Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ወያኔን በመቃወም ኢትዮጵያውያን  በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ጎዳና ታላቅ  የሰላማዊ ሰልፍ ትእይንት አካሄዱ

$
0
0

germen

ለተጠናከረው  ዘገባ ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

በጀርመኗ  ዋና  ከተማ በርሊን( Germany Berlin) ዛሬ ጳጉሜ 4፣2008ዓም (09 Sep 2016) ኢትዮጵያውያን  ወያኔን  በመቃወም  ታላቅ  ሰልፍ  አድርገዋል።  መላው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  በጨቋኞች  አምባገነንና  ከፋፋዮች መገዛት በቃን  ብሎ አደባባይ  ወጥቶ  ጸረ ወያኔ ትግሉን ለወራት አፋፉሞ  ቀጥሏል። ለተከበረው አርንጓዴ  ቢጫ   ቀይ  ባንዲራም እጅግ ከፍተኛ የሆነ  መስዋትንም  እየከፈለ ይገኛል። የኢትዮጵያ  የቁርጥ ቀን ልጆች በየቦታው እየተገረፉና  እየተደበደቡ በየእስር ቤቱ  ታጉረዋል። ከፊሎቹም  ያለምንም  ርህራሄ በወያኔ ወታደሮች ተገድለዋል።  በሃይለማርያም   የሚመራው  የወያኔ  አምባገነናዊ  መንግስት በንጹሃን የኦሮሞ እና የአማራ  ህዝብ  የፈጸመውን እንዲሁም እየፈጸመ ያለውን አፓርታይዳዊ  ግድያ፣ እስራት፥ድብደባና ጭቆና ለማውገዝና  አለም አቀፉ ማህበረሰብ በወያኔ ላይ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና እንዲያደርግ   በተለያዩ  የጀርመን  ከተሞች  የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያን የተለያዩ  ኢምባሲዎች  እና የመርሃዊ መንግስቱ መቀመጫ  በሆነችው  በበርሊን ጎዳና  ለተቋውሞ ወጥተዋል።  በዚህ  ለአገራችን  ፈታኝ  በሆነባት  ወቅት የወያኔን  አረመነዊያዊ  ተግባራቱን  ለአለም  በተለያዩ  መንገዶች  በመንቀሳቀስ  እያሳወቁ የሚገኙ  በጀርመን  አገር  የሚገኙ ኢትዮጵያውያን  ትላንት ጳጉሜ 3፣2008 ዓም ( 08 Sep 2016)በፍራንክፈርት የሚገኘውን  የኢትዮጵያን ቆንጽላ  ለሰአታት በመቆጣጠር ወያኔ ስልጣኑን  ለሽግግር መንግስት በሰላም  እንዲያስረክብ አለዚያ ግን በሃይልም  ቢሆን ከስልጣኑ  እንደሚወገድ ጀግንነት  በተሞላው  ድርጊት ለአምባሳደሩን  አሳውቀዋል።

በበርሊኑ  የተቋውሞ ሰልፍ  በኢትዮጵያውያ ውስጥ   ወያኔ   እየፈጸመ ያለውን  የመብት ረገጣ እስራት  እንዲሁም  ግድያ  የጀርመን  መንግስት አይቶ  እንዳላየ  ሰምቶ እንዳልሰማ መሆን  እንደሌለበት  እንዲሁም  በየአመቱ  ዳጎስ  ያለ  የገንዘብና  የቁሳቁስ  ጥቅማጥቅም  ክቡር  የሆነውን  የሰውን  ልጅ  ያለርህራሄ  ለሚያጠፋ እንደወያኔ  ላለው  መንግስት  መስጠቱን  እንዲያቆም  ተጠይቋል። የኤርትራን የሶማሌንና  የደቡብ  ሱዳን ስደተኞችን  ወደ  አውሮፓ እንዳይመጡ  በሚል  ሰበብ  የጀርመን  መንግስት ወያኔ  ጡንቻውን  የሚያጎልበትን  በሚሊዮኖች ዮሮ  የሚቆጠር

ገንዘብ  በየአመቱ   ይታወቃል። ሰልፈኞቹ  ዜጎችን  እያሸበር ለሚገድል ለሚያስር ለሚያሰቃይና ለሚያሳድድ  ለወያኔ  አገዛዝ የጀርመን  መንግስት   የሚያደርገውን  ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያጤነው አሊያም  እንዲያቆም  ጠይቀዋል። የጀርመን መንግስት ይህንን  ማድረግ ካልቻለ ወይም ካልፈለገ  እንደ ገዳዩ የወያኔ መንግስት ተጠያዊ ከመሆን  አያመልጥም።

ከጀርመን የውጭ  ጉዳይ ቢሮ  (Auswärtiges Amt) መነሻውን ባደረገው  በዚህ በበርሊኑ  ተቃውሞ  ላይ  ሰልፈኞቹ   በአጋዚ ጦር  ለተገደሉት ንጹሃን  ኢትዮጵያውያን  የተሰማቸውን ሃዘን ጥቁር  በመልበስ  ገልጸዋል። እጃቸውን ወደላይ  በማጠላለፍ  ኢትዮጵያውያን በጎንደር  በባህርዳር በጎጃም በኦሮምያና እንዲሁም  በሌሎች ክፍሎች ውድ  ህይወታቸውን  እየገበሩረለት ለሚገኘው  ትግል  አጋርነታቸውን  አሳይተዋል። ከዚህም  በተጨማሪ በእንግሊዘኛ  በጀርመንኛ በአማርኛ  የወያኔን አረመናዊ  ግድያ ፣ አምባገነናዊነት፣ ጎጠኝነት እንዲሁም  አሸባሪነት በተለያዩ መፈክሮች ለጀርመን ነዋሪዎች፣ ባለስልጣናት እንዲሁም  ታሪካዊዋን  የበርሊንን ከተማ ለማየት ለመጡት ቱሪስቶች ከፍ ባለ ድምጽ ሲያሰሙ  አርፍደዎል። ጀርመን ተወልዳ ያደገች የ17 አመት ኢትዮጵያዊ  ወላጆቹዋን አጅባ በተቋውሞ  ሰልፍ በመገኘት  ከእሱዋ  እድሜ  ያነሱትን ተማሪዎችን እንኩዋን  ያለመራራት በኢትዮጵያ ውስጥ በአልሞ  ተኩዋሽ ጭንቅላታቸውን በጥይት  በመምታት የሚገድለውን የወያኔ ሃርነት ትግራይ  መንግስትን ለመቃወም ከመታደሙዋ  በላይ በተማርችበት አቀላጥፋ  በምትናገረው  በተማረችበት ጀርመንኛ የተቋውሞውን  ሰልፍ  የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሳና ተሸክማ  በመምራት በትንግርት ለሚመለከቱት  የጀርመን ዜጎች ኢትዮጵያውያን ለ25

በሰልፉ  ላይ ሲነሱ ከነበሩት መፈክሮች መካከል የተወሰኑት ዓመታት በወያኔ መንግስት  የደረሰባቸውን  ስቃይ መከራና ግድያ በመፈክርና  በንባብ አስረድታለሽ። ይህች  የ17አመት ታዳጊ  ኢትዮጵያ  የሚያኮራ ታሪክና ጀግና ህዝብ ያላት መሆናን  ድምጿን በተሰጣት ድምጽ ማጉያ  ከፍ  አድርጋ በኩራት በበርሊን  ጎዳናዎች  ተገርመው  ለሚመለከቱት  ጀርመናዊያን እየደገጋገመች ስትናገርና  ሰልፈኞቹም ከሷ በመከተል  በአንድ  ድምጽ ሲያስተጋቡት በርግጥም የወያኔ የ25 ዓመታት የመከፋፈልና  የጎጠኝነት ስትራቴጄው ሞቶ አፈር  እንደላሰ ምስክር ነው። በዚህ አጋጣሚ   የወለዱዋትና ያሳደጓት  አባትና   ይህችን  ኩሩ  አበሻ  ስለሰጡን  ብቻ ባህሏን  ህዝቧን አገሯን እንድትወድ አድርገው  በሰው  አገር ስላሳደጉ መደነቅና መመስገን ይገባቸዋል።

ሰላማዊ  ሰልፉ  በርከት ባለ  የጀርመን የጽጥታ  ሃይል በመታገዝ ውብና  አላማውን  ሙሉ በሙሉ የመታ ሆኖ ተጠናቋል። ነገር ግን ከጥንሰሱ  እስከ  ፍጻሜው  ጉልበታቸውን  ገንዘባቸውንና  ጊዜያቸውን  ሰውተው  ይህንን የተሳካ የተቋውሞ  ሰልፍ  ያዘጋጁት  በመላው  ጀርመን  የሚገኙ  የስቪክ ማህበራት ከፍ ያለ አድናቆትና  ምስጋና ይገባቸዋል። ሰልፉን  በዋናነት  ሲመሩ  የነበሩት አቶ ታደሰ  ሃይሉ  እነዚህ የስቪክ  ማህበራት ሙሉ  ሃላፊነቱን ወስደው የወያኔን አረመናዊ ባህርይንና  በንጹሃን  ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን እያደረሰ  የሚገኘውን ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ለአለም ለማጋለጥ እንዲህ አይነት ስምምነት ኢትዮጵያዊነትና አንድነት የተሞላበትን ሰልፍ  ለማዘጋጀት፣ለማስተባበርና በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር ኮሚቴው  ከፍተኛ የገንዘብና የጌዜ መስዋትነት እንደከፈለ  ገልጸዋል።

የሰልፉ ዋና አላማዎች

1ኛ ለኢትዮጵያ ህዝብ አጋርነትን መግለጽ

2ኛ ወያኔ በኢትዮጵያ  ህዝብ ላይ  እየፈጸመ  ያለውን  ወንጀል   እንዲያቆም ማስጠንቀቅ

3ኛ አለአግባብ የታሰሩ የህዝብ ተወካዮች ጋዜጠኞች የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ

4ኛ ወያኔ ኢህአዲግ ሃገሩንና ህዝቡን ማስተዳደር ስላልቻለ በአስቸኩዋይ ከስልጣን እንዲወርድ ማሳሰብ

5ኛ የጀርመን መንግስት ወያኔን በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ  መርዳቱን እንዲያቆም መጠየቅ ይገኙበታል።

ይህ የተቋውሞ  ሰልፍ በጀርመን  የውጭ ጉዳይ ቢሮና  በመርሃዊ መንግስቷ አንጌላ መርክል ጽህፈት ቤት ብቻ ሳይሆን  በርሊን  ከታሪካዊውና በብዛት ከሚጎበኘው  ብራንደን በርግ ቶር አጠገብ  በሚገኘው በዩናይትድ ስቴትስና በፈረንሳይ ኢምባሲዎች እንዲሁም በአውሮፓ  ህብረት ህንጻ ፊት ለፊትም  ጭምር ነበር። የበርሊኑ  የተቋውሞ  ሰልፍ የአቋም መግለጫ ደብዳቤዎችን  ለጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐፕሊክ ፕሪዝዳንት፣ ለካንስለር አንጌላ መርክል፣ ለውጭ ጉዳይ ቢሮ፣ለፓርላማው እንዲሁም በጀርመን የልማትና እድገት እርዳት ቢሮ በመስጠት ተጠናቁዋል።

በተለያዩ  አገራት የሚገኙ  ኢትዮጵያውያን እንደዚህ የመሰለ  የተቋውሞ ሰልፎች ፣ ዲፕሎማሲያዊ  ግፊቶች እንዲሁም  የፔቲሽን  ፊርማዎችን  በማዘጋጀት  የአለም አቀፍ ማህበረሰብ  ወያኔ በሚመራው መንግስት ላይ  ከፍተኛ ጫና እንዲያደርጉበት እንቅስቃሴ  እያደረጉ  መሆኑ ይታወቃል። በጳጉሜ 2ቀን 2008ዓም የአውሮፓ  ህብረት ወያኔ በንጹሃን  ሰልፈኞች  ላይ  የወሰደውን  የግድያና  የሰብአዊ መብት ጥሰት ምርመራ  በማድረግ  ለወያኔ መንግስት ሊለግስ  ያቀደውን  እርዳታ ላልተወሰነ ጊዜ ማቀቡን  ይፋ  አድርጓል። ወያኔ  የሚመካባት  ዩናይትድ  ስቴትስ እንኩዋን የኋላ  ኋላ በኢትዮጵያ ውስጥ በንጹሃን  ህዝብ ላይ እየተወሰደ  ያለውን ወታደራዊ  እርምጃ  እንደሚያሳስባት በይፋ  መግለጽ  ለወያኔ  ጀርባዋን መስጠት እንደጀመረች አመላካች  ሆኗል።

By Zerihun Shumete/ From Germany


የአዲስ አበባ እንቅልፍ መንስዔው ምን ይሆን?

$
0
0

ይሄይስ አእምሮ (yiheyisaemro@gmail.com)

ውስጥ ውስጡን ከማጉረምረም ባለፈ አዲስ አበቤዎች የፍርሀት ቆፈናችንን አስወግደን በገጠራማዋ ኢትዮጵያ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ለመቀላቀል እስካሁን ድፍረቱን አላገኘንም፡፡ ይህ ነገር  በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ አሳሳቢነቱ ደግሞ ለአዲስ አበባ ለራሷ እንጂ ለመላዋ ኢትዮጵያ እንዳልሆነ ወረድ ብዬ ለማስረዳት እሞክራለሁ፡፡  “ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ” ነው ነገሩ፡፡

አዲስ አበባ ለወትሮው የተቃውሞ ማዕከል ነበረች፡፡ እባብን ያዬ በልጥ በረዬ እንዲሉ ሆኖባት እንደሆነም አላውቅም ከ97 ምርጫ ወዲህ ግን ይህች ኩሩ የአፍሪካ መዲና ሕወሓትን በሰማንያ ያገባች የፍቅር እማውራ የሆነች ያህል በፀጥታ መዋጥን የመረጠች ይመስላል፡፡ እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡ በውስጧ ላለን እናውቀዋለን፡፡ የዜጎች ልቅሶና ዋይታ፣ የኑሮ ውድነትና የአፈናው መጠን ዜጎችን ከሰውነት ተራ አውጥቶ ወደ እንስሳነት እየለወጠ በመሆኑ የሕዝቡ ዝምታ ወያኔን ወዶና አፍቅሮ ሳይሆን በሆነ ደንቃራ ሳቢያ ፀጥ ረጭ ማለቱን እንደመረጠ መረዳት አይከብድም፡፡

File Photo

File Photo

ለመሆኑ ለምን ዝም አልን? ደንቃራው ምን ይሆን? የሚመስለኝን ልናገር፡፡

ደንቃራ አንድ – ከ97 የከሸፈ የወያኔ ምርጫ ወዲህ ሕወሓት በማን ምክር እንደሆነ አላውቅም የአዲስ አበባን የሕዝብ አሠፋፈር በከፍተኛ ደረጃ ለዋውጦታል፡፡ ከክፍለ ሀገር አዲስ አበባ ስትገቡ ትግራይ የገባችሁ እስኪመስላችሁ ድረስ ተጋሩ ወንድምና እህቶቻችን ከመቀሌና አካባቢዋ ዘመቻ በሚመስል መልክ ተጠራርገው ወደ አዲስ አበባና አካባቢዋ እንዲሠፍሩ የወያኔው ጉጅሌ ሣያደርግ አልቀረም፡፡ የትም ቦታ ስትሄዱ ሁለትም ሦስትም አሥርም ሃያም ሰዎች ሆነው ሲሄዱ የሚነጋገሩበት ቋንቋ አብዛኛውን ጊዜ ትግርኛ ነው –  ወትሮ በደጋግ ዘመናት ያልለመደበት ይህን መሰል ግምኛ ጠባይ ስለትግሬ ሲነገር ደማችሁ የሚንተከተክ (ዘረኛ) ሰዎች ታገሱኝ፤ እውነት ደምን ቀርቶ አጥንትን እንደምታፈላ ደግሞ አውቃለሁና በምለው ነገር ሀቅነት ማንም ቅንጣት ያህል እንዲጠራጠረኝ አልፈልግም፤ እውነትን ብትመር ብትጎመዝዝ እንዳለች መቀበል ነው፤ ይሉኝታና መሸፋፈን አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝ እንኳን ተመክሮም ሆነ ተዘክሮ ዘመድ ለሚሆንህ ሰው እንጂ እንደበግ አጋድሞ ለሚያርድህ የትግሬ ወያኔ ዓይነቱ ደደብ ጭራቅ አይደለም፡፡ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ግዛቶች ብዙ ቀበሌዎች በትግርኛ ተናጋሪዎች እንደተሞሉ ለመረዳት የሥነ ሕዝብና የቤቶች ቆጠራ እስታትክቲክስ ሠራተኛ አያስፈልጋችሁም፡፡ በራሳችሁ ታውቃላችሁ፡፡ በነገራችን ላይ ትግሬዎች ኢትዮጵያን ለምን ሞሏት የሚል ቅሬታ የለኝም፤ ብዙዎቹ ከሕወሓት ጋር ያላቸው የክፋት ቁርኝት ነው የሚከነክነኝ፡፡ አንዳንድ ወንድሞች ታዲያን ይህን ዐይን ያወጣ “የወንድሞቻቸውን” ስህተት እየታዘቡ ሌላው ስለዚህ ስህተት ሲናገር መናደድ የለባቸውም – በአኮርባጅ እየተገረፈ ያለን ሕጻን “ዋ ታለቅስና! ዝም ብለህ ተገረፍ!” ብሎ እንደመቆጣትና ፈረንጆቹ `Adding an insult to injury” እንደሚሉት ነው – ድርብ በደል፡፡ ተጠቅመህም፣ እንዳልተጠቀምክ እንዲቆጠርልህ ፈልገህም እንዴት ሊሆን ይችላል? ብዙ ዕንቆቅልሽ … ብዙ ሞኝነት፡፡ በደል እንዲቆም ማድረግ ሲገባ “በደልህን ገሃድ አታውጣ” ብሎ ተበዳይ ላይ መፍረድ በሰማይም በምድርም ኩነኔ ነው፡፡ ከታላላቅ ምሁራን ጀምሮ ብዙ ብሶት ስላለኝ ነው …

የመንግሥት ሠራተኞች ባብዛኛው፣ ጦሩ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ፣ መከላከያንና ደኅንነትን፣ የውጭ ጉዳይንና ሌሎችንም የሚንስቴር መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም ንግዱንና የዕድርና የዕቁብ፣ የሰንበቴና የፅዋ ማኅበሩን የዜጎች ስብስብ የአመራር ቦታ ሣይቀር ሙሉ በሙሉ ወይም በአብዛኛው የያዙት ትግሬዎች መሆናቸውን መመስከር በተቃራኒ የቆመ ዘረኝነት አይመስለኝም፡፡ የዐዋጁን በጆሮ የመናገር ያህል ግልጽነት ነው፡፡ አንድ ወቅት ወደ ትግራይ ሄጄ ስመለስ በትግራይ ውስጥ የሚኖረው ትግሬ ሁለት ሚሊየን እንኳን እንደማይሆንና ቀሪው በመላዋ ኢትዮጵያ ተበትኖ በተቻለው መጠን እንደመዥገር ሀገሪቱን እየመጠመጠ እንደሆነ ከነባራዊው እውነት በመነሳት በጊዜው ገልጬ ነበር፡፡ ( በነገራችን ላይ ያን ትዝብት በድረ-ገፆች ከገለጥኩ ከጥቂት ሣምንታት በኋላ የኢሳት እንግዳ ሆና የቀረበችው ወ/ሮ ርስቴ የተባለች ጎንደሬ-ወልቃይቴዋ የቀድሞ የሕወሓት ቀጥሎም የኢሕዲን ተብዬው ታጋይ ስትናገርም ይህንኑ ነበር የተናገረችው፡፡ የኔን መጣጥፍ እንዳላነበበች እገምታለሁ፡፡ ግን እውነት እውነት በመሆኑ ሳይነጋገሩ ይግባቡበታልና እንዲያ ስትል እኔንም በጣም ገረመኝ፡፡ ለእውነቱ እርሷ ይበልጥ የቀረበች በመሆኗ የኔ የ2 ሚሊዮን ግርድፍ ግምት በዕውቀት ላይ በተደገፈ የርሷ መረጃ ጽድቅን አገኘ፡፡ በርግጥም ትግራይ ላይ ሰው ያለም አይመስልም፡፡ በወያኔ ተጠርተው ወደሌሎቹ ግዛች በመሄድ “ሥራ እየሠሩ” ነው፡፡)

ይህ የትግሬዎች – ማለትም የወያኔን ዕድሜ መርዘም የሚፈልጉና ለዚያ የሚዋደቁ የትግሬዎች ምልዓት ባለባት አዲስ አበባ ሕዝባዊ ተቃውሞን በቀላሉ መቀስቀስ ባይቻል አይገርምም፡፡ ሰው ለጥቅሙ ሲል የማያደርገው ነገር ስለሌለ እንኳንስ እነዚህ በዘረኝነትና በግል ጥቅም ታውረው ከትግራይ የመጡ ዜጎች ሌላው ጎሣ ሳይቀር ለነሱ ባሪያ በሆነበት ሁኔታ ከሕዝቡ ብዙ ነገር መጠበቅ በእስካሁኑ አካሄድ የሚቻል አልሆነም፡፡ ለምን ቢባል ትግሬው በዛ ማለት ስለላውም፣ ፀጥታውም፣ ምኑም ምናኑም በነሱ ቁጥጥር ሥር ስለሆነ ሰው ይፈራል – የሚገርማችሁ ዕብድና ሰካራም፣ ሴተኛ አዳሪና ቁራሌ እየሆኑ አሁን መንግሥት ከሆኑ በኋላም ሕዝቡን በስለላ ጥምድ አድርገው ይዘውታል – ሰሞኑን ደግሞ ብሶባቸዋል አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት አዲስ አበቤ እርስ በርሱ አይተማመንም – አንዱ አንዱን ይጠራጠራል፤ ጥላውንም ማመን አቅቶታል፡፡ ጎመን በጤና ባዩ በዝቶ የእንስሳነት ኑሮ ሰፍኗል፡፡ ምሁር የለ ወታደር፣ ፖሊስ የለ ነጋዴ፣ ማይም የለ ዐዋቂ፣ ዲያቆን የለ ቀሲስ፣ ጳጳስ የለ ፓትርያርክ፣ ደረሣ የለ ኢማም፣ ሼህ የለ ቃዲ … ሁሉም ተያይዞ ነፈዝ ሆኖላችኋል፡፡ ስኬታማ ውድቀት ማለት እንዲህ ነው፤ ስንገርም!!

ደንቃራ ሁለት – ሕወሓት ብዙ ወጣቶችን በአነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች አደራጅቶ የጥቅም ተጋሪ እንዲሆኑ አድርጓል፤ አእምሮ በጫጫበትና ስለሀገርና ወገን ማሰብ ዕርም በሆነበት ማኅበረሰብ ውስጥ ይህ ዓይነቱ ከፋፋይ ሥልት የራሱን አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር መገመት አለብን፡፡ ብዙ ሰዎች ስለሚያደርጉት ነገር ሳይሆን የሚያደርጉት ነገር በምን ያህል ፍጥነት ከበርቴ እንደሚያደርጋቸው ነው የሚያስቡት፡፡ ገንዘብ የሚገዛው ጭንቅላት ደግሞ ስለሀገር ቀርቶ ስለራሱም ማሰብ አይችልም፡፡ ሚሰቱንና ልጆቹን ሳይቀር ሸጦ በአቋራጭ መክበር የሚፈልግ ዜጋ በተበራከተበት የጨለማ ዘመን ውስጥ ብዙ መጠበቅ ያስቸግራል፡፡ አዎ፣ ብዙው ስታዩት ቀንም ሌትም፣ ቆሞም ተኝቶም የሚጨነቀውና የሚዋትተው ገንዘብ ስለማግኘት ነው – “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው”፡፡ ይህ ዓይነቱ ለሥጋው ብቻ ያደረ ገልቱ ዜጋ ሀገሪቱን ብቻ ሳይሆን ከፍ ሲል እንዳልኩት ወንድሙንና እህቱንም ይሸጣል፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እየበዙ ሲሄዱ ሀገር በባርነት ሥር እንዳለች የመቆየቷ ዕድል ከፍ ያለ ነው፡፡ መጸለይ ነው ጎበዝ! የተያዝነው የውጥርት ነው፡፡

ደንቃራ ሦስት – የ97ን ምርጫ ተከትሎ ሕወሓት አዲስ አበባ ላይ ያወረደው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከሕዝቡ አእምሮ ገና አልወጣም፡፡ እንዲያውም ይባስ ብሎ የወያኔው ጉጅሌ ዐረመኔነቱን በየጊዜው እያደሰ መጥቶ ሰሞኑን ደግሞ በጭራሽ ሊታመን የማይችል ጭፍጨፋ በእስረኞች ላይ ፈጽሟል – ይህን መሰሉ በ“ሕግ ጥላ” ሥር ያለን ምስኪን ዜጋ በዚህ መንገድ መጨፍጨፍ ደግሞ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ ይህ ጭፍጨፋ ሁለት መልእክት አለው ብዬ አስባለሁ- አንደኛው ሊያጠፋቸው የሚፈልጋቸውን የኅሊናና የደረቅ ወንጀል “የሕግ” እስረኞች ማጥፋት ሲሆን ሁለተኛው ሕዝቡን ማስፋራራትና ጭራቅ የመጣበት ያህል ቆጥሮ አንዳችም ተቃውሞ ሳያሳይ አርፎ እንዲቀመጥ ለማስጠንቀቅ ነው፡፡ በተለይ ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ ሁሉንም አየነው፤ ለየነው፡፡ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ዕይታ ውስጥ ሆኖ ይህን ወንጀል በጠራራ ፀሐይ ሲሠራ ወያኔን አንድም አካል ዝምቡን እሽ ማለት ቀርቶ ከረር ያለ የቃላት ማስጠንቀቂያ እንኳን የሰጠው የለም –  ከተለመደው የ“ይህ ጉዳይ አሳስቦናል” ዲፕሎማሲያዊ የከንፈር ሽንገላ ውጪ ማለቴ ነው፡፡ ወያኔዎች “ምንም ብናደርግ የሚደርስላችሁ ስለሌለ ፀጥ ረጭ ብላችሁ ለኛ ተገዙ! አለበለዚያ አንድ ባንድ እንፈጃችኋለን፤ የዓለምን ፖለቲካ እንዳሻቸው የሚወስኑት ወገኖች እንደሆኑ ከኛ ጎን ናቸው” የሚል መልእክት ነው እያስተላለፉ ያሉት – ደግሞም እውነታቸውን ነው፡፡ እንዲህ ያለ ግፍ ሌላ ሀገር ቢሠራ ኖሮ ብዙ ዓለም አቀፋዊ ጩኸትና ውግዘት እንዲሁም እስከማዕቀብ የሚደርስ ከፍተኛ ግጭት ይፈጠር ነበር – ወያኔዎች ግን እስካሁን መንገዳቸው ሁሉ ቀኝ በቀኝ የሆነላቸው ይመስላል፡፡ ይህ እስር ቤቶችን በእሳት በማጋየት ከእሳት ለመዳን በደመነፍስ የሚሮጥን ወይም እሳቱ የተነሣው እስረኛን ለመፍጀት ሆን ተብሎ በወያኔ ሣይሆን በድንገተኛ አደጋ መስሎት እሳቱን ለማጥፋት የሚሞክርን እስረኛ ቀድሞ በተዘጋጀ አልሞ ተኳሽ ማስጨፍጨፍ የትም ሀገር ያልታዬ አዲስ የወያኔ ግኝት ለመሆኑ ማንም የማይክደው እውነታ ነው፡፡ ይህ ዐረመኔነታቸው ሕዝብን በፍርሀት ቆፈን ውስጥ እንዳለ እስከወዲያኛው እንዲቆይ ለማድረግ የታለመ እንጂ እስረኛን ለመግደል የሚከለክላቸው ምድራዊ ኃይል ኖሮ አይደለም፡፡ ይህን ፍርሀት ባፋጣኝ ካልገፈፍን ይበልጥ የምንጎዳው እኛው አዲስ አበቤዎች ነን፡፡ እነሱ እንደሆኑ እኛ ፈርተን እስከተቀመጥን ድረስ እየጨፈጨፉን ለዘላለሙ ይኖራሉ፡፡ ከነሱ የጭካኔ በትር የሚያድነን የውጭ ኃል እንደሌለ ደግሞ በሚገባ መረዳት ይኖርብናል፤ ግፋ ቢል ከንፈር ይመጡልን እንደሆነ እንጂ አንዲትም ወንጭፍ ሰንዝረው በኛ ላይ የሚተኩሱትን ወያኔዎች አደብ ግዙ አይሉልንም፡፡ ይህን ጠንቅቀን ማወቅ አለብን፡፡ እኛ ስንጠነክር ወደኛ ሊሳቡ ይችላሉ፤ ከተልፈሰፈስን ግን የወያኔዎች እንደሆኑ በዚያው ይቀራሉ፡፡ ግልጽ እኮ ነው፡፡ ጥሌ “እያለህ ካልሆነ ከሌለህ የለህም” ብሎ ጨርሶታል፡፡

ደንቃራ አራት – የገጠሩ ሕዝብ በጎታውና በጉስጉሻው ለአንድ ሰሞን የሚያጋድደው(የሚሆነው) ጥራጥሬ አያጣም – እንደአብዛኛው ከተሜ ሙልጭ የወጣ ድሃ አይመስለኝም፡፡ እርግጥ ነው ተቃውሞውና ትግሉ ከተራዘመ ያም ያልቃል፡፡ ከተሜው በተለይም አዲስ አበቤው ግን ዛሬ ከሥራ ቢፈናቀል ቀጣዩ ቀን አሣር የሚሆንበትና ኑሮውን በብድር የሚገፋ ብዙ ጦም አዳሪ የመንግሥትና የግል ሠራተኛ የታጨቀባት ከተማ ናትና “ምን ላስጣ ከደጄ፣ ምን ልስጥ ለልጄ” በሚሉ ድሃ ዜጎች የተሞላች ናት፡፡ ሕዝብን አደሕይተው የሚገዙ ክፉ መንግሥታት የሚጠቀሙት እንግዲህ በዚህን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሕዝቡ “ምን ልቅመስ?” እያለ ከጋራ ትግል ወደኋላ ሲያፈገፍግ ነው፡፡

ለሕዝባዊ ትግል ዝግጅት ያስፈልገዋል፤ ምክክር ያስፈልገዋል፤ ስምምነት ያስፈልገዋል፡፡ ያ እንዳይሆን ግን በሃሳብ መለያየት ይኖራል፤ በኑሮና በኢኮኖሚ አቅም መለያየት ይኖራል፤ የአሰባሳቢ ማጣትም ይኖራል…፡፡ ችግሮች ተደራራቢና ውስብስብም ናቸው፡፡ ይህን ሁሉ ችግር በጣጥሶ ለማለፍ ድፍረትና ጀግንነት ያስፈልጋል፡፡ ከራስ ማሰብ ባለፈ የትልቅ አእምሮ ባለቤት መሆንንና ዘመን ተሻጋሪ ታሪካዊ ሥራ ለመሥራት ዝግጁ ሆኖ መገኘትን ይጠይቃል፡፡ ይህን ሚና ማን ይረከብ? አሳሳቢ ወቅታዊ ጥያቄ ይመስለኛል፡፡

ደንቃራ አምስት – በገጠሩ አካባቢ ያለው ሕዝብ ከፍተኛ ተመሳሳይነት (homogeneity) ስላለው ለመተማመንና ጥርጣሬን ለመቀነስ ብሎም በሂደት ለማስወገድ ትልቅ ዕድል አለው፡፡ በጎሣ ስብጥርም ሆነ በማኅበራዊ ትስስሩ ገጠሩ ከከተማው ይልቅ ይበልጥ እርስ በርስ ስለሚተዋወቅ ወኔው ካለው አንድን ነገር በጋራ አስቦ በጋራ ማድረግ አይቸግረውም – አሁን እያየነው ያለነውም ይህንን ነው፡፡ ከተማው ግን በተለይ አዲስ አበባ በየቀኑ በሚመጡላትና በሚመጡባት በርካታ ዜጎች የምትጥለቀለቅና በአንድ አዳር ከብረው በሚያድሩ ባለጊዜዎች የምትታመስ ከተማ በመሆኗና በገንዘብ ዝውውር ረገድም የት መጣ የማይባል እጅግ ብዙ ብር ሲረጭባት የሚውልና የሚያድር ከተማ ስለሆነች ሰው እርስ በርስ ለመተማመንና ልብ ለልብ ለመገናኘት ይቸግረዋል –  (ስለሆነም Heterogeneity አንዳንዴ አስቸጋሪ ነውና ማንኛውም ዕቅድና ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ይህን ችግር ታሳቢ አድርጎ መነሳት አለበት፡፡) በዚያ ላይ የወያኔ አጋፋሪዎች ሕዝብን በዘርና በጎሣ፣ በሃይማኖትና በጥቅማጥቅም በእጅጉ ከፋፍለውታልና ብሶቱ ሰማይ ቢነካም ለሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቃውሞ ተጠራርቶ ለመነሣት አቀበት ሆኖብናል፡፡ ከውጪ እየገፋ የሚመጣ ኃይል ካልተገኘ በእስካሁኑ ሁኔታ ከአዲስ አበባ ብዙም መጠበቅ የሚቻል አልመሰለኝም፡፡ እንዲህ እንደሆነ ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ግን በተለይ ወያኔዎች ሊረዱት ይገባል፡፡ የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡

መግቢያየ አካባቢ ወደጠቀስኩት ጉዳይ ልመለስና አዲስ አበቤዎች ሕዝባዊውን ሀገራዊ የእምቢተኝነት እንቅስቃሴ በሙሉ ንቃትና በስፋት ባለመሣተፋችን እንዴት ልንጎዳ እንደምንችል ልግለጽ፡፡

የአዲስ አበባ እስትንፋስ ወያኔ አይደለም፡፡ አዲስ አበባ የምትኖረው የገጠሩ ገበሬ ሲኖር ብቻ ነው፡፡ የገጠሩ ሕዝብ ሁሉን በሮቹን ቢዘጋ አዲስ አበባ ነፍሷን እንደምንም ብታውል አታሳድርም፡፡ ሁሉ ነገር የሚመጣው ከገጠር ነው – ከአየርና ከፀሐይ በስተቀር በአብዛኛው ሁሉም ነገር መነሻው ገጠር ነው፤ የፋብሪካ ግብኣቶች ሳይቀሩ የሚገኙት ከገበሬው ነው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው ገዳይ የወሮበሎች መንግሥትና በሚሊዮን የሚቆጠር በላተኛ አፍ ያለው ተጨቋኝ የከተማ ነዋሪ እንጂ ጤፍና ስንዴ ወይም ምሥርና አተር ወይም የበሬ ቁርጥና የባቄላ አሹቅ አይደለም፡፡ ለቅንጦት የምናውለው ስኳርና ጨው ሳይቀር ከአዲስ አበባ ውጪ ነው የሚገኘው፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም የምግብ ሸቀጦች ከገጠር ነው ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት፡፡ የገፈርሳና የለገዳዲ ሕዝብ ቢያምጽና ውኃችንን አንሰጥም ቢል ራሱ – አያድርግብንና ለምሣሌ – አዲስ አበቤዎች በሕይወት የምንቆየው ግፋ ቢል ከሦስት እስከ ሰባት ቀን ቢሆን ነው፡፡ የኅልውናችን መሠረት ገጠሩ ነው፡፡ ከኛ ለኛ ምን አለን? ምንም፡፡ አልባሽ አጉራሻችን ገበሬው ነው፡፡ ካለ ገበሬው ምንም ማለት ነንና እርሱ በጥይት አረር በወያኔ እየተቆላ ዝምታችን የሚጠቁመው ወያኔን እንደመደገፍና ጠንከር ሲልም ጥይት እንደማቀበል ያህል ነው፡፡ ለምን ቢባል ወያኔ ለዱላ መግዣ የሚጠቀምበትን ግብርና ቀረጥ እንከፍላለንና፡፡ ዝምታችንም ተቃውሞን ብቻ ሣይሆን እንደድጋፍም ሊቆጠር ይችላልና፡፡

የጎጃምና የአድኣ ጤፍ፣ የቦረና በቆሎና የጨርጨር ሠንጋ፣ የጉራጌ ቆጮና የከፋና ሲዳሞ ወይም የወለጋና ጋሞጎፋ  ቡና፣ የሸኖ ቅቤና የአፋር-ዳሎል ጨው፣ የአዶላና ሻኪሶ ወርቅና የቤንሻንጉሉ የደን ዕጣን፣ የሙገሩ ስሚንቶና የጋምቤላው እምነ-በረድ፣… ወደ አዲስ አበባ ካልገባ በወያኔ ኢቢሲ በሚታየው እጅግ የተጋነነና የሀሰት የልማት ዜና ሆዳችንን ቀብትተን አንዲት ቀን ልናድር አንችልም፡፡

ስለዚህ አዲስ አበቤዎች የገጠሩን ሕዝብ የመቀላቀልና የሚደረገውን ሕዝባዊ የእምቢተኝነት ተቃውሞ ከዳር የማድረስ ኃላፊነትና ግዴታ አለብን፡፡ የኅልውናችን መሠረት የሆነው የገጠሩ ሕዝባችን ለሁላችንም መብት እየተዋደቀ እኛ በዝምታችን ብንጸና ፀፀቱ ለማያባራ የታሪክ ስብራት እንዳረጋለን፡፡ ይህን ውሸት ነው የምትል በአድራሻየ ተከራከረኝ፡፡ አዲስ አበባ ጌጧ ገጠሩ ነው፤ ካለገጠሩ ባዶና የባዶ ባዶ ነን፡፡ ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡

አዲስ አበባ ያለገጠሩ ሽባ መሆንዋን ሰሞኑን እየታዘብን ነው፡፡ የሁለት ሺህ ብሩ ጤፍ እስከሦስት ሺህ ብር እንደገባ እየሰማን ነው፤ ይህም የሆነው በኦሮሞ ሕዝባዊ ትግል ምክንያት የገበያና መንገድ መዝጋት እንቅስቃሴዎች ከመጀመራቸው ገና ከማለዳው ነው፡፡ ይህ ትግል በስፋት ቢቀጥል መቶ ሺህ ብርም ይዘህ – ቢኖርህ እንኳን ማለቴ ነው – አንዲት ጣሣ ጤፍ ላታገኝ የምትችልበት ጠማማ ዕድል ሊፈጠር ይችላል፡፡ ስድስት ሚሊየን ገደማ አፍ ይዘህ ተዝናንተህ መቀመጥ አትችልም – እርስ በርስህ ትበላላለህ፡፡ ኦሮሞና አማራ በተባበሩ ማግሥት ወያኔዎች ድራሻቸው እንደሚጠፋ የምንናገረው እንግዲህ ለዚህ ነው፡፡ የሽሮ ድንፋታ ከእሳት እስክትወጣ ነው ይባላል – የወያኔም ድንፋታ ኦሮሞና አማራ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከባርነት ለመውጣት እስኪወስኑ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ አለቀ!!!

ሕዝቡ የከተማ የገጠር ብሎ ሳይፎካከር ሕዝባዊ ተቃውሞውን በአንድ ጀምበር ካደረገ ወያኔም በአንድ ጀምበር ይወገዳል – በዚያው ተመሳሳይ ጀምበር፡፡ ወያኔዎች እርግጥ ነው በገንዘብ ዕጥረት አይወገዱም – ለሚሊዮኖች ዓመታት የሚሆናቸውን ከበቂ በላይ የሆነ ሀብትና ንብረት ዘርፈው አሽሽተዋልና፡፡ በጥይት ዕጥረትም አይወገዱም – በበቂ ሁኔታ አጠራቅመዋልና፡፡ ግን ግን የኅልውና አማራጭ የሚያጣ ሕዝብ እንደንብ በአንዴ ሆ ብሎ ከሠፈረባቸው አጋዚም በሉት መከላከያና ደኅንነት አቅሙ ውሱን ነውና በእግር አውጪኝ የትሚናውን እንደሚፈረጥጥ ግልጽ ነው፡፡ የሮማንያ ሕዝብ የሞተው ሞቶ የተረፈው ተርፎ ሀገሩን ከኒኮላይ ቻውቸስኮ አምባገነን አገዛዝ ነፃ ያወጣው ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ባደረገው ሕዝባዊ ተጋድሎ ነው፡፡ በተናጠል ከሄድን ግን የትም አንደርስም፡፡ ለተራዘመ ትግል ደግሞ የሚያመች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዳራ የለንም፡፡ ስለዚህ ምርጫችን ሁለት ብቻ ነው፡፡ አንድም በነካካነው የቆሰለ የቤታችን (ዐውሬ) አነር እየተዘነጠሉ መኖር፣ አለዚያም በተናጠልም በቡድንም የነካካነውን ክፉኛ የቆሰለ አነር ገድለን ለሁላችንም የሚጠቅም አዲስ ሥርዓት መትከል፡፡ ለዚህ ደግሞ መሸዋወዱና “የነ እገሌ ትግል ይቅደም፣ የነ እገሌ ትግል ደግሞ ይቀጥል” በሚል የሞኛሞኞች የትግል ሥልት መጃጃል የለብንም፡፡ ከሆነ በአንዴ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ ወያኔን “ባጠፋን ይቅር በለን፣ የድፍረታችን ምንጭ ልማታችንና ሕዝባዊ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሥርዓታችን ባመጡብን ጥጋብ የተወለደው አቅል አሳች ስካር ነው” ብለን ሕወሓትን ይቅርታ ጠይቀን የከፋ የከረፋውን የውስጥ ቅኝ አገዛዝና የአፓርታይድ ጉዞ ማስቀጠል ነው፡፡ ከዚህ ውጪ “ገመቹ ይቅመሳትና ደስታ በተራው ይታገላል፣ የለም – ሐጎስ እስኪነሣ አሸምቀን እንጠብቅ፣ አሃ፣ ደቻሳ የቀመሳትን ዱላ ስንሻው ካልቀመሳት እንዴት በጋራ እንታገላለን? …” እየተባባሉ ወንዝ በማያሻግርና ካለፈ ተሞክሮ አንዳችም መማማር በሌለበት የድንቁርና አካሄድ ከቀጠልን እመኑኝ የትም አንደርስም – ለነገሩ ይሄ የምለው ነገር የአደባባይ ምሥጢር እንጂ “እመኑኝ አትመኑኝ” የሚያስብል አዲስ ግኝት እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ግን ግን ካለፈ ታሪክና ከአሁን የግል ጠባሳችን የማንማረው ምን ቢዞርብን ወይም ወያኔ ምን ዓይነት አፍዝ አደንግዝ ቢያስደግምብን ይሆን?

ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጥረህ ከአንዱ ወይ ከሌላው ጎሣ ያልተቀላቀልህ የለህምና በዚህ በወያኔ ዘራሽ የጎሠኝነት ልምሻ የተኮደኮድክ ሁሉ በአሁኑ ወቅት ሙሉ የመንቂያ ጊዜ ላይ ደርሰሃልና በቶሎ ንቃ፡፡ የጋራ ጠላትህንም ባፋጣኝ ለይና በጋራ ሆነህ ባላንጣህን ተፋለም፡፡ በቃ፡፡ ሌላ መፍትሔ የለም፡፡

በውጪ ያላችሁትም በቻላችሁት ሁሉ በትግሉ ተሣተፉ፡፡ ማጨብጨብና መሰለፍ፣ በየተወሰነ ጊዜ ጠላትን በሰላማዊ ሰልፍ ማውገዝም ብቻውን በቂ አይደለምና የትግል ሥልትህን ለውጥ፤ ሲበቃ በቃ ነውና የትግል ዘዴህን ባለመለወጥ ትርፍ በማያመጣ መጯጯህ ጊዜህን በከንቱ አታባክን፡፡ ኢትዮጵያውያን ዳያስጶራዎች በአካልም፣ በመንፈስም፣ በገንዘብም፣ በዕውቀትም፣ …. በሁሉም ረገድ በትግሉ ተሣተፉ፡፡ “ሩቅ ሆነው በርገር እየቆመጡ ድሃውን ያገር ቤት ሰው ጃዝ ይላሉ” ከሚለው ወደ እውነት የቀረበ አቃቂር ለመዳን ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ እንደሚባለው ሣይሆን በማንኛውም አቅጣጫ በንቃት መሣተፍ አለባችሁ – የመጨረሻው የጥፋት ወይም የትንሣዔ ዘመን የቀረበ ይመስለኛል – አሁንም ከሁለቱ አንዱን የመምረጡ ግዴታ የኛው ነው፡፡ የነፃነትን ዋጋ ሁሉም ይረዳ፡፡ በነፃ የሚገኝ ነገር ርካሽ ነው የሚባለው አንዳንዴ ትክክል ነው፡፡ ወዳገር ቤት ገብታችሁ በአመራርም ሆነ በውጊያ መሣተፍ ካለባችሁም በሩቅ ሆኖ በንዴት ከመብገንና ከመጨስ ባመቻችሁ ቀዳዳ ገብታችሁ ትግሉን ተቀላቀሉ፡፡ እርግጥ ነው – መናገር ቀላል ነው – ይህን የኔን ጨምሮ፡፡

 

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ያለመገበያየት አድማው በተሳካ ሁኔታ ለ4ኛ ቀን እንደቀጠለ ነው |አውቶቡስ የለም –ለመሥራት ያሰቡ መኪኖች እርምጃ ተወስዶባቸዋል

$
0
0

screen-shot-2016-09-09-at-9-58-44-am screen-shot-2016-09-09-at-9-57-32-am screen-shot-2016-09-09-at-9-58-29-am

(ዘ-ሐበሻ) አወዳይ የጫት ሃገር፣ ወትሮ ሱቆቿ ለ24 ሰዓታት ለ7 ቀናት ክፍት ነበሩ:: አሁን ግን ላለፉት 4 ቀናት በተቃውሞው የተነሳ እንደተከረቸሙ ነው:: ከአወዳይ ወደ ሌሎች ኢትዮጵያ ከተሞች የሚሄደው ታዋቂው አወዳይ ጫትም ጠፍቷል – ይሉናል አንድ የአካባቢው ነዋሪ:: እንደ አካባቢው ነዋሪ ገለጻ የአወዳይ ሕዝብ ያለመገበያየቱንና ከቤት አለመውጣቱን አድማ ላለፉት 4 ቀናት የተያያዘው ሲሆን ትራንፖርት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችም ቆመዋል::

ይህ በ ኦሮሚያ የተጠራውና 4ኛ ቀኑን የያዘው አድማ በሱሉልታም ቀጥሏል:: ወትሮ ለዓመት በዓል ገበያ ሽር ጉድ የሚበዛባት ሱሉልታ ከተማ ገበያዎቿ ሁሉ ተዘጋግተው ሙል በሙሉ ንግድ እንቅስቃሴ የለም::

በድሬደዋ፣ በሻሽመኔ፣ በአሪሲ፣ በአርጆ፣ በአምቦ፣በጉደር፣ ነቀምቴ፣ ባሌ ሮቤ፣ ወሊሶ፣ ቡራዩ፣ በባቱ፣ ደምቢዶሎ፣ ጋላሳ፣ አሪሲ ነጌሌ፣ ኦሎንኮሚና ሌሎችም የኦሮሚያ ከተሞች ንግድ ለ4ኛ ቀን ቆሟል:: መንገድ የለም:: አውቶቡሶች ከከተማ ወደ ከተማ መሄድ አይችሉም::

በተለይም በ4ኛው ቀን ተቃውሞ ላይ የሕዝብን ጥሪ ሳይቀበሉ ቀርተው የትንራንስፖርት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ሚኒባሶችና አውቶቡሶች ተሰባብረዋል:: ሕዝቡም መንገድ ላይ እያስቆመ ታርጋቸውን እየነቀለ እርምጃ እንደወሰደባቸው በፎቶ ግራፍ ጭምር ከተለቀቁ መረጃዎች መረዳት ተችሏል::

ከአምቦ በደረሰን መረጃ ወሊሶ ካምፓስ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አውቶቡስን ጨምሮ 3 መኪኖች ላይ ሕዝብ ጥቃት አድርሷል:: ሕዝቡ አድማውን ወደ ጎን ትተው በሚንቀሳቀሱ መኪኖች ላይ በወንጭፍ ድንጋይን በመጠቀም እያጠቃ ሲሆን አጋዚዎች ይህን መቆጣጠር አይችሉም::

በጃዊ ባለፈው ሳምንት 37 የሚሆኑ አጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል |በጎንደር አራዳ አካባቢ ወጣቶችና አጋዚ ተፋጠዋል፤ ፍሎሪዳ ሆቴል ከፍተኛ ወታራዊ መከነኖች ስብሰባ ተቀምጠዋል

$
0
0

በጎንደር አራዳ አካባቢ ወጣቶችና አጋዚ ተፈጠዋል፤ ፍሎሪዳ ሆቴል ከፍተኛ ወታራዊ መከነኖች ስብሰባ ተቀምጠዋል
 በጃዊ ባለፈው ሳምንት 37 የሚሆኑ አጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል
 ባንኮች ከ10 ሺህ ብር በላይ ወጪ እንዳያደርጉ እቀባ ተጥሏል፤ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2.3 ቢሊዮን ብር ደንበኞች ከባንኮች አውጥተዋል
 ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረግ በረራ ሁሉ በመከላከያ እውቅና እንዲሆን ተደርጓል 

ከሙሉቀን ተስፋው


ጎንደር፤ ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ የመብራት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በጎንደር ከተማ በማቋረጥ ከአየር ማረፊያ ጀምሮ በሁሉም ቀበሌዎች የአጋዚ ጦር አባላት ቤት ለቤት በመግባት መሣሪያ በመፈተሸ ሲቀሙ ውለዋል፤ የመገናኛ ዘዴዎች ሁሉ በመቋረጣቸው ብሎም ወጣቶች መነጋገር ባለመቻላቸው የተነሳ ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ዐማሮች መታሰራቸው ተሰምቷል፤ የባጃጅና የታክሲ ትራንስፖርት በግዴታ እንዲቆም ተደርጎ መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዳይደርስም ጥረት ተደርጓል፡፡ 

File Photo

File Photo


ጎንደር በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የመከላከያና የፖሊስ አባለት የተጥለቀለቀ ሲሆን ከፍተኛ የትግሬ ወታደራዊ መከነኖች ፍሎሪዳ ሆቴል ይህ ሪፖርት እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ስብሰባ ላይ ነበሩ፡፡

በተያያዘ ዜና አራዳ የሚባለው የገበያ አካባቢ የዐማራ ወጣቶችና በአጋዚ ወታደሮች መካከል ፍጥጫ መኖሩን መረጃው ደርሶናል፡፡ የጎንደር ወጣቶች ወንድሞቻችን አሳልፈን አንሰጥም እያሉ ሲሆን ከባሕር ዳርና ከቻግኒ ወደ ብር ሸለቆ የተወሰዱ ወጣቶች ከፍተኛ ስቅይት እየደረሰባቸው እንደሆነም እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ከጎንደር ከተማ ዛሬ ነው የወጣነው የሚሉ ሰዎች እንደነገሩን የመረጃ አውታሮችን ሙሉ በሙሉ በመቆለፍ የጎንደር ከተማን ዳግም ወደ ዕልቂት ለመውሰድ የታለመ ይመስላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ጃዊ፤ በጃዊ ነዋሪውን በማሰርና በማንገላተት ላይ በነበሩ 37 የሚሆኑ የትግሬ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ መገደላቸውን ተሰምቷል፡፡ ቁጥራቸው ያልታወቁ ወታደሮች ደግሞ ጃግኒ ሆስፒታል ለእርዳታ መምጣታቸው የታወቀ ሲሆን እስካሁን ድረስ በአካባቢው ይህ ነው የሚባል ሰላም የለም ብለዋል መረጃውን ያቀበሉን ምንጮቻችን፡፡

አጠቃላይ፤ በአገሪቱ ያሉ ባንኮች አንድ ደንበኛ በቀን ከ10 ሺህ ብር በላይ እንዳያወጣ በአገዛዙ ታዘዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ከንግድ ባንኮች ደንበኞች ገንዘባቸውን ወጪ አድርገዋል፡፡ ይህም በጥቂት ቀናት ብቻ የባንኮች ካዝና ባዶ ይሆናል በሚል ስጋት አገዛዙ ደንበኞች በቀን የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን እንዲወስ እንዳስገደደው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባና በአንዳንድ ትልልቅ ከተሞች 10 ሺህ ብር ይባል እንጅ በብዙ የወረዳና የዞን ከተሞች ከአንድ ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እንዳያወጡ ታግደዋል፡፡

በባሕር ዳር ያሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ለደንበኞቻቸው ለመክፈል ከግል ባንኮች እየተበደሩ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል፡፡

በተያያዘ መረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደርገውን በረራ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሚንስትር እውቅና እንዲሆን ተወስኗል፡፡ አንድ የመንገደኞች አውሮፕለን ከመነሳቱ በፊት በየአካባቢው ያሉ የትግሬ መከላከያ ክፍለ ጦሮች እውቅና ከተሰጠ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቬየሽን መሥሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ተጠልፈው ድንበር የሚሻገሩ የአውሮፕላን አብራሪዎችን በመፍራት የሲቪል አቬሽን መስሪያ ቤት ምንም ሥራ በመከላከያ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ሕዝባዊውን ሰላማዊ አመጽ ተከትሎ በአዲስ አበባ አስኮ አውቶቡስ የለም

$
0
0
አስኮ ሕዝብ አውቶቡስ ጥበቃ ላይ

አስኮ ሕዝብ አውቶቡስ ጥበቃ ላይ

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ 4ኛ ቀኑን የያዘውን የቤት ውስጥ የመቀመጥ እና ያለመገበያየት አድማ ቀጥሎ በአዲስ አበባ አስኮ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት እጥረት እንደተከሰተ ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች ያስረዳሉ::

እንደመረጃዎቹ ከሆነ በአስኮ አካባቢ ሕዝብ ወደ ተለያዩ ቦታዎች ለመዘዋወር አውቶቡሶችን ቢጠብቅም በርካታ አውቶቡሶች በስራ ማቆም አድማ ላይ በመሆናቸው በትራንስፖርቱ ላይ ችግር ፈጥሯል:: ጥቂት የሚባሉ የስ ር ዓቱ አገልጋይ አውቶቡሶችም ሕዝባዊውን ጥሪ ተላልፈው ለመንዳት ቢሞክሩም እርምጃ ስለተወሰደባቸው መንዳት አቁመዋል::

በፎቶ ግራፉ ላይ እንደምታዩት አስኮ አውቶቡስ መጠበቂያ በሕዝብ ተጨናንቃለች::

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች በቢሾፍቱ 3 ወጣቶችን ገደሉ |እናት በአደባባይ ሲያለቅሱ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች 4ኛ ቀኑን የያዘውን ሰላማዊውን ከቤት ያለመውጣትና ያለመገበያየት አድማ ተከትሎ ወትሮም ሰውን ለመግደል የማይራሩት የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች ዛሬ በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ከተማ 3 ወጣቶችን በጥይት ቆልተው መግደላቸው ታወቀ::

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ሕዝብ ሰላማዊ ትግል እያደረገ ቢሆንም የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች እና ስናይፐሮች በየከተማው ፈሰዋል:: በቢሾፍቱ ዛሬ ከተገደሉት 3 ወጣቶች መካከል ሁለቱ ታውቀዋል:: በአጋዚ ጥይት ሰለባ የሆኑቱም ተረፈ ሽብሩ እና በቀለ ዲባባ ሲሆኑ የአንደኛው ማንነት እየተጣራ ነው:: በተጨማሪም በርካታ የቆሰሉ ሰዎች እንዳሉ ይነገር እንጂ ዘ-ሐበሻ ለማረጋገጥ አልቻለችም::

ከዛሬው የቢሾፍቱ ግድያ በኋላ በተለይ የበቀለ እናት በአደባባይ ሲያለቅሱ የሚያሳይ ቪዲዮ ተለቋል ይመልከቱት:: የእናቶች ለቅሶ የሚያበቃው መቼ ነው??

የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ወታደሮች በቢሾፍቱ 3 ወጣቶችን ገደሉ | እናት በአደባባይ እያለቀሱ ነው

የምስራች ለተዋህዶ ልጆች በሙሉ –ቦይኮቱ በሚገባ እየተሳካ ነው |ዘመድኩን በቀለ

$
0
0

✔# የሙዳይምጽዋቱና ✔# የአስራትበኩራት እቀባውም እየተሳካና መስመሩን ይዞ እየሄደ ነው ።
✔በውስጥ መስመር እየደረሱኝ የሚገኙት መልእክቶች እጅግ ደስ የሚያሰኙና ከስኬት ጫፍ የሚያደርሱን መሆናቸውን እያየሁ ነው ። በተለይ በየከተማው የምትገኙ የጽዋ ማኅበራት አጀማመራችሁ መልካም ነውና በዚሁ ቀጥሉበት ።
✔ ወጣቶች ከቤተሰብ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ በደንብ ምከሩበት ። ለወላጆችም በቤት ውስጥ ሁሉን አስረዷቸው ።
✔ ባለ ጊዜዎች ሆይ! በቫይበርና በስልክ እኔን መወትወቱና መለመኑ ዋጋ የለውም ።እስትንፋሴ እስክትቆም ድረስ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከዘር ፖለቲካም እስክትጸዳ ድረስ እሟገታችኋለሁ ። ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት አንላቀቅም ።

በአዲስ አበባና በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የምንገኝ ምእመናን ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ሙዳየምጽዋትና አስራት በኩራታችንን በእጃችን ላይ በማቆየት እነዚህን በእኛው ገንዘብ እንደ ሐረር ሰንጋ እየደለቡ የወገናቸው ሞት የማይሰማቸውን የሃይማኖት ሳይሆን የፖለቲካ ሹመኞች የገቢ ምንጫቸውን ልናደርቅ ይገባል ።

zemedkun
“ልጆቻችሁ አርፈው እንዲቀመጡ አድርጉ ። ያለበለዚያ ግን ወጋችሁን ነው የምንሰጣችሁ ” አይነት ንግግር በመናገር ልባችንን ያደሙትን ፓትርያርክ አባ ማትያስን አዲስ አበባ ቁጭ አድርገን የምንቀልበው እኛው ነን ። ንቡረእድ ኤልያስን ከመሬት ተነስቶ ባለፎቅ ያደረግነው እኛው ነን ። ትናንት ባዶ እግራቸውን ያለምንም ሳንቲም ባዶ እጃቸውን ሲዞሩ የምናውቃቸውን ዛሬ ግን ያለምንም የሙያ መስፈርት የአንድ ብሄርና የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆናቸው ብቻ ወደ ኢንቨስተርነት የተለወጡትን ፣ አስመጪና ላኪም የሆኑ የደብር አለቆች ፣ ጸሐፊ ፣ ቁጥጥርና ፣ ሒሳብ ሹም ፣ ወዘተ በአንድ ቋንቋ እያወሩ ከደሃው ህዝብ ተሰብስቦ በሚገባው ገንዘብ ዓለማቸውን በሚቀጩ ዘራፊዎች ላይ እቀባው ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

እመኑኝ በአሁኑ ጊዜ የአስራት ገንዘቡን ዘወትር በማኅሌትና በሰዓታት በኪዳን ጸሎትና በቅዳሴ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሚያመሰግነው ምስኪኑ ካህን ፍርፋሪ አይደርሰውም ። ቤሳ ቤስቲን አልኳችሁ ምንም አይደርሰውም ። በተለይ ካህናቱና ዲያቆናቱ አማራ ፣ ኦሮሞ ፣ ጉራጌና የደቡብ ተወላጅ ከሆኑ ዋጋ የላቸውም ። እጣፈንታቸው የቀጭን ጌቶቹን ጫማ በመሸከም እንደውሻ እግራቸው ስር ከመለጥመጥ በቀር አንዳች ማድረግ አይቻላቸውም ።

የሚገርመው አንድም ቀን በማኅሌቱ ላይ ሳይታዩ ቅዳሴም ሳይገቡ ቤተክርስቲያንም ሳይደርሱ እቤታቸው ቁጭ ብለው ከሁለትና ከሦስት አብያተክርስቲያናት ደሞዝ የሚበሉ ደፋሮች አሉ ። ምክንያቱም ” ምርጥ ዘርና ባለጊዜዎች ” ነን ብለው ለራሳቸው ልዩ ያልተጻፈ ህግ አውጥተው ስለሚኖሩ ።

እነዚህ አለቆች አብዛኛዎቹ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ታጋይ ወታደሮችም ጭምር ስለሆኑ ፖሊስን ያዛሉ ፣ አግአዚን ይጠራሉ ፣ ሰንበት ትምህርትቤቶችን እንደፈለጉ ይዘጋሉ ሲፈልጉ ያሳስራሉ ይበትናሉ ። ምክንያቱም እነሱ ካድሬና የፓርቲ አባል አይነኬ አይጠጌ ስለሆኑ ማለት ነው ።

እናም እነዚህ ሰዎች አፍ አውጥተው መንግሥትን ህዝቡን አትግደል ፣ በእስር ቤት አጉረህ በእሳት አቃጥለህ አትጨፍጭፍ አይሉትም ። ምክንያቱም እነሱም የፓርቲው አባላት ስለሆኑ ፓርቲያቸውን ከመታደግ አንጻር ምህላና ጸሎት ያዛሉ ተብሎም አይጠበቅም ። እንዲያውም እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ቀይረው ማታ ማታ በየ መሸታ ቤቱ እንደሚንዘላዘሉት የፖሊስ ልብስ ለብሰው ሰላማዊ ሰልፈኞችን በመግደሉ በኩል ተሳታፊ አይሆኑም ብዬ ላለማመን አልሞክርም ።

እናም ወገኖቼ እነዚህን ደም መጣጮች፣ መዥገሮችና የቤተክርስቲያን ነቀርሳዎችን ከቤተክርስቲያን ትከሻ ላይ አራግፈን የመጣያው ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው ።
ለእነዚህ ዘረኞች የሆኑ ምድብ ፖለቲከኛና በስመ የሃይማኖት አባትነት በቅድስት ቤተክርስቲያን ተሰግስገው ለተቀመጡ ሰዎች የአስራት ገንዘቡን ገታ አድርገን ካልያዝነው ለእነሱ ለክ እንደ አባይ ወንዝ ያለ ነው ። ልክ እንደ ሳውዲ አረቢያ የነዳጅ ጉድጓድ ያለ ነው ። ከአሜሪካ ዶላሩ ፣ ከእንጊሊዝ ፓውንዱ ፣ ከአውሮጳ ዩሮው ፣ ከእስራኤል ሸክሉ ፣ ከስዊዝ ፍራንኩ ፣ ከአረቢያ ምድር በየሰው ቤት በእሳት ተቃጥለው የሚልኩት ሪያል የእነዚህ ማደለቢያ ነው ።

እና አስራቱን ምን እናድርግ ?
ለሱ መፍትሄው ቀላል ነው ።
1ኛ፦ ምስኪን ካህናትና ተንከራታች ደጅ ጠኚም ሆነው ረሃብ የሚያሰቃያቸውን አባቶችን እስከ ጊዜው ድረስ እነሱንም ቤተሰባቸውንም መርዳት ። በተለይ በተለይ ቤተሰብ ያላቸውንና በቤትኪራይ ውስጥ የሚኖሩትን ፣ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ካህናትን በንስሐ ልጆቻቸው በኩል መርዳት ።
2ኛ፦ የቤተክርስቲያን ተተኪ የሚያፈሩትን የአብነት ትምህርት ቤት መምህራንን እና ተማሪዎችን በመርዳት ጉባኤ ቤቶች እንዳይፈቱ ማድረግ ።
3ኛ፦ እንደ ዋልድባ ያሉትን በችግር ላይ የወደቁና ሊበተኑ የደረሱ ስመጥር ገዳማትን የሚያስፈልጋቸውን በማቀረብ ገዳማቱ ሳይፈቱ እና ገዳማውያኑም ሳይበተኑ በአስራት ገነረዘቡ መርዳት ።
4ኛ፦ እንደ ደጆችሽ አይዘጉ አይነት የሚታይና የሚዳሰስ አሳማኝ ሥራ የሚሠሩ ማኅበራትን በሚገባ በተጠናከረ መንገድ መርዳትና መደገፍ ።
5ኛ፦ እንደ መቄዶንያ የአእምሮና የህሙማን መርጃ ማእከል ያሉትን ፣ ጌርጌሶኖን ፣ የወደቀ አንሱ የመሳሰሉት በየጎዳናው በረሃብ የሚሰቃዩትን አረጋውያን እና ህጻናትን እርዱበት ።
ይሄን በማድረግ በዝባዦችን እንቅጣ ።
ይህን እቀባ በመቃወም በዚህ በእኔ ፔጅ ላይ ፒሪሪም ፓራራም ታራራራም እያሉ የሚያላዝኑ እነ ገብረምናምንን ፈጽሞ አልሰማችሁም ።
አሁን በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ስላለው ግፍና መከራ ለመናገር እውነት እውነት እላችኋለሁ ሰባኪም ፣ ፖለቲከኛም ፣ አትሌትም ፣ ሆነ ግንበኛ ፣ መሆንን አይጠይቅም ። ” ጉዳዩን ለመቃወም ሰው መሆን ብቻውን በቂ ነው ” ።
እኔን የየሚደንቀኝ ይህን መልእክት እንኳ እያዩ እየተመለከቱ ሼርና ኮመንት ለመስጠት እንኳ በፍርሀት ቆፈን መታሠራቸው ነው ።
ጉዞው እስከ ቀራንዮ ነው ፣ ድል ለእምዬ ተዋህዶ !!! ወድቀት ለዘረኞች ።
ይህንንም ራሴው ዘመድኩን በቀለ ጻፍኩት ።ለማንኛውም በነጻነት እንወያይ ከስድብና ከዛቻ በራቀ መልኩ እንነጋገር ። +251911608054 የቫይበር ስልኬ ነው ። በተለይ ይህን መልእክቴን በተመለከተ ደግሞ ✔Coment መስጠትና
✔Share ማድረግ በእጅጉ ይበረታተል ።
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ጷግሜን 4 /13/2008 ዓም
ኮሎኝ – ጀርመን

የህወሓት አባላት እና ደጋፊዎች አምስቱ ግለሰባዊ እና ተቋማዊ ጠባዮች

$
0
0
ከጌታቸው በቀለ | ጉዳያችን
መነሻ 
ህወሓት በትግል ወቅት ለእርዳታ የመጣውን እህል በጎን ስትሸጥ የሚያሳይ (ፎቶ ቢቢሲ

ህወሓት በትግል ወቅት ለእርዳታ የመጣውን እህል በጎን ስትሸጥ የሚያሳይ (ፎቶ ቢቢሲ

በእዚህ ፅሁፍ ውስጥ የህወሓት አባላት እና ደጋፊዎች ማለት እራሱን የሕዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ ብሎ የሚጠራው ድርጅት አባላት እና ደጋፊዎች ማለትም እራሳቸውን በግልፅ እና ስውር አባልነት የሚንቀሳቀሱ፣በተለያየ ጥቅሞች ሕልውናቸው ከድርጅቱ ጋር የተሳሰረ እንደሆነ የሚያምኑትን ሁሉ ያጠቃልላል። እዚህ ላይ ´´ህወሓት ማለት የትግራይ ሕዝብ ነው የትግራይ ሕዝብ ማለት ህወሓት ነው´´ የሚለውን የሳሞራ የኑስ ንግግር ተከትለው የሚያስቡ ካሉ ቢያንስ እኔ በአሁኑ ሰዓት እዚህ ድምዳሜ ላይ ስላልደረስኩ የሳሞራ እና አድናቂዎቻቸው ሃሳብ ሆና ትቆይ። በእዚህ መንገድ የሚያስቡ የማሰብ መብታቸውን እያከበርኩ ጊዜ የሚፈታው ስለሆነ በእሱ ላይ ጊዜ መውሰድ አልፈለኩም።ሆኖም ግን ይህ ፅሁፍ እራሳቸውን በቆይታ፣በስልጠና እና ባላቸው ማኅበራዊ ግንኙነቶች ሁሉ የህወሓት አባላት እና ደጋፊዎች የተላበሷቸውን አምስቱ ግለሰባዊ እና ተቋማዊ ጠባዮችን  ለመግለፅ እሞክራለሁ።እነኝህ አምስት ጠባዮች ከከፍተኛው እርከን እስከ ታች ያለው ካድሬ ድረስ በመጠን እየተለያዩ የሚንፀባረቁ ናቸው።ሆኖም ግን እያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸውን በንቃት መገንዘብ እና መመልከት ይጠይቃል።
የእዚህ ፅሁፍ አቅራቢ እነኝህን ፀባዮች እንዲሁ በግምት የሚያቀርባቸው ሳይሆኑ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ ባለበት ጊዜ በሥራም ሆነ በማኅበራዊ እና ቤተሰባዊ ግንኙነት ሁሉ የተመለከተው ምልከታ ስለሆነ ፅሁፉ በተራ ግምት እና መላ ምት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን መገንዘቡ ተገቢ ነው። 
 
አምስቱ  ፀባዮች 
1. ድብቅነት
ህወሓት አባላት፣ደጋፊዎች እና ድርጅቱ እራሱ ሕይወታቸው የተመሰረተው በድብቅነት ላይ ነው።ሀብታቸው፣ የሚሰሩት ሥራ፣ ማንን እንደሚወዱ እና እንደሚጠሉ ሁሉ በግልፅ ለእራሳቸው ሰው ካልሆነ በቀር አይገልጡም።ለምሳሌ አንድ ከእነርሱ ካምፕ ውጭ የሆነ ሰው ምን ያህል ጥሩ እና ምክንያታዊ ቢሆን ስለ ጥሩነቱ እና ምክንያታዊነቱ ከሚከራከሩት ይልቅ ቀድመው በተደበቀ ጥላቻ ውስጥ ሆነው ለሌላ ሰው ግን ጥሩነቱን ይናገራሉ።እዚህ ላይ አንዳንድ ማስረጃዎች ልጥቀስ።አቶ መለስ አቶ አዲሱን በአደባባይ ሲያሞግሱ ትሰማላችሁ።አቶ አዲሱ በአቶ መለስ ሞት ላይ አልቅሰዋል።አቶ መለስ ግን አቶ አዲሱ ከስልጣን የወረዱ ቀን ´´ኢትዮ ፈርስት´´ በአቶ አዲሱ መሰናበት ምን ተሰማዎት? ሲባሉ አቶ መለስ ´´ብዙ ሳይዘባርቅ መውረዱ ´´የሚል ቃል ሳያስቡት ተጠቀሙ (ይህ በዩቱብ መመልከት ይቻላል)። የአቶ መለስ ፈገግ እያሉ መግደል የህወሓቶች የተለመደች የድብቅነት ሕይወት አንዱ መገለጫ ነው።
ሌላው የድብቅነት መገለጫ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ክስተቶች ውስጥ እራሳቸው ፈፅመው ሌሎች እንዳደረጉት የሚሰሩት ድራማዎች ናቸው።አሁን እየታወቀ መጣ እንጂ በአማራው ሕዝብ በደቡብ ክልሎች መሰደድ፣መገፋት ጉዳይ ሁሉ ከጀርባ የሕግ ድጋፍ ሲሰጡ የነበሩ የህወሓት ሰዎች ናቸው።ይህ የድብቅነት ጠባይ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት አንዱ ማሳያ ደግሞ ከአቶ መለስ በኃላ ውሳኔ ሰጪው አካል ተሰውሮ ውሳኔ እየሰጠ አቶ ኃይለ ማርያምን ከፊት ማስቀደሙ ነው።አሁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየተሰሩ ያሉ በርካታ ድብቅ ስራዎች እንደሚኖሩ ካለፉ ታሪኮች መረዳት ይቻላል።
2/ ተንኮል እና ሴረኛነት
ተንኮል እና ሴራ በህወሓት እና በአባላቱ ዘንድ እንደ ትልቅ ዝና እና ገድል ይቆጠራል።ይመስለናል እንጂ የአቶ መለስ አድናቂዎች ህወሓቶች እና ደጋፊዎቻቸው አቶ መለስን የሚያደንቁበት ዋና ምክንያት እና እነርሱ በአደባባይ ´´ችሎታ´´የሚል ሽፋን ይስጡት እንጂ ብዙ ህወሓቶች እና ደጋፊዎች የሚያደንቁበትን መንገድ ጠጋ ብላችሁ ስትጠይቁ  የሚነግሯችሁ በህወሓት ላይ ያንዣበበው የስልጣን ተግዳሮቶች ሁሉ አቶ መለስ እንዴት በተንኮል እና በሴራ እንደተሻገሩ ሲናገሩ ትሰማላችሁ።ለእዚህም የ1997 ዓም ከቅንጅት ጋር ያደረጉት ድርድር እና ክህደር እንደ ትልቅ ገድል ሲወራ መስማት በህወሓት መንደር መስማት የተለመደ ነው። ስለዚህ ተንኮለኛ እና ሴረኛ የህወሓት አባልም ሆነ ደጋፊ እንደ ትልቅ ዝና ይነገርለታል።በጤናማው ዓለም ግን ይህ የክፉዎች ተግባር ነው።ለእዚህ ነው የሚሰሩትን ተንኮሎች እና ሴራዎች በተመለከትን ቁጥር በማኅበራዊ ሚድያ ሁሉ ሳይቀር በጤነኛ ዓለም አስተሳሰብ እሳቤ እያሰብን ስንብከነከን እንውላለን።ለሕወሐታውያን ግን ይህ ከትልቅ ጀብዱ የሚቆጠር ነው።
እስረኛ ሊያመልጥ ሲል ገደልነው፣እሳት በእስር ቤቱ ውስጥ ተነሳ፣ ታክሲ ውስጥ አሸባሪ ቦንብ አፈነዳ፣ በሀውዜን እና ሐሙሲት ገበያ ላይ አይሮፕላን ደበደበ፣ የኦሮምያ ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ኩምሳ አረፉ፣ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ እስር ቤት ለሞት የሚያደርስ ህመም ታመሙ፣ የብሔራዊ ባንክ ወርቅ ተዘረፈ፣ ይቀጥላል በርካታ ጉዳዮች የተንኮል እና የሴረኝነት ውጤቶች ብዙ ናቸው።ህወሃታውያን ደግሞ  በእዚህ ሁሉ ተንኮል ይቁራሩበታል።በግለሰብ ደረጃ ስታገኙአቸውም ተንኮልን እንደ ትልቅ እውቀት ይቆጥሩታል።
ህወሓቶች እና ደጋፊዎቻቸው ተንኮል እና ሴራ ሲሰሩ እየሳቁ ነው እንጂ በተጨማደደ ፊት አይደለም።የአገሬ እና የድርጅቴ ሰው አይደለም ባሉት ላይ ግን ተንኮል ሲያደሩ የሚጀምሩት ከቤተሰብ ነው።የመጀመርያ ኢላማቸው ቤተሰቡን መከፋፈል ነው።የህወሐቶች ሰለባ የሆኑ በርካታ ቤተሰቦች እና ወዳጆች ባላወቁት መንገድ ተቃቅረው ቆይተው ጉዳዩን ሲመረምሩት የወያኔ ሴራ እንደሆነ ይረዱታል።በህወሓት ዘንድ የምትናቅ እና የተንኮል ድር የማይደራባት ትንሽ መርፌ የለችም።በአንድ ድርጅት ውስጥ ከበር ካለው ዘበኛ እስከ የበላይ አለቃ ድረስ ተንኮል ለመሸረብ ደጋፊዎቻቸውን በማሰለፍ ታጥቀው ይነሳሉ።የኢትዮጵያ ቴሌ መስርያቤት፣ የመብራት ኃይል፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ሌሎችም በህወሓት የዘር መርዝ ተወግተው የቆሰሉ እና በርካታ ባላሙያዎችን እየወጉ እና ባላጠፉት ጥፋት እየወነጀሉ ከስራ አባረዋል፣የበይ ተመልካች ሆነዋል።በዘመነ ህወሓት  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለት ሥራ አስኪያጆች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ ሥራ አስኪያጅ እንዴት ሥራ እንደለቀቁ  ማስታወስ በቂ ነው።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ አስኪያጅ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ እና 90ዎቹ መጀመርያ የነበሩት በእስር እንዲማቅቁ የተደርጉበት እና ሌላው ሥራ አስኪያጅ ጧት በመኖርያ ቤታቸው ሞተው የተገኙበት ሁኔታ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስኪያጅ በመሆን ያገለገሉ ግለሰብ እንዴት ስራቸውን እንዲለቁ እንደተደረገ ለአብነት ማንሳቱ የህወሓትን ተንኮል እና ሴራ ግልፅ አድርጎ ያሳያል።
3/ ሰው መሳይ በሸንጎነት
ህወሓቶች እና ደጋፊዎቻቸው የሚታወቁበት እና የትካኑባት አንዷ መንገድ በሰው ፊት እና በአደባባይ ሰው መስሎ መታየት ነው።ህወሓት በውጭ ዓለም ስሙ በክፉ ሲነሳ የሚያመውን ያህልምንም አያመውም።ግለሰቦቹም እንዲሁ ናቸው።በአደባባይ ስትመለከቷቸው የሃይማኖት ሰዎች፣ወደ እምነት ቦታዎች አዘውትረው በመሄዳቸው ቀድመው የሚታዩ፣ ፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ የክርስቲያንም ሆነ የእስልምና እምነት ዋጋ የሚሰጣቸውን ነገር ሁሉ በመለጠፍ ፍፁም ሃይማኖተኛ ለመምሰል የሚቀድማቸው የለም።በማኅበራዊ ኑሮም ቀድመው ልሙት ባይ ይሆናሉ።ይህ ሁሉ ግን ከሀዘነታ ሳይሆን ከስልት አንፃር ብቻ የሚፈፅሙት መሆኑን ቆይታችሁ ጥረዱታላችሁ።
አንዲት በፈስ ቡክ ገፅ ላይ ነጠላ ለብሳ ወይንም ስትፀልይ የምታዩአት ወይንም የምትመለከቱት የህወሓት አባል ወይንም የተባይ ተጋሪ በገሃዱ ዓለም ላይ ያላቸው እምነት ያስደነግጣል።እነኝሁ ሰዎች በአደባባይ ስለሚሞተው ሕዝብ ስታወሯቸው የሃይማኖታቸውን አማልክት በመጥራት ስለምሞተው እና ስለሚታሰረው ሕዝብ አንዳች ጉዳይ እንደሌላቸው በድፍረት ሲናግሩ አፋቸውን አያደናቅፋቸውም።
4/ ዘረኝነት 
ለህወሓት እና ደጋፊዎቻቸው የእነርሱ መንደር ብቻ የበላይ አድርጎ የሚጠቀሙበት አንድ አባባል አለ። ´´ምንትስ አስር ይውለድ´´ የምትል።በግለሰብ የህወሓት አባላትም ሆኑ ደጋፊዎች ዘንድ ከእነርሱ መንደር ውጭ ላለ ሰው መጀመርያ ሞቅ ያለ ፈገግታ ሲያሳዩ ትመለከታላችሁ።በአጋጣሚ ዘወር ካላችሁ ፊታቸው በጥላቻ ሲገላምጧችሁ ትመለከቱና ፈገግታው የውሸት መሆኑን ትረዳላችሁ። በምንም ደረጃ የሚገኝ ሰውን በሰውነቱ ብቻ መመልከት ክልክል መሆኑ በህወሓት መንደር የተከለከለ ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው በጠባዩ፣ በመልካም ስራው፣ በችሎታው ሳይሆን ቀድመው የሚፈርጁት ከእነርሱ ሰፈር በመወለዱ እና ባለመወለዱ ነው። እነርሱ መንደር ከተወለደ እንደ አዋቂ፣ አስተዋይ እና የኢትዮጵያ ጠቃሚ ዜጋ እንደሆነ ያስባሉ ብቻ ሳይሆን ይደመድማሉ።ለምሳሌ አንድ መስርያ ቤት ውስጥ ሄደው ያገኙት ሰራተኛ ከእነርሱ መንደር ካልተወለደ በመስርያ ቤቱ ውስጥ የተቀጠረው የሆነ ተንኮል በህወሓት ላይ ሊሰራ እንጂ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር ነው ብለው ላለማመን አይምሯቸውን ዘግተውታል።
የህወሓት እና ደጋፊዎቹ ዘረኝነት የሚገለፀው በተለያየ መንገድ ነው።ከእነዚህ ውስጥ ዋነኛው እና አንዱ የእነርሱ ያልሆነ ያሉትን ማግለል እና አድልዎ መፈፀም ነው።በግለሰብ ደረጃ ያገሏችኃል።በንግድ ድርጅት ደረጃ፣በእምነት ድርጅት ደረጃ፣በማኅበራዊ ግንኙነት ሁሉ ያላቸውን ትስስር የሚፈፅሙት ´´በመንደር ውልደት´´ ከሚመስላቸው ጋር ብቻ ነው።አንድ ሰው የቱንም ያህል መልካም ሰው መሆኑ በጥላቻ እና ማግለል መርዝ ከመነደፍ አያድነውም።ይልቁንም ትውልዱ እየተጠቀሰ ይነቀፋል፣ ሲብስ ደግሞ ከአሸባሪ አይ ኤስ ኤስ ጋር ሁሉ እየተነፃፀረ ይሰደባል። እራሳቸውን የተለዩ ፍጥረቶች አስመስሎ ለማቅረብ መሞከር እና መኮፈስ የሕወሃቶች እና ደጋፊዎቻቸው ዋነኛ መለክያ ነው።
የህወሓት ዘረኝነት አይን ያወጣ እና እፍረተ ቢስ በሚባል ደረጃ የታየ ነው።የጦር ሰራዊቱን መኮንኖች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ፣የአዲስ አበባ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ፣ከፍተኛ የመንግስት ሹሞች እና ቁልፍ ቦታዎችን፣ከፍተኛ የንግድ ስራዎችን፣በውጭ አገራት የሚገኙ ኤምባሲ ሰራተኞች እና አምባሳደሮችን ሲወርድ በአዲስ አበባ በቀበሌ ደረጃ ሊቀመንበሮች እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሻንጣ አውራጅ እና ጫኝ ድረስ ከአንድ አካባቢ የመጡ መሆናቸውን ብቻ መጥቀሱ የጉዳዩ አሳፋሪነት እና አይን አውጣነት በሚገባ ያሳያል።
5/ ስግብግብነት 
ህወሓት እና ደጋፊዎቹ የሚለዩበት አንዱ ፀባይ ስግብግብነት ነው።እነርሱ ያልቀደሱት ቅዳሴ እንደማያርግ፣እነርሱ ሃሳብ ያልሰጡበት የጥናት ወረቀት እንደማይሳካ፣ እነርሱ በሽርክና ያልገቡበት ኩባንያ እንዲፈርስ፣እነርሱን የማያወድስ ፅሁፍ አሸባሪ፣ ለእነርሱ ድርጎ ያልሰጠ ነጋዴ አጭበርባሪ በማለት ሁሉም ቦታ መግባት ይፈልጋሉ። እድር ውስጥ፣ጉልት የምትሸተውን፣የቀን ሰራተኛውን ሌላው ቢቀር እራሳቸው የሾሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይቀር ከምህዋራቸው የሚወጣ ስለሚመስላቸው ተስገብግበው ሁሉም ላይ ለመታየት ይፈልጋሉ።
በገልሰብ ደረጃ ስትመለክቷቸው እምነት ቤቱ ቀድመው ፃድቃን ለመሆን ከመስተንግዶ እስከ መዝሙሩ፣ ከእርዳታ ሰጪ እስከ ወጥ ቤት ሁሉ ፊታቸውን ማስመታት ስራዬ ብለው ይይዙታል።በተለይ የኅብረተሰቡ የጋራ መገለጫዎች እንደ እድር፣አብያተ ክርስቲያናት፣መስጊዶች፣ የንግድ ማኅበራት፣የሰራተኛ ማኅበራት፣ ሌላው ቀርቶ የቤተሰብ ማኅበራት ውስጥ ሁሉ ምን እንደሚደረግ ለማዳመጥ እንዲገቡ ይደረጋሉ። ህወሓቶች ይህንን የሚያደርጉት ከላይ የተጠቀሱት ድብቅነት፣ተንኮል እና ዘረኘነት ከማኅበረሰቡ መልካም ባህርያት ጋር ፈፅመው የተቃረኑ ስራዎች እንደሆኑ ስለሚያውቁ በከፍተኛ የራስ መተማመን እጦት እና ጥርጣሬ ማዕበል ይመታሉ። ስለሆነም  የታክሲ ሹፌሩም ሆነ ተሳፋሪው፣አስተማሪውም ሆነ ተማሪው፣ ዲያስፖራውም ሆነ የአገር ነዋሪውን ሁሉ ይጠረጥራሉ።ለእዚህ ነው አንድ ኮሽታ በተሰማ ቁጥር በእነርሱ አጠራር ጠላቶቻቸው እስከ ሚኒስቴር ማዕረግ ደረጃ ድረስ እንደ ገቡባቸው በፍርሃት እና በድንጋጤ የሚናገሩት።
ባጠቃላይ ህወሓት እና ደጋፊዎቹ ከላይ የጠቀሱትን አምስት ጠባዮች ሲይዙ በአንድ ቀን እና ምሽት የመጡ ሳይሆኑ ለእራሳቸውም ሳይታወቃቸው ቀስ በቀስ በድርጅታቸው ደረጃ እና በግለሰብ ደረጃ ያደጉ ናቸው።ይህ ግን ለእነርሱ ላይታወቅ ይችላል።ይህ ደግሞ አሁን ያደረሳቸው ደረጃ እራስን ዝቅ አድርጎ ከማየት የመነጨ አጉል ጀብዱ የተቀላቀለበት ፍፁም ጭካኔ ቀድሞ ከነበረው አድጎ እና ገዝፎ ወደ ባሰ ፋሽሽታዊ ደረጃ አሻግሯቸዋል።ለእዚህ ማሳያዎቹ ሰሞኑን በኦሮምያ፣ጎንደር እና ጎጃም የሚፈፀሙት አረመንያዊ ድርጊቶች ናቸው።ግድያዎቹ የፍርሃት፣በእራስ ያለመተማመን እና ከፍርሃትም የሚመነጩ ናቸው። አንዳንዶች ደጋፊዎቻቸው አረመንይያው ድርጊቶችን እንደ ጀግንነት ሲቆጥሩላቸው ይስተዋላል። ይህ ግን ትክክል አስተሳሰብ አይደለም።በእራስ መተማመን ያለው እና አቅም ያለው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የእራሱን ወገን በመፍጀት እርካታ እና ጀግንነት ሊሰማው ባልተገባ ነበር።ለእዚህ አይነቱ የህወሓት ፀባያት መፍትሄው ስርዓቱ እራሱን ጠግኖ ሌላ አውሬ እንዲሆን መፍቀድ በአገርም ሆነ በሕዝብ ላይ እንደመቀለድ ይቆጠራል። ህወሓት እንደ ድርጅት እና ደጋፊዎቹ በርካቶችን እየወጉ ገድለዋል፣በየዋህ ልቦና የቀረቧቸውን በፈገግታ መርዝ እያስላሱ አምክነዋቸዋል። ለእዚህ ማሳያ እንዲሆን አንድ ጉዳይ ብቻ አንስቼ ላብቃ።ሰሞኑን በኢትዮጵያ በህወሓት እና በቀረው ሕዝብ መካከል ያለው ግብግብ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ እና አቶ በረከትን ጨምሮ በጎንደር ሲኒማ አዳራሽ በጠሩት ስብሰባ ዱላ ቀረሽ ንግግር እና እሮሮ በመጨረሻም አዳራሹ በድንጋይ ተደብድቦ ሾልከው አዲስ አበባ መጥተው ሳለ። በሕወሓታዊ ሽሩድ አቀራረብ አቶ አባይ ፀሐዬ፣በረከት ስምዖን፣ዶ/ር ካሱ ኢላላ እና አባ ዱላ አይናቸውን በጨው አጥበው፣የውሸት ፈገግታ እያሳዩ እና እየተቅለሰለሱ ስልጣን አንልቀቅ ግን እንታደስ የሚል አጀንዳ ይዘው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ብቅ አሉ። ህወሓቶች ማለት እንዲህ ናቸው።ያልተመቻቸው ጊዜ ስያሞግሱ ያሰሙሃል ዘወር ስትል የመውጊያ እና የጥላቻ ጦራቸውን ይስላሉ።ሕዝብ በ1997 ዓም ሆ! ብሎ ሲነሳ እንደራደር ይሉሃል።ጉዳዩ የበረደ ሲመስላቸው ´´ኢህአዴግ ሾላ አይደለም በድንጋይ የሚወርደው´´ይሉሃል። እነአቶ በረከትም ነገረ ህወሓትን በካድሬ አንደበታቸው ሊያነበንቡልህ በኢቲቪ መስኮት ቀለስለስ እያሉ የቀረቡት ለማታለል እንጂ በተመሳሳይ ሰዓት ግድያ እና እስር በንፁሁ ኢትዮጵያዊ ላይ እየተፈፀመ ነው።ህወሓት እና ደጋፊዎቹ በጋራ የምጋሯቸውን ፀባያት ከድርጅት እስከ ግለሰቦች ድረስ በጥንቃቄ መመልከት እና መከላከል የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው።ህወሓትን በሚገባ እወቁት።ደጋፊዎች ጋሻ ጃግረዎችንም ፀባይ ተረዱ።ፈፅሞ ከኢትዮጵያዊነት ባህሪ የተለየ መሆኑን ትረዳላችሁ።

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com


በቺካጎ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሕወሓት መንግስት የተገደሉ ወገኖቻቸውን በጸሎትና ሻማ ማብራት አሰቡ

$
0
0

foster-beach

(ዘ-ሐበሻ) በኢሊኒዮስ ግዛት ቺካጎ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት በትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የተገደሉ ወገኖቻቸውን በአንድ ላይ ተሰባስበው በጸሎት እና በሻማ ማብራት ማሰባቸውን የዘ-ሐበሻ የቺካጎ ወኪል ጋዜጠኛ ዘላለም ገብሬ ዘገበ::

ዛሬ በቺካጎ ከተማ ፎስተር ቢች የተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን ለወገኖቻቸው የሻማ ማብራት እና የጸሎት ፕሮግራም ካደረጉ በኋላ እጃቸውን ወደ ላይ በማጣመር በሃገር ቤት እየተደረገ ያለው ትግል አጋርነታቸውን አሳይተዋል::

በሕወሓት መንግስት የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ቃል የገቡት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ለትግሉ የሚያስፈልገውን ነገር ለማድረግም ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል:: አዲሱን ዓመት በደስታ ሳይሆን ጥቁር በጥቁር በመልበስ በሃዘን እንደሚያሳልፉም አስታውቀዋል::

ch

ሰበር ዜና: ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ቃለምዕዳን አስተላለፉ “ይህ ቀን ያልፋል፣ ገዳዮቹም ሆኑ ሥርዐታቸው ያሻራሉ፣ ኢትዮጵያ ግን ትኖራለች”

$
0
0

Ledet Message from His Holiness Abune Merkorios

(ዘ-ሐበሻ) አባ መርቆሬዎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወ ፓትርያርክ ዘ-ኢትዮጵያ አዲሱን ዓመት በማስመልከት በወቅታዊው የሃገራችን እና ሕዝቦቿ ሁኔታ ባለ 6 ነጥብ መልዕት አስተላለፉ:: “ይህ ቀን ያልፋል; ገዳዮቹም ሆኑ ሥርዐታቸው ይሻራሉ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ምን ጊዜም ገዳዮቹን ድል ነስቶ፣ ሃገሩን አስከብሮ በአንድነት እንደሚኖር እግዚአብሔርና ታሪክ ምስክር ናቸው” ብለዋል::

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ | PDF

ምነው! ፈጣሪ አምላክ!

$
0
0
mothers
አላለቅስም ያልኩት …
 እንባ የፈሪ ነው ብዬ ዋጥ ያ’ረኩት፣
አይቻል ተችሎኝ ይዤው የከረምኩት፣
ገንፍሎ ወጣና እንባዬ ፈሰሰ
ጉንጮቼን ሰንጥቆ ፌቴን አዳረሰ
በዛ እንባዬ መሀል አንገቴን አቅንቼ
ለፈጣሪ ጮኽኩኝ! እጆቼን ዘርግቼ
ምነው? ፈጣሪ አምላክ ምነው! ረሳኸን
ምነው! ይሄን በደል አላይልን አልከን
ምነው ? የኛን ጩኸት ሰምተህ ጨከንክብን
ብዬ ወተውትኩት አልኩበት እዬዬ
አሁንም ይፈሳል አልቆመም እንባዬ
ምነው! ፈጣሪ አምላክ! …
ወለላዬ

ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ ሃረር ካምፓስ በእሳት ነደደ

$
0
0

screen-shot-2016-09-10-at-2-01-20-am

(ዘ-ሐበሻ) በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ሃረር ካምፓስ የእሳት አደጋ ተነስቶ የሃረር ካምፓስን ማውደሙ ተዘገበ:: እንደዘገባዎች ከሆነ እስካሁን የተጎዳ ሰው እንዳለ ሪፖርት አልተደረገም::

በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ በዚህ አመት ብቻ ከ3 ጊዜ በላይ እሳት መነሳቱ የሚታወስ ሲሆን የትናንት ሌሊት መነሻው ያልታወቀ እሳት ቃጠሎ ሐረር ካምፓስ የተማሪዎች መኝታ ክፍሎችን አውድሟል::

ተማሪዎቹ ለዜና ምንጮች እንደገለጹት እሳቱ እንደተነሳ የ እሳት አደጋ እንዲመጣ ብንጠራም አጋዚ ወታደሮችን ላኩብን ሲሉ ተናገረዋል::

ቡዳ በፀበል እንጂ በሽምግልና አይለቅም። –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

woyane-satenaw-news-65ቡዳ እርኩስ መንፈስ ነው። ሰው ውስጥ ሳይፈቀድለት ይገባል። የሱ ባልሆነ ሰውነት ውስጥ ያለፍቃድ ገብቶ  ሰውን ሲያሰቃይ፣ ሲያንገላታ፣ እስከሞት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት ሲያደርግ ያለሰውየው ፈቃድ ነው። ያለፈቃድ በግድ በኃይል የገባው ቡዳ በየትኛውም መሸማገል አልያም ልመና አልያም መልካም ፈቃድ ከሰው ሰውነት ውስጥ አይወጣም። የመጣውም በግድ ነው የሚወጣውም በኃይል ነው። ቡዳ  ከሰው ሰውነት ውስጥ ሊወጣ  የሚችለው በፀበል ኃይል በአባቶች ሲገደድ ብቻ  ነው። ከቡዳው ኃይል የጸበሉ ኃይል ስለሚበልጥ ጸበሉ ሲነካው የተማጽኖ ቃላቶችን ያወጣል። እለቃለው፣ ዳግም አልመጣም፣ ተቃጠልኩኝ፣ የመሳሰሉትን በመለፍለፍ ከሰው ሰውነት ውስጥ ለቆ ይወጣል። ቡዳ ልመና አልያም ትህትና አይገባውም ቡዳ አሸናፊ የሚመስለው እና በሰው ሰውነት ውስጥ ነግሶ የሚኖረው ወደ ፀበሉ ኃይል ባለመሄድ ግዜ ስንሰጠው ብቻ ነው።

 

ወያኔ ሲጨንቀው እና  ሲጠበው መቀልበሻው ሲጠፋው የማያደርገው ነገር እንደሌለ 25 አመት ወደኃላም ከተጓዝን 42 አመት እየሰራ የመጣው ግፍና በደል ማሳያ መሆን ይችላል። የራሱን ልጆች ጭምር እየበላ እና እያስበላ የመጣ አሁንም የሚፈጽመው ቅጥ ያጣ ግፍ መገለጫው  ሆኖ  ስልጣኔን ሊያሳጣኝ ነው የሚላቸውንና ለአደጋ ያጋልጡኛል ብሎ የሚያስባሸው ሁሉ ለማጥፋት ወደኋላ የማይል ቡድን ነው። የህዝቡ ቁጣ ያስደነገጠው እና ህዝቡ ከወያኔ ጋር ያለውን መስመር መቋረጡን የተገነዘበው ወያኔ  በሃይማኖት አባቶች እንዲሁም በአገር ሽማግሌዎች በኩል በመምጣት  ህዝቡን ለማረጋጋት ሲሞክር የአሸማጋዮቹ ፍቃደኝነት በእባብ ልቦና ውስጥ ስይጣን በማደር ለአዳምና ሄዋን ሞት እንዳመጣባቸው ሁሉ ዛሬም በእናንተ ሽምግልና ውስጥ ወያኔ አድሮ ለህዝባችን ሞት ለማምጣት የምትሰሩ ሸፍጥ ይቅር የማይባል በኢትዮጵያን  ህዝብ ላይ ለሚደርሰው ጥፋት ተጠያቂ እንደሆናችህ ለማሳሰብ እንወዳለን።

 

እነ ሃብታሙ አያሌው፣ ተስፋሁን ጨመዳ (በህይወት የሌለ)የመሳሰሉት በፖለቲካ አመለካከታቸው በየእስር ቤት ህክምና የማግኘት መብታቸው ተገፎ በህመም እየተሰቃዩ ለሞት በመዳረግ እና እስከ ሞት አፋፍ ስቃይ ድረስ መከራ ሲፈጸምባቸው ምነዋ  ማሸማገል አቃታቹ? የነዚህ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ስቃይ እንደሚፋረዳችሁ ማወቅ እንዴት  ተሳናችሁ?

 

እናንተ አሸማጋዮች በህግ ጠለላ ስር ያሉ እስረኞች ላይ ዝምታችሁ ከምን የመነጨ ነው? በነገራችን ላይ ሙሁሩ እና  አገር ሊመሩ የሚችሉት የኢትዮጵያ  ልጆች እስር ቤት ውስጥ  ሲሆኑ ደደቡ እና ወንጀለኛው ደግሞ  አገር መምራት የማይችለው ስልጣን ላይ በመቀመት አገር ያተራምሳሉ። ለዚህም ነው ህግ የሌለባት አገር የሆነችው። ወደ ቀድሞ  አሳቤ ስመለስ በየትኛውም አለም ታይቶና ተሰምቶ  በማይታወቅ መልኩ የአንቦ እስር ቤት፣ የጎንደር እስር ቤት፣ የቅሊንጦ እስር ቤት በእሳት አቃጥለው ከእሳት ለማምለጥ የሚታገለውን እስረኛ በጥይት መጨፍጨፍ እንደዚህ አይነት ሰቅጣጭ ወንጀል ተሰምቶም ታይቶም አይታወቅም ታዲያ አሸማጋዮቹ ለምን አፋቸው ተለጎመ?

 

እናንተ አሸማጋዮች  አይን አይደልም ልብን የሚያስነባ ወንጀል በመንግስት ደረጃ በተደራጀ ወንጀለኛ እና ዘረኛ በሆኑ ወያኔዎች የኦሮሞ እና  የአማራ እናቶች እንባ ያለገደብ ሲፈስ አሸማጋዮቹ ኸረ ወዴት ናችሁ? ወላጋ ውስጥ ደንቢዶሎ ላይ ጧሪ ልጇን በጭራቅ ወያኔዎች ተገሎባት ልጄን እያለች በወላድ አንጀቷ እያነባች የወደቀው ልጇን ልታነሳው ስትንሰፈሰፍ አጋዚ ወያኔ እየደበደቡ የልጇ እሬሳ  ላይ እንድትቀመጥ በማድረግ የግፍ ግፍ ፈጸሙባት። እነዚህ ከሰውነት ሃሳብ የወጡ በኦሮሞ  እና  በአማራ ብሄር ላይ ያነጣተረ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸማቸው ሳያንስ ገድለውም የሚፈጽሙት ድርጊት ጆሮን ጭው የሚያደርግ ሳጥናኤል እንኳን አፉን የሚያሲዝ የክፋት እና የጥፋት ስራ ነው። እንደዚህ አይነት ግፍ በአለማችን ተሰምቶ  የማይታወቅ ግፍ በአገራችን ጭራቆ ወያኔዎች ሲፈጸም ምነዋ አሸማጋዩቹ ድምጻችሁ ጠፋ?

 

እናንተ አሸማጋዮች  ወያኔን ሊያሰጋውና ሊያጠፋው የሚችለውን እንቅስቃሴ ሲኖር ብቻ ከኋላ ጦር ሰብቆ ለሚጠብቀው ምህረት የለሹ እና ይቅርታን ለማያውቀው ለቂመኛው ወያኔ ህዝባችንን ለማታለል እና  ቁጣውን ለማብረድ በደሉን እና  ግፉን ተሸክሞ እንዲቀመጥ እየሞትክም እየታሰርክም እየተንገላታህም ቢሆን ወያኔን ዝም ብላችሁ ተቀበሉ ወያኔን አትንኩት አይነት ማሸማገል ከአሁን በኋላ ለራሳችሁ ስትሉ በአፋጣኝ ማቆም አለባችሁ። በኢትዮጵያ ውስጥ የተነሳው የህዝብ ማዕበል ገዳዮችን እና ጨቋኞቹን እንዲሁም በስሩ ያሉትን ርዝራዦች ለአንዴና ለመጨረሻ ሳያጠፋ አይመስለኝም እና አሸማጋዮች ወደ እውነት ብትመለከቱ ይበጃችኋል።

 

ሳጠቃልለው ወያኔ ሲጨንቀው ማሸማገል ወያኔ ሲመቸው ዝም ማለት ህዝቡ ቁጣውን ሲገልጽ መመካከር ያዋጣል ማለት ወያኔ ህዝቡን ሲጨፈጭፍ ዝምታን መምረጣችሁ እናንተም ከየት ወገን እንደሆናችሁ ተገንዝበናል። ከአሁን በኋላ ህዝባችን ወያኔን ደምስሶ የነጻነት ማማ ላይ ተቀምጦ ህዝቡን የሚያገለግል መሪ እና በህዝብ ውክልና ያለው ስርአት እስከሚመጣ ድረስ ትግሉ ወደከፍተኛ ተጋድሎ  ለለውጥ እራሱን እያደራጀ ወደመታጠቁ አድጓል።  10 ሲታሰር 100 ታጋይ ይነሳል 1000 ሰው ሲታሰር ሚሊዮን  ታጋይ ይነሳል ተነስቷልም ትግሉ ከዚህ ቀደሙ ሳይሆን በአስፈሪ እና በአስደንጋጭ ሁኔታ ገዳዩን እና አፋኝን ወያኔን ለማጥፋት ብረት ለበስ ሆኖ ከሁሉም አቅጣጫ ይፈነዳል ያኔ ማምለጫቹ ከወዴት ይሆን? ቡዳ በፀበል ኃይል እንጂ በሽምግልና  አይለቅም። አበቃው።

 

ከተማ  ዋቅጅራ

10.09.2016

Email- waqjirak@yahoo.com

 

 

የዐማራው ነገድ የጅምላ ፍጅትና ተጋድሎ ማስረጃዎች በከፊል!

$
0
0

amhara2

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት 

ዐማራው ከ1972 እስከ 2008 ዓም ባሉት ዓመታት በዘረኛው የትግሬ ወያኔ በጠላትነት ተፈርጆ ከፍተኛ የሆነ የዘር ጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበት መሆኑን ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ባለፉት አራት ዓመታት ተከታታይ መግለጫዎችን ማውጣቱ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በአጠቃላይ በወያኔ የዘር አገዛዝ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማሮች ከምድረ-ገጽ እንዲጠፉ ተደርጓል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ፣ ከዐማራው የጸዱ አካባቢዎችን ለመፍጠርና ዐማራውን አሰቃይቶ፣ አደህይቶና ከሰው በታች አድርጎ ተዋራጅ ለማድረግ ሀብት ንበረታቸውን በመንጠቅ ተባረዋል። አያሌዎች ለእስርና ለእንግልት ተዳርገዋል። በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እንዲሰደዱ ተደርጓል።
ከሁሉም በላይ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምትን ሕዝብ የሚገድሉትን ገድለው፣ የሚያሰድዱትን አሰድደው የቀረውን ከማንነቱ ለማፋታት ባደረጉት የተቀነባበረ ሤራ፣ የወላቃይት ጠገዴን የዐማራ ሕዝብ ልብ የሰበረ መሆኑ፣ ሕዝቡ የራሱን የወያኔን ሕገመንግሥት መሣሪያ በማድረግ፣ ማንነታችን ይከበር፣ እኛ ዐማሮች እንጂ፣ ትግሬዎች አይደለንም ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ፣ ሕጋችን በሚሉት መሠረት መልስ ከመስጠት ፋንታ፣ «ማነው ወንዱ፣ ማነውስ እኛ ካልነው ውጭ ጥያቄ የሚያቀርብ?» በሚል ዕብሪት በሰማላዊ ጥያቄ አቅራቢዎቹ ፣ ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ ጦርነት ከፍቶ አያሌዎችን ገድሏል። አስሯል።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ | PDF

ይ’ቺው የኔ እናት |ኄኖክ የሺጥላ

$
0
0

14232479_1755321964724076_5332355803589255244_n
የውስጧን ቃጠሎ
የልቧን ፍቅር
ጥይት ቀምቶባት
ስታዛዝን እይዋት
ጡቷን ያጠባችው
ከቁር እና ከብርድ
ፈትላ የሸፈነችው
ንጣ ራሱን ቅቤ ፥ ለጋ የቀባችው
ባንዲት ትንሽ ብረት
ባንዲት ትንሽ ጥይት
በረከቷን አጥታ
ይኸው ታለቅሳለች
አደባባይ ወጥታ!
የኔ እናት መከራ
እኔ የሷ ልጅ
ስታነባ እያየሁ
አንዴም ‘ማልቆጭ!
እናቴ እማምዬ
ደጓ ምነው ከፋሽ
ሳጥን እያዳመጥሽ ፥ በ’ንባ ጎርፍ ጠፋሽ?
እማይዬ እናቴ ፥ የኔ እርግብ የኔ ደግ
ሃዘንሽ ማቆሚያ ፥ መከራሽ ማብቂያው
እኔ በቃኝ ስል ነው ፥ የሱ መቆሚያው!
እማማ እምባሽን ፥ ይህንን አ’ረሳም
እማማ ሃዘንሽን ፥ ልቅሶሽን አ’ረሳም
ባንቺ ከመጡብኝ ለማንም አልሳሳም!
እማ በረከቴ ፥ እማ የኔ ፍቅር
አትቀሪም ተደፍተሽ
በወንድሜ ሃዘን እንደዚህ ተከፍተሽ
እልል ትያለሽ ፥ እመኝኝ እማማ
የኔን የልጅሽ ድል ፥ ከጫፍ ጫፍ ሲሰማ!
አይቀርም አልቅሰሽ
አይቀርም እማማ
እናት ያለህ ተነስ
እናት ያለህ ስማ!


ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ፤ የ1950 ዓ.ም የትግራይ ረሃብ፤ የመቀሌ ቆይታውና ትዝታው

$
0
0

tsegaye
በዶክተር አሰፋ ነጋሽ – (በሆላንድ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ) –
8th of September 2016 Email Address- Debesso@gmail.com

በትያትር ድርሰት ጽሁፎቹ ፤ በትርጉምና የግጥም ስራዎቹ ታዋቂነትን ያተረፈው ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ቀዌሳ (ነፍሱን ይማርና) በ1987 ዓ.ም እዚህ በስደተኛነት ነዋሪ የሆንኩበት ሆላንድ ሀገር መጥቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርጎልን ነበር። እንደሚታወቀው ጋሽ ጸጋዬ የወያኔ መንግስት ስልጣን ላይ እንደወጣ
የደረሰው ወይም የጻፈው አንድ “ሀሁ ፐፑ” የተሰኘ የትያትር ስራው ለህዝብ እንዳይታይ ታግዶበት ነበር። አዋሳን በመሰሉ የኢትዮጵያ ከተሞች ደግሞ ተዋንያን መድረክ ላይ ሆነው ትያትሩን ሲተውኑ በወያኔ ወታደሮች በዱላ እየተደበደቡ ተውኔቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ሌላው ቀርቶ በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ለታላቁ ጸረ-ፋሽስት፤ የኢትዮጵያ ሰማእትና አርበኛ ለአቡነ ጴጥሮስ ማስታወሻ የደረሰውን “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” የተባለውን ትያትር ለህዝብ እንዳይታይ የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ማገዱ ይታወቃል። “ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት” የተሰኘው ትያትር በዐጼ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ዘመን ካለአንዳች እገዳ ለህዝብ ይታይ የነበረ ትያትር ነው። በወያኔ ዘመን ግን ይህ ተወኔት እንዳይታይ እገዳ ተጣለበት። ይህ የትግራይና የኢጣሊያን ፋሽስቶች ርዕዮተዓለማዊ አንድነትና ጸረ-ኢትይጵያ የድርጊት መመሳሰል የሚያስረዳ ይመስለኛል። በእዚህ ምክንያት ገና ወያኔ ስልጣን ላይ እንደ ወጣ ጋሽ ጸጋዬን የመሰሉ ሰፋ ያለ ሀገራዊ አመለካከት ያላቸው የጥበብ ሰዎች የወያኔ ትግሬዎች መንግስት የጥቃት ሰለባ ሊሆኑ ችለዋል። ለነገሩ እንደ ወያኔ ያለ የፋሽስት ስርዓት በነጻነት እያሰቡ የጥበብ ስራዎቻቸውን የሚያዘጋጁ ሰዎችን አይታገስም።ታዲያ ጋሽ ጸጋዬ ስለ ወያኔዎች ጉዳይ አንስቶ እዚህ አምስተርዳም ከተማ ለተሰበሰብነው ኢትዮጵያውያን ሲናገር የሚከተለውን የ1950 ዓመተ ምህረቱን የትግራይ ገጠመኙን አጫወተን።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ | PDF

ዶ/ር ተበጀ ሞላ ለአምባሳደር ትርፉ ኪ/ማርያም ምላሽ ሰጡ “የራያ ሕዝብ ራያ እንጂ ትግሬ አይደለም”|ሊደመጥ የሚገባው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በአውስትራሊያ ባለሙሉ ስልጣን የሆኑት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለኤስቢኤስ ራድዮ በሰጡት ቃለምልልስ ዙሪያ ከተለያዩ አቅጣጫዎች “የሕወሓት ባለስልጣናትን ቃለምልልሶችን ማዳመጥ የማሰብ ችሎታን ይቀንሳል” እስኪያስብል ድረስ ትችቶች እየተሰነዘረባቸው ነው:: ዛሬ በኤስ ቢኤስ ራድዮ የቀረቡት ዶ/ር ተበጀ ሞላ አምባሳደሯ በራያ ሕዝብ ላይ ስላነሱት ነጥብ እና በሌሎቹም ጉዳዮች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል:: ዶ/ር ተበጀ “ከኢትዮጵያዊነት ባነሰ ማንነት ራሱን መግለጽ አለበት ከተባለ የራያ ሕዝብ – ራያ እንጂ ትግሬ አይደለም” ብለዋል:: ያድምጡትና አስተያየትዎን ይስጡ::

አብዱ ኪያር የሰረዘውን የአዲስ ዓመት የግዮን ሆቴል ኮንሰርት የአዲስ አበባ ወያኔዎች ተቆጣጠሩት |አብዱ ኪያርን አክብረናል

$
0
0

አብዱኪያር ዛሬ ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ሊደረግ የነበረውን የግዮን ሆቴሉን ኮንሰርት መሰረዙ አይዘነጋም:: ረቡዕ ዕለት ኮንሰርቱን በወቅቱ የሃዘን ምክንያት እንደማያደርግ ከገለጽና ወገናዊነቱን ካሳየ በኋላ ሕወሓት የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌዴሬሽን ተንደርድሮ ቦታውን ይዞ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ዝግጅት በግዮን ሆቴል አቀርባለሁ እያለ በየቴሌቭዥኑ እያስነገረ ነው:: ሁሉም ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ኮንሰርታቸውን በሰረዙበት በዚህ ወቅት የሕወሓት መንግስት እነርሱ የሰረዙትን ኮንሰርት እኔ አደምቀዋለሁ በሚል በነጻ ነው የዛሬውን ኮንሰርት በግዮን ሆቴል ያዘጋጀው:: የሚገርመው በማስታወቂያ የሚያስነግሩት በግዮን ሆቴል እናደርገዋለን በሚሉት ኮንሰርት 300 አርቲስት ይገኛል እያሉ እያስተዋወቁ ነው:: አማራውን ከሱዳን ወታደር አምጥተው እንዳስጨፈጨፉት ከሱዳን ዘፋኝ ሊያመጡ ነው? – ለማንኛውም ከትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ደጋፊዎችና አባላት ውጭ የአዲስ አበባ ሕዝብ ለ እንደዚህ ያለው ርካሽ ተግባር ተባባሪ እንደማይሆን እርግጠኛ ነን:: አብዱ ኪያር ግን እዚያው አዲስ አበባ ሆነህ ይህን ያህል መስዋዕትነት ስለከፈልክ ላቅ ያለ ክብር ይገባሃል::

abdu-kiar

የአድግራት እና የቀብሪድሃር ወግ

$
0
0

ከመሰረት ገደፋው

የሶማሊያው አምባገነን መሪ ሞሐመድ ሲያድ ባሬ ከ20 ዓመታት በላይ አገሪቱን በብረት መዳፋቸው ጨምድደው አስተዳድረዋታል፡፡

ባሬ በአንድ በኩል ሶሻሊስት ነኝ ቢሉም በእብሪት የተሞላ ብሔረተኝነት የተጠናወታቸውም ነበሩ፡፡ጂቡቲን ሪት ራሳቸው በመጠቅለል ከኢትዮጵያ የኦጋዴን አካባቢ ለመቀማትና ሰሜናዊ ኬኒያንም ወደ ሶማሊያ ለመጠቅለል ቃዡ፡፡ውጥናቸውን #ታላቋን_ሶማሊያ(#Greater_Somalia) የሚል ቅፅል አበጁለት፡፡በእብሪት ተነሳስተው ኢትዮጵያን ወረሩ፡፡ በአጭር ጊዜም ወደ ኢትዮጵያ በጥልቀት በብዙ መቶ ኪሎ ሜትሮች ወደ ውስጥ ገብተው ዘለቁ፡፡በጊዜያዊ ድል ተኩራሩ፡፡ ፈነደቁ፡፡
dawit

ኃላ ግን አስቀድመው እንዳሰቡት አልሆነም፡፡ በአብዛኛው በአጭር ጊዜ ሥልጠና በይድረስ ይድረስ የተዘጋጀ ሕዝባዊ ሠራዊት የሚበዛበት የኢትዮጵያ ጦር በታላቅ ጀግንነት ወደ መልሶ ማጥቃት ገባ፡፡ዓመት ባልሞላ ውጊያ የሶማሊያን ሰራዊት ወደመጣበት ነዳው፡፡ ፍርክስክሱን አወጣው፡፡የሶማሊያ ጦር የኦጋዴን አሣፋሪ የጦር ሜዳ ሽንፈት በሲያድ ባሬ አስተዳደር ላይ ጫናውን አበረታበት፡፡
በማኅበረ ምጣኔ-ሐብታዊ ቀውሱ ላይ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነበት፡፡ሲያድ ባሬም አገራቸውን ጥለው እግሬን አውጭ አሉ።

ልብ በሉ ይህ ሁሉ የሆነው እነሱ አማራ ብለው በሚጠሩት በፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማሪያም የስልጣን ዘመን ነው። ኢትዮ-ሶማሌዎች በዚያ በተወረሩበት ስዓት የደረሰላቸው አማራ እና ኦሮሞ የገበሬ እንጅ ከተከዜ ማዶ የመጣ ጦር አይደለም፤ ዛሬ ምን ተገኝቶ ይሆን ለዚህ ህዝብ ጀርባቸውን የሰጡት?

ስለዚህ ኢትዮ-ሶማሊዮች ኢትዮጵያዊነትን ከወደዱ ከሁሉም በላይ በግንባር ቀደምትነት የሲአድባሬን ወረራ ቀልብሶ ነፃ ላወጣቸው ህዝብ መሆን ነበረበት። እነሱ ግን ከዚያ ይልቅ ትናንት ጅጅጋ ላይ ላስጨፈረላቸው የተለየ ክብር እንዳላቸው ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠ አሳይተዋል።ድንቄም ብሄር ብሄረሰብ።ልዑካን ተብየውም እነ አባይ ወልዱን ሽርጥ አልብሰው፣ በእነ አባይ ፀሀየ በአማርኛ ተፅፎ የተዘጋጀላቸውን ሲያነቡ ነበር።

የሁለቱ ህዝቦች ግንኙነት በመልካም ወንድማማችነት ቢሆን ሁሉም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ኢትዮጵያ የሚከፋው ይኖራል ብየ አልገምትም።
ነገር ግን ወደ ተከዜ ማዶ ያመሩት የኢትዮ-ሶማሌ ልዑካን ከተናገሩት ንግግር ጨምሮ ጥሩ ያልሆነ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሜ በጅጅጋ በንግድ ስራ ተሰማርተው በሚኖሩ የአማራ ማህበረሰብ ላይ ማዋከቡ እንደቀጠለ እንደሆነ እየተሰማ ነው።

በተየያዘ ዜና በአመቱ መጨረሻ የአድግራት ዪኒቨርሲቲ ለአቶ አብዲ መሐመድ የክብር ዶክትሬት ድግሪ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

(ፎቶ፦ አባይ ወንዱ እና አብዲ መሐመድ)

ዳን አድማሱ ታሪክ ሠራ |አዝነንበት ነበር ግን አኩርቶናል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ድምጻዊ ዳን አድማሱ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ባዘጋጀው የአዲስ ዓመት የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ እንደማይገኝ ገልጾ ነበር:: ሆኖም ግን በመጨረሻው ሰዓት ከኢቢሲ ፕሮግራም ላይ ቀርቦ በአደባባይ ጥቁር በጥቁሩን ለብሶ በመግባት ዘፍኖ ከጨረሰ በኋላ እጆቹን ወደላይ በማጣመር ልክ እንደ አትሌት ሌሊሳ ፈይሳ ታሪክ ሰርቷል:: በራሳቸው በገዳዮቹ ቴሌቭዥን ላይ ቀርቦ ይህን በማድረጉ ኮርተንበታል:: ግን ያዘፈኑህም አስጨንቀውህ ሊሆን ይችላል:: ማን ያውቃል ጠመንጃ የያዘ ሰው በጭንቅላቱ አያስብም::እኛም ቀድመን ስለወቀስነው ይቅርታ ብለናል:: ዳን አድማሱ ኮርተንብሃል – አዝነንብህ ነበር ግን መጨረሻ ላይ አኩርተኸናል:: ለካስ አሪፍ አይቸኩልም የሚባለው እንዲህ ነው::
ebc

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live