው ምክንያት በርካታዎቹ ከ18 ዓመት እድሜ በታች የሆኑት ልጆች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገዋል ወይም ደግሞ ተገድለዋል፡፡ የደህንነት ኃይሎች የፌዴራል ፖሊሶችን እና ወታደሮችን ጨምሮ በጋራ ከሕግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ሙዚቀኞችን፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን፣ የጤና ባለሙያዎችን እና ሌሎችን እርዳታ የሰጡትን ወይም ደግሞ ለሸሹት ተማሪዎች መጠለያ የሰጡትን ሁሉ በዘፈቀደ በቁጥጥር ስር አውለዋል“ የሚል ዘገባ ነበር ይፋ ያደረገው፡፡

ዘ-ህወሀት እ.ኢ.አ በ2008 ዓ.ም መጠነ ሰፊ የሆነ የሕዝብ እልቂትን በመፈጸሙ ምክንያት ሌላው ቀርቶ የዘ-ህወሀት ቀንደኛ ጠባቂ፣ ዋና የስርዓቱ ተጠቃሚ እና ደጋፊ የሆነው የኦባማ አስተዳደር እንኳ ሳይቀር በተፈጠረው ዘግናኝ እልቂት እና ሕዝባዊ የደስታ እጦት ዴፕሎማሲያዊ በሆነ መልኩ ሳይወድ በግድ እንዲገልጽ ተገዷል፡፡
enba-mert-1-1
በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ አማረጺዎች ላይ እየተወሰደ ባለው ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ በጣም ያሳሰባቸው መሆኑን ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል፡፡

ፓወር ዘ-ህወሀት እየወሰደው ያለው የኃይል እርምጃ እጅግ በጣም አስከፊ ስለሆነ ግልጽ በሆነ መልኩ እና ገለልተኛ በሆነ አካል እንዲመረመር ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፓወር እንዲህ ብለዋል፣ “ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን እንዲገልጽ ለማድረግ መንግስት እንዲፈቅድ ዩናይትድ ስቴትስ ጠይቃለች“፡፡

“ዘ-ህወሀት በሰው ልጆች ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ እልቂት ፈጽሟል፡፡ እነዚህን እልቂት የፈጸሙትን ወንጀለኞች ለፍትህ አካል ማቅረብ እና ተማዕኒነት ያለው ዓለም አቀፍ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው:: ዘ-ህወሀት ሰላማዊ አማጺዎች ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ መፍቀድ አለበት” የሚሉት ሁሉ ለዴፕሎማሲያዊ ፍጆታ ሲባል ብቻ የተደረጉ እንቶ ፈንቶ ንግግሮች ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ ነሀሴ 10/2016 የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጥበቃ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር በርካታ በሆኑ መሳሪያ ባልታጠቁ አማጺዎች ላይ የዘ-ህወሀት ታጣቂ ኃይሎች እልቂት በፈጸሙባቸው አካባቢዎች እና ሕዝቡ መገዳደር ባደረገባቸው ቦታዎች ምርመራ ማድረግ የሚችሉ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንዲገቡ እንዲፈቅድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ዘ-ህወሀት ከዋና ኮሚሽነሩ ለቀረበለት ጥያቄ አልፈቅድም በማለት አፍንጫውን ነፍቶ አኩሩፏል፡፡

እ.ኤ.አ ነሀሴ 21/2016 የዩኤስ አሜሪካ የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብቶች እና የስራ ረዳት ዋና ጸሀፊ እና የኦባማ ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች ዋና መልዕክተኛ የሆኑት ቶም ማሊኖውስኪ የዘ-ህወሀት አገዛዝ “በሀገሪቱ ውስጥ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በአመጹ ዜጎች ላይ የተሰጠው ስልታዊ ምላሽ እራስን በእራስ ድል አድርጎ የማሸነፍ ያህል ነው“ በማለት አውጀዋል፡፡

ይህም ማለት “ዘ-ህወሀት በርካታ ሰላማዊ በሆኑ ዜጎች ላይ እልቂትን በፈጸመ ቁጥር እራሱን ለአስከፊ አደጋ እያጋለጠ እና ዕድሉን እያጨለመ ነው የሚሄደው፡፡ በጎራዴ ላይ ተንጠልጥለው

የሚኖሩ ሁሉ በጎራዴ ይጠፋሉ“ የሚል ዴፕሎማሲያዊ ንግግር ነበር ያደረጉት፡፡

እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን ዘ-ህወሀት መሮጥም ሆነ እራሱን መደበቅ አይችልም፡፡ ዘ-ህወሀት አልቆለታል። የዘህዋሃት ጉዳይ አክትሟል!

እ.ኤ.አ መስከረም 6/2016 የአውሮፓ ህብረት (አህ) ለዘ-ህወሀት የሚሰጠውን የአስቸኳይ ጊዜ የገንዘብ እርዳታ በመቁረጥ እርምጃ ወስዷል፡፡ የአውሮፓ ህብረት እንዲህ የሚል መግለጫ ሰጥቷል፡ “ለአፍሪካ የሚሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ የገንዘብ እርዳታን በሚመለከት በተጠቃሚ ሀገሮች መንግስታት መዋቅሮች አማካይነት ምንም ዓይነት ገንዘብ በማዕከል እንደማይያዝ ወይም ደግሞ እንደማይለቀቅ መታወቅ ያለበት ጠቃሚ ነገር ነው“ ነበር ያለው፡፡ በሌላ አገላለጽ የአውሮፓ ህብረት የዘ-ህወሀትን አውሬዎችን በቀጣይነት ሊመግብ አይችልም፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 11 በአሜሪካ ታሪክ በመጥፎ ትውስታ ስትታወስ ትኖራለች፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 11/2001 የአልቃይዳ አሸባሪ ቡድን በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አራት ዙር ጥቃቶችን በማቀናበር በ3,000 ንጹሀን ዜጎች ላይ እልቂትን የፈጸመ ሲሆን ለመናገር የሚያዳግት በቢሊዮኖች ዶላር ሊቆጠር የሚችል ንብረትን አውድሟል፡፡

አሜሪካውያን እና መላው ዓለም በአልቃይዳ ዕኩይ ድርጊት የተሰማውን ሀዘን እና ድንጋጤ ገልጿል፡፡

ሆኖም ግን ስሙ በዓለም አቀፉ የአሸባሪዎች የመረጃ ቋት ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው አሸባሪው ድርጅት ዘ-ህወሀት በጠራራ ጸሐይ ቀን በቀን መጠነ ሰፊ የሆነ እልቂትን ወንጀሎችን በንጹሀን ዜጎች ላይ እየፈጸመ ባለበት በአሁኑ ወቅት የኦባማ አስተዳደር አላየሁም፣ አልሰማሁም በማለት ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ይገኛል፡፡

ወቼ ጉድ! ይህ ሁኔታ በዓለም አቀፍ አሸባሪዎች ላይ የሚታይ ባለሁለት ምላስ አወናባጅ ፖሊሲ ነው፡፡

የኦባማ አስተዳደር አመለካከት እንዲህ የሚል ሆኖ ይገኛል፣ “ዘ-ህወሀት አሸባሪ ድርጅት ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን እነርሱ የእኛ አሸባሪዎች ስለሆኑ ተዋቸው አትንኳቸው“ ነው እያለ የሚገኘው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ እንደ ፕሬዚዳንት ዲ. ሩዝቤልት አመለካከት ሁሉ የላቲን አሜሪካ አምባገነን የነበረው ሶሞዛ ጋርሻ የታወቀ በጥባጭ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም “ሶሞዛ ጋርሻን ተውት እርሱ የእኛ በጥባጭ ነው” እንዳሉት መሆኑ ነው፡፡

enba-mert-1ኢትዮጵያውያን በመስከረም 2009 ዓ.ም የሚያከብሩት ምንም ዓይነት በዓልየለም፡፡

ለእነርሱ መስከረም እንደ ቶማስ ሁድ “ህዳር” ይቆጠራል፡፡

ምናልባትም ቶማስ ሁድ ይህን ጉድ ቢያይ “ህዳር” በሚል ርዕስ ያዘጋጃቸውን እና እንዲህ የሚሉትን የግጥም ስንኞች “መስከረም 2009 ዓ.ም በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በመቀየር ይሰይማቸው ይሆናል፡

ምንም ጸሐይ የለች እንዲሁም ጨረቃ፣
ተፈርክሳ ይሆን ከመሬት ላይ ወድቃ፣
ወይስ ተሰውራ ዓለማትን ንቃ ከህዋው ርቃ፡፡

ጧት የሚባል የለም እንዲሁም ምሽት፣
የሚያበሳጭ እንጅ የሚያደብን ቆሽት፡፡

ንጋትም ኮብልሏል ጨለማም አክትሟል፣
ሁሉም በየፊናው ካለም ተሰውሯል፣
የሁል ጊዜ ግብሩን ኡደቱን አቁሟል ፡፡

ትክክል ያልሆነ የቀናት ጎደሎ፣

የአምባሳደር ግርማ ብሩ የድብደባ ቪዲዮ ተለቀቀ

0
0

አምባሳደር ግርማ ብሩ ወደ መኖሪያ ቤቱ ከሄዱ ወጣት የኦሮሞ ኢትዮጵያን አክትቭስቶች መካከል አንዱን መደብደቡን መዘገባችን ይታወሳል:: ሁኔታውን የሚያሳይ ቭድዮ የኦሮሚያ ሚዲያኔትወርክ ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድ ለቆታል – ይዘነዋል

በጣሊያን ሮም ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት በአምባገነኑ ስርዓት ለተገደሉ ወገኖች ሻማ በማብራትና በጸሎት አዲሱን ዓመት አከበሩ

0
0

(ዘ-ሐበሻ) አዲሱን ዓመት በሐዘን እንጂ በደስታ አናከብርም ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ሮም ከተማ ተሰባስበው በሃገር ቤት በጨካኙ የሕወሓት አስተዳደር የተገደሉ ወገኖቻቸውን በማሰብ የሻማ ማብራት እና ጸሎት ፕሮግራም ማድረጋቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋብቢ ቭዲዮ አያይዞ በላከው መረጃ ዘገበ::
በሮም እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንድ ላይ ዘር እና ሃይማኖት ሳይገድባቸው በአዲሱ ዓመት ተገናኝተው ወገኖቻቸውን አስበው ውለዋል ያለው የዘጋቢያችን መረጃ; ሁሉም በአንድ ላይ ቁጭታቸውን በመግለጽ ትግሉን ከዳር ለማድረስ የትኛውንም መስዋ ዕትነት እንደሚከፍሉ ቃል ገብተዋል ብሏል::

በጣሊያን ሮም ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት በአምባገነኑ ስርዓት ለተገደሉ ወገኖች ሻማ በማብራትና በጸሎት አዲሱን ዓመት አከበሩ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live