Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ዝግጅት በሆላንድ –የፈደሬሽኑ እና የሆላንድ ካር ባለቤት የአቶ ታደሰ ተሰማ ፍጥጫ

$
0
0

14ኛው የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ዝግጅት በነገው እለት በደመቀ በሆላንድ ይከፈታል:: ከአውሮፓ፣ ከሰሜን አሜሪካ እና ከኢትዮጵያ የሚመጡ ከ28 ያላነሱ የእግር ኳስ ቡድኖች እና በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶች ከዛሬ ማክሰኞ ጅምሮ ወደ ሆላንድ በመግባት ላይ ናቸው።

Tadesse Tesema

አቶ ታደሰ ተሰማ

በኢትዮጵያ የመጀመርያው የስፖርት ጋዜጠኛ እና የአለም-አቀፍ አኦሎምፒክ አማካሪ ሆነው ያሚያገለግሉት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ  በዚህ በዓል የክብር እንግዳ ናቸው።

የዘንድሮው በዓል ከመጪው እሮብ 26 ጁላይ ጀምሮ እስከ እሁድ 30 ጁላይ ይካሄዳል። ከዚህ ቀደም የዝግጅቱን ሃላፊነት የሚወስዱት የአዘጋጁ ሃገር ክለቦች ነበሩ። ይህንን ዝግጅት ግን ፌዴሬሽኑ ራሱ በማዘጋጀቱ ልዩ ያደርገዋል።

ዘ ሄግ በሚከናወነው በዚህ የኢትዮጵያውያን መሰባሰብያ በዓል ላይ ልዩ-ልዩ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ። ከእግር ኳስ ጨዋታው ባሻገር ዘመናዊና የባህል ፋሽን ትዕይንት፣ የሙዚቃ እና የተለያዩ ስፖርታዊ መርሃግብሮች ይካሄዳሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞው ሆላንድ ካር ባለቤት አቶ ታደሰ ተሰማ የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ጋር ክፉኛ ተፋጥጠዋል። አቶ ታደሰ ተሰማ ይህንን የአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን ለማፍረስ መነሳታቸውን በአንደበታቸው ተናግረዋል። እቅዳቸውን  ለማሳካት አስቴር አወቀን ጨምሮ በርካታ ዘፋኞችን በግላቸው በማስመጣት የፌዴሬሽኑን ገቢ ለማዳከም ቆርጠው መነሳታቸውን የስፖርቱ አፍቃሪዎች ይናገራሉ።

አቶ ታደሰ ተሰማ በሆላንድ ካር ስም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከ100 በላይ ኩባንያዎች እና ግለሰቦች ላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣  መክሰራቸውን በካንጋሩ ፍርድ ቤት አሳውጀው ወደ ነበሩበት ወደ ሆላንድ ተመልሰዋል። ገንዘባቸው የተበላባቸው ሰዎች በመሰባሰብ  በኢንተርፖል በኩል ግለሰቡ ተይዘው  እንዲቀርቡ ቢጠይቁም ይህ ሊሆን አልቻለም።  ከስርያለሁ ያሉት እኚህ ግለሰብ ሆላንድ ላይ ዘመናዊ ምግብ ቤት በመክፈት ንግዳቸውን እያጧጧፉት ይገኛሉ። አቶ ታደሰ በዚህ አላበቁም።  በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ ዋስትናነት ኢትዮጵያ  እንዲገቡና መግለጫ እንዲሰጡም ተደርገዋል።    በኢንተርፖል እንዲያዙ ጥያቄ የቀረበባቸው እኝህ ሰው፤ በብራስልስ የህወሃት ኤምባሲ ጋር እጅና ጓንት ስለሆኑ ከህግ በላይ ናቸው።  የልብ ልብ ተሰምቷቸውም  በህዝብ ንብረት ይቀልዳሉ። እነ ኤርምያስ አመልጋ  የህዝብ ገንዘብ በመብላት ወንጀል ሲታሰሩ አቶ ታደሰ ግን እንደልባቸው እንዲገቡ እና እንዲወጡ ተደርገዋል። ምክንያቱም በየአመቱ የሟች ጠ/ም መለስን የሙት አመት እያከበሩ ግብር ያበላሉ።

አቶ ታደሰ ተሰማ በዘንድሮው የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል በዓል ላይ ከአስር በላይ አርቲስቶችን በመጋበዝ የፌደሬሽኑን ገቢ ለማግደል አቅደዋል። ከዚህ አጥፊ ተግባራቸው በፌዴዴሽኑ ቢጠየቁም አሻፈረኝ፡ብለዋል። እንዲያውም ይህንን ፌደሬሽን እንደሚያፈርሱት ነው የተናገሩት።  እኚህ ሰው ምንም እንኳን በዕጃቸው የህዝቡን ገንዘብ የያዙ ቢሆንም ይህንን በድፍረት ለመናገር የቻሉት ከጀርባቸው የተማመኑበት ሃይል ስላለ ነው።

የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌደሬሽን በአውሮፓ ላለፉት 14 አመታት ኢትዮጵያውያንን በማሰባበብ ትልቅ ስራ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው። አቶ ታደሰ ይህንን ተቋም እንደ ሰሜን አሜሪካው ለሁላት ለመክፈል ከተላኩ ይመስላል።  በአቶ ታደሰ በኩል እየተጠራችሁለዚህ እኩይ ተግባር የምትመጡ አርቲስቶች በሙሉ የሰሜን አሜሪካው አይነት ችግር እንዳይድደርስባችሁ ተጠንቀቁ።  በተለይ አንጋፋዋ  አስቴር አወቀ፣ ወደ ሆላንድ ስትገቢ የሚያስመጣሽ ሰው የስራ ግብር መከፈሉን አረጋግጪ።


Health: ደም በመስጠት የሚካሄድ ሕክምና

$
0
0

ደም በመስጠት የሚካሄደው ሕክምና ጉዳት አያስከትልም ማለት አይደለም፡፡ ከባድ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከነዚህ መካከል፣ ቫይረሶችን፣ባክቴሪያ ወይም ጥገኛ ነፍሳትን ወደ ሌላው ሰው የማስተላለፍ አደጋ አለ፡፡ በተጨማሪም የኩላሊትንና የሳንባን አሠራር የሚያዛባ አለርጂ ሊያስከትል ይችላል፡፡ በኒሞኒያ፣በኢንፌክሽን፣በልብ ድካምና በአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ የመጠቃትን አጋጣሚ ስለሚጨምር አንዳንድ ጊዜ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ በተለይ በአገራችን ብዙ ሰዎች ደም ፈሷቸው ሲሞቱ ይስተዋላል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ለማለት ይቻላል ለመዳን የሚችሉ ናቸው፡፡

Blood 2

የደም ባህርይ እና የሚያመጣው ተጽዕኖ

ደም እንደ ኦክስጅን፣አልሚ ምግቦችና በሽታ ተከላካዮች ያሉ ጥሩ ነገሮችን ወደ ሰውነት ሕዋሳት ያደርሳል፡፡ እንዲሁም ቆሻሻን ከሕዋሳት ውስጥ ያስወግዳል፣ከእነዚህም መካከል መርዛማ ካርቦን ዳይኦክሳይድ፣የተጎዱ እንዲሁም የሞቱ ሕዋሳትና ሌሎች ቆሻሻዎች ይገኙባቸዋል፡፡ደም ቆሻሻን በማስወገድ ረገድ የሚጫወተው ሚና፣ከሰውነት ከወጣ በኋላ መነካቱ አደገኛ ሊሆን የሚችልበትን ምክንያት ለመገንዘብ ይረዳል፡፡ እንዲሁም ለሕመምተኛ ደም ከመሰጠቱ በፊት በውስጡ የሚገኘው ቆሻሻ በሙሉ ተለይቶ ተወግዷል ብሎ ዋስትና መስጠት የሚችል ሰው የለም፡፡

ደም በሰውነታችን ውስጥ 100,000 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን በዚህ ጊዜ ደምን የሚያጣሩትንና በትክክል መሥራታቸው በደም ላይ የተመካውን ዋነኞቹን የሰውነት ክፍሎቻችንን ማለትም ልብን፣ኩላሊትን፣ጉበትንና ሳምባዎችን ጨምሮ በእያንዳንዱ የአካል ክፍል ውስጥ ያልፋል ለማለት ይቻላል፡፡

ደም መወሰድ ያለበት መቼ ነው?

ከባድ የመቁሰል አደጋ ሲያጋጥም ካልሆነ በስተቀር ለሕመምተኞች ደም መስጠት በደም ምትክ የሚሰጡ  አማራጭ የሕክምና ዘዴዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ደም ሥሮችን መተኮስ፣ ደም እንዳይፈስ ለማገድ አንዳንድ የሰውነት ክፍሎችን ኬሚካል ባለው ለየት ያለ ፋሻ መሸፈንና የደምን መጠን የሚጨምሩ መድኃኒቶችን መስጠት ይገኙበታል፡፡

ደም መስጠት

ደም ለሕይወት በጣም አስፈላጊ የሆኑ ተግባሮችን እንደሚያከናውን ምንም አያጠያይቅም፡፡ ደም ለፈሰሳቸው ሕመምተኞች ደም መስጠት በሕክምናው ማኀበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ብዙ ዶክተሮች ደምን እጅግ ዋጋማ ያደረገው በዚህ መንገድ ለሕክምና መዋሉ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ሆኖም በሕክምናው ዓለም ነገሮች እየተለዋወጡ ነው፡፡ ቀስ በቀስ አስገራሚ ለውጦች እየተካሄዱ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ በርካታ ዶክተሮችና የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች እንደበፊቱ ደም ለመስጠት አይቸኩሉም፡፡

ሆኖም ሙሉ ደምና የደም ክፍሎች የተገኙት ከሰው ደም በመሆኑ እንደ ቫይረስ ያሉ በሽታ አስተላላፊ ሕዋሳትን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ደም ለጋሾችን በጥንቃቄ መምረጥም ሆነ የላብራቶሪ ምርመራዎች ማድረግ አደጋውን አያስወግዱትም፡፡

በደም አያያዝ ረገድ የሚሠሩት ስህተቶችና የተወሰደው ደም ከሰውነት በሽታ መከላከያ ጋር ሊጋጭ መቻሉ ናቸው፡፡ የሌላን ሰው ደም የሚወስዱ ሰዎች፣የሌላ ሰው አካል የተተካላቸው ግለሰቦች ለሚያጋጥማቸው ዓይነት አደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ የሰው በሽታን የመቋቋም ተፈጥሯዊ ኃይል ባዕዱን አካል ላይቀበል ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደም መውሰድ በሽታ የመቋቋም ተፈጥሯዊ አቅምን ሊያሳጣ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ሕመምተኛው ከቀዶ ሕክምና በኋላ ለበሽታ እንዲዳረግና ቀደም ሲል በሰውነቱ ውስጥ ቢኖሩም ጉዳት የማያስከትሉበት በነበሩ ቫይረሶች እንዲጠቃ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ቁጥራቸውእያደገ የመጣው እንዲህ ያለ እውቀት ያላቸው የጤና አጠባበቅ ሠራተኞች፣ ለሕመምተኞች ደም በመስጠት የሚደረግ ሕክምናን በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄና ማስተዋል የተሞላበት ግምገማ እያደረጉ ነው፡፡

ለሕመምተኞች ደም በመስጠት የሚከናወን ሕክምና በርካታ አደጋዎች ቢኖሩትም፣ በተለይ ደግሞ ሌሎች አማራጮች እያሉ አሁንም በስፋት ጥቅም ላይ የሚውልበት ምክንያት

አንዱ በርካታ ሐኪሞች የሕክምና ዘዴዎችን ለመለወጥ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ወይም ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ያለደም የሚደረጉ አማራጭ ሕክምናዎች መኖራቸውን ባለማወቃቸው ነው፡፡ ሐኪሞች ደም ለመስጠት የሚወስኑት ቀደም ሲል ባገኙት ትምህርት፣ ከሌሎች ሐኪሞች በወረሱት እውቀትና በምርመራ ውጤት ላይ ተመሥርተው ነው፡፡ በተጨማሪም የቀዶ ሕክምና ዶክተሩ ችሎታ በሕክምናው ወቅት በሚፈሰው የደም መጠን ላይ የሚያመጣው ለውጥ አለ፡፡ በሕክምና ወቅት የሚፈሰው ደም ቀዶ ሕክምናውን እንደሚያከናውነው ባለሙያ በእጅጉ ይለያያል፣በመሆኑም በቀዶ ሕክምና ወቅት የደም መፍሰስን ማስቆም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች በተመለከተ ለቀዶ ሐኪሞች በቂ ማሠልጠኛ የመስጠቱ አስፈላጊነት እየጨመረ ሄዷል፡፡ ሌሎች ደግሞ ደም ከመውሰድ ውጪ ያሉት አማራጭ ዘዴዎች ዋጋቸው በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ፣ ሆኖም ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሁኔታው ከዚህ ተቃራኒ ነው፡፡

ከሙሉው ደም ውስጥ ከ38-48 በመቶ የሚሆኑት ቀይ የደም ሕዋሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ሕዋሳት ሕብረሕዋስ ውስጥ ኦክስጅንን ያስገባሉ ካርቦን ዳይኦክሳይድን ደግሞ ያስወጣሉ፡፡ በዚህ መንገድ ሕብረ ሕዋሱ በሕይወት እንዲቀጥል ያደርጋሉ፡፡

ለጋሾች የሚሰጡት ይህ ሙሉውን ደም ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ግን ኘላዝም ብቻ ይለግሳሉ፡፡ በአንዳንድ አገሮች ሙሉው ደም ለታካሚዎች ቢሰጥም ደሙ ከመመርመሩና ለሕመምተኞች ደም በመስጠት ለማከናወን ሕክምና ከመዋሉ በፊት በዋና ዋና ክፍሎች መከፋፈልም በጣም የተለመደ ነው፡፡

በቦረና ዞን ቦኩ ልቦማ የአጋዚ ሰራዊት በሕዝብ ላይ ጥይት ሲያርከፈክፉ የሚያሳይ ቪዲዮ

$
0
0

Borena
በኦሮሚያ የሕዝባዊ አመጹ በተለያዩ ከተሞች ቀጥሎ ውሏል:: በአርሲ አሁንም የተረጋጋ ነገር የለም:: ሕዝብ እንዳመጸ ነው:: በቦረናም እንዲሁ በተለይ በቦረና ዞን ሚዮ ቦኮ ሉቦማ ከተማ ዛሬ መንግስትን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፈኞች አደባባይ ወጥተው የአጋዚ ሠራዊት ጥይት ሲያርከፈክፍባቸው የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ተለቋል:: የአጋዚ ሠራዊት በቀጥታ ወደ ሰላማዊው ህዝብ ሲተኩስ የሚያሳየው ቪዲዮ ብዙዎችን እያስቆጣ ይበልጥም ተቃውሞውን እያፋፋመው ይገኛል:: በዚህ የአጋዚ ጥይት ቃባር ቃርባትፕ; ፋጡማ ዋቆ እና ሶራ ሃላቄ የተባሉ ሰላማዊ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል:: የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨመር ይችላል እየተባለ ነው::

በቦረና ዞን ቦኩ ልቦማ የአጋዚ ሰራዊት በሕዝብ ላይ ጥይት ሲያርከፈክፉ የሚያሳይ ቪዲዮ

ኢትዮጵያና ጎንደር፤ –ከመይሳው ታጠቅ!!

$
0
0

Gonder
እንደሚታወቀው ሀገራችን የረጅም ጊዜ የታሪክ ገጽታ እንዳላት በእኛ በሃገሬው ሰዎች ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃ በቀዳሚነት የታወቀ ነው። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በጎንደር ክፍለ ሀገር ውስጥ የተፈጠረውን ሕዝባዊ የማንነትና የሕግ የበላይነት ጥያቄ አስመልክቶ ከሚደረገው ወቅታዊ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ
Ø ኢትዮጵያና ጎንደር፤
Ø ወልቃይትና ጎንደር፤
Ø ትግራይና ጎንደር፤ በሚሉ ርዕሶች ለአንባብያን በአጭር በአጭሩ የቀረበ ነው።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የኦሮሞና አማራ ትክክለኛው የዘር ምንጭ – በፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ

$
0
0

• ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች ነው
• አዳም የተፈጠረው ጎጃም፤ ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው
• ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አጥንተዋል

 

Source: Addis Admass Newspaper

ኑሮአቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ታዋቂው የሥነፅሁፍ ምሁር ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ፤ የፃፉት‹‹የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ›› የተሰኘ አዲስ አነጋጋሪ የታሪክ መፅሐፍ ዛሬ ለገበያ ይቀርባል፡፡ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ ማን እንደሆነ በጥናት ደርሼበታለሁ የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ እስከ ዛሬ የተለያዩ የታሪክ ምሁራን ከተናገሩት ፍፁም የተለየና አዲስ የጥናት ውጤት ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡ የሁለቱ ቋንቋዎች አመጣጥም በጥናቱ ተካቷል ብለዋል። በሊንከን ዩኒቨርሲቲ በሂዩማኒቲስ የትምህርት ዘርፍ የሚያስተምሩት ፍቅሬ ቶሎሳ ፤ከዚህ ቀደም ‹‹Heaven to Eden›› እና ‹‹The Hidden and untold History of the Jewish People and Ethiopians›› የሚሉ መጽሐፍትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሙ ሲሆን ሁለቱም በኢንተርኔት “አማዞን” በተባለ የመፅሃፍ ሽያጭ ድረገፅ ላይ ከተፈላጊ መፃህፍት ተርታ ተሰልፈዋል፡፡ በሙያቸው ፀሃፌ-ተውኔትና የሥነ ፅሁፍ ምሁር ሲሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግም ይታወቃሉ፡፡

(ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ – የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር)

(ፍቅሬ ቶሎሳ፥ ፒ ኤች ዲ – የሁማኒቲስ ፕሮፌሰር)

አንጋፋው ምሁር ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በቅርቡ ለንባብ ባበቁት “አዳፍኔ” የተሰኘ መፅሃፋቸው ላይ፤“የኦሮሞን ታሪክ ሙሉ አደርጎ ሊፅፍ የሚችለው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ብቻ ነው” ሲሉ ለብቃታቸው ምስክርነትና ዕውቅና መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ በርካታ ቲያትሮችን ለደረክ ያበቁ ሲሆን ከእነዚህም መካከል “ጓደኛሞቹ”፣ “ፍቅር በአሜሪካ” እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በቅርቡም ‹‹ላሟ›› የተሰኘ ባለ ሁለት ገቢር ቲያትር ፅፈው ማጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሠሩ ለአጭር ጊዜ ዕረፍት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበረ ሲሆን ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር በታሪክ ጥናቶቻቸው ዙሪያ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡

በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሟቸው “Heaven to Eden” እና “The Hidden and untold History of the Jewish People and Ethiopians›› የሚሉት መፃህፍት በአለማቀፍ ደረጃ ሰፊ ተቀባይነት ያገኙበት ሚስጥር ምንድነው? በምን ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው የሚያተኩሩት?
የመፅሐፍቱ ይዘት ነው ወሳኙ፡፡ ተቀባይነት ያገኙት በቋንቋ አጠቃቀም ለአንባቢያን ምቹ ስለሆኑ ይመስለኛል፡፡ በአይሁዶች ታሪክ ላይ የሚያተኩረው መፅሐፍ፤በጉዳዩ ላይ ከተጻፉ ሌሎች መጻህፍትና በተለምዶ ስለ አይሁዶች ከሚታወቀው ምን የተለየ ነገር ይዟል? ብዙ ጊዜ ስለ አይሁዳውያን ሲወራ፣ቀዳማዊ ሚኒልክ የዛሬ 3ሺህ ዓመት፣ 40ሺህ አይሁዳውያንን ይዞ መጣ የሚለውን ነው የምናውቀው፡፡ ከመጡት መካከል 12ሺህ ያህሉ ንፁህ እስራኤላውያን ናቸው። 28ሺህ ያህሉ እነሱን በሥራ ያገለግሉ የነበሩ ኢያቡሳውያን የሚባሉ ነገዶች ናቸው፡፡ ቀዳማዊ ሚኒልክ ለ12 ሺህዎቹ ልዩ ቦታ ሰጥቷቸው፣ በሀገሪቷ ላይ ካህናት አድርጎ ታቦት እያስቀረፀ፣ ኢትዮጵያ ላይ በዚህ መልክ ሾሟቸው ነበር፡፡ ኢያቡሳውያን ደግሞ ንጉሱን በእጅ ስራና በውትድርና ያገለግሉት ነበር፡፡ ይሄ እንግዲህ አይሁዳውያን ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት ሁለተኛው ፍልሰት ነው፡፡

የመጀመሪያውና ብዙም የማይነገረው የአይሁዳውያን ፍልሰት፣ የእስራኤላውያኑ መሪ ሙሴ በህይወት እያለ አባ ብሄር የሚባል ልኡል ነበር። የሙሴ አማች ነው፡፡ አባ ብሄር የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሊሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፣አይሁዳውያን ተከትለውት መጥተው ነበር፡፡ ምክንያቱም አባ ብሄር ያገባት ልጅ የሙሴ እህት ነበረች፡፡ ሙሴ በወቅቱ ለአባ ብሄር ፅላት ቀርፆ እንዲሁም ቀይ ባህርን የከፈለባትን በትር ሰጥቶት፣ወደ ሳባ ከተማ መጥቶ ነግሷል፡፡ በወቅቱ ብዙ አይሁዳውያንም ተከትለውት መጥተው ነበር፡፡
ሶስተኛው ፍልሰት የምንለው፣የኢራቁ ናቡከደነፆር አሸንፏቸው በሚያሳድዳቸው ጊዜ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ አይሁዳውያን ወገኖች አሉን” ብለው ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፡፡ አይሁዳውያን በነዚህ መንገዶች ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፡፡ ትክክለኛዎቹ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ ያሉት ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ…? የሃይማኖታቸውን ስርአት፣ መፅሃፍትና ህግጋት ከመጠበቃቸው አንፃር ከሌላ ህዝብ ጋር ስላልተደባለቁ ትክክለኛው ያለው እነሱ ጋ ነው፡፡ ሌሎቹ ወደ አውሮፓ፣ እስያ፣ አሜሪካ የተሰደዱት እነዚህን ነገሮች በተለያዩ ጫናዎች የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ጠብቀው አላቆዩትም፡፡ ወደዚህ የመጡት ግን በግድ ባህላችሁን ሃይማኖታችሁን ለውጡ ተብለው በኢትዮጵያውያን አልተረበሹም፤ነፃነት ነበራቸው፡፡ መሬትና ሁሉ ነገር የተመቻቸላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነበር፡፡ ሌላ አገር ላይ ቦታ እንዳይኖራቸው ተደርገው በየጊዜው ይሰደዱ ነበር፡፡

እንደውም በሩሲያ ውስጥ በድንገት አይሁዳውያንን የመግደል ድርጊት ይፈፀም ነበር። ሩሲያውያኑ ተሰባስበው፤“ዛሬ አይሁዳውያንን ገድለን እንምጣ” እያሉ ይዘምቱባቸው ነበር፡፡ ወደ መንደራቸው ሄደው አውድመዋቸው ይመለሳሉ፡፡ ማንም ስለማይበቀልላቸው ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ ነበር የሚቀረው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከተሰጣቸው ክብር የተነሳ በትንንሽ ንጉስነት ጭምር ይሾሙ ነበር፡፡ በርካቶቹም ካህናትና ሊቀ-ካህናት ተደርገው ለአይሁድ እምነት ተሹመል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የሰለሞን ዘር ነን በሚሉት ውስጥም ገብተው፣ ስርወ መንግስት እስከ መመስረት የደረሱ ነበሩ፡፡ በዓለም ላይ አይሁዳውያን ደልቷቸው የኖሩት ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ነው፡፡ በጠቅላላው በኢትዮጵያ ሀገራት ማለትም፡- በግብፅ፣ የመን፣ ኑቢያ—ኢትዮጵያ ባስተዳደረቻቸው አካባቢዎች በሙሉ በክብር ተይዘው ነው የኖሩት፡፡ ትልቁ ማስረጃ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ፣ እናቱ ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ በስደቱ ዘመኑ እኛ ጋ ብቻ ነው ጥገኝነት ያገኙት። በወቅቱ ግብፅ ለሁለት ተከፍሎ ነበር፡፡ አንዱ ክፍል በሮማውያን ቁጥጥር ስር ነበር፡፡ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነው፡፡ ኢየሱስ ከመወለዱ ከ880 ዓመት በፊት አማራዎች፤ አማሩላ ደልታ ወደሚባል ቦታ ሄደው፣ አክሱማይት የተባለውን ህፃን ልጅ ዙፋን በመጠበቅ ያገለግሉ ነበር፡፡ በኋላ በ800 ዓመታት ውስጥ አማሩላ ደልታ የሚባል መንደር መስርተው ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ጋርና ከቅዱስ ዮሴፍ ጋር ሲሸሹ፣ እዚያ ነው ማረፊያ ያገኙት፡፡ ይሄ መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፤እኛ ግን ከተለያዩ መዛግብት እናገኘዋለን፡፡ በወቅቱ የአካባቢው ንጉስ አማናቱ ተትናይ ይባላሉ፡፡ ከጎጃም ከጣና አካባቢ ነው ወደዚያ የሄደው፡፡ ሌላው አይሁዳውያኑ መፅሐፍ ቅዱሳቸው ሲጠፋባቸው ከኛ ነው የወሰዱት፡፡ አፄ ደንቀዝ የተባለው ንጉሰ ነገስት ነው ከግዕዝ ወደ እብራይስጥ አስተርጉሞ የሰጣቸው፡፡

ትክክለኛውን የአይሁድ ባህልና እምነት በመጠበቅ በኢትዮጵያ ያሉት አይሁዳውያን ብቸኞቹ ናቸው ማለት ይቻላል? አዎ! ኦሪትን ይዘዋል፡፡ ግን በደማቸው ከኛ ተደባልቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ሃበሻ የተባሉት። ሃበሻ ማለት የተደባለቀ ነው፡፡ “አበሳ” ያለበት ወይም እንከን ያለበት ማለት ነው፤ ሃበሻ ማለት፡፡ በቀዳማዊ ሚኒልክ ጊዜ የመጡት ከኛ ጋር ተደባልቀው 560 ዓመት ከቆዩ በኋላ በባቢሎን ስደት ጊዜ ሶስተኛዎቹ ሲመጡ፣ነባሮችን ሲያዩአቸው በመልካቸው አይሁዳውያንን አልመስል አሏቸው። ስለዚህ፤“እናንተማ ክልስ ናችሁ፤አበሳ አለባችሁ” ብለው ይሰድቧቸዋል፡፡ ነባሮቹ አይሁዶች ደግሞ፤ “እናንተ ፈላሾች፤እኛ ሀገር አለን” እያሉ ይሰድቧቸው ነበር፡፡ በዚህም “አበሻ” እና “ፈላሻ” የሚለው መጠሪያቸው ሆነ፡፡ “ሀበሻ” የሚለው ቃል እኛን አይወክለንም የምለው ለዚህ ነው፤ሀበሻ አይሁዳውያኑን ነው የሚወክለው፡፡ እኛ የኢትዮጰያ ልጆች ነን፤ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡
“በሃበሻነቴ እኮራለሁ” ስንል የከረምነውስ—–ቀለጠ ማለት ነው? አዎ! እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ ሀበሻ አይደለሁም። ሀበሻ የሚለው ቃል የስድብ ቃል ነው፡፡ እኛን አይወክለንም፡፡ አይሁዳዊ ካልሆነ በስተቀር አንድ ሰው ራሱን “ሀበሻ ነኝ” ብሎ ሊጠራ አይገባውም። ስድብ አያኮራም፡፡ ብዙ ሰው ስለማያውቅ ነው በሀበሻነቴ እኮራለሁ የሚለው፡፡ በአረብኛም ብናየው “የተደባለቀ”፤ “ንፁህ ያልሆነ” ማለት ነው። ይሄ መልካም ቃል አይደለም፡፡ ግን ሀበሻ የሚለው “አበሳ” ከሚለው እንጂ ከአረብኛ የመጣ አይደለም። ሁለቱ አይሁዳውያን መሃል ያለ የመሰዳደቢያ ቃል ነው እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያንን አይመለከተንም፡፡

‹‹ኢትዮጵያ›› የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
ኢትዮጵያ የሚለው ‹‹ኢትዮጵ›› ከተባለው ሰው የመጣ ነው፡፡ ኢትዮጵ ማን ነው ካልን፣ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰው መልከፀዴቅ የሚባል የሳሌም ንጉሰ ነገስትና ሊቀካህን ነበር፡፡ ይህ ሰው ሃገር ያስተዳድራልም፤ሃይማኖትም ይመራል፡፡ እሱም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነበር፡፡ ይሄ እንዴት ይሆናል ከተባለ፣ኢየሱስ በምፅአት ቀን ሲመጣ፣ የንጉስ ንጉስ፣ የካህን ካህን ሆኖ ነው፤መልከፀዴቅም የዚህ ምሳሌ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ከዚሁ ጋር ምን ያገናኛታል ሊባል ይችላል፡፡ በጣም የሚያኮራ ግንኙነት አለው፡፡ የመልከፀድቅ ልጅ ኢትኤል ይባል ነበር፡፡ እግዚአብሔር ኢትኤልን ካለህበት የሳሌም ምድር ለቀህ ጣና ላይ ስፈር አለው፡፡ ‹‹ከዚያም ያንተ የልጅ ልጆች፣ እኔ ከ2000 አመታት በኋላ በምወለድበት ጊዜ በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ስለ መወለዴ ኮከብ አሳይሃለሁ” ይለዋል (እንደኔ ምርምር፤ይሄ ኮከብ የተባለው መልአኩ ገብርኤል ነው) በዚህ ሁኔታ ኢትኤል አሁን ወዳለችው ኢትዮጵያ ሲደርስ እግዚአብሔር፤‹‹ኢትዮጵ›› ተብለህ ተጠራ አለው፡፡ ‹‹ኢት›› – ስጦታ ማለት ነው፡፡ ‹‹ዮጵ” – ማለት ደግሞ ቢጫ ወርቅ ነው፡፡ ስለዚህ “ቢጫ ወርቅ ስጦታ” ተባለ፡፡ በኋላ ሃገሪቷን ኢትዮጵያ አሠኛት፡፡

በመፅሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ተብሎ የሚጠቀሰው ስም የትኛዋን ኢትዮጵያ ነው የሚወክለው? እሱ አሁን ያለችውን ኢትዮጵያን ነው የሚወክለው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ እስከ 13ኛው ክ/ዘመን ድረስ ለመላዋ አፍሪካ መጠሪያ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ በኋላም የመጣው አፍሪካ የሚለው ስም ከዚሁ ከኢትዮጵያ የተገኘ ነው፡፡ ከአፋሮች ነው አፍሪካ መጠሪያዋን ያገኘችው፡፡ በመፅሃፈ እዝራ ምዕራፍ ስድስት ላይ፤‹‹አፍሪካንሳውያን›› ይላል፡፡ ይሄ አፋሮችን ነው የሚወክለው፡፡ በመርከብ ስራ በቀይ ባህር ላይ የተራቀቁ ሰዎች ነበሩ፡፡ የዛሬ 3ሺህ አመት ንጉስ ሰለሞን ቤተመቅደሱን ሲሰራ፤ልዩ እንጨት፣ እጣን፣ ወርቅ (ኦፊር የተባለ ታዋቂ ወርቅ- በነሱ የተሰየመ) ጭምር ይነግዱና ለንጉሡ ያቀርቡ ስለነበር፣ስማቸው የገነነ ሆኖ አፍሪካንሳውያን የተባሉት፡፡ በሳይንሱም አፋር የሰው ዘር መገኛ እያልን ነው፡፡ ኢስያውያንም ስያሜያቸውን ያገኙት ከሣባ ቀድሞ ከነገሰው ‹‹ኢስአኤል›› ከተባለው ንጉስ ነው፡፡ ምድሪቱን ያስተዳድር ስለነበር ኢስያ ተባለች፡፡ ‹‹አፄ” የሚለውም ከዚህ የመጣ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሚለው ከግሪክ ቃል የመጣ ነው የሚለውስ —?

ኢትዮጵያ የሚለው ከግሪክ ቃል የመጣ ነው የሚለው ውሸት ነው፡፡ ይሄን አጣርቻለሁ፡፡ በነሱ መዝገበ ቃላት ውስጥ ይሄ ቃል የለም፡፡ ‹‹ፊቱ የተቃጠለ›› የሚለው ቃል በግሪክ ቋንቋ ኢትዮጵያ የሚለውን ሳይሆን ሌላ ትርጉም ነው የሚኖረው፡፡ ግሪኮቹ ከኛው ሰምተው ነው መልሠው ኢትዮጵያ ያሉን፡፡ እኛ ከነሱ በፊት ነበርን እንጂ እነሱ ከኛ በፊት አልነበሩም፤ ስማችንን ሊያወጡልን አይችሉም፡፡ በምርምርዎ አዳምና ሄዋን የተፈጠሩበት ቦታ የት ሆኖ አገኙት? ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ጎጃም፤ ዳሞትና ጣና አካባቢ ያለ ቦታ ነው፡፡
ለዚህ ድምዳሜ ማስረጃዎ ምንድን ነው? አንደኛ ኤደንን ከሚያጠጡ አራት ወንዞች ውስጥ አባይ የምንለው ነው ኤፌሶን የሚባለው። በኦፌር ወርቅ ዙሪያ የሚዞር መሆኑ ተፅፏል፡፡ በኔ ድምዳሜ፣የኤፌሶን ወንዝ የአሁኑ ዋቢ ሸበሌ ነው። ጤግሮስና ኤፈራጥስ ደግሞ ጊዮን ራሱ ጥንት ሜዲትራኒያን ባህር ይገባ ነበር፡፡ ድሮ ሜድትራኒያን “ኪቲ” ይባል ነበር፡፡ ጥንት ጊዮን ወንዝ ሜድትራኒያን ሲደርስ ተራራ ስለነበር ተጋጭቶ ይመለስ ነበር፡፡ ከዚያ ነው መሬት ተነቃንቆ፣ቦታው ተቆራርጦ አሁን ወዳለበት ኢራቅ የሄደው እንጂ አካባቢው እዚሁ ነበር፡፡

አዳም የት ተፈጠረ ለሚለው በመፅሃፈ ሄኖክ ላይ “ኤልዳ” በሚባል ቦታ ተፈጠረ ይላል፡፡ ኤልዳ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም አስሌዳውያን ወይም ኤልዳውያን የሚባሉ አሁንም ድረስ ጎጃም ውስጥ አሉ፡፡ ሄኖክ በመፅሃፉ ኤልዳ ነው የተፈጠረው ይላል፡፡ ከዚያ ወስዶ ነው እግዚአብሄር በ40 ቀኑ ወደ ኤደን ገነት የከተተው ይላል፡፡ ሄዋንን ደግሞ ከአዳም ጎን አውጥቷት ነው በ80 ቀኗ ወደ ኤደን ገነት የከተታት፡፡ ከዚህ ተነስቶ ነው ወንድ በ40፣ ሴት በ80 ቀን ክርስትና የሚነሱት። ይሄ አይነቱ ስርአት በዓለም ላይ የትም የለም፤እና ይሄ በሄኖክ መፅሃፍ የተፃፈውና አሁን ያለው እውነታ ይገኛል፡፡ ሌላው ኮሬብ የሚባል ዋሻ ውስጥ አዳም ተቀበረ ይላል፡፡ በእርግጥ በሲናይ በረሃ አካባቢ ኮሬብ የሚባል ቦታ አለ፤ ግን በተመሳሳይ ይህ ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥም አለ፡፡ ሌላው ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው ይላል፡፡ አራራት ተራራን ለመፈለግ ወደ ቦታው ሄጄ ነበር፤ በታንኳ ጣናን አቋርጬ፡፡ አራራት ተራራ የሚባለውን ሳገኘውና አቀማመጡን ሳጠናው፣ ለመርከብ ማሳረፊያነት በአናቱ ላይ ምቹ ሜዳ አለው፡፡ ኖህ ወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር ይላል፤መፅሃፍ ቅዱስ፡፡ በእርግጥም ቦታው የወይን ጠጅ ፍሬ ለማብቀል ተስማሚ ነው፡፡

አሁንም አትክልቶችና ጌሾ ይበቅልበታል፡፡ ከዚሁ ማስረጃ ሳልወጣ፣አዲስ አመትን አበቦች አብበው አከበረ፤የእንጨት መስዋዕትም አደረገ ይላል፡፡ ይሄ እንግዲህ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ ያለው የአዲስ ዓመት መቀበያ ስርአት፣ ከየት መጣነትን ሊያስረዳ ይችላል። በኋላ ወደ ክርስትናው የመስቀል በዓል ደመራነት ተለወጠ እንጂ በፊት ደመራ የሚነደው በአዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃው አሁንም ድረስ ክርስቲያን ያልሆኑ የሀገራችን ሰዎች የደመራ ስርአት አላቸው። ይሄ የአባታቸው የኖህ ትዝታ (ማስታወሻ) ነው ሲወረስ ሲዋረስ የመጣው፡፡ በዚህና በኖህ ጉዳይ ሰፊ ጥናት እያደረግሁ ነው፤ወደፊት ይፋ ይሆናል፡፡ አንድ እዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው፣ሌላ አራራት የሚባል ተራራ አርመን ውስጥ አለ፡፡ ተራራው ግን በረዶ ያለበት፣ ገደላገደል፣ እንኳን መርከብ ሊያሳርፍ ለሰው ልጅ የማይመችና የማያብብ ቦታ ነው፤ ስለዚህ ያ ሊሆን አይችልም፡፡ በሰንደቅ አላማው ላይም የተለየ መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡ ለኢትዮጵያ የተሰጠ ስጦታ ነው ሲሉ ምን ማለትዎ ነው? ሰንደቅ አላማው ለኖህ ከተሰጠው ምልክት የመጣ ነው፡፡ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የጎሉበት ቀለማት ሰማይ ላይ ታይተዋል፡፡ እነዚያ ቀለማት ናቸው ዛሬ ያሉት፡፡ ከንግስት ሳባ በፊት የነገሰው አፄ ኢሲአኤል ነው ሰንደቅ አላማ እንዲውለበለብ ያደረገው፡፡ ሰንደቅ አላማ የሚለው የመጣው የኢስአኤል መንግስት “ሰንደቅ አለማ” ከሚለው ነው፡፡ ከዚያ የመጣ ነው። እሱ በወቅቱ የመረጠው፡- አረንጓዴ ቢጫ፣ቀይና ሰማያዊ ቀለማት ነበር፡፡ ለሰንደቅ አላማው ያልተገዛና ያላውለበለበ ይቀጣል ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ አስገዳጅ ህግ ያወጣውም እሱ ነበር፡፡ በሰንደቋ አናት ላይ ኮከብ ነበር የሚቀመጠው፡፡ ኢየሱስ ሲወለድ የሚጠቁመውን ኮከብ ለማስታወስ ይጠቀም ነበር፡፡ በዓለም ላይ ሰንደቅ አላማን የፈለሰፈ የመጀመሪያው ሰውም ሊሆን ይችላል፡፡

የኢትዮጵ የልጅ ልጅ የሆነው ኢስአኤል ከፈለሰፈው ሰንደቅ አላማ ነው፣ዛሬ ያሉት የሰንደቅ አላማ ቀለማት የመጡት፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰንደቅ አላማው ላይ ከዚህ ተነስቶ አንድ አይነት አቋም ቢይዝ መልካም ነው፡፡ ኢስአኤል ለኦሮሞውም፣ ለአማራውም፣ ለትግሬውም፣ለአፋሩም ለሌላውም ብሄረሰብ ሁሉ አባት ነው፡፡ ከአባቶቻችን የወረደ ሰንደቅ አላማ እንጂ ከባዕድ የመጣ አይደለም፡፡ ሰውየው እጅግ ጠቢብ ነበር፤ልእለ ሰብዕ (superman) ነበር፡፡ 150 አንበሳ መግደሉን ለማስታወስ ጭምር አፄ ኢስአኤል የሰብዕ እና የአውሬዎች ንጉሰ ነገስት ብሎ ነበር ራሱን የሚጠራው፡፡ ሰውየው እጅግ ጠቢብ ከመሆኑ የተነሳ የጀነቲክ ኢንጅነሪንግን የፈለሰፈውም እሱ ነው፡፡ እንስሳን ከእንስሳ፣ ዘርን ከዘር እየቀላቀለ የፈለሰፈ የመጀመሪያው የጀነቲክ ኢንጅነር ነበር። በቅሎን የፈጠረውም እሱ ነው፡፡ አህያንና ፈረስን አዳቅሎ፡፡ ይህ ሰው የሁሉም ኢትዮጵያውን አባት ነው፡፡ የኢትዮጵ ልጅ ነው፡፡ የኢትዮጵ 10 ወንዶች ልጆች ናቸው፤ አሁን የምናያቸውን የኢትዮጵያውያን ጎሳዎች ሁሉ የፈጠሩት፡፡

ሰሞኑን ለአንባቢያን የሚቀርብ መፅሃፍ እንዳዘጋጁም ሰምቼአለሁ፡፡ የመፅሐፉን ይዘት በአጭሩ ሊነግሩኝ ይችላሉ? መፅሐፉ፤“የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የሚል ነው፡፡ አሁን ያሉት ኢትዮጵያውያን በሞላ የኢትዮጵ ልጆች መሆናቸውን ከላይ አስረድቻለሁ፡፡ አሁን እንደምናው በሁላችንም ላይ የማንነት ቀውስ አለ፡፡ የማንነት ቀውሱ የመጣውም እኛ ማን እንደሆንን በትክክል ባለማወቃችን ነው፡፡ ስለዚህ ይህ መፅሐፍ እኛ ማን እንደሆንን፣በርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎችና ሰነዶችን አስደግፎ፣ግልጥልጥ አድርጎ ያስረዳናል፡፡ ይህ የማንነት ቀውሳችን ከተስተካከለና ራሳችንን ካወቅን፣ በመካከላችን ግጭቶች ሊኖሩ አይችሉም፡፡ መፅሐፉ፤ፍቅር፣ ሰላምና ህብር ሊፈጥር ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እኛ የትልቅ ሰው ዘር ነን የሚለውን በማስረጃ የሚያሳየን ነው፡፡ የሰው ዘር ምንጭ ናሙናዎች መሆናችን ይተነትናል፡፡ ማንነታችንን በትክክል ተረድተን፣ አንድ ላይ ለመጓዝ ያስችለናል ብዬ አስባለሁ – ይህ ብዙ የተደከመበት የምርምር ውጤት፡፡

የኦሮሞና የአማራ የዘር ሀረግ አንድ ነው የሚለውን ነው መፅሃፉ የሚያስረዳው? አማራና ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በኢትዮጵያ ግዛት ያለው ብሄር፣ ጎሳ ከ10ሩ የኢትዮጵ ልጆች ነው የመጣው፡፡ ዝቅ ሲል ደግሞ የኢትዮጵ የልጅ ልጅ የሆነ፣ ጎጃም ላይ አዳምና ሄዋን ተፈጥረዋል ብዬ ባልኩት አካባቢ አንድ ጠቢብ ሰው ነበር፡፡ “ደሴት” ወይም “ደሸት” ይባላል፡፡ እሱ ነው የኦሮሞና የአማራ አባት፡፡ የዛሬ 3600 ዓመት 4 ወንዶች ልጆች ወለደ፡- መንዲ፣ መደባይ፣ ማጂ፣ ጅማ የሚባሉ፡፡ እነዚህ 4ቱም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሀገር መጠሪያ ሆነዋል። ማጂ ደግሞ ማራ እና ጀማን ይወልዳል። ዛሬ አማራ የምንለው ማራ ነው፡፡ “ማራ” ማለት “እውነተኛ ብርሃን” ማለት ነው፡፡ አማራ ያሉት አጋዚያን ወይም የግዕዝ ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ ማጂ ማራን ወለደ ካልን፤ ጀማ እና ማራ ወንድማማቾ ናቸው፡፡ ሁለቱ ወንድማማቾች በአካባቢው ካሉት ጋፋቶች ጋር መዋጋት ሰልችቷቸው፣ ሃገር ለቀው ወደ ሸዋ ሲመጡ አንድ ወንዝ ያገኛሉ፡፡ ወንዙን ጀማ አሉት። አሁን የጀማ ወይም የ“ዠማ” ወንዝ ማለት ነው። ከአካባቢው እየራቁ ሲሄዱ የጥንት አባቶቻቸውን ቋንቋ “ሱባ”ን ትተዉ አማርኛን መፈልሰፍ ጀመሩ፡፡ መደባይ፣ ጅማና መንዲ ደግሞ ግማሾቹ ጎጃም ላይ ቀሩ፤ ግማሾቹ ወለጋ ሄዱ፤ሌሎቹም እየራቁ በምስራቅ አፍሪካ ተሰራጩ፡፡ ኦሮሚኛ ቋንቋ የሚባለውንም ፈጠሩ፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው ዛሬ ያሉት ኦሮሞና አማራ የመጡት፡፡ ዘረ ደሸት ይባላሉ፡፡ የደሸት ልጆች ናቸው። የዘር ሀረጋቸው አንድ ነው፡፡ ቋንቋቸው የተለያየ የሆነው በሂደት ነው፡፡

ኦሮሞው የኩሽቲክ፣ አማራው የሰሜቲክ ዘር ናቸው፤ የመጡትም ከውጭ ነው የሚለው ለዘመናት የዘለቀ ታሪክስ …? እሱ ፈፅሞ ውሸት ነው፡፡ ሁለቱም ከውጭ አልመጡም፡፡ እንዳስረዳሁት እዚሁ የበቀሉ ናቸው። የአማራም የኦሮሞም አባት ደሸትም ሆነ ታላቁ አባት ኢትዮጵ ኩሽ ነው፡፡ መልከፀዴቅም ኩሽ ነው። ኦሮሞና አማራ ሁለቱም ኩሽ ናቸው፡፡ አማራ ሴም አይደለም፤ ኩሽ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ሲነገር የነበረው ውሸት ነው። ምናልባት የአማርኛ ቋንቋ ከሌሎች ጋር ሲደበላለቅ ሴሜቲክ ቤተሰብ ውስጥ ተገኝቶ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ኢትዮጵያውያን የኩሽ ዘሮች ናቸው። በዚሁ መፅሐፌ ላይ ስለ ቋንቋም አስረድቻለሁ፡፡ በእብራይስጥም ሆነ በአረቢክ የሌሉ እንደ ጨ፣ቀ፣ፀ ያሉ ድምጾች በአማርኛና በኦሮሚኛ ቋንቋ ውስጥ አሉ። ይሄን በዝርዝር በመፅሐፉ አስቀምጫለሁ፡፡ ኦሮሞና አማራ አንድ ነው የሚለው አመለካከት በተለይ በኦሮሞ ምሁራን ዘንድ እምብዛም ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም፡፡ በግድ ኦሮሞን አማራ ለማድረግ ነው በሚል ወቀሳ የሚሰነዝሩ አሉ … እንዲህ የሚሉት ሁሉም ከኢትዮጵ ዘር የመጣው የደሸት ልጆች መሆናቸውን ባለማወቃቸው ነው። ይሄ መረጃ ስለሌላቸው ራሳቸውን እንደ ባዕድ አግልለው ስለሚያዩ ነው እንጂ አሁን ይሄ እኔ ያቀረብኩትን ማስረጃ በቅን ልቦና አገናዝበው ለመረዳት ከሞከሩ፣ የትልቁ ሰው የኢትዮጵ፣ የጠቢቡና የሊቀካህናቱ የደሸት ልጅ እንደሆኑ በሚያውቁ ጊዜ፣ እነሱ እንደተሳሳቱ ተገንዝበው ወደ ማንነታቸው ላይ አተኩረው ይኮሩበታል ብዬ አስባለሁ፡፡ የመጣነው ከትልቅ ዘር ነው፡፡ ኦሮሞውም አማራውም የመጣው ከዚህ ትልቅ ሰው ነው፡፡ በዚህ ሁላችንም ልንኮራ ይገባናል፡፡
የአሁኗ እና የቀድሞዋ ኢትዮጵያ ልዩነታቸውና አንድነታቸው ምንድን ነው? በግዛት ከሄድን ጥንት መላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ነው የሚባለው፡፡ ከየመን አልፎ ሁሉ ይሄዳል፡፡ ግብፅ ውስጥ ፈርኦኖች የሚባሉት ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአባይ ላይ ከመርከብ ወርደው ሜዳ አግኝተው የሰፈሩበት ቦታ ነው፤ ግብፅ፡፡ የአፍሪካ ሁሉ ነገር ከኛ አይወጣም፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ የ3ሺህ ዘመን ነው ይባላል፡፡ እርሶ የደረሱበት የጥናት ውጤት ምን ይላል?አዎ፤ በተለምዶ 3ሺህ አመት ይባላል እንጂ ከ7ሺ በላይ ነው፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፡፡ ኖህ ኢትዮጵያ ላይ ነግሷል፤ ከዚያ ጀምሮ 7ሺህ አመት ነው፡፡

እስካሁን በነገሩን ታሪክ ውስጥ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው በማስረጃነት የሚጠቅሱት፡፡ መፅሐፍ ቅዱስን ብቻ የታሪክ ምንጭ ማድረግ ይቻላል? መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ አይደለም፡፡ 42 ሰነዶችን አሁን በሚወጣው መፅሐፌ ላይ በግልፅ አስቀምጫለሁ። እነዚህ ሰነዶች በተለያዩ ሰዎች በጥንት ጊዜ የተፃፉ ናቸው፡፡ ኑቢያ ውስጥ ጀበል ኑባ በተባለ ቦታ ተቀብረው የቀሩ፣በጥንት ፍርስራሽ የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን (ከእስልምና በፊት የነበረ) ድንጋይ ሳጥን ውስጥ ተቀብረው የነበሩ የብራና ሰነዶች አግኝቻለሁ፡፡ በዚያ ላይም የተመሰረተ ነው። ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ 42 ተጨማሪ የታሪክ ሰነዶችን ተጠቅሜያለሁ፤ይሄን መፅሐፍ ሳዘጋጅ፡፡ ቀጣይዋ ኢትዮጵያ ምን መምሰል አለባት ይላሉ? አሁን ማንነታችንን አውቀን፣ የማንነት ቀውሳችንን ፈትተን፣ሁላችንም የኢትዮጵያ ዘር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች—–መሆናችንን ተገንዝበን፤ በፍቅር፣ በሰላም፣ በመከባበር፣ በእኩልነት መኖር አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ ሁላችንንም ኢትዮጵ ያገናኘናል፡፡

የደህንነቱን አለቃ ጌታቸው አሰፋን ፎቶ አንስተሃል የተባለው የጥበቃ አባል የደረሰበት አልታወቀም ተባለ

$
0
0

Getachew-Assefa

ከልዑል ዓለሜ

ጌታቸዉ አሰፋ ብሄራዊ መረጃን በበላይነት መምራት ከጀመረበት ወቅት አንስቶ የእርሱን የፎቶ ግራፍ መረጃዎች በተመለከተ ከተለያዩ የኮምፒዉተር ኔት ወርክ ገጾች እና የግለሰብ ሰነዶች ማስረጃ ላይ በሙሉ ለማጥራት ብዙ ጥረት ከማድረጉ በተጨማሪ ተንቀሳቃሽ የምስል መረጃዎችንም በሙሉ ተለቅመዉ እንዲጠሩ ቀጫጭን ትእዛዞች ለሚመለከታቸዉ አካላት አስተላልፎአል:: በመሆኑም የደህንነቱ መረብ ጌታቸዉ አሰፋ በሚንቀሳቀስበት እና በሚገኝበት አካባቢ ላይ ምንም አይነት ተንቀሳቃሽም ሆነ የፎት ግራፍ ቀረጻ እንዳይካሄድ ከፍተኛ ክትትል ያደረጋል::

የብሄራዊ መረጃዉን አፋኝና ገዳይ ቡድን በቁንጮነት የሚመራዉ ጌታቸዉ አሰፋን ከካሜራ እይታ የመከላከል እና የመጠበቅ ሐላፊነት ማለት ግለሰቡን ከግድያ ሙከራ መከላከል ማለት ነዉ የሚል አቁዋም ያለዉን የደህንነት ብሂልን ተከትሎ ከፈተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን ይህን ሰዉ በካሜራ ቀርጾአል የተባለዉ የጥበቃ አባል በሰሞኑ በደህነቱ ሐይሎች ተጠልፎ የደረሰበት አለመታወቁን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል።
በካዛንቺስ አካባቢ ከተወሰኑ የደህንነት አባላት እና ከህወሃት የአመራሮች ጋር የአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በመሰለ ስፍራ ዉስጥ ተሰብሰበዉ የነበሩትን ጌታቸዉ አሰፋን ከስብሰባዉ ሲወጡ ጠብቆ በጥንቃቄ ፎቶ ሲያነሳ ታይቶአል የተባለዉ ጥበቃ በቁጥጥር ስር ከዋለ ወዲህ በተንቀሳቃሽ ስልኩ ዉስጥ በተደረገዉ ፈጣን ፍተሻ ላይ ምንም አይነት ምስል ባይገኝም የብሄራዊ መረጃዉ ከቴሌ ጋር ባደረገዉ የመስመር ስለላ መሰረት የጥበቃ አባሉ ፎቶ ግራፉን ካነሳ ወዲህ ምስሉን ወደ አልታወቀ አካል ማስተላለፉንና ከስልኩ ዉስጥ መረጃዎችን ማጥፋቱ በመረጋገጡ የጥበቃ አባሉ በደህንነቱ አካላት ትእዛዝ መሰረት ሊታፈን መቻሉን መረጃዎች አመልክተዋል።
ይህ የጥበቃ ሁኔታን ተንተርሶ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የጥንቃቄ ዘይቤ ለየት ባለ መልኩ ነገሮች መቀየራቸዉን ግምት ዉስጥ ያስገቡ የመረጃዉ አባላት ጌታቸዉ አሰፋ በዚህ ወቅት ላይ በእጅጉ ያሰጋቸዉ አንዳች የደህንነት ጉዳይ ይኖራል የሚል ጥርጣሬ አጭሮባቸዋል::
በአሁኑ ወቅት የደህንነት አባላቱ ዉስጥ ከፍተኛ አለመተማመን መፈጠሩን የገለጹልን ምንጫችን አያይዘዉ እነ ጌታቸዉ አሰፋ ብሄራዊ ደህንነት ከማስጠበቃቸዉ ይልቅ የራሳቸዉን ደህንነት በመጠበቅ ስራ ላይ ተጠምደዋል ሲሉ ተናግረዋል::
ድል አሊትዮጵያ ህዝብ !!

ክብደትን የመቀነስ ጥበብ |ካስተናጋጁማስታወሻ የተቀነጨበ –ከበእውቀቱ ስዩም

$
0
0

ያኔ ባቡር ሳይወጠን- የሃያ ሁለት ማዞርያ አየር ባስመረት ሽሮ ሳይታጠን -ዓባይን የደፈረው መሪ(ሆስኒሙባረክ)ሳይከነበል-ታምራት ገለታ ቃሊቲን ሳይዳበል- ታምራት ላይኔ ጌታን ሳይቀበል-ካገር ወጣሁ፡፡

Beweketu Seyoun joke about African leaders summit [Very Funny]

አሜሪካ እንደገባሁ በመጀመርያ የፈጸምኩት ተግባር ቢኖር መወፈር ነው፡፡ አትፍረድብኝ፡፡ አሜሪካ ውስጥ ሰው መንቀሳቀስ አቁሟል፡፡ ኑሮ ማለት ከሶፋ ወደ መኪና ፤ከመኪና ወደ አሣንሠር መንፏቀቅ ማለት ሆኗል ፡፡ ሁሉ ነገር የሚፈጸመው online ነው፡፡ ያሜሪካ ገበሬ ራሱ የሚያርሥና የሚያጭድ በላፕቶፑ ይመስለኛል፤ “ገብስዎን ለማጨድ ከፈለጉ አልቢን ማጭድ የሚለው ላይ ክሊክ ያድርጉ ” የሚል ላፕቶፕ ላይ ተጥዶ እየዋለ፤ ገበሬ ነኝ የሚል ስንት ፈረንጅ አለ(ሳልፈልግ ገጠመብኝ)

የሆነ ጊዜ ላይ፤ በዩንበርሲትያችን ውስጥ በሚገኘው ጂም ተመዝግቤ ስፖርት መሥራት ጀመርኩ፡፡ መሮጫ ማሽኔ ላይ ዱብ ዱብ እያልሁ፤ ካጠገቤ ባለው ማሽን ላይ ከሚሠግረው ናይጄርያዊ ጋር ሲያቀብጠኝ ራሴን አወዳድራለሁ ፡፡ መጀመርያ የብሄራዊ ስሜት እየገፋኝ( ከአበበ ቢቂላ አገር መጥቶ እንዴት በቀላሉ ያለከልካል እንዳልባል) ጥርሴን ነክሼ እሄን ሩጫ አስነካሁት ፡፡ እግርና ሳንባ ለብሄራዊ ስሜት ግድ እንደሌላቸው ያወኩት ሃያ ደቂቃ ከሮጥኩ በኋላ ነው፡፡ ሰው ያበበ ግደይን ተሰጥኦ ይዞ እንደአበበ ቢቂላ ካልሆንኩ ብሎ ይሟሟታል? ድንገት ትንፋሼ ብትን ብትን ይላል፡፡ የእንግላል እንዳልወድቅ የማሽኑን መደገፍያ እመረኮዛለሁ ፡፡ ጥቂት ቆይቸ ራሱ ናይጄርያዊውን ሰውየ እደገፋለሁ፡፡ ናይጄርያዊው ሁለት እግር ያለው ፈረስ ማለት ነው፡፡ የማሽኑ ሞተር ከጠፋ በኋላ እንኳ መሮጡን አያቆምም፡፡ በኋላ በጣም መረረኝ፡፡ ትንሽ ፈርገጥ ፈርገጥ ካልኩ በኋላ በጂሙ አዳራሽ ውስጥ በተሰቀለው ቲቭ ላይ የሚተላለፈውን ፊልም ስመለከት ውየ ወደ ቤቴ መመለስ ጀመርኩ ፡፡ ለኔ ጂም ቤት መግባት ማለት የስፖርት ቱታ ለብሶ ሲኒማ ቤት እንደመግባት ሆነ።

ደሞኮ አላፍርም፤ እንደ ሰዎች ሴክሲ ሆኖ መታየት ያምረኛል፡፡ ላፕቶፔ ላይ ቦርጭ የሚያጠፋ ሶፍትዌር ጭኘ ፤ ፎቶዎቼን ሸንቀጥ እያደረግሁ ፌስቡክ ላይ መለጠፍ ጀመርኩ፡፡ ምን ዋጋ አለው፡፡ ባለፈው አንዱ ከኔ ጋር የተነሣውን ፎቶ እንደወረደ ለቀቀው፡፡ ዘውዳለም ታደሰ የተባለ ያዲሳባ ተራቢ ያን ፎቶ አይቶ “ኧረ የኬንያ ፖሊስ መሰልክ ”ብሎ ከተረበኝ በኋላ የገዛ ሰውነቴ እንደ ወህኒቤት ዩኒፎርም ቀፈፈኝ ፡፡ የኬንያ ፖሊስ ይሄን የበቆሎ ገንፎ እየነፋ ፤እንደ ዋርካ ስለሚሰፋ ሌባን መጠቆም እንጂ ሌባን አባርሮ መያዝ አይችልም ይባላል፡፡( ምነው የማይመለከትህን የኬኒያ ፖሊስ ላይ ችክ አልህ? አለኝ አንዱ አሁን በኢኖቦክስ ፡፡ እና ሃያ ሁለት ማዞርያ እየኖርኩ ፤ ሰማንያ ዓመት ለመኖር እያቀድኩ፤ ያዲሳባን ፖሊስን እንድተች ትጠብቃለህ?)
አገሬ በገባሁ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ዘጠኝ ኪሎ ቀነስኩ፡፡ ሸገር ውስጥ ያ ሁሉ ከብት እያለቀ ፤ያ ሁሉ ሥጋ እየተበላ ሰው የማይወፍርበት ምንያት የገባኝ አሁን ነው፡፡ ያዲሳባ የኑሮ ውጣ ውረድ በራሱ የማይፎረሽበት ጅም ነው ወንድሜ ፡፡ መታወቂያ ለማውጣት የሆነ ቢሮ ሂድ፡፡ የሆነች ሴትዮ ትቀበልህና “ ሁለተኛ ፎቅ ሄደህ ክፈል” ትልሃለች ፡፡ እየተቅመደመድህ ትወጣለህ፡፡ እዚያ ስትደርስ አንዱ ይቀበልህና “ ይህን ደረሰኝ ይዘህ አራተኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው ሥራ አስኪያጅ ቢሮ ሂድ ፤ ማህተም ያደርግልሃል“ ይልሃል፡፡ እያለከለክህ እዚያ ስትደርስ፤ የባለማህተሙ ጸሀፊ ትቀበልህና “ሥራ አስኪያጁ ለሥራ ወጥተዋል፡፡ እስኪመለሱ ድረስ ሰባተኛው ፎቅ የሚገኘው ካፌ ሻይ ቡና እያልህ ቆይ፡፡”ትልሃለች ፡፡ ያዲሳባ ፎቅ ለወጉ ሊፍት ተገጥሞለታል፡፡ ግን ሊፍቱ ጥቂት ሠርቶ በመብራት ኃይል ስፖንሰር አድራጊነት ወደ እቃ መጋዘንነት ይቀይራል፡፡ሰባተኛው ፎቅ ላይ እስክትደር አንድ ሦስት ኪሎ ቀንሰሃል፡፡ እና እዛ ቁጭ ብለህ ሻይህን ፉት እያልህ ”አተት ሰባት ሰዎችን ገደለ”የሚል ዜና ሲተላለፍ በቲቪ ታያለህ፡፡ ስምንተኛው ያተት ሰማእት አንተ ልትሆን እንደምትችል ታስብና በስጋት ሌላ ሁለት ኪሎ ትቀንሳለህ፡፡ ከዚህ ሁሉ ወደ ጎረቤት አገር ዞር ብየ ለእናት አገሬ ብተርፍላት አይሻልም? ብለህ ማሰብ ትጀምራለህ፡፡ የህይወቴ ቤዛ፤ እንደምነሽ ቪዛ?

ቪዛ ስል የሚከተለው ትዝ አለኝ፡፡
የሆኑ ሽማግሌ እንደነገሩኝ በኃይለሥላሴ ጊዜ ላንድ ኢትዮጵያዊ ቪዛ ማግኘት፤ ወደ ፍኖተ ሰላም የሚሄድ አውቶብስ ትኬት ከማግኘት በጣም ይቀል ነበር፡፡ ሽሮሜዳ አካባቢ በእግርህ እየተንሸራሸርህ ትንሽ ካካፋ ዝናቡ እስኪያባራልኝ ለምን ቪዛ አልጠይቅም? ብለህ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ ጎራ ማለት ነው፡፡ አምባሳደሩ በቢሯቸው ተቀብለውህ አሪፍ ቡና እየጋበዙህ ኩኪሱን ገፋ እያደረጉልህ “ አንተ ወጣት ኢትዮጵያዊ ወደ አሜሪካ ለመሄድ ስለፈቀድህ በጆን ኤፍኬኔዲ ስም የተሰማኝን ደስታ እገልጽልሃለሁ፡፡ የማትቸኩል ከሆነ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ፡፡ ለመሆኑ ቪዛውን የት ላይ ብመታልህ ትመርጣለህ? ፓስፖርትህ ላይ ወይስ የቀበሌ መታወቂያህ ላይ? ”
አለቀ፡፡
ዛሬ የኢምባሲ ጥያቄዎች ምን ብለን ጠይቀን እንጣለው የሚሉ ነው የሚመስሉ ፡፡ ለምሳሌ የቺስታ አገር ዜጎች እንደሆንና ገንዘብ ለመሥራት እንደምንሄድ እያወቁ የባንክ ደብተራችንን ለምን እንደሚጠይቁን አይገባኝም፡፡ የዛሬ ምናምን አመት ክበበው ገዳና ተስፋየ ካሳ ከኢምባሲ ኢምባሲ ይንከራተቱ ነበር፡፡ አንዴ ፤ ጀርመን ኢምባሲ ገብተው ጥያቄ በጥሩ መንገድ ሲለመልሱ ከቆዩ በኋላ
“ተቀማጭ ገንዘብ ካላችሁ ልታሳዩ ትችላላችሁ?“ ስትል ጠየቀች ጀርመኒቱ፡፡

ተስፍሽ ፈጠን ብሎ መለሰ፡፡ “

“ጀርመን ደርሰን ስንመጣ ማሳየት እንችላለን”
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሁለቱ ቺስታ ኮመድያኖች እንደማሽላ ኣንገታቸውን ደፍተው ከኢምባሲ ወጡ፡፡ ያካባቢው ጎረምሶች ከበቧቸው፡፡
“ሰጧችሁ?ሰጧችሁ?” አሉ ጎረምሶች፡፡
“አዎ “ አለ ክበበው አንገቱን እንደደፋ “ ፓስፖርታችንን ሰጡን ”

በጎንደር ብአዴን እና ሕዝቡ ያደረገው ስብሰባ ተጠናቀቀ

$
0
0

selamawi selef

ግርማ ካሳ

ሐምሌ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከሰሜን ጎንደር ሕዝብ የተወጣጡ ሽማግሌዎች ከብአዴን ባለስልጣናት ጋር ዉይይት ማድርጋቸው ይታወሳል። በዚህ ወይይት ሐምሌ 17 ቀን በጎንደር ሰልፍ እንደሚደረግ ሽማግሌዎች ባሳወቁት መሰረት የብአዴን ባለስልጣናት ሰልፉ ለ10 ቀናት እንዲራዘም መጠየቃቸውም ተዘግቧል።

ሰልፉ ለሐምሌ 24 ቀን እንዲሚደረግ ዘገባዎች በስፋት እየጠቆሙ ሲሆን አቶ በረከት ስምኦንን እና የክልሉ አስተዳዳሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ያካተተ የብአዴን አመራር ከሕዝቡ ጋር በጎንደር ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት መወያየታቸዉንም ለማወቅ ተችሏል።

ከስፍራው የደረሱ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በስብሰባው የሕዝቡን አቋም ያንጸባርቁ የነበሩ ሲሆን፣ አቶ በረከትም ከሕዝቡ የተነሱ ብሶቶችና ጥያቄዎችን በማስታወሻ ደብተራቸው ላይ ማስፈራቸዉን ጠቁመዋል። አቶ በረከት የሕዝቡን ጥያቄ ይዘው እንደሚቀርቡና ተመልሰው መጥተው ለሕዝቡ ሪፖርት እንደሚያደረጉም ቃል ገብተዋል። “አንድ ደብተር ሙሉ ጥያቂያችሁን ፅፌ ይዤያለሁ ፣ ለሚመለከተው አካል ወስጄ አንድም ሳልቀንስ አቀርብና እንወያይበታለን። ከዛ መልሱን ይዤ ወደ እናንተ ተመልሼ እመጣለሁ” ነበር ያሉት።

ሕዝቡ ጌታቸው ረዳ የተባለው ግለሰብ እና ኢቢሲ በአማራው ክልል ህዝብ ላይ ሲያሾፉና ስድብ ሲዘነዝሩ እንዴት ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ሲሉም የብአዴን አመራር አባላትን አፋጠዉም ነበር። “ እንዴት ጌታቸው ረዳ የተባለ ጅል የአማራው ክልልን ህዝብ ሲሰድብ ዝም አላችሁ? እንዴት ብትንቁን ነው ይህን ትንሽ ሰው ሚኒስትር አድርጋችሁ የሾማችሁብን? ..” የሚሉት በጌታቸው ረዳ ላይ ከቀረቡት አቤቱታዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ነበሩ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጌታቸው ረዳና በኢቢሲ ሲቀርቡ የነበሩ ዘገባዎች አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸው ሕዝቡን በአሰቸኳይ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለባቸው የገለጹ ሲሆን ፣ አቶ በረከትም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ እየቀረበ ያለው ነገር ብዙ እንደማይጥማቸው ለሕዝቡ ገልጿል።

ሌላው የብአዴን አመራር አቶ ብናልፍ አንዷለም የተባሉኢ ግለሰብ ሲናገሩ ላዳመጠ የትግራዩ አባይ ወልዱ የሚናገር ነበር የሚመስለው። የክልሉን ህዝብ እንደሚወክሉ ፖለቲከኛ ሳይሆን በጥቅም የተገዙ፣ የለየለት የህወሃት ካድሬ መሆናቸዉንም ነበር ያረጋገጡት። እንደ ወንበዴ በሌሊት መጥቶ ዜጎችን ለማፈን የተንቀሳቀሰውን አሸባሪ ቡድን በማሞገስ ” የፌድራል ፖሊስ ህጋዊ ነው…” የሚል የመሳሰሉትን ፍሬከርስኪ አስተያየት ለመስጠት ሲሞክሩም በተሰብሳቢው ጩኸት ንግግራቸው በተደጋጋሚ ተቋርጧል። ሰዉዬ በተናገሩ ቁጥር ሕዝብ እያስቆማቸው ምናምንቴ ነበር የሚመስሉት።

ከሕዝቡ ይሰጡ ከነበሩ አስተያየቶች መካከል፡

“ ይሄን ሁሉ ግፍ በሰፊ ትዕግስታችን ችለን ተቀምጧል ።አሁን ግን ትግስታችን ተንጠፍጥፎ አልቋል”
“ ህወሓት አንዳች እርምጃ እወስዳለሁ ብትል የሚመጣው አፀፋ የከፋ እንደሆን የጎንደር ሕዝብ መልክቱን በብአዴን በኩል ልኮላታል”
“ የህወሓት የበላይነት እስከ መቼ? ከአሁን በኋላ ኢህአዴግ አብቅቶለታል ፣ ኢህአዴግ የጎንደር እናቶችን ደም እምባ ያስነባውን የመላኩ ተፈራን ስራ በሕወሓት አማካኝነት በጎንደር ሕዝብ ላይ ደጋግሞ እያደረገው ነው “
“ወንድሞቻችንን ከወልቃይት ገፍታችሁና አባራችሁ፣ ጎንደር መጠው ቢጠጉ፣ ህዝብን ንቃችሁ አፍናችሁ ወስዳችሁ ፣ ህወሓት የጎንደር ሕዝብን በደንብ ታውቀዋለች እንግዲህ ይለይልናል ፣ “

ይገኙበታል።

ለ10 ቀናት ተላልፎ የነበረዉና እሁድ ሐምሌ 24 ቀን በጎንደር ክተማ ይደረጋል ተብሎ የታቀደው የሰላማዊ ሰልፍ ነገር፣ እነ በረከት በተገኙነት ስብሰብ ላይ ሳይነሳ ስብሰባው ተበትኗል። በእርግጥ ሰላማዊ ሰልፉ በታቀደለት ቀን እንደሚካሄድ ሕዝቡ የስማ እንደሆነ ከጎንደር የሚደርሱ መረጃዎች ሲጠቁሙ፣ በሶሻል ሜዲያም ቅስቀሳዎች በስፋት እየተደረጉ ነው።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሕዝቡ ወገን መሆናቸዉን አስመስክረዋል። አቶ በረከትም በርጋታና በአክብሮት ነበር ሕዝቡን ሲያዳምጡ የነበሩት። ምን ያህል ሕዝቡ እንዳከረረ በመረዳታቸው አቶ በረከት አዲስ አበባ ያሉ ጓደኞቻቸውን አሳምነው መሰረታዊ የፖለቲክ ለዉጥ እንዲመጣ በመጨረሻው ሰዓት የድርሻቸዉን አዎንታዊ ሚና ይጫወቱ ይሆናል የሚል ግምት ያላቸው ጥቂቶች ቢኖሩ፣ አቶ በረከት የተላኩት ጊዜ ለማራዘም እና ህዝቡን ለማዘናጋት ነው የሚለው አስተያእይት ግን አይሎ የሚሰማ አስተያየት ነው።

በኦሮሚያ የተነሳው ቀዉስ፣ ሰሞኑን የቀድሞ የሕወሃት ጀነራሎች ያቀረቧቸው ጠንካራ ማስጠንቀቂያዎች ተደምረው፣ በኢሕአዴግ ዉስጥ ለዉጥ እንዲመጣ የማይፈለገውን አክራሪ ቡድን ወደ ጎን ተገፍቶ፣ ፔሪስትሮይካ በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚረዳ ሃይል ከኢሕአዴግ ዉስጥ ይወጣ ይሆን ? በቅርብ የምናየው ይሆናል። አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው፤ ጨዉ ለራስህ ስትል ጣፍጥ እንደተባለው አራት ኪሎ ያሉ ባለስልጣናት ለራሳቸው ያስቡበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።


በአሜሪካ የኢትዮጵያዊው የማደጎ ልጅ ፖሊስ የመሆን ሕልምና የነጭ አሳዳጊዎቹ ስጋት (ልዩ ዘገባ) –በታምሩ ገዳ

$
0
0

ሰሞኑን በጥቁር አሜሪካውያን እና በፖሊሶች መካከል የተከሰተው ተቃርኖ ከኢትዮጵአዊ ቤተሰብ ተወልዶ በነጭ አሳዳጊዎች እቅፍ እያደገ ለሚገኘው ኢትዮጵያዊ ጨቅላ ያለው አንደምታ ሲቃኝ << ወደፊት ፖሊስ ሆኜ ማህበረሰቡን ማገልገል ጽኑ ምኞቴ ነው>> ኢትዮጵያዊው የ6 ዓመቱ ህጻን (ልዩ ዘገባ) በታምሩ ገዳ


በአሜሪካ የኢትዮጵያዊው የማደጎ ልጅ ፖሊስ የመሆን ሕልምና የነጭ አሳዳጊዎቹ ስጋት (ልዩ ዘገባ)

“የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ አስቸኳይ ጥሪ እናደርጋለን”–ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

OFC
ከሕገመንግስታዊ አግባብ ዉጭ በዜጎች ላይ የሚወሰዱ የመንግስት እርምጃዎች እንዲቆሙ በፓርቲያችንም ሆነ የትግል ጓዶቻችን በሆኑ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሲሰጡ የቆዩ ጋዜጣዊ መግለጫዎችንና ጋዜጣዊ ኮንፌረንሶች እናስታዉሳለን፡፡ በተለይም የዜጎቻችን ከፊንፊኔ ዙሪያ የማፈናቀል ድርጊት እንዲቆም ሲቀርቡ የቆዩ ተማፅኖዎች የመንግስት ባለሥልጣኖች ጆሮ እንዳልገባ አረጋግጠናል፡፡ በሥልጣን ላይ ያለዉ ሥርአት ደጋፊዎች ጥቂት የማይባሉና ከአንድም በላይ ቤት ሲኖራቸዉ በመኖሪያ ቤት እጦት የሚቸገሩ ዜጎች ቁጥር የትየሌለ መሆኑና እነዚህም ዜጎች ከራሳቸዉና ከልጆቻቸዉ ጉሮሮ ቆጥበዉ የሰሩት መጠለያ፤ ለዚያዉም የክረምቱ ጊዜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ ላይ ሲፈርስባቸዉ ማየት ምን ያህል ዘግናኝና አሳዛኝ እንደሆነ መድረክ ከሰጠዉ መግለጫ ለመረዳት ይቻላል፡፡

ምንም እንኳን መንግስት ሕግና ሕጋዊነትን የማስከበር ግዴታ ቢኖርበትም፤ ሰርቶ ለአገሪቱ ገቢ እያመጣ ጎጆዉን የሚቀልስ ብቻ ሳይሆን በእንፉቅቅ እየተንቀሳቀሰ ጎሮሮዉን ለሚዘጋ ዜጋ ሳይቀር መንግስት ኃላፊነት እንዳለበት ተዘንግቶ ዜጎች በድቅድቅ ጨለማ ክረምት ሜዳ ላይ መጣላቸዉ አሳዝኖናል፡፡

ቀደም ሲልም በልማትና እንቬስትመንት ስም በተለይም በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም ሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚ የማያደርገዉንና በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሞ ሕዝብን ከቀዬያቸዉ የሚያፈናቅል ልማት ተብዬ እንቅስቃሴ እንዲቆም የኦሮሞ ሕዝብና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ከ2006 ጀምሮ በመቃወማችን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስት በተወሰደዉ የኃይል እርምጃ 74 ዜጎች ተገድለዋል፡፡ በዚህ በ2008፤ በተለይም ከስምንት ወራት ወዲህ መንግስት ከሕዝብ ፍላጎት ዉጭ ጥቂቶች የሥርአቱ ደጋፊዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገዉን፤ ነገር ግን መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች፤ በተለይም የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የተቃወመዉን የሕዝብን ድምፅ እንደመስማት በማን አለብኝነት በወሰደዉ ያልተገባ እርምጃ እስካሁን ከ400 በላይ የኦሮሞ ዜጎች በመንግስት ኃይሎች ተገድለዋል፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል፤ ከቀዬያቸዉና ከሥራቸዉ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ዜጎች ቁጥር ማወቅ አይቻልም፡፡

በመንግስት ኃይሎች በተወሰደዉ እርምጃ ነፍሰ ጡሮች፣ ዕድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ለጋ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ እናቶችና አዛዉንቶች ተገድለዋል፡፡ በቅርቡ እንኳን በምዕራብ ሸዋ ዞን በግንጪና በእጃጂ ወረዳዎች እንዲሁም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በጉራዋና ሐረማያ ወረዳዎች ታዳጊ ወጣቶች የሆኑ ተማሪ እሸቱ ወርቁ ሞረዳ፣ ተማሪ ታረቀኝ ላቺሳ፣ ተማሪ ሣብሪና አብደላ እና ተማሪ ሪሐና አህመድ የተባሉት ራሳቸዉን በኦሮሞ ሕዝብ ጠላትነት በፈረጁ የመንግስት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡ የእነዚህ ለጋ ወጣቶች ሕይወት መቀጠፍ የሚፈጥረዉን ስሜት ምን ሊመስል እንደሚችል የወላድ አንጀት ይፍረድ ከማለት ባለፈ ምንም ሊባል አይቻልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦችም ሆኑ የዓለም ሕብረተሰብ እንደሚመሰክረዉ የኦሮሞ ሕዝብ በበቀል ስሜት ተነሳስቶ በአንዳችም የሌላ ብሔር ዜጎች ላይ ግድያ መፈጸም ቀርቶ ያሳየዉ የጥላቻ እርምጃ እስካሁን አልነበረም፡፡ ይህ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብን አርቆ አስተዋይነት ከማሳየቱም በላይ፤ ላቅ ባለ ደረጃ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ከአፋኝ ሥርአት ጋር እንጂ ከጠባብ ፍላጎት ያልመነጨና ከንፁኃን ዜጎች ጋር አንዳች ቅራኔ እንደሌለዉ ያሳያል፡፡

ዛሬ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦፌኮ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የኢህአዴግን አገዛዝ የተቃወሙ የኦሮሞ ዘጎች በየእስር ቤቶች ታጉረዉ መገኘታቸዉ የሚታወቅ ሲሆን፤ ከነዚህ ዉስጥም አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ እነዮናታን ተስፋዬ፣ በረሃብ አድማ ላይ ናቸዉ፡፡ እነዚህ ዜጎች ያለ ወንጀል የታሰሩ መሆኑ እየታወቀም ቢሆንም፤ ነገር ግን በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ ቤተሰቦች፣ የትግል ጓዶችና ወገኖች ዉሳኔዉን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ታሳሪዎቹ ወገኖቻችን በታሰሩበት ቦታ ላይ የሚደርስባቸዉን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመቃወም ለፍትሕ አካል ያቀረቡት አቤቱታ ሰሚ በማጣቱ በራሳቸዉ ላይ የወሰዱት ቀጣይ የተቃዉሞ እርምጃ እንጂ የቅንጦት አይደለም፡፡

እነዚህም ሆኑ ሌሎች ዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብታቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አቤቱታቸዉ እንዲሰማላቸዉ በራሳቸዉ ላይ በወሰዱት የምግብ አለመመገብ አድማ መሞት የለባቸዉም፡፡ የሕክምናና የነፍስ ማዳን ዕርዳታ ሊደርግላቸዉ ይገባል፡፡ እነዚህ ዜጎች በእንክብካቤ እጦት ቢሞቱ ዉሎ አድሮ የሚያስከትለዉ ጉዳት ቀላል እንደማይሆን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ የኢፌዲሪ መንግስት፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ተከታታዮችና የዓለም ሕብረተሰብ በተለይም በአገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ የሚትገኙ ዜጎች ይህንን የይድረሱልን ጥሪያችንን በመቀበል የእነዚህ ንፁኃን ዜጎች ሕይወት ከሞት አፋፍ እንዲያተርፉልን የበኩላችሁን ድጋፍ እንዲታደርጉልን በእግዚአብሔርና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም እንማፀናለን፡፡
በመብት ረገጣና እንግልት የሕዝቦች የመብትና የነፃነት ትግል አይገታም!
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ
ሐምሌ 20 ቀን 2008
ፊንፊኔ

ፈረንሳይ ውስጥ በሰደተኞች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ኢትዮጵያዊ ሞተ፣ ሰድስት ቆሰሉ

$
0
0

france

ከታምሩ ገዳ

ፈረንሳይን ከእንግሊዝ በሚያዋስነው የካሊስ ወደብ አካባቢ ከፕላስቲክ ፣ከ ካርቶኖች እና ከቆርቆሮ ቁርጥራቾች የተሰሩ አጅግ ጎስቋላ በሆኑ ኑሮ ደሳሳ ጎጆዎች ውስጥ በሚኖሩ ከኢትዮጵያ፣ከኤርትራ፣ ከሱዳን እና ከመሳሰሉት ከሰሃራ በርሃ በታች ካሉ አገሮች የመጡ ሰደተኞች በአንድ ወገን ከአፍጋኒስታን የመጡ ስደተኞች በሌላ ወገን የተቧደኑበት እና በሰለት ፣ በቆመጥ እና በአጠናዎች በታጀበው ግጭት ሳቢያ የአንድ ኢትዮጵያዊ ሰደተኛ ህይወት ሲጠፋ ስደስት የሚደረሱ መቁሰላቸው ታዋቋል።

የራዲዮ ፍራናስ ኢንተርናሽናል የእንግሊዘኛው ፕሮግራም ከሰፍራው እንደዘገበው ሰኞ አመሻሹ ላይ የህልማቸው ውጥን እና መዳረሻቸውን ወደ እንግሊዝ ለመግባት ጥረት በሚያድረጉት የብለሹ/አምባገነኖች አገዛዞች ፣ የረሃብ እና የደህነት ሰለባዏች ከሆኑት ከምስራቅ አፍሪካ በመጡት ሰደተኞቹ እና በርስ በርስ ጦርነት ከምትታመሰው ከአፍ ጋኒሳታን በመጡት ሰደተኞች መካከል የተነሳው ጸብ እና አምባጓሮ ወደ አካላዊ ጥቃት ተሸጋግሮ ለጊዜው ስሙ ያለተገለጸው ፣ ነገር ግን ከኢትዮጵያ ሳይሰደድ እንዳልቀረ የሚገመተው የ37 አመቱ ሰደተኛ ደረቱ ላይ በቢላዋ ከድረሰበት ጥቃት ሳቢያ በመቁሰሉ በስፍርው ወደ የሚገኝ ሃኪም ቤት ቢወሰድም ሕይወቱን ማትረፍ አለተቻለም ተብሏል። ከዚሁ ግጭት ጋር በተያያዘ ስድስት ኢትዮጵያዊያኖች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ወደ ሁለት መቶ ሰደትኞች ጎራ ለይተው የተሳተፉ ሲሆን ፖሊስ ጉዳዩን ለማጣራት የሰው እና የቪዲዮ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ወደ እንግሊዝ የሚያሸጋግረውን አውራ ጎዳና ሆነ ዋሻ /ታናልን ቀደሞ ለመቆጣጠር እና በመኪናዎች ወስጥ ተሸሽጎ ለመግባት በሚደረገው እሽቅድምድም እና በአካባቢው ከሶስት ሺህ እስከ ስድስት ሺህ የሚኖሩበትን የካሊሱ ቁጥቋጦ/ጃንግልን በበላይነት ለመቆጣጠር የሚደረገው ፍልሚያ ከዚህ ቀደም በሱዳን ሰደተኞች እና በአፍጋኒስታን ሰደተኞች መካከል መደረጉ የሚታወስ ሲሆን ከአርባ በላይ ሰደተኞች የመቁሰል አደጋ ደረሶባቸው ነበር። ባለፈው ሳምንት እንኳን አንድ ስደተኛ ወደ እንግሊዝ ለመሄድ በመኪና ላይ ሲንጠለጠል ወድቆ ህይወቱ ማለፉ ዘገባዎች የገለጹ ሲሆን ከዚህ ቀደም የ አኢትዮጵያ ፣ከሱዳን ፣ከኤርትራ፣ከሶሪያ ፣ከፍልስጤም ፣ከአፍጋኒስታን ፣ከአኢራቅ ፣ከሞሮኮ እና ከመሳሰሉት አገሮች የመጡ ሰደተኞች በመኪና ፣በፈጣን ባቡር ተገጭተው አሊያም ከባሕር ሰጥመው መሞታቸው ዘገባዎች ያወሳሉ።

የፈረንሳይ መንግስት ባለፈው የካቲት ወር እዚያው ካሊስ ጢሻው አቅራቢያ በሺህ ለሚገመቱ ሰደተኞች ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ተስፋ በማድረግ በጊዚያዊ መጠለያነት ይጠቀሙበት የነበረው ደሳሳ ጎጆዎቻቸውን በማፈራረስ ፈረንሳይ ውስጥ የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲያገኙ/እንዲያቀርቡ ቢሞክሩም ጥረታቸው ሙሉ በሙሉ ያለመሳካቱ ባለስልጣናቱን የጠቀሱ ዘገባዎች ይናገራሉ።

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ “ስለ ኦሮሞና አማራ ትክክለኛ የዘር ምንጭ” ያብራራሉ!!

$
0
0

• ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች ነው
• አዳም የተፈጠረው ጎጃም፤ ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው
• ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አጥንቼ አለሁ ይላሉ …
e79d0cb4f04dde71d944922c7587068e_M
ኑሮአቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ታዋቂው የሥነፅሁፍ ምሁር ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ፤ የፃፉት‹‹የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ›› የተሰኘ አዲስ አነጋጋሪ የታሪክ መፅሐፍ ዛሬ ለገበያ ይቀርባል፡፡ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ ማን እንደሆነ በጥናት ደርሼበታለሁ
የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ እስከ ዛሬ የተለያዩ የታሪክ ምሁራን ከተናገሩት ፍፁም የተለየና አዲስ የጥናት
ውጤት ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡ የሁለቱ ቋንቋዎች አመጣጥም በጥናቱ ተካቷል ብለዋል፡
፡ በሊንከን ዩኒቨርሲቲ በሂዩማኒቲስ የትምህርት ዘርፍ የሚያስተምሩት ፍቅሬ ቶሎሳ ፤ከዚህ ቀደም
‹‹Heaven to Eden›› እና ‹‹The Hidden and untold History of the Jewish People and
Ethiopians›› የሚሉ መጽሐፍትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሙ ሲሆን ሁለቱም በኢንተርኔት
“አማዞን” በተባለ የመፅሃፍ ሽያጭ ድረገፅ ላይ ከተፈላጊ መፃህፍት ተርታ ተሰልፈዋል፡፡ በሙያቸው
ፀሃፌ-ተውኔትና የሥነ ፅሁፍ ምሁር ሲሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምሮችን
በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ አንጋፋው ምሁር ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በቅርቡ ለንባብ ባበቁት
“አዳፍኔ” የተሰኘ መፅሃፋቸው ላይ፤“የኦሮሞን ታሪክ ሙሉ አደርጎ ሊፅፍ የሚችለው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ብቻ ነው” ሲሉ ለብቃታቸው ምስክርነትና ዕውቅና መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ በርካታ ቲያትሮችን ለደረክ ያበቁ ሲሆን ከእነዚህም መካከል “ጓደኛሞቹ”፣ “ፍቅር በአሜሪካ” እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በቅርቡም ‹‹ላሟ›› የተሰኘ ባለ ሁለት ገቢር ቲያትር ፅፈው ማጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሠሩ ለአጭር ጊዜ ዕረፍት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበረ ሲሆን ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር በታሪክ ጥናቶቻቸው ዙሪያ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡

በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሟቸው “Heaven to Eden” እና “The Hidden and untold History of the Jewish People and Ethiopians›› የሚሉት መፃህፍት በአለማቀፍ ደረጃ ሰፊ ተቀባይነት ያገኙበት ሚስጥር ምንድነው? በምን ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው የሚያተኩሩት?
የመፅሐፍቱ ይዘት ነው ወሳኙ፡፡ ተቀባይነት ያገኙት በቋንቋ አጠቃቀም ለአንባቢያን ምቹ ስለሆኑ ይመስለኛል፡፡
በአይሁዶች ታሪክ ላይ የሚያተኩረው መፅሐፍ፤በጉዳዩ ላይ ከተጻፉ ሌሎች መጻህፍትና በተለምዶ ስለ አይሁዶች ከሚታወቀው ምን የተለየ ነገር ይዟል?
ብዙ ጊዜ ስለ አይሁዳውያን ሲወራ፣ቀዳማዊ ሚኒልክ የዛሬ 3ሺህ ዓመት፣ 40ሺህ አይሁዳውያንን ይዞ መጣ የሚለውን ነው የምናውቀው፡፡ ከመጡት መካከል 12ሺህ ያህሉ ንፁህ እስራኤላውያን ናቸው። 28ሺህ ያህሉ እነሱን በሥራ ያገለግሉ የነበሩ ኢያቡሳውያን የሚባሉ ነገዶች ናቸው፡፡ ቀዳማዊ ሚኒልክ ለ12 ሺህዎቹ ልዩ ቦታ ሰጥቷቸው፣ በሀገሪቷ ላይ ካህናት አድርጎ ታቦት እያስቀረፀ፣ ኢትዮጵያ ላይ በዚህ መልክ ሾሟቸው ነበር፡፡ ኢያቡሳውያን ደግሞ ንጉሱን በእጅ ስራና በውትድርና ያገለግሉት ነበር፡፡ ይሄ እንግዲህ አይሁዳውያን ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት ሁለተኛው ፍልሰት ነው፡፡
የመጀመሪያውና ብዙም የማይነገረው የአይሁዳውያን ፍልሰት፣ የእስራኤላውያኑ መሪ ሙሴ በህይወት እያለ አባ ብሄር የሚባል ልኡል ነበር። የሙሴ አማች ነው፡፡ አባ ብሄር የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሊሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፣አይሁዳውያን ተከትለውት መጥተው ነበር፡፡ ምክንያቱም አባ ብሄር ያገባት ልጅ የሙሴ እህት ነበረች፡፡ ሙሴ በወቅቱ ለአባ ብሄር ፅላት ቀርፆ እንዲሁም ቀይ ባህርን የከፈለባትን በትር ሰጥቶት፣ወደ ሳባ ከተማ መጥቶ ነግሷል፡፡ በወቅቱ ብዙ አይሁዳውያንም ተከትለውት መጥተው ነበር፡፡
ሶስተኛው ፍልሰት የምንለው፣የኢራቁ ናቡከደነፆር አሸንፏቸው በሚያሳድዳቸው ጊዜ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ አይሁዳውያን ወገኖች አሉን” ብለው ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፡፡ አይሁዳውያን በነዚህ መንገዶች ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፡፡
ትክክለኛዎቹ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ ያሉት ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ…?
የሃይማኖታቸውን ስርአት፣ መፅሃፍትና ህግጋት ከመጠበቃቸው አንፃር ከሌላ ህዝብ ጋር ስላልተደባለቁ ትክክለኛው ያለው እነሱ ጋ ነው፡፡ ሌሎቹ ወደ አውሮፓ፣ እስያ፣ አሜሪካ የተሰደዱት እነዚህን ነገሮች በተለያዩ ጫናዎች የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ጠብቀው አላቆዩትም፡፡ ወደዚህ የመጡት ግን በግድ ባህላችሁን ሃይማኖታችሁን ለውጡ ተብለው በኢትዮጵያውያን አልተረበሹም፤ነፃነት ነበራቸው፡፡ መሬትና ሁሉ ነገር የተመቻቸላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነበር፡፡ ሌላ አገር ላይ ቦታ እንዳይኖራቸው ተደርገው በየጊዜው ይሰደዱ ነበር፡፡ እንደውም በሩሲያ ውስጥ በድንገት አይሁዳውያንን የመግደል ድርጊት ይፈፀም ነበር። ሩሲያውያኑ ተሰባስበው፤“ዛሬ አይሁዳውያንን ገድለን እንምጣ” እያሉ ይዘምቱባቸው ነበር፡፡ ወደ መንደራቸው ሄደው አውድመዋቸው ይመለሳሉ፡፡ ማንም ስለማይበቀልላቸው ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ ነበር የሚቀረው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከተሰጣቸው ክብር የተነሳ በትንንሽ ንጉስነት ጭምር ይሾሙ ነበር፡፡ በርካቶቹም ካህናትና ሊቀ-ካህናት ተደርገው ለአይሁድ እምነት ተሹመል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የሰለሞን ዘር ነን በሚሉት ውስጥም ገብተው፣ ስርወ መንግስት እስከ መመስረት የደረሱ ነበሩ፡፡ በዓለም ላይ አይሁዳውያን ደልቷቸው የኖሩት ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ነው፡፡ በጠቅላላው በኢትዮጵያ ሀገራት ማለትም፡- በግብፅ፣ የመን፣ ኑቢያ—ኢትዮጵያ ባስተዳደረቻቸው አካባቢዎች በሙሉ በክብር ተይዘው ነው የኖሩት፡፡ ትልቁ ማስረጃ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ፣ እናቱ ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ በስደቱ ዘመኑ እኛ ጋ ብቻ ነው ጥገኝነት ያገኙት። በወቅቱ ግብፅ ለሁለት ተከፍሎ ነበር፡፡ አንዱ ክፍል በሮማውያን ቁጥጥር ስር ነበር፡፡ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነው፡፡ ኢየሱስ ከመወለዱ ከ880 ዓመት በፊት አማራዎች፤ አማሩላ ደልታ ወደሚባል ቦታ ሄደው፣ አክሱማይት የተባለውን ህፃን ልጅ ዙፋን በመጠበቅ ያገለግሉ ነበር፡፡ በኋላ በ800 ዓመታት ውስጥ አማሩላ ደልታ የሚባል መንደር መስርተው ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ጋርና ከቅዱስ ዮሴፍ ጋር ሲሸሹ፣ እዚያ ነው ማረፊያ ያገኙት፡፡ ይሄ መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፤እኛ ግን ከተለያዩ መዛግብት እናገኘዋለን፡፡ በወቅቱ የአካባቢው ንጉስ አማናቱ ተትናይ ይባላሉ፡፡ ከጎጃም ከጣና አካባቢ ነው ወደዚያ የሄደው፡፡ ሌላው አይሁዳውያኑ መፅሐፍ ቅዱሳቸው ሲጠፋባቸው ከኛ ነው የወሰዱት፡፡ አፄ ደንቀዝ የተባለው ንጉሰ ነገስት ነው ከግዕዝ ወደ እብራይስጥ አስተርጉሞ የሰጣቸው፡፡
ትክክለኛውን የአይሁድ ባህልና እምነት በመጠበቅ በኢትዮጵያ ያሉት አይሁዳውያን ብቸኞቹ ናቸው ማለት ይቻላል?
አዎ! ኦሪትን ይዘዋል፡፡ ግን በደማቸው ከኛ ተደባልቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ሃበሻ የተባሉት። ሃበሻ ማለት የተደባለቀ ነው፡፡ “አበሳ” ያለበት ወይም እንከን ያለበት ማለት ነው፤ ሃበሻ ማለት፡፡ በቀዳማዊ ሚኒልክ ጊዜ የመጡት ከኛ ጋር ተደባልቀው 560 ዓመት ከቆዩ በኋላ በባቢሎን ስደት ጊዜ ሶስተኛዎቹ ሲመጡ፣ነባሮችን ሲያዩአቸው በመልካቸው አይሁዳውያንን አልመስል አሏቸው። ስለዚህ፤“እናንተማ ክልስ ናችሁ፤አበሳ አለባችሁ” ብለው ይሰድቧቸዋል፡፡  ነባሮቹ አይሁዶች ደግሞ፤ “እናንተ ፈላሾች፤እኛ ሀገር አለን” እያሉ ይሰድቧቸው ነበር፡፡ በዚህም “አበሻ” እና “ፈላሻ” የሚለው መጠሪያቸው ሆነ፡፡ “ሀበሻ” የሚለው ቃል እኛን አይወክለንም የምለው ለዚህ ነው፤ሀበሻ አይሁዳውያኑን ነው የሚወክለው፡፡ እኛ የኢትዮጰያ ልጆች ነን፤ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡
“በሃበሻነቴ እኮራለሁ” ስንል የከረምነውስ—–ቀለጠ ማለት ነው?
አዎ! እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ ሀበሻ አይደለሁም። ሀበሻ የሚለው ቃል የስድብ ቃል ነው፡፡ እኛን አይወክለንም፡፡ አይሁዳዊ ካልሆነ በስተቀር አንድ ሰው ራሱን “ሀበሻ ነኝ” ብሎ ሊጠራ አይገባውም። ስድብ አያኮራም፡፡ ብዙ ሰው ስለማያውቅ ነው በሀበሻነቴ እኮራለሁ የሚለው፡፡ በአረብኛም ብናየው “የተደባለቀ”፤ “ንፁህ ያልሆነ” ማለት ነው። ይሄ መልካም ቃል አይደለም፡፡ ግን ሀበሻ የሚለው “አበሳ” ከሚለው እንጂ ከአረብኛ የመጣ አይደለም። ሁለቱ አይሁዳውያን መሃል ያለ የመሰዳደቢያ ቃል ነው እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያንን አይመለከተንም፡፡
‹‹ኢትዮጵያ›› የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
ኢትዮጵያ የሚለው ‹‹ኢትዮጵ›› ከተባለው ሰው የመጣ ነው፡፡ ኢትዮጵ ማን ነው ካልን፣ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰው መልከፀዴቅ የሚባል የሳሌም ንጉሰ ነገስትና ሊቀካህን ነበር፡፡ ይህ ሰው ሃገር ያስተዳድራልም፤ሃይማኖትም ይመራል፡፡ እሱም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነበር፡፡ ይሄ እንዴት ይሆናል ከተባለ፣ኢየሱስ በምፅአት ቀን ሲመጣ፣ የንጉስ ንጉስ፣ የካህን  ካህን ሆኖ ነው፤መልከፀዴቅም የዚህ ምሳሌ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ከዚሁ ጋር ምን ያገናኛታል ሊባል ይችላል፡፡ በጣም የሚያኮራ ግንኙነት አለው፡፡ የመልከፀድቅ ልጅ ኢትኤል ይባል ነበር፡፡ እግዚአብሔር ኢትኤልን ካለህበት የሳሌም ምድር ለቀህ ጣና ላይ ስፈር አለው፡፡ ‹‹ከዚያም ያንተ የልጅ ልጆች፣ እኔ ከ2000 አመታት በኋላ በምወለድበት ጊዜ በኢትዮጵያ  ግዛት ላይ ስለ መወለዴ ኮከብ አሳይሃለሁ” ይለዋል (እንደኔ ምርምር፤ይሄ ኮከብ የተባለው መልአኩ ገብርኤል ነው) በዚህ ሁኔታ ኢትኤል አሁን ወዳለችው ኢትዮጵያ ሲደርስ እግዚአብሔር፤‹‹ኢትዮጵ›› ተብለህ ተጠራ አለው፡፡ ‹‹ኢት›› – ስጦታ ማለት ነው፡፡ ‹‹ዮጵ” – ማለት ደግሞ ቢጫ ወርቅ ነው፡፡ ስለዚህ “ቢጫ ወርቅ ስጦታ” ተባለ፡፡ በኋላ ሃገሪቷን ኢትዮጵያ አሠኛት፡፡
በመፅሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ተብሎ የሚጠቀሰው ስም የትኛዋን ኢትዮጵያ ነው የሚወክለው?
እሱ አሁን ያለችውን ኢትዮጵያን ነው የሚወክለው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ እስከ 13ኛው ክ/ዘመን ድረስ ለመላዋ አፍሪካ መጠሪያ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ በኋላም የመጣው አፍሪካ የሚለው ስም ከዚሁ ከኢትዮጵያ የተገኘ ነው፡፡ ከአፋሮች ነው አፍሪካ መጠሪያዋን ያገኘችው፡፡ በመፅሃፈ እዝራ ምዕራፍ ስድስት ላይ፤‹‹አፍሪካንሳውያን›› ይላል፡፡ ይሄ አፋሮችን ነው የሚወክለው፡፡ በመርከብ ስራ በቀይ ባህር ላይ የተራቀቁ ሰዎች ነበሩ፡፡ የዛሬ 3ሺህ አመት ንጉስ ሰለሞን ቤተመቅደሱን ሲሰራ፤ልዩ እንጨት፣ እጣን፣ ወርቅ (ኦፊር የተባለ ታዋቂ ወርቅ- በነሱ የተሰየመ) ጭምር ይነግዱና ለንጉሡ ያቀርቡ ስለነበር፣ስማቸው የገነነ ሆኖ አፍሪካንሳውያን የተባሉት፡፡ በሳይንሱም አፋር የሰው ዘር መገኛ እያልን ነው፡፡ ኢስያውያንም ስያሜያቸውን ያገኙት ከሣባ ቀድሞ ከነገሰው ‹‹ኢስአኤል›› ከተባለው ንጉስ ነው፡፡ ምድሪቱን ያስተዳድር ስለነበር ኢስያ ተባለች፡፡ ‹‹አፄ” የሚለውም ከዚህ የመጣ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሚለው ከግሪክ ቃል የመጣ ነው የሚለውስ —?
ኢትዮጵያ የሚለው ከግሪክ ቃል  የመጣ ነው የሚለው ውሸት ነው፡፡ ይሄን አጣርቻለሁ፡፡ በነሱ መዝገበ ቃላት ውስጥ ይሄ ቃል የለም፡፡ ‹‹ፊቱ የተቃጠለ›› የሚለው ቃል በግሪክ ቋንቋ ኢትዮጵያ የሚለውን ሳይሆን ሌላ ትርጉም ነው የሚኖረው፡፡ ግሪኮቹ ከኛው ሰምተው ነው መልሠው ኢትዮጵያ ያሉን፡፡ እኛ ከነሱ በፊት ነበርን እንጂ እነሱ ከኛ በፊት አልነበሩም፤ ስማችንን ሊያወጡልን አይችሉም፡፡
በምርምርዎ አዳምና ሄዋን የተፈጠሩበት ቦታ የት ሆኖ አገኙት?
ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ጎጃም፤ ዳሞትና ጣና አካባቢ ያለ ቦታ ነው፡፡
ለዚህ ድምዳሜ ማስረጃዎ ምንድን ነው?
አንደኛ ኤደንን ከሚያጠጡ አራት ወንዞች ውስጥ አባይ የምንለው ነው ኤፌሶን የሚባለው። በኦፌር ወርቅ ዙሪያ የሚዞር መሆኑ ተፅፏል፡፡ በኔ ድምዳሜ፣የኤፌሶን ወንዝ የአሁኑ ዋቢ ሸበሌ ነው። ጤግሮስና ኤፈራጥስ ደግሞ ጊዮን ራሱ ጥንት ሜዲትራኒያን ባህር ይገባ ነበር፡፡ ድሮ ሜድትራኒያን “ኪቲ” ይባል ነበር፡፡ ጥንት ጊዮን ወንዝ ሜድትራኒያን ሲደርስ ተራራ ስለነበር ተጋጭቶ ይመለስ ነበር፡፡ ከዚያ ነው መሬት ተነቃንቆ፣ቦታው ተቆራርጦ አሁን ወዳለበት ኢራቅ የሄደው እንጂ አካባቢው እዚሁ ነበር፡፡
አዳም የት ተፈጠረ ለሚለው በመፅሃፈ ሄኖክ ላይ “ኤልዳ” በሚባል ቦታ ተፈጠረ ይላል፡፡ ኤልዳ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም አስሌዳውያን ወይም ኤልዳውያን የሚባሉ አሁንም ድረስ ጎጃም ውስጥ አሉ፡፡ ሄኖክ በመፅሃፉ ኤልዳ ነው የተፈጠረው ይላል፡፡ ከዚያ ወስዶ ነው እግዚአብሄር በ40 ቀኑ ወደ ኤደን ገነት የከተተው ይላል፡፡ ሄዋንን ደግሞ ከአዳም ጎን አውጥቷት ነው በ80 ቀኗ ወደ ኤደን ገነት የከተታት፡፡ ከዚህ ተነስቶ ነው ወንድ በ40፣ ሴት በ80 ቀን ክርስትና የሚነሱት። ይሄ አይነቱ ስርአት በዓለም ላይ የትም የለም፤እና ይሄ በሄኖክ መፅሃፍ የተፃፈውና አሁን ያለው እውነታ ይገኛል፡፡
ሌላው ኮሬብ የሚባል ዋሻ ውስጥ አዳም ተቀበረ ይላል፡፡ በእርግጥ በሲናይ በረሃ አካባቢ ኮሬብ የሚባል ቦታ አለ፤ ግን በተመሳሳይ ይህ ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥም አለ፡፡ ሌላው ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው ይላል፡፡ አራራት ተራራን ለመፈለግ ወደ ቦታው ሄጄ ነበር፤ በታንኳ ጣናን አቋርጬ፡፡ አራራት ተራራ የሚባለውን ሳገኘውና አቀማመጡን ሳጠናው፣ ለመርከብ ማሳረፊያነት በአናቱ ላይ ምቹ ሜዳ አለው፡፡ ኖህ ወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር ይላል፤መፅሃፍ ቅዱስ፡፡ በእርግጥም ቦታው የወይን ጠጅ ፍሬ ለማብቀል ተስማሚ ነው፡፡ አሁንም አትክልቶችና ጌሾ ይበቅልበታል፡፡ ከዚሁ ማስረጃ ሳልወጣ፣አዲስ አመትን አበቦች አብበው አከበረ፤የእንጨት መስዋዕትም አደረገ ይላል፡፡ ይሄ እንግዲህ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ ያለው የአዲስ ዓመት መቀበያ ስርአት፣ ከየት መጣነትን ሊያስረዳ ይችላል። በኋላ ወደ ክርስትናው የመስቀል በዓል ደመራነት ተለወጠ እንጂ በፊት ደመራ የሚነደው በአዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃው አሁንም ድረስ ክርስቲያን ያልሆኑ የሀገራችን ሰዎች የደመራ ስርአት አላቸው። ይሄ የአባታቸው የኖህ ትዝታ (ማስታወሻ) ነው ሲወረስ ሲዋረስ የመጣው፡፡ በዚህና በኖህ ጉዳይ ሰፊ ጥናት እያደረግሁ ነው፤ወደፊት ይፋ ይሆናል፡፡ አንድ እዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው፣ሌላ አራራት የሚባል ተራራ አርመን ውስጥ አለ፡፡ ተራራው ግን በረዶ ያለበት፣ ገደላገደል፣ እንኳን መርከብ ሊያሳርፍ ለሰው ልጅ የማይመችና የማያብብ ቦታ ነው፤ ስለዚህ ያ ሊሆን አይችልም፡፡
በሰንደቅ አላማው ላይም የተለየ መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡ ለኢትዮጵያ የተሰጠ ስጦታ ነው ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?
ሰንደቅ አላማው ለኖህ ከተሰጠው ምልክት የመጣ ነው፡፡ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የጎሉበት ቀለማት ሰማይ ላይ ታይተዋል፡፡ እነዚያ ቀለማት ናቸው ዛሬ ያሉት፡፡ ከንግስት ሳባ በፊት የነገሰው አፄ ኢሲአኤል ነው ሰንደቅ አላማ እንዲውለበለብ ያደረገው፡፡ ሰንደቅ አላማ የሚለው የመጣው የኢስአኤል መንግስት “ሰንደቅ አለማ” ከሚለው ነው፡፡ ከዚያ የመጣ ነው። እሱ በወቅቱ የመረጠው፡- አረንጓዴ ቢጫ፣ቀይና ሰማያዊ ቀለማት ነበር፡፡ ለሰንደቅ አላማው ያልተገዛና ያላውለበለበ ይቀጣል ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ አስገዳጅ ህግ ያወጣውም እሱ ነበር፡፡ በሰንደቋ አናት ላይ ኮከብ ነበር የሚቀመጠው፡፡ ኢየሱስ ሲወለድ የሚጠቁመውን ኮከብ ለማስታወስ ይጠቀም ነበር፡፡ በዓለም ላይ ሰንደቅ አላማን የፈለሰፈ የመጀመሪያው ሰውም ሊሆን ይችላል፡፡
የኢትዮጵ የልጅ ልጅ የሆነው ኢስአኤል ከፈለሰፈው ሰንደቅ አላማ ነው፣ዛሬ ያሉት የሰንደቅ አላማ ቀለማት የመጡት፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰንደቅ አላማው ላይ ከዚህ ተነስቶ አንድ አይነት አቋም ቢይዝ መልካም ነው፡፡ ኢስአኤል ለኦሮሞውም፣ ለአማራውም፣ ለትግሬውም፣ለአፋሩም ለሌላውም ብሄረሰብ ሁሉ አባት ነው፡፡ ከአባቶቻችን የወረደ ሰንደቅ አላማ እንጂ ከባዕድ የመጣ አይደለም፡፡
ሰውየው እጅግ ጠቢብ ነበር፤ልእለ ሰብዕ (superman) ነበር፡፡ 150 አንበሳ መግደሉን ለማስታወስ ጭምር አፄ ኢስአኤል የሰብዕ እና የአውሬዎች ንጉሰ ነገስት ብሎ ነበር ራሱን የሚጠራው፡፡ ሰውየው እጅግ ጠቢብ ከመሆኑ የተነሳ የጀነቲክ ኢንጅነሪንግን የፈለሰፈውም እሱ ነው፡፡ እንስሳን ከእንስሳ፣ ዘርን ከዘር እየቀላቀለ የፈለሰፈ የመጀመሪያው የጀነቲክ ኢንጅነር ነበር። በቅሎን የፈጠረውም እሱ ነው፡፡ አህያንና ፈረስን አዳቅሎ፡፡ ይህ ሰው የሁሉም ኢትዮጵያውን አባት ነው፡፡ የኢትዮጵ ልጅ ነው፡፡ የኢትዮጵ 10 ወንዶች ልጆች ናቸው፤ አሁን የምናያቸውን የኢትዮጵያውያን ጎሳዎች ሁሉ የፈጠሩት፡፡
ሰሞኑን ለአንባቢያን የሚቀርብ መፅሃፍ እንዳዘጋጁም ሰምቼአለሁ፡፡ የመፅሐፉን ይዘት በአጭሩ ሊነግሩኝ ይችላሉ?
መፅሐፉ፤“የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የሚል ነው፡፡ አሁን ያሉት ኢትዮጵያውያን በሞላ የኢትዮጵ ልጆች መሆናቸውን ከላይ አስረድቻለሁ፡፡
አሁን እንደምናው በሁላችንም ላይ የማንነት ቀውስ አለ፡፡ የማንነት ቀውሱ የመጣውም እኛ ማን እንደሆንን በትክክል ባለማወቃችን ነው፡፡ ስለዚህ ይህ መፅሐፍ እኛ ማን እንደሆንን፣በርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎችና ሰነዶችን አስደግፎ፣ግልጥልጥ አድርጎ  ያስረዳናል፡፡ ይህ የማንነት ቀውሳችን ከተስተካከለና ራሳችንን ካወቅን፣ በመካከላችን ግጭቶች ሊኖሩ አይችሉም፡፡ መፅሐፉ፤ፍቅር፣ ሰላምና ህብር ሊፈጥር ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እኛ የትልቅ ሰው ዘር ነን የሚለውን በማስረጃ የሚያሳየን ነው፡፡ የሰው ዘር ምንጭ ናሙናዎች መሆናችን ይተነትናል፡፡ ማንነታችንን በትክክል ተረድተን፣ አንድ ላይ ለመጓዝ ያስችለናል ብዬ አስባለሁ – ይህ ብዙ የተደከመበት የምርምር ውጤት፡፡
የኦሮሞና የአማራ የዘር ሀረግ አንድ ነው የሚለውን ነው መፅሃፉ የሚያስረዳው?
አማራና ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በኢትዮጵያ ግዛት ያለው ብሄር፣ ጎሳ ከ10ሩ የኢትዮጵ ልጆች ነው የመጣው፡፡ ዝቅ ሲል ደግሞ የኢትዮጵ የልጅ ልጅ የሆነ፣ ጎጃም ላይ አዳምና ሄዋን ተፈጥረዋል ብዬ ባልኩት አካባቢ አንድ ጠቢብ ሰው ነበር፡፡ “ደሴት” ወይም “ደሸት” ይባላል፡፡ እሱ ነው የኦሮሞና የአማራ አባት፡፡ የዛሬ 3600 ዓመት 4 ወንዶች ልጆች ወለደ፡- መንዲ፣ መደባይ፣ ማጂ፣ ጅማ የሚባሉ፡፡ እነዚህ 4ቱም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሀገር መጠሪያ ሆነዋል። ማጂ ደግሞ ማራ እና ጀማን ይወልዳል። ዛሬ አማራ የምንለው ማራ ነው፡፡ “ማራ” ማለት “እውነተኛ ብርሃን” ማለት ነው፡፡ አማራ ያሉት አጋዚያን ወይም የግዕዝ ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ ማጂ ማራን ወለደ ካልን፤ ጀማ እና ማራ ወንድማማቾ ናቸው፡፡ ሁለቱ ወንድማማቾች በአካባቢው ካሉት ጋፋቶች ጋር መዋጋት ሰልችቷቸው፣ ሃገር ለቀው ወደ ሸዋ ሲመጡ አንድ ወንዝ ያገኛሉ፡፡ ወንዙን ጀማ አሉት። አሁን የጀማ ወይም የ“ዠማ” ወንዝ ማለት ነው። ከአካባቢው እየራቁ ሲሄዱ የጥንት አባቶቻቸውን ቋንቋ “ሱባ”ን ትተዉ አማርኛን መፈልሰፍ ጀመሩ፡፡ መደባይ፣ ጅማና መንዲ ደግሞ ግማሾቹ ጎጃም ላይ ቀሩ፤ ግማሾቹ ወለጋ ሄዱ፤ሌሎቹም እየራቁ በምስራቅ አፍሪካ ተሰራጩ፡፡ ኦሮሚኛ ቋንቋ የሚባለውንም ፈጠሩ፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው ዛሬ ያሉት ኦሮሞና አማራ የመጡት፡፡ ዘረ ደሸት ይባላሉ፡፡ የደሸት ልጆች ናቸው። የዘር ሀረጋቸው አንድ ነው፡፡ ቋንቋቸው የተለያየ የሆነው በሂደት ነው፡፡
ኦሮሞው የኩሽቲክ፣ አማራው የሰሜቲክ ዘር ናቸው፤ የመጡትም ከውጭ ነው የሚለው ለዘመናት የዘለቀ ታሪክስ …?
እሱ ፈፅሞ ውሸት ነው፡፡ ሁለቱም ከውጭ አልመጡም፡፡ እንዳስረዳሁት እዚሁ የበቀሉ ናቸው። የአማራም የኦሮሞም አባት ደሸትም ሆነ ታላቁ አባት ኢትዮጵ ኩሽ ነው፡፡ መልከፀዴቅም ኩሽ ነው። ኦሮሞና አማራ ሁለቱም ኩሽ ናቸው፡፡ አማራ ሴም አይደለም፤ ኩሽ ነው፡፡
እስከ ዛሬ ሲነገር የነበረው ውሸት ነው። ምናልባት የአማርኛ ቋንቋ ከሌሎች ጋር ሲደበላለቅ ሴሜቲክ ቤተሰብ ውስጥ ተገኝቶ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ኢትዮጵያውያን የኩሽ ዘሮች ናቸው። በዚሁ መፅሐፌ ላይ ስለ ቋንቋም አስረድቻለሁ፡፡ በእብራይስጥም ሆነ በአረቢክ የሌሉ እንደ ጨ፣ቀ፣ፀ ያሉ ድምጾች በአማርኛና በኦሮሚኛ ቋንቋ ውስጥ አሉ። ይሄን በዝርዝር በመፅሐፉ አስቀምጫለሁ፡፡
ኦሮሞና አማራ አንድ ነው የሚለው አመለካከት በተለይ በኦሮሞ ምሁራን ዘንድ እምብዛም ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም፡፡ በግድ ኦሮሞን አማራ ለማድረግ ነው በሚል ወቀሳ የሚሰነዝሩ አሉ …
እንዲህ የሚሉት ሁሉም ከኢትዮጵ ዘር የመጣው የደሸት ልጆች መሆናቸውን ባለማወቃቸው ነው። ይሄ መረጃ ስለሌላቸው ራሳቸውን እንደ ባዕድ አግልለው ስለሚያዩ ነው እንጂ አሁን ይሄ እኔ ያቀረብኩትን ማስረጃ በቅን ልቦና አገናዝበው ለመረዳት ከሞከሩ፣ የትልቁ ሰው የኢትዮጵ፣ የጠቢቡና የሊቀካህናቱ የደሸት ልጅ እንደሆኑ በሚያውቁ ጊዜ፣ እነሱ እንደተሳሳቱ ተገንዝበው ወደ ማንነታቸው ላይ አተኩረው ይኮሩበታል ብዬ አስባለሁ፡፡ የመጣነው ከትልቅ ዘር ነው፡፡ ኦሮሞውም አማራውም የመጣው ከዚህ ትልቅ ሰው ነው፡፡ በዚህ ሁላችንም ልንኮራ ይገባናል፡፡
የአሁኗ እና የቀድሞዋ ኢትዮጵያ ልዩነታቸውና አንድነታቸው ምንድን ነው?
በግዛት ከሄድን ጥንት መላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ነው የሚባለው፡፡ ከየመን አልፎ ሁሉ ይሄዳል፡፡ ግብፅ ውስጥ ፈርኦኖች የሚባሉት ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአባይ ላይ ከመርከብ ወርደው ሜዳ አግኝተው የሰፈሩበት ቦታ ነው፤ ግብፅ፡፡ የአፍሪካ ሁሉ ነገር ከኛ አይወጣም፡፡
የኢትዮጵያ ታሪክ የ3ሺህ ዘመን ነው ይባላል፡፡ እርሶ የደረሱበት የጥናት ውጤት ምን ይላል?-
አዎ፤ በተለምዶ 3ሺህ አመት ይባላል እንጂ ከ7ሺ በላይ ነው፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፡፡ ኖህ ኢትዮጵያ ላይ ነግሷል፤ ከዚያ ጀምሮ 7ሺህ አመት ነው፡፡
እስካሁን በነገሩን ታሪክ ውስጥ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው በማስረጃነት የሚጠቅሱት፡፡ መፅሐፍ ቅዱስን ብቻ የታሪክ ምንጭ ማድረግ ይቻላል?
መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ አይደለም፡፡ 42 ሰነዶችን አሁን በሚወጣው መፅሐፌ ላይ በግልፅ አስቀምጫለሁ። እነዚህ ሰነዶች በተለያዩ ሰዎች በጥንት ጊዜ የተፃፉ ናቸው፡፡ ኑቢያ ውስጥ ጀበል ኑባ በተባለ ቦታ ተቀብረው የቀሩ፣በጥንት ፍርስራሽ የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን (ከእስልምና በፊት የነበረ) ድንጋይ ሳጥን ውስጥ ተቀብረው የነበሩ የብራና ሰነዶች አግኝቻለሁ፡፡  በዚያ ላይም የተመሰረተ ነው። ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ 42 ተጨማሪ የታሪክ ሰነዶችን ተጠቅሜያለሁ፤ይሄን መፅሐፍ ሳዘጋጅ፡፡
ቀጣይዋ ኢትዮጵያ ምን መምሰል አለባት ይላሉ?
አሁን ማንነታችንን አውቀን፣ የማንነት ቀውሳችንን ፈትተን፣ሁላችንም የኢትዮጵያ ዘር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች—–መሆናችንን ተገንዝበን፤ በፍቅር፣ በሰላም፣ በመከባበር፣ በእኩልነት መኖር አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ ሁላችንንም ኢትዮጵ ያገናኘናል፡፡

ማለዳ ወግ …የጀግና ልጅ ልደቱ በሀዘንና በመከራ ይከበራል! –ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

*   እንኳንም ተወለድሽ ህፃን ኤማንዳ ሐብታሙ

ዛሬ የወጣቱ አባዎራ ሐብታሙ የአብራክ ክፋይ ህጻን ኤማንዳ ሐብታሙ  4ኛው ዓመት የልደት ቀን መሆኑን ስሰማ ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቴን ለመግለጽ ፣ ብሎም በህግ ሽፋን በአቧቷ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በማውገዝ እንደ ዜጋ ማለት የምለውን ማለት ፈለግኩ  !

habtamu dgበሰለጠነው በእኛ 21ኛ ክፍለ ዘመን፣  በእኛ ሀገር ፣ ለሀገራቸው መጻኤ ህይዎት ለፍትህና ዲሞክራሲ መከበር ተግተው መጨረሻቸው መሳደድ ፣ መታሰር መገረፍና መሞት እጣ ፈንታቸው የሆነ ትንታግ ዜጎች እውቃለሁ ። ይህን ሁሉ አደጋ እየተመለከቱ ጥቂቶች የወጣትነት ለጋ እድሜያቸው በቀሰሙት እውቀት ለመደገፍ ሽተው ተደናቅፈዋል፣ እየተደናቀፉም ነው ። እንደ ሰው ሀብት ንብረት ከማካበት የወጣት ጎልማሳነት እድሜያቸውን ለፍትህ ነጻነት ሲታገሉ ከባድ መስዋዕት ሲከፍሉ  ከቤተሰብ ሀላፊነት ባሻገር የሀገርና የህዝባቸውን ነገር አንገንግቧቸው ” እኔም ለሀገሬ ” በሚል የከፈሉትንና እየከፈሉት ያለው የከበደ መስዋዕትነት የሚዘነጋ አይሆንም !

ከምንም በላይ ለዘመናት የሀገርና የህዘብን ኑሮ እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ እየጎተተው ያለውን የሀገራችን በአንባገነኖች የሚዘዎር ፖለቲካ ለመቀየር ትግል ከተጀመረ ከራረመ ። ውጤቱ አመርቂ ባልሆነው ፖለቲካውን በሰላማዊ መንገድ ለመቀየር የሚደረገው ትግል ውስብስብ በሆነበት ሰአት መድረሳችን ያሳዝናል!  መሳሪያ ሳያነግቡ ሀሳናቸውን በአደባባይ በመግለጽ የተሰለፉት ወገኖች እየደረሰባቸው ያለውን ጫና ለመረዳት ብዙ ርቆ መሔድ አያስፈልግንም ። የቅርብ የዛሬ ህያው ምክስራችንና ዋቢያችን በወህኒ ቆይታው በጠና ታሞ  የሚንከላዎሰው ወጣቱ ፖለቲከኛ ሐብታሙ አያሌው ይጠቀሳል …

ዛሬ  ህጻን ኤማንዳ የ4ኛ ልደቷን ስታከብር እንደ ህጻናት አባቷና እናቷ አጅበዋት ሻማ ለማብራት አልታደለችም ፣ ኤልማንዳ  አባቷ ሐብታሙ አንድ ልጁን  ከጎኗ ሆኖ ማድመቁ ቢቀር እሷ ስትደሰት እሱ ህመም ስቃዩ ፈውስ አግኝቶ ” እንኳን አደረሰሽ !” ለማለት አልታደለም  :( እናም ኤማልዳ በአባቷ ህመም በሀዘን ተሞልታ የዛሬ ልደት የምታከብር ምንዱብ ሆናለች ፣ የሀገሬ ፖለቲካ ፣ የሀገሬ አምባገነኖች አቧቷን የሚቀልዱበት የኢትዮጵያ ተገፊ ህጻን ኤማንዳ  :( ታሳዝናለች ፣ እኛም እናሳዝናለን  :(

እንደ ሀብታሙ ሁሉ ለሀገራችንና ለህዝባችን ያገባናል ያሉ ዜጎች ግፍ በሚፈጸምባቸው ዜጎች ቁጥር የትየለሌ እየሆነ መምጣቱ ያማል: ( ልጆችና ቤተሰብ ደግሞ የግፉ ዳፋ ቀማሾች ሆነዋል  !  የግል ጥቅምን ከማስቀደም ሀገሬ ብለው ያስተማራቸውን ወገንና ሀገር ለመታደግ በተነቃቁ ፣  ተምረው ተመራምረው ለሀገራቸው እድገት ግብአት የሚሆን ህልም በሰነቁ  ፣ ጥቂት የማይባሉ ዜጎች ፍትህ ተነፍጓቸዋል ፣ ብዙዎች በፍርደ ገምድል የፍትህ አሰጣጥ አመታትን በወህኒ ያሳልፉ ዘንድ ግድ ሆኗል  !  የትንታግ ወጣት ጎልማሶችና አባት ፖለቲከኞች መጨረሻቸው ስቃይ ፣ መከራና መገፋት ሆኗል …

ወጣቱ አባዎራ ሐብታሙ ከሀገር ወጥቶ ህክምና እንዲያገኝ ተወትውቶ የተሰየሙት የፍትህ አካላት ጉዳዩን የሚያዩበት አይን አሳዛኝ  ሆኗል ። ወጣቱ የቤተሰብ ኃላፊ በህመም  ተቀስፎ እየተሰቃየ የዳኞች አለመሟላት ፊዝ ይመስላል ፣ የቀጠሮው መደራረብም ወጣቱን ፖለቲከኛ ሀገሬው ” ፖለቲካ ኮረንቲ ነው! ” ብሎ እንዲርቅና ሐብታሙን  መቀጣጫ ለማድረግ የተወጠነ የፖለቲከኞች  የበቀል ሴራ ካልሆነ መልካም ነው  !

ዛሬ በዚህች ቀን ፍትህ ባይዘገይ ኖሮ በፍትህ ሥርአት ሐብታሙ አቅርብ ያለውን የዶክተሮች ምስክርነት ተቀብሎ ወደ ውጭ በላከው ነበር ፣ ስብዕና ቀድሞ ፣ ፍትህ በተግባር ማየት እውን ቢሆን ኖሮ ሐብታሙ በውጭ ሐገር ህክምናውን ከውኖ ለልጁ መልካም ምኞቱን ለአውሮፖ ይሁን ከእስያ ባንዱ የአለም ክፍል ” ልጀ ኤልማዳ እነሆ ተሽሎኝ እያገገምኩ ነው! ስላንችና ስለ ቀሩት የሀገሬ ቀጣይ ትውልድ ሰላማዊ ተጋድሎየን እቀጥላለሁ!  ያኔ ልደትሽ ደምቆ ከኢትዮጵያ ጋር ይከበራል  !” ይላት እንደነበር ሳስበው በዘገየው ፍትህ አዝናና ነፍሴ በሐዘን ትታወካለች   :(

በዘገየው ፍትህ ተስፋ ያልቆረጠው ጀግና ግን ዛሬም ይናገራል …በልጁ ልደት ዋዜማ በሚጠዘጥዘው የቁስል ህምም የሚሰቃየው ወጣቱ ተገፊ ፖለቲከኛ ሀብታሙ እኩለ ሌሊት ላይ  ሊጠይቁት ለሄዱት ወዳጆቹ ለእነ አይታክቴው ጋዜጠኛ ኤልያስና ዳንኤል እንዲህ ነበር ያላቸው  ”  ለእኔ ከሀገር ወጥቼ እንዳልታከም እንዲህ በኢህአዴግ የተጨከነብኝ የውክልና ሞት ስለተፈረደብኝ ነው። በእኔ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ፣ በእኔ ብቻ ሳይሆን በሚሊየኖች ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ይገባኛል።” ነበር ያለው ፣ እሱ ስለ እውነትም እንደሚሰራበት ደባ ሐብታሙ ግን በሕይወት ይኖራል ፣  አልጠፋም ፣ ይህ በፈጣሪ የተጣለ ተስፋችን ነው ፣ በፈጣሪ እንጠበቃለንና  !

እየሆነ ያለው ሁሉ ቢያምምን ፣ ህመሙ እንደ ታማሚው ወንድም  ጠዝጥዞን እንደ ዜጋ ያማል ፣ ያማል ብንልም ዳሩ  በሐብታሙና በቤተሰቡ ላይ የሚፈጸመው በደል አያልፍ የለም ያልፋል !  እሱም በተባ አንደበቱ እንዳለው እመኑኝ እንኳንስ ኢህአዴግ ደርግም ወድቋል !

አዎ  ! ፍትህ በተግባር የምናይበት ብሩህ ቀን  ናፍቆናል ፣ ዛሬ መካከል ፍንጣቂ ብርሃን እያየን የሰላማዊው ትግል ጀግና አርበኛው የሐብታሙ አያሌው ልጅ ኤማንዳና የመሰሎቿ ግፉዕ ዜጎች ልደት በአርበኝነት ታጋድሎ እየተወደሰ ደምቆ ይከበራል እያልን ምኞታችን እንገልጻለን  ! እስከዚያው ግን ጨቋኝ አገዛዝ በነገሰበት ሰማይ ስር ጊዜው የፈቀደው የጀግና ልጅ ልደቱ የሚከበረው እንዲህ በሀዘንና በመከራ ሆኗል ፣ የጀግና ልጆች ልደታችሁ ዛሬ በሀዘን ፣ ቁጭት በመለያየት የታጀበ  ቢሆንም ነገም ሌላ ቀን ነውና ጨለማው ይነጋል ፣ ከፍ ያለው ዝቅ ይላል ፣ ሁሉም አላፊ ነው ፣ ያልፋል  ! ይህ እስኪሆን ከጀግኖችና ከቤተሰባቸው ጎን ሰፊው ህዝብ ክብር ይቆማል ፣ ኤልማዳ እኛ ኢትዮጵያን የምንወድ አባትሽ ስለከፈለልን የመስዋዕትነት እዳ ከአንችና ከመሰሎችሽ ጎን ነን ! ዛሬ እንኳን ተወለድሽ የምንልሽ በዚያ ህዝባዊ መንፈስ ነው ፣ እመኝኝ ! ዛሬ አባትሽና መሰል አርበኞች በከፈሉና በሚከፍሉት የከበደ መራራ መስዋዕትነት የነገን ብሩህ ቀን ተስፋ ይመጣል !

ብቻ እንኳንም ተወለድሽ  ህጻን ኤማንዳ ሐብታሙ  !

ነቢዩ ሲራክ
ሐምሌ 21 ቀን 2008 ዓም

አማራው ኮሎኔል በ”VOA-ትግርኛ” –መለክ ሐራ

$
0
0
Gonderከጥቂት ወራት በፊት የወልቃይት ኮሚቴ አመራሩ ኮ/ል ደመቀ ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የትግርኛው ክፍል ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር፡፡ ዛሬ አሸባሪ የሚል የቅዠት ስም ቢለጠፍበትም፣ ቃለምልልሱ ሰላማዊነቱን ይመሰክራል፡፡ ወራሪ ትግሬዎቹ በጋዜጠኛው በኩል የፈጠራ መከራከሪያ እያቀረቡ ለማደናገር ቢሞክሩም፣ ጀግናው ደመቀ የሚቀመስ አልነበረም፡፡ በተለይ አስቂኙ የገላውዴዎስ አርአያ ቅጥፈት እንደማስረጃ ተቆጥሮ ጀግናውን ለመሞገት የተደረገው ሙከራ ያስተዛዝባል፡፡ ገላውዴዎስ፣ “ማኑዌል ባራዳ የተባለው ሚስዮናዊ ወልቃይት ትግራይ ውስጥ ነች ብሏል” በማለት አሳፋሪ የትርጉም ‹‹ስህተት›› መስራቱን እናስታውሳለን፡፡ ይህንን ጉድ ወጣት ምሁራን እና እንደ ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ ያሉ አንጋፋ የታሪክ ተመራማሪዎች በአደባባይ ማጋለጣቸውንም አይተናል፡፡
ኮ/ል ደመቀ ከህወሓት ጎን ተሰልፎ ደርግን መውጋቱም እንደመከራከሪያ ቀርቧል፡፡ ይህ ኮሎኔሉን ትግሬ ሊያደርገው እንደማይችል አሳምረው ያውቁታል፡፡ ትግሬ ሳይሆኑ አፋኙን ስርዓት ለመውጋት ህወሓትን የተቀላቀሉ ብዙዎች ናቸውና፡፡ እንዲያውም የህወሓትን የትጥቅ ትግል በየካቲት 11- 1967 ዓ.ም ደደቢት ላይ ከጀመሩት 11 ታጋዮች ውስጥ አንዱ አብተው ታከለ የተባለ የዛሬማ (ጎንደር) አማራ ነው፡፡ ይህንን ሃቅ አባይ ጸሃየና ስዩም እንደማይክዱ እናውቃለን፡፡ ሌላው ቀርቶ ገና ጫካ እያለ ከታማኝ በየነ ጋር በራዲዮ ብሽሽቅ ይገጥም የነበረው ሴኩቱሬ ጌታቸውስ ትግሬ ሆኖ ነው እንዴ ህወሓትን የተቀላቀለው? ከአማራ፣ ኩናማ፣ ሳሆ፣ አፋርና ሓማሴን ወዘተ ደርግን ለመውጋት ህወሓትን የተቀላቀሉ ብዙዎች ነበሩ፡፡ እረ እናውራ ከተባለ ብዙ ጉድ አለ፡፡ ራሳቸው ገድለው የጀግና ፊልም የሰሩለት ሙሴ/መሓሪ ተክሌስ ኤርትራዊ ወይስ ትግሬ? እስኪ አስመራ ያለችውን እህቱን ይጠይቁ? ወይም ከህወሓት የትጥቅ ትግል ጀማሪዎች አንዱ የሆኑትን የአስገደ ገ/ሳላሴን መፅሃፍ ያንብቡ፡፡ ባጭሩ፡ የኮ/ል ደመቀ ከህወሓት ጎን መታገል ቼጎቬራ እንጂ ትግሬ አያስብለውም! እሱም እቅጩን ነግሯቸዋል፡፡
ሌላው ደካማ መከራከሪያቸው ‹‹በወልቃይት የወንዝ፣ የተራራና የቦታ ስሞች ትግርኛ ናቸው›› ያሉት ነው፡፡ በመጀመርያ ደረጃ ወልቃይት ውስጥ የትግርኛ ስም ያለው አንድም ወንዝና ተራራ የለም! የተቀየረ ካልሆነ በስተቀር፡፡ ነገር ግን በጦርነት አልያም በሌላ የጉርብትና ንክኪዎች ምክንያት እንደ ዓዲ ረመፅ ያሉ አንዳንድ ቦታዎች በጊዜ ሂደት ትግርኛ ስያሜ ወርሰዋል፡፡ እንዲህ ያለው የስያሜ መወራረስ ደግሞ ብርቅ አይደለም፡፡ ትግራይ ውስጥም የአማርኛ ስም የየዙ ቦታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ፡ በዘመነ አፄ ዮሃንስ 4ኛ እንደርታ (ትግራይ) ውስጥ ‹‹የት-ነበርሽ›› የምትባል ከተማ እንደነበረች ደብተራ ፍሰሃ ጊዎርጊስ ከ117 ዓመት በፊት በትግርኛ ባዘጋጁት ‹‹ታሪክ ኢትዮጵያ›› መፅሃፍ ላይ ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እስካሁን ድረስ አማርኛ ስማቸውን እንደያዙ የቀጠሉ እጅግ ብዙ የትግራይ ቦታዎች አሉ፡፡ ስንቃጣ፣ አባ ጉና፣ አይናለም፣ ሸሬ፣ ላጨ… ወዘተ እንግዲህ በወያኔ ፍልስፍና ከሄድን እነኝህ አካባቢዎች ወደአማራ ክልል መግባት ነበረባቸው፡፡ እንደ ዶባ (የዛሬው አዘቦ)፣ ቦራ፣ ሰለዋ፣ ተንቤን፣ ጣንቋ አበርገለ፣ ሳምረ፣ ሰሃርቲ… ወዘተ ያሉ እጅግ በርካታ የአገውኛ ስም የያዙ አካባቢዎች፣ ወንዞችና ተራሮች ወደ ጎረቤታቸው ዋግ/አማራ ክልል መግባት ነበረባቸው፡፡ በዚህ ሂሳብ ከቀጠልን አክሱምም አይተርፍም! ለዚህ ነው እንዲህ ዓይነቱን ነገር እንደመከራከሪያ መጠቀማቸው አሳፋሪ ነው የምንለው፡፡ በነገራችን ላይ ዓዲ ረመጽ የሚለውን ስም ያወጣው፣ የጎንደር ነገስታት አቅም በተዳከመበት ወቅት ወልቃይትን ለመውረር የዘመተ የትግራይ ደጃዝማች ነው፡፡ ደጃዝማቹ የወልቃይት ጀግኖች እንደሳማ ሲያቃጥሉት አገሩን በምሬት ‹‹ዓዲ ረመፅ›› ወይም ‹‹የረመጥ አገር›› አለው፡፡ ይህ ሀይለ-ቃል በአካባቢውም ሰው ተለምዶ፣ ጦርነቱ የተካሄደበት ቦታ ስያሜ ሆኖ ለመቅረት በቅቷል፡፡ ጀግናው ይህንን ለማብራራት በጋዜጠኛው እድል አልተሰጠውም እንጂ፣ እንደተለመደው አፍ የሚያስይዙ ተያያዥ ታሪኮችን ያብራራ ነበር፡፡ በዚህ ዙርያ በሰፊው እንመለስበታለን፡፡ ለማንኛውም፣ በተንሸዋረሩ መረጃዎች ኮሎኔሉን ነጥብ ለማስጣል ያደረጉትን ሙከራና የጀግናውን መልሶች አይታችሁ ትፈርዱ ዘንድ የትግርኛውን ቃለ-ምልልስ እንደሚከተለው ወደ አማርኛ መልሰነዋል፡፡ መልካም ንባብ!
ጋዜጠኛ፡- ኮ/ል የወልቃይት ‹የአማራ ማንነት› ጥያቄ ህጋዊ ነው እንበል… ጥያቄው ደግሞ ህጋዊና ሰላማዊ መፍትሄ ይሻል፡፡ እናንተስ ጉዳዩ ህጋዊና ሰላማዊ ፍጻሜ እንዲያገኝ እየሞከራችሁ ነው?
ኮ/ል፡- በዚህ ጉዳይ ከወረዳና ከዞን (አመራሮች) ጋር መግባባት አልተቻለም… ህዝቡ ተሰብስቦ ‹‹ስለማንነታችን እንወያይ›› ማለቱ እንደወንጀል ተቆጥሮ ሰዎች እየታደኑ ነው፡፡ የማንነት ጥያቄ ማንሳት ወንጀል አይደለም… መብት ነው…ህገመንግስታዊ ጥያቄ ነው፡፡ በትግራይና በምዕራባዊው ዞን ያለው የፖለቲካ ሲስተም ግን (ይለያል)… ሰውን የማስፈራራት፣ ህጋዊውን ህገወጥ የማስመሰል እንዲሁም አዋቂ (ንቁ) የሚባሉ ሰዎችን በተለያዩ ሰበቦች የማጥፋት እቅድ ነው እየተከተሉ ያሉት፡፡ ይህ ፀረ ህገ-መንግስት ነው… መንግስት የታገለው፣ ወንድሞቻችን የታገሉት የተሻለ ዴሞክራሲ ለማምጣት ነበር ብለን እናስባለን፡፡ ስለዚህ ይህ ህገወጥ ድርጊት መወገዝ አለበት… ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጉዳዩን መርምረውና የህዝቡን ትክክለኛ ጥያቄ አይተው ውሳኔ መስጠት አለበቸው….
ጋዜጠኛ፡- ልክ ነው፡፡ ትክክለኛ መልስ መሰጠት አለበት፡፡ ነገር ግን ስለመንግስት አይደለም እየተነጋገርን ያለነው፡፡ የማንነት ጥያቄ ስላነሳችሁት ሰዎች ነው እየተነጋገርን ያለነው፡፡ ኮነሬል፡ ደጋግመው “ህጋዊ ነው ህገ-መንግስታዊ ነው” የሚል ቃል ይጠቀማሉ፤ ጥያቄው ህጋዊ እልባት ማግኘት የሚችለው ህጋዊ አሰራርን በመጠቀም ነው፡፡ በህገ መንግስቱ መሰረት ደግሞ ከወረዳ ምክር ቤት ወደ ዞን ም/ቤት፣ ከዚያ ወደክልል እያለ ነው ጉዳዩ ፌደራል መንግስት ጋ መድረስ ያለበት፡፡ እናንተስ በዚህ አግባብ ጥያቄውን ለማቅረብ ምን ያህል ዝግጁ ናችሁ ነው እያልኩ ያለሁት?
ኮ/ል፡- ካሁን በፊት በወረዳም በዞንም ደረጃ ተከራክረናል እኮነው የምልህ… “በፍጹም አንቀበላችሁም!” ተብለናል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ወረዳዎች ላይ ማመልከቻም ሊቀበሉን አልቻሉም (ምሳሌ፡ ጀጃው ደሞዝ የተባለው ወረዳ አስተዳዳሪ…)፡፡ የዞን አስተዳደሩ ደግሞ ማመልከቻውን ቢቀበለንም “የማንነት ጥያቄ የምትሉት ተቀባይነት የለውም” ብሎናል፡፡ ከዛም ይግባኝ ጠይቀን ወደ ክልል ሄድን፡፡ ክልል ላይ ደግሞ “ወረዳና ዞን ላይ የተሰጣችሁ መልስ የክልሉ አቋም ነው” የሚል ምላሽ ተሰጠን፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ወደ ፌደራል የተሄደው እያልኩህ ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡- እሺ… ‹‹ላለፉት 24 ዓመታት የወልቃይት ህዝብ በአስተዳደርና በሌሎች ነገሮች ተጠቃሚ አይደለም›› ብለውኝ ነበር፡፡ ስለዚህ ህዝቡ በመልካም አስተዳደርና በፖለቲካው ስርዓት ተጠቃሚና ተሳታፊ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ይህ ጥያቄ አይነሳም ነበር ማለት እንችላለን?
ኮ/ል፡- እርግጥ ይህንን መመለስ ያለበት ህዝቡ ነው፡፡ የመልካም አስተዳደርም የማንነት ጥያቄውም አለ- ሁሉም የየራሱ ተፅእኖ አለው፡፡ ምናልባት ህዝቡ እስካሁን ቢመቸው፣ በእኩል ዓይን ቢታይና ጥሩ አያያዝ ቢኖር ኖሮ ጥያቄውን ሊያነሳም ላያነሳም ይችላል- እሱን አላውቅም፡፡ አሁን ግን ህዝቡ በተጨባጭ እንዲህ ይላል፡- “የመልካም አስተዳደር ችግር በሁለተኛ ደረጃ የሚታይ ጉዳይ ነው፤ ቅድሚያ የማንነት ጥያቄው መመለስ አለበት፡፡”
ጋዜጠኛ፡- አቶ አባይ ወልዱ በወልቃይት-ጠገዴ በመሩት ኮንፈረንስ ላይ ተሰብሳቢዎች ያሰሙት ንግግር ግን እርስዎ ከሚሉት ጋር ይቃረናል፡፡ በዚህ ላይ ምን ይላሉ?
ኮ/ል፡- እንዲያውም እንኳን አነሳሀው፡፡ እኛኮ 100% የወልቃይት ተወላጆች የትግራይን አስተዳደር ጨርሶ አይደግፉም አንልም፡፡ አንዳንድ ካድሬዎችና የስርዓቱ አባሎች የግል ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ያወሩትን ሰምተናል፡፡ አብዛኛው ተሰብሳቢና ተናጋሪ ግን የወልቃይት ተወላጅ አይደለም- የመሃል ትግራይ ሰው ነው፡፡ “እኛ ትግሬ ነን” ነው የሚሉት፡፡ እኛም በትግሬዎች ማንነት ላይ ተቃውሞ የለንም፡፡ ሰላማዊ ሰልፎችንም ብናይ ወልቃይቴዎቹ አይወጡም፡፡ ትግሬዎቹ ናቸው ከተለያየ ቦታ በመኪና እየተጓጓዙ በጠገዴና በወልቃይት ሰልፍ የሚወጡት፡፡
ጋዜጠኛ፡- አንዳንድ ያነጋገርኳቸው ሰዎች “የማንነት ጥያቄው ህዝባዊ አይደለም፤ ለምሳሌ እንደ ኮ/ል ደመቀ ያሉት ይህንን ስርዓት ለማረጋገጥ ከህወሓት ጎን ታግለዋል፡፡ ይህንን ጥያቄ ያነሱት ስላኮረፉ፣ ጥቅማቸው ስለተነካ ወይም በሌላ ምክንያት ነው” ይላሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?
ኮ/ል፡- እርግጥ የህወሓት ታጋይ ነበርኩ፡፡ የታገልኩት ግን ደርግን ለመደምሰስ እንጂ የወልቃይትን ማንነት በግድ ትግሬ ለማድረግ አይደለም፡፡ ተገድጄ ትግሬ ለመሆን አልነበረም፡፡ ሌላው “ጥቅሙ ስለተነካበት ነው…” ለሚሉት፣ የተነካብኝ ጥቅም የለም፡፡ የጡረታ መብቴ ተጠብቆ በክብር ነው የተሰናበትኩት፡፡ ‹ከመከላከያ› ከተሰናበትኩ በኋላ እንደማንኛውም ዜጋ የመብት ጥያቄዎችን ማንሳት ደግሞ ህገ መንግስታዊ መብቴ ነው፡፡ ነገር ግን አንድ ሰው የመብት ጥያቄ ሲያነሳ በትግራይ መንግስት ስም ይለጠፍበታል፡፡ “አኩሩፎ ነው፣ ወይም የድሮ ስርዓት አባል ስለነበረ ነው” ወዘተ ይባላል…. እኔንም ‹‹አኩርፎ/ጥቅሙ ስለተነካ ነው›› የሚሉኝ እስካሁን ሌላ ስም ስላልሰጡኝ ነው፡፡ ይህ ተገቢ አይደለም፡፡ የትግራይና መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ታግለው ያመጡት ስርዓት፣ ጥያቄዎች ሲነሱበት በፍቅር በሰላምና በመግባባት መፍታት መቻል አለበት… በፍረጃ መሰረታዊ ለውጥ አይመጣም፡፡
ጋዜጠኛ፡- አንዳንድ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች (አባይ ወልዱ በመራው) “በወልቃይት የተራራና የወንዝ ስሞች ትግርኛ ናቸው፡፡ ይህንን ቦታ እንዴት ወደአማራ ማካለል ይቻላል?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ እርሶ በዚህ ላይ ምን ይላሉ?
ኮ/ል፡- መልካም፡፡ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ትግርኛ አለ፡፡ ነገር ግን አማርኛ ስሞች እየጠፉ በትግርኛ እንዲተኩም ተደርገዋል፡፡ የኛም አንዱ ጥያቄ ‹‹ቅርሶቻችን ለምን ይጠፋሉ›› የሚል ነው፡፡ ነባር የአካባቢ፣ የተራራና የጅረት ስሞች እየተቀየሩ ነው፡፡ ይህንን እንቃወማለን፡፡ ቅርስ የማጥፋቱን ስራ ተያይዘውታል…
ጋዜጠኛ፡- (ጣልቃ በመግባት) ኮ/ል የወልቃይት ዋና ከተማ ማን ይባላል?
ኮ/ል፡- ዓዲ ረመፅ ይባላል!
ጋዜጠኛ፡- ዓዲ ረመፅ የቆየ ነው ወይስ አዲስ ስም ነው?
ኮ/ል፡- ይሄኛው የቆየ ስም ነው አዲስ አይደለም…
ጋዜጠኛ፡- እሺ እርስዎ ካሉት…የአካባቢውን ቅርስና ታሪክ ከማበላሸት አንጻር የተቀየሩ ስሞችን መጥቀስ ይችላሉ?
ኮ/ል፡- ለጊዜው ዝርዝሩን አልያዝኩትም እንጂ ብዙ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ‹‹አንዳይ-ቀዳሽ›› የነበረውን፣ ‹‹ፍረ-ወይኒ››…ብለውታል… ሓድነት ብለው ስሙን የቀየሩት ቦታም አለ… ብቻ ስንቱን ብየ ልዘርዝርልህ! ይህ ልክ አይደለም፡፡ የህብረተሰቡ ፈቃድ መጠየቅ አለበት….
መለክ ሐራ

የሕወሓት ሠራዊት ከኦነግ ጋር በቦረና ውጊያ ገጠመ |የሞቱ ሰዎች አሉ

$
0
0

Zehabesha-News.jpg

(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት የሚመራው መንግስት በሞያሌ ቦረና አካባቢ በንጹሃን ዜጎች ላይ በመተኮስ ከ10 የማያንሱ ዜጎችን ካቆሰለ በኋላ ከኦነግ ሠራዊት ጋር ውጊያ መግጠሙ ተሰማ::

በቦረና በተደረገው ውጊያ ሕወሓት 4 የኦነግ ወታደሮችን ማቁሰሉን ሲገልጽ ኦነግ በበኩሉ ሁለት የሕወሓት ወታደሮችን መግደሉን ና 4 ማቁሰሉን አስታውቋል::

በዚህ በኢትዮ-ኬንያ ድንበር ሞያሌ ቦረና አካባቢ እየተደረገ ባለው ውጊያ የሕወሓት 44ኛው ክፍለጦር መሳተፉ ተሰምቷል:: ቦረና በዚህ ሳምንት በሕዝብ ተቃውሞ ስትናጥ እንደከረመች ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ዜናዎች ላይ መግለጿ አይዘነጋም::


የኦሮምያ ህዝብ በህዝባዊ እምቢተኝነቱ እንደቀጠለ ነው |የቪዲዮ ዜና ትንታኔ ከሳዲቅ አህመድ

$
0
0
«የለውጥ ትግሉ መላዉ ኢትዮጵያን አካቷል። የተበታተነዉን ትግል በአንድ ላይ ማቀናጀት ከተቻለ ድሉ ቅርብ ነዉ። ነጻነት የወል ነዉና ሁሉን የሚያማክል ነጻነትን ለማምጣት ያለዉ ብቸኛ እማራጭ አንድነት ነዉ።በአንድነት በድል ጎዳናዎች ላይ እንሒድ!»የሚል ህብረ ድምጽ ከየ አቅጣጫዉ ይሰማል።


Sport: የእንግሊዝ ፕ/ር ሊግን ሊያደምቁት የተዘጋጁት የዓለማችን ምርጥ አሰልጣኞች

$
0
0

የ2016/17 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በከፍተኛ ጉጉት እንዲጠበቅ ካደረጉት ጉዳዮች ውስጥ ግንባር ቀደሙ በዓለም ታላላቅ የሚባሉት ባለሙያዎች የሊጉ ውድድር ተሳታፊ መሆናቸው ነው፡፡ በዩሮ 2016 ውድድር ለጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ውጤታማ ተግባርን ለመፈፀም የቻለበት አንቶኒዮ ኮንቴ የቼልሲ ስራን መያዙ፤ እንዲሁም ጆዜ ሞውሪንሆ እና ፔፕ ጋርዲዮላ በማንችስተር ዩናይትድ እና የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኞች በመሆን ከዚህ በፊት ስፔን ውስጥ ጀምረውት የነበረው ከፍተኛ የሆነ የተቀናቃኝነት መንፈስን በማንችስተር ከተማ ሊደግሙት መዘጋጀታቸውንና ከወዲሁም በሊጉ ውድድር የርገን ክሎፕ፣ አርሴን ቬንገር፣ ማውሪሲዮ ፓቼቲኖ እና ክላውዲዮ ራኒዬሪን የመሳሰሉት ውጤታማ ባለሙያዎች መኖራቸው የ2016/17 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የአሰልጣኞች የውጊያ መድረክ በሚል ከወዲሁ እንዲገለፅ ምክንያት ሆኖታል፡፡

managers

አርሴን ቬንገር አርሰናልን ከድፍን 13 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ለማብቃት የሚጓጉበት የውድድር አመት ይሆናል፡፡ ሌይስተር ሲቲን ባለፈው የውድድር ዘመን በአስገራሚ ሁኔታ ለፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብር ያበቁት ጣልያናዊው አሰልጣኝ ክላውዲዮ ራኒየሪ የሻምፒዮንነት ክብራቸውን ለማስከበር ከፍተኛ የሆነ ጥረትን የሚያደርጉበት የውድድር ዘመን እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ እነዚህን ሁኔታዎች በመንተራስም የስፖርትስ ሜይል የእግር ኳስ ተንታኞች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን የሚያደምቁት ታላላቅ አሰልጣኞች በተለያዩ ዘርፎች በመከፋፈል ከዚህ በታች ባለው መልኩ የሙያው ብቃታቸውን አመዛዝነውታል፡፡

ጆዜ ሞውሪንሆ (ማን.ዩናይትድ)

ታክቲክስ 9/10

የፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ከሁሉም በላይ ትልቁ ጠንካራ ጎን የታክቲካል ብቃታቸው ውጤታማነት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ታክቲካቸውን ከቡድናቸው ተሰላፊዎች የጨዋታ ስታይል ጋር የማዋሃድ ተሰጥዋቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህ ኢንተር ሚላንን በ2009/10 ሲዝን ለቻምፒዮንስ ሊግ ለዋንጫ ድል ለማብቃት የተጠቀሙበት ያማረ ታክቲካል ስትራቴጂያቸው በቂ ማስረጃ ነው፡፡

ፐርሰናሊቲ 6/10

የጆዜ ሞውሪንሆ ፐርሰናሊቲ ተደናቂ የሙያው ብቃታቸው በትክክል የማይመትነው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፤ በተለይም ባለፈው ሲዝን የቼልሲ ስራን እንዲያጡ በዋነኝነት የሚጠቀስ ምክንያት ሆኗቸዋል ቢባልም ማጋነን አይሆንም፡፡ በተለይም የቼልሲ የቀድሟ ዶክተር ከነበረችው ኢቫ ካርኒዮሮ ጋር የፈጠሩት ግጭት ያለፈው ሲዝንን በውዝግብ ታጅበው ለመጀመር ያስገደዳቸው ሆኗል፡፡ በሪያል ማድሪድ አሰልጣኝነት ዘመናቸው ከስፔናዊው ግብ ጠባቂ አይከር ካስያስ ጋር የፈጠሩት አለመግባባት ኃላፊነታቸው በትልቅ ውዝግብ እንዲታጀብ ያስገደዳቸው ሆኗል፡፡ ሆኖም ግን ቢያንስ የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች የሞውሪንሆ የኦልድ ትራፎርድ ስራን መያዝ በመደሰት እጃቸውን ዘርግተው ተቀብለዋቸዋል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

የዝውውር እንቅስቃሴ -5/10

ሞውሪንሆ በ2004 የቼልሲ ስራን ለመጀመሪያ ጊዜ በያዙበት ወቅት ዲዲዬ ድሮግባ፣ ሪካርዶ ካርቫልሆ እና ማይክል ኤሲዮንን የመሳሳሉት ተጨዋቾችን በማስፈረም ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ጠንካራ አቋም ያለው ቡድንን ፈጥረውታል፡፡ ሆኖም ግን በቼልሲ ስራ የመጨረሻው ሲዝናቸው ከኃላፊነት እንዲነሱ ያስገደዳቸው የዛሬ ዓመት በፕሪ ሲዝን ዝውውር መስኮት የነበራቸው ተጨዋቾችን የማስፈረም እንቅስቃሴያቸው የተበላሸ መሆን ነው፤ ምክንያቱም በዝውውር መስኮቱ ያስፈረሟቸው አራት ተጨዋቾች ማለትም ባባ ራህማን፣ ፔድሮ ፓፒይ፣ ጅሎ ቦዲ እና ራዳሜል ፉልካኦ ስኬታማ ሊሆኑላቸው አልቻሉም፡፡ ሆኖም ግን ሞውሪንሆ በኦልድ ትራፎርድ ስራ ኤሪክ ባሌይ፣ ዝላታን ኢብራሂሞቪች እና ሄንሪክ ሚኪታሪያንን በመግዛት ያማረ የዝውውር እንቅስቃሴን አጀማመር አድርገዋል፡፡

ፔፕ ጋርዲዮላ /የማን.ሲቲ/

ታክቲክስ-9/10

ስፔናዊው አሰልጣኝ ከዚህ በፊት በባርሴሎናና ባየር ሙኒክ በርካታ ዋንጫዎች የተቀዳጀበት ውጤታማ ተግባርን ለመፈፀም የቻለው የተነደፈው ታክቲካል ስትራቴጂ ስኬታማ ሆኖለት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንፃር የጋርዲዮላ የታክቲክሱ የፉትቦል ስትራቴጂ በአዲሱ ሲዝን ኢትሃድን ቢያበራው አስገራሚ አይሆንም፡፡ የማንቸስተር ሲቲ ባለቤቶች ክለባቸው ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብር እንዲበቁ ያላቸውን ከፍተኛ ጉጉት በአግባቡ ለማሳካት የሚችልላቸው ትክክለኛው ባለሙያ ጋርዲዮላ እንደሚሆንም ይታመናል፡፡

ፐርሰናሊቲ 7/10

በባየር ሙኒክና ለሪያል ማድሪድ ጋርዲዮላ ሞውሪንሆ ስር የመጫወት እድልን ያገኘው ዣቪ አሎንሶ በቅርቡ በሰጠው መግለጫው ‹‹ጋርዲዮላና ሞውሪንሆ የሚለያዩት በሚከተሉት የፉትቦል ፊሉዞፊያቸው ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ን በሁለቱ ባህሪና አጠቃላዩ ፐርሰናሊቲ በአብዛኛው ተመሳሳይነት ያለው ሆኖ አግኝቼዋለሁ›› ብሎ ነበር፡፡ በእርግጥ ጋርዲዮላ ለቡድኑ ተጨዋቾች ደካማ ጎናቸውን ከመንገር የማይቆጠብበት ግልፅ የሆነ ባህሪው ከሞውሪንሆ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ በሁለቱ መካከል የፐርሰናሊቲ ልዩነት ቢኖር ጋርዲዮላ እንደ ሞውሪንሆ ሁሉ አወዛጋቢ መግለጫዎች የመስጠት ባህል የሌለው መሆኑ ነው፡፡

የዝውውር እንቅስቃሴ 7/10

እንደ ሞውሪንሆ ሁሉ ጋርዲዮላም አንዳንድ ተጨዋቾችን ባስፈረመበት ውሳኔው አልፎ አልፎ ስህተትን ሲሰራ ታይቷል፡፡ ለምሳሌ ዤራርድ ፒኬን ከማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ባርሴሎና የመለሰበት ተግባሩ ስኬታማ ሆኖለታል፡፡ በአንፃሩ ግን ሴስክ ፋብሪጋስና ዝላታን ኢብራሂሞቪችን በውድ ዋጋ የገዛበት ውሳኔው በስህተት የተሞላ ሲሆን ታይቷል፡፡

የማንቸስተር ሲቲ ስራን የጀመረው ግን ከወዲሁ የጀርመኑ ኢንተርናሽናል ኤልካይ ጉንዶጋንና ስፔናዊው አጥቂ ሚሊቶን በመግዛት በመሆኑ በአሁኑ የዝውውር መስኮት ስኬታማ ጊዜን ለማሳለፍ እንደሚችል ለመገመት አስቸጋሪ አልሆኑም፡፡ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥም ማንቸስተር ሲቲ ሌሎች ሁለት ተጨማሪ ምርጥ ብቃት ያላቸው ተጨዋቾችን ለማስፈረም ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ጋርዲዮላ የፕሪ ሲዝን ዝግጅት የሚጀምረው በስኳዱ እንዲኖሩት የሚመኛቸው ተጨዋቾችን በተሟላ ሁኔታ ለመያዝ ችሎ እንደሚሆን ነው፡፡

ከደጋፊዎች ጋር ያለው ግንኙነት 7/10

በ2012 ዓመት ጋርዲዮላ ለድፍን አራት ዓመታት የዓለማችን እጅግ ውጤታማ ክለብ ያደረገውን የባርሴሎና ስራን በመልቀቅ የክለቡ ደጋፊዎች በከፍተኛ ደረጃ አዝነዋል፡፡ ባርሴሎናን በመልቀቅ የባየር ሙኒክ ስራን ከያዘ ወዲህ ግን ከባቫሪያኑ ክለብ ደጋፊዎች ር ያንን ያህል በመልካም ጎኑ ሊጠቀስ የሚችል ግንኙነት ፈጥሮ ነበር ሊባል አይችልም፡፡ የጀርመን ሚዲያዎችም እንደ ባርሴሎና ሁሉ ለባየር ሙኒክ ውጤታማነት ከፍተኛ የሆነ የተቆርቋሪነት መንፈስን መያዙን በመጠራጠር በተደጋጋሚ ትችቶችን ሲያቀርቡበት መታየታቸው የተለመደ ባህላቸው ሆኖ ዘልቋል፡፡

ከዚህ በተረፈ ግን ጋርዲዮላ የሚከተለውን የጨዋታ ስታይል የየትኛውም ክለብ ደጋፊዎች ቢሆኑ ሊጠሉት የሚችሉት አይነት አይደለም፡፡ ከዚህ አንፃር በአሁኑ ስራው ከማንቸስተር ሲቲ ደጋፊዎች ጋር መልካም ግንኙነትን የመፍጠሩ ተስፋ የሰፋ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

አንቶኒዮ ኮንቴ /ቼልሲ/

ታክቲክስ 8/10

ኮንቴ ከዚህ በፊት በጁቬንቱስና በጣሊያን ብሔራዊ ቡድን የተከተለውን 3-5-2 የጨዋታ ሲስተምን በቼልሲ ዋና አሰልጣኝነት ዘመኑ ተግባራዊ እንደሚያደርገው ለመገመት አስቸጋሪ አልሆነም፡፡ በዚህ ፎርሜሽን የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን በዩሮ 2016 ውድድር ያልተጠበቀ ጥንካሬን እንዲይዝ የረዳው ሆኗል፡፡

ሆነም ግን ከጀርመን ጋር በተደረገው የውድድሩ ሩብ ፍፃሜ በዚህ ሲስተም የማጥቃት ታክቲክስን ተግባራዊ ማድረጉ ፍሬያማ ሳይሆንለት ቀርቷል፡፡ ከዚህ አንፃር የቼልሲ ደጋፊዎች በኮንቴ ስር ቡድናቸው በመከላከል ላይ ያተኮረ ታክቲክስን መሰረት በማድረግ ጎሎችን በፈጣን የካውንተር አታክ ሲስተም የማስቆጠር ስትራቴጂን እንደሚይዝ ቢጠብቁ አስገራሚ አይሆንም፡፡

ፐርሰናሊቲ 9/10

በዩሮ 2016 ውድድር ተሳትፎው ኮንቴ በጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ታክቲካል ኤሪያ በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች ላይ በከፍተኛ ስሜት ተውጦ ሲወራጭ የታየበት ተግባሩ በውስጡ ያለው ባህሪ ምን እንደሚመስል የማንፀባረቅ ኃይል ያለው ከፍተኛ የሆነ የማሸነፍ ወኔና ለሚመራው ቡድን ስኬታማነት ከፍተኛ የሆነ ተቆርቋሪነት መንፈስን መላበሱን በጭራሽ መጠራጠር አያሻም፡፡

ከዚህ አንፃር ጆዜ ሞውሪንሆ የቼልሲ ስራን ሲለቁ በክለቡ ደጋፊዎች በከፍተኛ ደረጃ የሚወደድ ሌላ አሰልጣንን ማግኘታቸው አጠራጣሪ የሆነበት እውነታን የኮንቴ የስታምፎርድ ብሪጅ ስራን መያዝ እንደሚለውጠው ይጠበቃል፡፡ ውጤታማ ዘመን ደግሞ ወደ ምዕራብ ለንደኑ ክለብ እንዲመለስ የሚያስችል ትክክለኛው ባለሙያም ጭምር ነው፡፡

የዝውውር እንቅስቃሴ 8/10

ኮንቴ በጁቬንቱስ አሰልጣኝነት ዘመኑ ፖል ፓግባን ከማንቸስተር ዩናይትድ በነፃ ዝውውር ከማስፈረምም አልፎ አርቱሮ ቪዳልን ማግኘቱ ስልጠናው የዝውውር እንቅስቃሴ ስትራቴጂ እንዳለው በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ያሳለፈው የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣንነት በመምራት መሆኑ ምንም ተፅዕኖን ሳይፈጥርበት በቼልሲ ስራው ከወዲሁ ቤልጅየማዊው ኢንተርናሽናል ሚኪይ ባትሹላይን በ33 ሚልየን ፓውንድ ሂሳብ ከኦሎምፒክ ማርሴይ የገዛበት ውልን ተፈፃሚ አድርጎታል፡፡የኮንቴ ቀጣዩ ተግባር የሚመስለውም የቼልሲ የተከላካይ መስመርን የአማካይ ክፍልን የሚያጠናክርበት አዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረም መቻል ነው፡፡ ከወዲሁ ስማቸው ከቼልሲ ዝውውር ጋር በመያያዝ ላይ ያሉት ንጎሎ ካንቴና ራድ ያንጎላን በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ስታምፎርድ ብሪጅ የመድረሳቸው ተስፋ ሰፊ ሆኖ በመታየት ላይ ነው፡፡ በተለይም ያንጎላን ለቼልሲ እንዲፈርም የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ጓደኛው ኤደን ሃዛርድ በዩሮ 2016 ውድድር ተሳትፏቸው ወቅት ይፋ ያደረገበት መግለጫን መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የደጋፊዎች ግንኙነት 9/10

የማንኛውም ክለብ ደጋፊዎች ቢሆኑ ለቡድናቸው ውጤታማነት ከፍተኛ የሆነ የተቆርቋሪነት መንፈስ ያለው ዋና አሰልጣኝ እንዲኖቸው መመኘታቸው የተለመደ ነው፡፡ በዩሮ 2016 ውድድር ተሳትፎው በእያንዳንዱ ግጥሚያዎች ላይ በከፍተኛ ስሜት ተውጦ የቡድኑን ተጨዋቾች በመምራት ባሀሪው ላይም ከሚታወቀው ኮንቴ የተሻለ ይህንን ክራይቴሪያን በተገቢው ሁኔታ የሚያሟላ ባለሙያን ማግኘት ይከብዳል፡፡ ከዚህ አንፃር ኮንቴ የቼልሲ የስራ ዘመኑ ከክለቡ ደጋፊዎች መልካም ግንኙነትን ፈጥሮ እንደሚዘልቅ ለመገመት አስቸጋሪ አይሆንም፡፡

አርሴን ቬንገር /አርሰናል/

ታክቲክስ 7/10

ፈረንሳዊው አሰልጣኝ አርሰናልን ከመሩበት 20 ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ስምንት ዓመታት ያሳለፉት ለቡድናቸው በርካታ ጎሎችን በማስቆጠር በማጥቃት ላይ ያተኮረ ስትራቴጂን በማስገኘት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ውበት በተላበሰ ፉትቦል አድምቀውት ነበር፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህም የቬንገር በማጥቃት ላይ ያተኮረ የፉትቦል ፊሎዞፊ ብዙም አልተቀየረም፡፡ ሆኖም ግን ይህ ፊሎዞፊያቸው በተጋጣሚ ቡድኖች ከበቂም በላይ የታወቀበት እውነታን ለመቀየር የሚችሉበት አማራጭ ታክቲክስ ሲቀይሩ አለመታየታቸው አርሰናልን ከ2003/04 ሲዝን ወዲህ አንድ እንኳን የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ክብርን ያሳጣው ሆኗል፡፡

ፐርሰናሊቲ 6/10

የፈረንሳዊው አሰልጣኝ ባህሪን አጥብቀው የሚጠሉት ወገኖች አሉ፡፡ በተለይም የተጋጣሚ ቡድን አሰልጣኞች ‹‹ሽንፈትን በፀጋ በመቀበል ችግር አለባቸው›› በሚል ይወቅሷቸዋል፡፡ በዛኑ መጠን ግን የቬንገርን ባህሪና ስብዕና የሚወዱት ወገኖችም አሉ፡፡ ከሚወደድላቸው ባህሪዎቻቸው ውስጥ ለሽንፈታቸው የራሳቸው ቡድን ተጨዋቾችን በይፋ ከመውቀስ መቆጠባቸውና ቡድናቸውን ከአስቸጋሪ ሁኔታ በፍጥነት እንዲላቀቅ ለማስቻል የሚያደርጉት ሙሉ ትኩረት ነው፡፡

የዝውውር እንቅስቃሴ 8/10

ቬንገር በአብዛኛው አዳዲስ ተጨዋቾችን በማስፈረም ተግባራቸው ስኬታማ ሲሆኑ ታይተዋል፡፡ በተለይም ቲዬሪ ሆንሪን ከጁቬንቱስ በማስፈረም በአርሰናል ታሪክ የክለቡ የምንጊዜውም ከፍተኛው ጎል አግቢ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

በ2015 ፕሪ ሲዝን ግን ፒተር ቼክን በማስፈረም የተገደበ የዝውውር እንቅስቃሴን በማድረግ ልላ የሜዳ ላይ ምርጥ ብቃት ያለው ተጨዋችን ለማስፈረም ተስኗቸዋል፡፡ ያንን ስህተታቸው በአሁኑ የዝውውር መስኮት ስዊዘርላንዳዊው አማካይ ግራንት ዣካን ከወዲሁ በማስፈረም እርማትን ማስገኘት ጀምረዋል፡፡ ቀጣዩ የቬንገር አላማ ትክክለናው ጎል አዳኝን ለቡድናቸው የፊት አጥቂ መስመር ለማስገኘት መቻል ነው፡፡

የደጋፊዎች ግንኙነት 5-10

ቬንገር በየዓቱ የአርሰናል የቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎን ማግኘት ትልቅ ኩራትን ሲፈጥርባቸው የሚታዩበት ባህሪያቸው ከክለባቸው ደጋፊዎች ውስጥ በግማሽ ያህሉ እንዲጠሉ በሞኝነት የሚጠቀስ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአርሰናል ደጋፊዎች የቡድናቸው በወሳኝ ወቅት ከፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት ፉክክር የመሸሽ ባህሉን በመጥላት በቬንገር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞን ማሰማታቸው የተለመደ ሆኗል፡፡

የርገን ክሎፕ /ሊቨርፑል/ 

ታክቲክስ 6/10

ጀርመናዊው አሰልጣኝ በቦሪሺያ ዶርትሙንድ ቆይታቸው ይበልጥ ስኬታማ ያደረጋቸው ታክቲክሳቸው ካውንተር ፕሬሲንግ የሚለው መመሪያቸው ነው፡፡ ይህንን የቡድናቸው ተሰላፊዎች በከፍተኛ ፍጥነት በታጀበ የማጥቃት እንቅስቃሴ በተጋጣሚ ቡድን ላይ ከፍተኛ ጫናን እንዲፈጥሩ የሚያደርጉበት ስትራቴጂን ወደ ሊቨርፑል ዘልቆ እንዲገባ አስችለውታል፡፡ ይህ ታክቲክስ በሊቨርፑል ፍሬያማ መሆን ለመጀመሩ ቡድኑ የ2015/16 ሲዝን የዩሮ 2015/16 ሲዝንን ለዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ግጥሚያ በመድረስ ማጠናቀቁ በቂ ማስረጃ በመሆኑም የክሎፕ ካውንተር ፕሬሲንግ ሲስተም በአዲሱ ሲዝንም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይጠበቃል፡፡

ፐርሰናሊቲ 10/10

የየርጊን ክሎፕ የግል ባህሪና አጠቃላዩ ሰብዕና በራሳቸው ቡድን ተጨዋቾች ብቻ ሳይሆን በተቃራኒ ቡድኖች አባላትና በገለልተኛ የፉትቦል አፍቃሪዎች ጭምር የሚደድ ነው፡፡ በተለይም የቡድናቸው ድልን በከፍተኛ የፈንጠዝያ ስሜት ሆነው ደስታቸውን የሚገልፁበት ባህሪያቸው ሁሉንም ክለቦችን ደጋፊዎችን የማዝናናት ደረጃው ከፍተኛ ነው፡፡

የዝውውር እንቅስቃሴ 7/10

ባሪሽያ ዶርትሙንድ ሁለት ጊዜ የጀርመን ቡንደስሊጋ ሻምፒዮንነት ክብር የተቀዳጀውና በ2013 የቻምፒዮንስ ሊግ ፋይናል በዌምብሊ ለማድረግ የቻለው በክሉፕ ብልህ የዝውውር እንቅስቃሴን መሰረቱ በማድረግ ነው፡፡

በተለይም ማትስ ሃሜልሰና ሮቤርቶ ሌዎንዶውስኪን በማስፈረም የዶርትሙንድ እጅግ ምርጡ ተጨዋቾች አድርገዋቸው ነበር፡፡ በአሁኑ የዝውውር መስኮት ከወዲሁ ለሊቨርፑል ያስፈረሟቸው ሶስት ተጨዋቾች ማለትም ሳይዶ ማኔ፣ ሊሪስ ካሪዩስና ጀይል ማቲፕ ግን የክለቡን ትልቅ ስታንዳርድን የሚመጥን ውጤታማ ብቃትን መያዛቸውን የሚጠራጠሩ አስተያየት ሰጪዎች አሉ፡፡

የደጋፊዎች ግንኙነት 9/10

ክሎፕ በዶርትሙንድ የስራ ዘመናቸው በክለቡ ደጋፊዎች በከፍተኛ ደረጃ ይፈቀሩ ነበሩ፡፡ ይህ ሁኔታ የአንፊልድ ስራ ሲይዙ በሊቨርፑል ደጋፊዎች በተደረገላቸው ያማረ አቀባበል ተደግሞላቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ጀርመናዊው አሰልጣኝን የሚጠላ አንድም የሊቨርፑል ደጋፊ መኖሩ አጠራጣሪ ነው፡፡

“እስክ ድል ደጃፍ ድረስ በአላህ ስም ተማምለናል!”–የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት

$
0
0

Muslims

July 27, 2016

ዛሬ በሃገራችን ከእምነት ነፃነት መነፈግ፣ በሕይወት የመኖር ዋስትና እስከ ማጣት ድረስ ጠመንጃ የአነገቡና ሣንጃ የወደሩ የአንድ መንደር ልጆች በተቆጣጠሩት አምባገነናዊ አገዛዝ ሥር የሕዝቦች መገደል፣ መታሠርና ከአገር መሰደድ እየባሰበት እንጂ የመክሰም ጭላንጭል አይታይበትም። የድብደባውና የማሸማቀቁ ዋና ዓላማ ሕዝብ የፍርሃት ድባብ ሰፍኖበት ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ ነው። የወያኔ ሥርዓት በደል ገፈት ቀማሽ የሆነው ሰላማዊው የሙስሊሙ ሕብረተሰብ የፍርሃትን ምሽግ ደርምሶ ታግለው እንዲያታግሉት ለመረጣቸው መሪዎቹ እስከ ድል ደጃፍ ድረስ ከጎናቸው መቆሙን በቃለ መሃላ አረጋግጧል። የዲያስፖራውም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም በድምፃችን ይሰማ መሪነት የሚያኪያሄደውን ሰላማዊ ትግል በመደገፍ ትግሉን የተቀላቀለው ውዲያው መሆኑ በታሪክ ዓምድ ላይ ሰፍሯል።

zehabesha-muslim.jpg

ይህ ታሪካዊ ትግል የወለደው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት ምሁራንን፣ የሕግና የሚዲያ ባለሙያዎችን፣ የሃይማኖት መሪዎችን እና የታወቁ አክትቪስቶችን ያካተተ ኮንፈረንስ ከጁላይ 15 እስከ ጁላይ 16 2016 ለዋሺንግተን ዲሲ ቅርበት ባላት በላልንሃም ሜሪላንድ በቅርቡ በፕሬዚደንት ኡርዱግዋን በተመርቀው በአዲሱ የቱርክ መስጊድ አዳራሽ ውስጥ አድርጓል። ስብሰባው ላለፍት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ያደረጉት የሞትና የሽረት ትግል በጥልቀት የተገመገመበት፣ የወደፊት አቅጣጫውን አመላካች የሆኑ ፅንሰ ሃሳቦች የተሰነዘሩበት ከመሆኑም በላይ ኢትዮጵያ የሁሉም ዜጋ እምነትና ነፃነት የሚከበርባት የጋራ አገር እንዴት መሆን እንደምትችል የስብሰባው ታዳሚዎችና እንግዳ ተናጋሪዎች ሃሳብ ተለዋውጠውበታል። የስብሰባውም ጠቅላላ ሂደት በዘመናዊ የስርጭት መሳሪያ በቀጥታ ከአዳራሹ ቅፅበት በቅፅበት ይተላለፍ ስለነበረ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ  ያገባኛል ባዮች በኢትዮጵያ ውስጥ ጭምር ተከታትለውታል።

በዚህ ስብሰባ ላይ ያለ አግባብ ፍርድ የተገመደለባቸው የወንድሞቻችን የፍርድ ሂደት የሕግ ሙያ ባላቸው እንግዳ ተናጋርዎቻችን በሰፊው ሲዳሰስ፣ የሙስሊሙ ሰላማዊ ትግል ለሌላው የሕብረተሰቡ ክፍል ያስተማረው ትምህርት ተወድሷል። የሚዲያ ባለሙያዎች ከሰላማዊ ትግሉ ጋር ተያይዞ የገጠማቸው ፈተናና ትግሉን ለማፋፋም በማድረግ ላይ ያሉት አስተዋጽኦ ለታዳሚው በይበልጥ ግልጽ አድርገውለታል። በዚሁ ስብሰባ ላይ የሚናሶታ እስቴት በመወከል በአሜሪካ ኮንግረስ ውስጥ የመጀመሪያ ሙስሊም አባል የሆኑት የኪትዝ ኤሊሶን የቪዲዮ መልእክት ለታዳሚው ሲቀርብ፣ “The Movement” ወይም ‘ንቅናቄው” የተሰኘው ስለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ የተዘጋጀው ዘጋቢ ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ ለተመልካች ቀርቧል። የታወቀው ገጣሚ ወንድማችን አሊ ሁሴን በውይይቶች መሃል አለፍ አለፍ ብሎ ያቀረባቸው ግጥሞች የታዳሚውን የታመቀ ስሜት ከሚገባ በላይ አገንፍለውት ነበር።

ዲያስፖራ ያለው የኢትዮጵያ ሙስሊም ህብረተሰብ እስካሁን ካዘጋጃቸው ስብሰባዎች ሁሉ በዓይነቱ የተለየ ነው ተብሎ የተመሰከረለት ይህ ስብሰባ የተለያየ እምነትና የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ተናጋሪ እንግዶች ያቀረቧቸው ሃሳቦች በነፃ የተንሸራሸሩበት ከመሆኑም በላይ በመደማመጥ፣ በመተሳሰብ፣ በመከባበርና በመስማማት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ አንድነት በመገንባት የጋራ ጠላትን ድል መምታት እንደሚቻል ግንዛቤ የተወሰደበት ውጤታማ ስብሰባ ነበር።

የወያኔ ዘረኛ ሥርአት ሕዝብን በጎሣ እና በሃይማኖት እየነጣጠለ የሚፈፅመውን የጅምላ ጭፍጨፋ ማቆም የሚቻለው ተጠቂው ሕዝብ በጋራ ሲታገል ብቻ መሆኑ በዚህ ስብሰባ ላይ ተሰምሮበታል። በዚህ ወሳኝ የትግል ወቅት በዳይና ገዳይ ሥርዓትን  መቃዎም ፖለቲካ ውስጥ መግባት ነው በሚል ሰንካላ የፈሪዎችና የአድር ባዮች አስተሳሰብ ራስንና ሌላውንም ሕዝብ ከትግል እንዲሸሽ ማድረግ የወያኔን ዓላማ ከማራመድ ተለይቶ መታየት የለበትም በሚለው ሁሉም እንግዳ ተናጋሪዎች ተስማምተውበታል።

ማንም ሕሊና ያለው ግለሰብ፣ ቡድንም ሆነ ድርጅት በደልና ጭፍጨፋ በሕዝብ ላይ ሲፈፀም እያየ ገለልተኛ ነኝ ሊል አይችልም። ዝምታው ከጨፍጫፊው ጋር ከመተባበር ተለይቶ ሊታይም አይችልም። ከተጨፍጫፊው ሕዝብ አብራክ

የወጣን ሁሉ እስላማዊ፣ ሞራላዊና ወገናዊ ግዲታ አለብንና።  ኡስታዞቻችንን አህመዲን ጀበል፣ በድሩ ሁሴን፣ ከማል ሸምሱንና ሙሃመድ አባተን ጨምሮ እርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሎ ስማቸው በወህኒ ቤቶች ሰሌዳ ላይ የተለጠፈው በአጠቃላይ 84 ንፁሃን ወገኖቻችንን ጉዳይ ከትግሉ ጎን ያላቆመን ምን ሊያቆመን ነው? እስከ ዛሬ ድረስ የገለልተኛነትን ጋቢ ተከናንበው የከረሙ ሁሉ ዛሬ የወያኔን አረመኔ ሥርዓት በአደባባይ ወጥተው ከማውገዝ ሌላ አማራጭ የላቸውም። በእርግጥ ማንነታቸው ለሁሉም በበለጠ ፍንትው ብሎና ጠርቶ የሚታይበት ወቅቱ አሁን ነው።

በታሣሪዎች ላይ ሽብር ነዝቶ፣ ሕዝቡም ተሸማቆ ከትግሉ እንዲያፈገፍግ ለማድረግም ሊሆን ይችላል ወያኔ የስም መለጠፉን  የሚጠቀምበት ብሎ ዝም ማለት የዋህነት ሳይሆን ሃላፊነትን መሸሽና ውንድሞቻችንን አሳልፎ መስጠት ነው። ለትግሉ የገባነውን ቃለመሃላም መርሳት ነው። ስለሆነም በዲያስፖራም ሆነ በአገርቤት በየጊዜው የገለልተኛነት አዋጅ በማወጅና በአጥር ላይ በመቀመጥ ትግሉን እንደ አጫዋች የሚመለከቱ ሁሉ ከሰው በላው የወያኔ ዘረኛ ሥርዓት ጋር የሚደረግውን የሞትና የሽረት ትግል ከሕዝብ ጎን በመሆን ነገ ሳይሆን ዛሬ መቀላቀል አለባቸው እንላለን። ማጣፊያ አጠረኝ ከአሁን በኋላ አያዋጣም። የትግሉን አቀበት በአንድነት ወጥተን በድል አምባ ላይ በሕብረት መሰባሰብ አለብን። ትግሉ ሲወጠን እስከድል ደጃፍ ድረስ አብርን ልንጓዝ በአላህ ስም ተማምለናልና!!

ትግላችን በአላህ ፈቃድ እስከድል ደጃፍ ድረስ ይገሰግሳል!

አላሁ አክበር!!!

የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ሕብረት

 

 

 

አስቸኳይ ወቅታዊ መልእክት! –ነፃነት ዘለቀ

$
0
0

ነፃነት ዘለቀ (ኢትዮጵያ) nzeleke35@gmail.com

strugleአሁን ያለንበት ወቅት ለወሬና ለፍልስፍና አመቺ አይደለም፡፡ በሞቀንና በበረድን ቁጥር ከያለንበት ሸጥና ጎጥ እየተነሣን በብዕርም ይሁን በአንደበት የምንወራከብበት ወይም እንካስላንትያ የምንገጥመት ወቅት ላይ አይደለንም፡፡ ጊዜው የጣር መጨረሻ ነው፤ ዘመኑ የነፃነት ትግል ወቅት ነው፡፡ ስለሆነም ከሚያናቁረን ይልቅ የሚያስማማንን ንግግርና ሃሳብ የምንወረውርበት ሊሆን ይገባል፡፡ ከእልህና ከስድብ ይልቅ መቻቻልና መግባባት የሠፈነበት የመጨረሻ ምዕራፍ ሊሆን ጊዜው ግድ ይለናል፡፡

ከቅርብ ወራት ወዲህ የሕዝብ ትግል እየተጋጋለና በስፋትም በጥልቀትም እየጋመ የመጣበት ሁኔታ በግልጽ እየታዬ ነው፡፡ የዘመናት የተናጠል ወያኔያዊ ግፍና በደል የፈጠረውን ይህን አጋጣሚ አለመጠቀም ምን ማለት እንደሆነ ሁላችንም ልናውቀው ይገባል፡፡ ወደሚያስማሙን ነገሮች ይልቅ ወደሚያቆራቁሱን ነገሮች የሚያዘነብል ማናቸውንም ዓይነት ተፃራሪ ሃሳብና አሠራር መቀበል የለብንም፡፡ የተበዳደልን እንኳን ብንሆን፣ የተቀያየምን እንኳን ብንሆን የግል ቂማችንንና ከሀገር ኅልውና አኳያ ተራ ሊባል የሚችል የግል ቁርሾኣችንን አስወግደን ለጋራ ሀገራዊ ነፃነት በጋራ መሰለፍ ይገባናል፡፡ የማይደገምን አጋጣሚ ለበጎ ነገር መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ጅልነት ይብቃ፡፡

እስካሁን በከንቱ ያጠፋነው ጊዜና ኃይል በቁጭት ሊያንገበግበን ይገባል፡፡ ወደራሳችን እንመለስ፡፡ በዘርና በጎሣ፣ በሃይማኖትና በቋንቋ እየተናከስን ወያኔዎች በቀደዱልን ፈር ስንተም እነሆ 25 ዓመታትን ዘለቅን፡፡ እነሱ እንጂ እኛ የተጠቀምነው ነገር ምንም የለም፡፡ በነዚህ ቀጣፊዎች ተበልጠን ለአገዛዛቸው ብዙ አስተዋፅዖ አደረግን፡፡ ለነሱ ዕድሜ መራዘም እነሱ ካደረጉት ይልቅ እኛ ያገዝናቸው በእጅጉ ይበልጣል፡፡ “እንትና ጨቁኖሃልና በለው!” ስንባል ግር ብለን በመታዘዝ ብዙ ጥፋት አድርሰናል እነሱ ራሳቸው በሞኝነታችን እስኪስቁና ቀሪው ዓለም ጉድ እያለ እስኪታዘበን ድረስ፡፡ “የእነእንትና ሃይማኖት እንዲህ ያለ መንግሥት ሊያቆምብህ ነው” ስንባል ውሸት ይሁን እውነት ከሁለተኛና ሦስተኛ ወገን ሳናጣራ በጭፍን በመቀበል ከወንድሞቻችን ጋር ጥላቻና ቂም በቀል አትርፈናል፤ አንዳችን አንዳችንን በጥርጣሬ ዐይን እንድናይም ተገደናል፡፡ ተዘርዝርሮ በማያልቅ የቆረጣ ሥልት እየተመታን ከሰውነት በታች ሆነን እንድንቀር ተደርገናል፤ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ ወያኔ ብቻ ሣይሆን ራሳችንም ነን፡፡

እስካሁን የነበረን አካሄድ አስቂኝና አስገራሚ ነበር – እንደጭፍግ(ትራጄዲ) ቲያትርም ሊታይ ይችላል፡፡ የአንዲት ሀገር ልጆች መሆናችንን ረስተን ነበር፡፡ የጋራ ዕጣ ፋንታ ያለን መሆናችንን ዘንግተን ነበር፡፡ አንዳችንን የሚያጠፋ ኃይል ሌላኛችንን የሚምረን ይመስለን ነበር፡፡  የሚያጣሉና የሚያጋጩን ለኛው ብለውና ከእውነት ተቆርቁረውልን ይመስለን ነበር፡፡ በዘርና በጎሣ ሲከፋፍሉን፣ በሃይማኖትና በዘውግ ለያይተው ሲያራኩቱን ለኛ ብለውና አዝነውልን ይመስለን ነበር፡፡ ከ25 ዓመታት የጅልነትና የቂልነት ቆይታ በኋላ ግን እውነቱ የተገለጠልን ይመስላል፡፡

የወለጋ ሕዝብ በወያኔ ላይ ሲያምፅ ለጎንደሩ ምንም የማይመስለው ጊዜ ነበር፤ የሸዋው ሕዝብ በዘረኛው አገዛዝ ላይ ሲያምፅ ለወለጋው ምንም የማይመስለው ወቅት ነበር፡፡ በሴቶች ላይ መቅሰፍት ሲታወጅ ወንዶች ምንም የማይመስላቸው ጊዜ ነበር፡፡ “ክርስትናን አጠፋን!” ተብሎ ሲፎከር ይህ ፉከራ ወደ እስልምናም ሊዛመት እንደሚችል የሚጠረጥር ሙስሊም አልነበረም፡፡ የአዲስ አበባ መሬት ከኗሪው እየተቀማ ለሀብታም ሲቸበቸብ የናዝሬትና የደብረ ብርሃን ነዋሪዎች ነገሬ ሳይሉት እንደሙዚቃ ያዳምጡት ነበር፡፡ ኦሮሞው ከይዞታው የመፈናቀሉ ዜና ለዐማራው የአውሮፓ ዜና ያህል ይሰማው ነበር፡፡ አንዳችም ነገር ሊጎድልበት የማይጠበቅበት አብርሃ ደስታ በኢትዮጵያዊነቱ ሰበብ ለእሥርና እንግልት ግደይ ተስፋጋብርም ለሞት ሲዳረግ ለባሌውና ለጎጃሙ ምስኪን ዜጋ የቅብጠት ያህል ይቆጠር ነበር፡፡ ተመስገን ደሳለኝና እስክንድር ነጋ ለሕዝብ መብት በመጮሃቸው ሳቢያ ዘብጥያ ሲወርዱ ለደቻሳና ለአላምረው ደንታ የማይሰጣቸው ጊዜ ነበር፡፡ ብዙ ዕንቆቅልሾችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ችግሩ ቀስ በቀስ የሁሉንም በር ማንኳኳቱ ተደረሰበትና ይሄውና አሁን የዐመፁ ቋያ እንደ ቋቁቻ በየክልሉ ይፈነዳዳ ጀመር፡፡ ይህ ደግሞ የምጡ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻው ገና ነው፤ የሚጠበቀው መጨረሻ ደግሞ እግዚአብሐየር ካልተጨመረበት እጅግ ዘግናኝ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ከእያንዳንዱ የዳመና ጉርምርምታ በኋላ ዶፍ አለ፡፡ ምንጮችና ኩሬዎች እየሞሉ አነስተኛ ወንዞችን ያጠግባሉ፤ አነስተኛ ወንዞችም አገር አቋራጭ ትላልቅ ወንዞችን ይመግባሉ፡፡ ያኔ የሚከሰተው ጎርፍ አደገኛና በቀላሉ የማይበርድ ነው፡፡ መጠንቀቅ ያን መሰሉን ጎርፍ ነው፡፡ ልብ በሉ – እኛ ካልተጠነቀቅን ደግሞ ወያኔ ስለጎርፍ የመጨነቅ ባሕርይ የለውም፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን በብልህነታችን እንታወቃለን፡፡ ሰው በቀደደልን የተንኮል ቦይ ገብተን በሚያስከፋ ደረጃ የተጎዳነው በዚህ ክፍለ ዘመን ብቻ ይመስለኛል፡፡ አሁን ግን ወደ ኅሊናችን እየተመለስን ነን ብዬ አስባለሁ፡፡ ዕድሜና መከራ አስተማሪዎች ናቸው፡፡ ባሳለፍናቸው የወያኔ መሪር የአገዛዝ ዘመናት ብዙ ተምረናል፡፡ ጠላትን ከወዳጅ የሚያስለይ በቂ ግንዛቤ ጨብጠናል፡፡ የበደለን ወያኔ እንጂ የተለዬ ዘር እንደሌለ ተረድተናል፡፡ ምክንያቱም ከሞላ ጎደል ሁላችንም ተጎጂዎች ነበርንና፡፡ አንጻራዊ የጥቅም መለያየት ቢኖር ሥርዓ የፈጠረው ሸውራራ የአገዛዝ ዘይቤ እንጂ ከሕዝብ የመነጨ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሕዝብና ሕዝብ መቼም ቢሆን ተለያይቶ አይለያይምና አጓቱን ሳይሆን ዐይቡን ማየት ያስፈልጋል፡፡ እናም መቼም ቢሆን ፍርዳችንና ተግባራችን ፍትሃዊ ይሁን፡፡

አሁን ማድረግ ያለብን ብዙ ነገር አለ፡፡ ጠላት ምን ጊዜም ጠላት ነውና መቼም አይለቀንም፡፡ እንኳንስ በነፃነት ትግል ወቅት ከነፃነት ማዶም ተሻሮ ብዙ ሊያምሰን እንደሚሞክር ግልጽ ነው፡፡ መፍትሔው ግን ቀላል ነው – እሱም መሣሪያና ትጥቅ ሣይሆን ዕውቀትንና ጥበብን መታጠቅ ነው፡፡ ከአንድ ታንክና ከብዙ ሚሣይል ይልቅ “ወንድምህን እንደራስህ ውደድ” የምትለዋ ዐረፍተ ነገር ብዙ ዋጋና ትርጉም አላት፡፡ ከአሥር የጦር አውሮፕላን ይልቅ “ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን፣ ነብርም ዥንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይቻለዋልን?” የምትለዋ ነባር መጽሐፍ ቅዲሣዊ ብሂል የበለጠ ፈውስ ናት፡፡ ከእልህና ከበቀል ስሜት ይልቅ “ወንድሜ/ጓደኛዬ ሰባት ጊዜ ቢበድለኝ ሰባት ጊዜውን ሁሉ ይቅር ልለው ነውን?” ተብሎ ለተጠየቀ ጥያቄ “ሰባት ጊዜ ሰባም ቢሆን ይቅር በለው” የተባለው የይቅር ባይነት ክርስቶሳዊ አስተምህሮ የቆረፈደን ፍቅር ያለሰልሳል፣ በጥላቻ የደነደነን ልብ ያሟሽሻል፡፡ እስካሁን የሆንነውን ሁሉ የሆንነው አንዳች የፀላዔ ሠናያት መንፈስ በመካከላችን – ወያኔን ተመስሎ – ናኝቶብን እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ፍቅራችንና መተዛዘናችን እንኳንስ ለኛ ለሌላም ይተርፋል፡፡ ስለሆነም ከስሜታዊነት ፀድተንና ከቂም በቀልና ጥላቻ ራሳችንን አስወግደን ፍትሃዊ ትግል እናካሂድ፡፡ የዘሩት መብቀሉ አይቀርም፤ ተኝተው ተፉት ወደራስ መመለሱም እንዲሁ፡፡ የደም ፍላት የትም አያደርስም፡፡ አስተዋይነት ግን ብዙ ወንዞችን ያሻግራል፡፡

ስለሆነም ከሰው በኋላ የመጡ ልዩነቶቻችንን ወደጎን እንተውና ለጋራ ኅልውናችን ተባብረን እንነሳ፡፡ ከአሁን በኋላ በዘርና በጎሣ፣ በሃይማኖትና በሰው ሰራሽ ድንበር እየተቧደንን አንተላለቅ፡፡ የጠላትን ዕቅድ ከመፈጸምና ከማስፈጸም እንቆጠብ፡፡ የተጀመረው ትግል ግቡን እንዲመታ በቀናነትና በጨዋነት በቻልነው መንገድ ሁሉ እንሳተፍ፡፡ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ዕውቀት ያለው በዕውቀቱ፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ … ሁሉም በየሚችለው ተባብሮ ሳይታክትና ሳይለግም ከታገለ ነፃነታችን ቅርብ ብቻ ሣትሆን እንደሚባለውም በየበራችን ሥር ናት፡፡ እነዚህ ጥቂት አሰለጦች ይህን ያህል ሊጫወቱብን የቻሉት ልዩነቶቻችንን እያራገቡ መሆኑ ተደጋግሞ የተነገረ ግልጽ እውነት ነው፡፡

ሙስሊሙ በመጀመሪያ ሰው ነው፡፡ ክርስቲያኑ በመጀመሪያ ሰው ነው፡፡ ፕሮቴስታንቱም ሆነ ብሃኢው ወይም ሌላው በሺዎች በሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ሥር የተኮለኮለው ምዕመን ሁሉ በመጀመሪያ ሰው ነው፡፡ ዐማርኛና ትግርኛ ወይም ፈረንሣይኛና እንግሊዝኛ የሰው ናቸው እንጂ ሰዎች አይደሉም፡፡ እነዚህ ሰብኣዊ ፍጠራን ናቸው – እንደሸሚዝ፣ እንደከናቴራና እንደጫማ፡፡ በቃ – ባሕርያዊ ያልሆኑ ከትውልድ ወደ ትውልድ በደም የማይተላለፉ የመገልገያ መሣሪያዎች ናቸው፤ በመገልገያ መሣሪያ ሰበብ ደግሞ ሰብኣዊ ፍጡር ሊተላለቅ አይገባውም፡፡ ከፈጣሪ ቀጥሎ ሰው ከምንም በላይ ነው፡፡ ቋንቋ የሚኖረው ሰው ሲኖር ነው፡፡ ሃይማኖት የሚኖረው ሰው ሲኖር ነው፡፡ ባህልና ወግ የሚኖረው ሰው ካለ ነው፡፡ ሰው የሚኖረው ደግሞ ሀገር ሲኖር ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ዕብዶች ብዙ ነገሮችን – የራሳቸውን ቁሣዊ ሕይወት ጭምር – ከሀገር አስበልጠው ሲመለከቱ ቢስተዋሉም እውነታው ግን ይህ ነው – ሀገር ከምንም ነገር በላይ መሆኑ፡፡ መቀመጫ ሳይኖር የት ላይ ተሁኖ ምን ነገር ማድረግ እንደሚቻል ራሳችሁ አስቡት፡፡ … መፈላሰፍ ይቅር ብዬ ነበርና ይቅርታ፡፡

ከሰው ደረጃ ደግሞ ትንሽ ዘቀቅ እንበል፡፡ ኢትዮጵያ የሰዎች መኖሪያ ናት፡፡ አላለልን ሆኖ እንጂ ወርቅ ምድር አለችን፡፡ ከእሥር ቤትነት አውጥቶ ወደ ተደላደለ የፍትህና ርትዕ ሕይወት የሚመልሰን ሰው አጣን፡፡ ከነልዩነቶቻችን እንደሰው ተቀብሎ በእኩልና በፍትህ የሚያስተዳድረን ሰው አጣን፡፡ ልዩነቶቻችንን ለመጠፋፊያነት ሳይሆን ለጌጥነት የሚጠቀምበት በብልኆች የተሞላ መንግሥት አጣን፡፡ አንዱን ከአንዱ እየለዬ የሻጉራ ሳይመለከት በእኩል የሚሰበስበን ሰው እስካሁን ማግኘት አልቻልንም፡፡ እንደ ዐወሬና እንደእንስስሳ እየቆጠረን የሚገዛና የሚነዳ ጭራቅ እንጂ እንደሰውና እንደራሱ ዜጋ ዐይቶ የሚያስተዳድር ብቁ ሰው ጠፋ፡፡ ችግራችን ይህ ነው፡፡ በተረፈ አንዱ በሌላው ላይ፣ በተለይ አንደኛው ሕዝብ በሌላ ወንድም በሕዝብ ላይ ምንም ቅራኔና ጥላቻ የለውም – ይህን እናውቃለን፡፡ ችግሩ ከላይ እንጂ ከታች አይደለምና፡፡

ነፃነታችንን የምናገኘው ከፍ ሲል የተጠቀሱትን የመሰሉ ነባር ችግሮቻችንን ስናስወግድ ነው፡፡ የአንዳችን ችግር ለሌላኛችን ሊሰማን ይገባል፡፡ ያኔ ነው አንድነት የምንፈጥረውና ኃይላችን የሚፈራው፡፡ ለተናጠል ጥቃት ከተመቻቸን ግን ሁሉም ገዢ ኃይል እየተፈራረቀ እንደእስካሁኑ መቅኖ ያሳጣናል፡፡ ሀገር አልባ ሆነን መቅረት ደግሞ የምንፈልግ አይመስለኝም፡፡

ወያኔን በሁሉም ቦታዎችና በአንድ ወቅት መወጠርና ወደ ድርድር (የማይመስል አማራጭ ነው) ወይም ወደ ሽግግር መንግሥት የሚገባበትን(የምንገባበትን) ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ የትም የምትኖሩ ምሁራን ዜጎቻችን እንቅልፍ ሊወስዳችሁ አይገባም –  ሲቻል በግልጽ ያ ሳይቻል ሲቀር በኅቡዕም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ መሥራት ይጠበቅባችኋል፡፡ በኋላ ሠርገኛ መጣ እንዳይሆንና የሕዝብ መስዋዕትነት በሌሎች ጭልፊቶች እንዳይሞጠለፍ መጠንቀቅ ይገባል፡፡

የነበሩንንና ወያኔ የዘራብንን ማኅበራዊ ቅራኔዎች በአፋጣኝ አስወግደን ወደጋራ መድረክ ካልገባን ከዚህ በባሰ እንጠፋለን፡፡ ላለመጥፋት አብነቱ ለመሠሪዎች ተንኮል አለመንበርከክና የተደራብንን የአፍዝ አደንግዝ ሰይጣናዊ ድር በጣጥሶ መጣል ብቻ ነው፡፡ የአዳምና የሔዋን ዘር ሆኖ፣ የአደምና የሃዋ ልጅ ሆኖ አንተ ትግሬ አንተ ኦሮሞ መባባል ከአለማወቅ የሚመነጭ እንጂ ከብልኅ አእምሮ የሚፈልቅ አይደለም፡፡ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ይባላልና እንወቅበት፡፡…

በቀደም ለት በኢሳት አንድ ዝግጅት ተከታትያለሁ – በዋሽንግተን የኢሳት ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ያዘጋጀው ነው፤ በዚያ ስብሰባ የሀገራችንን ሕዝብ የሚያኮራ አንድ ማለፊያ ትዝብት አለኝ፡፡ ከተናገሩት ሰዎች አንዱ ሌሊሳ የተባሉ በዋሽንግቶን የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ማኅበር አንድ አባል ይገኙበታል፡፡ የተናገሩት በዐማርኛ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውን ካሏቸው የጋራ መሣሪያዎች አንዱ ዐማርኛ መሆኑ ስለሚሰማኝ በእጅጉ ተደስቻለሁ፡፡ የስሜቴ ምንጭ ዐማርኛ መነገሩ አይደለም – ያስደሰተኝ ጠላት የተበተበባቸውን ወጥመጥ በጣጥሰው ኢትዮጵያውያን ለመቀራረብ መቁረጣቸወ ነው፡፡ ባፉት ጥቂት አሠረት ዓመታት በውነቱ እኛን ዐይጥና ድመት አድርጎ በተናጠል ቀጥቅጦ ለመግዛት ያልተሸረበብን ተንኮል የለም፡፡ ከነዚህ ተንኮሎች አንደኛው አንዳችን ለአንዳችን እሬት መስለን እንድንታይና የወል ዕሤቶቻችን ላይም ጥላቻ እንዲያድርብን የተደረገው ትልቁ ዘመቻ ነው፡፡ የጠላትን መንገድ ተከትለን አላስፈላጊ ኩርፊያ በመፍጠር እየተገፈታተርን መኖራችንን ለሚረዳ ሰው ይህ ወርቃማ ጅምር ምን ዓይነት ዘላቂ መልካም ነገርን እንደሚወልድ መገመት አያቅተውም፡፡ ቋንቋ በሥነ ልቦና ልክፍት ተጠምደው የሚወዛገቡበት የማንነት መገለጫ ሣይሆን ከልደት በኋላ የሚገኝ (acquired or learned) ተራ የመግባቢያ መሣሪያ ነው ብዬ ከፍ ሲል በገደምዳሜ እንደጠቀስኩት ተፈጥሯዊ ሥነ ልሣናዊ ሂደቱን ጠብቆ ነገና ከነገ ወዲያ ኦሮምኛ ወይም ትግርኛ የኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ቋንቋ ሊሆኑ ይችላሉ – በዐዋጅና በሌላ ሕገ ወጥ “መንግሥታዊ” ተፅዕኖ ከሆነ ግን አሁን እያስተዋልነው እንዳለው ዓይነት ችግር መከሰቱ አይቀርም፡፡ ቋንቋን ከጠቀሜታው አንጻር እንጂ ከቀዳሚ ተናጋሪዎቹ ማንነትና ምንነት ጋር እያስተያየን አመለካታችንን የምንለዋውጥ ከሆነ ደግሞ የጋራ የሚባል ነገር ይጠፋና ልክ እንደባቢሎናውያን ሆነን እንቀራለን፡፡ “የኔ ያንተ ነው፤ ያንተም የኔ ነው” በሚል የአንድነት ስሜት ከተዋዋጥን ግን አንድም ችግር የለብንም፡፡ ስለሆነም ይህ ጅማሮ በጣም ድንቅ ነውና ሁላችንም ከያለንበት የግል ዓለም እየወጣንና በተቻን መጠን  ግማሽ ግማሽ መንገድ እየተጓዝን መሀል ላይ እንገናኝ፡፡ በቃ፡፡ ያኔ ችግራችን ሁሉ ታሪክ ይሆናል፡፡

 

በቀላሉ ለብስጭት የሚዳረጉ እና ቂመኛ የሆኑ ወንዶች /ኤትሪያል ፊብሪሌሽን/ ለተባለ የልብ ሕመም ሊጋለጡ ይችላሉ ተባለ

$
0
0
A guy too angry with green shirts

ቁጣ የልብ ሕመምን ያስከትላል ተባለ

‹‹ በቀላሉ ለብስጭት የሚዳረጉ እና ቂመኛ የሆኑ ወንዶች /ኤትሪያል ፊብሪሌሽን/ ለተባለ የልብ ሕመም ስለሚጋለጡ የልብ ምታቸው የተዛባ ይሆናል ሲል የኒውዮርኩ ዴይሊ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ሲናደዱ አንደበታቸውን መቆጣጠር የሚሳናቸው፣ ቁጡ ወይም ትዕግስት የለሽ የሆኑ ብስጩ ወንዶች ለተዛባ የልብ ምት ችግር የመጋለጥ አጋጣሚ 30 በመቶ ሊጨምር እንደሚችል ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

የጥናቱ ቡድን ዳይሬክተር የሆኑት ኢሌን ኤከር ሲናገሩ፡- ‹‹ የቁጣን ስሜት ለመቆጣጠር ከመሞከር ይልቅ አውጥቶ መግለጽ በጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ለመከላከል ይረዳል ተብሎ ይታሰብ ነበር፡፡..በዚህ ጥናት ላይ እንደታየው ግን ቁጡ የሆኑ ወንዶች ለኤትሪያል ፊብሬሌሽን ብቻ ሳይሆን ሞት ለሚያስከትሉ ሌሎች ችግሮችም የመጋለጥ አጋጣሚያቸው ከፍተኛ እንደሆነ በተጨባጭ ተረጋግጧል፡፡››

የድምጽ ብክለት የነርቭ መቃወስ ያስከትላል

የጫጫታ መብዛት ወይም የድምጽ ብክለት የነርቭ መቃወስ፣ የደም ግፊት፣ የማዳመጥ ችሎታ እክል፣ የእንቅልፍ ማጣትንና የግልፍተኝነትን ባህሪይ ሊያስከትል ይችላል በማለት ኤቢሲ የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

የጫጫታ መብዛት በከተሞች የሚኖሩ ሰዎችን የሕይወት ጣዕም እየቀነሰባቸው ነው ያለው ኤቢሲ ጋዜጣ ፣ የዓለም ጤና ድርጅትን ዋቢ በማድረግ በጤናቸውም ላይ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ዘግቧል፡፡ የስፔን የሕገ መንግስት ፍርድ ቤት የከተማ ነዋሪዎች ጸጥታ ተረብሿል ተብሎ በተከሰሰ የሕዝብ መዝናኛ ድርጅት ላይ ባስተላለፈው ብይን የድምጽ ብክለት በጤንነት ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት እውቅና ሰጥቷል፡፡

ፍርድ ቤቱ ከመጠን ያለፈ ጫጫታ‹‹ አንድ ግለሰብ ያለውን የስነ ምግባር ደንብና አካላዊ ጤንነቱን የመጠበቅ መብቱ፣ የራሱንና የቤተሰቡን ሰላም እንዲሁም የመኖሪያ ቤቱን ያለመደፈር መብት ይጥሳል›› ብሏል፡፡ በፍርድ ቤቱ ብይን መሰረት ከባድ ጫጫታ ‹‹ የማዳመጥ ችሎታ እክል ፣ የእንቅልፍ ማጣት፣ የነርቭ መቃወስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊትና የግልፍተኝነት ባህሪ›› ሊያስከትል ይችላል ብሏል፡፡

የሌላን ሰው ደም የሚወስዱ ሰዎች የሌላ ሰው አካል የተተካላቸው ግለሰቦች ለሚያጋጥማቸው ዓይነት አደጋ የተጋለጡ ናቸው

ቫይረሶችን፣ባክቴሪያ ወይም ጥገኛ ነፍሳትን ወደ ሌላው ሰው የማስተላለፍ አደጋ አለው፡፡ በተጨማሪም የኩላሊትንና የሳንባን አሠራር የሚያዛባ አለርጂ ሊያስከትል ይችላል፡፡ በኒሞኒያ፣በኢንፌክሽን፣በልብ ድካምና በአንጎል ውስጥ የደም መፍሰስ አጋጣሚ ስለሚጨምር አደጋ አለው፡፡

 

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live