አይጋ ፎረም የተባለው የዘረኛው ሕወሓት መንስት ደጋፊ ድረገጽ ሰሞኑን በብአዴን ላይ ዘምቶበታል:: ” የብአዴን በበሰበሱ ነፍጠኞች እጅ ተጠልፎ የመውደቁ ትርኢት ወጣ ወጣና ተንከባለለ እንደሙቀጫ” የሚል ጽሁፍም በ እንግሊዘኛ ቋንቋ አስነብቦ ነበር:: ይህ ጽሁፍ ወደ አማርኛ ተተርጎሞ የቀረበላችሁ ምን ያህል ዘረኞቹ ሕወሓቶች በብ አዴን ላይ ያላቸውን ንቀት እንድታዩት ነው:: ያንብቡት::
በዶር ታረቀኝ በእግሊዝኛ ተጽፎ የቀረበ
መቀሌ
(ዝርግ ትርጉም መስቀሉ አየለ)
የቀደሙት ነገስታት ሆነ ብለው ድርቅን የሚፈጥሩት ብሎም የሚያባብሱት ለማመን በሚቸግር ሁኔታ ህዝቡን ለመቆጣጠር እንዲያስችላቸው ነበር። ነገር ግን ህልቁ መሳፍርት መስዋእትነት ከፍሎ እነዚህን ገዥዎች ከስራቸው ነቅሎ በመጣሉ በኩል የአንበሳውን ድርሻ የተወጣው ጀግናው ህወሃት የማህበራዊና ኢኮኖሚ እቅድ በመንደፍ ባለፈው አመት በኤሊኖ የአየር ጠባይ የተነሳ በአለም አቀፍ ደረጃ ተከስቶ የነበረውን ድርቅ በመቀልበስ ረገድ አመርቂ ውጤት አስመዘገበ። የተመዘገበውም ድል ህወሃትንና አጋሮቹን ያኮራና በአለም አቀፍ ደረጃ ክብርና ሞገስ ጭምር ያስገኘ አኩሪ ታሪክ ሆኖ አልፎዋል። ህወሃት ሁልጊዜም ከምንም ነገር ተነስቶ ተዓምር መፍጠር የዘወትር መለያው ነው።
ህወሃት ማለት በመርህ ላይ የቆመ፣ ትጉ፣የማይናወጽ፣ መልካምነት የባህሪ መገለጫው የሆነ፣ ትርፋማ እና በሁሉም ዘርፍ አለማችን እራሷ ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው ተዓምረኛ የፖለቲካ ፓርቲ ነው።በዚህ በጣም ተለዋዋጭ በሆነ አለማቀፋዊ ሁኔታም ውስጥ እንኳን አንድን በጣም ውስብስብ እና ግዙፍ አገርን ስር ከሰደደ ድህነትና ከለየለት ኋላ ቀርነት በማውጣት እንደ አለት የጸና የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማሥመዝገብ በኩል በዓለም ውስጥ ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ለመሆን በቅቷል::
ያለመታደል ሆኖ ባለፈው አመት ተከስቶ የነበርውን የድርቅ አደጋ አመርቂ በሆነ ሁኔታ ተቋቁመነው እንዳበቃን ብዙም ሳይቆይ በብዙ የአገሪቱ ክፍሎች ህዝባዊ ነውጥ ተነሳ ።የዚህም ህዝባዊ ነውጥ ዋነኛ ምክንያቱ የኪራይ ሰብሳቢነት ያስከተለው ችግር ቢሆንም ነገር ግን በአማራ ክልል የተነሳውን አመጽ በተመለከተ ግን መሰረታዊ ምክንያቱ ከዚህም አልፎ የሄደ ነበር ማለት ይቻላል ።ይኽውም ህወሃት ብዙ የደከመለትን የአገሪቱን የፖለቲካ መዋቅር ቀስ በቀስ በመገዳደርና ብአዴንን ከቆመለት ህዝባዊነት በማውረድ ግዜው ያለፈበትንና የቆሸሸውን የድሮ ነፍጠኛ ስርዓት ቅርጽ መስጠትን አላማ ያደርገ አፈንጋጭ የብአዴን ክንፍ ከፍተኛው የስልጣን እርከን ላይ መፈናጠጡ ነበር። ብአዴን እንደ አንድ ድርጅት መበስበሱንና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በእንደዚህ አይነት የነፍጠኛ እርዝራዦች ቁጥጥር ስር መውደቁን የሚያሳዩ የተወሰኑ ትዕይንቶችን ደረጃ በደረጃ ላሳይ።
ትዕይንት ፩
ብአዴን የሰላሳ አምስተኛ አመት የምስረታ በዓሉን ባከበረበት ግዜ ለራሱ ያልነበረ ቅርጽ በመስጠትና ደርግን በመጣሉ ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና የተጫወተ በማስመሰል የታሪክ ውርጃ በመፈጸሙ የተነሳ በወቅቱ ሁኔታው ያሳሰባቸው ብዙ ሰዎች ድምጻቸውን ለማሰማት ሞክረዋል። ብአዴን የራሱ ነፍስ የሌለው ደርግን ለመጣልም በተደረገው ትግልም ብአዴኖቹ ከሞነጫጨሯቸው ጥቂት ግጥሞችና የፍቅር ደብዳቤዎች ውጭ ምንም ሚና የተጫወቱት ነገር አለመኖሩም ገሃድ የወጣ እውነት ነው።እንደውም ብአዴን የህወሃትን ገድል የሚያሳይ ቪዲዮ ሰርቆ ፫፭ኛ ዓመት በዓሉን ሲያከብር በአማራ ቴሌቪዥን ላይ ምንም አይነት ለውጥ ሳያደርግ የራሱ ገድል አስመስሎ አሳይቷል። ብአዴን ይህንን ያደረገው በጦርነቱ ወቅት በባልተቤትነት ይዞት የነበረ አንድ ነጠላ የቪዲዮ ክር እንኳን ስለመኖሩ የሚታውቅ ነገር በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ነው።
በዚሁ የሰላሳ አምስተኛ አመቱ ክብረ በዓል ላይ ከሃቁ ባፈነገጠ መልኩ ተጣመውና ተጋነው ከቀረቡትጭብጦች መካከል ብአዴን ያለማንም እርዳታ በራሱ ግዜ እራሱን ችሎ የተፈጠረ አስመስሎ ለመዘከር የሄደበት ደረጃ ነው። ይህ ማለት ባጭሩ ብአዴንን ህወሃት የፈጠረው አይደለም ለማለት ተፈልጎ ነው። በርግጥ ብአዴን የህወሃት ስራ ነው ወይም አይደለም የሚለው ጥያቄ ቁምነገር ሆኖ አይደለም። በጣም አስፈላጊው ነገር ብአዴን ትግራይ ውስጥ በህወሃት የተሰራውን ፕሮጀክት እንዳለ ግልብጦ በመውሰድ የአማራውን ህዝብ ከነበረበት ድህነት በማውጣት ወደ ከፍተኛ የሶሺዮ ኢኮኖሚ እምርታ ማሸጋገሩ ነው። ነገር ግን ብአዴን ከጽንሰቱ ጀምሮ እራሱን ሆኖ የወጣ ለመምሰል የሚሞክርበት ዋናው አለማ በራሱ በብአዴንም ውስጥ ሆነ ከብአዴን ውጭ ያሉትን የነፍጠኛ ቅሪቶችን ሞራል በማጎልበት በውስጣቸው የተፈጠርውን ባዶነት በመሙላት ብሎም ሞራላቸውን ከፍ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ መሆኑ እሙን ነው። ስለሆነም የሰላሳ አምስተኛ አመቱን በዓል አከባበር ልብ ላለው ሰው ብአዴን ያው በድሮው ነፍጠኛ መዳፍ ስር እየገባ ለመሆኑ የመጀመሪያው አመላካች ሁኔታ ነበር ማለት ይቻላል።
ትዕይንት ፪
ብአዴን ከህወሃት እንጀራ ልጅነት እንደ ወረደ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በቀጥታ ወደ አንድ አይነኬ ጎሬላ ተዋጊ ቡድንነት ነበር የተቀየረው። ይኽ በነፍጠኛው ተጽእኖ ስር የውደቀው የጎሬላ ሃይል አንድ ብሎ ጠንካራ ክንዱን ማሳረፍ እና መጨፍጨፍ የጀመረው ምንም አይነት መከላከያ ያልነበራቸውን የቅማንት ብሔረሰብ ህጻናትና ሴቶችን ነበር። በምስኪን ቅማንቶች ላይ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ የቀድሞዎቹ ነፍጠኞች በቀሩት የኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ ሲፈጽሙት ከኖሩት ጭፍጨፋ ምንም አይነት ልዩነት ያልነበረው ሲሆን ይኽም እንግዲህ የነፍጠኛው ሃይል በግልጽ ስጋ ለብሶ እየመጣ እንደ ነበር የታየበት ሲሆን በቀጣይነት ለመውሰድ ለሚያስበው ግዙፍ ወረራ እንደ ሙከራ የተወደ ነበር ማለት ይቻላል።
ትዕይንት ፫
ተወስደዋል የሚባሉት የአማራ መሬቶች በብአዴን ውስጥ አቆቁጠው በወጡት የድል አጥቢያ አርበኞች ሲቀነቀን የቆየ ነው። ይህ ቡድን የመጀመሪያ ጡንቻውን በቅማንቶች ላይ ሲያሳርፍ ከራሳቸው ከቅማንቶችም ሆነ ከማእከላዊ መንግስቱ ይኽ ነው የሚባል ተግዳሮት ያላጋጠመው በመሆኑ ይበልጥ ሃይሉን በማጠናከርና የወሰን ክልሉን ወደ ረባዳማው ምእራብ ትግራይ ወልቃይት በማስፋት ውጥኑን ዳር ለማድረስ ይረዳው ዘንድ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በእጅ አዙር በመመሳጠር ወረራውን በስፋት መያያዝ የጀመረ ሲሆን ይኽም ብአዴን ሙሉ ለሙሉ በነፍጠኛው ቁጥጥር ስር የወደቀ ለመሆኑ ዋነኛው ማረጋገጫ ሆነ።
ሀ) ህዝባዊነትን ያላማከለ የመሬት ወረራ ማካሄድ የኖረ የነፍጠኞች መሰረታዊ መገለጫ ነው
ለ)የወልቃይት ይገባኛል ጥያቄውን ለመግፋት እየተሄደበት ያለውን መንገድ ለሚያየው ታዛቢ የፈደራል መንግስቱን ህገመንግስት ባፍጢሙ የደፋ ነበር ማለት ይቻላል።
ላንድ ብቸኛ ፓርቲ ጥቅም ሲባል የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ዋስትና የሆነውን ህገመንግስት ጨፍልቆ ማለፍ ሌላው የነፍጠኛ መገለጫ መሆኑ እየታወቀ ብአዴን እንደሚታየው ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በነፍጠኛው ቁጥጥር ስር ባይወድቅ እንዲህ ያለውን የህገመንግስት ጥሰት ነገሩን በዝምታ ያልፈዋል ብሎ ማሰብ አይቻልም ነበር።
ትዕይንት ፬
በጎንደር የተፈጠረውን አለመርጋጋት በተመለከት ብአዴን የያዘው አቁዋም የሚገርም ሲሆን ይኽ ውም ድርጅቱን ከፊቷ ከተንጣለለው አረንጉዋዴ ሁዳድ በስተቀር ሌላ ነገር የማታይን የሜዳ አህያ አስመስሎታል።ይህ ቡድን ማንኛውንም አይነት ነገር በመጠቀም የትግራይን ህዝብ ከማንገላታት ጀምሮ ህወሃትን በማሸንፍ ኢህአዴግን ማፍረስና የተነጠቀውን ክብሩን ማስመለስ እንደሚችል ያምናል። ለነፍጠኛው ክብር ማለት በሚሊዮን ይሚቆጠሩ ዜጎችን በረሃብ ቸነፈር እየቀጡ ጥቂቶችን ቁንጣን እስኪይዛቸው ከርሳቸውን መሙላትታና ብዙ እዳሪ እንዲወጣቸው ማስቻል ነው። የኦሮሞያ ክልላዊ መንግስት መግለጫ እንዳስቀመጠው “ነፍጠኛ ሲባል ስለ ቡና ሲያስብ ብቻ ጅማን ሰንጋ ሲያስብ ደግሞ ሃረርን የውይይት አርእስት የሚያደርግ ማለት ነው”። ነፍጠኛው በግልጽ ተደራጅቶ ድፍን ጎንደርን የጦርነት ቀጠና ሲያደርጋት፣ የትግራይ ሰዎችን እየመረጠ ሲገድልና በጠራራ ጸሃይ ንብረታቸውን ሲያወድም ብአዴን ተብየው ግን አይኔን ግንባር ያድርገው በማለት ነበር ለዚህ ሃይል የፖለቲካ ሽፋን ሊሰጠው የሞከረው።ይኽን ያህል የውንብድና ተግባር ሲፈጸምና ክልሉን ዳግም ወደ መላኩ ተፈራ የሽብር ዘመን ሲመልሰው ብአዴን ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዱ እንዲሁም የማእከላዊ መንግስትን ድጋፍ አለመጠየቁ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስትን አቁዋም ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባው ይሆናል። በ፩፱፱፯ ዓም በአዲስ አበባ የተዘመረውን (ትግሬ ወደ መቀሌ፣ እቃ ወደ ቀበሌ፣ ወያኔም ወደ ከርቸሌ) የሚለው መዝሙር በጎንደር ዳግም ሲዘመር፣ ንብረትም ሲወድም ሆነ የሰው ህይወት ሲጠፋ ብአዴንም ሆነ አመራሩ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ትዕይንት ፭
የፌደራል መንግስቱ ልኡካን ተዎካዮች ሳይቀሩ ለስራ ጉብኝት በሚሄዱባቸው አገሮች በሙሉ በአፍቃሬ ደርግና አፍቃሬ ነፍጠኛው ርዝራዥ ቁምስቅላቸውን ያያሉ። ከነዚህ ውስጡ ድምጻቸው ጎልቶ የሚሰማው የአፈረሱ ቀሳውስት፣ የቀይ ሽብር ተዋናዮች እና ወታደሮች እንዲሁም ስም አልባ አዝማሪዎች ሁሉም ከአማራው ብሔር የሚመዘዙ የደርግና የነፍጠኛ ጥርቅም ናቸው። ነገር ግን በተጻጻሪ መልኩ በብአዴን ስም የተቀመጡቱ ነፍጠኞች ክልላቸውን ወክለው ወደ ውጭ አገር በሚሄዱበት ግዜ የሞቀና የደመቀ አቀባበል የሚደረግላቸው መሆኑን የዚያን ሰሞን የዩናትድ ስቴትሱ ጉብኝት ጥሩ ጠቋሚ ነበር። ሰሞኑን በባህርዳር ውስጥ በብአዴን አመራርና የዲያስፖራው ማህበረሰብ መካከል የነበረው ዝግ ስብሰባ ያሳየው ነገር ቢኖር ብአዴን ምን ያህል የነፍጠኛው ሃይል ጀልባ እየሆነ የመጣ መሆኑን ጠቋሚ ነበር። የቀደሙት የብአዴን አመራሮች የህወሃት አሻንጉሊቶች ናቸው እየተባለ ስማቸው ይጠፋ ስለነበር ለስራ ወደ ውጭ አገር ሲሄዱም ከሌላው የፌደራል መንግስት ተወካይ ያነሰ መዋከብ ደርሶባቸው የማያውቅ ሲሆን ባልተለምደ መልኩ በ አሁኑ ሰዓት ያሉት የብአዴን ሰዎች ግን ምን ያህል የክብር አቀባበል እንደሚደረግላቸው ስናይ መሬቱን መልሰው መቀራመት ለሚፈልጉት የአሁን ዘመን ጉልት ናፋቂዎች እና እነሱ ለሚያራምዱት ጭፍን ብሄራዊ ስሜት የተንበረከኩ ለመሆኑ ትልቁ ማሳያ ነው።
ከዚህም በላይ ተጨማሪ ማረጋገጫዎች ሊቆጠሩ የሚችሉ ሲሆን በዋናነት ግን ምን መደረገት ይኖርበታል በአሁኑ ሰዓት የጎንደሩ ነውጥ እያደገና የአመጹ መሪዎችም ሁኔታውን በማጠናከር ወደቀሩት የአማራ አካባቢዎች ለማስፋፋት እየሞከሩ ነው። ችግሩ ይበልጥ አድጎና ገዝፎ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ከሚሄድበት ኩነት አንጻር ብአዴንም ሆነ የአማራብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከዚህ በኋላ እንደገና ሊቆጣጠሩት ይችላሉ ተብሎ የማይታሰብ ሲሆን የክልሉ መንግስትም ሆነ ፓርቲው ብ አዴን በሰላሳ ስድስት አመት ታሪኩ የዚህን አንድ መቶኛ ያህል ችግር አጋጥሞት ያውቃል ብሎ ማሰብ አይቻልም።በቅርቡ እንደምናስታውሰው የብአዴን አፈንጋጭ ሹመኞችና የድል አጥቢያ አርበኞች በምርጫ ዘጠና ሰባት ወቅት ባህርዳር ላይ በመሸነፋቸው እና ወንበር በማጣታቸው አደ አዲስ አበባ በመምጣት በፌደራል መንግስቱ ውስጥ የሚንስትርነት ወንበር አገኙ።
በዚህም የተነሳ አፈንጋጮቹ የብአዴን ክፍል በማእከላዊ መንግስት ውስጥ ለረጅም ግዜ ሲመኙት የኖሩትን የህወሃት ወንበር መቆናጠጥ አስቻላቸው። በርግጥ ህልማቸው በራሱ ችግር ነው ማለት አይደለም። ይልቁንም ህወሃት በኢህአዴግ ውስጥ ያለውን ድርሻ በማቻቻል አጋር ድርጅቶቹም የተሻለ ሃላፊነት ይዘው ጠንክረው እንዲወጡና በአገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሞያዊ እድገት ላይ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ ማስቻል በመርህ ደረጃ ተቀብሎ ሲሰራበት የኖረው ነገር ነበረና። ነገር ግን ውስጥ ውስጡን ሲብላላ ቆይቶ አሁን ችግር ሆኖ የወጣው ይኽ አፈንጋጭ ቡድን መሰረታዊ ከሆነው መርህ ውጭ ባፈነገጠ መልኩ ቀስ በቀስ የማእከላዊውን መንግስት ስልጣን በመቆጣጠርና፣ ህወሃትን በማዳከም ብሎም ከነፍጠኛው ጋር ግንባር በመፍጠር ወደ ለየለት የመሬት ቅርምት ውስጥ በመግባት ላይ መሆኑ ነው። ይህም አፈንጋጭ የብአዴን ክንፍ የነፍጠኛው ቡድን “ሀ “ብሎ ጎንደር በሚገኘው የስታር ሆተል ላይ ጥቃት ሲሰነዝር ሽፋን በመሰጠት ለትግራይ ህዝብ ማስተላለፍ የተፈለገው ማእከላዊ ነጥብ የጥቃቱ ሰለባዎችን ሊታደጋቸው የሚችል አቅም ያለው ህወሃት እንደሌለ ማሳየት የነበረ ሲሆን ነፍጠኛው በሙሉ በዚህ ሰዓት ይህንን ነገር እንደ ትግል እስትራተጅ ይዞት የተነሳው መሆኑን እሙን ነው።
ብአዴን የህወሃትና የትግራይ ህዝብ ለሰላም ወዳዱ፣ ትሁቱና ወንድሙ ለሆነው የአማራ ህዝብ የተበረከተ ስጦታ ሲሆን አለማውም ይህንን ህዝብ ከነበረበት ስር የሰደደ ድህነትና ኋላ ቀርነት ይዞት ይወጣል በሚል እሳቤ ነበር።ማንም በዚህ ሰዓት በበሰሜን ሸዋ፣ ወሎና ጎንደር በአካል ሄዶ መታዘብ እንደሚችለው ህወሃትና የትግራይ ህዝብ ለእነዚህ አካባቢዎች ከተክህራረዋ ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ከማንኛም አይነት አደጋ ዋስትና ከመስጠት ጀምሮ የራሳቸውን ሰዎች ቀርጸው እንዲያወጡና ብሎም ብአዴን የተሻለና ጠካራ አመራር ሆኖ እንዲወጣ ጉልህ ድረሻ ማበርከቱ በራሱ የሚያሳየው ነገር ቢኖር የትግራይ ህዝብና መንግስት ወንድሙ ለሆነው የአማራ ህዝብ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንዳለው አንዱ ማሳያ ነው።
ዛሬ አፍቃሬ ደርግና የነፍጠኛው እርዝራዥ ይኼን ገና ሳይወለድ የጨነገፈ የነፍጠኛውን ስርዓት መልሰው ለማቆም እያለሙ ነው።ነገር ግን አሁን ባለው ተጨባጭ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዲህ አይነቱ የጨነገፈ ስርዓት ተመልሶ የሚመጣበት ሁኔታ ይፈጠራል ብሎ ማመን ከንቱ ድካም ነው። አፈንጋጩ ብአዴንና እስከ ጥርሳቸው የታጠቁት በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ምንም የማያውቁት የአማራ ሚሊሽያዎች እንኩዋን ህወሃትን ያህል ሃይል አሰወግደው የነፍጠኛውን ስርዓት ሊያቆሙ ቀርቶ በአንድ የህወሃት ታጋይ የተተከለችውን የማእዘን ድንጋይ ከቦታዋ ማነቃነቅ አይቻላቸውም። ምናልባት ህወሃትን እንደ አንድ ሽፋሽፍት አራክሰውና አሳንሰው ማየት የሚፈልጉ ምንም ግንዛቤ የሌለላቸው አማራዎች ካሉ ልብ እንዲሉት የምንፈልገው ነገር ምንም አይነት መከላከያ የሌላቸውን ህጻናትና ሴቶች በመግደልና በማዋከብ እንዲሆም ንብረታቸውን በመዝረፍ እና ባማቃጠል የነፍጠኛውን ስርዓት መልሰን እናቆምለን ብላችሁ የምታምኑ ከሆነ በሞት የተለየችውን እናቱን ውሃ ልትቀዳ ሄዳ ነው ብሎ ማዶ ማዶ ሲመለከት የሚውልን ህጻን መሆናችሁ እንደሆነ እወቁት።
በማጠቃለል መልካም የሆነውና የተማረው የአማራ ህዝብ ክፍል የነፍጠኛውን ስርዓት እንደገና መልሶ ማቆም ወይንም የሂደቱ አካል አድርጎ ማስቀጠል ይቻላል ብለው ያምናሉ ተብሎ አይገመትም። በምሆኑም ግዜው ከመርፈዱ በፊት ብአዴን “አንድ ” ብሎ ሲነሳ ይዞለት የተነሳውን አላማ እዳይስት የማድረግ ሙሉ ሃላፊነት አለባቸው። ስለዚህ በሌለ እውነት ላይ የተገነባውን እና እንደ ባዶ ፊኛ የተወጠረውን የነፍጠኛ ስሜት በስቸኳይ ማስወገዱ ለነገ የማይባል ጉዳይ ሲሆን የኢህአዴግም ጥምሮች እንደ ፓርቲ ብአዴንን ከተጣባው የነፍጠኛ ጥርቅም እራሱን ያጸዳ ዘንድ የሚቻላቸውን ያህል የመርዳት ሃላፊነት ያለባቸው ሲሆን በመቀጠለም ግዜው ኢህአዴግም እራሱ በውስጡ ከተሰከሰኩ ጠባብ ብሔርተኞች እና ትምክህተኞች ውስጡን የሚያጸዳበት የስር ነቀል ተሃድሶ ግዜ ሊሆን ይገባዋል። ሙስናንም ሆነ ኪራይ ሰብሳቢነትን ውጤታማ በሆነ መልኩ መዋጋት ማለት ይኼው ነው።