Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

“በም/ሐረርጌ በመስጊድ ላይ ዛሬ ቦምብ ጥለዋል ነገ ደግሞ በቤተክርስቲያንም ሊጥሉ ይችላሉ”ሳዲቅ አህመድ በሕወሓት መንግስት ቦምብ ስለተጣለባቸው መጊዶች ይናገራል

$
0
0

< …ሕወሓት ትላንትም የሽብር ተግባራትን ሲፈጽም ነበር ዛሬም ተስፋ ሲቆርጡ በያንን እያደረጉ ነው። በምዕራብ ሐረርጌ በመስጊድ ላይ ያፈነዱት ነገ ተነገ ወዲያ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንም ሊያደርጉት ይችላሉ ተስፋ የቆረጠ ድርጅት … ተቃውሞው በጋራ ማስተባበር ያስፈልጋል መናበብ ያስፈልጋል ብሄራዊ የስንብት ቀን ይባል ሌላ አገር አቀፍ ሁሉንም ያሳተፈ ተቃውሞ ለማካሄድ የሁሉም የለውጥ ሀይሎች በጋራ መቆም ወሳኝ ነው። ስርዓቱን ወደ መቃብር ለመሸኘት ፤ቅንጅት፣ ህብረት የጋራ ትብብር ያስፈልጋል። ምዕራባውያኑ ግን… > ጋዜጠኛ ሳዲቅ አሕመድ በምዕራብ ሐረርጌ በሁለት መስጊዶች ላይ ፍንዳታ ተፈጽሞ ንጹሃን ሰለባ ስለሆኑበት ሂደት ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ቀሪውን ያዳምጡት)


“ከሁሉም በላይ የሀገርንና የህዝብን ደህንነትና አንድነት ይቅደም!!”–በዲያስፓራ የዓረና መድረክ ደጋፊዎች የተሰጠ የጋራ አቋም መግለጫ

$
0
0

arena

በኢትዮያ በተለያዩ ቦታዎች እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ በመሄድ ላይ የሚገኘው ህዝባዊ ተቃውሞና ብሶት በማስመልከት በውጭ ዓለም የሚኖሩ የዓረና መድረክ ደጋፊዎች ከተለያዩ ቦታዎች ሰሞኑን ባደረጉት አስቸኳይ የቴሌ ኮንፈረስ ውይይት የሚከተለውን ባለስምንት ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ ለመላ ኢትዮያውያን አስተላልፏል::

ዓይናቸውን በፍቅረ ንዋይና በስልጣን ጥምነት የተሰወሩ አምባ ገነኖች የትም ይብቀሉ የትም ተመሳሳይ ባህርይ አላቸው:: ዙሪያቸውን በወታደራዊ ሐይል ተከቦ ሲያዩት ዓለምን በመዳፋቸው ውስጥ ያስገቡት ይመስላቸውና ልባቸውን በትዕቢትና በትምክህት ስለሚሞላ ነፃነትና ፍትሕ ከሌለ ነገ ፈራሽ መሆኑን ከታሪክ አይማሩም:: ሰብኣዊ ርህራሄና የይቅርታ መንፈስ የላቸውም:: የህልውናቸውን መሰረት ሕብረተሰቡን በዘር፣ በጥቅምና በሀይማኖት ለያይተህ ግዛ የሚል ስለሆነ የህዝቡን ነፃ እንቅስቃሴ፣ አንድነትና መደራጀት ከጦር በላይ ይፈሩታል:: ራሳቸውን ልዩ ፍጡራንና ጀግኖች አድርገው በመመልከት ከሀገርና ከሕግ በላይ በመሆን የህዝቡን ጭኾትና ህይወት የዶሮን ያህል ግምት አይሰጡትም:: የዓይን ብሌየናቸው ገንዘብና ስልጣን ስለሆነ የሀገርንና የወገንን ፍቅር የላቸውም:: በርስትነት በያዙት የብዙሃኑ መገናኛ አማካኝነት ነጋ ጠባ የሚያስተጋቡት መዝሙርና የጉራ ነጋሪት በለው፣ ፍለጠው፣ ርግጠው፣ ቁረጠው፣ ግደለው ከሚል ቀረርቶ በስተቀር የህዝቡን ብሶት የማዳመጥና አርቆ የማየት ዓቅም፣ ሞራል፣ ብቃትና ተፈጥሮ የላቸውም:: ይህ በመሆኑም የህዝቡን ዓመፅ ቤተ መንግስታቸው አፋፍ ላይ ደርሶ እንደ እሳተ ጎመራ እስከሚለበልባቸው ድረስ ተቻችሎና ተከባብሮ አብሮ ከመኖር ይልቅ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል በማለት እስከመጨረሻ ህልፈታቸው ድረስ መሟሟትንና መተላለቅን ይመርጣሉ:: ሀገርንና ህዝብን አጥፍቶ መጥፋት ማለት ትርጉሙ ይኸው ነው::

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ | PDF

በጽናትና በኅብረት መቆም ለዓላማ ስኬት |ዴሞክራሲያ (የኢሕአፓ ልሳን)

$
0
0

Democracia
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ከተመሠረተ 44 ራሱን ይፋ ካወጣ ደግሞ 41 ዓመቱ ነው። ኢሕአፓ ሲመሠረት ጀምሮ ያነገባቸውና የታገለላቸው ዓላማዎች ዛሬም አንገብጋቢነታቸው አጠያያቂ አይደለም። ዋና ዋናዎቹ በሕዝብ የተመረጠ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት መመሥረት፣ የዜጎች መብቶች ያለገደብ መከበር፣ በነፃነት የመደራጀት መብትና በሕጋዊ መንገድ የዜግነት ግዴታቸውን ማከናወን፣ የብሄረሰቦች ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር፣ የሃይማኖት እኩልነትና የመንግሥት በሃይማኖቶች ጣልቃገብነት መታቀብ፣ የኑሮ ውድነትን የሚቆጣጠርና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲን ተግባራዊ ማድረግ፣ የሴቶችን መብት ማሰከበር…ወዘተ የሚሉት በዋናነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ | PDF

የማሪያም መንገድ ሲዘጋ የገብሬሉ ይከፈታል ብለን ነበር!!! –ግርማ ሠይፉ ማሩ

$
0
0

 

girmaseifu32@yahoo.com; girmaseifu.blogspot.com

girma seifu

ግርማ ሠይፉ ማሩ

አንድትን ፓርቲን ድንክ ለማድረግ ከመወሰናቸው በፊት አንድነት የሚከተለውን ሰላማዊ የትግል ስልታ፤ ሰላማዊ የሰለጠነ የስልጣን ሽግግር እንዲቀበሉ በተደጋጋሚ አሳሰብን ነበር፡፡ ከመሃከላችን እየመረጡ ማስር ትግሉን እንደማያዳክመው ይልቁንም እንደሚያጠነክረው ነግረናቸዋል፡፡ ከከፋም ትግሉ ወደ ሌላ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው በቅርብ ላገኘናቸው ሁሉ ነግረናል፡፡ መግለጫዎች አውጠተን አቋማችን ህዝብ እንዲረዳው አድርገናል፡፡ የመንግሰት ተቋማት ህዝብን እንዲያገለግሉ፣ ከተሰጣቸው ህዝብን የማገልገል ሃላፊነት ውጭ እንዳይንቀሳቀሱ የበኩላችን ለማድረግ ሞክረናል፡፡ ማነኛውም ያደረግናቸው እንቅስቃሴዎች ከፍርሃት ተቆጥሮብናል፡፡ ከሁሉም በላይ በምን ያመጣሉ ትዕቢት የፈለጉትን አድርገዋል፡፡ ይህ እንዲሆን በውስጣችን ታቅፈናቸው የነበሩትን ጭንጋፎች ተሳትፎ የሚያሳንሰው አይደለም፡፡ ይህም ቢሆን ግን ገዢው ፓርቲ በማይመለከተው የፓርቲ የውስጥ ጉዳይ ገብቶ ህገወጥ እርምጃ የፖሊስ ሰራዊት በማሰማራት ወስዶዋል፡፡ ዛሬ በሰላማዊ ትግል ጥላ ስር ለውጥ እናመጣለን ሲሉ የነበሩ ወጣቶች በማነኛውም መንግድ ለውጥ ለማምጣት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ተገፍተው የገቡበት መሆኑን ስለምናውቅ ምርጫቸውን ማክበር ብቻ ሳይሆን በባርነት ከመኖር ሞትን መምረጥ የሰው ልጅ ትክክለኛ ምርጫ ነው ብለን እናከብራቸዋለን፡፡

የታፈነ ህዝብ ለመተንፈስ የሚያደርገው የዚህ ዓመት ህዝባዊ እንቅስቃሴ በምንም መመዘኛ ሰህተት ሊሆን አይችልም፡፡ ጥያቄዎቹን በየቦታው ያስነሱት ጉዳዮች የተለያዩ ቢመስሉም መንግሰት እንደሚለው የመልካም አስተዳደር ጉድለት አይደለም፡፡ የህዝብ ጥያቄ ያልገባው መንግሰት ደግሞ መልሱን ሊያገኘው እንደማይችል ደግመን ደጋግመን ተናግረናል፡፡ በየቦታው የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ መንግሰት ህገወጥ እርምጃዎችን መውሰዱን ቀጥሎበታል፡፡

መንግሰት በቅርቡ እያደረገ ያለው ዜጎችን መቅጠፍ በምንም መመዘኛ ቀለም አልተሰጠውም እንጂ ከቀይ ሽብር- ነጭ ሸብር የሚለይ አይደለም፡፡ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካ ልዮነቶች በውይይት እና ህዝብ በሚመርጠው መስመር መፈታት አለበት ተብሎ በሚታመንበት ጊዜ መንግሰት ገዳይ ጥይቶቸን በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየረጨ ይገኛል፡፡ ይህ መቼም ቢሆን ከተጠያቂነት የሚያድን አይደለም፡፡ የህዝብ መተንፈሻ የሚባሉትን መሰመሮች ሁሉ የዘጋ መንግሰት ህዝብ ለምን አደባባይ ወጣችሁ ብሎ ለመግደል የሚያስችል ስልጣን ማንም አልሰጠውም፡፡ ነገር ግን ጊዚያዊ ማዘዣውን ተጠቅሞ በተግባር ዜጎችን እየገደለ ይገኛል፡፡ ይባስ ብሎ ከነብስ ወከፍ መሳሪያ አልፎ የቡድን መሳሪያዎች፣ በእኔ ግምት ለውጭ ወራሪ ሀይል የተዘጋጀን መከላከያ አንቀሳቅሶ የህዝብን ድምፅ ለማፈን እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ለሚታዘብ ወቅቱ የመንግሰት የእብደት ደረጃ ልክ ያለፈበት እንደሆነ ለመረዳት አያስቸግርም፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እሰከ ምስራቅ የጠየቀው ለሰው ልጅ የሚገባውን ነፃነት እና ክብር ነው፡፡ መንግሰት ደግሞ ሆዳችሁን ከሞላቸሁ ፎቅ፣ ባቡር እና መኪና መንገድ ካያችሁ መች አነሳችሁ የሚል ይመስላል፡፡ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰብሰበው ለወጣቶች የሚነግሩት በሙሉ ሆድ ሰለሚሞላበት መንገድ ነው፡፡ ወጣቱ በአደረጃጀት ካልገባ ማግኘት እንደማይቻል ያስረዱት ደግሞ የስፖርትና ወጣቶች ሚኒሰትር መስሪያ ቤት የወጣት አደረጃጀት ሃላፊ ናቸው የተባሉ ሰው ናቸው፡፡ በሀገራችን ያለው የተፈቀደ አደረጃጀት መንግሰትን ለማወደስ የተቋቋሙት የወጣቶችና የሴቶች ሊጎች ናቸው፡፡ እነዚህ አደረጃጀቶች ገዢው ፓርቲ ሲየስነጥስ እንባቸው የሚመጣ ናቸው፡፡ እነዚህ ደግሞ የወጣቱን ችግር ሊናገሩ አይችሉም፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በወጣት ሰም ስብሰባ ተቀመጡ የተባሉ ሰዎች አብዛኞቹ በእውነት ይናገራሉ ተብለው የሚጠበቁ እንዳልሆነ ብዞዎች የተሰማሙበት ነው፡፡ እነዚህ ተሰብሳቢዎች ቢያንስ እድሜያቸው የወጣት አይደለም፡፡ ወጣት ያልሆነ የወጣት ችግር አያውቅም ማለት ሳይሆን በዚህ ስብሰባ ለመካፈል ለሚከፈል አበል ለማግኘት ሲሉ ወጣቶችን ትተው እራሳቸውን መርጠው የመጡ ሰዎች ናቸው፡፡ በዚህ በትንሹ ያልታመኑ በትልቁ ሊታመኑ አይችሉም፡፡

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የምር ውይይት ማድረግ ከፈለጉ የወጣቶችና ሰፖርቲ ሚኒስትሩ ሬዲዋን ሁሴን ስብሰባ ላይ የነገራቸውን የሚናግሩ ወጣቶችን መሰብሰብ ሳይሆን በአዲስ አበባ እና በየክልሉ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡ ፈልገው የተከለከሉትን ወጣቶች ወይም ደግሞ የደህንነት ሰራተኞች በየጊዜው እያፈሱ በእስር ቤት የሚያጉሩዋቸውን ወጣቶች ማናገር አለባቸው፡፡ ለምሳሌ እነ አንጋው ተገኝ እና ጓደኖቹን ከጎንደር፣ እነ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወይንሸት ሰለሺ  ከአዲስ አበባ፣ እነ ምርቱ ጉታ ከአዳማ፣ እነ ዘሪሁን ገሰሰ ከወሎ፣ ወዘተ ጠርተው ምን ጎደለባችሁ? ማለት ነበረባቸው፡፡ ለነገሩ እንጂ ጉዳዩ ከወጣቶቹ ጋር የሚያልቅ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተሩ እና ጓዶቻቸው የምር ለዚህች ሀገር መፍትሔ የመፈለግ ፍላጎት ካላቸው ከማን ጋር መነጋገር እንዳለባቸው ይጠፋቸዋል ብዬ አላምንም፡፡

ዛሬ በጫካ የሚገኙት የሰላማዊ ትግል መስመር ሲዘጋ ወደ ትጥቅ ትግል የገቡት ልጆች በምንም መመዛኛ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለወጣቶቹ እንደገለፁት በውይይት የሚገኘውን ውጤት ዘንግተው እና በድንጋይ ውርወራ መንግሰት ለመገልበጥ ፈልገው አይደለም፡፡ ይልቁንም መንግሰታቸው ውይይት ሰለሚፈራ እና በተወያየበት ሁሉ በጉልበት አንበርክኮ ለመውጣት ሰለሚፈልግ ነው፡፡ አሁንም በከተማ በድንጋይ ውርወራ መንግሰት ፋታ ለመከልከል የተዘጋጁ ወጣቶች መንግሰት ባዘጋጀው አደረጃጀቶች/ፎረሞች ብቻ እንዲሳተፉ በመምከር መፍትሔ አይገኝም፡፡ የተለያየ አስተሳሰብ ያላች ወጣቶች ሊደራጁበት የሚችሉበት መንገድ መከፈት አለበት፡፡ ትላንት ለእስር የተዳረገቸው የአንድነት አባል የነበረችው ወይንሸት ሰለሺ  በኢህአዴግ ወጣት አደረጃጀት የነበረች ቀጥሎም የባለ ራዕይ ወጣቶች አባል የነበረች ነች፡፡ በሲቪል ሶሳይቲነት ይንቀሳቀስ የነበረው ባለራዕይ ወጣቶች መንቀሳቀስ ሲከለከል አንድነት ተቀላቅላ ስርዓቱን ለመለወጥ ቆርጣ ተነሳች፡፡ ለዚህም ብላ አንድነትን ተቀላቀለች፡፡ አንድነት በህገወጥ መንገድ ሲፈርስ ደግሞ በፌስ ቡክ ትግል የምታደርግ ንቁ ወጣት ነች፡፡ በእኔ እምነት ወይነሸት ላይ የሚያቀርቡት አንድም ወንጀል የለም፡፡ ወንጀለኞች ቢወነጅሏት ለልጇ ዲሞክራሲያዊት ሀገር ለመመስረት ባደረገቸው ጥረት ነው፡፡ ለሆዴ አላድርም ነፃነት ይበልጥብኛል ሰለአለች ብቻ ነው፡፡

አሁንም ጥሪያችን መንግሰት የማሪያሙን መንገድ ክፍት ያድርግ በነፃነት መደራጃት የምንችልበትን መንገድ ክፍት ማድረጉን ማረጋገጫ ይስጠን፣ ከዚያ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን እንደሚያደርግ ያውቃል፡፡ በአዲስ አበባ የተኮለኮሉ ኮብል እስቶኖችን መናፈቅ ትቶ በውይይት ወደ መፍትሔ ይገባል፡፡ ለመጀመር በአዲስ አበባ የወጣትና ሴቶች ፎረም አባል ያልሆኑ የአዲስ አበባ ልጆችን ለማነጋገር ከወሰኑ ትልቅ እርምጃ ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰትር ስራ ላለማብዛት እኛ የዞን ዘጠኝ ወጣቶችን ወክለናል ያነጋግሩዋቸው፡፡

መልካም አዲስ ዓመት በተለመደው ሁኔታ ሳይሆን ለለውጥ የእውነትም አዲስ ዓመት ማድረግ የሁላችንም ሃላፊነት መሆኑን መዘንጋት የለብንም፡፡ ክብር ህይወታቸውን ለሰጡ ጀግኖቻችን ….

ቸር ይግጠመን!!!!!

 

አሸባሪ ሕዝብና ለሽብር የተጋለጠ መንግሥት (ከይገርማል)

$
0
0
Peaceful #OromoProtests demonstrators arrested & beaten up. Police takes off shoes to prevent them from running.

Peaceful #OromoProtests demonstrators arrested & beaten up. Police takes off shoes to prevent them from running.

ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ የከፋፍለህ ግዛው ስርአት አብቅቶ የዴሞክራሲያዊ ስርአት እንዲመጣ በመጠየቁ ምክንያት ከትግሬ ወያኔ ጋር ግልጽ ጦርነት ውስጥ ገብቷል ማለት ከሚቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል::  ዛሬ ላይ የተጣለበትን የጭቆና ቀንበር መሸከም አቅቶት የማያማርር: በጥቃት ስሜት የማይብሰከሰክ ከትግራይ ወያኔና ከእድምተኞቹ ውጭ ያለ ሌላ ሰው ማግኘት ያስቸግራል:: በየአካባቢው የብሶት እንጉርጉሮ ይዜም: የለውጥ መፈክር ይስተጋባ ይዟል:: ከዚህም አልፎ ወያኔ በራሱ የፖለቲካ ፍልስፍና ከሞላቸው ጥቂት ካድሬወችና የጥቅም ተጋሪ የአመራር አባላት በስተቀር ሁሉም “የወያኔ የዘረኝነት አስተዳደር በቃን!” ብሎ አደባባይ ወጥቶ ድምጹን እያሰማ ነው:: የነገሩህን ሰምተህ: ያዘዙህን ፈጽመህ መኖር እንጅ መጠየቅ አትችልም የሚሉት ወያኔወች በተራቸው ድምጹን በሀይል ለማፈን እንቅልፍ አጥተው በመስራት ላይ ናቸው::

 

ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ኢትዮጵያ በልማት አድጋ ተመንድጋለች በሚል ሰበካ በገሀድ የምንኖረውን የድህነት ኑሮ አስረስተው በፕሮፓጋንዳ ሊያጠግቡን: የፈለገው አይነት መከራ ቢደርስብንም ልማት እንዳይደናቀፍ ሲባል ተቃውሞ ሳናሰማ ችለን እንድንኖር “እዚህ ብትጎሳቆሉም እዚያ ላይ ትካሳላችሁ” የሚል እንድምታ ባለው ውትወታ ሊያሳምኑን: የሚደክሙት ሀፍረት የለሽ የወያኔ ካድሬወችና አጫፋሪወቻቸው ማደናቆራቸውን ቀጥለዋል:: በርግጥ እዚህ ግባ በማይባል በዝቅተኛ ኑሮ ይኖሩ ለነበሩ ሁሉም በጃቸው ሁሉም በደጃቸው ለሆነ የዘመኑ ኢንቨስተሮችና ልማታዊ ባለሀብቶች ከልማትም በላይ ልማት ከዴሞክራሲም በላይ ዴሞክራሲ አለ:: ለእነርሱ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ነው:: ስለዚህ መቸም ያልታየ ልማት በወያኔ ጊዜ እየታየ ነው ብለው ደረታቸውን ነፍተው ይከራከራሉ:: በርሀብና በበሽታ የተጎሳቆለው ወገን ህመሙ ስለማይሰማቸው: ችግሩ ስለማይገባቸው በፈጠሩት ገነት ውስጥ ሁላችንም አብረን ተደስተን የምንኖርም ይመስላቸዋል:: ላባቸውን አንጠፍጥፈው በሚያገኟት አነስተኛ የወር ገቢ ገመናቸውን ሸፍነው ይኖሩ ለነበሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ከሙስና የጸዳ የወር ገቢ ለነበራቸው ዱሮ ደህና ኗሪ ይባሉ ለነበሩት ሰዎች ግን ያሁኑ ኑሮ ከሲዖልም የሲዖል ኑሮ ነው:: በምግብ እጦት እና በወያኔ ጥይት ለሚረግፉት ብዙሀን ጭቁኖች የወያኔ የአገዛዝ ዘመን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማያውቅ የመከራ ዘመን ነው::

 

ሕንጻ ቢገነባ ለባለጊዜወች ድሎት: ውሀ የመሰለ አስፓልት ቢሰራ ለመኪናወቻቸው ምቾት ከመሆን አልፎ  አንጀቱ በርሀብ ለታጠፈ: በዴሞክራሲ እጦት ድምጹ ለታፈነ: ሰላምና ፍቅር ርቆት በፍርሀትና በሰቀቀን እንዲኖር ለተገደደ ሕዝብ ያስገኘው ጥቅም የለም:: በወያኔወች ቀጭን ትዕዛዝ ድሀና የድሀ ጎጆ የሀገር ገጽታንና የከተማን ውበት ያደበዝዛሉ ተብሎ ድሀ ከተገፋና ጎጆው ፈርሶ በቦታው የሀብታም ህንጻ ከተገነባ: የዴሞክራሲ መብት ለጥቂቶች ብቻ ተለክቶ ከተሰጠ: የፍትህ ሚዛን ከተዛባ: አድሎና መገለል ከነገሰ: ርሀብና ተስፋ መቁረጥ ስር ከሰደደ: ልማታዊነቱ ምኑ ላይ ነው? የልማትን ትርጉም የሚያውቅ ሰው የወያኔን መንግሥት ልማታዊ ብሎ ሊጠራው ቀርቶ ሊያስበው አይደፍርም::

 

ሁሉም እንደሚያውቀው ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አሸባሪ በተባለው ሕዝብ ላይ ርምጃ እንዲወስድ ለመከላከያ ሠራዊት ከጥቂት ቀናት በፊት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል:: ይህን የርሳቸውን ትዕዛዝ ተከትሎ በተለይ በሰሜን ጎንደር ሕዝብ ላይ የምድር ጦርና የአየር ኃይል የተቀናጀ ጥቃት ተከፍቷል:: በዚህ ጥቃት ተወልደው በየአደጉበት ቀየ የአባ ጃሌው ልጆች በጥይት እየተበሳሱ እየወደቁ ነው:: እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ጾታ ሳይለይ የዚችን ዐለም በጎና ክፉ ጎኗን ለማየት ያልታደሉ ሕጻናት: መካሪና ዘካሪ የዕድሜ ባለጸጎች: ሮጠው ያልጠገቡ ተስፋ ናፋቂ ወጣቶችና ቤተሰብና አካባቢያቸውን በሀላፊነት የሚመሩ ጎልማሶች በገፍ በግፍ ህይወታቸውን ተነጥቀዋል::

 

ፓስተር ያሬድ ጥላሁን የሚባሉ የወንጌል አገልጋይ አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ሕዝቡን ገድሎ ድምጹን እንዲያፍን ለመከላከያ ሰራዊት የሰጡትን ትዕዛዝ አስመልክተው በጻፉት ደብዳቤ “በአንደበትዎ የተነገረውና በታሪክ መዝገብ ተቀርጾ የሚኖረው ይህ ውሳኔዎ በእግዚአብሔር፣ በሰውና በኅሊናዎ ዘንድ ከፍተኛ ተጠያቂነት እንደሚያመጣብዎ ሳስብ ከልብ አዝናለሁ።” ሲሉ ያቀረቡትን ቅሬታና “ፖለቲካዊ መፍትሔዎች ላይ እንዲተኮር፣ የኃይል እርምጃው እንዲቆም፣ ተዓማኒ እርምጃዎች እንዲወሰዱና ሌሎችንም ያሳተፈ አገራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ አቅምዎ እሰከሚፈቅድ የበኩሎትን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ፤ ይህንንም ማድረግ ካልቻሉ ከሚፈሰው የንጹሐን ደም እጅዎን እንዲያነጹ ሰውን በመልኩና በምሳሌው በፈጠረ በሕያው እግዚአብሔር ስም እማጸኖታለሁ።” የሚለውን ተማጽኖና በሳል ምክር አንብቤ አቶ ኃ/ማሪያምም ጊዜ አግኝተው ሙሉ ጽሁፉን  ቢያነቡት ስል ከልብ ተመኘሁ:: ለነገሩ ሰውየው  ግራ የገባቸው እንደሆኑ ተግባራቸው ብቻ ሳይሆን ስማቸውም የሚሰጠን የሆነ ጥቆማ ሳይኖረው አይቀርም:: የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሆነው ኃ/ማርያም ተብለው መጠራታቸው በራሱ የተምታታ ነገር እንዳለ የሚያሳይ አንድ ጭብጥ ነው:: አይደለም ታምር የመስራት የማማለድ ስልጣን እንኳ የላትም በሚል እምነት የተጠመቀ ሰው “ኃ/ማርያም” ተብሎ ሲጠራ ምን ማለት ነው?

 

የሆነው ሆኖ ትግሉ ተፋፍሟል:: ለመብትና ለነጻነቱ እየተዋደቀ ያለው ሕዝብ የወያኔን አልጋ ክፉኛ ይነቀንቅ: በመንግሥት ላይ ሽብር ይፈጥር ይዟል:: ከእንግዲህ በኋላ ሞትን ፈርቶ ራሱንና ወገኑን ለጭቆናና ለጥፋት አጋልጦ የሚሰጥ ወንድም ሆነ ሴት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም:: ከእንግዲህ በኋላ ብዙ ሆኖ በጥቂቶች መሳደድና መዋረድ አይኖርም:: ከእንግዲህ በኋላ የሚያለቅስ ወንድ በሀገሬ ምድር አይታይም: ከእንግዲህ በኋላ ልጆቹን አስቀጥፎ ሀዘኑን ውጦ የሚቀመጥ ወላጅ: አባት እናቱን አስገድሎ አርፎ የሚቀመጥ ልጅ ይኖራል ተብሎ አይታሰብም:: ሕዝብ አምርሮ ሲነሳ መፈናቀል ሳይሆን ማፈናቀል ይችላል: መታሰር ሳይሆን ማሰር ይችላል: መሞት ሳይሆን መግደል ይችላል:: በዚህ መሀል ነገሩ ሁሉ ተገለባብጦ መንግስት መሸበሩ ሕዝብ ማሸበሩ አይቀሬ ይሆናል:: ማን አሸናፊ ማን ተሸናፊ እንደሚሆን ወደፊት ይታያል::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

አድሏዊ ሐዘኔታ (Selective Sympathy) ምንድነው? – (ኤፍሬም እሸቴ)

$
0
0

አድሏዊ ሐዘኔታ (Selective Sympathy) ማለት ተመሳሳይ ችግር የገጠማቸው ሁለት ወገኖች ቢኖሩ፣ ለአንዱ አዝኖ ለሌላኛው አለማዘን፣ ወይም ለአንዱ የበለጠ አዝኖ ለሌላኛው የነካነካ ሐዘን፣ አላዘኑም ላለመባል፣ ዕንባ ሳይመጣ «ወይኔ ወይኔ» ብሎ እንደሚለቀሰው ወጉን ለማድረስ የሚደረግ ጥረት ዓይነት ነው።

Saudicry

ይብዛም ይነስም ሁሉም ሰው ለአንድ ጉዳይ እኩል አያዝንም። በተለይም ዓለማችን የመከራ መአት በሚወርድባት በዚህ ዘመን፣ በዓለም ላይ ያለው መከራ ሁሉ እኩል ዋጋ አያገኝም፣ ሞትም ሁሉ እኩል ትኩረት አይሰጠውም። ሁሉም ነገር አድሏዊነት ያለበት በሚመስል መልኩ በግልጽ የሚታይ ነገር ነው።

በሊባኖስ እና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ቦንቦች ይፈነዳሉ፤ ብዙ ሰዎችም ያልቃሉ። በምዕራቡ ዓለም በኩል ከዕለት ዜና ማጣፈጫነት የዘለለ ፋይዳ አያገኝም። ይሁን እንጂ በፈረንሳይና በቤልጂየም ተመሳሳይ ፍንዳታ እና የኣሸባሪዎች አደጋ ሲደርስ ግን ዓለም ትገለበጣለች። ይህ አድሏዊ ሐዘኔታ ብዙ ሰዎችን ያበሳጫቸዋል። «የነዛን ነፍስ ነፍስ አይደለም ወይ?» እያሉ ምርር ብለው ይጠይቃሉ።

ወደ አገራችን እንኳን ብንመጣ፣ ለረዥም ዓመታት ብዙ መከራ በሕዝቡ ላይ ሲወርድ ከርሟል። አንዳንድ ሰዎች ግን መከራው ከጆሯቸው አልፎ ውስጣቸውን አይኮረኩረውም። ሰዎቹ ክፉ ሰዎች እንዳልሆኑ እናውቃለን። ነግር ግን ኃዘኔታው ከልባቸው ሳጥን ተፈልቅቆ ያልወጣበት ምክንያት ምንድነው? በሌላ ጊዜ ግን እነዚሁ ሰዎች ተወልደው ባደጉበት፣ ዘመድ ወዳጆቻቸው በሚኖሩበት አካባቢ ያው ችግር መከሰት ሲጀምረ ስሜታቸው ይቀየራል። የሰዎቹ ችግር እጅጉን ውስጣቸውን ሰብሮ ይገባል። ለሌሎቹ አላዘኑም ለነዚህኞቹ ግን አዝነዋል። ለምን?

1ኛ. አንድ ሰው ለሌላው ያለው ኃዘኔታ ቶሎ እንዲሰማው የቅርብም ይሁን የሩቅ የደም ትስስር ብዙ ወጋ አለው። አውሮፓ ውስጥ ለተከሰተው አደጋ አሜሪካኖች ቶሎ ምላሽ ሰጥተው ነገር ግን የመካከለኛ ምስራቁ ላይ ፍንክች የማይሉት አንድም ከአውሮፓውያን ጋር ባላቸው የደም ትስስር ምክንያት ነው።

አሜሪካ የሁሉም አውሮፓ አገሮች ዝርያዎች ድብልቅ ናት። በፈረንሳይ ለሚደርሰው አደጋ ፈረንሳውያን-አሜሪካውያን ቶሎ ቢያዝኑ ወይም ቤልጅየም ዝርያ ያላቸው አሜሪካውያን ቶሎ አጋርነታቸውን ቢያሳዩ አይደንቅም ማለት ነው። የሰው ልጅ እንዲህ ነው።

በቤተ ክርስቲያን የሚዜመው የጥር ሥላሴ «ነግሥ» (ነግሥ ዘጥር ሥላሴ)

«ሠለስቱ ነገሥት ይለብሱ ነደ፣

ወይዐጸፉ በረደ፣

አሐዱሰ ወልድ ሶበ እማርያም ተወልደ፣

በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ፣

ወአስተርአየ እምህቡዕ ገሃደ።» ይላል።

«በለቢሰ ሥጋ ኮነነ ዘመደ» በምትለዋ «ሥጋ በመልበሱ (ስለለበሰ ወይም ሰው ስለሆነ) ዘመዳችን ሆነ» ሲል ስለ ክርስቶስ የተናገረውን ነው ማንሣት የፈለግኹት። እኛን መሰለ ያለበትን። ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ነው በተለየ አካሉ ወደዚህች ምድር የመጣው። እናም ሊቁ «ዘመዳችን ሆነ» አለው። ያገራችን ሰው «ትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋ» እንደሚለው ማለት ነው። ሰው ሆኖ ለራስ ወገን ማድላት የሰው ጠባይ ነው። ይህንን ጠባይ የሚያሸንፍ ሰው በርግጥም ታላቅ ሰው ነው።

ኃዘኔታችን የሚቀሰቀስበት 2ኛው ምክንያት እነርሱ የገጠማቸው ዓይነት ችግር ገጥሞን ከነበረ ችግራቸውና ኃዘናቸው እኛንም ቶሎ ሊሰማን ይችላል። ያልተራበ ያልተጠማ ሰው ስለመራብ እና ስለመጠማት እንደማያውቀው ሁሉ ያልተቸገረ ሰውም ስለ ችግረኛ ሊገባው አይችልም። ኃዘንም ሊሰማው አይችልም። አንዱ ባለቅኔ እንዲህ አለ።

«አብን ተዉትና ንገሩት ለወልድ፣

ተገርፏል ተሰቅሏል እርሱ ያውቃል ፍርድ።»

ከፍ ብለን ከሦስቱ አካላት መካከል በተለየ አካሉ ሰው የሆነው ክርስቶስ ነው እንዳልነው ሁሉ ሰው ሆኖ ብቻ ሳይቀር ስለ እኛ የተገረፈው፣ የተቸነከረው እና በመስቀል ላይ የተሰቀለው በተለየ አካሉ እግዚአብሔር ወልድ ስለሆነ ባለቅኔው ይህንን ሐሳብ አኳሽቶ ያቀርበዋል። በነገረ ሃይማኖት አብና መንፈስ ቅዱስ ከወልድ የተለዩ እንዳልሆነ የሚያውቀው ባለቅኔው መከራን የሚያውቃት መከራን የተቀበለ መሆኑን ለማሳየት ወልድን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ለይቶ «ለወልድ ብቻ ንገሩት» ይለናል። ሰሙ ሳይሆን ወርቁን ስለምንረዳ ትርጉሙ ይከሰትልናል። ያልተነካ ግልግል ያውቃል አለ ያገራችን ሰው።

በሦስተኛ ደረጃ የአይዲዎሎጂም ሆነ የሃይማኖት አንድነት አንዱ ሰው ለሌላው ለማዘን ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ከተለያዩ አጋጣሚዎች መገንዘብ እንችላለን። አጼ ካሌብ በናግራን (በየመን) ያሉ ክርስቲያኖች መከራ እየደረሰባቸው እንደሆነ ሲሰማ መከራቸው ተሰምቶት ጦሩን ጭኖ፣ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ የመን ሄዷል። ጠላቶቻቸውንም ተበቅሎላቸዋል። በግብጽ ያሉ ክርስቲያኖች በአረማውያን ሲገደሉ በኢትዮጵያ ያለን ክርስቲያኖች ሁል ጊዜም እናዝናለን። በሌላውም እምነት እንደዚያው ነው።

በተለያዩ የእስልምና አገራት የሚፈጸሙ ጉዳዮች እያንገበገቧቸው ሐሳባቸውን በኃዘንም ሆነ በቁጭት ሲገልፁ የምናውቃቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አሉ። የቱርኩ መሪ በቅርቡ የተደረገበት መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እጅጉን ያሳሰባቸው፣ ኋላ የተገኘው ውጤትም ያስደሰታቸው ሙስሊም ወንድሞቻችን በሰፊው ሲወያዩበት እንደነበር ከፌስቡክ ተከታትለናል። በወቅቱ «የቱርኩ መሪ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንዲህ ታዋቂ መሆኑን አላውቅም ነበር?» ላልኩት ሐሳብ አንድ ሙስሊም ወንድም ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቶኝ አመስግኜዋለኹ።

በተጨማሪም አይዲዎሎጂ ከእምነት ባልተናነሰ የደስታም ሆነ የኃዘን ተጋሪ ሊያደርግ ይችላል። በዘመነ ሶሺያሊዝም አገራችን በሶማሊያ በተወረረች ጊዜ  በዓለማቀፋዊ ወንድማማችነት መርሕ መሠረት ኩባውያን ደማቸውን አፍስሰውልናል። ኮሪያዎችና ሶቪየቶች ከጎናችን ቆመዋል። ያው ኀዘናችንን ተካፍለዋል ማለት ነው።

በአራተኛ ደረጃ፤ የጥቅም ትስስርም የአንዱ ኃዘን የሌላውም ኃዘን እንዲሆን ያደርገዋል። አልቃሽ «ማን ይመግበኝ፣ ማን አይዞህ ይበለኝ» እያለ ቢያለቅስ አንድም የሞተው ሰው ምን ያህል ደግ እንደነበር እያወሳ ነው፤ አንድም የሱንም የወደፊት ጉዳት እየነገረን ነው። አይጠቅም-አይጎዳ ዓይነት ለሆነ ሰው የሚታዘነውና፤ ሰብሳቢ፣ ረጂ፣ የክፉ ቀን ደራሽ ለሆነ የሚታዘነው መቼም አንድ አይደለም። ሰው እንደዚህ አውቆትም ይሁን ሳያውቀው ጥቅሙን ተከትሎ ይደሰታል፤ ጥቅሙን ተከትሎ ያዝናል።

ከዚህ ሁሉ ባሻገር ደግሞ፣ ዘመኑ የፈጠራቸው ሚዲያዎች በሚሰጡት እና በሚነሱት ትኩረት ምክንያት አንድ ችግር ሞቅ ያለ ኃዘኔታ ወይንም የቀዘቀዘ ምላሽ ሊያገኝ ይችላል። በሰማነው መጠን እናዝናለን፣ ባልሰማነው መጠን አናዝንም። የ1977 ዓ.ምሕረቱ ኢትዮጵያ ረሃብና ችጋር መላውን ዓለም ያንቀሳቀሰውና የኃዘኔታ ጎርፍ ያወረደልን ሚዲያው ትልቅ ትኩረት ስለሰጠው ነበር።

ሰው እንደመሆናችን ከላይ በዘረዘርናቸው በአንዱ ወይም በሌላው ምክንያት ለአንዱ አዝነን ለሌላው ላናዝን ንችላለን። ይሁን እንጂ ለተጎዳ ሁሉ፣ ኃዘኔታ ለሚያስፈልገው ሁሉ ያለ አድልዎ ማዘን የትልቅ ሰውነት ምልክት ነው። ፊት አይቶ አለማድላት/አለማዳላት እና የሰው ዘር በመሆኑ ብቻ፣ ቀረብ ካደረግነውም ወገናችን ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ብቻ ችግሩን እንደራስ ችግር ወስዶ ማዘን ትልቅነት ነው።

አገራችን ኢትዮጵያ የመከራ መአት በሚወርድባት በዚህ ዘመን ማንንም ከማን ሳንለይ ለሁሉም ወገናችን ማዘንን፣ በችግራቸው ጊዜ መድረስ፣ ቁስላቸውን መጠገንን፣ ዕንባቸውን ማበስን ልንተገብር የሚገባበት የቁርጥ ቀን ነው። ኃዘናችን ግን ጊዜያዊ ነጥብ ለማስቆጠር ሳይሆን ከእውነት ይሁን። በምንም ይሁን በምን ምክንያት ለሚሰቃየው ወገን ያለ ምንም ልዩነት እንዘንለት። ይህ የችግር ጊዜ አልፎፐ በሰላም ለመኖር ያቺን የሰላም ቀን እንመኝ።

ይቆየን

የፖለቲካ እስረኞች በሚገኙበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የ እሳት ቃጠሎ ተነሳ

$
0
0

kilinto prison

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ አመራር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባና አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞ አመራር አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎችም የሃይማኖትና የፖለቲካ እስረኞች በሚገኙበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እሳት ተነሳ::

በተለይ በ እስር ቤቱ ዞን 3 የሚባለው ማሰሪያ ቤት ውስጥ ቃጠሎው በ እጅጉ ጉዳት እንዳደረሰ የሚገልጹት ምንጮች በ እስረኞች ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳለ የታወቀ ነገር የለም:: ሆኖም ግን እስረኞች ሊያመልጡ ይችላሉ የሚል ስጋት ያደረበት ፖሊስ ለማስፈራራት ወደ ሰማይ ጥይቶችን ሲተኩስ እንደነበር ከ አይን እማኞች ገለጻ ለመረዳት ችለናል::

ይህ የእሳት አደጋ የተነሳው ከካፍቴሪያ ውስጥ እንደሆነ ይገለጽ እንጂ ማን ሃላፊነቱን እንደሚወስድ የተገለጸ ነገር የለም::

የ እሳት አደጋ በሰጠው መግለጫ 3 አባላቶቼ ተጎድተውብኛል ይበል እንጂ በእስረኞች ላይ ስለደረሰ ጉዳት አልገለጸም:: ሆኖም ግን እሳቱን ለመቆጣጠር 7 የ እሳት አደጋ ትራኮችና 2 አምቡላንሶች መሳተፋቸውን አስታውቋል::

የቅሊንጦን እስርቤት ወያኔ ራሱ እንዳቃጠለው የሚያስጠረጥሩ ሁኔታዎችን አይቻለሁ |ከአይን እማኝ

$
0
0

kilinto prison

የቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በተለይም ዞን 3 እሳት አደጋ መነሳቱን ተክትሎ በስፍራው የነበሩ አንድ የአይን እማኝ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መል ዕክት እንደሚከተለው ተስተናግዷል::

ወያኔወች ሆን ብለው እንደአቃጠሉት የሚያስጠረጥሩ ነገሮች ስላየሁ መረጃው ሊጠቅማችሁ ይችላል በማለት ለናተ ለማድረስ አሰብኩ፡:
 ቤቴ ጎሮ አካባቢ ሲሆን በጠዋት ወደ ዱከም ለስራ መሄድ ነበረብኝ እናም እግረ መንገዴን እህቶቸን ጥሩነሽ ቤጅግ ሆስፒታል ለማድረስ በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ጠዋቱ 2፡30 ስዓት ገደማ ሳልፍ በማረሚያ ቤቱ አካባቤ ምንም አይነት የሚሰማም ሆነ የሚታይ ችግር አልነበረም፤ ያ ማለት ከግቢ ዉጪ ለማጥቃት (ለማቃጠል) የሚንቀሳቀስ ምንም ሰዉ አልነበረም፤
 ጉዞየን ወደ ዱከም ቀጠልኩ ታዲያ በቅርብ ርቀት ላይ ማለትም አቃቂ ኬላ አለፍ ብሎ አንድ የነዳጅ ማመላለሻ መኪና(መቸ እንደሆን አላዉቅም) በጎኑ ወድቓል ምንም የፈሰሰ ነዳጅም አይታይም የእሳት ቃጠሎም የለም ነገር ግን ሁለት የእሳት አደጋ መኪኖች እዛዉ አካባቢ ቆመዋለ፤ እኔም በሀሳቤ ይህኔ እሳት ቢኖር ኖሮ አደለም እዚህ ድረስ መሀል ከተማም አይደርሱም ነበር እያልኩ ከራሴ ጋር እያወራሁ አለፍኩ፤
 ከዱከም ጉዳየን ጨርሸ 4፡40 ሰዓት ስመለስ እነዛ ያየኃቸዉ የእሳት አደጋ መኪኖች የሉም ታዲያ ትንሽ እንደሄድኩ የተኩስና የአምቡላንስ ድምፅ ሰማሁ ከጥሩነሽ ቤጅግ ወደቅሊንጦ የሚወስደዉ መንገድም በፖሊሶች ዝግ ነዉ ከዛም የቅሊንጦ እስር ቤት እየተቃጠለ እንደሆነ ሰማሁኝ፤ ከዛ በኃላ ከመሀል ከተማ በመብራትና በሳይረን ድምፅ እየቀወጡት ተጨማሪ እሳት አደጋና አምቡላነስ ወደ ቅሊንጦ አለፉ፤

መላምቶች
1. በማረሚያ ቤቱ አካባቢ ምንም አይነት ሰልፍም ሆነ ግርግር ሳይኖረ በጥቃት ሊቃጠል የማይችል መሆኑ
2. እሳቱ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይኄ ስለፈሩ በቅርብ እርቀት በተጠንቀቅና በምክንያት እሳት አደጋ ማቆማቸዉ
3. በስድስት ሰዓት ሸገር ዜና ከ7 በላይ የእሳተ አደጋ አለ የተባለ ሲሆነ አንድም የወደቀዉ የነዳጅ ቦቲ ላይ አለመኖሩ::


(አሳዛኝ ዜና) ጳውሎስ፣ ጦር ኃይሎች እና ፖሊስ ሆስፒታሎች ከቂልንጦ እስር ቤት በመጡ 49 አስከሬኖች ተጨናንቀዋል ተባለ

$
0
0

kilinto prison

(ይህን ዜና ስጽፈው እጄ እየተንቀጠቀና እምባዬ እየወረደ እንደሆነ ይታወቅልኝ – ከዘ-ሐበሻ አዘጋጆች አንዱ)

(ዘ-ሐበሻ) በቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ትናንት የተነሳውን ቃጠሎ ተከትሎ የመንግስት ወታደሮች እስረኞች ሊያመልጡ ነበር በሚል በመተኮስ የገደሏቸው እስረኞች ቁጥር እያሻቀበ ነው::
ከአዲስ አበባ የመጡ የታማኝ ምንጮች ዘገባ እንደሚያመለክተው ጦር ኃይሎች ሆስፒታል፣ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል እና ፖሊስ ሆስፒታሎች በአስከሬኖች ተጨናንቀዋል::
እንደዘገባዎች ከሆነ በአጠቃላይ ትናንት የተገደሉት እስረኞች ቁጥር ወደ 49 አሻቅቧል:: በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አሉ የተባሉ አስከሬኖች ቁጥር እስካሁን ያልታወቀ በመሆኑ ቁጥሩ ከ49 በላይም እንደሚያድግ የሚገልጹት ምንጮች በጦር ኃይሎች ሆስፒታል 13 የ አስከሬኖች; በጳውሎስ ሆስፒታል 22 እንዲሁም በፖሊስ ሆስፒታል 14 እስረኞች አስከሬን እንዳለ ገልጸዋል:: የ ሟቾች ቁጥር እስካሁን አልታወቀም:: ብዙ ቤተሰብ ተጨንቆ ወደ ቅሊንጦ ቢያመራም እስረኞችን ማየት እንደማይችሉ ተገልጾላቸው ተመልሰው ነበር:: ሌሎች እስረኞች ዛሬ ሌሊት በ20 መኪኖች ተጭነው ወደ አልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

የጀርመኗ ትልቋ ከተማ ሙኒክ  በወያኔ  የተገደሉትን ጀኖች ኢትዮጵያውያንን በደማቅ ሁኔታ አስባ ዋለች

$
0
0


በዘርይሁን ሹመቴ  / ከጀርመን

          

ኢትዮጵያዊያንና  ትውልደ  ኢትዮጵያውያን  ዛሬ በ(28.12.2008ዓም) በ 03. 09. 2016 በጀርመን ሙኒክ  ከተማ በወያኔ  የጥይት  እሩምታ  ውድ  ህይወታቸውን  ላጡ    ንጹሃን  በማሰብ   ታላቅ የሻማ ማብራት  መርሃ  ግብር  አድርገዋል ። በተጨማሪም   የህዝብን የመብት  ጥያቄ  በተገቢውና በሰላማዊ  መንገድ  ከመመለስ  ይልቅ  መግደልና  ማሰርን አማራጭ  መፍትሄ  ያደረገውን   የወያኔንን  መንግስት በዚሁ  መርሃ  ግብር  ታዳሚው  በታላቅ  ድምጽ  አውግዘዋል። ይህንን  መርሃ ግብር  በሙሉ ሃላፊነት  ያዘጋጁት  በሙኒክና  አከባቢዎች  የሚገኙ ወደ 14 የሚደርሱ  ማህበራዊ  ተቋውማት እንዲህም  የሃህማኖት ድርጅቶች  በመተባበር  ነው ።

በሀገር ውስጥ የሚደረገው ህዝባዊ እንቢተኝነት እና ህዝባዊ አመጽ አድማሱን እያሰፋ አብዛኛውን የአማራ ክልሎች አዳርሷል።ኦሮሚያ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ከ10 ወር በላይ በጽናት ህይወታቸውን እየገበሩ መራራ  ትግልን  ከወያኔ  ቅጥረኞች የአጋዚ  ወታደሮች  ጋር  እያካሄዱ  በሚገኝበት  መላው  የአማራ  ህዝብ እስከመጨረሻው የነጻነት ደጃፍ መስዋትን ለመክፈል ቆርጦ  ተነስቷል። ይህ የአንድነት ንቅናቄ  ጎጠኛውን  ወያኔን  ከማስደንገጡ  አልፎ  በንጹሃን  የኢትዮጵያ  ህዝብ  ላይ  የጦርነት አውጇል። በሙኒኩ  የሻማ  ማብራትና  የተቋውሞ  መርሃ  ግብር  ላይ  የተገኙት  ታዳሚያን ሀገር ቤት ያለው ወገን ህይወቱን ሳይሳሳ እየገበረ ባለበት በዚህ ወሳኝ ሰአት በጀርመን የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያን ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን መስዋእት በማድረግ ለትግሉያላቸውን አጋርነት እስከመጨረሻው  ድረስ  እንደሚያሳዩ አረጋግጠዋል። ከዚህም  በተጨማሪ  ይህ  የህዝባችን  በአረመናዊ  መንገድ  በወያኔ  ታጣቂዎች  እየደረሰበት  ያለው  ግድያ በመቃወም  ያላቸውን  አቅም ተጠቅመው  በሚኖሩበት በጀርመን ሀገር ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ግፊት በመፍጠር  ወያኔ  ስልጣንን  ለህዝብ እስከሚያስረክብበት  ጌዜ ይህን የዜግነት  ግዴታቸውን እንደማያቋርጡ  ገልጸዋል ።
የጀርመኗ ትልቋ ከተማ ሙኒክ  በወያኔ  የተገደሉትን ጀኖች ኢትዮጵያውያንን በደማቅ ሁኔታ አስባ ዋለች
በዚህ ወሳኝ ሰአት የወያኔ  ጎጠኛና  ከፋፋይ ስርአት  ለማስወገድ  የሚጠቅሙ  ማንኛውም  አይነት  እንቅስቃሴ  ከፍተኛ ተጽእኖ ሰጥተው  እንደሚሰሩ  ታዳሚዎቹ  በማረጋገጥ ፤ ለመላው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  ያላቸውን የወገን አለኝታቸውን እና አንድነታቸውን እነደማያቋርጡ  አረጋግጠዋል ። በትእይንቱ  ወያኔ አገሪቱዋን  ማስተዳደር  ስላልቻለ  ስልጣኑን  በፍጥነት ለህዝብ  ያስረክብ ፤  በኢትዮጵያ  በአጋዚ  ወታደር  የሚፈሰው  ደም  የኛ  ደም  ነው ፤ ተላላኪው  ህውሃት  እንጂ  የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም ፤ ኢትዮጵያ  ውስጥ  የሚደረገውን  ትግል  እንደግፋለን ወዘተ የመሳሰሉት መፈክሮች  ታዳሚው  በታላቅ  ድምጽ  ሲያስተጋቡ  ታይተዋል።

በሙኒኩ  የሻማ  ማብራትና  ተቋውሞ  በሀይለማሪያም  በሚመራው  በወያኔ መራሹ ጦር  በአሰቃቂ  ሁኔታ የተገደሉትን ከ500 በላይ  ንጹሃን  ሰልፈኞችን በኦሮምያ እንዲሁም  ከ150 በላይ ስርአቱን  በመቃወም  በሰላማዊ  መንገድ  በአማራ  ክልል  በአደባባይ ወጥተው ሀይወታቸውን በጥይት ያጡትን ዜጎቻቸንን  በማሰብ  የህሊና  ጸሎት  በማድረግ  ሰማእተናታቸውን  ዘክረው  ውለዋል። በኢትዮጵያ ነጻነት እኩልነት አንድነት እንዲሁም  ፖለቲካ  ለውጥን  ለማምጣት  ውድ  ህይወታቸው  ለከፈሉት  ለእነዚህ  ጀግኖች የዚህ መርሃ ግብር ታዳሚዎች  የተሰማቸውን  ጥልቅ ሃዘን በመግለጽ  ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላው  የኢትዮጵያ  ህዝብ  መጽናናትን ተመኝተዋል።

በውድ ልጆችዋ መስዋእትነት ኢትዮጵያ ነጻ ትወጣለች!

Zerihun Shumete / Germany

የኢትዮጵያ ምጥ

$
0
0

ያዬ አበበ

ኢትዮጵያ ምጥ ላይ ነች። ከዚህ በፊትም ሁለቴ አርግዛ አዋላጆቿ የሚያደርጉትን ስላላወቁ እናት ብዙ ደም ፈሷት ከሞት አፋፍ ድናለች። የሦስተኛው ምጥ አዋላጅ ኢሕአዴግ ይሳካለት ይሆን?
እንዴት እዚህ ደረስን?

በዘመናዊ ትምህርትና በምዕራባዊያንና ምስራቃዊያን ፍልስፍናና ርዕዮተ አለም የተቀረፀው የ1960ቹ ትውልድ ኢትዮጵያን እንደሌሎቹ አገሮች የዳበረችና የበለፀገች አገር ለማድረግ ምኞቱና እምነቱ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ፤ የንጉሱም እድሜ 80ዎቹ ውስጥ ስለነበረ፣ አለምአቀፋዊ ኢኮኖሚያዊ ሂደቶች/የነዳጅ ዋጋ ስለናረና፣ አለምአቀፋዊ ሁለት ግዙፍ የፓለቲካ ጎራዎች ገዝፈው ከመውጣታቸው ጋር ተደምሮ ኢትዮጵያን ከባህላዊ አስተዳደር ወደ ህዝባዊ አስተዳደር ተስፈንጥራ እንደትገባ የሚታገል አብዮታዊ ትግል ተጧጧፈ። አብዮትም ፈነዳ።
የተማሪው ንቅናቄ ያስተናገደውና ወደ ውስጡ ያሰረፀው የምስራቃውያን ርዕዮት ኢትዮጵያን ከኃላቀርነትና ድህነት ወደ ስልጣኔና ብልፅግና ለማሸጋገር አቻ የሌለው አማራጭ ተደርጎ በወታደሩ፣ በተማሪውና በፓለቲካ ድርጅቶች ሊሂቃን ውስጥ ቅቡልነት አገኘ። “ኢሕአዴግ ዛሬ ለምን ከአገልግሎት አሰጣጥ ተሃድሶ ይልቅ ወደ ፓለቲካዊ ስርዓት ተሃድሶ አይገባም?” ለሚለውም ጥያቄ ዋናው ምክንያቱ ርዕዮታለማዊ መሰረቱ ነው።

eprdf
ኢህአዴግ በ’ዴሞክራሲያዊ’ ማዕከላዊነት የሚሰራ ድርጅት ነው። በዚህ ሌኒናዊ አወቃቀር ውስጥ ውሳኔ ከማዕከላዊ ኮሚቴ ወደ ህዝብ ይፈሳል። ከህዝብ ወደ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔም ተፅዕኖም አይፈስም። ኢህአዴግ ይሄንን ለምን መረጠ? በተማሪው ንቅናቄ ወቅት ለኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ‘የሚመጥን’ ታሪካዊ፣ ማህበረሰባዊና፣ ፓለቲካዊ ሂደት የተገኘው ከምስራቃዊያን ርዕዮተአለም ሰለነበረ ነው።

ዛሬ በኢሕአዴግና በህዝብ መካከል ያለው ቅራኔ ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ከሚያይበትና ከበየነበት መንገድ የተነሳ ነው። ኢሕአዴግ ኢትዮጵያ ከኃላቀርነትና ድህነት መውጣት ምትችለው በአንድ አውራ ፓርቲ አመራር ብቻ ነው ብሎ ያምናል። ይሄ እምነቱ በግልፅ የተሰመረበት ጉዳይ ነው። የአገራችን ቅራኔ እምብርቱ ይሄ መሆኑን መገንዘቡ ኢሕአዴግ የኃይል እርምጃን መንገድ ብቻ ለመምረጡ ዋናው ማብራሪያ ነው።

የተማሪው ንቅናቄ አመራር አባል የሆነ አንድ ሰው ‘በሚልየኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መስዋዕትነንት አድርገን አገራችንን ለመለወጥ ዝግጁ ነን’ የሚል ነገር እንደነገራቸው አንድ አውሮፓዊ ፀሃፊ ጠቁመዋል። ያንን ያላቸው ሰው በ 1960ዎቹ ነው። ዛሬም ኢሕአዴግ ውስጥ ያንን አይነት ስሌት አንዳለ ከኢሕአዴግ ተግባር ማየት ይቻላል። “ህዝብ ጎርፍ ነው፣ ወደ ቀየስክለት ይፈሳል” የሚል እምነት ያላቸው ሰዎች የሚመሩት ኢሕአዴግ አገሪቱን ወደ እርስበርስ ግጭት ይዟት እየነጎደ ነው።

ወዴት እየሄድን ነው?
በንጉሱም፣ በወታደራዊው መንግስትም ውስጥ የአገሪቱ አቅጣጫ ያሳሰባቸው ሰዎች አገሪቱን ከአደጋ ለመታደግ ሞክረዋል። ከነ ገርማሜ ነዋይ አንስቶ እስከነ ጄኔራል ፋንታ በላይ ድረስ ለአገሪቱ የተሻለ አማራጭ እንዳለ የተረዱ ሰዎች ራሳቸውን ለድሃው ህዝብ ጥቅም ሲሉ አደጋ ውስጥ ጨምረዋል፣ ተሰውተዋል።

ዛሬም አገሪቱ ያለችበት አደጋ ሚታያቸው ሰዎች በኢሕአድግ ውስጥ አሉ ብሎ መገመት ይቻላል። አገሪቱን ከፅንፈኛ የግራ ርዕዮት ቁማራዊ ስሌት መታደግ ከሚችሉት ውስጥ አንዱ እነዚህ ሰዎች ናቸው። መሞከርም አለባቸው። ከውስጥ የሚነሳ ለውጥ ከሌለና የኃይል እርምጃው ከቀጠለ ግን ለየት ያሉ ሰዎች ተደማጭነታቸው በህዝቡ ውስጥ እየጨመረ ይመጣል። በተለይም የመንግስትን የኃይል እርምጃ ለመቋቋምም ሆነ ለመግታትና ለማሸነፍ ተመጣጣኝ ብቻ ሳይሆን የጭካኔ ስልት መምረጥ የግድ ነው የሚለውን መስመር የሚከተሉ ታጋዮች በአገሪቱ በሰፊው ይራባሉ።

በተለይም ተጠቃሚ ናቸው ተብለው በተመደቡ ብሄሮች ላይ ብሄር ተኮር ጭካኔ እየጨመረና የትግል ስኬት መለኪያና መስፈሪያም እየሆነ ይመጣል። በክልሎች ብቻ ሳይሆን በመደናዋም ጭምር በሰፊው ግጭቱ ብሄር ተኮር ቅብ ይዞ ይስፋፋል። ይሄንን ክፍተት የሚያገኙ በሶማሌያና በኬንያ የሚገኙ አክራሪ ቡድኖች የራሳቸውን አጀንዳ ለማራመድ መንቀሳቀሳቸውም አይቀሬ ነው። አይ ኤስ ኤስም ጎራ ይል ይሆናል። በዚህ አጋጣሚም ሌሎች የጎረቤትና አካባቢያዊ አገራትም ፓለቲካዊ ስሌታቸውን ከጥቅማቸው አንፃር ያሰላሉ፣ ተፅዕኖ ማድረጋቸውንም በጣልቃገብነት በሰፊው ይያያዙታል።

እስከዛሬ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተነዛው አሉታዊ የብሄር ፕሮፓጋንዳ ፍሬ ሚያፈራውም በዚህ ወቅት ይሆናል። በተለይም በብሄር ላይ ያተኮረው ‘የብሶት’ ቁጣ ዱላም የሚያርፍበትን ሚያገኘውም በዚህ አጋጣሚ ነው። የኢሕአዴግ አባላትና በተለይም የስርዓቱ አራማጅ የሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችን ማጥቃት የግጭቱ የሞራል ግዴታ ተደርጎ የወሰዳል። ይሄንን አይነት ‘ጀብድ’ ሚፈፅሙትም ‘ጀግኖች’ ይሆናሉ።

ይሄ ሁሉ ግን ከኢሕአድግ የርዕዮት ወንፊት/filter የተነሳ ነው። ኢሕአዴግ ከራሱ ሌላ ለአገሪቱ የሚበጅ ሃሳብ የለም ብሎ ስለሚያምንና፣ ይሄንንም እምነቱን እስከ መጨረሻው ይዞ ለመግፋት ዝግጁ ስለሆነ ነው። አገሪቱ ከብሄር ጦርነትና ከባዕዳን ጣልቃገብነት በኃላ ምን አይነት እጣፈንታ እንደሚኖራት ለመገመት አገራዊ ተሞክሮ ስለሌለን ቢያዳግትም፣ ህዝባዊ አገዛዝ እንፈጥራለን ብሎ ማሰብ ግን የዋህነት ነው። ከድጡ ወደ ማጡ እንወርዳለን።

ኢሕአዴግ እንዴት ጥሩ አዋላጅ ይሁን?

ኢሕአዴግ ብቁ አዋላጅ ለመሆን ወደ ሽግግራዊ ድርድር (negotiated transition) ከማምራት ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም። ሽግግራዊ ድርድር ማለት የሽግግር መንግስት ማቋቋም ማለት አይደለም። ሽግግራዊ ድርድር አሁን ካለንበት የአንድ ፓርቲ የበላይነት ወደ መድብለ ፓርቲ ስርዓት ለመሸጋገር የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታዎች የሚያመቻች ሂደት ነው። ሽግግራዊ ድርድሩ አዲስ የመንግስት ስርዓት ለመመስረት ሳይሆን ያለውን ህገመንግስታዊ አወቃቀርና ፓለቲካዊ ስርዓት ለማስተሳሰርና ወደ ህገመንግስታዊነት ሂደት ለመግባት ነው።
ሽግግራዊ ድርድር ለማድረግ ኢሕአዴግ ቢያንስ የሚከተሉትን ማድረግ ይጠበቅበታል፦

1 ኢሕአዴግ ራሱን ከአውራነት ወደ መደበኛ ፓርቲነት ደረጃ ለማውረድ መወሰን አለበት።
2 ኢሕአዴግ በፓርቲና መንግስት መካከል ልዩነት መኖር የለበትም የሚለውን አቋሙን መተው አለበት።
3 ህጋዊ ፓርቲዎች በአገር ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያቀጭጩና የሚያግዱ ህጎቹን መሻር አለበት።
4 ለሽግግራዊ ድርድር ህገመንግስታዊ መሻሻል ለማድረግ የሚያስፈልጉ ነጥቦች ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ፈቃደኛ መሆን አለበት።
5 ለሽግግራዊ ድርድር የሚያስፈልገውን የእርቅ ሂደት ለመጀመር በመንግስታዊ የኃይል እርምጃዎች ላይ ያተኮረ የአደባባይ የምርመራ ጉባኤ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን አለበት።
6 ለሽግግራዊ ድርድር በቅድሚያ በአገር ውስጥ ካሉ ህገመንግስቱን ከሚቀበሉ ህጋዊ ፓርቲዎች ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድርድር መጀመር አለበት።
7 ለሽግግራዊ ድርድር ህጋዊ ተቃዋሚዎችን እንዲያገለግሉ የህዝብ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና ጋዜጦች በቋሚነት የአገልግሎት ጊዜ መደልደል አለበት።
8 ለሽግግራዊ ድርድር በኃይል እርምጃ ውሳኔና ትዕዛዝ ላይ ከተሳተፉ ከፍተኛ አመሮች ውስጥ ከትጥቅ ትግሉ ጊዜ ጀምሮ በኢሕአዴግ ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ ግለሰቦች በሙሉ ከድርጅቱ በጡረታ ማሰናበት አለበት።
9 ከሽግግራዊ ድርድሮች በኃላ በአንድ ዓመት ውስጥ አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለማደረግ ፈቃደኛ መሆን አለበት።

ሆኖም ዛሬ ኢሕአዴግ ይሄን አይነት መንገድ ይከተላል ብሎ ማመን ግን አይቻልም።

ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚ ኃ/ማሪያም፡ “በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል”

$
0
0
ስዩም ተሾመ

ስዩም ተሾመ

ክቡር ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማሪያም ሰላምና ጤና ከእርስዎ ጋር ይሁን። ስሜ ስዩም ተሾመ ይባላል። በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የወሊሶ ካምፓስ መምህር ነኝ። በትርፍ ግዜዬ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የትንታኔ ፅሁፎችን እፅፋለሁ። በእርግጥ መፃፍ የጀመርኩት ከዘጠኝ ወር በፊት ሲሆን እኔ በምኖርበት ወሊሶ ከተማ የታየውን ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ በማስመልከት ነው። ከዚያ በኋላ ከ50 በላይ ፅሁፎችን በድረገፅ ላይ አውጥቼያለሁ። ከፅሁፎቼ ውስጥ “በቀውሱ የህዳሴን መንገድ ይቀይሱ – ለጠ/ሚ ኃ/ማሪያም) የሚል ይገኝበታል። ይህ መፃፍ የጀመርኩበት አጋጣሚና የፅሁፎቼ ዓላማ መንግስትና ሕዝብን የማሳወቅ እና የመፍትሄ ሃሳቦችን መጠቆም እንደሆነ እንዲያውቁልኝ ስለፈለኩ ነው። ይህን ፅሁፍም ከዚሁ አንፃር ተመልክተው፣ በፅሁፉ ለምዳስሰው ችግር አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጡት በቅድሚያ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

በቀጥታ ወደ ጉዳዩ ስገባ፣ ማክሰኞ ነሃሴ 24/2008 ዓ.ም በቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ፤ “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” ማለትዎ ይታወሳል። አንዳንድ ወገኖች ይህን ዓ.ነገር “በሕዝብ ላይ ጦርነት ታወጀ!” በማለት አስተያየት ሲሰጡ ነበር። በእርግጥ ያስተላለፉት ትዕዛዝ ወቅታዊ ስለሆነ፣ እርስዎ ዓ.ነገሩን ከተናገሩበት አውድ ውጪ ሊወሰድና የተለየ ትርጉም ሊሰጠው እንደሚችል በመገመት ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር። ነገር ግን፣ “በአማራና ኦሮሞ ሕዝብ ላይ ጦርነት ታውጇል” የሚባለው ነገር እየተደጋገመ ቀጠለ። ይሄ ነገር እኮ ሲደጋገም እውነት ይመስላል” አልኩና በጉዳዩ ላይ ለመፃፍ አንዳንድ ማጣቀሻ የሚሆኑ ፅሁፎችን ማንበብ ጀመርኩ።

መቼም በእንዲህ ያለ ጉዳይ ላይ የሚቀርብ ትንታኔ በተቻለ መጠን በተረጋገጠ መርህ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት። መጀመሪያ ላይ ለመፃፍ ስነሳ በጉዳዩ ዙሪያ ያለውን ግራ መጋባትና የተዛባ አመለካከትን ለመቅረፍ የሚያስችል አሳማኝ ፅሁፍ ለማውጣት ነበር። መጨረሻ ላይ የደረስኩበት ድምዳሜ ግን ለእኔ ራሱ በጣም ነው ያስደነገጠኝ። በእርግጥ እርስዎ ጠ/ሚኒስተር የሆኑት ሕዝብን ለማገልገል ካለዎት ቀና እሳቤ እንደሆነ ፍፁም ጥርጥር የለኝም። እኔም ከዚህ ድምዳሜ ላይ እደርሳለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም። ይሁን እንጂ እውነቱ ሁለታችንም እንዳሰብነው አይደልም። ክቡር ጠ/ሚኒስተር “በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል!”

hailemariam Desalegn

ከላይ በጠቀስኩት ምክንያት በዚህ ፅሁፍ የሚቀርበው ትንታኔ ከወቅታዊ ማስረጃዎች ይልቅ በታሪክ ፍልስፍና (Philosophy of History) ላይ የተመሰረተ ነው። ለዚህ ደግሞ በዘርፉ ፈር-ቀዳጅ የሆነው ሩሲያዊ የታሪክ ፈላስፋ ሊዮ ቶልስቶይ (Leo Tolstoy) “War and Peace” በተሰኘው መፅሃፉ የሰጠውን ትንታኔ መሰረት ያደረገ ነው። ሊዮ ቶልስቶይ በዚህ መፅሀፍ የአንድ ሀገር መንግስት በሌላ ሀገር ወይም በራሱ ሕዝብ ላይ ለምንና እንዴት ጦርነት እንደሚያውጅ፣ በጦርነት ወቅት ለምን ሰው ጨካኝ እንደሚሆን፣ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ትንታኔ ሰጥቷል።

ወደ ዝርዝሩ ከመግባታችን በፊት በቅድሚያ “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” የሚለውን ዓ.ነገር ሦስት ቦታ መክፈል ያስፈልጋል። በዚህ መሰረት፣ 1ኛ) “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች” – የዕዝ ሰንሰለት (Chain of commands)፣ 2ኛ) “አዝዣለሁ” – የማዘዝ ስልጣን (Commanding Power) እና 3ኛ) “የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ” – ምክንያት (Justification) በማለት ሦስት ቦታ ተከፍሏል። ከዚህ በመቀጠል፣ የእርስዎ፥ የክቡር ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ትዕዛዝ፣ በፀጥታ ኃይሎች እየተወሰደ ያለው እርምጃ፣ እንዲሁም እንዴት በሕዝብ ላይ የታወጀ ጦርነት ሊሆን እንደቻለ እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርቧል።

1ኛ) የዕዝ ሰንሰለት (Chain of commands)

“ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች” የሚለው ፅንሰ-ሃሳብ የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የክልል ልዩ ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታና ደህንነት መስሪያ ቤቶችን ያካትል። እነዚህ ተቋማት የሚመሩት ድርጅታዊ መዋቅርን በተከተለ የዕዝ ሰንሰለት (Chain of commands) መሰረት ነው። ከፀጥታና ደህንነት ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም የአስተዳደርና ቢዝነስ ተቋማት ስራና አመራራቸው በአንድ መሰረታዊ የአሰራር ሕግ ላይ የተመሰረተ ነው። በማንኛውም ድርጅት ውስጥ በተለያየ የእርከን ደረጃ ላይ ያሉ ሰራተኞች እና አመራሮች የስራ ድርሻቸውና የኃላፊነት ደረጃቸው የሚወስነውን በዚህ ሕግ መሰረት ነው። ሊዮ ቶልስቶይ በመፅሐፉ ይህን ሕግ እንደሚከተለው ይገልፀዋል፡-

“[M]en combine in such relations that the more directly they participate in performing the action the less they can command and the more numerous they are, while the less their direct participation in the action itself, the more they command and the fewer of them there are; rising in this way from the lowest ranks to the man at the top, who takes the least direct share in the action and directs his activity chiefly to commanding.” Leo Tolstoy, War and Peace, P.1157

ከላይ ከሀገሪቱ ጠ/ሚ ጀምሮ እስከ ታችኛው እርከን ላይ ያሉ ወታደሮች እና ፖሊሶች በሥራቸው ላይ ያላቸው ተሳትፎ፣ የማዘዝ ስልጣንና የሰራተኞቹ ብዛት በዚህ ሕግ ይወስናል። በዚህ መሰረት፣ ከታች ያለው ተራ ወታደር ወይም ፖሊስ በቁጥር በጣም ብዙ ነው፣ በስራው ላይ ያለው የማዘዝ ስልጣን በጣም ውስን ነው፣ ፀጥታን በማስከበሩ ሥራ ላይ ግን ቀጥተኛ ተሳታፊ (ፈፃሚ) ነው። የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ የሆኑት ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ደግሞ፤ በቁጥር አንድ ግለሰብ ናቸው፣ ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የማዘዝ ስልጣናቸው ሙሉ ነው፣ ፀጥታን በማስከበር ረገድ ያላቸው ቀጥተኛ ተሳትፎ ግን ምንም (ዜሮ) ነው። በተራው ወታደር/ፖሊስ እና በጠ/ሚኒስትሩ መካከል ያሉ አዛዦችና ኃላፊዎች ፀጥታን በማስከበሩ ረገድ ያላቸው ቀጥተኛ ተሳትፎ፣ ብዛትና የማዘዝ ስልጣን እንደ የስልጣን ደረጃቸው እየጨመረ ወይም እየቀነሰ ይሄዳል።

2ኛ) የማዘዝ ስልጣን (Commanding Power)

የስልጣን (Power) ፅንሰ-ሃሳብ ከላይ አንደኛ ላይ በተጠቀሰው ድርጅታዊ መዋቅር ውስጥ በተዘረጋው የዕዝ ሰንሰለት መሰረት በሚደረግ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ነው። ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” የሚለውን ትዕዛዝ ሲያስተላልፉ በዕዝ ሰንሰለቱ ውስጥ ያላቸውን የስልጣን ደረጃ በግልፅ ይጠቁማል። የሁሉም ፀጥታ ኃይሎች የበላይ አዛዥ ናቸው። በተራ ወታደር/ፖሊስ እና በጠ/ሚ ኃ/ማሪያም መካከል የተዘረጋው የስልጣን እርከን ዓላማና ተግባሩ – ትርጉሙ ምንድነው? በዚህ ላይ ሊዮ ቶልስቶይ የሚከተለውን ምላሽ ይሰጣል፡-

“Power is the relation of a given person to other individuals, in which the more this person expresses opinions, predictions, and justifications of the collective action that is performed, the less is his participation in that action.” Leo Tolstoy, War and Peace, P.1157

እንደ ቶልስቶይ አገላለፅ፣ በታችኛው የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ ወታደሮችና ፖሊሶች ያለባቸው ኃላፊነት ትዕዛዝን ተቀብሎ መፈፀም ነው። እንደ ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ የሚገኝ ሰው ኃላፊነትና ተግባሩ በፀጥታ ኃይሎች የሚፈፀሙ ተግባራት አግባብነትና አስፈላጊነት ላይ አሳማኝ ምክንያት ማቅረብ ነው።

በስልጣን እርከኑ ከላይ ወደታች እወረድን በሄድን ቁጥር አስተያየት፣ ትንበያና ምክንያት የማቅረብ ኃላፊነቱ እየቀነሰ፣ በፀጥታ ማስከበር ተግባሩ ያለው ቀጥተኛ ተሳትፎ እየጨመረ ይሄዳል። በመጨረሻ እርከን ላይ ያለው ተራ ወታደርና ፖሊስ በፀጥታ ማስከበር ተግባራት አግባብነትና አስፈላጊነት ላይ የራሱን አስተያየትና ምክንያት የመስጠት ስልጣንና ኃላፊነት የለውም። በተቃራኒው፣ የላይኛው የሥልጣን እርከን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት ደግሞ ሥራና ኃላፊነታቸው የፀጥታ ኃይሎች ለሚፈፅሙት ተግባራት አስፈላጊነትና አግባብነት ምክንያት (Justification) ማቅረብ ነው።

3ኛ) ምክንያት (Justification)

የሰው ልጅ ምክንያታዊ አስተሳሰብና የሞራል ስብዕና ያለው ፍጡር ነው። እንያንዳንዱ ግለሰብ ከዚህ በፊት ያደረገውን፣ አሁን እያደረገ ያለውን እና ወደፊት የሚያደርገውን ነገር አግባብነትና አስፈላጊነት የሚወስንበት የራሱ የሆነ ምክንያታዊ አስተሳሰብ እና የሞራል እሳቤ አለው። በዚህ መሰረት፣ ማሰብና ማገናዘብ የሚችል ሰው በሌላ ሰው ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት አይፈፅምም። ይህን የሚፈፅም ከሆነ ግን ጤናማ አዕምሮ የሌለው፤ ምክንያታዊ አስተሳሰቡን እና/ወይም የሞራል እሳቤውን ያጣ ሰው መሆን አለበት። ነገር ግን፣ ላለፉት ዘጠኝ ወራት እንዳየነው የሀገራችን የፀጥታ ኃይሎች በቀላሉ ሊስተናገዱ የሚችሉ ጉዳዮችን ሁሉ በጥይት፣ በዱላና በእስር ለመፍታት ይሞክራሉ።

ክቡር ጠ/ሚ፣ ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ባልታየ መልኩ በዘንድሮ አመት ብቻ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለሞት፣ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ ለአካል ጉዳትና ለእስር ተዳርገዋል። ማህበራዊ ድረገፆችን የሞላው የሀገራችን የፀጥታ አስከባሪዎች ጭካኔና ማንአለብኝነት በሚያሳዩ ምስሎች ነው። ከሕዝብ በተሰበሰበ ታክስ ደሞዝ የሚከፈላቸው ፖሊሶችና ወታደሮች ሰላምና ደህንነቱን ከማስጠበቅ ይልቅ ለምን ይገድሉታል? ለምን ያለ አግባብ ይደበድቡታል? ለምን ያለ ፍትህ አስረው ያሰቃዩታል?

ክቡር ጠ/ሚ እኔ በሰብዓዊነት (humanity) ላይ ፅኑ እምነት አለኝ። እርስዎም ሆኑ እያንዳንዱ ወታደር እና ፖሊስ እንደ ሰው ሰብዓዊ ስሜትና ርህራሄ አላቸው ብዬ አምናለሁ። ከምንም በላይ ደግሞ ተግባርና እንቅስቃሴያቸው በምክንያታዊ አስተሳሰብና በሞራል ስብዕና እንደሚመራ አምናለሁ። ነገር ግን፣ በራሳቸውም ሆነ በሌላ ሰው ላይ እንዲደርስ የማይፈልጉትን ነገር በኦሮሞ፣ አማራ፣ ኮንሶ፣…ወዘተ ነዋሪዎች ላይ ዘግናኝ የሆነ በደልና ጭቆና ሲፈፅሙ ይስተዋላል። እንደ ግለሰብ የማያደርጉትን ነገር በአለቃዎቻቸው ሲታዘዙ ግን ያደርጉታል። እንደ ሰው ያላቸውን ምክንያታዊነት (rationality) እና የሞራል ስብዕና ያሳጣቸዋል። ለዚህ ደግሞ ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች አሉ።

አንደኛ፡- የፀጥታ ኃይሎች እንደ ሰው ያላቸውን ምክንያታዊ አስተሳሰብ የሚያጡት በፀጥታ የማስከበር ሥራቸው ላይ በነፃነት የማሰብም ሆነ የመወሰን ስልጣንና ኃላፊነት ስለሌላቸው ነው። ምክንያቱም፣ እንደ ሰው የማሰብ ነፃነቱን ወይም ኃላፊነቱን ለበላይ አለቆቻቸው አሳልፈው ሰትተዋል። እንደ ሊዮ ቶልስቶይ አገላለፅ፡-

When a man works alone he always has a certain set of reflections which as it seems to him directed his past activity, justify his present activity, and guide him in planning his future actions. Just the same is done by a concourse of people, allowing those who do not take a direct part in the activity to devise considerations, justifications, and surmises concerning their collective activity.

ሁለተኛ፡- በግዳጅ ላይ የተሰማሩ ወታደሮችና ፖሊሶች ስለተግባራቸው ምክንያታዊነት ወይም አግባብነት የማሰብ ስልጣንና ኃላፊነት የላቸውም። ስለዚህ፣ የማሰብ ነፃነት የሌላቸው ሰዎች ምክንያታዊ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው መጠበቅ አይቻልም። ነገር ግን፣ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ባይኖራቸውም፣ እንደ ሰው የሞራል ስብዕና አላቸው። ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ዜጎችን ያለ ርህራሄ የሚደበድቡ፣ የሚያስሩና የሚገድሉ ፖሊሶችና ወታደሮች የሞራል እሳቤ የላቸውም። ምክንያቱም፣ በየበላይ ባለስልጣናት የሚቀርቡ ምክንያቶች (justifications) የፀጥታ ኃይሎችን ሞራል የጎደለው፥ ኢሰብዓዊ ድርጊት እንዲፈፅሙ ከሞራል እዳ ነፃ ያደርጋቸዋል። በድጋሜ ሊዮ ቶልስቶይ ባለስልጣናትና ኃላፊዎች በሚሰጧቸው ምክንያቶች በፀጥታ ኃይሎች የሞራል ስብዕና ላይ የሚፈጥረውን ተፅዕኖ እንዲህ ይገልፀዋል፡-

“These justifications release those who produce the events from moral responsibility. These temporary aims are like the broom fixed in front of a locomotive to clear the snow from the rails in front: they clear men’s moral responsibilities from their path. Without such justification there would be no reply to the simplest question that presents itself when examining each historical event. How is it that millions of men commit collective crimes- make war, commit murder, and so on?” Leo Tolstoy, War and Peace, P.1156

በአጠቃላይ፣ 1ኛ) በዕዝ ሰንሰለት (Chain of commands) ሕግ መሰረት ከታች ያሉት ወታደሮች እና ፖለሶች በፀጥታ ማስከበር ተግባሩ ላይ በቀጥታ ተሳታፊዎች ናቸው። 2ኛ) በፀጥታ በማስከበር ተግባሩ በቀጥታ ተሳታፊ የሆኑት ወታደሮችና ፖሊሶች በፀጥታ ማስከበር ሥራቸው ላይ የማዘዝ ስልጣን (Commanding Power) የላቸውም። 3ኛ) በፀጥታ አስከባሪዎች ተግባር አግባብነትና አስፈላጊነት ዙሪያ በባለስልጣናት የሚሰጡ አስተያየቶች እና ምክንያቶች (Justifications) የወታደሮች እና ፖሊሶችን ከምክንያታዊ አስተሳሰብና የሞራል ስብዕና ያጠፋዋል። በዚህ መሰረት፣ ዘወትር እንደምናየው በየከተማው ለግዳጅ የተሰማሩ ወታደሮችና አድማ በታኝ ፖሊሶች በዜጎች ላይ ስለሚፈፅሙት ድብደባ፣ እስርና ግድያ አግባብነት በጥልቀት እንዳያስቡ እና ሰብዓዊ ርህራሄ እንዲያጡ አድርጓቸዋል። ምክንያቱም፣ ፀጥታ የማስከበር ተግባሩ አስፈላጊነትና አግባብነትን በተለመለከተ አሳማኝ ምክንያት የማቅረብ ስልጣና እና ኃላፊነት ያለበት የበላይ አዛዡ ነው።

ክቡር ጠ/ሚ ኃ/ማሪያም፣ የሀገሪቱ የጦር ኃይሎች አዛዥ እንደመሆንዎ፣ የሁሉም የፀጥታ ኃይሎች ለሚፈፀመው ተግባር አግባብነትና አስፈላጊነት የመጨረሻውን ቃል የሚሰጡት እርስዎ ነዎት።

4ኛ) ጦርነት (War)

ስለዚህ የአንድ ሀገር መንግስት በሌላ ሀገር ሕዝብና መንግስት ላይ ጦርነት እንዲያውጅ የሚያደርገው፣ ወይም ደግሞ በራሱ ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላው ተግባር የሚፈፅመው እንዴትና ለምንድነው? የአንድን ሀገር መንግስትና ሕዝብ ወደ ጦርነት የሚያስገባው የባለስልጣናት ትዕዛዝ፣ የወታደሮች ፍላጎት ወይስ የፖለቲካ ልሂቃን ግፊት ነው? አብዛኛዎቹ የታሪክ ምሁራን የባለስልጣናት ውሳኔና የምሁራን ግፊት እንደሆነ ይገልፃሉ። ነገር ግን፣ እንደ ሊዮ ቶልስቶይ አገላለፅ፣ የአንድ ሀገር መንግስት በሌላ ሀገር ላይ ወይም በተወሰነ የሕብረተሰብ ክፍል ላይ ጦርነት የሚያውጅበትን ምክንያት እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡-

“The movement of nations [war] is caused not by power, nor by intellectual activity, nor even by a combination of the two as historians have supposed, but by the activity of all the people who participate in the events, and who always combine in such a way that those taking the largest direct share in the event take on themselves the least responsibility and vice versa.” Leo Tolstoy, War and Peace, P.1157

ከላይ በጥቅሱ ውስጥ እንደተገለፀው፣ ጦርነት በአንድ ወይም በሁለት አካላት ውሳኔና እንቅስቃሴ ምክንያት የሚጀመር ክስተት አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ በሁሉም አካላት ጥምር ተሳትፎ ምክንያት የሚከሰት ነው። ከሁሉም በላይ የጦርነት ዋና መነሻ ምክንያት በጦርነቱ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው፤ ወታደሮች፣ ፖሊሶች እና ሌሎች የፀጥታና ደህንነት ኃይሎች በውጊያ ላይ ለሚፈፅሙት ኢሰብዓዊ ድርጊት ኃላፊነት እንዳይሰማቸው የሚያደርገው አሰራር እንደሆነ ተገልጿል።

በአጠቃላይ፣ ጦርነት እጅግ በጣም መጥፎ ነገር ነው። የሰው ልጅ ምክንያታዊ ግንዛቤ ይጋርዳል፣ የሞራል ስብዕናን ያወርዳል። በዚህም ሰውን ከሌላ ተራ እንስሳ እኩል ያደርጋል። ጦርነት ምንም ጥሩ የለውም። አንዳንድ የዘርፉ ምሁራን፣ ለምሳሌ፡-የሩዋንዳ ዘር ማጥፋት (Rwanda Genocide in 1994)፣ የአይሁዳዊያን ዘር ማጥፋት (The Holocaust)፣ የዩክሬን ችጋር/ቸነፈር (The Holodomor)፣ የአሜሪካ ዘር ማጥፋት (The Armenian Genocide of 1915)፣ እና የመሳሰሉት የዓለም አሰቃቂ ክስተቶች የተፈፀሙት ጦርነት ጥላ ስር እንደሆነ ይገልፃሉ።

“The strategic rationale for genocide is never based on emotion — not prejudice, not hatred, not sexual aggression, not personal greed, not religious belief — but is rather always based on the cold calculus of war. Nearly every genocide or atrocity or massacre around the world in the last hundred years occurred in the context of war, and was a planned act of military strategy.” Philosophy Weekend: Can A Person Be Guilty Of Genocide?

5ኛ) “በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል?”

ክቡር ጠ/ሚ፣ እንደ የኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተርና የጦር ኃይሎች አዛዥነትዎ፤ “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” በማለት ያስተላለፉት መልዕክት በሕዝብ ላይ ጦርነት እንደማወጅ ይቆጠራልን? በሊዮ ቶልስቶይ የታሪክ ፍልስፍና መሰረት ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል እርስዎ የተናገሩትን ዓ.ነገር ከፋፍሎ መመልከት ያስፈልጋል።

በዚህ መሰረት፣ 1ኛ) “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች” በሚለው ሐረግ ጠ/ሚኒስትሩ የሀገሪቱን ፀጥታና ደህንነት መስሪያ ቤቶች “የዕዝ ሰንሰለት” (Chain of commands) በመጠቀም፣ 2ኛ) “አዝዣለሁ” በሚለው ቃል ደግሞ እንደ ጠቅላይ ሚኒስተርና የጦር ኃይሎች አዛዥ በሕግ የተሰጥዎትን “የማዘዝ ስልጣን” (Commanding Power) መሰረት በማድረግ፣ እና (3ኛ) ላይ በተጠቀሰው መሰረት “የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ” በማለት፣ የፀጥታ ኃይሎች በሕዝቡ ላይ ለሚፈፅሟቸው አሰቃቂ በደሎች፤ ግድያዎች፣ ድብደባዎችና እስራቶች ምክንያት (Justification) በማቅረብ፣ በህዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል።

አዎ… ክቡር ጠ/ሚ፣ “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” በማለት በሚመሩት ሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል።

በፅሁፉ መግቢያ ላይ እንደገለፅኩት፣ የእኔ ጥረት በተቻለኝ አቅም ሕዝብና መንግስትን ማሳወቅና የመፍትሄ ሃሳቦችን መጠቆም ነው። በሀገራችን የተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት አሁን ካለበት አስከፊ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት “በቀውሱ የህዳሴን መንገድ ይቀይሱ – ለጠ/ሚ ኃ/ማሪያም) በሚል ርዕስ ምክር አዘል ፅሁፍ ማቅረቤን በመግቢያዬ ላይ ጠቅሼያለሁ። በፅሁፉ ያቀርብኩት ሃሳብ ለችግሮቹ ሁሉ መፍትሄ ይሆናል እያልኩ አይደለም። ነገር ግን፣ በወቅቱ ላነሳኋቸው ችግሮች ተገቢ ትኩረት ተሰጥቶ ቢሰራ ኖሮ አሁን ካለንበት ደረጃ ላይ አንደርስም ነበር።

አሁንም ቢሆንም “ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ” የሚል ትዕዛዝ በማስተላለፍ በሕዝብ ላይ ጦርነት አውጀዋል። አስቸኳይ የመፍትሄ እርምጃ ካልተወሰደ ግን፣ በጦርነት ጥላ ስር የሚፈፀሙ ዘግናኝ ድርጊቶች በሕዝባችን ላይ መድረሳቸውን በማስመልከት በምፅፈው ቀጣይ ደብዳቤ ዳግም እንደምንገናኝ እርግጠኛ ነኝ። በዜጎች ላይ የሚደርሱ አሰቃቂ በደሎችና ጭቆናዎች መሰረታቸው ለስልጣን ጭፍን ተገዢ መሆን (blind obedience to authority) ነው።

ከሠላምታ ጋር

ስዩም ተሾመ (MBA)

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓስ

ወሊሶ

Email: seyee123@gmail.com

Blog Address: http://hornaffairs.com/am/author/seyoumteshome

ታምራት ላይኔ መንግስት ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ አለበት አሉ |መፍትሄዎችን አስቀምጠዋል |ክፍል 2 ቃለምልልሳቸውን ይዘናል

$
0
0

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ስለ በወቅታዊው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታዎችና ብሄራዊ እርቅ ዙርያ ከኤስቢኤስ ራድዮ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ጋር ማድረጋቸውና ክፍል አንድን በዘ-ሐበሻ ላይ ማስደመጣችን ይታወሳል:: አቶ ታምራት በክፍል 2 ቃለምልልሳቸው “መንግሥት በይፋ ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ አለበት” ካሉ በኋላ የተለያዩ መፍትሄ ሃሳቦችን አሳቀምጠዋል:: ቢያደምጡት ይጠቀሙበታል::

እጅግ በጣም አሳዛኝ ዜና! –አዳዲስ ምስጢሮች ስለቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎና ግድያ

$
0
0

ይህን ነገር ስፅፍላቸው አይኔ ደም እምባ እያለቀሰ እንደሆነ ተረዱኝ፡፡

ከሚኪያስ ሲመዲሳ

የቂልንጦ እስር ቤት እስረኞችን ፍርድ ቤት ከሚያመላልስ ከአንዱ ወዳጄ በቀጥታ የሰማሁትን ልንገራችሁ፡፡

“ዓርብ ማታ የማናውቀው አንዱ ትግርኛ ተናጋሪ መጣና ለተወሰኑ ሰዎች ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፎ ሄደ፡፡ ከዚያች ሰዓት ጀምሮ እኔ የማውቃቸው የኦሮሞ ፖሊሶች ከተመደቡበት ቦታ ተቀይረው ወደ ሌላ ከእስር ቤቱ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄዱ፡፡ የእስር ቤቱ ወሳኝ የጥበቃ ቦታዎችና ማማዎች እንዳለ በአጋዚዎች እንዲሸፈን ተደረገ፡፡ እኔም ከሩቅ ከእስር ቤቱ ጥበቃ ውጭ በቅርብ ርቃት ላይ አከባቢውን ዱላ ብቻ ይዤ እንዲቃኝ ተመደብኩ፡፡ ዓርብ ሌሊት ለቅዳሜ አጥቢ፤ በእስር ቤቱ ውስጥ አደጋ ሊፈጠር ስለሚችል ሁሉም የእስር ቤቱ የጥበቃ ሰራተኞች በተጠንቀቅ እንዲቆሙ የሚል ትዕዛዝ ሰማን፡፡ ነገሩ ከወትሮው አዲስ ሆኖብን ግራ ቢገባንም ትዕዛዙን ለምን እንዴት ብለን እንኳን የመጠየቂያ እድል ስላልነበረን ተቀብላን ቅዳሜ ጠዋት ደረሰ፡፡
kilinto prison

አራት ሰዓት ሊሆን አካባቢ ትንሽ ግር ግርና ተኩስ ተጀመረ፡፡ በዚያን ሰዓት ምንም የእሳት ጭስም ሆነ ነበልባል አይታይም ነበር፡፡ እኔ ከሩቅ ሆኜ መንገደኞችን ከመከልከል ውጪ ጠጋ ብዬ ሁኔታውን ለማጤን እድሉ አልነበረኝም ነበር፡፡ ትንሽ እየቆየ ሲሄድ ተኩሱ በረታ! አሁን የእሳት ጪስ መታየት ጀመረ፡፡ ከጥበቃ ማማው ላይ የነበሩ አጋዚዎች ወደታች በቀጥታ ስተኩሱ አያለው፡፡ ነገሩ ምንድነው ብዬ ጠጋ ማላት ጀመርኩ፡፡ አሁን ዕሳት እጅጉን እየነደደ መጣ፡፡ ቤት ውስጥ የነበሩ እስረኞች ራሳቸውን ለማዳንና ወደ ውጪ ለመውጣት መታገል ጀመሩ፡፡ ቃጠሎ በነበረበት አካባቢ በአብዘኛ ሁሉም እስረኞች በሚባል ደረጃ ከግቢ ሳይሆን ከእስር ቤቱ ውስጥ ወጥተው ተመልሰው እሳቱን ለማጥፋት ስረባረቡ በአይኔ ተመልክቻለው፡፡

ትንሽ ቆይቶ በፍፁም ለማመን በሚያስቸግር ሁኔታ አዲስ ነገር ማየት ጀመርኩ፡፡ እሳቱን እያጠፉ ባሉ እስራኞች ላይ ካላይና ከታች አጋዚዎች የጥይት እሩምታ ማዝነቡ ጀመሩ፡፡ እውነት ለመናገር አንድም እስረኛ ለማምለጥ ሙከራ ያደረገ የልም፡፡ በቃ ብዙ እስረኞች በጥይ ተመተው መሬት ላይ ሲወድቁ አየሁ፡፡ ገሚሶቹ ጓደኞቻቸው በጥይት ተመተውና መሬት ላይ ሲወድቁ ባዩ ጊዜ እራሳቸውን ለማዳን ተመልሶ ወደ እሳቱ ውስጥ በድንጋጤ የገቡም ብዙ ናቸው፡፡ ሌሎቹ በግቢው ውስጥ ከጥይቱ እሩምታ ለመሸሽ ወዲያና ወዲህ ሲሉ የተገደሉ ናቸው፡፡ እንዳልኩት በአብዛኛው የሞቱት እሳቱን እያጠፉ በነበረበት ወቅት ነው፡፡ የእሳት አደጋ ሰራተኞች የመጡት በጣም ቆይተው ብዙ ሰው አልቆ በአንቡላን ወደ ሆስፒታል መወሰድ ከተጀመረ በኋላ ነው፡፡ በኔ በኩል የሟቾች ቁጥር 20ና ሰላሳ እንደተባለ ሳይሆን እጅግ በርካቶች ናቸው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው በአብዛኛው የጥይቱ ሰለባ የሆኑት በዋህነት እሳቱን ለማጥፋት የተረባረቡ ምስክኑ እስረኞች ናቸው፡፡ በሆነው ነገር በጣም አዝኛለሁ፡፡ በእውነት ምን እየተደረገ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም በማለት በምሬት ዛሬ ከነጋ አጫውተውኛል”፡፡

ይህ ወዳጄ ስለነ በቀለ ገርባ ጠይቄውት የነገረኝ ነገር ቢኖር…እንደነ አቶ በቀለ ገርባ ያሉ ትልልቅ የፖለቲካ እስረኞች ከሌሎች ራቅ ብለው በብሎኬት የተሰራ ልዩ እስር ቤት ውስጥ ስለሚታሰሩ ለአደጋዉ ተጋላጭ የሚሆኑ አይመስለኝም ሲል መልሶልኛል፡፡

ያም ሆነ ይህ ጎበዝ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያለኸው የሀገሬ ሰው አሁን በግልፅ ወያኔ ሙሉ ጦርነት አውጆብናል፡፡ ከዛሬ ነገ ይሻላል ብለን ትግላችንን ያዝ ለቀቅ እያደርግን ቢንመጣም ነገሩ እየባሰበት መጥቷል፡፡ ስለዚህ በተለይ በኦሮሚያ ውስጥ አሁን ወጣቱ በተናጠልና በተበታተነ ሁኔታ ዘግናኝ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት አስተባባሪዎች አፀፈው በተደራጀና በተቀዳጀ ሁኔታ ምን መሆን እንዳለበት በአስቸኳይ ተወያይታችሁ ለህዝብ እንዲታሳውቁ በተሰው ወገኖቻችን ስም አደራ እላለሁ፡፡

ድል ለጭቁኑ ህዝብ ሞት ለወያኔ!!!

ለክቡር ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ [ዳንኤል ሺበሺ]

$
0
0

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡፦ ሠይፎትን ወደ አፎቱ እንዲመልሱ የሚጠይቅ የግል ደብዳቤ፤
***********************************
ክቡር ሆይ፣ ሺህ ዓመት ይንገሱ፡፡
enqilf Hailemariamየዛሬ አያረገውና እርሶዎን ያነ በምንጠራዎት በቤተሰባዊ አጠራር <ጋሽ ኃይሌ> ብዬ ጉዳዬን ልጀምር፡፡
ጋሽ ኃይሌ፦ ሁሌም ቢሆን ስለ እርሶዎ የገዘፈው ግላዊ ስብዕናዎትን በተለያዩ ትላልቅ ሚድያዎችም ጭምር ከመመስከሬ ቦዝኜ አላውቅም፡፡ ነገር ግን የኅወሓትን ትብታብ ውስጥ የታመቀውን የሀገሪቱን ውስብስብና ጥልቀት ያላቸው ችግሮችን በጣጥሰው ይወጣሉ ብዬ  እያሰብኩ ጊዜ እንደማላጠፋም ግን አልሸሸገዎትም፡፡
ይህን ደብዳቤ ሳዘጋጅ ምን ሊፈይዱ? በምል ሀሳብ ከራሴ ጋር ሙግት የገጠምኩ ሲሆን፤ ምንም ይሁን ምን አሁን ፊለ ፊታችን የምናውቀው እርስዎን ስለሆነ በእርስዎ በኩል ለዋናዎቹ እንዲደርስ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ ነው በቀጥታ ለእርስዎ የጻፍኩሎትና እባክዎትን በጽሞና እንዲያነቡና አንብበውም እንዲያሰላሰሉ በትህትና እጠይቅዎታለሁ፡፡

በአንድ በኩል ከጊዜ መንጎድ ጋር የፖለቲካ አቋማችን መራራቅ፤ በሌላ በኩል እርስዎ ያለ ሕዝብ ድጋፍ በፖለቲካ ሥልጣን ከፍከፍ ሲሉ እኔ ደግሞ በተቃራኒዮ በመንግስትዎ እየተደቆሰ ካለው ህዝብ ጋር መከራን በመምረጤ በሥልጣንም ሆነ በኢኮኖሚ ዝቅዝቅ ማለት እና እርስዎ በሥራ ጫና፤ እኔ ደግሞ በተቃራኒው ያለሁበት ሁኔታ ተዳምሮበት ምናልባትም መረሳሳትን አስከትሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ቅሉ አንዳንድ ትዝታዎችን ብጠቁም ለማስታወስ አይከብድዎትምና … ፡፡
ያነ በደጉ ዘመን ወደ ደርባባው ሱፎዎት ውስጠኛው ኪስዎ የገዛ እጄን በእምነት እየሰደድኩ ለኔ የምበቃኝን ያህል ገንዘብ በመውሰድ በእርስዎ ገንዘብ እርስዎን መጋበዘን፤ ሲቀላ (በአርባ ምንጭ ከተማ) በአሁኑ የኤርትራዉያኖቹ ዳህላክ ጫማ ቤት ለእግርዎ ተስማም ጫማ ስንመርጥ… ለኔም ሲገዙልኝ፤ ሼቻ አሻም ሬስቶራንት አስቀድሜ ምሣ አዝዤ ስጠብቅዎት፤ የወጋጎዳን መመስረትን ተከትሎ በአከባቢዬ የተቀሰቀሰውን ቀውስ ለማብረድ ስንመካከር አቤት የነበረን ፍቅርና መቀራረብ!

መውደድ ብቻም ሳይሆን ለምናከብራት ባለቤትዎ ለእተጌይቱ ሮማን ተስፋዬ’ም የምለው አለኝ፡፡ እርሳቸውም በትክክል የተሟላ የሴትነትና የእናትነት ፀጋ የተጎናፀፉ በዕውቀትና በጥበብ የተካኑና ለባልዋም ዘውድ ወይዘሮ መሆናቸውን በግሌ እመሰክርላታለሁ፡፡ ያኔ በዩኒቨርሲቲ መኖሪያ ቤታቸው እንጀራ ተቀራምተን ስንበላ በጆግ ውሃ እየቀዱ ስረጩብንና ሲያባረሩን፤ እኛም በውሃው ከመረስረስ ራሳችንን ለመከላከል ሲንል እርሶዎን ተሸክመን ወደ እልፍኞዎት አስገብተን በሩን በላይ ላይ እየዘጋን ስንጫወት፣ ስንስቅ፣ የተዘጋውን በር እንዲከፈትልዎት ሲማጸኑልን የነበረንበትን ጊዜ ዛሬ ላይ ሆኜ በህሊናዬ ሳስብ ያ! ዘመን ተመልሶ እንደማይመጣ አዕምሮዬ እየጠቆመም ቢሆንም ግን ገራገሩ ልቤ አሁንም በምኞቱ ቀጥሎበታል፡፡ ምን እያልክ ነው ያሉኝ እንደሆን እርሶዎን ባያገኙ ኖሮ ጋሼ እዚህ ላይ ስለመድረሳቸው እርግጠኛ አይደለሁም እያልኩ ነው፡፡
ዛሬም አንድ ነገር የማለት ግዴታ አለቦዎት፡፡
የአንድ መንግሥት ከሚጠበቅበት ትላልቅ ኃላፊነቶች ውስጥ ዋነኛው ሥርዓት አልበኝነትን መቆጣጠር፣ የህዝቦችን/የሰዎችን ፀጥታንና ሠላምንና የሀገሪቱን ግዛት አንድነትን ማስጠበቅ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ምንም እንኳ ያልተሳካልን ቢሆንም፡፡ በአንፃሩ በአሁኑ ወቅት በሀገራችኝ እየተስተዋለ ያለው ግን ሥርዓት አልበኝነት፣ ለህግ ያለመገዛት . . . ነው የሚያሰኝ ምልክት አለ ለማለት ይቸግረኛል፡፡ የተበደለ፣ የተገፋ፣ የተሰደበ፣ ፍርድንና እውነትን ያጣ፣ በዚህም የተማረረና በሀገርቱ ከተንሰራፋው ሙስናና አድልዎ የተነሣ በድህነት እየደቀቀ ያለው ህዝብ የተሰማውንና በውስጡ የታመቀውን ስሜቱን ከመግለጽ ውጭ፡፡

ስለዚህ እርሶዎ በቀን ነሐሴ 24, 2008 ዓም የተናገሩት ለትልቁ ምክር ቤትዎ ባይሆንም “እኔ በበኩሌ ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስዱ አዝዤያለሁ!” ብለው በድፍረት ተናግረዋል፡፡
ክቡር ሆይ፦ ለክብሮነትዎ ሁሌም ሠላምን እመኛለሁ፡፡ ሠላማችንን አያደፍርሱብን፡፡ ያወጁብን ነገር ታላቅ ጥፋት ነው፡፡ በህዝብዎ ላይ የተወጠነ አደገኛ ነገር ፡፡ ይህ ሕዝብኮ የጣሊያን ወራር ኃይል አይደለም፡፡ የአጥንትዎ ክፋይ ነው፡፡ በእርስዎ የሚተዳደር ሕዝብ፡፡ በገዛ ሀገርዎና  በሕዝብዎ ላይ በጠራራ ፀሐይ ጦርነት አውጀዋል፡፡ ተበድያለሁ ብሎ ደመ እንባ በሚያለቅስ ሕዝብ ላይ እንዴት የቡድንና የነፍስ-ወከፍ ጦር መሣሪያ የያዘ ጦር ኃይል በአንድ ጠቅላይ ጦር አዛዥ ይታዘዛል?? ወይስ አማራና ኦሮሞ ከመቼ ጀምሮ ነው የእርሶዎና የኢት/ያ ጠላት የሆኑት? በእውነት  በእርስዎና በአመራርዎ አፍርያለሁ፡፡ ስለዚህ በአስቸኳይ ሠይፍዎትን ወደ አፎቱ ይመልሱ!  የሕዝብዎት እንባ ምን እንደሆነ ለማዳመጥ ጆሮ ይስጡ እንጂ እደመስሳለሁ እያሉ የግዛትዎትን ነዋሪ ማሳደድዎትን ያቁሙ፡፡

ሌላውና እዚህ ጋ ጠቅሼ ማለፍ የሚፈልገው ነገር ቢኖር፦ እርስዎ ወደ ሥልጣን በመጡ ቁጥር ሁሌ እልቂትና መከራ በህዝብዎ ላይ ይበዛል፡፡ ግን ለምን  ይሆን??
ለምሣሌ፦ ➊ እርስዎ የወጋጎዳ ከፍ/አመራር በነበሩ ጊዜ የአርባምንጭ፣ የሳውላ የዳውሮና የአከባቢው እልቂትና ውድመት ይቅርና በገዛ በትውልድ ከተማዎ በሶዶ ብቻ መተኪያ የሌለው ሕይወታቸውን ያጡ  ምን ያህል እንደነበሩ ሁላችንም የምናውቀው ሲሆን፤ በዚህም እንደ ቅጠል የረገፈው የንጹኃንን ነፍስ፣ የወደመው ንብረትና የባከነው ጊዜ እንርሳው ብንል እንኳ የሚሆን አይደለም፡፡
➋ እርስዎ የደቡብ ክልል ከፍ/ባለሥልጣን በነበሩ ጊዜ በሀዋሳና በአከባቢዉ በከንቱ የፈሰሰው ንጹኃን የሲዳማና የሌላ አከባቢ ተወላጆችን ደም፤ የወደመው ንብረትና የባከነ ጊዜ እንዴት ምንም እንዳልተፈጠረ ልንቆጥር እንችላለን?
➌ አሁን ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ የሀገሪቱን የፖለቲካ ሥልጣን ጠቅልለው መርሄ መንግሥት ከሆኑ ወዲህም እንደ ቀድሞ አለቃዎት ሁሉ ተመሳሳይ አንዳንዴም የከፋ ነገር መፈጸምን ሥራዬ ብለው ተያይዘዋል፡፡ እባክዎትን ጋሽ ኃይሌ!! ልማጽኖዎት፡፡

ስለዚህ መጽሐፉ <ቢሰሙም ባይሰሙም” እንደሚል፤ እኔም ለእርስዎ የሚከተሉትን ምክር ቢጤ ጠቆም ላደርግና እንሰነባበት፡፡
#1ኛ- ለጽሁፌ መነሻ የሆነውን የአሸባሪ ንግግሮዎትን በአስቸኳይ ይሳቡ፡፡ ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ ክብር ነው እንጂ በፍጹም ውርደት ሊሆን አይችልም፡፡
#2ኛ፡ እኛ ተቃዋሚዎች ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል ስናነባ የነበርነው ለዛሬው መመሰቃቀልና ለከፋ አደጋ ያዳረጉ አፋኝ ህጎች በሙሉ መሰረዝ/መሻሻል ብቻም ሳይሆን ቀደም ሲል በዚህ የተፈፀሙ ኢ-ፍትሐዊ የሆኑ ውሳኔዎች በድጋሚ እንዲታዩ፣ አሳታፊና ሁሉንም ባለድርሻዎችን ያቀፈ የሽግግር ሥርዓት እንዲቋቋም የሚጋበዝ ውጥንዎን ከወዲሁ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉ፤
#3ኛ፡  ይህ የማይሆን ከሆነ ሹልክ ብለው ወደ አንድ  ሀገር ተጉዘው ጥገኝነት ይጠይቁ ባልልም (ከሕዝቦዎ ጋር መከራ መጋራትን ትተው መሰደድ ለአንድ ሀገር መሪ ክብር ነው ብዬ ስለማላምን)፤ ሥልጣንዎትን በፍላጎትዎ መልቀቅዎትን ያውጁና እቤትዎ ቁጭ ይበሉና ታሪክ ይሥሩ፡፡  በርግጥ ይህንን በማድረግዎ ዘለግ ያለ ዋጋ ያስከፍሎዎት ይሆናል፡፡ ቢሆንም ከትውልድና ከታሪክ አንፃር ሲመዘን ብድራቱ ታላቅ በመሆኑ፡፡

ደፍረው ይህንን ካደረጉ የግድ ይቅርታ መጠየቅ  አይጠበቅብዎትም፡፡ በቂያችን ነውና፡፡ ይሄንን በማድረግ ለትውልድ የሚተላለፍና ዘመን የማይሽረውን ታሪክ ተክለው ከማለፍዎ ሌላ ሀገሪቷን ማነው የሚመራው? እየተባለ የሚነሣውን ውዥንብር በማጥራት በትክክልም መሪ መሆንዎትን ያረጋገጡልናል፡፡ ቸር ያሰማን!

ከሰላምታ ጋር
ዳንኤል ሺበሺ – አክባሪዎ
ነሐሴ 30ቀን, 2008 ዓ.ም ተፃፈ፡፡


ከትላንትናው አረመንያዊ ጭፍጨፋ በፊት በቂሊንጦ ማረሚያ እንደነበሩ የታወቁ የ223 እስረኞች ስም ዝርዝር

$
0
0
kilinto prison
(updated)
1. አቶ በቀለ ገርባ
2. ወጣት ዮናታን ተስፋዬ
3. ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው
4. አቶ ደጀኔ ጣፋ
5. አቶ ጉርሜሳ አያኖ
6. አቶ አዲሱ ቡላላ
7. አቶ አበበ ኡርጌሳ
8. አቶ አግባው ሰጠኝ
9. መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ
10. አቶ ማስረሻ ታፈረ
11. አቶ መሳይ ትኩ
12. ወጣት ኤርሚያስ ፀጋዬ
13. ወጣት ፍሬው ተክሌ
14. ወጣት ዳንኤል ተስፋዬ
15. ወጣት ቴዎድሮስ አስፋው
16. አቶ ጉታ ባይሳ ሁንዴ
17. አቶ መሰለ መሸሻ
19. አቶ ፍራኦል ቶላ
20. አቶ ጌታቸው ደረጄ
21. አቶ በየነ ሩዶ
22. አቶ ተስፋዬ ሊበን
23. አቶ አሸብር ደሳለኝ
24. አቶ ደረጄ መርጋ
25. አቶ የሱፍ አለማየሁ
26. አቶ ሂካ ተክሉ
27. አቶ ገመቹ ሸንቆ
28. አቶ መገርሳ አስፋው
29. አቶ ለሚ ኤዴቶ
30. አቶ አብዲ ታምራት
31. አቶ አብደላ ከመሳ
32. አቶ ሀራኮኖ ቆንጮራ
33. አቶ መኮነን ገቢሳ ገደፉ
34. አቶ ፀጋዬ ጋዲሳ ኡባ
35. አቶ አቦንሳ አኩማ ሆንዳራ
36. ረዳት ሳጅን ቤኩማ ታደሰ ፊንዳ
37. አቶ ዲንሳ ፋፋ ድርባ
38. አቶ አልኩ አቦና መኩሪያ
39. አቶ እሸቱ ደባ ነገዎ
40. አቶ ታደሰ ነገኦ ገመዳ
41. አቶ ኡምኔሳ በዳሳ ሚዴቅሳ
42. አቶ ሮቢሌ አብዲሳ ክቲላ
43. አቶ በቀለ ተሬሳ ረጋሳ
44. አቶ ነገሰ በርሲሳ ደበሌ
45. አቶ ካሳሁን ሙሊሳ ሙለታ
46. አቶ አብዲ ታሪኩ ዴረሳ
47. አቶ ሶሬሳ ደሜ ቶሌራ
48. አቶ ታሪኩ ቦኪ ደበላ
49. አቶ አብዲሳ ቦካ ቱጅባ
50. አቶ እምሩ ነገዎ ጀማ
51. አቶ መልካሙ ታደለ ቢዬ
52. ረዳት ሳጅን ተስፋዬ አባተ ደምሴ
53. አቶ ተካልኝ ቡለቾ ገመዳ
54. ረ/ሳጅን ኩምሲሳ ዱጉማ ሚልኬሳ
55. አቶ ክንፈ መኮነን ተሰማ
56. አቶ ኪንስታብል ገመቹ ታሪኩ እጅጉ
57. አቶ ቶሎሳ በዳዳ ደበሬ
58. አቶ ሺፈራው ግርማ ሰንበታ
59. አቶ ቢኒያም ጫላ ገረሱ
60. አቶ ስንታየሁ መኮንን ገዳ
61. አቶ ኦላና ከበደ
62. አቶ ወልዴ ሞቱማ
63. መገርሳ ፍቃዱ
64. አቶ አርገምሲሳ ሌንጂሳ
65. ም/ሳጅን መሰረት አቦማ
66. አቶ አብዲሳ ኢፋ
67. አቶ ዋርደር ተመስገን
68. አቶ ተካልኝ መርዶሳ
69. አቶ ቦኪ እሸቱ
70. አቶ ብርሃኑ ቦኪ
71. አቶ ማሙሽ ቦኪ
72. አቶ ፍቃዱ አዱኛ
73. አቶ መኮንን ዘውዴ
74. አቶ ወርቁ ጉርሙ
75. አቶ ገረሙ አዱኛ
76. አቶ ደረጄ ታዬ
77. አቶ ጃለታ ሰንዳፋ
78. አቶ ላቀው ሮቢ
79. አቶ እንግዳ ቁሲ
80. አቶ ቶሽሌ ተስፋ
81. አቶ ታደለ ዓለሙ
82. አቶ ተሩ ኡንጉሬ
83. አቶ እጅጉ ቀበታ አያና
84. አቶ አዱኛ ኬሶ
85. አቶ ቢሉሱማ ዳመና
86. አቶ ጌቱ ግርማ
87. አቶ ጭምሳ አብዲሳ
88. አቶ ተሾመ ረጋሳ
89. አቶ ጫላ ዲያስ
90. አቶ ኦብሱማን ኡማ
91. ኒሞና ለሜሳ
92. አቶ ከበደ ጨመዳ
93. አቶ ምረቱ ጉሉማ
94. አቶ ዴቢሳ በየነ
95. አቶ ጌታሁን ደስታ
96. አቶ መንግስቱ ጉዲሳ
97. አቶ ተሰማ ሁንዴ
98. አቶ ቦንሳ (ኦብሳ) ኃይሉ
99. አቶ አሸብር ኦንቾ
100. አቶ ጃራ ኤቢሳ
101. አቶ ፋፋ ሬፋንራፋ
102. አቶ አጥናፉ ቢራሳ
103. አቶ አብዲ ታደሰ
104. አቶ ሀብታሙ ሀጫሉ
106. አቶ ቶኩማ ሙሌሳ
107. አቶ ደጋጋ ብርሃኑ
108. አቶ ዮሐንስ ኡርጌሳ
109. አቶ ዴብሳ በሊና
110. አቶ አብዱርህማን አደም
111. አቶ ዮሴፍ ዲዳ
112. አቶ ተስፋዬ በቀለ
113. አቶ ዴቢሳ ኤታንሳ
114. አቶ ናኦል ሻሚሮ
115. አቶ ለታ አህመድ
116. አቶ ቀጀላ ገላና
117. አቶ ሰብኬበ በቀለ
118. አቶ ገላና ነገረ
119. አቶ ኡርጌሳ ደመና
120. አቶ አሚን ዬዮ ሙመድ
121. አቶ አብዱ የሱፍ አቡዱ ኡመር
122. አቶ አብድልዋሴ ኢብራሂም አብደላ
123. አቶ አብድልቃድር መሃመድ ኢብራሂም
124. አቶ ሸምሰዲን አህመድ ኡመድ
125. አቶ መሃመድ አልዩ ኡመር አህመድ
126. አቶ መሃመድ ሶፍያን ሀመዴ
127. አበዲ መሃመድ አደም
128. ጀማል ቶፊቅ አሜቶ
129. አቶ ፋሮምሳ ሃሚሶ ጊዞ
130. አቶ ሃሩን አዪቦ መሀመድ
131. አቶ ናስር አሚን ኢብራሂም ኡመር
132. ጀማል አልዩ መሃመድ ብተቤ
133. አቶ አህመድ ከሊፍ አሚን
134. አቶ ከልፍ መሃመድ አደም
135. አቶ ብሩ ገለቱ ጋሪ
136. አቶ ያሲን መሃመድ አደም
137. አቶ አብደታ ነጋሳ
138. አቶ ደህናሁን ቤዛ ስመኝ
139. አቶ ቢሆንኝ አለነ ማረው
140. አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ለማ
141. አቶ አሸናፊ አካሉ አበራ
142. አቶ አንሙት የኔዋስ አለኽኝ
143. አቶ ሳለኝ አሰፋ ወንድምአገኝ
144. ምክትል ኢንስፔክተር ሙሉዬ ማናዬ ረታ
145. አቶ ፀጋው ካሳ እንየው
146. አቶ የአለም አካሉ አበራ
147. አቶ ሙሉ ሲሳይ መቆያ
148. አቶ ትንሳኤ በሪሶ
149. አቶ ጌታቸው ይርጋ
150. አቶ ግሩም አስናቀ
151. ገመቹ ከበደ ቄኖ
152. አቶ ሂንሳረሙ ቦጋለ ድንቄ
153. አቶ ደበላ ፈይሳ ጎንፋ
154. አቶ አህመድ መሃመድ መሬ
155. አቶ ብርሃኑ በዳዳ ጉሌና
156. አቶ ጉዲና ተስፋዬ ታደለ
157. አቶ ተሬሳ አስናቀ በየነ
158. አቶ ሸለመ ገመቹ ደሜ
159. አቶ አትርሳው አስቻለው ተካ
160. አቶ አማረ መስፍን መለሰ
161. አቶ ወርቄ ምስጋና ዋሴ
162. አቶ ጌታቸው መኮንን
163. አቶ በቃይነህ ሲሳይ ኮኮቤ
164. አቶ አለባቸው ማሞ መለሰ
165. አቶ አወቀ ሞጃ ሆዴፈንታ
166. አቶ ዘሪሁን በኔ ታረፉ
167. አቶ ተስፋዬ ታሪኩ በዛብህ
168. አቶ ቢሆነኝ አለነ ማረው
169. አቶ ታፈረ ፋንታሁን አጉሜሌ
170. አቶ ፈጃ ሙሉ ዘገየ
171. አቶ እንግዲያው ዋጀራ ወርቁ
172. አቶ አንጋው ተገኝ አርጋው
173. አቶ ፍራኦል ዳንኤል ረጋሳ
174. አቶ ግዛቸው ቶላ
175. አቶ ዳንኤል ታፈሰ በየነ
176. አቶ ቦረና ረጋሳ
177. አቶ ጉዲሳ በየነ
178. አቶ ሃይሉ ገመዳ
179. አቶ አመቲ ለሜሳ ጎባ
180. አቶ ቅናቴ ፈይሳ
181. አቶ ደስታ ዲንቃ ጎሴ
182. አቶ ለማ ባዬ ጉተማ
183. አቶ ዋዩ በቃ ገሌራ
184. አቶ አብደታ ባቴሪ በሪሳ
በሙስሊሙ ትግል በቂሊንጦ ታስረው ከሚገኙ ታሳሪዎች በከፊል ዛሬው እለት ቃጠሎ በደረሰበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታላቁ አሊም ሸህ ጀይላን አዳኖን ጨምሮ በርካታ ሙስሊሞች ይገኛል ከነሱ በጥቂቱ መንግስት ሸህ ኑሩን ካስገደለ በሽህ ኑሩ ግድያ የተከሰሱ ንጹሃን ሙስሊሞች
185.አብዱረህማን እሸቱ
186/ አደም አራጋው
187/ሙሃመድ የሱፍ
188/ እስማኤል ሃሰን
189/ አህመድ እድሪስ
190/ አህመድ ጀማል
191/ አንዋር ኡመር
192/ ሳላህ ሙሃመድ
193/ ከማል ሁሴን
194/ ኡመር ሁሴን
195/ኢብራሂም ሙሄ
196/አብዱ ሃሰን
ይመር በከድር ሙሃመድ መዝገብ የተከሰሱ ወጣቶች
198/ካሊድ መሀመድ
199/ዳርሰማ ሶሪ
200/ኢብራሂም ካሚል
201/አብዱልሃሚድ መሀመድ
202/አስማን መሀመድ
203/መሀመድ ኑሪ
204/ ፍፁም ቸርነት
205/ከድር መሀመድ
206/ሁሴን አሀመድ
207/ሻቡዲን ነስሩ
208/ ቶፍቅ ሚስበሃ
209/ሀሺም አብደላ
210/አብዱልሀፉዝ ሻፊ
211/ሀይሩ ኸይረዲን
212/ነዚፍ Temam
213/ ሙጂብ አሚኖ
214/  አብዱልጀባር አብደላ
215/ፉአድ አብዱልቃድር
216/ ሙሀመድ ከማል
217. ነብዩ ሲራጅ
218. ሰፋ በደዊ
219. መሃመድ ሰዒድ
220. ሰላሃዲን ከድር
221. ሙጂብ አደም እረሺድ
222. ከድር ታደለ
223. አህመድ ኡመር ናቸው
ማሳሰቢያ | ከላይ ከተጠቀሱት የእስረኞች ስም ውስጥ በሌሎች ማረሚያ ቤት የሚገኙ ነገርግን በስህተት ዝርዝር ውስጥ የተጨመሩ ካሉ ፤ እንዲሁም እስከ ትላንት ድረስ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንደነበሩ የሚታወቁ የፖለቲካ ፣ የሀይማኖትና ሌሎች ዝርዝር ውስጥ ያልተካተቱ እስረኞች ስም ዝርዝር መረጃ ያላችሁ ከዚህ ፖስት ስር በመለጠፍ ይተባበሩን።

የሁሉም እስረኞች ህይወት ይመለከተናል !

ሰበር ዜና: መንግስት በቃሊቲ እስር ቤት 2 እስረኞችን ረሸነ |ግድያው ከቅሊንጦ ወደ ቃሊቲ ተሸጋግሯል

$
0
0


(ቢቢኤን) የመንግስት ጥቃት ወደ ቃሊቲ ቃሊቲ እስር ቤት ተሸጋግሯል:: ትላንት ቅዳሜ ነሐሴ 28/2008 ለሊት 8 ሰዓት ከአስር አካባቢ መንግስት ኮሚቴዎቻችን በሚገኙበት በቃሊቲ እስር ቤት በዞን 1 ውስጥ ታስረው ከሚገኙ ታሳሪዎች መካከል 2 ሰዎችን የረሸነ ሲሆን ሁለቱን ደግሞ በጥይት መቶ ማቁሰሉን ማረጋገጥ ተችሏል ፡፡ ሁለቱን ክራውን ሆቴል አካባቢ ወስደው እንደገደሏቸው ምንጮቻችን ለቢቢኤን ገልጸዋል፡፡ መንግስት ከትላንት በስቲያ ለሊት በቂሊንጦ ከወሰደው ዘግናኝ የቃጠሎና የግድያ እርምጃ በኋላ ምሽቱን ደግሞ በቃሊቲ እስርቤት ተመሳሳይ አሰቃቂ ወንጀል የፈፀመው ‹‹እስረኞቹ ለማምለጥ በመሞከራቸው ነው›› የሚል የሐሰት ውንጀላ ያቀረበ ቢሆንም፤ ይህ የመንግስት ውንጀላ ግን ከእውነት የራቀ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገልፀዋል፡፡

የተረሸኑት ሁለቱ እስረኞች ማንነታቸውን ለማጣራት እየሞከሩ እንደሆነ የውስጥ ምንጮች የዘገቡ ሲሆን፤ ሟቾቹ የሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ኡስታዝ አህመዲን ጀበልና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ባሉበት ክፍል ውስጥ የታሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ግን እስካሁን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል

ሰበር ዜና: መንግስት በቃሊቲ እስር ቤት 2 እስረኞችን ረሸነ | ግድያው ከቅሊንጦ ወደ ቃሊቲ ተሸጋግሯል

መንግስት በቅርቡ በቃሊቲ ዞን 1 እና ዞን 2 ‹‹ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ታሳሪዎች ስም ዝርዝር›› በሚል ከ140 በላይ የሚሆኑ ታሳሪዎችን ስም ለጥፎ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ቀድሞውኑ ሊረሽናቸው ያሰባቸውን አካላት አሰናድቶ ያስቀመጠው መንግስት በአሁኑ ሰዓት በየእስርቤቱ ያለምንም ሃይ ባይና ከልካይ በማን አለብኝነት ዜጎቻችንን መረሸኑን ተያይዞታል፡፡

እነዚህ እጆቻቸው ባዶ የሆኑ፣ ያልታጠቁና በሕግ ስር የሚገኙ የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ታሳሪ ኢትዮጵያውያንን በጨለማ በመረሸን መንግስት እያደረገ ያለውን አረመኔያዊ ተግባር በአስቸኳይ ሊያቆም ይገባል፡፡ ወኪሎቻችን ላይ አንዲት እንኳ ችግር ቢደርስ ከችግሩ ጋር የተያያዙ አካላቶች በሙሉ ከሙስሊሙ ኢላማ ሊያመልጡ እንደማይችሉ አምባገነኑ መንግስት ማወቅ አለበት፡፡

አስከሬን ፍለጋ ጳውሎስ ሆስፒታል የሄዱ ቤተሰቦች በፖሊስ ተደበደቡ

$
0
0

paulos hospital

(ዘ-ሐበሻ) በትናንትናው እለት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተከሰተውን የ እሳት ቃጠሎ ተከትሎ እስካሁን የተረጋግጠ 49 አስከሬኖች በጳውሎስ; በፖሊስ እና በጦር ኃይሎች ሆስፒታሎች እንደሚገኙ ዘ-ሐበሻ በትናንትናው ዕለት መዘገቧ አይዘነጋም:: ይህን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው በቅሊንጦ የታሰሩባቸው ወገኖች ዛሬ አስከሬን አሳዩን በሚል ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ሄደው ነበር:: ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ግለስብ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት ጳውሎስ ሆስፒታልን የ እስረኞች ቤተሰቦች አጨናንቀውት ነበር::

የሟች አስከሬኖችን አሳዩን በሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከበላይ በመጣ ትዕዛዝ የተነሳ ይህን ማድረግ እንደማይችሉ ገልጸው ቤተሰቦቹን ለመመለስ ቢሞክሩም ቤተሰቦቹ ግን አስከሬን ካላየን አንሄድም በማለታቸው ፖሊስ መጥቶ እየደበደበ ከስፍራው እንዲሄዱ አስገድዷቸዋል::

እንደዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የመጡ የ22 እስረኞች አስከሬን ይገኛል::

ትናንት ዘ-ሐበሻ እስረኞች ከቅሊንጦ በ20 መኪና ተጭነው መሄዳቸውን ዘግባ ነበር:: እነዚህ እስረኞች ዝዋይ እና ቃሊቲ መወሰዳቸው ሲታወቅ ዛሬ ቅሊንጦ የሄዱ ቤተሰቦችም አንድም እስረኛ እዚህ የለም መባላቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል::

በመላው ዓለም ለምትገኙና በአዲሱ ዓመት ዘፈን ለማቅረብ እየተሰናዳችሁ ላላቹ የኪነጥበብ ባለሙያዎች የተላለፈ ማስጠንቀቂያ

$
0
0

Boycott
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትና የፍትህ ግብረ-ሃይል በአውሮፓ የላከው ግልጽ ደብዳቤ::

ታላቅ ህዝባዊ የትግል ጥሪ!!! ይድረስ በመላውአለምለምትገኙ ኢትዮጵያዊያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች

(ሙዚቀኞች፤ድምጻዊያን፤እንዲሁም ተወዛዋዦች) በያላችሁበት በተለይም
ለብሄራዊ ትያትር፤
ለሀገር ፍቅር ቲያትር፤
ለአዲስ አባባ መዘጋጃ ቤት፤
ለፖሊስ ሰራዊት፤
ለምድር ጦር ሙዚቀኞች እንዲሁም በውጭ ዓለም ዙሪያ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ከያኒያን በሙሉ

ለአዲስ ዓመት የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ለተዘጋጃችሁ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች በያላችሁበት። መስከርም 1 ቀን 2009 ዓ መ የኢትዮጵውያን ዘመን መለውጫ አዲስ ዓመት በአልን በመላው በአማራ፤ በኦሮሞ፤ በአፋር፤ በኦጋዴን፤በጋምቤላ በደቡብ አካባቤዎች እንደማይከበር በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ከአጋዚ ወታደሮች ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው በመዋደቅ ላይ የሚገኙ አስተባባሪዎች ገልፅውልናል። ወንድሞቻችን፤ እህቶቻችን፤ ህጻናትና ሽማግሌ አሮጌት በአጋዚ ወታደሮች እየታረዱና ደማቸው እየፈሰሰ እየሞቱ ይገኛሉ።

ይህ አመት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ “ጥቁሩ መስከረም” ወይንም ክፉ ዘመን ተብሎ ለነጻነት ፍቅር ሰለወደቁት እና እየወደቁ ላሉት ኢትዮጵያውን ወገኖቻችን ብሄራዊ የሀዘን ቀናችን ነው። የዚህን ዓመት እንቁጣጣሽ በጭፈራ፤ በዘፈን፤ በዳንኪራና በሆታ የምናሳልፍበት ቀን ሳይሆን በግፍ በአጋዚ ወታደሮች በኦሮሞ፤በአማራ፤በአፋር፤በሱማሌና በጋምቤላ በተጨፈጨፉትና በአሁኑ ስዓትም በግፍ እየተጨፍጨፉ በጥይት ቆስለው በሞትና በመኖር መካከል እየተሰቃዩ ያሉትን ወገኖቻችነን አስበን የምንውልበት ቀን ነው ውድ ወገኖቻችን ማንኛውም ደስታ ከኢትዮጵያ ህዝብ ድል በኋላ ይደርሳል። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ለኪነጥበብ ባለሞያዎች ያለው ፍቅርና አክብሮት ምን ያህል እንደሆነ የምታውቁት ይመስለናል።

ብትታመሙ አስታሞ ብትሞቱ አልቀሶ ቀብሮ ብትቸገሩ አለሁላችሁ ብሎ ከጎናችሁ የማይለይ መሆኑን በደንብ ታውቃላችሁ በመሆኑም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የትግል አጋርነታችሁን እንድታሳዩን ማንኛውንም የሙዚቃ ዝግጅት በሙሉ እንድትሰርዙ በጥብቅ እናሳስባለን።

ይህን የህዝብ ጥሪ ንቃችሁና ችላ ብላችሁ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ባትሰለፉ ታሪክና ትዉልድ ይቅር የማይለው ዘመን የማይሽርው በደል መሆኑን እናሳስባለን።

ህዝቡም ወደነዚህ የመዝናኛ ቦታዎች እንዳይሄድ በግፍ በተጨፍጨፉት ኢትዮጵያውያን ልጆች እንደውሀ በፈሰሰው ደማቸው እና በተከሰከሰው አጽማቸው እንማጸናለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር !!!

በህወሃት አገዛዝ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊትና የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘረኛና ኣምባገነናዊ ኣገዛዙ ጋር በማድረግ ላይ የሚገኘው የእምቢተኘነትና የአመጽ ትግል|ከነአምን ዘለቀ

$
0
0

Neamin Zeleke

ነዓምን ዘለቀ
በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተደረገ ያለው የእምቢተኘነትና የአመጽ ትግል ሳይቋረጥ ከመንፈቅ በላይ ባስቆጠረበት በአሁኑ ወቅት፣ ህወሃት እተማመንበታለሁ የሚለው የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት፣ ህወሃት/ኢህአዴግ የሚከተለው የዘረኝነት፥ የኣድሎና የበደል ፖሊሲ ትክክል አለመሆኑን ተገንዝቦ ህዝባዊ ትግሉን በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ። በዕለተ ዕሁድ ነሃሴ 29 ፥ 2008 ከ450 በላይ የሚሆኑ ወታደሮች በሰሜን ጎንደር የሚደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞውን በመደገፍ ወያኔን በማስወገዱ ሂደት ተጋድሎ እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው፣ የወያኔ ስርዓት እያከተመለት መሆኑን አመላካች ነው። ከዚህ በፊትም፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የጀግንነት ስራ ሰርተዋል። የህዝባዊ እምቢተኝነቱን ትግል ሲቀላቀሉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። በምርጫ 97 ወገን ላይ ተኩሱ ሲባሉ አሻፈረኝ በማለት ሄሊኮፕተር ይዘው ወደጎረቤት አገራት አምልጠዋል።
መከላከያ ሰራዊት ኣባላት የህዝቡን ስቃይ ሰምቷዋል፣ አሁን ደግሞ የህዝቡን ድምፅ አስተጋብቷል፣ እንደወገኑ ሁሉ የወያኔ አገዛዝ “በቃኝ” አያለ ይገኛል። የኦሮሚያ ክልል ህዝብ ለወራት የታገለውን፣ የአማራ ክልል ህዝብ የሞተለትን አላማ አንግቦ በመነሳት ላይ ይገኛል ። ህዝብና ሰራዊት የአንድ አገር ክፋዮች፣ የአንድ አገር ገጽታዎች ናቸው።

ከ90% በላይ የሆነዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እንደ ሲቪል ወገኖቹ ሁሉ ከአንድ ብሄር የበላይነት ተላቅቆ ሰላም፥ ፍትህና እኩልነት በሰፈነባት ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖር ይፈልጋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጽኑ ፍላጎት ምንም አይነት ጭቆናና መድሎ በሌለበት ስርዓት ዉስጥ ከአባቶቹ የተረከባትን አገር የግዛት አንድነት አስከብሮ ለሚቀጥለዉ ትውልድ ማስረከብ ነዉ እንጂ ወያኔና ምዕራብያውያን እንደሚያስቡት ለ “ምግብ ለመኖር” ብቻ የሚዋጋ ሰራዊት አይደለም።
“ውትድርና ዲሞክራሲያዊ ሳይሆን አምባገነን ነው።” ሆኖም ትክክለኛ ውለታውን የሚያከብርለት ጠንካራ አመራር ይፈልጋል። የታችኛው ሰራዊት የበላይ አመራሩን ጀግና፣ ትክክለኛና በውትድርና ሳይንስና ዕውቀት የታነጸ ክህሎት ያለው አድርገው ለማመን ለመከተልም ይፈልጋሉ።
ወታደሩ በዘር በተመሰረተ አድሎ ሳይሆን፣ በተግባር፥ በልምድና በአገልግሎት ላይ የተመሰረተ ዕድገት፣ የደሞዝ ጭማሪና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች እንዲሰጠው ይፈልጋል።
ሰራዊቱ አገራዊ ግዳጁን በሚወጣበትና በአገልግሎት ላይ ባለበት ግዜ ሁሉ ለስራዉ የሚያስፈለገዉን ቁሳቁስ ሁሉ መንግስት የማቅረብ ግዴታ አለበት፥ ይህ ሎጂስቲክን፥ ወታደራዊ ዩኒፎርሙንና የምግብ አገልግሎትን ያጠቃልላል።
ሞራሉ የላሸቀና አቅምና ብቃት በሌላቸው የህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ ጄኔራሎች የሚመራ ሰራዊት፣ ሙሰኛና ኢፍትሃዊ የሆነን ስርዓት ማገልገል አለመፈለጉ ብቻ ሳይሆን አገሩን ከጠላት መከላከልም አይችልም። የህዝብ ትግል ሲጎመራ፣ ሰራዊቱ በዘራፊና ዘረኛ ኣዛዦቹ ላይ አመጽ ማቀጣጠልና አፈሙዙን ወደ አነዚህ ጨቋኞች መመለሱ አይቀሬ ይሆናል።
ህወሓት ዘረኛ አገዛዝ ነዉ።ኣምባገነናዊ ጸረ-ሕዝብ ስርዓት ነው። ኢትዮጵያን የሚመራዉም በኣንድ ብሔር የበላይነት ላይ በተመሰረ ኣስተሳስብና ከዚሁ በሚመነጩ ፖሊሲዎች ነዉ። የወያኔ ስርዐት የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠይቀዉን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ የማይችል ስርዓት ነዉ። ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠይቀዉን ጥያቄ መመለስ የማይፈልገዉ የጥያቄዎቹ መልስ የሱ መጨረሻ መሆኑን ስለሚያዉቅ ነዉ።

አሁን ያለው የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራር ኢትዮጵያ ዉስጥ መሳሪያ አንስተዉ በተለያዩ ግንባሮች የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን ለማጥፋት የሚያስችለዉ ምንም አይነት ህዝባዊ ድጋፍ የለውም። በመጠነ-ሰፊ ችግሮችና ቅራኔዎች የተዘፈቀ ሰራዊት በሁሉም ኣቅጣጫ በሚጠመድ የህዝብ ትግል ኣካል ይሆናል አንጂ በህዝብ ላይ የማያባራ መከራና ግፍ ለሚፈጽም የዘረኛና የጨቋኙ የህወሃት አገዛዝ መሳሪያ ሆኖ በረጅሙ ሊቀጥል ኣይችልም።

militery

በህወሃት አገዛዝ ስር የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሞራል እጅግ የላሸቀ ነው። መንፈሱ የደከመ፣ አንድነቱ የላላ፣ በራሱ የማይተማመን እርስ በእስር በጎሪጥ ኣንዲተያይ የተደረገ፡ ዘረኛና ዘራፊ ጄኔራሎች የሚያዙት ነው። እንዲህ አይነቱ ሰራዊት ደግሞ በአንድነት በረጅሙ ለመዋጋት የሚያስችለው ሆኔታ ውስጥ የሚገኝ ኣይደለም።
ናፖሊዮን “መንፈሰ ጠንካራ ሰራዊት የራሱን ሶስት እጥፍ ወታደር ያሸንፋል’” በማለት አንድ ሰራዊት ሊኖረዉ ስለሚገባ የመንፈስ ጥንካሬና ሞራል ወሳኝነትና አስፈላጊነት ተናግሯል። ይህን ያለዉና ታላቅ የወታደራዊ ስትራቴጂና ታክቲክ ክህሎት አንደነበረው በሰፊው የተጻፈለት ናፖሊዮን፣ 300,000 አባላት የለዉን “ታላቁ ሰራዊት” ይዞ የተሸነፈዉ የሽምቅ ውግያ በገጠሙት ስፓኒሾችን በስፓንያ በሰራዊቱ ላይ ያደረሱበት ቡርቦራ አይነተኛ ምክንያትና ለውድቀቱም ከትልልቆቹ መንስኤዎች ኣንዱ ነበር። ከናፖሊዮን በኋላ ሽምቅ ተዋጊዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ በብዙ አገሮች ዉስጥ ትልልቅ መደበኛ ሰራዊቶችን ለሽንፈት ተደርገዋል። አልጄሪያ፥ ቻይና፥ ቬትናምና በቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት የነበረችዉ አፍጋኒስታን የሽምቅ ዉግያ አይነተኛ ምሳሌዎች ናቸዉ። በሽምቅ ውጊያ የደርግን ስርዓት በማዳከም መቻላቸውም ከምክንያቶች አንዱ ሆኖ ስልጣን ላይ የወጡት የህወሃት መሪዎች ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ በአራቱም ማዕዘን የገጠማቸዉን የአማጽያን እንቅስቃሴ ማሸነፍ የሚችሉበት ምንም አይነት ህዝባዊ ድጋፍ ሰለሌላቸዉ እነሱ በመጡበት መሸነፋቸዉ አይቀርም። ህወሃት ሽምቅ ተዋጊዎች ለማጥፋት የሚያደርገው “ቆሻሻ ጦርነት” ከጦር ወንጀለኝነት ጋር ስለሚያያዝ፣ በአለም አቀፍ ማህበረሰብም ይሁን በኢትዮጵያውያን መመርመሩ አይቀርም። ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ህወሃት የሚደረግለት ድጋፍ መቀነሱ አይቀርም። አሁን እንደሚታየው በህወሃትን ስር የሚማቅቀው ሰራዊት ጠንካራ የተቀናበረ ሽምቅ ውጊያና የህዝብ ኣልገዛም ባይነት በሁሉም የኢትዮጵያ ኣካባቢዎች ከተጠመደና ከተቀጣጠለ ኣገዛዙም “የስፓኝ ነቀርሳ” ይሆንበትና ወደ መፍረክረኩ ለጥቆም ኣብዛኛው የሰራዊቱ ኣባላት ወደ ህዝብ ትግል የሚቀላቀሉበት ሂደት ይፈጠራል።
ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚገኙ ስር የሰደዱና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተጠያቂዎቹ የሆኑት የህወሓት መሪዎችና የትግራይ ጄኔራሎች ናቸዉ። የእነዚህ መሪዎችና ጄኔራሎች ዘረኝነት፥ ጭካኔ፥ ስግብግብነትና ገንዘብ ማሸሽ አገራቸዉን ዋጋ እንደሚያስከፍል ሁሉ እነሱንም ከፍተኛ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሊያዉቁ ይገባል። የኣምባገነናዊነትና የዘረኝነት ተግባሮች የሌላ ብሄር ዜጎችን እንደሁለተኛ ዜጋ፡ ከዚያም በታች የመቁጠር አባዜያቸው፥ ለከት ያጣው ኢፍትሃዊ ተግባሮቻቸው፥ ዘረፋቸው፡ ኣፈናና ጭቆናቸው ሳቢያ ከህዝቡም ሆነ ከኣብዛኛው የመከላከያ ሰራዊት ኣባላት የተነጠሉ መሆናቸውን ሊያውቁ ይገባል። ይህንን ሁሉ በአይኑ የሚያየዉና የገፈትና የመከራ ህይወት ኣስከኣፍንጫው የተጋተው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ትዕግስቱ ተሟጥቶ አልቋል። በኦሮሞ ክልል ኣየታየ የሚገኘው ህዝባዊ የቁጣ ማዕበል ፡ ዛሬ በጎንደርና በጞጃም ዉስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በመደገም ላይ የሚገኘው በማያሻማ ሁኔታ ይህንኑ የሚያረጋግጡ ናቸው። ትግሉ በመላ የኢትዮጵያ ኣካባቢዎች የሚዛመትበትና የሚቀጣጠልበት፡ የወያኔ ኣርነት ትግራይ ኣገዛዝ እውር ድንብሩ ወጥቶ የሚጨብጠውን የሚለቀውን የሚያጣበት፥ ብሎም ተፍረክሮኮና ተንኮታክቶ በህዝብ ትግል የሚንበረክክበት ጊዜ እሩቅ ኣይሆንም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት ለፍትሃና ለአኩልነት የሚያደርገው የአመጽ ትግልና የኣልገዛም ባይነት ትግል፥ የህዝባዊ አምቢተኝነት ትግሎች ሁሉ የህወሓት ኣገዛዝ እስኪወገድ ድረስ በየኣካባቢው አንደ ሰደድ አሳት የሚቀጣጠል እንጂ የሚቆም ኣይሆንም።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live