Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

ታጣቂ ሕዝብ ሲገል ካህን ተዝካር ይዝቃል –በላይነህ አባተ

$
0
0

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

abune matiasበልጅነቴ አንድ ቀልደኛ አብሮኝ ይጫውት የነበረውን የመሪጌታ ልጅ “አባትህ ለቆ እሚጥልለት በበሽታና በአደጋ ሰው ሲረግፍ ነው” አለው፡፡ ለቆ የበጋው ወር አልፎ በልግ ሲገባና ዝናብ ሲዘንብ አገፍግፎ ከበቶችን እሚያስደስት ሳር ነው፡፡ ቀልደኛው ሰው ሞቶ ለሳልስት፣ ለሰባት፣ ለሰላሳ፣ ላርባ፣ ለሰማንያና ለሙተ-ዓመት የፍታትና የተዝካር ዘኬ ሲደገስ መሪጌታ ይደሰታል ማለቱ ነበር፡፡ ቀልደኛው የቀለደባቸው መሪጌታ ግን እንደ ቀልዱ ሳይሆኑ ያለምንም ክፍያ ብዙ ልጆችን አስተምረው ለኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ያበረከቱና ዘኬም እማይወዱ አባት ነበሩ፡፡

ያኔ በመሪጌታ የተቀለደው ቀልድ ዛሬ እውን ሆኗል፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ በጉራ ፈርዳና በመተከል ቤተክርስትያናቸው እየተቃጠለ ብዙ ምእመናን ተገድለዋል፡፡ በሊቢያ የቤተክርስትያኗ ልጆች እንደበግ ታርደዋል፡፡ በጋምቤላ ከምድራቸው መፈናቀልን የተቃወሙት ተገለዋል፡፡ በባዕዳን ታፍነው የተወሰዱት ህፃናትም ተረስተዋል፡፡ በወለጋ፣ በከፋ፣ በሸዋ፣ በአሩሲ፣ በሐረርጌ፣ በባሌና በቦረና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጨፍጨፋቸውን ዓለም ሳይቀር ዘግቦታል፡፡ በጎንደር የምእመናን ህይወት በታጣቂዎች ባሩድ መቀጠፉ ቀጥሏል፡፡ ከሰላሳ ዓመታት በፊት ጀምሮ ተከዜን እያቀለመ ወደ ሱዳን እሚፈሰውን የወልቃይትና የሁመራን ደም እሚገድበው ጠፍቷል፡፡ በዚህ መልክ በመላው ጦቢያ ለሚገደለው አብዛኛው ሕዝብ ተዝካር ወይም መታሰቢያ ይደገሳል፤ ካህን እያጣጣመ ይጎሰጉሳል፡፡

ተዝካር ጎስጓሽ ካህን ቤተክስትያኗን ቢያጥለቀልቃትም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታጣቂዎች ሲገደል ከገዳዮቹ ፊት ቀርቦ “አትግደል!” የምትለዋን የወንጌል ቃል ባደባባይ እሚናገር አባት ጠፍቷል፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በአካል ብቻ ሳይሆን በመንፍስም መካን ሆነው የቀሩ ይመስላል፡፡ እንኳን ምድሪቱና ሕዝቡ ለባዕድ ተንኮል እንዳይገዛ እሚገዝት በባዕድ ተንኮል ከወንበር ቁጭ ያሉትን ከሃዲዎች እግር እማይስም ካህን አጥሯል፡፡ ነገር ግን ባሎቻቸው የታፈኑባቸው ሚስቶች በሚያስገቡት ስለት፣ ልጆቻቸው እስርቤት የሚሰቃዩባቸው ወላጆች በሚከፍሉት አስራትና ወንድሞቻቸው የተሰደዱባቸው እህቶች በሚያስገቡት ስለት ክትፎ እሚዝቅ፣ ውስኪ እሚጨልጥ፣ በካባ እሚያጌጥ፤ በቆብ እሚዋብ፤ ከቪላ እሚኖርና በሉመዚን እሚሽቀረቀር ጳጳስና አቡን ሞልቷል፡፡ ገዳዩን በልማታዊ ከበሮ እያወደሰ፤ ሟቹን ፖለቲካ በሚባል ዜማ እያወገዘና በቤተክርስትያን ጸሎት እንዳይደረግለት እየከለከለ ተዝካሩን ግን እሚዝቅ ካህን ተትረፍርፏል፡፡

የኢዮጵያ ካህናት የማቴዎስ ወንጌል ፳፭፡፵፪-፵፬ “ተርቤ አላበላችሁኝምና፤ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፤ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፤ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና፡፡ ” የሚለውን የክርስቶስ ቃል ችላ ብለዋል፡፡ ሕዝብ ሲራብ እነሱ ባስራትና በስለት ገንዘብ ቦርጭ በቦርጭና ኩልኩልት በኩልኩት ሆነዋል፡፡ ሕዝብ ሲታረዝ እነሱ በአብለጭላጭ ካባና ቆብ ተለብደዋል፡፡ ሕዝብ ሲታሰርና ሲገረፍ የታሰረውንና የተገረፈውን በመጠየቅ ፋንታ ካሳሪውና ከገራፊው ጎን ቆመዋል፡፡ “ስንራብ አላበላችሁንም፤ ስንጠማ አላጠጣችሁንም፤ ስንታረዝ አላለበሳችሁንም፤ ስንታሰርና ስንገረፍ አልጠየቃችሁንም፤ ስንገደል አልደረሳችሁልንም” ብቻ ሳይሆን “ተገዳዮቻችን ጋር ተሰልፋችኋል!” እያለ እሚያለቅሰውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ላለመስማት ቆርጠዋል፡፡ የሕዝቡን ልቅሶ በመስማት ፋንታ ዜጎች በታጣቂዎች ሲገደሉ እነሱ የታጣቂዎችን አዛዦች ባደባባይ በልማታዊ ከበሮ እያወደሱ በድብቅ ደሞ የተገደሉትን ተዝካር መዘክዘክ ቀጥለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምእመናን መርገፍ ለካህናት ለቆ ሆኗል፡፡

ጅብ አህያ ሲጥል ጆፌ ጥንብ ያነሳል፤ ታጣቂ ሕዝብ ሲገል ካህን ተዝካር ይዝቃል፡፡

ሐምሌ ሁለት ሺ ስምንት ዓ.ም.


ኢህአዴግ እና አራት ነጥብ ―ጋዜጠኛ ቶማሰ ሰብሰቤ –ጋዜጠኛ ቶማሰ ሰብሰቤ

$
0
0

EPRDFበዚህ ሰዓት ከምንፈልጋችው  ብዙ ነገሮች አንዱ በምን እንተንፋሰ ነው።ለዚህም ነው ማህበራዊ ድህረ ገፆች ሲዘጉብን ግራ ግብት ያለን።አሁን እንደ ድሮ ህብረ ትርኢት ፣ ዜና ፣ግብርና ፣ፓርላማ ፣ፖሊስ እና ህብረተሰብ ፣መከላከያ ፣ አውደ ሰብ ፣ጎበዙ ገበሬ በግድ የሚያግቱን ብዙሃን መገናኛ ሰሚ በማጣጣቸው አዝነዋል።ህዝብ ላይ እንደ ቀለዱበት እየተቀለደባቸው ነው።ለህዝብ አይን ፣ ጆሮ  የማያዝኑ።ደስ እንዳላቸው መዘባረቅ።እቤት ችግራችንን እኛው እያየነው በጣም ተመችቷችሃል የሚሉን አሁን የበይ ተመልካች።ታክሲ ውስጥ ሬዲዮ ሰምቶ ውሸት ከሚለምድ ፌስ ቡክ የሚጠቀም ትውልድ።ቲቢ አይተው ልጆቻቸው ውሸት እንዳይለምዱባቸው  እናት እና አባት ሁሌ ፀሎት። ብቻ ድንዛዜ በልማታዊ ጋዜጠኝነት።

ለምን ማህበራዊ ሚዲያዎች በትልቁ ማዕበል እኛን ወሰዱን?ለምን የኢቲቪ ውለታ ረሳነው?

ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩትም ቀዳሚው ግን ወሬ ሰለቸን ነው።ከወሬው ደሞ ፖለቲካ።ከፖለቲካው ደሞ እኔ አውቅልሃለው ሪፖርት።ሪ ፖርቱ ደግሞ የገዥ  ፓርቲ።ዜናውን ሆነ መዝናኛውን መንግስት አቀባብሎ ይሰጠናል እኛ ወደ ህዝቡ መተኮስ።ህዝቡ ሲጋተው ኖሮ ። አቅለሽልሾት ይህው ዛሬ ነፃ ወጣ።ከሬድዮ ሰማው ብለው የሚያወሩት እማሆይ እንኳን በዕለተ ሰንበት ከፌስ ቡክ ላይ አየው አሉ።

ሌላው እኛ በዚህ ማዕበል የተወሰድነው በማህበራዊ ድህረ ገፆች እኔ አውቅልሃለው የለም።ማንን ሰው የፈለገው ዜና በደቂቃ ውስጥ ያገኛል።ለአለቃዬ እንዲመቸው አድርገ ዜናው ፃፈው የለም።ኢህአዴግ ሁሌም እንደ አክተር የማይሸንፋበት ወሬ እዚህ የለም።ቢኖርም ተከታይ የለውን ።በሀገራችን ያሉትን ሶስት የመንግስት ልሳን መገናኛ ብዙሃኖች ያላቸው የፌስ ቡክ ተከታይ ለአብነት በአንድ ላይ ብንደምር  ከአንድ መጠነኛ እውቅና ካለው ግለሰብ አይበልጡም።ለምን? እዚህ በንግድ ፋቃድ ሳይሆን ፣ እዚህ በገንዘብ ሳይሆን የምትደመጥ  ተወዳድረህ ነው።ውድድሩ ሰውን ያከበረ እና የሚመጥነው ያመጣ ነው።ያልሆነው ሆነ ብሎ ማውራት እራስ ከታማኝነት መራቅ ብቻ ሳይሆን ህዝብንም አታውቅም ብሎ መሳደብ ነው።ለዚህም ነው ዛሬ በኢህአዴግን ጋዜጠኝነት ላይ አራት ነጥብ ያረፈበት።

በኢህአዴግ የጋዜጠኝነት  ካርታ ላይ ሌላው አራት ነጥብ ያሳረፈበት እሱ ያሰበውን በተቃራኒ ማሰብ ያለመቻሉ ነው።በተሰመረው መሰመር መሮጥ ብቻ።

እሱ«አንዳንድ ሰዎች በጥቃቅን እና አነሰተኛ ተደራጅተን ህይወታችን ተለውጣል ሲል»
እኛ«ጥቃቅን እና አነሰተኛ ያለንን ጥቃቅን ብሮች ገደል ከተተው» የሚሉ መስራት በአራት ነጥብ ክልክል ነው።

እነሱ«የኢህአዴግ ምክር ቤት ዛሬ አመታዊውን ጉባዬ ጀመረ ሲሉ»
እኛ «ጉባዪው አየተካሄዱ ክቡር ሚኒስተሩ ተኙ»ማለት አራት ነጥብ ሰይጣናዊ ነው።

እነሱ«ዲሞክራሲ በሀገራችን ሰፍኖል ሲሉ»
እኛ «አሁንም ፍትህ እና እኩልነት የሌለባት ሀገር ናት ማለት አይቻልም»

እነሱ«ክቡር ፕሬዘዳንታችንን ባለ ወርቅ ወንበር ላይ አስቀምጠው ፎቶ አንሰተው ዜና ሲሰሩ»
እኛ«በካርቱም ስዕል ተጠቅመን  ፕሬዘዳንቱን ዛፍ ጫፍ አናት ላይ አድርገን ዛፉን በረከት ሰምኦን እያወዛወዘው ብንጠቀም» አራት ነጥብ ዘብጥያ።

እነሱ«የቱርኩ ፕሬዘዳንት ጣይብ ኤርዶኽን ህዝብ ከመፈንቅለ መንግስት ስለምን አተራፋቸው ብለው ትንታኔ ሲሰሩ»
እኛ«ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ ማሪያም መፈንቅለ መንግስት ቢደርሰባች  ለኢትዮጵያ ህዝን ጥሪ ለማድረግ አፍራለው የሚሉ ይመሰለኛል» ብትል አራት ነጥብ መንገድ ተሳስተሃል።ሽብርተኛ ነህ።

አነሱ«አቶ ሃይለ ማሪያም ዳግም የውጪ ጉዳይ ሚኒሰትር ፣መከላከያ ሚኒስትር እና የጤና ሚንስትር ዳግም ከህውሃት ሾሙ ሲሉ»
እኛ«ህውሃት ለምን  የትራንሰፖርት ፣ የአካባቢ እና ደን ፣ የውሃ እና ምናምን ሚኒሰትር ከራሱ አራቀው» ይህም ከሰራህ ቀይ መስመር አለፍክ።የልማታው ጋዜጠኘነት ካርታን ጥሰሀሰል።በዚህም ድንበር ሰላለፍክ የአሸባሪ ቅጥረኛ ተብለህ ከርቸሌ።

የግሉ ተቃዋሚ የሆነው የመንግስት ሚዲያ የመንግስት ደጋፊ ሰለሆነ ነው!

ይህ ለእኔ ታላቁ ልጄ ጨዋ የሆነው ታናሹ ልጄ ባለጌ ስለሆነ ነው የሚለው ደካማ ሎጂክ ነው።የግሉ መጠነኛ ተወዳዳሪ ርዕሶች አሉት።እንደ መንግስት ሚዲያ ኢህአዴግ የሮጠበት አይሮ  አይሮጥም።ተመረቀ ፣ ፀደቀ ፣ተገለፀ ፣ ሊጀመር ነው ፣ አሳሰቡ ፣አወገዙ የሚሉ የህዝብ ግንኙነት ዜናዎች የሉም እዚህ።

የግሉ ስራዎቻቸው  እንዲሸጥላቸው የቆጡን አውርድ ናቸው!

ይህን ደርግን ለመጣል የከተማ ወይስ የገጠር ጦርነት ስልት ነው የሚበጀው ብለው የተለያዩትን ሁለቱን ያን ጊዜ ፓርቲዎች ያስታውሱኛል።ህውሃት ገጠሩን መረጠ።አሸነፈ።ህውሃት ለማሸነፍ ብዙ ስልት ተጠቅሟል።ይህ እውነት ነው ሁሌም ለማሸነፍ ጥሩ ስልት መያዝ አለብህ።የግሉ ሚዲያ እንደዛ ስለሆነ አሸንፏል።

አሁን የኢህአዴግ የልማት ጋዜጠኝነት ሰርዓት በህዝቡ ቦታ የለውም።እንደውም ልማታዊው ጋዜጠኝነት ብዙዎቹን ገሏል።አንጋፋው ጋዜጣ አዲስ ዘመን ሀይለ ስላሴ ተነስተው ቢያዮ ሰሙን ይቀይሩለት ነበር ከስጋ ቤት አውጥተውት።ኢቲቢ ያሳየ እንደ ንጉስ በታየበት ያ ዘመን በወያኔ ልማታው ጋዜጠኝነት ኢቲቪ የቤት እቃ ሆን።አንጋፋው ሬዲዮዎች አርሶ አደሩም ዘጋቸው።

ዛሬ የመጣ የኋላዎቹን በላቸው።
ያሰበላቸው ኢህአዴግ
የበላቸው ኢህአዴግ
አሸናፊ   ህዝብ ሆነ።

ታዲያ ልማታዊ ጋዜጠኝነት ተከትሎ የከሰረው ኢህአዴግ ባለፉት 10 አመታት የግሉን ሚዲያ እየኮረከመው ነው።እኔ አውቅላችሃላው ቀጥሏል።በዚህም ብዙዎች ታሰረዋል ፣ ተሰቃይተዋል ፣ተሰደዋል ዛሮም ቀጥሏል።የግሎን ሚዲያ በአራት ነጥብ ለማዳረ ጥፋት ተቃርቧል።

ዛሬ ደግሞ ማህበራዊው ሚዲያን ለማፈን ተዘጋጅቷል።ይህ ደግሞ የመናገር መብት ጋር የሚጣላ ነው ።ወይም ኢህአዴግዬ ልክ እንደ እዣች ሀገር በይፋ ዝጋው።ዶሮዋን በረጅም ገመድ  አስረ ከምትለቃት አቅርበህ እሰረሃት ቢሆን ጫዋታው ደስ ይለናል።

ግን ――――――――ሀገር የምትለወጠው ስለሰሩት ብዙ በማውታት ሳይሆን ሰለቀረው በማሰብ ነው።ህዝብን በማፈን አይደለም።ጥይት መተማመኛ በማድረግ አይደለም።

ሀሳቤን ስጨርስ ኢህአዴግን በአራት ነጥብ ዘግቼው ነው ።

ጋዜጠኛ ቶማሰ ሰብሰቤ
3/12/16

ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚባሉ ታራሚ እንደሌሉት በድጋሚ አስታወቀ

$
0
0
andy

አንዳርጋቸው ጽጌ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰጠው የመጨረሻ ትዕዛዝ መሠረት፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመከላከያ ምስክርነት ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ቢሆንም፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚባሉ ታራሚ እንደሌሉት ለፍርድ ቤቱ በድጋሚ በደብዳቤ አስታወቀ፡፡ በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ክስ የተመሠረተባቸውና ‹‹ተከላከሉ›› የተባሉት አቶ አሸናፊ አካሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛ፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁንና አቶ አንሙት የኔዋስ አቶ አንዳርጋቸው የመጨረሻ መከላከያ ምስክር መሆናቸውን አሳውቀው ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. እንደሚያሰሙ እርግጠኛ እንደነበሩ ገልጸው፣ ምስክሩ በማረሚያ ቤት የሉም መባሉ እንዳሳዘናቸው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ አቶ አንዳርጋቸውን የክሱ ምሰሶ በማድረግ እነሱን (ተከሳሾቹን) እንዳሠለጠኑ፣ ተልዕኮ እንደሰጡና እንዳስታጠቁ አድርጐ የሐሰት ክስ የመሠረተባቸው፣ አቶ አንዳርጋቸው እንደማይገኙ (እንደማይያዙ) አስቦ እንደነበር ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡ ነገር ግን አቶ አንዳርጋቸው ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ በመናገራቸው ምክንያት እነሱ (ተከሳሾቹ) በመከላከያ ምስክርነት እንደቆጠሯቸው አስታውሰዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው የዕድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ በመሆናቸው መከላከያ ምስክር ሆነው መቅረብ እንደሌለባቸው በመጥቀስ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ እስከ ሰበር ድረስ በመሄድ ሊያስከለክል ቢጥርም፣ ሰበር ሰሚው ችሎት ይግባኙን ውድቅ አድርጐ ቀርበው እንዲሰሙ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የደረሰው ማረሚያ ቤት ‹‹እኔ ጋ የሉም›› ማለቱ ምን ማለት እንደሆነ እንዳልገባቸው ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አቶ አንዳርጋቸው የት እንዳሉ ዓቃቤ ሕግ ያውቃል›› የሚሉት ተከሳሾቹ፣ ማረሚያ ቤቱ የት እንዳሉ የማያውቅ ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የፀረ ሽብር ግብረ ኃይሉ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠይቀው እንደነበረም አስታውሰዋል፡፡ ያለምንም ምክንያት በመታሰራቸው ቤተሰቦቻቸው መበታተናቸውን የሚናገሩት ተከሳሾቹ፣ ‹‹ፍርድ ቤቱ ከሕግ አንፃር ምን ይላል? የታሰረ ሰው በማረሚያ ቤት የለም ሲባል ምን ማለት ነው?›› የሚል ጥያቄ ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በበኩሉ በሰጠው አስተያየት ማረሚያ ቤቱ ምስክሩ እሱ ዘንድ እንደሌሉ በተደጋጋሚ ስለገለጸና ፈጣን ፍትሕ መስጠት ተገቢ በመሆኑ፣ ተከሳሾቹ ቀደም ብለው ያሰሟቸው ምስክሮች በቂ ሆኖ ፍርድ እንዲሰጥለት ጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን አስተያየት ከሰማ በኋላ ተወያይቶ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

ተቃዉሞ በደብረ ማርቆስ ለ እሮብ ሐምሌ 13 ቀን

$
0
0

Debre Markos -satenaw

በደብረ ማርቆስ፣ ጎጃም ከተማ ረእቡ ሐምሌ 13 ቀን 2008 ዓ.ም የተቃዉሞ ሰልፍ እንደሚደረግ የደረሱ ምንጮች ያስታወቃሉ። በጎንደር የተጀመረዉን እንቅስቃሴ በማገዝ የደብረ ማርቆስ ተማሪዎች፣ ከፈታና በኋላ ተቃዉሞዎች ማሰማታቸው ይታወቃል። ሆኖም በተደራጀ መልኩ፣ ህዝቡ እርስ በርስ እየተናገገሩ፣ ሳይፈአር ድምጹን ማሰማት እንዲችል ታስቦ ነው ይሄ የሰልፍ ጥሪ እየተሰራጨ ያለው።

ጥሪዉን ያሰራጨው ድርጅት ማን እንደሆነ ባይታወቅም፣ ጥሪው ግን ህዝባዊ ድጋፍ ሊኖረው እንደሚችል ይታሰባል።

ዜጎች ተቃዉሞ የማሰማት ሙሉ መብት ያላቸው እንደመሆኑ፣ በደብረ ማርቆስ አጋዚ ህዝቡ መብቱን እንዳይጠቀም ለማድረግ ኢ-ሕገ መንስግታዊ ተግባራት ሊፈጸም ስለሚችል፣ ከዚህም ከአጋዚ የትንኮሳ ተግባራት የተነሳ አላስፈላጊ ወዳልሆነ ሁኔታ ከተኬደ፣ ከማክሰኞ ሐምሌ 12 ከሰአት በኋላ የትኛዉም የንግድ ሱቅ ለጥንቃቄ ሲባል እንዳይከፈት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የሰሜንና አካባቢዉ የዉስጥ አርበኞች የቁርጥ ቀን ጥሪ!! –ይድረስ ለመላዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ!!

$
0
0

የቁርጥ ቀን ጥሪ!!
ይድረስ ለመላዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ!!

እኛ በሐገራችን ኢትዮጵያ ከሁሉም ማሕበረሰብ ጋር ተስማምተን ተከባብረን ለመኖር የተፈጠርን ከአንዲት የእናት ምድር ምድረ ከርስ የተፈለቀቅን እርስ በእርሳችን ለዘመናት የተከባበርን አማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ቤንሻንጉልና፣ ኦጋዴኖች፣ ጉራጌዎችና ትግሬዎች የተለያዩ ህብረ ቀለማት የልዩነት ዉበቶች ነን ።
እኛ ጥቂቶች የምንመስል በነብር ዥንጉርጉርነት የምንገለጽ አንዳችን ለአንዳችን የምንቆስልና የምንደማ! ስንነካ እንደ አራስ ነብር የምንቆጣ! አናብሶች! ኢትዮጵያዊያኖች ነን!! እናንተ የምትሞቱለት ፓርቲ እንጂ ህዝብና ሐገር እንደሌላችሁ ጠንቅቃችሁ እወቁት እኛም ጠንቅቀን አዉቀናል! በሁለታችን መካከል ትልቅ ልዩነት ተፈጥሯል!~
Gonder

እርሱም እምነት ነዉ! ይህ እምነት ለእናንተ የመኖር ዛሬን የማደር ፍላጎት ሆኖ አግኝተነዋል! ለእኛ ግን እምነት ያ እናዳልሆነ ተረዱት!! በእኛ እምነት ዉስጥ ትዉልድ አለ! አርቀን የምንመለከተዉ ትዉልድ! ያ ትዉልድ ዛሬ ልብላ ዛሬ ልጥገብ የሚል ሆድ የለዉም! ያ ትዉልድ በሚቀጥለዉ የተረካቢነት ምሕዋር ዉስጥ እራሱን ለማኖር የእኛን የዛሬ ማንነት አጮልቆ የሚመለከት ዛሬ በእናንተ እንደ አልባሌ የሚታሰር፣ የሚገደል የሚሰድደ ጨቅላ ትዉልድ ነዉ! ያ ትዉልድ ከኦሮሞ፣ ከአማራ፣ ከአፋር፣ ከቤንሻንጉል፣ ከጋምቤላ፣ ከትግሬ፣ ከጉራጌ ከሁለመናችን የተከፈለ የደምና የስጋ ፍልቃቂ የኢትዮጵያዊነት ነጽብራቅ ነዉ።

ትናንት ኦሮምን ስትገሉ አማርን የምትገሉ አልመሰላችሁም ነበር! አማራን ስትገሉ ኦሮሞን የምትገሉ አልመሰላችሁን ነበር! ቤንሻንጉልን ስትጭፈጩ እንዲሁ ሌላዉን የምትጨፈጭፉ አልመሰላችሁም ነበር! የአንዱ ሐዘን ሌላዉ ደም ዉስጥ እንዳለ ለማወቅ አልፈለጋችሁም ነበር! ኢትዮጵያዊ ሁሉ የለቅሶ ቤት ድንኳን ዉስጥ ሲገባና ለቅሶ ሲቀመጥ ብሔር እንደማይጠይቅ ፈጽሞ አልተገነዘባችሁም የአንዱ ሐዘን የሌላዉ እንደሆነ አልገባችሁ ሊገባችሁም አትፈልጉም! በደላችሁ ሲደራረብ የእኛምዝምታችን ጣራ ሲደርስ ቂም የሚቋጥርባችሁ አልመሰላችሁም ነበር! ትልቅ ስህተት ደጋግማችሁ ሰራችሁ!!
እንናተ የዘንዶዉ ደም የነካችሁ የህወሃት አባላቶች በተለይም ተለጣፊ ጭፍሮች ኦህዴድ እና ብአዴን የመሳሰላችሁት፦…… እንዲሁም የህወሃት የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች ሁላችሁ….አሁን ሰአቱ አልቋል !

ከእንዲህ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሁሉ ከህወሃት እርሱም፦ በትግሬ ስም ከተቋቋመዉ የግፈኞች ስብስብ ጋር የተሰለፈ ሁሉ ደሙ ደመ ከልብ የሚሆንበት ወቅት ላይ ደርሰናል!! በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የመከላከያ ሐይል የምትባሉ ሁሉ ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ትጠየቃላችሁ!!
የመከላከያ እና የፖሊስና ሰራዊት እንዲሁም የልዩ ሕይል እና የአካባቢ ሚሊሻ ሌላም ሌላ የተባላችሁ ሁሉ ዘር ቀለም ቋንቋ ሐማኖት ሳይለያችሁ ዉስጥ ለዉስጥ ተደራጁ ተነጋገሩ ተመካከሩ እና እራሳችሁን ለቁርጡ ቀን አዘጋጁ ወደ ጠላት እንጂ ወደ ህዝብ መተኮስ እንዳትሞክሩ!!! እንዳታስቡ!!! ወደደም ጠላ ነገ ህወሃት ይሄዳል እናንተና እና ቤተሰቦቻችሁ ግን ከእኛ ጋር አብረን እንዘልቃለን እና አደራ…. ደም አንቀባባ!!

የሰሜን እና አካባቢዉ የዉስጥ አርበኞች፦ የቁርጥ ቀን ጥሪ!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

Hiber Radio: ኮ/ል ደመቀን ከጎንደር እስር ቤት ተለቀው ተመልሰው እንዲያዙ ሀሳብ ቀረበ |የሕወሓት መሪዎች ኮለኔሉን ፌዴራል አዟል በሚል አፍኖ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ ነው

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 10 ቀን 2008 ፕሮግራም

ጃዋር መሐመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስለ ጎንደሩ ተቃውሞ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ (ክፍል አንድ ሙሉውን ያዳምጡት)
habtamu05

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው የቀድሞ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ከጃዋር መሐመድ ጋር በአንድ ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ክፍል አንድ ያዳምጡት)

<..> አቶ ሽፍቅ አደም ከወልቃይት የአማራ ማንነት የሕዝብ ተመራጭ የኮሚቴ አባላት አንዱ ለህብር ከሰጡት ቃለ መጠይቅ (ቀሪውን ያድምጡ)

የአሜሪካ እና የም እራባዊያን አገራት ቁልፍ ሸሪክ የሆነቸው ቱርክ ከመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አመለጠች ፣በርካታ ዜጎቿ ሞተዋል፣ ሺዎች ቆስለዋል፣ አፈንጋጭ ወታድሮች እና ዳኞች ታስረዋል። ከመፈንቀለ ምንግስቱ የትረፉት ፕ/ቷ “አፈንጋጮቹ የዋጋቸውን ያገኛሉ”ሲሉ ዘተዋል(ልዩ ጥንቅር)

የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውድድር እና የትኛው ዕጩ ለኢትዮጵያ አሜሪካውያን መራጮች የተሻለ ነው (ሁለተኛ ክፍል ውይይት ከፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም ጋር)

በቬጋስ በስራ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የታክሲ አሽከርካሪ ጉዳይ

የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጥሪ

ሌሎችም አሉን

ዜናዎቻችን

ኮሎኔል ደመቀን ከጎንደር እስር ቤት ተለቀው ተመልሰው እንዲያዙ ሀሳብ ቀርቧል

የሕወሓት መሪዎች ኮ/ል ደመቀን ፌዴራል አዟል በሚል አፍኖ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሱ ነው

ሰሞኑን ጎንደር ውስጥ የተከሰተው ግጭት እና ውጥረት አገዛዙ ለዓመታት የዘራው የጥላቻ ፖለቲካ ውጤት መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

ግብጽ”አባይ ከሌለ ሕዝቤ አይኖርም ስትል”ዳግም ስጋቷን ገለጸች፣ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን እሰጣእገባ ለማስቆምም ካይሮ የእስራኤል ጥልቃ ገብነትን ትሻለች

በፕ/ር መረራ ጉዲና የሚመራው ኦፌኮ የዓለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን አገዛዙ በጎንደር የወሰደውን የመብት ረገጣ አወገዘ

ግድያው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቋል

“የአማራ እና የትግራይ ሕዝብ ለዘመናት በሰላም ኖሯል፣ወደፊትም በፍቅር እና በስምምነት ይኖራል”የጎንደር ነዋሪዎች

ኤርትራ የጸጥታው ምክርቤት የጣለባት ማእቀብ እንዲነሳላት እና ኢትዮጵያም ጦሯን ከአወዛጋቢው ድንበር እንድታስወጣ ጠየቀች

ለአሰመራ መንግስት ወታደራዊ መርጃ ሲያቀብሉ ነበሩ የተባሉ ኤርትራዊያኖች እና ኢትዮጵያዊያኖች ሰሞኑን የእስራት ፍርድ ተበየነባቸው

ሀብታሙ አያሌው በጸና እንደታመመ ነው

በሰልክ አሸባሪነት እና ደብዳቤ በፖስታ –በጋዜጠኛ ቶማሰ ሰብሰቤ

$
0
0

በስልክ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ማሰብ ማለት መሃል ፒያሳ ላደገች ልጅ እንደምትወዳት ልትነገራት ደብዳቤ መላክ ጋር ይመሳለል።

343ድሮ ደብዳቤ በፖስታ ብዙዎችን አጋብቷል።በደብዳቤ ፍቅራቸውን ፣ ሰራቸውን ሰርተዋል።አሁን በጣም ለምትወዳት ልጅ በደብዳቤ ወድሻለው ብትላት   ~ ብትፅፍላት ፋራነትህን  ወይም እድሜህን ታውቅብሃለች።ደሞ ምኑ መጣብኝ ትልሃለች።በዘመነ ኢህአዴግ ደርግ ይሆንብኛል ብላ ነው የምትታዘበው።

እኔ በአሁን ጊዜ የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ስልክን የሚጠቀም አሸባሪ ዛሬ  ለሚወዳት ልጅ ደብዳቤ ከፃፈው ጋር ይመሳሰልብኛል።የሽብር ጥቃት በስልክ መፈፀም ልክ እንደ ደብዳቤ መላክ ድሮ ነው የቀረው።በአሁኑ ጊዜ ደብዳቤ ለፍቅረኛው የማይፅፍ ትውልድ እጅግ የሚያሰጠይቀውን እና ንፁሃንን ለመግደል ስልክን ለሽብርተኝነት ይጠቀማል ብይ ማሳብ ይከብደኛል።

ሌላው በስልክ የሽብርተኝነት ስራ ለመስራት ኢትዮጵያ የምትመች ሀገር አይደለችም።በዚህም ኢህአዴግን እናመሰግናለን።በስልክ ሽብርተኝነት ሊፈፅሙ ሲሉ ከዚህ በፊት የተያዙ ግለሰቦች ያየ ሻቢያ እና መሰሎቹ ድጋሚ የተበላው ድራማ ይሰራሉ ብሎ ማሰብ ይከብደኛል።

ሽብር ሁሌም ስልቱን ይቀያይራል።ዛሬ የታወቀ ሴራ ነገ አይደገም።ሁሌም አዲስ መንገድ ነው ያለው።ይህን በፈረንሳይ ያየነው ነው።ሽብር ሰልቱን የሚደጋግመው በአፍጋኒስታን ነው።ጠንካራ መንግሰት በሌለበት።

በኢትዪጵያ ለምን የስልክ ሽብርተኝነት አይሰራም ?

ለዚህ ሁለት መልስ አለው።አንደኛው የስልክ ሽብርተኝነት ከዚህ በፊት የተሞከረ ነው።ሙከራው የከሸፈ።ዋጋ ያስከፈላቸው ነው።በዚህም የስራቸውን አግኝተዋል።ስለዚህም የትኛው አሸባሪ በታወቀበት የስልክ ስልት ጎንደርን ሊያውክ አይመጣም።ምክንያቱም በስልክ ጎንደርን ለመቀወጥ ማሰብ አንድ ፌደራል ፊት ሆኖ የሰማያዊ ፓርቲን ቲ ሸርት እንደ መልበስ ይከብዳል።

ሁለተኛው የኢህአዴግ መንግስት አነፍናፊነት ነው።ባል እና ሚስ እንኳን መብራት አጥፍተው መንግስት አየን አላየን ብለው ፍቅርን  በሚለዋወጡበት በዚህ ዘመን በስልክ ከኢህአዴግ ጋር መጫወት የራበው አንበሳ ፊት የምትቀልድ ሚዳንቋ መሆን ማለት ነው።የትም ስትንቀሳቀስ እንደ አንፍናፊህ ውሻ የሚከታልህ መንግስት መኖሩን የሚያውቅ ሽብርተኛ ስለ ኢህአዴግ ባህሪ እያወቀ  እንዴት ጎንደርን በስልክ ሊነውጥ አሰበ? እዚህ ጋር ነው  ጥያቄው።

የመጀመሪያው ደራሲው ማለትም ኢህአዴግ ስራው እየገረበ ነው ማለት ነው።የፈጠራ ችሎታው እየተዳከመ ነው ሊያስብል ይችላል።የሁለቱ ሰዎች ንግግር እንዲያሳምነት ማድረግ አለበት።ሆን ተብሎ ከተሰራ ድራማ የነፃ መሆኑን ማሳየት።አዲስ አበባ እንኳን በአንድ ንግግር አሰር ጊዜ የሚቆራረጥ ኔት ወርክ ጎንደር ላይ የእሰራኤል ነው እንዴ የሚጠቀሙት አለኝ አንዱ ወዳጄ።ይህም ወዳጄ ቆይ ሽብርተኛ እርምጃ የሚወስድበት ሰው እና ቦታ አያውቅም ሳያውቅ ነው እርምጃ የሚወስደው።ቀጣለ አስተያየቱን ቆይ  ጎንደር ለማተራመስ የአፍር ክልል በጀት ነው የሚያስፈልገው 5 ሚሊየን ብር የሰማው መሰለኝ።

ሌላ አስተያየት አሸባሪዎቹ ትግሬ ናቸው አማራ።ቆይ ቆይ እንዳትዘጋው ብሎኝ ግን አሸባሪዎች አንድ ከህውሃት አንድ ከበአዴን ስለሆኑ ነው እንዴ ስነጋገሩ የማይግባቡት።ግን ከሁሉም ፈገግ ያደረገኝ አስተያየት ፌስ ቡኬ መጣልኝ።

«የኢቲቪ ሪፖርትያዥ ሳደምጠው ሶስት ነገሮች ከመሰለ ዜና መጠናቀቅ በሃላ አሰብኩ።ምርጡ ወዳጄ ፃፈልኝ።

አንደኛው መሰለ የተቆጣው ደራሲው ትወናውን እንዲ ነው ብሎት አሳይቶት ነው!

ሁለተኛው አምስት ሚሊየን ብሩ ግን ለመላው ኢትዮጵያ አይበቃም።ህዝቡ በብሶት ሰላለ 5 ሚሊየን ብር ለመሳሪያ አይበቃም ወይስ ድጋፍ ለማድረግ ነው።

ሶስተኛ  የስልክ ሽብርተኝነት የማይሰራ መሆኑን የማያውቅ  እንኳን ሽብርተኛ  አንድ የጎጃም ገበሬ ማግኘት ይከብዳል።የ አሁን አለኝ የማታው የስልክ ድራማ ካየው በሃላ እወድሻለው ብዬ ጠይቄት እምቢ በፊት እምቢ ያለችኝ ልጅ ጋር ደብዳቤ መፃፍ ጀምሬለው።እንደ ኢህአዴግ ትወናው ከሰራልኝ ብሎኝ እርፍ።

ግን ሀቁ ለሁሉም ነው።እውነት የሽብር  ጥቃት ከሆን እናመሰግለን።ሁሌም ጠብቀን ለዚህ።ዝም ብሎ አይበላምና።ነገር ግን እውነታው ይሄ ነው።ህዝብ ባገኘው ክፍተት የሆድ ብሶት በአደባባይ ይዞ ከወጣ።ችግር አለ ማለት ነው።እነዚህ ሰዎች አዲስ አበባ ላይ ብመጡ የሚከተላቸው አያገኘኙም  ነገር ግን በማንነት ቀጠናው የመጣ ግን በቀላሉ ይሰተናገደል።መፍትሄው የወልቃይትን ህዝብ ማድመጥ ነው።መልሱ ግን አንተ ሳትሆን የምታውቅላቸው እነሱ ይሁኑ።ያኔ ሻቢያ እንኳን ኢህአዴግን ለማጥፍት ቢመጣ ወልቃይት ላንተ ይሞትልሃል።

ይህን አሰካልታመነ ድረስ ህዝብ ጥየቄውን መላሸ እስኪያገኝ ድረስ ይታገላል።

በጋዜጠኛ ቶማስ ሰብስቤ
7/19/16

አብርሀና አረና የፈተና ጉዞ –አብራሃም ሶሎሞን

$
0
0

Abrhaየብዙዎችን መደናገር ፣ ጥርጣሬን የሚመልስ ይመስለኛል። ትግራይነት ከህወሀትነት የተለየ በማይመስልበት ፣ የኢትዬጽያዊነት የአንድነት ጥሪ ፣ የመበተን አደጋ ስጋት ፣ ፤ የጠባብ የዘረኝነት አባዜ ሀይሉን አበርትቶ መሪ እንደሌለው ሊቀ ሀመር ከወዲህ ወዲያ በሚያማታበት ጊዜ የሀገራችንን የአንድነት ጥሪ ለመስበክ ሲነሳ የብዙዋችን የአንድነት ጥያቄ ልምላሜ የሚያስገኝ ፣ ከመበተን አደጋ የእሳት ማዕበል ላይ ውሀ አፍስሶ ለማቀዝቀዝ የተመረጠ ልዩ ወጣት ነበር። የሀገራችን “መሰልጠን” ማለቴ “መሰይጠን” የእለት እለት አብሾው እንደሚነሳበት እብድ የሚያክለፈልፈው ሲሆን እንደ እሱ አይነት ብዙዎች ግን የነጎደውን የእሳት ምንዥር የሚያጠፉና ፣ የሚነሳውንም የችግር ሰደድ ለማጥፋት የታደሉ ናቸው እላለሁ።

በእርግጥ ዛሬ ላይ ይህንን ፅሁፍ ስፅፍ ዋና መነሻዬ የትግል አጋሬ ስለነበረው ስለ አብርሀ ደስታ ሳስብ የተሰማኝን ስሜት ለሀገሬ ሰው ለመግለፅ ነው። ከሁሉም በላይ ስለ አብርሀ ሳስብ ዘወትር ትዝ የሚለኝ የሀገራችን የበከተ የፓርቲ ፓለቲካ ቁማር ውስጥ መጠመዱ እጅግ ያሳዝነኛል።በእርግጥ የቃል አጠቃቀሜ ፀያፍ ቢሆንም ያ እኔ ያልኩት ቃል ይሻላል ብዬ ነውና ከቻላችሁ አንብቡት። ከወሬ እና ከአሉባልት የማይላቀቀው ትግል ያሉት ትግላቸው የሚሰራውን ሰው ሁሉ አሽመድምደው ሲጥሉ ስመለከት ያሳዝነኛል። ለዚህም ብዙ ምሳሌ አለኝ ዛሬ ላይ ትኑር ትሙት እንኳን ድምፅን የማንሰማው የብርቱካን ጉዳይ የአንድነት የሞተ ፓርቲ ከጠፋቸው እንቁዎች መሀል ነበረች። ስለ ቀድሞው ትተን በይበልጥም በዚህ ዘመን ከወጣት የፓለቲካ ተስፈኞች እንደ እነ ሀብታሙ አያሌው ፣ የሽዋስ አሰፋ ፣ አብርሀ ደስታ ፣ዳንኤል ሽበሺ ያሉት ዕንቁዎች የሀገራችን ፍፃሜ የለሽ የሆነው የፓርቲ ፓለቲካ ያደከማቸው ናቸው ማለት እችላለሁ። በእርግጥ ሁሉንም የሀገሬ የፓለቲካ ተስፈኞች ዘርዝሬ ለመግለፅ ባልፈልግም ስለ አብርሀ ግን የማውቀውን ነገሮች በትንሹም ቢሆን ብገልፅ ደስ ይለኛል።

አብርሀ እጅግ ትሁትና ሰው አክባሪ ወጣት ነው ። ከሁሉም በላይ ልዬ ነገሩ ሰውን የማዳመጥና እና የመረዳት ክህሎቱ ይበልጥ እወድለታለው። አብርሀ ጋር በእስር አንድ ላይ ብዙ ቆይተናል ስልሆነም ማንም ሰው በእስር ወቅቱ ላይ ከእኔ የተሻለ ያለውን ነገሮችን ለመናገር የሚችል ያለ አይመስለኛም።

የነ እንትና “አረና” እያሉ የሚጠሩት ፓርቲያቸው እንደ አብርሀ አይነቱን ባለ ተስፋዎች ተስፋቸውን የሚያጠፋ ፣ ከምንቃወመው መንግስት በላይ አጥፊዎች መሆናቸውን ተረድቻለሁ። አብርሀ በእስር በነበረበት ወቅት የአብርሀ ጥያቂዎች ከሁለት አይበልጡም ነበር። ዘወትር ጠያቂዎች የታወቁ እና የምንለያቸው ነበሩ።

በሁለት አመት የእስር ወቅት አብርሀን ሳየው የአረና ፓርቲ አባል ነበር እንዴ ለማለት እጠራጠራለሁ። አንድም ነገር ከአረና አልነበረምና። ከሁሉም የሚገርማችሁ አንድ ነገር ልንገራችሁ የአብርሀ የእስር መፈቻ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚወስድለት ሰው ጠፍቶ ማን እንደወሰደለት ብነግራችሁ ታዝናላችሁ አንድም ስው እንደሌለው ለብቻው ነበር የነበረው። ነገር ግን የአረና ፓርቲ አባል ነበር። “የሀገሬ ሰው በላ ፓርቲ”። ለ አብርሀ ምግብ የሚያመጣለት አንድም ሰው አልነበረም ፣ የሚቀይረው ልብስ እንኳን አስቦ የሚያመጣለትም አንዲሁ ፣ በፍርድ ቤት የምልልስ ወቅት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለ35 ጊዜ በላይ ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት 25 ጊዜ በላይ ፣ በሰበር ፍርድ ቤት 15 ጊዜ በላይ ሲቀርብ አብሮት የነበረው ሰው አንድ ብቻ ነው።

ይህንን ነው የምላችሁ የሀገሬ የበከት ፓለቲካ። ዛሬ ሲፈታ መዋጮ ይሰብሰብ ፣ መቀሌ አየር ማረፊያ አቀባበል ሳይ በጣም ተገረምኩ። ምነው ያኔ ከጎኑ ብትሆኑለት ኖሮ አረናዎች ብዬ አሰብኩና ተውኩት ያው የሀገሬ የተቃዋሚ ፓርቲ ከገዢው ፓርቲ በምንም ስለማለየው። የእውነት ነው የምላችሁ በማረሚያ ቤት ምግብ የሚያመጣለት እጥቶ በጨጎራ ህመም ሲሰቃይ ያኔ የት ነበራችሁ አራናዎች ግን ፣ ስለ ቤተስቡ እናት ፣ እህት፣ ወንድሞቹ መረጃ የሚነግረው አጥቶ ሲጨነቅ አረ የት ነበራችሁ አረናዎች። ዛሬ ግን ሲፈታ ለመቀበል ተንጫጫችሁ።ውሽታሞች ለመሆናችሁ እኔ ምስክር ነኝ። አስመሳዬች ፣ለመሆናችሁ እኔ ምስክር ነኝ ሌላም አያስፈልግ።

ተስፈኛውን ወጣት ሰው አልባ አደረጋችሁት ፣ምስኪኑን ሰው ለብቻው ጣላችሁት። በመከራው እርቃችሁ በደስታው ጊዜ እንዝለል አላችሁ። አረ ከየት የመጣ ልቡ ነው። ብዙም ባልል በወደደኩ ነገር ግን አብርሀ ከሀምሌ 1 ከተፈታ እለት ጀምሮ የፈላጊው ሰው ቁጥር ሳስብ እጅግ ስለተገረምኩ ነው ። በይበልጥም የመቀሌው አየር መንገድ አቀባበል ፊልም ስለሆነብኝ ነው። አዎ የሀገሬ ፓለቲከኛ ይታሰራል ከዛ ሲፈታ ጠብቀን እንዘምርለታለን ፣ የሀገሬ ፓለቲከኛ ይታመማል ልክ በአልጋ ላይ ሲወድቅ ወደቀ ብለን በፌስቡክ እንገልፅለታለን። እሱ ይሞታል ፣እሱ ይራባል ፣እሱ ይጠማል። እኛ ደግሞ ለእሱ እንኖርለታለን ፣ ለእሱ እየበላን እየጠጣን እናሳየዋለን። አይደል እንዴ የሀገሬ ፓለቲካ………አየሆነ ያለው የሆነውም ይሀው ነው ያሳዝናል፣ በእርግጥ እንደ እኔ አይነቱ ከኢትዬጽያ ፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ለማይጠብቅ ሰው ቅር ላይለው ይችላል። ነገር ግን ተስፋቸውን ተስፋ በሌላቸው የሀገሬ ፓርቲዎች ላረጉ ፤ ከሀገር ጉዳይ ይልቅ ለውስጥ ችኩቻ እና ስልጣን ለሚሽሎኲለኩ ፓርቲዎች ላይ ተስፋን ላረጉ ግን ከልብ አዝናለሁ።
እናም …………………………….. ለእኔ

“ለእኔ የሚሰራውን የሚገሉት ፣ ባለራዕዬን የሚያጠፉት….ሌላ እንዳይመስላችሁ የሀገሬ ድንበር የለሽ የላሸቀ የፓርቲ ፓለቲካ እንጁ ሌላ እይደለም”።

Abraham Solomon

ማለባበስ ይቅር አለው ብዙ አደጋ…- አበበ ተድላ

$
0
0

welkeit trወገኖቼ በግል አጣዳፊ ምክንያት ከማህበራዊ ድረገፆች ራቅ ካልኩ ብቆይም ይሄንን ጉዳይ ግን ማለፍ ስለማልችል ጊዜዬን አጣብቤ ሃሳቤን ልገልፅ ወድጃለው።
መጀመሪያ ፋሺዝምን እስከመጨረሻው እንደ ከዚህ በፊት ታሪኩ ሊታገል የወሰነውን በጎንደር እና በመላው ኢትዮጵያ እንዲሁም በመላው አለም ላሉ አማራች አድናቆቴን ለመግለፅ ወዳለው። ሆኖም ግን ትንንሽ ውጊያዎችን ብቻ ሳይሆን ዋናውን ጦርነት ማሸነፍ እና ጠላታችንን ማንበርከክ ነውና ዋና አላማችን ትንንሽ ድሎችን በማራገብ ጊዜያችንን ሳናባክን ወደቀጣይ ስራ እንሸጋገር። ግን ጅማሬው ደስ ይላል!!!

ወደተነሳሁበት ሃሳብ ልነሳ። ድሮ ተዉ ይሄ የትህነግ እና የኦነግ የአፓርታይድ አከላለል ልክ አይደለም አማራ ሆን ተብሎ አገር እንዲያጣ ተደርጎ ነው የተሰራው አንድም አማራ ባልተወከለበት ነው የተሰራው ሲባል ብዙ ሰው በተለይ አማራው ኢትዮጵያ ውስጥ ሁላችንም እስካለን ምንም ችግር የለውም ብለው አለፉት። አማራው በዚህ በወቅቱ ትክክለኛ ምላሽ ያልተሰጠው አፓርታይድ አከላለል ምክንያት ስንት እንደከፈለ ቤት ይቁጠረው።

ሆኖም ግን ወልቃይት∕ፀገዴ ላለፉት 25 አመታት ለትህነግ እግር እሳት የሆኑበት አንድም ቀን ተኝተው አያውቁም። ይሀው አሁን ሁሉም ሰው በደላቸውን እየተረዳ እና እየተቀላቀላቸው ነው። ስለዚህ ፅናት ውጡቱን እያየን ነው። ታዲያ የአማራ በደል ልክ ወልቃይት∕ፀገዴ የሆነ ብቻ አይነት ሌላውን የተወሰነ መርሳት ግን ይታያል። ይሄ ነገር መቆም አለበት። ባንዴ ጠላት አታብዙ የሚሉ እንዳሉ አውቃለው ግን መሰረታዊ ችግሩን ሳንቃወም ላይ ላዩን መሄድ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም።

እውነቱ እንዲህ ነው መሆን ያለበት፦ አዎን ወልቃይት∕ፀገዴ፤ ጠለምት ሁመራ፤ራያ ወዘተን ጨምሮ ትህነግ ከጎንደር እና ከላኮመልዛ መሬት በጉልበቱ ወስዶ የ “ትግራይ” ብቻ ነው ብለዋል። ከላኮመልዛ እንዲሁ “ኦሮሚያ” እና “አፋር” ተብለው ለተፈጠሩ ክልሎች ተሰጥተው አማራ በገዛ ሃገሩ ሃገርህ አይደለም ተብልዋል። ከጎጃምም እንዲሁ “ቤኒሻጉል-ጉሙዝ” ብለው አማራን ሃገር አሳጡት። “ኦሮሚያ” የተባለው ከላኮመልዛ ጨምሮ ከሸዋ፤ ከሃረር፤ ከፈጠጋር፤ ከእናራያ፤ ከዳሞት ወዘተ ተወስዶ የኦሮሞ ብቻ ተብሎ አጠቃላይ ከ “ትግራይ” ህዝብ የሚበልጥ ስንት አማራ በገዛ አገሩ 2ኛ ዜጋ እንዲሆን ተደርግዋል።
ስለዚህ አማራው ቁርጥ ያለ አቐም መያዝ አለበት።

ኢትዮጵያዊነት ከሆነ አላማው አማራውን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የሆነበት ሃገር መሰራት አለበት። አሁን ባለው እና ብዙ ተቓዋሚዎች የሚያስቡት ኢትዮጵያ አማራን በገዛ አገሩ 2ኛ ዜጋ ለማድረግ የሚያስብ ነው እና ይሄ አይሆንም ማለት አለበት። የለም በብሄር ነው የሃገሪቱ አስተዳደር ነው መደራጀት ያለበት ከተባለ ደሞ አማራ አሰፋፈሩን እና ታሪኩን መረጃ አድርጎ እንዲሁም አሁን ያለውን የአማራ ህዝብን አሰፋፈር ግምት ውስጥ በማስገባት የአባቶቹን ሃገር የመጠየቅ ሙሉ መብቱ ሊጠበቅ ይገባዋል። እንደ ህብረብሄርም ሲባል አማራን አግልሎ እንደ ብሄር ብቻ ይታሰብ ሲባልም አማራን ግምት ውስጥ ያላስገባ ሃገር መመስረት የማይታሰብ መሆኑ አማራ እቅጩን መናገር አለበት።ይሄን ለማለት ግን መጀመሪያ መደራጀት ግድ ነው። አማራ እንደድሮ እንደ,መነ መሳፍንት ጊዜy መከፋፈል ታሪክ ሆኖ አንድ ላይ ሊነሳ ይገባዋል።

ስለዚህ አማራው ቁርጥ ማድረግ ያለበት ሲጀመር ይሄ “ህገመንግስት” ተብዬ የሚቀበሉና አማራ ባልተወከለበት የተሰራን የአፓርታይድ አከላለል የሚቀበሉ የወልቃይት∕ፀገዴ ጥያቄ ደገፉ ገረመሌ አይሰራም። ችግር ከስር መሰረቱ መነቀል ነው ያለበት እንጂ አለባብሰው ቢያርሱ ለአረም ይመለሱ ነው። ሌላው እባካቹ ልክ የአማራ ሃገር 4ቱ ክፍለሃገሮች ብቻ እንደሆኑ አድርጋቹ የምታቀርቡ አማራዎች በስህተት የትህነግን አላማ አታራምዱ። ሌላ የኢትዮጵያ ክፍለሃገራት ውስጥ ያሉትን አማራዎች መጤ አላቹላቸው ማለት ነው እንደትህነግ ስለዚህ አማራ ግዛቱ ከ4ቱ ክፍለሃገሮች በላይ ነው። ልብ በሉ ከ4ቱ ክፍለሃገር ጭምር ተበጣጥቃ ትንንሽ ክልል ተብዬዎች ተሰርተው ስንቱ አማራ አገርህ አይደለም እንደተባለ እና እንደተሰደደ እንደተገደለ ቤተሰብ እንደተበተነ አትርሱ። ከተቃወምን ሁሉንም እንጂ ቅንጭብ ቅንጭብ አድርገን መሆን የለበትም።

በተረፈ በፈጠራቹ እባካቹ እባካቹ የትህነግ እና ኦነግን ካርታ እናንተም እንደነ ኢሳትና ሌሎችም ተቀብላቹ ኦሮሚያ ክልል፣ ትግራይ ክልል፤ አማራ ክልል ወዘተ እያላቹ አትጥሩ። ይሄማ አፀደቅንላቸው ማለት ነው። አንድም የአማራ ተወካይ ሳይገኝ የተሰመረ የአፓርታይድን ድንበር ተቀበልን ማለት ነው ይሄ ደሞ ለአማራ የሞት ሞት ነው። ማለት ያለባቹ ወይ ትግራይ ተብሎ የተከለለው፤ኦሮሚያ ተብሎ የተከለለው ካልሆነ በትምህርተ ስላቅ ውስጥ “ “ አድርጉና “ትግራይ” ወይንም “ኦሮሚያ” ወዘተ በሉ እንጂ ይሄንን አፓርታይድ አከላለል አታፅድቁ። ወገን ትግል አንዴ ነው። ለዚህ ነው ባህላችንም እንዳይጠፋ ጎን ለጎን ስሩ ስል የነበረው። ላንዱ ትግል አንዴ ለሌላው ትግል ሌላ ጊዜ መመለስ የለም። አንድ እህታችን ትግል አስር ጊዜ የለም ትግል አንዴ ነው ብላ ጨርሳዋለች ከዚህ በፊት።

እናማ በቃ አሁን ዋናው ትህነግ የወልቃይት ኮሚቴ ብሎ ሊያጠቃ የፈለጋቸውን ሰዎች ማዳን እና የወልቃይትን ጉዳይ ዳር ማድረስ ቢሆንም የአማራ በደል በሙሉ ከስር መሰረቱ ተዘርዝሮ በየቀኑ ሊነገር ይገባል። ሁሉም አማራ አጠቃላይ በደሉን ሊያውቀው ሊታገልለት በደሉንም ለአለም ሊያሳውቅ ይገባል ከበደል አንድን ብቻ መርጦ መናገር አይጠቅምም። ወገን ህዝባችንን በዝርዝር ሁሉንም ነገር አስቀምጠን በደንብ ልናደራጀው እና አንድ ላይ እንዲነሳ ልናድርገው ይገባል እንጂ የሆነች በደል አንድ ሰሞን ከዛ ደሞ ሌላ በደል ሲከሰት የድሮውን ትተን አዲሱን ብቻ እያነሳን አይደለም መሆን ያለበት። ያማለት የሁሉንም በደል በአንድ ላይ እናንሳ ማለት ነው።
እንደ ኢትዮጵያ የምንኖር ከሆነ እንደ አማራ ሊከበር የሚገባው መብታችንን እና የሌሎች ኢትዮጵያዊናንን ልናከብረው የሚገባንን መብት በግልጽ ይቀመጥ። እንደብሄር ልንበጣጠስ ከታሰበና የተፈራው የእርስ በእርስ ውጊያም ሊመጣም ቁርጥ ከሆነ አማራ መብቱን በመረጃ አስደግፎ የት ድረስ ድንበሩን እንደሚጠይቅ በግልፅ ሊያስቀምጥ ይገባል። ያኔ ህዝቡ ከየት ተነስቶ የት እንደሚሄድና ምን ሃሳብ ቢያራምድ ወዴት እንደሚደርስ በግልፅ ይኖረዋል ማለት ነው። ከዛማ ይሄንን ጀግና የአማራ ህዝብ አደራጅቶ ማታገል ቀላል ነው የሚሆነው።44 ነጥብ፤

እናማ የምንናገረውን የምንፅፈውን እናስብ። ትንንሽ ድሎችን ብዙ ጊዜ አናጣጥም። አንድ ላይ ያልተቀናጀ አመፅ ፋሽስቶችን ነው የሚጠቅመውና ህዝባችንን ወደተመሳሳይ ሃሳብና ሁሉንም በደል አንስተን ህዝቡን በአንድ ላይ ለማስቆጣት እንስራ። የሆዳቸውን በሆዳቸው አድርገው አብረን ነን የሚሉትን ሁሉ አትመኑ። እዚህ ድረስ የኔ ክልል ነው እያለ አማራን በገዛ ሃገሩ እዚህ አገሩ አይደለም እያለ ያሰደደ የገደለ ገና ለገና የብሄር ፖለቲካ እነሱ እንዳሰቡት የሰራ ሲመስላቸው የአማራን ጥያቄ ደግፋለው የሚል ለኔ ፌዝ ነው። ለጊዜያዊ ፖለቲካ ጥቅም እንኳን አልፈልጋቸውም። ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው……………………………………

‪#‎የአማራ_ተጋድሎ‬!
‪#‎Amhara_Resistance‬!
ሃምሌ 2008
አበበ ተድላ

LikeShow more reactions

የ“አበበ በሶ በላ”ና “ጫላ ጩቤ ጨበጠ” ፖሊማኖታዊ አስተሳሰብ!  –በዮሴፍ ሙሉጌታ  ባባ (ዶ/ር)

$
0
0

 

kankokunmalimaali@gmail.com

ክፍል 10

(ማስታወሻ፡- ፖሊማኖታዊ የሚለው ቃል ‹ፖሊቲካዊና-ኅይማኖታዊ› የሚለውን ጽንሰ-ሐሳብ ይወክላል)

 

ዮሴፍ ሙሉጌታ  ባባ (ዶ/ር

ዮሴፍ ሙሉጌታ  ባባ (ዶ/ር

በኢትዮጵያ ፖሊቲካ ውስጥ ጐልቶ የሚታየውን ሁለት ጽንፈኛ አመለካከቶች እንዴት “ማስታረቅ” እንዳለብን ከዝህ በፊት በግልጽ ለማስቀመጥ ሞክረያለሁ። ከሁሉ በላይ፣ በአንድነት ኋይሎችና (ultra-right) በብሔርተኞች (ultra-left) መካከል ያለውን እልይ አስጨራሽ ፍልሚያን ማስታረቅ፣ አንድም ብሔራዊ መግባባት ላይ ለመድረስ፣ አልያም ባለመስማማት ለመስማማት (agreeing to disagree) በጣም ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን በአጽንኦት አስምረበታለሁ። እነኝህን ጽንፈኛ አመለካከቶች በማስታረቅ ሂዴት ውስጥ ግን፣ አንድ አንድ እንከኖች ስያጋጥሙን “ምን ማድረግ አለብን?” የሚለው ጥያቄ መልስ የሚያስፈልገው አንገብጋብ ጉዳይ ይመስለኛል። በሌላ አገላለጽ፡- “በተለያየ ምክንያት በአንድነት ኋይሎችና በብሔርተኞች መካከል ያለውን የለየለት ልዩነት ማስታረቅ የማይፈልጉ አንዳንድ ግለሰቦች ሲያጋጥሙን፣ እንዴት ማስተናገድ ይኖርብናል?” የሚለው ነው።

አህምሮው ጤነኛ የሆነ ግለሰብ፣ በአንድ ሀገር ውስጥ ዘላቂ ሠላም እንድሰፍን ከልብ ይመኛል፤ እንደ ዜጋም የራሱን አስተዋጾ ያበረክታል። የሕዝቡ ሠላም ማረጋገጥ የሚያስችሉ አሠራር እንድዘረጋ ደግሞ፣ የግለሰቦቹ አመለካከት (attitude) ወሳኝነት አለው። አንድ ማኅበረሰብ የአመለካከት ለውጥ ሳያደርግ የጋራ ግንዛቤ ላይ ፈጽሞ መድረስ አይችልም። ለምሳሌ፡- የተፈጥሮ ልዩነትን እንደ በታችነት ወይም እንደ በላይነት የሚረዳ ግለሰብ/ማኅበረሰብ፣ ለወንድና ለሴት ወይም ለነጭና ለጥቁር ሰው የሚሰጠው ክብር አንድ/እኩል ሊሆን አይችልም። “እኔ ወንድ አይደለሁም” ወይም “ጥቁር ገበያ” የሚለው አስተሳሰብ፣ የዝህ የተዛባ አመለካከት ውጤት መሆኑ በጣም ግልጽ ነው። ጉብዝናን ከወንድነት፣ ስርቆትን ከጥቁርነት ጋራ የሚያገናኝ መንስዔና-ወጤት (cause and effect) ላይ መድረስ ካልተቻለ፣ የአመለካከት ችግር አለ ማለት ነው። የአመለካከት ለውጥ ካልመጣ በስተቀር ደግሞ፣ አንድም በሴቶች ላይ የሚደርስ ጭቆና ማስቆም፣ አሊያም “ሌብነት ከነጮች ጋራ ሳይሆን ከጥቁሮቹ ጋራ ብቻ የተቆራኘ ነው” የሚል በጣም የተሳሳተ አረዳድ ፈጽሞ ማስቀረት አይቻልም። እንግድህ፣ የአመለካከት ለውጥ መጣ የሚንለው “ስርቆት ከቀለም ጋር፣ ጉብዝና ከጾታ ጋር ብቻ የተገናኘ ነው” የሚለውን የአስተሳሰብ ሽርሙጥና ማስቀረት ስንችል ብቻ ይሆናል ማለት ነው።

በሀገራችን ኢትዮጵያ የለየለት የአመለካከት ችግር ያለባቸው ሊሂቃን (በተለይ የፖሊቲካ መሪዎችና የኅይማኖት አባቶች) ያልነበሩበት ጊዜ አልነበረም። የወረደ አስተሳሰብ የተጠናወታቸው እነኝህ ግለሰቦች፣ አንድን ግለሰብ/ቡድን አንድም ፍጹም እርኩስ፤ አሊያም ፍጹም ቅዱስ አድርጎ ያቀርባሉ። ለፍልስፍናዊ ትንተናችን መንደርደሪያ ይሆነን ዘንድ፣ ሰለሞን ስዩም “የኦሮሞ ጉዳይና የኢትዮጵያ ብያኔ፤ ከማሻሻያ፣ አመፃ እስከ አብዮት” በተሰኘ መጽሐፉ ውስጥ ካሰፈረው ወስጥ የሚከተለውን ሐሳብ ወስደን ለአብነት እንመልከት፡-

በ2005 ዓ. ም የጥምቀት በአል አምቦ ከተማ እንዲህ ሆነ፤ ታቦቱ ወደ ማደርያ ሲመለስ በከተማዉ አንዱ መንገድ ላይ በአፋን ኦሮሞ፤ “Baga Ayaana Cuuphaa Nagahaan Geechan” (“እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ” ማለት ነዉ) የሚል የመልካም ምኞት ፖስተር ተሰቅሎ ነበር። ታቦቱን ከተሸከሙት ቄስ አንዱ ቀጥ ብሎ ይቆማል፣ ግራ የተጋቡት አጃቢዎች ምን እንደ ሆነ ጠየቁት፣ ቀሱም “ይህንን የሰይጣን ቋንቋ ካላነሱ ታቦቱ አልሄድም ብሎኛል” ይላቸዋል። ቀሪዉ አይጠቅመንም፤ እዉነቱ ግን ይህን የመሰለ ዝቃጭ አስተሳሰብ የያዙ ዛሬም አሉ ነዉ። አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ ትግሬ መስደብያ ቃላት ስያጥሩት “ጉሮሮ በሚፍቅ ቋንቋቸዉ” እንድል በ“አጤ ምንሊክ እና ኢትዮጵያ” መፅሀፉ። (ገጽ 56)

እንግድህ እኝህ “የተከበሩ” አባት “ኦሮሞና ሰይጣን የአንድ ሳንትም ሁለት ገጽታ መሆናቸዉን” መስክሮልናል። የ“መንፈስ ቅዱስ” ግልጠት መሆኑ ነዉ! ዓላማው “የሰለሞናዊ ሐረግ ፍልስፍና” ለማቀንቀን እንደ ነበር ግልጽ ነው!

   እኔ የተወለድኩበት አካባቢ (ነቀምት/ወለጋ)፣ የአማርኛ ቋንቋ እንደ ጭራቅ እንድታይ ካደረጉት ብዙ ምክንያቶች አንዱ እንድህ አይነቱ ትምክህተኝነት ነው። ምክንያቱም፣ ትላንትም ሆነ ዛሬ፣ በአንዳንድ ግለሰቦች ዘንድ “ጫላ ጩቤ ጨበጠ” የሚለዉ ዐረፈተ-ነገር፣ “ጫላ በሶ በላ” በሚለዉ ዐረፍተ-ነገር ሊተካ አልቻለም። ስለዝህ፣ የሰይጣን ቋንቋ የሚጠቀም ጫላ፣ ጠብ አጫር ካልሆነ በስተቀር፣ እንደ “ሰለጠነው” አበበ በሶ መብላት አይችልም ብሎ የሚያስቡ ሰዎች አሉ። የሐጎስ፣ የጫላ፣ የሱገቦ፣የከበደ፣ የኦባንግ ወዘተ የማንነት ጥያቄ አንፃራዊ ምላሽ ካገኘ ከ25 ዓመታት ቦኋላ፣ ዛሬም የ“አበበ በሶ በላ”ና የ“ጫላ ጩቤ ጨበጠ” ፖሊማኖታዊ አስተሳሰብ አለመርገቡ ያስገርማል !!!

   እና ምን ማድረግ አለብን? “የአመጽ ቋንቋ የአመጽን ቋንቋ ብቻ ነው የሚረዳ” የሚል ፍልስፍና መፍትሔ ያስገኝ ይሆን? አይመስለኝም! “የአማርኛ ቋንቋም የሰይጣን ቋንቋ ነው” የሚል ተመጣጣኝ ምላሽ የቅድሜ-ጥቅላሎት ሕፀፅ (fallacy of hasty generalization) እንድንፈጽም ያደርገናል። በሌላ አገላለጽ፣ ስለ አንድ ግለሰብ/ማኅበረሰብ ቀና አስተሳሰብ ያላቸው ብዙ ሰዎች ስላሉ፣ የአንድ ግለሰብ ወይም የጥቅት ሰዎች አመለካከት፣ የሁሉም ሰው እምነት ነው ማለት ፈጽሞ አይቻልም። በዝህ ሁኔታ፣ አንዱን ወገን ፍጹም እርኩስ፣ ሌላውን ደግሞ ፍጹም ቅዱስ አድርጎ ከመረዳት ይልቅ፣ “ጩቤና በሶ አበበንም ሆነ ጫላን ይመለከታል” የሚል ትክክለኛ አስተሳሰብ የሚከተሉ ሰዎች አሉ።

  በበኩሌ፣ ምንም እንኳ የቁቤ ትውልድ (qubee generation) ቢሆንም፣ “የአማርኛ ቋንቋ የሰይጣን ቋንቋ ሳይሆን፣ በትክክል የሰዉ ልጅ ቋንቋ ነው” ብዬ በቅንነት መንፈስ ስላሰብኩ ብቻ በግል ጥረት ለመማር ችያለው። ያ ደግሞ በጣም ጠቅሞኛል፤ አንድም፣ ከብዙ ሰዎች ጋር እንድቀራረብና ከእነርሱም ብዙ ነገር እንድማር ብዙ የረዳኝ ሲሆን፣ ሁለትም ከብዙ የሥነ-ጹሑፍ ሥራዎች ጋር እንድተዋወቅ ምክንያት ሆኖኛል። የአማርኛ ቋንቋ መጻፍና ማንበብ ባልችል ኖሮ፣ የእኔ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር፣ ሎሬት ፀጋየ-ገብረመድህን፣መንግስቱ ለማ፣ በእውቀቱ ስዩም፣ ገብረክርስቶስ ደስታ፣ ታገል ሰይፉ፣ እንዳለጌታ ከበደ፣ ማሞ ውድነህ፣ ሲሳይ ንጉሡ፣ መስፍን ሃብተማረያም፣ ገበየው አየለ፣ በዓሉ ግርማ፣ አዳም ረታ፣ ይስማእከ ወርቁ፣ ተስፋዬ ገ/አብ….ወዘተ ሥራዎች ሁሉ ቀርቶብኝ ነበር ማለት ነው!! አፋን ኦሮሞን (Afaan Oromo) ወይም የጉራግኛ ቋንቋን ወይም የግዕዝ ቋንቋን ወይም ደግሞ ማንኛውም ዓይነት ቋንቋ ባለመቻላቸው ብቻ ብዙ ነገር እንደቀረባቸው የሚያስቡ ግለሰበች ካሉ ቤት ይቁጠራቸዉ!

የሆነ ሆኖ፣ የዝህ “ቄስ” የቆሸሸ አስተሳሰብ አንድ የነቢይ መኮንን ግጥምን አስታወሰኝ፣  

መች ይበጠስ ይሆንይህ የቂም ሰንሰለት?

ይህ የቂም ጉማሬይሄ የቂም ኡደት

መች ይሆን አገሬልጅ የምወጣላት

ቂም አርጅቶ ሞቶሰዉ የሚኖርባት

በቀል ሬሳዉ ወጥቶሰዉ የምንሆንባት!

 

 ብሔራዊ መግባባት ላይ እነዳንደርስ እንቅፋት ከሚሆኑ ነገሮች አንዱና ዋነኛው እንድህ ዓይነቱ ንቀትና ጥላቻ ነው። ከማንኛውም ግለሰብ ፍጹምነት መጠበቅ ትክክል ባይሆንም፣ ፍደል ቆጥረናል የሚሉ የመንግስት ባለሥልጣናትና የኅይማኖት መሪዎች አንዳንድ ጊዜ ለምን እንደሚዘባርቁ ግልፅ አይደልም። የራስን የወረደ አስተሳሰብ በአደባባይ ማንፀባረቅ ከለየለት ድንቁርና የሚመነጭ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። ስሳይ ንጉሡ “የቅናት ዛር” በተሰኘው ልቦለድ ሥራው “ቀፎ ጭንቅላቱ ትንሿን የግል ፍላጎቱን እንጂ የሚያወራው ነገር የሚያስከትለው አደጋ ሊያስብለት አልቻለም” (ገጽ 133) ያለው ነገር በትክክል የእነኝን ግለሰቦች ተግባር ይገልጻል የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ። ለነገሩ በሀገራችን ኢትዮጵያ የመንግስት ባለሥልጣን ወይም የኅይማኖት መሪ መሆን የሚታየው፣ ከሚያስከትለው ትልቅ ኅላፊነት አንፃር ሳይሆን፣ ከሚያስገኘው ጥቅምና ክብር አንፃር ብቻ አየሆነ መቷል። ፍልስፍና ለእንድህ ዓይነቱ የአስተሳሰብ ሽርሙጥና ፈጽሞ ቦታ የለውም!!

   አብዛኛውን ጊዜ፣ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚንፀባረቀው የአመለካከት ልዩነት የበለጠ እንድለጠጥ የሚያረገው የብዙኅኑ ሕዝብ አስተሳሰብ ሳይሆን፣ የመንግስት ባለሥልጣናትና የኅይማኖት መሪዎች ድርግት ነው። እነኝህ ግለሰቦች ሕዝቡን በቅንነት መንፈስና በእኩልነት እንደሚመሩ ለት ተቀን ይሰብኩናል። ይሁን እንጅ፣ “የቀበሌ አስተሳሰብን” የሙጥኝ ብሎ እንኳን ሕዝብን ቤተሰብን መምራት አይቻልም። አንድ የኅይማኖት መሪ ወይም የመንግስት ባለሥልጣን ስለ ራሱም ሆነ ስለ ‹ሌላ›ው ወገን ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ሳይቀይር ሕዝቡን በቅንነት አገለግላለው ብሎ “ቃል መግባት” ስበዛ ሌብነት ነው።

   ብዙ ምሁራን ወይም የኅይማኖት መሪዎች በአንድ ሀገር ውስጥ ዘላቅ ሠላም እንድሰፍን ከተፈለገ፣ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት በምርምር ሥራዎቻቸው ውስጥ ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ። ተግባራቸው ግን ሌላ ነው። ለምሳሌ፡- ትናንት “የሰው ልጅ በሰውነቱ ብቻ መከበር አለበት” ሲል የነበረ አንድ “ምሁር” ወይም “የኅይማኖት መሪ”፣ የሚፈጸመውን ማንኛውም ዓይነት ኢ-ሰባአዊ ድርጊት በቀጥታ ከማውገዝ ይልቅ፣ 180 ድግሪ ተሽከርክሮ ተበዳዩ/ተጐጅው ከየትኛው ብሔር ወይም የየትኛው ኅይማኖት ተከታይ እንደሆነ ለማጣራት ጥረት ያደርጋል። “ክራይ ሰብሳብነት ፀረ-ዕድገት/ልማት ነው” የሚሉ ግለሰቦች፣ በአንድ ጀምበር የናጠጠ ሀብታም ይሆናሉ፤ ስያሰኛቸው ደግሞ ከአድስ አበባ ምሣ ተጋብዘው ለእራት ሎንደን ይከትማሉ…ወዘተ። ሆድና ህልና በተሰማሙበት ማኅበረሰብ ውስጥ እውነተኛ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት በጣም አስቸጋር ይመስለኛል።

  ያም ሆነ ይህ፣ በሀገራችን ውስጥ የሚታየውን ማንኛውም ዓይነት ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት ትክክለኛው መንገድ አስቀድሞ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት እንደሆነ ይህ ጸሐፊ በአጽንኦት ያሰምርበታል። ተወደደም ተጠላ፣ በአንድነት ኋይሎችና በብሔርተኞች መካከል ያለውን የለየለት የአመለካከት ልዩነት ማጥበብ የሚቻለው፣ የምዕራቡን ዓለም ፖሊቲካዊ ፍልስፍና በትክክል ስንረዳ ብቻ ይሆናል።

  • በአንድ በኩል፣ “ብሔራዊ ስምምነት ላይ መድረስ የሚንችለው አንድ ወጥ አመለካከት/ማንነት ስኖር ብቻ ነው” የሚል እምነት ስበዛ ግልብ አስተሳሰብ ይመስለኛል። አንድ ቋንቋ፣ አንድ ሀገር፣ አንድ ኅይማኖት ያላት ሶማሊያ እንኳ ለዝህ አልታደለችም። ለምሳሌ፡- በንገሡ ዘመን የኢትዮጵያ የትምህርት ሚንስቴር ሚኒስትር የነበሩት ሣህሌ ፀዳሉ፣ በ1933 የሚከተለውን በጣም የተሳሳተ አዋጅ አሳውጀው ነበሩ፡- “ያገር ጉልበት አንድነት ነው፣ አንድነትንም የሚወልደው ቋንቋ ልማድና ሃይማኖት ነው። ስለዝህ ኢትዮጵያ ቀዳማዊ መሆኗን ለማስከበር አንድነቷንም ለማጽናት እስከሁን በቆየው ልማዳችን ተማሪ ቤቶቻችንን አስፍተን ቋንቋችንና ሃይማኖታችንን በመላው በኢትዮጵያ ግዛት በአዋጅ እንዘርጋው፤ ይህ ካልሆነ እስከ መቼውም ድረስ አንድነት አይገኝም። በመላ በኢትዮጵያ ግዛት ለሥጋዊና ለመንፈሣዊ ሥራ ያማርኛና የግዕዝ ቋንቋ ብቻ በሕግ ጸንተው እንዲኖሩ ሌላው ማናቸውም የአረማዊያን ቋንቋ ሁሉ እንዲደመሰስ ማድረግ ያስፈልጋል።…ሚሲዮኖች ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎችንም ቢሆን እንዳይከፍቱ መከልከል ያስፈልጋል፤ ከከፈቱም የውጪ ቋንቋ ማስተማርም ቢሆን እድሉ ለኢትዮጵያውያን መሰጠት አለበት።” (ባህሩ ዘውዴ 2005፡ 132-141) “ማንነቴን የማትቀበል ኢትዮጵያ 99 ቦታ ትበጣጠስ” የሚሉ ግለሰቦች እብድ ስለሆኑ ሳይሆን፣ እንድህ ዓይነቱን ጸረ-ሰው ልጅ መብት አዋጅ ፈጽሞ ስለማይቀበሉ ብቻ ነው!
  • በሌላ በኩል፣ “የራስን ዕድል በራስ መወሰን” የሚለው ነገር፣ በአፊሪካ ቀንድ ዘላቂ ሠላም ያሰፍናል ብሎ መደምደም፣ የምዕራቡን ዓለም ፖሊቲካዊ ፍልስፍና በትክክል አለመገንዘብን ያመለክታል። እዝ ላይ እንደ አንድ ዜጋ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድን እውነታ በድፍረትና በግልፅ ለማስረዳት ይወዳለው፤ አሁን በሕግ-መንግስቱ ላይ በግልፅ የሰፈረው አንቀጽ 39 በኢትዮጵያ ምድር ብተገበር እንኳ፣ ኢትዮጵያ በሚትባል ሀገር ውስጥ ዘላቂ ሰላም ይሰፍናል ብሎ ማሰብ፣ ከ2ኛው የዓለም-ጦርነት ወድህ ምዕራቡ ዓለም በአፊሪካ/በኢትዮጵያ ውስጥ የዘረጋውን የእጅ አዙር ቅኝ-ግዛትን በሚገባ ያለማጠንን ያሳያል። የበለጠ ግልጽ ለማድረግ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ፣ ሁለትም ባለመስማማት ለመስማማት (agreeing to disagree) የሚለው ነገር በራሱ ዋጋ አይኖረውም። ይልቅ፣ አፊሪካ/ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላትን የዕድገት ፖሊስ እንደገና ማጠን  ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ጉዳይ ነው። ብዙ ምሁራን (አፊሪካዊያን/ኢትዮጵያዊያን) ይህንን እውነታ አያውቁም ማለት አይቻልም። የኢትሮፕያንስ (Westernized Ethiopians) ዋነኛ ችግር፣ የኢትዮጵያ ፖሊቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት፣ የምዕራቡን ዓለም የዕድገት ሞደል የመከተላቸው ጉዳይ ነው። ለምሳሌ፡- የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ኢህአዴግ አብዮታዊ ድሞክራስን መከተሉ ‹ትክክል› ነው። ይሁን እንጅ፣ ኢህአዴግ ከሕገ-መንግስቱ ይልቅ ኢትሮፕያንስን አብዝቶ ስለምሰማ፣ በአፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ችግር እየገጠመው ነው። ያም ሆነ ይህ፣ ሙስና ለምሉት ካንሰር መፍትሔው ምን እንደሆነ ወይም ያለብንን የውጭ እዳ መቼ ከፍለን እንደምንጨርስ የሚያውቁት ፈጣሪና ኢህአዴግ ብቻ ናቸው!!!

በአጠቃላይ፣ ከዝህ በፊት በግልፅ ለማስቀመጥ እንደሞከርኩት፣ የተማረ ክፍል የኢትዮጵያን/የአፊሪካን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ ጥቅሞችን ከማስጠበቅ ይልቅ፣ ለብዝበዛ አሳልፎ በመስጠት አፊሪካ/ኢትዮጵያ በእጅ አዙር ቅኝ-አገዛዝ ስር እንድትማቀቅ ያደረጉ ናቸው። አመለኛን ወይፈን ጨው እያላስን አንገቱ ላይ ገመድ እንደምናስርበት ሁሉ፣ አብዛኛው የኢትዮጵያ/የአፊሪካ ምሁራን ምዕራቡ ዓለም በራሱ ቁመት ለክቶና ቆርጦ በሰፋው የአኮኖሚና የፖሎቲካ ፖሊስ ሰተት ብሎ በመግባት፣ ምዕራባዊያን ገቶቻቸውን ማገልግል ቀጥሎበታል።  የራሳቸውን ታሪክ/ሥርዓት ትተው ቅኝ-ገዥዎች ትቶላቸው የሄዱትን አሰራር/ታሪክ መከተል ስለጀመሩ፣ የሰፍውን ሕዝብ ጥቅም ለግላቸው በማድረግ አህጉርቷን እየበዘበዙ ይገኛሉ። እንደዝህ ዓይነቱን አሠራር ተከትለን፣ በአፍሪካ አህጉር ዉስጥ ዘላቅ ሰላም ይሰፍናል አልያም አስተማማኝ የኢኮኖሚ እድገት ይኖራል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። የኢትዮጵያ ዕጣ-ፈንታም ከዝህ የተለየ አይደለም!

በበኩሌ፣ የ“አበበ በሶ በላ”ና “ጫላ ጩቤ ጨበጠ” ፖሊማኖታዊ አስተሳሰብ ፈተናን አንድ ቀን እናልፋለን የሚል ተስፋ ቢኖረኝም፣ በ‹ዶላርነት› ምክንያት ግን ይህ የሚሳከ አይመስለኝም። “The modern [contemporary] 20th [21st] centurey weapon of neo-imperialism is ‘dollarism’” Malcom X. ስለዝህ አካሄዳችን ተስፈ የሚያስቆርጥ ሆኖ አግንቸዋለሁ። የኔ ትውልድ ከእኔ የሚጠብቀው ብዙ ‹ነገር› ቢኖርም ቅሉ፣ የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስተውቃልና፣ ሁኔታውን አይቼ ገና ከአሁኑ ራሴን ከምርምር ዓለም ለማሰናበት እቅድ አለኝ።

በክፍል 11 የኢትዮእንግለዛዊያን የአስተሳሰብ ሽርሙጥና እንመለከታለን !!!

ቸር እንሰንብት!         

       

 

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በከፋ የፖለቲካ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ውስጥ ትገኛለች፡

$
0
0

ለሁሉም የሕዝብ ጥያቄ ምላሹ የኃይል እርምጃ የሆነው አገዛዙ መግደል፣ ማፈናቀል፣ ማሰደድ እንዲሁም የእርስ በርስ ግጭቶችን
መቀስቀስ ዋና ተግባሩ አድርጐታል፡፡ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን ተገቢውን ምላሽ መስጠት
ሲገባው የኃይል እርምጃ መውሰዱ አገዛዙ ወደለየለት አምባገነንነት ማምራቱን ያሳያል፡፡

በጐንደር ከተማ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የተነሳው ተቃውሞ እንዲሁም በአዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ ሀና ማሪያም ቀርሳ
ኮንቶማ አከባቢ የተፈጠረው ግጭት አገዛዙ የፈጠረው ጭቆናና አፈና ውጤት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

በጐንደር ከተማ እና በአዲስ አበባ ን/ስ/ላፍቶ ሀና ማሪያም ቀርሳ ኮንቶማ ነዎሪዎች ላይ የተወሰደው እርምጃ ኃላፊነት
የጐደለውና በማናለብኘነት የተወሰደ ነው፡፡ በተጨማሪም የሕዝቡን ጥያቄ “የሌላ ኃይል ፍላጐት አስፈፃሚዎች ያነሳሱት ነው”
በማለት መግለፁ ለሕዝብ ያለውን ንቀት የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

በመሆኑም አገዛዙ በንፁሃን ዜጐች ላይ የወሰደውን ኃላፊነት የጐደለው እርምጃ እያወገዝን የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነቱን ወደ
ጐን በመተው ለዚህ ምስቅልቅል ምክንያት የሆነውን አፋኝ ስርዓት ለማስወገድ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቆርጦ እንዲነሳና
ከሰማያዊ ፓርቲ ጐን እንዲሰ—

1878bc1f-fdb8-4551-a48e-9f924f55ba33

ወያኔ ያልፋል- ጠንቁ  ለትውልድ ይተርፋል –ይገረም አለሙ

$
0
0

generation

ዘለዓለማዊ የሚሆን ምድራዊ ኃይል የለም፡፡የግዜ እንጂ የሰው ጀግናም የለም፡፡በመሆኑም አንድ ቀን በወያኔ ላይ ጸኃይ ልትጠልቅበትና ከመኖር ወደ አለመኖር ሊሸጋገር አለያም እንደ ዛሬው ከፊሉን በሆድ ገዝቶ፣ ከፊሉን ስነ- ልቦናውን ሰልቦ፣ ወዘተ በአሽከርነት ያሰለፈበትን፤ብዙኃኑን ደግሞ በጠመንጃ አፍኖ ለመግዛት የበቃበትን አቅም አጥቶ የእጁን የሚያገኝበት ግዜ የዘገይ እንደሁ እንጂ መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ ዘላለማዊነት የለምና፡፡

ከጫካ ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እንደማይወደድ ያወቀው ወያኔ  ትግረኛ ተናጋሪውን ኢትዮጵያዊ  መጠጊያ መከታ ለማድረግ ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ብሎ ከመሰየም አልፎ ይህ የህብረተሰብ ክፍል በሌላው ኢትዮጵያዊ በጥላቻ እንዲታይና እርሱም ሌሎቹን እንዲጠላና ከርሱ ጋር እንዲጣበቅ ለማድረግ ብዙ ብዙ ሰርቷል፡፡ ከሌላው የሀገሪቱ ክፍል እየዘረፉ ወደ ትግራይ ማጋዙ፤ ከክልል አቅም በላይ የሆኑ ግንባታዎች መካሄዳቸው ወዘተ በሌለው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ትግሬ የሥርዓቱ ተጠቃሚ ነው የሚል አስተሳሰብ እንዲጎለብትና ጥላቻ አንዲያድርበት የማድረግ እኩይ ዓላማ ውጤቶች ናቸው፡፤

በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግድያ እስራት ከቤት ንብረት ማፈናቀል ለሰላማዊ ተቃውሞአቸው የጥይት ምላሽ መስጠት በተለይ ደግሞ በዘር ላይ የተመሰረተ ግፍ መፈጸምም እንዲሁ ሌላው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ወገኖቹ ላይ ጥላቻ እንዲያድርበት ለማድረግ የሚሰራ  እኩይ ተግባር ነው፡፡ ዋናው ዓላማ በሌሎች ሲጠሉ እነርሱም ሁሉንም እንዲጠሉና ከወያኔ ጋር አንዲጣበቁ ማድረግ ነው፡፡

ያለምንም ወንጀል የታሰሩ ዜጎች አማራነታችን እየተነገረን በትግረኛ  ተናጋሪ መርማሪዎች ተፈጸመብን በማለት የሚናገሩት ሊሰሙት እንኳን የሚዘገንን አረመኔያዊ ድርጊት  በአማራና ትገሬ መካከል ስር የሰደደ ጠላትነት እንዲፈጠር ለማድረግ ከመፈለግ ውጪ ሌላ ምክንያት ሊሰጠው የሚችል አይደለም፡፡ ይህ ከትግረኛ ተናጋሪ ውጪ ባሉት ኢትዮጵውያን ላይ ሁሉ በተለያየ ስልትና መንገድ የሚፈጸመው ኢ-ሰብአዊና ሕገ ወጥ ተግባር ከትግረኛ ተናጋሪው ወገን ተቃውሞ የማይገጥመው መሆኑ ደግሞ ትግሬና ወያኔ አንድ ናቸው የሚለው አስተሳብ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝና ጥላቻውን ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር እንዳያደርገው ያሰጋል፡፡

በመሆኑም ወያኔ በእነርሱ ስም ተደራጅቶ እነርሱን ጋሻና መከታ አድርጎ በሌሎች ወገኖቻቸው ላይ  የሚፈጽመውን አረመኔያዊ ተግባር ሁሉም ትግረኛ ተናጋሪ በአንድ አብሮና ተባብሮ መቃወም አንደማይችል ቢታወቅም የትግራይ ሽማግሌዎችና ምሁራን ደም አታቃቡን ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ ለልጆቻችን አትቅበሩብን በማለት ወያኔዎችን ሊመክሩ ከጥፋት ጉዞአቸውም ሊገቱዋቸው ይገባል፡፡

የወያኔዎችን ታሪክ በቅርብ የሚያውቁ እንደተናገሩትና አንደጻፉት ወያኔዎች በትግራይ ስም የተደራጁ ሰዎችን ሳይቀር  በገፍና በግፍ እየገደሉ፣ ከራሳቸውም ድርጅት በሀሳብ የተለዩትን በተለያየ ስልትና መንገድ እያስወገዱ ነው ለሥልጣን የበቁት፡፡ በሥልጣን ቆይታቸው ደግሞ አንደም ወንበራቸውን ላለማስነካት፣ ሁለትም የሀገሪቱን ሀብት ያለምንም ከልካይ ለመዝረፍ ሲሉ ተቀዋሚያቸውንም የአባልና አጋር ድርጅቶች አባላትንም የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውን ዜጎችንም ወዘተ አጥፍተዋል፡፡ በመሆኑም ስለ እርቅ ሲጠየቁ፣  እንነጋገር ሲባሉ፣ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ ሲቀርብባቸው የፈጸሙት ወንጀል ሁሉ እየታሰባቸው ከሥልጣናቸው ሲወርዱና ፍትህ አደባባይ ሲቆሙ እየታያቸው ውይይትን ሳይሆን ጉልበትን፣ ሕግን ሳይሆን ጠመንጃን ምርጫቸው አድርገው በጥፋት ላይ ጥፋት እየፈጸሙ ነገሩን ሁሉ ከሮ ወደሚበጠስበት ደረጃ እየገፉት ነው፡፡ ሳይጠል በቅጠል እንዲሉ እንዳይበጠስ መጣሩ ነው የሚበጀው

የትግራይ ሽማግሌዎችና ምሁራን ሀገር ቤት ያሉት ባይችሉ በውጪ የሚገኙት ተዉ ይህ አድራጎታችሁ አይበጅም ለእናንተም ልጆቻችሁና ለልጆቻችንም አይጠቅምም በማለት ደምጻቸውን ማሰማት ባለመቻላቸው የደደቢት ወያኔዎች ሁሉ ትግሬ ቢሆኑም ትግሬ ሁሉ ወያኔ አይደለም በማለት ሽንጣችንን ገትረን ለአመታት ያካሄድነውን ትግል ወደ ሽንፈት እየወሰደው ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ለሚያሰሙት ተቃውሞም ሆነ ለሚለግሱት ምክር ከወያኔ የሚሰጠው ምላሽ የጸረ ሰላም ኃይሎች፣ የጠባቦች፣ የትምክህተኞች፣ የኤርትራ ተላላኪዎች ወዘተ የሚል በመሆኑ የወያኔ እኩይ ድርጊት ለትውልድ የሚተላለፍ ነቅርሳ ተክሎ እንዳያልፍም ሆነ ትግሬና ወያኔ አንድ አይደሉም የሚለው አስተሳሰብ ተቀባይነት እንዲያገኝ የማድረጉ አቅም እየተሟጠጠ ነው፡፡

የቀረው አንድና የመጨረሻ እድል በትግራይ ተወላጆች እጅ ነው ያለው፡፡ ደም አታቃቡን ቂም አታውርሱን ማለትና ልጆቻቸውን ከቻሉ ከጥፋቱ መንገድ መመለስ ካልቻሉ አውግዘው ድጋፋቸውን መንሳትና እኛም የእናንተ አይደለንም እናንተም የእኛ አይደላችሁም በማለት ዛሬ በወያኔ አገዛዝ ውስጥም ሆነ ነገ ከወያኔ ሥርዓተ መንግሥት ህልፈት በኋላ ልጆቻቸውና ልጆቻችን በሰላምና በፍቅር የሚኖሩበትን ሁኔታ ከወዲሁ ለመፍጠር መጣር ይኖርባቸዋል፡፡ ምንግዜም ቢሆን ያልዘሩትን ማጨድ አይቻልምና የትግራይ ወገኖቻችን ቢዘገይም ጨርሶ ሳይጨልም ለነገ ለልጆቻችን የሚበጀውን መልካሙን ዘር ለመዝራት ነገ ሳይሆን ዛሬ ተነሱ፡፡

የአፋር ህዝብ የትግሬ ማንነት በግዴታ ከተጫነባቸው የሀገራችን ህዝቦች አንዱና የወያነ የዘር ፖለቲካ ተጠቂ ነው እንጂ የወልቃይትና የጎንደሬ የመብት ትግልን በፉጹም ሊያወግዘው አይችልም

$
0
0
740px-Afar_in_Ethiopia.svgዘረኛው የወያነ የኮምኒከሺን ቢሮ በፋይስቦክ ገፁ በሰሜን ጎንደር ዞን የተፈጸመውን ጥቃት እንደሚያወግዝ የአፋር ክልላዊ መንግስት አስታወቀ በማለት የአፋር ህዝብን የማይወክል መግለጫ በአፋር ክልላዊ መንግስት ስም አሰራጭቷል።
በአሁኑ ግዜ በኢትዮጲያ ያለው ሰርዓት ከአመጣጡ ጀምሮ በየገባበት ዘር ከ ዘር፣ ጎሳ ከ ጎሳ በማጋጨት የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚጥር አደገኛ ሰርዓት መሆኑን የሚጠፋው ሰው ካለ ለመጥፋት የተዘጋጀ ሰው ብዬ ነው የማምነው።
የአፋር ህዝብ እራሱ ከህወሀት ቀኝ ግዛት ያላመለጠ፣ እንደ ወልቃይቶቹ መሬቱና ህዝቡ ያለ ፈላጎታቸው ወደ ትግራይ ተካሎበት ላለፉት 25 አመታት እየታገለ የሚገኝ ህዝብ እንጂ የተበዳዩ ወልቃይቴም ሆነ የማንም የመብት ትግልን ሊያወግዝ የሚችልበት ምንም ምክንያት የለውም።
ካለፉት 25 አመታት በፊት ክልሎቹ ሲካለሉ አከላለሉ የሁሉን ም ህዝቦች ሰሜትና ፈላጎት፣ ታሪክና ጂኦግራፊ፣ባህል እንዲሁም የራሳቸው ህgገ -መንግስትን መሰረት ያደረገ ሳይሆን የታላቋ ትግራይ የሰፊ መሬት ባለቤት ማድረግን መሰረት ያደረገ እንደነበረ በግልፅ ታይተዋል።
ይህ ደግሞ በወልቃይት ብቻ ሳይሆን በአፋር ክልልም በኩል በባህልም በቋንቋም ምንም ነገራቸው ትግሬ ያልሆኑ የሳውኔ አፋሮች ከነ መሬታቸው በግዴታ ወደ ትግራይ እንዲካለሉ ተደርገዋል።
 
የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተባለዉን የወያነ ነፍስ ገዳይ ካድረዎች ስብስብ ምን ያህል በነጻነት የፈለገዉን የማሞገስና ያልፈልገዉን የማውገዝ ስልጣን እና ሞራል እንዳለው በወያነ ዘመን ፖለቲካን የሚንከታተል ሰዎች በሚገባ እናውቃለን።
ወያነ ደግሞ በሁሉም በኩል የህዝብን ቁጣ እየበርታበት ሲመጣ የሌላ ብሔር ድጋፍ እንዳለው ለማስመሰል የሄው ከጠዋቱ ማንነቱ የሆነውን የዘረኝነት ጡሩምባን በመንፋት ህዝቦች ፊታቸው ወደ እርስ በእርስ ግጭት እንዲያዞሩ ይጥራል።
ዛሬ በኢትዮጲያ ውስጥ በወያኔ ያልተበደለ፣ ያልተገደለና ያልተማረረ ብሔር ብቻ ሳይሆን ግለ ሰብ ማገኘት ብርቅ ከሆነ ቆይተናል።
እናም የአፋር ህዝብ እንደ ማነኛውም ኢትዮጺያዊ የተበደለ ህዝብ እነደመሆኑ መጠን ማነኛውም በወያኔ ላይ ከንዱ የሚያነሳን ህዝብ ጎን ይቆማል እንጂ አይቃወሚም።
 
እኛ አንድ ህዝብ ነን፣ ወያኔ ደግሞ አንድ ብቸኛ ጥላታችን ነው!!
 
ከአካደር ኢብራሂም ( አኩ አፋር )

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የዐማራ ሕዝብ እሁድ በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል፤ በባህር ዳር፣ ደሴና ደብረ ብርሃን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል

$
0
0

13770406_1227251003974404_8797464232962582825_n

ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የዐማራ ሕዝብ እሁድ በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል

  • በባህር ዳር፣ ደሴና ደብረ ብርሃን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል

በወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎች ላይ የሚደርሰውን አፈናና ግድያ እንዲቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ እሁድ ሐምሌ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ለማካሔድ የአገር ሽማግሌዎችና የሕዝብ ተወካዮች ለከተማ አስተዳደሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ጥያቄ አቅራቢዎቹ እንደገለጹት አርብ ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ አዎንታዊ መልስ እንደሚሰጣቸው ከከተማ አስተዳደሩ ተነግሯቸዋል፡፡

እሁድ ዐማሮች በሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እንደሚወጣ ብሎም በሕወሓት የሚደርሰውን አፈናና ግድያ እንደሚያወግዝ ሲሆን በጎንደር ታሪክ ታላቁ ሰላማዊ ሰልፍ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የዐማራው ሕዝብ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ የሚያደርገውን ሰልፍ በሰርጎ ገብ የወያኔ ሰዎች ችግር እንዳይፈጠርም ጥንቃቄ ተደርጓል ተብሏል፡፡ በጎንደር የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ በምንም መልኩ ሊከለከል እንደማይችል አዘጋጆች አክለው ገልፀዋል፡፡ “የከተማ አስተዳደሩ በሕወሓት ጫና ሰላማዊ ሰልፉን ፈቃድ ቢከለክልስ ምን ዋስትና አላችሁ” በማለት ለሰልፍ አዘጋጆች ላቀረብንላቸው ጥያቄ “እኛ የጠየቅነው ሰላማዊ ሰልፍ ነው፤ የከተማ አስተዳደሩ ሕወሓትን በመፍራት ሕዝቡን ይከለክላል የሚል እምነት የለንም፤ ካደረገው ግን ሥርዓት አልበኝነትን እንዲነግሥ ይሻል ማለት ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በባህር ዳር፣ ደሴና ደብረ ብርሃን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ኮሚቴዎች ተመርጠው እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተያያዘ በጎንደር የሚገኘውን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ ወደ ማዕከላዊ ተወስደው ከባድ የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉትን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች እንዲፈቱ የሚጠይቁ የዐማራ አመራሮች መበራከታቸው ታውቋል፡፡ ወደ ማዕከላዊ የተወሰዱት የጥያቄ አቅራቢው አባላትና የወልቃይት አማራ ተወላጆች በቤተሰቦቻቸው ለመጠየቅ ቢሄዱን እስካሁን አልተፈቀደላቸውም፡፡

 

አዲሱ የወያኔ ጸረ አማራ ቲዎሪ፡- አፍሪካዊ ናዚነቱን በይፋ ሲውጅ

$
0
0

Displaced-Amharas-from-West-Shewa-Aremya-province-Dec-2015-1.jpgወያኔ እስካሁን ሲያፈናቅልና ሲገድላቸው የቆዩ አማሮችን በተመለከተ አዲስ ቲዎሪ ፈጥሯል፡፡ ይህም አዲስ ቲዎሪ በማህበራዊ ሚዲያ ቃል አቀባያቸው በኩል ተቀባይነት ያለው ሃሳብ እንዲሆን እየተሰራበት ነው፡፡ አዲሱ ቲዎሪ (በእርግጥ ከዚህ ቀደም በሀሳብ ደረጃ ይራመድ ነበር) አማራን ያፈናቀልነውና የገደልነው በጸባዩ ነው የሚል ነው፡፡ አንዳንድ ሰው ዳንኤልን አትጥቀስ፤ ዋጋ የሌለው ግለሰብ ነው ይላሉ፡፡ እኔ በዚህ አላምንም፡፡ የወያኔ እቅድ እና ሀሳብ በእሱ በኩል ነው የሚወጣው፡፡ እና የተወሰኑትን የወያኔ ጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳዎች ከእሱ ሰሞናዊ ጽሁፎች እጠቅሳለሁ፡፡
ዳንኤል የወያኔን አቋም ለህዝብ ሲያደርስ እንዲህ ይላል፡-
“አማራ ሲፈናቀል… ‹‹ተገቢ ነው›› የሚል ሀሳብ ወይም ‹‹አስተሳሰባቸውን፣ አኗኗራቸውን ቢቀይሩ ኖሮ…›› የሚል ምክር-ቢጤ ማንም ሲያቀርብ አይቼ አላውቅም፡፡”
ይህም ማለት እንደ ወያኔ ሀሳብ አማራ ሲፈናቀል ሌላው ሰው አማራ አስተሳሰቡን እና ኑሮውን መቀየር ባለመቻሉ እንደሆነ እንዲረዳለት ነው የሚፈልገው ማለት ነው፡፡ ዳንኤል ወይም ጠቅላላው ወያኔ አማራው በራሱ አስተሳሰብና አኗኗር ተፈናቀለ ተብሎ አለመወሰዱ የቆጫቸው መሆኑን ያሳብቃል፡፡
ቀደም ብሎ የሚከተለውን ጽፎ ብሎ ነበር:-
“አዎ! ግድያና ማፈናቀል በተከሰተ ቁጥር፡-
–> ተጠቂው ማህበረሰብ የሚያንጸባርቀው ፖለቲካዊ አስተሳሰብ አስተዋኦ ይኖረው ይሆን? ብላችሁ መጠየቅ አትርሱ።
–> ማሕበራዊ ዝንባሌው ለጥቃቱ ምክንያት ይሆንን ብላችሁም እንድትጠይቁ
–> ሀይማኖታዊ እና የሥራ ዝንባሌውስ ቢሆን…… ይህንንም አትዘንጉ።
አዎ! ተጎጂው ሕዝብ “ምን ምን መቀየር እንደሚገባው” ነጻ የምክር አገልግሎት ማበርከት አትርሱ።
ጥቃትን በማያሻማ ቋንቋ ማውገዝ ምን ያስፈልጋል?
ተጎጂውን ሕብረተሰብ ራሱን “እንዴት እንደሚታረም” ማማከር ነው እንጂ።”
ልብ በሉ! ይሄ እንግዲህ የአንድ አገረ ገዥ የነጻነት ግንባር አቋም ነው! እስኪ አንድ በአንድ እናፍታታው፡-
አማራ ተጠቂ የሆነው በፖለቲካዊ አስተሳሰቡ ነው ለሚለው፡- ፖለቲካዊ አስተሳሰብ በዘር ተለይቶ ለመጠቃት ምክንያት ከሆነ አጥቂው ቡድን ወራሪ ወይም ጠላት ነው ማለት ነው፡፡ አንድ አገዛዝ እመራዋሁ የሚለውን ህዝብ በፖለቲካዊ አመለካከቱ ብቻ የሚያጠቃ ከሆነ የዛ አገዛዝ እና ህዝብ ግንኙነት የመንግስት እና የህዝብ ሳይሆን የአዳኝ እና ታዳኝ ነው ማለት ነው፡፡ ለመሆኑ ወያኔ በምን መለኪያ ነው አንድን ህዝብ በፖለቲካዊ አመለካከቱ ማጥቃት ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሚፈልገው? ባጭሩ አንድን ህዝብ በፖለቲካዊ አስተሳሰቡ ማጥቃት ዘር አጥፊነት እና ጠላትነትን ብቻ ነው የሚያመለክተው፡፡ አማራ በጠላት እጅ ነው እንድንል የሚያደርገንም እንዲህ ያለው አስተሳሰብ ነው፡፡
ማህበራዊ ዝንባሌው ለጥቃቱ መንስኤ ነው ለሚለው፡- አማራ የትኛው ማህበራዊ ዝንባሌው ነው በመንግስት ነኝ ባዩ ቡድን ተለይቶ እንዲጠቃ የሚያደርገው? የማህበራዊ ዝንባሌ ልዩነት ቢኖርስ ነው በማን አገር ነው ያንን ማህበራዊ ዝንባሌው የተለየ ህዝብ አጥፉት የሚለው? ወያኔ ሆይ አማራን የማጠቃው በዚህ በዚህ የማህበራዊ ዝንባሌው ነው ብለህ ልትነግረን ትችላለህ? እውን አማራ ራሱን ለጥቃት የሚዳርግ ማህበራዊ ዝንባሌ አለው? ካለውስ ማፈናቀሉ እና መግደሉ እንዲሁም ንብረቱን መዝረፉ እንደመፍትሄ ተወስዶ ነው? የተለየና አደገኛ ማህበራዊ ዝንባሌ ካለውስ በደረጃ ቅደም ተከተል ዝንባሌውን ማጥፋት ነው፤ ወይስ ህዝቡን ማጥፋት፤ ወይስ ሁሉንም አንድ ላይ ማጥፋት ነው እየተሰራበት ያለው?
ሀይማኖቱና የስራ ዝንባሌውነው እንድናጠቃው የሚደርገን ለሚለው፡- አማራ በሀይማኖቱ እስላምና ክርስቲያን ነው፤ እምነት የሌለውም ይኖራል፤ በሳይንስ የሚያምንም ይኖራል፡፡ ታዲያ የትኛው ሀይማኖቱ ነው በመንግስት ተለይቶ እንዲጠፋ እንዲፈረድበት ያደረገው? በክርስቲያንነቱ ወይስ በእስላምነቱ ወይስ በኢአማኒነቱ? ጉድ እኮ ነው ጎበዝ! ህገ መንግስት የምትሉት ላይ የተጻፈው የእምነት እኩልነት ሳንሰማ ተቀይሮ ሰዎችን በእምነታቸው ለይቶ ማጥቃት በሚል አንቀጽ ተቀየረ እንዴ? ለመሆኑ በዚህ ዘመን አንድ መንግስት ነኝ ባይ ቡድን ሰዎችን በእምነታቸው ምክንያት ለይቶ እንደሚያጠቃ በአደባባይ ሲናገር አይደንቅምን? እንደ ተአምር ሊቆጠርስ አይገባምን? የስራ ዝነባሌውስ እንዴት ሆኖ ነው ለተጠቂነት ሊያጋልጠው የሚችለው? የስራ ዝንባሌ አንድን ህዝብ ለማጥቃት መንስኤ ነው ስትሉ ምን ማለታችሁ ነው? አማራን በጠላትነት ያስፈረጀው እና እንዲፈናቀልና እንዲገደል ያደረገው የመስራት ነው ወይስ ያለመስራት ዝንባሌው ነው? በስራ ዝንባሌ ምክንያት በዘር ለይቶ የሚያጠቃ ቡድን የግድ ናዚ ወይም ውስጡ የናዚ አስተሳሰብ ያለው መሆን አለበት፡፡ ናዚ ነው አይሁዶችን በስራ ዝንባሌያቸው ብቻ ለይቶ ያጠፋ– እስከምናውቀው ድረስ፡፡ እና ጥያቄው ወያኔ አፍሪካዊ ናዚ መሆኑን በድፍረት ለመናገር ያበቃው ምክንያት ምድን ነው? በዚህ ወቅት አፍሪካዊ ናዚነትን ማወጅስ ለምን አላማ ታስቦ ነው? የሚል ነው፡፡
ተጎጅው ህዝብ እንዴት ጸባዩን ማረም እንደሚችል ምከሩ ብላችኋል፡፡ የዚህ መልእክት ግልባጩ ካልሆነ ግን ዋ! የሚል ማስጠንቀቂያ ይሆናል፡፡ እንዴው በአቡነ አረጋይ እንጠይቃችሁ እና የምታፈናቅሉትን አማራ እንዳታፈናቅሉት እና እንዳትገድሉት ምን ብለን እንምከር? የትኛውን ጸባይስ ነው ማረም እንዳለበት የምናስተምወረው? በጣም ተጨነቅን፡፡ ተጎጅው ህዝብ ምን መቀየር እንደሚገባው ምከሩም አላችሁ፡- እባካችሁ ምን ምን መቀየር እንደሚገባው አስረዱን፡፡ ከእውቀት ብርሀናችሁ እንድታካፍሉን እንሻለንና!
መደምደሚያ፡- አወ፡፡ አታፍሩም፡፡ አወ፡፡ ይሉኝታ የላችሁም፡፡ አንድ መንግስት ተብየ ቡድን አንድን ህዝብ ጸባይህ አላማረኝም ብሎ ሲያፈናቅል እና ሲገድል አጨብጭቡ እያላችሁ ነው፡፡ ይሄማ የመንግስት ጸባይ አይደለም እኮ፡፡ ይሄማ ከግለሰብም በጣም የማይረባ ቆሻሻ ግለሰብ ተግባር ነው እኮ፡፡ ይህንን ባላችሁበት አፋችሁ ጎንደር ላይ ሲሰልሉ የነበሩ ሰዎች ንብረት ተነካ እና ሊገድሉ የሄዱ አሸባሪዎች የአጸፋ መልስ ተሰጣቸው ብላችሁ ምድር ትደርመስ ሰማይ ይውረድ እያላችሁ ነው፡፡ ንብረታቸው የተነካባቸውን ሰላዮች እና የማህበረሰቡ ደህንነት ጠንቆች መውቀስ Blame the Victim ነው አላችሁ፡፡ ታዲያ ይሄ ተጎጅን መወንጀል ለእናንተ ሰላዮች ከሰራ ስለምንድር ነው አማራው ላይ ላደረሳችሁት በደል እስስካሁን ትዝ ያላላችሁ እና እንደገናም ራሱን ለመወንጀል ይሄንን ሁሉ የምትንደፋደፉት?
እውነት ለመናገር ጸባይ ለመጠቃት ምክንያት ከሆነ ከህዝብ ተለይታችሁ የጸባይ ማረሚያ መታገት የነበረባችሁ እናንተ ወያኔዎች ናችሁ፡፡ እወቁት፡፡ የእናንተ ጸባይ ከሰው ጋር አብሮ የማያስኖር እጅግ አደገኛ እና ለሰው ልጅ ደህንነት ጠንቅ ነው፡፡ ወያኔ ማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ሀይማኖታዊ እና ኢኮኖሚካዊ ጠንቅ ነው፡፡ በእውነት!
ድል ለአማራ ህዝብ!

Mikias Dawit

እነበቀለ ገርባ በእስር ቤት የረሃብ አድማ ላይ ናቸው | VOA

$
0
0

(የአሜሪካ ድምጽ ራድዮ) አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በእስር የሚገኙ አራት የኦሮሞ ፈደራሊስ ኮንግረስ አመራር አባላት በእስር ቤት ውስጥ በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ — አድማውን ለማድረግ የወሰኑት በማረምያ ቤቱ አስተዳደር ላይ ላቀረቡት የመብት ጥሰት አቤቱታ ጉዳያቸው የሚከታተለው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም መሆኑን አመልክተዋል።

የኤፌኮ አመራር አባላት አቶ ጉርሜሳ አያሌው፣አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ በቀለ ገርባ ከትላንት በስትያ ከቀትር በኃላ ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ የቤተሰቦቻቸው አባላት ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

የድምጽ ዘገባውን ከታች ያድምጡ:-

Health: የፍቅር ስጦታ የሆነውን ጽጌሬዳ አበባ ለምግብነት አስበው ያውቃሉ?

$
0
0

ኢሳያስ ከበደ | ለዘ-ሐበሻ ጤና

አበቦችን የምናውቃቸው በሽታቸው (በመዓዛቸው) ፣ በውበታቸውና በተለይ ደግሞ ለምንወደውና ለምናፈቅረው ሰው በምናቀርበው ገጸ በረከት ብቻ ሊሆን ይችላል፡፤ በአንዳንድ ሀገሮች የሚገኙ በርካታ ሕዝቦች ግን በብዙ መቶ ዓመታት ለምግብነት የሚያገለግሉ አበቦችን በመብላት ሲደሰቱ ቆይተዋል፡፡ ከዚህ በታች ለምግብነት ከቀረቡ አበቦች መካከል የተወሰኑትን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡

foods

ጽጌሬዳ አበባ

በሳይንሳዊ መጠሪያው / ጂነስ ሮዛ/ በመባል የሚታወቀው ይህ የጽጌሬዳ አበባ በመላው ዓለም በሰፊው የሚታወቅና በጣም የሚወደድ አበባ መሆኑ ሁላችንንም የሚያስማማ ነው፡፡ ከተፈጥሯዊው ጽጌሬዳ አበባ በተጨማሪ በሰው ሰራሽ ዘዴ የተዳቀሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡

የጽጌረዳ አበባ ጣዕም በአፈሩ ዓይነት፣ በአየሩ ሁኔታና በሌሎችም በርካታ ምክንያቶች የተነሳ ሊለዋወጥ ስለሚችል ጽጌሬዳም ሆነ ሌላ አበባ ለምግብነት ከመጠቀማችን በፊት አበባውን መቅመሱ የተሻለ እንደሆነ የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ የአበባው የስረኛ ክፍል የመምረር ባህሪ ስላለው ይህንን የአበባ ክፍል / መራራ ክፍል/ ቆርጦ በማውጣት ወይንም ሙሉውን አበባ ለምግብነት ካዘጋጀን ውጪያዊውን ክፍል ብቻ እንድንመገብ ይመከራል፡፡

የጽጌረዳ አበባ በሰላጣ፣ ጣዕሙ ለስለስ ባለ አይብ ወይም የተፈጨ ኦቾሎኒ ባሉ የምግብ ዓይነቶች ውስጥ በመጨመር ጣዕሙን መቅመስ ይቻላል፡፡ እንዲሁም በምንወደው የስጎ አይነት ውስጥ የተፈጨ ቀይ ጽጌሬዳ በመጨመር ይበልጥ እንዲጣፍጥና መልኩ እንዲያምር ማድረግ ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ ፓስታ ላይ ጽጌሬዳውን በጠስ በጠስ በማድረግ ጣል አድርጎ መመገብ ይቻላል፡፡ ጽጌሬዳ አበባ የአይስክሬምንና የምንወደውን የአልኮል መጠጥ ጣዕም ይበልጥ ለማጣፈጥም ሊያገለግል ይችላል፡፡

የዱባ አበባ

ከ16ኛው መቶ ዘመን ጀምሮ በአሜሪካ ለምግብነት ሲያገለግል የኖረው የዱባ አበባ ስሙ / ኩኩርቢታ ፒፓ/ በመባል የሚታወቅ ሲሆን የአሜሪካ ሕንዶች ሴቴዎቹ አበቦች / ከጀርባቸው ትንሽ አበባ የሚያበቅሉት/ እንዲራቡ በሚል ወንዴዎቹን አበቦች / ረዥምና ቀጭን አንጓ ያላቸው/ ብቻ ይመገቡ የነበረ ይመስላል፡፡

እነዚህን አበቦች ከማብሰላችን በፊት በዙሪያው የሚገኙትን እሾሀማ ቅጠሎች ማስወገድ እንደሚገባ የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው አሜሪካውያን ይገልጻሉ፡፡ ሴቴውን የአበባ ክፍል ካስፈለገን ልንጥለው እንደምንችልም ይመክራሉ፡፡ ለስለስ ያለ ጣዕም ያለው የዱባ አበባ ከወይራ ዘይትና ከበቆሎው እሸት ጋር ተደባልቆ እንዲሁም ዱባ ራሱ ተደርጎበት በዋና ምግቦችና በሾርባ ውስጥ ተጨምሮ ሲሰራ በጣም ይጣፍጣል፡፡ የዱባው አበባ ጣዕሙ ትንሽ ጠንከር የሚል ከሆነ ደግሞ ከቀይ ሽንኩርት፣ ከነጭ ሽንኩርት፣ ከቅጠላ ቅጠል እና ከምንፈልገው ቅመም ጋር አድርገን በዘይት ወይም በሌላ ቅባት በትንሹ ጠበስ ጠበስ ልናደርገው እንችላለን፡፡ እንዲሁም አይብ፣ ቀይ ሽንኩርትና ቅጠላ ቅጠል በአበባው ውስጥ እንጠቀጥቅና አፉን እንደፍነዋለን፡፡ ከዚያም ነጩን የእንቁላል ክፍል ለብቻው በደንብ ከመታን በኋላ አስኳሉን እንቀላቅልና የተጠቀጠቀውን የዱባ አበባ እንነክርበታለን፡፡ በመጨረሻም የተፈጨ ዳቦ ውስጥ ከትተን እናወጣና በደንብ ጠብሰን እንመገበዋለን፡፡

ለመጠጥና ለከረሜላ የሚያገለግሉ

መጠጥ ውስጥ የሚጨመሩ ጣፋጭ አበቦችና፤ የአበባ ከረሜላ የሚሰራባቸው አበቦች መኖራቸውንም ያገኘነው መረጃ አስነብቦናል፡፡

የበረዶ መስሪያ ዕቃ ውስጥ መጠኑ አነስተኛ የሆነ አንድ ሙሉ አበባ ወይም ቅጠሏን በጥሰን ውኃ እንሞላበታለን፤ ከዚያም እንደተለመደው በረዶ እስኪሆን ድረስ እናቀዘቅዘዋለን፡፡ እነዚህን የበረዶ አንኳሮች በምንወደው መጠጥ ውስጥ ጨምረን መጠጣት እንችላለን፡፡

ሌላው ነጩን የእንቁላል ክፍል መትተን የደረቀውን ንጹህ አበባ በደቃቅ ብሩሽ በስሱ እንቀባው የአበባውን ቅጠሎች ሙሉ ለሙሉ መቀባታችንን እናረጋግጥ፤ ከዚያም ተጠንቅቀን ደቃቅ ስኳር በወንፊት እንነስንስበት ፤ አበባው ላይ ያለው ስኳር ከበዛ እናራግፈው ሊደርቅ በሚችልበት ቦታ ላይ ለረጅም ሰዓት እናቆየው ሲል የነገረን ደግሞ ኩክስ ቲሶርስ ነው፡፡

ጥንቃቄ ማድረግ

አንዳንድ አበቦች መርዝነት ስላላቸው የሚበሉትን በጥንቃቄ ለይተን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከተጠራጠርን አንብላቸው፡፡

ጸረ ተባይ መድኃኒት ወይም ማንኛውም ኬሚካል የተጨመረባቸውን አበቦች ፈጽሞ አንመገብ፡፡ / ብዙውን ጊዜ ከአበባ ሻጮች፣ ከአትክልት ቦታዎችና ከአንዳንድ የችግኝ መሸጫ ሱቆች የሚገዙ አበቦች እነዚህ ኬሚካሎች ይደረጉባቸዋል/ ምንም ኬሚካል ሳይደረግባቸው በተፈጥሮ የበቀሉና ከመንገዶች ራቅ ብለው የሚገኙ አበቦችን ብቻ እንመገብ፡፡

አስምና ከአትክልቶች ጋር የተያያዘ አለርጂ ያለበት ሰው አበባ መመገብ የለበትም፡፡ እንደፍራፍሬዎችና ቅጠላቅጠሎች ሁሉ በተለይ ጥሬያቸውን የሚበሉ አበቦች በሚገባ መታጠብ አለባቸው፡፡

የሚበሉት አበቦች እጅግ በጣም በርካታ ቢሆኑም በኛ ሀገር በብዛት የሚገኙት ሁለቱ በመሆናቸው የነሱን ብቻ ለማቅረብ ተገደናል፡፡ ይሁን እንጂ ሌሎችንም አበቦች የመመገብ ፍላጎቱ ያለን ሰዎች ከስነ ምግብ ባለሙያዎች ምክር ቢጠይቁ ይመከራል፡፡

ታኩማ ኢሳኖ –አዲሱ መድፈኛ አርሰናልን ምን ያህል ይጠቅማል?

$
0
0

ሊሊ ሞገስ | ለዘ-ሐበሻ ስፖርት

– ይህ ጽሁፍ ነገ በሚኒሶታና አካባቢው ታትሞ በሚሰራጨው ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ላይ የወጣ ነው::

አርሰናል በአሁኑ የዝውውር መስኮት እስካሁን ሁለት አዲስ ተጨዋቾችን መግዛቱ ይታወቃል፡፡ የመጀመሪያው ከቦሪሽያ ሞንቼግላድባህ በ33.2 ሚሊየን ፓውንድ የተገዛው ስዊዘርላንዳዊው አማካይ ግራንት ዣካ ነው፡፡ የ23 ዓመቱ ስዊዘርላንዳዊው በዩሮ 2016 ተሳትፎ ውጤታማ እግርኳስን ለማበርከት መቻሉ አርሴን ቬንገር በትክክል የሚጠቅማቸው ተጫዋችን ለማስፈረም መቻላቸውን ያስመሰክሩበት ሆኗል፡፡
ከዛ ወዲህ ቬንገር ጃፓናዊውን ኢንተርናሽናል አጥቂ ታኩማ ኢሳኖን ከሳንፍሬሴ ሄሩሽማ ክለብ ገዝተውታል፡፡ ከዚህ በፊት ቬንገር ከፀሐይ መውጫዋ አገር ጃፓን ያስፈረሟቸው ሁለት ተጨዋቾች ማለትም ሹኒጂ ኡናሞታና ራዬ ሚያቺ አርሰናልን ለመጥቀም ተስኗቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰሜን ለንደኑ ክለብን ለመልቀቅ ተገድደዋል፡፡
Takuma-Asano-poses-during-a-press-conference-announcing-his-move-to-Arsenal

ሆኖም ግን ኢሳኖ የአርሴን ቬንገር ቡድንን ለመጥቀም የሚችልበት የራሱ የሆኑ ተደናቂ ብቃቶን አሟልቶ መያዙን በቅርበት የሚያውቁት ባለሙያዎችን ይመሰክሩታል፡፡ የኢሳኖ ትልቁ ጠንካራ ጎኑ የማይታን አይነት ከፍተኛ ፍጥነትን በተፈጥሮው መላበሱ ነው ጎሎችን አስቆጥሮ ደስታውን የሚገልፅበት የራሱ የሆነ ባህል አለው፡፡

ምክንያቱም ሁለት እጆቹን ከጭንቅላቱ በላይ በማንሳት በጥፍሮቹ የመቧጨር ምልክትን በማሳየት ከእያንዳንዱ ጎሎቹ በኋላ ደስታውን የሚገልፅበት የራሱ የሆነ ስታይል አለው፡፡ ይህንን የድመት ዘሮች ደስታ አገላለፅ ከግንዛቤ በማስገባትም ጃፓናዊያን ፉትቦል አፍቃሪዎች ‹‹ጃጉዋር›› የሚል ተቀፅላን አውጥተውለታል፡፡

ጃጉዋር በሚለው ተቀፅላው እንዲፀኑ ሌላው አንድ ምክንያት የሆናቸው ለተጋጣሚ ቡድን የተከላካይ መስመር ተጨዋቾች አስቸጋሪ የሆነው ከፍተኛ ፍጥነቱ ነው፡፡ ከከፍተኛ ፍጥነቱ ባሻገር የኳስ ስኬሉን ቴክኒካል ብቃቱ አስተማማኝ መሆኑ አርሴን ቬንገር የቡድናቸው የጨዋታ ሲስተምን በትክክል ለመመጠን የሚችልበት ስታይልን መላበሱን እንዲያምኑበት ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡
ሆኖም ግን ኢሳኖ ከአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች አንዱ ለሆነው አርሰናል ለመፈረም የቻለው በእስካሁኑ የእግርኳስ ህይወቱ ብዛት ያላቸው ጎሎችን ለማስቆጠር ባልቻለበት ሁኔታ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ግን ለሄሩሽማ ክለብ ዋናው ቡድን በ34 የጃፓን ጄ ሊግ ግጥሚያዎች ላይ ተሰልፎ ዘጠኝ ጎሎችን ለማስቆጠር የቻለበት ውጤታማ ፉትቦሉ የ2015 ውድድር ወጣት ኮከብ ተጨዋችነት ስያሜን ለማግኘት በቂው ሆኖለታል፡፡

በዘንድሮው ዓመት የክለቡ አሰልጣኝ ሰፊ ልምድን ያካበተው የ32 ዓመቱ  ፒተር ኡታላን በቡድናቸው የፊት አጥቂ ሚና መጠቀምን ምርጫቸው በማድረጋቸው ኢሳኖ ከእስካሁኑ 11 የጄ ሊግ ግጥሚያዎች ውስጥ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የመጀመር እድልን ያገኘው በአራት ጨዋታዎች ላይ ብቻ ነው፡፡
ሆኖም ግን ከፍተኛ ትኩረትን በሚስቡ ግጥሚያዎች ላይ ወሳኝነት ያላቸውን ጎሎችን ማስቆጠርን የተለመደ ባህሉ አድርጎት ለመዝለቅ ችሏል፡፡ በዲሴምበር 2015 በተከናወነው የክለቡ ወርልድ ካፕ ውድድር ተሳትፎውም የብዙዎችን ልዩ ትኩረትን የሳበለት ሆኗል፡፡ በተለይም በዛ ውድድር ሰንፍሬሴ ሄሩሽማ የዲ.ሪ ኮንጎውን ቲፒ ሚዜምቤን 3ለ0 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለመሸጋገር እንዲችል ምክንያት የሆነ ጎልን በማስቆጠር የታጀበ ታላቅ ፐርፎርማንስን ለማበርከት ችሏል፡፡

በግማሽ ፍፃሜው በአርጀንቲና ሪቨርፕሌት 1ለ0 በሆነ ጠባብ ውጤት ቢያሸንፍም አሳኖ በእግርኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈበት ትልቅ ውድድር ያሳየው ውጤታማ ፉትቦሉና ከዛ ወዲህም በአራት የጁ ሊግ ግጥሚያዎች ብቻ በመደበኛ ቋሚ ተሰላፊነት የመጀመር ዕድልን አግኝቶ ሁለት ወሳኝ ጎሎችን ለማስቆጠር መቻሉ ለአርሰናል ለመፈረም የተመቻቸ ሁኔታን እንደፈጠረለት ይታመናል፡፡
አርሰን ቬንገር የአርሰናል ስራን ከመያዛቸው  በፊት የጃፓኑ ግራሞፐስ ኤይትን በዋና አሰልጣኝነት ለሁለት ዓመታት መምራታቸውም በአገሪቱ በየጊዜው ብቅ የሚሉት ተደናቂ ብቃት ያላቸው ተጨዋቾች የሚጠቀሟቸው ወዳጆችን ጃፓን ውስጥ እንዲያፈሩ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡ ኢሳኖ በእስካሁኑ የፕሮፌሽል ፉትቦል ህይወቱ በ56 ግጥሚያዎች ተሰልፎ ያስቆጠራቸው ጎሎቹ 13 ብቻ ቢሆኑም ከፍተኛ ፍጥነቱና እጅግ የላቀ ቴክኒካል ብቃቱን መሰረት በማድረግ የተጋጣሚ ቡድን የተከለካይ መስመርን ለማስከፈት የሚችልበት የቲምዎርክ ደረጃው ግን ትልቅ ስታንዳርድን የነካ የሚባል ነው፡፡
ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም ቬንገር የ21 ዓመቱ ጃፓናዊው ባስፈረሙበት ማግስት በሰነዘሩት አስተያየት ኢሳኖን ‹‹በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የአርሰናል እጅግ ምርጡ ተጨዋች ለመሆን እንደሚችል ምንም አይነት ጥርጣሬ የለኝም›› በማለት ገልፀውታል፡፡ ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ኢሳኖ ለዋናው ቡድናቸው የሚጠበቅበት ትልቅ ጠቀሜታዎችን የሚሰጥበት ጊዜን የሁለት ዓመታት ቀጠሮን ያወጡለት እንግሊዝ ውስጥ የመጫወት ፈቃዱን ለማግኘት በቅድሚያ በሌላ አውሮፓ አገር ለሚገኝ ክለብ በውሰት ውል መጫወት እንደሚያስፈልገው ግንዛቤን በማሳደር ነው፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን ቬንገር የኢሳኖ በሁሉም የአጥቂ መስመር ሚናዎች ላይ ለመጫወት የሚችልበት ሁለገብ ብቃትን የተላበሰ ለመሆኑና በበርካታ ፓሶች ላይ የተመረኮዘ የጨዋታ ስታይሉ ለአርሰናል የጨዋታ ሲስተምን በትክክል ተስማሚነት ያለው ለመሆኑ አንዳችም ጥርጣሬ የላቸውም፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢሳኖ ከፍተኛ ፍጥነት በአሁኑ ወቅት በአርሰናል ስኳድ ከሚያገኙት ፈጣን ተጨዋቾችን ማለትም ሄክተር ቤሌሪንና ቲኦ ዋልኮትን የሚያስንቅ ነው፡፡
ምክንያቱም ኢሳኖ በቅርቡ በልምምድ ፕሮግራም ወቅት 50 ሜትር ርቀትን በ5.96 ሴኮንድ ለመግባት ችሏል፡፡ ይህ ጀማይካዊው የዓለም ሻምፒዮን ዮሴን ቦልት ተመሳሳይ ርቀትን በ5.5 ሴኮንድ ከገባበት ጊዜ በ0.4 ማይክሮ ሰከንድ ብቻ የዘገየበት ነው፡፡ ቬንገር ሌላው ኢሳኖን የማስፈረም ውሳኔ ላይ የደረሱበት ዋነኛ ምክንያት ለአርሰናል በማልያ ሽያጭ ከፍተኛ ገቢን የሚፈጥርለት መሆኑን ከግንዛቤ ማስገባታቸው ነው፡፡

ከወዲሁም በቶኪዮና በሌሎቹ የጃፓን ከተሞች የኢሳኖ ለአርሰናል መፈረም ትልቅ የመወያያ ርዕስን የፈጠረ ከመሆኑም ባሻገር ገና ለአዲሱ ክለቡ በአንድ ግጥሚያ ላይ እንኳን ሳይሰለፍ የኢሳኖ ስምን የያዙ የአርሰናል ማሊያዎቹ ለሽያጭ መቅረብ ጀምረዋል፡፡ ከዚህ አንፃር ቬንገር ጃፓናዊው አጥቂን ያስፈረሙበት ውሳኔያቸው ያንን ያህል የአርሰናል ደጋፊዎችን የሚያስከፋቸው አይሆንም፡፡

ኢትዮጵያ የማናት? –የወንዲ ማክ ተወዳጅ ነጠላ ዜማ ከካናዳው የኢትዮጵያ ቀን ቪድዮ ጋር የቀናበረ

$
0
0


ኢትዮጵያ የማናት? – የወንዲ ማክ ተወዳጅ ነጠላ ዜማ ከካናዳው የኢትዮጵያ ቀን ቪድዮ ጋር የቀናበረኢትዮጵያ የማናት? – የወንዲ ማክ ተወዳጅ ነጠላ ዜማ ከካናዳው የኢትዮጵያ ቀን ቪድዮ ጋር የቀናበረ

በስደት ከሚገኘው ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live