Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የእድገቱ ጉዳይ -እድገት ከነጻነት አይለይም–አክሎግ ቢራራ (ዶር)

$
0
0

Dr Aklog Biraraየቀለም ቀንድ ጥያቄ ባለሁለት አሃዝ እድገት አለ ሲባል ዋናዎቹ መስፈርቶች ምንድን ናቸው እና እንዲት? ለምሳሌ፤ አሁንም አገራችን የአንድ ወቅት ዝናብ ሲቋረጥ ከፍተኛ ችግር መድረሱንና ለጋሾችን መለመናችንን አላቆምንም፡፡ ለመሆኑ ይህ ለብዙዎቻችን ግልጽ ሊሆን ያልቻለ ተቃርኖ እንዴት ነው የሚገለጸው? ሌሎች አገሮች ከተፈጥሮ የሚከሰት ረሃብን እንዴት ተወጡት፤ እኛስ እንዴት ልንወጣው እንችላለን? ምሳሌዎች አሉ፤ እነማን? –[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ] —–


በፍራንክፈርት፣ በስቶክሆልም፣ በለንደን፣ በጄኔቫና በኦስሎ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ አስቸኳይ ጥሪ

$
0
0

Oromo amhara unity
የሀገራችንን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ወገኖቻችን እየከፈሉ ያሉትን ከፍተኛ መስዋዕትነት ለመደገፍ፣ ለማበረታታትና አጋርነታችን ለማሳየት ከአገር ውጭ በማንኛውም የአለም ክፍል የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በታች የሚከተሉትን እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ተዘጋጅተናል።

1ኛ: የሻማ ማብራት መርሐ ግብር

የፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚኖሩባቸው በዋና ዋና ከተሞች በህወሀት አጋዚ ጦር በጥይት ተደብድበው በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ውድ ሕይወታቸውን ያጡትን ሰማዕታት ለመዘከር የሻማ ማብራት ፕሮግራም ማካሄድ፣

2ኛ: የፊታችን እሁድ ኦገስት ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም የእምነት ተቋማት ለነዚሁ ሰማዕታት ፀሎተ ፍትሃት ማድረግ፣

3ኛ: ከፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን እስከሚቀጥለው አርብ ኦገስት 19 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በዋና ዋና ከተሞች ጨፍጫፊውን የህወሃት ስርዓት ለመቃወምና የሰፊውንና የነፃነት ፈላጊውን የኢትዮጵያ ህዝብ እልህ አስጨራሽ ትግል ለመደገፍ እንዲሁም አጋርነታችን ለማሳየት ታላቅ ትዕይተ ህዝብ ማድረግ፣

4ኛ: ከህወሃት ወያኔ የዘረኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ለመገላገል አደባባይ ሲወጡ በአጋዚ ጦር በጥይት ተደብድበው መተኪያ የሌላት ህይወታቸውን መስዋዕት ላደረጉ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርጃ የሚሆን ገንዘብ የማሰባሰብ፣

5ኛ: በአጋዚ ስናይፐር፣ መትረየስና ክላሽ ተደብድበው በየሆስፒታሉና መኖሪያ ቤታቸው የተኙ ወነገኖቻችንን ለማሳከምና

6ኛ: በህወሃት ማጎሪያ ቤቶች በአማራ፣ በኦሮሚያና አዲስ አበባ ታስረው የሚገኙ ዜጎቻችንን በስንቅና በሞራል ልንደግፍባቸው የምንችልባቸውን መንገዶች ለመወያየት ከፊታችን አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተለያዪ የመወያያ መንገዶች ውይይት ለማድረግ ተዘጋጅተናል።

በዚህ መሰረት እስካሁን ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግባቸው የታቀዱ ከተሞች:

አርብ ኦገስት 12 ቀን 2016 ዓ/ም
በጀርመን ፍራንክፈርትና በስዊድን ስቶኮልም

ሰኞ ኦገስት 15 ቀን 2016 ዓ/ም
በእንግሊዝ ለንደን

ማክሰኞ ኦገስት 16 ቀን 2016 ዓ/ም
በስዊዘርላንድ ጄኔቫ

አርብ ኦገስት 19 ቀን 2016 ዓ/ም
በኖርዌይ ኦስሎ

ሲሆኑ በሌሎች የአለማችን ታላላቅ ከተሞችም ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎችን ለማድረግ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው።

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መርሃ ግብሮች ስኬታማ ለማድረግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሚኖርበት አካባቢ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ታዋቂው የኦሮሚኛ ሙዚቃ ድምጻዊ ሙክታር ኡስማን በኮንሰርቱ ላይ ለወቅታዊው ትግል “በርቱ! ተስፋ አትቁረጡ”ሲል አቀነቀነ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ለ20ኛ ጊዜ በሰሜን አሜሪካ የተደረገው የኦሮሞ ስፖርት ፌስቲቫል ባለፈው ቅዳሜ በሚኒሶታ ሲዘጋ በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ላለው ሕዝባዊ ትግል ታዋቂው የኦሮሚኛ ሙዚቃ ዘፋኝ ሙክታር ኡስማን መታሰቢያ የሚሆን ተወዳጁን “Abdi Hin Kutatinaa” የሚለውን ዘፈኑን ተጫውቷል:: በዘፈኑም “ተስፋ አትቁረጡ! በርቱ” ሲል በሃገር ቤት እየታገሉ ያሉትን ወንድም እና እህቶቹን አበረታቷል:: ነዋሪነቱ በኖርዌይ የሆነው ሙክታር ለዚሁ ኮንሰርት አሜሪካ ሚኒሶታ ድረስ በመምጣት ዝግጅቱን ካቀረበ በኋላ ከዘ-ሐበሻ አዘጋጆች ጋር ተነጋግሯል:: በንግግሩም በሃገር ቤት እየተከፈለ ያለውን የሕዝብ መስዋ ዕትነት እንደሚያደንቅና እርሱም የሚቻለውን ሁሉ ለትግሉ እንደሚያደርግ ገልጿል:: በዚህ ኮንሰርት ላይ ያቀረበውን Abdi Hin Kutatinaa (ተስፋ አትቁረጡ) የሚለውን ዘፈኑን ከነመልዕክቱ ያድምጡት::

ከኢትዮ-ሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ከአብዲ መሐመድ ይልቅ የአፋር ግመሎች የኢትዮጵያን ባንድራ ያውቋታል

$
0
0

somalia Region
ከመሠረት ገደፋው

ይህንን ያልኩበት ምክንያት ሰሞኑን በጎንደር እና ባህርዳር የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ” #በልማታዊ_ጋዜጠኛ #አስማማው_አየነው በ”EBC” የሰጡትን መግለጫና ወግዘት አደመጥኩት፣ኮስተር ብለው ንግግራቸውን ቀጠሉና በእለቱ የተውለበለበው የደርግ ሰንደቃላማ ነው ሲሉ ተደመጡ። የሶስት ሽህ ታሪክ ያላትን ባንድራ የዛሬ 30 ዎቹ አመት ወደስልጣን ለመጣው ወታደራዊ ደርግ ብቻ መስጠታቸው ምን ያህል ከኢትዮጵያ የራቁ መሆናቸውን ያመለክታል ወይም እንደገደል ማሚቶ የተነገራቸውን ብቻ ነው የሚያስተጋቡት።

ለማንኛውም ክብር ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ ሰንደቃላማችን የደርግ ሳትሆን ከኖህ ዘመን እስከ ጎንደር የዘለቀች ናት።ወድፊትም በእያንዳንዳችን ልብ የታተመች ማህተም ስለሆነች ለዘላለም ትኖራለች።

እንዳው ሌላው ቢቀር እንኳን አቶ አብዲ ለዘመናት በምዕራብያዊያን ቅኝ ግዛት ሲማቅቁ የነበሩት አፍሪካዊያን ከነፃነት ማግስት በርካታ ሀገራት የነፃነት ተምሳሌት የሆነችውን የሀገራችንን ሰንደቃላማ እንደሚጠቀሙ አያውቁምን? ካላወቁ ይኸው ነገርኩዎት ክቡርነትዎ።

የአቶ አብዲ መሐመድን ንግግር ስሰማ አንድ የአፋር ሱልጣን የተናገሩት ትዝ አለኝ።

“የኢትዮጵያን ሰንደቃላማ እንኳን እኛ ግመሎቻችን ያውቋታል”።
(የአፋሩ #ሱልጣን_አሊሚራህ)

በቃለት መንግስት? –ሰለሞን ለታ

$
0
0

Woyanes shoud face justice አንድ የኦርቶዶክስ የእምነት አባት የነገሩኘን ሰለኢሀዲግ መንግስት አወዳደቅ ምን እንደሚመስል ላካፍላችሁ። እርሳቸው በሊቀ ትጉሃን ማእረግ  የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ናቸው::  የተገናኘንበት አጋጣሚ  1996 EC ክረምት ወር ላይ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በባህርዳር ከተማ በኦርቶዶክስና ወንጌላዊያን ከርስቲያናት መካከል የነበረውን ግንኙነት ለማጥናት ሂጀ በነበረበት ወቅት ነወ:: ረጅም ዘመን ያስቆጠረ በግምት 500 ገጽ አካባቢ የሚሆን ትልቅ መጽሃፍችውን  ይዘው ወደኔ ቀረቡና ልጀ ይህ መንግስት ሊውድቅ የሚችልበት ሚስጥር እዚህ መጽሃፍ ውስጥ ይገኛል አሉኝ። እኔም በመገረም  የሚሉኝን ለመስማት ጓጓሁ። ከዛም ትረካቸውን እንዲህ ጀመሩ።

“አንበሳው  በ ጂቡ ይበላል።ጂቡ ደግሞ በተኩላዎች ይበላል። ተኩላዎች በጉንዳኖች ይበላሉ”  የሚለውን ክፍል አነበቡልኝ። ታዲያ ይሔ ምንድን ነው አልኳችው።ሚስጥሩ ወዲህ ነው ።አንበሳው ሞአንበሳ ዘእመነገደ ይሁዳ ተብሎ ለርጂም ዘመናት በሀገራችን የሰፈነው ዘውዳዊው አገዛዝ ነው። እርሱ በጂቡ በደረግ በ1974 EC  ተበላ። ቀጥሎ እነዚህ የምታያችው ገዥዎች እንድተኩላ በየገደላገደሉ  ተሺሎክልከው ለነጻነት ታግለው  ጂቡን በሉት። ነገር ግን አላማቸውን የዘነጉ መርዛማ ፍሬ ያላቸው ቡድንተኞች ስለሆኑ  በጉንዳን በተመሰለው በሰፊው ህዝብ የብረት ክንድ ይደመሰሳሉ አሉኚ። በዎቅቱ እንደተረት መጽሃፍ ቆጥሬው የነበረ ሲሆን ባመቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ መንግስት ሲገጥመው ርሳቸው የንገሩኚን አስታውሸ ኢሃዴግ ኣበቃለት ብየ ነበር፥፥

ነገር ግን ዛሬ መንግስት ፩፪ ኣመት ሁኖታል፥፥ርሳቸው መጽሀፉ ውስጥ ሌሎች ማብራሪያዎችን ዕያነበቡ ስለመንግስቱ ባሀሪ ነገሩኝ፥፥ ህዝቡ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ ደም የሚመጥ ስርኣት ስለሚሆን ሲነቀልም ያደማል ብለውኚ ነበር ::አዎዳደቁ ድንገተኛ ነው:: ልክ ከባህር የዎጣ አውሎ ንፋስ ቤት ና ዛፍ  ዕንደሚገነጣጥለው ህዝብ የስርአቱን መሰረት ያፈራርሰዋል  ይጥለዋል አሉኝ:: መቼ እንደሚሆን አብረን እናያለን::

ቅኝ ተገዥነቱን ያወቀ ሕዝብ  በከፊል ነፃ ነው! –ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት            

$
0
0

 ሐሙስ ነሐሴ ፭ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፩

Moresh-901.jpgየኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ ከሆነ ድፍን 25 ዓመት ሆነው። በእነዚህ ረጅም ዓመታት፣ የተማሩትም ሆነ ያልተማሩት ዜጎች፣ በቅኝ ተገዥነት መያዛቸውን ያወቁትም ሆነ ለማወቅ የጣሩት በጣም ጥቂቶች ናቸው። እነዚህ በቅኝ ተገዥነት ተይዘናል ያሉት የጥቂቶቹ ድምፅ፣ በብዙኃኑ፣ ከሁሉም በላይ በጎሣ ፖለቲከኞቹ ድምፅ ተውጦ፣ ወያኔ፣ ያላንዳች ሀግ ባይ፣ ሩብ ምዕተ ዓመታት  የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት በእጅጉ የጎዱ ሥራዎችን እንዲሠራ ሠፊ ዕድል ሰጠው። በመሆኑም የኢትዮጵያዊነት አያያዥ ማገርና ወራጅ፣ መሠረትና ጭምጭም የነበሩትን፣ የኢትዮጵያዊነት ዕሴቶቻችን ከሥራቸው ነቀላቸው። ሕዝቡን በነገድ ከፋፍሎ እሣትና ጭድ አደረጋቸው። የኢትዮጵያ ነገዶች ሙጫ በመሆን ከሌሎች ነገዶችና ጎሣዎች ጋር ሰምና ፈትል ሆኖ፣ ኢትዮጵያዊነትን ሲገነባ የኖረውን የዐማራ ነገድ፣ በዘር ጠላትነት ፈርጆ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፈጸመበት። አምስት ሚሊዮን ዐማራ ከምድረ ኢትዮጵያ እንዲጠፋ ተደረገ። በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በከፋ፣ በሐረርጌ፣ በጎጃምና በጎንደር ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች በግፍ ሀብት ንብረታቸውን ነጥቀው ለርሃብ፣ ለድህነትና ለአገር አልባነት አሳልፎ ሰጣቸው። ይህ ዓለም በዝምታ እየተመለከተው ያለው የዘር ጥቃት፣ ዛሬ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ዐማሮች የቅኝ አገዛዙን ሰንሰለት በጣጥሰው፣ ፍፁም ነፃ የሆነ ዐማራዊ ማንነታቸውን አረጋግጠው፣ የኢትዮጵያን ትንሣዔ ለማብሰር ከአፋኙ የወያኔ የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ጋር የሞት ሽረት ትግል እያደረጉ ይገኛሉ።

የዐማራው ነገድ ዛሬ በትግሬ ወያኔ ቅኝ ተገዥ መሆኑን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቆርጦ የሕይዎት መስዋዕትነት እየከፈለ ነው። በዚህ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ፣ እስካሁን በጎንደር ከተማ፣ አዘዞ፣ ቆላድባ፣ አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ወልቃይት፣ ጋይንት፣ ደብረታቦር፣ ባሕር ዳር ወዘተርፈ ቁጥራቸው ገና በውል ያላወቅናቸው አያሌ ወንድምና እህቶቻችን ባልሞ ተኳሾች የጥይት አረር ወድቀዋል። በርካቶቹ በወያኔ እስር ቤቶች የመከራን ጽዋ እየተቀበሉ ነው። ዐማራውን ለዚህ ግፍ ያበቁት በወያኔ የመከላከያ፣ የፖሊስና የፀጥታ ሠራቶች የተቀጠሩ ብቻ ሳይሆኑ፣ ከሕዝቡ ጋር የሚኖሩት በየኮንዶሚኒየሙ በሰፈራነት የተሰገሰጉት ትግሬዎች መሆናቸውን ስንገነዘብ፣ «ለካ እስከ ዛሬ በጉርብትናም ሆነ በጋብቻ ከእነዚህ ሰዎች ጋር የፈጠርነው ግንኙነት፣ እኛን ለማጥቂያ ውስጣችንን ገልጠው እንዲያዩን ሁኔታዎችን ያመቻቸ ነው፤» ብለን እንድናስብ አስገድደውናል።

ባሕር ዳር እና ጎንደር በጥይት ለተቀጠፉት ሰዎች ገዳዮቹና አስገዳዮቹ በከተሞቹ ነዋሪ የሆኑት የወያኔ የውስጥ አርበኛ ትግሬዎች መሆናቸውን በተጨባጭ አረጋግጠናል። ይህም «ወያኔን እና ትግሬን ለዩ» ለሚሉ የዋሕ ፖለቲከኞችና የሰብአዊ መብት ጠበቆች ነን ለሚሉ ሁሉ የሚያራምዱት ሀሳብ መሠረት የሌለው መሆኑን አሳይቷል። ሕዝብን በሙሉ የክፋት ሥራ ተጠያቂ ማድረግ ተገቢ አይደለም የሚባለው፣ ሕዝቡ የጥፋት ተባባሪ አይደለም ከሚል መነሻ ሳይሆን፣ ሕዝብን በሕዝብነቱ መወንጀልም ሆነ ለጥፋቱ ተጠያቂ ማድረግ ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሔ አያስገኝም ከሚል መነሻ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ዛሬ የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ መሆኑ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ሌላውን ቁሣዊና ለወዲፊቷ ትግራይ ልማትና ዕድገት የተሠሩትን መጠነ ሠፊ ሥራዎች ትተን፣ በአገዛዙ ባለሥልጣኖች እንደ ዐማራውና ኦሮሞው አይጠረጠሩም፣ አይፈተሹም፣ በሥራቸው የመረጃ ታኮ አይለጠፍባቸውም፣ የመሥራትና የመንቀሳቀስ መብታቸው የተገደበ አይደለም፤ የፈለጉትን  ሠርተውና ተናግረው በሰላም ተኝተው ያድራሉ። ይህ ጥቅም አይደለም የሚል ካለ፣ ይህን መብት ያጡት የዐማራ ልጆች ጥቅሙ ከቁሣዊ አልፎ የኅልውና እና የነፃነት ዋጋ ያለው መሆኑን እየከፈሉት ባለው የደምና የሕይዎት ዋጋ ሊማር ይገባዋል።

ከሁሉም በላይ፣ የትግራይ ሕዝብ፣ ልጆቹ የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪዎች መሆናቸውን ስለሚያውቅ፣ በልጆቹ ድርጊት ይመካል። ከመመካትም አልፎ እየኮራ ሌሎችን ሲያዋርድ እያየን ነው። ይህም ለአጉል ትዕቢት ዳርጎት ሌሎችን «ሽንታም፣ ፈሪ» በማለት  በየምርመራ ጣቢያውና በየፓልቶክ ክፍሉ የምንሰማው የዕለት ተዕለት ስድባቸው ነው። ይህ ድርጊት የሌሎችን ነገድ ልጆች አዕምሮ አያነቁርም፣ ደም አያፈላም፣ አያስቆጭም የሚል ካለ «ግሞ ሲሉህ፣ ጥንቦ በለው» ተብሎ ያላደገ የማንነት መገለጫ ዕሴት የሌለው፣ የተዋራጅ ሕዝብ ባህል ብቻ ነው። በመሆኑ፣ ከ25 ዓመታት ትዕግሥትና የአብሮነት ፍላጎት በመነጨ፣ ዐማራው ወያኔ የጣለበትን ዕዳ፣ ያሸከመውን የመከራ ቀንበር ተሸክሞ መቆየቱ ግልጽ ነው።

የዐማራው ሕዝብ ዛሬ ግን ከመከራ አልፎ፣ ማንነቱን በመነጠቁ «አሻፈረኝ፣ መከራው በዛብኝ፣ ሸክሙ ከምችለው በላይ ሆነብኝ፣ ግፉ ከአናት በላይ ወጣ፣» ብሎ ማንነቱን ለማስከበርና ነፃነቱን ሙሉ በሙሉ ለማስመለስ ከአፋኙ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ሠራዊት ፊት ለፊት በባዶ እጁ እየተጋፈጠ ይገኛል። ይህም ዐማራው በቅኝ ቅዛት መያዙን ከማወቅ አልፎ፣ ለነፃነቱ ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ የደረሰ መሆኑን ያሳያል። ካልቆረጡ ከግብ አይደረስምና! በዚህ ረገድ የቁርጠኝነቱን ጉዞ፤ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በከፈተው የጀግንነት ድርጊት፣ ለዐማራው ወጣት አርአያነቱን አሳይቷል። ዐማራው ማንነቱን አስጠብቆ የኢትዮጵያ ትንሣዔ አብሳሪ የሚሆነውም በዚህ መንገድ ብቻ መሆኑን የትግሬ-ወያኔ ባሕሪ አስተምሮናል። ስለዚህ ትግሉ፣ መስዋዕትነትን ቀንሶ፣ ባጭር ጊዜ ውስጥ የድሉ ባለቤት የሚሆንበትን መንገድ መከተል ብልኅነት ብቻ ሳይሆን፣ አዋቂነትም ነው።

ለዚህም የሚረዳው፣ በየቀበሌውና ወረዳው የጎበዝ አለቆችን በመምረጥ የተደራጁ ቡድኖችን መፍጠር ሲቻለው ነው። በየደረጃው የተመረጡ የጎበዝ አለቆች በተመሳሳይ መልክ ከሚደራጁ አቻዎቻቸው ጋር ተያያዥና ተጋጋዥ የሆኑ ሥራዎችን ለመሥራት ሁኔታዎች በፈቀዱት መጠን የግንኙነት ሰንሰለት መፍጠር እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚም ነው። ይህ ግንኙነት በአስተማማኝ ሁኔታ ከተመሠረተ በኋላ፣ የወያኔን የስለላና የአፈና መዋቅር ኃይል ለማሳሳት፣ የገንዘብ አቅሙን ለማዳከም፣ በተለያዩ ቦታዎች የሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንቅስቃሴን፥ ሰልፍና የመሳሰሉን፣ ማካሄድ። ለትግሬ-ወያኔ አፋኝ ኃይል፣ የኃይል ምንጭ፣ የሥንቅና የትጥቅ አቅርቦት ክምችት ያለባቸውን ቦታዎች በማጥናት ድንገተኛ ወረራ በማድረግ የሕዝብ ማድረግ የግድ ይላል። ይህ ሁሉ ሲሆን፣ አመራሩ ከውስጥ ከሕዝቡ መሀል ያሉ፣ የንቅናቄው ተሳታፊዎች አምነው የመረጧቸውን እንጂ፣ ከርቀት «መንፈስ ነን» የሚሉ የአየር በአየር የፖለቲካ ሰዎች ነን ከሚሉት ጋር እንቅስቃሴው እንዳይያያዝ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። «የአህያ ባል ከጅብ አያድንም» እና በዚህ ረገድ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። ወያኔ እንኳን ሰበብ አገኝቶ፣ ራሱ ወንጀል ፈብርኮ፣ ሰዎችን ማሰር መግደሉ ይታወቃልና፣ ከውጭ ሆነው የሚፎክሩ ድርጅቶች፣ ለሕዝቡ መመቻ፣ መረጃ እየሰጡ ናቸውና በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ባለቤቱ ዐማራው ራሱ እንጂ፣ ሌሎች አለመሆናቸውን በግልጽ ሊያውቁት ይገባል።

በመሆኑም የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ የመላው ዐማራ ጥያቄ በመሆኑ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ፣ የሸዋ፣ የሐረርጌ፣ የአዲስ አበባ፣ የወለጋ፣ የአርሲ፣ የከፋ፣ የጋሞጎፋ፣ የሲዳሞ፣ የባሌ እንዲሁም በዓለም ላይ በስደት የሚኖረው ዐማራ የትግሉ አካል እንዲሆን፣ የንቅናቄው አስኳል የሆነው የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ የመሪነቱን ቦታ በመያዝ፣ ሕዝቡን መድረስ ይጠበቅበታል። ከሁሉም በላይ የእንቅስቃሴው ባለቤቶች «እኛ ነን፣ እኔ ነኝ» ለሚሉ ወገኖች አቅማቸውንና ቁርጣቸውን እንዲያውቁ፣ የንቅናቄውን ዕለታዊና ሳምንታዊ ዘገባዎች ለዓለም ማኅበረሰብ የሚሰማ፣ ሕዝቡ የሚፈልገውን ርዳታ ተቀብሎ በትግሉ ውስጥ ላሉት አመራሮች ማስረክብ የሚችል ታማኝ ግለሰብ ወይም ቡድን ካለ እርሱን፣ ከሌለ በፍጥነት ተሰይሞ፣ ሕዝቡ እንዲያውቀው ቢደረግ ውንዥንብሩን ያጠራዋል፤ የሰከነ ሥራም ለመሥራት ያስችላል ብለን እናምናለን።

ሌለው፣ ንቅናቄው ሊመራባቸው የሚገቡ ቋሚ መፈክሮች ያሹታል። መፍክሮቹን ማንም እንደፈለገ እንዳይለጥጣቸው ከወልቃይት ጠገዴና ከዐማራ ማንነት ጋር የተያያዙ፣ ይህንም ባጭሩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ሊዘጋጁ ይገባል እንላለን። ይህ ሲሆን ጎንደር ላይ የተቀጣጠለው የዐማራ የማንነት ጥያቄ፣ ቅኝ ገዥውን ቡድን ድባቅ መትቶ፣ ዐማራው ማንነቱናና ኅልውናውን አስጠብቆ፣ የኢትዮጵያን ነፃነት ዕውን ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅዖ ያደርጋል ብለን እናምናለን። በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ የዕውቀትም ሆነ የሀብት ባለቤቶች እነርሱ መሆናቸው ስለሚታወቅ፣ በዚህ ነፃነት ከማንም ይልቅ ተጠቃሚዎቹ ትግሬዎች ይሆናሉ። ስለዚህ በነገይቱ ኢትዮጵያ ትግሬዎች ያላቸውን ዕውቀትና ሀብት በሥራ ላይ አውለው በነፃነት ለመጠቀም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ነፃ መውጣቱ ፍቱን አብነት ነው። ለዚህም ከጠፊው የወያኔ ቡድን ጋር ሳይሆን፣ ከዘላለማዊው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና ከታሪክ ጋር መቆም ይጠበቅባችኋል።

ወያኔ ለትግሬም ሆነ ለኢትዮጵያ አጥፊ እንጂ፣ አልሚ አይደለም። የትግራይ ተወላጆች፣ በጊዜአዊ ሥልጣንና ጥቅም ተገብዛችሁ ሊሆን ይችላል፤ ይህ ግን ዘላቂ አይደለም። ከዘላቂ ጥቅም፣ ክብር፣ ማንነትና ከሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንድትቆሙ ጥሪያችን እናቀርባለን።

 

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የዐማራነት ማንነት በትግላችን ያብባል!

ዐማራነት ነፃነትና ዕኩልነት ነው!                                        

ዐማራነት ፍትሕና ኢትዮጵያያዊነት፣ ጀግንነትና መስዋዕትነት ነው!

ጤና ካልሰጠ አይደለም ጣት እጅም ሆነ እግር ከመባቀያው ላይ ተቆርጦ ሊጣል ይችላል:: (ከይገርማል)

$
0
0

Oromo amhara unityከወያኔ በፊት በነበሩት ጊዜያት ፖሊስ በሰወች መሀከል ምንም ልዩነት ሳያደርግ የመንግስትን ትእዛዝ ለማስፈጸም ይንቀሳቀስ ስለነበር “የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም” ይባል ነበር:: ይህ የሚያሳየን ፖሊስ “እናት; አባት: እህት: ወንድም: ልጅ: – – -ሳይል በህግ የሚፈለጉትን ለህግ በማቅረብ ለየትኛውም ወገን ህገወጥ ከለላ ሳይሰጥ ሁሉንም ህዝብ በእኩል አይን አይቶ ግዳጁን ይፈጽም ስለነበረ ነው:: በዚህም ምክንያት ፖሊሱ ልጀ: ወንድሜ: አጎቴ – – – ያድነኛል የማይባልበት ጊዜ ስለነበር “የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም” ይባል ነበር::

 

የዛሬው አባባል ግን ተቀይሯል:: አሁን ላይ እያየነው ያለነው የፖሊስ ዘመድ: የፖሊስ ወዳጅ መኖሩን ነው:: ለዚህም ዋናው ምክንያት የወያኔው መንግስት ዘረኛ አስተዳደር የፈጠረው የገዥ ብሄርና የተገዥ ብሄሮች መከሰት ነው:: በአሁኑ ወቅት ያለው ተጨባጭ እውነታ የሚያሳየው ተጠቃሚ የትግሬ ብሄርና ተጎጅ የአማራ: የኦሮሞ: የጋንቤላ: የደቡብ: – – – ብሄር ብሄረሰቦች መኖራቸውን ነው:: በዚህም የተነሳ ትግሬ የተባለ ሁሉ ጥቅሜን እያስከበረልኝ ነው የሚለውን ዘረኛ መንግስት በብቸኝነት ደግፎ በጽናት ቆሟል:: ይህን አጉራ-ዘለል የትግሬ ወያኔ ተግባር ያየ የአማራ ፖሊስና ታጣቂ ሀይል በበኩሉ ወገኑን ከጥቃት ለመከላከል ጠበንጃውን ወደወያኔ አዙሮ ወድሯል::

 

አማራው ወገኖቸ ናቸው ብሎ ባጎረሳቸው: ባለበሳቸው: መኖሪያውን አጣቦ መጠጊያ በሆናቸው: ቁስላቸውን ባከማቸውና እንባቸውን በጠረገላቸው ትግሬወች ያጎረሰበት እጁ ተነክሶ: መሬቱን ተነጥቆ: ከለበሳት ጨርቅ ውጭ አንድም ነገር ሳያንጠለጥል ተሳዶ: በየአካባቢው ታርዶ በደምና በእንባ እንዲታጠብ ተደርጓል:: የአማራን ህዝብ አፍነው መሬቱን እንደያዙ ለማስቀረት “በወልቃይት የመጣ በአይናችን የመጣ ነው:: አማሮች አርፋችሁ ተቀመጡ: አለዚያ ዋ!” ብለው አሮጊቶች ሳይቀሩ ጠበንጃ ይዘው በሰልፍ ሲያስፈራሩ ታይተዋል:: በየክልሎች የሚኖሩ ትግሬወች በወያኔ አስተዳደር ላይ ልቡ የሸፈተውን ብቻ ሳይሆን ቀልባቸው ያልወደደውን ጭምር እየጠቆሙ ለሞትና ለእስር ዳርገውታል: በውጭ ሀገር የሚኖሩት ትግሬወች ተሰባስበው ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ግድያና እስር ተደስተው እያሞገሱ ጨፍረዋል – በስለላ: በሀሳብ: በገንዘብና በቁሳቁስ ደግፈው ቆመዋል:: ታዲያ ይህንን ጉደኛ አስተዳደር ለመደገፍ የወያነን ትእዛዝ ተቀብሎ በወገኖቹ ላይ የሚተኩስ ፖሊስ ይኖራል? ለዚህም ነው “የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም” የሚለው “የትግሬ ዘመድ ትግሬ: የወያኔ ገረድ …ዴንና …”ዴድ”” መባል ያለበት::

 

በብአዴን ውስጥ ያላችሁ ወያኔ ጠል: አማራ ወዳድ የሆናችሁ ሰዎች የህዝብን ትግል አኮላሽተው የወያኔን ግፈኛ ስርአት ለማስቀጠል እየሰሩ ያሉትን አባላት በቁጥጥር ስር አውላችሁ ለዞንና ለወረዳወች የተጠንቀቅ መመሪያ አስተላልፉ:: ይህን ለማድረግ ስልጣናችሁን ተጠቅማችሁ የራሳችሁ ታማኝ ፖሊስ ወይም ታጣቂ ሀይል በማሰማራት የወያኔ ሰላዮችንና እምነት የማይጣልባቸውን ሰዎች ትጥቅ አስፈትቶ በቁጥጥር ስር በማዋል መሆን አለበት:: ይህ እርምጃ በያንዳንዱ ዞንና ወረዳ እንዲተገበር መመሪያ ማስተላለፍ ይኖርባችኋል::

 

በአማራ ክልል የሚኖሩትን ትግሬወች አሰባስባችሁ በየካምፖች እንዲጠበቁ አድርጉ:: ይህን ማድረጋችሁ ሁለት ጥቅም ይኖረዋል:: አንደኛው ወያኔ በየአካባቢው የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንዳያውቅ የመረጃ ምንጩን ማድረቅ ማስቻሉ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጥቃት ስሜት እየተብከነከነ ያለው አማራ በትግሬወች ላይ እርምጃ እንዳይወስድ ለመከላከል ስለሚበጅ ነው::

ሲፈጥረኝ አሳቢ ለምን አልጨነቅ ማስተዋል ላቃተው የኔቢጤ ገልቱ:

እንዳያር እንዳይከስል ባላዋቂ ቆስቋሽ ማሰብ በተሳነው-

እንደገና ዳቦ በታች በላይ እሳት በመሀል ግለቱ::

 

በአማራ ክልል የሚገኙትን የወያኔ ሰራዊትና ፖሊስ አባላት ትጥቅ ማስፈታት የሚከብድ አይሆንም: በውቅያኖስ ውስጥ ያረፈ ጠብታ መርዝ አንድም አሳ ሊገድል አቅሙ አይኖረውም:: እንዲያውም ወያኔን እያጫወቱ ወደመሀል አማራ በመሳብ ትጥቅ ማስፈታቱን መልመድ ይጠቅማችኋል:: በትግራይ – ሽሬ መሽጎ የነበረው የደርግ ሰራዊት የተመታው በወያኔ ሀይል ብቻ ሳይሆን በህዝቡም ርብርብ ነበር:: እናንተ “በአማራው ላይ እየደረሰ ያለው ዘርፈ-ብዙ ግፍ ያብቃ!” ብላችሁ ስትፈክሩ የሰማ አማራ ብቻ ሳይሆን ዋልያና ቀይ ቀበሮም በደስታ ይቦርቃሉ:: ልብ በሉ! በታሪክ ከትግራይ ያገኘነው አንድም ጥሩ ነገር የለም:: ያገኘነው ነገር ቢኖር ዘረኝነትንና ክፍፍልን: ተንኮልንና ውሸትን: ረሀብንና ኤድስን: አድርባይነትንና መሸማቀቅን ነው:: አዎ በሽታውም የመጣው በወያኔ ግዜ: ረሀቡ የጸናብን በወያኔ ጊዜ: ባህልና ታሪካችን የረከሰ በወያኔ ጊዜ: ለዘር ተኮር ግድያና ስደት የተዳረግነው በወያኔ ጊዜ ነው::

 

ፍልፈሉ ሳሞራ የኑስ እንደነገሩን “ወያኔ ማለት ትግሬ: ትግሬ ማለት ደግሞ ወያኔ ማለት ነው”::  መጀመሪያ ስልጣን ሳይዙ ከበረሀ ሆነው የሚያስተላልፉትን ቅስቀሳ ሰምተን ቢሆን ኖሮ ለዚህ ሁሉ ብሄራዊ ኪሳራ ባልተዳረግን ነበር:: ያኔ በረሀ እያሉ አማራ ብሄራዊ ጠላታቸው እንደሆነ: መሬት የመንግስት እንደሚሆን: ኢትዮጵያ በብሔረሰቦች እንደምትከፋፈልና መገንጠል የሚፈልግ ብሄር መብቱ በህገመንግስት እንደሚከበርለት ነግረውን ነበር:: አሁንም እየነገሩን ነው “ትግሬ ማለት ወያኔ ነው: ወያኔ ማለትም ትግሬ ነው::  ብለው:: ይህን መስማት አቅቶን “ወያኔንና ትግሬን እንለይ” እያልን የምናዜም ከሆነ ችግሩ የማንም ሳይሆን የራሳችን ይሆናል::

 

ጎጃሞች የተፈጥሮ ምሽጋችሁ የሆነውን አባይ ተጠቀሙበት:: ከጎጃም ወደሌሎች አካባቢወች የሚያስወጡና የሚያስገቡ መተላለፊያወችን ከዘጋችሁ ወያኔ መግቢያ ቀዳዳ አይኖረውም:: በመተከል የምትኖሩ አማሮች ተደራጅታችሁ ራሳችሁን መከላከል ብቻ ሳይሆን ህዝቡን አስተባብራችሁ ከራሳችሁ አልፋችሁ በወያኔ ላይ የሚደረገውን ትግል ለመደገፍ ተንቀሳቀሱ:: ፓዊን ብሎም መተከልን በቁጥጥር ስር ለማዋል ለሆድ ህመም ተብሎ የሚጠጣ የግራዋ ጭማቂን ያህል የሚመር-የሚከብድ አይሆንም::

 

አንድ ማመን ያለብን ነገር አለ: ካለመስዋእትነት ድል እንደማይኖር:: ስለዚህ አካላዊ ብቻ ሳይሆን ዐዕምሯዊ ዝግጅት ሊደረግ ግድ ነው:: አንድ ሰው በሞተ ቁጥር ትግሉ የበለጠ እየከረረና እየሰፋ መሄድ ይኖርበታል:: ከፊት የቆሙትን ወገኖቻችንን አስቀጥፈን የምናፈገፍግ የአንድ ሰሞን የአጓት ጥጋበኞች ልንሆን አይገባም:: ደም የሚከፈለው ለስር-ነቀል ለውጥ እንጅ ለጥገናዊ-ለውጥ መሆን የለበትም:: ይህን ትግል ለማክሸፍ የሚሞክር ዘመድ ቢኖር ከጠላት ጋር ተደርቦ ሊመታ ይገባል:: “ጣት ገማ ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም” የሚባለው ብሂል ጊዜ ያለፈበት ኋላ-ቀር አመለካከት ነው:: ጤና ካልሰጠ አይደለም ጣት እጅም ሆነ እግር ከመባቀያው ላይ ተቆርጦ ሊጣል ይችላል::

 

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

በፍራንክፈርት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ |በኦሮሚያና አማራ ክልል የተደረጉ ግድያዎችን አወገዙ

$
0
0

Screen Shot 2016-08-12 at 8.34.06 AM
(ዘ-ሐበሻ) በፍራንክፈርት ጀርመን የሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሕወሓት እያሰተዳደረ ያለው መንግስት በወንድም እና እህቶቻቸው ላይ እየወሰደው ያለውን ግድያ በማውገዝ ጥያቄዎቻቸው በሰላማዊ መንገድ እንዲመለስ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ገለጹ::

በኦሮሚያ ማስተር ፕላን ሰበብ ድሆችን ማፈናቀሉን እንደሚያወግዙ; የወልቃይት ህዝብ ጥያቄንም እንደሚደግፉ የገለጹት እነዚሁ ሰልፈኞች የጀርመን መንግስት ከዚህ ገዳይ ሥርዓት ጋር እንዳይተባበርና በ እርዳታ ሰበብ የሚገባው ገንዘብ ንጹሃን ዜጎችን መግደያ እንዳይሆን እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል::


የፊታችን እሁድ ነሐሴ 8, 2016 በ22 ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ

$
0
0

welo
(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር፣ በባህርዳር እና በደብረ ታቦር የተደረገው ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን እሁድ ነሐሴ 8, 2016 22 ከተሞች እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ አስታወቁ::

በሽዋ:- ደብረብርሃን፣ ደብረሲና፣ አንኮበር፣ ሸዋሮቢት፣ ሸኖ፣ አዲስ አበባ እንዲሁም በጎጃም: ዳንግላ፣ ደብረማርቆስ፣ ደጀን፣ ኮሶ በር፣ ቡሬ፣ አዴትና ሞጣ: በተጨማሪም በወሎ:- ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ መቄት፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ቆቦ እና አላማጣ አምባገነኑ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያ በመቃወምና የሕዝቡን ጥያቄዎች በመደገፍ የፊታችን እሁድ ነሐሴ 8, 2016 ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ::

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞችም እንዲሁ ተመሳሳይ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ እየተባለ ነው::

እየተበተነ ያለውን ፍላየር ይመልከቱ::

የኦሮሞና አማራ በአንድነት መቆም የሕወሓት ተገንጣይ ቡድን ቃል አቀባይን አቃጥሏቸዋል | Video

$
0
0

“እንዴት ጠቅላይ አንድነት የሆነው ትምክህተኛው አማራ እና ልገንጠል ባይ ጠባቡ ኦሮሞ ይተባበራል?!የሥርዓቱን በሚገባ ሥራ መስራት አለመቻል ነው፤ የነዛን መጠንከር አይደለም የሚያሳየው ” አሉ የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ:: የአማራና ኦሮሞን አንድነት ላለፉት 25 ዓመታት ሳይፈልገው የቆየው ይኸው ስርዓት የሁለቱ ታላላቅ ብሔሮች በአንድነት መቆም ምን ያህል እንዳስበረገገውና ለማጣላት የሰሩት ሴራ እንዳልሰራ በግልጽ ይናገራል:: ያድምጡት::

የኦሮሞና አማራ በአንድነት መቆም የሕወሓት ተገንጣይ ቡድን ቃል አቀባይን አቃጥሏቸዋል | Video

ከወያኔ ለመገላገልም  ሆነ ለመደራደር- መተባበርና መጠናከር –ይገረም አለሙ

$
0
0

Unity-1-741x437የዶ/ር መረራ ጉዲናን አባባል ልዋስና “በቅድሚያ ሁለት ነገር ልበል”፡፡ የወልቃይት ጠገዴ ኮሚቴ አባላትን ኮሽታ ሳያሰማ ከጎንደር አፍኖ ለመውሰድ ያደረገው ሙከራ ያልተሳካላት ወያኔ  የህዝብ ጥያቄ በወኪል አይቀርብም፣ ጥያቄ ካለው ራሱ ህዝቡ ያቀርባል አለን፣ ሰማን፡፡ አረ አንዴት ሆኖ ? ብለን ታዝበን፣ ወይነው ደደቢት ሲገቡ ትግራውያንን እንወክላለን ማለታቸውንስ አንደምን ዘነጉት ብለን ጠይቀን ውለን ሳናድር በጎንደርና በጎጃም   ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ   ጥያቄውን ሲያቀርብና በቃችሁን ብሎ ሲነግራቸው ደግሞ  ባለቤት የሌለው ሰልፍ አሉ፡፡  ሀራምባና ቆቦ፡፡

ሁለተኛው  ዶር መረራ አሜሪካ በተደረገ ሰብሰባ ላይ የተናገሩት ነው፡፡ ድርጅታቸው በምርጫ 2002  ለመሳተፍ ከበቃባቸው ምክንያች አንዱ  ወያኔ ለተቀዋሚዎች  የተወሰነ ወንበር ሊሰጥ ይችላል ይባል ስለነበር ትንሽ ፍርፋሪ ብናገኝ በማለት አንደነበር  እውነቱን አፈረጡት፡፡ ሌሎቹ አንደርሳቸው ደፍረው አይናገሩት አንጂ አምስት አመት እየጠበቁ በምርጫ የሚሳተፉት ፖለቲከኞች ዋንኛው ዓላማቸው ፍርፋሪ ወንበር አግኝተው በተለይ ራሳቸውን ፓርላማ ማስገባት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ምርጫ 97ትን ያየ በምርጫ አይቀልድም ያለው ወያኔ ፍርፋሪ የሚያቀምስ አልሆነም አንጂ፡፡

ሰሞነኛው የድርድር ወሬ፤

ድርድር የሚባለው ነገር ሰሞኑን በየቦታው እየተነሳ ነው፡፡ ጉዳዩ በዚህ ወቅት እንዲነሳ ያስቻለው ሁለት ምክንያት ይመስለኛል፣ አንደኛው የገዢዎችን ገዳይ ሰራዊት እያሰለጠኑ፣ ገንዘብ እየረዱ የባለሥልጣኖችን ጡንቻ እያፈረጥሙ ህዝብ የሚያስገድሉ የሚያስገዙ ሀያላን የሚባሉት መንግሥታት የሚተማመኑበት ኃይል መንገዳገዱ ሲታያቸው ሁሉንም ወገን በማግባባትም በማስገደድም እናደራድር ማለታቸው፤ ሁለተኛው ደግሞ ወያኔ በጨነቀው ግዜ ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻና  ለወንዝ መሻጋሪያ የሚጠቀምበት መሆኑ፤ ከቀደመ ታሪካቸው መታወቁ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በምርጫ 97 ማግስት ቅንጅትና ህብረት በጋራ የጠሩትን የቤት መዋል አድማ ለማስቀረት በዲፕሎማቶች አደራዳሪነት (በአሜሪካ ኤንባሲ ጉዳይ አስፈጻሚ ዋና ተዋናይነት) ከጸሀይ በታች በማናቸውም ጉዳይ እንደራደራለን ብሎ አድማውን ያሰረዘው ወያኔ የፈጸመው ክህደት የቅርብ ግዜ ማስረጃ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ በመሆኑም  አይሆንም ብሎ ከመዘናጋት ሊሆን የችላል ብሎ መዘጋጀት ተገቢ ነውና ነው የጉዳዩ መነሳት ወቅታዊም ተገቢም ይመስለኛል፡፡

ሕዝብ በደሙ ባቀለመው ትግል ማነው የሚደራደረው?

ኢትዮጵያውያን የወያኔን አገዛዝ  ለሀያ አምስት ኣመት ቻሉ፡፡ ጩኸታቸው የቁራ ሆኖ፣ ትእግስታቸው በፍርሀት ተቆጥሮ ወያኔዎች ከመታረም ይልቅ በንቀታቸው ገፉበት፤ ሁሉን ነገር በጠመንጃችው መከወን አንደሚችሉ በመተማመን ማሰሩን፣ መግደሉን፣ ማሰቃየቱን  ዋና ስራቸው አደረጉት፡፡ ለህዝብ ጥያቄ ምላሻቸው አሸባሪ ሆነ፡፡ የእነርሱ ጣት የሚስበውን ቃታ የሌላው ኢትዮጵያዊ ጣት መሳብ የማይችል እስኪመስላቸው ድረስ በጠብ-መንጃቸው ተማመኑ፡፡

በተቃራኒው ተቀዋሚ ብለው ለራሳቸው ስም ሰጥተው፣ እዛና እዚህ የየራሳቸውን ጎጆ ቀልሰው፣ አለን የሚሉ ፖለቲከኞች በህዝብ ስም ለራሳቸው ስልጣን፣ በዴሞክራሲ ስም ለየግል ጥቅማቸው የሚጥሩ ሆኑ፡፡ ይህም ሆኖ ህዝቡ ከዛሬ ነገ ይማራሉ በሚል  ምረጠን ሲሉት መርጦ፤ ሰልፍ ሲጠሩት አደባባይ ወጥቶ፣ በገንዘቡም በቁሳቁሰም በሚችለው እየደገፈ ለውጤት አንዲያበቁት ጣረ፡፡ የግል ጉዳያችሁን በየጓዳችሁ አስቀምጡና በጋራ ጉዳይ ተነጋገሩ፣ እማማ ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ለማላቀቅና ህዝቡን የሥልጣኑ ባለቤት ለመድረግ ተባበሩ እያለም ጠየቀ፡፡ ፖለቲከኞቹ ግን “አድሮ ቃሪያ”  ከመሆን አላላፉም፡፡ እናም  አበው ማርም ሲበዛ ይመራል አንደሚሉት በቅዱስ መጽኃፍም ለሁሉም ግዜ አለው ተብሉ እንደተጻፈው ህዝቡ ተቀዋሚዎቹን ማስታመሙ የወያኔንም አገዛዝ መሸከሙ  በቃኝ አለና ጠሪም መሪም ሳይሻ ርስ በርስ ተጠራርቶ፣ እያንዳንዱ ራሱን በራሱ መርቶ  አደባባይ ወጥቶ ከመትረየስ ጋር ተፋጠጠ፡፡ እኛም ቤት ጠመንጃ እኛም ልብ ውስጥ ወኔ አለ ብሎም መግደል ለለመዱት ሞትም እንዳለ አሳያቸው፡፡

ከዚህ በኋላ የድርድር ነገር ቢነሳ ለጥያቄው መነሳት ምክንያቱ የህዝቡ ትግል ነውና በህዝብ ደም ላይ ቆሞ የሚደራደረው ማነው? ሊታሰብበት ብቻ ሳይሆን በቶሎ መልስ ሊፈለግለት የሚገባ ጥያቄ ይመስለኛል፡፡ወያኔ አንድም ለምርጫ አጃቢነት ሁለትም ለመድብለ ፓርቲ ማሳያነት ሶስትም ለትኩሳት ማብረጃነት የሚጠቀምባቸው  በምርጫ ቦርድ መዝገብ ላይ ብቻ የሚታወቁ ብዙ ፓርቲ ተብየዎች አሉ፡፡ ዶ/ር መረራ ፍርጥ አድርገው እንደነገሩን የፓርላማ ወንበር ፍርፋሪ ለማግኘት የተቀመጡ ፓርቲዎችም አሉ፡፡ በውጪ ደግሞ  የህዝብ እንቅስቃሴ ሲታይ ብቅ እያሉ መግለጫ ከመስጠት ያለፈ ተግባር የማናይባቸው ፓርቲም ህዝባዊ ድርጅትም የሚባሉ አሉ፡፡ ከእነዚህ  አንዳንዶቹ ህዝቡ ራሱን በራሱ አነሳስቶ ባካሄደው ትግልና በደም ባቀለመው ተጋድሎ  የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ደፋ ቀና ሲሉ አይተንና ሰምተን ታዝበናል፡፡ወያኔ የሚገባው በሚያውቀው ቋንቋ ሲያነጋግሩት ነው ብለው ይህንኑም በተግባር እያሳዩ ያሉ ድርጅቶም አሉ፡፡

ታዲያ! ሀያላኑ በወያኔ ላይ ያላቸው መተማመን ተሸርሽሮ፣ ወያኔም ብተኩሱ እንተኩሳለን ከሚለው መልእክትና ለግድያ የላካቸው  ከሞቱበት ዘመቻ በጠመንጃ የትም እንደማይደርስ “ተምሮ” ሁለቱም ለጥገናዊ ለውጥ ተስማምተው ድርድር ቢሉ ለዚህ ውጤት መገኘት መስዋዕትነት የከፈለውንና አሁንም እየከፈለ ያለውን ህዝብ ወክሎ የመደራደር ብቃትም፣ ሞራልም፣ ተአማኒነትም ወዘተ የሚኖረው ማነው? ወይም የትኞቹ ናቸው? ወይንስ “የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ ” በሚባለው የአፍ ፈሊጥ ሁሉም? ይህ እየሞተ እየደማ እየታሰረና እየተሰቃየ ያለ ህዝብ መቼም እነ እገሌ ይወክሉኝ ይደራደሩልኝ ሊል አይችልም፣ እንዴት ሆኖ፡፡  እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ማሰብና ራስን ለቤተ መንግስት ለማብቃት ሳይሆን ሀገሪቱን ዴሞክራሲያዊት ለማድረግ ከምር የሚታገሉ ኃይሎች መሰባሰብ መነጋገር ማቀድ ቀድሞ መዘጋጀት የሚገባቸው፡፡

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ፣. ለመሆኑ  ፖለቲከኞቻችን ፣ምሁራኖቻችን ከምር ለለውጥ እንዲነሱ  የስንት ሰው ህይወት መጥፋት አለበት? በአንድ ጀንበር ከመቶ ያለነሱ ዜጎች መገደል የግል አጀንዳውን በየኪሱ አስቀምጦ ከገዳዩ አገዛዝ ሕዝብን ለመገላገልም ሆነ ለድርድር ለማንበርከክ  በቁርጠኝነት አንዲነሳ ያላደረገው ፖለቲከኛም ሆነ ምሁር ስለ ወያኔ ገዳይነት ለመደስኮር ምን የሞራል ብቃት ይኖረዋል?  በዚህ ውቅት አርበኞች ግንቦት 7 እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ጥምረት የመፍጠራቸው ዜና አስደሳችና ወቅታዊ ነው፡፡ አለመታደል ሆኖ አርአያነቱን ከመከተልና ከሚመስሉትና ከሚመስላቸው ጋር ከመተባበር ለተቃውሞ የሚጣደፉና እንከን ለማውጣት የሚሯሯጡ አንደማያጠፉ ይገመታል፡፡

ሀያላኑ በሚያውቁበት ጥቅማቸውን የማስጠበቅ ስልት፣ ወያኔም በተካነበት  እንደ ሰንቤሌጡ አጎንብሶ  ወጀቡን የማሳለፍ ብልጠት ተስማምተው የድርድር ነገር ቢነሳ ቀድሞ የሚጠሩትና ተሸቀዳድመው የሚገኙት የወያኔ መጠባበቂያዎቹ ናቸው፤ከዛ የወንበር ፍርፋሪ ለማግኘት የሚታገሉት፡፡ እነዚህ የወያኔን ህልውና ለመታደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመስማማት የሚገዳቸው አይደሉም፡፡መሰረታዊ የለውጥ ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች ከእነዚህ ጋር ተዳብለው ለድርድር ቢቀርቡ ተግዳሮት የሚገጥማቸው ከወያኔ በላይ ከእነዚህ ፓርቲዎች ይሆናል፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አክብረው  የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች በምርጫ የሚያዘውን ሥልጣን በድርድር ስም በአቋራጭ ለማግኘት አልመው ተቀባይነት የማያገኙ ጥያቄዎችን በማንሳት ድርድሩ ለውጤት አንዳይበቃ  እያደረጉ ኃይሎችን  በመቃወም ከዚህ አድራጎታቸው እንዲቆጠቡና ለድርድሩ መሳካት አንዲሰሩ  ጠየቁ የሚል ፕሮፓጋንዳ ልንሰማ አንችላለን፡፡

ለመታገልም ለመደራደርም መጠንከር፣መተባበር፤

በቃኝ ብሎ የመጨረሻው መጀመሪያ የሆነውን ትግል የጀመረው ህዝብ  የሚያካሂደው ትግል  በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ እንዲቀጥል የሚያስችሉ እገዛዎችን ከማድረግ ባሻገር  በግል በመጠናከርና በጋራ ተባብሮ በመስራት በሕዝብ ተቀባይነት ያለው፣ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ   ከወያኔ አንጻር  አማራጭ ተደርጎ የሚታይና ከእርሱ ውጪ ድርድር ውጤት አያመጣም ሊባልለት የሚበቃ ሀይል ሆኖ መውጣት ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሀይል በአንድ በኩል ከህዝቡ ትግል በተጨማሪ ወያኔን ለድርድር ለማንበርከክም ሆነ እምቢ ካለ ለማስወገድ የሚያስችል የተጠናከረ ትግል ማካሄድ፣ ከዚህ ጋር አብሮ በምንም ይሁን በምን ወያኔ ወደ ድርድር ከመጣ በሚል የመደራደሪያ አጀንዳዎችን አስቀድሞ ማዘጋጀትና አይነኬ ቀይ መስመሩን በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡

ይህ ሲሆን ወያኔ ለመጠባበቂያነት ያስቀመጣቸው የግለስብ ፓርቲዎች ቢያንስ በሀያላኑ መንግስታት ዘንድ ለድርድር አይታሰቡም፡፡ ለወንበር ፍርፋሪ የሚታገሉት ደግሞ  ብቻቸውን ለድርድር ለመቅረብም ሆነ  መሰረታዊ የለውጥ አጀንዳ ያላቸውን ለመሞገት የሞራል ብቃት አይኖራቸውም፡፡ የእኛን አድል ፈንታ ሲወስኑልን የኖሩትና አሁንም በዚሁ ለመቀጠል የሚዳዳቸው ሀያላንም አንዳንድ ፕሮፓጋንዳቸው እንጂ ተግባራቸው ጎልቶ የማይታይ ፖለቲከኞችን በጓዳ በር እየጠሩ የሚያካሂዱት ስራም ይሁን ሴራ ውጤት አንደማያመጣላቸው ይገነዘባሉ፡፡

እናም በሀገራችን በአብዛኛው አይሆንም የተባለው  ሲሆን፣  ይሆናል የተባለው ሳይሆን ሲቀር እያየን የመጣን አንደመሆኑ አይሆንም ብሎ ተዘናግቶ አጋጣሚ ቢሆን ሱሪ በአንገት ከመንደፋደፍ በሁሉም ዘርፍ ተዘጋጅቶ መገኘት ጠቃሚ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በየግል መጠናከርና በጋራ  ተባብሮ መቆም በጣም በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡ ትግሉ  ለሥልጣኑ መቀጠል  ሀያ አራት ሰአት ከሚሰራ ሀይል ጋር በመሆኑም ግዜ የለም፡፡አዎ ሕዝቡ ቀድሟል ግዜ የለም ፡፡

እንደው ለመሆኑ ይህ የግፍና የገፍ ግድያ በቁጭት ያላነቃው፣ በምሬት ያላነሳሳውና ያላስተባበረው፣ ከራስ በላይ አንዲያስብም ያላደረገው ወዘተ ፖለቲከኛና ምሁር መቼና ምን ሲሆን ይሆን የሚነሳው ! !

ሪዮ ኦሎምፒክ: ሶፊያ አሰፋ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ለፍጻሜ አለፈች

$
0
0
ጥሩ ደረጃ ላይ የነበረችው እቴነሽ በውድድሩ መሃል ላይ ጫማዋ በመውለቁ ለሁለት ዙር ያህል በአንድ ጫማ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ እቴነሽ ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይግባኝ መጠየቋን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወስኗል፡፡

ጥሩ ደረጃ ላይ የነበረችው እቴነሽ በውድድሩ መሃል ላይ ጫማዋ በመውለቁ ለሁለት ዙር ያህል በአንድ ጫማ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ እቴነሽ ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይግባኝ መጠየቋን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወስኗል፡፡

sofia assefa

Updated | (ዘ-ሐበሻ) በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ እየተካሄደ ባለው ኦሎምፒክ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል የተወዳደረችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሶፊያ አሰፋ ለፍጻሜ ማለፏን አረጋገጠች::

ሶፊያ በተወዳደረችበት ምድብ የማጣሪያውን ውድድር 9:18:75 በመገባት ሁለተኛ ወጥታ ነው ለማለፍ የቻለችው:: በሶስት ምድብ በተደረገው በዚሁ የሴቶች መሰናክል በሌሎች ምድቦች እቴነሽ ዲሮና ሕይወት አያሌው ተሳትፈው የነበረ ቢሆንም ሳይቀናቸው ቀርቷል:: ጥሩ ደረጃ ላይ የነበረችው እቴነሽ በውድድሩ መሃል ላይ ጫማዋ በመውለቁ ለሁለት ዙር ያህል በአንድ ጫማ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ እቴነሽ ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይግባኝ መጠየቋን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወስኗል፡፡

ሶፊያ የተወዳደረችበትን ምድብ በአንደኝነት ያጠናቀቀችው በትውልድ ኬንያዊት የሆነችውና አሁን ለባህሬን የትምሮጠው ሩት ጃቤት ናችት::

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ አንድነት ጉባኤ በወያኔ አገዛዝ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን የዘር ማጥፋት በተመለከተ መግለጫ አወጣ

$
0
0

dem

“የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ።(ወደ ገላትያ ሰዎች 5:12) ጉዳዩ: በወያኔ አገዛዝ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን የዘር ማጥፋት ይመለከታል።
ይህን አስከፊና አሳዛኝ ድርጊት ሙሉ በሙሉ በማውገዝ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ከሁለት ሳምንታት በፊት ያወጣውን መግለጫ በመደገፍ እኛም ልክ እንዳ አባቶቻችን የአቋም መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል።
እንደሚታወቀው ሁሉ አገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 25 ዓመታት በዘረኛው ወያኔ የግፍ አገዛዝ ስር ወድቃ ትገኛለች። ይህ አንባ ገነንና ዘር አጥፊ መንግስት ሃገራችንን እና ህዝቧን እንዲሁም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ለማጥፋት ስራ ከጀመረ ይኸው ከ25 ዓመታት በላይተ ቆጥረዋል። ለአገዛዙ የማይመቹትንና አላማውን የሚያደናቅፉትን እውነተኛ አባቶች የቤተክረስቲያኗን ህግ በድፍረት በመጣስ በማን አለብኝነት ሲያሰቃይ ኖሯል።

 

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በአንድ እግር ጫማ ለመሮጥ የተገደደችው እቴነሽ ዲሮ ይግባኟ ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወሰነ

$
0
0
ጥሩ ደረጃ ላይ የነበረችው እቴነሽ በውድድሩ መሃል ላይ ጫማዋ በመውለቁ ለሁለት ዙር ያህል በአንድ ጫማ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ እቴነሽ ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይግባኝ መጠየቋን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወስኗል፡፡

ጥሩ ደረጃ ላይ የነበረችው እቴነሽ በውድድሩ መሃል ላይ ጫማዋ በመውለቁ ለሁለት ዙር ያህል በአንድ ጫማ ውድድሩን ለማጠናቀቅ ተገዳለች፡፡ እቴነሽ ለዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ይግባኝ መጠየቋን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወስኗል፡፡

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በሪዮ በተደረገው የ3000 ሜትር መሰናክል በውድድሩ ላይ ጫማዋ ወልልቆ በአንድ እግር ጫማ ውድድሩን ለመጨረስ የተገደደችው ኢትዮጵዊቷ አትሌት እቴነሽ ዲሮ የዓለም አቀፉን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይግባኝ በመጠየቋ ወደ ቀጣዩ ዙር እንድታልፍ ተወሰነላት::

የ25 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት አትሌት እቴነሽ ጫማዋ ወልቆ ይህም ቢጎትታትም በ7ኛነት በ9:34.70 ሰዓት በመገባት ውድድሩን አጠናቃለች:: ይህ ሰዓት ለፍጻሜው ውድድር የማያሳልፋት ቢሆንም በይግባኟ መሰረት ግን እንድታልፍ ተፈቅዷል:: በዚህም መሰረት በ3000 ሜትር መሰናክል ሩጫ ኢትዮጵያ በሶፊያ አሰፋና በ እልፍነሽ ዲሮ ትወከላለች::

እቴነሽ በአሁኑ ሰዓት በትዊተር መነጋገሪያ ሆናለች:: ስለርሷ እየተሰጡ ያሉ አስተያየቶች መካከል የተወሰኑትን ይመልከቱ::

በደ/ማርቆስ ከ1000 በላይ ዐማሮች ታስረዋል፤ ነገም የተጋድሎ ሰልፍ ይኖራል • በከሚሴ መሣሪያ እየተነጠቀ ነው • በአርማጭሆ ከፍተኛ መጠን ያለው ጦር ገብቷል

$
0
0

ዐማራ እንዴት ዋለ? ነሃሴ 7 ቀን 2008 ዓ/ም

• በከሚሴ መሣሪያ እየተነጠቀ ነው
• በአርማጭሆ ከፍተኛ መጠን ያለው ጦር ገብቷል
• በወልዲያ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሞጣ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደብረ ብርሃንና ሌሎች ከተሞች ነገ የተጋድሎ ሰልፍ ይጠበቃል
• የሚታሰሩ ዐማሮች ቁጥር ጨምሯል፣ ገበሬዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ እየታገዱ ነው

ከሙሉቀን ተስፋው


ደብረ ማርቆስ፤ በደብረ ማርቆስ ከተማ በርካታ የአጋዚ ወታደሮች ከተማዋን ወረዋት ቢዉሉም ሞትን የማይፈሩት የበላይ ዘለቀ ልጆች ለተጋድሎ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡ ከጠዋቱ 4፡30 አካባቢ የተጀመረው የተጋድሎ ሰልፍ እስከ 8፡00 እንደቆየ ለማወቅ ችለናል፡፡ ከከተማዋ ሦስት የተለያዩ አቅጣጫዎች የነበረውን ሰልፍ ለመበተን ጥረት ተደርጓል፡፡ በሰልፉ ሁለት ዐማሮች የተሰው ሲሆን ቁጥሩ ወደ አራትም ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጧል፡፡

deremarkos
በደብረ ማርቆስ ከተማ ከሕዝብ ጎን ተሰልፏል የተባለ አንድ የዐማራ ፖሊስም በአጋዚ ጦር መገደሉን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በደብረ ማርቆስ በአጋዚ የተገደሉት ዐማሮች በድብደባ እንደሆነ ነው መረጃ ያቀበሉን ሰዎች የገለጹት፡፡ በጥይት በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ከሰአት በኋላ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ የማርቆስ ወጣቶች በቀበሌ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት መታሰራቸው ታውቆ ነበር፡፡ ከመሸ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ የታሰሩ ሰዎች ብዛት ከ1000 እንደሚበልጥና የፖሊስ ጣቢያዎችና የቀበሌ ጽ/ቤቶች ሁሉ በመጥበቡ ምክንያት ሲኒማ አዳራሽ ተዘግተዋል ተብሏል፡፡


በደብረ ማርቆስ ነገም የተጋድሎ ሰልፍ እንደሚኖር የሚጠበቅ ሲሆን ዛሬ ከተሰሙት መፈክሮች ‹‹እንኳን ለወልቃይት ለባድመስ ታግለን አይደል!›› የሚለው የማኅበራዊ ሚዲያውን ተቆጣጥሮ ውሏል፡፡
ከሚሴ፤ በከሚሴ ያሉ ዐማሮች መሣሪያቸውን እየተገፈፉ እንደሆነ በጠዋት ነው መረጃው የደረሰን፡፡ የተጋድሎ ሰልፉን ያስተባብራሉ የሚባሉትን ወጣቶች እንደታሰሩም ለማወቅ ችለናል፡፡


አብደራፊ/አብራጂራ፤ ወደ ምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊና አብራጂራ ከተሞች ከሦስት አቅጣጫዎች የመከላከያ ሠራዊት ከነሙሉ ትጥቁ ሲገባ መሰንበቱን ለማወቅ ችለናል፡፡ በሶረቃ በኩል የገባው የመከላከያ ሠራዊትና ትጥቅ 8 ኦራል እና 5 ዘመናዊ ታንኮች ሲሆን በመተማና በኹመራ በኩል የገባው የጦር መጠን ከዚህ የዘለለ ነው ተብሏል፡፡ ለምን ዓላማና እንዴት እንደገባ ለጠየቅናቸው ጥያቄ ‹‹በቄስና በመነኩሴ እያስገዘቱ ለይቅርታ ነው የመጣነው ቢሉም አሁን ላይ ግን ዐማሮችን ማደን ይዘዋል›› ሲሉ ገለጸዋል፡፡


አጠቃላይ፤ በወልድያ፣ ደሴና ኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደጀን፣ ሞጣ፣ ብቸና፣ ፍኖተ ሰላም ከተሞች ወጣቶች በብዛት እየታሰሩ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚደርሱን፡፡ በወልድያ የሰሜን ወሎ የብአዴን ኃላፊ አቶ አበባው ሲሳይና የቅጥረኛ ካቢኔዎቹ በርካታ ወጣቶችን ፒያሳና አዳጎ በሚባሉ ሰፈሮች እንዳሳሰሩ ለማወቅ ችለናል፡፡ በግል ቢዚነስ የሚንቀሳቀሱ ብሎም የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ይገኙበታል፡፡ በደሴና በኮምቦልቻ ከተማዎች ለነገ ሠልፍ ይኖራል በሚል የፈሰሰው የአጋዚ ጦር መጠን ብዛት አለው ተብሏል፡፡


በደሴ ከተማ በቀን ሥራና በሊስትሮነት የተሠማሩ ልጆችን ፖሊሶች በመዞር እያስፈረሙና እየመዘገቡ ነገ ሰልፉ ላይ ብትገኙ ወዮላችሁ ስማችሁን መዝግበናል እያሉ ውለዋል፡፡ በኮምቦልቻ ከተማ ደግሞ የቀን ሠራተኞችንና የኔ ቢጤዎችን እስከ ቅዳሜ ድረስ ሠርታችሁ ከተማ መገኘት የለባችሁም፤ ቦርከና ወንዝ ልብስ ስታጥቡ ዋሉ ተብለዋል፡፡


በምስራቅ ጎጃሟ የብቸና ከተማ ዛሬ ማንኛውም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴ ባንክን ጨምሮ ዝግ ሆኖ ውሏል፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ የሚመጡ አርሶ አደሮች እንዳይገቡም ተከልክለዋል፡፡ የዐማራን ሕዝብ ለመግደል የተመደቡት የአጋዚ ጦር አባላት የሚመገቡት በከተመዋ ከሚገኘው ‹‹ጽጌረዳ ሆቴል›› እንደሆነ ነው የተነገረን፡፡ በሞጣ፣ በደጀን፣ በዕድውኃ፣ በፍኖተ ሰላም ከገጠር የሚመጡ ገበሬዎች እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል፡፡
ከመንዝ ላሎ እና ማማ ምድር ወደ ደብረ ብርሃን የሚመጡ ገበሬዎች ላይ ከፍተኛ ፍተሻና ወከባ እንዳለም ለማወቅ ችለናል፡፡

ይህ ሁሉ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው::


ኢትዮጵያ ሆይ! ከሰይጣን ተላላኪ ካህን እንዲገላግልሽ እጆችሽን ወደ ሰማይ ትዘረጊያለሽ! -በላይነህ አባተ

$
0
0

1-eregna-newyorkበላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

መጽሐፉ እስተንፋስ ያለው ሁሉ እንዲተነፍስ ያዝዛል፡፡ ዳሩ ግን ካህናት ይህንን የመጽሐፍ ቃል በመሻር የሕዝቡን እስተንፋስ ለመዝጋት የሰይጣን ተላላኪ ሆነው ተሰልፈዋል፡፡ ሰይጣን  እንደ እግዚአብሔር በአካል ባይታይም በጭራቅነቱ፣ በውሸታምነቱ፣ በከሐዲነቱ፣ በአታላይነቱ፣ በሌባነቱ፣ በስግብግብነቱ፣ በከፋፋይነቱና በክብርየለሽነቱ ይታወቃል፡፡ እነዚህ የሰይጣን ባህሪያት በባዕዳን ከወንበር የተጎለቱትን ባንዳ ገዥዎች ይገልጧቸዋል፡፡ ካህናት በተለይም አቡኖችና አቡኖችን እንደ መጋዣ የተሸከሙት ጳጳሳት ለገንዘብና ለስልጣን ሲሉ አምላካቸውንና አገራቸውን ክደው የባንዳዎች ተላላኪ ሆነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ልሳን ሊዘጉ ሲሯሯጡ ይታያል፡፡

ኢትዮጵያ ሆይ! እነዚህ ካህናት ልጆችሽ ሲታረዱ፣ ሲገረፉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲሰደዱና ሲራቡ አብረዋቸው ቆመው አያውቁም፡፡ ዛሬ ይባስ ብለው እነዚህ ቆብ ደፊ፣ ሸማ ጠምጣሚ፣ ዘንግ ሰባቂ፣ ጸናጽል አፋጪና ከበሮ ደላቂ ካህናት ከፎቃቸውና ከሉመዚናቸው እየወጡ የቁርጥ መቁረጫ መስቀላቸውን አንጠልጥለው ከጭንቅ የገቡትን ነፍሰ-ገዳዮች ለመታደግ ልፋጭ እንደለመደ ውሻ ከልጆችሽ ደጆች ሲልከሰከሱ ይታያሉ፡፡ አንቺም ይህን በሰይጣንና በሰይጣን ተላላኪዎች የሚፈጸም ከራስ ዳሽን የረዘመ ግፍ ችለሽ ተቀምጠሻል፡፡ እባክሽ እማማ እነዚህን የሰይጣን ተላላኪ ካህናት “ልጆቼ ሲገደሉ አትግደል አላላችሁም፤ ሲገረፉ አትግረፍ አላላችሁም፤ ሲራቡ አላበላችሁም! ሲሸጡኝ አልከለከላችሁም” ብለሽ ደጀ ሰላም እንደ ገባ ውሻ አብከንክነሽ አባሪያቸው፡፡

ኢትዮጵያ ሆይ! እግዚአብሔር ለልጆችሽ ክፉና ደጉን እንዲለዩበት አእምሮ፣ ሃይማኖትና ጥበብ ከዓለም በፊት ሰጥቷቸው ነበር፡፡ ቅዱሱ መጽሐፍም ነጣቂዎችንና ተኩላዎችን ከፍሪያቸው ታውቃላችሁ ሲልም አስተምሯቸው ነበር፡፡ ምነዋ ዛሬ የተማሩት ልጆችሽ የተማሩትን ረስተው ካህናትን በስራቸው ከፍሪያቸው መለየት አቃታቸው? በየትኛው የቅድስና ሥራቸው የነፍሰ-ገዳይ ተላላኪ አቡንና ጳጳሳትን ብፁዓንና ቅዱሳን እያሉ ጠሯቸው? እባክሽ እናት ዓለም ልጆችሽ ቆብ የደፋውን ተላላኪ ካድሬ አባ እያሉ እንዳይጠሩ፤ መስቀል የጨበጠውን የሰይጣን ተከታይ ይፍቱኝ እንዳይሉ፤ ካባ የደረበውን ከርሳም አቡንና ጳጳስ ብፁዕና ቅዱስ እያሉ ከመለኮት እንዳይጣሉ ምከሪያቸው!

ኢትዮጵያ ሆይ! እንደ ዛሬው በባዕዳን ሴራ የደም አበላ ስትሆኝ ልጅሽ አቡነ ጴጥሮስ እንደ እንደተሰዋልሽ ታስታውሻለሽ! ምነዋ ዛሬ በስንት ለጋ ልጆች ሰማእታት ተንበሽብሸሽ የካህን ሰማእት መካን ሆንሽ? ምነዋ እናትዬ ጅብ ሲበላ ጅብ ተከትለው የፍታትና የተዝካር ልፋጭ በሚጎትቱ የካህን ውሾች ተሞላሽ?

ኢትዮጵያ ሆይ! ከጠላቶችሽ እንጅ ከአንቺ ጋር የሚሰለፍ እንደማይኖር ታውቂያለሽ፡፡ ዙምባቤ ሌባ ሲታሰር ባዙቃ እሚነፉት ምዕራባውያን ባሳደጓቸው ውሾች የልጆችሽ ደም እንደ ጎርፍ ሲፈስ ውሾቹን መቀለቡን እንደቀጠሉም ትረጃለሽ፡፡ ይህንን ሴራ የተገነዘቡት ልጆችሽም ክብርሽን ለመመለስ ደማቸውን እያፈሰሱ እንደሆነም ታውቂያለሽ! ምነዋ ታዲያ እናት ዓለም የሰማእት ልጆችሽን ተዝካር እሚዝቅ እንጅ ነፍሳቸውን የሚታደግ ካህን አጣሽ? ምን ብታስቀይሚው ለሰይጣን እሚላላክ ሲኖዶስ ከእምብርትሽ እንደ ጦር ተከለብሽ?

ኢትዮጵያ ሆይ! ከሰይጣን ተላላኪ ካህን እንዲገላግልሽ እጆችሽን ዛሬም ወደ ሰማይ ትዘረጊያለሽ!

 

ነሐሴ ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.

ተይ አንቺ ውሻ!!!   በዮሴፍ ሙሉጌታ  ባባ (ዶ/ር)

$
0
0

 

kankokunmalimaali@gmail.com

ክፍል 12

Woyane Generals -- satenaw  ጭብጥን በጭብጥ መመከት የማይፈልጉ አንድ አንድ ሰዎች፣ ብዕርን እንደ ጦር ይፈራሉ። በእርግጥ ሰውዬው እንዳለ ‹‹ብዕር የወጋዉን ቁስለኛ ዶክተር አያድነዉም!›› ከማንኛውም የጦር መሣሪያ በላይ እሳት የሚተፋ ብዕር የሚፈራ ለዝህ ይመስለኛል። በሀገራችን ኢትዮጵያ ‹‹ፍደል ቆጠርኩ›› የሚል ጥሩንባ ነፊ፣ ለተነሳው ሐሳብ/‹‹ክርክር›› ምክንያት ማቅረብ ስያቅተው፣ ተቃራኒውን/ሌላውን ወገን ለማሸማቀቅ፣ የስድብ ውርጅብኝ ማጦዝ ይጀምራል። እንድህ ዓይነቱ ሕፀፅ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› (Argumentum ad Hominem) ይባላል!! በሥነ-አመክንዮ፣ ሐሳብን በሐሳብ መመከት ማለት፣ ‹‹አንድ በቂ ምክንያት ከሃምሳ ሰበቦች የተሻለ ነዉ!›› የሚለውን አባባል በትክክል መረዳት ማለት ነው።

በሕዝብ ስም የራሳቸውን ኑሮ አደላድሎ መኖር የሚፈልጉ ሰዎች፣ ማንኛውንም ‹‹ነገር›› ከነባራዊ እውነት (Objective Truth) አንፃር ለመረዳትና ለማብራራት አይፈልጉም። ያላቸው ብቸኛ አማራጭ፣ በተለያዩ ድኅረ-ገጾች ላይ ቅዱሱን ነገር ፍጹም እርኩስ፣ እርከሱን ደግሞ ፍጹም ቅዱስ አድርጎ ማቅረብ ነው። ይህንን ስያደርጉ ትክክለኛ ስማቸውን ይቀይራሉ። በዝህ የተነሳ፣ አብዛኛው ሰው የሚደርስበትን ትችትና ስድብ በመፍራት፣ እውኔታውን ለመጻፍ አይደፍርም። በተለይ፣ አድናቆትንና ክብርን አብዝቶ የሚሹ ምሁራንና ጻሐፍዎች፣ ከሌላ ወገን የሚሰነዘርባቸውን ሂስ/ማስፈራሪያ/ስድብ መቋቋም ይሳናቸዋል።

አንድ ጸሐፍ/ተመራማር አንዱን ወገን ላመስደሰት፣ ሌላውን ደግሞ ለማስከፋት እስከጻፈ ድረስ፣ መቼም ቢሆን ቡከን መሆኑ የማይቀር ነገር ነው። የምርምር ዓለም እስከገባኝ ድረስ፣ የአንድ ጸሐፍ/ተመራማር ዋና ተልዕኮ መሆን ያለበት አንድን ወገን በጅምላ ማዋረድ (ማስከፋት)፣ ሌላውን ወገን ደግሞ ማወደስ (ማስደሰት) ሳይሆን፣ በሰከነ መንፈስ እውነቱን ጽፎ ማኅበረሰቡን/ግለሰቡን ማስተማር፣ መገጸጽና ማስረዳት ብቻ ነው።

ይሁን እንጂ፣ ሌላውን ወገን ላለማስቀየም በሚል ሰበብ፣ የማያምኑበትን ነገር እንደ ወረደ ተቀብለው ጽፈው የሚያስተምሩ ሰዎች አሉ። ይህ ደግሞ ቡከንነትና በጣም አሳፋር ድርጊት ነው። ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ስብሃት ገብረ-እግዚብሄር ለተስፋዬ ገ/አብ የለገሰውን ምክር መቼም ቢሆን መርሳት የለብንም፤ “ሰዎች ሲያደንቁህ አትኩራራ! ሲያጥለሉህ ደግሞ አትደንግጥ። የምረግሙህም የሚያደንቁህም በብዛት ይፈጠራሉ። መልስ እንዳትሰጥ። ይህን እርሳዉና ሌላ መፅሐፍ ጀምር።”

‹‹የሰው ልጅ ህሊና ትንሹ እግዚአብሔር ነው!›› ከተባለ፣ አንድ ግለሰብ ትክክለኛውን ነገር ጽፎ ማስተማር እንጅ፣ የለሎችን ዛቻ/ስድብ ፈርቶ እውነቱን መደበቅ የለበትም። በዓሉ ግርማ እንድህ ይላል፤ ‹‹ድፍረት የሌላት ብዕር ወረቀት ባታበላሽ ይመረጣል፣ ከአድርባይ ብዕር ባዶ ወረቀት ብዙ ይናገራል።›› እንድህ ዓይነቱ ድፍረት ግን ንብረትና ልጆች ላፈሩት ግለሰቦችም ሆነ ‹‹ከአስር ድግሪ አንድ ግሮሰሪ›› ቢሎ ለሚፈላሰፉ አድርባዮች ላይዋጥላቸው ይችላል። ይሁን እንጅ፣ ገንዘብና ህሊና የተሰማሙበት ጊዜ አልነበረም፤ አይኖርምም። ስለዝህ፣ የሰው ልጅ ለእውነት የመኖርና የመሞት ግዴታ አለበት።

ፍልስፍና በተፈጥሮው የአዞ-ቆዳ አለው! ‹‹ዳንሰኛውን ከዳንሱ ነጥሎ ማዬት የማይችሉ ሰዎች›› የሚሰነዝሩትን ማንኛውም ዓይነት አፍራሽ ትችት (ስድብ፣ ማስፈራሪያ፣ ዛቻ…ወዘተ) የማስተናገድ አቅም አለው።  በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ፣ ስፍር-ቁጥር የሌላቸው ጥያቄዎች ይከሰታሉ። ለእነኝህ ጥያቄዎች እንዳስፈላግነቱ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔዎችን ማፈላለግ፣ የፍልስፍና ተፈጥሯዊ (ሳይንሳዊ አላልኩም!) ግዴታ ነው። ይህንን ተልዕኮ በማሳካት ሂዴት ውስጥ፣ ከሌላ ወገን ለሚሰነዘርበት ማንኛውም ዓይነት አፍራሽ ትችቶች እጅ መስጠት የፍልስፍና ተፈጥሮአዊ ባህርይ አይደለም። በሰው ልጅ ታሪክ ውሰጥ፣ ፍልስፍና ፈላስፎችን እየቀበረ፣ ራሱ ግን ሕያው ሆኖ የሚኖርበት ዋና ምክንያት ይሄው ነው። ለምሳሌ፣ በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ የሰውሻዊያንን ፈተና ማለፍ የሚቻለው፣ በእውቀት ደረጃ ሳይሆን፣ በጥበብ (በፍልስፍና) ብቻ ስንመራ መሆኑን ለአንድ አፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም።  ለመሆኑ ሰውሻዊያን ማን ናቸው?

ሰውሻዊያን ሰው ያላሰበውን የሚያሳስቡ ሰዎች ናቸው!! ሰውሻውያን የተባሉበት ዋና ምክንያት ደግሞ፣ ድርጊታቸውና አካሄዳቸው ሉሉ ከሚትባል የአፄ ኃይሌ ሥላሴ ውሻ ጋር በጣም ስለምመሳሰል ነው። ዶ/ር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅ ጉዞና የሕይወቴ ትዝታዎች በተሰኘ መጻፉ ውስጥ ሰለዝች ጉደኛ ውሻ እንድ ሲል አስፍሮ ነበር፡-

‹‹በአፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ተንኮል የሚያስብባቸዉን ሰው ፊቱን አይታ የምትናገር ውሻ አንደነበራቸው፣የውሻዋ ፊት በጣም ከተቆጣ እጅ ሊነሳ የሄደው ባለስልጣን እንዲገደል ወይም እንዲታሰር፣ መጠነኛ ቁጣ ከሆነ ደግሞ፣ ስልጣኑ እንደምቀነስበት፣ አንድ ቀን በጣም ቀልደኛ ነው የሚባለዉ የአፄ ኃይለ ሥላሴ በለስልጣን፣ አቶ ይልማ ዴሬሳ የሚባለው (ይህ ሰው አነጄነራል መንግስቱ ኖዋይ የአፄ ኃይለ ሥላሴን በለሥልጣን ሰብስቦ የጨረሱ ግዜ፣ አቴጌ ታማለች ብለው ሲጠሩት እኔ ኢኮኖምስት ነኝ እንጅ ሀኪም አይደለሁም ብሎ ዲኖዋል ይባላል) አፄውን እጅ ሊነሱ ሲሄዱ፤ ውሻው ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለች አሉ። የውሻዋን ጨወታ በትክክል የሚያውቁ አቶ ይልማም ‹ተይ አንቺ ውሻ ሰዉ ያላሰበውን፣ አተሳስቢ› አሉዋት ይባላል።››

   በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ አንድ ተመራማሪ/ጸሐፍ ትምክህተኝነትንና ጠባቢነትን አስወግዶ፣ በንፁህ ህሊና ከሱ የሚጠበቀውን ተልዕኮ በሚወጣበት ጊዜ፣ የሉሉን መንቃራ አመል የተላበሱ ሰዎች ሆን ብሎ ችግር ይፈጥራሉ።  ሰውሻዊያንና ሉሉ የአንድ ሣንትም ሁለት ገጽታ ናቸው ያልኩበት ምክንያት ለዝህ ነው። ‹‹ተው ወንድም-አለም ሰው ያላሰበዉን፣ አታሳስብ!›› ማለት ግን ጠቢብነት ነው። ፈጣሪ ከሰውሻዊያን ፍልስፍናዊ ወጥመድ ይሰውረን እያለኩኝ፣ በማረፊያ በቀለ ግጥም የዛሬ መጣጥፌን ላሳርግ!

 

እንደ ተንጣለለ―አንደ ውብ ከተማ

ባንድ ጎንህ ብርሃን―በሌላው ጨለማ

ግማሽን ገልጠህ―ግማሽህን ግጠም

ልክ እንደ ጨረቃ―ተደበቅ ግድየለም

ይበቃኛል በርግጥ―ግማሽህን ማየት

ግማሽ በመሆኑ―ሰው የመሆን እዉነት

 

በክፍል 13 ‹‹የዶ/ር መረራና በእውቀቱ መንገድ!›› እንመለከታለን

ቸር እንሰንብት!!!  

 

የማንቂያ ደውል።- ዳዊት ዳባ

$
0
0

Bell-123909540w1በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እንቢተኝነት የነፃነት የእኩልነት የፍትህና የኢኮኖሚ ጥያቄ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው መሆኑ ቢታወቅም፤ ትግሉ የህዝባችንን ጥያቄ በመለሰ መልኩ እንዲጠናቀቅ ምን  ይጠበቃል የሚሉትን ከብዙዎቹ ጥቂቶቹን ለመዳሰስ እንሞክራለን።

የፖለቲካ ድርጅቶች፤- የህዝባችንን ጥያቄ በሀይልና በማሸበር ለማፈን የተለመደውን ተግባሩን ወያኔ ተያይዟል። ህዝብ እንደተፋው አሁንም ለመቀበል ዝግጁ አይደልም።  ድርጅቶች ወቅቱ የሚጠይቀውን ሀላፊነት ተገንዝባችሁ የህዝቡን ጥያቄ ግምት ውስጥ ያስገባና ለውጡን ሊሺከምና ሊያሻግረን የሚችል ብሎም ባለድርሻዎችን ሁሉ ያሳተፈ መፍትሄ እንደምትሰሩ ይጠበቃል።

ትግሉን የሚያንቀሳቅሱ ሀይላት፤- እስካሁን የሰራችሁት ስራ  የሚያመለክተው አንድ ታላቅ ነገር በዜጎች ዘንድ ለውጥ የሚታለም ብቻ ሳይሆን የሚታይ አልፎም የሚጨበጥ ማድረግ ችላችሗል።  አድካሚ የሆነው ስራና የበዛ ሀላፊነትን ለመሸከም መድፈራችሁ የአጥፊውን ወገን ያለፈበትና ያለቀለት ታክቲክ በማክሸፍ ደረጃ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። አበው እንደሚሉት ለአንበሳ አይመትሩም ለብልህ አይመክሩም ቢሆንም ለለውጥ ፈላጊውም ሆነ ላገዛዙ አልፎም ለውጪ አገራት  ጥርት እንዲልና ዞሮ ዞሮ መዳረሻው ይህ ስለሆነም “የስርአት ለውጥ” የሚለውን የሚሰማ አድርጉት። አጨራረሱ በቅጡ ታስቦበታል ነው  ግምቱ።

ያሉን ጥቂት የመገናኛ ብዙሀን ትግሉን ያለወገንታዊነት በእኩልነት ሽፋን እየሰጣችሁ መሆኑን እርግጠኛ ሁኑ። የሚተላለፉ መልእክቶች ሆኑ ወቅታዊ ትንታኔዎች የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ የሚያደርሱን  እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ቢደረግም ጥሩ ነው። ሁላችንም እንደምንገነዘበው የተሳሳተ ድምዳሜ ፖለቲካዊ መፍትሄ የመስራቱን ሂደት አስቸጋሪ ያደርገዋል። በንኪያ ሰላምታ የህዝብ ትግል ይጎዳል። ጊዜው የሚሻው የሜዲያ ሽፋን አይነት ትግሉ እራሱ ነው። በመሬት ላይ የሚቀናጅበትን፤ ቀጣይ የሚሆንበትንና አዳዲስ የትግል ፈጠራዎች የሚያጭር ቢሆን ጠቃሚ ነው። መሳርያ የያዘውን የለውጡ አካል የሚሆንበትን ሂደት ማፍጠን ይቻላል። የሚሞተውንና የሚታሰረውን ሰው መቀነስ ይቻላል። ትግሉ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች ማስጀመር ይቻላል…..ብዙ ብዙ።

ህዝባዊ ሀርነት ትግራይ፤- ህዝብ የችግሩን ምንጭ በትክክል ተገንዝቧል። “የወያኔ የበላይነት ይብቃ” ነው እያለ ያለው። አስተዳዳራዊ መዋቅሮች እየፈራረሱ ነው። አጋር ድርጅቶች በድርጅታዊ ነፃነትና እኩልነት ጥያቄ ማንቁረት ይዘዋል።  መሳርያ የያዘው እያጉረመረመ ነው። ቅሬታውን ተኩሶ እስኪገልፀው መጠበቅ ይቻላል። የሲቪል አስተዳደሩን አፍረሶ በወታደር አገዛዝ መተካት ለችግሩ መፍትሄ ተደርጓል። ኦሮሚያ ላይ ይህ ሆኗል። አማራ ክልልም በቀጣይ የሚጠበቅ ነው። ግን አልሰራም አይሰራምም። ይህ በአለማቀፍ ደረጃ የሚፈጥረው ተፅኖ እያያችሁ ነው። ትላልቆቹ ብሄረሰቦች የሚለውን እውነት የወለደው ይህው ነው።  በአጠቃላይ ቀላል የሆነ ማንቂያ ደውል ለናንተ መስቀመጥ የሚቻልበት ሁኔታ ያለ አይመስልም። ያም ሆኖ ጊዜው የሚሻውን ለየት ያለ የመፍትሄ ሀሳብን ይዞ መምጣትና መሞከር ይቻላል። መንግስታዊ ሽብር እየፈፀማችሁና ዜጎችን እየጨፈጨፋችሁ ለመዝለቅ መሞከሩ ግን የትም አያደርስም።

የወያኔ ሀርነት ትግራይ ደጋፊዎች፤- ከተለመደው ፋይዳ የሌለውን ደረቅ ክርክራችሁን አቁሙ። የህዘብ አሸናፊነት አይቀሬ ነውና አገዛዙ ያዋጣኛል ብሎ የገፋበትን  ሽብርና ጭፍጨፋ ላይ በማንኛውም መንገድ የሚገለፅ ድርሻ እያደረጋችሁ እንዳልሆነ ለራሳችሁ እርግጠኛ ሁኑ።  ሊሰሟችሁ የሚችሉ አይመስለንም።  ከቻሉ ከመንግስታዊ ሽብር እንዲታቀቡ መምከሩ ይጠቅማችሗል።  ይህ ባይሆን ግን ህዘብ በየትኛውም መሰዋትነት ድሉን ይጨብጣል። ኪሳርው በህዋዋትና በናንተ ኪሳራ ይወራረዳል።

ድል የህዝብ ነው።

ዳኮታ የጥናት ማእከል።

8/13/2016

dakotareserech2@yahoo.com

የአማራ ተጋድሎ –የቀጥታ ዘገባ | Live Blog

$
0
0

deremarkos

ይህ ገጽ በየሰዓቱ አዳዲስ መረጃዎች ሲገኙ ለናንተ መረጃዎችን እናደርስበታለን:: ስለሆነም ይመላለሱ::

የአማራ ክልል አስተዳደር በህወሓት እጅ ስር ወደቀ!
በባይነሳኝ ወልደማርያም

(ማምሻውን) በተገኘ ውስጣዊ መረጃ የአማራ ክልል አስተዳደር በትግራይ ህወሓት እጅ ስር ወድቋል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከመደበኛ ስራቸው ተነስተዋል።
የአማራ ክልል ምክርቤት በአስቸኳይ ስብሰባው ገዱ አንዳርጋቸውን በይፋ ከስልጣን ያነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የአማራ ክልል አስተዳደር በ5 ኮማንድ ፖስቶች ተዋቅሯል።
1.ምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት
2.ምስራቅ ጎጃም ኮማንድ ፖስት
3.ጎንደር ኮማንድ ፖስት
4.ወሎ ኮማንድ ፖስት
5.ባህርዳር ኮማንድ ፖስት

ምስራቅ ጎጃም ኮማንድ ፖስት በዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ከደብረማርቆስ ይመራል። ምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት በብናልፍ አንዷለም፤ ወሎ ኮማንድ ፖስት በአለምነው መኮንንና ገነት ዘውዴ ጥምረት፤ ጎንደር ኮማንድ ፖስት በተፈራ ደርበውና አይለኝ ሙሏለም ይታዘዛሉ። ተጨማሪ ኮማንድ ፖስት ሰሜን ሽዋ ላይ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁሉም ኮማንድ ፖስቶች በአንድ እዝ ስር ሆነው በደመቀ መኮነን እገዛ በአባይ ፀሃዬ ይመራሉ። የአማራ ክልል ፀጥታና ደህንነት ቢሮ መሉ በሙሉ በህወሓት ማዕከላዊ የፖለቲካ አመራር ስር እንዲሆን ተወስኗል።

ወሎ
ሕዝብ በስልኮቹ ፎቶግራፎችን በማንሳትም በመታገል ላይ ነው:: ይህ የምታዩት ፎቶ የተነሳው በወሎ ክፍለሃገር ነው:: እነዚህ የትግራይ ነፃ አውጪ አልሞ ተኳሾች በፈራረሱ ህንፃዎች ስር ሁሉ ተደብቀዋል:: ሕዝብ ይያቸው:: የትግራይ ነጻ አውጪ አማራ መሬት ላይ ምን ይሠራል?

wello

 

መቄት – ወሎ

በሰሜን ወሎ ዞን ውስጥ የምትገኘውና ለጎንደር አዋሳኝ የሆነችው መቄት ከተማ ውስጥ ሕዝብ የልዩ ሚኒሻዎችን እና የአጋዚ ጦርን ሳይፈራ ሰልፍ ወጥቷል:: እንደሚሰማው ከሆነ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር በርካታ ሰልፈኞችን ቢያስርም ሰልፈኞቹ ግን 02 ቀበሌ ገረገራ ከሚባለው ወደ ፍላቂት 01 ቀበሌ እየመጡ ነው:: ሰሜን ወሎ ዞን ውጥረቱ አይሏል::

meket citywelo meket 2

መቄት – ወሎ

በወሎ መቄት ከተማ እየተደረገ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ ፎቶግራፍ ደርሶናል:: በርካታ ሕዝብ ወጥቶ በመቄት ከተማ ተቃውሞውን እያሰማ ነው:: ሕዝቡ የሕወሓት መንግስት በቃን እያለ እይጮኸ ነው::

‪‎ማሻ‬ መቅደላ – ሙስሊም መሆን ወንጀል የሆነባት ከተማ

አብዱራህማን አህመድ ቢቢኤን:-

8/12/08 የዛሬውን የወሎ ተቃውሞን ተከትሎ ሰሞኑን በማሻ ከተማ ጠንከር ያለ ፍተሻ ሲደረግ እንደነበር ቢታወቅም ዘወትር እስልምናን ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱት የወረዳዋ ንውሶች ዛሬ በማለዳው በመነሳት በማሻ መናሃሪያ ፍተሻ በማካሄድ ወደደሴ ለመሄድ ጀለብያ ለብሰው የተገኙ ሙስሊሞችን ከመኪና አውረደው ፖሊስ ጣቢያ እንዳሰሯቸው ታውቋል።

dereje Habtewold

ደብረማርቆስ

አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት አብማ ቅድስት ማሪያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን ምዕመናን እንዳይገቡ ተከለከሉ። ከተማዋ ውጥረት ውስጥ ናት። ምንም አይነት እንቅስቃሴ አይታይም። ነዋሪው ከቤቱ መውጣት አልቻለም። ጠቅላላ ወጣቱ ታፍሷል። እስር ቤቶች ሞልተው በርካታ የከተማው ኑዋሪ በጅምላ ንጉስ ተክለሃይማኖት ሁለተኛ ደረጃትምህርት ቤት ታጉሯል። የትራስፖርትም ሆነ ሌሎች የህዝብ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል። ህዝቡን ስለፈሩት ሶስት ቀን ሙሉ ታንክ እየነዱ የከተማውን ህዝብ ሲያስፈራሩት ቆይተዋል::

ወልዲያ

weldiaወልዲያ የተወረረ ከተማ መስሏል:: ምንም አይነት የሚቀሳቀስ ነገር የለም:; ሱቆች ሁቴሎች እደተዘጉ ናቸው:: የመኪና እቅስቃሴ የለም:: በማይታወቁ ሚኒሻዎች እና በአጋዜ ወታደሮች ከተማው ተከቦ ነው ያለው:: አድኖ ተካ የተባለው ወድንድም ወልደያ ሆስፒታል በነርስ የሚሰራ ሲሆን የሕወሓት ተላላኪዎች ትናናን የት እንደወሰዱት አይታወቅም:: ጓድኞቹ እና ቤተሰቦቹ የት እንዳለ ቢጠይቁም ወልዲያ እንዳለ ቢነገራቸውም ሊያገኙት አልቻሉም::

ደብረብርሃን

ከስንታየሁ ቸኮል
ዛሬም ደብረ ማርቆስ አደገኛ ውጥረት ይታያል ሰው በቁጣ እየተሰባሰበ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ሸበልበረንታ ብቸና መፋጠጡ እንደቀጠለ ነው! ደብረ ብርሃን ወሬው በሙሉ የአማራ ሕዝብ ከደደቢት ወራሪ ጋር የጀመረው የጀግንነት ተጋድሎ አጋርነታቸውን ለማሳየት ሆኗል፡፡ ሞት የማያፈራ እሳት የጨበጠ የወሎ ወጣት አደባባዮን በተቃውሞ ሰልፍ ሊያጥለቀልቀው ከጫፍ ደርሷል፡፡ መጪው ጊዜ ለዘረኞች ጨለማ ሲሆን ጭቁን ሕዝብ በድል መንገድ ላይ ይገኛል!!
(ደብረብርሃን)

ሸዋሮቢት

ጀግናው የቀወት ወረዳ ህዝብ ሸዋሮቢት ከተማ ከፍትኛ የተሳካ ተቃውሞ በማለዳው ጅምሮታል ፣አድሚራሎቻችን የትግሉን አቅጣጫ ይቀይሩታል ። ይፋት እና ቀወት ወረዳበአንድነት የጀመሩት ትግል ወደ ምንጃር እንደሚያመራ ሚስጥራዊ የመረጃ ክፍላችን ገልጾአል ፣የወረዳ አስተዳዳሪዎች ፣ዛሬ ምሽት ላይ አፈና በሸዋሮቢት ከተማ ማሪያም ሰፈር በሚሰኘው ቦታ የሚገኘውን የወረዳ አስተዳደር ጥቃት ለማድረስ መዘጋጀቱን ሲጠቁም ፣ይህ ሊሆን የሚችለው በንጹሃን ዜጎች ላይ ክፉኛ ደም የፈሰሰ ከሆነ እነኢህን ሰዎች መሰዋእትነት ከማቅረብ ወደኋአላ አይባልም ሲል አድሚራል ተናግሯል ።

ሰበር ዜና: አማራ ክልል በአባይ ጸሐዬ እጅ ወደቀ |ክልሉ በ5 ኮማንድ ፖስቶች ተዋቀረ

$
0
0

abay Tsehaye
በባይነሳኝ ወልደማርያም

(ማምሻውን) በተገኘ ውስጣዊ መረጃ የአማራ ክልል አስተዳደር በትግራይ ህወሓት እጅ ስር ወድቋል። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከመደበኛ ስራቸው ተነስተዋል። የአማራ ክልል ምክርቤት በአስቸኳይ ስብሰባው ገዱ አንዳርጋቸውን በይፋ ከስልጣን ያነሳል ተብሎ ይጠበቃል።

የአማራ ክልል አስተዳደር በ5 ኮማንድ ፖስቶች ተዋቅሯል።
1.ምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት
2.ምስራቅ ጎጃም ኮማንድ ፖስት
3.ጎንደር ኮማንድ ፖስት
4.ወሎ ኮማንድ ፖስት
5.ባህርዳር ኮማንድ ፖስት

ምስራቅ ጎጃም ኮማንድ ፖስት በዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል ከደብረማርቆስ ይመራል። ምዕራብ ጎጃም ኮማንድ ፖስት በብናልፍ አንዷለም፤ ወሎ ኮማንድ ፖስት በአለምነው መኮንንና ገነት ዘውዴ ጥምረት፤ ጎንደር ኮማንድ ፖስት በተፈራ ደርበውና አይለኝ ሙሏለም ይታዘዛሉ። ተጨማሪ ኮማንድ ፖስት ሰሜን ሽዋ ላይ ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁሉም ኮማንድ ፖስቶች በአንድ እዝ ስር ሆነው በደመቀ መኮነን እገዛ በአባይ ፀሃዬ ይመራሉ። የአማራ ክልል ፀጥታና ደህንነት ቢሮ መሉ በሙሉ በህወሓት ማዕከላዊ የፖለቲካ አመራር ስር እንዲሆን ተወስኗል።

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>
<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596344.js" async> </script>